36
ቃለ-ጉባኤ ሲምፖዚየም ኢትዮጵያ አባይን ለልማት በመጠቀም መብትና አስፈላጊነት ላይ የምሁራን ተልእኮ BDU CLUSTER & CDS ሚያዚያ 20-21/2006; ባህር ዳር, ኢትዮጵያ

BDU CLUSTER & CDS - 1st Nile... · bdu cluster & cds ሚያዚያ 20-21 ... ተ/ብርሀን የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ- ... የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ

Embed Size (px)

Citation preview

Page 1: BDU CLUSTER & CDS - 1st Nile... · bdu cluster & cds ሚያዚያ 20-21 ... ተ/ብርሀን የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ- ... የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ

ቃለ-ጉባኤ ሲምፖዚየም

ኢትዮጵያ አባይን ለልማት በመጠቀም መብትና አስፈላጊነት ላይ የምሁራን ተልእኮ

BDU CLUSTER & CDS ሚያዚያ 20-21/2006; ባህር ዳር, ኢትዮጵያ

Page 2: BDU CLUSTER & CDS - 1st Nile... · bdu cluster & cds ሚያዚያ 20-21 ... ተ/ብርሀን የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ- ... የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ

ቃለ-ጉባኤ - ኢትዮጵያ አባይን ለልማት በመጠቀም መብትና አስፈላጊነት ላይ የምሁራን ተልእኮ - ሚያዚያ 20-21/2006; ባህር ዳር, ኢትዮጵያ

1 | P a g e

ኢትዮጵያ አባይን ለልማት በመጠቀም መብትና አስፈላጊነት ላይ የምሁራን ተልእኮ “INTELLECTUALS IMPERATIVES ON ETHIOPA’S UTILISATION OF

THE NILE FOR DEVELOPMENT” በሚል ርዕስ የተካሄደው ወርክሾፕ

ቃለ-ጉባኤ

የስብሰባ ቦታ:- ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ/ኦዲተሪየም

ቀን:- 20/08/2006 ዓም

በሲምፖዚየሙ የተገኙ እንግዶችና ተሳታፊዎች

1. የተከበሩ ፊልድ ማርሻል ኡማር ሐሰን አልበሽር፤ የሱዳን ሪፖብሊፕሬዚዳንት

2. የተከበሩ አቶ ካሳ ተ/ክለብርሃን፤ የኢፌዲሪ የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ

3. አቶ ብናልፍ አንዱአለም፤ የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምክትል ር/መስተዳደር

4. የፌደራል ሚኒስትሮችና ከፍተኛ ባለስልጣናት

5. የ34ቱ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዚዳንቶችና ም/ፕሬዚዳንቶች

6. ከአማራ ክልል ከተለያዩ ቢሮዎች ጥሪ የተደረገላችው እንግዶች

7. የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክና አስተዳደር ስታፍ ሰራተኞች

8. የኢትዮጵያ ተማሪዎች ህብረት ፕሬዚዳንትና ተወካዩች

የስብሰባው ሪፖርት አቅራቢዎች:- አቶ በላቸው ጌትነት(ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ) እና አቶ ውብነህ በለጠ(አማራ ዲዛይን እና ቁጥጥር ሥራዎች ድርጂት)

የስብሰባው አጀንዳ:-

ኢትዮጵያ አባይን ለልማት በመጠቀም መብትና አስፈላጊነት ላይ የምሁራን ተልእኮ

በሚል በሚካሄደው ሲምፖዚየም ለሁለት ቀናት (April 28-29 2014) ለውይይት

የሚቀርቡ አጀዳዎችን በማስተዋወቅ ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት የተጀመረ ሲሆን፤ በሁሉቱ

Page 3: BDU CLUSTER & CDS - 1st Nile... · bdu cluster & cds ሚያዚያ 20-21 ... ተ/ብርሀን የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ- ... የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ

ቃለ-ጉባኤ - ኢትዮጵያ አባይን ለልማት በመጠቀም መብትና አስፈላጊነት ላይ የምሁራን ተልእኮ - ሚያዚያ 20-21/2006; ባህር ዳር, ኢትዮጵያ

2 | P a g e

የውይይት ቀናት የሚደረግባቸው ውይይቶችና የሚቀርቡ ፅሁፎች በፕሮፌሰር አብይ

ይግዛው እንድሚከተለው ቀርበዋል::

በመጀመሪያው የእንኳን ደህና መጣችሁ በዶ/ር ባይሌ ዳምጤ፤ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ

ፕሬዚዳንት፣ የመክፈቻ ንግግር በክቡር አቶ ካሳ ተ/ብርሀን የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ-

ጉባኤ እና የዕለቱ ክብር እንግዳ፤ በመቀጠል በክቡር ፊልድ ማርሻል ኡማር ሐሰን

አልበሽር፤ የሱዳን ሪፖብሊክ ፕሬዚዳንት በሚያቀርቡት ንግግር ወደ ዕለቱ መወያያ

አጀንዳዎች እንደሚገባ ፕሮግራም አስተዋዋቂው ገልፀዋል፡፡

የዕለቱ መወያያ አጀንዳዎች፤

1) በናይል ወንዝ እና በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ የሚካሄዱ ምርምሮችና

ህትመቶች (CONCEPT NOTE ON RESEARCH AND PUBLICATION ON THE

NILE RIVER & GRAND ETHIOPIAN RENAISSANCE DAM - GERD)

2) የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይና ብሔራዊ ደህንነት ፖሊሲ መሰረታዊ መርሆች መሆናቸው

ተገልጿል፡፡

በሁለተኛው ቀን ደግሞ በአባይ ተፋሰስና በአባይ ውሃ አጠቃቀም ዙሪያ 4 (አራት)

ጽሁፎች እንደሚቀርቡና ውይይት እንደሚካሄድባቸው ሲገለጽ የጽሁፎቹም ርዕስ

እንደሚከተለው የዕለቱ ፕሮግራም መሪ ፕሮፌሰር አብይ አቅርበዋቸዋል::

1) ውሃና የውሃ ህግ ሁኔታዎች በናይል ወንዝ (Hydro-legal regime of the Nile river); by

Dr Mussa M., MoWDE

2) የውሃ ፖለቲካ እና ዲፕሎማሲ በናይል ወንዝ ተፋሰሰ (Hydro-politics and Diplomacy

in the Nile River basin); by Ato Ermias Ayalew, BDU, school of law

3) የናይል ውሃ ሀብት አጠቃቀምና የምሁራን ተልዕኮ (Overview of Nile Hydrology and

imperatives of intellectuals); by Ato Goraw Goshu, BDU, BNWI

4) ናይል ሚዲያና ምሁራን- የኢትዮጵያን የናይል ውሃን ለመጠቀም ባላት ፍላገት በንቁ

መሳተፍ አስፈላጊነት (The Nile, the media and Intellectuals; a need for proactive

engagement for constructive discourse in the Nile basin to maximize Ethiopia’s

interest on Nile), by Zerihun Abebe, AAU

Page 4: BDU CLUSTER & CDS - 1st Nile... · bdu cluster & cds ሚያዚያ 20-21 ... ተ/ብርሀን የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ- ... የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ

ቃለ-ጉባኤ - ኢትዮጵያ አባይን ለልማት በመጠቀም መብትና አስፈላጊነት ላይ የምሁራን ተልእኮ - ሚያዚያ 20-21/2006; ባህር ዳር, ኢትዮጵያ

3 | P a g e

ከላይ የተገለፁትን አጀንዳዎች ለታዳሚዎች ካቀረቡ በኋላ የዕለቱ ፕሮግራም ተጀምሯል::

I. የመጀመሪያ ቀን ስብስባ:- 20/08/06 ዓ.ም

የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር

በዶ/ር ባይሌ ዳምጤ - የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት

የተከበሩ ኡመር ሐሰን አልበሽር የሱዳን ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት፤ የተከበሩ አቶ ካሳ

ተ/ክለብርሃን የኢፌድሪ የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ፣ የተከበሩ አቶ ብናልፍ

አንዱአለም፣ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክትል ፕሬዚዳንት፣ አቶ ላቀ

አያሌው፡ የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ፣ የተከበራችሁ ሚኒስትሮች፤ የ34ቱ

የመንግስት ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶችና ም/ፕሬዚዳንቶች፤ የተማሪዎች ህብረት ኃላፊዎችና

ሌሎች የተጋበዛችሁ እንግዶች፣

ክቡራንና ክቡራት

በመጀመሪያ ወደ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ እንኳን ደህና መጣችሁ እያልኩ ፕሬዚዳንት ኡመር

ሐሰን አልበሽር በመካከላችን በመገኘትዎ ከፍተኛ ክብር ተሰምቶኛል፡፡ የዛሬዋ ዕለት

ለዩኒቨርሲቲያችን የተለየችና ታሪካዊ ቀን ነች፡፡ ሚያዚያ 20 ቀን 2014 ዓ.ም የተከበሩ

ፊልድ ማርሻል ኡመር ሐሰን አልበሽር ዩኒቨርሲቲያችንን የጎበኙባት ታሪካዊ ቀን በመሆንዋ

ስናስታውሳት እንኖራለን፡፡

ሚስተር ፕሬዚዳንት፤ በአፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙ ምሁራን ከመሪዎቻቸው ጋር ያላቸው

ግንኙነት የላላ እንደሆነና ለየአገሮቻቸው እድገት የሚጠበቅባቸውን ሚና ለመወጣት አሉታዊ

ተፅእኖ እንደፈጠረባቸው ከፍተኛ ቅሬታ ያሰማሉ፡፡ በመሆኑም መሪዎቻቸው ወደ

ዩኒቨርሲቲዎች በመምጣት ከምሁራንና ከተማሪዎች ጋር መልካም ግንኙነት እንዲፈጠርና

የሚፈለገውን ሰብአዊ ልማት ግንባታ እውን ማድረግ ይፈልጋሉ፡፡ በአህጉራችን ያሉ መሪዎች

የአገራችውን ልማት ለማፋጠን ሌት ተቀን ይሰራሉ፡፡ ነገር ግን የተደረጉት ጥረቶች

አህጉራችን ያለባትን ዘርፈ-ብዙ ችግሮች ለመቅረፍ አልቻሉም፡፡ ዩኒቨርሲቲዎች መንግስታት

የሚተገብሯቸውን ኢኮኖሚያዊ፤ ፖለቲካዊና ማህበራዊ የልማት ስራዎች ለማገዝ በጥሩ ቁመና

ላይ አይደሉም፡፡ ምክንያቱ ደግሞ በአፍሪካ ያሉ ዩኒቨርሲቲዎች ትኩረት የሚሰጡት ለንድፈ

Page 5: BDU CLUSTER & CDS - 1st Nile... · bdu cluster & cds ሚያዚያ 20-21 ... ተ/ብርሀን የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ- ... የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ

ቃለ-ጉባኤ - ኢትዮጵያ አባይን ለልማት በመጠቀም መብትና አስፈላጊነት ላይ የምሁራን ተልእኮ - ሚያዚያ 20-21/2006; ባህር ዳር, ኢትዮጵያ

4 | P a g e

ሃሳብ (Theories) እንደሆነና ንድፈ ሃሳቦችን (Theories) ወደ አፍሪካ ተጨባጭ ሁኔታ

በማምጣት ለአገራቸው ለውጥ ጥረት እንደሚያደርጉ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ መሪዎቻችን

ወደ ዩኒቨርሲቲዎች በመምጣት፣ ንድፈ ሃሳቦችን የአገራቸው ተጨባጭ ሁኔታ በማምጣትና

ወደ ተግባር ለመለወጥ ለአገራቸው እድገት ከፍተኛ ሚና እንዲጫወቱ ጥረት ማድረግ

ይጠበቅባቸዋል፡፡ በዩኒቨርሲቲዎች ያለውን እምቅ አቅም በመጠቀም የአገራቸውን ልማትን

ጥረት እንዲያግዝ ጥረት ማድረግ አለባቸው፡፡ ተጨባጭ የሆኑ ነገሮችን በክፍል ውስጥ

ማስተማር ጉልህ ጠቃሚ አለው፡፡ ልማትን ለማፋጠን የሚደረገው ጥረት እውን የሚሆነው

ንድፈ ሃሳቦች (Theories) ወደ ተግባር የአገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ከግምት ውስጥ ለማስገባት

ተግባራዊ ሲሆኑ ብቻ ነው፡፡ ንድፈ ሃሳቦች (Theories) ካለ ተግባራዊ ስራ ጥቅም ሊሰጡ

አይችሉም፡፡ ተግባራዊ እንቅስቃሴዎች በንድፈ ሃሳብ (Theories) ካልተደገፈ ለውጥ

አያመጡም፡፡

የምዕራባዊያን ዩኒቨርሲቲዎች ከመሪዎቻቸውና ሌሎች አገሮች መሪዎች ጋር የጠበቀ

ግንኙነት አላቸው፡፡ ምሁራንና ተማሪዎቻቸው ከመሪዎቻቸው ጋር በተለያዩ ጉዳዩች ጠንካራ

ውይይቶችን በማካሄድ ለአገሮቻቸው ብሎም ለሌሎች የአለም ክፍሎች ያሉ ችግሮችን

ለመፍታት ከፍተኛ አስተዋፅኦ አድርገዋል፡፡ በአፍሪካ አገሮች የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎችና

የአገር መሪዎች መካከል ጠንካራ ግንኙነት በመፍጠር ምዕራባዊያን ዩኒቨርሲቲዎች ለአገራቱ

ልማት ያበረከቱትን አስተዋጽኦ በአፍሪካም መድገም ይቻላል፡፡ የእርስዎና የፌደሬሽን ምክር

ቤት አፈ-ጉባኤ እንዲሁም ሌሎች ሚኒስተሮችና ባለስልጣናት እዚህ መገኝት ወደፊት

በዩኒቨርሲቲያችንና በመሪዎቻችን መካከል ጠንካራ ግንኙነት ለመፍጠር የመሰረት ድንጋይ

ነው፡፡ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ይህን አይነት ሲምፖዚየም ለወደፊት በጠነከረ መልኩ

እንዲካሄድ ጥረት ያደርጋል፡፡

ሚስተር ፕሬዚዳንት ዩኒቨርሲቲያችን 40 ሺ ተማሪዎችን ተቀብሎ በ8 ካምፓሶች በማስተማር

ላይ ሲሆን አገሪቱ ውስጥ ካሉ ግዙፍ ዩኒቨርሲቲዎች አንዱ ነው፡፡ ከሱዳን አቻ ዩኒቨርሲቲዎች

ጋር ግንኙነታችን ለማሳደግና ለማጠናከር በመስራት ላይ ነን፡፡ ከካርቱም ዩኒቨርሲቲ ጋር

አጫጭር ኮርሶች ፕሮግራም ግንኙነት ፈጥረናል፡፡ ከያላ ዩኒቨርሲቲ ጋርም ግንኙነት

ለመፍጠር በሂደት ላይ ነን፡፡ እዚህ ሲምፖዚየም ላይ ከተለያዩ የአገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎች

ፕሬዚዳንቶች ይገኛሉ፡፡ ሁሉም ከሱዳን ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ጠንካራ ግንኙነት በመፍጠር

Page 6: BDU CLUSTER & CDS - 1st Nile... · bdu cluster & cds ሚያዚያ 20-21 ... ተ/ብርሀን የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ- ... የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ

ቃለ-ጉባኤ - ኢትዮጵያ አባይን ለልማት በመጠቀም መብትና አስፈላጊነት ላይ የምሁራን ተልእኮ - ሚያዚያ 20-21/2006; ባህር ዳር, ኢትዮጵያ

5 | P a g e

በጋራ ለመስራት ፍላጎት አላቸው፡፡ ዛሬ የፌደራል ሚኒስተሮች፤ የክልሉ ከፍተኛ

ባለስልጣናት፤ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዚዳንቶችና ም/ፕሬዚዳንቶች፤ የተማሪዎች

ህብረት ተወካዩችን ሌሎችም በምሁራን ሚና ለመወያየት እዚህ ይገኛሉ፡፡ በዚህ ሲምፖዚየም

ስለ ታላቁ ህዳሴ ግድብ ዘርፈ-ብዙ ጠቀሜታና የናይል ወንዝ ፍትሃዊ አጠቃቀም ላይ ትኩረት

ሰጥተን እንወያያለን፡፡ በውይይቱ ብዙ ጠቃሚ ሃሳቦች እደሚነሱና ለውሳኔ ሰጪ አካላት

ግብዓት እንደሚሆኑና የሲምፖዝየሙ ተሳታፊዎች ግንዛቤ እንደሚጨብጡ እንጠብቃለን፡፡

የተከበሩ ፊልዱ ማርሻል ኡመር ሐሰን አልብሽር ከዚህ ታሪካዊ ሲምፖዘየም ላይ

በመገኘታቸው ለማመስገን እንደገና እንዲፈቅድልኝ በትህትና እጠይቃለሁ፡፡ በመጨረሻም

የተከበሩ አቶ ካሳ ተ/ክለብርሃን፣ የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤና የዕለቱ የክብር እንግዳ

የመግቢያ ንግግር እንዲያደርጉልንና ክቡር ፕሬዚዳንት አልበሽርን እንዲጋብዙልን ጠቃሚ

የሆኑ መልዕክቶችን እንዲያስተላልፉልን በትህትና እጠይቃለሁ፡፡

የመክፈቻ ንግግር

በክቡር አቶ ካሳ ተ/ብርሃን፣ የኢፌዴሪ የፌደሬሽን ምክር አፈ-ጉባኤና የዕለቱ የክብር ዕንግዳ

የተከበሩ ፊልድ ማርሻል ኡመር ሐሰን አልበሽር፤ የሱዳን ሪፖብሊክ ፕሬዚዳንት፤

የተከበራችሁ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ ባለስልጣናትና ሌሎች የሲምፖዚየሙ

ተሳታፊዎች፤ የተከበሩ ፕሬዚዳንት አልበሽር በዚህ ሲምፖዚየም ላይ እንዲገኙ

ያቀረብንላቸውን ግብዣ በመቀበል በመካከላችን በመገኘታቸው የተሰማኝን ከፍተኛ ደስታ

ልገልፅላችሁ እወዳለሁ፡፡ ከሁሉ አስቀድሜ በዚህ ታሪካዊ መድረክ ላይ ተገኝቼ የመግቢያ

ንግግር እንዳደርግ እድሉ ስለተሰጠኝ በራሴና በፌደሬሽን ምክር ቤት ስም ምስጋናየን

አቀርባለሁ፡፡

እንደሚታወቀው ይህ መድረክ በአባይና በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ላይ የሚያጠነጥን ቢሆንም

በዋናነት በሀገራችን ልማትና ዲሞክራሲያዊ ግንባታ ላይ የሚያጠነጥን እንደሚሆን ሁላችንም

እንገነዘባለን፡፡ የመጀመሪያው አገራችን ከሁለተኛው ሚሊኒየም በኋላ አገራችን በህዳሴ ጉዞ

ላይ እንዳለች እየገለጽን ነው ያለነው፡፡ ለዚህ ህዳሴ ጉዞ መነሻ የሚሆነው አገራችን በአንድ

ወቅት የስልጣኔ ማማ ላይ ነበረች፡፡ እንደሚታወቀው አገራችን የስልጣኔ ማማ ላይ የነበረችና

ለብዙ አመታት የነበሩባት ውስጣዊ ችግሮች እጅግ ወደ ኋላ ቀርታ በአለም ላይ በድህነትና

Page 7: BDU CLUSTER & CDS - 1st Nile... · bdu cluster & cds ሚያዚያ 20-21 ... ተ/ብርሀን የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ- ... የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ

ቃለ-ጉባኤ - ኢትዮጵያ አባይን ለልማት በመጠቀም መብትና አስፈላጊነት ላይ የምሁራን ተልእኮ - ሚያዚያ 20-21/2006; ባህር ዳር, ኢትዮጵያ

6 | P a g e

በኋላ ቀርነት ከሚታወቁት አገሮች ትታወቃለች፡፡ ይህን ለመቀየር ባለፉት ሃያ አመታት

አዲስ የህዳሴ ምዕራፍ እንደጀመረችና ይህም በአሁኑ ትውልድ ሊረጋገጥ እንደሚችል

ተቀምጧል፡፡ ዛሬ የምንነጋገርበት ታላቁ የህዳሴ ግድብ ህዳሴያችንን ለማረጋገጥ ቁልፍ

የልማት አጀንዳችን ነው፡፡ አገራችን የጥንታዊ ስልጣኔ መነሻዋ ኪነ ህንፃ ላይ የተመሰረተ

እንደሆነ ምሁራን ያስረዳሉ፡፡ በሌላ በኩል የጀመርነውን የህዳሴ ጉዞ እውን የሚሆነው በውሃ

ሃብት ላይ የተመሰረተ የእድገት ፍልስፍና መሰረት ስናደርግ እንደሆነ ያስረዳሉ፡፡ ለረዥም

ዘመናት እኛ ኢትዮጵያዊያን ውሃን በከፍተኛ ደረጃ እንፈራዋለን፡፡ ብዙዎቻችን በአደግንበት

አካባቢ ብዙ ወንዞችንና ሌሎች የውሃ ምንጮችን የሰይጣን ባህር በማለት ውሃን

እንድንፈራው፤ በውሃ ላይ አንዳንመራመርና ውሃን ጥቅም ላይ እንዳናውለው እንቅፋት ሆኖ

ቆይቷል፡፡ ስለዚህ ይህን አመለካከት በመቀየር፡ በውኃ ላይ የተመሰረተ የዕድገት ፍልስፍና

በመከተል ውሃን የእድገታችን ዋና መሰረት በማድረግ የአገራችን እድገት ወደ ላቀ ደረጃ

ማሳደግና በክፍለ አህጉራችን የሚኖረንን ድርሻ በሰላማዊ መንገድ ከፍ ማድረግ ነው፡፡

2ኛው በህዝባችን ውስጥ የነበረውን ስነልቦናና አመለካከት የመስበር ችሎታ አለው፡፡ ከዚህ

በፊት አባይን ለሃይድሮ ኤሌክትሪክ ሃይል መጠቀምና ለሌሎች ልማቶች እናውለዋለን የሚል

አመለካከት በህዝባችን የማይታሰብ •እንደነበር እናስታውሳለን፡፡ የግድቡ መሰራት ግን

በአገራችን በህዝብና መንግስት አቅም ሊሰሩ አይችሉም የሚለውን የቆየ አመለካከት የሰበረና

በህዝቡ ዘንድ በራስ መተማመንን እንዲጎለብት ከፍተኛ አስተዋፅኦ አድርጓል፡፡የዚህ አይነት

አመለካከት በህዝባችን ዘንድ መጎልበቱ የተጀመረው ልማት ወደ ኋላ እንዳይመለስ ከፍተኛ

አስተዋፅኦ ይኖረዋል፡፡ በአካባቢያችን ካሉ አገሮች ጋር ትስስርን በማጠናከር የጋራ ልማትና

ለውጥ እንዲኖር ያደርጋል፡፡ ይህ በውስጣችን በሚኖር ትጋትና ጥንካሬ ላይ የተመሰረተ

ነው፡፡

በ4ኛ ደረጃ የስስትና የስጋት አመለካከቶችና በዚህ ምክንያት የሚታዩ ጠባብ የሆኑ ፍላጎቶችና

አመለካከቶች የመስበር አቅም አለው፡፡ እዚህ ላይ የምናውለው ኢንቨስትመንትና የምናፈሰው

ጉልበት ለእኛ ብቻ አይደለም፡፡ ሁሉንም የናይል ተፋሰስ አገሮች የሚጠቅም ነው፡፡ ክቡር

ፕሬዚዳንት ፊልድ ማርሻል አልበሽር እንዳረጋገጡልን ኢትዮጵያ ውስጥ የሚሰሩ የልማት

ስራዎች በአገራቸው ላይ ተጨባጭ ለውጦች በማምጣት ላይ መሆናቸውንና የአገሪቱን

ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ላይ ናቸው፡፡ ስለሆነም በቀጠናው ውስጥ የሚኖረውን የጠባብነትና

የስስት አመለካከት የመስበርና የማስተካከል ትልቅ ድርሻ አለው፡፡

Page 8: BDU CLUSTER & CDS - 1st Nile... · bdu cluster & cds ሚያዚያ 20-21 ... ተ/ብርሀን የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ- ... የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ

ቃለ-ጉባኤ - ኢትዮጵያ አባይን ለልማት በመጠቀም መብትና አስፈላጊነት ላይ የምሁራን ተልእኮ - ሚያዚያ 20-21/2006; ባህር ዳር, ኢትዮጵያ

7 | P a g e

ሌላው ተጨማሪ ነጥብ የጀመርነው የህዳሴ ጉዞ አንድ ወቅት ተጀምሮ የሚቆም እንዳይሆን

የትውልዶችን የጋራ ጥረት የሚፈልግ ነው፡፡ ለጥረታችን መሳካትም በአገራችን አስተማማኝ

ሰላም መኖር አለበት ፡፡ በህዳሴው ግድብ የተገኘው ተስፋ ለሰላማችን ከፍተኛ አስተዋፅኦ

ይኖረዋል፡፡ በአገራቸው ውስጥ በሚደረጉ የልማት ስራዎች ለረዥም ዘመናት ተገልለው

የነበሩት የአገራችን ህዝቦች ተጠቃሚነትንም እውን ያደርጋል፡፡ ይህንን ለማረጋገጥ የምሁራን

ድርሻ ከፍተኛ ነው፡፡ ይህ መድረክ የምሁራን ድርሻ ምን መሆን እንዳለበት በግልፅ

እንደሚያሳይ ከፍተኛ እምነት አለኝ፡፡ በመጨረሻም የአገር ልማት ጥናት ማዕከልና የባህር

ዳር ዩኒቨርሲቲ ይህን የተሳካ ሲምፖዚየም/ መድረክ በማዘጋጀታቸው ከፍተኛ ምስጋናየን

አቀርባለሁ፡፡ የተከበሩ ፊልድ ማርሻል ኡመር አልበሽር ንግግር እንዲያደርጉልን በትህትና

እጋብዛለሁ፡፡

የሲምፖዚየሙ ዓብይ መልዕክት

በክቡር ፊልድ ማርሻል ኡመር ሐሰን አልበሽር- የሱዳን ሪፖብሊክ ፕሬዚዳንት

ክቡር አቶ ካሳ ተ/ብርሃን፤ የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ፣ ክቡር የአማራ ክልላዊ

መንግስት ምክትል ፕሬዚዳንት፤ ክቡራን የኢትዩጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዚዳንቶችና ምክትል

ፕሬዚዳንቶች ፣ ተማሪዎችና የወደፊት የአገሪቱ መሪዎች፤ ባለፉት ሶስት ቀናት ስለአፍሪካ

ሰላምና ደህንነት በሚመክረው 3ኛው የጣና ፎርም ላይ ተገኝቸ ነበር፡፡ በእነዚህ ቀናት

የከተማዋ አስተዳደርና የክልሉ መንግስት ላደረጉልን መልካም መስተንግዶ ምስጋናየን

አቀርባለሁ፡፡ በቆይታየ የባህር ዳር ከተማን እድገት ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ በክልሉ ያለውን

እድገት ለማየት ችያለሁ፡፡ይህ ለውጥ በክልሉ ህዝብ፤ መንግስትና በፌደራል መንግስት የጋራ

ጥረት የተገኘ ስለመሆኑ ጥርጥር የለኝም፡፡ በናይል ወንዝ አጠቃቀም ላይ የተሳካ መድረክ

በማዘጋጀታችሁ እንኳን ደስ አላችሁ እላለሁ፡፡ መድረኩ በየዓመቱ የጣና ፎርም በተካሄደ

በበነጋው እንደሚካሄድ እምነት አለኝ፡፡ በመድረኩ ላይ የምትወያዩባቸው ጉዳዮች የወንድሜን

የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ራዕይ ለማሳካት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳለው

ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ክቡራንና ክብራት፤ ወርክሾፑ የታለመለትን አላማ እንዲሳካ እየተመኘሁ

በመድረኩ በናይል ወንዝ ፍትሐዊ አጠቃቀም ላይ ትኩረት ሰጥታችሁ እንደምትወያዩ ተስፋ

አደርጋለሁ፡፡ በውይይቱ የተደረሰባቸው መግባቢያ ሃሳቦች በተፋሰሱ አገሮች ላሉ የፖሊሲ

አውጭና ለውሳኔ ሰጪ አካላት ግብአት እንደሚሆኑ እምነት አለኝ፡፡ በመጨረሻም

Page 9: BDU CLUSTER & CDS - 1st Nile... · bdu cluster & cds ሚያዚያ 20-21 ... ተ/ብርሀን የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ- ... የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ

ቃለ-ጉባኤ - ኢትዮጵያ አባይን ለልማት በመጠቀም መብትና አስፈላጊነት ላይ የምሁራን ተልእኮ - ሚያዚያ 20-21/2006; ባህር ዳር, ኢትዮጵያ

8 | P a g e

በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ መንግስት በዚህ ወርክ ሾፕ ላይ እንድገኝ

ስለተጋበዝኩኝ ከፍተኛ ምስጋና አቀርባለሁ፡፡

ለውይይት የቀረቡ የመያያ ሃሳቦች

1. በናይል ወንዝና በህዳሴ ግድብ ዙሪያ በምሁራን ሊሰሩ የሚገባቸው ጥናቶች አቅራቢ፤ አቶ

ዘፋንያ አለሙ እና የሴንተር ፎር ቨሎፕመንት ስተዲስ ዋና ስራ አስፈጻሚ (CDS)

አቶ ዘፋኒያ ኢትዮጵያ ከጥንት ጀምሮ የነበራትንና አሁን ያለችበት ሁኔታ በአራት ዋና ዋና

መገለጫዎች መድበውታል፡፡ የመጀመሪያው የረዥም ጊዜ ታሪክ ያላትና የስልጣኔ ባለቤት

የነበረች፤ 2ኛው መገለጫ የነፃነት ተጋድሎዋ ለሌሎች ጭቁን የሆኑ ህዝቦች አርዓያ የሆነች፤ 3ኛ

በአንድ ወቅት ብዙህነትን ማስተናገድ ተስኗት የመበታተን አደጋ ተጋርጦባት የነበረች እና

የመጨረሻው ብዙህነትን በማስተናገድ በፊት ከነበረችበት የስልጣኔ ቁንጮ በመጓዝ ላይ ያለች አገር

ናት፡፡

ኢትዮጵያ አባይን ለመጠቀም መሰረታዊ የሆነ መብት እንዳላትና መብቷንም በመጠቀም ህዳሴዋን

ማፋጠን እንዳለባት ለሁሉም ግልፅ ነው፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ የምሁራን ድርሻ ምን መሆን

አለበት የሚለው ዋናው የመድረኩ መወያያ አጀንዳ ነው፡፡ እንደሚታወቀው የህዳሴውን ግድብ

ተግባራዊ ለማድረግ ኢትዮጵያ ውሃውን የመጠቀም መብት እንዳላት ለማሳየት ሳይሆን

ኃላቀርነትና ድህነትን ለማስወገድ የሚደረጉ ጥረቶች ውስጥ ከፍተኛውን ድርሻ ስለሚይዝ ነው፡፡

ስለሆነም ግድቡን መገንባት የአገራችን የህልውና ጥያቄ ነው፡፡ የህዳሴውን ግድብና በሌሎች

የልማት እንቅስቃሴዎች ተግባራዊ በማድረግ የህዳሴውን ጉዞ ለማስቀጠል የምሁራ ድርሻ ሊሆን

የሚችለው፡፡

1. አዳዲስ ሃሳቦችን በማፍለቅ፤ መንግስትና ህዝብ በሚፈለገው አቅጣጫ እንዲጓዙ ማድረግ፤

2. አዳዲስ ሃሳቦችን ከተግባር ጋር በማቀናጀትና የልማት ስራዎችን መደገፍ፤

3. ዘመን ተሻጋሪ የሆኑ የምርምር ስራዎችን በመስራት ለፖሊሲ አውጪዎች ግብዓት

የሆኑ ሃሳቦችን ማመንጨት የመንግስትና

4. የወጡ ፖሊሲዎችና ስትራቴጅዎች በመተቸት ጠንካራ ጎናቸውንና ድክመታቸውን

ለፖሊሲ አውጪዎች ግልፅ አድርጎ ማሳየት መስተካከል ያለባቸውን አማራጭ ሃሳቦችን

በማሳየትና የአባይ ጉዳይ የኢትዮጵያ የህሊና ጉዳይ ለመሆኑ ሶስት ዋና ዋና መገለጫዎች

አሉት፡፡

Page 10: BDU CLUSTER & CDS - 1st Nile... · bdu cluster & cds ሚያዚያ 20-21 ... ተ/ብርሀን የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ- ... የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ

ቃለ-ጉባኤ - ኢትዮጵያ አባይን ለልማት በመጠቀም መብትና አስፈላጊነት ላይ የምሁራን ተልእኮ - ሚያዚያ 20-21/2006; ባህር ዳር, ኢትዮጵያ

9 | P a g e

በአባይ ተፋሰስ ውስጥ የሚኖረው የኢትዮጵያ ህዝብ በድህነትና ኃላቀርነት ችግሮች የተተበተበ

ነው፡፡ ወንዙን መጠቀም ለብዙ ዘመናት በድህነትና በኃላቀርነት ሲማቅቁ የነበሩ ህዝቦችን ችግር

መቅረፍ የህልውና ጉዳይ ነው፡፡ ምንም እንኳ አገራችን የምስራቅ አፍሪካ ውሃ ማማ ብትሆንም

ያላትን የውሃ ሃብት በመጠቀም ከውጭ ዕርዳታ ጥገኝነት ለመላቀቅ አልቻለችም፡፡ ስለዚህ

ወንዞቿን አባይን ጨምሮ ፍትሐዊ በሆነ መንገድ በመጠቀም ልማቷን ማፋጠንና ከጥገኝነት

ለመላቀቅ ሌላው የህልውና ጉዳይ ነው፡፡ ምሁራን የአባይን ወንዝ በፍትሐዊነት ባለው መንገድ

ለመጠቀም ምን አይነት አጠቃቀም ስልት መጠቀም አለባቸው በሚለው ዙሪያ ጥናትና ምርምር

ማካሄድ፡፡

በወንዙ አጠቃቀም ዙሪያ ጠንካራ ጥናትና ምርምር በማካሄድ ብዥታ ማስወገድ፣

ስለግድቡ ጠቀሜታና ተዛማጅነት ባላቸው ጉዳዮች የህብተሰቡን ንቃተ-ህሊና ከፍ በማድረግ

ለግድቡ የሚያደርጉትን አስተዋፅኦ እንዲያድግ ማድረግ፣

በተፋሰሱ አገሮች የውሃ አጠቃቀም ፍትሐዊነት እንዲኖር ተፅዕኖ ለሚያደርጉ ዓለም አቀፍ

ማህበረሰብ ጥናትና ምርምሮቻቸው ግንዛቤ እንዲኖራቸው ማድረግ (እንዲገነዘቡ ማድረግ)፣

ኢትዮጵያ የህዳሴው ግድብን የምትሰራው የታችኞቻቹ ተፋሰስ አገሮችን በተለይም ግብፅን ሆን

ብላ ለመጉዳት ነው የሚለውን የተሳሳተ ፕሮፓጋንዳ የተፋሰሱ አገሮች ህዝቦች እውነታውን

እንዲገነዘቡት ማድረግ፣

ከአቶ ዘፋኒያ በቀረበላቸው የመነሻ ሃሳቦች ላይ ተመርኩዞ የምሁራን ሚና ምን መምሰል እዳለበት

አምባሳደር ብሃን ክርስቶስ፣ ፕሮፌሰር አብይ ይግዛውና የኢትዮ የተማሪዎች ህብረት ፕሬዚዳንት

ማብራሪያቸውን እንደሚከተለው ሰጥተዋል፡፡

አምባሳደር ብርሃነ ገ/ክርስቶስ፤ የውጭ ጉዳይ ሚኒሲቴር ሚንስትር ዴኤታ

በመጀመሪያ የሰሜን ምዕራብ ክላስተር አስተባባሪ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲና የአገር ልማት ጥናት

ማዕከል (Center for Development stories) ይህን መድረክ በማዘጋጀታቸው በማመስገን

ያለምሁራ ተሳትፎና ያለህዝባችን ተሳትፎ የህዳሴው ግድብና ሌሎች የልማት ስራዎችን በማሳካት

ድህነት መቀነስን አንችልም፡፡ ስለሆነም የዛሬው መድረክ አገራችን የምታልመውንና

የምትፈልገውን ለመቀዳጀት እድንችል በር ከፋች ነው፡፡

የአገራችን አጠቃላይ /የረዥም ጊዜ/ ግብ የህዝቦችን የነፍስ ወከፍ ገቢ ማሳደግና የኑሮ

ሁኔታቸውን ማሻሻል ነው፡፡ ከዛሬ ስምንት ዓመት በኋላ ግባችን የእያንዳንዱ ሰው ነፍስ ወከፍ ገቢ

Page 11: BDU CLUSTER & CDS - 1st Nile... · bdu cluster & cds ሚያዚያ 20-21 ... ተ/ብርሀን የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ- ... የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ

ቃለ-ጉባኤ - ኢትዮጵያ አባይን ለልማት በመጠቀም መብትና አስፈላጊነት ላይ የምሁራን ተልእኮ - ሚያዚያ 20-21/2006; ባህር ዳር, ኢትዮጵያ

10 | P a g e

1,500 አሜሪካ ዶላር እንዲሆን ከ35 - 40 ዓመት በኋላ ደግሞ የእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ገቢ

30000 ዶላር እዲሆን ነው፡፡ የምንሰራቸው ማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ስራዎች የነፍስ

ወከፍ ገቢያችን ለማሳደግ የሚደረጉ ጥረቶች ናቸው፡፡ ይህን ግብ ለማሳካት በመንግስትና በህዝቦች

መካከል የጋራ መግባባት መፍጠር አለበት፡፡ የጋራ መግባባት ሲባል ምንም እንኳ በተለያዩ ፖለቲካ

ፓርቲዎችና በህዝቦች“ በግለሰቦች መካከል የሃሳብ ልዩነቶች ቢኖሩም የጋራ የሆኑ አገራዊ ጉዳዮች

ላይ መግባባት ማለት ነው፡፡ በአደጉ አገሮችና በብዙ ታዳጊ አገሮች በፖለቲካ ፓርቲዎች፣

በምሁራ፣ በመንግስት ባለስልጣናት ወዘተ… መካከል ከፍተኛ የሃሳብ ልዩነት ይሰተዋላል ፡፡ በጋራ

አገራዊ ጉዳዩችን ግን ልዩነታቸውን ወደ ኋላ በመተው አብረው በትብብር በመስራት አገራቸውን

ወደፊት የሚወለዱ የልማት ስራዎች ላይ በጋራ ይሰራሉ፡፡ በእኛ አገርም ይህ አይነት አስተሳሰብ

መጎልበት አለበት፡፡ ምሁራን በዚህ ዙሪያ ከፍተኛ ሚና ሊኖራቸው ይገባል፡፡

1ኛ. የተለያየ አመለካከት ቢኖረንም እንኳ የጋራ የሆኑ አገራዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ አመለካከት

እንዲኖር መስራት አለባቸው፡፡

2ኛ. ጥናትና ምርምሮችን በማካሄድ ህብረተሰቡ ግንዛቤ እንዲኖረው በማድረግ ሚናቸውን ሊወጡ

ይችላሉ፡፡

3ኛ. የመንግስት ፖሊሲዎችና ስትራቴጅዎችን በመተቸትና ምርምር በማድረግ ያሉባቸዉን

ጉድለቶች በመለየት ፖሊሲ አማራጮችን ማፍለቅ

ፕሮፌሰር አብይ ይግዛው

በአባይ ግድብና አጠቃላይ ወንዙ አጠቃቀም ላይ መወያየት አስፈላጊነት ወቅታዊ መሆኑን

ጠቁመው ምሁራን ብዙ መስራት እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡ ፕሮፌሰሩ በተለያዩ የስራ

አጋጣሚዎች ወደሌሎች አገሮች ሲሄዱ ያዩትንና የታዘቡትን ለወርክሾፕ ተሳታፊዎች አካፍለዋል፡፡

የመጀመሪያው በዩኒቨርሲቲዎችና በመንግስት አካላት መካከል ከፍተኛ ትስስር ማየታቸውንና

ትስስሩም ለአገራቸው እድገት መልካም አጋጣሚ እንዲኖር በእኛም አገር የሚፈለገው እድገት

ደረጃ ላይ ለመድረስ ምሁራንና የአገሪቱ መሪዎች መካከል የተሻለ ግንኙነት ለመጀመር አብሮ

የመስራት ባህል እንዲኖር ማድረግ አለበት፡፡ በሁለተኛ ደረጃ የታዘቡት ከአፍሪካና ከሌሎች አገሮች

ለስራ ጉዳይ ወደ አውሮፓ አገሮች የሚሄዱ ሰዎችን ከየት መጣህ፣ ለምን መጣህ፣ መቸ

ትመሳለህና ሌሎች ጥያቄዎችን ይጠይቃሉ፡፡ ከዚህ የተረዳሁት የእያንዳንዱ አውሮፓዊ አገር ዜጋ

Page 12: BDU CLUSTER & CDS - 1st Nile... · bdu cluster & cds ሚያዚያ 20-21 ... ተ/ብርሀን የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ- ... የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ

ቃለ-ጉባኤ - ኢትዮጵያ አባይን ለልማት በመጠቀም መብትና አስፈላጊነት ላይ የምሁራን ተልእኮ - ሚያዚያ 20-21/2006; ባህር ዳር, ኢትዮጵያ

11 | P a g e

ለአገሩ ደህንነት ስራ ይሰራል፡፡ በማደግ ላይ ያሉ አገሮች ህዝቦች ግን በግለሰባዊ ጥቅሞች

በመታለል የአገራቸውን ደህንነት አሳልፈው ሲሰጡ ይታያሉ፡፡

የእኛ አገር ምሁራን ከዩኒቨርሲቲዎቻችን ዙሪያ ከሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ያለን

ግንኙነትና ከመንግስት አካላት ጋር አብሮ የመስራት ባህላችን ምን ይመስላል; አገራዊ ጉዳዮች ላይ

የምናደርገው አስተዋፅኦ ምን ያህል ነበር?; ብየ ራሴን ስጠይቅ ብዙ እንደሚቀረን ይሰማኛል

በማለት የምሁራን ሚና በሚፈለገው ደረጃ ላይ እንዳልደረሰ ገልፀዋል፡፡ በቅርብ ጊዜ

በዩኒቨርሲቲዎች ምሁራን የሚሰሩ የማህበረሰብ አገልግሎትና የምርምር ስራዎች እየተጠናከሩ

ቢሆኑም ገና ብዙ መጓዝ እንደሚጠበቅ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡ የአገሪቱን ፖሊሲዎችና

ስትራቴጅዎች በመተንተን ያሉባቸውን ጠንካራና ደካማ ጎኖች በመለየት የፖሊሲ አማራጮችን

የማቅረብ ልምዳችን ገና አልዳበረም፡፡ መንግስት ማለት ከህዝብና ከምሁራን ጋር ሊሰራ የሚችል

አካል ማለት ነው፡፡ በሌላ በኩል ምሁራን ማለት በንድፈ ሃሳብ የተማሩትንና፤ በስራና በማንበብ

ያዳበሩትን እውቀት ከህብተሰቡና ከመንግስት ጋር አብሮ በመስራት ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት

የሚችሉ ናቸው፡፡ በአገራችን ተጨባጭ ሁኔታ በምሁራና በመንግስት መካከል ያለው ግንኙነት

በጣም የላላ ነው፡፡ ምሁራን በትምህርትና በስራ ያዳበሩትን እውቀት አካባቢያቸውን መሰረት

ያደረገ የልማት ስራዎች በመስራት በኩል ብዙም አልተራመዱም፡፡ ሁላችንም የአገራችንን እድገት

እንሻለን፡፡ የሚፈለገው እድገት ግን ሊሳካ የሚችለው በጋራ የሆኑ አገራዊ ጉዳዩች ጥሪ ላይ

ምሁራን የመጀመሪያ ተሰላፊዎች ስንሆን ነው፡፡ መንግስትና ምሁራን በጋራ የሆኑ ጉዳዩች ላይ

አብረን ስንሰራ ነው፡፡ ስለዚህ የአባይ ግድብ ትልቅ የሆነ አገራዊ አጀንዳ ነው፡፡ በዚህ ትልቅ

አገራዊ አጀንዳ ላይ የምሁራን ድርሻ ጥንታዊ ፅሁፎችን በመስራት የህዳሴው ግድብ ለአገራችን

ብሎም ለተፋሰስ አገሮች ያለውን ጠቀሜታ መረዳትና የሌሎች ተፋሰስ አገሮች ህዝቦችና ለአለም

አቀፍ ማህበረሰብ እንዲያውቁት ማድረግ፡፡ ይህን ለመስራት በአሁኑ ሰዓት በ33 ዩኒቨርሲቲዎች

እምቅ አቅም አለ፡፡ ባለቤትነት ወስዶ ስራዎችን አቀናጅቶ ሊሰራ የሚችል አንድ ተቋም መኖር

አለበት፡፡ በመጨረሻም ሙያዊ አገልግሎታችን የሚገባንን አገልግሎት ልንሰጥ የሙያ ግዴታ

አለበት፡፡

የግብፅ ምሁራን በናይል ወንዝ ጉዳይ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ጥናታዊ ጽሁፎችን በመስራት

ለመንግስት የሚሰጡት ድጋፍ ከፍተኛ ነው፡፡ ህዝቡ በወንዙ አጠቃላይ ሁኔታ አንድ አይነት

አቋም እንዲኖረው ከፍተኛ ስራ ሰርተዋል፡፡ ከአባይ ወንዝ አጠቃቀምና በሌሎች ጉዳዮች በእኛ

Page 13: BDU CLUSTER & CDS - 1st Nile... · bdu cluster & cds ሚያዚያ 20-21 ... ተ/ብርሀን የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ- ... የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ

ቃለ-ጉባኤ - ኢትዮጵያ አባይን ለልማት በመጠቀም መብትና አስፈላጊነት ላይ የምሁራን ተልእኮ - ሚያዚያ 20-21/2006; ባህር ዳር, ኢትዮጵያ

12 | P a g e

አገር ምን ያህል ጥናትና ምርምር ተሰርተዋል ተብሎ ቢጠየቅ እንደኔ እምነት በጣም አነስተኛ

ነው፡፡ የአገራችን ሚዲያዎችም ለግድቡ የሚሰጡት ሽፋን እጅግ በጣም አነስተኛ ነው፡፡

እንዲያውም አሉታዊ ገጽታዎች ላይ ትኩረት ማድረግ ይቀናቸዋል፡፡ ባለፉት አመታት

የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ከሁለት ወደ ሰላሳ ሶስት ደርሰዋል፡፡ በእነዚህ ዩኒቨርሲቲዎች ከፍተኛ

ቁጥር ያላቸው ምሁራን አሉ፡፡ ከፍተኛ ቁጥር ምሁራንንም በማፍራት ላይ ናቸው፡፡ እምቅ አቅም

እንዳለን ያመለክተናል፡፡ ይህ ትልቅ አቅም በጥናትና ምርምር ስራ ላይ ትኩረት አድርጎ ቢሰማራ

የህዝባችንን ግንዛቤ ማሳደግ እንችላለን፡፡ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብም ግንዛቤ መፍጠር ያስችላል፡፡

በተፋሰሱ የታችኞቹ አገሮች በተለይ በግብፅ ትክክለኛ መረጃ ላይ መሰረት ያላደረጉ የጥናት

ስራዎችና የሚዲያ ፕሮፖጋንዳን መመልከት ይቻላል፡፡ ስለሆነም በአገራዊ ጉዳዮች የህዳሴው

ግድብን ጨምሮ ዩኒቨርሲቲዎች የጥናትና ምርምሮች በቂ በጀት በመመደብ ምሁራኖቻቸውን

ሊያንቀሳቅሱ ይገባል፡፡

ዶ/ር በላይነህ አየለ፤ በባህርዳር ዩኒቨርሰቲ የግብርናና አካባቢ ሳይንስ ኮሌጅ ዲን

ስለ ህዳሴው ግድብና ተያያዥነት ባላቸው ጉዳዮች ጥናትና ምርምር ማካሄድ ተገቢና ሁላችንም

የምናምንበት ነው፡፡ ጥናቶችንም ለመስራት በዩኒቨርሲቲዎቻችን ምቹ ሁኔታዎች ተፈጥረዋል፡፡

በቅርብ አመታት ለጥናትና ምርምር ስራዎች የሚመደበው በጀት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ

ነው፡፡ የጥናትና ምርምር ስራዎችን የሚሰሩ ምሁራንም ቁጥር እየጨመረ ነው፡፡ ዩኒቨርሲቲያችን

ለነዚህ ምሁራን ዕውቅና በመስጠትና ሽልማቶችን በማበርከት የበለጠ እንድንሰራ እያበረታታን

ነው፡፡ የተሰሩ ስራዎች በቂ ናቸው ብየ አላምንም፡፡ ከጉዳዩ ፋይዳነት በጣም መስራት

ይጠበቅብናል፡፡ የድህረ ምረቃ ተማሪዎቻችን በዚህ ዙሪያ መመረቂያ ጽሁፎቻቸውን እንዲሰሩ

ማበረታታት አለብን፡፡ መምህራንም በስፋት እንዲሰሩ የትኩረት አቅጣጫ ዩኒቨርሲቲዎች መስጠት

አለባቸው፡፡ ስለአባይና ህዳሴው ግድብ መሰራት የሚገባቸው ጥናቶች በጣም በርካታ ናቸው፡፡

ስለተፋሰሱ ሐይድሮሎጂ፡ ጥልቅ ጥናቶች ማጥናት ይጠበቅብናል፡፡ ባለፉት አመታት የተሰሩት

የአፈርና ውሐ ጥበቃ ስራዎች ለግድቡ ያላቸው ፋይዳ ሌላ በርካታ የምርምር ስራ ሊሰራባቸው

የሚገባ ነው፡፡

አቶ ሞላ እባቡ፤ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ኢንፎርሜሽንና ስትራቴጂክ ኮሚኒኬሽን ምክትል

ፕሬዚደንት

ከግብጽና ከአለም አቀፍ የሚመጣብንን ጫና ለመቋቋም ውስጣዊ ጥንካሬ ወሳኝ ነው፡፡ ውስጣዊ

ጥንካሬ ሊገነባ የሚችለው፡ በህዝቦች መካከል መቻቻል ሲኖር፤ በምሁራንና በመንግስት መካከል

Page 14: BDU CLUSTER & CDS - 1st Nile... · bdu cluster & cds ሚያዚያ 20-21 ... ተ/ብርሀን የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ- ... የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ

ቃለ-ጉባኤ - ኢትዮጵያ አባይን ለልማት በመጠቀም መብትና አስፈላጊነት ላይ የምሁራን ተልእኮ - ሚያዚያ 20-21/2006; ባህር ዳር, ኢትዮጵያ

13 | P a g e

ጠንካራ ትስስር ሲኖርና ፍትሐዊ ሀብት ክፍፍል በአገሪቱ ሲሰፍን ነው፡፡ ይህ ከሆነ መንግስት

ለነዚህ እውን መሆን ጠንካራ ስራ መስራት ይጠበቅበታል፡፡ ምሁራንም ከፍተኛ እገዛ ማድረግ

አለባቸው፡፡ እንደ ግብፆች የተጠናከረ ጥናትና ምርምር በማካሄድ የፐብሊክ ዲፕሎማሲ መስራት

ይጠብቅባቸዋል፡፡ በዚህ በኩል የሰራናቸው ስራዎች የግብፅ ምሁራን ከሰሯቸው ስራዎች ጋር

ሲነጻጸር እጅግ በጣም አነስተኛ ናቸው፡፡ የግብፅ ምሁራን በሐይድሮ-ፖለቲካና በወንዙ አጠቃላይ

ገጽታ በርካታ ስራዎችን በመስራት ህዝባቸውን፣ ወዳጆቻቸውን፤ የአለም አቀፍ ተቋማትንና

ታላላቅ አለም አቀፍ ምሁራንን በማሳመን ከእነሱ ጎን እንዲሰለፉ አድርገዋል፡፡ ስለዚህ ከምሁራን

የሚጠበቅባቸውን ድርሻ ተወጥተዋል፤ ማለት ነው፡፡ የኢትዮጵያ ምሁራን ተመሳሳይ አለም አቀፍ

ድፕሎማሲያዊ ስራዎቸ እንዲሰሩ ምን መደረግ አለበት የሚለው መሰረታዊ ጥያቄ ነው፡፡ የአለም

አቀፍ ማህበረሰብ ዘንድ በግድቡ ላይ ያለውን ብዥታ ለማስወገድና እውነታውን ተገንዝቦ

ከኢትዮጵያ ጎን ለማድረግ ጥናትና ምርምር በተጠናከረ መንገድ መሰራት አለበት፡፡ ምሁራን ለዚህ

ከፍተኛውን ሚና ሊጫዎቱ ይገባል፡፡

1. የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይና ብሔራዊ ደህንነት ፖሊሲ መሰረታዊ መርሆች

አቅራቢ፤ አምባሳደር ብርሃነ ገ/ክርስቶስ፡ የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ዴኤታ

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ መንግስት በ1994 ዓ.ም የውጭ ጉዳይና ብሔራዊ ደህንነት

ፖሊሲ አውጥቷል፡፡ የዚህ ፖሊሲ መሰረቱ የአገሪቱን ብሄራዊ ጥቅምና ደህንነት ማስጠበቅ ነው፡፡

የብሔራዊ ጥቅማችንና ደህንነታችን ሊጠበቅ የሚችለው ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ልማት

በማረጋገጥና ዲሞክራሲያዊ ስርዓት በመገንባት የህዝባችን ሁለንተናዊ ፍላጎት ሲሟላ ነው፡፡

በአገራችን ቀጣይነት ያለው ልማት ማረጋገጥ ካልቻልንና ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ካልገነባን ከከፋ

ድህነት አዙሪት ውሰጥ አንወጣም፤ የውጭ ዕርዳታ ጥገኞች እንደሆን እንቀጥላለን፤ ብሎም

የመበታተን አደጋ ያጋጥመናል፡፡ ስለሆነም ዘላቂነት ያለው ልማት ለማረጋገጥና ዲሞክራሲያዊ

ስርዓት ለመገንባት ኢንቨስትመንትን ማስፋፋት፤ መልካም አስተዳደር ማስፈን፤ ወዘተ ቅድሚያ

የሚሰጣቸው ጉዳዮች ናቸው፡፡ የህዳሴው ግድብ ዘላቂነት ያለው ልማት ከማረጋገጥ አነፃር የጎላ

ጠቀሜታ አለው፡፡ የህዝባችንን በራስ መተማመን ያሳድጋል፡፡ ስለዚህ ግድቡ የውጭ ጉዳይና

የብሔራዊ ደህንነት ፖሊሲ አብይ አጀንዳ ነው፡፡ ይህ ለደህንነታችንና ለህልውናችን መሰረት

የሆነውን ግድብ ከዳር ለማድረስ የመንግስትን የህዝብንና የምሁራንን የጋራ ጥረት በጣም

ይጠይቃል፡፡ የግድቡ ስራ ለማጠናቀቅና ለሀገራችን ሁለንተናዊና ዘላቂነት ያለው ልማት

ለማረጋገጥ የምሁራን ሚና በጣም ወሳኝ ነው፡፡ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ (public diplomacy)

Page 15: BDU CLUSTER & CDS - 1st Nile... · bdu cluster & cds ሚያዚያ 20-21 ... ተ/ብርሀን የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ- ... የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ

ቃለ-ጉባኤ - ኢትዮጵያ አባይን ለልማት በመጠቀም መብትና አስፈላጊነት ላይ የምሁራን ተልእኮ - ሚያዚያ 20-21/2006; ባህር ዳር, ኢትዮጵያ

14 | P a g e

መስራት አንዱና ወሳኙ የምሁራኑ ሚና ነው፡፡ ምሁራን ፐብሊክ ዲፕሎማሲ እንዴት ሊሰሩ

ይችላሉ የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችላል፡፡ በሁለት መልኩ ሚናቸውን ሊወጡ ይችላሉ፡ አንደኛው

መንገድ የውጭ አገር ትምህርት ዕድል አግኝተው በሚሄዱበት ጊዜ፡ ለአጫጭር ወርክሾፖች

በሚወጡበት ወቅት ወይም ለስራ ጉዳይ ወደ ውጭ በሚሄዱበት ጊዜ በሚሄዱባቸው

ዩኒቨርሰቲዎች ወይም ተቋማት ስለ አባይ ውሃ ፍትሃዊ አጠቃቀም በማስረዳት ሲሆን፤

ሁለተኛው መንገድ የጥናትና ምርምር ስራዎችን በመስራት በዓለም አቀፍ ጆርናሎችና በሌሎችም

በማሳተም የሌሎች አገሮች ምሁራን እንዲገነዘቡ በማድረግ ነው፡፡

ውጫዊ የአገራችን ደህንነት ስጋት የሆኑትን በተቻለ መጠን መቀነስ ወይም ሙሉ በሙሉ

ማስወገድ ሁለተኛው የውጭ ጉዳይና የደህንነት ፖሊሲያችን የትኩረት አቅጣጫ ነው፡፡ ይህን

አላማ ለማሳካት ከጎረቤቶቻችንና ሌሎች ለልማታችን ወሳኝ አስተዋጽኦ ሊያደርጉልን ከሚችሉ

አገሮች ጋር ያለንን ግንኙነት ማጠናከር አለብን፡፡ ለዚህ ይረዳ ዘንድ በክፍለ አህጉራዊ፣

አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ሁኔታዎችን መተንተን ያስፈልጋል፡፡ ተለዋዋጭ የሆነውን ዓለም አቀፍ

ኢኮኖሚያዊ፤ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ሁኔታዎች በአገራችን ላይ የሚኖራቸውን ተፅዕኖ

በመተንተን የፖሊሲ አቅጣጫዎች ማፍለቅ ያስፈልጋል፡፡ በመሆኑም ምሁራን በዓለም አቀፍ

ጉዳዮች ጥናቶችን በማካሄድ ለኢትዮጵያ የሚበጃትን መንገድ ማሳየት አለባቸው፡፡ በውጭ ጉዳይ

ሚኒስቴር ባለሙያዎችና አምባሳደሮች ብቻ ዲፕሎማሲያዊ ስራ ተሰርቶ የትም አይደረስም፡፡

አምባሳደር ኢብራሂም

የዓባይ የትብብር ማዕቀፍ (CFA)

እንደሚታወቀው የአባይ ውሃ አጠቃቀም ኢፍታዊነት ሰፍኖበት የቆየ ነው፡፡ የታችኞቹ ተፋሰስ

አገሮች በተለይም ግብጽ በተፋሰስ ውስጥ ያላትን የበላይነት የተለያዩ ስርዓቶች በመጠቀም

ለማስቀጠል ከፍተኛ ጥረት ስታደርግ ቆይታለች፡፡ በሌላ በኩል የላይኞቹ የተፋሰስ አገሮች

ኢትዮጵያን ጨምሮ ፍትሐዊ የሆነ የውሃ አጠቃቀም እንዲኖር ጥረት ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡ ከብዙ

ጥረት በኋላ እ.ኤ.አ በ1997 ዓ.ም የናይል ኢንሸቲቭ (Nile Initiative) ተቋቋመ፡፡ ኢንሸቲቩ ዋና

አላማው ቋሚ የሆነ ኮሚሽን ማቋቋም ነው፡፡ የሚቋቋመው ኮሚሽን የCFA ጋር ማዕቀፍ የተቃኘ

መሆን ነበረበት፡፡ የናይል ኢንሼቲቭ መቋቋምን የላይኞቹና የታችኞቹ ተፋሰስ አገሮች በተለይም

ግብፅና ኢትዮጵያ ይፈልጉታል፡፡ ነገር ግን የሁለቱ አገሮች በተቋሙ ላይ የነበራቸው ፍላጎት

Page 16: BDU CLUSTER & CDS - 1st Nile... · bdu cluster & cds ሚያዚያ 20-21 ... ተ/ብርሀን የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ- ... የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ

ቃለ-ጉባኤ - ኢትዮጵያ አባይን ለልማት በመጠቀም መብትና አስፈላጊነት ላይ የምሁራን ተልእኮ - ሚያዚያ 20-21/2006; ባህር ዳር, ኢትዮጵያ

15 | P a g e

የተለያየ ነበር፡፡ ግብዕ ተቋሙን የምትፈልገው በፊት የነበረውን ስርዓት እንዲያስቀጥልላት ነው፡፡

በኢትዮጵያ በኩል ኢፍትሃዊ የውሃ ስርዓት ተወግዶ የላይኛውና የታችኛው ተፋሰስ አገሮች የጋራ

ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ ነው፡፡

እነዚህ አቋሞች ከ2002 እስከ 2006 ዓ.ም ድረስ በነበረው ድርድር ሂደት ውስጥ ይንፀባረቁ ነበር፡፡

በዚህ ሂደት ውስጥ ዋና ተደራዳሪዎች የነበሩት ግብፅና ኢትዮጵያ ነበሩ፡፡ ምክንያቱም ግብፅ

የውሃው ዋና ተጠቃሚ በመሆኗና ኢትዮጵያ ደግሞ አብዛኛው የናይል ውሃ ምንጭ በመሆኗና

የውሃ ሃብቷን ፍትህዊነት ባለው መንገድ ለመጠቀም ባላት ፍላጎት ነው፡፡ በድርድሩ ወቅት ግብፅ

የቀድሞው ኢፍታሐዊ የሆነ አጠቃቀም ስርዓት የሚያረጋግጥ እንዲሆን ከፍተኛ ጥረት ታደርግ

ነበር፡፡ በኢትዮጵያ በኩል አዲስ ስርዓት እንዲመሰረትና ሁሉም የተፋሰሱ አገሮች ተጠቃሚነት

እንዲረጋገጥ ጥረት ስታደርግ ቆይታለች፡፡ የግብዕ የናይል ውሃ ከፍተኛ ተጠቃሚነት ወደፊትም

እዲቀጥል ምሁራንና የአገሪቱ ሚዲያዎች ከፍተኛ ሚና ይጫዎታሉ፡፡ ለህዝባቸው የተፋሰስ

አገሮች በተለይም ኢትዮጵያ የምትሰራው የህዳሴ ግድብ ሆን ተብሎ የግብፅን ኅዝብ ለመጉዳት

እንደሆነ በተለያዩ ቋንቋዎች ይጽፋሉ፡፡ ለዚህ የሚያቀርቧቸው መከራከሪያ ነጥቦች ኢትዮጵያ የብዙ

ወንዞች ባለቤት እንደሆነችና አባይን ሳትጠቀም ሌሎችን ወንዞችን ብቻ በመጠቀም ልማቷን

ማረጋገጥ እንደምትችል በቂ ዝናብ እንዳላትና የዝናብ ውሃን በመጠቀም የግብርና ምርቷን

ማሳደግ እንደምትችልና ህዝባቸውንና አለም አቀፋን ማህበረሰብ ለማሳመን ጥረት ሲያደርጉ

ቆይተዋል፡፡ ግድቡ የሚሰራው ለራሷጥቅም ሳይሆን በስተጀርባው የሌላ አገር ማለትም የእስራኤል

ጣልቃ ገብነት እንዳለበት ለማሳመን ጥርት በማድረግ ላይ ናቸው፡፡ የአባይ የውሃ አጠቃቀም ጉዳይ

ፖለቲካዊ ብቻ እንደሆነ ምሁራንም ሆነ ሚዲያዎች በስፋት ይጽፋሉ፡፡ በርከት ያሉ የአገሪቱ

ዩኒቨርሲቲዎች ከናይል ጋር የተያያዙ ፕሮጀክቶችና ተቋማት አላቸው፡፡ የወንዙን ውሃ አጠቃቀም

ዋና አጀንዳቸው ነው፡፡ በዚህ ዙሪያ የሰራቸው በርካታ ስራዎች የግብፅ ህዝብና መንግስት

እንዲሁም የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች በወንዙ ውሃ አጠቃቀም ላይ ተመሳሳይ አመለካከት

እንዲኖረው አድርጓል፡፡ በጣም ሰፊ የሆነ የፖለቲካ አይዲዮሎጂ ልዩነት በፓርቲዎች መካከል

ቢኖርም ስለናይል ውሃ አጠቃቀም አንድ አይነት አቋም አላቸው፡፡

1ኛ. ከእነሱ ልምድ መቅሰም የሚገቡን ነገሮች በዩኒቨርሲቲዎቻችን ያሉ ምሁራን ያላቸውን

ፖለቲካዊ አመለካከት ወደ ኋላ በመተው በአገራዊ ጉዳዮች ላይ አብሮ መስራት

እንዳለባቸው፡፡

Page 17: BDU CLUSTER & CDS - 1st Nile... · bdu cluster & cds ሚያዚያ 20-21 ... ተ/ብርሀን የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ- ... የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ

ቃለ-ጉባኤ - ኢትዮጵያ አባይን ለልማት በመጠቀም መብትና አስፈላጊነት ላይ የምሁራን ተልእኮ - ሚያዚያ 20-21/2006; ባህር ዳር, ኢትዮጵያ

16 | P a g e

2ኛ. የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎችንና መንግስት ወደ ተቀራረበ አመለካከት በማምጣት ለአገሪቱ

ፈጣን እድገት የሚጠቅሙ የልማት ስራዎን ከፍተኛ ተሳትፎ እዲኖር ያደርጋሉ፡፡

3ኛ. ተከታታይነት ያላቸውና ተጨባጭ መረጃን መሰረት ያደረጉ የጥናትና ምርምር ስራዎች

በመስራት አለም አቀፍ ማህበረሰብን ድጋፍ ማግኘት እንደሚቻል ያስረዳናል፡፡

በአገራችን ገፅታ ግንባታና ዲፕሎማሲ የምሁራን ሚና

በአምባሳደር ፍስሃ ይመር

በውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ሂደት ውስጥ የሚኖራቸው ሚና የሚጀምረው በፖሊሲ ቀረፃ ወቅት

ለፖሊሲው ጠቃሚ የሆኑ ሃሳቦችን በማፍለቅ ነው፡፡ በመቀጠል የወጣውን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ

በመተንተን ያሉበትን ደካማ ጎኖችና ጥንካሬዎችን በማሳየት ፖሊሲ ክለሳ እንዲደረግ ማድረግ

ነው፡፡ የፖሊሲውን ግቦችና አጠቃላይ መርሆዎችን ለማገናዘብ ለተማሪዎቻቸው፣ ለህዝብና ለአለም

አቀፍ ማህበረሰብ ማስገንዘብ ሶስተኛው የምሁራን ሚና ነው፡፡

በምዕራባዊያን በተለይም አሜሪካ በውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ትግበራዎች በምሁራንና በመንግስት

መካከል ያላቸው ግንኙነት Cross pollinational/ cross feretiliational ተብሎ ይጠራል፡፡ ይህም

ማለት ምሁራን በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመግባት ይሰራሉ ተመልሰው ወደ ዩኒቨርሲቲዎች

በመግባት ያስተምራሉ፣ ይመራመራሉ፡፡ ምንም እንኳ ምሁራን በውጭ ጉዳይ በፖሊሲ

አውጪዎና አተገባበር ላይ ተፅዕኖ ያሳርፋሉ በሚል ትችት የሚያቀርቡ ቢኖርም ከፍተኛ

ጠቀሜታው አንደኛ ጠቀሜታው በንድፈ ሃሳብ ደረጃ ያዳበረውን ዕውቀት በአገር ተጨባጭ

ሁኔታ በውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በመስራት ተግባራዊ ለማድረግ ይረዳዋቸዋል፡፡ ሁለተኛው

ጠቀሜታ በተግባር ያካበቱትን ልምድ ዩኒቨርሲቲ ተመልሰው ተማሪዎቻቸውን በተግባርና በንድፈ

ሃሳብ ለማስተማር ይረዳቸዋል፡፡

በኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ በምሁራንና በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መካከል ያለው ትስስር

እስካሁን የላላ ነው፡፡ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲን ለሌሎች የማስገንዘብ ስራና ዲፕሎማሲያዊ ስራዎች

ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ብቻ ነው የሚል የሁሉም አካላት አመለካከት ነው፡፡ የውጭ ጉዳይና

የደህንነት ፖሊሲው ላይ ጥናት መስራት፣ መተቸትና ማስተዋወቅ አልፎ አልፎ የተሰሩ ቢኖርም

የሚፈለገውን ያህል አልተሰራም፡፡ ስለሆነም በእናንተ በኩል በዚህ ዙሪያ ሰፊ ስራ ይጠበቅባኋል፡፡

Page 18: BDU CLUSTER & CDS - 1st Nile... · bdu cluster & cds ሚያዚያ 20-21 ... ተ/ብርሀን የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ- ... የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ

ቃለ-ጉባኤ - ኢትዮጵያ አባይን ለልማት በመጠቀም መብትና አስፈላጊነት ላይ የምሁራን ተልእኮ - ሚያዚያ 20-21/2006; ባህር ዳር, ኢትዮጵያ

17 | P a g e

አማራጭ የፖሊሲ ሃሳቦችን በማፍለቅ ሚናችሁን ልትወጡ ይገባል፡፡ በፖሊሲ ትችት ስም

ፖሊሲው ምንም ፋይዳ እንደሌለው አቋምን ማራመድ ግን ሚና አይደለም አፍራሽ እንቅስቃሴ

ነው፡፡

ምሳሌ፡- በታላቁ የህዳሴ ግድብ ከውጭ ጉዳይ ፖሊሲ አንፃር የምሁራን ሚና ምን እንዳለበት

እንመልከት፡፡ በአሁኑ ሰዓት በሚፈለገው መንገድ ግድቡ በመሰራት ላይ ቢሆንም ከግራና ከቀኝ

አደጋዎች አሉበት፡፡ ግድቡ እውን እንዳይሆን የሚተናኮሉት ግብፅና በስተጀርባ ሆነው

የሚንቀሳቀሱ አገሮች ተቋማትና ግለሰቦች ናቸው፡፡ ምሁራን የግብፅንና በስተጀርባ ያሉት

ተቋማትና ግለሰቦችን አፍራሽ ተልዕኮ መመልከት ይጠበቅባችኋል፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት

በህዳሴው ግድብ ላይ ያላቸው ፖሊሲን ማስተዋወቅና ማስገንዘብ አፍራሽ ተልዕኳቸውን

ለመመልከት አንዱ ስልት ነው፡፡ የግድቡ አጠቃላይ በተፋሰሱ አገሮች የሚያመጣው አሉታዊ

ተፅዕኖ እንደሌለና አዎንታዊ ተፅዕኖ እንዳለው ማሳወቅ ይጠበቅብናል፡፡ ግብፆች እንደሚሉት

በፈሰሱ ውስጣዊ ችግር ላይ ተመስርቶ የተጀመረ እደሆነና ቀደም ሲል ማለትም ከ2008 ዓ.ም

(እ/ኤ/አ) ግድቡን ለመስራት እንቅስቃሴ አገራችን እንደጀመረች ማስገንዘብ ይጠበቃል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ኃላፊዎች ባቀረቡት የመወያያ ሃሳቦች ላይ የተለያዩ አስተያየቶች

ቀርበዋል፡፡

ከወልዲያ ዩኒቨርሲቲ

በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኃላፊዎች የቀረቡ ሃሳቦችና በአጠቃላይ በሲምፖዚየሙ ላይ የተነሱ

ሃሳቦችና በአጠቃላይ በሲምፖዚየሙ ላይ የተነሱ ጉዳዩች በጣም ጠቃሚዎች ናቸው፡፡ የምሁራን

ሚና ምን ምን እንደሆነ በተለያዩ አቅራቢዎች በግልፅ ተቀምጠዋል፡፡ እነዚህ ተለይተው

የተቀመጡ ሚናዎችን ለመተግበር ወደፊት ከምሁራን ብዙ ይጠበቃል፡፡ ሚናችንን ለመጫዎት ግን

የራስን ጥቅም ቅድሚያ የመስጠት አዝማሚያነት እየጎለበቱ እንደመጡ በዩኒቨርሲቲ ቆይታየ

መገንዘብ ችያለሁ፡፡ የአገራችን ብሔራዊ ጥቅም ወደ ኋላ በመተው የራስን ጥቅም ማስቀደም

የብሔራዊ ደህንነታችን አደጋ ውስጥ ይገባል፡፡ ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገበት ያለው የህዳሴ ግድብ

ከዳር ላይ ሲደርስ ይደናቀፋል፡፡ ስለሆነም ልዩነት ግብፆች የህዳሴውን ግድብ እንዳያደናቀፍ

በአጠቃላይ ኢትዩጵያ በአባይ ወንዝ እንዳትጠቀም የሚከተሉት መንገድ ሁልጊዜም ተመሳሳይ

ነው፡፡ ልዩነታችን አጥንተው በደካማ ጐናችን ገብተው የማተራመስ ስራ ነው የሚሰሩት፡፡

ለግለሰባዊና ለብሔር ጥቅም ከፍተኛ ትኩረት መስጠታችን ለነሱ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል፡፡

Page 19: BDU CLUSTER & CDS - 1st Nile... · bdu cluster & cds ሚያዚያ 20-21 ... ተ/ብርሀን የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ- ... የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ

ቃለ-ጉባኤ - ኢትዮጵያ አባይን ለልማት በመጠቀም መብትና አስፈላጊነት ላይ የምሁራን ተልእኮ - ሚያዚያ 20-21/2006; ባህር ዳር, ኢትዮጵያ

18 | P a g e

ስለሆነም የተለያየ የፖለቲካ አመለካከት እንኳ ቢኖረንም የምሁራ ሚናችንን በመወጣት ለጋራ

ብልፅግና አብሮ መስራት ይጠበቅብናል፡፡

ለብዙ አመታት በውጭ አገር ሲሰሩ የቆዩና በተለያዩ ሙያዎች በአገር ውስጥ የሰሩና ከፍተኛ ልምድ

ያላቸው ሰዎች ወደ ዩኒቨርሰቲዎች በማስመጣት ልምዳቸውን እንዲያካፍሉ ማድረግ ጥሩ ነው፡፡

ቀደም በቀረቡ አስተያየቶች ምሁራን ጥናትና ምርምሮችን መስራት ይጠበቅባቸዋል የሚል ነገር

ተነስቷል፡፡ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ስናይ አለም አቀፍ ስታንዳርድ ያላቸው ጥናቶች ለማካሄድ

በየዩኒቨርሲቲዎቻችን ያሉ ምሁራን ምን ያህል እውቀቱና ክህሎቱ አላቸው? ለመጻፍስ መሰረታዊ

የቋንቋ ክህሎት ችግሮች የሉብንም ወይ? እነዚህ ችግሮች እያሉ የሚጠበቅብንን ሚና መጫዎት

እንችላለን? አንችልም፤ ብዙዎቻችን በዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ ተገኝተን ሃሳቦቻችንን

በሚፈለገው መንገድ ለመግለጽ ችግሮች አሉብን፡፡ ለዚህ ዋናው ምክንያት የመናገርና የመጻፍ

ክህሎቶቻችን ዝቅተኛ በመሆኑ ነው፡፡ በዚህ ላይ ብዙ ስራ መሰራት አለበት፡፡ ተከታታይ

አጫጭር ስልጠናዎችን በመስጠት የመምህራንን የምርምር አቅም ማጎልበት ያስፈልጋል፡፡

የመከላከያ ዩኒቨርሲቲ ተወካይ

ምሁራን የሚጠበቅባቸውን ሚና በሁለት መንገድ ሊወጡ ይችላሉ፡፡ እነሱም ተቋማዊ በሆነ

መንገድና የድህረ ምረቃ ጥናት ከወንዙ ከአጠቃቀም ጋር ተያያዥነት ያላቸው በመስራት፣

በተናጠል ጥናታዊ ጽሑፎችን ማድረግ በዋናነት በግለሰብ ደረጃ የሚጠበቅ የምሁራ ሚናዎች

ሲሆኑ፤ በተቋም ደረጃ የትምህርት ክፍሎችን በመክፈትና የጥናትና ምርምር ተቋማትን በማቋቋም

የተደራጀና የተቀናጀ ስራ መስራት ያስፈልጋል፡፡ በሁለቱም መንገድ ተጨባጭ በሆነ መረጃዎችን

መሰረት በማድረግ ጠንካራ የምርምር ስራዎች ከሰራን ህዝባችንና አለምአቀፉን ማህበረሰብ

ማስገንዘብ እንችላለን፡፡

ፕሮፌሰር መንገሻ ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ

እንደዚህ ያሉ ወርክሾፖች መካሄዳቸው በህዳሴው ግድብና በሌሎች የልማት ጉዳዩች ያሉ

ብዥታዎችን ለማስወገድ በጣም ከፍተኛ ነው፡፡ የዩኒቨርሲቲ አመራሮች፣ መምህራንና ተማሪዎች

በዚህ ሲምፖዚየም ላይ በመሳተፋችን ግንዛቤ እንዲኖረን አስችሎናል፡፡ ማንኛውም ሰው ለአገር

እድገት የሚፈለግበትን ሚና መጫዎት የሚችለው በሚሰሩ የልማት ስራዎችና ፖሊሲዎች ስለ

አጠቃላይ ችግሮች ግንዛቤ ሲኖረው ነው፡፡

Page 20: BDU CLUSTER & CDS - 1st Nile... · bdu cluster & cds ሚያዚያ 20-21 ... ተ/ብርሀን የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ- ... የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ

ቃለ-ጉባኤ - ኢትዮጵያ አባይን ለልማት በመጠቀም መብትና አስፈላጊነት ላይ የምሁራን ተልእኮ - ሚያዚያ 20-21/2006; ባህር ዳር, ኢትዮጵያ

19 | P a g e

በዩኒቨርሲቲያችን ያሉ ምሁራንና ተማሪዎች ከፍተኛ ግንዛቤ እንዲኖራቸው በተከታታይ

ወርክሾፖችን ማካሄድ ይኖርብናል፡፡ ይህ ከሆነ ምሁራን የሚጠበቅበትንን ሚና እንወጣለን፡፡

የህዝባችንን ግንዛቤ ለማሳደግ ያስችለናል፡፡ አለም አቀፉን ማህበረሰብም ለማሳመን ያግዘናል፡፡

እንደዚህ አይነቱ ወርክሾ ዩኒቨርሲቲዎች ላይ ብቻ ተንጠልጥሎ መቅረት የለበትም፡፡ እስከ

መጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ድረስ በመውረድ ለነገዉ አገር ተረካቢ ትውልድ ግንዛቤ መፍጠር

ያስፈልጋል፡፡ ልክ እንደ ግብፆች፤ በአባይ ወንዝ ላይ አንድ አይነት አቋም እንዲኖረን ያስችለናል፡፡

መንግስት በዚህ ዙሪያ በስፋት መስራት አለበት፡፡ ዩኒቨርሲቲዎችም የጥናትና ምርምሮችን እየሰራ

ወደታችኞቹ የትምህርት እርከኖች በመውረድ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን መስራት አለባቸው፡፡

አቶ ሚዛኔ፤ ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ

የዚህ አይነት መድረክ መዘጋጀቱ ግንዛቤ ለመፍጠርና በምሁራንና በመንግስት መሪዎች መካከል

ግንኙነት እዲጠናከር በማድረግ አብሮ ለመስራት ያስችላል፡፡ እስካሁን በነበሩት ጊዚያት በምሁራንና

የመንግስት ባለስልጣናት ከምሁራን ጋር ተቀራርቦ አብሮ ከመስራት ይልቅ በአሉታዊ ጎን

መመልከት ምሁራንም ከመንግስት ባለስልጣናት ጋር በመቀራረብ የሙያ ድጋፍ ከመመልከት

በጥርጣሬ ማየት አለ፡፡ በመሆኑም በመካከላችው ክፍተቶች ተፈጥረዋል፡፡ እንደዚህ አይነት

መድረክ በመካከላችን ያለውን ከፍተት በመሙላት አብረን መስራት እንድንችል ያደርገናል፡፡

መንግስት የሚሰራቸውን ስራዎች ለመደገፍ ያነሳሳናል፡፡ ስለህዳሴው ግድብ ግንዛቤ ለመፍጠር

የሚጠበቅብንን ሚና ተጫውተናል ባንልም በተወሰነ መጠንም ቢሆን በመስራት ላይ ነን፡፡ ይህ

ሲምፖዚየም ከዚህ የበለጠ እንድንሰራ ያግዘናል፡፡

ዶ/ር ባይሌ ዳምጤ

በአገር ገፅታ ግንባታና ለህዳሴው ግድብ መሳካት የምሁራን ሚና ከመድረክ በሰፊው ተገልጿል፡፡

ምሁራን በግለሰብና በተቋም ደረጃ ለአገር ገፅታ ግንባታ ሚናቸውን መወጣት እንዳለባቸው

ተገልጿል፡፡ በተናጠልም ሆነ በተቋም ሚናቸውን እዲወጡ የመረጃ መሰረተ ልማት በጣም ወሳኝ

ነው፡፡ ተጨባጭና ከትውልድ ወደ ትውልድ ሊሸጋገር የሚችል የመረጃ ስርዓት መገንባት አለብን፡፡

በአባይ ተፋሰስና በሌሎች ወንዞቻችን ላይ የተሰሩ ጥናቶች በጣም ውስን ናቸው፡፡ ከፍተኛ የሆነ

የመረጃ ክፍተት አለ፡፡ ይህም ክፍተት ለመሙላት ዩኒቨርሲቲዎች ተቋማዊ አቅማቸውን

Page 21: BDU CLUSTER & CDS - 1st Nile... · bdu cluster & cds ሚያዚያ 20-21 ... ተ/ብርሀን የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ- ... የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ

ቃለ-ጉባኤ - ኢትዮጵያ አባይን ለልማት በመጠቀም መብትና አስፈላጊነት ላይ የምሁራን ተልእኮ - ሚያዚያ 20-21/2006; ባህር ዳር, ኢትዮጵያ

20 | P a g e

በማጠናከር መስራት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ለዚህ ደግሞ የተጠናከረ የመረጃ መሰረት ልማት

ያስፈልጋቸዋል፡፡ የመረጃ መሰረተ ልማቱ መጠናከር የስራ ድግግሞሽ (Duplication of efforts)

ያስወግድልናል፡፡ ጥራት ያለው መረጃ እንዲኖረን ያስችለናል፡፡ የሙህራንን አቅም ያሳድጋል፡፡

በአገሪቱ የሚካሄድ የልማት ስራዎች ከሚፈለገው መንገድ ለማገዝ ያስችለናል፡፡

ሌላው ነጥብ በምሁራንና በመንግስት መካከል ለሚኖረው ግንኙነትና ጠቀሜታ ነው፡፡ በመንግስትና

በምሁራን መካከል ጠንካራ ትስስር መኖር ሁለት ጠቀሜታዎች ይኖሩታል፡፡ የመጀመሪያ በጋራ

የአገራዊ ጉዳዩች አብሮ ለመስራት መልካም እድል የሚፈጥር ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ጽንሰ

ሐሳብን ከተግባር ጋር በማቀናጀት ለማስተማር ከፍተኛ እገዛ ያደርጋል፡፡ አሁን ባለው ተጨባጭ

ሁኔታ በየዩኒቨርሲቲዎቻችን የሚካሄደው የመማር ማስተማር ስራ በንድፈ ሃሳብ ላይ

የተንጠለጠለ ነው፡፡ የሁለትዮሽ ትስስሩ የተጠናከረ ቢሆን ከፍተኛ ልምድ ያላቸው የመንግስት

ባለስልጣናትና ባለሙያዎች ወደ ዩኒቨርሲቲዎቻችን በመጋበዝና በማምጣት ልምዳቸውን

እንዲያካፍሉ ቢደረግ የንድፈ ሃሳብን ከተግባር ጋር በማጣመር ለማስተማር ያስችለናል፡፡

የማነ ብርሃን፤ ከመቀሌ ዩኒቨርሲቲ

ከውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ኃላፊዎች የቀረቡ የመወያያ ሐሳቦች ለመገንዘብ እንደቻልኩት ከውጭ

ጉዳይና የደህንነት ፖሊሲው ላይ ጥናት በማካሄድና በመተንተን ለህዝባችንና ለአለም አቀፍ

ማህበረሰብ ማስተዋወቅ ከፍተኛ ኃላፊነት ይጠበቅብናል፡፡ ኃላፊነታችን ከተወጣን ደግሞ በአገራችን

ገፅታ ግንባታ ላይ የጎላ ድርሻ ይኖረናል ማለት ነው፡፡ ምሁራን ሚናቸውን ለመወጣት

ዩኒቨርሲቲዎችና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አብረው መስራት አለባቸው፡፡ መንግስት ለምሁራን

የፐፕሊክ ዲፕሎማሲ ስራ እንዲሰሩና ከውጭ ጉዳይ ፖሊሲው ላይ ጥናትና ምርምር

እንዲመራመሩ እድሎችን መፍጠር አላማ አለው፡፡

በተሰጡ አስተያየቶችና ለተነሱ ጥያቄዎች በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ ኃላፊዎች የተሰጠ

መልስ

አምባሳደር ዲና ሙፍቲ

በመንግስት ባለስልጣናትና በዩኒቨርሲቲ ምሁራን መካከል የሚደረግ እንደዚህ አይነት ውይይት

መቀጠል አለበት የተባለው እኛም እንደግፈዋለን፡፡ ተመሳሳይ ውይይቶች ወደፊት ለማድረግ

እንጥራለን፡፡ ቀጣይነት እንዲኖረው የዩኒቨርሰቲዎችንም ጥረት ይጠይቃል፡፡ በመድረኩ የቀረቡ

Page 22: BDU CLUSTER & CDS - 1st Nile... · bdu cluster & cds ሚያዚያ 20-21 ... ተ/ብርሀን የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ- ... የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ

ቃለ-ጉባኤ - ኢትዮጵያ አባይን ለልማት በመጠቀም መብትና አስፈላጊነት ላይ የምሁራን ተልእኮ - ሚያዚያ 20-21/2006; ባህር ዳር, ኢትዮጵያ

21 | P a g e

ፅሁፎች፤ የተሰጡ ሃሳቦችና የተደረሰባቸው ድምዳሜዎች በመጽሄት ወይም በሌላ መልኩ

ተዘጋጅተው ለልዩ ልዩ ተቋማት መሰራጨት አለባቸው፡፡ ግንዛቤ ለመፍጠር ይረዳሉ፤

ለአፈጻጸምም ያግዛሉ፡፡

አማባሳደር ፍስሃየ ይመር

በውጭ ጉዳይና ብሄራዊ ደህንነት ፖሊሲ እንዲሁም በሌሎች የመንግስት ፖሊሲዎችና

ስትራቴጂዎች ላይ ትችቶች በምሁራን በሚቀርብበት ጊዜ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት

አሉታዊ መልኩ የመመለከት ባህል አለ፡፡ ምሁራንም በፖሊሲ ትችት የሚሰራ ጥናታዊ ፅሑፍ

ከፖሊቲካ አንጻር ብቻ በማየት ብዙ ጊዜ መስራት አይደፍሩም የሚል ሃሳብ ተነስቷል፡፡ ይህ

አይነት አመለካከት የለም ማለት አልችልም፡፡ ነገር ግን የተሳሳተ አመለካከት ነው፡፡ ምሁራን

ፖሊሲዎችን በሚተቹበት ጊዜ ትኩረት ማድረግ ያለባቸው፡ የሚሰጡት ትችት ለፖሊሲው የበለጠ

መዳበርና ለአፈጻጸም ከፍተኛ እገዛ የሚያደርግ መሆኑን ነው፡፡ አሉታዊ ገጽታው ላይ ብቻ

ትኩረት ማድረግና ማጣጣል ለፖለቲከኞች ላይዋጥላቸው ይችላል፡፡ ፖለቲከኞችም የፖሊሲ

ትንታኔዎችን በማጤን ጠቃሚ የሆኑ ነጥቦችን በመውሰድ ፖሊሲዎችን ማዳበር አለባቸው፡፡

ፐብሊክ ዲፕሎማሲ ከነባሩ የዲፐሎማሲ አቀራረብ የሚለየው በምንድን ነው የሚል ጥያቄ

ተነስቷል፡፡ ነባሩ የዲፕሎማሲ ስራ መንግስት ለመንግስት ግንኙነት ነበር፡፡ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ

ግን ህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ማለት ነው፡፡ የሚተገበረው በሲቪል ማህበራት፤ በሙያ ማህበራት፤

በባለሙያዎች ጥምረት ወዘተ ነው፡፡ በእኛ አገር በህዳሴው ግድብ የፐብሊክ ዲፕሎማሲ የሚሰሩ

የባለሙያዎች ጥምረት በአሁኑ ስዓት እየተጠናከሩ ነው፡፡ ለምሳሌ አገር አቀፍ የባለሙያዎች

ፓናል (National Panel of Experts)ና የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ባለሙያዎች ለአባይ

(Ethiopian International Professional Support for Abay):: ሌሎች ተመሳሳይ

የባለሙያዎችና የሲቪል ማህበራት ጥምረት መጠናከር ለፐብሊክ ዲፕሎማሲያችን ወሳኝ ናቸው፡፡

አምባሳደር ኢብራሒም

የቋንቋ ችግር ጥናትና ምርምር ለማካሄድ መሰናክል እንደሆነ ተነስቷል፡፡ ቋንቋ የምርምር

ስራዎችን ለመስራት መሰናክል መሆን የለበትም፡፡ በአማርኛ፤ በኦሮምኛ፤ በትግርኛና በሌሎች አፍ

መፍቻ ቋንቋዎቻችን በመጻፍ እንግሊዝኛና ሌሎች አለማቀፍ ቋንቋዎች የሚችሉ

ይተረጉሟቸዋል፡፡ ምሁራን የሚሰሯቸው የጥናት ስራዎች ለህዝብ ተደራሽነት እንዲኖራቸው፤

Page 23: BDU CLUSTER & CDS - 1st Nile... · bdu cluster & cds ሚያዚያ 20-21 ... ተ/ብርሀን የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ- ... የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ

ቃለ-ጉባኤ - ኢትዮጵያ አባይን ለልማት በመጠቀም መብትና አስፈላጊነት ላይ የምሁራን ተልእኮ - ሚያዚያ 20-21/2006; ባህር ዳር, ኢትዮጵያ

22 | P a g e

በየቀኑና በየሳምንቱ የሚታተሙ ጋዜጠኞችን መጠቀም ጥሩ ነው፡፡ ግብፅ ውስጥ አብዛኛው

የጋዜጦች አምድ የሚሸፈኑት፡ በዩኒቨርሰቲ ምሁራን ጥናታዊ ጽሁፎችና ቃለ መጠይቆች ነው፡፡

ዩኒቨርሲቲዎችም የራሳቸው ጋዜጦችና ጆርናሎች አሏቸው፡፡ ስለናይል ወንዝ የሚሰጡት ሽፋን

ከሌሎች ጉዳዮች የበለጠ ነው፡፡ የእኛ ዩኒቨርሲቲዎች ተመሳሳይ ስራ መስራት ይጠበቅባቸዋል፡፡

በተለያዩ የትምህር ዘርፎች ከውሃ ጋር በተገናኘ፤ የተለያዩ ባለሙያዎችን ማፍራት አለባቸው፡፡

አምባሳደር አሊ

የውጭ ጉዳይ ሚኒሰቴር ተመሳሳይ ውይይቶችን በሌሎች ዩኒቨርሰቲዎችና የማህበረሰብ ክፍሎች

ማድረግ አለበት የሚል ሃሳብ ከአስተያየት ሰጪዎች ተነስቷል፡፡ በተጨማሪም በውጭ የሚኖሩ

ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያን የጥናትና ምርምር ስራዎችን እንዲደግፉና ጥናቶችንም

በመስራት የፐብሊክ ዲፕሎማሲ እንዲሰሩ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ስራዎች መስራት አለበት

የሚል ሃሳብ ተነስቷል፡፡ ምንም እንኳን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሚሰራቸው ስራዎች ቢኖሩም፤

ቀጣይ የሚደረጉ ውይይቶች በዋናነት መሰራት ያለባቸው በዩኒቨርሲቲዎች መሆን አለባቸው፡፡

በዚህ ውይይት መድረክ የሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዚዳንቶችና ም/ፕሬዘዳንቶች ወይም

ተወካዮቻቸው ተገኝተዋል፡፡ ስለሆንም ለየዩኒቨርሰቲዎቻቸው ማህበረሰብ ተመሳሳይ ውይይቶችን

ማካሄድ አለባቸው፡፡ እሰከታችኞቹ የትምህርት እርከኖች በመውረድ ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ

መስራት የዩኒቨርሲቲዎች መሆን አለበት፡፡ ሥራዎች በቅብብሎሽ ካልተሰሩ ውጤታማ ሊሆኑ

አይችሉም፡፡

አገር ውስጥ ያሉትን የህብረተሰብ ክፍሎች በሳይንስ የተደገፉ ምርምርና ጥናት በመስራት

የወቅታዊ መረጃዎች ባለቤት እንዲሆንና ለአገሩ ራሱ ቆሞ እንዲናገር ከማስቻል ባሻገር በውጭ

የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የምርምር ስራዎችን እንዲያግዙና

ምርምሮችንም በመስራት ለአገራቸው ፐብሊክ ዲፕሎማሲ እንዲሰሩ ዩኒቨርሲቲዎች መላ ፈላጊ

ሊሆኑ ይገባል፡፡ ኮርሶች እንዲሰጡ በመጋበዝ፤ በዩኒቨርሲቲዎች ተቀጥረው እንዲሰሩ በማድረግና

በሌሎች መንገዶች በውጭ ያሉ ምሁራን የምርምርና የልማት ስራዎቻችንን እንዲያግዙ ማድረግ

ትችላላችሁ፡፡

አምባሳደር ብርሃነ ገ/ክርስቶስ

በየዩኒቨርሲቲዎች ያሉ ምሁራን ጠንካራ ጥናትና ምርምሮችን ለመስራት ብዙ ማነቆዎች

እንዳሉባቸውና ለአገራቸው የሚጠበቅባቸውን ሚና ለመጫዎት መሰናክል እንደሆነባቸው ከተለያዩ

Page 24: BDU CLUSTER & CDS - 1st Nile... · bdu cluster & cds ሚያዚያ 20-21 ... ተ/ብርሀን የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ- ... የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ

ቃለ-ጉባኤ - ኢትዮጵያ አባይን ለልማት በመጠቀም መብትና አስፈላጊነት ላይ የምሁራን ተልእኮ - ሚያዚያ 20-21/2006; ባህር ዳር, ኢትዮጵያ

23 | P a g e

አስተያየት ሰጪዎች መገንዘብ ይቻላል፡፡ የዩኒቨርሲቲ ኃላፊዎችና መምህራን ለተነሱ ችግሮች

የመፍትሄ ሀሳብ በማፈላለግና ችግሮችን በመቅረፍ አገሪቱ ከእናንተ የምትጠብቀውን ኃላፊነት

መወጣት ይጠበቅባችኋል፡፡ በውጭ ጉዳይና ደህንነት ፖሊሲ ትግበራ ላይ አበረን የምንሰራቸው

ስራዎች አሉ፡፡ የዛሬው መድረክ አበረን ለመስራት መሰረት የጣለ ነው፡፡ በውጭ ጉዳይና

ዲፕሎማሲ የሚሰሩ የምርምር ስራዎችን እንደግፋለን፡፡ አገራችን በርካታ የፐብሊክ ዲፕሎማቶች

ከምንግዜውም በላይ ያስፈልጉታል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎች በዲፕሎማሲና አለም አቀፍ ግንኙነት

የትምህርት ክፍሎች በመክፈት ዲፕሎማቶችን ማፍራት አለባችሁ እኛም እገዛ እናደርጋለን፡፡

በሁለተኛው ቀን ሶስት ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበዋል፡፡ ፅሁፎቹ በናይል ወንዝ ሐይድሮ ፖለቲካ

(Hydro-politics of the Nile)፤ የናይል ተፋስስ ሐይድሮሎጂ (Overview of the Nile

Watershed Hydrology)ና የመገናኛ ብዙሃንና የምሁራን ሚና ላይ ያተኮሩ ናቸው፡፡ በቀረቡ

ጽሁፎች ላይ ውይይቱን ይመሩ የነበሩት ዶክተር ኃ/ሚካኤል አበራ፤ የሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ

ፕሬዚዳንት የቀረቡ ፅሁፎች በናይል ተፋሰስና የወንዙ አጠቃቀም አጠቃላይ ፊዚካል፤

ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ሁኔታዎች ላይ ግንዛቤ እንድንጨብጥ የሚያግዙ ናቸው በማለት ገጸዋል፡፡

በሶስቱም ጽሁፎች የተነሱ ዋና ዋና ነጥቦች

1. በላይኞቹና በታችኞቹ ተፋሰስ አገሮች ዘላቂነት ያለው ልማት በማምጣት የጋራ ተጠቃሚነትን

ለማረጋገጥ ሁሉም አገሮች በትብብር መስራት እንዳለባቸው፣

2. መገናኛ ብዙሃንና ምሁራን የጋራ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረግ

እንደሚችሉ፣

3. ኢትዮጵያ ምንም እንኳ የናይል ወንዝ ውሃን በመጠቀም ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ሀይል

የማመንጨት አቅምና ሰፊ መስኖ ልማት አቅም እንዳላትና የሌሎችን አገሮች ጥቅም በማይጎዳ

መንገድ በመጠቀም የልማት ዕድገት ማረጋገጥ እንደምትችል፣

4. የላይኞቹም ሆነ የታችኞቹ ተፋሰስ አገሮች የውሃ ፍላጎት በየጊዜው እየጨመረ መምጣቱንና

ፍላጎታቸውን ለማርካት በየጊዜው ውይይቶችን በማካሔድ አብረው መስራት እንዳለባቸው

ጭብጥ እንድንይዝ አድርገውናል፡፡

ከወንዙ የሚገኙ ዘርፈ ብዙ ጥቅሞችን ለማረጋገጥ አገራችን የምታደርገውን እንቅስቃሴ ለመደገፍ

እንደ ዶክተሩ አስተያየት ምሁራን ሊተገብረው የሚገቡ ተግባራት፡-

በተፋሰሱን ሀይድሮሎጂና ሌሎች ቴክኒካል በሆኑ ጉዳዮች ዙሪያ ጥናቶችን ማካሄድ፣

Page 25: BDU CLUSTER & CDS - 1st Nile... · bdu cluster & cds ሚያዚያ 20-21 ... ተ/ብርሀን የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ- ... የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ

ቃለ-ጉባኤ - ኢትዮጵያ አባይን ለልማት በመጠቀም መብትና አስፈላጊነት ላይ የምሁራን ተልእኮ - ሚያዚያ 20-21/2006; ባህር ዳር, ኢትዮጵያ

24 | P a g e

የታላቁ የህዳሴ ግድብ ኢኮኖሚያዊ፤ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ፋይዳ ላይ ጥናቶችን

በመስራት ለታችኞቹ ተፋሰስ አገሮች፤ ለአገራችን ህዝቦችና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ

ማስረዳት፣

የምርምር ስራዎችን ከመስራት ባሻገር በተለያዩ አጋጣሚዎች (ወደ ውጭ ኮንፈረንስ

ላይ ለመሳተፍ፤ ለትምህርት ስንሄድ፤ አፍሪካ ውስጥ ካሉና ከሌሎች አገሮች

የኒቨርሲቲዎች ጋር በጋራ በመስራት፤ ለሌሎች የአፍሪካ አገሮች ተማሪዎች ሰኮላርሺፕ

በመስጠት፤ ወዘተ) የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ስራዎችን መስራት ዩኒቨርሲቲዎችና ምሁራን

በተናጥል መስራት፣

በአገራችን ከፍተኛ ተጽዕኖ ሊያሳድሩ የሚችሉ አገሮችን ቋንቋ በቅድመ ምረቃ (under

graduate)ና በድህረ-ምረቃ (Post graduate) በመክፈት የህዝብ ለህዝብ ትብብርን

ማጠናከር፡፡

ከላይ የተጠቀሱ ተግባራትን ለመተግበር ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች፡-

የሚሰሩ የጥናትና ምርምሮች በራሳችን ፋይናንስ መመራት አለባቸው፡፡ ስለሆነም

መንግስትና ዩኒቨርሲቲዎች ለምርምር ከፍተኛ በጀት በመመደብ ምሁራንን ማንቀሳቀስ

ይጠቀምባቸዋል፡፡ በውጭ በጀት ድጋፍ የሚሰሩ ጥናቶች በድጋፍ ሰጭ አካላት ማዕቀፍ

(Research Framework) ስለሚሰሩ አላስፈላጊ ድምዳሜ ላይ በመድረስ የአገራችንን

ጥቅም ሊጎዱ ይችላሉ፣

ተጨባጭ መረጃ ላይ የተመሰረቱና ድግግሞሽን የሚያስቀሩ መሆን አለባቸው፡፡ በተጨባጭ

መረጃ ላይ ተመስርቶ የሚሰራ የጥናትና የምርምር ስራ ህዝባችንንም ሆነ የአለም አቀፉን

ማህበረሰብ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ከፍተኛ እገዛ ያደርጋል፡፡

በተሰጡ አስተያየቶችና ለተነሱ ጥያቄዎች በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ ኃላፊዎች የተሰጠ

መልስ

አምባሳደር ዲና ሙፍቲ

በመንግስት ባለስልጣናትና በዩኒቨርሲቲ ምሁራን መካከል የሚደረግ እንደዚህ አይነት ውይይት

መቀጠል አለበት የተባለው እኛም እንደግፈዋለን፡፡ ተመሳሳይ ውይይቶች ወደፊት ለማድረግ

እንጥራለን፡፡ ቀጣይነት እንዲኖረው የዩኒቨርሰቲዎችንም ጥረት ይጠይቃል፡፡ በመድረኩ የቀረቡ

Page 26: BDU CLUSTER & CDS - 1st Nile... · bdu cluster & cds ሚያዚያ 20-21 ... ተ/ብርሀን የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ- ... የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ

ቃለ-ጉባኤ - ኢትዮጵያ አባይን ለልማት በመጠቀም መብትና አስፈላጊነት ላይ የምሁራን ተልእኮ - ሚያዚያ 20-21/2006; ባህር ዳር, ኢትዮጵያ

25 | P a g e

ጽሁፎች፤ የተሰጡ ሃሳቦችና የተደረሰባቸው ድምዳሜዎች በመጽሄት ወይም በሌላ መልኩ

ተዘጋጅተው ለልዩ ልዩ ተቋማት መሰራጨት አለባቸው፡፡ ግንዛቤ ለመፍጠር ይረዳሉ፤

ለአፈጻጸምም ያግዛሉ፡፡

አማባሳደር ፍስሃየ ይመር

በውጭ ጉዳይና ብሄራዊ ደህንነት ፖሊሲ እንዲሁም በሌሎች የመንግስት ፖሊሲዎችና

ስትራቴጂዎች ላይ ትችቶች በምሁራን በሚቀርብበት ጊዜ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት

አሉታዊ መልኩ የመመለከት ባህል አለ፡፡ ምሁራንም በፖሊሲ ትችት የሚሰራ ጥናታዊ ጽሑፍ

ከፖሊቲካ አንጻር ብቻ በማየት ብዙ ጊዜ መስራት አይደፍሩም የሚል ሃሳብ ተነስቷል፡፡ ይህ

አይነት አመለካከት የለም ማለት አልችልም፡፡ ነገር ግን የተሳሳተ አመለካከት ነው፡፡ ምሁራን

ፖሊሲዎችን በሚተቹበት ጊዜ ትኩረት ማድረግ ያለባቸው የሚሰጡት ትችት ለፖሊሲው የበለጠ

መዳበርና ለአፈጻጸም ከፍተኛ እገዛ የሚያደርግ መሆኑን ነው፡፡ አሉታዊ ገጽታው ላይ ብቻ

ትኩረት ማድረግና ማጣጣል ለፖለቲከኞች ላይዋጥላቸው ይችላል፡፡ ፖለቲከኛችም የፖሊሲ

ትንታኔዎችን በማጤን ጠቃሚ የሆኑ ነጥቦችን በመውሰድ ፖሊሲዎችን ማዳበር አለባቸው፡፡

ፐብሊክ ዲፕሎማሲ ከነባሩ የዲፐሎማሲ አቀራረብ የሚለየው የሚል ጥያቄ ተነስቷል፡፡ ነባሩ

የዲፕሎማሲ ስራ መንግስት ለመንግስት ግንኙነት ነበር፡፡ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ ግን ህዝብ ለህዝብ

ግንኙነት ማለት ነው፡፡ የሚተገበረው በሲቪል ማህበራት፤ በሙያ ማህበራት፤ በባለሙያዎች

ጥምረት ወዘተ ነው፡፡ በእኛ አገር በህዳሴው ግድብ የፐብሊክ ዲፕሎማሲ የሚሰሩ የባለሙያዎች

ጥምረት በአሁኑ ስዓት እየተጠናከሩ ነው፡፡ ለምሳሌ አገር አቀፍ የባለሙያዎች ፓናል (National

Panel of Experts) ና የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ባለሙያዎች ለአባይ (Ethiopian International

Professional Support for Abay):: ሌሎች ተመሳሳይ የባለሙያዎችና የሲቪል ማህበራት

ጥምረት መጠናከር ለፐብሊክ ዲፕሎማሲያችን ወሳኝ ናቸው፡፡

አምባሳደር ኢብራሒም

የቋንቋ ችግር ጥናትና ምርምር ለማካሄድ መሰናክል እንደሆነ ተነስቷል፡፡ ቋንቋ የምርምር

ስራዎችን ለመስራት መሰናክል መሆን የለበትም፡፡ በአማርኛ፤ በኦሮምኛ፤ በትግርኛና በሌሎች አፍ

መፍቻ ቋንቋዎቻችን በመጻፍ እንግሊዝኛና ሌሎች አለማቀፍ ቋንቋዎች የሚችሉ

Page 27: BDU CLUSTER & CDS - 1st Nile... · bdu cluster & cds ሚያዚያ 20-21 ... ተ/ብርሀን የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ- ... የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ

ቃለ-ጉባኤ - ኢትዮጵያ አባይን ለልማት በመጠቀም መብትና አስፈላጊነት ላይ የምሁራን ተልእኮ - ሚያዚያ 20-21/2006; ባህር ዳር, ኢትዮጵያ

26 | P a g e

ይተረጉሟቸዋል፡፡ ምሁራን የሚሰሯቸው የጥናት ስራዎች ለህዝብ ተደራሽነት እንዲኖራቸው፤

በየቀኑና በየሳምንቱ የሚታተሙ ጋዜጦችን መጠቀም ጥሩ ነው፡፡ ግብፅ ውስጥ አብዛኛው

የጋዜጦች አምድ የሚሸፈኑት፡ በዩኒቨርሰቲ ምሁራን ጥናታዊ ጽሁፎችና ቃለ-መጠይቆች ነው፡፡

ዩኒቨርሲቲዎችም የራሳቸው ጋዜጦችና ጆርናሎች አሏቸው፡፡ ስለናይል ወንዝ የሚሰጡት ሽፋን

ከሌሎች ጉዳዮች የበለጠ ነው፡፡ የእኛ ዩኒቨርሲቲዎች ተመሳሳይ ስራ መስራት ይጠበቅባቸዋል፡፡

በተለያዩ የትምህር ዘርፎች ከውሃ ጋር በተገናኘ፤ የተለያዩ ባለሙያዎችን ማፍራት አለባቸው፡፡

አምባሳደር አሊ

የውጭ ጉዳይ ሚኒሰቴር ተመሳሳይ ውይይቶችን በሌሎች ዩኒቨርሰቲዎችና የማህበረሰብ ክፍሎች

ማድረግ አለበት የሚል ሃሳብ ከአስተያየት ሰጪዎች ተነስቷል፡፡ በተጨማሪም በውጭ የሚኖሩ

ኢትዮጵያንና ትውልደ ኢትዮጵያን የጥናትና ምርምር ስራዎችን እንዲደግፉና ጥናቶችንም

በመስራት የፐብሊክ ዲፕሎማሲ እንዲሰሩ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ስራዎች መስራት አለበት

የሚል ሃሳብ ተነስቷል፡፡ ምንም እንኳን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሚሰራቸው ስራዎች ቢኖሩም፤

ቀጣይ የሚደረጉ ውይይቶች በዋናነት መሰራት ያለባቸው በዩኒቨርሲቲዎች መሆን አለባቸው፡፡

በዚህ ውይይት መድረክ የሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዚዳንቶችና ም/ፕሬዚዳንቶች ወይም

ተወካዮቻቸው ተገኝተዋል፡፡ ስለሆነም ለየዩኒቨርሰቲዎቻቸው ማህበረሰብ ተመሳሳይ ውይይቶችን

ማካሄድ አለባቸው፡፡ እሰከታችኞቹ የትምህርት እርከኖች በመውረድ ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ

መስራት የዩኒቨርሲቲዎች መሆን አለበት፡፡ ሥራዎች በቅብብሎሽ ካልተሰሩ ውጤታማ ሊሆኑ

አይችሉም፡፡

አገር ውስጥ ያሉትን የህብረተሰብ ክፍሎች በሳይንስ የተደገፉ ምርምርና ጥናት በመስራት

የወቅታዊ መረጃዎች ባለቤት እንዲሆንና ለአገሩ ራሱ ቆሞ እንዲናገር ከማስቻል ባሻገር በውጭ

የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የምርምር ስራዎችን እንዲያግዙና

ምርምሮችንም በመስራት ለአገራቸው ፐብሊክ ዲፕሎማሲ እንዲሰሩ ዩኒቨርሲቲዎች መላ ፈላጊ

ሊሆኑ ይገባል፡፡ ኮርሶች እንዲሰጡ በመጋበዝ፤ በዩኒቨርሲቲዎች ተቀጥረው እንዲስሩ በማድረግና

በሌሎች መንገዶች በውጭ ያሉ ምሁራን የምርምርና የልማት ስራዎቻችንን እንዲያግዙ ማድረግ

ትችላላችሁ፡፡

አምባሳደር ብርሃነ ገ/ክርስቶስ

Page 28: BDU CLUSTER & CDS - 1st Nile... · bdu cluster & cds ሚያዚያ 20-21 ... ተ/ብርሀን የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ- ... የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ

ቃለ-ጉባኤ - ኢትዮጵያ አባይን ለልማት በመጠቀም መብትና አስፈላጊነት ላይ የምሁራን ተልእኮ - ሚያዚያ 20-21/2006; ባህር ዳር, ኢትዮጵያ

27 | P a g e

በየዩኒቨርሲቲዎች ያሉ ምሁራን ጠንካራ ጥናትና ምርምሮችን ለመስራት ብዙ ማነቆዎች

እንዳሉባቸውና ለአገራቸው የሚጠበቅባቸውን ሚና ለመጫዎት መሰናክል እንደሆነባቸው ከተለያዩ

አስተያየት ሰጪዎች መገንዘብ ይቻላል፡፡ የዩኒቨርሲቲ ኃላፊዎችና መምህራን ለተነሱ ችግሮች

የመፍትሄ ሀሳብ በማፈላለግና ችግሮችን በመቅረፍ አገሪቱ ከእናንተ የምትጠብቀውን ኃላፊነት

መወጣት ይጠበቅባችሗል፡፡ በውጭ ጉዳይና ደህንነት ፖሊሲ ትግበራ ላይ አብረን የምንሰራቸው

ስራዎች አሉ፡፡ የዛሬው መድረክ አብረን ለመስራት መሰረት የጣለ ነው፡፡ በውጭ ጉዳይና

ዲፕሎማሲ የሚሰሩ የምርምር ስራዎችን እንደግፋለን፡፡ አገራችን በርካታ የፐብሊክ ዲፕሎማቶች

ከምንግዜውም በላይ ያስፈልጓታል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎች በዲፕሎማሲና አለም አቀፍ ግንኙነት

የትምርት ክፍሎች በመክፈት ዲፕሎማቶችን ማፍራት አለባችሁ እኛም እገዛ እናደርጋለን፡፡

የሁለተኛው ቀን ስብሰባ 21/08/06 ዓም

በሁለተኛው ቀን ሶስት ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበዋል፡፡ ፅሁፎቹ በናይል ወንዝ ሐይድሮ ፖለቲካ

(Hydro-politics of the Nile)፤ የናይል ተፋስስ ሐይድሮሎጂ (Overview of the Nile

Hydrology) ና የመገናኛ ብዙሃንና የምሁራን ሚና ላይ ያተኮሩ ናቸው፡፡

የውሃ ፖለቲካ እና ዲፕሎማሲ በናይል ወንዝ ተፋሰሰ

በአቶ ኤርሚያስ አያሌዉ -በባ/ዳር ዩኒቨርሲቲ የህግ ት/ርት ክፍል

አቶ ኤርሚያስ አያሌው ጽሁፋቸውን ማቅረብ የጀመሩት ምን ከምን መቅደም አለበት የሚለውን ንድፈ-

ሃሳባቸውን ተፈጥሮ ሃብትን መንከባከብና ማልማት ለመከፋፈል ከማሰብ መቅደም አለበት በማለት ነበር::

ሌላው በአለም ላይ ያሉ እውነቶቸ አንደኛው ሌላኛውን የመቆጣጠር (hegemony) እና ከዛ ለመውጣት

የሚኖር ተቃውሞ (counter hegemony) እንዲሁም የሃይል ሚዛንን (power) አስመልክቶ ደግሞ soft

and hard ሊባል የሚችል ማለትም ሶፍት የሚባለው የማሳመን አቅም ላይ የተመሰረተ መሆኑን እና

ሃርድ ደግሞ ኢኮኖሚያዊ፣ እስትራቴጂካዊና የመሳሪያ አቅም እንደሆነ አቅርበዋል:: ከዘህ ጋር በተያያዘ

አሁን ያለው ሁኔታ የአካባቢ ጥበቃና ስነ-ምህዳር ጉዳዮች የተረሱበት በዛ ላይም ድህነት ተጨምሮበት

ነገሮቸ ሁሉ የተባባሱበት ሁኔታ ተፈጥሯል:: ግብፅ ከዚህ አንፃር የማሳመን ሃይሏን ተጠቅማና

ኢኮኖሚያዊ ብቃቷን ከስዊስ ካናል ና ከእስራኤል ያላት ቀረቤታ ጋር ተያይዞ የናይልን ውሃ ለራሷ ብቻ

ወይም በትንሹ ለሱዳን አካፍላ ለመጠቀም ችላ ቆይታለች:: ነገር ግን በዚህ ዘመን የነበረውን የግብጽ

የሃይል የበላይነት መቃወም የሚቻልበት (counter hegemony) ላይ የደረሱት የናይል ተፋሰስ ሃገሮች

ኢትዮጵያን ጨምሮ ሁኔታ ተፈጥራል:: ስለሆነም የተፋሰሱ ሃገራት ግብፅን ጨምሮ ሊሰሩት የሚገባው

Page 29: BDU CLUSTER & CDS - 1st Nile... · bdu cluster & cds ሚያዚያ 20-21 ... ተ/ብርሀን የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ- ... የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ

ቃለ-ጉባኤ - ኢትዮጵያ አባይን ለልማት በመጠቀም መብትና አስፈላጊነት ላይ የምሁራን ተልእኮ - ሚያዚያ 20-21/2006; ባህር ዳር, ኢትዮጵያ

28 | P a g e

የጋራ ራዕይ ያለው ትብብር፣ አሳታፊ ጠንካራና ሁሉን አቀፍ የሆነ አስተዳደር እና የአካባቢ ሃብትን

መሰረተ ያደረገ የህግ ማዕቀፍ ብሎም ዘላቂ የፖለቲካ መረጋጋት፣ የከባቢው ሃገራት ደህንነት እና

ኢኮኖሚ ብልፅግና ማረጋገጥ ይገባል:: እስካሁን ባለው ሁኔታ የተፋሰሱ ሃገራት እስካሁን ማድረግ የቻሉት

1ኛ. የናይል ተፋሰስ የትብብር መድረክ (Nile Basin Initiative-NBI) በማቋቋም ሃገራት የምክክርና

የመከራከሪያ መድረክ መፍጠር ችለዋል እና 2ኛ) የናይል ወንዝ ተፋሰስ ማዕቀፍ ስምምነት (Nile River

basin Framework Agreement) ደግሞ የናይል እና አካባቢው ለተፋሰሱ ሃገራት ያለው ጠቀሜታ፣

የትብብር እና መተጋገዝ አስፈላጊነትን እንዲሁም ፍትሃዊና ምክኒያታዊ የውሃ አጠቃቀም ለማስፈን

የድርሻውን እየተወጣ ይገኛል::

የናይል ዉሃ ሀብት አጠቃቀምና የምሁራን ተልዕኮ በአቶ ጎራዉ ጎሹ - በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የብሉ ናይል ዉሃ ኢንስትቲዩት ዳይሬክተር

አቶ ጎራው ጎሹ የፅሁፋቸው ይዘት በሶስት ርዕሶች ላይ ያተኮረ ሲሆን፤ 1ኛ) የጥቁር አባይ ውሃ ሃብትና

አጠቃቀሙ 2ኛ) የናይል ውሃ ሃብትና አጠቃቀሙ እና 3ኛ) በናይል ውሃ አጠቃቀም የምሁራን ሚና

በሚል የቀረቡ ናቸው:: በመጀመሪያ የጥቁር አባይ ውሃ ሃብትን ነጥሎ ማየት እንደሚያስፈልግ ገልፀው

ይህ የውሃ ሃብት አመታዊ ፍሰቱ 48 ሚሊዮን ኪሜ3 ወይም 1536 ሜ3 በሴኮንድ (1912-1997)

እንደሆነ እና ካሉት ንዑስ ተፋሰሶች ትልቁ እንደሆነ፤ በቆዳ ስፋቱ ደግሞ በኢትዮጵያ ካሉት ተፋሰሶች 1ኛ

ሆኖ የአገራችንን 17%ቱን የቆዳ ሽፋን እንደሚሸፍን በጥቅሉ 176000 ኪሜ2 እንደሚሆን ተገልጿል::

በናይል ተፋሰስ ትልቁ ገባሪ ወንዝ ጥቁር አባይ ነው:: ከአየር ንብረት አንፃር የመፈራረቅ ባህሪይ ያለው

ሁኖ የላየኛው የተፋሰሱ ክፍል ከ15-18 0C፣ የተፋሰሱ የታችኛው ክፍል ደግሞ 300C ይደርሳል

እንዲሁም ዝናቡም እስከ 1421 ሚ.ሜ በአማካኝ ይደርሳል:: የውሃ ፍሰቱን በግራፍ ተደግፎ ስናይ ሱዳን

እና ኢትዮጵያ ደንበር ላይ ለ30 ዓመታት (1960-1990) በተደረገ ክትትል ተመሳሳይነት ያለውና ከፍተኛ

ሲሆን ካርቱም ላይ ግን የመቀነስ ሁኔታን አሳይቷል:: ይህ ማለት ኢትዮጵያ ምንም አይነት ውሃ

እየተጠቀመች እንዳልሆነ እና ሱዳን ውሃውን እየተጠቀመችበት መሆኑን ይገልፃል:: ኢትዮጵያ የአባይ

ወንዝን ከመጠቀም አንፃር ስናይ አበዛኛው ህዝብ በዝናብ ውሃ የሚያመርት እና ምንም ከዚህ ግባ የሚባል

የመስኖ ልማት እንደሌለ መረጃዎች ያመላክታሉ:: ፊንቻ የሃይድሮ ፓዎር ፕሮጀክት በ8145ሄ/ር ላይ ብቻ

የመስኖ ልማት እንዳለ ይታወቃል:: ጥናቶች እንደሚያሳዩት ግን እስከ 815,581 ሄ/ር እንደሚደርስና

45.856 ሄ/ር በአነስተኛ፣ 130,395 ሄ/ር በመካከለኛ እና 639,330 ሄ/ር በከፍተኛ ስኬል ሊለማ

እንደሚችል ይገለፃል:: ከዚሀ አንፃር ሱዳን ወደ 1.3 ሚሊዮን ሄ/ር ግብፅ ደግሞ 1 ሚሊዮን ሄ/ር መሬት

በመስኖ ያለማሉ:: ከሃይድሮ ፓዎር ልማት አንፃር ኢትዮጵያ ውስጥ ከ120 በላይ አቅሙ ያላቸው

ቦታዎች የተለዩ ሲሆን 3634 - 7629 ሜጋዋት አጠቃላይ የሃይል ምርት እንደሚኖር ይህ ደግሞ ከ20-

40% ከአጠቃላይ አቅም አንፃር እንደሆነ እና ከአስዋን 2.5 ጊዜ እንደሚበዛ ጥናቶች ያመላክታሉ:: ሌላው

የተገለፀው ጉዳይ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በግንባታ ላይ ያለ እና ከአገራችን ከሚነሳው ውሃ ፍሰት

Page 30: BDU CLUSTER & CDS - 1st Nile... · bdu cluster & cds ሚያዚያ 20-21 ... ተ/ብርሀን የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ- ... የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ

ቃለ-ጉባኤ - ኢትዮጵያ አባይን ለልማት በመጠቀም መብትና አስፈላጊነት ላይ የምሁራን ተልእኮ - ሚያዚያ 20-21/2006; ባህር ዳር, ኢትዮጵያ

29 | P a g e

44% ና 60% ደግሞ አስዋን ግድብ ውሃ እንደሚያረጋጋ (regulate)፤ 15860 ጊጋዋትሃወር በአመት

እንደሚመረትበትና በአጠቃላይ 74 ቢሊዮን ኪሜ ውሃ ግድቡ እንደሚይዝ ይጠበቃል:: በቀንም 2 ሚሊዮን

ዩሮ ገቢ እንደሚያስገኝ ተገምቷል:: የህዳሴ ግድብ ጠቀሜታው ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለታችኛው

ተፋሰስ ሃገራትም እንደሆነ ሲገለፅ፤ ሱዳንን ከጎርፍ ይጠብቃል፣ አመቱን ሙሉ የተረጋጋ የወንዙን ፍሰት

እንድታገኝ ይረዳል፣ ድርቅን ይከላከላል፣ ከደለል ይጠብቃል፣ አዲስ የሃይል ምንጭ ማግኘት ያስችላል

እንዲሁም በተመሳሳይ ግብፅን የአስዋን ግድብ ውሃ ስርገትን ይከላከላል፣ አመቱን ሙሉ የተረጋጋ

የወንዙን ፍሰት እንድታገኝ ይረዳል፣ ድርቅን ይከላከላል፣ ከደለል ይጠብቃል፣ የውሃ ብክነትን ይከላከላል

በተጨማሪም የሃይል አቅርቦትን ያሻሽላል::

ሁለተኛው የናይል ውሃ ሃብትን እንዳጠቃላይ ስናይ ተፋሰሱ የአየር ንብረት መለዋወጥ የሚያጠቃው

አካባቢ ነው:: ጥቁር አባይ ዋናው የተፋሰሱ ገባሪ ሲሆን 85% ከዚሁ ተፋሰስ የሚገኝ ነው:: ናይል ተፋሰስ

11 አገሮችን የሚያካልል እና ለዘመናት የታችኛው ሃገሮች ብቻ በውሃው ጥገኛ ሆነው የኖሩበት ሁኔታ

ይታያል:: በአሁኑ ጊዜ የላይኛው ተፋሰስ ሃገራት በወንዙ የመጠቀም ፍላጎት እየጨመረ መምጣቱ ጋህድ

ሆኗል:: የአስዋን ግድብ የውሃ በጀት 15 ቢኪሜ ከኢኳቶሪያል ፕላቶ እና 79.5 ቢኪሜ ደግሞ ከጥቁር

አባይ ተፋሰስ የሚገኝ ነው:: የአስዋን ግድብ ውሃ ስርጭት 45% ለአመታዊ መስኖ፣ 8% ለቤዚን መስኖ

እና ቀሪው 47% ደግሞ ወደ ባህር የሚፈስ ነው:: ይህ ስርጭት ሲታይ በጣም ከፍተኛው ውሃ

አገልግሎት ሳይሰጥ ወደ ባህር መሄዱ ከአጠቃቀም አኳያ ግብፅ ማሻሻል ያለባት ነገር እንዳለ ያሳያል::

የናይል ያለፉት ዘመናት አጠቃቀም በጣም አከራካሪ የነበረ ጉዳይ ነው፤ በተለይ የ1959 ስምምነት

የውሃውን 55.5 ቢኪሜ ለግብፅ ቀሪውን 18.5 ቢኪሜ ደግሞ ለሱዳን የሚሰጥ እና የላይኛውን ተፋሰስ

ሃገሮች ያገለለ ነበር:: ስለሆነም ይህን ሁኔታ ለመቀየርና በ1998 እኤአ የናይል ተፋሰስ የትብብር መድረክ

(Nile Basin Initiative-NBI) በማቋቋም ወደ ስራ ተገብቷል:: የውሃ አጠቃቀሙን ለማሻሻል የላይኛው

ተፋሰስ ሃገራት የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራን ማከናወን እና ፍትሃዊና ምክኒያታዊ የሆነ የውሃ አጠቃቀምን

ማስፈን የሚያስፈልግ ሲሆን፤ በታችኛው ተፋሰስ ሃገራት ደግሞ የውሃ አጠቃቀምን ማሻሻል፣ የውሃ

ትነትን መቆጣጠር፣ ፍትሃዊና ምክኒያታዊ የውሃ አጠቃቀምን ማስፈንና የመስኖ ውሃ አጠቃቀምን

ማሻሻል እንደሚያስፈልግ ተገለጿል::

ከውሃ ሃብት አስተዳደር አንፃር ዋና ተግዳሮቶች (Challenges) ተብለው የቀረቡት:- በቂ የውሃ መጠን

በጥራት አቅርቦትን ማረጋገጥ፣ አየር ንብረትን ከመተንበይ ጋር ተያይዞ ያለ ሊገመት የማይቻል መሆን፣

ያለንን የውሃ መጠን ጥራትና ሂደቱንና መስተጋብሩን የማወቅ እጥረት፣ የውሃ ፍላጎት መጨመር፣

ከምግብ ዋስትና ጋር ተያይዞ የውሃ እጥረት ዋናው ጉዳይ መሆን፣ በአለም 215 አገር አቋራጭ ወንዞች

እና 300 የከርሰምድር ውሃ ተፋሰሶች መኖር፣ ከውሃ ጋር የተያያዙ 70 የሚደረሱ ግጭቶች ሲሆኑ

አለማቀፋዊ እውነታዎችን ስናይ ደግሞ የሚገባውን ያህል መታወቅ ያልቻለ የአየር ንብረት እና ዘመኑ

ሰውን ብቻ ማዕከል ያደረገ መሆኑ (Era of Anthropocene) የውሃ ፍላጎት መጨመር፣ አቅርቦቱ

Page 31: BDU CLUSTER & CDS - 1st Nile... · bdu cluster & cds ሚያዚያ 20-21 ... ተ/ብርሀን የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ- ... የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ

ቃለ-ጉባኤ - ኢትዮጵያ አባይን ለልማት በመጠቀም መብትና አስፈላጊነት ላይ የምሁራን ተልእኮ - ሚያዚያ 20-21/2006; ባህር ዳር, ኢትዮጵያ

30 | P a g e

መቀነስና የመጠኑ ሁኔታ የሚለዋወጥና እርግጠኛ መሆን አለመቻል የሚሉት እንደሚገኙበት ተገልጿል::

ይህ እውነታ ከኢትዮጵያ አንፃር ደግሞ አገራችን የተለያዩ ፖሊሲዎችና እስትራቴጂዎች መኖራቸው፣

ውሃ ከምግብ ዋስትና እና ኢኮኖሚ ልማት አንፃር ቀዳሚ ሆኖ የተያዘ መሆኑ፣ የፖሊሲ-ሳይንስ ቁርኝት

አሰፈላጊ ሆኖ መታየቱ እና ለፖሊሲ አውጭዎች ሊገባ በሚችል መልኩ ሳይንስ እንዲቀርብ መፈለጉ ዋና

ዋና ናቸው:: በመጨረሻም የምሁራን ተልዕኮ ምን መሆን አለበት በሚል:- ለፖሊሲ አሰፈላጊ የሆኑ

መረጃዎችን ማሰባሰብና መቀመር፣ ከውሃ ጋር በተያያዘ ተከታታይ ወርክሾፖች ማካሄድ፣ የግንዛቤ

መፍጠሪያ ስራዎች መስራት፣ ለምርምር እና ልማት ችግሮችን ከመለየት አንፃር ማህበረሰብ እና ባለድርሻ

አካላትን ያማከለ እስትራቴጂ ማዘጋጀት በሚል ለውይይት ቀረበዋል:: እግረመንገዱንም በባህር ዳር

ዩኒቨርሲቲ የብሉ ናይል ውሃ ኢንስቲትዩት ከምርምርና ማስተማር ተግባር ጋር አያይዞ በጥቁር አባይ

ተፋሰስ አካባቢ የተዘጋጀውን የ5 ዓመት እስትራቴጅክ እቅድ እና ያከናወናቸውን የምርምር ስራዎች፣

የማህበረሰብ አገልግሎቶች እና የማማከር ስራዎቸ ተገልፀዋል::

ናይል ሚዲያና ምሁራን- የኢትዮጵያን የናይል ዉሃን ለመጠቀም ባላት ፍላገት በንቁ መሳተፍ አስፈላጊነት

በአቶ ዘሪሁን አበበ - ከአዲሰ አበባ ዩኒቨርሲቲ

አቶ ዘሪሁን አበበ ፅሁፋቸው ትኩረት ያደረገው ሚዲያ ያለውን ፋይዳ ሲገልፁ ሚዲያ እንደ ውጭ ጉዳይ

ፖሊሲ መሳሪያነት ሊያገለግል እንደሚችል፣ ለህዝብ ግንኙነትና ዲፕሎማሲ፣ ለመንግስት ኃይል (Soft

Power) ከተሰሚነት አንፃር እንደሚሆን፣ ለተዋስኦ ግንባታ መሳሪያነት (instruments of Discourse

formation) እንደሚያገለግል ገልፀዋል:: ከዛም የአባይ ውሃን ፖለቲካ ባለፉት ዘመናት የነበረበትን ሁኔታ

ሲገልፁ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም መገለጫዎችንም አያይዘው አቅርበዋል:: ስለ ግብፅ ሁኔታና

በመጨረሻም የብዙሃን መገናኛ ሚናና በኢትዮጵያ የናይል ብሔራዊ ጥቅም ዙሪያ በአገር ውስጥና ከውጭ

ግንኙነት አንፃር መሰራት የሚገባቸውን ጉዳዮቸ ተንትነዋል:: በመጨረሻም በቀጣይነት ምን መሰራት

አለበት እነዚህን ስራዎች ማን ምን ይስራ የሚለውን ሃሳባቸውን በማቅረብ ንግግራቸውን ቋጭተዋል::

በቀረቡ ጽሁፎች ላይ ውይይቱን ይመሩ የነበሩት ዶ/ር ኃ/ሚካኤል አበራ፤ የሲቪል ሰርቪስ

ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት የቀረቡ ፅሁፎች በናይል ተፋሰስ ና የወንዙ አጠቃቀም አጠቃላይ ፊዚካል፤

ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ሁኔታዎች ላይ ግንዛቤ እንድንጨብጥ የሚያግዙ ናቸው በማለት

ገልጸዋል፡፡ በሶስቱም ጽሁፎች የተነሱ ዋና ዋና ነጥቦች፡-

Page 32: BDU CLUSTER & CDS - 1st Nile... · bdu cluster & cds ሚያዚያ 20-21 ... ተ/ብርሀን የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ- ... የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ

ቃለ-ጉባኤ - ኢትዮጵያ አባይን ለልማት በመጠቀም መብትና አስፈላጊነት ላይ የምሁራን ተልእኮ - ሚያዚያ 20-21/2006; ባህር ዳር, ኢትዮጵያ

31 | P a g e

1. በላይኞቹና በታችኞቹ ተፋሰስ አገሮች ዘላቂነት ያለው ልማት በማምጣት የጋራ

ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ሁሉም አገሮች በትብብር መስራት እንዳለባቸው፣

2. መገናኛ ብዙሃንና ምሁራን የጋራ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ

ማድረግ እንደሚችሉ፣

3. ኢትዮጵያ ምንም እንኳ የናይል ወንዝ ውሃን በመጠቀም ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ሀይል

የማመንጨት አቅምና ሰፊ መስኖ ልማት አቅም እንዳላትና የሌሎችን አገሮች ጥቅም

በማይጎዳ መንገድ በመጠቀም የልማት ዕድገት ማረጋገጥ እንደምትችል፣

4. የላይኞቹም ሆነ የታችኞቹ ተፋሰስ አገሮች የውሃ ፍላጎት በየጊዜው እየጨመረ

መምጣቱንና ፍላጎታቸውን ለማርካት በየጊዜው ውይይቶችን በማካሔድ አብረው

መስራት እንዳለባቸው ጭብጥ እንድንይዝ አድርገውናል፡፡

ከወንዙ የሚገኙ ዘርፈ ብዙ ጥቅሞችን ለማረጋገጥ አገራችን የምታደርገውን እንቅስቃሴ ለመደገፍ

እንደ ዶክተሩ አስተያየት ምሁራን ሊተገብሯቸው የሚገቡ ተግባራት፡-

በተፋሰሱን ሀይድሮሎጂና ሌሎች ቴክኒካል በሆኑ ጉዳዮች ዙሪያ ጥናቶችን ማካሄድ፣

የታላቁ የህዳሴ ግድብ ኢኮኖሚያዊ፤ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ፋይዳ ላይ ጥናቶችን በመስራት

ለታችኞቹ ተፋሰስ አገሮች፤ ለአገራችን ህዝቦችና ለአለም አቀፉ ማህበረስብ ማስረዳት፣

የምርምር ስራዎችን ከመስራት ባሻገር በተለያዩ አጋጣሚዎች (ወደ ውጭ ኮንፈረንስ ላይ

ለመሳተፍ፤ ለትምህርት ስንሄድ፤ አፍሪካ ውስጥ ካሉና ከሌሎች አገሮች የኒቨርሲቲዎች

ጋር በጋራ በመስራት፤ ለሌሎች የአፍሪካ አገሮች ተማሪዎች ሰኮላርሺፕ በመስጠት፤

ወዘተ.) የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ስራዎችን መስራት ዩኒቨርሲቲዎችና ምሁራን በተናጥል

መስራት፣

በአገራችን ከፍተኛ ተጽዕኖ ሊያሳድሩ የሚችሉ አገሮችን ቋንቋ በቅድመ ምረቃ (under

graduate) ና በድህረ-ምረቃ (Post graduate) በመክፈት የህዝብ ለህዝብ ትብብርን

ማጠናከር፡፡

ከላይ የተጠቀሱ ተግባራትን ለመተግበር ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች፡-

የሚሰሩ የጥናትና ምርምሮች በራሳችን ፋይናንስ መመራት አለባቸው፡፡ ስለሆነም

መንግስትና ዩኒቨርሲቲዎች ለምርምር ከፍተኛ በጀት በመመደብ ምሁራንን ማንቀሳቀስ

Page 33: BDU CLUSTER & CDS - 1st Nile... · bdu cluster & cds ሚያዚያ 20-21 ... ተ/ብርሀን የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ- ... የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ

ቃለ-ጉባኤ - ኢትዮጵያ አባይን ለልማት በመጠቀም መብትና አስፈላጊነት ላይ የምሁራን ተልእኮ - ሚያዚያ 20-21/2006; ባህር ዳር, ኢትዮጵያ

32 | P a g e

ይጠቀምባቸዋል፡፡ በውጭ በጀት ድጋፍ የሚሰሩ ጥናቶች በድጋፍ ሰጭ አካላት ማዕቀፍ

(Research Framework) ስለሚሰሩ አላስፈላጊ ድምዳሜ ላይ በመድረስ የአገራችንን

ጥቅም ሊጎዱ ይችላሉ፡፡

ተጨባጭ መረጃ ላይ የተመሰረቱና ድግግሞሽን የሚያስቀሩ መሆን አለባቸው፡፡ በተጨባጭ

መረጃ ላይ ተመስርቶ የሚሰራ የጥናትና የምርምር ስራ ህዝባችንንም ሆነ የአለም አቀፉን

ማህበረሰብ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ከፍተኛ እገዛ ያደርጋል፡፡

በቀረቡ ፅሁፎች ላይ የተሰጡ አስተያየቶች

ፕሮፌሰር አፈወርቅ፤ ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ

በሶስቱም አቅረቢዎች በናይል ተፋስስ ሀይደሮሎጂና ሀይድሮ ፖለቲካ ጠቅላላ ዕውቀት በበኩሌ

እንዲኖረኝ ረድተውኛል ማለት እችላለሁ፡፡ በተፋሰሱ አጠቃላይ ሁኔታዎች ጥልቅ የሆኑ

ምርምሮችን በመስራትና የተሰሩ ጥናቶችን ለተማሪዎቻችን ተከታታይነት ባለው መልኩ በማቅረብ

የተማሪዎቻችንን ግንዛቤ ማሳደግ አለብን፡፡

እምቢያለ በየነ፤ ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ

የጋራ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በተፋሰሱ አገሮች መካከል ያለውን ትብብር ለማጠናከር መሰራት

አለበት፡፡ የሚል የመፍትሄ ሀሳብ ከጽሁፍ አቅራቢዎች በአንዱ ቀርቧል፡፡ የተፋሰሱ አገሮች

ፍትሃዊ የውሃ አጠቃቀም እንዲኖር ብዙ ድርድሮች ተካሂደዋል፡፡ የጋራ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ

እንዲቻል በተቋም እንዲመራ ተቋማትን ለማቋቋም ጥረት ተደርጓል፡፡ ነገር ግን የተደረጉ ጥረቶች

ከቁም ነገር ሊደርሱ አልቻሉም፡፡ ስለዚህ ከአሁን በኋላ የሚደረጉ ድርድሮች እንዴት ውጤታማ

ሊሆኑ ይችላሉ?

ሌላው የምሰጠው አስተያየት በብዙ ፅሁፎች ሰለ ተፋሰሱና ወንዙ የሚቀርቡ መረጃዎች ብዙ

ልዩነቶች ይታያባቸዋል፡፡ ምሳሌ የተፋሰሱ ስፋት፤ አመታዊ የወንዙ ውሃ መጠን፤ በተፋሰሱ

ውስጥ የሚገኙ አገሮችና ሌሎችም፡፡ እነዚህ ልዩነቶች ከምን መጡ? እንደኔ አስተያየት ጥልቀት

ያላቸው ጥናትና ምርምሮች አለመሰራትና ጽሁፎችም በሚጻፉበት ጊዜ ወቅታዊ መረጃዎችን

አለመጠቀም ነው፡፡ ስለሆነም ክፍተቶችን ለመድፈን በተቀናጀ መንገድ ጥናትና ምርምሮች

መሰራት አለባቸው፡፡

Page 34: BDU CLUSTER & CDS - 1st Nile... · bdu cluster & cds ሚያዚያ 20-21 ... ተ/ብርሀን የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ- ... የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ

ቃለ-ጉባኤ - ኢትዮጵያ አባይን ለልማት በመጠቀም መብትና አስፈላጊነት ላይ የምሁራን ተልእኮ - ሚያዚያ 20-21/2006; ባህር ዳር, ኢትዮጵያ

33 | P a g e

የመጨረሻው አስተያየቴ በጥናቶች የሚቀርቡ የመፍትሄ ሃሳቦች ላይ ትኩረት ያደረገ ነው፡፡

የጥናትና ምርምር ዋና አላማ ችግሮችን በመለየት ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችሉ የመፍትሄ

ሀሳቦችን ለውሳኔ ሰጪዎች ለመጠቆም ነው፡፡ በጥናቶች ላይ የምንሰጣቸው የመፍትሄ ሃሳቦች

ለፖሊሲ አውጭዎች ግብዓት ሊሆኑ የሚችሉና ብሎም የአገራችንን ተጠቃሚነት ሊያረጋግጡ

የሚያስችሉ መሆን አለባቸው፡፡ ኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ላይ ያላት አቋም ግብጽ በናይል

ውሃ አጠቃቀም ላይ ያላትን የበላይነት ለመቀልበስ (Counter-hegemony) ሳይሆን የራሷን ሀብት

ፍትሃዊ በሆነ መንገድ በመጠቀም ድህነትን ማስወገድ ነው፡፡

ከጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ

በፅሁፍ አቅራቢዎችም ሆነ በሌሎች አስተያየት ሰጪዎች የአባይን ወንዝ ለሐይድሮ-ኤሌክትሪክ

ማመንጫና ለመስኖ ለመጠቀም ከታችኞቹ የተፋሰስ አገሮች ጋር አበራ መስራት አለባት የሚል

ሀሳብ ሲንጸባረቅ ቆይቷል፡፡ እንደተረዳሁት ግብፅ ከዚህ በፊት የነበረው ኢፍተሃዊ የሆነ አጠቃም

እንዲቀጥል ጥረት በማድረግ ላይ ባለችበት ሁኔታ ውሃችንን እንጠቀም ብለን የምንጠይቀው ማንን

ነው? የራሳችንን ሃብት ማንንም ይሁንታ ሳንጠብቅ መጠቀም እንችላለን፡፡

ሌላው አስተያየት፤ የተሰሩት የጥናትና ምርምር ስራዎች ውስን በመሆናቸው ከፍተኛ የመረጃ

ክፍተቶች አሉ፡፡ የምሁራን የጥናትና ምርምር ቴክኒካል ብቃት ማነስ፤ ኩረጃዎችና ሌሎችም

ለመረጃ ክፍተት መኖር ከፍተኛ አስተዋጽኦ አላቸው፡፡ ስለሆነም ለፖሊሲ አውጪዎችና ለውሳኔ

ሰጪ አካላት የመረጃ ምንጭ በመሆን ድጋፍ ሊሰጡ አልቻሉም፡፡ በነበረው ከቀጠለ ፋይዳው የጎላ

አይሆንም፡፡ ስለሆነም የፐሊብሊክ ዲፕሎማሲ ለመስራት እነዚህ ችግሮች መቀረፍ አለባቸው፡፡

አቶ ላቀ፤ በአብክመ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ጸ/ቤት ሃላፊ

የተጠናከረ መረጃ ባለመኖሩ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ ለህብረተሰቡ ግንዛቤ ለማስጨበጥ

በምንቀሳቀስበት ጊዜ ችግሮች ያጋጥሙናል፡፡ እስከታችኛው የህብረተሰብ ክፍል ድረስ በመዝለቅ

እንደዚህ ዓይነት ውይይቶች ቢካሄዱ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ያስችላል፡፡ ስለዚህ ዩኒቨርሲቲዎች

ለህብረተሰቡና ለመጀመሪያና ለሁለተኛ ደረዳ ተማሪዎች ግንዛቤ ለማስጨበጥ ተመሳሳይ የውይይት

መድረኮችን ማዘጋጀት አለባቸው፡፡ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን ለማገዝም ጥርት ያለ መረጃ

በየርከኑ ላሉ የመንግስት አካላት መስጠት ከምሁራን የሚጠበቅ ስለሆነ ተጠናክሮ መቀጠል

አለበት፡፡

Page 35: BDU CLUSTER & CDS - 1st Nile... · bdu cluster & cds ሚያዚያ 20-21 ... ተ/ብርሀን የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ- ... የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ

ቃለ-ጉባኤ - ኢትዮጵያ አባይን ለልማት በመጠቀም መብትና አስፈላጊነት ላይ የምሁራን ተልእኮ - ሚያዚያ 20-21/2006; ባህር ዳር, ኢትዮጵያ

34 | P a g e

ዩኒቨርሲቲዎች የህዳሴው ግድብ ከዳር ለማድረስ በሚደረገው ርብርብ የሚጠበቅባቸውን አስተዋፅኦ

እንዲያበረክቱ ተመሳሳይ ወርክሾፕ በያመቱ ከዚህ በበለጠ እንዲካሄድ ኃላፊነት ወስዶ ሊሰራ

የሚችል ተቋም መኖር አለበት በማለት የውይይቱ ተሳታፊዎች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

ዶክተር ባይሌ ዳምጤ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ኃላፊነቱን ወስዶ እንደሚሰራና ለዚህም ብሉ ናይል

ውሃ ኢንስቲትዩት ተቋቁሞ በመስራት ላይ የበለጠ በማጠናከር ኃላፊነቱን እንዲወጣ ይደረጋል

በማለት ለሁለት ቀን ሲካሄድ የቆየው ወርክሾፕ መፈፀሙን ገልጸዋል፡፡

በመጨረሻም ተሰብሳቢ ምሁራንና የምሁራን አመራሮቸ ባለ 10 ነጥብ የጋራ አቋም በማውጣት

ሲምፖዚየሙ ተጠናቋል::

የአቋም መግለጫ

በሁለቱ ቀናት የተካሄደውን ውይይት መነሻ በማድረግ ባለ 10 ነጥብ የሚደረሱ ተግባራትን

ተሰብሳቢ ምሁራን የጋራ አቋም አድርገው ያወጡ ሲሆን፤ እንደሚከተለው ቀርቧል::

1. የተፋሰሱን ሃገራት ከናይል ውሃ አጠቃቀም አንፃር ንቁ ተሳትፎ እንዲኖራቸው ማድረግ፣

2. ለተቀናጀ ውሃ ሃብት አስተዳደር አስተዋፅኦ እናድርግ፣

3. በውሃ ሃብት አጠቃቀም ዙሪያ ፍፁም የበላይነትን (Hegemony) እንዋጋ ብሎም

ፍትሃዊና ነፃ የሆነ ክርክርን እናስፍን፣

4. የሰራናቸውን ስራዎች ማስተዋወቅ እና ከሃገራት ጋር መተባበር፣

5. የአረንጓዴ ልማት እስትራቴጂን መደገፍ፤ ያለንን ሃብትና አቅም ሁሉ ወደ ኃላ ሳንል

ማቅረብ፣

6. ያገራችንን ፍላጎት በማክበር እውቀታችንን ማውጣትና ማስተላለፍ፣

7. ፕሮግራሞችን በማቋቋም በናይል ውሃ ላይ መረጃና እውቀት ለማግኘት መስራት፣

8. የሙያ ቅንጅትን መፍጠር፣

9. እኛ ምሁራን ዝግጁነታችን እንገልፃለን፣

10. የታላቁ የህዳሴ ግድብን ሚና እንገነዘባለን፤ በሀገሮች መሀል መተባበርን ሊያመጣ

እንደሚችል ስለሆነም የታላቁን የህዳሴ ግድብ ምጣኔ ሃብታዊ አሰተዋፅኦ ሊያጠና

የሚችል ማዕከል እናቋቁማለን፡፡

Page 36: BDU CLUSTER & CDS - 1st Nile... · bdu cluster & cds ሚያዚያ 20-21 ... ተ/ብርሀን የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ- ... የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ

ቃለ-ጉባኤ - ኢትዮጵያ አባይን ለልማት በመጠቀም መብትና አስፈላጊነት ላይ የምሁራን ተልእኮ - ሚያዚያ 20-21/2006; ባህር ዳር, ኢትዮጵያ

35 | P a g e

-------------------------------------------------------------------------------------// --------------------------------------------------------