6
የአንበሳው ጥሪ ለሰው ልጆች ሁሉ አለም አቀፍ አገልግሎት ጥምቀቶች “ጨውና ብርሃን ሁኑ” ማቴዎስ.5፥13-16 በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል

17. የጥምቀቶች ዶክትሪን

Embed Size (px)

Citation preview

Page 1: 17. የጥምቀቶች ዶክትሪን

የአንበሳው ጥሪ ለሰው ልጆች ሁሉ አለም አቀፍ አገልግሎትጥምቀቶች

“ጨውና ብርሃን ሁኑ” ማቴዎስ.5፥13-16 በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል

Page 2: 17. የጥምቀቶች ዶክትሪን

ዋንኛ ጥምቀቶች

1. ጥምቀት ዋናዎቹ ሦስት ናቸው። እነርሱም የውሃ፣ የመንፈስና የእሳት ጥምቀቶች በመባልይታወቃሉ። ነገር ግን ሌሎች ጥምቀቶችም አሉ። እነዚህን ከዋንኞቹ ጋር አያይዘን ለማየትእንድንችል ደረቅ ጥምቀቶችና የስርዓት ጥምቀቶች ብለን እንከፍላቸዋለን።

2. ደረቅ ጥምቀቶች አንድን ሰው ሆነ ነገር ከአንድ ሰው ጋር እዲተባር የማድረግ ብቃት ያለውነው። ደረቅ ስንል የሚጠመቀው ሰው በውሃ ውስጥ አይጠልቅም ማለት ነው። በዚህ ጥምቀትውስጥ ውሃ ቢኖርም ከመረጨት አያልፍም።1. የሙሴ ጥምቀት፦ (1.ቆሮ.10፥2 ሕዝበ እስራኤል የኢየሱስ ጥላ ከሆነው ከሙሴ ጋር እንዲተባበሩ በባሕርና

ከደመና በታች ተጠመቁ። ይህም ፍንጥቅጣቂ ውሃ በስተቀር መዘፈቅ የለውም።

2. የእሳት ጥምቀት፦ ይህ የመከራ ጥምቀት ስንዴው ከገለባው ተለይቶ ገለባው የሚቃጠልበት ጥምቀት ነው።ይህ ገና ያልተፈጸመ ነገር ግን ሁላችን እንደየአቅማችን አሁንም የምንለማመደው ደረቅ ጥምቀት ነው።(ሚል.3፥1-7, 4፥1, ማቴ.3፥11, 13፥25, ሉቃ.3፥16, 2.ተሰ.1፥7-9, ራዕ.19፥11,20)

3. የመስቀል ጥምቀት፦ ኢየሱስ ራሱን ከሃጢያታችን ጋር አጣመሮ ቅጣትን ተቀበለ። የሁላችን ሃጢያት በእሱላይ ፈሰሰ። (ማቴ.20፥22, ማር.10፥38-39, ሉቃ.12፥50)

4. የመንፈስ ጥምቀት፦ ይህ በዓለ አምሣ ቀን የተፈጸመው ማንኛውም አማኝ በደህንነት ወቅት የሚቀበለውነው። ይሁንና ወደዚህ ሙላት ልምምድ ሊመጣ ይገባዋል።

“ጨውና ብርሃን ሁኑ” ማቴዎስ.5፥13-16 በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል

Page 3: 17. የጥምቀቶች ዶክትሪን

ጥምቀቶች

3. የመንፈስ ጥምቀት፦ መንፈስ ቅዱስ አንድ ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ ሲያምን ከኢየሱስ ጋርበመንፈስ አንድ ያደርገዋል። ደግሞ ወደ ንጉስ ካህናት ማህበር ለዘለዓለም ይቀላቅለዋል።(1.ቆሮ.6፥17, 12፥13, ቆላ.2፥12)

4. ይህ የመንፈስ ጥምቅት ከዋንኞቹ ጥምቀቶች አንዱ እንደመሆኑ መጠም ልምምድ ብቻ ሳይሆንማንነትም ነው። (ዮሐ.3፥6-8)

5. ይህ አሁን አማኞች የሚያገኙት የመንፈስ ጥምቀት በብሉይ ኪዳን ከሐዋርያት ዘመን በፊትፈጽሞ አልነበረም። ይህን ስንል ግን ሰዎች በመንፈስ አይሞሉም ነበር ማለት አይደለም። ነገርግን አሰራሩን ክብሩና መጠኑ ይለያያል። (ቆላ.1፥25-26,ዮሐ.14፥20, ሐዋ.1፥5, 2፥3, 11፥15-17)

6. የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ሌላው አላማው የኢየሱስ ክርስቶስን አካል ወደ አንድነት ለማምታትናለማነጽ ነው። (ኤፌ.4፥5,ቆላ.3፥10-11,ዕብ..2፥11)

7. የመንፈስ ቅዱስ በአማኙ ውስጥ ያለው ዋንኛ ሥራው አማኙን ወደ ቅድስና ማምጣትየእግዚአብሔር ሕግ በአማኙ ልብ እንዲጻፍና አማኙ እግዚአብሔርን እንዲታዘዝ ማድረግ ነው።(ሮሜ.6፥3-4, ቆላ.2፥12, ኤፌ.1፥3-6, ቆላ.2፥10, ዕብ.8)

“ጨውና ብርሃን ሁኑ” ማቴዎስ.5፥13-16 በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል

Page 4: 17. የጥምቀቶች ዶክትሪን

ጥምቀቶች

8. አማኝ በመንፈስ ቅዱስ ሲጠመቅ መንፈስ በሃይል ሲመጣበትና ሲኖርበት የተለያዮ ነገሮችይሆናሉ። ለምሳሌ፦

1. በክርስቶስ የነበረ ሃሳብ በኛም ይፈጸማል (ኢሳ.61፥1)

2. ትንቢት ልንናገር እንችላለን (ሐዋ.19፥6-7)

3. በልሳን ልንናገር እንችላለን (ሐዋ.2፥1-5,19፥6-7)

4. ልንፈተን እንችላለን (ማቴ.3፥16-17,4፥1-6)

5. ሰዎች እንደሚገባቸው መናገር ብቃት እናገኛለን (ሐዋ.2፥8-11, 4፥31, 7፥1-)

6. ሚስጥርን መረዳትና መናገር እንችላለን (1.ቆሮ.2፥10-16, 14፥2)

7. ወንጌልን በሃይልና በስልጣን በተአምራትም በመታገዝ ልናገለግል እንችላለን (ሐዋ.1፥8,4፥33.6፥8, ዮሐ.16፥15)

8. ለሹመት ብቁ ያደርገናል (ሐዋ.6፥3)

9. ታላላቅ ትምሕርቶችን እንሸከማለን (ዮሐ.16)

10. ሕጉን እንድንረዳና እንድንታዘዘው ብቃትን ይሰጠናል (ሮሜ.8)

11. ያትመናል፣ ወደ እረፍት ያመጣናል፣ ያጽናናል፣ አዕምሯችንን በሰላሙ ይጠብቃል፣ ከጌታ የሆነው ብቻ ይነግረና። በፍቅር በደስታና በሰላሙ ልባችንን ይሞላናል….ወዘተ

“ጨውና ብርሃን ሁኑ” ማቴዎስ.5፥13-16 በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል

Page 5: 17. የጥምቀቶች ዶክትሪን

ጥምቀቶች

9. የውሃ ጥምቀት፦ የማዳን ጉልበትና የበጎ ሕሊና ልመና የጸሎት መድረክና ከኢየሱስጋር በሞቱና በትንሳኤው መተባበራችንን መግለጫ ነው። (ሐዋ.8፥36-38,1.ቆሮ.10፥1-2)

10.የውሃ ጥምቀት ለመንፈስ ጥምቀትም መንገድን ይከፍታል። የጌታ ደቀመዝሙርእንድንሆን መንገድ ይከፍታል። (1.ጴጥ.3፥21,ሐዋ.2፥38,40-41,8፥12-37,ማቴ.28፥19, 1.ቆሮ.10፥1)

11. ሕጻናት አይጠመቁም ታቅፈው ይባረካሉ። ይህም ይሆነው ኢየሱስ ያደረገው ይህንብቻ ስለሆነ ነው። ነገር ግን ወደ እግዚአብሔር ቤት እንዲመጡ አይከልከሉም። ነፍስያወቀና በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ያመነ ሁሉ የውሃን ጥምቀት የመውስድ መብትአለው። ሕዝበ እስራኤል ከፋሲካ በዓል በኃላ ተጠበቁ። ጥምቀት ፋሲካን አቀድምም።

12.ከውሃ ጥምቀት በፊት በደህንነት ወቅት መንፈሱ ከጌታ መንፈስ ጋር አንድ ሲሆንአማኙ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታን ሊቀበል ይችላል። ነገር ግን በመንፈሳዊ ሕይወቱማደግ ከወደደ የውሃን ጥምቀት መጠመቅ ወሳኝ ነው። (ሐዋ.10፥44-48)

“ጨውና ብርሃን ሁኑ” ማቴዎስ.5፥13-16 በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል

Page 6: 17. የጥምቀቶች ዶክትሪን

ጥምቀቶች

13.ስርዓታዊ ጥምቀቶች፦ እነዚህ ጽድቅን ለመፈጸም ወይም የተላዮ ፈውሶችን ለመቀበልየምንጠመቃቸው ናቸው። ኢየሱስ፦ (ማቴ.3፥13-17) የዮሐንስ ጥምቀት፦ ማቴ.3፥1-11,ዮሐ.1፥25-33, ሐዋ.19፥2-4) የማኞች ጥምቀት፦ ሐዋ.2፥38,41, 8፥36-38, 9፥18, 10፥47-48,16፥33) ንዕማን ከለምጹ ለመንጻት በዮርዳኖስ ባሕር ተጠመቀ። (2.ዜና.5፥14)

14.ጥላና አካል ሕጉና አካሉ፦ የጥምቀት አላማ ምንድ ነው? (ማር.16፥16, ሐዋ.2፥38, ዕብ.9፥6-13, ማር.7፥1-)

15.ጥምቀት በሕጉ፦ የመታጠቢያው ሳሕን የጥምቀት ጥላ ነበር። (ዘጸ.38፥8,40፥7) ካህናቱ ወደቅድስት ከመግባታቸው በፊት መታጠባቸው የግድ ነበር። በቅድስት መጋረጃና በአደባባይመካከል ያለው መታጠቢያው ሳሕን ሲሆን ይህ ደግሞ የጥምቀት ጥላ ነበር። ይህ የቀይ ባሕርምጥላ ነበር። (1.ቆሮ.10፥1-5)

16.ጥምቀት ለመጽደቅ ሳይሆን ጥምቀት ለክህነትና በመንፈሳዊ ሕይወታችን ለማደግ የሚተቅምምስክርነት ነው። ምክንያቱም ጥምቅትን ሳይሻገሩ ሲና ተራራ ስር መድረስ ፈጽሞአይታሰብም። (ዘሁ.19፥8-9,13)

17. (ዘሌ.13፥14-46,14)- አንድ ለምጻም ለመንጻት ሦስት የመንጻት ጊዜ ይወስዳል። ለምጻሙፈጽሞ ከለምጹ የሚነጻው በሰምንተኛው ቀን። (ሕዝ.36፥2432)

“ጨውና ብርሃን ሁኑ” ማቴዎስ.5፥13-16 በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል