25
በበበበበ በበበበበ በበ በበበበበ በበበ በበበ በበበበበበበ 2006 በበበ በበበ በበበበ በበበ በበበበበ በበበበ 0

reddplusethiopia.files.wordpress.com…  · Web view · 2015-11-18በሰው ልጅ የእድገትና የልማት ተግባራት የተነሳ በተፈጠረው የአየር ንብረት

Embed Size (px)

Citation preview

Page 1: reddplusethiopia.files.wordpress.com…  · Web view · 2015-11-18በሰው ልጅ የእድገትና የልማት ተግባራት የተነሳ በተፈጠረው የአየር ንብረት

በኢፌዲሪ አካባቢና ደን ሚኒስቴር

የሬድ ፕላስ ሴክሬታሪያት

የ2006 በጀት ዓመት ዓመታዊ የሥራ

አፈጻጸም ሪፖርት

ሐምሌ 2006 ዓ.ም አዲስ አበባ

0

Page 2: reddplusethiopia.files.wordpress.com…  · Web view · 2015-11-18በሰው ልጅ የእድገትና የልማት ተግባራት የተነሳ በተፈጠረው የአየር ንብረት

በአካባቢና ደን ሚኒስቴር የሬድ ፕላስ ሴክሬታሪያት

የ2006 በጀት ዓመት ዓመታዊ ሪፖርት

1.መግቢያ1.1. የፕሮጀክቱ ዳራ

የሃገራችንን የደን ሀብት በማልማት፣ በመንከባከብና በመጠበቅ ለህብረተሰቡ የሚሰጠውን የሥርዓተ ምህዳር አግልግሎቶችን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጥቅሞችን በመጨመር አስተዋጽዖ እንዲያበረክት መንግስት በቀየሰው

ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ ስትራቴጂ ውስጥ አንዱ ምሰሶ አድርጎ ተቀምጧል፡፡

በሰው ልጅ የእድገትና የልማት ተግባራት የተነሳ በተፈጠረው የአየር ንብረት ለውጥ የአሁኑ ጊዜ የዓለማችን መሪ አጀንዳ ሆኖ እያነጋገረ ይገኛል፡፡ ለዚሁ የአየር ንብረት ለውጥ ምክንያቶች መካከል በድንጋይ ከሰልና ነዳጅ በማቃጠልና በደን ጭፍጨፋ አማካኝነት ወደ ከባቢ አየር በከፍተኛ መጠን የሚለቀቁ ሙቀት አማቂ በካይ ጋዞች ቀዳሚዉን ቦታ ይይዛሉ፡፡ ይህን ችግር ለመፍታት የዓለማችን ሀገራት የተለያዩ እርምጃዎች እንዲወስዱ በየጊዜው እየተገናኙ ይመክራሉ፣ ይደራደራሉ፡፡ በዓለም አቀፍ

ደረጃ ከሚለቀቁ ሙቀት አማቂ በካይ ጋዞች ውስጥ ከደን ዘርፍ የሚለቀቀው ሀያ በመቶውን ያህል ይይዛል፡፡ በመሆኑም እ.ኤ.አ 2005 ጀምሮ በተወሰኑ የደን ሃብት ባላቸው ታዳጊ ሀገራት መሪነት የደኑን ዘርፍ ልቀት ለመቀነስ በተባበሩት መንግስታት የአየር

ንብረት ለውጥ መከላከያ ኮንቬንሽን ላይ (United Nations Convention on Climate Change-UNFCCC) ሀሳብ አቅርበው በሂደት ተቀባነት አግኝቷል፡፡ በዚሁ መሰረት ታዳጊ ሀገሮች ከደን ዘርፍ የደን ጭፍጨፋና መራቆትን

በመከላከል ለሚያደረጉት የበካይ ጋዝ ቅነሳና በደን ልማት አማካኝነት ከከባቢ አየር ለሚመጡት ካርቦን (carbon sequestration) የገንዘብ ድጋፍ የሚያስገኝ የ Reducing Emissions from Deforestation and Forest Degradation (REDD+) ፖሊሲ ስርዓት በመዘርጋቱ በርካታ ሀገራት የአቅም ግንባታ፣ የቴክኒክና የስልት

ዝግጅት እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡ ኢትዮጵያም ለዝግጅት ምዕራፍ ድጋፍ ካገኙ ሀገሮች አንዷ ሆናለች፡፡

ከደን የሚለቀቅ በካይ ጋዝ ቅነሳ (REDD+) እንቅስቃሴ በሀገራችን የተጀምረው እ.ኤ. አ በ 2008 ሲሆን፤ ይኸውም የጀመረው የቀድሞ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ሀገሪቱ በዚህ ዓለም አቀፍ ፕሮግራም ተጠቃሚ እንደምትሆን በመገንዘብ ለደን

ካርቦን ትብብር ፋሲሊቲ (Forest Carbon Partnership Facility, FCPF) በፕሮግራሙ ለመሳተፍ ፍላጎት በገለፀበት ሀሳብ መግለጫ (Program Idea Note, PIN) አማካኝነት ነው፡፡ ከዚያም በመቀጠል ሀገሪቱ ከደን ካርቦን

ትብብር ፋሲሊቲ ባገኘችው አዎንታዊ ምላሽና የገንዘብ ድጋፍ እ.ኤ. አ ከ 2010 እስከ 2011 የፕሮግራሙን የዝግጅት ምዕራፍ የስራ ዕቅድ (REDD+ Readiness Preparation Proposal- R-PP) አዘጋጅታ በደን ካርቦን ትብብር ፋሲሊቲ

ገምጋሚ ኮሚቴ በመጋቢት 2011 ጸድቆላታል፡፡ ይህ የስራ ዕቅድ (R-PP) ሀገሪቱ ለ REDD+ ፕሮግራም ዝግጁ ለመሆን ማከናወን ያለባትን ተግባራት የሚዘረዝር ሰነድ ሲሆን ከኦክቶበር 2012 ጀምሮ ከዓለም ባንክ ባገኘችው ገንዘብ ድጋፍ

አማካኝነትና አስፈላጊውን ተቋም (ሴክሬታሪያት) በማቋቋም እና አሰራር በመዘርጋት ትግበራውን ከጥር 2013 እ.አ.አ. ጀምሮ እያከናወነች ትገኛለች፡፡

1

Page 3: reddplusethiopia.files.wordpress.com…  · Web view · 2015-11-18በሰው ልጅ የእድገትና የልማት ተግባራት የተነሳ በተፈጠረው የአየር ንብረት

ምንም እንኳን REDD+ ቀድሞ የተነደፈ ፕሮግራም ቢሆንም ሀገሪቱ በ 2011 በነደፈችው በዓለም ደረጃ የታወቀችበትና ትኩረት የሳበውን ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ (Climate Resilient Green Economy)

ስልት ውስጥ የREDD+ ፕሮግራም ለአረንጓዴው ኢኮኖሚ ምስረታ የሚያበረክተው ከፍተኛ አስተዋፅዖ በመገንዘብ መንግስት በፍጥነት ከሚተገበሩና ትኩረት ከተሰጣቸው የአረንጓዴው ልማት ስትራቴጂ ወሳኝ ምሰሶዎች ተብለው ከተለዩት አራት ዋና ዋና

ፕሮገራሞች ውስጥ አንዱ ሆኖ ተቀምጧል፡፡

1.2. የዝግጅት ምዕራፍ ዓላማና ፕሮገራሙ ለሀገራችን የሚያስገኛቸው ጠቀሜታዎች፣

ከደን የሚለቀቅ በካይ ጋዝ ቅነሳ (REDD+) የዝግጅት ምዕራፍ ዋና ዓላማ የዓለም አቀፉን የ REDD+ ፕሮግራም ሦስት የትግበራ ደረጃዎችን/ ምዕራፎችን ማለትም የዝግጅት ምዕራፍ (Readiness phase) ፤ የፓይለቲንግ

(demonstrations at sub-national levels) ና ውጤትን መሰረት ያደረገ ክፍያ/ ድጋፍ (performance based payment) ተከትሎ ሀገሪቱ ወደፊት በፕርግራሙ ከዓለም አቀፉ REDD+ ሜካኒዝም ተጠቃሚ እንድትሆን

ዝግጁ ማድረግ ነው፡፡

ምንም እንኳን ኢትዮጵያ ከሌሎች ያደጉ ሀገራት አንፃር ብክለት መጠኗ እጅግ ትንሽ ቢሆንም በዚህ ፕሮገራም መሳተፏ አንደ ሀገር የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላክል የድርሻዋን በመወጣት ከካርቦን ንግድ ከምታገኘው ጥቅም ባሻገር የ REDD+ ፕሮግራም

ትግበራ የደን ዘርፉ እንዲጠናከር ከፍተኛ ሚና በመጫወት ለሀገሪቱ ብዙ ተጨማሪ ጥቅም ያስገኝላታል፡፡ የ REDD+ ፕሮግራምን በመተግበር ሀገሪቱ የደን ሽፋኗን በመጨመር ለኤሌክትሪክ ኃይል ምንጭነት፤ ለመስኖና ሌሎች ልማቶችን ለማካሄድ

የምትጠቀምበትን የዉሃ ሀብት በማጎልበት፤ የግብርና ምርታማነትን በመጨመርና ምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ፤ ከቱሪዝምና ከደን ሀብት የሚገኘውን ገቢ በማሣደግ እና አጠቃላይ የዜጎችን ኑሮ በማሻሻል የደኑ ዘርፍ የሚጫወተውን ስትራቴጂያዊ ሚና

እንዲጎላ ከፍተኛ አስተዋፅዖ ያደርጋል፡፡

1.3. የዝግጅት ምዕራፍ ዋና ዋና ተግባራት

ከደን የሚለቀቅ በካይ ጋዝ ቅነሳ የዝግጅት ምዕራፍ (REDD+ Readiness Phase) በአካባቢና ደን ሚኒሰቴር ስር በተቋቋመው ሴክሬታሪያት አማካኝነት ከዓለም ባንክ፤ እንዲሁም ከኖርዋይና እንግሊዝ መንግስታት ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ

አማካኝነት እስከ ሦስት ዓመት የሚከናወኑት ዋና ዋና ተግባራት የሚከተሉት ናቸው፡፡ እነሱም፡- (1) በፕሮግራሙ ዙሪያ አጠቃላይ ሀገር አቀፍ አቅም ግንባታ ማድረግ (capacity building on REDD+) ፣ (2) ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክርና

አጠቃላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎችን መስራት (Consultation and participation) ፣ (3) የዝግጅት ምዕራፉን ለማሳካትና ቀጣይ የፕሮግራሙን ትግበራ የሚመራና ትግበራውን የሚያስተባብር ተቋም መገንባትና የአመራርና

የቴክኒክ ቡደን አካላትን መመስረት (establishing REDD+ Management Structure) ፣ (4) ለፕሮግራሙ ስልት መንደፍ (developing REDD+ Strategy) ፣ (5) ለፕሮግራሙ ትግበራ የሚያስችሉ አጠቃላይ ተቋማዊ፤

የፖሊሲ፤ የህግና ሌሎች ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር፣(6) ከፕሮግራሙ ትግበራ በፊት በታሪክ ሀገሪቱ በየዓመቱ ከደን ዘርፍ የምትለቀውን በካይ ጋዝ የዓለም አቀፍ ደረጃዎችን በመከተል በትክክል መመጠን (establishing baseline

2

Page 4: reddplusethiopia.files.wordpress.com…  · Web view · 2015-11-18በሰው ልጅ የእድገትና የልማት ተግባራት የተነሳ በተፈጠረው የአየር ንብረት

emissions/reference levels) ፣ (7) በትግበራ ወቅት የፕሮግራሙን ውጤታማነት ለመለካትና የክፍያ መጠን ለመወሰን የሚያስችል የልኬት፤ ዘገባና ኦዲት ስርዓትን መዘርጋት (establishing measurement, reporting

and verification system) ፤ እና (8) የዝግጅት ምዕራፉን መከታተያና ግምገማ ስርዓት መዘርጋት ይገኙበታል፡፡

1.4. የዝግጅቱ ምዕራፍ ትግበራ ያለበት ደረጃ

የዝግጅት ምዕራፍ ከተጀመረበት ጥር 2013 እ.አ. አ ጀምሮ የተለያዩ ዋና ዋና ተግባራት ተከናውነዋል፡፡ ለዝግጅት ምዕራፉ ትግበራ የሚያስፈልገው የፋይናንስ ፍላጎት በሙሉ ሴክሬታሪያቱ ከዓለም ባንክ ጋር በመተባበር ከዓለም ባንክ ( የደን ካርቦን

ፓርትነርሺፕ ፋሲሊቲ) 3.6 ሚሊዮን ዶላር፤ ከኖርዌይ መንግስት 5 ሚሊዮን ዶላርና ከእንግሊዝ መንግስት (DFID) 5 ሚሊዮን ዶላር በአጠቃላይ ወደ አስራ አራት ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ድጋፍ አግኝቷል፡፡

በተቋም ዝርጋታ መንግስት የአካባቢና ደን ሚኒሰቴርን በማቋቋም ወሳኝ እርምጃ ወስዷል፡፡ በዚሁ ሚኒስቴር በተቋቋመው ደን ዘርፍ ስር ሆኖ የዝግጅት ምዕራፉን ለማሳካትና ቀጣይ የፕሮግራሙን ትግበራ የሚመራና ትግበራውን የሚያስተባብር ተቋም

መገንባትና የአመራርና የቴክኒክ ባለሙያዎችን በማሟላት የ REDD+ ሴክሬታሪያት ተቋቁሞ ስራ ጀምሯል፡፡ ሴክሬታሪያቱ ከተቋቋመ ወዲህ ለሀገር አቀፉ ዝግጅት ምዕራፍ አመራር የሚሰጥ ስቲሪንግ ኮሚቴ፤ ቴክኒካዊ ድጋፍ የሚያደርግ የፌደራል

ቴክኒክ ኮሚቴና የተለያዩ ተግባራትን የሚደግፉ 3 ንዑስ ኮሚቴዎችን በማቋቋም ከአባላት ጋር በርካታ ስብሰባዎችን አከናውኗል፡፡ ከነዚሁም ማኔጅሜንት አካላት ጋር በመገናኘት ግንዛቤ ለማስጨበጥና አብሮ ለመሥራት ተንቀሳቅሷል፡፡ በተጨማሪም

ሴክሬታሪያቱ በክልል ደረጃ የዝግጅት ምዕራፉን የሚስተባብሩ የ REDD+ አስተባባሪዎችን መርጦ የአቅም ግንባታና ግንዛቤ ማስጨበጫ እንቅስቃሴዎችን አድርጓል፡፡

የREDD+ ሴክሬታሪያት ከፍተኛ የደን ሽፋን ባለው የኦሮሚያ ክልል ውስጥ በክልል ደረጃ ያለውን ደን የሚያጠቃልል የREDD+ ፓይለት ፕሮግራም በመንደፍ ለፕሮግራሙ ዲዛይን የሚሆን 3 ሚሊዮን ዶላር ገንዘብ እንዲያገኝ በማድረግ

ሥራውን አስጀምሮ በመከታተልና ድጋፍ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ሴክሬታሪያቱ በኦሮሚያ ክልል ማስተባበሪያ በማቋቋም ላይ ይገኛል፡፡ ሌሎች ፓይለቶችን በሌሎች ክልሎች ለማካሄድ አማካሪ ቀጥሮ ለማሰራት በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡

የREDD+ Strategy ስራን የሚደግፍ ከዋና ዋና ባለድርሻ አካላት የተውጣጣ ግብረኃይል በማቋቋም የመጀመሪያውን ስብሰባ በታህሳስ አካሂዷል፡፡ እንዲሁም ሴክሬታሪያቱ ለብሔራዊ REDD+ Strategy ዝግጅት ግብዓት የሚሆኑ በዓለም አቀፍና በሀገር ውስጥ የአማካሪ ድርጅቶች የሚከናወኑ ሁለት ጥናቶችን በአማካሪ ድርጅቶች አማካኝነት ለማካሄድ የአማካሪ

ድርጅቶችን መረጣ በማድረግ ጥናቶቹን በቅርቡ ለማስጀመር በእንቅስቃሴ ላይ ይገኛል፡፡ ሴክሬታሪያቱ ለአንደኛው ጥናት 6 የሚሆኑ አማካሪ ድርጅቶችን በማወዳደር አንዱን ለመምረጥ ስራ ለማስጀመር በእንቅስቃሴ ላይ ሲገኝ ለሌላኛውን ጥናት 6

ኩባንያዎች መርጦ የቴክኒክና ፋይናንስ ፕሮፖዛሎች ለውድድር እንዲያቀርቡ ተጋብዘዋል፡፡

በልኬት፤ ዘገባና ኦዲት (baseline emissions and MRV system) ስርዓትን በመዘርጋትና የደን ዘርፍ በካይ ጋዝ ምጠና ዙሪያ ከዓለም ምግብና እርሻ ድርጅትና ሌሎች አጋሮች ጋር በመሆን ለመስራት ቅደም ዝግጅት ስራዎችንና ዕቅዶችን

3

Page 5: reddplusethiopia.files.wordpress.com…  · Web view · 2015-11-18በሰው ልጅ የእድገትና የልማት ተግባራት የተነሳ በተፈጠረው የአየር ንብረት

በመንደፍ ላይ ይገኛል፡፡ ከዓለም ምግብና እርሻ ድርጅት ጋር ተደጋጋሚ ምክክርን ቴክኒካዊ ስራዎችን በማከናወን ሴክሬታሪያቱ ይህን ስርዓት ለመገንባት የሚያስችለው ሰፊ ዕቅድና በጀት አውጥቷል፡፡

2. በ2006 በጀት ዓመተ የተከናወኑ ተግባራት ዝርዝር ማብራሪያ

2.1. ብሔራዊ የሥራ አመራር አደረጃጀትን መደገፍ

የሬድ ፕላስ ሴክሬታሪያት አደረጃጀትን በሰው ሀይል ለማብቃት በተያዘው እቅድ መሠረት 73 በመቶ ባለሙያዎች ማሟላት የተቻለ ሲሆን የMRV አማካሪ ለመቅጠር ዓለም አቀፍ ማስታወቂያ በማውጣትና በማወዳደር በተቀመጡት

መስፈርቶች ተመርጦ የቅጥር ሂደቱ በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ በሴክሬታሪቱ የሬድ የቴክኒክ አማካሪ ለመቅጠር ማስታወቂያ ቢወጣም ተወዳዳሪ መገኘት ባለመቻሉ ቅጥሩ አልተፈጸመም፡፡

የሬድ ፕላስ ሴክሬታሪያቱን ሥራዎች አመራር ለመስጠት የስቲሪንግ ኮሚቴ ስብሰባ፤ ቴክኒካዊ ድጋፍ የሚያደርግ የፌደራል ቴክኒክ ኮሚቴ ስብሰባዎችና የተለያዩ ቴክኒካል ተግባራትን የሚደግፉ 3 ንዑስ ኮሚቴዎች በማቋቋም በተቻለ መጠን ወቅቱን የጠበቀ

ስብሰባዎች በማካሄድ በዓመቱ የፕሮጀክቱን ሥራዎች አግዘዋል፡፡ እነዚህም የሬድ ፕላስ የዝግጅት ምእራፍ ትግበራ ወቅት የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን ( ከመንግስት፣ መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች፣ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና ህብረተሰቡ) ያሣተፈ የኮሚቴ አደረጃጀት በማካተት በሬድ ፕላስ ዙሪያ ግንዛቤ በመፍጠርና የሚኖራቸውን የሥራ ድርሻ እና ሃላፊነት ቢጋር በማዘጋጀት የዝግጅት

ምእራፉን እንዲደግፉ የተደረገ ሲሆን በዚህ መሠረት እያንዳንዳቸው 2 ስብሰባዎችን አካሂደዋል፡፡

በሬድ ፕላስ የሚመለከታቸውን አካላት አቅም ለመገንባት በተያዘው እቅድ መሠረት ለ 3 የሴክሬታሪያቱ አባላትና እና አካባቢና ደን ሚኒስቴር (አደሚ) በተለያየ ደረጃ ያሉ ሃላፊዎች ዓለም ዓቀፍ ስብሰባ እንዲሣተፉ ተደርጓል፡፡ ለ 22 የፌደራል/የክልሎች

የ REDD+ SC, TWG እና የሴክሪታሪያቱ አባላትን ያካተተ ትምህርታዊ ጉብኝት ከካርቦን ፕሮጀክት ጋር በተያያዘ በሀገር ውስጥ መልካም ልምድ ባላቸው ሁምቦ፣ ወላይታ ሶዶና ባሌ- ዶዶላ አካባቢዎች ተካሂዷል፡፡ ነገር ግን ሌሎች ከሀገር

ውጭ የተያዙ የአቅም ግንባታ ሥልጠናዎችና ትምህርታዊ ጉብኝቶች ከመስሪያ ቤቱ ሃላፊዎች ጋር በመመካከር በቀጣይ በትኩረት የሚሰሩ ይሆናል፡፡

የፕሮጀክቱን እንቅስቃሴ ወደ ክልሎች ለማውረድና በቅርበት ለማስተባበር ያመች ዘንድ ክልላዊ REDD+ SC, TWG

በኦሮሚያ ክልል የተቋቋመ ሲሆን የፕሮጀክት ማስተባበሪያ ክፍል ተመስርቶ ሥራ ጀምሯል፡፡ በሌሎች ክልሎች በቀጣይ

በጀት ዓመት ለመፈጸም በእቅድ ተይዞ የሚሰራ ይሆናል፡፡ እንዲሁም ከኦሮሚያ ክልል በተጨማሪ በደቡብ እና በትግራይ

ክልሎች ከተለያዩ የሬድ ባለድርሻ አካላት ለተውጣጡ የክልል ተወካዮች ለሁለት ተከታታይ ቀናት የግንዛቤ ማስጨበጫ

ሥራ በማከናወን እና ወደፊት ሬድ በክልሎች ውስጥ በምን ዓይነት የአስተዳደር መዋቅር መተግበር እንዳለበት ፕሮፖዛል

እንዲያዘጋጁ ተደርጓል፡፡

4

Page 6: reddplusethiopia.files.wordpress.com…  · Web view · 2015-11-18በሰው ልጅ የእድገትና የልማት ተግባራት የተነሳ በተፈጠረው የአየር ንብረት

የፕሮጀክቱን የአፈጻጸም ሪፖርት ወቅቱን በመጠበቅ የሩብ ዓመት 4 ጊዜ፣ ፕሮግረስ ሪፖርት 6 ጊዜ እንደአስፈላጊነቱ

ለሚመለከታቸው አካላት ማለትም ለሚ/ ር መ/ ቤቱ፣ ለዓለም ባንክ፣ ለኖርዌይ እና ለእንግሊዝ- ዲፊድ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡

2.2. ብሔራዊ የሬድ ፕላስ ስትራቴጂን ዝግጅት መደገፍ

በሬድ ፕላስ የግንዛቤ ማስጨበጫ ዙሪያ በሁለት ክልሎች 2 መድረክ በማዘጋጀት ውይይት ተደርጓል፡፡ በወንዶ ገነት የደንና የተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ አማካኝነት የአሰልጣኞች ሥልጠና ለክልል የሬድ የክልል ተጠሪዎች እና ከተለያየ ባለድርሻ አካላት ለተውጣጡ 35 የቴክኒክ ባለሙያዎች በREDD+, REL/MRV, Forest inventory ላይ የአቅም ግንባታ

ሥልጠና ተሰጥቶአል፡፡ በሬድ ፕላስ ዙሪያ በሀገር አቀፍ ደረጃ ግንዛቤ ለመፍጠርና በስፋት ለማስተዋወቅ የተለያዩ የኮሚኒኬሽን ሥራዎችና ማቴሪያሎች ጥቅም ላይ የዋሉ ሲሆን ከነዚህም መካከል፡- የሬድ አርማ መቅረጽና

በህትመቶች ውስጥ ማካተት፣ የሬድ አርማ ያለበት ስቲከር ( ብዛት 100 ቅጂ) ማሰራጨት፣ ለሴክሬታሪያቱ ሠራተኞች ቢዝነስ ካርድ (3000 ቅጂ) ፣ የሬድ አርማና የተለያዩ መልእክት ያለው ማታወሻ ደብተር (1000 ቅጂ) ፣ መጽሔት

( በሬድ ላይ የተጻፈ 1000 ቅጂ) ፣ በቢሮ የተዘጋጀ ብሮሸር (2000 ቅጂ) ፣ በግብርና ሚኒስቴር ድረ- ገጽ ውስጥ የሬድ ገጽ በመክፈት ከ 20 በላይ ልዩ ልዩ ዶክመንቶችን መጫን፣ የሬድ ፕላስ መደበኛ ኢሜል መክፈት

([email protected]) ፣ በ 2 ቪዲዮ የተቀዳ ዶክመንት መረጃ መያዝ ( በችግኝ ተከላና ኢትዮ- ኖርዌይ የጋራ ስምምነት ስብሰባ) ፣ 2032 ቲሸርት 1800 ኮፍያ እና 230 ቁልፍ መያዣ ( በችግኝ ተከላ፣

በትምህርታዊ ጉዞ እና በባህል ስፖርት ፌዴሬሽን ጋር በተካሄዱ ዝግጅቶች ላይ) የሬድ አርማና መልእክት ያለበት ማሰራጨት፣ ከ 100 በላይ ፎቶ መረጃዎች በደን አካባቢ የተሰበሰቡ እና ሌሎችን የኮሚኒኬሽን መሣሪያዎችን በመጠቀም በአጠቃላይ ለ 21,350 ህብረተሰብ ግንዛቤ መፍጠር ተችሏል፡፡ እንዲሁም የሬድ ፕላስ ኮሚኒኬሽን

ስትራቴጂ ለማዘጋጀት አማካሪ ድርጅት በጨረታ በመለየት እየተሰራ ሲሆን የመነሻ ሪፖርት አቅርቦ የተሰጠው አስተያየት በማካተት መረጃ በማሰባሰብ ሂደት ላይ ይገኛል፡፡

በሀገር አቀፍ ደረጃ በደን ምንጣሮና መመናመን መንስዔዎች ላይ ጥናት ለማካሄድ የአማካሪ መረጣ ሂደት በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል፡፡ እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል የ‘’Drivers of Deforestation and Degradation; Legal

and Institutional Framework; Reference Level; and Consultation and Participation Plan’’ ጥናቶችን ለማካሄድ በዓለም ባንክ በኩል በአማካሪ መረጣ ወቅት በአማካሪዎች የቀረበውን የቴክኒክ ዶክመንቶችን

በመገምገምና ሥራዎችን በመከታተልና በመደገፍ ላይ ይገኛል፡፡ ሌሎች ተቋማዊና የአካባቢና ማህበረሰብ ተፅእኖዎችን መከላከያ መንገዶች ለመቀየስ የሚያስችሉ ሁለት ጥናቶችም በውጭ ሀገርና በሀገር ውስጥ አማካሪ

ድርጅቶች ጥምረት በክልሉ በመካሄድ ላይ ይገኛሉ፡፡ በ SESA and ESMF ላይ ጥናት ለማካሄድ በተያዘው እቅድ

መሠረት ጥናቱን የሚያካሂድ አማካሪ ለመምረጥ ለመጨረሻ ግምገማ የተመረጡ 6 አማካሪ ድርጅቶች የቴክኒክና

የፋይናንስ ዶክመንት እንዲያዘጋጁ የተጠየቁ ሲሆን ያቀረቡት ፕሮፖዛል ተገምግሞ በመጨረሻ ከሚመረጠው የአማካሪ

ድርጅት ጋር በመፈራረም በአዲሱ በጀት ዓመት ሁለተኛው ወር ላይ ሥራው ይጀመራል ፡፡ እንዲሁም የሬድ ፕላስ

5

Page 7: reddplusethiopia.files.wordpress.com…  · Web view · 2015-11-18በሰው ልጅ የእድገትና የልማት ተግባራት የተነሳ በተፈጠረው የአየር ንብረት

ሴክሬታሪያት ሌሎች ፓይለቶችን በሌሎች ክልሎች ለመለየት፤ የፕሮጀክት መነሻ ሀሣብ ሰነድ ለማዘጋጀትና ለመተግበር

በአማካሪ ድርጅት በመታገዝ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል፡፡

2.3. ተጨማሪ ሥራዎች

በተለያዩ ጊዜያት ከዓለም ባንክ የሚመጡ የሥራ ቡድኖች ጋር በሬድ ፕላስ አተገባበር ዙሪያ ተከታታይ ውይይት ማካሄድ፣ በዓለም ምግብና እርሻ ድርጅት MRV ጥናት እንዲካሄድ የፕሮጀክት ዝግጅት ማድረግ፣ ከኖርዌይ መንግስት

ጋር የጋራ የትብብር ምክክር ማካሄድ፣ የኦሮሚያ ፓይለት ማደራጀት፣ በሬድ ፕላስ ላይ በ 3 ዩኒቨርስቲዎች ትምህርታዊ

ገለጻ መስጠት፣ የሬድ ፕላስ ፕሮጀክት የክትትልና ግምገማ ማእቀፍ ማዘጋጀት እና ለተለያዩ ተቋማት ድጋፍ መስጠት

የሚሉት ተጠቃሽ ናቸው፡፡

3. የፊዚካል ሥራዎች አፈጻጸም ሠንጠረዥ

ተ.ቁ የተግባራት ዝርዝር መለኪያየዓመቱ እቅድ

የዓመቱምር

መራእቅድ ክንውንአፈጻጸም በመቶኛ

ክፍል 1. ብሔራዊ የሥራ አመራር አደረጃጀትን መደገፍ

1.1 የሬድ ፕላስ ሴክሬታሪያት ሠራተቾች ቅጥርና ደመወዝ

ሀ የሴክሪታሪያቱ ሠራተኞች ደመወዝ ክፍያ በቁጥር 10 10 10 100ለ የእቅድ ክትትልና ግምገማ ባለሙያ ቅጥር በቁጥር 1 1 1 100ሐ የዓለም ዓቀፍ ቴክኒክ አማካሪ ባለሙያ ቅጥር በቁጥር 1 1 - -መ የ MRV ባለሙያ ቅጥር በቁጥር 1 1 1 90 በሂደት

ላይ

ሠ የፓይለት ፕሮጀክት አስተባባሪ ቅጥር በቁጥር 1 1 1 1001.2 መደበኛ የሆኑና/ ያልሆኑ ስብሰባዎችን ማካሄድ

ሀ የፕሮጀክቱ ስቲሪንግ ኮሚቴ ስብሰባ በቁጥር 4 4 1 25ለ የፕሮጀክቱ TWG ስብሰባ በቁጥር 4 4 3 75ሐ የፕሮጀክቱ የስትራቴጂ ሥራ ግብረ ሀይል ስብሰባ በቁጥር 8 8 3 37.5መ የፕሮጀክቱ የ SESA ሥራ ግብረ ሀይል ስብሰባ በቁጥር 8 8 4 50

6

Page 8: reddplusethiopia.files.wordpress.com…  · Web view · 2015-11-18በሰው ልጅ የእድገትና የልማት ተግባራት የተነሳ በተፈጠረው የአየር ንብረት

ተ.ቁ የተግባራት ዝርዝር መለኪያየዓመቱ እቅድ

የዓመቱምር

መራእቅድ ክንውንአፈጻጸም በመቶኛ

ሠ የፕሮጀክቱ የ REL/MRV ሥራ ግብረ ሀይል ስብሰባ በቁጥር 8 8 4 50ረ መደበኛ ያልሆኑ ስብሰባዎችን ከአጋር አካላት ጋር ማካሄድ በቁጥር 4 4 8 200

1.3 አቅም ግንባታ

ሀ ለሬድ ፕላስ ሴክሬታሪያት ሠራተኞች ስልጠና መስጠት በሰልጣኝ 7 7 - -ለ የሬድ ፕላስ እና አደሚ ሀላፊዎች/ ባለሙያዎች አለም አቀፍ

ስብሰባዎች ላይ ማሣተፍ፣በተሣታፊ

3 3 3 100

ሐ የፌደራል/ የክልሎች የ REDD+ SC and TWG አባላትን

በዓለም ዓቀፍ የሬድ ሥልጠናዎች/ ስብሰባዎች ማሣተፍ፣በተሣታፊ

8 8 - -

መ የፌደራል/ የክልሎች የ REDD+ SC, TWG እና የሴክሪታሪያቱን አባላት ትምህርታዊ ጉብኝት ማካሄድ፣ ( ከሀገር ውጭ)

በተሣታፊ 15 15 - -

ሠ የፌደራል/ የክልሎች የ REDD+ SC, TWG እና የሴክሪታሪያቱን አባላትን ትምህርታዊ ጉብኝት ማካሄድ፣ ( በሀገር ውስጥ)

በተሣታፊ 50 50 22 50

ረ የ REDD+ የመማማሪያ መድረክ (ኔትወርክ) መመስረት በተመሰረተ መድረክ

1 1 - -

1.4 የአፈጻጸም ሪፖርት ማዘጋጀት

ሀ የሩብ ዓመት ሪፖርት ማዘጋጀት - የፊዚካልና የሂሣብ በሪፖርት 4 4 4 100ለ ፕሮግረስ ሪፖርት ማዘጋጀት (REDD+ Readiness Progress

Fact Sheet)በሪፖርት 4 4 4 100

ሐ ፕሮግረስ ሪፖርት ማዘጋጀት ( for Joint Implementation

Support Mission ) እንደተጠየቀበሪፖርት 2 2 2 100

1.5 ያልተማከለ የሬድ ፕላስ ሥራ አመራር አደረጃጀት መደገፍ

ሀ ክልላዊ የ REDD+ SC and TWG መመስረት በክልል 3 3 1 33ለ ብሔራዊና ሁሉን አቀፍ የባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ

ማካሄድበመድረክ 2 2 1 50

ክፍል 2. ብሔራዊ የሬድ ፕላስ ስትራቴጂን ዝግጅትን መደገፍ

2.1 የሬድ ፕላስ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮችን በፌደራልና

በክልሎች ማካሄድበመድረክ 2 2 2 100

2.2 የአሠልጣኞች ሥልጠና መስጠት ( REDD+, REL/MRV,

Forest inventory)በሰልጣኝ 90 90 35 40

2.3 አጠቃላይ የኮሚኒኬሽን ማቴሪያል ማዘጋጀት (መጽሔት) በሰነድ 1 1 1 1002.4 የሬድ ፕላስ ድረ- ገጽ ማዘጋጀት፣ በድረገጽ 1 1 - -2.5 በደን ምንጣሮና መመናመን መንስዔዎች ላይ ጥናት ማካሄድ፣ በጥናት

ሰነድ1 1 1 90

7

Page 9: reddplusethiopia.files.wordpress.com…  · Web view · 2015-11-18በሰው ልጅ የእድገትና የልማት ተግባራት የተነሳ በተፈጠረው የአየር ንብረት

ተ.ቁ የተግባራት ዝርዝር መለኪያየዓመቱ እቅድ

የዓመቱምር

መራእቅድ ክንውንአፈጻጸም በመቶኛ

2.6 በ SESA and ESMF ጥናት ማካሄድ በጥናት ሰነድ

1 1 1 802.7 ለሬድ ፕላስ ፓይለት መለየትና የፕሮጀክት መነሻ ሀሣብ ማዘጋጀት በተዘጋጀ

ሰነድ1 1 1 75

2.8 ረቂቅ የሬድ ፕላስ ስትራቴጂ ማዘጋጀት በተዘጋጀ ሰነድ

1 1 - - ክፍል 3. ለሬድ ተቋማዊና ህጋዊ አተገባበር ማዕቀፍ ዝግጅት

ማድረግ

3.1 ለብሔራዊ የሬድ ፕላስ ፕሮጀክት ተግባራትና ፋይናንስ ፍሰት

የምዝገባ ሥርዓት ሰነድ ማዘጋት፣በተዘጋጀ ሰነድ

1 1 - -

4. የፋይናንስ አጠቃቀም

ከዓለም ባንክ ለእቅድ ዘመኑ ሥራዎች ማስፈጸሚያ ተመድቦ ከተለቀቀው ብር 36,317,350.00 በጀት ውስጥ ብር 6,366,588.64 ገንዘብ የመንግስትን የፋይናንስ ህግ በተከተለ አግባብ ሥራ ላይ የዋለ ሲሆን አፈጻጸሙም

17.53 በመቶ ነው፡፡

5. ያጋጠሙ ችግሮች

እስከ አሁን በአጠቃላይ በትግበራ ሂደት ያጋጠሙ ችግሮች፡- የዝግጅቱ ምዕራፍ ፕሮጀክት ከሶሰት ወር በላይ ዘግይቶ መጀመር፤

የሴክሬታሪያቱ ሠራተኞች ቅጥር መጓተት፤

ከግዥ ባለሞያ ቅጥር መዘግየትና ከመስሪያ ቤት ዝውውር ጋር ተያይዞ የፕሮጀክቱ ግዥ መጓተት፣

ሴክሬታሪያቱ አዲሱን ሚኒስቴር መስሪያ ቤት (አደሚ) ለማቋቋም ለስድስት ሣምንታት ሙሉ ጊዜውን በመስጠት በመስራቱ በፕሮጀክቱ ስራዎች ላይ ጫና መፈጠሩ፣

ከዚሁ ጋር ተያይዞ የፕሮጀክቱ ገንዘብ አጠቃቀም ዝቅተኛ መሆንም የሚሉት ይጠቀሣሉ፡፡

6. የተወሰዱ የመፍትሔ ሀሣቦች

የሴክሬታሪያቱ ቁልፍ ሰራተኞችን ቅጥር ለማፋጠን በተደረገው ጥረት በአሁኑ ሰዓት 10 ሰራተኞችን ቅጥር በማስፈፀም ሴክሬታሪያቱ አሁን በተሻለ አቅም እየሰራ ይገኛል፡፡ ከላይ የተጠቀሱትን ተግዳሮቶች ለመፍታት ሴክሬታሪያቱ ከአዲሱ ሚኒስቴር

መስሪያ ቤቱ ጋር በከፍተኛ ርብርብ በመንቀሳቀስ የማካካስ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡ የገንዘብ አጠቃቀምን ለማሻሻል ሴክሬታሪያቱ በፕሮጀክቱ ሰነድ መሰረት ከፍተኛ ገንዘብ የሚያስወጡትን ስራዎችና ግዥዎች በመለየት በቅድሚያ ትኩረት ሰጥቶ

ከበላይ አካላት ባገኘው ድጋፍና ርብርቦሽ አብዛኛው የቁሳቁስ ግዥ እንዲከናወን ተደርጎ የነበረበትን የረጅም ጊዜ ችግር

8

Page 10: reddplusethiopia.files.wordpress.com…  · Web view · 2015-11-18በሰው ልጅ የእድገትና የልማት ተግባራት የተነሳ በተፈጠረው የአየር ንብረት

በመቅረፍና በአሁኑ ወቅት ሚ/ ር መስሪያ ቤቱ በተከራየው ቢሮ በመግባት ምቹ ሁኔታ ተፈጥሮለት ስራን በተሻለ ሁኔታ እያከናወነ ይገኛል፡፡

7. ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች

በ FCPF እና በፕሮጀክቱ የክትትልና ግምገማ ማእቀፍ እቅድ ውስጥ በተቀመጡት አመላካች መለኪያዎች መሠረት R-PP ውን ለመተግበር የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን ያሣተፈ የስቲሪንግ ኮሚቴ፤ ቴክኒካዊ ድጋፍ የሚያደርግ ቴክኒክ ኮሚቴና

የተለያዩ ቴክኒካል ተግባራትን የሚደግፉ 3 ንዑስ ኮሚቴዎች ተቋቁመው በሥራ ላይ የሚገኙ ሲሆን የ R-PP ውን ትግበራ ወቅቱን ጠብቀው በመሰብሰብ ውሣኔዎችን በማሣለፍና ቴክኒካል ድጋፍ በማድረግ እንዲከታተሉ ስለሚጠበቅባቸው የሚገኙት

ተሰብሳቢዎች ቢያንስ 67 በመቶ አባላት ምልዓት ጉባዔ እንዲሆን ይጠበቃል፡፡ ነገር ግን በተካሄዱት ስብሰባዎች በሙሉ ምልዓተ ጉባዔው ከ 50 በመቶ በታች የነበሩ ሲሆን ይህንን ለመፍታት በተደረገው ጥረት በስብሰባው ወቅት

የሚከፈለው አበል ማነስ ለአባላት ተሣትፎ መቀነስ ዓቢይ ምክንያት ሆኖ በመቅረቡ እንዲሻሻል ተሰብሳቢው ጠይቋል፡፡ ከመንግስት የፋይናንስ አሰራር አንጻር በቅርቡ ከተሻሻለው በላይ መሄድ እንደማይቻል ማብራሪያና ውሳኔ

የተሰጠ ቢሆንም ለቀጣይ ለሚካሄዱ ስብሰባዎች ትኩረት በመስጠት ምልዓተ ጉባዔው ተሟልቶ እንዲገኝ በማድረግ መግባባት ፈጥሮ ሥራውን በተቀላጠፈ መልኩ ለማስኬድ ትኩረት መሰጠት ያለበት መሆኑን ሊሰመርበት ይገባል፡፡

የሬድ ፕላስ ፕሮግራም ለዝግጅት ምእራፍ ማስተግበሪያና ለሌሎች ፕሮግራሞች ከአጋር ድርጅቶች ከፍተኛ የገንዘብ ድጋፍ በማግኘት ላይ ይገኛል፡፡ ሆኖም ግን የገንዘብ አጠቃቀሙ እስካሁን በተለያዩ ምክንያቶች አጥጋቢ ስላልሆነ ይህን ለማካካስ

ለሴክሬታሪያቱና ለሌሎች አጋር አካላት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ (አደሚ) ልዩ ትኩረት በመስጠት አስፈላጊውንና ቀልጣፋ ድጋፍ ሊያደረግለት ይገባል፡፡

9