Upload
others
View
8
Download
0
Embed Size (px)
Citation preview
ydb#B B/@éC½ B/@rsïCÂ ?ZïC KLL mNGSTdb#B nU¶T Uz@È
DEBUB NEGARIT GAZETA OF THEFEDERAL DEMOCRATIC REPUBLIC OF ETHIOPIA
bdb#B B/@éC½ B/@rsïCÂ?ZïC KLል Mክር b@T
-ÆqEnT ywÈ ደንብ
በደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት
የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ካውንስል ማቋቋሚያ ደንብ ቁጥር 97/2004
ደንብ ቁጥር 46/1998በደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ
መንግስት ምክር ቤት
የጤና አገልግሎት አሰጣጥና አስተዳደር ደንብ
Regulation No 46/2005
Health Service Delivery, Administration and
Management Regulation of the Southern
Nations, Nationalities and People Regional
Government
የሀገሪቱን የጤና ፖሊሲ ተግባራዊ ለማድረግና
የክልሉም የቴና አገልግሎ አሰጣጥ ደረጃውን
የጠበቀና በሥርዓት የሚመራ እንዲሆን
ለማስቻል የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች
ክልላዊ መንግሥት የጤና አገልግሎ አሰጣጥና
አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 84/1996 ማጽደቁ
ይታወሳል፡፡ ይህንንም አዋጅ ለማስፈጸም ይረዳ
ዘንድ ደንብ ማዘጋጀት አስፈላጊ ስለሆነ የደቡብ
ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ
መንግስት ምክር ቤት በክልሉ መንግስት የጤና
አገልግሎት አሰጣጥና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር
In order to implement the country’s health policy
and to enable the provision of health services in
the Southern Nations, Nationalities and Peoples
regional state have certain standards and systems,
the regional council has proclaimed health service
delivery and administration proclamation, No.
84/2004. For the proper implementation of this
proclamation, it has become necessary to issue a
regulation; and hence the Council of the SNNP
Regional Government in accordance with powers
vested in it by Article 22 sub articles 1 of SNNP
Regional Government Health Service Delivery,
((((( Year No ---------Hawassa, 1st Dec. 2005
17/2011
፲፰ ›mT q$_R ----- ሀዋሳህዳር ፳፪ ቀን ፲፱፻፺፰ ዓ.ም
Page 1993 of 2280
84/1996 አንቀጽ 22 ንዑስ አንቀጽ፩ ሥር
በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህን ደንብ
አውጥቷል፡፡
1. አጭር ርዕስ
ይህ ደንብ "የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና
ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት የጤና
አገልግሎ አሰጣጥና አስተዳደር ደንብ ቁጥር
46/1998" ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡
2. ትርጉም
የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው
ካልሆነ በስተቀር በዚህ ደንብ ውስጥ፡
1. "ገቢ" ማለት ሆስፒታሎችና ጤና
ጣቢያዎች ከሚሰጧቸው ማናቸውም
የጤና አገልግሎቶች፣ የመድኃኒት
ሽያጭና ከሌሎች አገልግሎቶችና ዕቃዎች
ሽያጭ የሚገኝ ገቢ እንዲሁም በዓይነትም
ሆነ ነጥሬ ገንዘብ የሚገኝ እርዳታ ነው፣
2. "ሶስተኛ ወገን" ማለት የአገልግሎት
ተጠቃዎችን ወጪ /በኢንሹራንስም ሆነ
በሌላ መልክ/ የሚሸፍን የግል ወይም
የመንግሥት አካል ማለት ነው፡፡
3. "የጤና አገልግሎት" ማለት የበሽታ
መከላከልን፣ ቁጥጥርን፣ ተላላፊ
በሽታዎች ቅኝትን፣ የአካል፣ የላቦራቶሪ፣
የራጅና ሌሎች ጤና ነክ አጠባበቅ
ምርቶችን ያጠቃልላል፡፡
Administration and Management Proclamation
No. 84/2004 has issued this regulation.
1. Short title
This regulation may be cited as the “Heath
Service Delivery, Administration and
Management Regulation of the Southern
Nations, Nationalities and Peoples regional
Government No 46/2005
2. Definitions
Unless the context requires otherwise in this
regulation
a. “Revenue” means all revenue accruing to
health institutions from health services they
render sales of drug, other goods and
services and donations they obtain in cash or
in kind;
b. “Third Party” means public or private
organization which finances expenses of
beneficiaries of diseases, monitoring of
contagious diseases, physical, laboratory, x-
ray and other schemes;
c. “Health Service” means prevention and
control of diseases, monitoring of
contagious diseases, physical, laboratory, x-
ray and other health examinations and
curative treatment and includes
dissemination of health care education;
Page 1994 of 2280
4. "ነፃ ህክምና" ማለት ወጪው አግባብ
ባለው የመንግሥት ወይም በሌላ አካል
ተሸፍኖ የመክፈል አቅም ለሌላቸው ዜጎች
የሚሰጥ የጤና አገልግሎት ነው፡፡
5. "ክፍያ የማይጠየቅበት የጤና አገልግሎት"
ማለት የኅብረተሰቡን የጤና አጠባበቅ
ልምድ ከማሳደግ እንዲሁም በሕዝብ ጤና
አጠባበቅ ጉልህ ሚና ያላቸውን የጤና
አገልግሎቶች ከመስጠት ጋር በተያያዘ
ለሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል ያለክፍያ
የሚሰጥ አገልግሎት ነው፣
6. "አዋጅ" ማለት የደ/ብ/ብ/ሕ ክልላዊ
መንግሥት የጤና አገልግሎት አሰጣጥና
አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 84/1996 ነው፣
7. "ወጪን የሚሸፍን አካል" ማለት
የመክፈል አቅም ለሌላቸው ወይም
ለሌሎች የኅብረተሰብ ክፍሎች
የሚወጣውን የጤና ወጪ የሚሸፍን
አካል ማለት ነው፣
8. "ጤና ቢሮ" ማለት እንደ አግባቡ
የደ/ብ/ብ/ሕ ክልላዊ መንግሥት የጤና
ቢሮና በሥሩ በየደረጃው በሚገኙ
d. “Fee waiver” means provision of health
service free of charge to persons who can
not afford payment because of low income,
whose costs are covered by appropriate
public body;
e. “Exempted Services” means health services
provided free of charge to all irrespective of
level of income by reason of them being of
public health nature that widely affect the
general public and improving the health
seeking behavior of the society,
f. “Proclamation” Shall mean the SNNP
Regional Government Health Services
Delivery, Administration and Management
Proclamation No. 84/2004
g. “Agency Financing Health Expenses’ ” shall
mean any administrative body, which by
appropriation budget, covers the medical
expenditure of patients or patients who
cannot afford to pay.
h. “Bureau” shall mean a governing body
established pursuant to Article 7 of the
SNNP Regional Government Health Bureau
Page 1995 of 2280
የአስተዳደር እርከኖች ያሉትን የጤና
መምሪያዎችንና ጽ/ቤት የሚያጠቃልል
ነው፡፡
9. "የሆስፒታል የሥራ አመራር ቦርድ"
ማለት ሆስፒታሎችን በበላይነት
የሚያስተዳድር የደ/ብ/ብ/ሕ ክልላዊ
መንግሥት የጤና አገልግሎት አሰጣጥና
አሰተዳደር እርከኖች ያሉትን የጤና
መምሪያዎችንና ጽ/ቤትን የሚያጠቃልል
ነው፡፡
፲. "ሕክምና ነክ ያልሆኑ አገልግሎቶች"
ማለት በአንቀጽ ፪ በንዑስ አንቀጽ ፫
ከተጠቀሱት አገልግሎቶች ውጭ በሌላ
አካል ሊሰጡ የሚችሉ አገልግሎቶች
ማለት ነው፡፡
፲፩. "ሌላ ወገን" ማለት የግል፣ የመንግሥት
ወይም መንግስታዊ ያልሆነ አካል ሆኖ
ህክምና ነክ ያልሆኑ አገልግሎቶችን
ኮንትራት በመውሰድ የሚያንቀሳቅስ አካል
ነው፡፡
፲፪. "የግል ሕክምና መስጫ ዩኒት" ማለት
ከሆስፒታሎች መደበኛ የሕክምና
አገልግሎት ጎን ለጎን በሆስፒታሉ
የሚቋቋም ለተመላላሽ ወይም ተኝገው
ለሚታከሙ ታካሚዎች የሕክምና
የአገልግሎት የሚጥበት ዩኒት ነው፣
and institutions under the Bureau;
i. “Board” Shall mean a governing body
established pursuant to Article 7 of the
SNNP Regional Government Health
Services Delivery, Administration and
Management Proclamation No 84/2004 to
oversee the operation of a particular
Hospital;
j. “Non-clinical Services” Shall mean Services
other than those listed under Article 2 Sub-
article C3 of this regulation which is to be
out sourced to other parties.
k. “Other Party” shall mean Private,
government or non-governmental
organization or institution other than the
Bureau and the Hospital;
l. “Private wing” Shall mean a unit established
in the public hospital in addition to the
general ward providing inpatient and/or
outpatient health services;
Page 1996 of 2280
፲፫."የሆስፒታል ስራ አመራር" ማለት የሆስፒ
ታሉን አጠቃላይና የዕለት ተዕለት ተግባር
በበላይነት የሚያስተዳድር አካል ነው፣
፲፬. "ተራፊ ሂሳብ" ማለት የእርጅና ቅናሽን
ጨምሮ ቀጥተኛ ወጪዎች ተቀንሰው
የሚቀረው ሂሳብ ነው፣
፲፭. በዚህ ደንብ ውስጥ ያልተካተቱ ዋና ዋና
ቃላቶችና ሀገጎች በአዋጁ የተሰጣቸው
ትርጉም ይኖራቸዋል፡፡
3. ዓላማዎች
1. ዋና ዓላማ
በክልሉ መሠረታዊ የጤና አገልግሎትን
ለማስፋፋትና ለማጠናከር እንዲሁም
ፍትሃዊና ጥራቱ የተሻሻለ ለማድረግ
እንዲቻል ሀብት በማፍራትና ወጪን
በመጋራት ላይ የተመሰረተ ቀልጣፋና ዘላቂ
የጤና አገልግሎ ሥርዓትን መዘርጋት ነው፡
፡
2. ዝርዝር ዓላማዎች
1. ሆስፒታሎችና ጤና ጣቢያዎች ገቢያቸውን
ከመንግሥት ከሚመደ ብላቸው በጀት
በተጨማሪ እንዲጠ ቀሙ በማድረግ
የተቋማቱን የጤና አገልግሎ ጥራት
ማሻሻል፣
m.“Hospital Management” shall mean the
governing body of a hospital overseeing the
day-to-day operations of the hospital;
n. “Surplus” shall mean the revenue of the
private wing net of direct operational costs
including depreciation;
o. Terms not defined in this Regulation shall
have the meaning assigned to them in the
Proclamation.
3. Objectives
1. General Objectives
Expand equitable and quality basic health
Service delivery system and provide efficient
and sustainable health services based on cost
sharing and income generating schemes in the
region.
2. Specific Objectives
1. Enable health facilities to use their retained
income, in addition to the block budget
apportioned by the government, for better
health service delivery.
Page 1997 of 2280
2. የነፃ ሕክምናና ያለክፍያ የሚሰጡ የጤና
አገልግሎቶች አሰጣጥ ሥርዓ ቱን
በማሻሻል እንዲሁም የጤና አገልግሎትና
የወጪ አሸፋፈንን በመለያየት ሠርዓቱን
ፍትሐዊና ዘለቄታዊ ማድረግ፣
3. የሆስፒታሎችን አመራርና አሠራት
በማሻሻል አገልግሎታቸው የተቀላጠ ፈና
ቀስ በቀስ በገቢያቸው የሚተዳ ደሩ
በማድረግ የመንግሥት አቅጣጫ ወደ
መሠረታዊና መከላከል ላይ እንዲያተኩር
ማድረግ፣
4.በልዩ ልዩ ሕክምና ነክ ያልሆኑ ሥራዎች
የተሻለ ልምድና ችሎታ ያላቸው
የመንግሥት፣ የግልና መንግሥታዊ
ያልሆኑ ድርጅቶች በኮንትራት በማሠራት
ሆስፒታሎች በሕክምና ሥራዎች ላይ
እንዲያተኩሩ ማድረግ፣
5.ሆስፒታሎች የግል ሕክምና አገልግሎት
መስጫ ዩኒት የሚያቋ ቁሙበትን ስርዓት
በመዘርጋት የባለሙያዎችን ፍልሰት
መቀነስ፣ ለታካሚዎች አማራጭ የህክምና
አገልግሎት መስጠትና ተጨማሪ ገቢ
የሚያገኙበትን ሁኔታ መፍጠር፤
2. Make equitable and sustainable waiver and
exempted health service system in order to
improve the health service delivery system
3. Improve the management of hospitals and
make their services efficient so that
hospitals gradually create adequate
resources that will help them operate
independently and thus government could
concentrate on basic and preventive health
services.
4. Enable hospitals use their full time and
energy on clinical services only there by
outsourcing non-clinical services to
government, private and non- government
organizations which have better experience
and capacity on the field.
5. Lay down a system where by hospitals
establish private wings in order to reduce
the outflow of health personnel, provide
alternative choices of health services to
patients and create conditions where
hospitals could generate additional revenue.
Page 1998 of 2280
ክፍል አንድ
የሆስፒታሎችና የጤና ጣቢያዎች የገቢ
አጠቃቀም
4.የገቢ ምንጭ
1. ሆስፒታሎች/የጤና ጣቢያዎች ገቢ
ከሚከተሉት እና መሰል ምንጮች የሚገኝ
ሊሆን ይችላል፡፡
ሀ/የሆስፒታሎችና የጤና ጣቢያዎ ች
ዋንኛው ገቢ መንግሥት በየዓመቱ
በጥቅል የሚመድበት በጀት ይሆናል፡፡
ለ/ ከጤና፣ ከተለያዩ ዲያግኖስቲክ ከመኝታና
ከሕክምና አገልግ ሎቶች ክፍያ፣
ሐ/ ከመድኃኒትና አላቂ የሕክምና መገልገያ
ዕቃዎች ሽያጭ፣
መ/ ከነፃ ሕክምናና ከጤና ኢንሹ ራንስ ጋር
በተያያዘ ከሶስተኛ ወገን ከሚበሰብ ገቢ፣
ሠ/ ሆስፒታሎች ከሚሰጡት የማማከር፣
የሥልጠናና የምርምር አገልግሎ፣
ረ/ ጤና ነክ ካልሆኑ ሌሎች ዕቃዎችና
አገልግሎቶች፣
Part One
Revenue Utilization of Hospitals and Health
centers
4. Sources of revenue
Source of revenue of hospitals/health centers
may include the following :
1. The Major source of revenue for hospitals
and health centers shall be the Block
budget appropriated by the government.
2. Fees collected from health care and
diagnostic services and other services
related with medical treatment;
3. Sale of drugs and medical supplies,
4. Revenue collected from third parties in
connection with waiver and health
insurance schemes.
5. Fees collected from consultancy training
and research activities carried out by the
hospital/health center;
6. Income from non-medical services and
Page 1999 of 2280
ሰ/ በዓይነትም ሆነ በገንዘብ ከለጋሾች የተገኘ
ቀጥተኛ እርዳታ፡፡
5. የገቢ አሰባሰብ
1. የሆስፒታሎች/ጤና ጣቢያዎች ገቢ
የሚሰበሰበው በክልሉ መንግሥት
የፋይናንስ አስተዳደር አዋጅና ደንብ
ስለገቢ አሰባሰብ የተደነገገውን በመከተል
ይሆናል፡፡
2. ማንኛውም የሆስፒታል/ጤና ጣቢያ ገቢ
የሚበሰበው በፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት
ቢሮ ለዚህ አገልግሎት በሚያሳትመው
ደረሰኝ ብቻ ነው፣
3. ሆስፒታሎችና ጤና ጣቢያዎች
የሚያገኙት ገቢ በጤና አገልግሎት
ተቋሙስም በተከፈተ መደቡ "A" በሆነ
ልዩ የባንክ አካውንት ውስጥ ይቀመጣል፡፡
4. ማናቸውም ሆስፒታል/ጤና ጣቢያ
የሰበሰበውን ገቢ የመንግሥት የሂሳብ
አያያዝ ሥርዓት በመከተል መዝግቦ
በየወሩ ለፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ
ሪፖርት ማድረግ አለበት፣
5. ማንኛውም ሆስፒታል/ጤና ጣቢያ
የአገልግሎቶችን ክፍያ የሚያስከፍለው
goods;
7. Direct donations in cash or in kind.
5. Collection of Revenue\
1. Collection of revenue of hospitals/health
centers hall only be made in accordance with
the rules laid down in the Regional
government Financial Administration
Proclamation and Regulations issued there
under;
2. Revenues of hospitals/health centers shall
only be collected using the Revenue
Receipt of the Finance and Economic
Development Coordination Bureau;
3. Revenues of Hospitals/Health centers shall
only put in a Bank account A Kept under
the name of the facility.
4. Hospitals/health centers shall record the
revenue collected from such sources in
accordance with government accounting
procedures and report the same monthly to
the finance and Economic Development
Coordination Bureau.
5. Hospitals/health centers shall only require
Page 2000 of 2280
በቢሮው የተወሰነውን መሠረት በማድረግ
ብቻ ይሆናል፣ ዝርዝሩ በመመሪያ
ይወሰናል፡፡
6. ከሶስተኛ ወገን የሚሰበሰብ ገቢ በቢሮው
በሚወጣ መመሪያ መሠረት ይሆናል፡፡
7. ማንኛውም ሆስፒታል/ጤና ጣቢያ ገቢ
ለመሰብሰብ፣ በአግባቡ መረጃ ለመያዝና
ለመጠቀም የሚያስችል አቅም መገንባት
አለበት፡፡
6. የገቢ አጠቃቀም
1. ሆስፒታሎችና ጤና ጣቢያዎች ከመንግ
ሥት በጥቅል የሚያገኙትንና የሚሰበስ
ቡትን ገቢ በበጀት ዓመቱ ያሳውጃሉ፣
2. የሆስፒታሉ/የጤና ጣቢያው በጀት
ዓጠቃቀም በሆስፒታል ቦርድ/በጤና
ጣቢያው የስራ ዓመራር በጸደቀው
አመታዊ ዕቅድ መሰረት ይሆናል፡፡
3. ሆስፒታሎች/ጤና ጣቢያዎች ገቢያቸውን
ጤና ቢሮው የሚያወጣውን መመሪያ፣
ሊኖራቸው የሚገባቸውን የአገልግሎት
ደረጃ እና የውስጥ አደረጃጀት መሠረት
በማድረግ ከዚህ ቀጥሎ ለተመለከቱት
ተግባራት ሊያውሉ ይችላሉ፡-
payment at the user fee and bypass fee and
bypass fee tares set by the Bureau.
Directive issued by the bureau will
determine details.
6. Collection of fees from third parties shall
be made in accordance with the directives
issued by the bureau.
7. Any hospital/health center shall build its
capacity to properly collect record, deposit
and make use of its revenue.
6. Utilization of revenue
1. Hospital/health centers shall proclaim the
revenue they collect and the block budget
allocated by the government every fiscal
budget year;
2. The Budget utilization of hospitals/health
centers shall be in accordance with the
ratified annual plan of the hospital’s
board/health enters management
committee.
3. The revenue of hospitals/health centers
shall only be utilized in accordance with
the directives issued by the bureau to meet
the health facilities’ requires standard and
avail the necessary manpower and medical
equipment, That is to :
Page 2001 of 2280
ሀ/ በሕሙማን አላላክና አቀባበል ሥርዓት
ውስጥ የጤና ድርጅቱ ያለውን አቅም
ለማሳደግ ፣
ለ/ የመድኃኒትና የሌሎች የሕክምና
መገልገያ መሣሪያዎችንና ቁሳቁሶችን
አቅርቦት ለማሻሻል፣
ሐ/ በጤና ተቋሙ የሚሰጡ አገልግ ሎቶችን
ለማስፋፋት የሚረዱ ግዥዎችንና
ግንባታዎችን ለመፈፀም፣
መ/ የጤና ድርጅቱን መረጃ አያያዝ ስርዓት
እና ሌሎች የአሠራር ሥርዓቶችን
ለማሻሻል፣
ሠ/ የጤና ድርጅቱን ሠራተኞች ብቃትና
ውጤታማነት ለማሳደግ የስራ ላይ
ስልጠና ለመስጠትና ጤና ነክ
ምርምሮችን ለማካሄድ፣
ረ/ የጤና አጠባበቅ ትምህርትን በማጠናከር
በሽታዎችን የመከላከልና የመቆጣጠር
ተግባራትን ለማከናወን፡፡
ሰ/ ሌሎች በሆስፒታሉ /ቦርድ/የጤና ጣቢያ
የስራ አመራር የሚወስኑ ተግባራትን
ለማከናወን፡፡
4. በበጀት ዓመቱ መጨረሻ ሥራ ላይ ያልዋለ
በጀት በቀጣዩ የበጀት ዓመት ከሚፈቀደው
በጀት ጋር በተጨማሪነ ታውጆ ስራ ላይ
a. To improve the services provided under
the Referral system
b. To improve the supply of drugs, medical
equipment and supplies;
c. To improve procurement and carry out
construction works to improve the health
care services of the hospital;
d. To develop health care information
system and manuals and to improve
procedures;
e. To conduct on job raining programs and
other similar health related researches so
as to improve the efficiency and
productivity of employees in the
facilities;
f. To strengthen health education activities
and undertake disease control and
preventive activities.
g. To undertake other activities inline with
the objectives designated by the hospital
board and health centers management
committee;
4. The unutilized budget of the
hospitals/health centers in the budget year
shall be proclaimed and utilized in the
Page 2002 of 2280
ይውላል፡፡
5. የገቢ አጠቃቀም ዝርዝር በሚወጣው
መመሪያ ይወሰናል፡፡
7. በገቢ የማይሸፈኑ ወጪዎች
በዓንቀጽ ፮ ንዑስ አንቀጽ /፫/ ንዑስ አንቀጽ
የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ ሚከተሉት
ወጪዎች በገቢ ሊሸፈኑ አይችሉም፡፡
ሀ/ ማንኛውም የውጭ ሀገር ጉዞና ስልጠና
ለ/ ከሶስት ወራት በላይ የሀገር ውስጥ
የረጅም ጊዜ ስልጠና
ሐ/ ለሌላ አካል ተላልፈው የሚሰጡ የተለያዩ
ድጎማዎችና ስጦታዎች
መ/ ለአሽከርካሪዎች ትጥቅ
ሠ/ ለቋሚ የመንግስት ሰራተኞች ደመወዝ
ረ/ ለሌሎች በገቢ ለመጠቀም ከተቀመጡ
ዓላማዎች ውጭ የሆኑ ተግባራት፣
8. የወጪ አመዘጋገብ
1. የሆስፒታሎች/ጤና ጣቢያዎች የሰበሰቡትን
ገቢ የሆስፒታሎች የሥራ አመራር
ቦርዱ/የጤና ጣቢያው የስራ አመራር
ባፀደቀው የስራ ዕቅድ መሠረት ጥቅም ላይ
following budget year together with the
block budget appropriated to the next
budget year;
5. Details of revenue utilization shall be
determined in a directive.
7. Payments not allowed from retained
revenues
Without prejudice to the generality stated in
Article 6 sub article 3,g, the following
expenses shall not be covered from facilities’
revenue:
1. Any kind of foreign trip and training.
2. Long term domestic training programs
more than three months.
3. Any kind of subsidy given to the third
party.
4. Payments for hiring consultants.
5. Salary for permanent government
employees,
6. Revenue utilization other than those
activities, designed to meet the objectives
there in.
8. Recording of expenses
1. Hospitals/health centers shall utilize their
revenues in accordance with the ratified
work plan of the hospital management
Board/health center management and shall
Page 2003 of 2280
በማዋል ወጪውን በተገቢው የሂሳብ መደብ
ይመዘግባሉ፣
2. ሆስፒታሎች/ጤና ጣቢያ ከሰበሰቡት ገቢ
ላይ የሚፈጸሙ ክፍያዎች በተለያ መዝገብ
ተመዝግበው ይያዛል፣
3. ማናቸውም ሆስፒታል/ጤና ጣቢያ
የሰበሰበውን ገቢ ወጪ ሊያደርግ የሚችለው
የመንግሥትን የወጪ አፈፃፀም ሥርዓት
ተከትሎ መሆን አለበት፡፡
9. ሪፖርት አቀራረብ
1. ሆስፒታሎችና ጤና ጣቢያዎች መሪ
ዕቅድና ዓመታዊ መረጃ ዝርዝር ዕቅድ
ለቦርድ/ለጤና ጣቢያ ሥራ አመራር፣ ለጤና
ቢሮ እና ለፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ
ያቀርባሉ፡፡
2. ሆስፒታሎች/ጤና ጣቢያዎች የሥራ
ክንውንን፣ የገንዘብ አሰባሰብን፣
አጠቃቀምንና አያያዝን ያጋጠሙ
ችግሮችንና የተወሰዱ እርምጃዎችን
የሚያሳይ ሪፖርት ለቦርዱ/ለጤና ጣቢያው
ሥራ አመራር በየ3 (ሶስት) ወሩ ያቀርባሉ፡፡
3. ሆስፒታሉ/ጤና ጣቢያው የገንዘን አሰባሰብና
አጠቃቀም ሪፖትት ለጤና ቢሮው እና
ለፋይናንስና ኢኪኖሚ ልማት ቢሮ በየወሩ
ያቀርባሉ፡፡
0.. ...åÄåኦዲት
record expenses under appropriate code of
expenditure.
2. Payments of hospitals/health centers from
their retained revenues shall be recorded
separately.
3. Hospital/health centers shall follow
government disbursement procedures when
making payments out of their revenue.
9. Reporting
1. Hospitals/health centers shall prepare and
submit indicative and annual detailed
activity and financial plans to the
board/health centers management, health
bureau and Finance and Economic
Development Coordination Bureau.
2. Hospital/health centers shall submit
quarterly activity and revenue collection
and utilization report to the board/health
centre management every quarter together
with a report that states problems
encountered and measures taken.
3. Hospitals/health centers shall submit
monthly revenue collection and utilization
reports to both health bureau and Finance
and Economic Development Coordination
bureau.
Page 2004 of 2280
1. ሆስፒታሎች/ጤና ጣቢያዎች ገቢ
ለታለመለት ዓላማ መዋሉን ለማረጋገጥ
በሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት
ቁጥጥርና ክትትል ይደረግበታል፡፡
2. እያንዳንዱ በጥሬ ገንዘብም ሆነ በቼክ
የሚከፈል ወይም የሚሰበስብ ወጪና ገቢ
በሆስፒታሉ/ጤና ጣቢያዎ የውስጥ ኦዲተር
መመርመር የኖርበታል፡፡
3. የኦዲት ሪፖርቶች ለቦርዱ፣ ለጤና ቢሮ፣
ለፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ማስተባበሪያ
ቢሮና ለሌሎች ለሚመለከታቸወ አካላት
መድረስ አለባቸው፡፡
ክፍል ሁለት
በነፃ እና ክፍያ ሳይጠየቅ የሚጡ የጤና
አገልግሎቶች
01. የነፃ ህክምና አገልግሎት
1. የነጻ ሕክምና ማስረጃ እንዲሰጡ
የተፈቀደላቸው አካላት፣
1. የቀበሌ አስተዳደር ጽ/ቤት
2. የወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት
3. ማዘጋጃ ቤት/ከተማ አስተዳደር
2. የነፃ ሕክምና አገልግሎት ተጠቃሚዎች
የነጻ የህክምና አገልግሎት ማግኘት የሚችሉት፣
1. የመክፈል አቅም የሌላቸው ሆነው
ከወረዳና ከቀበሌ ጽ/ቤት የነፃ ህክምና
10. Audit
1. To verify whether the revenue of the
hospital/health center is used for designated
purposes the accounts shall be supervised
and monitored by the concerned bodies;
2. The internal auditor of the hospital/health
center shall audit every payment made in
cash or cheque and every revenue collected
by the hospital/health center;
3. Audit reports shall be submitted to the
board, the Health Bureau, Finance and
Economic Development Coordination
Bureau as well as to other appropriate
bodies.
Part Two
Waiver Scheme and Exempted Health
services
11. Waiver Scheme:
1. Authorities to issue waiver certificates
are:
1. Kebele Administration office
2. Woreda Administration office
3. Municipality/city Administration
2. Beneficiaries of Waiver Scheme
Beneficiaries of waiver scheme are the following
1. Persons who cannot afford to pay for
health services and thus provide evidence
Page 2005 of 2280
ማስረጃ የሚያቀርቡ
2. የጎዳና ተዳዳሪዎች ሆነው ከቀበሌ/ወረዳ/
ከተማ አስተዳደር ማስረጃ የሚያቀርቡ፣
3. በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ ምክንያቶች
ከመኖሪያ አካባቢያቸው ተፈናቅለው
ከቀበሌ/ወረዳ/ ከተማ አስተዳደርና
ከማዘጋጃ ቤት ማስረጃ የሚያቀርቡ፣
4. በጤና ተቋማት የ24 ሰዓት የድንገተኛ
አገልግሎ ተጠቃሚ ሆነው መክፈል
የማይችሉና ወይም ወጪ የሚሸፍን ሌላ
ተጠያቂ አካላ የሌላቸው ናቸው፡፡
3. የነጻ ሕክምና ማስረጃ የሚያገለግልበትጊዜ1. የነጻ ሕክምና ማስረጃ የሚያገለግለው
ማስረጃው ከተሰጠበት ጊዜ ጀምሮ
ለአንድ የበጀት ዓመት ብቻ ነው፡፡
2. የነፃ ሕክምና ማስረጃ የሚፀድቀው
በበጀት ዓመቱ መጀመሪያ ወር ነው፡፡
4. የነፃ ሕክምና ወጪ አሸፋፈን
1. ወረዳዎች በሥራቸው ለሚገኙ
መክፈል ለማይችሉ ነዋሪዎቻቸው
ዓመታዊ የጤና በጀት በመመደብ
ይይዛሉ፡፡
2. የወረዳው አስተዳደር የሚደርሰውን
ማስረጃ መሠረት በማድረግ
ታካሚው ላገኘው የሕክምና
አገልግሎት የተጠየቀውን ክፍያ
from the Kebele offices;
2. Street children who can provide evidence
from the Kebele/ Woreda/ City
administration.
3. The homeless and displaced persons when
they provide evidence from
Kebele/Woreda/City administration and
municipality.
4. Persons receiving 24 hours emergency
care provided by health institutions, who
can not afford to pay for the service, and
people with no third party accountable for
them
3. Validity of waiver certificate
1. The waiver certificate shall be valid only
for one budget year since from the date of
issuance.
2. The waiver certificate shall be endorsed
at the beginning of the budget year.
4. Financing waivers
1. Woredas shall appropriate health budget
quota that may be used to cover waivers.
2. The woreds/city administration shall on
the basis of supporting documents from
health facilities evidencing the cost of
health services provided to beneficiaries
Page 2006 of 2280
ይፈፅማል፣
3. ከሌሎች መንግስታዊና መንግስታዊ
ካልሆኑ ድርጅቶች የሚላኩ የነጻ
ታካሚዎች ወጪዎች በላኪው
ድርጅት ይፈጸማል፡፡
4.ከሌሎች ክልሎች የሚመጡ የነጻ
ታካሚዎች በቅብብሎሽ ስርዓቱ
መሠረት አገልግሎት እንዲያገኙ
ይደረጋል፡፡ የቅብብሎሽ ስርዓቱን
ሳይጠበቁ የሚመጡ ታካሚዎች
የመጣሻ ክፍያ ይከፍላሉ፣
5.ከሌሎች የክልሉ ወረዳዎች በቅብብሎሽ
ስርዓት የሚመጡ የነፃ ታካሚዎች
ወጪ አሸፋፈን ቢሮው በሚያወጣው
መመሪያ ይወሰናል፡፡
6.ከሌሎች ክልሎች የሚመጡ የነጻ
ታካሚዎችን ወጪ አሸፋፈን
በሚመለከት ከክልሎቹን ከፌ/ጤና
ጥበቃ ሚ/ር በሚወጣ መመሪያ
መሠረት ይወሰናል፡፡
7.ወጪውን የሚሸፍነው አካል ከጤና
አገልግሎት መስጫ ተቋማት ጋር
አገልግሎቱን ስለሚሰጡበት ሁኔታ
የውል ስምምነት ይፈጽማል፡፡
effect payment on account of health
budget appropriated to the kebeles under
it.
3. The cost of health services received by
persons certified by government or non
governmental organizations shall be
covered from the budget appropriated to
such public body;
4. Persons entitled to waivers coming from
other regions shall receive such services
in accordance with the referral system put
in place. Persons who infringe the referral
system shall pay the pass by fee.
5. The cost of covering waivers coming
from other regions’ woredas in
accordance with the referral system will
be determined by a directive issued by
the bureau.
6. Issues concerning financing of waivers
coming from other regions will be
determined according to a directive to be
issued under the Federal Ministry of
Health and Regional Government health
bureaus in the future.
7. The agency financing Health Expenses
shall conclude an agreement, with the
health institution, which specifies the
Page 2007 of 2280
8. የነፃ ሕክምና ወጪ የሚሸፈነው
በመንግስት የጤና ድርጅት
ለሚታሙት ብቻ ነው፡፡
5. የነፃ ሕክምና ተጠቃሚ እና አስፈፃሚ
ተግባርና ኃላፊነት
1. የህብረተሰብ የሥራ ድርሻ
ሀ/ የነጻ ህክምና ተጠቃሚ የሚሆኑ
ግለሰቦችን ለመለየት በሚደረገው
ሥራ ንቁተሳትፎ ማድረግ
ለ/ የነፃ ህክምና ማስረጃን በአግባቡ
መያዝና በአገልግሎት ጊዜ
ነዋሪዎች መታወቂያ እና ማስረጋ
ማሳየት፤
ሐ/ የተሰጠው የነጻ ህክምና ማስረጃ
ለሌላ አካል አሳልፎ አለመስጠት
2. የቀበሌ አስተዳደር ጽ/ቤት የሥራ
ድርሻ
ሀ/ በየበጀት ዓመቱ የነጻ ህክምና
አገልግሎት ማግኘት የሚባቸው
ነዋሪዎች ህብረተሰቡን በሳተፈ
መልኩ መለየት
ለ/ የነጻ ህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ
የተለዩት ነዋሪዎች ዝርዝር
ለወረዳ/ከተማ አስተዳደር መላክና
እንዲረጋገጥ ማድረግ
ሐ/ የቀበሌ ማህበራዊ ፍ/ቤት ከቀበሌው
type of service to be provided.
8. The cost of Waivers shall only becovered for those who get the healthservices from government healthfacilities.
5. Responsibility of waiver beneficiaries
and implementing bodies.
5.1.Responsibility of the community;
5.1.1. Participate actively in the screening
of persons eligible for waivers.
5.1.2. Keep the waiver certificate
appropriately and show it together
with residence identification card
when service is provided.
5.1.3. Waivers shall not give the waiver
certificate to the other bodies.
5.2.Responsibility of the kebele
administration.
5.2.1. Every budget year, kebele
administrations shall notify lists that
contain the names of people eligible
for fee waiver schemes.
5.2.2. The kebele administration shall send
the list of fee waivers to the
woreds/city administration and gets
it confirmed.
Page 2008 of 2280
አስተዳደር ጽ/ቤት በሚቀርበው የነፃ
ሕክምና ጥያቄ መሠረት የመጨረሻ
ውሳኔ ይሰጣል፡፡
መ/ የነጻ ሕክምና የተፈቀደለትን
ግለሰብ የኑሮ ደረጃ በየጊዜው
በመከታተል የመክፈል አቅም ያገኘ
ሆኖ ሲገኝ ይህንኑ ለወረዳው ከተማ
መስተዳድር ያስታውቃል አገልግሎ
ቱም እንዲቋረጥ ያደርጋል፡፡
3.የወረዳ ከተማ አስተዳደር የሥራ
ድርሻ
ሀ/ ከቀበሌ ተለይቶ የሚመጡ የነጻ
ህክምና አገልግሎት ተጠቃሚዎች
ዝርዝር ያረጋግጣል
ለ/ በሥሩ ለሚኙ ቀበሌ ነፃ ታካሚዎች
የህክምና ወጪ ለመሸፈን
የሚያስችል በጀት ይይዛል
ሐ/ ከመንግስት የጤና ተቋማት ጋር
ስለ ነፃ ታካሚዎች ወጪ አሸፋፈን
የውል ስምምነት ይፈራረማል፤
መ/ ከጤና ተቋማት የሚቀርቡ የክፍያ
ጥያቄዎችን እያጣራ በውሉ
መሰረት ክፍያ ይፈጽማል
4. ጤና ተቋማት የሥራ ድርሻ
ሀ/ ለነፃ ታካሚዎቹ ከሌሎች ከፋይ
ተገልጋዮች ባልተለየ መልኩ
አገልግሎቱን መስጠት፣
5.2.3. The Kebele Social court shall give
final decision on the waiver scheme
request.
5.2.4. Monitor closely the improvement in
the living standards of beneficiaries
and inform the Woreda/city
administration when the beneficiary
acquires the ability to pay and thus
terminates the service.
5.3.Responsibility of the woreda/city
administration.
5.3.1. Confirm the list of fee waivers
received from the kebele
administration.
5.3.2. Appropriates budget quota that may
be used to cover waivers in its
kebeles.
5.3.3. Concludes an agreement, with the
health institutions, that specifies the
financing of wavers.
5.3.4. Verifies and disburses payment
certificated received from health
facilities.
5.4.Responsibility Health Institutions
1. Render health services without making
distinction between waived and paying
Page 2009 of 2280
ለ/ ታካሚዎች በአገልግሎት
የሚከፍሉት የክፍያና መጠንና የነፃ
ሕክምና ሊገኝ የሚችልበትን ሁኔታ
በግልፅ ቦታ መለጠፍ እንደ
አስፈላጊነቱም ህዝብ እንዲያውቅ
ትምህርታዊ ቅስቀሳ ማካሄድ፣
ሐ/ ከነፃ ታካሚ ወጪን የሚሸፍን
አካል ጋር ስለአገልግሎት አሰጣጥና
ወጪው ስለሚከፈልበት ሁኔታ
ውል መፈራረም፣
መ/ ለነጻ ታካሚዎች ከተሰጠው
የህክምና አገልግሎት ጋር የተያያዙ
መረጃዎቸን በማቅረብ ወጪውን
ለሚሸፍነው አካል በየ ሩብ ዓመቱ
ጥያቄ በማቅረብ ያስፈጽማል፡፡
ሠ/ ለነጻ ታካሚዎች ለተሰጠ የሕክምና
አገልግሎ ሊከፈል የሚገባውን
ሂሳብ ስብስቦ ገቢ ማድረግ፣
ይህንንም ለማስፈጸም የሚያስችል
የአሰራር ሥርዓት ይዘረጋል፡፡
6. ክትትልና ቁጥጥር
የቀበሌው አስተዳደር በአቅራቢያው ወረዳ
ከሚገኝ የጤና ተቋም፣ የወረዳው ጤና
ጥበቃ ጽ/ቤት፣ ከወረዳው/ከተማ አስተዳ
ደርና ሌሎች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር
በመሆኑ በዓመት ሁለት ጊዜ ስለ ነፃ
ታካሚዎች ፈቃድ አሰጣጥ እና አፈፃፀም
patients;
2. Post the fee payable and the conditions
under which health services are provided
free of charge and conduct educational
programs to make the public ware of this
fact;
3. Conclude an agreement with the Agency
financing Health Expenses, on the type of
service and mode of payment;
4. Submit to the concerned body quarterly
request for reimbursement of costs by
presenting supporting documents
evidencing services provided to persons
entitled to waivers and implements;
5. Collect and deposit payments made in
reimbursement of costs incurred for
health services provided to patients
entitled to waivers and develop a system
by which the collection is to be made.
6. Monitoring and Supervision
The kebele Administration together with the
health institutions operating in neighboring
Woredas,/city administration of the woreda
of which it is part of, and other concerned
Page 2010 of 2280
ይመግማል፡፡የእርማት እርምጃም ይወስዳል፡፡
1. የነፃ ሕክምና ማስረጃ ዝግጅት
1. የነፃ ሕክምና ማስረጃ ሰጪው አካል
ለነጻ ታካሚዎች የሚያገለግል ወጥ
የሆነ ቅጽ ያዘጋጃል፡፡ ይዘቱ በመመሪያ
ይወሰናል፡፡
2. የነፃ ሕክምና ማስረጃ በአራት ቅጂ
የሚዘጋጅ ሆኖ፡-
ሀ/ በቤተሰቡ፣
ለ/ በጤና ተቋሙ
ሐ/ በወረዳ ከተማ አስተዳደር እና
መ/ በፈቃድ ሰጪው አካል ዘንድ
እንዲያዝ ይደረጋል፣
3. ፈቃድ ሰጪው አካል ለሰጠው የነጻ
ሕክምና ማስረጃ ትክክኛነትና
አግባብነት ኃላፊነቱንና ተጠያቂነቱን
የሚወስድ ሲሆን፣ ማስረጃው ትክክለኛ
ሆኖ ባይገኝ ለአደረሰው የሥራ
አፈጻጸም በደል አግባብ ባለው ህግ
መሠረት ተጠያቂ ይሆናል፡፡
፲፪.. ...KFÃKክፍያ የማይጠየቅባቸው የጤና አገልግሎ
ዓይነቶች
በአዋጁ አንቀጽ 13 መሠረት በደ/ብ/ብ/ሕ/
ክልላዊ መንግስት ሥር ባሉ ጤና ተቋማት
ያለክፍያ የሚሰጡ የጤና አገልግሎቶች
bodies conduit biannual evaluation about the
issuance and administration of waiver
certificate and takes corrective measures.
1. Preparation of waiver certificate
1. The body authorized to give waiver
Certificates shall issue original formats
for waivers. A directive will determine its
content.
2. The wavier certificate shall be prepared
in four copies and distributed to the;
a. Household;
b. Health institution;
c. Woreda/city administration;
d. Issuing authority.
3. The issuing authority shall be responsible
for the authenticity of the waiver
certificate it issued and shall be liable
under appropriate law for any fraudulen
certificates issued.
12. Type of exempted Health Services
As stated in article 13 of the proclamation,
following are the list of exempted services
provided free of charge by the health
Page 2011 of 2280
የሚከተሉት ናቸው፡፡
ሀ/ በመሠረታዊ የጤና አገልግሎት መስጫ
ተቋማት የሚሰጥ የቤተሰብ እቅድ
አገልግሎት
ለ/ በመሰረታዊ የጤና አገልግሎ መስጫ
ተቋማት የሚጥ የቅድመ ወሊድ፣ ወሊድ
እና ድህረ ወሊድ አገልግሎት፣
ሐ/ ፀረ- ስድስት የሕፃናት እና እናቶች
ክትባት፣
መ/ የሳንባ ነቀርሳ በሽታ ከተረጋገጠ በኋላ
ክትትልና ህክምና፣
ሠ/ በፈቃደኝጀት ላይ የተመሰረተ ኤች/አይ/ቪኤድስ ምርመራና ከእናት ወደ ጽንስእንዳይተላለፍ መከላከል፣
ረ/ የሥጋ ደዌ ሕክምና
ሰ/ ወረርሽኝ መከታተልና ቁጥጥር
ሸ/ ፌስቱላ
ቀ/ ለጤና ባለሙያዎች የሥራ አካባቢ ስጋት
የሚያቃልሉ የክትባትና የሕክምና
አገልግሎት፣
በ/ ወጪያቸው በመንግሥት የሚሸፈን ሆኖ
ወደፊት ያለ ክፍያ እንዲጡ የሚወሰኑ
ሌሎች የጤና አገልግሎቶች፡፡
፲፫. ክፍያ የማይጠየቅባቸው አገልግሎቶች ወጪ
አሸፋፈንና ሪፖርት አደራረግ
1. ክፍያ የማይጠየቅባቸው የሕክምና
አገልግሎቶች ወጪ በመንግሥት
በሚመደብ በጀት እና ከበጎ አድራጊዎች
በሚኝ እርዳታ የሚሸፈን ይሆናል፡፡
institutions under the SNNP Regional
Government:
1. Family planning service in primary
health care units.
2. Pre natal, delivery and post natal services
in primary health care units;
3. Immunization of mothers and children
against six child illnesses;
4. Diagnosis, treatment and follow-up of
Tuberculosis;
5. Voluntary Counseling and Testing ofHIV/AIDS and prevention of HIV/AIDStransmission from mother to child;
6. Leprosy management;
7. Epidemic follow follow-up and control;
8. Fistula management;
9. Immunization and treatment of health
professionals to reduce risk related to
occupational hazards;
10. Other services to be provided free of
charge on reason of future endorsement
by the Government.
13. Financing of exempted services and
reporting
1. Costs of exempted health services shall be
paid out of budget appropriated by the
government or donations obtained from
Page 2012 of 2280
2. አገልግሎት ሰጪው ጤና ተቋም
ስለአገልግሎቶቹ በየወቅቱ መረጃ በመያዝ
ለጤና ቢሮው ሪፖርት ማድረግ አለበት፡፡
ክፍል ሶስት
የሆስፒታሎች የሥራ አመራር ቦርድ
፲፬. የሆስፒታሎች የቦርድ አስተዳደር
1.የሆስፒታሎች የሥራ አመራር ቦርድ
ማቋቋም
1. በደ/ብ/ብ/ሕ/ክልል መንግሥት ስር ያለ
ማንኛውንም ሆስፒታል በበላይነት
የሚያስተዳድር ተጠሪነቱ እንደ
ሆስፒታሉ ደረጃ ለጤና ቢሮው የሆነ
የሥራ አመራር ቦርድ ይቋቋማል፡፡
2. የሆስፒታሎች የሥራ አመራር ቦርድ
እንደሁኔታው ቢያንስ አምስት ቢበዛ
ሰባት አባላት ይኖሩታል፡፡
3. የአባላት አሰያየሙም የፆታ ተዋጽኦን
ባገናዘበ መልኩ ይሆናል፤
4. የቦርዱ ሰብሳቢ እንደየ ሆስፒታሉ ደረጃ
በቢሮ ይሰየማል፤
5. የሆስፒታሉ ሠራተኞች ተወካይ የቦርድ
አባል ይሆናል፣
6. የሆስፒታሉ ዋና ሥራ አስኪያጅ የቦርዱ
donors.
2. The health institution providing exempted
health services shall maintain records
related to such services and report the
same to the Bureau.
Part Three
The Board of Hospitals
14. Hospital Board
1. Establishment of Hospital Management
Boards
1. Hospital management boards that are
accountable to the Bureau according to the
level of the hospital, that will oversee the
operation of hospitals, that will oversee
the operation of hospitals under SNNP
regional government will be established;
2. A hospital management board will have
a minimum of five and maximum seven
members;
3. Nomination of membership will take
into account gender balance;
4. Board chairperson, according to the
level of the hospital, will be assigned by
the bureau;
5. Employees’ representative will be a
board member.
Page 2013 of 2280
አባልና ፀሐፊ ይሆናል፣
2. ለቦርድ አባልነት የሚቀርቡ ዕጩዎች
የቢሮው ኃላፊ ለቦርድ አባልነት
በዕጩነት የሚያቀርባቸውን ሰዎች
የሚመርጠው በሚከተሉት መስፈርቶች
ይሆናል፡፡
1. ለጤናው ዘርፍ መሻሻል አስተዋፅዎ
ሊያደርግ የሚያስችል የሙያ ብቃት፣
ጊዜና ልምድ ያለው፣
2. ሆስፒታሉ በተቋቋመበት አካባቢ ነዋሪ
የሆነና በኅብረተሰቡ የሚወከል፡፡
3. በቦርድ አባልነት ለማገልገል ፈቃደኛ
የሆነና ተነሳሽነት ያለው፡፡
4. አግባብነት ካላቸው የመንግሥት
መስሪያ ቤቶች የሚወከሉ ኃላፊዎች፣
3. የቦርዱ ሥልጣንና ኃላፊነት
1. የሆስፒታሉን አጠቃላይ የሥራ
እንቅስቃሴ በበላይነት ይመራል፣
ይከታተላል፣
2. የሆስፒታሉን የአጭር፣ የመካከለኛና
የረዥም ጊዜ ዕቅድ መርምሮ
ያጸድቃል፣
3. የሆስፒታሉን ወርሃዊ፣ የሩብ፣ የግማሽ
6. General Manager of the hospital will
serve as member and secretary of the
board;
2. Candidates for Board Membership
The bureau head shall nominate candidates
for Board membership on the basis of the
following considerations,
1. Experience, professional efficiency, and
time that will enable him/her contribute
to the improvement of the health sector;
2. Resident in the area in which the hospital
is established, prominent in the
community
3. Willingness and motivation to serve as
board member;
4. Heads form appropriate government
offices
3. Duties and Responsibilities of the Board.
The Board shall:
1. Oversee and supervise the activities of
the hospital;
2. Approve short, medium and long term
plans of the hospital;
3. Receive and decide upon monthly,
Page 2014 of 2280
እና ዓመታዊ የሥራ እንቅስቃሴ
ሪፖርት መርምሮ ውሳኔ ይሰጣል፣
4. የሆስፒታሉ የገቢ ምንጮች
የሚዳብሩበትን መንገድ ይቀይሳል፣
በአግባቡ በመሰብሰባቸውን እና ገቢ
መደረጋቸውን ይቆጣጠራል፡፡
5. የሆስፒታሉን የሥራ አካሄድ የሚወስኑ
መመሪያዎችን ያወጣል፣
6. የሆስፒታሉን የሥራ አስኪያጅ
ይቀጥራል የስራ ድክመት ካሳየ
ከሀላፊነት ያነሳል፣ የመምሪያና
አገልግሎት ኃላፊዎች ቅጥርና ዕድገት
ያጸድቃል፣
7. በሚጸድቀው ደንብ መሠረት በውል
ለሶስተኛ ወገኖች ሊሰጡ የሚችሉትን
ከሕክምና ውጪያሉ አገልግሎቶች
ይወስናል፣
8. በሆስፒታሉ ውስጥ ለሚገኙ የኃላፊነት
የሥራ መደቦች የሚከፈለውን የኃላፊነት
አበል ይወስናል፣
9. የሆስፒታሉን የሥራ ዕቅድ ያጸድቃል፣
የበጀት ረቂቅ መርምሮ ለቢሮው ኃላፊ
ያቀርባል፣
፲. የሆስፒታሉን የበጀት አጠቃቀም
ይከታተላል፡፡
፲፩. የሆስፒታሉ የሥራ እንቅስቃሴዎች
ግልጽነት እና ተጠያቂነት ባለበት
quarterly, semi-annual and annual reports
of the hospital;
4. Devise ways and means by which the
revenue of the hospital may be improved
and shall ensure that such revenues are
efficiently collected and deposited;
5. Issue directives that shall guide the
proper carrying out of the activities of the
hospital.
6. Employ the general manager and deposes
when and if he is inefficient, and approve
the employment and promotion of heads
of departments of the hospital;
7. In accordance with the Regulation to be
issued, determine non-clinical services
that may be outsourced;
8. Determine the responsibility allowance
payable to persons assigned to posts of
responsibilities;
9. Approve the work plan of the hospital,
examine the budget proposal and refer
the same to the bureau head for approval;
10. Follow up the budget utilization of the
hospital.
11. Ensure that all activities of the hospital
are carried out with transparency and
Page 2015 of 2280
ሁኔታ እንዲ ከናወኑ ያደርጋል፣
፲፪. ቢሮው የሚያወጣቸው መመሪያዎች
በሆስፒታሉ ውስጥ በትክክል ሥራ
ላይ መዋላቸውን ይከታተላል፣
፲፫. በሆስፒታሉ ዋና ሥራ አስኪያጅ
የሚቀርቡለትን ሌሎች ጉዳዮች
መርምሮ ውሳኔ ይሰጣል፣
፲፬. የአገሪቱ የጤና ፖሊሲና ጤና ነክ
መመሪያዎች በሆስፒታሉ በአግባቡ
መተርጎማቸውን ይከታተላል፡፡
4. የቦርድ ሰብሳቢ ስልጣንና ተግባር
1. ቦርዱን በሰብሳቢነት ይመራል፣የቦርዱ
ስብሰባዎች ጊዜያቸውን ጠብቀው
መካሄዳቸውን ይቆጣጠራል፣
2. የቦርዱን አጠቃላይ የሥራሂደት
በበላይነት ይመራል ይቆጣጠራል፣
3. የቦርዱ አባላት በአግባቡ በየስብሰባው
መገኘታቸውን ይከታተላል፣
ይቆጣጠራል፣
4. እንደ አስፈላጊነቱ አስቸኳይ ስብሰባዎችይጠራል፣
5. ከቦርዱ አባላት 1/3ኛ አስቸኳይ ስብሰባ
እንዲጠራ ሲጠይቁ ስብሰባዎችን
ይጠራል ያስተባብራል፣
accountability;
12. Ensure that all directives issued by the
bureau are properly implemented in the
hospital;
13. Examine and decide upon all matters that
are presented to it by the General
Manager.
14. Ensure that the country’s health policy
and directives related to health matters
are properly implemented in the hospital.
4. Powers and Duties of the Chairperson of
the Board
The Chairperson shall:
1. Chair the meetings of the Board and
ensure that Board meetings are held in
accordance with the adopted time
schedule;
2. Oversee and follow-up the activities of the
Board;
3. Ensure that Board members attend all
meetings of the Board;
4. As necessary call extra-ordinary meetings;
5. Coordinate and call extra-ordinary
meetings, when such meeting is proposed
by at least one-third of members of the
Board;
Page 2016 of 2280
6. ቦርዱን በመወከል አስፈላጊ በሆኑ
ስብሰባዎች ላይ ይካፈላል፣ ስለተካፈ
ለባቸውም ስብሰባዎች፣ ኮንፈረንሶች
አጭር ዘገባ ለቦርዱ ያቀርባል፣
7. የቦርዱን ሪፖርት በማጠናቀር ለቢሮ
ያቀርባል፣
8. የስብሰባዎች አጀንዳ በቦርዱ ፀሐፊ
ተዘጋጅተው ሲቀርቡ አግባብነታቸውን
እየመረመረ ለቦርዱ በማቅረብ ተፈጻሚ
ነታቸውን በቅርብ ሆኖ ይቆጣጠራል፣
9. የሆስፒታሉ የገቢ ማስገኛ ስልቶችን
ውጤታማነት ይከታተላል
ያስተባብራል፤
፲. ከቁጥጥሩ ውጭ በሆነ ምክንያት
ለተወሰነ ጊዜ በቦርዱ ስራ ላይ
በማይገኝበት ወቅት ይህንኑ ለቢሮው
አሳውቆ ያስወክላል፣
፲፩.ቦርዱ የሰጠውን ማንኛውንም ተጨማሪ
ኃላፊነቶችን ተቀብሎ ይሰራል፡፡
5. የሆስፒታሉ ዋና ሥራ አስኪያጅ
ተግባርና ኃላፊነት
1. ሆስፒታሉ ዋና ስራ አስኪያጅ
ተጠሪነቱ ለቦርዱና በየደረጃው ላሉ
ጤና ቢሮዎች ሆኖ የሆስፒታሉን
6. Participate in meetings and conferences
representing the Board and submit short
report to the Board concerning these
meetings and conferences;
7. Compile reports and submit the same to
the Bureau;
8. Review the agenda presented to him by
the secretary of the Board, submit the
same to the Board and ensure the
decisions of the Board are properly
executed;
9. Follow-up and coordinate the
effectiveness of the Hospital’s income
generating schemes;
10. Delegate a member for a limited period
of time when he is out of work for
reasons beyond control and notifies this
to the bureau.
11. Carry- out other duties as may from time
to time entrusted to him by the Board;
5. Powers and Duties of the General
Manager.
1. The General Manager as the chief
executive of the hospital shall direct and
manage the activities of the hospital in
accordance with instructions given to
Page 2017 of 2280
ተግባራት በበላይነት ይመራል፡፡
2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፩
የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ዋና
ስራ አስኪያጁ፣
ሀ/ በሲቪል ሰርቪስ ህግ መሠረት
የሆስፒታል ሠራተኞችን ይቀጥ
ራል፣ ያስተዳድራል፣ ያሰናብታል፣
ለ/ የሆስፒታሉን የሥራ ፕሮግራምና
በጀት አዘጋጅቶ ያቀርባል፣
ሲፈቀድም በሥራ ላይ ያውላል፣
ሐ/ የሆስፒታሉን የሥራ ክንውንና
የሂሳብ ሪፖርት አዘጋጅቶ ለቦርዱ
ያቀርባል፤
መ/ ተጠሪነታቸው ለዋና ሥራ
አስኪያጅ የሆኑትን የሆስፒታሉን
ኃላፊዎች በሲቪል ሰርቪስ ህግ
መሠረት አወዳድሮ በመምረጥ
ለቦርድ አቅርቦ ያስፀድቃል፣
ሠ/ ከሶስተኛ ወገኖች ጋር በሚደረጉ
ግንኙነቶች ሁሉ ሆስፒታሉን
ይወክላል፡፡
3. ዋና ሥራ አስኪያጁ ለሆስፒታሉ
የሥራ ቅልጥፍና በሚያስፈልግ
him/her by the Management Board.
2. Without prejudice to the generality stated
in sub-Article 1 of this Article, the
General Manager shall:
a) Employ, administer and dismiss
employees of the hospital in
accordance with the Region’s civil
service rules and regulations.
b) Prepare and submit to the
Management Board the budget and
work program of the hospital; and
implement same upon approval;
c) Prepare and submit to the
Management Board the operational
and financial reports of the hospital;
d) Select by competition heads of
departments accountable to him on
the basis of the civil service rules and
submit the list to the Board for
approval;
e) Represent the hospital in all its
dealings with third parties;
3. The General Manager may delegate part
of his powers and duties to the officials
and other employees of the hospital to the
Page 2018 of 2280
መጠን ሥልጣንና ተግባሩን በከፊል
ለሆስፒታሉ የሥራ ኃላፊዎችና
ሠራተኞች በውክልና ሊያስተላልፍ
ይችላል፡፡
4. የሆስፒታሉ ሥራ አሥኪያጅ የቦርዱ
ፀሐፊ ሆኖ ያገለግላል፡፡ ሥራ
አሥኪያጁ በቦርዱ ፀሐፊነት
ተግባሩ፡-
ሀ/ የሆስፒታሉን ቦርድ አጀንዳ
ከሰብሳቢው ጋር በመሆን
ያዘጋጃል፣
ለ/ የቦርዱን ቃለ ጉባዔ
ይይዛል፣
ሐ/ የቦርዱን የሥራ ክንውን
ሪፖርት ያዘጋጃል፣
6. የቦርዱ ተጠያቂነት
1. የቦርዱ ሰብሳቢና አባላት በዚህ አንቀጽ
ንዑስ ፭ /፫/ እና ፬ የተሰጣቸውን
ተግባር በጥንቃቄ መፈጸም
አለባቸው፣
2. ሰብሳቢውና አባላቱ ተግባራቸውን
በአግባቡ ባለመፈጸማቸው ምክንያት
በሆስፒታሉ ላይ ለሚደርሰው ጉዳት
በአንድነትና በነጠላ ተጠያቂ
ይሆናሉ፣
extent necessary for the efficient
performance of the activities of the
hospital;
4. The manager of the Hospital shall serve
as secretary of the Board. The Manager
in his capacity as secretary shall:
a) Together with the chairperson of the
Board prepare the agenda of the
Board;
b) Keep the minutes of all meetings of
the
c) Prepare report on the activities of the
Board;
6. Board Accountability
1. The board chairperson and members will
perform the duties and responsibilities
bestowed on them on this article sub
article 5 (3) and (4) of this regulation;
2. The chairperson and members will be
held accountable individually and in a
group for any damage incurred in the
hospital due to negligence;
3. Member with a differing vote will not
Page 2019 of 2280
3. በአብላጫ ድምጽ በሚሰጠው ውሳኔ
ለሚደርሰው ጉዳት የተለያ ድምጽ
ያው አባል ተጠያቂ አይሆንም፣
7. የስብሰባ ሥነ ሥርዓት
1. የቦርዱ አባላት ቢያንስ በወር አንድ
ጊዜ መደበኛ ስብሰባ ያካሂዳሉ፣
2. እንደየሁኔታው አስቸኳይ ስብሰባ
በቦርዱ ሰብሳቢ ይጠራል፣
3.መደበኛ ስብሰባው ከመካሄዱ ከሶስት
ቀናት በፊት አስፈላጊው አጀንዳ
ተቀርጾ ለአባላት ይላካል፣ ያለፈው
ቃለጉባዔ ተፈርሞ ለቢሮው ይላካል፣
4. ስብሰባው የሚካሄደው ከአባላቱ
ከግማሽ በላይ ሲገኙ ነው፣
5.አከራካሪና አማራጭ ጉዳዮች ሲቀርቡ
በዕለቱ በተገኙት ተሰብሳቢዎች
በድምጽ ብልጫ በአብዛኛው
የተደገፈው ሃሳብ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡
ተሳታፊዎቹ ለሁለት በእኩል
ከተከፈሉ ሰብሳቢው የደገፈው ሃሣብ
ይጸድቃል፣
6. ቦርዱ አሠራሩን የሚወስን የውስጥ
መተዳደሪያ ደንብ ሊያወጣ ይችላል፡፡
8. የቦርድ አባላት መብትና ግዴታ
be held accountable in the case of
majority decision causing damages in
the hospital.
7. Procedures of Board Meetings
1. Members of the Board shall hold at least
one ordinary meeting every month;
2. The chairperson shall as necessary call
extra-ordinary meeting.
3. The agenda of any meeting shall be
prepared and distributed to members of
the Board at least three days in advance
of such meeting. The Minutes of all
precious meetings shall be signed and
submitted to the bureau.
4. A meeting shall only proceed if more
than half of the members are present.
5. If members have taken different
positions on an issue or if alternative
views are presented concerning same
issue, the line to be taken shall be
decided by a majority vote is equal the
side supported by the chairperson shall
be the position of the meeting.
6. The Board can issue directives
regulating its internal procedures.
8. Rights and duties of Members the Board.
1. Each member has the duty to strictly be
Page 2020 of 2280
1.እያንዳንዱ የቦርድ አባል በመደበኛውና
በአስቸኳይ ስብሰባ ላይ ሰዓቱን
በማክበት የመገኘት ግዴታ አለበት፣
2.የቦርዱ አባላት ለሆስፒታሉ ዕድገትና
ልማት ያልተቆጠበ የአስተዳደርና
የቴክኒክ ድጋፍ የመስጠትና
በሚወስኑት ውሳኔም የግልና የጋራ
ኃላፊነት አለባቸው፣
3.ከቦርዱ ውሳኔ ውጭ አባላት
በተናጠልም ሆነ በቡድን የሥራ
ማሻሻያም ሆነ ሌሎች ጉዳዮች
እንዲፈፀሙ በሥራ አስኪያጁ ላይ
ተፅዕኖ ማድረግ የለባቸውም፣
4.የቦርዱ አባላት አግባብ ያለውን
የመንግሥት መመሪያ መሠረት
በማድረግ በጤና ቢሮ የሚወሰን አበል
ይከፈላቸዋል፡፡
9. የቦርድ አባላት የሥራ ዘመን
1. የቦርዱ አባላት የሥራ ዘመን 3
ዓመት ይሆናል፣
2. ማናቸውም የቦርድ አባል የሥራ
ዘመኑ ከመጠናቀቁ በፊት በግ
ምክንያት ከቦርዱ አባነት መልቀቅ
ቢፈልግ ከአንድ ወር በፊት
ለቢሮው/መምሪያ በጽሑፍ ማስታወቅ
present at each ordinary and extra-
ordinary meeting and shall observe the
time scheduled for such meeting.
2. Members of the Board shall have the
obligation to give their unreserved
administrative and technical support to the
growth and development of the Hospital
and are jointly and individually
responsible for all damages caused due to
their decisions.
3. Members of the Board shall not
individually or in-group order the General
Manager to perform an act without the
decision of the Board.
4. Members of the Board shall be entitled to
receive an allowance as may be
determined by the bureau..
9. Duration of Membership
1. The duration of service of members of the
Board shall be three years.
2. If a member of the Board decides to resign
from the Board for personal reasons, he
shall give notice in writing of his/her
decision to the bureau/desk one month
prior to the date of his resignation.
Page 2021 of 2280
አለበት፣
3. አንድ የቦርድ አባል የተጣለበትን
ኃላፊነት በአግባቡ ለመወጣት
ያለመቻሉ ሲረጋገጥና ይኸው በቦርዱ
ስብሰባ ላይ ቀርቦ ውሳኔ ሲሰጥበት
እንዲሰናበት ለቢሮ በጽሁፍ
እንዲቀርብ ይደረጋል፣
4. የቦርደ አባላት ያደረጉት አስተዋጽኦ
ታይቶ በድጋሚ ሊመረጡ ይችላሉ፣
5. የሥራ ዘመኑን ያጠናቀቀ ቦርድ
በአዲስ ቦርድ የሚተካበት ጊዜ
የስራውን ቀጣይነት ለማረጋገጥ
ከቀድሞው ቦርድ አባላት ቢያስ
1/3ኛው የአዲሱ ቦርደ አባል ሆነው
እንዲቀጥሉ ይደረጋል
፲. ተጠሪነት
ቦርዱ ተጠሪነቱ እንደ ሆስፒታሉ ደረጃ
ለጤና ቢሮው ይሆናል፡፡
፲፩. የጤና ቢሮው ኃላፊነት
1. ሆስፒታሉ ተገቢውን ጥቅል የበጀት
ድጋፍ ማግኘቱን ይከታተላል፣
2. ሆስፒታሉ የመንግስትን የጤና ፖሊሲ፣
ስትራቴጂና ፕሮግራም መሠረት አድርጎ
ለመሥራት በሚያደርገው ጥረት እገዛ
3. If a member of the Board is unable to
discharge his responsibilities, and decision
is reached in a board meeting to this effect
the Board may recommend to the bureau
in writing that he/she be dismissed from
the Board.
4. Board members, assessed their
contributions, could be elected for s econd
round.
5. When a new Board replaces an outgoing
Board, to ensure continuity, at least one-
third of the members of the outgoing
Board may be authorized to continue as
members of the new Board.
10. Accountability
The Board, according to the level of the
hospital, shall be accountable to the Bureau.
11. Responsibility of the Health Bureau/Zonal
Health Desk
The Health Bureau shall:
1. Ensure that block budget support is given
to each Hospital.
2. Assist the Hospital in its endeavor to
carry out its responsibilities on the basis
Page 2022 of 2280
ያደርጋል፣
3. በሆስፒታ ውስጥ ተገቢ የአሰራር
ሥርዓት እንዲዘረጋ የባለሙያ እገዛ
ያደርጋል፣
4. ሆስፒታሉ ተጨማሪ የሰው ኃይል
ቁሳቁስና ገንዘብ የሚያገኝበትን ሁኔታ
ያመቻቻል፣
5. ለቦርዱ ተገቢውን የቴክኒክና የአስተዳደር
ድጋፍ ይሰጣል፣
6. የቦርድ አባላትን ይሰይማል፣ ያነሳል፣
በጎደሉ አባላት ምትክም ሌሎች አባላትን
ይመድባል፣
7. የቦርዱን ስራ ይከታተላል፣ የቆጣጠራል
ክፍል አራት
ሕክምና ነክ ያልሆኑ አገልግሎቶችን በኮንትራት
ወይም በውል ስመስጠት
፲፭. ሆስፒታሎች ሕክምና ነክ ያልሆኑ
አገልግሎቶች በኮንትራት/በውል/
ስለሚሰጡበት ሁኔታ፣
1. መርህ
ከሕክምና ውጪ ያሉ አገልግሎቶች በሌላ
ወገን እንዲከናወኑ የሚደረገው
of the Health policy, strategy and
program of the Government,
3. Give technical support to the hospital to
enable it set-up proper systems of
operation.
4. Create the condition that enables the
hospital obtain the necessary manpower,
material and finance.
5. Give the necessary administrative and
technical support to the Board
6. Appoint, dispose members of the Board
replace new members of board in place of
outgoing members of board.
7. Oversee and follow up the operations of
the board.
Part Four
Outsourcing of non-clinical services of
Hospitals
15. Outsourcing of Non-clinical Services
1. Principles
Non-clinical Services shall be outsourced in
Page 2023 of 2280
1. ወጪ ለመቀነስ፣
2. በተመሳሳይ ወጪም ቢሆን የተሻለ
ቀልጣፋና ጥራት ያለው አገልግሎ
ለማግኘት፣
3. ሆስፒታሎች ሙሉ ጊዜያቸውንና
ጉልበታቸውን በሕክምና ሥራ ላይ ብቻ
እንዲያውሉና ጥራት ያው አገልግሎት
እንዲያበረክቱ፣
4. ለተሻለ አገልግሎት አሰጣጥና ምርምር
አመቺ ሁኔታን ለመፍጠር፡፡
2. ሊተኮርባቸው የሚገባ ዋና ዋና ጉዳዮች
ሕክምና ነክ ያልሆኑ አገልግሎቶች በግል
እንዲከናወኑ ከመደረጉ በፊት የሚከተሉት
ግምት ውስጥ መግባት ይኖርባቸዋል፡፡
1. አገልግሎቱ በሌላ ወገን እንዲከናወን
በማድረግ የተሻለ ውጤት የሚያስገኝ
መሆኑን ማረጋገጥ፣
2. በሌላ ወገን እንዲከናወኑ በውል
የሚሰጡ አገልግሎቶችን ወጪ ማወቅና
አገልግሎቶቹ በሆስፒታሎች ቢከናወኑ
ወይም በሌላ ወገን እንዲመናወኑ በውል
ቢሰጡ በዋጋና በአገልግሎ ጥራት
የትኛው የተሻለ እንደሚሆን ማስላት፣
3. ሚዛናዊ የሆነና ሥራውን በተገቢው
order to:
1. Reduce cost of services:
2. Provide efficient and effective services
at similar cost;
3. Enable hospital use their full time and
energy on clinical services and render
equality services;
4. Create conductive environment for
better service delivery and research.
2. Key considerations
The following shall be taken into
consideration when planning to outsource
non-clinical services;
1. Ensure that efficiency can be improved by
outsourcing the service;
2. Estimate the costs of services considered
for outsourcing and analyze the benefit to
be obtained on price, and service quality
by outsourcing or by providing the
services through the hospital management;
Page 2024 of 2280
ሁኔታ ለማከናወን እና የሆስፒታሉን
ጥቅም ማስጠበቅ የሚያስችል ውል
ማዘጋጀት፣
4. በኮንትራት ሊሰጡ የታሰቡ
አገልግሎቶችን ሲያከናውኑ የነበሩ
ሠራተኞችን፣
ሀ/ የሥራ ዕድል የሚያገኙበትን ሁኔታ
የሚያመቻች ውል በማዘጋጀት፣
ለ/ እራሳቸውን አደራጅተው በሌላ ወገን
እንዲከናወኑ በኮንትራት መልክ
የሚወስዱበትን መንገድ
በማመቻቸት ወይም/ እና
ሐ/እንደልምዳቸው ክፍተት ወደሚገኝ
ባቸው የሥራ ቦታዎች በማዘዋወር
ከሥራ መፈናቀል የሚያስከትውን
አሉታዊ ተፅዕኖ ለመዘነስ ጥረት
ማድረግ፣
5. በውል ለሌላ ወገን የሚሰጡትን
አገልግሎቶች በዋጋ፣ በመጠንና በጥራት
መመዘን በሚያስችል ሁኔታ በዝርዝር
ማስቀመጥ፣
6. በውል ለሌላ ወገን ሊሰጡ ከታሰቡ
አገልግሎቶች ጋር የሚዛመዱትን
የክትትልና የቁጥጥር ተግባራት
በሆስፒታሎ አመራር ሥር ማቆየት፡፡
3. በሌላ ወገን እንዲከናወኑ የሚሰጡ
አገልግሎቶች
3. Develop a fair but strong contract that will
help carry out the services properly,
safeguard the interests of the hospital;
4. Minimize displacement of staff by:
a) Developing a contract that incorporates
the workers under the contractor;
b) Facilitating conditions under which staff
of the hospital organize themselves to
contract the services to be outsources;
and /or
c) Shifting the workers to be displaces to
other areas with gaps, according to their
capability.
5. Quantify,price and measure the services to
be outsourced;
6. Retain monitoring and evaluation
functions associated to outsourced
services.
3. Services to be considered for outsourcing
Page 2025 of 2280
1. በውል ለሌላ አካል ሊሰጡ የሚችሉ
ሕክምና ነክ ያሆኑ አገልግሎቶች
የሚከተለሉት ናቸው፡፡
ሀ/ የጽዳት አገልግሎት፣
ለ/የእጥበት /የላውንደሪ/ አገልግሎት፣
ሐ/ የምግብ ዝግጅትና አቅርቦት፣
መ/የቋሚ ንብረት ጥገና
አገልግሎት፣
ሠ/ የህትመት አገልግሎት፣
ረ/ የጥበቃ አገልግሎት፣
ሰ/ የመጓጓዣ አገልግሎት፣
ሸ/ የሕግ አገልግሎት.
2. የሆስፒታሉ የሥራ አመራር ቦርድ
እንደ አስፈላጊነቱ ሌሎች አገልግሎቶች
በሌላ ወገን እንዲከናወኑ ሊወስን
ይችላል፡፡
4. በውል የሚሰጡ አገልግሎቶችን መምረጥ
1. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 3
የተዘረዘሩ አገልግሎቶች በውል ሊሰጡ
የሚችሉት ለሌሎች ወገኖች በመስኩ
የተሻለ ብቃት ያላቸው መሆኑ
ሲታመንበት ይሆናል፣
2. የሆስፒታሉ የሥራ አመራር ቦርድ
በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፫
ከተዘረዘሩት አገልግሎቶች ውስጥ
የተሻለ ብቃት ባላቸው ሌሎች ወገኖች
1. Non- clinical services that can be
considered for outsourcing are the
following;
a) Cleaning services
b) Laundry
c) Food preparation and supply
d) Fixed assets maintenance and
services
e) Printing services
f) Protection/security services
g) Transportation services
h) Legal services
2. The hospital board may, as necessary,
decide to include other services to the
above list
4. selection of services for outsourcing
1. Services listed under this articles sub
article 3may be outsourced after
ascertaining that the private sector acquires
better expertise in the field.
2. The management board of the hospital
shall select services, from those listed
under this article sub Article3 above, which
can be better, provided by the private sector
and instruct gradual implementation of the
Page 2026 of 2280
ቢከናወኑ የበለጠ ውጤት ሊገኝባቸው
ይችላል የሚባሉ አገልግሎቶችን
በመምረጥ ደረጃ በደረጃ ተግራዊ
እንዲሆኑ ይወስናል፣
3. የሆስፒታሉ ሥራ አመራር ዝርዝር
ጥናቶችን በማድረግ በሌላ ወገን
እንዲከናወኑ በውል የሚሰጡ
አገልግሎቶችን ጨረታ ያወጣል፣
አሸናፊውን በመምረጥ የውሳኔ ሃሳብ
ለቦርዱ ያቀርባል ሲፀድቅም ተግባራዊ
ያደርጋል፣
5. የአገልግሎት አሰጣጥ የሥራ ዝርዝር ሰነድ
አዘገጃጀት
በሌላ ወገን እንዲከናወኑ በውል የሚሰጡ
ሕክምና ነክ ያልሆኑ አገልግሎቶች ጨረታ
ከመውጣቱ በፊት አገልግሎቶቹን
ለመስጠት ሊከናወኑ የሚገባቸውን
ሥራዎች ዝርዝር፣ አገልግሎቶቹን
ለመስጠት ተዋዋዩ ሊጠቀምባቸው
የሚገባውን ግብዓቶች ዓይነትና ጥራት
አንዲሁም የመጨረሻው ውጤት ምን
መምሰል እንደሚባው የሚያሳይ ሰነድ
መዘጋጀት ይኖርበታል፡፡
6. የጨረታ ሠነድ ማዘጋጀት
ሕክምና ነክ ያልሆኑ አገልግሎቶች በሌላ
ወገን እንዲከናወኑ ለመስጠት ለሚወጣ
ጨረታ የሚያገለግሉ ሰነዶች የመንግስት
ዕቃና አገልግሎት ግዢ ማንዋልን
same.
3. The hospital management shall conduct
detailed study, invite potential bidders,
evaluate bid proposals and submit the
evaluation report to the board for approval.
5. Terms of reference
Before inviting bidders for outsourcing of
non-clinical services the hospital shall prepare
terms of reference, which describes among
others the type of materials that the bidder
shall use in providing the services and the out-
come that is expected.
6. Bidding documents.
Bidding documents for outsourcing of non-
clinical services shall be prepared on the basis
on the Government Procurement Manual.
Page 2027 of 2280
ተከትለው መዘጋጀት አለባቸው፡፡
7. የውሉ ዘመን
ሕክምና ነክ ያልሆኑ አገልግሎቶች በሌላ
ወገን እንዲከናወኑ በውል የሚሰጡት
በሆስፒታሉ ቦርድ ለሚወሰን ጊዜ ብቻ
ይሆናል፡፡
8. የክፍያ ስልት
አገልግሎቱ የሚከፈለው ዋጋ አንድ ወጥና
የማይለዋወጥ መሆኑ በውሉ መመልከት
አለበት፡፡ ውል ሰጪም ሆነ ተቀባይ የውል
ሥምምነቱን ለመቀየር ሲፈልጉ ቢያንስ 6
ወራት ቅድሚያ ማስጠንቀቂያ ይሰጣሉ፡፡
9. የውል አስተዳደር
የሆስፒታሉ ስራ አመራር የውሉን
አፈፃፀም ይከታተላል ይቆጣጠራል፡፡
1. በውሉ መሠረት በሆስፒታሉ ለውል
ተቀባይ ማስረከብ የሚባውን የሥራ
ኃላፊነት፣ ቦታና የመሥሪያ ቁሳቁስ
ማስረከብ፣
2. ሥራን ለማስጀመር የቅድሚያ ክፍያ
አስፈላጊ ከሆነና በስምምነቱ ውስጥ
ተካቶ ካለ መፈጸም፣
3. ውል ተቀባዩ በውሉ መሠረት ብቃት
ያላቸው ሠራተኞች እና መሣሪያዎች
መመደቡን ማረጋገጥ፣
7. Duration of Contract
The hospital management board shall
determine the duration of the contractfor
outsourcing of non-clinical services.
8. Mode of payment
The price to be paid for services shall be
original and fixed amount and shall be
designated in the agreement. If either of the
parties insist to change the agreement, then a
six month notice shall be given.
9. Contract administration
The management of the hospital shall
administer and follow the contract. The
management shall
1. Handover the authority, necessary work-
space and equipment to the contractor;
2. Make advance payments, if it is
necessary and provided in the contract;
3. Ensure that the contractor has assigned
qualified personnel and the necessary
equipment;
4. Notify to all relevant bodies the
Page 2028 of 2280
4. ውል ተቀባዩ ሥራ መጀመሩን በወቅቱ
ለሚመለከታቸው አካላት ማሳወቅ፣
5. በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ
ሥራዎች እንዴት እየተከናወኑ እንዳለ
ክትትል ማድረግ ለዚህም መለኪያ
ማዘጋጀት፣
6. ከዋጋና ከጥራት አንጻር የተጠበቀው
ውጤት መገኘት አለመገኘቱን
መገምገም፣
7. በሚጠበቀው ውጤትና የሥራ
አፈጻጸም ላይ ልዩነት ሲከሰት ይህንን
ሪፖትር ማድረግ፣
8. በሆስፒታሉ ከኮንትራት ሥራ ጋር
የተያያዙ የሕግ ጉዳዮችን ለሕግ
ባለሙያ ማማከር፣
9. በግምገማው ውጤት ላይ ተመስርቶ
ኮንትራቱ መቀጠል አለመቀጠሉን
በሚመለከት ለሆስፒታሉ ስራ አመራር
ቦርድ የውሣኔ ሃሳብ ማቅረብ አለበት፡፡
ክፍል አምስት
የግል ሕክምና መስጫ ዩኒቶች
፲፮. የግል ሕክምና መስጫ ዪኒቶች ስለ ማቋቋም
contractor’s presence and commencement
of work;
5. Monitor directly or indirectly the
activities of the contractor, prepare
evaluation criteria;
6. Evaluate the activities of the contractor to
find out whether the required result with
regard to price and service quality has
been achieved;
7. Report to management board in due time
if the work done by the contractor is not
satisfactory;
8. Seek legal advice for all matters of the
hospital in relation with contractual
activities
9. Forward proposal on the basis of the
outcome of the evaluation recommend to
the management board whether the
contracts hall be renewed or not.
Part Five
Private Wings in Public Hospitals
16. Establishment of Private Wings:
Page 2029 of 2280
1.የግል የሕክምና መስጫ ዩኒቶች ለቋቋም
በቅድሚያ ሊሟሉ ስለሚገባቸው
ሁኔታዎች፣
1. አንድ ሆስፒታል የግል የሕክምና
መስጫ ዩኒት ሊያቋቁም የሚችለው
በአንጻራዊ ሲታይ በኅብረተሰቡ ዘንድ
ተቀባይነት ያለው አገልግሎ
የሚሰጥባቸው የሕክምና ዘርፎች
ሲኖሩት ነው፣
2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፩.፩
የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ
ማንኛውም ሆስፒታል በመደበኛ
የሕክምና አገልግሎ ክፍል ውስጥ
የማይሰጡ የህክምና አገልግሎቶችን
በግል የሕክምና መስጫ ዩኒት ሊሰጥ
አይችልም፣
3. ሆስፒታሉ በተቻለ አቅም በመደበኛ
የሕክምና አገልግሎት መስጫ ክፍል
የሚሰጠው አገልግሎት ሳይጓደል
የግል የህክምና መስጫ ዩኒት በትፍር
ሰዓታቸው በዙር እየተቀያየሩ
የሚያገለግሉ የጤና ባለሙያዎች
እንዲኖሩት ማድረግ አለበት፣
4. የግል የሕክምና መስጫ ዩኒት
ሲቋቋም ተኝተው ለሚታከሙ
የመደበኛውን የህክምና አገልግሎት
መስጫ ጊዜና ክፍሎ በማጣበብና
በመሻማት መሆን የለበትም፡፡
1.Conditions to be fulfilled to establish
private wings.
1. The hospital shall establish private wings
in services that it has strength and are of
greater public demand.
2. Notwithstanding what is stated in this
article sub article 1(1), a hospital shall in
no way establish services that are not
provided in the general ward on a purely
private basis.
3. Hospitals shall make sure that the
necessary health personnel are available
and working on a rotation basis during
their part time without negatively
affecting the services of the general ward.
4. The establishment to private wings and
inpatients treatment therein shall not in
any way significantly affect and complete
the space and time provided for the
general ward. Therefore, the Hospital shall
Page 2030 of 2280
በመሆኑም ለግል ሕክምና መስጫ
ዩኒት ሊውል የሚችል የተለየ ክፍል
መኖሩ መረጋገጥ አለበት፣
5. የግል የህክምና መስጫ ዩኒት
መቋቋም በመደበኛ የሕክምና
አገልግሎ መስጫ ክፍሎት
የሚሰጠውን የቀጠሮ ጊዜ ለማሳጠር
የሚረገውን ጥረት ማወክ የለትም፣
6. የግል የሕክምና መስጫ ዪኒት
ሊቋቋም የሚችለው በሆስፒታሉ ሥራ
አስኪያጅ ተጠንቶ የቀረበው የውሣኔ
ሃሳብ በሥራ አመራር ቦርደ ሲጸደቅ
ይሆናል
2.የካፒታል
ተኝተው ለሚታከሙ የግል የሕክምና
መስጫ ዮኒት የሚቋቋመው ከሚከተሉት
ምንጮት በሚገኝ ካፒታል ይሆናል፡፡
1. ከእርዳታ፣
2. ከሆስፒታሉ የውስጥ ገቢ፣
3. ከመንግሥት ከሚኝ የበጀት ድጋፍ፣
4. እንዳስፈላጊነቱ ከሌሎችም ምንጮች፣
3.የአገልግሎ ክፍያ አወሳሰን
1. የግል የሕክምና መስጫ ዩኒቶች
ለሚሰጡት አገልግሎት የሚከፈለው
ክፍያ በሆስፒታሉ ሥራ አስኪያጅ
ተጠንቶ በሆስፒታሉ ቦርድ ተገምግሞ
make sure that there is space to be used
for the private wing.
5. The establishment of private wings must
not compromise the drive to reduce the
waiting times in the general words.
6. The proposal to establish a private wing in
a public hospital shall be endorsed by the
managing board and approved by the head
of the health bureau.
2.Capital
The hospital may mobilize funds for in
patients from the following sources to
refurbish and start-up its private wing.
1. Donor finance;
2. Retained revenue of the hospital
3. Support from government capital
budget
4. Other sources, as necessary.
3. Fee Setting
1.Fees for services rendered by the private
wing shall be set by the Bureau after being
evaluated by the Managing Board on the
basis of the study conducted by the
manager of the hospital;
Page 2031 of 2280
በቢሮው በኩል ቀርቦ ሲጸድቅ ተግባራዊ
ይሆናል፣
2. የአገልግሎ ክፍያ አወሳሰን
የሚከተሉትን መርሆዎች ያገናዘበ
መሆን አለበት፣
ሀ/ ዋጋን በእርከን ስለመወሰን
የአገልግሎት ክፍያ አወሳሰን የሕክምና
አገልግሎቱን ብቃት እና በግል
የሕክምና መስጫ ዩኒቱ የሚሰጠውን
የእንክብካቤ ደረጃ ያገናዘበ መሆኑ
አለበት፣
ለ/ ወጪን መመለስ ዓላማ በማድረግ
ዋጋን ስለመወሰን
በግል የሕክምና መስጫ ዮኒቶች
ውስጥ ለሚሰጠው አገልግሎት
የሚፀመው ክፍያ የመደበኛ የሕክምና
መስጫ ክፍሎችን ወጪ ለመደጎም፣
የባለሙያ መረጋጋት እንዲኖር
የማበረታቻ ክፍያ ለመፈጸም፣ የግል
የሕክምና መስጫ ዩኒቶችን በተገቢው
መንገድ ለመምራት የሚያግዝ ትርፍ
ማስገኘት የሚያስችል መሆን
አለበትመ
ሐ/ የዋጋ ልዩነት
ሆስፒታሎች በግል የሕክምና ዮኒቶች
ውስጥ ለሚሰጡት አገልግሎቶች
ከኢትዮጵያውያን እና ከውጭ አገር
ዜጎች የሚጠይቁት ዋጋ የተለያየ
2. Fees for services shall be set incompliance
with the following principles;
a) Principle of Graduated fee levels
Fees shall be set taking into
consideration the type of medical
services and the level of patient
handling in the private wing.
b) Principle of Cost Recovery
The fee for services provided in private
wings shall exceed total cost to
generate re venue that will be used to
cross subsidize the costs of the general
ward, to give incentives to staff to
secure manpower stability, and to
improve the services of the
privatewing.
c) Principle of Differential Pricing
Hospital shall set different fees for
Ethiopians and non-Ethiopians. The
non-Ethiopians shall pay at least double
of what Ethiopians pay for the same
service.
Page 2032 of 2280
መሆኑ አለበት፡፡ ስለሆነም የውጭ
አገር ዜጎች ለተመሳሳይ አገልግሎት
ኢትዮጵያውያን ከሚከፍሉት ዋጋ
ቢያንስ እጥፍ ጨምረው እንዲከፍሉ
ይደረጋል
4. የታካሚዎች አቀባበል
በግል ሕክምና መስጫ ዩኒት ተመለሰላሽ
ታካሚዎች አገልግሎት የሚያገኙት
በመደበኛው ተመላላሽ ክፍል ውስጥ ከስራ
ሰዓት ውጪ ብቻ ይሆናል፡፡
5.ለግል ሕክምና መስጫ ዩኒት ታካሚዎች
ስለሚደረግ አንክብካቤ
የግል ሕክምና መስጫ ዩኒት ታካሚዎች
የተሻለ የመኝታ፣ የምግብና ሌሎችም
አገልግሎቶች እንዲያገኙ ይደረጋል፡፡
6. የሆስፒታሎች ግዴታ
ማናቸውም ሆስፒታል
1. በሆስፒታሉ ውስጥ በማንኛውም ጊዜ
ስለሚሰጡ አገልግሎቶችን ክፍያ ዝርዝር
መረጃ መስጠት፣
2. ከመስተንግዶ፣ ከምግብ፣ ከመኝታ
ክፍሎት አገልግሎት እና ከቆይታ ጊዜ
በስተቀር ሁሉም ታካሚዎች በመደበኛ
እና በግል የህክምና መስጫ ዩኒቶች
የሚያገኙት የሕክምና አገልግሎት
ተመሳሳይ መሆኑን ማሳወቅ፣
4. Patient Reception
The outpatients in the private wing shall
get medical services in the general ward
only after the regular working time
5. Right of the Patient in Private wing
Patients in private wing shall be accorded
good hotelling service including food and
bed services.
6. Obligations of the Hospital
The hospital shall:
1. Advise all patients coming to the
hospital on services given ad payments
required at any time;
2. Advise all patients that the medical care
in the two wards are generally similar
except with regard to reception,
accommodation services and waiting
time;
Page 2033 of 2280
3. በግል ወይም በመደበኛ የሕክምና
አገልግሎ መስጫ ክፍሎ አገልግሎ
ለማግኘት የሚኖረውን የቀጠሮ ጊዜ
መግለጽ አለባቸው፡፡
7. የሥራ ሰዓት
የግል የሕክምና መስጫ ዩኒት የስራ
ሰዓት እንደየአካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ
የሚወሰን ሆኖ
1. ለግል የሕክምና መስጫ ዩኒቶች የባለሙያ
ምደባ በሚደረግበት ጊዜ ሁሉ ምደባው
በመደበኛ የሕክምና አገልግሎ መስጫ
ክፍሎች የሥራ እንቅስቃሱ ላይ አሉታዊ
ተፅዕኖ የማይኖረው መሆኑ መረጋገጥ
አለበት፡፡
2. በመደበኛ የሥራ ሰዓቶች በግል የሕክምና
መስጫ ዩኒት የሚመደቡ ባለሙያዎች
በመደበኛ የሕክምና አገልግሎት መስጫ
ክፍል በዕለቱ ያልተመደቡ መሆብ
አለባቸው፣
8. በግል የሕክምና ዩኒቶች ሠራተኞችን
ስለመመደብ
1. የሆስፒታሉ ማኔጅመንት ባለሙያዎ
ችን ለመመደብ የሚያስችል የመም
ረጫ ሙያዊና ሥነ-ምግባራዊ መስፈር
ት ያካተተ መመሪያ አዘጋጅቶ በቦርዱ
3. Advise all patients on the waiting time
required ineither the private or the
general ward.
7. Working Hours
The working hours of the private wing,
depending up on the objective conditions of
zones/woredas,will be as follows:
1. The deployment of human resources should
always be arranged in such a way that the
private wing allocation should not have a
qualitative and quantitative impact on the
general ward:
2. Every specialist may work in the private
wing during working hours if and only if
she/he is not scheduled in the general ward;
8. Staff Deployment in the Private wings
1. The Hospital Management shall develop,
and get endorsement from the board, a
guideline containing professional
qualification and ethics criteria for
recruiting and assigning qualified persons
and make such criteria known to the
employees.
Page 2034 of 2280
ያስጸድቃል፣ ሠራተኞቹም መመሪያ
ዎችን እንዲያውቁት ያደርጋል፣
2. በሚጸድቀው መመሪያ መሰረት
የሆስፒታሉ የሕክምና ባለሙያዎች
በየተራ በግል የህክምና ዩኒቶች ውስት
ይመደባሉ፡፡
9. ተራፊ ሂሣብ ድልድል
በግል የሕክምና ዩኒቶች ከሚሰጡ
አገልግሎቶች የሚገኝ ገቢ ቢሮው
የሚያወጣውን መመሪያ ተከትሎ ቦርዱ
በሚያፀድቀው የድልድል ቀመር መሠረት
ለሆስፒታሉ እና በትርፍ ጊዜያቸው
በሥራው ተሳታፊ ለሆኑ ሠራተኞች
የሚከፋፈል ይሆናል፡፡ የድልድል መመሪያ
በሚዘጋጅበት ወቅት የግል ሕክምና
መስጫ ዩኒቱን ትርፋማነት መሠረት
አድርጎ ደረጃ በደረጃ እያደገ የሚሄድ
የክፍያ አሰራር ስልት መዘርጋት
ይኖርበታል፡፡
፲. የተራፊ ሒሣብ አጠቃቀም
1. ሆስፒታሉ ከግል የሕክምና መስጫ
ዩኒቶች እንቅስቃሴ የሚያገኘው ተራፊ
ሂሣብ በዋነኝነት የግል እና መደበኛ
የሕክምና መስጫ ክፍሎችን የጤና
አገልግሎ ለማሻሻል ያውላል፣
2. ከዚህ በላይ በተመለከተው ሳይወሰን
ከግል የሕክምና መስጫ ዩኒት የሚኝ
2. Health professionals will be deployed in
the private wing on rotation basis as per
the approved guideline.
9. Distribution of surplus
Revenue obtained from the services of the
private wing will be apportioned according
to a payment scheme to be approved by the
board between the hospital and staff who
devoted their part-time in the private wing.
The distribution guideline shall incorporate
a scheme of payment that increases
proportional to the rate of profitability of the
Private Wing.
10. Use of surplus
1. The surplus generated from the activities
of private wing shall principally be used to
improve the quality of health services in
both the private and general wards;
2. In addition to what is stated above the
surplus generated by Private Wing may be
used for purposes determined by the
hospital board, which includes:
Page 2035 of 2280
ተራፊ ሒሳብ በቦርዱ በሚሰጥ ውሳኔ
የሚከተሉትን ለሚጨምሩ አገልግሎ
ቶች እንዲውል ለማድረግ ይቻላል፣
ሀ/ የግል የሕክምና መስጫ ዩኒቱን
አገልግሎት ለማስፋፋት፣
ለ/ የዲያግኖስቲክ እና የማከም
አገልግሎት የሚሰጥባቸውን
የሆስፒታሉን ክፍሎት ለማሻሻል፣
ሐ/ የመደበኛ የሕክምና መስጫ ክፍሉች
አገልግሎ ጥራት ለማሻሻል፣
፲፩. የግል የሕክምና መስጫ ዩኒት አስተዳደር
1. የግል ሕክምና መስጫ ዩኒት አስተዳደር
በሆስፒታሉ የአስተዳደር ሠራተኞ
የሚታገዝ ሆኖ፣ ተጠሪነቱ ለሆስፒታሉ
ስራ አመራር የሆነ አስተባባሪ ይኖረዋል፣
2. የግል የሕክምና መስጫ ዩኒቱን
በበላይነትየሚመራው የሆስፒታሉ ስራ
አመራር ነው፡፡
፲፪. የሆስፒታሉ የሥራ አመራር ቦርድ
ተግባርና ኃላፊነት
የሆስፒታሉ የሥራ አመራር ቦርድ
1. ሆስፒታሉ የግል የህክምና መስጫ ዩኒት
ለማቋቋም የሚያቀርበውን ጥያቄ
መርምሮ ውሣኔ ይሰጣል፣
2. የግል የህክምና መስጫ ዩኒትን በጀትና
የተራፊ ሒሣብ ድልድልን መርምሮ
a) To expand the private wing services;
b) To improve the diagnostic and
therapeutic facilities of the hospital;
c) To improve the quality of service in
the general ward;
11. The management of Private Wing
1. The Private wing operations shall be
supported by the staff of the hospital and
shall have a coordinator who will report
to the Hospital Management
2. The Hospital Management shall oversee
the activities of the Private wing
12. Responsibility of the Hospital Board
The Board shall:
1. Review and decide on the proposal of a
hospital to start a private wing;
2. Review and approve the annual budget
and surplus distribution plan of the
Private wing;
13. Responsibility of the Hospital
Management.
Page 2036 of 2280
ያፀድቃል፡፡
፲፫. የሆስፒታሉ ስራ አመራር ኃላፊነት
1. የሆስፒታሉ የግል ሕክምና መስጫ ዩኒት
የሚሰጠውን የጤና አገልግሎት ዓይነት
በማጥናት ለቦርዱ የውሳኔ ሃሳብ
ያቀርባል፣
2. የግል የሕክምና መስጫ ዩኒቱን የዕለት
ተዕለት የሥራ እንቅስቃሴዎች
ይከታተላል፡፡
3. በግል የሕክምና መስጫ ዩኒት
የሚመደቡ የሕክምና መስጫ ዩኒት
የሚመደቡ የሕክምና ባለሙያዎችና
ሌሎች ሠራተኞች ምደባ ያጸድቃል፣
4. የግል የሕክምና መስጫ ዩኒቱን
የፋይናንስ እና የሥራ እንቅስቃሴ
ሪፖርት መርምሮ ለቦርዱ እንዲቀርብ
ያደርጋል፡፡
፲፬ . የአስተባባሪ ተግባር
የግል የህክምና መስጫ ዩኒት አስተባባሪ
1. በተለያዩ ክፍሎች የሚመደቡ ባለ ልዩ
ሙያ ሐኪሞችን ምደባ ያስተባብራል፣
2. የግል ሕክምና መስጫ ዩኒቱን ድጋፍ
ሰጪ ሠራተኞችን ያስተባብራል፣
3. የሕክምና ባለሙያዎች ለሰጡት
አገልግሎ ቦርዱ በሚያጸድቀው
The Hospital management shall:
1. Study the type of services that may be
rendered by the Private wing and submit
its proposal to the Board for its approval;
2. Monitor the day to day functioning of the
private wing;
3. Approve the assignment of health
professionals and other support staff to
the Private Wing;
4. reviews the financial and activity reports
of the private wing and submit the same
to the Board;
14. responsibility of the Private Wing
Coordinator
The coordinator of the Private wing shall:
1. Coordinate the deployment of specialist to
different departments;
2. Coordinate the support staff in the Private
wing;
3. Ensure that health personnel get their
remuneration on monthly basis based on
the directive to be issued by the Board;
Page 2037 of 2280
መመሪያው መሠረት ሊከፈላቸው
የሚባውን ሂሳብ በየወሩ ማግኘታቸውን
ያረጋግጣል፣
4. የግል የሕክምና መስጫ ዩኒቱን የሥራ
ዕቅድ ያዘጋጃት፣ በትክክል ሥራ ላይ
መዋሉን ያረጋግጣል፣
5. የፋይናንስ እና የሕክምና መረጃዎች
የሚዛመዱ መሆኑን፣ ለገቢ ምንጭ
የሆነው አገልግሎ በማን እንደተሰጠና
ቀጥተኛ ወጪው ምን ያህል እንደሆነ
ያረጋግጣል፣
6. በግል የህክምና መስጫ ዩኒቱ አገልግሎ
ላይ ከተጠቃሚዎችና ከሠራተኞች
የሚቀርቡ አስተያየቶችን ይመረምራል፣
የእርምት አስተያየት ለሆስፒታሉ ሥራ
አመራር ያቀርባል፣
7. የግል የሕክምና መስጫ ዩኒቱን
የፋይናንስ እንቅስቃሴ ይከታተላል፣
ተገቢው የሂሣብ ሰነድ የተያዘ መሆኑን
ያረጋግጣል፣
8. በሂሳብ ሹሙ የተዘጋጀውን የሂሣብ
መግለጫ መርምሮ ለሆስፒታሉ ሥራ
አመራር ያቀርባል፣
9. የየወሩን፣ የሩብ ዓመት እና ዓመታዊ
ሪፖርት በማዘጋጀት ለሆስፒታሉ ስራ
አመራር ያቀርባል፣
4. Prepare work plan for the Private Wing
and follows on its proper implementation;
5. Ensure that the financial and medical
records are linked and it reflects by whom
the revenue is generated and how much
direct cost is involved;
6. Review feedbacks from clients and the
staff on the service provided and
proposes corrective measures to the
hospital management;
7. Follows up on the financial performance
of the private wing and make sure that
appropriate financial records are made;
8. Reviews financial statements prepared
by the finance officer and submits it to
the hospital management;
9. Prepares monthly, quarterly reports and
submits it to the hospital management;
15. Finance and property
The financial management system and
property administration of the Private Wing
shall be laid down in directive to be
Page 2038 of 2280
፲፭ . ሂሣብና ንብረት
የግል የሕክምና መስጫ ዩኒቱን የሂሣብ
አያያዝ እና የንብረት አመዘጋገብ
የሚወሰን ዝርዝር መመሪያ ተዘጋጅቶ
በቦርዱ ሲጸድቅ ሥራ ላይ ይውላል፡፡
፲፮
፲፯. የማስፈጸም አቅም መፍጠር
ሆስፒታሎች በዚህ ደንብ ውስጥ
የተካተቱትን ተግባራት ለመፈፀም
የሚያስችላቸውን የሰው ሀይልና
አደረጃጀት አቅም መፍጠር አለባቸው፡፡
፲፰. የደንቡ ተፈጻሚነት ወሰን
ይህ ደንብ ተለይቶ እስካልተገለጸ ድረስ
ተፈፃሚ የሚሆነው በመንግሥት ጤና
ተቋማት ብቻ ነው፡፡
፲፱. መመሪያ ስለማውጣት
የጤና ቢሮው ለዚህ ደንብ አፈፃፀም
የሚያግዙ መመሪያዎችን ያወጣል፡፡
፳. ተፈፃሚነት ስለማይኖራቸው ሕጎች
ከዚህ ደንብ ጋር የሚቃረን ማንኛውም
ደንብ ወይም መመሪያ በዚህ ደንብ
በተጠቀሱ ጉዳዮች ላይ ተፈጻሚነት
አይኖረውም፡፡
፳፩. ደንቡ የሚፀናበት ከዛሬ ህዳር 22 ቀን
ጀምሮ የፀና ይሆና፡፡
approved by the Board
16.
17. Capacity to implement
The hospitals shall have the necessary
manpower and administration capacity to
implement activities embodies in this
regulation.
18. Scope of the Regulation:
This regulation, unless specified, will be
applicable on government health facilities
only.
19. Power to issue directives
The Bureau may issue directive for the
proper implementation of this regulation.
20. Inapplicable Laws
Any regulation, directive or rule, which is
inconsistent with this Regulation, shall
have no effect with respect to matters
provided herein.
21. Effective data
This Directive shall enter into force as of
1st December, 2005
Hailemariam Desalegn
Page 2039 of 2280