8
18.3.2020 www.vinje.kommune.no https://www.vinje.kommune.no/informasjon-fraa-kommunen.525646.nn.html?printable=1 1 av 8 Oversatt til amharisk ኮሮና ቫይረስን አስመልክቶ ከኮሙነ የተሰጠ መረጃ (Informasjon frå kommunen i høve koronaviruset) የእረፍት ግዜ ማሳለፊያ ቤት (hytte) ላላችሁ ሰዎች የተዘጋጀ መረጃ በኮሮና ቫይረስ ህመም-19 (Covid-19) ወረርሽኝ ወቅት ራስን ማግለልን፣ ለብቻ ተለይቶ መቆየትን፣ እንዲሁም በዕረፍት ግዜ ማሳለፊያ ቤቶች በሚደረግ ቆይታ ላይ የተጣለ ማዕቀብን በሚመለከት የጤና እና የእንክብካቤ ሚኒስቴር አዲስ መመሪያ አውጥቷል። መመሪያውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ። ከበሽታው የመተላለፍ አደገኛነት በተጨማሪ በአካባቢና በክልል ደረጃ ያሉ የጤና አገልግሎቶች ለጥቃት በእጅጉ የተጋለጡ ናቸው። ህመሙ ወደ ጤና ባለሙያዎችም ሊተላለፍ ስለሚችል። በአሁኑ ሰዓትም በዚሁ የተነሳ ብዙ የጤና ባለሞያዎች ራሳቸውን አግልለው ይገኛሉ። ይህም በኮሙናችን ውስጥ ለሚኖሩትና ቆይታ ለሚያደርጉ ሰዎች ተመጣጣኝ የጤና አገልግሎት ርዳታ ለመስጠት ያለንን አቅም ይቀንሳል። አንድ ሰው በእረፍት ማሳለፊያ ቤቱ (hytta) እያለ ድንገተኛ አደጋ ሊደርስበት ይችላል፥ የመሰበር፣ የመውደቅ፣ በጭንቅላት ውስጥ የደም መፍሰስ፣ የልብ ህመም ... Vinje ኮሙነ 3676 ነዋሪዎች ብቻ ያሏት ትንሽ ኮሙነ ነች። ግን 5700 የሚበልጡ የእረፍት ግዜ ማሳለፊያ ቤቶች (hytter) ያሏት ሲሆን 20 000 እስከ 25 000 የሚደርሱ ሰዎች በአብዛኛዎቹ የአመቱ ቀናቶች በኮሙነዋ ውስጥ ቆይታ ያደርጋሉ። ተላላፊ በሽታው በአካባቢያችን፣ በብሔራዊና በዓለም አቀፍ ደረጃ የበለጠ እንዳይዛመት ለማድረግ ይህ እርምጃ በስራ ላይ እንዲውል ተደርጓል። እኛ በአሁኑ ግዜ ከምንገኝበት ሁኔታ አንጻር የተወሰደው እርምጃ ትክክለኛ ግን ከባድ እርምጃ ነው። የአየር አምቡላንስ በስምሪት ላይ ስለሚገኝ በእረፍት ግዜ ማሳለፊያ ቤታችሁ ሆናችሁ ድንገት ብትታመሙ የሄሊኮፕተር አምቡላንስ ይመጣልናል ብላችሁ እንዳትጠብቁ ልናስጠነቅቃችሁ እንፈልጋለን። ይህም በኮሮና ተላላፊ በሽታ አደገኛነት የተነሳ ነው። አንድን ሄሊኮፕተር ከቫይረሱ ነጻ ለማድረግ ረጅም ግዜ ይወስዳልና። ለተጨማሪ ንባብ እዚህ ይጫኑ። በዚህ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሁላችሁም እራሳችሁን እንድታረጋጉ አጥብቀን እንመክራለን። የሱፐርቪዥን (ቁጥጥር) እገዛ፥ የእረፍት ጊዜ ማሳለፊያ ቤት ያላችሁ ሰዎች በአሁኑ ወቅት በዕረፍት ግዜ ማሳለፊያ ቤቶች በሚደረግ ቆይታ ላይ የተጣለውን ማዕቀብ እንድታከብሩ እንፈልጋለን። በፊናችንም በሚቻለን ሁሉ በእረፍት ጊዜ ማሳላፊያ ቤቶች ላይ አስፈላጊ የሆነ ጥብቅ ውጪያዊ ቁጥጥር እናደርጋለን። Vinje ኮሙነ የቁጥጥር ስራ ለመስራት የባለሞያዎች እገዛ ያስፈልገዋል። እነሱም እጅግ አስፈላጊ እርምጃ መሆኑን ባዩ ጊዜ የስራውን ኃላፊነት ይወስዳሉ። ይህ አገልግሎት ለናንተ የእረፍት ጊዜ ማሳለፊያ ቤት ባለቤቶች ለሆናችሁ የሚያስወጣችሁ ወጪ አይኖርም። እኛ የተለያዩ አድራሻዎችንና የግንኙነት መረጃዎችን ዝርዝር በማዘጋጀት ለተለያዩ ጉዳዩ የሚመለከታቸው መሥሪያ ቤቶች እንልካለን። እነሱም በዙር ቁጥጥር ያደርጋሉ። እርምጃ መውሰድ የማያስፈልግ ከሆነም ይህንኑ አስመልክቶ መልስ ይላክላቸዋል። ጥያቄዎቻችሁን [email protected] ላኩ። ለናንት፣ ራሳችሁን አግልላችሁ (quarantine ውስጥ) ለምትገኙ

(Informasjon frå kommunen i høve koronaviruset) (hytte) · 2020. 8. 3. · እንደ ከዚህ በፊቱ በስፍራው ቆይታ ማድረግ ወይም በአካል መገኘት

  • Upload
    others

  • View
    0

  • Download
    0

Embed Size (px)

Citation preview

  • 18.3.2020 www.vinje.kommune.no

    https://www.vinje.kommune.no/informasjon-fraa-kommunen.525646.nn.html?printable=1 1 av 8

    Oversatt til amharisk

    ኮሮና ቫይረስን አስመልክቶ ከኮሙነ የተሰጠ መረጃ

    (Informasjon frå kommunen i høve koronaviruset)

    የእረፍት ግዜ ማሳለፊያ ቤት (hytte) ላላችሁ ሰዎች የተዘጋጀ መረጃ

    በኮሮና ቫይረስ ህመም-19 (Covid-19) ወረርሽኝ ወቅት ራስን ማግለልን፣ ለብቻ ተለይቶ መቆየትን፣ እንዲሁም

    በዕረፍት ግዜ ማሳለፊያ ቤቶች በሚደረግ ቆይታ ላይ የተጣለ ማዕቀብን በሚመለከት የጤና እና የእንክብካቤ

    ሚኒስቴር አዲስ መመሪያ አውጥቷል። መመሪያውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ።

    ከበሽታው የመተላለፍ አደገኛነት በተጨማሪ በአካባቢና በክልል ደረጃ ያሉ የጤና አገልግሎቶች ለጥቃት በእጅጉ

    የተጋለጡ ናቸው። ህመሙ ወደ ጤና ባለሙያዎችም ሊተላለፍ ስለሚችል። በአሁኑ ሰዓትም በዚሁ የተነሳ ብዙ የጤና

    ባለሞያዎች ራሳቸውን አግልለው ይገኛሉ። ይህም በኮሙናችን ውስጥ ለሚኖሩትና ቆይታ ለሚያደርጉ ሰዎች

    ተመጣጣኝ የጤና አገልግሎት ርዳታ ለመስጠት ያለንን አቅም ይቀንሳል። አንድ ሰው በእረፍት ማሳለፊያ ቤቱ (hytta)

    እያለ ድንገተኛ አደጋ ሊደርስበት ይችላል፥ የመሰበር፣ የመውደቅ፣ በጭንቅላት ውስጥ የደም መፍሰስ፣ የልብ ህመም

    ...

    Vinje ኮሙነ 3676 ነዋሪዎች ብቻ ያሏት ትንሽ ኮሙነ ነች። ግን ከ 5700 የሚበልጡ የእረፍት ግዜ ማሳለፊያ ቤቶች

    (hytter) ያሏት ሲሆን ከ 20 000 እስከ 25 000 የሚደርሱ ሰዎች በአብዛኛዎቹ የአመቱ ቀናቶች በኮሙነዋ ውስጥ

    ቆይታ ያደርጋሉ። ተላላፊ በሽታው በአካባቢያችን፣ በብሔራዊና በዓለም አቀፍ ደረጃ የበለጠ እንዳይዛመት ለማድረግ

    ይህ እርምጃ በስራ ላይ እንዲውል ተደርጓል። እኛ በአሁኑ ግዜ ከምንገኝበት ሁኔታ አንጻር የተወሰደው እርምጃ

    ትክክለኛ ግን ከባድ እርምጃ ነው።

    የአየር አምቡላንስ በስምሪት ላይ ስለሚገኝ በእረፍት ግዜ ማሳለፊያ ቤታችሁ ሆናችሁ ድንገት ብትታመሙ

    የሄሊኮፕተር አምቡላንስ ይመጣልናል ብላችሁ እንዳትጠብቁ ልናስጠነቅቃችሁ እንፈልጋለን። ይህም በኮሮና ተላላፊ

    በሽታ አደገኛነት የተነሳ ነው። አንድን ሄሊኮፕተር ከቫይረሱ ነጻ ለማድረግ ረጅም ግዜ ይወስዳልና። ለተጨማሪ ንባብ

    እዚህ ይጫኑ።

    በዚህ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሁላችሁም እራሳችሁን እንድታረጋጉ አጥብቀን እንመክራለን።

    የሱፐርቪዥን (ቁጥጥር) እገዛ፥

    የእረፍት ጊዜ ማሳለፊያ ቤት ያላችሁ ሰዎች በአሁኑ ወቅት በዕረፍት ግዜ ማሳለፊያ ቤቶች በሚደረግ ቆይታ ላይ

    የተጣለውን ማዕቀብ እንድታከብሩ እንፈልጋለን። በፊናችንም በሚቻለን ሁሉ በእረፍት ጊዜ ማሳላፊያ ቤቶች ላይ

    አስፈላጊ የሆነ ጥብቅ ውጪያዊ ቁጥጥር እናደርጋለን።

    Vinje ኮሙነ የቁጥጥር ስራ ለመስራት የባለሞያዎች እገዛ ያስፈልገዋል። እነሱም እጅግ አስፈላጊ እርምጃ መሆኑን ባዩ

    ጊዜ የስራውን ኃላፊነት ይወስዳሉ። ይህ አገልግሎት ለናንተ የእረፍት ጊዜ ማሳለፊያ ቤት ባለቤቶች ለሆናችሁ

    የሚያስወጣችሁ ወጪ አይኖርም። እኛ የተለያዩ አድራሻዎችንና የግንኙነት መረጃዎችን ዝርዝር በማዘጋጀት ለተለያዩ

    ጉዳዩ የሚመለከታቸው መሥሪያ ቤቶች እንልካለን። እነሱም በዙር ቁጥጥር ያደርጋሉ። እርምጃ መውሰድ

    የማያስፈልግ ከሆነም ይህንኑ አስመልክቶ መልስ ይላክላቸዋል። ጥያቄዎቻችሁን ለ

    [email protected] ላኩ።

    ለናንት፣ ራሳችሁን አግልላችሁ (quarantine ውስጥ) ለምትገኙ

    https://www.vinje.kommune.no/informasjon-fraa-kommunen.525646.nn.html?printable=1https://lovdata.no/dokument/LTI/forskrift/2020-03-15-294https://www.nrk.no/sorlandet/advarer-folk-mot-a-dra-pa-hytta_-du-kan-ikke-vente-a-fa-hjelp-der-1.14940894https://www.nrk.no/sorlandet/advarer-folk-mot-a-dra-pa-hytta_-du-kan-ikke-vente-a-fa-hjelp-der-1.14940894mailto:[email protected]

  • 18.3.2020 www.vinje.kommune.no

    https://www.vinje.kommune.no/informasjon-fraa-kommunen.525646.nn.html?printable=1 2 av 8

    በ Vinje ውስጥ ቋሚ ነዋሪ ሆነው ራስዎትን እንዲያገሉ ተደርገው ከሆነና ሌሎች ሊያግዙዎት የሚችሉ ሰዎች ከሌሉ

    የምግብ ግዢና ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ ጉዳዮችን በተመለከት ከበጎ ፈቃድ አገልግሎት ማእከል (frivilligsentralen)

    እገዛ ማግኘት ይችላሉ። የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ማእከሉን ለማግኘት፤ ስልክ፥ 48 13 53 61፣ ወይም ኢሜይል

    [email protected]

    በተረፈ ከማህበራዊ ንክኪ መራቅን በተመለከተ ከሕዝብ ጤና ማዕከል (FHI) የሚሰጡ ወቅታዊ መረጃዎችን

    ይከታተሉ፣ እዚህ ይጫኑ።

    የኃኪም ቢሮ

    ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ የተፈጠረው በተጠንቀቅ የመቆም ሁኔታ በኮሙነ ውስጥ ተጨማሪ ስራን ፈጥሯል።

    የኮሙነው ሀኪም ብቸኛ ስራም ይኸው ሆኗል። ሁሉም በ Vinje ኮሙነ የሚገኙት የጤና አገልግሎቶች ከማርች 13

    ቀን ጀምሮ የድንገተኛ አገልግሎት (የድንገተኛ አደጋ ህክምና ጣቢያ) ብቻ ነው የሚሰጡት። ከዚህ ቀደም በሀኪሞች

    ቢሮ ተይዘው የነበሩት ቀጠሮዎች በሙሉ ላልተወሰነ ጊዜ ተሰርዘዋል። ወደፊት ተጨማሪ መረጃዎች ይቀርባሉ።

    የጤና ጣቢያዎች ዕለታዊ የሥራ እንቅስቃሴም የሚያካትተው አስፈላጊ የሆኑ ክትትሎችንና ክትባቶችን ብቻ ነው።

    የጤና ባለሙያ ነርሷን ያነጋግሩ።

    ፈጣን የአዕምሮ ጤንነት እርዳታ ለማግኘት ከ 08:00 – 16:00 ሰዓት ባለው ግዜ በስልክ ቁጥር 958 16 360 ይደውሉ።

    ሕዝባችን በዚህ ሁኔታ ውስጥ ለሚያሳየው ትዕግሥትና ግንዛቤ የምንሰጠው ቦታ ከፍተኛ ነው።

    የአእምሮ ጤንነት

    አገልግሎት ማግኘት የሚቻለው ከሰኞ እስከ አርብ ከ 08:00 – 15:30 በስልክ ቁጥር 958 16 360 በመደወል ነው።

    ከስራ ሰዓት ውጪ ድንገተኛ ርዳታ ለማግኘት ወደ ድንገተኛ ህክምና ጣቢያ በስልክ ቁጥር 116 117 መደወል፣ ወይም

    የአእምሮ ህክምና ርዳታ ስልክ 116 123 መደወል። ይኸኛው ስልክ ለ24 ሰዓት ክፍት ነው።

    የጤና ጣቢያና የትምህርት ቤት የጤና አገልግሎት

    ሕጻናት፣ ወጣቶች እና ወላጆች እንደ አስፈላጊነቱ ከጤና ባለሞያዋ ነርስ ጋር ግንኙነት መፍጠር ይችላሉ።

    የሚያናግሩት ሰው የሚያስፈልጋቸው ከሆነ፣ ወይም እርዳታ የሚፈልጉበት ነገር ካለ።

    የግንኙነት መረጃን እዚህ ያገኛሉ።

    ኢንቴግሬሽን፣ ትምህርት ቤቶችና መዋዕለ ሕጻናት

    የኢንተግሬሽን አገልግሎት በ Åmot ትምህርት ቤት ውስጥ ያለው ቢሮ ከ 13.03 ጀምሮ እስከ 27.03 ድረስ ተዘግቷል።

    የስደተኞች አማካሪ Haytham Monifi Abu Areef እና የኢንተግሬሽን ኮኦርዲኔተር Marte Myrset Laberg

    ቢሮአቸውን እቤታቸው አድርገው ነው የሚሰሩት። ከሰኞ እስከ አርብ ከ 08:00 – 16:00 በኢሜይልና በስልክ

    ልታገኟቸው ትችላላችሁ። ኢሜይል: [email protected] ስልክ 476 48 562፣ እንዲሁም

    [email protected] . ስልክ 450 13 024.

    እንደ ተቀሩት የአገሪቱ ክፍሎች ሁሉ በ Vinje ኮሙነም ከአርብ 13.03. ጀምሮ እስከ 27.03. ድረስ ትምህርት ቤቶች

    ተዘግተዋል። ይህ የበሽታውን ተላላፊነት ለመገደብና የኮሮና ቫይረስን መዛመት ለመግታት የተወሰደ አስፈላጊ

    https://www.vinje.kommune.no/informasjon-fraa-kommunen.525646.nn.html?printable=1mailto:[email protected]://www.fhi.no/nyheter/2020/fhi-presiserer-rad-om-sosial-distansering/?fbclid=IwAR2AVNm1fi5KtC4Dv9AUmw0TwiU45P3fzzVWPrO8xFasGu4hgDU6nKQ_NvEhttps://www.vinje.kommune.no/barn-unge-og-familie.498826.nn.htmlmailto:[email protected]:[email protected]

  • 18.3.2020 www.vinje.kommune.no

    https://www.vinje.kommune.no/informasjon-fraa-kommunen.525646.nn.html?printable=1 3 av 8

    እርምጃ ነው። በጤና አገልግሎት ተቋማት ውስጥ ተመድበው ለሚሰሩ ወላጆች የመዋዕለ ሕጻናት ወይም የትምህርት

    ቤት ቦታ አቅርቦት ይዘጋጅላቸዋል።

    በባህል ትምህርት ቤት የሚሰጠው ትምህርት ላልተወሰነ ግዜ ተቋርጧል።

    የኮሙነ መሥሪያ ቤት እና የምደባ ቢሮ

    ከማርች 16 ጀምሮ የኮሙነው መሥሪያ ቤት ለተጠቃሚዎች ዝግ ይሆናል። በመጀመሪያው ዙር ይህ ሁኔታ

    ለሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት የሚቆይ ይሆናል። ተጠቃምሚዎች ቀጠሮ አስይዘው መምጣት ይችላሉ። አለበለዚያ

    ስልክ ቁጥሮችንና መረጃዎችን በድረገጻችን ላይ “kontak oss” በሚለው ስር ፈልገው ያግኙ። በዚህ ተመሳሳይ ጊዜ

    የስልካችን ሴንትራል ቦርድ (ማዞሪያ) በየቀኑ ከ 8:00 – 15:30 ድረስ ክፍት ነው።

    የምደባው ቢሮ ከማርች 13 ቀን ጀምሮ ለተጠቃሚዎች ዝግ ነው።

    የሕጻናት እንክብካቤ ምደባ

    እንደ ተቀሩት የአገሪቱ ክፍሎች ሁሉ በ Vinje ኮሙነም ከአርብ 13.03. ጀምሮ እስከ 27.03. ድረስ ትምህርት ቤቶች

    ተዘግተዋል። ይህ የበሽታውን ተላላፊነት ለመገደብና የኮሮና ቫይረስን መዛመት ለመግታት ሲባል የተወሰደ አስፈላጊ

    እርምጃ ነው። ለማህበረሰቡ ወሳኝ የሆኑ ሥራዎችን የሚያከናውኑትን አስመልክቶ እድሜያቸው 1 ዓመት ከሆናቸው

    አንስቶ እስከ 4ተኛ ክፍል ላሉ ሕጻናት የህጻናት እንክብካቤ አገልግሎት እናቀርባለን።

    የዚህ ዋና ዓላማ ለማህበረሰቡ ወሳኝ የሆኑ ሥራዎችን የሚያከናውኑ ወላጆች አስተማማኝ የሆነ የህጻናት እንክብካቤ

    እንዲያገኙ ማስቻል ነው። ይህ የህጻናት እንክብካቤ የሚደረገው ቀደም ሲል ሕጻናቱ ይሄዱበት በነበረው መዋዕለ

    ሕጻናት/ የሕጻናት ትምህርት ቤት/ SFO ውስጥ በተለመደው የሥራ ሰዓት ይሆናል።

    የምደባው መስፈርቶች፥

    ወሳኝ የሆኑ ማህበራዊ የሥራ ኃላፊነቶች ያላቸው ወላጆች፤ ትርጉሙን ከታች ይመልከቱ

    እነዚህ ወላጆች ሥራ የሚገቡባቸውን ቀናቶች ብቻ የሚመለከት

    ለማህበረሰቡ ወሳኝ የሆኑ የሥራ ኃላፊነቶች፤

    አመራሮች፣ የቀውስ ጊዜ አመራሮች

    መከላከያ

    ሕግና ሥርዓት

    ጤና እና እንክብካቤ

    የነፍስ ማዳን አገልግሎት

    የሲቪል ሴክተር የመረጃና መገናኛ ቴክኖሎጂ (መመቴክ) ደህንነት

    ተፈጥሮና አካባቢ

    የአቅርቦት ደህንነት

    ውሀና ፍሳሽ

    የፋይናንስ አገልግሎት

    የኃይል አቅርቦት

    የኤሌክትሮኒክስ የመገናኛ አገልግሎት

    መጓጓዣ

    ሳተላይት ነክ አገልግሎቶች

    https://www.vinje.kommune.no/informasjon-fraa-kommunen.525646.nn.html?printable=1

  • 18.3.2020 www.vinje.kommune.no

    https://www.vinje.kommune.no/informasjon-fraa-kommunen.525646.nn.html?printable=1 4 av 8

    መድሀኒት ቤት / ፋርማሲ

    ግሮሰሪ

    የጽዳት ሥራ

    የኮሙነ ቁልፍ ሰራተኞች

    ሁኔታዎች በፍጥነት ነው የሚለዋወጡት። ዛሬ ትክክል ነው የተባለ ነገር ነገ ሊለወጥ ይችላል። ሁሉም ነገር በፍጥነት

    ስለሚከሰት እኛ ለሁሉም ሰው በየሰዓቱ የተሟላ መረጃ መስጠት አይቻለንም። ስለሆነም ሁሉም ሰው የሚኖሩትን

    ለውጦች በተመለከተ በሚከተሉት ምንጮች በኩል የተሟላ መረጃ ለማግኘት ጥረት እንዲያደርግ እናሳስባለን።

    የሕዝብ ጤና ማዕከል፣ www.fhi.no

    ጤና ኖርዌይ፣ www.helsenorge.no

    በኖርዌይ የሚገኙ ማእከላዊ ሜዲያዎች፣ ለምሳሌ NRK

    ተቋማት

    Norheimstunet የእንክብካቤ ማዕከል፣ Rauland የእንክብካቤ ማዕከል፣ Vinje የህሙማን መኖሪያ፣ Bruli,

    Svingen እና Reine ተቋማት ለዘመድ አዝማድ ጠያቂዎችና እዚያ ለማይኖሩትና ለማይሰሩት ሁሉ ዝግ ናቸው።

    ከዘመዶቻቸው ጋር ለመገናኘት የሚፈልጉ ሰዎች በቅድሚያ ከሚመለከተው ክፍል ጋር በስልክ መነጋገር አለባቸው።

    የባህል ማዕከልና መጻሕፍት ቤት

    የባህል ማዕከላትና መሰብሰቢያዎች፣ የመዋኛ ሥፍራዎች፣ የስፖርት መሥሪያና መወዳደሪያ አዳራሾች ሁሉ ላልተወሰነ

    ግዜ ተዘግተዋል።

    የ Vinje የሕዝብ መጻፍት ቤት ዝግ ነው።

    የመጻህፍት ቤቱ ወቅታዊ ሁኔታ

    የኮሮና ቫይረስን መዛመት ለመግታት ሲባል በተወሰደ እርምጃ መጻህፍት ቤቱ ከ 13.03.2020 ጀምሮ ተዘግቷል።

    እንደ ከዚህ በፊቱ በስፍራው ቆይታ ማድረግ ወይም በአካል መገኘት አይቻልም። የመጽሀፍ መመለሻው መስኮት

    አሁንም ያገለግላል። ግን በውሰት ላይ የሚገኙና ያልተመለሱ መጽሀፎች እንዲመለሱ የሚላከው ማስጠንቀቂያ

    ላልተወሰነ ጊዜ ተቋርጧል። የውሰት ጊዜን ለማሳደስ በኢንተርኔት ድረገጽ ላይ ባለን ካታሎግ በኩል የመጽሀፍ መዋሻ

    ካርድ ቁጥራችሁንና PIN-ኮዳችሁን በመጠቀም ገብታችሁ ማሳደስ ትችላላችሁ።

    የግንኙነት መስመር

    ስልክ፥ 35 07 26 60

    ኢሜይል፥ [email protected]

    ካታሎጉን እዚህ ያገኛሉ Vinje folkebibliotek

    ስራው ገና ያልተገባደደ አቅርቦት

    በኢንተርኔት ድረገጽ ላይ ከሚገኘው ካታሎጋችን ምን ዓይነት የመጻሕፍት፣ የፊልሞችና የድምጽ መጻሕፍት ስብስብ

    እንዳለን ማየት ትችላላችሁ። እርስዎ እንደ ተዋሽ በኢንተርኔት ወይም በስልክ የሚዋሱትን መጽሀፍ የሚያዙበትን፣

    መጽሀፍትን ለመውሰድ/ ለማግኘት ቀጠሮ የሚይዙበትን ሥርዓት ለመፍጠር እየሰራን ነው። ተጨማሪ መረጃ

    በተከታይ ይቀርባል።

    አማራጭ አቅርቦት

    https://www.vinje.kommune.no/informasjon-fraa-kommunen.525646.nn.html?printable=1http://www.fhi.no/http://www.helsenorge.no/https://www.nrk.no/norge/koronaviruset-1.14874108mailto:[email protected]://vest-telemark-felles.mikromarc.no/Mikromarc3/web/default.aspx?db=vest-telemark-felles&unit=12151

  • 18.3.2020 www.vinje.kommune.no

    https://www.vinje.kommune.no/informasjon-fraa-kommunen.525646.nn.html?printable=1 5 av 8

    አሁንም BookBites Bibliotek በተባለው ነጻ app በኩል የኤሌክትሮኒክስ መጻሕፍትንና የኤሌክትሮኒክስ የድምጽ

    መጻሕፍትን ማግኘት ይችላሉ። ለመመዝገብ እገዛ የሚያስፈልጎት ከሆነ (የመዋሻ ካርድ ቁጥር ወይም PIN-ኮድ

    ስለሌሎት) በስልክ ወይም በኢሜይል መጻሕፍት ቤቱን ማግኘት ይችላሉ።

    ጋዜጦችንና መጽሔቶችን PressReader በተባለው ነጻ app በኩል ማንበብ ይችላሉ። ከርስዎ የሚፈለገው ነገር

    ወደ መጻሕፍት ቤቱ የ Åmot ገመድ አልባ የኢንተርኔት መረብ/ HotSpot ቀረብ ካለ ቦታ አፕሊኬሽኑን መክፈት

    ነው። ይህንን ከመጻህፍት ቤቱ ፊት ለፊት ካለው የመኪና ማቆሚያ ስፍራ ማድረግ ይቻላል። አንድ ጊዜ ወደ

    ኢንተርኔት መረቡ ከገቡ፣ ከዚያ በኋላ ሌላ መረብ ውስጥ ቢገቡ እንኳን ለብዙ ሰዓታት መስመር ላይ መቆየት

    ይችላሉ።

    የብሔራዊ መጻሕፍት ቤቱን ድረ ገጽም መጠቀም ይቻላል። በ Bokhylla.no ድረ ገጽ ላይ የዲጂታል ህትመቶችንና

    ስካን የተደረጉ ጽሁፎችን ማግኘት ይቻላል።

    የቱሪስት እንዱስትሪ

    የ Vinje ኮሙነ የ Covid-19 (ኮሮና) ቫይረስ ቀጣይ መዛመትን ለመከላከል በኮሙነው ሲኒየር ሀኪም በኩል ጠንከር

    ያለ እርምጃ ለመውሰድ ወስኗል። ይህ እርምጃ ምናልባት በ Covid-19 ቫይረስ ተጠቅተው ሊሆን የሚችሉ ሰዎች ወደ

    ኮሙነው እንዳይገቡ መከላከል የሚያስችል እርምጃ እንደሆነ አድርገን ነው የምንመለከተው።

    የቱሪስት እንዱስትሪው ምግብ ቤቶችን፣ ሆቴሎችን፣ የማደሪያ ቦታዎችንና የበረዶ ላይ መንሸራተቻ ቦታዎችን ከነገ፣ ከ

    13.03.2020 ጀምሮ እስከ ፋሲካ ማብቂያ ድረስ እንዲዘጋ የ Vinje ኮሙነ በኮሙነው ሲኒየር ሀኪም በኩል ትእዛዝ

    ሰጥቷል።

    ውሳኔው በኢንዱስትሪው ላይ ከሚፈጥረው ከፍተኛ ጫና አንጻር በቀላሉ የሚታይ ውሳኔ አይደለም። ከዚያም በላይ

    ሰዎች ወደ ኮሙናችን እንዳይመጡ መከልከል የሚያሳምምም፣ የሚከብድም ነገር ነው።

    የውሳኔው መሠረታዊ ምክንያት ብሔራዊውን መመሪያና ተላላፊ በሽታዎችን ስለመከላከል የወጣውን ሕግ መሠረት

    ያደረገ ነው።

    Vinje ኮሙነ 3676 ነዋሪዎች ብቻ ያሏት ትንሽ ኮሙነ ነች። ግን ከ 5700 የሚበልጡ የእረፍት ግዜ ማሳለፊያ ቤቶች

    (hytter) ያሏት ሲሆን ከ 20 000 እስከ 25 000 የሚደርሱ ሰዎች በአብዛኛዎቹ የአመቱ ቀናቶች በኮሙነዋ ውስጥ

    ቆይታ ያደርጋሉ። ተላላፊ በሽታው በአካባቢያችን፣ በብሔራዊና በዓለም አቀፍ ደረጃ የበለጠ እንዳይዛመት ለማድረግ

    እርምጃው በስራ ላይ እንዲውል ተደርጓል። እኛ በአሁኑ ግዜ ከምንገኝበት ሁኔታ አንጻር የተወሰደው እርምጃ ትክክለኛ

    ግን ከባድ እርምጃ ነው።

    ሁሉም ሰው እቤቱ እንዲሆንና አላስፈላጊ ግንኙነቶችን ከማድረግ እንዲቆጠብ በአጽንኦት እናሳስባለን።

    በዚህ ሁኔታ ውስጥ እያለን ሰዎች በእረፍት ጊዜ ማሳለፊያ ቤታቸው እንዲገለገሉ አንፈልግም። ይልቅ በሚኖርበት ቤት

    ውስጥ እንዲቆዩ ነው የሚፈለገው። ምክንያቱም በበሽታው ተበክለው ሊሆኑ የሚችሉ ሰዎች ወደ ኮሙናችን

    እንዲመጡ ስለማንፈልግ። ይህንን በሚመለከት የእረፍት ጊዜ ማሳለፊያ ቤት ባለቤት ለሆኑት ሁሉ ዛሬ ጥዋት

    (12.03.2020) ላይ መልዕክት ተልኮላቸዋል።

    በዚህ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሁላችንም እራሳችንን ማረጋጋት እንዳለብን ነው የምንመክራችሁ። ከመጠን በላይ የሆነ

    ምግብ እንድንሸምት የሚያደርግ ምንም ዓይነት ምክንያት የለም። ይህ ድርጊት የግሮሰሪ መደብሮቻችን ላይ

    ከፍተኛ ጫና ይፈጥራል።

    https://www.vinje.kommune.no/informasjon-fraa-kommunen.525646.nn.html?printable=1https://support.bookbites.com/hc/no/articles/360004289531-Hvordan-kommer-jeg-i-gang-med-BookBites-https://www.pressreader.com/catalog

  • 18.3.2020 www.vinje.kommune.no

    https://www.vinje.kommune.no/informasjon-fraa-kommunen.525646.nn.html?printable=1 6 av 8

    ሁኔታዎች ዛሬ ከሚገኙበት አንጻር የምንወስዳቸው እርምጃዎች አስፈላጊና ትክክል ናቸው ብለን ብናስብም፣

    እርምጃዎቹ ለሚያስከትሉት አለመመቸቶች ይቅርታ እንጠይቃለን።

    የበረዶ ላይ ተንሸራታች ሞተር ፈቃድ

    ከኮረና ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ ለጊዜው ዕለታዊ ፈቃድ መግዛት አስፈላጊ አይደለም።

    ከመኖሪያ ኮሙነ ውጪ በሌላ ኮሙነ በሚገኝ የእረፍት ጊዜ ማሳለፊያ ቤት ውስጥ ቆይታ ማድረግ የተከለከለ ስለሆነ፣

    የአመት ካርድ ለኮሙነው ነዋሪዎች ብቻ ነው የሚፈቀደው።

    በ Vinje ኮሙነ ውስጥ ነዋሪ ላልሆኑ ነዋሪዎች በተሰጠ የበረዶ ላይ ተንሸራታች ሞተር ፈቃድ መጠቀም

    አይፈቀድም።

    የጉዞ ማዕቀቦች

    በሁሉም የኮሙነው ቁልፍ ሠራተኞች ላይ የጉዞ ማዕቀብ ተጥሎባቸዋል። የኮሙነው ቁልፍ ሠራተኞች በውስጡ የጤና

    ባለሙያዎችንም ያጠቃልላል።

    ቁልፍ ሠራተኞች ሆነው በጉዞ ላይ የነበሩ ሰዎች ለ 14 ቀናት ራሳቸውን አግልለው ቤታቸው እንዲቆዩ ተደርገዋል።

    ጤናማ ሕይወትና ፊዚዮ ቴራፒ

    የጤናማ ሕይወት ማዕከል ማናቸውንም የቡድን እንቅስቃሴዎች ላልተወሰነ ግዜ እንዲቋረጡ አድርጓል። ይህ

    የሲኒየሮች ቡድንን፣ በህሙማን መቆያ ማዕከል የሚገኙ የስፖርታዊ እንቅስቃሴ ቡድኖችን፣ የሳምባ ህሙማን

    (KOLS) ቡድንን እና ሌሎች የስፖርታዊ እንቅስቃሴ ቡድኖችን ይመለከታል።

    ፊዚዮ ቴራፒ ከ ማርች 16 ጀምሮ ዝግ ነው።

    የ Vest-Telemark የሳይኮሎጂና ፔዳጎጂ አገልግሎት

    በኮሮና ወረርሽኝና የበሽታውን መዛመት ለመከላከል በተወሰደው እርምጃ ምክንያት ከማርች 16 እስከ ማርች 27

    ባለው ጊዜ ውስጥ የሳይኮሎጂና ፔዳጎጂ አገልግሎት መስጫ ቢሮዎች ዝግ ናቸው።

    በነዚህ ቀናቶች ውስጥ በት/ቤትና በመዋዕለ ሕጻናት የተያዙ ቀጠሮዎች ሁሉ ተሰርዘዋል።

    ጉዳይ አስፈጻሚዎች ስራቸውን እቤታቸው ሆነው ነው የሚያከናውኑት።

    አንዳንድ ነጠላ ጉዳዮችን በተመለከተ የስልክ እና የዲጂታል ግንኙነቶችን ማድረግ ይቻላል።

    ጥያቄ ካለዎት ሥራ አስኪያጁን በስልክ ቁጥር 35068300 / 40920833 ያግኙት።

    NAV

    በ Seljord, Kviteseid, Nissedal, Fyresdal Vinje እና Tokke ያሉት የእለታዊ አገልግሎት መስጫ ቦታዎች ከ

    16.03.2020 ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ ተዘግተዋል።

    NAV የሚሰጠውን የኮሙነ አገልግሎት እርዳታ በአስቸኳይ የሚፈልጉ ከሆነ በስልክ ቁጥር 406 16 218 ይደውሉ።

    መንግሥታዊ አገልግሎቶች፥ ቋሚ ጉዳይ አስፈጻሚ ያሎት ከሆነ በዲጂታል የአፈጻጸም እቅዶት ውስጥ ለርሷ/ ለርሱ

    ሊጽፉ ይችላሉ። አለያም ስልክ መደወል ወይም መልዕክት መላክ ይችላሉ።

    https://www.vinje.kommune.no/informasjon-fraa-kommunen.525646.nn.html?printable=1

  • 18.3.2020 www.vinje.kommune.no

    https://www.vinje.kommune.no/informasjon-fraa-kommunen.525646.nn.html?printable=1 7 av 8

    በ www.nav.no ድረ ገጽ ላይ ወይም በስልክ ቁጥር 55553333 መረጃ ያገኛሉ።

    አሠሪዎች WWW.NAV.NO/BEDRIFT የሚለውን ድረገጽ ይጠቀሙ፤ ወይም በስልክ ቁጥር 55553336

    ይደውሉ።

    የተጠሪዎች የቀጥታ ስልክ ቁጥሮች

    Seljord , Kviteseid,Nissedal : 412 23 954 Tore Dag Lid

    Fyresdal ,Tokke ,Vinje: 404 76 863 Margit K. Bergland

    IA –አማካሪ : 994 49 230 Olav Aalandslid

    የቀጥታ ስልክ ቁጥሮች :

    የ VINJE የስልክ ማውጫ – መንግሥታዊ አገልግሎቶች

    ASLAUG RINGHUS ስልክ ቁጥር 401 03 791

    ANNE RAGNHILD ØVREBØ ስልክ ቁጥር 401 04 134 SUSANNE LIEN TLF 406 16 823

    VIVIANA BURGOS TLF 409 14 647

    CECILIE NESHEIM TLF 469 24 948

    Gerd Kari Skaalen, የ NAV ኃላፊ 958 32 211

    Solbjørg Frantzen, የ NAV ረዳት ኃላፊ 909 46 708

    የፖስታ አድራሻ: NAV VEST-TELEMARK, HOTELLVEGEN 42, 3880 DALEN

    ቤተ ክርስቲያን

    የኮሮና ቫይረስን መዛመት ለመከላከል የቤተ ክርስቲያን ቢሮ ተዘግቷል። ቢሮው ላልተወሰነ ጊዜ ዝግ ሆኖ ይቆያል።

    ሰራተኞቹ ቤታቸው ሆነው ነው የሚሰሩት።

    የሰበካው የቄሶች ሃላፊ፥ Tor Eivind Erikstein ፣ ስልክ ቁጥር : 952 37 673

    የቤተክርስቲያኑ የበላይ ጠባቂ፥ Kjell Magne Grave ፣ ስልክ ቁጥር : 35 06 25 87/ 481 20 117

    ተጨማሪ መረጃዎችን በኢንተርኔት ድረ ገጻችን www.vinje.kyrkja.no ላይ ያገኛሉ።

    ሁሉም የእምነት አገልግሎቶች ተሰርዘዋል።

    ስለ ኮሮና በተለያዩ ቋንቋዎች የተዘጋጁ መረጃዎች

    ከ Folkeinstituttet ስለኮሮና ቫይረስ በተለያዩ ቋንቋዎች የተዘጋጀውን መረጃ እዚህ ያገኛሉ።

    ከ Folkehelseinstituttet ስለ በመኖሪያ ቤት ውስጥ እራስን ስለማግለል እና ስለ ለብቻ ማቆየት የቀረበውን መረጃ

    እዚህ ያገኛሉ።

    ኮሮና ቫይረስን አስመልክቶ ከ Vinje ኮሙነ የተሰጠ መረጃ፥

    አረቢኛ

    https://www.vinje.kommune.no/informasjon-fraa-kommunen.525646.nn.html?printable=1http://www.nav.no/http://www.nav.no/BEDRIFThttp://www.vinje.kyrkja.no/https://www.fhi.no/nettpub/coronavirus/fakta/generell-informasjon-koronavirus-pa-flere-sprak/https://www.fhi.no/nettpub/coronavirus/rad-til-personer-som-er-smittet-eller-har-vart-utsatt-for-smitte/informasjon-om-hjemmekarantene-og-isolasjon-pa-ulike-sprak/https://www.fhi.no/nettpub/coronavirus/rad-til-personer-som-er-smittet-eller-har-vart-utsatt-for-smitte/informasjon-om-hjemmekarantene-og-isolasjon-pa-ulike-sprak/https://www.vinje.kommune.no/getfile.php/4665560.2639.mtuajzswzks7bj/Informasjon+på+Arabisk+-+koronasituasjonen+i+vinje.pdf

  • 18.3.2020 www.vinje.kommune.no

    https://www.vinje.kommune.no/informasjon-fraa-kommunen.525646.nn.html?printable=1 8 av 8

    የንጽህና አጠባበቅ ፖስተሮች፥

    እንግሊዝኛ

    አረቢኛ

    ሶማሊኛ

    ትግሪኛ

    ኩርድኛ

    ቅጽ

    ስለ አገልግሎት ጉዳይ

    ሰነዶች

    አገናኞች

    ተጻፈ፤ በ Kyrre Einar Hegg

    ለመጨረሻ ግዜ የተሻሻለው: ማርች 18 ቀን 2020

    https://www.vinje.kommune.no/informasjon-fraa-kommunen.525646.nn.html?printable=1https://www.vinje.kommune.no/getfile.php/4665416.2639.tkqualauubpuwa/20200305-hygieneplakat-engelsk.pdfhttps://www.vinje.kommune.no/getfile.php/4663712.2639.iwnlbjqmtktwsj/Vaner_som_forebygger_smitte_-arabisk.pdfhttps://www.vinje.kommune.no/getfile.php/4663713.2639.pbunjtauzuukqq/Vaner_som_forebygger_smitte-_somali_.pdfhttps://www.vinje.kommune.no/getfile.php/4663715.2639.kbwunlnmbnlqlu/Vaner_som_forebygger_smitte-tigrinja.pdfhttps://www.vinje.kommune.no/getfile.php/4663717.2639.muzauzjbqjusla/Vaner_som_forebygger_smitte-_kurdisk_sorani_.pdf