30

ቅፅ 2 ቁጥር 110 ቅዳሜ ህዳር 19 ቀን 2013 ዓ.ም

  • Upload
    others

  • View
    19

  • Download
    0

Embed Size (px)

Citation preview

Page 1: ቅፅ 2 ቁጥር 110 ቅዳሜ ህዳር 19 ቀን 2013 ዓ.ም
Page 2: ቅፅ 2 ቁጥር 110 ቅዳሜ ህዳር 19 ቀን 2013 ዓ.ም

11ግዮን ቁጥር 110 ህዳር 2013 ዓ.ም

ቅፅ 2 ቁጥር 110 ቅዳሜ ህዳር 19 ቀን 2013 ዓ.ም

ቀጣይ ዕትም ቅዳሜ ህዳር 26/2013 ዓ.ም

ይጠብቁን

ቁጥር 109

ግዮን

ክፍል አንድ 1-24

ክፍል ሁለት25-28

ግዮን ቁጥር 110 ህዳር 2013 ዓ.ም

Page 3: ቅፅ 2 ቁጥር 110 ቅዳሜ ህዳር 19 ቀን 2013 ዓ.ም

22ግዮን ቁጥር 110 ህዳር 2013 ዓ.ም

መንግሥት በሰሜን ዕዝ የሰራዊቱ አባላት ላይ የደረሰውን ዘግናኝ ጭፍጨፋ ተከትሎ በጦር መሳሪያ የጀመረው ሕግን የማስከበር ዘመቻ፣ በያዝነው ሳምንት መነሻ ቀናት ተቀዛቅዞ የነበረ ቢኾንም የአየር ጥቃቱ ግን

ቀጥሎ ነበር፡፡ መንግሥት የ72 ሰዓታት የእፎይታ ጊዜን ለትህነግ አዛዦችና ወታደሮች እስከሰጠበት ጊዜ በአውደ ውጊያው ጀቶች፣ ድሮኖች፣ ታንኮችና ሮኬቶችን ጨምሮ ብረት ለበስ ተሸከርካሪዎችና በነፍስ ወከፍ የሚታደሉ ከባድና ቀላል የጦር መሳሪያዎች ጥቅም ላይ ውለዋል፡፡ መከላከያ በሚመራው ዘመቻ ልዩ ኃይሎችና ሚሊሻዎች ከባባድ መሳሪያ ባይጠቀሙም በጋራ ያስመዘገቡት ድል ግን ለትህነጎች ጥጋብ ማስተንፈሻ ኾኗል፡፡ ከዘመቻው መነሻ ጀምሮ ትህነግ ይዟቸው የነበሩትን ቦታዎች ያስለቀቁት ኃይሎች፣ መሬትን መቆጣጠር ብቻ ሳይኾን ወታደሮችንና መሣሪያቸውን መማረክ የየቀን ዜና ኾኖ ሠነባብቷል፡፡ በጦር አውድማው ብቻ ሳይሆን፣ አዲስ አበባን ጨምሮ በግለሰቦችና በተቋማት ሳይቀር የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች በወቅቱ ቋንቋ “ገቢ” ሲደረጉ ቆይተዋል፡፡

የጦርነቱ ውጊያዎች እየተገባደደ ትህነግም ይዞታውን እየለቀቀ ወደ መቀሌ ሲከማች ግን፣ እንደ መሬቱ ኹሉ ትጥቁንም ማጣቱን በተሰጠው የእፎይታ ጊዜ አሳውቋል፡፡ የሦስት ቀናት ጊዜ መሠጠቱን፣ የሰገሌን ጦርነት እየጠቀሱ “ለተሸናፊ ጊዜ መስጠት አያስፈልግም” እያሉ ብዙዎች ቢተቹትም፣ የጉዳት መጠኑንም ይኹን የታሰበለትን ጥቅም ለይቶ ለማወቅ አስቸጋሪ ኾኗል፡፡ ያም ኾነ ይኽ፣ መቀሌ በታንክ ተከብባ ትህነግ በጭንቀት ተወጥራ እጇን በመስጠት ፋንታ ሳትጠየቅ መግለጫ ከመስጠት አልተቆጠበችም፡፡

በትህነግ ከወጡ መግለጫዎች ለየት የሚለው፣ በአቶ ጌታቸው ረዳ የቤት መገልገያ ቁሳቁሶችን “እንደ ጦር መሳሪያ ተጠቀሙበት” ተብሎ የተነገረው አዋጅ ነው፡፡ ሕዝብን ለማገልገል በሚል ሽፋን ሕዝብን የሚያስጨርስ እንዲህ ዓይነት መግለጫ በመስጠታቸው ብቻ፣ የሽልማት ወረታ ባያገኝ እንኳ ለትግራይ ሕዝብ ሲል የኛ የሚሉት አካል ዝም ማለቱ ያስተዛዝባል፡፡ መግለጫውን የሰማ ሰው ለመላው ኢትዮጵያዊ ብቻ ሳይኾን ለትግራይ ሕዝብም ያላቸውን ንቀት ይረዳል፡፡ “የቤትህን ቢላ ያዝና የከበበህ ታንክ ሲጠጋህ እንደ አንባሻ ቁረሰው፤… መጥረቢያ ያዝና ጠመንጃ የያዘን ተጠግተህ ፍለጠው፤… ጦርም ካለህ አውሮፕላን ሲበር ካየህ ቀርቅርበት፤…” ዓይነት ምክር አይሉት የሞት ፍርድ በሕዝቡ ላይ ፈርደውበታል፡፡ የትግራይ ሕዝብ በጣሊያን ወረራ ጊዜ እንኳን ያላደረገውን ይኽን ዓይነት የጅል ተግባር ባይፈጽምም፣ የከበበውን አደጋ አሳንሶ እንዲያይና ለጉዳት እንዲዳርገው ማድረጉ የሚያጠራጥር አይደለም፡፡ መከላከያም ኾነ የአማራ ልዩ ኃይል ዘመናዊ መሳሪያ የታጠቀውን የትህነግ ኃይል በወታደራዊ አማርኛ እየደመሰሰ መጥቶ፣ የቤት ቁሳቁስን በታጠቀ ስብስብ ይሸነፋል ማለት ዘበት ነው፡፡ በአንድ በኩል፣ ሠራዊቱ አዝኖላቸው ከሞትና ከጭቆና ሊታደጋቸው እንዲችል ልቡን ያራራል ብለው አስበው ሊኾን ይችላል፡፡

በሌላ በኩል ስናየው፣ ለውጊያ ከሚያገለግሉ የጦር መሣሪያዎች ውጭ ወታደር ያልኾነውን ተርታ ዜጋ ተጠቀም ያሉት ቁሳቁስ በዓለም አቀፍ ሕግ የተከለከለ መኾኑን ወደጎን ያሉበት የመጀመሪያ አጋጣሚ አለመኾኑን እንረዳለን፡፡ ለዚህ ደግሞ በማይካድራ የተፈፀመው ዘግናኝ የዘር ጭፍጨፋ ጉልህ ማስረጃ ይኾነናል፡፡ በከተማዋ ያሉ “ሳምሪ” የተሰኙ የትህነግ ወጣት ክንፍ አደረጃጀቶች፣ ትዕዛዝ ተቀብለው ከምሽት ጀምረው እስከ ንጋቱ ድረስ

ዘር የለየ ድንገተኛ ጭፍጨፋ አካሂደዋል፡፡ የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን በያዝነው ሳምንት ይፋ እንዳደረገው፣ ከ600 በላይ የማይካድራ ነዋሪዎች የተገደሉት በሠንጢ፣ በገመድ፣ በቢላዋና ገጀራን በመሳሰሉ መገልገያ ቁሳቁሶች ነው፡፡ ይኽ በኾነበት ሁኔታ ጨፍጫፊዎቹ ሸሽተው ሱዳን መጠለላቸው ሳያንስ፣ ለፍርድ አለመቅረባቸው ተዘንግቶ እርዳታ እንዲያገኙ እየተጮኸ ነው፡፡ ንጹሐኑንና ወንጀለኞቹን መለየቱ ከባድ ቢሆንም፣ ተጣርቶና ካሉበት ተይዘው ለፍርድ እስኪቀርቡ ድረስ ወደ ተለያዩ ቦታዎች እያመለጡ እነሱን መያዝ አድካሚና አስቸጋሪ እንዳይኾን ከወዲኹ ሊታሰብበት ይገባል፡፡ ዓለም የሰማውን ይኽን ዘግናኝ ተግባር በመቀሌ ለመድገም በማሰብ በተመሳሳይ መሣሪያዎች እርምጃ እንዲወስዱ መቀስቀሱ፣ ቀስቃሾቹ አካላት ላይ ለሚሰባሰበው ማስረጃ ተጨማሪ ኾኖ ማገልገሉ አይቀርም፡፡ ከትግራይ ተወላጅ ውጭ ያለውን ኢትዮጵያዊ በማስጨፍጨፍ የበቀል ተመሳሳይ እርምጃ እንደማይፈፀም ቢያውቁትም፣ ራሳቸው ፈፅመው ተፈፀመብን ለማለት ተዘጋጅተው እንደነበረም ሲነገር ቆይቷል፡፡ ያም ኾነ ይኽ፣ በ3ቱ ቀን የእፎይታ ጊዜ ቁጥራቸው ቀላል የማይባል የትህነግ ታጣቂዎች እጃቸውን ለመንግሥት ኃይሎች መሥጠታቸውን አልጀዚራን የመሳሰሉ የውጭ ሚዲያዎች ሳይቀር ዘግበውታል፡፡ የሰሜኑ ውጊያ ሙሉ በሙሉ ተጠናቅቆ ሌሎች ጭፍሮቻቸውን ለማስወገድ ወደ ሌሎች የሀገሪቱ ክፍል አፈሙዙ መዞሩ የማይቀር ነው፡፡ በሚወሰደው እርምጃ ምንም ግንኙነት የሌለው ሕብረተሰብ እንዳይጎዳ በራሪ ወረቀት የተበተነውን ያህል፣ እያውለበለቡ እጅ የሚሰጡበት ነጭ ጨርቅ ቢበተንም ችግራቸውን በመጠኑም ቢሆን ሊቀንሰው ይችላል፡፡ በርግጥ እነኚህ የደም ነጋዴዎች እንደሳዳምና ጋዳፊ ዓይነት ሕዝባቸውን ጨፍጭፈዋል የሚባሉ መሪዎች መጨረሻቸው ምን እንደሚኾን ጠፍቷቸው አይደለም፡፡ የከተማ ሕዝብን በውጊያ ከሚደርስ ጉዳት ለማዳን ብለው መሸሻቸው እንደሚነገርላቸውና ትህነጎች እንደሚጠሏቸው ጓድ መንግሥቱ ኃይለማርያም በተራቸው “ፈረጠጡ” እንዳይባሉ ሞትን ሊመርጡ ይችላሉ፡፡

በሕይወት ተርፈው ቅጣት ላለመቀበል ካላቸው ፍላጎት የተነሳ፣ ቢሸነፉ ሕዝቡ ምን ማድረግ እንዳለበት ኑዛዜያቸውን ሳይቀር አርባቸው ሳይደርስ ለሕዝብ ይፋ አድርገዋል፡፡ በመግለጫውም ላይ ከተነሱ ነጥቦች ዋናው መሸነፍን ስለማመን ነው፡፡ በውጊያው ብንሸነፍም ጦርነቱ አያበቃም የሚል ይዘት ያለው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ ለመንግሥት የተሰነዘረ በማስመሰል ደጋፊ ለማግኘትና ለማሳመጽ የተሞከረበት ይኽ የመጨረሻ መልዕክት ግን “ከወደቁ በኋላ መንፈራገጥ ለመላላጥ” ከሚለው ብሒል የተለየ ትርጉም ያለው አይመስልም፡፡ የጨነቀው እርጉዝ ያገባል ሲባል እንጂ፣ ሀሳብ ያጣል ሲባል ባይሰማም እያየነው እንገኛለን፡፡ እንደሚሸነፉ እያወቁና እያመኑ፣ ድሃውን የትግራይ ተወላጅ ቢላዋና ሰንጢ ይዘህ የተደራጀውን የመንግሥት ወታደር ውጋ ማለት ራስህን አጥፋ እንደማለት ይቆጠራል፡፡ ይኽ ንስሀ ሊያስከለክል የሚችልን ራስን በከንቱ የማጥፋት ሀሳብ፣ “ብንሸነፍም ሕዝቡ አይገዛም” ብሎ በሕዝቡ ዕጣ ፈንታ ላይ ለመዘባበት ከመሞከር የዘለለ ረብ የለውም፡፡

የትግራይ ሕዝብን የውጭ አካል ያስተዳድረው ሳይባል፣ ለሚመጣው አካል አትታዘዝ ማለት እድሜ ልክህን ስትባላ ኑር ከማለት የሚለይ አይደለም፡፡ በትህነግ እየተመራ ለብዙ ዓመታት በሰቆቃ የቆየው ምሥኪን ሕዝብ የተሻለ እንጂ የባሰ ይመጣል የሚል እምነት እንደማይኖረው ከታሪክ መማር ይቻላል፡፡ ከትህነግ በፊት ለብዙ ሺህ ዓመታት የኖረን ሕዝብ እኛ ብቻ ነን ነፃነት ያመጣንልህ ማለት፣ ለሺህ ዘመናት አባቶችህ ጀግና ሳይሆኑ ባሪያ ነበሩ ብሎ ታሪኩንና ማንነቱን ከመስደብና ከመናቅ አይለይም፡፡ አሸናፊና ተሸናፊ ሁሌም ያለና የሚኖር ነው፡፡ መሸነፍንም በፀጋ መቀበል የትልቅነት ባህሪ ነው፡፡ ሕዝብ በሰላም ተዘዋውሮ እንዲኖር የሚፈልግ አካል ለዘመናት የሚዘልቅ ደም መቃባትና ሸፍትነት ውስጥ እንዲገባ መጠየቅ እኔ ከሞትኩ እናንተም ሙቱ ከማለት አይለይም፡፡

“ኑ አብረን “ኑ አብረን እንሙት”እንሙት” የትህነግ የትህነግ የፍጻሜ ፊሽካየፍጻሜ ፊሽካ!!

በዝግጅት ክፍሉ

በዚህ ሳምንት

Page 4: ቅፅ 2 ቁጥር 110 ቅዳሜ ህዳር 19 ቀን 2013 ዓ.ም

33ግዮን ቁጥር 110 ህዳር 2013 ዓ.ም

ዜናዎች

የፀጥታው ምክር ቤት በኢትዮጵያ ላይ የጠራው ስብሰባ ተበተነ

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በኢትዮጵያ እየተካሄደ ባለው ሕግን የማስከበር የጦርነት ዘመቻ ሳቢያ ጠርቶት የነበረው ስብሰባ ያለስምምነት ተጠናቋል፡፡ ከኢትዮጵያ መንግሥት ፍላጎት ውጭ የተጠራው ይህ ስብሰባ ከዚህ በፊት እንዲቀር የተደረገው የአፍሪካ ሀገሮች ድጋፍ ባለመሥጠታቸው ነበር፡፡ ሀገራቱ የኢትየጵያ መንግሥት እየወሰደ ያለው እርምጃ ሕግን የማስከበር ተግባር ነው በማለት ስብሰባው በድጋሚ እንዲበተን ማድረጋቸው ታውቋል፡፡ እየተጠናቀቀ በሚገኘው ዘመቻ ላይ የተለያዩ አካላቶች ስጋታቸውን እየጠቀሱ ቢሆንም፣ ቀስ በቀስ ግን ድጋፋቸውን ማሳወቅ ቀጥለዋል፡፡ የአውሮፓ ኅብረትም በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ እንደማይገባም አሳውቋል፡፡ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ያካሄደው ስብሰባ የተጠራው በእንግሊዝ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመንና ቤልጂየም ግፊት መሆኑ ታውቋል፡፡

13 የህወሓት የጥፋት ተላላኪዎች በቦረና ዞን በቁጥጥር ሥር ዋሉጥፋት ሊያደርሱ ዝግጅት ላይ የነበሩ 13 የህወሓት ተላላኪዎች በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን

በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተገለፀ፡፡ ተጠርጣሪዎቹ በቦረና ዞን ጎሞሌ ወረዳ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ እና የኅብረተሰብ ጥቆማ ነው በቁጥጥር ሥር የዋሉት፡፡ የዞኑ ኮሙኒኬሽን ጽሕፈት ቤት እንዳስታወቀው ተጠርጣሪዎቹን ጥፋት ሳያደርሱ ቀድሞ መያዝ ተችሏል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ የህወሓት ጁንታ የጥፋት ተላላኪዎች መኾናቸውን የወረዳው ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ገልፆ፣ በኅብረተሰቡ የነቃ ተሳትፎ ጉዳት ሳያደርሱ በቁጥጥር መዋላቸውን አስታውቋል፡፡ ፖሊስ የአካባቢውን ፀጥታ ለማስጠበቅ ከነዋሪዎች ጋር በትብብር እየሰራ መሆኑንም ገልጿል፡፡

የመጨረሻው የዘመቻው ምዕራፍ መጀመሩን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አስታወቁ

ለህወሓት ወንጀለኛ ቡድን የተሰጠው በሰላም እጅ የመስጫ የ72 ሰዓት ጊዜ መጠናቀቁን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታውቀዋል። በዚህም ሕግ የማስከበር ዘመቻው የመጨረሻው ምዕራፍ መጀመሩን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል። በተሰጠው የ72 ሰዓታት ጊዜም በሺዎች የሚቆጠሩ የወንጀለኛው ቡድን ልዩ ኃይል እና ሚሊሻ አባላት እጃቸውን ለመከላከያ ሠራዊት መስጠታቸውንም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አስታውቀዋል። በዚህ ዘመቻ ለንፁሃን ሰዎች ከፍተኛ ጥንቃቄ ይደረጋል፤ የመቐለ ከተማን የከፋ ጉዳት እንዳያገኛትም የሚቻለው ሁሉ ይደረጋል ብለዋል። ሠራዊቱ በሰላማዊ ዜጎች፣ በቅርሶች፣ በቤተ እምነቶች፣ በልማት ተቋማትና በንብረቶች ላይ ጉዳት ሳይደርስ በሕግ የሚፈለጉትን አካላት ለሕግ ለማቅረብ ጥንቃቄ የተሞላው የዘመቻ ስልት የነደፈ መኾኑን እናረጋግጣለን ብለዋል። የመቐለና አካባቢው ሕዝብ ትጥቅ ፈትቶ በቤቱ በመቀመጥ ከወታደራዊ ዒላማዎች በመራቅ፣ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ጥሪ መቅረቡንም አሳውቀዋል።

ኢዜማ በማይካድራ በተፈጸመው ማንነትን ማዕከል ባደረገ ጭፍጨፋ የተሰማውን ሀዘን ገለጸ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) “የታሪካችን ጥቁር ጠባሳ የሆነው የማይካድራ ጭፍጨፋ ካላስተማረን ምን ሊያስተምረን ይችላል?” በሚል አርዕስት ባወጣው መግለጫ በማይካድራ በተፈፀመው ብሔርን መሠረት ያደረገ የንፁሃን ዜጎች ጭፍጨፋ የተሰማንን መሪሪ ሀዘን ገልጹዋል። “በሀገራችን በህወሓት አመራርነት የተተገበረው የዘር ፓለቲካ መጨረሻው መልክ እየተለየ፣ ቋንቋ እየተሰማ፣ ሥም እየተጠየቀ እና መታወቂያ እየታየ መተራረድ እንደሚሆን ሳይታለም የተፈታ ነበር።” ያለው መግለጫው “ብዙዎች ይህን እና ከዚህም ሊብስ የሚችለውን ግዜ በማሰብ ነበር ከጀመርነው የጥፋት መንገድ በግዜ እንድንወጣ ሲያሳስቡ የቆዩት። ዘርን መሰረት ያደረገ ፓለቲካ ማንም ይተግብረው ማን ትላንትም፣ ዛሬም ፣ ነገም አጥፊ ነው።” ሲል ኮንኗል፡፡ ፓርቲው ኢትዮጵያ ከገባችበት አዙሪት ለመውጣትም የችግሩ ምንጭ የሆነውን የዘር ፓለቲካ ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ በማስወገድ ዜግነት ላይ ብቻ መሰረት ያደረገ ፖለቲካ መመስረት ተገቢ መኾኑንና ለዚህም እንደሚታገል አስረድቷል።

የደመወዝ አከፋፈል ማስረጃ የተሟላ አይደለም ተባለ

የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የ2011 የበጀት አመት የሂሳብ ኦዲት ሪፖርት በፌደራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ተዘጋጅቶ ሐሙሥ ዕለት ለተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ወጪ አስተዳድር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ቀርቦ ነበር፡፡ ሪፖርቱ በቀረበበት የውይይት መድረክ ላይ በኦዲት በተገኙት ተገቢ ያልሆኑ አሠራሮች የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ ቋሚ ኮሚቴው አሳስቧል፡፡ እንደ ሪፖርቱ ከሆነ የግዢ ፕሮፎርማ አሰባሰብና የግዢ አፈፃፀም ሂደት እንዲሁም የደመወዝ አከፋፈሉ ማስረጃ የተሟላ አለመሆኑ ተነግሯል፡፡ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ስልክ ቁጥር ላልተረጋገጠ ስልክ ክፍያ መፈፀም በሚልም ግኝቱ የገመገመውን ውጤት ይፋ አድርጓል፡፡

የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ በበኩላቸው እንደ ኦዲት ሪፖርቱ ከሆነ የመንግሥት ግዢና ፋይናንስ ሥርዓቱን ባልተከተለ መልኩ ግዢና ክፍያ መፈፀሙ፣ የክፍያ ተመን ሳይኖራቸው ክፍያ መፈፀማቸው የመንግሥት ንብረት በአግባቡ አለመያዛቸውና የጥሬ ገንዘብ ጉድለት መኖሩ ታውቋል፡፡

በትግራይ ክልል የተፈጸሙ ወንጀሎችን የሚያጣራ የምርመራ ቡድን

ሥራውን መጀመሩ ተገለጸበትግራይ ክልል በግፍ ተፈጽመዋል የተባሉ

ወንጀሎችን የሚያጣራ የምርመራ ቡድን ወደ ስፍራው በማቅናት ስራ መጀመሩን የኢፌዴሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አስታወቀ። የሕወሓት የጥፋት ቡድን ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም በትግራይ ክልል በሚገኘው የአገር መከላከያ ሰራዊት የሰሜን እዝ ላይ የፈፀመውን ጥቃት ተከትሎ መንግሥት የሕግ ማስከበር ተግባር እየከናወነ ይገኛል። የኢፌዴሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር) በትግራይ ክልል እየተወሰደ ያለውን የሕግ ማስከበር እርምጃ አስመልክቶ ለውጭ አገሮች ጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል። ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ ማይካድራን ጨምሮ በትግራይ ክልል “በግፍ ተፈጽመዋል የተባሉ ወንጀሎችን” የሚያጣራ የምርመራ ቡድን አካባቢው ላይ ደርሷል ብለዋል። የሕወሓትን አመራሮች በከባድ ወንጀል ሊያስጠይቁ የሚችሉ ወንጀሎችን መፈጸማቸውን ጠቅላይ አቃቤ ሕጉ አብራርተዋል። በተለይም የሰሜን እዝ ካምፖች ላይ የተፈፀመው ድርጊት የአገር የመከላከያ ኀይልን በማጥቃት የተፈጸመ በመሆኑ በከባድ ወንጀል የሚያስጠይቅ መሆኑን ገልጸዋል።

ግብጽ የናሚቢያንና ዛምቢያን ድጋፍ ጠየቀች

ኢትዮጵያ በዓባይ ግድብ ላይ እየገነባች ባለችው ግድብ ዙሪያ በሚደረገው ውይይት ድጋፍ እንዲያደርጉላት ግብጽ ናሚቢያንና ዛምቢያን ጠየቀች፡፡ የግብጽ ኢል ሞኒተር እንደዘገበው፣ የሁለቱ ሀገራት ባለሥልጣናት ለጉብኝት ግብጽ በተገኙበት ወቅት የተቀበሏቸው ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲሰ ጥያቄውን አቅርበዋል፡፡ የናሚቢያ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ሳም ኒጆማ እና የዛምቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጀሴፍ ማላንጂ ካይሮ ተገኝተው ግብጽ በአፍሪካ ውስጥ ስላላት ሚና መወያየታቸው ተነግሯል፡፡ ከሕዳሴ ግድብ ግንባታ ጋር በተገናኘ ኢትዮጵያ ሱዳንና ግብጽ በሚያካሂዱት ድርድር ላይ ሀገራቱ እገዛ እንዲያደርጉ መጠየቃቸው ተዘግቧል፡፡ ግብጽ ከሰሀራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት ያላትን አተያይ ለማሻሻል እንደምትሰራም ፕሬዝዳንት አልሲሲ መናገራቸው ታውቋል፡፡ በግብጽ ድጋፍ የተጠየቁት ናሚቢያና ዛምቢያ በተባበሩት መንግሥታት ውስጥ ድጋፍ ስላላቸው በአስፈላጊ ጊዜ እንዲጠቅሟት ማሰቧ ተሰምቷል፡፡ የዓባይ ግድብን በተመለከተ ተጀምሮ የነበረው ድርድር ሱዳን ስለባለሙያዎቹ ማብራሪያ ይሰጠኝ በማለቷ መቋረጡ ይታወቃል፡፡

ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም እውቅና ሊሰጣቸው ነው

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን እንዳስታወቀው ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ስለ ሰብዓዊ መብቶች መከበርና የሰብዓዊ መብቶች ጥሰትን በመከላከል ላደረጉት አስተዋጽኦ እውቅና ሊሰጣቸው ነው። የሰብአዊ መብቶች ቀን ከታህሳስ 1 ጀምሮ በኢትዮጵያ መከበር እንደሚጀምር ኮሚሽኑ ገልጿል። አከባበሩም የተለያዩ ሁነቶች ያሉት እንደሆነም ታውቋል። የሰብዓዊ መብቶችን ከመጠየቅና ግንዛቤ ከመፍጠር ጀምሮ በርካታ የጉዳዩ ባለቤቶች ይሳተፉበታል ተብሏል። ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያምም በሕይወት ዘመናቸው ላደረጉት የሰብዓዊ መብት ተጋድሎ ይህ እውቅና የሚሰጣቸው መኾኑን ኮሚሽኑ ገልጹዋል።

Page 5: ቅፅ 2 ቁጥር 110 ቅዳሜ ህዳር 19 ቀን 2013 ዓ.ም

44ግዮን ቁጥር 110 ህዳር 2013 ዓ.ም

የአዘጋጁ መልዕክት

አዘጋጅአዘጋጅቀጸላ ክፍሌ

አምደኞችአምደኞችአቦነህ አሻግሬ ዘ ኢየሱስ (ፕ/ር)

ወንድሙ ነጋሽ (ኢ/ር)ውብሸት ታዬ

በኃይሉ ገ/እግዚእሔርሁሴን ከድር

ሙስጠፋ ሓሚድ የሱፍዶ/ር ዘሪሁን ሙላቱ

ተስፉ (ኢትዮጵያ) አልታሰብሠሎሞን ለማ ገመቹ

ጸሐፊጸሐፊገነት ብርሃኑ

ክርኤቲቭ ዲዛይንክርኤቲቭ ዲዛይንእየሩሳሌም ወንድምነህ

ግዮን መጽሔትግዮን መጽሔትኢትዮ ሐበሻ ኅትመትና ኢትዮ ሐበሻ ኅትመትና

ማስታወቂያ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር ማስታወቂያ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር በየሳምንቱ ለኅትመት የምትበቃ መጽሔትበየሳምንቱ ለኅትመት የምትበቃ መጽሔት

ዋና አዘጋጅዋና አዘጋጅፍቃዱ ማ/ወርቅ

አድራሻ፡- አራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 09 የቤት ቁጥር 1035

ማኔጂንግ ኤዲተርማኔጂንግ ኤዲተርኄኖክ ገለታው

ከፍተኛ አዘጋጅከፍተኛ አዘጋጅብሩክ መኮንን

የዝግጅት ክፍሉ አድራሻየዝግጅት ክፍሉ አድራሻአራዳ ክ/ከ ወረዳ 09 የቤት ቁጥር 552/1አምባቸው ህንፃ 2ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁ. 207

ፖስታ ቁ. 676 ኮድ 1029 ስልክ ፡ +251 911 227661

+251 912 165606 +251 118 12 2333

ኢ-ሜይል፡ enqu2013@ gmail.com

[email protected]

Gihon-meg Fekaduwww. facebook.com/enqu2013

በዚህ መጽሔት ላይ የሚወጡ ጽሑፎች በሙሉ ማተሚያ ቤቱን አይመለከትም

አታሚአታሚቴዎድሮስ ገብሩ ማተሚያ ቤት ፤ አራዳ ክፍለ ከተማ

ወረዳ 10 የቤ.ቁ. 066/ሀ 0911223335/ 0911420506

ነባሩን የኢትዮጵያ ማኅበረ ፖለቲካዊ አንብሮ ጥላሸት በመቀባት “ለውጥ” ለማምጣት የታገለው ያ ትውልድ፣ ካበጀው ይልቅ የፈጀው አያሌ መኾኑን ቆጥሮ መድረስ አያዳግትም፡፡ ኢትዮጵያችን ዳግም የታነጸችበትን የሃገረ

መንግሥት ምሥረታ ሂደት የተለየ ቀመርና መስፈርት አበጅቶ ከማነወር፣ ወሰንና ወደር አልባ የጭቆና ሀቲቶችን በመደርደር ትናንትን በጽልመት እስከመሞሸር ትውልዱ ያልሞከረው አልነበረም፡፡ በዚህ ብቻ ግን አላበቃም፡፡ የኢትዮጵያውያንን ዘመናት የተሻገረ የአንድነትና የውሕደት ታሪክ ወደጎን በመግፋትም “ጨቋኝ” እና “ተጨቋኝ” ፈጥሮ ማቆሚያ ወደሌለው ግጭትና ቀውስ ለመውሰድ ሞክሯል፡፡

በዚህም ሳቢያ ያልፈበረከው የሀሰት ተረክ፣ ያልወጠነው የፍጅት ተረት አልነበረም፡፡ በዚህ ስሁት መስመር ውስጥ ደግሞ ከሻዕቢያ እስከ ህወሓት፤ ከኦነግ እስከ ኦብነግ ቀዳሚ ሰልፈኞች ኾነው መጥተዋል፣ አንዳንዶቹም አልፈዋል ፤ ጥቂቶቹም እያለፉ ነው፡፡ በተለይም ደግሞ ድኅረ 1983 በፖለቲካው መድረክ “አሸናፊ” ኾኖ የወጣው ህወሓት በአፋአዊነት ይራመድ የነበረውን አቋም ወደገዢ ዕሳቤነት ለመለወጥ የሄደበት ርቀት አዳዲስ ችግሮች እንዲወለዱ መግፍኤ ኾኗል፡፡

በዚህም ሳቢያ እንግዳ የኾኑ የፖለቲካ ጠባያት ክሱት ሲኾኑ ታዝበናል፡፡ አብሮ የመኖርም ይኹን የመቀጠል ዕጣችን ላይ ትልልቅ ጋሬጣዎች ሲዘነጠፉም ለማየት በቅተናል፡፡ ለዚህ ነው፣ በኢትዮጵያችን የዛሬ እውነታ ውስጥ ህወሓት የችግሮቹ የጡት አባት ከመኾን የዘለለ ሚና የለውም ለማለት የምንደፍረው፡፡ የህወሓት ሕልውና መጥፋት ኢትዮጵያ የተጣቧት ችግሮች እንዲቀንሱ ያለው ፋይዳ ትልቅ ቢኾንም የነገሮች ማሳረጊያ ሊኾን ግን አይችልም፡፡ ህወሓት በማኅበረ ፖለቲካችን ውስጥ ያነበራቸው ዕሳቤዎች፣ መዋቅሮችና ሕገ መንግሥታዊ ደገፎች የድርጅቱን ሕጋዊ ሰውነት በማክሰም ብቻ የሚጠፉ አድርጎ ማሰብም ሲበዛ ተላላነት ነው፡፡

ድርጅቱ ቆሞ በሰደፉ፣ ሞቶ በሰንኮፉ ማጋደል የሚያስችሉ አደገኛ ሽብልቆችን የቀረቀረባቸው መታጠፊያዎች አሉ፡፡ መንግሥት በድርጅቱ ላይ እየወሰደ ያለው ሕግን የማስከበር ዘመቻ ውጤቱ ምሉዕ የሚኾነውም

እነኚህን ቀስቶች በወግ በወጉ መንቀል ሲችል ብቻ ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ ዓይኑን አፍጥጦና ጥርሱን አግጥጦ የሚታየው ዜጋ ጠል ፖሊሲ እልባት የሚያገኝበትን መንገድ መፈለግ ተገቢ ይኾናል፡፡ ይኽ ደግሞ “ታቦት” ኾኖ የኖረውን ሕገ መንግሥት ጠልቆ ከመፈተሽ ይጀምራል፡፡

ሲቀጥል ደግሞ ለዜጎች ባይተዋርነት ታህታይ ምንጭ የኾነውን አስተዳደራዊ መዋቅር መከለስ ለነገ የሚባል አጣዳፊ ሥራ አይደለም፡፡ የሃያ ሰባት ዓመታቱን የዜጎች ዕልቆ ቢስ ፍዳና መከራ አስቀምጠን ያለፉትን ኹለት ዓመታት እውነታ ብንገመግም እንኳን ዘውግን ማዕከል ያደረገው አስተዳደር በዚሁ ከቀጠለ ለኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያን ተጨማሪ ሰቆቃን ከመስፈር የሚዘልል ዓላማ እንደሌለው መረዳት እንችላለን፡፡ መንግሥት ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት የመጪው ዘመን አሸናፊ ሀቆች እንዲኾኑ ቁርጠኝነቱ ካለው፣ ህወሓት ወለድ ሕማማት በመሉ ተሻጋሪና ተንከባላይ ዕዳ ኾነው የቀጣዩ ትውልድ የጠብና የንትርክ አጀንዳነታቸው እንዲያበቃ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በጉዳዮቹ ላይ መፍትሔ ማስቀመጥ ይጠበቅበታል፡፡

የባሕልና የቋንቋ ልይይቶች የኢትዮጵያዊያን ጌጦች እንጂ መጠፋፊያ አለመኾነቸውን ፍትሓዊ መልስ በመስጠት የግጭት ነጋዴዎችን ሕልም ማምከን ይኖርበታል፡፡ ኢትዮጵያ ከዘመን አመጣሽ ሕገ መንግሥትም ኾነ መዋቅር በላይ መኾኗንም በተጨባጭ እርምጃ ማሳየት ይገባዋል፡፡ በህወሓት ብቻ ሳይኾን በእርሱ ብቃይ አስተሳሰቦች ላይ ሙሉ ድል መጎናጸፍ የሚቻለውም ይኽ ሲኾን ብቻ ነው፡፡ ከዚያ ውጪ ያለው መንገድ “አለባብሰው ቢያርሱ…” እንዲሉ አዙሪቱን ከመድገም፣ ድጡን ማጥ ከማድረግ የሚሻል አይኾንም፡፡ በትውልድ ነገ ላይ ታሪካዊ ስህተት መፈጸምም ይኾናል፡፡ ለዚህም ሲባል መንግሥት አሁን ለገባንበት ችግር ምንጭ በኾነው ድርጅት ላይ ከሚወስደው እርምጃ ጎን ለጎን ሕጋዊና መዋቅራዊ ለውጥ ለማምጣት ተግባራዊ እንቅስቃሴ የሚጀምርበት ቀን ነገ ሳይኾን ዛሬ መኾኑን ለማስታወስ እንወዳለን፡፡

የችግሩን ምንጭ የችግሩን ምንጭ ከማድረቅ ጎን ከማድረቅ ጎን መዋቅራዊ ለውጥመዋቅራዊ ለውጥ እንሻለን! እንሻለን!

Page 6: ቅፅ 2 ቁጥር 110 ቅዳሜ ህዳር 19 ቀን 2013 ዓ.ም

55ግዮን ቁጥር 110 ህዳር 2013 ዓ.ም

ነገረ ግዮን

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ከአንድ ሣምንት በፊት ባስደመጠን ጆሮ ገብ ዜና፣ የህወሓታዊያን የንግድ

ኢምፓየርና የሙስና መርከብ የኾነው “ኤፈርት” (34 የፋይናንስ ተቋማቱ) ዕግድ ተጥሎባቸዋል፡፡ የኤፈርት ጉዳይ ህወሓትን ከፈላጭ ቆራጭ አምባገነንቱ ለማስወገድ በተደረገው መልከ ብዙ ትግል ውስጥ የኋላኋላም ቢኾን አንድ አጀንዳ የነበረ ጉዳይ እንደነበር አይዘነጋም፡፡ “ዘላቂ ሥልጣንን ለማረጋገጥ የፖለቲካ የበላይነትን በኢኮኖሚ አቅም ማፈርጠም አስፈላጊ ነው” በሚለው ያልተጻፈ የህወሓት መርኾ ሳቢያ አገዛዙን ከመንበሩ ለመፈንገል በተደረገው ጥረት የሬሚታንስ ተዐቅቦ በማድረግ የፋይናንስ አቅሙን ለማመንመን ጥረት ተደርጓል፡፡ በርግጥም እንደ ኤፈርት ዓይነት የማያልቅ የፋይናንስ ምንጭ ህወሓት አይደለም በሥልጣን ዘመኑ በድኅረ ለውጡም ዕድሜ ኖሮት ሀገር እንዲያምስ የዝኾን ጉልበት እንደሰጠው ከሰሞነኛው የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ መግለጫ ስንረዳ ይኽንን ግዙፍ ተቋም ወደኋላ ሄደን ማንነው ለማለት እንገደዳለን፡፡

ኤፈርት ማንነው?

ኤፈርት የትግራይ መልሶ ማቋቋሚያ ፈንድ ወይም በእንግሊዘኛው ምህጻረ ቃል “EFFORT” ‹ኢንዶመንት ፈንድ ፌር ዘ ሪሃብሊቴሽን ኦፍ ትግራይ›› ተብሎ የሚጠራው ግዙፍ የንግድ ኮርፖሬሽን ነው፡፡ መለስ ዜናዊ በአንድ ወቅት እንደተናገሩት የዚህ ተቋም የሀብት ምንጭ በትጥቅ ትግሉ ጊዜ ይካሄዱ የነበሩ የተለያዩ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች (ዘረፋ እና በዘረፋ የተገኙ ሸቀጦች ሽያጭ) ነው፡፡ የህወሓቱ ‹ኤፈርት› በቢሊዮን የሚቆጠር ሀብት በማፍራት ገረድ ቀዳሚና አቻ የማይገኝለት ይሁን እንጂ የኢሕአዴግ አባል ድርጅቶች ‹በትጥቅ ትግሉ ወቅት አገኘን› ያሉትን ንብረት በመያዝ የኢንዶውመንት ተቋማትን መመሥረታቸው አይዘነጋም፡፡

እዚህ ጋር መነሳት አልያም መጠየቅ የሚገባው ጥያቄ ተቋማቱ ስለምን በ“ኢንዶውመንት” ስም መቋቋም አስፈለጋቸው የሚለው ነው፡፡ በርግጥም ህወሓት፣ የኤፈርት ድርጅቶችን በሀገር ውስጥ “የኢንዳውመንት ፈንድ” (የስጦታ ገንዘብ) በማለት፣ ለትርፍ ባልተቋቋመ ድርጅት ስም እንዲመዘገብ ያደረገችው ዓለምን ለማታለልና ሕጋዊ ለመምሰል ከመሻት ውጪ ለእውነት የቀረበ ዓላማ ይዛ አልነበረም፡፡ ኢንሳይክሎፒዲያ ብሪታኒካ መዝገበቃላት `endowment` ለሚለው ቃል የሚሰጠው ትርጉም `the part of institution’s income derived from donations` የሚል ሲኾን ትርጉሙም “በሥጦታዎች የሚገኝ የአንድ ተቋም ገቢ” እንደማለት ነው፡፡ በዚህ ትርጉም መሠረት የህወሓት የፋይናንስ ተቋማት የኾኑት የኤፈርት ድርጅቶች በስጦታ የተገኙ ናቸው ማለት ነው፡፡

እንደ `Ze Addis` የበይነ መረብ ገጽ ገለጻ ከኾነ ደግሞ ኢንዳውመንት ፈንድ፣ አንድ የኤኮኖሚክስ ጽንሰ ሀሳብ ነው፡፡ ትልልቆቹ የዓለማችን ዩንቨርስቲዎች እነ ሃርቫርድ፣ ዬል ወዘተ… የሚተዳደሩት በኢንዳውመንት ፈንድ ነው፡፡ የኢንዳውመንት ፈንድን ጽንሰ ሀሳብ ባጭሩ ስንመለከተው፣ ለጋሽ ሰዎች ላመኑበት የበጎ አድራጎት ዓለማ ገንዘብ ይለግሳሉ፣ የለገሱት ገንዘብ ኢንቨስት ይደረጋል፣ ከትርፉ የተወሰነው ገንዘብ ብቻ ለኢንዳውመንቱ ዓላማ ለበጎ አድራጎት ብቻ ይውላል፡፡ የተቀረው ትርፍ ተመልሶ ኢንቨስት ይደረጋል፡፡ በምንም መልኩ ቢሆን ዋናው (ፕሪንሲፓሉ) አይነካም፡፡ ከተገኘው ትርፍም የሚወጣው ትንሽ ፐርሰንት ብቻ ነው፡፡ ይኽም ለበጎ ኣድራጎት ይውላል፡፡

“ኢንዳውመንት” ወይም “የስጦታ ፈንድ” የተባለውም ለዚህ ነው፡፡ ሀርቫርድ ኢንዳውነት ፈንድ ውስጥ 25 ቢሊዮን ዶላር አለ፡፡ ይህ ፈንድ ኢንቨስት እየተደረገ በዓመት ከሚገኘው ወደ ሁለት ነጥብ አምስት ቢሊዮን ውስጥ ወደ አንድ ቢሊዮኑን ለትምህርት ቤቱ ስኮላር ሺፕና መሰል በጎ ግልጋሎቶች ይውላል፡፡ የቀረው ተመልሶ ኢንቨስት ይደረጋል፡፡ ለትርፍ ያልተቋቋመ፣ የሚያገኘውንም ወለድ ለበጎ አገልግሎት ብቻ የሚያውል ስለሆነ ኢንዳውመንት ፈንድ፣

በመንግሥት ታክስ አይደረገም፡፡

የኢንዳውመንት ፈንድ መነሻ ካፒታሉ፣ ከበጎ አድራጊዎች ይሰበሰባል፣ ከዛ ኢንቨስት ይደረጋል፣ ከተገኘው ወለድ ወይም ትርፍ ጥቂት ፐርሰንቱ ብቻ ለበጎ አድራጎት ይወጣል፡፡ ይህ ብር ለበጎ አድራጊት ብቻና ብቻ ይውላል፡፡ በምንም መልኩ ቢሆን ዋናውን ብር(ፕሪንሲፓሉን) ማውጣት አይቻልም፡፡

ለኤፈርትም ኾነ ለሌሎቹ የኢሕአዴግ እሕት ድርጅቶች የንግድ ተቋማት “ኢንዶውመንት” የሚል ሥም የሰጡት የቀድሞ ጠ/ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ናቸው፡፡ ይኽ ግን የተሳሳተ ብቻ ሳይኾን ሕዝቡንም ያሳሳተና ነገሩን አደባብሶ ከትችት ለማምለጥ የተቀየሰ ማታለያ ነው፡፡ በተለያዩ ሀገራት በነጻነት የትጥቅ ትግል ላይ ዘመናቸውን ያሳለፉ ፓርቲዎች ወይም አማጺ ቡድኖች ከምርኮና ከሌሎች የተለያዩ ምንጮች ሀብት ይሰበስባሉ፡፡ ይኽም በሚያካሂዱት ትግል ውጤታማ ለመኾን የሚያስችላቸውን ኢኮኖሚያዊ አቅም ለመፍጠር ነው፡፡ እዚህ ጋር ህወሓት በትጥቅ ትግሉ ዘመን ለምን ሀብት አፈራ ተብሎ ላይጠየቅ ይችላል፡፡ ወቀሳውና ትችቱ “ሀብቱን እንዴት ተጠቀመት” በሚለው ጭብጥ ዙሪያ ነው፡፡ የኢንዶውመንት ተቋማት

ኄኖክ ገለታው

የኤፈርት ፍጻሜ፣የኤፈርት ፍጻሜ፣ የኢትዮጵያን የኢትዮጵያን ለኢትዮጵያዊያን? ለኢትዮጵያዊያን?

Page 7: ቅፅ 2 ቁጥር 110 ቅዳሜ ህዳር 19 ቀን 2013 ዓ.ም

66ግዮን ቁጥር 110 ህዳር 2013 ዓ.ም

ነገረ ግዮን

የኢትዮጵያ ሕዝብ ንብረት ነበር፡፡ ብሩን ከኢትዮጵያ ሕዝብ ወስዶ፣ ጥቅሙን የኔ ብቻ ማለት ህወሓት ቤት ባያሳፍርም፣ ስህተት መኾኑ ግን ሀቅ ነው፡፡ በዚህ አጋጣሚ፣ ብሔራዊ ባንክ ይህን ደብዳቤ ቢያወጣው ለሕዝቡ ጥሩ ግንዛቤ ይሰጣል፡፡ ሲቀጥል፣ እንደሌሎቹ ኢንዳውመንት ፈንዶች፣ ኤፈርት ገንዘቡን ሳይሆን ኢንቨስት የሚያደርገው፣ ራሱ ትልቅ የንግድ ኩባንያ ነው፡፡ ኦዲት ተደርጎ የማያውቀው ይሄ ኩባንያ እንደ ኢንዳውመንት ፈንድ ብሂል፣ የሚያገኘውን ገንዘብ በጎ አድራጎት ላይ ሲያውል አንድም ቀን ታይቶ አይታወቅም፡፡ የነ ስብሃት ነጋ የግል ኪስ ከመሆን ባሻገር፡፡ ስለዚህ ሲጀምር ጀምሮ የኢንዳውመንት ፈንድ የሚለው መስፈርት አያሟላም፡፡ በሕግ ሽፋን ለማጭበርበር ካልሆነ በስተቀር፡፡

በአናቱም ገበሬው ጥራቱ ባልተጠበቀ ማዳበሪያ መከራውን እየበላ የሀገር ምርት የሚጠበቀውን ያህል መጨመር አለመቻሉ፣ ኮንስትራክሽኑ በኮንትሮባንድ ግብዓት እየተሞላ ጥቂቶች ኪሳቸው ደልቦ ዘርፉ መቀጨጩ፣ ገቢና ወጪ ንግዱ እጅግ በጣም ጥቂት ኩባንያዎች እጅ ውስጥ ገብቶ በላቡ ጥሮ የሚያድረው ነጋዴ ግን እንደዋዛ መክሰሙ፣ እንደ አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች ገልጻ ሌቦቹ ይህችን ደሃ ሀገር እንደ ጸጉራም ውሻ ያለች መስላ እንድትሞት ውስጧም ቀፎ እንዲሆን አድርገዋታል፡፡ ለዚህ ሁሉ ተጠያቂው ህወሓት መሪ ሳይሆን ከደላላ ጋር የሚሞዳሞድ ነጋዴ ፓርቲ ሆኖ ሚናውን

መለየት ሳይችል መኖሩ ነው ይላሉ ተቺዎች፡፡ መሪዎቹን ከፓርቲ ዘዋሪነት ይልቅ የንግድ ካፓ አድርጎ ማኖሩ ነው ሀገርን በገለልተኛ ስሜት እንዳይመራ እንቅፋት የሆነበት፡፡ በተለይ የኢህአዴግ መሥራች የሆነው ህወሓት ቅልጥ ያለ ነጋዴ ፓርቲ መሆኑ ወትሮም ሀገር ለማስተዳደር የሞራል ብቃት የሌለው ብቻ ሳይሆን፣ ገበያንና ፖለቲካን አደበላልቆ የተምታታበት ፓርቲ ሆኖ መሆኑን ብዙዎች ይናገራሉ፡፡ ለዚህም ነው ከሕወሓት መሪዎች ጥቂት የማይባሉት በከባድ ሙስና የተጠረጠሩትና የፋይናንስ ምንጫቸውም ለዕግድ ሊበቃ የቻለው፡፡

የኤፈርት የዘረፋ ድርጅቶች

ኤፈርት፣ ኢትዮጵያ ውስጥ አትራፊ የሚባለውን ዘርፍ በሙሉ የተቆጣጠረ ነው፡፡ ያልገባበት ዘርፍ የለም፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ጥሩ ውጤት የነበራቸው ድርጅቶች በሙሉ በግድና በጉልበት ወደ ኤፈርት እንዲገቡ ሆነዋል፡፡ የዝርፊያው ሂደት ምን ይመስል እንደነበር ጥቂቶቹን ብቻ ከ`Ze Addis` ገጽ ባገኘነው መረጃ መሠረት እንመልከት፡-

1.ሕይወት ሜካናይዜሽንና ሌሎች እርሻዎች

በንጉሡ ዘመን፣ ኢትዮጵያ የሀገር ልማትና እድገት ለማምጣት ትከተል ከነበረው ኢኮኖሚክ ፖሊሲ አንዱ የኮርፖሬት ኮሜርሻል እርሻን ማስፋፋትና፣ እጅግ ትልልቅ የመንግሥት እርሻዎችን ማስፋፋት ነበር፡፡ ሁሉም ቦታ ገንዘብና ሀብትን ከማሰራጨት፣ ውጤት ሊያመጡ የሚችሉ ቦታዎችን መርጦ ልማቱን ማፋጠን የሚል አካሄድ ነበር፡፡ በተለይ በርሻው በኩል ኮምፕሬሄንሲቭ ፓኬጅ ፕሮጀክት የሚባል ትልቅ የእርሻ ልማት ፕሮግራም ነበር፡፡ CADU, ARDU, WADU, TADU… ወዘተ የሚባሉ አስገራሚ ፕሮጀክቶች ነበሩ፡፡ ለምሳሌ ካዱ (ጭላሎ አግሪካልቸራል ዴቬሎፕመንት ዩኒት) አርሲ ላይ ብቻ በማተኮርና ከፍተኛ የግብርና ልማት በማካሄድ ያንንን አካባቢ የልማት ማዕከል ማድረግ ዓላማ ነበረው፡፡ አድርጓልም፡፡ ሌሎቹም እንደዛው፡፡

የሀገሪቱ ፣ ከተለያዩ ሀገራት ብድር በመውሰድ፣ ክፍተኛ ልማት ተካሂዶበት፣ ለሀገር የውጭ ምንዛሪ እንዲያስገኝ የተደከመበት የሁመራ የመንግሥት እርሻ አንዱ ነው፡፡ በወቅቱ በጎንደር ጠቅላይ ግዛት ይገኝ የነበረውን ይህን ቦታ ለማዘመን፣ የሀገሪቱ አቅም ብቻውን በቂ ስላልሆነ፣ የንጉሡ አስተዳደር፣ በኢትዮጵያ ሕዝብ ስም፣ በፓርላምው ውይይትና ፈቃድ፣ በርካታ ሚሊዮን ዶላሮችን በመበደር እንዲለማ አድርገው ነበር፡፡ በዚህም ብድር፣ የሁመራ ኤርትራ መንገድ፣ የተከዜ ድልድይ፣ ከመቶ ሺህ በላይ የመግስት እርሻ ወዘተ እንዲለማ ሆኗል፡፡ የብድር ሰነዱን እና መሰል ዶክመንቶችም ይገኛሉ፡፡

በአስተዳደር የጎንደር አካል የነበረውንና በኢትዮጵያ ሕዝብ ሀብት ተንጠፍጥፎ የተሰራውን ይህን ድርጅት፣ በመጀመርያ ስብሀት ነጋ አስዘርፎ፣ በርካታ መሳርያውን ለሱዳን ሸጠ፡፡ በኋላ ህወሓት አዲስ አበባ ስትገባ፣ የእርሻ መሳርይዎቹን ከጣና በለስን ፕሮጀክት በመዝረፍ “የህወሓት እርሻ” ብላ ያንን የሚያህል የመንግሥት እርሻ ወረሰች፡፡ የቀድሞው መንግሥት ጠቅላይ

በተለያየ መንገድ ከሥርዓቱ በከፍተኛ ደረጃ ተጠቃሚ ለመኾን መቻላቸውን በእንግሊዝ ታላቁ የውጪ እርዳታ ድጋፍ አድራጊ ተቋም UK Department for International Development (DFID) እና በአዲስ አበባ ንግድ ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤቶች የተካሄዱ ጥናቶች ይጠቁማሉ፡፡ በተለይ የእንግሊዙ ጥናት የሚያሳየው የኢንዶውመንት ተቋማቱ ከመንግሥት የተለየ ጥበቃ ይደረግላቸው እንደነበር ነው፡፡ በተለይም ኤፈርት!

ኤፈርት እንዴት ተቋቋመ?

የእነአቶ መለስ ቀልድን ወደጎን ያለ ሁሉ ኤፈርት የተስፋፋ የንግድ ኤምፓየር የዘረጋው ገንዘቡን ከየት አግኝቶ ነው የሚል ጥያቄን ሲጠይቁ ኖረዋል፡፡ ችግሩ ግን መልስ የሚሠጥ ጠፍቶ መቆየቱ ነው፡፡ ህወሓት መንግሥት ከሆነ በኋላ በትጥቅ ትግሉ ወቅት ያካበተውን ሀብት ለተቀሩትም የሀገሪቱ ሕዝቦች ያካፍል ብሎ ማሰቡ ከፓርቲው ባሕሪ አንጻር የማይታሰብ ነው፡፡ ሕወሓት ከነበረው ባሕሪ አንጻር የሚቆጣጠረውን ሀብትም ሆነ ሥልጣን ለማንም የማካፈል ተፈጥሮ ስለሌለው ከደርግ ሳይሆን ኢትዮጵያ ከተባለች ሀገር ያገኘውን ንብረት ለሀገሪቱ ሕዝብ ጥቅም ማስቀደም ተስኖታል፡፡ ደርግ ሀብት አልነበረውም፡፡ የነበረው ሀብትም ምናልባት በብድር እና እርዳታ የተገኘ እንደሁ እንጂ እዚህ ግባ የሚባል አልነበረም፡፡ እሱም ቢሆን የኢትዮጵያ ሕዝብ ገንዘብ ነው፡፡ አምባሳደር ካሳ ከበደ ከግዮን መጽሔት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ይፋ እንዳደረጉት ሕወሃት ደርግ ሊወድቅ ሁለት ቀን ሲቀረው ከቤተ-እስራኤል (ፈላሻ) ማጓጓዝ ጋር በተገናኘ የተፈጸመ 35 ሚሊዮን ዶላር ከኒውዮርክ ባንክ ወስዶ ኤፈርትን ደጉሞበታል፡፡

እንደ ኢንጂነር ግደይ ጸርዓጽዮን ያሉ የፖለቲካ ጉምቱምች እና ተራው ሕዝብ ጭምር በተደጋጋሚ ጊዜ የሚያነሳው አንድ ጥያቄ በቀጥታ የሚያነጣጥረው ለዚህ የተደራጀ የሀገር ዝርፊያ ወንጀል ምሽግ ከሆኑት ተቋማት ቀንደኛው በሆነው ኤፈርት ላይ ነው፡፡ ኤፈርት ይመርመር የሚለው ጥያቄ ቅርጽ እየያዘና በቂ መነሻ ሐሳቦችን እየሰነቀ ዘመቻ ወደ መምሰል ደረጃ የተቃረበውም በዚህና መሠል ምክንያቶች ነው፡፡ ሕወሓት ከመምራት ይልቅ ተሳክቶለት ሲሰራ ኖረው ንግድን ማጧጧፍን፣ በዚያ ንግድ ቁምጣ ለባሽ መሥራቾቹን በወርቅ ላይ ማረማመድን፣ ገንዘብ አሽሽቶ ሀገርን እርቃን ማስቀረትን፣ በውጭ ሀገር ባንኮች የሀገር ሀብትን መዝብሮ ንዋይ ማከማቸትን ነው፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ከፍ ሲል የጠቀስነው `Ze Addis` ገጽ እንደሚያትተው ከኾነ ኤፈረት ሲቋቋም፣ በጎ አድራጊዎች ገንዘብ አዋጥተውለት አልነበረም፡፡ ከኢትዮጵያ ሕዝብ በተዘረፈ ገንዘብ ነው፡፡ ህወሓት የሥራዋ መጀመርያ አድርጋ የጀመረችው፣ ባንክ መዝረፍ ነው፡፡ በመቀጠልም፣ የመንግሥት ድርጅቶች መዝረፍ ነው፡፡ ባንክ የሕዝብ ተቀማጭ ገንዘብ ነው፡፡ በዚህም መሠረት ገና ከጅምሩ የኢንዳውመንት ፈንድ እሳቤን ያሟላ አይደለም፡፡ ከሕዝብ የተዘረፈና ለሕዝብ ሊመለስ የሚገባው የተዘረፈ ብር ነበር፡፡ ከዛ ባሻገር፣ ንግድ ባንክ ለኤፈርት ድርጅቶች ከሦስት ቢሊዮን ብር በላይ አበድሮ/ሰጥቶ በኋላ “write off”(የተበላሸ ብድር) እንደተደረገለት ይታወቃል፡፡ ንግድ ባንክ ውስጥ ያለው ገንዘብ የኢትዮጵያ ሕዝብ አንጡራ ሀብት ነው፡፡ ስለዚህ ኤፈርትም፣ ሲጀመር ጀምሮ ሊሆን የሚገባው

ህወሓት አዲስ አበባ ስትገባ፣ የእርሻ መሳርይዎቹን ከጣና

በለስን ፕሮጀክት በመዝረፍ “የህወሓት እርሻ” ብላ ያንን

የሚያህል የመንግሥት እርሻ

ወረሰች፡፡ የቀድሞው መንግሥት

ጠቅላይ ሚኒስትር ፍቅረሥሳሴ

ወግደረስ “እኛና አብዮቱ” በሚለው መጽሐፋቸው ገጽ 418

ላይ ያኔ የነበረው ወረራ እንዲህ

ሲሉ ያስታውሱታል

Page 8: ቅፅ 2 ቁጥር 110 ቅዳሜ ህዳር 19 ቀን 2013 ዓ.ም

77ግዮን ቁጥር 110 ህዳር 2013 ዓ.ም

ነገረ ግዮን

ሚኒስትር ፍቅረሥሳሴ ወግደረስ “እኛና አብዮቱ” በሚለው መጽሐፋቸው ገጽ 418 ላይ ያኔ የነበረው ወረራ እንዲህ ሲሉ ያስታውሱታል፡-

“በዚህም የተነሳ ህወሓት አካባቢውን በያዘበት ጊዜ እንዳልሆነ አድርጎ ፕሮጀክቱን አፈራረሰ። ለፕሮጀክቱ ሥራ ይጠቅማሉ ተብለው የመጡትን የግንባታና የእርሻ መሣሪያዎች በሙሉ እየጫኑ ወደሚፈልጉበት አካባቢ አጓጓዙ። ጠቃሚ መስሎ የታየውን ማንኛውንም እቃ እየነቀለ ወሰደ።” ከኤፈርት ኢንዳውመንት ድርጅቶች ውስጥ አንዱ የሆኑት እነ ሕይወት ሜካኔይዜሽን፣ ወዘተ እንዲህ ከኢትዮጵያ ሕዝብ የተዘረፉ ንብረቶች ናቸው፡፡ የህወሓት መሬት ተብሎ ስም ተሰጥቶት የነ ስብሃት ነጋ የግል ንብረት የሆነው ይኼ መሬት፣ ባስቸኳይ ለሕዝብ ጥቅም ለመንግሥት ገቢ መሆን ይኖርበታል፡፡ የተዘረፈ ሀብት ነውና፡፡

2. ወይራ ትራንስፖርትና ፒሬሊ

በዘመነ መንግሥቱ፣ ኢትዮጵያ ትከተል የነበረው ፖለቲካል ኢኮኖሚ ሶሻሊስታዊ ስለነበር፣ የሀገሪቱ ሀብት ያለው መንግሥት እጅ ነበር፡፡ ይህን ተከትሎም፣ በሀገሪቱ ውስጥ በርካታ መንግሥታዊ የልማት ድርጅቶች ነበሩ፡፡ ኤፈርት የተመሰረተው እነዚህ በመዝረፍም ነበር፡፡ በተለያዩ ዘዴዎች፡፡

ምሳሌ እናንሳ፡፡ ወይራ ትራንስፖርት በኢትዮጵያ የታወቀ መንግሥታዊ የልማት የትራንስፖርት ድርጅት ነበር፡፡ ከስድስት መቶ በላይ ትልልቅ መኪናዎች ነበሩት፡፡ አዲስ አበባ ከዮሴፍ ቤተ ክርስትያን አለፍ ብሎ ወደ ቃሊቲ መስመር ላይ እጅግ ግዙፍ ሕንጻም ሰርቷል፡፡ ድንገት ህወሓት፣ ይኽ ድርጅት ፕራይቪታይዝድ መሆን አለበት ብላ ነገር አመጣች፡፡ ያኔ የፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሴው ኃላፊ የህወሓት ሰው ነበር፡፡ አባቱ ዳኛ፣ ልጁ ቀማኛ ሆነና፣ ይኼንስ ሽቱ ላይ በቋሚ አሴት ዘርፍ ብቻ ከአንድ ቢሊዮን በላይ ቋሚ ንብረት ያስመዘገበው ይሄንን ድርጅት፣ ኤፈርት በፕራይቬታይዜሽን 200 ሚሊዮን ብር ገዛው ተባለ፡፡ ያኔ የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ ወይዘሮ ፍሬሕይወት ትባል ነበር፡፡ አበደች! ምንም ማድረግ አልቻለችም፣ ማቄን ጨርቄን ሳትል ድርጅቱን ለቃ ወጣች፡፡ እስካሁን በሕይወት ልትኖር ትችላለች፡፡ አንድ ቀን በዚህ ዙርያ መግለጫ ብትሰጥ ትልቅ የታሪክ ውለታ ነው፡፡

3. መንግሥታዊ ከለላ የታከለበት ዝርፊያ

የፒሬሊ ጎማ ብቸኛ አስመጭና አከፋፋይ ኤፈርት ነው፡፡ ይህ ፕሮፖዛል የሌላ ሰው ነበር፡፡ ሙሉ የቢዝነስ እቅዱን አስገባ ብለው ፕሮጀክት ዶክመንቱን ከዘረፉት በኋላ፣ ኤፈርት ይህን ንግድ ጀምሮታልና ዞር በል ተባለ፡፡ ወዲያውም ከኤፈርት ውጭ ማንም ሰው ፒሬሊ ጎማን ቢሸጥ ፣ ከፍ ብሎ አንገቱን ፣ ዝቅ ብሎ ባቱን ዓይነት ማስጠንቀቂያ ቀጠለ፡፡ የፒሬሊን ፋይናንሻል ስቴትመንት የወር ትርፉ ብቻ ከ9 ሚሊዮን ዶላር በላይ ነበር፡፡

4. ሜጋ፣ ኩራዝን በቁሙ የበላው ድርጅት

ሌላው ኢትዮጵያ ውስጥ ትልቅ ገንዘብ የሚንቀሳቀስበት የኢኮኖሚ ዘርፍ፣ መጻሕፍትን ማሳተም ነበር፡፡ ያኔ ኩራዝ የሚባል መንግሥታዊ የልማት ድርጅት ነበር፡፡ የትምህርት መጻሕፍቶችን በሙሉና ሌሎችንም መጻሕፍቶች ከኢትትመማድ (ኢትዮጵያ ትምርት መምሪያ ማደራጃ ድርጅት) ጋር በመሆን የሚያሳትም ትልቅ ማተሚያ ቤት ነበር፡፡ ይህም ትልቅ የሕዝብና የመንግሥት ድርጅት፣ ህወሓት ዒላማ ውስጥ ገባ፡፡ በጥቂት ቀናት ውስጥ ኃላፊዎቹን በሙሉ “ደርግ ኢሰፓ” የሚል ቅጽል ስም ሰጥታ ካባረረች በኋል፣ ደፋሯ እና አልጠግብ ባይዋ ህወሓት ኩራዝን እንደ ቅንቅን ወረሰችው፡፡ ያለምንም ይሉኝታ የኩራዝ ማተሚያዎች፣ ሱቆች፣ ወዘተ ሜጋ የሚል ስም ተለጥፎባቸው የህወሓት ንብረትና የኤፈርት ተባሉ፡፡ ባንድ ሌሊት! ከዚህ በተጨማሪም፣ በርታ ኮንስትራክሽን ፈርሶ ከጣና በለስና ከመኮድ በተወሰዱ መሳርያዎች ሱር ኮንስትራክሽን ተፈጥሯል፡፡ ሌላም ሌላም…

እስከ ሜቴክ የተዘረጋ አልጠግብ ባይነት

ኢሕአዴግ ደርግን ጥሎ ሀገር የመምራት ወንበሩን ከተረከበ ከ9 ዓመታት በኋላ ደርግ የጀመራቸውን ተግባራት ጠቃሚነት በማጤን እነዚያኑ ተቋማት በአንድ በመጨፍለቅ በአዲስ መዋቅር ውስጥ አካትቶ የብረታብረት እና ኢንጂነሪንግ ኮርፓሬሽን በሚል ስያኔ አንድ ግዙፍ ተቋም መሰረተ፡፡ የብረታብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (Metal and engineering corporation) በምህጻረ ቃሉ METEC ተብሎ የሚጠራው የልማት ድርጅት ሲሆን የተቋቋመው በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 183/2020 ዓ.ም ሰኔ 2 ቀን 2002 ዓ.ም ነው፡፡ የተቋሙ የንግድ ፍቃድ የወጣው ከምስረታው ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ በሥራ አስኪያጅነት ሲመሩት በነበሩት ሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው ስም ነው፡፡

ሜቴክ ከፍተኛ መጠን ያለው በጀት የፈሰሰበትን ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ፣ 10 የስኳር ማምረቻ ፋብሪካዎችን ፣የማዳበሪያ ማምረቻ ኩባንያን፣ የኬሚካል ማምረቻ ኢንደስትሪን፣ እንዲሁም ሌሎች ተዘርዝረው የማያልቁ ታላላቅ ፕሮጀክቶችን ጨምሮ በመላው ሃገሪቱ የሚገኙ ከ18 በላይ ኢንዱስትሪዎችን አጠቃሎ የያዘ፣ ተጠሪነቱ ለመከላከያ ሚኒስቴር የሆነ ግዙፍ ተቋም ነው፡፡ በብዙዎች ዘንድ ሜቴክ መከላከያ ሰራዊቱ የራሱን ገቢ በመፍጠር ራሱን እንዲችል ከቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የወረደውን ቀጭን መመሪያ ለመተግበር የተቋቋመ ድርጅት ነው ተብሎ ይታመናል፡፡ ኾኖም በኢትዮጵያ ታሪክ በመንግሥት ውስጥ ተደራጅተው ከባድ ጥፋት ከፈጸሙ የወንጀል ቡድኖች ሁሉ የላቀ የማፊያ ቡድን መፈልፈያ ለመሆን በቅቶ ታዝበናል፡፡ የሜቴኩ ማፊያ ቡድን መዋቅር ከላይኛው የመንግሥት አካል ጀምሮ እስከ ታህታይ መዋቅሩ ድረስ መረቡን የዘረጋው በህወሓት ሰዎች ነበር፡፡ ቡድኑ ከመንግሥት የሚረከባቸው ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ ተብሎ የሚመደብለትን በጀት ለግለሰቦች ጥቅም በማዋል ሀብትን በግልጽ እና በአደባባይ ተከፋፍሎ ሀገሪቱን እርቃኗን ምን ያህል በነጋዴነት የማይታማ የፖለቲካ ድርጅት ያሻውን ሲያደርግ ለመቆየቱ ንጥል ማሳያ ሊኾን ይችላል፡፡

ማጠቃለያ

የመጋቢት 2010ሩ ለውጥ በኢትዮጵያ ክሱት ከኾነ በኋላ ኤፈርትን በተመለከተ ይፋ የተደረገ አንድ ዜና ነበር፡፡ በኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ዙርያ የትግራይ ፖለቲከኞችና ምሁራን በሀርመኒ ሆቴል ባካሄዱት ምክክር ኤፈርትን ጨምሮ ሁሉንም የህወሓት ንብረት አክሲዮኖችን ለሕዝብ መሸጥ ሊጀምር ስለመኾኑ ተነግሮ ነበር፡፡ ጉዳዩ በዶክተር ደብረፂዮን ገብረሚካኤል አማካኝነት በይፋ መገለጹን ተከትሎ፣ ኤፈርት የኢትዮጵያዊያን አንጡራ ሀብት በጠራራ ጸሐይ ተዘርፎ የተቋቋመ ድርጅት መኾኑን በማስታወስ የንግድ ተቋሙ በመንግሥት እንዲወረስ ተጠይቋል። ጩኸቱ በሰዓቱ ሰሚ ባያገኝም እያደር ግን ህወሓት በቀላሉ በማይነጥፈው የፋይናንስ አቅሙ ታግዞ በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችን በገንዘብ ስፖንሰር እያደረገ ሀገሪቱን አኬልዳማ ማድረጉን ሊያቆም ግን አልቻለም፡፡ በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ሰሞነኛ መግለጫ መሠረት እንኳን ለመጠላላት ፕሮፓጋንዳ እያገለገለ የሚገኘው “ድምጺ ወያነ” የተባለው የቴሌቭዥን ጣቢያ ላይ ትልልቆቹ ትምዕት እና መሶቦ ሲሚንቶ እያንዳንዳቸው 8 ሚሊዮን እና 61 ሚሊዮን ብር በላይ የአክሲዮን ድርሻ አላቸው፡፡ መንግሥት በዚህ በኩል እጅግ የዘገየ ውሳኔ አሳልፏል ከማለት ውጪ አስተያየት መስጠት ያስቸግራል፡፡ ድርጅቶቹ በሀገር ኢኮኖሚ ውስጥ ያላቸው ድርሻ ግዙፍ መኾኑ ግን አያጠያይቅም፡፡ በመኾኑም መንግሥቱ እነዚህ ተቋማት ላይ ዕግድ ከመጣል ጎን ለጎን ሙሉ በሙሉ የራሱ ንብረት አድርጎ አገልግሎታቸውን እንዲቀጥሉ ማስቻል ይኖርበታል፡፡ ይኽ የሚኾነው በሁለት ምክንያት መኾኑን ማስታወስ ደግሞ ጠቃሚ ነው፡፡ የመጀመሪያው በተቋማቱ ውስጥ ተቀጥረው የዕለትና የወር ጉርሳቸውን የሚያገኙ ኢትዮጵያዊያን ሕይወት አደጋ ውስጥ እንዳይወድቅ ሲኾን ኹለተኛው ግን ከፍ ሲል በማሳያ እንደዘረዘርነውም እነኚህ የንግድ ተቋማት ቀደም ባሉት የኢትዮጵያ መንግሥታትም ይኹን ድኅረ 1983 በኢትዮጵያዊያን ሀብት የተቋቋሙ በመኾናቸው የኢትዮጵያዊያን ኾነው ተግባራቸውን በላቀና ፍትሓዊ መልኩ መቀጠል የሚገባቸው ስለኾነ ነው፡፡

Page 9: ቅፅ 2 ቁጥር 110 ቅዳሜ ህዳር 19 ቀን 2013 ዓ.ም

88ግዮን ቁጥር 110 ህዳር 2013 ዓ.ም

የግዮን እንግዳ

“ቴዎድሮስ አድኃኖም የእስር ትዕዛዝ “ቴዎድሮስ አድኃኖም የእስር ትዕዛዝ ሊወጣበት ይገባል”ሊወጣበት ይገባል”

“ጆባይደን የኢትዮጵያን ሕልውና የሚፈታተን ነገር ያደርጋል ብዬ አላምንም”

ግዮን፡- የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራንፕ የሕዳሴ ግድቡን በተመለከተ በተናገረው ንግግር በምርጫው አሸናፊ እንዳይኾን ኢትዮጵያውያን የሠሩት ሥራ ቀላል አይደለም ይባላል፡፡ የእርሶ ሚና ደግሞ በጣም የገዘፈ ነው የሚሉ ወገኖች አሉና ምን ይላሉ በዚህ ዙሪያ?

ፕ/ር አለማየሁ፡- እኔ ግልፅ በኾነ መንገድ ዶናልድ ትራንፕን ተሟግቸዋለሁ፤ ታግየዋለሁም፡፡ እስከ ምርጫው መጨረሻም “ትራንፕ ዩሮፋግ” የሚል ሰፋ ያለ ጽሑፍ አቅርቤ ከነማስረጃው ሕገ መንግሥቱን እንዴት እንደጣሰው ወንጀለኛ ነው በሚል አስቀምጫለሁ፡፡ በአጭሩ በእኔ እምነት ትራንፕ ማለት ወያኔ ማለት ነው፡፡ በዘር የሚከፋፈል፣ ጥላቻ የሚነዛ ግለሰብ ነው፡፡ ስለዚህ ይኽ ሰው የወያኔ አምሳል ነው፡፡ ስለዚህ የትራንፕ ንግግር ኢትዮጵያ ላይ ጦርነት ማወጅ ነው፡፡ በጎንዮሽ ኢትዮጵያ

ላይ ጦር ነው የሰበቀው፡፡ ይኽን አድሎ የጀመረው ዛሬ ሳይሆን ከዓመት በፊት ሕዳር ስድስት ነበር፡፡ ይኸውም ኢትዮጵያውያንን “ኑ ላደራድራችሁ” ብሎ እዚያው አታልሎ እጅ ጠምዝዞ ለማንበርከክ ነበር የፈለገው፡፡ ይኽም ከአልሲሲ ጋር ተስማምተው ያደረጉት ነው፡፡ እኔ ደግሞ ይኼን ነገር ተከታትዬ በየጊዜው በተለያዩ መልኩ ስትራቴጅው ምን እንደኾነ ሳስረዳና ሳሳውቅ ነበር፡፡

ይኽን ሊያደርጉ ነው፣ ይኽን እየፈጠሩ ነው፣ በማለት በተለይ እርዳታ ሊያቆሙ

እንደሚችሉ፣ ዓለም ባንክ ብድር እንደሚከለክል ወዘተ በሙሉ በግልፅ አስገንዝቤ ነበር፡፡ እንደውም ለገንዘብ ሚኒስትሩ የጻፍኩት ላይ እነዚህን ነገሮች በሙሉ በደንብ አስፍሬያለሁ፡፡ ትክክል በኾነ መንገድ ጀምረው ኢትዮጵያን ለማንበርከክ ያደረጉትን ጥረትና መጨረሻ ላይ ደግሞ እንደማይሰራላቸው ተናግሬ ነበር፡፡ ስለዚህ ከትራንፕና መሰል አካላት ጋር ያለኝ ጦርነት ከግል ጦርነት ያልተለየ ስለኾነ ለረጅም ጊዜ የተካሄደ ነበር፡፡ በርግጥ አንዳንዴ ደግሞ ትራንፕ መልካም ነገሮችን ሲያደርግ ከመደገፍ አልቦዘንኩም፡፡ ለምሳሌ 2017 ላይ ሥልጣን

ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም በሃገረ-አሜሪካ ሳን ቤርናርዲኖ የካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስ መምህር

ናቸው፡፡ በሥነመንግሥት፣ ሲቪል መብትና በአሜሪካ ሕገመንግሥት ዙሪያ ዳጎስ ያሉ ጥናቶች በማድረግ የሚታወቁት ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም፣ በአፍሪካ በተለይም ደግሞ በኢትዮጵያ ይስተዋል የነበረውን የሰብዓዊ መብት ረገጣ ላለፉት ዐሥራ ሦስት ዓመታት በተከታታይ ጦማሮችን በማዘጋጀት ለዓለማ አቀፉ ማኅበረሰብ የአገዛዙን ባህሪ ሲያጋልጡ ቆይተዋል፡፡ በኢትዮጵያ ከኹለት ዓመት በፊት የመጣውን ለውጥ ተከትሎ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ የአማካሪዎች ካውንስል ዋና ሊቀመንበር በመኾን ከማስተማር ሥራቸው ጎን ለጎን ሀገራቸውን የሚያገለግሉት ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያምን፣ ስለሕይወታቸው፣ ስለኢትዮጵያ አጠቃላይ ፖለቲካዊና ነባራዊ ጉዳዮች የሚከተለውን ሰፊ ቆይታ ከጋዜጠኛ ፍቃዱ ማኅተመወርቅ ጋር አድርገዋል፡፡ የመጀመሪያውን ክፍል እንኾ!

ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም

Page 10: ቅፅ 2 ቁጥር 110 ቅዳሜ ህዳር 19 ቀን 2013 ዓ.ም

99ግዮን ቁጥር 110 ህዳር 2013 ዓ.ም

የግዮን እንግዳ

እንደያዘ በተለይ ለአፍሪካ ሀገራት የሚለግሱትን ገንዘብ በተመለከተ የሚሰሩበትን ነገር ሳናጣራ ለሙስና ማስፋፊያ ገንዘብ አንሰጥም ማለታቸውን ደግፌ ነበር፡፡ ስለዚህ ትራንፕ ከእርዳታችን ጎን ለጎን ሙስናውን እንመለከታለን ሲል ከባድ ድጋፍ ሰጥቼዋለሁ፡፡ በኋላ ግን ወራት ባልሞላው ጊዜ ውስጥ ነገሩን በሙሉ አበላሸው፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞ መታየት ያለበት የኦባማ መንግሥት በቀጥታም ባይኾን በእነ ሱዛን በኩል የወያኔ ደጋፊ መኾኑ ይታወቃል፡፡ ትራንፕ ደግሞ ኦባማ ሠራ የተባለውን ነገር በሙሉ ማጣጣልና ማጥፋት ስለሚፈልግ ለወያኔ ተቃዋሚዎች ወይም ለእኛ የተመቸ ጊዜ ነበር፡፡ በዚህም ለወያኔ በኦባማ ደረጃ የሚታይ ምንም ዐይነት እርዳታ አልሰጠም፡፡ ነገር ግን ኢትዮጵያ ላይ ይኽንን ንግግር በማድረጉ ጦርነት እንዳወጀ ነው የምቆጥረው፡፡ ስለዚህ ለዚህ ሰውዬ መልስ መስጠት የሚቻለው እርሱን ከሥልጣኑ በማባረር ነው፡፡ በመኾኑም በግሌ ያደረግኩት አንደኛው ጥረት በተለይ ኢትዮጵያውያኖች በተለያዩ ግዛቶች(ስቴትስ) ያሉትን የሞት ሞታችሁን ኾናችሁ ወጥታችኹ ምረጡ እያንዳንዷ ድምጽ ታስፈልጋለች፡፡ ምክንያቱም ኹለት ሺህ ላይ ቡሽ ያሸነፈው ጠቅላላ በአምስት መቶ ድምጽ ነው፡፡ ስለዚህ በተቻላቸው አቅም ወጥተው እንዲመርጡ መቀስቀስ ነው፡፡ ቅስቀሳዬ ደግሞ በጽሑፍና በአንዳንድ ፎረሞች ላይ ሃሳቦቼን በማራመድ ነበር፡፡ በተጨማሪም ለዲሞክራቶች የሚኾን ብዙ ገንዘብን አሰባስበን፡፡ በግላችንም፣ በድርጅትም ደረጃ፣ የእነርሱንም ሰዎች አካተን በተቻለን መጠን እንዲያውቁን እና እንደረዳናቸው እንዲያውቁ በማድረግ ቅስቀሳውን አደረግን፡፡ ይኽ በመሆኑም ባይደን ሥልጣኑን ተቆጣጠረ፡፡ እንግዲህ በምንም ዓይነት መልኩ ባይደን ወጥቶ የኢትዮጵያ ግድብ ይደበደባል እንደማይል ባለሙሉ ዕምነት ነኝ፡፡ ሰውዬው እንደዚህ ዓይነት ቅሌት የለበትም፡፡ ለግብጽም ወግኖ ኢትዮጵያን ያጠቃል ብዬ እንደዚህ ግልጽ በኾነ መንገድ አላስብም፡፡ ኢትዮጵያ ላይ ጦር አዝምቱ አይልም፡፡ ነገር ግን ትራንፕ ይኽን ያደረገበትን ምክንያት ሳስብ እ.ኤ.አ 2016 ለሥልጣን ሲወዳደር ምርጫው መጨረሻ ላይ ከግብጽ ወደ 10 ሚሊዮን ብር ለእርሱ መቀስቀሻ ተልኮ ነበር፡፡ የዚህን ውለታ ለመመለስ ያደረገው ነው ብዬ እንድገምት እገደዳለሁ፡፡ ግብፅ 10 ሚሊዮን ብር መስጠቷ ደግሞ በብዙ መልኩ የተረጋገጠ ነው፡፡ ይኼ ደግሞ አሁን ከሥልጣን ከወረደ በኋላ በሕግ የሚጣራ ይኾናል፡፡ ይኽን ያደረጉት ደግሞ በግድቡ በኩል ኢትዮጵያን እንዲያንበረክኩላቸው ነው፡፡ ስለዚህ እኛ ደግሞ ይኽን የትራንፕን ከግብፅ ጋር መወገን ማምከኛችን በምርጫ መጣል ነበርና ዲሞክራቶች እንዲያሸንፉ ትንሽም ቢኾን በቅስቀሳው አስተዋጽዖ አድርገናል የሚል ዕምነት አለኝ፡፡

ግዮን፡- ከአዲሱ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት (ከጆባይደን) ለኢትዮጵያ ምን የተለየ ነገር ይጠብቃሉ? ከአሜሪካ ፖሊሲ ይወጣል ብለው ያስባሉ?

ፕ/ር አለማየሁ፡- እንደሚታወቀው አሜሪካ ሁልጊዜ የራሷን ጥቅም ነው የምታስጠብቀው፡፡ ነገር ግን ትራንፕና ባይደን የተለያዩ ሰዎች ናቸው፡፡ ሰማይና ምድር ማለት ናቸው፡፡ ትራንፕ የውጪ ፖሊሲ የለውም፡፡ በዘፈቀደ የሚሰራ ግለሰብ ነው፡፡ አያነብም፣ እልም ያለ

መሀይም ነው፣ ከእርሱ ምንም የሚጠበቅ ነገር የለም፡፡ ባይደን ግን በሴኔቱ ውስጥ ከ40 በላይ ዓመታትን ሰርቷል፡፡ ምክትል ፕሬዝዳንት ኾኖ ደግሞ ስምንት ዓመት አገልግሏል፡፡ የበሰለ ሰው ነው፡፡ የሚሰራውን የሚውቅ ግለሰብ ነው፡፡ የዲፕሎማሲ ጉዳዮችን ጠንቅቆ የሚያውቅ ነው፡፡ ስለዚህ አስተማማኝ መንገድ ነው የሚፈልገው፡፡ በእርግጥ ልክ ኦባማን እንደተጠቀሙበት አንዳንድ ሰዎች ተጠቅመው ኢትዮጵያ ላይ ወያኔን ለመርዳት ብለው የሚያደርጉት ተጽዕኖ ሊኖር ይችላል፡፡ ግን እንደምገምተው አሁን ላይ መሸጋገሪያ ከመንግሥት ሊያገኝ አልቻለም፡፡ ትራንፕ ዝም ብሏል፡፡ ትራንፕ እስከመጨረሻው ዝም ይላል የሚል ግምት አለኝ፡፡ ስለዚህ እነርሱ ተዘጋጅተው ይኽንን ነገር አትኩረው በቲውተር

ከመጻፍ በስተቀር የሚያደርጉት ነገር የለም፡፡ የሰብዓዊ ጥሰት አይፈጠር፣ ሰው አይሙት የሚል አቋም ካልኾነ ባይደን ኢትዮጵያ ላይ የተሻለ አስተያየት ይኖረዋል ብዬ ነው የምገምተው፡፡ ለዚህ ደግሞ ብዙ ምክንያቶችን ማንሳት ይቻላል፡፡ ለምሳሌ አፍሪካ ቀንድ አካባቢ የአልሸባብን መንሰራፋት አይሹም፡፡

ኢትዮጵያ ጠንካራ ካልኾነች ከባቢው በሙሉ ያልተረጋጋ ይኾናል፡፡ ቀጣናው ካልተረጋጋ ደግሞ የአፍሪካ ቀንድ ላይ እንደነቦኮሃራም ሊፈነጩ ነው ማለት ነው፣ ይኽን ደግሞ አይፈቅዱም፡፡ በዚኽም ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር መልካም ግንኙነትን ይመሠርታሉ፡፡ በሌላ ጎኑ ትራንፕ ሲል የነበረውን ማስታወስ ያስፈልጋል፡፡ በኢትዮጵያ ላይ ጫና እናሳርፋለን ነበር የሚለው፡፡ ጫና ማለት የዓመት ችሮታ አንሰጥም ነው፣ ከዓለም ባንክ የምታገኙትን እናስቀንሳለን ነው፡፡ በዲፕሎማሲ በኩል አንዳንድ ነገር እንዳታደርጉ ተጽዕኖ እናደርጋለን ነው፡፡ ሌላ ትራንፕ ሕግ የማያከብር ሰው ነው፡፡ ሕግ የማያከብረው ትራንፕ ማድረግ ያልቻለውን ነገር ባይደን ሊያደርግ አይችልም፡፡ ምክንያቱም ትራንፕ ሞከረ፣ ዕርዳታ አቆምኩ አለ፣ ኹለት መቶ ስድሳ ሚሊዮን ብር አቆመ፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት ደግሞ እሺ ከቆመ ቆመ ምንም ችግር የለም ብሎ ዝም አለው፡፡ ከዚህ ሌላ ምንድነው ምንም ሊያደረግ አልቻለም፡፡ ባይደንም ቢኾን ከዚያ የተሻለ ነገር በዲፕሎማሲ በኩል ለማድረግ ይሞክራል እንጂ ይኽን የትራንፕን ፖሊሲ ተከትሎ የኢትዮጵያ ሕልውና የሚፈታተን ነገር ያደርጋል ብዬ አላምንም፡፡ ሁላችንም ልንገነዘበው የሚገባው የኢትዮጵያ ዕጣ ፈንታ በትራንፕ፣ በባይደን፣ በዩኤስ ኮንግረስ የሚወሰን አለመኾኑን ነው፡፡ በኢትዮጵያ ሕዝብና በኢትዮጵያ ሕዝብ ብቻ ነው፡፡ ይኸንን በደንብ አድርገን ማረጋገጥ አለብን፡፡ ለሦስት ሺህ ዘመን ነፃነታችንን ያስጠበቅነው የነጮችን ወይም የአውሮፓውያንን እግር እየሳምን አይደለም፡፡ እንደውም አውሮፓውያን እኛ ጋር መጥተው ሊያንበረክኩን ሲሉ አስተምረን የላክናቸው ነን፡፡ በአድዋ ቢባል በሁለተኛው የዓለም ጦርነት፣ ቀደም ባሉት ዘመናት ግብጽ ለመውረር በሞከረች ጊዜ ሁሉ በራሳችን አቅም በመተማመን መክተናል፡፡ ስለዚህ እኛ የምንቀጥለው እኛ በወሰንው ውሳኔ ብቻ ነው፡፡ በርግጥ ከውጭ ብዙ ተጽዕኖ ሊያደርሱብን ይችላል፡፡ እነዚያ ተጽዕኖዎች ምናልባት የኢትዮጵያን ልማታዊ ግስጋሴ ሊያዘገዩት ይችሉ ይኾናል፡፡ ግን መጨረሻ ላይ መደርሳችን አይቀርም፡፡ ይኽንን ሁሉ ትግል አልፈን መጨረሻ ላይ ስንደርስ ለአፍሪካ ጮራ ነው የምንኾነው፡፡ ምክንያቱም ኢትዮጵያን ተመልከቷት፣ ያ ኹሉ ተጽዕኖ ደርሶባት፣ ያ ጫና ተደርጎባት ሊያሸንፏት አልቻሉም፡፡

ሦስት ሺህ ዘመን ነጻነቷን አስጠብቃ ቅኝ ሳትያዝ እስከዛሬ የደረሰችበት የራሷ ምክንያት አላት፡፡ በእኔ እምነት ኢትዮጵያውያን በጣም ልዩ ሕዝቦች ነን፡፡ ኢትዮጵያ ከሌላው የምትለይባቸው ብዙ ማሳያዎች አሉ፡፡ ለምሳሌ በመጽሐፍ ቅዱስ ከ40 ጊዜ በላይ ተጠቅሳለች፣ ነብዩ መሐመድ ተከታዮቻቸውን ወደ ኢትዮጵያ ሒዱ እዚያ ጥሩ አገር ጥሩ መንግሥት አለ ኢትዮጵያን አትንኩ ብለው የተናገሩባት ሀገር ናት፡፡ የአፍሪካ ሕብረት የተቆረቆረባት ሀገር ኢትዮጵያ ናት፣ የመንግሥታቱ ድርጅት ሲመሠረት ግንባር ቀደም መሥራቿ ኢትዮጵያ ናት፡፡ በ1940ዎቹ

እኛ የምንቀጥለው እኛ በወሰንው ውሳኔ ብቻ ነው. በርግጥ ከውጭ

ብዙ ተጽዕኖ ሊያደርሱብን ይችላል.

እነዚያ ተጽዕኖዎች ምናልባት የኢትዮጵያን ልማታዊ ግስጋሴ

ሊያዘገዩት ይችሉ ይኾናል

ግን መጨረሻ ላይ መደርሳችን አይቀርም

ይኽንን ሁሉ ትግል አልፈን መጨረሻ ላይ ስንደርስ ለአፍሪካ

ጮራ ነው የምንኾነው

ምክንያቱም ኢትዮጵያን ተመልከቷት፣

ያ ኹሉ ተጽዕኖ ደርሶባት፣ ያ ጫና ተደርጎባት ሊያሸንፏት

አልቻሉም...

Page 11: ቅፅ 2 ቁጥር 110 ቅዳሜ ህዳር 19 ቀን 2013 ዓ.ም

1010ግዮን ቁጥር 110 ህዳር 2013 ዓ.ም

የግዮን እንግዳ

ሚዲያዎች ሲዘግቡ ቪዲዮ ላይ የተናገሩትን መረጃ አስቀምጨዋለሁ፡፡ ከተቻለን በቪዲዮ ያየናቸውን ሰዎች መርማሪዎችን ልከን ሰዎቹን እንዲያነጋግሩ ለማድረግ እንሞክራለን፡፡

ግዮን፡- ህወሓት በዚህ ደረጃ ራሱን አዘጋጅቶ ጦርነት ይከፍታል ብለው አስበው ነበር? የጦርነቱን አካሄድስ እንዴት አዩት?

ፕ/ር አለማየሁ፡- እነሱ ጦርነት የመክፈት ችሎታ የላቸውም፡፡ ምክንያቱም በዓለም አቀፍ ሕግ ጦርነት ሊከፍት የሚችለው አንድ ሀገር በሌላ ሀገር ላይ ነው፡፡ ለምሳሌ በአሜሪካ ሕገመንግሥት በግልፅ የተቀመጠ ነገር አለ፡፡ ምክር ቤቱ ወይም ኮንግረሱ ብቻ ጦርነት ከፍቷል ብሎ በሕግ መወሰን አለበት፡፡ ጦርነት ማለት ሕጋዊ እርምጃ ነው፡፡ ለምሳሌ በአሜሪካና በቬትናም መካከል የተደረገው ጦርነት “ጦርነት” አይደለም፡፡ ምክንያቱም ኮንግረሱ የወሰነው እና የመከረበት ስላልሆነና የአሜሪካ ፕሬዝዳንቶች በስሜት የጀመሩት ስለሆነ ሕጋዊ እርምጃ አይደለም፡፡ ያም ራሱ በሕገመንግሥታዊ መንገድ ከታየ “ፖሊሲ አክሽን” ተብሎ ነው የሚታየው፡፡ ስለዚህ ይኽ ጦርነት በኮንግረሱ እውቅና የሌለው ወታደራዊ እርምጃ ነው፡፡ ኢራቅ ደግሞ አፍጋኒስታንን ስትጋብዝ ኮንግረሱ ጦርነት አላወጀም፡፡ የኃይል መጠቀም ሥልጣን ነው የሰጠው፣ ለፕሬዝዳንቱ፡፡ የኒውክሌር ቦንብ እያዘጋጁ ነው፣ ሽብርተኞች መሽገዋል በሚል

ገደማ፣ በዓለም ወሳኝ የታሪክ ምዕራፍ ውስጥ ኢትዮጵያ ሁልጊዜ ነበረች፡፡ ከአፍሪካ ሀገራትም ትለያለች፣ ከሌላውም ዓለም እንዲሁ፡፡ ስለዚህ እኛ እራሳችንን አለማወቃችን እንጂ ከዓለም የተለየንና ገናና ማንነት ያለን ኩሩ ሕዝቦች ነን፡፡ ሁሌ እኛ የምንዳከመው ራሳችን በራሳችን እንጂ ማንም የውጭ ኃይል በግሮን አይደለም፡፡ ይኽን ደግሞ እኔ ሳልኾን ታሪክ ምሥክር ነው፡፡ ወደኋላ ዞረን እንመልከት እስቲ፣ ግራኝ አሕመድ ሞከረ ጠፋ፣ ጣሊያን ሞከረ ጠፋ፣ ፖርቱጋሎች ሞከሩ ጠፉ፣ እንግሊዞች አጼ ቴዎድሮስ ላይ ሞከሩ ጠፉ፣ ግብጾች ሞከሩ ጠፉ፡፡ ከውጭ ያሸነፈን ኃይል የለም፡፡ ስለዚህ የሚያጠፋን የራሳችን ጥላቻና የራሳችን አለመተማመን ብቻ ነው፡፡

ግዮን፡- በቅርቡ በሰሜን ዕዝ የመከላከያ ሠራዊት ላይና በማይካድራ ሰላማዊ ዜጎች ላይ ዘግናኝ ጭፍጨፋ መካሄዱ የሚታወስ ነው፡፡ እርሶ ይኽን ሁነት በተመለከተ ነገሩን ወደ ዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ለመውሰድ እየተንቀሳቀሱ ነውና ስለሂደቱ ቢነግሩን?

ፕ/ር አለማየሁ፡- ያው የፍርድ ነገር ሲመጣ መረጃ ዋናው ነው፡፡ ማይካድራ ላይ እስካሁን ያለኝ መረጃ የሚጠቁመው የጦር ወንጀሎች ተፈፅመዋል የሚል ነው፡፡ የጦርነት ወንጀል ሲባል ደግሞ በየትኛውም ዓለም ላይ ኾነ በአገሩም ሕግ ይመስለኛል ወንጀለኛ መቅጫ ላይ “ዘር ማጥፋት” የሚባል የወንጀል ዓይነት እናዳለ አውቃለሁ፡፡ ይኽ የወንጀል ዓይነት የሚለው አንድ ጦርነት ሲካሄድ ወይም ግጭት ሲኖር ንጹሐኑ መነካት የለባቸውም፡፡ አንድ የሚሸሽ ጦር እየሸሸ ያንን መከላከል ሲያቅተው ንጹሐኑን እየጨፈጨፈ ከሄደ የጦር ወንጀል ነው፡፡ ንጹሐንን መንካት አይቻልም፡፡ በኑረንበርግ ሕግም ኾነ ብዙ ዓለም አቀፍ ሕጎች አሉ፡፡ በዓለም አቀፍ የወንጀል ሕግም ቢኾን የሮም ድርድር በሚባለው በዚያም ላይ የተመዘገበ ነው፡፡ ማይካድራ ላይ ከሕግ አንጻር እኔ የተመለከትኩት ከ500 ሰዎች በላይ በታጠቁ ኃይሎች ጄኖሳይድ እንደተፈጸመባቸው ነው፡፡ የተፈፀመው ነገር ደግሞ ዘር ተኮር ስለሆነ በጄኖሳይድ ያስከስሳል፡፡ ስለዚህ ሦስት ዓይነት የክስ ቻርጅ ይኖርባቸዋል፡፡ የመጀመሪያው ዘር ማጥፋት ሲሆን ኹለተኛው ደግሞ የጦር ወንጀል ነው፡፡ በሦስተኛ ደረጃ ደግሞ “crime againest humanty” የሚባለው ወንጀል ነው፡፡ ሦስተኛው የወንጀል ዓይነት የሰቆቃውን ዓይነትና መጠን የሚገልፅ ነው፡፡ ማለትም ሰው ደብድበዋል፣ ንብረት አውድመዋል፣ በአሰቃቂ ሁኔታ ገድለዋል፣ የሰውን ሰብዓዊ መብት ገፈዋል ወዘተ… የሚለውን የሚገልፅ ነው፡፡ ስለዚህ ወንጀለኞቹ በዚህም ሊጠየቁ ይችላሉ፡፡

በሌላ በኩል ብዙ ሰዎችን እየጠለፉ መውሰድም በዓለም አቀፍ ሕግ የሚያስጠይቅ ነው፡፡ ለምሳሌ ከራያ አካባቢ ከ10 ሺህ የሚልቁ እስረኞችን የሰወሩበት ሂደት ራሱን የቻለ ወንጀል ነው፡፡ በተለይ ደግሞ በጦር ሠራዊቱ ላይ የፈፀሙት ወንጀል በዓለም ሕግ ከፍተኛውን ቦታ የሚይዝ ነው፡፡ በትኛውም ቦታና ሀገር እጅ የሰጠ ኃይል ላይ እርምጃ አይወሰድም፡፡ እንደውም መጠነኛ የኾነ እንክብካቤ ይደረግለትና ይቀመጥ ነው የሚለው ፤ የዓለም ሕግ፡፡ በማይካድራ በኩልም የተጨፈጨፉ ወገኖች ስም ዝርዝር ይፋ ቢኾን መልካም ነው፡፡ እዚህ ላይ እናንተም ብትተባበሩኝ ደስ ይለኛል፡፡ ያ ሲኾን ነው ፍርድ ቤት ይዞ መቅረብ የሚቻለው፡፡ በዚህ ጉዳይ ማስረጃውን ይዘን ከቀረብን ዐቃቢ

ሕጉ ነፃ በኾነ መልኩ ይኽን ወንጀል መመርመር ይችላል፡፡ የተሰጠውን ማስረጃ ወስዶ ለኢትዮጵያ መንግሥት ያቀርብና እነዚህን ሰዎች ያዝዋቸው፡፡ አለዚያ እኛ ሕጋዊ እርምጃ እንወስዳለን የሚል መልዕክትም ያስተላልፋል፡፡ የዓለም አቀፍ ወንጀል ሕግ የሚወስዳቸው እርምጃዎች የአንድ አገር መንግሥት አልችልም ሲል ወይም የስምምነቱ አባል ሳይኾን ሲቀር ነው፡፡ ለምሳሌ ኬንያ የዚያ ስምምነት አካል ስለነበረች ባለፈው ምርጫ በተፈጠረው ችግር ተጠይቀውበታል፡፡ ኢትዮጵያ ግን የዚህ ስምምነት አካል አይደለችም፡፡ ግን በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ መንግሥት “international crime court” ይመልከትልኝ የማለት ሙሉ መብት አለው፡፡ ስለዚህ ጉዳዩ በኹለት መንገድ ሊታይ ይችላል፡፡ አንዱ እኛ በግለሰቦች ወይም በሲቪክ ማህበራት ደረጃ ጉዳዩን ለ”ICC” ፕሮስኪውተር ዐቃቢ ሕግ ማቅረብ እንችላለን፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥትም ማቅረብ ይችላል፡፡ ነገር ግን ይኽንን ለማድረግ የማቾች ሙሉ መረጃ ሊኖረን ይገባል፡፡ በተጨማሪም የተደረገውን አጠቃላይ ዝርዝር ሁኔታ ማካተት አለብን፡፡ ይኽን ለማድረግ ደግሞ በእናንተ በኩልም በኢሜል መረጃዎችን ብታደርሱን ለእኛ ትልቅ እርዳታ ነው፡፡ በተለይ አሁን ላይ ጉዳት የደረሰባቸው አካባቢዎች ኢንተርኔትና ስልክም ስለሌለ መረጃዎች እየደረሱኝ አይደለም፡፡ ያው ይኽን ደግሞ መናገር ያለበት በዓይኑ ያየ ሰው ሊኾን ስለሚገባ ጥንቃቄ ያስፈልገዋል፡፡ በእርግጥ

Page 12: ቅፅ 2 ቁጥር 110 ቅዳሜ ህዳር 19 ቀን 2013 ዓ.ም

1111ግዮን ቁጥር 110 ህዳር 2013 ዓ.ም

የግዮን እንግዳ

ተቋማቱን ያገኙትና በንብረቱም የበለፀጉት ሕጋዊ ባልኾነ መንገድ ነው፡፡ ሀብቱ ያለአግባብ በጉልበት ከሕዝብ የተነጠቀ ሊኾን ይችላል፡፡ መኪናው በብድር ተገዝቶ ከባንክ ያልተከፈሉ ሊኾኑ ይችላሉ፣ ሕንፃው ተሰርቆ በመጣ ገንዘብ ተገንብቶ ሊኾን ይችላል፣ መሬቱ በፖለቲካ ውገናና በውንብድና የተያዙ ሊኾኑ ይችላሉ፡፡ ስለዚህ ብዙ ሕግ ተጥሶ የተፈራ ንብረት ስለኾነ በሕግ ሊታይ የሚችል ነው፡፡ በሌላ በኩል እነዚህ ድርጅቶች ይኽን አሸባሪውን ቡድን በገንዘብና በቁሳቁስ ሲደግፉ የተገኙ የወንጀለኛ ድርጀቶች መኾናቸው ሲረጋገጥ ተቋሞቹ በሕግ ይጠየቃሉ፡፡ ይኽ ሁኔታ በኹለት መልኩ የሚታይ ነው፡፡ አንደኛው ንብረቱ ራሱ ተከሳሽ ሆኖ የሚቀርብበት ሲኾን ሌላው ደግሞ የንብረቱ ባለቤት የወንጀል ተጠያቂ የሚደረግበት አሠራር ነው፡፡ 34ቱ ድርጅቶች የማን ናቸው የሚለውም በዚህ ግምት የሚወስዱ ናቸው፡፡ እነርሱ ላይ የሚወስደውም እርምጃ ለየት ያለ ነው፡፡ ንብረቱ በፍትሐብሔር የሚታይ ሲኾን የተቋሙ አዛዥ፣ ባለቤትና ማናጀር የነበሩ ግለሰቦች ደግሞ ጉዳያቸው የሚታየው በወንጀል ነው፡፡ ምክንያቱም “ድርጅቱን ተጠቅማችሁ ይኽን ወንጀል ፈፅማችኋል” የሚለው ጥያቄ ስለሚነሳ ማለት ነው፡፡

ግዮን፡- ሰሞኑን የህወሓት ሰዎች በዓለም አቀፍ መድረክ ተጽዕኖ ለመፍጠር እየሞከሩ ነው፡፡ ይኼን ነገር እንዴት ያዩታል? በእርሶ በኩልስ በሀገሪቱ እየተካሄደ ስላለው ነገር ለዓለም አቀፍ ዲፕሎማቶች ለማሳወቅ የሔዱበት ርቀት ምን ይመስላል?

ፕ/ር አለማየሁ፡- ይህ በኹለት መንገድ የሚታይ ሲኾን የመጀመሪያው ህወሓት የሚያቀርበው ማወናበጃ ውጤቱ ሰውን መረበሽና ማወናበድ መኾኑ ነው፡፡ ይኽ ደግሞ ሰውን አወናብዶ በሀገር ውስጥ ለውጥ ይመጣል ብሎ መጠበቅ በተለየ መልኩ የሚታይ ነገር ነው፡፡ ዓላማው በዚህም በዚያም ጮኸው ከሕግ ተጠያቂነት ማምለጥ ነው፡፡ 27 ዓመት ሙሉ የሰሩትን ወንጀል ሸምጥጠው በድርድሩ ከተጠያቂነት ለማምለጥ የሚሰሩት ሸፋጥ ነው፡፡ ስለዚህ ይኽ እነርሱ የሚሰሩት ሥራ ይኽን ይቀይራል የሚል ዕምነት የለኝም፡፡ ይህን ያህል ጥፋት ጠፍቶ

ከእነርሱ ጋር ለድርድር ሊቀመጥ የሚችል ኃይል ሊኖር አይችልም፡፡ በሁለተኛ ደረጃ የሚታየው ደግሞ የቴዎድሮስ አድኃኖም ጉዳይ ነው፡፡ ቴዎድሮስ አድኃኖም የቀረበበትን ክስ እስካሁን አላስተባበለም፡፡ አለማስተባበሉ ደግሞ የመንግሥትን ውንጀላ ተቀብሎታል ማለት ነው፡፡ ከዚህ አኳያ በኢትዮጵያ መንግሥት በኩል እርምጃ ሊወሰድባቸው የሚገቡ ጉዳዮች አሉ፡፡ ለምሳሌ ቴዎድሮስ አድኃኖም በዚህ ደረጃ ተጠያቂ እስከ ኾነ ድረስ የእስር ትዕዛዝ ሊወጣበት ይገባል፡፡ ይኽ የሚያሳየው በግለሰቡ ላይ ሕጋዊ እርምጃ እየተወሰደ መኾኑን ነው፡፡ በሌላ በኩል የኢትዮጵያ መንግሥት ቴዎድሮስ አድኃኖም በሚሰራበት ተቋም በኩል ስሞታ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ የሚሰራበት ተቋም አንድ አቋም ወስዶ ግለሰቡን እንዲመረምረው ማድረግ ይኖርበታል፡፡ ውጭ ያለን ሰዎች ደግሞ ግለሰቡ ከሥነምግባር ያፈነገጡ ነገሮችን ሲያደርግ ለሚሰራበት ተቋም ማቅረብና እንዲመረምረው ማድረግ አለብን፡፡ በግለሰብ ደረጃም ሰውየውን መክሰስ እንችላለን፡፡ ይኽ በቀላል መልኩ የሚታይ አይደለም፡፡ በዚህ ግለሰብ ላይ ቢያንስ ዐሥር ወይም አምስት ሺህ ሰው ይመርመርልኝ የሚል ጥያቄ ቢያቀርብ ግለሰቡ ተጠያቂ ይሆናል፡፡ ስለዚህ በውጭ የሚኖረው የዳያስፖራ ምሁራን ይኽን ማድረግ ይችላል፡፡ እኔ በግሌ በዚህ ዙሪያ ለመሳተፍ ዝግጁ ነኝ፡፡ ነገር ግን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ምሁራን ከዚህ ቀደም እንዳየሁት እንዲህ ዓይነቱ ነገር ላይ ለመሳተፍ ዝግጁ አይመስሉም፡፡ በዚህ ደረጃ ላይ የተወሰኑ ምሁራን እንኳ ቢሳተፉ ከጎናቸው ቆሜ ጉዳዩን ለማስኬድ ዝግጁ ነኝ፡፡ በጥቅሉ ጥቂት ሰዎችም ቢኾኑ እንቅስቃሴ ቢያደርጉ ለውጥ ማምጣት ይቻላል ብዬ አምናለሁ፡፡

ማስታወሻ፡- ውድ አንባቢያን ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገ/ማርያም ጋር ያደረግነው ቆይታ በዚህ የሚገታ አይደለም፡፡ ፕሮፌሰር በአፍላ የወጣትነት ዕድሜያቸው ከኢትዮጵያ ስለወጡበት ሁኔታ፣ ወደሀገራቸው ዳግመኛ ለመመለስ 48 ዓመታት ስለምን እንደተቆጠሩ፣ ድኅረ ለውጡ ባለው የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ እና እርሳቸው ስለሚመሩት የዳያፖራ ትረስት ፈንድ ቆይታ አድርገናል፡፡ የሳምንት ሰው ይበለን፡፡

ነው አገሪቱን እንዲያረጋጋ ፕሬዝዳንቱ የተፈቀደለት፡፡ ስለዚህ መንግሥት ብቻ ነው ጦርነትን ሊከፍት የሚችለው፡፡ ወያኔዎች ደግሞ መንግሥት አይደሉም፣ የክልል አስተዳዳሪዎች እንጂ፡፡ የክልል አስተዳደር ወታደራዊ እርምጃ ከወሰደ መንግሥትን ተቃወመ እንጂ ጦርነት ከፈተ አይባልም፡፡ እነሱ ያደረጉት ግን የሽብር ተግባር መፈፀም ነው፡፡ ቀደም ሲል TPLF አሸባሪ እንደሆነ ገልጬ ነበር፡፡ ስለዚህ አሸባሪ ጦርነት ሊከፍት አይችልም፡፡ አሸባሪ ሽብር ብቻ ነው መፍጠር የሚችለው፡፡ የህወሓቶችን ሽብር ለየት የሚያደርገው 27 ዓመት በሕገወጥ መንግሥትነት በመቆየታቸው መሳሪያ አከማችተው ድርጅታዊ ቅርፅ ለመያዝ አስችሏቸዋል፡፡ አልሻባብም በሥልጣን ላይ ኖሮ ይኽን ተግባር ቢፈጽም ያው ነው፡፡ እነርሱም የሠሩት የአልሸባብን ሥራ ነው፡፡ ለምሳሌ ኤርትራ ላይ ሮኬት ተኮሱ፡፡ ይኼ የሽብር ሥራ ነው፡፡ ለምሳሌ አሜሪካን አገር 2001 ላይ ሃያ የሚኾኑ የሳውድ ዐረቢያ አሸባሪዎች መጡ፡፡ ትልቅ ሕንጻ አጥፍተውም ሦስት ሺህ ሰዎችን ገደሉ፡፡ ታዲያ እነዚህ ሰዎች አሜሪካ ላይ ጦርነት ከፍተዋል ማለት ነው? አልከፈቱም፡፡ እዚያ ላይ የሞተውና ከዚያ ጥቃት ጋር የተያያዘው ነገር በሙሉ ዘጠኝ ዐሥራ አንድ የሽብር ጥቃት ነው የሚባለው፡፡ በእኘ ሀገር የተፈጸመውንም በግሌ “የሕዳር ሃያ አራት የሽብር ጥቃት” ብዬ ነው የማምነው፡፡

ግዮን፡- ከሕግ አንፃር ህወሓት አሁን እያደረገው ያለው ነገር በአሸባሪነት ሊያስፈርጀው ይችላል? አሸባሪ ለመባልስ በሀገሪቱ ፓርላማ ካልፀደቀ ዓለማቀፋዊ ተቀባይነት ይኖረዋል፣ ቢያብራሩት?

ፕ/ር አለማየሁ፡- አዎ ጥያቄ የለውም፡፡ የተሻሻለው የፀረሽብር ሕግ ላይ ይኽን በተመለከተ የሚለው ነገር አለ፡፡ ለምሳሌ የመንግሥት ተቋማትን ማጥፋት የሽብር ተግባር እንደኾነ ይጠቅሳል፡፡ በዓለም አቀፍ ሕግም አንድ ሕጋዊ ያልሆነ መንግሥት በሌላው ሀገር ላይ ጥቃት ሲፈፅም ሽብር ነው፡፡ ለምሳሌ ህወሓት ኢትዮጵያን አልፎ ኤርትራ ላይ ሽብር ፈፅሟል፡፡ ይኽ ደግሞ አልሸባብ ከሶማሊያ ወጥቶ ኬንያ ላይ ከፈፀመው ጥቃት ጋር የሚመሳሰል ነው፡፡ ስለዚህ የሀገሪቱ መንግሥት እነዚህን ሰዎች በሽብር የመጠየቅ ሙሉ መብት አለው፡፡ አምልጠው ከሀገር ቢወጡ እንኳ በኢንተርፖል በኩል በሕግ ጥላ ሥር እንዲውሉ ለማድረግ ይሞከራል፡፡ አለዚያ ደግሞ እንደ ስፔንና ኔዘርላንድ ዩኒቨርሳል ስምምነት የትም ቦታ ወንጀሉ ቢፈጸም ግለሰቡ በተገኘበት ቦታ በቁጥጥር ሥር እንዲውል ይደረጋል፡፡

ግዮን፡- ዐቃቢ ሕግ በቅርቡ በህወሓት 34 የፋይናንስ ተቋማት ላይ እገዳ መጣሉ ይታወሳል፡፡ ይኽን በተመለከተ በተለይም መንግሥት በቀጣይ ምን ማድረግ አለበት ይላሉ?

ፕ/ር አለማየሁ፡- የንብረት ጉዳይ በፍትሐብሔር የሚታይና ብዙ መንስኤ ሊኖረው የሚችል ነው፡፡ በመጀመሪያ መንግሥት ሊጠይቅ የሚችለው ድርጅቶቹ ከየት በመጣ ገንዘብ ተቋቋሙ የሚለውን ነው፡፡ ለምን ከተባለ ጥርጣሬ አለኝ ቢልና ከባንክ ተበድራችሁ አልከፈላችሁም፣ በነጻ ነው ያገኛችሁት፣ በቅናሽነው ያገኛችሁት፣ ተሰርቆ ነው የተቋቋመው የሚለውን ነገር ቢያነሳ የማጣራት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ይኽን በሚያደርግበት ጊዜ ደግሞ ማድረግ ካለበት ቅድመ ሁኔታ ውስጥ አንዱ የባንክ አካውንታቸውን ማገድ ነው፡፡ ያላቸውን ንብረት እንዳያንቀሳቅሱ ማድረግ ይችላል፡፡ ይኼ በመንግሥት ደረጃ ብቻ ሳይኾን በግለሰብ ደረጃም ማሳገድ ይችላል፡፡ ይኽ ዛሬ ብቻ ሳይኾን ከአጼ ምኒልክ ጀምሮ ሲሠራበት የነበረ ሕግ ነው፡፡ በጥቅሉ እነዚህ ሰዎች

Page 13: ቅፅ 2 ቁጥር 110 ቅዳሜ ህዳር 19 ቀን 2013 ዓ.ም

1212ግዮን ቁጥር 110 ህዳር 2013 ዓ.ም

ምልከታ

አሜሪካና ሩሲያ ሕዋ ላይ የጦር መሳሪያ ያንቀሳቅሳሉ ሲባል ሰምተናል! ይህ ሁሉ የሚተገበረው በሳይበር

ቴክኖሎጂ ስለመሆኑ አንጠራጠርም! ይህ በእንዲህ እንዳለ ስለማናዉቀው ዓለም ከማዉራታችን በፊት በሳይበር ጥቃት ስለሚከወኑ ጦርነቶች ብናወራ የተሻለ ይሆናል፡፡ እንግሊዛዊው ቻርለስ ዳርዊን የሰው ልጅ እዚህ ደረጃ የመገኘቱ ምሥጢር ዝግመተ ለዉጥ ነው ይለናል በሳይንስ እይታው! ይህን የዳርዊን መነጽር የጦርነትን ዝግመተ ለዉጥ ብናስረዳበት ይሻላል፡፡ የጦርነት ቴክኖሎጂ ቀስ በቀስ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየዘመነ የሰው ልጅ ከደረሰበት ሥልጣኔ ጋር እኩል አብሮ የተጓዘ ለዉጥ ነው፤ ለዚህም ራቅ ብሎ መጀመር አያስፈልግም የአድዋዉን ድል ማሰብ በቂ ነው፡፡ አድዋ ላይ ከጠላት ጋር የተደረገው እልህ አስጨራሽ ጦርነት ፊትና ፊት በባህላዊ የጦር መሣሪያዎች የተማከቹበት ነው፡፡ ጦርነት ከእንደነዚህ ዐይነት መሰል ድርጊቶች ተነስቶ ዛሬ ላይ የቴክኖሎጂ ውጤት በሆነው ሳይበር ላይ ደርሶ ጦርነቶች በሳይበር ጥቃት እየተጋጋሉ ይገኛሉ፡፡ ጦርነቱም በድምጽ የለሽ አድቢዎች ይካሄዳል፤ ወይም ጥይት በማያጮሁ ጦረኞች ይተኮሳል፡፡ ተኩሶቹም ዒላማቸውን እንዲጠብቁ ተደርገው ይሰነዘራሉ፡፡

ጥናቶች እንደሚያሳዩት በአሁኑ ጊዜ በዓለማችን በጦር መሳሪያ ከሚደረገዉ ጦርነት ይልቅ የሳይበር ጥቃቶች እና ዲጂታል የስለላ ሥራዎች በሀገራት ብሔራዊ ደህንነት ላይ ትልቅ ስጋት እያሳደሩ ነዉ። ሳይበር የአገልግሎቱ ደህንነት የተረጋገጠ ካልሆነ በአሉታዊ ጎኑ የሚፈጥራቸው ቀውሶች ቀላል አይደሉም፡፡ የሳይበር ጥቃት ሆን ተብሎ ያልተፈቀዱ የኮምፒውተር ሥርዓቶችን መሠረተ ልማቶች እና ኔትዎርኮች ላይ አጥፊ ሶፍትዌሮችን በመጠቀም በሕገወጥ መንገድ ዳታዎችን መበዝበዝ እና አገልግሎት የማስተጓጎል ተግባር ነው፡፡ ስለዚህም የሳይበር ጥቃት ጦርነቶች በግለሰብና ግለሰብ በግለሰብና ተቋማት፤ በተቋማትና ተቋማት እንዲሁም በዋናነት በሃገርና ሃገራት በኩል ከፍተኛ የጦር ሜዳ ዉጊያ ከሆነ ሰነባብቷል፡፡ አንድ ሀገር ምንም እንኳ በራሷ ሉአላዊነቷን አስጠብቃ የምትተዳደር ቢሆንም የግድ ያለተቃርኖ መኖር አትችልም፡፡ ለዚህም የምትከተላቸው የፖለቲካ ኢኮኖሚና ማኅበራዊ ትስስሮች

ተቃርኖዎችን እንድታስተናግድ ትገደዳለች!

የሳይበር ጥቃት ጦርነት በሃገር ላይ ከሚያደርሰው ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊ፣ አካላዊ/ዲጂታል ሥነ-ልቦናዊ፣ ማህበራዊ እና መልካም ስምን ከማጉደፍ አንጻር ሕዝብን ወደ እርስ በእርስ ግጭት የፖለቲካ ቀውስ የሕዝብ አመኔታ ማጣት የገንዘብ ስርቆት የማኅበረሰብ ቀውስ የአገልግሎት መቋረጥ የሀገር ሉዓላዊነት ማሳጣት የመሠረተ ልማቶችን አገልግሎት ከማቋረጥ አኳያ የሳይበር ደህንነት እንዲሁ የዋዛ ፈዛዛ መታየት የሌለበት መከላከል ያለበት ዉጊያ ነው፤ ለዚህም የሳይበር ጦር ሸማቂዎች እንደ ተልዕኮና ዓላማቸው ጥቃት የሚያደርሱበትን ተቋም አስቀድመው በግልጽ ይገነዘባሉ! እንደ ሰላም ሚኒስቴር የፋይናንስ ደህንነት መረጃ ማዕከል ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ብሔራዊ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ ኤጀንሲ የኢሚግሬሽን ዜግነት እና ወሣኝ ኩነት ኤጀንሲ የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ስትራቴጂያዊ ጥናት ኢንስቲትዩት ሁሉ በዋነኝነት ሰለባዎች መሆናችው እጅጉን ጥንቃቄ ይሻሉ፡፡

ከወራት በፊት ኢቢሲ በዘገባው እንዳስደመጠን ኢትዮጵያን ጨምሮ በ150 አገራት የተከሰተውና “ዲክሪፕት ዎነክራይ” በመባል የሚታወቀው የሳይበር ጥቃት ኢላማ አድርጓቸዋል የተባለው የቴሌ ኮሚዩኒኬሽን መሠረተ ልማት የገንዘብና ፋይናንስ የኤሌክትሪክና ኢንዱስትሪ መቆጣጠሪያ ሥርዓትና ሆስፒታሎች ዋነኞቹ እንደሆኑ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ማሳሰቡ ይታወሳል።

የሳይበር ጦርነቶች የራሳቸው ዓላማና ግብ አላቸው! በተለይ ጂኦፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊ አንድምታዎችን እቅድ አድርጎ የሚነሳ ዉጊያ ነው፡፡ በኛ ሀገር እንኳን ብንመለከት ፖለቲካዊ የሳይበር ጥቃት ሙከራዎች ለማድረስ ከግብጽ በኩል መሰንዘሩን ሰምተናል፡፡ እንዲህ ያሉ የጂኦ ፖለቲካዊ ጦርነቶች ብዙውን ጊዜ ዝም ተብለው የሚታለፉ ሳይሆን ከፍተኛ ምርመራ መደረግ የሚገባቸው ናቸው፤ ጂኦፖለቲካዊ ጥቃቶች የሚመረመሩበት ምክንያቶች ለብዙ የሳይበር ጥቃቶች ምላሽ ስለሚሰጡ ነው። የጸረ ሳይበር አጥኚዎች ማንኛዉንም የደኅንነት ጥቃቶች ከጂኦፖለቲክስ ጋር አጋብተው የሚተነትኑት ምክንያት ለዚሁ በመሆኑ ነው።

ረቂቅ የዘመኑ ረቂቅ የዘመኑ ጦርነትጦርነት!!ዳግም ግዛቸው

ከወራት በፊት ኢቢሲ በዘገባው እንዳስደመጠን ኢትዮጵያን

ጨምሮ በ150 አገራት

የተከሰተውና “ዲክሪፕት ዎነክራይ” በመባል የሚታወቀው

የሳይበር ጥቃት ኢላማ አድርጓቸዋል የተባለው የቴሌ

ኮሚዩኒኬሽን መሠረተ ልማት

የገንዘብና ፋይናንስ የኤሌክትሪክና ኢንዱስትሪ መቆጣጠሪያ

ሥርዓትና ሆስፒታሎች ዋነኞቹ

እንደሆኑ የኢንፎርሜሽን መረብ

ደህንነት ኤጀንሲ ማሳሰቡ

ይታወሳል።

Page 14: ቅፅ 2 ቁጥር 110 ቅዳሜ ህዳር 19 ቀን 2013 ዓ.ም

1313ግዮን ቁጥር 110 ህዳር 2013 ዓ.ም

“በየሄደበት ሁሉ በሁለቱም እጆቹ ላይ ሁለት ሰዓቶችን ያጠልቃል ፤ አንደኛው የሀገሩን የአርጀንቲናን የሰዓት አቆጣጠር ይከተላል፤ ሁለተኛው ሰዓት ደግሞ የሚሄድበትን ሀገር ሰዓት ይቆጥራል፡፡ አሁን ግን የአርጀንቲናውም የአለሙም ሰዓት ቆሟል። ዲያጎ አርማንዶ ማራዶና፣ የእግር ኳሱ ንጉስ ከዚህች አለም በሞት ተለይቷልና። የጊዜ መቁጠሪያው የ24 ሰዓት ርዝመት፣ የሰዓቱ የ60 ሰከንድ መዘውር ማራዶናን በ60 አመቱ በቃህ ብሎት ቆጠራውን አቁሟል። በእግሩም በእጁም እግር ኳስን እንደፈለገው ያሾረው ባለ ዘውድ ንጉስ ትዝታውን ብቻ ትቶልን አልፏል! የማራዶና ድንቅ ዘመን ኢትዮጵያዊያን አድናቂዎቹም በግጥም ያሞግሱት ነበር።

ወንዲፍራው ተሰማ

ማኅበራዊ ሚዲያ

“አሁን የደርግ ሠራዊት ጨፍጫፊ ፣ ደፋሪ፣ ዘራፊ እየተባላችሁ በክፋትና በእብደታዊ ድንቁርና የታጨቀ የተሳሳተ ትርክት ሲነገራችሁ ያደጋችሁ የዚህ ትውልድ ጓደኞቼ እውነቱን አሁን በአይናችሁ አያችሁት አይደል? እንዳለመታደል ሆኖ ሀገር በገንዘብ ተለውጣ ማፊያዎቹ ቀን ወጥቶላቸው በሆዳም ሹመኞች እየተመሩ ቅድስቲቷን ሀገር አረከሷት። የደርግ የተባለው ያ ድንቅ የኢትዮጵያ ሠራዊት ያኔም የተዋጋው ይህን ማፊያ ቡድን ነበር ዛሬም መከላከያ ሠራዊታችን እየተዋጋ ያለው እነዚህኑ ማፊያዎች ነው እንኳን ከታሪክ ትርክት ተላቆ ትውልዱ እውነቱን በአይኑ አየ። ሀገር መገነጣጠል፣ በዘር ማፋጀት፣ እልፍ ዜጎችን ለስደት መዳረግ ከነአካቴውም ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር እንዳትኖር ነበር የዛሬ 45 አመት ጫካ የገባው ይኸው ዛሬ ድረስ ይህን አላማውን ለማስፈፀም የሀገር ሀብት ያወድማል ህዝብ እንዳይስማማ ለጦርነት ይማግዳል።”

ወዲ ሻምበል ዘብሔረ ኢትዮጵያ

“ከአማራ ልዩ ሀይል ና ሚሊሺያ የተማርኩት አስገራሚ ነገር፣ የህወሓት ገዳይ ቡድን ሳምረ በሚል መጠሪያ ተደራጅቶ በእነ ኮሎኔል የማነ ገ/ሚካኤል ንፁሃን አማራዎች በማይካድራ በሳንጃ ና በገጀራ ሲጨፈጨፉ ፤ አስከሬናቸው በጫካ እየተገኘ አሰቃቂ ነገር እየተመለከቱ እነዚህ የአማራ ልዩ ሀይሎች ግን እጅግ በረቀቀ ወታደራዊ ድሲፕሊን ጠላትን ብቻ ነጥለው በመምታት ፤ የማረኩትን የህወሓት ልዩ ሀይል ምግብና ውሀ ከራሳቸው አንስተው እየሰጡ ይኸው መቀሌን እስከ መክበብ ደርሶዋል ፤ በእውነት ይኸ ልዩ ክብር የሚሰጣቸው ጉዳይ ነው፤ በጣም ገርሞኛል።”

ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና፣ በኢሳት ዕለታዊ

“ሳምሪ የሚባል ቡድን የለም ሕወሃት እንጂ፣ ወልቃይቴ የሚባል ብሔርም የለም አማራ እንጂ፡፡ ግልጽ በሆነ ቋንቋ ሕወሃት ምንም ያልታጠቁ 600 የአማራ ህዝብን ጨፍጭፈዋል። ይህም የዘር ማጥፋት ወንጀል ነው። በሰሜን እዝም እንዲሁ በሺህ የሚቆሩ ብሔራቸው አማራዎች ናቸው ብሎ ያሰባቸውን ወታደሮች በሙሉ በስራና በግብዣ በማዘናጋት ከሀሉም በተለየ መንገድ ገድለዋል አቃጥለዋል በእሬሳቸው ላይ ጨፍረዋል። እኛም ተገቢው እርምጃ እንዲወሰድና ትውልድ ይህን እንዲያውቅ መዝግበን ይዘናል። በተረፈ ወልቃይቴ ተገደለ ሳምሪዎች ይህን አደረጉ የምትሉ ሰዎችና ተቋማት ከዚህ የማለባበስና የመደምሰስ ድርጊታችሁ የማትቆጠቡ ከሆነ ከተባባሪነት ተለይታችሁ አትታዩም። ወንጀለኛም ተጎጂም በማንነቱ ይጠራ ዘንድ ህግ ያዛል። የምንገነባት ሀገር ከይሉኝታ ከሴራና ከአድልዎ ነጻ እንድትሆን መሰል መንሸራተቶች እርምት ሊወሰድባቸው ይገባል።”

የኑስ መሐመድ፣ ጋዜጠኛ

“ተተኪ እንዳለው ባወቀ፣ ሞት እንዲህ ባልተጨነቀ። ነው ያሉት ያ የሕወሀት ሴጣኖች ፈጣሪና ፈልፋይ መለስ ዜናዊ የሞተ ጊዜ አርቲስቶች ተብዬዎቹ። ተተኪ አለው ያሉት ሰው ተተኪዎቹ እዩዋቸው ምን እየሰሩ ነው ያሉት። ተተኪ ማለት ጨፍጫፊ ማለት ነው።ለማንኛውም መለስ ዜናዊ እንኳን ለአገር ለራሷ ለሕወሀት የሚሆን ሰው ሳያፈራ እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል መርህ ሲመራ የነበረ ሰው ለመሆኑ አሁን የሕወሀት ጁንታ የፈፀማቸውን ጭፍጨፋ በማየት ማረጋገጥ ይቻላል። መለስ ዜናዊ ነፍስህን አይማረው!!”

ክንፈሚከኤል (አበበ ቀስቶ)

“፩) የጥቁርና ነጭ ሰው ደም ቀይ ነው!! አባቶቻችን የነጭ የበላይነትን ተቃውመው የላቀ መስዋዕትነትን የከፈሉት ሰው ሁሉ ዕኩል ነው በሚለው ሃቅ ነው። በዚህ ዕሳቤ ለነጮች የሚደነብር ዋጃግንት ትናንት አባቶቻቸው ለጣሊያን ፋሽስት እንቁላል ሲቀቅሉ የነበሩ የባንዳ የልጅ ልጆች ናቸው። በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ የሚገባ ወይም እገባለሁ የሚል ሁሉ ወደ ወጪ ብለን አዝዘናል!! በላይ ይሙት!! ፪) የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) ዳይሬክተር የሆኑት የጁንታው ቡድን ወኪል ‘ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም በዓለም አቀፍ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት (ICC) ክስ ሊመሰረትባቸው ነው’ የሚለው ከበሮ ድለቃ የነጭ አምላኪነት ውርስ ነው። ዶ/ር ቴዲ በልደታ ፍ/ቤት ተዳኝተው ቀሪ እድሜያቸውን ቂሊንጦ፣ ቃሊቲ፣ ሽዋ ሮቢት (ሽዋ ፈረስ ቤትም ኢመቸኛል!!) ወይም ዝዋይ ሊያሳልፉ ይገባል። ይኸው ነው!!”

ጌትነት አልማው ጥሩነህ፣ ጦማሪ

“ጨካኞች አሳፋሪ ታሪክ በሰሩባት ሀገራቸው እና መደበቂያ ምሽግ ባደረጓት ትግራይ ባንዲራዎች መካከል በተጣበበች ሽንቁር ቢሯቸው፣ በደከመ አንደበታቸው፣ በሰለቸና በጥቂት በሳምንታት ውስጥ በተጎሳቆለ ፊታቸው፣ በተቆራረጠ ድምፃቸው፣ በከፍተኛ ስጋትና ፍርሃት ውስጥ መገኘታቸውን በገህድ በሚያሳብቅ ቁመናቸው የሚሰጡት መግለጫ ተቋርጧል:: አዲሱ ከመሸ የመጣው ቃል አቀባይም የተለመደ ውሸታቸውን አጣጥሞ ሳይናገር መሽቶበት በተቆራረጠ ስልክ ለማውራት ተገዷል:: አሁን ሁሉም ነገር እያለቀ ነው:: የቀረችው መቀሌ ናት:: ዙሪያዋን የተቆፈረባት ምሽግ እና የተጠመደባት ፈንጅ ከእይታችን ውጭ አይደለም:: አሸባሪው ቡድን ከሞት የተረፉ ዕድሜና ማጭበርበር ጠገብ አዛውንቶችን ማምሻም ዕድሜ ነው ብሎ ለማስጠበቅ መፍጨርጨሩ እንደማይቀር ገሀድ ዕውነታ ነው:: የዚህን ቡድን በደም የተጨማለቀ ወንጀለኝነት ካስተዋልን የመቀሌን ህዝብም ለእልቂት ዳርጎ መትረፍ ወይም መጥፋት አያስብም አይባልም:: እንደ ፍልፈል በማሳቸው የቀበሮ ጉድጓዶች ውስጥ ተወትፎ ወይም ራሱን ቀይሮ እና አታሎ ለመሰዎር ሲሞክር መያዙ አይቀርም:: ሁላችንም እርግጠኞች የምንሆነው ግን ፊት ለፊት ተዋግቶ ለመሞት እንደማይወስን ነው:: ምክንያቱም ገዳይ አስገዳይ ዘራፊ እና ስግብግብ ሌባ እንጅ ጀግና አይደለምና:: ኢትዮጵያ በጀግኖቿ ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!”

ተመስገን ጥሩነህ፣ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት ዋና ዳይሬክተር

“በህወሓት_መቃብር_ላይ! ህወሓትን አርቆ ለመቅበር የሚታየው ሀገራዊ አንድነት እና የትብብር ግለት (Momentum) ሳይበርድ ህወሓት የዘራችውን እሾህ አንድ በአንድ ነቅሎ ለመጣል ከዚህ የተሻለ ጊዜ አናገኝም:: 1) ሕገመንግሥታዊ ማሻሻያ በማድረግ የዜጎችን የሀገር ባለቤትነት ማረጋገጥ! 2) ብሔራዊ አንድነታችንን መልሶ መገንባት! 3) የግጭት መንስኤዎች ለሆኑ የአስተዳደር ወሰኖች ጥያቄዎች ዘላቂ እና አካታች መፍትሔ ማበጀት! 4) ሀገራችንን ለ40 ዓመታት ያመሰቃቀለውን የዘውግ ፖለቲካ በህግ ማገድ! 5) ከቡድኖች ይልቅ ዜጎችን በሙሉ የሚያሳትፍ የጋራ ሀገራዊ ርዕይን መቅረጽ!”

አርክቴክት ዮሐንስ መኮንን

መጠቃቱን አትይ ጀርመን በአርጀንቲናይሸነፉ ነበር ባይኖር ማራዶናየማራዶና አባት በጣም አጭር ናቸውዋንጫ ለመቀበል ቁመት አነሳቸውማራዶና መጦ እሽኮኮ አረጋቸው”

Page 15: ቅፅ 2 ቁጥር 110 ቅዳሜ ህዳር 19 ቀን 2013 ዓ.ም

1414ግዮን ቁጥር 110 ህዳር 2013 ዓ.ም

ባለፈው ማክሰኞ ማኅበራችሁ ያዘጋጀው ፕሮግራም ምን ነበር?

ወ/ሮ እንግዳዬ፡- ማክሰኞ ያቀረብነው ፕሮግራም ከዚህ በፊት ተጀምሮ ተንጠልጥሎ የቆየ፣ አሁን በኢንሼቲቭ አፍሪካ ጨርሰን የፕሮጀክቱን ዓላማ ለሕዝብ ይፋ ለማድረግ ነው፡፡ ፕሮጀክቱን ውጤታማ ኾነው የጨረሱትንና ጥሩ ውጤት ያመጡትን በቀጣይ የገበያ ክህሎት እንዲያገኙ እውቅና ለመስጠትና የፕሮጀክቱን ፍፃሜ ለማብሰር የታሰበ ነው፡፡ ፕሮግራሙን አስታኮ ማህበሩ ትልልቅ ሥራ ለሰሩ ሴቶች እውቅና ለመስጠት ችሏል፡፡

ፕሮጀክቱ ምን ነበር?

ወ/ሮ እንግዳዬ፡- የSIO የሚል ነጋዴ ሴቶችን ማበልፀግ ወይም ማሳደግ የሚል ነው፡፡ የፕሮጀክቱ ዓመት ተኩል ዕድሜ የተከበረበት ነው፡፡ ፕሮግራሙ የፕሮጀክቱ ማበልፀጊያና ማጠናከሪያ ነው፡፡ ፕሮጀክቱ ያለቀና የተተገበረ ነው፡፡ አሁን ኢንሼቲቭ አፍሪካ እስካሁን ባልተለመደ ሁኔታ እታች ድረስ ያሉትን ተደራሽ በማድረግ እየሰራን ነው፡፡

ፕሮጀክቱ ውጤታማ ነበር?

ወ/ሮ እንግዳዬ፡- ውጤታማ ነበር፡፡ ለምሳሌ ሴት ነጋዴዎች ያመረቱትን ምርት በከፍተኛ ደረጃ ወደ ገበያ ማስገባት እንዲችሉ አድርጓል፡፡ ከትንሽ ንግድ ወደ ትልቅ ንግድ እንዲያድጉ የሚያጠናክር ፕሮጀክት ነበር፡፡

ከጀመራችሁ ጀምሮ በፕሮጀክቱ ውጤታማ

ወ/ሮ እንግዳዬ እሸቱ

የሆኑ ሰዎችን መጥቀስ ይቻላል?

ወ/ሮ እንግዳዬ፡- አዎ፣ የፕሮግራሙ ቀን የሸለምናቸው አሉ፡፡ ለምሳሌ የምርት አገልግሎቶቻቸውን በእኛ ምክንያት ሌላ ገበያ ውስጥ ማስገባት የቻሉ ወ/ሮ ሳራ ዱጎ፣ ወ/ር አስካለ አረጋ፣ ወ/ሮ ወይንሸት ተስፋዬ በቆዳ ሥራዎች ላይ እንዲሁም ወ/ሮ ማኅደር አድማሱን የመሳሰሉ ሌሎች ሴቶችም ውጤታማ ከተባሉት መካከል ይገኛሉ፡፡ ከተለያዩ ክልሎች ምርታቸውን ያመጡ አሉ፡፡ ማር ከትግራይ አምጥተው ወደውጭ መላክ የጀመሩ አሉ፡፡

የሀገር ውስጥ ገበያንና የውጭ ገበያውን የተቀላቀሉ ብዙ ናቸው?

ወ/ሮ እንግዳዬ፡- ነጋዴዎቹ ወደ ውጭ ሀገራት ምርታቸውን መላክ ብቻ ሳይሆን የሀገር ውስጥ ገበያውንም በደንብ ገብተው ምርታቸውን በደንብ ማሰራጨት የቻሉ ናቸው፡፡ ፕሮጀክቱ ምክር አዘል ጭምር ስለነበር ውጤታማ ነበር፡፡ ያጎደላቸውን እያየን በጥራትም ሆነ በአሠራር ግድፈታቸውን እንዲያስተካክሉ እናግዛቸዋለን፡፡ ነጋዴዎቹ ካሟሏቸው መስፈርቶች አንፃር ደረጃ አላቸው፡፡ ለምሳሌ አልባሳትን በተመለከተ አንድ ከዱከም የመጣች ነጋዴ የኦሮሞን ባህል ከዘመናዊ ዲዛይን ጋር አቀናጅታ ታቀርብ ነበር፡፡ ከደቡብ የመጣች የአካባቢውን ባህል የሚያንፀባርቅ ምርት ይዛ ትመጣ ነበር፡፡ ከጉራጌ አካባቢም የተለያዩ ምርቶችን የምታመጣ አለች፡፡ እነኚህን የመሳሰሉ ነጋዴዎችን ነው መርጠን የሸለምነው፡፡

በፕሮግራማችሁ ላይ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ተገኝተው ዕውቅና ሰጥተዋችሁ ነበር፡፡ ከእነሱ መካከል ድጋፍ ያደረጉላችሁ አሉ? ከመንግሥት የምትፈልጉትን እያገኛችሁ ነው?

ወ/ር እንግዳዬ፡- አዎ ከመንግሥት እስካሁንም ድጋፍ እያገኘን ነው፡፡ ከቴክኒክ ጀምሮ በተለያዩ መንገዶች ድጋፍ እናገኛለን፡፡ ለምሳሌ ሴቶች እንዴት ሊደገፉ ይችላሉ በሚል መንግሥት ካለው ልምድ አኳያ ከፋይናንስ ጀምሮ በገንዘብ ሚኒስቴር ገቢም እናገኛለን፡፡ ሥራችን ውጤታማ እንዲሆን የተለያዩ ድጋፎችን ያደርጉልናል፡፡ ዋናው ዓላማችን ሴቶች ገበያቸውን አስፋፍተው መሥራት እንዲችሉ ማድረግ ነው፡፡ ለማደግ ሰራተኛ መቅጠር ይጠበቅባቸዋል፡፡ በዚህን ጊዜ የሠራተኞቹን መብት እንዲከበርላቸው የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር፣ የአሰሪዎች ፌዴሬሽንና የአሰሪዎች ኮንፌደሬሽን ተቀናጅተን አብረን በመሆን ትልቅ ሥራ መሥራት እንዳለብን ተናግረዋል፡፡

የሴቶች ጉዳይ ሚኒስቴርም ድጋፍ እናደርጋለን ብለዋል፡፡ ሥራው የዱላ ቅብብሎሽ ስለሆነ የብዙዎችን ድጋፍና መተጋገዝ የሚፈልግ ነው፡፡ የመንገድ ትራንስፖርት ሚኒስትሯም በእለቱ መልዕክታቸውን ልከዋል፡፡ የትራንስፖርት ሴክተሩን ባዘመነ መልኩ አገልግሎት እየሰጡ ላሉ ግለሰቦች ዕውቅና ከሰጣችሁ እኛም የቴክኒክ ድጋፍ በማድረግ ከጎናችሁ ሆነን አለም የደረሰበት እንደርሳለን

“ዋናው ዓላማችን ሴቶች ገበያቸውን አስፋፍተው መሥራት እንዲችሉ ማድረግ ነው”

ማህበራዊ ጉዳይ

1414ግዮን ቁጥር 110 ህዳር 2013 ዓ.ም

ማህበራዊ ጉዳይ

ወ/ሮ እንግዳዬ እሸቱ የኢትዮጵያ ነገዴ ሴቶች ማኅበር ፕሬዝዳንት ናቸው፡፡ ስለማኅበሩ አመሠራረት፣ ስላለፈባቸው ሂደቶች፣ ስላስመዘገባቸው ውጤቶችና ከሌሎች ማኅበራት ጋር ስላለው የሥራ ግንኙነት የሚከተለውን ቆይታ አድርገዋል፡፡

Page 16: ቅፅ 2 ቁጥር 110 ቅዳሜ ህዳር 19 ቀን 2013 ዓ.ም

1515ግዮን ቁጥር 110 ህዳር 2013 ዓ.ም

ተጨማሪ ጥያቄዎች አለዎት?ተጨማሪ ጥያቄዎች አለዎት?በድህረ ገፃችን በድህረ ገፃችን www.initiativeafrica.netwww.initiativeafrica.net በኩል በምንገልጸው ዕለታት በአንዱ በሚሰናዳው የመረጃ መቀያየሪያ ክፍለ ጊዜ ላይ ይታደሙ ወይም በኩል በምንገልጸው ዕለታት በአንዱ በሚሰናዳው የመረጃ መቀያየሪያ ክፍለ ጊዜ ላይ ይታደሙ ወይም

በ 011 662 26 40 41 ይደውሉ፡፡በ 011 662 26 40 41 ይደውሉ፡፡

የሚል መልዕክት ነው ያስተላለፉልን፡፡ ይህ ድጋፋቸው ለወደፊቱ ብቻ ሳይሆን አሁን እያደረጉት ያሉትም ነው፡፡ ከቀረጥ ነፃ በማስገባትና በሌላም የመንግስት አካላት ብዙ ድጋፍ ያደርጉልናል፡፡ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ደግሞ ከባህል አኳያ ከአልባሳት ጀምሮ ቱባ የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ባህሎቻችን መሸጥ ይቻላል በሚል መርህ ሲረዱን ቆይተዋል፡፡ ባህላችን ገቢ ማስገኛ እንዲሆን በተቻላቸው ድጋፉቸውን እንደሚቀጥሉ አሳውቀውናል፡፡ በአጠቃላይ በእለቱ የተገኙት የ5ቱ ሚኒስትሮቻችን መልዕክት በተመሳሳይ ድጋፋቸው እንዲቀጥል ያሳዩበት ነው፡፡ ከመንግስት ባለሥልጣናት በተጨማሪ የኢንሺቲቭ አፍሪካ ዳይሬክተሩ ውጤታማ የሆነ ንግግር አድርገዋል፡፡

ፕሮግራሙ ውጤታማ በመሆኑ ምን ተሰማዎት? ለቀጣይ ሥራስ ምን ፈጠረቦ?

ወ/ሮ እንግዳዬ፡- ከፍተኛ የሆነ ደስታ ነው የፈጠረብኝ፡፡ የዛሬ 3 ወር ገደማ ተስፋ ቆርጠን የነበረ ቢሆንም፣ ኢንሼቲቭ አፍሪካ አይዟችሁ እረዳችኋለሁ ብሎ የቀረንን ብር እንድንቀበልና ሠራተኞቻችን ትንሽ ነገር አግኝተው መንቀሳቀስ እንዲችሉ አድርጎልናል፡፡ እኛ የአፍሪካ መዲና እንደመሆናችን የሸቀጥ ማራገፊያ እንዳንሆን ተነጋግረን በወሰነው መሠረት ነው የሰራነው፡፡ ኢትዮጵያውያን የሥራ ባህላችንን መቀየር አለብን፡፡ ይህን ማድረግ ያለብን ደግሞ ከራሳችን በመጀመር ነው፡፡ ራሳችን የሥራ ባህላችንን ለመቀየር በከፍተኛ ደረጃ ራሳችንን መስዋዕት በማድረግ ትንሽ ያለችውን ማብዛት መቻል አለብን፡፡ የንግድ አሠራራችን ተቀባባይ ተከታታይ መሆን አለበት፡፡

የኢትዮጵያ ነገዴ ሴቶች ማኅበር ከተመሠረተ ምን ያህል ጊዜ ሆነው? በሀገር ውስጥና በውጭ ምን ያህል አባላቶች አሉት?

ወ/ሮ እንግዳዬ፡- በሀገራችን ውስጥ 14 ትልልቅ ማኅበራት አሉ፡፡ አካል ጉዳተኞችን ውጭ ላኪዎችን ጨምሮ ብዙ አሉ፡፡ በክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች ጨምሮ 14 ማህበራት አሉ፡፡ 260 የሚሆኑ ቅርንጫፎች በሀገር አቀፍ ደረጃ አሉ፡፡ 285 ሺህ የሚሆኑ ነጋዴ ቤት የማህበሩ አባላት አሉ፡፡ ማኅበሩ የኢጋድ አባል ሀገራትን በመሰብሰብ የ8ቱ ሀገራት ተጠሪዎች ግንኙነት መሥርተናል፡፡ ጽሕፈት ቤቱ ያለው አዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ጋር ነው፡፡ አፍሪካ ካልቸር የሚል ሌላ ማኅበርም ተቋቁሞ ከ40 በላይ የአፍሪካ ሀገራት ያሉበት ተቋም በምክትልነት እያገለገልኩ እገኛለሁ፡፡ በአፍሪካ ሕብረት እኔ ተወክዬ የዓለም አቀፉ አባል እንድሆን ተደርጓል፡፡

በፕሮግራሙ ላይ ለኢንሼቲቭ አፍሪካው ክቡር ገና ሽልማት አቅርባችኋል፡፡ በቀጣይነት ከእነሱ ጋር የምትሰሩት ፕሮግራም አላችሁ?

ወ/ሮ እንግዳዬ፡- አዎ ለ10 የእኛ ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤቶች ራሳቸውን እንዲያጠናክሩ ፕሮጀክት ተቀርጿል፡፡ በሰው ኃይልና በገቢም እንዲጎለብቱና ራሳቸውን ማስተዳደር እንዲችሉ ለ10ሩ ማህበራት ድጋፍ አድርገዋል፡፡ ሽልማቱን ለኢንሼቲቭ አፍሪካ የሰጠንበት ምክንያት በኢትዮጵያ አቆጣጠር ከ1995 ጀምሮ ነጋዴ ሴቶች ማኅበርን ከመመሥረቱም በፊት የሐረርና ድሬደዋ ነጋዴ ሴቶች ማህበርን በመደገፍ ከአውሮፓ ሕብረት የገንዘብ ድጋፍ በመጠየቅ በሁለቱ ከተሞች ላይ ቢሮ ከፍተው እቃ ገዝተው አዳራጅተው አቋቁመውልናል፡፡ ተቋሙም ሆነ እሳቸው የረጅም ጊዜ የማህበራችን ደጋፊ ናቸው፡፡ አብረውን ብዙ ሠርተዋል፡፡ ሽልማቱ ለግላቸው ቢሆንም ደስ ይለን ነበር፡፡ ወደፊት ብዙ ብናስብም ምሥጋናችን ከብዙ ሚሊዮን ብር በላይ የሚሆን ሽልማት ነው፡፡ በሰሩልን ሥራ በጣም ደስተኞች ነን፡፡ በጣም ነው የምንኮራባቸው፡፡ እታች ያለችውን አንዲት ነጋዴ የማየት አቅም አላቸው፡፡ የገዘፉ ችግሮች ያሉት እታች ስለሆነ ይህን ማየታቸው ያስመሰግናቸዋል፡፡ ዞሮ ዞሮ እሳቸው የመሠረቱት ድርጅት ስለሆነ አቶ ክቡር ገና ብለን ከምንሸልም ተቋሙን መሸለሙ ተገቢ ነው ብለን ነው፡፡

ማህበራችሁ በቀጣይነት ሊሠራ ካሰበው አንፃር ማስተላለፍ የሚፈልጉት ካለ?

ወ/ሮ እንግዳዬ፡- ሩጫው ማራቶን ስለሚሆን መተጋገዝ ይጠይቃል፡፡ የብዙዎችን ድጋፍ የሚፈልግ ሥራ ላይ ነው የተገኘነው፡፡ ሁሌ ተሳክቶልናል ሁሉንም አስደስተናል ማለት ባንችልም የተሻለ ለመሥራት እንድንችል የሠራነውን ከግምት በማስገባት እገዛ እንዲደረግልን እንፈልጋለን፡፡ ችግራችንን እየነገሩን በጎውን እየነገሩን አብረውን የሚሠሩ እንዲበዙልን እንፈልጋለን፡፡ በአጋርነት አብረን ሠርተን ሀገራችንን ከኢኮኖሚ ድቀትና ተመጽዋችነት ልንታደጋት ይገባል፡፡ ይህ ለሴቶች ብቻ ሳይሆን እያንዳንዱ ዜጋ ባለቤት ሆኖ በጋራ መሥራት ይገባናል ስል መልዕክት ማስተላለፍ እፈልጋለሁ፣ አመሠግናለሁ፡

ማህበራዊ ጉዳይ

1515ግዮን ቁጥር 110 ህዳር 2013 ዓ.ም

ማህበራዊ ጉዳይ

ኢንሼቲቭ አፍሪካ የግሉን ንግድና ዘርፍ ማኅበራትና ምክር ቤቶችን ለማጠናከር

የሚያስችል የፕሮጀክት ስምምነት አካሄደ

ከሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች አንዱ የሆነው ኢንሼቲቭ አፍሪካ #አዳጊ የኢኮኖሚ ተዋንያንን አቅም ማጎልበት$ በሚል መጠሪያ ባወጣው #ኢኖቬቲቭ ግራንት ፈንድ$ የፕሮጀክት ማስታወቂያ

ጥሪ ተወዳድረው ለተመረጡ 29 የንግድና ዘርፍ ማኅበራትና ምክር ቤቶች ጋር የፕሮጀክት ስምምነት ፊርማ ሥነ-ሥርዓት አካሄደ፡፡

ይህ ፕሮግራም የተካሄድው ሕዳር 9 ቀን 2013 ዓ.ም በሀርመኒ ሆቴል ሲሆን ለዚህ ፕሮጀክት በጠቅላላ ከተያዘው 30 ሚሊዮን ብር ውስጥ እንደሆነ ታውቋል፡፡

በፕሮግራሙ መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢንሼቲቭ አፍሪካ ጊዚያዊ ሥራ አስኪያጅ አቶ የኋላሸት ገ/ሚካኤል ሲሆኑ እሳቸውም በቅድሚያ ድርጅቱ የዛሬ 18 ዓመት የተቋቋመ መሆኑን ገልጸው ከፕሮግራሞቹ መካከል በትምህርትና ወጣቶች ልማት፣ በጾታ እኩልነት፣ በዴሞክራሲና በሰብአዊ መብት እንዲሁም የግሉን ንግድና ዘርፍ ማህበራትና ምክር ቤቶችን መጠናከር ላይ ማተኮሩ ናቸው ብለዋል፡፡

አቶ የኋላሸት በማያያዝም የዛሬው ፕሮግራም ዋነኛው #የግሉ ዘርፍ ከታች ወደ ላይ በሚደረግ የፖሊሲ ለውጥ ተሳታፊ እንዲሆኑ ማብቃት$ የተሰኘው ፕሮጀክት አንዱ አካል የሆነው ኢኖቬቲቭ ግራንት ፈንድ እንደሆነ ተናግረው በዚህ ፕሮግራም በሀገሪቱ የሚገኙ የንግድና ዘርፍ ማህበራት እና ምክር ቤቶች በተለይም በሴቶችና ወጣቶች ላይ ያተኮሩ የቢዝነስ ማህበራት እንዲወዳደሩ በወጣው የማመልከቻ ጥሪ ማስታወቂያ 57 ተወዳዳሪዎች መቅረባቸውንና ከነዚህም መካከል መስፈርቱን ያሟሉት እነኚሁ ከላይ የተጠቀሱት ማህበራትና ምክር ቤቶች ተመርጠው ወደ ሥራ ለመግባት የሚያስችላቸውን የፕሮጀክት ስምምነት ፊርማ ለማካሄድ መብቃታቸውን ጠቅሰዋል፡፡

እነኚሁ ማህበራትና ምክር ቤቶች የተመረጡበትን መስፈርትም ጊዚያዊ ሥራ አስኪያጁ ሲገልጹ ከመንግሥት ሕጋዊ እውቅና ያላቸው በመሆኑ፣ በአመራር ቁርጠኝነት፣ የሚመሩበት የተለያዩ መመሪያዎች መኖርና የፕሮግራም ማኔጅመንታቸው የተሻለ ሆነው በመገኘታቸው እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡

በመጨረሻም አቶ የኋላሸት ሲናገሩ በዚህ ፕሮጀክት አሸናፊ የሆኑት የግሉ ዘርፍ ማህበራትና ምክር ቤቶች ፕሮጀክቱ ወደ ሥራ ከገባ በኋላ በስምምነቱ መሠረት ፕሮግራሞቹ ከፋይናንስ ጋር በተጣጣመ መልኩ በግልጽና በማያሻማ ሁኔታ መተግበር ይኖርበታል፡፡ በየሦስት ወሩም የግምገማና ክትትል ተግባራት እንደሚከናወን አበክረው አስገንዝበዋል፡፡

ከፕሮጀክቱ ተጠቃሚ ከሆኑት መካከል አንዳንዶቹን አነጋግረን ነበር፡፡ በቅድሚያ ያነጋገርናቸው የቢሾፍቱ ከተማ ነጋዴ ሴቶች ማኅበር ምክትል ሊቀመንበር የሆኑትን ወ/ሮ ትእግስት በጄጋን ሲሆን እሳቸውም #በእስካሁኑ ከተለያዩ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጋር የፕሮጀክት ስምምነት የሚካሄደውና ድጋፍ የሚሰጠው በብሔራዊ ደረጃ ለተቋቋሙት ማህበራት ነበር፡፡ ኢንሼቲቭ አፍሪካ ዝቅ ብሎ በከተማ ወይም በዞን ደረጃ ለሚገኙ ማህበራት ተደራሽ መሆኑ አስደስቶናል፡፡ በየሶስት ወሩ የክትትልና ግምገማ ፕሮግራም መኖሩ ደግሞ ለማህበራችን ጥንካሬ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያለው የፕሮጀክት ስምምነት ነው$ ብለዋል፡፡

በመቀጠል ያነጋገርናቸው የአዳማ ከተማ እና የኦሮሚያ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤቶች የስራ አመራር ቦርድ ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑትን አቶ መገርሳ ረጋሳን ነው፡፡ እሳቸውም #ብዙውን ጊዜ ነጋዴው ንግዱን የሚያካሂደው በልምድ ነው፡፡ ከኢንሼቲቭ አፍሪካ ጋር በመተባበር ለመሥራት የተስማማነው ግን ነጋዴውን ወደ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እንዲገባ በሚያስችል የአቅም ግንባታ ላይ ያተኮረ ሲሆን በዚህ በምናገኘው ሥልጠና የገንዘብ አጠቃቀማችንን፣ የንግድ አሰራራችንን በማሻሻል ለበለጠ ውጤት እንድንበቃ ያስችለናል$ ብለዋል፡፡

Page 17: ቅፅ 2 ቁጥር 110 ቅዳሜ ህዳር 19 ቀን 2013 ዓ.ም

1616ግዮን ቁጥር 110 ህዳር 2013 ዓ.ም

ዓለም አቀፍ አንደበት“ብዙ ሰዎች በእዚህ ሊግ ደረጃ መጫወቴን

አስመልክተው ሁሌም አይመጥነውም ይሉኛል፤ እንደዚህ ያሉ ነገሮችን ስታደምጥ ደግሞ በፕሮፌሽናል ተጨዋችነት ደረጃ ወደ ውጪ ሀገር ወጥተህ መጫወትን ታልማለህና እኔም ይሄን

እድል ለማግኘት ያልጣርኩበት ጊዜ የለም፤ ያም ሆኖ ግን ብዘ ግዙ እንደዚህ ያሉ እድሎችን የማገኝባቸው

አጋጣሚዎ ለምጫወትበት የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ፊርማዬን ካኖርኩ በኋላ እና ኮንትራትም በሚቀረኝ ጊዜ በመሆኑ የሚመጡትን የመጫወት እልሜን እስካሁን ሳላሳካ ቀርቻለሁ፤ አሁን በቅርቡ እንኳን ኮቪድ ወደ አገራችን በገባበት ሰሞን ያገኘሁት ሌላ እድልም ነበር፤ የፈለገኝ ቡድንም ከክለቤ ጋር መነጋገሩም ይታወሳል፤ ሆኖም ግን ለክበቤ የምጫወትበት ኮንትራት ስላለኝ ወደ ውጪ ሀገር ወጥቶ ሳልጫወት ቀርቻለሁ፤ ከእዚህ በኋላ ግን በፕሮፌሽናል ደረጃ ወጥቶ ለመጫወት አሁንም ሰፊ እድሉ ስላለኝ ያንን እልሜንና ምኞቴን ምሳካቴ አይቀሬ ነው”

አስቻለው ታመነ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን (ዋልያዎቹ) እግር ኳስ ተጫዋች

ሀትሪክ ስፖርተ ጋዜጣ፣ ህዳር 12 ቀን 2013 ዓ.ም

“አሁን ቋንቋው ተቀየረ፡፡የጠረጴዛው ቋንቋ ብዙ ተሞክሯል፡፡ መንግስት በአንቀልባ አዝሎ ነው እሽሩሩ ሲላቸው የነበረው እንዲየውም ዝግይቷል እዚህ መድረስ አልነበረባቸውም፡፡ በእሹሩሩና በድርድር ኢትዮጵያ ሕዝቦች እየከፈሉ ያሉትን ዋጋ በየክልሉ

እየሞተ፣እየወደቀ ያለው፣ እየታረደና ነበፍስ ወደ ገደል እየተጣለ በታም አሰቃቂ ሁኔታ ላይ ነው ያሉት፡፡ በየቀኑ

ሰው ይታረዳል፡፡ ይህን የሚያደርግ ቡድን ወንበሩንም ጠረጴዛውን አልፈልገውም ከዚህ በኋላ ቋንቋዬ ይህ ነው ብሎ ክሊክ አደረገ፡፡ ጥይት ተተኩሶ ሰው ሞቷል አካል ጎድሏል ንብረት ወድሞአል ስቃይ ተፈጥሯል፡፡ ይህ ሁሉ ድርድርና ጠረጴዛ የምትፈልግ ሽማግሌ እየተላከ ትንሽ ስብሰባ ተደርገው ወደ አንድ ቋት ውስጥ ሊገቡ ሲል ሽምግልናና ድርድር ይፈልጋሉ፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት ሊባንን ይገባል፡፡ ሰላም የሚፈልግ ሰው በትክክለኛ እጅን ለሕግ ሰጥቶ ነው፡፡”

፶ አለቃ ብርሃኑ አማረ፣ የቀድሞ ጦር ሰራዊት ማህበር ሰብሳቢሸገር ታይምስ መጽሔት፣ ሕዳር 2013 ዓ.ም

“ህፃናትን ለጦርነት መጠቀም፣መመልመል፣ማሰልጠን ወዘተ…. እነዚህ ሁሉ በአለማቀፍ የጦር ወንጀል የሚያስጠይቁ ናቸው፡፡ ከኛ ህገ መንግስት ጀምሮ በሃገር ውስጥም ህጎች አሉ፡፡ ድርጊቱ በባህሪው አለማቀፍ የጦር ወንጀል ያደርገዋል፡፤ ያ ሲሆን

ደግሞ በዚህ ሂደት ውስጥ የተሳተፉ ሰዎች ሙሉ በሙሉ የህግ ተጠያቂነት አለባቸው፡፡ እኛም በሚዲያ

እንደምየው፣ምናልባትም 14 እና 15 አመት የሚሆናቸው በርታ ህፃናት ምንም በማያውቁት ጉዳይ ትምህርታቸውን አቋርጠው ወደ ጦርነቱ እንዲገቡ ተደርገዋል፡፡ በእርግት ተጨማሪ ማጣራት ይፈልጋል፡፡ ይህ ድርጊት ግን በሃገር ውስጥም በአለማቀፍ ህግም ያስጠይቃል”

አቶ መሱኡድ ገበየሁ፣ የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች ኅብረት ዳይሬክተርና የሕግ ባለሙያ

አዲስ አድማስ ጋዜጣ፣ህዳር 12 ቀን 2013 ዓ.ም

“ቀመሩ ካሻሻላቸው የጋራ ገቢዎች የማከፋፈያ ስሌት መካከል አንዱ በፌዴራልና በክልል መንግሥት የተቋቋመ የልማት ድርጅት የትርፍ ድርሻ ክፍፍልን የሚመለከት ነው፡፡ ቀደም ብሎ በነበረው ቀመር መሰረት በጋራ ካቋቋሙት የልማት ድርጅት የሚገኝ ትርፍን የሚከፋፈሉት ባዋጡት ካፒታል መሰረት

ነበር፡፡ አሁን በተደረገው ማሻሻያ ግን በጋራ ካቋቋሙት የልማት ድርጅት የሚገኝን ትርፍ እኩል ሃምሳ በመቶ

እንደኪፋፈሉ ነው በቀመሩ የተወሰነው”

አቶ ላቀ አያሌው፣የገቢዎች ሚኒስትር ሚኒስትርሪፖርተር ጋዜጣ፣ህዳር 13 ቀን 2013 ዓ.ም

“የህወሓት የሁከት ቡድን ህግ የማስከበር ዘመቻውን በቶሎ እንዳይጠናቀቅ ብቻ ሳይሆን ወደ ቀጣናዊ ብሎም ዓለም አቀፋዊ ጦርነት ለማስፋት እና ራሱን ለማዳን የሚያደርገው ጥረት በኢትዮጵያ

መንግስተ ብቻ ሳይሆን በመላው ዓለምም የታወቀ ሆኗል፡፡ በዚህ ጥሩ ማሳይ የሚሆነው ደግሞ በሳምንቱ መጨረሻ በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ዘርፍ ኃላፊ ቲቦር ናሽ አስተያየት ነው፡፡ አምባሳደሩ ህወሓት ከባህር ዳር እና ጎንደር ባለፈ የጎረቤት ሀገር ኤርትራ መዲና የሆነችውን አስመራ በሮኬት ካጠቃ በኋላ በትዊትር

ገፃቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ The united states strongly condemns the TPLF’s unjustifiable attacks against

Eritrea on November 14 and its efforts to internationalize the conflict in Tigray” በማለት የህወሓት ስብስብ ዓለም አቀፍ ጦርነት ለመቀስቀስ የሚያደርገውን ጥረት ተችተዋል፡፡ ይህ የአምባሳደሩ አስተያየት የህወሓትን እኩይ ባህሪ ብቻ ሳይሆን መቀሌ የመሸገው ቡድን ህልውናውን በጦርነት ወደሚያረጋግጥ የሽብር ቡድን መቀየሩን የሚያስረጋግጥ ነው፡፡

ዶ/ር ምህረት ዳናቶ፣ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሸለቆ ተፋሰሶች ጥናት ተባባሪ ፕሮፌሰር

አዲስ ልሳን ጋዜጣ፣ህዳር 12 ቀን 2013 ዓ.ም

“የቦርድ አባላት እና ከፍተኛ ስራ አመራሮች የቴክኒካል እና የአመራር ክህሎት እንዲኖራቸው ግድ ነው፡፡ ይህ ማለት ግን በፖለቲካ ሹመት ወይም በፖለቲካ የተሾሙ የቦርድ አባላት እና አመራሮች የሉም ማለት አይደለም፡፡ ነገር ግን በእኔ አስተሳሰብ ይህ በፖለቲካ መሾማቸው ወይም ፖለቲካ ሹመኛ መሆናቸው በቂ ዕውቀት እና ችሎታ

እስካላቸው ድረስ ችግር የለውም፡፡ ነገር ግን የመንግስት የልማት ድርጅቶች ብቃት እና ክህሎት ያላቸውን እና ምንም

አይነት የፖለቲካ ግንኙነት የሌላቸውን ከፍተኛ አምራሮችን ሲቀጥሩ አይታዩም ወይም የመቅጠር አዝማማያያቸው ጥቂት ነው፡፡ ይህ መረጃ በሁሉም ጉዳይ ላይ ትክክል አይለም፡፤ ለምሳሌ ኢትዮጵያ አየር መንገድ በራሱ እና በሴክተሩ ላይ ከፍተኛ እውቀት ያላቸውን ሰዎች የመቅጠር ሙሉ ችሎታ አለው፡፡ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክም ሌላኛው የመንግስት የልማት ድርጅት ሲሆን፣በኢትዮጵያ ካሉ የግል ባንኮች እኩል ወይም ደግሞ በተሻለ ሁኔታ የስራ አመራሮች ያሉት ድርጅት ነው”

በየነ ገብረ መስቀል፣ የቀድሞ የመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታ እና አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር

አዲስ ማለዳ ጋዜጣ፣ህዳር 12 ቀን 2013 ዓ.ም

“ሁልጊዜ ምሁራንን ከውጭ የምናስመጣ ከሆነ ለምንድን ነወ ከፍተኛ ወጪ እያወጣን ዜጎቻችንን የምስተምረው? እዚህ

ማሰልጠን ለምን አስፈለገ? ከደርግ ጊዜ ጀምሮ እስካሁን ድረስ የአመለካከት ብድር ለማግኘት አንዴ ወደ ምሥራቅ ሌላ ጊዜ ደግሞ ወደ ምዕራብ ተንከራተናል፡፡ አሁንም እየተንከራተትን ነው አልቆመም፡፡ ከዚህ አስተሳሰብ ራሳችን ነጻ ካላደረግን፣ከርዕዮተ-ዓለማዊ ቅኝ ግዛት

ራሳችንን ነጻ ካላደረግን፣ምንጊዜም በሁለት እግራችን መቆም አንችልም፤ነጻ ነን ማለት አይዳልም፡፡ከማናቸውም

እንቅስቃሴያችን በስተጀርባ የነጭ አእምሮ ነው ያለው፡፡ በተለያየ መንገድ እዳንቀራረብ፣እንዳንፈላለግ፣እንዳንተማመን የሚደርገን የእነሱም ሁኔታ ነው፡፡ ስለዚህም የተፈለገው ያህል ተልዕኮ መወጣት ያልተቻለበት አንዱ ምክንያት ይህ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡ ሌላውም ከዚህ ጋር ተያይዞ ሊነሳ የሚችል ነገር አለ በምሁራኑም አካባቢ ቢሆን ከፍተኛ ችግርና ፍርሃት ነው ያለው፡፡

ጠና ደዎ(ዶ/ር)፣ በአዲስ አበባ ዪኒቨርሲቲ የፍልስፍና መምህርሲራራ ጋዜጣ፣ህዳር 12 ቀን 2013 ዓ.ም

1616ግዮን ቁጥር 110 ህዳር 2013 ዓ.ም

Page 18: ቅፅ 2 ቁጥር 110 ቅዳሜ ህዳር 19 ቀን 2013 ዓ.ም

1717ግዮን ቁጥር 110 ህዳር 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ

የመቀሌ ዙሪያየመቀሌ ዙሪያ ወሳኝ እርምጃ ወሳኝ እርምጃ

ወድ አንባቢያን፣ ሕዳር 24 ቀን 2013 ዓ.ም ዓ.ም በሰሜን ዕዝ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት ላይ ህወሓት የፈጸመውን ዘግናን ጨዕፍጨፋ ተከትሎ መንግሥት ሕግ የማስከበር

ተጋድሎ እያደረገ እንደኾን ይታወቃል፡፡ እኛም ላለፉት ሁለት ተከታታይ ሳምንታት ጦርነቱንና ተያያዥ ሁነቶችን ለውድ አንባቢያንም ኾነ ለታሪክ ይረዳ ዘንድ በቅደምተከተል እየዘገብን እንገኛለን፡፡ እንኾ ሦስተኛው ሳምንት ምን መልክ ኖሮት እንዳለፈ በሚከተለው መልኩ አሰናድተነዋል፡፡

ሕዳር 10/2013

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር አመራሮች ጋር ተወያዩ። በውይይቱ ወቅት የሕወሓት ጁንታ ከዚህ የባሰ ጥፋት ከማድረሱ በፊት በአስቸኳይ ለፍርድ እንዲቀርብ፣ የከተማው ሕዝብ እንዳይጎዳ ሕግ ለማስከበር በሚደረገው ዘመቻ በከተሞች አካባቢ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲደረግ ስምምነት መደረሱን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት አስታውቋል፡፡ በተያያዘም በዚህ ዕለት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ሙሉ ነጋ እና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ፍሰት ቃል አቀባይ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ለሚድያ አካላት ማብራሪያ ሰጥተዋል። የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር ሙሉ ነጋ በትግራይ እየተካሄደ ስላለው የሕግ ማስከበር ሥራና አስተዳደሩ በትግራይ ክልል ቅድሚያ ሰጥቶ የሚሠራባቸውን ሥራዎች አብራርተዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተሩ ቴድሮስ አድሐኖምን በተመለከተ ቅሬታ እንዳለውና ደስተኛ አለመኾኑን አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ገልጸዋል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ፍሰት ቃል አቀባይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታው አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደተናገሩት ዶክተር ቴድሮስ በአገሪቱ ውስጥ ምን እንደተከሰተ ከመንግሥት በኩል ለመረዳት አለመሞከራቸውን ተናግረዋል። በተጨማሪም ዶ/ር ቴድሮስ “አንዳንድ በሮችን ማንኳኳታቸውን” መንግሥት እንደሚያውቅ አመልክተው ይህንንመ በተመለከተ መንግሥት በቀጣይ ምን ማድረግ እንዳለበት ይወስናል ሲሉ አስረድተዋል። በተያያዘም የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክትር የኾኑት ዶ/ር ቴድሮስ አድሓኖም ከፌደራል መንግሥቱ ጋር ግጭት ውስጥ የሚገኘው ህወሓትን የሚደግፍ የማግባባት ሥራ አከናውነዋል ሲሉ የኢትዮጵያ ጦር ኃይሎች ኤታማዦር ሹም ጄነራል ብርሃኑ ጁላ ሕዳር ዘጠኝ ቀን ተናግረው ነበር።

በሌላ በኩል ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል አክሱም ከተማ በእጃችን ላይ ትገኛለች ሲሉ ለሮይተርስ በፅሁፍ በላኩት መልዕክት ገልፀዋል። ሽረ ከተማ ግን በፌዴራል ወታደሮች ቁጥጥር ሥር እንደኾነችም አረጋግጠዋል። ዶክተር ደብረፅዮን ሽረ ከ3 ቀን በፊት በፌዴራል ወታደሮች ቁጥጥር ሥር እንደኾነች የገለፁ ሲኾን አክሱም ከተማ ግን በቁጥጥራችን ሥር ናት ብለዋል። ዶ/ር ደብረፅዮን አክለውም የፌዴራል ወታደሮች አክሱምን እንዲቆጣጠሩ ተልከዋል በዚህም ወጊያ እየተደረገ ነው ሲሉ ገልፀዋል። በሌላ መልኩ የህወሓት ቡድን በትግራይ ክልል በንጹሃን ዜጎች ላይ መድፍ በመተኮስ ጥቃት እየፈጸመ መኾኑ ተገለጸ። በአገር መከላከያ ሠራዊት የሚደርስበትን ጥቃት መቋቋም ያቃተው የህወሓት ቡድን ከሰሜን ዕዝ የሰረቃቸውን ታንኮች ጥሎ መሄድ መጀመሩ ተገልጿል።

በደቡብ ዕዝ የሰው ሀብት ልማትና ሚዲያ አስተባባሪ ኮሎኔል ደጀኔ ጸጋዬ እንዳሉት ዘራፊው የህወሓት ቡድን የመከላከያ ሠራዊቱን መቋቋም ተስኖታል። በዚህም ከሰሜን ዕዝ የሰረቃቸውን ሁለት ቲ-72 ታንኮችና ሌሎችም ቁሳቁሶቹን እየጣለ ሸሽቷል ብለዋል። ለእኩይ ዓላማ የተሰለፈው ይህ ቡድን የመከላከያ ሠራዊቱን በትር መቋቋም ሲሳነው በንፁሃን ዜጎች ላይ መድፍ በመተኮስ ጥቃት እያደረሰ መኾኑን ገልጸዋል። የመከላከያ ሠራዊት በተቆጣጠራቸው አካባቢዎች ነዋሪዎች በደስታ ስሜት እየተቀበሉን ነው ብለዋል። የህወሓት ቡድን መጨረሻው እየደረሰ መኾኑን የገለጹት ኮሎኔል ደጀኔ ከመሸገበት አውጥቶ ለሕግ ለማቅረብ በሂደት ላይ መኾኑን መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ቀደም ብለው ቡድኑ በሦስት ቀናት ውስጥ በሠላም እጁን እንዲሰጥ የጊዜ ገደብ ማስቀመጣቸው ይታወሳል።

ሕዳር 11/2013

የትህነግ ቡድን ለኹለተኛ ጊዜ 3 ሮኬቶችን ወደ ባህርዳር ተኩሷል። ሰዓቱ ከሌሊቱ 7፡40 ሲኾን ቦታው አውሮፕላን ማረፊያና መኮድ አካባቢ ነው። ሮኬቱ የጎላ ጉዳት ባያደርስም የገበሬዎችን የበቆሎ ማሳና የአሳፋልት መንገድን መደርመሱ ታውቋል፡፡

የአሜሪካ ስቴት ድፓርትሜንት ወያኔን የምሥራቅ አፍሪካ አሸባሪ እንደኾነች የሚያሳይ መግለጫ አውጥቷል። አሜሪካ በዚህ መግለጫዋ የሰሜን እዝ ወታደሮችን በመጨፍጨፍ ጦርነቱን የጀመረው ወያኔ መኾኑን፤ የማይካድራው ዘር ተኮር ጭፍጨፋ ወያኔ መፈፀሙ፤ በአማራ ክልል እየፈፀመ ያለውን የሮኬት ጥቃት ማድረሱ፤ በኤርትራ ላይ ሮኬት ማስወንጨፉንና ለዚህ ሁሉ ጥፋት ተጠያቂ መኾኑን አካትቷል።

በሌላ በኩል የኢትዮጵያ መንግሥት በዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ላይ እርምጃ እየወሰደ መኾኑ ተሰማ። እርምጃ እየተወሰደባቸው የሚገኙት ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ሁኔታ ዓለም በተሳሳተ መንገድ እንዲያውቀውና በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ጫና እንዲበረታ በማድረጋቸው ነው ተብሏል። የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ወቅታዊውን ሁኔታ በጥንቃቄ እንዲኹም በሞያዊ ሥነ ምግባር እንዲዘግቡ ማሳሰቢያ ቢሰጣቸውም በእንቢተኝነት በቀጠሉት ላይ እርምጃ መወሰዱን አሳውቋል። ዶቼ ቨለ (DW) እና BBC የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ከተሰጣቻው መካከል ይገኙበታል። ሮይተርስ ደግሞ በሀገር ውስጥ ያላቸው ዘጋቢ በኢትዮጵያ ጉዳይ ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ እንዳታደርግ፣ ዘገባዎችን፣ ዜናዎችን እንዳትሠራ ሙሉ በሙሉ እንደታገደች የብሮድካስት ባለስልጣን ገልጿል።

በዚህ ዕለት የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አክሱም እና አድዋን ሙሉ በሙሉ የተቆጣጠረ ሲኾን ዙሪያዋን ወደ ተቆጣጠረው የአዲግራት ከተማ አየገሰገሰ እንደሚገኝ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ማጣሪያ ገለጸ። በምዕራብ ግንባር የህወሐት ጁንታን ኃይል እያጠቃ ያለው የመከላከያ ሠራዊት፣ ከሽሬ በኋላ ሰለኽለኻ ላይ የመሸገ የህወሐት ኃይልን ሰብሮ በመግባት አክሱምን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩን አስታውቋል። ሰለኽለኻ ላይ የመሸገው የጁንታው ኃይል መንገዱን በዶዘር ቆርጦና አስፓልቱን አበላሽቶ በቦታው ከባድ መከላከያ ቢያደርግም የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የጁንታውን ተከላካይ ኃይል ሰብሮ መግባቱ ተገልጹዋል። ከአክሱም ወደ አድዋ በነበረው ጉዞ በአንዳንድ ቦታዎች ላይ የጁንታው ኃይል ለመከላከል ቢሞክርም፣ በመከላከያ ሠራዊቱ ድል መኾኑ ተጠቁሟል። መከላከያ እንጥጮን እና የአዲግራትን ዙሪያ ተቆጣጥሮ ወደ አዲግራት ከተማ እየገሠገሠ ይገኛል ተብሏል። አያሌ የጁንታው ተዋጊዎች እጃቸውን የሰጡ ሲኾን ከድተው ከጁንታው ጋር ኾነው ሲዋጉ የነበሩ ወታደሮችም እንደሚገኙበት ተገልጿል።

ሕዳር 12/2013

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት በዚህ ዕለት ማለዳ የህወሓትን ጁንታ ኃይል ድል አድርጎ የአዲግራት ከተማን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ማጣሪያ አስታወቀ፡፡ የመከላከያ ሠራዊቱ ከዚህ ድል በኋላ ወደ መቐለ እያመራ መኾኑንም አስታውቋል፡፡ በሌላ መልኩ የፌዴራል መንግሥት ለትግራይ ሕዝብ አጠቃላይ ደኅንነት እና ጤንነት ከፍተኛ ዋጋ የሚሰጥ ስለኾነ፣ በትግራይ ክልል መረጋጋት እንዲሰፍን እና ዜጎቻችን ከጉዳት እና እጦት ነፃ እንዲኾኑ አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርጉ ጠቅላይ ሚኒስትር አስታወቁ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ሕግ በማስከበር ተልዕኮው የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት ባለፉት ጥቂት ቀናት ያስመዘገበው ድል የሚደነቅ ነው ብለዋል። ሠራዊታችን ትናንት ምሽት በአዲግራት ዙሪያ ያሉትን አካባቢዎች ከተቆጣጠረ በኋላ ዛሬ ደግሞ አዲግራትን ከሕወሓት ኃይል ሙሉ በሙሉ ነፃ አውጥቷል ብለዋል። የፌዴራል መንግሥት በተቆጣጠራቸው ከተማዎች እና አካባቢዎች የሚገኙ ዜጎች፣ በፀጥታ ኃይሎች ጥበቃ እየተደረገላቸው ወደ ዕለት ተዕለት እንቅስቃሴያቸው መመለስ ጀምረዋል። ከመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር በመሆን፣ ሰብዓዊ እና ማሕበራዊ ፍላጎቶች የሚሟሉበትን መንገድ እናመቻቻለን ሲሉ ተናግረዋል። የሰብዓዊ ድጋፍ ክንውኖችን ለመከታተል በፌዴራል መንግሥት የተዋቀረው ከፍተኛ ኮሚቴ፣ ተመጣጣኝ እና ወቅታዊ ድጋፍ ለማቅረብ የሚያስችል መረጃን እንዲያሰባስቡ ተጨባጭ ሁኔታውን የሚያጣሩ ልዑካንን ወደ ስፍራው መላኩንም ገልጸዋል። በተጨማሪም

በዝግጅት ክፍሉ

የደብረጽዮን ሮኬትና የተማጽኖ ደብዳቤ

የጠለቀችው የህወሓት የዲፕሎማሲ ጀምበር

አሁንስ የኦነግ ሸኔ ተስፋ ማን ነው?

ታሪክ የማይዘነጋው የማይካድራ ሰቆቃ

Page 19: ቅፅ 2 ቁጥር 110 ቅዳሜ ህዳር 19 ቀን 2013 ዓ.ም

1818ግዮን ቁጥር 110 ህዳር 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ

ኮሚቴው ባለፉት ቀናት መኖሪያቸውን ጥለው የተሰደዱትን ዜጎች ሁሉ ወደ ቀዬአቸው ለመመለስ እና ለማቋቋም ከባለድርሻ አካላት ጋር መሥራቱን እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።

በሌላ በኩል የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታን ለማደናቀፍ ጁንታው ህወሃት አደራጅቶ የላካቸው የጥፋት ኃይሎች እየተደመሰሱ መኾኑን በሀገር መከላከያ ምዕራብ ዕዝ የ22ኛ ክፍል ጦር ዋና አዛዥ አስታወቁ፡፡ የክፍለ ጦሩ ዋና አዛዥ ብርጋዴር ጀኔራል ነገሪ ቶሊና እንደገለጹት ኢትዮጵያን መበታተን ዋነኛ ግቡ ያደረገው የህወሃት ጁንታ በሰሜን ዕዝ ሠራዊት ላይ የፈጸመው ጥቃት እጅግ የሚያምና የክፍለጦሩን የሠራዊት አባላት ያስቆጣ ነው፡፡ ህወሓት ያደራጃቸውና “ኢትዮጵያ ልትፈርስ ነው” በሚል ፕሮፓጋንዳ የተመሩ ኦነግ ሸኔና ሌሎችም የህወሓት የጥፋት ቡድኖች ከውጭ ኃይሎች ጋር በመቀናጀት ከምዕራብ ወለጋ እስከመተከል የሚያደርጉት የጥፋት ሴራ እንዳለ አዛዡ ጠቁመዋል፡፡ የአካባቢው ሕብረተሰብ ከመቼውም ጊዜ በላይ ከሠራዊቱ ጎን መኾ ኑን የገለጹት ጄነራሉ በመተከል ዞን የሕዳሴ ግድቡ አካባቢ የጥፋት ቅጥረኞቹ ልክ እንደጁንታው ህወሓት ሁሉ እየተደመሰሱ ነው ብለዋል፡፡

የእንግሊዝ መንግስት በትግራይ ክልል እየተካሄደ ያለውን የሕግ ማስከበር ዘመቻ አስፈላጊነት በሚገባ መረዳቱን በዩናይትድ ኪንግደም የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈሪ መለሰ ገለጹ። የህወሓት የጥፋት ቡድን ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም በትግራይ ክልል በሚገኘው የአገር መከላከያ ሠራዊት ሰሜን ዕዝ ላይ ያደረሰውን ጥቃት ተከትሎ መንግሥት በክልሉ የሕግ ማስከበር ዘመቻ እያካሄደ ይገኛል። በዩናይትድ ኪንግደም የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈሪ መለሰ ዘመቻውን በተመለከተ ለእንግሊዝ መንግሥትና ለተፎካካሪ ፓርቲዎች የማስረዳት ሥራ መከናወኑን ገልጸዋል። በተደረጉት ገለጻዎች የእንግሊዝ መንግሥት የሕግ ማስከበር ዘመቻውን አስፈላጊነት በሚገባ መረዳቱን አመልክተዋል። ዋናው የእነሱ ሀሳብ የሕግ ማስከበር እርምጃው በአጭር ጊዜ እንዲጠናቀቅና የሰብዓዊ ቀውስ እንዳይደርስ ነው ብለዋል። በእንግሊዝ በተለያዩ ከተሞች የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በአገር መከላከያ ሠራዊቱ ላይ የደረሰው ጥቃት እጅጉን እንዳስቆጣቸውም አምባሳደር ተፈሪ ገልጸዋል።

ዳያስፖራው ኮሚቴዎችን በማቋቋም በትግራይ ክልል የሚካሄደውን የሕግ ማስከበር ዘመቻ በሚኖሩበት አካባቢ ላሉ የእንግሊዝ መንግሥት ባለስልጣናት እያስረዱና እያስገነዘቡ እንደኾነ ጠቁመዋል። ኤምባሲው እቅድ በማውጣት በእንግሊዝ የተለያዩ መገናኛ ብዙኃን በመቅረብ ስለዘመቻው ማብራሪያ እየተሰጠ መኾኑን አምባሳደር ተፈሪ አመልክተዋል።

ሕዳር 13/2013

የህወሓት አጥፊ ቡድን ለዓመታት የሕዝብ ሀብት ሲመዘብር፣ ኢ-ሰብዓዊ የኾነ ድርጊት ሲፈጽምና የራሱን ኪስ ሲያደልብ ኖሮ ዛሬ የግፍ ጽዋው ሞልቶ ሲፈስ በስሙ ከመነገድ ውጭ ምንም ያልፈየደለትን የትግራይን ሕዝብ መሸሸጊያው ማድረጉን የብልጽግና ፓርቲ ገለጸ፡፡ የእኩይነቱ ጥግ የትግራይ ሕዝብ ከሌላው የአገሪቱ ሕዝብ ጋር በፍቅር ኖሮ ሳለ እንደተወረረና በጠላት እንደተከበበ አድርጎ ፕሮፓጋንዳ በመሥራት ለስደት እየዳረገውና ድርብ በደል እያደረሰበትም ይገኛል ብሏል፡፡ በሌላ መልኩ የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ከአዲግራት ወደ መቀሌ በሚወስደው መንገድ ላይ የምትገኘውን እዳጋ ሐሙስ ከተማን ተቆጣጥሯል። የመከላከያ ሠራዊቱ የዘመቻው የመጨረሻ ግብ የሆነችውን መቀሌን ለመያዝ እየገሠገሠ እንደሚገኝ ተገልጹዋል።

በመሠረተ ልማቶች ላይ ከፍተኛ ውድመት እየፈጸመ በመሸሽ ላይ የሚገኘው የህወሓት ሕገወጥ ቡድን በአክሱም አውሮፕላን ማረፊያ ላይ ጉዳት ማድረሱ ተጠቆመ። የቱሪስት መዳረሻ በኾነችው የአክሱም ከተማ የተገነባው የአውሮፕላን ማረፊያ በ526 ሚሊዮን 860 ሺህ 200 ብር ወጪ የተገነባ መኾኑን፣ ለአካባቢው ማሕበረሰብና ለአገር ማሕበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥቅሙ ሰፊ እንደነበር ተገልጿል። የአየር ማረፊያው መጎዳት የአክሱም ሐውልትን ከጉዳት ለመታደግ የሚደረገውን የጥገና ሥራ እንደሚያስተጓጉልና በርካታ ችግር ሊያስከትል እንደሚችል ተጠቁሟል። በተያያዘም የህወሓት ቡድን በትላልቅ ፕሮጀክቶች ላይ ጥቃት እንዳይፈፀም ጠበቅ ያለ ጥበቃ እየደረገ መኾኑን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ተናገሯል። በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ፣ በኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫዎችና ሰብስቴሽኖች፣ በተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶች ጥበቃው መጠናከሩን ኮሚሽኑ በመግለጫው ተነግሯል። በቦሌና በየክልሉ በሚገኙ ኤርፖርቶች፣ በዩኒቨርስቲዎች፣ በውሃ ግድቦች፣ በነዳጅ ዲፖዎች፣ ፋብሪካዎችና ድልድዮችም ፣በስደተኛ ካምፖች፣ በሳተላይት ጣቢያዎች፣ በማዕድን ማውጫዎች እንዲሁም በሌሎች ተቋማትና ፕሮጀክቶች ላይ ሊሰነዘሩ የሚችሉትን ጥቃቶች አስቀድሞ ለማክሸፍ ጥብቅ ክትትልና ቋሚ ጥበቃ እየተደረገ መኾኑንም ኮሚሽኑ አስታውቋል።

ከዚሁ ከፍተኛ ጥበቃና ቁጥጥር ጋር በተያያዘ በወንጀል የጠረጠሩ 93 የህወሓትና የኦነግ ሸኔ ቡድን አባላትን በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተሰምቷል። በተደረገ ፍተሻና አሰሳ እንዲኹም በሕብረተሰቡ ጥቆማም 30 የመከላከያና የፖሊስ የደንብ ልብስ፣ 47 የተለያዩ ጠመንጃዎች፣ 43 የተለያዩ ሽጉጦች፣ 1 ሺ 376 የተለያዩ ጥይቶች፣ 7 ቦምቦች፣ 2 የጦር ሜዳ መነፅር፣ 102 ድምፅ አልባ መሣሪያዎች መያዛቸውን ሰምተናል። በተጨማሪም 8 የእጅ ራዲዮ መገናኛ፣ የተለያዩ የቴሌኮሚዩኒኬሽን መሣሪያዎች፣ 534,870 ብር እና

የተለያዩ ተሸከርካሪዎች መያዛቸው ተነግሯል።

በሌላ በኩል በወልቃይት ጠገዴ ዳንሻ አካባቢ ዲቪዥን የሠፈራ ጣቢያ ለጥፋት ዓላማ ሊውል የነበረ ከፍተኛ የጦር መሣሪያ በቁጥጥር ሥር መዋሉን በሰሜን ዕዝ የ5ኛ ሜካናይዝድ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ ብ/ጄኔራል ሙሏለም አድማሱ አስታወቁ። በቁጥጥር ሥር የዋሉ የጦር መሣሪያዎች 207 ክላሽ፣ 9 ሺህ 80 ጥይት፣ 26 አርባ ጎራሽ፣ 18 አስር ጎራሽ፣ የተለያዩ ሽጉጦች ማካሮፍ 26፣ ስታር 5፣ fort five 4፣ Breta 1፣ Map 2 እንዲኹም 108 የተለያዩ የቦምብ ዓይነቶች ናቸው። ከ1986 ዓ.ም ጀምሮ የህወሓት የቀድሞ ታጋዮች እና ከተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች የመጡ ሰዎች እንዲሠፍሩ ሲደረግበት በቆየው የመኖሪያ ጣቢያ በተደረገ ኦፕሬሽን ያለምንም የተኩስ ልውውጥ በልዩ ወታደራዊ ጥበብ መሣሪያዎቹ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ብርጋዴር ጄነራሉ ገልፀዋል።

የመከላከያ ሠራዊት በአድዋ ተምቤን መሥመር ማይቅናጥል በተባለውና ልዩ ስሙ ሰላስል በተሰኘው በሐውዜን ተምቤን መገንጠያ መንገድ የገጠመውን የጁንታውን ኃይል ድል አደረገ። በዚሁ መገንጠያ ላይ የሠራዊቱን ግሥጋሴ ለመግታት በኮሎኔል ጸጋዬ ማርክስና በኮሎኔል ሸሪፎ የሚመራው የጁንታው አንድ ክፍለ ጦር ሙሉ በሙሉ ተደምስሷል። የመከላከያ ዘመቻ ዋና መመሪያ እንዳስታወቀው የመከላከያ ሠራዊት ክፍለ ጦሩን ሙሉ በሙሉ ከደመሰሰ ቡኋላ ወደ መቀሌ የሚያደርገውን ጉዞ አጠናክሮ ቀጥሏል። በተያያዘ መልኩ በሕግ ማስከበር ዘመቻ የተሠማራው የሀገር መከላከያ ሠራዊት በሁሉም አቅጣጫ ድልን በመጎናጸፍ ወደ መቀሌ እየገሰገሰ እንደሚገኝ በኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የሕብረት ዘመቻ ዋና መምሪያ አስታወቀ።

የመምሪያው ኃላፊ ተወካይ ብርጋዴል ጀኔራል ተስፋዬ አያሌው የሠራዊቱን የሕግ ማስከበር ዘመቻ አጠቃላይ ገጽታ በምስል አስደግፈው ገለጻ አድርገዋል። ብርጋዴል ጀኔራል ተስፋዬ አያሌው እንዳሉት፤ ጽንፈኛው የህወሓት ቡድን የመንግሥትን በትረ ሥልጣን በኃይል ለመቆጣጠር በማለም በሀገር መከላከያ ሠራዊት ላይ ከፍተኛ ክህደት ፈጽሟል። በዚህም የአገር መከላከያ ሠራዊት የህወሓትን ጁንታ ጥቃት በመቀልበስ በከፍተኛ ቁጭትና ወኔ የሕግ ማስከበር እርምጃውን በድል እያከናወነ ይገኛል ብለዋል። “በምዕራብ ግንባር ከዳንሻ በመነሳት በርካታ ኪሎ ሜትሮችን አቆራርጦ ባእከር፣ ሁመራና ሽሬን መቆጣጠር ችሏል” ብለዋል። “ከባድመ፣ ጾረና እና ዛላንበሳ የተነሳው ሠራዊት ደግሞ በከፍተኛ ድል አዲግራትን ተቆጣጥሮ ወደ መቀሌ እየገሰገሰ ይገኛል” ብለዋል። ከራያና ጭፍራ በሁለት አቅጣጫ የተነሳው ሠራዊትም የደቡብ ግንባር ሲኾን፤ ሠራዊቱ ጨርጨር ላይ በመገናኘት በመሆኒ አድርጎ ከመቀሌ 60 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ወደምትገኘው ሔዋና መጠጋቱን ገልጸዋል። ጽንፈኛ ቡድን ጥቃቱን ሲፈጽም የትግራይ ሕዝብ ከጎኑ እንደሚሰለፍ አስቦ እንደነበር ገልጸው፤ ሕዝቡ ግን “በችግር ጊዜ ከጎኔ የነበረውን የአገር መከላከያ አልወጋም” በማለት በተቃራኒው ለሠራዊቱ ድጋፉን ማሳየቱን አብራርተዋል።

በሌላ መልኩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ሕዳር 13 ቀን በሰጡት መግለጫ የጁንታው አባላት የጥፋት ጉዟችሁ ጀንበሯ እየጠለቀች መኾኑን አምነው፣ በቀጣይ 72 ሰዓታት ውስጥ እጃቸውን በሰላም እንዲሰጡ ጠይቀዋል። ጠ/ሚኒስትሩ የመቀሌ ከተማ ነዋሪዎች በጀመርነው ሕግን የማስከበር እርምጃ ቁልፍ ተዋናዮች እንድትኾኑ፣ ከሠራዊታችን ጎን በመቆም ይሄንን የክህደት ቡድን አባላት ለፍርድ በማቅረብ ወሳኝ ሚናችኹን እንድትወጡ ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።

ሕዳር 14/2013

የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ጀነራል ኮሚሽነር አራርሳ መርዳሳ እንዳስታወቁት ቀለብተኛው ኦነግ ሸኔ ከዚህ በኋላ የክልሉን ሰላም መንሳት አይችልም ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ሽፍታው በክልሉ የሚያደርሰውን ጥፋት ለመከላከልና የሕግ የበላይነትን ለማስከበር ጠንካራ ሥራ ሲሠራ መቆየቱን ኮሚሽነሩ ተናግረዋል፡፡ በዚህም 1 መቶ 60 የሚኾኑት ሲደመሰሱ፣ 68 በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ገልጸዋል፡፡ በተጨማሪም 1 ሺህ የሚኾኑ ሰዎች ለቡድኑ በቀጥታና በተዘዋዋሪ ድጋፍ ሲያደርጉ የነበሩ እና 1 መቶ 4 የሚኾኑት ከህወሓት የጥፋ ቡድን ጋር በቀጥታ ግንኙነት የነበራቸው መኾኑ ተረጋጦ በቁጥጥር ሥር ውለዋል ነው ብለዋል፡፡

የትግራይ ሕዝብ የተሰጠውን እድል በመጠቀም የጽንፈኛው ኃይል አሳልፎ እንዲሰጥ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈፃሚ ደ/ር ሙሉ ነጋ ጠየቁ። የጊዜያዊ አስተዳሩ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ሙሉ እንደተናገሩት፣ በትግራይ ክልል እየተካሄደ ካለው የሕግ ማስከበር ሥራ ጋር በተያያዘ ንጹሃን ዜጎች እንዳይጎዱ መንግሥት በከፍተኛ ኃላፊነት እና ጥንቃቄ እየሠራ ይገኛል። “መንግሥት ሕዝባችን እንዳይጎዳ እና ደም እንዳይቃባ እያደረገ ያለው ኃላፊነት የተሞላበት ጥንቃቄ እንደ ጊዜያዊ አስተዳደር አድናቆት አለኝ” ያሉት ዶ/ር ሙሉ ነጋ፣ የጥፋት ኃይሉ ህወሓት ግን ለትግራይ ሕዝብ ምንም ዓይነት ደንታ እንደሌለው በገሃድ አሳይቶናል በማለት ተናግረዋል። በተጨማሪም በመቐሌ በሚደረገው የመጨረሻ ዘመቻ ጁንታው የሚፈልገው ህዝቡን ደም ማቃባት ስለኾነ የፌዴራል መንግሥት እና የመከላከያ ሠራዊቱ ይህ እንዳይኾሆን በጥንቃቄ መሥራት አለባቸው ሲሉ ዋና ሥራ አስፈፃሚው አሳስበዋል።

ሌላው በዚህ ዕለት አቶ ሬድዋን ሁሴን ህወሓት ወደ ባህር ዳር የሮኬት ጥቃት መሰንዘሩን ገልፀዋል። ጥቃቱ ጠዋት 12:20 አካባቢ እንደተፈፀመ የተገለፀ

Page 20: ቅፅ 2 ቁጥር 110 ቅዳሜ ህዳር 19 ቀን 2013 ዓ.ም

1919ግዮን ቁጥር 110 ህዳር 2013 ዓ.ም

ወቅታዊቡድን የተለያዩ የሐሰት ወሬዎችን በማሰራጨት ነዋሪዎች ከየአካባቢያቸው እንዲለቁ ማድረጉንም አስታውሰዋል። “ይህንን ያደረገበትም ዋናው ምክንያት ለዘረፋ እንዲመቸው መኾኑ ተደርሶበታል” ብለዋል። እንደ ብርጋዴር ጄነራል ብርሃኑ ገለፃ፤ የህወሃት ጁንታ የቡድኑን ታጣቂዎች የሲቪል ልብስ በማልበስ የአገር መከላከያ ሠራዊቱን እንዲወጉ ለማድረግ ጥረት አድርጓል። ኾኖም ሠራዊቱ የሕግ ማስከበር ዘመቻውን በጥንቃቄና በውጤታማነት ለማከናወን መቻሉን ገልጸዋል፡፡

ሕዳር 15/2013

መንግሥት የሰጠውን የ72 ሰዓት ጊዜ በመጠቀም እጅግ በርካታ የትግራይ ሚሊሻና ልዩ ኃይል አባላት በየግንባሩ እጅ እየሰጡ መኾኑን የአስቸኳይ ጊዜ መረጃ ማጣሪያ አስታወቀ። በአፋር ክልል በኩል ብዙዎች ገብተው እጅ የሰጡ ሲኾን በማይ ጸብሪ ተቆርጦ የቀረው ኃይል እጁን በሰላም በመስጠት ላይ መኾኑንም ጠቅሷል። ሌላው የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የደህንነት አማካሪ የኾኑት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ወደ ሞቃድሾ በማቅናት በትግራይ ክልል እየተሠራ ያለውን ሕግ የማስከበር ዘመቻ ለሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሙሐመድ አብዱላሂ ሙሐመድ ገለጻ አድርገውላቸዋል። የሕግ ማስከበር ዘመቻው በታቀደው መልኩ በጥሩ ሁኔታ እየተከናወነ መኾኑን እና የሥርዓት አልበኛው የህወሓት ጁንታ ጉዳይ በአጭር ጊዜ መቋጫ እንደሚያገኝ አቶ ገዱ ተናግረዋል። የሶማሊያ መንግሥትም ኢትዮጵያ እያካሄደች ያለውን የሕግ ማስከበር ዘመቻ ሙሉ ለሙሉ እንደምትደግፍ ፕሬዝዳንት ሙሐመድ አብዱላሂ ሙሐመድ ለአቶ ገዱ እንዳረጋገጡላቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቢሮ ይፋ አድርጓል።

የህወሃት ጁንታ በሚያናፍሰው ፕሮፓጋንዳ ሕዝቡ ሊደናገር እንደማይገባው በሕግ ማስከበር ዘመቻ ላይ የተሠማሩ የአገር መከላከያ ሠራዊት አባላት ተናገሩ። ጁንታውን በመቆጣጠር ለሕግ ለማቅረብ ዝግጁ መኾናቸውንም አረጋግጠዋል። የሠራዊቱ አባላት እንደገለጹት፤ የህወሃት ጁንታ የሐሰት ፕሮፓጋንዳ የተለመደና ሁሉም የሚያውቀው ነው። ጁንታው አጥፍቶ አላየሁም፣ ሰርቆ ደብቆ አልነበርኩም በማለት እንዲኹም የሌለ ነገር ፈጥሮ መዋሸት የተካነበት ሥራው መኾኑን ገልጸዋል። በመኾኑም ሕዝቡ በህወሃት የፈጠራ ወሬ ሊደናገርና ሊሸበር አይገባውም ብለዋል፡፡ የሠራዊቱ አባላት በህወሃት ጁንታ ታፍኖ የኖረውና ነፃነት የሚሻው የትግራይ ሕዝብ የሠራዊቱን ድጋፍ በመፈለጉ ሕግ የማስከበር ዘመቻው በውጤታማነት መቀጠሉን ገልጸው፤ ለአገራችን ልእልና መከበር ዝግጁ ነን ሠራዊቱ እስካለ ድረስ ሕዝቡም ስጋት አይግባው ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። በሌላ መልኩ በትግራይ ክልል “በግፍ ተፈጽመዋል የተባሉ ወንጀሎችን” የሚያጣራ የምርመራ ቡድን ወደ ስፍራው በማቅናት ሥራ መጀመሩን የኢፌዴሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አስታወቀ። የሕወሓት የጥፋት ቡድን ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም በትግራይ ክልል በሚገኘው የአገር መከላከያ ሠራዊት የሰሜን ዕዝ ላይ የፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ መንግሥት የሕግ ማስከበር ተግባር እየከናወነ ነው።

በሌላ በኩል የኢትዮጵያ መንግሥት እና ህወሓት በተመሳሳይ ሚዛንና በእኩል ሥነ ምግባር የሚቀመጡ አይደሉም ሲሉ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ገለፁ። አቶ ኃይለማሪያም በፅሁፋቸው በርከት ያሉ ከኢትዮጵያ ጋር በተያያዘ ትንታኔ የሚሰጡ እና የአፍሪካ ቀንድ ባለሙያ የተባሉ አካላት ሁሉንም አቀፍ ብሔራዊ ውይይት እንዲደረግ ጥሪ በማቅረብ ላይ ተጠምደዋል ይላሉ። እንዲሁም መንግሥት በህወሓት ውስጥ ባለው ቡድን ላይ እየወሰደው የሚገኘውን ሕግን የማስከበር እርምጃ እንዲያቋርጥ ጥሪ በማቅረብ ላይ መኾናቸው አንስተዋል። ይኽም ፊት ለፊት ሲያዩት መልካም ሀሳብ ይመስላል ያሉት የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ከምንም ቢነሱም የሰላም ጥሪያቸው ግጭትን ለመፍታት እንደኾነ በፅሁፉ ላይ አብራርተዋል። ይህን ምክረ ሀሳብ የሚሰጡ ሰዎች በደንብ አስበውበት በአፍሪካ ችግሮች የሚፈቱበትን የተለመደ መንገድ የማስተጋባት ልምድ እንዳላቸው እንደሚያምኑ ገልፀዋል። የዓለም ሀገራት መንግሥታት የተሳሳተ ሚዛን እንዲኖራቸው ያደረገውም መንግሥትን እና ህወሓትን ዓለም አቀፍ ማኅበረሰቡ በእኩል ሥነ ምግባር ማየቱ ቁልፍ ችግር ነው ብለዋል። ሚዛናዊነት የሚጎድለው እንዲህ አይነቱ ሀሳቦችን በአንድ መጠቅለል አይሠራም ያሉት አቶ ኃይለማሪያም ለዚህም ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የደቡብ ሱዳንን ችግር ያየበት መንገድ ጥሩ ማሳያ እንደኾነ አንስተዋል። ደቡብ ሱዳን ነፃ ሀገር ከኾነች በኋላ የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ የተካሄደው የሰላም ውይይት ከሥልጣን መጋራት ባሻገር ምንም ጉዳይ አለማካተቱን በማንሳት ስምምነቱ በግጭት ወቅት ለተፈጠረው የጀምላ ግድያ ተጠያቂነትን ያላሰፈነ ነው ብለዋል። የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ቁልፉ ችግር በደቡብ ሱዳን የነበረውን አካሄድ በኢትዮጵያ ለመድገም መንግሥት እና ህወሓትን ሚዛናዊነት በጎደለው መልኩ በእኩል ሥነ ምግባር በማስቀመጥ የዓለም ሀገራት መንግሥታት የተሳሳተ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ማድረጋቸው እንደኾነ ነው ያሰፈሩት።

ለ27 ዓመታት በህወሓት የበላይነት ሲመራ የነበረው ኢህአዴግ ኢኮኖሚው እና ፖለቲካውን በተገቢው መንገድ ባለመምራቱ በሕዝባዊ አመፅ የአመራር ለውጥ መምጣቱን አስታውሰው አሁን ላይ ህወሓት ስትራቴጂ በመቀየስ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የተሳሳተ ሚዛን እንዲይዝ በማድረግ ሌላ ግንዛቤ ለመፍጠር እና ድርድር እንዲኖር ለማድረግ እየሠራ ይገኛል ብለዋል።

የህወሃት ጁንታ ታጣቂ ኃይል በማይካድራ የፈጸመውን ጭፍጨፋ በመቀሌ ለመድገም ዝግጅት እያደረገ መኾኑን የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ዋና

ሲኾን የደረሰ ጉዳር ስለመኖሩ አልተገለፀም። ዒላማው ኤርፖርቱ እንደነበረም ገልጸዋል። በሌላ መልኩ ዩናይትድ አረብ ኢምሬት በግጭቱ ምክንያት ለተፈናቀሉ ሰዎች የ5 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ እሰጣለሁ አለች፡፡ በአፍሪካ ቀንድና በምሥራቅ አፍሪካ ቀጣና ሰላምና መረጋጋት እንዲመጣ በኢትዮጵያ የሕግ የበላይነት መከበርና የኢትዮጵያ አንድነት መከበር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች አስታውቃለች፡፡ የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት በኢትዮጵያ የሕግ የበላይነት መከበር እንዳለበትና አሁን የተጀመረው ውጊያ መቆም እንዳለበት አስታውቋል፡፡ ሚኒስትሩ ሼክ አብዱላህ ቢን ዛይድ በኢትዮጵያ የሕግ የበላይነት መከበር በአፍሪካ ቀንድ ለሚኖረው ሰላምና መረጋጋት ቁልፍ ሚና እንዳለው ገልጸዋል፡፡ እየተካሄደ ያለው ውጊያም እንዲቆምና በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ በአፍሪካ በተለይም በቀጣናው ካሉ አጋሮቿ ጋር መምከሯን አስታውቃለች፡፡

የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ከህወሓት ጋር ግንኙነት አላቸው ያላቸውን የ4 ተጨማሪ ኩባንያዎች የባንክ ሒሳብ እንዲሁም ቋሚና ተንቀሳቃሽ ንብረቶችን ማገዱን ተናገረ፡፡ ከዚህ ቀደም የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ከህወሓት ጋር ግንኙነት አላቸው ያላቸውን 34 ድርጅቶች የባንክ ሒሳብና ቋሚ ተንቀሳቃሽ ንብረት ማገዱ ይታወሳል፡፡ የታገዱት ኩባንያዎች ቁጥር 38 መድረሱን ም/ጠ/ዐቃቤ ሕግ ፍቃዱ ፀጋ ነግረዋል፡፡ ከ38ቱ ኩባንያዎች መካከል በስም መመሳሰል የኤፈርትን የኢሜል አድራሻ በመጠቀማቸው ከህወሓት ጋር ተዛምዶ ይኖራቸዋል በሚል ጥርጣሬ የባንክ ሒሳባቸው ታግደው ከነበሩት ኩባንያዎች ቢያንስ አንዱ ከዝርዝሩ ሊወጣ እንደሚችል አቶ ፀጋዬ ተናግረዋል፡፡ የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ኩባንያዎቹ ላይ የወንጀል ምርመራ መጀመሩን ተናግረዋል፡፡ እገዳው በድርጅቶቹ ውስጥ ተቀጥረው የሚያገለግሉ ሰራተኞችን ሕይወት እንዳያመሰቃቅል ለድርጅቶቹ አዲስ አስተዳደር ተሹሞላቸው ሥራቸውን እንዲቀጥሉ ለማድረግ እየተሠራ መኾኑንም ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል የጀርመን መንግሥት በትግራይ ክልል እየተካሄደ ያለውን የሕግ ማስከበር ዘመቻ ትክክለኛ ገጽታ እንዲረዳ መደረጉን በጀርመን የኢትዮጵያ አምባሳደር ሙሉ ሰለሞን ገለጹ። አምባሳደሯ በህወሓት የጥፋት ቡድን ላይ የሕግ ማስከበር እርምጃው ከተጀመረ ጊዜ አንስቶ ለጀርመን መንግሥት ባለሥልጣናት፣ ለፓርላማ አባላትና ለዓለም አቀፍ የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡ ማብራሪያ እየተሰጠ መኾኑን ገልጸዋል። በሌላ መልኩ ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ድርጅት 858 የሰሜን ዕዝ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላትን እንዳልተቀበለ አስታወቀ። የትግራይ ቴሌቪዥን ሕዳር 13 ቀን ምሽት ዘገባው ባሰራጨው መረጃ በትግራይ መንግሥት ሥር ያሉ 858 የሰሜን ዕዝ የአገር መከላከያ ሠራዊት አባላትን ለዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል አስረክበናል ብሎ ነበር። በርክክቡ ወቅትም የቀይ መስቀል አባላት በአካል ተገኝተው ነበርም ሲል ነው ቴሌቪዥን ጣቢያው የገለፀው። ይሁንና ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ተቋም 858 የአገር መከላከያ ሠራዊት አባላትን እንዳልተቀበለ አሳውቋል። ቀይ መስቀል በሰሜን ኢትዮጵያ በተከሰተው ጦርነት የተጎዱ ዜጎችን ህክምና እንዲያገኙ በማድረግ ላይ መኾኑን አስታውቋል። ድርጅቱ ከሁለቱም ወገኖች የተጎዱ ዜጎችን በ11 አንቡላንሶችን በማሠማራት ድጋፍ በማድረግ ላይ መኾኑንም ገልጿል።

ሌላው በዚህ ዕለት መንግሥት በአጥፊው የህወሓት ቡድን ላይ እየወሰደው ያለው እርምጃ የአገርን ሕልውና ለማስጠበቅ እና ሕግን ለማስከበር ያለመ እንደኾነ የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ገለጹ፡፡ ም/ጠ/ዐቃቤ ሕግ አቶ ፍቃዱ ጸጋ እና የፌደራል ፖሊስ ም/ኮሚሽነርአቶ ዘላለም መንግሥቴ በወቅታዊ አገራዊ ጉዳይ ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ አጥፊው የህወሓት ቡድን የአገር ደጀን የኾነውን የመከላከያ ሠራዊት በተኛበት ሲወጋው በመንግሥት ላይ አማራጭ የሌለው ሕግ የማስከበር የውዴታ ግዴታ ኃላፊነት እንደወደቀበት ም/ጠ/ዐቃ ሕግ ፍቃዱ ጸጋ ተናግረዋል፡፡ ከሀዲው ቡድን ጦርነቱን የጀመረው “እኛ ከሌለን ይህች አገር አትኖርም” በሚል የትምክህተኛ አስተሳሰብ አገረ መንግሥቱን በኃይል በማፍረስ ያጣውን ሥልጣን እና ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ለመመለስ በማለም ነው ብለዋል፡፡ በመኾኑን በከሀዲው ቡድን ላይ የሚካሄደው ዘመቻ ወረራ ሳይኾን የአገርን ሕልውና የማስጠበቅ እና ሕግን የማስከበር ተልዕኮ ያለው ሥራ እንደኾነ አረጋግጠዋል፡፡ በሕግ ማስከበርና የሕልውና ዘመቻው ሂደት ሊደርስ የሚችለውን ሰብዓዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ቀውስ ለመቀነስ መንግሥት በወንጀል የሚፈለጉ የጥፋት ቡድኑ አባላትና የጦር መኮንኖች እጅ እንዲሰጡ ከመጠየቅ ጀምሮ የተለያዩ የጥንቃቄ እርምጃዎች በመውሰድ ላይ መኾኑንም ገልጸዋል፡፡

ሕግ የማስከበር ሥራውን በፍጥነት በማከናወን ጁንታው ሊያደርስ ያሰባቸውን ተጨማሪ ጥፋቶች ማስቀረት መቻሉን የምዕራብ ዕዝ የሎጂስቲክስ ክፍል ምክትል አዛዥ ብርጋዴር ጄነራል ብርሃኑ ጥላሁን ተናገሩ። ብርጋዴር ጄነራል ብርሃኑ እንደገለጹት፤ የህወሓት ጁንታን ጥቃት ተከትሎ የአገር መከላከያ ኃይሉ ፈጣንና ውጤታማ የሕግ ማስከበር ዘመቻ እያካሄደ ይገኛል። ቡድኑ ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም በሰሜን ዕዝ ላይ ክህደት በፈጸመበት ወቅት የቻለውን ያህል ወታደራዊ ቁሶችን ከዘረፈ በኋላ ያልቻለውን ደግሞ አበላሽቶ ሄዷል ብለዋል። “የትግራይ ሕዝብ በዚህ ቡድን እኩይ ተግባር ማዘኑን በየደረስንባቸው አካባቢዎች መረዳት ችለናል” ብለዋል። የሕወሓት ጁንታ በትግራይ የአክሱም አየር ማረፊያን ጨምሮ የተለያዩ መሠረተ ልማቶችን በማውደም የሕዝብ ጠላት መኾኑን በግልጽ ማሳየቱን ጠቅሰው፤ “በዚህ ድርጊቱ በርካታ የአካባቢው ነዋሪ ማዘኑን ገልጾልናል” ብለዋል። የሕወሓት ፅንፈኛ

Page 21: ቅፅ 2 ቁጥር 110 ቅዳሜ ህዳር 19 ቀን 2013 ዓ.ም

2020ግዮን ቁጥር 110 ህዳር 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ

ዳይሬክተር ሜጄር ጀኔራል መሀመድ ተሰማ ተናገሩ። ቡድኑ ድርጊቱን የሚፈጽመው ልዩ ቡድን አዘጋጅቶና በአልመዳ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ያዘጋጀውን የመከላከያንና የኤርትራ ሠራዊት ዩኒፎርሞችን በማልበስ እንደኾነም ነው የጠቆሙት። ሜጀር ጀነራል መሀመድ ተሰማ ይኽን ያሉት ወቅታዊ ጉዳይን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ ነው። የህወሓት ፅንፈኛ ኃይል በየጊዜው እርስ በርሳቸው የሚጣረሱ መረጃዎችን በማሰራጨት ሕዝብን እያደናገረ እንደሚገኝም ነው የተናገሩት። ለአብነትም ቡድኑ ከቀናት በፊት “በራያ ግንባር 21ኛ ክፍለጦርን ደምስሰናል፤ አድዋ ላይ የመጣውን ኃይል በመደምሰስ አካባቢውን ተቆጣጥረናል” ሲል መናገሩን አንስተዋል። ነገር ግን በዕለቱ እርሳቸውን ጨምሮ የሠራዊቱ አመራሮች በተገለጹት ስፍራዎች ላይ በመገኘት ለመገናኛ ብዙኃን ገለጻ ማድረጋቸውንና ገለጻውም አየር ላይ መዋሉን ነው የተናገሩት። ይህም የጁንታውን የሐሰት ፕሮፓጋንዳ የሚያረጋግጥ መኾኑን ገልጸዋል። የቡድኑ አፈቀላጤዎች ተደብቀው መግለጫ ከመስጠት ይልቅ እውነታቸውን ከኾነ “ደምስሰን አስለቅቀናል” ባሏቸው ቦታዎች ላይ በመገኘት መግለጫ መስጠት በቻሉ ነበር ብለዋል። የቡድኑ መሪዎች ሕግ የማስከበሩን ዘመቻ በትግራይ ሕዝብ ላይ የተቃጣ ሕዝባዊ ጦርነት ለማስመሰል እየጣሩ መኾኑንም ገልጸዋል። ነገር ግን የትግራይ ሕዝብ ዘመቻው ጽንፈኛ ቡድኑን ብቻ እንደሚመለከት በተግባር ማሳየታቸውን አብራርተዋል። የትግራይ ሕዝብ ሠራዊቱ በተቆጣጠራቸው ቦታዎች ለሠራዊቱ ያለውን ድጋፍ በተግባር ከማሳየቱም በላይ ጁንታው ምን ያህል ሲበድላቸው እንደቆየ ተናግረዋል፡፡ የህወሓት የጥፋት ኃይል ያሰበው ሴራ ሁሉ እየከሸፈበት መኾኑን ጠቅሰው፤ አሁን ላይ ደግሞ አዲስ የጥፋት እቅድ ማውጣቱን ደርሰንበታል ብለዋል ሜጀር ጀነራል መሐመድ። በዚህም በማይካድራ ንፁሃን ላይ የፈጸመውን ጭፍጨፋ በመቀሌ ለመድገም ዝግጅት እያደረገ መኾኑን ገልጸው ድርጊቱን ለመፈጸም ደግሞ ልዩ የገዳይ ቡድን ማዋቀሩንም ተናግረዋል። የገዳይ ቡድን አባላቶችን በአልመዳ ጨርቃጨርቅ ፍብሪካ አማካኝነት ያዘጋጀውን የኢፌዴሪ መከላከያ እና የኤርትራ ሠራዊት ዩኒፎርሞችን በማልበስ ጭፍጨፋውን ለመፈጸም ተዘጋጅቷል ብለዋል። ቡድኑ ይኽን የሚያደርገው የኢትዮጵያና የኤርትራ ሠራዊት በጋራ በመኾን ንፁሃንን እንደጨፈጨፉ በማስመሰል ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ድጋፍ ለማግኘት መኾኑንም ገልጸዋል። የህወሓት ፅንፈኛ ቡድን ከሥልጣን ውጭ ለሕዝብ ምንም ዓይነት ርህራሄ እንደሌለው አመላካች መኾኑንም ጠቁመዋል። በትግራይ ክልል ሠራዊቱ በተቆጣጠራቸው አካባቢዎች የሚኖሩ ዜጎች እንዳደረጉት ሁሉ የመቀሌ ነዋሪዎችም ውግንናቸው ለሠራዊቱና ለኢትዮጵያዊያን ወንድሞቻቸው እንደሚኾንም ያላቸውን እምነት ገልጸዋል። ተገደው ለቡድኑ እየተዋጉ ያሉ ታጣቂዎችም በሐሰት ፕሮፓጋንዳ ሳይታለሉ በአቅራቢያቸው ላለው የመከላከያ ሠራዊት እጃቸውን እንዲሰጡም ጥሪ አቅርበዋል።

በሌላ መልኩ የጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ መንግሥት ከሕወሓት ጋር በእኩል ይደራደር ማለት ሀገሪቱን የሚበታትን አማራጭ ነው ሲሉ የጅቡቲው ፕሬዝዳንት ኡመር ጌሌህ ለአፍሪካ ሪፖርት መጽሄት በሰጡት ቃለ ምልልስ ተናግረዋል፡፡ ሕወሓት የተባለው ድርጅት ፌደራል መንግሥቱን በኃይል ለማንበርከክ ራሱን ያደራጀ ኃይል ነው ያሉት ፕሬዝዳንት ጌሌህ ዐቢይ ከድርድር ይልቅ ሕወሓትን የመቅጣት አማራጭ መከተላቸው ትክክለኛ ውሳኔ እንደኾነ በሚጠቁም መልኩ፣ ማንም ሰው ራሱን በዐቢይ ጫማ ውስጥ አስቀምጦ ችግሩን ማየት እንዳለበት ተናግረዋል፡፡

ህወሓት በማይካድራ አማራዎች ላይ የፈፀመውን ዘግናኝ የዘር ጭፍጨፋ ኢሰመኮ አጣርቶ ከ600 በላይ ንፁሃን መገደላቸውን ይፋ ማድረጉን ተከትሎ BBC በሰበር ዜና ዘግቦታል። በተያያዘም ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን እና ዓለም አቀፍ ተቋማት ወደ ሱዳን ከሸሹ ወገኖች የሚቀበሉትን መረጃ በሚገባ እንዲፈትሹ እና እንዲያጣሩ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ አሳስቧል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያው ይህን ያሳሰበው፣ የሕወሓት ቅጥረኞች የተዛባ መረጃን የማሰራጨት ተልዕኮ ተቀብለው ወደ ሱዳን ከሸሹ ዜጎች ጋር እንደ ተቀላቀሉ ተዓማኒ መረጃ የደረሰው መሆኑን በመበግለጽ ነው።

ሕዳር 16/2013

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ሕዳር 15 ቀን ምሽት በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ለምክክር በZoom ተቀምጦ ነበር። ነገር ግን ስብሰባውን የአፍሪካ አገራት ባለመደገፋቸው ያለመፍትሔ ተጥናቅቋል፡፡ በአንፃሩ የፈረንሳይ ፣ የእንግሊዝ ፣ የቤልጂየም ፣ የጀርመን እና የኢስቶንያ ዲፕሎማቶች አሜሪካን በመደገፍ ውይይቱ እንዲቀጥል ጥሪ ማቅረባቸውን ታውቋል። በሌላ በኩል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አገራት በውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ላለመግባት መርህ መገዛት እንዳለባቸው ገለጸዋል። ኢትዮጵያ ከመንግሥታቱ ማኅበር መሥራች አባልነት ጀምሮ ለዘርፈ ብዙ ዓለም አቀፍ ትብብር እና ለዓለም መረጋጋት ቃል የገባቻቸው መርሆዎች እና የፈረመቻቸው ሕግጋት ጽኑ እና የማይገሰሱ መኾናቸውን ጠቅሰዋል። በመኾኑም አገሪቱ በዓለም አቀፍ ሥርዓት መሠረት የሕጎች ጠባቂ ለመኾኗ በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች በተመድ እና በአፍሪካ ኅብረት ሰላም አስከባሪ ተእልኮዎች ውስጥ የምታደርጋቸው ተሳትፎዎች ምስክር ናቸው ብለዋል።

ኢትዮጵያ እያካሄደችው ያለውን የሕግ ማስከበር ዘመቻ ዓለም አቀፉ

ማኅበረሰብ ለመርዳት ያለውን ፍላጎት እንደምታደንቅ ጠቁመው፣ ይህ ግን ዓለም አቀፍ ሕግን መሠረት አድርጎ ሊተገበር እንደሚገባው በአጽንኦት ገልጸዋል። በመኾኑም ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የኢትዮጵያ መንግሥት የድጋፍ ጥሪ እስኪያቀርብ ድረስ ሊጠብቅ እንደሚገባ አሳስበዋል። ሁሉን ነገር በራሱ ፍላጎት ብቻ የማድረግ አባዜ የተጠናወተው ሕወሓት ግን የለውጡን ሂደት በሙሉ በማጣጣል፣ በማደናቀፍ እና ኃይልን በመጠቀም ወደ ሥልጣን ለመመለስ መሞከሩን አመልክተዋል። ላለፉት ሦስት ዓመታት ገደማ የሕወሓት አመራሮች የዴሞክራሲ ሂደቱን ለማደናቀፍ የሚያስችሉ ጥቃቶችን ለማድረስ ፈፃሚዎችን ሲያሰለጥኑ እና ሲያስታጥቁ እንዲሁም በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ብሔር እና ሃይማኖትን መሰረት ያደረጉ ወንጀሎችን እንዲፈጸሙ በገንዘብ ሲደግፉ መቆየታቸውን ጠቅሰዋል።

እነዚህ አመራሮች ክህደትን በመሰነቅ ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ላይ ደግሞ ጨለማን ተገን በማድረግ በሰሜን ዕዝ የአገር መከላከያ ሠራዊት ላይ አሳፋሪ ጥቃት መፈጸሙን ተናግረዋል። አመራሮቹ ከጦሩ ውስጥ ከሀዲዎችን በመመልመል ባልታጠቁ ወታደሮች ላይ በውድቅት ሌሊት ጅምላ ግድያ ከመፈጸማቸው በላይ የሰሜን ዕዝ ይዞታዎችን በሕገ ወጥ መንገድ ለመዝረፍ ሞክረዋል፤ አጠቃላይ ወታደራዊ ሎጂስቲክሱን ለመንጠቅ ራሳቸው እንደመሰከሩት በሀገር መከላከያ ኃይል ላይ “መብረቃዊ ጥቃት” መፈጸማቸውን ገልጸዋል። ይህም ጥቃቱ ሕገ መንግሥታዊ ባልኾነ መንገድ ሥልጣንን ለመንጠቅ የተፈጸመ ግልጽ የክህደት ተግባር ለመኾኑ ማሳያ ነው፤ በአገሪቱ ሕግ መሠረትም ጥቃቱ የወንጀል ድርጊት ነው ብለዋል።

ህወሓት ወንጀለኝነቱን ይበልጥ ለማረጋገጥ ማይካድራ ከተማ ውስጥ 600 ንጹሐን ሰዎችን በግፍ ገድሏል፤ በህወሓት የተፈጸመውን ይህን ጅምላ ግድያ አምነስቲ ኢንተርናሽናል በቅድመ ዘገባው አሰቃቂ ወንጀል ሲል የገለጸው መኾኑን አመልክተው፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽንም ባደረገው ማጣራት ድርጊቱ በሰብአዊነት ላይ የተፈጸመ ወንጀል እና የጦር ወንጀል መኾኑን አረጋግጧል ብለዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት በሀገር መከላከያ ሠራዊት ላይ ጥቃት ከተፈጸመበት ጊዜ ጀምሮ እያደረገው ያለው ሕግን የማስከበር ዘመቻም፣ የሀገርን ሉዓላዊነት እና አንድነት የማስጠበቅ፣ በግዛቷ ውስጥ ሕግ እና ሥርዓትን የማስመለስ እና ወንጀል ፈጻሚ ከሀዲዎችን ለሕግ የማቅረብ መኾኑን ጠቅሰዋል። የሀገሪቱን ፖለቲካዊ አንድነት እና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት ለማስጠበቅ ደግሞ በአፈንጋጩ የህወሓት ጁንታ ላይ ሕጋዊ እርምጃ መውሰድ ግድ የሚል እንደኾነ አመልክተዋል።

እንደ አንድ ሉዓላዊ ሀገር ኢትዮጵያ በድንበሯ ውስጥ ሕጓን የመተግበር ብሎም ግዛቷን የማስከበር መብት እንዳላትም ጠቁመው፤ “እያደረግን ያለውም ይኽንኑ ነው” ብለዋል። በፌዴሬሽኑ ላይ ጦር በሰበቁ ቡድኖች ላይ እየወሰድናቸው ያሉ እርምጃዎችም መንግሥትን ሕገ መንግሥታዊ ባልኾነ መንገድ ለማስወገድ የሚደረግ ሂደትን በሚከለክለው እና ዴሞክራሲያዊ አስተዳደርን በሚያበረታታው የአፍሪካ የዴሞክራሲ ቻርተር፣ ምርጫዎች እና አስተዳደር መንፈስ እና ዓላማዎች ጋር በሚጣጣም መልኩ ነው ሲሉ አትተዋል።

በሌላ መልኩ በሰሜን ምዕራብ ግንባር የሠራዊቱን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ ማብራሪያ የሰጡት የግንባሩ የሚዲያ ስራዎች አስተባባሪ ኮሎኔል አባተ ንጋቱ ሠራዊቱ በሕወሓት ጁንታ ቡድን ላይ እየወሰደ ባለው ሕግን የማስከበር እርምጃ በአጥፊ ቡድኑ ላይ ከባድ ሰብአዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ ማድረሱን ተናግረዋል፡፡ በዘመቻውም ሠራዊቱ የጠላትን ኃይል ደምስሶ ክላሽን ጨምሮ ከ10 ሺህ በላይ ነብስ ወከፍ እና ከ5 ሺህ በላይ የቡድን መሣሪያዎች በቁጥጥር ሥር አውሏል ብለዋል፡፡ ከዚያም ባለፈ ጀግናው ሠራዊት ይህ ቡድን ቀደም ሲል ከሠራዊቱ ዘርፏቸው የነበሩትን ታንኮች፣ መድፎች እና ሮኬቶችንም በቁጥጥር ሥር አውሏል ብለዋል፡፡ ሠራዊቱ ሀገር የጣለችበትን ግዳጅ በላቀ ቁመና እየፈጸመ ነው ያሉት ኮሎኔል አባተ የስግብግብ ጁንታው አባላት ለፍርድ እስኪቀርቡ ድረስ ሕግ የማስከበር እርምጃው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል፡፡

በዕለቱ ከተሰሙ ጉዳዮች መካከል አንዱ የኾነው ደግሞ በማይካድራ ንፁኃን በግፍ የተገደሉባቸው ቦታዎች መገኘት ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ባወጣው መረጃ በህወሓት በትንሹ 600 ሰዎች መግደሉን ይፋ አድርጓል፡፡ በየቦታው የተገደሉ ሰዎች ስለሚገኙ ቁጥሩ ከዚህ ሊያሻቅብ እንደሚችልም አመላክቷል፡፡ በማይካድራ ከተማ አብነትና ሴንትራል መውጫ በተባሉ ገጠራማ ቦታዎች 74 ንጹሃን የተቀበሩበት ሥፍራ ተገኝቷል፡፡ 56 ዜጎች በአንድ ጉድጓድ ተቀብረው ነው የተገኙት፡፡ የውሃ ጉድጓድ ውስጥም የሰለባዎቹ አስክሬን መኖሩም ተረጋግጧል፡፡ በህወሓት ልዩ ኃይልና ሳምሪ በተባለው ገዳይ ቡድን በግፍ የተገደሉ ንጹኃን ከሰው እይታ ለማራቅ ነበር ይህንን ያደረጉት ይላሉ የአይን እማኞች ለአብመድ በሰጡት ምስክርነት፡፡ ህወሐት ከጅምላው ግድያ በኋላ የዘር ማጥፋቱን ወንጀል ከአለምዓቀፉ ማኅበረሰብ ለመደበቅ የግድያው ሰለባ ንፁሃንን አስክሬን ከከተማዋ አርቆ መደበቁን ከጥቃቱ የተረፉ የከተማዋ ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡ ህወሐት ከጭፍጨፋው በተጨማሪም በከተማዋ የሚኖሩ አማራዎች በስጋት እንዲሸሹ የማድረግ ትልም እንደነበረውም ተገልጿል፡፡ በገዳይ ቡድኑ ህይወታቸው ያለፉ የንፁሃን ዜጎች አስክሬን በክብር እንዲያርፍ ተደርጓል፡፡

Page 22: ቅፅ 2 ቁጥር 110 ቅዳሜ ህዳር 19 ቀን 2013 ዓ.ም

2121ግዮን ቁጥር 110 ህዳር 2013 ዓ.ም

ነፃ ሃሳብ

መታሰቢያ መልዓከሕይወት

ትግራይ ውስጥ ያለው ትግራይ ውስጥ ያለው መሠረታዊ ችግር ምንድን ነው? መሠረታዊ ችግር ምንድን ነው?

አንድ አካባቢ ለብዙ ዓመታት የቆየና በተደጋጋሚ የሚከሰት ችግር ሲፈጠር ሁሌ ወታደራዊ አቅም በመጠቀም መፍትሔ ለማፈላለግ ከመሞከር

ይልቅ ጥልቅ የኾነ ሳይንሳዊ ጥናት በማድረግ ችግሩ ከመሠረቱ እንዲፈታ ለማድረግ መጣር በእጅጉ ተገቢ ነው፡፡ የዚህ ጽሁፍ አዘጋጅ ትግራይ ውስጥ ያለውን ችግር በሦስት ከፍሎ ያየዋል፡፡

አንደኛ፡- ትግራይ ተብሎ በአሁኑ ጊዜ የሚጠራው የአገራችን ክፍለ የረጅም ዘመን ሥልጣኔ ያለው አካባቢ ነው፡፡ ከሶስት ሺ አመታት በላይ ሥልጣኔ የተካሄደበት ቦታ በመኾኑ መሬቱ እጅግ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት ነው፡፡ ስለኾነም አካባቢው በአፈር ለምነት ስለተጎዳ የትግራይ ሕዝብ የምግብ ዋስትና ምንግዜም አሳሳቢ ችግር ነው፡፡ ህወሓት ሃያ ሰባት ዓመት ኢትዮጰያን ሲያስተዳድር በክልሉ ከሕዝቡ መሠረታዊ ችግር ጋር ምንም የማይገናኝ የፎቅ ግንባታዎች፣ በበቂ ሙያተኛ ያልተጠኑ ፋብሪካዎች እና ሌሎች የልማት ሥራዎች የተሠሩ ቢኾንም እነዚህ የልማት ሥራዎች የሕዝቡን ሕይወት በመለወጥ በኩል እዚህ ግባ የማይባሉ ናቸው፡፡ ሊኾን የሚገባው ግን በተለይ ለዘመናት የተጎዳውን መሬት እንዴት እንዲያገግም መሠራት አለበት የሚለው ላይ በሳይንስ የተደገፈ ጥናት ማካሔድና ወደ ተግባር መግባት ነበር፡፡

ሁለተኛ፡- የትግራይ ክልል መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ የትግራይ ሕዝብ ከሌሎች ሕዝቦች ጋር በንግድ፣ በሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት እንዲተሳሰር የሚመች በኾነ መልኩ አይደለም፡፡ በትግራይ ተወልዶ ያደገ ሰው ከትግርኛ ቋንቋ ውጭ ምንም ሳይሰማ ስለሚያድግ ዓለም ሁሉ ትግርኛ ተናጋሪ ልትመሥለው ትችላለች፡፡ ከምስራቅ በኩል ከአፋር ክልል ጋር የሚያዋስን እጅግ ከባድ ገደል በመኖሩ ነጋዴዎች እንደልባቸው ተንቀሳቅሰው የኖሩበት ሁኔታ የለም፡፡ በስተ ደቡብ በኩል ከአፋር ክልል እስከ ተከዜ ሸለቆ ድረስ የተዘረጋ ሰንሰለታማ ተራራ ያለ በመኾኑ የመልክዓ ምድር አቀማመጥ የትግራይ ሕዝብ ከአገው፣ ከራያና ከአማራ ሕዝቦች ጋር እንደልቡ እንዳይገናኝ እንቅፋት ሁኖ ቆይቶአል፡፡ በስተምዕራብ በኩልም ከባድ የተከዜና የመረብ ወንዝ ሸለቆ እና ወንዝ ያለ በመኾኑ ሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት አመቺ እንዳይኾን አድርጎታል፡፡ በስተሰሜን በኩል የኤርትራ ድንበር ያለ በመኾኑ ድንበሩ ለረጅም ጊዜ ሲዘጋ ሲከፈት ስለኖረ በዚህ በኩልም የሕዝብ ለሕዝ ግንኙነት አልጋ በአልጋ እንዳልነበር ግልጽ ነው፡፡ እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ተፈጥሮአዊ እና ሰው ሰራሽ እንቅፋቶች የትግራይን ሕዝብ ሁሌ በታጠረ አካባቢ እንዲኖር ምክንያት የነበሩ በመኾኑ ትግራይ ውስጥ ተወልዶ ያደገ ዜጋ ባሕሪው ለየት ያለና ከሌሎች ማሕበረሰቦች ጋር የመኖር ችሎታው የወረደ እንዲኾን አድርጎታል፡፡

ሶስተኛ፡- በትግራይ ባሕላዊ አኗኗር ውስጥ ትግሬዎች ልጆቻቸውን ሲያሳድጉ ሴቶቹ በጣም ተጨቁነው የሚያድጉ ሲኾን ወንዶቹ ልጆች ደግሞ እንደልባቸው ኹነው አንድም ቁጣ ወይም ተግሳጽ ሳይደርስባቸው ነው፡፡ ስለዚህ ወንዶቹ ልጆች ሲያድጉ ሁሉ ነገር እንደልጅነታቸው ስለሚመሥላቸው ድፍረት የተሞላበት በርካታ ተግባራት ይፈጽማሉ፡፡ በአንድ ወቅት የመለስ ዜናዊ እናት ተጠይቀው ሲመልሱ ስለ ልጃቸው እንዲህ ብለው ነበር “ልጄ መለስ በልጅነቱ ባገኘው ነገር ነበር የሚመታኝ ስሜቱን መቆጣጠር አይችልም ነበር” ብለው ነበር፡፡ ሌላው ጽንፍ የረገጠ፣ እጅግ ክርር ያለ አስተሳሰብ በትግራይ ክልል በዚህ መልኩ እንዴት ሊፈጠር ቻለ የሚለውን ጥያቄ ከላይ የተጠቀሱት ነጥቦች በተወሰነ መልኩ መልስ የሚሰጡ ቢኾንም ሌሎችም በርካታ ምርምሮች የግድ መካሄድ ይኖርባቸዋል፡፡

የዚህ ጽሑፍ አዘጋጅ ቱሪስቶችን በማስተናገድ ለረጅም ጊዜ የሠራሁ በመኾኑ ሁሉንም ሊባል በሚቻል ሁኔታ የትግራይ ግዛቶችን የማየት ዕድል አጋጥሞኛል፡፡ ለምሳሌ ሐውዜን የምትባለው ከተማ በመሐል ትግራይ የምትገኝ እጅግ ትንሽ ከተማ ስትኾን እኔ ባየኋት ጊዜ ትንሽ ከመኾንዋ የተነሳ የባጃጅ አገልግሎት እንኳን አልነበራትም፡፡ ነገር ግን በሳምንት ኹለቴ ነጋዴዎች ከመላው ትግራይ እየመጡ ይገበያዩባታል፡፡ በዚህ ገበያ ውስጥ በተደጋጋሚ ለመዘዋወር እድሉ ነበረኝ፡፡ በጉብኝቴ ወቅት ከተገነዘብኩት ነገር አንዱ ከትግርኛ ቋንቋ ውጭ ሌላ አንድም ቋንቋ ለማዳመጥ አልቻልኩም፡፡ ይህ የሚያሳየው በገበያ ቦታ እንኳን የብሔር ሥብጥር አለመኖሩን ነው፡፡ የህወሓት አባላት ለ27 ዓመታት አዲስ አበባ ቆይተው ቁሞ ቀር መኾናቸው ሌላም ሰፊ ጥናት የሚፈልግ ነገር ነው፡፡ በተጨማሪም እነሱ የሚያራምዱት አስተሳሰብ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይኾን በመላው ዓለም ተቀባይነት ያጣ ነው፡፡ ህወሓቶች የዛሬ 45 ዓመት የጀመሩትን አስተሳሰብ አሁንም ችክ ብለው መንገታገታች በጣም የሚያስገርም ነው፡፡

ይህ ጽሁፍ ሕወሓት በእብሪት በከፈተው ጦርነት ምክንያት የፌደራል መንግሥትና የክልሉ ልዩ ኃይል ጦርነት ላይ በነበሩበት ወቅት በመኾኑ በዚህ ጽሁፍ ይህ አስከፊ ጦርነት ማስቀረት ይቻል ነበር ወይ? በፌደራል መንግሥት በኩልስ ያልተከናወኑ ሥራዎች ነበሩ ወይ የሚሉ ጥያቄዎችና ሌሎችም ጉዳዮች ይዳሰሳሉ፡፡

በመጀመሪያ መነሳት ያለበት ጥያቄ የህወሓት ደጋፊ የኾኑ የትግራይ ተወላጆች ዶ/ር ዐቢይ ሥልጣን ላይ በቆዩበት ከኹለት ዓመት ተኩል በላይ እንዴት ወሳኝ ሥልጣን ላይ ሊቆዩ ቻሉ? የሚለው ሲኾን

ኹለተኛ ደግሞ አሁንም የህወሓት ደጋፊ የኾኑ የትግራይ ተወላጆች እንዴት ሰሜን ዕዝ ውስጥ ሊመደቡ ቻሉ? የሚለው ነው፡፡ ምክንያቱም እነዚህ የሠራዊት አባላት ከትግራይ ልዩ ኃይል ጋር ተባብረው ወንጀል ሊፈጽሙ እንደሚችሉ እንኳን ወታደራዊ ሳይንስ የተማሩ ጀነራሎች ይቅርና ማንም ተራ ሰው ሊገምተው የሚችለው ስለኾነ ነው፡፡ እነዚህ ወታደሮች መመደብ የነበረባቸው ደቡብ፣ ምዕራብ፣ ምስራቅ ዕዝ ውስጥ ነበር፡፡

ሌላው ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ለማሳሰብ እንደሞከርኩት የህወሓት እኩይ ተግባር ለማስፈፀም ሥራ ላይ የሚውለውን ገንዘብ እንደ ኤፈርት ያሉ ተቋማት ኹለት ዓመት ተኩል ያለ ማንም ከልካይ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ እየተዘረፈ የሕወሓትን ካዝና ሲያጣብብ መቆየቱ ሁላችንም የዶ/ር ዐቢይን መንግሥት ልንጠይቅ የሚገባ ነው፡፡ በእኔ ዕምነት ዶ/ር ዐቢይ የህወሓትን የገንዘብ ምንጭ ለማድረቅ ተግተው ሠርተው ቢኾን ኖሮ አሁን እየተካሄደ ያለው ጦርነት ባልታሰበ ነበር፡፡ ምክንያቱም እስከ አሁን እየሞትን ያለነው በጥይት ሳይኾን በህወሓት ገንዘብ ነው፡፡ ህወሓቶች ሌላው የግድ ሊያውቁት የሚገባ ነገር ለአርባ አምስት ዓመት የታገሉለት ትግራይን ወደ መንግሥትነት የመለወጥ ቅዠት በምንም መልኩ ሊሳካ እንዳማይችል ነው፡፡ ለዚህም አምስት ምክንያቶች መጥቀስ ይቻላል፡፡

አንደኛ፡- ትግራይ ቋሚ የኾነ የውሃ እጥረት ያለባት ክልል ነች፡፡ ውሃ ደግሞ እንደሚታወቀው ከሩቅ ቦታ መጓጓዝ የማይቻል፤ ነገር ግን ለሰው ልጆች ከኦክስጅን ቀጥሎ በእጅጉ የሚያስፈልግ ነው፡፡ ስለዚህ ይህንን ግብዓት ከሩቅ ቦታ ማጎጎዝ ከቶውንም የማይታሰብ ነው፡፡

ኹለተኛ፡- በክልሉ የምግብ ዋስትና ፈታኝ መኾኑ

የትግራይ መሬት ለዘመናት ታጥቦ ያለቀ ስለኾነ የትግራይ ሕዝብን የምግብ ፍጆታ በበቂ ሁኔታ ማቅረብ ምንግዜም ፈታኝ ተግባር ነው፡፡

ሦስተኛ፡- የውጭ ምንዛሬ የሚያስገኙ ሸቀጦች በበቂ ሁኔታ አለመኖር የሚጠቀስ ሲኾን እንደሚታወቀው የትግራይ ክልል በወርቅ፣ በእምነበረድ፣ በብረት ማዕድን ከፍተኛ ሐብት እንዳለ አንዳንድ ጥናቶች ያመላክታሉ፡፡ ነገር ግን ማዕድናትን የሚገዙት የበለፀጉ አገሮች በመኾናቸውና እሴት ያልተጨመረባቸው በመኾኑ የመዓድን ገቢን ተማምኖ አገር መመስረት በዕጅጉ አስቸጋሪ ነው፡፡ በመኾኑም የትግራይ ክልል መንግሥት ቢመሠርት እንደ መንግሥት የመቀጠሉ ዕድል በእጅጉ ጠባብ ነው፡፡

አራተኛ፡- የትግራይ ክልል የተራራ ሐብት የሌለው ክልል ነው፡፡ ኢትዮጵያ ውስጠ ቁመታቸው ከ3900 እስከ 4500 ሜትር ከፍታ ያላቸው ተራሮች ወደ ሃያ አምስት የሚጠጉ ያሉ ሲኾን ሃያ ኹለቱ በአማራ ክልል ይገኛሉ፡፡ የቀሩት ደግሞ በኦሮሚያና በደቡብ ክልል የሚገኙ ናቸው፡፡ ትግራይ ክልል ውስጥ አንድም ዝናብ አምጪ ተራራ የለም፡፡ በትግራይ ክልል ያለው ከፍተኛ ቦታ ከፍታ እስከ 2600 ሜትር የሚደርስ ነው፡፡

አምስተኛ፡- ትግራይ ብትገነጠል የራስዋ የኾነ ኤሌክትሪክ ከንፁህ ታዳሽ ኃይል ማመንጨት ስለማትችል የዜጎች ሕይወት እጅግ አስቸጋሪ ይኾናል፡፡ ኢንቨስትመንት የመሳብ እድልም አይኖራትም፡፡

በመኾኑም ማንኛውም የትግራይ ተወላጅ ትግራይን መገንጠል በምንም መልኩ መተግበር እንደሌለበት ተገንዝቦ አጀንዳውን ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ማስወገድ ይኖርበታል፡፡ ቋንቋን በተመለከተ ህወሓቶች ሥልጣን እንደያዙ ትግርኛ ቋንቋን የሥራ ቋንቋ ለማድረግ ሙከራ አድርገው ነበር፡፡ ነገር ግን እንደማያዋጣቸው ስለገባቸው በቀጥታ አማርኛ መማር ነው የጀመሩት፡፡ በተጨማሪ አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ ኢትዮጵያ ውስጥ እርስ በእርሳችን ለመግባባት ከአማርኛ ቋንቋ ሌላ ምንም አማራጭ የለንም፡፡

ህወሓት ከተወገደ በኋላ ትግራይን እንዲያስተዳድሩ የሚመደቡ ግለሰቦች አሁንም የብልጽግና ፓርቲን ፍላጎት ለማስፈፀም ተብሎ የሚሾሙ ሳይኾኑ የግድ በክልሉ ሥር ነቀል ለውጥ ሊያመጡ የሚችሉ፣ ከዘረኝነት የፀዱ፣ ለሚይዙት ሥልጣን የሚመጥን በቂ የትምህርት ዝግጅት ያላቸው መኾን ይገባቸዋል፡፡ የትግራይ ሕዝብ በየወረዳውና ዞኑ የራሱን ወኪሎች መምረጥ አለበት፡፡ በቅርቡ ያሳተምኩት “አቃፊ ማንነት” በሚል ርዕስ በተጻፈ መጽሐፍ ላይ አብዲ ኢሌ በሠራው አስፈሪና አሰቃቂ ወንጀል ምክንያት ከሥልጣን ተወግዶ ያደረገ ለውጥ ማየት እንደተቻለና ለምን ዶ/ር ዐቢይ ይህንን ተግባር በሁሉም ክልሎች ለመድገም አቅም አጡ የሚለውን ጉዳይ ደጋግሜ ትኩረት እንዲሰጠው ሙከራ አድርጌአለሁ፡፡ ዶ/ር ዐቢይ በተደጋጋሚ ከነገሩ ነገር አንዱ በመከላከያ ሠራዊት ላይ ከፍተኛ የሚባል REFORM ማድረጋቸውን ነው፡፡ ነገር ግን የተካሄደው ሪፎርም ሠራዊቱ እራሱን እንኳን ለአደጋ የጣለ ሁኔታ መከሰቱ ትራጄዲ ነው፡፡ የተሠራው የሪፎርም ሥራ ምንም አጥጋቢ እንዳልኾነ አመላካች ነው፡፡ ይህንንም የኢትዮጵያ ሕዝብ ተወካዬች ምክር ቤት ጉዳይን ገምግሞ ትክክለኛ የዕርምት እርምጃ እንደሚወስድ ዕምነቴ ነው፡፡

ሌላው በጣም የገረመኝ ነገር ከትግራይ ክልል ውጭ ያሉ የትግራይ ተወላጆች ከኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ጎን መኾናቸውን የሚያሳይ ሰልፍ አለመውጣታቸው ነው፡

Page 23: ቅፅ 2 ቁጥር 110 ቅዳሜ ህዳር 19 ቀን 2013 ዓ.ም

2222ግዮን ቁጥር 110 ህዳር 2013 ዓ.ም

በቀለ ቆልቻ (ከወላይታ ሶዶ)

፡ በአንድ አገር ያሉ ሕዝቦች ከመንደራቸው ውጭ ማሰብ አለመቻል ከኋላ ቀርነትና ካለመሠልጠን የሚመጣ ችግር ነው፡፡ ኢትዮጵያ በድሕነት እስከኖረች ድረስ ይህ ሁኔታ ይቀጥላል፡፡ ትክክለኛ የኢኮኖሚ ዕድገት ሲመዘገብ፣ ሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ሲጠናከር፣ ነጋዴዋ ሩቅ ቦታ ሂደው መነገድ ሲጀምሩ የመንደር ቋንቋዎች እየጠፉ በሁሉም ነገር ማለትም በአለባበስ፣ በአኗኗር፣ በቋንቋ እና በሌሎችም በርካታ ነገሮች እየተመሳሰልን እንደሄዳለን፡፡ ያኔ ነው ትክክለኛው ኢትዮጵያዊነት የሚፈጠረው፡፡ “Nation building process” ወይም መንግሥትና የአንድ አገር ዜጎችን የመፍጠር ሂደት የረጅም ጊዜ እልሕ አስጨራሽ ሂደት ነው፡፡ ይህ በተሳካ ሁኔታ ሊካሄድ የሚችለው አመፀኞችን በወታደራዊ ኃይል ዝም በማሰኘት ሳይኾን ሁሉንም ዜጎች የአገሪቱን ሐብት ፍትሐዊ በኾነ መንገድ የኢኮኖሚ ተጠቃሚ ማድረግ ሲቻል ነው፡፡ በመኾኑም ሕገ መንግሥቱን አርመን ሁሉንም ዓይነት የመንግሥታዊ ሥርዓት ዜጎንች አሳታፊ በኾነ መልኩ አገራችንን ማልማት ስንችል ነው፡፡

በዶ/ር ዐቢይ ኹለት ዓመት ተኩል የሥልጣን ዘመን ማየት የቻልነው ነገር ቢኖር ከአንዱ አሰቃቂ ዜና ወደ ሌላ አሰቃቂ ዜና በመሸጋገር ነው፡፡ በዚህ ምክንያት ብዙ ሰዎች ዶ/ር ዐቢይን “እግረ ደረቅ” እያሉ ሲጠሩዋቸው ሰምቻለሁ፡፡ ሌላው በዶ/ር ዐቢይ ላይ ግልጽ የኾነ ባሕርይ ችግር ሳይፈጠር እርምጃ የመውሰድ ምንም ዓይነት ችሎታ የላቸውም፡፡ ዶክተር ብዙ ከማደመጥ ብዙ ማውራት ይወዳሉ ቻይናዎች አንድ ተረት አላቸው “የሰው ልጅ ኹለት ጆሮ ኹለት ዓይን አንድ አፍ ነው ያለው በመሆኑ ብዙ ከመናገር ብዙ መሥማትና ብዙ ማየት ይጠበቅበታል” ይላሉ፡፡ ይህ አባባል ትልቅ ትምህርት ሰጪ አባባል ነው፡፡

ህወሓት የፈፀመው የአገር ክህደት ወንጀል ከዚህ ቀደም በአማራ ክልል አመራሮች ግድያ ወቅት የሠራዊቱን አመራሮች በመግደል መከላከያን ለማፍረስ ተሞክሮ ነበር፡፡ ከዚያ ክስተት በመማር በርካታ የዕርምት ሥራዎች መሥራት ያስፈልግ ነበር፡፡ ዶ/ር ዐቢይ በጦርነት መሐል የጦር ኃይል ጠቅላይ አዛዝ ሹምሽር ማድረግ በምንም መልኩ ተቀባይነት ያለው ተግባር አይደለም መከላከያ ፈረሰ ማለት እንኳን እንደ ግብጽ ጡንቻቸውን ያፈረጠሙ አገሮች ይቅርና አልሸባብ እንኳን በቀላሉ አገራችንን ሊወር ይችላል፡፡

በጣም ደስ የሚለው ዜና ግን ከሠራዊቱ ተባረው ያለጡረታ፤ ያለ ሕክምና አገልግሎት ሲሰቃይ የነበሩ የቀድሞ የሠራዊቱ አባላት በከፍተኛ ቁጥር ለመዋጋት ዝግጁ መኾናቸውን መግለጻቸው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ቢፈርስም የኢትዮጵያ ሕዝብ አገሩን ለመጠበቅ ዝግጁ መኾኑን ያሳያል፡፡ ሌላው ሰሞኑን ያስገረመኝ ዜና በአገር ክህደት ሥራ ላይ የተሰማሩ ጀነራሎች አህያ እንደሰረቀ ሌባ መደበኛ ፍርድ ቤት መቅረባቸው ነው፡፡ እነዚህ ጀነራሎች በአስቸኳይ የጦር ፍርድ ቤት ተቋቁሞ በአጭር የፍርድ ሂደት የመጨረሻው ቅጣት ማግኘት አለባቸው፡፡

“አቃፊ ማንነት” በሚለው መጽሐፍ ላይ ስለ ህወሓት እንዲህ ብዬ ነበር “ሕወሓት በጣም ዕድለኛ ድርጅት ነው፡፡ ወደ ሥልጣን ሲመጣ ደርግ የኢትዮጵያን ሕዝብ ንብረት ወርሶ አስረክቦታል፡፡ ከሀብቱም በተጨማሪ የኢትዮጵያን ሕዝብ ለመብቱ የማይቆረቆር የተኮላሸ ትውልድ አድርጎ ቆይቶታ፡፡ ህወሓት ከስልጣን ሲወርድ ደግሞ ዶ/ር ዐቢይ እጅግ ዘግናኝ ወንጀል የፈፀሙ የህወሓት ባለስልጣናትን በዝምታ በማለፋቸው አሁን የህወሓት ሰዎች መቀሌ ቁጭ ብለው የዘረፉትን እያጣጣሙ ይበላሉ” ብዬ ነበር በገጽ 242 ላይ

አሁን የኾነው ግን የዘረፉትን እያጣጣሙ መኖር ሰልችቶአቸው በድጋሚ በሕገ ወጥ መንገድ ወደ ሥልጣን ለመምጣት አረመኔአዊ ተግባር መፈጸም ነው፡፡ ይባስ ተብሎ እነዚህ ወንጀለኞች ወደ ብልጽግና ፓርቲ እንዲገቡ ተደጋጋሚ ጥያቄ ቀርቦላቸው ነበር፡፡

ሲጠቃለል፡- የዚህ ጽሁፍ አዘጋጅ ማንኛውንም ችግር በዘላቂነት ለመቅረፍ ጥልቅ የኾነ ሳይንሳዊ ጥናት በማድረግ ትክክለኛውን መፍትሔ ለማፈላለግ ጥረት መደረግ አለበት ብሎ ያምናል፡፡ በመኾኑም የግሌን ምልከታ አቅርቤያለሁ፡፡ ጉዳይ የሚያሳስባችሁ ሌሎች ዜጎች ያላችሁን ጥናት ብትጨምሩበት እና በትግራይ ክልል ያለማቋረጥ፣ በተደጋጋሚ የሚከሰተውን ጦርነት የኢትዮጵያዊነት መሸርሸር ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስወገድ የበኩላችሁን እንድትሰሩ ከልብ አሳስባለሁ፡፡ ወታደራዊ እርምጃ ብቻ መፍትሔ አይኾንም፡፡

ዕይታ

በአገርና ሕዝብ ጥቃት ዙሪያ ማንኛዉም ዜጋ መደራደር፣ መጨቃጨቅ፣ ማኩረፍ፣ እገሌ ያመጣዉ ጣጣ በማለት ኃላፊነትን ለብቻው የምናሸክመዉ አካል ሊኖር አይችልም፡፡ ምክንያቱም የተፈጠረው ችግር በማንም ይሁን በማን ታቅዶና ታስቦ

የተፈጠረ ሰዉ ሰራሽ አደጋ በመሆኑ ለመደራደር ጊዜ ሊኖረንም አይችልም፡፡ በመሆኑም ይህንን ትልቅ አገራዊ አጀንዳ እያንዳንዱ ዜጋ የእኔ ችግር በሚል ስሜት ተነሳስቶ በጋራ ካልመከትነዉ ፉክክሩ ለአዉሬ አሳልፎ ይሰጠናል፡፡ ወደድንም ጠላን፣ አመንን አላመን ችግር ፈጣሪዎች ማንም ይሁኑ ማን ድክመትም ይኑር ክፍተት ለመወቃቀስ ለመነጋገር ጊዜዉ አሁን አይደለም፡፡ በአንድ አከባቢ የእሳት አደጋ ቢነሣ ቅድሚያ መሠራት ያለበት የእሳት ማጥፋት ዘመቻ እንጂ የቃጠሎ መነሻ ምክንያቱ የሚጣራው እሳቱ ከጠፋ በኋላ መሆኑን ሁላችንም ጠንቅቀን እናዉቃለን፡፡ ለዚህ ነው በአገራችን ለተጋረጠብን አደጋ በጋራ ተረባርበን መስመር ካስያዝን በኋላ ወይም አገር የማዳን ሥራ ከሠራን በኋላ ሌላዉን በቀጣይ ማየት አለብን የምለው፡፡ አሁንም ሕዝብ በንቃት መነሳት ያለበት ቅድሚያ ማግኘት ለሚገባዉ ቅድሚያ የመስጠት ሥራ ለመሥራት መኾን ይጠበቅበታል፡፡

ከዚህ ጋር አያይዘን መገንዘብ ያለብን ጉዳይ ቢኖር በሰሜኑ ኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ላይ የደረሰዉ ጥቃትና ጉዳት የአገር ጉዳት የኢትዮጵያ ሕዝብ ሕልውና የደፈረ የአገር አጥር ያፈረሰ ከድፍረትም በላይ ድፍረት መሆኑ እንደ ዜጋ ሁላችንንም ሊቆጨን ይገባል፡፡

ይህ ጉዳይ የህወሓት አመራር ከጫካ ወደ አገር ቤት ሲገባ አብሮ የገባ ለ30 ዓመታት የኢትዮጵያ ሕዝብ ሲያደማና ሲያቆስል የቆየበት እና የሕዝብና አገር ክህደት ዛሬ የተጀመረ አዲስ ነገር አለመሆኑን ልንረዳ ይገባል፡፡ ቀድሞም ቢሆን ከዝንብ ማር አይጠበቅምና ከኢህአዴግ (ሕወሐት) መልካም ነገር መጠበቅ ስህተት መሆኑን ጠንቅቀን እናዉቃለን፡፡ በሕዝብ ጫንቃ ላይ የቆየ ነውና፡፡

ይሁን እንጂ የአብዛኛዎቻችን አስተሳሰብ አመለካከት ኃላፊነቱን መወጣት ያለባቸዉ መንግሥትና መከላከያ ሠራዊቱ ላይ ብቻ ማሸከም ከሆነ አጉል ፉክክር ስለሚሆን ይህ አካሄድ ደግሞ ክፍተት ፈጥሮ አንድነታችንን እንዳይጎዳ በጥንቃቄ ከሃዲውን ቡድን በጋራ መመከት ይኖርብናል፡፡ አብዛኛዉ ሰው ችግሩን ያመጣዉ ሥርዓቱ ነው ለተፈጠረው ጉዳት ተጠያቂው ሥርዓቱን የሚመራው አካል ይወጣበት የሚል ወገንም አይታጣም፡፡ ይህንን አስተሳሰብና አመለካከት ወደ ጎን ትተን በቅድሚያ እየተቀጣጠለ ያለውን እሳት እናጥፋ፡፡ ሌላዉ የዉስጥ ችግር እንደመሆኑ መጠን በቀጣይ የኢትዮጵያ ሕዝብ ራሱ የሚፈታዉ ይሆናል፡፡ ያጠፋዉም ያለማዉም ወደፊት ይለያል፡፡ ቅድሚያ መሠራት ያለበት የእናት ጡት ነካሾችንና ከሐዲ ቡድኑን ከኢትዮጵያ ምድር ማጥፋት ነው፡፡ ይህ ስሜት ነው አገርንና ሕዝብን ሊታደግ የሚችለው፡፡

መዘዙና ጣጣዉ ለዓመታት የታቀደና የታለመ አገርንና ሕዝብን ለመበታተንና ለመቆራረጥ ታስቦ በሥልጣን ዙሪያ የሚቆይ በተግባር ላይ የሌለ ባዶ ፕሮፖጋንዳ በሕዝብ አናት ላይ እያዘነቡ ለዘመናት ሕዝብን ሲያዘናጉ ቆይተው አሁን ለሕዝብ ልጆች የጦርነት ቤት ሥራ እያስረከቡ ይገኛሉ፡፡ ይሁን እንጂ የኢትዮጲያ ሕዝብ የዚህ ዓይነት ፈተና አዲሱና ብርቁ አይደለም፡፡ የረዥም ጊዜ ልምድና ብቃትም አለውና አኩርፎ እኔ ምን ችገረኝ የሚል አእምሮና አቋም አይኖረዉም፡፡ ፈተናዉን መሻገር ይችልበታልና፡፡ ከፈተናው በኋላ ግን በእነዚህ ንግግርን እንጂ ተግባርን ከማያውቁ በሥልጣን ጥመኞች ሥርዓት እየተደለለ ዕድሜዉን አይጨርስም፡፡ ሥልጣን ፍላጎት ላይ ብቻ ሣይሆን ዕዉቀትና ልምድ ተሰጥኦ ብልሃት ካልታከለበት አሸዋ ላይ የቆመ ሕንፃ ዓይነት እንጂ ጥንካሬ አይኖረዉም፡፡

አሁን ያለንበትም የበሬዉን ተረት ካስታወሳችሁ በሬ ሆይ በሬ ሆይ ሣሩን ብቻ አይተህ ገደሉን ሳታይ ዓይነት ሆኗል፡፡

ከ1983 ዓ.ም ለዉጥ ሥርዓት ጀምሮ ሥልጣንን የሕዝብ አገልጋይነት ሣይሆን ለተወሰኑ ቡድኖች የጥቅም ምንጭ እና መበልፀጊያ አድርጎ የግል ሕይወታቸዉ ተገንብቷል፡፡ መጨረሻ ላይ ሥልጣን የጥቅም ምንጭ የሀብት ማመንጫ መሆኑ በአብዛኛዉ ዘንድ ስለታመነ ሕዝብን ከሕዝብ ጋር በማጋጨት አገርን በማፈረካከስ በመጨረሻ ላይ አሁን ለምንገኝበት ቀዉስ ዳረጉን፡፡

ቀድሞም ሌባ ሲሰርቅ አይጣላም ሀብት ሲከፋፈል ነው ጸቡ የሚነሣው፡፡ ስለዚህ ሕዝብ ሆይ አሁን ያለንበትን የጋራ ችግር ወይም በአገርና ሕዝብ ሕልውና ላይ የሚያንዣብበዉን አደጋ በጋራ ተከላክለን ለቀጣይ ይህንን ባዶ ጡት በሚያጠባው አታላይ ሥርዓት ላይ ተገቢውን ሥራ ለመሥራት ልብ ያለው ልብ ይበል፡፡ ተጠያቂዉን መጨረሻ ላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ ይለየዋል፡፡

የኢትዮጵያ አምላክ ይርዳን!

ተጠያቂዉተጠያቂዉ ማን ይኾን?ማን ይኾን?

ዕይታ

Page 24: ቅፅ 2 ቁጥር 110 ቅዳሜ ህዳር 19 ቀን 2013 ዓ.ም

2323ግዮን ቁጥር 110 ህዳር 2013 ዓ.ም

ከ1550 ጀምሮ እስከ ትላንቱ የጥቅምት ወር መጨረሻ 2013 ዓ.ም ጡት ነካሹን እና ‹‹የታሪክ አተላውን›› /ይህችን ቃል ሊቀመንበር መንግሥቱ

ኃይለማርያም ነበሩ የሚጠቀሟት/ ቡድን ለማስወገድ ሲባል ርምጃ ለመውሰድ መንግሥታዊ ውሳኔ እስከተላለፈበት ቀን ድረስ በሰሜን፣ በሰሜን ምሥራቅና በተለይም በሰሜናዊ ምዕራብ ኢትዮጵያ መሬት ቁጥር ሥፍር የሌላቸው ውጊያዎች ተካሂደዋል፡፡

ከኢጣሊያ ወራሪ ሠራዊትና ለዚያ ሠራዊት መንገድ ከሚመሩና በምንዳ ካደሩ ከሃዲዎች ጋር፡፡ ከዓድዋ ዘመቻ በፊትና በዘመቻው ጊዜ፤ በማይጨው ጦርነት ዋዜማ፣ በአምስቱ ዓመታት የዓርበኝነት ወቅቶችና ከዚያም በኋላ ዛሬ ‹‹ምዕራባዊ ትግራይ ዞን›› በሚባለው ሥፍራና አዋሳኝ የጎንደር ሁለት አውራጃዎች ሥር በሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች፤ ብሎም በራያ-አዘቦና በሰሜን ወሎ ራያ ቆቦ፣ በዋግ ላስታ አውራጃዎች ሥር በሚገኙ በርካታ ሥፍራዎች፤ የእናት ኢትዮጵያ ልጆች ርስ በርሳቸው፣ ከቅጥረኛ ወንበዴዎችና ከውጭ ወራሪዎች ጋር አያሌ ፍልሚያዎችን አካሂደዋል፡፡

ወደ ፊት ራቅ ብለን ከእነ ራስ አሉላ አባነጋ፣ ከአፄ ዮሐንስ ተጋድሎ አሃዱ ብለን… ቀረብ ወዳለው በመመለስ፤ የእነ ራስ ዕምሩ ኃይለሥላሴን ዘመቻዎች፣ የእነ ራስ አሞራው ውብነህንና በእነሱ ሥር የነበሩ ዓርበኞችን ተጋድሎዎች፣ የእነ ራስ ኃይሉ ከበደን ታላቅ ኢትዮጵያዊ ዓርበኝነትና መስዋዕትነት፣ የእነ ቢትወደድ አዳነንና የወልቃይት ጠገዴ ወረዳ ኢትዮጵያውያን ጀግኖችን ውጣ-ውረድና ወደ ትውልዳቸው በመንፈስ የተዛመ አይበገሬ የጀግንነት ተግባር ስናስብ፤ የትም ሆነን በዓይናችን የሚመላለሰው ከፍ ሲል የተጠቀሱት የደም መሬቶች በተለይም የሰሜንና የሰሜናዊ ምዕራብ ኢትዮጵያ አውራጃ፣ ወረዳዎችና ቀበሌዎች ናቸው፡፡

እጅግ ከረዥሙ በጣም ጥቂት በአጭሩ፤ ከፍ ሲል በተገለጹት የሃገራችን ሰሜናዊ፣ ሰሜናዊ ምሥራቅና ምዕራብ አካባቢዎች፤ በኢትዮጵያውያን መሳፍንቶችና መኳንንቶች መካከል ለሥልጣን የበላይነትና ለርስት ጉልት ማስፋፊያ ሲባል አያሌዎች ደማቸውን አፍሰዋል፡፡ በአንደኛውና በሌላኛው ‹‹ልንገሥ፣ የበላይ ልሁን›› ባይ መስፍንና መኳንንት ደጋፊነት ስም ወደ ሃገራችን ጎራ ያሉ ባዕዳንም፤ በኢትዮጵያውያኑ መካከል ለነበረው ግጭትና ውጊያ መባባስ የበኩላቸውን ሚና ተጫውተዋል፡፡ የየአውራጃውና የየጎጡ ጦር አምላኪ መሳፍንቶች ርስ በርሳቸው ሠይፍ ሲማዘዙና ጡንቻ ሲጠማዘዙ ቆይተው በተዳከሙ ጊዜም፤ በዘመኑ ኃያል የነበሩት ቱርኮች ጠባቂ ያልነበረውን የሃገራችንን ባሕረ-ገብ መሬት ወረው ይዘዋል፡፡

ከቱርኮችም በኋላ ተገዳዳሪዎቻቸው የነበሩት ፖርቹጋሎች ‹‹ኃይማኖታዊ አጋርነትን ሽፋን በማድረግ›› በኢትዮጵያ የእጅ አዙርም ይሁን የቀጥተኛ ቅኝ ገዥነቷን መረብ ለመጣል ሙከራ አድርጋለች፡፡ የቱርክና የፖርቹጋል ሃገራችንን

በየምክንያቱ ይዘው ለመቆየት አድርገውት የነበረው ሙከራ ሳይሳካ ሲቀር፤ የእነሱን እግር ተከትላ ሠራዊት በኢትዮጵያ ላይ ያዘመተችው ግብፅ ነበረች፡፡ የእሷም ቀዳማይ ቀቢፀ-ተስፋ ወይም ሊሳካ ያልቻለ ዓላማ፤ አንድም በእነ አፄ ቴዎድሮስና አፄ ዮሐንስ ባደረጉት ወሰን-የለሽ የኢትዮጵያን ጠላቶች የመመከት ጥረት የተኮላሸ ሲሆን በሌላ በኩል እስከ ዛሬ ድረስ አልሰክን ያለው ፍላጎቷ ዓይነተኛ መለያ የሆነው ‹‹የዓባይን ወንዝ እስከ ምንጩ በቁጥጥሯ ሥራ የማዋል›› ነበር፡፡

ከግብፅ ኢትዮጵያን የመውረር ድርጊት በስተኋላ በ19ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ የቀጠለው፤ የአውሮፓ ኃያላን ሃገሮች ኢትዮጵያን የመቀራመት ሤራና በተግባርም ቅኝ ለመግዛት ብሎም የራሳቸው ርስት የማድረግ ሙከራ ነው፡፡ በዚህ በኩል ዓይነተኛዎቹ የሃገራችን አጥቂ ሃገሮች እንግሊዝና ኢጣሊያ መሆናቸውንም ታሪክ ይመሰክራል፡፡ በተለይ ታላቂቱ ብሪታኒያ በራሷ አቅም ሊሆንላት ያልቻለውንና በግብፅ ተይዞ የቆየውን የኢትዮጵያን መሬት፤ በግብፅና በሱዳን በነበረው የቅኝ ገዥ አስተዳደሯ ሥር ለመጠቅለል ያደረገችው ሙከራ ሳይሳካለት በመቅረቱ፤ ለሸሪኳ ኢጣሊያ በ1885 ዓ.ም አሳልፋ መስጠቷ ወዘተ / የፀረ-ሕዝቦች እንቅስቃ በሰሜን ሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ፤መስከረም 1977 ዓ.ም ቅጽ ፩ /የሃገርና ሕዘብ ደኅንነት ጥበቃ ሚኒስቴር ተቋም ጥናታዊ ሰነድ./ ታሪክ ምስክርነቱን ሰጥቶ ያለፈበት ጉዳይ ብቻ ሳይሆን ያኔ በሰሜን ኢትዮጵያ ምድር የተቀበረው መርዝ ወይም ልዩነትን ፈጣሪ የፖለቲካ ፈንጂ፤በቅብብሎሽ ለዛሬዎቹ የእናት ጡት ነካሾች የደረሰ መሆኑን በግልጽ አመልካች ነው፡፡

ሕወሓት የውንብድና ተግባሩን -ሀ- ብሎ በጀመረ ሰሞን በብሔር ትግል ዙሪያ ጠመንጃ እስከማንሳት ድረስ ለመሄድ ‹‹ተገደድኩ›› ያለበትን ምክንያት በርካታ የመንደርተኛ፣ የአኩራፊና ከአስተዳደጋቸው ጉድለት ያለባቸው ጎረምሶች በየሰፈሩ የሚያመነጩትን ጮርቃ ቃላት እየደረደረ…. ‹‹ፖለቲካው ትንተና›› ያለውን የጥላቻ ዘር መዝራቱን ሥራዬ ብሎ ይዞታል፡፡ ለምሣሌ ያህል ከወያኔዎች ቀደምት የበረሃ መራር፣ ጥንስሱ የተንኮልና የተንኮል ብቅልና ጌሾ ብቻ የነበረ አስተምሮ አንዱ፡- የትግራይ ሰው ‹‹…በዐማራ ገዥዎች ዘንድ እንደጠላትና እንደ ሁለተኛ ዜጋ ስለሚታይ ይጠረጠራል፡፡ አይታመንም፡፡ በዚህም የትግራይ ሕዝብ ጠባብ የሆነ የዐማራ ጥላቻ አለው፡፡ ስለዚህ ጭቁኑ የትግራይ ሕዝብና ጭቁኑ የዐማራ ሕዝብ በአንድ ላይ ተሰልፈው በአሁኑ ወቅት መደባዊ ትግል ሊያካሂዱ አይችሉም፡፡ ምክንያቱም በመካከላቸው ጠባብነት ሰፍኖ ስለሚገኝ ነው፡፡ በመሆኑም በኢትዮጵያ ውስጥ የመደብ ትግል ከማደረግ በፊት ለብሔረሰቦች ዕኩልነት መታገል አማራጭ የሌለው የትግል ስልት ነው›› የሚለው ተጠቃሽ ነው፡፡

ከማለዳው ‹‹ለብሔረሰቦች መብትና ዕኩልነት እታገላለሁ›› የሚል ዓላማ እንደሚያራምድ ፍንጭ ሰጥቶ የነበረው ሕወሓት፤ በ1968 ዓ.ም ደግሞ ቀዳሚ የስብከት አጀንዳውን

በመለወጥ ‹‹ወታደራዊው መንግሥት በሥልጣን እስካለና የኢትዮጵያን ሕዝብ አስተባብሮ በአንድ ‹ዴሞክራቲክ የኅብረት ግንባር› የሚያታግል መሪ የፖለቲካ ድርጅት እስከሌለ ድረስ ‹ትግራይን ከኢትዮጵያ በመገንጠል ነፃ መንግሥት ለመመሥረት እታገላለሁ›…›› የሚለውን የገንጣይነት ዓላማውን እንደሚያራምድ ግልጽ አድርጎ ነበር፡፡

ዛሬ ወደ በረሃ በወረደበት ጊዜና በትጥቅ ትግሉ ወቅትም በይፋ ሲስተዋልበት በነበረው ዕብሪቱ እንዲሁም ራሱን ‹‹የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ መንግሥት›› አስኳልና ወሳኝ ኃይል አድርጎ በመላው ሃገራችን ያሻውን በታኝ፣ ከፋፋይ፣ አጥፊና አውዳሚ ድርጊቶችን በግልጽ ዝርፊያና ቅጥ የለሽ በሆነው የአፈና፣ የአረመኔነትና የወደር-የለሽ የጭካኔ ተግባራት አጅቦ ለመቀጠል ባለው የማይሰክን ፍላጎት መሠረት የቀደመ የዕብሪትና ኢትዮጵያን የዕልቂት ዐውድማ የማድረግ ዐመሉን ይዞ ‹‹ጦር አውርድ›› በማለት የመቀበሪያ ጉርጓዱን በጥልቁ ቆፍሮ ተነስቷል፡፡

ሕውሓት ‹‹ትግራይ ከ700 ዓመተ ዓለም ጀምሮ እስከ 10ኛው ክፍለ ዘመን ድረስ ‹ብሔረ አግዐዚ፣ ብሔረ ሃበሽ፣ አክሱማዊ መንግሥት› በሚሉ የተለያዩ ስሞች የተጠራች ሃገር ነበረች፤ ከ14ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ በአፍሪቃ ቀንድ የነበሩ መሳፍንት መንግሥታት አንዱ የሌላውን የመውረር መልክ ቢኖራቸውም የየራሳቸው ታሪካዊ አመጣጥና ዕድገት ያላቸው የተለያዩ መንግሥታትና ሕዝቦች ነበሩ፤ በ14ኛው ክ/ዘ የአክሱም መንግሥት ቢወድቅም እስከዚያው ድረስ በዓለም ታሪክ ጎልቶ የሚታወቀው መንግሥትና ሕዝብ የአክሱም ብቻ ነበር፤ ኢትዮጵያ እንደማንኛውም የሦስተኛ ዓለም ሃገሮች የአሁኑን ዳር ድንበሯንና መልካ-ምድራዊ ቅርጿን ይዛ የቆመችው ከ1881 እስከ 1890 ዓ.ም በአፄ ምኒልክ ዘመነ-መንግሥት ነው፤ የትግራይ ሕዘብ ባለው ታሪካዊ አመጣጥ ምክንያት ‹ዐሜን ብሎ ተረግጦ የማይገዛ ሕዝብ መሆኑን አፄ ምኒልክ ስለተገነዘቡ› የትግራይን መሳፍንት በመከፋፈል ሕዝቡን እርስ በርሱ ለማጨፋጨፍ ወስነዋል፡፡ በውሳኔያቸውም መሠረት ራስ አሉላን ከራስ ሐጎስ ጋር አዲ-ጓደድ ላይ፣ ደጃዝማች ገብረሥላሴን ከራስ ስዩም ጋር ጊዳሩ ላይ፣ ራስ ስብሃትን ከደጃዝማች ገበረሥላሴ ጋር ገኸረ ላይ እንዲዋጉ አድርገዋል ወዘተ.›› / የፀረ-ሕዝቦች እንቅስቃ በሰሜን ሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ፤መስከረም 1977 ዓ.ም ቅጽ ፩ /የሃገርና ሕዘብ ደኅንነት ጥበቃ ሚኒስቴር ተቋም ጥናታዊ ሰነድ./ የሚል የማወናበጃ ታሪክ ፈጥረውና መርዙን በማር ለውሰው ሲያወናብዱት ለነበረው የ1960ዎቹ የትግራይ ክፍለ ሃገር ወጣት ትውልድ ሲግቱት ኖረዋል፡፡

ከ1983 ዓ.ም ግንቦት ወር ማግስት ጀምሮም ይህንና ይህንኑ የመሰለውንና የኢትዮጵያን ሕዝብ በአንድነት የማያቆም፣ በጥርጣሬና በጠላትነት ዓይን እንዲተያይ የሚያስገድድ፤ ብሎም ኢትዮጵያን የሚበትን መርዝ በ‹ብሔር ብሔረሰቦች ሕዝቦች ፈጣሪ ነን› ባይነታቸው ዕብሪትና

በጡት ነካሾች ምክንያት - በጡት ነካሾች ምክንያት - መስዋዕትነት እንደገናመስዋዕትነት እንደገናሠሎሞን ለማ ገመቹ.

ምልከታ

Page 25: ቅፅ 2 ቁጥር 110 ቅዳሜ ህዳር 19 ቀን 2013 ዓ.ም

2424ግዮን ቁጥር 110 ህዳር 2013 ዓ.ም

አቦነህ አሻግሬ ዘኢየሱስ (ፕሮፌሰር)

‹‹ለኢትዮጵያ ጭቁን ዜጎችና ብሔሮች ነፃነትና መብት መስዋዕትነት የከፈልን፣ የትግሉንም ችቦ ለሌሎች የብሔር መብት፣ ዕኩልነትና ነፃነት አቀንቃኞች የሰጠን ብቸኛዎቹ ተጋዳላዮች እኛ ነን›› በሚለው ትምክህታቸው፤ በመላው ሃገራችን የጥላቻን ዘር ዘርተዋል፡፡

ከእነሱ ወደ ትግል መውጣት በፊት ጀምሮም ይሁን አነሱ የገንጣይ አስገንጣይነታቸውን ትግል እስካጧጧፉበት፣ ‹‹መንግሥት ሆነናል›› ብለውም ኢትዮጵያን እንዳሻቸው ሲያተራምሷት እስከ ነበሩበትና በሕዝባዊ ግፊት የዝንተ-ዓለም አሻንጉሊታቸው ሆኖ ይቀጥል ዘንድ ይመኙት በነበረው ‹‹ኢሕአዴግ›› ውስጥ ‹‹ትራንስፎርሜሽ›› የሚባለው የለወጥ ማዕበል ተነስቶ ወደ መቀሌ እንዲሰባሱበ እስከተገደዱበት ጊዜ ድረስ፤ በሃገራችን ‹‹እነሱን የመሰለ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውያን የሚያስብና የሚጨነቅ መንግሥትም ይሁን የፖለቲካ ፓርቲ እንዳልተፈጠረ አድርገው ሲቆጥሩ የቆዩት እነሆ ዛሬ በጫሩት እሳት እየነደዱ ነው፡፡

ያም ሆነ ይህ ከትላንት ወዲያ፣ ትላንትና ዛሬም ጭምር፤ በሰሜን ጎንደር መሬት፡፡ በሰሜናዊ ምሥራቅ ሰሜናዊ ምዕራብ አቀበትና ቁልቁለቶች፣ ኮረብታዎችና ጉድባዎች፣ የተከዜ፣ የራያ ጨረጨር፣ መሆኒ፣ ማይጨው፣… ሸለቆዎችና በረሃዎች፣ የአድርቃይ ማይፀምሪ ጋራና ሸንተረሮች፡፡ ከደባርቅና ከወገራ አውራጃ ጀምሮ እስከ ሁመራና የሱዳኗ ዐመዳይት የወሰን ከተማ ድረስ በተንጣለለው መሬት፤ የኢትዮጵያ ልጆች ደም የፈሰሰው አንድ፣ ሁለት፣ ሦስት ጊዜ ብቻ አይደለም፡፡ በስሜን አውራጃ የጠለምት፣ የበየዳና፣ የጃን አሞራ ወረዳዎች፤ በወገራ አውራጃ የወልቃይትና የጠገዴ ወረዳዎች፤ በትግራይም እነ ፈረስማይ፣ ሀበስት፣ ዓዲ-ገብሩ፣ ዓዲ-ዳዕሮ፣ ዕንዳባህጸማ ወዘተ. ያሉት ወረዳዎችና ሌሎች ተጓዳኝ ሥፍራዎች የወያኔው ልዩ ይዞታዎች ወይም ቀዳማይ ‹‹ነፃ›› የሚባሉ መሬቶች የሚባሉ ብቻ ሳይሆኑ ብዙ ግፍ የተዋለባቸው፣ የሰው ልጅ ዕልቂትን ያስከተሉ መራር ፍልሚያዎች የተካሄዱባቸውም ነበሩ፡፡ ሁመራ፣ ቃፍታ፣ ጽንብላ፣ ሽሬ፣ዓዲ-ዳዕሮ፣ ባድሜ፣ ሽራሮ፣ ማይ ተመን፣ ማይ ህበይ በረሃ፣ ማይ ተኒ፣ ማይ ኩህሊን፣ ግይጽ በረሃ፣ ሰፈዋ፣ ገዳሪፍ፣ ዓዲ-ጎሹ፣ ዓዲ-ረመጽ፣ ሰየምት አድያቦ፣ ደደቢት፣ ይርጋ፤በጥቅሉ በአብዛኛው የወልቃይትና የሽሬ አውራጃ…. የተዓምራትና የሰው ልጅ ከባባድና የሚዘገንኑ የስቃይ ዓይነቶችን እየተቀበለ ያሸለበባቸው የግፍ መሬቶችና ሸለቆዎች… የትየለሌ ናቸው፡፡

በተለይ ‹‹በትግራይ ክፍለ ሃገር በሽሬ አውራጃ በሰየምት አድያቦ ወረዳዎች ውስጥ የሰው አፅም ያልተከሰከበት በረሃና ቋጥኝ የለም፡፡ ከሠላሳ ሁለት ጊዜ የወያኔና የኢድኅ ጦርነት ዕልቂት ሌላ፤ ሃገሩ በወያኔ ቁጥጥር ሥር ከዋለ በኋላ ‹የኢዲኅ ደጋፊ ነበርክ፣ ነበርሽ› ተብለው በወያኔ አፈሙዝ እየተረሸኑ በየፈፋው… የተደፉት፣ አፈር ተነፍጓቸው ፀረ-ትግራይ ‹ኾራ ኹር አምሐሩ› (የአማራ ቡችላ) እየተባሉ ለአሞራ ቀለብ የሆኑትን፤ የወለደና የተዋለደ፣ ተሸማቆ ያየ ቤት ጎረቤት ይቁጠረው›› እያሉ እንደ ግደይ ባሕሪ ሹም ያሉ ኢትዮጵያውያን ‹‹አሞራ›› በተሰኘውና በ1985 ዓ.ም ለንባብ በበቃው መፅሐፋቸው ገጽ 196. ላይም ይሁን በሌሎች ገጾች የሚያስነብቡን ብዙ ያልተነገረ ወይም የኢትዮጵያ ሕዝብ ዘንድ በአግባቡ ያልደረሰ ሐቅም አለ፡፡

የራሱን መቃብር በራሱ የክፋት አንካሴ መልሶ በጥልቁ መቆፈር የጀመረው የዛሩው ወያኔ፤ ዓላማው ምንም የነበረ ይሁን ምን፤ ‹‹የትግራይ መሬት የሚሸከመው አንድ ለትግራይ

ሕዝብ ነፃነት የሚታገል ድርጅት ብቻ ነው›› የሚለውን አቋም ከመነሻው በመያዝ፤ በመሪዎቹ አማካይት የ‹‹ግንባር ገድሊ ትግራይ›› ወይም የግገት ድርጅት መሪ የሆኑትን ሰዎች፤ በ1968 ዓ.ም በአጋሜ አውራጃ ‹‹ማርዋ›› በተባለ ሥፍራ አስቀድመው ያደረጉትን የ‹‹አንድ እንሁን›› ቃል ምክንያት በማድረግ አታለውና ቃላቸውን አጥፈው በተኙበት ከማረኩና ‹‹ወረአትሊ›› ወደተባለው ቦታ ወስደው ዮሐንስን፣ ታደሠንና ሌሎችን ከገደሉ በኋላ ድርጅቱን አፍርሰዋል፡፡ ያፈረሱትንም ድርጅት አባሎች በትነዋል፡፡ በዕኩይ ስብከታቸው አጥምቀውም የእነሱ ጀሌዎች አድርገዋል፡፡ ያን የመሰለ ድርጊት እነ ስብሃት ነጋ ዓባይ ፀሐዬ… የፈፀሙ ስለመሆናቸውም፤ በወቅቱ ከሕወሓት እስር ቤት ማምለጥ የቻለው ተፈራ ካሣ እና በጊዜው በአፈናው ቦታ ባለመኖሩ ምክንያት ወጥመዳቸው ውስጥ ያልገባው ኃይለኪሮስ አሰግድ / የፀረ-ሕዝቦች እንቅስቃ በሰሜን ሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ፤መስከረም 1977 ዓ.ም ቅጽ ፩ /የሃገርና ሕዘብ ደኅንነት ጥበቃ ሚኒስቴር ተቋም ጥናታዊ ሰነድ./ የመሰከሩት ነው፡፡

የግገት መሪዎች በሕወሓት መሪዎች ክህደትና ፍፁም ጭካኔ የተመላበት ሠይፍ ከተቀሉ፣ ደብዛቸው እንዲጠፋ፣ ድርጅታቸው እንዲፈርስና አባሎቻቸውም እንዲበተኑ ከተደረገ በኋላ በ1969 ዓ.ም ሕወሓቶች የዘመቱት በትግራይ እና በዐማራ ልጆች ኅብረት ተቋቁመው በነበሩት እና አፍላውን ወታደራዊ መንግሥት ተዋግተው ዘውዳዊ ሥርዓቱን መልሰው ለማንገስ ፍላጎት በነበራቸው የኢ.ዲ.ሕ.ን ታጣቂዎች ላይ ነበር፡፡ ከእነሱም ጋር ብዙ ዕልቂት የታየበትን አሰቃቂ ውጊያ ካካሄዱ በኋላ ከትግራይ መሬት ወደ ጎንደር ወደዛሬው ወልቃይት ፀገዴ አውራጃ እንዲያፈገፍጉ አስገድደዋቸዋል፡፡

ወያኔዎች በኢዲዩ ላይ ካካሄዱት የድምሰሳ ዘመቻ በኋላ፤ የትግራይ ክፍለ ሃገር ተወላጆችን ጨምሮ ከመላው ኢትዮጵያ ተሰባስበው፤ የወታደራዊውን አብዮታዊ መንግሥት መርሆዎች ገና በማለዳው በመቀናቀን ስም የትጥቅ ትግል ለማካሄድ የተሰባሰቡትን የኢሕአፓን ሠራዊት አባላት፤ ከየካቲት ወር እሰከ ሚያዚያ ወር 1970 ድረስ በአጋሜ አውራጃ ውስጥ በመውጋት ከትግራይ መሬት እንዲወጡ አድርገዋል፡፡ ከፍ ሲል በተገለጸው መፅሐፋቸው ከገጽ 200-201 ግደይ ባሕሪ ሹም እንደሚሉን ሕወሓቶች፡- ‹‹ላምና ፍየሉን እንጠብቅልሃለን ብለው ያለ ፍላጎቱ ለስደት የዳረጉትነረ ሕዝብ (ሕፃን ሽማግሌን ጨምሮ) ‹ወዲ ኸውሊ› በተባለው በረሃ በበሽታ፣ በረሃብና በቁርጥማት፣ በተቅማጥ እየተነዳ፤ እንደ ቅጠል በጅምላ ሲረግፍ፤ የዓለም ጋዜጠኞችን ጋብዘው ለበጎ አድራጊ ድርጅቶች ‹ለሕዝባችን የሰጣችሁን የእህል ዕርዳታ አልበቃ ብሎ ይኸው በረሃብ እየረገፈ ነውና መጥታችሁ ማየት ትችላላችሁ› እያሉ መለመኛ አድርገውታል፡፡ በዚህ መልክ ያገኙትን እህልም ሽታውን ብቻ ለተለመነበት ወገን አቅርበው ቀሪውን በቶን ለሱዳን ሀብታም ነጋዴዎች በመሸጥ ተዝናንተውበታል…›› ብለዋል፡፡

ሰኔ 5 ቀን 1968 ዓ.ም የሽሬን ግምጃ ቤት ከመዝረፍና ከዚያም በእነ ፍቅረይ አርዓያ አማካይነት ‹‹በፈረስ ካብ›› አካባቢ ገሠሠ አየለን የገደሉ፤ በየካቲት 14/1968 በሽራሮ ከተማ የገሠሠ ሞት እንዳይሰማ ወይም ተድበስብሶ እንዲቀር ‹‹ምስጢር ሊገልጡ ይችላሉ›› ተብለው የተገመቱ የሕወሓትን ደጋፊዎች የጨፈጨፉ… /‹‹አሞራ›› በግደይ ባሕሪሹም በ1985 ዓ.ም የተፃፈ መፅሐፍ ከገጽ 165-166 መመልከት ይቻላል/ ሰው የፊጥኝ አስረው ገድለው የቀበሩ፣ እናትን በልጇ

አስከሬን ላይ እንድትቀመጥ ያስገደዱ፣ ‹‹ወንድ ነን›› ብለው ወንድ ልጅን አስገድደው የደፈሩና ያስደፈሩ፣ በበረሃ ሳሉ በገዛ ወንድሞቻቸው ላይ የመጨረሻውን የጭካኔ ተግባር ሁሉ ፈፅመውና ተለማምደው ሲያበቁ ወደ መንግሥትነት ደረጃ የመጡ መሆናቸው የማይታወቅ ይመስል፤ ስለ ሰብዓዊነት፣ ስለ ፍትሕ፣ ስለ ‹‹ብሔር ብሔረሰቦች ሕዝቦች›› ፈጣሪነታቸው፣ ስለ መብትና ነፃነት ተጋዳላይነታቸው፣ ከእነሱ ውጭ የአብዮታዊ ዴሞክራሲም ይሁን የነጭ ካፒታሊዝም… ርዕዮት አራማጅ እንደሌለ በዓለም አደባባይ ያለ አንዳች ሃፍረት ስለራሳቸው የመሰከሩ፤ አጨብጫቢዎቻቸውን እና በእነሱ ብልት የሚፎክሩ ሎሌዎቻቸውን እንደ ሰም አቅልጠው፣ እንደ ብረት ቀጥቅጠው ከሠሯቸው በኋላ ‹‹መለስ ሌጋሲያችን ነው…›› እያሉ በየደረሱበት እንዲለፍፉላቸው ያደረጉ፣ የፍፁም አድርባይነትን ርጉም ስብዕና ኩሩ ሆኖ በኖረው ኢትዮጵያዊ ማኅበረሰብ ውስጥ ያለማመዱ ወያኔዎች መሆናቸውን፤ ይኸው ዛሬ ታሪክ በአደባባይ በራሳቸው ዕኩይ ግብር መስክሮባቸዋል፡፡

ስለዛሬዎቹ ጡት-ነካሾች ይነገር ከተባለ የሚጠቀሰው እስካሁን የተባለው ብቻ አይደለም፡፡ ከተባለውና ከተፃፈውም በላይ ቃላት ሊገልፁት የማይቻላቸው አያሌ የግፍ ታሪኮችም አሏቸው፡፡ ለምሳሌ ያህል በወያኔዎች የውንብድና መርህ መሠረት እንደ ሰየምት አድያቦ ባሉ በረሃዎች በራሳቸው ታጣቂዎች በሚገደሉ ተጋዮች ምክንያት አሞራ ጦም አድሮ አያውቅም፡፡ በደደቢት በትግራይ ሕዝብ ላይ የናዚ ሥርዓት የሚፈፀምበት ‹‹ባዶ ሹድሽተ›› ወይም ዜሮ ስድስት ተብሎ የሚጠራ እሥር ቤትመረ ነበር፡፡ በዚያን መሰሉ እስር ቤት፣ የቁም ገሀነም የሰው ልጅ በተለይም ሕወሓትን ዕምቢኝ ያሉ የትግራይ ክፍለሃገር ተወላጅ ኢትዮጵያውያን እንዴት ያለውን የስቃይ ዓይነት እየተጋፈጡ ሕይወታቸው እንዳለፈ በጥቂቱም ቢሆን ለመገንዘብ፤ የግደይ ባሕሪሹምን ‹‹አሞራ›› የተሰኘ መፅሐፍ ከገጽ 207 እስከ 209 በጥሞና መቃኘት መልካም ነው፡፡ በዚሁ ተጠቃሽ ሊሆን የሚችል መፅሐፍ በገጽ 198 እና 199 ላይ የሠፈረውን በአስተውሎት በማንበብም ‹‹ንትግራይ ዓደይ በል›› ወይም ‹‹ለሃገሬ ትግራይ በል›› እየተባለ የትግራይ ክፍለ ሃገር ሰው ‹‹ኢትዮጵያዊ ነኝ›› በማለቱ ምክንያት እንዴት ያለው የዘረኝነት ጅራፍ ሲወርድበት እንደነበርም ማወቅ ይቻላል፡፡

ስለ ወያኔ አመጣጥ፣ የግፍና የግፈኝነት፣ የዘረኝነትና የበታኝነት ባሕሪያት ታሪክ ብዙ ይመሰክራል፡፡ አብዛኞቹ የሰሜን፣ የሰሜን ምሥራቅና ምዕራብ የኢትዮጵያ ምድሮችም አንደበት ቢኖራቸው ከተነገረውና ከተፃፈውም በላይ ስለ ሕወሓት አምሳለ የጭካኔ አውራነት ለኢትዮጵያዊው ትውልድ እጅግ ብዙ በነገሩት ነበር፡፡ ይሁንና የቅርቡ ሃገራዊ ዘመቻና ዳግማዊው መስዋዕትነት፤ በትግራይ ሽሬ፣ አክሱም፣ ዓድዋ፣ አጋሜ፣ ክልተ-አውላሎ፣ እንደርታ፣ ራያና አዘቦ፣ ተምቤን አውራጃዎች፤ በጎንደር፣ በወሎ፣ በአፋር በኩል ወደፊት ገስግሶ ወደ ወርቅ አምባና ጎያ፣ ወደ ሕንጣሎና ሽኩት፣ ወደ አጉላ ተቃርቧል፡፡ ይህ ፅሑፍ ወደ ኅትመት ሲሄድ፤የመጨረሻው ፍልሚያ ኅዳር 17 ቀን 2013 ዓ.ም በመቀሌና አቅራቢያዋ መካሄዱ ይፋ ሆኖ ነበር፡፡ ከዚያስ መቀሌ ምን ትሆናለች? የኢትዮጵያውያኑ የትግራይ ልጆች ነፃነት ትንሳዔ ወይስ የሕወሓትና የድርጅቱ ዕብሪተኛ መሪዎች የመከፈኛ ጨርቅ? ለማንኛውም የ‹‹ታሪክ አተላና የኢትዮጵያውነት ክህደት አዝመራ የለማበት›› የወያኔ ነገር ‹‹እጅግም ስለት ይቀዳል አፎት፤ እጅግም ዕብሪት ያደርሳል ከሞት›› ይሉት ነገር ሆኗል፡፡ ታሪክም በሂደቱ ወደ አዲስ ታሪካዊ አስተምህሮ ክፍል የሚወስደን ይሆናል ተብሎ ይታሰባል፡፡

ምልከታ

Page 26: ቅፅ 2 ቁጥር 110 ቅዳሜ ህዳር 19 ቀን 2013 ዓ.ም

2525ግዮን ቁጥር 110 ህዳር 2013 ዓ.ም

ወቅታዊምርመራ

22ግዮን ክፍልግዮን ክፍል22ግዮን ክፍልግዮን ክፍልለዛ

26

27

ነገረ ግዮን

24

አቦነህ አሻግሬ ዘኢየሱስ (ፕሮፌሰር)

ቢዝነስ ዜናዎች28

የአዘጋ

ጁ መል ክትዕዕየቱሪዝም የቱሪዝም ማዕከሎቻችንንማዕከሎቻችንን ወደነበሩበት ወደነበሩበት

ገጽታ መመለስ ይገባል!ገጽታ መመለስ ይገባል!

ባሳለፍነው ሳምንት የሰማነው ዜና ያስደነግጣል፡፡ የኢትዮጵያችን የሥነ መንግሥት፣ የቤተ ክህነት፣ የሥነ ሕንጻ፣ የጥበብና ወዘተ… መነሻና መሠረት የኾነችው አክሱም አሳዛኝ አደጋ አጋጥሟታል፡፡ ይኽም የበርካታ የውጪና የሀገር ውስጥ ጎብኚዎቿ መመላለሻ

የኾነው አየር ማረፊያዋ ጉዳት የደረሰበት መኾኑ ነው፡፡ ይኽ በእውነቱ አክሱም ትናንት በታሪካችን፣ ዛሬ ደግሞ በቱሪዝማችን ያላትን ግዘፍ የነሳ ስፍራ ላስተዋለ ትልቅ ሀዘን ነው፡፡ የኢትዮጵያዊነታችን ያልተነገሩ ምሥጢሮች እና ያልተፈቱ እንቆቅልሾችን የያዘችው ጥንታዊቷ አክሱም ልማቷን፣ ታሪካዊነቷንና ገናናነቷን በማይሻ እና ፍጹም ኃላፊነት በማይሰማው ኃይል እንዲህ ያለው ነገር መፈጸሙ ኢትዮጵያን ለሚወድ ሁሉ ቅስም ሰባሪ ነው፡፡ ቢኾንም ግን አዝኖና ተቆጭቶ እጅን ማጣጠፍ መፍትሔ የማይኾበት ዘመን ላይ መኾናችንን ማስታወስ ተገቢ ነው፡፡ በመኾኑም አክሱም እንደትናንቱ ሁሉ ነገም የቱሪዝም ፈርጥ ኾና እንድትቀጥልና ነባር ገጽታዋ ወደቦታው እንዲመለስ ጥረት ማድረግ ከያንዳንዱ ሀገር ወዳድ ዜጋ የሚጠበቅ ግዴታ ነው፡፡

ለአንድ ዓመት በተጠጉት ያለፉት ወራት ዓለም አቀፉ የኮሮና ወረርሽኝ ጡንቻውን ካሳረፈባቸው ዘርፎች አንዱና ዋነኛው ቱሪዝም እንደኾነ አይዘነጋም፡፡ በተለይም በሀገራችን በርካታ የጉብኝት ሥፍራዎች ዝግ ኾነው የቆዩ ከመኾናቸው አኳያ እንደሀገር ኢኮኖሚያችን ላይ ያሳደረው ተጽዕኖ በቀላል የሚታይ አይደለም፡፡ በመኾኑም በቅርቡ በሚመለከታቸው የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶችና ተቋማት ውሳኔ መሠረት የጉብኝት ስፍራዎቹን ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግ ለጎብኚዎች ክፍት ማድረግ ተጀምሯል፡፡ የቱሪዝም ማዕከሎቻችንን ቅድመ ኮቪድ 19 ወደነበሩበት ቁመና ሙሉ በሙሉ መመለስ ባይቻልም እንኳን ከማናቸውም የጸጥታም ይኹን የደህንት ስጋት ነጻ አድርጎ አገልግሎታቸውን መቀጠል ግን አስፈላጊ ነው፡፡ እንደ አክሱም ያሉ የመስህብ ቁንጮዎችን በቶሎ ወደነበሩበት መልክና ገጽታ መመለስ ጊዜ ሊሰጠው የማይገባውም በዚህና ተያያዥ ምክንያት ነው፡፡ መንግሥትም የፈረሰውን በመጠገን፣ የተበላሸውን በማስተካከል ዓለምን አጀብ ያሰኙት የቱሪዝም ስፍራዎቻችን ወደነበሩበት ተግባር እንዲመለሱ በቶሎ ጥረት ማደረግ ይጠበቅበታል ስንል መልዕክታችንን ለማስተላለፍ እንወዳለን፡፡

እንግል-አማር-ዝኛአፈወርቅ በቀለ ከልሌ

Page 27: ቅፅ 2 ቁጥር 110 ቅዳሜ ህዳር 19 ቀን 2013 ዓ.ም

2626ግዮን ቁጥር 110 ህዳር 2013 ዓ.ም

ለዛ

የታሪክ ማስታወሻምኒልክን አንድ እንግሊዛዊ “ ከጥቁርና ከነጭ ማን ይበልጣል ?”ሲል ይጠይቃቸዋል::ጃንሆይ “ አስበህ እንደጠየቅከኝ አስቤ መልስ እሰጥሃለው” ብለው በቀጠሮ ይለያያሉ፡፡ ከዛም ሊቃውንቶቻቸውን ሰብስበው ለተጠየቀው ጥያቄ መልስ እንዲሰጡ ይጋብዟቸዋል፡፡ ለጊዜው ምንም መልስ አልተገኘም፡፡ በኃላ አለቃ ድንቄ የተባሉ ብልህና አዋቂ ሰው “ አይቸገሩ ጃንሆይ !መልሱን እኔ እሰጥዎታለሁ “ አሏቸው፡፡ምኒልክም በፅሞና ይጠብቋቸው ጀመር፡፡ አለቃ ድንቄም “ ፈረንጁ ከጥቁርና ከነጭ ማን ይበልጣል አይደል ያለው ?ፍላጎቱ ይገባናል፡፡ እርስዎም በፈንታዎ “ ከአይንህ ነጩ ነው ጥቁሩ የሚያይልህ ?” ብለው ይጠይቁት መልሱን ከዛ ያገኘዋል “ አሏቸው፡፡ እውነትም ምኒልክ ለፈረንጁ ይህን ሲሉት በነገሩ ተደንቆ ዝም አለ፡፡ ምንጭ ፡ አዲስ ዘመን ጋዜጣ ታህሣሥ 6 ቀን 1978 ዓ.ም

ለጠቅላላ ዕውቀት- የአለማችን ትልቋ ሀገር ሩስያ ስትሆን 17.09 ሚሊየን km2 የሆነ የቆዳ ስፋት

አላት::

- በአለማችን ላይ በርሀማዋ ሀገር ሊቢያ ስትሆን ከአጠቃላይ የቆዳ ስፋቷ 99% የሚሆነው በረሀማነት የሚፈረጅ ነው::

- በአለማችን ላይ ምንም አይነት ወንዝ የሌላት ሀገር ሳውድ አረቢያ ነች::

- ለሴቶች የመምረጥ መብትን ቀድማ የሰጠች ሀገር ኒውዝላድ ነች::

- አሜሪካ በአለማችን ላይ ብዙ ክርሰቲያኖች የሚኖሩባት ሀገር ስትሆን ከአጠቃላይ የህዝብ ብዛቷ 245.9 ሚሊየን የሚሆኑት ክርሰቲያኖች ናቸው::

- ብዙ የሆነ የእስልምና ሐይማኖት ተከታይ ህዝብ ያላት ሀገር ኢንዶኔዢያ ስትሆን ከ209 ሚሊየን በላይ የሚሆነው ህዝቧ ሙስሊሞች ናቸው::

- በአለማችን ላይ ከፍተኛ የሆነ የሀይቅ ብዛት ያላት ሀገር ካናዳ ስትሆን ወደ 3 ሚሊየን የሚጠጉ ሀይቆች ሲኖራት ይህም በአለማችን ላይ ካሉት የሀይቆች ብዛት 60% ይሸፍናል::

- በአለማችን ላይ ከፍተኛ የሆነ የግድያ ወንጀል የሚፈፀምባት ሀገር ኤል ሳልቫዶር ስትሆን በአማካኝ ከ100,000 ሰዎች ውስጥ 55.5% የሚሆኑት ግድያ ይፈፀምባቸዋል::

- በሀገሯ ፓርላማ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የሴቶች ቁጥር ያላት ሀገር ሩዋንዳ ስትሆን በፓርላማዋ ካሉት ጠቅላላ መቀመጫዎ ውስጥ 56.3% (50/80) የሚሆነው የተያዘው በሴቶች ነው::

- ዴንማርክ በአለማችን ላይ አነስተኛ የሆነ የሙስና ወንጀል የሚፈፀምባት ሀገር ናት::

ጠቃሚ ምክሮች- ትንሽ ወስደህ ብዙ ስራ፤ በህይወትህ ሊጠቅሙህ የሚችሉ ነገሮችን ብቻ አንብብ፡፡

አስተዉል! የጊዜህን 20 ፐርሰንት ነገሮችን ቅሰም 80 ፐርሰንቱን ግን የቀሰምከዉን ወደተግባር ለመለወጥ ተጠቀምበት፡፡

- ቴሌቪቭን ለጥቂት ጊዜ እይ ፤ ሳያቋርጡ ቲቪ ማየት ዉስጥህ ያለዉን እምቅ ችሎታ እንዳትጠቀም እንቅፋት ይሆንብሃል፡፡

- የእግር ጎዞ አድርግ ፤ችግር አጋጥሞህ መፍትሄዉ እምቢ ካለህ ወጣ ብለህ የእግር ጎዞ አድርግ፡፡ ይህን ማድረግህ አእምሮዉ እንዲፍታታና እንድታሰላስል ይረዳሃል፡፡

- ካንተ ከተሻሉ ሰዎች ጋር አብረህ አሳልፍ፤ አስታዉስ! የአእምሮህ ብስለት የሚለካዉ አብረህ ብዙ ጊዜ ከምታሳልፋቸዉ አምስት ሰዎች የአስተሳሰብ ዉጤት ተደምሮ ነዉ፡፡

- አትኩሮ የማንበብን ልምድ አዳብር፡፡ ንባብን በቻልከዉ ቦታና ጊዜ ልማድ በማድረግ አእምሮህን መግበዉ፡፡ ነገር ግን ፊስ ቡክን የመሳሰሉ ሶሻል ሚዲያዎች ላይ ስትጠቀም መርጠህ አንብብ፡፡ ፌስቡክ ላይ ያየኸዉን ሁሉ ለማንበብ መሞከር ዉድ ጊዜህን የሚያባክን መሆኑን ትገነዘባለህ፡፡

- የምትወደዉን ስራ ሁሌም ለማሻሻል ጣር፤ ጎበዝ በሆንክበት ሙያ ከማንም የተሻልክ ሆነህ እንድትገኝ በየቀኑ አዳብረዉ፡፡

- በቂ እንቅልፍ ተኛ፤ በቂ እንቅልፍ ስትተኛ አእምሮህን ለሚቀጥለዉ ቀን የህይወት ሩጫ በትክክል እንድታዘጋጅ ይረዳሃል፡፡

- አዲስ ሙያ ለመማር እራስህን አዘጋጅ፤ ዉስጥህን ደስ ሊያሰኝ የሚችል ጊዜ ማሳለፊያ ወይንም ትርፍ ሙያ ለመማር ፍቃደኛ ሁን፡፡

- ከሰዎች ጋር ያለህን ግንኙነት አዳብር፤ አዳዲስ ሰዎችን ለማወቅ ፈቃደኛ ሆነህ የህይወት ልምድ ተለዋወጥ፡፡

- ድምፅህን ከፍ አድርጎ የማዉራት ልምድን አዳብር፤ ሰዎች በተሰበሰቡበት ቦታ ሃሳብ ስትሰጥ ወይንም ረጋ ብለህ ድምፅህ ለሰዎች በሚሰማ መልኩ ጮክ ብለህ ተናገር፡፡ ይህን ማድረግህ በራስ የመተማመን መንፈስን ያድስልሃል፡፡

የሆሊውድ ደራሲያንና ኢትዮጵያውያኑከዚህ በታች በተዘረዘሩት የሆሊይዉድ ፊልሞች ላይ ሁለቱ ሀገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ወይም የነበሩ ቦቻዎችን፤ 3ቱ ደግሞ ኢትዮጵያ ውስጥ የነበሩ ወይም የነገሱ ሰዎች ሲሆኑ ነገር ግን ፊልሞቹ የተጠቀሙት ታሪክ ወይም ቦታ ከኢትዮጵያ የተገኘ ስለመሆኑ በግልፅ አያብራሩም።

ፊልም 1 Lucy ሉሲ የተገኘችበትን ትክክለኛ ቦታ በደምብ ለተመልካች ባለማብራራት

ፊልም 2 Zotopia ዙቶፒያ ዩቶፒያ ከሚል ቃል የተገኘ ስም ነው። ዩቶፒያ ሀገር ወይም ቦታ ነው። በዚህ ሀገር ወይም ቦታ ህዝቡን በቅን የሚመራ መሪ እና ፈጣሪያቸውን በእጅጉ የሚፈሩ ህዝቦች ይኖሩበት የነበረ ተብሎ የሚታሰብ ሀገር ሲሆን Utopia በሚል የታተመ Thomas more በተባለ ፀሀፊ የተፃፈ መፅሀፍ እንዳለም ልብ ልትሉ ይገባል። ይህ መፅሀፍ የባህርዳር ዮኒቨርሲቲ መምህርት በሆነችው ዶ/ር መስከረም ለቺሳ ተተርጉሞ በአማርኛ ለአንባብያን በቅቷል።

ፊልም 3 Thor ቶር ዩቶር ከተባለ ኢትዮጵያዊ ንጉስ ስሙን የወረሰ ሲሆን ንጉስ ዮቶር ልክ በፊልሙ ላይ እንደሚታየው ቶር የሚወረውረው መዶሻ ወይም የተለየ ሀይል ባይኖረውም ኢትዮጵያን በንግስና ማስተዳደሩ ግን በተለያዩ ኢትዮጵያዊ የታሪክ መፃህፍት ላይ በግልፅ ተቀምጧል።

ፊልም 4 Clashes of the Titans

አንድሮሜዳ የተባለችው ልዕልት ኢትዮጵያዊ መሆኗ በሁሉም አለም የሚታወቅ እውነታ ሆኖ ሳለ የዛሬ 4000 ዓመት ይህች ኢትዮጵያዊት ይህን አኩሪ ተግባር በመፈፀሟ አበሳጭቷቸው የነበሩ ጥቂት ነጭ ዘረኞች በመኖራቸው በዚህ ፊልም ያለችው ዋና ሴት ገፀ ባህርይ በነጭ ሴት ተክተው ሰርተዋል።በተጨማሪም ግሪክ ውስጥ ያሉ ጥንታዊ

ስእሎች ሳይቀሩ ጥቁርነቷን የሚመሰክሩ ናቸው። ሮማዊው ገጣሚ ኦቪድ በግልፅ አንድሮሜዳ በኢትዩጵያዊት ጥቁር ልዕልት መሆኗን ፅፏል። አሁን በቅርቡ ደግሞ (ጥር 2019) BBC, ካልቸር በተባለ ፕሮግራሙ ላይ እንዴት ጥቁር ልዕልት በሰዓሊያን እንድትነጣ ተደረገች? በሚል ስራው ብዙ ነጭ ዘረኞችን አዋርዷል።

Page 28: ቅፅ 2 ቁጥር 110 ቅዳሜ ህዳር 19 ቀን 2013 ዓ.ም

2727ግዮን ቁጥር 110 ህዳር 2013 ዓ.ም

ቋንቋ

(ካለፈው የቀጠለ)

በእርግጥ የአንዳንድ የውጭ አገር ምርቶች፣ የንግድ ስያሜዎችን፣በተለይ ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያላቸውን ሳይንሳዊ ስያሜዎችን እና መድኃኒቶች፣

ወደ አማርኛ ቋንቋ ለመመለስ አይቻልም፡፡ ምሳሌ፡- ቶዮታ፣ ማርቼዲስ፣ቮልስ ዋገን፣(የተሸከርካሪ መኪናዎች ስያሜ) ሸራተን፣ሂልተን፣ራዲሰን ብሉ (የሆቴሎች መለያ ስያሜ) አንፒሲሊን፣ ቴትራሳይክሊን፣ ፔኒሲሊን፣ (ዓለም አቀፍ የመድኃኒት ስያሜዎች) ኦክስጂን፣ሃይድሮጂን፣ሂልየም፣ (ሳይንሳዊ ስያሜዎች ) … ወዘተ ማለት ነው፡፡

በሌላ በኩል በውጭ አገር የሚመረቱ ምርቶች፣ ለምሳሌ ማሽኖች፣ የኤሌክትሮኒክስ ውጤቶች፣ የተንቀሳቃሽ ድምጽ ወ-ምሥል (ፊልሞች) ወዘተ… ሸቀጦች ወደ አረብ አገራት፣ ወደ ጣሊያን፣ ስፔን፣ ጀርመን፣ ቱርክ፣ ግሪክ የሚገቡ፣ ስለ ሸቀጦቹ መግለጫ፣ በየሚገቡበት አገር ቋንቋ ትርጉማቸው ወይም ማስረጃዎቻቸው ተያይዞ ካልቀረበ በስተቀር፣ በየአገሮቹና በየሕዝቦቻቸው ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ ይህ ደግሞ ለየአገሮቹ ሕዝብ፣ ለቋንቋቸው ልዕልና፣ ክብርና ኩራት ነው፡፡ እኛ ግን ስለአጠቃቀማቸው በሚገባን ቋንቋ፣ ምንም ዓይነት መረጃ ሳይኖረን (ኤሌክትሮኒክ መገልገያዎች፣ መድኃኒቶች፣) ሸቀጦች ማራገፊያ ሆነናል፡፡ መድኃኒቶችና ሌሎች ምርቶችን ልብ ይላል፡፡ የሕክምና ባለሙያዎች፣ መድኃኒቶችን ለሕመምተኞቻቸው እንዲሰጥ የሚወስኑት፣ የመድኃኒት ማዘዣ ወረቀቶች፣ ጠርቶ በማይነበብ የእንግሊዘኛ ጽሑፍ ነው፡፡ አይደለም ተርታ ሰው፣ ባለሙያውም ቢሆን በደንብ አይረዳውም፡፡ ሌላው ቀርቶ፣ የመድኃኒት ቀማሚው፣ የሐኪሞችን ማዘዣ አንብቦ የሚረዳው በችግርና በመከራ ብዛት ነው፡፡ በመሠረቱ የሐኪሞች የመድኃኒት ማዘዣ በቀላሉ የሚረዱት፣ በመሰረቱ የመድኃኒት ማዘዣን፣ ሕመምተኖቹ በቀላሉ አንብበው የሚረዱት፣ አወሳሰዱም ግልፅና ግራ የማያጋባ መሆን ነበረበት፡፡ ሕመምተኛው ስለታዘዘለት መድኃኒት ምንነት፣ አወሳሰዱን፣ መድኃኒቱ የሚያስከትለውን ጎናዊ ችግር የማወቅና የመረዳት መብት አለው፡፡ ስለሆነም ማንኛውም የሐኪም መድኃኒት ማዘዣ ግልፅ መሆን አለበት፡፡ እስከ አሁን የመድኃኒት ማዘዣዎችን ለታማሚዎቻቸው በአማርኛ የሚጽፉ አንድ ሐኪም አውቃለሁ፡፡ እጅግ የተከበሩ የዓለም ሎሬት የሕክምና ዶ/ር ጥበበ የማነ-ብርሐንን፡፡

በአለፉት ዘመናት ለምን እንደሆነ ምሥጢሩ ባይታወቅም፣ በአማርኛ የንግግርና የጽሕፍት ቋንቋ ላይ፣ በአገር መሪዎች፣ በምሁራን፣ በጋዜጣና መጽሔቶች፣ በመገናኛ ብዙኀን፣ በአዳዲስ መጻሕፍት(ታሪክ፣ ልቦለድና ሌሎችም) በመንግሥትና በግል መሥሪያ ቤቶች፣ በአገር ውስጥ አምራች፣ ድርጀቶች፣(በተለይ ውኃ በላስቲክ አሽገው የሚያከፋፍሉ ለምሳሌ፡- የንግድ ስያሜዎቻቸው፣ ዴይሊ፣ አቫንቲ፣ አኳ አዲስ፣ አኳሴፍ፣ ዋን፣ የተሰኙ ሲሆኑ ለዚያውም በአማርኛ ሆሄ) በማስታወቂያ ሥራዎች፣ በተንቀሳቃሽ ምሥል ወ-ድምጽ ሥራዎች፣ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት (የትምህርት ሚ/ርን፣ ጤና ጥበቃ፣ ወዘተ…. ይጨምራል)፡፡ ይገለገሉባቸዋል፡፡ ቋንቋ ራሱን ችሎ መራመድ ያቃተው ይመስል፣ የባዕድ ቋንቋ ምርኩዝ

በመሐል እየተደነቀሩ የንግግር ወይም የጽሕፈት ቋንቋው እንግሊዝኛውን ተከትሎ ሊያስኬዱት ጥረት ሲያደርጉ ይስተዋላል፡፡ እንግሊዝኛና አማርኛ ተደበላልቋል፡፡ አማርኛ የእንግሊዝኛ ጥገኛ እየሆነ ነው፡፡ ለዚህም ነው የዚህን ጽሑፍ እርዕስ እንግል-አማርዝኛ ያልኹት፡፡ የአማርኛ የንግግርና የጽሕፈት ቋንቋ፣ ሥርዓት አልበኛ(በዘፈቀደ) የመሆን አዝማሚያ እያሳየ ነው፡፡ በብዙኀን መገናኛዎች (ቴሌቪዥን ሬዲዮ ጋዜጦች) በአማርኛ ቋንቋ የሚተላለፉ መርሐ ግብሮች ማለትም፡- ዜናዎች፣ ዘገባዎች፣ ቃለ ምልልሶች፣ ማስታወቂያዎች፣ መርሐ ግብሩ የሚተላለፈው በአማርኛ ቋንቋ ሆነ እያለ፣ (በእንግሊዝኛ ቋንቋ በሚተላለፍ አማርኛ አይቀላቀልባቸውም) እንግሊዝኛ ቋንቋ ቃላት ይደቀልባቸዋል፡፡ ደግሞ እኮ ራሱን የቻለው የእንግሊዘኛ ቃል በሥርዓቱ በአማርኛ ቋንቋ ቢተላለፍ መልካም ነበር፡፡ እራሱኑ እንግሊዘኛውን ያዛቡታል ለምሳሌ፡- “life boy” የሚል ሳሙና የለም፡፡ አልተፈጠረምም፡፡ “Life Bouy” እንጂ፡፡ እነርሱ መልዕክቱን ሲያስተላልፉ “life boy” ብለው ነው፡፡ በ”boy” እና “bouy” መሐል ሠፊ የሆነ የቃል ትርጉም ወይም ፍቺ ልዩነቶች አሉ፡፡ ልዩነታቸውን የእንግሊዘኛው መዝገበ ቃላት ፈትሸው ይመልከቱት፡፡ በዕለት አጻጻፍ የሆሄዎቹ ቅደም ተከተል የተስተካከሉ አይሆንም፡፡ አረፍተ ነገሮች ተስተካክለው አይጻፉም፡፡ በአሁን ጊዜ በእግሊዝኛ የተጻፉ ቃላት ፣በአማርኛ ተቀድተው በግድ ይነበባሉ፡፡ ወይም በእንግሊዝኛ የተጻፉ ቃላት በአማርኛ ሆሄ ተቀድተው እንዲነበቡ ግዴታ ያለ ይመስላል፡፡

በአማርኛ የንግግርና የጽሕፈት ቋንቋ ላይ፣ ከባድ የሆነ ተጽእኖ የተፈጠረው፣ በአለፉት ሠላሳ ዓመታት ውስጥ ነው፡፡ የዚህም ዋና ዋና ምክንያቶች፣ የመንግሥታት መቀየር፣ የሥርዓተ ትምህርቱ መለወጥና፣ ከደርዝ ወጣ ማለታቸው እንደሆኑ መገመት ይቻላል፡፡ በመሆኑም ቋንቋው ሆን ተብሎ ወይም በማወቅና ባለማወቅ፣ በመንግሥት ባለሥልጣናት፣ በትምህርት መስጫ ተቋማት፣ በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች፣ በንግድ ተቋማት፣ በብዙኀን መገናኛ ባለሙያ ሠራተኞች፣ በምሁራን (አንዳንድ) ተብዬዎች በማስታወቂያ ሥራ ሸቃቾች፣… ወዘተ፣ በተጨማሪም ቋንቋው እንዲዳከም ብሎም እንዲጠፋ በሚሹ፣ የአማርኛ ቃላቶች በባዕድ ቋንቋ ቃላቶች እንዲተኩ ለማድረግ፣ ሠፊ የሆነ ዕድል ሰጥቶአቸዋል፡፡ ወይም አግኝተዋል::

ከዚህም በመነሳት ለምሳሌ፡- ፕሮጀክት /ትልም/ ፕሮግራም /መርሐ-ግብር/ ቢዝነስ /ነገረ-ንዋይ/ ቻሌንጅ /ተግዳሮት፣ችግርና ፈተና/ ኮማንድ ፖስት /የዕዝ ቀጠና/ ኮንስታብል /ወታደር/ ክላስተር /ኩታ ገጠም/ ፎቶ ኮፒ /የምሥል ቅጅ/ ፐብሊክ ሰርቪስ /የሕዝብ አገልግሎት/… ወዘተ፣ የሚሉት የእንግሊዝኛ ቃላት፣ አማርኛውን (የእንግሊዝኛ ቃላቱን በአማርኛ ሆሄ የአሰፈርኳቸው፣ እግረ መንገዴን እንዲያ እየተጻፉ እያሉ መሆኑን ለማመላከት ነው) እየተኩ ይገኛሉ፡፡ ኧረ ስንቱ ተጠቅሶ ያልቃል?

የንግድ ተቋማት ስያሜማ፣ የሚያሳዝኑ ከመሆናቸው በላይ (ለእኔ)፣ የሚያስገርሙኝም ናቸው፡፡ ምሳሌ፡- ማንቸስተር፣ ጎሚስታ፣ ክሊንተን ዳቦ ቤት፣ ኦባማ ግሮሰሪ፣ አዲስ ቪው፣ እስካይ ላይት ሆቴል፣ ኢንተር ኮንትኔታል ሆቴል፣ ቡክ ላይት …. ወዘተ

ከሁሉም በላይ አስከፊው፣ በታላላቅ ዓለም አቀፍ ሆቴሎች፣ (እነርሱ ኢንተርናሽናል ነው የሚሉት)፣

የሚሰጡትን አገልግሎት ዝርዝር፣ እንግዶችን በሚቀበሉበት ሥፍራ፣ በረዣዥም የማስታወቂያ ሰሌዳዎቻቸው ላይ፣ መግለጫዎቻቸውን የሚጽፉት በእንግሊዘኛ፣ አሁን አሁን ደግሞ በቻይንኛ ብቻ መሆኑ ነው፡፡ ቻይንኛ የሚለውን ቃል አሁን ሳስብ አንድ ነገር ትዝ አለኝ፡፡ በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ መንግሥትና የቻይና መንግሥት ባላቸው ቅርርብነት የተነሳ ቻይናዎች በአዲስ አበባ ከተማችን (የሌላውን ስለማላውቅ ነው) ብዙ የመሥረተ ልማት ሥራዎች እያከናወኑ ይገኛሉ፡፡ ለምሳሌ ያህል የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ግንባታ ልብ ማለት ይቻላል፡፡ ታዲያ ይህ በእንዲህ እንዳለ ግንባታው በሚካሆድበት አካባቢና ሥፍራ፣ የግንባታው ተቋራጭ ተቋም ስያሜ፣ እንዲሁም በግንባታው ዙሪያ ሊደርሱ ለሚችሉ አደጋዎች ማስጠንቀቂያዎች፣ በሙሉ በቻይንኛ አንዳንዴም በቻይንኛ እና በእንግሊዘኛ ተጽፈው ይገኛሉ፡፡ ጽሑፎቹ ለማን እንዲነበቡ ተደርገው የተጻፉ ስለመሆናቸው ሳስብ፣ ምላሽ አጣና ይገርመኛል፡፡ ቻይናዎች ግንባታ በሚያካሂዱበት በማንኛውም ሥፍራ፣ (china aid) ከሚል እንግሊዘኛ ጽሑፍ በስተቀር፣ አንድም አማርኛ መግለጫ የለም፡፡ - ለምን?

በመሠረቱ ቋንቋ ይለመዳል፡፡ በባዕድ ሐገር ቋንቋ መናገር መቻል፣ ችሎታ እንጂ ዕውቀት አይደለም፡፡ ልምድ እንጂ፡፡ ቋንቋ አንዱ የዕውቀት ማግኛ እንጂ፣ በራሱ ዕውቀት አይደለም፡፡ ማንበብና መጻፍ የማይችሉ መኀይማን (ፈረንጅ ቤት ተቀጣሪ ሠራተኞች) ጣሊያንኛ፣ እንግሊዘኛ፣ ፈረንሳይኛ፣ አረቢኛ … ወዘተ አቀላጥፈው ይናገራሉ፡፡- በልምድ፡፡ እነዚያ ታዲያ ቋንቋውን መልመድና መናገር መቻላቸው ምሁራን አያደርጋቸውም፡፡ የኛ ሐገር አንዳንዱ ምሁራን ተብየዎች (መሪዎችንም ይጨምራል) በአማርኛ ንግግራቸው ውስጥ እንግሊዝኛን ካላዳቀሉ፣ ማኅበረሰቡ እንደ “ምሁር” ቅቡል አድርጎ፣ የሚከተላቸው ወይም የሚቀበላቸው አይመስላቸውም፡፡

የዚህ ጽሑፍ አንባቢ፣ ስለቋንቋ የአነሳሳኋቸውን አንዳንድ ነጥቦች መዘህ፣ “ታዲያ ምን ይጠበስ?” ትለኝ ይሆናል፡፡ እኔም “ምንም” እልህና ሐሳቡ ለቋንቋው ባለቤት፣ ተናጋሪና ጸሐፊ ይድረስ፣ ሐሳቡን እያወጣና እያወረደ፣ የመወያያ ዕድል ይፍጠር እልሀለሁ፡፡

በመጨረሻም፣ የአማርኛ ቋንቋ ባለቤት አለው፡፡ ይኸው የቋንቋው ባለቤት ሊጠብቀው፣ ሊያሳድገው፣ ሊያዳብረው ይገባል፡፡ በተለይ የጽሕፈት ቋንቋው፣ ሞክሼ የምንላቸው ፊደላት (ሞክሼ የምንላቸው በተለምዶ እንጂ ራሳቸውን ችለው የቆሙና ፍቺ ያላቸው ናቸው) በትክክለኛው ቦታቸው እንዲኖሩ መደረጋቸውን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡ በፌደራሉ ዋና ከተማ አዲስ አበባ፣ የሚታዩ መሥሪያ ቤቶች፣ አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች፣ ባጠቃላይ መታወቂያቸውና ማስታወቂያቸው በእንግሊዘኛ ቋንቋ ከመሆኑ የተነሳ፣ አንዳንዴ ባዕድ ሐገር ከተማ ያለሁ ያለሁ ይመስለኛል፡፡ ገራሚው ደግሞ ብሔራዊው ቋንቋ ከታች ተረግጦ፣ የባዕድ ቋንቋ ከላይ ሲውል ነው፡፡ በመሆኑም ቋንቋው ደረጃውን የጠበቀ ይሆን ዘንድ፣ መንግሥት (የፌደራሉ) ወይም የአማራ ክልላዊ መንግሥት፣ የአማርኛና የሌሎች ብሔር ብሔረ ሰቦች ቋንቋ ፖሊሲ ቢያበጁ ወይም ቢቀርጹ፣ እንዲሁም የቋንቋ መፍቻ መዝገበ ቃላቶች፣ በአንድ ማዕከል እንዲዘጋጅ ቢደረግ፣ መፍትሔ ሳይሆን አይቀሩም፡፡

እንግል-እንግል-አማርአማር-ዝኛ-ዝኛአፈወርቅ በቀለ ከልሌ

Page 29: ቅፅ 2 ቁጥር 110 ቅዳሜ ህዳር 19 ቀን 2013 ዓ.ም

2828ግዮን ቁጥር 110 ህዳር 2013 ዓ.ም

2828ግዮን ቁጥር 110 ህዳር 2013 ዓ.ም

ቢዝነስ ዜናዎችአቢሲኒያ ባንክ ከፍተኛውን የተቀማጭ

ገንዘብ ዕድገት አስመዘገበከግል ባንኮች 25ኛ ዓመት ላይ ከደረሱት ጥቂት ባንኮች

መካከል አንዱ የሆነው የአቢሲኒያ ባንክ በ2012 የሒሳብ ዓመት፣ የተቀማጭ ገንዘብ መጠኑን 47 ቢሊዮን ብር በማድረስ ከፍተኛ የሚባለውን ዕድገት ማስመዝገቡንና ከታክስ በፊት 1.08 ቢሊዮን ብር ማትረፍ መቻሉን አስታወቀ፡፡ ባንኩ የ2012 የሒሳብ ዓመት ለባለአክሲዮኖች ይፋ ባደረገበት ሪፖርቱ፣ በሒሳብ ዓመቱ መጨረሻ ላይ ማሰባሰብ የቻለው ተቀማጭ ገንዘብ በኢንዱስትሪው ከፍተኛ የሚባል የዕድገት ምጣኔ ያሳየበት ነው፡፡ የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሊቀመንበር አቶ መሠረት ታዬ እንደገለጹትም፣ ለአንድ የንግድ ባንክ ዕድገት ዋነኛ መሠረቱ ተቀማጭ ገንዘብን ማሳደግ በመሆኑ፣ ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ አቢሲኒያ ባንክ በ2012 የሒሳብ ዓመት ግልጽ አቅጣጫ አስቀምጦ በመንቀሳቀሱ ከፍተኛ የሚባለውን የተቀማጭ ገንዘብ ዕድገት ሊያስመዘግብ ችሏል፡፡ በዚህ መሠረት ባንኩ በሒሳብ ዓመቱ 15.48 ቢሊዮን ብር ወይም 48.1 በመቶ ዕድገት በማስመዝገብ፣ አጠቃላይ የተቀማጭ ገንዘብ መጠኑን ከ32.15 ቢሊዮን ብር ወደ 47.63 ቢሊዮን ብር ለማድረስ ችሏል፡፡ ይህ አፈጻጸም ባንኩ በሒሳብ ዓመቱ ማሰባሰብ አለብኝ ብሎ ካቀደውም በላይ ውጤት የተገኘበት ስለመሆኑ ተናግረዋል፡፡ ባንኩ በሒሳብ ዓመቱ አቅዶ የነበረው 14.5 ቢሊዮን ብር ነበር፡፡ ከዚህ አንፃር አፈጻጸሙ በ1.18 ቢሊዮን ብር ጭማሪ ያሳየ መሆኑን የቦርዱ ሊቀመንበር ገልጸዋል፡፡ የተቀማጭ ገንዘቡ ዕድገት የተገኘው በዋናነት የገንዘብ አስቀማጭ ደንበኞቹን ቁጥር በማሳደጉ መሆኑም ተመልክቷል፡፡ የቦርድ ሊቀመንበሩ እንዳመለከቱትም ባንኩ በ2012 የሒሳብ ዓመት ብቻ 1.3 ሚሊዮን አዳዲስ ደንበኞችን ማፍራት በመቻሉና የባንኩን ጠቅላላ የገንዘብ አስቀማጭ ደንበኞችን ቁጥር ከቀደመው የሒሳብ ዓመት በእጥፍ በማሳደግ 2.6 ሚሊዮን ብር እንዲደርስ አስችሏል፡፡

የኮሙዩኒኬሽን ሳተላይት በሽርክና ለመሥራት መንግሥት ዕቅድ እንዳለው ተገለጸ

መንግሥት በሚቀጥሉት ሦስት ወይም አራት ዓመታት ወደ ህዋ ለማምጠቅ ያቀደውን የኮሙዩኒኬሽን ሳተላይት፣ በግልና በመንግሥት አጋርነት ለመገንባት ዕቅድ ሙያዙ ተጠቆመ፡፡ ከ350 ሚሊዮን በላይ ዶላር በሚገመት ወጪ እንደሚገነባ የተነገረለት የኮሙዩኒኬሽን ሳተላይት በትምህርት፣ በግብርና፣ እንዲሁም ጤናና መሰል ዘርፎች የላቀ አስተዋጽኦ አንደሚኖረው ተገልጿል፡፡ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዲ ይልማ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የሳተላይቱ መገንባት ለአገሪቱ ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት የታለመ ቢሆንም፣ ለግንባታው ያስፈልጋል ተብሎ የታሰበውን የገንዘብ መጠን መንግሥት መሸፈን ስለማይችል፣ በተለያዩ አማራጮች በተለይም በግልና በመንግሥት አጋርነት ወይም በዝቅተኛ የወለድ መጠን ሊገኝ በሚችል ብድር ለመገንባት እንደታቀደ ገልጸዋል፡፡ መንግሥት በሽርክና ለማልማት ፍላጎት ያለው ቢሆንም፣ ዋና ዳይሬክተሩ ዝርዝሩን ከመግለጽ ተቆጥበዋል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጭነት አገልግሎቱን ወደ አትላንታና አላስካ ማስፋፋቱን ተገለጸ

በአሁኑ ወቅት የኮሮናቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝ የተጓዦችን የእንቅስቃሴ አድማስ መገደቡ ይታወቃል። ይህም በአየር የትራንስፖርት ዘርፍ ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ተጽዕኖ አስከትሏል። ለችግሩ መፍትሄ ለመፈለግ የእቃ ጭነት አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙ አየር መንገዶች ግን “እያደገ የሚገኝ ትርፍ እያስመዘገቡ ነው” ተብሏል፡፡ በአለም አቀፍ ደረጃ የጭነት አገልግሎት እየሰጡ ከፍተኛ ትርፍ እያስመዘገቡ ከሚገኙት አየር መንገዶች አንዱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ነው። ‘አየር መንገዱ የኢትዮጵያ ጭነት እና ሎጂስቲክስ አገልግሎቶች’ በሚል ትናንት ይፋ ባደረገው የጭነት አገልግሎት ተመራጭ ሆኖ እየሰራ እንደሚገኝ ሲምፕል ፍላይንግ አስነብቧል።

አህጉር አቋራጭ የሆነውን የጭነት አገልግሎቱን ከወር በፊት መጀመሩን አስታውሶ፤ አየር መንገዱ በደቡብ ኮሪያ እና በአሜሪካ መካከል የጭነት አገልግሎት በመስጠት ቁልፍ ሚና መጫወቱን ዘግቧል። በአሁኑ ወቅትም የአገልግሎት ተደራሽነቱን በማስፋፋት ወደ አትላንታና አላስካ የጭነት አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አየር መንገዱ በትዊተር ገጹ አስነብቧል።

ቡና ኢንሹራንስ ኩባንያ የትርፍ ምጣኔው መጨመሩን አስታወቀ

ቡና ኢንሹራንስ አክሲዮን ማኅበር በ2012 የሒሳብ ዓመት ከመድን ሥራ ውል ያገኘው የትርፍ መጠን ሲቀንስ ከተለያዩ ኢንቨስትመንቶቹ ያገኘው ገቢ ግን ማደጉን አስታወቀ፡፡ ኩባንያው የ2012 የሒሳብ ዓመት አፈጻጸሙን ይፋ ባደረገበት ጠቅላላ ጉባዔ ላይ እንደገለጸው፣ በሒሳብ ዓመቱ የመድን ውል ሥራ ያስገኘለት ትርፍ መጠን 27.9 ሚሊዮን ብር ነው፡፡ ይህ የትርፍ መጠን ከቀዳሚው ዓመት የመድን ውል ሥራ ትርፍ ሲነፃፀር በ6.59 ሚሊዮን ብር ያነሰ ሆኗል፡፡ ኩባንያው በ2011 የሒሳብ ዓመት ከመድን ውል ሥራ አግኝቶ የነበረው የትርፍ መጠን 34.44 ሚሊዮን ብር እንደነበር ታውቋል፡፡ በ2012 ደግሞ ከዚሁ ዘርፍ አገኛለሁ ብሎ አቅዶ የነበረው 14.9 ሚሊዮን ብር ነው፡፡ አፈጻጸሙ ከዕቅዱ 66.6 በመቶ ነው፡፡

ቡና ኢንሹራንስ ከመድን ውል ሥራ ያገኘው ትርፍ ቅናሽ ሊያሳይ ከቻለባቸው ምክንያቶች በዋነኝነት የተጠቀሰው በተሽከርካሪ የውል ዓይነቶች ምክንያት በተፈጸመ በሕጋዊ ተጠያቂነት ለመጠባበቂያ የተያዘው የካሳ መጠን በመጨመሩ ነው፡፡ ይህም ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መከሰት በኋላ የጭነት ምልልስ መጨመርን ተከትሎ በተከሰቱ በርካታ አደጋዎች ምክንያት እንደሆነም የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዳኛቸው መሐሪ በዓመታዊ ሪፖርታቸው ጠቅሰዋል፡፡ ኩባንያው ከመድን ሥራ ውል ያገኘው ትርፍ ቢቀንስም በሌሎች የገቢ ምንጮች በ22 በመቶ ዕድገት በሒሳብ ዓመቱም ከተለያዩ የገቢ ምንጮች 34.46 ሚሊዮን ብር ገቢ ያገኘ ሲሆን፣ ይህ ገቢ ከዕቅዱ አንፃር ሲታይ 22 በመቶ ብልጫ አለው መባሉን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል፡፡

የኢትዮጵያ ነጋዴ ሴቶች ማኅበር ዕውቅና የመስጠት ፕሮግራም አካሄደ

የኢትዮጵያ ነጋዴ ሴቶች ማኅበር በአዲስ አበባ ቸርችል ጎዳና በሚገኘው ኤሊያና ሆቴል ሰፊ የምርት ማሳያ አዳራሽ በመከራየት የአባላቱ ምርቶች እንዲታዩ ብሎም ከገዢው ጋር ዘላቂ የሆነ የገበያ ትስስር እንዲፈጠር ለማድረግ ሰፊ ሥራ እንደተሰራ ተገለጸ፡፡ ማኅበሩ ይኽን ያለው የፕሮጀክቱ መጠናቀቅን ለማብሰርና ለስኬታማነቱ ድጋፍ ላደረጉ የማኅበሩ አባላትና አጋሮች ዕውቅና ለመስጠት ባዘጋጀው መድረክ ነው፡፡ ከተመሠረት 10 ዓመታትን ያስቆጠረው የኢትዮጵያ ነጋዴ ሴቶች ማኅበር በክልል ደረጃ የተዋቀሩ 14 ማኅበራትና በሥሩም ከ260 በላይ ቅርንጫፎችን ያቀፈ መኾኑ ተገልጹዋል፡፡ በመድረኩ የመንግሥት የተለያዩ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ሚኒስትሮችና ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

በአዲስ አበባ የኤሌክትሪክ አውቶብስ ሙከራ ሊጀመር ነው

በአዲስ አበባ ከተማ የኤሌክትሪክ አውቶብስ የሙከራ ትግበራ ለማድረግ የዝግጅት ስራዎች በመከናወን ላይ መሆናቸው ተገልጿል። በዚህም የኤሌክትሪክ አውቶብስ በከተማው ላይ የሙከራ ትግበራ ለማከናወን ተቀማጭነቱ ለንደን ካደረገው ሲ40 ሲቲስ ጋር በቅንጅት በመስራት ላይ ይገኛል ተብሏል። ቢሮው ከሲ40 ሲቲስ ጋር በመተባበርም የኤሌክትሪክ አውቶብስ የሙከራ ትግበራ በከተማዋ ፈጣን አውቶብስ ኮሪደር ላይ እንዴት እንደሚተገበር አለም አቀፋዊ የሁለት ቀናት የቪዲዮ ኮንፈረንስ አውደ ጥናት አካሂዷል። የአዲስ አበባ መስተዳድር እና የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የተለያዩ የመፍትሄ ሃሳቦችን ተግባራዊ በማድረግ ላይ እንደሚገኙ ገልፀዋል።

በመሪ እቅዱ ላይ የተቀመጡ የከተማ ፈጣን አውቶብስ ኮሪደሮች የማልማት ስራዎችን በማከናወን ለችግሩ የመፍትሄ አካል የሆኑትን የከተማ ፈጣን አውቶብስ የሚጠቀምባቸውን በናፍጣ የሚሰሩ እና ሌሎቹን አውቶቡሶች በቀጣይ ወደ ኤሌክትሪክ የመቀየር እቅድ አንዱ ነው፡፡ የፕሮጀክቱ ዋና አላማም በአዲስ አበባ የከተማ ፈጣን አውቶብስ እና በሌሎችም የከተማዋ ኮሪደሮች ላይ ባትሪ-ኤሌክትሪክ አውቶቡሶችን /ኢ-ባስ/ በመጠቀም የግሪን-ሀውስ ጋዝ ልቀት ፣ የአየር ብክለት እና የህብረተሰቡን የጤና ችግር መቀነስ ነው።

Page 30: ቅፅ 2 ቁጥር 110 ቅዳሜ ህዳር 19 ቀን 2013 ዓ.ም