4
የአንበሳው ጥሪ ለሰው ልጆች ሁሉ አለም አቀፍ አገልግሎት ትንሣኤ ሙታን “ጨውና ብርሃን ናችሁ።” ማቴዎስ.5፥13-16 በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል

20. የሙታን ትንሳኤ ዶክትሪን

Embed Size (px)

Citation preview

Page 1: 20. የሙታን ትንሳኤ ዶክትሪን

የአንበሳው ጥሪ ለሰው ልጆች ሁሉ አለም አቀፍ አገልግሎት

ትንሣኤ ሙታን

“ጨውና ብርሃን ናችሁ።” ማቴዎስ.5፥13-16 በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል

Page 2: 20. የሙታን ትንሳኤ ዶክትሪን

ትንሣኤ ማለት ምንም ማለት ነው?1. ትንሳኤ ስንል አንድ ሰው ከሞት ተነስቶ ከዛ በኃላ መሞትም ሆነ መበስበስ ሳይችል ሲቀር ያ ሰው

ትንሳኤን ተቀበለ ማለት እንችላለን፣ በጳውሎስ አገላለጽ የሰው ልጆች የሚበሰብሰው ሥጋቸውበማይበሰብሰው አካላቸው ሲዋጥ ትንሳኤ ሆነ ማለት ነው።

2. ኢየሱስ የእኛ ብቸኛ ምሳሌ ነው

“አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩራት ሆኖ ከሙታን ተነሥቶአል፣” 1ቆሮ.15፦20

“እርሱም የአካሉ ማለት የቤተ ክርስቲያን ራስ ነው። እርሱም በሁሉ ፊተኛ ይሆን ዘንድ፥ መጀመሪያ ከሙታንም በኵር ነው፣” ቆላ.1፦18

ሀ. የኢየሱስ ሞት ምሳሌነት:-

“5 መልአኩም መልሶ ሴቶቹን አላቸው። እናንተስ አትፍሩ የተሰቀለውን ኢየሱስን እንድትሹ አውቃለሁና፤ 6 እንደ ተናገረ ተነሥቶአልና በዚህ የለም፤ የተኛበትን ስፍራ ኑና እዩ። 7 ፈጥናችሁም ሂዱና። ከሙታን ተነሣ፥ እነሆም፥ ወደ ገሊላ ይቀድማችኋል በዚያም ታዩታላችሁ ብላችሁ ለደቀ መዛሙርቱ ንገሩአቸው፣”

ማቴ 28፦6

1. ሁላችን ልንጠይቃቸው የሚገባን ትክክለኛ ጥያቄዎች አሉ፣ ሰዎች ሲሞቱ በምን አይነት አካልይመጣሉ? እንዴትስ ይነሳሉ? ትንሳኤ መንፈሳዊ ወይስ ፍጥረታዊ ነው? ይህን ጥያቄ ሰው ሊጠይቅእንደሚችል ጳውሎስ ተረድቷልና እንዲህ ይለናል።

“ጨውና ብርሃን ናችሁ።” ማቴዎስ.5፥13-16 በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል

Page 3: 20. የሙታን ትንሳኤ ዶክትሪን

“35 ነገር ግን ሰው። ሙታን እንዴት ይነሣሉ? በምንስ ዓይነት አካል ይመጣሉ? የሚል ይኖር ይሆናል። 36 አንተ ሞኝ፥ አንተ የምትዘራው ካልሞተ ሕያው አይሆንም፤ 37 የምትዘራውም፥ ስንዴ ቢሆን ከሌላም ዓይነት የአንዱ

ቢሆን፥ ቅንጣት ብቻ ነው እንጂ የምትዘራው የሚሆነውን አካል አይደለም፤ 38 እግዚአብሔር ግን እንደ ወደደ አካልን ይሰጠዋል ከዘሮችም ለእያንዳንዱ የገዛ አካሉን ይሰጠዋል። 39 ሥጋ ሁሉ አንድ አይደለም፥

የሰው ሥጋ ግን አንድ ነው፥ የእንስሳም ሥጋ ሌላ ነው፥ የወፎችም ሥጋ ሌላ ነው፥ የዓሣም ሥጋ ሌላ ነው፣40 ደግሞ ሰማያዊ አካል አለ፥ ምድራዊም አካል አለ፤ ነገር ግን የሰማያዊ አካል ክብር ልዩ ነው፥ የምድራዊም

አካል ክብር ልዩ ነው፣”1ቆሮ.15፦35

1. የጥያቄዎቹ መልስ ግን በአጭሩ ትንሳኤ ማለት በሁለቱም አካል የሚገለጥመንፈሳዊም ፍጥረታዊም ክስተት ወይም ለውጥ ነው፣

ማቴ 28፦18 “ስልጣን በሰማይና በምድር ተሰጠኝ”

1. ኢየሱስ ከትንሳኤው በኃላ በአካል ተገልጦ ዮሐ 20፦27 ከእነርሱ ጋር ምግብ መመገብችሏል።

“ጨውና ብርሃን ናችሁ።” ማቴዎስ.5፥13-16 በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል

Page 4: 20. የሙታን ትንሳኤ ዶክትሪን

በሉቃስ.24፦43, ዮሐንስ.21፦13 ደግሞም ከመቀጽበት ወደ መንፈሳዊው አካል ተለውጦ ከፊታቸውሲሰወር እንመለከተዋለን፣ ይህ ደግሞ በመንፈሳዊው ዓለም መንቀሳቀስ ብቃት እንዳለው እንድንመለከትያደርገናል፣ ሉቃ.24፦31 ኢየሱስ ሥጋ ወይስ መንፈስ ነው የሚለው ቃል በሉቃስ. 24፦36-43 ላይበደንብ ተብራርቶ ተቀምጧል፣

“ ይህንም ሲነጋገሩ ኢየሱስ ራሱ በመካከላቸው ቆሞ። ሰላም ለእናንተ ይሁን አላቸው። ነገር ግን ደነገጡና ፈሩ መንፈስም ያዩ መሰላቸው። እርሱም። ስለ ምን ትደነግጣላችሁ? ስለ ምንስ አሳብ በልባችሁ ይነሣል? እኔ ራሴ እንደ ሆንሁ እጆቼንና እግሮቼን እዩ፤ በእኔ እንደምታዩት፥ መንፈስ ሥጋና አጥንት የለውምና እኔን ዳስሳችሁ እዩ አላቸው። ይህንም ብሎ እጆቹንና እግሮቹን

አሳያቸው። እነርሱም ከደስታ የተነሣ ገና ስላላመኑ ሲደነቁ ሳሉ። በዚህ አንዳች የሚበላ አላችሁን? አላቸው። እነርሱም ከተጠበሰ ዓሣ አንድ ቁራጭ፥ ከማር ወለላም ሰጡት፤ተቀብሎም በፊታቸው በላ፣”

ሮሜ.6፦3-11. ትንሳኤውን የሚመስል ትንሳኤ ለመማለድ፣ 1.ጢሞ. 2፦3-7

“ጨውና ብርሃን ናችሁ።” ማቴዎስ.5፥13-16 በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል