4
የአንበሳው ጥሪ ለሰው ልጆች ሁሉ አለም አቀፍ አገልግሎት የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት አስፈላጊነት “ጨውና ብርሃን ናችሁ።” ማቴዎስ.5፥13-16 በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል

01. የመጽሐፍ ቅዱስ ዶክትሪን አስፈላጊነት

Embed Size (px)

Citation preview

Page 1: 01. የመጽሐፍ ቅዱስ ዶክትሪን አስፈላጊነት

የአንበሳው ጥሪ ለሰው ልጆች ሁሉ አለም አቀፍ አገልግሎት

የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት አስፈላጊነት

“ጨውና ብርሃን ናችሁ።” ማቴዎስ.5፥13-16 በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል

Page 2: 01. የመጽሐፍ ቅዱስ ዶክትሪን አስፈላጊነት

የቃሉ አስፈላጊነት

1. የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት (ዶክትሪን) ኢየሱን ክርስቶስን የምናውቅበትናየምንወድበት ብቸኛ መንገድ ነው።

“ለእግዚአብሔርም ክብርና ምስጋና ከኢየሱስ ክርስቶስ የሚገኝ የጽድቅ ፍሬ ሞልቶባችሁ፥ ለክርስቶስ ቀን ተዘጋጅታችሁ ቅኖችና አለ ነውር እንድትሆኑ የሚሻለውን ነገር ፈትናችሁ ትወዱ ዘንድ፥ ፍቅራችሁ በእውቀትና በማስተዋል ሁሉ ከፊት

ይልቅ እያደገ እንዲበዛ ይህን እጸልያለሁ።” ፊሊ.3፥10

2. የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት በትክክል ከተማርንና በልባችን ከተተከለ ከኢየሱስክርስቶስ ጋር ትክክለኛ እርምጃን እንራመዳለን።

“..የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ፤”ዕብ.12፥2-3

3. የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርትን የምንቀበለው በጸጋ ከመንፈስ ቅዱስ እገዛና እርዳታስር ሆነን ነው። ይህም መለኮታዊ ድፍረትንና ሕይወትን ያበዛልናል።

“’እንግዲህ ሁልጊዜ ታምነን፥ በእምነት እንጂ በማየት አንመላለስምና በሥጋ ስናድር ከጌታ ተለይተን በስደት እንዳለን የምናውቅ ከሆንን፥” 1.ቆሮ.1፥13, 2.ቆሮ.5፥6-8

“ጨውና ብርሃን ናችሁ።” ማቴዎስ.5፥13-16 በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል

Page 3: 01. የመጽሐፍ ቅዱስ ዶክትሪን አስፈላጊነት

ቃሉ አስፈላጊነት

4. የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት በትክክለኛ መልኩ በልባችን ሲቀመጥ ወይም ሲሳል ትክክለኛለሆነ መለኮታዊ እይታ ምንጭ ይሆናል።

‘’ክፉ ሰው መንገዱን በደለኛም አሳቡን ይተው ወደ እግዚአብሔርም ይመለስ እርሱም ይምረዋል፥ ይቅርታውም ብዙ ነውና ወደ አምላካችን ይመለስ።አሳቤ እንደ አሳባችሁ መንገዳችሁም እንደ መንገዴ አይደለምና ይላል እግዚአብሔር፦” ኢሳ.55፥7-9,

“’የሰውንም አሳብ በእግዚአብሔርም እውቀት ላይ የሚነሣውን ከፍ ያለውን ነገር ሁሉ እናፈርሳለን ለክርስቶስም ለመታዘዝ አእምሮን ሁሉ እንማርካለን’” 2ቆሮ.10፥5

5. የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት እግዚአብሔር በዘመኑ ያለውን እቅዱንና ሃሳቡንየምንረዳበትን ብቃት ይሰጠናል። (ኢሳ.26፥3-4,28፥29,)

“እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን።”ሮሜ.8፥28

“’በክርስቶስ ለማድረግ እንደ ወደደ እንደ አሳቡ፥ የፈቃዱን ምሥጢር አስታውቆናልና፤ዘመን ፍጻሜ ይደረግ ዘንድ ያለው አሳቡም በሰማይና በምድር ያለውን ሁሉ በክርስቶስ ለመጠቅለል ነው።እንደ ፈቃዱ ምክር ሁሉን የሚሠራ እንደ እርሱ አሳብ፥ አስቀድመን

የተወሰንን በክርስቶስ ደግሞ ርስትን ተቀበልን።” ኤፌ.1:10-12

“ጨውና ብርሃን ናችሁ።” ማቴዎስ.5፥13-16 በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል

Page 4: 01. የመጽሐፍ ቅዱስ ዶክትሪን አስፈላጊነት

ቃሉ አስፈላጊነት

6. የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ሰውን አንድ ሃሳብ ያለው በአንድ ልብ የሚጓዝ ሰውያደርገዋል።“ሁለት አሳብ ላለው በመንገዱም ሁሉ ለሚወላውል ለዚያ ሰው ከጌታ ዘንድ አንዳች እንዲያገኝ አይምሰለው።”ያቆ.1፥8

7. የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ከሌለን ስይጣን በቀላሉ አዕምሯችንን ይበክለናል።“ነገር ግን እባብ በተንኮሉ ሔዋንን እንዳሳታት፥ አሳባችሁ ተበላሽቶ ለክርስቶስ ከሚሆን ቅንነትና ንጽሕና ምናልባት እንዳይለወጥ ብዬ

እፈራለሁ።” 2.ቆሮ.11፥3

8. የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ይመረምራል፣ ያርማል፣ መረጃን ይሰጣል፣ በመንፈስእንድናድግ ያግዛል ለመልካም ስራም ያዘጋጃል።

“የእውነትን ቃል በቅንነት የሚናገር የማያሳፍርም ሠራተኛ ሆነህ፥ የተፈተነውን ራስህን ለእግዚአብሔር ልታቀርብ ትጋ።”2.ጢሞ.2፥15

“የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል።”2.ጢሞ.3፥16-17

“ጨውና ብርሃን ናችሁ።” ማቴዎስ.5፥13-16 በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል