4
ካለመናገር ደጃዝማችነት ይቀራል ጭውውት በየወሩ የሚወጣ የድሕረ ገጽ መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 1 ሄሊኮፍተሩን ማን ወሰደው. ከድሬደዋ ተነስቶ በልምምድ ላይ የነበረው MI-35 gunship ሄሊኮፍተር በፓይለቱ ተጠልፎ ኤርትራ እንዳረፈ የተሰማ ወሬ ነው። የኢትዮጵያ መንግሥት ባወጣው መግለጫ ጠላፊው ለምን እንደጠለፈ ምክንያቱን ባይናገርም የጠላት እጅ እንዳለበት መጠቆሙ አልቀረም። ጠላት ሲሉ ደግሞ ኤርትራን ማለታቸው ለመሆኑ ማብራሪያም አላስፈለገም። $25 ሚሊዮን እንደሚያወጣ የተተመነው ሄሊኮፍተር አብራሪ ሻንበል ሳሙኤል ግደይ መሆኑ በዜና አውታሮች ሲወራ ምክትል አብራሪው የመቶ አለቃ ቢልልኝ ደሳለኝ እንደ ነበረና የበረራ ቴክኒሻያኑ ጸጋ ብርሃን ግደይ እንደነበረም ተዘግቧል። ወፍ ሲበር ማየት ይችላሉ የተባለላቸው የሃገራችን የበረራ ባለሙያዎች ተዘናግተው ወይስ ተጭበርብረው እንደሆነ ግን የተሰጠ ማብራሪያ የለም። ስልጣን መለዋወጥ መለመዱ መልካም ነው። የተለያየ የቦርድ ሊቀመንበር የተፈራረቀበት የኢትዮጽያ አየር መንገድ እነሆ ዳግመኛ አዲስ ሊቀመንበር እንዳገኘ እየተዘገበ ነው። የአቶ እስዬ አብርሃ የአምባሳደር ስዩም መስፍን የአቶ አዲሱ ለገሰን የመሪነት ባህል የተላመደው አየር መንገድ አሁን ደግሞ አቶ አዲሱ ለገሰ በቃኝ ብለው በፈቃዳቸው ሲለቁ አባ ዱላ ገመዳ ካላችሁ ይሁና ብለው ሹመቱን እንደተቀበሉ ሰማን። ሹመት ያዳብር እንዳንል ይህ ሃላፊነት እንጂ ሹመት አይደለም ያሉን በረከቱና አፋችንን በዳቦ አልን። ነገር ግን በቃኝ ማለት መጀመሩ መልካም መሆኑን መናገር ተገቢ እንደሆነ እያመንን። የሚሾሙት ደግሞ ሃላፊነት የተደራረባቸው ባይሆኑ መልካም ነው እንላለን። ውሻ አፍ ቢፈታ ጩኸት ቀርቶ መደንፋቱ መልመጥመጡ እግር መሳም፣ ጭራ መምታት ማወዛወዝ ዘሎ ማቀፍ ፍቅረ ሰላም። ሎሌነትን ለማሳየት ታማኝነት ለማስመስከር፣ ውሻ ሁሉ በየቤቱ ይጣር የሚል ያልተሰማ ንግርት ነበር? አንድ የሆነው ባህሪያቸው፤ የውሾቹ ጠባያቸው፤ ቢናገሩስ አፍ አውጥተው ሹክ ቢሉ የቃኙትን ፣ ባደባባይ ቢያሳብቁ ውሻ ሆነው ያጤኑትን፤ ምን ይፈጠር ነበር? ወንድሞቼ እስቲ አስቡት ለደቂቃ፤ ምስክር ቢሆን ላየው ሁሉ ከደፉ ላይ በሰቆቃ። አስቡት እስቲ ላንድ አፍታ፣ ልንሰማ የምንችለውን ጉድ ውሻ በድንገት አፍ ቢፈታ። ከተኮላ መኮንን የግጥም ስብስብ የተወሰደ ታህሳስ 26 2007 January 4, 2014 ማውጫ የሳምንቱ ክስተት ከደረሰን ምርጫና ዲሞክራሲ ሄሊኮፍተሩን ማን ወሰደው ትጥቃቸውን የቀየሩ ገጽ 2 አባቴን ማን ያውቃል ገጽ 3 Photo Caption ምስጋና ይህንን መጽሔት እንድናዘጋጅ ላበረታታችሁን ሁሉ ምስጋናችን ይድረሳችሁ። እንዳበረታታችሁን ጀምረናል እንደ ድጋፋችሁ ደግሞ እናድጋለን። የምታዩትን ስህተት ከጠቆማችሁን እንታረማለን ጥሩ ሥራችንን ካበረታታችሁን ደግሞ ለበለጠ ውጤት እንጥራለን። እምነት እንደጣላችሁብን ሁሉ በእናንተ ላይ የጣልነውን እምነት ተቀበሉን። ደምመላሽ ደበበ ተኮላ መኮንን 1. ጭውውት መጽሔት ሁላችሁንም እንኳን ለገና በዓል አአደረሳችሁ ይላል። ለፈገግታ እቴጌ ጣይቱ አለቃ ገብረሓናን አይወዷቸውም ነበርና ለፋሲካ በሙክት ፋንታ የበሬ እግር ውሰዱለት ብለው ባለሟሎቻቸውን አዘዙ። አለቃም ሁኔታው የንቀት መሆኑ ስለገባቸው ተናደው፣ ወይ ጉድ ይህማ በዛ፣ እመቤታችን እግር እያነሱ ለሁላችንም መስጠት ከጀመሩ ንጉሱ ምን ተረፋቸው አሉ ይባላል። ለአለቃ ገብረ ሓና መጽሐፍ የተወሰደ። [email protected]

አባቴ ልጅ ነበር - ውውት_1.pdf · PDF fileየተቀዱ አባባሎች “Never tell me the sky’s the limit when there are footprints on the moon.” ጨረቃ ላይ

  • Upload
    lamdang

  • View
    258

  • Download
    13

Embed Size (px)

Citation preview

ካለመናገር ደጃዝማችነት ይቀራል

ጭውውት በየወሩ የሚወጣ የድሕረ ገጽ መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 1

ሄሊኮፍተሩን ማን ወሰደው.

ከድሬደዋ ተነስቶ በልምምድ ላይ የነበረው MI-35 gunship ሄሊኮፍተር

በፓይለቱ ተጠልፎ ኤርትራ እንዳረፈ የተሰማ ወሬ ነው። የኢትዮጵያ

መንግሥት ባወጣው መግለጫ ጠላፊው ለምን እንደጠለፈ ምክንያቱን

ባይናገርም የጠላት እጅ እንዳለበት መጠቆሙ አልቀረም። ጠላት ሲሉ

ደግሞ ኤርትራን ማለታቸው ለመሆኑ ማብራሪያም አላስፈለገም። $25

ሚሊዮን እንደሚያወጣ የተተመነው ሄሊኮፍተር አብራሪ ሻንበል ሳሙኤል

ግደይ መሆኑ በዜና አውታሮች ሲወራ ምክትል አብራሪው የመቶ አለቃ

ቢልልኝ ደሳለኝ እንደ ነበረና የበረራ ቴክኒሻያኑ ጸጋ ብርሃን ግደይ

እንደነበረም ተዘግቧል። ወፍ ሲበር ማየት ይችላሉ የተባለላቸው የሃገራችን

የበረራ ባለሙያዎች ተዘናግተው ወይስ ተጭበርብረው እንደሆነ ግን የተሰጠ

ማብራሪያ የለም።

ስልጣን መለዋወጥ መለመዱ መልካም ነው።

የተለያየ የቦርድ ሊቀመንበር የተፈራረቀበት የኢትዮጽያ አየር

መንገድ እነሆ ዳግመኛ አዲስ ሊቀመንበር እንዳገኘ እየተዘገበ ነው።

የአቶ እስዬ አብርሃ የአምባሳደር ስዩም መስፍን የአቶ አዲሱ ለገሰን

የመሪነት ባህል የተላመደው አየር መንገድ አሁን ደግሞ አቶ አዲሱ

ለገሰ በቃኝ ብለው በፈቃዳቸው ሲለቁ አባ ዱላ ገመዳ ካላችሁ

ይሁና ብለው ሹመቱን እንደተቀበሉ ሰማን። ሹመት ያዳብር

እንዳንል ይህ ሃላፊነት እንጂ ሹመት አይደለም ያሉን በረከቱና

አፋችንን በዳቦ አልን። ነገር ግን በቃኝ ማለት መጀመሩ መልካም

መሆኑን መናገር ተገቢ እንደሆነ እያመንን። የሚሾሙት ደግሞ

ሃላፊነት የተደራረባቸው ባይሆኑ መልካም ነው እንላለን።

ውሻ አፍ ቢፈታ

ጩኸት ቀርቶ መደንፋቱ መልመጥመጡ

እግር መሳም፣

ጭራ መምታት ማወዛወዝ ዘሎ ማቀፍ

ፍቅረ ሰላም።

ሎሌነትን ለማሳየት ታማኝነት

ለማስመስከር፣

ውሻ ሁሉ በየቤቱ ይጣር የሚል ያልተሰማ

ንግርት ነበር?

አንድ የሆነው ባህሪያቸው፤

የውሾቹ ጠባያቸው፤

ቢናገሩስ አፍ አውጥተው ሹክ ቢሉ

የቃኙትን ፣

ባደባባይ ቢያሳብቁ ውሻ ሆነው

ያጤኑትን፤

ምን ይፈጠር ነበር? ወንድሞቼ እስቲ

አስቡት ለደቂቃ፤

ምስክር ቢሆን ላየው ሁሉ ከደፉ ላይ

በሰቆቃ።

አስቡት እስቲ ላንድ አፍታ፣

ልንሰማ የምንችለውን ጉድ ውሻ በድንገት አፍ ቢፈታ።

ከተኮላ መኮንን የግጥም ስብስብ የተወሰደ

ታህሳስ 26 2007 January 4, 2014

ማውጫ

የሳምንቱ ክስተት

ከደረሰን

ምርጫና ዲሞክራሲ

ሄሊኮፍተሩን ማን ወሰደው?

ትጥቃቸውን የቀየሩ ገጽ 2

አባቴን ማን ያውቃል ገጽ 3

Photo Caption

ምስጋና ይህንን መጽሔት እንድናዘጋጅ ላበረታታችሁን ሁሉ ምስጋናችን

ይድረሳችሁ። እንዳበረታታችሁን ጀምረናል እንደ ድጋፋችሁ ደግሞ

እናድጋለን። የምታዩትን ስህተት ከጠቆማችሁን እንታረማለን ጥሩ

ሥራችንን ካበረታታችሁን ደግሞ ለበለጠ ውጤት እንጥራለን።

እምነት እንደጣላችሁብን ሁሉ በእናንተ ላይ የጣልነውን እምነት

ተቀበሉን።

ደምመላሽ ደበበ ተኮላ መኮንን

1.

ጭውውት መጽሔት

ሁላችሁንም እንኳን ለገና

በዓል አአደረሳችሁ ይላል።

ለፈገግታ

እቴጌ ጣይቱ አለቃ ገብረሓናን

አይወዷቸውም ነበርና ለፋሲካ

በሙክት ፋንታ የበሬ እግር

ውሰዱለት ብለው ባለሟሎቻቸውን

አዘዙ። አለቃም ሁኔታው የንቀት

መሆኑ ስለገባቸው ተናደው፣ ወይ

ጉድ ይህማ በዛ፣ እመቤታችን እግር

እያነሱ ለሁላችንም መስጠት

ከጀመሩ ንጉሱ ምን ተረፋቸው አሉ

ይባላል።

ለአለቃ ገብረ ሓና መጽሐፍ የተወሰደ።

[email protected]

ካለመናገር ደጃዝማችነት ይቀራል

ጭውውት

በየወሩ የሚወጣ የድሕረ ገጽ መጽሔት

ትጥቃቸውን ቀይረው ካሜራ ያነገቱ የቀድሞ ታጋዮች።

የኢትዮጵያ ተማሪዎች እንቅስቃሴ በተነሳ ቁጥር ስማቸው ይነሳል። ለኢሕአፓና

ለፓርቲው ሠራዊት መመስረት ቅድሚያ ሚና ተጫውተዋል። በግራ በኩል የቆመውና

በካላሽን ምትክ ካሜራ ያንጠለጠለው የዛሬው አብዲሳ የበረሃው እሮባ የሠራዊቱ መሪ

ነበር። ከዓርባ ዓመት በፊት ለትግል ብለው አውሮፕላን ከባህር ዳር ከጠለፉት መካከል

አንዱ እሱ ነበር። እራሱን ብቻ ሳይሆን የግሉ የነበረችውን ሽጉጡንም ለዚሁ ጠለፋ

እንደለገሰ የሚያወራው እሱ ሳይሆን ሌሎች ናቸው። ዛሬ እንደትላንቱ ዝም አልልም

ብሎ የሚያውቀውን ለአንባብያን ለማቅረብ ተነስቷል። የተሠራውን ጥሩ ሥራ ለመናገር

አያፍርም። ለተደረገው ስህተተ ደግሞ መሸፋፈንን አይቀበልም። እንደ አመራር

ለተደረገው ስህተት የግሉን ሃላፊነት ለመቀበል ወደ ኋላ እንደማይል ይናገራል።

ድርጅቱን በትናንትናና በዛሬ እይታ እያወዳደረ መተረክ ጀምሯል። በእሱ እምነት

“ታሪክ የሠሩት ለትግሉ ሕይወታቸውን የከፈሉት ናቸው። እኛ ግን እውነቱን በመተረክ

ለመጭው ትውልድ ትምህርት መስጠት አለብን” ብሎም ያምናል። በተለያዩ የአሜሪካ

ከተሞች እየተዘዋወረ በትግል አብረውት ከነበሩት ጋር እየተወያየ ነው። የዚያ

ትውልድ ታሪክ የመሪ ታሪክ ሳይሆን የሁሉም ታጋይ ታሪክ ነበርና ታሪኩም በጅምላ

እንጂ በተናጠል መነገር የለበትም ይላል። ካሜራውን ያነገተው የድምጽ መቅረጫውን

ያነገበው ብእርና ማስታወሻ ተሸክሞ እየዞረ ያለው አብዲሳ ጅምሩን እንደሚጨርሰው

ደጋግሞ ቃል ይገባል። እናቸንፋለን ብሎ ገብቶት የነበረው ቃል ለምን ተግባራዊ ሊሆን

እንደአልቻለም ሊያጫውተን ነው። ባለፈው በተደረገው ይናደዳል። የትላንትናው

እንዳይደገም ደግሞ ተመክሮአችንን የማካፈል ግዳጅ አለብን ብሎ ያምናል።

ስለግል ኑሮው አሁንም አይጨነቅም። ልጆች ወልዶ አሳድጓል። ካናዳን ሃገሬ ቶሮንቶን

ቤት ጎጆዬ ካለ ዓመት እየመጣ አልፏል። ዛሬ ግን የሚሰማው ጆሮውን አሰልችቶት፣

የሚያነበውን ማመን አቅቶት ዝምታዬ ማብቃት አለበት ብሎ የድሮ ጓደኛወን ተነስ ብሎ

የሚያውቀውን ሊናገር፣ የተሰማውን ሊያወያይ፣ ውሸት ያለውን ሊያስተባብል ቆርጦ

ተነስቷል። ፎቶው ላይ እንደሚታየው ቁመቱ ዘንጣፋ አይደለም። ልበ ሙሉነቱና

ግልጽነቱ ግን አደገ እንጂ አልቀጨጨም። የሚያውቀው እስካሁን ያልተናገረው ብዙ

ነገር እንዳለ ካጀማማሩ መተንበይ ይቻላል።

“ታሪክ የሠሩት ለትግሉ ሕይወታቸውን የከፈሉት ናቸው። እኛ ግን እውነቱን

በመተረክ ለመጭው ትውልድ ትምህርት መስጠት አለብን”

ካለመናገር ደጃዝማችነት ይቀራል

“በዩንቨርስቲ ትግል ወቅት ያልሆንኩትን ጉልበተኛ ነበር ብለው ያወራሉ።

እኔ እስከማውቀው ድረስ አፍላ ታጋይ እንጂ ጉልበተኛ አልነበርኩም”።

ይህንን የሚለው በቀኝ በኩል የቆመውና በሽበቱ የሚኮራው ዳዩት ስዩም ነው። በዩንቨርስቲ የተደረጉ የትግል ትውስታዎች ሲነሱ ዳዊት መነሳቱ

አልቀረም። ዛሬ ለምስክርነት የተነሳው ዳዊት በሠራዊቱ ውስጥ የጠቅላይ

አመራር አባል ነበር። ኤርትራ ውስጥ ድርጅቱን ወክሎ ይመላለስ ስለነበረ

“አምባሳደር” የሚል የቅጽል ሥም የሰጡት ግለሰቦች እንደ ነበሩ በውይይት ላይ ተነስቶ ሲሰማ የተኮረኮረ ያክል ስቋል። ዛሬ ትዳር መስርቶ የልጆች

አባት መሆኑን ብቻ ሳይሆን ላኦስን የመኖሪያ ሥፍራው ያደረገው ዲያን

ቢያን ፉን ለማስታወስ ነው ለሚሉት ማስተባበያ አልሰጠም። ታሪካችንን

እንጻፈው ብሎ ከአብዲሳ ጋር መነሳቱን ሲናገር እንባ እየተናነቀው ነው።

በነበረው ሃላፊነት በተለይ በሜዳ ለተከሰተው ሁሉ ተጠያቂ ነህ ለሚሉት መልስ አለው። ደረጃውን እንጂ ሃላፊነቱን ለመሸሽ አይከጅልም።

ባልነበረበት እንደ ነበረ ተደርጎ የተወራውንም ለማስተባበልም ሆነ

ለማመን ደግሞ በጽሑፍ ማስፈሩ ይበልጥ ይረዳል ብሎ ያምናል።

የሚጻፈው ታሪክ ደግሞ የሁላችንም ንብረት ነውና ከሚገኘው ገቢ

ተጠቃሚው ሁሉም መሆን እንዳለበት አጥብቆ ይናገራል። ከትላንትናው የትግል አጋሩ የዛሬው ጓደኛው ጋር የነበራቸው ግንኙነት ከሜዳ በፊት

የነበረ እንደ ነበረ ያወቅነው የጋራ ትዝታቸውን ሲያወጉን ነው።

እንደትላንቱ ግልፍተኝነት አላየንበትም። ከመናገር ይልቅ ማዳመጥን

ሲመርጥ አስተውለናል። ለሚነሱ ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት ወደ ኋላ አይልም።

ሊያወያዩአቸው ፈቃደኛ የሆኑትን ሁሉ ለማነጋገር ፈቃደኛ እንደ ሆኑ

ሲናገር የትላንትናው የትግል ስህተት ካለመደማመጥና ካለመወያየት የመጣ

ነው ብሎ በማመን ነው። አምባ ገነንነት አልነበረም ብሎ መከራከር

እንደማይቻል እየተናገረ የቅራኔ የልዩነት አፈታት መንገዳችን ስህተት ነበር ሲልም በሙሉ ልቡ ነው። ብዙ የሚነገሩ የትግል ታሪክ ክስተቶች

መኖራቸውን እያበሰረ ዛሬ እሱና አብዲሳ የጀመሩት እቅድ የተጀመረው

የዛሬ 30 ዓመት ቢሆን ኖሮ ምን ይሆን ነበር?ብለው ለጠየቁት “ጥሩ

ይሆን ነበር። አልሆነም። የዛሬ 30 ዓመት ያለን የማስታወስ ችሎታና ዛሬ

ያለን ሰማይና ምድር ነው። ነገር ግን አልተደረገም ከሚል ተንደርድሮ

አናደርግም ለማለት መከጀል ድክመት ይሆናል ይላል። ከብዙ ግለሰቦች ጋር ስወያይ የረሳሁትን እያስታወሱኝ ነው። ለዚህም ነው በጋራ

የምናስታውሰውን እንጻፈው የምንለው” ብሎ ይደመድማል። መሸበት

ብቻ አይደለም መብሰልም አይተንበታል። ዛሬ ሠራተኞች ቀጥሮ

በማሠራት በግል የማምረት ሥራ ላይ እንዳለ የነገረን ዳዊት “ሙሴ ጋሌብ” ሆኖ እንደሆነና እንዳልሆነ የሚነግረን አላገኘንም። ተማሪ እያለ

ካኪ እንደለበሰ ሁሉ ዛሬም ከረባት አስሮ አላየነውም። በቁምጣ አገኘንው

እንጂ።

የጀመሩት ተሳክቶላቸው የሥራቸውን ውጤት በቅርቡ እንደምናይ

ጭውውት ምኞቱ ነው። ዛሬ ላይ ሆነን ትላንትናን መገምገም ቀላል ነው።

በትላንትናው እይታ የትላንትናውን ለአንባብያን መተረክ ግን ብዙ ሥራን

ይጠይቃል። በተለይ ለነበሩት ሳይሆን በወቅቱ ላልነበሩት ምን ተደረገ?

ብለው ለሚጠይቁ ለዛሬዎቹ ወጣቶች ለመተረክ ማለታችን ነው። ሁለቱም ያደጉ ልጆች አፍርተዋል። ኢትዮጵያም ደርሰው እንደ ተመለሱ

መረጃ ይሆን ዘንድ ሰሜን ተራራ የተነሱትን የለጠፍነውን ፎቶግራፍ

ለመረጃ ለግሰውናል።

ጭውውት መልካሙን ይመኝላቸዋል። ያስጀመራችው ያስጨርሳችው ዘንድ ምኞቱን ይገልጻል።

አባቴን ማን ያውቃል?

መልኬን አመሳስሎ አፍ ግንባሬን አይቶ

ፈገግታዬን ገጼን ቁመቴን ለክቶ፤

አካሄዴን ሳይቀር ሁሉን አወዳድሮ ፤

የሱ ነው አይደለም ይላል ተከራክሮ።

ሥራ የፈታ ሰው ለምን ይጨነቃል?

ካለእናቴ በቀር አባቴን ማን ያውቃል?

ጭውውት

በየወሩ የሚወጣ የድሕረ ገጽ መጽሔት።

አባቴ ልጅ ነበር

እንኮኮውን ሳልጠግብ ጭኑን

ሳልዘልበት፣

ደረቱን ታሽቼ ክንዱን

ሳልተኛበት፣

አባቴ አንቀላፋ ሞተ አረፈ

ድንገት።

ታዲያ በዚያን ሰዓት እድሜውን

ሳስበው፣

የሞተው አባቴ አርባ ሸምግሎ

ነው።

ዛሬ ግን ሳጤነው ዘመኑን ሳሰላ፣

የትላንትናውን ሳስበው የኋላ፤

ከእኔ እድሜ ላይ ቆሜ ቁልቁል

እያየሁት፣

አርባ ልጅ መሆኑን አሁን

ተረዳሁት።

ከተኮላ መኮንን የግጥም ስብስብ የተወሰደ

“በዩንቨርስቲ ትግል ወቅት ያልሆንኩትን ጉልበተኛ ነበር

ብለው ያወራሉ። እኔ እስከማውቀው ድረስ አፍላ ታጋይ

እንጂ ጉልበተኛ አልነበርኩም”።”

“የዛሬ 30 ዓመት ያለን የማስታወስ ችሎታና ዛሬ ያለን ሰማይና ምድር

ነው። ነገር ግን አልተደረገም ከሚል ተንደርድሮ አናደርግም ለማለት

መከጀል ድክመት ይሆናል”

ካለመናገር ደጃዝማችነት ይቀራል

ጭውውት

በየወሩ የሚወጣ የድሕረ ገጽ መጽሔት።

በንጉሡ ዘመን በሕግ አምላክ፣ በኃይለሥላሴ አምላክ፣

ወድቃ በተነሳችው ሰንደቅ ዓላማ፣ ሲባል ካለበት ቆም

በማለት የተፈጠሩትን ችግሮች ሁሉ በሕግ አክብሮ

የተቀበለ ኩሩ ሕዝብ ቢኖር የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው::

በኋላም የወሮበላው ደርግ መንግሥት ከዙፋኑ ላይ

ሲፈናጠጥ ጋሻ ጃግሬዎቹ ልጆቹን ዓይኑ እያየ እየረሸኑ

በየቀበሌው አስከሬን እንደ ስጥ ዘርረው ሲያውሉ፥

የወላጆችን አእምሮ ለማዞር በሲባጎ እያነቁ በየአደባባዩ

“እኔን ያየህ ተቀጣ” “ቀይ ሽብር ይፋፋምብኝ” የሚል

መፈክር ለጥፈው እንደ ንግድ ማስታወቂያ

በየመተላለፊያው ላይ ሲዘርሯቸው፣ ለጅብ እራት

እንዲሆኑ በየጫካው ሲጥሏቸው፣ አስተውሎ አሻፈረኝ

ብሎ ያመጸ ሕዝብ ነው። እንደ እምነቱ አምላኩንም

ተማጽኑኗል። በሚችለው ሁሉ ታግሏል፥ ያ ባይሆንማ

ኖሮ የመንግሥቱ ኃይለማርያም ነፍሰ ገዳይ መንግሥት

ተገርስሶ አይወድቅም ነበር።

የደርግ መንግሥት በሕዝቡና በታጋይ ልጆቹ

መስዋእትነት ሲንኮታኮት የነዚያ የገዳዮች ቁንጮ እግሬ

አውጪኝ ብሎ ሲሸሽ የቀሩትን ገዳዮች ሊገድል

አልተነሳም፣ እራሱን ሕግ ሳይኖር የሕግ ተገዢ አድርጎ

ሰነበተ እንጂ።

ኢሕአደግ ከገጠር ወደ ከተማ ባሸናፊነት ሲገባ፣

በየአቅጣጫው የወታደሩ መንግሥት መዋቅር ሲፈራርስ

እራሱን በራሱ የጠበቀ እንደ ተፈራው ሳይገዳደል ሥነ

ሥርአት ያለው ኩሩ ሕዝብ መሆኑን ያስመሰከረ ሕዝብ

ቢኖር የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው።

ባለፉት ታደጋጋሚ ምርጫዎችም በነቂስ እየወጣ

አያውቅም የሚሉትን ያሳፈረ አስተዋይ ሕዝብ ነው::

በተለይም በ1997 ምርጫ በሌላው ዓለም ባልታዬ

መልኩ በነቂስ ወጥቶ በሥነ ሥርአት ምርጫውን

ያደረገ፣ በጨዋነቱ እኛንም ሆነ የዓለምን ሕዝብ

ያስገረመ ድንቅ ሕዝብ ነው:: ከምርጫው ውጤት

በኋላም የተፈጠረው ብጥብጥ እጅጉን ያሳዘነው ይኸው

ዲሞክራሲ አልገባውም የተባለው ሕዝብ ነው። ታዲያ

የዚህን ትእግስተኛ ሕዝብ የልብ ትርተና ምርጫ

መንግሥትም ሆነ ተቃዋሚዎች የማክበር ግዴታ

እንዳለባቸው መገንዘብ የግድ ይሏል። አሁንም

እየተቃረብ ያለው ምርጫ ካለፉት ምርጫዎች በተሻለ

መንገድ መመቻቸትና መካሄድ እንዳለበት መገንዘብ

ይኖርብናል። ጋዜጦች፣: ሬዲዎኖች: ቴሌቪዥኖች

ባጠቃላይ የመገናኛ አውታሮች ለመንግሥትም ሆነ

ለተቃዋሚው በእኩልነት መጠቀም የሚችሉበት መንገድ

መመቻቸት ይኖርበታል። ኢሕአደግም ሆነ ተቃቃሚዎች

በተገቢው መንገድ ሀሳባቸውን ካለፍርሃት ለዚህ ኩሩ

ሕዝብ የማቅረብና የማስረዳት ታሪካዊ ግዴታ

አላባቸው እንላለን:: መራጩ ሕዝብም እሮሮውን

ያዳመጠውን እየሾመ ያላዳመጠውን እየሻረ ፍላጎቱን

የሚያሟላለትን እየደገፈ የማይቀበለውን ካርዱን እየነፈገ

መብቱን መጠቀም ይኖርበታል። ኢትዬጵያ የሰላምና

የብልፅግና ሀገር እንድትሆን የዴሞክራሲ ባህሉ ከመዳህ

ወጥቶ ወፌ ቆመች ይባልላት ዘንድ የሁሉም ሰው ምኞት

የሰላም ወዳድ ግለሰብ እምነት መሆን ይገባዋል::

ካሁን በኋላ የማንም

እናት ከል አትልበስ!!

ምርጫና ዴሞክራሲ

የተቀዱ አባባሎች

“Never tell me the

sky’s the limit when

there are footprints

on the moon.”

ጨረቃ ላይ የሰው ዱካ

እያየሁ እያለ የሁሉም ጣራው

ሰማይ ነው አትበሉኝ።

“If you don’t like

something, change it.

If you can’t change it,

change your attitude.”

–Maya Angelou

አንድን ነገር ካልወደድከው

ቀይረው መቀየር ካልቻልክ

ግን አመለካከትህን ቀይር።

ካንድ አርሶ አደር የተጋራነው

“እኝህ ሰው

ከምሑርም

ምሑር ከሊቅም

ሊቅ ናቸው፣

ለምን ቢሉ

የተናገሩት ምኑም

አልገባንም”