9
በፍቅር እንደመር በይቅርታ እንሻገር! ወንድወሰን ሽመልስ ከግብርና ወደ ኢንዱስትሪ እንዲሸጋገር በሚጠበቀው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እውን መሆን ጉልህ ድርሻ ያላቸው የኢንዱስትሪ ፓርኮች ተገንብተው ለሥራ ዝግጁ እየሆኑ ይገኛል። ሆኖም ፓርኮቹን ከመገንባትና አስመርቆ ለሥራ ክፍት ከማድረግ በተጓዳኝ ድጋፍና ክትትል ማድረግ እንዲሁም የኢንዱስትሪ ጥሬ ዕቃ አገር ፍዮሪ ተወልደ በዕድሜ አልያም በተለያዩ ፅኑ ህመሞች ሕክምና ሲደረግ ቆይቶ ከሚከሰት የህልፈተ ሕይወትና የአካል ጉዳት ውጪ ሩጫቸውን ሳይጨርሱ አንዳንዴም ገና ሳይጀምሩ በጨቅላ ዕድሜያቸው የሚቀጩ እንዳሉ ማድመጥ በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ውስጥ የሚያጋጥም ነው። ለዚህ አንዱ መንስኤ ደግሞ የሕክምና ስህተት ነው። የቀላል ራስ ምታት ምክንያታቸውን 78ኛ ዓመት ቁጥር 189 ሰኞ መጋቢት 9 ቀን 2011 ዓ.ም ያንዱ ዋጋ 5.75 ብር የኢንዱስትሪ ፓርኮቹ ስኬት በግብዓት አቅርቦት ይወሰናል ፈውስ ፍለጋ ... በ2ኛው ገጽ ዞሯል በበኃይሉ ንጉሴ የከተሞች የስራ ዕድል ፈጠራና የምግብ ዋስትና ዘርፍ በከተሞች ለሚኖሩ ዜጎች ሰፊ የስራ ዕድል በመፍጠር ስራ አጥነትንና ድህነትን መቀነስ ችሏል። ከድህነት በታች የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎችን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ ኃላፊነት የተጣለበት ዘርፍ ነው። የዘርፉ አስፈጻሚ አካላት የስራ እድል ፈጠራ እና የምግብ ዋስትና ኤጀንሲዎች፣ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማትና የአነስተኛ ብድርና ቁጠባ ተቋማት ናቸው። የዘርፉ ተልዕኮ ውጤታማ እንዲሆን በአመለካከት፣ በእውቀትና በክህሎት የጎለበተ የሰው ሃብት ወሳኝ ነው። የሰው ሀብት ልማትን ለማረጋገጥ ከሚረዱ የተለያዩ ዘዴዎች አንዱ ስልጠና ነው። የስልጠና ስርዓትን በመዘርጋት፣ ቅድመ ስልጠና ስራዎችን በተደራጀ ሁኔታ ስራ ላይ በማዋል ሀገራዊ ዕድገትን እውን ማድረግ እንደሚቻል ያደጉ አገራት ተሞክሮ ያሳያል። በመሆኑም የሰው ሀብት ልማትን ለማረጋገጥ የስልጠና ደረጃዎችን ማሳደግ ለስራ እድል ፈጠራው መጎልበት ስልጠና ከፍተኛ ሚና አለው። ተልዕኮውን በአግባቡ የተረዳና በተገቢው አመለካከት፣ እውቀትና ክህሎት የተካነ አመራርና ባለሙያ ለአንድ ተቋም ውጤታማነት እንዲሁም ስኬት ትልቁን ድርሻ ይወስዳል። ለዚህም በስልጠና የታገዘ የሰው ሀይል ልማት ስራዎችን ማከናወን ያስፈልጋል። በሁሉም ክልሎችና በሁለቱ ከተማ አስ ተዳደሮች ለዩኒቨርሲቲ ምሩቃን፤ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ስትራቴጂ አስፈጻሚ አካላት ማለትም የቴክኒክና ሙያ፣ የብድርና ፋይናንስ ተቋማት፣ የስራ ፈጣሪነት አስተሳሰብ ክህሎት ላላቸው፣ ለዘርፉ ባለሙያዎችና አመራሮች፣ ለኢንተርፕራይዝ ልማት አንቀሳቃሾች የተለያዩ ስልጠናዎች ይሰጣሉ። ዘርፉ በፖሊሲ፣ በስትራቴጂ፣ በመመሪያዎች፣ በማንዋሎች፣ በስታንዳርዶች፣ በእቅድ ዝግጅት፣ በፓኬጅ፣ በሪፎርም መሳሪያዎችና በመልካም አስተዳደር፣ በድጋፍ ማእቀፎች፣ በአጫጭር የቴክኒክ ክህሎት፣ በስራ አመራር፣ በአመለካከት፣ በክህሎት፣ በተለያዩ ርእሶች ላይ የአሰልጣኞች ሥልጠና፣ በንግድ ልማት አገልግሎት እና በሌሎች ዙሪያ የአጭር፣የመካከለኛና የረጅም ጊዜ ስልጠናዎች እየሰጠ ይገኛል። የፈጻሚዎችንና አስፈጻሚዎችን ስራ አፈጻጸም ጥራት ለማሻሻል የሚያስችል የተደራጀ የአቅም ግንባታ ስልጠና የጎላ ሚና ይጫወታል። የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን ስርዓት ባለውና በተደራጀ መልኩ ለማከናወን በዘርፉ የሚሰጡ ስልጠናዎች ከውጤታማነት አንጻር ክፍተት ያሉባቸው እንደሆኑ የተለያዩ መረጃዎች ይጠቁማሉ። እኛ በአካል ተገኝተን ከታዘብናቸው የስልጠና መድረኮች በተጨማሪም በተለያዩ ስብሰባዎችና የስልጠና መድረኮች ላይም ችግሮች እንዳሉ መታዘብ ችለናል። በቅርቡ በተካሄደው የዘርፉ የግማሽ ዓመት አፈጻጸም ላይ ከተነሱት ጉዳዮች አንዱ የሚሰጡ ስልጠናዎች የዘርፉን የስራ እድል ፈጠራ ስራ በማገዝ ረገድ ክፍተት እንዳለባቸው ነው። በፌዴራል የከተሞች የስራ እድል ፈጠራ እና የምግብ ዋስትና ኤጀንሲ የጥናትና ምርምር ዳይሬክቶሬት በከተሞች ስራ እድል ፈጠራ እና ምግብ ዋስትና ዘርፍ የተሰጡ ስልጠናዎች አስመልክቶ ግምገማዊ የዳሰሳ ጥናት (Evaluative Research) ለማድረግ የጥናት ሃሳብ (ፕሮፖዛል) አዘጋጅቷል። በጥናት ሃሳቡ ላይ ከተካተቱት ሃሳቦች የሚከተለው ይገኝበታል። “በመጀመሪያው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዘመን የሚሰጡ ማንኛውም ሥልጠናዎች አስቀድሞ በተለዩና ችግር ፈቺ በሆኑ የክህሎት ክፍተት በመሙላት ላይ ያተኮሩ እንዲሆኑ ጥረት ተደርጓል:: ነገር ግን የዕድገት ደረጃን ታሳቢ ያደረገ የድጋፍ አሰጣጥ ሥርዓት ተግባራዊ ማድረግ ላይ የመምህራን የሙያ ስብጥርና ብቃት ውስንነት፣ የወርክሾፖች አለመሟላት፣ ድጋፎችን ለኢንተርፕራይዞች እስካሉበት ድረስ ተንቀሳቅሰው አገልግሎቱን የማቅረብ ውስንነትና የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ከአነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት ጋር ተቀናጅቶ የመስራት ሁኔታ እና እያደገ የመጣውን የቴክኖሎጂና የክህሎት ፍላጎት ከመሙላት አንጻር ክፍተቶች እንዳለ የዘርፉ ሪፖርት ያመላክ ታል። ከፍተኛ ገንዘብ፣ ጉልበትና ጊዜ ወጥቶበት የሚከናወን ስልጠና ግቡን ካላሳካና ማምጣት ያለበትን ለውጥ ካላመጣ ኤጀንሲው ብሎም ለሀገር ከፍተኛ ኪሳራን ይፈጥራል።” በሀገራዊ ፖሊሲና ስትራቴጂዎች፣ በከተማ ልማት ፖሊሲና ስትራቴጂ፣ በአምስት ዓመቱ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ፣ በቴክኒክ ሙያ ትምህርትና ስልጠና ስትራቴጂ፣ በኤጀንሲው የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ስትራቴጂ እና በምግብ ዋስትና ስትራቴጂ፣ በድጋፍ ማእቀፍ ማስፈጸሚያ መመሪያዎች፣ በስታንዳርዶች እና በማኑዋሎች ላይ ስልጠናዎች ይሰጣሉ። ስልጠናዎች የሚመሩበት ወጥነት ያለው አሰራር ባለመኖሩ በስልጠና አፈጻጸም ላይ የተለያዩ ጉድለቶች ይስተዋላሉ። ስልጠናዎች በቂ ዝግጅት ሳይደረግባቸው እንዲሰጡ ማድረግ፣ ፋይዳቸውን በአግባቡ አለመመዘን፣ የይዘት ችግር፣ የአቀራረብ ችግር፣ ለስልጠና በቂ ጊዜ ያለመመደብ፣ የወቅታዊነት ችግር፣ የአሰልጣኞች ብቃት ችግር፣ ተመሳሳይ ስልጠና በተበታተነ መልኩ መስጠት፣ በስልጠና ወቅት ከሚስተዋሉ ችግሮች ውስጥ ዋና ዋናዎቹ ናቸው። ስልጠና የሰልጣኞችን አቅም በመገንባት አንድን የተወሰነ ስራ ለማከናወን አዲስ እውቀት ናክህሎት ማስተላለፍን እንዲሁም አመለካከት መለወጥን ይመለከታል። ስልጠና አንድ ሰው ተግባሩን በብቃት፣ በጥራትና በቅልጥፍና ለማከናወን የሚያስችለውን የእውቀት፣ የክህሎት፣ የግንዛቤና የአመለካከት ለውጥ የሚያገኝበት ስልታዊ ሂደትና መሳሪያ ነው። የፌዴራል የከተሞች ሥራ ዕድል ፈጠራ እና የምግብ ዋስትና ኤጀንሲ የኢንዱስትሪ ... በ2ኛው ገጽ ዞሯል ፈውስ ፍለጋ ሄዶ ሌላ በሽታ ፎቶ፡- በገባቦ ገብሬ በጋዜጣው ሪፖርተር አዲስ አበባ፡- የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ትላንት በጌዴኦ ዞን ገደብ ወረዳ በመጠለያ ውስጥ የሚገኙ ተፈናቃዮችን መጎብኘታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት አስታውቋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ትላንት ማለዳ ላይ በስፍራው በመገኘት ከተፈናቃዮችም ጋር መወያየታቸውንና በውይይቱም ተፈናቃዮቹ ያሉባቸውን ችግሮች ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ማስረዳታቸውን ፅህፈት ቤቱ ዘግቧል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጌዴኦ ተፈናቅለው በመጠለያ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ጎበኙ በአውሮፕላን አደጋው ህይወታቸው ያለፈው ኢትዮጵያውያን ስርዓተ-ቀብር ተፈፀመ ግርማ መንግስቴ አዲስ አበባ፡- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነው ቦይንግ 737-8- ማክስ መጋቢት 1 ቀን 2011 ዓ.ም በደረሰበት አደጋ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈው ኢትዮጵያውያን ስርዓተ ቀብር ትናንት በቅድስት ስላሴ ካቴድራልና ኮልፌ በሚገኘው የእስላም መካነ-መቃብር ተፈፀመ። በስርዓተ ቀብሩ ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረ ማርያም፣ የአየር መንገዱ የቦርድ ሰብሳቢና ምክትል ሰብሳቢ፣ ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት፣ አምባሳደሮች፣ ሌሎች የአየር መንገዱ ኃላፊዎችና ሠራተኞች፣ የሟች ቤተሰቦች እና በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ኀዘንተኞች ተገኝተዋል። ከወራት በፊት ከምዕራብና ምሥራቅ ጉጂ እንዲሁም በጌዴኦ ዞን አካባቢዎች በተከሰተ ግጭት በርካታ ዜጎች ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸው ይታወሳል። ላለፉት 8 ወራት የፌዴራል፣ የክልልና አካባቢው መስተዳድሮች በመተባበር ለተፈናቃዮቹ ሰብዓዊ እና ተያያዥ ድጋፎችን ሲያቀርቡ እንደነበረ የሚታወቅ ሲሆን፣ ሰሞኑን የሰላም ሚኒስትሯ ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚልም በስፍራው በመገኘት ከተፈናቃዮቹ ጋር ውይይት ማድረጋቸው ይታወሳል። በአውሮፕላን ... በ2ኛው ገጽ ዞሯል

78ኛ ዓመት ቁጥር 189 ሰኞ መጋቢት 9 ቀን 2011 ዓ.ም ያንዱ ዋጋ 5.75 …ማድረግ ላይ የመምህራን የሙያ ስብጥርና ብቃት ውስንነት፣

  • Upload
    others

  • View
    20

  • Download
    0

Embed Size (px)

Citation preview

Page 1: 78ኛ ዓመት ቁጥር 189 ሰኞ መጋቢት 9 ቀን 2011 ዓ.ም ያንዱ ዋጋ 5.75 …ማድረግ ላይ የመምህራን የሙያ ስብጥርና ብቃት ውስንነት፣

በፍቅር እንደመር በይቅርታ እንሻገር!

ወንድወሰን ሽመልስ

ከግብርና ወደ ኢንዱስትሪ እንዲሸጋገር በሚጠበቀው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እውን መሆን ጉልህ ድርሻ ያላቸው የኢንዱስትሪ ፓርኮች ተገንብተው ለሥራ ዝግጁ እየሆኑ ይገኛል። ሆኖም ፓርኮቹን ከመገንባትና አስመርቆ ለሥራ ክፍት ከማድረግ በተጓዳኝ ድጋፍና ክትትል ማድረግ እንዲሁም የኢንዱስትሪ ጥሬ ዕቃ አገር

ፍዮሪ ተወልደ

በዕድሜ አልያም በተለያዩ ፅኑ ህመሞች ሕክምና ሲደረግ ቆይቶ ከሚከሰት የህልፈተ ሕይወትና የአካል ጉዳት ውጪ ሩጫቸውን ሳይጨርሱ አንዳንዴም ገና ሳይጀምሩ በጨቅላ ዕድሜያቸው የሚቀጩ እንዳሉ ማድመጥ በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ውስጥ የሚያጋጥም ነው። ለዚህ አንዱ መንስኤ ደግሞ የሕክምና ስህተት ነው። የቀላል ራስ ምታት ምክንያታቸውን

78ኛ ዓመት ቁጥር 189 ሰኞ መጋቢት 9 ቀን 2011 ዓ.ም ያንዱ ዋጋ 5.75 ብር

የኢንዱስትሪ ፓርኮቹ ስኬት በግብዓት

አቅርቦት ይወሰናል

ፈውስ ፍለጋ ... በ2ኛው ገጽ ዞሯል

በበኃይሉ ንጉሴ

የከተሞች የስራ ዕድል ፈጠራና የምግብ ዋስትና ዘርፍ በከተሞች ለሚኖሩ ዜጎች ሰፊ የስራ ዕድል በመፍጠር ስራ አጥነትንና ድህነትን መቀነስ ችሏል። ከድህነት በታች የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎችን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ ኃላፊነት የተጣለበት ዘርፍ ነው። የዘርፉ አስፈጻሚ አካላት የስራ እድል ፈጠራ እና የምግብ ዋስትና ኤጀንሲዎች፣ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማትና የአነስተኛ ብድርና ቁጠባ ተቋማት ናቸው። የዘርፉ ተልዕኮ ውጤታማ እንዲሆን በአመለካከት፣ በእውቀትና በክህሎት የጎለበተ የሰው ሃብት ወሳኝ ነው። የሰው ሀብት ልማትን ለማረጋገጥ ከሚረዱ የተለያዩ ዘዴዎች አንዱ ስልጠና ነው። የስልጠና ስርዓትን በመዘርጋት፣ ቅድመ ስልጠና ስራዎችን በተደራጀ ሁኔታ ስራ ላይ በማዋል ሀገራዊ ዕድገትን እውን ማድረግ እንደሚቻል ያደጉ አገራት ተሞክሮ ያሳያል። በመሆኑም የሰው ሀብት ልማትን ለማረጋገጥ

የስልጠና ደረጃዎችን ማሳደግ ለስራ እድል ፈጠራው መጎልበትስልጠና ከፍተኛ ሚና አለው። ተልዕኮውን በአግባቡ የተረዳና በተገቢው አመለካከት፣ እውቀትና ክህሎት የተካነ አመራርና ባለሙያ ለአንድ ተቋም ውጤታማነት እንዲሁም ስኬት ትልቁን ድርሻ ይወስዳል። ለዚህም በስልጠና የታገዘ የሰው ሀይል ልማት ስራዎችን ማከናወን ያስፈልጋል።

በሁሉም ክልሎችና በሁለቱ ከተማ አስ ተዳደሮች ለዩኒቨርሲቲ ምሩቃን፤ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ስትራቴጂ አስፈጻሚ አካላት ማለትም የቴክኒክና ሙያ፣ የብድርና ፋይናንስ ተቋማት፣ የስራ ፈጣሪነት አስተሳሰብ ክህሎት ላላቸው፣ ለዘርፉ ባለሙያዎችና አመራሮች፣ ለኢንተርፕራይዝ ልማት አንቀሳቃሾች የተለያዩ ስልጠናዎች ይሰጣሉ። ዘርፉ በፖሊሲ፣ በስትራቴጂ፣ በመመሪያዎች፣ በማንዋሎች፣ በስታንዳርዶች፣ በእቅድ ዝግጅት፣ በፓኬጅ፣ በሪፎርም መሳሪያዎችና በመልካም አስተዳደር፣ በድጋፍ ማእቀፎች፣ በአጫጭር የቴክኒክ ክህሎት፣ በስራ አመራር፣ በአመለካከት፣ በክህሎት፣ በተለያዩ ርእሶች ላይ የአሰልጣኞች ሥልጠና፣ በንግድ ልማት አገልግሎት እና በሌሎች ዙሪያ የአጭር፣የመካከለኛና የረጅም ጊዜ ስልጠናዎች እየሰጠ ይገኛል።

የፈጻሚዎችንና አስፈጻሚዎችን ስራ አፈጻጸም

ጥራት ለማሻሻል የሚያስችል የተደራጀ የአቅም ግንባታ ስልጠና የጎላ ሚና ይጫወታል። የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን ስርዓት ባለውና በተደራጀ መልኩ ለማከናወን በዘርፉ የሚሰጡ ስልጠናዎች ከውጤታማነት አንጻር ክፍተት ያሉባቸው እንደሆኑ የተለያዩ መረጃዎች ይጠቁማሉ። እኛ በአካል ተገኝተን ከታዘብናቸው የስልጠና መድረኮች በተጨማሪም በተለያዩ ስብሰባዎችና የስልጠና መድረኮች ላይም ችግሮች እንዳሉ መታዘብ ችለናል። በቅርቡ በተካሄደው የዘርፉ የግማሽ ዓመት አፈጻጸም ላይ ከተነሱት ጉዳዮች አንዱ የሚሰጡ ስልጠናዎች የዘርፉን የስራ እድል ፈጠራ ስራ በማገዝ ረገድ ክፍተት እንዳለባቸው ነው።

በፌዴራል የከተሞች የስራ እድል ፈጠራ እና የምግብ ዋስትና ኤጀንሲ የጥናትና ምርምር ዳይሬክቶሬት በከተሞች ስራ እድል ፈጠራ እና ምግብ ዋስትና ዘርፍ የተሰጡ ስልጠናዎች አስመልክቶ ግምገማዊ የዳሰሳ ጥናት (Evaluative Research) ለማድረግ የጥናት ሃሳብ (ፕሮፖዛል) አዘጋጅቷል። በጥናት ሃሳቡ ላይ ከተካተቱት ሃሳቦች የሚከተለው ይገኝበታል።

“በመጀመሪያው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን

ዘመን የሚሰጡ ማንኛውም ሥልጠናዎች አስቀድሞ በተለዩና ችግር ፈቺ በሆኑ የክህሎት ክፍተት በመሙላት ላይ ያተኮሩ እንዲሆኑ ጥረት ተደርጓል:: ነገር ግን የዕድገት ደረጃን ታሳቢ ያደረገ የድጋፍ አሰጣጥ ሥርዓት ተግባራዊ ማድረግ ላይ የመምህራን የሙያ ስብጥርና ብቃት ውስንነት፣ የወርክሾፖች አለመሟላት፣ ድጋፎችን ለኢንተርፕራይዞች እስካሉበት ድረስ ተንቀሳቅሰው አገልግሎቱን የማቅረብ ውስንነትና የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ከአነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት ጋር ተቀናጅቶ የመስራት ሁኔታ እና እያደገ የመጣውን የቴክኖሎጂና የክህሎት ፍላጎት ከመሙላት አንጻር ክፍተቶች እንዳለ የዘርፉ ሪፖርት ያመላክ ታል። ከፍተኛ ገንዘብ፣ ጉልበትና ጊዜ ወጥቶበት የሚከናወን ስልጠና ግቡን ካላሳካና ማምጣት ያለበትን ለውጥ ካላመጣ ኤጀንሲው ብሎም ለሀገር ከፍተኛ ኪሳራን ይፈጥራል።”

በሀገራዊ ፖሊሲና ስትራቴጂዎች፣ በከተማ ልማት ፖሊሲና ስትራቴጂ፣ በአምስት ዓመቱ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ፣ በቴክኒክ ሙያ ትምህርትና ስልጠና ስትራቴጂ፣ በኤጀንሲው የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ስትራቴጂ እና በምግብ ዋስትና ስትራቴጂ፣

በድጋፍ ማእቀፍ ማስፈጸሚያ መመሪያዎች፣ በስታንዳርዶች እና በማኑዋሎች ላይ ስልጠናዎች ይሰጣሉ።

ስልጠናዎች የሚመሩበት ወጥነት ያለው አሰራር ባለመኖሩ በስልጠና አፈጻጸም ላይ የተለያዩ ጉድለቶች ይስተዋላሉ። ስልጠናዎች በቂ ዝግጅት ሳይደረግባቸው እንዲሰጡ ማድረግ፣ ፋይዳቸውን በአግባቡ አለመመዘን፣ የይዘት ችግር፣ የአቀራረብ ችግር፣ ለስልጠና በቂ ጊዜ ያለመመደብ፣ የወቅታዊነት ችግር፣ የአሰልጣኞች ብቃት ችግር፣ ተመሳሳይ ስልጠና በተበታተነ መልኩ መስጠት፣ በስልጠና ወቅት ከሚስተዋሉ ችግሮች ውስጥ ዋና ዋናዎቹ ናቸው።

ስልጠና የሰልጣኞችን አቅም በመገንባት አንድን የተወሰነ ስራ ለማከናወን አዲስ እውቀት ናክህሎት ማስተላለፍን እንዲሁም አመለካከት መለወጥን ይመለከታል። ስልጠና አንድ ሰው ተግባሩን በብቃት፣ በጥራትና በቅልጥፍና ለማከናወን የሚያስችለውን የእውቀት፣ የክህሎት፣ የግንዛቤና የአመለካከት ለውጥ የሚያገኝበት ስልታዊ ሂደትና መሳሪያ ነው።

የፌዴራል የከተሞች ሥራ ዕድል ፈጠራ እና የምግብ ዋስትና ኤጀንሲ

የኢንዱስትሪ ... በ2ኛው ገጽ ዞሯል

ፈውስ ፍለጋ ሄዶ ሌላ በሽታ

ፎቶ

፡- በ

ገባቦ

ገብሬ

በጋዜጣው ሪፖርተር አዲስ አበባ፡- የኢፌዴሪ ጠቅላይ

ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ትላንት በጌዴኦ ዞን ገደብ ወረዳ በመጠለያ ውስጥ የሚገኙ ተፈናቃዮችን መጎብኘታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት አስታውቋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ትላንት ማለዳ ላይ በስፍራው በመገኘት ከተፈናቃዮችም ጋር መወያየታቸውንና በውይይቱም ተፈናቃዮቹ ያሉባቸውን ችግሮች ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ማስረዳታቸውን ፅህፈት ቤቱ ዘግቧል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጌዴኦ ተፈናቅለው በመጠለያ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ጎበኙ

በአውሮፕላን አደጋው ህይወታቸው ያለፈው ኢትዮጵያውያን ስርዓተ-ቀብር ተፈፀመግርማ መንግስቴ

አዲስ አበባ፡- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነው ቦይንግ 737-8- ማክስ መጋቢት 1 ቀን 2011 ዓ.ም በደረሰበት አደጋ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈው ኢትዮጵያውያን ስርዓተ ቀብር ትናንት በቅድስት ስላሴ ካቴድራልና ኮልፌ በሚገኘው የእስላም መካነ-መቃብር ተፈፀመ።

በስርዓተ ቀብሩ ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረ ማርያም፣ የአየር መንገዱ የቦርድ ሰብሳቢና ምክትል ሰብሳቢ፣ ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት፣ አምባሳደሮች፣ ሌሎች የአየር መንገዱ ኃላፊዎችና ሠራተኞች፣ የሟች ቤተሰቦች እና በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ኀዘንተኞች ተገኝተዋል።

ከወራት በፊት ከምዕራብና ምሥራቅ ጉጂ እንዲሁም በጌዴኦ ዞን አካባቢዎች በተከሰተ ግጭት በርካታ ዜጎች ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸው ይታወሳል።

ላለፉት 8 ወራት የፌዴራል፣ የክልልና አካባቢው መስተዳድሮች በመተባበር ለተፈናቃዮቹ ሰብዓዊ እና ተያያዥ ድጋፎችን ሲያቀርቡ እንደነበረ የሚታወቅ ሲሆን፣ ሰሞኑን የሰላም ሚኒስትሯ ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚልም በስፍራው በመገኘት ከተፈናቃዮቹ ጋር ውይይት ማድረጋቸው ይታወሳል።

በአውሮፕላን ... በ2ኛው ገጽ ዞሯል

Page 2: 78ኛ ዓመት ቁጥር 189 ሰኞ መጋቢት 9 ቀን 2011 ዓ.ም ያንዱ ዋጋ 5.75 …ማድረግ ላይ የመምህራን የሙያ ስብጥርና ብቃት ውስንነት፣

ግርማ መንግሥቴ

አዲስ አበባ የአገሪቱ ብቻ ሳትሆን የአፍሪካ መዲናና የበርካታ ዓለም አቀፍ ተቋማት መናኸሪያ እንዲሁም ከአንድ መቶ በላይ ዲፕሎማቶች መቀመጫ መሆኗ ይታወቃል፡፡ ከዚህም ባሻገር ከተማዋ በየጊዜው የምታስተናግዳቸው ትላልቅ ዓለም አቀፍና አህጉራዊ አቀፍ ጉባኤዎችና ስብሰባዎች ከተማዋን የበርካታ የውጭ አገር ዜጎች መዳረሻ አድርጓታል፡፡ በዚህም የተነሳ የአዲስ አበባ ገጽታ በውጭው ማህበረሰብ ዘንድ የአገሪቱ ገጽታ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡

ይሁን እንጂ በከተማዋ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የዝርፊያና የሌብነት ተግባራት እየተበራከቱ መሆኑንና ይህም የከተማዋን ገጽታ ከማበላሸቱም ባሻገር ህብረተሰቡን ስጋት ላይ እየከተተው እንደሆነ ይነገራል፡፡ ከንቲባ ታከለ ኡማም በቅርብ በተካሄደ አንድ መድረክ ላይ በከተማችን ‹‹የሴቶች ቦርሳዎች ይነጠቃሉ፣ የሞባይል ስልኮች ይዘረፋሉ፣ የተለያዩ ወንጀሎች ይፈጸማሉ›› በማለት ሲገልፁ ተሰምቷል። በአዲስ አበባ እየተስተዋለ ያለው ችግር ሰፊና ውስብስብ ሲሆን በሕገወጥ ድርጊት ተሳትፈዋል የተባሉ በርካታ ተጠርጣሪዎች መኖራቸውንና ለወንጀል ተግባር የሚያገለግሉ አራት ሺህ የሞተር ብስክሌቶች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውም ታውቋል፡፡

ውስጥ ማምረት እንደሚገባ ምሑራን ይገልጻሉ፡፡አቶ ዘመዴነህ ንጋቱ፣ የምጣኔ ሀብት ባለሙያና

የፌርፋክስ አፍሪካ ሊቀመንበር ናቸው፡፡ እርሳቸው እንደሚሉት፤ በኢትዮጵያ በኢኮኖሚው ዘርፍ እየመጡ ከሚገኙ ስኬቶች አንዱ የኢንዱስትሪ ፓርኮች በሰፊው ሥራ ላይ መዋል መጀመራቸው ነው፡፡ ለምሳሌ እስከአሁን ለምረቃ ከበቁት ሰባት የኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ኤክስፖርት ማድረግ ጀምሯል፤ በሺዎች ለሚቆጠሩ ሰዎችም የሥራ ዕድል ፈጥሯል፡፡ ሐዋሳን ጨምሮ በቅርቡ እየተከፈቱ ወደ ሥራ የገቡትም በርካታ የውጭ ባለሀብቶችን ስበዋል። በዚህ መልኩ የኢንዱስትሪ ፓርኮች እየተስፋፉ መሄድም ራሱን የቻለ ዓለምአቀፍ የኢንዱስትሪ መንደር መፍጠር ነው፡፡

ይሁን እንጂ አሁን ወደ ኢንዱስትሪ ፓርኮቹ የገቡትም ሆኑ ወደፊት የሚገቡት በሚሠሩት ሥራ ስኬታማ እንዲሆኑና ቀጣይነት ያለው ውጤት እንዲያስመዘግቡ የሚያስችሉ የክትትልና ድጋፍ ሥራዎችን ማከናወን ይጠይቃል፡፡ ይህ ደግሞ አንደኛ፣ ችግሮች እንዳያጋጥሟቸው ቀድሞ መሥራትን፤ ሁለተኛም፣ ችግሮች ካጋጠሟቸው በኋላ በተቀላጠፈ መልኩ መፍትሔ የሚያስገኙ አሠራሮችን መዘርጋትና የፖሊሲ አቅጣጫዎችን ማስቀመጥ ይፈልጋል፡፡

ይሄን ሃሳብ የሚጋሩት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ሀብት ባለሙያ የሆኑት ዶክተር ቆስጠንጢኖስ በርኸ በበኩላቸው እንደሚሉት፤ የኢንዱስትሪ ፓርኮች መገንባትና ተመርቀውም ወደሥራ መግባት ለኢኮኖሚ ሽግግሩ ወሳኝ ሚና አላቸው፡፡ የቻይናን ኢኮኖሚ ያሸጋገሩትና ማህበራዊ ለውጥም ያመጡት የኢንዱስሪ ፓርኮች እንደሆኑ ይታመናል፡፡ ይሁን እንጂ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን ከመገንባትና መርቆም ለሥራ ዝግጁ ከማድረግ ባለፈ ኢንዱስትሪዎቹ የሚጠቀሟቸውን የጥሬ ዕቃዎች ግብዓት አገር

2 መጋቢት 9 ቀን 2011 ዓ.ም አዲስ ዘመን

የሀገር ውስጥ ዜናመፍትሄ የሚሹት የባቡር ላይ ወንጀሎች

የኢንዱስትሪ ፓርኮቹ ...ከ1ኛው ገጽ የዞረ ውስጥ ማምረት የሚቻልበት መንገድ መፍጠር

ይገባል፡፡ለምሳሌ፣ የጨርቃጨርቅ ፋብሪካዎች

ጥጡን፣ መስፊያ ክሩንም ሆነ ቁልፉን ከውጭ የሚያመጡት ከሆነ ከአገር ውስጥ የሚገኘው ሠራተኛው ብቻ ይሆናል፡፡ በተለይ ለጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ጥጥ ወሳኝ እንደመሆኑ ጥጥን በአገር ውስጥ ማምረት ብቻ ሳይሆን በምርምር ታግዞ በጥራትና በተመጣጣኝ ዋጋ ማግኘት የሚቻልበትን ዕድል መፍጠር ይገባል፡፡

እንደ ዶክተር ቆስጠንጢኖስ ገለጻ፤ የአግሮ ኢንዱስትሪ ፓርኮች በአመዛኙ በግብርና ምርቶች ላይ የተመሰረቱ እንደመሆናቸው ኢንዱስትሪዎቹ በገቢ የግብዓት ምርቶች ላይ እንዳይንጠለጠሉ የግብርናውን ዘርፍ ከተለመደው አካሄድ በማላቀቅና በማዘመን ያለውን አቅም አሟጦ መጠቀም ተገቢ ይሆናል፡፡ ሰፋፊ የእርሻ መሬቶችን መጠቀምም ይገባል፡፡ ምክንያቱም በአገሪቱ ሊታረስ ከሚችለው መሬት ውስጥ 14 በመቶው ብቻ ነው እየታረሰ ያለው፤ በየዓመቱ 122 ቢሊዬን ሜትር ኪዩብ ውሃ ከሚያመነጩ የኢትዮጵያ ወንዞችም ለመስኖ መዋል የቻለው እዚህ ግባ የሚባል አይደለም፡፡

ለምሳሌ፣ በሶማሌ ክልል ሰፊ የእርሻ መሬት ብቻ ሳይሆን ይሄን ሊያለሙ የሚችሉ ወንዞችም ይፈስሳሉ፡፡ እናም መንግሥት እነዚህን ሀብቶች እንዴት መጠቀም እና ይሄንን ማልማት የሚችሉ አካላትንም እንዴት ማምጣት እንደሚቻል በሚሠራበት ሂደት ላይ አተኩሮ መሥራት ይኖርበታል፡፡ ለአግሮ ኢንዱስትሪዎች ግብዓት የሚሆኑ ሌሎች የፋብሪካ ምርቶችንም በአገር ውስጥ አቅም መሸፈን የሚቻልበት ዕድል ሊፈጠር ይገባል፡፡ ስኳር ፋብሪካዎችም ለምግብና ከረሜላ ፋብሪካዎች ስኳር በማቅረብ ትልቅ ሚና ስላላቸው የተጓተቱ የስኳር ፋብሪካዎችም በተመሳሳይ ፍጥነት ሊሠራባቸው ያስፈልጋል፡፡

ኢንቨስትመንቱን ከማበረታታት፣ በዘርፉ የተሰማሪ ባለድርሻዎችና የመንግሥት ተቋማት

አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲሰጡ፣ ክትትልም እንዲያደርጉ ማስቻል፤ እንዲሁም የደህንነት ስጋት የሌለበት ሰላማዊ እንቅስቃሴን መፍጠር በሚቻልበት ሂደት ላይም በትኩረት መሥራት ይገባል፡፡ ይሄም የአካባቢውን ህዝብ ጭምር ተጠቃሚነትን እያረጋገጡ መሄድን ይጠይቃል፡፡

አቶ ዘመዴነህ በበኩላቸው እንደሚሉት፤ የኢንዱስትሪ ፓርኮቹ በሴክተር ተከፋፍለው የተቋቋሙ ናቸው፡፡ ለምሳሌ፣ የጨርቃጨርቅና አልባሳት ኢንዱስትሪዎች በመጀመሪያ እየተሠሩና ጥሩ እየሄዱ ነው፤ አሁን ደግሞ የአግሮ ፕሮሰሲንግና የመድሃኒት ፓርኮች ትኩረት ተሰጥቷቸዋል። ኢትዮጵያ ቡና፣ ሰሊጥና ሌሎችም የግብርና ምርቶች በጥሬው ወደ ውጭ ትልካለች። ለአብነት፣ ቡና በጥሬው በዓመት 800 ሚሊዮን ዶላር ገደማ ኤክስፖርት ይደረጋል፤በእነዚህ ፓርኮች እሴት ሲጨመርበት ግን በዓመት ከሁለት እስከ ሦስት ቢሊዮን ዶላር ማግኘት ይቻላል፡፡

ይሁን እንጂ ይህ ውጤት የሚገኘው ኢንዱስትሪ ፓርኮቹ የሚፈልጉትን ግብዓት በአገር ውስጥ አምርቶ ማቅረብ ሲቻል ነው። ኢትዮጵያም ከአፍሪካ ከፍተኛ ስንዴ አምራች አገር ብትሆንም ስንዴን ከውጭ ታስገባለች፤ በተመሳሳይ ሰፊ የእንስሳት ሀብት እያላት የቆዳና የስጋ ኢንዱስትሪዎች የግብዓት እጥረት እንዳለ ያነሳሉ፡፡ ከዚህ አኳያ የኢንዱስትሪ ፓርኮች በኢንፖርት ግብዓት ላይ እንዳይንጠለጠሉ መሥራት፤ ግብርናውን በማዘመንና የበለጠ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ምርታማነቱን ማሳደግ፤ ምርቶቹንም በጥራትና በብዛት ማቅረብ ይገባል። ለውጤቱ ዘላቂነትም ኢንዱስትሪዎቹን መሰረት ያደረጉ ዘርፈ ብዙ ተግባራት ማከናወን ያስፈልጋል።

አቶ ዘመዴነህ እንደሚገልጹት፤ ይሄንን ሐላፊነት የሚወጣ በመንግሥት በኩል አንድ ጠንካራ ተቋም መፍጠር ይጠይቃል፡፡ ይህ ተቋም በአንድ በኩል ቃል ተገብቶላቸው የመጡበት እንዲፈጸምላቸው የሚደግፍ፤ በሌላ በኩል ደግሞ

ባለሀብቶቹ ቃል ገብተው የመጡበትን በሥራ ላይ እያዋሉ ስለመሆናቸው የሚከታተል መሆን አለበት፡፡ በተመሳሳይ እነዚህ ፓርኮች ቀጣይነት ያለው ስኬት እንዲያስመዘግቡ ለእነዚህ ፓርኮች የሚሆን የሰው ሐይል ስልጠናና የቴክኖሎጂ አቅም ማሳደግ ተግባርም ትኩረት ተሰጥቶ ሊሠራበት ይገባል፡፡

ዶክተር ቆስጠንጢኖስ በበኩላቸው እንደ ሚሉት፤ ኢትዮጵያ እስከአሁን በአነስተኛ መሬት ላይ በሚከናወን ግብርና ላይ ቆይታለች። ይህ ሂደት ለዘላቂ ልማትና ለአየር ንብረት ለውጥ ጠቃሚ ሊሆን ቢችልም፤ ሰፋፊ እርሻ በሌለበት አንድ አገር ራሷን መቀለብ አትችልም፡፡ ለምሳሌ፣ ባለፉት ሦስት ዓመታት ወደ 770 ሚሊዬን ዶላር ወጥቶ ስንዴ ተገዝቷል፡፡ በተመሳሳይ ህዝቡ የሚፈልገው የምግብ ዘይት በአገር ውስጥ እየተመረተ ያለ ቢሆንም፤ ሁሉም ነገር በአንዴ ተቀይሮ ፓልም ዘይት ከቀረጥ ነፃ እንዲገባ መደረጉ ከጃንሆይ ጊዜ ጀምሮ በደርግም የነበሩና ኢህአዴግም ፕራይቬታይዝ ያደረጋቸው ኢንዱስትሪዎችን በሙሉ ገድሏል፡፡

ይሄን መሰል አካሄድ መታረም ስለሚገባው፤ አሁንም ኢንዱስትሪዎችን ከመገንባትና ለሥራ ዝግጁ ከማድረግ ጎን ለጎን፤ ኢንዱስትሪዎቹ ተወዳዳሪነታቸውና ውጤታማነታቸው እን ዲጎለብት ከግብዓት ጀምሮ አሽጎ ለመላክ እስከሚያስችሉ ዕቃዎች ድረስ ያሉ ነገሮች ላይ በትኩረት መሥራት ያስፈልጋል። ይሄን ማድረግ ካልተቻለ ግን ኢንዱስትሪዎቹ ይቆማሉ ማለት ባይቻል እንኳን፤ በገቢ ምርት ላይ ስለሚንጠለጠሉ ውጤታማነታቸውና ተወዳዳሪነታቸው ጥያቄ ውስጥ ይገባል። ይህ ደግሞ የሚጠበቅባቸውን አገራዊ ሽግግር የመፍጠር ሚናቸውን ይጎዳዋል። በመሆኑም የኢንዱስትሪ ፓርኮችን ለሥራ ዝግጁ የማድረግ ሂደቱ ፋብሪካዎቹ በግብዓትነት የሚጠቀሟቸውን ጥሬ ዕቃዎች በተገቢው መልኩ ለማቅረብ የሚያስችሉ የአቅርቦት ሰንሰለቶች በአግባቡ ተፈትሸው ሊሠራባቸው ይገባል።

ፈውስ ፍለጋ ሄዶ ...ለማወቅ ወደ ሐኪም ቤት አቅንተው ‹‹ምነው እግሬን በሰበረው›› የሚያስብሉ የአካል ጉዳቶች ከፍ ሲልም እስከ ህልፈተ ሕይወት የሚደርስ አደጋ እንደሚያጋጥም ሲነሳ ይደመጣል፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ ልዩ ስሙ አቧሬ አካባቢ ነዋሪ አቶ ወንድወሰን አዝብጤም የችግሩ ሰለባ መሆናቸውን ከዓይናቸው ልውረድ አልውረድ የሚል እንባቸው ጋር ትንቅንቅ ፈጥረው ገለጹልን፡፡

አቶ ወንድወሰን ከዓመት በፊት በሁለቱም እጃቸው ላይ ለወጣባቸው እባጭ መፍትሔ ለማግኘት ወደ የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ማምራታቸውን አስታውሰዋል፡፡ በወቅቱም ሐኪም ከተመለከታቸው በኋላ የባሰበት የግራ እጃቸው በመሆኑ ቅድሚያ የቀዶ ጥገናው ይኸው እጃቸው ይደረጋል፡፡ ቀዶ ጥገናውም በጥሩ ሁኔታ በመጠናቀቁ ከዓመት ቀጠሮ በኋላ ሲመጡ በሌላ ሐኪም የቀኝ እጃቸው ይሠራላቸዋል፡፡ ሕክምናውን የሰጠቻቸው ሐኪም ቀላል ቀዶ ጥገና እንደሚሰጣቸው ስትገልጽላቸውም ከዚህ ቀደም ተኝተው መታከማቸውንና ለ26 ዓመታት የስኳር ሕመምተኛ እንደሆኑ ሊያስረዷት ይሞክራሉ። ይሁን እንጂ በማግስቱ እንዲሠራላቸው በመወሰኑ ታህሳስ 3 ቀን 2011 ዓ.ም ከጠዋቱ ሦስት ሰዓት ከሩብ የገቡ ስምንት ሰዓት ሊሆን ሲል መውጣታቸውንም ነው የተናገሩት፡፡ ቀዶ ጥገና የተደረገበት ቀን ጨምሮም ሁለት ቀን ድንገተኛ ክፍል ገብተው ነበር፡፡

ቀዶ ጥገናው ከተጠናቀቀ በኋላም በሦስተኛው ቀን ወደ ጤና ጣቢያ ሄደው ፋሻ እንዲያስቀይሩ መላካቸውንም አቶ ወንድወሰን አስታውሰዋል። በተባሉበት ዕለት ወደ ጤና ጣቢያ ሲያመሩም በቅድሚያ ሐኪሙ ዓይቶት እንደሚፈታ ተገልፆላቸው ተመልሰዋል፡፡ የካቲት 12 ሆስፒታል በማቅናትም የሕክምና ባለሙያዎችን ሲያናግሩ ተመሳሳይ ምላሽ አግኝተዋል፡፡ ቀዶ ጥገናውን ወደ ሠራቻቸው ሐኪም በመሄድ ያጋጠማቸውን ቢነግሯትም ጤና ጣቢያ ይህን የመሥራት ግዴታ አለባቸው በማለት ልታስተናግዳቸው ፈቃደኛ እንዳልሆነች ነው የገለጹት፡፡

ከ1ኛው ገጽ የዞረ ‹‹ምንም እንኳ ሕመሙ እኔ ጋር ቢሆንም ሞያው ግን የሕክምና ባለሞያዋ ጋር ነው›› በማለት ዕምነት የጣሉባት ሐኪም ያደረገችላቸው ሕክምና ቆዳቸውን በመግፈፍ ይብሱን ጣቶቻቸው እንዳይታጠፉና እንዳይዘረጉ ብሎም እንዲሸበሸብ እንዳደረጋቸው ተናግረዋል፡፡ ቀድሞ በሹፍርና ሥራ የዕለት ጉርሳቸውን ይበሉበት የነበረ እጃቸው በአሁኑ ወቅት ከሥራ ውጪ ሆኗል፡፡ ስለ ጉዳዩ ሊያናግሯት ቢሞክሩም አጥጋቢ ምላሽን አላገኙም።

ለበላይ አካል ቅሬታ ማቅረባቸው ተገቢ እንዳልሆነና እንዲተውት ከሌሎች የተቋሙ የሕክምና ባለሙያዎች ጋር በመሆን በር ዘግታ እንዳናገረቻቸውም አቶ ወንድወሰን ተናግረዋል። መፍትሔ እስኪያገኙ አቤቱታቸውን ማሰማት እንደማያቆሙ በመናገራቸውም በተቋሙ ተገቢውን አገልግሎት እንኳ ሊያገኙ እንዳልቻሉ ነው በምሬት የገለጹት፡፡ ከዚህ የከፋ ብዙ ፈተናም በታካሚዎች ላይ እንደሚደርስ በመጠቆም፤ በርካቶች ወዴት እንደሚኬድ ባለማወቅ ችግራቸውን ይዘው ይቀመጣሉና መንግሥት የጤና ተቋማትን ቢፈትሽ ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

በየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ዋና ፕሮቮስት ዶክተር አየለ ተሾመ፤ ተገልጋዩ ቢሯቸው በመሄድ ቅሬታቸውን በቃል ማቅረባቸውን ቢያምኑም ቅሬታቸው ግን የተደበላለቀ ነው ብለዋል፡፡ ከቀዶ ጥገናው በኋላ እጃቸው አለመዳኑን በቅሬታነት የሚያነሱ ሲሆን፤ ለዚህ እንደ ማሳያ የሚያቀርቡት ሌላኛው እጃቸው ተመሳሳይ ሕክምና ተደርጎለት በቶሎ መዳኑን ነው። ተመሳሳይ ቀዶ ጥገና ከዚህ በፊት በጥሩ ሁኔታ ተደረገ ማለት በሌላ ወቅት ለሚደረግ ቀዶ ጥገና በሠላም መጠናቀቅ ዋስትና ሊሆን አይችልም። ውጤታማ አልሆነም ማለት ሐኪሙ ስህተት ፈጥሯል ማለትም አይደለም ይላሉ፡፡

ቁስሉ በፍጥነት ካልዳነ የሕክምና ባለሙያው ተከታትሎ በድጋሚም ቀዶ ጥገና ሊደረግ ይችላል። ሁሉም ክትትል የሚደረገው ግን ቀዶ ጥገና በተደረገበት ተቋም ላይሆን ይችላል። ቁስሉን ለማስጠረግ በአቅራቢያ በሚገኝ ጤና ጣቢያም ሊሄዱ ይችላሉ። ነገር ግን ጤና ጣቢያዎች አንዳንዴ በሆስፒታል የተጀመረ ሕክምና

በዚያው ማለቅ አለበት የሚል ምላሽ ይሰጣሉ። ይህን ያመጣውም የአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ያሉ ክፍተቶችና የቅብብሎሽ ሥርዓቱ ድክመት ነው። ከዚህ ውጪም ተገልጋዮችን እንደ ግንዛቤ ደረጃቸው ማነጋገር ላይ የሚስተዋሉ ክፍተቶችም የቅሬታ መነሻ ሲሆኑም ይስተዋላል፡፡

ተገልጋዩ አቤቱታቸውን ካሰሙ በኋላ በአግባቡ አገልግሎት ሊሰጣቸው አለመቻሉን ማንሳታቸውን ዋና ፕሮቮስቱ ገልፀዋል፡፡ ችግሩን ለመፍታት የሕክምና ባለሙያዎችን የማነጋገር ሥራ ተሠርቷል። ተገልጋዮች ሕመማቸው ከሚፈጥርባቸው የጤና መጓደል በተጨማሪ ብዙ ዓይነት ባህርይን ሊያሳዩ እንደሚችሉ በመገንዘብ ሐኪሞች በሠከነ አዕምሮ የመቀበል ኃላፊነት እንደሚኖርባቸውም አምነዋል፡፡

ሌላኛው ቅሬታ የሕክምና ስህተት ተፈጥሯል የሚል በመሆኑ ይህንንም ለማጥራት ተሞክሯል። ግለሰቡ 30 በሚጠጉ ዓመታት የስኳር ሕመምተኛ መሆናቸውን በማንሳት ይህም ቶሎ ቁስል እንዳይድን በሽታ የመከላከል አቅም ማነስ የሚያስከትል በመሆኑ እንደሌሎች ሰዎች ሁሉ ቀዶ ጥገና ሠላማዊ እንዳይሆን ሊያደርግ ይችላል። በማጥራቱም በተረጋገጠው መሠረት ምንም ዓይነት የሕክምና ችግር የለም በማለት ባለጉዳዩ ያነሱትን ቅሬታ አስተባብለዋል፡፡ ነገር ግን ተገልጋዩ አሁንም ችግር እንደገጠማቸው ካመኑ ቅሬታዎችን ለሚመለከተው የሕክምና አገልግሎት አሰጣጥ የሥነምግባር ኮሚቴ በጽሑፍ ሊያቀርቡ እንደሚችሉ ዋና ፕሮቮስቱ አስታውቀዋል፡፡

ቅሬታዎችን የሚመለከተው ኮሚቴ ገለልተኝነትስ የሚለውን ጉዳይ አስመልክቶ ዶከተር አየለ፤ ውስጣዊ ኮሚቴው ከወገንተኝነት ሙሉ በሙሉ የፀዳ ነው የሚል ማረጋገጫ መስጠት አዳጋች ቢሆንም የኮሚቴውን ውሳኔ ከመቀበል ይልቅ ሚዛን ላይ አስቀምጦ መመልከት የተቋሙ የበላይ አስተዳደር ኃላፊነት በመሆኑ በየደረጃው እንደሚታይ አካሄዱን አብራርተዋል፡፡ ይህ አጥጋቢ ካልሆነም ገለልተኛ ወደሆኑ ተቋሞች በመሄድ አቤቱታ ማሰማት የሚቻልበት አሠራር ምቹ ነው፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምግብ፣

መድሐኒት፣ ጤናና እንክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለሥልጣን የሕግ አገልግሎት ክፍል ኃላፊ ወይዘሮ ዱሬ ዘላለም፤ ከግለሰቦች፣ ከፍርድ ቤት፣ ከዐቃቤ ሕግና ከፖሊስ ጣቢያ የሕክምና ስህተት ተፈጥሯልና ይጣራ በሚሉ አቤቱታዎች ወደ ባለሥልጣኑ እንደሚደርሱ ገልፀዋል፡፡ ባለፉት ሦስት ዓመታትም ከዚህ ጋር የተያያዙ 161 ቅሬታዎች ቀርበዋል፡፡ ከዚህ ውስጥ ቅሬታው ትክክለኛ ሆኖ ተጠያቂ የተደረጉ፣ በነፃ የተለቀቁም እንዲሁም በመታየት ላይ ያለና ውሳኔ ያላረፈባቸው ጉዳዮችም አሉ፡፡

የተሰጠው ውሳኔ ዓይነትም ከፍተኛ ከሆነው ለአንድ ዓመት ከአምስት ወር የሞያ ፍቃድ እገዳ ጀምሮ የሕክምና ሞያ ፍቃድ ሙሉ በሙሉ እስከ መሠረዝ ይደርሳል፡፡ ለባለሥልጣኑ የሚቀርቡ ቅሬታዎች የሚጣሩት ከሕክምና ሞያ የተውጣጡ ሐኪሞች፣ ከምክር ቤት ሁለት ሰዎች እንዲሁም ከሕግ ባለሙያዎች ባቀፈ ኮሚቴ ነው፡፡ ኮሚቴው ከሚያሳርፈው አስተዳደራዊ ውሳኔ ጎን ለጎን በፍርድ ቤት ደግሞ የፍትሐ ብሔርና የወንጀል ተጠያቂነቱ ይኖራል፡፡

ወደ ባለሥልጣኑ ከሚመጡት ቅሬታዎች መካከል በብዛት የአካል ጉዳት ሲሆን፤ ሕልፈተ ሕይወትም እንዳለ ነው ኃላፊዋ የተናገሩት፡፡ በተለይም የእናትና የጨቅላ ሕፃናት ሞት ይጠቀ ሳል፡፡ ችግሮቹ ከሚፈጠሩባቸው ምክንያቶች ውስጥ የሞያ ብቃት ማነስ አንዱ ቢሆንም ዋነኛው ግን በቸልተኝነት የሚመጣ ችግር እንደሆነ ማረጋገጥ ተችሏል። ችግሮቹን ለማቃለልም ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን በየጊዜው የንቅናቄ መድረኮች ይዘጋጃሉ።

ኃላፊዋ እንደሚሉት፤ ባለሥልጣኑ ከተለያዩ ተቋማት ጋር በመሥራት ለሆስፒታሎች፣ ለጤና ጣቢያዎች ብሎም ለግልም ሆነ ለመንግሥት የጤና ተቋማት ሥልጠናዎችን እየሠጠ ይገኛል። በዚህ ደረጃ ቅሬታዎችን ማቅረብ የሚቻልበት አሠራር እንዳለ ግንዛቤ ክፍተት እንዳለ በመግለጽም፤ በቀጣይ ተገልጋዮች በሕክምና ስህተት እንደተፈጠረባቸው ሲያምኑና መሠል ችግሮች ሲያጋጥም ወደ ባለሥልጣኑ ቀርበው ቅሬታቸውን ማስገባት እንደሚችሉም አስታውቀዋል።

ወንጀሎቹ በጠራራ ፀሃይ ከሚፈጸሙባቸው ስፍራዎች ውስጥ አንዱ ደግሞ የባቡር ትራንስፖርት እንደሆነ ነዋሪዎች ይናገራሉ፡፡ በተለይ ጉዳዩን በቅርብ የሚያውቁት፤ “የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት ኮርፖሬሽን” እና በሰላምና ፀጥታ ጉዳይ ቁልፍ ባለድርሻ አካል የሆነው የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን እንደሚነግሩን በትራንስፖርት ዘርፉ የሚታዩ ወንጀሎች ቀላል አይደሉም፤ እንደውም እየሰፉ፣ እየረቀቁና እየተወሳሰቡ በመሄድ ላይ ናቸው።

የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ባዘጋ ጀው የባለ-ድርሻ አካላት የውይይት መድረክ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ በቀለ አሰፋ በቪዲዮ አስደግፈው ባቀረቡት ሪፖርት ላይ እንደታየው የሚፈፀሙት ወንጀሎች የተለያዩ ናቸው። ከነዚህ ውስጥ አንዳንዶቹ ግን ለምን እንደሚፈጸሙ እንኳን ለመገመት የሚያዳግቱ ናቸው፡፡ ከነዚህም መካከል ወሳኝ የሆኑ ቁሶችን፤ ለምሳሌ እሳት ማጥፊያውን ካለበት ቦታ ገንጥሎ በማንሳት ሀዲዱ መሀል መጣል ይጠቀሳል፡፡

በወቅቱ በቀረበው የቪዲዮ ምስል ላይ ማየት እንደተቻለው በአካባቢው ላይ የሚገኝ ንብረትን መውሰድ፣ ኪስ ማውለቅ፣ ሞባይል ምንተፋ የመኪኖች ባቡር መስመር ውስጥ ዘሎ መግባት፣ የአንዳንድ ሰዎች መሀል ሀዲድ ላይ ተኝቶ መገኘት፣

የመኪኖች ዘሎ መግባትና ባቡሩን መግጨት፣ የአንዳንድ ተጓዦች ስርአት አልበኝነት፣ ከፖሊስ ጋር ግብ ግብ መግጠም፣ ወዘተ አይነት ወንጀሎች ይፈፀማሉ።

አቶ ጥላሁን አላምረው የቀላል ባቡሩ የዘወትር ደንበኛ ናቸው። የስራ ቦታቸው ስታዲየም በመሆኑ ምክንያት ከሀያት ደርሶ መልስ በቀን ሁለቴ ከባቡሩ ጋር ግንኙነት አላቸው። “ምን ገጠመኝ አለዎት” ስንል ጠይቀናቸው ነበር። አቶ ጥላሁን “የሞባይል ስርቆት” ካንድም ሁለት ሶስቴ ያጋጠማቸው ሲሆን “የጎረምሶች የርስ በርስ ድብድብ”ም አጋጥሟቸው እንደሚያውቅ ነግረውናል።

ከሁሉም ከሁሉም የከፋውና የሁልጊዜ ክስተት የሆነው የወንጀል ተግባር ቲኬት ማጭበርበር ነው። የኮርፖሬሽኑ የኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ኃላፊ አቶ ደረጀ ተፈራ እንደገለፁት፤ በተወሰኑ የትራንስፖርቱ ተጠቃሚዎች አካባቢ የስነምግባር ችግር የሚታይ ሲሆን ይህም የአጭር ርቀት ቲኬት እየቆረጡ ረጅም ርቀት በመጓዝ፤ ጭራሹንም ሳይቆርጡ በመግባት ኮርፖሬሽኑን ለኪሳራ እየዳረጉት ይገኛሉ፡፡ “የመዲናችን አዲስ አበባ ከተማ የቀላል ባቡር ትራንስፖርት የ”ሁለት፣ አራት እና ስድስት ብር” ታሪፍ ከሌሎች አገራት ጋር ሲነጻጸር በጣም ዝቅተኛ ነው፡፡ ይህም በመንግስት ድጎማ መሆኑን መረዳት ይገባል፡፡ ተጠቃሚው ይህን የመንግስት ድጎማ በቅንነት ሊመለከተውና

የሚጓዝበት ርቀት የሚጠይቀውን ትክክለኛ ታሪፍ ከፍሎ መጓዝ ይገባዋል።” ሲሉም አሳስበዋል።

ይህንኑ የኃላፊውን አስተያየት የሚጋራው ደግሞ የኮርፖሬሽኑ ባልደረባና በጉዞ ወቅት ቲኬት ተቆጣጣሪ የሆነው ወጣት (ስሙ እንዲገለፅ ያልፈለገ) ሲሆን ሳይቆርጡ እየገቡና ራሳቸው ወንጀለኛ ሆነው ሳለ ቲኬት ሲጠየቁ የሚሳደቡ ብዙዎች ናቸው። ከፖሊስ አቅም በላይ ለመሆን የሚያደርጉት ሙከራ ቀላል አይደለም፤ ለህግ ያለመገዛቱ ነገር፣ ከነሱም ብሶ ግልምጫቸው የሚገርም ነው። እንደ ተቆጣጣሪው አስተያየት “ችግሩ በዚሁ ከቀጠለ በጣም አደገኛና አሳሳቢ ነው።”

በውይይት መድረኩ ላይ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ባልደረባ እንደተናገሩት፤ ከሆነ ችግሩ አሳሳቢ ብቻ ሳይሆን አጥፊም ስለሆነ ባጭሩ ሊቀጭ ይገባዋል። ተወካዩ እንደዘረዘሩት በርካታ ጊዜያት ባቡር ተሳፋሪ ወንጀለኞችን መያዝ የተቻለ ሲሆን በፍተሻውም 32 ጥይቶች፣ 300 ሽጉጦች፣ ጩቤ፣ ሺሻ፣ ሀሺሽ ወዘተ በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ኮርፖሬሽንም ችግሩን ለመቆጣጠር ጥረቶችን እያደረገ ይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ሰሞኑን 240 የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሰጪ ወጣቶች በቁጥጥር ስራው ላይ ማሰማራቱን ከኮርፖሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

በአውሮፕላን ...

ስርዓተ ቀብሩ በሁለት የመካነ-መቃብር ስፍራዎች የተከናወነ ሲሆን የ16ቱ አስከሬን በቅድስት ስላሴ ካቴድራል፤ የአንዱ ደግሞ ኮልፌ በሚገኘው የእስላም መካነ-መቃብር ተፈፅሟል።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ በስርዓተ-ቀብሩ ላይ ተገኝተው ቃለ-ቡራኬ ያሰሙ ሲሆን የሌሎች ሃይማኖት አባቶችም ተገኝተው የኀዘኑ ተካፋይ ሆነዋል።

በቀብር ስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙ የኀዘኑ ተካፋዮች እንደገለጹት የደረሰው አደጋ እጅግ መራርና አስከፊ ከመሆኑም በላይ የሟቾች ሁኔታም እጅግ አሳዛኝ ነው። በስርዓተ-ቀብሩ ላይ ያገኘነውና ያነጋገርነው ወጣት ብሩክ እዝራ እንደገለጸልን ኀዘኑ የቤተሰቦቻቸውና የዘመድ አዝማድ ብቻ ሳይሆን የሀገር ኀዘን ነው። «እኔ እዚህ የመጣሁት ዘመድ ወይም የማውቀው ሰው ሞቶብኝ አይደለም። ሁኔታው እጅግ አሳዛኝ እና የሀገር ኀዘን ስለሆነ ነው፣ እግዚአብሄር ነብሳቸውን ይማር» ሲልም ተናግሯል።

በአደጋው 18 ኢትዮጵያዊያንን ጨምሮ 157 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉ ይታወሳል።

በጋዜጣው ሪፖርተር አዲስ አበባ፡- መጋቢት 7 ቀን 2011 ዓ.ም ምሽት ከአማራና

ሌሎች ክልሎች በተለያዩ ምክንያቶች የተፈናቀሉ ዜጎችን በዘላቂነት ለማቋቋም በሸራተን አዲስ ሆቴል በተዘጋጀው የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ላይ የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን እንደገለጹት መደጋገፍ እና መረዳዳት ባህሉ በሆነ ማህበረሰብ ውስጥ የተፈናቀሉ ወገኖችን በዘላቂነት ለማቋቋም ሁሉም ዳር እስከ ዳር ሊረባረብ ይገባል፡፡

የፕሮግራሙ ዓላማ በሰው ሠራሽና በተፈጥሮ ምክንያት በአማራ ክልል ውስጥ ከቀያቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች የሁሉንም አቅም አስተባብሮ በዘላቂነት መልሶ ለማቋቋም የሚያስችል ድጋፍ ማሰባሰብ ነው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህም ላይ በመመስረት በተለያዩ አካባቢዎች የተፈናቀሉ ወገኖችን በዘላቂነት ለማቋቋም ኃላፊነትና አደራም ለመሸከም ነው ብለዋል፡፡

ስልጣኔ በገራው አስተሳሰብ እንኳን የሰው ልጅ ይቅርና በብዝሃ ህይወት ውስጥ የሚታቀፉ ፍጡራን ሳይቀር በገዛ ፈቃዳቸው ከቦታ ወደ ቦታ የሚዘዋወሩበት ሁነት እንጂ በግዳጅ የመኖርያ ቀያቸውን ለቀው የሚፈናቀሉበት ሂደት የለም ያሉት አቶ ደመቀ የኋላ ገመናችንም ጥቁር እንግዳን የማክበር ባህል የነበረን ህዝቦች እንደነበርን አንስተዋል፡፡ ዛሬ ግን ዕርስ በርስ የመደጋገፍ ባህላችን ውሉ ላልቶ አንዳችን ላንዳችን የመከባበር ባህላችን ደፍርሶ እንዲሁም የሰብዓዊነት ሚዛን የውሃ ልኩ ተጥሶ በየጊዜው ቁጥሩ የሚጨምር የተፈናቃይ ወገኖቻችንን ስናስብ እኛው አፈናቃይ፤ እኛው ተፈናቃይ መሆናችን አሳዛኝ ነው ብለዋል፡፡

እነዚህ ዛሬ ዕርዳታ የምናሰባስብላቸው ወገኖቻችን ይህንን ሁሉ መከራ የሚቀበሉበት በራሳችን ድክመትና ጉድለት ብቻ ነው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉዳዩ ህዝብን ማዕከል አድርጎ በአብሮነትና በአስተዋይነት ቢያዝ ኖሮ እነዚህ ዜጎች እንደቀድሟቸው ትርፍ አምራች እንጂ ዕርዳታ ጠያቂዎች አይሆኑም ነበር ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት እኛ ዛሬ ገንዘባችንን የምናሰባስበው ወገናችንን ይበልጥ ለማበልፀግ፣ ስርዓታችንን ይበልጥ ለማዘመን ፤የተሻለ ህይወትና ምቹ የመኖርያ አካባቢ እንዲኖራቸው፤ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን እንዲጠቀሙና ሀብት እንዲካፈሉ ለማድረግ መሆን ሲገባው አለመታደል ሆኖ በተግባር የምናየው ድህነትን ለመካፈል ሆኗል፡፡ በአሁኑ ሰዓት ወደ ከፍታ የሚወስዱ ብዙ ፀጋዎችና ዕድሎች እያሉ ወገን በወገኑ ተፈናቅሎ ወገን ለወገኑ ሲለምንለት ማየት ለአፈናቃዩም፤ ለተፈናቃዩም ትልቅ የልብ ስብራት ነው፡፡

ሌላው ዓለም ስልጣኔ ላይ ልቆ ለመሰልጠን በሚተጋበት ዘመን እና ድህነትን እንደፀጋ እየተካፈልን ዕድሜ ማራዘም አጥፍቶ እስኪያጠፋን መጠበቅም፣ መፍቀድም የለብንም ብለዋል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ። ሰዎች ነገን የተሻለ ለማድረግ ካልጣሩ፣ ኃላፊነት የማይሰማቸውም ከሆኑ፣ የስልጣኔን ብርሃንም ካላዩ፣ የራሳቸው ፍላጎት ተገዢ ይሆናሉም ብለዋል፡፡

በአሁኑ ሰዓት የተፈጠረውን የለውጥና የነፃነት ድባብ በአግባቡ ልንጠብቀው፣ በተሟላ ሁኔታ በተግባር ልንተረጉመውና የተያዘውን እጅግ የሚያኮራና ተስፋ ሰጪ የለውጥ ጉዞ ወደፊት የማራመድና የመዘመን አጀንዳችንን ጠበቅ አድርገን መያዝና መጓዝ ይጠበቅብናል ያሉት አቶ ደመቀ ለዚህም ሁሉንም አቅማችንን ወደ ልማትና ኢንቨስትመንት ማዞር አለብን ብለዋል፡፡

በአገራችን በተለያዩ ጊዜያትና በተለያዩ አካባቢዎች አስከፊ ሰው ሠራሽና ተፈጥሯዊ አደጋዎች ሲያጋጥሙ አስቸጋሪና ፈታኝ ሁኔታዎችን ተቋቁመን የፈታንበትን መንገድ በማጠናከር በሁሉም አካባቢዎች የተፈናቀሉ ወገኖቻችንን ወደ ዘላቂ ህይወታቸውና አምራች ቁመናቸው እንዲመለሱ መረባረብ ይጠበቅብናል ሲሉም አሳስብዋል፡፡

የአማራ ክልል ርስሰ መስተዳደር ዶክተር አምባቸው መኮንን በበኩላቸው አገራችን ኢትዮጵያ የቀደምት ስልጣኔ ባለቤት የሆነችና አብሮ መኖርና መቻቻልን ለዓለም በተግባር ያስተማረች፤ የደማቅ ታሪክና የረቂቅ ጥበብ ባለቤት፣ የነፃነት ፋና ወጊ የጥቁር ህዝቦች ኩራት ብትሆንም የርስ በርስ አለመግባባትና ግጭት በተለያዩ አገራችን ክፍሎች እየተከሰቱ ህዝባችንን ለሞትና እንግልት እየዳረጉ ይገኛሉ ብለዋል፡፡

በተለይ የዜጎች መፈናቀል ዘርንና ማንነትን መሰረት ያደረገ መሆኑ ለሃገሪቱ አደገኛ ቁርሾ፣ ለዜጎቿ የማያቋርጥ ስቃይን የሚያስከትልና የመሪዎችን ድክመት የሚያመላክት በመሆኑ ከወዲሁ የማያዳግም ዕርምጃ መውሰድን ይጠይቃል ያሉት ዶክተር አምባቸው መግባባት፣ መከባበር እና ፍቅር ካለ አገራችን ለኛ ብቻ ሳትሆን ለሌሎችም የምትበቃ ስለሆነች የአገራችን ህዝቦችም እንደዚህ ዓይነት ችግሮች በቀጣይ እንዳይደገሙ ለማድረግ ተንኳሾችና አፈናቃዮችን በማጋለጥ ለዘላቂ መፍትሔው መሥራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡

በአማራ ክልል ውስጥ የሚገኙ የሌሎች ብሄር ተወላጆች ሙሉ መብታቸው ተጠብቆና መብታቸው ተከብሮ ከአማራ ወንድሞቻቸውና እህቶቻቸው ጋር በተለመደው መከባበርና መተሳሰብ አብሮ የመኖር ባህል ተጠብቆ እንዲኖር የክልላችን መንግሥት በቁርጠኝነት ይሠራልም ሲሉም ተናግረዋል፡፡

ዶክተር አምባቸው እንደገለጹት አገራዊ መግባባትን ለመፍጠር በርካታ ጥረቶች እየተደረጉ ቢሆንም ከምንም በላይ የዜጎች በተደጋጋሚ መፈናቀል፣ ከሞቀ ቤታቸውና ንብረታቸው እየተለዩ ለእንግልት መዳረግ፣ አምራች እጆቻቸው ለልመና መዘርጋታቸው፣ እጅግ አሰዛኝ ሁኔታን እየፈጠረ ነው፡፡

እንደ ዶክተር አምባቸው ገለጻ እንደሃገር በፍቅርና በመቻቻል ከመኖር አልፎ ተጋብቶና ተዛምዶ በመኖር የሚታወቀው የኢትዮጵያ ህዝብ ወደ መጠራጠርና አለመተማመን እንዲያመራ የሚገፋፉ ኃላፊነት የጎደላቸው ትንኮሳዎችና ፀብ አጫሪ ሰበካዎች ይደመጣሉ። በተግባርም ግጭት ሲከሰት፣ ዜጎች ሲፈናቀሉ፣ ንብረት ሲወድምና ክቡር የሰው ልጅ ህይወት ሲቀጠፍ ማየት እየተለመደ መጥቷል፡፡ ይህ በፍጥነት ካልቆመና የመፈናቀል ፋይል ካልተዘጋ ለውጡን ማስቀጠልና ተስፋ ማለምለም አስቸጋሪ ይሆናል፡፡ በመሆኑም ይህ አጥፊ የመገፋፋት ምዕራፍ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ተዘግቶ ዜጎች በሰላም እዲኖሩ ማስቻል ይገባል፡፡

በዕለቱ በተካሄደው የገቢ ማሰባሰብ ሂደትም በአጠቃላይ ከ610 ሚሊየን ብር በላይ የተሰበሰበ ሲሆን ድጋፉ በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ከፕሮግራሙ አዘጋጆች ለማወቅ ተችሏል፡፡

የተፈናቀሉ ወገኖቻችንን መልሶ ለማቋቋም እያንዳንዱ ዜጋ እንዲረባረብ ጥሪ ቀረበ

ከ1ኛው ገጽ የዞረ

Page 3: 78ኛ ዓመት ቁጥር 189 ሰኞ መጋቢት 9 ቀን 2011 ዓ.ም ያንዱ ዋጋ 5.75 …ማድረግ ላይ የመምህራን የሙያ ስብጥርና ብቃት ውስንነት፣

ውቤ ከልደታ

አሁን አሁን የአገራችን የፖለቲካ አጀንዳ ግራ አጋቢ ሆኖብኛል። እኛ ኢትዮጵያውያን ፖለቲካ የእለት እንጀራችን እስከሚመስል ድረስ በተለያዩ አሉባልታዎችና የፖለቲካ ወሬዎች ተጠምደን ጊዜያችንን ስናባክን መዋል የየእለት ውሏችን ከሆነ ሰነባብቷል። ለዘመናት የዘለቁት ጠንካራ ማህበራዊ እሴቶቻችን እየተሸረሸሩ ርስ በርስ መጠራጠርና መከፋፈል የየእለት ጉዳያችን እየሆነ ነው። ለጋራ እሴቶቻችን ከምንሰጠው ዋጋ በላይም ግለኝነትና አካባቢያዊ ማንነት ትልቁን ስፍራ መያዝ ጀምሯል። ከ”እኛነት” ይልቅ “እኔነት” አይሎብናል። “ትብብር” የሚባለው ጠቃሚ ጉዳይ የሚታየን የውጭ ጠላት ሲመጣ ብቻ ነው።

በዚህ ሂደት ውስጥ ደግሞ ማህበራዊ ሚዲያው ትልቁን ስፍራ እየያዘ ነው። አንዳንድ ጊዜ ሆን ተብሎ የብጥብጥ አጀንዳዎች እየተፈጠሩ በነዚህ ማህበራዊ ሚዲያዎች ይረጫሉ፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ ከትንሽ እውነታ ተነስተው ነገሮች አቅጣጫውንና መልካቸውን እንዲቀይሩ ተደርገው ህዝብን ከህዝብ ለማጋጨት በሚያስችል መልኩ ይቀረፃሉ። ፖለቲካው የኢኮኖሚ፣ ኢኮኖሚው የማህበራዊ፣ ማህበራዊው የፖለቲካ ወዘተ ጥያቄ ሆኖ ይቀርባል። ሁሉም ግን ህዝብን መጥቀምን ማዕከል ያደረጉ አይደሉም። በህዝብ ስም እየማሉና እየተገዘቱ ከጀርባ ሆነው ህዝብን ለማበጣበጥ የሚፈልጉ ሃይሎች የሚያሴሩት ደባ ነው። የሚያሳዝነው ደግሞ እንዲህ አይነት አጀንዳዎችን በመፍጠር በአገሪቱ አለመረጋጋት እንዲፈጠር የሚያደርጉት አንዳንድ ሃይሎች ራሳቸውንና ቤተሰባቸውን በምቹ ስፍራ ላይ አስቀምጠው በደሃው ህዝብ ህይወት የሚቀልዱ መሆናቸው ነው። አንዳንዶቹም ችግሩ አፍጦ የመጣ እለት “ህዝብ ሆይ የራስህን እዳ ራስህ ተወጣው” ብለው እነሱ ከተረጋጋው የአውሮፓ ወይም የአሜሪካ ሰላማዊ ስፍራ ተመቻችተው ለመቀመጥ የተዘጋጁ ናቸው።

ነገር ግን በየጊዜው የሚለዋወጡትና በትክክል በማን እንደተዘጋጁ የማይታወቁት ባለቤት አልባዎቹ አጀንዳዎች ፈር እንዲይዙ መንግስት ተገቢውን እርምጃ መውሰድ አለበት። አንድ አጀንዳ ተፈጥሮ ጉዳት ካስከተለ በኋላ መልሶ ረገበ ሲባል ሌላ አጀንዳ ይቀረጻል። አንዱ ችግር ተፈታ ሲባል ሌላ ይከተላል። ለምሳሌ ባለፉት 11 ወራት የተፈጠሩትን አጀንዳዎች በጥቂቱ እንቃኛቸው። በለውጡ ሰሞን የተፈጠረው አጀንዳ አንድን ብሄር ከሌላ ብሄር የማጋጨት አጀንዳ ነበር። በዚህም በሱማሌና ኦሮሚያ፣ በጌዲዮና ጉጂ፣ በአማራና ትግራይ እንዲሁም በወላይታና ሲዳማ ህዝቦች መካከል ልዩነቶችን በመፍጠርና በማጋጨት አገርን የማበጣበጥ ስራ ተሰርቷል። ከዚያ በኋላ ደግሞ

መጋቢት 9 ቀን 2011 ዓ.ም 3

ይህ አምድ በተለያዩ ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ዜጎች ነፃ አስተያየታቸውን የሚሰጡበት ነው፡፡

በዓምዱ ላይ የሚወጡ ጽሁፎች የዝግጅት ክፍሉን አቋም አያመለክቱም፡፡

ርዕሰ አንቀፅ

አዲስ ዘመን

አጀንዳ

በ1933 ዓመተ ምህረት ተቋቋመ በየዕለቱ እየታተመ የሚወጣ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ መጋቢት 9 ቀን 2011 ዓ.ም

አድራሻ:- አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 የቤት ቁጥር 001 የፖ.ሣ.ቁ፡- 30145

ዋና አዘጋጅ - ፍቃዱ ሞላ ኢ ሜይል - [email protected] አድራሻ - የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ - 13 የቤት ቁጥር - B402 H11 ስልክ ቁጥር - 011-126-42-40 የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ ስልክ - 011-126-42-22 የገበያ ልማትና ፕሮሞሽን ዘርፍ የኢሜይል አድራሻ [email protected] ስልክ - 011- 156-98-73 ፋክስ - 011- 156-98-62 የማስታወቂያ መቀበያ ክፍል ስልክ - 011- 156-98-65 የማስታወቂያ ሽያጭ ማስተባበሪያ ስልክ - 011-1-26-43-39 ማከፋፈያ ስልክ - 011- 157-02-70

የዕለቱ ምክትል ዋና አዘጋጅ፡- ወርቁ ማሩስልክ ቁጥር- 011-126-43-19 አዘጋጆች፡- ግርማ መንግስቴ ወንድወሰን ሽመልስ መርድ ክፍሉ ፍዮሪ ተወልደ ብርሃን ፈይሳ

website www. press.et email. [email protected]

Facebook Ethiopian Press Agency የዝግጅት ክፍል ፋክስ- 251-011-1-56-98-62

በፓርቲ ከመነገድ ወጥተን ለህዝብ ጥቅም እንስራ

አዲሱ የግጭት አጀንዳ

በአገራችን የፖለቲካ ፓርቲዎች ግሽበት ይታያል፡፡ ሰሞኑን የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ አሰራር የቃልኪዳን ሰነድ የተፈራረሙ ፓርቲዎች ቁጥር 107 መድረሱን ስንመለከት እውን ይህ ሁሉ ፓርቲ በትክክል ለህዝብ ለመስራት የተፈጠረ ነው የሚል ጥያቄን ማጫሩ አይቀርም፡፡ በሌላ በኩል የፓርቲ ንግድ ተጀመረ የሚል ጥያቄንም ያጭራል፡፡ ይህ ካልሆነ ስንት አይነት አስተሳሰብ ኖሮ ነው እነዚህ ሁሉ ፓርቲዎች ልዩነትን የሚያራምዱት? ወይስ ፓርቲ ለመመስረት ልዩነት የግድ አይደለም? የሚል ሙግት ያስነሳል፡፡

በርግጥ በኛ አገር አብዛኞቹ ፓርቲዎች ብሄራዊ ማንነት ላይ ያተኮሩ ናቸው፡፡ ነገር ግን እያንዳንዱ ብሄር እንኳን ፓርቲ ቢኖረው አገራችን ከ80 በላይ ብሄር ስለሌላት እነዚህ ሁሉ ፓርቲዎችን መመስረት አያስፈልግም፡፡ ህብረ ብሄራዊ ፓርቲ እንመስርት ቢባል ደግሞ ይህንን ያህል የተዘበራረቀ ሃሳብ መፍጠር አይቻልም፡፡ ታዲያ ፓርቲዎቻችን ከየት መጡ? እውን ፓርቲዎቻችን የተመሰረቱት ህብረተሰቡ የሚያነሳቸውን ጥያቄዎች መሰረት አድርገው ነው?

በሌላ በኩል የፖለቲካ ፓርቲዎቹ ሃሳብ ላይ የተመሰረተ ልዩነት ያራምዳሉ ወይ ብሎ ለሚጠይቅም በቂ መልስ ላያገኝ ይችላል፡፡ ምክንያቱም በዓለም ላይ ያለው የርዕዮተ ዓለም ልዩነት ከአራት ግፋ ቢል ደግሞ ከአምስት የዘለለ አይደለም፡፡ እነዚህ አስተሳሰቦች የዜጎችን መሰረታዊ ጥያቄዎች የመመለስ ብቃት እንዳላቸውም ሳይንስ ያረጋግጣል፡፡ ታዲያ ይህ የአገራችን የፖለቲካ ፓርቲዎች ግሽበት እንዴት ተከሰተ ብለን ስንጠይቅ ፓርቲ ስንመሰርት በእውቀት ላይ ሳይሆን በስሜት ላይ ተመስርተን እንደሆነ ያመላክታል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከሁለት ወራት በፊት ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በተወያዩበት ወቅት በአገራችን እውነተኛ ዴሞክራሲን ለማረጋገጥ ፓርቲዎች ውህደት ፈጥረው ቢጠናከሩ የተሻለ እንደሚሆን መምከራቸው የሚታወስ ነው፡፡ ይህ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሰጡት አስተያየት ጠንካራ ፓርቲ ተፈጥሮ በውድድሩ ለህዝብ የተሻለ አማራጭ ያለው ፓርቲ ይፈጠር የሚል ትርጉም ያለው በመሆኑ ሊደገፍና ሊበረታታ የሚገባው ሃሳብ ነው፡፡ ፓርቲዎችም በዚህ ደረጃ ተጠናክሮ ለመውጣት አጋጣሚውን ሊጠቀሙበት ይገባል፡፡

ነገር ግን አሁን የሚታየው ከዚህ የተለየ ነው፡፡ የተበጣጠሱና የተበታተነ ሃሳብ ይዘው የተሰለፉ በርካታ ፓርቲዎች ናቸው ያሉት፡፡ ይህ ደግሞ በአንድ በኩል ለህዝብ የሚጠቅም አማራጭ ሃሳብ የያዘ የፖለቲካ ፓርቲን ለመለየት አዳጋች ያደርገዋል፤ በሌላ በኩል ደግሞ የአገሪቱ ሃብት አላግባብ እንዲባክንና ለአገር የሚጠቅሙ ፓርቲዎች ተገቢውን ትኩረት እንዳያገኙ ያደርጋል፡፡

በሌላ በኩል ለስም ብቻ የሚንቀሳቀሱ አንዳንድ ፓርቲዎች ለአገራዊ እድገትና

በጅግጅጋ የሃይማኖት ግጭት ለመቀስቀስ ከፍተኛ ጥረት ተደርጓል፤ ይህ ትንሽ ቆይቶ በጎንደርም ተደግሟል። በአጠቃላይ በነዚህ ወቅታዊ ግጭቶች በሚሊየን የሚቆጠሩ ዜጎች ተፈናቅለዋል፤ በሺዎች የሚቆጠሩትም ህይወታቸውን አጥተዋል። በርካታ ማህበራዊ ቀውሶችም ተፈጥረዋል።

ከሰሞኑ አዲስ የተቀረጸልን አጀንዳ ደግሞ “አዲስ አበባ የማን ናት?” የሚል ነው። ይህ ጥያቄ አከራካሪ አይመስለኝም። አዲስ አበባ የማን ናት የሚለው ጥያቄ ኢትዮጵያ የማን ናት፣ መቀሌ የማን ናት፣ ባርዳር የማን ናት፣ አዳማ የማን ናት፣ ሃዋሳ የማን ናት፣ ወዘተ ከሚለው ጥያቄ የተለየ አይመስለኝም። ምክንያቱም ሁሉም የኛው የኢትዮጵያውያን ናቸውና። ለመሆኑ በህገመንግስቱም ቢሆን እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በሁሉም አካባቢ ተዘዋውሮ የመስራትም ሆነ ሃብት የማፍራት መብቱ የተጠበቀ አይደለምን? አንድ አማራ በኦሮሚያ ክልል፣ አንድ ትግራይ በአማራ ክልል፣ ወላይታው በትግራይ ክልል፣ ወዘተ የመኖር መብትስ የለውም? በኔ እምነትም ሆነ በህገ መንግስቱ መሰረት እነዚህ መብቶች የተከበሩ ናቸው። ታዲያ ጥያቄው ከምን የመነጨ ነው? ከተማዋን ለማስተዳደር ነው? ከማስተዳደር በስተጀርባስ ምን አለ?

እዚህ ላይ ግን ልብ ሊባል የሚገባው መሰረታዊ ጉዳይ አለ። አዲስ አበባ በኦሮሚያ ክልል መሀል ውስጥ የምትገኝ የአገሪቱ ዋና ከተማ ናት። በሁሉም አቅጣጫ ወጣ ቢባል የምናገኘው ኦሮሚያን ነው። በየእለቱም በርካታ የኦሮሚያ ነዋሪዎች አዲስ አበባ ውለው ይመለሳሉ። በተቃራኒውም ኦሮሚያ ውሎ የሚገባው የአዲስ አበባ ነዋሪ ቁጥር ቀላል አይደለም። ይህ ደግሞ በኦሮሚያ ክልልና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መካከል ያለውን ጥብቅ ትስስር ያሳያል። ይህ ደግሞ የቋንቋ ጥያቄ ሊያስነሳ ይችላል። በአዲስ አበባ ከአማርኛ ቋንቋ በተጨማሪ አፋን ኦሮሞ የስራ ቋንቋ እንዲሆን ምክንያት ሊሆን ይችላል። ጥያቄው ከዚህ አንጻር ከታየ ደግሞ መልስ ማግኘት ያለበት የመብት ጥያቄ በመሆኑ ጤናማ ነው።

ለመሆኑ አፋን ኦሮሞ ተጨማሪ የስራ ቋንቋ እንዳይሆን ምን የሚያግደው ነገር ይኖራል? በዓለም ላይ ከአንድ በላይ የስራ ቋንቋ ያላቸው አገራት ቁጥር ቀላል አይደለምና ምኑ ላይ ነው የከበደን። በሌላ በኩል ጥያቄ የምናቀርበውም ቢሆን የእኔነትን የምንገልፅበት መንገድ መስተካከል ያለበት ይመስለኛል።

በዓለም ላይ 57 አገራት ከአንድ በላይ የስራ ቋንቋ እንደሚጠቀሙ መረጃዎች ያሳያሉ። ደቡብ አፍሪካ ደግሞ ከዚህ አንጻር ትልቅ ምሳሌ መሆን ትችላለች። ምክንያቱም በደቡብ አፍሪካ 11 የሚሆኑ ቋንቋዎች በመንግስት ተቋማት አገልግሎት ላይ እንደሚውሉ መረጃዎች ይጠቁማሉ። ከዚህ በተጨማሪ 41 አገራት ሁለት ቋንቋ፣ 12 አገራት ሶስት ቋንቋ እንዲሁም 3 አገራት አራት ቋንቋዎችን በስራ ቋንቋነት ይጠቀማሉ።

በጎረቤት አገራት ያለውን ሁኔታ ስንመለከት ደግሞ ጅቡቲ፣ኤርትራ፣ ሱዳንና ሶማሊያ ሁለት ሁለት ቋንቋዎችን በይፋ በስራ ቋንቋነት እንደሚጠቁሙ መረጃዎቹ ያሳያሉ።

እኛ ኢትዮጵያውያን እኮ የውጭ አገር ቋንቋ እየተማርን እንገኛለን። በርካታ የባለስልጣንና የባለሃብት ልጆች እኮ ከአማርኛ ቋንቋ ይልቅ እንግሊዚኛ ቋንቋ ይቀላቸዋል። ይህ ለምን ሆነ ስንል ለእንግሊዝኛውና ለአማርኛው የምንሰጠው ቦታ መለያየት ነው። በሁሉም አካባቢ ያለው ቦታ የኢትዮጵያ መሆኑን መረዳት ተገቢ ነው። ከዚህ ውጭ ግን ቦታን ለአንድ ማህበረሰብ ብቻ መስጠት የፖለቲካ ቁማር ካልሆነ በስተቀር ትርጉሙ አይገባኝም።

ሌላው የሰሞኑ የውዝግብ ምንጭ ደግሞ በቅርቡ የወጣው የጋራ መኖሪያ ቤቶች እጣ እንደነበር እናስታውሳለን። በርግጥ የዚህ ችግር ዋነኛ ተጠያቂዎች ቀደም ሲል የነበሩ አመራሮች መሆናቸውን መገመት አያዳግትም። ምክንያቱም ፕሮግራሙ በራሱ ከተመሰረተበት ዓላማ ውጪ የተካሄደ ነውና። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መልሶ ማልማት በሚል የጀመረው ፕሮግራም አላማ አንድም የከተማዋን ገጽታ ሊለውጥ የሚችል ግንባታ ማካሄድ ሲሆን በሌላ በኩል ለነዋሪዎቹ ምቹ የመኖሪያ ስፍራን መፍጠር ነበር። በዚህም መሰረት አዲስ አበባ ወደላይ እንጂ ወደጎን ማደግ የለባትም በሚል ተደጋጋሚ ስብከቶችን ከባለስልጣት ስንሰማ ኖረናል። ነገር ግን ከዚህ በዘለለ መልኩ አስተዳደሩ የከተማዋን ነዋሪዎች እያፈናቀለ ከከተማ ውጪ በሚገነባው የጋራ መኖሪያ ቤት ሲሰጥ ቆይቷል። ይህ ደግሞ አብዛኛው ነዋሪ ሲያማርር የቆየ ነው።

በርግጥ በመኖሪያ ቤት እጥረት እና በቤት ኪራይ የተማረረ ዜጋ በዚህ መልኩ ከከተማ ውጭም ቢሆን ሂድ ሲባል አልፈልግም የማለት ድፍረትም ሆነ መብት አልነበረውም። ይህ ማለት ግን ቀደም ሲል በዚህ መልኩ ከከተማ ውጪ ወደሚሰሩ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ሲገባ የነበረው በፍላጎቱ ነበር ለማለት አያስደፍርም። አብዛኞቹ ወጣቶች በዚያ መልኩ ከከተማ ውጪ በተገነቡ የመኖሪያ ቤቶች ከመግባት ይልቅ ከቤተሰቦቻቸው ተነጥለው በነበሩበት አካባቢ ቀርተዋል። አንዳንዱቹም የጎዳና ኑሮን መርጠዋል።

ነገር ግን አዲስ አበባ በአንድ በኩል በግብታዊነት በፈረሱ ሰፈሮች የባሰ የቆሸሸችበት ሁኔታ በስፋት ይስተዋላል። በሌላ በኩል ደግሞ በልማት ስም በርካታ ዜጎች ለዘመናት ከኖሩበትና ከተወለዱበት ስፍራ ተፈናቅለው ከከተማ ውጪ እንዲወጡ ተደርጓል። ነገር ግን የፈረሱ ሰፈሮችን ማልማት ሲቻል ለምን በዚህ መልኩ ከከተማ ወጥቶ ቤት መገንባት አስፈለገ የሚለው ጥያቄ ለአመታት ሳይመለስ የቆየ ነው።

በሌላ በኩል ደግሞ አንዳንዶቹ በተለይ በቅርቡ የተላለፉት የኮዬ ፈጬ የጋራ መኖሪያ ቤቶች

ከአስተዳደሩ ውጪ በሚገኝ የኦሮሚያ ክልል አካባቢ የተገነቡ ናቸው መባሉ አጠቃላይ የቤት ልማት ፕሮግራሙ ዓላማውን መሳቱን አመላካች ነው? በከተማዋ መልሶ መልማትን የሚፈልጉ በርካታ መንደሮች የቆሻሻ ክምር ሆነው እያለ ከከተማ ውጪ አርሶ አደሩን እያፈናቀሉ በዚያ ሁኔታ ሰፊ ግንባታ ማካሄድ ለሁሉም ያልጠቀመ ኪሳራ ነው።

ሰፊ ቦታን የሚሸፍኑትና ከተማዋን አቋርጠው የሚያልፉት የወንዝ ዳርቻዎቻችንም ቢለሙ ምን ያልህ የከተማዋን ውበት እንደሚጨምሩ መገመት አያዳግትም። በየመንደሩ በልማት ስም ፈርሰው መልሰው ያልተገነቡትና የሌባ መናኸሪያ የሆኑት መንደሮችም ቁጥራቸው ቀላል አይደለም። ታጥረው ለበርካታ አመታት የልማት ያለህ እያሉ የከረሙት ሰፈሮችና ቦታዎችም እንኳስ ለቤት አጥ ለሌላም የሚተርፉ ናቸው። ታዲያ ይህንን ትቶ ሌላ መሻት ምን ይሉታል። ጉዳዩ በእጁ ላይ ዳቦ ይዞ ሌላ ዳቦ ፍለጋ እንደሚሮጥ ህጻን አልጠግብ ባይነት ይመስለኛል።

በሌላ በኩል ደግሞ በዚያ አይነት ሁኔታ በርካታ ገንዘብና ጉልበት ፈሶባቸው የተገነቡ ቤቶች በቅርቡ ለቤት ፈላጊዎች ሲተላለፉ ይህ የኔ ቦታ ነውና በዚህ መልኩ መሰራቱ ትክክል አይደለም ብሎ ወደ ሙግት መግባቱም በራሱ ሌላ ችግር ነው። እጣው የደረሳቸው አካላት መንግስትን አምነው ለአመታት ከኑሯቸው ላይ ቀንሰው ሲቆጥቡ የነበሩ ዜጎች ናቸው። መንግስት ደግሞ ቆጥቡ እያለ ሲያበረታታ እንደነበር የሚታወቅ ነው።በሁለቱ ወገን ያለ መንግስት ደግሞ አንድ ነው።ከአንድ ፓርቲ የወጣ ነው።የኢህአዴግ አመራር ነው።ታዲያ ከዛሬ ነገ ቤት ይደርሰኛል እያሉ በተስፋ የኖሩ ዜጎችን ጭላንጭል ተስፋ ካሳዩ በኋላ መልሶ ተስፋ ማሳጣት ምን ይባላል? እነዚህ ዜጎችስ ኢትዮጵያውያን አይደሉምን? እነዚህ ዜጎች በየትም የአገሪቷ ክፍል ሃብት የማፍራትም ሆነ የመኖር መብትስ የላቸውምን?

በኔ እምነት የኮዬ ፈጬ ጉዳይ በዚህ መልኩ መነሳቱ የተሰራብን የጥፋት አጀንዳ ፍሬ እያፈራ መሆኑን ያመላክተኛል። በአንድ አገር ውስጥ እየኖርን ቦታና ወሰን እየለካን በዚህ መልኩ መነታረካችን የምን ውጤት እንደሆነም መገመት አያዳግትም። አዲስ አበባም ሆነ ኦሮሚያ የኢትዮጵያ አካላት ናቸው። በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚኖር ቤተሰብ የሌለው የአዲስ አበባ ነዋሪ አለ ማለት ይከብዳል። ባይኖርም ደግሞ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የኔ ነው ማለት ነውር አይደለም። ከኦሮሚያ አዲስ አበባ ለመኖር የማይመጣ አለ? ታዲያ አዲስ አበባ የጋራችን አይደለችም? የአዲስ አበባ መጎዳትስ የሁላችንም መጎዳት አይደለምን? አዲስ አበባ እኮ ዘር የላትም፤ እንኳንስ ኢትዮጵያዊ የሌላውም ዓለም ህዝብ የሚኖርባት የጋራ ከተማ ናት። ታዲያ በዚህ መልኩ የጋራችን የሆነን ቦታ እንዴት ነው ይህ አይገባችሁም እያልን ልዩነት

የምንፈጥረው። ለኔ አልገባኝም። ይህ ማለት ግን በአዲስ አበባ ዙሪያ ያሉ ኢትዮጵያውያን ይፈናቀሉ፣ እነሱ ተባረው ሌላው በአካባቢው ላይ ይኑር የሚል አመለካከት ይዤ እንዳልሆነ ልብ በሉልኝ።

አሁን ባለው ሁኔታ እውነት እንኳንስ የክልል ወሰንን ቀርቶ በኢትዮጵያና በጎረቤት አገራትስ መካከል በትክክል የሚታወቅ ወሰን ወይም ድንበር የታለ? ድንበሮቻችን በአንድ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ እንዳሉት “አርተፊሻል ድንበሮች” ናቸው። በክልሎች መካከል ያለው የአስተዳደር ወሰንም ተመሳሳይ ነው።

በጥቂቱ ወደ ኋላ መለስ ብለን በደርግ ዘመን የነበረውን የአገራችንን አስተዳደራዊ ወሰን ስንመለከት የአገራችን የክልል አወቃቀር በክፍለሃገር እንደነበር ይታወቃል። ይህ በሆነበት ሁኔታ አሁን በኢህአዴግ ዘመን ደግሞ ያለው ብሄራዊ ማንነትን መሰረት ያደረገው አደረጃጀት ነው። ነገር ግን ይህ ለአስተዳደር እና ለህዝቡ ፍትሃዊ አገልግሎት ለመስጠት ታስቦ ካልሆነ በስተቀር የባለቤትነት ጥያቄን ለማረጋገጥ አልነበረም። በዚህ ሁኔታ ይህ አካባቢ የኔ ነው። ያንተ አይደለም በሚል አተካራ ለመግጠም የሚያስችል ምን አይነት መነሻ ይኖረናል።

በርግጥ የፌዴራል ስርዓቱን በአግባቡ ከተጠቀምንበት ጠቃሚ መሆኑ እውን ነው። ምክንያቱም ዜጎች ማንነታቸውን አውቀው፣ በማንነታቸው ኮርተው ራሳቸውን ሲያከብሩ አገራቸውን ሊያከብሩ ይችላሉ። ይህ የሰው ልጅ የተፈጥሮ ባህርይ ነው። ሰው በቅድሚያ ራሱን መውደዱ፣ ከዚያም ቤተሰቡን፣ ቀጥሎም አካባቢውን እያለ አገር መውደድ ይከተላል። ራሱንም ሆነ ቤተሰቡን የማይወድ ሰው አገሩን ሊወድ አይችልምና። ፌዴራሊዝም ተመሳሳይ ገጽታ ያለው ይመስለኛል። ነገር ግን ፌዴራሊዝምን የተረዳንበትም ሆነ ተግባራዊ የምናደርግበት አካሄድ በተሳሳተ አቅጣጫ ከተመራ የሚያስከትለው ቀውስ ከባድ ነው።

ሰሞኑን የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ኢትዮጵያ መጥተው የላሊበላን ቅርስ ለማደስ ቃል ሲገቡ ስናይ የምንገኝበት ደረጃ ላይ ጥያቄ የምናነሳበት እንደሚሆን እገምታለሁ። አያቶቻችን የሰሩትን ግንብ ለማደስ እንኳ የማንችልበት ደረጃ ላይ የደረስነው ለምንድነው ብለን እንድናስብም ያስገድደናል። ከጥንቱ ስልጣኔ ልቀን መሄድ እንኳ ቢያቅተን የያዝነውን አስጠብቀን መቆየት ለምን ተሳነን ማለትን ይጠይቃል። አሁን የምንራኮተው በተሳሳተ አጀንዳ ውስጥ መሆኑን ግልፅ አድርጎም ያሳየናል። ዛሬ ከኛ የሚጠበቀው እንዴት ተባብረን እንደግ መሆን ሲገባው ለመነጣጠልና ለመናቆር፣ ያለችውንም ለማጥፋት ከሆነ ቀጣዩ ትውልድ የመኖር ህልውናው አደጋ ውስጥ ይወድቃልና ሁላችንም እናስብበት።

ለህዝቦች እድገት ትልቅ አስተዋፅኦ ሊያበረክቱ የሚችሉና ትክክለኛ የህዝብ ጥያቄን ይዘው የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎችንም ሞራልና ክብር ዝቅ የሚያደርግ ነው፡፡ በሚሊዮን የሚቆጠር የህዝብ ድጋፍ ያላቸውና ለህዝባቸው ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት ለአመታት የታገሉ ፓርቲዎች በየመንደሩ በጥቂት ደጋፊዎችና ቡድኖች ተፈጥረውና የጠራ አላማ ሳይኖራቸው እንታገላለን ከሚሉ የስም ፓርቲዎች ጋር እኩል በአንድ መድረክ መሰለፋቸውም የሞራል ጥያቄን ያስነሳል፡፡

ከዚህም ባሻገር ፓርቲን የገንዘብ ማግኛና መተዳደሪያ ያደረጉ አካላት መኖራቸው የፓርቲዎች ህልውና ላይ የራሱን አሉታዊ አሻራ ያሳርፋል፡፡ አንዳንድ ፓርቲዎች ለህዝብ ታግለው ለውጥ ከማምጣት ይልቅ ከመንግስትና ከጥቂት ደጋፊዎቻቸው በሚሰፈርላቸው ቀለብ ህልውናቸውን ለማቆየት ይጥራሉ፡፡ ይህ ደግሞ ለህዝብ ተገቢውን አስተዋፅኦ ከማድረግ ይልቅ አድርባይ እንዲሆኑና ለመንግስትና ድጎማ ለሚያደርግላቸው አካል ተገዢ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብ የሚፈልገው ሰላምና ብልፅግናን ነው፡፡ ህዝባችን ለዘመናት ወደኋላ ያስቀረውና በአለም ማህበረሰብ ዘንድ ጭምር መዘባበቻ ያደረገው ድህነትና ኋላቀርነት ተወግዶ እንደበለፀጉት አገራት የተሻለ ኑሮ መኖርን ይመኛል፡፡ ለዚህ ደግሞ አስተማማኝ ሰላምን የሚያረጋግጥለት፣ በእኩልነትና በፍትሃዊነት የሚያስተዳድረው፤ ለዚህም የተሻለ ፖሊሲና ስትራቴጂ ቀርጾ የሚሰራለት መሪን ይፈልጋል፡፡

ከዚህም ባሻገር ቀልጣፋና ፍትሃዊ አገልግሎት፣ ሁሉንም ያማከለ ፍትሃዊ አስተዳደር እና ከአድልዎ የፀዳ አስተዳደራዊ መንግስት እንዲኖር ይፈልጋል፡፡ ይህ ሲሆን ልማቱን ለማረጋገጥ ጠንክሮ ለመስራትም ሆነ ሰላሙን ለማስጠበቅ ወደ ኋላ አይልም፡፡ በአገራችን ነባራዊ ሁኔታም በቅርቡ ለመጣው ለውጥ የህዝቡ አስተዋፅኦ ከዚህ የመነጨ ነው፡፡

በመሆኑም አሁን ያሉት የፖለቲካ ፓርቲዎችም ሆኑ መሪዎቻቸው ደጋግመው ሊያስቡና ከፓርቲ ህልውና ይልቅ የሃገር ህልውናና እድገት ቅድሚያ ሊሰጠው እንደሚገባ መረዳት አለባቸው፡፡ ከሚመሩት ፓርቲ ይልቅ የአገር ህልውና እንደሚበልጥም ሊገነዘቡ ይገባል፡፡ አሁን እንደሚታየው አንዳንድ የፓርቲ አመራሮች የፓርቲ ቁጥር ሲያንስ ወይም ጥምረት ሲፈጠር የመሪነት ሚናዬን አጣለሁ ከሚል መንፈስ ወጥተው መሪም ሳይሆኑ ለአገራቸው ጠቃሚ ስራ መስራት እንደሚችሉ ሊገነዘቡ ይገባል፡፡ ለዚህ ደግሞ ፓርቲዎቻችን ከልዩነት ይልቅ በጋራ ጉዳዮች ላይ ትኩረት በመስጠት ለጋራ እድገትና ብልፅግና መንቀሳቀስ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ይህ ሲሆን ህዝቡም የሚበጀውን ለመለየት አይቸገርም፤ የአገር ሃብትም አይባክንም፤ የምንፈልገው እድገትም ይከተላል፡፡

Page 4: 78ኛ ዓመት ቁጥር 189 ሰኞ መጋቢት 9 ቀን 2011 ዓ.ም ያንዱ ዋጋ 5.75 …ማድረግ ላይ የመምህራን የሙያ ስብጥርና ብቃት ውስንነት፣

መዝናኛመገቢት 9 ቀን 2011 ዓም አዲስ ዘመን 5

በአጫሾች «ጫማ»የሚገርመው ደግሞ ይህንን እንዲያደርጉ ፈቃድ የሰጣቸው

የገዛ መምህራቸው መሆኑ ነው። እንዲያውም መምህሩ ስለ ሲጋራ በሚያስተምሩበት የትምህርት ክፍለ ጊዜ፤ ተማሪዎቹ ልዩነታቸውንና የጣዕማቸውን ለያይተው እንዲረዱላቸው በማሰብም ነው ለተማሪዎቻቸው ያቀረቡላቸውም ተብሏል። ነገር ግን ከተማሪዎቻቸው መካከልም የፈለጉት ሲያጨሱ ያልፈለጉት የሚያጨሱትን ይመለከቱ ነበር።

ነገሩ በመገናኛ ብዙሃን መነጋገሪያ ከሆነም በሁዋላ ዩኒቨርሲቲው፤ ትምህርቱ ለተማሪዎቹ አስፈላጊ መሆኑንና እንደ እነርሱ አባባል «የሲጋራ ቴክኖሎጂ»ን ለሚመለከተው የትምርት ክፍል እንደሚያግዛቸውም ነው የተገለጸው። ይህ ማለት ግን ተማሪዎቹ ሁሌም እያጨሱ ይማራሉ ማለት እንዳልሆነም ተጠቁሟል።

አንድ ተማሪ በበኩሉ «እያጨስን ሳይሆን ትምህርቱን በይበልጥ ለመረዳት ያህል ያደረግነው ምዘና ነው» ሲል ነገሩን ደግፎ አስተያየቱን ሰጥቷል። በርካቶች በበኩላቸው ተማሪዎቹን አደጋ ላይ የሚጥል ድርጊት ነው በማለት እየተቃወሙት ይገኛሉ። ዩኒቨርሲቲው በበኩሉ ዓላማው ትምህርቱን ግልጽ ለማድረግ ያህል መሆኑን እንዲሁም ተማሪዎቹ ከማጨሳቸው በፊት ስልጠና ተሰጥቷቸወ ያደረጉት መሆኑንም ነው ያስረዳው።

ሌሎች በበኩላቸው «የመዝጊያ ፈተናቸው ምን ሊሆን ይችላል፤ ማን በፍጥነት ያጨሳል የሚል ይሆን?» ሲሉም ተሳልቀውባቸዋል። አንዳንዶች ደግሞ «እነዚህ ተማሪዎች ማጨስ ቢፈልጉ እንኳን ከዚህ በሁዋላ ወደ ድብቅ ስፍራዎች መሄድ አይጠበቅባቸውም» ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

ይህ ዓይነቱ ግራ የሚያጋባ ትምህርት ትክክል መሆን አለመሆኑ የየግል አመለካከታችን ቢሆንም፤ ጥቅሙን ለማወቅ ግን እነርሱን መሆን ያስፈልጋል። እነርሱም ስለ ሲጋራ ዓይነቶችና የጣዕም ልዩነቶች ለማወቅ ሲሉ አይደል በአጫሾች «ጫማ» የተገኙት።

ብርሃን ፈይሳ

ኦዲቲ ሴንትራል ከሰሞኑ ካወጣው ዘገባ ጋር ያያዘው ፎቶ ያለተለመደ መሆን ጉዳዩን መነጋገሪያ አድርጎታል። ፎቶው በአንድ የመማሪያ ክፍል ውስጥ እያጨሱ የሚመሩ ተማሪዎችን ምስል የሚያሳይ ነው። ይህ አስደናቂ ጉዳይም በእግረ መንገድ የገባን ሰውም ቢሆን እንዲያነበው የሚገፋፋ ሲሆን፤ በማህበራዊ ድረገጾች ላይም ከፍተኛ መነጋገሪያነትን የፈጠረ ጉዳይ ሆኗል።

እርግጥ ነው አንድን ነገር በትክክል ለመረዳት ጉዳዩን ከስር መሰረቱ ማወቅ እንዲሁም ነገሩን መላበስ እንደሚገባ ይታመናል። በሩቅ ሆነው ያዩትን ቀርበውና የጉዳዩ ተዋናይ ሆነው ሲመለከቱትም የተሻለ መረዳትና ግልጽነትን ይፈጥራል። ትምህርት የንድፍና የተግባር ጥምር ውጤት የሆነውም ለዚህ ነው።

ነገር ግን በንድፍ ያሉትን ነገሮች ሁሉ ወደ ተግባር መቀየር የግድ ላይሆን ይችላል። ለምሳሌ ያህል ስለ ሞት ምንነትና ምክንያት በንድፍ የተማሩትን በተግባር ለማወቅ መሞት አይጠበቅም። ስለ ሲጋራ ለማስረዳት እያጨሱ መሆን አለበት የሚል አመለካከትም ተቀባይነት ያለው አይሆንም። ምክንያቱም ሲጋራ ለጤና ጎጂ እና ሱስ የሚያስይዝ ንጥረ ነገር ያለው በመሆኑ፤ እንዳይጠቀሙት የሚመከር ነዋ።

በፎቶው ላይ ምስላቸው የሚታዩት ተማሪዎች ግን ስለ ሲጋራ ዓይነቶች ለማወቅ ነው እያጨሱ የሚማሩት። ፎቶው የተገኘው ከቻይና ሲሆን፤ ዩናን በተባለ የእርሻ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የሚማሩ ተማሪዎችም ናቸው አጫሾቹ።

እዚህ የመማሪያ ክፍል የገባ ሰው እንደተለመደው መጽሐፍትንና ለትምህርት የሚያስፈልጋቸውን መሳሪያዎች ከተማሪዎቹ ጠረዼዛ ሊመለከት ይችላል። ክፍሉ ግን በጭስ ስለሚታፈን የመማሪያ ክፍል ስለመሆኑ አጠራጣሪ ነው። ተማሪዎቹ በእጃቸው ሲጋራቸውን እየሳቡ ነው ትምህርታቸውን የሚከታተሉት።

ፎቶ በአንበሳ ጊቢመርድ ክፍሉ

ድንገት እግር ከጣለኝ አንድ ስፍራ በተገኘሁበት፤ ከልጅነቴ ጀምሮ ስሰማው የኖርኩትንና አድጌም ትዝታው ያለቀቀኝን ዘፋኝ በአካል አገኘሁት። እጅግ ከመደሰቴ የተነሳ ዝለል ዝለል ነበር ያለኝ (እንደ ልጅነቴ)። ተማር ልጄ፣ አዲስ አበባ ቤቴ፣… የማደንቀው አቀንቃኝ አለማየሁ እሸቴ፤ የምወዳቸው ዘፈኖች ናቸው። ታዲያ የምወደውን ሰው ሳገኝ አጋጣሚውን ተጠቅሜ በትንሿ የእጅ ስልኬ ምስላችንን አስቀረሁ። ለዘመን ምስጋና ይድረሰውና የሚወዱትን፣ የሚያደንቁትን ሰውም ሆነ የትኛውንም ነገር ከስልካችን ማከማቸት አስችሎናል። አለማየሁ እሸቴን ልጅ እያለው አባቴ የሚዘፍንበት ቦታ ድረስ ወስዶኝ አይቸው ነበር። ግን ፎቶ ለመነሳት አልቻኩም፤ ምክንያቱም በጊዜው የፎቶ ካሜራ የሚገኘው ፎቶ ቤት አሊያም አንበሳ ግቢ ነበር። ገጠመኜ ልጅነቴን፤ ልጅነቴም ሌሎች ትውስታዎቼን አከታተለብኝ እኮ(ነገርን ነገር ያነሳዋል አይደል የሚባለው)። አንበሳ ግቢም ብዙ ትዝታዎች አሉኝ፤ እንዲያውም የሚበዙት የልጅነቴ ፎቶዎች እዚያ የተነሱ ናቸው (ከአንበሳ ጋር አለመሆኑ ግን ይታወቅልኝ)። የዚያኔ አብዛኛዎቹ ፎቶ አንሺዎች እዚያ ስለሚገኙ የመስክ ፎቶ ለመነሳት ወደ ስድስት ኪሎ መሄድ የግድ ነበር (ያውም በሳምንቱ ታጥቦ ለሚደርስ ፎቶ)። መቼም የዛሬ ልጆች ይሄንን ሲሰሙ ይደነቁ ይሆናል፤ ያው ካሜራ በእጃቸው ነዋ። ፎቶ ቤትም ቢሄዱ በደቂቃዎች ውስጥ ፎቷቸውን ከእጃቸው ማስገባት ይቻላል። በእኛ ጊዜ ግን አንድ ፎቶ ሳምንት ይፈጅበታል፤ አንዳንዴም ሲታጠብ ሊበላሽና ሊጠቁር ይችላል። እንዲያም ሲሆን አማራጭ የለም የሆነውን ከመቀበል በቀር። መቼም በእኔ ዕድሜ ያለ ሰው አንበሳ ግቢ ብዙ ትዝታ አይጠፋውም። ስድስት ኪሎ ከሚለው የአካባቢው መጠሪያ በላይም «አንበሳ ግቢ» ሚለው ስሙ በእኛ ዘንድ(በዘመኑ ልጆች ለማለት ነው) ይበልጥ ይታወቃል። ምክንያቱም ቅዳሜና ዕሁድ ለልደት ወይም ለሽርሽር ቤተሰብ አዘውትሮ የሚጓዘው ወደዚያው ነበር። የሐምሌ 19 እና ብሄረ ፅጌ መናፈሻም የወቅቱ መዝናኛዎች መሆናቸውን አልዘነጋሁም። በአንድ ልደቴን ፎቶ ለመነሳት ከቤተሰቦቼ ጋር ወደ አንበሳ ግቢ አቀናን። ፎቶ እንደ ቀልድ ስለማይገኝም ያሉንንና ፎቶ ብንነሳባቸው የምንላቸውን አዳዲስ ልብሶች በሻንጣ ይዘናል። አንበሳ ግቢ ስንደርስም ብዙ እንደኛ ከቤተሰቡ ጋር ፎቶ ለመነሳት በመጡ ሰዎች ተጨናንቋል። እኛም ፎቶ ለመነሳት የሚሆነንን ስፍራ ብንፈልግም የሰዉ መብዛት ሊያፈናፍነን ስላልቻለ

እስኪጨርሱ መጠባበቅ ያዝን። ከፊት ለፊታችን ያለው ፎቶ አንሺም የሚያነሳቸውን ሰዎች፤አንዴ አበባ እያስያዘ... አንዴ ጥድ ስር እየከተተ… ሲሻው ደግሞ ሳር ላይ እያንከባለለ ሲያነሳቸው ቆይቶ «ብርሃን ስለበዛበት ፊልሙ ተቃጠለ» የሚል ምላሽ ሰጥቶ ድጋሚ ለማንሳት ይዘጋጃል። በሌላ ጥግ ያለው ፎቶ አንሺ ደግሞ ልብሳቸውን እየቀያየሩ «እንዲህ አንሳን…ደግሞ እንደዚህ ሆነን...›› በሚሉ የአንድ ቤተሰብ አባላት ትዕዛዝ ተሰላችቷል። ተነሺዎቹ በያዙት ልብስ ሁሉ ለመነሳት ቆርጠው የመጡ በመሆናቸው የድካም ስሜትም አይታይባቸውም። የታከተው ፎቶ አንሺም የያዘው ፊልም መሙላቱን ሲነግራቸው የቤተሰቡ ንዴት እስከ መተናነቅ አድርሷቸው ነበር። እኛም በተራችን ፎቶ አንሺያችንን ይዘን ወደ ተለቀቀው ስፍራ አመራን። ፎቶ አንሺውም 30 ፎቶ ብቻ እንደሚያነሳንና በፍጥነት እንድንዘጋጅ ነገረን። ሁላችንም ቀድመን በየትኛው ልብስ እንነሳ በሚል ሃሳብ ውስጥ ገብተን ከሻንጣው አንዱን ስናነሳ ሌላውን ስንጥል ረጅም ጊዜ ፈጀን። እንደምንም ከመራረጥን በኋላ አንዳንዶቻችን ቆመን፤ ሌላኛዎቻችን ከቆሙት ስር በርከክ እያልን ለፎቶው ተዘጋጀን። ያው የድሮውን ካሜራ ታውቁት የለ፤ አንዴ «ብልጭ» ብሎ ምስሉን እስኪይዝ መንቀሳቀስ አይፈቀድም። አንድ ሁለት ፎቶዎች እንደተነሳን ግን አንድ ሰው «ልጆቹን እግራችሁ ላይ አስደግፋችሁ፣ አበባ አስይዛችው፣ ጥዱ አናት ላይ አስቀምጣች... ለምን አትነሱም» የሚል ሃሳብ ሰነዘረ። ይህንን የሰሙት እናትና አባቴም ምክሩን ተቀብለው ሲያቅፉን፤ እሽኮኮ ሲያደርጉን፣ ደግሞ ሌላ የሚመች ቦታ ፍለጋ በሚል ግቢውን በመዞር የደከምነው አይረሳኝም። ያኔ እኮ ፎቶ ለመነሳ ፕሮግራም ተይዞ፣ ልብስ ተሸክፎ፣ ቤተሰብ ተሰባስቦ፤ አንዳንዴም የቤት እንስሳ ተይዞ ነበር። አረንጓዴ የሆነ እና አበባ በብዛት የሚገኝነት የአትክልት ስፍራ ማግኘትም የግድ ይላል (እንደ አሁኑ እያቀናበረ በሌለንበት የሚያኖረን ቴክኖሎጂ አልነበረማ)። ከዚያማ በዕድሜ፣ በቁመት አሊያም እንደ ቤተሰቡ ሁኔታ አግድም በሰልፍ አሊያም ፊትና በኋላ ከፍና ዝቅ እያሉ መነሳት ነው። አሁንማ ሁሉም ተለውጧል፤ ወደ ፎቶ ቤት የሚኬደው መታጠብ ላለበት ፎቶ ሲሆን ብቻ ነው (በዚህ ምክንያት አልበም ከየቤቱ አልጠፋ ይሆን?)። ጊዜውም የ«የሰልፊ ስቲክ» ነው፤ ፎቶ ለመነሳት በእጃችን ላይ ያሉትን ስልኮች መጠቀም አሊያም በእንጨት መሳዩ መቀሰሪያ ራሳችንን እያየን ምስላችንን ማስቀረት ነው። በዚህ ወቅት አንበሳ ግቢ የሚኬደውም አንበሳ እና ሌሎች እንስሳቶችን ለመጎብኘት እንጂ በዋናነት ፎቶ ለመነሳት አለመሆኑን ሳስብ «አይ ጊዜ» ያሰኘኛል።

Page 5: 78ኛ ዓመት ቁጥር 189 ሰኞ መጋቢት 9 ቀን 2011 ዓ.ም ያንዱ ዋጋ 5.75 …ማድረግ ላይ የመምህራን የሙያ ስብጥርና ብቃት ውስንነት፣

መጋቢት 9 ቀን 2011 ዓ.ም አዲስ ዘመን 7 ዓለም አቀፍ

መርድ ክፍሉ

እአአ 2019 ጥር 23 ጁአን ጓኢዶ እራሱን የቬንዝዌላ ፕሬዚዳንት አድርጎ ከሾመ በኋላ በአገሪቱ መንግሥት መቀየር ቀላል ነው ብሎ አስቦ ነበር፡፡ እሱና የአሜሪካ መንግሥት የማዱሮን መንግሥትና ደጋፊዎቹን አቅልለው መገመታቸው ዋጋ አስከፍሏቸዋል፡፡ የቬንዝዌላ መከላከያ ኃይል በአገሪቱ ሊካሄድ የታሰበውን መፈንቅለ መንግሥትና በድንበር አካባቢ ሊገባ የነበረውን የዕርዳታ ምግብ ማገት እንቅስቃሴ ላይ የቀረበለትን የተሳትፎ ጥያቄ ሳይቀበል ቀርቷል፡፡ የአሜሪካው ምክትል ፕሬዚዳንት ማይክ ፔንስ እንደሚናገሩት ከሆነ ለጓኢዶ ሊደረግ የነበረው ወታደራዊ ድጋፍ ሊከሽፍ የቻለውና በአገሪቱ የተቃዋሚ ቡድኖች ቁጥር በመጨመር የየራሳቸው ነፃ መሬት እንዲያገኙ የማድረግ ሥራው ያልተሳካው በክልል መንግሥታት አለመተባበር ነው፡፡

በአሁን ወቅት ጓኢዶ ሊያደርገው ያሰበው መፈንቅለ መንግሥት ሳይሳካ ቀርቷል፡፡ ቬንዝዌላ በከባድ የኢኮኖሚ ችግር ውስጥ ትገኛለች። አሜሪካን የጣለችው ማእቀብ ሰላማዊ ዜጎች ላይ ከፍተኛ ጫና ፈጥሯል፡፡ ቀጣዮቹ ወራት ለማዱሮና ለደጋፊዎቹ ከባድ የሆኑ የጉዞ ቀናት እንደሚሆኑባቸው ይጠበቃል፡፡ በአገሪቱ የሚደረገው የጦር ጣልቃ ገብነት በየጊዜው እያደገ ሲሆን የፖለቲካ ስልጣንን በመቀራመት ለቀጣይ ምርጫ አማራጭ ለማምጣት ትንቅንቆች ይስተዋላሉ፡፡

አሁን የቀረው አንዱ አማራጭ ችግሩን ለመፍታት ዳግም ምርጫ ማካሄድ ነው። በተቃዋሚዎችና በመንግሥት በኩል ብዙ ድጋፎች ስላሉ ህዝቡ መምረጥ እንደሚችል እየተነገረ ይገኛል፡፡ ነገር ግን ቬንዝዌላውያን ለማዱሮ ድጋሚ ምርጫ ድምፃቸውን ከሰጡ ዓመት አልሞላቸውም፡፡ በዚህም አዲስ ምርጫ ማካሄድ ከባድ ችግር ሊፈጥር ይችላል፡፡ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የማዱሮን ድጋሚ ምርጫ የተቃወሙ ሲሆን ምክንያታቸውን ግን አልገለጸም፡፡

በአገሪቱ የሚገኙ ቀኝ ዘመሞች በድጋሚ ምርጫው ማዱሮ ሊያሸንፍ እንደሚችል የተናገሩ ሲሆን በምክንያትነት ያስቀመጡት ተቃዋሚ ፓርቲዎች በምርጫው እንደማይሳተፉ በማሳወቃቸው ነው፡፡ የተቃዋሚ ፓርቲ ዕጩዎች በወንጀል የተጠረጠሩ በመሆናቸው ከምርጫው ታግደዋል፡፡ የማዱሮ ደጋፊዎች የድጋሚ ምርጫውን ቢያደርጉ የሚያገኙትና የሚያጡትን ነገር ያዩት አይመስልም፡፡ ማዱሮም

በድጋሚ ቢመረጥ ደካማና አደገኛ ሁኔታ ላይ ያለ ፕሬዚዳንት ያደርገዋል፡፡ ነገር ግን የተቃዋሚ መሪ የሆነው ጓኢዶ በተወሰነ መልኩም ቢሆን ምርጫውን ለምን እንደፈለገው ግልጽ የሆነ ነገር የለም፡፡ ጓኢዶ ስልጣን ለመያዝ የሚጠቅሰው ህገመንግሥት ከጅምሩ ተቃውሞ የገጠመው ሲሆን ማዱሮ ስልጣን ላይ ለመቆየት ጥረት ቢያደርግም በህገ መንግሥቱ አዲስ ምርጫ በ30 ቀናት ውስጥ ማካሄድ እንደሚቻል ያስቀምጣል፡፡

ተቃዋሚዎች በአገሪቱ የምርጫ ካውንስል እምነት የላቸውም፡፡ ምክንያቱም በአገሪቱ ነፃና ትክክለኛ ምርጫ ተደርጎ ባለማወቁ ነው። ይህ የሚያሳየው አዲስ ምርጫ ለማከናወን ፈታኝ መሆኑን ነው፡፡ ዋናው ጥያቄ ምርጫውን ለማከናወን ማን ኃላፊነቱን ይውሰድ የሚለው ነው፡፡ በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ የምርጫ ጥያቄው በአገሪቱ የሚገኙ ተቃዋሚዎቸችን ለሁለት ከፍሏል፡፡ በጎዳናዎች ላይ የነበሩ ብጥብጦችን የመሩ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ስልጣን ለመያዝ ከፍተኛ ፍላጎት አሳይተዋል፡፡

ጓኢዶ እራሱ የጎዳና ነውጦችን ሲመራ የነበረና በአሁን ወቅት በቤት ውስጥ እስራት ላይ የሚገኘውን ሌፖልዶ ሎፔዝን ይደግፋ፡፡ በዚህም ለጓኢዶ ምርጫ በእቅድ ውስጥ እንደሌለ ፖለቲካ ተንታኞች ይናገራሉ፡፡ አሜሪካና ተቃዋሚዎች ፍላጎታቸው የስልጣን ሽግግር እንዲካሄድ ብቻ ነው፡፡ ከዚህ መረዳት የሚቻለው ማዱሮ ጓኢዶ ምርጫ እንዲካሄድ የጠራበትን መንገድ በማናናቅ በምርጫው ማንነታችንን እናሳየዋለን የሚል ንግግር አድርጓል፡፡ በተመሳሳይ ይሁኔታ ማዱሮ ምርጫው እንዲካሄድ ከተቃዋሚዎች ጋር አብሮ ለመሥራት የሚያስችለውን እንቅስቃሴ ጀምሯል። ስለምርጫው አጠቃላይ ሁኔታም ሃሳብ እየሰበሰበ ይገኛል፡፡

በቅርቡ ጓኢዶ እራሱን ፕሬዚዳንት አድርጎ መሾሙ የሚታወስ ሲሆን ሜክሲኮ እና ኡራጋይ ድርድር እንዲደረግ ጥረት አድርገዋል፡፡ ሁለቱ አገራት በተባበሩት መንግሥታት ስብሰባ ላይ በቬንዝዌላ ያለው ችግር የሚፈታበት መንገድ ሊበጅ እንደሚገባ ሃሳብ ሰጥተው ነበር፡፡ በድጋሚ ማዱሮ ከተቃዋሚዎች ጋር ድርድር ለማድረግ ጥሪ ቢያቀርብም ጥሩ ምላሽ አላገኘም። እንደሚታየው ነገር ከሆነ ሜክሲኮ ያቀረበችው የድርድር ሃሳብ ወደ ሁለትዮሽ የማድላት አዝማሚያ ታይቶበታል።፡

ጓኢዶ ያቀደው መፈንቅለ መንግሥት ሊማ ከተባለ ቡድን ጋር በመነጋገር ሲሆን ቡድኑ የቀኝ ዘመም የፖለቲካ አመለካከት ያለው ነው፡፡ ጓኢዶ

ከቡድኑ ጋር በመተባበር አገሪቷን የማስተዳደር እቅድ አለው፡፡ ነገር ግን የሊማ ቡድን ከሜክሲኮ ጋር ግንኙነት ያላቸው ሲሆን አንድሬ ማኑኤል ሎፔዝ ኦብራዶር ከሉማ ቡድን እንዲወጣ የተደረገው ለጓኢዶ ፕሬዚዳንትነት እውቅና መሰጠት የለበትም በማለቱ ነው፡፡ በእነዚህ ምክንያቶች ተቃዋሚዎች የኡራጋይና የሜክሲኮን ጥሪ ችላ ብለው አልፈውታል፡፡ ተቃዋሚዎቹ ሁለቱ አገራት ለማንም ሳይወግኑ መሥራት አይችሉም የሚል ትችት አቅርበዋል፡፡

ይህ ሁኔታ አዲስ ነገር አይደለም፡፡ ምክንያቱም የቀድሞ የስፔን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆሴ ሉዊስ ሮድርጌዝ ጃፓትሮ በተቃዋሚዎችና በማዱሮ መካከል ስምምነት እንዲመጣ ዓመታት የለፉ ሲሆን እአአ 2018 አቅራቢያ የተቃዋሚ አመራሮች በመጨረሻው ሰዓት አንፈርምም ብለው ጥለው ወጥተዋል፡፡ ባለፉት ጊዜያት የነበሩ ልምዶች እንደሚያሳዩት ተቃዋሚዎች ለድርድር በጠረጴዛ ዙሪያ ሲቀመጡ ማዱሮን ለማጥቃት አስበው ነው፡፡ ጓኢዶ እና የአሜሪካ መንግሥት አስተዳደር ይህን አመለካከት በስፋት ያራምዳሉ፡፡

በስተመጨረሻ በቬንዝዌ የሚታየው ችግር ትክክለኛ አማራጭ ለመምረጥ አንዱን መንገድ እንጂ ሁሉንም አማራጭ መንገድ እየተከተለ አይደለም፡፡ ይህን ጉዳይ ለማስረዳት በቅርቡ የተከሰተ ሁነት ማንሳት ይቻላል።በአሜሪካና

በማዱሮ መንግሥት ላይ የተነሱ ትችቶች የቬንዝዌላን ተቃዋሚዎች ከጨዋታ ውጪ አድርጎት ነበር፡፡ በቬንዝዌላ መሀል ሰፋሪ የሚባሉ ፖለቲከኞች ሲኖሩ በዚህ ውስጥ ስመጥር ሰዎች ተካተውበታል፡፡ በዚህ የቀድሞ የመንግሥት ባለስልጣናት የህገመንግሥቱ ጠበቂዎች ነን የሚል ስም ለራሳቸው ሰጥተዋል፡፡ ለአገሪቱ ደህንነትም ንግግር ሳይሆን የማዱሮን መንግሥት መቀየርና ህዝበ ውሳኔ መደረግ አለበት የሚል ሃሳብ ያቀርባሉ፡፡ ይህ አካሄድ አገሪቱን የሚበታትን መሆኑን የፖለቲካ ተንታኞቸች ይናገራሉ፡፡ በምን ዓይነት መንገድ አሁን ያለውን የቬንዝዌላ መንግሥት መተካት እንደሚቻል የተቀመጠ ነገር የለም፡፡ ህዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ 10 በመቶ የህዝቡን የድጋፍ ፊርማ የሚሰበስበው ማን እንደሆነ አልተወሰነም፡፡ በሌላ በኩል ማዱሮ ስልጣን ላይ እንዳይቆይ ድምፅ የሚሰጡ ዜጎች የሚመርጡት ሌላ ፓርቲ አላዘጋጁም፡፡ በእነዚህ ሁኔታዎች የአገሪቱ ችግር እየተባባሰ ይገኛል፡፡

ነገር ግን በሚነሱ ሃሳቦች መካከል ተቃርኖዎች በዝተዋል፡፡ የአገሪቱ ነዋሪ የሆነው ሶሶሎጂስት ኤድጋርዶ ላንደር እንደሚለው፤ በአገሪቱ ዴሞክራሲ የሚባል ነገር የለም፡፡ ለዚህ ማሳያ ደግሞ በአገሪቱ ሊካሄድ የነበረው መፈንቅለ መንግሥት በአሜሪካ መንግሥት፣ በሊማ ቡድን እና በአክራሪ ቬንዝዌላውያን መመራቱ ነው።፡

ላንደር እንደሚለው መፈንቅለ መንግሥት ከመካሄዱ ቀደም ብሎ ውይይት ተደርጎ የነበረ ሲሆን ህዝቡ ጓኢዶን እንደማይፈልግ ተናግሮ ነበር፡፡ በውይይት ችግሩን ለመፍታት አማራጭ መንገዶች ሁሉም ዝግ ሆነዋል፡፡ የቬንዝዌላ ተቃዋሚዎች ከድርድር ይልቅ መፈንቅለ መንግሥት አማራጭ ነው ብለው ተቀብለዋል፡፡ ድርድርን አልቀበልም ያለ ተቃዋሚ በምን ዓይነት መንገድ ማስተናገድ እንደሚቻል አይታወቅም። በዚህ አደገኛ ሁኔታ ቀላል መፍትሔ ማግኘት አይቻልም፡፡ ነገር ግን አንዳንድ ጉዳዮች ግልጽ እየሆኑ መጥተዋል፡፡

አሜሪካ የጣለችው ማዕቀብ እያለ ምርጫ ማካሄድ አደገኛ መሆኑ እየተነገረ ይገኛል፡፡ ኒካራግዋ እአአ 1990 ላይ በማእቀብ ውስጥ ሆና ምርጫ ስታካሂድ በነፃነት አልነበረም፡፡ በወቅቱ የአሜሪካ መንግሥት አስተዳደር ተቃዋሚዎች ምርጫውን እንዲያሸንፉ ድጋፍ አድርገው ነበር። በአሁኑ ወቅትም በአሜሪካ አስተዳደር ውስጥ አብዛኛው ሰዎች በፖሊሲ አውጭነት እየሠሩ ይገኛሉ፡፡ በቬንዝዌላም የተጣለው ማዕቀብ ሳይነሳ ምርጫ ማካሄድ አሜሪካ የፈለገችውን ፓርቲ እንድታስመርጥ ዕድል መስጠት ነው።በቬንዝዌላ የማዕቀብ መጣል ዋነኛው ችግሩ ኢኮኖሚ እንዲወድቅ ከማድረጉ ባለፈ የነዳጅ ዘይቶችን በማገት ችግሩ እንዲባባስ በር ከፍቷል፡፡

የተባባሰውና መቋጫ ያጣው የቬንዝዌላ ችግር

Page 6: 78ኛ ዓመት ቁጥር 189 ሰኞ መጋቢት 9 ቀን 2011 ዓ.ም ያንዱ ዋጋ 5.75 …ማድረግ ላይ የመምህራን የሙያ ስብጥርና ብቃት ውስንነት፣

መጋቢት 9 ቀን 2011 ዓ.ም አዲስ ዘመን

ኢኮኖሚ

በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትና በአካባቢ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ትብብር በየሣምንቱ ሰኞ ተዘጋጅቶ የሚቀርብ

9

ግርማ መንግሥቴ

እንደ ማንኛውም ሜጋ ፕሮጀክት የ“ረጲ ከደረቅ ቆሻሻ የኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጫ ጣቢያ”ም ሲፀነስ የራሱን አላማ ይዞ ነው።

ይህ በካምብሪጅ ኢንዱስትሪያል ሊሚትድ ስራ ተቋራጭና በቻይናው ኢኢፒ የተገነባውና፣ በ65 ሺህ ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ፣ 120 ሚሊዮን ዶላር (ከ2ነጥብ6 ቢሊየን ብር በላይ) የፈሰሰበትና ዘርፈ-ብዙ ፋይዳ ያለው ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ ያስገኛቸዋል የተባሉ ፋይዳዎች አንድ፣ ሁለት ተብለው ተቀምጠው ነበር። በተለይ በቀን 50 ሜጋ ዋት የሚያመነጭ ሀይል ይሰጣል የመባሉ ጉዳይና ቆየት ብሎ “ወደ 25 ሜጋ ዋት ወርዷል” መባሉ ሲያነጋግር ቆይቷል። አሁንም እያነጋገረ ነው።

የረጲ ከደረቅ ቆሻሻ የኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጫ ፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ አቶ ሰለሞን ታደሰን ጠይቀን እንደተረዳነው የረጲ ከደረቅ ቆሻሻ የኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጫ መብራት ሀይል ከካምብሪጅ ኢንዱስትሪያል ሊሚትድ ጋር የተፈራረመው እአእ ጃንዋሪ 2013 ነው። ወደ ስራ የተገባው ግን ዘግይቶ ሴፕቴምቤር 2014 ነው። ይህም የሆነበት ምክንያት በኮንትራት ስምምነቱ ላይ የተቀመጡና ቅድመ-ክፍያን የመሳሰሉ ጉዳዮች ባለመሟላታቸው ነው።

ተቋራጩን በተመለከተ የሚነሱ የተለያዩ አስተያየቶች መኖራቸውን ጠቅሰን ትክክለኛውን እንዲያስረዱ የጠየቅናቸው ኃላፊው መብራት ሀይል ግንባታውን የሰጠው ለካምብሪጅ ኢንዱስትሪያል ሊሚትድ ነው ይላሉ። ነገር ግን ካምብሪጅ ከቻይናው ሲኤንኢሲ ጋር ውል ተፈራረሙና መጡ፤ የኢትዮጵያ መብራት ሀይልም አፀደቀላቸው። ወደስራም ገቡ። አሁን በእኛ በኩል የሚታወቀው ፕሮጀክቱ በሁለቱ ተቋራጮች በጋራ መሰራቱን ነው።” በማለት መልሰውልናል። በጣቢያው ተገኝተን ያነጋገርናቸው የፕሮጀክቱ ቁጥጥርና ጥገና ስራ አስኪያጅ ሚስተር ሴም ንይም የሚያረጋግጡት ይሄንኑ በጋራ እየሰሩ መሆናቸውን ነው።

ይህ ነሀሴ 13/2010 ዓ.ም የተመረቀ ፕሮጀክት ወደ ስራ ለመግባት አልዘገየም ወይ? ላልናቸውም

“በርግጥ ከአራት አመት በላይ ዘግይቷል። ለምን ዘገየ፣ እንዴት ዘገየ? የሚለው ወደፊት በልዩ ሁኔታ የሚታይ ነው። አሁን ግን ስራው ከ96 በመቶ በላይ ተጠናቋል። ተቋራጩ በተሰጠው አስተያየት መሰረት ሁሉንም ነገር አሟልቶ ሲገኝ እንረከበዋለን።” ያሉ ሲሆን ማመንጫ ጣቢያው ከሶስት ወር በኋላ ወደኦፕሬሽን ስራ ይገባል ተብሎ እንደሚጠበቅ አስረድተዋል። ሚስተር ሴም ንይ ግን ስራውን ሙሉ ለሙሉ ማጠናቀቃቸውንና ለማስረከብ ዝግጁ መሆናቸውን ነው የሚያስረዱት። እጅግ ቢበዛ ምን ያህል ጊዜ ይቆያል? ላልናቸውም “እኛ 100 በመቶ አጠናቀናል፤ ከዚህ በኋላ እጅግ ቢቆይ ምናልባት በሁለት ወር የሚረከቡን ይመስለኛል” ነበር ምላሻቸው።

ከዚህ ፕሮጀክት ጋር በተያያዘ ሲያወዛግብ የቆየው የፕሮጀክቱ ኃይል የማመንጨት አቅም ጉዳይ ነው። ሲጀመር በአመት 50 ሜጋ ዋት ሀይል ያመነጫል ተብሎ የነበረው እያደር ሟሸሸና “አይ አቅሙ 25 ሜጋ ዋት ነው” ወደሚል አሽቆለቆለ። አቶ ሰለሞንም ከዚሁ ጋር በተያያዘ አስተያየታቸውን

ሰጥተውናል። 50 ሜጋ ዋት፣ 25 ሜጋ ዋት የሚለው ነገር

ላይ ምክንያቱ ያልታወቀ ብዥታ ያለበት ጉዳይ ነው ያሉት ስራ አስኪያጁ፤ በጉዳዩ ላይ እስካሁንም ድረስ ብዥታው እንዳልጠራ ይናገራሉ። ከዚሁ ጋር በተያያዘ ከኮንትራክተሩ ጋርም ክርክር ላይ ነን። ነገር ግን ከሁለቱ አንዱን ይዘን መሄድ ይሻላል በሚል፤ በተለይም የአዲስ አበባ ቆሻሻን ከማፅዳትና ሀይል ማመንጫውን ወደ ስራ ከማስገባት አኳያ ለጊዜው 25 ሜጋ ዋት በሚለው ተስማምተን እየሄድን ነው፤ ይህም የሆነው ከፍተኛ አመራሩ በሚያውቀው ደረጃ ነው በማለት አስረድተዋል።

የኮንትራት ስምምነቱ ላይ ያለውንና “በአመት 185 ጊዋሰ/ጊጋ ዋት ሰዓት/ ሀይል ይሰጣል” የሚለውን ያሟላል የሚሉት ኃላፊው አሁን ስምምነት ላይ ያልተደረሰው 50 ወይም 25 ሜጋ ዋት የሚለው ላይ መሆኑንም አስረድተዋል። “እኛ 50 ሜጋ ዋት ነው እያልን ነው ያለነው። ኮንትራክተሩ ደግሞ 25 ሜጋ ዋት ነው የሚለው። ወደ ክርክር እንግባ ከተባለ ጉዳዩ ሌላ መልክ ነው የሚይዘው። ስለዚህ አሁን

የተደረሰበት ውሳኔ በቅድሚያ ጣቢያው ወደ ስራ ይግባ የሚለው ነው። በተለይ የአዲስ አበባን ቆሻሻ ከማስወገድ አኳያ ስራውን ይጀምር፤ ከዛ በኋላ 50 እና 25 ሜጋ ዋት የሚለውን ወይ በውይይት ወይ በክስ የምንሄድበትና ህግ የሚፈታው ይሆናል። በሙከራው እንደተረጋገጠው ግን 25 ሜጋ ዋት ማመንጨት እንደሚችል ነው። 50 ሜጋ ዋት የሚለው ግን ካሁን በኋላ አይገኝም። የፕሮጀክቱ ፕላንም ሆነ ዲዛይኑ ለ25 ሜጋ ዋት እንጂ ለ50 ሜጋ ዋት አይመጥንም።” ሲሉም እቅጩን ተናግረዋል።

50 እና 20 ሜጋ ዋት በሚለው ብዙም ያልተመሰጡት ሚስተር ሴም ፕሮጀክቱ በቀድሞው የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ክቡር ዶክተር ሙላቱ ተሾመ መመረቁን ወደሚያሳየውና በህንፃው መግቢያ በረንዳ ላይ የተሰቀለውን ፅሁፍ፣ ከፅሁፉም ውስጥ 185 ጊ.ዋ.ስ የሚለውን በማመልከት እሱን ማምረት እንደሚችልና እየሰሩ ያሉትም ከዚሁ አንፃር መሆኑን ገልፀውልናል።

ሀይል ማመንጫ ጣቢያው ለአገሪቱ ምን ያህል ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ አለው? የሚለውን ለማወቅ ባደረግነው ጥረት ለጊዜው ካነጋገርናቸው አካላት ያገኘነው መልስ “በአመት የሚገኘውን 185 ጊ.ዋ.ስ ግን በገንዘብ ማባዛትና የሚገኘውን ገንዘብ ማወቅ ይቻላል” ከሚል በስተቀር በአሀዝ የሚያስቀምጥልን ከሁለቱም ወገን አላገኘንም።

አቶ ሰለሞንን አሰራሩ ለምን ተወሳሰበ፤ ከሙስና የፀዳ ነው ብለው ያምናሉ? ብለን ጠይቀናቸውም ነበር። “እኔ ከመጣሁ ገና ስድስት ወሬ ነው። አሰራሩን ሳየው ግን ትክክለኛ አካሄድን የተከተለ ነው። ለማንኛውም እሱ በኋላ የሚጣራ ነው። አሁን ዋናው ጉዳይ ጣቢያውን ወደስራ ማስገባት ነው የሚፈለገው። ሌላው በኋላ ገሀድ የሚወጣ ጉዳይ ነው።” ብለውናል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘና በስምምነት ከመፍታት ይልቅ ለምን በህግ እንዲታይ አልተደረገም በሚል ለቀድሞዋ ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢንጂነር አዜብ ጥያቄ ቀርቦላቸው ጉዳዩ በህግ እንዲታይ ቢደረግም ከተቋራጩ ጋር የተገባው ኮንትራት ግልፅ አልነበረም ሲሉ መመለሳቸው ይታወሳል።

በምስጢርነቱ የቀጠለው የረጲ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት አቅም

የአካባቢ ትርጉምና የጥበቃው አተገባበርአበበ ወልደ ጊዮርጊስ

የስነ-ፍጥረታት መኖሪያ የሆነችውን ምድራዊ ከባቢን መሬት፣ የውሀ አካላት፣ ስነ-ምህዳራዊ አቀማመጥ፣ህያዋን እንስሳት፣ የአካባቢ አየር፣ ፀሐይና ሙቀቷ የሚፈጥሩትን መሰተጋብራዊ ውህደቶችን መጠበቀ አስፈላጊ ነው። በአስተሳሰቡ የላቀው፣ ተፈጠሮን ለራሱ ኑሮ በሚመች መልኩ በመግራት ጥቅም ላይ እንዲውል ያደረገው የሰው ልጅ ብቻ ነው፡፡ ይህንን መሰተጋብራዊ ውህደት ሰው የተባለ ፍጡር ሁሉ ካላስፈላጊ ጉዳቶች መጠበቅም ኃላፊነት አለበት።

የሰው ልጅም ከጥንታዊው የጋርዩሽ ዘመን አልፎ ወደ ኢንዱስትሪ መር ካፒታሊስት ስርዓት ሲሸጋገር፤ ተፈጥሮ ያደለችውን ሀብት ይበልጥ መጠቀም ሲጀምር አካባቢውን ከመንከባከብና ከመጠበቅ ይልቅ ለብክለት ዳርጓታል። አለም ዛሬ ላለችበት የሙቀት መጨመርና ለከባቢ አየር ንብረት ለውጥ ምክንያትም ሆኗል። ለብክለቱም ከትላልቅ ኢንዱስትሪና ከትራንስፖርት ዘርፉ የሚለቀቁ በካይ ጋዞች፣ ወደ ውሃ አካላት ሚለቀቅ ቆሻሻ፣ የደን ሀብቶችን ማመናመን አስተዋጽኦ እንዳላቸው አብዛኞቹ ሞያተኞች ይስማማሉ፡፡

በአካባቢ ጥበቃ የደንና የአየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን የፖሊሲ ህግና ደረጃዎች ጥናትና ዝግጅት ጀኔራል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር አየለ ሀጌና ገለፃ የፍልስፍና ሊህቃን ሰዎችን ከአካባቢ ለይተው ይመለከታሉ። በተለይም ሰዎች በአካባቢዊ ስነ-ምህዳርና መላው ፍጥረታት ላይ የበለይነት አላቸው ብለው የእምነት አስተሳሰባቸውን ሚያራምዱም አልጠፉም።

በእነዚህ የፍልስፍና ተከታዮች ዘንድ ያለው ከባቢያዊ ጥበቃ አስተሳሰብ ለአካባቢ ጥበቃ የሚደረገው ሰዎችን ለመጠበቅ ወይም የሚጠበቀው አካባቢ ለሰዎች ከሚሰጠው ጥቅም አንፃር ብቻ በመመዘን ነው፡፡ በመሆኑም የፍልስፍናዎቹ መሰረት ሰው ተኮር እንጂ ሌሎች ፍጥረታትን ወይም የተፈጥሮ ሀብቶችን እንዲሁም ለአካባቢ ጥበቃ ተገቢው ቦታ የተሰጠ

አልነበረም። እውቁ የዓለማችን ቀደምት ፈላስፋ ኢማኑኤል ካንት እንደሚለው፣

“ይህ አስተሳሰብ ብዙም ተከታይ ያለው አይደለም፡፡ ይልቁንም ቦታው በአዲስ አስተሳሰብ ተተክቷል ለማለት የሚያስደፍር ነው፡፡ ይበልጥ ሰፊ ተከታይ የያዘው ፍልስፍና አካባቢን ከሰዎች ጣልቃ-ገብነት መከላከልን መሰረት ያደረገ አስተሳሰብ ዘላቂ ልማት በማረጋገጥን የአካባቢ ጥበቃ ቀጣይነት እንደ አንዱ ዋና ምሶሶ የሚወስድ ነው፡፡ በተጨማሪ አካባቢን ከሰዎች ላይቶ የሚመለከት ሳይሆን በመስተጋብር የሚያምን ነው፡፡ ይህ አስተሳሰብ አካባቢ ተኮር ብቻንም አይደለም፡፡ ሰዎች አካባቢያቸውን ዘላቂነት ባለው መንገድ በመጠበቅ እንዲጠቀሙበት የሚያበረታተም ጭምር ነው።

በዓለም አቀፍ ደረጃ የአካባቢ ዘላቂነት ጉዳይ ትኩረት ማግኘት የጀመረው ከ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮ ባለው ጊዜ ውስጥ ነው። በዚህ ጅማሮው በሀገራት መካከል ከውቅያኖሶች፣ ዝርያቸው በመናመንና በመጥፋት ደረጃ ላይ የሚገኙ እንስሳትና ዕጽዋት፣ ከተለያዩ ተፈጥሯዊ ሀብቶች ጋር በተያያዘ የሚነሱ ችግሮችንና ብክለትን መከላከልን ታሰቢ ያደረገ እንደነበረም ይጠቀሳል።

እ.ኤ.አ በ1972 በስዊድን ሀገር በተካሄደው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ስብሰባ ሁሉን አቀፍ የሆኑ ከባቢዊ ጉዳዮች ሰፊ ትኩረት የተሰጠበት ወቅት ነበር፡፡ ዓለም ስለከባቢ ሁኔታ ትኩረት መሰጠት አለበት ብሎ አዲስ የአስተሳሰብ ምዕራፍ ጅማሮ መሰረት የተጣለበት ነው። በተመሳሳይ እ.ኤ.አ በ1992 በተደረገ የአከባቢ ልማት ስብሰባ ዘለቄታ ያለው ልማትን ለማምጣት፣ የተፈጥሮ ሀብቶችን በዘላቂነት ጥቅም ላይ ማዋል እንዲሁም አካባቢን ከብክለት መከላከልን ትኩረት ያደረገ ነበር፡፡ የአካባቢ ጥበቃ ጉዳይም ከፍተኛ ትኩረት ያገኘበትም ነው፡፡

በመሆኑም ከ1990ዎቹ ወዲህ የወጡ ህጎች የአካባቢን ትርጉም ሲያስቀምጡ፤ አካባቢ ማለት በመሬት፣ በከባቢ አየር ንብረት፣ በውሃ፣ በሕያዋን፣ በድምፅ፣ በሽታ፣ በጣዕም፣ በማህበራዊ ጉዳዮች፣ በስነ-ውበት ሳይወሰን፣ በተፈጥሯዊ ሁኔታቸው ወይም

በሰው አማካኝነት ተሻሽለው በቅንጅት ያሉበት ቦታ ነው። እንዲሁም መጠናቸውን ወይም ሁኔታቸውን፤ የሌሎች ህያዋን በጎ ሁኔታን ተጽዕኖ የሚያሳድሩ ድምር ውጤትም መሆኑን የአካባቢ ጥበቃ አካላት ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 295/1995 አፅንኦት በመስጠት ይገልጻል፡፡

የአካባቢ ጥበቃ የስረዓተ-ምህዳር ቀጣይነትን ለማረጋገጥ የሚኖረው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ፤ ሰዎችም የአካባቢ አካል በመሆናቸው ይባልጥ ተጠቀሚ ይሆናሉ የሚለውን መሰተጋብራዊ አስተሳሰብ ከግምት ውስጥ ያስገባ ነው፡፡ የአካባቢ ትርጉም በሥራ ላይ የሚገኝ ቢሆንም የአካባቢ ጥበቃ ህግጋት ለሰዎች ከሚሰጡት ጥቅም ብቻ ሳይሆን ጥበቃ የሚደረግለት የአካባቢውን ዘላቂነት ማረጋገጥ የሁሉም ፍጥረታት ጥበቃና ሕልውና በመሆኑ ነው፡፡

እ.ኤ.አ በ1972 የስቶክሆልም ኮንቬንሽን፤ በ1992 ዓ.ም በሪዮ ዲጀኔሮ በተካሄደው የተባበሩት መንግሥታት የአካባቢ ልማት ስብሰባ አካባቢን ከሰዎች ጠልቃ-ገብነት አስቀድሞ መከላከል ላይ ትኩረት እንዳደረጉ መረዳት አስፈላጊ ነው።

በዚህ መሰረት አንደኛው መርህ በአካባቢ ላይ የሚደርስውን ጉዳት ቀድሞ መመርመርና ማወቅ፣ የልህቀት መጠንን መቆጣጠር፣ የተለያዩ ምርቶችን ደረጃ መወሰን፣ በቀላሉ ሊተገበሩ የሚችሉ ከአካባቢ ጋር ተስማሚ የቴክኖሎጂ ምርቶችን መጠቀም የከባቢ ብክለትን መከላከል መርህ ውስጥ ጎልተው የሚጠቀሱ ተግባራት ናቸው፡፡

ሁለተኛው መርህ ቅድመ ጥንቃቄን መሰረት በማድረግ አንድ የልማት እንቅስቃሴ በአካባቢ ላይ ጉዳት ያስከትላል ተብሎ ሲታሰብ፣ ቀድሞ ወደ ነበረበት ይዞታው መመለስ ካልተቻለ፣ አደጋ ሊያስከትል ይችላል በሚል ስጋት ሲኖር የአደጋውን መጠን በሳይንሳዊ መንገድ ማረጋገጥ አለመቻል፣ ወጪ ቆጣቢ ዕርምጃዎችን ለመውሰድ እንደ ማትግያ ምክንያት መወሰድ የለበትም።

አንዳንድ አካባቢ ላይ የሚደርሱ ጉዳቶች የከፋ ሊሆን ስለምችል ጉዳቱን መከላከሉ ጉዳይ ወሳኝ ነው፡፡ በብራዚል ሪዮ በተካሄደው የተባበሩት መንግሥታት የአካባቢ ልማት

ስብሰባ ለተጎጂዎች ተገቢውን ካሳ በመክፈል ብቻ የሚያበቃ ሳይሆን ጉዳት የደረሰበትንም አካባቢ መልሶ እንዲያገግም የሚያስችለውን ወጪ እንዲሸፍን ያስገድዳል።

ዶ/ር አየለ እንደሚሉት መርሆዎቹ አንዱ ከሌላኛው የሚበልጥም የሚያንስም አይደለም፡፡ ይልቁንም መርሆዎቹ ውጤታማ ለመሆን በየደረጀው በሚገኙት አስተዳደራዊ እርከኖች ፖሊሲዎችንና ህግጋትን በማካተት መተግበረን የሚጠይቁ ናቸው፡፡

አደገኛ ቆሻሻዎች በዓይነትም ሆነ በመጠን እየጨመረ መጥቷል። ከአደገኛ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ጋር በተያያዘ በሰው ሕይወትና በአካባቢ ደህንነት ላይ እያደረሰ ያለው ተፅዕኖም ከፍተኛ ነው። ኢትዮጵያ ድንበር ዘለል አደገኛ ቆሻሻዎችን ለመቆጣጠር የባዝልና የባማኮ ኮንቬንሽን ስምምነቶችን ተቀብላለች።

እነዚህን ስምምነቶች ለመተግበር የሚያስ

ችል ብሔራዊ ህግ በማስፈለጉ ምክንያት አደገኛ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ አግባብነት ካባቢያዊ ተቀባይነት ባለው መንገድ መከናወኑን በሚገባ ማረጋገጥ እጅግ አስፈላጊ ነው።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በአየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን አማካኝነት የዓለም ሀገራት ስብሰባ በመቀመጥ በኢንዱስትሪ የበለጸጉት ከኢንዱስትሪዎቻቸው ወደ ከባቢ አየር የሚለቁትን ለሙቀት መጨመር መንስኤ የሆነውን በካይ ጋዝ እንዲቀንሱ ከስምምነት ደርሰዋል። በስምምነቱም ውጤት ተመዝግቧል። ይሁን እንጂ የስነ-ፍጥረት መኖሪያ የሆነችውን ምድራዊ ከባቢን ለመጠበቅ የልቀት ቅነሳ ድርድሩ መቀጠል እንዳለበት ሁሉም ባለድርሻ አካላት ትኩረት ማድረግ ይገባቸዋል። ኢትዮጵያም ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ የመገንባት ሥራዋ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባዋል።

ሲጀመር በአመት 50 ሜጋ ዋት ሀይል ያመነጫል ተብሎ የነበረው እያደር ሟሸሸና “አይ አቅሙ 25 ሜጋ ዋት ነው” ወደሚል

አሽቆለቆለ

Page 7: 78ኛ ዓመት ቁጥር 189 ሰኞ መጋቢት 9 ቀን 2011 ዓ.ም ያንዱ ዋጋ 5.75 …ማድረግ ላይ የመምህራን የሙያ ስብጥርና ብቃት ውስንነት፣

ፖለቲካመጋቢት 9 ቀን 2011 ዓ.ም አዲስ ዘመን 11

“አክቲቪዝም በኢትዮጵያ” ከየት ወዴት?ወንድወሰን ሽመልስ

በአንድ አገር ብቻ ሳይሆን በዓለም ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ብሎም አካባቢያዊ ጉዳዮችን መነሻ በማድረግ የህዝብን ንቃተ ሕሊና ለመቅረጽና ወደተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር አክቲቪዝም ትልቅ ድርሻ ስለማበርከቱ በርካታ ዓለምአቀፍ ማሳያዎች ይነሳሉ። በኢትዮጵያም በተለይም የማህበራዊ ሚዲያ መስፋፋትን ተከትሎ ይሄው ተግባር እየተበራከተ እንደመሆኑ በአዎንታዊም ሆነ አሉታዊ ገጽታው የሚነሱ ነገሮች አሉ። ታዲያ የአክቲቪዝም እንቅስቃሴ በእትዮጵያ እንዴት ይገለጻል፤ ያሉት መልካም ገጽታዎችና ችግሮችስ ምን ይመስላሉ፤ በቀጣይስ ምን ሊሠራ ይገባል፤ በሚሉ ጉዳዮች ላይ የጋዜጠኝነትና ኮሚዩኒኬሽን ምሑራን የሚሉት አላቸው።

አክቲቪዝምና አክቲቪስትአቶ በረከት ሐሰን፣ በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ

የጋዜጠኝነትና ኮሚዩኒኬሽን ትምህርት ክፍል መምህር ናቸው። እርሳቸው እንደሚሉት፤ አክቲቪዝም በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ እንዲሁም አካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ ተሃድሶን ለማምጣት፣ ማህበረሰቡንም ከአንድ ደረጃ ወደ ሌላ ደረጃ የሚያሸጋግር ለውጥ ለማምጣት በግለሰቦች ወይም በቡድኖች የሚከናወን ተግባር ነው። እነዚህ ግለሰቦች ወይም ቡድኖች ደግሞ በአንድ አገር ደረጃ ብቻ ሳይሆን ዓለምአቀፋዊ ጉዳዮችን ጉዳያቸው አድርገው የአየር ንብረት ለውጥ፣ የሰብዓዊ መብት፣ ጾታና ሌሎች ጉዳዮች ላይ ለውጥ እንዲመጣ በሰፊው የሚሞግቱበት እንቅስቃሴ ነው።

የአክቲቪዝም ሚና በዋናነት አንድን ማህበረሰብ ማሻገር ነው ሲባል፤ አንድን ጉዳይ በማንሳት የመጣለትን ሃሳብ፣ አቅጣጫና ጉዳይ ዝም ብሎ ወደማህበረሰቡ በማድረስ ማህበረሰቡን ይቀይራል ማለት አይደለም። ትልቁ የአክቲቪዝም ሚና የሚሆነው አንድን ጉዳይ አንስቶ (ለምሳሌ ስለ ሰብዓዊ መብት ጥሰት) እና አንድን አቅጣጫ ብቻ ወስዶ በመመልከት ማህበረሰቡ በዚያ ጉዳይ ላይ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን እንዲቃወም መሥራት ነው። ይህ ሲሆን ግን ብዙ ማጥናትንና ስለጉዳዩ ማወቅን፤ ማህበረሰቡን ማሻገር የሚችል የሃሳብ ልዕልናን መታጠቅን ይጠይቃል። በእነዚህና መሰል ጉዳዮች ላይ የሚያተኩሩ በርካታ የአክቲቪዝም እንቅስቃሴዎች በዓለም ዙሪያ ያሉ ሲሆን፤ የማህበራዊ ሚዲያው እንዳሁኑ በስፋት ከመጀመራቸው በፊትም በሚዲያዎች ጭምር ከፍተኛ እንቅስቃሴዎች ተካሂደዋል።

በእስከአሁን ሂደት የአክቲቪዝም እንቅስቃሴዎች በርካታ ለውጥን ሲያመጡ መመልከት ተችሏል። በተለይ የማህበራዊ ሚዲያው (እንደ ፌስ ቡክ፣ ቲዊተርና ሌሎችም) የአክቲቪዝም እንቅስቃሴን በከፍተኛ ደረጃ አግዘዋል። በኢትዮጵያም ይሄው እንቅስቃሴ የመንግሥት ለውጥ እስከማድረግ አድርሷል። በሌሎች የዓለም አገራትም የአክቲቪዝም እንቅስቃሴው በጣም እያደገ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ በተለይም የማህበራዊ ሚዲያውን በመጠቀም ከፍተኛ ለውጥ ማምጣት ተችሏል። ለዚህ ደግሞ የ2012ቱ የዐረብ አብዮት አንድ ማሳያ ሲሆን፤ የአሜሪካው ዎል ስትሪት እንዲሁም ኡጋንዳና ቬንዙዌላ የነበሩ የአክቲቪስት ተጽዕኖዎችም ተጠቃሽ ናቸው።

በአክሱም ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነትና ኮሚዩኒኬሽን ትምህርት ክፍል መምህር አቶ ፅጋቡ ሞትባይኖር በበኩላቸው እንደሚሉት፤ አክቲቪስትነት ከጋዜጠኝነት ይለያል። ምክንያቱም፣ ጋዜጠኝነት ተጨባጭ የሆነ ሐቅን ወደ ህብረተሰቡ በማስተላለፍ ዳኝነቱን ለህብረተሰብ ይሰጣል፤ በአንጻሩ አክቲቪዝም፣ አንድን ሃሳብ ተከታዮቹ እንዲቀበሉት የማድረጊያ ሂደት ነው። ሆኖም በአንድ አገር ሁለንተናዊ ሂደት ውስጥ ሁለቱም አስፈላጊ ናቸው። በበርካታ አገራትም እንደ ጋዜጠኝነቱ ሁሉ ዓላማን መሰረት ያደረጉ የአክቲቪዝም እንቅስቃሴዎች ለውጥን ሲያመጡ ታይቷል።

ለአክቲቪዝም ሥራው ደግሞ የማህበራዊ ሚዲያው ሰፊ አማራጭ ሰጥቷል። በጋዜጠኝነት ውስጥ ያሉት ሳይቀር ሙያው የሰጣቸውን አቅም ተጠቅመው ወደ አክቲቪስትነት የሚሄዱበትን ዕድል ፈጥሯል። ሚዲያውም በዚያው ልክ እያደገ ይገኛል። ሆኖም አክቲቪስትነቱን ጋዜጠኝነቱ በሰጣቸው ዕውቀትና ልምድ ተጠቅመው መሥራት ቢችሉ መልካም ይሆናል።

አክቲቪዝም በኢትዮጵያእንደ አቶ ፅጋቡ ገለጻ፤ በተለያዩ የዓለም አገራት

አክቲቪስቶች እያደጉ ነው ያሉት። ይህ ደግሞ የማህበራዊ ሚዲያው ምህዳር መስፋት ውጤት ነው። ሆኖም አጠቃቀሙ በሌላው ዓለምም ሆነ በኢትዮጵያ የራሱን አዎንታዊም ሆነ አሉታዊ ተጽዕኖ እያሳደረ ይገኛል። ከዚህ አኳያ ሲታይ አክቲቪዝም በኢትዮጵያ የተወሰኑ ሰዎች በትክክል

የሚጠቀሙበትና የተሻለ ሃሳብ እንዲንሸራሸርበት እያደረጉበት ሲሆን፤ በአንጻሩ በአብዛኛውና በብዙ ቁጥር የሚገለጹት አክቲቪስቶች ግን ለህዝቡ የትኛው ቢሆን ይጠቅማል በሚል ሳይሆን እነርሱ በሚፈልጉት መልኩ እንዲጓዝ የሚያደርጉበት መስክ ሆኗል። አክቲቪስትነትን በአግባቡ ባለመረዳት ያለው የአጠቃቀም ሂደት እነርሱ የሚፈልጉት የተወሰነ ቡድን ወይም የህብረተሰብ ክፍል ወይም የፖለቲካ ፓርቲ ሊሆን ይችላል የዚያ ሃሳብና ፍላጎት ብቻ እንዲደመጥ የሚያደርጉበት ሂደትም እንደ አገር ዋጋ እያስከፈለ ይገኛል።

ይህ ደግሞ ሚዛናዊ በሆነና አንዱን ሲጠቅም ሌላውን በማይጎዳ መልኩ እንዲጓዝ የሚያደርጉ ሃሳቦች እየራቋቸው የመምጣቱ፤ የእኔን ተቀበሉ እንጂ ለህዝብ ሃሳብ መሥራትና እውነትን አድርሶ ዳኝነትን ለህዝብ የመስጠት አካሄድ የመጥፋቱ ማሳያ ነው። በሁሉም አካባቢ የሚታየውም የራስን ጎራ ለይቶ ፍጭት ማድረግ ነው። እውነተኛና ሚዛናዊ አክቲቪስት ግን መሥራት ያለበትን የህብረተሰብ ለውጥ አምጪ ሃሳቦች የማመንጨትና የህዝቡን ንቃት ማሳደግ ነበር። እናም የፈለገው ሰው ተነስቶ የፈለገውን የሚጽፈበትና አክቲቪስት የሚሆንበት አግባብ እየታየ፤ በተከታይ ብዛትም የጻፈውን ሰው እንዲያምነው እየሆነ ነው። በዚህም ግላዊ አስተሳሰቦች እየገነኑና ህብረተሰባዊ ጉዳዮች እየተዘነጉ ወደከፋ ችግሮች እየወሰዱ ይገኛል።

እንደ አቶ በረከት ገለጻ ደግሞ፤ አክቲቪዝም በኢትዮጵያ ለምልሞ ወጥቷል የሚባለው ባለፉት ሦስትና አራት ዓመታት ነው። በተለይ በኢትዮጵያ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ቁጥር እየጨመረ መሄድና 16 ሚሊዬን የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች መኖር አክቲቪስቶች በቀላሉ በርከት ያሉ ተከታይ እንዲያፈሩና ሃሳቦቻቸውን የሚጋሯቸው እንዲያገኙ አድርጓቸዋል።

ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ የአክቲቪዝም እንቅስቃሴ ትልቁና መሰረታዊው ችግር የሙያ ድንበር/መስመር ማጣትና መጣረሶች ናቸው። ጋዜጠኛውም ሆነ ፖለቲከኛው አክቲቪስት፤ አክቲቪስቱ ጋዜጠኛም ፖለቲከኛም ሲሆን ይታያል። እነዚህ ደግሞ በኢትዮጵያ የሚስተዋሉ መሰረታዊ ስህተቶች ናቸው። አንድ ጋዜጠኛ አክቲቪስት የሚሆን ከሆነ የጋዜጠኝነቱን ሙያ ያበላሻል፤ በተመሳሳይ አክቲቪስቱ ጋዜጠኛ፣ ፖለቲከኛውም አክቲቪስት ሲሆን በዚያው ደረጃ የሚታይ ነው።

አቶ በረከት እንደሚሉት፤ ይህ አካሄድ የኢትዮጵያ የአክቲቪዝም እንቅስቃሴ በተለይም የማህበራዊ ሚዲያው ባህሪ በአብዛኛው መነሻና መሰረት የሌላቸው ሃሳቦችን ሲያንሸራሽሩ፤ የውሸት ዜናዎችንና መልዕክቶችን ሲያስተላልፉ፤ አንዳንዴም ከግላዊ ቅሬታ ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን ሲያነሱ ይታያል። ይህ የሃሰትና መሰረት የሌለው ወሬ ጉዳይ ደግሞ በዓለምአቀፍ ደረጃ ትልቅ ችግር ተብሎ የሚታሰብ ነው።

በዚህ መልኩ የውሸት ዜናም ሆነ የግል ቅሬታን ይዞ በመውጣት፣ ብዙ ላይክና ሼር በማግኘት ሂደት ውስጥ ሳይታሰብ ወደ አክቲቪስትነት የሚገባበት አካሄድ ደግሞ አክቲቪዝም ለምን ዓላማ እየተካሄደ እንደሆነ በመዘንጋት ወዳልተፈለገ አቅጣጫ ለሚያመሩ ሃሳቦች መበራከት በር ከፍቷል። ይህ የአክቲቪስቶች ችግር ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያ ያለው የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚ ህብረተሰብ የአጠቃቀም ዘይቤም ችግር ሲሆን፤ ህብረተሰቡ ከማህበራዊ ሚዲያዎች የሚወስዳቸው መረጃዎች

የትኞቹ ናቸው ብሎ ለይቶ ያለመረዳት ክፍተትም ነው።

ሆኖም በአገሪቱ ከፍተኛ ለውጥ እንዲመጣ ያደረጉ አክቲቪስቶች መኖራቸው አይዘነጋም። እነዚህ አክቲቪስቶች ትክክለኛ መረጃ በመስጠትና ተገቢ የሆነ መረጃን በተገቢው መንገድ በማድረስ ህዝቡን በከፍተኛ ሁኔታ በማነሳሳት በአገሪቱ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ሁነት ላይ ለውጥ እንዲመጣ አድርገዋል። ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ የአክቲቪዝም እንቅስቃሴ ሲታይ በአብዛኛው በውሸት ዜናና በግል ቅሬታ ላይ ተመስርተው የሚቀነቀኑ ናቸው።

አንድ መረጃም ከአንድ አካል ስለመጣ ብቻ ሰበር ዜና ተብሎ የሚወጣ አይደለም። የተሰጠውን መረጃ ትክክል ስለመሆን አለመሆኑ ማረጋገጥና አክቲቪስቱ ከቆመበት ዓላማ (ለምሳሌ፣ ከሰብዓዊ መብት፣ ከሴቶች መብት፣ ከአከባቢ ጥበቃ፣ ወዘተ.) አኳያ በማገናዘብ ለህብረተሰቡ የሚጠቅምና ወደሚፈለገው ደረጃ የሚያሸጋግር ስለመሆን አለመሆኑ ማረጋገጥ መቻል አለበት።

ለምሳሌ፣ አሜሪካ ውስጥ የጥቁሮች መብት እንዲከበር ተግተው የሚሠሩ አክቲቪስቶች አሉ፤ በመላው ዓለምም ለአየር ንብረት ለውጥ ችግር መቀረፍ የሚሟገቱ አክቲቪስቶች አሉ፤ ለሴቶች እኩልነትና ተጠቃሚነትም የሚሞግቱ አሉ። ዋናው ጉዳይ ዓላማቸውን ለማሳካትና ህዝባዊ ሽግግርን ለመፍጠር የትኛው መረጃ ነው ትክክልና የሚጠቅመው ብለው መመርመርና በግንዛቤ ላይ ተመስርተው ሃሳባቸውን ማራመድን የሚጠይቅ መሆኑን መገንዘብ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ ግን ይሄን የማድረግ ጉድለት ይታያል።

አሉታዊ ገጽታውአቶ በረከት እንደሚናገሩት፤ በኢትዮጵያ

ያለው የአክቲቪዝም እንቅስቃሴ በዚህ መልኩ መገለጽ፣ አክቲቪስቶች የቆሙለትን ዓላማ አውቀው እንዳይሠሩ አድርጓቸዋል። በዚህ መልኩ ዓላማን አውቆ ያለመሥራት ሂደትም በሚያስተላልፏቸው መልዕክቶች ጥላቻን፣ ጸብና ቂመኝነትን ጭምር ሲዘሩ ይስተዋላል። ሲፈልጉ የፖለቲካ፣ ሲያሻቸው የአካባቢ ጥበቃ፤ ሲላቸውም የጾታ ጉዳይ፤ ካልሆነም የብሔርና ሌላም ጉዳይ ይዘው እዚያም እዚህም ሲረግጡ መታየታቸውም ለዚሁ ነው። እናም ለአገርና ህዝብ መለወጥ ጉልህ ድርሻ ያደረጉ ጥቂት አክቲቪስቶች ተግባር በተቃራኒው ይሄን መሰል የሙያ፣ የዓላማና ተልዕኮ መጣረስ የሚታይባቸው አክቲቪስቶች በሚፈጥሩት ስህተት አገርና ህዝብ ወዳልተፈለገ ችግር እንዲያመሩ እያደረጋቸው ይገኛል።

ይህ አካሄድ ደግሞ የእንደዚህ ዓይነት አክቲቪስቶች የአክቲቪስትነት ጉዳይ ጥያቄ ውስጥ ያስገባዋል። ምክንያቱም እነዚህ ሰዎች አንድም፣ በሚያነሷቸው የውሸትና ስሜት ቀስቃሽ ጉዳዮችም ሆነ ግለሰባዊ ቅሬታዎች ምክንያት በሚያገኟቸው የተከታይና ተጋሪ ብዛት ሳያስቡት ወደአክቲቪስትነት የገቡ፤ አንድም ዓላማና ተልዕኳቸውን ለይተው የሚታገሉበትን ምክንያትን አውቀው የገቡ ሊሆኑ ስለሚችሉ ነው። የውሸት ዜና በወጣ ቁጥር ደግሞ ሰዎችን ወደተሳሳተ አቅጣጫ እየመራ፤ የጥላቻ መልዕክቶችም ሲበዙ ለግጭት ምንስኤ እየሆነ፤ ሌላው ቀርቶ አክቲቪስቱ ባስተላለፈው መልዕክት ስር የሚሰጡ አስተያየቶች ለጥላቻ በር እየከፈቱ መሆናቸውን በኢትዮጵያ መመልከት ተችሏል።

በማህበረሰብ ሚዲያው እንቅስቃሴና አጠቃቀም ባለው ሰፊ ጉድለትም ሃይማኖትን፣

ብሔርን፣ ግለሰባዊ ማንነትን፣ ወዘተ መሰረት ያደረጉ ስድቦች፣ የጥላቻ መልዕክቶችና ጥቃቶች መደበኛ በሚመስል ገጽታ በሰፊው የሚንሸራሸሩበት አሳፋሪ፤ ብሎም ኢትዮጵያዊ የሚታወቅበትን ሁሉን አክባሪነት ገጽታና ኢትዮጵያዊነትን የማይመጥን ከመሆኑም በላይ፤ ወደፊት ችግር ይፈጥራል ተብሎ የሚነገርለት ሳይሆን አሁን ላይም ችግር ፈጥሮ በህዝቦች መካከል መጠራጠርና መቃቃር እንዲፈጠርና ግጭት እንዲከሰትም አድርጓል። ይህ ደግሞ የማህበራዊ ሚዲያው ጥቅም እንዳለው ሁሉ የአጠቃቀም ግድፈት ሲኖርም ጉዳት እንዳለው ማየት የተቻለበት ነው። አሁን ባለው የችግር ደረጃ ሊታረም የማይቻል ከሆነና በዚሁ ከቀጠለ ጉዳቱ ከዚህም የከፋ ስለሚሆን ማስተካከያ ሊደረግበት ይገባል።

አቶ ፅጋቡ በበኩላቸው እንደሚሉት፤ ምንም እንኳን አሁን ላይ ሚዲያዎች እየተበ ራከቱ የመጡና የተወሰኑ አማራጮችን ማየት ቢጀምርም ቀደም ሲል ይህ አማራጭ ባለመኖሩ ህብረተሰቡ መረጃን ቶሎ ቶሎ ባለበት ቦታ ለማግኘት የመገናኛ ብዙሃኑ ይሄን ማድረግ ባለመቻላቸው የማህበራዊ ሚዲያዎችን በአማራ ጭነት መያዙ የአክቲቪዝም እንቅስቃሴዎች እንዲያድጉ እንደ አንድ ሰበብ ሆኗል። ሆኖም አንድ አክቲቪስት ለገጹ ጓደኛም ሆነ ተከታይ ሲያፈራ የሚያራምደው ሃሳብ ለህዝብ ለውጥና አንድነት፤ ለተሻለ ተጠቃሚነትና የጋራ ዕድገት መሆን እንጂ ራስን ጠቅሞ ሌሎችን ለመጉዳት መዋል አይገባውም።

ነገር ግን አሁን የሚታየው ማንም ሰው ተነስቶ አክቲቪስት ስለሚሆን የፈለገውን ሃሳብ ፈጥሮ እያራመደና ወደሌሎችም በማ ጋባት ችግር እያስከተለ ይገኛል። ሆኖም ኢትዮጵያውያን ነጋቸውን የተሻለ ማድረግ ስለሚችሉበት ጉዳይ የሚመክሩበትና ለዚሁ በጋራ መሥራት የሚገባቸው እንጂ፤ በአክቲቪስትነት ስም ጎራ ከፍለው በሚሻኮቱ ግለሰቦች አጀንዳ የሚናቆሩና የሚጣሉ መሆን፤ አክቲቪስቶችም ቢሆኑ ህዝቡን ወደተሻለ ለውጥና አብሮነት ስለማሻገር እንጂ በራስ ስሜትና ፍላጎት እየገፉ ወዳልተፈለገ መገፋፋትና ግጭት እንዲያመራ ማድረግ አልነበረባቸውም። እናም አክቲቪዝሙ አሁን ላይ እየፈጠረው ያለው ችግር ከቀጠለ የባሰ አደጋ ማስከተሉ ታውቆ ሊሠራ ይገባል።

መፍትሔና መልዕክትእንደ አቶ ፅጋቡ ገለጻ፤ አሁን ቴክሎጂ

እያደገና ተጠቃሚውም እየበዛ ከመሆኑ አንጻር አክቲቪዝምን ማጥፋት አይቻልም። እናም አማራጭ ሊሆን የሚችለው አንድም ህብረተሰቡ አማራጭ እንዲኖረውና የሚጠቅመውን ሃሳብ ለይቶ እንዲይዝ ማድረግ፤ ሁለተኛም አክቲቪዝሙ የጋዜጠኝነት ጽንሰ ሃሳብን ተገንዝቦ በዛ አግባብ ህብረተሰባዊ ተጠቃሚነት ላይ አተኩሮ እንዲሠራ ማስቻል ነው።

በተመሳሳይ ውጤታማ የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀምን የሚመለከት ጠንካራ ሕግ አውጥቶ መተግበር ይገባል። ምክንያቱም አሁን ባለው የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ሁኔታ ህዝቡ በሚፈለገው ልክ ንቃተ ህሊናው አድጓል ማለት ስለማይቻል፤ ለምን እንጠቀማለን የሚለው ባለመታወቁም፣ አገሪቱንም ሆነ ህዝቡን ዋጋ እያስከፈለ ስለሆነ አጠቃቀሙ መታረቅ ስላለበት ይሄንን መቆጣጠር የሚቻልበት አካሄድ ሊኖር ያስፈልጋል። በዚህም አክቲቪስቶች ከቁርሾ ወጥተው ለህዝብ ጠቃሚ መረጃን ማጋራት፤

መንግሥትም ለጊዜውም ቢሆን ይሄን የጥፋት ዘር የማሰራጨትና የግጭት መንስኤ መልዕክቶች የማጋራት አካሄድ የሚቆጣጠርበትን ዕድል መፍጠር አለባቸው።

ከዚህ በተጓዳይ አብዛኛው ህብረተሰብ ገጠር የሚኖርና የሚዲያም ተደራሽነት የሌለው እንደመሆኑ ከማህበረሰብ ራዲዮኖች ጀምሮ ሚዲያውንና ጋዜጠኝነትን ማሳደግ፤ መንግሥትም ይሄንን በመደገፍ የህብረተሰቡን አማራጭ ማብዛት ይገባል። በተመሳሳይ ጥሩ ስነምግባር ያላቸውና ለመልካም የህዝብ ለውጥ የሚሠሩ አክቲቪስቶችን መንግሥት እየደገፈ በምን መልኩ ሁሉንም ኢትዮጵያዊ መጥቀም ይችላሉ በሚለው ላይ ሃሳብ እንዲያንሸራሽሩ ማድረግ ያስፈልጋል።

አቶ በረከት በበኩላቸው እንደሚሉት፤ እንደ አገር 16 ሚሊዬን ሰው የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚ ሆነ ማለት፤ በዚያው ልክ የዚህ ማህበራዊ ሚዲያ ተደራሽ ያልሆነውን ሰፊ የገጠሩ ህብረተሰብ ክፍል በተመሳሳይ የውሸትና የግል ቅሬታ ስሜት መልዕክቶች ለመመረዝ የሚኖረው ዕድል የሰፋ ነው። ይሄን መሰል የተዛባ መረጃ ስርጭት ደግሞ በህብረተሰቡ ውስጥ የሚፈጥረው አደጋ አሁን እየታየ ባለው መልኩ የሚገለጽ ነው።

አሁን ባለው ሁኔታ የመንግሥትም ሆነ የሚዲያ ተቋማት አጀንዳዎች የሚቀረጹትም ሰፊውን የህብረተሰብ ጉዳይ ሳይሆን የ16 ሚሊዬን የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚን ማዕከል የማድረግቸው ሂደት መታረም አለበት። ምክንያቱም ሰፊው የገጠርና የአርሶአደሩ ማህበረሰብ ስሜትና ፍላጎትም ከግምት ሊገባ ይገባዋል እንጂ፤ እንደ አንድ ግብዓት ከመጠቀም ባለፈ የማህበራዊ ሚዲያውን ተከትሎ መሾምና መሻር ተገቢ አይደለም። አብዛኛው ህብረተሰብ ከማህበራዊ ሚዲያው ውጪ እንደመሆኑም ፖሊሲና እቅዶችም በዚሁ አግባብ ሊቃኙ ይገባል።

በተመሳሳይ አንዱን በማኮሰስ፣ ኢትዮጵያ ዊነትን ወደኋላ የሚስብ፣ ሃይማኖትን ወይም ብሔርን ከፍና ዝቅ በሚያደርግ የሚሰነዘሩ የጥላቻ መልዕክቶችን ማርገብ የሚቻልበት አካሄድ መታየት አለበት። ባለው ተጨባጭ ሁኔታም ትልልቅ የሚባሉ መገናኛ ብዙሃን ባሉበት አገር ላይ መረጃዎችን ቀድመው ለህዝብ ተደራሽ የሚያደርጉት የማህበራዊ ሚዲያዎች ናቸው። ይህ ደግሞ የሚዲያ ተቋማት ምን ያክል ወደኋላ እንደቀሩ አመላካች ነው። ከዚህ አኳያም የመን ግሥት የሥራ ሐላፊዎች/ባለስልጣናት በያንዳንዱ ሁነትና ጊዜ ለመገናኛ ብዙሃን ክፍት መሆን አለባቸው።

ይህ ሲሆን ተገቢውን መረጃ በሰዓቱ ለማህበረሰቡ ማድረስ ስለሚቻል ማህበራዊ ሚዲያው በሐሰት መረጃ በህብረተሰቡ ላይ የሚያሳድረውን ተጽዕኖ መቀነስ ይቻላል። ሚዲያዎችም በተቻለ መጠን አቅማቸውን ገንብተው፣ የሰው ሐይላቸውንም አደራጅተውና ተደራሽነታቸውን አስፍተው መረጃን በተገቢው ወቅት ለማህበረሰቡ ማድረስ የሚችሉበትን አግባብ ለመፍጠር መሥራት ይጠበቅባቸዋል። ከመደበኛው የመረጃ ማሰራጫ አውታራቸው ባለፈም የተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮችን ተጠቅመው ትኩስና ወቅታዊ መረጃዎችን ለህብረተሰቡ ማድረስ ይኖርባቸዋል።

ከዚህ ባለፈ በአክቲቪዝም ጉዞ ውስጥ የሚታይን የሙያ መጣረስና የዓላማ መሳት አካሄድን የሚያርም ዕርምጃ መውሰድ ይገባል። ለዚህም ተቋማት በተለይም ሚዲያዎች እንደ ቢቢሲና ሌሎችም ካሉ ዓለምአቀፍ ተቋማት ተሞክሮዎችን በመውሰድ ለአባሎቻቸው የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም መመሪያ ማዘጋጀት ይኖርባቸዋል። ለምሳሌ፣ ጋዜጠኞች ተቋማቸውን ወክለው ለዘገባ ሲሰማሩ ለተቋማቸው መረጃ እንዲያመጡ እንጂ በስማቸው በከፈቱት የግል የማህበራዊ ሚዲያ መረጃውን እንዲለቅቁት አይደለም።

ሆኖም እነዚህ ጋዜጠኞችም ሆኑ ፖለቲከኞችና የፖለቲካ አመራሮች በማህበራዊ ገጻቸው ስድብና ጥላቻን ሲያስተላልፉ ይታያል። ይህ ደግሞ ግለሰቦቹ ባሉበት ተቋምም ያን መሰል አስተሳሰብ አለ ተብሎ እንዲገመት ስለሚያደርግ የሚዲያ፣ የከፍተኛ ትምህርት፣ የፖለቲካና ሌሎችም ተቋማት የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም መመሪያ ሊያዘጋጁ የግድ ይላል።

አክቲቪስቶችም በጥቂቶች እንደሚታየው ሁሉ አክቲቪስትነት ቀላል ሙያ እንዳልሆነ ተገንዝበው ከዚህ መሰል አካሄድ በመውጣት ህዝብና አገርን መሰረት አድርገው ወደመሥራት ቢገቡ መልካም ነው። በትክክለኛ መረጃ ታግዘውና ዓላማቸውንም ለይተው በሁሉም መስክ አገርና ህዝብን ለማሸጋገር መሥራት ይጠበቅባቸዋል። ይሄን መሰል አካሄድ ሲለመድም አሁን ያለውን ችግር መሻገር ይቻላል። ይህ የማይሆንና ባለው ሁኔታ የሚቀጥል ከሆነ ግን አገርም ሆነ ህዝብ ከእነዚህ አካላት ከሚያገኙት ጥቅም ይልቅ ጉዳታቸው ያመዝናል።

አቶ በረከት ሐሰን፤ አቶ ጽጋቡ ሞት ባይኖር፤

Page 8: 78ኛ ዓመት ቁጥር 189 ሰኞ መጋቢት 9 ቀን 2011 ዓ.ም ያንዱ ዋጋ 5.75 …ማድረግ ላይ የመምህራን የሙያ ስብጥርና ብቃት ውስንነት፣

መገቢት 9 ቀን 2011 ዓ.ም አዲስ ዘመን

ማህበራዊ/ትምህርት

ከኢፌዴሪ የትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በየሳምንቱ ሰኞና ዓርብ የሚቀርብ

13

ወንድወሰን ሽመልስ

የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ዘርፉ በአገሪቱ ሁለንተናዊ ዕድገት ውስጥ የማይተካ ሚና ያላቸውን የሰው ኃይልና ቴክኖሎጂን

በማውጣት ትልቅ ኃላፊነት የተጣለበት ነው። ይሄን ኃላፊነት ለመወጣትም ከ1994 ዓ.ም ጀምሮ ወደሥራ የገባ ሲሆን፤ በሚፈለገው ልክ ባይሆንም አበረታች የሚባል ሥራን ሲያከናውን ቆይቷል። ሰሞኑንም የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ዘርፍ የ2011 በጀት ዓመት የስምንት ወር እቅድ አፈጻጸም በአዳማ የተገመገመ ሲሆን፤ በመድረኩም ከፌዴራል፣ ከክልልና ተቋማት፣ እንዲሁም ከአጋር አካላት የተገኙ ባላድርሻዎች ተሳትፈዋል።

እኛም በዛሬው ዕትማችን በዚህ ጉባኤ በተደረገ ግምገማ በተለይ በሙያ ደረጃ ምደባና የብቃት ምዘና፣ የሰልጣኝ አሰልጣኝ ልማትና የተቋማት ግንባታ፣ እንዲሁም የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ሥራዎችን አስመልክቶ የታዩ ጉዳዮችን፤ የተለዩ ችግሮችንና የተቀመጡ የመፍትሔ ሃሳቦችን አስመልክቶ የፌዴራል የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሐብታሙ ክብረት ጋር ያደረግነውን ቆይታ ለንባብ እንዲመች አድርገን ይዘን ቀርበናል።

የሙያ ደረጃ ምደባና የብቃት ምዘና ሥራዎችጉባኤው ካተኮረባቸው ጉዳዮች አንዱ የሙያ

ደረጃ ምደባና የብቃት ምዘና ሥራዎች በምን መልኩ እንደተከናወኑና የሚታዩ ችግሮችን በትኩረት ገምግሟል። በዚህም የተደራሽነት ጉዳይ፤ ሙያ ደረጃ ጥራት ችግር እና ነባር የሙያ ደረጃዎች ክለሳ ላይ መዘግየቶች ታይተዋል። የአዳዲስ ሙያ ዝግጅት ጉዳይም የተነሳ ሲሆን፤ የአርሷደር የብቃት ምዘናና የአጫጭር ስልጠና የሙያ ብቃት ምዘና እንዲሁም በኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን የሚደገፉ የጥቃቅንና አነስተኛ አንቀሳቃሾች ምዘና አፈጻጸም ዝቅተኛ መሆኑም ጎልቶ ተነስቷል።

ለምሳሌ፣ በአርሷደር ምዘና የዓመታዊ እቅዱ በጣም ሰፊ መሆን፤ እንዲሁም የሥራ ምዘናና ገበያ ተኮር አጫጭር ስልጠና፣ ስልጠናው ከተጠናቀቀ በኋላ በምዘና መቋጨት እንዳለበት እቅድ ላይ ተቀምጦ ነበር። ይሄም ቢሆን አፈጻጸሙ ደካማ ሆኖ ታይቷል። የጥቃቅንና አነስተኛውም በተመሳሳይ ዝቅተኛ መሆኑ ታይቷል። በእነዚህ ላይም ዝርዝር ግምገማና ሰፊ ውይይት በማድረግ አቅጣጫ ተቀምጧል።

በዚህም የአጫጭር ስልጠናዎች ዘላቂነት እንዲኖራቸው ማስቻልና ማንኛውም ስልጠናም ውጤታማ እንዲሆንና ዘላቂነት እንዲኖረው ማድረግ እንደሚገባ ጉባኤው አስምሮበታል።የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንም በአራቱ የድጋፍ ማዕቀፎች ከተሰጠ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽኑ የጥራት መለኪያው ምዘና

እንደመሆኑ ሥራው ዘላቂና አስተማማኝ ሆኖ የልማታዊ ባለሀብት መፈልፈያና የኢንዱስትሪያሊስቶች መሰረት እንዲሆን ማስቻል እንደሚገባ ተመላክቷል።

የሙያ ደረጃዎችም ቢሆኑ ጊዜ ያለፈቻቸው እየታዩ በኢንዱስትሪው ፍላጎት መሰረት እንዲከለሱ የሚል አቅጣጫ ተቅምጧል። በዚህ ረገድ በተለይ በቀጣይ አራት ወራት ሊከናወኑ የሚገባቸውን ተግባራት በመለየት በእቅዱ ያልተፈጸሙና የተንከባለሉትንም ኃይልን አስተባብሮ መሥራት እንደሚገባ ተመልክቷል። በዚህም ከሙያ ዝግጅት ጀምሮ ተጨማሪ የሙያ መሣሪያ ዝግጅት ሥራ እቅድንም በአራት ወራት ውስጥ ለማሟላት በጉባኤው መስማማት ተችሏል።

የሰልጣኝ አሰልጣኝ ልማትና የተቋም ግንባታ

ጉባኤው የተመለከተውና በርካታ ነገሮች የተነሱበት ሌላው ጉዳይ የሰልጣኝ አሰልጣኝ ልማትና የተቋማት ግንባታ ሲሆን፤ በዚህም ካለው ነባራዊ ሁኔታ አኳያ ሲታይ የሰልጣኝ ቅበላ ሂደቱ የተሻለ መሆኑ ተገምግሟል። የአጫጭር ስልጠናም ቢሆን በተሻለና ጥራት ባለው መንገድ እየተሰጠ መሆኑ ታይቷል። በተለይ አንዳንድ ክልሎች በጥራት ዙሪያ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተቀናጅተው በመሥራት ያሳዩት ተግባር መልካም ጅምር መሆኑ የታየ ሲሆን፤ የልምድ ልውውጥም ተካሂዶበታል።

የተቋማት ግንባታን በተመለከተም አዳዲስ

ኮሌጆችን በማቋቋም በተለይም ህዝብን በማስተባበር ኮሌጆችን በወረዳ ደረጃ ለማዳረስ የተደረጉ ጥረቶች መኖራቸው የታየ ሲሆን፤ በዚህ ረገድ ጥሩ የሠሩ ክልሎች (እንደ ሶማሌ ክልል ያሉ ታዳጊ ክልሎች ሳይቀር የክልሉ መንግሥት ከፍተኛ በጀት በመመደብ ሞዴል የሚሆኑ አዳሪ ኮሌጆችን በመገንባት) በሞዴልነት ወጥተው ተሞክሯቸውን ማስተላለፍ ችለዋል። የአሰልጣኞች ጉዳይን በተመለከተም በአሰልጣኝ ቅጥር ረገድ ጥሩ ነገር መኖሩ ተገምግሟል።

ይሁን እንጂ በዚህ ጉዳይ ስር የተከናወኑ መልካም ሥራዎች የመኖራቸውን ያክል በእጥረትነት የተነሱም አሉ። ከእነዚህ መካከል አንዱ፣ የአካል ጉዳተኞችን ተጠቃሚ በማድረግ በኩል አፈጻጸሙ ዝቅተኛ እንደመሆኑ በቀጣይ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ተገምግሟል። በአጫጭር ስልጠናዎችም ቢሆን አሁንም ድረስ ምዘና ሳያልፉ የሥራ ዕድል እየተፈጠረላቸው መሆኑ፤ መደበኛ ስልጠና አጠናቃቂዎችም በተመሳሳይ ሁኔታ ከሥራ ማስተሳሰር መኖሩ እንደክፍተት የተነሳ ነው።

በተለይ አጫጭር ስልጠና ላይ ከውጭ ስምሪት ጋር በተያያዘ ከሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ጋር ተያይዞ ለግል ኮሌጆች የተሰጠ ቢሆንም፤ የጥራት ችግርና ኪራይ ሰብሳቢነት ስሜት እንዳለበት ተገምግሟል። በፈቃድ አሰጣጥ ሂደት ላይም ተናብቦ ያለመሥራት በመኖሩም እነዚህ ታርመው በተለይ ከአገር ገጽታ መበላሸት ጋር

የሚያያዝ እንደመሆኑ በትኩረት ሊሠራበት እንደሚገባ ተለይቷል። የተቋማትን ስታንድርድ ጠብቆ ኦዲት በመሥራትም የሚጎድላቸው በመኖሩ እንዲስተካከል አቅጣጫ ተቀምጧል። ለዚህም በህግና አሠራር መሰረት እንዲመራና በዚያው አግባብ የክትትልና ድጋፍ ስርዓቱ እንዲከናወን ይደረጋል።

የ”ሲ” ደረጃ አሰልጣኞች ጉዳይም በተለይ ከ”ሲ” ስልጠና መቼ እንወጣለን፣ የሚለው በጉባኤው በስፋት የተነሳ ሲሆን፤ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት አሰልጣኞችን ደረጃ በደረጃ በአሠራርና ሕግ መሰረት አቅማቸውን ማብቃት እንደሚገባም ተመላክቷል። የዘርፉን ስትራቴጂ ማስፈጸሚያ ደንብና መመሪያዎች መውጣት እንደሚገባቸውና እስከአሁንም ባልጸደቁ መመሪያዎች መሥራት በመኖሩ ትክክል ስላልሆነ አሁን ላይ በረቂቅ ደረጃ ያሉ መመሪያዎች ቶሎ ጸድቀው ወደሥራ እንዲገባባቸው የሚል ሃሳብም ተነስቷል።

በቴክኒክና ሙያ ዘፍር ሴቶችን በአሰልጣኝነትና በአመራርነት በማሳተፍ ረገድ አሁንም ክፍተት እንዳለ ተለይቷል። ይሄንንም በደንብና መመሪያ መመለስ ስለሚገባ በዚያው አግባብ ለመተግበር የሚያስችሉ ጅምር ሥራዎች አሉ። እንደ አጠቃላይ የሰልጣኝ አሰልጣኝ ልማትና የተቋማት ግንባታ ሥራው ምንም እንኳን ብዙ ርቀት የተሄደ፣ በቀጣይም ሥራው የሚሠራ ቢሆንም የታዩ ክፍተቶች በቀጣይ አራት ወራት በትኩረት ተሠርቶ ሊታረሙና ሊስተካከሉ እንደሚገባቸው፤ በውጤት ተኮር አሠራሩ መሰረትም በቀሪው ጊዜ የዓመቱን እቅድ ለማሳካት መሥራት እንደሚገባም አቅጣጫ ተቀምጧል።የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ልማት ሥራዎች

ሦስተኛው የጉባኤው አብይ ጉዳይ በቴክኒክና ሙያ ስልጠና ስትራቴጂ መሰረትም የቴክኒክና ሙያ ተቋማት የጥቃቅንና አነስተኛ መፈልፈያና የቴክኖሎጂ ማዕከል እንደሚሆኑ ባስቀመጠው አግባብ እየተሠራ መሆን አለመሆኑን በስፋት የተመለከተበት ነው። ከዚህ አኳያ ያለው ጅማሮ ጥሩ እርሾ ያለው ስለመሆኑ፤ ነገር ግን በጥራት ዙሪያ ደንበኞችን ማርካት ላይ ጉድለት እንዳለ ተለይቷል። ይህ ደግሞ አንደኛ፣ በአስተሳሰብ ወጣ ገባነት የተፈጠረ እንደሆነና አሰልጣኞችም ሆነ ተቋሙ ይህ ተግባር የእኔ ነው ብለው አለመያዛቸው፤ ሁለተኛም የአጋር አካላትና የአስፈጻሚ አካሉ ተቀናጅቶ አለመሠራት፤ ሦስተኛም፣ በፌዴራል ደረጃ የወረደው የጋራ እቅድ ታች ላይ ተግባራዊ አለመሆን ውጤት ነው።

ከቴክኖሎጂ ጋር በተያያዘም፣ ቴክኖሎጂን የማፍለቅ ሂደት ከአሰልጣኞች የዕድገት ደረጃ ጋር መያያዝን ጉባኤው እንደ ችግር ተመልክቶታል። ምክንያቱም አንድ አሰልጣኝ አንድ ቴክኖሎጂ ማውጣት አለበት የሚለው ሊያሠራቸው እንዳልቻለና ቴክኖሎጂው ደግሞ በባህሪው ለአንድ መምህር ቀርቶ በአንድ

ተቋም ሊሠራ እንደማይችል በመገንዘብ መመሪያው መታየት እንዳለበት ግንዛቤ ተይዟል። ለዚህም ጥናት ተደርጎ በጥናቱ ግኝት መሰረት እንዲሠራ አቅጣጫ ተቀምጧል። ሆኖም ጥቃቅንና አነስተኛን መደገፍ እንደ ሸክም የሚታይ ሳይሆን ከዚህ ተቋም የሚጠበቅ እንደመሆኑ በዚህ ላይ ሁሉም በባለቤትነት መሥራት እንደሚገባቸው ነው የተቀመጠው።

የዘርፉን ገጽታ ከመገንባት አኳያ በተቋሞች የሚሠሩ ቴክኖሎጂዎችንና ሌሎችንም የፈጠራ ሥራዎች ፌስቲቫል በማዘጋጀት ህዝቡ እንዲያያቸውና ግንዛቤ እንዲይዝባቸው ማድረግ እንደሚገባ ተመላክቷል። ይሄንንም ከተቋም ጀምሮ ሁሉም በየደረጃው ካካሄደ በኋላ በዚህ ዓመት (ሰኔ መጀመሪያ) በአገር አቀፍ ደረጃ የቴክኖሎጂ ፌስቲቫል የሚካሄድበት አቅጣጫ ተቀምጧል።

እንደ ማጠቃለያጉባኤው በእነዚህና ሌሎች ጉዳዮች ላይ በስፋት

ተወያይቶና ችግሮችን ለይቶ አቅጣጫ አስቀምጠቋል። ሆኖም ችግሮቹ ሰፊና ሰብሰብ ያሉ እንደመሆናቸው በተወሰኑ ጊዜ ይፈታሉ ተብሎ አይወሰድም። እናም እንደየባህሪያቸው በአጭር፣ በመካከለኛና በረዥም ጊዜ የሚፈቱ ይሆናል። ከዚህ አኳያ ከላይ የተጠቃቀሱትን ጨምሮ በርከት ያሉ ሥራዎች በአራት ወር ውስጥ ይፈታሉ ተብሎ የተቀመጡ ሲሆን፤ የተቀሩት የተግባር እቅድ(አክሽን ፕላን) የሚፈልጉ ናቸው። ምክንያቱም የፖሊሲና ስትራቴጂ ችግሮች አሉ፤ የአሠራርና አደረጃጀት ችግሮች አሉ፤ የፋይናንስ፣ የቴክኖሎጂና የሰው ኃይል ችግሮች አሉ።

ለምሳሌ፣ በዘርፉ የፋይናንስ ጉዳይ ትልቅ ችግር ነው። ይህ ግን የረዥም ጊዜ የፋይናንስ ምንጭ በማፈላለግ እንጂ በዚህ አራት ወር ውስጥ ሊፈታ አይችልም። በተመሳሳይ የሰው ኃይልና የመምህራን ችግርን በቀንም ሆነ በማታ መርሐ ግብሮች በምን መልኩ ሠርቶ ማብቃት ይቻላል በሚለው ላይ ሠርቶ የሚመጣ ውጤት ነው። የ”ሲ” አሰልጣኞችንም ወደ “ቢ” ደረጃ ለማሳደግ እንዴት ይኬዳል የሚለውም በተከናወነ ጥናት መሰረት ወደተግባር የሚገባ ይሆናል። የምዘና ስርዓቱን ማሻሻል፣ በተለይ ከሐሰተኛ ማስረጃ ጋር በተያያዘ የሚስተዋሉ ችግሮችን ከማስወገድ አኳያ የምዘና ስርዓቱን የማዘመንና አገራዊ ባህሪ ማስያዝን ስለሚጠይቅም በዚህ ላይ የተጀመሩ ሥራዎች አሉ። እነዚህ ደግሞ በአጭር ጊዜ ሳይሆን በመካከለኛና በረዥም ጊዜ ሥራ የሚፈቱ መሆናቸው ታይቷል።

በመሆኑም ጉባኤው፣ በእቅድ ተይዘው ያልተፈጸሙትን ከማሳካትም ሆነ በስትራቴጂ የሚመለሱትን ሥራዎች ከዳር ለማድረስ እንዲቻል፤ የፌዴራል አካላት፣ ክልሎች፣ ኮሌጆችና አጋር አካላት በተናጥልም ሆነ በጋራ ለመሥራት የየድርሻቸውን ኃላፊነት ለመወጣት የቤት ሥራ የወሰዱበት ነው።

የቴክኒክና ሙያ ዘርፉ የለውጥ ጅማሮ

ሰላማዊት ውቤ

ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ቀናቶች የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ አቶ ነጉሱ ጥላሁን ለሀገሪቱ ዋንኛ ቴሌቪዥን ጣቢያ ሲናገሩ እንደተደመጠው በጌዴኦ ላሉ ተፈናቃዮች የዕለት ምግብ ተደራሽ ለማድረግና ለዘለቄታው ለማቋቋም መንግሥት ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ ነው።

ዛሬ ምግብና ሌሎቸ ድጋፎችን ፈላጊ ተፈናቃዮች በጌዴኦ ዞን ብቻ ሳይሆን በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ይገኛሉ። ከወደ ትምህርት ሚኒስቴር ኮሚኒኬሽን ዳይሬክቶሬት የወጣው መረጃ እንደሚጠቁመው በእነዚህ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ከሚገኙ ተፈናቃዮች መካከል ቁጥራቸው እጅግ ብዙ የሆኑ ተማሪዎችም ይገኙባቸዋል።

የእነዚህ ተማሪዎች ቁጥር በትምህርት ቤት ወይም በመጠለያ የምገባ ፈላጊው ቁጥር በእጅጉ እንዲጨምር አድርጎታል። በኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር በትምህርት ቤት ማሻሻል መርሐ ግብር ባለሙያና የትምህርት ቤት ምገባ ተጠሪ አቶ አሸናፊ ጌታቸው እንደሚናገሩት ቁጥሩን የጨመሩት በተለይ በድርቅ የሚጠቁ አካባቢዎችና በግጭት ምክንያት ከአካባቢያቸው የተፈናቀሉ ተማሪዎች ናቸው። ከግጭትና በዚሁ ሳቢያ ከተፈጠረ መፈናቀል ጋር ተያይዞ የተመጋቢ ተማሪዎቸ ቁጥር በእጅጉ ቢጨምርም ቁጥራቸው በዛም ሆነ አትመገቡም ማለት አይቻልም።

በአሁኑ ወቅት እንደ ትምህርት ሚኒስቴር መደበኛውንም ሆነ በድርቅ ከሚጠቁ አካባቢዎችና በግጭት ምክንያት ከአካባቢያቸው የተፈናቀሉ ተማሪዎችን ለመመገብና ማንኛውንም ትምህርትን ለማስቀጠል ግብዓት የሚሆን ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችል ሥራው ጎን ለጎን እየተካሄደ ይገኛል።እስከአሁን ባለው ጊዜ ለእነዚህ ተማሪዎች በኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴርና በክልሎች ከአልባሳት ጀምሮ የትምህርት መርጃ መሣሪያዎችንና የምግብና መጠለያ ድጋፍ ሲደረግ ቆይቷል። አሁን ላይም ይሄን ድጋፍ በዘላቂነት

አጠናክሮ ለማስቀጠል ትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ይገኛል።

ከጥረቱ ዋናው ደግሞ ተማሪዎች በምግብ እጦት ምክንያት ትምህርት እንዳያቋርጡና በትምህርታቸው ውጤታማ እንዲሆኑ ኃላፊነት የመወጣት ሥራ መሠራት እንዳለበት አምኖ በጀት እንዲመደብ እየተንቀሳቀሰ መሆኑ ነው። እንደ ባለሙያው በጀቱ ከግጭት ጋር ተያይዞ በደረሰ መፈናቀል ዙሪያ ለተማሪዎች ተደራሽ ለማድረግ ትምህርትን በአደጋ ጊዜ የማስቀጠል ጉድኝትን ተንተርሶ በዘንድሮ ትምህርት ዘመን የተያዘ ሲሆን ድጋፉን ምን ያህሉና በምን ያህሉ ክልሎችና አካባቢዎች ያሉ ናቸው የሚሹት የሚለውም አኦኤም በሚያወጣቸው የተፈናቃይ ተጎጂ ተማሪዎችን እና ሌሎችንም የዳሰሳ ጥናት ተለይቷል። በዚህ ጥናት መሰረት ምን ያህል ተማሪዎች በጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያዎች እንዳሉ የታወቀ ሲሆን በተለየው መረጃ መሰረት እንደ ሀገር በአጠቃላይ አንድ ነጥብ አንድ ሚሊዮን የሚደርሱ ተማሪዎች ተፈናቅለዋል ተብሎ ይታሰባል።

እነዚህን የምገባ መርሐ ግብር ተደራሽ ለማድረግ በኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር የተዘጋጀ ዕቅድ አለ። ከፌዴራልና ከክልል የሚያስፈልገው በጀትም ተለይቷል። በጀቱ ከፌዴራሉና ከየክልሎቹ ምን ያህል ይጠበቃል ለሚለው ምላሽ የሚሰጥ ሲሆን በአጠቃላይ 296 ሚሊዮን 173 ሺህ 921 ብር ይፈለጋል። ከፌዴራል የሚጠበቀው በጀት 236 ሚሊዮን 939 ሺህ 137 ብር ሲሆን ከክልሎች ደግሞ ወደ 59 ሚሊዮን 234 ሺሀ 784 ብር እንደሚፈለግም ባለሙያው አጫውተውናል። ይሄው በጀት ታዲያ በደቡብ፣ አማራ፣ኦሮሚያ ፣ሶማሌና ቤንሻንጉል ክልሎች ለሚገኙ ተጎጂዎች ከፌዴራልና ክልሎች ተመድቦ ወደ ምገባ ፕሮግራሙ ሲስተም እንዲገባ የማድረግ እንቅስቃሴ እየተካሄደ ነው። በጀቱ ምገባ ብቻ ሳይሆን የትምህርት መርጃና ሌሎች አልባሳትም የሚሸፈኑበት ነው። የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር ይሄን ዕቅድ ለሠላም ሚኒስቴርና ለአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ልኮ በመጠባበቅ ላይ ይገኛል። ከክልልና ከፌዴራል የሚመደበው

ይሄ በጀት ተፈናቃይ ተማሪዎቹን ወደ ትምህርት ለማምጣት የሚያስችል ቢሆንም አልተፈቀደና ለተማሪዎቹ ማድረስ አልጀመረም።

በአጠቃላይ ባለሙያው በአሁኑ ወቅት ከዚሁ ጎን ለጎን እየተካሄደ ያለውን መደበኛ ምገባ መርሐ ግብር አስመልክተው እንዳብራሩልን እንደ ሀገር በተለያየ መንገድ ለምሳሌ፦ የክልል ትምህርት ቢሮዎች በጀት ይዘው የሚያካሂዱት፣በዓለም የምግብ ፕሮግራም በጀት ተመድቦ የሚደረጉ እንዲሁም የተለያዩ በጎ አድራጎት አካላት ትምህርት ቤቶች ላይ በመገኘት የሚያካሂዱት የምገባ መርሐ ግብር አለ።

በተለያዩ ድርጅቶች በተካሄደው ምገባ በ39 ወረዳዎች ላይ 602 ትምህርት ቤቶች የሚገኙ 264 ሺህ ተማሪዎችን ተጠቃሚ ያደረገ ሥራ ተሠርቷል። እንዲሁም ክልሎች በጀት መድበው በተካሄደ መርሐ ግብር በተለይ አማራ ደቡብና ጋንቤላ 493 ትምህርት ቤቶች የሚገኙ 303 ሺህ 345 ተማሪዎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርጓል።

በዓለም ምግብ መርሐ ግብር በጀት ተይዞ በተካሄደው መርሐ ግብር ደግሞ በ849 ትምህርት ቤቶች የሚገኙ 313 ሺሀ 395 ተማሪዎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርጓል። እንደ አጠቃላይ በ2011 የትምህርት ቤት ምገባ መርሐ ግብር ተጠቃሚ የሆኑ ተማሪዎች ቁጥር 880 ሺህ 806 ነው።

ሀገር በቀል ሲባል ሀገር ውስጥ የሚበቅሉ ሰበሎች ወይም ጥራጥሬዎች ለተማሪዎቹ ምገባ እንዲውሉ የሚደረግበት መርሐ ግብር ሲሆን በዚህ በኩል በ39 ወረዳዎች 252 ሚሊዮን 383 ሺህ 68 ብር አካባቢ ወጪ ሆኗል። በክልሎች ደግሞ ተለይተው በተያዙ በ493 ወረዳዎች 54 ሚሊዮን 200 ሺህ ብር በጀት ጠይቋል። የዓለም ምግብ መርሐ ግብር ደግሞ 63 ሚሊዮን 963 ሺህ 88 ብር በጀት ተይዞ ምገባው ተካሂዷል። በአጠቃላይ ከፌዴራል የሚጠበቀው በጀት 236 ሚሊዮን 939 ሺህ 137 ብር ሲሆን ከክልሎች ደግሞ ወደ 59 ሚሊዮን 234 ሺህ 784 ብር ጠቃላይ 370 ሚሊዮን 546 ሺህ 156 ብር በጀት ተይዞ ተማሪዎቹ የምገባ መርሐ ግብር ተጠቃሚ እንዲሆኑ የተደረገበት እንቅስቃሴ ነበር።

በዘንድሮ ትምህርት ዘመን በተለያዩ ግጭቶች ምክንያት ከአማራ፣ከደቡብ፣ከኦሮሚያ ከሶማሌና ቤንሻንጉል ጉምዝ

ክልሎች የተፈናቀሉ ተማሪዎችን በምግብና በተለያዩ የትምህርት ግብዓቶች ለመደገፍ ከፌዴራል መንግሥት 236 ሚሊዮን 939 ሺህ 137 ብር ከክልሎች ደግሞ 59 ሚሊዮን 234 ሺሀ 784

ብር ገደማ ይጠበቃል።

ለአንድ ነጥብ አንድ ሚሊዮን ተፈናቃይ ተማሪዎች ድጋፍ የማድረግ ጥረት

አቶ አሸናፊ ጌታቸው፤

ከነዚህ ተፈናቃዮች አብዛኞቹ ተማሪዎች በቅርቡ ወደ ትምህርት ገበታ የሚመለሱበት ሁኔታ እየተመቻቸ ነው፤

Page 9: 78ኛ ዓመት ቁጥር 189 ሰኞ መጋቢት 9 ቀን 2011 ዓ.ም ያንዱ ዋጋ 5.75 …ማድረግ ላይ የመምህራን የሙያ ስብጥርና ብቃት ውስንነት፣

14 መጋቢት 9 ቀን 2011 ዓ.ም

• ለኤችአይቪይበልጥተጋላጭነን!

እንመርመርራሳችንንእንወቅ።

በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ

በዓለም ከቀዳሚ ተወዳጅ ሊጎች መካከል ይጠቀሳል፤ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ። ነገር ግን በአንድ ነገር ይታማል፤ ክለቦቹ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ በሚያሳዩት ደካማ ብቃት። ለዚህም በማሳያነት የሚነሳው የሊጉ ተሳታፊ ክለብ(ቼልሲ) ለመጨረሻ ጊዜ ባለ ጆሮ ረጅሙን ዋንጫ ያነሳው እአአ በ2012 መሆኑ ነው። ከዚህም ባሻገር በዚህ የውድድር መድረክ የተሻለ ታሪክ መጻፍ የቻለው ክለብ ሊቨርፑል ብቻ ነው።

በዘንድሮው ሻምፒዮንስ ሊግ ግን፤ ከተለመደው ውጪ አራት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ክለቦች ለሩብ ፍጻሜው ደርሰዋል። ዋንጫውን ለተከታታይ ዓመት ለማንሳት በግስጋሴ ላይ የሚገኘው የፔፕ ጋርዲዮላው ማንቺስተር ሲቲ፣ የሊጉን ዋንጫ ለመጀመሪያ ጊዜ የክለባቸው ለማድረግ እየተጉ ያሉት ቀያዮቹ ሊቨርፑሎች፣ በአዲሱ አሰልጣኛቸው ከነበሩበት ቀውስ ወጥተው አስደማሚ የውድድር ዓመት በማሳለፍ ላይ የሚገኙት ቀያዮቹ ሰይጣኖቹ ማንችስተር ዩናይትዶች እንዲሁም በውድድር ዓመቱ የዋንጫ ተፋላሚ ከሆኑት መካከል አንዱ ቶትንሃም ሆትስፐር ናቸው።

እአአ ከ1999 ጀምሮ ባሉት የውድድር ዓመታት የእንግሊዝ ክለቦች የተሻለ እንቅስቃሴ ያሳዩት በ2007/2008 እና 2008/2009 ነው። በወቅቱ አራት አራት ክለቦቻቸው ስምንት ውስጥ የገቡ ሲሆን፤ ከዚያን በፊትም ይሁን በኋላ ግን ዕድሉን አላገኙም። ከአራቱ ክለቦች የሻምፒዮንስ ሊጉን ዋንጫ ያነሱት ሁለቱ ክለቦች ብቻ ሲሆኑ፤ ማንቸስተር ሲቲ እና ቶተንሃም ግን በመድረኩ የተመዘገበ የአሸናፊነት ታሪክ የላቸውም።

በአንጻሩ የላሊጋው ክለቦች በመድረኩ ጫና የፈጠሩ ሲሆን፤ ያለፉትን አምስት ዋንጫዎችም የስፔን ክለቦች ነበሩ የወሰዷቸው። በተለይ በዚህ ውድድር ስኬታማ የሆነው ሪያል ማድሪድ፤ አንድ ጊዜ በተቀናቃኙ ባርሴሎና የበላይነቱን አሻግሮ ከመስጠት ባለፈ ለአራት ተከታታይ ዓመታት ዋንጫውን በማንሳት አቻ ያልተገኘለት ክለብ ነው። ነጫጮቹ ዋንጫውን ለ13ጊዜያት በማንሳትም ማንም የማይደርስበትን ክብረወሰን አርቀው ሰቅለዋል።

ለክለቦች በየሃገራቱ ከሚካሄዱት የሊግ ጨዋታዎች ባሻገር በዚህ ውድድር ውጤት ማስመዝገብ በእግር ኳስ ታላቅ ክብርን የሚያቀዳጅ ነው። ከዚህም ባሻገር ከአውሮፓ ምርጥ ክለቦች ተወዳድሮ አሸናፊ የሚሆነው ክለብ ምርጥ የመባል እንዲሁም በባሎን ድ ኦርም

ተጫዋቾችን የማስመረጥ ሰፊ ዕድል ይፈጥርለታል። የፕሪምየር ሊጉ ግለቦችም ይህንን ለማሳካት እንደሚፋለሙም ይጠበቃል።

በአራቱ ዓመታት ተሳትፏቸው ለሶስት ጊዜያት ስምንት ውስጥ መግባት የቻሉት ውሃ ሰማያዊዎቹ ዋንጫውን ማንሳት የዚህ ዓመት ስኬታቸው ነው። አሰልጣኙ ፔፕ ጋርዲዮላ ፕሪምየር ሊጉን ከመቀላቀላቸው አስቀድሞ ከባርሴሎና ጋር ሁለቴ ዋንጫውን ያነሱ ሲሆን፤ ክለባቸው በሻምፒዮንስ ሊጉ የነበረው እንቅስቃሴ ለአሸናፊነት ሊያበቃቸው እንደሚችልም ይገመታል። ለዚህም ከሻካታር ዶንቴስክ እና ከሻልክ ጋር በነበራቸው ጨዋታ ያስመዘገቡት ውጤትም ማሳያ ነው። የክለቡ አጥቂ ሰርጂዮ አጉዌሮ አሁንም ግብ በማምረት ላይ ሲሆን፤ በየ70 ደቂቃው አንድ ግብ እያስቆጠረ እንደሚገኝም የሻምፒዮንስ ሊጉ መረጃ ያሳያል።

እአአ በ2017 የውድድር ዓመት 16 ውስጥ መግባት የቻለው ቶትንሃምም በተመሳሳይ ከስምንቱ ክለቦች መካከል አንዱ ሆኗል። የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ሩብ ፍጻሜ ድልድል መሰረትም ሁለቱ ክለቦች ከሊጋቸውም አልፈው አቅማቸውን የሚለኩበት መድረክ ፈጥሮላቸዋል።

ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ይፋ በተደረገው በዚህ የጨዋታ መርሃግብር መሰረትም አንድ የእንግሊዝ ቡድን ግማሽ ፍጻሜውን መቀላቀል እንደሚችል ማረጋገጥ ይቻላል። በአንድ ጎል ብልጫ የተለያየ ደረጃ ላይ የተቀመጡት የሁለቱ ክለቦች የግብ አምራቾች አጉዌሮ እና ሃሪ ኬይንም ለክለባቸው ግቦችን በማስቆጠር ይፎካከራሉ።

ያለፈው የውድድር ዓመት ለፍጻሜ ደርሰው

በሪያል ማድሪድ የተሸነፉት ቀያዮቹ፤ በመድረኩ የተሻለ ተሳትፎ አላቸው። የአምስት ጊዜ የዋንጫ ባለቤት የሆኑት ሊቨርፑሎች በምድብ ጨዋታዎች የነበራቸው እንቅስቃሴ ጥሩ የሚባል ሲሆን፤ በሩብ ፍጻሜው ከፖርቶ ጋር የሚገናኙ ይሆናል። ያለፈው ዓመት 16 ውስጥ የተገናኙት ሁለቱ ክለቦች በሊቨርፑል ሰፊ የጎል ብልጫ መጠናቀቁም የሚታወስ ነው።

በቀድሞው የክለቡ ተጫዋችና በአሁኑ አሰልጣኛቸው ሶሻየር ከነበሩበት ያገገሙት ማንችስተር ዩናይትዶች፤ ጉዳት እየፈተናቸውም የፈረንሳዩን ክለብ ፒኤስጂን ያሸነፉበት ውጤት አስደናቂ የሚባል ነበር። ቀያዮቹ ሰይጣኖች ሶስት ጊዜ ዋንጫውን በማንሳት ከእንግሊዝ ክለቦች ሁለተኛውን ስፍራ ይይዛሉ። በሩብ ፍጻሜ ድልድሉ የሚገናኙት ከስፔኑ ኃያል ክለብ ባርሴሎና ጋር ሲሆን፤ ይህም ጨዋታ ሳይፈትናቸው እንደማይቀር ይጠበቃል። ሁለቱ ክለቦች እአአ 2009 እና 2011 የፍጻሜ ጨዋታ ቢገናኙም ድሉ የካታሎኑ ክለብ ነበር።

ስምንቱን ከተቀላቀሉት ክለቦች መካከል ከእንግሊዝ ክለቦች ውጪ የተገናኙት ደግሞ አያክስ እና ጁቬንቱስ ናቸው። አያክስ ከሊቨርፑል ቀጥሎ አራት ዋንጫዎችን በማንሳት የሚቀመጥ ክለብ ሲሆን፤ በኮከቡ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ሃትሪክ ሳይታሰብ ሩብ ፍጻሜውን የተቀላቀለው የጣሊያኑ ክለብ ሁለቴ የዋንጫ ባለቤት ሆኗል።

በግማሽ ፍጻሜውም የማንቺስተር ሲቲ እና የቶትንሃም አሸናፊ ከጁቬንቱስና አያክስ አሸናፊ ጋር የሚገናኝ ይሆናል። የማንችስተር ዩናይትድና ባርሴሎና አሸናፊ ደግሞ ከሊቨርፑል እና ፖርቶ አሸናፊ ጋር ይጫወታል።

የአፍሪካ ብስክሌት ሻምፒዮና ነገ ይጠናቀቃል

ብርሃን ፈይሳ

ብርሃን ፈይሳ

በዘንባባ ያሸበረቀው የውቧ ባህርዳር ጎዳናዎች ባላለፉት ቀናት ከመኪና ይልቅ ብስክሌቶች ነበሩ የሚታዩባት። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ብስክሌት መጠቀም እየቀነሰ የመጣባት ባህርዳርም በርካታ አፍሪካዊያን የብስክሌት ጋላቢዎችን ስታስተናግድ ቆይታ ለማጠናቀቅ አንድ ቀን ብቻ ቀርቷታል።

ኢትዮጵያ ያላት የመልከዓምድር አቀማመጥ እንዲሁም ከአየሩ ጋር በተያያዘ ለብስክሌት ስፖርት ምቹ መሆኗ ይነገራል። በተለይ በትግራይ እና በአማራ ክልሎች ደግሞ ተዘውታሪነቱ የላቀ ነው። አብዛኛውን ጊዜ ኢትዮጵያን ወክለው እስከ ኦሊምፒክ መሳተፍ የቻሉ ጋላቢዎች ከትግራይ ክልል የተገኙ ናቸው። ክልሉ በርካታ ክለቦችን በመያዝ ወጣቶችን የሚያሰለጥን ሲሆን፤ ያፈራቸው ስፖርተኞችም በውጭ ሃገራት ክለቦች እስከ መጫወት ደርሰዋል።

በአማራ ክልልም በተመሳሳይ በርካታ የብስክሌት ስፖርተኞች የሚወጡ ሲሆን፤ ጥረት ኮርፖሬሽንን እና አምባሰልን የመሳሰሉ ክለቦችን ማንሳት ይቻላል። በአፍሪካ አህጉር ትልቅ የሆነውን ብስክሌት ሻምፒዮናም ክልሉ (ባህርዳር ከተማ) በማካሄድ ላይ ትገኛለች።

በአፍሪካ ብስክሌት ኮንፌዴሬሽን የሚመራው የአፍሪካ ብስክሌት ሻምፒዮና በየዓመቱ የሚካሄድ ውድድር ሲሆን፤ የዘንድሮው ለ14ኛ ጊዜ ነው። ያለፈው ዓመት መጨረሻ የኮንፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ከኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን ጋር በመወያየትም ከመግባባት ደርሰዋል። በዚህም መሰርት ለአዘጋጅነቱ ፍላጎት ካሳዩት ከተሞች መካከል ባህርዳር የፌዴሬሽኑን መስፈርት በማሟላት ተመራጭ ሆናለች።

በዚህም መሰረት ላለፉት ስድስት ወራት ዝግጅት ሲካሄድ ቆይቶ፤ ውድድሩ በደማቅ ሁኔታ በመካሄድ ላይ የሚገኝ ሲሆን፤ ነገ ይጠናቀቃል። ይህንን ውድድሩን ከሌላው ጊዜ ለየት የሚያደርገው የ2020 የቶኪዮ ኦሊምፒክ ማጣሪያ በመሆኑ ነው፤ በመሆኑም በርካታ ሃገራት ተሳታፊ እንደሚሆኑ ይጠበቅ ነበር። ይሁን እንጂ ከ46ቱ የኮንፌዴሬሽኑ አባል ሃገራት የተመዘገቡት 17 ሲሆኑ፤ በውድድሩ ላይ እየተካፈሉ ያሉት ግን 13 ቡድኖች፤ 180

ልዑካን ናቸው። በውድድሩ ላይ እየተሳተፉ የሚገኙትም አዘጋጇን ኢትዮጵያ ጨምሮ፤ ቡርኪናፋሶ፣ ሩዋንዳ፣ ኤርትራ፣ ቤኒን፣ ኮትዲቯር፣ ግብፅ፣ ናሚቢያ፣ ሞሪሽየስ፣ ሲሼልስ፣ አልጄሪያ፣ ዴሞክራቲክ ኮንጎ እና ደቡብ አፍሪካ ናቸው።

ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በተካሄደው የመክፈቻ መርሐ ግብር ላይም፤ የክልሉ ፕሬዚዳንት ዶክተር አምባቸው መኮንን፣ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳውና ሚኒስትር ዴኤታው ሀብታሙ ሲሳይ፣ የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ርስቱ ይርዳ፣ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር ወልደ ጊዮርጊስ፣ የአፍሪካ ብስክሌት ማህበር ፕሬዚዳንት ዶክተር መሃመድ ወጋይ፣ የኢትዮጵያ ብስክሌት ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ወርቁ ገዳ እንዲሁም የክልል እና የሃገራት ፌዴሬሽን ሥራ አስፈጻሚ አባላት ተገኝተዋል።

ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በተጀመረው በዚህ ሻምፒዮና በመጀመሪያው ዕለት ኢትዮጵያ ሦስት ወርቅ እና አንድ ነሐስ በማስመዝገብ ነበር መምራት የጀመረችው። በወጣት ሴቶች 15 ኪሎ ሜትር የቡድን ክሮኖ ኢትዮጵያዊያኑ ብስክሌተኞች ተፎካካሪያቸውን ኤርትራዊያንን በመብለጥ የወርቅ ሜዳሊያውን ወስደዋል። በአዋቂ ሴቶች 30 ኪሎ ሜትር የቡድን ክሮኖም በተመሳሳይ የወርቅ ሜዳሊያውን ወስደዋል። በወጣት ወንዶች የ30 ኪሎ ሜትር የቡድን ክሮኖም የበላይነቱ በኢትዮጵያዊያን

ሲያዝ በአዋቂ ወንዶች 46 ነጥብ 6 ኪሎ ሜትር የነሐስ ሜዳሊያውን ወስደዋል።

ኢትዮጵያ ከአዘጋጅነቷ ባሻገር በውድድሩ ተሳታፊ እንደመሆኗ ዝግጅቷን ቀድማ ነው የጀመረችው። ባለፈው ታኅሣሥ ወር የብሄራዊ ቡድን ምልመላ የተካሄደ ሲሆን፤ በተደረገው ማጣራት 35 የብስክሌት ጋላቢዎችን በብሄራዊ ቡድኑ በማካተት አንድ ወር ያህል ልምምድ ሲደረግ ቆይቷል።

ኢትዮጵያ በዚህ ሻምፒዮና እንደ ኤርትራ እና ደቡብ አፍሪካ የተሻለ ስም ያላት ሃገር ስትሆን፤ ከረጅም ዓመታተ በኋላ በሪዮ ኦሊምፒክ በስፖርቱ መሳተፏም ይታወሳል። በአምናው ሻምፒዮና ቡድኑ ሁለተኛ በመውጣት አመርቂ ውጤት አስመዝግቧል። አሁን ደግሞ በራሳቸው አየር ላይ በሚያደርጉት ውድድር የተሻለ ውጤት እንደሚመዘገብ የሚጠበቅ ሲሆን፤ በዚህም በቶኪዮ ኦሊምፒክ ኢትዮጵያ የምትወከልበት አንድ ስፖርት ይሆናል።

ውድድሩ አራት ተግባራትን የሚያጠቃልል ሲሆን፤ እነርሱም በቡድን የሰዓት ሙከራ፣ በግል የሰዓት ሙከራ፣ የጎዳና ውድድር እንዲሁም ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚካሄደው የቅልቅል ውድድር ናቸው። ይህ ውድድር 50 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ሲሆን፤ ሦስት ሴት እና ሦስት ወንዶች ርቀቱን እኩል ተካፍለው በቅብብል ይወዳደራሉ።

የእንግሊዝ ክለቦች የሻምፒዮንስ ሊጉ ጉዞቡድኑ በቻን ዝግጅት ላይ ግብረ መልስ ይሰጣል

ብርሃን ፈይሳ

በሃገር ውስጥ ሊጎች ብቻ ለሚጫወቱ ተጫዋቾች ዕድል ለመስጠት በሚል የተጀመረው የቻን ዋንጫ፤ በየሁለት ዓመቱ እየተካሄደ አሁን ስድስተኛው ላይ ደርሷል። ኢትዮጵያ ደግሞ የስድስተኛው የቻን ዋንጫ አዘጋጅ እንድትሆን ከአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ፈቃድ ከተሰጣት ከዓመት በላይ ሆኗታል። የቀራት የመሰናዶ ጊዜም በወራቶች የሚቆጠር ዕድሜ ብቻ ነው ያለው።

ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን እንዲሁም ከሌሎች መንግስታዊ አካላት ጋር የሚያከናውነው ስራ ጊዜውን ከግምት ያስገባ አይመስልም። አዲስ ዘመን ጋዜጣ በተለያዩ ጊዜያት በጉዳዩ ላይ በሰራው ዘገባ ፌዴሬሽኑ የተለያዩ ስራዎችን በማከናወን ላይ እንደሚገኝ ነው የገለጸው። ውድድሩን የማዘጋጀት ፍላጎትና ዝግጁነት መኖሩንም እንዲሁ፤ ነገር ግን ስራው በግልጽ የሚታይ አልሆነም።

በቻን የሚሳተፉት ሃገራት 16 ሲሆኑ፤ በአራት አራት ቡድኖች ተከፍለውም በአንድ ስታዲየም ውድድራቸውን ያደርጋሉ። በዚህም መሰረት አራት ስታዲየሞች ለውድድሩ አስፈላጊ በመሆናቸው፤ በአዲስ አበባ ከተማ በመገንባት ላይ የሚገኘው ብሄራዊ ስታዲየም፣ የባህርዳር፣ የመቐሌ እና የሃዋሳ ስታዲየሞች ተመርጠዋል። ዝግጅቱን አስመልክቶ የካፍ የባለሙያ ቡድኖች በየወቅቱ ቅኝት የሚያደርጉ ሲሆን፤ ባሳለፍነው ሳምንትም በኢትዮጵያ በነበረውን ጉብኝት አጠናቆ መመለሱን ሶከር ኢትዮጵያ አስነብቧል።

ለአምስት ቀናት በነበረው ጉብኝት ልኡኩ በስታዲየሞቹ ተዘዋውሮ የዝግጅቱን ግምገማ በማጠናቀቅ ተመልሷል። በቅኝቱ መሰረትም የቻን 2020 የኢትዮጵያ መሰናዶ ምን ደረጃ ላይ ይገኛል የሚለውን ግብረ መልስ በተያዘው

ሳምንት ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እና ለሀገሪቱ መንግስት እንደሚልክም ታውቋል።

ባለፈው ሐሙስ አዲስ አበባ የገቡት የቡድኑ አባላት፤ አርብ ዕለት በሀዋሳ ዓለም አቀፍ ስታዲየም ጉብኝታቸውን በማድረግ ነው ግምገማቸውን የጀመሩት። ጉብኝቱን በመቀጠልም በመቐለ የትግራይ ዓለም አቀፍ ስታዲየምን ተመልክተዋል። በቅኝታቸውም የመጫወቻ ሜዳውን፣ በስታዲየሙ ቅጥር ግቢ የተሰራውን የመለማመጃ ሜዳ እንዲሁም የመቐለ ዩኒቨርሲቲን ስታድየም ጎብኝተዋል። በስታድየሙ ውስጣዊ እና ውጫዊ ምልከታ ካደረጉ በኋላም በሀዋሳ ስታዲየም የተገጠመው መብራት በመቐለ አለመከናወኑን እንደ ጉድለት ማንሳታቸውን ዘገባው ጠቁሟል።

ሶስተኛ መዳረሻቸውን በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታድየም በማድረግም፤ የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ (ፔዳ ጊቢ) የአፄ ቴዎድሮስ ስታድየም የመለማመጃ ሜዳውን ተመልክተዋል። ከትናንት በስቲያም የመጀመሪያ ዙር ግንባታው በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘውን ብሄራዊ ስታዲየም ጎብኝተዋል። በዚህም ስታዲየሙ የሚጠናቀቅበትን ጊዜ አስመልክቶ ጥያቄ ማቅረባቸውን ሶከር ኢትዮጵያ አስታውሷል።

ውድድሩ ከሚካሄድባቸው ስታዲየሞች ባሻገር ለልምምድ የሚያገለግሉትን በወጣቶች አካዳሚ ያሉ ሁለት ሜዳዎችን እንዲሁም አንጋፋውን የአዲስ አበባ ስታዲየም ተመልክተዋል። በሰጡት ግብረመልስ መሰረትም አንድ ተጨማሪ የመለማመጃ ሜዳ በቶሎ መሰራት እንዳለበት ለፌዴሬሽኑ አሳስበዋል።

በቅኝት ቡድኑ የተካተቱት፤ የካፍ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት የሆኑት ሊሆድጋር ቴንጋ እና ሞሰስ ማጎጎ፣ የካፍ የክለቦች ፍቃድ ሰጪ ኃላፊ አህመድ ሀራዝ እንዲሁም ሁለት የሚዲያ ባለሙያዎች ናቸው።

ቡድኑ የኦሊምፒክ ዝግጅቱን

ቀጥሏልብርሃን ፈይሳ

እአአ በ2020 በጃፓን ቶኪዮ ለሚካሄደው ኦሊምፒክ በእግር ኳስ ለመሳተፍ ብሄራዊ ቡድኖች የማጣሪያ ጨዋታቸውን በማድረግ ላይ የሚገኙ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድንም በመጪው ሐሙስ ይጫወታል። በዝግጅት ላይ የሚገኘው ቡድኑ በዕቅዱ መሰረት ባለፈው ሳምንት ሁለት የወዳጅነት ጨዋታዎችን አካሂዷል።

የብሔራዊ ቡድኑ ዋና አሰልጣኝ አብርሃም መብራቱ ያለፉትን ወራት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በመዘዋወር እና ባልደረቦቻቸውንም ወደ ስታድየሞች በማሰማራት ከፕሪምየር ሊጉ እና ሌሎች ሊጎች ለኦሊምፒክ ቡድኑ የሚሆኑ ተጫዋቾችን ሲመለከቱ ቆይተዋል።

በዚህም በሀገሪቱ ሁለተኛ ሊግ ከሆነው ከፍተኛ ሊግ ስምንት ተጫቾችን ማካተት ተችሏል። አሰልጣኙ ለወጣት ተጫዋቾች ምርጫ ወደ ከፍተኛ ሊግ ቢያመሩም የተመለከቱት ግን በአንፃራዊነት ለረጅም ጊዜ የተጫወቱ እና በእግር ኳስ ጊዜያቸው በማብቃት ላይ የሚገኙት በርካታ ተጫዋቾች እንደሆኑ መታዘባቸውን ለሶከር ኢትዮጵያ በሰጡት አስተያየት ጠቁመዋል።

በምልመላቸውም ለቡድኑ አንድ የውጭ ተጫዋችን ጨምሮ ለ34 ተጫዋቾች ጥሪ አድርገዋል። በጥሪው መሰረትም ቡድኑ ማረፊያውን በዋቢ ሸበሌ ሆቴል በማድረግ ልምምዱን የጀመረው ባለፈው ሳምንት ሲሆን፤ ከሲሺየልስ ብሄራዊ ቡድን ጋር ሁለት የወዳጅነት ጨዋታዎችንም አከናውኗል።

የአቋም መለኪያ ጨዋታዎቹን ተከት ሎም ለቡድኑ ብቁ የሆኑ ተጫዋቾችን በመለየት ከቡድኑ ጋር አብረው የሚቀጥሉ ይሆናል። በዚህም በቅድሚ 26 ተጫዋቾችን በመምረጥ ስምንቱ የተቀነሱ ሲሆን፤ በቀጣይም ሦስት ተጫዋቾችን ወደ ክለባቸው እንዲመለሱ ተደርገዋል። ሐሙስ በአዲስ አበባ ስታዲየም ከማሊ ጋር ለሚደረገው ጨዋታም ቡድኑ ዝግጅቱን ቀጥሏል። የመልሱን ጨዋታም በ19 ባማኮ ላይ የሚያደርግ ይሆናል።

በዚህ ውድድር ህግ መሰረት የወንዶች ቡድን ተጫዋቾች ከ23 ዓመት በታች ሲሆኑ፤ በሴቶች በኩል ግን የዕድሜ ገደብ አልተደረገባቸውም። የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድንም በማጣሪያው የሚሳተፍ ሲሆን፤ የመጀመሪያ ጨዋታውንም በቀጣዩ ወር ማገባደጃ ላይ ያደርጋል።

ቡድኑ አሰልጣኝ ሳይኖረው የቆየ በመሆኑ አዲስ አሰልጣኝ መቅጠር አስ ፈላጊ በመሆኑ ፌዴሬሽኑ አሰልጣኞችን አወዳድሯል። በዚህም በሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ብሄራዊ ቡድኑን ስትመራ የቆየችው የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ አሰልጣኟ ሰላም ዘርዓይ ማለፏ ታውቋል። በመሆኑም ቡድኑ በቅርቡ ጥሪ ተደርጎለት ወደ ልምምድ እንደሚገባ ይጠበቃል።

በውድድሩ ላይ የሚሳተፉት 15የወንድ ቡድኖች ሲሆኑ፤ ከስድስት ኮንፌዴሬሽኖች የተወጣጡ ሃገራትም ይሆናሉ። ጃፓን ለእግር ኳስ ጨዋታዎቹ አምስት ስታ ዲየሞችን አዘጋጅታለች። ብራዚል እና ጀርመን በሪዮው ኦሊምፒክ በወንድና በሴት ሻምፒዮን የሆኑ ቡድኖችም ናቸው።

ኢትዮጵያዊያን አሸናፊ የሆኑበት የቡድን ውድድር፤