16
ጸጋ የሌለው ትውልድ ስለ ጸጋ አያውቅም፡፡ መልአከ መንክራት ግርማ ወንድሙ በቁጥር 95 በሬድዬ አቢሲንያ ካስተማሩት… ገፅ 1 በስመአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን፡፡ አቤቱ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ ለዚህ ሰዓት ያደረስከን አምላክ ክብር ምስጋና ይግባህ ቀሪው ግዝያችንን ባርክልን በመንፈስህና በኃይልህም አስተምረን በፀጋህ ጥበብ ጎብኘን የዘልአለም ኪዳንህን ስጠን ልቦናችንን በመንፈስህና በጽድቅህም በበጎ ሃሳብም አፅናልን በቅዱስ ልጅህ በእየሱስ ክርስቶስ ስም በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ስም አሜን፡፡ ፀጋ የሌለው ትውልድ ስለ ፀጋ አያውቅም ነው የዛሬ ርዕሳችን፡፡ ፀጋና ሞጎስ ይለያያሉ፡፡ ከሁሉ በፊት ለአዲስ ኪዳን የተሰጠ ጸጋ ሲኖር ሲጀምር በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ነው፡፡ በታላቁ ሚልኪያስ ምዕራፍ 1 ቁጥር 9 ላይ እንዲህ ይላል ‹‹አሁንም ጸጋ ይሰጠን ዘንድ እግዚአብሔርን ለምኑ›› ይላል፡፡ ይሄ የመዳረሻው ዘመን ላይ ሲደርስ ሚልኪያስ የተናገረውን ጸጋ በጸሎት፤ በምስጋና፤ በልመና፤ በሱባዔ፤ በምልኮት የሚገኝ መንፈሳዊ ኃይል ነው፡፡ ጸጋ ልዩ የሚያደርገው የአዲስ ኪዳን ጸጋ የእግዚአብሔር ማደርያ መሆን ነው፡፡ የእግዚአብሔር አምላክ መኖርያ፤ የእግዚአብሔር አምላክ ሓሳብ መፅደቅያና የእግዚአብሔር አምላክ በጎ አካሄድ በገለጫ፤ የእግዚአብሔር ቸርነት፤ ኃይሉን ማሳያ ጸጋ ይባላል፡፡ ስለዚህ ጸጋን ለማግኘት አሁንም ጸጋ ይሰጠን ዘንድ እግዚአብሔርን ለምኑ ባለው በሚልኪያስ ሓሳብ ውስጥ ስንመለከት እግዚአብሔር ነው ጸጋን የሚሰጠው፡፡ እግዚአብሔር ጸጋን ከሰጠ ታድያ ጸጋን ደግሞ ለሌላው ማካፈል ነው፡፡ አሁን አንዳንድ አስተማሪዎች ሰውን አትከተሉ፤ ሰውን አትዩ ይላሉ፡፡ እንዴት ነው ሰውን መከተል የሚባለው?፡፡ ሰውን መከተልስ በምን መንገድ ነው?፡፡ እነሱን የሚያስተምሩት እንዲከተሉ ይናገራሉ፡፡ ሌላው መንፈሳዊ ኃይሉ ደግሞ ይተቻሉ፤ ይቃወማሉ እና ሰውን አትከተሉ ይላሉ፡፡ እነሱን የሚተሏቸውን ደግሞ ያወድሳሉ፤ ያጠናክራሉ፤ በርቱ ይላሉ፡፡ ሌላው ደግሞ የተሻለ ምናልባት የተሻለ በጸጋ ከመጣ እነሱን አትከተሉ ይላሉ፡፡ እንዴት ነው ለመሆኑ ሰውን መከተል የሚቻለው? ሰው መከተል በምን አይነት መንገድ ነው? ወደ እግዚአብሔር የሚመልስ ነው፤ በእግዚአብሔር ኃይል ጋር የሚያጣብቅ ነው ወይስ በራሱ ዓለም፡፡ በመጽሓፍ ቅዱስ ውስጥም እኮ ሙሴ የእስራኤልን ህዝብ ሲመራ ህዝቡን ሙሴ ተከትሎ ነው ነፃ የወጣው፤ እያሱም የእስራኤልን ህዝብ ሲመራ እያሱን ተከትሎ እግዚአብሔርን ነው ያገኘው፤ ኤልያስም ኤልሳን በልብሱ ጣል አደረገበት ተከተለው ቀምበሩንም ሁሉንም ሰብሮ ሌሎችን አርዶ አብልቶ አጠጥቶ ኤልያስን ተከትሎታል፡፡ እንደውም በረከትህ በኔ ላይ በእጥፍ ይደር ብሎ ለምኖ በረከት ፍለጋ ከዮርዳኖስ ማዶ እስከ እያሪኮ ዙርያውን ያሉ ሃገሮች እግዚአብሔር ሊወስደኝ ነው ብለው ኤልያስ መጎናፀፍያ ወድቆ ኤልሳ አንስቶ የዮርዳኖስ ወንዝ በልብሱ ለብሶ ተሻግረዋል፡፡ አላሻግር ያለው ወንዝ አድርቆ ተሻግረዋል፡፡ ማንን በመከተሉ ነው ይሄ ታድያ? ኤልያስን መከተሉ ነው፡፡ እና በዚህ መካከል ያለውን መንፈሳዊ በረከት አለማስተዋል ጸጋ የሌለበት ትውልድ ስለ ጸጋ አያውቅም የሚለውን ትምህርት እንድንማር ያስገድደናል፡፡ ጸጋ ከእግዚአብሔር ስጦታ ውስጥ አንደኛው ነው፡፡ የጸጋው አይነት ደግሞ በጣም ይለያያል፡፡ ስራው ብዙ ነው፡፡ አንዱ ጸጋው ስራው ብዙ ነው፡፡ ጸጋ የሚታደገው በመንፈስ ቅዱስ ነው፡፡ ጸጋ የሚታገዘው በእግዚአብሔር አምላክ ኃይል ውስጥ ነው፡፡ የጸጋው መኖርያ መሆን ሲቻል

ፀጋ የሌለው ትውልድ ስለ ፀጋ አያውቅም.pdf

Embed Size (px)

Citation preview

Page 1: ፀጋ የሌለው ትውልድ ስለ ፀጋ አያውቅም.pdf

ጸጋ የሌለው ትውልድ ስለ ጸጋ አያውቅም፡፡

መልአከ መንክራት ግርማ ወንድሙ በቁጥር 95 በሬድዬ አቢሲንያ ካስተማሩት… ገፅ 1

በስመአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን፡፡

አቤቱ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ ለዚህ ሰዓት ያደረስከን አምላክ ክብር ምስጋና ይግባህ ቀሪው

ግዝያችንን ባርክልን በመንፈስህና በኃይልህም አስተምረን በፀጋህ ጥበብ ጎብኘን የዘልአለም ኪዳንህን ስጠን ልቦናችንን

በመንፈስህና በጽድቅህም በበጎ ሃሳብም አፅናልን በቅዱስ ልጅህ በእየሱስ ክርስቶስ ስም በእመቤታችን በቅድስት ድንግል

ማርያም ስም አሜን፡፡

ፀጋ የሌለው ትውልድ ስለ ፀጋ አያውቅም ነው የዛሬ ርዕሳችን፡፡ ፀጋና ሞጎስ ይለያያሉ፡፡ ከሁሉ በፊት ለአዲስ ኪዳን

የተሰጠ ጸጋ ሲኖር ሲጀምር በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ነው፡፡ በታላቁ ሚልኪያስ ምዕራፍ 1 ቁጥር 9

ላይ እንዲህ ይላል ‹‹አሁንም ጸጋ ይሰጠን ዘንድ እግዚአብሔርን ለምኑ›› ይላል፡፡ ይሄ የመዳረሻው ዘመን ላይ ሲደርስ

ሚልኪያስ የተናገረውን ጸጋ በጸሎት፤ በምስጋና፤ በልመና፤ በሱባዔ፤ በምልኮት የሚገኝ መንፈሳዊ ኃይል ነው፡፡ ጸጋ ልዩ

የሚያደርገው የአዲስ ኪዳን ጸጋ የእግዚአብሔር ማደርያ መሆን ነው፡፡ የእግዚአብሔር አምላክ መኖርያ፤ የእግዚአብሔር

አምላክ ሓሳብ መፅደቅያና የእግዚአብሔር አምላክ በጎ አካሄድ በገለጫ፤ የእግዚአብሔር ቸርነት፤ ኃይሉን ማሳያ ጸጋ

ይባላል፡፡ ስለዚህ ጸጋን ለማግኘት አሁንም ጸጋ ይሰጠን ዘንድ እግዚአብሔርን ለምኑ ባለው በሚልኪያስ ሓሳብ ውስጥ

ስንመለከት እግዚአብሔር ነው ጸጋን የሚሰጠው፡፡ እግዚአብሔር ጸጋን ከሰጠ ታድያ ጸጋን ደግሞ ለሌላው ማካፈል

ነው፡፡

አሁን አንዳንድ አስተማሪዎች ሰውን አትከተሉ፤ ሰውን አትዩ ይላሉ፡፡ እንዴት ነው ሰውን መከተል የሚባለው?፡፡ ሰውን

መከተልስ በምን መንገድ ነው?፡፡ እነሱን የሚያስተምሩት እንዲከተሉ ይናገራሉ፡፡ ሌላው መንፈሳዊ ኃይሉ ደግሞ

ይተቻሉ፤ ይቃወማሉ እና ሰውን አትከተሉ ይላሉ፡፡ እነሱን የሚተሏቸውን ደግሞ ያወድሳሉ፤ ያጠናክራሉ፤ በርቱ

ይላሉ፡፡ ሌላው ደግሞ የተሻለ ምናልባት የተሻለ በጸጋ ከመጣ እነሱን አትከተሉ ይላሉ፡፡ እንዴት ነው ለመሆኑ ሰውን

መከተል የሚቻለው? ሰው መከተል በምን አይነት መንገድ ነው? ወደ እግዚአብሔር የሚመልስ ነው፤ በእግዚአብሔር

ኃይል ጋር የሚያጣብቅ ነው ወይስ በራሱ ዓለም፡፡

በመጽሓፍ ቅዱስ ውስጥም እኮ ሙሴ የእስራኤልን ህዝብ ሲመራ ህዝቡን ሙሴ ተከትሎ ነው ነፃ የወጣው፤ እያሱም

የእስራኤልን ህዝብ ሲመራ እያሱን ተከትሎ እግዚአብሔርን ነው ያገኘው፤ ኤልያስም ኤልሳን በልብሱ ጣል አደረገበት

ተከተለው ቀምበሩንም ሁሉንም ሰብሮ ሌሎችን አርዶ አብልቶ አጠጥቶ ኤልያስን ተከትሎታል፡፡ እንደውም በረከትህ

በኔ ላይ በእጥፍ ይደር ብሎ ለምኖ በረከት ፍለጋ ከዮርዳኖስ ማዶ እስከ እያሪኮ ዙርያውን ያሉ ሃገሮች እግዚአብሔር

ሊወስደኝ ነው ብለው ኤልያስ መጎናፀፍያ ወድቆ ኤልሳ አንስቶ የዮርዳኖስ ወንዝ በልብሱ ለብሶ ተሻግረዋል፡፡ አላሻግር

ያለው ወንዝ አድርቆ ተሻግረዋል፡፡ ማንን በመከተሉ ነው ይሄ ታድያ? ኤልያስን መከተሉ ነው፡፡ እና በዚህ መካከል

ያለውን መንፈሳዊ በረከት አለማስተዋል ጸጋ የሌለበት ትውልድ ስለ ጸጋ አያውቅም የሚለውን ትምህርት እንድንማር

ያስገድደናል፡፡ ጸጋ ከእግዚአብሔር ስጦታ ውስጥ አንደኛው ነው፡፡

የጸጋው አይነት ደግሞ በጣም ይለያያል፡፡ ስራው ብዙ ነው፡፡ አንዱ ጸጋው ስራው ብዙ ነው፡፡ ጸጋ የሚታደገው

በመንፈስ ቅዱስ ነው፡፡ ጸጋ የሚታገዘው በእግዚአብሔር አምላክ ኃይል ውስጥ ነው፡፡ የጸጋው መኖርያ መሆን ሲቻል

Page 2: ፀጋ የሌለው ትውልድ ስለ ፀጋ አያውቅም.pdf

ጸጋ የሌለው ትውልድ ስለ ጸጋ አያውቅም፡፡

መልአከ መንክራት ግርማ ወንድሙ በቁጥር 95 በሬድዬ አቢሲንያ ካስተማሩት… ገፅ 2

ደግሞ የሚከተሉትን የቅዱስ ሉቋስ ወንጌል ምዕራፍ 1 ቁጥር 28 መፅሓፋችሁን ገልጣችሁ ተመልከቱ ‹‹መልአኩም ወደ

እርስዋ ገብቶ፦ ደስ ይበልሽ፥ ጸጋ የሞላብሽ ሆይ፥ ጌታ ከአንቺ ጋር ነው፤ አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ አላት።››

እንግዲህ አሁንም ጸጋ ይሰጠን ዘንድ እግዚአብሔርን ለምኑ በተባለው መሰረት የሚለምኑ አባቶች ሲኖሩ ያ ጸጋ መገለጥ

ስጀመር በአዲስ ኪዳን በቅዱስ ገብርኤል በኩል መጣ ‹‹ጸጋ የሞላብሽ ሆይ፥ ጌታ ከአንቺ ጋር ነው›› አለ፡፡ እግዲህ

የእግዚአብሔር አብሮ የመኖር ትልቁ ኃይል ጸጋ ሲኖር ነው፡፡ የጸጋ ሙላት በሰው ህይወት ውስጥ ሲጀምር ጸጋ ተስፋና

ኃይል ሲገለጥ የዚህ ግዜ የእግዚአብሔር የመኖርያ ኃይል በመሆን እናገለግላለን፡፡ በመጀመርያ ደረጃ ጌታ ካንቺ ጋር

ነው ከማለቱ ጋር ተያይዞ የጸጋ ኃይል ቀድመዋል፡፡ ያ የጸጋ ኃይል ህይወትን በልዑል እግዚአብሔር መንፈስ የሚይዝ

ነው፡፡ ያ የጸጋ ኃይል ታላቅ የሆነ ስራን ለመስራት የእግዚአብሔር ክብርና ኃይል ለመግለፅ የሚያመቻች ነው፡፡ ‹‹ጸጋ

የሞላብሽ ሆይ፥ ጌታ ከአንቺ ጋር ነው፤ አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ አላት።›› የጸጋን ኃይል ለማግኘት መባረክ

ያስፈልጋል፡፡ የጸጋ ኃይል በመባረክ ውስጥ የሚገለጥ ነው፡፡ እመቤታችን የመጀመርያ የጸጋ ባለቤት የአዲስ ኪዳን

ኃይልና የሰማያዊው ክብር መግለጫ የሆነች እናት አለችን፡፡

ታድያ እሷ አለችን ብቻ እያልን የምንኖር አይደለንም ከጸጋዋ የምንካፈልበትን መንፈሳዊ ተስፋና ኃይል መጨበጥ

ያስፈልጋል፡፡ አሁን የጸጋ ሰባኪዎች ብቻ ሳንሆን የጸጋ መኖርያዎችም መሆን ቀዳሚ ታላቅ የሆነ የእግዚአብሔር አምላክ

ስጦታ መግለጫ ነው፡፡ ብዙዎቻችን የጸጋ ሰባኪዎች ነን፡፡ ስለጸጋ መገለፅና ስለ ጸጋ መታየት ደግሞ ምቀኞች ነን፡፡

ስለዚህ ምቀኛ በሆነ ልብ ውስጥ የጸጋ ሚስጢር መጠበቅ አስቸጋሪ ነው፡፡ ጸጋ የሌለው ትውልድ በጸጋ ውስጥ

ለሚያልፉትና የጸጋ ሚስጢር ለተሰጣቸው ሰዎች ጠንቅ የመሆን ባህሪ አላቸው፡፡ እንደ ሰይጣን ማለት ነው፡፡

ቅዱስ የሆነው መልአክ ወደ እመቤታችን ሲመጣ የእመቤታችንን ጸጋ ገለጠ፡፡ ግን አይሁዶች ደግሞ ድንግል ማርያም

በዓይነ ቁራኛ ይመለከትዋት ነበር፡፡ ይሄ በሰው ሰውኛ ነው፡፡ በመልአክት ዘንድ የጸጋ ሙላት ያላት በሰው ልጆች ዘንድ

ግን፤ በአይሁዶች ዘንድ ግን እንደገና በክፉ ዓይን የሚያይዋት ዓይነት ሆኖ በእመቤታችን በተዓምረ ማርያም ላይ ብዙ

ነገሮችን እናያለን፤ ብዙ ነገሮችንም እናነባለን በሰው ልጆች ህይወት ላይ ያለው ክፉ ኃይልና ክፉ ሓሳብ ከተፈጥሮ

ባሻገር ዲያብሎስ ግፊት ሁሉ የሚሰራቸውንና የሚፈፅማቸውን ነገሮች እንገነዘባለን፡፡

ስለዚህ በጸጋ ውስጥ የመኖርን ታላቅ መንፈሳዊ በረከት ልናውቅ የሚገባው እውነቶች በመጽሓፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙ

ቦታዎች አሉ፡፡ በቅዱስ ሉቋስ 1፡30 ላይ መላዕኩም እንዲህ አላት ‹‹ማርያም ሆይ በእግዚአብሔር ፊት ጸጋ አግንተሻልና

አትፍሪ›› በእብራይጡ ፈንኤል ቫሆሴት በማለት ይታወቃል፡፡ ፈንኤል ቫሆሴት የእግዚአብሔር ጸጋና ሞጎስ ማለት

ነው፡፡ ፈንኤል ማለት ደግሞ የእግዚአብሔር ፊት፤ የእግዚአብሔር ብርሃን፤ የእግዚአብሔር ኃይል፤ የእግዚአብሔር

ሞጎስ፤ የእግዚአብሔር ስጦታ፤ የእግዚአብሔር ቸርነት፤ የእግዚአብሔር ምህረት ተብሎ ይተረጎማል፡፡ ጸጋ ማለት

ነው፡፡ አሁን በእግዚአብሔር ፊት ጸጋ አግኝተሻልና አትፍሪ የሚለው ቃል ደግሞ የበለጠ የጸጋው ኃይል በእግዚአብሔር

ፊት ማቆምን መቻሉ ነው፡፡ በጌታ ፊት የሚቆም ኃይልና ተስፋ በእመቤታችን ህይወት ውስጥ እና በእመቤታችን ፊት

ላይ አለ ማለት ነው፡፡ ከእግዚአብሔር ፊት ጸጋ አግኝተሻልና በስጋውያን ፊት ማለት አይደለም፡፡ በእግዚአብሔር ፊት

ነው፡፡ በመሪዎች ፊት አይደለም፡፡ በእግዚአብሔር በኃያሉ ዓለምም በፈጠረው ፊት ነው፡፡ ስለዚህ የዘልዓለም አምላክ

ፊት ነው እኮ፡፡ በግዝያዊ ሰዎች ፊት አይደለም፡፡ በዘልዓለም ንጉስ በሆነው አምላክ ፊት ነው፡፡ ስለዚህ ፀጋ የሌለው

Page 3: ፀጋ የሌለው ትውልድ ስለ ፀጋ አያውቅም.pdf

ጸጋ የሌለው ትውልድ ስለ ጸጋ አያውቅም፡፡

መልአከ መንክራት ግርማ ወንድሙ በቁጥር 95 በሬድዬ አቢሲንያ ካስተማሩት… ገፅ 3

ትውልድ ስለ ፀጋ አያውቅም፡፡ በመጀመርያ ደረጃ ይሄ ነው ችግሩ፡፡ እመቤታችን ግን በእግዚአብሔር ፊት ጸጋን ያገኘች

እናት ናት፡፡

ስለዚህ ትልቁ እንደመለያ የምናደርገው የመናፍቁን ትውልድ ነው፡፡ የመናፍቁን ትውልድ ዝምብሎ በባዶ የሚያጓራ

በየግዜውና፤ በየሰዓቱ የሚፋንኑ፤ የማስመሰል ተስፋዎችን የሚናገር፤ ክፉ መንፈስ ያደረባቸው እና ክፉ ነገሮች

የበዛባቸው ሲሆኑ፡፡ በኛም ደግሞ ስለጸጋና ስለ እመቤታችን እናወራና፤ ላወራነው ቃላት ተመልሰን ጠላት ምንሆን

ነን፡፡ በሁለቱንም ዓለም የተሸነፍን ነን ውዳቂ ፍጥረቶች የመሆናችን ገፅታ ይነበባል፡፡ ስለዚህ ስለ እመቤታችን

የምናወራውም እዛ እመቤታችን የካዱትም በሁለቱ እርግማን አለ፡፡ ክፉ መንፈስ አለ፡፡ ምክንያቱም እኛም የምናወራው

በጎ ህሊና አይደለም፡፡ በመልካም እምነት አይደለም፡፡ በቃላት ነው፡፡ በተግባራችን ግን ብዙ ግፈኞች፤ ብዙ አረመኔዎች

ነን፤ ብዙ አጥፊዎች ነን፤ ብዙ ፋኖዎች ነን፡፡ በእግዚአብሔር ፊት ጸጋን ለማወቅና ለመረዳት በመጀመርያ ደረጃ

በእምነት ውስጥና በፍቅር መኖር አለብን፡፡ የጸጋ ሰው ለመሆን እምነት፤ ፍቅር፤ ሰላም፤ በጎነት ቅንነት እና የቀደሙ

አባቶችን መንፈሳዊ ኃይል መከተል ያስፈልጋል፡፡

ከቀደመው መንፈሳዊ ኃይል በራቅንበት ግዜና ሰዓት ደግሞ የጠላት ኃይል ዘመናዊ ሆነን ቀረን፡፡ ዘመናዊ መሆን ማለት

ደግሞ እንደ ሬድዮ ጣብያ መለፍለፍ፤ መቀባጠር ነው፡፡ እንግዲህ ሬድዮ ጣብያ መሆን ያህል ነው፡፡ እንደ ጋዜጠኛ

ማውራት መቻል ነው፡፡ ያ ብዙም አያስገርምም፡፡ ሰው እንዲናገር ነው አምላክ ያለው፡፡ ከእንስሶች የሚለየው በመናገሩ

ነው፡፡ ታድያ መናገሩን ከተግባር ካወጣው መቀባጠር ይቻላል ማለት ነው፡፡ ብዙ መቀባጠር የበዛበት ግዜ እና ሰዓት

ነው፡፡ ቢሆንም በዚህ መቀባጠር ዘመን ውስጥ ጸጋ የለም ብሎ መደምደም ራሱን የቻለ ትልቅ የሆነ የክፋት ትውልድ

ምልክት ነው፡፡ ስለዚህ በእግዚአብሔር ፊት ጸጋን አግኝተሻልና አትፍሪ የሚለው ቃል ፍርሃትን ማስወገስ ሚቻለው

በጸጋ ውስጥ ነው፡፡ አለበለዛ ብዙ ሚያስፈሩ፤ የሚያስደነግጡን፤ ባላቸው ኃይል ተቀባይነት ለማሳጣት የሚሯሯጡ፤

ነገሮችን ለማዳፈን የሚጋልቡ ፈረሰኞች ብዙዎች አሉ፡፡ እና ያ ደግሞ በጸጋ ውስጥ ሊመጣ የሚችል ምንም ነገር

የለም፡፡ ከእግዚአብሔር ፊት ጸጋ አግኝተሻልና አትፍሪ ነው ትልቁ ቃል፡፡ ጸጋ ካለ ፍርሃት የለም፡፡ ለምን?፡፡

እመቤታችን በፍርሃት ውስጥ አይደለም ጌታን የፀነሰችው፡፡ በጸጋ ውስጥ ነው፡፡ በጸጋ ውስጥ ያሉ ደግሞ አይፈሩም፡፡

የሚፈሩት በፊታቸው ያለውን መንፈሳዊ ኃይልና የእግዚአብሔርን ክብር ነው፡፡ ስለዚህ በጸጋ ፊት ፍርሃት እንደሌለ

አረጋግጨ ልነግራችሁ እወዳለው፡፡ፀጋ የሌለው ትውልድ ግን ስለ ፀጋ አያውቅም፡፡

በመጀመርያ ደረጃ የጸጋ ኃይልና ጥበብ መኖርያ ለመሆን ካስፈለገ ቁጥር አንድ የእግዚአብሔርን ክብር ማስቀደም ነው፤

የእግዚአብሔርን እምነት ማስቀደም ነው፡፡ የእግዚአብሔርን እምነት ለማስቀደም ደግሞ በራሱ ህይወት ውስጥ

መጀመር አለበት፡፡ በራስህ ህይወት ካልጀመረ ህይወት እንዲጀምር መናገር ዝም ብሎ የቲኦሪ እና ዘመኑ ወሬ ብቻ

ይሆናል፡፡ እንደዚህ እንዳይሆን ግን በጸጋ መጀመር አለበት፡፡ በጸጋ ሲጀመር እግዚአብሔር አምላክ ትፀንሽያለሽ ወንድ

ልጅም ትወልጂያለሽ ስሙንም እሱስ ትይዋለሽ፡፡

በቃ የተገለፀ አካል፤ የገለፀ ተግባር፤ የገለፀ ዕይታ፤ የገለፀ የሚታይ ነገር መኖር አለበት ጸጋ፡፡ የሚደበቅ፤ ዋሻ ውስጥ

የሚቀመጥ አይደለም፤ በዋሻ ውስጥ የሚኖር አይደለም፡፡ ጸጋ ይገለጣል፤ ይወጣል፤ ወደ ውጪ ይወጣል፤ ይታያል፡፡

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ትፀንሽያለሽ አላት ስለዚህ በቃ ባንቺ ውስጥ ይደበቃል አይደለም፡፡ ይታያል

Page 4: ፀጋ የሌለው ትውልድ ስለ ፀጋ አያውቅም.pdf

ጸጋ የሌለው ትውልድ ስለ ጸጋ አያውቅም፡፡

መልአከ መንክራት ግርማ ወንድሙ በቁጥር 95 በሬድዬ አቢሲንያ ካስተማሩት… ገፅ 4

ነው፡፡ ስለዚህ ፀነሰች፡፡ ይወለዳል አለ፡፡ ተወለደ ስሙንም ራሷ እየሱስ አለችው፡፡ መድኃኒት አለችው፡፡ እሱም ደግሞ

ልክ በእናቱ የነበረው ኃይል በሱ ላይ ሲደርስ የሉቋስ ወንጌል 2፡40 ላይ እንዲህ ይላል ‹‹ሕፃኑም አደገ፥ ጥበብም

ሞልቶበት በመንፈስ ጠነከረ፤ የእግዚአብሔርም ጸጋ በእርሱ ላይ ነበረ። ›› ይላል፡፡ እንግዲህ ጸጋ በእመቤታች የጀመረው

ተላለፈ ማለት ነው፡፡ ጸጋን የሞላብሽ ሆይ፥ በእግዚአብሔር ፊት ጸጋ አግንተሻልና አትፍሪ ያለውን ቃል ወደ ተግባር

የሚለውጥ ዕይታ በመድኃኒታች እየሱስ ክርስቶስ ህፃኑም አደገ ጥበብም ሞልቶበት በመንፈስ ጠነከረ ይላል፡፡ ጥበብ

አለው፡፡ እየጠነከረ ሲመጣ የጥበብ ኃይል ሞልቶበታል፡፡ በመንፈስም ጠነከረ፡፡ ጥበብ በድንግል ማርያም ማህፀን

ነው፡፡ ጸጋ በእርሱ ላይ ነበር ያለው በውስጡ የጀመረውን ወደ ውጪ እንዲታይ ገለጠው፡፡ በፊቱ ላይም

የእግዚአብሔር ጸጋ ይነበባል፡፡ ቀጥታ ይታይ ነበረ፡፡

ስለዚህ የሚታይ ጸጋ እንጂ የሚደበቅ ጸጋን መቀበል በዚህ ዘመን ውስጥ አስቸጋሪ ነገር ነው፡፡የሚታይ ጸጋ ለበረከት፤

ለፍቅር፤ ለሰላምና እና ሌሎችንም ለመባረክ የሚያግዝ ይሆናል፡፡ የማይታይ ጸጋ በቃ ምንድነው ይሄ ድብብቆሽ እኮ

ነው፡፡ የህይወት ድብብቆሽ ውስጥ እንድንገባ አዲስ ኪዳን አልነገረንም፡፡ እነዲህ የድብብቆሽ ኑሮ ተኖሮ ዛሬ ዛርና

ውቃቤ የተጫወተበትን ትውልድ ለማየት አልፈለግንም፡፡ ምክንያቱም የእግዚአብሔር ጸጋው የዕይታው ኃይል ብያንስ

እንኳን የምናይበት ጸጋ አላገኘንም፡፡ ሁሉ መቸገሩን፤ በመናፍስት መያዙን፤ መጎዳቱን ለማየት አልቻልንም፡፡

ለምንድነው ጸጋችንን በተለያየ አይነት መንገድ ተርጉመነዋል፡፡ ወደ መንፈሳዊ በረከት ለመሄድ አልቻልንም የኛ

ትርጓሜዎች በጣም ተራርቀዋል፡፡ የኛ ትርጓሜ በቃ የጸጋ ስጦታ ድፍን ያለ፤ ጭልም ያለ ህይወት እየመሰለነን ነው

የመጣው፡፡ ስለዚህ በጸጋ ውስጥ የመገለጥ ኃይል እንዳለ ልናውቅ ይገባል፡፡ ከዛ ውጭ በሆነ መንገድ ጸጋን ዝም ብለህ

ከሜዳ ተነስተህ የምትፈልገው ነገር አይደለም፡፡

የጸጋ ኃይል መሰረታዊ መነሻዎችን ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ ለምንድነው ጸጋ የሚያስፈልገው የሚለውንም እግረ መንገድህን

ለመለየት የምትችልበትን ዕውቀት ማዳበር ያስፈልጋል፡፡ ስለዚህ ጸጋ ከእመቤታችን ወደ ሕፃኑ ኢየሱስ ክርስቶስ መጣ፡፡

እንግዲህ ከማህፀን ጀምሮ ይተላለፋል ማለት ነው፡፡ ክፋትም ልክ እንደዚሁ ይተላለፋል፡፡ ደግሜ ላነብልህ

እሞክራለው፡፡ የሉቋስ ወንጌል ‹‹በመንፈስ ጠነከረ የእግዚአብሔርም ጸጋ በሱም ላይ ነበረ›› መጸለይ ስትጀምሩ

የሚፀነሱት ህፃናቶት ጋር የእግዚአብሔር ክብር አብሮ ይሆናል፡፡ በእናንተ ላይ ያደረ የበረከት ተስፋና ኃይል ጸጋን

ጨምሮ አብሮ ይወለዳል ማለት ነው፡፡ ለምን? መልአኩ በቅድስት ድንግል ማርያም ህይወት ውስጥና ከላይ ያየው

የእግዚአብሔርን ጸጋ ሙላት ነው፡፡ የጸጋ ሙላት ማየቱን በማረጋገጥ ሲናገር ጸጋን የሞላብሽ ሆይ ጌታ ካንቺ ጋር ነው፡፡

አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ አላት፡፡ ከዛ በኋላ አሷ ደግኖ የፀነሰችው ልጅ አደገ፡፡ ካደገ በኋላ በጥበብ ተሞላ፤

በመንፈስ ደግሞ ጠነከረ፡፡ የእግዚአብሔር ጸጋ በእርሱ ጋር ነበር ብሎ ደግሞ ያረጋግጥልናል፡፡ በመጀመርያ እናቱን

የተቀበለችውን ጸጋ ነው መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የጸጋ ባለቤት ሆኖ ሳለ ግን ግድ የእናቱን በረከት ማግኘት

ግዴታ ነው፡፡ ይህም የፍቅሩ እና የአምላክነቱ ወደ ሰው ለማሳየት ብቻም ሳይሆን ሰው አምላክ፤ አምላክ ሰው

ለማድረግ የጸጋን ሚስጢርን ከእናቱ ተካፈለ፡፡ የጸጋ ባለቤት ሆነ ለምን? መጀመርያ ጸጋ የተሰጠው ለሷ ነው፡፡ የሷን

ስጦታ ራሱ የጸጋው ባለቤት እየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔር ቃል በህይወትዋ ውስጥ በመገለጥ አከበረው፡፡ ጸጋ

የመገለጥ እንጂ የማጨለም የዋሻ ንሮ አይደለም፡፡ የዋሻ፤ የድብብቆሽ ኑሮ አይደለም፡፡ ያም የራሱ የሆነ ትምህርት

አለው፡፡ ያም ቢሆን እንኳ የራሱ የሆነ ግዜ አለው፡፡ የራሱ የሆነ ሰዓት አለው፡፡ ግን ብዙም መሰረታዊው ነገር መገለጥ

Page 5: ፀጋ የሌለው ትውልድ ስለ ፀጋ አያውቅም.pdf

ጸጋ የሌለው ትውልድ ስለ ጸጋ አያውቅም፡፡

መልአከ መንክራት ግርማ ወንድሙ በቁጥር 95 በሬድዬ አቢሲንያ ካስተማሩት… ገፅ 5

ነው፡፡ መጨለም አይደለም፡፡ ማጨላለምም አይደለም፡፡ መገለጥ ነው፡፡ የእግዚአብሔርም ኃይል ማሳየት ነው፡፡

ክብሩን ማሳየት ነው፡፡ ከጸጋ ክፍል ውስጥ ከመነሻው ጀምሮ ያለውን ኃይል አጠንክሮ መታየት ነው፡፡ ስለዚህ

ዲያብሎስም ይህንን መንገድ ተጠቅመዋል፡፡ ለልጆቹ ላይ ታይቶ በልጆቹ ላይ ስራ ይሰራል ክፋቱን፤ ተንኮሉን፤

ምቀኝነቱን፤ ሟርቱን፤ ሰልብናውን፤ ጥፋቱን፤ አዚሙን፤ ድንዛዜውን፤ ድንጋዜዉን፤ ጠቡን ይመራል፡፡ ይሄው

በዓለማችን ከመንፈሳዊው እስከ ዓለማዊ ድረስ የክፉ መንፈስ የመምራት ኃይል የተገለጠበት ዘመንና ግዜ ጎልቶ

የሚታየው በኛ ነው፡፡ በመንፈሳዊ እስከ ዓለማዊ ድረስ፡፡ ያደግነው እንግዲህ በጠብ ግዜ፤ በነገር ግዜ፤ በጦርነት ግዜ

ስለሆነ እኛ አሁን ያለን ጸጋ ሳይሆን የክፉ ነገር ሁሉ መግለጫዎች ሆነን መገኘት ነው፡፡ የክፉ ነገር ሁሉ መግለጫዎች

ሆነን የምንታይ ወደ መጨረሻው ዘመን የሚወስደውን የአረመኔዉን ትውልድ ባህሪ ማንፀባረቅያ መሆናችን ምንም

ማረጋገጫ የሚያስፈልገው አይደለም፡፡ ለምን? በጸጋ ውስጥ አልወተለድንም፡፡

አዎ ክርስትያኖች፡፡ ነን ግን በብዙ ክፉ እና በዚህ ዓለም ግን ግማሾቻችንም ዓመፃ፤ ሓጥያት በጎ ነገር ነጥቆናል፡፡

ግማሾቻችንም የሌሎች የምቀኛ መንፈሶች ህይወታችን ውስጥ በመግባት ነጥቆናል፡፡ ሌላው የጣኦት መንፈስን

አዘውትረን የተራመድን እና እንደ በጎ ነገር ያየን ነው፡፡ ሌላው የጥንቆላ መንፈስ፤ የዓውደ ነገስት ዓለም መንፈስ

መንፈሳዊውን ዓለም ሰብሮ ጥሎ ወጥሮ ገንዞታል፡፡ እና እንዲህ አይነት አካሄድ ባለበት ውስጥ ጸጋን መግለጥ በጣም

አስፈሪ ነው፡፡ ለዚህ ብዙ ሰዎች እየፈሩ ጸጋቸው በዋሻ ይጨርሳሉ አንዳንዶቹ ይሄ ታድያ የመገለጥን ኃይል ለማሳየት

ዕድሉ ሲጠፋ ምልክቶች ናቸው፡፡ ስለዚህ ኤልያስም አንድ ወቅት ላይ ጸጋውን ላለመግለጥ ክትክታ ስር ተኝቶ ልሙት

ብሎ ነበር፡፡ ብዙ መንፈሳዊ በረከቶችን የሰራ ተስፋ ቆርጦ ግዜና ሰዓት ላይ ኤልዛቤልን ፈርቶ፤ ጠንቋይን ፈርቶ፤

አስማተኛዋን ፈርቶ ሞትን ለምኖ ነበር በክትክታ ስር ተኝቶ፡፡ ከዚህ በኋላ እንዳውም የጌታ መልአክ መጥቶ አርባ ቀንና

አርባ ሌሊት እንዲሄድ ያደረገው የመለአክትን እንጀራ ከበላ በኋላ ነው፡፡ ከዛ በኋላ ሞትን አላየም፡፡ የመላእክት እንጀራ

ስለበላ የሚሞት ስጋ አልነበረውም፡፡ የሚኖር ህያው እንዲሆን አድርጎታል፡፡

ስለዚህ የጸጋ ባለቤት እግዚአብሔር ነው፡፡ የእኛን ክፉ መሻት መከተል እንዳንችል የሚያግዘን ደግሞ ጸጋ ነው፡፡ እና

ጸጋ ሲኖር ለጸጋው እንኖራለን፡፡ እመቤታችን ለጸጋው ኖረች የጸጋዉን ባለቤት ወለደች፡፡ የዮሴፍ ልጅ አይደለምን ይሉ

ነበረ፡፡ ይሄንን እናገኛለን፡፡ የሚገርም ነው፡፡ እንግዲህ ጸጋ ወደ ሌሎች ዞሮ ይገባል ማለት ነው፡፡ ሌሎችንም የሚናገር

ነው እግዚአብሔር ጸጋ፤ ሌሎችንም የሚያስረዳ ነው እግዚአብሔር ጸጋ፡፡ አብሮ ተወልዶ፤ አብሮ አድጎ እንደገና

ሌሎችን መናገር የሚችል፤ ሌሎችን ሊያደምጡት የሚችሉ ኃይል እስከ መሆን ደረሰ ማለት ነው፡፡ ‹‹ሁሉም

ይመሰክሩለት ነበር ከአፉ ከሚወጣ ከጸጋው ቃል የተነሳ እተደነቁ›› ይላል፡፡ ተደነቁ የጸጋው ቃል የሌሎችን ልብ እና

ሕሊና ነካ፡፡ ጸጋ ሲኖር እንዲህ ነው፡፡ ጸጋ ሲኖር የሌሎችን ልብ ትነካለህ፡፡ ጸጋ ከሌለህ ግን ጋዜጠኛ ነህ፡፡ ምናልባት

ቃላት ማሳርንና ቃላት አጠረቃሞ አንድ ግዜ መበተንን አና በጸጋ መካከላ ያለውን ኃይልን፡፡ ዛሬ ሰዎች ኢየሱስ ስራን

በጀመረ ግዜ፤ መናገር በጀመረ ግዜ፤ ማስተማር በጀመረ ግዘ፤ ድምፁን ማውጣት ሲጀምር ከአፉ ከሚወጣ ከጸጋው

ቃል የተነሳ ይላል፡፡ ቃሉ ራሱ የጸጋ ቃል ነው አየህ፡፡ የሰው ቃል አይደለም፡፡ አሁን ሁሉ የሚናገረው በሰው ቃል

ነው፡፡ በሰው ቃል ስንናገርና በጸጋው ቃል ስንናገር ልዩነት አለው፡፡ በሰው ቃል ስንናገር የራሳችን ሓሳብ አለበት፡

የራሳችን የይሆናል የግምት ነገር አለበት፡፡ በጸጋው ቃል ግን ስንናገር በደንብ የሰውየውን ሕይወት

እንናገራለን፡፡የዘመኑን፤ የግዜውን አቅጣጫ እንናገራለን፡፡ ነብያትም ይህንን በመንፈሳዊ ኃይል ሲቀበሉት በመንፈስ

Page 6: ፀጋ የሌለው ትውልድ ስለ ፀጋ አያውቅም.pdf

ጸጋ የሌለው ትውልድ ስለ ጸጋ አያውቅም፡፡

መልአከ መንክራት ግርማ ወንድሙ በቁጥር 95 በሬድዬ አቢሲንያ ካስተማሩት… ገፅ 6

ቅዱስ በውስጣቸው ሲኖር የዘመኑን ነገር ተናግረዋል፡፡ በዘመኑ ነገር የሚናገሩት ሌሎች ደግሞ የውድቀትንና የጥፋትን

ነገር ተናግረዋል፡፡ እነዛ ሓሰተኛ ነብያቶች ናቸው፡፡ ሓሰተኛውንና እውነተኛውን ለመለየት በመንፈስ የሚናገረውን በጸጋ

ሚናገረውን መለየት፡፡ ቀደሙ ነብያቶች የሚናገሩት በመንፈስ በቅዱስ መንፈስ ነበር፡፡ ዛሬ በአዲስ ኪዳን ደግሞ

የሚናገሩት በጸጋ እና በመንፈስ ቅዱስ ነው፡፡ ትልቅ ስጦታ ተሰጥቶናል፡፡ ያም ስጦታ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ

ተረጋግተዋል፡፡ ቃል ስጋ በመሆኑ ማለት ነው፡፡ እና በጣም የሚገርም ነገር ነው፡፡ ከአፉ ከሚወጣው ከጸጋው ቃል

የተነሳ እየተደነቁ ‹‹ይሄ የዮሴፍ ልጅ አይደምን?›› ይሉ ነበር፡፡ በቅርብ የሚውቁት ሁሉ ልባቸው ተነካ፡፡ አነጋገሩ

ከሚጠበቅ በላይ ሆነባቸው፡፡ እነሱ ከሚናገሩት፤ ከሚያውቁት፤ ከሚያወሩትና በታሪካቸው ከነበረው ነገር የበለጠ

የሚስደንቅ ነገር ይገጥማቸው ሲናገሩ ሁሉም ይመሰክሩለት ነበር፡፡ ከአፉ ከሚወጣው ከጸጋው ቃል የተነሳ እየተደነቁ

አለ፡፡ በቃ ይሄንን ፅፈዋል ቅድስ ሉቋስ::

እንግዲህ የጸጋው መሰረት እንዴት ታላቅ እየሆነ እንደመጣ እናያለን፡፡ የሓንስ ወንጌል 1፡14 ደግሞ የበለጠ

የሚያረጋግጥልን ነገር አለ፡፡ ‹‹ቃልም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ›› ይላል፡፡ ጸጋ አድሮ መኖር

የሚችል ኃይል ነው፡፡ ከዛም በላይ ደግሞ እንዲህ ሲናገር ‹‹አንድ ልጅም ከአባቱ ዘንድ እንዳለው ክብር የሆነው ክብሩን

አየን።›› ክብሩን ያየነው በኢየሱስ ክርስቶስ ውስጥ ባለው ጸጋ ነው፡፡ ምክንያቱም ቃል ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም

ተመልቶ በእኛ አደረ፡፡ በቃ ይህ ጸጋ ቀጥታ ሲተረጎም ስጦታ ነው፡፡ የእግዚአብሔር ስጦታ፡፡ በእግዚአብሔር ስጦታ

ውስጥ የእግዚአብሔር ክብር ነው፡፡ በእግዚአብሔር ክብር ውስጥ የእግዚአብሔር ኃይል ነው፡፡ በእግዚአብሔር ኃይል

ውስጥ የእግዚአብሔር ሥራ መገለጥ ነው፡፡ በእግዚአብሔር ሥራ መገለጥ ውስጥ ደግሞ አማኞች የእምነት ጉልበት

ያገኛሉ፡፡ አምላካችን አለን ይላሉ፡፡ ወደ ጠንቋይ ቤት አይሄዱ፤ ወደ ደብተራው መተተኛው አይሄዱ፤ ወደ ሓሰተኛም

አይሄዱም፤ ሁሉ ግዜ በአፋቸው ወደ የሚያወሩትን ሰዎች አያምኑም፡፡ የሚያምኑት አንድ ታላቅ ብርቱ የሆነው

የእግዚአብሔርን ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ እና በአብ በወልድ መንፈስ ቅዱስ ተጠምቀው፤ በእመቤታችን በቅድስት

ድንግል ማርያም ኃይልና ጥበብ ውስጥ ኖረው የጸጋ ባለቤቶች እንዲሆኑ በፅናት ይመኛሉ፡፡ በፅናት ያምናሉ፡፡

አየህ ጸጋንና እውነትን ተሞልቶ በኛ አደረ፡፡ ታድያ ዛሬ እውነትም ጸጋም ስለሌለ መቀባጠር እናበዛለን፡፡ የጸጋ ሰዎችንም

እንጠላለን፤ እናሳድዳለን፤ ለማደናቀፍ እና ለመጣል ምክንያት እንፈልጋለን፤ ሞራላቸውን ለመስበር እንሮጣለን፡፡

ከመንፈሳዊው እስከ ዓለማዊው ድረስ ያለው የዓመፃ ድምፆችን እንረባረብባቸዋለን፤ ለማሳሳት ጥረት እናደርጋለን፡፡

ብዙ አይነት ጥፋቶች ለማድረስ እንሞክራለን፡፡ እንግዲህ የጸጋ ልጆች አይደለንም፡፡ ጸጋ የሌለው ትውልድ ስለ ጸጋ

አያውቅም፡፡ የጸጋ ልጆች አይደለንም፡፡ አሳሳቾች ልጆች ነን፡፡ ማሳሳት ነው ስራችን፡፡ መንፈሳዊ ነገርን የሚጀምረው

ማውረድ ነው ስራችን፡፡ ማጥፋት ነው ስራችን፡፡ ደግሞ የሚገርመው እኮ ካሳሳትነው በኋላ የመጀመርያ ስህተት

አንጸባራቂዎች እኛው ነን፡፡ መጀመርያም አሳሳቾች እኛ ነን፡፡ የሞራል ድጋፍ የለንም፤ ማበረታታት የለም፤ ቅድስናን

ማበልፀግ የለም፡፡ የግብጽ አባቶች አንዱ አንዱን ይደግፈዋል፤ አንዱ አንዱን ያበረታዋል፡፡ እኛ ጋር አንዱ አንዱን

ያማዋል፤ አንዱ አንዱን ይነቅለዋል፤ አንዱ አንዱን ያሳድደዋል፤ አንዱ አንዱን ይበላዋል ማለት ይቻላል፡፡ አንዱ በአንዱ

ላይ ወሬ አውርቶ ስልጣንና ማዕርግ ያገኛል፡፡ አንዱ አንዱን ከቦታ ነቅሎ እንዲራብ እንዲሰደድ፤ እንዲጠማ፤

እንዲማረር፤ መናፍቅ እንዲሆን ያደርጉታል፡፡ በዚህ ዘመን ውስጥ ብዙ መንፈሳዊ የጸጋ ጀማራች የነበሩ ልጆች

አውቃለው፡፡ እንዴት አዋክበው አዋክበው ወደ ዳር እንዳወጥዋቸው፡፡ በአሁኑ ግዜ ያንኑ ግፊት የሚያጠናክሩ በሁሉም

Page 7: ፀጋ የሌለው ትውልድ ስለ ፀጋ አያውቅም.pdf

ጸጋ የሌለው ትውልድ ስለ ጸጋ አያውቅም፡፡

መልአከ መንክራት ግርማ ወንድሙ በቁጥር 95 በሬድዬ አቢሲንያ ካስተማሩት… ገፅ 7

መንገድ መልስ ሰጪዎች ነን የሚሉ መቀላመጥ የሚያበዙ ባልተጠበቀ መንገድ ክፋታቸው የተገለጠባቸው ጥቂቶች

አይደሉም፡፡ ስለዚህ በእውነት የጸጋ ልጆች ጸጋቸው ይታያል፡፡ የጸጋ ልጆች ጸጋቸው ይመሰክራል፡፡ ማንም

ባይመሰክርለትም የሚመሰክርለትም ኃይል አለ፡፡ ምን ያስፈልጋል ይሄ ጸጋው ራሱ ይመሰክራል፡፡ ምክንያቱም ‹‹ቃልም

ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ›› ነዋ የሚለው፡፡ እግዚአብሔር ስሙ የተሰገነ ይሁን፡፡

በእኛ እንዲያድር የሰዎች ፍቃድ አይደለም፡፡ ያንተም፤ የትልልቆችም፤ የትንንሾችም ሰዎች ፍቃድ አይደለም፡፡

የማዕረግተኛውም፤ የመንፈሳዊውም ፍቃድ አይደለም፡፡ ይህ ፍቃድ ከሰማይ ብቻ ነው፡፡ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ

በእኛ አደረ በቃ አለቀኮ፡፡ የጠፋው በዓለማችን እውነት እና ጸጋ ነው፡፡ ያንን እውነትና ጸጋ በኢሱስ ክርስቶስ ሰጠን

በእሱ በኩል አየነው፡፡ ከዛም በላይ ደግሞ ይህንን ማየት ይቻላል፡፡ አንድ ልጁ ከአባቱ ዘንድ እንዳለው ክብር ሆኖ

ክብሩን አየን፡፡ በቃ የእግዚአብሔርን ክብር አየነው በኢሱስ ክርስቶስ በኩል፡፡ በስጦታው በኩል አየነው፤ በመወለዱ

በኩል አየነው፤ በድንግል ማርያም በኩል አየነው፤ በመንፈስ ቅዱስ ግብርና ኃይል በኩል አየነው፡፡ ስለዚህ ለዚህ

መንፈሳዊ ኃይል መኖር የጸጋ ስጦታና ታላቅ የሆነው የእግዚአብሐየርን ክብር እግረ መንገዱን መግለጥ ማለት ነው፡፡

ታድያ እንዴት ነው ይሄ ነገር በጸጋ ላይ ጸጋ ደግሞ እንደሚሰጠን የዮሓንስ ወንጌል 1፡16 ላይ እንዲህ ይላል ‹‹እኛ

ሁላችን በሙላት ተቀበልን በጸጋ ላይ ጸጋ ተሰጥቶናልና›› ይላል፡፡ በስጦታ እኮ ነው የምንኖረው፤ ለሌላው በረከት

ለመሆን እኮ ነው የምንኖረው፡፡ አንዳንድ ግዜ ጸጋችንን አናውቀውም፡፡ በተሰጠን ጸጋ ላይ ደግሞ ተንኮል ውስጥ

የምንገባበት አጋጣሚ አለ፡፡ እንዴት ነው የተቀበልነውን ጸጋ ለካፋት ላይ እናውለዋለን፡፡ እኛ ኢትዮጵያውያን ትልቁ

አደጋችንና ትልቁ ጥፋታችን የተቀበልነውን ጸጋ ለጥፋት ማዋል ነው፤ ለተንኮል ማዋል ነው፡፡ ለምሳሌ በአስራ

ስድስተኛው ክፍለ ዘመን እና በእራ ሰባተኛው ክፍለ ዘመን ሰዎች ወደ ቅዱስ ቁርባን እንዳይጠጉ እንከለክል ነበር፡፡

ለምንድነው የምንከለክለው?፡፡ የዛው ሂደት መጥቶ እስከ 2000 ዘመን ድረስ ይሄው አለ አሁንም እየሰሩበት ነው፡፡

ለምንድነው ቅዱስ ቁርባን የምንከለክለው?፡፡ አንተ ሓጥያተኛ ነህ ሓጥያተኛ ወደ ጌታ አይቀርብም እንላለን፤ ሌላ አንተ

ገና ልጅ እኮ ነህ፡፡ ልጅ ስለ ሆንክ ቅዱስ ቁርባን መውሰድ የለብህም እስከ አሁን ድረስ የምንለው ነው፡፡ ገና ነህ

ሓጥያትህ አልጨረስክም እና በዛው በሓጥያጥና በዓመፃ ቆይ ማለት እኮ ነው፡፡ ይሄ በ 15ኛው፤ 16ኛው እና 17ኛው

ክፍለ ዘመን የሦስትና የአራት መቶ እና የስድስት መቶ ዘመን ያህል እንኳን ከእግዚአብሔር ክብር እየለየን የኖርን ሰዎች

ነን፡፡ ደግነቱ የክርሰቶስ ስጋ እና ደምን አልተውንም አላቋረጥነውም፡፡ ይሄም ደግሞ የእግዚአብሔር ስጦታ ሆኖ ነው፡፡

በእኛ አሰራር በእኛ ባህሪ ግን ሰዎችን አርቀናል፡፡ በጣም አርቀናል፡፡ ለምንድነው ይሄ? ሲባል ሚስጥሩ ለመስተፋቅሩ፤

ለመተቱ፤ ለሟርቱ እንዲሰራላቸው ሲሉ ነው፡፡ አጋንንት እንደ ልቡ ሰውን እንዲይዘው ብለው ነው፡፡ አጋንንት እንደ

ልቡ እንዲጫወትበት፤ እርኩሳን መናፍሰት በሰው ልጅ ህይወት ላይ እንዲኖር፡፡ በተደበቀ ተንኮል በኩል የተከሰተ

የእርግማን አሰራር ነው፡፡ ከክርስቶስ ስጋና ደም ለይቶ መኖር የተለመደ ጠባያችን ነው፡፡ ጋብቻውን ያለ ክርስቶስ ስጋና

ደም ያደርጉታል ሚወለዱት ልጆች ቃልቻዎች፤ ጠንቋዮች፤ መተተኞች፤ ሟርተኞች፡፡ ወደ መንፈሳዊ ሲመጣ አጋንንት

ጎታች፤ እርኩሳን መናፍት ጠሪ፤ አቆራኚ እና አፍዝዝ አደንግዝን የሚወድ አይነት ትውልድ እንዲሆን አስተዋፅኦ

አድርገናል፡፡

Page 8: ፀጋ የሌለው ትውልድ ስለ ፀጋ አያውቅም.pdf

ጸጋ የሌለው ትውልድ ስለ ጸጋ አያውቅም፡፡

መልአከ መንክራት ግርማ ወንድሙ በቁጥር 95 በሬድዬ አቢሲንያ ካስተማሩት… ገፅ 8

ታድያ እንዴት ነው እኛ ሁላችን ከሙላቱ ተቀበልን በጸጋው ላይ ጸጋ ተሰጥቶናል የሚለውን ወደ ተግባር የተረጎምነውን

የቱ ጋር ነው ብለን ራሳችን ስንጠይቅ ትልቅ መሰረታዊ ነገር አጥተነው ኖረናል፡፡ የተሰጠንን የጸጋ ኃይል አርቀን

ኖረናል፡፡ ስለዚህ ሙላታችን አሁን ወደ ክፉ ሙላት ሆኖብን ነው የኖርነው፡፡ ምላሻችን የክፉ ሙላት ውጤት ሆኖ ነው

የሚኖረው፡፡ የዛ ግልብ ባህሪ ዛሬ ብዙዎች ባላቸው መዕረግ፤ ባላቸው ስልጣን ውስጥ ለተንኮል ብቻ የሚዘጋጁ ዕለት

ዕለት በስጋዊ ዓለም ውስጥ ያለውን የጥቅም ግፎች ውስጥ መግባት የተለመደ ነገር ሆነዋል፡፡ ጉቦውንም ምኑን ምኑን

የሚያሳድዱትና የሰው ልጆችን ከበጎ አካሄድ የሚያርቁ፤ እምነትን ጥርጣሬ ውስጥ የሚከቱ፤ የፍቅረ ንዋይ ሃሳብና

ስሜት ህይወታቸውን የጋለባቸው እንግዲህ የጸጋ ሙላት አላቸው ልንል አንችልም፡፡ ምክንያም የሚሰራው ግፍ

የእግዚአብሔር ጸጋ ያለው ሰው መግለጫ አይደለምና ነው፡፡ የምንናገረው ግፍ፤ የምናወራው ግፍ የእግዚአብሔር ጸጋ

ምልክት አይደለም፡፡

ስለዚህ ጸጋ ይገለጣል ተደብቆ አይደለም የሚሰራው፡፡ በግልፅ ነው፡፡ በህዝብ ፊት ነው እግዚአብሔር ጸጋ እኛ ሁላችን

ከሙላቱ ተቀበልን በጸጋ ላይ ጸጋ ተሰጥቶናልና፡፡ ‹‹ሕግ በሙሴ ተሰጥቶን ነበርና›› ይላል የዮሃንስ ወንጌል 1፡16፡፡

አንግዲህ ጸጋ ይሰጣል ከድንግል ማርያም ክርስቶስ እንደተቀበለ፤ ክርስቶስ እንዳገኘ ሰጪ ሆኖ ከእርስዋ እንደወሰደ፡ ከዛ

በኋላ ደግሞ ለእኛ ይሰጥ ዘንድ ከስጋ ጸጋን አካፈለን፡፡ ለዚህ የጸጋው ባለቤት ሆኖ ጸጋን ይሰጠን ዘንድ ዝቅ አለ፡፡ ዝቅ

ብሎ ከሰው ህይወት ልጅ ህይወት ውስጥ በተዋህዶ የከበረ እና በተዋህዶ የተገለጸ አካል ይዞ ታየ፡፡ ከዛ በኋላ ግን

ከሙላቱ እንድንካፈል የእግዚአብሔር በጎ ፍቃድ ውስጥ የጸጋ ስጦታ የተረጋገጠበትን ስልጣን ሕይወታችን አገኘ፡፡

በዚሁ በዮሓንስ 1፡17 ላይ እንዲህ ይላል ‹‹ጸጋና እውነት ግን በኢየሱስ ክርስቶስ ሆነ።›› ይላል አያችሁ፡፡ የእግዚአብሔር

ስም የተመሰገነ ይሁን፡፡ እውነትን ያገኘነው በኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ቤተ ክርስትያን የሁለት ስልጣንና ኃይል ባለቤት

ናት፡፡ የጸጋ እና የእውነት ታድያ በዚህ በ 21ኛ ክፍለ ዘመን ጸጋ እና እውነት አለ ወይ?፡፡ በዚህ በ 2008 ዓ/ም ጸጋ እና

እውነት አለ ወይ? ብለን ስንፈልግ ብዙ ቦታ ላይ ሓሜት ነው ያለው፤ ብዙ ቦታ ላይ ቅዋሜ ነው ያለው፤ ብዙ ቦታ ላይ

እርግማን ነው ያለው፤ ብዙ ቦታ ላይ ውድቀት ነው ያለው፡፡ ብዙ ቦታ ላይ ሸለቆ ሽንፈት ነው ያለው፤ ቁልቁሊት ነው

ያለው፡፡ በዚህ ቦታ ላይ እንዴት ነው ጸጋ እና እውነት ግን በኢሱስ ክርስቶስ ሆነ በቃ፡፡ በእርሱ በኩል ተገለጠልን፤

በእርሱ በኩል ተሰጠን የሆነው ሁሉ በኛ ይሆን ዘንድ እግዚአብሔር ክብሩን እና ኃይሉን ሰጠን፡፡ ይሆን ዘንድ ነው፡፡

በኛ ይሆን ዘንድ ነው፡፡ ስለዚህ የሚሆነውን እንዲሆን ያደረገው በጸጋ እና በእውነት ውስጥ ነው፡፡ ስለዚህ ጸጋ የሌለው

ትውልድ ስለ ጸጋ መወቅም መረዳትም አይፈልግም፡፡ የራሱን ዓለምና የራሱን ወንጌል፤ የራሱን ትርጉም ይዘዋል፡፡

አሁን ትልቁ ችግር በዚህ በኛው ዘመን ውስጥ የራሳችንን ትርጉም እናስጨበጭባለን፤ እናስጨበጭብበታለን እንጂ በጸጋ

ውስጥ የመገለጡ ጉዳይ ላይ እምነት የለንም፡፡ በዚህ ዘመን እግዚአብሔር ይሰራል ወይ ብለም ማመን ተስኖናል፡፡

ተስፋ ቆርጠናል፡፡ ኤልያስም እኮ ተስፋ ቆርጦ ነበረ በዓልን ያልሳሙ ሰባት ሺህ ሰዎች አለኝ ሲለው ደነገጠ፡፡ አንዳንዴ

የእግዚአብሔርን ቦታ ይዘን እንፈርዳለን፡፡ ስለዚህ የክፉ ትውልዱ መለያና ምልክቱም አንዱ ይሄ ነው፡፡ እንዴት በዚህ

ዘመን ህዝቡ ይጮሃል ብለው የሚደናገሩ አሉ፡፡ ኑ እና እዩ ችግሩ እስኪ ተካፈሉ፤ ሓሳቡን አድምጡት፤ ውስጡ

ያለውን ችግር ምንድ ነው? በሉት፤ ህመምህ ምንድው?፤ በረከትህ ማጣትህ ምንድነው? በሉት፡፡ እስቲ በሉት እስቲ

ጠጋ በሉት እናንተ ራሳችሁ እኮ ከዚህ በረከት ተካፋዮች አልሆናችሁም፡፡ በአንፃራዊ ባህሪ ውስጥ የህይወት እብደት

የሆናችሁ ጥቂቶች አይደላችሁም፡፡ በህይወት ያበዳችሁ፡፡

Page 9: ፀጋ የሌለው ትውልድ ስለ ፀጋ አያውቅም.pdf

ጸጋ የሌለው ትውልድ ስለ ጸጋ አያውቅም፡፡

መልአከ መንክራት ግርማ ወንድሙ በቁጥር 95 በሬድዬ አቢሲንያ ካስተማሩት… ገፅ 9

እንዴት ነው ነገሩ?፡፡ ጸጋ፤ የጸጋ ኃይልና ጥበብን ካላወቅን አደጋው ከባድ ነው፡፡ ቀላል አይደለምን፡፡ አንድ ነገር

ልንገራችሁ፡፡ ኤልሳ የኤልያስን ጸጋ ተቀበለ ግን ወደ አንዲት ቦታ መሄድ ሲጀምር ወደ ቤቲኤል ሲወጣ አንተ መላጣ

ውጣ፤ አንተ መላጣ ውጣ እያሉ ህፃናቶች ሰደቡት፡፡ ከዛ በኋላ ዘወር ብሎ አያቸው በእግዚአብሔር ስምም

ረገማቸው፡፡ ከዱርም ሁለት ድቦች ወጥተው ከብላቴናዎቹ አርባ ሁለቱም ሰባበርዋቸው ይላል፡፡ አየህ አደጋ አለው

ካላወቅከው ጸጋን አደጋ አለው፡፡ እነዚህ ልጆች የኤልያሳ ጸጋ ነብይና የኤልያስ በረከት ያደረበት፤ የኤልያስ መንፈስ

የኖረበት እንደሆነ አላወቁም፡፡ ግን ተሳደቡ ከዛ በኋላ እርግማን ተቀበሉ አለ ዕድሚያቸው፤ አለ ግዝያቸው ሞቱ፡፡

መጽሓፈ ነገስት ካልዕ 2፡23 ላይ ተመልከት፡፡ ጸጋን ካላወቅክ አደጋ አለው፡፡ አደገኛ አደጋ አለው፡፡ የእግዚአብሔርን

ስጦታ ካላወቅክ አገልግለህ፤ አገልግለህ ትመክናለህ፡፡ የሆነ ቦታ ላይ ትወድቃለህ፡፡ የሆነ ቦታ ላይ ትታያለህ፡፡ የሚያይህ

ኃይል አለ፡፡ የሰማይ አምላክ መንፈስ ነው፡፡

በመንፈስ አንድ ብንሆን እኮ ይህ ሁሉ ነገር የለም፡፡ በመንፈስ መለያየታችን በራሱ ችግር አለ ማለት ነው፡፡ እና ጸጋ እና

እውነት ግን በኢየሱስ ክርስቶስ ሆነ፡፡ በቃ እሱ ከሰጠ ምን ትፈልጋለህ?፡፡ እግዚአብሔር ጸጋን ከሰጠ ምን አለ፡፡ ሰዎችን

አትከተሉ ትላለህ፡፡ እሺ አዎ ሰውን መከተል የለበትም፡፡ ግን የሚከተለው እንዴት ነው?፡፡ የሚናገው ቃል

የእግዚአብሔር አይደለም ማለትህ ነው?፡፡ ክርስቶስስ ምን አለ?፡፡ ያለው ‹‹ስጋ የበላ ደሜ የጠጣ የዘልዓለም ህይወት

አለው ነው፡፡›› ነው ያለው እንዲህ የዘልዓለም ህይወት ያለው ሰው አትከተሉ ማለትህ ነው? ፡፡ ክርስቶስ ሰው

አይደለም?፤ ክርስቶስ ሰው ሆኖ አይደለም የመጣው?፡፡ ክርስቶስ ሰው ሆኖ የአባቱን ክብር፤ የአባቱን…፡፡ የጸጋ

ባለቤቶች ከሆኑ ምን አንተ ዓይንህን ደም አለበሰው?፡፡ ለምን ደም ይለብሳል ዓይንህ?፡፡ ምክንያቱም እኛ ሁላችን

ከሙላቱ ተቀበልን፡፡ በጸጋ ላይ ጸጋ ተሰጥቶናል ነው የሚለው፡፡ ይህንን ስጦታ ለአህያና ለፈረስ አይደለም የተሰጠው

እኮ፡፡ እግዚአብሔርን የወደደው ስራ ከሰራ ምን አገባህ አንተ?፡፡ ና አሁን እኮ ዙርያውን ዳርዳሩን መጋለብ አይደለም

ቀጥታ መምጣት ነው፡፡ ወንበር እንደሆነ ሞልተዋል እንሰጥሃለን፤ ቦታም እንሰጥሃለን፤ ሌላው መድረክም እንኳን

እንሰጥሃለን እኮ፡፡ ምን ዙርያውን ትዞራላችሁ?፤ ለምን ባልሆነ መንገድ ትጣመማላችሁ? አለምክንያት አይደለም

የክፋት ትውልዶች ነን፡፡ መሰረታዊ ዕውቀታችንን ከክፋት ጋር የተያያዘ ነው፡፡ በዓለማዊውም፤ በመንፈሳዊውም ሆነ

የቁራነኝነት ተንኮል ከደማችን ጋር አለ፡፡

ጸጋ አይደለም አብሮን የተወለደው፡፡ አስተውሉ ጸጋ ከቅድስት ድንግል ማርያም አብሮ ኖሮ ከኢየሱስ ክርስቶስ ላይ

አድረዋል፡፡ እኛም ክፋት እንደ ጸጋ ሆኖ ክፋት አብሮን ተወልዶናል፡፡ የክፋት ስጦታዎች አሉን፡፡ የዚህ ክፋት ሰጪ

ደግሞ ሌላ ኃይል ነው፡፡ ሁሉ ግዜ አጨንጋፊዎች ነን፤ ሁሉ ግዜ አጥፊዎች ነን፤ ሁሉ ግዜ አምካኞች ነን፤ ሁሉ ግዜ

አደብዛዞች ነን፤ ሁሉ ግዜ አጨላላሚዎች ነን፡፡ ሁሉ ግዜ እኮ ነው ከታሪኮች ውስጥ ብዙ ክፍል ላይ ብዙ ቦታ ላይ

ከመሪዎች ብዙ ስፍራዎች እና ጎዞዎች ላይ ሁሉ ስናነብ ሁሉ ግዜ ሞቶች ነን፤ ሁሉ ግዜ እርግማኖች ነን ምን አይነት

ትውልዶች ነን?፡፡

የሓበሻ ልጅ እንደዚህ ሆኖ ሲቀር በጣም ይገርማል፡፡ ይሄ ደግሞ ከአምልኮት መንፈሳዊ በረከት መራቃችን ያመጣብን

ጉድ ነው፡፡ እስራኤሎች ይህ ነበረ ትልቁ ችግራቸው፡፡ ከበረከት ተስፋ ሲጥሉ 70 ዓመት ለባርነት 40 ዓመት ለባርነት

እንደዚህ መማቀቅ የተለመደ ዕጣቸው ነበር፡፡

Page 10: ፀጋ የሌለው ትውልድ ስለ ፀጋ አያውቅም.pdf

ጸጋ የሌለው ትውልድ ስለ ጸጋ አያውቅም፡፡

መልአከ መንክራት ግርማ ወንድሙ በቁጥር 95 በሬድዬ አቢሲንያ ካስተማሩት… ገፅ 10

እና ጸጋ እና እውነት በኢየሱስ ክርስቶስ ሆነ፡፡ አዎ ሆነ፡፡ ለእኛም ተሰጥቶናል፡፡ ይህ ጸጋ ግን ብዙዎችን ለማዳን ነው፤

ብዙዎችን ለማክበር ነው፤ ብዙዎችን ወደ ክርስቶስ ለመመለስ ነው እንጂ ወደ ጫካ ለመውሰድ፤ ወደ ጥንቆላ ስፍራ

ለመውሰድ፤ ድቤ እንዲመቱ ለማድረግ አይደለም፡፡ ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ አንተ ልክ እንደ ገሊላ የሶምሶምን

የጸጋ ኃይል ለመላጨት ትቸኩላለህ፤ የጸጋ ኃይል ለማጥፋት ትቸኩላለህ፤ ፤ማደናገር ትቸኩላለህ፤ የተቀባይነትህን ጸጋና

ሞጎስ፤ ክብርና ኃይል ለተንኮል ማዋል በራሱ አስቸጋሪ ነገር ነው፡፡ የእግዚአብሔር የሆነ ነገር ሳትለይ መራመድ

እንቅፋቱ እየጠነከረ እንዲመጣ ያደርጋል፡፡ ስለዚህ ይህም አሉባልተኝነት ነው፡፡ የአሉባልተኝነት ህይወትን የመያዝ

ሚስጢር ነው፡፡

ወደ ሐወርያት ደግሞ ልውሰድህ ስለ ጸጋ፡፡ የሓወርያት ስራ 4:33 ላይ እንዲህ ይላል ‹‹ሐዋርያትም የጌታን የኢየሱስ

ክርስቶስን ትንሣኤ በታላቅ ኃይል ይመሰክሩ ነበር፤ በሁሉም ላይ ታላቅ ጸጋ ነበረባቸው።›› ይላል፡፡ በሁሉም ላይ ታላቅ

ጸጋ ነበረባቸው ይላል፡፡ እሺ ዛሬ ኢየሱስ ክርስቶስን ብንናገር ያ ጸጋ በእና ላይ ቢኖር ይህን ያህል የሚያስፈራ፤ ይህን

ያህል አደናጋሪ ነው፡፡ አስራት አውጡ፤ የእግዚአብሔርን በረከት ያዙ፤ ወደ ክርስቶስ ስጋና ደም ቅረቡ፤ ጸሎት ቤት

ስሩ፤ በየዕለቱ አምልኮት አድርጉ ማለት ይሄ ጠንቋይነት ነው?፤ ይሄ መተተኝነት ነው?፡፡ በረከታችሁን እዩ፤

የእግዚአብሔርን ስጦታ በዛው ቅመሱ፤ ሰላምና ጸጋ፤ ሰላምና በረከት ከእናንተ ጋር መሆኑ አረጋግጡ ማለት ይሄ

ተንኮል ነው?፤ ማለት ይሄ ሓጥያት ነው?፡፡ የለመዳችሁት ተንኮል ስላለ ይሄ እውነት ይፃረራቹሃል፡፡ ጸጋ የሌለው

ትውልድ ስለ ጸጋ አያውቅም፡፡

ሐወርያት ግን የጀመሩት ቤተክርስትያንን ሲጀምሩ እንዲህ ነው፡፡ ሐወርያትን የጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን ትንሳኤ

በታላቅ ኃይል ይመሰክሩ ነበር፡፡ ሞት ተሸረዋል አየህ፡፡ ሰውን አትከተሉ ትላለህ፡፡ ሰውን ትንሳኤን ያገኘ ሞትን የሰበረ

ነው እኮ ይሄውልህ፡፡ ታድያ ምን ይከተሉ?፡፡ ማንን ይከተሉ?፡፡ እንዴት ነው ታድያ የሚማሩት?፤ እንዴት ነው ታድያ

የሚረዱት?፤ ምን ብለው ይስገዱት፡፡ በግራ በኩል ይስገዱ?፡፡ እዛ ሲሰግዱ ደስ ይልሃል ወደ ግራ ሄደው ሲሰግዱ፡፡ እዛ

ሲሄዱ ምንህም አይደለም፡፡ እንዳውም ትስቃለህ፡፡ ጠንቋይ ቤት ሄደው ሲሰግዱ አይታይህም ያ፡፡ እንዲህ አይነቱን

ነገር እዛ ሄደው ሰገዱ ቢባል እንኳን ይገርማል ነው የምትለው እንጂ ውስጥህ አይቃወመውም፡፡ ለምን?፡፡ የመናፍስት

አንድነት አለ፡፡ የክፉ ተግባር ባህሪ አንድነት አለ፡፡

አስቲ አርቲስቶችን ተመልከታቸው፡፡ ቀደም ቢጂአይ አይቻለው 30 ዓመት ጥሩምባ የምትንፋን ሴት 165,000 ብር

የጥሮታ ገንዘብ ሲሰጥዋት አይቻለው፡፡ ስጦታ ሰውን ማየት የተቸገረውን በማሰብ ለ 30 ዓመት ጥሩምባ እየነፉ

የነበሩትን እናት ቢጂአይዮች የሰሩትን ተግባር እያየሁ ለመንፈሳዊያን ሰዎችን ህይወት ሳገናዝብ ደግሞ የጣዕረ ሞት

ያህል ነው የሆነብኝ፡፡ መንፈሳዊነት ጣዕረሞት ውስጥ ነው ያለው፡፡ ጣዕር ላይ ነው ያለ ብየ ማየት ችያለው፡፡ ሁሉ ግዜ

ሲፈቃቀሩ፤ ሲተሳሰቡ፤ የአንድ አንዱን ችግር ሲሸፍን፤ የአንድ አንዱን ድካም ሲሸፍን፤ የአንድ አንዱን ሲያበረታታ፤

የአንድ አንዱን ችግር ሲያስብ በመንፈሳዊ ቦታ ላይማ ሰባኪዎቻችን ይህን ነገር አያዩም፤ ይሄ ነገር የላቸውም፡፡ ዓለም

ይሄን ያህል ነው አርቲስቶች ይሄን ያህል ናቸው፡፡ ይሄን ያህል ይተዛዘናሉ፡፡ መንፈሳዊ ሰባኪዎች ግን አንድም ቀን

አብረው በልተው አያውቁም፡፡ ተናክሰው፤ ተባልተው፡፡ እንዳውም እንደ ውሻ እርስ በርስ ሲናከሱ ማየት የተለመደ

ነው፡፡ ዕድላችን ነው፡፡ የሄው ሲነሱን ነው የሚኖሩት እኮ፡፡ ሲሰብኩም ከነክሰውን ነው የሚሰብኩ፡፡ ሲናገሩ ከነክሰውን

Page 11: ፀጋ የሌለው ትውልድ ስለ ፀጋ አያውቅም.pdf

ጸጋ የሌለው ትውልድ ስለ ጸጋ አያውቅም፡፡

መልአከ መንክራት ግርማ ወንድሙ በቁጥር 95 በሬድዬ አቢሲንያ ካስተማሩት… ገፅ 11

ነው የሚናገሩት፡፡ እንግዲህ ምንድነው መንፈሳዊነት ስንል?፡፡ የለም የለም ቦታውን ስፍራውን ያዘው ክፉ የሆነው የዚህ

ዓለም ገዢ ነው፡፡ቅድሰት ቤተክርስትያንን ኃይልና የጸጋ ስጦታዎችን ተግባር የማይተረጉሙ አረማውያን ቦታዉን እና

ስፍራውን ለክፋትና ለድርጊት፤ ለምቀኝነትና ለዓመፃ አውለውታል፡፡ ስለዚህ በጎነት ወደ ዓለም ተሻግሮ እዛ ዓለምም

እያሳዩ በዓለም ላይ የዓለምን በጎነት እየገለፁ ነው፡፡ የእግዚአብሔርን አይደለም፡፡ የዓለምን በጎነት፡፡ እንዲህ ነን፡፡

እናንተን እንዲህ እናያለን፤ እንዲህ አይነት መነፅር አለን፤ ወደቁትን እናነሳለን፡፡ ቤተ ክርስትያን ይህንን ልትሄድበት

የምትችልበትን ኃይል በልጆችዋ ውስጥ በጠብ ተለውጠዋል፡፡ በጠብና በነገር ተለውጠዋል፡፡ ስለዚህ ጸጋ የሌለው

ትውልድ ስለ ጸጋ አያውቅም፡፡

ስለዚህ ዓለም ናት አሁን የምታናግረው፡፡ ደረስኩላችሁ ትላለች ለልጆችዋ፡፡ መንፈሳውያን ደረስንላችሁ አይሉም፡፡

ብለውም አያውቁም፡፡ የሚሉትን አባቶች፤ የሚሉትን ወንድሞች አጥተናቸዋል፡፡ ደረስናለችሁ አይዟችሁ የሚሉትን

አጥተናቸዋል፡፡ ቢሉ እንኳ በቲፎዞ አይነት መልክ እነጂ በበጎ አይነት አይደለም፡፡ ከሆነ ነገር ጋር የተገናኘ መሆን

አለበት፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር ግን የተገናኘ ግን አይደለም፡፡ ስለዚህ ጸጋን የማያውቅ ትውልድ ስለ ጸጋ አያውቅም፡፡

በሁሉም ታላቅ ጸጋ ነበረባቸው ይላል ሓወርያት ስራ ሲጀምሩ በጸጋ ነው አየህ፡፡ በጸጋ ጀመሩ የክርስቶስን ትንሳኤ

ሰበኩ፡፡

ሌላው የሚገለፅ ጸጋ ሆኖ ስናይ በሐወርያት ሥራ 6፡8 ላይ እንዲህ ይላል ‹‹እስጢፋኖስም ጸጋንና ኃይልን ተሞልቶ

በሕዝቡ መካከል ድንቅንና ታላቅ ምልክትን ያደርግ ነበር።›› ዛሬ እሱ ቢመጣ የሱዳን አስማተኛ ነበር የምትሉት፡፡ እኔን

እንደምትሉት ትሉት ነበረ ማለት ነው፡፡ እርግጠኛ ነን እንደዚህ እንደምትሉት፡፡ በቃ ይሄ ነው ቋንቋችን፡፡

እስጢፋኖስም ጸጋንና ኃይልን ተሞልቶ በሕዝቡ መካከል ድንቅንና ታላቅ ምልክትን ያደርግ ነበር።› በምልክት አትመኑ

ትላለህ፡፡ ምልክት የእግዚአብሔርን ህዝብ እንዲያምንና እንዲፀና ያደርገዋል፡፡ ምልክት ስሌለለህ አይደለም እንዴ

መናፍቅ የሆነ ሰው?፡፡ ሌላው ደግሞ ሁሉ ግዜ የምንለው ነገር አለ፡፡ ጸበል ነው፤ ጸበል ነው… ሰው አያድንም ጸበል ነው

የሚያድነው ትላለህ፡፡ እሺ ጥሩ መፃጉእ እኮ ጸበል አላዳነውም ኢየሱስ ክርስቶስ በስጋ መጥቶ ነው ያዳነው፡፡

ትሰማኛለህ ጸበል ያኔ አላዳነውም፡፡ ክርስቶስ የመጣው ደግሞ ለጸበል አይደለም የመጣው ትሰማለህ፡፡ የመጣው የሱን

ክብርና ኃይል ባንተ ውስጥ ሊያኖር ነው፡፡ ከዛም በላይ ደግሞ ድንቅና ታላላቅ የሆኑ መንፈሳዊ ፅናቶችን

በእግዚአብሔር ስም እንድትሰራ ነው፡፡ ማርክሲስም ለምን ድነው በሶቬት ሕብረት ነፃ መድረክ ያገኘው?፡፡

ኃይማኖተኞቹ የሰይጣን ኃይል ለማስወጣት ደንዝዘው ስለተቀመጡ አይደለም እንዴ?፡፡ ኃይማኖች ሕብረተሰብን

የማደንዠዣ ዕፅ ነው ያለው ሌኒን እኮ ካህናትም ቀሳውስቱም ኃይማኖትን መግለፅ አልቻሉም ገባህ?፡፡ በማርኪሲስት

ዘመን ውስጥ ኃይማኖትንም መግለፅ አልቻሉም፤ ክፉ መንፈስን ማስወጣት አልቻሉም፡፡ እነሱም አመለኞችና ሱሰኞች

ሆኑ፤ ሲጋራ አጫሾች ሆኑ፤ ሓሹሽ ወሳጆች ሆኑ ሰይጣን ሕብረተሰቡ እያነቀ ኃይማኖትን መሳደብ ጀመረ፡፡ በሌኒን

መጽሓፍ በኩል ኃይማኖት የሕብረተሰብን የማደንዠዣ ዕፅ ነው አለና ተናገረ፡፡

ኃይማኖት መገለጥ ካልቻለ ኃይማኖትነቱ ለክፉዎች ቋንቋ መግለጫ ነው የሚሆነው፡፡ ተሰማኛለህ ኃይማኖት መገለጥ

አለበት፡፡ የመገለጥ ስራ መስራት አለበት፡፡ ‹‹እስጢፋኖስም ጸጋንና ኃይልን ተሞልቶ በሕዝቡ መካከል ድንቅንና ታላቅ

ምልክትን ያደርግ ነበር።›› ነዋ የሚለው፡፡ ምልክትቶች የለሌለበት እምነት ውስጥ ኃይል አይታይም፡፡ ኃይል ካለ ደግሞ

Page 12: ፀጋ የሌለው ትውልድ ስለ ፀጋ አያውቅም.pdf

ጸጋ የሌለው ትውልድ ስለ ጸጋ አያውቅም፡፡

መልአከ መንክራት ግርማ ወንድሙ በቁጥር 95 በሬድዬ አቢሲንያ ካስተማሩት… ገፅ 12

የእግዚአብሔር ምልክት አለ፡፡ እና እስጢፋኖስ ያንን ጸጋ አሳየ፡፡ ያ ጸጋ በመታየቱ ብዙ ደቀ መዛሙርት የእስጢፋኖስን

ክብርና መንፈስ ተከተለ፡፡ የእግዚአብሔር ኃይልና ጥበብን ተከተለ፡፡ የሐወርያት ስራ 11:23 ላይ እንዲህ ይላል ‹‹እርሱም

መጥቶ የእግዚአብሔርን ጸጋ ባየ ጊዜ ደስ አለው፥ ሁሉንም በልባቸው ፈቃድ በጌታ ጸንተው ይኖሩ ዘንድ መከራቸው››

ይላል፡፡ አየህ የእግዚአብሔርን ጸጋ ባየ ግዜ ደስ አለው ይላል፡፡ ለምን እናንተ ደስ አይላችሁም?፡፡ በቤተ ክርስትያናችን

መድረክ ነው፡፡ እስጢፋኖስ ላይ ሦስት ዓመት አገልግለናል፡፡ እዛ ነበርን፡፡ ፉሪ ስላሴ ነበርን፤ ጉራራ ኪዳነ ምሕረት

ነበርን፤ ሽንቁሩ ሚካኤል አገልግለናል እዛው ደግሞ መድኃኔ ዓለም አገልግለናል፤ መሪ አቦ አገልግለናል?፡፡ ምን

ያላገለገልንበት ቦታ አለ፡፡ ለምን በዚህ ደስ አላላችሁም?፡፡ መድኃኔ ዓለም ጫካ ውስጥ በዚህ በእንጦጦ በኩል እዛ

ውስጥ አገልግለናል፤ መገናኛ እግዚአብሔር አብ አቦ አገልግለናል፡፡ ስንት ብለን ከምስራቅ እስከ ምዕራብ ድረስ፤

ከምዕራብ እስከ ሰሜን ያሉው ግዛቶች ብዙዎች ቦታዎች አገልግለናል፡፡ ለምን በዚህ ደስ አላላችሁም?፡፡ ምክንያቱም

ጸጋ የማያውቅ ትውልድ ስለ ጸጋ አያውቅም፡፡

ስለዚህ ይሄ ነው ወገኖች ሁላችሁም መጸለይ ስትጀምሩ፤ እናንተ መንፈሳዊውን ህይወት መከተል ስትጀምሩ፤ መማር

ስትጀምሩ የጸጋ ጠላቶች ከክብር ይነሳሉ፡፡ ይደነግጣሉ፤ ይፈራሉ፤ አካሄዳቸውን ያስባሉ እንደገና ምክንያቱም

ማደናቀፍን ለማጠናከር ብዙ መንገድ ላይ ለመሮጥ ይጥራሉ፡፡ እና ይህ አካሄድ አደገኛ አካሄድ ነው፡፡ ስለዚህ ጸጋን

የማያውቅ ትውልድ ስለ ጸጋ መናገርም አይፈልግም፤ ማወቅም አያውቅም፤ ሊደሰትም አይችልም፡፡ ምክንያቱም

የተወለደበት ሁኔታ ላይ ያለ አደጋ አለ፡፡ እውነትን እንዳይረዳ መከለያና መጋረጃዎችም አሉ፡፡ ስለዚህ የሓወርያት ሥራ

11፡23 ላይ ‹‹እርሱም መጥቶ የእግዚአብሔርን ጸጋ ባየ ጊዜ ደስ አለው፥ ሁሉንም በልባቸው ፈቃድ በጌታ ጸንተው ይኖሩ

ዘንድ መከራቸው፤›› በቃ፡፡ ምንድነው የጸጋው አገልግሎት?፡፡ ምን እያደረገ ነው? ብለህ ማየት አልፈለግክም፡፡ ስለዚህ

ስህተቱ እና አደጋው እዚህ ጋር ነው፡፡ ጸጋ የተገለጠ ሥራ ይሰራ መሆኑን ማመን በራሱ ራሱ የቻለ አንደኛ አካሄድ

ነው፡፡ በሁለተኛ ደረጃ ጸጋ ወዴት ነው የሚወስደው የሚለውን መለየት ሁለተኛ ነገር ነው፡፡ የጸጋው በረከት ደግሞ

የቱን ያህል የሰፋ ነው የሚለውን ነገር ለማገናዘብ ግዜና ሰዓት መስጠትን ያስፈልጋል፡፡ ከዛ ውጪ ያለውን አካሄድ

ድፍን ያለ የተደበቀ አረማዊነት ነው፡፡ የሐወርያት ሥራ 13፡43 ላይም ተመልከት ‹‹ጉባኤውም ከተፈታ በኋላ

ከአይሁድና ወደ ይሁዲነት ገብተው ከሚያመልኩ ብዙዎች ጳውሎስንና በርናባስን ተከተሉአቸው፥ እነርሱም

ሲነግሩአቸው በእግዚአብሔር ጸጋ ጸንተው እንዲኖሩ አስረዱአቸው።›› በርናባስንና ጳውሎስን የተከተሉት ሰውን

አትከተሉት ትላለህ አይደል?፡፡ ይሄው ሰውን ተከትለዋል በርናባስንና ጳውሎስ ሰውች ናቸው ተከተልዋቸው፡፡ ግን

ከተከተልዋቸው በኋላ ያሉት ነገር ምንድነው?፡፡ እኛን አይደለም በእግዚአብሔር ጸጋ ፀንተው እንዲኖሩ አስረድዋቸው

ይላል፡፡ እሺ እኔ መምህር ግርማ ነኝ እኔን ተከተሉ ብየ ያስረዳሁበት ግዜ አለ እንዴ?፡፡ የክርስቶስን ቃል ትምህርትን

ተከተሉ ለጸጋ ትበቃላችሁ ብየ መግለፅ ይሄ ነውር ነው?፡፡ ይሄ ሓጥያት ነው?፡፡ ይሄ ነው የቤተ ክርስትያን ጉዞ ውስጥ

እግዚአብሔርን እንዲከተሉ ማድረግ?፡፡ ቅዱስ ቁርባንን ማድረግ፤ አስራት እንዲያወጡ ማድረግ ይሄ ወንጀል ነው?፡፡

ስለዚህ በጸጋ ፀንተው እንዲኖሩ አስረድዋቸው ነው የሚለው ህዝቡ ግን ተከትለውባቸዋል፡፡ በጸጋ ውስጥ የመኖርን

ኃይል አስረድተውባቸዋል፡፡

ስለዚህ ሰውን አትከተሉ፡፡ ማንን ለመነካካት ነው?፡፡ በእርግጥ አዎ ሰውን መከተል አደጋ አለው፡፡ በአንፃራዊ ባህሪ ግን

ሲታይ ሰውን መከተል በጸጋ በኩል ነው መከተል?፤ በክርስቶስ ስጋና ደም በኩል ነው መከተል? ወይስ በደብዛዛው

Page 13: ፀጋ የሌለው ትውልድ ስለ ፀጋ አያውቅም.pdf

ጸጋ የሌለው ትውልድ ስለ ጸጋ አያውቅም፡፡

መልአከ መንክራት ግርማ ወንድሙ በቁጥር 95 በሬድዬ አቢሲንያ ካስተማሩት… ገፅ 13

የካድሬ አይነት መከተል ነው?፡፡ በአብዮቱማ ሰውን ተከትለን ነበር አብዮተኞች ሆነን፡፡ አብዮቱ ሲዳፈን ሁሉም ነገር

ተዳፈነብን ያ የመትል ከሆነ እሺ ጥሩ መልካም ነው፡፡ በመለኮታዊ ብርሃን በኩል ባለው ቃል ከሆነ ግን እንሳሳታለን፡፡

እኛ አባቶቻችን ተከትለን ነው ለመንፈሳዊ በረከት ለመብቃት የምንታገለው፡፡ አባቶቻችንም መከተላችን ሰውን መከተል

አይደሉም እንዴ?፡፡ ስለዚህ ይሄ ነው ሂደቱ እና የሓወርያት ሥራ 14:3 ላይም እንዲህ ይላል‹‹ምልክትና ድንቅ በእጃቸው

ይደረግ ዘንድ እየሰጠ ለጸጋው ቃል ስለ መሰከረው ስለ ጌታ ገልጠው እየተናገሩ ረጅም ወራት ተቀመጡ።›› ይላል፡፡

ምልክትና ድንቅ በእጃቸው ይደረግ ዘንድ እየሰጠ ለጸጋው ቃል፡፡ አዎ በመቁጠርያ እየቀጠቀጡ ክፉውን መናፍስት

አሁን ማናገር መቻላቸው ላንተ ምንህ ነበረ?፡፡ ደስታ አልነበረም? የተደበቀውን ሚስጢር ማውጣት፡፡ አሁን

ስለመቁጠርያ መዘለባበድ ጀምረዋል ብዙዎች፡፡ የመቁጠርያን ኃይል ለቤተ ክርስትያን መስጠቴ ለብዎቹ እንደ ውርደት

ቆጥረውታል፡፡ እንደ ውድቀት ቆጥረውታል፡፡ አረ ባክህ ትቀልዳለህ እንዴ?፡፡ መቁጠርያ እኮ የአባቶቻችን መንፈሳዊ

መሳርያ ነው፡፡ እየቆጦሩበት ለእግዚኦ መሓረነ ክርስቶስ አይደለም ያዙት እኮ በውስጣቸው የተከተለን ክፉ መንፈስ

የሚቀጠቅጡበት ነው፡፡

መቁጠርያ እየሸጠ ትላለህ፡፡ እሺ እንግዲህ ስለ መቁጠርያ እያስተማርኩ እኔ ፆሜን ልደር?፡፡ እስቲ እውነቱን እንደውም

እስቲ ንገረኝ?፡፡ እኔ ስለ መቁጠርያ እያስተማርኩ ሌሎቹ ይሸጣሉ እነዛን አትነካቸውም፡፡ እነዛን ምንህም አይደሉም፡፡

እኔ ግን እያስተማርኩ እያገለገልኩ ያችን መቁጠርያ ቢጠቀሙባት እነሱን እየተጠቀሙበት እኔን የዕለት ጉርሴ እያገኘሁ

የትራንስፖርት፤ የነዳጁን፤ ቤተሰቡን ነገር እያቻቻልኩኝ ቢሄድ ይሄ ነውር ነው?፡፡ ይሄ ነውር ነው አሁን?፡፡ ግን ከኔ

ውጭ ነጋዴዎች ቢሸጡት ግን ምንም አትናገርም፡፡ ምክንያቱም እኔን አስተምራለው ነጋዴዎች ግን ይሸጣሉ፡፡

የሚጠቀመው ሌላ የሚያስተምረው ሌላ፡፡ እና ታድያ ያው እስኪ መቁጠርያ ጥቅሙን ልንገርህ አንደኛ መቁጠርያ

በእግዚአብሔር ስም ሲባረክ አንተ ውስጥ ያለውን ጠላት ይቀጠቅጣል፡፡ ስትመታው ምልክቶች አሉት፡- ማቃጠል፤

መብላት፤ መውረር፤ እንደ ድንጋይ መሆን፤ በሰውነት ውስጥ የሚንቀሳቀስ አይነት ነገር ማየት እነዚህ ምልክቶች

ናቸው፡፡ እነዚህ ምልክቶች ተማራቸው፡፡ ከዛ በኋላ መንፈሱ እንዳለ በዛ ታውቃለህ፡፡ ይሄ ደግሞ ያንተ ስጦታ

አይደለም፡፡ እኔ ያገኘሁስ ስጦታ ነው፡፡ እግዚአብሔር የሰጠን ስጦታ ነው፡፡ አንተ አይደለህም የሰጠሀኝ፡፡ እናንተ

አይደላችሁም የሰጣችሁኝ፡፡ በጊዜና በዘመን ውስጥ እግዚአብሔር በየግዜው የሚገልፀው ነገር አለ ለትውልዱ፡፡

የሚገልጸው ነገር የለም የምትል እንደሆነ ተሳስተሃል፡፡ በየዘመኑ እግዚአብሔር የሚገልጸው ነገር አለ፡፡ አንድ ወቅት ላይ

እኮ በመጽሓፈ ነገስት 3፡11 ላይ እግዚአብሔር በበገና ደርዳሪ በኩል ተናግረዋል፡፡ በገናው የተናገረው ነገር በጣም

በሚደንቅ ግዜ ከዔልሳ አልፎ በገናው እንዲናገር አድርገዋል እግዚአብሔር፡፡ በበገና በኩል መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ይህን ደግሞ ተመልከት እግዚአብሔር በየዘመኑ የሚሰጠው ስጦታ አለ፡፡ ይህ ስጦታ ደግሞ የጸጋው ክፍል አንድ ነው፡፡

ስለዚህ መቁጠርያ መቁጠርያ ትላላችሁ፡፡ እንደዛ ከማለት ኑና ቁጠሩ፡፡ ችግር የለውም፡፡ ስለዚህ ሰዉን ለማሳሳት

አትንደርደሩ፡፡ የተቀባይነታችሁ መንፈስ አታበላሹ፡፡ መንገድ ላይ አታጨላልሙት፡፡ ሰው እንግዲህ አውቀዋል የድሮ

የመታለያና በዓውደነገስቱ ተከልሎ የኖረው ግዜ አልፈዋል፡፡ ስለዚህ መቁጠርያ በሰውነት ውስጥ የሚቀመጡን

መንፈሶች መረበሻያ ነው፡፡ መደብደብ ምናምን ትላለህ፡፡ ሰይጣን ተደብድቦ አይደለም ወደ ምድር የወረደው?፡፡

ስለዚህ ያንን ወደ ምድር የወረደዉን በንፋስ መልክ ተጠግቶ ህይወት የሚያጠቃውን ሲመቱት፤ አብሮ የተወለደ ይሁን

በተንኮለኞች የገባዉም ይሁን እጅ ይሰጣል፡፡ ስለዚህ ህዝቡን ጠይቅ፤ ተቸግረው የተፈወሱትን ጠይቅ፤ ተቸግረው

Page 14: ፀጋ የሌለው ትውልድ ስለ ፀጋ አያውቅም.pdf

ጸጋ የሌለው ትውልድ ስለ ጸጋ አያውቅም፡፡

መልአከ መንክራት ግርማ ወንድሙ በቁጥር 95 በሬድዬ አቢሲንያ ካስተማሩት… ገፅ 14

መንፈሱን የደረሱበትን ጠይቅ የራስህን ዓለምና ወንጌል አትፍጠር፡፡ ስለዚህ መቁጠርያ ከዲያብሎስ መዋግያ ስልት

ውስጥ አንዱ ነው፡፡ ጸጋ የሌለው ትውልድ ስለ ጸጋ አያውቅም፡፡

የጸጋ ሐወርያቶች ግን እንዲህ ብለዋል ‹‹ምልክትና ድንቅ በእጃቸው ይደረግ ዘንድ እየሰጠ ለጸጋው ቃል ስለ መሰከረው

ስለ ጌታ ገልጠው እየተናገሩ ረጅም ወራት ተቀመጡ።››፡፡ የሐወርያት ሥራ 14:26 ላይ ‹‹ከዚያም ስለ ፈጸሙት ሥራ

ለእግዚአብሔር ጸጋ አደራ ወደ ተሰጡበት ወደ አንጾኪያ በመርከብ ሄዱ።›› ይላል ሐወርያት አየህ፡፡ የሐወርያት ሥራ

15:11 ላይም ‹‹ነገር ግን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ እንደ እነርሱ ደግሞ እንድን ዘንድ እናምናለን።›› ይላል በኢየሱስ

ክርስቶስ ጸጋ እንድን ዘንድ፡፡ የሐወርያት ሥራ 15:40 ‹‹ጳውሎስ ግን ሲላስን መረጠ፥ ወንድሞችም ለእግዚአብሔር ጸጋ

አደራ ከሰጡት በኋላ ወጣ›› ይላል፡፡ እስቲ ለኔ ጸልዩልኝ፡፡ ለእግዚአብሔር አደራ ጸጋ ለምን አትሰጡኝም?፡፡ ለምን

አትጸልዩልኝም?፡፡ ጀነራሎች ወታደሮቻቸውን ሲሰብኩ እነዲህ ብለው ይሰብኩዋቸዋል፡፡ ነገ ወደ እኛ ማዕረግ

የምትደርሱት አለምክንያት አይደለም፡፡ ታታሪነት፤ እውነተኝነት፤ ታዛዥነት፤ አክባሪነት ይህ ሁሉ አንድ ራሱን የቻለ

ወታደራዊ የሞያ ብቃት ነው፡፡ ከዛ በኋላ ወደ እኛ ማዕረግ ትደርሳላችሁ፡፡ ጀነራል ትሆናላችሁ፤ ኮነሬል ትሆናላችሁ፤

ሻለቃ ትሆናላችሁ፤ ሻምበል ትሆናላችሁ ይሏቸዋል፡፡ እሺ ብጹአን አባቶቻችን ወደ እኛ ማዕረግ የምትደርሱት ይህን

ስታደርጉ ነው፤ ይህን ስትጸልዩ ነው ይህንን ስታገኙ ጸጋን ይሰጣቹሀል፡፡ ወደኛ ማዕረግ ትደርሳላችሁ፡፡ ቅዳሴው ላይ

ተመልከቱ ወደኛ ማዕረግ ይደርስ ዘንድ ይላል፡፡ ቄሱ ዲያቆኑን ይደርስ ዘንድ ብሎ ከእግዚአብሔር መንፈስንና ጸጋን

ይለምናል፡፡ ሲደረስ ደግሞ ይሄው እንደዚህ መከራ ነው፡፡ በጸጋ ውስጥ ስንኖር እንደምንም ብለን ተፍጨርጭረን

ከክፋት ትውልድ ማምለጥ ስንጀምር ድፍን በማድረግና መንፈሳዊ ሞራላችንን ለማድቀቅ በየቦታው መንጫጫት

እንጀምራለን፡፡ ልክ ነው አውሬ ባለፈበት ቦታ ላይ ውሾች ይጮሃሉ፡፡ ስለዚህ ችግር ነው፡፡

የሐወርያት ሥራ 15:40 ‹‹ጳውሎስ ግን ሲላስን መረጠ፥ ወንድሞችም ለእግዚአብሔር ጸጋ አደራ ከሰጡት በኋላ ወጣ››

ይላል፡፡ አደራ የሰጡት ለእግዚአብሔር ጸጋ ነው፡፡ አስቲ ለኔም ጸልይልኝ ጸጋ እንዲሰጠኝ፡፡ እስቲ አሁን የምሄድበት

ስህተት ከሆነ ና እና ምከረኝ፡፡ እስቲ የምትሄድበት ስሕተት ነው ለምን አትለኝም?፡፡ ዙርያው ማጓራቱ ምን

አመጣው?፡፡ ዙርያው መደንፋቱ መን አመጣው?፡፡ እኔ ጋር መምጣት ነው፡፡ ክርስቶስ ለአንድ ለጠፋው ለአዳም

አይደለም የመጣው?፡፡ አንተም ለኔ ለጠፋሁት ናና ለኔ ንገረኝ፡፡ የቱ ጋር ነው የጠፋሁት?፡፡ እውነተኞች ከሆንንን

በእውነት ቦታ መቆም አለብን፡፡ ዙርያውን እንደ ዛር ማጓራት የለብንም፡፡ ዛር ነው ዙርያውን የሚያጓራው፡፡ ውቃቢ

ነው ዙርያ ያጓራና በኋላ ሲጫጫስለት ይበርድለታል፡፡ እና እንደዚህ አይነት አካሄድ የእውነተኛ ሰዎች ቋንቋና ንግግር

አይደለም፡፡ ጸጋ የማያውቅ ትውልድ ስለ ጸጋ ማውራት አይችልም፡፡

መጀመርያ ጸጋ ከውስጥ ተነስቶ ወደ ውጭ የሚወጣ ነው፡፡ በጨላለመ መንገድ ውስጥ የሚያልፍ አይደለም፡፡ ጸጋ

ጨለምተኝነት አይደለም፡፡ በአጠቃላይ አነጋገር ጸጋ የሰው ህይወት ውስጥ የሚገፅ ነው፡፡ የሰውን ችግር የሚካፈል

ነው፤ ሰውን ብሶት፤ የሰውን መራራ ለቅሶ፤ የሰውን መራራ ህይወት የሚለውጥ ነው ጸጋ አየህ፡፡ ጸጋ እንደዛ ነው፡፡

የሰው ስቃይ ውስጥ የሚገባ ነው ጸጋ፡፡ የሰው ሽታ ውስጥ፤ የሰው ህይወት ውግያ ውስጥ የሚገባ ነው ጸጋ፡፡ ሲሸተን

የሚውለው እኮ የሰው ስቃይ ነው፡፡ ብዙ ሺ ሰው መጥሮ ሽቶ አይደለም የሚሸተን፡፡ የሚሸተን መከራ ነው፡፡ እዛ

ውስጥ ነው የምንውለው፡፡ የሰው ስቃይ ውስጥ ነው የምንውለው፡፡ ያጨበጨበልን ሁሉ የወደደን አይምሰልህ ደግሞ፡፡

Page 15: ፀጋ የሌለው ትውልድ ስለ ፀጋ አያውቅም.pdf

ጸጋ የሌለው ትውልድ ስለ ጸጋ አያውቅም፡፡

መልአከ መንክራት ግርማ ወንድሙ በቁጥር 95 በሬድዬ አቢሲንያ ካስተማሩት… ገፅ 15

ስለዚህ ያጨበጨበ ሁሉ ወዳጅ አይደለም፡፡ ያጨበጨበው ሁሉ ያፈቀረ አይምሰልህ፡፡ እንደውም የአገራችን ህዝብ

ሲያጨበጭብ እግር ነው የሚቆርጠው፡፡ ሲያይም ቡዳ ነው የሚሆነው፡፡ ይበላሃል፡፡ አንዳንዱ ተበልተዋል እንዳይሆን

ስለ ጸጋ ለመለየት አቅም ያጣነው፡፡ አጨብጭበውልን የበሉልን ብዙዎች ናቸው፡፡ የሰው ዓይን ዛፍ ያደርቃል ሲሉ

አልሰማችሁም?፡፡ ስለዚህ ጸጋ በራሱ የሚገለጥ እንጂ በዋሻ የሚደበቅ አይደለም፡፡ ጸጋ በሰው ህይወት ውስጥ ለማዳን

የሚዘጋጅ፤ ማዳንን ኃይል የሚገልጥ እንጂ፤ የተንኮልን ክፉ ነገር የሚገልጥ እንጂ የሚደብቅ አይደለም፡፡

የሐወርያት ሥራ 18:27 ‹‹እርሱም ወደ አካይያ ማለፍ በፈቀደ ጊዜ፥ ወንድሞቹ አፅናኑት›› ይላል፡፡ እስቲ እኔን ያፅናናህ

ሰባኪ ናና ወይም እስቲ በሚድያ ቅረብና መምህር ግርማ አፅናንቸዋለውና ብለህ ተናገርና እስቲ፡፡ መክሬዋለው በልና

ተናገር፡፡ ከዚህ ከያዘው ክፉ ተግባር ይመለስ ዘንድ መክሬዋለው ያልክ ሰባኪ 100,000 ብር እሸልማለው፡፡ እኔ ጋር

መጥተህ የመከርከኝ ሰባኪ፤ እኔ ጋር መጥተህ የመከርከኝ አባት 100,000 ብር እኔ እሸልማለው፡፡ እንዳውም በዚህ

ሰሙን ውስጥ እሸልማለው፡፡ ምን ብለህ የመከርከኝ አባት አለህ?፡፡ ምን ብላችሁ የገሰፃችሁን አባቶች አላችሁ?፡፡ ይሄ

ስራስ ጥሩ አይደለም ያላችሁ አባቶች አላችሁ ወይ?፡፡ ይሄ ስራስ ጥሩ አይደለም ያላችሁ ሰባኪዎች እኔ ጋር መጥታችሁ

የነገራችሁኝ አላችሁ ወይ ነው?፡፡ ጸጋ የማያውቅ ስለ ጸጋ አያውቅም፡፡ ‹‹ወንድሞቹ አጸናኑት›› ይለናል የሐወርያት ሥራ

18:27፡፡ እኔን ያፅናናችሁኝ የት ጋር ነው ያላችሁ?፡፡ በርቱ ያላችሁ አባቶች የት ጋር ናችሁ?፡፡ ‹‹ይቀበሉትም ዘንድ ወደ

ደቀ መዛሙርት ጻፉለት፤ በደረሰም ጊዜ አምነው የነበሩትን በጸጋ እጅግ ይጠቅማቸው ነበር፤›› ይላል፡፡ ጸጋ ይጠቅማል

አይህ፡፡ የጸጋ ስጦታ ሌላውን ይጠቅማል፡፡ ሌላውን የሚጠቅም ህይወት መኖር አለበት፡፡ የነቀፌታ ትርጉሙም አዝሎ

መሮጥ ሳይሆን የጸጋ ኃይል መግለጫ እንዲሆን ማበረታታትን ይጠይቃል፡፡ አቅምና ጉልበታችንን ለጸጋ ድጋፍ መሆን

አለበት፡፡ ቤተ ክርስትያናችን ይህንን መንገድ የሚከተሉ ልጆች ከሌሏት ብዙ ነው አደጋው፡፡ ዙርያው ነው አደጋው

የመናፍቁ ዓለም ሌላ ነው፤ በግራ በኩል ያለው ኃይል ሌላ አደጋ ነው፤ የማይታወቁ የኢሉሚናቲ ሌላ አደጋ ነው፤

የቴክኖሎጂ ባህሪ እና ጠባይ ተከትለው ህዝቡን የሚለውጥ የክፉ መንፈስ ዓለም ሌላ አደጋ ነው፡፡ ስለዚህ ዙርውን

ያለው ነገር ለማገናዘብ ያንተ ተንኮልም ሌላ አደጋ ነው፤ የብዙ ሰዎች ተንኮል ራሱ ሌላ አደጋ ነው፡፡ ስለዚህ በእውነት

‹‹በጸጋ እጅግ ይጠቅማቸው ነበር›› ይላል፡፡ እነ ቅዱስ ጳውሎስ፡፡

የሐወርያት ሥራ 20:24 ‹‹ነገር ግን ሩጫዬንና ከጌታ ከኢየሱስ የተቀበልሁትን አገልግሎት እርሱም የእግዚአብሔርን ጸጋ

ወንጌልን መመስከር እፈጽም ዘንድ ነፍሴን በእኔ ዘንድ እንደማትከብር እንደ ከንቱ ነገር እቆጥራለሁ።›› ይላል፡፡ አየህ

ጸጋ ደግሞ የሚመጣ ራስህን ስትክድ ነው፡፡ ለወንጌል ራስህን ስትክድ፤ ለወንጌል ለወንድምህ በጎ ስታስብ፤ ለወንጌል

ለሌላው በረከት የመሆን ዕድልን ስትይዝ፤ ወንጌልን በተግባር ስታውለው፤ የተራበው ጎን ሰትቀመጥ፤ የተጠማው ጎን

ስትኖር፤ በመንፈስ የደቀቀውን ስታበረታ፤ ክፉውን ጠላት ስታስወግድለት፤ ፤ ለጸሎትና ለአምልኮት ግዜ ስትሰጥ

ይሄውልህ ራስ መካድ ነው ይሄ፡፡ ሐወርያት ይህንን መንገድ ሄደዋል፡፡

‹‹አሁንም ለእግዚአብሔርና ያንጻችሁ ዘንድ በቅዱሳንም ሁሉ መካከል ርስትን ይሰጣችሁ ዘንድ ለሚችል ለጸጋው ቃል

አደራ ሰጥቻችኋለሁ።›› ይላል ደግሞ ይሄውልህ ቅዱስ ጳውሎስ በሐወርያት ሥራ 20:32 ላይ፡፡ አደራው ለጸጋው ቃል

መስጠት ነው አየህ፡፡ የጸጋው ቃል ኃይልና ብርታት እንዲሆን ነው፡፡ እኔም የምሰጠው ለጸጋው ቃል የእግዚአብሔር

ልጅነትን ነው፡፡ ክርስቶስን ተከተሉ እኔን ተከተሉ አይደለም፡፡ ስጋ የክርሰቶስ ውሰዱ የክርሰቶስን ደም ተቀበሉ ይሄ

Page 16: ፀጋ የሌለው ትውልድ ስለ ፀጋ አያውቅም.pdf

ጸጋ የሌለው ትውልድ ስለ ጸጋ አያውቅም፡፡

መልአከ መንክራት ግርማ ወንድሙ በቁጥር 95 በሬድዬ አቢሲንያ ካስተማሩት… ገፅ 16

ላንተ ሞት ከሆነ ተሳስተሃል ይሄ ህይወት ነው፡፡ የምንኖረው ለእግዚአብሔር የጸጋው ቃል ነው፡፡ ያ የጸጋ ከእመቤታችን

ከቅድሰት ድንግል ማርያም ህያው የሆነ ህልውናን ለሰው ልጆች እንዲሰጥንም በኢየሱስ ክርስቶስ ተገለጠ፡፡ ገለጠው

አንድ ልጁን የእግዚአብሔር አብን ክብር ተረከው አለ እኪ በቃ ምን አደከመህ፡፡ ስለዚህ ወገኖቼ እናንተ የለመናችሁት

በሙሉ ወንጌልን የተከተላችሁ ቃሉን የተማራችሁ ለጸጋው ቃል አደራው ሰጥቻቹሃለው በቃ አሁን፡፡ ይሄው ነው በቃ

ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ፡፡ የመቁጠርያ ውግያን ያላወቁ ሰዎች እንዳደናብራችሁ እናንተ በርቱ ለልጆቻችሁ

አስተምሩ ልጆቻችሁ ይሄን መንፈሳዊ ኃይል እንዲያውቁ አድርጉ፡፡ ይሄ ዝም ብለው የሚዘላብዱት የዚህ የመንፈሳዊ

በረከት ተስፋ በጸጋ ያልተቀበሉ ናቸው፡፡ በጸጋ ያልተቀበሉ ደግሞ መቀላመድ ዋናው ስራቸው ነው፡፡ ስለዚህ

እውነተኛው ነገር ቢኖረ ፊት ለፊት መጋጠም ነው፡፡ ፊት ለፊት መተየየት ነው፡፡ ይሄ እኮ ነው እውነተኞች ፊት ለፊት

ነው የሚመጡት፡፡ ፊት ለፊት ሩቅ ደግሞ ሳይሆን እዚህ የኤረር ሥላሴና ጀሞ ኡራዔል ነው ያለነው፡፡ ፊት ለፊት ነው

ሌላ ነገር የለም፡፡ ጦርነት እኮ ፊት ለፊት ነው፡፡ ውጊያም ፊት ለፊት ነው፡፡ ጀነራል የሚመራው ወታደሮቹም በጠላቶች

ፊት ለፊት ነው፡፡ ከዛ ውጭ አይደለም፡፡ ጓዳ ውስጥ የተደበቀ ወታደር ድል አያደርግም፡፡ ጓዳ ውስጥ ያለ ወታደር

አሸንፎ አያውቅም፡፡ ስለዚህ በጓዳ ውስጥ የምታወሩትን ነገር እየቆማችሁ ፊት ለፊት ኑ እውነትንና ጸጋን የመለየት

ኃይል የዛን ግዜ ይታወቃል፡፡

ስለዚህ በሮሜ 3፡24 እንዲህ ይላል ‹‹በኢየሱስ ክርስቶስም በሆነው ቤዛነት በኩል እንዲያው በጸጋው ይጸድቃሉ።››

ይላል ደግሞ እዚህ ጋር፡፡ በእግዚአብሔር ስጦታ በኩል ማለት ነው፡፡ ሓጥያተኞች ሆነን ንስሃ ስንገባ አድካሚ ባሆነ

መንገድ በክርስቶስ ስጋና ደም እንጸድቃለን በቃ ሓጥያትን ትተን ዓመፃን ትተን፡፡ እንዲያውም በጸጋው ይጸድቃሉ አለ

በቃ። ይህ ማለት ዝም ብሎ እንደዚህ መናፍቁ አይደለም፡፡ በክርስቶስ ስጋና ደም ሓጥያታችን ይሰረይልናል፡፡

የሚያስተሰርይልን አባት አንተ ሳትሆን እግዚአብሔር ነው አየህ፡፡ ሓጥያታችን በአንተ ተይዞ ቢሆን ስንት ነገር በወጣ

ነበር፤ ስንት ነገር ባወራን ነበር፡፡ የተያዘው በእግዚአብሔር ዘንድ ነው በክርስቶስ ስጋና ደም ያጥብልናል፡፡

‹‹እንዲያውም በጸጋው ይጸድቃሉ›› አለ በቃ። ይሄ ነው በክርስቶስ ስጋና ስጦታ በኩል ማሸነፍ አለ፡፡ ዕድሜ ልካችንን

ከክፉ ትውልድ ጋር ከክፉ ባህርያችን ጋር ስንታገል እንኖራለን፡፡ ለእውነት መታገል ደግሞ አያሳፍርም፡፡

ሌላ በሮሜ 4፡4 ‹‹ለሚሠራ ደመወዝ እንደ ዕዳ ነው እንጂ እንደ ጸጋ አይቈጠርለትም›› ይላል፡፡ ደመወዝም ያስፈልጋል

አየህ፡፡ ለሚሠራ ደመወዝ እንደ ዕዳ ነው እንጂ እንደ ጸጋ አይቈጠርለትም፡፡ ይሄኛው የመኖር ሕግ ነው፡፡ እዚህ ጋር ያለ ጸጋ

ግን ለሌሎች የሚተርፍ ሕግ ነው፡፡ ለሌሎችን የሚበቃ፤ ሌሎችን ሕግ ነው፡፡ እንግዲህ ስለ ጸጋ የተማርነው በዚሁ ይበቃል

በሚቀጥለው ደግሞ ስለ ኃይል እንማራለን፡፡ የእግዚአብሔር ኃይል ምን እንደሚሰራ፤ የእግዚአብሔር ኃይል ለማን

እንደተሰጠ?፤ የእግዚአብሔር ኃይል ምን እንደሚያከናውን፡፡ ስለዚህ ትውልዳችንን በጸጋ መቀየስ እንጂ በተንኮል መቀየስ

እና በቅራኔ መቀየስ፤ በምቀኝነት መቀየስ አስፈላጊ አይደለም፡፡ ይሄ ዝም ብሎ አጨብጫቢዎችን ፈልገን የምናደርገው

ተግባር ነው፡፡ በጸጋ ውሰጥ ማለፍ የክርስትያኖች ውበት ነው፡፡ የክርስትያኖች ስጦታ ነው፡፡ እና በጸጋ ውስጥ እንድናልፍ

ኢየሱስ ክርስቶስ ለጸጋ እና ለእውነት ነው የተገለጠው፡፡ በአካለ ስጋም የተገኘው ይህንን በህይወታችን ውስጥ ሊያኖር ነው፡፡

ስለዚህ በክርስቶስ ስጋና ደም ታትመን፤ የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ተጠብቀን፤ በኃይማኖት ጸንተን፤ የዲያብሎሰን ሰራዊት

አራግፈን ጥለን፤ የእግዚአብሔር ልጆች እንድንባል እግዚአብሔር አምላካችን ያብቃን አሜን፡፡