4
የአንበሳው ጥሪ ለሰው ልጆች ሁሉ አለም አቀፍ አገልግሎት ንስሃ “ጨውና ብርሃን ናችሁ።” ማቴዎስ.5፥13-16 በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል

10. የንስሃ ዶክትሪን

Embed Size (px)

Citation preview

Page 1: 10. የንስሃ ዶክትሪን

የአንበሳው ጥሪ ለሰው ልጆች ሁሉ አለም አቀፍ አገልግሎት

ንስሃ

“ጨውና ብርሃን ናችሁ።” ማቴዎስ.5፥13-16 በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል

Page 2: 10. የንስሃ ዶክትሪን

ንስሃ

1. ንስሃ በዕብራይስጡ ‘‘ናቻም‘‘ ይባላል። ትርጉሙም የአዕምሮ የአስተሳሰብለውጥ ማምጣት ማለት ነው። (ዘፍ.6፥6፣ መሳ.2፥18፣ 1.ሳሙ.15፥35፣መዝ.90፥13፣ ኤር.15፥6፣ 42፥10፣ አሞፅ.7፥3,6)

2. እግዚአብሔር ንስሃ ገባ የሚለው ቃል የንስሃን ምንነት ለእኛ ለማሳየት እንጂእግዚአብሔር ሃሳቡን ስለሚቀየር አይደለም። እግዚአብሔር በሃሳቡ ፍጹምነው። (1.ቆሮ.10፥11፣ 2.ጢሞ.3፥17፣ ዘፍ.6፥6)

3. በግሪኩ ‘’ሜቴኔዎ” ማለት ንስሃ ማለት ነው። ቀጥተኛ ትርጉሙ የማያዳግምከስሜታዊ ነገሮች ሁሉ ነጻ የሆነ የአዕምሮ ለውጥ ማድረግ ማለት ነው።

4. በዕብራይስጡም ሆነ በግሪኩ ንስሃ የአዕምሮ ለውጥ ማለት እንደሆነእንመለታለን። የአዕምሮ ለውጥ አንድ ሰው አደረገ ማለት ንስሃ ገባ ማለትነው።

“ጨውና ብርሃን ናችሁ።” ማቴዎስ.5፥13-16 በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል

Page 3: 10. የንስሃ ዶክትሪን

ንስሃ

5. ለደህንነት ንስሃ መግባት ወይም ትክክለኛ የአዕምሮ ለውጥ ማድረግ አስፈላጊ ነው። ንስሃየምንገባው ደግሞ ስለ ኢየሱስና ስለ ትምህርቱና ስለ መንግስቱ ያለን አስተሰብን በመቀየርነው። (ማቴ.12፥41, ማር.1፥15, ሉቃ.13፥3,5, 15፥7,10, 16፥30-31, ሐዋ.17፥30, 20፥21,26፥20, ዕብ.12፥17, 2.ጴጥ.3፥9)

6. የማያምን ሰው አስቀድሞ ንስሃ የሚገባው ለትምህርቱ ሳይሆን ሰለ ጌታችን ኢየሱስንክርስቶስ ያለው አስተሳሰብ ላይ ነው።

7. በግሪኩ “ሜታኔዬ” ንስሃ የሚለው ቃል በአዲስ ኪዳን ውስጥ ለሚያምኑ ሰዎችም ተጽፎእንናገኘዋለን፦

1. ለመልካም ሥራ የሚሆን የአዕምሮ የአስተሳስን ለውጥ በአማኙ ላይ መምጣት እንዳለበት ለማሳትነው። ዕብ.6፥1

2. ከተሳሳተ ትምህርት ንስሃ እንዲገቡ የአዕምሮ ለውጥ የትምህርት የአስተሳስብ ለውጥ እንዲያደርጉለማዘዝ ነው። (2.ቆሮ.12፥21, ራዕይ.2፥5,11,22, 3፥19)

8. እግዚአብሔር ሹመት በመሾሙ፣ ደህነትን ለሰው በመስጠቱ፣ መንፈሳዊ ስጦታን ለሰውልጆች በመስጠቱ ንስሃ አይገባም (አይጸጸትም) ሃሳቡን አይቀይርም። (ሮሜ.11፥29,ዕብ.7፥21)

“ጨውና ብርሃን ናችሁ።” ማቴዎስ.5፥13-16 በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል

Page 4: 10. የንስሃ ዶክትሪን

ንስሃ

9. በአማርኛው መጽሐፍ ቅዱስ ተጸጸተ ተብለው የተጻፉት ሁሉ በዕብራይስጡበግሪኩ ሆነ በእግሊዘኛው ንስሃ የሚለውን ቃል ይይዛሉ። ስለዚህ ተጸጸተየሚለውን ቃል ስናገኝ የአዕምሮ ለውጥ አደረገ የሚለውን እንደሚይዝ ልናውቅይገባል።

10. ሰው ከቀደመ ሃሳቡና ድርጊቱ ስሜታዊ ተግባሮችን ሳይጨምር ንስሃ ይገባል።(ማቴ.21፥29,27፥3፣ሐዋ.20፥21፣ሮሜ.2፥4፣2.ቆሮ.7፥9-10፣ዕብ.6፥1,6፣2.ጴጥ.3.9)

11. የደህንነት ንስሃ አንድ ጊዜ ከተደረገ በኃላ ለሁል ጊዜ ነው እንጂ ሁልጊዜየደንነትን ንስሃ አይደረገም። (ሉቃ.15፥7)

12. ንስሃና ኑዛዜ በጣም የተለያዮ እንደመሆናቸው መጠን በሕጉም የተለያዮ የንስሃናየኑዛዜ መስዋዕቶችን እናገኛለን። (ዘሌ.2,3,4,5)

“ጨውና ብርሃን ናችሁ።” ማቴዎስ.5፥13-16 በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል