8
5 ኛ ትምህርት ለሐምሌ 25 2012

5ኛ ትምህርትለሐምሌ 2012 ወንጌል የሰሙትን ልቦች በሙሉ ነክቶ ነበር፡፡ ... ወንጌልን መስበክ ከችግሮች የፀዳ ስራ አይደለም፡፡

  • Upload
    others

  • View
    19

  • Download
    0

Embed Size (px)

Citation preview

  • 5ኛ ትምህርት ለሐምሌ 25፥ 2012

  • ምስክሩን ያዘጋጃል

    ያሳድጋል

    ያበረታል እንዲሁም ይመራል

    ቃሉን ይሰጣል

    ይለውጣል

    ምስክርነት ያለመንፈስ ቅዱስ ባዶ ነው፡፡ ምክንያቱም

    የዘላለም ህይወትን ፍሬ ሊያፈራ አይችልም፡፡

    ለዚህም ነው ኢየሱስ ደቀመዛሙርትን የመንፈስ ቅዱስን

    ሀይል ሳይቀበሉ ምስክርነታቸውን እንዳይጀምሩ

    ያዘዛቸው፡፡

    መንፈስ ቅዱስ እንዴት ምስክርነትን ፍሬያማ

    ያደርገዋል?

    መንፈስ ቅዱስ ከምስክርነት ጋር

    የተቆራኘው እንዴት ነው?

  • “ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜኃይልን ትቀበላላችሁ፥ በኢየሩሳሌምም በይሁዳም ሁሉ

    በሰማርያም እስከ ምድር ዳርም ድረስ ምስክሮቼ

    ትሆናላችሁ አለ።” (ሐዋ 1:8)

    ኢየሱስ ከማረጉ በፊት ረዳት (ጰራቅሊጦስ) እንደሚመጣ

    ቃል ገብቶ ነበር፡፡ ይህም መንፈስ ቅዱስ ነው፡፡ ኢየሱስ

    የሰጠንን ተልዕኮ እንድናከናውን ይረዳናል፡፡

    መንፈስ ቅዱስ ምን ምን ተግባራትን ያከናውናል?

    ምስክርነት የመንፈስ ቅዱስ የስራ አጋር መሆን ነው፡፡

  • ያሳድጋል“እግዚአብሔርንም እያመሰገኑ በሕዝብ ሁሉ ፊት ሞገስ ነበራቸው።ጌታም የሚድኑትን ዕለት ዕለት በእነርሱ ላይ ይጨምር ነበር።” (ሐዋ 2:47)

    የሐዋርያት ስራ መፅሀፍ ህይወታቸውን እንዲጠቀምበት

    በፈቀዱት ዘንድ የመንፈስ ቅዱስ ስራ ምን እንደሚመስል

    ያሳየናል፡፡

    አንዳንድ ጊዜያት በብዛት እስከ 3000 ወይም 5000

    የሚጠጉ (ሐዋ 2፡41 ፣ 4፡4) ወደጌታ የሚመለሱ ሰዎች

    ነበሩ፡፡ አንዳንዴም መላ ቤተሰብ የሚመለስባቸው ጊዜያት

    አሉ፡፡ (10፡ 44፣ 48)

    ይህንን ዕድገት ተከትሎ በተከታታይ አጥቢያ

    ቤተክርስትያናት ይተከሉ ነበር፡፡ (ሐዋ 16፡ 5)

    መንፈስ ቅዱስ መልዕክተኞቹን በሃይል ሞልቷቸው ነበር፡፡

    ወንጌል የሰሙትን ልቦች በሙሉ ነክቶ ነበር፡፡

    ሁሉም ሰው ለእግዚአብሔር አስፈላጊ ነው፡፡ እርሱ ለእያንዳንዱ

    ሰው ህይወቱን ሰጥቷል፡፡ ሁሉም ስለእርሱ እንዲያውቁ እና

    እንዲቀበሉት ይሻል፡፡ ይህንን ስራ ደግሞ እኛ እንድንሰራ

    ሹሞናል፡፡

  • “በመንፈቀ ሌሊት ግን ጳውሎስና ሲላስ እየጸለዩእግዚአብሔርን በዜማ ያመሰግኑ ነበር፥ እስረኞቹም

    ያደምጡአቸው ነበር፡፡” (ሐዋ 16:25)

    ወንጌልን መስበክ ከችግሮች የፀዳ ስራ አይደለም፡፡ ነገር ግን መንፈስ

    ቅዱስ እነ እስጢፋኖስን፣ ጳውሎስን እንዲሁም ሲላስን እንዳበረታቸው

    ያበረታል፡፡

    የልዩነት ግድግዳዎችን እያፈረሰ የቤተክርስትያንን አንድነት ይጠብቃል፡፡

    (11:15፣ 15:28).

    የተገቡ በሮችን በመክፈት እና በመዝጋት ወደትክክለኛዎቹ ቦታዎች እና

    ወደ ትክክለኛዎቹ ሰዎች መለኮታዊ በሆነ መንገድ ይመራናል፡፡ በእርሱ

    ስራ አማካኝነት ወንጌል በአውሮፓ እንዲሁም በአፍሪካ ሊሰበክ ችሏል፡፡

    (8:26-38፣ 16:6-10).

    መንፈስ ቅዱስ በሃይል ሊሞላን፣ ሊያበረታን፣ ሊያስተምረን፣ ሊመራን፣

    ሊያስተሳስረን፣ የምድራችንን ታላቁ ተልዕኮ ይህም ሰዎችን ወደክርስቶስ

    እና ወደ እውነቱ የመምራት ስራ አካል ሊያደርገን ይናፍቃል፡፡

  • “ነገር ግን ቃሉን ከሰሙት ብዙዎች አመኑ” (ሐዋ 4:4)መንፈስ ቅዱስ ምስክርነታችን በእግዚአብሔር ቃል እንዲመሰረት ያበረታታናል፡፡

    የሚከተሉትን ምሳሌዎች አጢኗቸው፡፡

    ፀሃፊዎቹን ያነሳሳቸው ራሱ መንፈስ ቅዱስ በመሆኑ የእግዚአብሔር ቃል የሰዎችን

    ህይወት የመለወጥ ሀይል አለው፡፡ ዛሬም በትህትና የሚያነቡትን ሁሉ ይህ መንፈስ

    ቅዱስ ልባችውን እየነካ ይገኛል፡፡

    ሐዋ 2:14-21. ጴጥሮስ

    በጴንጤቆስጤ ቀን ንግግሩ ኢዮኤልን

    እና መዝሙረ ዳዊትን ጠቅሶ

    ነበር፡፡

    ሐዋ 7. እስጢፋኖስ

    የእስራኤልን ህዝብ ታሪክ በመማክርት

    ጉባኤ ፊት ተጠቅሞት ነበር፡፡

    ሐዋ 8:35. ፊሊጶስ ከትንቢተ

    ኢሳያስ አንድ ጥቅስ በመነሳት ወደ መላው

    መጽሀፍ ቅዱስ ማብራራት ቀጠለ፡፡

    ሐዋ 17:3. ጳውሎስ

    ንግግሮቹን በእግዚአብሔር

    ቃል ላይ መሰረተ፡፡

  • “የእግዚአብሔርም መንፈስ በኃይል ይወርድብሃል፥ከእነርሱም ጋር ትንቢት ትናገራለህ፥ እንደ ሌላ

    ሰውም ሆነህ ትለወጣለህ።” (1ሳሙ 10:6)

    መንፈስ ቅዱስ ሰዎችን እንደማንነታቸው ይጠቀማቸዋል፡፡ ጭፍን ጥላቻን በመገርሰስ እና

    መጥፎ ባህርያትን በመለወጥ በክርስቶስ ፀጋ እና እውነት ይሞላቸዋል፡፡

    በሴቶችና በወንዶች፣ በሀብታምና በደሀ እንዲሁም

    በተማረ እና ባልተማረ መካከል ልዩነት አያደርግም፡፡

    ቀይ ሀር ትሸጥ የነበረችውን ሊድያን (ሐዋ 16:14-15)፣ ባርያውን አናሲሞስን (ፊልሞና 10)፣ በሮም አገረ ገዥ የነበረውን ሰርግዮስን (ሐዋ 13:6-12)፣አርዮስፋጎሳዊውን ዲዮናስዮስን (ሐዋ 17:34) …ለውጧቸዋል፡፡

    በዚያን ጊዜ እንደነበረው አሁንም ሀይለኛ ነው፡፡

    ሁሉንም አይነት ሰው በመለወጥ አሁንም ታዕምራትን

    ይሰራል፡፡

    ይኛ ስራ ሰዎችን መለወጥ አይደለም፡፡ ይህ የመንፈስ

    ቅዱስ ሚና ነው፡፡ የተጠራነው እንድንመሰክር ነው፡፡

  • “ክርስቶስና ደቀመዛሙርቱ እንዳደረጉት በኢየሱስ እንዳለው

    እውነት ያለ ምስክርነት ማፍራት አለብን፡፡ በመንፈስ ቅዱስ

    ችሎታ በመተማመን ስለእግዚአብሔር ምህረት፣ መልካምነት፣

    ስለተሰቀለውና ስለተነሳው አዳኝ በመመስከር ጨለማን

    ከብዙዎች አእምሮ በማውጣት ከብዙ ልቦች ምስጋና እና ውዳሴ

    ወደ እግዚአብሔር እንዲያርጉ ምክንያቶች ለመሆን

    ተጠርተናል፡፡ በሁሉም ሴትና ወንድ የእግዚአብሔር ልጆች

    የሚከወን ታላቅ ስራ አለ፡፡”

    ኤለን ጂ ዋይት (Selected Messages, 1ኛ መፅሀፍ, ምዕ 37, ገፅ 263)