33
የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት መጋቢት 2004 በህገ ወጥ የቁም እንስሳት ንግድ ዙርያ የተደረገ ጥናት ሪፖርት

147 (repaired)(1)

Embed Size (px)

DESCRIPTION

informal livestock cross border trading

Citation preview

Page 1: 147 (repaired)(1)

የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት

መጋቢት 2004

በህገ ወጥ የቁም እንስሳት ንግድ ዙርያ የተደረገጥናት ሪፖርት

Page 2: 147 (repaired)(1)

የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት Page ii

ማውጫገጽ1.ማጠቃለያ ...................................................................................................................................................1

2.መግቢያ ......................................................................................................................................................4

3. ዓላማው ....................................................................................................................................................5

4.የጥናቱ አስፈላጊነት.................................................................................................................................... 5

5.ዝርዝር ዳሰሳ..............................................................................................................................................6

5.1. ድሬደዋ አከባቢና ሽንሌ ዞን ..............................................................................................................6

5.2. ጅጅጋና አካባቢው..............................................................................................................................8

5.2.1. ቶጎ ውጫሌ ...............................................................................................................................9

ሠንጠረዥ 1.ላለፉት 4 ዓመታት ወደ ሱማሌ ላንድ በህጋዊ መንገድ የተላኩ የቁም እንስሳት ብዛትናየተገኘው የውጭ ምንዛሪ ገቢን የሚያሳይ ሰንጠረዥ.................................................................................10

5.2.2. ሀርትሼክ..................................................................................................................................10

5.3 አፋር ክልል......................................................................................................................................11

5.4.ትግራይ ክልል...................................................................................................................................12

5.4.1.ሁመራ (የትግራይ ምእራባዊ ዞን) ............................................................................................12

5.5.አማራ ክልል......................................................................................................................................13

ሠንጠረዥ 2. ከሐምሌ 2003 እስከ ጥር 2004 ከአማራ ክልል በኮንትሮባንድ (በህገ ወጥ መንገድ) ወደሱዳን ሲወጡ የተያዙ የቁም እንስሳት ........................................................................................................14

5.6.ሞያሌ ................................................................................................................................................15

6. የኮንትሮባንዱ ንግድ ዋና ዋና መንስኤዎች ..........................................................................................16

7. ለመንኤዎቹ የመፍትሄ ሀሳቦች...........................................................................................................17

8. በአካባቢው የታዩ ዋና ዋና ችግሮች ....................................................................................................18

9. ለችግሮቹ የተቀመጡ የመፍትሔ ሃሳቦች...........................................................................................19

10.የኳራንቲን አገልግሎት ..........................................................................................................................20

ሠንጠረዥ -3 በ2004 በጀት ዓመት የስድስት ወር የቁም እንስሳት የወጪ ኮንትሮባንድ (ከሐምሌ2003-ታህሳሥ 2004) ሪፖርት ...................................................................................................................1

ሠንጠረዥ-4 በ2004 በጀት ዓመት የስድስት ወር የቁም እንስሳት ኤክስፖርት (ከሐምሌ 2003-ታህሳሥ2004) ............................................................................................................................................................2

ሠንጠረዥ ፡-5. የድርጊት መርሃ ግብር ....................................................................................................... 3

Page 3: 147 (repaired)(1)

1.ማጠቃለያ

የቁም እንስሳት ህገ ወጥ የንግድ እንቅስቃሴ በአፋርና በትግራይ (ሁመራ) ክልሎች የጸረ ኮንትሮባንድጥምር ኮሚቴ እስከታችኛው ቀበሌ እርከን ድረስ በተቀናጀ መልኩ ከአገር ሽማግሌዎችና መላውህብረተሰብ በህገ ወጥ የንግድ እንቅስቃሴ አስከፊነትና በአገር ኢኮኖሚ ላይ የሚያስከትለውን ተጽዕኖበመወያየት የጋራ አቋም በመያዙና ወደ ተግባርም በመግባት ውጤታማ ሥራ በማከናወናቸውየመቀነስ ዝንባሌ ያሳያል፡፡

በሱማሌ ክልል፤በኦሮሚያ ክልል እና በአማራ ክልል ያለው የህገ ወጥ የቁም እንስሳት ንግድ እንቅስቃሴበተመለከተ ጸረ-ኮንትሮባንድ ኮሚቴ ተመስርቶ ህገ ወጥ እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር እንቅስቃሴ እያደረገቢገኝም የጥምር ኮሚቴው እንቅስቃሴ ተከታታይነት የሌለው በመሆኑ፤ህብረተሰቡ በህገ ወጥ የንግድእንቅስቃሴ አስከፊነትና በአገር ኢኮኖሚ ላይ የሚያስከትለውን ተጽዕኖ ያለው ግንዛቤ አነስተኛ መሆን፤

ከዚህም በተጨማሪ ካለው ረዥምና ሰፊ የድንበር ወሰንና ያንኑ ያህልም በቁጥር ለመገመትየሚያስቸግሩ የኮንትሮባንድ መውጫ በሮች በመኖራቸው፤ ህዝቡ በጎሳ፤በእምነት፤በባህል የተሳሰረመሆኑ እና ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ያለ መስራት ችግሮች ምክንያት የህገ ወጥ የቁም እንስሳት ንግድእንቅሰቃሴ በሰፊው እየተከናወነ ይገኛል፡፡

ለምሳሌ በህርትሼክና በሀርሺም መካከል ባለው መውጫ በር በብዙ ቁጥር የሚገመት እንስሳት በተለይምበጎችና ፍየሎች ወደ ሱማሌ ላንድ እየወጡ ሲሆን ግመሎችና የቀንድ ከብቶች እንደቀደም ተከተላቸውበብዛት እንደሚወጡ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

በአማራ ክልል በሽንፋ አቅጣጫ ወደ ቲሃ የሚወጣ የቀንድ ከብት በቀን አስከ 300 እንደ ሚወጣመረጃዎች የሚጠቁሙ ሲሆን ይህም ምን ያህል አሳሳቢና በዓመት ቁጥሩ ምን ያህል እንደሆነ ማስላትናየችግሩ ስፋት መገንዘብ አያዳግትም፡፡

በሞያሌ በኩል ያለው የህገ ወጥ የቁም እንስሳት ንግድ እንቅስቃሴ በተመለከተ እንስሳቱ ያለ ምንም እገዳእና ቁጥጥር ሳይደረግባቸው ሙሉ በሙሉ በህገ ወጥ መልኩ በቀን በአማካይ እስከ 500 የቁም እንስሳትእንስት ከብቶችን ጭምር በኮንትሮባንድ አጎራባች አገር ወደ ሆነችው ኬንያ ይወጣሉ፡፡

በግንቦት 2010 እ.ኤ.አ (END MARKET ANALYSIS OF ETHIOPIAN LIVESTOCK AND MEAT)በሚል ርዕስ የተጻፈው ጥናት እንደሚያመለክተው በ2007 ዓ.ም ሱማሌ በበርበራና በቦሳሶ ወደብ በኩል3.05 ሚሊዮን በጎችና ፍየሎች 200000 የቀንድ ከብቶች ለወጪ ገበያ ያቀረበች ሲሆን ከዚህ ውስጥግማሽ የሚሆነው የኢትዮጵያ እንስሳት መሆናቸውን በመጥቀስ በ2005-06 እ.ኤ.አ በኮንተሮባንድለወጪ የቀረቡ እንስሳት 328000 የቀንድ ከብቶችና 1.1 ሚሊዮን በግና ፍየሎች እንደሆኑና ይህምአገራችን በህጋዊ መንገድ ለወጪ ንግድ ካቀረበችው በሰባት እጥፍ እንደሚበልጥ የጥናት ጽሁፉይጠቁማል፡፡

ከጅጅጋ ኳራንቲን ባለሙያዎች በተገኘው መረጃ መሰረት በህገ ወጥ መልኩ ወደ ሱማሌ ላንድየሚወጡት እንስሳት መጠን 80 ከመቶ እንደሚሆንና በህጋዊ መልኩ የሚወጣው 20 ከመቶ መሆኑንመረጃው ያሳያል፡፡

Page 4: 147 (repaired)(1)

የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት Page 2

በሠንጠረዥ 1.ላይ እንደሚያሳየው በ2003 ዓ.ም በጅጅጋ በቶጎ ውጫሌ በኩል በድምሩ 96416 የቁምእንስሳት በህጋዊ መንገድ በመላክ 34 ሚሊዮን የአሜርካን ዶላር የተገኘ ሲሆን ይህም በአጠቃላይከሚወጣው የቁም እንስሳት 20 ከመቶ ድርሻ እንዳለውና ሌላው 80 ከመቶ የሚሆነው ግንበኮንትሮባንድ መልክ እንደሚወጣና ችግሩም ምንያህል አሳሳቢ እንደሆነ መረዳት የቻላል፡፡

በአብዛኛው የጠረፍ አካባቢ የሚገኙ አጎራባች አገሮች ህጋዊ ንግዱን ከማበረታታት ይልቅየሚያዳክሙ መሆናቸውና በተዘዋዋሪ መልኩ ህገ ወጡን ንግድ የሚያበረታቱ መሆኑንመገንዘብ ይቻላል፡፡ ለአብነትም በህጋዊ መንገድ ከኢትዮጵያ ወደ ሱዳን ለሚገቡ እንስሳት በአንድከብት ብር 400 ቀረጥ የሚያስከፍሉ ሲሆን በኮንትሮባንድ ለሚገባ እንሰሳ ግን ብር 20 ብቻማስከፈላቸው ጥሩ ማሳያ ይሆናል፡፡

ከላይ በዝርዝር እንደቀረበው ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው እንስሳት በኮንትሮባንድ መልክ ወደ አጎራባችአገሮች እንደሚወጡና አገሪቷ ከዘረፉ ማግኘት የሚገባትን የውጭ ምንዛሪ እያጣች መሆኑን ለመገንዘብይቻላል፡፡ስለዚህ ይህ ለአመታት የቀየ ችግር አሳሳቢና ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡

በቁም እንሳሰቱ ግብይት ከፍተኛ አቅም ያላችውና በዋናነት ስራዬ ነው ብለው ወደ ስራ የገቡ ነጋዴዎችባለመኖራቸው ህገወጡን በማዳከም ህጋዊ ንግዱ አሸንፎ እንዲወጣና ህገ ወጦቹ ወደ መስኩ እንዲመጡአለማድረጉ በአገሪቷ የሰፈነው የኮንትሮባንድ ንግድ ጉልህ ማሳያ መሆኑን መገንዘብ ይቻላል፡፡

በአጠቃላይ ህገ ወጥ የቁም እንስሳት ንግድ መንስኤዎችና ችግሮች በተመለከተ አስተማማኝ የገበያትስስር በየአካባቢው አለመኖር ያሉት የስጋና የስጋ ውጤቶች ማደራጃ ወይም ቄራዎች እንስሳቱበሚገኝበት አካባቢ ሳይሆን በመሃል አገር ላይ ማዕከል ማድረጋቸው እና በሙሉ አቅማቸውአለመስራታቸው፤ጎረቤት አገሮች ኮንትሮባንዱን ንግድ በመከላከል ተግባር ላይ ተሳታፊ ከመሆን ይልቅየሚያበረታቱ መሆኑ፤ዋንኛ መንስኤዎች ሲሆኑ

ከዚህም በተጨማሪ የጠረፍ አካባቢዎች ከመሃል አገር ገበያዎች የራቁ በመሆናቸው፤ረዥምና ሰፊየድንበር ወሰን በመኖሩና ያንኑ ያህልም በቁጥር ለመገመት የሚያስቸግሩ የኮንትሮባንድ መውጫ በሮችመኖራቸው እና በድንበር አካባቢ የሚኖሩ ህዝቦች በባህል፣ በቋንቋ፣ በእምነት፣ በዘርሃረግ፣ወዘተየተሳሰሩ መሆናቸው ለችግሩ መባባስ መንስኤ መሆናቸውን ለአብነት መጥቀስ ይቻላል፡፡

ህገ ወጥ የቁም እንስሳት እንቅስቃሴ ንግድን ለመቆጣጠር እንዲቻል ተጀምሮ በሂደት ላይ የሚገኘውንየቁም እንስሳት የግብይት ስርዓትንና የህግ ማዕቀፎችን ከወዲሁ በማጠናቀቅና የህግ መሰረትእንዲኖራቸው በማድረግ ህገ ወጡን የቁም እንስሳት ዝውውር ስርዓት እንዲይዝ ማድረግ፤

የኤክስፖርት ቄራዎች በግል ባለሀብቶች እንዲቋቋሙ የመንግስት አቅጣጫ ቢሆንም በአንዳንድአካባቢዎች የግል ባለሀብቶች ደፍረው ለመግባት ባለመቻላቸው መንግስት በተጠኑና ስትራቴጂክ በሆኑቦታዎች ላይ የኤክስፖርት ቄራዎችን በማቋቋም በሂደት ለግል ባለሀብቶች እንዲተላለፍ በማድረግየግብይት ስርዓቱን በማሻሻል የተሻለ ዋጋ እንዲፈጠር ሁኔታዎችን ማመቻቸትና የግብይት ስርዓቱንየሚከታተልና የሚመራ የመንግስታዊ መዋቅር መፍጠር እና ተከታታይነት ያላቸው ወቅታዊ የግብይትመረጃዎች ለህብረተሰቡ እንዲደርስ ማድረግ፡፡

በዲፕሎማሳዊ በሆነ መንገድ ከዚህ በፊት ከአጎራባች አገሮች በተደረጉ ስምምነቶች መሰረት ህገ ወጡንእንቅስቃሴ የመከላከሉን ተግባር ተግባራዊ ማድረግ ፤የሀገር ሽማግሌዎችና የጎሳ መሪዎችና ህብረተሰቡ

Page 5: 147 (repaired)(1)

የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት Page 3

ስለ ኮንትሮባንድ ንግድ በሀገር ኢኮኖሚና በህጋዊ ንግዱ ላይ የሚያደርሰውን ተጽዕኖ እና በህጋዊ መልክየሚከናወነው የንግድ እንቅስቃሴ ያለው ጠቀሜታ ግንዛቤ ማስጨበጥ፤

በየአካባቢው ያለው የፀረ-ኮንትሮባንድ ጥምር ኮሚቴ በማጠናከር እንደ አካባቢው መልካምድር አቀማመጥአስቸጋሪነትና ስፋት አንጻር የሰው ሓይል፤የሎጅስቲክና የተሸከርካሪ አቅርቦትን በማሻሻል በተቀናጀመልኩ ተከታታይነት ያለው ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ ህገ ወጡ ንግድ የሚቀንስበትና ብሎምየሚገታበትን ሁኔታዎች ማመቻቸት የግድ ይላል፡፡

ሌላው ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው የኳራንቲንና ኢንስፔክሽን አገልግሎት አሰጣጥ ሲሆን በአጠቃላይክልሎቹ እንደገለጹት መመሪያውን ባልተከተለ መልኩ በህጋዊ መንገድ ህገ ወጥ ንግድ እየተካሄደመሆኑን እና መስፈርቱን የማያሟሉ፤በእድሜና በኪሎግራም ለመውጣት የማይፈቀድላቸውእንስሳት፤እንስት ላሞች፤ዲቃላ ከብቶች እንዲሁም መስፈርቱን በማያሟላ መኪና ተጭነው የተላላጡእና የደሙ እንስሳት በህጋዊ መንገድ በአብዛኛው ቦታዎች (አማራ ክልል፤ጅጅጋ፤ሁመራ) ከብቶቹሳይታዩ ሰርትፍኬት ተዘጋጅቶላቸው በመውጣት ላይ ይገኛሉ፡፡

ደረጃውን የጠበቀ ኳራንቲን ባለመኖሩ በገልፍ ገበያ ተፈላጊ የሆኑ የኢትዮጵያ ዝርያ ያላቸውን የቦረናየቀንድ ከብቶችና የሱማሌ በላክ ሄድ (ዋንኬ) በጎች ወደ ጅቡቲ ከገቡ በኋላ በጅቡቲ ኳራንቲን ቆይተውበጅቡቲ ስም እየተላኩ ጅቡቲ ተጠቃሚ እየሆነች ትገኛለች፡፡ስለዚህ ጥናት ተደርጎ ደረጃቸውን የጠበቁኳራንቲን መገንባትና ተከታታይነት ያለው የክትትልና የቁጥጥር ስርዓት በመዘርጋት ስርዓቱን የጠበቀየኳራንቲን ጣቢያ አገልግሎት መስጠት አስፈላጊ ነው፡፡

Page 6: 147 (repaired)(1)

የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት Page 4

2.መግቢያ

የእንስሳት ዘርፍ ለአለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ለግብርና ክ/ኢኮኖሚ ያበረከተው አስተዋጽኦ 30%እና በውጭ ምንዛሪ ግኝት ደግሞ 16% ድርሻ እንደነበረው ይታወቃል(የጽ/ቤቱ ዶኩመንት 2003) ፡፡ሀገራችን እንስሳትንና የእንስሳት ውጤቶችን ለውጪ ሀገር ገበያ በማቅረብ ከፍተኛ የውጪ ምንዛሬየማግኘት አቅም ያላት ሲሆን ለአብነትም ያህል በስጋና በቁም እንስሳት የወጪ ንግድ ባለፈው የ2003በጀት ዓመት 210 ሚሊየን ዶላር ተገኝቷል፡፡

ይህ እያደገ የመጣው የቁም እንሰሳት ንግድ ግምት ውስጥ በማስገባትና ሌሎች ነባር ሁኔታዎችበመመልከት በዕድገትና ትራንስፎርሜሽን የመጪው አምስት ዓመት ዕቅድ በእንስሳት ሀብት ልማትዘርፍ ሥጋ አሁን ካለበት 10ሺ ቶን ወደ 111ሺ ቶን፣ የቁም እንስሳት 334ሺ ወደ ከ2.5ሚሊየንበማሳደግ በአምስት አመቱ የእድገትና ትራንስፎረሜሽን መጨረሻ ዓመት 1 ቢሊዮን ዶላር የውጭምንዛሪ ለማግኘት ዕቅድ ተይዟል፡፡

ሆኖም ግን ህገወጥ የቁም እንስሳት ንግድ በሃገሪቷ በተለያዩ የጠረፍ አካባቢዎች ተንሰራፍቶ የሚገኝሲሆን በተለያዩ ህገወጥ መውጫ በሮች ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የቁም እንስሳት ወደ ጎረቤት ሃገሮችሶማሊያ፣ ኬንያና ጅቡቲ እና ሱዳን እንደሚወጡ የተለያዩ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

ለምሳሌ ያህል ለመጥቀስ በዚህ ጥናት Analysis of the Ethio-Sudan cross-border cattle trade:The case of Amhara Regional State በሚል ርዕስ IPMS/ILRI እኤአ 2007 የተደረገው ጥናትከአማራ ክልል ወደ ሱዳን ወደ 24,000 ዳልጋ ከብቶች በዓመት እንደሚወጡ እና ይህም እኤአ 2006ዓ ም በመተማ ዮሐንስ በኩል በህጋዊ መንገድ ወደሱዳን የተላኩት ዳልጋ ከብቶች 60% መሆኑተመልክቷል፡፡

እንዲሁም የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (UNDP) እኤአ ግንቦት 20 1997 ጥናት(Livestock Marketing and Cross Border Trade in the Southeast of Ethiopia) መሰረትበሁለቱ የሶማሊያ ወደቦች (በርበራና ቦሳሶ) በዓመት 120 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ዋጋ ካላቸውና ወደውጭ ከሚወጡት እንስሳት ውስጥ ሰማኒያ ከመቶ ወይም 96 ሚሊዮን የአሜርካን ዶላር ዋጋ ያላቸውምንጫቸው ከኢትዮጵያ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡

ህገ ወጥ የቁም እንስሳት ንግድ መንሰራፋት መንስኤዎችም የተለያዩ ቢሆንም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውእንስሳት በህገወጥ መንገድ ከሀገራችን በመውጣታቸው እነዚህ እንስሳት በህጋዊ መንገድ ለአለም ገበያቢቀርቡ ሀገራችን ማግኘት የምትችለውን በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር የአሜሪካን ዶላር በአመትበማጣት ላይ እንደምትገኝ ያሉ መረጃዎች ይጠቁማሉ ፡፡

በዋቢነት ለመጥቀስም በእንስሳት ገበያ ባለሥልጣን በ1993 ዓ ም በተደረገው ጥናት በደቡብ፤ ደቡብምስራቅና ምስራቅ አቅጣጫዎች ወደ ጎረቤት አገሮች በሚደረገው ህገወጥ ንግድ በዋናነት (የቁምእንስሳት) በዓመት ከአንድ መቶ ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ አገሪቱ ታጣለች፡፡

ስለዚህ ይህንን ችግር ለመቀነስና ሀገራችን ከዘርፉ ማግኘት የሚገባትን ጥቅም ከፍ ለማድረግ እንዲቻልእና እቅዱን ለማሳካት የኢትዮጵያ ስጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ፤ከገቢዎችና ጉምሩክ

Page 7: 147 (repaired)(1)

የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት Page 5

ባለስልጣን፤ከግብርና ሚኒስቴር፤ከንግድ ሚኒስቴር፤ከቁም እንስሳት ላኪዎች ማህበር እንዲሁም ከሌሎችከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ህገ ወጥ የቁም እንስሳት ንግድ በሀገሪቱ በተለያዩ የጠረፍአካባቢዎች ምን ይመስላል፤ዋና ዋና መውጫ በሮች የመለየትና በምን መልክ መቆጣጠር እንደሚቻልበተለያዩ የክልል ከተሞች የመስክ ጉብኝት በማድረግ ያሉት ጭብጥ ሁኔታዎች በማየት ሀገሪቱ ከዘርፉማግኘት የሚገባትን ጥቅም ለማሳደግ ያሉትን ችግሮችና የመፍትሄ ሀሳቦች በማቅረብ የሚመለከታቸውባለ ድርሻ አካላት መመሪያዎቻቸውን በማስተካከል የጥምር ኮሚቴዎችን በማጠናከር እቅዱን ማሳካትጊዜ ሊሰጠው የማይገባ መሆኑን በማስገንዘብ ይህ አጭር ሪፖርት ተዘጋጅቷል፡፡

3. ዓላማውየህገወጥ ንግድ መንስኤዎች መለየትና ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ የሚሆኑትን አቅጣጫዎችን በመንደፍ ባለድርሻ አካላት በማሳተፍ ተግባራዊ እንዲሆን ማድረግ

4.የጥናቱ አስፈላጊነትበዋና ዋና መውጫ በሮች በኩል እየተካሄደ ያለውን ህገወጥ የእንስሳት ንግድ ላይ ጥናት በማካሄድህገወጥ ንግዱን ሊቀንሱ የሚችሉ ተግባራዊ የመፍትሄ አቅጣጫዎችን ማመላከት ነው፡፡

ጥናቱን ለማካሄድ የተጠቀምንበት ስልት

በቀጥታ ከሚመለከታቸው በወጪ ንግድ ከተሰማሩ ነጋዴዎች፣ ከክልሉ የመንግስት አመራር

አካላት እና ከሚመለከታቸው ሴክተር መ/ቤቶች( ጥምር ኮሚቴ ጋር ውይይት ተደርጓል

በወጪ ንግዱ ዙሪያ የሚደረጉ የግብይት ሂደትና ስርዓት እንዲሁም የጤና ጥራት ቁጥጥርን

ቦታው ድረስ በመሄድ ዳሰሳ ተደርገዋል

ክፍተኛ የእንስሳት አቅርቦት በምንጭነት የሚያገለግሉ ቦታዎች ዳሰሳ ተደርጓል

የህገ ወጥ የቁም እንስሳት መነሻና መውጫ በሮችን መለየትና ለችግሩ መባባስ ምክንያት የሆኑጉዳዮችን መለየት ተችሏል፡፡በጎረቤት ሀገሮች ያሉትን የገበያ ማዕከላት በመመልከት ከህገወጥ ንግዱ ጋር ያላቸውን ቁርኝትለማጤን ተችሏል፡፡

Page 8: 147 (repaired)(1)

የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት Page 6

5.ዝርዝር ዳሰሳ

5.1. ድሬደዋ አከባቢና ሽንሌ ዞንድሬደዋ በምስራቅ ኢትዮጵያ ከሚገኙ ከፍተኛ ህገወጥ የቁም እንሰሳት ንግድ ከሚካሄድባቸው አካባቢዎችዋንኛው ሲሆን ከተማው የህጋዊ ወጪ ንግድ መተላለፊያ መስመር ሆኖም ያገለግላል፡፡

ቡድኑ በአካባቢው ከተቋቋመው ጸረ-ኮንትሮባንድ ኮሚቴ ጋር ባደረገው ውይይት በድሬደዋና አካባቢውየህገ ወጥ የቁም እንሰሳት ንግድ እንቅስቃሴ አስመልክቶ ራቅ ካሉት አካባቢዎች ማለትም ባሌ ፤ ቦረና፤ አርሲ ምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ ወዘተ ስፍራዎች ከመሃል አገር ሳይቀር በርካታ ቁጥር ያላቸውየቁም እንስሳት ብዙ መንገድ አቋርጠው በዚህ አካባቢ በማለፍ በተለያዩ ህገ ወጥ መንገድ በተለያዩ ህገወጥ መውጫ በሮች በመጠቀም ወደ ጅቡቲ፤ሱማሌ ላንድ እንደ ሚወጡ ለመገንዘብ ችሏል ፡፡

ከሚወጡትም የቁም እንስሳት መካከል እንስት የቀንድ እንስሳት፤የቀንድ ከብቶች ፤ (ጥጃዎች ፤ወይፈኖች ) ፤አልፎ አልፎም ፍየሎችና በጎች እንዲሁም ግመሎችንም ይጨምራል፡፡ ቀደም ሲል በቀንእስከ 200 መኪና ያላነሰ በኮንትሮባንድ ይወጣ እንደነበረና ከጊዜ ወደ ጊዜ ስልቱን እየቀየረ መጠኑ ከፍእያለ የመጣ ቢሆንም ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ የአካባቢው የጸረ- ኮንትሮባንድ ጥምር ኮሚቴ ተቋቋሞ ከዞንእስከ ቀበሌ በመደራጀት እንቅስቃሴ በማድረጉ ህገ ወጥ ንግዱ በተወሰነ መልኩ መቀነሱን ከተደረገውውይይት ለማወቅ ችሏል፡፡

በድሬደዋ እና አካባቢው ለህገ ወጥ የቁም እንስሳት በመነሻነት የሚያገለግሉ ገበያዎች የድሬደዋገበያ፤የቢኬ ገበያ፤እና የባቢሌ ገበያ ናቸው፡፡

የባቢሌ የገበያ ማዕከል በአገር አቀፍ ደረጃ ካሉት የግመል ገበያዎች ያቬሎ ከሚገኘው ሀሮበኬ ገበያቀጥሎ በከፍተኛ መጠን የግመል እንሰሳት ገበያ የሚካሄድበት የገበያ ማዕከል ነው፡፡

ገበያ ማዕከሉ በሳምንት ሁለት ጊዜ ሰኞና ሀሙስ የሚካሄድ ሲሆን የሰኞ ገበያ ትልቁ ገበያ ነው፡፡ገበያውበዋናነት የግመል ግዥና ሽያጭ የሚከናወንበት ቢሆንም በተጨማሪም የዳልጋ ከብት፤በግ፤ፍየልናእንዲሁም የጋማ ከብት(አህያ) ግብይት ይካሄዳል፡፡

ከወረዳው የንግድና ኢንዱስትሪ የገበያ ጥናት ባለሙያ ባገኘነው መረጃ መሰረት በአማካይ በሰኞ ገበያ ቀንእስከ 3000 ግመሎች እዚህ ገበያ ላይ ይቀርባሉ፡፡

እዚህ ገበያ የሚቀርቡት እንስሳት መነሻቸው በአብዛኛው ከምስራቅና ምእራብ ሐረርጌ ዞኖች ሲሆንከባሌ፤ከቦረና፤ከጎዴ፤ከጭረቲ እና ከሌሎች ርቀት ካላቸው አካባቢዎች ይቀርባሉ፡፡ በግብይቱም ሂደትተሳታፊዎች አርቢዎች፤ደላሎች፤ህጋዊ ነጋዴዎች፤እና የውጭ ሀገር ዜጎች መመልከት ችለናል፡፡

እነዚህም ከሱዳን ፤ከሱማሌ ላንድ ፤ከየመንና ከግብጽ የመጡ የውጭ ዜጎች ፍቃድ ሳይኖራቸው በቀጥታገበያው ውስጥ በመግባት በአካል ተገኝተው በደላላዎችና ፈቃድ ካላቸው ኢትዮጵያውያን ነጋዴዎች ጋርበመሆን ለአገር ውስጥ ዜጎች ብቻ የተፈቀደውን ንግድ ላይ በመሳተፍ ግዥ ሲያከናውኑንና ሲያስገዙተመልክተናል፡፡ይህ ድርጊታቸው የገበያውን የግብይት ስርዓት በማዛባት ላይ መሆናቸውንና ገበያውምህጋዊንና ህገ ወጥ ንግዱን እያስተናገደ መሆኑን መገንዘብ ይቻላል፡፡የቁም እንስሳቶቹም የሚጓጓዙትበአብዛኛው በነጂዎች አመካኝነት በእግር ነው፡፡

Page 9: 147 (repaired)(1)

የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት Page 7

ከእነዚህ የገበያ ማእከሎች ድሬደዋ፤ቤኪ እና ባቢሌ የሚገዙት የቁም እንስሳት በህገ ወጥ መንገድየሚጓጓዙበት እና የሚወጡበት አቅጣጫ

ከቢኬ ሜቶ ጣቢያ ሓሬ ዲከል(ጅቡቲ)

ከቢኬ ኡመር ጉልፍ ዱርዱር ዲከል(ጅቡቲ)

ድሬደዋ ሽንሌ ጋድ አዲጋላ ኡመር ጉልፍ ዱርዱር ዲከል(ጅቡቲ)

ድሬደዋ ሽንሌ ጋድ ሜቶ ሀሬ ዲከል(ጅቡቲ)

ድሬደዋ አዲጋላ ሐጂም ዲከል(ጅቡቲ)

ባቢሌ ፋፈም ቆቦ ቦቃ ጭናክሰን ደንበል አሻ ሀጂም(ሱማሌ ላንድ)

ባቢሌ ጭናክሰን ቱሉጉሌት ዶሮናጂ ሱማሌላንድ

ባቢሌ ጅጅጋ ቶጎውጫሌ ሱማሌ ላንድ(ህጋዊና ህገ ወጥ በሆነ መልኩ)

ቡድኑ ከድሬደዋ ገቢዎችና ጉምሩክ ድሬደዋ ቅርንጫፍ ኃላፊ፤ከደሬደዋ ኳራንቲን ባለሙያዎች እናየሽንሌ ዞን መስተዳድር ጋር በመሆን የቁም እንስሳት ህገ ወጥ እንስሳት እንቅስቃሴን መተመለከተውይይት ተደርጓል፡፡

ሽንሌ ዞን ከሱማሌ ክልል ዞኖች አንዱ ስትሆን በሰሜን ምስራቅ በኩል ትገኛለች፡፤ዞኑ ከጅቡቲ እናከሱማሌ ላንድ ጋር በድንበር ይገናኛል፡፡

የሽንሌ ዞን ከምስራቅ ሐረርጌ፤ከምእራብ ሐረርጌ፤ከአርሲና ከባሌ የሚመጡ ህገ ወጥ የእንስት እንስሳትጥጃዎች ማረፊያና ማስተላለፊያ በመሆን ወደ ጅቡቲና ሱማሌ ላንድ ለሚሄዱ ህገ ወጥ እንስሳት መነሻሆና ታገለግላለች፡፡

እንስሳቶቹ ከሽንሌ ዞን በመነሳት ከዋናው መስመር ከ60-65 ኪ.ሜ በመራቅ በረሃውን ተከትለውስለሚሄዱ ለቁጥጥርና ክትትልም አመቺ አይደለም፡፡ ሌላው ከቤኪ፤መኢሶና አፍደም ላይ የግብይትስርአቱን ከአካሄዱ በኋላ ሳር እናበላለን በሚል ሰበብ ወደ ድንበሩ ከተጠጉ በኋላ በአዲጋላ በኩል ወደጅቡቲ ያስወጣሉ፡፡

በዞኑ የዞኑ የቆዳ ስፋትና የእንስሳት ክምችን በአማከለ መልኩ የተሰሩ የገበያ ማዕከላት አለመኖሩ በዞኑከሚታዩት አበይት ችግሮች አንዱና ዋንኛው ሲሆን ይህም ለህገ ወጡ ንግድ መንሰራፋት ምክንያትሆኖአል፡፡

ስለዚህ የዞኑን ቆዳ ስፋትና በረሃነት እንዲሁም የእንስሳት ክምችትን መሰረት ባደረገ መልኩ የግብይትማዕከላትን በማቋቋም ከላኪና ህጋዊ ፈቃድ ካላቸው ላኪዎችና ነጋዴዎች ጋር የግብይት ትስስርንበመፍጠር ተግባራዊነቱን በመከታተል የእንስሳት ፍልሰቱን መቀነስ ይቻላል፡፡

Page 10: 147 (repaired)(1)

የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት Page 8

5.2. ጅጅጋና አካባቢው

ቡድኑ በጅጅጋ ለሚገኙት ለሚመለከታቸው መ/ቤት የስራ ኃላፊዎች፤ ነጋዴዎችና ማህበራት ተወካዮችተልዕኮውን በመግለጽ በህገ ወጥ እንስሳት ንግድ እንቅስቃሴ ፤መንስኤዎችና ችግሮች እንዲሁምየመፍትሄ ሀሳቦች ዙርያ ሰፋ ያለ ውይይት አድርጓል፡፡

የገቢዎችና ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የስራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች ጋር በተደረገው ውይይት በአሁኑወቅት በጠረፍ አካባቢዎች አባላትን በመመደብ ከፍተኛ ቁጥጥርና ክትትል እየተደረገ እና ከጥምርኮሚቴ ጋር በቅንጅት መስራት በመጀመራችው በተወሰነ መልኩ ኮንትሮባንዱ እንቅስቃሴ የመቀነስአዝማሚያ ቢያሳይም ከአካባቢው ካለው ስፋት አንጻር ከአንዱ መቆጣጠሪያ ጣቢያ እና ከሌላውመቆጣጠሪያ ጣቢያ መካከል ያለው ርቀት በጣም ሰፊ በመሆኑ አሁንም በርካታ ቁጥር ያላቸው የቁምእንስሳት በኮንትሮባንድ መንገድ ከሀርትሼክ እስከ ጋሻሞ ባሉት መውጫ በሮች ወደ ሱማሌ ላንድናፑንት ላንድ እየወጡ መሆኑን ተገልጸዋል፡፡

በተመሳሳይ ሁኔታም የክልሉ የንግድና ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ እንደገለጹት በክልሉ የኮንትሮባንድንግድ እንቅስቃሴ እየቀነሰ መሆኑን የገለጹ ሲሆን ለዚህም በዋናነት ከመሃል አገር ወደ ጠረፉ አካባቢስኳር፤ ዘይት እንዲሁም ሌሎች የሀገር ውስጥ ምርቶች መምጣት በመጀመራቸው እና በመንግስት 6የሚሆኑ የፍጆታ እቃዎችን በፍራንኮ ቫሉታ ወደ አገር ውስጥ እንዲገባ በመፍቀዱ ኮንትሮባነድ ንግዱበአንጻራዊነት እንዲቀንስ አስተዋጽኦ እንዳበረከተ ገልጸዋል፡፡

አያይዘውም ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ከዚህ በፊት ብቻውን ሲሰራ የነበረውን አሰራር በመቀየርከንግድና ትራንስፖርት፤ከአስተዳደር ም/ቤት፤ከአስተዳደርና ፍትህ፤ከፌደራል ፖሊስና መከላከያ ጋርበቅንጅት የጥምር ኮሚቴ በማቋቋም በየወሩ ወር በገባ በ25ኛው ቀን ላይ በመገናኘት የጋራ ውይይትበማድረግ በሚከሰቱ በችግሮች ዙርያ በመወያያትና የመፍትሄ ሃሳቦችን በማስቀመጥ በሂደት ችግሮችንእየተፈቱ መሆናቸውን አስምረውበታል፡፡

የመውጫ በሮችንም በተመለከተ

ከደገሀቡር በመነሳት በሀርሼንና በሀርትሼክ መካከል (አበከር) አድርጎ ወደ ሱማሌ ላንድይገባል

ከጨረቲ፤ከአፍዴር፤ከጎዴ፤ከቀብሪድሀር በመነሳት በሀርትሼክና በሀርሺን መካከል በመውጣትወደ ሱማሌ ላንድ ይገባል

ከባቢሌና ከፊቅ በመነሳት ጅጅጋን ወደ ግራ በመተው በቀብሪበያህ በኩል ሀርቲሼክን ወደቀኝ በመተው ሱማሌ ላንድ ይገባል

ከኮምቦልቻ ከሃረርና ጉርሱም በመነሳት በጭናክሰን አድርገው በተፈሪበርና ለፌሳ መካከልበማለፍ ቶጎ ውጫሌን ወደቀኝ በመተው ሱማሌ ላንድ ይገባል

የሚወጡትም የቁም እንስሳት የዳልጋ ከብት፤በግናፍየል እንዲሁም ግመሎች ይገኙበታል፡፡

Page 11: 147 (repaired)(1)

የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት Page 9

ከሱዳን የመጡ የውጭ ዜጎች በባቢሌ ገበያ ከሱማሌ ላንድ የመጡ የውጭ ዜጎች በባቢሌ ገበያግብይት ላይ

5.2.1. ቶጎ ውጫሌ

ቶጎውጫሌ ከጅጅጋ 65 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የምትገኝ ከተማ ነች፡፡ ከተማዋ የህጋዊ የቁም እንስሳትየወጪ ንግድ መውጫ በር ሆና ታገለግላለች፡፡ ከኢትዮጵያ ድንበር በግምት 2 ኪ.ሜ ርቀት ላይየምትገኘው ሱማሌላንድ ቶጎውጫሌ ላይ ሰፊ የቀንድ ከብት ግብይት ይካሄድባታል፡፡ በዚህ ገበያ ህጋዊናህገ ወጥ የቁም እንስሳት ንግድ በሰፊው የሚካሄድበት ሲሆን ቡድኑ በ08/06/04 በገበያ ማዕከሉበመገኘት የገበያውን እንቅስቃሴ ለማየት ችሏል፡፡ በአማካይ ከ50 በላይ አይሱዙና ኤፍ.ኤስ.አር አይሱዙመኪናዎች በየቀኑ ወደ ገበያው ይመጣሉ ( በአረፋና በኢድ የሙስሊም በዓላት ወቅት የሚቀርበውየቁም እንስሳት ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ እንደሚያሻቅብ የአካባቢው ነጋዴዎች ይገልጻሉ)

የቁም እንስሳቱም የሚመጡት ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ሲሆን በዋናነትም ከባሌ፤ ከቦረና፤ከኢሉባቦር (ጨወቃ)፤ከጅማ፤ ከወለጋ የመጡ በርካታ ቁጥር ያላቸው እንስሳት ለማየትተችሏል፡፡ከሚቀረቡትም እንስሳት በእድሜም ሆነ በክብደት በአብዛኛው ከዚህ ቀደም በግብርና ሚኒስቴርበወጣ መመሪያ ከተፈቀደው 320 ኪ.ግ ወይም ከዚያ በላይ የሚለውን በመጣስ ዕድሜአቸው ከ 1ዓመት ተኩል በታችና ክብደታቸው ደግሞ በአማካይ ከ150 ኪ.ግ በታች የሆኑ ጥጃዎች መሆናቸውንለማየት ተችሏል፡፡

የቁም እንስሳት ጭነው ወደ ገበያው የሚገቡ መኪናዎች ለእያንዳንዳቸው ብር 150እንደሚከፈልና ለተጨማሪ ወጪዎች መዳረጋቸውን ነጋዴዎቹ በምሬት ይናገራሉ፡፡

ሌላው ከነጋዴዎቹ መገንዘብ የተቻለው የቁም እንስሳት ግብይቱ የሚካሄደው ከኢትዮጵያ ድንበር2 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምትገኘው የሱማሌላንዷ ቶጎውጫሌ መሬት ላይ በመሆኑና ከአገር ውስጥየወጣ የቁም እንስሳ ካልተሸጠ ወደ ሀገር ውስጥ መመለስ ስለማይችል እና እዚያም ለማቆየትምየመኖ ችግር በመኖሩ ነጋዴው እንስሳቱን አቆይቶ እና ተደራድሮ በተሻለ ዋጋ ለመሸጥ እድልስለማይኖራቸው በተገኘው ዋጋ በቅናሽ በመሸጥ ለኪሳራ ይዳረጋሉ ፡፡

አንዳንድ ጊዜ ሽያጩ ከተካሄደ በኋላ ገንዘቡ ወዲያው ስለማይከፍሏቸው ነጋዴው ሱማሌላንድላይ ገንዘቡን ለማግኘት በሱማሌ ላንድ በሚደረገው ቆይታና መጉላላት ለከፍተኛ ወጪ ስለሚዳረጉ ኪሳራ ውስጥ በመግባት ከግብይቱም በመውጣት አልፎ አልፎም ወደ ህገ ወጡ ንግድለመቀላቀል ይገደዳሉ፡

Page 12: 147 (repaired)(1)

የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት Page 10

በቶጎ ውጫሌ ከኢትዮጵያ ወደ ሱማሌ ላንድ የሄዱና ለገበያ የቀረቡ ጥጃዎች ፎቶ ግራፍ

ሠንጠረዥ 1.ላለፉት 4 ዓመታት ወደ ሱማሌ ላንድ በህጋዊ መንገድ የተላኩ የቁም እንስሳትብዛትና የተገኘው የውጭ ምንዛሪ ገቢን የሚያሳይ ሰንጠረዥ

ተ.ቁ ዝርዝር መለኪያ 2000 2001 2002 2003 ምርመራ

1 የቀንድ ከብት ቁጥር 15901 16579 33619 65619

2 ግመል ፤ 143 137 7646 13937

3 በግ ፤ 2767 10500 8834

4 ፍየል ፤ 580 8026

ድምር ፤ 19391 27216 41265 96416

የተገኘው የውጭ ምንዛሪ ዶላር 6,902,938 7,545,172 17,300,716 34,093,050

ምንጭ፡-የጅጅጋ ኳራንቲን ጣቢ

5.2.2. ሀርትሼክ

በመጨረሻም ቡድኑ ከጅጅጋ 70 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምትገኘው ሀርት ሼክ ገበያ ላይ በመገኘት የቁምእንስሳት ገበያውን ለማየት እና መረጃዎችን ለመሰብሰብ ችሏል፡፡ በአካባቢው በከፍተኛ ደረጃ የውሃአቅርቦት ችግር በመኖሩ አንድ በርሜል ውሃ እስከ 80 ብር እንደሚሸጥ እና የገበያ ማዕከሉም ከፍተኛየውሀ አቅርቦት ችግር እንዳለበት ነዋሪዎቹ ገልጸዋል፡፡

የገበያ ማዕከሉ የተገነባው በቮካ ኢትዮጵያ ሲሆን ገበያው ላይ በርካታ ቁጥር ያላቸው በጎችና ግመሎችለግብይት የሚቀርቡበትና እንስሳቶቹም በሃርትሼክ በኩል በህገ ወጥ መንገድ ወደ ሱማሌ ላንድእንደሚወጡ ከስፍራው ከነበሩ ነጋዴዎች እና ነዋሪዎች ለመረዳት ተችሏል፡፡

በግንቦት 2010 እ.ኤ.አ (END MARKET ANALYSIS OF ETHIOPIAN LIVESTOCK ANDMEAT) በሚል ርዕስ የተጻፈው ጥናታዊ ጽሁፍ እንደ ሚያመለክተው ሱማሌ ላንድ እኤአ በ2007ዓ.ም በኮንትሮባንድ መልክ በሀርትሼክና በለፌሳ በኩል በቶጎ ውጫሌ አድርጎ ሱማሌ ላንድ የገባ ከ1.5ሚሊዮን በላይ በግና ፍየል እንዲሁም 100,000 የሚገመት የቀንድ ከብት ለወጪ ገበያ አቅርባለች፡፡

Page 13: 147 (repaired)(1)

የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት Page 11

በአጠቃላይ የሱማሌ ክልል በእንስሳት ሀብት ክምችት በተለይም ግመል፤ፍየል እና በግ የሚታወቅሲሆን ከእነዚህም ውስጥ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው እንስሳት በተለያዩ መውጫ በሮች ወደ ሱማሌላንድ፤ፑንትላንድ፤እንዲሁም ወደ ጅቡቲ እንደሚወጡ ከዚያም በራሳቸው ስም ወደ አጎራባች አረብአገሮች እንደሚላኩ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ይህንንም ከላይ በፎቶግራፉ የሚታዩት በጎች እና ፍየሎችመመልከት ይቻላል፡፡ አዚህም አካባቢ የሚታየው ዋንኛው ችግር የክልሉ የድንበር ስፋት በአማከለመልኩ የክትትልና ቁጥጥር ለማድረግ የሚያስችል የሎጅስቲክና የተሸከርካሪ አቅርቦት በበቂ ደረጃአለመኖር ፤ በሱማሌ ላንድና በኢትዮጵያ ሱማሌ መካከል ያለው የጠነከረ የጎሳ ትስስር እና የፍጆታዕቃዎች በበቂ ሁኔታ ያለመድረስ ነው፡፡

ከሀርት ሼክ በህገ ወጥ መንገድ ወደ ሱማሌ ላንድ ለመላክ የተዘጋጁ በጎች

5.3 አፋር ክልልየአፋር ክልል ከኢትዮጵያ አርብቶ አደር ክልሎች አንዱ ሲሆን ክልሉ በዋናነት ግመል፤በግና ፍየልእንዲሁም የቀንድ ከብት የሚረባበት አካባቢ ነው፡፡ክልሉ እንደ አጎራባቹ ሱማሌ ክልል ሰፊ የሆነየድንበር ወሰን ያለው ነው፡፡

ወደ ክልሉ እንስሳት ከተለያዩ አጎራባች ክልሎች የመገበያያ ቦታዎች ጎሊና(ወልዲያ)፤አለውሃ(ትግራይናአማራ)፤ዳንዲ(ትግራይ )እና ከክልሉ ፤ጭፍራ እና ከመሳሰሉት ተገዝተው ወደ ክልሉ ትልቁ የገበያማዕከል አሳይታ ይገቡና ግብይቱ ከተከናወነ በኋላ የቁም እንስሳቱ በህገ ወጥ መንገድ በአፋምቦ በኩልወደ ዳካ በመሻገር በእግር ወደ ጅቡቲ ይወጣሉ፡፡

ሌላው የህገ ወጥ የቁም እንስሳት መውጫ ከአካባቢው በመነሳት ከአዳይትና ገዳማይቱ በኩል አድርገውበሽንሌ ዞን በኩል ወደ ጅቡቲ እንደሚገቡ ከክልሉ የጸረ-ኮንትሮባንድ ኮሚቴ የተገኘው መረጃያመለክታል፤፤

Page 14: 147 (repaired)(1)

የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት Page 12

ሆኖም በአሁኑ ወቅት ያለው የቁም እንስሳት ህገ ወጥ የንግድ እንቅስቃሴ የመቀነስ ሁኔታዎችይታያሉ፡፡ ለዚህም በዋናነት የሚጠቀሰው በክልሉ ፕሬዝዳንት የሚመራ የጸረ-ኮንድሮባንድ ጥምርኮሚቴ ተቋቋሞ ህገ ወጡን ንግድ ለመቀነስና ብሎም ለመግታት የሚያስችለውን እቅድ ነድፎ እስከታችኛው አስተዳደር እርከን በማውረድ ኮሚቴው በከፍተኛ ደረጃ በመንቀሳቀሱና በየሁለት ሳምንቱእተገናኘ የሚያጋጥሙትንና ያጋጠሙትን ችግር እየፈተሸ እና መፍትሄ እያስቀመጠ በቅንጅት እየሰራበመሆኑ ነው፤፤

ክልሉ በኮንትሮባንድ ንግድ ላይ የጠራ የመከላከል አቋም እንዳለው ህዝቡን ከላይ እስከ ታች ግንዛቤበማስጨበጥ ፤የአካባቢው ሽማግሌዎችን በማሳተፍ በአገሪቷ የወጪ እና ገቢ ንግድ የሚያሳድረውንተጽዕኖ በዝርዝር በማስረዳት ህብረተሰቡ ሰፋ ያለ ግንዛቤ እንዲያገኝ በመደረጉ ነው፤፤

ይህም ለሌሎች ተመሳሳይ ክልሎች መልካም ተሞክሮ ሊሆን እንደሚችል ቡድኑ ያምንበታል፤፤

5.4.ትግራይ ክልልየትግራይ ክልል የቁም እንስሳት የኮንትሮባንድ ንግድ እንቅስቃሴ ከሚካሄድባቸው ክልሎች አንዱስትሆን በሰሜን በኩል ከኤርትራ እና በሰሜን ምእራብ በኩል ከሱዳን እንደምትዋሰንና የህገ ወጡ የቁምእንስሳት መውጫም በሁመራ ደቡባዊ ምእራብ አቅጣጫ በተለያዩ መውጫ በሮች ወደ ሱዳን እንደሚገቡ ቡድኑ የክልሉን የገቢዎችና ጉምሩክ፤ንግድ መምሪያ፤ እና ሌሎች የሚመለከታቸው ክፍሎችበማነጋገር ለመረዳት ተችሏል፡፡

በህገ ወጥ መንገድ የሚወጡት የቁም እንስሳት የሚመጡትም ከተለያዩ ቦታዎች ሲሆን በዋናነትምደቡብ ትግራይ፤ ራያና ሰሜን ወሎ፤ሰሜን አርማጮ እና ቀፍታ ሁመራ ወረዳዎች መሆናቸውንናየሚወጡትም እንስሳት በአብዛኛው የዳልጋ ከብትና ግመሎች ናቸው፡፡

5.4.1.ሁመራ (የትግራይ ምእራባዊ ዞን)ቡድኑ ከመቀሌ ወደ ሁመራ በመጓዝ በአካባቢው የህገ ወጥ የቁም እንስሳት እንቅስቃሴ ለመቃኘትሞክሯል፡፡ በትግራይ ምዕራባዊ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሰብሳቢነት ፤የገቢዎችና ጉምሩክ የሁመራ መቅረጫጣቢያ ሀላፊ፤ግብርና መምሪያ ሃላፊ፤አስተዳደርና ጸጥታ ሐላፊ፤ፌደራል ፖሊስ ፤የዞኑ ፖሊስ ፤ንግድናእንዱስትሪ መምሪያ ሐላፊ፤ የፌደራል ኳራንቲን ተወካይ በተገኙበት ስለ ህገ ወጥ እንስሳት ንግድመነሻ እና ፤መውጫ በሮች፤መንስኤዎችና መፍትሄዎች ዙርያ ሰፊ ውይይት ተደርጓል፡፡

በውይይቱ በአካባቢው የህገ ወጥ እንስሳት ንግድ እንቅስቃሴ መኖሩን ተገልጾ ከሚያዚያ ወር 2003ዓ.ም የዞኑ ጀምሮ የጸረ-ኮንትሮባንድ ጥምር ኮሚቴ በጋራ በመሆን በቅንጅት በተጠናከረ መልኩመንቀሳቀስ በመጀመሩ የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴው መቀነሱን ለመገንዘብ ተችሏል፡፡

ጥምር ኮሚቴው በዞን ደረጃ በየወሩ ወር በገባ በ9ኛው ቀን በወረዳ ደረጃ በየ 15 ቀኑ እንዲሁም በቀበሌደረጃ በየሳምንቱ እየተገናኙ አጠቃላይ ከጸጥታና ኮንትሮባንድ ንግድ ጋር በተያያዘ ግምገማ በማካሄድያጋጠሙ ችግሮች ላይ በጋራ በመወያየት እና መፍትሄ በማስቀመጥ ችግሮቹን እየፈቱ በመሄዳቸውየህገወጥ ንግዱ እንቅስቃሴ መቀነሱ አንዱ ምክንያት እንደሆነ ተገልጻል፡፡ በዞኑ የግብይት ሁኔታዎችበሚፈለገው ደረጃ ያልተመቻቹና በአግባብም ያልተሰራበት አንድም ደረጃውን የጠበቀ የእንስሳት ገበያማዕከልናየእንስሳት ማቆያ የሌለበት መሆኑን ለመገንዘብ ተችሏል፡፡

Page 15: 147 (repaired)(1)

የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት Page 13

5.5.አማራ ክልልበአማራ ክልል ህገ ወጥ የቁም እንስሳት ንግድ ከሌሎች ምርቶች ትልቁን ድርሻ ይይዛል፡፤ለዚህምዋናው ምክንያት ሰፊ የጠረፍ ድንበር መኖሩ ለክትትልና ቁጥጥር አስቸጋሪና ሁሉም ቦታዎችለመድረስና ለመሸፈን አለመቻል ሲሆን ሌላው ደግሞ የግብይቱ ስርአት አለመመቻቸት ነው፡፡ ይኸውምሱዳን አገር የቀንድ ከብት ዋጋ ከሀገር ውስጥ ዋጋ ጋር ሲነጻጸር በሀገር ውስጥ የአንድ ቀንድ ከብትዋጋ ብር 2500-3000 የሚያወጣ ሲሆን ይህ የቀንድ ከብት ሱዳን ተሸግሮ የሚሸጠው እስከ 5000 ብርነው፡፡

ስለዚህ በዚህና በሌሎች ከታች በተዘረዘሩት ምክንያቶች ብዙ እንስሳት በኮንትሮባንድ መልኩ ይወጣሉ፡ይህንን ችግር ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ክልሉ የጸረ-ኮንትሮባንድ ጥምር ኮሚቴ ቀደም ብሎቢቋቋምም አንዴ ሞቅ አንዴ ላላ እያለ ነበር አሁን ግን የጋራ እቅድ በማዘጋጀት ለሴክተር መ/ቤቶችኦርየንቴሽን በመስጠት ኮንትሮባንዱን ለመቆጣጠር እንቅስቃሴ ጀምሯል ፡፡

ጥምር ኮሚቴው ስራውን በመገምገም ከህገ ወጥ ነጋዴው ጋር በመሆን በህገ ወጥ ንግዱ ተሳታፊየነበሩ የመዋቅር አካላት በማጋለጥ እና በማሰር እንቅስቃሴውን አጠናክሮ በመቀጠሉ የህገ ወጡእንቅስቃሴ በመተማ በኩል ቢቀንስም ህገ ወጥ ነጋዴዎቹ ስልታቸውን በመቀየር ወደ ሽንፋ አቅጣጫመዞራቸውንና በአካባቢው በተደረገ ክትትል በተለያዩ ግዚያት 200 ፤ 150 እና 50 በድምሩ 400የቀንድ ከብት በዚህ በጀት ዓመት መያዛቸውን ከአካባቢው የተገኘ መረጃዎች ያረጋግጣሉ፡፡ በመተማቁጥጥሩ ሲጠናከር ኮንትሮባንድ ነጋዴዎች ወደ ሺንፋ 53 ኪ.ሜ በመራቅ በቀን እስከ 300 ከብት በህገወጥ መንገድ በአማካይ እየወጣ መሆኑን ገቢዎችና ጉምሩክ ገንደ ውሃ መቅረጫ ጣቢያ ሓላፊ ጋርከተደረገው ውይይት ለመገንዘብ ተችሎዋል፡፡

መረጃዎቹ እንደሚጠቁሙት 60 ከመቶ የሚሆነው የቁም እንሰሳ የሚወጣው በኮንትሮባንድ መልክመሆኑንና ከቆላማው አካባቢ ለኮንትሮባንዱ ንግድ 78 ከመቶ ድርሻ እንዳለው መረጃዎቹ ያመለክታሉ፡፡

በምሳሌነት ለመጥቀስ Yacob Aklilu, “the most excessive taxation system on cattle in EastAfrica” ን በመጥቀስ (END MARKET ANALYSIS OF ETHIOPIAN LIVESTOCK ANDMEAT)” በሚል ርዕስ እ.ኤ.አ ግንቦት 2010 በቀረበው የጥናት ጽሁፍ በተገለጸው መሰረት በህጋዊመንገድ ከኢትዮጵያ ወደ ሱዳን ለሚገቡ እንስሳት በአንድ ከብት ብር 400 ቀረጥ የሚያስከፍሉ ሲሆንበኮንትሮባንድ ለሚገባ እንሰሳ ግን ብር 20 ብቻ ያስከፍላል ፡፡

ይህም የሚያሳየው በሱዳን በኩል የህጋዊ የቁም እንስሳት ንግድ እንቅስቃሴን የሚያዳክምና የህገ ወጡንየቁም እንስሳት ንግድን የሚያበረታታ መሆኑን ያሳያል፡፡

ይህንን ህገ ወጥ የቁም እንስሳት ለመቆጣጠር ካለው ሰፊ ሜዳና የድንበር ስፋት(ከመተማ ዮሀንስ ግራናቀኝ) አንጻር በገቢዎችና ጉምሩክ ኬላ መቆጣጠሪያ ጣቢያ ያለውን የሎጅስቲክና የተሸከርካሪ አቅርቦትእና የሰው ሀይል ችግር ቢቀረፍና ጥናት ተደርጎ በሺንፋና ሳንጃ ላይ መቆጣጠሪያ ኬላ ቢቋቋም ችግሩሊቀንስ እንደሚችል ከውውይቱ ለመረዳት ተችሏል፡፡

የህገ ወጥ የቁም እንስሳት መነሻቸው በዋናነት ከሰሜን አርማጮ፤ ሰሜን ወሎ(ራያናቆቦ)፤ሰከላናመራዊ(ጎጃም) በአነስተኛም ደረጃም ቢሆን ከባሌ፤አዳማ፤ቦረና፤፤አርሲ ሲሆኑ ወደ ውጪምየሚወጡት ከሱዳን ጋር ባለው ሰፊ ድንበር የኮንትሮባንድ መውጫ በሮች በመኖራቸው

በሳንጃ አድርጎ በአሴራ ወደ ሱዳንና

Page 16: 147 (repaired)(1)

የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት Page 14

በመተማ ዮሃንስ 50ኪ.ሜ በስተደቡብ በኩል አድርጎ በሽንፋ ወደ ቲሃ (ሱዳን )

በቁንዝላ ቋራ በመሄድ በሺንፋ በኩል አድርጎ ወደ ቲሃ(ሱዳን) እንዲሁም

ከነገደ ባህር ወደ ሽንፋ በመሄድ በይሙት በኩል አድርጎ ወደ ቲሃ(ሱዳን) ይገባል፡፡

በአካባቢው ለወጪ እንስሳት የሚደረገው የጤና አገልግሎት አሰጣጥንም በተመለከተ ሥርዓቱንየተከተለ ሳይሆን እንስሳቱ በሌሉበት እና ሳይታዩ ነጋዴው የእንስሳቱን ቁጥር ብቻ በመግለጽ የጤናሰርትፍኬት ከጎንደርና ከሌሎች አካባቢዎች ይዘው ይመጣሉ፡፡ ይህም አሰራር ከመመሪያው ወጪበመሆኑ ሊቆም ይገባዋል፡፡

እንደሌሎቹ አካባቢዎች ሁሉ በአማራው ክልል ጠንካራ አቅም ያላቸው የቁም እንስሳት ላኪዎችያልተሰማሩበትና ጥቂት በመስኩ የተሰማሩትም እንስሳትን በዱቤ በመሸጥ ገዥዎቹ ክፍያውንሳይፈጽሙ ስለሚሰወሩ በርካታ ላኪዎች ለኪሳራ ተዳርገዋል፡፡ስለዚህ የዱቤ አሰራርም ከወዲሁሊታሰብበትና መፍትሄ ሊሰጠው ይገባል፡፡

ሠንጠረዥ 2. ከሐምሌ 2003 እስከ ጥር 2004 ከአማራ ክልል በኮንትሮባንድ(በህገ ወጥ መንገድ) ወደ ሱዳን ሲወጡ የተያዙ የቁም እንስሳትተ.ቁ የእንስሳት ዓይነት መለኪያ መጠን በገንዘብ

1 በሬ በቁጥር 896

2 ላም 453

3 ወይፈን 335

4 ጊደር 83

5 ጥጃ 214

6 ፍየል 326

7 አህያ 8

8 ግመል 1

9 በግ 147

ድምር 2463 10395700

(ምንጭ፡- ገቢዎችና ጉምሩክ ባህር ዳር ቅርንጫፍ) ከዚህ ሰንጠረዥ መገንዘብ የሚቻለው የቁምእንስሳት ኮንትሮባንድ ንግድ እንቅስቃሴ መኖሩን ያሳያል፡፡

Page 17: 147 (repaired)(1)

የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት Page 15

5.6.ሞያሌሞያሌ ወረዳ በደቡብ ኢትዮጵያ በኦሮሚ›ያ ክልላዊ መንግስት በቦረና ዞን እና በሱማሌ ክልላዊመንግስት በሊበን ዞን የሚገኝ ሲሆን ህብረተሰቡ በአብዛኛው አርብቶ አደር ነው፡፡ የቀንድከብት፤ግመል፤ፍየልና በግ በከፍተኛ ሁኔታ የሚረባበት አካባቢው ነው፡፡

በዚህም ዞን እንደሌሎች ክልሎች የህገ ወጥ እንስሳት ንግድ እንቅስቃሴ ይካሄድበታል፡፡ የገቢዎችናጉምሩክ የሞያሌ ቅርንጫፍ እንደገለጸው በዚህ ሞያሌ መውጫ በር በህጋዊ መልክ የሚወጣ የቁምእንስሳት እንደሌለ እና ወደ ኬንያ የሚሄደው እንስሳ በሙሉ የሚጓዘው በህገ ወጥ መልኩ መሆኑንተገልጾዋል፡፡ የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት በየ ቀኑ በኢትዮጵያ ሞያሌ በቦሌ በኩል በቀን በሺዎችየሚቆጠሩ ከብቶች (እንስት በብዛት) ወደ ኬንያ እንደሚወጡ ታውቆአል፡፡የሚወጡትም እንስሳትየተኮላሸ ከብት(ሰንጋ)ና፤ላሞች ናቸው፡፡የጥናት ቡድኑ ኬንያ የሚገኘውን የገበያ ማዕከል በመሄድለማየትና ለማረጋገጥ ችሏል፡፡

ቡድኑ ድንበር ተሻግሮ በጥዋቱ የኬንያ ገበያ ለመመልከት በሄደበት ወቅት የኬንያው ጉምሩክ ባለሙያእንደገለጹልን ከሆን ገበያው ከመድረሳችን በፊት 20 መኪናዎች(500 ከብቶች) ጭነው ወደ ናይሮቢመሄዳቸውን የገለጹልን ሲሆን በገበያው ውስጥ የነበሩ ከብቶች ቁጥር በግምት 1500 እስከ 2000ይደርሳል፡፡ባለሙያው እንደገለጹት ከብቶቹ በሙሉ የመጡት በኮንትሮባንድ ከኢትዮጵያ መሆኑንናኢትዮጵያ እነዚህን ከብቶች በህጋዊ መንገድ ወደ ኬንያ እንዲገባ ብታደርግልን ኬንያ ቀረጥ በመሰብሰብተጠቃሚ ልትሆን ትችል ነበር ብለዋል፡፡

ከኢትዮጵያ በኮንትሮባንድ የወጡ የቁም እንስሳት የግብይት ስነ ስርዓት በሰሜን ኬንያ በሚገኘው ገበያከተከናወነ በኋላ ወደ ናይሮቢ በመውሰድ ከፊሎቹን ራንች ውስጥ እንዲቆዩ በማድረግ አደልበው ወደውጪ እንዲላኩ ይደረጋል፡፡መረጃዎቹ እንደሚያመለክቱት ኬንያ ከምታቀርበው እንስሳት ከ25-30 ከመቶየሚሆነው ምንጫቸው ኢትዮጵያ መሆኑን ያመላክታል፡፡

ቡድኑ ቦታው ድረስ በሄደበት ወቅት ያየውን ህገ ወጥ የቁም እንስሳት ፍሰት ተመልክቶ ከገቢዎችናጉምሩክ ሞያሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ውይይት በማድረግ ቡድኑ በገባበት ማግስት 20 ሰንጋዎችመያዛቸውን ለመመልከት ችሏል፡፡

ያለውን ችግር መነሻ በማድረግ ቡድኑ ከዞኑ አስተዳዳሪ ጋር ባደረገው ውይይት የህገ ወጡ ንግድእንቅስቃሴ መኖሩን ና ለዚህም በዋናነት የሚጠቀሱ ምክንያቶች

የሞያሌ ከተማ እና አካባቢው በሁለት መስተዳድር መተዳደሩ ለቁጥጥር አመቺ አለመሆን

በሁለቱ የጠረፍ ድንበር አካባቢ የሚኖረው ህብረተሰብ በጎሳ በባህልና በልማድ የተሳሰረ በመሆኑለክትትልና ቁጥጥር አመቺ አለመሆኑ

የጸረ-ኮንትሮባንድ ጥምር ኮሚቴ እንቅስቃሴ ያለመኖር

የህብረተሰቡ የግንዛቤ ችግር እና እንደሌሎቹ ሁሉ የእንስሳት ግብይት ሁኔታዎች ያልተመቻቸእና መሰረታዊ ለውጥ ያልታየበት መሆኑ ነው፡፡፡

Page 18: 147 (repaired)(1)

የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት Page 16

ክልሉ የአካባቢውን የእንስሳት ለመቀነስ በበጀት አመቱ አስር ከመቶ ለመቀነስ አቅዶ እየተንቀሳቀስቢሆንም በገበያ እጦት ምክንያት እቅዱን ለማሳካት እንደሚቸገር በመግለጽ ይህንን እቅድ ለማሳካትበአስቸኳይ የገበያ ችግር መቅረፍ እንደሚገባው ገልጸዋል፡፡

የእነዚህ እንስሳት መነሻ ቦታዎች ቦረና ዞን(ያቬሎ-ሀሮበኬ ገበያ፤ድብሉቅ፤) ስሩጳ እና ኮንሶ ሲሆኑበሜጋ በኩል በማድረግ በቦሌ(ሞያሌ) ወደ ኬንያ ይገባሉ፡፡

እንስት እንስሳትና በሬዎች ከሞያሌ (በቦሌ በኩል) ከሞያሌ (በቦሌ በኩል) ወደ ኬንያ ሲጓዙ የተያዙወደ ኬንያ ሲጓዙ

6. የኮንትሮባንዱ ንግድ ዋና ዋና መንስኤዎች1. አስተማማኝ ገበያ በየአካባቢው አለመኖርና ቢኖርም ዋጋው የሚስብና ከጎረቤት አገሮች ዋጋ ጋር

የሚወዳደር ወይም የተሻለ አለመሆን፤ በአካባቢው የተሻለ ውጤታማ ሊሆን የሚችል የግብይት

ስርዓት አለመኖርና የግብይት መሰረተ ልማት ዝርጋታ አናሳ መሆን፣

2. ጎረቤት አገሮች ኮንትሮባንዱን ንግድ በመከላከል ተግባር ላይ ተሳታፊ ከመሆን ይልቅ

የሚያበረታቱ መሆኑ፤ይህም የሚገለጸው በህጋዊ መንገድ በሚገባ እንስሳ ላይ የሚጣለው ቀረጥ

ከፍተኛ መሆንና በተቃራኒው በህገ ወጥ የሚገባ እንስሳ በነጻ የሚገባ መሆኑ ነው፡፡

3. የጠረፍ አካባቢዎች በመልካምድርዊ አቀማመጣቸው ከመሃል አገር ገበያዎች የራቁ በመሆናቸው

ከዚያ ራቅ ካሉት እንደ ሱማሌ ቦረና እና አፋር አካባቢዎች ወደ መሃል የኤክስፖርት ገበያዎች

ከማቅረብ ይልቅ የትራንስፖርት ወጪና የተሻለ ዋጋ ወደ አለው ጎረቤት አገሮች ማቅረቡ

የተሻለ አማራጭ በመሆኑ፣

4. ከመሃል አገር ለጠረፍ አካባቢዎች የሚቀርበው የፍጆታ ዕቃ አለመኖር ወይም አነስተኛ መሆንና

በተቃራኒው ከጎረቤት አገሮች በኩል የየዕለት የፍጆታ ዕቃዎች ለመጥቀስም ያህል

ስኳር፤የተፈበረኩ የምግብ ምርቶችና ለጠረፍ ሞቃት አካባቢዎች የሚስማሙ አልባሳት ከመሃል

አገር በተሻለ ዋጋ የሚቀርብ በመሆኑ

Page 19: 147 (repaired)(1)

የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት Page 17

5. ህገ ወጥ የቁም እንስሳት ንግዱ ለብዙ ጊዜያት ሲካሄድ የቆየ በመሆኑ በልምድ፣ በፋይናንስ

አቅርቦት፣ በመረጃ ልውውጥ የተጠናከረ ፣ በተሳታፊዎች በሚደረግለት ድጋፍ ከህጋዊ ንግዱው

በተሻለ መልክ የተመቻቸና አዳዲስ ተሳታፊዎችን በበለጠ ሁኔታ መሳብ መቻሉ፣

6. ረዥምና ሰፊ የድንበር ወሰን በመኖሩና ያንኑ ያህልም በቁጥር ለመገመት የሚያስቸግሩ

የኮንትሮባንድ መውጫ በሮች መኖራቸው፣እነዚህንም መውጫ በሮችን ለመቆጣጠር በሰው

ኃይልም ሆነ በሎጅስቲክ አለመጠናከራቸው፤

7. በድንበር አካባቢ የሚኖሩ ህዝቦች በባህል፣ በቋንቋ፣ በእምነት፣ በዘርሃረግ፣ወዘተ ከመተሳሰሩም

ባሻገር ለጠረፍ አካባቢ ነዋሪዎች ለአብዛኛው ህብረተሰብ የኑሮ ምሰሶአቸው እንስሳትን

በማርባትና ከእንስሳት ሽያጭ የሚያገኙት ገቢ የሚጠቀሙ በመሆናቸው የበለጠ

የሚያስተሳስራቸው በመሆኑ ይህ ግንኙነታቸው ለህገወጥ ንግዱ መጠንከር አስተዋፅኦ ማድረጉ፣

7. ለመንኤዎቹ የመፍትሄ ሀሳቦች1. የኤክስፖርት ቄራዎች በግል ባለሀብቶች እንዲቋቋሙ የመንግስት አቅጣጫ ቢሆንም

በአንዳንድ አካባቢዎች የግል ባለሀብቶች ደፍረው ለመግባት ባለመቻላቸው መንግስትበተጠኑና ስትራቴጂክ በሆኑ ቦታዎች ላይ የኤክስፖርት ቄራዎችን በማቋቋም በሂደትለግል ባለሀብቶች እንዲተላለፍ በማድረግ የግብይት ስርዓቱን በማሻሻል የተሻለ ዋጋእንዲፈጠር ሁኔታዎችን ማመቻቸት

2. በዲፕሎማሳዊ በሆነ መንገድ ከዚህ በፊት በሁለቱ አገሮች በተደረጉ ስምምነቶች መሰረትህገ ወጡን እንቅስቃሴ የመከላከሉን ተግባር ተግባራዊ ማድረግ እና የሎጅስቲክናየተሸከርካሪ አቅርቦትን በማሻሻል በተቀናጀ መልኩ ተከታታይነት ያለው ክትትልና ቁጥጥርበማድረግ ህገ ወጡ ንግድ የሚቀንስበትና ብሎም የሚገታበትን ሁኔታዎችን ማመቻቸት

3. በሀገር ውስጥ በተለይም በጠረፍ አካባቢዎች አምራቹንና ነጋዴውን በማስተሳሰር በሃገርውስጥ የተሻለ ዋጋ ለመፍጠር አካባቢዎቹ ላይ በሂደት በመንግስትና በግል ባለሀብቶችኤክስፖርት ቄራዎችን ማቋቋምና እና የግብይቱን ስርአቱን የሚከታተልና የሚመራየመንግስታዊ መዋቅር መፍጠር እና ተከታታይነት ያላቸው ወቅታዊ የግብይት መረጃዎችለህብረተሰቡ እንዲደርስ ማድረግ፡፡

4. በሀገር ውስጥ የሚመረቱ የፍጆታ እቃዎችን ስኳር፤ዘይት፤አልባሳት…ወዘተ ከጎረቤትአገሮች ከሚገቡት ምርቶች ዋጋ ጋር በተመጣጣኝ ዋጋ ለጠረፍ አካባቢዎች በጅንአድወይም ማህበራትን በማጠናከር በበቂ ደረጃ እንዲደርሳቸው ማድረግ ፤

5. ህገ ወጡን ንግድ ለማዳከም ህጋዊ ነጋዴውና አስፈጻሚ አካላት በተቀናጀ መልኩ ተግባራዊስራዎችን በማከናወን ፤የነጋዴዎችን የገንዘብና(የካፒታል) የማስፈጸም አቅማቸውንበማሳደግ ፤ወቅታዊ የግብይት መረጃዎች በማቅረብ ክትትልና ጠንካራ ቁጥጥር በማድረግበግብይቱ ዙርያ ያላቸውን ግንዛቤ እንዲያሰፉና ወደ ህጋዊ አሰራር እንዲመጡ ማድረግ፤

Page 20: 147 (repaired)(1)

የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት Page 18

6. በየአካባቢው ያለው የፀረ-ኮንትሮባንድ ጥምር ኮሚቴ በማጠናከር እና እንደ አካባቢውመልካምድር አቀማመጥ አስቸጋሪነትና ስፋት አንጻር የሰው ሓይልና የሎጅስቲክ አቅርበትናተሻከርካሪ በማቅረብ ከፍተኛ ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ የኮንትሮባንድ መውጫ በሮችንበመቆጣጠር ህግን ማስከበር

7. በተለይም በአርብቶ አደር አካባቢዎች የግብይት ማህበራትን በማደራጀትና በሁለንተናዊመልኩ በማብቃት በእንስሳት ወጪ ንግድ እንዲሰማሩ ማድረግ ከዚህም በተጨማሪበጠረፍ አካባቢ ነዋሪዎችን በስነ ልቦና ሆነ ባህላዊ ትስስሩ ከመሃል አገር ጋር እንዲተሳሰርተከታታይ የሆነ ትምህርት መስጠት፤

8. በአካባቢው የታዩ ዋና ዋና ችግሮች1. በጠረፍ አካባቢዎች የሚገኙ ገበያዎች የሚገኙበት ቦታ ለጎረቤት አገሮች በጣም ቅርብ እና

ደረጃቸው ተጠብቆ የተገነቡ አለመሆናቸው ለአብነትም የሞያሌ (40ሜትር) የሁመራና ናየመተማ ገበያ ቦታዎች የሚገኝበት ስፍራ ለጠረፍ በጣም የቀረበ እና በ15 ኪ.ሜ ክልልውስጥ በመሆናቸው ለክትትልና ቁጥጥር አመቺ አለመሆናቸው

2. የእንስሳት ዝውውርና እንቅስቃሴ በሚመለከት በሀገሪቱ ስርዓቱ ገና ባለመጀመሩ ምክንያትየሚገድብ የህግ ማዕቀፍ ባለመኖሩ ህገ ወጥ ነጋዴዎች ያለ ገደብ ስለሚንቀሳቀሱ በተለይምለህገ ወጡ ንግድ ሁኔታዎች የተመቻቸ መሆናቸው

3. የውጭ ዜጎች ፍቃድ ሳይኖራቸው እስከ መሀል አገር ዘልቆ በመግባት ለሀገር ውስጥ ዜጋብቻ የተፈቀደውን ገበያ ውስጥ በመግባት እንስሳትን በቀጥታ በመግዛትና መርጦ በማስገዛትየግብይት ስርዓት በማዛባት ላይ መሆናቸው

4. ከንግድ ሚኒስቴር ሀጋዊ የንግድ ፈቃድ ለማውጣትና ለማደስ ቀልጣፋ ባለመሆኑ ጊዜናተጨማሪ ወጪ በመጠየቁ እና ሚጠይቀው ካፒታል ከፍተኛ በመሆኑ ነጋዴዎች ህጋዊፈቃድ አውጥተው ከመንቀሳቀስ ይልቅ ወደ ህገ ወጥ ንግድ ሊቀላቀሉ እንደሚችሉ

5. በአንዳንድ አካባቢዎች የጸረ ኮንትሮባንድ ኮሚቴ ከክልል ጀምሮ በተዋረድ የህገ ወጡን ንግድለመቆጣጠርን ለህብረተሰቡ የህገ ወጡን ንግድ በሀገር ኢኮኖሚ ላይ የሚያስከትለውንተጽዕኖ ግንዛቤ በማስጨበጥ ዙርያ በቅንጅት ያለመንቀሳቀስ ክፍተቶች ይታያሉ ለአብነትበቦረና እና በሊበን ዞኖች በተለይም ሞያሌ ወረዳ

6. እንስት እንስሳትና ጥጃ እንዲሁም የውጭ ዝርያ ያላቸው እንስሳት አወጣጥና እገዳበተመለከተ ግልጽና የማያሻማ በጽሁፍ የተዘጋጀ መመሪያ ያለመኖር

7. የጠረፍ አካባቢ ህብረተሰብ ኮንትሮባንድ ንግድ በህገሪቱ ኢኮኖሚና ደህንነት እንዲሁምማህበራዊ ኑሮ እና በህጋዊ መንገድ በሚንቀሳቀሰው ነጋዴ ላይ የሚያሳድረውን ተጽኖየግንዛቤ ችግር መኖሩና ለገበያ አማራጭና ለተሻለ ዋጋ በህገ ወጡ ንግድ መሳተፍና ተባባሪመሆን

Page 21: 147 (repaired)(1)

የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት Page 19

8. በሀገሪቱ ደረጃቸውን የጠበቁ የቁም እንስሳት ኳራንቲንና ኢንስፔክሽን እንዲሁም እንስሳትቼክ ፖስቶች እንዲሁም የእንስሳት የማቆያ ቦታ ያለመኖር

9. ለኤክስፖርት የተዘጋጁ እንስሳት የጆሮ መለያ ቁጥር አሰጣጥ ወጥ አለመሆንናበተቆጣጣሪው አካል የተሰጠው ቁጥር በማንኛውም ቦታ የመቀርና የመለወጥ ዕድሉ ከፍተኛመሆኑ

9. ለችግሮቹ የተቀመጡ የመፍትሔ ሃሳቦች1. በሞያሌም ሆነ በሌሎች ጠረፍ አካባቢዎች የሚገነቡት የቁም እንስሳት መሰረተ ልማቶች (ገበያ

ማዕከላት) ጥናትን መሰረት ባደረገ መልኩ ከጠረፍ አካባቢዎች ራቅ ብለው ምቹና የእንስሳትክምችትን ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ደረጃቸውን ጠብቀው እንዲገነቡ ማድረግ፡፡

2. ተጀምሮ በሂደት ላይ የሚገኘውን የቁም እንስሳት የግብይት ስርዓትንና የህግ ማዕቀፎችንከወዲሁ በማጠናቀቅና የህግ መሰረት እንዲኖራቸው በማድረግ ህገ ወጡን የቁም እንስሳትዝውውር ስርዓት እንዲይዝ ማድረግ

3. ለዜጎች የተፈቀደውን የአገር ውስጥ ገበያ የውጭ ዜጎች ገብተው የግብይት ስርዓቱን እንዳያዛቡበሚል ከዚህ ቀደም በግብርና ሚኒስቴር የተላለፈው መመሪያ ተግባራዊ በማድረግ አፈጻጸሙንመከታተል

4. በንግድ ሚኒስቴር ያለውን የቁም እንስሳት የወጪ ንግድ የፈቃድ አሰጣጥ ሂደት በመፈተሸቀልጣፋ እንዲሆን ማድረግ

5. የፀረ-ኮንትሮባንድ ጥምር ኮሚቴው ከክልል በተዋረድ እስከ ቀበሌ ያለው ተግባራዊ ሊሆኑየሚችሉ የኮንትሮባንዱን ለመከላከል የሚያግዙ ተግባራትን በማቀድ ተጠናክሮ እንዲቀጥልመስተዳድር አካላት (ከክልል እስከ ቀበሌ) ስራውን በሐላፊነት የእኔ ጉዳይ ነው ብሎበቁርጠኝነት እንዲከታተልና እንዲመራው የጋራ የውይይት መድረክ በመፍጠር ተግባራዊእንዲሆን ማድረግ

6. በእንስት የቀንድ ከብት ፤ጥጃ እና የወጭ ዝርያ ያላቸው እንስሳት አወጣጥ ዙርያ ግልጽናየማያሻማ ገላጭ የሆነ መመሪያ እንዲኖር ማድረግ

7. የሀገር ሽማግሌዎችና የጎሳ መሪዎችና ህብረተሰቡ ስለ ኮንትሮባንድ ንግድ በሀገር ኢኮኖሚናበህጋዊ ንግዱ ላይ የሚያደርሰውን ተጽዕኖ እና በህጋዊ መልክ የሚከናወነው የንግድ እንቅስቃሴያለው ጠቀሜታ ግንዛቤ ማስጨበጥ

8. ደረጃቸውን የጠበቁ የኳራንቲን ጣቢያዎችና ቼክ ፖስቶች የእንስሳት አቅርቦትን ክልሉን በአማካለመልኩ በተጠኑ ቦታዎች ላይ መገንባትና ማጠናከር

9. የወጪ እንስሳት የመለያ ቁጥር(ኢር ታግ) በሚስጢር ኮድ ተሰጥቶት በሀገር መከላከያ ሚ/ርተዘጋጅቶ ለቁጥጥር በሚያመች መልኩ በስራ ላይ እንዲውል ማድረግ

Page 22: 147 (repaired)(1)

የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት Page 20

10.የኳራንቲን አገልግሎት

የግብርና ሚ/ር በአዋጅ ቁጥር 4/1987 በአንቀጽ 19/8 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ወደ ሀገር ውስጥየሚገቡትም ሆነ በሚወጡት እንስሳት እጽዋት እና የእንስሳት ውጤቶች ላይ ተገቢውን የኳራንቲንናኢንስፔክሽን እንዲያደርግ ስልጣን ተሰጥቶታል፡፡

በዚህ አገልግሎት አሰጣጥ መመሪያ ላይ እንደተገለጸው አንድ ህጋዊ ነጋዴ እንስሳትን ወደ ውጪለመላክ የጤና ማረጋገጫ ወረቀት ከመጠየቁ በፊት እነዚህን ቅድመ ዝግጅቶች ማሟላት አለበት

ክትባትና ሕክምና የሚያገኙበት ድርጅት/ጣቢያ

የኳራንቲን ጊዚያቸውን የሚፈጽሙበት ጣቢያ

ተፈላጊውን ክብደት እስኪያገኙ የሚቆዩበት ማደለቢያ ጣቢያ…..ወዘተ እንዲኖረው ያስፈልጋልይላል፡፡

ሌላው በበመመሪያው የተገለጸው ደግሞ በቁም ወደ ውጪ ገበያ የሚቀርቡ የቀንድ ከብቶች፤በጎች፤ፍየሎችና ግመሎች ተገቢውን ክትባትና ሕክምና ማግኘት ይኖርባቸዋል፡፡በኳራንቲን ጣቢያ ቢበዛእስከ 30 ቀናት ሊቆዩ ይገባል፡፡የሚል ቢሆንም

ቡድኑ የተገነዘበው ነገር ቢኖር አሁን ያለው ኳራንቲን እየሰራ ያለው መመሪያውን ባልተከተለ መልኩመሆኑን ነው፡፡

ነጋዴው ከብቶቹን ከመግዛቱ በፊት የሚገዛውን የከብት ቁጥር ብቻ በመግለጽ ሰርትፍኬትእንደሚዘጋጅለት

መኪና ላይ እያሉ ምንም አይነት ክትባት ሳይሰጥና የማቆያ ጊዜያቸውን ሳይጨርሱ ሰርትፊኬቱንእንዲያገኙ ማድረግ

አንድ ነጋዴ ማሟላት ያለበትን ቅድመ ዝግጅት ማሟላቱን ሳይጠየቅና ምንም ዝግጅት ሳይኖረውፈቃድና ሰርትፍኬት እንዲያገኝ መደረጉ

በአጠቃላይ ክልሎቹ እንደገለጹት በህጋዊ መንገድ ህገ ወጥ ንግድ እየተካሄደ መሆኑን እና መስፈርቱንየማያሟሉ፤በእድሜና በኪሎግራም ለመውጣት የማይፈቀድላቸው እንስሳት፤እንስት ላሞች፤ዲቃላከብቶች እንዲሁም መስፈርቱን በማያሟላ መኪና ተጭነው የተላላጡ እና የደሙ እንስሳት በህጋዊመንገድ ሰርትፍኬት ተዘጋጅቶላቸው በመውጣት ላይ ይገኛሉ፡፡

ለዚህ ህገ ወጥ አሰራር ምክንያቶች/መንስኤዎች

የፌደራል ንግድ ሚንስቴር ለወጭ እንስሳት ፈቃድ ሲሰጥና ሲያድስ ነጋዴዎቹ ተገቢውን መስፈርትማሟላታቸውን ከግብርና ሚ/ር ማረጋገጫ እንዲያመጡ ሳይጠይቅ ፈቃድ መስጠቱ

በእንስሳት ንግዱ ዙርያ የተሰማሩ ነጋዴዎችም ሆነ እንስሳት አርቢው ህብረተሰብ በድንበር ዘለልየእንስሳት በሽታዎች ዙርያ ያላቸው ግንዛቤ አናሳ መሆን

Page 23: 147 (repaired)(1)

የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት Page 21

የእንስሳት ዝውውርና እንቅስቃሴ በሚመለከት የህግ ክፍተትና ጉድለት መኖሩ

የየአካባቢው የእንስሳት በሽታዎች ስፋትና ስርጭት የሚያመላክቱ መረጃዎች ውስንነት እና ጉድለት

መመሪያዎችና ደንቦች እንዲሁም የስራ ኃላፊነትና የስራ ድርሻቸውን በተመለከተ በፌደራልለተወከሉ ባለሙያዎችና ውክልና የተሰጣቸው ክልሎች በሚገባ እንዲያውቁት አለመደረጉ እናየክትትልና የቁጥጥር አለመኖር

የእንስሳት ኳራንቲን የሥራ ክፍል በሥሩ በሚገኙ የኳራንቲንና የቼክ ፖስትና ጣቢያዎች አሠራር

ወጥ አለመሆን እና ለሥራ ክፍሉ ከዚህ በፊት የወጡ መመሪያዎችና ደንቦች በየጊዜው አለመሻሻል፣

በሀገሪቱ የሚገኙ የኳራንቲንና የቼክ ፖስት ጣቢያዎች ባለሙያዎችና በሥራው ዙሪያ የወጣውን

መመሪያ ጠንቅቆ አለማወቅ /አለመረዳት/ እና ተግባራዊ አለማድረግ፣

በእነዚህ ጣቢያዎች ካለው የሥራ /የኤክስፖርት/ ስፋት አንፃር እና መንግስት ካስቀመጠው እቅድ

አንፃር ከግብ ለማድረስ ጣቢያዎቹ በሠው ኃይልና በሎጀስቲክስ ያልተሟላ መሆን፣

ለኤክስፖርት ለተዘጋጁ እንስሳት የጆሮ መለያ ቁጥር አሰጣጥ ወጥ አለመሆንና በተቆጣጣሪው አካል

የተሰጠው ቁጥር በማንኛውም ቦታ የመቀየርና የመለወጥ እድሉ ከፍተኛ መሆኑ፣

የኤክስፖርት ሥራውን ስፋት በአማከለ መልኩ የኳራንቲን ጣቢያና ሰርቪስ የሚሰጡ ጣቢያዎች

በአገሪቱ ማዕከላዊ ቦታዎች መደራጀት /ለምሣሌ፡- አዳማ፣ድሬዳዋ/ እና በጠረፍ አካባቢዎች

አገልግሎቱ አለመኖር፣

የመድሃኒትና የክትባት አቅርቦት አስተማማኝ አለመሆንና ከሚመለከታቸው አካላት ውጪ ደረጃውን

ባልጠበቀ ሁኔታ መያዝ፣

ለክልሎች የተሰጠው የሠርቲፍኬሽን ውክልና መመሪያና ደንብ የሌለውና ለክትትልም አስቸጋሪ

መሆን፣

በኳራንቲን የቼክ ፖስት ጣቢያዎች በሱፐርቪዥን እና የክትትል ሥራ ከዋናው መ/ቤት ክትትልና

ድጋፍ ደካማ መሆን፣

በኳራንቲን ጣቢያዎች ለሥራው የሚመደቡ ባለሙያዎች ተከታታይ የሆኑ ስልጠናዎች፣

በተደራጁት ኳራንቲን ቦታና /አዳማ፣ድሬዳዋ/ የልምድ ልውውጥ አለማግኘት፣

በኤክስፖርት ሥራ ተሰማርተው የሚገኙ ባለሀብቶች ስለ ሥራው /ስለ ኳራንቲን/ አዋጅ፣ ደንብና

መመሪያ አሠራር በቂ ግንዛቤ አለመኖርና ለደንቡ መፈጸም ተነሳሽነት አለመኖር፣

ለእንስሳት መጓጓዣነት የሚሆኑ ተሽከርካሪዎች ለዚሁ ተግባር ያልተዘጋጁ መሆናቸው በእንስሳው

አካላዊ ጉዳት ማድረስ ማለትም ስብራትና ከፍተኛ ቁስለት ስለሚገጥማቸው /በተለይም ግመልና

ከብት/ በተቀባይ አገራት ስለኢትዮጵያ እንስሳት ያላቸውን ፒክቸር / ስዕል/ የተበላሸ መሆን፣

Page 24: 147 (repaired)(1)

የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት Page 22

በኳራንቲን ጣቢያዎች በጉዞ ላይ ለሚሞቱና ለሚጐዱ እንስሳት የአወጋገድ የማገገሚያ መመሪያና

ደንብ አለመኖር፣ /የእንስሳት በሽታ ስርጭትን ማባባስ/

የእንስሳት ዝውውር /ማለትም ከክልል ክልል/ ልቅ መሆን ለእንስሳት በሽታ ስርጭትና

ለኮንትሮባንድ ንግድ መስፋፋት መንስኤ መሆን፣

በሰፋፊና በዋና ዋና የእንስሳት ገበያ ማዕከላት /ለምሣሌ፣ ያቤሎ፣ባቢሌ፣ገንዳውሃ፣ሁመራ../

አቅራቢያ ለተገዙት እንስሳት ደረጃውን የተጠበቀ መጫኛ፣ ማራገፍያ፣ መመገቢያና ውሃ የሚገኝበት

ቦታዎች አለመኖር፣

የቄራዎች የስጋና የስጋ ውጤቶች ማደራጃ አለመኖር፣ / ያሉትም በአጥጋቢ ሁኔታ

አለመሰራት/ጐንደር፣ባ/ዳር፣መልጌ ወንዶ/ ቄራዎች፣

ከሁለት ዓመት በፊት በሱማሌ ክልል የኳራንቲን ቼክ ፖስት ላይ የተመደቡት ባለሙያዎች ወደ

ሥራ አለመግባት ፣

Page 25: 147 (repaired)(1)

ሠንጠረዥ -3 በ2004 በጀት ዓመት የስድስት ወር የቁም እንስሳት የወጪ ኮንትሮባንድ (ከሐምሌ 2003-ታህሳሥ 2004) ሪፖርት

ምንጭ፡- ገቢዎችና ጉምሩክ

ተ.ቁ

የወጪኮንትሮባንድ

ዓይነት

የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ስም

ጠቅላላ ድምር

መቀሌ ድሬደዋ ባህር ዳር ጅጅጋ

መለኪያ

የተያዙየቁም

እንስሳትብዛት በገንዘብ

የተያዙየቁም

እንስሳትበገንዘብሲተመን

የተያዙየቁም

እንስሳትብዛት

በገንዘብሲተመን

የተያዙየቁም

እንስሳትብዛት

በገንዘብሲተመን

የቁምእንስሳትብዛት

በገንዘብሲተመን

1 ቀንድ ከብት በቁጥር 66 159,100 44 44,000 1,849 9,166,100 73 301,000 2032 9,670,2002 በግ በቁጥር 42 33,600 56 27,900 147 88,200 667 319,060 912 468,7603 ፍየል በቁጥር 160 68,132 260 156,000 127 62,200 547 286,3324 ግመል በቁጥር 7 57,000 1 10,000 8 67,0005 አህያ በቁጥር 2 2,000 8 15,000 10 17,000

ድምር 117 251,700 260 140,032 2,265 9,435,300 867 682,260 3,509 10,509,292

Page 26: 147 (repaired)(1)

የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት Page 2

ሠንጠረዥ-4 በ2004 በጀት ዓመት የስድስት ወር የቁም እንስሳት ኤክስፖርት (ከሐምሌ 2003-ታህሳሥ 2004)

ተ.ቁ

የወጪ እንስሳት መለኪያ

የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ስም

ጠቅላላድምር

መቀሌ(ሁመራ) ድሬደዋ ባህር ዳር

(ገንዳውሃ)

ጅጅጋ አፋር(ጋላፊ)

ቀንድ ከብት በቁጥር 10,199 459 60,871 67,168

በግ በቁጥር 556 17,843

ፍየል በቁጥር 2,080 5,739 10,177

ግመል በቁጥር 12,975 1,640 4,025

ድምር 25,809 7,838 60,871 99,213 218,053 411,784

በገንዘብ ሲተመን ዶላር 9,856,380 1,236,705 24,351,420 31,005,943 መረጃ የለም 66,450,448

ምንጭ፡-ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን

Page 27: 147 (repaired)(1)

የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት Page 3

ሠንጠረዥ ፡-5. የድርጊት መርሃ ግብርተ.ቁ መንሲኤዎችና ችግሮች መፍትሄዎች የሚከናወኑ ተግባሮች

የሚመለከታቸውአካላት

የጊዜ

ሰሌዳ

የአጭር የረጅም

1

የጠረፍ አካባቢዎች በመልካምድርዊአቀማመጣቸው ከመሃል አገር ገበያዎች የራቁበመሆናቸውአስተማማኝ ገበያ በየአካባቢውአለመኖርና ቢኖርም ዋጋው የሚስብና ከጎረቤትአገሮች ዋጋ ጋር የሚወዳደር ወይም የተሻለአለመሆንና በአካባቢው የተሻለ ውጤታማ ሊሆንየሚችል የግብይት ስርዓት አለመኖርና የግብይትመሰረተ ልማት ዝርጋታ አናሳ መሆን፣

የኤክስፖርት ቄራዎች በግል ባለሀብቶችእንዲቋቋሙ የመንግስት አቅጣጫ ቢሆንምበአንዳንድ አካባቢዎች የግል ባለሀብቶችደፍረው ለመግባት ባለመቻላቸው መንግስትበተጠኑና ስትራቴጂክ በሆኑ ቦታዎች ላይየኤክስፖርት ቄራዎችን በማቋቋም በሂደትለግል ባለሀብቶች እንዲተላለፍ በማድረግየግብይት ስርዓቱን በማሻሻል የተሻለ ዋጋእንዲፈጠር ሁኔታዎችን ማመቻቸትናየግብይት ስርዓቱን የሚከታተልና የሚመራየመንግስታዊ መዋቅር መፍጠርተከታታይነት ያላቸው ወቅታዊ የግብይትመረጃዎች ለህብረተሰቡ እንዲደርስማድረግ፡፡

1.ነባር የግብይት ማዕከላትን የውስጥመሰረተ ልማቶችን በማሟላትለግብይት ምቹ እንዲሆኑ ማድረግ2.ለህጋዊ ቁም እንስሳት ነጋዴዎችየሀገር ውስጥም ሆነ የውጭ ገበያዎችንበማመቻቸት ረገድ ወቅታዊ የግብይትመረጃዎችን በመስጠት የግብይትትስስሮች እንዲኖር ማድረግ3.የግብይት ህብረት ስራ ማህበራትንበማደራጀት የማስፈጸምን የገንዘብአቅማቸውን በማጠናከር እንስሳትንለውጪ ገበያ እንዲያቀርቡ ማስቻል

1.ጥናት ተደርጎበጅጅጋ፤በደጋሀቡርላይ መንግስትናበግል ባለሃብቶችየኤክስፖርትቄራዎች መገንባት2.የግዥ ጣቢያዎችማቋቋም

ንግድ ሚ/ር፤ግብርና፤ህብረትሥራ፤ባለሀብቶች፤የኢስወቴኢ፤ክልሎች

2

ጎረቤት አገሮች ኮንትሮባንዱን ንግድ በመከላከልተግባር ላይ ተሳታፊ ከመሆን ይልቅ የሚያበረታቱመሆኑ፤የህም የሚገለጸው በሀጋዊ መንገድ በሚገባእንስሳ ላይ የሚጣለው ቀረጥ ከፍተኛ መሆንናበተቃራኒው በህገ ወጥ የሚገባ እንስሳ በነጻ የሚገባመሆኑ ነው፡፡

በዲፕሎማሳዊ በሆነ መንገድ ከዚህ በፊትበሁለቱ አገሮች በተደረጉ ስምምነቶችመሰረት ህገ ወጡን እንቅስቃሴየመከላከሉን ተግባር ተግባራዊ ማድረግእና የሎጅስቲክና የተሸከርካሪ አቅርቦትንበማሻሻል በተቀናጀ መልኩ ተከታታይነትያለው ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ ህገወጡ ንግድ የሚቀንስበትና ብሎምየሚገታበትን ሁኔታዎችን ማመቻቸት

1.ከዚህ ቀደም ከጎረቤት አገሮች ጋርየተደረጉ ስምምነቶች እንዲከበሩ የጋራውይይት በመፍጠር ዲፕሎማሳዊስራዎችን መስራት2.የነበሩት ስምምነቶች ከወቅቱ ጋርበማገናዘብ እንዲሻሸል ማድረግ3.አስፈላጊ የሚሆኑ አቅርቦቶቹንበማሟት በተቀናጀ መልኩ ጠንከር ያለክትትልና ቁጥጥር ምድረግ

የፌደራልጉዳዮች፤ገቢዎችናጉምሩክ፤ክልሎች፤

Page 28: 147 (repaired)(1)

የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት Page 4

3

ከመሃል አገር ለጠረፍ አካባቢዎች የሚቀርበውየፍጆታ ዕቃ አለመኖር ወይም አነስተኛ መሆንናበተቃራኒው ከጎረቤት አገሮች በኩል የየዕለትየፍጆታ ዕቃዎች ለመጥቀስም ያህልሱካር፤የተፈበረኩ የምግብ ምርቶችና ለጠረፍሞቃት አካባቢዎች የሚስማሙ አልባሳት ከመሃልአገር በተሻለ ዋጋ የሚቀርብ በመሆኑ

በሀገር ውስጥ የሚመረቱ የፍጆታእቃዎችን ስኳር፤ዘይት፤አልባሳት…ወዘተከጎረቤት አገሮች ከሚገቡት ምርቶች ዋጋጋር በተመጣጣኝ ዋጋ ለጠረፍ አካባቢዎችበጅንአድ ወይም ማህበራትን በማጠናከርበበቂ ደረጃ እንዲደርሳቸው ማድረግ ፤

1.ለጠረፍ አካባቢዎች ከመሀል አገርመቅረብ የተጀመረው የፍጆታእቃዎችና ተጠናክሮ እንዲቀጥልማድረግ እና በተመሳሳይ ሁኔታምበፍራንኮ ቫሉታ መግባት የተጀመረውየፍጆታ እቃዎችና አልባሳት ቀጣይነትእንዲኖረው ማድረግ

1.በአካባቢውየሸማቾች የህብረትስራ ማህበራትበማቋቋም መሰረታዊየፍጆታ እቃዎችናአልባሳትእንዲያቀርቡማስቻል

ህብረትስራ፤ገቢዎችናጉምሩክ፤ክልሎች

4

ህገ ወጥ የቁም እንስሳት ንግዱ ለብዙ ጊዜያትሲካሄድ የቆየ በመሆኑ በልምድ፣ በፋይናንስአቅርቦት፣ በመረጃ ልውውጥ የተጠናከረ ፣በተሳታፊዎች በሚደረግለት ድጋፍ ከህጋዊንግዱው በተሻለ መልክ የተመቻቸና አዳዲስተሳታፊዎችን በበለጠ ሁኔታ መሳብ መቻሉ፣

ህገ ወጡን ንግድ ለማዳከም ህጋዊነጋዴውና አስፈጻሚ አካላት በተቀናጀመልኩ ተግባራዊ ስራዎችን በማከናወን፤የነጋዴዎችን የገንዘብ የማስፈጸምአቅማቸውን በማሳደግ ፤ወቅታዊ የግብይትመረጃዎች በማቅረብ ክትትልና ጠንካራቁጥጥር በማድረግ በግብይቱ ዙርያያላቸውን ግንዛቤ እንዲያሰፉና ወደ ህጋዊአሰራር እንዲመጡ ማድረግ፤

1.ለህጋዊ ነጋዴዎች የብድርአገልግሎት በመስጠት የካፒታልአቅማቸውን ማጠናከር2.የተለያዩ ወቅታዊ መረጃዎችንናስልጠናዎችን መስጠት3.የገበያ ማስፋፋት ስራዎችንበመስራት ከተቀባዮች ጋር የገበያትስስር እንዲፈጥሩ ማድረግ

ንግድ ሚ/ር ፤የኢስወቴኢ፤ክልሎች

5

ረዥምና ሰፊ የድንበር ወሰን በመኖሩና ያንኑያህልም በቁጥር ለመገመት የሚያስቸግሩየኮንትሮባንድ መውጫ በሮችመኖራቸው፣እነዚህንም መውጫ በሮችንለመቆጣጠር በሰው ኃይልም ሆነ በሎጅስቲክለማጠናከር አቅምና ጊዜ ወሳጅ በመሆኑ

በየአካባቢው ያለው የፀረ-ኮንትሮባንድጥምር ኮሚቴ በማጠናከርና እንደ አካባቢውመልካምድር አቀማመጥ አስቸጋሪነትናስፋት አንጻር የሰው ሓይልና የሎጅስቲክአቅርቦትና ተሻከርካሪ በማቅረብ ከፍተኛክትትልና ቁጥጥር በማድረግ የኮንትሮባንድመውጫ በሮችን በመቆጣጠር ህግንማስከበር

1.የሰው ኃይል የሎጅስቲክናየተሸከርካሪ አቅርቦት ማሟላትናጠንከር ያለ ቁጥጥር ክትትል ማድረግ2.ለጠቋሚዎቸ የህግ ከለላ በማድረግለጠቋሚና ያዥ የሚከፈለውን አበልማሻሻል(60 ፐርሰንት)3.ጥናት ተደርጎ በተመረጡ መውጫበሮች አስፈላጊ መሰረተልማቶችንበማሟላት የመቆጣጠሪያ ጣቢያዎችንማቋቋም(ሺንፋና ሳንጃ)

ገቢዎችናጉምሩክ፤ክልሎች

6

በጠረፍ አካባቢዎች የሚገኙ ገበያዎች የሚገኙበትቦታ ለጎረቤት አገሮች በጣም ቅርብ እና ደረጃቸውተጠብቆ የተገነቡ አለመሆናቸው ለአብነትምየሞያሌ (40ሜትር) የሁመራና ና የመተማ ገበያቦታዎች የሚገኝበት ስፍራ ለጠረፍ በጣም የቀረበእና በ15 ኪ.ሜ ክልል ውስጥ በመሆናቸውለክትትልና ቁጥጥር አመቺ አለመሆናቸው

በሞያሌም ሆነ በሌሎች ጠረፍ አካባቢዎችየሚገነቡት የቁም እንስሳት መሰረተልማቶች (ገበያ ማዕከላት) ጥናትን መሰረትባደረገ መልኩ ከጠረፍ አካባቢዎች ራቅብለው ምቹና የእንስሳት ክምችትን ግንዛቤውስጥ በማስገባት ደረጃቸውን ጠብቀውእንዲገነቡ ማድረግ፡፡

1.ነባርና አዳዲስ የሚገነቡ የገበያማዕከላት ከድንበር 30 ኪ.ሜ ርቀትላይ እንዲገነቡ ማድረግ2.ነባሮችም ሆኑ አዳዲስ የሚገነቡገበያዎች የውስጥ መሰረተ ልማቶችደረጃቸውን እንዲጠብቁ ማድረግ(መተማ፤ሞያሌ፤ቶጎውጫሌ፤ሁመራ)

ክልሎች፤ግብርና፤

Page 29: 147 (repaired)(1)

የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት Page 5

7

የእንስሳት ዝውውርና እንቅስቃሴ በሚመለከትበሀገሪቱ ስርዓቱ ገና ባለመጀመሩ ምክንያትየሚገድብ የህግ ማዕቀፍ ባለመኖሩ ህገ ወጥነጋዴዎች ያለ ገደብ ስለሚንቀሳቀሱ በተለይምለህገ ወጡ ንግድ ሁኔታዎች የተመቻቸመሆናቸው

ተጀምሮ በሂደት ላይ የሚገኘውን የቁምእንስሳት የግብይት ስርዓትንና የህግማዕቀፎችን ከወዲሁ በማጠናቀቅና የህግመሰረት እንዲኖራቸው በማድረግ ህገወጡን የቁም እንስሳት ዝውውር ስርዓትእንዲይዝ ማድረግ

1.የተጀመረው የግብይት ስርዓቱንማጠናቀቅ2..የእንስሳት ዝውውርን በተመለከተመመሪያ ማውጣት3.ከላይ እስከ አምራቹ ድረስ ላሉትተዋንያን ግንዛቤ ማስጨበጥ4.አፈጻጸሙን መከታተል

ንግድ ሚ/ር፤ክልሎች ፤ግብርና፤ገቢዎችናጉምሩክ

8

የውጭ ዜጎች ፍቃድ ሳይኖራቸው እስከ መሀልአገር ዘልቆ በመግባት ለሀገር ውስጥ ዜጋ ብቻየተፈቀደውን ገበያ ውስጥ በመግባት እንስሳትንበቀጥታ በመግዛትና መርጦ በማስገዛት የግብይትስርዓት በማዛባት ላይ መሆናቸው

ለዜጎች የተፈቀደውን የአገር ውስጥ ገበያየውጭ ዜጎች ገብተው የግብይት ስርዓቱንእንዳያዛቡ በሚል ከዚህ ቀደም በግ/ሚየተላለፈው መመሪያ ተግባራዊ በማድረግአፈጻጸሙን መከታተል

1.ከዚህ በፊት የውጭ ዜጎችንበተመለከተ የተዘጋጀው መመሪያበማውረድ ለፈጻሚና ለአስፈጻሚአካላት ግንዛቤ በማስጨበጥአፈጻጸሙን መከታተል

የውጭ ጉዳይሚ/ር፤ፌደራልጉዳዮች፤ክልሎች

9

ከንግድ ሚኒስቴር ሀጋዊ የንግድ ፈቃድለማውጣትና ለማደስ ቀልጣፋ ባለመሆኑ ጊዜናተጨማሪ ወጪ በመጠየቁ እና ሚጠይቀውካፒታል ከፍተኛ በመሆኑ ነጋዴዎች ህጋዊ ፈቃድአውጥተው ከመንቀሳቀስ ይልቅ ወደ ህገ ወጥንግድ ሊቀላቀሉ እንደሚችሉ

በንግድ ሚኒስቴር ያለውን የቁም እንስሳትየወጪ ንግድ የፈቃድ አሰጣጥ ሂደትበመፈተሸ የተንዛዙ አሰራሮችንእንዲስተካከል ማድረግ

1.የወጪ ንግድ ፈቃድ አሰጣጥበውክልና በክልሎች ወይም አማካይበሚሆኑ ቦታዎች እንዲሰጥ2.ለእንስሳት ወጪ ንግድ የሚታየውካፒታል መጠን የላኪዎችን አቅምያገናዘበ ቢሆን

ንግድ ሚ/ር

10

በአንዳንድ አካባቢዎች የጸረ ኮንትሮባንድ ኮሚቴከክልል ጀምሮ በተዋረድ የህገ ወጡን ንግድለመቆጣጠርን ለህብረተሰቡ የህገ ወጡን ንግድበሀገር ኢኮኖሚ ላይ የሚያስከትለውን ተጽዕኖግንዛቤ በማስጨበጥ ዙርያ በቅንጅት ያለመንቀሳቀስክፍተቶች ይታያሉ ለአብነት በቦረና እና በሊበንዞኖች በተለይም ሞያሌ ወረዳ

የፀረ-ኮንትሮባንድ ጥምር ኮሚቴው ከክልልበተዋረድ እስከ ቀበሌ ያለው ተግባራዊሊሆኑ የሚችሉ የኮንትሮባንዱን ለመከላከልየሚያግዙ ተግባራትን በማቀድ ተጠናክሮእንዲቀጥል ማድረግ እና በሂደት በሚከሰቱችግሮች እልባት መስጠት

1.የጸረ-ኮንትሮባንድ ኮሚቴየሚመራበት መመሪያ እንዲኖርማድረግ2. የክልል መስተዳድር አካላት (ከክልልእስከ ቀበሌ) ስራውን በሐላፊነት የእኔጉዳይ ነው ብሎ በቁርጠኝነትእንዲከታተልና እንዲመራው የጋራየውይይት መድረክ በመፍጠር3..ዝርዝር ተግባራትን ማቀድናበተዋረድ እንዲያውቁት ማድረግ

ገቢዎችና ጉምሩክ፤ክልሎች፤ንግድሚ/ር

Page 30: 147 (repaired)(1)

የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት Page 6

11

እንስት እንስሳትና ጥጃ እንዲሁም የውጭ ዝርያያላቸው እንስሳት አወጣጥና እገዳ በተመለከተግልጽና የማያሻማ በጽሁፍ የተዘጋጀ መመሪያያለመኖር

በእንስት የቀንድ ከብት ፤ጥጃ እና የወጭዝርያ ያላቸው እንስሳት አወጣጥ ዙርያግልጽና የማያሻማ ገላጭ የሆነ መመሪያእንዲኖር ማድረግ

1.ግልጽ የሆነ መመሪያ በማዘጋጀትማሰራጨት2.አፈጻጸሙን መከታተል

ግብርና ሚ/ር

12

የጠረፍ አካባቢ ህብረተሰብ ኮንትሮባንድ ንግድበህገሪቱ ኢኮኖሚና ደህንነት እንዲሁም ማህበራዊኑሮ እና በህጋዊ መንገድ በሚንቀሳቀሰው ነጋዴላይ የሚያሳድረውን ተጽኖ የግንዛቤ ችግር መኖሩናለገበያ አማራጭና ለተሻለ ዋጋ በህገ ወጡ ንግድመሳተፍና ተባባሪ መሆን

የሀገር ሽማግሌዎችና የጎሳ መሪዎችናህብረተሰቡ ስለ ኮንትሮባንድ ንግድ በሀገርኢኮኖሚና በህጋዊ ንግዱ ላይየሚያደርሰውን ተጽዕኖ እና በህጋዊ መልክየሚከናወነው የንግድ እንቅስቃሴ ያለውጠቀሜታ ግንዛቤ ማስጨበጥ

1.ተሰሚነት ያላቸው የሀገርሽማግሌዎችና የጎሳ መሪዎቸ የጸረ-ኮንትሮባንዱ ኮሚቴ አባል እንዲሆኑማድረግ2.ተከታታይነት ያለው ስልጠናበመስጠት ግንዛቤ ማስጨበጥ

ክልሎች

13

በሀገሪቱ ደረጃቸውን የጠበቁ የቁም እንስሳትኳራንቲንና ኢንስፔክሽን እንዲሁም እንስሳት ቼክፖስቶች እንዲሁም የእንስሳት የማቆያ ቦታያለመኖር

ደረጃቸውን የጠበቁ የኳራንቲን ጣቢያዎችናቼክ ፖስቶች የእንስሳት አቅርቦትን ክልሉንበአማካለ መልኩ በተጠኑ ቦታዎች ላይመገንባትና ማጠናከር

1.በሱማሌ ክልል እና ቦረና ዞንደረጃውን የጠበቀ ኳራንቲንና ቼክፖስት ማቋቋም2.በሁመራ፤በመተማ፤በቦረና ዞን፤ጅጅጋእና ድሬደዋ ላይ ደረጃውን የጠበቀእንስሳት ማቆያ ቢሰራ

ግብርና ሚ/ር

14

ለኤክስፖርት የተዘጋጁ እንስሳት የጆሮ መለያቁጥር አሰጣጥ ወጥ አለመሆንና በተቆጣጣሪውአካል የተሰጠው ቁጥር በማንኛውም ቦታ የመቀርናየመለወጥ ዕድሉ ከፍተኛ መሆኑ

የወጪ እንስሳት የመለያ ቁጥር(ኢር ታግ)በሚስጢር ኮድ ተሰጥቶት በሀገር መከላከያሚ/ር ተዘጋጅቶ ለቁጥጥር በሚያመችመልኩ በስራ ላይ እንዲውል ማድረግ

የሀገሪቱን የቁም እንስሳት የወጪንግድ ዕቅድን በአማከለ መጠን ኢርታግ እንዲዘጋጅ ቢደረግ

ግብርና ሚ/ር

15

በዘርፉ ልማትና ግብይት ዙርያ በሚመለከታቸውፌደራል መ/ቤቶች የሚሰጡት እገዛ ፤ክትትልናቁጥጥር አነስተኛ መሆን

በተለያዩ ሴክተር መ/ቤቶች መካከልያለውን የህግ ክፍተትና በቅንጅት ያለመስራት ችግርን ለመቅረፍ የጋራመድረኮችን መፍጠር

የጋራ ዕቅድ በማዘጋጀት የዕቅዱንተግባራዊነት የሚከታተል ናየሚገመግም አካል (ጥምርኮሚቴ)ማቋቋም

ፌደራልመ/ቤቶች፤ክልሎች

Page 31: 147 (repaired)(1)

የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት Page 7

ዋቢ ድርጅቶች

1. የድሬደዋ ኳራንቲን

2. የገቢዎችና ጉምሩክ ድሬደዋ ቅርንጫፍ

3. የሽንሌ ዞን አስተዳደር ም/ቤት

4. የባቢሌ ወረዳ ማዘጋጃ ቤት

5. የባቢሌ ወረዳ አስተዳደርና የገጠር ልማት ጽ/ቤት

6. የጅጅጋ ኳራንቲን

7. የገቢዎችና ጉምሩክ ጅጅጋ ቅርንጫፍ

8. የሱማሌ ክልል ንግድና ትራንስፖርት

9. የጅጅጋ አካባቢ የቁም እንስሳት ላኪዎች

10. የአፋር ክልል አስተዳደር ም/ቤት

11. የገቢዎችና ጉምሩክ ሚሌ ቅርንጫፍ

12.መቀሌ ክልል አስተዳደር

13. የመቀሌ ክልል ንግድ ቢሮ

14. የገቢዎችና ጉምሩክ መቀሌ ቅርንጫፍ

15. ሁመራ ገቢዎችና ጉምሩክ መቅረጫ

16. የሁመራ አስተዳደር፤ንግድና እንዱስትሪ፤ግብርና፤ኳራንቲን፤መከላከያ፤ፌደራል ፖሊስ

17.መተማ አስተዳደር ፤ንግድና ትራንስፖርት፤ገንዳ ውሀ ገቢዎችና ጉምሩክቅርንጫፍ፤ኳራንቲን፤ገቢዎችና ጉምሩክ መተማ ዮሃንስ መቅረጫ ጣቢያ

18. አማራ ክልል ንግድና ትራንስፖርት፤ግብርና ቢሮ፤የእንስሳት ሀብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ ፤ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ባህርዳር ቅርንጫፍ

19. የቁም እንስሳት ላኪዎች ማህበር(አዳማ)

20. አዳማ ኳራንቲን

21. ያቬሎ አስተዳደር፤ሞያሌ ገቢዎችና ጉምሩክ ቅርንጫፍ፤ፌደራል ፖሊስ

Page 32: 147 (repaired)(1)

የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት Page 8

ዋቢ መጽሃፍት

1. Elisabeth Farmer may 2010 End Market analysis of Ethiopian LiveStock and Meat

2. Ayele Solomon, Assegid Workalemahu, M.A. Jabbar M.M. Ahmed and Belachew

Hurissa, 2003, Livestock marketing in Ethiopia: a review of Structure, performance

and development initiatives

3. Nisar Majid, September, 2010, Livestock Trade in the Djibouti, Somali and Ethiopian

Borderlands

4. IPMS/ILRI ,2007 ,Analysis of the Ethio-Sudan cross-border cattle trade: The case

of Amhara Regional State

5. UNDP ,2007,Livestock Marketing and Cross Border Trade in the Southeast of

Ethiopia

6. የእንስሳት ገበያ ባለስልጣን,2003,በደቡብ በደቡብ ምስራቅ ኢትዮጵያ ህገወጥ የቁም እንስሳት

መንስኤዎች ጥናትና ሪፖርት

D MARKET ANALYSIS OF1. ETHIOPIAN LIVESTOCK

AND MEATEND MARKETANALYSIS OF

ETHIOPIAN LI

Page 33: 147 (repaired)(1)

የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት Page 9

በአማራ ክልል፤በትግራይ ክልል፣ በአፋር ክልል፣ በሱማሌ ክልል እና በኦሮሚያ ክልልበቦረና ዞን አካባቢ በተደረገው የህገ ወጥ የቁም እንስሳት ንግድ እንቅስቃሴን በተመለከተበተደረገው ጥናት እና የጥናት ሪፖርት ላይ የተሳተፉ አባላት ዝርዝር

1. አቶ ሙሠማ ፈረጃ (አስተባባሪ) ከኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት

2. ዶ/ር በቀለ ዲማ ከንግድ ሚኒስቴር

3. ዶ/ር ኤልያስ ደሴ ከግብርና ሚኒስቴር

4. ኮሎኔል በርሀ ካሳ ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን

VESTOCK AND MEATENDMARKET ANALYSISOFTHIOPIAN LIVESTOCK ANDMEAT