20
1 በውስጡ የሚከተሉትን ይማራሉ: ገፅ በትምህርት ቤትዎ የሚሰጡ የድጋፍ ዓይነቶች በተመለከተ 2 በልጅዎ /ቤት ውስጥ ስላሉት አስፈላጊ ዝግጅቶች 3 በት /ቤት ዝግጅቶች ላይ መሳተፍ እና ከሰራተኞች ጋር መነጋገር እንዲችሉ አስቶርጓሚ እንዴት ይጠይቃሉ 4 የእንግሊዝኛ ቋንቋ ተማሪዎች እና የዓለም ቋንቋ ክረዲቶች 4 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መስፈርቶች ዝርዝር 5 ስለ የ9 ክፍል ጠቃሚ መረጃዎች 6 ሶርስ: የልጅዎ ውጤት እና አቴንዳንስ የመከታተልያ መሳሪያ 8 ወላጆች/አሳዳጊዎች የቤት ስራን ለማጠናቀቅ እንዴት ድጋፍ ሊያደርጉ እንደሚችሉ 10 ወላጆች/አሳዳጊዎች ከተማሪዎቻቸው ጋር ለመሳተፍ የሚያስችሉ ጥቂት መንገዶች 12 ለት/ቤት አማካሪዎች በጣም በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎች 13 Naviance: የመስመር ላይ (online) የኮሌጅ እና የስራ ዕቅድ መሳሪያ 14 የልዩ ፍላጎት ትምህርት አገልግሎቶችን የሚያገኙ 9 ክፍል ተማሪዎችን መደገፍ 15 የአካል ጉዳት ያላቸው ተማሪዎች ድህረ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማዘጋጀት 15 ከፍተኛ ችሎታ ላላቸው የመሸጋገርያ ሁሉተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች 16 ለመመረቅ የክልል አስፈላጊ ፈተናዎች 18 የቃላቶች መግለጫ 19 ሲያትል የሕዝብ ትምህርት ቤቶች የእያንዳንዱ የተማሪ ጉዞ የማየት ግዴታ አለበት። ዘር፣ ጾታ፣ ማህበራዊ ና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ፣ የቋንቋ ብቃት፣ የመማር ዘዴ ወይም አካል ጉዳተኝነት ሳይለይ ሁሉም ልጅ የሚያስፈልጋቸውን ማንኛውም ነገር ማድረግ የእኛ ኃላፊነት ነው ብለን እናምናለን። ቤተሰቦች በዚህ ሥራ ውስጥ ወሳኝ አጋሮቻችን ናቸው። 9 ክፍል ስኬታማነት የምረቃ ትንበያ ማሳያ ነው! ይህ መፅሐፍ ልጅዎ ስኬታማ 9ኛ ክፍል ዓመት እንዲሆንለት(ላት)ለማገዝ እና ልጅዎ ለመመረቅ በትክክለኛው መንገድ እንዳለ(እንዳለች)ለመከታትል የሚያግዝ መሳርያ ነው። በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ቤተሰቦች ተሳታፊ ማድረግ (EFIHS)የሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች እና ጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ የጋራ ትብብር ነው። 8ወደ 9ክፍል ሽግግር እና ከዚያ በላይ የቤተሰብ መሳሪያ April 5, 2019 8 th to 9 th Grade Transition and Beyond Family Toolkit AMHARIC

8 ወደ 9ኛ ክፍል ሽግግር እና ከዚያ በላይ የቤተሰብ ... · የእንግሊዝኛ ቋንቋ ተማሪዎች እና የዓለም ቋንቋ ክረዲቶች

  • Upload
    others

  • View
    21

  • Download
    0

Embed Size (px)

Citation preview

1

በውስጡ የሚከተሉትን ይማራሉ: ገፅ

❖ በትምህርት ቤትዎ የሚሰጡ የድጋፍ ዓይነቶች በተመለከተ 2

❖ በልጅዎ ት/ቤት ውስጥ ስላሉት አስፈላጊ ዝግጅቶች 3

❖ በት /ቤት ዝግጅቶች ላይ መሳተፍ እና ከሰራተኞች ጋር መነጋገር እንዲችሉ

አስቶርጓሚ እንዴት ይጠይቃሉ 4

❖ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ተማሪዎች እና የዓለም ቋንቋ ክረዲቶች 4

❖ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መስፈርቶች ዝርዝር 5

❖ ስለ የ9 ኛ ክፍል ጠቃሚ መረጃዎች 6

❖ ሶርስ: የልጅዎ ውጤት እና አቴንዳንስ የመከታተልያ መሳሪያ 8

❖ ወላጆች/አሳዳጊዎች የቤት ስራን ለማጠናቀቅ እንዴት ድጋፍ ሊያደርጉ እንደሚችሉ 10

❖ ወላጆች/አሳዳጊዎች ከተማሪዎቻቸው ጋር ለመሳተፍ የሚያስችሉ ጥቂት መንገዶች 12

❖ ለት/ቤት አማካሪዎች በጣም በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎች 13

❖ Naviance: የመስመር ላይ (online) የኮሌጅ እና የስራ ዕቅድ መሳሪያ 14

❖ የልዩ ፍላጎት ትምህርት አገልግሎቶችን የሚያገኙ የ 9 ኛ ክፍል ተማሪዎችን መደገፍ 15

❖ የአካል ጉዳት ያላቸው ተማሪዎች ለ ድህረ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማዘጋጀት 15

❖ ከፍተኛ ችሎታ ላላቸው የመሸጋገርያ ሁሉተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች 16

❖ ለመመረቅ የክልል አስፈላጊ ፈተናዎች 18

❖ የቃላቶች መግለጫ 19

ሲያትል የሕዝብ ትምህርት ቤቶች የእያንዳንዱ የተማሪ ጉዞ የማየት ግዴታ አለበት። ዘር፣ ጾታ፣ ማህበራዊ ና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ፣ የቋንቋ ብቃት፣ የመማር ዘዴ ወይም አካል ጉዳተኝነት ሳይለይ ሁሉም ልጅ የሚያስፈልጋቸውን ማንኛውም ነገር ማድረግ የእኛ ኃላፊነት ነው ብለን እናምናለን። ቤተሰቦች በዚህ ሥራ ውስጥ ወሳኝ አጋሮቻችን ናቸው።

የ 9 ኛ ክፍል ስኬታማነት የምረቃ ትንበያ ማሳያ ነው! ይህ መፅሐፍ ልጅዎ ስኬታማ የ 9ኛ ክፍል ዓመት እንዲሆንለት(ላት)ለማገዝ እና ልጅዎ ለመመረቅ በትክክለኛው መንገድ

እንዳለ(እንዳለች)ለመከታትል የሚያግዝ መሳርያ ነው።

በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ቤተሰቦች ተሳታፊ ማድረግ (EFIHS)የሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች እና ጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ የጋራ ትብብር ነው።

ከ 8ኛ ወደ 9ኛ ክፍል ሽግግር እና

ከዚያ በላይ የቤተሰብ መሳሪያ April 5, 2019

8th to 9th Grade Transition and Beyond Family Toolkit AMHARIC

2

በትምህርት ቤትዎ ስለሚቀርቡ የድጋፎች ዓይነቶች መፈለግ

በልጅዎ ትምህርት ቤት ማንን እንደሚገናኙ

ለልጅዎ ስኬት የሚደግፉ በጣም ጠቃሚ የሆኑ የመገናኛ ዝርዝር የልጅዎ ትምህርት ቤት ይጠይቁ።. እነዚህ ወላጆች እና አሳዳጊዎች ጥያቄዎች ወይም ስጋቶች ሲኖሩዋቸው ሊያነጋግሩዋቸው የሚችሉ ሀብቶች ናቸው።

❖ አማካሪ

❖ የትምህርታዊ ጣልቃገብነት ባለሙያ

❖ ምክትል ርእሰመምህር

❖ መምህራን

❖ ከትምህርት በኋላ ቲቶሪንግ

❖ የወጣት ጤና ማዕከል

❖ ረዳቶች

About the Kinds of Supports Your School Provides AMHARIC

3

በልጅዎ ት/ቤት ውስጥ ስላለው ጠቃሚ ዝግጅቶች ይወቁ l

የስርዓተ ትምህርት ምሽት: የስርዓተ ትምህርት ምሽት በየዓመቱ በመሰከረም እና በጥቅምት ውስጥ ይካሄዳል። በልጅዎ ትምህርት ቤት ወደሚኖረው የስርዓተ ትምህርት ምሽት መሄድዎን እርግጠኛ ይሁኑ!

በልጅዎ ትምህርት ቤት የሥርዓተ ትምህርት ምሽት የሚከታተሉበት ምክንያቶች :

• በአብዛኛዎቹ ትምህ •

• ርት ቤቶች የልጅዎን የትምህርት መርሃ ግብር ለመከታተል እና የመማሪያ አካባቢቸውን በቀጥታ ልምድ ማግኘት ይችላሉ።

• በት/ቤት ውስጥ የልጅዎ አስተማሪዎችና ሌሎች ጠቃሚ ሰዎችን ይተዋወቃሉ። o ከእያንዳንዱ መምህር ጋር የሚገናኙበትን የተሻሉ መንገዶች ይማራሉ እና ከእርስዎ ጋር ለመነጋገር ከሁሉ

የተሻለውን የመገናኛ መንገድ ለነሱ ማሳወቅ ይችላሉ ። ▪ እንደ ኢሜይሎች፣ የስልክ ጥሪዎች፣ ወዘተ የመሳሰሉ። ▪ እያንዳንዱ መምህር ለማግኘት በጣም የተሻለው ሰዓት የትኛው ነው?

o በእያንዳንዱ የልጅዎ ክፍሎች ስለ ስርዓተ ትምህርቱ እና በክፍል ውስጥ የሚጠበቁ ነገሮች መማር o በዓመቱ ሙሉ ለልጅዎ ትምህርት ሊጠቅም የሚችል ወሳኝ መርጃ ለእነሱ ማሳወቅ

• ከሌሎች ወላጆች/አሳዳጊዎች መተሳሰር: የልጅዎን እኩዮች ወላጆች ለማግኘት እና በቡድን ጥያቄ እና መልስ ጊዜ ውስጥ ለመሳተፍ ይችላሉ። አንዳንድ ጊዜ ወላጆች ከሌሎች በተነሱ ጥያቄዎች የበለጠ ይማራሉ።

• ከሁሉም በላይ፣ በዚህ ዝግጅት መሳተፍ የእነሱን ልምድ እና ምን እየተማሩ እንደሆነ ለማወቅ ፍላጎት እንዳልዎት ያሳያል።

የስርኣተ ትምህርት ምሽት ዝግጅት እና መረጃውን በሙሉ እንዲረዱት ለማገዝ አስፈላጊ ከሆነ አስተርጓሚ እንዲኖርዎ መጠየቅ።

የልጅዎ ትምህርት ቤት እርስዎን በት/ ቤት ውስጥ ስለሚገኙ ሀብቶች እንዲያውቁ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎችን እንዴት ድጋፍ መስጠት እንደሚችሉ እንዲረዳዎ ሌሎች አስፈላጊ ዝግጅቶች ይኖሯቸዋል።

Find out about important events at your child’s school AMHARIC

4

አስተርጓሚ መጠየቅ:

For updated information go to: https://www.seattleschools.org/departments/english_language_learners

የሲያትል የህዝብ ት/ቤቶች ሁሉም ቤተሰቦች በልጃቸው ትምህርት እና የት /ቤት ዝግጅቶች ላይ እንዲሳተፉ

ያበረታታል። ይህ ስራ ያለ እርስዎ እገዛ ልንሰራው አንችልም!!

የእንግሉዝኛ ቋንቋ ተማሪዎች (ELL) እና አለምአቀፍ ፕሮግራሞች ዲፓርትሜንት በሲያትል የህዝብ ት/ ቤቶች ውስጥ ለሚገኙ ቤተሰቦች በሙሉ በዋናዎቹ ዘጠኝ ቋንቋዎቻችን የትርጉም እና የአስቶርጓሚ አገልግለቶች ያቀራባል: አማርኛ፣ አረብኛ፣ ቻይንኛ፣ ኦሮሞኛ፣ ስፓኒሽኛ፣ ሶማሊኛ፣ ታጋሎግኛ፣ ትግሪኛ እና ቬትናምኛ ሌሎች ቋንቋዎች በሁለት ቋንቋ ተናጋሪ የቤተሰብ አስተባባሪ በኩል በመጠየቅ ይገኛሉ።

እባክዎን በ: 206-252-0072 ይደውሉ ወይም ወደ: [email protected] ኢሜይል ያድርጉ:: የ ASL ትርጉም ከ 504 አስተባባሪው ጋር ይገኛል:: እባክዎን ወደ: [email protected] ኢሜይል ያድርጉ::

አስተርጓሚ የሚፈልጉ ወይም አስተርጓሚ ለመጠየቅ የሚፈልጉ ከሆነ ለማሳወቅ የልጅዎን አስተማሪ፣ አማካሪ፣ ርእሰ መምህር፣ ወይም ኬዝ ማናጀረ ( አይኢፒ ላላቸው ተማሪዎች)ያነጋግሩ።

የእንግሊዝኛ ቋንቋ ተማሪዎች (ELL) እና የአለም ቋንቋ ክረዲቶች

For updated information go to: https://www.seattleschools.org/departments/english_language_learners

ቤተሰቦች ልጆቻቸው የእናታቸውን ቋንቋ ለመገንባትና ለመጠበቅ ከፍተኛ ድጋፍ ይሰጣሉ። ከአንድ በላይ ቋንቋዎች እውቀት መኖሩ ከሌሎች በርካታ ጥቅሞች መካከል አንዱ የልጅዎን የፈጠራ አስተሳሰብ እና የችግር አፈታት ክህሎቶችን ከፍ ሊያደርግ ይችላል።

በፀደይ 2011 ፣ ሲያትል የህዝብ ት /ቤቶች የቋንቋ ብቃት ለመገምገም እና ለተማሪዎች በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ብቃት-ተኮር ክሬዲቶችን ለመስጠት ፖሊሲ እና አካሄድ አፅድቋል።ልጅዎ ከእንግሊዝኛ ውጭ ሌላ ቋንቋ መናገር፣ ማንበብ እና መጻፍ የሚችል(የምትችል) ከሆነ(ከሆነች)፣ በዚህ ፕሮግራም

መሳተፍ ይችላል(ትችላለች)።ተማሪዎች ከ 1-4 የ 2 ኛ ደረጃ ትም /ቤት የዓለም ቋንቋ ክሬዲት ማግኘት ይችላሉ:: እነዚህ ክሬዲቶች የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት የምረቃ መስፈርት እና ለ 4 ዓመት የዓለም(የውጭ አገር) ቋንቋዎች ኮሌጅ የመግቢያዎች መስፈርቶችን ለማሟላት ሊያግዙ ይችላሉ።

በአለም ቋንቋ ክሬዲት ፈተና (እስከ 4 ክሬዲቶች የሚያስገኝ ) ወይም በከፍተኛ ምደባ (AP) ወይም ዓለም አቀፍ ባካሎሬት (IB) የቋንቋ ፈተናዎች በማለፍ የቋንቋ ክህሎታቸውን ያሳዩ ተመራቂዎች State Seal of Biliteracy ያገኛሉ። The Seal ዛሬ ባለው አለም ውስጥ የእንግሊዘኛ ቋንቋ መናገር፣ ማንበብ እና መጻፍ እና ቢያንስ አንድ ሌላ ቋንቋ መጠቀም ጥቅሙን ለማጉላት የታሰበ ነው።

የዓለም ቋንቋ ክሬዲት አማራጭ የሌላ ቋንቋ ዕውቀት ያላቸው ተማሪዎችን እውቅና ይሰጣል። በአፍ መፍቻ ቋንቋው ክረዲት ያገኘው አንድ ተማሪ እንዲህ ብሏል ፣ “የዓለም ቋንቋ ክረዲት ማግኘት ቋንቋየን እና ህዝቤን ያከብራል።” አዎንታዊ ማንነት ይገነባል::

ስለየዓለም ቋንቋ ክሬዲት ፕሮግራም ተጨማሪ ለማወቅ የልጅዎን አማካሪ ያነጋግሩ።

Requesting an Interpreter and English Language Learners AMHARIC

5

የሁለተኛ ደረጃ የምረቃ መስፈርቶች ዝርዝር

በ 2021 እና ከዚያ በላይ ያሉ ተማሪዎች ለመመረቅ 24 ነጥቦች ማግኘት አለባቸው:: በአንድ ሴሚስተር 6 ክፍሎች የሚወስድ አንድ ተማሪ በየሴሚስተሩ 3.0 ክሬዲቶች ማግኘት ይችላል, ይህም ማለት በዓመት ጠቅላላ 6 ክሬዲቶች ያገኛል::ስለዚህ፣ አንድ ተማሪ በአራቱም ዓመት በየዓመት ሙሉውን ፕሮግራም ስድስት ክፍሎች ከወሰደ እና ካለፈ፣በዚሁ በ 24 ክሬዲቶች ይመረቃል።. (እባክዎ በዚህ ሰነድ የመጨረሻ ገፅ ላይ የቃላት መግለጫዎች ይመልከቱ።)

ኮርሶች ክረዲቶች ተጠናቅቋል ለ 4-ዓመት ኮሌጅ ተጨማሪ የሁለተኛ ደረጃ መስፈርቶቾ ተጠናቅቋል

Fine Arts .50 Fine Arts-2 credits. 1 can be personal pathway.

ለ 4 ዓመት ኮሌጅ አነስተኛ የመመዝገብያ መስፈርት ለማየት: Ready Set Grad (Washington State Achievement Council) አንዳንድ ኮሌጆች ተጨማሪ መስፈርቶች አሏቸው.

Fine Arts .50 የሁለተኛ ደረጃ እና ከዛ በላይ እቅድ

Fine Arts .50 ሰዓት የአገልግሎት ትምህርት የተጠናቀቁ ሰዓቶች _______

Fine Arts .50

Language Arts 9A .50 Language Arts - 4 credits.

ተማሪዎች በክልሉ የተወሰኑ ፈተናዎች ወይም የተፈቀዱ የቋንቋ ኣማራጭ ፈተናዎችን እና ሂሳብ እንዲያልፉ ይጠበቅባቸዋል። ከ 2019-20 ጀመሮ የ ሳይንስ ፈተና ማለፍ ይጠብቅባቸዋል።.

Language Arts 9B .50

Language Arts 10A .50

Language Arts 10B .50

Language Arts 11A .50

Language Arts 11B .50

Language Arts 12A .50

Language Arts 12B .50 Algebra1A or Integr Math .50 Mathematics

-3 credits 3 የሂሳብ ክሬዲቶች እና

የሲንየር ዓመት ኳንቲቴቲቨ ሒሳብ

*** ተማሪዎች Algebra I ወይም Integrated Math 1 ፣ እና Geometry ወይምIntegrated Math 2 ወይም Algebra 2 መውሰድ ወይም በ OSPI ተቀባይነት ያላቸው ተመጣጣኝ የሙያ እና የቴክኒካዊ ትምህርት ኮርሶች ክረዲት ማግኘትአለባቸው::

Algebra 1B or Integr Math .50 Geom. 1Aor Integr Math2 .50 Geom. 1Bor Integr Math2 .50

Algeb 2Aor CTE opt *** .50

Algeb 2Bor CTE opt *** .50

Science with a lab .50 Science – 3 credits.

* ተማሪዎች Phys A/Chem A and Biology A and B ማጠናቀቅ አለባቸው:: ከ 3 የሳይንስ ክሬዲቶች ውስጥ ቢያንስ 2 በ ላቦራቶሪ ሳይንስ ሦስተኛው ክሬዲት

በተማሪዎች ፍላጎቶች መሰረት ይመረጣል፣ እና የ CTE ሳይንስ-ተኮር ያካተት ትምህርት ሊጨምር ይችላል::

Science with a lab .50

Science with a lab .50

Science with a lab .50

Science or CTE option* .50

Science or CTE option* .50

Physical Education (PE) .50 Health and PE – 2 credits

የ PE ብቃት ፈተና-በክፍል ውስጥ ይካሄዳል:: ተማሪው (PE) ውድቅ ካልወሰደው፣ ተማሪው አሁንም ፈተናውን ማለፍ አለበት::

Physical Education .50

Physical Education .50

Health .50

Career & Tech Ed (CTE) .50 CTE – 1 credit

ተቀባይነት ያላቸው ኮርሶች ለማወቅ የዲስትሪክቱ ኦፊሳላዊ የኮርሶች ዝርዝር ይመልከቱ። Career & Tech Ed (CTE) .50

WA State History **** .50 (SPS) Social Studies – 3 credits.

****WA State አብዛኛውን ጊዜ በመለስተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ነው የሚወሰደው.:: ተማሪዎች በ 11 ኛ ወይም 12 ኛ ክፍል የ OSPI (ዋሽንግተን ስቴት) ተቀባይነት ያገኘ የciviccs ግምገማ ማጠናቀቅ አለባቸው::

World History 1 .50

World History 2 .50

World History 3 .50

US History 11A .50

US History 11B .50

American Govt .50

WL or Personal Path** .50 WL or Personal Pathways-2 credits

2-3 ዓመታት በአንዱ የዓለም ቋንቋ

**Personal Pathway የዓለም ቋንቋ (WL) ፣ የ ሙያ እና የ ቴክኒካዊ ትምህርት (CTE) ፣ ስነ ጥበብ ፣ ወዘተ ሊሆኑ ይችላሉ-ከስራ ግቦች ጋር የተያያዙ ትምህርቶች

WL or Personal Path** .50

WL or Personal Path** .50

WL or Personal Path** .50

Electives as needed (4 credits)

.50 ea

ጠቅላላ መስፈርቶች

24 ክሬዲቶች

አንዳንድ የ4-ዓመት ኮሌጆች ቢያንስ 2 ነጥብ ( "C" አማካኝ) የ Grade Point Average (GPA) ይጠይቃሉ::

እያንዳንዱ ተማሪ ኮርሶችን ማለፍ እና ከ 2 ኛ ደረጃ ት /ቤት ሊመረቅ ይችላሉ። አንዳንዶች በ 9ኛ ክፍል የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ተማሪዎችን እንዴት እንደሚሆኑ እየተማሩ ነው። በቤተሰቦቻቸው እና በትምህርት ቤት ሰራተኞች ድጋፍ፣ እንደ 9 ኛ ክፍል ያሉ የመማር ችሎታቸውን ማሻሻል ይችላሉ፣እናም የመመረቅ እድላቸውን ከፍ ይላል። በጣም ወቅታዊ የሆነውን መረጃ እያዩ መሆንዎን ለማረጋገጥ የመስመር ላይ የምረቃ መረጃን ይመልከቱ: https://www.seattleschools.org/cms/One.aspx?portalId=627&pageId=18711

High School Graduation Requirements Checklist AMHARIC

6

9ኛ ክፍል የ2ኛ ደረጃ ትምህርት በጣም አስፈላጊው ዓመት ነው::

ከሁሉ በላይ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ለልጅዎ ወይም ሴት ልጅዎ በስራ ግባቸው ላይ ስኬታማ ለመሆን የሚያስፈልጉ ክህሎቶችን እና እውቀቶችን አግኝተው ከ 2 ኛ ደረጃ ት / ቤት እንዲመረቁ ነው:: የኮሌጅ ዝግጅት የግድ ከመካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ወይም ከዚያ ቀደም ብሎ መጀመር አለበት:: ከ2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለመመረቅ ተማሪው ከ9ኛ ክፍል ጀምሮ በሚከተሉት አራት አካባቢዎች ላይ ልዩ ትኩረት በመስጠት መስመር ላይ መሆን ይጠበቅበታል::

1. በት/ቤት ሁልጊዜ የመገኘት ሁኔታ ወሳኝነት አለው::

ተማሪዎች በክፍል ውስጥ የማይገኙ ከሆነ እየተማሩ አይደለም ማለት ነው:: ጥናቶች እንደሚያሳዩት በአንድ ሰሚስተር ከአምስት ቀናት በላይ የሚቀሩ ተማሪዎች ትምህርቱን የማለፋቸውና ክሬዲት የማግኘት ሁኔታቸው በጣም ዝቅተኛ ነው:: እነዚህ ተማሪዎች ትምህርታቸውን የማቋረጥ ሁኔታም በጣም ከፍተኛ ነው::

ወላጆች እንዴት ሊረዱ ይችላሉ?

➢ ሁልጊዜ በት/ቤት የመገኘት ጠቀሜታን ለተማሪዎት ያውሩ::

➢ ተማሪዎ ሁልጊዜ ጥዋት በጊዜ ከቤት እንዲወጣ ይርዱት::

➢ ለተማሪዎት ወደመኝታ የመሄጃና የቤት ስራ መስሪያ ሰዓቶችን ያስቀምጡ::

➢ ለተማሪዎት የቴሌቭዥን እና የመሳሰሉትን የመመልከቻ ጊዜዎችን ይገድቡ::

2. የሚቆጠር የክሬዲት መጠን

የዘጠነኛ ክፍል ተማሪዎች 24 ክሬዲት አግኝተው ለመመረቅ ቢያንስ ስድስት ክሬዲት ማግኘት ይጠበቅባቸዋል:: ይህን ያሟሉ ተማሪዎች 85% ያህል ከሌሎች ተማሪዎች ይበልጥ የመመረቅ እድል አላቸው:: ወላጆች እንዴት ሊረዱ ይችላሉ?

➢ ተማሪዎት ለመመረቅ የሚያስፈልጉትን ኮርሶች መውሰዱን ያረጋግጡ

➢ የ9ኛ ክፍል ኮርሶችን በሙሉ ማለፉን ያረጋግጡ::

➢ ተማሪዎት ድጋፍ በሚፈልግበት ወቅት አስተማሪዉን እንዲጠይቅ ያበረታቱ::

➢ ስለ ሁሉም የልጆችዎ አስተማሪዎች የነጥብ አሰጣጥ አሰራሮችን ማወቅዎትን ያረጋግጡ::

➢ ሶርስ በሚባለው የሲያትል የህዝብ ት/ቤቶች ኦንላይን ሲስተም ላይ ይመዝገቡ:: ይህም ወላጆች

በየዕለቱ የተማሪዎቻቸውን አቴንዳንስና የትምህርት ዉጤታቸውን የሚከታተሉበት ነው::

➢ የተማሪዎትን መምህራንና አማካሪዎችን ይወቁ:: አብረው በመስራት መፍትሄ ሊያገኙላቸው

የሚችሉ ችግሮች ካሉ እንዲነግሩዎት ያበረታቷቸው::

የወላጆች ተሳትፎ ቁልፍ ነው::

ተማሪዎት አንድ ጊዜ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ከደረሰ ምናልባት መሳተፍ እንደሌለብዎት ይነግሮት ይሆናል::

ነገር ግን አይመኑት:: ተማሪዎት ቀደም ሲል ሲያደርጉት እንደነበረው ድጋፍዎትን የበለጠ ይፈልጋል! የሚከተሉትን ማድረግዎትን እርግጠኛ ይሁኑ:

✓ የተማሪዎትን የአካሄድ ሁኔታ እና ለመመረቅ እያሳየ ያለውን እድገት

ለማወቅ የ እድገት(ፕሮግረስ)

ሪፖርት (በየአምስት ሳምንቱ) እና

የዉጤት ካርድ (በየ ዘጠኝ

ሳምንቱ) ኮፒውን ያግኙ::

✓ በት/ቤቱ የማስተዋወቂያ

ፕሮግራሞች: ስብሰባዎችና

ኮንፍረንሶች ላይ ይሳተፉ::

✓ ተማሪዎትን ስለ የቤት ስራዎቻቸው ለመጠየቅ የሚችሉበትን ሰዓት ይመድቡ::

✓ ልጅዎት እርዳታ የሚፈልግ ከሆነ

በት/ቤት ውስጥ ማንን ደውለው

ማነጋገር እንዳለብዎት ይወቁ::

9th Grade is the most important year in high school AMHARIC

7

ዕውነታ

ከኮሌጅ የተመረቁ ትምህርታቸውን ካቋረጡት ይልቅ በአማካይ በዓመት ከ 12,900 ዶላር በላይ ያገኛሉ::

የተማሪዎትን የመመረቂያ መስፈርቶች

ይረዱ:: በሚከተለው የወረዳው ድህረ

ገጽ ላይ ይገኛል::

www.seattleschools.org

በመጀመሪያ “Students” ከዚያም

“Academics,” በመቀጠልም

“Graduation Requirements.” በሚለው ቁልፍ ላይ ይጫኑ ወይም የመመረቂያ መመሪያውን ለማግኘት

የተማሪዎትን አማካሪ ይጠይቁ::

ዕውነታ

ጥናቶች እንደሚያሳዩት 2ኛ ደረጃን ያጠናቀቁና ከኮሌጅ የጨረሱ ተማሪዎች ካልጨረሱት ተማሪዎች ይልቅ በህይወት ዘመናቸው በሚሊዮን የሚጠጋ ዶላር የሚያገኙ ከመሆኑም በላይ ስራ ያለማግኘት ዕድላቸው

በጣም ዝቅተኛ ነው::

ወላጆችን በ2ኛ ደረጃ የተማሪዎች

ስኬታማነት (EFIHS) ላይ ማሳተፍ

በሲያትል የህዝብ ት/ቤቶችና በጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ ተነሳሽነትና

ትብብር የተዘጋጀ ሲሆን በዩ. ኤስ. ትምህርት ክፍል በገንዘብ የሚደገፍ

ነው::

3. የ9ኛ ክፍል ኮርሶችን ማለፍ ወሳኝነት አለው::

ተማሪዎች 60% እና ከዚያ በላይ ካገኙ ትምህርታቸውን ለማለፍ እና ክሬዲቶችን ለማግኘት ይችላሉ:: ነገር ግን ኮሌጅ ለመግባት ተማሪው በተቻለ መጠን የተሻለ ውጤት ለማግኘት ከፍተኛ ጥረት ማድረግ ይጠበቅበታል:: ከ2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለመመረቅ በአማካይ "C " ማግኘት ያስፈልጋል:: ዝቅተኛ ውጤት ያገኙ ተማሪዎች ለምረቃ ብቁ ለሚያደርጋቸው የስቴት ፈተና ወይም ለኮሌጅ የመግቢያ መስፈርት አልተዘጋጁም ማለት ነው::

ምንም እንኳ ተማሪዎች የወደቁበትን ኮርስ ከት/ሰዓት ውጭ ወይም በበጋው ወቅት

ቢደግሙትም በ 11ኛ እና 12ኛ ክፍል ለሚሰጡት ከፍተኛ ኮርሶች ያላቸው ዝግጁነት አነስተኛ

ስለሚሆን ይህ ደግሞ ለ 4 ዓመት የኮሌጅ ትምህርት ለማመልከት ዘቅተኛ

ዝግጁነትእንዲኖራቸው ያደርጋቸዋል::

ወላጆች እንዴት ሊረዱ ይችላሉ? ➢ ተማሪዎት ሁልጊዜ የቤት ስራዎችን መስራቱን ያረጋግጡ::

➢ ከተማሪዎት ጋር ግቦችን በማስቀመጥ ስለ እድገታቸው ይጠይቋቸው::

➢ እርዳታ ሲፈልግ አስተማሪዎቹን እንዲጠይቅ ተማሪዎትን ያበረታቱ::

➢ ስለ ሁሉም የልጆችዎ አስተማሪዎች የነጥብ አሰጣጥ አሰራሮችን ማወቅዎትን ያረጋግጡ::

➢ A የ2ኛ ደረጃ ት/ቤት እና ከዚያ በኋላ ያለውን እቅድ ኮፒውን ለማግኘት ት/ቤትዎትን

ይጠይቁ::

➢ ተማሪዎት ደጋፊ ኮርሶችን(electives) ፍላጎታቸውን ለማሰስና ከፍተኛ ትምህርቶችን

ለመውሰድ ይችሉ ዘንድ እንዲጠቀሙባቸው ያበረታቷቸው::

4. የ2ኛ ደረጃ ትምህርት የብቃት ማረጋገጫ ፈተና አስፈላጊ ነው:: For updated information go to: : https://www.seattleschools.org/cms/One.aspx?portalId=627&pageId=18711

በዋሽንግተን ስቴት ከሚገገኙ ማናቸውም ት/ቤቶች ለመመረቅ ተማሪዎት የንባብ: የጽሁፍ:

የሂሳብ እና የሳይንስ ፈተናዎችን ማለፍ ይጠበቅበታል::

ወላጆች እንዴት ሊረዱ ይችላሉ? ➢ ለተመራቂ ተማሪዎት ስለ ስቴቱ የፈተና መስፈርት ይረዱ::

➢ ተማሪዎት የስቴቱ ፈተና ለመመረቅ አማራጭ ሳይሆን አስፈላጊ መሆኑን መገንዘቡን እርግጠኛ

ይሁኑ::

➢ ተማሪዎት መዘጋጀቱንና በፈተናው ቀን በቂ እንቅልፍ ጥሩ ቁርስ ማግኘቱን ያረጋግጡ::

➢ የፈተና ውጤት እንደተለቀቀ የልጅዎትን ውጤት ማየቶትን ያረጋግጡ:: ተማሪዎት

በማናቸውም ክፍል የሚፈለገውን ደረጃ የማያሟላ ከሆነ የት/ቤቱን አማካሪ ያነጋግሩ::

9th Grade is the most important year in high school, page 2 AMHARIC

8

ፀጋዎች (The source) For the most up to date information, go to https://www.seattleschools.org/cms/One.aspx?portalId=627&pageId=16245

ሶርስ እርስዎ እና ልጅዎ አቴንዳንስ ፣በኮርሶቻቸው ላይ ያላቸው እድገት ፣ እና የጎደሉ አሳይመንቶች ለመከታተል የሚያስችል የዌብ ፀጋ ነው። ተማሪዎች የየራሳቸው ሶርስ አካውንት ሊኖራቸው ይችላል።ወላጆች/አሳዳጊዎች የልጆቻቹ ግስጋሴ ለመከታተል እና ለመደገፍ የተለያየ የሶርስ አካውንት ሊኖራችሁ ይችላል። ወላጆች /አሳዳጊዎች እያንዳንዱ የልጆዎን መረጃ ለማየት የሚያስችል አንድ አካውንት ሊኖራችሁ ይችላል።ሶርስ የሚከተሉትን እንዲያደርጉ ያስችልዎታል:

• የልጅዎን የክፍል ፕሮግራም መመልከት

• ውጤቶችን መመልከት እና መከተታል • የአቴንዳንስ ሪከርድ መመልከት

• የጎደለውን አሳይመንት መከተታል

• ወደ መምህራን ኢሜይል ማድረግ

• የልጅዎ የመደበኛ ፈተናዎች ውጤት መመልከት

• በአንዳንድ ሁኔታዎች፣ መጪ አሳይመንቶች መመልከት

• እና ሌሎች …

የጎደሉ አሳይመንቶችን ለማየት እዚህ ጠቅ ያድርጉ። የልጅዎን የመደበኛ ግምገማዎች(ፈተናዎች)ውጤቶች ለማየት እዚህ ጠቅ ያድርጉ፥

ውጤቶች አቴንዳንስ

AMHARIC

9

ሶርስ አካውንት ለመክፈት

1. ሶርስ አካውንት ከመክፈትዎ በፊት: a. በሲያትል የህዝብ ት/ ቤቶች ውስጥ ተመዝግበው ለሚገኙት እያንዳንዱ ልጅዎ፣ እርስዎ እንደ የተማሪው ወላጅ ወይም አሳዳጊ

መመዝገብ አለብዎት። b. የኢሜይል አድራሻዎ በእያንዳንዱ የተማሪዎ መዝገብ መኖር አለበት። በቤተሰብዎ ውስጥ ያሉ እያንዳንዱ የ SPS ተማሪ ተመሳሳይ

የኢሜይል አድራሻ እንደሰጡ እርግጠኛ ይሁኑ::

በሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ያሉ እያንዳንዱ ልጆችዎ በመዝገባቸው ላይ እርስዎ እንደወላጅ ወይም እንደኣሳዳጊ መመዝገብዎ እና ተመሳሳይ ኢሜይል አድራሻ መኖርዎት ለማረጋገጥ ከፈለጉ ከልጅዎ ትምህርት ቤት ጋር ያረጋግጡ። እንደ አማራጭ፣ ከአንድ ትምህርት ቤት በላይ ልጆች ካሎት፣ ወደ የምዝገባ አገልግሎት በ 206-252-0760 በመደወል የሁሉም ልጆችዎ መረጃ ማዘመን እና በእያንዳንዳቸው አንድ አይነት የኢሜይል አድራሻ መኖሩን ማረጋገጥ ይቻላል።

2. ሶርስ አካውንት ለመከፈት: a. እባክዎን http://ps.seattleschools.org/ይጎብኙ እና ሴትአፕ(setup) የሚለውን ጠቅ ያድርጉ:: b. በእያንዳንዱ የት/ቤት ተማሪ የተመዘገበውን የኢሜይል አድራሻ ያስገቡ፣ ከዚያም Enter ጠቅ ያድርጉ:: c. ከ [email protected] የተላከ መልዕክት ለማየት ኢሜይልዎን ይመልከቱ።

ይህ ኢሜይል ካልደረሰዎት: 1) ስፓን ወይም ትራሽ ፎልደር ይመልከቱ:: 2) የኢሜል አድራሻዎን ለመስጠት ትምህርት ቤቱን ወይም የምዝገባ አገልግሎትን በ 206-252-0760 ያነጋግሩ::

d. ኢሜል ይክፈቱና አገናኙን(link) ጠቅ ያድርጉ:: e. Username (በትምህርት ቤቱ መዝገብ ላይ ያለው የኢሜል አድራሻ) ያስገቡ እና የይለፍ ቃል (Password)ይፍጠሩ።

1) የይለፍ ቃልዎ(password) 5 ወይም ከዚያ በላይ ካራክተሮች መሆን አለበት። 2) እባክዎ በይለፍ ቃልዎ(password) ውስጥ እፓስትሮፍ ‘ አይጠቀሙ።

f. ሶርስ መመርመር ለመጀመር Enter ጠቅ ያድርጉ። እርዳታ ለማግኘት እባክዎ [email protected] ን ይገናኙ::

ወይም በትምህርት ቤትዎ ዋናውን ቢሮ ማግኘት ይችላሉ::

በተጨማሪም ቤት ውስጥ ኮምፒዩተር ከሌለዎት፣ የሶርስን አካውንትዎ በሚከተሉት ኮምፒተር በመጠቀም መግባት ይችላሉ : • የሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች ነፃ የሞባይል አፕ • የህዝብ ቤተ-መጽሐፍት

• የልጅዎ ት / ቤት

• በኣቅራብያዎ የሚገኝ የማህበረሰብ ድርጅት

ቤተሰቦች ብዙ ጊዜ የሚጠይቁት: “ሶርስ በምንያህል ግዜ ማየት አለብኝ?” መልስ : አብዛኞቹ መምህራን ሶርስን በየሁለት ሳምንት ያዘምኑታል፣ ነገር ግን ይህ የግድ አይደለም። አስፈላጊ ነው ብለው በሚያስቡበት ጊዜ ሁሉ በተደገጋሚ ማየት ይችላሉ፣ነገር ግን ሶርሱን በየሁለት ሳምንቱ ከተመለከቱ ትክክለኛውን መረጃ ሊያዩ ይችላሉ። የትምህርት ክትትልን በቅርበት መከታተል ከፈለጉ፣ በተደጋጋሚ ሶርስን መፈተሸ ይችላሉ። በ ሶርስ ላይ ያለው መረጃ እርግጠኛ ካልሆኑ የልጅዎን አስተማሪዎች ኢሜይል ማድረግ ይችላሉ።

ስኩሎጂ: አንዳንድ መምህራን የቤት ስራዎች፣ መልእክቶች፣ ዝግጅቶችን፣ እና የቀን መቁጠሪያዎችን ለመለጠፍ ስኩሎጂ ሊጠቀሙ ይችላሉ። በሶርስ አካውንትዎ አማካኝነት ወደ ስኩሎጂ መግባት ይችላሉ ።

The SOURCE Account Set Up AMHARIC

10

ወላጆች የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የቤት ስራቸውን እንዲያጠናቅቁ እንዴት ሊረዱዋቸው ይችላሉ? ጥናቶች የቤት ስራዎች ከኣንደኛ ደረጃ ወይም ከመካከለኛ ትምህርት ቤት ይልቅ በ 2 ኛ ደረጃ ት/ቤት ይበልጥ ጥቅሞች እንዳሉት ያሳያሉ።በቤት ሥራ ላይ የወላጅ ተሳትፎ ጠንካራ ተፅዕኖ አለው የሚሉ ጥቂት ጥያቄዎች አሉ።ወላጆች፣ወጣቶች የቤት ሥራን ሲቃወሙ ወይም ይህን ለማድረግ የሚያስችላቸውን ክህሎቶች ሲያንሳቸው ምንም እንኳን ማጨናነቅ ባይችሉም፣የት/ ቤት ስኬት የቤት ስራን ማጠናቀቅ ላይ ያሉትን መሰናክሎች ለማሸነፍ የወላጆች ፈቃደኛነት ላይ የተመሠረተ ሊሆን ይችላል።

ወላጆች ምን ማድረግ ይችላሉ?

ወላጆች፣ስለ የቤት ስራ አስፈላጊነት ግልጽ መልእክቶችን እና የተወሰነ የድጋፍ ስልቶችን በመስጠት የቤት ስራቸውን በማገዝ ወጣቶች እንዲሳካላቸው ሊያደርጉይችላሉ ። ወላጆች ለልጆቻቸው የቤት ስራን በተመለከተ ሊሰጥዋቸው የሚችሉ ሶስት ቁልፍ መልዕክቶች አሉ። የቤት ስራ የትምህርት አስፈላጊ ክፍል ነው:: ወጣቶች የቤት ስራቸውን እንዲያጠናቅቁ እና ብግዜ እንዲያስረክቡ መጠበቅ። ወጣቶች የቤት ስራ ኃላፊነት እንዲወስዱ እና የጊዜ አስተዳደር ችሎታ እንዲኖራቸው ማድረግ። እንደ አስፈላጊነቱ የወላጅ ወይም የሌላ ድጋፍ ይቀርባል::: አንዳንድ ወጣቶች በትክክል በቤት ስራ በጣም ይቸገራሉ፣ ምክንያቱም በጣም ከባድ ሆኖ ስለሚያገኙት ወይም በራሳቸው እንዴት እንደሚሠሩት ስለማያውቁ ነው። ሆኖም ግን ወላጆች ማበረታቻ ሲሰጡዋቸው እና ሲቸገሩ እርዳታ ማግኘት እንደሚችሉ ሲያረጋግጡላቸው ወጣቶች ተስፋ የመቁረጥ ወይም የመበሳጨት እድላቸው ዝቅተኛ ይሆናል ። ወጣቶች ያልገባቸው ወይም የተቸገሩበት የቤት ስራቸው በመለየት ላይ ለመርዳት ይችላሉ። ወጣቶች እርስዎ ከሚሰጡዋቸው የቤት ስራ እገዛ በላይ የሚፈልጉ ከሆነ፣እነሱ ወይም እርስዎ የሚያስቸግራቸው የትምህርት ዓይነት መምህር ማነጋገር ይችላሉ። ወይም ተጨማሪ የበለጠ እርዳታ ለማግኘት አማካሪውን ሊያነጋግሩ ይችላሉ። ልጅዎ ከአስተማሪ ጋር ለመወያየት እንዲዘጋጅ ለማድረግ ክእርስዎ ጋር ጥያቄዎችን የመጠየቅ ልምምድ ሊያደርግ ይችላል። የተማሪ ተነሳሽነት የማይሰሩ ከሆነ ወላጆች መምህራንን በቀጥታ እንዲያነጋግሩ ይበረታታሉ። በጣም ስኬታማ የሆኑ ተማሪዎች እና ብልህ ወላጆች እንኳን ከቤት ውጭ በትምህርት ቤት ውስጥ ከሚገኘው የቤት ሥራ ማእከል ወይም የትምህርት አስጠኚ ተጠቃሚ ይሆናሉ። ወላጆች የልጆቻቸው የቤት ስራ አይሰሩም። ይህ መልዕክት የወላጅ ሚና የእነሱ ሥራ መስራት ሳይሆን እነሱን ማበረታታት እና ስራቸውን እንዲያከናውኑ ማገዝ መሆኑን ለወጣቶች ለመንገር ነው።

ከ Homework: A guide for Parents By PEG DAWSON, EDD, NCSP, Seacoast Mental Health Center, Portsmouth, NH

National Association of School Psychologists ተወስዶ የተሻሻለ

Homework Help, page 1 AMHARIC

11

የቤት ስራን ለመደገፍ ስትራቴጂዎች

ከነዚህ መልእክቶች ባሻገር፣ ወላጆች ወጣቶችን የቤት ስራቸውን ሊረዱባቸው የሚችሉባቸው ጠቃሚ መንገዶች አሉ በየእለቱ የወጣትዎን የቤት ስራ መከታተል:: የቤት ሥራን ለማጠናቀቅ የወላጅ ድጋፍ ያላቸው ወጣቶች በቤት ስራ ላይ የበለጠ ጊዜ እንደሚያሳልፉ ጥናቶች ያሳያሉ። ወላጆች ወጣት ልጆቻቸውን ለማበረታታት፣ትኩረት ለመስጠትና ከቤት ስራ ጋር የተያያዙ አሉታዊ ስሜቶችን ለመዋጋት የሚያስችሉ ስትራቴጂዎች ሊሰጧቸው ይችላሉ። አንዳንድ ወጣቶች፣ በተለይም በዕድሜ እየገፉ ሲሄዱ፣ የወላጆች እርዳታ ወይም ክትትል ይቃወማሉ፣ በትንሹ ወላጆች ስለ የቤት ስራ እና ስራውን መቼ ለማጠናቀቅ እንዳቀዱ መጠየቅ ይችላሉ:: ‘‘ምን ማድረግ ይጠበቃል እና መቼ ነው የሚሰራው?’’ ወላጆች ወጣት ልጆቻቸው የቤት ስራ እቅድ እንዲያወጡ በሚረዱበት ጊዜ ለወላጆች በየዕለቱ መደጋገም ይሆናል። ግልፅ የሆነ የተለመደ የቤት ስራ እቅድ መመስረት:: ከተለመዱ ተግባራት የተያያዙ ስራዎች ለማከናወን በጣም ቀላል ነው። ወላጆች የቤት ሥራን ለማጠናቀቅ በየቀኑ በመሥራት የቤት ስራውን በተቀላጠፈ መንገድ ማከናወን ብቻ ሳይሆን፣ ለኮሌጅ እና ሥራን ጨምሮ ለመጪው ህይወት ተግባራዊ ሊያደርጋቸው የሚችሉበትን ስርዓት ያበረታታል። የቤት ሥራዎችን ለመስራት የሚከናወኑ ተግባራት የሚከተሉትን ያካትታሉ፥:

• ልጅዎ ውጤታማ የሆነ የመማሪያ ቦታ እንዲፈጥር ያግዙ:: ሁሉም ተማሪዎች የሚማሩትና የሚያጠኑት በተመሳሳይ መንገድ አይደለም:: በአጠቃላይ፣ አንድ ተማሪ ከረብሻ እና መቆራረጥ ነፃ የሆነ፣ ጥሩ ብርሃን እና ምቹ የሆነ ወንበር ባለው ቦታ ላይ የበለጠ ተነሳሽነት እና በጥናት ላይ ማተኮር ይችላል።

• ታዳጊዎች የቤት ሥራዎቻቸውን ለመጨረስ የሚያስፈልጉት ነገሮች በሙሉ መኖራቸውም እርግጠኛ ይሁኑ። (ለምሳሌ፣ እርሳሶች፣ ማጥፊያ፣ ወረቀት፣ መዝገበ ቃላት፣ ካልኩሌተር)::

• የቤት ሥራ ለመስራት ጥሩ ጊዜን ይወስኑ (ለምሳሌ፣ ከትምህርት በኋላ፣ ከእራት በኋላ ወይም በፊት)::

• የቤት ስራን ለማጠናቀቅ እቅድ ያውጡ ( ለምሳሌ :የሚከናወኑ ተግባራትን ሁሉ ይዘርዝሩ፣ ወጣቶች እያንዳንዱን ስራ መቼ እንደሚጀምሩ እና ስራውን ለመፈፀም ምን ያህል ጊዜ እንደሚወስድ ይገምቱ)::

• ወጣቶች የተዋቀረ ስርዓቶችን ማቋቋም እና በእቅዳቸው መቆየት እንዲችሉ መርዳት። ወጣት ልጆችዎ የመስርያ ቦታቸውን እንዲያፀዱ እና የቤት ስራዎችን ለመከታተል የሚያስችሉ ስርዓቶችን እንዲኖራቸው ያግዙዋቸው።

ከ Homework: A guide for Parents By PEG DAWSON, EDD, NCSP, Seacoast Mental Health Center, Portsmouth, NH

National Association of School Psychologists ተወስዶ የተሻሻለ

Homework Help, page 2 AMHARIC

12

ለወላጆች/አሳዳጊዎች ከተማሪዎቻቸው ጋር መሳተፍ የሚያስችላቸው አንዳንድ መንገዶች

• ልጅዎ ለድርጊታቸው ተጠያቂ እንዲሆን ያድርጉ:: ይህም ማለት እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል ለድርጊታቸው ተጠያቂ ናቸው፣

እና እያንዳንዱን የስነምግባር ደንቦች እና የአቋም ደረጃዎች መከተል ይጠበቅበታል። ልጆቻችሁን ተጠያቂ የማድረግ

የመጀመሪያው እርምጃ እርስዎ ስለሚጠብቁት ነገር ግልጽ ማድርግ ነው።

• ልጅዎን ስለ አካዴሚያዊ ግቦች እና የሥራ ፍላጎቶች ይጠይቁት(ቋት)። ስለ ኮሌጅ እና የሥራ እድሎች የተለያዩ የመረጃ

ምንጮችን በመሰብሰብ እገዛ ያድርጉ።

• ልጅዎ ከንባብ የተገኙ ትርጉማቸው የማያውቃቸው 5 ቃላቶች እንዲመርጡ ያድርጉ እና እያንዳንዱን ቃል በአረፍተ ነገሩ

ውስጥ እንደገና እንዲያነቡት ያድርጉ። በእያንዳንዱ ዓረፍተ ነገር ውስጥ እንዴት ጥቅም ላይ እንደሚውል መሠረት በማድረግ

ለእያንዳንዱ ቃል ያላቸውን ትርጓሜዎች ተነጋገሩ።

• የማኅበራዊ ጥናት ወይም የሳይንስ መጽሀፍ በማንበብ፣ ልጅዎ ጽሑፉን ለመረዳት አስፈላጊ የሆኑትን ቃላቶች እንዲያወጡ

ያድርጉ። የራሳቸውን የይዘት መዝገበ ቃላት ሲፈጥሩ አጫጭር መግለጫዎችን መጨመር ይችላሉ።

• ልጅዎ የፅሁፍ ማስታወሻዎችን መዝግበው እንዲይዙ ማድረግ

• በህይወትዎ የሚያዩትን የሂሳብ ግንኙነትን ይወያዩ:

o ለቤተሰባችን የኤሌክትሪክ ወይም የውሃ ቢል አስተዋፅኦ ያላቸው ነገሮች ምንድን ናቸው?

o መረጃዎች መሰብሰብ: በመኪና የተጓዙበት ርቀት እና የግዜ ርዝማኔ::

o ቤታችንን ቀለም ለመቅባት ምን ያህል ቀለም እንደሚያስፈልገን እንዴት ማወቅ እንችላለን?

o በጋዜጣ ወይም መጽሔት ውስጥ ዝርዝር ወይም ሰንጠረዥ ሲመለከቱ፣ ተማሪዎችዎ ምን ዓይነት ድምዳሜዎች ላይ

ሊደረሱ እንደሚችሉ ይጠይቁ።

• በቤት ውስጥ ስለሳይንስ ተነጋገሩ:: ልጅዎ በሳይንስ ትምህርት የተማረው(የተማረችው)ለቤተሰብ ማብራራት

ይችላል(ትችላለች)? የልጅዎ የሳይንስ ደብተር በአንድ ላይ ተመልከቱት።

• ልጅዎ በዙሪያቸው ስላለው ዓለም ጥያቄዎችን እንዲጠይቅ(እንድትጠይቅ) ያበረታቱ:: ጥያቄን በቀጥታ ከመመለስ ይልቅ

በመመልከት፣ በማሰስ፣ በመመርመር ወይም በጥናት ላይ ተንተርሰው መልስ እንዲሰጡ ያግዟቸው።

ከ from the 2014 Seattle Public Schools’ Family Literacy, Math, & Science Toolkits that were developed by the District’s Literacy, Math, and Science coaches and Family Engagement Office ተወስዶ የተሻሻለ

Some Ways for Parents/Guardians to Engage with Their Students AMHARIC

TIGRIGNA

13

ለት/ቤት አማካሪዎች በጣም በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎች

ልጄ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ስኬታማ እንዲሆን ምን ማድረግ እችላለሁ?

መልስ: ይሳተፉ !የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ወደ ራሳቸው መቻል እያመሩ ነው። ቢሆንም፣ የወላጆች ተሳትፎ እና ቁጥጥር ያስፈልጋል። ይህ የምንተዋቸው ግዜ አይደለም! በቤት እና በትምህርት ቤት ውስጥ ይሳተፉ። ተማሪዎች ከመካከለኛ ደረጃ ወደ ሁለተኛ ደረጃ ሲሸጋገሩ የአዋቂዎች ተሳትፎ ብዙ ጊዜ ጠቀሜታ እንዳለው ጥናቶች ያሳያሉ። በልጅዎ ህይወት ውስጥ ስለ የትምህርት አስፈላጊነትን ለመግለፅ ከእርስዎ የበለጠ ማንም ሰው እንደሌለ ያስታውሱ። በቤት ውስጥ ስለሚደረግ የውይይት ጊዜ ይጨምሩ። ሰለ የክፍል ሥራዎችን፣ ንጥፈቶች እና የቤት ስራን ይወያዩ። ልጅዎ እንዴት እንደሚሰራ እና/ወይም በክፍል ውስጥ ምን እየተማሩ እንደሆነ እና እንዴት ማገዝ እንደሚችሉ ይጠይቁ።

መማክርት ልጄን ለኮሌጅ እቅድ እና ማመልከቻዎች ይረዱዋቸዋል?

መልስ: ይህ የሥራችን ጠቃሚ እና አስደሳቹ ክፍል ነው። በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መጀመሪያ ላይ ከእርስዎ ጋር ከተገናኘን እና የስራ ግንኙነት ከገነባን ፣ ለእናንተ እና ለልጅዎ በጣም አጋዥ ልንሆን እንችላለን።

ልጄ ከአንድ ክፍል /መምህር ጋር ችግር እያጋጠመው ነው:: ክፍሉ ሊቀየር ይችላል?

መልስ: ከአስተማሪው ጋር በቀጥታ የሚደረግ ግንኙነት ብዙ ችግሮችን ሊፈታ ይችላል:: የሚጀምረው ከዚህ ነው! ኢሜል ለግንኙነት

አስተማማኝ ስልት ሊሆን ይችላል፣ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ መልእክቶች በዋናው ጽ/ቤት ወይም በድምጽ መልእክት መተው ይቻላል።የቀን የስልክዎ ቁጥር ማካተትዎን ያረጋግጡ። ችግሩ እየቀጠለ ከሄደ፣አማካሪ ያስውቁ።

ልጄ ሲታመም፣ ያመለጠው ሥራ እንዴት ማግኘት እችላለሁ?

መልስ: ያመለጡትን አሳይመንቶች ለማግኘት የልጅዎን አስተማሪ በቀጥታ ኢሜል መላክ ወይም መደወል ይችላሉ። ያመለጠውን አሳይመንት ለመፈተሽ ሶርስ እና ስኩሎጂ ገጾችን ማየት ይችላሉ። በተጨማሪ፣ ልጅዎ የቤት ሥራውን እንዲያከናውን ከጓደኛው/ዋ ጋር እንዲገናኙ ማበረታታት ይችላሉ።

ተማሪዬ ከክፍል ውስጥ በአንዱ የማያልፍ ከሆነ፣ የሰመር ትምህርት ወይም ክሬዲት መልሶ ማግኘት አስፈላጊ ነው?

መልስ: በኮርሱ ላይ ይወሰናል:: ከልጅዎ አማካሪ ጋር መነጋገር በጣም አስፈላጊ ነው።

ስለ ልጅዎ ስጋት ካለብዎ ወይም ለውጥ ካደረጉ እና ለምን ለውጥ እንዳረጉ የማያውቁ ከሆኑ --የቤተሰብዎ ዶክተር ያነጋግሩ። በተጨማሪም የወጣቱ የጤና ማእከል፣ የትምህርት ቤቱን ነርስ፣ ወይም የልጅዎን የትምህርት ቤት አማካሪ ማግኘት ይችላሉ።

አጠቃላይ ስጋት ካለዎት እና ማንን መደወል እንዳለብዎት የማያውቁ ከሆነ፣እባክዎን ለልጅዎ የትምህርት ቤት አማካሪ ይደውሉ።

ከ Seattle Public School’s Ballard High School “Welcome to 9th Grade Parent Orientation” Packetተወስዶ የተሻሻለ

Most Frequently Asked Questions of School Counselors AMHARIC

14

Naviance: የመስመር ላይ (online) የኮሌጅ እና የስራ ዕቅድ መሳሪያ

Naviance ከ 8 ኛ እስከ 12 ኛ ክፍል ያሉ የሲያትል የህዝብ ት/ ቶች ተማሪዎች እና ቤተሰቦቻቸው ከመከር 2018 ጀምሮ ያለ ነው። በ Naviance አማካኝነት ፣ ተማሪዎች ኮሌጆችንና የሙያ ጉዞዎችን መመርመር ይችላሉ፣ከሞያ እና ግላዊ ባህርያቸው ክህሎቶችን እና ተሰጥኦዎችን ይተነትናሉ፣ እና አካዳሚያዊ ግቦች ላይ ለመድረስ በሚያደርጉት ጉዞ ላይ በእቅዳቸው ለመቆየት ያስችላቸ ዋል። Naviance የድህረ ከፍተኛ ደረጃ ትምህርት እቅድ ግንኙነት ለተማሪዎች ለአማካሪዎች እና ለቤተሰቦች ትብብር ያበረታታል።

የተማሪ ጥቅሞች Naviance ተማሪዎች ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት በኋላ የሚከተሉትን እድል በመስጠት ለሕይወታቸው የሚሆን ዕቅድ እንዲያወጡ ያስችላቸዋል :

• የኮሌጅ ዕድሎች እና የስራ መስኮችን ማሰስ • የ 4 ዓመት ኮርስ እቅድ ማዘጋጀት እና ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ምረቃ ክትትል ማድረግ • የስኮላርሽፕ ፍለጋን ጨምሮ ለኮሌጅ የገንዘብ አማራጮችን መገንዘብ • ተስማሚ የሆኑ ኮሌጆችን፣ የኮሌጅ መስፈርቶችን እና የሙያ መስኮችን መለየት • የራስ መግለጫ፣ የትምህርት ማስረጃ እና የመምህራን የድጋፍ ደብዳቤን ጨምሮ ለሥራ እና ለኮሌጅ ማመልከቻዎች የሚያገለግሉ

የሰነድ መረጃዎች ማዘጋጀት

የቤተሰብ ጥቅሞች

Naviance ወላጆች ተማሪዎቻቸው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸው ካጠናቀቁ በኋላ የሚከተሉትን እድል በመስጠት ለሕይወታቸው

የሚሆን ዕቅድ እንዲያወጡ ያስችላቸዋል: • የኮሌጅ ዕድሎች እና የስራ መስኮችን ከተማሪዎ ጋር ማሰስ • ተማሪዎ ለኮሌጅ እና ለሙያ ዕቅድ ሂደት ባለቤትነት እንዲወስዱ ማድረግ • ልጅችዎ ጥንካሬዎቻቸውን፣ ፍላጎቶቻቸውን፣ እና ግቦቻቸውን እንዲመረምር ማገዝ • የስኮላርሽፕ ፍለጋን እና የገንዘብ ድጋፍ መረጃዎች ጨምሮ ለኮሌጅ የገንዘብ አማራጮችን መዳሰስ • በጣም አስፈላጊ የሆኑ ቀኖችን መከታተል

የ Naviance አጠቃላይ እይታ ይመልከቱ: https://www.seattleschools.org/academics/college_career_readiness/naviance

ተማሪዎች ወደ Naviance እንዴት እንደሚገቡ

ከመስከረም 2018 ጀምሮ፣ ከ 8ተኛ እስከ 12 ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች በሲያትል የህዝብ ት/ ቤቶች ድህረ ገፅ በተማሪ መግብያ በኩል ወደ Naviance መግባት ይችላሉ።

የሁለተኛ ደረጃ ት / ቤት እና ከሱ በላይ ዕቅድ ዋሽንግተን ክልል ሁሉም ተማሪዎች የሁለተኛ ደረጃ ት/ ቤት እና ከሱ በላይ ዕቅድ እንዲያዘጋጁ ይጠይቃል። ሲያትል የህዝብ ክትምህርት ቤቶች 8ኛ ክፍል ለሚገቡ ተማሪዎች፣ የ 4 ዓመት የሁለተኛ ደረጃ ኮርሶች እቅድ፣የራስ መግለጫ፣የድህረ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እቅድ፣ የሙያ እና የኮሌጅ ግቦችን

ጨምሮ የ 5 ዓመት እቅድ ማዘጋጀት እንደሚጀምሩ ይጠብቃል። ተማሪው የሁለተኛ ደረጃ ት / ቤት ዕቅድን በሚያዘጋጅበት ወቅት ዕቅዱ በጊዜ ሂደት ይዘምናል:: የትምህርት ቤት አማካሪዎች፣ ሰራተኞች እና ወላጆች በክልሉ በተረጋገጡ መሳሪያዎች፣ተማሪዎችን የግል ዕቅዳቸውን እንዲያዳብሩ ያግዛሉ።

ለተጨማሪ መረጃ እባክዎን ወደ የሲያትል የህዝብ ት/ቤቶች ድህረገጽ ይሂዱ: http://www.seattleschools.org/cms/One.aspx?portalId=627&pageId=29495189

AMHARIC

15

የልዩ ፍላጎት ትምህርት አገልግሎት የሚያገኙ የ9ኛ ክፍል ተማሪዎች መደገፍ

ጥናቶች እንደሚያሳዩት፣ከአጠቃላይ የ 9 ኛ ክፍል ተማሪዎች ለረዥም ጊዜ በመቅረት እና በኮርስ የመውደቅ ችግሮችን የልዩ ፍላጎት ተማሪዎች ከፍተኛ ቦታ ይይዛሉ። ከትምህርት የመቅረት መንስኤ መመልከት እና መፍታት በጣም አስፈላጊ ነው። ለብዙ ቀናት ከትምህርት ገበታ መቅረት (ከ 10% በላይ የትምህርት ቀናት መቅረት) ወደ ኮርሱን መውደቅ ያመራል። ተማሪዎች ከትምህርት የሚቀሩበት ምክንያቶች ምንድን ናቸው?

• ከልጁ አካል ጉዳተኝነት ጋር የተያያዙ ቀሪዎች ናቸው?

• በ IEP ውስጥ መመዝገብ እና መታየት ያለባቸው የጤና ችግሮች አሉ?

• የመጓጓዣ ጉዳይ ነው?

• ፍርሃት ወይም ጭንቀት የመሳሰሉ ከአካል ጉዳተኝነት ጋር የተዛመዱ ፈጣን ምላሽ የሚፈልጉ ቀሪዎች። በተቻለ መጠን፣ተማሪው እዚያ ለመገኘት እንዲችል የትምህርት ቤቱ የአየር ሁኔታን እንዴት ማሻሻል እንደሚቻል ጨምሮ ቀሪዎችን ለማሻሻል መፍትሔዎችን እና ስልቶችን ለማዘጋጀት ተማሪዎችን ማሳተፍ ነው። ወላጆች/ አሳዳጊዎች በትምህርት መከታተል እና በኮርስ ማለፊያ ላይ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመቅረፍ የተሻሉ ዘዴዎችን ለመወያየት የ IEP ስብሰባ (የግል የትምህርታዊ ፕሮግራም ላላቸው) ወይም ሌላ የትምህርት ቤት የቡድን ስብሰባ መጠየቅ ይችላሉ። የስብሰባ ቀጠሮ ለመያዝ የልጅዎን አማካሪ ወይም የ IEP ኬዝ ማናጀር መጠየቅ ይችላሉ። በስብሰባው ወቅት አስተርጓሚ የሚያስፈልግዎ ከሆነ አስቀድመው ይጠይቁ።

የአካል ጉዳት ያለባቸው ተማሪዎች ለድህረ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማዘጋጀት ለ WSAC/Gear Up Resource Guide አገናኝ እነሆ : የአካል ጉዳት ያለባቸው ተማሪዎች ለድህረ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማዘጋጀት:: http://www.gearup.wa.gov/file/preparing-students-disabilities-postsecondary-education-resource-guide-use-gear-school-staff ይህ የመገልገያ መመሪያ የሙያ እና የስራ ትምህርት ቤቶች፣ የሁለትና የአራት ዓመት ኮሌጆች እንዲሁም ዩኒቨርሲቲዎችን ጨምሮ በድህረ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ተቋማት ውስጥ ትምህርታቸውን ለመቀጠል የሚያስቡ የአካል ጉዳት ያለባቸው ከሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ጋር የሚሰሩ ቤተሰቦች ለመርዳት የተዘጋጀ ነው።ምክንያቱም የ ድህረ ሁለተኛ ደረጃ ተቋማት ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ስለሚለያዩ ነው፣አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ስኬታማ እንዲሆኑ መብቶቻቸው ፣ ኃላፊነቶቻቸው እና እራሳቸውን መቆም እንዳለባቸው ማወቅ በጣም አስፈላጊ ነው።

Supporting 9th Grade Students who Receive Special Education Services AMHARIC

16

ሲያትል የመንግስት ትምህርት ቤቶች (SPS)

ከፍተኛ ብቃት(HC) ያላቸው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች መንገዶች

HIGH SCHOOL HIGHLY CAPABLE (HC) PATHWAYS

ከፍተኛ ብቃት ያላቸው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የኮርስ ምክሮች

እንደ አንድ የ2019-2020 የትምህርት አመት አካል፣ በአሁኑ ከፍተኛ ብቃት ያላቸው ተማሪዎች ሶሱቱ የመሸጋገርያ ሁለተኛ

ደረጃ ትምህርት ቤቶች (Garfield, Lincoln & West Seattle) ያካተተ፣አላማችን በእያንዳንዱ ከፍተኛ ብቃት ያላቸው

ተማሪዎች የመሸጋገርያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ሊገመት የሚችል፣ ወጥ የሆነ እና ቀጣይነት ያለው ከፍተኛ ትምህርት

አሰጣጥ ዝግጅቶችን መፍጠር ነው። መዝጋቢዎች በምዝገባው ሂደት ለማገዝ ዝግጁ ሲሆን የት/ቤት አማካሪዎች ደግሞ

ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ቤት ከተመደቡ በኋላ እንደ አስፈላጊነቱ ለመርዳት ዝግጁ ናቸው። ይህ የስራ ቅደም ተከተል፣

የሚገባውን መምረጥ፣ወደ ላቀ ትምህርት መመደብ፣እና እጥፍ ክረዲት ያላቸው ኮርሶች ን ያጠቃልላል። በተማሪው ፍላጎት፣ ምዝገባ እና ሰራተኞች መሰረት ከ 2019-2020 የትምህርት ዓመት ጀምሮ በሶስቱ ዓመት የትምርት ግዜ የተወሰኑ ኮርሶች በየተራ ቅደም ተከተል ሊሰጡ ይችላሉ።

ከ6 ኛ-12 ኛ ላሉ ክፍሎች ለ ከፍተኛ ብቃት መንገዶች እና የትምህርት ቤት ምደባ በተመለከተ ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ የ

Advanced Learning 6th-12th Grade Students ገፅ ይጎብኙ። ለእርስዎ ምቾት ሲባል ፣ ከታች በተደጋጋሚ ለሚጠየቁ

ጥያቄዎች የተወሰኑ ምላሾች ቀርበዋል (FAQs):

ተደጋግሞው የሚነሱ ጥያቄዎች (FAQ)

• አንድ ተማሪ በ SPS የሁለተኛ ደረጃ ት / ቤቶች በከፍተኛ ደረጃ ኮርሶች ለመመዝገብ ከፍተኛ ብቃት ላላቸው

(HC) ወይም የላቀ ትምህርት (AL) አገልግሎቶች ብቁ መሆን አለበት? ምንም እንኳን የ HC ወይም AL ብቁነት ባይኖራቸውም፣ ሁሉም ብቃቶች፣ ከፍተኛ ምደባ፣ BI እና የእጥፍ ክረዲት ኮርሶች ለሁሉም ተማሪዎች

ክፍት ናቸው። The International Baccalaureate Accelerated (IBX) መርሀግብር በ Ingraham ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መመዝገብ የሚፈልጉ ተማሪዎች ለ HC አገልግሎቶች ብቁ መሆን ኣለባቸው።

• አንድ ተማሪ በሁሉም የ SPS የሁለተኛ ደረጃ ት / ቤት የ HC Pathway Course Recommendations መውሰድ ይችላል?

አያቻልም:: ለ HC አገልግሎቶች ብቁ የሆኑ ተማሪዎች ከሦስቱ የ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በአንዱ መውሰድ ይችላል። በዚህ የሽግግር ሂደት

ውስጥ፣ የተወሰኑ ኮርሶች በተማሪ ፍላጎት፣ ምዝገባ እና በሠራተኞች መሰረት በየተራ ቅደም ተከተል ሊሰጡ ይችላሉ።

• አንድ የሁለተኛ ደረጃ ት / ቤት በ 2018-2019 Garfield ሁለተኛ ደረጃ ት / ቤት ወይም Ingraham ሁለተኛ ደረጃ ት / ቤት ውስጥ

የተመዘገበ ከሆነ፣ለ 2019-2020 የትምህርት ዓመት ት / ቤቱን መለወጥ ያስፈልገዋል?

አያስፈልግም። በአሁኑ ጊዜ በከፍተኛ ብቃት መርሃ ግብር በ Garfield ወይም Ingraham ውስጥ የሚገኙ ሁሉም ተማሪዎች እዛው ይቀጥላሉ።

• በ 2018-2019 ውስጥ በከፍተኛ ብቃት መርሃ ግብር በ Garfield ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተመዘገበ / ች ተማሪ , ተማሪው በ 2019-

2020 ወደ Lincoln ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እንዲቀየር መጠየቅ ይችላል?

አዎ። ምንም እንኳን በ 8ኛ ክፍል በHCC ውስጥ ትምህርት ቤት ባይኖሩም፣በ2019-20 ትምህርት ዘመን ለ 10 ክፍል HC ለመግባት ብቁ

የሆኑ ተማሪዎች፣ Garfield ካሉ ወይም Lincoln HC pathway የመማርያ አካባቢ ካሉ ወደ Lincoln ለማመልከት መምረጥ ይችላሉ።

ቤተሰቦች ክፍት የመመዝገቢያ ጊዜ ውስጥ የምርጫ ቅጹን ማስገባት አለባቸው። ተጨማሪ ስለ ክፍት የምዝገባ ግዜ ያንብቡ።

AMHARIC

17

• ለ HC አገልግሎቶች ብቁ የሆኑ ተማሪዎች በ በራሳቸው "HC Pathway ሁሉተኛ ደርጃ " ለመሳተፍ ይጠየቃሉ?

አይጠየቁም። በአንደኛ ደረጃ ወይም መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የከፍተኛ ብቃት ያላቸው አገልግሎቶችን ለመቀበል ብቁ መሆናቸው የተለዩ

እና ኮርሳቸው HCC መሆኑን በግልፅ የተገፁ ተ ማ ሪዎች፣ለ HC ብቁ የሆኑ ተማሮዎች ፍላጎት ፣ በኮሌጅ እና የስራ ግቦች ላይ በመመርኮዝ

የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ኮርሶችንመምረጥ ይችላሉ:: ባህላዊ የ HC ኬዝ ሞዴል በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አይቀጥልም; ይሁን እንጂ የ HC

እና (AL) አገልግሎቶች የሚያገኙ ተማሪዎች ወደ የላቀ ደረጃ ኮርስ የመቀጠል እድል ይኖራቸዋል።

• የሁለተኛ ደረጃ ዲፕሎማ የተማሪን HC ወይም AL መመዘኛ ያሳያል?

የሁለተኛ ደረጃ ዲፕሎማ የተማሪው የ HC ወይም AL ወይም ሌላ ልዩ ፕሮግራም የሚያሳይ ምንም ምልክት የለውም። በ FERPA ጥበቃ ሕጎች

ምክንያት በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ዲፕሎማ ወይም ትራንስክርፒት ምንም የልዩ ፕሮግራም ስያሜዎች ሊዘረዘሩ አይችሉም። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዲፕሎማ የተማሪው የስቴት እና የዴስትሪክት ኮርስ /ክሬዲት መስፈርቶችን ማጠናቀቅን የሚያረጋግጥ ሰነድ ነው።

• የሁለተኛ ደረጃ ት /ቤት የተማሪ ትራንስክርፒት የተማሪውን HC ወይም AL ሁኔታ ይዘረዝራል?

በ FERPA ጥበቃ ሕጎች ምክንያት በየትኛውም የሁለተኛ ደረጃ ት / ቤት ወይም ዲፕሎማ ላይ ልዩ ፕሮግራም እና /ወይም የተመረጡ

አገልግሎቶች ላይዘረዘር ይችላል። ይሁን እንጂ የሁለተኛ ደረጃ ት/ ቤት ኮርሶች (AP, IB, Running Start, Tech Prep and

College )ሁሉም በ ትራንስክርቢቱ ይገለፃሉ።

• ሁሉም የምረቃ መስፈርቶች ከተሟሉ አንድ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ቀድሞ ሊመረቅ ይችላሉ? አዎ፣ አንድ ተማሪ ለተወሰነ የምረቃ አመት ሁሉንም የክልሉ እና የዲስትሪክቱ የመመርቅያ መስፈርቶች ካሟላ፣ተማሪው / ዋ የመመርቅያ ክረዲት የተጠናቀቀ መሆኑን ለማረጋገጥ እና ቀደም ብሎ ለመመረቅ ከት/ ቤት አማካሪያቸው ጋር ቀጠሮ መያዝ ይቻላል። ተማሪዎችና ቤተሰቦች የተማሪው የታቀዱ ትምህርቶች ሁሉንም የምረቃ መስፈርቶች ያሟሉ መሆናቸውም ለማረጋገጥ የምረቃ መጽሔት ማየት እና ከትም /ቤት አማካሪያቸው ጋር መገናኘ አለባቸው።

• አንድ ተማሪ ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ክሬዲት ብቁ የሚያደርግ በመለስተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ኮርሱን ካጠናቀቀ፣ እነዚህን

ክሬዲቶች ወደ የተማሪው የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ትራንስክሪፕት የማዛወር ሂደት እንዴት ነው? ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ክሬዲት ብቁ የሚያደርግ በመለስተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ኮርሱን ያጠናቀቁ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች፣ከሁለተኛ ደረጃ ት /ቤት አማካሪዎ የመካከለኛ ትምህርት ቤት ክሬዲት ቅጽ መጠየቅ ይችላሉ።የክረዲቱ ብቁነት ለመወሰን ተማሪዎች እና ቤተሰቦች የተጠናቀቁ ቅጾችን ወደ አማካሪ ቢሮ መመለስ አለባቸው።

From the Seattle Public Schools Office of Student Support Services, Advanced Learning

Revised January 16, 2019 For updated information go to: https://www.seattleschools.org/cms/one.aspx?pageId=14554

(www.seattleschools.org > Academics > Advanced Learning)

18

ለመመረቅ ኣስፈላጊ የክልል ፈተናዎች

For updated information go to: : https://www.seattleschools.org/cms/One.aspx?portalId=627&pageId=18711

ሁሉም የ 10 ኛ ክፍል ተማሪዎች የ Smarter Balanced Assessments (SBA) የእንግሊዝኛ ቋንቋ (ELA) እና የሂሳብ

ፈተናዎች መውሰድ አለባቸው።

ሁሉም የ 11 ኛ ክፍል ተማሪዎች የ Washington Comprehensive Assessment of Science* ፈተና ጭምር

መውሰድ አለባቸው።

* ከ 2019-2020 የትምህርት አመት ጀምሮ የሳይንስ ምዘና ማለፍ የምረቃ መስፈርት ነው።

ተማሪ የ እንግሊዝኛ ቋንቋ (ELA) እና/ወይም የሂሳብ ፈተናዎችን ካላለፈ፣ከ 11 ኛ ክፍል ጀምሮ የሚከተሉት አማራጮች

ይኖራሉ።:

1. ተማሪው በ 11ኛ እና/ወይም 12ኛ ክፍል እንደአስፈላጊነቱ የ SBA ፈተናዎችን እንደገና ሊወስድ ይችላሉ (መኸር እና / ወይም ፀደይ)::

2. አንድ ተማሪ በ SAT ወይም በ ACT ፈተና የማለፍያ ውጤት ማግኘት ይችላል:: SAT ካለ ምንም ክፍያ በትምህርት ቀን ለ junior

ተማሪዎች ይሰጣል:: አንድ ተማሪ የምረቃ አማራጭ (ችን) ለመጠቀም ን SBAC መሞከር አለበት።

የ 2017-2020 ምድብ:

የምረቃ የፈተና መስፈርቶች SAT with Essay

(March 2016 or later)

SAT (March 2016

or later)

ACT with Writing

ACT (no Writing)

ሂሳብ 430 430 16 16

የእንግሊዝኛ ቋንቋ 410 N/A 14 N/A

3. አንድ ተማሪ በትምህርት ቤት ውስጥ በ COE (Collection of Evidence) ክፍሎች መመዝገብ ይችላል፣ በክፍል ውስጥ ክረዲት

ሊያገኝ ይችላል፣እና የማለፊያ ውጤት የሚያገኝ የስራ ተግባራትን ያቀርባል። አንዳንድ ት/ ቤቶች የምረቃ መስፈርቱን ለማሟላት አንድ ዓመት ሙሉ የኮሌጅ መሸጋገርያ ትምህርት ሊያቀርቡ ይችላሉ።

4. አንድ ተማሪ በ ELA ወይም በሂሳብ በሁለት አማራጭ ክረዲት ማለፍ ይችላል ፣ እንደ ራኒግ ስታርት ወይም ኮሌጅ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ያሉ

5. ለ ልዩ ፍላጎት ትምህርት ተማሪዎች፣ ተጨማሪ የመሸጋገርያ ዘዴዎች ሊኖሩ ይችላሉ።

በትም/ቤትዎ ውስጥ የትኞቹ አማራጮች ሊቀርቡ እንደሚችሉ ለማወቅ የት/ ቤቱን አማካሪ ወይም የትምህርት ጣልቃገብነት ባለሙያን ያነጋግሩ::

State Testing Requirements for Graduation AMHARIC

19

የቃላቶች መግለጫ

ACT እና SAT የኮሌጅ መግቢያ ፈተናዎች ብዙ ኮሌጆች የ ACT ወይም የ SAT ፈተናዎች ውጤቶችን እንደ የምዝገባውን ሂደት አካል እንዲሆን ይጠይቃሉ :: በአብዛኛው ኮሌጆች እና ዩኒቨርሲቲዎች የመግብያ ውሳኔዎች ለማድረግ የሚጠቀሙባቸው የመግቢያ ፈተናዎች ናቸው:: የ ACT እና SAT ፈተናዎች ዓላማ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ለኮሌጅ ዝግጁ መሆናቸውን ለመለካት እና ኮሌጆችን ሁሉንም አመልካቾችን ለማነፃፀር ጥቅም ላይ ሊውል የሚችል አንድ የጋራ መረጃ ነጥብ ነው። አብዛኞቹ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ACT ፣SAT ወይም ሁለቱም ፈተናዎች ጁኒየር ተማሪዎች በፀደይ ወቅት፣ሲንየር ተማሪዎች ደግሞ በመከር ወቅት ይወስዳሉ። ኮሌጅ ከማመልከትዎ በፊት ውጤትዎን ከፍ ማድረግ የሚፈልጉ ከሆነ ፈተናውን እንደገና ለመውሰድ ጊዜዎ መተው በጣም አስፈላጊ ነው።

የላቀ ትምህርት ተማሪ (AL) እና ከፍተኛ ችሎታ ያላቸው( HC)መሸጋገርያ( Advanced Learner (AL) and Highly Capable (HC) Pathway)

ተማሪዎች ተመሳሳይ ዕድመ ካላቸው የክፍል ጓደኛቻቸው በላይ ለየት ያለ የመማር እና የመረዳት ችሎታ ካሳዩ ፣ በወላጆች፣ በመምህራን፣ በሌሎች ሰራተኞች፣ ወይም በየማኅበረሰብ አባላት ተለይተው ፣በወላጆቻቸው ብቁ መሆናቸውን በተገቢው ግምገማ ሂደት ውስጥ እንዲሳተፉ ይደረጋል። የላቀ ትምህርት አገልግሎት አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች (ሁለቴ ልዩ የሆኑ ተማርዎች)እና ልዩ ችሎታ ያላቸው ተማሪዎች ወይም ከሁሉም ማሕበራዊ፣ኢኮኖሚያዊ፣ ዘር እና ባህል ሊያጠቃልል ይችላል።

የላቀ ትምህርት ተማሪ (AL) የላቀ ትምህርት ከ ኪንደርጋርተን እስክ 8ኛ ክፍል ለሚገኙ ተማሪዎች የብቁነት ምድብ ነው። ጥቆማ በመጨረሻው የትምህርት ዓመት ወይም በበጋ ወቅት ይካሄዳል። ፈታናው በየዓመቱ በመከር ወቅት ይካሄዳል።.  ከፍተኛ ችሎታ ያላቸው( HC)መሸጋገርያ

ከፍተኛ ችሎታ ያላቸው መሸጋገርያ(HC)፣ ተመሳሳይ ከፍተኛ ችሎታ ያላቸው ሰዎች ስብስብ (HCC)ተብሎም ይታወቃል።በሁለቱም በማንበብ/ELA እና በሂሳብ ትምህርቶች የከፍተኛ ትምህርት ሞዴል ያቀርባል።በሁለቱም አካዳሚክ መስኮች ላይ በአሁኑ ወቅት ከደረጃ በላይ ውጤት ላላቸው ተማሪዎች በጣም ጠቃሚ ነው። በሂሳብ ሁለት ዓመት እና በንበብ/ELA እስከ ሁለት አመት መቅደም ጥናት መሰረት ያደረገ ሞዴል ስለሆነ ከከፍተኛ ፍጥነት ለሚጠቀሙ ተማሪዎች በጣም ውጤታማ ሊሆን ይችላል::

ከስራ ጋር የተያያዘ ትምህርት / የሙያ እና ቴክኒካዊ ትምህርት (CCL/CTE)( Career Connected Learning/Career and Technical Education (CCL/CTE))

የ CCL/CTE)) ክፍሎች ወይም ኣንዳንድ የተፈቀዱ የ CCL/CTE)) ኮርስ ያልሆኑ በመቃኘት እና በመዘጋኘ ክረዲት ማግኘት ይቻላል።።ለተፈቀዱ ኮርሶች ኦፊሴላዊ የዲስትሪክት የኮርስ ዝርዝርን ይመልከቱ።

ክረዲት

” ክሬዲት ምንድን ነው?” ክሬዲቶች ተማሪዎች በአጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የትምህርትን መስፈርቶች ያሟሉ መሆናቸውን ለመገምገም ከሚጠቀሙባቸው ቀዳሚ ዘዴዎች መካከል ኣንዱ ነው ። ክሬዲቶች ኮርስ ወይም አስፈላጊ የትምህርት ቤት ፕሮግራም ሲጨርሱ እና ሲያልፉ ይሰጣሉ። የሲያትል የህዝብ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች ዲፕሎማ እንዲያገኙ ክረዲቶች ማከማቸት ያስፈልገዋል።

የሁለተኛ ደረጃ ት/ ቤት እና ከሱ በላይ ዕቅድ( High School and Beyond Plan)

ዋሽንግተን ክልል ሁሉም ተማሪዎች የሁለተኛ ደረጃ ት/ ቤት እና ከሱ በላይ ዕቅድ እንዲያዘጋጁ ይጠይቃል። ሲያትል የህዝብ ክትምህርት ቤቶች 8ኛ ክፍል ለሚገቡ ተማሪዎች፣ የ 4 ዓመት የሁለተኛ ደረጃ ኮርሶች እቅድ፣ይራስ መግለጫ፣የድህረ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እቅድ፣ የሙያ እና

የኮሌጅ ግቦችን ጨምሮ የ 5 ዓመት እቅድ ማዘጋጀት እንደሚጀምሩ ይጠብቃል። ተማሪው የሁለተኛ ደረጃ ት / ቤት ዕቅድን በሚያዘጋጅበት ወቅት ዕቅዱ በጊዜ ሂደት ይዘምናል:: የትምህርት ቤት አማካሪዎች፣ ሰራተኞች እና ወላጆች በክልሉ በተረጋገጡ መሳሪያዎች፣ተማሪዎችን የግል ዕቅዳቸውን እንዲያዳብሩ ያግዛሉ።

Naviance

Naviance ተማሪዎች ኮሌጆችንና የሙያ ጉዛቸውን እንዲመረምሩ ፣ብቃቶችን እና ችሎታን በስራና በጠባይ ተኮርነት ዳሰሳ እንዲያደርጉ እና አካዳሚያዊ ግቦች ላይ ለመድረስ በሚያስችላቸው መንገድ ላይ ለመቆየት ያግዛሉ::

Explanation of Terms AMHARIC

20

OSPI (የሕዝብ ትምህርት ቤቶች የበላይ ተቆጣጣሪ ጽ / ቤት)

የህዝብ ትምህርት ቤቶች የበላይ ተቆጣጣሪ ጽህፈት ቤት በዋሽንግተን ክልል ውስጥ ያሉ የ k-12 ትምህርት በበላይነት የሚቆጣጠር ድርጅት ነው። OSPI ከአንድ ሚሊዮን በላይ የህዝብ ትምህርት ቤቶችን ተማሪዎች በመወከል መሰረታዊ የትምህርት ፕሮግራሞችን ለማስተዳደር እና የትምህርት ማሻሻያ ለማድረግ ከ 295 የትምህርት ድስትሪክቶች ጋር በመተባበር ይሰራል።

የግል ጎዳና( Personal Pathway)

የግል ጎዳና በተማሪው ፍላጎት እና በሁለተኛ ደረጃ ት/ ቤት እና ከዛ በላይ እቅድ በመነሳት በተማሪው የሚመረጡ ወደ ድህረ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት የስራ ወይም የትምህርት ውጤትን የተያያዙ ኮርሶች ናቸው። ይህም ለተማሪው ትምህርት ትኩረት ለመስጠት የታሰቡ የሙያ እና የቴክኒካዊ ትምህርት ወይም የአለም ቋንቋዎች ሊያካትት ይችላል።

ራኒግ ስታርት

ራንግ ስታርት ቢያንስ የ 11 ኛ ክፍል በቂ ክረዲት ያገኙ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች በማህበርሰብ ኮሌጅ የሚሰጥ አማራጭ ኮርስ ነው። SAT የኮሌጅ መግቢያ ፈተና

(የ ACT እና SAT ኮሌጅ መግቢያ ፈተናዎችን ከላይ ይመልከቱ) Seal of Biliteracy

በአለም ቋንቋ ክሬዲት ፈተና (እስከ 4 ክሬዲቶች የሚያስገኝ ) ወይም በከፍተኛ ምደባ (AP) ወይም ዓለም አቀፍ ባካሎሬት (IB) የቋንቋ ፈተናዎች በማለፍ የቋንቋ ክህሎታቸውን ያሳዩ ተመራቂዎች State Seal of Biliteracy ያገኛሉ። The Seal ዛሬ ባለው አለም ውስጥ የእንግሊዘኛ ቋንቋ መናገር፣ ማንበብ እና መጻፍ እና ቢያንስ አንድ ሌላ ቋንቋ መጠቀም ጥቅሙን ለማጉላት የታሰበ ነው።

የአገልግሎት ትምህርት( Service Learning)

የአገልግሎት ትምህርት ፣ትምህርት (የመማሪያ ክፍል እና ማህበረሰብ) ከእውነተኛ የዓለም ጉዳዮች ጋር የሚያገናኝና የማህበረሰብ ፍላጎቶችን የሚያሟላ የመማር ማስተማር ዘዴ ነው። ሲያትል የሕዝብ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎችን ከመመረቃቸው በፊት የ 60 ሰዓታት የአገልግሎት ትምህርት መውሰድ አለባቸው። ተማሪዎች በተደጋጋሚ የበጎ ፈቃድ ሥራ አገልግሎት ይሰጣሉ፣ ይህም በስራ ልምዳቸው ያሰፍሩታል።

ሶርስ( The Source) ሶርስ ቤተሰቦች እና ተማሪዎች፣የተማሪውን የትምህርት መርሃ ግብር ለመመልከት፣ ነጥቦች ለመከታተል፣ አቴንዳንስ ለመከታተል፣ የጎደሎ አሳይመንቶች ለማየት፣ ወደ አስተማሪዎች ኢሜይል ለማድረግ፣ እና በአንዳንድ ሁኔታዎች የሚመጣውን አሳይመንቶች ለመከታተል የሚያስችል የ ድህረ ገፅ ሀብት ነው። ሲያትል የህዝብ ት/ቤቶች ፣ቤተሰቦች እና ተማሪዎች መረጃቸው በተንቀሳቃሽ ስልክ በቀላሉ ለማየት የሚያግዛቸው መተግበርያ አለው።

ስኩሎጂ (Schoology)

አንዳንድ መምህራን የቤት ስራዎች፣ መልእክቶች፣ ዝግጅቶችን፣ እና የቀን መቁጠሪያዎችን ለመለጠፍ ስኩሎጂ ሊጠቀሙ ይችላሉ። በሶርስ አካውንትዎ አማካኝነት ወደ ስኩሎጂ መግባት ይችላሉ ።.

ስማርተር ባላንስድ ግምገማዎች (SBA) For updated information go to: : https://www.seattleschools.org/cms/One.aspx?portalId=627&pageId=18711

ከ 2 ኛ ደረጃ ት/ ቤት ለመመረቅ፣ ተማሪዎች የስማርተር ባላንስድ ግምገማዎች ሒሳብ እና እንግሊዝኛ ቋንቋ ወይም ሌላ የተፈቀደ አማራጭ ፈተና ማለፍ አለባቸው። ከ 2019-20 ጀምሮ ተማሪዎች የሳይንስ ምዘናም ጭምር ማለፍ አለባቸው። የዋሽንግተን ክልል ለሁሉም ዲስትሪክቶች የስማርተር ባላንሰድ ግምገማዎች(ፈተናዎች) በፀደይ ወቅት እንዲሰጡ ይጠይቃል። እነዚህ ፈተናዎች: o ተማሪዎች የኮሌጅንና የስራ ዝግጁነት መስፈርቶች ምን ያህል እንደሟሉ ይለካሉ። o መምህራንና ዲስትሪክቶች ተጨማሪ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው ተማሪዎች ለመለየት ያግዛቸዋል። o ከ 3 ኛ እስከ 8 ኛ እና 10 ኛ ለሆኑ ተማሪዎች ይሰጣል:: o በ 11 ኛ እና በ 12 ኛ ክፍሎች ያሉ ተማሪዎች የመመረቅያ መስፈርቶችን ለማሟላት የሚያስፈልግ ከሆነ የስማርተር ባላንሰድ ግምገማዎች ሊወስዱ

ይችላላሉ።

የዓለም ቋንቋ ክረዲቶች( World Language Credits)

በፀደይ 2011 ፣ የሲያትል የህዝብ ት/ቤቶች ከእንግሊዘኛ ሌላ ቋንቋ ተናጋሪዎች የቋንቋ ብቃትንና የብቃት ደረጃ ላይ የተመሠረተ ክሬዲቶችን ለመውሰድ ፖሊሲ እፅድቀዋል።ልጅዎ ከእንግሊዝኛ ውጭ ሌላ ቋንቋ መናገር፣ ማንበብ እና መጻፍ የሚችል(የምትችል) ከሆነ(ከሆነች)፣ በዚህ ፕሮግራም መሳተፍ ይችላል(ትችላለች)።ተማሪዎች ከ 1-4 የ 2 ኛ ደረጃ ትም / ቤት የ የዓለም ቋንቋ ክሬዲት ማግኘት ይችላሉ:: ለ 4 ዓመት ኮሌጅ ወይም ዩኒቨርሲቲ ለመግባት እቅድ ያላቸው ሁሉም ተማሪዎች ፣የዓለም ቋንቋዎች (እንደ ስፓኒሽ፣ ፈረንሣይኛ፣ ወዘተ )ቢያንስ ለሁለት አመታት እንዲከታተሉ ይመከራል ።