12
ዜና መፅሔት ራዕይ፡ ቀጣይነት ባለው ዕድገት በ2016 ዓ.ም. በዓለም ተወዳዳሪ ከሆኑ 10 የስኳር አምራች አገራት ተርታ መሰለፍ! ቅፅ 4 ቁጥር 3-መጋቢት 2008 ዓ.ም www.ethiopiansugar.com|| facebook.com/etsugar ጣፋጭ በስኳር ኮርፖሬሽን የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ ዜና መጽሔት :+251-(0)11-552-7475/6322 : +251-(0)11-515-1283 : 20034 Code 1000 A.A የስኳር ልማት ግቦችን ለማሳካት የባለድርሻ አካላት ተቀናጅቶ መስራት ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ የስኳር ልማት ግቦችን ለማሳካት የባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሠራር ወሳኝ መሆኑን የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ሚኒስትር ዴኤታ ገለጹ፡፡ ሚኒስትር ዴኤታው አቶ በየነ ገብረ መስቀል ስኳር ኮርፖሬሽን በለውጥና በልማት ሠራዊት ግንባታ የካቲት 30 ቀን 2008ዓ.ም በግዮን ሆቴል ባዘጋጀው ስኳር ፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች በኤልኒኖ ምክንያት ድርቅ በተከሰተባቸው አካባቢዎች የሚገኙ የአርሶና አርብቶ አደር እንስሳት ላይ ጉዳት እንዳይደርስ የሚያደርጉት ድጋፍ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ በቅርቡ የመተሐራ ስኳር ፋብሪካና የጣና በለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት በየአካባቢያቸው ለሚገኙ የአርብቶና አርሶ አደር እንስሳት የሚውል መኖና የመጠጥ ውሃ ድጋፍ አድርገዋል፡፡ የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ የህዝብ አደረጃጀት፣ ህዝብ ግንኙነት እና ማህበራዊ ጉዳዮች አገልግሎት ሓላፊ አቶ ሲሳይ ደርቤ እንደገለፁት፣ ፋብሪካው በቅርቡ ከ1.5 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው የእንስሳት ስኳር ፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች በድርቅ ለተጎዱ አካባቢዎች የሚያደርጉት ድጋፍ ተጠናክሮ ቀጥሏል » ወደ ገጽ3 ዞሯል » ወደ ገጽ 3 ዞሯል ስኳር ኮርፖሬሽን ለጠብታ መስኖ ግንባታ ከእስራኤል ኩባንያ ጋር ውል ተፈራረመ ስኳር ኮርፖሬሽን በወልቃይት ስኳር ልማት ኘሮጀክት የጠብታ መስኖ (Drip Irrigation) ቴክኖሎጂ ተግባራዊ ለማድረግ ከእስራኤሉ ኔታፊም ኩባንያ ጋር ውል ተፈራረመ፡፡ የኮርፖሬሽኑ የሕግ አገልግሎት ሥራ አስፈጻሚ አቶ ፋሲል ገብረማርያም እንደገለጹት ኮርፖሬሽኑ ከኩባንያው ጋር የተፈራረመው የውል ስምምነት በፕሮጀክቱ ሰባት ሺህ ሄክታር መሬት በጠብታ መስኖ ለማልማት የሚያስችል ነው፡፡ • የህዝብና የመንግሥት ክንፍ የውይይት መድረኮች ተካሄዱ » ወደ ገጽ 3 ዞሯል በውስጥ ገጾች -> በኮርፖሬሽኑና በመሠረታዊ ሠራተኛ ማህበር መካከል እየተካሄደ የሚገኘው የህብረት ስምምነት ድርድር በመጠናቀቅ ላይ ነው>>ገጽ 4 -> የክልሎች ፕሬዚዳንቶች የስኳር ልማት ፕሮጀክቶችን ጎበኙ>> 5 -> የስኳር ልማት የኤልኒኖ ተጽዕኖን የመቀነስ ሚና >> ገጽ 9 የመንግሥት ክንፍ የውይይት መድረክ ላይ እንደተናገሩት፣ በዘርፉ የሚከናወኑ ሥራዎች ሳይደነቃቀፉ በሚፈለገው መልኩ እንዲፈጸሙ የባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሠራር ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ ከመሃል አቶ በየነ ገብረመስቀል የመንግስት ልማት ድርጅቶች ሚኒስትር ዴኤታ የውይይት መድረኩን ሲመሩ

ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 3 መጋቢት 2008

Embed Size (px)

Citation preview

Page 1: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 3 መጋቢት 2008

ዜና መፅሔት

ራዕይ፡ ቀጣይነት ባለው ዕድገት በ2016 ዓ.ም. በዓለም ተወዳዳሪ ከሆኑ 10 የስኳር አምራች አገራት ተርታ መሰለፍ!

ቅፅ 4 ቁጥር 3-መጋቢት 2008 ዓ.ምwww.ethiopiansugar.com|| facebook.com/etsugar

ጣፋጭ

በስኳር ኮርፖሬሽን የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ ዜና መጽሔት:+251-(0)11-552-7475/6322 : +251-(0)11-515-1283 : 20034 Code 1000 A.A

የስኳር ልማት ግቦችን ለማሳካት የባለድርሻ አካላት ተቀናጅቶ መስራት ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ

የስኳር ልማት ግቦችን ለማሳካት የባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሠራር ወሳኝ መሆኑን የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ሚኒስትር ዴኤታ ገለጹ፡፡

ሚኒስትር ዴኤታው አቶ በየነ ገብረ መስቀል ስኳር ኮርፖሬሽን በለውጥና በልማት ሠራዊት ግንባታ የካቲት 30 ቀን 2008ዓ.ም በግዮን ሆቴል ባዘጋጀው

ስኳር ፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች በኤልኒኖ ምክንያት ድርቅ በተከሰተባቸው አካባቢዎች የሚገኙ የአርሶና አርብቶ አደር እንስሳት ላይ ጉዳት እንዳይደርስ የሚያደርጉት ድጋፍ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

በቅርቡ የመተሐራ ስኳር ፋብሪካና የጣና በለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት በየአካባቢያቸው ለሚገኙ የአርብቶና አርሶ አደር እንስሳት የሚውል መኖና የመጠጥ ውሃ ድጋፍ አድርገዋል፡፡

የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ የህዝብ አደረጃጀት፣ ህዝብ ግንኙነት እና ማህበራዊ ጉዳዮች አገልግሎት ሓላፊ አቶ ሲሳይ ደርቤ እንደገለፁት፣ ፋብሪካው በቅርቡ ከ1.5 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው የእንስሳት

ስኳር ፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች በድርቅ ለተጎዱ አካባቢዎች የሚያደርጉት ድጋፍ ተጠናክሮ ቀጥሏል

» ወደ ገጽ3 ዞሯል

» ወደ ገጽ 3 ዞሯል

ስኳር ኮርፖሬሽን ለጠብታ መስኖ ግንባታ ከእስራኤል ኩባንያ ጋር ውል ተፈራረመስኳር ኮርፖሬሽን በወልቃይት ስኳር ልማት ኘሮጀክት የጠብታ መስኖ (Drip Irrigation) ቴክኖሎጂ ተግባራዊ ለማድረግ ከእስራኤሉ ኔታፊም ኩባንያ ጋር ውል ተፈራረመ፡፡

የኮርፖሬሽኑ የሕግ አገልግሎት ሥራ አስፈጻሚ አቶ ፋሲል ገብረማርያም እንደገለጹት ኮርፖሬሽኑ ከኩባንያው ጋር የተፈራረመው የውል ስምምነት በፕሮጀክቱ ሰባት ሺህ ሄክታር መሬት በጠብታ መስኖ ለማልማት የሚያስችል ነው፡፡

• የህዝብና የመንግሥት ክንፍ የውይይት መድረኮች ተካሄዱ

» ወደ ገጽ 3 ዞሯል

በውስጥ ገጾች

-> በኮርፖሬሽኑና በመሠረታዊ ሠራተኛ ማህበር መካከል እየተካሄደ የሚገኘው የህብረት ስምምነት ድርድር በመጠናቀቅ ላይ ነው>>ገጽ 4 -> የክልሎች ፕሬዚዳንቶች የስኳር ልማት ፕሮጀክቶችን ጎበኙ>> 5-> የስኳር ልማት የኤልኒኖ ተጽዕኖን የመቀነስ ሚና >> ገጽ 9

የመንግሥት ክንፍ የውይይት መድረክ ላይ እንደተናገሩት፣ በዘርፉ የሚከናወኑ ሥራዎች ሳይደነቃቀፉ በሚፈለገው መልኩ እንዲፈጸሙ የባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሠራር ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

ከመሃል አቶ በየነ ገብረመስቀል የመንግስት ልማት ድርጅቶች ሚኒስትር ዴኤታ የውይይት መድረኩን ሲመሩ

Page 2: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 3 መጋቢት 2008

ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት

ቅፅ 4. ቁጥር 3 | መጋቢት 2008 ዓ.ም | 2

የስኳር ልማት ግቦችን ለማሳካት የባለድርሻ ...

ሁሉም አካላት ካለፉት ስህተቶቻቸው በመማር አለመድገማቸውን ማረጋገጥ ያስፈልጋል ያሉት አቶ በየነ፣ የታዩ ችግሮችን ለመፍታት ኮርፖሬሽኑም ሆነ ባለድርሻ አካላት ተቀናጅተው በጋራ መስራት እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል፡፡ ይህንንም ለመተግበር የተጀመሩ የውይይት መድረኮች ሳይቆራረጡ መቀጠል እንደሚኖርባቸው አሳስበዋል፡፡

የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ እንዳወቅ አብቴ በበኩላቸው መንግሥት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ኮርፖሬሽኑ የለውጥና የልማት ሠራዊት በመገንባት መንቀሳቀስ የፈለገበትን ምክንያት ሲያስረዱ፣ የማስፈጸም አቅም በተሻለ ደረጃ ለመፍጠርም ሆነ ከባለድርሻ አካላት ጋር ገንቢና ጤናማ የሆነ የተልእኮ ስኬትን በመጋራት ላይ የተመሰረተ ግንኙነት ለማድረግ ስለሚያግዝ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ከዚህ አኳያ የውይይት መድረኩ የጋራ ክፍተቶችን በማሳየትና የትኩረት አቅጣጫዎችን በመጠቆም የበለጠ እጅ ለእጅ ተያይዞ ለመሄድ የሚያስችል ዝግጅት ለማድረግም ይረዳል ብለዋል፡፡

ከባለድርሻ አካላት አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶች በጊዜና በጥራት የሚቀርቡበት ሁኔታ አስቀድሞ ካልተመቻቸ የስኳር ልማት ዘርፍ እቅድን ማሳካት ፈጽሞ ሊታሰብ አይችልም ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፣ ኮርፖሬሽኑ ለወጠናቸው ግቦች ስኬት የማስፈጸም አቅምን በከፍተኛ ደረጃ ማሻሻል፣ ከባለድርሻዎች ጋር ቅንጅታዊ አሰራር መፍጠርና ማጠናከር እንደሚያስፈልግ አስረድተዋል፡፡

በቅንጅት መድረኩ ላይ በመንግሥት ክንፍ ከተለዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በተያያዘ የሚታዩ እጥረቶችን አስመልክቶ ለውይይት መነሻ የሚሆን ሃሳብ በኮርፖሬሽኑ የመሰረተ ልማት ኮንትራት አስተዳደር ሥራ አስፈጻሚ አቶ ራህመቶ አኒቶ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

የውይይቱ ተሳታፊዎች የነበሩት የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ሚኒስቴር፤ የውሃ፣ መስኖና ኤሌክትሪክ ሚኒስቴር፤ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል፤ ኢትዮ ቴሌኮም፤ የአዋሽ ተፋሰስ ባለስልጣን፤ የኢትዮጵያ ውሃ ሥራዎች ዲዛይንና ቁጥጥር ኮርፖሬሽን እና የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ሓላፊዎችና ተወካዮች በኮርፖሬሽኑ አገልግሎት አሠጣጥ ዙሪያ በርካታ ጥያቄዎች፣ አስተያየቶችና ቅሬታዎችን አቅርበው ውይይቱን በመሩት ሚኒስትር ዴኤታው አቶ በየነ ገብረ መስቀል፣ አቶ እንዳወቅ አብቴ እና በኮርፖሬሽኑ ሓላፊዎች ምላሽ ተሰጥቷባቸዋል፡፡ በወቅቱ ከባለድርሻ አካላት በኮርፖሬሽኑ ላይ ከተነሱት ክፍተቶች ውስጥ የግንባታ ሥራ ከተጀመረ በኋላ ተደጋጋሚ የዲዛይን ለውጥ ማድረግ፣ የተጠየቁ ክፍያዎች ረዘም ላለ ጊዜ ሳይፈጸሙ መቆየት፣

ድክመቶችን ወደ እራስ ከመመልከት ይልቅ የሌላ አካል ችግር ብቻ አድርጎ መውሰድ፣ ለሥራ የሚያስፈልግ በቂ በጀት አለመመደብ፣ ውሳኔዎችን መቀያየር እና ለቅንጅታዊ ሥራ ትኩረት አለመስጠት የሚሉት በዋነኛነት ይጠቀሳሉ፡፡

በኮርፖሬሽኑ በኩል ደግሞ የአዋሽ ተፋሰስ ባለስልጣን ድርቁ ከፈጠረው ችግር ጋር ተያይዞ በተለይ ለመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ፍትሃዊ የሆነ የውሃ አቅርቦት እያደረገ ባለመሆኑ ፋብሪካው ለጉዳት እየተጋለጠ እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡ የችግሩን አሳሳቢነት በማጤንም ባለስልጣኑ አስቸኳይ መፍትሔ እንዲሰጥበት አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡

በሌላ በኩል በስኳር ሥርጭት ሒደት ችግሮችና የመፍትሔ ሐሳቦች ላይ ተነጋግሮ የአሰራር ቅልጥፍናን ለማረጋገጥ እና ተገልጋዩ ሕዝብ የስኳር ሥርጭትን በሚመለከት የሚያነሳቸውን የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመቅረፍ በሚያስችሉ መፍትሔዎች ላይ ትኩረት ያደረገ የህዝብና የመንግሥት ክንፍ የውይይት መድረክ መጋቢት 6 ቀን 2008ዓ.ም በኢትዮጵያ ሆቴል ተካሄዷል፡፡

የአዲስ አበባ የሸማቾች ማኅበራት፣ የኢንዱስትሪ ግብዓት አገልግሎት ድርጅት (ጅንአድ)፣ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ እና የኢትፍሩት ሓላፊዎችና ተወካዮች በተሳተፉበት በዚህ ውይይት ላይ ንግግር ያደረጉት የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ እንዳወቅ አብቴ እንደገለጹት፣ ኮርፖሬሽኑ እያቀረበ ያለው 60ዐ ሺ ቶን ያህል አመታዊ የስኳር ምርት የሚያዝናና ባይሆንም የሕብረሰቡን ፍላጐት ያሟላል ብለዋል፡፡

ይሁንና የስኳር አቅርቦት መጠኑን በአግባቡ ለተጠቃሚው ከማድረስ አንፃር ችግሮች እንደሚታዩ የተናገሩት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፣ ለችግሩ ሁሉም በእኩል ደረጃ ተጠያቂና ተወቃሽ መሆን እንደሌለበት አስታውቀዋል፡፡ በመሆኑም የስኳር ሥርጭቱን ኃላፊነት በተሞላበትና የጋራ ተልዕኮን በመሸከም መንፈስ በቅንጅት ማሳካት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መመካከር፣ የመፍትሔ አቅጣጫዎችን ማስቀመጥና ይህንኑ በቀጣይ ተግባራዊ ማድረግ የውይይት መድረኩ ዓላማ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

በዕለቱ በስኳር ሥርጭት ዙሪያ የሚያጋጥሙ ችግሮች ላይ ትኩረት ያደረገ ለውይይት መነሻ የሚሆን ገለጻ በኮርፖሬሽኑ የግብይት ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ጣይቱ አሊ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል፡፡በውይይቱ ወቅት ከተሳታፊዎች ከተነሱት ጥያቄዎችና ቅሬታዎች ውስጥ የስኳር ኮታ ድልድል የየአካባቢውን ህዝብ ብዛት ያገናዘበ አለመሆኑ፤ የስኳር ጥራት መጓደል፤ የስኳር ማዳበሪያ ጥራት ችግር፤ የኪሎ ማነስ(ጉድለት)፤

» ከገጽ 1 የዞረ

ከመሃል አቶ እንዳወቅ አብቴ የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ የውይይት መድረኩን ሲመሩ

» ወደ ገጽ 3 ዞሯል

Page 3: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 3 መጋቢት 2008

በስኳር ኮርፖሬሽን ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ | 3

ስኳር ፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች በድርቅ ለተጎዱ...

መኖና ውሀ በአካባቢው ለሚገኙ አርብቶ አደሮች አቅርቧል፡፡

እንደ ሓላፊው ገለጻ የመተሀራ ስኳር ፋብሪካ የ2008 ዓ.ም የምርት ሂደቱን ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ከፈንታሌ ወረዳ መስተዳድር ጋር ድርቁን ለመከላከል የሚያስችል የጋራ ግብረ ሀይል በማቋቋምና ባለፉት አምስት ወራት የራሱን የጭነት መኪኖች በመመደብ የሸንኮራ አገዳ ገለባ እንዲሁም ለእንስሳቱ እና ለማህበረሰቡ ንጹህ የመጠጥ ውሀ አቅርቧል፡፡

በተጨማሪም በድርቁ ሳቢያ እናቶች እና ህጻናት የጤና ጉዳት እንዳያጋጥማቸው

በፋብሪካው ሆስፒታል የነጻ ህክምና እና የአልሚ ምግብ ድጋፍ እተደረገላቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ሓላፊው አክለውም እስካሁን በፈንታሌ ወረዳ የሚገኙ 18 የገጠር ቀበሌዎች፣ ከምዕራብ ሀረርጌ አንጫር ወረዳ የመጡ አርብቶ አደሮች እንዲሁም ከፋብሪካው በቅርብ ርቀት ላይ የሚገኙ የአፋር ክልል አርብቶ አደሮችን ጨምሮ በ12 አካባቢዎች ፋብሪካው በራሱ ተሽከርካሪ የሸንኮራ አገዳ ገለባ በማቅረብ ላይ ይገኛል፡፡

በዚህ ድጋፍም ከ11ሺ በላይ አባወራዎች እና እማወራዎች ተጠቃሚ ሲሆኑ፣ ከአንድ

ስኳር ኮርፖሬሽን ለጠብታ መስኖ ግንባታ ከእስራኤል ...

ኔታፊም በወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት ተግባራዊ የሚያደርገው የጠብታ መስኖ ቴክኖሎጂ ውስን የውሃ ሀብት በአግባቡ ለተፈለገው ዓላማ ለማዋል ከፍተኛ ጠቀሜታ እንደሚኖረው አቶ ፋሲል ተናግረዋል፡፡

ቴክኖሎጂው የሸንኮራ አገዳ ምርትን ለማሣደግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል

ያሉት አቶ ፋሲል ግንባታው በ18 ወራት ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቅ አስታውቀዋል፡፡

የጠብታ መስኖ ቴክኖሎጂው ተግባራዊ የሚደረገው ሀፖሊም ከተባለው የእስራኤል ባንክ በተገኘ 200 ሚሊዮን ዶላር ብድር ሲሆን ብድሩም በዘጠኝ አመታት ተከፍሎ የሚያልቅ ይሆናል፡፡

ከኮርፖሬሽኑ ጋር የጠብታ መስኖ ቴክኖሎጂ ተግባራዊ ለማድረግ የተፈራረመው የእስራኤሉ ኔታፊም ኩባንያ በአፍሪካ፣ በእስያና በሌሎች አገሮች በመስራት በዘርፉ ከፍተኛ ልምድ ያለው ነው ብለዋል ሥራ አስፈጻሚው፡፡

» ከገጽ 1 የዞረ

» ከገጽ 1 የዞረ

በኮርፖሬሽኑ የስኳር መጋዘን አገልግሎት ላይ የመልካም አስተዳደር ችግሮች በተደጋጋሚ መከሰት እና ስኳር ከመጋዘን ለመውሰድ ያለው ቢሮክራሲያዊ ሂደት ረጅም ነው የሚሉት በዋነኛነት ይጠቀሳሉ፡፡

የውይይት መድረኩን የመሩት የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ በሰጡት ምላሽ በኮርፖሬሽኑ ላይ በስኳር ጥራት፣ በኪሎ

ማነስ (መጉደል)፣ በማዳበሪያ ጥራት፣ ስኳር መኪና ላይ የመጫን አቅም ማነስ እና በስኳር መጋዘን አካባቢ የተነሱ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ገምግሞ ለመፍታት ኮርፖሬሽኑ ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል ብለዋል፡፡ የስኳር ኮታ ድልድልን እና ስኳር ለመውሰድ ያለውን ውጣ ውረድ ለመፍታትም ኮርፖሬሽኑ ከንግድ ሚኒስቴር እና ንግድ ቢሮ ጋር እንደሚነጋገር እና በጋራ እንደሚሰራ አክለው ገልጸዋል፡፡

በተከታታይ የተካሄዱት ሁለቱ መድረኮች በየሦስት ወሩ በመደበኛነት እንደሚቀጥሉ እና በቀጣይም በሌሎች ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ተመሳሳይ የህዝብና የመንግሥት ክንፍ የውይይት መድረኮች እንደሚዘጋጁ ታውቋል፡፡

የስኳር ልማት ግቦችን ... » ከገጽ 2 የዞረ

ሚሊዮን በላይ የሚገመቱ የቤት እንስሳት እንደሚገኙ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡እንደ አቶ ሲሳይ ገለጻ ፋብሪካው በድርቁ ሳቢያ ያጋጠመው ችግር እስከሚስተካከል ድረስ የጀመረውን ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡

በተያያዘ ዜና የጣና በለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን ምዕራብ በለሳ ጉኋላና ዋግህምራ ወረዳዎች በድርቅ በተጎዱ አካባቢዎች ለሚገኙ አርብቶ አደሮች እንስሳት መኖ የሚሆን የአገዳ ድጋፍ አድርጓል፡፡

ፕሮጀክቱ በ41 መኪኖች ለከብት መኖነት የሚውል የሸንኮራ አገዳ ለተጠቀሱት ወረዳዎች ማድረስ መቻሉን ገልጾ፣ በቀጣይም የማጓጓዣ መኪኖችን ቁጥር በመጨመር የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል፡፡

በተመሳሳይ ከዚህ ቀደም የወንጂ ሸዋ፣ የከሰምና የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካዎች እንዲሁም የወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት በአካባቢዎቻቸው ለሚገኙ በድርቁ ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡

Page 4: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 3 መጋቢት 2008

ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት

ቅፅ 4. ቁጥር 3 | መጋቢት 2008 ዓ.ም | 4

በኮርፖሬሽኑና በተቋሙ የመሠረታዊ ሠራተኛ ማህበር መካከል የህብረት ስምምነት ተፈረመ

በስኳር ኮርፖሬሽን እና ዋናው መ/ቤትን ጨምሮ ሁሉንም ስኳር ፋብሪካዎችና የስኳር ልማት ፕሮጀክቶችን ባቀፈው የመሠረታዊ ሠራተኛ ማህበር መካካል የህብረት ስምምነት ተፈረመ፡፡

የህብረት ስምምነት ድርድሩ ከህዳር 21 ቀን 2008 ዓም ጀምሮ ሲካሄድ ቆይቶ መጋቢት 24 ቀን 2008ዓ.ም በኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት ተፈርሟል፡፡

በፊርማ ሥነ ስርዓቱ ላይ የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ እንዳወቅ አብቴ ባደረጉት ንግግር የኮርፖሬሽኑ አመራር መሰረታዊ የሠራተኛ ማህበሩን እንደ አንድ ትልቅ የስራ አጋር አድርጐ እንደሚመለከተው እና ተገቢውን እውቅና እንደሚሰጠው አስታውቀዋል፡፡

በኮርፖሬሽኑ አጠቃላይ የስራ ሂደት ላይ መሰረታዊ የሰራተኛ ማህበሩ የነቃ ተሳትፎ እንዲኖረው አስፈላጊው ጥረት ይደረጋል ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፣ በአንጻሩ ማህበሩ ኮርፖሬሽኑ አሁን የሚገኝበትን እጅግ ወሳኝ

ምእራፍ ተገንዝቦ የሚጠበቅበትን ኃላፊነት በአግባቡ እንደሚወጣ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡

የኮርፖሬሽኑ መሰረታዊ የሰራተኛ ማህበር ሊቀመንበር አቶ ተመስገን ወልደመስቀል በበኩላቸው ኮርፖሬሽኑ ላቀዳቸው ሥራዎች መሳካት ማህበሩ ከተቋሙ ጋር በመሆን የሚጠበቅበትን ሁሉ ለመስራት ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በስኳር ኮርፖሬሽን ታሪክ በአንድ ወጥ የህብረት ስምምነት ለመደራደር በተደረገው እንቅስቃሴ በተደራዳሪዎች መካከል የነበረው መግባባትና ቀናነት ድርድሩ ያለምንም ችግር በሰላማዊ መንገድ እንዲጠናቀቅ ማስቻሉንም ተናግረዋል፡፡

በዕለቱ ከህብረት ስምምነቱ አንቀጾች በኮርፖሬሽኑ አመራር የበለጠ ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገባቸው ጉዳዮች በድርድሩ ወቅት ተሳታፊ በነበሩት ወ/ሮ አልማዝ እንዳይላሉ ቀርበው ማብራሪያ

ተሰጥቶባቸዋል፡፡

በመጨረሻም በህብረት ስምምነት ድርድሩ ተሳታፊ የነበሩ 16 አባላት ከኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ እጅ የምስጋና ምስክር ወረቀት ተቀብለዋል፡፡

በፊርማው ሥነ ስርዓት ላይ የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን፣ የኢትዮጵያ አሠሪዎች ፌዴሬሽን እና የአገር አቀፍ እርሻ ተክል፣ አሳና አግሮ ኢንዱስትሪ ሠራተኛ ማህበራት ፌዴሬሽን ተወካዮች እንዲሁም የስኳር ኮርፖሬሽን የመሰረታዊ ሠራተኛ ማህበርና የዘርፍ ማህበራት አመራሮች እና የኮርፖሬሽኑ፣ የስኳር ፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች የሥራ ሓላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

የህብረት ስምምነቱ የኢንዱስትሪ ሠላምን በማስፈን ምርትና ምርታማነትን ከማሳደግ ባለፈ የሰመረ የሥራ ግንኙነት እንደሚመሰርት ይጠበቃል፡፡

የኤች አይ ቪ/ኤድስ አካቶ ትግበራ ግምገማዊ ሥልጠና ተሰጠየኮርፖሬሽኑ የጤና ዳይሬክቶሬት ከተቋሙ ጋር አብረው ለሚሰሩ ሴክተር መስርያ ቤቶች እና ወረዳዎች፣ የ ኤች አይ ቪ/ኤድስ ጉዳዮች አስተባባሪዎች እና ዘርፍ ኃላፊዎች የአካቶ (Mainstreaming) ትግበራ ሥልጠና ሰጠ፡፡

ከመጋቢት 5 እስከ መጋቢት 7/2008 ዓ.ም በአዳማ በተካሔደው ሥልጠና 70 ሠልጣኞች ተሳትፈዋል፡፡ በሥልጠናው የአቻ ለአቻ ሥልጠና ፣የትስስር ሥራዎች፣ የበራሪ ጽሑፍ ዝግጅት ፣ ኮንዶም ስርጭት እና ተያያዥ ጉዳዮች ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

ከዚህ በተያያዘ ከመጋቢት 8 እስከ መጋቢት 10 2008 ዓ.ም ለ50 የኮርፖሬሽኑ ሠራተኞች በኤች አይ ቪ /ኤድስ ዙርያ ግምገማዊ ሥልጠና

ተሠጥቷል፡፡ ሥልጠናውን አስመልክቶ ማብራርያ የሰጡት በጤና ዳይሬክቶሬቱ የኤችአይቪ /ኤድስ ጉዳዮች አስተባባሪ ሲስተር ካሰች ሺበሺ እንደገለጹት በስኳር ልማት ሴክተር የኤች አይ ቪ/ኤድስ ስርጭትን ለመቀነስ መንግሥት ባስቀመጠው አቅጣጫ በርካታ ስራዎች እየተከናወኑ ነው፡፡

ከኮርፖሬሽኑ ጋር አብረው የሚሠሩ አንዳንድ ሴክተር መሥርያ ቤቶች እና ስኳር ልማት ፕሮጀክቶች በእኩል ደረጃ እየተንቀሳቀሱ አለመሆኑንና ከስኳር ልማት ፕሮጀክቶች መካከልም የኤችአይቪ /ኤድስ ስርጭትን ለመግታት በጀት ያልያዙ እንደሚገኙ ጠቁመዋል፡፡

ስልጠናው በተሰጠበት ወቅት

የፊርማው ሥነ ስርዓት ሲካሄድ

Page 5: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 3 መጋቢት 2008

በስኳር ኮርፖሬሽን ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ | 5

የክልሎች ፕሬዚዳንቶች የስኳር ልማት ፕሮጀክቶችን ጎበኙ

የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል እና የአማራ ክልል ፕሬዚዳንቶች የኦሞ ኩራዝ እና የጣና በለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክቶችን ጎበኙ፡፡

በዚሁ መሠረት የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ደሴ ዳልኬ በግንባታ ላይ የሚገኙትን የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1፣2፣3 እና 5 ስኳር ፋብሪካዎችን ከስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ እንዳወቅ አብቴ እና ሌሎች የክልሉ እና የኮርፖሬሽኑ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በመሆን ጥር 27 ቀን 2008ዓ.ም ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡

በተመሳሳይ በአማራ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው እና የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ እንዳወቅ አብቴ የተመራ ከፍተኛ የልኡካን ቡድን በጣና በለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት የሚገነቡ ቁጥር 1 እና 2 ስኳር ፋብሪካዎችን እንዲሁም የአገዳ ልማት፣ የመስኖ፣

የማህበራዊ አገልግሎት መስጫ እና የመሰረተ ልማት ተቋማትን የካቲት 13 ቀን 2008ዓ.ም ተዘዋውሮ ጎብኝቷል፡፡

በጉብኝቱ ወቅት በተደረገ ውይይት በጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ ቁጥር አንድ እና ሁለት ያለው የሥራ እንቅስቃሴ እና ያጋጠሙ ችግሮች ለውይይት ቀርበው የመፍትሔ አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል፡፡ በዚሁ ወቅት የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የጉብኝቱ ዓላማ የፕሮጀክቱን ችግሮች በጋራ በመፍታት የሚገነቡት ስኳር ፋብሪካዎች ውጤታማ ሆነው የሀገሪቱን የልማት ግቦች እንዲያሳኩ ለማገዝ ነው ብለዋል፡፡

የኦሞ ኩራዝ 1፣ የጣና በለስ 1 እና 2 ስኳር ፋብሪካዎች ግንባታ በኢትዮጵያ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

የደቡብና የአማራ ክልሎች ትሬዝዳንቶች በኦሞና በጣና በለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክቶች ያደረጉት የስራ ጉብኝት

በዓለም ለ105ኛ ጊዜ በአገራችን ደግሞ ለ40ኛ ጊዜ የተከበረውን ዓለም ዓቀፍ ሴቶች ቀንን ምክንያት በማድረግ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ባዘጋጀው የ 5 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር የተሳተፉ የኮርፖሬሽኑ ሴት ሠራተኞች

Page 6: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 3 መጋቢት 2008

ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት

ቅፅ 4. ቁጥር 3 | መጋቢት 2008 ዓ.ም | 6

በደቡብ ብ/ብ/ሕ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደሴ ዳልኬ የተመራው ልዑክ በኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ያደረገው የስራ ጉብኝት

Page 7: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 3 መጋቢት 2008

በስኳር ኮርፖሬሽን ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ | 7

በአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገዱ እንዳርጋቸው የተመራው ልዑክ በጣና በለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ያደረገው የሥራ ጉብኝት

Page 8: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 3 መጋቢት 2008

ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት

ቅፅ 4. ቁጥር 3 | መጋቢት 2008 ዓ.ም | 8

ውይይቱ በተካሄደበት ወቅት

የአርጆ ዲዴሳ ስኳር ፋብሪካ አመራር ከአካባቢው ማህበረሰብ ከተውጣጡ ባለድርሻ አካላት ጋር በልማት ተሳትፎና ተጠቃሚነት ዙሪያ ጥር 28 ቀን 2008ዓ.ም በበደሌ ከተማ ተወያየ፡፡

ውይይቱ የተካሄደው ከኢሉ አባቦራ እና ምስራቅ ወለጋ ዞኖች ከተውጣጡ የዞን፣ የወረዳ፣ የቀበሌ አመራሮችና ህብረተሰቡን ከወከሉ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶችና የባለድርሻ አካላት ጋር ሲሆን፤ 190 የሚሆኑት እነዚህ የውይይቱ ተሳታፊዎች በፋብሪካው አካባቢ ከሚገኙ ሁለት ዞኖች፣ ሰባት ወረዳዎችና 11 ቀበሌዎች የመጡ ናቸው፡፡

በወቅቱ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአርጆ ዲዴሳ ስኳር ፋብሪካ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አበራ ማሞ ፋብሪካው በተለያዩ ጊዜያት ባካሄዳቸው የአገዳ ተከላ ዘመቻዎች እና በተያያዥ የልማት ሥራዎች ላይ የአካባቢው ማህበረሰብ በመሳተፍ ላበረከተው ከፍተኛ አስተዋጽኦ ምስጋናቸውን አቅርበው፣ ፋብሪካው የማህበረሰቡ እንደመሆኑ መጠን በቀጣይም ማህበረሰቡ በልማቱ የበለጠ ተጠቃሚ ለመሆን የፋብሪካው አጋር ሆኖ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል፡፡ ፋብሪካው በተቻለ መጠን ለማህበረሰቡ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልጸዋል፡፡

በውይይቱ ላይ በፋብሪካው ነባራዊ ሁኔታ፣ ማህበረሰቡን የልማቱ ተጠቃሚ ለማድረግ በተከናወኑ ሥራዎች እንዲሁም በማህበረሰብ የልማት ተሳትፎና ለወደፊት ትኩረት ሊሰጣቸው በሚገባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ለውይይት መነሻ የሚሆን ጽሑፍ በፋብሪካው ህዝብ ግንኙነት ክፍል ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ በቀረበው ጽሁፍ ላይ ልማቱ በፈጠረው ሰፊ የስራ ዕድል ከዩኒቨርሲቲና ከቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች በተለያዩ ሙያዎች የተመረቁ ወጣቶች በፋብሪካው ውስጥ ተቀጥረው ራሳቸውንና ቤተሰቦቻቸውን በመጥቀም ላይ እንደሚገኙ እና በቴክኖሎጂ ሽግግርም ተጠቃሚ እየሆኑ እንደመጡ ተገልጿል፡፡ እንዲሁም በ35 አነስተኛና ጥቃቅን ማህበራት የተደራጁ ከ320 በላይ የአካባቢው ስራ አጥ ወጣቶች ከራሳቸው አልፈው ለሌሎች ወጣቶች የስራ እድል በመፍጠር ላይ እንደሚገኙ ተብራርቷል፡፡

የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ፋብሪካው የአካባቢውን ማህበረሰብ እየጠቀመ ለመሆኑ የየአካባቢያቸው ሰዎች ምስክር መሆናቸውን ተናግረው፣ ፋብሪካው በቀጣይ የበለጠ ተጠቃሚ እንደሚያደርጋቸው በማመን እንደ ራሳቸው ንብረት እንደሚንከባከቡትና ደህንነቱንም

እንደሚጠብቁ ገልጸዋል፡፡ አክለውም ወደፊት የአካባቢው ማህበረሰብ ሸንኮራ አገዳ አልምቶ (አውትግሮወር) ለፋብሪካው ማቅረብ በሚችልበት አሰራር ላይ ግንዛቤን ለመፍጠር ልምድ ካላቸው ስኳር ፋብሪካዎች ተሞክሮ የሚገኝበት ሁኔታ እንዲመቻች ጠይቀዋል፡፡

በውይይቱ ማጠቃለያ ላይ የምስራቅ ወለጋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ነመራ ቡሊና የኢሉ አባቦር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሻፊ ኡመር ፋብሪካው ያቀዳቸው ዘርፈ ብዙ ሥራዎች በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ የተያዘውን ግብ ከማሳካት አኳያ ትልቅ ድርሻ እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡

በየደረጃው ያሉ አመራሮች ከፋብሪካው ጋር ትስስር በመፍጠር እና የአካባቢውን ማህበረሰብ ግንዛቤ በማሳደግ ህብረተሰቡ በፋብሪካው ስራ ላይ በስፋት እንዲሳተፍ እና ከልማቱ የበለጠ ተጠቃሚ እንዲሆን በቁርጠኝነት መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡ ፋብሪካው ያሉበትን ችግሮች ለመፍታትም የሁለቱም ዞኖች ስቲሪንግ ኮሚቴዎች በመደበኛነት በመገናኘት እንደሚሰሩ አስታውቀዋል፡፡

የአርጆ ዲዴሳ ስኳር ፋብሪካ አመራር ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በልማት ተሳትፎና ተጠቃሚነት ዙሪያ ተወያየ

Page 9: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 3 መጋቢት 2008

በስኳር ኮርፖሬሽን ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ | 9

የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና መስሪያ ቤት እና የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ሠራተኞች ደም ለገሱ

የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና መስሪያ ቤት እና የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ሠራተኞች በፈቃደኝነት ደም ለገሱ::

በመተሐራ የፋብሪካው ሠራተኞችና የሥራ ኃላፊዎች የተሳተፉበትን የሦስት ቀናት የደም ልገሳ መርሐ ግብር በጋራ ያዘጋጁት የኦሮሚያ ክልል ጭሮ የደም ባንክ እና የመተሀራ ስኳር ፋብሪካ ሆስፒታል ሲሆኑ፣ የኮርፖሬሽኑን ዋና መ/ቤት መርሐ ግብር ያስተባበረው ደግሞ የኮርፖሬሽኑ የሥርዓተ ጾታ ዳይሬክቶሬት ነው፡፡የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ሠራተኞችና የሥራ

ኃላፊዎች የለገሱት ደም በተለያዩ ምክንያቶች ደም የሚያስፈልጋቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች ክቡር ሕይወት ከአደጋ እንደሚታደግ ያላቸውን እምነት መግለጻቸውን እና በመርሐ ግብሩ በመሳተፋቸው ደስተኛ መሆናቸውን የፋብሪካው የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ያደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡

በተመሳሳይ በኮርፖሬሽኑ ዋና መስሪያ ቤት የተካሄደው የደም ልገሳ መርሐ ግብር በአገራችን ለ40ኛ ጊዜ “መልካም አስተዳደር በማስፈን የሴቶችን እኩል ተሳትፎና ተጠቃሚነት እናረጋግጥ!” በሚል መሪ ቃል

የተከበረውን ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን በማስመልከት ነው፡፡

በልገሳ መርሐ ግብሩ ላይ የተሳተፉ ሠራተኞች በሰጡት አስተያየት ክቡር የሆነው የሰው ልጅ ሕይወት በተለያዩ ምክንያቶች የከፋ አደጋ እንዳይደርስበት የለገሱት ደም አስተዋፅኦ እንደሚያበረክት ተናግረዋል፡፡

በሥርዓተ ጾታ ዳይሬክቶሬት ለሁለተኛ ጊዜ በተዘጋጀው በዚህ የደም ልገሳ መርሐ ግብር ላይ በርካታ የዋናው መስሪያ ቤት ሠራተኞች ተሳትፈዋል፡፡

የዋና መ/ቤት ሠራተኞች ደም ሲለግሱ

የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ሠራተኞች ደም ሲለግሱ

Page 10: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 3 መጋቢት 2008

ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት

ቅፅ 4. ቁጥር 3 | መጋቢት 2008 ዓ.ም | 10

ባሳለፍነው የፈረንጆች ዓመት የተከሰተው ኤልኒኖ የአየር ለውጥ በበርካታ የዓለም ክፍሎች በተለይም በምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ላይ ተጽዕኖውን አሳርፏል፡፡ የአየር ለውጡ ከሚንጸባረቅባቸው መንገዶች አንዱ ተጽዕኖው ባረፈባቸው ክፍላተ ዓለማት የሚገኙ ወንዞች የውሃ መጠን መቀነስ ነው፡፡ በዚህም ኤልኒኖ በተለይ በዝናብ ወራት ወቅት ብቻ የእርሻ ስራ የሚያከናውኑ ሀገራትን የምጣኔ ሀብት መጉዳቱ የሚጠበቅ ነው፡፡

በሌላም በኩል የተሟላ የመስኖ መሰረተ ልማት ያላቸው ታላላቅ ግድቦች መኖር የአካባቢው የውኃ ሀብት በአግባቡ ጥቅም ላይ ሳይውል እንዳይፈስ ማድረግ የሚያስችል በመሆኑ በተለይ ምጣኔ ሀብታቸው

በዝናብ ወቅት በሚከናወን የእርሻ ስራ ላይ ጥገኛ በሆኑ ሀገራት ላይ ኤልኒኖ እያስከተለ ያለውን ድርቅ ለመቋቋም ከፍተኛ ሚና መጫወት ይችላሉ፡፡

በኤልኒኖ ምክንያት ድርቅ ከተጋረጠባቸው ሀገራት አንዷ ኢትዮጵያ ነች፡፡ ሀገሪቱ ሰፊ የውሃ ሀብቷን በጥቅም ላይ ለማዋል በርካታ ህዝብ ተጠቃሚ ያደረጉና የሚያደርጉ ትልልቅ ግድቦች እና የመስኖ መሰረተ ልማቶች ሥራ እያከናወነች ትገኛለች፡፡ ለአብነትም ለኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት በተገነባው ጊዜዊ ግድብ (ኮፈር ዳም) አማካኝነት በልማቱ አካባቢዎች የሚኖረው የህብረተሰብ ክፍል በመስኖ በቆሎ እያመረተ ተጠቃሚ መሆን ጀምሯል፡፡

» ወደ ገጽ11ዞሯል

ቆይታ

የስኳር ልማት የኤልኒኖ ተጽዕኖን የመቀነስ ሚና

እንደ ደቡብ ኦሞ ዞን አስተዳዳሪ አቶ አለማየሁ ባውዲ ገለፃ፣ የኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት በዞኑ በሚገኙ ሁሉም ወረዳዎች በተከሰተው የአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ የአካባቢው ህዝብ በድርቅ እንዳይጠቁ ከፍተኛ እገዛ አድርጓል፡፡ በዚህም በወይጦ፣ በዞ እና ኦሞ በተዘረጉት የመስኖ መሰረተ ልማቶች በመጠቀማቸው አካባቢያቸው ለድርቅ አለመጋለጡን ነው አስተዳዳሪው የጠቆሙት፡፡

ከዚህ ቀደም የነበረውን የሰላማጎ አካባቢን የድርቅ ተጋላጭነት ሲያወሱም የስኳር ልማት ፕሮጀክቱ ወደ አካባቢው ከመጣ

ወዲህ ለወረዳው ምንም ዓይነት የምግብ እርዳታ አቅርበው እንደማያውቁ ተናግረዋል፡፡ “የውሃም ሆነ የከብቶች መኖ እጥረት ገጥሞናል የሚል ሪፖርት እስካሁን አልደረሰንም” የሚሉት አቶ አለማየሁ ይህ እንዲሆን ያስቻለው የኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ነው በማለት ፕሮጀክቱ ለአካባቢው ማህበረሰብ ያለውን ጠቀሜታ አስረድተዋል፡፡

“የስኳር ልማት ፕሮጀክቱ የመስኖ መርሐ ግብር እርሻን የማያውቁ የቦዲ ብሔረሰብ ነባር እና አዳዲስ መንደሮች ነዋሪዎች በቆሎ በማምረት ለአራተኛ ጊዜ በሔክታር እስከ 70 ኩንታል ምርት እንዲያገኙ አስችሏቸዋል፤ ለአምስተኛ ጊዜም በቆሎ ለመዝራት በዝግጅት ላይ ናቸው” የሚሉት ደግሞ በኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት-1 የህዝብ አደረጃጀት፣ ካሳ እና መልሶ ማቋቋም ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ አስረስ አደሮ ናቸው፡፡

የሰላማጎ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጳሺማ ወልኮሮ በበኩላቸው የስኳር ልማት ፕሮጀክቱ ወደ አካባቢው ከመግባቱ በፊት ወረዳቸው ለምግብ እጥረት እና እርዳታ የተጋለጠ

መሆኑን አስታውሰው፣ አሁን በኤልኒኖ ምክንያት በአካባቢው ምንም ዓይነት ተጽዕኖ እንዳልደረሰ ተናግረዋል፡፡

እንደሳቸው ገለፃ የስኳር ልማት ፕሮጀክቱ በአካባቢው ከመከፈቱ በፊት ኦሞ ሻሺ በተባለ አካባቢ በአርብቶ አደሮች ይመረት የነበረ የበቆሎ ምርት መጠን እጅግ አነስተኛ ከመሆኑ የተነሳ የአካባቢውን ዓመታዊ የምግብ ፍጆታ ለመሸፈን የማይታሰብ ነበር፡፡ ከዚህ አንጻር የወረዳዋ ነዋሪዎች የምግብ ዕርዳታ ይደረግላቸው እንደነበር እና አሁን ግን ምንም አይነት እርዳታ እንደማይፈልጉ አረጋግጠዋል፡፡ በቀደሙ ጊዜያት ለራሳቸውና ለእንስሳታቸው ምግብ እና ውሃ ፍለጋ ይንከራተቱ የነበሩ አርብቶ አደሮችም አሁን በአቅራቢያቸው ማግኘት ችለዋል፡፡

በፈቃደኝነት በመንደር ከተሰባሰቡት አርብቶ አደሮች አንዱ ናቸው የቦዲ ብሔረሰብ ተወላጅ አቶ ቦጪ ዶርባ፡፡ የመንደራቸው ሰዎች መጀመርያ አካባቢ ምን ያህል ፕሮጀክቱን ይጠራጠሩት እና እያንዳንዷን እንቅስቃሴ በጥንቃቄ ያዩት እንደነበር አስታውሰው፣ ኋላ ግን የቦዲና የሙርሲ ማህበረሰብ አባላት

በመስኖ ልማት እየተጠቀሙ ያሉትን የደቡብ ኦሞ ዞን በና፣ ጸማይ፣ ዳሰነች እና ኛንጋቶም ወረዳ አርብቶ አደሮችን ከጎበኙ በኋላ አመለካከታቸው መለወጡን ይናገራሉ፡፡

“በሀገሪቱ ስኳር ልማትን በመጀመር ቀዳሚ የሆነውን ወንጂ ስኳር ፋብሪካንም ጎብኝተን ልምድ ተጋርተናል፡፡ ኢንደስትሪው ምን ያህል ተጠቃሚ አድርጎ የቀድሞ በምግብ እርዳታ ላይ የተንጠለጠለ ሕይወታቸውን እንደቀየረው ለመረዳት ችለናል፡፡” ያሉት አቶ ቦጪ የዞን አስተዳደሩን እና የስኳር ልማት ፕሮጀክቱን መሬት ጠይቀው ለእያንዳንዳቸው 1 ሔክታር በመስኖ የሚለማ የሸንኮራ አገዳ መሬት እንደተሰጣቸው ገልጸዋል፡፡ ይህ በመሆኑም ግባታው እየተፋጠነ የሚገኘው ፋብሪካ ቁጥር 1 ስኳር ማምረት የሚጀምርበትን ጊዜ በጉጉት እየተጠባበቁ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም የሸንኮራ ማሳቸውን ከመንከባከብ ጎን ለጎን በፕሮጀክቱ እገዛ በቆሎ ለአራተኛ ጊዜ አምርተው ለአምስተኛ ዙር በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ገልጸው፣ የውኃ ኩሬዎች በየመንደሩ ስለተዘጁላቸውም

Page 11: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 3 መጋቢት 2008

በስኳር ኮርፖሬሽን ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ | 11

የስኳር ልማት የኤልኒኖ ተጽዕኖን .. » ከገጽ 10 የዞረ

ውሃ እና የግጦሽ መሬት ፍለጋ ሩቅ መኳተኑ ቀርቶልናል ብለዋል፡፡ ልጆቻቸውም መንደራቸው ላይ በተገነባው ትምህርት ቤት እየተማሩ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡ በሌላ በኩል የኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ለመስኖ የሚጠቀመውን የኦሞ ወንዝ ውሃን መጠን አስመልክቶ የፕሮጀክቱ መስኖ ግንባታ እና ጥገና ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ በኃይሉ ጌታቸው እንደተናገሩት፣ ፕሮጀክቱ በዋና እና ተጨማሪ የመስኖ ቦዮች ከኦሞ ወንዝ ከሚወስደው 22.76 ሜትር ኪዩብ ውሃ ውስጥ 0.0023 ሜትር ኪዩብ ብቻ ተጠቅሞ የተቀረውን ወደ ወንዙ ይመልሳል፡፡

በተመሳሳይ ከጊቤ ኃይል ማመንጫ ለዚሁ ዓላማ የሚውለው ውሃ ተመልሶ የሚገባው ወደ መደበኛ መስመሩ ሲሆን፣ ይህም በወንዙ የውሃ መጠን ላይ ምንም መዋዠቅ ያለማስከተሉ ታውቋል፡፡

ባለፉት 10 ዓመታት ኢትዮጵያ እያስፋፋች ያለችው ትላላቅ የመስኖ መሰረተ ልማት ሥራ በተለይም ከሸንኮራ ልማት ጋር ተያይዞ

የሚካሄደው የመስኖ ልማት አውታር ኤልኒኖን ማስቀረት ባይችልም እንኳ ልማቱ በሚካሄድባቸው አካባቢዎች የድርቅ ጉዳት እንዳይከሰት ግን ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል፡፡

በአጠቃላይ በኤሊኒኖ ምክንያት በአንዳንድ የአገራችን አካባቢዎች የተከሰተውን የድርቅ አደጋ ለመቋቋም የስኳር ፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች በየአካባቢያቸው ለሚገኙ የማኅበረሰብ አባላት ንጹህ የመጠጥ ውሃ፤ ለእንስሳት ደግሞ ውሃ፣ ለስኳር ምርት የማይውለውን የሸንኮራ አገዳ የላይኛው ክፍል እና እስር ሣር በማቅረብ ድጋፍ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ የአፍሪካ የውሃ ማማ የምትባለው ኢትዮጵያ ሰፊ የውሃ ሀብቷን በአግባቡ ለመጠቀም መብቱ እንዳላት ይታወቃል፡፡ ከዚህ የተነሳ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ መንግሥት የድርቅ ተጋላጭነትን ለመቀነስና ከዝናብ ጥገኝነት ለመላቀቅ የሀገሪቱን ውሃ ሃብት በአግባቡ ጥቅም ላይ ለማዋል ትልልቅ እና አነስተኛ የመስኖ ግድቦች እየሰራ ይገኛል፡፡ ይህም በቀጣይ ኤልኒኖንም ሆነ ሌሎች መሰል ተጽእኖዎችን ለመቋቋም ያስችላል፡፡

Page 12: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 3 መጋቢት 2008

www.ethiopiansugar.com || facebook.com/etsugar

በሀገራችን ዘመናዊ የስኳር ኢንዱስትሪ ልማት የኢትዮጵያ መንግሥት ኤች ቪ ኤ (HVA) ከተባለ የሆላንድ ኩባንያ ጋር የአክስዮን ስምምነት ከፈረመበት 1944 ዓ.ም አንስቶ ይጀምራል፡፡

በስምምነቱ መሠረትም አንጋፋው የወንጂ ስኳር ፋብሪካ ግንባታው ተጠናቆ በመጋቢት ወር 1946 ዓ.ም ሥራ ጀመረ፡፡ የወንጂን አዋጭነት ያጤነው ኤች ቪ ኤ (HVA) ከዘጠኝ ዓመት በኋላ ለሀገሪቱ ሁለተኛ የሆነውን የሸዋ ስኳር ፋብሪካ ገንብቶ ህዳር 5 ቀን 1955ዓ.ም በይፋ ሥራ አስጀመረ፡፡ በተመሳሳይ የመተሐራ ስኳር ፋብሪካም በኤች ቪ ኤ (HVA) አማካኝነት ተገንብቶ በ1962ዓ.ም ለአገራችን ሦስተኛው የስኳር ፋብሪካ መሆን ቻለ፡፡ ከአዲስ አበባ

በ200 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ከ10ሺ ሄክታር በላይ በሸንኮራ አገዳ የተሸፈነ መሬት ያለው ሲሆን፣ አማካይ ዓመታዊ ስኳር የማምረት አቅሙም በዓመት 136ሺ 692 ቶን ነው፡፡

ፋብሪካው ባካሄደው የማስፋፊያ ፕሮጀክት የኤታኖል ፋብሪካ ገንብቶ ከ2003ዓ.ም አጋማሽ ጀምሮ ኤታኖል በማምረት ላይ ይገኛል፡፡ ኤታኖል የማምረት ዓመታዊ አቅሙም በአመት እስከ 12.5 ሚሊዮን ሊትር ይደርሳል፡፡ በሌላ በኩል “ባጋስ” ተብሎ ከሚጠራው የሸንኮራ አገዳ ገለባ ዘጠኝ ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል በማመንጨት የራሱን የኃይል ፍላጎት እያሟላ የሚገኝ እድሜ ጠገብ ፋብሪካ ነው፡፡

ስለ መተሐራ ስኳር ፋብሪካ ሲነገር የካይዘን ስራ አመራር ፍልስፍናን ማንሳት የግድ ይላል፡፡ ፋብሪካው ካይዘንን በሚገባ በመተግበርና ውጤት በማስመዝገብ ቀዳሚ ነው፡፡ ከዚህ የተነሳ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ በተካሄደው የካይዘን ውድድር በተቋም፣ በልማት ቡድንና በግለሰብ አንደኛ በመሆን የዋንጫና የሜዳሊያ ሽልማቶችን አግኝቷል፡፡

በዚህ ብቻ አላበቃም በተመሳሳይ መስከረም 8 ቀን 2008 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሒልተን ሆቴል በተዘጋጀው ሀገር አቀፍ የካይዘን ውድድር ላይ ካይዘንን በማስቀጠል በተቋምና በልማት ቡድን ደረጃ በድጋሚ የአንደኝነት የክብር መዳሊያዎችን እና ዋንጫዎችን ከኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ እጅ ተቀብሏል፡፡

እናስተ

ዋውቃችሁ የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ