16
ነገረ- ኢትዮጵያ ሚያዝያ 10 ቀን 2006 ዓ.ም. ቅፅ 1 ቁጥር 9 ጎንደር፡- በጎንደር ከተማ ቀበሌ 18 ከ30 ሺህ በላይ ቤቶች የተገነቡባቸው ሶስት ሰፈሮች ሊፈርሱ መሆኑን በስፍራው የሚገኙ የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች አስታወቁ፡፡ በከተማዋ ቀበሌ 18 ከተመሰረቱ ከ7 አመት 15 7 9 4 ወደ ገፅ 4 ዞሯል... ወደ ገፅ 15 ወደ ገፅ 15 ዞሯል... ቅፅ 1 ቁጥር 9 ዋጋ 8 ብር አርብ ሚያዝያ 10 2006 ዓ.ም አርሶ አደሮች መሬታቸውን ያለካሳ እየተነጠቁ ነው ኦቦ ሙክታር ከድር ተሳካላቸው! በጠራራ ፀሐይ የሚዘርፉን ተቋማት ይድረስ ለ‹‹ጄኔራሎቹ አለቃ››! መድረክ-የፖለቲካ አስመሳይነት መጨረሻ? 16 7 14 ጥራኝ ጎዳናው! ጥራኝ መንገዱ! ሰሎሞን ተሰማ ጂ. መሳይ ከበደ (ፕ/ር) መንግስት ለምን ህዝብን ይሰልላል? አለማየሁ ገ/ማርያም (ፕ/ር) አዲስ አበባ፡- ሰማያዊ ፓርቲ (ሰማያዊ) ‹‹የተነጠቁ መብቶችን እናስመልስ!›› በሚል መሪ ቃል ሚያዝያ 19 ቀን 2006 ዓ.ም በአዲስ አበባ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚያካሂድ አስታውቋል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ ከአሁን ቀደም የተለያዩ ጥያቄዎችን በማንሳት በመንግስት ዘንድ ምላሽ እንዲሰጣቸው ቢጠይቅም ጥያቄዎቹ ምላሽ ያልተሰጣቸው ከመሆኑም ባሻገር ችግሮቹ ጭራሹን እየተባባሱ በመምጣታቸውና ህዝብም እየተማረረ በመሆኑ ሰላማዊ ሰልፉን መጥራት እንዳስፈለገ የፓርቲው ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ተ/ ያሬድ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ የተቃውሞ ሰልፍ ጠራ በጎንደር 30 ሺህ ቤቶች እንደሚፈርሱ ታወቀ ‹‹በከተማዋ ውጥረት ነግሷል›› በምስራቅ ወለጋ ዜጎች እየተፈናቀሉ ነው እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤ አደረሳችሁ ! የዘመኑ ፖለቲካ መስዋዕቶች 5

9 የዘመኑ ፖለቲካ መስዋዕቶች · ô+ ù pÛ Ø ea ጎንደር፡- በጎንደር ከተማ ቀበሌ 18 ከ30 ሺህ በላይ ቤቶች የተገነቡባቸው

  • Upload
    others

  • View
    35

  • Download
    0

Embed Size (px)

Citation preview

ነገረ- ኢትዮጵያሚያዝያ 10 ቀን 2006 ዓ.ም. ቅፅ 1 ቁጥር 9

ጎንደር፡- በጎንደር ከተማ ቀበሌ 18 ከ30 ሺህ በላይ ቤቶች የተገነቡባቸው ሶስት ሰፈሮች ሊፈርሱ መሆኑን በስፍራው የሚገኙ የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች አስታወቁ፡፡ በከተማዋ ቀበሌ 18 ከተመሰረቱ ከ7 አመት

15

7

9

4

ወደ ገፅ 4 ዞሯል... ወደ ገፅ 15

ወደ ገፅ 15 ዞሯል...

ቅፅ 1 ቁጥር 9 ዋጋ 8 ብርአርብ ሚያዝያ 10 2006 ዓ.ም

አርሶ አደሮች መሬታቸውን ያለካሳ

እየተነጠቁ ነው

ኦቦ ሙክታር ከድር ተሳካላቸው!

በጠራራ ፀሐይ

የሚዘርፉን ተቋማት

ይድረስ ለ‹‹ጄኔራሎቹ አለቃ››!

መድረክ-የፖለቲካ አስመሳይነት መጨረሻ?

16 714

ጥራኝ ጎዳናው! ጥራኝ መንገዱ!

ሰሎሞን ተሰማ ጂ.መሳይ ከበደ (ፕ/ር)

መንግስት ለምን ህዝብን ይሰልላል?

አለማየሁ ገ/ማርያም (ፕ/ር)

አዲስ አበባ፡- ሰማያዊ ፓርቲ (ሰማያዊ) ‹‹የተነጠቁ መብቶችን እናስመልስ!›› በሚል መሪ ቃል ሚያዝያ 19 ቀን 2006 ዓ.ም በአዲስ አበባ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚያካሂድ አስታውቋል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ ከአሁን ቀደም የተለያዩ ጥያቄዎችን በማንሳት በመንግስት ዘንድ ምላሽ እንዲሰጣቸው ቢጠይቅም ጥያቄዎቹ ምላሽ ያልተሰጣቸው ከመሆኑም ባሻገር ችግሮቹ ጭራሹን እየተባባሱ በመምጣታቸውና ህዝብም እየተማረረ በመሆኑ ሰላማዊ ሰልፉን መጥራት እንዳስፈለገ የፓርቲው ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ተ/ያሬድ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ የተቃውሞ ሰልፍ ጠራ

በጎንደር 30 ሺህ ቤቶች እንደሚፈርሱ

ታወቀ‹‹በከተማዋ ውጥረት ነግሷል››

በምስራቅ ወለጋ ዜጎች እየተፈናቀሉ ነው

እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤ አደረሳችሁ !

የዘመኑ ፖለቲካ መስዋዕቶች5

ነገረ- ኢትዮጵያሚያዝያ 10 ቀን 2006 ዓ.ም. ቅፅ 1 ቁጥር 9 2

ርዕሰ አንቀፅ ነገረ-ኢትዮጵያ ጋዜጣ ጥር 2006 ዓ.ም ተመሰረተች፡፡ ነገረ-ኢትዮጵያ በሰማያዊ

ፓርቲ አሳታሚነት የምትታተም ፖለቲካዊ፣ ወቅታዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ

ጉዳዮችን የምትዳስስ በየሳምንቱ አርብ የምትወጣ ጋዜጣ ናት፡፡

ጋዜጣዋ ሚዛናዊና ነጻ ሆና የማገልገል መርህ አላት፤ ማንኛውም ሀሳብ በነጻነት የሚስተናገድባትና የሚንሸራሸርባት እንድትሆን እንፈልጋለን፡፡ ገዥው ፓርቲም ቢሆን አቋሙንና ፖሊሲውን ለመግለጽ ቢፈልግ የሰፊ ሚዲያ ባለቤት ነው ብለን ዕድሉን አንነፍገውም፤ በራችን

ለሁሉም ክፍት ነው፡፡

ነገረ-ኢትዮጵያነገረ-ኢትዮጵያ

የአሳታሚ አድራሻ:- የካ ክ/ከተማ ቀበሌ 09/10 ቤት ቁ.460 E-mail:- [email protected] P.O.Box: 180298

ዋና አዘጋጅ ፡- ጌታቸው ሺፈራው የካ ክ/ከተማ ቀበሌ 01/02 ቤት ቁ. 07/859/14 E- mail:[email protected] ስልክ ቁጥር:- 09-10-45-99-32

ምክትል ዋና አዘጋጅ፡- በላይ ማናዬ የካ ክ/ከተማ ቀበሌ 01/02 ቤት ቁ.099 E-mail:- [email protected] ስልክ ቁጥር:-09-20-19-09-72

አምደኞች ፡- ፕ/ር አለማየሁ ገ/ማርያም ታዴዎስ ታንቱ ታምራት ታረቀኝ አፈወርቅ በደዊ እያስፔድ ተስፋዬ

ሕትመትና ክትትል ሳሙኤል አበበ 0913 98 46 40

አታሚ፡- ሰማያዊ ፓርቲ

እንዲህም ተብሏል!

ሌይ አውት ዲዛይን ፡-

ተሰማ ደሳለኝ

በፋሲካው ኢትዮጵያን እናስባት!

ፋሲካ እየሱስ ክርስቶስ በሞቱ የሰውን ልጅ ያዳነበትና ትዕንቢቱ ይፈጸም ዘንድ ከሙታን የተነሳበት ስለመሆኑ ቅዱስ መጽሃፉ ይነግረናል፡፡ ይህ ቀን እየሱስ ክርስቶስ በደሙ የሰውን ልጅ ከሐጢያት ባርነት ነጻ ያወጣበት ነው፡፡ እንደ አለመታደል ሆኖ ኢትዮጵያውያን ይህንን የነጻነት ቀን የምናከብረው በዘመናዊ ጭቆና ውስጥ ሆነን ነው፡፡ በርካታ ኢትዮጵያውያን ለአያሌ አመታት ከኖሩበት ቀየና ቤታቸው

እየተፈናቀሉ ነው፡፡ በቤንሻንጉል ጉምዝ፣ አምቦ፣ ወለጋ እና ሌሎችም አካባቢዎች ኢትዮጵያውያን ከ20 አመት በላይ ከኖሩበት ቀየ ‹‹አገራችሁ አይደለም!›› ተብለው እየተፈናቀሉ ነው፡፡ በባህር ዳር፣ ጎንደርና ሌሎችም የኢትዮጵያ ከተሞች ለዓመታት የኖሩበት ቤታቸውን መንግስት ቅያሬ ሳይሰጣቸው፣ ዝግጅት ሳይደረግበት እያፈረሰባቸው ይገኛል፡፡ እነዚህ በሞቀ ቤታቸው ያምናዋን ፋሲካ ያከበሩ ኢትዮጵያውያን ዘንድሮ ፋሲካን የሚያሳልፏት በመከራ ነው፡፡ፋሲካ እየሱስ ክርስቶስ ትግስትን፣ ሰላምንና ፍቅርንም ያስተማረበት ቀን ነው፡፡ ይህ ፍቅር፣ ሰላምና ትግስት በዛሬዋ ኢትዮጵያ እየጠፋ ነው፡፡ ከ100 አመት በፊት ተሰራ የተባለ ታሪክ ዛሬ ኢትዮጵያውያንን እርስ በእርስ አናቁሮ ስልጣንን ለማስጠበቅ እየዋለ ነው፡፡ ገዥዎቻችን በዚህ ፋሲካ ሰሞንም ስለ ፍቅር፣ ሰላምና አብሮ መኖር ይልቅ ከመቶ አመት በፊት ስለተፈጸመ ታሪክ እንድንቆዝም፣ የዘመኑን ባርነታችን እንድንረሳ ለማድረግ እየጣሩ ነው፡፡ ፋሲካ የትግስትና የፍቅር ምልክት እንደመሆኑም ኢትዮጵያውያን በማህላችን የተፈጠረውን የጥላቻ ዘር፣ የተደቀነብንን ፈተና እና የቆመብንን እንቅፋት በትግስት ማለፍ ይኖርብናል፡፡ ስለ ኢትዮጵያ የወደፊት እጣ ፈንታ ቆም ብለን ልናስብበት የሚገባን ወቅትም ነው፡፡

ህገ መንግስቱ ‹‹መንግስት በሐይማኖት ጣልቃ አይገባም›› ቢልም ገዥው ፓርቲ 23 አመታት ይህን ራሱ ያጸደቀውን ህገ መንግስት ሊያከብር አልቻለም፡፡ የውጭ ወራሪዎች በኢትዮጵያ ገዳማትና አብያተ ክርስትያናት ላይ ጉዳት ሲያደርሱ ኖረዋል፡፡ ባለፉት ጥቂት አመታት ግን ኢትዮጵያውያን አማኞች በራሳቸው ‹‹መንግስትም›› በደል

እየደረሰባቸው ቀጥለዋል፡፡ ለዘመናት ተከብሮ የኖረው የዋልድባ ገዳም ለስኳር ምርት በሚል ተከልሏል፡፡ የዋልድባ መነኮሳት ይህችን ፋሲካ ሲያከብሩ መንግስት ባሳደረባቸው ጫና ልባቸው ተሰብሮ ነው፡፡ በቅርቡ ደግሞ መንግስት ማህበረ ቅዱሳን ላይ ጫና እያደረገ እንደሚገኝ መረጃዎች እየጠቆሙ ነው፡፡ በራስህ ላይ እንዲሆን የማትፈልገውን በሌላም እንዲሆን አትፍቀድ እንዲሉ ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች ለዘመናት በሰላም አብረዋቸው በኖሩት ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ላይ የሚደረገውን ጣልቃ ገብነትም አይተው የሚያልፉት ጉዳይ አይሆንም፡፡ ፋሲካውን መንግስት በሐይማኖት ላይ የሚያደርገውን ጫና በመቃወም ስለ አርነት፣ ስለ ኢትዮጵያዊነት በማሰብ ልናከብረው ይገባል፡፡ስለ ነጻነት፣ ፍትህ፣ እውነት፣ ስለ አገራቸው ዴሞክራሲያዊ ግንባታ የታተሩ ኢትዮጵያውያን እስር ቤት ውስጥ ታጉረው ይገኛሉ፡፡ አገራችን በገጠማት የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮች አብዛኛዎቹ ዜጎቻችን የሚበሉትና የሚለብሱት አጥተው ጎዳና ወጥተዋል፡፡ ከቀያቸውና ከሞቀ ቤታቸው የሚባረሩት ሲጨመሩበት መከራውን የበዛ አድርጎታል፡፡ ስለ አንድነታችን ሳይሆን ስለ ልዩነታችን በተሰበከባቸው 23 አመታት ውስጥ ጎረቤታሞች ከኢትዮጵያዊነት ይልቅ በቋንቋ ልዩነት የሚቦደኑበት አጋጣሚ ተበራክቷል፡፡ እውን ፋሲካን ከልብ የምናከብር ከሆነ እነዚህ በተለያዩ ችግሮች ጎዳና ላይ የወጡ፣ እስር ቤት ውስጥ የታጎሩ ኢትዮጵያውያንን ማሰብ ይጠበቅብናል፡፡ ቋንቋ ሳይገድበንም ስለ ኢትዮጰያና ኢትዮጵያውያን አስበን በፍቅር አብረን በዓሉን ማክበር ይገባናል፡፡ አገርን ስናስብ ስለ ራሳችንም ማሰባችን የማይቀር ነው፡፡ የኑሮ ውድነት ኢትዮጵያውያን የማይችሉት ደረጃ ላይ እየደረሰ ነው፡፡ ሙስና ተስፋፍቷል፡፡ የውሃ፣ የመብራት፣ የስልክ አገልግሎት ማግኘት አልተቻለም፡፡ እነዚህ አገልግሎቶች መሰረታዊ አገልግሎቶች ናቸው፡፡ በዚህ ወቅት ግን ኢትዮጵያውያን በኑሮ ውድነቱ ምክንያት ለበዓል የሚያስፈልጋቸው ሸቀጦች በሚገባ አያገኙም፡፡ ሌላው ይቅርና በበዓሉ የውሃ፣ የመብራትና የስልክ አገልግሎት የማያገኙት ኢትዮጵያውያን በርካቶች ናቸው፡፡ ፋሲካ እነዚህ አገልግሎቶችን ማግኘት መብታችን መሆኑን በሚገባ የምንገነዘብበት፣ በመከራ ላይ የሚገኙትን ኢትዮጵያውያን የምናስብበትና የምናግዝበት፣ ስለ አብሮ መኖርና ቀጣይ እጣ ፋንታችን የምንመክርበት፣ መብታችን አሳልፈን ባለመስጠት ከዘመናዊ ጭቆና እና ባርነት የምንወጣበት በአጠቃላይም ስለ ኢትዮጵያ የምናስብበት መሆን ይገባዋል!

መልካም በዓል!

‹‹ኢህአዴግ የኢትዮጵያ የመጨረሻው አምባገነን ስርዓት ነው፡፡ ዓለምም ሆነ ኢትዮጵያ እንደ ኢህአዴግ ያለ አምባገነንን ለመሸከም የሚያስችል ትክሻ የላቸውም፡፡ አምባገነንነትን ቤተ መጽሃፍት እንጂ በተግባር የማናይባቸው ጊዜያት እሩቅ አይደሉም፡፡ ይህ ይሆን ዘንድ መታሰሬ ደግሞ የሚከብድ መስዕዋትነት አይደለም፡፡……ፋናውን ለማየት እጓጓለሁ፡፡ ይህ ረዥም ጊዜ

ሊቆይም ላይቆይም ይችላል፡፡ ምንም ይሁን ግን በአቋሜ እጸናለሁ፡፡››

እስክንድር ነጋ ( ጋዜጠኛና የፖለቲካ ተንታኝ)

ነገረ- ኢትዮጵያሚያዝያ 10 ቀን 2006 ዓ.ም. ቅፅ 1 ቁጥር 9

ለምን ፈራን?

አቤት አንተ ህዝብ ትዕግስትህ!

3

ልብ አድርጉ

በላይ ማናዬ

ወደ ገፅ 6 ዞሯል ...

ዮናታን ተስፋዬ

ወደ ገፅ 6 ዞሯል ...

አዕምሮው በስራ የደከመ፣ አካሉ የዛለ ሁሉ ከዋለበት ተመልሶ ቤቱ ለማረፍ ጥድፊያ ላይ የሚገኝበት ሰዓት ነው፣ የስራ መውጫ ሰዓት፡፡ በዚህ ሰዓት አብዛኛው ሰው የሚያሳስበው የዋለበት ስራ አሊያም የነገ ውሎው እንደማይሆን መገመት ይቻላል፡፡ የሚያሳስበው እንዴት ቤቴ ባሰብኩት ጊዜ መድረስ እችላለሁ የሚለው ነው፡፡ እዚያ ቤት ውስጥ የሚናፈቁ ልጆች፣ የሚሳሳላቸው እናቶች፣ አባቶች፣ በየፊናቸው ውለው ዓይን ለዓይን ለመተያየት የቋመጡ ፍቅረኛሞች፣ በማታው ክፍለ ጊዜ ትምህርታቸውን የሚከታተሉ ሰዎች...ሁሉም ሰዓታቸውን ጠብቀው ለመገናኘት ይቸኩላሉ፡፡ ከስራ ወጥቼ ወደ ቤቴ ለማምራት መጀመሪያ ከካዛንችስ-ስድስት ኪሎ የሚያደርሰኝን ታክሲ መጠቀም ነበረብኝ፡፡ ከዚያ ደግሞ ሌላ ታክሲ፡፡ ልክ እንደ አብዛኛዎቹ ቀናት ካዛንችስ ስደርስ የታክሲ ሰልፉ በጣም ረዝሞ ነበር፡፡ ሰልፎቹ ሁለት አቅጣጫን የተከተሉ፣ ግን ደግሞ ፊት ለፊት የተፋጠጡ ናቸው፡፡ የስድስት ኪሎው ተጓዥ ፊቱን ወደ ምዕራብ አዙሮ ሲሰለፍ፣ የፒያሳ-አራት ኪሎው ደግሞ ጀርባውን ሰጥቶ ፊቱን ወደ ምዕራብ አድርጎ ተሰልፏል፡፡ ከምስራቅ አቅጣጫ መጥቼ የስድስት ኪሎውን ሰልፍ ጫፍ አግኝቼ መሰለፍ ነበረብኝ፡፡ እናም የተሰላፊዎች ፊት እየገረፈኝ መጨረሻው እየናፈቀኝ ጉዞየን ወደ ሰልፉ ጫፍ አደረኩ፡፡ በሚገርም ሁኔታ እጅጉን ረጅም ሰልፍ ሆኖ ነበር ያገኘሁት፡፡ሰልፉን ይዤ ታክሲው ጋር ለመድረስ ያለማጋነን (ሰዓት ይዤ ነበር) 43 ደቂቃዎችን መጠበቅ ግድ ሆኖብኛል፡፡ ታክሲ ውስጥ ግብቼ ስድስት ኪሎ እንደደረስኩ ደግሞ ሌላ ሰልፍ...(ለዚህም ሰዓት ያዝኩ፡፡) ይህን የማደርገው ዘወትር ልብ ያላልኩትን በታክሲ ሰልፍ የማጠፋውን ጊዜ ለመገመት ነበር፡፡ በዚህኛው ወደ ፈረንሳይ ለጋሲዮን በሚያደርሰኝ የታክሲ (ባጃጅ) ሰልፍ ደግሞ 32 ደቂቃዎችን በሰልፍ ላይ አባከንኩ፡፡ በድምሩ ስራ ውዬ ቤቴ ለመግባት (የጠዋት ሰልፉን ሳይጨምር) 75 ደቂቃዎች ወይም አንድ ሰዓት ከሩብ በታክሲ ሰልፍ አሳልፋለሁ ማለት ነው፡፡ ይህ የዘወትር ብክነት ነው፤ ደግሞ ምንኛ አሰልች እንደሆነ መገመት ቀላል ነው፡፡በዚህ ቁም-ነገር ብዬ በታክሲ ሰልፍ የሚባክነውን ሰዓት በመዘገብኩበት ዕለት ቤቴ እንደገባሁ ያደረኩት የመጀመሪያው ነገር አልፎ አልፎ የዕለት ውሎዬን የምመዘግብበትን ማስታወሻ ማገላበጥ

ነበር፡፡ ማስታወሻዬን ትንሽ ገለጥ ገለጥ እያደረኩ ሳስስ አንድ በአጭሩ የተጻፈችና በትምዕርተ-ጥቅስ ውስጥ የተቀመጠች ጽሁፍ አየሁ፡፡ ትዝ አለችኝ፡፡ የአንድ ጎልማሳ አጭር ትዝብትን የያዘች ነበረች፡፡ እንዲህ ትላለች፡-‹‹አቤት አንተ ህዝብ ትዕግስትህ! ይህን ሁሉ ተሰልፈህ ቤቴ እገባለሁ ብለህ...አቤት ትዕግስት!››ማስታወሻዬ ላይ ሰውየው የተማረሩበትንና የህዝቡን ትዕግስት የታዘቡበትን ምክንያትም ጨምሬ አስፍሬ ነበር፡፡ በማስታወሻ ደብተሬ የሰፈረውን ሳይ ጎልማሳው ስለእኔ የዛሬ ትዕግስት የተናገሩ ይመስለኛል፡፡ 75 ደቂቃዎችን በታክሲ ሰልፍ ላይ ማባከን! ይህን ሁሉ ጊዜ ዘወትር በትዕግስት መጠበቅ...አቤት ትዕግስት! (በዚህ ጊዜ

እያንዳንዱ ዜጋ በዚህ መልኩ የሚባክንበት ጊዜ ቢሰላና ተደምሮ እንደ ሐገር የምናባክነው ምን ያህል ሊሆን እንደሚችል ቢታወቅ ስል አሰብኩ፡፡ ለነገሩ ጊዜ ወርቅ ነው ብሎ ነገር እኛ ጋ የለም፡፡)የህዝቡን ትዕግስት አደነቅሁ፡፡ እውነትም የዚህ ህዝብ ትዕግስት ግሩም ነው፡፡ ወደ ስራ ለመግባት ሰልፍ...ቤቱ ለመመለስ ሰልፍ! በየሄደበት ሰልፍ! ታዲያ ይህ የህዝብ ትዕግስት ያልተደነቀ ምን ሊደነቅ ይችላል? ግን ግን ለዓመታት እየባሰ እንጂ መሻሻል የማይታይበትን የትራንስፖርት ችግር በውስጡ ይዞ ከማጉረምረም ባለፈ እዚህ ግባ የማይባል እንቅስቃሴ የማያደርገው ህዝብ ያስቻለውን መቻል ማድነቅ ነው ወይስ መኮነን የሚገባው? ለመሆኑ መቼ ይሆን ይህን ትዕግስቱን የሚረዳለት አስተዳደር የሚኖረው? መቼስ ነው ከዚህ የውስጥ መደመሙና ከሚታየው የፊቱ መጨፍገግ የሚወጣው?በሚከፍለው ግብር ከመንግስት ማግኘት ያለበትን የአገልግሎት አቅርቦት እንደ መብት ባለመቁጠር መሰለፍን ግዴታው ያደረገው ይህ ህዝብ ዝምታው እንደምን ያለ ቢሆን ነው? (ዝምታ ወርቅ ነው ማለት እንዲህ ይሆን እንዴ?) ይህ ህዝብ ጥሮ ግሮ ባገኛት ገንዘብ ዳቦ ለመግዛት እንኳ ሰልፍ ይጠብቀዋል፡፡ በማደያዎች ነዳጅ ለማስቀዳት ሰልፍ አለበት፡፡ (አሁን አሁን ደግሞ ጋዝ በጀሪካን አንቀዳም ብለዋል፡፡) ከቀበሌ ስኳርና ዘይት እንዲሁም ስንዴ ለመግዛት ሰልፍ ይጠብቀዋል፡፡ በከፈለው ግብር ጠብ የሚል ነገር በማያገኝበት ሁኔታ ቃሉን ጠብቆ ግብር ለመክፈል ወደ ገቢ መስሪያ በሄቶች ሲያመራ

ይሰለፋል፡፡ ከቶ ይህ ህዝብ ሳይሰለፍ አገልግሎት የሚያገኘው የትና መቼ ይሆን?ጎልማሳው ‹አቤት አንተ ህዝብ ትዕግስትህ!› ያሉት ወደው አይደለም፡፡ በስልክ የጀመረውን ጉዳይ ከእልባት ሳያደርስ ጉሮሮው አንዳች ጠጣር ነገር እንደተሰነቀረበት ሁሉ ድንገት ድምጹ ቁርጥ ቁርጥ ብሎ ከወዲያኛው ከሚያናግረው ሰው ጋር የያዘው ወግ ሲቋረጥ ከዝምታ ውጭ ትንፍሽ ሲል አይታይም፡፡ እንዲያውም የለመደው ሁሉ ነው የሚመስለው፡፡ በዚህ የስልክ መቆራረጥ የሚመጣበትን ኪሳራ የሚያስበው አይመስልም፡፡ የኢንተርኔት ካፌዎች በኔትወርክ አለመኖር የሚቀርባቸውን ገቢ ልብ ያሉት አይመስሉም፡፡ ግብር ሳያጓድሉ እየከፈሉ፣ ለቴሌ ያለባቸውን ግዴታ እየተወጡ በዚያኛው ወገን መደረግ ያለበትን ግዴታና እነሱ መብታቸውን መጠየቅ እንዳለባቸው የዘነጉት ይመስላሉ፡፡ ነው ወይስ እንደተባለው ትዕግስት ያረበበበት ህዝብ ስለሆነ መብቱንም ከመጠየቅ ይታገሳል?ህዝብ ገራም ነው፡፡ ጠዋት ከቤቱ ሲወጣ አማን የነበረው የሰፈሩ መንገድ ማታ ወደ ቤቱ ሲመለስ ድራሹ ጠፍቶ ሲፈራርስ ይታገሳል፡፡ በአዲስ መልክ ሊሰራልን ነው እያለ ይጠብቃል፡፡ ከነገ ነገ ተሰርቶ እንደፈለግን በነጻነት እንወጣለን እንገባለን ብሎ በጉጉት ይጠብቃል፡፡ ልጆቹ ያለአንዳች መንገላታት ውሃ በመሰለው መንገድ ወደ ት/ቤት ሲሄዱለት፣ ውለው ሲመለሱለት ለማየት በማሰብ ይታገሳል፡፡ የፈረሰው መንገድ ግን እንደታሰበው ቶሎ አልተሰራም፡፡ በብዙ አካባቢዎች በርካታ የመንገድ ስራዎች ስላሉባቸው ነው ይህኛው የዘገየው እያለ አሁንም ይታገሳል፡፡ መንገዱ ግን እንደፈረሰ ነው፡፡ ማታ ሁለት ሰዓት ላይ ቴሌቪዥን ይከፈታል፡፡ የሰፈሩ መንገድ በአዲስ መልክ እየተገነባ መሆኑን በዜና ይከታተላል፡፡ ይህን ያህል ፐርሰንቱ ተጠናቅቋል ይባላል በዜናው፡፡ መሬቱ ግን አሁንም እንደተናደ ነው፡፡ ህዝቡ አሁንም በትዕግስት ይጠብቃል! ቀናት ቀናትን ቢወልዱም መንገዱ ግን እንደፈረሰ ነው፡፡ ላይሰሩ ለምን አፈረሱት ብሎ

ህዝብ ገራም ነው፡፡ ጠዋት ከቤቱ ሲወጣ አማን የነበረው የሰፈሩ መንገድ ማታ ወደ ቤቱ ሲመለስ ድራሹ ጠፍቶ ሲፈራርስ ይታገሳል፡፡ በአዲስ መልክ ሊሰራልን ነው እያለ ይጠብቃል፡፡ ከነገ ነገ ተሰርቶ እንደፈለግን በነጻነት እንወጣለን እንገባለን ብሎ በጉጉት ይጠብቃል፡፡

ባለፈው ክፍል ላይ እንዳወጋኋችሁ ከመነን የመጣነው ተማሪዎች ከምኒልክ ት/ቤት ታሳሪዎች ጋር ለመተዋወቅ በቅተናል፡፡ ቀጥሎ ደግሞ ወደ ጋራዡ ልመለስና የሆነውን ላውጋችሁ፡፡ከመኪና ወርደን ቀይ አሽዋ ነው (ጠጠር ነገር ላይ) ተንበረከክን፡፡ ከዛ ወደ ስድስት የሚጠጉ ፌደራሎች ከበቡን፡፡ አንዳቸውም አማርኛ በቅጡ አያወሩም፡፡ ሁለቱ የቁም መጥረጊያ እንጨት ይዘው መጡ፡፡ በለው የልቤ ምት! አታሞ ያስንቃል፡፡ “አንዱ አንቴ ነህ ቤሁኬት መንጊስት ምቲገለቢጠው፡፡” ብሎ በግራዬ የነበረውን ጓደኛዬን አሳረፈበት፤ በዛው እሱ ላይ ተረባረቡበት፡፡ ሌላኛው ጓደኛዬ እና እኔ የምንገባበት እስኪጠፋን ተደናግጠን ተራችንን መጠበቅ እጣችን ሆነ፡፡ ብሬን ደብድበው መሬት ላይ ጥለውት ወደኔ መጡ፡፡ አንዱ እጄን ጎተተና ወገቤን ሲለኝ ከተንበረከኩበት ወደቅኩ፡፡ እዛዉ

(በትዝታ ትንሽ ወደኋላ) (2)ሌላኛው በእግሩ ጠለዘኝና “ሸርሙጣ እናትክን! በናንተ ረብሻ ሀገር ሰላም ነሳችኋት!” ደገመኝ፡፡ በቃ ከዛ በኋላ ዱላዎቹ እየተደጋገሙ ያርፉ ጀመር፡፡ በጉርምስና ልሳን ማቃሰት ያዝኩኝ፡፡ እኔን ሲጠግቡ ሰናይን ያዙትና አሳሩን አበሉት፤ እሱ ላይ አንዱ ዱላ ተሰበረ፡፡ ከዛ በኋላ መታወቂያችንን ጠየቁን፤ ብሬም እኔም የተማሪ ሰጠን፡፡ ሰናይ አልነበረውም፡፡ በቃ ሌላ ዙር ጀመሩት፡፡ ተሰብሮ የወደቀዉን ዱላ አንስተው እጁን ለሁለት ወጥረው እጅ እጁን በተሰበጣጠሩት የዱላው ጫፎች ገረፉት፡፡ እጁ በጣም ተነፋፍቶ ነበር በበነጋታው ለምን መታወቂያ የለህም... ማንልኮህ ነው... ሌላም ሌላም፡፡ ከዛ አካባቢው ላይ የነበረ የፍልጥ ክምር ላይ አስደግፈውት አንዱ ክንዱን አንገቱ ላይ አሳርፎ ጉሮሮዉን አፈነው፡፡ በጣም አስጨነቁት፡፡ ይሳደባሉ፡፡ ይራገማሉ፡፡ የማይመለከቱንን

ልንመልሳቸው የማንችላቸውን ጥያቄዎች ያከታትሉበታል፡፡ የሆነ ሰዓት ላይ አንደኛው ሳንጃ ከወገቡ ላጥ አደረገና አንገቱ ላይ ሰድሮ ‹‹ማነው የሚልካችሁ?... ማነው ወረቀት በትኑ ያላችሁ?›› ማለት ጀመረ፡፡ ብሬ በወደቀበት እግሬን ጭምቅ አደረገኝ፡፡ እኔ ራሴ ሰውነቴን ድንጋጤ ወሮታል፡፡ በዚህ መሃል አንድ አዛዣቸው ነገር መጣና አስቁሞ ወደ 2ኛ እንድንወሰድ አዘዛቸው፤ ተጭነን፤ ወጣን፡፡ ሁለተኛ ወደ ፒያሳ መንገድ ላይ ነው (አሁን ፈርሷል መሰለኝ)፡፡ እዛ ስንደርስ ወርደን መሬት ላይ አንድ ጥግ ይዘን ተቀመጥን፡፡ ወደ ማታ ላይ በየተራ አንድ ክፍል ውስጥ እየገባን ምርመራ (ማሰቃየት) ተደረገብን፡፡ ክፍሉ ውስጥ ሶስት ሲቪል የለበሱ ናቸው የሚመረምሩት፡፡ ይሳደባሉ፤ ይራገማሉ፤ ይጠይቃሉ፡፡ ማን ነው አስተባብሩ

ያላችሁ?... ማነው የሚያሰለጥናቸው?... የት ነው ወረቀት የምታባዙት?... ዶክተሩ ነው አይደል የሚመለምላችሁ?...... (እኔ በሰዓቱ የሚጠይቁኝ አንዱም አልተገለፀልኝም ነበር፡፡ ብቻ የሚፈልጉት መልስ ስለሌለኝ እንደኛው እግሬን ቆልምሞ ቁርጭምጭሚቴን በካቴና ይቆጋኝና አናቴን ደቁሶ አንድ ጥያቄ ይጠይቀኛል፡፡ መልሴ “እኔ የማቀው የለም” ነበር፤ ባውቅስ ልነግረው ኖሯል!!? አውራጣቴን ረግጦ በተደጋጋሚ ቆጋኝ፡፡ በካቴና ቁርጭምጭሚቴን ደም እስኪቋጥር ቀጠቀጠኝ፡፡ ማስፈራራቱም ለጉድ ነበር፡፡ ገና ሌሊት እናድርባችኋለን... በዘይት ነው የምንጠብሳችሁ

ነገረ- ኢትዮጵያሚያዝያ 10 ቀን 2006 ዓ.ም. ቅፅ 1 ቁጥር 9 4

ጉራማይሌ!

ምን የምትለው አለህና አርፈህ ተቀመጥ ብለዋቸው ይሆን? የርሳቸው ቀኝ እጅ ሆነው በዜጎች ላይ ኢ-ሰብአዊ ደርጊት ሲፈጽሙ የነበሩት የክልሉ የፀጥና ደህንነት ሹምም ጸሐይ ጠልቃባቸው ኮብልለው አሜሪካ ሲደርሱ ለራሴም ነጻነት አልነበረኝም በማለት ነው የቀላመዱት የህሊና ጸጸት ይሆን? እንዲህ እያልን ከእነርሱ በፊትም ሆነ በኋላ የተፈጸሙ ድርጊቶችን መጥቀስ ይቻላል፡፡በአንጻሩ ድምጻዊው አብዱ ኪያር «የዛሬን ለመኖር ማስመሰል አልችልም ለማይረባ ጸሎት እኔ አሜን አልልም» እንዳለው ተቃራኒውን ቢፈጽሙ ሊያገኙት የሚችሉትን አካላዊ ድሎት ሹመትና ሽልማት ቢያውቁም እውነት አርነት ያወጣኛል ብለው ለህሊና ጥያቄ ቅድሚያ ሰጥተው ከራስ በላይ ሀገርና ሕዝብ ብለው ክቡር መስዋትነት የከፈሉ ዜጎችን ብናስታውስ እውቁን የቀዶ ሕክምና ባለሙያ የነበሩትን ፕ/ር አስራት ወ/የስን ከመጀመሪያው ረድፍ ወስጥ እናገኛቸዋለን፡፡ ኢህአዴግ አዲስ አበባ ገብቶ ሙሉ በሙሉ

ኢትዮጵያን መቆጣጠሩን ካረጋገጠ በኋላ በአፍሪካ አዳራሽ በጠራውና የሰኔው ኮንፈረንስ እየተባለ በሚታወቀው ጉባኤ ላይ ፕ/ር ዓሥራት የከፍተኛ ትምህርት ተቋምን ወክለው ተገኙ፡፡ የኤርትራ ጥያቄ የቅኝ ግዛት ጥያቄ ነው ብለው የታገሉት ሰዎች በዛ ኮንፈረንስ ዓላማቸውን የኤርትራን መገንጠል የሚያመቻች ውሳኔ ላይ ለመድረስ ሲጣጣሩ የኮንፈረንሱ ተሳታፊ ሁሉ አንደም ደጋፊ አንድም በዝምታ ተመልካች በሆነበት ወቅት አስራት በአዲሶቹ ንጎሶች ጥርስ ውስጥ ያስገባቸውን ቃል ተናገሩ፡፡ ይህ ጉባኤ ይህን የማድረግ ሥልጣን የለውም፣ እኔን የወከለኝ ተቋምም በዚህ ላይ እንድወስን ውክልና አልሰጠኝም በማለት ተቃውሞ አሰሙ፡፡ (ሙሉ ንግግሩን ከኢንተርኔት ማዳመጥ ይቻላል፡፡) አሥራት ከዚህ በኋላ ነገሩ ሁሉ አያምርም ብለው ጎመን በጤናን መርጠው በሙያቸው ኮርተውና ተከብረው መኖርን አልመረጡም፡፡ ሀገራዊ ኩራት ሳይኖር ግለሰባዊ ኩራት እንዴት ይታሰባል፡፡ እናም የስንት ሰው ህይወት የታደጉት እወቁ የቀዶ ሕክምና ባለሙያ መአህድን መስርተው የፖለቲካውን ትግል

በመሪነት ተያያዙት፣ አርነት የሚያወጣውን የእውነት መንገድ ጀመሩት፡፡በጉባኤ አደራሽ በተናገሩት ጥርስ የተነከሰባቸው አስራት በርሳቸው መሪነት የመአህድ አንቅስቃሴ ከዳር ዳር በሀገር ውስጥም በውጪም ሲቀጣጠል ወደ ጥቃት ተሸጋገረና ተከሰሱ፣ ታሰሩ፣ ተፈረደባቸው፣ ታመሙ፣ ጥቁር አንበሳ ተኙ፣ (ሲያክሙበት የነበረው ሆስፒታል) ለከፍተኛ ህክምና ተብሎ አሜሪካ ተላኩ፡፡በመጨረሻም ሀኪሙ ሀኪም አጥተው በሽታቸው እንኳን በውል ሳይታወቅ ሞቱ፣ አጽማቸው በሀገራቸው ምድር አረፈ፡፡ ለስንቱ አስክሬን ማረፊያ የሚፈቀደው ቅድስት ስላሴ ቤተ ክርስቲያን ለርሳቸው ተከልክሎ ባለወልድ ከተቀበሩ የፊታችን ሰኔ አስራ አምስት ዓመት ይሆናቸዋል፡፡ የሀሰትን መንገድ ተጠይፈው አካላዊ ድሎትን ንቀው ለጊዜያዊው ሳይሆን ለዘላቂው፣ ለግላዊው ሳይሆን ለሕዝባዊውና ሀገራዊው ጉዳይ ቅድሚያ ሰጥተው የእውነትን መንገድ ተከትለው በከፈሉት አኩሪ መስዋዕትነት ፕ/ር ዓሥራትን ታሪክ አይረሳቸውም፣

ከገፅ 6 የዞረ .... እውነት አርነት...

መቼም በየትኛውም አገር ‹‹የመከላከያ ሚኒስትር›› ተብሎ ህዝብ የማያውቀው ባለስልጣን አለ ለማለት ይከብዳል፡፡ በእኛ አገርም ቢሆን የመከላከያ ሚኒስትር እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የተከበረ አሊያም የሚፈራ ስልጣን ሆኖ ቆይቷል፡፡ ይህ ይከበርና ይፈራ የነበር ቦታ ግን በእርስዎ ዘመን አብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ የሚያውቀው አልሆነም፡፡ እውነቴን ነው የምልዎት እኔ እራሴ በቅርቡ የአገራችን የመከላከያ ሚኒስትር ደብዛው ሲጠፋብኝ አንድ ወዳጄን ‹‹የመከላከያ ሚኒስትሩ ማን ነው?›› ብዬ ጠየኩት፡፡ አንድ የማላውቀውን ስም ነገረኝ፡፡ አላምነው ስል ቢጨንቀው ኢንተርኔት ውስጥ ገብቶ ስምዎንና ሳሞራ ስር ያለውን አንድ ፎቶ ግራፍዎን አሳየኝ፡፡ ይገርማል! ለካስ እርስዎ ነዎት የ‹‹ጀኔራሎቹ አለቃ››!ለምን እንደጠፉ ግን ገባኝ፡፡ መቼም በዚህ ዘመን ፖለቲካ በተለይም ፓርቲዎ ኢህአዴግ ውስጥ ‹‹ከየትኛው ፓርቲ ነው?›› መባሉ የተለመደ ነውና እኔም ተመሳሳይ ጥያቄ ጠየኩ፡፡ ይገርምዎታል ጥያቄውን ስጠይቅ ‹‹ከህወሓት ናቸው!›› እንደሚለኝ እርግጠኛ ነበርኩ፡፡ ግን ያልጠበኩት ነገር ሰማሁ፡፡ ደኢህዴን ናቸው ብሎኝ አረፈው፡፡ ስለ ደኢህዴን ትንሽም ብትሆን አውቃለሁ፡፡ ጥይት ሲጮህ ያልሰማ ፓርቲ ነው አሉ፡፡ እናም ይበልጡን ገረመኝ፡፡ ጥይት ሲጮህ ያልሰሙት እንዴት የጀኔራሎች አዛዥ ይሆናሉ? የሚል ሌላ ጥያቄ አነሳሁ፡፡ አልተመለሰልኝም፡፡ አሁን እርስዎን ልጠይቅዎት! የመከላከያ ሚኒስትርነት እንዴት ነው? ከጀኔራሎቹ ጋርስ እንዴት ተስማምተው እየሰሩ ነው? እውነቱን ለመናገር ጥይት ሳይሰሙ ያደጉ የእኔ ቢጤ ከሆኑ የጀኔራሎቹ ታዛዥ እንጅ አዛዥ ሊሆኑ እንደማይችሉ እኔም አጥቼው አይደለም፡፡ ለካስ ለዚህ ነው የመከላከያ ሚኒስትርነትን ስምና ዝናም ይዘውት የተደበቁት! በእርግጥ ይህ የእርስዎ ብቻ ችግር አይደለም፡፡ ያኔ ‹‹ባለ ራዕዩ›› በነበሩበት ወቅት የሚያስፈራው ጠቅላይ ሚኒስትርነትን አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ይዘውት ጠፉ አይደል? እንዲያውም አንዳንዶቹ ደኢህዴኖች ስልጣንን ይዘው የመጥፋት አመል አለባቸው እያሉ እያሟችሁ ነው፡፡ ነገሩ እናንተ ይህን አትሰሙም፡፡ እርስዎ ከእነ ሳሞራ ጋር፣ ኃይለማርያም ከእነ ስብሃት፣ በረከት፣ ደብረጽዮን፣ አዜብ ሁሉን አመል ችላችሁ እየኖራችሁ አይደል? አቤት ጽናታችሁ! አቤት ስልጣንን የማጥፋት ጥበባችሁ፡፡ እውነቴን ነው የእናንተን ያህል እስረኛ ያለ መስሎ አይሰማኝም፡፡ ያ ጓደኛዬ እርስዎን ካስተዋወቀኝ በኋላ ከእርስዎ ይልቅ የሰሜን፣ የምስራቅ፣ የኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን….. እየተባለ ምድረ ጄኔራል ሲጠራ የእርስዎ ስም ዳግም ቢጠፋብኝ አይ እኚህ ሰውየ ወደ ኤርትራ ኮብልለው ይሆናል ብዬ ነበር፡፡ ግን ደግሞ በውጭም ቢሆን ስለ እርስዎ ማንም የሚያወራ አላገኘሁም፡፡ የእርስዎ ነገር እንዲህ

እየገረመኝ በቅርቡ ግን በፓርላማ ብቅ ብለው እንደነበር ሰማሁ፡፡ አይ የጄኔራሎች አለቃማ ጦር ሜዳ ላይ ድምጹን ሲያሰማ ነበር ደስ የሚለው፡፡ ግን የመከላከያ ሚኒስትር የሚለውን ክብር ይዘው፣ የጀኔራሎች አለቃ የሚያሰኝ ማዕረግ ተሰጥቶዎት ግብጽ እንዲህ ስትደነፋብን ምንም ነገር አይሉም? አይ የእኔ ነገር ለካስ እርስዎም ፓርቲዎም የጥይት ጮኸት ከበረደ በኋላ ነው ወደ ቤተ-መንግስት የገባችሁት፡፡ እርስዎ ግን በጣም አወዛጋቢ ሰው ሆነው ቀጥለዋል፡፡ እንዲህ እልም ብለው ጠፍተው በፓርላማ ብቅ ብለው የሚናገሩት ነገርም እልቅናዎን ጥርጣሬ ውስጥ የሚያስገባ ነው፡፡ ረቡዕ ሚያዚያ 1 በወጣው ሪፖርተር ጋዜጣ ‹‹መከላከያ ሚኒስትር የወቅቱን የብሄር ተዋጽኦ ለፓርላማ ይፋ አደረገ›› የሚል ዜና ወጥቷል፡፡ እናም በዚህ ዜና ጠፍቶ የከረመው ስሞዎንና የእርስዎ ነው የሚባለው ስልጣንንም እንደገና አየሁት፡፡ በፓርላማ ተናገሩት ከተባለው ንግግር አንጻር እንኳ እርስዎ ከዚህም በላይ ቢጠፉ ‹‹እሰየው!›› የሚያሰኝ ነው፡፡ እንዲህ የሚዋሽበት ከሆነ የመከላከያ ሚኒስትርነት ከእነ አካቴውስ ባይኖር! በዚህ ዘገባ እንዳየሁት እርስዎ አሁንም ‹‹ነፍጠኛ›› ሰራዊት እየመሩ ነው፡፡ በሪፖርትዎ አማራ 29.46 በመቶውን የመከላከያ ድርሻ ይይዛል ማለትዎን ሰማን፡፡ አቤት! ሪፖርት፡፡ እስካሁን የሚገርመኝ የነበረው 11.2 ተብሎ የሚነገረው የአገራችን እድገት ነበር፡፡ አሁን ግን የእርስዎን ሪፖርት የሚያስልቅ አልተገኘም፡፡ የደቡብ ህዝቦች በ25.05 ሁለተኛውን የመከላከያ ደረጃ አስይዘውታል አሉ፡፡ እዚህ ላይ ግን አንድ ጥያቄ ልጠይቅዎት! እርስዎ እንደ ጀኔራሎቹ አይበሳጩም ብዬ ነው እንጅ ይህስ የሚጠየቅ አልነበረም፡፡ ግን አቶ ሲራጅ የደቡብ ህዝቦችን ይህን ያህል የመከላከያውን ቦታ ያዙት ከተባሉ እራስዎን በስንት ፐርሰንት አስበው ቢጨምሩላቸው ነው? አይ የእኔ ነገር ለካስ አቶ ኃይለማርያምም አሉበት!

አቶ ሬድዋንም ስለመከላከያው ሲያወሩ ሰምቻለሁ፡፡ ግን እርስዎ ያቀረቡት ሪፖርት ስለ መከላከያ ሰራዊቱ ነው የልማት ሰራዊት ስለምትሏቸው ኮብል ስቶን ላይም ስለተሰማሩት ወጣቶች ጭምር ነው? ለካስ የትምህርት ሰራዊትም አለ! ስለ የትኛው ሰራዊት ነው የሚያወሩት? ሲዳማና ወላይታ ትግርኛ መናገር ጀምረው ይሆን?ሌላም ጥያቄ ልጠይቅዎት የኦሮሞ ተወላጆች 24 ነጥብ ምናምን (እርሰዎም በውል አያውቁትም ብዬ ነው) ድርሻ አለው ያሉት የድሮውን የኦነግ ሰራዊት ጨምረውበት ነው? ምን አልባት ሌንጮ ለታ በቅርቡ ይመለሳሉ እየተባለ እየተወራ ነው፡፡ እናስ የኦነግ ሰራዊት ቀድሞ ተቀላቀላችሁ እንዴ? ነው እንደ እርስዎ የጠፋውን ባጫ ደበሌን በ23.9 በመቶውን የመከላከያ ቦታ ያዘው ተባለ?እኔ የምለው አቶ ሲራጅ መከላከያ ሰራዊት ሲባል ከጀኔራሎቹ ውጭ ያለው ሰራዊት ነው እንዴ? በእርግጥ አዎን! ቢሉኝም የእርስዎ ሪፖርት ኢትዮጵያ ውስጥ የለም፡፡ በእርግጠኝነት ግን ተሸውደዋል ማለት ነው፡፡ ፈረንጆቹ ባለፉት ወራት ውስጥ አንዷን ቀን ምን ይሏታል መሰልዎት ‹‹አፕሪል ዘ ፉል››፡፡ በቃ! በዛች ቀን ሲቀላለዱ፣ ያልሆነውን እንደሆነ አድርገው ሲያሞኙ የሚውሉበት ቀን ነው፡፡ እርግጠኛ ይሁኑ በ‹‹ሚያዙዋቸው›› ጀኔራሎች ተሸውደዋል፡፡ አማራ አንደኛ፣ ደቡብ ሁለተኛ፣ እርስዎ የመከላከያ ሚኒስትር... እያሉ ‹‹አፕሪል ዘ ፉል›› በእርስዎ ላይ አክብረውብዎታል፡፡ እንጅማ እርስዎ ‹‹የሚመሩት›› መከላከያ ሚኒስትር እኮ ነው ከኢህአዴግ በፊት በ99.6 በላይ ህወሓት ወንበር የያዘበት፡፡ እስኪ ደኢህዴን 25 በመቶውን መከላከያ ያስያዙትን ጀኔራሎች አንድ፣ ሁለት፣…ብለው ይጥሩልኝ? በቅርቡ ምን ሰማሁ መሰልዎት! እርስዎ የሚያወሩት የብሄር ስብጥር ጥያቄ ሲነሳ ደኢህዴኖች ተወርፋችኋል አሉ፡፡ ማን ነበር ማዕረጉን አውልቆ ይሸጣል የተባለው? እርስዎስ ምን ተባሉ? ከነበሩ ማለቴ ነው!

ይድረስ ለ‹‹ጄኔራሎቹ አለቃ››!

ትውልድ አይዘነጋቸውም፡፡ የእውነትን መንገድ መከተል ተስኖአቸው ባለቡት ሲረግጡ የሚኖሩት ፖለቲከኞቻችን ግን የአሥራትን ተግባር ሊያወሱ ገድላቸውን ሊዘክሩ ቀርቶ ስማቸውን ሲጠሩ እንኳን አለመስማታችን የሳዝናል ያሳፍራል፡፡ ድምጻዊው ቴዎድሮስ ካሳሁን የኋላው ከሌለ የለም የፊቱ እንዳለው ምንም እንኳን ተግባራችን ከሙት መንፈሳቸው ፊት ለመቆም የማያስችለን ቢሆን እንደምንም እየተውተረተርንም ቢሆን አስራትንም ሆነ ሌሎቹን የትናንት ጀግኖቻችንን ማስታወስ መዘከር ተገቢ ነው፡፡ የመጽኃፉ ቃል እውነት ነጻ ያወጣችኋል ሲል በአንጻሩ ሀሰት ለባርነት ይዳርጋችኋል ማለቱ ነው ብለን ከተረዳን እየታገልን ለድል ያለመብቃታችን ዴሞክራሲን እየናፈቅን ያለማግኘታችን አንድነትን እየሰበክን ተለያይተን መቆማችን ለም መሬት ይዘን መራባችን፣ በጥቅሉ አካላዊም መንፈሳዊም ነጻነት ማጣታችን ምክንያቱ አርነት ያወጣችኋል ከተባልነው እውነት መጣላታችን ይሆን?

ዴሲሳ - ከላፍቶ

ከገፅ 1 የዞረ ...ሰማያዊ ፓርቲ

ሰማያዊ ፓርቲ ግንቦት 25 ቀን 2005 ዓ.ም ያደረገውን ጨምሮ በአዲስ አበባና ሌሎች አካባቢዎች ሰላማዊ ሰልፎችንና ህዝባዊ ስብሰባዎችን ባደረገበት ወቅት የኑሮ ውድነት፣ የእምነት ጣልቃ ገብነት፣ ሉዓላዊነት፣ ዜጎችን ከቀያቸው ማፈናቀል እንዲቆምና ሌሎችም መሰረታዊ ጥያቄዎችን አንስቶ የነበረ ቢሆንም ጥያቄዎቹ ምላሽ ሊያገኙ እንዳልቻሉ የህዝብ ግንኙነቱ ገልጸዋል፡፡ ከዚህ በተቃራኒ በእስልምና እና ኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ተከታዮች ላይ የሚደረገው ጣልቃ ገብነት፣ ዜጎችን ከቀያቸው ማፈናቀሉ፣ የኑሮ ውድነት፣ ሙስና አሁንም ድረስ ተባብሰው መቀጠላቸው ሰላማዊ ሰልፉን በመጥራት ህዝቡ እነዚህን የተነጠቁ መብቶች እንዲያስመለስ ማስተባበርና ማታገል የግድ በማለቱ ነው ብለዋል፡፡ በተመሳሳይ ለገዥው ፓርቲ ስልጣን እንጂ ለህዝብ አገልግሎት የማይጨነቁት ተቋማት ስራቸውን በሚገባ ባለመስራታቸው ህዝብ ለከፈለው ክፍያ የሚገባውን አገልግሎት እያገኘ አለመሆኑም ሌላኛው ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፉ ምክንያት መሆኑን ተገልጹዋል፡፡ በተለይ የውሃ፣ የመብራት፣ የቴሌኮሚኒኬሽንና የትራንስፖርት አገልግሎቶች ህዝብን እያማረሩ መቀጠላቸው መፍትሄ ስለሚያስፈልገው የሰላማዊ ሰልፉን አስፈላጊነት እንዲሚያጎላው ኃላፊው አስታውቀዋል፡፡ ምንም እንኳ የህዝብ መብት መነጠቅና የአግልግሎቶች እጦት ሰላማዊ ሰልፉን ወቅታዊ ቢያደርገውም የሰማያዊ ፓርቲ በአመት ውስጥ ከያዛቸው ፕሮግራሞች መካከል አንዱ ህዝብ የተቀማቸውን መብቶች ማስመለስ መሆኑንና ይህም በተደጋጋሚ በተለያዩ ሚዲያዎች መገለጹን አቶ ብርሃኑ ተክለያሬድ ገልጸዋል፡፡ሰላማዊ ሰልፉ እሁድ ሚያዚያ 19 ከቀኑ 4 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት ካዛንቺስ ከሚገኘው የፓርቲው ጽህፈት ቤት እስከ ጃንሜዳ እንዲሆን የተወሰነ ሲሆን ጃንሜዳ የተመረጠበት ምክንያትም መብቱን የተነጠቀውና ማህበራዊ አገልግሎቶችን በሚገባ ማግኘት ያልቻለው ህዝብ በነቂስ ወጥቶ ጥያቄዎቹን እንዲያነሳ ሰፊ ቦታ በማስፈለጉ ነው ብለዋል፡፡ የተቃውሞ ሰልፍ በእንደራሴ ሆቴል አካባቢ ከሚገኘው የፓርቲው ጽ/ ቤት በአድዋ ድልድይ፣ በባልደራስ፣ በእንግሊዝ ኤምባሲ አድርጎ መድረሻውን ጃንሜዳ እንደሚያደርግ ተገልጻል፡፡ በአሁኑ ወቅት በየክፍለ ከተማው የሰላማዊ ሰልፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ተቋቁሞ ሰላማዊ ሰልፉን ለማድረግ ዝግጅት እያደረገ እንደሆነ የገለጹት ኃላፊው በኃይል የተቀሙትን መብቶች ለማስመለስ በሚደረገው ጥረት ተቃዋሚ ፓርቲዎች፣ ሲቪክ ማህበራት፣ ሚዲያውና እያንዳንዱ ዜጋ ተሳትፎ በማድረግ አገራዊ ግዴታውን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ነገረ- ኢትዮጵያሚያዝያ 10 ቀን 2006 ዓ.ም. ቅፅ 1 ቁጥር 9

‹‹ ‹‹

5

ፖለቲካ

ጌታቸው ሺፈራው

ወደ ገፅ 10 የዞረ ...

ወደ ገፅ 10 የዞረ ...

በፖለቲካው መስክ ስለ ሰብአዊ መብት መከበር፣ ስለ ዴሞክራሲ መስፈን፣ ስለ ህዝቦች መብት መረጋገጥ ራሳቸውን ቀዳሚ አድርገው መስዕዋትነት የከፈሉ፣ በዘመኑ ይሁዳዎች ተላልፈው የተሰጡ፣ በወቅቱ አይሁዳውያን ከሌሎች ጋር የተሰቀሉ ሰላማዊያን በርካቶች ናቸው፡፡ ከማህተመ ጋንዲ እስከ ማርቲን ሉተር ኪንግና ማንዴላ ድረስ ራሳቸውን ለሌሎች አሳልፈው ሰጥተዋል፡፡ ይሁንና እነዚህ የዴሞክራሲ ሰማዕታት በአምባገነኖች ተረግጠው፣ ተደብድበው፣ ታስረው፣ ተሰቃይተው አልቀሩም፡፡ በስተመጨረሻው ሰዓት ላይ እነዚህ ሰዎች የፖለቲካውን ፋሲካ ደርሰውበታል፡፡ አገራቸውና ህዝባቸው በነጻነት መናገር፣ በእኩልነት መኖር፣ በፍትህ መዳኘት ችለዋል፡፡ኢትዮጵያውያን ለረዥም ዓመታት ክርስትናን ሲከተሉ ከኖሩት ህዝቦች መካከል ይመደባሉ፡፡ በዚህም ምክንያት እየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጅ ሲባል የከፈለውን መስዋዕትነትና ይህን መስዋዕትነት ተከትሎ የተገኘውን ድል (ፋሲካም) ሲያከብሩ ኖረዋል፡፡ በፖለቲካው መስክም ኢትዮጵያውያን ለህዝብ ሲሉ መስዋዕት የሆኑ በርካታ ጀግኖች አሏቸው፡፡ በተለያዩ ወቅቶች የኢትዮጵያን ሉዓላዊነትና ክብር ለማስጠበቅ ስቃይን የተቀበሉ፣ መስዕዋት የሆኑ፣ የተሰቀሉ፣ የተገደሉ ጀግኖች እናት ነች ኢትዮጵያ፡፡ በዚህ መስዋዕትነት የተገኘው ድል (ፋሲካ) ኢትዮጵያን በቅኝ ግዛት ካልተገዙት በጣት ከሚቆጠሩ ጥቂት የዓለማችን አገራት መካከል አንዷ እንድትሆን አስችሏታል፡፡ ኢትዮጵያውያን ሳያዩ እንዳመኑት ሁሉ የሌሎች አገራት ህዝቦች (አፍሪካና ካሪቢያን) እንዲሁም በመላው ዓለም የሚኖሩ ጥቁሮች ኢትዮጵያንና ጀግኖቿን ሳያዩ አምነው፣ ተምሳሌትም አድርገዋቸው ለነጻነታቸው ታግለዋል፡፡ ቀድማ ለሌሎቹ ተምሳሌት የሆነችው ኢትዮጵያ አርነት ግን ለእራሷ ህዝብ ተምሳሌትነቷ አልዘለቀም፡፡ መስዕዋት ልጆቿ ለሌላው ህዝብ አርነትን ለማውጣት በስንቅነት አላገለገሉምና አሁንም

የዘመኑ ፖለቲካ መስዋዕቶች የኢትዮጵያ ፋሲካ ምን ያህል ይርቃል?

ድረስ ነጻነት፣ ፍትህና እኩልነት ተነፍጎን ፋሲካን እየተጠባበቅን እንገኛለን፡፡ ኢትዮጵያ ለሌሎች እጆቿን እንዳልዘረጋች በአሁኑ ወቅት ስቃይና መከራ በዝቶባት ወደ አምላኳ የዘረጋችው እጅ አልታጠፈም፡፡ ይህ ማለት ግን ኢትዮጵያውያን ሁሉ ዝምታን መርጠዋል ማለት አይደለም፡፡ በተለያዩ ወቅቶች እምብይተኝነትን መርጠው የጭቆናን የመጨረሻ ጽዋ የቀመሱትን ኢትዮጵያውያን ተምሳሌትነት ቀስመው አሁንም ድረስ ለህዝብ ነጻነት፣ ለአገር ክብርና ለእውነት በሰላማዊ መንገድ፣ በፍቅርና በሰላም አሸንፈው የኢትዮጵያን ፋሲካ ለማየት የሚጓጉ ሰማዕታት አልጠፉም፡፡ ቃሊት ከሚገኘው አንዱዓለም አራጌ እራሱን እስከሰዋው መምህር የኔሰው ገብሬ፣ ከጋዜጠኛ እስክንድርና ርዕዮት እስከ በቀለ ገርባ፣ ከውብሸት ታዬ እስከ ክንፈ ሚካኤል ደበበ የዘመኑን አፋኝነት ተቃውመው፣ ጨለማ ውስጥ የተጣለችውን እውነት ይዘው፣ ለዘመኑ አምባገነኖችና ይሁዳዎች ስቃይ ቤት ውስጥ መስዋዕት እየሆኑ ይገኛሉ፡፡ እነዚህ የፖለቲካው መስዋዕቶች እስር ቤትም ውስጥ ሆነው ለአገራችን ህዝብ መብትና ለዴሞክራሲ ዋጋ መክፈላቸው ትክክል መሆኑን እየተናገሩ ቀጥለዋል፡፡በውጭ የነበረውን የተደላደለ ህይወት ትቶ በአገሩ ዴሞክራሲ ግንባታ የሚችለውን ጠጠር ለመጣል ኢህአዴግ ስልጣን በያዘበት ማግስት ወደ አገሩ የገባው እስክንድር ነጋ ባለፉት 23 አመታት ስለ እውነት፣ ስለ አገሩ ህዝብ ነጻነትና ዴሞክራሲ ከፍተኛ መስዋዕትነት ከፍሏል፡፡ በዚህ 9 ጊዜ በታሰረባት

አገሩ እሱ ያለተስፋ መቁረጥ ስለ ፍቅር፣ ለውጥ፣ እየሰበከ መስዕዋት መሆኑን ቀጥሏል፡፡ የፖለቲካ ተንታኙ፣ጋዜጠኛውና የህሊና እስረኛ እስክንድር ነጋ እንዲጎበኝ በተፈቀደለት በአንድ ወቅት ‹‹እኔ እና ኢህአዴግን የሚያስማማን ነገር አለ፡፡ እኔ መታሰር እችላለሁ፡፡ ኢህአዴግ ደግሞ የማሰር ህገ-ወጥ አቅም አለው፡፡ ይህ እኔንና ኢህአዴግን ያስማማናል፡፡ ይህ ጉዳይ ኢትዮጵያውያን እስኪነሱ ድረስ ሊቀጥል ይችላል፡፡›› ሲል ለእኔና ለጓደኞቼ አልበገሬነቱን አጫውቶናል፡፡ እስክንድር ይቀጥላል! ‹‹አስራ ስምንት አመት ተፈርዶብኛል፡፡ አሁን ሁለት አመት ታስሬያለሁ፡፡ አስራ ስድስት አመት ይቀረኛል ማለት ነው፡፡ ለኢትዮጵያ ዴሞክራሲ አስተዋጽኦ ከሚደረገው ትግል አንጻር ይህ ትንሽ መስዋዕትነት ነው፡፡››እስክንድር ‹‹I shall persevere!›› (እጸናለሁ) በሚል ከቃሊቱ በጻፈው ድንቅ ደብዳቤም ‹‹ግለሰቦች ይቀጣሉ፣ ይሰቃያሉ፣ ይገደላሉም፡፡ ዴሞክራሲ ግን የማይቀለበስ የሰው ዘር መዳረሻ ስርዓት ነው፡፡ ልዘገይ እችላለሁ፡፡ ግን አልሸነፍም፡፡ እኔ እስር ቤትም ቢሆን ሰላማዊ እንቅልፍ እተኛለሁ፡፡ አሳሪዎቼ በሞቀ አልጋና ከሚስቶቻቸው ጋር ቤታቸው ውስጥ ተኝተው የእኔን ሰላም አያገኙትም፡፡›› ሲል እስከ መጨረሻው (የዴሞክራሲ ፋሲካ) ለትግሉ ያለውን ቀናይነት በውል አሳይቷል፡፡ወጣቱ ፖለቲከኛ አንዱዓለም አራጌ በቅርቡ ከእስር ቤት በጻፈው መጽሃፍ እንደሚገልጸው እስራት ብቻ ሳይሆን ሊገሉትም እንደሚችሉ እያወቀ

ነው መስዋዕት የሆነው፡፡ ይህን እስር ቤት ውስጥ ሆኖም ቢሆን ቀጥሏል፡፡ ‹‹እኔና እኔን መሰል ሰዎች ያልሆነውን ሆናችሁ ተብለን የምንገፋው የመከራ ህይወት በኢትዮጵያችን የነጻነት ቀን እንዲጠባ የሚረዳን ከሆነ የሚከፈለው መስዕዋትነት ቢያንስ እንጂ ፈጽሞ አይበዛም፡፡ በትውልድና በታሪክ ፊት ለከበረ ነጻነት ሲባል ዋጋ መክፈል ተመርቆ መፈጠር እንጂ ከቶም አለመታደል አይሆንም፡፡…. ለልጆቼም፣ ለራሴም ሳይማር ላስተማረኝ ወገኔም ለዴሞክራሲና ነጻነት ከመታገል የከበረ ምንም ነገር አለመኖሩን ሁል ጊዜም እገነዘባለሁ፡፡ ለዚህ ክቡር የተፈጥሮ መብት ስል ወደ ቃሊቲ ወህኒ ቤት መውረድ ከከፋም መሞት ከፊቴ የሚጠብቀኝ ፅዋ ላፍታ እንኳን ስቼው አላውቅም፡፡›› በሚል የመስዋትነቱን ቃል በልበ ሙሉነት ያብራራል፡፡ ጋዜጠኞቹን እየበላ የሚገኘው የጸረ ሽብር አዋጁ ሰለባ የሆነው ውብሸት ታዬ ሌላኛው የወቅቱ ይሁዳዊ ፖለቲካ መስዋዕት ነው፡፡ በእስር ላይ ሆኖም ቢሆን የኢትዮጵያን ህዝብ ብቻ ሳይሆን አሳሪዎቹን ጭምር በፍቅር ለማሸነፍ ጥረት እንደሚያደርግ አስመስክሯል፡፡ ቤተሰብ በቅርበት እንዳያገኘው ተደርጎ ታስሮ፣ በህመሙ ጊዜ ሀኪም ቤት የማይቀርበው ውብሸት ‹‹በግሌ የእስር ቆይታዬ በነፍሴ ውስጥ እንደ ውቅያኖስ የጠለቀ ፍቅር እና የእናንተን አጋርነት በማይነጥፍ አሳቢነት አገኘሁበት እንጂ ጥላቻን አልተማርኩበትም፡፡›› ሲለን የምንረዳው መስዕዋት ስቃይ የበዛበትን እስር ቤት አለመሰልቸቱንና ለአላማው ያለውን ቁርጠኝነት ነው፡፡ ያለ አግባብ የታሰሩ ኦሮምኛ ተናጋሪዎችን ጉዳይ እየተከታተለ ለዓለም ዓቀፍ የመብት ተሟጋቾች እና ለሚመለከታቸው ሁሉ ያሳውቅ የነበረው

1) ከ1983 ዓ.ም በፊትና ከዛ በኋላ ያሉት የጂኦፖለቲካዊ (geopolitical)፣ ታሪካዊ እና የማህበረሰቡ የኢኮኖሚ ሁኔታ በተለይ በኢትዮጵያ ምን ይመስላል? ለወደፊቱ የአሜሪካ ጥቅም ምን ጠቀሜታ አለው? 2) በኢትዮጵያ የመልካም አስተዳደር እጦትና የህግ የበላይነት ጥሰት በየጊዜው መከሰት በኢትዮጵያና በአካባቢው አገሮች ላይ የሚያመጣው ጦስ ምን ሊሆን ይችላል?3) በአጭር ጊዜ እቅድ ላይ (Short sighted policy) እና የጎሣ ፌዴራሊዝም በሚከተለው የኢትዮጵያው አገዛዝ መካከል ያለው ጥብቅ ግንኙነት ወደ ፊት ምን መዘዝ ያስከትል ይሆን?ሶስቱንም ነጥቦች በዝርዝር ለመግለፅ ልሞክር፡- ሁላችንም እንደምናውቀው ኢትዮጵያ መገኛ (Location):- የቆዳ ሥፋት፣ እምቅ የተፈጥሮ ሀብት ባለቤት እና ታሪካዊት ሀገር በመሆኗ የተነሣ በሰሜን የምሥራቅ አፍሪካ አካባቢ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ አላት ማለት ይቻላል፡

የኢትዮጵያ ሥትራቴጂካዊ ጠቀሜታና የኢትዮ-አሜሪካ ግንኙነት ሲዳሰስ

ደረጀ መላኩ([email protected])

በቅድሚያ የነፃ ሀሳብ ገበያ በመሆን ላይ ለምትገኘው ‹ነገረ ኢትዮጵያ› ጋዜጣ እና ለአዘጋጆቿ ልባዊ ምስጋናዬን ማቅረብ እፈልጋለሁ፡፡ ከላይ በተጠቀሰው ርዕስ ላይ (ኢትዮጵያ በአፍሪካ ውስጥ ያላትን ሥትራቴጂካዊ ጠቀሜታን ከማብራራቴ በፊት የሚከተሉትን ሶስት ነጥቦች ለአንባቢው ማስታወስ

ጠቃሚ ሳይሆን አይቀርም፡፡

፡ በሌላ በኩል የአፍሪካው ቀንድ (ሰሜን ምስራቅ አፍሪካ) የመካከለኛው ምስራቅ ወይም የአፍሪካው ክፍል አንድ አካል በመሆኑ እዚያ የሚነደው እሳት ኢትዮጵያን በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ እንደሚለበልባት ከታሪክ የተማርን ይመስለኛል፡፡ ኢትዮጵያ የአካባቢው የውሃ ማማ (The wa-ter tower of Africa) ተብላ የምትጠራ ሲሆን ሰማንያ ስድስት ፐርሰንቱ የናይል ወንዝ የውሃ መጠን ከኢትዮጵያ ከሚፈሡ ጅረቶች የተገኘ ነው፡፡ እንዲሁም የኢጋድ አባል ሀገራት ተብለው ከሚታወቁት ጂቡቲ፣ ኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ሶማሊያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሱዳን፣ ኡጋንዳ፣ የቀድሞዋ የኢትዮጵያ አካል ኤርትራ ከሚኖሩት ህዝቦች ውስጥ ግማሾቹ ኢትዮጵያውያን ናቸው፡፡ እ.ኤ.አ 1970 በፊት (ቀዝቃዛው ጦርነት በጋመበት ዘመን) ባሉት ሥትራቴጂካዊ ጠቀሜታ የምዕራባውያን የሥለላ መረብ ይርመሠመስበት ነበር፡፡ ነበር ልበል ያ ግርማ ሞገሳችን (ሥልታዊ የባህር በራችን) በሴረኞች ደባ ለጊዜው ከእጃችን ስለወጣ፡፡ ማን

ያውቃል ከሠላማዊ ትግል አኳያ በርትተን ከሠራን ወደ ቀድሞው ክብራችን እንመለሥ ይሆናል፡፡ ዛሬስ ኢትዮጵያ ስትራቴጂካዊ ወይም

ስልታዊ ጠቀሜታ አላትን?በዛሬው ዘመን የእስራኤል እና ፍልስጤም ግጭት፣ ሶማሊያ የጨነገፈች ሀገር መሆኗ፣ አሁን ደግሞ ደቡብ ሱዳን እየተከተለቻት ነው መባሉ መቋጫ ያልተበጀለት የኢትዮጵያና ኤርትራ ግጭት፣ በቀንዱ አካባቢ የእስልምና አክራሪ ቡድኖ ስጋት፣ በታላቁ የአባይ ግድብ ግንባታ ምክንያት ኢትዮጵያ እና ግብፅ ፍጥጫ ውስጥ በመግባታቸው የተነሣ ዛሬም ቢሆን ኢትዮጵያ ስትራቴጂክ ጠቀሜታ እንዳላት በርካታ የፖለቲካ ጠበብት ሲናገሩ ይሰማል፡፡ እንደውም ኢትዮጵያ በአፍሪካው ቀንድ አካባቢ የሚከሰቱ ችግሮችን ለመቅረፍ አቅም አላት ይባላል፡፡ ይሁንና ኢትዮጵያ ሥልታዊ ሀገር ለመሆን የሀገሪቱን ጥቅም የሚያስጠብቅ ብሔራዊ መንግስት (National gov-ernment) ሊኖራት ይገባል፡፡ መልካም አስተዳደር ባልሰፈነበት እና የህግ የበላይነት በሌለበት በዛሬው ሁኔታ የትም መድረስ የምንችል አይመስለኝም፡፡ ኢትዮጵያ አምባገነናዊ እና በጎሣ ፖለቲካ የተጠመቀ እንዲሁም የህግ የበላይነትን ጥያቄ ውስጥ የሚከት ሥርዓት ፍዳዋን የምታይ ሀገር በመሆኗ እንኳን ለአካባቢው ሀገራት ቀርቶ ለራሷም ሠላም ታሰፍናች

ተብሎ አይጠበቅም፡፡ ባለፉት 15 ዓመታት የዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ጥበቃ ድርጅቶች (አምነስቲ ኢንተርናሽና እና ሂማን ራይትስዎች) እንዲሁም አሜሪካ መንግሥት (US state de-partment country report) ባወጡት ሰነድ መሰረት ኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶችን እና ነፃነትን በመግፈፍ የምትታወቅ ቁጥር አንድ ሀገር ናት፡፡ ከእዚህ በተጨማሪ በአምባገነን እና ጎሰኛ ስርዓት እግር ተወርች የታሠረችው ኢትዮጵያ የድሆች ደሀ ስትሆን፣ በምጣኔ ሀብትም ሆነ በሰው ልማት (Eco-nomic & human development) በመጨረሻው ጠርዝ ላይ ትገኛለች፡፡ ጥቂት ማስረጃዎችን ማቅረብ ይቻላል፡፡ ለምሳሌ፡- 1) የነፃ ጋዜጠኞችን መብት ከመጠበቅ አኳያ ኢትዮጵያ በአፍሪካ 44ኛ፣ ከዓለም ሀገራት ደግሞ 177ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች (Freedom house 2013)2) መልካም አስተዳደር ደግሞ 47.6% ነጥብ አላት (Moibrahim, 2013%)

‹‹ሞት ያለነጻነትና ፍትህ ከመኖር የተሻለ መሆኑን ለሁሉም ማሳየት እፈልጋለሁ፡፡ ለወጣቱም መናገር የምፈልገው ምንም ነገር ባለመፍራት ከአካባቢውና በአገር ደረጃ ከሚገኙት ጨቋኞች የሚቀሙትን ነጻነትና

መብት እንዲጠይቅ ነው››

ነገረ- ኢትዮጵያሚያዝያ 10 ቀን 2006 ዓ.ም. ቅፅ 1 ቁጥር 9 6

ከገፅ 3 የዞረ ... አቤት አንተ ህዝብከገፅ 3 የዞረ ... ለምን ፈራን

የሚጠይቅ አልታየም፡፡ ትዕግስት ነው!መንግስት የህዝቡን ትዕግስት አያይም፡፡ ይልቁንስ የዘረጋው ማሞኛው እንደሰራ እያየ ይገለፍጣል እንጂ፡፡ ብዙ ቦታዎችን አፈራርሶ ስራ በመጀመር ከተማውን ሁሉ ልማት በልማት ያደረገው አድርጎ ለማሳየት ይጠቀምበታል፡፡ ለዓመት የተያዘ ፕሮጀክት በዓምስት ዓመታት እንኳ ከተጠናቀቀ እሰየው ነው፡፡ ህዝብ ግን ያን ዓምስት ዓመት በትዕግስት ይጠብቃል፡፡ ይህ ህዝብ ውሃ ቀድቶ ለመጠጣትም ይታገሳል፡፡ ውሃ ስትሄድ በቃ ሄደች ብሎ ዝም ይላል፡፡ በሳምንት አንድ ቀን ትመጣ ይሆናል ብሎ በናፍቆት ይጠብቃል፡፡ ቀን በስራ ሲደክም ውሎ በሚተኛበት ሰዓት ውሃ መጣች ቀረች እያለ ቧንቧ ውሃዋን ሲከፍት ሲዘጋ ብዙውን ጊዜውን እንቅል አጥቶ ያድራል፡፡ ውሃ የሰማይ መና ሆና በጸሎት ትወርድ ዘንድ ተማፅዕኖ ይቀርብላታል፡፡ ህዝብ ውሃ ይጠማል፡፡ እንዲህም ሆኖ ግን ቀኑን ጠብቆ የውሃ አገልግሎት ይከፍላል፡፡ ጨዋ ህዝብ... ታጋሽ ህዝብ... ስንቱን ነገር በትዕግስት ያስተናግዳል! ‹አቤት አንተ ህዝብ ትዕግስትህ!›የሚገርመው ግን የዚህን ህዝብ ትዕግስት የሚመለከት የመንግስት አካል አለመኖሩ ነው፡፡ ዘወትር በትራንስፖርት ችግር የሚንገላታውን ህዝብ ይቅርታ የሚጠይቅ፣ ለትዕግስቱ ምስጋና የሚያቀርብ ባለስልጣን አለመኖሩ ያስተዛዝባል፡፡ ምናልባት ህዝቡ ይህንም በትዕግስት እያየው ይሆናል፡፡ መብራት ተቆራርጦብሃልና ይቅርታ....የስልክ አገልግሎት ተጓድሎብሃልና ይቅርታ...ውሃ ስላስጠማንህ ይቅርታ...በዚህ ጊዜ ሁሉ ላሳየኸው ትዕግስት እናመሰግናለን የሚል የመንግስት ክፍተኛ ሹም አለመኖሩ ያሳዝናል፡፡ ህዝብ ግን ይህንም በትዕግስት ይመለከታል፡፡በእርግጥም ህዝብ ታጋሽነቱ ከሚጠበቀው በላይ

ምናምን-በዛ፡፡ እድሜዬ በቀደመው ስርዓት ተብሎ ሲወራ የሰማሁት ጭንቅላቴ ላይ ብልጭ ቢልብኝ መቼስ የቸገረው ወደ ፈጣሪው አይደል! ፀሎት ማድረስ ጀመርኩ፡፡ በኋላ ላይ የሆነ ሰው መጣ፡፡ ፖሊስ ነው-ያንዳችን ዘመድ ነበር፡፡ አናገረን፡፡ በብስጭት፤ አፅናናንና ከሌሊቱ 7 ሰዓት ላይ ወደ ማጎሪያ ቤት እንድንወሰድ አደረገ፡፡ ሞልቶ ነበር፡፡ በረንዳ ላይ አደርን፡፡ ብርዱ ይቆረጥማል፡፡ ጠዋት ከኛ ቀድመው የገቡትን 7 የምኒልክ ተማሪዎች እና ከሚሰሩበት ህንፃ ላይ ድንገት ታፍሰው የመጡ ጎጃሜዎች (ያነጋገር ዘያቸው) አገኘንና አንደኛው ክፍል ገብተን ህመማችንን የባጥ የቋጡን ስንቀበጣጥር እረሳሳነው፡፡ በሳምንቱ ሰኞ ፍርድ ቤት በ300 ይሁን በ500 ብር ዋስ ተለቀቅን፡፡ ተፈትተን ጓደኞቼ ሊጠይቁኝ ሲመጡ ታዲያ ሌላ ጉድ አወጉኝ፡፡ እኛ ታስረን ሳለ ለካ ት/ቤት (መነን) አምፀው ነበር እንድንፈታ፤ እና አሳራቸውን እንዳበሏቸው ጠባሳቸውን እያሳዩ ነገሩኝ፡፡ በዛ ያሉ ልጆችም ወደ ደዴሳና ዝዋይ እንደተወሰዱ ሰማሁ፡፡ ባንድ በኩል ቆጨኝ፡፡ በሌላ በኩል ራሴን እንደ እድለኛ ቆጠርኩት፡፡ በተፈታሁ በሳምንቱ ጥር 12 ነበር፡፡ ሚካኤል ወደ ክብረ መንበሩ ይመለሳል፡፡ እኔም ከጓዶቼ ጋር ታቦት ልናጅብ የካ ሚካኤል ነበርን፡፡ እዛ ኃይለኛ ብጥብጥ ተነሳ፡፡ በተለምዶ ወጣቶች ተሰብስበው የሚቆሙበትና ታቦታቱ እዛ ሲደርሱ ቆመዉ የሚባርኩበት ቦታ ነበር፡፡ ከወትሮው በተለየ ወያኔ ያፈነውን ድምፅ ለማሰማት እድል ተፈጠረ፡፡ የወያኔ መጠቀሚያ በነበሩት ጳጳስም ላይ ህዝበ ክርስቲያኑ ተቃውሞውን ያሰማ ነበር፡፡ ከፊት ለፊቱ ደግሞ ፖሊስ ጣቢያ ስለነበር ነገሩ መክረር ጀመረ፡፡ የባሰበት ደግሞ በቦታው የፌደራል ፖሊስ የጫኑ ኦራሎች ሲመጡ ነው፡፡ ታቦቱ በቦታው ከመድረሱ በፊት ቀውጢ ተነሳ፡፡ ድንጋይ መወርወር ተጀመረ፡፡ የሰው ብዛትና ፌደራሎቹ አልተመጣጠኑም ነበርና ፖሊስ ጣቢያው የድንጋይ ዶፍ ወረደበት፡፡ ከትንሽ ደቂቃ በኋላ ግን ከወደ መገናኛ በኩል የጥይት ድምፅ ሰማን፡፡ የማይሆን መሆን ጀመረ፡፡ በአብዛኛው ወጣት የነበረው ወደ ጥይቱ አቅጣጫ ሮጠ፡፡ የሩምታው ድምፅ ግን በማከታተል አካባቢውን አደበላለቀው፡፡ ከፊቴ እንድ ወጠምሻ ልጅ ወደ ፖሊስ ጣቢያው በጣም ቀርቦ ድንጋይ ይወረውራል፡፡ እኔም ተከተልኩት፤ ድንገት ድንጋይ ላነሳ ዞር ስል ግን ከበታው ላይ የነበርነው እኔና እሱ ብቻ መሆናችንን ተገነዘብኩ፡፡ ያ ብቻ ሳይሆን ከሩቅ እሰማው የነበረው የተኩስ እሩምታ እየቀረበ ሲመጣ ተሰማኝ፡፡ በቀኜ በኩል ወደ ሾላ ገበያ የሚያስገባ (አልጋ ተራ መሰለኝ) መንገድ ነበር... ወዲያው ወደዛ መሮጥ ጀመርኩ፡፡ ሌሎች ልጆች እናቶች ሴቶች አባቶች ከወዲያ በኩል እየተጯጯሁ ይሮጣሉ፡፡ ተቀላቀልን፡፡ በዛ ሰዓት ነበር ከኋላ እየተተኮሰብን እደሆነ ያወቅኩት፡፡ አንዲት እናት ነጭ በነጫቸውን እንዳደረጉ ግንባራቸውን ተመተው ከፊቴ ተደፉ፡፡ ሌላ ወጣት ልጅ እግሩን ተመቶ ወደቀ፡፡ ሁለት ህፃን ልጆች እና ሌላ እናት ወድቀው በላያቸው ላይ ሰው ሁላ ነፍሴ አውጭኝ ይላል፡፡ ከዛ በኋላ እኔም በደመ ነፍስ ተፈተለኩ፡፡ ጥይት ሰው ሲገድል አይደለም ሲተኮስም እንዲህ በቅርበት ሰምቼ አላውቅም፡፡ ዞሬ እንኳን ለማየት አልደፈርኩም፡፡ ምን ይደረግ? ጠብ እኔ ማውቀው ቢከፋ በድንጋይ እንጂ መሳሪያ ጭራሹኑ አይታሰብም፡፡ ብቻ ከአንዱ የሽቦ አልጋ ላይ ዘልዬ መፈናጠሬን አስታውሳለሁ፡፡ በየትኛው ይሁን ብቻ በሆነ ጠባብቅ ወደ ሴተኛ አዳሪዎች መኖሪያ ገባሁ፡፡ አንዷ ሴት እጄን ጎትታ አስገባችኝ፡፡ ቤቱ ውስጥ ሴቶቹ ተጨንቀው አንዲት አሮጊት ደግሞ እየፀለዩም እየተራገሙም ነበር፡፡ “ሚካኤል ቁጣዉን ያውርድባችሁ! ክብሩን እንዳዋረዳችሁ በአክናፋቱ ይውረድባችሁ!” አያቆሙም፡፡ ከተወሰነ ሰዓት በኋላ ተኩሱ ረገብ አለ፡፡ ጠፋ፡፡ ሴቶቹም ተረጋጉ፡፡ ከዉጪ አፈሳው ተጧጡፎ ነበር፡፡ ሁለት ልጅ እግር ሴቶች ተከታትለው ገቡና ዉጪ ስላለው ሁኔታ አስረዱን፡፡ እኔንም እንዳልወጣ አምሽቼ እንድሄድ ካልሆነ እንዳድር በየመንገዱ ፍተሻ እንዳለና ወጣቶቹን እያፈሱ እንደሆነ ነገሩኝ፡፡ አሮጊቷም መከሩኝ፡፡ ሰዓቱ ገፋና ሌላ ልጅ መጣች፡፡ ታቦቱ መግባቱን፣ መቅደስ ውስጥ ተደበቁትን ሳይቀር ብዙ ሰው ከቤተ-ክርስቲያኑም እንደታፈሰ ነገረችን፡፡አካባቢው ረጭ ብሏል፡፡ ፀጥ! የመጨረሻዋ ቀን ያቺ

ነበረች መሰለኝ ሰው ሁሉ ወደ ፍርሃት አኮፋዳው ተሸብቦ የገባበት ጠፋ፡፡ ሴቶቹ ዳቦ አስቆረሱኝ! አንድ ወንድ (ወንድ?) ብቻዬን በቤቱ የተገኘሁ እኔ ነበርኩ፡፡ ቡና አፈሉ፣ ጠላ ሰጡኝ እንጀራም በላሁ፡፡ እንዳይመሽ የለም ወሬዬን ከሴቶቹ ጋር እየጠረኩ መሸ፡፡ አሮጊቷ መረቁኝና-ሴቶቹ ሸኙኝ፡፡ እስራኤል ኤምባሲን እንዳለፍኩ ከወደ ላምበረት የሚመጡ ልጆች ወደዛ እንዳልሄድ፣ እስካሁን ፍተሻ እና አፈሳ እንዳለ ነገሩኝ፡፡ ግራዬን ይዤ በጫካ ውስጥ ሸከሸኩት፡፡ ለወትሮው ደፍሬ የማልሄድበትን የኮተቤ መኃኒዓለም መቃብር ስፍራ አቋርጬ ሰፈሬ ገባሁ፡፡ እቤት ስደርስ መንደርተኛው ተሰብስቦ አገር ያዙልን ይላል፡፡ ወያኔ ላይ የእርግማን መአት ያወርዳሉ፡፡ ሲያዩኝ ወያኔን ትተው እኔን በስድብ ወረዱብኝ፡፡ ዝም ብዬ ገባሁ፡፡ ከጀርባዬ ብዙ የሚያማርሩ ድምፆች በጋራ ወያኔንም፣ ተስፋ የጣሉበትን ቅንጅትንም ሲያማርሩ ይሰማኛል፡፡ ውስጤም አብሮ ዝም አለ፡፡ ለረጅም ጊዜ ይሄ ዝምታ አብሮኝ ዘለቀ፡፡ ዝም እንዳልኩ ስንቶቹ የዘመን እኩዮቼ የተቀጩበትን የቅንጅት መንፈስ ስታዘበው ዓመታት አለፉ! ዝም እንዳልኩ በጊዜው የተፈፀመውን ግፍ የመራዉን እኩዩ መለስ ዜናዊ ለፍርድ ሳይቀርብ ማረፉን ሀምሌ ላይ ሰምቼ ነሐሴ መቀበሩን ታዘብኩ፡፡ ዝም እንዳልኩ፡፡ ዝም እንዳልኩ ግን አልቀረሁም፡፡ እዚህ ያነሳሳሁትና ሌሎችም ብዙ ኮተቤ መምህራን ኮሌጅ እና መርካቶ ያየኋቸው ግፎች እንዴት ዝም ያስብሉኛል! እንዴት እረፍት ይሰጡኛል! እኔ የተረፍኩት እየተገዛሁ ለመኖር አይደለም!!! እኔ ከምመሰክረው በላይ አያሌ ከባባድ ግፎች እዚህች አገር ላይ በወያኔ ተፈፅመዋል፡፡ ይህን በፀጥታ ማለፍ ታሪካዊ ስህተት ነው፡፡ መንቃት ግድ ይላል፡፡ ከአኮፋዳው መውጣት አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው፡፡ ይሄ የኔ ዘመን ነው፡፡ እንዳንዶች ይህ ትዉልድ ፈሪ ነው ብለው ደምድመዋል፡፡ ግን ፈሪም ከሆነ ፈሪ የሆነበት ምክንያት ያለፈው ትዉልድ እንደሆነ ግን አያስቡም፡፡ የአንድ ዘመን ሰዎች እርስ በርሳቸው በግፍ ተላለቁ፡፡ የተረፉት እኛን ወለዱ፡፡ እኛንም ስለ ዘመናቸው አስከፊነት የጭካኔ ጥጎችን እንደ ተረት ተረኩልን፡፡ እንደመማሪያ ሳይሆን እንደማስፈራሪያ፡፡ እርግጥ እነሱም ‹‹ሆረሩ›› ገና ካይናቸው አልጠፋም፡፡ ለጠቀና የዛው ትዉልድ ትርፍራፊዎች በዘመናቸው ትረካ ፍርሃት ቋጠሮ የተተበተበብንን የዚህ ዘመን ባለተራዎች ዳግም ሰብረነው ከወጣንበት ፍርሃት ዉስጥ መልሰው ዶሉን፡፡ አሁንም እንደፈራን ነን፡፡ ግን ተስፋ አለን፡፡ በጨለማ ውስጥ ሁሌ ብርሃን አለ፡፡ ሀገራችን ወደ ቀደመ ክብሯ እስካልተመለሰች፣ ፍተሃዊነት እኩልነት ነፃነት እስኪሰፍንባት ትግል የቱንም ያህል እንዲኮላሽ ቢደረግ መልሶ ማቆጥቆጡ አይቀርም፡፡ ምክንያቱም የሰው ልጅ ከተፈጥሮው ውጪ መሆን ስለማይቻለው!!! ተፈጥሮው ጭቆናን የሚቀበል ጫንቃ ስለሌለው፡፡ እናም እንታገላለን፡፡ የተሻለ ስርዓት ለመመስረት እንታገላለን፡፡ ህዝብ የስልጣን ባለቤት እስኪሆን እንታገላለን፡፡ ይህ የኛ ዘመን ነው፡፡ ሁሉ በፍቅር እና በፅናት ይሆናል! ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!

አውራጣቴን ረግጦ በተደጋጋሚ

ቆጋኝ፡፡ በካቴና ቁርጭምጭሚቴን ደም እስኪቋጥር

ቀጠቀጠኝ፡፡ ማስፈራራቱም ለጉድ ነበር፡፡ ገና ሌሊት

እናድርባችኋለን... በዘይት ነው

የምንጠብሳችሁ

ይመስላል፡፡ ይህ ትዕግስት ግን ዘላለማዊ አይሆንም፡፡ ለትዕግስቱ ምላሽ የሚሆንን ተጨባጭ ነገር ይፈልጋል፡፡ የታገሰለት ጉዳይ ተፈጽሞ ማየት ይሻል፡፡ ይህ ሳይሆንለት ከቀረ ግን ትዕግስቱ ያልቃል፡፡ ያኔ ደግሞ የሚከተለው ዝምታ መሰበር ይሆናል፡፡ የዝምታው መሰበርም እሩቅ አይመስልም፡፡ አዎ ይህ ህዝብ ብዙ ታግሷል፡፡ ሊነጋ ሲል ይጨልማል እንዲል መጽሐፉ አሁን የህዝቡ ትዕግስት አስፈሪ ደረጃ ላይ መድረሱ አያጠራጥርም፡፡ ትዕግስቱን ከመጤፍ ላልቆጠረው መንግስት በዚህ ወቅት ፍርሃቱ አይሏል፤ ኮሽ ባለ ቁጥር ይበረግጋል፤ ግለሰቦችን ሳይቀር በህልውናው ላይ የተነሱ አድርጎ የፈሪ ዱላ ይሰነዝርባቸዋል፡፡ ምክንያቱም ይህ ታጋሽ ህዝብ ለጨቋኞች ዝምታው ያሸብራል፡፡ በትዕግስቱ ውስጥ ያለው ድባብ ያስፈራል፡፡ አርምሞው ይገረምማል፡፡ እናም ‹አቤት አንተ ህዝብ ትዕግስትህ!› ባልንበት አንደበት ‹አቤት አንተ ህዝብ ቁጣህ!› ማለታችን አይቀርም፡፡ በዚህ ጊዜ የሚያስፈልገው ግፍን ያራዘመው አምባገነናዊ መንግስት አይደለም፡፡ በዚህ ጊዜ የሚያስፈልገው የማስተባበር ስራን የሚሰራ የተደራጀ ኃይል ነው፡፡ አማራጭ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ነጻ ማህበራትና ሌሎች ኃላፊነት የሚሰማቸው አካላት የህዝብ ዝምታ በተሰበረ ጊዜ ትዕግስተኛውን ህዝብ በትዕግስትና በጥበብ ማስተባበር ይጠይቃቸዋል፡፡ ለዚህም ዝግጁ መሆን ያስፈልጋል፡፡ የህዝብ ዝምታ መሰበሪያ ጊዜው መቅረቡን የሚያሳዩ ምልክቶችን ከማስተዋል ባለፈ ሁነቱ መቼ እንደሚከሰት በእርግጠኝነት ማወቅ የሚቻል አይመስልም፡፡ ልብ ያለው ልብ ይበል...ለውጡን ለማስተናገድ መዘጋጀት ያስፈልጋል፡፡ ኢትዮጵያ የዘመነና ዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ይገባታል!መልካም በዓል!

ግን በብዙው አዕምሮ የሰረጸ ምድራዊ ቃል ያለ ይመስላል፡፡ የምትፈልጉትን ታገኙ ከምትሹት ቦታም ትደርሱ ዘንድ ብቸኛውና አቋራጩ የሀሰት መንገድ ነው የተባለም ይመስላል፡፡ልጅ አሳድግ ብዬ በሀገር እኖር ብዬ ሚስቴን ለሹም ሰጠሁ እህቴ ናት ብዬ እንዳለው የሀገሬ ሰው ኑሮ መረግ ሆኖ አልገፋ ያላቸው፣ የእለት እንጀራ አጥጧቸው ከቆሙት በታች ከሞቱት በላይ ይሉ አይነት ህይወት የሚገፉ፣ ለእለት እንጀራ ብለው በሀሰት መንገድ ቢጓዙ፣ ውሎ ለማደር ሲሉ በእውነት ላይ አምጸው በሎሌነት ቢሰለፉ ጨክኖ የሚፈርድባቸው ላይኖር ይችላል፡፡ ኑሮው የሞላ የተረፈው የሚባለው በአለው ላይ ለመጨመር፣ በተሸከርካሪ ወንበር ላይ የሚንደላቀቀው ይበልጥ ከፍ ለማለት፣ ትንሽ ሥልጣን የጨበጠው ብዙውን ለመጠቅለል፣ ወዘተ ከእውነት ሸሽቶ ከሀሰት ሲዛመድ፣ መንፈሱን አኮስምኖ ለስጋው ሲያድር፣ ሞራሉን ገድሎ አሸርጋጅ ሲሆን የሚያፍር ህሊና መጣፋቱ እንጂ የሳፍራል፡፡ውርደትና ክብረት የሚለዩበት መስመሩ እየጠፋ መምጣቱ እንጂ ከሰው ተራም የማያስቆጥር ተግባር ነበር፡፡ እንዲህ አይነቱ ተግባር በተለይ ሕዝብን ወክለው በመድረክ በሚታዩ፣ የመንግሥት ሥልጣን በጨበጡም ሆነ ወደዛው ለመድረስ በሚታገሉ ፖለቲከኞች ሲፈጸም የሀፍረት ደረጃው ከፍ ይላል፡፡ ውርደቱ የሀገርና የህዝብ ይሆናል፡፡ ውሸት ለመናር አትሻም ምላሴ ለእውነት እሞታለሁ አልሳሳም ለነብሴ የሚለው የተዋቂው ድምጻዊ ጥላሁን ገሰሰ የዘፈን መልእክት እውነት ነጻ ያወጣል፣ እስከዛው ግን ለአደጋ ያጋልጣል፣ ቢሆንም በሀሰት መንገድ እየተጓዝኩ ረክሼ ከመኖር እውነት ተናግሬ መከራን መቀበል እመርጣለሁ የሚል ነው፡፡ የተዘፈነበት ዘመንም እንደዛሬው በሀሰት መንገድ ደረት ነፍቶ መሄድ የማይቻልበት ነበር፡፡ እውነት አርነት ያወጣችኋል የሚለውን ቃል ጠብቀው ለመጓዝ ጽናት እየጎደላቸው ወይንም ፍላጎት እያጡ አልያም በሀሰት መንገድ ተጉዞ የሚገኘው ጥቅም እያማለላቸው በእውነት ላይ ሸፍተው ከራሳቸውም ከፈጣሪያቸውም ተጣልተው ሰላም አጥተው የሚኖሩት የበዙ ቢሆንም ለእውነት ቆመው ለህሊናቸው አድረው ለመስዋዕትነት የተዳረጉና በዚህ ተግባራቸውም ጊዜያዌ ሥልጣንና የድሎት ኑሮ ሳይሆን ዘለዐለማዊ ክብርን የተቀዳጁ

ወገኖች በየዘመናቱ አልፈዋል፡፡በእውነት ላይ ያመጹት ወገኖች የእነዚህ ጀግኖች ገደል ሊዘክሩ ቀርቶ ስማቸውን ሊጠሩ አንኳን ድፍረቱ አይኖራቸውም፡፡ ለዚህ ደግሞ ምክንያታቸው በቂ ነው፣ የእነርሱን ተግባር ማወደስ ራስን ማኮሰስ ይሆንባቸዋል፣ የእነርሱን ስም መጥራት አድማጭ ተመልካቹ እነርሱን ሰማቸው ከተጠራው ጋር በህሊና ሚዛን እያወዳደረ አሳንሶ እንዲያያቸው ሲብሰም ንቆ እንዲጠየፋቸው ማድረግ ነው፡፡ በአለፉት የመንፈስ ጀግኖች የሙት መንፈስ ፊት በድፍረት ለመቆም የሚያስችል ወኔ አለመኖርም ሌላው ምክንያት ነው፡፡እናም በእውነት ላይ አምጾ በሀሰት መንገድ መንጎዱ ጉዳቱ የከፋ ነው፡፡ ሌላ ሌላው ጊዜው ሲደርስ ቀስ እያለ የሚመጣ በመሆኑ ላይሰማ ይችላል፡፡ ድምጻዊው አብዱ ኪያር፡- «ማለፍ አንኳን ቢቻል እውነትን እረግጦ እንዴት ነው የሚኖረው ከጸጸት አምልጦ» እንዳለው ህሊናን በጥቅም ደልሎ ማስተኛት በአልኮሆል አደንዝዞ ጥያቄ እንዳያነሳ ማድረግ አይቻልም፡፡ ለዚህ ማሳያ የሚሆኑ አንድ ሁለት ምሳሌዎችን እንይ፣ ኢህአዴግ ለስልጣን ሲበቃ ለአቅመ አዳም/የደረሰ ሁሉ የሚያስታውሳቸው ይመስለኛል አቶ ሀሰን ዐሊን፡፡ የኦሮምያ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዝዳንት ነበሩ፣ ቢሮአቸው ከመስቀል አደባባይ ወደ ቦሌ በሚወስደው መንገድ ኦሎምፒያ ሳይደርሱ በዘመን ደርግ ግብርና ያሰራውና ኢህዴድ የጠቀለለው ሕንጻ ውስጥ፡፡ በወቅቱ እዛው ህንጻ ውስጥ ይሰሩ የነበሩ ሰዎች እንደተናገሩት አቶ አሊ ከቦታ ቦታ ሲንቀሳቀሱ የሚያስከትሉት አጀብ መንግስቱ ኃይለማርያም እንኳን አልነበራቸውም፡፡ እያንዳንዱ ቢሮ እየገቡ አፍንጫቸወን ይይዙና በኦሮምኛ ምንድን ነው መጥረጊያ የላችሁም ክፍሉ ነፍጠኛ ነፍጠኛ ይሸታል ይሉ ነበር፡፡ እኒህን ሰው እንደዛ ከሰዋዊ ባህርይ ያወጣቸው ይሄ ነው ያ ነው ማለት ማብራራት የሚያስፈልግ አይመስለኝም፡፡ የሀሰት መንገድ ጊዚያዊ በመሆኗ ታቀብጣለች ታባልጋለች አቅል ትነሳለች እንጂ ወደ ክብረት አታደርስምና እንደዛ ካደረጋቸው ስልጣን ተነስተው በሀገር መኖር አቅቷቸው ስደት ሲገቡ ድምጻቸው አልተሰማም፡፡ ህሊናቸው በጸጸት ነፍሳቸው በሀፍረት

ከገፅ 13 የዞረ .... እውነት አርነት...

ወደ ገፅ 4 ዞሯል ...

ነገረ- ኢትዮጵያሚያዝያ 10 ቀን 2006 ዓ.ም. ቅፅ 1 ቁጥር 97

አለማየሁ ገ/ማርያም (ፕ/ር)

ወደ ገፅ 12 ዞሯል ...

በእርግጥም በኢትዮጵያ ጦርነት ሰላም ነው (ሆኖም ግን ህዝቡ ወደ ታላቅ ቁጣ እና አመጽ እየተገፋ ቢሆንም ሁሉም ነገር ሰላም እንደሆነ አድርገው የማስመሰል ስራቸውን እያከናወኑ መሆናቸው ቀጥሏል፡፡) ድንቁርና ከፍተኛ ደስታ ነው፡፡ (ሰዎች ጥቂት ባወቁ ቁጥር የበለጠ ደስተኛ እየሆኑ የመሄድ ሁኔታ እናም እውነቱን በማጣመም እና በማኮላሸት ህዝቡን ደንቆሮ አድርጎ ማቆየት) እና ባርነት ነጻነት ነው (“አምባገነኖች የሚያልሙት ነጻነት ሚስጥራዊነት ነው” ሲሉ ቢል ሞየርስ ተናግረዋል)፡፡በነጻነት የማሰብ ነጻነት ለአምባገነኖቹ የግብአተ መሬት መግቢያ ምልክት ነው፡፡ ያልተሸበበው አዕምሮ ለድንቁርና አስፈሪ ነገር ነው፡፡ በኦርዌል ድርሰት 2+2=5 ነው፣ ምክንያቱም እያንዳንዱ/ዷ ሰው ይህን ተገድዶ/ዳ እንዲቀበል/እንድትቀበል ጫና ስለሚጣልበት/ባት ነው፡፡ በኢትዮጵያ ያለው 6.5% የኢኮኖሚ ዕድገት ከ11-15% ካለው የኢኮኖሚ ዕድገት ጋር እኩል ነው፣ማንም የሚያምንበት እስካገኙ ድረስ (ያ ማለት ከዓለም ባንክ እና ከዓለም አቀፉ የፋይናንስ ድርጅት በስተቀር)፡፡ የኦርዌል የ1984 ድርሰት የመፈክር ቀመር በኢትዮጵያ 2014 እንዲህ በሚል ታድሷል፡ ድህነት ብልጽግና ነው፣ ረኃብ ጥጋብ ነው፣ የመንግስት ዕኩይ ምግባሮች ወይም ስህተቶች ሰብአዊ መብቶች ናቸው፣ ጭቆና እና የዴሞክራሲ እጦት የዴሞክራሲ መንበሽበሽ መገለጫ ነው፣ ድንቁርና ምሁርነት ነው፣ በኢትዮጵያ ድንቁርና የብሄራዊ ድንቁርና አንድ የመሆን ፍትሀዊነት ነው፡፡ የመንግስት ዋና ዓላማ ለማጣመም፣ እውነታውን ለመለጠጥ እና በማሸት ድንቁርናን፣ አፈ ልጉምነትን እና ያለመጠየቅ ሁኔታዎች በአሉበት እንዲቆዩ ለማድረግ ነው፡፡

መንግስት ለምን ህዝብን ይሰልላል?መንግስት ለምን ህዝብን ይሰልላል?ኔልሰን ማንዴላ እንዲህ ብለው ነበር፣ “ትምህርት ዓለምን ለመለወጥ የምንጠቀምበት ጠንካራ መሳሪያ ነው“፡፡ እውቀት፣ መረጃ፣ ንቃተ ህሊና እና ምሁርነት በ21ኛው ክፍለ ዘመን በወንዶች እና በሴቶች እጅ የሚገኙ የእራሳቸውን፣ የቤተሰቦቻቸውን እና የአካባቢውን ማህበረሰብ ህይወት ለመለወጥ፣ እንዲሁም የየሀገሮቻቸውን ዕጣ ፈንታ ለመወሰን በጣም ጠቃሚ የሆኑ መሳሪያዎች ናቸው፡፡ በኢትዮጵያ ላለው ገዥ አካል ተቃራኒው በትክክል ይመጥነዋል፡፡ ድንቁርና እና ሚስጥራዊነት በስልጣን ላይ እንደ መዥገር ተጣብቆ ለመቆየት እና ለውጥ እንዳይመጣ ለመከላከያነት በጣም ጠንካራ የሆኑ መሳሪያዎች ናቸው፡፡ “የአስከፊይቷ ኢትዮጵያ ታናናሾቹ ወንድሞች” ብቸኛው ዓላማ “ሚስጥራዊነት ኃይል ነው፣ ሚስጥራዊነት ጥንካሬ ነው”፡፡ ሚስጥራዊነት ከድንቁርና ጋር ሲቀላቀል ፍጹም የሆነ ስልጣንን ይሰጣል፡፡ በአውቆ ደንቆሮዎች (ፈልገው ደንቆሮ የሆኑ) እጅ ያለ ስልጣን ብዙሀኑን ለማሰቃየት፣ ለማዳከም እና ወኔ የለሽ ለማድረግ ማረጋገጫ ይሰጣል፡፡ “ማደንቆር፣ ማደህየት፣ እና መከፋፈል ቆሻሻን እንደማስወገጃ የሚያገለግሉ የጫማ ብሩሾች” የመሳሰሉት “ለውስጣዊ የፓርቲ” (በኢትዮጵያ በመንግስት ውስጥ መንግስት) በመሆን የሚያገለግሉ አዚሞች ናቸው፡፡በተለያዩ አጋጣሚዎች ሳቀርበው እንደነበረው የመከራከሪያ ጭብጥ ገዥው አካል በአብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ ዘንድ የተጠላ እና በንቀት የሚታይ አምባገነን ፍጡር ነው፡፡ ስለሆም እንቅልፍ የለሽ ሌሊቶችን ያሳልፋል፡፡ ትንሽ የአዕምሮ ሰላም ለማግኘት ጥረት አድርገዋል፣ ሆኖም ሰላሙን ለማምጣት ባይችሉም፡፡ የአንዱን ጎሳ አባላት በሌላው ላይ ለማስነሳት በማለም ማቋረጫ የሌለው

የጥላቻ የፕሮፖጋንዳ ዘመቻዎችን ያካሂዳል፡፡ በሙስሊሙ ማህበረሰብ እና በክርስትና እምነት ተከታይ ወገኖቻችን ዘንድ ጦርነት እንዲነሳ ለማድረግ ሌት ከቀን ተንቀሳቅሷል፡፡ እናም አምላክ ምስጋና ይግባው እና ይህ ዲያብሎሳዊ እኩይ ምግባሩ ሁሉ ሙሉ በሙሉ ከሽፈውበታል! ተጽዕኖ ሊፈጥሩ የሚችሉ የማያቋርጥ ፕሮፓጋንዳ፣ የተሳሳተ መረጃ መስጠት፣ ሆን ብሎ የውሸት መረጃ መስጠት፣ ሌሎችን ሰላማዊ ሰዎች የዕኩይ ምግባሩ ደጋፊ እንዲሆኑ ማጥመቅ፣ ያለፉትን ዘመናት የበከቱ መፈክሮች እና ያፈጁ ያረጁ የማይለወጡ የመከኑ ቀኖናዎችን በማንገብ በስልጣን ላይ እንደ መዥገር ተጣብቆ ለመኖር ያለ የሌለ የሞት ሽረት ትግል ማድረግ የሚሉት ናቸው፡፡ በተጨባጭ የሚታዩ የሰብአዊ መብት ድፍጠጣዎችን በሸፍጥ በተሞላ የሀሰት አሃዛዊ መረጃ በማቅረብ የኢኮኖሚ እድገት እና ልማት አለ ለማለት በውሸት ካባ አሽሞንሙነው ያቀርባሉ፡፡ላለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ያህል አቶ መለስ እና ወሮበላ ሎሌዎቻቸው ኢትዮያውያንን/ትን በድንቁርና ዘፍቀው ሀሴት በማድረግ ለማቆየት ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል፡፡ በዜጎች ላይ የጠብመንጃ አፈሙዝ ደግነው ህዝቡ በግድ ምንም ጭራቃዊነት ድርጊት የለም የሚል ምስክርነት እንዲሰጥ፣ እኩይ ተግባራት የሉም ብሎ እንዲናገር፣ ‹‹ምንም ጭራቃዊ ተግባራት አላየሁም! አልሰማሁም›› ብሎ እንዲመሰክር ሲያስገድዱት ቆይተዋል፡፡ አቶ መለስ እና የዕኩይ ምግባር ተባባሪዎቻቸው ዓለም አቀፍ የሬዲዮ ሞገዶች እና የሳተላይት ስርጭቶች ለህዝብ እንዳይደርሱ ለማድረግ እና ለማፈን እጅግ ብዙ ገንዘብ አውጥተዋል፡፡ የወሳኝ መረጃዎች እና ሀሳቦች አማራጭ የመረጃ ምንጭ የሆኑትን የኢንተርኔት አገልግሎት አግደዋል፡

፡ ፍሪደም ሀውስ የተባለው ድርጅት እ.ኤ.አ በ2012 ባወጣው ዘገባ ኢትዮጵያ በኢንተርኔት እና በተንቀሳቃሽ ስልክ አጠቃቃም ከዓለም በመጨረሻው ደረጃ ላይ እንደምትገኝ ገልጿል፡፡ አገልግሎቱ ዝቅተኛ ሽፋን ቢኖረውም በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ በዚሁ ላይ የማያላውስ የቁጥጥር ስርዓት በመዘርጋት የኢንተርኔት ስለላ ዕኩይ ምግባርን በአገር አቀፍ ደረጃ በመተግበር እና የእራሱን ዜጎች ሰብአዊ መብት በመደፈጥጥ ከሰሃራ በታች ካሉ የአፍሪካ አገሮች ብቸኛው አምባገነን መንግስት ሆኗል፡፡ መንግስት ነጻውን ፕሬስ ይዘጋል፣ የመረጃ ዘጋቢዎችን ያስራል፣ እንዲሁም የእራሱን አስደንጋጭ የሰብአዊ መብት ድፍጠጣ ወንጀሎችን የተንሰራፋውን አስፈሪ ሙስና የሚያጋልጡትን አታሚዎችን እና ብሎግ ላይ ሀሳባቸውን የሚገልጹ ባለሙያዎችን ያስራል፡፡ መንግስት “የዕድገት እና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ” እያለ የሚጠራው ብዙ የተደሰኮረለት ዕቅድ “ኢትዮጵያን ከ13 ወራት ጸሐያማ ብርሀንነት ወደ ድንቁርና እና ወደማያቋርጥ የጨለማ የኑሮ አዘቅት ውስጥ እያሸጋገራት ይገኛል፡፡”በገዥው አካል እየተከናወኑ ያሉት ሁሉም የምርመራ እና የስለላ ፕሮግራሞች ማጠንጠኛ ዓላማ “ኢትዮጵያ የተዋረደች ግዛት” ሆና ደንቆሮ ንጉሶች፣ ንግስቶች፣ ልዑሎች እና ልዕልቶች የሚገዟት እንድትሆን በስፋት የታቀደ ሸፍጥ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ያለው የትምህርት ስርዓት በሙስና

ወደ ገፅ 12 ዞሯል ...

በዜጎች ላይ የጠብመንጃ አፈሙዝ ደግነው ህዝቡ በግድ ምንም ጭራቃዊነት ድርጊት የለም የሚል ምስክርነት እንዲሰጥ፣ እኩይ ተግባራት የሉም ብሎ እንዲናገር፣ ‹‹ምንም ጭራቃዊ ተግባራት አላየሁም! አልሰማሁም›› ብሎ እንዲመሰክር ሲያስገድዱት ቆይተዋል፡፡

መሸትሸት ሲል አልያም በአሳቻ ቦታና ጊዜ መሰረቅና መዘረፍ ምናልባት ላያስገርም ይችል ይሆናል፡፡ ሰው በተሰበሰበበት ሁሉ እያየና እየሰማ የሚፈፀም ዘረፋና ስርቆት ቢያንስ በግለሰብ እና በተደራጀ የወንጀል ቡድን ቢፈፀም ያስገርማል፡፡ በመንግስት በኩል ቢሆንስ በግለሰብ እና በተደራጀ የወንጀል ቡድን ቢፈፀም ያስገርማል፡፡ በመንግስት በኩል ቢሆንስ ዘረፋው የተፈፀመው ለዘረፋና ስርቆት ተሳታፊዎች ደግሞ ሕግና ደንብ ወጥቶላቸው መመሪያ ተዘርግቶላቸው ዘረፋና ስርቆቱን እንዲፈፅሙ በታዘዙ ተቋማት ቢሆንስ? ይህ በእርግጥም ላያስደንቅ ሊያስደንቅም ላያስገርምም ሊያስገርምም ይችል ይሆናል፡፡ ለምን ካላችሁ ይኸው ህግና ደንብ ወጥቶላቸው በሀገራችን በኢትዮጵያ እየዘረፉን ያሉ ተቋማት አሉ አይደል እንዴ? ለጊዜው በጠራራ ፀሐይ እየዘረፉን ያሉትን የመንግስት ተቋማት ለማየት እንሞክር፡፡ የግል ተቋማቱን ሌላ ጊዜ እንመለስባቸዋለን፡፡ ሀ) ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት፡- ቱቦው ተዘርግቷል፣ በቱቦው ውስጥ የሚፈስ ውሃ ግን የለም፡፡ ወይም ቢኖርም አልፎ አልፎ ነው፣ በወሩ ግን የውሃው የአገልግሎት ክፍያ ከፍ እንዳለ የሚሰጥዎት የክፍያ ደረሰኝ ያመለክታል፡፡ ውሃው በጠፋ ቁጥር በጀሪካን በተገዛውና ለተሸከምነውም ጭምር ያስከፍል ይመስል፡፡ በመዲናችን በአዲስ አበባ የውሃ ሽፋኑ 94% እንደደረሰ ይደሰኩራል፡፡ ዳሩ በ8 ቀናት ልዩነት እንኳ ውሃ የማያገኙ ሰፈሮች እንዳሉ እናውቃለን፡፡ አንድ ጀሪካን ውሃ ከ10 ብር በላይ እንደሚሸጥ መቼም ሳታዩ ወይም ሳትሰሙ የቀራችሁ አይመስለኝም፡፡ አንዳንዴማ በመዲናችን ያለው

በጠራራ ፀሐይ የሚዘርፉን ተቋማት የውሃ እጥረት ሲታይ ሲናይ በረሃ ይሁን ወይም የምስራቅ አፍሪካዋ የውሃ ማማ በሆነች ሀገር ርዕሰ ከተማ መኖርዋን ሊጠራጠሩ ይችላሉ፡፡ እንደማነፃፀሪያ ከፍተኛ የውሃ ሽፋን አላት ስለተባለችው አዲስ አበባችን አነሳሁ እንጂ በሌሎች ከተሞች ያለው እጥረት ከመዲናዋ እጅግ የባሰ እንደሆነ እሙን ነው፡፡ ሕብረተሰቡ ተባብሮ ከእለት ጉርስ ቆርሶ ከሚፈልገው ቀንሶ የውሃ ነገር የሕይወት ጉዳይ ነው በሚል መርህ ውሃ እንዲገባት እና እንዲጠቀም ይጥራል፡፡ ዳሩስ ለሕዝብ ሮሮ ቁብ የማይሰጥ ቸልተኛ ከሕብረተሰቡ ጥቅም ይልቅ ለራሱ የሚያደላ ሌባና ዘራፊ በሚኖርበት ተቋም አሰራር እንደምን የሕብረተሰቡን ምኞትና ጉጉት ያዳምጣል፡፡ ሮሮውስ እንደምን ይሰማል፡፡ ሕዝቡ በውሃ ጥም ሲሰቃይ የተቋሙ አለቆችና ጭፍሮቻቸው በውድ የአልኮል መጠጦች እየተራጩ ነውና የውሃ ጥቅሙንም ወደ መዘንጋቱ ስላዘነበሉ ለሕዝቡ ሮሮ ጆሮ ባይሰጡ ብዙም አይገርምም፡፡ አንዳንዴም የውሃ መጥፋት እጅግ ሲብስ የተቋሙ አለቆች በሚዲያ ቀርበው ሲጠየቁ መንገዶች ባስልጣንንና መብራት ኃይልን ሲከሱ ይሰማል፡፡ ለካስ እነዚህ ተቋማት ህዝቡን ብቻ ሳይሆን የማይሰሙት እርስ በርሳቸውም አይሰማሙም፡፡ አንዳንዴ የተፈጠረው ችግር ይቀረፍ ዘንድ የሚያስችሉ ጥናቶች እየተደረጉ እንደሆነ ይወራል፡፡ በቅርብ ጊዜ መቼ እንደሆነ ባናውቅም ችግሮቹን የሚፈቱ ፕሮጀክቶች እየተነደፉ እንደሆነ ይነገራል፡፡ ዳሩ ፕሮጀክቶቹ ተተግብረው የሚታዩበት ወቅት ከሰማይ የራቀ ነው፡፡ ወይም ፈፅሞ ላይተገበርም ይችላል፡፡ ታዲያ ፕሮጀክቶቹ ሲቀየሩ ወይም በሌላ ሲታጠሩ ጥቅም ላይ ይውላል፡፡ የተባለው የህዝብ

ገንዘብ የት እንደገባ አይነገርም፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትራችን የሕብረተሰቡን የውሃ ችግር ላነሳ አንድ ጋዜጠኛ፤ ‹‹በርካታው የሕብረተሰብ ክፍል የንፁህ ውሃ አገልግሎት በበቂ ሁኔታ ያገኛል፡፡ አንተ ያለኸው ይህን ያህል ፐርሰንት ከሆነው የህብረተሰብ ክፍል ስለሆንክ ነው ጥያቄውን ያነሳኸው›› ማለታቸውን ሰማሁ፡፡ ይገርማል! የውሃ ሽፋን ግን የሚለካው በተዘረጋው የውሃ ቱቦ ነው ወይስ ሕብረተሰቡ በሚያገኘው አገልግሎት፡፡ ሲጀምር 1%ም ሆነ 100% ሕብረተሰቡ ያነሳው የአገልግሎት ጥያቄ መመለስ አለበት፡፡ ባይቻል እንኳ ጠዋትና ማታ ሮሮዬ ከነገ ዛሬ ይፈታል እያለ ተስፋ ለሚያደርግ ሕዝብ ይህ ዓይነት ምላሽ ከታላቋ ኢትዮጵያ ርዕሰ መስተዳድር አይጠበቅም፡፡ ችግሩ በአፋጣኝ ይፈታ ካልሆነ ችግሩ እስኪፈታ አይዞአችሁ በትዕግስት ጠብቁ ብሎ ተስፋን መለገስም ሌላው ተግባር ነው፤ ይህም ባይሆን ዝምታ የተሻለ ይመስለኛል፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ የተዘረፈውና የተሰረቀው ሳያንሰው በሮሮው በማሳለቅ መሪና ተቋምን የሚሻ አይደለም፡፡ ለ) ቴሌኮሚንኬሽን፡- ሰው ሊከፍል የሚገባው ለተጠቀመበትና ለተገለገለበት ነገር ከሆነና ከሆነ ብቻ ነው ሕጋዊና ትክክለኛ የሚሆነው፡፡ ኢትዮ-ቴሌኮም ግን ለተቆራረጠና መልዕክት ላላስተላለፍንበት ጥሪና ጊዜው ካለፈ ወይም ከምንፈልገው ጊዜ በኋላ ለሚደርስ የፅሑፍ መልዕክትና ለተቆረጠ ወይም ላላገኘነው የድህረ ገፅ (Internet) እና ሌሎች አገልግሎቶቹ እነሆ በጠራራ ፀሐይ እየዘረፈን ነው፡፡ በግለሰቦች እንኳ የተዘረፈ ሰው ያጣውን የራሱን ንብረት እንደ ቀን በሕጋዊ መንገድ ሊያገኘው እንደሚችል ተስፋ ያደርጋል፡፡ እኛ በጠራራ ፀሐይ ሕግ በወጣለት ተቋም የተዘረፍን

ዜጎች ግን ገንዘባችን ይመለሳል የሚል ተስፋ እንኳ የለንም፡፡ የዘረፈው መጠን በብር ብዛት ወይም ማነስ አይወሰንም፡፡ 10 ሳንቲምም ተሰረቅን 10 ሚሊዮን ብር ያው ነው፡፡ ተዘርፈናል፡፡ እየተዘረፍንም ነው፡፡ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ሌብነት እስካልተያዝን ድረስ ስራ እንደሆነ የሞራልና የሃይማኖትን ዋጋውን ለሚያከብረው፤ ሌብነትን በምንም መልኩ ለሚፀየፈው የኢትዮጵያ ሕዝብ ተናግረው ነበር፡፡ ለነገሩ ይኸው ኢትዮ-ቴሌኮም እያየነው እየሰረቀን እየዘረፈን መቼ ያዝ ነው? ለኢህአዴግ እና አስተዳደሩ በጠራራ ፀሐይ የሚዘረፍ ተቋማትን ማደራጀት ወንጀል ያልሆነ ተግባር መሆኑኮ ቆየ፡፡ ዶ/ር ካሱ ኢላላ በጊዜያቸው ኢትዮ ቴሌኮም የምትታለብ ላም እንደሆነች ገልፀው ነበር፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝም ይህንኑ ቃል በጊዜያቸው እየደገሙት ይገኛሉ፡፡ እኔ የምለው ይህች ላም ለባለቤቶችዋ ወተት (የተትረፈረፈ) የምታስገኘው የሌሎችን አጥር ሰብራ ሳር እየጋጠች ነው እንዴ? ሌላው የሚገርመኝ ደግሞ የኢትዮ-ቴሌኮም የጥራት ችግር ጉዳይ ሲነሳ የአህአዴግ ባለስልጣናት የሚያነሱት የመምቻ/ የማጥላያ የፖለቲካ ቃል/ የውጪውን ዓለም ትልልቅ ተቋማት በግሉ ክፍለ ኢኮኖሚ ይያዙ የሚለውን ግፊት ነው፡፡ ልክ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስቴር ስለ ሌብራሊዝም ሲጠየቁ ስለ ኒዮ ሌበራሊዝም /Neo-liberals/ እንደሚያብራሩት መሆኑ ነው፡፡ እኔ በግሌ ኢትዮ-ቴሌኮም በግል ወይም በመንግስት እጅ መሆኑ አይደለም የሚያስጨንቀኝ፡፡ አመዛኙ

ማንደፍሮ ጥላዬ

ነገረ- ኢትዮጵያሚያዝያ 10 ቀን 2006 ዓ.ም. ቅፅ 1 ቁጥር 9 8

ዝክረ ታሪክ

ታዴዎስ ታንቱ የመ.ሣ.ቁጥር 43414

ወደ ገፅ 13 ዞሯል ...

ወደ ገፅ 15 ዞሯል ...

ጃፈር ስዩም[email protected]

ቆራጦቹ የኢትዮጵያ አርበኞች በቅርብ ርቀት እየተጠባበቁ በተበታተነ አካሔድ ወደ ዝንጆሮ ውኃ ተንቀሳቅሰዋል፡

፡ የፋሽስት ኢጣሊያ ወራሪ ኃይል ተዋጊዎች በዝንጆሮ ውኃ አጠገብ ሰፈር እንዳበጁ ታውቋል፡፡ የኢትዮጵያ አርበኞች ከመስክ የመረጃ ስምሪት ምድብ አረጋግጠዋል፡፡ የፋሽስት ኢጣሊያ ወራሪ ኃይል ተዋጊዎች የቅርብ ርቀት የአርበኞች ተግባራዊ እንቅስቃሴን በማስመልከት መረጃ ያንሳቸዋል፡፡ በእርግጥ መረጃው ደርሷቸዋል፡፡ በጥቅል መልኩ እንደ ነበር ግን ታውቋል፡፡ ጥቅል መረጃ ደግሞ ዝርዝር የአርበኞች አሰላለፍን ስለማያመለክት በወታደራዊ የመረጃ አደረጃጀት ጉድለት ይያዛል፡፡ ሰፈሩ ለምን ዝንጀሮ ውኃ እንደተባለ አናውቅም፡፡ ምናልባት በአንድ ታሪካዊ ሁነት መነሻ የፀደቀ ስያሜ ሊሆን ይችላል፡፡ አሊያም በዝንጀሮ መንጋ ሰበብ ተሰይሟል፡፡ በሸዋ ጠቅላይ ግዛ በጅሑር ውስጥ መሆናችን ይመዝገብልን! ነፃነትን አጥቶ ከመኖር በላይ ምን ሞት ሊኖር ይችላል? ሀገርን በነጻነት ለትውልድ የማቆየት ኃላፊነት በቅብብሎሽ የወረደ የወር ተረኝነት ብሔራዊ ግዳጅ መሆኑን አንጣ! የአድዋ ጦር ሜዳ ወርቃማ የጀግነት ታሪክ ደግሞ በአርበኞች ገድል ይደምቃል፡፡ ለልጆቻችን ተገዥነት ፈፅሞ አናወርስም! ከአባቶቻችንና እናቶቻችን ነፃነት ወርሰናል! ለልጆቻችን ታዲያ እንዴት ቅኝ ተገዥነትን እንተውላቸው? ክንዳችንን ሳንተራንስ ጦርነቱ ፈፅሞ አይቆምም! ይህ በታሪካችን የጥንታዊት ኢትዮጵያ የጀግኖች አርበኞች የአቋም ድምፅ ነው!በአሁኑ ሰዓት የኢትዮጵያ አርበኞች ከዝንጀሮ ውኃ አጠገብ ደርሰዋል! የፋሽት ኢጣሊያ ወራሪ ኃይል ተዋጊዎች ዘግይቶ በደረሳቸው መረጃ የኢትዮጵያ አርበኞች የት እንደ ደረሱ አውቀዋል! ጦርነቱ እንደማይቀር ታውቋል! ኢትዮጵያዊነት ከጀግንነት ተነጥሎ አይታይም! ጀግንነትም የኢትዮጵያዊ ብሔርተኝነት ነፀብራቅ ነው! ኢትዮጵያዊነት አርበኝነት ነው! አርበኝነትም ከጠባብነት፤ ከጎሰኝነት፤ ከጎጠኝነትና ከመሰል ፀረ አንድነት እሳቤዎች በጣም ይለያል! ኢትዮጵያዊ ብሔርተኝነት በግዛት አንድነት አጥብቆ ያምናል! ለአንዲት ጋት መሬት እንኳን ይሰስታል! ለእፍኝ አፈር እንኳን ይቀናል! ብሔርተኛው ዳግማዊ አፄ

እናንተም ውረዱ እስከ ፈረፈሩ፣ እኛ እንወርዳለን እስከ ፈረፈሩ፣ በኋላ ይለያል ፈሪና ደፋሩ፡፡ (ከሥነ-ቃል የተወሰደ)

ቴዎድሮስ ንጉሰ ነገስት ዘኢትዮጵያ ፈረንጆችን ጫማ አሳጥበው እንዳስወጧቸው ልብ ይሏል! ጀግኖች የኢትዮጵ አርበኞች የቀደምት ብሔርተኞችን አቋም በምሉዕ ይዘቱ ወርሰዋል! ድም! ድም! ድም! ዱዋ! ዱዋ! ዱዋ! ቆራጦቹ የኢትዮጵያ አርበኞች በሁለት አቅጣጫ በፋሽስት ኢጣሊያ ወራሪ ኃይል ተዋጊዎች ላይ ተኩስ ከፍተዋል! አሁን ጅሁር ውስጥ ዝንጀሮ ውኃ በተባለው ቦታ ከተፋፋመ ጦርነት መካከል መሆናችን ይመዝገብልን! ቆራጡ አርበኛ ቅጣው አዘነ በቀኝ መስመር ወደ ወራሪው ኃይል ተጠግቷል! በሁለት ዙር ዝናር ይስተዋላል! ያለጫማ በገምባሌ ይታያል! ጎፈሬው ራሱን አተልቆ ፊቱን አሳንሶታል! በአለባበስ ከሳርና ቅጠል ጋር መመሳሰል የግድ ሆኗል! ተኩሱ ቀልጧል! ጦርነቱ እየተጋጋለ ይሔዳል! ጀግናው ቅጣው አዘነ ለነፍሱ ቅንጣት ታህል አይሳሳም! ለሕይወቱ አይጨነቅም! ጀግና ተገዥነትን እንጂ መስዋዕነትን አይፈራም! የዝንጀሮ ውኃ መንደር በሰው ደም ርሷል! ጥቂት አርበኞች በክብር ወድቀዋል! ጣሊያኖችና ባንዶች እንደ ገብስ ታጭደዋል! ጦርነቱ ሌሊትም ቀጥሎ አድሯል! ቆራጡ አርበኛ ቅጣው አዘነ እንደ ቀትር እባብ እየተወረወረ የባንዳን ግምባር በጥይት ይበረቅሳል! ጦርነቱ ዛሬ ሁለተኛ ቀኑን ይዟል! ተኩሱ ቀልጧል! የኢትዮጵያ አርበኞች በየውጊያ መስመራቸው የፋሽስት ኢጣሊያ ወራሪ ኃይል ተዋጊዎችን ከአፈር ጋር አዋህደዋል! በከፍተኛ ደረጃ አጥቅተዋል! ጦርነቱ ሁለት ቀን ሙሉ ቀነና ሌሊት ተካሒዷል! ዕብሪተኛው ወራሪ ኃይል የጀግናን ልክ በውጊያ መስክ በተግባር ሊያይ ተገድዷል! ይህ በታሪካችን የጥንታዊት ኢትዮጵያ የጀግኖች አርበኞች የትግል ድል ድምፅ ነው! ከሸዋ ጠቅላይ ግዛት ከጅሁር ወረዳ ከዝንጀሮ ውኃ ጦር ሜዳ! ህዳር 1929 ዓ.ም!ዕብሪተኛው የፋሽስት ኢጣሊያ ወራሪ ኃይል የጀግኖችን መሬት ለቅቆ ለመውጣት ዝግጁ አልነበረም፡፡ የኢትዮጵያ አርበኖች ደግሞ ዘላቂ ድልን ሳይጎናጸፉ ትጥቃቸውን እንደ ማይፈቱት

ታውቋል! ታሪክ ሠሪው አርበኛ ቆርጧል! ለዕብሪተኛ ተገቢው ዋጋ ይሰጠዋል! ዕብሪተኛው የስራውን ውጤት በሀፍረት ይሰበስባል! ፍፃሜው ሊሆን የሚችለውን ለመናገር ነቢይነት አያሻም! ዕብሪት ዘወትር ውጤቱ ውድቀት ነውና! ቆራጡ አርበኛ ቅጣው አዘነ በአርበኝነት ታሪካችን አሁን በሸዋ ጠቅላይ ግዛት በሰላሌ አውራጃ ውስጥ ይገኛል! ለማይቀረው ጦርነት ተዘጋጅቷል! ትግሉ የጠየቀውን መስዋዕትነት ሁሉ ይከፍላል! ጀግናው የጀግና ዘር በሀገር ፍቅር ነድዷል! ለኢትዮጵያ ህዝብ ክብር ቆርጦ ተነስቷል! ግፈኛው የፋሽስት ኢጣሊያ ወራሪ ኃይል አሁን ከደብረ ብርሃን በሰላሌ በኩል አቋርጦ ለመሔድ ተንቀሳቅሷል፡፡ ጀግኖች የኢትዮጵያ አርበኞች እንቅስቃሴውን አውቀዋል፡፡ መረጃው ደርሷቸዋል! ወራሪው ኃይል አሁን ሰላሌ ገብቷል! የኢትዮጵያ አርበኞችን አቅም የናቀ ይመስላል! ድል የመስዋዕትነት ፍሬ ነው! ጀግናው ቅጣው አዘነ ከጥቂት አርበኞች ጋር የራሱን የውጊያ መስመር ይዟል! የፋሽስት ኢጣሊያ ወራሪ ኃይል ወደ አርበኞች ተጠግቷል! በስላሴ ውስጥ ጉረኔ ሰብር በተባለ ቦታ መሆናችን ይመዝገብልን! ይህ የታሪክ ድምፅ ነው! የፋሽስት ኢጣሊያ ወራሪ ኃይል አሁን የኢትዮጵያ አርበኞች ካደፈጡበት በቅርብ ርቀት ይስተዋላል! ሞት ያማረው ባንዳ ከፊት ይታያል! አድፋጮች የኢትዮጵያ አርበኞች ለቅድሚያ ተነሳሽነት ወስነዋል፡፡ ብዙም ሳይቆ ተኩስ ከፍተዋል! በልበ ሙሉነት ጦርነቱን ቀጥለዋል፡፡ ወራሪው ኃይል እንደገመተው የኢትዮጵያ አርበኞች አቅመ ቢስ አልነበሩም፡፡ በጥቂት ሰዓታት ጊዜ የወራሪውን ኃይል ተዋጊዎች በታተኑት፡፡ ባንዳ እንደ ቅጠል ረግፏል! የታሪክ ትቢያ ሆኗል! ቆራጡ አርበኛ ቅጣው አዘነ በግምባር ቀደም ተዋጊነቱ አድናቆትን ተችሯል! ለህይወቱ ሳይሳሳ ተዋግቷል! ባሁኑ ሰዓት ከሞት የተረፉ የፋሽስት ኢጣሊያ ወራሪ ኃይል ተዋጊዎች በየአቅጣጫቸው ሲፈረጥጡ ይስተዋላል! ድል የኢትዮጵያ አርበኞች ሆኗል!

ይህ በታሪካችን የጥንታዊት ኢትዮጵያ የጀግኖች አርበኞች የትግልና ድል ድምፅ ነው! ከሸዋ ጠቅላይ ግዛት ከስላሴ አውራጃ ከጉረኔ ሰብር ጦር ሜዳ! ታህሳስ 21 ቀን 1929 ዓ.ም!ቆራጡ የኢትዮጵያ ጀግና ቅጣው አዘነ አሁንም በስላሴ አውራጃ ውስጥ በከፍተኛ የውጊያ ዝግጁነት ሥነ-ልቦና ይታያል! የለመደው ጀግና የፋሽስት ኢጣሊያ ወራሪ ኃይል ተዋጊዎችን ደም ሳያፈስስ ውሎ ለማደር አይፈቅድም! አሁን የፋሽስት ኢጣሊያ ወራሪ ኃይል ተዋጊዎች ወደ እንሳሮ እንደወረዱ ታውቋል! የመስክ ስለላ ምድብ ለኢትዮጵያ አርበኞች ተገቢውን መረጃ በሰዓቱ መግቧል! ወራሪው ኃይል የሰላማዊ ነዋሪዎችን ቤቶች በማቃጠል ስራ ተጠምዷል! ምክንያቱ ደግሞ ግልፅ ነበር! ከሽፍቶች ጋር ግንኙነት እንዳላቸው ተነግሯቸዋል! ቤቶቻቸውን አቃጥሎ ንብረታቸውንም ዘርፏል፡፡ ቆራጦች የኢትዮጵያ አርበኞች ወራሪው ኃይል በእንሳሮ ነዋሪዎች ላይ የፈፀመውን ግፍ ሰምተዋል! ሰምተው ዝም አላሉም፡፡ የውጊያ ስልት ቀየሱ፡፡ ወራሪው ኃይል ሲመለስ ለማጥቃት ወሰኑ፡፡ ስለዚህ በሰላሴ አውራጃ ውስጥ ወዶ በተባለ መንደር አደፈጡ፡፡ የወራሪውን ኃይል ተዋጊዎች አመጣጥ ባግባቡ ተረድተዋል! በከፍተኛ የውጊያ ስነ-ልቦና በተጠንቀቅ ቆመዋል! የፋሽስት ኢጣሊያ ወራሪ ኃይል ተዋጊዎች የሚጠብቃቸውን አላወቁም፡፡ የህዝቡን ቤቶች አቃጥለውና ንብረቱን

ይህ የለውጥ መንፈስ አልተዳፈነምን?በተወሰነ መልኩ ሲታይ የተዳፈነ ይመስላል በሚለው ላይ ብዙዎች ይስማማሉ። ግን ሙሉ በሙሉ አልተዳፈነም፤ አይጠፋምም። ይህን ውድ መንፈስ በአንድ በኩል ገዢው ፓርቲ የሀገርን ሀብት ጭምር በመጠቀም እሱን ሳይደግፉ መብላት፣ ልጆችን ማሳደግ እንደማይቻል ለማሳየት የሄደበትን አስከፊ መንገድና የሰራቸውን ስራዎች የተመለከተ ሰው በርግጥ “ለመኖር” ሲል ጭቆናን ዋጥ አድርጎ መቀበሉ የማይቀር ነው። በሌላ በኩል ደግሞ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ውስጥ ከፍተኛ አመራር የነበሩ ግለሰቦች በደረሱባቸው ጭቆናና ጫና በሰላማዊ ትግል ላይ ተስፋ መቁረጣቸው እንዲሁም ሌሎቹ ሀገር ውስጥ ያሉትም ተፎካካሪ ፓርቲዎች የተወሰኑት በፖሊሲዎቻቸው እና አማራጮቻቸው ዙሪያ ህዝብን ከማማከርና ከማስተባበር እንዲሁም ከማነቃቃት ይልቅ እርስ በእርስ በመባላት፣ በመናናቅና በመሰዳደብ ላይ ማተኮራቸው መንፈሱን ለመግደል ቀላል ያልሆነ ተጽእኖ ፈጥሯል። ገዢው መንግስት ውስጣቸው ገብቶ በመከፋፈሉ እና በሚያስተዳድራቸው ሚዲያዎች ልዩነቶቻቸውን ብቻ አጋንኖ በማሳየት ጧት ማታ እርባና ቢስ እንደሆኑ፣ አላማ እና ፕሮግራም የሌላቸው መሆኑን ማስተጋባቱ ህዝቡ ለነጻነት በሚያደርገው ሰላማዊ ትግል ላይ አስተባብሮ

ትዝታ ወ-ቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ 2

የሚመራው አካል በመኖሩ ላይ ጥርጣሬ ውስጥ እንዲገባ በርካታ ስራዎች ተሰርተዋል። ለዚህም አንድ ቀላል ምሳሌ ልስጥ እና ልለፍ፦ ከጥቂት ሳምንታት በፊት አንድነት ለዴሞክራሲ እና ለፍትህ (አንድነት) ፓርቲ የአማራ ክልል ም/ፕሬዝዳንት የተናገሩትን ንግግር የሚቃወም ሰላማዊ ሰልፍ በባህርዳር ከተማ ጠርቶ ነበር። ብዙ ሰዎች ተገኝተውበት እንደነበር በማህበራዊ ሚድያ የተለቀቁት መረጃዎች ያሳያሉ። በእለቱ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ይህንን ዜና ከነጭራሹ አልዘገበም። ሆኖም ኢቴቪ ከፓርቲዎች ጋር የተያያዘ አንድ ዜና ግን አቅርቦ ነበር። “የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ የተሰኘው ፓርቲ አንድነትን ከአባል ፓርቲነት አገደው” ይላል። እንደዚህ አይነት በርካታ ምሳሌዎችን ማቅረብ ይቻላል። አየህ? እንደ ኢህአዴግ ሆነህ ስታስበው ትኩሱ ዜና የፓርቲዎች መከፋፈል እና መበታተን እንጂ የአንድነት ፓርቲ በርካታ ህዝብን ያሳተፈ የባህርዳር ሰላማዊ ሰልፍ ሊሆን አይችልም።

የለውጡን መንፈስ ለማነቃቃትይህን የለውጥ መንፈስ ድጋሚ ለማስረጽ እጅግ አዳጋች ቢመስልም ጠንክሮ ቢሰራበት ግን በአጭር ጊዜ ለነጻነት የምናደርገውን ትግል ወደፊት መውሰድ እንችላለን ብዬ አምናለሁ። ህዝቡ በተለያዩ አጋጣሚዎች ማለትም በሰላማዊ ሰልፍ፣ በህዝባዊ ምርጫዎች እና ታላቁ ሩጫን በመሰሉ ውድድሮች

ላይ መልስ ሰጥቷልና።የተጽእኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ሚና

ተፎካካሪ ፓርቲዎችን እርስ በእርስ የሚያስተሳስሩ ግለሰቦች መፈጠር እዚህ ጋር ትልቅ ሚና አለው። እነዚህ ግለሰቦች ትልቅ ፈተና ስለሚጠብቃቸው ራሳቸውን በታጋሽነት ማዘጋጀቱ ግድ ይላቸዋል።ምርጫ 97ን እንደ ምሳሌ ብንወስድ ትልቁ ተፎካካሪ ፓርቲ የነበረውን ቅንጅት ተፎካካሪ ፓርቲዎች ተባብረው ባይመሰርቱትና እንደተከፋፈሉ ሳይቀናጁ ወደ ምርጫ ቢመጡ በወቅቱ ያየነውን ስሜት፣ህብረትና ውጤት ምናልባትም የማየት እድላችን ይጠብ ነበር። በወቅቱ ቅንጅት ላይ ጉልህ ተሳትፎ የነበራቸው ሰዎች ይህን ሚና በአሁኑ ወቅት ኑሮውን በአሜሪካ

ሀገር ላደረገ አንድ ግለሰብ ይሰጣሉ። ግለሰቡ ከሌሎች ጓደኞቹ ጋር በመሆን የመሰረታት ፓርቲ እድሜዋ አጭር የነበረ ቢሆንም ትልቅ ራእይን ይዛ በመነሳቷ ትልቁ ቅንጅት እንዲፈጠር አስገራሚ ድርሻን ተወጥታለች። ፈጽሞ ሊቀራረቡ የማይችሉ አካላትን ከማቀራረብ አልፎ በአንድነት እንዲሰሩ፣ በአንድ ፓርቲ ከለላ ስር ሆነው የለውጥ መንፈስን እንዲዘምሩ ትልቅ ሚናን ተጫውቷል። ይህ ካለፈ በኋላ ሲናገሩት ለአፍ የሚቀል ቢሆንም እጅግ አዳጋችና እልህ አስጨራሽ እንደነበር በቦታው የነበሩ ያስታውሱታል፤በተለያየ አጋጣሚም ገልጸውታል። ዛሬም ተፎካካሪ ፓርቲዎችን ሰብሰብ አድርገው (ሰንገው) የሚይዙ ግለሰቦች ያስፈልጉናል። እነዚህ ግለሰቦች ፖለቲካውን በቅርብ ርቀት የተከታተሉ፣ ተሰሚነት ያላቸውና የካበተ ልምድ ቢኖራቸው ደግሞ አካሄዱን የበለጠ ያሳምረዋል። ምንም እንኳ አንዳንዶች “ፓርቲዎቹ ቢበዙም ከውስጣቸው አንዳንዶቹ ነጥረው ይወጣሉ” የሚል አቋም ቢኖራቸውም እኔ ግን እስካልተቀራረቡና የእርስ በርስ ግንኙነታቸውን አሻሽለው የለውጥ መንፈስን በጋራ እስካልገነቡ ድረስ በተከፋፈለ አካሄድ ግን የሚሆን ላለመሆኑ በርካታ አስረጂ ተጨባጭ ምሳሌዎችን ማምጣት ይቻላል። ኢህአዴግ በቀደደላቸው ቦይ በመፍሰስ ብሄርን መሰረት

ሚዲያ ወሳኝ ነው። ያ ነጻነትን የመሻት

የለውጥ መንፈስ እንደገና ተነቃቅቶ ውስጣችን እንዲሰርጽ ከፈለግን

ራሳችንን ለሚዲያዎች ማቅረብ መቻል

ይኖርብናል።

ነገረ- ኢትዮጵያሚያዝያ 10 ቀን 2006 ዓ.ም. ቅፅ 1 ቁጥር 99

ጭምጭምታ

ዘመናይ ዘ አራት ኪሎነገረ ኢትዮጵያ የተሰኘችዉ የሰማያዊ ፓርቲ ልሳን፣ በሰባተኛ እትሟ፣ በዚህ ሳምንትም ብዙ ቁም ነገሮችን ይዛ ብቅ ብላለች። የአንድነት ፓርቲ እያደረገ ስላለው የሚሊዮኖች ንቅናቄ ሰፋ ያለ ዘገባ ጋዜጣዋ

መያዟ አስደስቶኛል። የሚሊዮኖች ንቅናቄ የአንድ ፓርቲ ጉዳይ ሳይሆን የሕዝብ ጉዳይ ነውና። ይህ አይነቱም በሰማያዊና በአንድነት ፓርቲ መካከል እየታየ ያለዉ የመቀባበልና የመደጋገፍ መንፈስ ሊበረታታ የሚገባው፣ በእርግጠኝነት ሕዝባችንን የሚያስደስት ነው ብዬ አስባለሁ። ነገረ ኢትዮጵያ በዚህ ረገድ እያበረከተች ላለውም አስተዋጾ ምስጋናዬን አቀርባለሁ።ጋዜጣዋ በዚህ ሳምንት እትሟ፣ አቶ ታምራት ታረቀኝ፣ የ«ሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻ ምርጫ» በሚል ርእስ ያቀረቡትን ጽሁፍ አስነብባናለች። አቶ ታምራት በርካታ ቁም ነገሮችን አቅርበዋል። «ከልብ ለለውጥ የምንታገል፣ ለሰላማዊ ትግሉ አሸናፊነት በጽናት የምንቆም፣ ከራስ በላይ ሀገር ከሥልጣን ይበልጥ ሕዝብ የሚል የጸና እምነት ካለን ወቅታዊውም አስፈላጊውም ጥያቄና ትግል ምርጫ ነው፡፡ ስለሆነም በዚህ መንፈስና ዝግጁነት ላይ የሚገኙ ተቀዋሚዎች በሙሉ የውህደትና የህብረት እንካ ሰላንቲያቸውን አቁመው፣ ስሜት ለማነሳሳት የሚያደርጉትንም እንቅስቃሴ ገታ አድርገው ለነጻና ፍትሀዊ ምርጫ እውን መሆን የተጠና የታቀደና የተባበረ እንቅስቃሴ ሊጀምሩ ተገቢና ወቅታዊ ነው፡፡ ምርጫ በሰርገኛ መጣ በርበሬ ቀንጥሱ አይነት እንቅስቃሴ ተካሄዶ ውጤት ሊያመጣ አይችልምና» ሲሉ የተቃዋሚዎች አንገብጋቢ የትኩረት አቅጣጫ ምርጫዉ ላይ መሆን እንዳለበት አጠንክረው ያሳስባሉ።በምርጫዉ ረገድ ያቀረቧቸው ነጥቦችን በአብዛኛው እጋራለሁ። ከአንድነት አመራሮች አካባቢ፣ ከ«ሚሊዮኖች ድምጽ ለመሬት ባለቤትነት» እና «ከሚሊዮኖች ድምጽ ለፍትህ» ቀጥሎ፣ የ«ሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻ ምርጫ» በሚል ትኩረቱን ምርጫዉ ላይ ለማድረግ ሃሳብ እንዳለ የሚጠቁሙ አንዳንድ ፍንጮች ደርሰዉኛል። ስለዚህ አቶ ታምራት ያቀረቡት ሃሳብ፣ በአንድነት ፓርቲ ዘንድ ተቀባይነት ሊኖረው ይችላል ብዬ አስባለሁ። በአገር ዉስጥ ሰላማዊ ትግል የሚያደርጉ ፓርቲዎች፣ በአገሪቷ ለዉጥ እንዲመጣ ከፈለጉ በምርጫ ገዢዉን ፓርቲ ማሸነፍ አንዱና ትልቁ መሳሪያቸው ነው። ምርጫ ለማሸነፍ የምርጫ ዝግጅቶች ያስፈልጋሉ። ብዙ ሥራ ይጠይቃል። የገንዘብ አቅም ያስፈልጋል። አቶ ታምራት ያሉትን ልድገምና ሰርገኛ መጣ በርበሬ ቀንጥሱ ሊሆን አይችልም።«ተቃዋሚዎች የዉህደትን እና የሕብረት እንካ ሰላንቲያውን አቁመው» ሲሉ አቶ ታምራት የገለጹት አባባል ላይ ግን ችግር አለኝ። ይህን ሲሉ በዉህደት ወይንም በሕብረት መስራት በምርጫዉ ረገድ ሊያመጣ የሚችለዉን ከፍተኛ አዎንታዊ አስተዋጾ የዘነጉት መስለኝ። ብዙ ሆኖ ለምርጫ መወዳደር የሕዝቡን ድምጽ ይከፋፍላል። የሚጠቅመው ገዢዉን ፓርቲ ነው። አሜሪካም ሆነ ሌሎች የዉጭ ድርጅቶች ለምርጫዉ ዶላር አይበትኑልንም። አቅም፣ ገንዘብን ጉልበትን ማስተባበር ያስፈልጋል። በ547 ወረዳዎች የፓርላማ ተወዳዳሪዎችን፣ በክልል ምክር ቤቶች ደግሞ በርካታ የክልል ተወካዮችን ማሰለፉ ትልቅ ሥራ ነው። አንድ ድርጅት ይሄን ሁሉ ላድርግ ቢል በጣም ሊከበደው ይችላል። ከተመራጮች በተጨማሪ በየምርጫ ጣቢያዎቹ ታሳቢዎችን የማሰለፉን ነገርም አንዘንጋዉ። በመሆኑም የድርጅቶች አንድ ላይ መምጣት ቁልፍ ነገር ነው። አቶ ታምራት ለምርጫዉ መዘጋጀት እንደሚያስፈልግ ያቀረቡትን ምክሮች እየተጋራዉ፣ አብሮም የዉህደቱ እንቅስቃሴ፣ ቢያንስ እስከ ተወሰነ ጊዜ ድረስ፣ መቀጠል አለበት የሚል ጠንካራ እምነት አለኝ።ፓርቲዎች አብረዉ እንዴት መስራት እንደሚችሉ በሕግ ተደንግጓል። ሶስት አማራጮች ነው ያሏቸው። የመጀመሪያው ቅንጅት ነው። በምርጫ ዘጠና ሰባት ወቅት «ቅንጀት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ»፣ በምርጫ 2002 ደግሞ «መድረክ»፣ የበርካታ

ደርጅቶች ቅንጅቶች ነበሩ። ፓርቲዎች ለተወሰነ ጊዜ፣ በሕግ በመቀናጀት በጋራ ለምሳሌ ለምርጫ መወዳደር ይችላሉ። መቀናጀቱ ባልከፋ ነበር። ነገር ግን ከሁለቱ ምርጫዎች ተመክሮ፣ ለጊዜዉ ሲባል መቀናጀት፣ የራሱ የሆነ ትልቅ ችግር ይኖረዋል። ለምሳሌ «የየትኛው ፓርቲ ተወካይ በየትኛው ወረዳ ይወዳደር?» የሚለው ጥያቄ፣ በራሱ ትልቅ ራስ ምታት ነው። በ2002 ምርጫ፣ መድረክ ዉስጥ ያሉ የኦሮሞ ድርጅቶች፣ የአንድነት ፓርቲ በኦሮሚያ ዉስጥ ተወዳዳሪዎች ማሰለፍ የለበትም በሚል ሽንጣቸዉን ገትረው ሲከራከሩ እንደነበረና መድረክ ከምርጫዉ በፊት የመፍረስ አደጋ አጋጥሞት እንደነበረ የምናስታወሰው ነው። ሌላው የቅንጅት ችግር አንዱ ፓርቲ ዴሞክራሲያዊ ካልሆነና በጥቂት ግለሰቦች የሚመራ ከሆነ፣ ጥቂት ግለሰቦች ቅንጅቱን በሙሉ ሊያምሱት ይችላሉ። «እኛ ያልነው ካልሆነ፣ የጠየቅነውን ቦታ ካልያዝን» በሚል በቀላሉ ድርጅታቸውን ይዘው ሊወጡ ይችላሉ። ያም ቅንጅቱን በቀላሉ ያፈርሰዋል። ቅንጅቱ ሲፈርስ ደግሞ የሕዝብ ሞራል ይሰበራል። የሕዝብ ሞራል ሲሰበር ደግሞ ያንን ሞራል እንደገና ለማነሳሳት ከባድ ከመሆኑም በተጨማሪ ለአምባገነኖች ይመቻል። ሌላው በሕግ የተቀመጠዉ ግንባር የሚባለው አሰራር ነው። ምርጫን በተመለከተ ግንባርና እና ቅንጅት ተመሳሳይነት አላቸው። ስለዚህ በቅንጅት ዉስጥ ይኖራሉ የተባሉ ችግሮች ሁሉ በግንባም ዉስጥ ይኖራሉ። አሁን ባለው ሁኔታ የሚመረጠው ከተቻለ መዋሃድ ነው የሚል አስተያየት አለኝ። ድርጅቶች ከተዋሃዱ፣ አንድ ወይንም ጥቂት ግለሰቦች በተለያዩ ምክንያት ፓርቲዉን በሚለቁበት ጊዜ፣ ድርጅቱን አይፈርሱትም። ወይም ድርጅቱ ተከፋፈለ ሊባል አይችልም። ለምሳሌ የተከበሩ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ የአንድነትን ፓርቲ ለቀዋል። እርሳቸዉ በመልቀቃቸው አንድነት አልፈረሰም ወይም አልተከፋፈለም። ተመሳሳይ የፖለቲክ ፕሮግራም ያላቸው እንደ አንድነት፣ ሰማያዊ፣ መኢአድ፣ ያሉ ድርጅቶች ዉህደቱን በተመለከተ ሊያስቡበት ይገባል ባይ

ነኝ። ምርጫዉ የሚደረገው ከ13 ወራት በኋላ ነው። የምርጫ ተወዳዳሪዎች ክረምቱ ሳያልፍ ታውቀው፣ በየወረዳው ቅስቀሳዎች መጀመር ይኖርባቸዋል። እስከ ታች ድረስ ሕዝቡን ማስተማርና ማደራጀት ያስፈልጋል። በመሆኑም የዉህደት ሥራ የሚሰራ ከሆነ፣ በሚቀጥሉት ሶስት፣ አራት ወራት ዉስጥ መጠናቀቅ ያለበት ይመስለኛል።እርግጥ ነው መቸኮል አያስፈልግም። እርግጥ ነው ጥንቃቄ ያስፈልጋል። ግን እስቲ አስቡት፣ ሕዝባችን የሚመራዉ ትልቅ ድርጅት እየፈለገና እየጠየቀ ባለበት ሁኔታ፣ አሁን በመኢአድ እና በአንድነት እያየን እንዳለው አይነት ለአመታት የሚደረግ የዉህደት ንግግር ምን ይባላል? ይህ ድካም ነው። እንዲሁ በትናንሽ ምክንያቶች ነገሮችን መጎተት የሕዝብን ስሜት መጉዳት ነው። ተመሳሳይ የፖለቲካ ፕሮግራም ያላቸው የፖለቲካ ድርጅቶች፣ ቅንነት ካላቸው፣ ከግል ዝናና ስልጣን ይልቅ የአገርንና የሕዝብን ጥቅም ካስቀደሙ፣ በዴሞክራሲያዊ አሰራር ካመኑ፣ የማይዋሃዱበት ምንም ምክንያት አይኖርም።በስፋት እንደተዘገበው በመኢአድ እና በአንድነት መካከል የሚደረገው ዉህደት ሊጠናቀቅ ትንሽ ነበር የቀረዉ። ነገሮች ትንሽ ስለተጓተቱ ለጊዜው መኢአዶች መቆየቱን በመምረጣቸው፣ ሁሉም ነገር እንደፈረሰ አድርገው የሚናገሩ እንዳሉም ታዝበናል። ነገር ግን ከአንድነትም ሆነ ከመኢአድ መሪዎች የምንሰማው ያሉ ልዩነቶች በጣም ትንሽ እንደሆኑና ለዉደት ያላቸው ተስፋ ትልቅ እንደሆነ ነው። በሰማያዊና በአንድነት መካከልም ንፋስ እንዲገባ፣ አለመግባባት እንዲፈጠር የሚጥሩ ሊኖሩ እንደሚችሉ ይታወቃል። ነገር ግን ሁለቱ ደርጅቶች በሚያደርጓቸው እንቅስቃሴዎች እንዳየነው፣ በአላማ ቁርጠኝነትና በጽናት ተመሳሳይነትን እያሳዩ እንደሆነ ነው። የአንድነት ወጣት አመራሮችና ሰማያዊዎች ብዙ የሚተዋወቁ፣ አብረዉ የሰሩና የሚተማመኑ እንደሆነም እየሰማን ነው።እንግዲህ የመኢአድ፣ የሰማያዊና የአንድነት አመራር አባላት፣ ቢያንስ በሚቀጥሉት ሶስት ወራት ቁጭ ብለው በመነጋገር፣ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ አንድ ጠንካራ አገር አቀፍ ድርጅት እንዲመሰርቱ ጥሪ አቀርባለሁ። አቶ ታምራት ታረቀኝ እንዳሉት፣ ከዚያ በኋላ ዉህዱ ፓርቲ፣ የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻ ምርጫ፣ የሚል ዘመቻን አዉጆ ሕዝቡ ለሰላማዊ የምርጫ ማንቀሳቀሱን በተጠናከረ መልኩ ይገፋበታል። ይህን ስጽፍ አንዳንዶች «ምኞቱን የሚጽፍ፣ የፖለቲካዉን ተጨባጭ ሁኔታ የማያገናዝብ» የሚል ትችት ሊያቀርቡ ይችላሉ። ነገር ግን ከዚህ በፊት የተደረጉ ስህተቶች ላይ፣ ድካማችን ላይ አላተኩርም። የማተኩረው ልናደርግ የምንችለው ላይ፣ አቅማችንና ጥንካሬያችን ላይ ነው። በአንድነት፣ በመኢአድና በሰማያዊ አመራሮች ዘንድም፣ ያለው ፍላጎትና አላማም ይሄው እንደሆነ ስለማውቅ ነው። ለጊዜዉ እዚህና እዚያ ጥቃቅን መሰናክሎች ቢኖርም፣ መልካም ዜና ያሰሙናል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።ከማጠቃለሌ በፊት ስለአረና ትግራይ ልናገር። አረና ትግራይ ምንም እንኳን የክልል ድርጅት ቢሆንም፣ ብዙ ጊዜ አንዳንድ የፓርቲው አመራሮች የሚጽፏቸውና የሚናገሯቸው አባባሎችን ስንመለከት፣ እንደ አንድነት ያሉ ድርጅቶች ካላቸው አቋም ጋር የሚቀራረብ ድርጅት ሊሆን እንደሚችል ነው የማስበው። ለአረና ፓርቲ ትልቅ ከበሬታና አድናቆት አለኝ። ትልቅ ትኩረት ተሰጥቶት ከአረና ጋር የተጀመሩ ዉይይቶች ተጠናክረው መቀጠል አለባቸው ባይ ነኝ። በተቻለ መጠን የፖለቲካ ፕሮግራም መቀራረብ እስካለ ድረስ፣ የዴሞክራቲክና የኢትዮጵያ ብሄረተኝነት ካምፕን ማስፋት ያስፈልጋል።

ግርማ ጌታቸው ካሳ ዘብሄረ ኢትዮጵያ

([email protected])

የፓርቲዎች መዋሃድ በጣም አስፈላጊ ነው

ግርማ ካሳ ኦቦ ሙክታር ከድር በማዕረግ ደረጃ ምክትል ጠ/ሚኒስትርና የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር ሚኒስትር ነበሩ፡፡ በዚህ ጊዜ ታዲያ ባሉበት የስልጣን እርካብ መረጋጋት አይታይባቸውም ነበር፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ሌላ አሻግረው የሚያዩት ስልጣን ነበረ፡፡ በስልጣን ደረጃ የቱ ይበልጣል እንዳትለኝ እንጂ ሰውየው አብዝተው የሚፈልጉት፣ አሻግረውም ያዩት የነበሩበትን ቢያሳንሱ ነው፡፡ያ አሻግረው ሲመለከቱት የነበረው ስልጣን የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት መሆንን ነበር፡፡ በዚህም ኦቦ ሙክታር ከድር ተሳክቶላቸዋል! አሁን የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት እሳቸው ናቸው፡፡ በቀድሞ ቦታቸው ደግሞ አስቴር ማሞን ተክተዋል፡፡ አንዳንድ ዋዘኞች ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ከፍተኛ የሚባለውን የስልጣን እርከን ለሴት ሰጠች እያሉ ይተርካሉ፡፡ እኔ ግን ከንቱ አወዳሾች ናችሁ እላቸዋለሁ፡፡ ምክንያት ካልከኝ ደግሞ ኢትዮጵያ በማዕረግ ደረጃ ምክትል ጠ/ሚኒስትርነት ቀርቶ ንግስትነትን የመሰለ ስልጣን (የመጀመሪያው ወይም አንደኛው የስልጣን እርካብ) በተደጋጋሚ በሴት ተይዞ አልነበረምና ነው አሁን በአስቴር የምታሽቃብጡት ልላቸው እወዳለሁ፡፡ ሴትማ ገና ዋናው ስልጣንም ይገባታልና በዚህች አታሞጋግሱ!ዋናው ጉዳይ የኦቦ ሙክታር ምኞት መስመሩ ነው፡፡ እንኳን ደስ አለዎት ማለትም ይኖርብናል መሰለኝ (ዘገያችሁ ካልተባልን)፡፡ ታዲያ ሰውየው በአዲሱ ስልጣናቸው ላይ አንድ ሴራ እየተሸረበባቸው ነው አሉ፡፡ አዎ ሰውየው ኦሮሞ ስላልሆኑ ኦሮሚያን ፕሬዚዳንት ሆነው ለመምራት አይቻላቸውም ይላሉ፡፡ እሳቸውን የየም ብሔረሰብ ተወላጅ ናቸው ማለታቸው እኮ ነው፡፡ የም ሆኖ ኦሮሚያን አይመራም ማለታቸው እኮ ነው፡፡ አቤት ክፋታቸው፡፡ መቼም ይህች ስራ የማን እንደሆነች መገመት ከባድ አይሆንም፡፡ የኦቦ አባ ዱላ ሴራ ናት ይሉኛል ውስጥ አዋቂዎቼ፡፡ኦቦ አባ ዱላ ገመዳ በኦህዴድ ውስጥ የራሳቸው ቡድን አላቸው፡፡ ኦቦ ሙክታርም የራሳቸው አላቸው፡፡ አንጃ የሚባለው አይነት እኮ ነው፡፡ (ብቻ እንዳይጫረሱ እንጂ...) እና ደግሞ ኦቦ ሙክታር የሟቹ ኦቦ አለማየሁ ሌጋሲ አስቀጣይ ናቸው አሉ፡፡ ደግሞ ለህወሓት ታማኝ ናቸው...አስቴር ማሞንም ጨምሮ፡፡ ኧረ እንዲያውም ታማኝ ብቻ ሳይሆን አሽከር ናቸውም ይባላል፡፡ ታዲያ አልኩህ...ኦቦ ሙክታር ኦሮሚያን ለማስተዳደር የቋመጡት እነ ኦቦ አባ ዱላን ለማብሸቅና ለመጎሸም ነበር፡፡ በዚህም ተሳካላቸው፡፡የኦቦ አባዱላ ሰዎችም ቀላል ሰዎች አይደሉም፡፡ ሰውየውን ኦሮሞ አይደለህም እያሉ ለማሸማቃ እየሞከሩ ነው፡፡ ኦቦ አለማየሁን እስከ ግባዕተ መሬት ድረስ መሬት አስግጠውታል፤ ኦቦ ሙክታርን አይተኙለትም ይባላል፡፡ ኦቦ ሙክታር ግን አይገርሙህም...ከዓመታት በፊት በጅማ ተከስቶ ከነበረው ሐይማኖታዊ ግጭት ጀርባ ነበሩበት እየተባሉ እኮ ይታማሉ፡፡ ደግሞ ከዘመዶቻቸው ቤት የጦር መሳሪያዎች ተገኝተውባቸዋል ተብሏል፡፡ ታዲያ እኒህ ሰው አሁን የክልል ፕሬዚዳንት ሲሆኑ አይገርሙህም!ደግሞ አስቴርና ኦቦ ሙክታር ጥብቅ ወዳጆች ናቸው ይባላል፡፡ ኧረ እንዲያውም በአንድ ወቅት የአዳምና የሄዋን አይነት ነገር ጀምረውም ነበር አሉ፡፡ ታዲያ ኦቦ ሙክታር የነበሩበትን ስልጣን ለአስቴር ቢሰጧቸው ምን ይገርማል፡፡ ያም ሆነ ይህ ግን የኦቦ ሙክታርና የኦቦ አባ ዱላ ፍትጊያ ወዴት ሊያመራ እንደሚችል እናያለን፡፡ ኦቦ ሙካታር የቋመጡለትን የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንትነትም አግኝተውታል፡፡ ምን ሊያደርጉበት አስበው ይሆን?ግን ግን የኦቦ አለማየሁ አቶምሳ አሟሟት እንዲህ ሆኖ ሊቀር!? ነው ወይስ ኦቦ ሙክታር ስላጣናቸውን ተጠቅመው ‹ይጣራ› ይሉ ይሆን? ለነገሩ ለራሳቸውም መስጋት ይኖርባቸዋል፡፡ ብዙ የሙስና ድር ያደራባቸው ሰዎች መርዘውም ሆነ አነጣጥረው የሚያጠቁትን ሰው በልባቸው ይዘዋል፡፡ ብቻ እሳቸውም የኦቦ አለማየሁ አይነት ነገር እንደማይገጥማቸው ተስፋ እናደርጋለን፡፡ እስኪ በቀጣይም ሌላ ጉዳይ እንድናወራ ያድርገን!

ኦቦ ሙክታር ከድር ተሳካላቸው!

ፓርቲዎች አብረዉ እንዴት መስራት

እንደሚችሉ በሕግ ተደንግጓል።

ሶስት አማራጮች ነው ያሏቸው።

የመጀመሪያው ቅንጅት ነው። በምርጫ

ዘጠና ሰባት ወቅት «ቅንጀት ለአንድነትና

ለዲሞክራሲ»፣ በምርጫ 2002 ደግሞ «መድረክ»፣ የበርካታ ደርጅቶች ቅንጅቶች ነበሩ። ፓርቲዎች

ለተወሰነ ጊዜ፣ በሕግ በመቀናጀት በጋራ ለምሳሌ ለምርጫ

መወዳደር ይችላሉ።

ነገረ- ኢትዮጵያሚያዝያ 10 ቀን 2006 ዓ.ም. ቅፅ 1 ቁጥር 9 10

ከገፅ 5 የዞረ ...የኢትዮጵያ ሥትራቴጂካዊ ... ከገፅ 5 የዞረ ...የዘመኑ ፖለቲካ ...

ወደ ገፅ 15 ዞሯል

በቀለ ገርባ በተለመደው የአሸባሪነት እስር ቤት ውስጥ ተውርውሯል፡፡ በቀለ ከተፈረደበት ሰባት አመት ውስጥ በይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት ወደ 3 ዓመት ከ 7 ወር ተሻሽሎሎለታል ተብሎ ዝዋይ እስር ቤት ውስጥ ከርሟል፡፡ በአሁኑ በይግባኝ የተወሰነው የእስራት ጊዜ ያለቀ ቢሆንም ሊፈታ ግን አልቻለም፡፡ በቀለ ገርባ ይህ ኢ-ፍትሃዊነት በተፈጸመበት ወቅትም አይበገሬነቱን፣ ሰላማዊነቱን በአጠቃላይ መስዋዕትነቱን አስመስክሯል፡፡ አሸባሪ ተብሎ በተፈረደበት ወቅት የተናገረውም ይህንኑ የሚያመላክት ነው፡፡ ‹‹በሕይወት ዘመኔ፣ ኢ-ፍትሐዊነት፣ አድልዎን፣ ዘረኝነትንና ጭቆና ተጸይፌ ተቃውሜያለሁ። በራሴ ምርጫ ሳይሆን በፈጣሪ ፈቃድ የተፈጠርኩበት የኦሮሞ ሕዝብ ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶቹ ተከብረውለት በእኩል አይን እንዲታይ ባደረኩት ሰላማዊ ትግል ምክንያት መስዋትነት መክፈል መቻሌ ለእኔ ክብር ነው።›› ቡአዚዝ እራሱን ሰውቶ የዓረቡን ዓለም ባነቃቃበት ወቅት ኢትዮጵያዊው መምህርም ተመሳሳይ መስዋዕትነት ከፍሏል፡፡ የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ የአማርኛው ፕሮግራም በወቅቱ ያነጋገረው አንድ እማኝ መምህር የኔሰው ገብሬ የከተማው አስተዳደር አባላት በተሰበሰቡበት ስብሰባ ላይ በመገኘት ‹‹ወጣቶች ያለፍርድ እስከ 15 ቀን ታስረዋል፡፡ ወጣቶቹ ፍርድ ቤት የመቅረብ መብታቸው ሊከበርላቸው ይገባል፡፡ ወጣቶች ዝም ብለው መታሰር የለባቸውም፡፡ ሊለቀቁ ይገባል፡፡›› የሚል ጥያቄ ማንሳቱን አውርቷል፡፡ አብዛኛውን ወጣት ሆድ አደር አድርገው የሚቆጥሩት ባለስልጣናት የኔሰውም በቀላሉ በሆዱ የሚታለል ስለመሰላቸው 200 ብር ሰጥተው ከቦታው ዘወር እንዲል ይደራደሩታል፡፡ መምህር የኔሰው ግን ለዚህ ርካሽ መደራደሪያ እውነትን የሚለውጥ ሆኖ አልተገኘም፡፡ እሱም ‹‹እኔ እራሴን በብር አልሸጥም፡፡ ገንዘብ አልፈልግም፡፡ የምፈልገው ወጣቶቹ እንዲፈቱ ነው›› ይላቸዋል፡፡ የባለስልጣናቱ ጨካኝነትና አምባገነንነት የተገነዘበው ወጣት የኔሰውም ከስብሰባ አዳራሹ በመውጣት እራሱን በእሳት አያያዞ መስዕዋት አደረገ፡፡ ልክ እንደ እስክንድር፣ ውብሸትና ሌሎቹም በሰላ ብዕሯ ምክንያት ‹‹አሸባሪ›› የተባለችው ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ ደግሞ ለህዝባቸውና ለእውነት መስዋዕት የሚሆኑ እንስቶችም እንዳሉን አይነተኛ ማሳያ ነች፡፡ ርዕዮት በታሰረች በ793 ቀን ከቃሊቲ በጻፈችው ደብዳቤ ‹‹…..ከኢህአዴግ ምንም አይጠበቅም፡፡ የእኛ ብቸኛው አማራጭ መሆን ያለበት ዘመናዊ መሆንና የሚከፈለውን ከፍለን በሰላማዊ ትግላችን መቀጠል ነው፡፡›› ስትል የቃሊቲ ስቃይ ቤት፣ ህመሟም፣ ሴትነቷም ለትግልና ለመስዋዕትነት እንዳልበገራት ዳግመኛ አረጋግጣለች፡፡ ይህች አልበገሬ ጋዜጠኛ ይህን የምትለው የተመቻቸ ሁኔታ አግኝታ አይደለም፡፡ ከአባትና እናቷ ውጭ ማንም እንዳይጎበኛት ተከልክላለች፡፡ ከምንም በላይ ጡቷ እየደማ፣ በከፍተኛ በሽታ እየተሰቃየች ማጎሪያ ቤት ስጥ የሚገኙትን ታሳሪዎች መብትም በጣሰ መልኩ ሀኪም ቤት እንዳትሄድ ቆይታለች፡፡ በዚህ ርህራሄ የሌለው ስርዓትና ሁኔታ ውስጥ ሆና ግን የምታስበውና መስዋዕት የምትሆነው ለ30ና 50 ብር ለኢህአዴግ ባለስልጣናትና ፓርቲው ትዕዛዝ በሆድ አደርነት ሰላማዊ ሰልፍ ለሚወጡት ጭቁን ኢትጵያውያንና ለቀጣዩዋ ኢትዮጵያ ጭምር ነው፡፡

የኢትዮጵያውያን ፋሲካ መቼ ነው?መስዋዕትነት ባለበት ድልም አለና የእነዚህ ኢትዮጵያውያን ትግል አንድ ቀን ወደ ድል ጎዳና እንደሚያመራ የሚያጠራጥር አይደለም፡፡ የእነዚህ ጀግኖች በመስዋዕትነት፣ ግርፋት፣ ስቃይ የታጀበ አይበገሬነት ወደ ነጻነት (የዴሞክራሲው ፋሲካ) የሚቀየርበት ቀን መቼ እንደሆነ ባይታወቅም እነሱ ግን እንደቀረበ ይናገራሉ፡፡ ዛሬ እውነት ተነፍጎ ስለ እውነትና የነገዋ ነጻነት የሚሰብከው አንዱዓለም አራጌ ‹‹እውነት ምንም ያህል ትቢያ ላይ ብትጣልም፣ ትቢያዋን አራግፋ በድል የምትቆምበት የመኸር ዘመን ይመጣል፡፡ ያን ጊዜም የነጻነት ብርሃን እንደ ማለዳ ጸሃይ የሚፈነጥቅ ይሆናል፡፡›› ሲልም የሚተነብየው ስለ ቀጣዩ ፋሲካ ነው፡፡ እስክንድር በበኩሉ

‹‹ኢህአዴግ የኢትዮጵያ የመጨረሻው አምባገነን ስርዓት ነው፡፡ ዓለምም ሆነ ኢትዮጵያ እንደ ኢህአዴግ ያለ አምባገነንን ለመሸከም የሚያስችል ትክሻ የላቸውም፡፡ አምባገነንነትን ቤተ መጽሃፍት እንጂ በተግባር የማናይባቸው ጊዜያት እሩቅ አይደሉም፡፡ ይህ ይሆን ዘንድ መታሰሬ ደግሞ የሚከብድ መስዕዋትነት አይደለም፡፡……ፋናውን ለማየት እጓጓለሁ፡፡ ይህ ረዥም ጊዜ ሊቆይም ላይቆይም ይችላል፡፡ ምንም ይሁን ግን በአቋሜ እጸናለሁ፡፡›› እያለ የዴሞክራሲውን ፋሲካ ጸንቶ እየጠበቃት መሆኑን ይነግረናል፡፡አብዛኛው ‹‹ያልታሰረ ምሁር›› በሙሉ ጊዜው ለለውጥ ይህ ነው የሚባል ስራ እየሰራ ባልሆነበት በአሁኑ ወቅት እስር ቤት ውስጥ ስቃይን እየተቀበሉ ያሉት ወጣቶች ለውጡ እንዴት መምጣት እንዳለበት፣ ፋሲካው መቼ እንደሆነ ለመተንተን፣ ለመምከር አልቦዘኑም፡፡ ‹‹በየትኛውም መንገድ ኢህአዴግ ሊፈጥርብን የሚችለውን እንቅፋት በጥልቀት ማየት ይጠበቅብናል፡፡ በተበታተነ ሁኔታ ላይ ያለውን ግንባር አንድ አድርገን መታገልን መማር አለብን፡፡ መጭውን ጊዜ ማለም የየትናውም ዜጋ ግዴታ መሆን አለበት፡፡….የሚጠበቅብንን ሚና ከተወጣንና በእምነታችን እስከጸናን ድረስ የተስፋው ቀን ሩቅ አይሆንም፡፡›› የምትለዋ ትንታጓ ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ ነች፡፡በእርግጥ የዘመኑ ኢትዮጵያውያን ወጣት ሰማዕታት እስር ቤት ውስጥ ሆነው ብቻ ሳይሆን ልክ እንደ እየሱስ ክርስቶስ ወደ ሞት እያመሩም ስለ ፍቅር፣ ስለ ነጻነት፣ ስለ አገራቸውና ህዝብ ምክር ለመለገስ አልታከቱም፡፡ ወጣቱ መምህር የኔሰው ገብሬ በወጣቶች ላይ ስለሚፈጸመው ጭካኔ ጥያቄ አንስቶ በይሁዳዊ ስልት በርካሽ ገንዘብ ሊደልሉት የሞከሩትን ሆድ አደሮች ከተሰበሰቡበት አዳራሽ በመውጣት እራሱን በእሳት ለማያያዝ በፈለገበት ወቅት ስለ ፋሲካው አውርቷል፡፡ ስለ ለውጡ መክሯል፡፡ በዛች የስቅለት ቀን ስለ ፍትህና ነጻነት፣ ስለ አገራችን ወጣቶች አርዕነት ተናግሮ ራሱን በተምሳሌትነት ሰውቷል፡፡ የኔሰው ከስብሰባ አዳራሹ በሚወጣበት ወቅትም ‹‹ሞት ያለነጻነትና ፍትህ ከመኖር የተሻለ መሆኑን ለሁሉም ማሳየት እፈልጋለሁ፡፡ ለወጣቱም መናገር የምፈልገው ምንም ነገር ባለመፍራት ከአካባቢውና በአገር ደረጃ ከሚገኙት ጨቋኞች የሚቀሙትን ነጻነትና መብት እንዲጠይቅ ነው›› ማለቱን ከእሱው ጋር የነበሩት እማኝነታቸውን ገልጸዋል፡፡ የእነዚህ ወጣቶች ቆራጥነት፣ ሰላማዊነት፣ የፍትህ ናፍቆት፣ ሰቆቃ ስናይ እውነትም ዛሬ ስለ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን የሚሰሩት አገር ወዳዶች ለሌባና ወንበዴ የማይገባውን ስቃይ እየተቀበሉ ነው፡፡ እነዚህ ወጣቶች ላይ ያረፈው የአምባገነኖች ጅራፍ፣ የዘመኑ አይሁዳዊያን በትርና ይሁዳዊ በርካሽ እውነተኛን የመሸጥ ተግባር በአገራችን ዴሞክራሲም የስቅለት ቀን ላይ መሆናችንን እንገነዘባለን፡፡ እስክንድር ‹‹……ፋናውን ለማየት እጓጓለሁ›› ሲል፣ አንዱዓለም ‹‹ትቢያዋን አራግፋ በድል የምትቆምበት የመኸር ዘመን ይመጣል፡፡ ያን ጊዜም የነጻነት ብርሃን እንደ ማለዳ ጸሃይ የሚፈነጥቅ ይሆናል፡፡›› በማለት ሲተነብይ ስለ ነገዋ የዴሞክራሲ ፋሲካ ነው! እየሱስ ክርስቶስ ሳይገባው ተገርፎ፣ መስቀል ላይ ተቸንክሮ፣ ደሙን አንጠፍጥፎ፣ ከሌቦች ጋር ሞት ተፈርዶበት ያስተማረው ህዝበ ክርስቲያኑን ነው፡፡ እነ የኔሰው ገብሬ፣ ርዕዮት፣ አንዱዓለም፣ እስክንድር…ለህዝብና ለአገር እንጂ ለራሳቸው ብቻ ቢሆን ሆድ አደርም መሆን ሳይጠበቅባቸው፣ አሁን እየደረሰባቸው ያለው የእስር ቤት ስቃይ ሳይደርስባቸው መኖር እንደሚችሉ አጥተውት አይደለም፡፡ ግን እነሱ ስለ እውነት፣ ስለ አገር፣ ህዝብ መስዋዕት ሲሆኑ ለእኛ ለቀሪዎቹ ተምሳሌት መሆን ፈልገው ነው፡፡ የኔሰው በመጨረሻዋ የመስዋዕትነት ቀን ራሱን በእሳት ሲያያይዝ ‹‹ወጣቱ ባለመፍራት ከአካባቢውና በአገር ደረጃ ከሚገኙት ጨቋኞች የሚቀሙትን ነጻነትና መብት እንዲጠይቅ ነው›› ብሏልና የኢትዮጵያውያን የዴሞክራሲው ፋሲካ ይቀርብ ዘንድ የራሳችንን አስተዋጽኦ በማበርከት ኢትዮጵያዊ አደራችን እንጠብቅ!ለኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ሲሉ መስዋዕት ለሆኑት ሁሉ ክብር ይገባቸዋል!መልካም በዓል!

3)ሙስና ቤቱን ከሠራባቸው ግንባር ቀደም ሀገራት አንዷ ኢትዮጵያ ናት፡፡ በዘመናዊ መለኪያ (ሙስና ከማጥፋት አኳያ ማለቴ ነው) ያገኘችው ነጥብ አስደንጋጭ ሲሆን ይኸውም 33% ነው) (Trans-parency international) 4)በኢትዮጵያ ያለው የምጣኔ ሀብት 49.4% ነው (ከ50% በታች ዝቅተኛ እንደሆነ አንባቢውን አስታውሣለሁ) (Global Financial) 5)ከሠብአዊ እድገት አኳያ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ከሚገኙ ሀገራት አንዷ ኢትዮጵያ ስትሆን ያገኘችው ነጥብ 0.396 ደረጃም ደግሞ 173ኛ ነው (UNDP 2013)6)88.6% ህዝብ በድህነት አረንቋ ውስጥ የተዘፈቀ ሲሆን በባለሙያዎች መለኪያ መሰረት (Multidi-mensional poverty Index) 0.562 ይደርሳል፡፡፡ (Oxford Poverty & human development initiative, 2011) የኢትዮጵያ አገዛዝ ፍፁማዊ አምባገነን ብቻ ሳይሆን የሀገሪቱን ምጣኔ ሀብትንም የተቆጣጠረ ነው፡፡ ለጋሽ እና አበዳሪ ሀገራትን ለመለመን የሚወጣው የምጣኔ ሀብት እድገት ልፈፋ የጠቀመው የሥርዓቱን ፊት አውራሪዎች እና አሽኮሎሌዎቻቸውን ሳይሆን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ዛሬም ቢሆን አላለፈላቸውም፡፡ እ.ኤ.አ 2012 በአፍሪካ ምጣኔ ሀብታዊ ማዕከል የምርምር ተቋም ጥናት መሠረት በምርት ብዛትና ጥራት፣ በውጭ ገበያ፣ እና በሰዎች ብልፅግና አኳያ ከመጨረሻዎች አራት የአፍሪካ ሀገራት ኢትዮጵያ አንዷ ናት (አራቱ ሀገራት ሩዋንዳ፣ ቡርንዲ፣ ብርኪናፋሶ እና ኒጀር ናቸው)፡፡ አገዛዙ በሚከተለው የተሳሳተ የመሬት ባለቤትነት ህግ የተነሣ ገበሬውም ሆነ ከተሜው የእኔ የሚለው ስሜት የለውም፡፡ እንዲሁም ታላቅ የደን ውድመት እና የአየር ንብረት ለውጥ እየተከሰተ ይገኛል፡፡ የዚህ የውጤት ደግሞ ኢትዮጵያን የድሆች ደሀ አድርጓታል፡፡ ከ100 ሚሊዮን በላይ ህዝቧ አብዛኛው ከ1 የአሜሪካን ዶላር በታች በቀን የሚገኝባት ሀገር ኢትዮጵያ ለእያንዳንዱ የጂቡቲ ዜጋ ዛሬ በቀን 4 የአሜሪካን ዶላር ትከፍላች፡፡ “it is a cruel joke but sadly true” ነው የሚሉት ፈረንጆቹ? ‹‹ከሞኝ ደጃፍ ሞፈር ይቆረጣል!›› እንዲሉ ኢትዮጵያውያን ባይተዋር ወይንም የበይ ተመልካች ሆነናል፡፡ ያሳዝናል! ማሳዘን ብቻ አይደለም፡፡ ህሊናን ያደማል፡፡ ሆድንም ይበጠብጣል፡፡ በሀገሪቱ ምዕራባዊ ድንበር አካባቢ የሚገኙ ለም መሬቶች የሱዳን ገበሬዎች መፈንጫ ሲሆኑ፣ በደቡብ እና ደቡብ ምስራብ ኢትዮጵያ የሚገኙ ነባር ገበሬዎች በግዴታ በማፈናቀል ለም መሬቶችን ጠላቶቻችን በዓለም ላይ ካሉ ሀገራት ሁሉ ርካሽ በሆነ ዋጋ አገዛዙ አስረክቧል፡፡ እነዚህና ሌሎች ምክንያቶች ተደራርበው የሀገሪቱን ዜጎች የመኖር አቅም ሥለሚፈታተኑ ድንገት ሊፈነዳ የሚችል ህዝባዊ አመፅ ሊቀሰቀስ እንደሚችል እንደ ፕሮፌሰር ጌታቸው በጋሻውን የመሳሰሉ የፖለቲካ ጠበብት ያስጠነቅቃሉ፡፡

Provide this kid of spark ምንም እንኳን ኢትዮጵያ ታሪካዊት እና ብዙ የውጪ ወራሪዎችን አሸንፋ የዘመናት መንግስትነት ታሪክ ያላት ሀገር ብትሆንም ዛሬ እንደ ሀገር ለመቀጠል እንዳትችል የውስጥም የውጭም ሴራ ከፊቷ ተደቅኖ ይገኛል፡፡ ኢትዮጵያ በአብዛኛው ዜጎች እውቅና የተሰጠው አስተዳደርም መመስረት የቻለችም አይመስለኝም፡፡ ዓለም አቀፍ እውቅና ያላቸው ጋዜጠኞች እስክንድር ነጋ፣ ውብሸት ታዬ፣ በህመም የምትሰቃየው ርዕዮት አለሙ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች አንዱአለም አራጌ፣ በቀለ ገርባ እና ሌሎች በእስር እየማቀቁ ይገኛሉ፡፡ በቅርቡ ደግሞ (March 8, 2014) ነፃነት ብለው የጠየቁ ሴት ወጣቶችን ለተወሰነ ጊዜ ዘብጥያ ወርውሯቸው ነበር፡፡ ወደ ነፃና ፍትሃዊ የፖለቲካ ምርጫ፣ የፓርላማ ዴሞክራሲ በነፃነት ሀሰብን ለመግለፅ እና ነፃ የሲቪል ማህበራት ለመመስረት የሚያስችሉ መንገዶች ሁሉ እየተዘጉ ነው፡፡ የኢአህዴግ አገዛዝ ስልጣኑን የጨበጠው በኃይል በመሆኑ ሰብዓዊ መብቶችን ገፏል፡፡ ወደ ፊትም በዚሁ መቀጠሉ አይቀሬ ነው፡፡ ይህ ደግሞ ኢትዮጵያን ለመድፈር ምኞታቸው ለሆነ ባዕዳን ኃይሎች ጥቃት አጋልጦናል፡፡ ወደድንም ጠላንም፣ አመንም አላመንም ኢትዮጵያ በታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ተዳክማለች፡፡ ባላት

የጂኦግራፊያዊ ቀረቤታ የተነሳ በሶማሊያ ምድር የተለኮሰውን እሳት ለማጥፋት ትችላለች ተብሎ ሊታሰብ ይችላል፡፡ ይሁንና በውስጧ የፖለቲካ መረጋጋት ባለመኖሩ አልሆነላትም፡፡ አንዴ በራሷ ጊዜ ዛሬ ደግሞ በአሚሶም (AMISOM) ስር ጦር ብትልክም በሶማሊያ ምድር ሠላም ማስፈን አልቻለችም፡፡ ለምን? ምክንያቱም ‹‹የውስጥ ቀጋ የውጭ አልጋ›› ወንዝ የማያሻግር ፖለቲካዊ ፍልስፍና በመሆኑ ይመስለኛል፡፡ ከኢሳያስ በኋላ የኤርትራ እጣ ፈንታ ምን እንደሚሆን የሚታወቅ አይመስልም፡፡ በርካታ የፖለቲካ ጠበብት ግምት ግን ኤርትራ የጨነገፈች ሀገር ልትሆን ትችላለች የሚል ነው፡፡ በኢትዮጵያ ስልጣን ኮርቻ ላይ የተፈናጠጠው አገዛዝ እድሜ ከሰጠው ኢትዮጵያን ሊጠቅም የሚችል ሥራ ያከናውናል ተብሎ አይጠበቅም፡፡ ምክንያቱም የስርዓቱ ዋነኛ ተልዕኮ ኤርትራ ነፃ ሀገር ሆና እንድትቀጥል በመሆኑ ይመስለኛል፡፡

አሜሪካና ኢትዮጵያ...እንደ ፓልሄንዝ (Poul Henzie) ጥናት ከሆነ ታላቋ አሜሪካ ጥቅሟን ለማስጠበት ከአፍሪካው ቀንድ በተለይም ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ማድረግ የጀመረችው ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ጋር በተያያዘ ነው፡፡ አንዳንድ ምሁራን ደግሞ ታላቋ ብሪታኒያ በአካባቢው የነበራትን ጥቅም ለማስቀጠል የታለመ ነው ይላሉ፡፡ ግራም ነፈሰ ቀኝ እ.ኤ.አ 1953 አሜሪካ እና ኢትዮጵያ ባደረጉት ስምምነት በአስመራ የሚገኘውን የቃኘው ጣቢያ አሜሪካ የባህር ኃይል፣ የአየር ኃይልና የስላሳ መረቧን እንድትጠቀም ኢትዮጵያ ስትፈቅድ አሜሪካ በበኩሏ የኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም አገዛዝ ጓዟን ጠቅልላ እስከሚያባርራት ድረስ ለኢትዮጵያ መጠነ ሰፊ የወታደራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እርዳታ አድርጋለች፡፡ እ.ኤ.አ 1980 አጋማሽ ላይ የቀድሞው ሶቬየት ህብረት ወዳጅ የነበረውን ወታደራዊ አገዛዝ ከሥልጣኑ አሽቀንጥሮ ለመጣል መጠነ ሰፊ እርዳታ ለሻዕቢያና ወያኔ አቅርባ እንደነበር የሚዘነጋ አይመስለኝም፡፡ ሁለቱም የቀድሞ ፋኖዎች አስመራ እና አዲስ አበባ ላይ መንግስት ለመመስረት ወግ ሲደርሳቸው አሜሪካ ከሁለቱም ሀገራት ወዳጅነት ነበራት፡፡ ከጥቂት አመታት በኋላ ከኤርትራ ጋር የነበራት ፍቅር ቢቀዘቅዝም አሁን ድረስ ለአዲስ አበባው አገዛዝ መጠነ ሰፊ እርዳታ ታቀርባለች፡፡ የአሜሪካ እርዳታ የተመሠረተው በአጭር ጊዜ አላማ ላይ በመሆኑ የኢትዮጵያውን አገዛዝ ከማጠናከር ባሻገር ለኢትዮጵያ ህዝብ እድገት የማይጠቅም፣ የአሜሪካንንም የረጅም ጊዜ ጥቅም ክፉኛ እንደሚጎዳ የፖለቲካ ተንታኞች ይናገራሉ፡፡ ከእነዚህ ባሻገር አሜሪካ አምባገነኑ የኢህአዴግ አገዛዝ መጠነ ሰፊ እርዳት በመስጠቷ የተነሳ አብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ ቅሬታ ውስጥ ወድቋል፡፡ ከታሪክ እንደምንማረው ኢትዮጵያ ሊወሯት የመጡትን ጠላቶቿን አሳፍራ የመለሰች ሀገር ነበረች፡፡ ዛሬ ግን በህወሓት/ኢህአዴግ አገዛዝ ላይ የኢትዮጵያ ህዝብ ልብ እየሸፈተ በመሆኑ የውጪ ወራሪ ኃይሎችን የመመከት ወኔው እየቀዘቀዘ ስለመሆኑ ምሁራን ይናገራሉ፡፡ ለማንኛውም ክፉን ያርቅልን፡፡ ዛሬ የኢትዮጵያ እምቅ የተፈጥሮ ሀብት በመቆጣጠር ደጋፊዎቹን በማምነሽነሹ የዴሞክራሲያዊ ኃይሎችን ማሰር እና ማንገላታት በመቻሉ ጠንካራ መስሎ ቢታይም የኢትዮጵያ ህዝብ የመከራ ቀንበሩን ትከሻው መሸከም ሲያቅተው ድንገት ቢገነፍል ሀገሪቱን ከቀውስ እራሱንም ከውድቀት ማዳን የማይቻል እንደሆነ የታወቀ ጉዳይ ይመስለኛል፡፡ ይሄ ብቻ አይደለም፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ የነደደው እሳት ጎረቤቱንም ሊለበልብ ይችላል፡፡

እንደ መደምደሚያ አሜሪካኖች ምንጊዜም ቢሆን ከአንድ ሀገር ጋር የሚያድርጉት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መሠረቱ ብሄራዊ ጥቅማቸውን ከማስጠበቅ አኳያ ነው፡፡ ስለሆነም በአፍሪካው ቀንድ በተለይም በኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊና ሰብአዊ መብቶችን የሚያከብር መንግስት እንዲቆም ድጋፋቸውን ሊሰጡ ይገባል፡

ነገረ- ኢትዮጵያሚያዝያ 10 ቀን 2006 ዓ.ም. ቅፅ 1 ቁጥር 911

የኔ-ሐሳብ

እንደመግቢያ... ፖሊስ የህዝብ ነው!ይህን ርዕሰ ጉዳይ አንስቶ ለመወያየት ሰፊና ጥልቅ ምርምርን ይጠይቃል፡፡ ምናልባትም ደራሲ፣ ተርጓሚና ጋዜጠኛ ማሞ ውድነህ በፖሊስ እና ርምጃው ጋዜጣ ያለን ነገር ይኖር ይሆን? ጋዜጣውን መበርበር ግድ ይላል፡፡ ወዳጄ የሽዋስ አሰፋ በእንቁ መፅሔት ላይ ‹‹ፖሊስ የህዝብ ነው›› በሚል ርዕስ ተደባዳቢውን እና ተሳዳቢውን ባለጌ ፖሊስ ፅፎበታል፡፡ የራሱን ወገን እና ህዝቡን የሚያዋርድ፣ የሚደበድብ፣ በገዛ ህዝቡ ላይ የሚተኩስ፣ ህግን የሚጥስ ፖሊስ እንዴት የህዝብ ሊሆን ይችላል? እስኪ እንጠይቅ?ለዛሬው ፅሁፌ መነሻ ምክንያት ሊሆነኝ የቻለው ብርሃኑ ተክለያሬድ ነገረ ኢትዮጵያ ጋዜጣ ቅጽ-1-ቁጥር-7 ‹‹11 ቀናት ከጣይቱ ልጆች ጋር /የእስር ቤት ማስታወሻ/›› በሚል ርዕስ የአስነበበኝ ፅሁፍ አጥንቴ ድረስ ዘልቆ ስለገባ እና ልቤን ስለሰበረኝ በህሊናዬ እየተመላለሰ ዝምታየን ስለሰበረው የ‹ፖሊስ ህዝብ ነው!› ነገር እረፍት ስለነሳኝ እኔም የታዩኝን ለማለት ያህል ነው፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብም ይላል ‹‹ፖሊስ የህዝብ ነው!›› እኔም እላለሁ አዎ! ‹‹ፖሊስ የህዝብ ነው!›› ግን ማጅራት መችው ፖሊስ የማን ነው? ስል እጠይቃለሁ፡፡

ማርች 8፤ ማጅራት መችው ፖሊስና ‹የጣይቱ ልጆች› በነጻነት ሩጫ የ11 ቀን

እስርእኔ እንደሚገባኝ ከሆነ ህግ እንዲከበር፣ የህግ የበላይነት በጉልቤዎች አፋኝነት ድል እንዳይሆን፣ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲከበር፣ የኢትዮጵያ ልጆች በህግና በህግ በእኩል ዓይን እንዲኖሩ ህጉን የሚያስከብር፣ ለህግ የበላይነት የቆመና በህገ-መንግስቱ የተደነገጉት የሰው ልጅ ሰብዓዊና መሰረታዊ ነጻነቶችና ዴሞክራሲያዊ መብት በማንም ጉልቤ እና ማጅራት መች እንዳይጣሱ አጥር፣ ከለላ የሚሆን ፖሊስ የህዝብ ነው፤ ፖሊስም ሲመለመል፣ ሲሰለጥን፣ ወደ ሙያው ሲሰማራ ትጥቁ ጠመንጃ ብቻ ሳይሆን ህግ ነው፡፡ ጠመንጃውን ያነገተው ራሱን ከህግ በላይ አድርጎ ዜጎችን ሊረግጥ አይደለም፤ ፖሊስ የሚይዘው ዱላ ማጅራት መምቻ ከሆነ ‹‹ፖሊስ የህዝብ ነው›› ሳይሆን ‹‹ፖሊስ ማጅራት መች ነው››፤ ለማጅራት መችው ወሮበላ ፖሊስም ለራሱ ህግን የሚያስከብር ህዝባዊ ፖሊስ ሊኖረው ይገባል፡፡‹‹ፖሊስ የህዝብ ነው!›› ይህ ንግግር እንዴት ባህል ሆነ ካልን ለማጅራት መችዎች ፖሊሶች አይመችም፤ ህግን አክብረው ለሚንቀሳቀሱ ጉልበተኞች ሲያስጠነቅቁን በህግ አምላክ ስንል የህግ ጥበቃ የሚያደርጉትን ነው፡፡በኢትዮጵያ ውስጥ በዘመነ ወያኔ አገዛዝ በፖሊስ ውትድርና ስልጠና ላይ፣ በልምምድ ወቅት የወፍጮ ቤት ቱቦ የመሰለ ካኪ ለብሰው በከተማ ሲሰማሩ እና በ‹‹ውጅሌነት›› በገጠር ሲሰገሰጉ ወይም የልምምድ ስልጠና ጨርሰው በፖሊስ ሙያ በየመስኩ ሲሰማሩ በስራ ላይ እያሉ ወይም ከስራቸው ውጭ በራሱ ዜጋ ላይ ከዘራውን ያላነዘረ፣ የጎማ ዱላውን በሰው ገላ ላይ ያላሳረፈ፣ ሰውንም ከሰውነት በታች በሚያደርግ ፀያፍ ስድብ ያልዘለፈ ያላዋረደ፣ ያልደበደበ፣ ያላሰቃየ፣ ቃታ ያልሳበ፣ ቢያንስ እንኳ እራሱ ባያደርገው በእነዚህ በገዛ ወገኖቻቸው ላይ የከፋ ተግባር ለሚፈፅሙ ማጅራት መችዎች ተባባሪ ያልሆነ ፖሊስ በኢትዮጵያ ውስጥ ካለ ራሱን ነፃ ያወጣ ምን ጉድ ነው? እስኪ እኔ ነኝ ብሎ ይንገረን፡፡በባለፈው ጊዜ ነፍስ ገዳይ ፖሊሶችን እና በፍ/ቤት ጥፋተኛ ተብለው የተቀጡትንና የሰሩትን የወንጀል አይነት በመዘርዘር አዲስ አድማስ ጋዜጣ ያስነበበኝ መሆኑን አስታውሳለሁ፡፡ ለዚህ ዘገባም የአገሪቱ ፖሊስ ተቋማትና ፖሊሶች የሰጡት ምላሽም ሆነ ምንም አይነት ማስተባበያ ወይም ጥናታዊ ጽሁፍ አለመኖሩን ሳስብ ደግሞ እንዴት ‹‹ፖሊስ የህዝብ ነው!›› ለማለት እንደምንደፍር ግራ ይገባኛል፡፡ ምክንያቱም ተቋሙም ሆነ ፖሊሱ እንደ ባለሙያ

በሳሙኤል አወቀ

ማጅራት መችው ፖሊስም የህዝብ ነው እንዴ?

ፖሊስ የህዝብ ነው ብሎ ወንጀለኞችንና ማጅራት መችዎችን ከህዝብ ጋር ሆኖ እንዲጠየቁ ሲያደርግ አላየሁምና፡፡ ለዚያውም ለህግ የበላይነት አምርረው የተነሱ እና አጋጣሚውን ተጠቅመው ለፍርድ የበቁ ዜጎች በመኖራቸው እንጂ ለመረጃ እና ሚዲያ ሳይወራ የሆኑ የገጠር ክፍሎች የሚፈፀመውን ጊዜ ያወጣው፡፡ እና እነዚህ ፖሊሶች የህዝብ ናቸው እንዴ? እውነት ባልተወለደ አንጀቱ በያዘው ጠብመንጃ በባህር ዳር ከተማ በምሽት ላይ ንፁሃን ዜጎችን እንደወጡ ያስቀረው ጨፍጫፊው ፖሊስም የህዝብ ፖሊስ ነው? ኧረ እንዴት ያለነገረ ነው?እስኪ የጣይቱ ልጆች ምን አሉ? ምን አጠፉ? የኢህአዴግ እናት ሊጎችና የሴት ሊጎች በአልገባቸው የዘር አጥር መርዘኛ ፕሮፕጋንዳ የኢትዮጵያን አንድነት ለማጥፋትና ለመወያየት ወያኔ ባረቀቀው የዘረኝነት ከፋፋይ ፖለቲካ ተሸውደው ትርጉሙን እንኳ በግልፅ ሳይገባቸው ‹‹ብሔር፣ ብሔረሰቦች፣ ህዝቦች›› …….እያሉ ሲያላዝኑና ሲጮሁ ምን ተባሉ? እውነት ግን ይህ የኢትዮጵያን ህዝብ ፍላጎት ይወክል ይሆን? ወያኔ የመደማመጫ በሮችን ሁሉ ዘግቶ በየት መሃል ትክክለኛው ሃሳብ ሊወጣ ይችላል?7ቱ የጣይቱ ልጆች ምን አሉ? የጣይቱ ልጆች ያደረጉት ነገር ቢኖር በዓለም የሴቶች ቀን ‹‹ማርች 8›› ኢህአዴጎች ለብሔር፣ ብሔረሰቦች፣ ህዝቦች ሲሮጡ እነርሱ ደግሞ ለኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ሴቶች ነፃነት ሮጡ፡፡ በቃ ይህ ነው ወንጀላቸው! ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ወንጀል ከሆነ፡፡ ‹‹ተከብረሽ የኖርሽው በአባቶቻችን ደም እናት ኢትዮጵያ የደፈረሽ ይውደም›› ‹‹የጣይቱ ልጆች ነን! ፍትህ እንፈልጋለን! እኩልነት እንፈልጋለን! በጨለማ መኖር ሰልችቶናል! ያለውሃ መኖር ስልችቶናል! እስረኞችን ማሰቃየት ይቁም! የፖለቲካ እስረኞችና ይፈቱ!›› ነው ያሉት፡፡ ይህ

ደግሞ በኢህአዴግ ህገ-መንግስትም በዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ድንጋጌም የተረጋገጠ የሲቪልና የፖለቲካ መብት ነው፤ ፖሊስ ይህን ካላከበረ እንዴት የህዝብ ሊሆን ይችላል? እኔ ግን እላለሁ... ፖሊስ የኢህአዴግ ብቻ ነው እንዴ? ኢህአዴግስ የማን ነው ማንን ነው የሚገዛ? ከፈለገ ራሱን ይግዛ እንጂ የጣይቱ ልጆች ግን ነፃነትን ናፍቀዋል፡፡ እናም አገዛዙ አይቀጥልም፡፡ የጣይቱ ልጆች ለነጻነት ሮጠው ሩጫው ሲጠናቀቅ አረፍ ሊሉ ሲሉ ሲከታተሏቸው የነበሩ የወያኔ ደህንነቶች አላወቋቸውምና ከመንጋው እንዳይቀላቀሉባቸው ሰግተው ነበር፡፡ ‹‹ቁረጥ፤ ቁረጥ፤ እርሱ ጋር ቁረጥ››… የሚል ድምጽ ሰማሁ ይላል የዓይን ምስክሩ ብርሃኑ ተክለያሬድ በማስታወሻ ፅሁፉ! የጣይቱ ልጆች በመንጋዎች መሃል ለነፃነት ጥሪ ለፍትህ ለእኩልነት ሲጮሁና ሲዘምሩ ‹‹እምባየ በአይኔ ግጥም ዓለ›› ይላል፡፡ አዎ! ልክ ነው ጣይቱ የጣሊያን ጦርነትን በመላና በዘዴ በማስተባበር ከቅኝ ግዛት መንጋጋ እንድንወጣ ዛሬ የአፍሪቃ የነፃነት ተምሳሌት የኢትዮጵያ ልጆች እንድንሆን የበኩሏን ታሪክ ሰርታ በአርዓያነት አልፋለች፡፡ ‹‹ጣይቱይዝም›› የነፃነት ታጋዮችም የጣይቱን ታሪክ አንስተው የህወሃት ዘረኛ ፖለቲካና ባንዳዊ አስተዳደር ለመታገል ቆርጠው በመነሳታቸው በፍቅር፣ በእልህ፣ በወኔና በፅናት ልናነባ ይገባል፡፡ ልንከተላቸውም ማቅማማት የለብንም፡፡ ብዝበዛና ጭቆና እረፍት ነስቶናልና፡፡ ለነፃነት፣ ለፍትህ፣ ለእኩልነት ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውያን ስንል ማጅራት መችዎችን ተቋቁመን፣ ፍፁም ሰላማዊ ሆነን ሩጫው ይቀጥላል፡፡ የወያኔ ስርዓትም ተንኮታኩቶ ይወድቃል፡፡ ያኔም የነፃነትን ዋጋ ያውቀዋል፡፡ የማጅራት መችዎች ጉልበትም ይልፈሰፈሳል፡፡ ህዝባቸውን ለመጨፍጨፍ ያነገቱት ጠመንጃም ያዝላቸዋል፡፡ የአገር ክህደት አዝለፍልፎ ይጥላቸዋል፡፡ ብርሃኑ በማምረር እንዲህ ሲል ይጠይቃል…‹‹ኦ! ኢትዮጵያ እስከ መቼ ልጆችሽ በአመለካከት ልዩነት ይታሰራሉ? እስከ መቼስ አምባገነኖች ቆራጥ የህዝብ ልጆችን ያለ ከልካይ እያሰሩ ይደበድባሉ? ለማን አቤት ይባላል…….›› ይላል፡፡ እኔ ‹‹ማጅራት መች ፖሊሶች›› በህዝብ ፖሊስ እስኪቀየሩ ይመስለኛል፡፡ የጣይቱ ልጆች ትግልም ለዚህ ነውና የማይቀረው ለውጥ ያስተካክለዋል፣ እርግጠኛ ነኝ፡፡ ያኔ ከለውጥ በኋላ ለነፃነት፣ ለፍትህ፣ ለእኩልነት፣ በመጮህ ጊዜ አናጠፋም፡፡ የነፃነት ጮራ ይፈነጥቃል፡፡ ፍትህ ለሁሉም ትሆናለችና ያኔ የኢትዮጵያ ልጆች በህግ የበላይነት እና በዴሞክራሲያዊ ስርዓት ሲተዳደሩ የህዝብ ፖሊሶች እንጂ ማጅራት መች ፖሊሶች የሉም፡፡ የዚያን ጊዜ ‹‹ኮማንደር›› የሚል ማዕረግ የለጠፉ ማጅራት መች ፖሊስ እንደማይኖር እርግጠኛ ነኝ፡፡ ትግሉ መራር ነው፡፡ ከጣይቱ ልጆች ጋር ግን ጊዜው አጭር ይሆናል፡፡

የእስር ቤቱ መዝሙርና የእስር ቤቱ ዋርድያ

የብርሃኑን ማስተዋሻ ሳነብ እጅግ በጣም ሃፍረት የተሰማኝ ደግሞ የ29 እስረኞች ክፍል /ጉረኖ/ የ‹‹ሌብነት መዝሙር›› እና የሰማያዊ ወጣቶች የነፃነት፣ የፍትህ፣ የእኩልነት፣ የኢትዮጵያና የኢትዮጵያዊነት በእስር ቤቱ ውስጥ መዝሙር ሲዘመር እና የእስር ቤቱ ጠባቂ /ዋርድያ/ ፖሊሱ ሁኔታ ነው፡፡ ይኸውም ብርሃኑ እንደመሰከርልን የሌቦች መዝሙር በእዚያች ስርዓት በእስር ቤቱ ውስጥ ብሔር፣ ብሔረሰቦች በሚለው ዜማ …‹‹ሌቦች….ሌቦች ….ነን ሌቦችእኛ የሸገር ልጆችየምንዘርፈው ወደ ቦሌመጨረሻችንም ነው ከርቸሌታሰርንም በዋስ እንወጣለንተመልሰንም እንሰርቃለንእኛ ልጆችሽ ተደራጅተን እንዘርፋለን በቀን …..በቀን … ላላላላላላ…..ላላላለላላላለላ…..›› የሚለው እና 3ቱ የሰማያዊ ፓርቲ ወጣት አመራሮች ከ29 እስረኞች የሌብነት መዝሙር በኋላ የመዘመር ተራቸው ደርሶ እንዲዘምሩ ሲታዘዙ /በገጠር ደረቅ ጣቢያ እስር ቤቶች ውስጥ እስረኛ ሲገባ አዲስ እስረኞች በነባር እስረኞች ተገርፎም ቢሆን የመብራት/የላባ/ ክፈል ተብሎ ገንዘብ ተገዶ ይክፈላል፡፡ ገንዘብ ከሌለው ዘፈን፣ እስክስታ፣ ሽለላ፣ ቅረርቶ፣ ያቀርባል/ እንደዚያ መሆኑ ነው ተጠርጣሪዎች ሰማያዊዎችን አላወቁምና ጋበዟቸው፡፡ እነርሱም እንዲህ ሲሉ መዘመር ጀመሩ፡-‹‹የትግል ጉዞው ታሪካዊ አላማው ፍፁም ህዝባዊራዕያችንም ኢትዮጵያዊ ፓርቲያችን ነው ሰላማዊ››…….እያሉ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው መዘመር ሲጀምሩ የእስር ቤቱ በር በሃይል እንደተንጓጓ ገልፆ ምን እንደተከሰተ ሳይጨርስልን የብርሃኑ ፅሁፍ እንደ ፊልም ልብ አንጠልጥሎ ‹ይቀጥላል›…… ብሎን ተቋርጧል፡፡ ይቀጥላል፡፡ ……ትግሉም እንደዚህ ነው፤ የጣይቱ ልጆች የነፃነት የፍትህ የእኩልነት ጥያቄ እስካልተመለሰ ድረስ ሰላማዊ ትግሉ ይቀጥላል ……እኔ ግን ያስደነገጠኝ፣ የደነዘዘኝ የተጠርጣሪዎች መዝመር ለዋርዲያው ፖሊስ አልተሰማውም ይሆን ወይስ ሟቹ የኢፌዴሪ ጠ/ሚ/ር መለስ ዜናዊ ‹‹መስረቅ ስራ ነው መያዝ ወንጀል ነው›› ያለውን ነውረኛ አስተሳሰብ ተቀብሎታል ይሆን ወይ? ይህ ፖሊስ የሌቦች ፖሊስ ወይስ የህዝብ ፖሊስ ይሆን? እኔም እላለሁ፡፡ የሌብነት ስርዓት አራማጅ የሌቦች ፖሊስ የህዝባዊ ፖሊስ ይሆን ዘንድ ኑ! ለነፃነታችን እንታገል ጉዞአችንን ከጣይቱ ልጆች ጋር ይሆናል፤ ትግላችንም ይሰምራል፤ ያኔ ማጅራት መች ፖሊሶች ያፍራሉ፤ ሌቦች በህግ ይዳኛሉ፡፡አንዳንድ ጊዜ ስለ ወያኔ ስርዓት ፖሊሶች ሳስብና የሚቀለድባቸውን ስሰማ በተለይ በምርጫ 97 ምክንያት ብዙ ተቀልዶባቸዋል፡፡ ምን አልባት የፖሊስ መለዮ ለብሰው ፖሊስና ህዝቡን አለያይተው ህዝብና ፖሊስ ተባብሮ ህግ እንዳይከበርና አምባገነኖች እንዳይወርዱና እንዳይጠየቁ በስልጣናቸው ተቆናጠው ለመኖር ሲሉ የፖሊስ ገፀ ባህሪ ፈጥረው ከባዕድ አገር የተሰገሰጉ እና በፖሊስ ስም የሚነግዱ አስመሳይ የወያኔ ቅጥረኞች ይኖሩ ይሆን? ስል እጠይቃለሁ፡፡ ይህን የሚያውቁት ማጅራት መች ፖሊሶች ናቸው፡፡ የኢትዮጵያ ልጆችማ በማጅራት መችዎቹ መለዮ ለባሾች እና ጠመንጃ አንጋቾች ነፃነታቸውን ተነጥቀው እየተገደሉ፣ እየተደበደቡ እየታሰሩ፣ እየተሰቃዩ፣…. ‹‹ፖሊስ የህዝብ ነው!›› ሲሉ ጨዋ ባህልን ጠብቀው ከማጅራት መችዎች ጋር በስቃይ ይኖራሉ፡፡ፖሊስ የህዝብ ከሆነ የህዝብ ነን የሚሉት ከማጅራት መችዎች እራሳቸውን ለይተው ለህዝብ እና ለህግ መቆማቸውን ያሳዩን እላለሁ፡፡ ቸር ያሰማን፣ ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!

የሰብአዊ መብት ድንጋጌም የተረጋገጠ የሲቪልና የፖለቲካ መብት ነው፤ ፖሊስ

ይህን ካላከበረ እንዴት የህዝብ

ሊሆን ይችላል? እኔ ግን እላለሁ... ፖሊስ የኢህአዴግ ብቻ ነው እንዴ? ኢህአዴግስ

የማን ነው ማንን ነው የሚገዛ?

ነገረ- ኢትዮጵያሚያዝያ 10 ቀን 2006 ዓ.ም. ቅፅ 1 ቁጥር 9 12

ከገፅ 7 የዞረ መንግስት ለምን ...የተዘፈቀ እና ገዥው አካል ለያዘው ዕኩይ ዓላማ ድጋፍ እንዲያገኝ ዜጎችን በግድ ያለውድ አባል እንዲሆኑ የማጥመቂያ መሳሪያ ነው፡፡ ገዥው አካል ለወጣቱ ደረጃውን ያልጠበቀ ጥራት የሌለው ትምህርት በማቅረብ እና ከዘመኑ ጋር የሚሄዱ የመማሪያ ዕድሎችን በመንፈግ ለዘላለም ወጣቱን የእውቀት ሽባ አድርጎ ማስቀመጥ ብቻ አይደለም ዓላማው፡፡ ሆኖም ግን ወጣቱ በኢንተርኔት አጋዥነት ህይወቱን ለመለወጥ የሚያስችለውን ዕውቀት እንዳይሸምት እና የሀገሩን መጻኢ ዕድል እንዳይወስን ለማድረግ የተሸረበ እኩይ ምግባር ጭምር እንጅ፡፡እ.ኤ.አ በመስከረም 2010 “አገር አቀፍ ማጥመቅ” በሚል ርዕስ ትምህርትን ለፖለቲካ ጥቅም እያዋለ ባለው የአቶ መለስ አገዛዝ ላይ የሰላ ተችት አቅርቤያለሁ፡፡ “የትምህርት ሚኒስቴር” ከጥቂት ዓመታት በፊት ያወጣው የርቀት ትምህርትን ህጋዊ ያለመሆን (የትምህርት ፕሮግራሞች በተለመደው መልክ በዩኒቨርስቲ ግቢዎች የመማሪያ ክፍሎችን በመጠቀም ካልሆነ በስተቀር) በሚል በአገር አቀፍ ደረጃ የተላለፈው የዕግድ መመሪያ (የኦርዌል አንዱ የሆነውን “የዕውነት ሚኒስቴር” (ድንቁርና) እንዳስታውስ አደረገኝ፡፡ በሚያስገርም ሁኔታ አቶ መለስ እና ቁንጮ የጦር አበጋዞቻቸው “የድህረ ምረቃ ትምህርታቸውን” የተከታተሉት በውጭ አገር የርቀት ትምህርት ፕሮግራም አማካይነት ነው፡፡) ገዥው አካል የህግ እና የትምህርት ሙያዎችን በመንግስት ቁጥጥር ስር ባሉት ዩኒቨርስቲዎች ብቻ እንዲሰጡ በማወጅ የፓርቲ ዕጩ አባላትን በመቀፍቀፍ የትምህርት እና የህግ ሙያዎችን በጅምላ ጠቅልሎ ለመያዝ የታለመ መሰሪ ተግባር እንደሆነ ገልጫለሁ፡፡ በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት የአካዳሚክ ነጻነት የለም፡፡ እ.ኤ.አ የካቲት 2008

“አምባገነንነት በአካዳሚው ማህበረሰብ ውስጥ“ በሚል ርዕስ በመቀሌ ዩኒቨርስቲ የህግ ትምህርት ቤት ውሰጥ የአካዳሚክ ነጻነት እጦት በሚል ርዕስ ትኩረትን የሳበ ትችት አቅርቤ ነበር፡፡

ገዥው አካል ህዝቡን የሚሰልለው ለምንድን ነው?

ገዥው አካል ህዝቡን በሚስጥር ይሰልላል፡፡ ምክንያቱም ህዝቡን ስለሚፈራው ነው፡፡ እ.ኤ.አ በ1962 ፕሬዚዳንት ጆን ኬኔዲ ለአሜሪካ ህዝብ እንዲህ የሚል ሀሳብ አቀረቡ፣ ‹‹ደስ የማይሉ እውነታዎችን፣ የውጭ ሀሳቦችን፣ ባዕድ ፍልስፍናዎችን እና ተወዳዳሪነት ያላቸውን እሴቶች ለአሜሪካ ህዝብ ኃላፊነት ለመስጠት አንፈራም፡፡ ለአንድ አገር ህዝቡ እውነታውን እና ሀሰቱን በግልጽ አደባባይ እንዲዳኝ የማይሰጥ መንግስት የእራሱን ህዝብ የሚፈራ ብቻ ነው፡፡›› በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል ህዝቡን ይፈራል፣ እናም የተጠናወተውን የፍርሀት በሽታ ለማስወገድ ሲል ህዝቡን በሚስጥራዊ የምርመራ ፕሮግራሞች መሰለል እና ማስፈራራትን እንደመፍትሄ ወስዶ በመተግበር ላይ ይገኛል፡፡በጣም በአሳዛኝ ሁኔታ የሚያስገርመው እውነታ ግን በአሁኑ ጊዜ እንደ ሃይማኖት የያዘው ሚስጥራውነት በህገመንግስቱ ላይ ያለውን የመረረ ጥላቻ ያመላክታል፡፡ በአንቀጽ 12 (1) ስር ‹‹የመንግስት ተግባራት እና ተጠያቂነት›› በሚል የተጠቀሰው የኢትዮጵያ ህገመንግስት መንግስትን ለግልጽነት እና ተጠያቂነት ኃላፊነት እንዳለበት በግልጽ አስቀምጦታል፡፡ እንዲህም ይላል፣ ‹‹መንግስት የሚያከናውናቸው ተግባራት ሁሉ ግልጽነት ባለው ሁኔታ በይፋ ለህዝብ ግልጽ ይደረጋሉ፡፡›› ገዥው አካል ይህንን ህገ መንግስታዊ ድንጋጌ በተቃራነው ወስዶ

‹‹የመንግስት እንቅስቃሴ በአጠቃላይ ሚስጥራዊ እና ለህዝቡ ግልጽነት በጎደለው ሁኔታ ተግባራዊ ይደረጋል የሚል ትርጉም በመስጠት በዚሁ መሰረት ትኩረት ሰጥቶ እየፈጸመው ይገኛል፡፡›› ሚስጥራዊነት ህዝቡን ለማታለል ጠንካራ መሳሪያ ነው፡፡ደህና፣ “ታላቁ ወንድም” አቶ መለስ ዜናዊ ላይመለሱ ከኢትዮጵያ ወደ ዘላለማዊው ዓለም ሄደዋል፣ ሆኖም ግን “በእርቀት የምስል ማሳያ የኤሌክትሮኖክ ሰሌዳ” ላይ ብቅ እያሉ እና በመቃብራቸው ውስጥ በመንፈስ ሆነው “ታናናሽ ወንድሞቻቸውን” ማለትም “የውስጣዊ ፓርቲ” አባላትን በማዘዝና በማገልገል ላይ ይገኛሉ፡፡ አሁንም ራዕያቸውን ያልማሉ፣ ያስተውላሉ፣ ይመለከታሉ፣ ያጮልቃሉ፣ አተኩረው ያያሉ፣ የስለላ ተግባራትን ያካሂዳሉ፣ ለብዙ ጊዜ አፍጥጠው ይመለከታሉ፣ ያዳምጣሉ፣ ያነፈንፋሉ፣ እናም ድምጻቸውን ከፍ አድርገው አደንቋሪ መዝሙራቸውን ይዘምራሉ፣ እንዲህ እያሉ፣… ፓርቲው በአጠቃላይ ለእራሱ ሲል ስልጣንን ጠቅልሎ መያዝ አለበት፡፡ ለሌሎች ደግነት ደንታ የለንም፣ እኛ ፍላጎታችን ከስልጣናችን ንጹህ ስልጣን ላይ ተንጠልጥለን መቆየት ብቻ ነው፡፡ ንጹህ ስልጣን ማለት በአሁኑ ጊዜ ምን ማለት እንደሆነ ትገነዘባላችሁ የሚል እምነት አለን፡፡ እኛ ምን እንደምናደርግ ስለምናውቅ ከአለፉት ንጉሳዊ አገዛዞች እንለያለን፡፡ ሌሎቹ በሙሉ እኛን የሚመስሉት እንኳን ፈሪዎች እና አስመሳዮች ነበሩ፡፡ የጀርመን ናዚዎች እና የሩሲያ ኮሙኒስቶች በአሰራር ዘዴያቸው እኛን ይመስላሉ፣ ሆኖም ግን የእራሳቸውን ፍላጎት ለመገንዘብ ድፍረቱ አልነበራቸውም፡፡ ያስመስሉ

ነበር፣ ምናልባትም ስልጣንን ከፈቃድ ውጭ እና ለተወሰነ ጊዜ በመያዝ ማስመሰያነት እያቀረቡ የሰው ልጆች በምድረ-ገነት በነጻ እና በእኩልነት ይኖራሉ እያሉ ከንቱ ስብከት ይሰብኩ ነበር፡፡ እኛ እንደ እነርሱ አይደለንም፡፡ ማንም እስከ አሁን ስልጣን ይዞ በራሱ ፈቃድ ስልጣኑን አሳልፎ እንደማይሰጥ እናውቃለን፡፡ ስልጣን በእራሱ መንገድ አይደለም፣ ግብም አይደለም፡፡ ማንም አብዮትን ለመጠበቅ ሲል አምባገነንነትን አይመሰርትም፡፡ የማሰቃየት ዓላማው ማሰቃየት ነው፡፡ አሁን ግንዛቤ ማግኘት እንደጀመራችሁ ይገባኛል፡፡የኢትዮጵያ የውስጥ ፓርቲ ስለ21ኛው ክፍለ ዘመን ጥቂት እውነታዎችን መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡ ሚስጥራዊነት ደካማነት ነው፣ ድንቁርና ደደብነት ነው፡፡ ነጻነት የሰው ልጅ ውስጣዊ ባህሪ መገለጫ ነው፣ እናም እውነት እነሱን እና ኢትዮጵያውያንን/ትን በሙሉ ነጻ ታወጣለች፡፡ ኦርዌል እንዲህ በማለት ጽፈው ነበር፣ “ሸፍጥ በተንሰራፋበት ስርዓት ውስጥ እውነትን መናገር አብዮታዊ ድርጊት እንደመፈጸም ያህል ይቆጠራል፡፡ ሆኖም ግን ጸጥ ማለት እንደ አብዮታዊ ድርጊት ቅቡል በሚሆንበት ጊዜ ምን ማድረግ ይቻላል?““በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ምሁራን፣ አካዳሚክስ፣ ፕሮፌሰሮች እና የተማረው ልሂቅ ትውልድ የደንቆሮዎችን አምባገነንነት በተጨባጭ ተግባራት በምስክርነት እየተመለከተ እንደ ድንጋይ ሀውልት ተገትሮ ጸጥ ካለ በእያንዳንዷ ጉዳይ ላይ ድምጽ ለሌላቸው ድምጽ የሚሆኑ ዜጎች ኃላፊነት በጥቂቶች ላይ ብቻ የሚወድቅ በመሆን ሸክሙ የበዛ ይሆናል፡፡” “የትምህርት ሙስና እና ኢትዮጵያን ማደንቆር“ ከሚለው ቀደም ሲል ካቀረብኩት ትችቴ የተወሰደ ነው፡፡ እንኳን ወደ አስከፊዋ የፌዴራል ሬፑብሊክ ኢትዮጵያ በሰላም መጣችሁ!ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!

ህዝብም ይህ ብዙም የሚያሳስበው ጉዳይ አይመስለኝም፡፡ ስለማያገኘው የአገልግሎት ጥራትና ተደራሽነት እንጂ፣ በእርግጥ ይህ ተቋም በመንግስት እጅ ባይሆን ከዚህ በተሻለ ሁናቴ ጥራትና ተደራሽነት ኖሮ መንግስትም አሁን ከሚያገኘው ገንዘብ የላቀ የግብር እና ታክስ መሰብሰብ እንደሚችል አምናለሁ፡፡ ለነገሩ የኢህአዴግ መንግስት የሚያሳስበው የሕብረተሰቡ አገልግሎቱን ማግኘትና ማጣት እንዲሁም የሚሰበስበው ትርፍ ሳይሆን ቴሌኮም በግሉ ክፍለ ኢኮኖሚ ቢሆን የሚያጣው የሕብረተሰቡን የመረጃ ነፃነት ማፈን እና የፖለቲካ አቅም ነው፡፡ ሐ) መብራት ኃይል፡- ሕዝቡ ባለ በሌለ አቅሙ መብራት ይጠልፋል፡፡ ህዝብ ቆጣሪ ያስገባል፡፡ መብራቷን ግን በተደጋጋሚ መጥፋቷን አላቋረጠችም፡፡ መብራት ኃይል ላላበራንበት ማስከፈሉ ሳያንሰው መብራቷ ጠፍት ብልጭ በምትልበት መካከል ለሚቃጠሉት የቤት እቃዎች ኃላፊነት ቢወስድ አንዳንድ ቦታዎችምኮ መብራት ለማስገባት ያወጣነውን ወጪ ምናለ ጥሩ ፋኖስ በገዛንበት የሚሉ ሰዎች እንዳሉ ታውቃላችሁ አይደል?መ) የትራንስፖርት ተቋማት፡- ሀ) የከተማ አውቶብስ (ባስ)፡- በተለይ በአዲስ አበባ ከፍተኛውን የሕዝብ ቁጥር በማመላለስ የአንበሳውን ድርሻ የሚይዘው አንበሳ ከተማ አውቶብስ ነው፡፡ ዳሩ የገንዘብ ክፍል ያው የቀነሰ ቢመስልም ሕብረተሰቡን በመዝረፍ ረገድ ተወዳዳሪ የሚገኝለት አይመስለኝም፡፡ በተለይ የሚዘርፈው ጊዜ በገንዘብ ቢተመን (በዘመናዊው ዓለም ጊዜ ገንዘብም አይደል ታዲያ!) ሕዝቡ ያለምንም ከለላ በፀሐይና በብርድ ሲቆራመት የተቋሙ ባለስልጣናት፤ ሹፌሮችና ትኬት ቆራጮች ምናቸው ነው? ጠዋት 2 ሰዓት መድረስ ያለበት ባስ ምናልባት የሚደርሰው 3 ሰዓት ላይ ይሆናል፡፡ ሕዝቡ ታዲያ ከስራ መግቢው ረፈደ አልረፈደ ተሳቆ ምናልባት መቀመጫ ባገኝ ብሎ በባስ ፌርማታ አካባቢዎች ላይ ያለውን የሚሰነፍጥ ሽታ እየሳበ በሽታ እየሸመተ ይጠብቃል፡፡ ዳሩ ሲመጣ ወይ ሞልቶ ሊሆን ይችላል አለያም ሳይሞላም በፌርማታው ሳይቆም እብሰ ሊል ይችላል፡፡

ይህ ሕዝብ ‹‹ልወዝውዘው በእግሬን!›› እያንጎራጎረ በእግሩ እንኳ ልሂድ እንዳይል ተስፋ ያስቆርጠዋል፡፡ ተስፋው እውን እንዳይሆን አይኑ እያየ በጠራራ ፀሐይ ጊዜና ገንዘቡን የሚዘርፈውን ተቋም ይመለከታል፡፡ በየጊዜው ይህን ያህል አውቶብሶች ተገዙ ይባላል፡፡ ዳሩ የሕዝቡ ችግር በኢቲቪ ወሬ ካልሆነ በቀር ሲፈታና ሲቃለል አይስተዋልም፡፡ አሁን አሁንማ አዛውንቶችንና አካል ጉዳተኞችን ማስቀደምም እየቀረ ነው፡፡ ሕፃናትም ከመጋፋት ውጪ አማራጭ አጥተዋል፡፡ በባሰ የሚሳፈረው ወጣትም አያቱ ለሚሆኑት አቅመ ደካማ አባት ወይም እናት መነሳት እንደነውር እየቆጠረው ያለ ይመስላል፡፡ ኧረ የህሊና ያለህ!!!ቢሆንማ ለአካል ጉዳተኞች ተሸከርካሪ ወንበር ማስገቢያ ድራምፕ/ተዳፋት በእያንዳንዱ የከተማ አውቶብስ ላይ መግጠም በተገባ ነበር፡፡ ሀገራችን የፈረመቻቸው ዓለም አቀፍ የአካል ጉዳተኞች መብት ኮንቬንሽኖችም የሚያዙት ይህ እንዲሆን ነው፡፡ በሀገራችን ላይ አውቶብስ ድራምፕ እንዲሰራ ቢደረግ ለአካል ጉዳተኞች ብቻ ሳይሆን ለአዛውንቶችም ለነፍስ ጡሮችም በተሸለ መልኩ ማገልገል በቻለ ነበር፡፡ ዳሩ ለዘረፋው እንጂ ለግልጋሎት የሚተጋ የአውቶብስ ተቋም ለጊዜው የለንም፡፡ ለነገሩ የከተማ አውቶብስን አነሳሁ እንጂ ሀገር አቋራጭ አውቶቡሶችም ቢሆን ህዝብን ለማጉላላት፤ ያልተፈቀደ ታሪፍ ለመጨመር ማን ብሏቸው?እናንተ የሀገር አቋራጭም ሆነ የከተማ አውቶብስ አመራሮች፤ ሹፌሮች ረዳቶችና ቲኬት ቆራጮች የህዝብን ሮሮ እያዩ እንዳላዩ መሆን ተገቢ ነውን? በዚህ ልክ ጊዜና ገንዘብን መዝረፍስ ህሊና ካለው ይጠበቃልን? የአውቶብስ እጥረት ቢኖር እንኳ መፍትሔዎችን መሻት እንጂ እንዲህ ዜጎችን ማንገላታት ከወጣችሁበት ማህበረሰብ ሞራልና የሀይማኖት እሳቤ ጋርስ ይሄዳልን?በሀገራችን ላይ ከአውቶብስ ውጪም በታክሲ ለመሄድ የገንዘብ አቅም ቢኖርዎትም ግፊያና ሰልፍ ያንኑ ያህል ነው፡፡ ሰልፍ ታዲያ ልክ እንደ ባሱ ሁሉ በእድሜ የገፋ እና አካል ጉዳተኞችን ሲያስቀድም አይሰተዋልም፡፡ በተለይ ረዥም ከሆነ አልፎ አልፎ ግን አንዳንድ አስተዋዮች ቅድሚያ ሲሰጡ ሲታዩ

ጦቢያ እውነትም ሰው እንዳላጣች ይገነዘባሉ፡፡በተለይ በስራ መግቢያና መውጫ ሰዓት አውቶብስ ለመጠበቅ ያለውን ሰልፍና ግፊያ ስታዩ ህዝቡ የተሰለፈው ፖለቲካ ሪቮሉሽን ለማስነሳት ይመስላል፡፡ ልጅ እያለሁ ሁሌ ለምን እንደምንሰለፍ (ት/ቤት) ግራ ይግባኝ ነበር፡፡ ለካስ የሀገራችን ኑሮ ሁሌ ሰልፍ ስለሆነ እንድንለማመድ ኖሯል፡፡ ለባስ ሰልፍ ካፌ፤ ሱቅ፤ … ሰልፍ ሁሌ ሰልፍ! በአረቡ ዓለም አብዮት ሲነሳ ለምን እዚህ እንዳልተነሳ ታውቃላችሁ? ህዝቡ ለብዙ ነገር ሲሰለፍ ስለተዳከመ ለፖለቲካው ለውጥ መሰለፍ ስላልቻለ እኮ ነው እንጂ ተመችቶን ወይም ፈርተን መሰላችሁ….ለ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ፡- አይገርማችሁም! ሌላው በጠራራ ፀሐይ ዘራፊ ተቋማችን የአፍሪካችን ኩራት የሆነው ኢትዮጵያ አየር መንገድ ነው፡፡ ከማን ይዘርፋል? ካላችሁኝ በተለይ አረብ ሀገር ከሚሄዱና ከአረብ ሀገርት ከሚመጡ አንገታቸውን ደፍተው ሊሰሩ ከሚሄዱና ሰርተው ከመጡ ወይም ህይወትና ዓለም አልጣጣም ብሏቸው በህመም ምክንያት በውጪው ዓለም ሊታከሙ ከሚሄዱና ታክመው ወይም ብሶባቸው ‹‹ለሀገሬ አፈር አብቃኝ!››

ብለው ከሚመጡ ዜጎች ነው፡፡ ሌላው ህብረተሰብ በመጠኑም ቢሆን የአየር መንገዱን ዘራፊነት ነቄ ስላሉ ካገኟቸው ጥቂት አጋጣሚዎች በሌሎች አየር መንገዶች ስለሚጠቀሙ ብዙም አይዘረፉም፡፡ ለነገሩ ስላልቻለ እንጂ አየር መንገዳችን ሌሎች አየር መንገዶችን ቢያግድ ደስታው እንደሚሆን ላይታለም የተፈታ ነው፡፡ ምክንቱም ለዘረፋ አይመቹትማ!ፍትሐዊ የሆነ ውድድር እኮ ለዘረፋ አይመችም፡፡ የሀገሬ ሰው ‹‹አልበር እንደ አሞራን›› ሁሌ የሚያንጎራጉረው በዘመናዊ ዓለም በአየር መብረር እንደሚቻል ሳይረዳ ቀርቶ እኮ አይደለም፡፡ ለመብረር የሚከፍለው ክፍያ አሞራ እንደ መሆን ሁሉ የማይቻለው ቢሆንበት እንጂ! ሰሞኑን ሀገረ ኬንያ በቦይንግ አውሮፕላኖች በቀነሰ ዋጋ ዜጎቿን ለማጓጓዝ መወሰኗን ሰምታችኋል፡፡ መቼም፤ የእኛዎቹ የሀገር ውስጥ በረራ አባት አውሮፕላኖች /ፎከር አውሮፕላኖች/ ግን በአየር መብረሩን ለባለስልጣናት ለአንዳንድ ጠንካራ ገቢ ላላቸውና ለዘራፊዎች ብቻ እንድንተው በሚያስከፍሉት ዋጋ ጮክ ብለው ነግረውናል፡፡ በሚያስከፍሉት ክፍያ ፍርሐት አውሮፕላንን ቀርቤ አይቼ እንኳን የማላውቀው እኔ ከዚህ በላይ ስለ አየር መንገዳችን አላውራ መሰለኝ!‹‹በቂ የሆነ አማራጭ እንዳይኖር እየተደረገ እና ያለውም ተቋም እራሱን ሳያሻሽል ወይም በሚገባ ተግባሩን እንዲፈፅም ሳይሆን ሕብረተሰቡ በአንድ ነገር ብቻ ፍትሐዊና አግባብ ባልሆነ ክፍያና ሁናቴ እንዲጠቀም ማድረግ ሕሊና ቢሶች የሚፈፅሙት ሌብነትና ዘረፋ ነው፡፡ ብዙዎቹ የሀገራችን ሌቦች ቢሰርቁ እንኳን እንጥፍጣፊ ሞራል ስላላቸው ሲዘርፉ አይገድሉም፤ ሲሰርቁም ለተሰረቀው የሚጠቅሙ ለሌባው ግን እርባና የሌላቸውን ነገሮች ይመልሳሉ ወይም ይተዋሉ፡፡ ለምሳሌ ስልክ ሲሰርቁ ሲም ካርድ ይመልሳሉ፡፡ ብር ቢሰርቁ መታወቂያ፣ ፓስፖርትና ሌሎች አስፈላጊ ዶክመንቶችን ይተዋሉ፤ ከአንዳንዶች ፍፁም ሞራላዊ ሕሊና ከሌላቸው በስተቀር እኔ እንዲያውም የአንዳንድ የኢትዮጵያ በጠራራ ፀሐይ ዘራፊ ተቋማት የሁለተኛው ዓይነት ባህሪ ያላቸው ሌቦችና ዘራፊዎች ተግባር እየፈፀጀሙ ያሉ ይመስለኛል፡፡ ከሕዝቡ የሚሰርቁት የሚዘርፉት የሚፈልጉት ብቻ ሳይሆን የማይፈልጉትም ጭምር ነው፡፡

ከገፅ 7 የዞረ በጠራራ ፀሐይ... ‹‹በቂ የሆነ አማራጭ እንዳይኖር እየተደረገ እና ያለውም ተቋም

እራሱን ሳያሻሽል ወይም በሚገባ ተግባሩን

እንዲፈፅም ሳይሆን ሕብረተሰቡ በአንድ ነገር ብቻ ፍትሐዊና

አግባብ ባልሆነ ክፍያና ሁናቴ እንዲጠቀም

ማድረግ ሕሊና ቢሶች የሚፈፅሙት ሌብነትና

ዘረፋ ነው፡፡

ነገረ- ኢትዮጵያሚያዝያ 10 ቀን 2006 ዓ.ም. ቅፅ 1 ቁጥር 913

ከገፅ 8 የዞረ ... እናንተም ውረዱ ..

ዘርፈው በወዶ በኩል በማለፍ ወደ ምሽጎቻቸው ለመመለስ ይመጡ ነበር፡፡ ወደ እንሳሮ የወረዱት ከልዩ ልዩ ምሽጎች ተውጣጥተው እነደ ነበር ታውቋል! አሁን የወራሪው ኃይል ተዋጊዎች ወደ ወዶ መንደር ተቃርበዋል! የኢትዮጵያ አርበኞች በተጠንቀቅ እንደ ነበሩ አንዘንጋ! የፋሽስት ኢጣሊያ ወራሪ ኃይል ተዋጊዎች አሁን ጀግኖች የኢትዮጵያ አርበኞች ካደፈጡበት በቅርብ ርቀት ተስተውለዋል! የፋሽስት ኢጣሊያ ወራሪ ኃይል ተዋጊዎች የኢትዮጵያ አርበኞች ስለነበሩበት ሁኔታ ምንም መረጃ አልደረሳቸውም፡፡ ጀግኖቹ የኢትዮጵያ አርበኞች ለቅድሚያ ተነሳሽት ፀንተዋል! ጀግናው ቅጣው አዘነ ዳቦ በማር ሊገምጥ ነው!! የወራሪው ኃይል ተዋጊዎች አሁን የኢትዮጵያ አርበኞች ካደፈጡበት ደርሰዋል! ድም! ድም! ድም! ዱዋ! ዱዋ! ዱዋ! የኢትዮጵያ አርበኞች ቅድሚያ ተነሣሽነትን ወስደዋል! ተኩሱ ተፋፋመ! ወራሪው ኃይል በቁጥር ከአርበኞች በጣም ይልቅ ነበር! ሆኖም ልበ ሙሉ የኢትዮጵያ ጀግኖች ተአምር ለመሥራት ጊዜ አልፈጀባቸውም! ልበ ጠናናውን ፋሽስት አደባዩት! ከአፈር ጋር አዋሐዱት! ጥቂት አመለጡ፡፡ ጀግኖች አርበኞች በርካታ የነፍስ ወከፍ የጦር መሣሪያዎችን ከመሰል ጥይቶች ጋር ማርከዋል! ጀግናው አርበኛ ቅጣው አዘነ ለሕይወቱ ቅንጣት ታህል ሳይሳሳ ተዋግቷል! በጀግንነቱ ተደንቋል! ይህ በታሪካችን የጥንታዊት ኢትዮጵያ የጀግኖች አርበኞች የትግልና ድል ቀጥታ ድምፅ ነው! ከሸዋ ጠቅላይ ግዛት ከሰላሌ አውራጃ ከወዶ ጦር ሜደ! መጋቢት 17 ቀን 1929 ዓ.ም! አንበሣው ቅጣው አዘነ አሁንም በሰላሌ አውራጃ ውስጥ ነው! ግዳይ መጣል ልማዱ ነው! በፋሽስት ኢጣሊያ ወራሪ ኃይል ደም ነጋ ጠባ ይዋኛል! ሞት አይፈራም! ቅኝ ተገዥነትን አይቀበልም! ጦርነቱ ይቀጥላል! አሁን ከፍቼ ምሽግ የወጣ የወራሪው ኃይል ተዋጊ ይግተለተላል! ምናልባት ለግዳጅ ሥምሪት ተነስቷል! የኢትዮጵያ አርበኞች እንቅስቃሴውን ተከታትለዋል! ወዲያው አደጋ ጣሉበት፡፡ አድፍጠው ቆሉት! ሳያስብ አጨዱት! ጀግናው ቅጣው አዘነ በቆራጥነት ተዋግቷል፡፡ ማን ይፈራል ሞት? በዚህ ጦርነት ከኢትዮጵያ አርበኞች ሁለት ጀግኖች ተሰውተዋል፡፡ ይህ በታሪካችን የጥንታዊት ኢትዮጵያ የጀግኖች አርበኞች የጦርነትና የመሥዋዕትነት ድምፅ ነው፡፡ ከሸዋ ጠቅላይ ግዛት ከሰላሌ አውራጃ ከድስጌ ጦር ሜዳ! ግንቦት 15 ቀን 1929 ዓ.ም!ጦርነቱ ቀጥሏል! የኢትዮጵያ አርበኞች ከፍጻሜው

ድል በፊት ትጥቃቸውን እንደማይፈቱ ታውቋል፡፡ የጀግና ልጅ ጀግና ሆኖ ይቀረጻል! ታሪክ ይናገራል! ጀግናው አርበኛ ቅጣው አዘነ አሁን እንሣሮ ወረዳ ውስጥ ከጠብመንጃው ጋር ይነጋገራል! የፋሽስት ኢጣሊያ ወራሪ ኃይል መጥቷል! ሐሳቡ ታውቋል፡፡ እንሣሮ ወረዳ ውስጥ ይድኖ ወደ ተባለ መንደር ለመግባት ቋምጧል፡፡ በዘመናዊ የጦር መሣሪያ በጣም ተጠናክሯል! በቅድሚያ ተነሳሽነት በኢትዮጵያ አርበኞች ላይ ተኩስ ከፈተ፡፡ የኢትዮጵያ አርበኞች ለአፀፋው አልዘገዩም! ጦርነቱ ወዲያው ተጋጋለ! ቀኑን ሙሉ ተካሄደ፡፡ ጦርነቱ እስከ ምሽቱ ቀጥሎ ነበር! ነገር ግን አሸናፊው ማን እንደ ሆነ ሳይረጋገጥ ማደር የግድ ሆነ፡፡ በነጋታውም ከማለዳው አንሥቶ ፍልሚያው ተፋፍሞ ቀለጠ፡፡ ጀግኖቹ የኢትዮጵያ አርበኞች አይበገሬነታቸውን በተግባር አሳይተዋል! በአድዋ ጀግኖች ስነ ልቦና ለወሣኙ ድል ቆርጠው ተነሥተዋል፡፡ ጀግናው አርበኛ ቅጣው አዘነ በፍልሚያው ግምባር ቀደም ተኳሽ ሆኗል! ተኩሱ ቀልጧል! ጦርነቱ ቀጥሏል! የኢትዮጵያ አርበኞች የወራሪውን ኃይል ተዋጊዎች እየወቁ የሬሣ ምርት ከምረዋል! ከሁለት ቀናት ጦርነት በኋላም አሸናፊውን ከተሸናፊው ለመለየት ግን ሳይቻል ቀርቷል፡፡ የኢትዮጵያ አርበኞች ወራሪውን ኃይል ድባቅ በመምታት የዚህችን የነፃነት እመቤት የሆነችውን ሀገር ሉዓላዊነት ዳግም ለማረጋገጥ ቆርጠዋል! ለሦስት ተከታታይ ቀናት ጦርነቱ ተካሄዷል! መስዋዕትነት ተከፍሏል፡፡ በአራተኛው ቀን ከማለዳው አንስቶ አሰቃቂው ጦርነት መቀጠሉ የግድ ሆነ፡፡ የኢትዮጵያ አርበኞች አሁን አጥቅተዋል! ከሦስት ቀናት እልህ አስጨራሽ ጦርነት በኋላ በአዲስ ወኔ ተነሥተዋል! ጦርነቱ ቀጥሏል! አሰቃቂ ጦርነት ሆኗል! ጀግኖች ወድቀዋል! የእንሣሮ ወረዳ መሬት በደም ተለውሰዋል! የባንዳ ሬሣ ተከምሯል! የኢትዮጵያ አርበኞች አሁን ድል ተቀዳጅቷል! ወራሪው ኃይል ሲፈረጥጥ ይስተዋላል! በመራራ ትግል ጣፋጭ ድል ተመዝግቧል፡፡ በዚህ ለአራት ቀናት በተካሄደው ጦርነት በርካታ አርበኞች በጀግንነት ተዋግተው በክብር ወድቀዋል! ታሪክ ግን የሁሉንም ስም ዝርዝር በመፅሐፍ ለዛሬው ወር ተረኛ ትውልድ ለማስተላለፍ አቅም ያጣ ይመስላል! በጥቂቱ ግን ልናገኝ ችለናል 1. አርበኛ ባላምባራስ ዳኘ ስንታየሁ 2. አርበኛ ባላምባራስ መንገሻ ስንታየሁ 3. አርበኛ ባላምባራስ ጌጤ 4. አርበኛ አስፋው ደነበ 5. አርበኛ ጠርዝነህ ፈቄ 6. አርበኛ ታደሰ 7. አርበኛ ጥላሁን ክብረት 8. አርበኛ ደርቤ ክብረት 9. አርበኛ ወርቄ ታፈረ 10. አርበኛ መርን ወልዴ 11. አርበኛ ወልደ ገብርኤል አያልቅበት 12. አርበኛ ወሰንየለህ ፈሰሰ 13. አርበኛ ደብረወርቅ አንበሴ 14. አርበኛ

ወዳጆ ቀርሼ 15. አርበኛ ሀብተየስ ካሴና 16. አርበኛ መንገሻ ወርቅነህ በታላቅ ጀግንነት መስዋዕት ከሆኑት መካከል ይገኙባቸዋል! ይህ በታሪካችን የጥንታዊ ኢትዮጵያ የጀግኖች አርበኞች የትግልና ድል ቀጥታ ድምፅ ነው! ከሸዋ ጠቅላይ ግዛት ከሰላሌ አውራጃ ከእንሳሮ ጦር ሜዳ! ከግንቦት 24 እስከ 28 ቀን 1929 ዓ.ም!ቆራጡ የጦር ባለሙያ ቅጣው አዘነ በመቀጠልም ውላ በተባለው ቦታ ግንቦት 29 ቀን 1929 ዓ.ም ከወራሪው ኃይል ጋርተዋግቶ አኩሪ ውጤት አስመዝግቧል! እንዲሁም በእንሣሮ ወረዳ ውስጥ ካቢ ጉለሌ ቀበሌ መስከረም 16 ቀን 1930 ዓ.ም ከፍተኛ ጦርነት አካሄዷል! በዚህ ጦርነት በርካታ አርበኞች በቆራጥነት መስዋዕት መሆናቸው ታውቋል! ልበ ሙሉ አርበኛ ቅጣው አዘነ አሁንም በመቀጠል ወኮ ጩሳ በተባለ ቦታ መስከረም 20 ቀን 1930 ዓ.ም ከወራሪው ኃይል ጋር ከጧቱ አንድ ሰዓት አንስቶ እስከ አስር ተዋግቷል፡፡ በዚሁ ጦርነተ ሥዩም መከተ የተባለ ቆራጥ አርበኛ በጀግንነት ተሰውቷል! ወራሪው ኃይል ግን ተሸንፎ ተባርሯል! ጀግናው አርበኛ ውድ የኢትዮጵያ ልጅ ቅጣው አዘነ የፋሽሽት ኢጣሊያ ወራሪ ኃይል የኢትዮጵያን መሬት ለቅቆ እስካልወጣ ለአፍታም ትጥቁን እንደማያላላ ታውቋል! በጦርነቱ ሊገፋበት ቆርጧል! አሁንም በመቀጠል መኮ በተባለ ቦታ ከወራሪው ኃይል ጋር ተዋግቶ ጀግንነቱን ደግም አስመስክሯል! በዚሁ ዕለት ወራሪው ኃይል ተሸንፎ መፈርጠጡንም ለማወቅ ተችሏል! ድል የለመደው ጀግና ድሉን አረጋግጧል፡፡ ጦርነቱ ቀጥሏል! ሞት ያልጠገበው ባንዳ ከፊት ይግተለተላል! ጣሊያኖች ከኋላው ሆነው ይማግዱታል! አሁንም ቆራጡ አርበኛ ቅጣው አዘነ መኮ በተባለ መንደር በከፍተኛ የውጊያ ስነ ልቦና ይስተዋላል! ፈርጣጩ የፋሽስት ኢጣሊያ ወራሪ ኃይል አቅሙን አጎልብቶ ተመልሷል! አርበኞችን ይፈታትናቸዋል! ለድል ሳይሆን ለሞት ተሰልፏል! ጦርነት ተከፍቷል! በጥቂት ሰዓታት ጦርነት የፋሽስት ኢጣሊያ ወራሪ ኃይል ፈረጠጠ! የአርበኞች ድል ተበሰረ! ጥቅምት 21 ቀን 1930 ዓ.ም!የጀግናው አርበኛ የቅጣው አዘነ ገድል በዚህ ብቻ አላበቃም፡፡ ጦርነቱ ቀጥሏል! ድል ይመዘገባል! በዚያን ዘመን በብሄራዊ ስሜት የነደደ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵውያት እንደ ነበሩ አንርሣ! ታሪክ ይናገራል! ማን ሊያስተባብል ይችላል? ጦርነት ነው መፍትሔው! ይህ የቆራጡ አርበኛ ቅጣው አዘነ አቋም ነው! ባሁኑ ሰዓት ጎሽ ውኃ ጁር በተባለ ቦታ በከፍተኛ ጦርነት መካከል

ግንባር ቀድሞ ተኳሽ ሆኖ ይስተዋላል! ከድል ወዲህ ትጥቅ መፍታት አይታሰብም! ጦርነቱ ቀጥሏል! የኢትዮጵያ አርበኞች የነፍስ ወከፍ የጦር መሣሪያ ተኩስ አፋፍመዋል! ቆራጡ አርበኛ ቅጣው አዘነ ወኔው እየጋለ ሔዷል! ተኩሱ ቀልጧል! አሁን የኢትዮጵያ አርበኞች ወራረውን ኃይል አጥቅተው የበላይነታቸውን አረጋግጠዋል! የፋሽስት ኢጣሊያ ወራሪ ኃይል ተዋጊዎች ፈርጥጠዋል፡፡ ያለ ጥርጥር የኢትዮጵያ አርበኞች አሸንፈዋል! በዚህ ጦርነት ተስንቱ የተባለ አርበኛ ተሰውቷል! ይህ በታሪካችን የጥንታዊት ኢትዮጵያ የጀግኖች አርበኞች የጦርነትና የአሸናፊነት ቀጥታ ድምፅ ነው፡፡ ከሸዋ ጠቅላይ ግዛት ከጎሽ ውሃ ጁር ጦር ሜዳ! ታህሣሥ 30 ቀን 1930 ዓ.ም!ልበ ሙሉ የጦር ሰው ቅጣው አዘነ በኢትዮጵያ ጀግኖች ታሪክ ባሁኑ ሰዓት በእንሳሮ ወረዳ ውስጥ የጎፍ በተባለ ቦታ በውጊያ ላይ ይስተዋላል! የኢትዮጵያ አርበኞች እንደ ተለመደው በከፍተኛ ወኔ ጦርነቱን አፋፍመውታል! ማን ይፈራል ሞት? ጦርነቱ ተጠናክሮ ቀጥሏል ከጥቂት ሰዓታት ውጊያ በኋላ ወራሪው ኃይል ተልፈስፍሷል! የኢትዮጵያ አርበኞች ይጎማለሉ ገቡ! በዚህ ጦርነት አይነኬ የተባለ አርበኛ በክብር ወድቋል! የቆሰሉ እንደነበሩ ታውቋል! ወራሪው ኃይል ምሱን አግኝቷል! የተረፈው እግሬ አውጭኝ ብሏል! ይህ በታሪካችን የጥንታዊት ኢትዮጵያ የጀግኖች አርበኞች የጦርነትና የድል ቀጥታ ድምፅ ነው! ከሸዋ ጠቅላይ ግዛት ከእንሣሮ ወረዳ ከየጎፍ ጦር ሜዳ! የካቲት 20 ቀን 1930 ዓ.ም! አንበሣው ቅጣው አዘነ አሁንም በከፍተኛ ወኔ በውጊያ ላይ ነው! አንሳይ ውስጥ ሳላይሽ በተባለ ቦታ ከመሸገው ወራሪ ኃይል ጋር ውጊያው ተጧጡፏል፡፡ የኢትዮጵያ አርበኞች ወራሪውን ኃይል ከብበው ከአፈር ጋር አዋህደውታል! በዚህ ጦርነት የባንዶች አለቃ የነበረው ግራዝማች ስዩም ሙላት አጣምሬ የተባለ ከሀዲ ተደምስሷል! ግራዝማች በለጠ ባዩ የተባለ ባንዳ ደግሞ ቆስሏል! ድል የኢትዮጵያ አርበኞች ሆኗል! መጋቢት 20 ቀን 1930 ዓ.ም!ጦርነቱ ቀጥሏል! ቀጥሏል! ቀጥሏል! ቀጥሏል! አሁን እንደገና በሰላሌ አውራጃ ውስጥ ጉሬኔ በተባለ ቦታ መሆናችን ይመዝግብልን! ጀግናው ቅጣው አዘነ አሁንም በጦርነቱ በከፍተኛ ወኔ ይታያል! የኢትዮጵያ አርበኞች ወራሪውን ኃይል አጥቅተዋል! 12 ጠብመንጃዎችን ከመሰል ጥይቶች ጋር ማርከዋል! ድል የኢትዮጵያ አርበኞች ሆኗል! መጋቢት 1930 ዓ.ም!

ይቀጥላል...!

ስማቸው ቢለያይም ቁጥራቸው እጅግ ቢበዛም ክርስቲያን የሚለውን መጠሪያ የሚጋሩ ሁሉ የሚያምኑበት ቅዱስ መጽኃፍ በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 8 ቁጥር 1-3 ላይ «እናንተ በቃሌ ብትኖሩ በእውነት ደቀመዛሙርቴ ናችሁ፤ እውነትንም ታውቃላችሁ፣ እውነትም አርነት ያወጣችኋል» አላቸው ተብሎ ተጽፏል፡፡ የሰው ልጆች በተለይ እኛ የሶስት ሺህ ዘመን ነጻነት እየተረክን ለዴሞክራሲውም ለልማቱም ጀርባችንን ሰጥተን ትናንት በዘመናቸው ይበጃል ያሉትን ሰርተው ሀገርን በክብር ጠብቀው ያለፉ አባት እናቶቻችንን እየረገምን መኖር የቀለለን ሀበሾች ከዚህ የፈጣሪ ቃል ርቀን ከእውነት ተጣልተን፣ በሀሰት ካባ ተጀቡነን የምንኖር በመሆናችን ከፍቅራችን ይልቅ ጠባችን ይብሳል፤ ከአንድነታችን ይልቅ ልዩነታችን ይጎላል፣ አለማዊው ኑሮ እያማለለን ልንሰራበት የተሰራው ገንዘብ እየሰራብን አካላዊ ነጻነታችንን በገዢዎች፣ መንፈሳዊ ነጻነታችንን በጥቅም ፈላጊነት አጥተን እንኖራለን፡፡ብዙ የማይባሉ ለነፍሳቸው አድረው ለፈጣሪያቸው የተገዙ ዓለማዊውን ህይወት ንቀው በጾም በጸሎት የሚኖሩ መኖራቸው በጀ እንጂ እንደኛ ከእውነት ተጣልተን ከሀሰት ጋር የጠበቀ ፍቅር መመስረት፣ ቅንነትን አሽቀንጥረን ጥለን በተንኮልና በሴራ መቆሸሽ፣ ተደጋግፈን ለመራመድ ሳይሆን አንዱ አንዱን ጥሎ ለማለፍ ትንቅንቅ ውስጥ እንደመሆናችን ፈጣሪ ቁጣውን ባዘነበብን ነበር፡፡ ግና ታጋሽነቱ ከጥቂቶቹ ቅዱሳን ልመናና ጸሎት ጋር ተዳምሮ ከነክፋታችን እንኖር ዘንድ ተፈቅዶልናል፡፡ ሀሰት ለጊዜያዊ ክብር ታበቃለች፤ ዓለማዊ ሹመት

ታምራት ታረቀኝ

‹እውነት አርነት ያወጣችኋል›(የዮሐንስ ወንጌል ም. 8 ቁ. 1-3)ታቀዳጃለች፤ ሆድን ሞልቶ አካልን አሳምሮና አስጊጦ ለመታየት ታስችላለች፡፡ በአንጻሩ እውነትን ፈላጊና ማዕድን ቆፋሪ አንድ ናቸው፣ ርቀው በሄዱ ቁጥር ለመከራ ይጋለጣሉ እንደሚባለው እውነት የቅርብ ግዜ ውጤቷ ችግር ነው፣ አደጋ ነው፡፡ እናም ከዚህ ለመሸሽና የሀሰትን በረከት ለመቋደስ ከእውነት የሚሸሽው ቁጥር የትየለሌ ሆኗል፡፡ መጽኃፉ ግን ይላል «..ስለዚህ እላችኋለሁ ለነፍሳችሁ በምትበሉት ወይንም ለሰውነታችሁ በምትለብሱት አትጨነቁ፡፡ ነፍስ ከመብል ሰውነትም ከልብስ ይበልጣልና፡፡» (የሉቃስ ወንጌል ም.2 ቁ.!2) ከእውነት ተራርቆ ከሀሰት ጋር ፍቅር ሲጀመር እንደ በቀቀን የተነገሩትን መልሶ መናገር፣ እንደ ገደል ማሚቶ የጌቶቹን ድምጽ መልሶ ማስተጋባት እንጂ ለምን እንዴት ማን መቼ ወዘተ ብሎ ጠይቆ እውነቱን ከሀሰት ሕጋዊውን ከህገ ወጥ ለይቶ ለእውነት መቆም ይሉ ነገር ጭራሽ አይታሰብም፡፡ ትንሽ ጉርሻ የሚያስገኝ ከሆነ፣ አንድ እርከን እድገት ያመጣል ተብሎ ከታሰበ ይህም ቢቀር በአለቆች ዘንድ መታመንና መወደድን ያተርፋል ተብሎ ከተገመተ ከጳጳሱ ቄሱ መሆን ነው፡፡ በተጨበጨበበት ሁሉ እስክስታ ይወረዳል፣ ምናምንቴ ጥቅም የሚያስገኝ ከሆነ ደግሞ እስኪጨበጨብም አይጠበቅ እስክስታውን መቻል ያለመቻሉም ከቁም ነገር አይገባ ብቻ ለጌቶች ለመታየት እንዘጭ እንዘጭ ማለት ነው፡፡ከእውነት እየራቁ በሀሰት ባህር እየጠለቁ በሄዱ መጠን ወደ ፊት ማሰብ ወደ ኋላም ማስታወስ አይኖርም፣ ዛሬን ብቻ መኖር፡፡ እናም ማስተዋል ይጠፋል፣ ማመዛዘን ይጎድላል ሀሰት ጊዜያዊ እውነት

ግን ዘለቄታዊ መሆኗን ለማሰብ ህሊና ፋታም ግዜም አይኖረውም፡፡ ይህ የሚታየው ደግሞ ድሀ ኃብታም፣ ተራ ባለሥልጣን፣ ወዝ አደር፣ አርሶ አደር፣ ነጋዴ የመንግሥት ሰራተኛ፣ ተቀዋሚ ገዢ ፖለቲከኛ ሳይለይ በሁሉም ዘራፍ ነው፡፡ ሥልጣናቸውን ተመክተው ወይንም ጌታዋን የተማመነች በግ ላቷን ከውጪ ተሳድራለች እንዲሉ ሆኖ አለያም ህሊናና ሆድ ቦታ ተለዋውጠው በድፍረትም ይሁን በይሉኝታ ቢስነት በማን አለብኝነትም ይሁን በልኑርበት ባይነት የሚፈጽሙት በእውነት ላይ የሸፈቱበት ተግባር በሉቃስ ወንጌል ም.02 ቁ.2 ላይ «..ነገር ግን የማይገለጥ የተከደነ፣ የማይታወቅም የተሰወረ ምንም የለም፡፡ ስለዚህም በጨለማ የምትነጋገሩት ሁሉ በብርሃን ይሰማል፣ በእልፍኝ ውስጥም በጆሮ የምትናገሩት በሰገነት ላይ ይሰበካል» ተብሎ ተጽፏልና ጊዜው ደርሶ በምንም በማንም መቼምና እንዴትም ከነአካቴዋ ልትጠፋ የማትችለዋ የተሸፈተባት እውነት የአሸናፊነት አክሊሏን ደፍታ በሀሰት ላይ ደል ተቀዳጅታ ብቅ ስትል በሀሰት የተገኘው ክብሩ በውርደት፣ ሀብቱ በድህነት፣ ሹመቱ በሽረት፣ ይለወጣል፡፡ ገዝፎ የታየው ይኮስሳል ያበጠው ይተነፍሳል ወዘተ፡፡ ይህ በየዘመናቱ የተፈጸመ ቢሆንም ከትናንት ተምሮ ለእውነት መገዛት፣ ሆድን አሸንፎ ለህሊና ማደር ለዛሬ ብቻ ሳይሆን ነገንም በማሰብ የሞራል ሰው መሆን፣ አለማዊውን አማላይ ኑሮ ንቆ ለፈጣሪ ቃል መገዛት እየከበደ በጥፋት መንገድ መቀጠል የማያስፈራም የማያሳፍርም ተግባር መስሏል፡፡ ወጣቱ ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን፡- ዋሽቶ ለመኖር አይችልም ከቶ ታግሎ ይኖራል እንጂ ያለውን በልቶ፣

ደልቶኝ የሞላ ኑሮ መኖር ባልጠላም ገንዘብ ለማግኘት ብዬ አላጣም ሰላም፡፡በማለት እንዳዜመው ያለመንገዱ የሚገኝ ገንዘብን ተጠይፈው በሀሰትና በቅጥፈት ሊመጣ ከሚችል ድሎት ርቀው ከፈጣሪያቸው ታርቀውና የህሊና ሰላም አግኝተው የሚኖሩ ቁጥር የማይገቡ ናቸው፡፡ ድምጻዊው አስኮንኛት ኪሴን እኔ አልሞላም ኪሴን፣ ነብሴ እጅ እንዳሰጭው ለኪሴ ታጣይኛለሽ ከነብሴ ቢልም ስለ ኪስ መሙላት እንጂ ስለመኮነን ሆነ ከነብስ ጋር መጣላት የሚታሰቡ አልሆን እያሉ ነው፡፡ ሆድን በጎመን ቢደለሉት ጉልበት በዳገት ይለግማል እንዲሉ ስጋን በገንዘብ በሥልጣን ቢደልሉት ህሊና በዚህ አይረካምና ጥያቄ ማንሳት ሲጀምር ነፍስ ለምን እያለች ስትሞግት ምላሽ ጠፍቶ ከራስ ጋር መጣላት ሲመጣ በከአፈርኩ አይመልሰኝ ስሜት ለባሰ ጥፋት በሚዳርግ ተግባር ላይ መሰማራት ይመጣል፡፡ ከህሊና ጥያቄ የሚያስመልጥ ከነፍስ ሙግትም የሚገላግል እየመሰለም መለኪያ ጨብጦ በአልኮል እየተነከሩ ማደር የእለት ተእለት ተግባር ይሆናል፡፡እውነት ነጻ ያወጣችኋል የሚለው የፈጣሪ ቃል ቢሆንም ሀሰት ያበለጽጋችኋል የሚል ያልተጻፈ

ወደ ገፅ 6 ዞሯል ...

ነገረ- ኢትዮጵያሚያዝያ 10 ቀን 2006 ዓ.ም. ቅፅ 1 ቁጥር 9

ዛሬ ላይ ግን፣ ከኢትዮጵያ ዳር ድንበሮችም አልፎ በወጪ አገራት በሚገኙ የአትዮጵያ ማኅበረሰብ አባላትም ዘንድ ተንሰራፍቷል፡፡ “ጥራኝ ደኑ! ጥራኝ ዱሩ!” በሚለው ሽለላ ምትክ፣ “ጥራኝ ጎዳናው!

ጥራኝ መንገዱ!” ወደሚል ተሸጋግሯል፡፡ ለምን?

14

ወጣት

የኢትዮጵያ ወጣቶች በሦስት መስቀለኛ መንገዶች ላይ ቆመዋል፡፡ የመጀመሪያው መንገድ ከባህልና ከልማድ የተወረሰ ነው፡፡ ዘፈን፣ ቀረርቶና ሽለላም አለው፡፡ አፋሩ፣ “ዳሀር ቦር ናሬ!” ይላል፡፡ (“ግመሎቼና ከብቶቼ፣ እውጪ ማደር ልማዳችሁ ነው፤ እኔም እንደናንተ ጠላቴን ሳመነዥገው ደጅ-አድራለሁ!” እያለ ይዘፍናል፡፡) ኦሮሞውም፣ “አቢቹ ነጊያ ነጊያ!” የሚል ዜማ አለው፡፡ (የወንድሞችህን ገዳዮች አሰቃይተህ እስከምትገላቸው ድረስ፣ እንቅፋትም አይንካህ! ድል-በድል ያድርግህም!” የሚል መልዕክት አለው፡፡ የአማርኛ ተናጋሪውም ቢሆን፣ “ጥራኝ ደኑ! ጥራኝ ዱሩ!....ላንተም ይሻልሃል ብቻ ከማደሩ!” እያለ ይሸልላል፡፡ ይህ የሚሆነው እንግዲህ ወጣቱ ያኮረፈ ጊዜ ነው፡፡ ምክንያቱ ሊለያይ ይችላል፤ ነገር ግን፣ ወጣቱ ኩርፊያውን ለመግለጽ የሚጠቀምበት ባህላዊ መንገድ “ሽፍትነትን” ነበር፡፡ አብዛኞቹም ሽፍቶች በአካንዱራ (በባህላዊ የጦር ስልት) የተካኑና የተፈጥሮ አደጋዎችን መቋቋም የሚችል ተክለ-ሰውነት የነበራቸው ናቸው፡፡ የቤተ-ክህነትም ሆነ የዘመናዊ ትምህርት የላቸውም፡፡ (ዛሬ ላይ፣ ይሄን ባህልና ልማድ ጠብቆ ለመሄድ የሚያመች ነባራዊ ኹኔታ የለም፡፡ ደኖች ተጨፍጭፈዋል፤ ተቃጥለዋልም፡፡ በሌላም በኩል፣ የዘመናዊ ትምህርትና የዘመናዊ አኗኗር ዘይቤዎች ወጣቱ ባህልና ልማዱን ተከትሎ እንዳይሄድ ደንቃራ ሆነውበታል፡፡) ስለሆነም፣ የኢትዮጵያ ወጣቶች በሚሰባሰቡባቸው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና ኮሌጆች፣ እንዲሁም በሀገር ውስጥና በውጪም ሀገራት ጎዳናዎች ላይ ተቃውሞአቸውን የማሰማት አማራጭን መጠቀም ጀምረዋል፡፡ ነገሩ፣ በ1945/6 ዓ.ም ከኮሪያ ዘመቻ በተመለሱ የክብር ዘበኛ ወጣት መኮንኖችና በቀ.ኃ.ሥ ዩኒቨርሲቲ-ኮሌጅ ተማሪዎች አማካይነት እንደተጀመረም ይታወቃል፡፡ ዛሬ ላይ ግን፣ ከኢትዮጵያ ዳር ድንበሮችም አልፎ በወጪ አገራት በሚገኙ የአትዮጵያ ማኅበረሰብ አባላትም ዘንድ ተንሰራፍቷል፡፡ “ጥራኝ ደኑ! ጥራኝ ዱሩ!” በሚለው ሽለላ ምትክ፣ “ጥራኝ ጎዳናው! ጥራኝ መንገዱ!” ወደሚል ተሸጋግሯል፡፡ ለምን? ከላይ እንደጠቀስነው፣ የደኑ መጨፍጨፍና መቃጠል፣ የወጣቱ በዘመናዊ ትምህርት እያደገ መሄድ፣ የዓለም አቀፉ ተጽዕኖ እያደገ መሄድ፣ የግለኝነት ንቃተ-ህሊና መጎልበትና የተከታታይ ሥርዓቶች ያሰረፁት ፍርሃት (ቦቅቧቃነት-Conscious Ob-jector) ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ገጣሚው ኃይሉ ገብረ ዮሐንስን (ከ1958-66ዓ.ም ድረስ፣) “ኧረ! የወንድ ያለህ!” እያለ ያስጮኸው ይኼው የወንድ/የወኔ ዕጦት ጣጣ ወጣቱ አካባቢ ስላጣ ነበር፡፡ ያም ሆኖ፣ ዛሬ-ዛሬ፣ “ጥራኝ ጎዳናው! ጥራኝ መንገዱ!” የሚለው የወጣቶች እንቢተኝነት፣ ከአረቦቹ የፀደይ አብዮት በኋላ የሚጠበቅ ነው፡፡ በሦስተኝነት የሚመጣው አማራጭ የወጣቶች ብሔራዊ እንቢተኝነት የሚገለጽበት መንገድ ደግሞ ሽብርተኝነት ነው፡፡ ይህንን መንገድ ለመከተል የሚያመች ነባራዊ ሁኔታ የለም የሚሉ በርካታ ኢትዮጵያውያን አጋጥመውኛል፡፡ በግንባር ቀደምትነት የሚመጡት ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም ናቸው፡፡ የእርሳቸውን ንግግሮችም የሚጋሩ በርካታ የግል መገናኛ ብዙኃን ፀሐፍትና አዘጋጆችም አሉ፡፡ የገዢው ፓርቲ ባላጋራ መሪዎችም (ተቀናቃኝ የፖለቲካ ማኅበሮችም) ከፕ/ር መስፍን አባባል ጋር ይስማማሉ፡፡ “የገዢው ፓርቲ መሪዎችና ካድሬዎች፣ ይኼንን ከኢትዮጵያውያን ባህልና ልማድ ጋር የማይሄድ ቋንቋ የሚጠቀሙት የተቃዋሚ አባላትንና የግል ጋዜጠኞችን ለማሰርና ለማሸማቀቅ እንዲያመቻቸው ብለው ነው፤” ሲሉም ይከራከራሉ፡፡ በእርግጠኝነትም፣ የእነ አንዱዓለም አራጌንና የርዕዮት ዓለሙን እስር ከዚህ ጋር ያገናኙታል፡፡ በ1989/90 ላይ ተደርገው የነበሩትንም የነዶ/ር ታዬ ወ/ሰማያትና የሌችንም የፖለቲካና የሙያ ማህበራት መሪዎች

ጥራኝ ጎዳናው! ጥራኝ መንገዱ!ሰሎሞን ተሰማ ጂ.

[email protected]

የእስር ሂደት ያወሳሉ፡፡ በብያኔውና በትርጓሜው ላይ ብንስማማም-ባንስማማም “ሽብርተኝነት” የኢትዮጵያ ወጣቶች ሊሳቡበት ከሚችሉበት የእንቢተኝነት መንገዳቸው አንዱ ነው፡፡ (በእርግጥ! አለ ወይስ የለም? የሚለውን ክርክር ለየቅላን ብንተወው ይሻላል፡፡)እስካሁን የተነጋገርንባቸውን ሦስት ሃሳቦች በሌላ ቋንቋ መነጋገር አስፈላጊ ነው፡፡ ቅርብ ጊዜ ወዲህ፣ የኢትዮጵያ ወጣቶች የተቃውሞና “የአልገዛም ባይነት” እንቅስቃሴዎችን በተጠናከረ ኹኔታ እያሳዩ ይገኛሉ፡፡ እንቅስቃሴዎቻቸውም ሦስት ዓይነት መልኮችን በመያዝ ላይ ናቸው፡፡ የመጀመሪያው የጎዳና ላይ ትዕይንተ-ተቃውሞ ነው፡፡ መነሻውም-መድረሻውም ሰላማዊ እንደሆነ እናውቃለን፡፡ በዋናነት በከፍተኛ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችና፣ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ ይታይ ነበር፡፡ ከዓመት ከመንፈቅ ወዲህ ደግሞ፣ በፖለቲካ ፓርቲዎችም ውስጥ የማይናቅ አቅም አጎልብቷል፡፡ ሁለተኛው ደግሞ፣ የሽምቅ ውጊያ ይዘት አለው፡፡ ላለፉት ሠላሳ አመታት ገደማ የኦሮምኛ፣ የሶማሊኛና የአፋርኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች በእጅጉ ሲለፉበትና ሲደክሙበት ቆይተዋል፡፡ የትግራይና የኤርትራ ወጣቶችም በዚሁ ዓይነት መንገድ “ናጽነት” አገኘን ብለዋል፡፡ ከሦስት ዓመታት ወዲህ ደግሞ፣ ይሄው የሽምቅ ውጊያ (የርስ-በርስ ጦርነት) አዝማሚያ ወደ ጋንቤላ፣ ወደ ደቡባዊት ኢትዮጵያና ወደ አማርኛ ተናጋሪ ወጣቶችም ዘንድ ተዛምቶ ከፍተኛ እንቅስቃሴዎች ባብዛኛው የኢትዮጵያ ገጠራማ ክፍሎች ውስጥ መታየት ጀምሯል፡፡ (የአኙዋክ ወጣቶች ንቅናቄ (አወን)፣ የደቡብ ወጣቶች የጋራ ንቅናቄ (ደወጋን)፣ እና የአማራ ወጣቶች የጋራ ንቅናቄ (አወጋን) የሚባሉት ካለፉት ሦስት ዓመታት ወዲህ የተመሠረቱ “ወጣት-ተኮር” ድርጅቶች ናቸው፡፡)በሦስተኛው ዓይነት የኢትዮጵያ ወጣቶች ተቃውሞአቸውንና “ያልገዛም ባይነታቸውን” የሚገልጹበት መንገድ በኅቡዕ የመደራጀት አማራጭ ነው፡፡ ይህ ዓይነቱ አደረጃጀት መነሻውም-ሆነ-መድረሻው ምስጢራዊ ነው፡፡ ሄዶ-ሄዶም፣ የራሱን የመገናኛ ኮድና የራሱን ጠንካራ የሰው ኃይል አደራጅቶ (Networked Structure) ወደ ሽብርተኝነት ያድጋል፡፡ በርግጥ! ብዙዎች “የኢትዮጵያ ህዝብ የባህል፣ የሃይማኖትና የማኅበራዊ ኹኔታ ለዚህ አደረጃጀት (ለሽብርተኝነት ኔትዎርክ) የሚመች አይደለም” ይላሉ፡፡ ከዚህ ሃሳብ አቀንቃኞች መካከልም ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም ይገኙበታል (“አደጋ ያንዣበበበት የአፍሪካ ቀንድ” የሚለውን መጽሐፋቸውን መመልከቱ ጥሩ ነው፡፡) በሌላ በኩል ደግሞ፣ ኢትዮጵያን የሽብርተኝነት አደጋ እየተጋረጠባት ነው በማለት፣ ገዢው ፓርቲ ወያኔ-ኢህአዴግም ሁለት አዋጆችን አውጥቷል፡፡ አንደኛው “የፀረ-ሽብር ሕግ” (አዋጅ ቀጥር 652/2001) እየተባለ የሚታወቀው ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ “ሽብርተኝነትን በገንዘብና ቁሳቁስ መደገፍን የሚከለክል ሕግ” (አዋጅ ቁጥር 780/2005) ነው፡፡ እዚህ ላይ ሊጤን የሚገባው ትልቅ ቁምነገር አለ፡፡ እርሱም፣ ሽብርተኝነት ከባህልና ከሃይማኖት፣ ብሎም ከፖለቲካ-ኢኮኖሚ ጋር አያይዞ አለመመልከቱ

ጥሩ ነው፡፡ ከ1957 ዓ.ም ወዲህ እንዳየነው ከሆነ፣ የኢትዮጵያ ወጣቶች አይሮፕላን የመጥለፍም ሆነ የአቬሽን እንቅስቃሴዎችን የማስተጓጎል ባህልና ዝንባሌ አልነበራቸውም፡፡ ግና፣ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እስከ ኮሞሮስ ደሴቶች አካባቢ በግዳጅ እስካረፈው አይሮፕላናችን ድረስ ኢትዮጵያውያኑ ጉዳት የማደረስ አቅምም ክህሎትም እንዳላቸው ታይቷል፡፡ ነገሩ የዓለም ዓቀፉ ትኩሳትም ማሳያ (ነጸብራቅ) አካል ነው፡፡ በቀላል አማርኛም የየዘመኑን ፋሽን የመከተልም ዝንባሌ (ስበት) ተደርጎም ሊወሰድ ይችላል፡፡ ከሁሉም በላይ ግን፣ ወደ ሽብርተኝነትና ወደ ኅቡዕ መዋቅሮች ውስጥ ሊገቡ የሚችሉት ወጣቶች ከአንድ ከተወሰነ ሃይማኖት፣ የኢኮኖሚ መደብ፣ ከሆነ ዘር/ብሔር፣ አለያም ደግሞ ከአንድ የማኅበራዊ መድሎ ከደረሰበት ክፍል ብቻ አድርጎ ማሰላሰሉ አያዋጣም፡፡ ወደ ሽብርተኝነቱ ጎራ ለመቀላቀል የሚፈልጉ ወጣቶች ካሉ የሚከተሉት ሦስት አማራጮች ምቹ መደላድሎች ይሆኗቸዋል፡፡ 1ኛ) የፖለቲካ-ኢኮኖሚው የሚፈጥርባቸው ኩርፊያ ነው፡፡ በዚህ በኩል ደግሞ፣ ገዢዎቻችን እንደሚነግሩን ሳይሆን ስር-የሰደደ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ዱካክ ወጣቱን አስኮርፎታል፡፡ መሥራት ከሚችሉት መካከል 45% (በመቶ) የሚሆኑት የኢትዮጵያ ወጣቶች ሥራ-አጥ ናቸው፡፡ ከነዚህም ውስጥ አብዛኞቹ ችሎታውና አቅሙ እያላቸው በክልል መንግሥታትና ሹመኞች (ፖለቲካዊ በሆነ አድሎና መድሎ) ለሥራ-የደረሱ እጆቻቸውን አጣጥፈው የተቀመጡ ናቸው፡፡ ጉዳይ ፖለቲካዊ በመሆኑና ኢኮኖሚያዊ ተጽዕኖውም ፋታ የማይሰጥ በመሆኑ ከፍተኛ ኩርፊያን አስከትሏል፡፡ ኩርፊያውም እያደገ ወደ ከባድ የተስፋ መቁረጥን ደረጃ በመድረስ ላይ ይገኛል፡፡ 2ኛው) ችግር ደግሞ ከወጣቱ ንቃተ-ኅሊና ጋር የማይሄድ የገዢዎቹ ቅስቀሳና ፕሮፓጋንዳ ነው፡፡ ገዠዎቹ “ወጣቱ የወደፊቷ ኢትዮጵያ ተረካቢ ነው፤” እያሉ ሲሸነግሉት ኖረዋል፡፡ ነገር ግን፣ ወጣቱ “የአሁኒቷም ኢትዮጵያ ባለድርሻ ነኝና የሚገባኝን ድርሻዬን አምጡ፤” በማለት ላይ ይገኛል፡፡ (የገዢዎቹ “ወደፊት ጠብቁና” የወጣቶቹ “አሁኑኑ አምጡ” ንትርክ ማቆሚያም ያለው አይመስልም፡፡ ስለሆነም አስገድዶ ድርሻን ለመንጠቅ የሽብር አማራጭ ሊከተል ይችላል፡፡) ዛሬ፣ ተደራጅተው የልጃገረዶችን ተንቀሳቃሽ ስልኮችና ጌጣጌጦች ከመንጠቅ አልፈው፣ ትልልቅ የኮንትሮባንድና የዕጽ-ማዘዋወር ተግባራት ላይ ኔትወርክድ ሆነው ሊደራጁ ይችላሉ፡፡ 3ኛው ነጥብ ደግሞ፣ የወጣቶቹ በዘመን አመጣሽ አስተሳሰቦች መማረክና በባዕዳን ኃሎች የመጠለፍ እድላቸው እያደገ የመሄዱ ጉዳይ ነው፡፡ በ1960ዎቹ የነበሩት የኢትዮጵያ ወጣቶች በኮሚኒዝም አስተምህሮዎችና መሪዎች እንደተሳቡት ሁሉ፣ ያሁኖቹ ደግሞ በመካከለኛው ምስራቅና በሩቅ ምስራቅ አካባቢ ባሉ የኅቡዕ ድርጅቶችና መሪዎች ሊማረኩ የማይችሉበት ምንም ምክንያት የለም፡፡ ይህ የስሜት የ(Impression) ጉዳይ ነው፡፡ በዚያ ላይ ደግሞ፣ በአሁኑ ሰዓት ድንበር-ዘለል የኅቡዕ ድርጅቶ እጅግ ከፍተኛ የሆነ ጉርሻና ጠቀም ያለ ክፍያን ለወጣቱም ሆነ ለቤተሰቡ ይከፍላሉ፡፡ ይህ ማበረታቻም ከስሜት ድጋፍ ሰጭነታቸው ባሻገር፣ ሳቢና ማራኪ ነው፡፡

ይህንን የሽብር አማራጭ ሳይጠቀሙ የተሻለና እጅግ አመርቂ ለውጥ ለማምጣት የሚያስችለው መንገድ የትኛው ነው በሚለው ላይ የበለጠ መነጋገር፤ መወያየትም የተገባ ነው፡፡ በግሌ፣ የ“ጥራኝ ደኑም ሆነ ከሽብሩ መንገድ” ይልቅ “የጥራኝ ጎዳናው! የጥራኝ መንገዱ!” አማራጭ እጅግ አዋጪ እንደሆነ አምናለሁ፡፡ ይህንን የምለው የግብጽን፣ የቱኒዚያንና የሌሎችን አረብ አገር “የፀደይ ወራት!” ብሔራዊ እንቢተኝነት እንድገም ለማለት ፈልጌ አይደለም፡፡ በዚህ አመለካከቴም፣ ከልጅ ተመስጌን ደሳለኝና ከተወሰኑት ባልደረቦቹ የተለየ አቋም ነው ያለኝ፡፡ እነርሱ፤ “መስቀል አደባባይን የጣህሪር አደባባይ እናደርጋታለን” የሚል ሃሳብ ያንፀባርቃሉ (አዲስ ታይምስ መጽሔት፣ 2005ዓ.ም፣ ቁጥር-3ን ይመልከቱ፡፡) እኔ የምለው፤ በ1966፣ እና በ1983ዓ.ም እንዳደረግነው ሕዝባዊ እንቢተኝነታችንን ለታጣቂ ኃይሎች ላለማስረከብ፣ በቅድሚያ ጠንክረን መሥራት ይገባናል ነው፡፡ የመጀመሪያው ሥራ፣ ወጣቱንና ሕዝቡን በተሳካ ኹኔታ በማደራጀት ነው፡፡ ከገጠር እስከ ከተማ ድረስ ጠንካራና ሰላማዊ የሆነ ድርጅት መሥራት የግድ ይላል፡፡ ከገዢው ፓርቲ ጋር የሚደረገውም ትንቅንቅ ቀላል አይሆንም፡፡ ያንን ተቋቁሞ የተሳካ አደረጃጀትና ታዓማኒነት ያለው የፖለቲካ አመራር ማዘጋጀትም ያስፈልጋል፡፡ “ሥልጣን” የምትባለውን ጉደኛና አደገኛ “ሰይጣንም” ለመያዝ፣ በወታደሩና በፀጥታ ኃይሎች አካባቢ የሰላማዊ ታጋዮቹ አላማና ርዕይ ተቀባይነት እንዲያገኝ ያለመታከት መሥራትን ይጠይቃል፡፡ የወጣቶቹ ሰላማዊ አደረጃጀትና ተዓማኒነት ያለው አመራር ዕውን ከሆነ፣ በወታደራዊውም ሆነ በፀጥታና በደኅንነቱ አካላት ዘንድ ያሉትን በመቶ ሺ የሚገመቱ ወጣቶችን ልብ ለማሸፈት አቅም ይኖረዋል፡፡ ከዚህም ሌላ፣ በሰላማዊ መንገድ የሚደራጁት ወጣቶች ያሏቸውን የተለያዩ የመገናኛና የመልዕክት ማስተላለፊያ ዘዴዎች ይበልጥ ጠንካራና የማይታወኩ አድርገው መሥራት አለባቸው፡፡ ለዚህም ተግባር የሚያግዙ በርካታ በጎ ፈቃደኞችንና የተለያዩ ጥቅማ-ጥቅሞችን የሚያገኙ የቴሌ፣ የፖስታ፣ የመንገድ ትራንስፖርት፣ የአቬሽንና የመገናኛ ብዙኃን ሰራተኞችን ከወዲሁ ማዘጋትም የግድ ነው፡፡ በአሁኑ ሰዓት ያሉትንና በተለያዩ ኤጀንሲዎች ተጽፎ የሚሰጣቸውን መግለጫና ዜና ለእጀራቸው ብለው የሚያቡትን (የሚያነበንቡትን) ጋዜጠኞች መጥላቱም ሆነ ማጥላላቱ ጊዜ ማጥፋት ብቻ ነው፡፡ ከእነርሱ ይልቅ፣ ከኋላ ሆነው የሚያቅዱትና ስልቶችን የሚነድፉት “ጎበዞችና ጎበዛዝት” ላይ ማተኮሩ ተገቢ ነው፡፡ይህ ሃሳብ ወደ አንድ አቅጣጫ ይመራናል፡፡ ወጣቱ ያለውን ውሱን ጥሪትና የሰው ሃይል በሚገባው ቦታና ሰዓት አውሎ፣ ትግሉን አስተማማኝና እጅግ ሰላማዊ መሆኑን ለማረጋገጥ ከፈለገ፣ የሚያተኩርባቸውን “ጎበዞችና ጎበዛዝት” ማንነት፣ አድራሻ ቦታ፣ የዘወትር እንቅስቃሴያቸውንና የእነማን ወዳጅና ጠላት እንደሆኑ ኹሉ አብጠርጥሮ ማወቅ አለበት፡፡ እነማን የንግድ ሸሪኮቻቸው እንደሆኑ፣ እነማንስ ቂመኞቻቸው እነደሆኑ ከወዲሁ ለይቶ ማወቅ ይገባዋል፡፡ ይህንን ማድረጉ ለሁለት ነገሮች ይጠቅመዋል፡፡ አንደኛ፣ እባብ ተይዞ በትር ስለማይፈለግ ነው፡፡ በእርግጥም፣ ለፍርድ መቅረብ ያለባቸውን ከሌለባቸው ለመለየት ስለሚበጅ ነው፡፡ ሁለተኛ፣ “መረጃ አይናቅም፣ አይደነቅም!” ከሚለው መርሆም በመነሳት ነው፡፡ ለብሔራዊ እንቢተኝነት የሚዘጋጁትን ወጣቶችና ደጋፊዎቻቸውን እነማን እያሳደዷቸው እንደሆኑና እነማንስ ያላግባብ በህዝብና በሀገር ክብር ላይ እየቆመሩ እንዳሉ ማወቁ በራሱ ትልቅ ፋይዳ አለው፡፡

(ክፍል-2ን ሳምንት ይጠብቁን፡፡)

ነገረ- ኢትዮጵያሚያዝያ 10 ቀን 2006 ዓ.ም. ቅፅ 1 ቁጥር 915

ከገፅ 10 የዞረ የኢትዮጵያ ሥትራቴጂካዊ ......

ጎንደር፡- በጎንደር ከተማ ቀበሌ 18 ከ30 ሺህ በላይ ቤቶች የተገነቡባቸው ሶስት ሰፈሮች ሊፈርሱ መሆኑን በስፍራው የሚገኙ የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች አስታወቁ፡፡ በከተማዋ ቀበሌ 18 ከተመሰረቱ ከ7 አመት በላይ የሆናቸው አርማጭሆ፣ ገንፎ ቁጭና ህዳሴ የተባሉ ሰፈሮች ውስጥ የተገነቡ ከ30 ሺህ የሚልቁ ቤቶችን እንዲያፈርሱ ለነዋሪዎች ትዕዛዝ በተሰጠበት ስብሰባ የተካፈሉ ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡በስብሰባው ላይ ነዋሪዎቹ፣ ‹‹ህገ ወጥ ከሆነ ያኔ ሕገ ወጥ ነው ልትሉን ይገባ ነበር፡፡ ህገ ወጥ ነው ከተባለስ ይህ ሁሉ ዜጋ በርካታ ገንዘብ አፍስሶ ቤት ከሰራና ለ7 አመት ከኖረ በኋላ ህጋዊ ማድረግ አይቻልም ነበር? ይህም ካልሆነ ተለዋጭ ቦታ ተሰጥቶንና ሰፊ ጊዜና ተለዋጭ ጊዜ ተሰጥቶን እንጂ በድንገት ተነሱ ልትሉን አይገባም›› የሚል መከራከሪያ ማንሳታቸው ታውቋል፡፡በተጨማሪም፣ ‹‹እኛ የራሳችን አገርና ቦታ ላይ የምንገኝ ዜጎች ነን፡፡ ቤታችንን የሰራነው ማንም ሳያግዘን በራሳችን ጥረት ነው፡፡ የኤርትራ፣ የሱዳን፣ የሶማሊያ ዜጎች ወደ ኢትዮጵያ ተሰደው ሲገቡ የሚገባቸው ነገሮች ይሰጣቸዋል፡፡ እኛ ግን ያለምንም ቅድመ ዝግጅት፣ ካሳና ተለዋጭ ቦታ ሳይሰጠን ቤታችሁን አፍርሱ መባላችን ዜግነታችንም ጥያቄ ውስጥ ያስገባ ነው›› ብለዋል ነዋሪዎቹ፡፡

በጎንደር 30 ሺህ ቤቶች እንደሚፈርሱ ታወቀ

- ‹‹በከተማዋ ውጥረት ነግሷል›› የከተማዋ ባለስልጣናት በበኩላቸው፣ ‹‹መንግስት ህገ ወጥ ነው ብሎ የሚያምነውን ሁሉ ማፍረስ መብቱ ነው፡፡ አይደለም ጎንደር አዲስ አበባ ውስጥም ቤት ይፈርስባቸዋል፡፡›› በሚል ለማሳመን ሞክረዋል፡፡ ‹‹በዚህ ጊዜ ውስጥ ልጆቻችን ይዘን የት ልንሄድ ነው... ሽማግሌዎችስ የት ይደርሳሉ?›› የሚሉ ሌሎች አንገብጋቢ ጥያቄዎችን አንስተው አጥጋቢ መልስ ያላገኙት ነዋሪዎቹ ከባለስልጣናቱ ጋር ባለመስማማታቸው አብዛኛዎቹ ‹‹ማፍረስ ከተፈለገ እናንተው አፍርሱት እንጂ እኛ አናፈርስም፡፡›› በሚል ስብሰባውን አቋርጠው መውጣታቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ነዋሪዎቹ እስከ ሚያዚያ 7 አፍርሱ፣ ካለፈረሳችሁ እኛው ስለምናፈርሰው እቃችሁን አውጡ ቢባሉም አሁንም ድረስ በአቋማቸው ጸንተው የሚመጣውን ለመቀበል መዘጋጀታቸውን ምንጮቻችን ጨምረው ተናግረዋል፡፡ በሌላ በኩል ህዝቡ በክረምት ተፈናቅሎ የት ይደርሳል በሚልና እንዲፈርስ በሚፈልጉት የከተማው ባለስልጣናት መካከል ውጥረት መንገሱን ለማወቅ ተችሏል፡፡በተጨማሪም ህዝብን አሳምጻችኋል የተባሉ 12 ሰዎች መታሰራቸውና ከጎንደር በተጨማሪ ቆላ ድባና ሌሎች ከተሞችም ቤቶች እንዲፈርሱ ትዕዛዝ መሰጠቱን መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡ በተመሳሳይ ከሰሞኑ በባህር ዳር ከተማ ነዋሪዎችን ከማፈናቀል ሂደት ጋር በተገናኘ ህዝብና ፖሊስ በመጋጨታቸው የሰው ህይወት ማለፉ ይታወሳል፡፡

መራዊ፡- በምዕራብ ጎጃም ዞን ሜጫ ወረዳ ያለ ፈቃዳችን መሬታቸውን አሳልፈን አንሰጥም ያሉ አርሶ አደሮች እስርና ድብደባ እየደረሰባቸው መሆኑን ከአካባቢው የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡ በመራዊ አካባቢ ሜጫ ወረዳ እናሸንፋለን ቀበሌ መንግስት የከርሰ ምድር ውሃ ቁፋሮ እናካሂዳለን በሚል ከ400 በላይ የሚሆኑ አርሶ አደሮች ከመሬታቸው እንዲለቁ የተደረገውን እርምጃ አርሶ አደሮቹ በመቃወማቸው እስርና ድብደባ እየደረሰባቸው መሆኑን የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡በአካባቢው ከአሁን ቀደም ተመሳሳይ እርምጃዎች የተወሰዱ ሲሆን የአርሶ አደሮቹ መሬት በአበባ ኢንቨስትመንት ላይ ለተሰማሩ ባለሀብቶች ተሰጥቶባቸዋል፡፡ ይህም በአሁኑ ወቅት መንግስት ውሃ ለመቆፈር በሚል አርሶ አደሮቹ ከመሬታቸው እንዲለቁ የሚወስደው እርምጃ በተመሳሳይ

አርሶ አደሮች መሬታቸውን ያለካሳ እየተነጠቁ ነው

ለአበባ እርሻ ሊሰጥባቸው እንደሆነ በማመናቸው ከመሬታቸው አንለቅም ብለዋል፡፡ እስካሁን ለአበባም ሆነ ለሌሎች ተግባራት መንግስት ከአርሶ አደሮቹ መሬት ሲወስድ ያለ ምንም ካሳ በመሆኑ አርሶ አደሮቹ አሁንም ቢሆን ያለ ካሳና ያለምንም ፈቃድ እየተነጠቁ በመሆኑ ተቃውሟቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ አድርጓዋል፡፡ ከአርሶ አደሮች ባሻገር በከተሞች የሚኖሩ የአርሶ አደሮቹ ቤተሰቦች ጭምርም ችግር እየደረሰባቸው መሆኑን ምንጮች ጨምረው ተናግረዋል፡፡ በተለይም ታሳሪዎቹን የሚጠይቁት የአርሶ አደሮቹ ቤተሰቦችና ሌሎች የአካባቢውና በየከተማው የሚኖሩ ግለሰቦችም ለእስር መዳረጋቸውን ለመረዳት ተችሏል፡፡ አርሶ አደሮቹ መሬታቸውን ያለ ፈቃዳቸው አሳልፈው እንደማይሰጡ በመግለጽ ጠንካራ ተቃውሞ ማንሳታቸውን ተከትሎ በአካባቢው ፖሊስና መከላከያ በብዛት መሰራጨቱን ምንጮች አክለው ገልጸዋል፡፡

በምስራቅ ወለጋ ስቡ ስሪ ወረዳ ‹‹ይህ አገር የእናንተ አይደለም፡፡ አገራችሁን ግቡ፡፡›› በሚል 200 ያህል አርሶ አደሮች እንደተፈናቀሉ አስታወቁ፡፡ በ1990ዓ.ም ጀምረው በአካባቢው የኖሩት እነዚህ ዜጎች ‹‹የመኖሪያ መታወቂያ ተሰጥቶን፣ ውጡ ተብለን እየታሰርንና እየተባረርን እንኳ ግብር እያስከፈሉን፣ ንብረት አፍርተን አገራችሁ አይደለም ተብለን እየተፈናቀልን ነው›› ሲሉ ምሬታቸውን ለዝግጅት ክፍላችን ገልጸዋል፡፡ አርሶ አደሮቹ ከዚህ ቀደም በ1992 በተመሳሳይ ቤትና ንብረታቸው ወድሞ ተፈናቅለው የነበረ ቢሆንም መንግስት እንደገና እንዳቋቋማቸው ይገልጻሉ፡፡‹‹በአንድ በኩል አገራችሁ አይደለም ውጡ!›› የሚሉት የአካባቢው ባለስልጣናት በሌላ በኩል ደግሞ ‹አካባቢውን ልንሰራበትና ልናሰራበት ነው ይሉናል፡፡ በ1992ም መንግስት እንደገና አቋቁሞናል፡፡ አሁንም ቦታው ከተፈለገ መንግስት ተገቢውን ካሳ ሊሰጠን ይገባል፡፡› ብለን ስንጠይቅ ደግሞ ‹እናንተን መንግስት አያውቃችሁም፡፡

በምስራቅ ወለጋ ዜጎች እየተፈናቀሉ ነውይሉናል› በሚል እየደረሰባቸው ያለውን ህገ ወጥ ተግባር ይናገራሉ፡፡ተፈናቃዮቹ ከጥር 22 2006 ዓ.ም ‹‹ለቃችሁ ውጡ፡፡ ለቃችሁ ካልወጣችሁ ለቤትና ንብረታችሁ ብቻ ሳይሆን ለህይወታችሁም ኃላፊነት የላችሁም›› መባላቸውን ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ተደጋጋሚ እስራትና ድብደባ እንደደረሰባቸው ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ‹‹ለቃችሁ ውጡ!›› በተባሉበት ወቅት አቤቱታ ሲያቅረቡ የነበሩ 42 ሰዎች ያለ ምንም ምግብ ለ30 ቀናት ታስረው መቆየታቸውንና በየ ጊዜው ፖሊስ ከፍተኛ ድብደባ እንደሚያደርግ ገልጸዋል፡፡ ከቀያችን ተፈናቅለን፣ ልጆቻችን ትምህርታቸውን አቋርጠው፣ በችግር ላይ እንገኛለን የሚሉት ተፈናቃዮቹ ‹‹ሀገርና ተቆርቋሪ የሌለን ዜጎች ሆነናል፡፡ ከ16 አመት በላይ የኖርንበትን ቀያችን ለቀን ወደ የት እንሂድ? የሚመለከታችሁ አካላት ሁሉ በተግባር እርዱን›› ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ከገፅ 8 የዞረ .... ትዝታ ወ-ቅንጅትአድርገው የተደራጁ ፓርቲዎችም ቆም ብለው ራሳቸውን መመርመር ያለባቸው ወቅት አሁን ይመስለኛል።

ሚዲያ“አፍሪካ ውስጥ ሚዲያውን ከያዝክ የጦር መሳሪያ ባይኖርህ እንኳ መምራት ትችላለህ” የሚል አባባል ሰምቼ ነበር። ትንሽ የተጋነነ ቢመስልም የማይካድ ሀቅ ነው። ለዚያም ይመስላል ወታደራዊ መንግስታት በመፈንቅለ መንግስት ጊዜም ይሁን በሌሎች ሰላማዊ ያልሆኑ አጋጣሚዎች የመንግስትን ስልጣን ሲቆናጠጡ ፈጠን ብለው የሚዲያ ተቋማትን የሚይዙትና ስልጣን በእጃቸው እንደገባ የሚያውጁት። ዛሬ በአለም ላይ መንግስታት ሚዲያዎቻቸው ከሀገራቸው አልፎ በአለም ዘንድ ተሰሚነት እንዲኖረው ሲሰሩ ሌሎች አምባገነን ሀገሮች ደግሞ ሚዲያዎች ወደ ሀገራቸው እንዳይገቡ በማገድ ስራ ላይ ተጠምደዋል። ለምሳሌ ቻይና ፌስቡክን የመሰሉ የማህበራዊ ሚዲያዎችን ስትዘጋ፣ ሰሜን ኮሪያ በበኩሏ ምእራባዊያን ሚዲያዎችን ከሀገሯ አየር ላይ ማገዷ በምሳሌነት ይጠቀሳሉ። በ21ኛው ክፍለ-ዘመን የሚዲያ ሚና ትልቅ ነው። ዛሬ በተለያየ የአለም ጥግ የሚኖሩ ሰዎች በተወሰኑ ሚዲያዎች ጥላ ስር ተሰባስበዋል።ሚዲያ ወሳኝ ነው። ያ ነጻነትን የመሻት የለውጥ መንፈስ እንደገና ተነቃቅቶ ውስጣችን እንዲሰርጽ ከፈለግን ራሳችንን ለሚዲያዎች ማቅረብ መቻል ይኖርብናል። ትዝ ይለን እንደሆን በ97 ምርጫ ወቅት ለለውጥ የሚደረገውን ትግል በማንቃት፣ ግንዛቤ በመፍጠር፣ በማስተማርና በማስተባበር በኩል ከፍተኛውን ሚና የሚይዘው ሚዲያ ነው (በተለይ የግሉ ፕሬስና በውጭ የሚገኙ ሬዲዮዎች) ስለዚህ ምንም እንኳ ዛሬ ያሉት ሚዲያዎች በቁጥር እጅግ የተመናመኑ ቢሆኑም ባለው ቴክኖሎጂና እድል በመጠቀም ራሳችንን ከሚዲያው ጋር በማስተሳሰር፣ሚዲያዎች የሚሻሻሉበትን መንገድ በመጠቆም፣ ሚዲያዎቹ ተጠናክረው የሚቀጥሉበትን መንገድ በማመቻቸት ላይ የበኩላችንን ብናበረክት የሚዲያዎችን ተጽእኖ ፈጣሪነት ማሳደግ ይቻላል።

የተፎካካሪ ፓርቲዎች ነገርከላይ እንደ ገለጽኩት ተፎካካሪ ፓርቲዎች ህዝብን የማደራጀት፣ግንዛቤን የማስጨበጥ፣የማንቃት እና ከፖለቲካዊ ድብርት የማላቀቅ ትልቅ ሀላፊነት አለባቸው። አንዳቸው ሌላቸውን ሲኮንኑ መመልከት እጅግ ያሳዝናል። እርግጥ ነው ትችት ዴሞክራሲያዊ ስርአትን ለመገንባት ትልቅ መሳሪያ ቢሆንም የትችቱ ይዘት ገንቢና “ከእኔ ውጪ ላሳር”

ከሚል መንፈስ ነጻ መሆን ይኖርበታል። ለኢትዮጵያ የሚሻለው ላይም የየራሳቸው አተያይ መኖሩ ጤናማ አስተሳሰብ ነው። አላማቸው የተቀራረበ ቢሆንም እንኳ እርስ በርስ መተባበርና አብሮ መስራቱ ቢያቅታቸው እንደምን በጥላቻ ይተያያሉ? እለት ተእለት የሚፈጽሙት ድርጊታቸውም በአብዛኛው ይህንኑ ስህተታቸውን የሚያጠናክር ሲሆን እንጂ መሻሻል ላይ እምብዛም ናቸው። ከምርጫው በኋላ የነበረው መከፋፈል ዘመኑን ደግሞ ከምርጫ በፊትም እየተመለከትን እያዘንን ነውና እርስ በርሳችሁ በመተቻቸት እና በመነቋቆር ጊዜያችሁን የምታሳልፉ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ሆይ ቆም ብላችሁ አስቡ! ገዢው ፓርቲ እናንተን የሚያጠቃበትን በር እየከፈታችሁለት መሆኑን ልብ ልትሉ ይገባል።ህዝብ ዘንድ ያላችሁ እምነት ገደል ከገባ የመጨረሻቹ መጨረሻ መሆኑን አትርሱ!

ሲቪክ ማህበራት በምርጫ 97 ወቅት የሲቪክ ማህበራት ሚና ትልቁን ድርሻ ከሚወስዱት ተርታ ይመደባል። ህብረተሰቡን በማንቃት ለምርጫ እንዲመዘገብ፣በሰላማዊ መልኩ መንግስትን መቀየር እንደሚቻል ወዘተ በርካታ ጉዳዮች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራዎችን ሰርተዋል። በተለይ በተለይ በዚህ ዙሪያ ታሪክ የሚያስታውሳቸው የንግድ ምክር ቤቱ ግለሰብ አቶ ክቡር ገና ናቸው። “ይቻላል” በሚለው መፈክር የሚታወቁት አቶ ክቡር ህዝቡ ዘንድ የነበረውን “ኢህአዴግ በምርጫ ስልጣን ለማይለቀው ነገር ምን አስመረጠኝ?” የሚለውን ስጋትና ጥርጣሬ በመፋቅና ለምርጫ እንዲሳተፍ በማድረግ ለሀገሪቷ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ትልቅ አስተዋጽኦ አበርክተው ነበር። ሆኖም ከጥቂት አመታት በፊት ተራድኦ ድርጅቶችን የሚመለከተው አዋጅ ህዝባዊ ድርጅቶችን አቀጭጯቸዋል። መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ሰብዓዊ መብትን፣ችግር አፈታትና ዴሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታን የሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ የመስራት(ግንዛቤ የማስጨበጥ) መብታቸውን ይገድባል። ከ10 ፐርሰንት በላይ የሚሆን ፈንድ ከሀገር ውጭ እንዳይቀበሉ ይደነግጋል። ይህም በዚህ ዙሪያ የሚሰሩ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን በማቀጨጭ ወይም በማጥፋት የማህበረሰቡን የፖለቲካ ተሳትፎና ንቃተ-ህሊናን የማዳበር ስራ ላይ ክፍተት እንዲኖር የራሱ አስተዋጽኦ ይኖረዋል።ሆኖም እነዚህ ድርጅቶች ተስፋ ባለመቁረጥ ባለችው ቀዳዳ በመጠቀም ለመጪው ምርጫ የበኩላቸውን ቢያበረክቱ በእርግጠኝነት ከ97 የላቀ ውጤት የምናስመዘግብበት የህዝብ ማዕበል ይደገማል።

፡ ይሁንና እንደቀድሞው በአጭር ጊዜ አላማ ላይ የተመሠረተ ግንኙነት የአሜሪካን ሆነ የኢትዮጵያን ህዝብ ዘላቂ ጥቅም የሚያስጠብቅ አይሆንም፡፡ በመጨረሻም የሚከተለውን መራር እውነት አንባቢን ላስታውስና ልሰናበት፡፡ የታሪክ ፌዝ ሆነና ኤርትራ ከእናቷ ኢትዮጵያ ሸፍጥ በተሞላ ህዝበ-ውሳኔ ስትለይ አሜሪካም ሆነች የምዕራቡ ዓለም ዝምታን መርጠው ነበር፡፡ በቅርቡ ግን በጥቁር ባህር ዳርቻ የምትገኘው ስልታዊ የዩክሬን ግዛት ክሬሚያ የሩሲያ አንድ አካል በመሆኗ የምዕራቡ ዓለምና አሜሪካን ምን ያህል እንዳስቆጣቸው ከመገናኛ ብዙሃን ሰምተናል፡፡ ግራም ነፈሰ ቀኝ አንድ የነበረችው ኢትዮጵያ ለሁለት ተከፍላለች፡፡ ኢትዮጵያ በመዳከሟ ማን ተጠቀመ? እርግጥ ነው ሞቷን የሚመኙ ከበሯቸውን ሊደልቁ ይችላሉ፡፡ ታላቋ አሜሪካ ግን ዘላቂ ጥቅሟ የሚጠበቅ አይመስለኝም፡፡

ከኢራቅ ውድቀት፣ ከሶሪያና ከአፍጋኒስታን ደም መፍሰስ ምን ተገኘ? የዘይት ጥማታቸውን አርክተው ሊሆን ይችላል፣ ባህላቸውን አስፋፍተው ሊሆን ችላል፣ እልፍም ካለ የጦር መሳሪያቸውን ሸጠው ሊሆን ይችላል፣ በተረፈ ግን ቻይናን የመሰለ ተፎካካሪ ተፈጥሮባቸዋል፡፡ በተዳከመችና በተከፋፈለች ኢትዮጵያ የአሜሪካን ዘላቂ ጥቅም አስጠብቃለሁ ማለት ዘበት ነው፡፡ ስለሆነም አንዲትና ጠንካራ ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ እንድትኖር መሰናክል አትፍጠሩብን፡፡ አምባገነን የሆነውን የኢህአዴግ አገዛዝ በሰለጠነ መንገድ ለመጣል ዋነኛው ኃላፊነት የኢትዮጵያ ህዝብ ቢሆንም ቅሉ እናንተ ምዕራባውያን ከቀረጥ ከፋዩ ህዝባችሁ የዛቃችሁትን ዶላር ለአገዛዙ በመስጠት አታስቀጥቅጡን እላለሁ፡፡ (አቶ ደረጀ መላኩ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ናቸው፡፡)

ለፈ

ገግታ

ነገረ- ኢትዮጵያሚያዝያ 10 ቀን 2006 ዓ.ም. ቅፅ 1 ቁጥር 9 16

አሁን ላይ ሐገር አቀፍ ፓርቲዎችንና የጎሳ ፓርቲዎችን በአንድ አቀናጅቶ ጠንካራ ተቃዋሚ መድብለ ፓርቲ የመፍጠሩ ጉዳይ ከገቢራዊነት የሸሸ ምንም ሆኗል፡፡ ለዚህ እውነታ ደንበኛ ማሳያ የሚሆነው ደግሞ ብዙ የተደከመበት መድረክ የተሰኘው የተቃዋሚ ፓርቲዎች ስብስብ አንድነትን ወይም ሐገራዊ ህብረትን ማምጣት አለመቻሉ ነው፡፡ በተጨማሪም ጠንካራ ከሚባለው አንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ (አንድነት) ፓርቲ ሊቀመንበርነት የወረዱት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ በይፋ ‹‹መገንጠልን እቃወማለሁ፤ ነገር ግን የመገንጠል መብትን እደግፋለሁ›› ሲሉ መደመጣቸው ሌላው ማሳያ ይሆናል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ ከሁሉም ወገኖች ሊነሳ የሚችለው ነጥብ ወይም ሊመረመር የሚገባው ነገር አለ ከተባለ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ሐገር አቀፍ ፓርቲዎችና የጎሳ ፓርቲዎች የራስን እድል በራስ የመወሰን እስከ መገንጠል መብት ሊደራደሩበት የማይቻላቸው አቋም መሆኑ ነው፡፡ ሌላው የራስን እድል በራስ መወሰን መብት ላይ የሚነሳ አብይ ጉዳይ ፓርዎች የጎሳ ውክልና ባልወሰዱበት ክል ወይም አካባቢ የፖለቲካ ቀቅስቀሳም ሆነ ምርጫ ለማድረግ አለመቻላቸው ነው፡፡ የራስን እድል በራስ መወሰን እስከ መገንጠል ለኢትዮጵያ አንድነት መነሻ ሆኖ እከቀጠለ ድረስ ወይንም ክልሎች ለጎሳ ፖለቲካ ብቻ የተተው እስከሆኑ ድረስ የጎሳ ፖለቲከኞች አገር አቀፍ ፓርቲዎችን ከማስወገድ አላማ የላቸውም፡፡ በዚህ ሁኔታ ውስጥ አንድነት ገቢራዊ የማድረጉ ጉዳይ ቢከሽፍ ወይንም ሙሉ በሙሉ ባይሳካ የሚገርም አይሆንም፡፡ የመድረክን መመስረት በይፋ ከደገፉና ስብስቡን ካደነቁ ሰዎች መካከል አንዱ እኔ ነበርኩ፡፡ መድረክ የጎሳ ውክልናን እና እውቅናን ህጋዊ መሰረት አድርጎ የአንድነትን ወይንም የሐገር አቀፍነትን ጥያቄ በአዲስ መልክ ያመቻቸ ተስፋ የሚጣልበት የተቃዋሚዎች ስብስብ አድርጌ ወስጄው ነበር፡፡ ሆኖም ግን መድረክ ይህን ሐገራዊ አንድነት

ማምጣት አለመቻሉ የጎሰኝነት አመለካከት ከጎሳ እኩልነት ጥያቄ ልቆ መውጣትን ያመላከተ ሆኗል፡፡ ይበልጥ የሚያሳዝነው ደግሞ ዛሬም የኢትዮጵያ የጎሳ ፓርቲዎች ስታሊናዊ አስተምሮ (Stalinist dogma) ላይ ተጣብቀው የራስን እድል በራስ መወሰን እስከ መገንጠል መብትን ብቸኛ የጎሳዎች የእኩልነት ማረጋገጫ መንገድ አድርገው ማየታቸው ነው፡፡ የጎሳ ፖለቲካ አራማጆች ያለፈውን ኢ-ፍትሃዊ የታሪክ ሁነት ለመሻር የአሁኑን የሐገር አንድነት ማንኳሰስ እንደማያስፈልግና ይህን ለማድረግም ከአንድ በላይ መንገዶች እንዳሉ በፍጹም በአዕምሯቸው መጥቶላቸው የሚያውቁ አይመስሉም፡፡ ይህ ከፍተኛ የሆነ ከየራስን እድል በራስ የመወሰን መብት ላይ ያላቸው ተጣብቆ ግን ለዴሞክራሲ ካላቸው ቁርጠኝነት አልያም ቀናዒነት ሳይሆን የጠባብ ልሂቃን ፍላጎትን መሰረት ያደረገ ነው፡፡በበኩሌ እነዚህ የጎሳ ፓርቲዎች በተግባር ከገዥው ኢህአዴግ የተለዩ እንዳልሆኑ ድምዳሜ ላይ ከደረስኩ ቆይቻለሁ፡፡ ኢህአዴግና እነዚህ የጎሳ ፓርቲዎች በርዕዮተ ዓለምም ሆነ በፖለቲካ መስመር ተመሳሳይ ነገሮችን ይጋራሉ፡፡ የጎሳ ፓርቲዎቹ የሚለዩት መሪዎቻቸው የገዥው ልሂቃን አካል ባላመሆናቸው ብቻ ነው፡፡ እነዚህ ተቃዋሚ ነን የሚሉ የጎሳ ፓርቲዎች ከኢህአዴግ የተለየ አማራጭ ፖለቲካ የላቸውም፡፡ እንዲያውም ኢትዮጵያን በጎሳ የመሰነጣጠቁን ተግባር ለጎሳ ልሂቃን ህጋዊ የመስሪያ ክልል እንደመፍጠር አድርገው ያዩታል፡፡ በዚህም የእነሱ ምኞት ሐገር አቀፍ ፓርቲዎችን ወይም የአንድነት ልሂቃንን ከመወዳደር በመከልከል ጎሳዊ የስልጣን ስርዓትን ጠብቆ ወደ መሪነት መውጣት ነው፡፡ እናም እንወክለዋለን በሚሉት ጎሳ ዘንድ እራሳቸውን ብቸኛ ህጋዊ ተወካይ እንደሆኑ አድርገው በማቅረብ፣ ሌሎችን ቡድኖች ኢትዮጵያዊ እንዳልሆኑ ሁሉ በጎሳ ብዝሃነትና በኢትዮጵያ አንድነት ላይ አማራጭ እቅዶች እንደሌላቸው አድርገው ያውጃሉ፡፡ ሰዎች በጎሳ እንዲገለጹ ይደረጋሉ፤ በዚህም እኛ

እና እነሱ ብለው ቡድን ይሰራሉ፡፡ ስለዚህም ግለሰቦች ቦታ ይነፈጋቸውና ሁሉንም መብታቸውን ለሚመደቡበት ቡድን አሳልፈው እንዲሰጡ ይደረጋሉ፡፡ የራስን የጎሳ ግዛት በድንበር ከልሎ ሌሎች እንዳይወዳደሩ መከላከልም ሆነ ራሳቸው በጎሳ ዘለል የፖለቲካ ምህዳር ውስጥ ለመወዳደር አለመፍቀድ የሚያረጋግጥልን ተቃዋሚ የጎሳ ፓርቲዎች ዴሞክራሲያዊ ያልሆነን የፖለቲካ ቅጅ ለማወጅ ቁርጠኛ መሆናቸውን ይሆናል፡፡ በእርግጥም ጎሳን መሰረት አድርጎ እየተወዳደሩና ሌሎችን ከጎሳዬ ውጭ ነህ በሚል ምክንያት ከውድድር እየከለከሉ ስለ ዴሞክራሲ ማውራት እጅጉን ከባድ ነው፡፡የእኛ ተስፋ ግለሰቦች በፖለቲካ ነቅተውና ፓርቲዎችን አቋቁመው ኢ-ፍትሃዊነትን አርመው ነጻነትን ዘብ እንዲቆሙለት ነው፡፡ በተግባር ግን በኢትዮጵያ ዘመናዊ ታሪክ ውስጥ ስግብግብ የፖለቲካ ልሂቃን በሰራተኛ መደቡና በጎሳ ቡድኖች ስም ራሳቸው ወደ ስልጣን ማማ ለመውጣት ሲራኮቱ ነው የሚታዩት፡፡ ለዚህም ነው የሚያመጡት የፖለቲካ ስርዓት ሁሉ ኢ-ዴሞክራሲያዊ የሆነው፡፡ ማናቸውም ህዝብን ለማንቃት አልደከሙም፡፡ በህዝብ ስም ስልጣንን ለመቆናጠጥና የከፋፋይ ፍላጎታቸውን ለማስረጽ ዳከሩ እንጂ!አሁን የማያወላውለው መደምደሚያ የሚሆነው ሐገር አቀፍ ፓርቲዎች ከዚህ በኋላ ከጎሳ ፓርቲዎች ጋር ህብረትን ለመፍጠር በሚል የሚያጠፉት ጊዜና ጉልበት ሊኖር አይገባም የሚለው ነው፡፡ የእኔ ስጋት

የጎሳ ፓርቲዎችን መለያ አጥልቆ ከሐገር አቀፎቹ ጋር ህብረት መፍጠር ጊዜ ለመግዛትና በጎሳ በታጠሩ ክልሎች ቀስ በቀስ መሰረትን ለመጣል በሚል ሽፋን የተቃውሞ ፖለቲካን ማራመድ እየወደቀ ካለ መንግስት ጋር ማበር እንዳይሆን ነው፡፡ የጎሳ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በማያሻማ መልኩና በይፋ የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት እስከ መገንጠል የሚለው አካሄዳቸውን እስካልተው ድረስ የተቃዋሚነትን ሽፋን ያጠለቁ የኢህአዴግ የትሮይ ፈረስ አታላዮች ከመሆን አይዘሉም፡፡ ስለዚህ እነዚህን ፓርቲዎች ወደ ሐገራዊ አንድነት ከማምጣት ይልቅ ሐገር አቀፍ ፓርቲዎች የራሳቸውን አማራጭ ፖሊሲና ራዕይ በግልጽ በማቅረብ ብሄራዊ ኃይላትን ማሰባሰብ ላይ ማተኮር ይኖርባቸዋል፡፡ የሁሉንም ጎሳና ሐይማኖቶች እኩልነት ከመቀበል በተጨማሪ በአንድነት ኃይላት የሚቀርበው አማራጭ ፖሊሲ ይህን እኩልነት በተሳለጠ ሁኔታ፤ ግን ደግሞ የኢትዮጵያን አንድነት በምንም መልኩ ለድርድር እንዳያቀርብ ተደርጎ መቀመጥ ይኖርበታል፡፡ በመሆኑም የጎሳ ፓርቲዎች በራሳቸው ምሽግ ታጥረው ስለ መከፋፋልና ማግለል የጎሳ ፖለቲካ ቢያቀነቅኑም ሐገር አቀፍ የአንድነት ፓርቲዎችና ኃይላት ህዝቡን በዴሞክራሲ በማብቃት ሐገራዊ አንድነትን መሰረት አድርገው መስራት ግድ ይላቸዋል፡፡ በዚህም የትግል መፈክሩ ‹‹ዴሞክራሲያዊ አንድነት ወይስ ከፋፋይ ፖለቲካ›› የሚል መሆን አለበት፡፡

መሳይ ከበደ (ፕ/ር) አስመሳይነት መጨረሻ?መድረክ-የፖለቲካ

በበኩሌ እነዚህ የጎሳ ፓርቲዎች በተግባር ከገዥው ኢህአዴግ የተለዩ እንዳልሆኑ ድምዳሜ ላይ ከደረስኩ ቆይቻለሁ፡፡ ኢህአዴግና እነዚህ የጎሳ ፓርቲዎች በርዕዮተ ዓለምም ሆነ በፖለቲካ መስመር ተመሳሳይ ነገሮችን ይጋራሉ፡፡ የጎሳ ፓርቲዎቹ የሚለዩት መሪዎቻቸው የገዥው ልሂቃን አካል

ባላመሆናቸው ብቻ ነው፡፡

ነፃነት የማግባት ሃሳብ አልነበራትም። ነፃ ሆኖ መኖር ነበር ህልሟ። በአንዱ ቀን ግን ስለማግባት አሰበች። ማሰብ ብቻ አይደለም አገባች። የማግባቷ ሰበብ የባሏ ስም ነበር። ሥሙን ሲነግራት ወደደችው። “እኩልነት እባላለሁ” ብሎ ነበር የተዋወቃት። ....እንደፈለጋት አውቃለች። የነፃነት እና የእኩልነት ጥምረት ደጋግሞ ታሰባት። እሱን ስለማግባት አሰበች። ሃሳቧ ሰመረ። ተጋቡ!ትዳሯን ለመርገም ብዙ አልቆየችም። ባሏ በስም እንጂ፣ በግብሩ የእኩልነት ጠላት መሆኑን ለማወቅ ጊዜ አልፈጀችም። በውሳኔዋ አምርራ አዘነች።ወዳ ለገባችበት ትዳር ብላ ሁሉን ለማለፍ ብትሞክር አልቻለችም። ባሏ እንደሚስት ሳይሆን እንደ ባሪያው ነው የሚያያት። የበታቹ እንደሆነች ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ሊያሳያት ይፈልጋል። በጣም ከጠበቀችው ስብዕና ጋር የማይሄዱ ነገሮች ባሏን ለመፍታት እንድትወስን አደረጓት። ከሁሉ በላይ ውሳኔዋን እንድታፋጥን ያደረጋት የባሏ ስም “እኩልነት” አለመሆኑን መስማቷ ነው። ስሙን ደብቆ ነው የተዋወቃት። እስካሁንም አልነገራትም። ከማን ጋር እየኖረች ያለችው? ማወቅ አለባት!! ስለሱ ሊነግሩኝ ይችላሉ ያለቻቸውን ሰነዶች ሁሉ በረበረች። በመጨረሻ ማንነቱን አወቀች። አዎ! የባሏ ትክክለኛ ስም “ባርነት” ነው!!

****** ባርነት ከነፃነት ምን ህብረት ይኖረዋል። ይምጣ ብቻ! ከዚህ በኋላ እንደተፋቱ... ከንግዲህ ተጋብተው መዝለቅ እንደማይችሉ ትነግረዋለች።

ያላቻ ጋብቻ!! ...መጣ። ያወቀችውን ሁሉ ዘርዝራ ነገረችው። ከንግዲህ ፈትቼሃለው አለችው። ... አቤት የመታት ጥፊ!!! የባርነት ጥፊው እንዴት ሃይለኛ ነው!! ጭውውው አለባት። “ ትሰሚያለሽ! አንዳችም የመወሰን ስልጣን የለሽም። በኔ ስር ነሽ፣ ከእኔም ስር ነሽ። አትንጠራሪ! ይገባሻል? አቅምሽን አውቀሽ ቁጭ በይ!!” ይሄንን ተናግሮ በሩን በላይዋ ላይ ዘግቶባት ወጣ። ነፃነት እንዲህ አልጠበቀችም ነበር። የዋህነቷ ታሰባት። ፀፀት ውስጧን እያኘካት አምርራ አለቀሰች።ከዛ ቀን በኋላ በባርነት ቤት ውስጥ እንደተቆለፈባት መኖር ቀጠለች። ባሏ ምን ያህል ጉልበተኛ እንደሆነ አውቃለች። ከዚህ ሲኦል ትዳር የምትወጣበት ቀን ራቀባት። ለነፃነት ባርነትን ተሸክማ ከመኖር በላይ የሚከብድ ምን አለ? እንዴት ነው ልትወጣ የምትችለው? እንዴት? ማሰብ አለባት። በዚህ በባርነት ቤት ውስጥ ቁጭ ብላ ከርቀት ድምፅ ይሰማታል። አንድ ድምፅ አይደለም። የተለያዩ ድምፆች። የማን ድምፆች እንደሆኑ ታውቃለች። አንዱ “ፍትሕ” ነው፣ ሌላኛው “ እኩልነት” ነው- ትክክለኛው እኩልነት፣ ሌላኛው ሰላም ነው። ከነሱ ጋር ያሉ ሌሎች ድምፆችንም ትሰማለች። ሁሉም ስለሷ ነው የሚጮሁት። “ነፃነት ትፈታ!! የባርነት ጭካኔ ማስታገሻ መሆኗ ይቁም!” ሲል ትሰማዋለች ፍትህ። “ሁሉም እኩል ነው!! ማንም የበላይ፣ ማንም የበታች የለም! ነፃነት ትፈታ!” ሲል ትሰማዋለች እኩልነት።

ግን ብዙ ነገራቸውን አትሰማም። ድምፃቸው የሰለለ ነው። ባርነት ቤት ድረስ የሚመጣው ድምፃቸው ብዙ አይሰማትም። ከቤቱ ብዙ ርቀው እንዳልሆነ ታውቃለች። ቅርብ ናቸው፣ የባርነት ቤት ግድግዳ ግን ሆነ ተብሎ ድምፃቸው ወደውስጥ ብዙ እንዳይሰርግ ታስቦ የተሰራ ነው። ...ቢሆንም ተስፋ አትቆርጥም።ባሏ ባርነት፣ ከጭቆና፣ አምባገነንነት... እና መሰል ጓደኞቹ ጋር እየዋለ ይመጣል። በገባ በወጧ ቁጥር ሲለው በእርግጫ፣ ሲለው በጡጫ ይነርታታል። ፊቷ በዱላው በላልዟል። አሁን ማን ከቀደመ ውበቷ ጋር አነፃፅሮ “እቺ ነፃነት ናት” ብሎ ደፍሮ ይናገራል? እራሷ እንኳን መስታወት ስታይ እራሷን ትጠራጠራለች። በእንባ ብሶቷን ልታጥበው ትሞክራለች። እዚህ ትዳር ውስጥ የገባችበትን ቀን ትረግማለች። ቢሆንም ተስፋ አትቆርጥም። በጭለማው የባርነት ቤት ውስጥ ብሩህ ነገን ታያለች። ነፃ አውጪዎቿን ትናፍቃለች። የነፍትህን የሰለለ ድምፅ እየሰማች ትፅናናለች።

“ከዛሬ የተሻለ ነገ አለ” ስትል ራሷን ትሰብካለች። ነገ፣ ከባርነት ቤት መውጣትን አይደለም የምታስው፣ የባርነት ቤትን ማፍረስ ነው የምትፈልገው!! ለዚህ ግን አንድ ነገር ማድረግ አለባት። የነፍትህ ድምፅ በሚመጣበት በኩል የባርነትን ቤት ግድግዳ መሰርሰር... አጠገቧ ያገኘቻቸውን ስል ነገሮች ተጠቅማ መሰርሰር ጀመረች። የባርነት ቤት ከጠበቀችው በላይ ጠንክሮ የተሰራ ነው። ግድግዳው በባህሪው ጊዜ በሄዴ ቁጥር የሚወፍር ነው። ቢሆንም፣ ከዚህ በላይ ከመወፈሩ በፊት ከጊዜ ጋር መሽቀዳደም አለባት። ግድግዳውን መሰርሰር ቀጥላለች... ነገ ተስፋ ሆኗታል። የባርነት ግድግዳው ወፍራም ነው፣ የነፃነትም ተስፋዋ ወፍራም ነው። ግድግዳውን መሰርሰሯን ቀጥላለች። ነገ! ነገ!! ነገ!!! አዕምሮዋ ውስጥ ይደውላል.... ነገ.... ብሩህ ነገ! እየሰረሰረች ነው። የነገ ፀሐይ በምትወጣበት ግድግዳ በኩል..... የሀዘን እንጉርጉሮዋን በተስፋ ዘፈን ለውጣ እየሰረሰረች ነው.... “ነገዬ ውጪ ውጪ...” እያለች....

አገኘሁ አሰግድ

ሰማያዊ ፓርቲ እሁድ ሚያዚያ 19/2006 ዓ.ም ከጠዋቱ 4 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት ‹‹የተነጠቁ መብቶቻችንን እናስመልስ›› በሚል መሪ ቃል ከፓርቲው ጽ/ቤት ተነስቶ ጃን ሜዳ ሰላማዊ ሰልፍ ያደርጋል፡፡ በዚህ ሰልፍ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ

በመሳተፍ መብቱን እንዲያስመልስ እንጠይቃለን፡፡

ኑ የተነጠቁ መብቶቻችንን እናስመልስ!ሰማያዊ ፓርቲ

ታላቅ ሠላማዊ ሰልፍ