41
በበበበ በበበበ በበበበ በበበበበ በበበበበበበ በበበበ በበበበ በበበበ በበበበበ

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የዩኒቨርሳል የገጠር መንገድ አክሰስ ኘሮግራም

  • Upload
    dana

  • View
    85

  • Download
    0

Embed Size (px)

DESCRIPTION

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የዩኒቨርሳል የገጠር መንገድ አክሰስ ኘሮግራም. የኘሮግራሙ ይዘት. ክፍል አ ንድ መግቢያና ዳራ ክፍል ሁለት የተዘጋጁ ጽሑፎች ቅኝት ክፍል ሶስት የዋና ዋና ችግሮች ትንተና ክፍል አራት የኘሮግራም ቀረፃ ክፍል አምስት ማጠቃለያና አስተያየት. መግቢያና ዳራ. ለልማት እጅግ አስፈላጊ ከሆኑት ጉዳዮች አንዱ አስተማማኝ የመሠረተ ልማት አገልግሎት እንደሆነ ይታወቃል ፡፡ - PowerPoint PPT Presentation

Citation preview

Page 1: በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የዩኒቨርሳል የገጠር መንገድ አክሰስ ኘሮግራም

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊመንግስት የዩኒቨርሳል የገጠርመንገድ አክሰስ ኘሮግራም

Page 2: በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የዩኒቨርሳል የገጠር መንገድ አክሰስ ኘሮግራም

የኘሮግራሙ ይዘት• ክፍል አ ንድ

መግቢያና ዳራ

• ክፍል ሁለት

የተዘጋጁ ጽሑፎች ቅኝት

• ክፍል ሶስት

የዋና ዋና ችግሮች ትንተና

• ክፍል አራት

የኘሮግራም ቀረፃ

• ክፍል አምስት

• ማጠቃለያና አስተያየት

Page 3: በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የዩኒቨርሳል የገጠር መንገድ አክሰስ ኘሮግራም

መግቢያና ዳራ

• ለልማት እጅግ አስፈላጊ ከሆኑት ጉዳዮች አንዱ አስተማማኝ የመሠረተ ልማት አገልግሎት እንደሆነ ይታወቃል፡፡

• በጥበብ በተሳሰረው ዓለም ውስጥ ብቁ ተወዳዳሪ መሆን የሚቻለው ቀልጣፋ የመሠረተ ልማት አገልግሎት ሲኖር ብቻ

ነው፡፡

• በተለይ የመንገድ መሠረተ ልማት የገበያ አድማሱን ለማስፋት፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም አስተዳደራዊ

አገልግሎቶችን እንዲፋጠን ለማድረግና የህዝቡ ኑሮ እንዲሻል ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋል፡፡

Page 4: በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የዩኒቨርሳል የገጠር መንገድ አክሰስ ኘሮግራም

• በሃገሪቱ ያለው የመንገድ አውታር ስርጭት በዝቅተኛ ደረጃ የሚገኝ ሲሆን የክልላችንም በተመሳሳይ ዝቅተኛ

ነው፡፡

• የክልሉን የመንገድ አውታር ለማስፋፋት ጥረት መደረጉ ቢታወቅም በሽፋኑም ሆነ በጥራቱ በሚጠበቀው ደረጃ

ነው ማለት አይቻልም፡፡

• በመሆኑም ይህን ችግር ለመፍታት ኘሮግራም ቀርጾ ወደ ተግባር መግባት አስፈላጊ ሆኗል፡፡

Page 5: በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የዩኒቨርሳል የገጠር መንገድ አክሰስ ኘሮግራም

መግቢያና ዳራ

• በአሁኑ ወቅት የክልሉ የመንገድ ኔት ወርክ 7619.9 ኪ. ሜትር ያህል ነው

• በክልሉ ከሚገኘው ጠቅላላ የመንገድ ኔት ወርክ 3952 ኪ. ሜ በኢመባ ስር የሚተዳደር ሲሆን ቀሪው 3665.9 ኪ. ሜ ደግሞ

የክልሉ የገጠር መንገዶች ባለሥልጣን የሚያስተዳድረውነው፡፡

• የክልሉ የመንገድ ጥግግት /Road densisty Ratio/ 48 ኪ. ሜ በ1000 ካ.ኪ. ሜ ነው፡፡

• የጥገና ሽፋኑ 16665 ኪ. ሜ የደረሰ ሲሆን የሚከናወነውምበ4 የጥገና ጽ/ ቤቶች አማካይነት ነው፡፡

Page 6: በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የዩኒቨርሳል የገጠር መንገድ አክሰስ ኘሮግራም

የኘሮግራሙመነሻዎች• ገጠርን መሠረት ያደረገው የልማት ስትራቴጂ

- የገጠር ልማትን ማፋጠን

- የገጠርና የከተማ ትስስር

- የግብርና እና ኢንዱስትሪ ልማት ትስስር

• በገበያ የተቃኘው የኢኮኖሚ ሥርዓት

- ዓለም አቀፍ ትስስር (Globalization) ማጠናከር እና ተወዳዳሪ ሆኖመገኘት፤

- ብቃት ያለው አቅርቦትና ምርት ማጓጓዝ

• የእስከአሁኑ የገጠር መንገድ ግንባታ ሂደት

• የገጠር ወጣቶችና ሴቶች ፖኬጃቸውን ተከትሎ በልማቱ የሚያሳተፍስትራቴጂ

• በሰው ጉልበት የገጠር መንገድ ለመገንባት የሚሰጠውሥልጠና

• የምዕተ ዓመቱን (Millenium) የልማት ግብ የማሳካት ግዴታ፤

• በገጠር መንገድ ግንባታ የአነስተኛ ኮንትራክሽን እና የአማካሪ ተቋማት ተሳትፎ አዋጭነት

Page 7: በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የዩኒቨርሳል የገጠር መንገድ አክሰስ ኘሮግራም

የኘሮግራሙ ዓላማ

• የገጠር መንገድ ልማትን ለማስፋፋት በመስኩ የጥቃቅንና አነስተኛ የመንገድ ሥራ ተቋማትን ለመፍጠርና ለመደገፍ የሚያስችል የጋራ ኘሮግራም

በመቅረጽ በቀጣይ አምስት ዓመታት ሁሉንም የክልሉ የገጠር ቀበሌዎች ደረጃቸውን በጠበቁ የክረምት ከበጋ

ገጠር መንገዶች ማገናኘት እና አስፈላጊውን ጥገና በማድረግም በኢኮኖሚ ልማት እንቅስቃሴ ብቁ

ተወዳዳሪ መሆን የሚቻልበትን ሁኔታ ማመቻቸት የኘሮግራሙ የተጠቃለለ ዓላማ ነው፡፡

Page 8: በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የዩኒቨርሳል የገጠር መንገድ አክሰስ ኘሮግራም

ክፍል ሁለት የተዛማጅ ጽሁፎች ቅኝት

2.1 የሰው ጉልበት ቴክኖሎጂ

- ምንነት

- የተለያዩ አገሮች ልምድና ተሞክሮ / ጋና፣ ኬኒያና ታንዛኒያ/- በአገራችን በተለይ በክልላችን ያለው ተሞክሮ

2.2 የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት

- ምንነት

- ለከተማና ገጠር ልማት ትስስር ለድህነት ቅነሳ ያላቸውጠቀሜታ

2.3 የማስፈፀሚያ / የመፈፀም አቅም ምንነትና ይዘት

Page 9: በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የዩኒቨርሳል የገጠር መንገድ አክሰስ ኘሮግራም

የሰው ኃይል ቴክኖሎጂ

• ምንነት

• በካባድ ማሽን ዕገዛ የሚሰራን በቀላል ማሽኖች በቀላሉ በአካባቢ በሚገኙ የእጅ መሣሪያዎች በመጠቀም

መሠረተ ልማቶችን ማስፋፋት በተለይም መጋቢ የገጠር መንገዶችን የመገንባትና ነባሮችንም የመጠገን ሥራ

መስራት ማለት ነው፡፡

Page 10: በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የዩኒቨርሳል የገጠር መንገድ አክሰስ ኘሮግራም

የኘሮግራሙ አስፈላጊነት

• የክልሉን በአጠቃላይ እና የገጠሩን በተለይ ማህበራዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ እድገትን ለማፋጠን ይረዳል

• የክልሉን ገጠሮች ከሃገሪቱ የኢኮኖሚ ማዕከሎች እና ከዓለም ገበያ ጋር ለማስተሳሰር አንድ አገር አቀፍ የመንገድ መረብ ይፈጥራል፡፡

• ገጠሩንና ግብርናውን ማዕከል ያደረገው የልማት ስትራቴጂ ገጠሩን ከከተማ፣ ግብርናን ከኢንዱስትሪ ጋር እያስተሳሰረና ትስስሩንም

የበለጠ እያጠናከረ እንዲሄድ ያስችላል፡፡

• ከግብርና ውጭ ያሉትን የገጠር ወጣቶች እና ሴቶች በጥቃቅንና አነስተኛ የኮንሰትራክሸን ተቋማት በማደራጀት ወደ ኢንዱስትሪው እንዲገቡ የሚያስችላቸውን ሁኔታ ያመቻቻሉ፡፡

Page 11: በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የዩኒቨርሳል የገጠር መንገድ አክሰስ ኘሮግራም

• የሰው ጉልበት ቴክኖሎጂን ለመጠቀም ምቹ ሁኔታዎች ከሚባሉትመካከል

- በቂ የግንባታ ጥሬ ዕቃዎች በአካባቢው መገኘት፤

- ተፈላጊው የሰው ጉልበት በተመጣጣኝ ዋጋ መገኘት፤

- ቴክኖሎጂውን ለማስፋፋት መንግስት ያለው ቁርጠኝነት

- በዘርፉ ክህሎት ያላቸው ዝቅተኛ ተቋራጮች መገኘት ሊጠቀሱ ይችላሉ

Page 12: በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የዩኒቨርሳል የገጠር መንገድ አክሰስ ኘሮግራም

በሰው ኃይል ቴክኖሎጂ የሌሎች አገሮች ተሞክሮ

• በሰው ኃይል ቴክኖሎጂ ጥሩ ልምድ ያላቸውን የአፍሪካ አገሮችን / ጋና፣ ኬኒያና ታንዛኒያ/ ተሞክሮ ለመዳሰስ

ተሞክሮ

• የተገኙ ልምድና ተሞክሮዎች ቴክኖሎጂውን በመጠቀም የገጠር መንገዶችን

በፍጥነትና በጥራት ለመገንባት ፤ መልሶ ለመገንባትና ለመጠገን የተለየና ብቁ የሆነ አደረጃጀት በመፍጠር

ብቃት ያለው አመራርና ተታታይ የሆነ የሱፐርቪዥን አገልግሎት መስጠት እንደሚያስፈልግ፤

Page 13: በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የዩኒቨርሳል የገጠር መንገድ አክሰስ ኘሮግራም

• በዋናነት የገጠር መንገድን በባለቤትነት የሚመራው መ/ ቤትና ሌሎች አጋር አካሎች ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጡት እንደሚገባ፤

• ምንም እንኳ ቴክኖሎጂው ወጭ ቆጣቢ ቢሆንም የመንገድ ሥራ በባህሪው ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቅ በመሆኑ

ቴክኖሎጂውን ለማስፋፋት በበጀት አመዳደብ የመንግስት ቁርጠኝነት ከፍተኛ መሆን እንዳለበት

• ኮንትራክሮች ወደ ሥራ ከመግባታቸው በፊት የንድፈ ሃሳብና የተግባር ሥልጠና የሙከራ የኮንትራት ሥልጠና መስጠት

እንደሚገባ

• ለአንድ ኢንተርኘራይዝ የሚያስፈልገው የሰው ኃይል ብዛት እንደ ሥራው ሁኔታ ከፍና ዝቅ ሊል እንደሚችል

Page 14: በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የዩኒቨርሳል የገጠር መንገድ አክሰስ ኘሮግራም

• የሚደራጁ ኢንተርኘራይዞች ሥልጠና እንዳጠናቀቁ ወዲያውኑ ወደ ሥራ እንዲገቡ መሣሪያዎች በኪራይ ወይም በብድር

የሚሟሉበት መንገድ ቀድሞመመቻቸት እንዳለበት፤

• ቴክኖሎጂውን ሙሉ በሙሉ ተግባራዋ ለማድረግ ኘሮጀክቶች በሚካሄዱባቸው አካባቢዎች የቀን ሠራተኛ ስለመገኘቱ የዳሰሳ

ጥናት ማድረግ እንደሚገባ፤

• የኮንስትራክሽን መሣሪያዎችን በተመለከተ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መሣሪያዎችን ይጠቀሙ እንደነበር፤

ትራክተር ከነተሳቢው፤ የእጅ ጋሪ፣ መጠቅጠቂያ፣ የውሃ ሞተር፣ ቫይቭሬተር፣ ሞተር ሳይክል፣ የድልድይ ሞልዶች፣ የውሃ

ኮንቴነር፣ የውሃ ልክ፣ መጥረቢያ፣ አካፋ፣ ገጀራ፣ ዛቢያ፣ ማቶክ፣ ዶማ፣ ሬክ፣ መረጃ፣ መጋዝና ጃሎ

Page 15: በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የዩኒቨርሳል የገጠር መንገድ አክሰስ ኘሮግራም

የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት• ምንነት ምንም እንኳ ወጥ የሆነ አሰያየምና መስፈርት

ባለመኖሩ ከአገር አገር የሚለያይ ቢሆንም የንግድ ድርጅቶችን በስራው ዓይነት፣ መጠንና ጥራት መሠረት

• ጥቃቅን

• አነስተኛ• መካከለኛ ተብለው ይከፈላሉ በአገራችንም በተመሳሳይ የሠራተኛ ብዛትን ሽያጭን፣

ንብረትን ወይም ካፒታልንና የተጣራ ግኝትን መሠረት በማድረግ የንግድ ድርጅቶን በ3 ክፍሎች በመክፈል

ወደ ተግባር ተገብቷል፡፡

Page 16: በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የዩኒቨርሳል የገጠር መንገድ አክሰስ ኘሮግራም

ጥቃቅን የንግድሥራ የሚባለው- በግል ይዞታና በግል የሚንቀሳቀሱ- እስከ 20,000 ብር ካፒታል ያላቸው- አነስተኛ የገበያ ድርሻ ያላቸው- ከ5 የማይበልጡ ወይም ያነሱ ሠራተኛ ያሏቸው አነስተኛ የንግድሥራ- የተከፈለ ካፒታላቸው ከ20 ሺህ ብር እስከ 500 ሺህ ብርየሆነ

- ከ6-49 ሠራተኛ ያሏቸው፡፡

Page 17: በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የዩኒቨርሳል የገጠር መንገድ አክሰስ ኘሮግራም

• መካከለኛ የንግድሥራ የተከፈለ ካፒታላቸው ከብር 500 ሺህ በላይ የሆነናከ50-99 ሠራተኞች ያሏቸው ሲሆኑ ከ100 በላይ

ሠራተኞች ያሏቸው ደግሞ ከፍተኛ ናቸው፡፡

• በክልላቸው ያለው ሁኔታ ተመሳሳይ ሲሆን ከላይ የተገለፀው እንዳለ ሆኖ ጥቃቅንና አነስተኛ የንግድ

ሥራዎች ከፍተኛ የቴክኖሎጂና የምክር አገልግሎት ተቋማትን አይጨምርም፡፡

Page 18: በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የዩኒቨርሳል የገጠር መንገድ አክሰስ ኘሮግራም

የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማትአስፈላጊነት

• በአንስተኛ የመነሻ ካፒታል ሊቋቋሙመቻላቸው

• ብዙ የሰው ኃይል የማሰማራት አቅማቸው

• በከፊል ለሰለጠነውና ላልሰለጠነው የህብረተሰብ ክፍል የሥራ ዕድልመፍጠራቸው

• ቀላልና ያልተወሳሰበ ቴክኖሎጂመጠቀማቸው

• አብዛኛው የሃገር ውስጥና የአካባቢ ምርት በጥሬ ዕቃነት መጠቀማቸው

• የውጭምርቶችን በመተካት ረገድ የማይናቅ ሚና ያላቸው መሆኑ

• ለመካከለኛና ትላልቅ ኢንዱስትሪዎች / ተቋማት በግብዓትነት የሚያገለግሉ የጥሬ ዕቃዎች ምንጭመሆናቸው

• በገበያ ውስጥ የተወዳዳሪነት ስሜትን ማሳደራቸው

• ለፍትሃዊ የገቢ ክፍፍል መመቸታቸው

• ለልማታዊ ባለሃብት ምንጭመሆናቸው

Page 19: በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የዩኒቨርሳል የገጠር መንገድ አክሰስ ኘሮግራም

የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ችግሮች

• በዘርፉ ላይ የሚታዩ አሉታዊ አመለካከቶች / በሁሉም ደረጃዎች ግልጽ የሆነ ግንዛቤ አለመኖር/

• የጥሬ ዕቃዎች እጥረትና በመጠን አለመሟላት

• የብድር አቅርቦት ችግር

• የመስሪያና መሸጫ ቦታ አለመመቻቸት፤

• በገበያ ውስጥ ተወዳዳሪ መሆን አለመቻል ወዘተ ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡

Page 20: በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የዩኒቨርሳል የገጠር መንገድ አክሰስ ኘሮግራም

የማስፈፀምና የመፈፀም አቅም ግንባት

• የማስፈፀም አቅም ግንባታ ይዘት እየተቀረፀ ካለው ኘሮግራም አኳያ ሲታይ የሚከተሉትን ያካተተ መሆን

ይኖርበታል፡፡ ተቋማቱን ከማደራጀት የሰው ኃይል በብቃት ከማፍራት የአሰራር ደንቦችንና መመሪያዎችን በተጣጠመና አመች

በሆነ መንገድ ከማሻሻልና ከመቅረጽ

Page 21: በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የዩኒቨርሳል የገጠር መንገድ አክሰስ ኘሮግራም

ክፍል ሦስት የችግሮች ትንተና

የዋና ዋና ችግሮች ትንተና

• የገጠር መንገድ ልማት

• የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ሥልጠና

• የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ልማት

Page 22: በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የዩኒቨርሳል የገጠር መንገድ አክሰስ ኘሮግራም

3.1 የገጠርመንገድ ልማት የበጀት እጥረት የሰለጠን የሰው ኃይል እጥረት የዝቅተኛ ደረጃ ሌበር ቤዝ ቴክኖሎጂ ኢንተርኘራይዞች በዘርፉአለመሰማራት

በመንገድ ግንባታና ጥገና የህ/ ሰቡ ተሳትፎና ግንዛቤ ደረጃ አናሳመሆን

የኮንስትራክሽን መሳሪያዎች እጥረትና ያሉትም ያረጁ መሆን የክልሉ ተፈጥሮአዊ መሬት አቀማመጥ ለመንገድ ሥራ አመቺአለመሆን

አብዛኛው የቀበሌ መንገዶች የጥራት ደረጃቸው ዝቅተኛና ዲዛይን የሌላቸው መሆኑና ክረምት ከበጋ የማያገለግሉ መሆናቸው

የገጠር መንገዶች በባለቤትነት / በቋሚነት ተረክቦ ተገቢውን ጥገናና አንክብካቤ የሚያደርግላቸው አካል አለመኖር

የኮንስትራክሽን መሣሪያዎችን ማኔጅመንት እና በአግባቡ የመጠቀምችግር

Page 23: በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የዩኒቨርሳል የገጠር መንገድ አክሰስ ኘሮግራም

3.2 ጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ተፈላጊ ዕቃዎችና መሣሪያዎችን በተሟላ መልኩ

ማግኘት አለመቻል የተሟላ የቴክኒክና የሥራ አመራር ሥልጠና አለማግኘት የባለድርሻ አካላት ተቀናጅቶ አለመስራት የግንዛቤ ማነስ የተሟላ የብድር አገልግሎት አለማግኘት የጥራት ማነስ የዘመናዊ ቴክኖሎጂመረጣ፣ ትውውቅ ስርጭት ስርፀትእጥረት

የገበያ መረጃ አለማግኘት /አለማሟላት

Page 24: በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የዩኒቨርሳል የገጠር መንገድ አክሰስ ኘሮግራም

3.3 የቴ/ ሙያማስ/ ተቋማት ልማት የትብብር ሥልጠና አለመጠናከር የማሰልጠኛ ተቋማት የሚሰጧቸው ሥልጥናዎችውስነት

የማሠልጠኛ መሣሪያዎች እጥረት /አለመኖር የኘሮሞሸን ሥራ አለመጠናከር የተባባሪ መ/ ቤቶች የክትትልና ድጋፍ ችግር

ጠቅለል ባለ መልኩ ከላይ የተዘረዘሩ ችግሮችን ለመቅረፍ የሚያስችሉ የመፍትሔ እርምጃዎችንና

አቅጣጫዎችን ማስቀመጥ ያስፈልጋል

Page 25: በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የዩኒቨርሳል የገጠር መንገድ አክሰስ ኘሮግራም

ክፍል አራት ኘሮግራም ቀረፃ

• ይዘት ታሳቢዎች በኘሮግራሙ ዓመታት /2003-2007 የሚከናውኑ

ተግባራት የልማት ዕቅድ

• የመንገድ ልማት ዕቅድ

• የቴክኒክ ሙያ ት/ስ/ ልማት ዕቅድ

• የጥ/አ/ት/ ልማት እቅድ

Page 26: በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የዩኒቨርሳል የገጠር መንገድ አክሰስ ኘሮግራም

የሥልጠናና የጥ/አ/ የማስፈፀሚያ በጀት ግምትናምንጭ

የባለድርሻ አካላት ተግባርና ኃላፊነት የአፈፃፀም አቅጣጫዎች የክትትልና ግምገማ ስርዓትስጋቶች የኘሮግራሙ ዘላቂነት የመድበለ ዘርፍ ጉዳዩች የትኩረት አቅጣጫ

ኘሮግራሙ በመንገድ ልማት፣ በቴ/ሙያ/ ሥልጠናናየጥ/አ/ ኢንተርኘይዞች ልማት ላይ የተመሠረቱ

የተሳሰሩና የተቀናጁ ሥራዎችን አካቶ የያዘ ነው፡፡

Page 27: በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የዩኒቨርሳል የገጠር መንገድ አክሰስ ኘሮግራም

ኘሮግራሙን ለመቅረጽ የተወሰዱታሳቢዎች

• በግንባር ቀደምነት ኃላፊነቱን በመውሰድ የጋራ ኘሮግራሙን የቀረፁት አካላት በትግበራው ወቅት

በቅርብ በመገናኘትና በመቀናጀት የተናጥልና የጋራ የሥራ ድርሻቸውን ሙሉ በሙሉ እንደሚወጡ፤

• የወረዳ አስተዳደሮች ለታቀዱት ሥራዎች ማስፈፀሚያ በቂ በጀት እንደሚመድቡና ተጠቃሚውን ህብረተሰብ

በማስተባበርም ለዕቅዱ ማስፈፀሚያ የሚሆን ገቢእንደሚያሰባስቡ፤

• መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችና ተባባሪ አካላት ለመንገድ ሥራው ድጋፍ እንደሚያደርጉና ይህንን

በማስተባበር በኩል ሰፊ ጥረት እንደሚደረግ

Page 28: በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የዩኒቨርሳል የገጠር መንገድ አክሰስ ኘሮግራም

• በተለያዩ መልኩ በጥ/አ/ ተቋማት የሚደራጁ ወጣቶችና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ሥራው አምነውበትና ተገቢውን ግንዛቤ ይዘው እንደሚንቀሳቀሱ

• በቴ/ሙ/ትም/ ሥልጠና ሥር የሚገኙ ኮሌጆች ሥልጠናዎችን በተሟላ መንገድና በተያዘው የጊዜ ገደብ እንደሚሰጡና

በቀጣይም ለውጤታማነቱ ተገቢውን ጥራት እንደሚያደርጉ፤

• ለኮሌጆች የሚያስፈልገው የሥልጠና መሳሪያ ግዥ በተቀመጠውመርሐ ግብር መሠረት ተፈጽሞ እንደሚሟላ

• በተለያዩ መ/ ቤቶች በኮንስትራክሽንና ተያያዥ ሙያዎች ተቀጥረው የሚሰሩ በዘርፉ ጥሩ ልምድና ተሞክሮ ያላቸው ባለሙያዎች እንደሚገኙ፤

Page 29: በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የዩኒቨርሳል የገጠር መንገድ አክሰስ ኘሮግራም

• በክልሉ ከሚገኙ ኮሌጆች በተለያዩ የኮንስተራክሽንና ተያያዥ ሙያዎች ተመርቀው ከሚወጡ ባለሙያዎች ማግኘት እንደሚቻል

• የግንባታ መሣሪያዎች ግዥ በተያዘው መርሐ- ግብር መሠረት እንደሚፈፀምና ለሚደራጁ ኢንተርኘራይዞች በሊዝ/ በብድር እንደሚሰራው፤

• ለዕቃዎችና መሣሪያዎች ግዥና ለሥራ ማስኬጃ የሚያስፈልገው በጀት በብድር ሊሟላ እንደሚችል

• አንድ የሰው ኃይል ቴክኖሎጂ ኘሮጀክት በዓመት በአማካይ 10 ኪ. ሜ መንገድ መስራት እንደሚችል

• ለአንድ ኪ. ሜትር አዲስ የጠጠር መንገድ ግንባታ ብር 500,000 በጀትእንደሚያስፈልገው

• የተደራጁ ኢንተርኘራይዞች ከግንባታ ጐን ለጐን የጥገና ሥራውን እንደሚያከናውኑ፤

• አንድ መንገድ ከተገነባ በኋላ ደግሞ ወቅታዊ ጥገና እንደሚደረግለት

• ኢንተርኘራይዞቹ ከሚያደርጉት የመንገድ ጥገናና ግንባታ ሥራ ጐን ለጐን ለሌንግዝ ማን የጥገና ስልትም መንገዶች አስተማማኝ ጥገና

እንደሚደረግላቸው፡፡

Page 30: በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የዩኒቨርሳል የገጠር መንገድ አክሰስ ኘሮግራም

• ለመደበኛ ጥገና በኪ. ሜትር 20,000 ፣ ለወቅታዊ ጥገናበኪ. ሜትር ብር 60,000 እንዲሁም ለሰው ርዝመት( ሌንግዝ ማን ጥገና ቴክኖሎጂ) በኪ. ሜትር በዓመት

ብር 4,000 እንደሚፈልግ የፌዴራል የሚመለከታቸውመ/ ቤቶች የሚያደርጉት ድጋፍና የሥራ ትብብር

የተጠናከረ እንደሚሆን

• የክልሉ መንግስት፣ ምግብ ዋስትና፣ ረጂ ድርጅቶች፣የህ/ ሰቡ ለሚፈለገው በጀት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ

እንደሚያደርጉ፣ ወዘተ የሚሉትን ታሳቢ በማድረግ በ5 ዓመታት የሚከናወኑ ሥራዎች እንደሚከተለው

ቀርበዋል፡፡

Page 31: በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የዩኒቨርሳል የገጠር መንገድ አክሰስ ኘሮግራም

የገጠር መንገድ ልማት

ጥቅል ዓላማ የቀበሌ መዳረሻ መንገድ ግንባታ እንክብካቤና ጥገና

ሥራዎችን በማከናወን ሁሉንም የገጠር ቀበሌዎች ክረምት ከበጋ በሚያገለግሉ መንገዶች መገናኘት በዚህም ለገጠር ህብረተሰብ የገበያና የማህበራዊ

አገልግልቶችን በማዳረስ የህዝቡን የኑሮ ደረጃ ማሻሻልነው፡፡

Page 32: በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የዩኒቨርሳል የገጠር መንገድ አክሰስ ኘሮግራም

ጥቅል ግብ በኘሮግራሙመጨረሻ ዓመት 21450 ኪ. ሜትር መንገድ መገንባት ተቋራጮችን ጨምሮ 18304 ያህል ባለሙያዎችን ማሰልጠን 25346 የሥራ ዕድል መፍጠር የሚያስችሉ 551 የግንባታ ሥራ

ተቋራጮች እና አማካሪዎች እንዲደራጁ ማድረግ የገጠሩ ህብረተሰብ በመንገድ ሥራው ኘሮጀክት ላይ ማሳተፉ

(20%) የቴክኒክ ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማትን በስፋት በመጠቀም የገጠር

መንገድ ግንባታ፤ ጥገናና የማስተዳደር አቅም ይፈጥራል፡፡ የግብርና ምርቶችንና የኢንዱስትሪ ውጤቶችን ገበያና ግብይትለማሳለጥ

የገጠሩን ህብረተሰብ የኑሮ ደረጃ ለማሻሻልና ድህነትን ለመቅረፍ

Page 33: በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የዩኒቨርሳል የገጠር መንገድ አክሰስ ኘሮግራም

የገጠር መንገድ ልማት

• በኘሮግራሙ የመነሻ ሰነድ ላይ በግልጽ እንደሚከተለው በሚቀጥሉት 5 ዓመታት ሁሉንም

የክልሉ የገጠር ቀበሌዎች በክረምት ከበጋ መንገዶች ከዋና መንገዶች ለማገናኘት ብሎም ባለድርሻ አካላት

በመቀናጀትና የጋራ ኘሮግራም በመቅረጽ መንቀሳቀስ እንደሚገባ ይታመናል፡፡

• በሚቀጥሉት የኘሮግራም ዓመታት የሚሰሩ የመንገድ ልማት ሥራዎች ከተገመቱት ከክልሉ የገንዘብና

ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የተገኘውን መረጃ መሠረት በማድረግ ሲሆን በዚህም መሠረት በክልሉ 128

የገጠር ወረዳዎች 3113 ቀበሌዎች እንደሚገኙ በመነሻነት ተወስዷል፡፡

Page 34: በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የዩኒቨርሳል የገጠር መንገድ አክሰስ ኘሮግራም

• በባለሥልጣኑ የዕቅድ፣ ክትትልና ግምገማ የሥራ ሂደት ከተሰበሰቡ መረጃዎች በድምሩ 9432. ኪ. ሜትር የበጋ መንገዶች

በወረዳ የመንገድ ቴክኒሻያኖች አማካይነት የተሰራ መሆኑንና በዚህም 1369 ቀበሌዎችን ተጠቃሚ ማድረግ እንደተቻለ የታወቀ

ሲሆን ይህንኑ መረጃ ለመነሻነት በመጠቀም በኘሮግራሙ ዓመታት የሚሰሩ መንገዶችን ለመገመት ተሞክሯል፡፡

• የተገኘው መረጃ መሠረት በማድረግ የሚገነቡ መንገዶችተለይተዋል

በጠቅላላ 21450 ኪ. ሜትር መንገድ ይገነባል አንድ ኢንተርኘራይዝም በዓመት በአማካይ 10 ኪ. ሜትር

እንደሚሰራ ይጠበቃል፡፡ አዲስ የሚደራጁ ኢንተርኘራይዞች ብዛት 551 ሲሆኑ የመደራጃ

ጊዜያቸውም ከ2003-2007 ዓመታት ውስጥ ይሆናል፡፡

Page 35: በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የዩኒቨርሳል የገጠር መንገድ አክሰስ ኘሮግራም

በአምስት ዓመቱ በመደበኛና በወቅታዊ ጥገና 34640 ኪ. ሜትር መንገዶች ጥገና እንደሚያገኙ ይጠበቃል፡፡

ለአንድ ኢንተርኘራይዝ የሰው ኃይል ፍላጐት የተገመተው 33 ሲሆን የትምህርት ዝግጅታቸው

ዲኘሎማ ከደረጃ 3 እስከ ደረጀ 4 እና ሰርተፊኬትን ያካትታል ከዚህ በተጨማሪም 13 የሚደርስ የድጋፍ

ሰጭ ሠራተኛ ያስፈልጋል፡፡ የአንድ ኢንተርኘራይዝ የመሳሪያ ፍላጉት 34 የሚደርስ

የመሳሪያ ዓይነትና ጠቅላላ የዋጋ ግምት እስከ ብር9,271,698 እንደሚደርስ ይገመታል፡፡

Page 36: በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የዩኒቨርሳል የገጠር መንገድ አክሰስ ኘሮግራም

• ኘሮግራሙን ለማስፈፀም በድምሩ ብር 17.2 ቢሊዮን የሚያስፈልግ ሲሆን ይህም

- 65% ለመንገድ ግንባት፤

- 31.22 % ለመሣሪያ ግዥ ፤

- 3.40 % ለመንገድ ጥገና ፤

- 0.38 % ለአቅም ግንባታ ፤

Page 37: በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የዩኒቨርሳል የገጠር መንገድ አክሰስ ኘሮግራም

የወጭ ዝርዘሩ እንደሚከተለው ተጠቃሎ ቀርቧል

የወጭ ዓይነት

የሚያስፈልግ

በጀት ድምር

በሚሊዮን ብር

ምርመራ

ለአቅም ግንባታ 3.10 ከ9 ኮሌጆችና ከኤጀንሲው ሁለት ሁለት

• ለአሰልጣኞች ሥልጠና 0.15

• ለመምህራን ሥልጠና 0.25

• ለተሞክሮ ጉብኝት 2.80

የመሣሪያ ግዥ 5,151,11

• ለኢንተርኘራይዞች 5,108,71

• ለማሰልጠኛ ተቋማት

ለመሳሪያ

42.40

ለመንገድ ግንባታ 10,725.00 21450 ኪ. ሜ 0.50

• ለመንገድ ጥገና 562.00

•መደበኛ 329.00 16450X0.02

•ወቅታዊ 105.00 1750X0.06

Page 38: በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የዩኒቨርሳል የገጠር መንገድ አክሰስ ኘሮግራም

የአፈፃፀም አቅጣጫዎች

• ክረምት ከበጋ የሚያስኬዱመንገዶችን መገንባት

• የመንገድ መረብ ሽፋን ከመነሻ እስከ መድረሻ ማዳረስ

• አነስተኛ መካከለኛ የሥራ ተቋራጮችንና አማካሪዎችንማደራጀት

• ተስማሚ የመንገድ ቴክኖሎጂመጠቀም

• የወረዳ መንገድ ሃብት እና የተዳፋት መሬት ማኔጀመነትንመከተል

• የህብረተሰቡን ተሳትፎ ማረጋገጥ

Page 39: በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የዩኒቨርሳል የገጠር መንገድ አክሰስ ኘሮግራም

ሥጋቶች• የታሰበውን ያህል ኢንተርኘራይዞችን መፍጠር አለመቻል

• የብድር አገልግሎት በወቅቱ አለመቅረብ

• የሚመደበው በጀት በቂ አለመሆን

• በተያዘው የጊዜ ሠሌዳ መሠረት ኘሮግራሙን አለመጀመር

• የህብረተሰቡ ተሳትፎና የባለቤትነት ስሜት የሚጠበቀውን ያህልአለመዳበር

• ለጥገናና እንክብካቤ የሚሰጠው ትኩረት አነስተኛ መሆን

• የአንዳንድ ግብዓቶች የዋጋ መናር

• በወቅታዊ ጉዳዮች በመጠመድ ለኘሮግራሙ ትኩርተ አለመስጠት

• የጉልበት ሠራተኞች መንገድ በሚሰራባቸው አካባቢዎች በሚፈለገው ብዛት ወቅትና በተመጣጣኝ ክፍያ አለማግኘት

Page 40: በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የዩኒቨርሳል የገጠር መንገድ አክሰስ ኘሮግራም

ውሳኔ የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች1. ለኘሮግራሙ አፈፃፀም የሚያስፈልግ በጀት

17.2 ቢሊዮን ሲሆን፡- 20% በህዝብ ተሳትፎ የሚሸፈን ይሆናል 65 % ለመንገድ ግንባታ 31.22 % ለመሣሪያ ግዥ 3.40 % ለመንገድ ጥገና 0.38 % ለአቅም ግንባታ የሚውል ሲሆን 20

በህብረተሰብ ተሳትፎ የሚሸፈን ይሆናል፡፡

Page 41: በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የዩኒቨርሳል የገጠር መንገድ አክሰስ ኘሮግራም

2. የሚገነባው መንገድ 21450 ኪ. ሜትር ስለሆነ በቀሪው ጊዜ(2003-2007) የሚገነባ ስለመሆኑ መግባባት መደረስ አለበት

3. የተለያዩ አደረጃጀቶችን በተመለከተ

• 551 ተቋራጭና አማካሪዎችና ሌሎች

• የወረዳ ገጠር መንገድ ጽ/ ቤት ( ዞኖችጨምሮ)4. የማሽነሪና ሌሎች መሣሪያዎችን ግዥና አቅርቦት በተመለከተ

5. በየደረጃው ያሉ የአስተባባሪ ኮሚቴዎችን ዓይነትና ብዛትመወሰን