12
ጣፋጭ በስኳር ኮርፖሬሽን የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ :+251-(0)11-552-7475/6322 : +251-(0)11-515-1283 : 20034 Code 1000 A.A [email protected] www.etsugar.gov.et www.facebook.com/etsugar ራዕይ፡ በቀጣይ ዕድገት ላይ የተመሰረተና በአለም ተወዳዳሪ የሆነ የስኳር ኢንዱስትሪ መፍጠር ቅፅ 2. ቁጥር 1 መስከረም 2006 ዓ.ም ዜና መፅሄት ተወዳዳሪ የስኳር ኢንዱስትሪ መገንባት! Building Competitive sugar industry! በእድገትና ትራንስፎርሜሽን መርሃ ግብር በስኳር ልማት ዘርፍ ተይዞ የነበረው ዕቅድ አፈጻጸም አበረታች እንደሆነ በሚኒስትር ማዕረግ የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ አባይ ፀሃዬ ገለጹ፡፡ ዋና ዳይሬክተሩ ከነሐሴ 1/2005ዓ.ም ጀምሮ ለሦስት ቀናት የኮርፖሬሽኑ የ2005 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ2006 በጀት ዓመት የፊዚካልና የፋይናንስ ዕቅድ ውይይት በተካሄደበት ወቅት እንደገለጹት ባለፉት ሦስት የመርሃ ግብሩ ዓመታት የዘርፉ ዕቅድ በተገቢው የስኳር ልማት ዕቅድ አፈጻጸም አበረታች መሆኑ ተገለጸ የስኳር ኮርፖሬሽን ከፍተኛ አመራሮችና ሠራተኞች የታላቁ መሪን ራዕይ ለማሳካት በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ ገለጹ የስኳር ኮርፖሬሽን ከፍተኛ አመራሮችና ሠራተኞች እንዲሁም በአዲስ አበባ የሚገኙ የወንጂ/ሸዋ፣ የመተሃራ፣ የፊንጫኣና የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካዎች ላይዘን ጽ/ቤት ሠራተኞች የታላቁ መሪ የክቡር አቶ መለስ ዜናዊ የስኳር ልማት ራዕይን ለማሳካት በቁርጠኝነትና በትጋት እንደሚሰሩ ዝክረ መለስ 1ኛ አመት መታሰቢያን ባከበሩበት ወቅት ገለጹ፡፡ በኮርፖሬሽኑ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ነሐሴ 14 ቀን 2005ዓ.ም በተካሄደው መርሃ ግብር የክቡር አቶ መለስ ዜናዊ 1ኛ ዓመት መታሰቢያ “ቃልህን ጠብቀን ወደላቀ ደረጃ ለማድረስ ቃላችንን አድሰናል!” በሚል መሪ ቃልና በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል፡፡ የስኳር ምርትን በ2006 በጀት ዓመት ወደ 549 ሺህ ቶን ለማሳደግ ታቀደ • በምርት ዕድገቱ የአገር ውስጥ የስኳር ፍላጎትን በማሟላት የውጭ ምንዛሪን ማዳን እንደሚቻል ተጠቁሟል • ከ69 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎችም የሥራ እድል ይፈጠራል » ገጽ.3 » ገጽ.4 » ገጽ.4 የፋና ወጊው ዳግም ልደት ›› ገጽ. 8 የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ ››ገጽ. 10 በውስጥ ገፆች የአገሪቷን የስኳር ምርት ፍላጎት ለማሟላት በአመት በአማካይ በሶስት ነባር ፋብሪካዎች የሚመረተውን 300ሺህ ቶን ስኳር በ2006 በጀት ዓመት ወደ 549 ሺህ ቶን ለማሳደግ መታቀዱን በስኳር ኮርፖሬሽን የዕቅድና ፕሮጀክት ዘርፍ አስታወቀ፡፡

ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4

  • Upload
    meresaf

  • View
    927

  • Download
    40

Embed Size (px)

DESCRIPTION

ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 በስኳር ኮርፖሬሽን

Citation preview

Page 1: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4

ጣፋጭ

በስኳር ኮርፖሬሽን የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ :+251-(0)11-552-7475/6322 : +251-(0)11-515-1283 : 20034 Code 1000 [email protected] www.etsugar.gov.et www.facebook.com/etsugar

ራዕይ፡በቀጣይ ዕድገት ላይ የተመሰረተና በአለም ተወዳዳሪ የሆነ የስኳር ኢንዱስትሪ መፍጠር

ቅፅ 2. ቁጥር 1 መስከረም 2006 ዓ.ምዜና መፅሄትተወዳዳሪ የስኳር ኢንዱስትሪ መገንባት!

Building Competitive sugar industry!

በእድገትና ትራንስፎርሜሽን መርሃ ግብር በስኳር ልማት ዘርፍ ተይዞ የነበረው ዕቅድ አፈጻጸም አበረታች እንደሆነ በሚኒስትር ማዕረግ የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ አባይ ፀሃዬ ገለጹ፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ ከነሐሴ 1/2005ዓ.ም ጀምሮ ለሦስት ቀናት የኮርፖሬሽኑ የ2005 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ2006 በጀት ዓመት የፊዚካልና የፋይናንስ ዕቅድ ውይይት በተካሄደበት ወቅት እንደገለጹት ባለፉት ሦስት የመርሃ ግብሩ ዓመታት የዘርፉ ዕቅድ በተገቢው

የስኳር ልማት ዕቅድ አፈጻጸም አበረታች መሆኑ ተገለጸ

የስኳር ኮርፖሬሽን ከፍተኛ አመራሮችና ሠራተኞች የታላቁ መሪን ራዕይ ለማሳካት በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ ገለጹ

የስኳር ኮርፖሬሽን ከፍተኛ አመራሮችና ሠራተኞች እንዲሁም በአዲስ አበባ የሚገኙ የወንጂ/ሸዋ፣ የመተሃራ፣ የፊንጫኣና የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካዎች ላይዘን ጽ/ቤት ሠራተኞች የታላቁ መሪ የክቡር አቶ መለስ ዜናዊ የስኳር ልማት ራዕይን ለማሳካት በቁርጠኝነትና በትጋት እንደሚሰሩ ዝክረ መለስ 1ኛ አመት መታሰቢያን ባከበሩበት ወቅት ገለጹ፡፡

በኮርፖሬሽኑ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ነሐሴ 14 ቀን 2005ዓ.ም በተካሄደው መርሃ ግብር የክቡር አቶ መለስ ዜናዊ 1ኛ ዓመት መታሰቢያ “ቃልህን ጠብቀን ወደላቀ ደረጃ ለማድረስ ቃላችንን አድሰናል!” በሚል መሪ ቃልና በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል፡፡

የስኳር ምርትን በ2006 በጀት ዓመት ወደ 549 ሺህ ቶን ለማሳደግ ታቀደ• በምርት ዕድገቱ የአገር ውስጥ የስኳር ፍላጎትን በማሟላት የውጭ ምንዛሪን ማዳን እንደሚቻል ተጠቁሟል• ከ69 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎችም የሥራ እድል ይፈጠራል

» ገጽ.3

» ገጽ.4

» ገጽ.4

የፋና ወጊው ዳግም ልደት

›› ገጽ. 8

የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ

››ገጽ. 10

በውስጥ ገፆች

የአገሪቷን የስኳር ምርት ፍላጎት ለማሟላት በአመት በአማካይ በሶስት ነባር ፋብሪካዎች የሚመረተውን 300ሺህ ቶን ስኳር በ2006 በጀት ዓመት ወደ 549 ሺህ ቶን ለማሳደግ መታቀዱን በስኳር ኮርፖሬሽን የዕቅድና ፕሮጀክት ዘርፍ አስታወቀ፡፡

Page 2: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4

ዜና መፅሄት በስኳር ኮርፖሬሽን ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት

ገፅ2

ww

w.etsugar.gov.et || w

ww

.facebook.com/etsugar

ጣፋጭ

ለኢትዮጵያ ህዳሴ ታላቅ መሰረት የሆነውን የእድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ለማሳካት የኢፌዴሪ መንግሥት ዕድገትን የሚያፋጥኑና የገቢ ምርቶችን የሚተኩ ግዙፍ የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶችን ቀርጾ እየተገበረ ይገኛል፡፡ ከእነዚህ ፕሮጀክቶች መካከልም የስኳር ልማት ዘርፍ ከሚያስገኘው በርካታ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጠቀሜታዎች አንጻር የተሰጠው ትኩረት ከፍተኛ ነው፡፡

በአምስት አመቱ መርሃ ግብር 10 አዳዲስ የስኳር ፋብሪካዎችን በመገንባትና የሦስት ነባር ስኳር ፋብሪካዎችን የማስፋፊያ ስራ በማጠናቀቅ አገሪቱ በዓመት በአማካይ የምታመርተውን 300ሺህ ቶን የስኳር ምርት ወደ 2.25 ሚሊዮን ቶን ለማሳደግ ታልሞ መጠነ ሰፊ የልማት ሥራዎች በመከናወን ላይ ናቸው፡፡

የስኳር ልማት ፕሮጀክቶች የአገር ውስጥ የስኳር ምርት ፍላጎትን ከማሟላት ባሻገር ለዜጎች ሰፊ የስራ ዕድል በመፍጠር፣ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በመተካት፣ የውጭ ምንዛሬ በማስገኘት፣ የኤሌክትሪክ ኃይል በማመንጨት፣ ኤታኖል በስፋት በማምረት፣ በልማት ተረስተው የነበሩ ቆላማ አካባቢዎችን ወደ ከፍተኛ ዕድገት በማሸጋገር እና የሕዝብን ፍትሃዊ የልማት ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ለአገሪቱ የኢኮኖሚ እመርታ የአንበሳውን ድርሻ እንደሚያበረክቱ ይታመናል፡፡

ስኳር ኮርፖሬሽን ባለፉት ሦስት ዓመታት ባካሄዳቸው ዘርፈ ብዙ ተግባራት የማስፋፊያ ሥራቸው የተጠናቀቀው የወንጂ/ሸዋና የፊንጫኣ ስኳር ፋብሪካዎች በ2006ዓ.ም ተጨማሪ ምርት የሚያመርቱ ሲሆን፣ የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታው በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘው የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካም ከ2006 በጀት አመት አጋማሽ ጀምሮ ወደ ምርት ይገባል፡፡

በሌላ በኩል ግንባታቸው የተጀመረው የኩራዝ አንድ፣ የከሰም እና የጣና በለስ አንድና ሁለት በድምሩ የአራት አዳዲስ ስኳር ፋብሪካዎች ግንባታ በ2006 ዓ.ም ተጠናቆ በ2007 ዓ.ም ወደ ምርት የሚገቡ ሲሆን፣ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 እና 3 ስኳር ፋብሪካዎች እንዲሁም የወልቃይት ስኳር ፋብሪካ ግንባታዎችም በ2006ዓ.ም ይጀመራሉ፡፡ በመሆኑም በ2006ዓ.ም የስኳር ፍላጎታችንን በራሳችን አቅም ከማሟላት ባለፈ አዳዲሶቹ ፕሮጀክቶች ሲጠናቀቁ በዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን መጨረሻ ጀምሮ ምርቱን ወደ ውጭ ገበያ ማቅረብ እንጀምራለን፡፡

ከስኳር ልማቱ ጎን ለጎንም የሕዝብን የልማት ተጠቃሚነት ከማስፋትና ከማረጋገጥ አኳያ ውጤታማ ተግባራትን ለማከናወን ተችሏል፡፡ በስኳር ልማቱ ሳቢያ ከቀያቸው ከሚነሱ ዜጎች ጋር በተካሄደ ሰፊ ምክክርና መግባባት ለንብረታቸውና ምርታቸው በቂ ካሳ የተሰጣቸው ሲሆን፣ በመስኖ የሚለማ ምትክ መሬትም ተመቻችቶላቸዋል፡፡ እንዲሁም በሚሰፍሩባቸውና በመንደር በሚሰባሰቡባቸው አካባቢዎች የማህበራዊ ተቋማትና የመሰረተ ልማት አውታሮች ተገንብቶላቸዋል፡፡ ባህላቸው፣ እምነታቸውና አኗኗራቸውም ተጠብቆላቸዋል፡፡ ከዚህ ባሻገር ልማቱ በሚካሄድባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ የአርብቶ አደር እና አርሶ አደር ልጆችን በተለያዩ የሙያ መስኮች በማሰልጠን በፕሮጀክቶቹ በቋሚነት ተቀጥረው የሥራ ዕድል እንዲያገኙ እየተደረገ ነው፡፡

መንግሥት መላውን ሕዝብ ከጎኑ አሰልፎ የፀረ ድህነት ትግሉን እያቀጣጠለ እና የሕዝቡን የዘመናት የልማት ተጠቃሚነት ጥያቄ ደረጃ በደረጃ እየፈታ በሚገኝበት በዚህ ወቅት፣ የግል ጥቅማቸው የተነካባቸው ፀረ ልማት ኃይሎች በአካባቢው የሚካሄደውን ልማት ሆን ብለው ለማደናቀፍ እየጣሩ ይገኛሉ፡፡ ስለሆነም ሕዝቡ እንደከዚህ ቀደም ጊዜያቶች ሁሉ የእነዚህን ኃይሎች መሰረተ ቢስ ወሬ በማክሸፍ ለልማቱ ስኬት እያደረገ ያለውን ርብርብ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት በዚህ አጋጣሚ ለማሳሰብ እወዳለሁ፡፡

በቀጣይ በስኳር ልማት ዘርፍ የተጀመሩትን የልማት ሥራዎች በፍጥነትና በተሻለ ሁኔታ መፈጸም እንዲቻል ከህንድ፣ ከብራዚልና ከሌሎች የስኳር አምራች አገራት ምርጥ ተሞክሮ አጥንተናል፤ ያገኘነውን ልምድም ለአገራችን በሚጠቅም መልኩ ቀምረን የዘርፉን ዕቅድ፣ አደረጃጀት፣ አሠራር እና የሰው ኃይል የስልጠና አቅጣጫ አስተካክለን ወደ ስራ ገብተናል፡፡ በተጨማሪም በስኳር ፋብሪካዎቻችን ከፍተኛ ለውጥ እንዲመጣ ያስቻለውን የካይዘን የአመራር ፍልስፍና በ2006 በጀት ዓመት በተጠናከረና በሚፈለገው ደረጃ ለመተግበር አቅደን እየተንቀሳቀስን እንገኛለን፡፡

ኮርፖሬሽኑ በቂ የሰው ኃይል፣ በቂ የፋይናንስ አቅምና የመሰረተ ልማት አውታሮች በሌሉበት ሁኔታ የተጀመሩትን አዳዲስና ግዙፍ የስኳር ልማት ፕሮጀክቶች ከግብ ለማድረስ ከፌዴራልና ከክልል መንግሥታት የባለድርሻ አካላት ጋር ባደረገው የተቀናጀ አሠራር ባለፉት ሦስት አመታት በዘርፉ የተመዘገበው ውጤት አበረታች ነው፡፡

ለተገኘው ውጤት አስተዋጽኦ ላበረከቱ የስኳር ኮርፖሬሽን፣ የስኳር ፋብሪካዎችና የስኳር ልማት ፕሮጀክቶች አመራሮችና ሠራተኞች እንዲሁም ለፌደራልና ለክልል መንግሥታት የባለድርሻ አካላትና የልማቱ ተባባሪ ለሆነው መላው ሕዝባችን ምስጋና እያቀረብኩ፣ አዲሱ አመት የነገዋን በኢኮኖሚ የበለፀገች ኢትዮጵያን ለማየት ስኬታማ ሥራዎችን የምናከናውንበት ዘመን እንዲሆንልን እመኛለሁ፡፡

የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር መልዕክት

ክቡር አቶ አባይ ፀሃዬ በሚኒስትር ማዕረግ የስኳር ኮርፖሬሽን

ዋና ዳይሬክተር

Page 3: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4

ገፅ3

ጣፋጭዜና መፅሄት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ

የስኳር ልማት ዕቅድ አፈጻጸም ...

ሁኔታ መፈጸም በመቻሉ የተገኘው ውጤት አበረታች መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በአምስቱ አመት መርሃ ግብር ግዙፍ አዳዲስ የስኳር ልማት ፕሮጀክቶችን በተለያዩ የአገሪቷ ክልሎች ለመጀመር ሲታሰብ ልማቱ በሚካሄድባቸው አካባቢዎች ምንም አይነት የመንገድ፣ የኤሌክትሪክ ኃይልና የስልክ መሰረተ ልማት አውታሮች በሌሉበት ሁኔታ እንደነበርና የአገር ውስጥ ኮንትራክተሮችም በዘርፉ ልምድ እንዳልነበራቸው ዋና ዳይሬክተሩ አስረድተዋል፡፡ እነዚህ ተግዳሮቶችም በመርሃ ግብሩ አፈጻጸም ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳደራቸውን ሳይጠቅሱ አላለፉም፡፡

ከዚህ አንጻር ለፕሮጀክቶቹ ተግባራዊነት አስፈላጊ ሁኔታዎችን ለማመቻቸት የዕቅዱ የመጀመሪያ ዓመት ሙሉ በሙሉ የቅድመ ዝግጅት ጊዜ እንደነበር ያስታወሱት አቶ አባይ፣ ሥራዎች በከፊል መከናወን የጀመሩት ከ2004ዓ.ም ጀምሮ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

አዳዲስ የስኳር ልማት ፕሮጀክቶች ያሉበትን ደረጃ አስመልክተው ሲያብራሩም፣ ግንባታቸው የተጀመረው የኩራዝ አንድ፣ የከሰም እና የጣና በለስ አንድና ሁለት በድምሩ የአራት አዳዲስ ስኳር ፋብሪካዎች ግንባታ በ2006 ዓ.ም ተጠናቆ በ2007 ዓ.ም ማምረት ይጀምራሉ ብለዋል። የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 እና 3 ስኳር ፋብሪካዎች እንዲሁም

የወልቃይት ስኳር ፋብሪካ ግንባታም በ2006ዓ.ም እንደሚጀመር አክለው ገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩል የማስፋፊያ ሥራቸው የተጠናቀቀው የወንጂ/ሸዋና የፊንጫኣ ስኳር ፋብሪካዎች በ2006ዓ.ም ተጨማሪ ምርት እንደሚያመርቱና የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታው በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘው የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካም ከ2006 በጀት ዓመት አጋማሽ ጀምሮ ወደ ምርት እንደሚገባ አስታውቀዋል፡፡ እነዚህ ሶስቱ ፋብሪካዎች በተሟላ መልክ ማምረት ሲጀምሩ የአገር ውስጥ የስኳር ፍላጎትን ከማሟላት ባሻገር መንግሥት በየዓመቱ ከሁለት ሚሊዮን ኩንታል ስኳር በላይ በውጭ ምንዛሪ እየገዛ የሚያስገባበትን ወጪ ማዳን እንደሚቻል ጠቁመዋል፡፡

የዘርፉን የልማት ሥራዎች በተቀናጀ መልኩ ከግብ ለማድረስ በ2006 በጀት ዓመት የፋብሪካዎች ግንባታ፣ የቤቶች ግንባታ፣ የግድብና የመስኖ ግንባታ፣ የአገዳ ተክል ልማት እንዲሁም በፕሮጀክቶች አካባቢ ለሕዝብ የሚሰሩ ሥራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ነው ያሉት፡፡

ከዘርፉ አዲስነትና ስፋት የተነሳ ሥራው ከክልል መንግሥታት፣ ከፌደራል መ/ቤቶች የባለድርሻ አካላት፣ ከአገር ውስጥና ከውጭ ኩባንያዎች እንዲሁም የስኳር ፋብሪካዎችና

ፕሮጀክቶች በሚገኙባቸው አካባቢዎች ከሚኖሩ ሕዝቦች ጋር ተቀናጅቶ መስራትን እንደሚጠይቅ አቶ አባይ አመልክተዋል፡፡

በዘርፉ ካጋጠሙ ተግዳሮቶች መካከል የኮርፖሬሽኑ አመራሮችና ሙያተኞች እንዲሁም የባለድርሻ አካላትና የኮንትራክተሮች የመፈጸም አቅም ማነስ ዋነኛው መሆኑን አመልክተው፣ የአመራርና የክህሎት ክፍተቶችን ለመሙላት በአገር ውስጥና በውጪ ባለሙያዎች የሚሰጡ የተለያዩ ሥልጠናዎችን ለማዘጋጀት እና ካይዘንን በተጠናከረና በሚፈለገው ደረጃ ለመተግበር በ2006 በጀት ዓመት መታቀዱን አስታውቀዋል፡፡

በመጨረሻም በዘርፉ በ2005 በጀት ዓመት ታቅደው ያልተፈጸሙ ተግባራትን በ2006 በጀት ዓመት ለማጠናቀቅና የ2006 በጀት ዓመት ዕቅድን ለማሳካት የኮርፖሬሽኑ አመራርና ሠራተኞች በላቀ የሥራ ተነሳሽነትና ቁርጠኝነት መስራት እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል፡፡

ለሶስት ቀናት በተካሄደው ስብሰባ የኮርፖሬሽኑ የ2005 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም እና የ2006 በጀት ዓመት የፊዚካልና የፋይናንስ ዕቅድ በኮርፖሬሽኑ የዕቅድና ፕሮጀክት ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ሽመልስ ከበደ በዝርዝር ቀርቦ በሠራተኞች ሰፊ ውይይት ተካሄዶበታል፡፡

የ 2005 ዕቅድ አፈጻጸምና የ 2006 ዕቅድ በአመራሩና በሠራተኛው ዘንድ ተነሳሽነትን ፈጥረዋል

Page 4: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4

የስኳር ኮርፖሬሽን ከፍተኛ አመራሮችና ሠራተኞች...

በዕለቱ ታላቁን መሪ ለማስታወስ የጧፍ ማብራት ሥነ ሥርዓትና የህሊና ፀሎት የተደረገ ሲሆን፣ የአቶ መለስ የስኳር ኢንዱስትሪ ራዕይን መሰረት አድርገው በዘርፉ እየተከናወኑ የሚገኙ ሥራዎችን የሚያስቃኝ ዘጋቢ ፊልምም ቀርቧል፡፡

በመርሃ ግብሩ ላይ የኮርፖሬሽኑ የኦፕሬሽን ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ወዮ ሮባ ባስተላለፉት መልእክት አቶ መለስ በአገሪቷ የስኳር ልማት በስፋት እንዲጀመርና እንዲስፋፋ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱ መሪ እንደነበሩ አስታውሰው፤ የእሳቸውን ራዕይ ለማሳካት በዘርፉ የተጀመሩ ሥራዎችን በላቀ ደረጃና በተሻለ ፍጥነት ከፍጻሜ ለማድረስ ቃል እንገባለን ብለዋል፡፡

አክለውም ታላቁ መሪ አገሪቷ ወደ ከፍተኛ የእድገት ምዕራፍ እንድትሸጋገር ያከናወኗቸው በርካታ ውጤታማ ሥራዎች ሁልጊዜም ሲታወሱና ሲወደሱ እንደሚኖሩ ገልጸው፣ በቀጣይም ራዕያቸውን ከግብ በማድረስ የኢትዮጵያን ህዳሴ ለማረጋገጥ ከኮርፖሬሽኑ ከፍተኛ አመራሮችና ሠራተኞች የላቀ ድርሻ መወጣት እንደሚጠበቅ አሳስበዋል፡፡

በመጨረሻም የመለስ ዜናዊ ፋውንዴሽን የጥናትና የምርምር ማዕከል ለማቋቋም የሚደረገውን እንቅስቃሴ አመራሩና ሠራተኛው በእውቀቱና በገንዘቡ እንዲደግፍ ጥሪ ተደርጓል፡፡

የስኳር ምርትን በ2006 በጀት .....

በስኳር ልማት ለሕዝብ የሚከናወኑ

ሥራዎች የ2005 እቅድ አፈጻጸምና

የ2006 እቅድ ውይይት ተካሄደ

የዘርፉ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ሽመልስ ከበደ ለዜና መጽሔቱ ዝግጅት ክፍል እንዳስታወቁት፣ ለምርቱ እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚኖራቸው የወንጂ/ሸዋና የፊንጫኣ ስኳር ፋብሪካዎች የማስፋፊያ ሥራዎች በመጠናቀቃቸው በ2006ዓ.ም በጥቅምት ወር ወደ ተጨማሪ ምርት የሚገቡ ሲሆን፣ የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታው በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘው የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካም ከታህሳስ 2006ዓ.ም ጀምሮ ማምረት ይጀምራል፡፡

በዚህ መሰረት በ2006 በጀት አመት ወንጂ/ሸዋ 95,000 ቶን ስኳር፣ ፊንጫኣ 200,000 ቶን ስኳር፣ ተንዳሆ 123,600 ቶን ስኳር እንዲሁም መተሐራ 130,000 ቶን ስኳር እንደሚያመርቱ ይጠበቃል ያሉት አቶ ሽመልስ፣ እነዚህ ፋብሪካዎች በጠቅላላው የሚያመርቱት የስኳር መጠን የአገሪቷን የስኳር ፍላጎት ከማሟላት በተጨማሪ በየዓመቱ ምርቱን ከውጪ አገር ለማስገባት ይወጣ የነበረውን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ያስቀራል ብለዋል፡፡

በአዳዲስ የስኳር ልማት ፕሮጀክቶችና በነባር ስኳር ፋብሪካዎች የሚፈጠር የሥራ ዕድልን በተመለከተም በ2006 በጀት ዓመት በስኳር ኮርፖሬሽን፣ በኮንትራክተሮችና በጥቃቅንና አነስተኛ ማህበራት አማካኝነት ለ49,059 ወንዶችና ለ20,195 ሴቶች በጠቅላላው ለ69,254 ዜጎች ቋሚ፣ ጊዜያዊና የኮንትራት የሥራ ዕድል እንደሚፈጠር ገልጸዋል፡፡

አቶ ሽመልስ ከበደ የዕቅድና ፕሮጀክት ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር

የታላቁ መሪ የክቡር አቶ መለስ ዜናዊ የስኳር ልማት

ራዕይን እናሳካለን!

ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት 4

ቅፅ 2. ቁጥር 1 | መስከረም 2006

Page 5: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4

5

በስኳር ልማት ለሕዝብ የሚከናወኑ

ሥራዎች የ2005 እቅድ አፈጻጸምና

የ2006 እቅድ ውይይት ተካሄደ

የስኳር ኮርፖሬሽን ሠራተኞች

ለአረንጓዴ ልማት ስትራቴጂ

ተግባራዊነት መዘጋጀታቸውን ገለጹ

ስልጠና ሲሰጥ“አረንጓዴ ቦታዎችን ለመጪው ትውልድ እናስረክብ!”

በነባር ስኳር ፋብሪካዎችና በአዳዲስ የስኳር ልማት ፕሮጀክቶች ለሕዝብ የሚከናወኑ ሥራዎችን አስመልክቶ የ2005 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ2006 በጀት ዓመት እቅድ ውይይት ከሐምሌ 26 እስከ 30/2005 ዓ.ም ድረስ በደብረ ዘይት ስራ አመራር ኢንስቲትዩት ተካሄደ፡፡

የስኳር ኮርፖሬሽን የሕዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ባዘጋጀው በዚህ መድረክ ከሁሉም ነባር ስኳር ፋብሪካዎችና አዳዲስ የስኳር ልማት ፕሮጀክቶች የተውጣጡ ምክትል ስራ አስኪያጆች፣ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች በጠቅላላው 20 ተሳታፊዎች ተገኝተዋል፡፡ በወቅቱ በ2005 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም ላይ የታዩ ጠንካራና ደካማ ጎኖች ተለይተው ሰፊ ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን፣ በ2006 በጀት ዓመት በየፋብሪካዎቹና ፕሮጀክቶቹ የሚተገበሩ የሕዝብ ሥራዎች መነሻ እቅድ ቀርቦም ውይይት ተካሄዷል፡፡

በሌላ በኩል በሀብትና ንብረት ግመታና ካሳ ክፍያ ሥርዓት አዋጅና ደንብ፣ በመልሶ ማቋቋም፣ በስራ ዕድል ፈጠራና ለጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ማህበራት ድጋፍ አሰጠጥ ዙሪያ እንዲሁም ስለ አውትግሮወርስ ልማት ምንነት ስልጠናዎች ተሰጥተዋል፡፡

በመድረኩ ማጠቃለያም በቢሾፍቱ ከተማ ወደ መካከለኛ ባለሀብትነት የተሸጋገሩ የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት የስራ እንቅስቃሴ ተጎብኝቷል፡፡ ከልምድ ልውውጡ የተገኘው ተሞክሮም በቀጣይ በፋብሪካዎችና በፕሮጀክቶች ከስራ እድል ፈጠራ አኳያ ለማህበራት ለሚደረገው ድጋፍ ትምህርት መስጠቱን ተሳታፊዎቹ ተናግረዋል፡፡

የስኳር ኮርፖሬሽን ሠራተኞች የደን ችግኞችን በመትከልና በመንከባከብ አገሪቷ ለነደፈችው የአረንጓዴ ልማት ስትራቴጂ ተግባራዊነት የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ለማበርከት መዘጋጀታቸውን ገለጹ፡፡

“አረንጓዴ ቦታዎችን ለመጪው ትውልድ እናስረክብ!” በሚል መሪ ቃል ሐምሌ 12/2005ዓ.ም ሲ ኤም ሲ አሉላ ጫካ በተባለ አካባቢ ችግኞችን የተከሉት የኮርፖሬሽኑ ሠራተኞች አገራዊና ወቅታዊ ጥሪን በማክበር የዜግነት ግዴታቸውን ለመወጣት መነሳሳታቸውን አስታውቀዋል፡፡

በመርሃ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የችግኝ ተከላ አስተባባሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ ሠናይት በላይ እንደተናገሩት ኮርፖሬሽኑ በስኳር ኢንዱስትሪ ዘርፍ እያካሄደ ያለውን መጠነ ሰፊ የልማት እንቅስቃሴ ዘላቂና አስተማማኝ ለማድረግ በአካባቢ ጥበቃና ልማት ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ የውይይት መድረኮችና የአሰልጣኞች ሥልጠና ለፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች እንዲዘጋጁ አድርጓል፡፡

የስኳር ልማቱ በሚካሄድባቸው አካባቢዎች የችግኝ ጣቢያዎችን በማቋቋምና ከአካባቢው ህብረተሰብ ጋር በመተባበር የችግኝ ተከላ በመከናወን ላይ እንደሚገኝ የገለጹት ወ/ሮ ሠናይት በነባር ስኳር ፋብሪካዎች ለሰደድ እሳት ቁጥጥር ስራ እንዲሁም አካባቢዎቹን ለማስዋብና አረንጓዴ ቦታዎችን ለመንከባከብ ተግባራትም ትኩረት መደረጉን አመልክተዋል፡፡

በመጨረሻም የኮርፖሬሽኑ ሠራተኞች በቀጣይ ጊዜያቶች ተጨማሪ ችግኞችን በመትከልና በመንከባከብ የታላቁ መሪ የክቡር አቶ መለስ ዜናዊን የአረንጓዴ ልማት ስትራተጂን ለማስቀጠል በቁርጠኝነት እንደሚንቀሳቀሱ ቃል ገብተዋል፡፡

በስኳር ኮርፖሬሽን የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ

ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት

Page 6: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4

Just Another Newsletter Title

የፊንጫኣ ስኳር ፋብሪካ የካይዘን ሥራ አመራር ፍልስፍናን በሰራተኛው ዘንድ በማስረጽ ፣ሰፊ ንቅናቄ በመፍጠር እና በመተግበር ወጪ መቀነስ መቻሉ ተገለጸ ፡፡

የፋብሪካው የሕዝብ ግንኙነት ክፍል በላከው ሪፖርት እንዳመለከተው ፋብሪካው የካይዘን ሥራ አመራር ፍልስፍናን ተግባራዊ በማድረጉና በፍልስፍናውና አተገባበሩ ዙሪያ ተከታታይ የስልጠና እና የውይይት መድረኮችን በማካሄዱ እንዲሁም የነበሩ ተግዳሮቶችና ችግሮች በሠራተኛውና በአመራሩ ለይቶ በማውጣትና መፍትሄዎችን በመቀመሩ በድርጅቱ ሠራተኞች ዘንድ የተፈጠረው የሥራ መነሳሳትና የውድድር መንፈስ ፣ የአመለካከት ለውጥ ፣የቡድን ስሜት ፣ የሥራ ሰዓት አከባበር ሁኔታ ፣ የብክነት አወጋገድና የወጪ ቆጣቢነት መንፈስ እያደገ መጥቷል፡፡

በፋብሪካው የተለያዩ የስራ ክፍሎች የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ እየታየ ያለው የውድድር መንፈስ ከፍተኛ እንደሆነና በተለይ በመስክ መሳሪያዎች ጥገና የስራ ክፍል በአጭር ጊዜ ውስጥ ከአስራ ስድስት ያላነሱ ወጪ ቆጣቢ ተግባራት ተከናውነው ስራ ላይ እንዲውሉ መደረጉ በሌሎች የስራ ክፍሎች ዘንድ የመነሳሳት ስሜት መፍጠሩ ታውቋል፡፡

ከእነዚህ በካይዘን ሥራ አመራር ፍልስፍና ትግበራ

በካይዘን ትግበራ ወጪን መቀነስ

ተቻለ

አማካይነት ከተመዘገቡ አበረታች ውጤቶች መካከል የኩትኳቶና የማዳበሪያ ርጭት ስራን በጣምራ ማከናወን የሚችል ማሽን ሞዲፋይ የማድረግ እና ከአስር ዓመት በላይ አገልግሎት ሳይሰጥ የተቀመጠ የአይሱዙ መኪናን የሞዲፊክ ስራዎች በመስራት ጠግኖ ለአገልግሎት እንዲውል ማድረግ በፋብሪካው ከተመዘገቡ ውጤቶች መካከል በአቢይነት የሚጠቀሱ መሆናቸውን የሕዝብ ግንኙነት ክፍሉ ዘገባ አመልክቷል፡፡ ይሄው የመስክ መሳሪያዎች ጥገና የሥራ ክፍል ያስመዘገበው አርአያነት ያለው ውጤትም በፋብሪካው የተለያዩ የስራ ክፍሎች እንዲቀጣጠል የእርስ በእርስ ልምድ ልውውጥ የማድረግ ስራ ፋብሪካው እያከናወነ ይገኛል፡፡ በዚህ የስራ ክፍል

ብቻ በተገኙ አበረታች ውጤቶች ከ6.5 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ መቆጠብ መቻሉ ታውቋል፡፡

በተመሳሳይም የካይዘን ሥራ አመራር ፍልስፍናን በጤናው ዘርፍ ተግባራዊ በማድረግ በፊንጫኣ ስኳር ፋብሪካ ጤና ጣቢያ በስድስት ወራት ውስጥ ብቻ ከ1.8 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ መቆጠብ መቻሉን፤ በዚህም የተመላላሽ እና ተኝቶ ታካሚዎች እንዲሁም የህክምና ፈቃድ ጠያቂዎች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ መቀነሱን እና በወባ ትንኝ መከላከል ዙሪያ የተሻለ አፈጻጸም መመዝገቡን ዘገባው አያይዞ አመልክቷል፡፡

የካይዘን ውጤት የኩትኳቶ እና የማዳበሪያ

ርጭት ስራን በጣምራ የሚሰራ ማሽን

የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ሠራተኞችና ቤተሰቦቻቸው ጤናቸው የተጠበቀ እንዲሆን በማድረግ የፋብሪካውን ምርትና ምርታማነት ከፍ ማድረግ የሚያስችል የጤና ኤክስቴሽን ፓኬጅ ትግበራ እቅድ ይፋ ሆነ፡፡

በተቋሙ ልዩ ልዩ መኖሪያ ካምፖች ከሠራተኞችና ቤተሰቦቻቸው ጋር በተካሄዱ የውይይት መድረኮች ላይ እንደተመለከተው የተቋሙ የጤና ኤክስቴሽን ፓኬጅን ለማስፈፀም የወጣው እቅድ የአካባቢው ነዋሪን ጤና በመጠበቅ ምርትና ምርታማነቱ እንዲጨምር የሚያስችልና በመከላከል ላይ ያተኮረ ነው፡፡

በአካባቢ ጤና አገልግሎት ዙሪያ ያሉት ችግሮች የተቋሙ ሆስፒታልና በየካምፑ የሚገኙ ክሊኒኮች በመኖራቸው ብቻ እንደማይፈቱም በውይይቱ መገለጹን የፋብሪካው የሕዝብ ግንኙነት ክፍል በላከው ዘገባ ገልጿል፡፡ይልቁንም በመኖሪያ አካባቢዎች የአንድ ለአምስት አደረጃጀት በመፍጠርና 16ቱን የጤና ፓኬጆች በተቋሙ ውስጥ አሟልቶ በመተግበር ለኑሮ ምቹና ጽዱ አካባቢን ፈጥሮ ምርታማ የልማት ተቋም እንዲሆን ማስቻል ተገቢነቱ ተመልክቷል፡፡

በየመድረኮቹ እንደተብራራው ከሆነ የእቅዱ አፈጻጸም በዋናዎቹ የጤና ኤክስቴሽን ፓኬጆች ላይ ማለትም የቤተሰብ ጤና አጠባበቅ፣ ኤች.አይቪ/ኤድስ፣ ወባ እና ቬተር ወለድ በሽታዎችን የመከላከል፣ የመኖሪያና የሥራ አካባቢን ንጽህና እንዲሁም የጤና አጠባበቅ ሥነምግባር ትምህርትና አገልግሎት መስጠት ላይ ያተኩራል፡፡ እቅዱን ተግባራዊ ለማድረግም በተቋሙ ውስጥ በሚገኙ ስምንት የመኖሪያ ካምፖች ውስጥ 1055 የአንድ ለአምስት ቡድኖች መደራጀታቸውን ክፍሉ በላከው ሪፖርት ተመልክቷል፡፡

የውይይቱ ተሳታፊዎች የጤና ኤክስቴሽን ፓኬጆችን በተቋሙ ለመተግበር እጅግ የዘገየ መሆኑን ገልፀው ሆኖም አሁን ለተጀመረው እንቅስቃሴ ተግባራዊ ርብርብ ለማድረግ ዝግጁነታቸውን አረጋግጠዋል፡፡መንግስት ለዜጐች ጤና አጠባበቅ ይረዳ ዘንድ የዘረጋቸው መርሃ ግብሮችም በአገሪቱ ውስጥ ተጨባጭ ለውጦች ማምጣቸውን የገለፁት ሠራተኞችና ቤተሰቦቻቸው በተቋማቸው ውስጥ የፓኬጁ ትግበራ መጀመሩ መጠነ ሰፊ ጠቀሜታ እንደሚኖረው ገልጸዋል፡፡

በተቋሙ የጤና ኤክስቴሽን ፓኬጅ አተገባበር እቅድ ይፋ ሆነ

ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት 6

ቅፅ 2. ቁጥር 1 | መስከረም 2006

Page 7: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4

7

የመተሃራ ስኳር ፋብሪካ በ2006 የምርት ዘመን 1 ነጥብ 3 ሚሊዮን ኩንታል ስኳር በማምረት የፋብሪካውን ወርቃማ የምርት ዘመን ብቃት መመለስ እንዲችል ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ፡፡

የተቋሙ አመራሮችና ሰራተኞች የ2005 በጀት ዓመት እንደተጠናቀቀ ባካሄዱት የጋራ ምክክር እንደተገለፀው በ2006 ዓ.ም የምርት ዘመን ከ7000 ሄክታር ማሳ ላይ የሸንኮራ አገዳ ተቆርጦ ለፋብሪካዉ ግብአት በማቅረብ፣ 1 ነጥብ 3 ሚሊዮን ስኳርና ወደ 10 ሚሊዮን ሊትር የሚጠጋ ኢታኖል ለማምረት ዕቅድ ተይዟል ፡፡ ዕቅዱን በትክክል ለመተግበር የሚያስችሉ የሰው ኃይልና ሌሎች ግብዓቶችን የማሟላት ፤የተዛቡ አመለካከቶችንና የክህሎት ክፍተቶችን የማስተካከል ሰፊ ስራዎችም ከወዲሁ እንደሚከናወኑ በምክክር መድረኮቹ መገለጹን የፋብሪካው የሕዝብ ግንኙነት በላከው ሪፖርት አመልክቷል፡፡

ፋብሪካው ከሐምሌ 2005 ዓ.ም አጋማሽ እስከ ጥቅምት 2006 ዓ.ም ድረስ በሚያካሂደው የመደበኛ ጥገናና የማሻሻያ ስራዎች በዋናነት በቦይለር ቁጥር አራት የታነደም ኤ ኬን ሃንድሊንግና ሚል ፕላንት እንዲሁም የዲፊዩዘር

ፋብሪካው በምርት ዘመኑ 1 ነጥብ 3 ሚሊዮን ኩንታል ስኳር ለማምረት አቅዷል

የዘር አገዳ ዝግጅት

ፕላንቶች ላይ ከፍተኛ የማሻሻያ ስራዎች እንደሚከናወኑ ታውቋል ፡፡

ካለፉት ጥቂት ዓመታት ወዲህ ማሽቆልቆል የታየበትን የፋብሪካውን የማምረት አቅም ወደነበረበት ወርቃማ የምርት ዘመን ለመመለስ አመራሩና ሰራተኛው ቁጭትና ተነሳሽነቱ ከፍተኛ መሆኑ በውይይት መድረኩ ላይ ተንጸባርቋል ፡፡

የክረምት ወቅት ጥገናን በብቃትና በቁጭት በአጭር ጊዜ ውስጥ በማጠናቀቅ እንዲሁም

ለምርታማነት እንቅፋት የሆኑ ውስጣዊ የአመለካከት ችግሮቹን በመመከት የተቋሙን ግብ እንደሚያሳካ ሰራተኛው በጋራ የወሰነና ያለምንም ትርፍ ሰዓት ክፍያ በእረፍት ቀንም ጭምር ገብቶ እየሰራ መሆኑን የሕዝብ ግንኙነት ክፍሉ በሪፖርቱ ጠቁሞ የፋብሪካው ሰራተኞችና አመራሮች ለተቋማዊ ምርታማነት ማነስ ማነቆ ናቸው ያሏቸውን አሉታዊ አመለካከቶች በፅኑ ለመዋጋትና የተቋማቸውን ወርቃማ የምርት ዘመን ለማደስ ቃል መግባታቸውን አመልክቷል፡፡

ፕሮጀክቱ የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ስርጭትን ለመግታት እየሰራ ነው

የአርጆ ዴዴሳ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ሰራተኞችና የአካባቢው ነዋሪዎች እራሳቸውን ከኤች.አይ.ቪ/ኤድስ እንዲጠብቁ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ በማካሄድ ላይ መሆኑ ተገለጸ፡፡

የፕሮጀክት ጽ/ቤቱን የሰው ሀብት ስራ አመራር ዘርፍ ጠቅሶ የፕሮጀክቱ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል እንዳመለከተው ቀደም ሲል ከቋሚና ጊዜያዊ ሠራተኞች ለተውጣጡ 18 ሠራተኞች ከሰኔ 22 እስከ ሰኔ 23 ቀን 2005 ዓ.ም ለሁለት ቀናት የአቻ ለአቻ አወያይ ስልጠና ከተሰጣቸው በኋላ ከሐምሌ ወር 2005 ዓ.ም ጀምሮ 1ለ25 በተባለው አደረጃጀት መሰረት በጊዜያዊ ሰራተኞች መኖሪያ ሰፈርና በስራ አካባቢ በመገኘት ለፕሮጀክቱ ሰራተኞችና የአካባቢው ነዋሪ ህብረተሰብ በኤች.ኤይ.ቪ/ኤድስ መከላከል ዙሪያ የግንዛቤ ትምህርት በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡

ፕሮጀክት ጽ/ቤቱ ከኤች.አይ.ቪ/ኤድስ መከላከል ስራ ጋር በተያያዘ የፕሮጀክቱ ሠራተኞችና የአካባቢው ነዋሪዎች እራሳቸውን ከኤች.አይ.ቪ/ኤድስ እንዲጠብቁ ለማስቻል ኦሳ/OSSA/ ከተባለው ግብር ሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር የኮንዶም ስርጭት ስራ በማካሄድ ላይ እንደሚገኝም ዘገባው አመልክቷል፡፡

በፕሮጀክቱ ክልል በፈቃደኝነት ላይ የተመሠረተ የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ምርመራ አገልግሎት ለማካሄድ የሰው ሀብት ስራ አመራር ዘርፍ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የቅድመ ዝግጅት ስራ በማከናወን ላይ እንደሚገኝም ተመልክቷል፡፡

ቀደም ሲል ፕሮጀክት ጽ/ቤቱ አል-ሀበሻ ስኳር ፋብሪካ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ይተዳደር በነበረበት ወቅት የህክምና አገልግሎት ይሰጥ የነበረው ክሊኒክ በተሟላና

በተደራጀ መልኩ ባለመሆኑ ፕሮጀክቱ በአዲስ መልክ ስራውን በጀመረበት ወቅት ለሰራተኞች ተገቢውን የህክምና አገልግሎት መስጠት እንዲቻል የህክምና አገልግሎት መስጫ ክሊኒኩ የነበሩበትን ከፍተቶች በመድፈን የተሟላ አገልግሎት መስጠት በሚያስችለው መልኩ የጥገና ስራ እየተደረገለት እንደሚገኝ ሪፖርቱ ጠቁሟል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘ የመኖሪያና የስራ ቦታን ለፕሮጀክቱ ሰራተኞችና የአካባቢው ነዋሪዎች ከጤና አኳያ ምቹ ለማድረግ በአካባቢው ከሚገኙት የዞን ጤና መምሪያዎችና ከወረዳ ጤና ጣቢያዎች ጋር በመተባበር የፀረ-ወባ መድሃኒት ርጭት የተካሄደ ከመሆኑም በላይ በቁጥር 350 አጎበር ለፕሮጀክቱ ሠራተኞች እንዲሰራጭ ተደርጓል፡፡ የህክምና የአገልግሎት መስጫ መሳሪያዎችን እና መድኃኒቶችን ለማሟላትም ፕሮጀክት ጽ/ቤቱ እየሰራ መሆኑ ተመልክቷል፡፡

በስኳር ኮርፖሬሽን የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ

ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት

Page 8: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4

እንደዛሬው ሳይሆን ከሃምሳ ዘጠኝ ዓመታት በፊት ፤ አሁን ላይ ለአንድ ቀን እንኳ ከምግብ ጠረጴዛችን እንደምን እናጣታለን ብለን አጥብቀን የምንፈልጋትን ስኳር የያኔዎቹ የአገሬ ሰዎች የጣፋጭነቷን እና የአጣፋጭነቷን ምስጢር አያውቁምና ከዚህች የፋብሪካ ምርት ጋር አይተዋወቁም ነበር፡፡ ምስጢሯን ለያኔዎቹ ኢትዮጵያዊያን ቀስ በቀስ የገለጠላቸው በ1946 ዓ.ም. ወንጂ ላይ የተቋቋመውና በአገራችን የስኳር ኢንዱስትሪ ታሪክ ፋና ወጊ የሆነው የወንጂ ስኳር ፋብሪካ ነበር፡፡

ታዲያ አንጋፋው ወንጂ ስኳር ፋብሪካ በአፍላ ጉልበቱ ወደ ምርት በገባበት በመጀመሪያዎቹ ዓመታት ለገበያ የሚያቀርበው ስኳር ለምርቱ ባይተዋር ከነበሩት የአገሬ ሰዎች የስኳር ፍላጎት በላይ ነበር፤ ያኔ እንዲህ እንደዛሬው የስኳር ፍላጎት በአገሪቱ ሦስት ስኳር ፋብሪካዎች ከሚመረተው በላይ ሆኖ በመንግስት ከፍተኛ የገንዘብ ድጎማ በውጭ ምንዛሬ ገብቶ በተመጣጣኝ ዋጋ ማቅረብ አላስፈለገም ነበር፡፡ እናም ወንጂ ስኳር ፋብሪካ ያኔ የገበያ እጥረት ፈትኖት ነበር፡፡ “ማን ይናገር የነበረ ፤---- “ እንዲሉ የዛሬ አዛውንቶችና ያኔ የፋብሪካው ሰራተኞች የነበሩ በግርምት ትዝታቸውን ሲያወሱ ፋብሪካው የገጠመውን የገበያ ችግር ለመወጣት በጊዜው የነበሩ ኢትዮጵያዊያንን ከስኳር ምርት ጋር የማስተዋወቁን ተግባር ትኩረት ሰጥቶ እንዳከናወነ ያወሳሉ፡፡ በዛን ጊዜ የፋብሪካው ሰራተኞች ስኳርን ከአገሬው ሰዎች ጋር ለማስተዋወቅ ከቦታ ቦታ እየተዘዋወሩ ሻሂ በማፍላትና ያለምንም ክፍያ እንዲጠጡ በመጋበዝ የጣፋጭነቷን ምስጢር የመግለጥና ገበያውን የማስፋፋት ስራ ይሰሩ ነበር፡፡

የወንጂ ስኳር ፋብሪካ ሠራተኞች ስኳርን የማስተዋወቅ ስራቸው ለውጤት በቅቶ የአገሬ የያኔ ከተሜዎች የስኳር ፍላጎት እያደገ መጣና ሌላ ተጨማሪ ስኳር ፋብሪካ መገንባት የግድ ሆነ፡፡ እናማ አንጋፋውን ፋብሪካ የገነባው የሆላንዱ ኤች.ቪ.ኤ ኩባንያ እዛው ወንጂ ላይ የመጀመሪያውን ፋብሪካ ከገነባ አስር ዓመት እንኳ ሳይሞላው የሸዋ ስኳር ፋብሪካን በ1955 ዓ.ም. ገነባና ወደ ምርት አስገባ፡፡ አንጋፋው ወንጂ እና ሸዋ የስኳር ፋብሪካዎች ታዲያ ከ 50 እስከ 60 ዓመታት ለዘለቀ ጊዜ የአገሪቷን የስኳር ምርት ፍላጎት የማርካት ስራን ወደኋላ ከተገነቡት

ከመተሐራ እና የፊንጫኣ ስኳር ፋብሪካዎች ጋር በመሆን ሲያከናውኑ ቆይተዋል፡፡

አንጋፋው ወንጂ ስኳር ፋብሪካ በከፈተው በር የተከተሉት ሦስቱ ተጨማሪ ስኳር ፋብሪካዎች ታዲያ የአገር ውስጥ ፍላጎትን ማርካት እየተሳናቸው መምጣት የጀመሩት ከጥቂት በጣት ከሚቆጠሩ ዓመታት ወዲህ ነው፡፡ ምስጢሩ ደግሞ አገሪቷ እያስመዘገበችው ያለው ፈጣን ኢኮኖሚያዊ ዕድገትና ከመሰረተ ልማት አውታሮች በፍጥነትና በስፋት ከመስፋፋት ጋር ተያይዞ ከከተሜው አልፎ የገጠሩ ሕዝብ የስኳር ምርት ተጠቃሚ መሆኑ ነው፡፡ የከተሞች መስፋፋት፣ የትላልቅ ሆቴሎች፣ስኳርን በግብዓትነት የሚጠቀሙ በርካታ ኢንዱስትሪዎች፣የተለያዩ ንግዶች፣ ወዘተ መስፋፋት በአገር ውስጥ የስኳር ምርት ብቻ እየተፈጠረና በእጅጉ እያደገ የመጣውን የምርቱን ፍላጎት ማርካት አለመቻሉ ሌላው ዋነኛው ምስጢር ነው፡፡

“በእንቅርት ላይ…. “ እንዲሉ ደግሞ ዕድሜ ጠገቦቹ የወንጂ እና የሸዋ ስኳር ፋብሪካዎች ከአገልግሎት ዕድሜያቸው መርዘም የተነሳ እና ዘመን ያለፈባቸው የኋላቀር ቴክኖሎጂ ውጤቶች ከመሆናቸው ጋር ተዳምሮ የማሽነሪዎቻቸውን መለዋወጫዎች በገበያ ላይ ማግኘት አለመቻሉና እንደዚሁም በዚሁ ሳቢያ የምርት ወጪያቸው አዋጭ አለመሆን የፋብሪካዎቹን የመዘጋት ጉዳይ አስፈላጊ አደረገው፡፡ ወንጂ እና ሸዋ ስኳር ፋብሪካዎች ሲዘጉ ታዲያ በሌላና በአዲስ መልኩ የሚወለዱበት ሌላ መንገድ ትተው ነው! የአዲሱን

እና ዘመናዊውን የወንጂ/ሸዋ ስኳር ፋብሪካን ልደት አስከትለው!

ይህን እየተፈጠረ ያለውን የአገር ውስጥ የስኳር ፍላጎት ያጤነው የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. መንግስት የምርት አቅርቦት ችግሩን ከመፍታት ባሻገር ለስኳር ልማት ዘርፍ አገራችን ያላትን ምቹ አየር ንብረት፣ ተስማሚ የአፈር ይዘት ፣ በቂ የውኃ ሀብትና የዘርፉን ስትራተጂያዊ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታን ባገናዘበ መልኩ በነደፈው የአምስት ዓመት የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ውስጥ ዘርፉ ትልቅ ትኩረት እንዲሰጠው አድርጓል፡፡ እናም እቅዱ በነባር ስኳር ፋብሪካዎች ላይ የማስፋፊያ ስራን ማከናወንን አካቷልና ዕድሜያቸው የገፋው የወንጂ እና ሸዋ ስኳር ፋብሪካዎችን በአዲስና ዘመናዊ ፋብሪካ መተካት ትኩረት ተሰጥቶት አዲሱ የወንጂ/ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ግንባታ በ2003 ዓ.ም. ተጀምሮ በ2005 ዓ.ም. በስኬት ተጠናቀቀ! የአንጋፋው ወንጂ እና የሸዋ ስኳር ፋብሪካዎች ዳግም ልደትም ዕውን ሆነ! በአዲስ መልክ!

ታዲያ አንጋፋዎቹን እነዚህን ፋብሪካዎች የሚተካውና በ2006 ዓ.ም. ወደ መደበኛ ምርት የሚገባው አዲሱ ወንጂ/ሸዋ ስኳር ፋብሪካ በመጀመሪያ በቀን 6,250 ቶን አገዳ የመፍጨት አቅም የሚኖረው ሲሆን ይህም የአሮጌዎቹን ሁለት ፋብሪካዎች አቅም በእጥፍ የሚበልጥ ነው፡፡ ይህ አቅሙም ወደፊት እንዲያድግ ተደርጎ ከ10 እስከ 12 ቶን አገዳ በቀን መፍጨት ወደሚችልበት ደረጃ ይሸጋገራል፡፡

የፋና ወጊው

ዳግም ልደት - በአዲስ መልክ

ከ 50 ዓመት በፊት ሻይን ያለምንም ክፍያ በየመንገዱ

በመጋበዝ ነበር የስኳር ምርት የሚተዋወቀው

መቆያጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት 8

ቅፅ 2. ቁጥር 1 | መስከረም 2006

Page 9: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4

9

የአዲሱ የወንጂ/ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ግንባታ መጠናቀቅ መንግስት በአምስት ዓመቱ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ውስጥ በስኳር ልማት ዘርፍ ለማከናወን ካቀዳቸው ተግባራት መካከል አንዱ የሆነው የነባር ስኳር ፋብሪካዎች የማስፋፊያ ፕሮጀክቶችን የማጠናቀቅ እቅድ መሳካቱን አመላካች ነው፡፡ በተመሳሳይ የፊንጫኣ ስኳር ፋብሪካ የማስፋፊያ ስራ መጠናቀቅም ሌላው በዘርፉ ከተያዙ እቅዶች ከፊሎቹ ከወዲሁ መጠናቀቅ መጀመራቸውን የሚሳይ የዕቅዱ ስኬት ነፀብራቅ ነው፡፡ በዚህ የአምስት ዓመት እቅድ አስር አዳዲስ ስኳር ፋብሪካዎችን መገንባትና የግዙፉን የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ ግንባታን ማጠናቀቅ ከማስፋፊያ ስራዎች በተጓዳኝ ሊከናወኑ የታቀዱ ተግባራት መሆናቸውን ማስታወስ ታዲያ ተገቢ ይሆናል፡፡

ነባሮቹን እንዲተካ የታለመው የአዲሱ የወንጂ/ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ግንባታ በተሳካ ሁኔታ በመጠናቀቁ ወንጂ ስኳር ፋብሪካ በ2005 ዓ.ም. መጀመሪያ ላይ ስራ እንዲያቆም ተደርጓል፤ ሸዋ ስኳር ፋብሪካም ወንጂን ተከትሎ በ2006 ዓ.ም. ስራ ያቆማል፡፡ እነዚህ አንጋፋ ስኳር ፋብሪካዎች ከግማሽ ዓመታት በላይ ተሸክመውት የቆዩትን ስኳር የማምረት ኃላፊነት በተሻለና በዘመነ መልኩ ከተጨማሪ ምርቶች ጋር መወጣት እንዲጀምር ለአዲሱ ፋብሪካ አስረክበዋል፡፡

ይህ ዘመናዊ ስኳር ፋብሪካ በመጀመሪያ ወደ ምርት ሲገባ በዓመት 1.7 ሚሊዮን ኩንታል ስኳርና 10299 ሜትር ኩብ ኤታኖል የማምረት አቅም የሚኖረውና በቀጣይም በሚካሄድ የማስፋፊያ ስራ ዓመታዊ የማምረት አቅሙ ወደ 2.7 ሚሊዮን ኩንታል ያድጋል፡፡ፋብሪካው የራሱን የኃይል ፍለጎት በማርካትም እስከ 22 ሜጋ ዋት የሚደርስ የኤሌክትሪክ ኃይል ወደ ብሔራዊ ቋት ያስገባል፡፡ በተጨማሪም ይህ ፋብሪካ የተለያዩ የዘመኑ ቴክኖሎጂ ውጤቶች የሆኑ ማሽነሪዎች የተገጠመለት በመሆኑ የምርት ሂደቱን በአስተማማኝ እና በብቃት እንዲያከናውን ያስችሉታል፡

፡ ለአብነት ያህል ብንወስድ በተለያዩ የምርት ሂደቶች በሚከናወኑባቸው ቁልፍ የፋብሪካው ማሽነሪዎች ተለዋጭ ማሽነሪዎች በመጠባበቂያነት ስለተገጠሙ ፋብሪካው በእንደነዚህ ያሉ ቁልፍ ቦታዎች ላይ በሚከሰት ብልሽት ምክንያት የምርት ሂደቱ የሚቆምበት ሁኔታ እጅግ አነስተኛ ነው፡፡

አዲሱ ፋብሪካ በቴክኖሎጂ የተሻለ በመሆኑ በምርት ሂደት ወቅት ብክነት የመቀነስ፣ ጥቂት ኃይል ተጠቅሞ የተሻለ ምርት የማምረት፣ ጉዳት የማያስከትሉ የምርት ሂደት ውጤቶችን የማስወገድ፣ የፋብሪካውን የውስጥ ማሽነሪዎች ለጉዳት የሚያጋልጡ አላስፈላጊ ባዕድ ነገሮችን ለይቶ የማስቀረት አቅም እንዲኖረው ተደርጎ የተገነባ ነው፡፡ በተጨማሪም ፋብሪካው በርካታ የሰው ኃይል የማይፈልግ እና የፋብሪካውን ማሽነሪዎች የስራ አፈጻጸም በአንድ ቦታ ላይ ሆኖ መቆጣጠር የሚቻልበት ቴክኖሎጂ የታጠቀ ነው፡፡

ታዲያ አንድ የነባር ስኳር ፋብሪካዎቻችንን ሁኔታ የሚያውቅና ወደዚህ ፋብሪካ ብቅ ብሎ የምርት ሂደቱ እንዴት እንደሚከናወን የተመለከተ ሰው ይህ ዘመናዊና በርካታ ግዙፍ ማሽነሪዎች የተገጠሙለት ፋብሪካ የስራ እንቅስቃሴን የሚከታተሉና በስራ ላይ የተሰማሩ የፋብሪካው ሰራተኞች ቁጥር እጅግ ማነስን ሲመለከት መገረሙ አይቀሬ ነው፡፡ ሌላው ደግሞ የፋብሪካው የስኳር ምርት በጆንያ ከታሸገ በኋላ ወደ ግዙፎቹ የስኳር ማከማቻ መጋዘኖች የሚደርሰው ያለምንም የሰው ኃይል ከፋብሪካው እስከ መጋዘኖቹ በተዘረጋ ቤልት አማካይነት በመሆኑ የፋብሪካውን የሰው ኃይል መቆጠብና በሌላ አስፈላጊ ስራ ላይ ማሰማራት የሚያስችል ነው፡፡ አዲሱ ፋብሪካ በ2005 ዓ.ም. መጨረሻ ባከናወነው የሙከራ ምርት የተመረተው ስኳር ጥራት አገር አቀፍ እና ዓለም አቀፋዊ መመዘኛዎችን የሚያሟላ ሆኖ ነው የተገኘው፡፡

የስኳር ኮርፖሬሽን እና የወንጂ/ሸዋ ስኳር

ፋብሪካ ከፍተኛ አመራር አካላት ታዲያ በጥራቱ የተሻለ፣ በመጠኑ እጥፍ የሆነ የስኳር ምርት አዲሱ ፋብሪካ እንዲያመርት በሚያስችለው ሁኔታ እንዲገነባ ሲያደርጉ በቴክኖሎጂው ብቻ በመተማመን ሳይሆን ሌሎች ሊከናወኑ የሚገባቸው የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ጎን ለጎን እንዲካሄዱ በማድረግም ነው፡፡ በዚህም የቀድሞዎቹ ስኳር ፋብረካዎች ሰራተኞች በአዲሱ ፋብሪካ ለወራት እንዲሰሩ በማድረግና ከዘመናዊው ፋብሪካ ማሽነሪዎች ጋር እንዲተዋወቁ በማድረግ በቀጣይ ሰራተኞቹ ፋብሪካውን እራሳቸውን ችለው የሚያንቀሳቅሱበትን ሁኔታ በማመቻቸት ነው፡፡

ከዚህም ሌላ የኮርፖሬሽኑና የፋብሪካው አመራሮች አዲሱን ፋብሪካ ወደ ስራ ሲያስገቡ ይበልጥ ምርታማ እና ወጪ ቆጣቢ አንዲሆን ለማድረግ ሌላ ትጥቅ እንዲታጠቅ አድርገዋል - የካይዘን ፍልስፍና ትጥቅ! እዚህ ላይ ታዲያ በቅርቡ የካይዘን ኢንስቲትዩት በአገር አቀፍ ደረጃ በመንግስታዊ እና መንግስታዊ ባልሆኑ ተቋማት መካከል በካይዘን ፍልስፍና እና አተገባበር ዙሪያ ባካሄደው ውድድር ወንጂ/ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ከመቶ በላይ ተወዳዳሪዎቹን በአፈጻጸሙ ልቆ የዋንጫ ተሸላሚ መሆኑን ልብ ይሏል! ይህ የወንጂ/ሸዋ ስኳር ፋብሪካ የካይዘን ፍልስፍና ትጥቅ እና ከአዲሱ ቴክኖሎጂ ጋር በሚገባ የተዋወቁ ሰራተኞቹ ደግሞ አዲሱ ፋብሪካ የሚጠበቅበትን እንዲያከናውን ከጎኑ ተሰልፈዋል!

የዘመነ ቴክኖሎጂ ባለቤት የሆነ ስኳር ፋብሪካ ከመገንባት ባሻገር ታዲያ የወንጂ/ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ያለውን የሸንኮራ አገዳ ማሳ የማስፋፋት ስራውንም ጎን ለጎን ለማስኬድ ትኩረት ሰጥቶ ሰርቷል፡፡ በዚህም የነበረውን አጠቃላይ ሰባት ሺህ ሄክታር የአገዳ መሬት ወደ 16 ሺህ ሄክታር ለማሳደግ እየሰራ ይገኛል፡፡ በአሁኑ ወቅትም ዶዶታ በተባለ ቦታ 3,000 ሄክታር እንዲሁም በወለንጪቲ 1,000 ሄክታር መሬት በሸንኮራ አገዳ እንዲሸፈን ያደረገ ሲሆን ተጨማሪ 5,000 ሄክታር መሬት በወለንጪቲ በ2006 እና በ2007 ዓ.ም. በሸንኮራ ለመሸፈን የዋና እና የመለስተኛ ውኃ ማስተላለፊያ ቦይ (ካናል) ግንባታ አጠናቋል፡፡

የወንጂ/ሸዋ ስኳር ፋብሪካ የሸንኮራ አገዳ እርሻ ማስፋፊያ ፕሮጀክትን ከሌሎች በተለይም ከፊንጫኣ ስኳር ፋብሪካ ለየት የሚያደርገው በማስፋፊያ የሚለማው ዘጠኝ ሺህ ሄክታር የሸንኮራ አገዳ መሬቱ የሚለማው በአገዳ አብቃይ ገበሬዎች አማካይነት መሆኑ ነው፡፡ ፋብሪካው መጀመሪያ ከነበረው ሰባት ሺህ ሄክታር የሸንኮራ አገዳ መሬቱ መካከል አንድ ሺህ ሄክታሩ የተያዘው በአገዳ አብቃይ ገበሬዎች ነው፡፡ እናም እነዚህ ነባር እና በማስፋፊያ እየለማ ያለው መሬት አገዳ አብቃይ የሆኑ ገበሬዎች ከፋብሪካው ጋር በሚኖራቸው የኮንትራት ስምምነት መሰረት ለፋብሪካው በሽያጭ የሸንኮራ አገዳ ያቀርባሉ፡፡ በተጨማሪም አገዳ አብቃይ ገበሬዎቹ በመሬታቸው በሚያከናውኑት የሸንኮራ አገዳ ልማት ስራ ይከፈላቸዋል፡፡ ፋብሪካው እነዚህ አገዳ አብቃይ ገበሬዎች አገዳ በሚያበቅሉበት ወቅት የመሬት ዝግጅት፣ የጸረ-ተባይ መድኃኒት ርጭት፣የማዳበሪያ እና ሌሎች የቴክኒክ እገዛዎችን በማድረግ በቂ አገዳ በፋብሪካው የምርት ወቅት ያለምንም ችግር መቅረብ እንዲችል ያደርጋል፡፡

በአዲሱ፣ ዘመናዊውና አገዳ የመፍጨት አቅሙ ከነባሮቹ ፋብሪካዎች በእጅጉ የሚልቀው የወንጂ/ሸዋ ስኳር ፋብሪካ እና በአገዳ አብቃይ ገበሬዎች መካከል ያለው በጋራ መጠቃቀም ላይ የተመሰረተ ግንኙነት ከአዲሱ ፋብሪካ ልደት ጋር ተያይዞ ይበልጥ እየተጠናከረና እየሰፋ የሚሄድብት ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡ ይህም የስኳር ልማቱ የአካባቢውን ገበሬዎች ከማንም በላይ ተጠቃሚ ማድረጉን አመላከች ነው፡፡ ይህ ብቻ እንኳ ሲታይ የስኳር ልማት ዘርፍ ለዜጎች በተለይም የስኳር ልማት በሚካሄድባቸው ፕሮጀክቶችና ፋብሪካዎች አካባቢዎች ለሚኖሩ ነዋሪዎች የሚፈጥረውን ሰፊ የስራ እድል እና ምቹ የገበያ ትስስር በግልጽ የሚያሳይ ነው፡፡

አዎ! እዚህ ላይ ማንም መገንዘብ የሚችለው ስኳር ኮርፖሬሽን በዚህች አገር ላይ ድህነትን ታሪክ የማድረግ ሚናውን እየተወጣ የመሆኑ ጉዳይ ይበልጥ በግልጽ የሚታይበት ሁኔታን ነው!

የዘመናዊው ፋብሪካ ከፊል ገጽታ

በስኳር ኮርፖሬሽን የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ

ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት

Page 10: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4

ዜና መፅሄት በስኳር ኮርፖሬሽን ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት

ገፅ10

ww

w.etsugar.gov.et || w

ww

.facebook.com/etsugar

ጣፋጭ

የተንዳሆስኳር ፋብሪካ

የአገሪቷን የስኳር ምርት ፍላጎት ለማሟላትና ምርቱን ኤክስፖርት በማድረግ የውጭ ምንዛሬ ለማግኘት የጎላ ድርሻ የሚኖረው የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ በሚኒስትሮች ም/ቤት ደንብ ቁጥር 122/1998 ተቋቋመ፡፡ መንግሥት የተንዳሆ ስኳር ልማት ፕሮጀክትን ከመጀመሩ አስቀድሞ አዋጪነቱንና አጠቃላይ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ጠቀሜታዎቹን በበቂ ሁኔታ አጥንቶ ነው ወደ ስራ የገባው፡፡ ለዚህ ግዙፍና ዘመናዊ ፋብሪካ እውን መሆንም ታላቁ መሪ ክቡር አቶ መለስ ዜናዊ ከሃሳብ ማመንጨት እስከ ፕሮጀክቱ ተግባራዊነት ድረስ የነበራቸው ድርሻ የላቀ ነው፡፡

በአፋር ብሔራዊ ክልል በ50ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የሚለማ የሸንኮራ አገዳን በግብዓትነት የሚጠቀመው የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ ከአዲስ አበባ በ660 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ ግንባታው በሁለት ምዕራፍ የሚከናወነው ይህ ፋብሪካ በሙሉ አቅሙ ማምረት ሲጀምር በቀን 26ሺህ ቶን አገዳ ይፈጫል፡፡ የምርት መጠኑም ደረጃ በደረጃ እያደገ በአመት 619 ሺህ ቶን ስኳር እንደሚያመርት ይጠበቃል፡፡ ይህም ማለት አገሪቷ ያሏት ሦስት ነባር ስኳር ፋብሪካዎች በአመት በአማካይ የሚያመርቱትን የስኳር ምርት መጠን/300ሺህ ቶን/ ተንዳሆ ብቻውን ከእጥፍ በላይ ያመርታል ማለት ነው፡፡

በተጨማሪም ከስኳር ተረፈ ምርት ከሚያመነጨው 120 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ሃይል ውስጥ 90 ሜጋ ዋቱን ወደ ናሽናል ግሪድ የሚያስገባ ሲሆን፣ 63 ሺህ ኪዩቢክ ኤታኖልም ያመርታል ተብሎ

ይጠበቃል፡፡ ከዚህም በተጓዳኝ የአፋር አርብቶ አደር በመስኖ የሚለማ የእርሻና ግጦሽ መሬት እንዲያገኝ በማስቻል ለእንስሶቹ ሳርና ውሃ ፍለጋ ከቦታ ቦታ ሲንከራተት ያሳለፈውን የጉስቁልና ሕይወት ከማሻሻል አንፃር የጎላ ድርሻ ይኖረዋል፡፡

በግዙፍነቱ ብቻ ሳይሆን በተሻለ የዘመናዊ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚነቱም ከሌሎቹ ነባር ስኳር ፋብሪካዎች የሚለየው ተንዳሆ በየጊዜው ይፈጠሩ በነበሩ በርካታ ሰው ሰራሽና ተፈጥሮአዊ ችግሮች ምክንያት ሥራው ተጓቶ ቆይቷል፡፡ ይሁንና የስኳር ኮርፖሬሽን ከተቋቋመበት ጥቅምት 2003 ዓ.ም ወዲህ ግን ኮርፖሬሽኑ በተከታታይ በወሰዳቸው እርምጃዎችና ባደረጋቸው ማስተካከያዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ ከነበረበት ችግር ተላቆ በአሁኑ ወቅት የፋብሪካው የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ ወደሚጠናቀቅበት ደረጃ ላይ ሊደርስ ችሏል፡፡ ወደዚህ የስኬት ምዕራፍ የተደረሰውም የአፋር ክልል መንግሥትን ጨምሮ በርካታ ባለድርሻ አካላትን ያካተተ የስትሪንግ ኮሚቴ ተቋቁሞ ከኮርፖሬሽኑ ጋር በመቀናጀት በፕሮጀክቱ አፈጻጸም ዙሪያ የቅርብ ክትትልና ግምገማ ማድረግ በመቻሉ ነው፡፡

ለፋብሪካው ከሚያስፈልገው 50ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የሚለማ ሸንኮራ አገዳ ውስጥ 25ሺህ ሄክታሩ የሚለማው በአውትግሮውርስ ሲሆን፣ በመጀመሪያ ምዕራፍ እየተገነባ ለሚገኘው ፋብሪካ ከሚያስፈልገው 25 ሺህ ሄክታር መሬት ውስጥ 10ሺህ 572 ሄክታሩ በተንዳሆ ስኳር ልማት ፕሮጀክት በአገዳ

ቅኝት

Page 11: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4

ገፅ11

ጣፋጭዜና መፅሄት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ

የተንዳሆስኳር ፋብሪካ

ተሸፍኗል፡፡ የፋብሪካው የመጀመሪያ ምዕራፍ በ2006 በጀት ዓመት አጋማሽ ተጠናቆና ሙሉ ፋብሪካው ተፈትሾ ወደ ስኳር ማምረት ይሸጋገራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ የሁለተኛው ምዕራፍ ስራም የመጀመሪያው አገልግሎት መስጠት በጀመረ በሁለት አመት ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ታሳቢ ተደርጓል፡፡

የፋብሪካው የአገዳ ልማት የሚከናወነው በአዋሽ ወንዝ ላይ በተገነባው የተንዳሆ ግድብ አማካኝነት ነው፡፡ ከ1.86 ቢሊዮን ሜትር ኪዩብ ውሃ በላይ የመያዝ አቅም ያለው ይህ ግድብ ከ60 ሺህ ሄክታር መሬት በላይ ማልማት ይችላል፡፡ ከተንዳሆ ግድብ ተነስቶ አገዳው በሙሉ እስከሚለማበት አሳኢታ ድረስ ካለው 67 ኪሎ ሜትር የዋና ውሃ መውሰጃ ቦይ (Main Canal) ውስጥ 44 ኪሎ ሜትሩ ተጠናቆ የመስኖ ልማት ላይ ውሏል፡፡

ከእነዚህ ሥራዎች ጎን ለጎን የስኳር ልማቱ በሚካሄድባቸው አካባቢዎች የሚገኙ

አርብቶ አደሮችን የማኅበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማት በተሟላላቸው መንደሮች በማሰባሰብ ቋሚ ኑሮ እንዲጀምሩ እየተደረገ ነው፡፡ በዱብቲ በሦስት መንደሮች (አስቦዳ፣ አንድለቡሪና ቦይና) 1,500 አባወራ/እማወራ በመንደር ተሰባስበዋል፡፡

የአካባቢው አርብቶ አደሮች ከእንስሳት እርባታ በተጨማሪ በእርሻ ሥራ እንዲሰማሩ ለማስቻል መስኖ ገብ መሬት አዘጋጅቶ ከመስጠት እስከ ሁለንተናዊ የባለሙያዎች ድጋፍና ክትትል ድረስ የዘለቁ ሥራዎች በመከናወን ላይ ናቸው፡፡ በዚህ መሰረት ት/ቤቶች፣ ጤና ተቋማት፣ የንፁህ መጠጥ ውሃ፣ መስጊድ፣ ወፍጮ ቤት እና ሌሎች የማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማትና የመሰረተ ልማት ግንባታዎች ከመንደር ማሰባሰብ ስራ ጋር አብረው በመካሄድ ላይ ይገኛሉ፡፡

ከእነዚህም ውስጥ የሰባት ማህበራዊ ተቋማት ግንባታዎች በሰባት መንደሮች (ቦይና፣ አስቦዳ፣ ኢቲሉ፣ እንደቡሪ፣ ጋሱሪ፣ አንደለቡሪና ዋይዴዴኤስ) ሙሉ በሙሉ ተጠናቀው ለክልሉ ርክክብ ተፈጽሟል፡፡ በሁለት መንደሮች (ሄድለቡሪና ኪፊሉ) ደግሞ ግንባታቸው በአማካኝ 77.5% ደርሷል፡፡ በሌላ በኩል በዱብቲ ጋብላይቱ፣ በአይሮላፍ፣ ጋሱሪና ኡንዳቡሪ እየተሰሩ ካሉ የመስኖ መሬት ዝግጅቶች ውስጥ የተጠናቀቀውን 2,119 ሄ/ር ለ1,577 አባወራ/እማወራ በማከፋፈል ማልማት ተጀምሯል፡፡ 7,910 ሄ/ር የመስኖ እርሻ መሬት ደግሞ በዝግጅት ሂደት ላይ ነው፡፡ በአጠቃላይ ኮርፖሬሽኑ ለክልሉ ተወላጆች ወደ 12 ሺህ

ሄክታር የሚጠጋ በመስኖ የሚለማ የእርሻና የግጦሽ መሬት ለማስረከብ እየሰራ ነው፡፡

በፕሮጀክቱ የተፈጠረ የሥራ እድልን በተመለከተ እስካሁን ከ7ሺህ በላይ የሚሆኑ ዜጎች ጊዜያዊ፣ ቋሚና የኮንትራት የስራ ዕድል አግኝተዋል፡፡ ከኮንትራትና ቋሚ ሠራተኞች ውስጥ ከ430 በላይ የሚሆኑት በተለያዩ የሙያ መስኮች የሰለጠኑና እስከ ኃላፊነት ደረጃ የደረሱ የአፋር ብሔረሰብ ተወላጆችና የአካባቢው ማህረሰብ ሲሆኑ፣ ካሉት አጠቃላይ ሰራተኞች 37 በመቶውን ድርሻ ይዘዋል፡፡

የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ ተጠናቆ በሙሉ አቅሙ ማምረት ሲጀምር 50 ሺህ ለሚጠጉ ዜጎች የስራ ዕድል እንደሚፈጥር እና በዚህ ጊዜም የአካባቢው ተወላጆች እና ነዋሪዎች ከአሁኑ በተሻለ ሰፊ የስራ ዕድል የሚያገኙበት ሁኔታ እንደሚኖር ይጠበቃል፡፡ ኮርፖሬሽኑ ከአፋር ክልል ጋር በመተባበር ለክልሉ ተወላጆችና ነዋሪዎች በእርሻ ስራና በቴክኒክ ሙያዎች ላይ ስልጠናዎችን በመስጠት ሄድ ማኖች፣ ፎርማኖችና የማሽን ኦፕሬተሮች ሆነው በፕሮጀክቱ እንዲቀጠሩ እያደረገ ነው፡፡

ከሚያስገኘው በርካታ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጠቀሜታዎች አንጻር ከፍተኛ ትኩረት የተሰጠው ግዙፉ የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ የአገሪቷን የስኳር ፍላጎት ከማሟላት ባለፈ የውጭ ምንዛሬን በማስገኘት ለስኳር ልማት ዘርፍ ዕድገት ጉልህ ድርሻ እንደሚያበረክት ትልቅ ተስፋ ተጥሎበታል፡፡

ከ1.86 ቢሊዮን ሜትር ኪዩብ ውሃ በላይ የመያዝ አቅም ያለው የተንዳሆ ግድብ

Page 12: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4