83
ስስ ስስስስ ስስስስስስ ስስስስ ስስስስስስ ስስ ስስስስ ስስስ ስስስስስስ ስስስስስ ስስስስስ ስስስስ ስስስስ ስስስ 2005 ስ.ስ ስስስ

ስለ አካባቢ እንክብካቤ ክበባት ለትምህርት ቤት ክበባት ተጠሪ

Embed Size (px)

Citation preview

Page 1: ስለ አካባቢ እንክብካቤ  ክበባት  ለትምህርት ቤት ክበባት ተጠሪ

ስለ አካባቢ እንክብካቤ ክበባት ለትምህርት ቤት ክበባት ተጠሪ

መምህራንና ለክበባት አመራሮች ተዘጋጀ ስልጠና

ህዳር 2005 ዓ. ም

ወረታ

Page 2: ስለ አካባቢ እንክብካቤ  ክበባት  ለትምህርት ቤት ክበባት ተጠሪ

የተዘጋጀዉ፡- በይድነቃቸዉ ጀምበር(አጥመአአመ)

ኢ-ሜል፡- [email protected]

ሞባይል: - 0918195147

ህዳር 2005 ዓ.ም

Page 3: ስለ አካባቢ እንክብካቤ  ክበባት  ለትምህርት ቤት ክበባት ተጠሪ

የስልጠናዉ አጠቃላይ እይታ

ስልጠናዉ የተደገፈዉ በጣና በለስ የተቀናጀ የተፋሰስ

ልማት ፕሮጀክት ሲሆን በስልጠናዉም የትምህርትቤት የክበብ

ተጠሪዎች መምህራንና የክበባት አማራሮች ተሳታፊ ይሆናሉ፡፡

Page 4: ስለ አካባቢ እንክብካቤ  ክበባት  ለትምህርት ቤት ክበባት ተጠሪ

ትዉዉቅ

ስም፣ መ/ ቤት፣ ኃላፊነት፣

በስልጠናው በመሳተፍዎ የተሰጠዎት ኃላፊነት፣

ከስልጠናው የሚጠብቁት (Expectation)፣ የስልጠና ገዥ ደንቦች/ ህጎች (Ground Rules)፣ 

Page 5: ስለ አካባቢ እንክብካቤ  ክበባት  ለትምህርት ቤት ክበባት ተጠሪ

በስልጠናዉ የሚዳሰሱ ርዕሶች

መግቢያ

የአካባቢን ና የዘላቂ ልማትን ምንነትን ማስገንዘብ

ለምን እራሳችንን ከአካባቢ ጋር አቆራኘን

ዋና ዋና የሀገራችን የአካባቢ ችግሮች ምንድን ናቸዉ

የአካባቢ ችግሮችን ለመፍታት የአካባቢ ትምህርት ያለዉ ሚና

የአካባቢ እንክብካቤ ክበባት ምንነት

የክበብ መመስረቻ መመሪያ

ዋና ዋና ስራወች

Page 6: ስለ አካባቢ እንክብካቤ  ክበባት  ለትምህርት ቤት ክበባት ተጠሪ

መግቢያ

የአካባቢ መቆሳቆል፣የተፈጥሮ ሀብት አግባብ ያልሆነ

አጠቃቀምና ዘላቂነት የለለዉ አጠቃቀም በኢትዮጽያ በዋናነት

የሚጠቀሱ የአካባቢ ችግሮች ናቸዉ፡፡

እነዚህን ችግሮች ለመፍታት በተቀናጀና አገር አቀፋዊ በሆነ

ሁኔታ ህብረተሰቡን በተለይም ወጣቶችን የማስተማር ስራ

በሰፊዉ መሰራት አለበት

Page 7: ስለ አካባቢ እንክብካቤ  ክበባት  ለትምህርት ቤት ክበባት ተጠሪ

ይህንንም ችግር ለመፍታት መንግስት የተለያዩ ስራወችን

እየሰራ ይገኛል ከነዚህም ዉስጥ የአካባቢ ጥበቃን የሚሰራ

የተቋም አደረጃጀትን መፍጠር አንዱ ነዉ፡፡

በዚህምመሰረት በክልል ደረጃ የአካባቢ ጥበቃ መሬት

አስተዳደርና አጠቃቀም ቢሮ ተቋቁሞ በዞን፣በወረዳና በቀበሌ

መዋቅር እዲኖረዉ ተደርጓል

መስሪያቤቱም ከተቋቋመ ጀምሮ በአካባቢ ጥበቃ ዙሪያ

ህብረተሰቡን ግንዛቤ ለማሳደግ ስራወችን እየሰራ ይገኛል

Page 8: ስለ አካባቢ እንክብካቤ  ክበባት  ለትምህርት ቤት ክበባት ተጠሪ

በዚህምመሰረት በክልል ደረጃ የአካባቢ ጥበቃ መሬት

አስተዳደርና አጠቃቀም ቢሮ ተቋቁሞ በዞን፣በወረዳና በቀበሌ

መዋቅር እዲኖረዉ ተደርጓል

መስሪያቤቱም ከተቋቋመ ጀምሮ በአካባቢ ጥበቃ ዙሪያ

ህብረተሰቡን ግንዛቤ ለማሳደግ ስራወችን እየሰራ ይገኛል

Page 9: ስለ አካባቢ እንክብካቤ  ክበባት  ለትምህርት ቤት ክበባት ተጠሪ

በትምህረት ቤት ደረጃና በዩኒቨርስቲ ደረጃ ያሉ ተማሪወች የአካባቢ

ጥበቃና እንክበብካቤ ስራወችን እንዲሰሩ በትምህርትቤት ደረጃ

የአካባቢ እንክብካቤ ክበብ እንዲቋቋምመንግስት በአደረጃጃት

ደረጃ አዉርዶታል

ይህንን አደረጃጀትም መስሪያቤታችን የማጠናከር ስራ እየሰራ ይገኛል

የክበባቱን አደረጃጀትም ለመደገፍ እንዲያስችል በክልል ደረጃ

የአካባቢ እንክብካቤ ክበባት ማቋቋሚያ መመሪያ ወጥቷል

ይህምመመሪያ የአካባቢ እንክብካቤ ክበባትን በትምህርት ቤቶችና

በክበባት ለማቋቋም የሚረዳ ነዉ

Page 10: ስለ አካባቢ እንክብካቤ  ክበባት  ለትምህርት ቤት ክበባት ተጠሪ

1. አካባቢ ስንል ምንማለት ነው?

Page 11: ስለ አካባቢ እንክብካቤ  ክበባት  ለትምህርት ቤት ክበባት ተጠሪ

አካባቢ ማለት በዙሪያችን የሚገኙ ፊዚካላዊ፣ ኬሚካላዊ፣ ስነ

ህይወታዊ ማህበራዊና

ባህላዊ ጉዳዮች መስተጋብር ነው፡፡

ይህን ጠቅለል አድርገን ስንመለከተው ደግሞ ግዑዝና ስነ

ህይወታዊ ሁኔታዎችን ይይዛል፡፡

ግዑዝ (Physical) አየር፣ ውሃ፣ ድንጋይ ወዘተ ሲይዝ ስነ

ህይወታዊው (Biological) ደግሞ ዕፅዋት፣ እንስሳትና

ጥቃቅን ህይወት ያላቸውን ያካትታል፡፡

Page 12: ስለ አካባቢ እንክብካቤ  ክበባት  ለትምህርት ቤት ክበባት ተጠሪ
Page 13: ስለ አካባቢ እንክብካቤ  ክበባት  ለትምህርት ቤት ክበባት ተጠሪ

የእነዚህ የሁለቱ ጥምረት (መስተጋብር) ደግሞ ስርዓተ

ምህዳርን (Ecology) ይፈጥራል፡፡ ስለዚህ የው ልጅ በተፈጥሮና በሰው ሰራሽ አማካኝነት የሚገኝ

ፀጋ በአግባቡ ተጠቅሞ ለኑሮው መሠረት ያመቻቻል፡፡

በየቀኑ እያንዳንዳችን በጋራም ሆነ በግላችን ባለን ህይወት

አካባቢን የሚጎዳ ዉሳኔም ሆነ ድርጊት እንወስናለን

ይህም ዉሳኔያቸን ለአካባቢ ችግሮች መፈጠር በቀጥታም

ሆነ በተዘዋዋሪ ምክኒያት ይሆናል

Page 14: ስለ አካባቢ እንክብካቤ  ክበባት  ለትምህርት ቤት ክበባት ተጠሪ

ስለዚህ ችግሩን ለመፍታት በሚደረጉ ጥረቶች ላይ የበኩላችን

ድርሻ መወጣት መቻል አለብን

ይህንንም ሀላፊነት ለመወጣት እራሳችንን ስለአካባቢ

ምንነትና ችግሮች በእዉቀት ማነጽ አለብን

“ይህንንም ማድረግ ስንጀምር think globally, and act locally” የሚለዉን አለማቀፋዊ መርህ መመራት

እንጀምራለን

Page 15: ስለ አካባቢ እንክብካቤ  ክበባት  ለትምህርት ቤት ክበባት ተጠሪ

ለምን ስለአካባቢ እንጨነቃለን?

Page 16: ስለ አካባቢ እንክብካቤ  ክበባት  ለትምህርት ቤት ክበባት ተጠሪ

የሰዉ ልጅ ኑሮ የተመሰረተዉ በተፈጥሮ ከአካባቢ በሚገኝ

ስነህይወታዊና ቁሳዊ ሀብት ላይሙሉ ለሙሉ የተመሰረተ

ስለሆነ

በአካባቢ ላይ የሚመጣ አወንታዊ ለዉጥ ለሰዉ ልጅ የኑሮ

ሁኔታ መሻሻልና ለምርት መጨመር አይነተኛ ጥቅም አለዉ

Page 17: ስለ አካባቢ እንክብካቤ  ክበባት  ለትምህርት ቤት ክበባት ተጠሪ

በኢትዮጽያ ያሉ ዋና ዋና የአካባቢ ችግሮች

1. የህዝብ ብዛት በፍጥነት መጨመር የኢትዮያ ህዝብ ብዛት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመሔድ

ላይ ነው፡፡

ለዚህ ደግሞመንስኤው የህብረተሰቡ የግንዛቤ ማነስ

ሲሆን በዚህ ሰበብ በርካታ ሁኔታዎች ይከሰታሉ፡፡

የእርሻ መሬት መጣበብ፣ የተፈጥሮ ዕፅዋት መመናመን፣

Page 18: ስለ አካባቢ እንክብካቤ  ክበባት  ለትምህርት ቤት ክበባት ተጠሪ

መሬትን ደጋግሞ ማረስ፣ድህነት፣ጊዜያዊ መኖሪያ ኢኮኖሚያዊ

እድል ለማግኘት አካባቢን መጉዳት፣ ለአካባቢ ትኩረት

የማይሰጥ ኢኰኖሚያዊና ማህበራዊ ተቋሞች /ድርጅቶች/ ስራ ክንዋኔ ተጋግዘው ዋነኛ የአካባቢ ችግሮች ይፈጥራሉ፡፡

Page 19: ስለ አካባቢ እንክብካቤ  ክበባት  ለትምህርት ቤት ክበባት ተጠሪ

2. የደን ሐብት መመናመን

የህዝብ ቁጥር እየጨመረ ሲሔድ ፍለጐት ይበዛል፡፡

ደንን ለመኖሪያ ቤት ስራ፣ ለማገዶ፣ ለቁሣቁስ መስሪያና

ለመሣሠሉት ለማዋል ያለው ፍላጐት ይጨምራል፡፡

ይህን ለማድረግ ደግሞ ለብዙ ዓመታት ተጠብቆ የኖረውን የደን

ሃብት ይጨፈጨፋል፣ ይወድማል፡፡

በተጨፈጨፈው ደን መጠን የሚተካ ባለመኖሩ ደግሞ ችግሩ

እየተባባሰ በመሔድ ለሌላ ቀጣይ ችግር ያስተላልፈናል፡፡

Page 20: ስለ አካባቢ እንክብካቤ  ክበባት  ለትምህርት ቤት ክበባት ተጠሪ

በተለይም ተተኪ የሌላቸው የአገር በቀል ዛፎች ከምደረ ገፅ

በመጥፋታቸው ለአካባቢ አየር መበከል እንጋለጣለን፡፡

የደን ሃብታችን ሲመናመን በረሃማነት ይስፋፋል፡፡

የቤትም ሆነ የዱር እንስሳት ምግብና መጠለያ ያጣሉ በውሃ

ሃበታችን ላይ እጥረትና ብክነት ይፈጥራል፡፡

ይህ ደግሞ በውሃ ትራንስፖርትና በመብራት አገልግሎት

እንዲሁም በዓሣ ምርታችን ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ያሣድራል፡፡

ይህም በአገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ችግር ይፈጥራል፡፡

Page 21: ስለ አካባቢ እንክብካቤ  ክበባት  ለትምህርት ቤት ክበባት ተጠሪ

3. የመሬት መጐሣቆል የደን ሃብታችን ሲመናመን የጎርፍ መጠን ይጨምራል አፈር

በጐርፍና በነፋስ መወሰድና መሸርሸር ይቀጥላል፡፡

ለምርት አገልግሎት የምንጠቀምበት የላይኛው አፈር ታጥቦ

ለቦረቦር ለድንጋያማ መሬት ቦታውን ይለቃል፡፡

Page 22: ስለ አካባቢ እንክብካቤ  ክበባት  ለትምህርት ቤት ክበባት ተጠሪ

አፈርን የሚከላከል ዕፅዋት ሲጠፋ የእንስሳት ግጦሽ

አይኖርም፡፡

ልቅ ግጦሽ ስለሚስፋፋ መሬት አፈሩን የሚከላከልበት ሽፋን

ሲያጣ ይጐዳል፡፡

በዚህ ምክንያት ደግሞ ምርታማነት ይቀንሳል የሚመረተው

ምርትና የህዝብ እደገት አይመጣጠንም፡፡

ስለሆነም የኑሮ ውድነት ይባባሳል መሬትን ለማልማት ሰው

ሰራሽ ማዳበሪያና ሌሎች የአፈር መከላከያ ስራ መስራትን

ይጠይቃል፡፡

ይህ ደግሞ ከፍተኛ ወጭን ያስከትላል፡፡

Page 23: ስለ አካባቢ እንክብካቤ  ክበባት  ለትምህርት ቤት ክበባት ተጠሪ

3. የአካባቢ ብክለት

የህብረተሰቡ ቁጥር ሲጨምር በተለይም በገጠሩ ህብረተሰብ

አካባቢውን አየተወ ወደ ከተማ ይገባል፡፡

ከተማዎች ከአቅማቸው በላይ የሆነ ህዝብ በማስተናገዳቸው

ለአካባቢ ፅዳት ጉድለትና ለብክለት ይጋለጣሉ፡፡

ከህብረተሰቡ የሚወጣው ደረቅና ፈሳሽ ቆሻሻ፣

ከኢንዱስትሪዎች የሚለቀቅ የኢንዱስትሪ ዝቃጭ፣

ከተሽከርካሪዎች የሚወጣውጢስና ሌሎችም የጤና ችግርን

ያመጣሉ፡፡

Page 24: ስለ አካባቢ እንክብካቤ  ክበባት  ለትምህርት ቤት ክበባት ተጠሪ

ከላይ በጥቂቱ የተገለፁትን ችግሮች ስንመለከት አንዱ

ከሌላው ጋር ተያያዥነት ያላቸው፣ አንዱ ለሌላው መባባስ

ምክንያት የሚሆን ሲሆን በአጠቃላይ ግን የመጨረሻ ውጤቱ

በአገራችን ኢኮኖሚ ላይጫና መፍጠርና ድህነትን ማባባስ

ነው፡፡

ስለሆነም ይህን የኢኮኖሚ ችግር በተለይም ሰው ሰራሽ ችግር

ለመቅረፍ የአካባቢ ችግር በተለይም ሰው ሰራሽ ችግር

ለመቅረፍ የአካባቢ ትምህርት አስፈላጊ ነው፡፡

Page 25: ስለ አካባቢ እንክብካቤ  ክበባት  ለትምህርት ቤት ክበባት ተጠሪ

የአካባቢ እንክብካቤ ክበብ ምንማለት ነዉ?

Page 26: ስለ አካባቢ እንክብካቤ  ክበባት  ለትምህርት ቤት ክበባት ተጠሪ

የአካባቢ እንክብካቤ ክበብ

ትርጉም የአካባቢ እንክብካቤ ክበብ ማለት በአንድ የማህበረሰብ

አካባቢ የሚኖሩ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች አካባቢን

ለመጠበቅና ለማልት በአካባቢያቸው ችግርና እንክብካቤ

ዙሪያ በጋራ ለመስራት ተመሣሣይ ፍላጐት ያላቸው ሰዎች

በአንድ ላይ ተደራጅተው የሚፈጥሩት ተቋም ነው፡፡

Page 27: ስለ አካባቢ እንክብካቤ  ክበባት  ለትምህርት ቤት ክበባት ተጠሪ

የአካባቢ እንክብካቤ ክበብ ዓላማ

በተለያየ ደረጃና አካባቢ የሚቋቋሙ የአካባቢ እንክብካቤ

ክበባት አጠቃላይ ዓላማ ለህብረተሰቡ ስለ አካባቢ

እንክብካቤ፣ አጠቃቀምና ልማት በማስተማር በራስ አነሳሽነት

በአካባቢው የሚገኝ ሃብትና ጉልበትን በመጠቀም ዘላቂ

አካባቢያዊ ልማት እንዲያመጣ በስፋት ማንቀሳቀስ ነው፡፡

ከዚህ አጠቃላይ ዓላማ በመነሳት የሚከተሉት ዝርዝር

ዓላማዎች ይኖሩታል፡፡

Page 28: ስለ አካባቢ እንክብካቤ  ክበባት  ለትምህርት ቤት ክበባት ተጠሪ

ለህብረተሰቡ በሰዎች፣ በተፈጥሮ፣ በአካባቢ እና በኢኮኖሚ

ልማት መካከል ያለውን መተሳሰርና ቁርኝት ማስተማር

በህብረተሰቡ ውስጥ የአካባቢ እንክብካቤና ልማት ፅንሰ

ሃሳብ እንዲሰርፅ ያለሰለሰ የግንዛቤ ማሣደጊያ ስራ መስራት

የክልሉ ቀሪ የተፈጥሮም ሆነ ታሪካዊ ሐብት የሚጠበቅበትን

ሁኔታ እና የወደሙትም እንዲተካ ህ/ ሰቡ ተገቢውን ዋጋና

ግምት ሰጥቶ ኃላፊነቱን እንዲወጣማድረግ፡፡

Page 29: ስለ አካባቢ እንክብካቤ  ክበባት  ለትምህርት ቤት ክበባት ተጠሪ

ለልማት፣ ለአካባቢ እንክብካቤና ጥበቃ ስራ በተግባር

የሚንቀሳቀስ ብቃት ያለው የሰው ኃይል ማፍራት

የክበቡ አባላት በሚያደርጉት ግንባር ቀደም እንቅስቃሴ

አማካኝነት የአካባቢን የተፈጥሮ ሚዛን በሚያሻሽሉ የልማት

እንቅስቃሴዎች ውስጥ ንቁ ተሣትፎ ማድረግ

ህ/ ሰቡን ለጋራ አካባቢ ልማትና የአካባቢ እንክብካቤ

ተግባራትን በራሱ ተነሳሽነት እንዲያካሂድ የአካባቢ እንክብካቤ

ክበባትን በማቋቋምና በማጠናከር ክበባቱን በብቃትና በስፋት

ሊያንቀሳቅሱ የሚችሉ የአሰራር ስልቶችን መንደፍ

Page 30: ስለ አካባቢ እንክብካቤ  ክበባት  ለትምህርት ቤት ክበባት ተጠሪ

ክበባት ለሌሎች አርአያ ሊሆን የሚችል በአካባቢያቸው ያሉትን

የአካባቢ ችግሮች መለየትና መቅረፍ የሚያስችሉ ተግባራትን

ማካሔድ

በትምህርት ቤቶች/ ተቋማት/ ፣ ድርጅቶች መኖሪያ አካባቢ፣

ቀበሌ ገበሬ ማህበር፣ ወዘተ የአካባቢ ትምህርትን

በማስፋፋት ህብረተሰቡ ስለ አካባቢ መራቆት፣ መጐሣቆል፣

ጠንቆችና መንስኤዎች ግንዛቤውን ማሣደግ፡፡

Page 31: ስለ አካባቢ እንክብካቤ  ክበባት  ለትምህርት ቤት ክበባት ተጠሪ

የአካባቢ እንክብካቤ ክበባት ሚና

የአካባቢ ትምህርትና እንክብካቤ ስራዎች ዘላቂነት

እንዲኖራቸውና በህዝብ ዘንድም ተቀባይነት እንዲያገኙ

በአካባቢ ልማት ዘርፍ ዋና ተዋናኝ የሆነው የታችኛውን

የህብረተሰብ ክፍል ግንዛቤ በማሣደግ በአካባቢ እንክብካቤ

ክበብ ስር ተደራጅቶ ተገቢውን የዜግነት ሚና በወጫወት

አካባቢውን ተንከባክቦ በማልማትጤናማና ለኑሮ ምቹ የሆነ

አካባቢ እንዲፈጠር ማስቻል ነው፡፡

Page 32: ስለ አካባቢ እንክብካቤ  ክበባት  ለትምህርት ቤት ክበባት ተጠሪ

የአካባቢ እንክብካቤ ክበባት በህብረተሰቡ ውስጥ

የሚያደርጉት የተለያየ የአካባቢ ነክ እንቅስቃሴ፡- የአካባቢ ችግሮችን ምንነት፣ ዓይነትና መንስኤዎች የሚያውቅ

ተፈጥሮን ተንከባካቢና አፍቃሪ ዜጋ ማፍራት

የአካባቢ ችግሮችን በውል ተገንዞቦ ተግባራዊ ተሣትፎ

የሚያደርግ ህብረተሰብ እንዲፈጠር ማድረግ

የህብረተሰቡን ግንዛቤ በማሣደግ ማህበረሰቡ በራሱ

ተነሳሽነት የአካባቢ ችግሮችን በመፍታት ቀጥተኛ ተሳታፊ

እንዲሆን ማድረግ

Page 33: ስለ አካባቢ እንክብካቤ  ክበባት  ለትምህርት ቤት ክበባት ተጠሪ

ህዝቡ የተፈጥሮ ባህላዊ ሀብቱንና እሴቱን እንዲጠብቅ፣

እንዲንከባከብ እና በአግባቡ እንዲጠቀም ግንዛቤው ከፍ

እንዲል ማድረግ

በየአካባቢው እየተመናመኑ ያሉት ሀገር በቀል የተፈጥሮ

ሐብቶች ዕፅዋት፣ የዱር እንስሳት/ ትኩረት በመስጠት

የሚጠበቁበትንና የሚለሙበትን ስልቶች ማመቻቸትን

ያካትታል፡፡

Page 34: ስለ አካባቢ እንክብካቤ  ክበባት  ለትምህርት ቤት ክበባት ተጠሪ

የአካባቢ ክበባት ቀጥሎ በተመለከተውውስጥሊቋቋሙ

ይችላሉ

በ1 ኛና በ2 ኛ ደረጃ ት/ ቤቶች፣ በኮሌጆች፣ በዩኒቨርሲቲዎች፣

በመምህራን ማሰልጠኛና መሰል የትምህርት ተቋማት

በፋብሪካዎች፣ በመኖሪያ አካባቢ፣ በተለያዩ ማህበራት

( በገበሬ፣ በሴቶች፣ በወጣቶች፣ በሙያ ማህበራት ወዘተ) ፣ በመንግስት መስሪያ ቤቶች፣ በመሣሠሉትና በአጠቃላይ

በየትኛውም ቦታ ስለ አካባቢ እንክብካቤ የጋራ ፍላጐት

ባላቸው ሰዎች ማቋቋም ይቻላል፡፡

Page 35: ስለ አካባቢ እንክብካቤ  ክበባት  ለትምህርት ቤት ክበባት ተጠሪ

የአካባቢ ክበባት ጠቀሜታ የአካባቢ ክበባት የሚከተሉት ጠቀሜታዎች አላቸው

በክበቡ አባላት ውስጥ የአካባቢ ግንዛቤ መፍጠርና ማሣደግ

በክፍል ውስጥ በመደበኛ ትምህርት ለተማሪዎች በበቂ ሁኔታ

የማይቀርቡ /የማይሰጡ/ ስለ አካባቢና ልማት ነክ ጉዳዮች አጥጋቢ

መረጃ ማስተላለፍ፡፡ ለምሳሌ ስለጤና፣ ድህነት፣ ስለ ህዝብ ቁጥር

መጨመር፣ ስለ ደን መመንጠር፣ ስለ አፈር መከላት፣ ስለ ማገዶ

… እንጨት እጥረት፣ ስለ ብዝሀ ህይወት አጠባበቅ ወዘተ

በመሣሠሉት ጉዳዮች ላይ የክበቡ አባላት የፓናል ውይይት

እንዲያደርጉ ከፍተኛ የተዋናይነት ስራ ይሰራል፡፡

Page 36: ስለ አካባቢ እንክብካቤ  ክበባት  ለትምህርት ቤት ክበባት ተጠሪ

በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃና ልማት ስራ ውስጥ የህዝቡን

ተሣተፎ ማሣደግ

ከፍተኛ ውድ ግብዓትን ሳይጠቀሙ በአካባቢው በሚገኙ

ቁሣቁሶች ትምህርት ማስተላለፍ የሚቻል ሲሆን በአነስተኛ

ወጭ ለብዙ ህዝብ ስለ አካባቢ ምንነት፣ ታሪክ፣ ልምድ፣

ባህል፣ ወዘተ በመግለፅ ስለ አካባቢውመሻሻል፣ መልማት፣

ተስማሚነት ወዘተ ሁኔታዎችን ማመቻቸት፡፡

Page 37: ስለ አካባቢ እንክብካቤ  ክበባት  ለትምህርት ቤት ክበባት ተጠሪ

የክበቡ አባላት ቀጥሎ በተጠቀሱት ሁኔታዎች ተጠቃሚ

ሊሆን ይችላል

… በአውደ ጥናት፣ በስልጠና፣ በጉባኤዎች ወዘተ

በመሣሠሉት መሣተፍ

በልምድ ልውውጥመሣተፍ

አካባቢያዊ መረጃዎችን በስፋት ከሌሎች በተሻለ ሁኔታ

የማግኘት ልምድ ( ስላይድ ፊልሞች፣መረጃዎች፣ የቪዲዮ

ፊልሞች፣ መጋዚኖች ወዘተ)

Page 38: ስለ አካባቢ እንክብካቤ  ክበባት  ለትምህርት ቤት ክበባት ተጠሪ

የክበቡን መረጃዎች ማወቅ፣ ዜና መፅሔት ማግኘት

በአካባቢ ክበብ መሣተፍ

አካባቢያቸውን ለማልማትና የተሻለ ለማድረግ በሚደረገው

እንቅስቃሴ የነቃ ተሣትፎ ማድረግ፣ ወዘተ ከብዙዎቹ

በጥቂቶቹ የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

Page 39: ስለ አካባቢ እንክብካቤ  ክበባት  ለትምህርት ቤት ክበባት ተጠሪ

የአካባቢ ክበባት አደረጃጀት መመሪያ

አደረጃጀት ማንኛውም ሰው የመኖሪያ አካባቢ፣ ዕድሜ፣ የስራ ቦታ፣ ፆታና

ኃይማኖት ሳይገድበው ከሌሎች ተመሣሣይ ፍላጐት ካላቸው

ጋር ውይይት በማድረግ የአካባቢ እንክብካቤ ክበብ ሊመሰርቱ

ይችላሉ፡፡

Page 40: ስለ አካባቢ እንክብካቤ  ክበባት  ለትምህርት ቤት ክበባት ተጠሪ

የአካባቢ ክበብ ለመመስረት ውሣኔ ላይ ከተደረሰ በኋላ ማስታወቂያ

በአማካኝ ቦታዎች በመለጠፍ፣ በሌላ የመቀስቀሻ ዘዴዎች / በድምፅ

ማጉያ/ እንዲሁም እርስ በርስ በሚደረግ ግንኙነት መረጃ

በመለዋወጥ፣ በስብሰባ፣ በገበያ፣ በእምነት ቦታ፣ ወዘተ መልዕክት

በማስተላለፍና በመጋበዝ፣ ጥሪ በማስተላለፍ የአካባቢ እንክብካቤ

ክበብ መመስረት ይቻላል፡፡ ከዚህም በኋላ የክበቡን መመስረት

የሚደግፉና የሚመለከታቸው አካላት ወይም ደርጅቶች ለክበቡ አባላት

በሙያ፣ በማቴሪያልና በሞራል ድጋፍ እንዲያደርጉ ግንኙነት መፍጠር

ያስፈልጋል፡፡ ክበቡን ይበልጥ ለማጠናከር አባላት የሚመሩበት

የራሳቸው የሆነ ውስጠ ደንብ ሊኖራቸው ያስፈልጋል፡፡

Page 41: ስለ አካባቢ እንክብካቤ  ክበባት  ለትምህርት ቤት ክበባት ተጠሪ

ድጋፍ የአካባቢ እንክብኮቤ ክበብ እንደተመሠረተ ቀሪ ተግባሩ

የሚሆነው አባላትን ማሰባሰብና በክበብ አባልነት ማቀፍ

ይሆናል፡፡ በዚህም ክበቡ በተቋቋመበት አካባቢ የሚገኙ

ነዋሪዎች፣ የማህበር አባላት፣ የመስሪያ ቤት ሰራተኞች፣

የትምህርት ቤት /የተቋም/ ተማሪዎች የኢንዱስትሪ ሰራተኞች

በፈቃደኝነት አባል እንዲሆኑ መጠየቅ ያስፈልጋል፡

Page 42: ስለ አካባቢ እንክብካቤ  ክበባት  ለትምህርት ቤት ክበባት ተጠሪ

ክበቡ የተመሠረተበት የፅህፈት ቤት ወይም የመስሪያ ቤት

ኃላፊ፣ የተቋሙ ወይም የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር

አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋሉ፡፡ ይኸውም፡- ክበቡን የሚያስተባብርና የሙያ ድጋፍ ሊሰጥ የሚችል

ባለሙያ መመደብ

ክበቡ ከተቋቋመበት አካል /አካባቢ/ ሙሉ ፈቃድ፣ ዕውቅናና

ጥሩ ስሜት መኖር

ለስራ ማከናወኛ የሚሆን ጽ/ ቤት፣ የስራ ቁሳቁስና ሌሎች

ድጋፎችንጭምር ማድረግ፡፡

Page 43: ስለ አካባቢ እንክብካቤ  ክበባት  ለትምህርት ቤት ክበባት ተጠሪ

አባልነት

የአካባቢ እንክብካቤ ክበባትን ዝርዝር የአባልነት መመዘኛ

ነጥቦች መብትና ግዴታ ክበባቱ በሚያዘጋጁት የመተዳደሪያ

ደንብ የሚወሰን ሲሆን ማንኛውም የአካባቢ እንክብካቤ

ክበባትን ዓላማዎች አምኖ በፈቀደኝነት የተቀበለ በክበባት

ውስጥ ገብቶ ለመሣተፍና አስተዋፅኦ ለማድረግ ፍላጐት

ያለው ሁሉ አባልና ተባባሪ አባል መሆን ይቻላል፡፡

Page 44: ስለ አካባቢ እንክብካቤ  ክበባት  ለትምህርት ቤት ክበባት ተጠሪ

ተባባሪ አባል፡- ሲባል ለምሳሌ የሚቋቋመው ክበብ በአንድ

ት/ ቤት ውስጥ የተማሪዎች የአካባቢ እንክብካቤ ክበብ ሲሆን

አንድ ከት/ ቤት ውጭ የሚሰራ ግለሰብ የክበቡን አላማ

አምኖበትና ተቀብሎት አባል ለመሆን ጥያቄ ቢያቀርብ ክበቡ

ግለሰቡን የሚቀበለው በተባባሪ አባልነት ደረጃ ነው

Page 45: ስለ አካባቢ እንክብካቤ  ክበባት  ለትምህርት ቤት ክበባት ተጠሪ

የመጀመሪያ የስብሰባጥሪ

በየትኛውም ቦት የአካባቢ እንክብካቤ ክበብ ለማቋቋም ፈቃድ

ተገኝቶ የአባላት ምዝገባ ከተካሔደ በኋላ ቀጥሎ የሚኖረው

ስራ የመጀመሪያ የስብሰባ ጥሪ ማካሔድ፡፡

በስብሰባ የጥሪ ማስታወቂያ ላይ የስብሰባው ቦታ፣ ቀን፣

ሰዓት፣ የስብሰባው ዓላማና የመወያያ አጀንዳ መካተት

ይኖርበታል፡፡

Page 46: ስለ አካባቢ እንክብካቤ  ክበባት  ለትምህርት ቤት ክበባት ተጠሪ

የጥሪው ማስታወቂያ በፅሁፍ ከሆነ በግልፅ በሚታይና

ተነባቢ በሆነ ፅሁፍ ተለጥፎ ለመታየት አመች ቦታ ላይ

መለጠፍ ይኖርበታል፡፡

መልዕክቱ በድምፅ ማጉያ ወይም በመገናኛ ብዙኃን

የሚተላለፍ ከሆነ አብዛኛው አባላት ሊሰሙ /ሊያዳምጡ/ በሚችሉበት ጊዜ ሆኖ መልዕክቱን የሚያስተላልፈው

/የሚያነበው/ ሰው ድምፅ ጥርት ያለና ተሰሚነት ያለው ሆኖ

ተደጋግሞ እንዲተላለፍ መሆን አለበት፡፡

Page 47: ስለ አካባቢ እንክብካቤ  ክበባት  ለትምህርት ቤት ክበባት ተጠሪ

በመስራች ስብሰባው ላይ ከክበቡ አባላት በተጨማሪ ክበቡ

የተቋቋመው

በትምህርት ቤት /ተቋም/ ከሆነ መምህራንና ስራ አመራሩ፡

በቀበሌዎች አካባቢ ከሆነ የቀበሌዎቹ ስራ አመራር አባላት፣

ታዋቂ ግለሰቦች፣ ክበቡ እንዲቋቋም ድጋፍ ያደረጉና ያበረታቱ

ግለሰቦችና የድርጅቶች ተወካዮች እንዲገኙ መደረግ አለበት፡፡

Page 48: ስለ አካባቢ እንክብካቤ  ክበባት  ለትምህርት ቤት ክበባት ተጠሪ

የመጀመሪያ ስብሰባ ማካሔድ ጥሪ የተደረገላቸው ተሰብሳቢዎች መገኘታቸው ከተረጋገጠ በኋላ

ስብሰባውራን የጠራው አስተባባሪ ኮሚቴ ለተሰብሳቢዎች በስብሰባው

ላይ ለተገኙ እንግዶች የስብሰባውናን ዓለማ በአጭሩ ያስተዋውቃል፡፡

በመቀጠልም የአካባቢ እንክብካቤ ክበብ ማቋቋም አስፈላጊነትና

በአካባቢ ላይ እየደረሰ ያለውን አካባቢያዊ ችግር በሚመለከት በቂ ገለፃ

ማድረግና ይህን ችግር መግታት የሚቻለው በጋራ ክንድና በመተባበር

ስለሆነ ለዚህ ሲባልም የአካባቢ እንክብካቤ ክበቡ መቋቋሙንና ክበቡም

የሚመራበትን ሂደት በሚመለከት ማብራሪያ መስጠት፣ የክበቡን የዕለት

ተዕለት ስሪ የሚያስተባብር የስራ አመራር ኮሚቴ ማቋቋም አስፈላጊ

መሆኑን ማብራሪያ መስጠት፡፡

Page 49: ስለ አካባቢ እንክብካቤ  ክበባት  ለትምህርት ቤት ክበባት ተጠሪ

አጠቃላይ ስብሰባ / ጠቅላላ ጉባኤ/ የክበቡ አባላት ጠቅላላ ስብሰባ የክበቡ የበላይ አመራር

ሲሆን የጠቅላላ ስብሰባው የሚካሔድበት ጊዜና ምልዐተ

ጉባኤን በሚመለከት በመተዳደሪያ ደንቡ ላይ የሚወሰን ሆኖ

በየትኛውም ክበብ ውስጥ በመስራች ስብሰባ ላይ

መገኘታቸው ሲረጋገጥ ስበሰባው እንደ ምልዐተ ጉባኤ

ተቆጥሮ ስብሰባው ይቀጥላል፡፡

Page 50: ስለ አካባቢ እንክብካቤ  ክበባት  ለትምህርት ቤት ክበባት ተጠሪ

የአካባቢ እንክብካቤ ክበባት አባላት ጠቅላላ ጉባኤ የሚከተሉት ስልጣንና

ኃላፊነቶች ይኖረዋል፡፡

ጠቅላላ ስብሰባው የሚመራዉ በክበቡ ሊቀ መንበር ሆኖ እራሱ በማይኖርበት

ጊዜም በምክትል ሊቀ መንበሩ ይመራል

ጠቅላላ ስብሰባው የክበቡን መተዳደሪያ ደንብ ያፀድቃል፣ ያሻሽላል፣

ይሰርዛል፡፡

የክበቡን የገቢ ምንጭ ይወስናል፣ በጀቱንም ያፀድቃል

የክበቡን የስራ አመራር ኮሜቴ አባላት በመተዳደሪያ ደንቡ በሚወሰነው

መሠረት ይመርጣል፣ ይሽራል /ይቀይራል/ ፡፡ በአካባቢ ችግትች ላይ ይወያያል

የአባላት ጠቅላላ የስብሰባ ጊዜ ይወስናል

Page 51: ስለ አካባቢ እንክብካቤ  ክበባት  ለትምህርት ቤት ክበባት ተጠሪ

የክበቡን አመታዊ የስራ ዕቅድ ያፀድቃል

የክበቡን ስራ አመራር ኮሚቴ የስራ እንቅስቃሴ ሪፖርት ያዳምጣል፣

ያፀደቃል

የክበቡን ስራ አመራር ኮሚቴ የስራ እንቅስቃሴ ሪፖርት ያዳምጣል፣

ያፀድቃል፡፡

የክበቡን አጠቃላይ የእንቅስቃሴ አቅጣጫ በተመለከተ የመጨረሻ ውሣኔ

ይሰጣል

በክበቡ አመራር ላይ የታዩ ደካማና ጠንካራ ጐኖችብን በመለየት

ይገመግማል

የክበቡ ስራ አመራር ኮሚቴ የሚያከናውነውን ስራ ተግባር ወይም የክበቡ

ስራ እንዴት መደራደት እንዳለበት ምንምን ዝርዝር ተግባራትን

እንደሚያከናዉን ይወስናል

Page 52: ስለ አካባቢ እንክብካቤ  ክበባት  ለትምህርት ቤት ክበባት ተጠሪ

በክበቡ እንቅስቃሴ ውስጥጥሩ ተሣትፎ ላሳዩ የክበብ አባላትና

መሪዎች በየዓመቱ በሚደረግ ስብሰባ የምስክር ወረቀትናሽልማት

የሚሰጥበትን ሁኔታ ይወስናል፣ ይሸልማል

የስብሰባ ሂደቱ በክበቡ ፀሐፊ በቃለ ጉባኤ መዝገብ ይያዛል፡፡

ጠቅላላ ስብሰባው በሚያፀድቀው የክበቡ ደንብ የሚወሰን ሆኖ የአካባቢ

እንክብካቤ ክበብ አባልነት ለሁሉም የህብረተሰቡ ክፍል እንደሚቋቋመው

የክበቡ ዓይነት ለማንኛውም ሰው/ ፆታን፣ እምነትን፣ ስራን፣ እደሜን

ሳይለይ / ክፍትና አሣታፊ መሆን ይኖርበታል፡፡ በፍለጐትና በንቁ ተሣትፎ

“ ” ላይ የተመሠረተ መሆን ይኖርበታል፡፡ ከብዛት ጥራት እንደሚባለው

የአባላት ቁጥር የሚያሣስብ ጉዳይ አይደለም፡፡

Page 53: ስለ አካባቢ እንክብካቤ  ክበባት  ለትምህርት ቤት ክበባት ተጠሪ

የክበባት የስራ አመራር ኮሚቴ በክበቡ ጠቅላላ ጉባኤ የሚመረጥ የክበቡን የእለት ተዕለት ስራ

የሚያከናውን የክበቡ የስራ አመራር አባል የሆነ ኮሚቴ ይቋቋማል

የኮሚቴው ስልጣንና ተግባር አስፈላጊነት፣ አወቃቀርና አሰራር በክበባት

የመተዳደሪያ ደንብ የሚገለፅ ሲሆን የኮሚቴ አባላት ብዛትና

የሚኖራቸው ኃላፊነት እንደሁኔታው የሚሰፋና የሚጠብ ሆኖ በብዛት

ሊይዝ /ሊያቅፍ/ የሚገባው ሊቀመንበር፣ ፀሐፊ፡ ገንዘብ ያዥ፣

የፕሮግራም አስተባባሪ፣ የሂሳብ ሹም፣ የንብረት ሰራተኛ አስፈላጊ ሆኖ

ከተገኘም ምክትል ሊቀ መንበር ሊኖረውና ሊመረጥ ይችላል፡፡

Page 54: ስለ አካባቢ እንክብካቤ  ክበባት  ለትምህርት ቤት ክበባት ተጠሪ

የሚቋቋመው የስራ አመራር ኮሚቴ ክበቡን የማስተባበርና

የመምራት፣ የማሣደግና የማጠናከር ኃላፊነት አለበት፡፡ ከዚህ

በተጨማሪ፡- የጠቅለላ ጉባኤውን ውሣኔዎች ያስፈፅማል

የክበቡን አላማዎች ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል አመታዊ

የስራ ዕቅድ ያዘጋጃል፣ ሲፈቀድለትም በተግባር ያውላል

ከክበቡ አላማዎች ጋር የተያያዘ ዓላማ ካላቸው መንግስታዊ

እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርድቶች ጋር ግንኙነት ይመሰርታል፡፡

Page 55: ስለ አካባቢ እንክብካቤ  ክበባት  ለትምህርት ቤት ክበባት ተጠሪ

የክበቡን የስራ ክንውን ሪፖርት ያዘጋጃል ለሚመለከታቸው ወገኖችም

ያሰራጫል፡፡

በክበቡ መተዳደሪያ ደንብ መሠረት የክበቡን የእለት ተዕለት የስራ

እንቅስቃሴ፣ ግንኙነትና አሠራር ሂደት በስብሰባ ያፀደቃል

የስብሰባ አመራር ሂደቱን ይወስናል

በኮሚቴው አባላት መካከል የስራ ክፍፍል እንዲኖር ያደርጋል፣ አስፈላጊ

ሆኖ ሲያገኘው ለስራ መቃናት የሚረዱትን ንዑሣን ኮሚቴዎች በስሩ

ያደራጃል

የክበቡን የገቢ ምንጭ ሁኔታ ያጠናል ለጠቅላላ ጉባኤ አቅርቦ

ያፀድቃል፡፡

Page 56: ስለ አካባቢ እንክብካቤ  ክበባት  ለትምህርት ቤት ክበባት ተጠሪ

የክበቡን ዓለማዎች በማሣወቅ ወደ ክበቡ የሚመጡ አባላትን ያሰባስባል

የመታወቂያ ካርድ በማዘጋጀት ይሰጣል፡፡

ቋሚ የስብሰባ ጊዜ እንዲኖረው ስለሚያስፈልግ የስብብሰባ ጊዜውን

ይወስናል

ኮሚቴው በሚያደርገው በእያንዳንዱ ስብሰሳ ፄሐፊ ቃለ ጉባኤ ይይዛል

በቃለ ጉባኤው ውስጥመካተት የሚኖርባቸው ዋናዋና ነጥቦች

የስብሰባውን ቀን፣ ሰዓት፣ በስብሰባው ለይ የተገኙ አባላት ስም / ፆታና

በስራ አድራሻ ተለይቶ የመወያያ አጀንዳ የስብሰባው ቦታ፣ በስብሰባው

ላይ የተነሱ ዓበይት ጉዳዮች፣ የተደረሰበት የጋራ ውሣኔ፣ የስምምነት

ሁኔታና ስብሰባው የተጠናቀቀበት ሰዓት ከሚጠቀሱት ዋናዋናዎቹ ናቸው፡፡

Page 57: ስለ አካባቢ እንክብካቤ  ክበባት  ለትምህርት ቤት ክበባት ተጠሪ

የተያዘው ቃለ ጉባኤ በተገኙ አባላት ፊርማ ከተደረገ በኋላ

ለወደፊቱ የስራ መመሪያና ማገናዘቢያነት እንዲያገለግል

በፋልይ መቀመጥ አለበት፡፡ የኮሚቴው ውሣኔ የ3 ኛ ወገን

እውቅና ድጋፍ ተሣትፎን የሚጠይቅ ሆኖ ሲገኝ ክበቡ

ለተደራጀበት ትምህርት ቤት፣ ተቋም፣ ገጠር ቀበሌ

አስተዳደር፣ ፋብሪካ ወዘተ መድረስ አለበት፡፡

Page 58: ስለ አካባቢ እንክብካቤ  ክበባት  ለትምህርት ቤት ክበባት ተጠሪ

የስራ ግንኙነትና ተጠሪነት የአካባቢ እንክበካቤ ክበባት ተጠሪነታቸው ለክበቡ ጠቅላላ

ጉባኤ ሆኖ በተጓዳኝ ለተቋቋሙለት ተቋም፣ ትምህርት ቤት፣

የሙያ ማህበር፣ ቀበሌ፣ ድጋፍ ለሚያደርጉላቸው መንግስታዊና

መንግስታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች፣ ለሲቪል ማህበራት ለወረዳ

አካባቢ ጥበቃ፣ መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ፅህፈት ቤት

እና ለሌሎች በአካባብ ጥበቃና ልማት ዙሪያ ለሚሰሩ

ድርጅቶች ወዘተ የክበቡን የስራ እንቅስቃሴ ሪፖርት

በመተዳደሪያ ደንቢ ላይ በሚወሰነው መሠረት ያቀርባሉ፡፡

Page 59: ስለ አካባቢ እንክብካቤ  ክበባት  ለትምህርት ቤት ክበባት ተጠሪ

ሌሎች ግንኙነትን በሚመለከት

በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የአካባቢ እንክብካቤ ክበባት፣

በክልል ደረጃም ሆነ ከክልል ውጭ እንዲሁም በውጭ ሐገር

ከሚገኙ ክበባት ጋር ግንኙነት መፍጠር

ከሌሎች አቻ ክበባት ጋር ለምሳሌ የኤች አይ ቪ

ኤድስ፣የድራማና የሀገርህን እወቅ ክበብ ወዘተ ጋር

በመተባበር መስራት

ክበቡ ከተቋቋሙት ትምህርት ቤት፣ የቀበሌ አስተዳደር ወዘተ

ጋር

Page 60: ስለ አካባቢ እንክብካቤ  ክበባት  ለትምህርት ቤት ክበባት ተጠሪ

የአካባቢ እንክብካቤ ክበባት የትምህርት ማስተላለፊያና

ማስተማሪያ መንገዶች

የስራ ክፍል የክበቡ የስራ እንቅስቃሴ በተለያዩ ቡድኖች ተከፋፍሎ ቢመራ

ለክበቡ እደገት ቁጥጥርና ክትትል ከፍተኛ ጠቃሚነት

ይኖረዋል፡፡ የእያንዳንዱን ስራ የሚያስተባብር ወይም የመማራ

የቡድን መሪ ይኖረዋል፡፡

የቡድን መሪው ስለቡድኑ እንቅስቃሴ ሪፖርት ማቅረብ

ይኖርበታል፡፡

Page 61: ስለ አካባቢ እንክብካቤ  ክበባት  ለትምህርት ቤት ክበባት ተጠሪ

በክበቡ ውስጥ ስንት ቡድን እንደሚኖር እንዲሀም በአንድ

ቡድንውስጥ ምን ያህል አባላት እንደሚኖሩ፣ ክበቡ

የሚቋቋምበት አካባቢ ባህሪ እንደየ አካባቢው ሁኔታ

የሚወሰን ይሆናል፡፡

በስራ ክፍፍሉ ወቅት እያንዳዱ ተግባራት እንደየ ክበባቱ

ባህሪያትና አደረጃጀት የሚለያይ ይሆናል፡፡

በስራ ክፍፍሉ ወቅት እያንዳንዱ አባል በባለቤትነት ሊሰራቸው

የሚገባቸው ተግባራት ተለይቶ መሰጠት ይኖርበታል፡፡

Page 62: ስለ አካባቢ እንክብካቤ  ክበባት  ለትምህርት ቤት ክበባት ተጠሪ

ቤተመፃህፍት ማዘጋጀት የክበባት ቤት መፃህፍት አባላትንና አባል ያልሀኑ ሁሉ

የሚጠቀሙበት ሆኖ ለተጠቃሚዎች ስለ አካባቢ እንክብካቤና

አጠቃቀም ዕውቅና እና ክህሎታቸውንም ለማዳበር ከማገዝም

በላይ ፍላጐትም እንዲኖራቸው ያደርጋል፡፡ የቤተ መፃህፍቲ

አደረጃጀት እንደ ክበቡ ልዩ ባህሪ የሚለያይ ሆኖ በውስጡእ

አባላትንና ታዳሚዎችን ሊማርኩ /ሊስቡ/ የሚችሉ የተለያዩ

አካባቢ ነክ መፃህፍ፣ መፅሔቶች፣ ቪደዮ ፊልሞች፣ መጋዚዎች

እና ልዩልዩ ወቅታዊ መረጃዎችንና ፅሁፎችን ቢይዝ ይመረጣል፡፡

Page 63: ስለ አካባቢ እንክብካቤ  ክበባት  ለትምህርት ቤት ክበባት ተጠሪ

ቤተመዘክር የአካባቢ እንክብካቤ ክበባት ቤተ መዘክር በማቋቋም

የአካባቢውን ህብረተሰብ ባህልና ቅርስን የሚያሣዩ ኢግዚቪሽን

በማዘጋጀት /ማደራጀት/ ፣ ለማስተማሪያነት መጠቀም፣

በሙዚየሙውስጥ የክበቡን አጀማመር ታሪክና እንቅስቃሴ

የሚያሣዩ ገላጭመረጃ ትኩረት ቢሰጠውጥሩ ነው፡፡

Page 64: ስለ አካባቢ እንክብካቤ  ክበባት  ለትምህርት ቤት ክበባት ተጠሪ

ከዚህ ሌላ ትምህርታዊ መልዕክት የሚኖራቸው ለምሳል

የዕፅዋት ዝርያዎች፣ የወፎች ላቨ፣ የድንጋይ /አለቶች/ እና

መጠን ጠቋሚመረጃን ቢይዝ ይመረጣል፡፡

ለቤተ መዘክር ተብሎ ናሙና በሚወሰድበትና በሚሰበሰብበት

ጊዜ የተፈጥሮ ሃብትብንና የአካባቢን የሚጐዳ እንዳይሆን

ጥንቃቄ ሊወሰድ ይገባል፡፡

Page 65: ስለ አካባቢ እንክብካቤ  ክበባት  ለትምህርት ቤት ክበባት ተጠሪ

ሚኒሚዲያ ሚኒሚዲያ ለአካባቢ እንክብካቤ ክበባት ትልቅ መልዕክት

ማስተላለፊያ መድረክ ነው፡፡

አባላቱም ሆኑ ሌሎች ክበቡ የተቋቋመበት የህብረተሰብ ክፍል

ትኩስና ወቅታዊ መረጃዎችን የሚያገኝበት ዘዴና መድረክ

ነው፡፡

የአካባቢ ክበባቱም መልዕክት ለማስተላለፊያነት

የሚጠቀሙበትና በሚኒሚዷያ ውስጥ በመሣተፋቸውም

የራሣቸውን ክህሎት የሚያዳብሩበት ነው፡

Page 66: ስለ አካባቢ እንክብካቤ  ክበባት  ለትምህርት ቤት ክበባት ተጠሪ

የውድድር ስሜትመፍጠር ጤናማ ውድድር ለእደገት መሠረት ነው በዚህም የክበቡ

አባላት ሁሉ ለክበቡ የስራ እንቅስቃሴ እኩል አስተዋፅኦ

ያደርጋሉ ማለት ስለማይቻል በአባላት መካከል ፉክክር

በመፍጠር የተሻለ ተሣትፎ፣ ብቃትና አስተዋፅኦ ላበረከቱ

አባላት ማበረታቻ ሽልማት መስጠት፡፡

እንዲሁም በአቻ ክበባት መካከልም የውድድር ስሜት

በመፍጠር የክበባቱን ስራማጠናከርና ማጎልበት ይቻላል፡፡

Page 67: ስለ አካባቢ እንክብካቤ  ክበባት  ለትምህርት ቤት ክበባት ተጠሪ

ፕሮጀክት መቅረፅ የፕሮጀክት ስራ በግል ወይም በቡድን የተግባር ስራን በማከናወን

በሚታይ፣ በሚጨበጥና በሚገመገምመልኩ የሚገለፅ የመማር

ማስተማር ዘዴ ነው፡፡

የፕሮደክት ስራ የብከብ አባላት እና በአካባቢ እንክብካቤ ስራ

ከተሰማሩ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ እና ሌሎች ድርጅቶች

ጋር በመሆን ዕቅድ በማውጣት ተግባራዊ ስራ አማካኝነት ንድፈ

ሃሣብን ከተግባር እንዲዋሃዱ አመች በመሆኑ በመማር ማስተማር

ሂደቱ የባህሪ ለውጥን ለማምጣት ከፍተኛ ጠቀሜታ አለወ፡፡

Page 68: ስለ አካባቢ እንክብካቤ  ክበባት  ለትምህርት ቤት ክበባት ተጠሪ

በክበቡ አባላት በአካባቢው ህብረተሰብ ንቁ ተሣትፎ

ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ የአካባቢ ልማት ፕሮጀክቶች

በመስኩ ከተሰማሩ መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ

ድርጅቶች በመተባበር ቀርፀው ስራ ላይ እንዲውል ያደርጋሉ፡፡

ፕሮጀክቶቹም ሊተገበሩ የሚችሉና በአካባቢ እንክብካቤ

ልማት ዙሪያ የሚያተኩሩ ይሆናሉ፡፡

Page 69: ስለ አካባቢ እንክብካቤ  ክበባት  ለትምህርት ቤት ክበባት ተጠሪ

የችግኝጣቢያ ማቋቋም

ከፍተኛ የሆነ የደን ሐብት ሽፋንን መልሶ ለመተካት

እንዲያስችል ክበባት ከፍተኛ ኃላፊነት ያለባቸው በመሆኑ

ይህንን ኃላፊነት ለመወጣት የራሣቸው የሆነ የችግኝ ጣቢያ

ማቋቋም የዛፍ ዘር መሰብሰብ / በተለይ አገር በቀል ዝርያ

ቢሆን ይመረጣል/ ችግኝ ማፍላትና የረከላ ወቅቱም

ከመድረሱ በፊት የችግኝ መትከያ ጉድጓድ አዘጋጅቶ

Page 70: ስለ አካባቢ እንክብካቤ  ክበባት  ለትምህርት ቤት ክበባት ተጠሪ

ወቅቱ ሲደርስ አባሉቱንና ህብረተሰቡን አስተባብሮ የችግኝ

ተከላ ማካሔድ፣ የተተከለውንም መጠበቅና መንከባከብ የጓሮ

አትክልት ማፍያና የመትከያ ቦታን አዘጋጅቶ በማልማት የገቢ

ምንጭን ማዳበርና የአመጋገብ ባህልንም ማሀሳሻል

ያስፈልጋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ የተለያዩ ችግኞችን በማፍላት ለአካባቢው

ህብረተሰብ መሸጥ ይቻላል፡፡

Page 71: ስለ አካባቢ እንክብካቤ  ክበባት  ለትምህርት ቤት ክበባት ተጠሪ

የታዋቂ ግለሰቦችን ልምድመቅሰሚያመድረክ ማዘጋጀት ለአካባቢ እንክበካቤ ክበብ አባላት የሙያና የልምድ መቅሰሚያ ሆኖ

የሚያገለግል መድረክ በማዘጋጀት ታዋቂ ግለሰቦችን በየጊዜው

በመጋበዝና ትምህርት እንዲሰጡማድረግ፡- በአካባቢ እንክብካቤ ስራ አርአያ የሆኑ ግለሰቦች ልምዳቸውን

እንዲያካፍሉ ማድረግ

የእደሜ ባለፀጋ አረጋውያንን ንግግር እንዲያደርጉ መጋበዝ

ባለሙያዎችን፣ በልማት እንቅስቃሴያቸው የሚታወቁ ግለሰቦችን ጐበዝ

… ተማሪዎችን፣ ወዘተ በማሣተፍ እውቀታቸውንና ልምዳቸውን

እንዲያካፍሊ ማድረግ፡፡

Page 72: ስለ አካባቢ እንክብካቤ  ክበባት  ለትምህርት ቤት ክበባት ተጠሪ

የመስክ ጉብኝት ፕሮግራምማዘጋጀት የክበቡ አባላትን የሚያሣትፍ ትምህርታዊ የጉዞ ፕሮግራሞችን

ማዘጋጀት የተፈጥሮ አካባቢን እንዳለ መመልከትና ማጥናት

ስለሚያስችል ለአካባቢ እንክብኮቤ ስራመቃናት ከፍተኛ ቦታ

ይሰጣቸዋል፡፡ የክበቡ አባላትም ስለ አካባቢ የሚኖራቸውን

እውቀት፣ ፍላጐትና ዝንባሌ ከማጐልበትም በላይ ከአካባቢ

ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት እንዲኖር ያስችላል፡፡ በዚህም የመስክ

ጉብኝት ፕሮግራሙ የሚመረጡት፡-

Page 73: ስለ አካባቢ እንክብካቤ  ክበባት  ለትምህርት ቤት ክበባት ተጠሪ

በክበቡ እንቅስቃሴ ውስጥ የላቀ አስተዋፅኦ ያላቸው

ከጉብኝት በኋላ ስለጐበ˜ ቸዉ ቦታዎችና ያገኙትን ዕውቀት

የማካፈል ልምድና ችሎታ ያላቸው

በጉብኝቱ ፕሮግራም ለመሣተፍ ፈቃደኛ የሆኑ

የፆታ ስብጥርን ከግምት ውስጥ ያስገባ

የሚጐበኘው ቦታ ከክበቡ አላማ ጋር የተቆራኘ መሆን

Page 74: ስለ አካባቢ እንክብካቤ  ክበባት  ለትምህርት ቤት ክበባት ተጠሪ

በቀጣይ የክበቡ እንቅስቃሴ ውስጥመፍትሔ የሚፈለግበት ( የተጐዳ

አካባቢንና ያገገመ አካባቢን የሚያመለክት) ፓርኮች፣ የተጠበቁ

ደኖችን፣ በማህበረሰብ እየተካሔደ የሚገኝ የአካባቢ ልማት፣ ታሪካዊ

…ቦታዎች ወዘተ

ፕሮግራሙ ሲዘጋጅ ልምድ ባላቸው ሰዎችና ተገቢው ዝግጅት

ተደርጐበት መሆን አለበት ስራውን ለማመቻቸትና ለጥንቃቄ

እንዲያመች ጉብኝቱ ከመጀመሩ በፊት የሚጐበኘውን ቦታ የተወሰኑ

የስራ አመራር አባላት አስቀድመው እንዲያዩት ቢደረግ ጥሩ ይሆናል፡፡

ከጉብኝት በኋላ በቂ ሪፖርት ተዘጋጅቶ መቅረብ አለበት፡፡

Page 75: ስለ አካባቢ እንክብካቤ  ክበባት  ለትምህርት ቤት ክበባት ተጠሪ

ከአቻ ክበባት ጋር ግንኙነት መፍጠር

የአካባቢ እንክብካቤ ክበብ አባላት ልምድና የስራ ተሞክሮ ከሚያገኙበት

መድረክ አንዱ ከሌሎች በሀገር ውስጥ ከሚገኙ አቻ ክበባት እና ከሌሎች

አጋር አካላት ጋር ግንኙነት በመፍጠር የልምድ ልውውጥ በማድረግ ነው፡፡

በዚህ ግንኙነት አባላት ሰፊ ልምድ ያካብታሉ፣ ኃላፊነት የመወጣት

ብቃታቸውን ያጐለብታሉ፤ ዕውቀት ይቀስማሉ፤ ከሌሎች ያገኙትን ጠንካራ

አሰራር ከራሳቸው ተጨባጭ ሁኔታ ጋር አገናዝበው ተግባራዊ ያደርጋሉ፤

አላስፈላጊ የሆኑ እንቅስቃሴዎችንም ለማረም ያግዛቸዋል፡፡

Page 76: ስለ አካባቢ እንክብካቤ  ክበባት  ለትምህርት ቤት ክበባት ተጠሪ

ክበባት የሚያደርጉት ጉብኝት ግንኙነትና ልምድ ልውውጥ

የጋር ፍላጐታቸውንና ዕቅዶቻቸውን አስተሳስረው ለመጓዝ

ያግዛል፡፡ በተጨማሪም ለአባላት የሞራል ማጠናከሪያ

ማበረታቻምጭምር ነው፡፡

Page 77: ስለ አካባቢ እንክብካቤ  ክበባት  ለትምህርት ቤት ክበባት ተጠሪ

የተለያዩ ፊልሞችን ማሣየት ክበባት ከተለያዩ በአካባቢ እንክብካቤና ልማት ስራ ላይ

ከተሰማሩ መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች፣ ከሲቪል

ማህበራት፣ ከልዩልዩ ተቋማት፣ ወዘተ ልዩልዩ ፊልሞችን በመዋስ

ለአባላትና ለማህበረሰቡ በየጊዜው የፊልም ፕሮግራም እያዘጋጁ

በማሣየት ህዝቡ በአካባቢው ላይ እየደረሰ ያለውን ጫና ተረድቶና

ተገንዝቦ አካባቢያቸውን ለመንከባከብ እና ለመጠበቅ እንዲነሳሳ

ያደርጋሉ፡፡ በየጊዜውጥሩጥሩ ፊልም የሚቀርብ ከሆነም አባል

ያልሆኑ ግለሰቦችጭምር ወደ ክበቡ የበለጠ እንዲሳቡ ያደርጋል፡፡

Page 78: ስለ አካባቢ እንክብካቤ  ክበባት  ለትምህርት ቤት ክበባት ተጠሪ

የአካባቢ እንክብካቤ ክበባት የተለያዩ ባህላዊና አካባቢ ነክ

በዓላትን ምክንያት በማድረግ ለምሳሌ ( የዓለም የአካባቢና

የበረሃማነት ቀን፣ ህዳር 12 ህዳር ሲታጠን ቀንን ወዘተ) ፕሮግራም ነድፈው በየአካባቢያቸዉ ህብረተሰቡን

በማስተባበር የፅዳት ዘመቻ ማድረግ አለባቸው፡፡

Page 79: ስለ አካባቢ እንክብካቤ  ክበባት  ለትምህርት ቤት ክበባት ተጠሪ

ከዚህ ውጭ በየጊዜው የፅዳት ስራ ፕግራም ወጥቶለት

የሚከናወን ተግባር ስለመሆኑ በማስተማር በከተማ አካባቢ

የከተማ ውስጥ ቆሻሻ ለምሳሌ ፌስታል፣ ቁርጥራጭ

… ብረቶች፣ የቤት ጥራጊ ወዘተ ፣ በፋብሪካ አካባቢ ከፋብሪካ

… የሚወጣ ፍሳሽ ልዩ ልዩ ዝቃጭ፣ ወዘተ እንዲቀበር

የማድረግ፣ በአርሶ አደሩ አካባቢ የቦይ ከፈታ፣ የረጋ ውሃ

ማስወገድ፣ የመፀዳጃ ቤት ቁፋሮ ዝግጅት፣ የምንጭጠረጋ፣

ወዘተ.. ፣ ማከናወን ያስፈልጋል፡፡

Page 80: ስለ አካባቢ እንክብካቤ  ክበባት  ለትምህርት ቤት ክበባት ተጠሪ

የየዕለቱ የፅዳት ዘመቻ እንደተጠናቀቀም በዘመቻ ለተሣተፈው

ህዝብ ቆሻሻን እንደገና መጠቀም ስለሚቻልበት ሁኔታ

ህብረተሰቡ በግሉ ቆሻሻውን ለየብቻ በመለየት እያጠራቀመ

መበስበስ የማይችለውን በማቃጠል፣ መበስበስ የሚችለውን

በጉድጉድ በማከማቸት ሰው ሰራሽ ማዳበሪያ እያዘጋጀ አርሶ

አደሩ ለማሣው፣ የከተማ ነዋሪው ለጓሮ አትክልቱና ለአበባ

ቦታው መጠቀም እንደሚችል አጭር ገለፃ መስጠት መለመድ

ይኖርበታል፡፡

Page 81: ስለ አካባቢ እንክብካቤ  ክበባት  ለትምህርት ቤት ክበባት ተጠሪ

የሃሳብመስጫ ሳጥንማዘጋጀት

የሃሳብ መስጫ ሳጥኑ ስለ ክበቡ እንቅስቃሴ ጠቃሚመልዕክቶችንና

ትችቶችን እንዲያገኙ ስለሚረዳቸው ለሁሉም በሚያመች እና በሚታይ

ቦታ፣ ሊቆለፍ በሚችል ዝናብ በማያገኘው /በማያበላሸው/ ሁኔታ

መዘጋጀት ይኖርበታል፡፡

አባላቱም ሆኑ ሌሎች በሃሳብ መስጫ ሳጥኑ እንዲጠቀሙማበረታታት

ከክበቡ የሚጠበቅ ሲሆን በሳጥኑ ውስጥ የተሰበሰቡ አስተያየቶችና

ጥያቄዎች በየሣምንቱ አንድ የአስተያየትና የጥያቄ መልስ መስጫ

ፕሮግራም አዘጋጅቶ በፅሁፍ የተዘጋጀ ከሆነ በቦርድ ላይ መለጠፍ፣

በቃል የሚመለስ ከሆነ በስብሰባ ላይ መልሱን መስጠት ይገባል፡፡

Page 82: ስለ አካባቢ እንክብካቤ  ክበባት  ለትምህርት ቤት ክበባት ተጠሪ

የአካባቢ እንክብካቤ አባላት ንግግር እንዲያደርጉ

ስለመጋበዝ በአካባቢ፣ ብሔራዊና ዓለም አቀፋዊ የተፈጥሮ ሚዛን መዛባት

እንዲሁም ወቅታዊ በሆኑ የአካባቢና የልማት ችግሮችና

መፍትሔዎቻቸዉ ላይ ያተኮረ ዝግጅት በማድረግ አባላት

ንግግር እንዲደርጉ ማመቻቸት፣ ለተወሰኑ የክበቡ አባላት

ወቅታዊ ርዕስ በመስጠት ለታዳሚዎችጠለቅ ያለ ግንዛቤ

ሊያስጨብጥ የሚችል ገለፃና ንግግር እንዲያደርጉ መጋበዝ

ሌላው ተገቢ ጉዳይ ነው፡፡

Page 83: ስለ አካባቢ እንክብካቤ  ክበባት  ለትምህርት ቤት ክበባት ተጠሪ

አመሰግናለሁ