36
የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ህብረት ቤተ ክርስቲያን ሎስ አንጀለስ የሃያ አንድ ቀን ጾም እና ጸሎት October 14 – November 3, 2019 መሪ ጥቅስ፦ በስሜ የተጠሩት ህዝቤ ሰውነታቸውን አዋርደው ቢጸልዩ ፊቴንም ቢፈልጉ ከክፉ መንገዳቸው ቢመለሱ በሰማይ ሆኜ እሰማለሁ ኃጢአታቸውንም ይቅር እላለሁ ምድራቸውንም እፈውሳለሁ” 1ዜና 714 በመለስ ገበየሁ ጥሩነህ የተዘጋጀ

October 14 November 3, 2019 · 2019-10-16 · የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ህብረት ቤተ ክርስቲያን ሎስ አንጀለስ የሃያ አንድ ቀን ጾም

  • Upload
    others

  • View
    2

  • Download
    0

Embed Size (px)

Citation preview

Page 1: October 14 November 3, 2019 · 2019-10-16 · የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ህብረት ቤተ ክርስቲያን ሎስ አንጀለስ የሃያ አንድ ቀን ጾም

የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ህብረት ቤተ ክርስቲያን ሎስ አንጀለስ

የሃያ አንድ ቀን ጾም እና ጸሎት

October 14 – November 3, 2019

መሪ ጥቅስ፦ “በስሜ የተጠሩት ህዝቤ ሰውነታቸውን አዋርደው

ቢጸልዩ ፊቴንም ቢፈልጉ ከክፉ መንገዳቸው ቢመለሱ በሰማይ ሆኜ

እሰማለሁ ኃጢአታቸውንም ይቅር እላለሁ ምድራቸውንም

እፈውሳለሁ” 1ኛ ዜና 7፤14

በመለስ ገበየሁ ጥሩነህ የተዘጋጀ

Page 2: October 14 November 3, 2019 · 2019-10-16 · የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ህብረት ቤተ ክርስቲያን ሎስ አንጀለስ የሃያ አንድ ቀን ጾም
Page 3: October 14 November 3, 2019 · 2019-10-16 · የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ህብረት ቤተ ክርስቲያን ሎስ አንጀለስ የሃያ አንድ ቀን ጾም

የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ህብረት ቤተ ክርስቲያን ሎስ አንጀለስ

የሃያ አንድ ቀን ጾም እና ጸሎት

October 14 – November 3, 2019

ዓላማ

• ራስን ማየት እና መመርመር

• መንፈሳዊ መነቃቃት እና ተሓድሶ በግል ሀይወታችን፤ በአገልግሎታችን እና

በቤተ ክርስቲያን እንዲመጣ

• የወቅቱን የእግዚአብሔርን አጀንዳ አውቆ በጊዜው ካለው ከእግዚአብሔር

ሃሳብ ጋር አብሮ ለመፍሰስ

አፈጻጸሙ

በዋናው ቤተ ክርስቲያን

• ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ከ 10፡30 am—2፡00pm

• ምሽት 6፡00pm – 8:00 pm

በኢንግልዉድ፣ ሳንታ ሞኒካ፣ ኦሬንጅ ካውንቲ፣ ቫሊ፣ ሳንታ ባርባራና፣ ፎንታና

• ከሰኞ እስከ አርብ ምሽት ከ6፡00—8፡00pm

• እሑድ ከ 4፡00pm —6፡00 pm

የጸሎት አቅጣጫዎች

• እግዚአብሔርን ስለ ማንነቱ እና ስለ ጌትነቱ ማመስገን

• ንስሓ እና እውነተኛ መመለስ በግል ህይወታችንም ሆነ እንደ ቤተክርስቲያን

• ቤተ ከርስቲያን በቀደመው ክብሯ እና ሞገሷ መመላለስ እንድትችል

Page 4: October 14 November 3, 2019 · 2019-10-16 · የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ህብረት ቤተ ክርስቲያን ሎስ አንጀለስ የሃያ አንድ ቀን ጾም

• ወንጌል በኃይል እና በሥልጣን እንዲሰበክ ለወንጌል ራሳቸውን የሰጡ

አገልጋዮች እንዲነሱ

• በመንፈስ ቅዱስ ኃይል እና ምሪት መውጣት እና ማገልገል እንዲሆን

• ቤተ ከርስቲያን በጥራትም በቁጥርም እንድታድግ

• ቤተክርስቲያንን የሚገዳደር ክፉ እንዲመታ እና ለቤተከርስቲያን ተግዳሮቶቿን

ጥሳ የምትሄድበት አቅም እንዲሰጣት።

• በግል ህይወታችን ላይ እውነተኛ መነቃቃት እንዲመጣ

• በምድራችን ያለውን ችግር እግዚአብሔር እንዲፈታ እና ሰላም እና አንድነት

በምድራችን ላይ እንዲሆን።

እነዚህ አርዕስቶች እንደ መነሻ ናቸው እንጂ እነዚህ ብቻ ናቸው ማለት አይደለም።

የእያንዳንዱን ቀን የጸሎት ርዕስ በቀኑ ስር ይመልከቱ።

መሪ ጥቅስ፦ 2ኛ ዜና 7፤14

ክፍሉ ሰሎሞን ቤተ መቅደሱን ሰርቶ በጨረሰ ጊዜ በቤተ መቅደሱ ምረቃ ላይ

ለእስራኤል ሕዝብ በጸለየው ጸሎትና እግዚአብሔር የሰጠው ተስፋ ነው። ሆኖም

ተስፋው ሁኔታዊ ነው። እግዚአብሔር እንደሚሰማቸው እንደሚረዳቸው ምድራቸውን

እንደሚያስብ ቃል ቢገባላቸውም ከእነርሱ ደግሞ የሚጠበቅ ነገር እንዳለ ይናገራል።

1ኛ) “ህዝቤ ሰውነታቸውን አዋርደው ቢጸልዩ፤”

ሰውነትን ለማዋረድ ራስን ዝቅ አድርጎ በትህትና ወደ እግዚአብሔር መቅረብ

ያስፈልጋል። እግዚአብሔር ትህትናን ይወዳል ስለዚህ ነው ለትሁታን ጸጋን ይሰጣል

ትዕቢተኞችን ግን ይቃወማል። ወደ እግዚአብሔር ፊት ስንቀርብ ምንም እንደሌለው

ሆነን ከእርሱ ለመቀበል መቅረብ አለብን።

2ኛ) “ፊቴንም ቢፈልጉ፤”

እግዚአብሔር በብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ላይ ፈልጉኝ ይላል። ደግሞም በፍጹም

ልባችን ከፈለግነው እንደሚገኝ ተናግሯል።

Page 5: October 14 November 3, 2019 · 2019-10-16 · የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ህብረት ቤተ ክርስቲያን ሎስ አንጀለስ የሃያ አንድ ቀን ጾም

“አሁንም እግዚአብሔርን ትፈልጉ ዘንድ ልባችሁን ነፍሳችሁን ስጡ” 1ኛ ዜና 22፤19

እግዚአብሔርን መፈለግ፤ አንድ ጊዜ የሚሆን ሰሞነኛ ጉዳይ ሳይሆን ልባችንንና

ነፍሳችንን ሰጥተን የምናደርገው ጉዳይ ነው። እግዚአብሔር ስንፈልገው ደግሞ የሚገኝ

ታማኝ አምላክ ነው።

3ኛ) “ከክፉ መንገዳቸው ቢመለሱ፤”

ይሄ ንስሐን፣ ከክፉ መንገድ፣ ማለትም እግዚአብሔራዊ ካልሆን መንገድ መመለስን

ያመለክታል። ዛሬ፤ መንገዳችን ምን ይመስላል? እውነት እንነጋገር ከተባለ፤ እኛ፣

ክርስቲያን ነን፣ አገልጋዮች ነን፣ ብለን የምንጣራ ሰዎች በውጭ ካሉ አለማዊያን የማንሻል

መሆናችን የታወቀ ነገር ነው። በብልጠትም ሆነ በክፋት፣ ራስ ወዳድነት፣ እኔነት፣

ለስማችን እና ለክብራችን መኖር፣ ስግብግብነት፣ የእግዚአብሔርን ቤት ሞልቶታል

ቢባል ማጋነን ነው ብዬ አላስብም። እንዲያውም የማያምኑ ሰዎች ከእናንተስ እኛ

እንሻላለን እያሉ ይዘባበቱብናል። የጽድቅ ዋጋ ቀንሷል። ለእግዚአብሔር መኖር እና

መሰጠት ሞኝነት ሆኖ በመቆጠር ላይ ይገኛል። ነገር ግን ጥሪያችን እንዲህ አልነበረም

እናንተ የምድር ጨው ናችሁ፣ የአለም ብርሃን ናችሁ ተብሎ ነው የተነገረልን። እኛን

የሚመጥን ሕይወት እየኖርን አይደልም። ራሳችንን መርምረን መመለስ አለብን። ወደ

እርሱ ስንመለስ እግዚአብሔር የእርሱን በረከት ያፈስልናል። ብዙ የብሉይ ኪዳን

አገልጋዮች እና መሪዎች በአመራራቸው እና በአገልግሎታቸው ውጤታማ ያደረጋቸው

በንስሓ ወደ እግዚአብሔር መመለሳቸው ነው።

4ኛ) “ምድራቸውን እፈውሳለሁ”፤

ከላይ የተጠቀሱትን ነገሮች ስናደርግ እግዚአብሔር ጸሎታችንን እንደሚሰማ፣

ምድራችንን እንደሚፈውስ ቃል ገብቶልናል። አሁንም ቢሆን እግዚአብሔር እኛ ወደ

እርሱ ከተመለስን ራሳችንን መርምረን እውነተኛ ንሰሓ እና መመለስ ካደረግን

በመካከላችን ተገኝቶ ጸሎታችንን ሊመልስ እና ሊባርከን የታመነ አምላክ ነው።

Page 6: October 14 November 3, 2019 · 2019-10-16 · የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ህብረት ቤተ ክርስቲያን ሎስ አንጀለስ የሃያ አንድ ቀን ጾም

የጾም አይነቶች

በመጽሐፍ ቅዱስም ሆነ በዘመናችን ባለው ሁኔታ ሰዎች የተለያየ አይነት ጾም ይጾማሉ

1. በአንዳንድ የምግብ ዓይነቶች ተገድቦ መጾም፦ ይሄንን ጾም በዳንኤል መጽሐፍ ላይ

ዳናኤልና ጓደኞቹ፤ ሲድራቅ፣ ሚሳቅና አብድናጎ፤ በንጉሡ ምግብ እንዳይረክሱ

ብለው ቆሎ (ጥራጥሬ) ብቻ እየበሉ (አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አትክልትና ውሃ”

በእንግሊዝኛ vegetables ይለዋል፣) ጾመዋል።ዛሬም ውሃ ወይም ጁስ እየጠጡ

የሚጾሙ ሰዎች አሉ።

2. ውለው ራት እየበሉ መጾም፦ በሃያ አራት ሰአት አንድ ጊዜ እየበሉ የሚጾሙት ጾም

አለ። ይህን አይነት ጾም ብዙ ሰዎች የሚለማመዱት እና የሚያደርጉት ነው። ነህምያ

አያሌ ቀን በጾም እና በጸሎት እንደነበር ይናገራል። ነህምያ 1፤14

3. መሉ ጾም፦ሙሉ ጾም ምንም አይነት ምግብ ሳይወሰድ የሚጾም ጾም ነው። ይሄንን

ጾም ጌታ ኢየሱስ፤ እንዲሁም ሙሴ ለአርባ ቀንና ሌሊት እንደጾሙ ይናገራል። ማቴ

4 እና ዘጸ 32 እንዲህ አይነቱን ጾም ለመጾም ከጌታ ምሪት መቀብል እና ድምጽ

መስማት ይጠይቃል። ምክንያቱም እንዲህ አይነቱን ጾም ለመጾም ብለው

ሰውነታቸውን የጎዱ እና በሽታ ላይ የወደቁ ስላሉ። ሆኖም አርባ ቀን ባይሆንም

ብዙ ሰዎች ያለ ምግብ እና ያለ ውሃ ከአምስት እስከ አስር ቀን የጾሙ ሰዎች

አውቃለሁ።

4. የአዕምሮ ጾም፦ ስንጾም ሆዳችን ብቻ ሳይሆን አዕምሮአችንም መጾም አለበት።

አዕምሮ ስንል፤ አይናችን፣ ጆሮአችን የስሜት ኅዋሳቶቻችን ሁሉ ማለት ነው።

ለአንዱ ስሜታችን ልጓም አድርገንለት ሌላውን ልቅ መተው አንችልም። በዚህ

ዘመን በተለይ፤ ኤለክትሮኒክስ (የተለያዩ ሶሻል ሚዲያ) በጾማችን ውስጥ መካተት

አለባቸው። መቼም ይሄ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሌለ ዘመኑ ያመጣው ነገር ነው።

የኤሌክትሮንክስ ሱስ ከምግብ ሱስ እንደሚበልጥ ምንም ጥርጥር የለውም።

ኤሌክትሮኒክስ ሳይጠቀሙ መዋል የማይችሉ በጣም ብዙ ሰዎች አሉ። ከሱስ በላይ

ሆኗል። ይህ ሲባል የኤሌክትሮኒክስ ጠቀሜታ እጅግ ባጣም ከፍተኛ መሆኑን

አይካድም። ሆኖም ያለምንም በቂ ምክንያት በሚዲያ ላይ ተጥደን በመዋላችን፤

የቃል፣ የጸጸሎት እና ከቤተሰብ ጋር የምናሳልፈው ጊዜ መበላት የለበትም።

አንዳንድ የዚህ አገር ቤተክርስቲያናት ላይ ከኤሌክትሮኒክስ መጾም ተጀምሯል።

Page 7: October 14 November 3, 2019 · 2019-10-16 · የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ህብረት ቤተ ክርስቲያን ሎስ አንጀለስ የሃያ አንድ ቀን ጾም

ማለት መሠረታዊ (basic) የሆኑትን ነገሮች ብቻ ይጠቀማሉ። ሌላውን ይጾማሉ።

ፌስቡክ እና ዩቱዩብ አንዳንዴ መጾም አለባቸው ብዬ አስባለሁ። ምክንያቱም፣ በቂ

ጊዜ፤ ለጌታ እና ለቃሉ እንዲሁም ለቤተሰብ መሰጠት አለበት።

የትኛውን ጾም ወይንም እስከ ስንት ሰአት እንጹም ?

ጾም እግዚአብሔርን ለመፈለግ በተረጋጋ ሁኔታ ከጌታ ጋር ለማሳለፍ የሚደረግ ነገር

እንጅ የጾም ማራቶን ማድረግ የለብንም። ስለዚህ የጤናም ችግር ያለበት ሰው ለምን

ረጅም ሰአት አልጾምሁም ብለን መጨነቅ አስፈላጊ አይደለም። የምንችለውን ያህል

እንደ አቅማችን ብንጾም መልካም ነው። ሆኖም መወሰን ደግሞ ያስፈልጋል። መቸም

ሥጋችን መጾም አይፈልግም። ሰበብ አድርገን ለመብላት ደግሞ መቻኮል የለብንም።

ስንወስን ደግሞ ከእኛ ጋር የሚቆም እና የሚያበረታ ጸጋ የሚባል ነገር አለ።

በመጽሐፍ ቅዱስ የተጾሙባቸው ምክንያቶች

የመጽሐፍ ቅዱስ ሰዎች በተለያዩ ምክንያቶች ጾም ጸሎት ይዘው ጸልየዋል። ይህን

ያደረጉበት ምክንያት በጾም ጸሎት ውስጥ ሐይል ስላለ ነው። ከእነዚህም ጥቂቶቹን ከዚህ

በታች እናያለን።

1) አገልጋዮችን ለአግልገሎት ለመለየት

በሐዋ 13፤1 “በአንጾክያ ቤተ ክርስቲያን ሲጾሙ እና ሲያመልኩ” ይላል። የአንጾክያ ቤተ

ክርስቲያን፤ ጾምን፣ ፤ ለአምልኮ ትጠቀምበት ነበር። ምክንያቱም ጾም እና ጸሎት

አምልኮም ነው። በጾምና በጸሎት እያሉ፣ መንፈስ ቅዱስ “ሳውልና በርናባስን

ለጠራኋቸው ስራ ለዩልኝ” ብሎ ተናገረ። የአንጾክያ ቤተ ክርስቲያን በጾምና በአምልኮ

ትተጋ ነበር። መንፈስ ቅዱስም ይናገራል። ለመጣው የመንፈስ ቅዱስ ድምጽ ደግሞ

ፈጽመው ይታዘዙ ነበር። ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ጥብቅ ህብረት ስለነበራቸው መንፈስ

ቅዱስ ሲናገር ይለዩት ነበር። ይሄ ድምጽ የማን ነው? ብለው ግራ አይጋቡም። ጾምና

ጸሎት ለእግዚአብሔር ድምጽ ቅርብ ያደርገናል።

Page 8: October 14 November 3, 2019 · 2019-10-16 · የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ህብረት ቤተ ክርስቲያን ሎስ አንጀለስ የሃያ አንድ ቀን ጾም

2) ለተሐድሶ

“ይህንም ቃል በሰማሁ ጊዜ ተቀምጨ አለቀስሁ፤ አያሌ ቀንም አዝን ነበር። በሰማይም

አምላክ ፊት እጾም እና እጸልይ ነበር።” ነህ 1፤4። ነህምያ በምርኮ ምድር በንጉሱ ቤት

ተቀጥሮ ሲኖር ከኢሩሳሌም የመጡ ሰዎች ሰለ ኢየሩሳሌም መፍረስ ሲነግሩት ታላቅ

ሐዘን ውስጥ ገባ። ይህን ሀዘንና ሽክም ይዞ በግዚአብሔር ፊት በጾም እና በጸሎት ነው

የቀረበው።

ነህምያ ሲጾምና ሲጸልይ፤

• ለስራው የሚሆን ራእይ ተቀበለ

• በንጉሱ ፊት ሞገስን አገኘ

• ለሰራው የሚሆነውን እርዳታ አገኘ

• ለስራው ህዝቡ ሁሉ ተባበረው በአንድ ህሳብ አብረውት ተነሱ

• ጦብያና ሰንባላጥ እና ሌሎች ተቃዋሚዎቹንም ለማሸነፍ ቻለ

• ለስራው የሚሆን አቅርቦት እና ሐይል አገኘ

• ስራውን በአጭር ጊዜ ውስጥ አጠናቀቀ

እነዚህ በረከቶች ሁሉ የመጡት ከጾም እና ጸሎት ነው። ነህምያ አጥብቆ የጸለየውና

የሰራው ለተህድሶ ነው። ድግሞም እግዚአብሔር ይህን ጸሎቱን ሰምቶት የፈረሰውን

ቤተ መቅደስ አድሷል። ዛሬም በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ብዙ የፈራረሱ ነገሮች አሉ።

ምናልባት ህንጻዎች እንዲያውም የተሻለ ተገንብተው እና አምሮባቸው ይሆናል፤ ነገር

ግን ብዙ የፈረሰ ህይወት እና አገልግሎት ሞልቷል። ለዚህ ለፈረሰው ህይወታችንና

አገልግሎታችን አጥብቀን ልንጸልይ ይገባል።

3) ንሥሐ ለመግባት እና ወደ እግዚአብሔር ለመመለስ

ሰዎች ከእግዚአብሔር መንገድ ወጥተው ኃጢአትን ሲሰሩ እና ከእግዚአብሔር ሲርቁ

ንሥሐ ገብተው ወደ እግዚአብሔር ለመመለስ በጾም እና በጸሎት ወደ እግዚአብሔር

ፊት ይቀርባሉ። ኢዩ 2፤12_13 “አሁንስ ይላል እግዚአብሔር በፍጹም ልባችሁ በጾምም

በለቅሶ በዋይታ ወደ እኔ ተመለሱ፤ ልባችሁን እንጂ ልብሳችሁን አትቅደዱ አምላካችሁ

እግዚአብሔር ቸር እና መሐሪ፣ ቁጣው የዘገየ ምህረቱ የበዛ ለክፋትም የተጸጸተ ነው፤

Page 9: October 14 November 3, 2019 · 2019-10-16 · የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ህብረት ቤተ ክርስቲያን ሎስ አንጀለስ የሃያ አንድ ቀን ጾም

ወደ እርሱ ተመለሱ።” እስራኤላዊያን ከእግዚአብሔር መንገድ ወጥተው በራሳቸው

መንገድ በሄዱ ጊዜ የሐጢአታቸው ብዛት ብዙ መከራ አምጥቶባቸው ነበር። ቃሉ

እንደሚናገር፤ ከአምላካቸው ቤት ደስታ እና እልልታ ጠፍቶ ነበር። እህላቸውን ተምች

እና ደጎብያ እንዲሁም የአንበጣ ሰራዊት ያጠፋባቸው ነበር። በዚሁ ሁሉ መከራ ውስጥ

ያልፉ በነበረ ጊዜ፤ ኢዩኤል ወደ እግዚአብሔር በንስሐ፣ በጾም እና በጸሎት ወደ

እግዚአብሔር እንዲመለሱ ጥሪ ያደርግ ነብር።ንስሐ ወደ እግዚአብሔር ከሚያቀርቡን

ነገሮች ዋናው ስለሆነ፣ መንገዳችን ከእግዚአብሔር መንገድ ሲወጣ እና በራሳችን መንገድ

ስንጓዝ በጾም እና በጸሎት በንስሐ ወደ እርሱ መመለስ አለብን። መርሳት የሌለብን ነገር

ቢኖር ለመጀመሪያ የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን ተጠርተን ከእግዚአብሔር ጋር ጉዞ

ስንጀምር ወደ እግዚአብሔር ያቀረበን ነገር ንስሐ ነው። ዛሬም በእየለቱ ንስሐ

ከህይወታችን መጥፋት የለበትም።

4) በውጊያ ጊዜ

እስራኤላዊያን በተለያየ ጊዜ ብዙ ጠላቶች እየተነሱባቸው ብዙ ውጊያ በህይወታቸው

ውስጥ ነበር። ከብዙ አገሮች ጋር የዋጉ ነብር። በውጊያቸው ውስጥ አካሄዳቸው

ከእግዚአብሔር ጋር ትክክል ሳይሆን ሲቀር በቅላሉ ይሽነፉ ነበር አካሄዳቸው ደግሞ

ጌታን በምስማት እና ጥሩ ህብረት ከእርሱ ጋር ሲኖራቸው ጦርነቱን ያሽንፉ ነበር።

ለምሳሌ ኢያሱ 7 ስንመለክት እስራኤላዊያን በጦርነት ተሽነፉ ብዙዎች ከነርሱ መካከል

ተመተው ወደቁ። ተመተው የወደቁብት ወይንም በጦርነቱ ውስጥ ለሽንፈታቸው

ምክንያት የነበረው የካን ኃጢአት ነበር። በጦርነቱ እንደገና ለማሸነፍ ንስሀ መግባት እና

መመለስ ነበረባቸው። አስቴር 4፤1᎐7 አስቴር እና ህዝቧ የሀማን ውጊያ ያሽነፉት እና

ድል የተቀዳጁት በጾም እና በጸሎት ነበር። ሶስት ቀን በግዚአብሔር ፊት በጾም እና

በጸሎት ሲወድቁ፣ ነገር ተገለበጠ። የአስቴር እና የህዝቧ ጸሎት የጠላትን አዋጅ እንደ

ገለበጠ ሁሉ፤ ዛሬም በተለያየ ሁኔታ የሚዋጋንን የጠላት ሐይል በጸሎት ማሸነፍ

እንችላለን። የብሉይ ኪዳን ውጊያ በአካል የሚደረግ ነበር፤ ማለትም ውጊያው ምድራዊ

ነበር። ድሉም ምድራዊ ነበር። የአዲስ ኪዳን ውጊያ ደግሞ መንፈሳዊ ነው። ሐዋሪያው

ጳውሎስ፤ ውጊያችን ከደም እና ከስጋ ጋር አይደለም፣ ከጨለማው አለም ገዢዎች፣

ከክፋት መንፈሳዊያን ሰራዊት ጋር ነው እንጂ (ኤፌ 6፤12) የብሉይ ኪዳኑ ውጊያ

Page 10: October 14 November 3, 2019 · 2019-10-16 · የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ህብረት ቤተ ክርስቲያን ሎስ አንጀለስ የሃያ አንድ ቀን ጾም

መንፈሳዊነትን፣ መጾም መጸለይን ከጠየቀ ይሄኛውማ የበለጠ በመንፈስ መሆንን

የሚጠይቅ ነገር ነው። ስለዚህ በጾም እና በጸሎት መትጋት ያስፈልገናል ማለት ነው።

5) ምሪት ለመቀበል

ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ሰዎች የእግዚአብሔር ምሪትን በህይወታቸው እና በመንገዳቸው

ላይ ለመቀበል በጾም እና በጸሎት በፊቱ ቀርበዋል። ለምሳሌ ያህል በዘጸ 32 ሙሴ

በእግዚአብሔር ፊት ለአርባ ቀንና ሌሊት በጾም እና በጸሎት አሳልፏል። ሙሴ

የእስራኤልን ህዝብ ይመራ በነበረ ጊዜ ጥሪ የተቀበለው ከእግዚአብሔር እንደ ነበር በዘጸ

3 ማየት እንችላለን። ሆኖም ምንም ጥሪው ከእግዚአብሔር ቢሆንም እለት እለት

ሕዝቡን የሚመራበት አቅም እና ጥበብ እንዲሁም መመሪያ ስለሚያስፈልገው

በእግዚአብሔር ፊት በጾም እና በጸሎት ይወድቅ ነበር። በተለይም አመራር ላይ ያሉ

ሰዎች ከሌላው ሰው ይልቅ ብዙ መጾም እና መጸለይ ያስፈልጋቸዋል። ሐዋሪያው

ጳውሎስም “ብዙ ጊዜ በመጾም” ብሎ በ2ኛ ቆሮ 11 ላይ ያነሳል፤ አብዝቶ ይጾም እንደነበር

ነው የምናየው።። አብዝቶ በጾም እና በጸሎት በጌታ ፊት መቅረብ ከእግዚአብሔር

ዘንድ ምሪት ለመቀበል እና በአገልግሎትም ውጤታማ ለመሆን እጅግ ጠቃሚ ነገር

ነው። ከላይ የጠቀስኋቸውን እንደ ዋና ዋና አድርጌ አነሳኋቸው እንጂ በብዙ ምክንያቶች

ጾም እና ጸሎት ተደርጓል።

• ጾም እና ጸሎትን እንደ አገልገሎት ቆጥረው የሚጾሙ ነበሩ (ሉቃ 2፤37)

• ለልጆቻቸው፣ ለከብቶቻቸው እና ለንብረታቸው በጾም እና በጸሎት

እንደቀረቡ ዕዝራ 8 ላይ እናያለን

• በኃዘንና በጥቃት በፍርድ ጊዜ

• ቀድሞ በእግዚአብሔር የተነገረን የተስፋ ቃል ለመውረስ

• በሌሎቹም ጉዳዮች ላይ ጾም እና ጸሎት ተደርጓል።

ዛሬም በሚያጋጥሙን ችግሮች ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት መጾም ያስፈልጋል። ጾም እና

ጸሎት እግዚአብሔር በሐይል ከሚጠቀምባቸው ነገሮች አንዱ ነው። በዘመናችንም

ቢሆን ባለፉት ዘመናት በቤተ ክርስቲያን ጥብቅ ጾም እና ጸሎት ይደረግ በነበር ጊዜ ብዙ

የእግዚአብሔር ክንድ ይገለጥ ነበር። መንፈስ ቅዱስ በሐይል ይሰራ ነበር። ጾም እና

Page 11: October 14 November 3, 2019 · 2019-10-16 · የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ህብረት ቤተ ክርስቲያን ሎስ አንጀለስ የሃያ አንድ ቀን ጾም

ጸሎትን ማቃለል የመንፈሳዊ ህይወት ድንዛዜ ምልክት ነው እንጅ የማደግ ወይንም

የመብሰል ምልክት አይደለም።

ጌታ የማይወደው ጾም

ጌታ የሚወደው እና የማይወደው ጾም አለ። አንድ ነገር መደረጉ ብቻ አይደለም። ለምን

እና እንዴት መደረጉም በእግዚአብሔር ፊት ወሳኝ ነገር ነው። እግዚአብሔር የውስጥ

መንፈስን እና ልብን የሚመረምር አምላክ ስለሆነ አንድን ነገር ያደረግንበትም መንፈስ

እጅግ ወሳኝ ነገር ነው።

1ኛ ለታይታ የሚደረግ ጾም እና ጸሎት

እግዚአብሔር ከሚጸየፋቸው ነገሮች አንዱ ታይታ ነው። እኛን ሰዎችን ደግሞ ከታናሽ

እስከ ታላቅ፣ ከመሪ እስከ ተመሪ የሚገዳደረን ነገር ቢኖር በሰው መታየት እና በሰው

መደነቅ ነው። የሰው ልጅ ትልቁ ጠላት ሰይጣን አይደለም። ምክንያቱም ሰይጣን

በአጭር ጊዜ ጸሎት ከአጠገባችን የሚሄድ ነገር ነው። ይሄን ያህል በእግዚአብሔር ልጆች

ፊት ለመቆም አቅም የለውም። ነገር ግን፤ ከራሳችን መላቀቅ እና ከታይታ ማምለጥ ቀላል

ነገር አይደለም። “ለሰዎች ትታዩ ዘንድ ምጽዋታችሁን በፊታቸው አታድርጉ፥” ማቴ 6

ለሰዎች ለመታየት ማድረግ የሌለብን ሶስት ነገሮችን ይናገራል። ስትሰጡ፣ ስትጾሙ እና

ስትጸልዩ ለታይታ ብላችሁ አታድርጉ ይላል። በሰው ፊት ለመታየት በምናደርገው ነገር

ሁሉ ዋጋችን ከዚሁ ብቻ ይሆናል። ከጌታ ጠብቀን ስናደርግ ከጌታ እንቀበላለን።

2ኛ ለትምክህት ወይንም በመመጻደቅ (ፈሪሳዊ) መንፈስ መሆን የለበትም

ጌታ ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ ሲናገር ከፈሪሳዊያን እርሾ ተጠበቁ አላቸው። በሉቃ 18፤

አንድ ፈሪሳዊ እና አንድ ቀራጭ ለጸሎት ወደ መቅደስ እንደ ወጡ፤ ፈሪሳዊው ጽድቁን

በመቁጠር እና ሌላውን በማቃለል እንደ ጀመረ ይነግረናል። እንዲዚህ ሰው

ሰላላደረግኸኝ አመሰግንሀለሁ። በሳምንት ሁለት ጊዜ እጾማለሁ አለ። በጾሙ

ተመክቷል። መመካት ብቻ ሳይሆን ሌላውን ያቃልላል። ሰለዚህ ከእንደዚህ አይነቱ

መንፈስ ይጠብቀን።

Page 12: October 14 November 3, 2019 · 2019-10-16 · የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ህብረት ቤተ ክርስቲያን ሎስ አንጀለስ የሃያ አንድ ቀን ጾም

እግዚአብሔር የሚወደው ጾም

ኢሳ 58 እግዚአብሔር የሚወደው ጾም ምን እንደሆነ እና የሚጠላውንም ይናገራል።

እስራኤላዊያን ይጾማሉ፣ የሚጾሙት ግን እግዚአብሔር የሚፈልገውን አይነት

አልነበረም። ሲጾሙ ግፍ እና በደል በሰራተኞቻቸው ላይ ያደርሳሉ። ሰራተኞቻቸውን

ያስጨንቃሉ፣ ክፉ ነገር ያደርጋሉ፣ እንደዚህ አይነቱን ጾም ፈጽሞ ጌታ አይከብርበትም።

አንድ ሰው ሲናገር እንዲህ አለ። አንድ ሰው በመንገድ ሲሄድ በጣም ተራበና አንድ

ሰው መንገድ ላይ አገኘ። ሰውየውን ደብድቦ ከገደለ በኋላ ገንዘቡን ቀማውና ምግብ

ገዝቶ በላ። የተገደለው ሰው ኬክ ይዞ ስለነበር ሰዎች፣ ሰውየውን ከምትገድለው ምናለ

የያዘውን ኬክ ቀምተህ ብትበላ ሲሉት፤ ቀኑ ሮብ ስለነበር ኬኩ ጾም ስለነካው የጾም

አልበላም ብየ ነው አለ ይባላል። በጾም ቀን ሰው መግደል ይችላል ጾም የነካው ግን

አይበላም። ዛሬም ቢሆን ብዙ ሰዎች ብዙ ይጾማሉ ይጸልያሉ ነገር ግን እየጾሙ ክፉ

ነገር የሚያደርጉ፣ የሚያሙ፣ ሰዎችን የሚበድሉ፣ የሚሳደቡ፣ የሚራገሙ፣ ሌላ ሌላ ነገር

የሚያደርጉ አሉ። እንደዚህ አይነቱ ጾም እውነተኛ ህብረት ከጌታ ጋር የሚፈጥር

አይደለም። ሃይማኖታዊ እርካታን ለማግኘት ብቻ ነው። በጾምን ቀን ከምግብ ብቻ

አይደለም መጾም ያለብን ከነገርም፣ ከሌላም ነገር ጭምር ነው።

በጾማችሁ ቀን፤ ለፍትህ ትቆሙ ዘንድ

ቁጥር 5 “የበደልን እስራት ትፈቱ ዘንድ፣ የተገፉትን አርነት ትሰድዱ ዘንድ፣ ቀንበርንስ

ሁሉ ትፈቱ ዘንድ አይደለምን?” ለድሆች እና ለተጠቁት መቆም ያስፈልጋል። በጾማችን

ቀን ልናደርጋቸው የሚገቡ ነገሮች እንደሆኑ እግዚአብሔር ይናገራል።

ካለን ለሌሎች ማካፈል

ቁጥር 7 “እንጀራህን ለተራበ ትቆርስ ዘንድ፣ ስደተኞችን ድሆች ወደ ቤትህ ታገባ ዘንድ፣

የተራቆተውን ብታይ ታለብሰው ዘንድ ከስጋ ዘመድህ እንዳትሸሽግ አይደለምን።”

ያለንን ለሌሎች ማካፈል እጅግ መልካም ነገር ነው። አንዳንድ ሰዎች ሲጾሙ ቁርስና

ምሳቸውን አይበሉም። በሃያ አራት ሰአት አንድ ጊዜ በመብላት ይጾማሉ። ያልበሉትን

ቁርስ እና ምሳ ለድሆች ይሰጣሉ ‘። እኛ የወንጌል አማኞች፤ መዳን በጸጋ ስለሆነ

መስጥት ከጽድቅ ጋር ስለማይገናኝ ለመስጥት ያለን ትጋት ከሌሎች ሐይማኖቶች ይልቅ

Page 13: October 14 November 3, 2019 · 2019-10-16 · የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ህብረት ቤተ ክርስቲያን ሎስ አንጀለስ የሃያ አንድ ቀን ጾም

የደከመ ነው። ነገር ግን ጌታችን ሰጭ፤ ከመስጥትም አልፎ ራሱን የሰጠ ጌታ ነው።

ስለዚህ የእርሱ ደቀማዛሙርት ነን ካልን አብዝተን ልንሰጥ ይገባል። በዚህም የጾም ጊዜ

ድሆችን ማሰብ ይጠበቅብናል።

የጾምና የጸሎት ውጤቶች

ከላይ ያነሳኋቸውን ነገሮች አድርገን እውነተኛውን ጾም በጾምን ጊዜ

1ኛ) ትጣራለህ እግዚአብሔር እነሆኝ ይልሀል

እግዚአብሔር ስንጾም፤ ጾማችንን እና ልመናችንን ይሰማል ማለት ነው። ከላይ በግፍ

የሚጾሙትን ሲናገር ሰለምን ጾምን አንተም አልተመለክትህም ይላሉ ይላል። ይጾማሉ፤

ጾም እና ጸሎታቸው ግን ከጣራ ያለፈ የማይሆነው እውነተኛውን ጸሎት እና ጾም

ስለማያደርጉ ነው። እውነተኛ ሆነን በፊቱ ስንቀርብ እግዚአብሔር በትክክል ይሰማናል።

2ኛ) ብርሃንህ በጨለማ ይወጣል

በሌላ አነጋገር፤ በህይወታችን ላይ ያለ ማንኛውም ጨለማ ተወግዶ ብርሃናችን ለሌሎች

ያበራል። እኛ ለጨለማው አለም ልናበራ የተጠራን ሰዎች ነን። እናንተ የዓለም ብርሃን

ናችሁ (ማቴ 5፤13)። አማኝ ሁሉ ለራሱ ብቻ ሊኖር የተጠራ ሳይሆን ለጨለማው አለም

ሁሉ ሊያበራ ነው የተጠራው።

3ኛ) በእግዚአብሔር ደስ ይልሃል

እውነተኛውን የእግዚአብሔር ደስታ እንለማመዳለን ማለት ነው።

Page 14: October 14 November 3, 2019 · 2019-10-16 · የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ህብረት ቤተ ክርስቲያን ሎስ አንጀለስ የሃያ አንድ ቀን ጾም

እኛ የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ኅብረት የሃያ አንድ ቀን ጾም እና ጸሎት ለምን

አስፈለገን?

እኛ የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ኅብረት አማኞች በዚህ ጊዜ መጭውን የሃያ አንድ ቀን ጾም

እና ጸሎት በትጋት ለመሳተፍ ለምን አስፈለገን? ወይንስ ሌሎች ስለሚያደርጉት ነው

የምናደርገው? ሌሎች ስለሚያደርጉት ብቻ የምናደርገው ከሆነ ዋጋ አይኖረውም::

በእርግጥ ጌታን እንድንፈልግ የሚያደርገን ነገር አለ ብለን ካመንን እና ከጸለይን

ውጤታማ እንሆናለን ማለት ነው። በዚህ ጊዜ በእርግጥም ጌታን በጥብቅ መፈለግ

አለብን ከምንላቸው ምክንያቶች፤

1. የግል ህይወታችን ብዙም ካለመነቃቃቱ የተነሳ፤ ለመንፈሳዊ ነገር ያለን ትኩረት

የወረደ በመሆኑ።

2. ለመመስከር እና ለመጸለይ ያለን ልብ ዝቅ ያለ መሆኑ።

3. በግል ህይወታችንም ሆነ እንደ ቤተ ክርስቲያንም ያለን መንፈሳዊ እድገት

ተገቢውን ያህል አለመሆኑ። ከአመት አመት የሚጨመሩ ነፍሳት ቁጥር አናሳ

መሆኑ ተገቢ እና በቂ እድገት በመካከላችን አለመኖሩ።

4. የስርጭት ጣቢያዎቻችን አንዳንዶች ላይ መጠነኛ እድገት ቢኖርም ተገቢ

እድገት አለማሳየታቸው። አንዳንዶቹ ደግሞ ዝቅ እያሉ መሄዳቸው።

5. በተለያየ ዘርፍ ያሉ አገልግሎቶች በትጋት እና በመሰጠት የጌታን ስራ

አለመስራት። ጥቂቶች የተሰጡ ቢኖሩም በአብዛኛዎቻችን ላይ ድካም

ይታያል።

6. በብዙ አቅጣጫ በመካከላችን ዝለት ስላለ። ከዝለታችን እንድንነቃቃ እና

በመካከላችን እውነተኛ ተሃድሶ እና የጌታን መገኘት እንዲሆን።

7. ሁሉም የጸጋ ስጦታዎች እንደሚገባ እየሰሩ ስላልሆነ፣ እንዲሰሩ እውነተኛ

መንፈሳዊ እንቅስቃሴ እንዲሆን።

8. በአገልግሎት እና በሕይወት ያለን ጥራት እየጨመረ እንዲመጣ። ሰብረን እና

ጥሰን የምንሄድበትን አቅም እንዲሰጠን።

Page 15: October 14 November 3, 2019 · 2019-10-16 · የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ህብረት ቤተ ክርስቲያን ሎስ አንጀለስ የሃያ አንድ ቀን ጾም

ኦክቶበር 14 አንደኛ ቀን

ምስጋና ስለ ማንነቱ

የንባብ ክፍል መዝ 150

እግዚአብሔር ስለማንነቱ እና ስለ ታላቅነቱ ሊመሰገን ይገባል። ጊታ ኢየሱስ

ለደቀመዛሙርቱ ጸሎትን ሲያስተምር “አባታችን ሆይ፤ በሰማያት የምትኖር፣ ስምህ

ይቀደስ” በሚል ጸሎት ነው ያስጀመራቸው። ወደ ፊቱ ስንቀርብ መጀመሪያ ለአባትነቱ

እውቅና መስጥት ያስፈልገናል። እርሱ አባቴ ነው ብለን ስንቀርብ ነው ድፍረት

የሚኖረን። ሐዋሪያው ጳውሎስም በኤፌ 3፤14 አባትነት ከሚሰየምበት ከአብ ፊት

እንበረከካለሁ ብሏል። ሲንበረከክ ወይንም ለጸሎት ሲቀርብ ለእግዚአብሔር አባትነት

እውቅና በመስጥት ነው። ልጆች ወደ አባታቸው ቀርበው የፈለጉትን ለመጠየቅ

የሚያግዳቸው ነገር የለም። በመካከላቸው መልካም ግንኙነት እስካለ ድረስ ማለት ነው።

ለአባትነቱ እውቅና ከሰጠን በኋላ፤ “ስምህ ይቀደስ” እንላለን። ወደ እግዚአብሔር

ህልውና እና መገኘቱ ለመግባት በምስጋና በአምልኮ እና በውዳሴ በፊቱ መቅረብ

ያስፈልጋል። ዮሃንስ ራዕይ 5፤11 “ምስጋና በረከት ክብር ውዳሴ ሊቀበል ይገባዋል ”

ይላል። ምክንያቱ 1ኛ) ስለሚገባው ነው። ያለ ምንም ምክንያት፣ አምላክ እና ጌታ ስለሆነ

ብቻ ይገባዋል ። 2ኛ) በመስቀል ላይ በመዋል፤ ሕዝብን ከቋንቋ እና ከነገድ የዋጀ፤

ነፍሱን ለሌሎች ቤዛ አድርጎ የሰጠ በመሆኑ፤ ምስጋናና አምልኮ፣ ውዳሴ፣ ከብር፣

ሊቀብል ይገባዋል።

የጸሎትና የምስጋና አቅጣጫዎች

• እግዚአብሔርን ስለ አምላክነቱ ማመስገን

• ውዳሴ እና አምልኮ ማቅረብ

• ህዝብን ከቋንቋ እና ከነገድ ስለዋጀ ማመስገን

• ስለ ደኅህንነታችንና

• በሌሎቹም በእለታዊ ጸሎቶች ላይ መጸለይ

Page 16: October 14 November 3, 2019 · 2019-10-16 · የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ህብረት ቤተ ክርስቲያን ሎስ አንጀለስ የሃያ አንድ ቀን ጾም

ኦክቶበር 15 ሁለተኛ ቀን

ስለተደረገልን ነገር እግዚአብሔርን ማመስገን

የንባብ ክፍል ዘጸ 15፤1-3

ዳዊት፤ አድርገህልኛልና አመሰግንሀለሁ ይላል። ሐዋሪያው ጳውሎስ ደግሞ፤

ስለማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን ይላል። 2ኛ ቆሮ 9፡15 እግዚአብሔር

የሁለንተናችን አምላክ ነው ማለትም፤ የመንፈሳችንም የስጋችንም አምላክ ነው። በእለት

ከእለት ኑሮአችን ላይ እግዚአብሔር ጣልቃ እየገባ ይመራናል። ብዙ ተስፋ በቆረጥን እና

የኔ ነገር አበቃ ባልንባቸው ነገሮች ሁሉ ታሪክ እየቀየረ፣ ተስፋ የቆረጥንበትን ነገር

እየቀየረ፣ በጊዜ የሚመራን እውነተኛ አባታችን ነው። እግዚአብሔር ላደረገልን ነገር ሁሉ

ልናመሰግነው ይገባል። እስራኤላዊያን የኤርትራን ባህር ከፍሎ ካሻገራቸው እና

ጠላቶቻቸውን በቀይ ባህር ከጣለላቸው በኋላ እንዲህ ብለው ተቀኙ፤ “በክብር ከፍ

ከፍ ብሏልና ለእግዚአብሔር እዘምራለሁ፤ ፈረሱንና ፈረሰኛውን በባህር ጣለ። ጉልበቴ

ዝማሬዬ እግዚአብሔር ነው፤ መድሃኒቴ ሆነልኝ፣ ይህ አምላኬ ነው አመሰግነውማለሁ”

ዘጸ 15፤1-3 በጉዞአቸው ላይ የረዳቸውን እግዚአብሔርን አመሰገኑ። እግዚአብሔር

ምስጋና ይገባዋል። ብዙ ጊዜ የተለያየ ነገር ሲገጥመን ብዙ እንጸልያለን እናጸልያለን።

እግዚአብሔር ለሚያደርገው ነገር ምስጋና ማቅረብ ግን ያንሰናል። ያደረገውን እየቆጠርን

ልናመሰግንው ይገባል።

የጸሎትና የምስጋና አቅጣጫዎች

• እግዚአብሔር አመቱን በሰላም አስጀምሮ እዚህ ስላደረስን ምስጋና

• ስለ መዳናችን እና እርሱን ስለማወቃችን

• በኑሮአችን፣ በመንፈሳዊ ህይወታችን፣ በአገልግሎታችን፣ ጌታ ጣልቃ እየገባ

ስለመራን እና እዚህ ስላደረሰን

• በቤተክርስቲያን ስላለው አገልግሎት

Page 17: October 14 November 3, 2019 · 2019-10-16 · የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ህብረት ቤተ ክርስቲያን ሎስ አንጀለስ የሃያ አንድ ቀን ጾም

ኦክቶበር 16 ሶስተኛ ቀን

ራስን መመርመር፤ የግል ህይወት ተሃድሶ

የንባብ ክፍል ሰቆ 5፤21 አቤቱ ወደ አንተ መልሰን፤ እኛም እንመለሳለን ዘመናችንን

እንደቀድሞው አድስ

በዚህ የጾም ጸሎት ጊዜ ትኩረት ከምናደርግባቸው ነገሮች አንዱ ተሀድሶ ነው (የግል

ህይወት ተሀድሶ፣ የአገልግሎት ተሃድሶ እና የቤተክርስቲያን ተሃድሶ)። አንድ ነገር

መታደስ አስፈለገው ማለት በፊት ከነበረው ማንነቱ ለቋል ወይንም ትንሽ የመቀየር ነገር

አለው ማለት ነው። ይሄን ደግሞ ልናውቅ የምንችለው ራሳችንን መመርመር ስንችል

ነው። “አቤቱ መርምረኝ ልቤንም እውቅ ፈትነኝ መንገዴንም እወቅ በደልንም በእኔ

ውስጥ ብታገኝ እይ የዘላለምንም መንገድ ምራኝ” መዝ 29፤ 23_24 ብዙ ጊዜ፤

ቤተክርስቲያን ደክማለች፣ ህይወት እንደ ድሮው አይደልም፣ ይባላል። እውነት ነው፤

ህይወታችን የሚገባውን ያህል በጨለማው አለም ላይ እያበራ አይደለም። ለዚህ ተጠያቂ

የምናደርገው ግን ሌሎቹን ነው። ራሳችንን ምንም እንደሌለንበት ነው የምናስበው። ነገር

ግን ከራሳችን ነው መጅመር ያለብን። እራሳችንን በየቀኑ መመርመር አለብን፤

ትክክለኛውን እኛነታችንን ሰዎች አይደሉም የሚነግሩን። በእውነት እና በመንፈስ ሆነን

በፊቱ ስንቀርብ ልናስተካክለው የሚገባንን ነገር ይነግረናል። በዚህ ቀን ሁላችንም

የሌሎቹን ሰዎች ኃጢአት ይቅር እንዲል ሳይሆን፣ የእኛን የግል ህይወታችንን በፊቱ

እናቀርባልን፤ እንድናስተካክለው የሚገባንን ደግሞ ልናስተካክል እና ንሰሐ ልንገባ

ይገባል። “ከወዴት እንደ ወደቅህ አስብ ንሰሐም ግባ” ዮሐ 3፤17 ሕይወታችን የት ነው

ያለው? ንስሐ እንግባ! ራሳችንን እንመርምር።

የዕለቱ የጸሎት አርዕስቶች

• ለእግዚአብሔር እንደሚገባ ባልኖርንበት ነገር ንስሐ

• እራሳችንን እግዚአብሔር እንዲያሳየን

Page 18: October 14 November 3, 2019 · 2019-10-16 · የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ህብረት ቤተ ክርስቲያን ሎስ አንጀለስ የሃያ አንድ ቀን ጾም

• በብዙ ድካሞች እየተመላለስን ድካሙንና ችግሩን የሌሎች ብቻ አድርገን

በማሰባችን ንስሃ

• ዕውር፣ የተራቆትህ፣ መሆንህን ስለማታውቅ እንደተባለው ደህና ነኝ የሚል

የድንዛዜ መንፈስ ከእኛ እንዲወገድ (ራእ 2፤15-20)

• እውነተኛ ንሥሐህ እና መመለስ እንዲሆን

ኦክቶበር 17 አራተኛ ቀን

የአገልግሎት ተሃድሶ

የንባብ ክፍል ነኅምያ 1 እና 1ኛ ቆሮ 3

በአገልግሎት ዙሪያ የጌታን ስራ እንደ ትርፍ የሚመለከቱና እና በቸልተኝነት የሚሰሩ

ብዙ ሰዎች አሉ። የጌታ ስራ ከማንኛውም ስራ እና አገልግሎት የላቀ እና የከበረ ነው።

ሐዋሪያው ጳውሎስ ለአግሪጳ፤ ከጌታ የተቀበልከውን አገልግሎት እንድትፈጽመው

ተጠንቀቅ በሉልኝ ይላል (ፊል 4፤7) ። አገልግሎት ከሰዎች የተቀበልነው አይደለም።

የአገልግሎት ጸጋን ማንም አይሰጥም፤ የሚሰጥ እግዚአብሔር ብቻ ነው።

የቤተክርስቲያን አገልጋዮች የሚያደርጉት ነገር፣ ጸጋን ለይቶ ማሰማራት ነው። ስለዚህ

ከጌታ የተቀበልነው መሆኑን አምነን በታማኝነት እና በትጋት ማገልገል አለብን። ሌላው

ደግሞ፤ በአገልግሎት የሚገባውን ያህል የጌታን ክብር እያየን ሰላልሆነ፣ የጌታ ክብር

በአገልግሎታችን እንዲገለጥ ያስፈልጋል። ስለዚህ ጉዳይ አጥብቀን መጸለይ አለብን።

በአገልግሎታችን ላይ እውነተኛ ተሐድሶ ያስፈልገናል። ልማዳዊ የሆኑ ነገሮችን ብቻ

እየፈጸምን ልንኖር አይገባንም። ከጌታ እየሰማን፣ አዳዲስ ራዕይ እየተቀበልን፣ ትኩስ

በሆነና በጋለ ህይወት ሆነን ማገልገል አለብን።

የዕለቱ የጸሎት አርዕስቶች

• በአገልግሎታችን እውነተኛ ትጋት እና መሰጠት እንድናሳይ

• አገልግሎት ከጌታ የተቀበልነው መሆኑን በማሰብ በአክብሮት እንድናገለግል

• በአገልገሎታችን እውነተኛውን የጌታን ክብር እንድናይ

Page 19: October 14 November 3, 2019 · 2019-10-16 · የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ህብረት ቤተ ክርስቲያን ሎስ አንጀለስ የሃያ አንድ ቀን ጾም

• አባቶቻችን ባገለገሉበት ሐይልና ክብር እንድናገለግል

• በጌታ ፊት ሲታይ ተቃጥሎ የሚቀር ሳይሆን ጌታ የሚቀበለውን አገልግሎት

እንድናገለግል።

ኦክቶበር 18 አምስተኛ ቀን

የቤተክርስቲያን ተሃድሶ

የንባብ ክፍል ራዕ 3፤15-20

የሎዶቅያ ቤተ ክርስቲያን በምድራዊ ሃብት እና ብልጽግና የተባረከች፣ ምንም

ያልጎደለባት ነበረች። ከዚህ የተነሳ ያላት ስጋዊ ምቾት መንፈሳዊ አይኗን ደፍኖባት

ስለነበረ፤ “እውር፣ የተራቆትሽ፣ ደሃ እና ጎስቋላ መሆንሽን ስለማታውቂ” ብሎ

ይጠራታል። እርሷ ስለ ራሷ የምትናገረው እና ጌታዋ ስለ እርሷ የሚናገረው ፈጽሞ

የተራራቀ ነው። ዛሬም ቢሆን ቤተክርስቲያን ስለ ራሷ የምትናገረው እና ጌታ ስለ እርሷ

የሚናገረው የተለያየ ይሆናል ብዬ አስባለሁ። የሎዶቅያ ቤተክርስቲያን አይኗ የተዘጋባት

ብቻ ሳትሆን፣ ጌታዋን ከመካከልዋ አስወጥታ ለብቻዋ ሃይማኖታዊ ስርዓት ፈጻሚ

ሆናለች። እውነት ነው፤ የተጓደለ ሃይማኖታዊ ስርዓት የለም፤ ነገር ግን ጌታ የሌለበት

ስርዓት ብቻ ሆና ቀረች። ጌታዋ በውጭ ሆኖ ያንኳኳል፤ እባክሽ ከፈችልኝ ልግባ እና

እውርነትሽን ላስወግድ፣ ደንቆሮነትሽን ጆሮሽን ከፍቼ እኔን እንድትሰሚ ላድርግ

ይላታል። ዛሬም፤ ጌታ በውጭ ሆኖ ስርዓት ብቻ እየፈጸምን እንዳይሆን መፍራት እና

መጠንቀቅ አለብን። ልባችንና በራችንን ከፍተን ጌታን ልናስገባ ይገባል። የቤቱ ባለቤት

ውጭ ሆኖ እኛ ዋና እንዳንሆን ልንፈራ ያስፈልጋል።

የዕለቱ የጸሎት አቅጣጫ

• ቤተ ክርስቲያን ጌታ እንደሚያያት ራሷን ማየት እንድትችል

• ከጌታ ጋር እንዳንተተላለፍ፤ እኛ ሃብታም ነን እያልን፣ እርሱ ደሃ፣

የተራቆታችሁ እንዳይለን

• ልባችንን ለጌታ ከፍተን ማስገባት እንዲሆንልን

Page 20: October 14 November 3, 2019 · 2019-10-16 · የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ህብረት ቤተ ክርስቲያን ሎስ አንጀለስ የሃያ አንድ ቀን ጾም

• የቃል የአምልኮ እና ይጸሎት ህይወታችን እንዲታደስ

• ቤተክርስቲያን እንደሚገባ ጌታን እንድትገልጥ፤ ጌታን ባልገለጠችበት እና

ብርሃን ባልሆነችበት ነገር ላይ ንስሐ መግባት።

ኦክቶበር 19 ስድስተኛ ቀን

የሐገር ተሃድሶ

የንባብ ክፍል ዳን 6 እና 9

ዳንኤልም ሆነ ሌሎች የብሉይ ኪዳን መሪዎች እና አገልጋዮች ንስሐ የገቡት እና

የተናዘዙት ስለራሳቸው ኃጢአት ብቻ ሳይሆን ሰለ ቀደሙት አባቶቻቸው እና መሪዎች

ጭምር ነበር። ምክንያቱም ኃጢአት እና መዘዙ ትውልድን ተሻግሮ የመገስገስ እና

የማጥፋት አቅሙ ቀላል ስላልሆን። የኃጢአት እና የግፍ ሐይል አልፎ ወደ ትውልዶች

ስለሚሄድ ይሄው ከአዳም ጀምሮ የኃጢአት፣ የክፋት እና የአምጽ ሐይል እየጨመረ

ነው የመጣው። ስለዚህ በአባቶቻችንም፣ ማለት በሃገር መሪዎች የተሰራውን ግፍ እና

በደል እግዚአብሔር ይቅር እንዲል እና ምህረት በምድራችን ላይ እንዲመጣ መማለድ

እና መጮህ ያስፈልገናል። ያቤጽ በ1ኛ ዜና 4፤9-10 እንዲህ ሲል ለሀገሩ ጸለየ፤ አቤቱ

መባረክን ባርከኝ፣ ሐገሬንም አስፋ፣ እጅህም በእኔ ላይ ትሁን፣ አንተን እንዳልበድል

ከክፋት ጠብቀኝ። እግዚአብሔርም ጸሎቱን ሰማው፤ አገሩን ባረከለት። ዛሬም

ለሐገራችን መባረክ እና አንድነት፣ ሰላም መፍሰስ አጥብቀን በዕንባ እና በለቅሶ ልንጸልይ

ያስፈልጋል።

የዕለቱ የጸሎት አቅጣጫ

• በምድራችን ላይ የተሰራውን ግፍ እና በደል እግዚአብሔር ይቅር እንዲል

• በምድራችን ላይ የነበረውንና አሁንም ያለውን ዘረኝነት እና መናናቅ ጌታ ይቅር

እንዲል

Page 21: October 14 November 3, 2019 · 2019-10-16 · የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ህብረት ቤተ ክርስቲያን ሎስ አንጀለስ የሃያ አንድ ቀን ጾም

• ለጥላቻ እና ለመከፋፈል ምክንያት የሚሆኑ የሃገር መሪዎች እና ፖለቲከኞችን

እንዲሁም አክቲቪስቶችን ይቅር እንዲል፤ ካልተመለሱ ከሥፍራቸው

እንዲወገዱ።

• አድሎ፣ ጉቦኝነት እና ደሀውን በመበዝበዝ የተሰራውን ስራ ጌታ ይቅር

እንዲል።

• ከዚህ በኋላ ያለው ዘመን በምድራችን ላይ የፍቅር እና የሰላም እንዲሆን

• የሃገሪቱን መሪዎች እግዚአብሔር እንዲረዳቸው፤ ከክፉ እንዲጠብቃቸው እና

አገራቸውን በታማኝነት ማገልገል እንዲችሉ (2ኛጢሞ 2፤1_15)

ኦክቶበር 20 ሰባተኛ ቀን

በምዕመናን መካከል ያለ ፍቅር እና አንድነት

እንዲታደስ

የንባብ ክፍል 1ኛ ቆሮ 13 እና ዮሐ 13

በክርስትና ህይወት ጉዞ ላይ ትልቁን እና ዋናውን ቦታ የያዘው ነገር ቢኖር ፍቅር ነው።

ፍቅር ከሌለን የምናደርገው ነገር ሁሉ ባዶ እንደሆነ ከንቱም እንደሆነ ሐዋሪያው

ጳውሎስ በ1ኛ ቆሮ13 ላይ ይናገራል። ጌታም ለደቀመዛሙርቱ ሲናገር በፍቅራችሁ

ያውቋችኋል ነው ያለው። የአማኞች ዋና መታወቂያቸው ምንድን ነው? ቢባል፣ የእርስ

በእርስ መዋደድ ነው። የእርስ በእርስ መዋደድ ሲባል በቢጤ እና በጎራ ተለያይቶ

መዋደድ ማለት አይደለም። በጌታ የዳነ ወንድማችን በመሆኑ ብቻ ልንወደው እና

ልናፈቅረው እንደሚገባ የጌታ ቃል ይነግረናል። ዛሬ በመካከላችን እውነተኛና ንፁህ

በሆነ፤ ክርስቶስ እኛን በወደደበት ፍቅር ሌሎቹን እንወዳለን ወይ? ዛሬ፤ ያ እውነተኛ

የክርስቶስ ፍቅር በህይወታችን መኖሩን ራሳችንን መፈተሽ አለብን። ያለዚያ

አገልግሎታችን እና ያደረግናቸው ሩጫዎች ሁሉ በዜሮ መባዛታቸው ነው። ፍቅር

የሌለበት ማንኛውም ነገር ሁሉ ውጤቱ ዜሮ ነው።

Page 22: October 14 November 3, 2019 · 2019-10-16 · የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ህብረት ቤተ ክርስቲያን ሎስ አንጀለስ የሃያ አንድ ቀን ጾም

የጸሎት አርዕስት

• በእውነት ለወንድሞቻችን እና ለእህቶቻችን ባላሳየነው ፍቅር ጌታ ይቅር

እንዲለን

• እውነተኛው የክርስቶስ ፍቅር በመካከላችን እንዲፈስ፤ ክርስቶስ እኛን

በወደደበት ፍቅር እርስ በእርሳችን እንድንዋደድ

• ቃሉ እርስ በእርሳችሁ ተናነጹ እንደሚል፤ በመተናነጽ ፋንታ በተናናቅንበት

እና በተለያየንበት ነገር ላይ ጌታ ይቅር እንዲለን።

• ቅዱስ ቃሉ ፍቅራችሁ ያለግብዝነት ይሁን እንደሚል፣ ያለግብዝነት

እንድንዋደድ

• አህዛብ በፍቅራችን እንዲያውቁን

• ወንድሜ ከእኔ ይሻላል የሚል መንፈስ በመካከላችን እንዲፈስ

ኦክቶበር 21 ስምንተኛ ቀን

ጸሎት እና የግል ጥሞና (የግል መሠዊያችን)

እንዲታደስ

የንባብ ክፍል ሉቃ 7 10 ፤38-42

ማሪያም እና ማርታ የኢየሱስ ወዳጆች ነበሩ። በተለይ ዮሐ 11 የጌታ ወዳጆች ብሎ

ይጠራቸዋል። ማሪያም ሁልጊዜ በእግሩ ስር አትጠፋም ነበር። ማርታ ደግሞ በብዙ

ነገር ትባክናለች፤ ጌታን ለማስደሰት ብዙ ትደክማለች። ምንም ብዙ ብትደክምም ጌታን

ደስ ማሰኘት አልቻለችም። ጌታ እንዲያውም “ማርታ በብዙ ነገር ትጨነቂያለሽ

ትታወኪያለሽም” ነው ያላት። ጌታ የወደደው የማርታን ምርጫ ሳይሆን የማሪያምን

ምርጫ ነበር። ዛሬም ብዙ ጌታን ለማስደሰትም ሆነ ራሳችንን ለማስደሰት ደፋ ቀና

እንላለን፤ እንባካንለን፣ እንሮጣለን። ጌታ ግን በእኛ ሩጫ እና መባከን ብዙ የሚደሰት

አይመስለኝም። ጌታ ለማርታ፤ “የሚያስፈልገው አንድ እና ጥቂት ነገር ነው ፤ እርሱንም

ማርያም መርጣለች” አላት። የማሪያም ምርጫ በእግሩ ስር ሆኖ ከእርሱ መስማት ነበር።

ከዚህ የሚበልጥ ምርጫ የለም፤ ግሩም ምርጫ ነው። በጌታ እግር ስር ሆኖ ዕለት ዕለት

Page 23: October 14 November 3, 2019 · 2019-10-16 · የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ህብረት ቤተ ክርስቲያን ሎስ አንጀለስ የሃያ አንድ ቀን ጾም

መማር፣ መመሪያን መቀብል ያስፈልጋል። ዛሬ እኛ አማኞች ያለን የግል የጥሞና ጊዜ

ምን ይመስላል? በእውነት በየቀኑ ከጌታ ጋር የግል ጊዜ አለን ወይ? የጸሎት እና የቃል

ንባባችን ጊዜ ምን ይመስላል? የብዙዎቻችን የጥሞና ጊዜ ፈርሷል ብዬ ብናገር ያጋነንሁ

አይመስለኝም። የሙሉ ጊዜ አገልጋዮች እና መሪዎች እንኳን አገልግሎታቸውን

የሚሰጡት ድሮ በሚያውቁት ልምድ እና ከአንዳንድ መጽሐፍ በሚያነቧቸው እውቀቶች

እንጂ ዕለት ዕለት በጌታ ፊት እየቀረቡ መመሪያ መቀብል ብዙም አይታይም። ስለዚህ

ነው የዛሬዋ ቤተክርስቲያን አቅም የሌላት እና ደካማ የሆነችው። ብዙ በጌታ ፊት ጥሞና

የለንም፤ ነገር ግን እንዲመጣ የምንፈልገው መንፈሳዊ መነቃቃት ትልቅ ነው።

በመጀመሪያ፤ የፈረሰው መሰዊያችን (የጥሞና ጊዜ) በእያንዳንዳችን ህይወት ይታደስ።

ከዚያ በኋላ በህይወታችን የምንፈልገው መነቃቃት ሁሉ ይመጣል።

የዕለቱ የጸሎት አቅጣጫ

• ከጌታ እግር ስር ሆነን የጌታን ፊት እንደሚገባ ባልፈለግንበት ነገር ላይ ጌታ

ምህረት እንዲያደርግ ንስሐ

• የጣልነው የጥሞና ጊዜ እንደገና በበለጠ ሁኔታ እንዲታደስ

• ጌታን በመባከን ለማስደሰት ከመሞከር በእግሩ ስር ሆነን ከእርሱ መስማትን

ምርጫችን እንድናደርግ

• በግላችን ለቃሉ እና ለጸሎት እንዲሁም ጌታን ለመታዘዝ ያለን ህይወት

እንዲያድግ

ኦክቶበር 22 ዘጠነኛ ቀን

የአምልኮ ህይወት እንዲታደስ

የንባብ ክፍል ያዕቆብ 1 ያዕቆብ ሰለ እውነተኛ አምልኮ ምንነት ይናገራል። እውነተኛ

አምልኮ ማለት፤ መበለቶችን መርዳት እና ወላጅ የሌላቸውን ልጆች መርዳት ነው

ይላል። እውነተኛ አምልኮ በተግባር የሚገለጥ እንጅ በአንደበት የሚነገር ብቻ

አይደልም። ብዙ ጊዜ አምልኮን ከዝማሬ ጋር ብቻ እናገናኘዋለን። እውነት ነው ዝማሬ

Page 24: October 14 November 3, 2019 · 2019-10-16 · የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ህብረት ቤተ ክርስቲያን ሎስ አንጀለስ የሃያ አንድ ቀን ጾም

የአምልኮ ክፍል ነው፤ ሆኖም መታዘዝ የሌለበት ዝማሬ አምልኮ ነው ማለት አይቻልም።

ዝማሬ አምልኮ ሊሆን የሚችለው መታዘዝ እና መስተጋብር ሲጨመርበት ነው።

አምልኮ በጨለማው አለም ላይ ብርሃን መሆን፣ ክርስቶስን ማሳየት ነው። እናንተ የአለም

ብርሃን ናችሁ፤ የምድር ጨው ናችሁ፤ እንደሚል እውነተኛ አምልኮ ብርሃንነታችንና

ጨውነታችንን ለማያምኑ ሰዎች ማሳየት ነው። አብርሃም አምልኮውን የገለጠው ፈጽሞ

እግዚአብሔርን በመታዘዝ ነው። አንድ ልጅህን ሰዋልኝ ሲለው እሽ ብሎ ታዘዘ። በዘፍ

22 በእውነት እንደምትፈራኝ አወቅሁ አለው። መታዘዝ እና እግዚአብሔርን መፍራት

የሌለበት አምልኮ፣ አምልኮ ሊባል አይችልም። በዚህ ዘመን ምን ያህል መታዘዝ እና

ፈሪሃ እግዚአብሔር አለ ብለን ስናስብ፤ ከመቸውም ጊዜ ይልቅ ፈሪሃ እግዚአብሔር

ከምዕመናን እና ከአገልጋዮች ህይወት እየጠፋ ያለበት ጊዜ ነው። እንግዲህ፤ አምልኮ

በአራት ነገር ይገለጣል፤

1. በማፍቀር፤ ከማንም በላይ እግዚአብሔርን እንውደድ። የምናደርገውን ሁሉ

እግዚአብሔርን ከመውደድ እናድርገው።

2. በመታዘዝ፤ እግዚአብሔርን ምንም እስክማይቀረን ድረስ እንታዘዘው።

“መታዘዝ ከመስዋዕት፣ ማዳመጥም የአውራ በግ ስብ ከማቅረብ ይበልጣል”

ይላልና (1ኛ ሳሙ 15፤23።

3. በፈሪሃ እግዚአብሔር፤ ፈሪሃ እግዚአብሔር ሲባል፤ አብርሃም እግዚአብሔርን

እንደፈራው ከአክብሮት ጋር ማለት ነው እንጂ፤ እግዚአብሔርን እንደ ጠላት

እንየው ማለት አይደለም።

4. በዝማሬ እና በምስጋና፤ እግዚአብሔርን ሁልጊዜ በዝማሬ እና በውዳሴ

ስለማንነቱ ልናመሰነው እና ልናደንቀው ይገባል።

የዕለቱ የጸሎት አቅጣጫ

• እንደሚገባ ጌታን ባላመለክንበት ላይ ንስሐ

• እውነተኛውን አምልኮ፤ ማለትም ወላጅ የሌላቸውን ልጆች እና ባልቴቶችን

በመደገፍ አምልኮአችንን በተግባር መግለጥ እንድንችል

• በውጭ ላለው አለም ጨው እና ብርሃንነታችን እንዲገለጥ፣ እንዲታይ

Page 25: October 14 November 3, 2019 · 2019-10-16 · የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ህብረት ቤተ ክርስቲያን ሎስ አንጀለስ የሃያ አንድ ቀን ጾም

• ለእግዚአብሔር የሚገባውን አምልኮና ክብር ማቅረብ እንድንችል። ፈሪሃ

እግዚአብሔር እና መታዘዝ በህይወታችን ላይ እንዲጨምር

ኦክቶበር 23 አስረኛ ቀን

ወደ ወንጌል ምስክርነት እንመለስ

የንባብ ክፍል ሐዋ 1፤8 ማቴ 28፤18_20

በእውቀት ደረጃ እንደሚታወቀው በተግባር ለማድረግ ለብዙዎች ዳገት እንደሆነው

የቤተክርስቲያን ዋና ተልዕኮዋ የወንጌል ስርጭት ነው። ቤተክርስቲያን በምድር ላይ

ያለችው በጎ አድራጎት ድርጅት ሆና ልማት ልታከናውን ሳይሆን የክርስቶስ ምስክር ሆና

ወንጌልን ላልሰሙት ለማሰማት እና ወንጌልን ለማሰራጨት ነው። ይህን አደራ ሊሰራ

የሚችል ማንም የለም። ይሄ ተልዕኮ ለቤተ ክርስቲያን ብቻ የተሰጠ ነው። የዳነ ሰው

ሁሉ ሊያደርገው የሚገባ ነገር መመስከር ነው። ባለፉት ዘመናት ቤተክርስቲያን በስደት

በነበረችበት ጊዜ ምዕመናን ሁሉ መስካሪዎች ነበሩ። ከዚህ የተነሳ ቤተክርስቲያን አደገች፤

ብዙ አብያተ ክርስቲያናት ተመሰረቱ። የመንግስት ሰራተኞች ለስራ ተመድበው ወደ

ገጠር ሲወጡ አጥቢያ ቤተክርስትያን ይተክላሉ። የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ከዘጠና

በመቶ በላይ አጥቢያዎች የተተከሉት፤ በመንግስት ሰራተኞች ነበር እንጂ በሙሉ ጊዜ

አገልጋዮች አልነበረም። ዛሬ መመስከር ከብዙዎቻችን አንደበት ላይ እየጠፋ፣ ለጥቂቶች

ብቻ እየተተወ የሄደ ነገር ነው። መመስከር ለሁሉም የተሰጠ ነገር እንደ መሆኑ፤

የመመስከር ህይወታችን እንዲታደስ አጥብቀን መጸለይ ያስፈልጋል።

የዕለቱ የጸሎት አቅጣጫ

• የተሰጠንን የምስክርነት አደራ እንደሚገባ ባለመወጣታችን ንስሐ

• ቤተ ክርስቲያን ወንጌልን ዋና አጀንዳዋ አድርጋ እንድትንቀሳቀስ ከተልዕኮዋ

የሚያወጧትን ነገሮች ሁሉ ማስወገድ እንድትችል። አንደኛውን አንደኛ

አድርጋ እንድትቀጥል።

• የመመስከር ሐይል በሁሉም አማኝ ላይ እንዲፈስ፣ ጌታ አቅም እንዲሰጠን

Page 26: October 14 November 3, 2019 · 2019-10-16 · የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ህብረት ቤተ ክርስቲያን ሎስ አንጀለስ የሃያ አንድ ቀን ጾም

• የወንጌልም ሐይል በመካከላችን እንዲሰራ ብዙዎች እንዲጨመሩ

• አዳዲሶችን የምናገኝበት እና እውነተኛ ደቀ መዝሙር የምናደርግበት ጥበብ

እና ሐይል እንዲሰጠን

ኦክቶበር 24 አስራ አንደኛ ቀን

መንፈስ ቅዱስ በመካከላችን በሙላት እንዲሰራ

የንባብ ክፍል ዘካ 6፤4-6 ሐዋ 2፤1-4

ክርስትና ህይወት ያለ መንፈስ ቅዱስ ዳገት እና ተራራ ነው። ለዘሩባቤል የተነገረው

በመንፈሴ ነው እንጅ በሐይል እና በብርታት አይደልም የሚል ነው። የእግዚአብሔር

ስራ በሰው ሐይል ወንም ጥበብ የሚሰራ አይደልም። በመንፈስ ቅዱስ ነው የሚሰራው።

የሀዋሪያቱን አገልግሎት የቀየረው ነገር ቢኖር መንፈስ ቅዱስ ነው። ባለሀምሳ የተባለው

ቀነ መንፈስ ቅዱስ ከተሞሉ በኋላ የነበራቸው አገልግሎት ፈጸሞ የተለየ ነበር። በንድ

ስብክት ሶስት ሺህ ሰዎች ዳኑ። እነርሱም በታላቅ ሀይል ተሞልተው ወንጌልን የሰበኩበት

ወንጌል ከኢየሩሳሌም ወጥቶ ወደ አለም ዙሪያ ሁሉ የሄደብት ጊዜ ነበር። ዛሬም መንፈስ

ቅዱስን አብዝተን ልንፈልግ ይገባል።

የዕለቱ የጸሎት አቅጣጫ

• በመንፈስ ቅዱስ ሐይል ለመሞላት ጥማት እና ናፍቆት እንዲያድርብን

• ልባችንና መንፈሳችንን ለመንፈስ ቅዱስ እንድንከፍት

• መንፈስ ቅዱስ በሀይል እንዲሰራ የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት እና ሙላት

ያልተለማመዱ ሰዎች እንዲለማመዱ።

• ቤት ክርስቲያናችን መንፈስ ቅዱስ በሐይል የሚሰራባት እንድትሆን (አሁን

ከሚሰራባት በላይ ማለት ነው።)

Page 27: October 14 November 3, 2019 · 2019-10-16 · የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ህብረት ቤተ ክርስቲያን ሎስ አንጀለስ የሃያ አንድ ቀን ጾም

ኦክቶበር 25 አስራ ሁለተኛ ቀን

ለእግዚአብሔር ያለን ፍቅር እንዲጭምርና እንዲታደስ

የንባብ ክፍል 2ኛቆሮ 5፤14-5 ዮሃ 20፤21 ሮሜ 8፤35-37

የመንፈሳዊ መነቃቃት ምንጩ እና ዋናው ለእግዚአብሔር ያለን ፍቅር ነው። ባለፉት

ዘመናት በብዙ መከራ ያለፉት ሰዎች ያን ሁሉ መከራ እንዲቀበሉ ያደረጋቸው ነገር

ምንድን ነው ሲባል ለእግዚአብሔር ያላቸው ፍቅር ነው። ዋጋ እንድንክፍል እንድንሰጥ

ሊያደርገን የምችል ነገር ለእግዚአብሔር ያለን ፍቅር ነው። ብዙ ዋጋ ከፍለን ለማገልገል

ካዳገተን ለጌታ ያለን ፍቅር ቀዝቅዟል ማለት ነው። ዮሃ 4፤21 የሚወደኝ ቢኖር ትዕዛዜን

ይጠብቃል እኔም እወደዋለሁ ራሴንም እገልጥለታለሁ የላል። የምናደርጋቸውን ነገሮች

በሙሉ ጌታን ከመውደድ አንጻር ብቻ እናድርጋቸው። አንቀሳቃሽ ሀይላችን የጌታ ፍቀር

መሆን አለበት። እርሱ ለእኛ ያለው ፍቅር ከመታወቅ ያልፋል (ኤፌ 3፤18)።

የእግዚአብሔርን ጥልቅ ፍቅር ልንረዳው አንችልም እጅግ ጥልቅ ነው። የርሱን ፍቅር

ለመረዳት ስንጸልይ እየተደነቅን እንኖራለን። ዛሬ እኛ ለእግዚአብሔር ያለን ፍቅር ምን

ይመስላል ራሳችንን? ብለን ማየት አለብን። በእውነት የምናደርጋቸውን ሁሉ

እምናደርጋቸው ከጌታ ፍቅር የተነሳ ነው

የዕለቱ የጸሎት አቅጣጫዎች

• ለእግዚአብሔር ያለን ፍቅር እንዲታደስ

• ከእግዚአብሔር ይልቅ ሌሎቹን ባስቀደምንበት እግዚአብሔር ይቅር እንዲለን

ንስሐ

• የምናደርገውን ሁሉ ከጌታ ፍቅር የተነሳ እንድናደርገው

• በእውነት በእግዚአብሔር ፍቅር እንድንቃጠል፤ ዋጋ እንድንከፍል የሚያደርግ

የጌታ ፍቅር በእኛ ላይ እንዲሆን።

• አለምን የሚወድ የግዚአብሔር ፍቅር በእርሱ የለም ስለሚል በእውነት የአለም

ፍቅር ከእኛ እንዲወጣ

Page 28: October 14 November 3, 2019 · 2019-10-16 · የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ህብረት ቤተ ክርስቲያን ሎስ አንጀለስ የሃያ አንድ ቀን ጾም

ኦክቶበር 26 አስራ ሶስተኛ ቀን

የስርጭት ጣቢያዎች

የንባብ ክፍል ሐዋ 13-14

ቤተ ክርስቲያናችን ወደ አራት የሚደርሱ የስርጭት ጣቢያዎች አሏት። ከእነዚህ ሶስቱ

እሁድ ጥዋት የራሳቸውን የአምልክ ፕሮግራም የሚያደርጉ ሲሆን አንደኛው የስርጭት

ጣቢያ ቅዳሜ በወር አንድ ጊዜ ብቻ ያደርጋል። እነዚህ ጣቢያዎች የሚገባውን ያህል

እንዲያድጉ በጸሎት መደገፍ ያስፈልጋል። ወንጌል ያለ ጸሎት ሊስፋፋ አይችልም።

በመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን ሐዋ 2፤42-44 ወንጌል በፍጥነት እንዲስፋፋ ካደረገው

ነገር ምዕመናን በጸሎት መትጋታቸው ነበር።

የዕለቱ የጸሎት አቅጣጫዎች

• የስርጭት ጣቢያወች ያሉትን ሰብስቦ ከማገልገል ባለፈ ሌሎች አዳዲስ

ነፍሳትም በመካከላቸው እንዲጨመሩ

• ወደ አጥቢያነት እንዲያድጉ

• አካባቢያቸውን በወንጌል እንዲደርሱ ጌታ እንዲረዳቸው

• የሚገዳደራቸውን ሀይል ጌታ እንዲመታ፤ ጥሰው እንዲሄዱ

• በገንዘብ አቅምም፤ በአመራር ጥራትም፤ በሰው ሀይልም እንዲያድጉ

ኦክቶበር 27 አስራ አራተኛ ቀን

የጸጋ ስጦታወች በሙላት በቤተክርስቲያን በሙላት

እንዲሰሩ

የንባብ ክፈል 1ኛጴጥ 2፤9-10 1ኛቆሮ 12

አንድ ሰው ሲናገር እንዲህ አለ። የአዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን ኳስ ሜዳ አይደለችም

አለ፤ ኳስ ሜዳ ሃያ ሁለት ሰው ይጫወታል ሃምሳ ሺህ ሰው ቲፎዞ ይሆናል ጨዋታውን

Page 29: October 14 November 3, 2019 · 2019-10-16 · የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ህብረት ቤተ ክርስቲያን ሎስ አንጀለስ የሃያ አንድ ቀን ጾም

ያያል። እውነት ነው የአዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን ጥቂት ሰዎች ተዋናይ ሆነው ሌሎች

የሚመለከቱባት ሳትሆን ሁሉም ጌታ በሰጠው ጸጋ የሚያገለግልባት ናት። ሐዋሪያው

ጴጥሮስ 1ኛ ጴጥ 2፤9 ከጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን የጠራችሁ የእርሱን በጎነት

እንድትነግሩ የተመረጠ ትውልድ የንጉስ ካህናት ናችሁ ይላል። ከጨለማ ወደሚደነቅ

ብርሃን ሲጠራን የንጉስ ካህናት ሊያደርገን ነው። ካህን ማለት ደግሞ በእግዚአብሔር

እና በሰው መካከል የሚሆን ማለት ነው። አገልጋይ ማለት ነው። በአዲስ ኪዳን ሁሉም

ሰው ካህን ነው። ስለዚህ ሁሉም በተሰጠው ጸጋ ማገልገል አለበት። የጸጋ ስጦታወች

የተሰጡት ለቤተክርስቲያን ነው። ስለዚህ ሁሉም ጸጋወች እንዲሰሩ መጸልይ እና

ምዕመናንን ማበረታታት ያስፈልጋል። ሃዋሪያው ጳውሎስ ለጢሞቲወስ እጆቸን

በመጫን ባንተ ያለውን የትንቢት ጸጋ አበረታታለሁ፤ እንዲሁም እሳት እንደሚያቀጣጥል

አቀጣጥላለሁ ይለዋል። ዛሬም ጸጋዎች በቤተክርስቲያን ስለሌሉ ብቻ ሳይሆን ምናልባት

ስለተዳፈኑ ሊሆን ስለሚችል በምዕመናን ውስጥ ያለ ጸጋ እንዲነሳሳ ማበረታታት

ያስፈልጋል።

የዕለቱ የጸሎት አቅጣጫዎች

• ሁሉም ጸጋ ስጦታዎች በሙላት በቤተክርስቲያናችን እንዲሰሩ

• በተለያየ ምክንያት የተዳፈኑ የጸጋ ስጦታወች እንዲነሳሱ

• የሐይል ስጦታወች በቤተክርሰቲያን ውስጥ እንዲሰሩ

• የጸጋ ስጦታወችን በሰፊ ልብ ማስተናገድ እንዲቻል

• በዘመኑ ያሉ እውነተኛ ያልሆኑ ሀሰተኛ ነብያት እና መምህራንን የፈርኦንን

ጠንቋዮች የእግዚአብሔር ጣት እንደዋጠች እውነተኛይቱ የእግዚአብሔር ጣት

ተገልጣ እንድትውጣቸው። ።

Page 30: October 14 November 3, 2019 · 2019-10-16 · የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ህብረት ቤተ ክርስቲያን ሎስ አንጀለስ የሃያ አንድ ቀን ጾም

ኦክቶበር 28 አስራ አምስተኛ ቀን

ለቤተክርስቲያን ሽማግሌዎች እና የሙሉ ጊዜ

አገልጋዮች

የንባብ ክፍል 1ኛ ጢሞ 3፤ ቲቶ 1

የእግዚአብሔር ቃል ለሚያስተዳድሩንና ለሚመሩን ሰዎች መጸለይ እንዳለብን

ይናገራል። መሪነት ቀላል አገልግሎት አይደልም። አጠቃላይ የቤተ ክርስቲያኗን አካሄድ

እድገት እና እንቅስቃሴ የሚወስን ነገር ነው። የእግዚአብሔር ቃል በሃዋ 20፤39 በገዛ

ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተክርስቲያን ትጠብቋት ዘንድ ለመንጋው ሁሉ እና

ለራሳችሁ ተጠንቀቁ። መሪዎች በመጀመሪያ ለራሳቸው ህይወት መጠንቀቅ ማለት

ራሳቸውን መመገብ በቃሉ እና በጸሎት መትጋት ይኖርባቸዋል። ቀጥሎም ለመንጋው

የሚሆነውን ነገር ምግብም ሆነ ምሪት ከጌታ እየተቀበሉ መምራት ይኖርባቸዋል።

ምክንያቱም መንጋው ከጌታ በአደራ የተቀበሉት ስለሆነ ባላደራወች እንጅ ባለቤቶች

አለመሆናቸውን አስበው ከጌታ ጋር ጥብቅ ህብረት ያስፈልጋቸዋል። ለመምራት

መመራት ስለሚያስፈልግ መሪዎች ከጌታ እየሰሙ እንዲያገለግሉ አጥብቀን

ልንጸልይላቸው ይገባል። መሪዎች ሶስት ሃላፊነት አለባቸው። 1ኛ የራሳቸውን ህይወት

በጥንቃቄ መምራት፤ 2ኛ እንደባለአደራ መኖር፤ አደራቸውን መወጣት፤ 3ኛ ለመንጋው

መጠንቀቅ እና መምራት

የዕለቱ የጸሎት አቅጣጫ

• ለመሪዎቻችን የእግዚአብሔር ጸጋ እንዲጨመርላቸው

• ልማዳዊ ከሆኑ ነገሮች አልፈው በምሪት ህዝቡን እንዲመሩ

• አዳዲስ ራዕይ ከጌታ መቀበል እንዲችሉ

• የአመራር ክህሎት እና ሞገስ በላያቸው ላይ እንዲሆን

• ለመንጋው በሚራራ ልብ ለመንጋው በመንከባክብ እና በመጠንቀቅ እንዲመሩ

• የራሳቸውንም ህይወት በምሳሌያዊ ኑሮ መምራት እንዲችሉ

• ለጸሎት ለቃሉ እና ለቤተሰብ በቂ ጊዜ እንዲኖራቸው

Page 31: October 14 November 3, 2019 · 2019-10-16 · የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ህብረት ቤተ ክርስቲያን ሎስ አንጀለስ የሃያ አንድ ቀን ጾም

• ህዝቡ በመታዘዝ እና በማክበር እንዲከተላቸው

• እነርሱም ህዝብን የሚያስከትል ተጽዕኖ መፍጠር እንዲችሉ

ኦክቶበር 29 አስራ ሰድስተኛ ቀን

ለልጆች / ለትውልዱ

የንባብ ክፍል ኤፌ 5፤14-18፤ ምሳሌ 22:6

ልጅህን በሚሄድበት መንገድ ምራው ከእርሱም ፈቀቅ አይልም ይላል (ምሳሌ 22:6)።

እውነት ነው ልጆች በህጻንነታቸው በሚገባ መቅረጽ ከቻልን ዘመናቸውን ሁሉ መዋጀት

ቻልን ማለት ነው። ሆኖም ልጆች የሚሰሙት ከቤተሰብ ብቻ አይደለም።

ከአካባቢያቸው፣ ከትምህርት ቤት ከጓደኞቻቸው፣ ጋር ብዙ ስለሚያሳልፉ ብዙ ነገር

ተምረው ይመጣሉ። በዙሪያቸው ያለው የሚሰሙት የሚያዩት ሁሉ ለወደፊት

አካሄዳቸው ትልቅ ትጽዕኖ አለው። ዛሬ በትምህርት ቤት አካባቢ የሚያዩት ሁሉ ብዙ

ክፉ ነገር አለ። ምድሪቱ በክፉ ጨለማ እየተዋጠች ነው። ስለዚህ ትውልዱን ማስጣል

የእኛ ሃላፊነት ነው። ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና ዘመኑን ዋጁ ይላል። እውነት ነው

ከመቼውም ጊዜ ይልቅ ቀኖቹ ከፉ እየሆኑ ነው። ሆኖም የቀኑን ክፋት ብቻ ልናዜም

አልተጠራንም። የተጠራነው የቀኑን ክፋት ልንሰብር እና ልናፈርስ ነው። ልጆቻችን

ከዘመኑ ከፋት በላይ እንዲሆኑ እና ለትውልዳቸው መፍትሄ አድርጎ እንዲያቆማቸው

እኛ ስለእነርሱ በጸሎት ልንተጋ ያስፈልጋል።

የዕለቱ የጸሎት ትኩረት

• ከዘመኑ ክፋት ትውልዱን እግዚአብሔር እንዲታደግ

• በትምህርት ቤት በአካባቢያቸው የሚማሩት ክፉ ነገር ሁሉ ወደ ውስጣቸው

አንዳይገባ

• በትውልዱ ላይ እየመጣ ያለ ክፉ ነገር ሁሉ እግዚአብሔር እንዲሰብረው

• በትምህርት ካሪኩለም የወጡ ክፉ ነገሮች እግዚአብሔር እንዲሽራቸው

• ለወላጆች ልጆቻቸውን የመምራት ጸጋ እንዲጨመርላቸው

Page 32: October 14 November 3, 2019 · 2019-10-16 · የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ህብረት ቤተ ክርስቲያን ሎስ አንጀለስ የሃያ አንድ ቀን ጾም

ኦክቶበር 30 አስራ ሰባተኛ ቀን

ኢየሩሳሌምን ለክርስቶስ

የንባብ ክፍል አስቴር 8-9፤ ሮሜ 9

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስሐዋርያኡን ወንጌልን እንዲሰብኩ ሲያዝዛቸው መጀመሪያ

ከኢየሩሳሌም እንዲጀምሩ ነው። ከዚያ በኋላ ወደ ቅርባቸው ወደ ጎረቤት እንዲሸጋገሩ

ነው ያዘዛቸው። ወንጌል ከቤተሰቦቻችን መጀመር አለብን። እኛ ድነን ቤተሰቦቻችን

ገሃነም ቢሄዱ ምን አይነት ጥልቅ ህዘን እንደሚሆንብን መርሳት የለብንም። ሐዋሪያው

ጳውሎስ የነፍሴ ጭንቀት እስራኤል እንዲድኑ ነው ይላል። አስቴርም ስለህዝቧ

የዘመዶቼን ጥፋት አይ ዘንድ እንዴት እችላለሁ ብላለች። ለቅርብ ቤተሰቦቻችን

እንዲድኑ መጸልይ መማለድ እንዲሁም መመስከር አለብን። የራሳችንን ኢየሩሳሌም

መድረስ በሚል ራዕይ ያልዳኑ ዘመዶቻችንን ዝርዝር ጽፈን መጸለይ ከጀመርን ሁለት

አመት ሆኖናል። ስንቶቻችን ነን በትጋት ይህን እያደረኝ ሲባል በጣም ጥቂቶች ነን።

አንዳንዶች እንዲየውም ረስተነዋል ማለት ይቻላል። ይህ ነገር ሊረሳ የማይገባው እና

የሁልጊዜ ጩኸታችን መሆን ይኖርበትል።

የዕለቱ የጸሎት ትኩረት

• አንተ ዳን ቤተሰቦችህም ይድናሉ በተባለው መሰረት ያልዳኑ ቤተሰቦቻችን

እንዲድኑ

• ለቤተሰቦቻችንና ለቅርብ ዘመዶቻችን ወንጌል የምናደርስበትን ጥበብ

እንዲሰጠን

• ወንጌልን ስንናገር መንፈስ ቅዱስ ልባቸውን እንዲለውጥ

• ለቤተሰቦቻችን ምሳሌያዊ ህይወት ማሳየት እንድንችል። በህይወታችንም

እንድንመሰክርላቸው

• በእውነተኛ ሸክም እና ፍቅር ወደ ጌታ ይዘናቸው እንድንቀርብ

Page 33: October 14 November 3, 2019 · 2019-10-16 · የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ህብረት ቤተ ክርስቲያን ሎስ አንጀለስ የሃያ አንድ ቀን ጾም

ኦክቶበር 31 አስራ ስምንተኛ ቀን

የሚመጣው አመት 2020 የበረከት አመት እንዲሆን

የንባብ ክፍል 2ኛ ጴጥ 1፤1-21

አዲስ አመት እየተቀበልን አሮጌውን እየሸኘን ብቻ የምንኖር ሰዎች አይደለንም።

የእግዚአብሔር አላማና ፕሮግራም በህይወታችን ላይ አለ። አመታትን እንዲሁ መቁጠር

ብቻ እንዳይሆን እግዚአብሔር በኛ ሊሰራው ያለው ነገር እንድፈጸም በትጋት በፊቱ

መሆን መቻል አለብን። ሐዋሪያ ጴጥሮስ 2ኛ ጴጥ 1፤5-7 ስለዚህም ምክንያት ትጋትን

ሁሉ እያሳያችሁ በእምነታችሁ ላይ በጎነትን ጨምሩ ፤በበጎነት ላይ እውቀትን ጨምሩ……

ይላል። በዚህ ክፍል ላይ በተደጋጋሚ ጨምሩ የሚል ቃል አለ። ክርስትና እድሜ

የመቁጠር ሳይሆን የመጨመር ነው። ስለዚህ 2020 የመጨመር አመት እንዲሆንልን

በእግዚአብሔር ፊት መጸለይ አለብን “መጨመር” በሁሉ አቅጣጫ በአግልግሎት

በህይወት፣ በኑሮ፣ በጤና በማንኛውም ነገር እንዲሁም በወንድማማች ፍቅር እና

በህብረታችን እግዚአብሔር መጨመር እንዲያደርግልን። ጨምሩ ነው የተባልነው እንጅ

ቀንሱ አልተባልንም።

የዕለቱ የጸሎት ትኩረት

• የሚመጣው አመት የመልካም እና የበረከት አመት እንዲሆን

• ከእግዚአብሔር ጋር የምንሰራ ነንና እንደተባለ ከእርሱ ጋር የምንሰራ

እንድንሆን። የእርሱ ሃሳብ በሌለበት እንዳንገኝ እግዚአብሔር በእኛ ላይ

ያለውን አላም የምንፈጽምበት እንዲሆን

• በሁሉ ነገር ላይ የመጨመር አመት እንዲሆን

• ብዙ ነፍሳት የሚጨመሩበት አመት እንዲሆን

Page 34: October 14 November 3, 2019 · 2019-10-16 · የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ህብረት ቤተ ክርስቲያን ሎስ አንጀለስ የሃያ አንድ ቀን ጾም

ኖቬምበር 1 አስራ ዘጠነኛ ቀን

ሰለምንኖርባት ከተማ ሎስ አንጀለስ እና አካባቢው

የንባብ ክፍል ኤፌ 6፤10-18

ዲያቢሎስን ተቃወሙት ከእናንተም ይሸሻል ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ ወደ እናንተም

ይቀርባል። የምንኖርባት ሎስ አንጀለስ ከተማ የብዙ ነገሮች መፍለቂያ ምንጭ ሆና

ለአለም መልካም ነገሮችን አበርክታለች። በመንፈሳዊ ነገር ከመቶ አመት በፊት በአዙዛ

መንገድ ላይ የወረደው መንፈስ ቅዱስ ለመላ አሜሪካ ብቻ ሳይሆን ለመላው አለም

በረከት ሆኗል። ብዙ ሚሲወናዊያን ከዚህ ወጥተው ወንጌልን ለአለም አድርሰዋል።

በቴክኖሎጅውም ቢሆን ብዙ ለአለም የሚጠቅሙ መልካም ነገሮች ከዚህ ከተማ

ወጥቷል። በተቃራኒው ደግሞ ክፉ ነገሮችም በተለይ በፊልም ኢንዱስትሪው በኩል

ወጥተዋል። ከሆሊውድ የሚወጣ ክፉ ነገር አለምን ያጥለቀለቀ ልቅነት አለ። ይህን ክፉ

ነገር ማፍረስ እና የወንጌል ሐይል ከዚህ እንዲወጣ እና እንዲሁም አዙሳ መንገድ ላይ

የተፈጠረው ሪቫይቫል እንደገና እንዲደገም ተግተን መጸለይ አለብን። በዚህ ከተማ

ያለው መንፈስ በጣም ጠንካራ ነው እያልን ለእርሱ እውቅና እየሰጥን ስንዘምርለት

መኖር የለብንም። አንድ ሃያል እና ብርቱ ብቻ ነው የምናውቀው እርሱ የእናንተ እና የኔ

ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። የጠላትም ሐይል እያወጅን የወንጌልን ሐይል ማሳነስ

የለብንም። እኛ እስከጸለይን ድረስ የማይናድ ተራራ፤ የማይመታ የጠላት ምሽግ የለም።

ቅዱሳን ወንድሞቸ እና እህቶቸ በዚህ አጋጣሚ ልነግራችሁ የምፈልገው ነገር እባካችሁ

የሆሊውድን ታላቅነት የክፉን ሐይል አታውጁ። እኛ የተጠራነው የጌታን ታላቅነት

ልናውጅ ነው።

የዕለቱ የጸሎት ትኩረት

• በዚህ ከተማ ከአዙሳ ከፍ ያከ ሪቫይቫል እንዲመጣ

• በሎስ አንጀለስ ያለው ክፉ ነገር እንዲመታ። ከከተማው ከፋት በላይ

የምንሆንበት አቅም እና ጉልበት እንዲሰጠን

• ከዚህ ከተማ ብዙ ሚሲወናዊያን እንዲወጡ

Page 35: October 14 November 3, 2019 · 2019-10-16 · የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ህብረት ቤተ ክርስቲያን ሎስ አንጀለስ የሃያ አንድ ቀን ጾም

• በዚህ ከተማ የአለምን ትኩረት የሚስብ የወንጌል ሐይል እንዲገለጥ

ኖቨምበር 2 እና 3

ምስጋና

ሁለቱ ቀናት የምስጋና ቀን ይሆናሉ። አንደኛው ስለያዝነው አመት ምስጋና ሲሆን

ሁለተኛው ይህን የጾም ጸሎት ጊዜ በሰላም እንድንጨርስ ጌታ ስለረዳን

የንባብ ክፍል መዝ 85፡1-2፤ 1ኛ ተሰ 5፡18፤ መዝ 138፡1_2

እግዚአብሔር ሁልጊዜ ሊመሰገን የሚገባው አምላክ ነው። ያደረገልን ነግሮች ብዙ

ናቸውና ልናመሰግነው ይገባል። ያላደረገልን ነገሮች ቢኖሩ እንኳን ለእኛ የማይጥቅሙ

ሰለሆኑ ብቻ ነው እንጅ እግዚአብሔር ከሚጠቅመን ነገር አንዳች ፈጽሞ

አያስቀርብንም። አባታችን ሰለሆነ የማይጠቅመንን ነገር ይከለክላል። አባት ምንም እንኳ

ልጆች የሚጠቅም መስሏቸው ቢያለቅሱም እርሱ እንደ ማይጥቀም ስለሚያውቅ

አይሰጣቸውም። ይሄን ነገር እየጻፍሁ አንድ ነገር ትዝ አለኝ። የመጀመሪያዋ ልጃችን

ከአንደኛ ክፍል ወደ ሁለተኛ ክፍል ስትገባ ጥሩ ትምህርት ቤት ስላገኘን ትምህርት ቤት

ቀየርንላት። እርሷ ግን ትምህርት ቤት መቀየሯን አልተቀበለችውምና እምቢ አለች፤

አለቀሰችም። እኔ ግን አዲሱ ትምህርት ቤት የተሻለ እንደሆነ ስለማውቅ እምቢ ብዬ

አስገባኋት። እርሷ ግን እኔን እንደ ክፉ አባት አየችኝ። መንም እንኳን እንደ ክፉ አባት

እርሷ ብትቆጥረኝም እኔ የማደርገው ለልጄ የወደፊት ሕይወት የሚሻለውን በማየት

ነው። የእርሷ ለቅሶ እና ሃዘን አባቴ ከለከልኝ ማለቷ ለምይጠቅማት ነገር ስለሆንው እኔን

ሊለውጠኝ እና እርሷ ያለችውን እንዳድርግ ሊያስግድድደኝ አልቻለም። እግዚአብሔር

በኛ ላይ የአጭር ጊዜ ፕሮግራም ሳይሆን ዘላለማዊ ዕቅድ አለው። የሚያደርግልን ሁሉ

ከዘላለማዊ እቅዱ አንጻር እንጂ እኛን ለጊዜው ከሚያስደስተን ነገር አንጻር አይደለም።

የዕለቱ የጸሎት ትኩረት

• እግዚአብሔር ስላደረገልን መልካም ነገር ሁሉ ማመስገን

Page 36: October 14 November 3, 2019 · 2019-10-16 · የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ህብረት ቤተ ክርስቲያን ሎስ አንጀለስ የሃያ አንድ ቀን ጾም

• እኛ ባይገባንም ለምነነው ስለከለከልን ነገር ማመስገን

• ስለ 2019 ምስጋና

• በዚህ አመት እግዚአብሔር ጠብቆ እዚህ ስላደረስን (በብዙ ተግዳሮት

ብናልፍም)፤ በዚህ አመት ስለተፈጸሙ መልካም ነገሮች ሁሉ ምስጋና

• በዚህ የጾም እና የጸሎት ጊዜ በፊቱ እንድንሆን ስለረዳን

እውነተኛውን ጾም እና ጸሎት እንድናደርግ እግዚአብሔር ይርዳን!