24
ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ ወደ ሀገራችን የገባው የግብፅ ሕዝብ ዲፕሎማቲክ ልዑክ ለአራት ተከታታይ ቀናት ከጠቅላይ ሚ/ር መለስ ዜናዊ ጀምሮ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርን፣ የተለያዩ መንግስታዊ ተቋማት ኃላፊዎችንና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ የሆኑትን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስን ሲያወያዩ ቆይተው ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡ የተልዕኳቸው ዓላማም የተለያዩ አስተያየቶች እየቀረቡበት ይገኛሉ፡፡ ሚስተር ሙስጠፋ አልጊንዲ በተባሉት ግብፃዊ የተመራው የልዑካን ቡድን፣ ‹‹በግድብ ግንባታው ኢትዮጵያ እንድትጠቀም እንፈልጋለን፡፡ ሆኖም፣ ግብፅን እንደማይጎዳ በባለሙያዎች ማስጠናት አለብን›› የሚል ጥያቄውን አቅርቧል፡ ፡ ከዚህ በተጨማሪ፣ የአባይ ተፋሰስ ሀገራትን የትብብር በኢትዮጵያ የዓለም የፕሬስ ነፃነት ቀን አከባበር ሳንሱር መደረጉን ሲ.ፒ.ጄ ገለፀ ባለፈው ማክሰኞ የፕሬስ ነፃነት ቀንን አስመልክቶ በዩኔስኮ ስፖንሰር አድራጊነት በኢትዮጵያ የተካሄደው ዝግጅት ሳንሱር መደረጉን ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች የሆነው ሲ.ፒ.ጄ ገለፀ፡፡ በአከባበር ዝግጅቱ ቀድሞ ከተያዘው መርሐ-ግብር በተቃራኒ የመንግስት ባለሥልጣናትና ለመንግስት ቀረቤታ ያላቸው ጋዜጠኞች ብቻ ጥናታዊ ጽሑፎችንና ንግግሮችን እንዲያቀርቡ መደረጉን በማስታወስ፣ ‹‹በትክክለኛው መርሐ-ግብር ላይ ከተቀመጠው በተቃራኒ፣ የአውራምባ ታይምስ ማኔጂንግ ኤዲተር ዳዊት ከበደ ከአወያይነት እንዲነሳና የሪፖርተር ጋዜጣ ዋና ሥራ አስኪያጅ የሆነው አማረ አረጋዊ ደግሞ ሊያቀርብ ያዘጋጀውን የጥናት ወረቀት ርዕስ እንዲቀይር ተደርጓል›› ያለው ሲ.ፒ.ጄ፣ ለዝግጅቱ ሳንሱር መደረግ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤትን ተጠያቂ አድርጓል፡፡ ሲ.ፒ.ጄ ክስተቱን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ እንዳስነበበው፣ የቡድኑ የአፍሪካ ተጠሪ የሆነው ሞሐመድ ኪየታ፣ ‹‹በዓለም የፕሬስ ነፃነት ቀን የተፈፀመውን የዝግጅት ሳንሱር የተባበሩት መንግስታት ድርጅት መቼም ቢሆን ሊረሳው ካለመቻሉ በላይ፣ መንግስት ዝግጅቱን በኃይል በማስቀየር ከፕሬስ ነፃነት ጋር በተያያዘ ለወትሮም ያለውን መጥፎ ገፅታ አጉልቶታል›› ብሏል፡፡ አከባበሩ ከመካሄዱ ቀደም ብሎ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት አዘጋጆቹ በታዘዙት መሠረት የመርሐ-ግብር ለውጥ የማያደርጉ ከሆነ፣ ዝግጅቱን በኃይል እንደሚያግድ በመግለፅ ማስፈራራቱን የገለፀው ሲ.ፒ.ጄ፣ ‹‹የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ሽመልስ ከማል፣ የብሮድካስት ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ደስታ ተስፋው እና የብሔራዊ ጋዜጠኞች ኅብረት ሊቀ-መንበር አቶ አንተነህ አብርሐም የሳንሱሩ ዋና ተዋናዮች ናቸው›› ሲል ወቀሳ ሰንዝሯል፡፡ አግባብነት የሌላቸው የቡና ኬላዎች ወደ ገፅ 19 ዞሯል ገፅ 5 ገፅ 3 ገፅ 9 በውስጥ ገጾች ኢሕአዴግ የኢትዮጵያን ሕዝብ በሶስት መደብ ከፍሎታል፡፡ መንግስቱ ኃ/ማርያምን በገዳይነቱ እናውቀዋለን፤ በኢትዮጵያ አንድነት ግን አይታማም፡፡ ኢፈርት ከ15 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል አለው፤ ለትግራይ ማኅበራዊ ልማት ያበረከተው ግን ከ30 ሚሊዮን ብር አይበልጥም፡፡ አቶ አስገደ ገ/ሥላሴ (የህወሃት መስራች እና የአረና ትግራይ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል) ‹‹የኤርትራን መንግስት ማስወገድ የባሕር በራችንን የማያስመልስ ከሆነ ዓላማ የለሽነት ነው›› የቢን ላደን ፍፃሜና የኦባማ አዲስ የስኬት ምዕራፍ እያልጎመጎምን የምናስታምመው ሕመም ፕሬስ እና ነፃነቱን ካብ ለካብ ያስተያየው የፕሬስ ነፃነት ቀን ገፅ 4 አብዲሳ አጋ እና የማይዘነጋ ውለታው ከአዲስ አበባ ጓዳዎች አንዱ አማኑኤል ሆስፒታል አሳሳቢው የሕፃናት ሞት ‹‹ግብፃውያኑ መንግስት እስከሚመሰርቱ ጊዜ ብንሰጣቸው ብዙ ለውጥ አያመጣም›› አምባሳደር ዲና ሙፍቲ /የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ/ - ከልዑካኑ ሶስቱ ለግብፅ ፕሬዝዳንትነት ይወዳደራሉ ገፅ 16

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 166 ቅዳሜ ሚያዚያ 29 2003 ኢሕአዴግ … · ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ አውራምባ ታይምስ 4ኛ

  • Upload
    others

  • View
    19

  • Download
    0

Embed Size (px)

Citation preview

Page 1: አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 166 ቅዳሜ ሚያዚያ 29 2003 ኢሕአዴግ … · ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ አውራምባ ታይምስ 4ኛ

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 166 ቅዳሜ ሚያዚያ 29 2003

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ ወደ ሀገራችን የገባው የግብፅ ሕዝብ ዲፕሎማቲክ ልዑክ ለአራት ተከታታይ ቀናት ከጠቅላይ ሚ/ር መለስ ዜናዊ ጀምሮ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርን፣ የተለያዩ መንግስታዊ ተቋማት ኃላፊዎችንና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ የሆኑትን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስን ሲያወያዩ ቆይተው ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡

የተልዕኳቸው ዓላማም የተለያዩ አስተያየቶች እየቀረቡበት ይገኛሉ፡፡ ሚስተር ሙስጠፋ አልጊንዲ በተባሉት ግብፃዊ የተመራው የልዑካን ቡድን፣ ‹‹በግድብ ግንባታው ኢትዮጵያ እንድትጠቀም እንፈልጋለን፡፡ ሆኖም፣ ግብፅን እንደማይጎዳ በባለሙያዎች ማስጠናት አለብን›› የሚል ጥያቄውን አቅርቧል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ፣ የአባይ ተፋሰስ ሀገራትን የትብብር

በኢትዮጵያ የዓለም የፕሬስ

ነፃነት ቀን አከባበር ሳንሱር

መደረጉን ሲ.ፒ.ጄ ገለፀባለፈው ማክሰኞ የፕሬስ ነፃነት

ቀንን አስመልክቶ በዩኔስኮ ስፖንሰር አድራጊነት በኢትዮጵያ የተካሄደው ዝግጅት ሳንሱር መደረጉን ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች የሆነው ሲ.ፒ.ጄ ገለፀ፡፡

በአከባበር ዝግጅቱ ቀድሞ ከተያዘው መርሐ-ግብር በተቃራኒ የመንግስት ባለሥልጣናትና ለመንግስት ቀረቤታ ያላቸው ጋዜጠኞች ብቻ ጥናታዊ ጽሑፎችንና ንግግሮችን እንዲያቀርቡ መደረጉን በማስታወስ፣ ‹‹በትክክለኛው መርሐ-ግብር ላይ ከተቀመጠው በተቃራኒ፣ የአውራምባ ታይምስ ማኔጂንግ ኤዲተር ዳዊት ከበደ ከአወያይነት እንዲነሳና የሪፖርተር ጋዜጣ ዋና ሥራ አስኪያጅ የሆነው አማረ አረጋዊ ደግሞ ሊያቀርብ ያዘጋጀውን የጥናት ወረቀት ርዕስ እንዲቀይር ተደርጓል›› ያለው ሲ.ፒ.ጄ፣ ለዝግጅቱ ሳንሱር መደረግ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤትን ተጠያቂ አድርጓል፡፡

ሲ.ፒ.ጄ ክስተቱን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ እንዳስነበበው፣ የቡድኑ የአፍሪካ ተጠሪ የሆነው ሞሐመድ ኪየታ፣ ‹‹በዓለም የፕሬስ ነፃነት ቀን የተፈፀመውን የዝግጅት ሳንሱር የተባበሩት መንግስታት ድርጅት መቼም ቢሆን ሊረሳው ካለመቻሉ በላይ፣ መንግስት ዝግጅቱን በኃይል በማስቀየር ከፕሬስ ነፃነት ጋር በተያያዘ ለወትሮም ያለውን መጥፎ ገፅታ አጉልቶታል›› ብሏል፡፡

አከባበሩ ከመካሄዱ ቀደም ብሎ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት አዘጋጆቹ በታዘዙት መሠረት የመርሐ-ግብር ለውጥ የማያደርጉ ከሆነ፣ ዝግጅቱን በኃይል እንደሚያግድ በመግለፅ ማስፈራራቱን የገለፀው ሲ.ፒ.ጄ፣ ‹‹የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ሽመልስ ከማል፣ የብሮድካስት ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ደስታ ተስፋው እና የብሔራዊ ጋዜጠኞች ኅብረት ሊቀ-መንበር አቶ አንተነህ አብርሐም የሳንሱሩ ዋና ተዋናዮች ናቸው›› ሲል ወቀሳ ሰንዝሯል፡፡

አግባብነት የሌላቸው የቡና ኬላዎች

ወደ ገፅ 19 ዞሯል

ገፅ 5 ገፅ 3 ገፅ 9

በውስጥ ገጾች

ኢሕአዴግ የኢትዮጵያን ሕዝብ በሶስት መደብ ከፍሎታል፡፡

መንግስቱ ኃ/ማርያምን በገዳይነቱ እናውቀዋለን፤ በኢትዮጵያ አንድነት ግን አይታማም፡፡

ኢፈርት ከ15 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል አለው፤ ለትግራይ ማኅበራዊ ልማት ያበረከተው ግን ከ30 ሚሊዮን ብር አይበልጥም፡፡

አቶ አስገደ ገ/ሥላሴ (የህወሃት መስራች እና የአረና ትግራይ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል)‹‹የኤርትራን መንግስት ማስወገድ የባሕር በራችንን የማያስመልስ ከሆነ ዓላማ የለሽነት ነው››

የቢን ላደን ፍፃሜና

የኦባማ አዲስ የስኬት ምዕራፍ

እያልጎመጎምን

የምናስታምመው ሕመም

ፕሬስ እና ነፃነቱን ካብ ለካብ ያስተያየው

የፕሬስ ነፃነት ቀን

ገፅ 4

አብዲሳ አጋ እናየማይዘነጋ ውለታው

ከአዲስ አበባ ጓዳዎች አንዱአማኑኤል ሆስፒታል

አሳሳቢው የሕፃናት ሞት

‹‹ግብፃውያኑ መንግስት እስከሚመሰርቱ ጊዜ ብንሰጣቸው ብዙ ለውጥ አያመጣም››

አምባሳደር ዲና ሙፍቲ /የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ/

- ከልዑካኑ ሶስቱ ለግብፅ ፕሬዝዳንትነት ይወዳደራሉ

ገፅ 16

Page 2: አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 166 ቅዳሜ ሚያዚያ 29 2003 ኢሕአዴግ … · ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ አውራምባ ታይምስ 4ኛ

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 166 ቅዳሜ ሚያዚያ 29 2003

T’@Í=”Ó ›?Ç=}` Ç©ƒ ŸuÅ

ª“ ›²ÒÏõì<U TV

(›É^h ¾ካ ¡/Ÿ kuK? 03/04 ¾u?.l 1540)

U/ª“ ›²ÒЋ Ó³¨< KÑW¨<wgƒ �Â

Ÿõ}— ›²ÒÏ ›u?M ¯KT¾G<

›²ÒϨc”cÑÉ Ñ/Ÿ=Ç”

Ÿõ}— ]þ`}a‹

›?MÁe Ñw\c<^õ›?M Ó`T

ኮፒ ኤዲተርƒ°Óeƒ ¨”ÉS<

¯UÅ™‹ ታዲዎስ ጌታሁን cKV” VÑeSpÅe õeN

iÁß“ Te�¨mÁ }hK cÃñ}hK ¨ÇÏ0911629281

¢Uú¨<}` îG<õ SpÅe õeN

Ó^ò¡e ›?Ç=}` ’w¿ Seõ”

(0911 18 09 33)E-Mail:[email protected]

¾´Óσ ¡õK< eM¡eM¡:- ®911 62 92 78 ®911 62 92 82 0911 15 62 48

þ.X.l [email protected]://www.awramba.com

›d�T>¨<ብሉ ኤርዝ ጀነራል ቢዝነስ

ኃላ/የተ/የግል/ማህበር

ር ዕ ሰ አ ንቀፅ

ማን ምን አ ለ

2

‹‹...ዋነኛው አሳሳቢ

ጉዳይ በሕገመንግስቱ እና በሌሎች

የሚዲያ ሕጎች፣ ፕሬስ የተለያየ

መረጃ የመስጠት መብትና ግዴታ

አለበት፤ ሕዝብም መረጃ የማግኘት

መብት አለው ቢባልም፣ ጋዜጦችና

መጽሔቶች አቅም አጥተው ከተዘጉ

በሕገመንግስቱ የተደነገገው መብት

ተግባራዊ ሳይሆን ይቀራል፡፡ አማራጭ

መረጃዎችና የተለያዩ አስተሳሰቦች

በሕብረተሰብ የማንሸራሸር ሁኔታ

አይኖርም፡፡ . . . ››

የፕሬስ ነፃነት ማበብን

የሚፈልግና ጥቃቶቹ የሚያሳስበው

ማንኛውም ግለሰብ፣ ከላይ የሰፈሩትን

ቃላት ሲያነብ በእጅጉ መብሰልሰሉና

መጨነቁ አይቀርም፡፡ ምክንያቱም

‹‹ፕሬስ የተለያየ መረጃ የመስጠት

መብትና ግዴታ አለበት፡፡ ሕዝብም

መረጃ የማግኘት መብት አለው››፡

፡ . . . ይሁንና ሕገመንግስቱ ይህን

የማይገስስ መብት አስመልክቶ

ያስቀመጣቸው ድንጋጌዎች ተግባራዊ

እንዳይሆኑ ትልቅ ጋሬጣ ተጋርጦ

እያየን ነው፡፡ አዎን! ያሳስባል፤

ያስጨንቃል፡፡

ከላይ ያሰፈርነውን ሀሳብ

ቀንጨብ አድርገን የወሰድነው

የጋዜጣና መጽሔት አሳታሚዎች

አስተባባሪ ኮሚቴ፣ ብርሃንና ሰላም

ማተሚያ ድርጅት ያደረገውን ከፍተኛ

የዋጋ ጭማሪ ተከትሎ፣ ሚያዚያ 10

ቀን 2003 ዓ.ም ለአሳታሚ ድርጅቶች

ካሰራጨው የአቋም መግለጫ ደብዳቤ

ላይ ነው፡፡

እጅግ ፈታኝ በሆነ የፕሬስ

ነፃነት ምህዳር ውስጥ ያሉትን

ውስብስብ ችግሮች እንደምንም

ተቋቁመው ለመንቀሳቀስ ጥረት

በማድረግ ላይ ለነበሩ የግል ጋዜጦችና

መጽሔቶች፣ በድንገት 45 በመቶ

ያህል ጭማሪ ማድረግ በእርግጥም

ሕገመንግሥቱ ለፕሬስ ነፃነት

መረጋገጥና መጎልበት የደነገገው

መብት ተግባራዊ ሳይሆን እንዲቀር

የሚያደርግ ነው፡፡ በአንድ በኩል

በሕገመንግሥት የተረጋገጠ መብት

ወይም ስኬት፣ በሌላ በኩል ደግሞ ይህ

መብት ተፈፃሚ እንዳይሆን ሥልታዊ

ጋሬጣዎችን መደርደር የ21ኛዋ ክ/

ዘመን ኢትዮጵያ ሚዲያ ነጸብራቅ

ሆነዋል፡፡ ሊገሰስ የማይገባውን የፕሬስ

ነፃነት ይፈልቁታል፣ ይፈትኑታል!

የዘንድሮው የዓለም የፕሬስ

ነፃነት ቀን መሪ ቃልም ይህንኑ እውነታ

የሚያንፀባርቅ ነበር፡፡ ‹‹የ21ኛው

መቶ ክ/ዘመን ሚዲያ፡- አዲስ

ስኬቶችና አዲስ ጋሬጣዎች›› የሚል

ሲሆን፣ በያዝነው ሳምንት በመላው

ዓለም በተለያዩ ሥርዓቶች ተከብሮ

ውሏል፡፡ በአገራችን የተከበረበት

መንገድ ግን ፕሬሱ እውነትም ምን

ያህል ጋሬጣዎች እንደተደቀኑበት

የሚያመለክትና ቀጣዩን ሂደት ደግሞ

በስጋት እንድንጠብቅ የሚያደርገን

ሆኖ አልፏል፡፡ ይህን በሥልታዊ

አፈናዎች የተሞላ አሳሳቢ አካሄድም

መላው ሕዝባችን ማወቅ አለበት ብለን

እናምናለን፡፡

ዕለቱ በአገራችን

‹‹የተከበረው›› ባለድርሻ ናቸው

የተባሉ አካላት በተገኙበት በሒልተን

ሆቴል ሲሆን፣ የታላላቅ ዓለም አቀፍ

ተቋማት ተወካዮችም የሥነ-ሥርዓቱ

ታዳሚዎች ነበሩ፡፡ ከእነዚህም መካከል

የወቅቱ የተባበሩት መንግሥታት

ድርጅት (ተ.መ.ድ) ዋና ጸሐፊ

ባን ኪ-ሙን ተወካይ፣ በተ.መ.ድ

የትምሕርት፣ የሳይንስ እና የባሕል

ድርጅት (ዩኔስኮ)፣ የአፍሪካ ሕብረት

ሊቀ-መንበር የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

የዕለቱ መር-ግብርም

ከሳምንት በፊት ተዘጋጅቶ ተጠናቅቋል፡

፡ በዕለቱ የአገራችን የ20 ዓመት የግሉ

ፕሬስ እንቅስቃሴ ምን ይመስል ነበር?

ምን ጉድለቶች አሉበት? መጎልበት

ያሉባቸው ጉዳዮችስ ምን ይመስላሉ?

ወዘተ የሚሉ አንኳር አጀንዳዎች

ይነሳሉ ተብሎ ተጠብቆ ነበር፡፡ ለዚህ

ሲባል ደግሞም ዝግጅት ተደርጎበታል፡

፡ የሆነው ግን በተቃራኒው ነበር፡

፡ የ21ኛው መቶ ክ/ዘመን

የኢትዮጵያ ሚዲያ የለየለት ጋሬጣ

እንደተጋረጠበት በዝግጅቱ ላይ ገዝፎ

መንፀባረቅ የያዘው ገና ከጅምሩ ሆነ!

ከሳምንት በፊት ወጥቶ

የነበረውና ዘርፉን ለመገንባት

አስተዋጽኦ ያደርጋል በሚል

በተሳታፊዎቹ ዝግጅት የተደረገበት

መርሀ-ግብር ታጥፎ ንፋስ

አመጣሽ ዓይነት አዲስ መርሀ-

ግብር መታደል ጀመረ፡፡ በንፋስ-

አመጣሽ መርሐ-ግብሩ አንድ ነገር

እንዲያቀርቡ ከተጠየቁት አንዱ

የሆኑት የብሮድካስት ባለሥልጣን

ዋና ዳይሬክተር ምንም ዝግጅት

እንዳላደረጉ መሸሸግ አልቻሉም፡፡

በመሰረቱ ማንም ቢሆን

ዝግጅት ባላደረገበት ሁኔታ ‹‹አንድ

ነገር በል›› ብሎ ሰበር ማሳሰቢያ

መንገር የአገሪቱ ፕሬስ እንዴት ባለ

እይታ እየታየ እንዳለ የሚያመለክት

ከመሆኑም በተጨማሪ፣ በአንፃሩ

በትክክለኛው መርሀ-ግብር መሰረት

ዝግጅት ያደረጉትን ለቅሞ በማውጣት

የተፈጸመው ድርጊት እንኳን ለዘርፉ

በተወሰነ ደረጃ ቅርበት ላለው ለማንም

ቢሆን አሳፋሪና አሸማቃቂ ተግባር

ነው፡፡ እየተጠናከረ የመጣውን ዘመቻ

አደገኛነት የሚያረጋግጥ ሆኖም

አግኝተነዋል፡፡

አካሄዱ ፈፅሞ ተገቢነት

የጎደለው ነው፡፡ ይህ የዓለም

የፕሬስ ነፃነት ቀን አከባበር እውነታ

በኢትዮጵያ ሊሸሸግ ያልቻለውን

የገለማ ገመና አደባባይ ያወጣበት

ሆኗል፡፡ ዓለም ታዝቦታል፡፡ አሳሳቢና

ማንንም ጤነኛ አእምሮ ያለውን

ግለሰብ የሚያስጨንቅ ጉዳይ ነው፡

፡ አብዛኛው ተሳታፊ በሁኔታው

በማዘን ስብሰባውን አቋርጦ ወጥቷል፡

፡ በመርሀ-ግብሩ መሰረት የራሱን

ድርሻ ለማበርከት ሲዘጋጅ የነበረው

ባልደረባችን ‹‹የአይናችሁ ቀለም

አላማረንም›› እንዲሉ ዓይነት

ስሙ እንዲሰረዝ ተደርጎ ለመመለስ

የተገደደ ሲሆን፣ ሌሎች ወገኖችም

ተመሳሳይ ተግባር ተፈፅሞባቸዋል፡፡

የምንገኘው ዓለም በፍጥነት

በምትገሰግስበት በ21ኛው ክ/ዘመን

መባቻ ላይ መሆኑን ለማስታወስ

እንገደዳለን፡፡ ኢትዮጵያችንን ወደ ኋላ

የምትጎትቱ ከተግባራችሁ በአስቸኳይ

ታቀቡ ስንል መልዕክታችንን

እናስተላልፋለን፡፡ ሕገመንግስታዊው

የፕሬስ ነፃነት ድንጋጌዎች ይከበር!

ኢትዮጵያ ለዘላለም

ትኑር!!!

የካቲት 2000 ዓ.ም ተመሠረተ

አውራምባ ታይምስ፡- በብሉ ኤርዝ ጀነራል ቢዝነስ ኃላ/የተ/የግል/ማህበር ስር የሚታተም፤ በፖለቲካዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር፤ በንግድ ሚኒስቴር በቁጥር 020/2/6572/2001 የተመዘገበ ሳምንታዊ ጋዜጣ ነው፡፡

አድራሻ አራዳ ክ/ከተማ ቀበሌ 09

የቤት ቁጥር 191

ከአራት ኪሎ ወደ ፒያሳ በሚወስደው መንገድ ፣ ከራስ መኮንን ድልድይ አለፍ ብሎ ወደ ሀገር ፍቅር ቲያትር መገንጠያ አስፋልት ላይ በሚገኘው ባህረ ነጋሽ ሕንፃ ግቢ ውስጥ፡፡

አታሚ፡-

ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ክ/ከተማ፡- አራዳቀበሌ፡- 17የቤት ቁጥር፡- 984

‹‹የዓለም የፕሬስ ቀን በሚከበርበት ዕለት ነፃነቴን ተነፍግያለሁ፡፡››

አቶ አማረ አረጋዊ /የሪፖርተር ጋዜጣ ዋና ሥራ አስኪያጅ/

የዓለም የፕሬስ ነፃነት ማክሰኞ ዕለት በሒልተን ሆቴል በተከበረበት ዕለት ቀደም ሲል የተዘጋጀው የፕሮግራም መርሐ-ግብር

በመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ተቀይሯል፣ ሳንሱር ልንደረግ አይገባ ሲሉ

ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ ከተናገሩት፡፡

‹‹ሕዝብ እንደማያውቅ፣ ጭራ እንጂ የእንቅስቃሴው ማዕከል እንደሆነ አድርጎ

የማያይ አካሄድ ነው ያለው፡፡››

አቶ ገብሩ አስራት/የወቅቱ የመድረክ ሊቀ-መንበር/

የእናንተ ትውልድ ዴሞክራሲያዊና የበለጸገች ኢትዮጵያን የመፍጠር

ሕልማችሁ ለምን ከሸፈ? በሚል ከአዲስ ወሬ ጋዜጣ ለቀረበላቸው ጥያቄ ከሰጡት

ማብራርያ የተወሰደ፡፡

በ21ኛው መቶ ክ/ዘመን መባቻ ላይ፡-

አገራችንን ወደኋላ የምትጎትቱ ከተግባራችሁ በአስቸኳይ ታቀቡ!

ማን ምን አ ለ

‹‹ይህ ለአሜሪካ ጥሩው ቀን ነው!››

ባራክ ሁሴን ኦባማ /የአሜሪካ ፕሬዝዳንት/

አሜሪካ ከዘጠኝ ዓመታት በላይ ስታሳድደው የነበረው ኦሳማ ቢን ላደን መገደሉን ተከትሎ ለሕዝባቸው ካደረጉት ንግግር፡፡

Page 3: አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 166 ቅዳሜ ሚያዚያ 29 2003 ኢሕአዴግ … · ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ አውራምባ ታይምስ 4ኛ

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 166 ቅዳሜ ሚያዚያ 29 2003

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

3

በየተራ ይፈላል፡፡ ዛሬ አንዷ ቤት ውስጥ ተፈልቶ ከሆነ፣ ነገ ደግሞ ሌላዋ ቤት ይሆናል፡፡ አንዳንዴም አንዷ ቤት ጧት፣ ሌላዋ ጋር ደግሞ ከሰዓት፡፡

ቡና ምግብ የሚሆንበት ጊዜም አለ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ከቡና ጋር የቡና ቁርስ ተብሎ ጠንከር ያለ ነገር ስለሚቀርብ፣ ሌላ ምግብ ሳያስፈልግ ወደ ሥራ ይገባል፡፡ ይህም በራሱ ሌላው ጥቅሙ መሆኑ ነው፤ ለአብዛኞቹ ዘመዶቻችን ቡናን ከምግብ የሚያስበልጡ እናቶችም አሉ፡፡ በአጽዋማት ጊዜ በቤታቸው አቅራቢያ ለሥራ የተሰማሩ የገበሬ ቤተሰቦች፣ ቤት የሚውሉ ልጆቻቸው በጾም ፍች ሰዓት ‹‹ኑ ምሳ ደርሷል›› ሳይሆን፣ ‹‹ኑ ቡና ደርሷል›› ብለው ነው ከሥራ የሚያሳርፏቸው፡፡ ኧረ ስንቱን እናወራው ስለቡና፡፡

የሀገሬ ዓመት በዓሎች ያለቡና ዓመት በዓሎች አይመስሉም፡፡ ነጫጭ ሲኒዎቹ ተደርድረው ጥቁር ቡና ሲንቆረቆርባቸው፣ ከቄጠማውና ቆሎው ጋር እንዴት እንደሚያምር ሁላችንም የምናውቀው ነው፡፡ ይህ ገጠር ከተማ አይደለም፡፡

ቡና ለኮሌጅ ተማሪ፣ ለመንግሥት ሰራተኛ ልዩ ነገር ነው፡፡ እኔ ሰባት ዓመት ሕክምና ሳጠና ቡና እየጠጣሁ ነው፡፡ ተመርቄ ጋምቤላ በረሃ ውስጥ ስሰራ አብዛኞቹ ጓደኞቼ ቀን ሲተኙ እኔ በመካከለኛ ሲኒ አንድ ቡና ጠጥቼ፣ ፋኔን (Fan) ፊት ለፊቴ ከፍቼ ያለማቋረጥ ለረጅም ሰዓታት አነብ ነበር፡፡ (ጋምቤላ ውስጥ የምሳ ሰዓት ከ6፡30 -9፡00 ወይም ከ5፡30 - 10፡00 እንደሆነ ልብ ይሏል፡፡) አሁንም በሌላ ሥራ ላይ እያለን እኔም ሆንኩ ጓደኞቼ ጋምቤላም ሆነ አዲስ አበባ ከምሳ በኋላ አንድ ሁለት ሲኒ የጀበና ቡና አይቀርብንም፡፡ ሱስ ሆኖብን አይደለም፤ ብቻ ያሳርፈናል፡፡ የጨዋታና የደስታ ጊዜ ይፈጥርልናል፡፡ ከ40 ወይም 30 ዓመታት ወዲህ ጀበናን ተክቶ የነበረው የሻይና የቡና ማሽን ከነማይጥመው ቡናው አሁን እየተተወ ይመስላል፡፡ ብዙዎቻችን ወደ ጀበናችን ተመልሰናል፡፡ (እንኳን ደህና መጣን!)

ጎበዝ! ቡና ለእኛ ይህን ያህልና ከዚህም ላይ ከሆነ፣ እኛንና ቡናን ለማለያየት መመኮረ በእኛ ላይ ጦር ከመምዘዝ ይተናነሳል? ከ1-2 ዓመት በፊት አንድ ሲኒ ቡና (የጀበና) ከ50 ሳንቲም አይበልጥም ነበር፡፡ ዛሬ 3 ብር ገብቷል፡፡ ይሁን እስኪ! ጊዜ ያመጣውን ብለን ተቀብለን ለ50 ሚሊ ሊትር ቡና 3 ብር እየከፈልን እንጠጣለን፡፡ ይሄ መቼም በጤናማ የገበያ ሥርዓት እየተገፋ ነው እዚህ የደረሰው ለማለት ይከብዳል፡፡ የስኳር መጥፋትም (መወደድ) አንዱ ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡ ይህን ሁሉ ታግሰን እያለን፣ ይባስ ተብሎ አሁን እየተፈጸመ ያለው ግን አሳዛኝ እና ለአብዛኛው ኢትዮጵያዊ ደንታ-ቢስነትን የሚያሳይ ነው፡፡ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ቡና ከሚመረትባቸው አካባቢዎች አንድ ኪሎም ቢሆን ይዞ ማለፍ አይቻልም!! ይዞ የተገኘ ሰው ይወረሳል!!

በዚህ የተነሳ የአንድ ኪሎ ቡና ዋጋ ጣሪያ ነክቷል፡፡ ይህ እንዴት ሊዋጥ ይችላል? እርግጥ ነው አሁንም ሁሉም ነገር ‹‹ጥብስ›› ሆኗል፡፡ ሆኖም ግን፣ አቅም አግኝቶ ወይም ዕቃውን አግኝቶ የገዛ ሰው ይወረሳል ሲባል አልሰማሁም፡፡ ከቡና በስተቀር፡፡ ቡናን የምናመርተው እኛ፤ የምንወደው፣ የምናከብረው እኛ፤ ዓለምን የሚያስደንቅ ልዩ ሥርዓት የሰራንለት እኛ፤ ለዓለም ያስተዋወቅነው እኛ፤ ታዲያ ቡናን እኛ ካልተጠቀምንበት ማን ሊጠቀምበት ነው? ከላይ እንደገለጽኩት ምግብ እንኳ ሲጠፋ ቡናን ቀማምሰው የሚውሉትን እናቶቻችንና አባቶቻችን አያሳዝኑም?

ሚዛን ተፈሪ አካባቢ 1 ኪሎ ቡና ለከተማው ሰው 60 ብር ይሸጣል፡፡ ወደ 20 ኪ.ሜ ወጣ ብሎ በኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት የቡና እርሻዎች አንደኛው በበቃ

በ21ኛው መቶ ክ/ዘመን መባቻ ላይ፡-

አገራችንን ወደኋላ የምትጎትቱ ከተግባራችሁ በአስቸኳይ ታቀቡ!

ይገኛል፡፡ ለወትሮው በበቃ ውስጥ ተወደደ ተብሎ 1 ኪሎ ቡና 30 ብር ይሸጥ ነበር፡፡ የሚያሳዝነው ግን ከሚዛን ተፈሪ 1 ኪሎ ቡና ይዞ መውጣት አይቻልም፡፡ በጎጃም መስመር የወንበራ (ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ወረዳ ውስጥ የሚገኝ) ቡና ከ100 ብር

በላይ ሆኗል፡፡ ለምን? ማንም ገዝቶ ከቦታ ቦታ ማዘዋወር ስለማይችል በድብቅ ካሳለፉ ሰዎች ወይም ተዘረጋ በተባለው የሽያጭ መንገድ ብቻ ስለሚገኝ፡፡ ይሄ ሌላ በሕዝብ ላይ የሚጫን ግፍ አይደለም?

እኔ በአዋጅ፣ በደንብ ወይም በመመሪያ መልክ እንዲህ ይደረግ መባሉን እንኳን አላውቅም፡

እናቴና ጓደኞቿ፣ እንዲሁም የአደግሁበት አካባቢ ኅብረተሰብ፣ እኔም ራሴ ያንኑ አካባቢ በትምህርት ምክንያት እስክለቅና በሸዋ ዘዬ ‹‹ቡና›› ብዬ መጥራት እስክጀምር ድረስ፣ ቡን (ቡ ይላላል) እያልን እንጠራው ነበር፡፡ ስለእናቴ (እድሜና ጤና ይስጣትና) ከማውቃቸው ነገሮች ውስጥ ለቡና ያላት ትልቅ ፍቅር አንደኛው ነው፡፡ ጓደኞቿም እንደዚሁ፡፡ አባቴና መስሎቹ ቡና ቢወዱም፣ አንዳንዴ ወደ መሸታ ቤት ጎራ እያሉ አረቄውንም ጠላውንም አየሞካከሩ ከቡና ጥቂት ዘወር ይሉ ነበር፡፡ ለእናቶቻችን የቡናን ፍቅር ያወረሷቸው አያቶቻችን ናቸው፡፡ እናቶቻኝ/ወላጆቻችን ይህን ፍቅር ለእኛም ያወረሱት እነርሱ በወረሱበት መንገድ ነው፡፡

ሰለእኔ የልጅነት አካባቢ ብዙ አልኩ እንጂ በመላው ኢትዮጵያ (ከገጠር እስከ ከተማ) ቡና ልዩ ቦታ አለው፡፡ እርግጥ ነው ማኅበረሰቡ እንደሚወደው ሁሉ፣ መንግሥትም ቡናን ይወደዋል፡፡ የሁለቱም መውደድ ግን ለየቅል ነው፡፡ ሁለቱም ቡናን ከሚወዱበት ምክንያት አንፃረ ያቀነቅኑለታል፡፡

አ ያ ቶ ቻ ች ን ፣ ከዚያም በፊት የነበሩት የጥንት ዘመዶቻችን፣ የአያቶቻችን ልጆች፣ እኛም ጭመር ቡናን ስለመጠጥነቱ ብቻ አይደለም የምንወደው፡፡ የአጠጣጥ ሥርዓቱ አንዱ ምክንያት ነው፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ ማኅበራዊ መስተጋብርን በማጎልበት ቡና ተወዳዳሪ የለውም፡፡ በከተሞች አካባቢ እየተቀዛቀዘ የመጣ ቢመስልም፣ በዚህ ረገድ በገጠሪቱ ኢትዮጵያ ቡና ቦታውን አልለቀቀም፡፡ ይህ እንግዲህ ከመጠጥነቱ ባሻገር ከምንጠቅሳቸው ጥቅሞቹ ውስጥ ከላይኛው ረድፍ የሚመደብ ነው፡፡ የቡና ሥርዓት ላይ ብዙ ማኅበራዊ ጉዳዮች ይነሳሉ፡፡ ውይይት ይደረግባቸዋል፡፡ ውሳኔዎች ይወሰናሉ፡፡ ከዚያም ወደ ትግበራ ይገባል፡፡ በቡና አማካይነት የተጣሉ ይታረቃሉ፡፡ ለተጣሉ ጎረቤታሞች የመታረቃቸው አፋጣኝ መገለጫ ለቡና አብረው መቀመጣቸው ነው፡፡ እናቶች ብቻቸውን (ያለወንዶች) ለቡና የሚሰባሰቡ ከሆነ፣ አጋጣሚውን በመጠቀም ስለትዳራቸው፣ ስለልጆቻቸው፣ ስለባሎቻቸው፣ ስለኑሮአቸው ወዘተ በሰፊው ይነጋገሩበታል፡፡ ችግሮቻቸውን ይፈቱበታለ፡፡ ይህ በመሆኑ ምድርና ሰማይ ተላቅቆ አንድ ሌላ ቀን ከተጀመረበት ሰዓት አንስቶ የቡና ጊዜ አስኪደርስ ሁሉም ይቸኩላሉ፡፡ ብዙ ጊዜ ቡና

፡ አንድ ወይም ሁለት ኪሎ ቡና ከድሆች እጅ እንዲወረስ ያዘዘው አካል ምን አስቦ አዘዘው? ከጓደኛዬ ጋር ወደ አንደ የቡና እርሻ ውስጥ ገብተን ለመጠየቅ ሞክረን ነበር፡፡ አንድ የሚመለከተው ሰው፣ ‹‹አሁን በእርግጥ ቡና የለኝም፡፡ ቢኖረኝም አልሰጣችሁም›› አለን፡

፡ ‹‹የውጭ ምንዛሬ የሚያስገኘውን እህል እያባከንክ ነው›› ብለው ከሰውኛል አለን፡፡ አስከትሎም፣ ‹‹ኖሮኝ ሁለት፣ ሁለት ኪሎ ብሰጣችሁም፣ ኬላ ላይ ፖሊስ ይረከባችሁና አንዱን ለራሱ ሌላውን ደግሞ ለመንግሥት ገቢ ያደርገዋል›› አለን፡፡

እጅግ አሳፋሪና አሳዛኝ

ነው፡፡ የውጭ ምንዛሬ የሚገኘው የሕዝብን ፍላጎት ሙሉ በሙሉ ጨፍልቆ ነው? እርግጥ ነው ያለቡና መኖር ይቻላል፡፡ ግን እንዲህ በጫና ሲሆን ያምማል፡፡ እኛ ሌላ ሀገር የለንም፡፡ ስለዚህም የሀገራችንን ምርቶች እንኳ ሳንሳቀቅ እና ሳንማረር የመጠቀም

መብታችን ይጠበቅልን፡፡ ጉዳዩ የሚመለከተው አካል አፋጣኝ እልባት ቢሰጥበት መልካም ነው፡፡ በትንሹም በትልቁም ዜጎችን ያለአግባብ ማበሳጨት በጎ ተግባር አይደለም፡፡

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይጎብኝ!

አግባብነት የሌላቸው የቡና ኬላዎች

በያየህ ነጋሽ (ዶ/ር)

ቡና ለእኛ ይህን ያህልና ከዚህም ላይ ከሆነ፣ እኛንና ቡናን ለማለያየት መመኮረ በእኛ ላይ ጦር ከመምዘዝ ይተናነሳል? ከ1-2 ዓመት በፊት አንድ ሲኒ ቡና (የጀበና) ከ50 ሳንቲም አይበልጥም ነበር፡፡ ዛሬ 3 ብር ገብቷል፡

፡ ይሁን እስኪ! ጊዜ ያመጣውን ብለን ተቀብለን ለ50 ሚሊ ሊትር ቡና 3 ብር እየከፈልን እንጠጣለን፡፡ ይሄ መቼም በጤናማ የገበያ ሥርዓት እየተገፋ ነው እዚህ የደረሰው ለማለት ይከብዳል፡

ስለ ‹‹አማላዩ›› ፊልም ተመልካቾች ምን ይላሉ

ከዓለም ሲኒማ ተመልካቾች የተሰበሰበ

በጣም የተዋጣለት ፊልም ነው 1. ግሩም ኤርሚያስ የተዋጣለት 2. አማላይ ነው በተለይ ለእንደእኔ ትውልደ 3. ኢትዮጵያዊ ይመቻል በጥራት ስለሰራችሁት 4. አመሰግናለሁ ፊልም ማለት እንደዚህ ነው 5. ሁለት የተለያዩ ስቶሪዎች በፍቅር 6. አይቻለሁ ግሩም እኔን በጣም ነው ያማለለኝ 7. አስተዋውቁኝ እኔና ጓደኞቼ የእውነት ማለናል፡፡ 8.

ምስጋና ለዓለም ሲኒማ

ከባለሙያዎች የተሰጠ አርቲስት መርዓዊ ስጦት - ዘመኑን የዋጀ ፊልም አርቲስት ሠይፉ አርአያ - የወጣቶችን ልብ የሚማርክ ዘመናዊ ፊልም አርቲስት ጌትነት እንየው - በጣም የሚጣፍጥ ቀለል ያለ ታሪክ አርቲስት ቢኒያም ወርቁ - በሁሉም መስክ የተዋጣለት ፊልም ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ - በባለሙያዎች የተሰራ ምርጥ ፊልም የሜዳሊያ ደራሲ አማኑኤል መሀሪ - ምርጥ ፕሮዳክሽን ሊያዩት የሚገባ

የአማላዩ ፊልም እውነታዎች በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የተቀረፀ - በCanon 5D እና 7D የተቀረፀ- በከፍተኛ በጀት የተዘጋጀ፣ 7 ወራትን የፈጀ - በየጊዜው መረጃዎችን በጋዜጣዊ መግለጫ ያበሰረ - ለቀለም እርማት ሥራ ወደ ለንደን የተጓዘ - ከተመረቀ ጀምሮ ሳምንቱን ሙሉ በ21 እይታ የታየ- ተመልካቾችንና ባለሙያዎችን ያስማማ ምርጥ ፊልም - አማላዩ-

በእምቢልታ ሲኒማ፣ በኤድና ሞል፣ በአለም ሲኒማ፣ በዩፍታሄ ሲኒማ፣

በፓናሮሚክ ሳምንቱን ሁሉ ይገኛል

በቅርብ ቀን በሰሜን እና በምሥራቅ

የኢትዮጵያ ክፍል ይታያል፡፡ ‹‹አማላዩ›› ከካም ግሎባል ፒክቸርስ

አማላዩ ሮማንቲክ ኮሜዲ

Page 4: አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 166 ቅዳሜ ሚያዚያ 29 2003 ኢሕአዴግ … · ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ አውራምባ ታይምስ 4ኛ

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 166 ቅዳሜ ሚያዚያ 29 2003ፊ ቸ ር4

‹‹በዚህ ምሽት ለአሜሪካ ሕዝብና ለዓለም አንድ መግለጽ የምፈልገው ጉዳይ አለ፤ የአልቃኢዳው መሪ፣

አሸባሪውና በሺህ ለሚቆጠሩ ንፁሀን መሞት ተጠያቂ የሆነው ኦሳማ ቢንላደን አሜሪካ ባካሄደችው ወታደራዊ እርምጃ

ተገድሏል..››

ይህ ንግግር በመላው ዓለም የሚገኙ ሚዲያዎች ባለፈው እሁድ ሌሊት ተቀባብለው ያስተጋቡት የፕሬዝዳንት ኦባማ መልዕክት ነው፡፡ የዓለማችን ፖለቲከኞችና ተንታኞች የሳምንቱ ዋነኛ የመነጋገሪያም ሆነ፡፡ በእርግጥም የኦሳማ ቢንላደን ጉዳይ በየትኛውም የዓለም ጥግ የሚገኙ ሕዝቦችን ትኩረት ከመሳብ አልፎ በዓለም ፖለቲካ፣ ዲፕሎማሲና ኢኮኖሚ ላይ ሳይቀር የራሱን ጥላ ጥሎ እንደከረመ የመረጃ መረቦች ይፋ እያደረጉ ነው፡፡

በተለይ ባለፉት አስር ያህል ዓመታት ሰውየውን ካለበት ለመያዝ አሊያም ከምድረገጽ ለማጥፋት በትሪሊዮን የሚቆጠር ዶላር ወጪ ላደረገችው አሜሪካ ይህ ከስኬት በላይ ነው፡፡ ለዚህም ነበር ፕሬዝዳንት ኦባማ በፍጹም የድል አድራጊነት ሞገስ ‹‹በዚህ ምሽት ለአሜሪካ ሕዝብና ለዓለም ሕዝብ መግለጽ የምፈልገው ጉዳይ አለ፡፡…›› ሲሉ የመላውን ዓለም ሕዝብ ጆሮ ያርገበገበውን ዜና ይፋ ያደረጉት፡፡

መስከረም 11/2001የዛሬ አስር ዓመት ገደማ የዓለማችን

ቀደምት የዲፕሎማሲ ማዕከል በሆነችው ኒውዮርክ የነበሩትን የሁለቱን ረዣዥም መንትያ ህንፃዎች መውደም በቴሌቪዥን መስኮት የተመለከተ በፕላኔታችን ልዕለ ኃያል አገር ላይ ይህ መሰሉ የተቀናጀ ጥቃት እንዴት ሊደርስ ቻለ? ከራሷ አልፋ አጋሮቿን በደህንነት ከለላ ዋስትና ትሰጣለች የሚባልላት አሜሪካ ከመንትዮቹ የንግድ ማዕከላት በተጨማሪ የመከላከያ መ/ቤቷ በሆነው ፔንታጎን ላይ ያን መሰል መዓት እንዴት ሊወርድ ቻለ? ሲል በግርምት መጠየቁ አይቀርም፡፡

በጉዳቱ በሺህ የሚቆጠሩ ንጹሀን ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡ አሜሪካዊያን በቁጣ ነደዱ፣ ብሔራዊ ስሜታቸውና ጥቃታቸውን የመበቀል ጥማቸውም ጣራ ነካ፡፡ የአገሪቱ ፖሊሲ አውጪዎችም አዲስ ስትራተጂ ነደፉ፤ እንዲሁም የጸረ-ሽብር ትግሉን ከፊት ሆነው ለመምራት በአንድ ልብ ተነሱ፡፡ የፖለቲካ ተንታኖች እንደሚያስረዱት አሜሪካ ከዚያ በኋላ ከሌሎች አገራት ጋር የሚኖራት ውጭ ጉዳይ ፖሊሲ በዚሁ ሽብርተኝነትን የመዋጋት ማዕከላዊነት ላይ የተዋቀረ ሆኗል፡፡

የሕዝባቸውን ቁጣ የተመለከቱት ፕሬዝዳንት ጆርጅ ቡሽም የሕዝባቸውን ስሜት በገዛና በአገርኛ ብሂል በተሞላ መራር የአቋም መግለጫቸው አሸባሪዎቹን ‹‹የትም አታመልጡም አሜሪካ የገባችሁበት ገብታ ለፍርድ ታቀርባችኋለች›› ሲሉ ዛቱ፡፡ ለዚህ ስኬት የዓለም መንግስታትም ከልዕለ ሀያሏ ጎን ለመሰለፍ ሁለቴ ማሰብ አላስፈለጋቸውም፡፡ ከዚህ ጥቃት ወዲህ ከአሜሪካ እና ብሪታኒያ ጋር በጸረ ሽብር ትግሉ መስክ በቅርብ የሚሰሩ (ኢትዮጵያን ጨምሮ) አስር አጋር መንግስታት አሉ፡፡

የመስከረም 11/2001 ጥቃት በተፈጸመ ማግስት ታዋቂው አሜሪካዊ ጋዜጠኛ ፋሪድ ዘካሪያ አንድ እጅግ አነጋጋሪ ፊቸር በኒውስዊክ መፅሄት አስፍሮ ነበር፡፡ ፋሪድ በሚያዘጋጀው መጽሄት (ኒውስዊክ) የፊት ለፊት ገፅ ላይ ሰፊ ሽፋን ተሰጥቶት የተስተናገደው ይህ ጽሁፍ ‹‹The politics of rage: why do they hate US›› የሚል ርዕስ ያለው ነው ‹‹እኛ የቆምነው ለነፃነት ነው ግን ይጠሉናል፤ በመበልጸጋችን ምክንያት ጥርሳቸውን ነክሰውብናል፤ ጥንካሬያችን ምቾት አልሰጣቸውም፡፡ ይህ እውነት ነው፡፡ ነገር ግን በዓለም ዙሪያ በቢሊዮን የሚቆጠሩ አቅመ ደካሞች፣ ድሆችና የተጨቆኑ ሕዝቦች አሉ፤ እነዚህ በሺህ የሚቆጠሩ ንፁሃንን ለመፍጀት ግን ራሳቸውን አያጠፉም፡፡ ኦሳማ ቢንላደን ለዚህ ድርጊቱ ኃይማኖትን እንደምክንያት አድርጎ ያቀርባል፡፡ ለእርሱና ለታከታዮቹ ይህ በሙስሊሞች እና በምዕራባውያን መካከል የሚደረግ ቅዱስ ጦርነት ነው፡፡ ሙስሊሞች ደግሞ በዚህ አይስማሙም፡፡

እያንዳንዱ ሙስሊም አገር ይህንን ጥቃት አውግዟልና›› ብሏል፡፡

በፋሪድ ዘካሪያ እምነት ይህ አይነቱ ፅንፈኝነት ከእስልምና ጋር አብሮ የተወለደ አይደለም፡፡ ይህ የተከበረ ኃይማኖት፤ በቅዱስ ቁርአን ላይ በግልጽ የሰፈሩ ፍቅር፣ ሰላምና መቻቻልን መነሻ ያደረገ በእነዚህ መርሆች የሚራመድ ሰላማዊ ኃይማኖት እንጂ እነ ቢንላደን እንደሚሉት የአሜሪካን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ለመቃወም የተመሠረተ ኃይማኖት አይደለም ሲል ይከራከራል፡፡

አሜሪካ ድህረ መስከረም 2001

እ.ኤ.አ የመስከረም 11/2001 ጥቃት አሜሪካ ለፀጥታና ደህንነት ቅድሚያ የሰጠ ፖለሲ በመላው ዓለም እንድትተገብር ምክንያት ሆኗል፡፡ በአሜሪካ የሚመራው ጥምር ኃይል አፍጋኒስታን ውስጥ ለቢንላደን ይፋዊ ከለላ ሰጥቶ አገሪቱን ሲገዛ የነበረው የታሊባን አስተዳዳርን በታትኖ በሀሚድ ኻርዛይ የሚመራ መንግስት አፍጋኒስታን ላይ ከማስቀመጥ ጎን ለጎን ከአልቃይዳ ጋር ቁርኝት አላቸው የሚባሉ ህዋሶችንና የማሰልጠኛ ካምፖችን አውድሟል እስከ ቶራ ቦራ ተራሮች ድረስ የዘለቀ ወታደራዊ እርምጃ ተወሰደ፡፡ በዚህ ወታደራዊ ኦፕሬሽን ላይ ቀላል የማይባል ቁጥር ያላቸው የቡድኑ ዋነኛ አስተባባሪዎች ተገድለዋል፡፡

ባለፉት ዓመታት ውስጥ ከአልቃኢዳ ወሳኝ አስር ሰዎች መካከል መሀመድ አታፍ፣ አቡ ሙሳብ አልዛርቃዊ፣ አቡ ሐምዛ ራቢያ፣ ሚደሐት ሙርሲ፣ አቡ ላይዝ አል ሉቢ፣ መሀመድ ሀሰን አልሐኪም፣ ሰይድ አል ሙስሪ፣ ራሺድ ራውፍ የተገደሉ ቢሆንም ቢንላደንን ማግኘት ግን ለአሜሪካና አጋሮቿ ከባድ ሆኖ ቆይቷል፡፡

የፓኪስታን ፀጥታ ኃይሎች ድራማ

ፓኪስታን በፀረ ሽብር ትግል የአሜሪካ ቁልፍ አጋር ብትሆንም ሰሞኑን እየወጡ ያሉ መረጃዎች ግን የቢንላደንና የፓኪስታንን ፀጥታ ኃይሎች ቁርኝት ጠበቅ ያለ መሆኑን የሚያጋልጡ ናቸው፡፡ ዘገባዎቹ የፓኪስታን የፀጥታ ኃይሎች ቢንላደን የት እንዳለ ከማወቅም አልፎ የተለየ ጥበቃ ሲያደርጉለት መቆየታቸውን የሚያሳዩ መረጃዎች ይፋ ተደርገዋል፡፡ የአሜሪካ ማዕከላዊ የስለላ ድርጅት (ሲ.አይ.ኤ) አባላት ለበርካታ ወራት ያህል ሰውየው የሚገኝበትን ስፍራ ጠንቅቀው ካወቁ በኋላ እጅግ ቅርብ በሆነ ርቀት ክትትል ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡ ይህ የስለላ ተቋሙ ድርጊት ግን ለፓኪታን የጸጥታ ኃይሎች ግልጽ አልነበረም፡፡

ከግድያው በኋላ የወጡ ሪፖርቶች ደግሞ ቢንላደን ከኩላሊት ህመም እንዲያገግም አንድ ዶከተር ተመድቦለት ሚስጥራዊ በሆነ መልኩ በሳምንት ሁለት ጊዜ የህክምና እርዳታ ሲደረግለት እንደነበር የሚገልፁ ናቸው፡፡ የፓኪስታን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ግን ተጨባጭነት የሌለው ሲሉ ክሱን ውድቅ አድርገውታል፡፡ ድሏን እያጣጣመች ያለችው አሜሪካ ባለስልጣናት ይህን መሰሉን ምላሽ ይጠብቁት እንደነበር በሚያስገምት ሁኔታ በዲፕሎማሲያዊ ስልት ሁኔታውን በመገምገም ለቀጣዩ ዘመቻቸው ዝግጅታቸውን አጧጡፈውታል፡፡

ሞቶም አቀባበሩ የሚያወዛግበው ሰውዬ

እ.ኤ.አ መስከረም 18/2001 በአሜሪካ

ኮንግረስ የጸደቀው ሕግ (Authorization to Use Military Force Act) የመስከረሙን ጥቃት በመሩ፣ ባስተባበሩና በተሳተፉት ላይ ተገቢና አስፈላጊ የእርምጃ ትዕዛዝ የመስጠት ኃላፊነት ለአገሪቱ ፕሬዝዳንት ሰጥቷል፡፡ በዚህ የኮንግረስ አዋጅ መሰረት ነው ፕሬዝዳንት ኦባማ ሰውየው እንዲገደል በፊርማቸው ቀጥተኛ ትዕዛዝ የሰጡት፡፡ በዚህ መሰረት የተገደለው ቢንላደን ግን ከግድያው በኋላ ባህር ውስጥ እንዲቀበር መደረጉ ሌሎች ተጨማሪ ክርክሮች እንዲነሱ ምክንያት ሆኗል፡፡

በእስልምና ሕግ አንድ ሰው ሕይወቱ ባለፈ በ24 ሰዓታት ውስጥ የቀብር ስነ ስርዓቱ መፈፀም እንዳለበት የዕምነቱ አባቶች ይገልጻሉ፡፡ ሆኖም በስም ያልተጠቀሰች አንድ የሙስሊም አገር ቢንላደን በአገሯ እንዲቀበር የቀረበላትን ጥያቄ ውድቅ በማድረጓ፤ እንዲሁም የሌሎች አገሮች ፍቃደኝነት ለማወቅ ደግሞ ጊዜ ስለሚፈጅ በባህር ውስጥ እንዲቀበር መወሰኑን የኦባማ የፀረ ሽብር

አማካሪ የሆኑት ጆን ብሬናን ለኒው ዮርክ ታይምስ ገልፀዋል፡፡

ሚስተር ብሬናን በክስተቱ ማግስት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰውየው በእስልምና ኃይማኖት ስርዓት መሠረት ቀብሩ ባህር ውስጥ እንደተፈፀመ ቢገልፁም እርምጃው በእስልምና እምነት ተከታይ ወገኖች ተቃውሞ ገጥሞታል፡፡ የዓለማችን ትልቋ የሙስሊም አገር የሆነችው ኢንዶኔዥያ ከፍተኛ የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ድርጊቱን አውግዟል፡፡ ‹‹አንድ ሙስሊም ሙያው ምንም ይሁን ምን፤ ወንጀለኛም ቢሆን በአግባቡ ፀሎት ተደርጎለት በነጭ ጨርቅ ተሸፍኖ መሬት ላይ መቀበር እንዳለበት የእስልምና ሕግ ያዛል›› ሲል ተቃውሞውን ገልጿል፡፡

በታዋቂው የግብፅ አል አዝሀር ዩኒቨርሲቲ የሚያስተምሩት ሼክ አህመድ አልታይብ በበኩላቸው ‹‹እርምጃው የእስልምናን መሠረታዊ መርህ፣ ኃይማኖታዊ እሴትና ሰብአዊ ክብርን ያላገናዘበ›› ሲሉ ለኢራኑ ፕሬስ ቲቪ አስተያየት ሰጥተዋል፡፡ አሜሪካ ግን የእስልምና እምነት በሚያዘው መሠረት አስከሬኑ ታጥቦና በነጭ ጨርቅ ተሸፍኖ የቀብር ስነ ስርዓቱ እንደተከናወነ ትገልፃለች፡፡ በእርግጥ ይህን የአቀባበር አማራጭ አሜሪካ ሆነ ብላ ያደረገችው ነው የሚሉ ወገኖች በተከታዮቹ ዘንድ የጉዳዩን ማጠንጠኛ ከሰውየው መገደልና ያለመገደል ይልቅ የራሱ ክብር ባለው የአቀባበር ስርዓቱ ላይ እንዲያጠነጥን የማድረግ የስነ ልቦና ጨዋታ ነው ይላሉ፡፡ የኢራቁ መሪ የነበሩት ሳዳም ሁሴን በተሰቀሉበት ዕለት የእስልምና በዓል የሚከበርበት የነበረ ከመሆኑ በተጨማሪ ሰብአዊ ክብራቸውን የሚያንቋሽሽ ድርጊት ተፈጽሞ እንደነበር በዋቢነት ይጠቅሳሉ፡፡ በሁነቱ ላይ ሳይሆን ከሁነቱ በኋላ በሚፈጸሙ ክዋኔዎች የስነ ልቦና ጨዋታ መፍጠር ይሉታል፡፡

ይግባኝ የሌለው ቅጣት

የደህንነት ስጋቶችና የቢን ላደን ሚስቶች ምርመራበኢስላማባድ የሚገኘው የአሜሪካ

ኤምባሲ የበቀል ጥቃት ሊፈፀምበት ይችላል በሚል ስጋት ለተወሰነ ጊዜ የተዘጋ ሲሆን ኢንዶኔዥያ እና ፊሊፕንስም የሽብር ጥቃት ሊፈፀም ይችላል በሚል የፀጥታ ኃይሎቻቸው በተጠንቀቅ እንዲቆሙ ትዕዛዝ ሰጥተዋል፡፡

አውስትራሊያ በበኩሏ የፀረ-ምዕራባዊያን ጥቃት ሊፈፀም ይችላል በሚል ስጋት ዜጎቿ ወደ ፓኪስታን እንዳይጓዙ አስጠንቅቃለች፡፡ ትናንት አመሻሹ ላይ የወጡ ሪፖርቶች እንደሚጠቁሙት የቢንላደን ሦስት ሚስቶች በቁጥጥር ስር ውለው በሲአይኤ ምርመራ እየተካሄደባቸው ይገኛል፡፡ ከእነዚህ መካከል አንዷ የሆነችው አማል አልሳዳህ የሰውየው ሚስት ብትሆንም ላለፉት አምስት አመታት ግን ጨርሳ እንዳላየችው ለመርማሪዎቹ ቃሏን ሰጥታለች፡፡

US Navy Seal ማነው?

ይህ ቡድን በልዩ ትዕዛዝ የሚፈፀሙ ወቅታዊ ኦፕሬሽኖችን በአየር፣ በባህርና በምድር የሚያከናውን ልዩ ወታደራዊ ኃይል ነው፡፡ ባለፈው ሰኞ ማለዳ በሲ.አይ.ኤ አስተባባሪነት ወደ 40 የሚጠጉ የዚህ ልዩ ኃይል አባላት ከኢስላማባድ በሰሜን ምዕራብ አቅጣጫ በምትገኘው አቦታባድ ከተማ ባካሄዱት ወታደራዊ እርምጃ የተገደለው ኦሳማ ቢን ላደን ኦፕሬሽኑ ሲፈፀም ፕሬዝዳንት ኦባማን ጨምሮ በርካታ አሜሪካ ባለስልጣናት በከፍተኛ ተመስጦ ውስጥ ሆነው በቀጥታ የሳተላይት ስርጭት ከዋይት ሀውስ እየተከታተሉት ነበር፡፡

ፕሬዚዳንት ኦባማ በትናንትናው ዕለት በኬንቱኪ ግዛት ወደሚገኘው የልዩ ወታደራዊ ኃይል ማዘዣ ጣቢያ በማቅናት የቢንላደንን ግድያ በስኬት የፈጸሙ የዚህ ቡድን አባላትንና ኦፕሬሽኑን በበላይነት የመሩትን አድሚራል ዊሊያም ማክራቨንን በአካል ተገኝተው አመስግነዋል፡፡ ፕሬዝዳንቱ ከዚህ በተጨማሪ በመስከረም 11/2001 ጥቃት የተፈጸመበትንና ግራውንድ ዜሮ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ የጥቃቱ ሰለባ ከሆኑ ቤተሰቦች ጋር በመሆን በትናንትናው ዕለት ጉንጉን አበባ አስቀምጠዋል፡፡

ምንም እንኳ የቢን ላደን መገደል ከፍተኛ ዋጋ ያስከፈለና ቀላል የማይባል ስኬት ቢሆንም ባለድሎቹ ድሉ የትግሉ ሁሉ መቋጫ ያለመሆኑን ጠንቅቀው የተረዱ መሆናቸውን በሚገልጽ ሁኔታ ‹‹ሰውየው ተገደለ ማለት ሽብርተኝነት አከተመለት ማለት አይደለም›› የሚሉ መልዕክቶችን እያስተላለፉ ይገኛሉ፡፡ በትንሹ ቡሽ የ‹‹ይገደል›› ፊርማ ሞት የተፈረደበት የአሸባሪዎች ቁንጮ ቡሽ እንደቋመጡለትና እንደዛቱበት ባይሳካላቸውም በመጀመርያው ጥቁር ፕሬዝዳንት ኦባማ የአዛዥነት ዘመን መቋጨቱ ለኦባማ ቀጣይ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ከሰማይ የወረደ በረከት ተደርጎ ተወስዷል፡፡

ሁኔታው ልክ አንድ አሜሪካዊ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ለመገናኛ ብዙኃን እንደገለጸው ነው፡፡ ‹‹ኦባማ…›› አለ ወጣቱ ‹‹… በቀጣዩ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ወቅት እኔን ብትመርጡ የበለጠ ትጠቀማላችሁ የሚሉበትን ካርታ መዘዋል፡፡ ይህ ለእሳቸው ሌላ የአዲስ ምዕራፍ መባቻ ነው፡፡…››

የቢንላደን ፍጻሜና

የኦባማ አዲስ የስኬት ምዕራፍ

በዳዊት ከበደ

ፕሬዚዳንት ኦባማ በትናንትናው ዕለት

በመስከረም 11/ 2001 የጥቃት ሰ

ለባ ለሆኑ ወገኖች በኒውዮርክ ግራው

ንድ ዚሮ የአበባ ጉንጉን ሲያስቀምጡ

እኛ የቆምነው ለነፃነት ነው ግን ይጠሉናል፤

በመበልጸጋችን ምክንያት ጥርሳቸውን ነክሰውብናል፤

ጥንካሬያችን ምቾት አልሰጣቸውም፡፡ ይህ እውነት

ነው፡፡ ነገር ግን በዓለም ዙሪያ በቢሊዮን የሚቆጠሩ አቅመ ደካሞች፣ ድሆችና የተጨቆኑ ሕዝቦች አሉ፤ እነዚህ በሺህ የሚቆጠሩ ንፁሃንን ለመፍጀት ግን

ራሳቸውን አያጠፉም፡፡ ኦሳማ ቢንላደን ለዚህ ድርጊቱ

ኃይማኖትን እንደምክንያት አድርጎ ያቀርባል፡፡

አማል አልሳዳህ የሰውየው ሚስት ብትሆንም

ላለፉት አምስት አመታት ግን ጨርሳ እንዳላየችው

ለመርማሪዎቹ ቃሏን ሰጥታለች፡፡

Page 5: አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 166 ቅዳሜ ሚያዚያ 29 2003 ኢሕአዴግ … · ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ አውራምባ ታይምስ 4ኛ

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 166 ቅዳሜ ሚያዚያ 29 2003

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

5

ማስታወቂያ

‹‹… ሙያዊ ኃላፊነቴን እየተወጣሁ በነበርኩበት ጊዜ፣ ከብዕሬና ከአንደበቴ በቀር ምንም እንዳልነበረኝና እነዚህንም ስጠቀም የኢራን መንግስት ካስቀመጣቸው የሕጎች እና የደንቦች ጠባብና ውስን ገደቦች በፍፁም አልፌ እንደማላውቅ ግልፅ ላደርግ እወዳለሁ፡፡ ነገር ግን፣ እራሳቸው ያስቀመጧቸውን ሕጎችና ገደቦች በመጣስ ልቋቋመው ከምችለው በላይ ሕመምና ስቃይን ጥለውብኛል -- ይህም ለሳምንታት ከተሰቀለ፣ አልያም በሕይወቱ ከተቀበረ ሰው ሕመምና ስቃይ ጋር ተስተካካይ ነው፡፡››

ይህንን መልዕክት ያስተላለፈው የዘንድሮ የዩኔስኮ (UNESCO) ጉሌርሞ ካኖ የፕሬስ ነፃነት ሽልማት ተሸላሚ፣ ኢራንያዊው ጋዜጠኛ አሕመድ ዘይባዳቢ ነው፡፡ አሕመድ ስድስት ዓመት ተፈርዶበት አሁንም በእስር ቤት የሚገኝ ሲሆን፣ ከዚህ ፍርድ በተጨማሪ የአምስት ዓመታት ግዞትም ይጠብቀዋል፡፡ ይህ ብቻ አይደለም፤ ከዚህ በኋላ እድሜ ልኩን በፖለቲካዊ እና ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ እንቅስቃሴ እንዳያደርግና በጋዜጠኝነት ሙያው እንዳይሰራ፣ እንዲሁም ከማንኛውም ዓይነት የጽሑፍ ተሳትፎ እንዲታቀብ በኢራን መንግስት ተወስኖበታል፡፡ የዚህ ሁሉ ምክንያትም እ.አ.አ በ2009 የሀገሪቱን ብሔራዊ ምርጫ ተከትሎ የተነሳውን ውዝግብ አስመልክቶ በፃፋቸው የተለያዩ መጣጥፎች ‹‹መንግስት

ለመገልበጥ አሲረኻል›› ተብሎ ነው፡፡ (እንዲህ ዓይነቱን ሁኔታ በሀገራችንም መታዘባችን አይዘነጋም፡፡ ዛሬስ?)

ዩኔስኮ እ.አ.አ በ1986 ከጋዜጣ ቢሮው ፊት ለፊት በተገደለው፣ በኮሎምቢያዊው ጋዜጠኛ ጉሌርሞ ካኖ ኢሳዛ ስም በየዓመቱ የዓለም የፕሬስ ነፃነት ቀን መከበርን አስመልክቶ ሀሳብን ለመግለፅ ነፃነት በሙያቸው ለተዋደቁ፣ መከራና ስቃይ ለተጋፈጡ ግለሰቦችና ተቋማት የሚሰጠውን ሽልማት በማግኘቱ ነበር አሕመድ ከላይ የተቀነጨበውን መልዕክት ያስተላለፈው፡፡ ሚያዚያ 25 (May 3) የዓለም የፕሬስ ነፃነት ቀን ተብሎ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ እ.አ.አ በ1993 ሲታወጅ፣ የዕለቱ አከባበር መሠረታዊ የፕሬስ ነፃነት መርሆዎችን ማስታወስና ማስረገጥ፣ በጋዜጠኝነት ሙያቸው ዋጋ የከፈሉትን ማስታወስ፣ የፕሬስ ነፃነት ያለበትን ደረጃ መገምገም፣ እንዲሁም ለፕሬስ ነፃነት ጀርባቸውን የሰጡ መንግስታት ፊታቸውን እንዲመልሱና መሰል ዓላማዎችን ያነገበ ነው፡፡

ይህ ዕለት በመላው ዓለም የሚከበር ሲሆን፣ በኢትዮጵያም ይህንን ቀን ለማክበር የተዘጋጁ የፕሬሱ አባላትና የመንግስት ባለሥልጣናት ባሳለፍነው ማክሰኞ በሒልተን ሆቴል ተሰብስበው ነበር፡፡ ታዲያ ቀኑ እንዴት አለፈ? በዕለቱ የነበረው ሁኔታ የዓለም የፕሬስ ነፃነት ቀን በኢትዮጵያ ተከብሮ አለፈ ለማለት ያስደፍር ይሆን? በፍፁም፣ በእኔ በኩል ተተራመሰ እንጂ ተከበረ ልለው አልተቻለኝም፡፡ በሌላ በኩል ግን በሀገራችን ፕሬስ እና ነፃነቱ ምን ደረጃ ላይ እንዳሉ በይፋ የጠቆመ ዝግጅት ይሆን ዘንድ እድሉን የፈጠረ ነበር፡፡

በመጀመሪያ ደረጃ፣ እንዲህ

ዓይነቱን ቀን ማክበር ለመንግስትም ሆነ በተለምዶ ‹‹ነፃ›› የሚል ተቀፅላ ለተሰጠው የግሉ ፕሬስ ጠቀሜታው የጎላ እንደሆነ ጥርጥር የለውም፡፡ በተለይ በዩኔስኮ ድጋፍ፣ የሆርን ኦፍ አፍሪካ ፕሬስ ኢንስቲትዩት፣ የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ጋዜጠኞች ማኅበር እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጋዜጠኞች ኅብረት አዘጋጅተውትና የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ትብብር ታክሎበት ዕለቱ እንደሚከበር ስሰማ፣ ለፕሮግራሙ የሰጠሁት አንድ ግምት ነበር፡፡ ለመንግስት የሚወግኑ ወይም መንግስት ያቋቋማቸው ተብለው የሚታሙ ማኅበራት፣ እንዲሁም እራሱ መንግስትም የሚሳተፉበት በመሆኑ፣ ‹‹ከመቼውም በላይ የፕሬስ ነፃነት ሰፍኗል››፤ ‹‹ዓለም አቀፍ ስታንዳርድን የጠበቀ የፕሬስ ሕግ አለን››፤ እንዲሁም፣ ‹‹ጋዜጠኛን ማሰር ድሮ ቀርቷል›› የመሳሰሉ እወጃዎችና ምስክርነቶች መሰማታቸው እንደማይቀር ጠርጥሬ ነበር፡፡ በሌላ በኩል በዝግጅቱ ላይ የሀገራችንን የፕሬስ ነፃነት አስመልክቶ በጥናታዊ ጽሁፍ አቅራቢነት እና በአወያይነት የተጋበዙ የግሉ ፕሬስ አባላት በመኖራቸው ደግሞ ከመንግስትም ሆነ ከተያያዥ አካላት የደረሰባቸውንና እየደረሰባቸው ያለውን ባለብዙ ፈርጅ በደልና አፈና የመተንፈስ እድሉ ስለሚኖራቸው፣ ዝግጅቱ ሚዛናዊ እንደሚሆን ተስፋ ነበረኝ፡፡ ስለዚህም፣ ይፋ የወጣ ጥምዘዛ አልጠበኩም ነበር፡፡ በዕለቱ የሆነው ግን የተመለከተን ብቻ ሳይሆን የሰማንም አሳፍሯል፡፡

ነገሩ እንዲህ ነው ...በዚህ ዝግጅት ላይ የፎርቹን

ጋዜጣ ማኔጂንግ ኤዲተር የሆነው አቶ ታምራት ገብረጊዮርጊስ የሚዲያ ቢዝነስን አስመልክቶ ያዘጋጀውን ጽሑፍ ሲያቀርብ፣ መድረኩን ደግሞ እርሱ እንዲመራና ርዕሰ

ጉዳዩን እንዲያወያይ መጋበዙ የተነገረው የአውራምባ ታይምስ ጋዜጣ ማኔጂንግ ኤዲተር ዳዊት ከበደ፣ (እኔን ጨምሮ) ከሌሎች የሥራ ባልደረቦቹ ጋር ሰኞ ዕለት ማምሻውን በሥራ ቦታው እያለ ነበር አንድ ስልክ የተደወለለት፡፡

ዳዊት በነጋታው በሚካሄደው የዓለም የፕሬስ ቀን ዝግጅት ላይ የማወያየትም ሆነ መድረክ የመምራት ሚና ይኖረው ዘንድ በመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊዎች እንዳልተፈለገ በዚህ ስልክ አማካኝነት ጥቆማ ይደርሰዋል፡፡ የባለሥልጣናቱ ሁኔታ ከምን የመነጨ እንደሆነ ሁላችንም ተጠያይቀን መልስ ሳናገኝ ተለያየን፡፡

ማክሰኞ ጠዋት ለአንድ ሰዓት ያህል የዘገየው ይህ ፕሮግራም ያካተተውን መርሐ-ግብር የሚዘረዝረው ወረቀት ለታዳሚያን በሚታደል ጊዜ፣ ዳዊት ቀደም ሲል በተነገረው ርዕሰ ጉዳይ እና ሚና በዝግጅቱ እንደሚካፈል በመመልከታችን የመንግስት ባለሥልጣናቱ ሀሳባቸውን ቀይረው ይሆናል የሚል ግምት ነበረን፡፡ እናም ጋዜጠኛ ሚሚ ስብሀቱ መረሐ-ግብሩ በሚገልፀው መሠረት ሚዲያን ከሕዝብ ጥቅም ጋር በማያያዝ ፅሁፏን ታቀርባለች፣ አቶ መሠረት አታላይ ደግሞ የእርሷን ጽሑፍ ያወያያል ብሎ ታዳሚው እየተጠባበቀ ሳለ፣ አቶ ብሩክ ከበደ (ከሬዲዮ ፋና) የአወያይነት ቦታውን ያዘ፡፡ ያወያያል የተበለው መሠረት አታላይ ደግሞ እራሱን የቻለ የጽሑፍ አቅራቢ ተደርጎ ወደ መድረክ ተጠራ፡፡ ሌላም ሰው አለ፤ በጽሑፍ አቅራቢነት ወደ መድረኩ የተጠራ - የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን ዳይሬክተር፣ አቶ ደስታ ተስፋው፡፡

አቶ ደሰታም ሆኑ መሠረት አታላይ በወቅቱ ጽሑፍ ለማቅረብ

እንዳልተዘጋጁ ለታዳሚው በግልፅ ተናግረዋል፤ በተለይ አቶ ደስታ እንግድነት ተጠርተው ይሆን እንጃ እንጂ፣ መርሐ-ግብሩ ላይ ከሰፈሩት ግለሰቦች ውስጥ በጭራሸ የሉበትም፡፡

በዚህ ጊዜ የሪፖርተር ጋዜጣ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አማረ አረጋዊ፣ ፊቱን ቅጭም አድርጎ ከመድረኩ አስተናባሪዎች ጋር በሆነ ጉዳይ ይከራከራል፡፡ ጋሽ አማረ ከፕሮግራሙ አዘጋጆች መካከል አንዱ የሆነው የሆርን ኦፍ አፍሪካ ፕሬስ ኢንስቲትዩትም ኃላፊ ነው፡፡ ያልተዋጠለትና የሚያብከነክነው ነገር እንዳለ መገመት አያዳግትም፡፡ በመርሐ-ግብሩ መሠረት ‹‹የ21ኛው ክፍለ ዘመን ሚዲያ፤ አዳዲስ አማራጮች፣ አዳዲስ ጋሬጣዎች›› በተሰኘው የዩኔስኮ መሪ ቃል እና በኢትዮጵያ የሁለት አሥርት ዓመታት ሚዲያ ሥነ-ምህዳር ዙሪያ ቀጣዩን ጽሑፍ ያቀርባል ተብሎ የሚጠበቀው ጋሽ አማረ ነበር፡፡

ብዙም ሳይቆይ እነሚሚ ስብሀቱ ለሶስት ያቀረቡት ‹‹ጽሑፍ›› እና መጠነኛ ውይይት እየተገባደደ መጣ፡፡ ጋሽ አማረ አሁን መነጋገሪያውን በመያዝ ‹‹[ቢያንስ] በዓለም የፕሬስ ነፃነት ቀን “censor” ልንደረግ አይገባም›› በማለት የፕሮግራሙ አካሄድ አግባብ አለመሆኑን ተናገረ፡፡ ከዚያማ ውዝግቡ ተጧጧፈ፡፡ መድረኩን በአወያይነት ሲመራ የነበረው የሬዲዮ ፋናው አቶ ብሩክ ቦታውን ለቀጣዩ አወያይ እንዲለቅ በተጠየቀ ጊዜ እርሱ እጅ ላይ ባለው መርሐ-ግብረ መሠረት የአጠቃላዩ ፕሮግራም አወያይ እርሱ እንደሆነ ይገልፃል፡፡ እዚህ ላይ ነው አብዛኛው ታዳሚ ግራ የተጋባው፡፡ ከየት

በግዛው ለገሠ

ወደ ገፅ 18 ዞሯል

ፕሬስ እና ነፃነቱን ካብ ለካብ ያስተያየው

የፕሬስ ነፃነት ቀን

Training Courses include: -Report Writing - Advanced Writing Skills - Proposal Writing -Academic Writing -Business Writing -Presentation Skills -Facilitation Skills -Speak Easy -Train the Trainer -Pedagogic Training Unique Features of Our Trainings•Highly interactive (hands on activities) , customized, and definitely up-grading your skills•Supported by cutting edge technology•Full pack of materials: Instructor’s and participant’s manual, pre and post tests, quick-reference guide

Specialized Trainings for ProfessionalsFrom

IMPACT Research & Capacity Building

www.impactsole.comIMPACT Born to fill the gap!

Registration begins on 11 April 2011

Bole RD, DH GEDA Tower, Rm No 3-12 Call 0116 63 41 12 or 0921 78 49 33

ሰንዳፋ አካባቢ የተጀመረው የወተት ማምረት ሥራ

ወደ ገፅ 20 ዞሯል

Page 6: አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 166 ቅዳሜ ሚያዚያ 29 2003 ኢሕአዴግ … · ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ አውራምባ ታይምስ 4ኛ

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 166 ቅዳሜ ሚያዚያ 29 20036

በሼርቡርግ፣ ፈረንሳይ በ1847 የተወለደው ጆርጅስ ሶሬል በምህንድስና ሰልጥኗል፡፡ የመጀመሪያ ፅሁፉን በሰላሳ ዘጠኝ ዓመቱ በማሳተም ለፖለቲካ ፅንሰ-ሀሳብ አስተዋጽኦ ማበርከት የጀመረው አንፃራዊ በሆነ መልኩ ዘግይቶ ነው፡፡ ከስድስት ዓመት በኋላ መጠነኛ ውርስ አገኘና ከመንገድ መሀንዲስነት ሙያው

በመውጣት ትኩረቱን በጥናት እና በፅሁፍ ላይ አደረገ፡፡ በፍልስፍና ዙሪያ፣ በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚክስ እና በማህበራዊ ፅንሰ-ሀሳቦች ላይ የፃፈ ሲሆን ሁሉንም ጉዳዮች በአብዛኛው እራሱን በማስተማር አማካኝነት የደረሰባቸው ናቸው፡፡ የሶፌል ይበልጥ የሚታወቁት “Reflections on Violence” እና “The Illusions of Progress” ሥራዎቹ ሁለቱም የታተሙት በ1908 ነው፡፡ ጥልቅ ግንዛቤዎች እና ጉልህ የመጀመሪያነት ይዘት ያለባቸው ሥራዎችን ያቀረበው ሶሬል በምሁራዊም ሆነ በፖለቲካዊ ረገድ እረፍት የለሽ ነበር፡፡ የቡርዥዋ ፖለቲካን እና ባህልን አምርሮ ይጠላል፤ እንዲሁም በአብዛኛው እራሱን በግራ ዘመሙ ፖለቲካ በኩል ይመለከታል፡፡

ሶሬል በ1892 ገደማ ከተለመደው ወጣ ያለ ማርክሲስት ሆኖ ነበር፤ ሆኖም ከዚያ በኋላ በአዲሱ ክፍለ ዘመን መግቢያ የእምነቱን አቅጣጫ ወደ አናርኪዝም ለወጠ፡፡ ከመጀመሪያው የዓለም ጦርነት በፊት በነበሩት ዓመታቶች ከፀረ-ፓርላማዊ ሥርዓት ሩቅ ቀኝ ዘመሞች ጋር ህብረት ፈጥሮ ነበር፤ ሆኖም ይህ የሆነው የሩሲያ አብዮት እርሱ ለሚደግፋቸው ሀቀኛ የሠራተኛው ህብረቶች ሥልጣን የመያዝን እድል (ኋላ ውሸት ሆኖ ቢገኝም) የሚያቀርብ ሲመስል በድጋሚ አቋሙን ከመቀየሩ በፊት ነው፡፡ ሁሉም ፓርቲዎች እርሱ በተለየ ሁኔታ በሚጠላው ቡድን ማለትም በመሀከለኛው መደብ ምሁራን ቁጥጥር ስር እንደሆኑ በማመን የትኛውንም የፖለቲካ ፓርቲ ተቀላቅሎ አያውቅም፡፡ ሶሬልን በተለመደ አገላለፅ ለመመደብ የማይችል ነው፤ እንዲሁም እጅግ ከፍተኛው ተፅዕኖ በፋሺዝም መነሳት ላይ ያሳደረው ሳይሆን አይቀርም፡፡ በ1922 ሞተ፡፡

ሶሬል የወቅቱን የምዕራቡን ሥልጣኔ እየከሰመ እና እየሞተ እንደሆነ አድርገው ከተመለከቱት - ኒቼ፣ ማክስ ዌበር እና ኦስዋልድ ስፔንግለርን ጨምሮ - ከአያሌ የክፍለ ዘመኑ መሸጋገሪያ ፈላስፎች መካከል አንዱ ነበር፡፡ የቡርዥዋን ባህል በማውገዝ እና መንግስት ማንሰራራት በማይችልበት ሁኔታ እንዳበቃለት በመቀበል እምነቱን ክህሎት ባለው የሠራተኛው መደብ ላይ ጥሏል፡፡ ተጠራጣሪ፣ ነቃፊ እና ፀለምተኛው ሶሬል የሀገራትን የይስሙላ እድገት ወይም መሻሻል ያወግዛል፡፡ ይበልጥ ከባድ የነበረውን የጥንታዊውን ዓለም የተዋጊነት እሴቶች ያደንቃል፤ በተለይ በሪፐብሊካዊዋ ሮም የተመለከተውን ወኔ፣ ጥንካሬ፣ ታታሪነት፣ በሞራል ትክክለኛ ጠባይ እና አርበኝነት፡፡ ታሪክን እነዚህ የሞራል እሴቶች ግንባር ቀደም የሚሆኑባቸው የጠንካራነት ዘመናት እና የመንኮታኮት ዘመናት ተደጋጋሚ መለዋወጥ አደርጎ ተመልክቶታል፡፡ እናም የእርሱ ተስፋ የቡርዥዋን ውድቀት እና የበላይነት ጠራርጎ የሚያስወግድ አዲስ የታታሪነት ዘመን ነበር፡፡ እንዲህ ላለ ዓላማ ብቸኛው ምቹ መሣሪያም የሠራተኛው መደብ ነበር፡፡ ጥያቄው ግን በቀድሞዎቹ የተዋጊነት እሴቶች (ሠራተኞቹ) እንዴት ሊሞሉ ይችላሉ የሚለው ነበር፡፡

የመደብ ግጭት (ብጥብጥ) እና አብዮት ህብረተሰብን ቀይሮ እነዚህን እሴቶች ወደቀደመ ቦታቸው ሊመልሳቸው እንደሚችል ሶሬል ያምናል፡፡ ዓለምን እና እራሳቸውን በባለቤትነት በመያዝ እርምጃ በሚነፃው እና ሽግግር በሚያደርገው የተካነ የሠራተኛው መደብ የሚመራ የህብረተሰብ አብዮታዊ ለውጥን ወይም ሽግግርን ተመልክቷል፡፡ ከካርል ማርክስ ጋር ተመሳሳይ ነገር አላቸው፡፡ ሶሬል የማርክስ አድናቂ ሲሆን ተፅዕኖውም አድሮበታል፤ ሆኖም የበርነስታይንን የከላሽነት (revisionism) ሂሶች ሙሉ ለሙሉ ይደግፋል፡- - የሄግል ጎጂ ተፅዕኖ የታሪካዊው ቁስ አካልነት (materialisim) በእውነት ላይ አለመመስረት፣ የወዝአደሩ (proletariat) አምባገነናዊነት ተገማችነት የለሽ እና የማይሆ መሆን፡፡ ይሁንና የበርነስታይንን አንድ ሶሻሊስት ፓርቲ ለሰላማዊ የፓርላማ ሥርዓት መሳካት ላይ ያተኩራል የሚሉውን አማራጭ ሊቀበለው አልቻለም፡፡ ምንጊዜም ቢሆን ፓርቲዎች እርሱ እጅጉን በሚጠላው በመሀከለኛው መደብ ምሁራኖች ቡድን የበላይ ቁጥጥር ስር ናቸው፤ በሠራተኛው መደብ ፓርቲዎችም ቢሆን ይህ እውነት ነበር፡፡ ሶሬል መንግስት እና የፖለቲካ ፓርቲዎችን ማውገዙ ወደ ማህበራዊ አናርኪስት ልማድ፣ በተለይም ይበልጥ የቅርብ ወደሆነው የሲኒዲካሊስት ይዘቱ ፊቱን እንዲያዞር አደረገው፡፡

(የአናርኪዝም ተቀፅላ የሆነው “አናርኮ-ሲንዲካሊዝም” በማርክሲዝም ሌኒኒዝም መዝገበ ቃላት ውስጥ ‹‹በአጠቃላይ የፖለቲካ ትግልን የማይቀበል፤ በሠራተኞች ንቅናቄ ውስጥ የሠራተኛ ማህበርን እንደብቸኛ ድርጅት አድርጎ የሚመለከት፤ የሥራ ማቆም አድማን ለሠራተኛው የሚበጅ ብቸኛ የትግል ስልት አድርጎ የሚቆጥር›› ተብሎ ተገልጿል፡፡ አናርኮ-ሲንዲካሊስቶቹ ደግሞ ‹‹ሠራተኛው ሥልጣን ሳይዝ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ የሚሰራባቸውን ፋብሪካዎች ከነቅርንጫፎቻቸው የራሱ በማድረግ

አካባቢውን መምራት አለበት ብለው የሚሟገቱና ለሶሻሊዝም ግንባታ የግንባር ቀደም ፓርቲ መኖር እንደማያስፈልግ የሚሰብኩ›› ተብለው ተጠቅሰዋል፡፡)

አናርኮ-ሲንዲካሊዝም በአስራዘጠነኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ የተነሳ ሲሆን ሙሉ ለሙሉ የዳበረውም በፈረንሳይ ነው፤ ከሠራተኛ ማህበራት ጋር የተቆራኘ የአናርኪዝም ዓይነት ነበር፡፡ እንደውም ሕገ-ደንብም ሆነ አደረጃጀት የነበረው ብቸኛው የአናርኪዝም ዓይነት ነው፡፡ ሀሳቡ የሠራተኛ ማህበራቱ ብቻቸውን ናቸው አጠቃላይ አመፅን ወይም አድማን እንደመሣሪያ በመጠቀም አብዮትን ለስኬት ሊያበቁ የሚችሉት የሚል ነበር፤ ከዚያ በኋላም የመሀከለኛው መደብ ፖለቲከኞች ፓርቲዎች ሳያስፈልጉ በሠራተኛ ማህበራት በፈቃደኝነት ላይ የተመሠረተ ህብረት አማካኝነት ህብረተሰብን ይመራሉ ይላል፡፡ አብዛኛቹ የፈረንሳይ ማህበራት በዚያን ወቅት አነስተኛ፣ አካባቢያው እና በዕደ ጥበባት ላይ መሠረት ያደረጉ እንደመሆናቸው በሀሳቡ ላይ የተጠቀሱትም ፕሮፌሽናል ብሔራዊ አመራሮች ያሉባቸው የብዙሃን ማህበራት አልነበሩ፡፡ እናም በእነዚህ ማህበራት አማካኝነት ሠራተኛው ሀቀኛ በሆነ መንገድ ኢኮኖሚውን እና ህበረተሰብን ሊቆጣጠር ይችላል፡፡ የሶሬልን ትኩረት የሳበው ይህ ነበር፡፡

ሶሬል እራሳቸውን በሚያስተዳድሩ ሠራተኞች ስር አዲስ የምርት ዘመን ታይቶታል፡፡ የሶሻሊስ ትጋቶቹ በኖሩም ሊጠበቅ እንደሚችለው ያህል የካፒታሊዝም ጠላት አልነበረም፡፡ የግል ንብረትን አይቃወምም፤ ይልቁንም ለግላዊ እራስን መቻል አስፈላጊ ድጋፍ እንደሆነ አድርጎ ይመለከተዋል፡፡ በተጨማሪም ነፃ ገበያን እንደ የታታሪነት እና የኢንተርፕራይዝ ማበረታቻ የተመለከተው ሲሆን ከሁሉን-አቅራቢ መንግስት እሳቤ ጋር እጅጉን ጠላት ናቸው፡፡ ካፒታሊስቱን እንደታላቅ የሥራ ፈጣሪ ባይመለከተውም የሠራተኛው በዝባዥ ስለመሆኑ ሙሉ ለሙሉ አይቀበልም፡፡ እንዲሁም እድገትን ዓለምን ወደ ቡርዥዋዊነት ከመለወጥ ጋር የሚያያይዙ እሳቤዎችን የሚቃወም ቢሆንም በኢኮኖሚያዊ እና ቴክኖሎጂያዊ እድገቶች በእርግጠኝነት ያምናል፡፡ ወደፊት የሚመጣውም የከፍተኛ ምርት እና የቴክኖሊጂ ምጥቀት ዓለም ነው፡፡

ከአብዮት እና ከለውጥ ሂደቶች ጋር ሲነፃፀር ሶሬል ወደፊት ስለሚመጣው ህብረተሰብ ዝርዝሮችን በማስቀመጥ ረገድ አነስተኛ ትኩረት ነበር የሰጠው፡፡ የእድገትን የልል ሊበራል እሳቤዎች በመቃወምም በሰዎች ዘንድ ተነሳሽነትን የሚፈጥረው የህሊና ብቃት ሳይሆን የውስጥ ስሜት እንደሆነ ያስረግጣል፤ እንዲሁም በገሀዱ ፖለቲካ ውስጥ ታላላቅ ንቅናቄዎችን የሚያንቀሳቅሱትና መነቃቃትን የሚፈጥሩት አፈ-ታሪኮች (myths) እንጂ ፅንሰ-ሀሳቦች አይደሉም፡፡ “Reflections on Violence” በተሰኘ ሥራው ለሃይማኖታዊም ሆነ ፖለቲካዊ ንቅናቄዎች የመንፈስ መነቃቃት ሆነው የቆዩትን አፈ-ታሪኮች “ማህበራዊ ቅኔዎች” ብሎ በመጥራት ይዳስሳቸዋል፡፡ እነዚህ አፈ-ታሪኮች እርሱ ሠራተኛውን መደብ የሚበዘብዙትና ወደ የዝግታ ለውጥ (reformisim)

የፖ ለቲካ ፈ ላ ስፎችበግዛው ለገሠ

ኢያን አዳምስ እና አር. ደብሊው. ዴይሰን በጋራ ባሰናዱት “FIFTY MAJOR POLITICAL THINKERS” መፅሐፋቸው

ከቀደምት አንስቶ እስከ ቅርብ ጊዜ ካሉት ውስጥ አምሳ የፖለቲካ ፈላስፎችን በመምረጥ ለዓለም አስረክበው ያለፏቸውን

ፖለቲካዊ እሳቤዎች በዝርዝር አዋቅረው አቅርበዋቸዋል፡፡ እኛም ለአንባቢ በሚያመች መልኩ እንዲህ አቅርበናቸዋል፡፡

የሚመሩት የቡርዥዋ ምሁራን ውጤቶች ናቸው ብሎ ከሚያስባቸው ‹‹ዩቶፒያዎች›› ጋር ሊምታቱብን አይገባም፡፡ በክርስቲያን የፍርድ ቀን እምነትን፣ በማዚኒ በጣሊያን የብሔረተኛ ትራንስፎርሜሽን እምነትን፣ በማርክሲስት ደግሞ የወዝአደሩ አብዮት እምነትን እንደ የአፈ-ታሪክ ምሳሌዎች ይጠቅሳቸዋል፡፡

ሶሬልን ወደማርክሲዝም የሳበው እጅግ የተወደሰለት ሳይንሳዊ ይዘቱ አልነበረም፤ እንዲያውም መሠረተ ቢስ እንደሆነ በመግለፅ አይቀበለውም፡፡ ነገር ግን ለማርክሲዝም ትኩረት እንዲሰጥ ያደረገው የማዕከላዊ አፈ-ታሪኩ ኃይል ነበር፡፡ የትኛውም ዓይነት ፅንሰ-ሀሳብ ወይም ምክኑያዊ ስሌት በሰዎች ላይ ስኬታማ አብዮትን ለማካሄድ አስፈላጊ ስለሆኑት ሥነ-ሥርዓት የመላበስ፣ የወኔያምነት እና እራስን መስዋዕት ለማድረግ የመዘጋጀት ምግባሮች መንፈሳዊ መነቃቃትን ሊያመጣ እንደማይችል ያስባል፡፡ ይህንን ሊያደርጉ የሚችሉት አፈ-ታሪኮች ብቻ ናቸው፡፡ ሶሬል አፈ-ታሪክ ወይም “myth” ሲል ዓለም በሆነ ድንገተኛ ክስተት የምትለወጥበት የወደፊት ራዕይ ማለቱ ነው፡፡ ከዚህ ራዕይ አንፃር ሰዎች የኋላ ኋላ በመጨረሻው ሁከት ወይም ብጥብጥ ድልን እንደሚያስጨብጠው ትግል አንድ አካል ህይወታቸውን ማነፅ ይችላሉ፡፡ እነዚህን አፈ-ታሪኮች እጅግ ኃያል እና አሳማኝ የሚያደርጋቸው ሙሉ ለሙሉ በእምነት ላይ የተመሠረተው ድል የማድረግ እርግጠኝነት ነው፡፡

ይሁንና ሶሬል የአፈ-ታሪክ ፅንሰ-ሀሳቡን በቀመረ ጊዜ ፍላጎቱ ወይም አትኩሮቱ ከማርክሲስት የወዝአደር አብዮት አፈ-ታሪክ ወደ አናርኮ-ሲንዲካሊዝም አፈ-ታሪክ አቅጣጫውን ቀይሯል፡፡ ይህ የአናርኮ-ሲንዲካሊዝም አፈ-ታሪክ የካፒታሊዝምን መውደቅ የሚያመጣ፣ ቡርዥዋዚን የሚያወድም እና ሠራተኛውን የበላይ ተቆጣጣሪ የሚያደርግ የአጠቃላይ አመፅ ወይም የሥራ ማቆም አድማ ራዕይ ነው፡፡ ሠራተኞቹ በትግሉ እራሳቸውን አጠናክረውና ታንፀው፣ ለሥራቸው እና ለባልደረቦቻቸው ትጉህ እና ታማኝ ሆነው፣ እንዲሁም ቤተሰብ ላይ ማዕከል ላደረገ ማስታወቂያ

ጥብቅ የሞራል ሕግ ተገዢ ሆነው አዲስ ‹የምርት ሂደት ሥነ-ምግባር› ቀዳሚነቱን ይቆናጠጣል፡፡ እንደህ ዓይነቱ ህብረተሰብ አንድ የገበያ ኢኮኖሚ የሚያስፈልገውንና ቡርዥዋዚው አጥቶት የነበረው የፈጠራ እና የማሻሻል ችሎታን የሚያፋጥን የሥራ ፈጣሪነት መነቃቃትን ለማቅረብ ሥነ-ምግባሩ እና ኃይሉ ይኖረዋል፡፡

በመደበኛው ሰዓት፣ ከአጠቃላዩ የሥራ ማቆም አድማ በፊት ሠራተኞች ከቡርዥዋ ፓርቲዎች ወይም ፓርላማ ጋር በመቀላቀል እራሳቸውን ለውድቀት ሊዳርጉት አልያም ለቡርዥዋ የመሻሻል ማባበያዎች ሊሸነፉ አይገባቸውም፡፡ ሠራተኞቹ በመጋፈጥ እና በብጥብጥ የመንፈስ ንፅህናቸውን አጠናክረው ሊቀጥሉበት ይገባል፡፡ እዚህ ላይ ብጥብጥ ሥልጣኔን ለማደስ እና ለማቆየት አስፈላጊ ሆኖ ታይቷል፡፡

በሌላ በኩል፣ ብጥብጥ ናፋቂ እና ኃይል አወዳሽ ቋንቋ በመጠቀም ይታወቅ እንጂ ሶሬል የብጥብጥ አቀንቃኝ የመሆኑ ነገር የማያሻማ አይደለም፡፡ በወቅቱ በአናርኪስት አብዮት ስም ይደረጉ የነበሩትን ህሊና የለሽ ጭፍጨፋ እና ግድያዎችን ይጠላል፣ እንዲሁም ለቴክኖሎጂ ከነበረው ስሜት ጋር ዓላማውን የሳተ የሚለውን የኢንዱስትሪያዊ ሻጥርን ሳይቀር ይጠላል፡፡ ብጥብጥ ለራሱ ለአብዮቱ ነው፤ ሶሬል አንዳንድ ጊዜ ሥርዓት ያለው እና ከሞራል አንፃር ቁርጠኛ የሆነ ወዝአደር የከፍተኛ ብጥብጥ ስጋትን ማሳደሩ ብቻ መሀከለኛውን መደብ ለማራድ ወይም ለማርበድበድና አዲስ ሥርዓት ማስፈለጉን እንዲቀበል ለማድረግ በቂ እንደሆነ ቢያስብም፡፡

በአጠቃላይ በአፈ-ታሪክ ላይ መሠረት ያደረገው የሶሬል በሠራተኛው ብዙሃን አብዮታዊ ብጥብጥ አማካኝነት የሙሉ ለሙሉ ሽግግር አጠቃላይ ጭብጥ እጅግ ከፍተኛ ተፅዕኖውን ያሳረፈው ከሶሻሊስቶች ወይም ከአናርኪስቶች ይልቅ በፋሺስቶች ላይ ነበር፡፡

የሠራተኛ ማህበራትን መሠረት ያደረገ አብዮትጆርጅስ ሶሬል /1847-1922/

Page 7: አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 166 ቅዳሜ ሚያዚያ 29 2003 ኢሕአዴግ … · ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ አውራምባ ታይምስ 4ኛ

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 166 ቅዳሜ ሚያዚያ 29 2003

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

7

የ አቤቶ ወግአቤ ቶክቻው[email protected]

Page 8: አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 166 ቅዳሜ ሚያዚያ 29 2003 ኢሕአዴግ … · ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ አውራምባ ታይምስ 4ኛ

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 166 ቅዳሜ ሚያዚያ 29 20038

ጠያቂ አላገኘም ያገር ልጅ ዘመድ፣

ብሶቱን ተካፍሎ ርሀብ የሚያበርድ፡፡

ይሄ ኑሮ ነው ወይ የኑሮ እኩሌታ፣

ዳዴ! አይል ወይ አይቆም ሁልጊዜ አንድ ቦታ፡፡

(ይልማ ከበደ1954)

ተወደደም ረከሰ፣ በየሱቁ ይገኝ የነበረ ስኳር እንደ ሜርኩሪ ሆነና አረፈው፡፡ ይህንን አባባል ብዙ ጸሐፍት ስለተጠቀሙበት አልደግመውም፡፡ ሳሙና ዋጋው ከተተመነ በኋላ ይበልጡን ዋጋው ተወደደ፡፡ ዘይት ከቀን ቀን ከዋጋው እየጨመረ ከስርጭቱ እየቀነሰ መጣ፡፡ (ወይ እዳ) በገዛ ሀገራችን መታወቂያ ካላመጣችሁ አትገዙም መባል ተጀመረ፡፡ ይሁና፤ የተኛንበት ዘመን ብዙ ነውና ይበለን፡፡ ነጋዴ ከቀን ቀን ዋጋ ሲጨምር አሜን እያልን እየተቀበልን፡፡

እላለሁ ነጋዴዎች ተገቢውን ዋጋ ብቻ ያስከፍሉ፡፡ የዕለት ከዕለት የፍጆታ ሸቀጦችን በብዛት ያቅርቡልን ብሎ መጠየቅ አመጽ ማስነሣት ሳይሆን፣ መብትን ማስከበር መብትን መጠየቅ ነው፡፡ ነገሩ እንዲህ ነውና . . . ነጋዴ ሕዝብን ያለመበዝበዝ ግዴታ ያለበት ሲሆን፣ ሕዝብ ደግሞ በነጋዴ ያለመበዝበዝ መብት አለው፡፡

ነጋዴ እና ቸርቻሪ ነን ባዮች ሕዝቡን ጨርቁን አስጥሎ ለመስደድ ቆርጠው የተነሱ ይመስል ከመንግስት ጋር እሽቅድምድም ይዘዋል፡፡ መንግስት ዋጋ ተምንኩ ሲል፣ እነሱ ከላይ ከላይ ዋጋ ይጨምራሉ፡፡ ሸማቹ

ጥም ብ -አ ን ሳ ዎ ች የ ሞ ተ እ ን ስ ሳ ከ በ ው ለመብ ላ ት

የሚጣደፉትን ያህል፣ ሰባራ ራስ ያለው፣ ጥፍሮቹ የተሞረዱ፣ ፀጉሩ የተንጨባረረ እና እርስ በእርስ እየተጋጩ የሚያፏጩ ጥርሶች የተቸረው ድብርት ዙሪያዬን በመንፈሱ አጥሮ ሊሰለቅጠኝ ሲል፣ የፃድቃንን ብርታት ተውሼ ‹‹ነፃ›› ወደሚያወጣኝ መሳቢያ ተፈተለኩ፡፡

አሳዳጄ ብቻውን ቢሆንም፣ ‹‹ግር›› ብሎ ነው የመጣብኝ፤ እልፍ እልፍ እያልኩ አንገቴን ቆልመም በማድረግ ስመለከተው፣ ሻካራ መዳፉ ውስጥ አስገብቶ የዕለት ፀሐዬን ሊጨልምብኝ ከሚግ 29 ጄት በላይ ይምዘገዘጋል፡፡

እኔም፣ ዕለታዊ ፀሐዬም ‹‹ብራ›› ሆነን ለመዋል ካለን ግዙፍ ፍላጎት የተነሳ፣ የድል ዋዜማ ቃና ያለው ትንፋሽ እኔ እየተነፈስኩ መሳቢያው ጋር ብደርስም፣ ነፃ መውጣት መች እንዲህ ቀላለ!? ያስባለኝ ውጥን ተወጥኖ ጠበቀኝ፡፡

አዎ! ከ’ግር ጥፍሬ እስከ ራስ ፀጉሬ ነፃ አውጪዬ ነው ብዬ የተማማልኩለት መሳቢያ ተቆልፏል፡፡ መሳቢያው ተከፍቶ በውስጡ ካለው ሳንቲም ቆንጥሬ በመውሰድ በለመድኩት አኳኋን ካልተምነሸነሽኩ፣ የተንጠፈጠፈ ኪሴን አይቶና አድብቶ ያሳደደኝ አውሬ (ድብርት) እንደሚንቀረቅበኝ የቆየ ልምድ አለኝ፡፡

መሳቢያውን የቆለፈው ሰው መክፈቻውን አርቆ እንዳስቀመጠው ጭምጭምታ ሰማሁ፡፡ ጠላቴ የስፕሪንግ ያህል የሚተጣጠፍና የሚዘረጋ ዕጁን ሲሰነዝርብኝ፣ ድቡልቡል አናቴን ልሙጥ መሬት አስመስለው፡፡ ዕለታዊ ፀሐዬም ወዲያው ጨለመች፤ እኔም

ኮሜንተሪ

መሳቢያውን በቆለፈው ሰው ላይ ቂም ቋጥሬ ግንኙነቴን ፈታሁት፡፡

... ጌትነት (ጌታመሆን) ብዙዎች የሚመኙትና የሚናፍቁት የሕይወት ዘመን መልካም አጋጣሚ ነው፡፡ በማጭበርበርም ሆነ በትህትና ጌታ ለሆነ ሰው ብዙዎች ያሸረግዳሉ፤ ይሰግዳሉ፤ አንዳንዴም ግለሰቡን (ጌታ-ውን) ያመልኩታል - ተከታዮቹ፡፡

የአንድ መንደር ጌታ መሆን ትንሽ ሥልጣን አይደለም፤ ያ’ንድ ሀገር ጌታ መሆን ደግሞ፣ የጌትነት ወርድና ቁመቱ በሰማኒያ ሚሊየን ሕዝብ ልክ የተለጠጠ ሥልጣን ያጎናፅፋል፡፡ በእርግጥ በአንዲት ሀገር ላይ አንድ ጠቅላይ ጌታ ቢኖርም፣ በየተዋረዱ ብዙ ‹‹ክፍት›› እና ‹‹ነፃ›› መሆን የሚገባቸውን ጉዳዮች በመቆለፍ ነዋሪዎችን የሚያስለቅሱ ጥቃቅንና ጎረምሳ ጌቶች አሉ፡፡

በተለይ ይህ ወቅት በጣም አያሌ ክፍት ሊሆኑ የሚገባቸው ጉዳዮች የተቆለፉበት በመሆኑ፣ ‹‹ለምን?›› ማለት ተገቢ ጥያቄ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ በዚህ ሰዓት ምንም ዓይነት ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማሕበራዊ ቁልፍ በነዋሪው እጅ የለም፡፡ ይህ ደግሞ መንግሥት በፈለገው ሰዓት የፈለገውን መስክ ይከፍታል፣ ቀልቡ ያላረፈበትን ደግሞ ይቆልፋል ማለት ነው፡፡

የአንድ ጌታ የበላይነት፣ አለ ቅጥ በተስፋፋ ቁጥር ሀገሪቱ ፍፁም ወደ ሆነ ቁልፍልፎሽ ከመሸጋገሯ በላይ፣ ዜጎቿ ከጌቶች ጋር አላስፈላጊ ውጥንቅጥ ውስጥ ይከረቸማሉ፡፡

አንድ ሰው የተቆለፈበትን መስክ ለመክፈት አስቀድሞ ቁልፍ ይጠይቃል፤ የቁልፉ ጌታ አሻፈረኝ ካለ፣ ቁልፍ ጠያቂው ወደ ሰበራ (መስበር) ያመራል፡፡ እንግዲህ ይሄ የሚሆነው በቁልፍ ጠያቂው ሥርዓት አልበኝነት ሳይሆን፣ በቁልፍ ሰጪው ‹‹ግትር›› አቋም ምክንያት ነው፡፡

ለምሳሌ፣ ያሁኗ ኢትዮጵያ ፖለቲካ አናት ላይ የአንድ ፓርቲ ‹‹ጋን›› ተንጠልጥሎ ይታያል፡፡ አንዲት ትልቅ ሀገርን በአንድ ፓርቲ ፖለቲካዊ አቋም ብቻ መቆለፍ የሚመራቸው እንጂ የማይጥማቸው ወገኖች፣ የፖለቲካው መስክ ተከፍቶ ጉራማይሌ አቋማቸውን የመስኩ አንድ አካል አድርጎ ማካተትን ይፈልጋሉ፡፡

ፍላጎታቸው በግትር አቋም የሚጨነግፍ ከሆነ፣ እንደ ድንኳን ሰባሪ ወደ ቁልፍ ሰበራ ያመራሉ፡፡ በእርግጥ ‹‹ሰበራ›› ከቃሉ ጀምሮ የሽብርተኝነት መንፈስ ያለበት ክስተት ነው፡፡ ነገር ግን ፖለቲካዊ ሰበራ እንዲካሄድ እና በየቦታው ምሽጎች እንዲቆፈሩ ምክንያት የሚሆነው ‹‹መንግሥት›› ነው፡፡ ምክንያቱም የሌሎቹን አቋም የመቀበል ፍላጎቱ የወረደ ነው ከሚባል፣ የተዘጋ ነው ቢባል ይሻላል፡፡

አይከብድም? ይከብዳል እኮ! አንዲት ዘርፈ-ብዙ (በታሪክም በአስተሳሰብም) የሆነችን ሀገር በአንድ ሰገነት ሥር ሰብስቦና በአንድ ጋን ጠፍሮ ‹‹ቼ በለው›› ማለት የሰማኒያን ክፍልፋይ (Fraction) አለመረዳት ይመስለኛል፡፡

ፖለቲካው በመንግሥት አቋም

ብቻ ተጠቅጥቆ በመቆለፉ አይደል እንዴ ብዙ ኢትዮጵያውያን ውጪ ባህር ማዶ ማደር የጀመሩት? . . . መከፈት አለበት፤ ተከፍቶም ብዙዎች ወደ ሀገራቸውና ወደ ፖለቲካው መስክ መግባት አለባቸው፡፡ ተባብረው ያቆሙት ቤት ቢፈርስ እንኳን በደቦ ይገነባል፤ አንድ ሰው ‹‹ብቻዬን›› እገነባለሁ ሊል ይችላል፤ ሊገነባም ይችላል፡፡ ግን ግንባታው ዘመናትን እየፈጀ አፋጣኝ ልማት የሚፈልጉ ዜጎች ፍላጎታቸው ሳይሰምር ቢያልፉስ?

ለብቻ መኖር ይቻላል፤ ግን ኢትዮጵያ ከ’ግር ጥፍሯ እስከ ራስ ፀጉሯ ድረስ ገዳም አይደለችም፤ ብትሆን ነበር በአንድ ልብስና በአንድ ፀሎት መመራት የምትችለው፡፡ ፀሎትን የሚያምኑ ሰዎች ብቻ ይኑሩ ቢባል የአቋም መዘበራረቅ ይመጣል፡፡ ስላልተባለም ፀሎተኛውም ግብዙም አብረው እየኖሩ ነው፡፡ የፖለቲካው መስክም አብዮታዊ ዴሞክራሲን ብቻ ሳይሆን፣ ሌሎችንም ማቀፍና ከብዙሀን ጋር ተባብሮ መስራት አለበት፡፡

ለምንድነው ኢኮኖሚው አንደርቢ ይመስል በአንድ ወቅት ብቻ እየተነሳ (እየተከፈተ) ቁርጠኛ የሚሆነው? ለምን ቀን በቀን ወለል

ተደርጎ ተከፍቶ ሸማቹ በፈለገበት ሰዓት እንዲሸምት አይደረግም? የመኖር ነፃነት በተለያዩ ሰው ሰራሽ ችግሮች እየተጠፈነገ ነዋሪው መፈናፈኛ የሚያጣው ለምንድን ነው? . . . መልስ ይፈልጋሉ ጥያቄዎቹ፡፡

የኢሕአዴግ አገልጋዮች ግን የእያንዳንዱ እንቅስቃሴ ቁልፍ በእጃቸው ነው፡፡ ምክንያቱም የአብዩቱ አገልጋዮችና ታማኝ ጠባቂዎች በመሆናቸው፣ የምስጢር ቁልፍ ሳይቀር ይሰጣቸዋል፡፡ ቁልፉን እያንሿሹ በሲቪሉ ኅብረተሰብ አጠገብ በማለፍ ‹‹ቁልፍ ሰው›› መሆናቸውን ነግሮ ለማስጎምዥት ከፍተኛ ዘመቻ ይከፍታሉ፡፡

የዘመቻቸው አስኳል ደግሞ መላው ነዋሪ በአንድ የአስተሳሰብ ጥላ ሥር ተሰባስቦ ድጋፍ እንጂ፣ ተቃውሞ እንዲያሰማ ማድረግ ነው፡፡ ከዕምነታቸው ጋር ኅብረት የሌላቸው ዜጎች መንገዳቸው ይቆለፍባቸዋል፡፡

ነገር ግን የሰው ልጅ መብቶች እስከ ሰይጣን ድረስ የተለጠጡ ናቸው፡፡ በአምልኮ ደረጃ እንኳን የፈለገውን የማመንና የመከተል መብት አለው - የሰው ልጅ፡፡ ወደ ፖለቲካው ሲመጣ ደግሞ ከዛ ከፍ ሊል ይገባል እንጂ፣ አንድ ፓርቲ በሰራው ጎጆ ውስጥ ታጉራችሁ፣ ‹‹እኔ ያላንቺ መች ያምርብኛል››ን አቀንቅኑ ማለት ከአማልክት እንበልጣለን እንደማለት ነው፡፡

. . . ብዙዎች ነፃ ወደሚያወጣቸው ፍትህ ይሮጣሉ፡፡ ግን ሁሉም የተመኩበት ፍትህ ነፃ ያወጣቸዋል? የፍትህ ጠኔ ወግሯቸው አሰቃቂ ኑሮ የሚኖሩ ዜጎች የሉም? በአሳዳጃቸው በኢ-ፍትሀዊነት ተሰልቅጠው የተበሉ ነፃነት ናፋቂዎች በኢትዮጵያ ምድር የሉም ተብሎ ይታመናል? . . . አይታመንም፡፡ አቤት ምን ያልተቆለፈ መስክ አለ?

ግን የእነሱን ጭማሪ ያክል እድገት በየወሩ እንደማያስመዘግብ የታወቀ ነውና ግራ መጋባትን ሲጋፈጥ ይስተዋላል፡፡

መንግስት ኑሮን አረጋጋሁ ብሎ የዋጋ ተመን አወጣ - ቢተምንም ባይተመንም ለውጥ የሌለውን የቢራን ዋጋ ጨምሮ ማለቴ ነው፡፡ በሌላ ጽሑፌ እንዳልኩት፣ የእኛ የዕለት ምግብ ዕንጀራ በወጥ፣ እንጅ ቢራ እና ለስላሳ አይደለም፡፡ ተመኑ በወጣ ሰሞን ያኮረፉ ነጋዴዎች፣ እቃዎች ተደርድረው እያየናቸው ‹‹የለም›› ሲሉ ከረሙ፡፡ ዋጋ መለጠፍ ግዴታ ነው ቢባልም፣ በብጣሽ ወረቀት ሞነጫጭረው የለጠፉት የዋጋ ዝርዝር ሸቀጥ ሊሆን አልቻለም፡፡ የለም በማለታቸውም ገፉ፡፡

ሸማቾቹ በእጃቸው ላይ የነበሩ ጥሬ እቃዎች ሲያልቁ፣ መንግስትም የተጨበጠ አማራጭ ማቅረብ ሲሳነው፣ ስግብግብ ነጋዴዎችን ደጅ መጥናት ጀመሩ፡፡ የለም ሲሉት በነበረው ሸቀጥ ላይ ከፍ ያለ የዋጋ ጭማሪ አድርገው ‹‹አለ›› ማለት ጀመሩ፡፡ ይህንን ያዩ

አንዳንዶች መንግስት የዋጋ ተመን ብሎ ባይነካካቸውና ባያስጨርሰን ይሻል ነበር ሲሉ ተደመጡ፡፡

ይህ መተረማመስ ወራትን ተሻግሮ እንደ ከዚህ በፊቱ ድስት ጥዶ የዘይቱን ማለቅ ያየ ሮጥ ብሎ ከሱቅ ማግኜት አልቻለም፡፡ ብዙዎችም ቡና በጨው ሳይወዱ ለመጠጣት ተገደዱ፡፡ ልብሳቸውን በአመድና በእንዶድ ማጠብ እስኪከጅሉ ድረስ የሳሙና ዋጋ የማይቀመስ ሆነ፡፡ አሁን ደግሞ መንግስት የቸርቻሪነትና የአከፋፋይነት መብቱን መንግስት ነክ ለሆኑ ተቋማት አሳልፎ ሰጥቷል፡፡ እውነት ይሄ ግና እስከምን ድረስ ያስኬዳል;

ግራ ቀኙን ለማዬትአንድ፡- ለመንግስት

መስሪያ ቤት ሰራተኞች የደሞዝ ጭማሪ ከመደረጉ በፊት ደሞዝ ሲጨምር አብረው ዋጋ የሚጨምሩትን ነጋዴዎች ለመቆጣጠር ተብሎ የዋጋ ተመን መደረጉ በብዙ ሚዲያዎች ተወራ፡፡ ደስ ብሎን ሳናበቃ የደሞዝ ጭማሪው ምን ያክል እንደሆነ

ሳናውቅ የዋጋ ጭማሪን መንግስት ራሱ አንድ ብሎ ጀመረው፡፡ ማባሪያና ማቆሚያ ያጣው የየወሩ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ያልነካካው ማን አለ;

በመጀመሪያው ወር የትራንስፖርት ወጭው አንድ መቶ ብር የነበረ ግለሰብ፣ በሁለተኛው ወር ወደ አንድ መቶ አስራ አምስት ብር፤ በሶስተኛው ወር ወደ አንድ መቶ ሃያ አምስት ብር፤ በአራተኛው ወር ወደ አንድ መቶ ስልሳ ብር እያደገ ይገኛል፡፡ ለመሆኑ የትኛው ኢትዮጵያዊ ሰራተኛ ነው በየወሩ ይህንን ያክል ጭማሪ መሸከም የሚችለው; በደሞዙ ወይም በገቢው ይህን ያክል ጭማሪ መቋቋም የሚያስችል እድገት እያገኘ ያለው የትኛው ሰው ነው; ሁሉም የትራንስፖርት አማራጮች እጅግ እጅግ አስጨናቂ በሆኑበት በዚህ ዘመን በእግር መሄድን ምርጫ ማድረግ የብዙዎች ግዴታ እየሆነ ነው፡፡

በታክሲ መሳፈር ከፍ ያለ ዋጋን፣ በአውቶብስ መሳፈር ደግሞ ከሚኖረው ጭቅጭቅ፣

ከሌባ ጋር ግብግብ፣ ከታፈነ አየር ጋር እሰጥ አገባ እንዳለ ሆኖ፣ ዋጋውም ከታክሲው እምብዛም ልዩነት የሌለው ነው፡፡ ሁሉንም እንቻለው ብንል እንኳ የአውቶብስ ትራንስፖርት እንደ ልብ አለመገኘቱ ለማማረራችን መንስዔ ይሆናል፡፡ (በቅንፍ ውስጥ፤ መንግስት የኅብረተሰቡን የትራንስፖርት ፍላጎት ለማሟላት የአጭር ጊዜና የረጅም ጊዜ እቅድ ነድፎ እየተንቀሳቀሰ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው ... ድንቄም! ይሄኔ ሃይገር የመሰለ ነገር ሰብስቦ ለማስገባት ይሆናል፡፡)

እነዚህን ሁሉ ችግሮች እያስተዋለ መንግስት አሁንም ስራውን አልፈታም፡፡ ወር እየጠበቀ የዋጋ ጭማሪ ማድረጉን ተያይዞታል፡፡ የዚህን ምክንያት በተመለከተ በየጊዜው ምክንያቶች ይደረደራሉ፡፡ የዓለም የነዳጅ ዋጋ ስለጨመረ የአረብ ሀገራት በአብዮታቸው ምክንያት ያቀርቡት የነበረው የነዳጅ መጠን ስለቀነሰ ወዘተ ይባላል፡፡ እና ምን ይጠበስ; የዓለም የነዳጅ ዋጋ ስለጨመረ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደ ቆዳ ከመወጠር ሌላ አማራጭ የለውም; ለመንግስት ሰዎች ስብሰባ የቅንጦት ውሃና ኩኪስ መግዣ በየጊዜው እንደ ርችት ለሚረጩት የጽህፈት መሳሪያዎች ወይም ለሌላ አልባሌ መዝናኛ የሚወጡ ወጭዎችን ቆጥቦ ነዳጅ ላይ ድጎማ ማደረግ አይቻልም እንዴ;

ሁለት፡- የደሞዝ ጭማሪው የተደረገው ለመንግስት ሰራተኞች እንጅ ለሁሉም የሀገሪቱ ሰራተኞች አይደለም፡፡ እንደውም ይህንን ልብ ብለን ከተመለከትነው

በታዲዎስ ጌታሁን

የተቆለፈች ከተማ

ተቃዋሚ ፓርቲን እንጅ ተቃዋሚ ነጋዴን የሚቆጣጠር ጠፋደሳለኝ ሥዩም

[email protected]

ወደ ገፅ 23 ዞሯል

ነገር ግን የሰው ልጅ መብቶች እስከ ሰይጣን ድረስ የተለጠጡ ናቸው፡፡ በአምልኮ ደረጃ እንኳን የፈለገውን

የማመንና የመከተል መብት አለው - የሰው ልጅ፡፡ ወደ ፖለቲካው ሲመጣ ደግሞ ከዛ ከፍ ሊል ይገባል

እንጂ፣ አንድ ፓርቲ በሰራው ጎጆ ውስጥ ታጉራችሁ፣ ‹‹እኔ ያላንቺ መች ያምርብኛል››ን አቀንቅኑ ማለት

ከአማልክት እንበልጣለን እንደማለት ነው፡፡

የዓለም የነዳጅ ዋጋ ስለጨመረ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደ

ቆዳ ከመወጠር ሌላ አማራጭ የለውም; ለመንግስት ሰዎች ስብሰባ

የቅንጦት ውሃና ኩኪስ መግዣ በየጊዜው እንደ ርችት ለሚረጩት

የጽህፈት መሳሪያዎች ወይም ለሌላ አልባሌ መዝናኛ የሚወጡ

ወጭዎችን ቆጥቦ ነዳጅ ላይ ድጎማ ማደረግ አይቻልም እንዴ;

Page 9: አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 166 ቅዳሜ ሚያዚያ 29 2003 ኢሕአዴግ … · ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ አውራምባ ታይምስ 4ኛ

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 166 ቅዳሜ ሚያዚያ 29 2003

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

የማያጉረመርም ሕሊና9ኮሜንተሪ

ዛሬ ላጉረመርምበት የ ም ሻ ው የ አ ስተሳ ሰ ባች ን (የአመለካከታችን) ዘይቤ ነው፡፡ በሕዝባችን የወለ አመለካት ላይ አጥብቄ

አጉረመርማለሁ፡፡ አንዳንድ ጊዜ በአስተሳሰባችን ላይ ማጉረምረም፣ በባሕላችን ላይ ማጉረምረም እናም በኑሯችን ላይ ማጉረምረም ተገቢ ይመስለኛል፡፡ ድምፃዊት ዘሪቱ ከበደ ‹‹የምንበላው አርቴፊሻል፣ የምናየው አርቴፊሻል ... እያለች በውብ ጣዕመ ዜማ ማጉረምረሟንም ሳላደንቀው አላልፍም፡፡ አዎን እናጉረምርም እንጂ! ‹‹ጉርምርሜ›› የሚል ዘፈን የምንሰማው በሰርግ ዘፈን ላይ ነበር፡፡ በሰርግ ዘፈን ላይ ብቻ ሳይሆን በሌላውም እናጉረምርም እንጂ! የማጉረምረም መብትኮ በሕገመንግሥቱ የተከበረ ነው (አንቀጽ 29ኝን ይመልከቱ)፡፡ በእርግጥ ሕገመንግሥቱ ይህን መብት ሲጠቅሰው ‹‹የአመለካከት እና ሀሳብን በነፃ የመያዝና የመግለፅ መብት›› ይለዋል፡፡ እኔም ይህንን መብት ነው ጠበብ አድርጌ ‹‹የማጉረምረም መብት›› የምለው፡፡

ስ ን ት የሚያጉተመትሙን ሁኔታዎች ሞልተው፣ ሰንት የሚያጉረመርሙን ጉዳዮች ተርፈ ‹‹አታጉረምርሙ›› ማለት ኢ-ሰብዓዊ ነው፡፡ ወይም የሚያጉረመርሙንን ነገሮች አስቀሩልን፡፡ ይህ ካልተቻላችሁ ግን ‹‹አታጉረምርሙ›› አትበሉን፡፡ የማጉረምረም መብታችን ይከበር፡፡

በ ጥ ን ታ ዊ ቷ ኢትዮጵያ የማጉረምረም መብቱን ከተጠቀመባቸው ሰዎች አንዱ ዘረያዕቆብ ነው፡፡ በእግርጥ ፈላስፋው ዘረያዕቆብ ብዙ ጊዜ ያጉረመረመው በሃይማኖቱ ላይ ነው፡፡ ያጉረመረመባቸው ሀሳቦች

ሁሉ ትክክል ናቸው ባንልም፣ ይህ ሰው ግን ሊደነቅ የሚገባው አጉረምራሚ ነበር፡፡ ወገኖቼ፣ የሚያጉረመርም ሰው አይንሳን፡፡ ዛሬ ድረስ የምንኮራበት አጉረምራሚስ እሱ አይደል እንዴ? እንድናጉረመርም አድርጎን ‹‹አታጉረምርሙ›› ከሚለ ግፈኛም (ግለሰብ፣ ማኅበረሰብ፣ ተቋም፣ መንግሥት፣ ባህል፣ ሃይማኖት) ይሰውረን፡፡

ከአንድ የገበሬ ቤተሰብ በ1592 ዓ.ም ተወለደ የሚባለው ተፈላሳፊው ዘረያዕቆብ ይህን ይላል፡- ‹‹ይህ በቅዱሳት መጽሐፍት የተፃፈ ሁሉ እውነት ይሆን? ብዬ አሰብኩ፡፡ በጣም አላወኩምና የተማሩና ተመራማሪ ሰዎች እውነትን እንዲነግሩኝ ሄጄ ልጠይቃቸው ብዬ ብዙ አሰብኩ፤ እንደገናም ሰዎች በየልባቸው ያለውን ካልሆነ በቀር ሌላ ምን ይመልሱልኛል ብዬ አሰብኩ፡፡ ሰው ሁሉ ‹‹የእኔ ሃይማኖት እውነተኛ ናት›› ይላል፡፡ በሌላ ሃይማኖት የሚያምኑ ሐሰተኞች የእግዚአብሔር ጠላቶች ናቸው፡፡ ዛሬም ቢሆን ፈረንጆች ሃይማኖታችን መልካም ናት፣ ሃይማኖታችሁ ግን መጥፎ ናት ይሉናል፡፡ እኛም መልሰን እንደዚህ አይደለም፣ የእናንተ ሃይማኖት መጥፎ የእኛ ሃይማኖት ግን መልካም ናት እንላቸዋለን፡፡ እንደገናም የእስልምና፣ የአይሁድ አማኞችን ብጠይቃቸው እንዲሁ ይሉናል፡፡ በዚህም ክርክር ፈራጁ ማን ይሆናል? ሰዎች ሁሉ እርስ በእርሳቸው ወቃሾችና ተወቃሾች ሆነዋል፡፡ አንድ እንኳን ከሰው ልጅ የሚፈርድ አይገኝም፡፡ እኔ መጀመሪያ ስለብዙ ሃይማኖቶች ጉዳይ አንድ የፈረንጅ መምህር ጠየኩ፡፡ አሱ ግን ሁሉን እንደ ራሱ ሃይማኖት አድርጎ ፈታው፡፡ ኋላም አንድ ትልቅ የኢትዮጵያ መምህር ጠየኩ፤ እርሱም ሁሉንም እንደ ሃይማኖቱ አድርጎ ተረጎመው፡፡

ሙስሊምና አይሁድንም ብንጠይቅ እንዲሁ እንደየሃይማኖታቸው ይተረጉማሉ፡፡ ታዲያው እውነት የሚፈርድ የት አገኛለሁ? የእኔ ሃይማኖት ለእኔ እውነት እንደሚመስለኝ እንዲሁ ለሌላውም ሃይማኖቱ እውነት ይመስለዋል ... ፡፡ (መጽሐፈ ዘረያዕቆብ ከገፅ 12-13) ዘረያዕቆብ እንዲህ እያለ በገዛ እምነቱ ላይ እያጉረመረመና አብዝቶ እየጠየቀ የእውነት አሰሳውን ይቀጥላል፡፡

ማንጎራጎር ወይም ማጉረምረም መልካም ነው፡፡ ለምን ዛሬም በባልቴቶች ወግ እንመራለን? ለምን በአባቶቻችን ሀሳብ እንቆዝማለን? ለምን ያነበብነውን ብቻ እንተፋለን? የምንቀበለው እንጂ የምንሰጠው የለንም? የምንወስደው እንጂ የምናበረክተው የለም? የእኛሰ አዕምሮ ለምን እንደ ፅኑ ባሕር ረግቶ ይቀመጣል? ይናወጥ፣ ይበጥበጥ እንጂ! ቅቤ እንኳ የሚወጣው ከተናጠ ወተት ነው፡፡ አዎ! በባሕላችን ላይ እናጉረምርም፡፡ በአመለካከታችን፣ በኑሯችን ላይ እናጉረምርም፡፡ አለያማ ለውጥ የለም፡፡ ኑሯችንም ከሞት የከፋ ይሆናል፡፡

በአንድ ወቅት ጥቂት ጓደኞች ተሰባስበን ምሳ ብጤ ተያይዘናል፡፡ አንድ ወዳጃችን ከደጅ መጥቶ ተቀላቀለን፡፡ ‹‹አረፍ በል፣ የደረስክበትን ተቋደስ›› ብንለው ምሳ መብላቱን ነገረን፡፡ ክርክራችን ሲበዛበት ወዳጅነታችን አስገድዶት ለፍቅራችን ሲል እዚያው በቆመበት አንድ ሁለት ጎራረሰ፡፡ ይህን ጊዜ ሌላው ወዳጃችን ቱግ አለ፤ ‹‹ስማ፣ እህልኮ ክቡር ነው፡፡ እንዴት ቆመህ ትበላለህ? ገበታ እኮ ክቡር ነው›› ሲል ገሰፀው፡፡ የቆመው ወዳጃችንም፣ ‹‹ክቡርማ ገበታው አይደለም፡፡ ክቡር እኔና አንተ ነን›› ሲል መለሰ፡፡ ያም በፈንታው፣ ‹‹እንዴት እንዲህ ትላለህ? ወንበር ያዝና ቁጭ ብለህ ብላ፡፡ ገበታን

ልታከብረው የገባሀል›› ቢለው፣ ‹‹የለም፣ ገበታው ቢያውቅ ኖሮ እኔ ገበታውን ሳይሆን ገበታው እኔን ሊያከብረኝ ይገባ ነበር፡፡ ገበታው ለእኔ ተፈጠር እንጂ እኔ ገበታውን ላከብረውና ላመልከው አልተፈጠርኩም›› ሲል አመረረ፡፡ ‹‹እንዴት ከባሕላችን ትወጣለህ? ባሕላችን አይደለም ወይ?›› ሲልም፣ ‹‹የእኔ ወንድም፣ ወንበር ላይ ተቀምጬ የምበላው ገበታ ክቡር ስለሆነ ወይም ባሕላችን ስለሆነ አይደለም፡፡ እኔ ወንበር ላይ የምቀመጠው በሌላ ምክንያት ሳይሆን መቀመጡ ለአበላል ስለሚያመቸኝ ነው›› ብሎ ሞገተ፡፡ ባሕሉን ወክሎ በተከራከረው ጓደኛችን ሕሊና ውስጥ ወላጆቼን፣ አያቶቼን፣ ቅድመ-አያቶቼንና ምንጅላቶቼን አየኋቸው፡፡ በወዲህኛው ጓደኛችን ውስጥ ደግሞ አዲሱንና መጪውን ዘመን አየሁት፡፡ በእርግጥ ባሕልና ሥርዓት አስፈላጊ መሆናቸውን አውቃለሁ፡፡ ሰለእነሱም እቆማለሁ፡፡ ነገር ግን ባሕልና ሥርዓት አይጠየቅም፣ አይመረመርም ማለት አይደለም፡፡ ምግብን ማባከን፣ የአመጋገብ ሥርዓት አለመጠበቅ ወይም ሌሎች ወገኖች ሊመገቡት ይችሉ የነበረውን ምግብ በከንቱ ማበላሸት ኢ-ሞራላዊ ነው፡፡ ነገር ግን ከዚህ ያለፈው አስተያየታችን ጤነኛ አይመስለኝም፡፡ ምናልባት በወላጆቻችን ዘመን ክፉ ችግርና ፅኑ ረሀብ ስለነበር፣ አያሌ መከራ ስላሳለፉ ለገበታና ለእህል ከፍ ያለ አስተያየትና ወደአምልኮ የተጠጋ አክብሮት ሰጥተውት ሊሆን ይችላል፡፡ ወላጆቻችን ባሳለፉት የሰቆቃ ዓመታት ምክንያት እህል ከምንም ላይ እንዲከበርና ከፈጣሪ እኩል እንዲፈራ አስገድዷቸው ይሆን? ስል መጠርጠሬ አልቀረም፡፡ በዚሁ ዙሪያ ላይ ሌሎችም የማነሳቸው ጥያቄዎች አሉ፡፡ ለምሳሌ ወደ አንድ ሆቴል

ገበታው ቢያውቅ ኖሮ እኔ ገበታውን ሳይሆን ገበታው እኔን ሊያከብረኝ ይገባ ነበር፡፡

ገበታው ለእኔ ተፈጠር እንጂ እኔ ገበታውን ላከብረውና ላመልከው አልተፈጠርኩም›› ሲል አመረረ፡

፡ ‹‹እንዴት ከባሕላችን ትወጣለህ? ባሕላችን አይደለም ወይ?››

ሲልም፣ ‹‹የእኔ ወንድም፣ ወንበር ላይ ተቀምጬ የምበላው ገበታ ክቡር ስለሆነ ወይም ባሕላችን ስለሆነ አይደለም፡፡ እኔ ወንበር

ላይ የምቀመጠው በሌላ ምክንያት ሳይሆን መቀመጡ ለአበላል

ስለሚያመቸኝ ነው››

በሰሎሞን ሞገስ (ፋሲል)[email protected]

እገባለሁ፡፡ ለመስተንግዶ ወንበር ይዤ ገና ስቀመጥ ከሌላው ጠረጴዛ ላይ የማላውቀው ግለሰብ ምግቡን እያሳየ ‹‹እንብላ›› ይለኛል፡፡ ሰውዬው ፈፃሞ አያውቀኝም፡፡ ሰለባህሪም ሆነ ስለማንነቴ ምንም መረጃ የለውም፡፡ እሺ መጣሁ ብዬ ወንበር ስቤ ብቀርብ ግን ጋባዤ ይደናገጣል፡፡ ታዲያ ባሕላችን የሆነው አብሮ መብላቱ ነው ወይንስ ‹‹እንብላ›› ማለቱ? ብዬ እጠይቃለሁ፡፡ እኔም ሌላውን እንብላ እላለሁ፡፡ መጥቶ ቢቀርብ ግን ምቾት አይሰማኝም፡፡ አላስፈላጊ ነገሮችም ልጠረጥር እችላለሁ፡፡ ‹‹እንብላ›› የምለውም የአፍ ልማድ ሆኖብኝ ነው፡፡

በአጭሩ ለማለት የተነሳሁት፣ በተለያዩ ሁኔታዎች ውስጥ አስተሳሰባችንን እንፈትሽ፤ ባሕላችንን እንመርምር፣ እንጠይቅ፣ እንሞግት ነው፡፡ ምሳሌዎቼ ላያረኳችሁ ይችላሉ፡፡ የመንገዱን ጫፍ ካያችሁልኝ ግን በቂዬ ነው እላለሁ፡፡ በኑሯችን ላይ፣ በአመለካከታችን ላይ እናጉረምርም፡፡ ማጉረምረም ስላልቻልን ሶስት ሺህ ዘመናት ያለ ለውጥ በበሬ ጫንቃ እያረስን በአህያ ጀርባ ተጉዘናል፡፡ ማጉረምረም ስለተሳነን አዲስ ሀሳብ የለንም፡፡ የምንተርተው እንኳ የዱሮውን ተረት ነው፡፡ በቅርቡ ‹‹የስሙኒ ዶሮ የብር ከሀምሳ ገመድ ይዛ ጠፋች›› ስል በምሳሌ አወጋሁ፡፡ ዛሬ ግን የዶሮ ዋጋ ከመቶ ብር በላይ ሆኗል፡፡ ተረቱ እንኳን ምን ያህል ጥሎን እንዳረጀ ተመልከቱ፡፡ አዲስ ነገር አናስብም፤ አዲስ ነገር አንፈጥርም፤ አዲስ ነገር አንመኝም፡፡ በሌላው ላይ ብቻ ሳይሆን በራሳችንም ላይ እናጉረምርም፡፡ እንደ ግብፅ ሕዝብ በሕብረት፣ እንደ ዘረያዕቆብ በተናጥል እናጉረምርም፡፡ ግን ለምን ማጉረምረም ተሳነን?

አልበርት ካሙ የተባለው አልጄሪያ የተወለደ ስመ-ጥር ፈረንሳያዊ ፈላስፋ፣ ‹‹A Happy Death›› በ ሚ ሰ ኝ

መጽሐፉ፣ ቀጥሎ ከቀረበው ሀተታ ጋር የሚመሳሰል ምልከታውን አስፍሯል፡- ከጎተራው እህል ያጣ ሰው ክብረ-ቢስ ህላዌን እንዲገፋ መገደዱ አይቀርም፡፡ የእለት እንጀራውን ያገያገኝ ዘንድም የማይሆነው የለም፡፡ ይሽቆጠቆጣል፡፡ ይወሸክታል፡፡ ያጎበድዳል፡፡ አጎንብሶ መኖርን ይለምዳል፡፡ አንደበቱ ቅይድ ነው፡፡ አዕምሮው ነፃነት የለውም፡፡ ልቡ ትጠቁራለች፡፡ ነብሱ በክፋት ትመረዛለች፡፡ በጥርስ ውጋት እንደሚያሰቃይ ሕመምተኛ ፋታም የለው፡፡ ተደፍነው የማያልቁ ቀዳዳዎቹን ሊወትፍ ከላይ ታች ሲሯሯጥ ሌላ ነገር ማሰብም አይሆንለት፡፡ መንገዱን ይስታል፡፡ ሽንፈት ደጋግሞ እየጎበኘው ውኔውን ይሰልበዋል፡፡ በረባውም ባልረባውም ይብሰከሰካል፡፡ ቀለቡ ከአካሉ ይነጠላል፡፡ ብርሃን ተሰውሮበት ፊቱ የምሬትን ካባ ይጎናፀፋል፡፡ ሳይኖርበት እድሜውን ይቆጥራል፡፡ ሳይደርስበት ከእርጅና ደጅ ይገኛል፡፡ በመጨረሻም በሀዘን ተቆራምዶ ይሞታል፡፡ ይህ ሰው በቂውን ገንዘብ አግኝቶ አርነት ካልወጣ በስተቀር፣ እጅና እግሩ እንደተጠፈነጉ ይግባው፡፡ የፈቀደውን ሊያደርግ፣ ወደ ወደደው ሊጓዝ አይቻለውም፡፡ በገንዘብ ጥላ ስር ሲልፈሰፈስ ዘመኑን መፍጀት እጣ ፈንታው ነው፡፡ እረፍትን አያውቃትም፡፡ ደስታም የእርሱ አይደለችም፡፡

ገንዘብ የንፍገት ጥላውን አጥልቶብን ብርሃናችንን

የሰወረብን ብዙዎች አለን፡፡ በየጎዳና፣ በየመስኩ፣ በየስርቻው የጨፈገጉ ፊቶቻችን ላይ አስጨናቂ ታሪኮቻችንን አትመን ስንንገላወድ አንታጣም፡፡ ጧት ቋጠሮቻችንን አንጠልጥለን የእግር መንገድ ላይ እየተንጋጋን ወደየስራዎቻችን ስንሰማራ እንገኛለን፡፡ እንቅልፍ የናፈቁ አይኖቻችንን፣ ኩርፊያቸውን የመደበቅ ግድ የሌላቸው ጉንጮቻችንን፣ የተቋጠሩ ግንባሮቻችንን ተሸክመን፤ ከአንገታችን በመጠኑ ሰበቅ ብለን የግዳችንን ስንጣደፍ ለአፍታ ያህል ድልድይ ላይ ቆሞ ላስተዋለን ምን እንመስል? የወር ቀለባችንን በፌስታል ተሸክመን እያዘገምን ከገበያ ስንመለስም እንገኛለን፡፡ የጎደለው በምን ብልሃት እንደሚሟላ፣ የጠፋው የት ተብሎ እንደሚገኝ እያብሰለሰልን፣ ልክ አልሆን ያለንን ስሌት አስተካክለን አደብ ልናስይዝ ከሒሳብ ጋር ስንሟገት፣ ለሰላምታቸው ምላሽ የነፈግናቸው ስንት ወዳጆቻችን ታዝበውን ይሆን? አንዱ የዋህ ሁኔታችንን ልብ የማለት ግድ ኖሮት ‹‹ምነው? ስለምን እንዲህ የትካዜ ዳዋ ዋጣችሁ? ስለምንስ በጭንቀት ተወጣራችሁ? ፈገግ ልትሉ አትወዱምን?›› ብሎ ቢጠይቀን፣ ‹‹አይ አንተ - ገጣሚው ደበበ ሰይፉ ‹አለመሳቅማ ይቻላል - አለማልቀስ ነው እንጂ ጭንቁ› ማለቱን አልሰማህም?›› ሳንለው እንቀራለን?

በየሱቁ ተኮልኩለን፣ በየጋዝ ማደያው ተሰልፈን ስንጥመዘመዝ የምንታየውም እኛው ነን፡፡ ትናንት ስንጠብቅ ነበር፤ ዛሬም እየጠበቅን ነው፤ ምናልባት ነገም ጠባቂዎች ነን፡፡ እርግጥ ነው የማጣትና የእኛ ትውውቅ የተጀመረው አሁን አይደለም፡፡ እንደለበስነው ቆዳ

የተላመድነው፣ እንደ እጃችን መዳፍ አብጠርጥረን የምናውቀው የከረመ ወዳጃችን ነው፡፡

ለወትሮው ሊጠይቀን ደጋግሞ በመጣ ቁጥር እንደ አመሉ የምናስተናግድበት መላ አይጠፋንም ነበር፡፡ አሁን ግን ትከሻችን አለቀና፣ ጉልበታችንም ላመና፣ የእርሱም ጠባይ ያለቅን ከፋና እየኮረኮመ እንዳይሆኑት አደረገን፡፡ እንግዲህ በየአውቶብስ ፌርማታው፣ በየታክሲ መጫኛው እያልጎመጎምን የምናስታምመው የዚህን ኩርኩም ሕመም ነው፡፡

መቼም የታክሲ ተራ ጀብዱዎችን ጉድ ያስብላል፡፡ ሙሉ ትኩረታችንን አንድ ነገር ላይ ብቻ አድርገን፣ አብረውን የቆሙ ወዳጆቻችንን በቅፅበት ዘንግተን፣ በደካሞች ላይ እየተረማመድን ወደታክሲው በር የምናደርገው ተምዘግዛጊ ሩጫ ውስጥ አንዳች አውሬነት አለ፡፡ እንዳሰብነው ወደውስጥ ብንገባ እንኳ ከመንጋ መሀል አፈትልኮ አሸናፊ መሆን የሚፈጥርብን ደመ-ነፍሳዊ እርካታ እድሜው አጭር መሆኑ ያሳዝናል፡፡ ኑሮ በታክሲ ረዳት ተመስላ ዳግም ብቅ ትላለች፡፡ ሒሳቡ ላይ ተጨምራ ያደረች ስሙኒን ላለመክፈል እናንገራግራለን፡፡ መክፈላችን አይቀርም፡፡ አቅመ-ቢስነታችን ይቆጠቁጠናል፡፡ የከፈልናት ስሙኒ ጎድላ ሕይወታችንን ባታዛንፈውም፣ በየጊዜው በየፈርጁ የሚጨመሩ ስሙኒዎች ሲደመሩ ሊያንገዳግዱን እንደሚቻላቸው አንክድም፡፡ የጭማሪው ሸምጥ ግልቢያ መግቻ ልጓም እንደታጣለት አንድ ተጨማሪ ዋቢ አገኘን፡፡ በደምባራዋ የኑሮአችን በቅሎ ላይ እንዲህ ያለ መቆሚያ የሌለው ቃጭል ተጨምሮበት እንደምን

እረፍትን ያገኟል? ደስታንስ የት አግኝተው ያውቋታል?

ከሁሉም የሚከፋው ‹‹ነገ ከዛሬ ይሻል ይሆናል›› ይል የነበረ ተስፋችን ሲከስም በስፍራው ያቆጠቆጠው ‹‹ነገስ ምን ይመጣ ይሆን›› የሚል ስጋት እድገቱን መጨመሩ ነው፡፡ ፍርሃት ይሆናል ተብሎ ከተፈራው ነገር በባሰ ስጋን እንደሚያሳሳ የተማርነው በተግባር ነው፡፡ ፍርሃት - የመጪው ጊዜ ፍርሃት - በደም ስራችን እየተላወሰ ሲያዛጋ ስንሰማው የምንሰራውንም አናውቅ፡፡ የምንረግጠውንም አናውቅ፡፡ የምንናገረውንም አናውቅ፡፡ እንደኛው ጠብታ ዘይት ፍለጋ በፀሐይ ሲንቃቃ አብሮን ከዋላ ብጤያችን ጋር እንናጫለን፡፡ ወይ በጊዜ ብዛት ተዛምዶን ተከራይነቱን የረሳን ወንደላጤ ላይ እንጮሃለን፡፡ አንዳንዴ ቁጣ ቁጣ ይለናል፤ ከቆመ ግንድ ጋር ሳይቀር ለፀብ እንጋበዛለን፡፡ አንዳንዴ መንገድ የዘጋብንን አዝጋሚ በርግማን አስበርግገን፣ በርካሽ ቃላት አበሻቅጠን እናስደነግጣለን፡፡ አንዳንዴ ተመልሰን የእናታችን ጉያ ብንወሽቅ እንወዳለን፡፡ እፎይታን ከእንባ እንሻታለን፡፡

ሲዘሩ ሳናያቸው ድንገት በቅለው ድንክ ያሳከሉንን የሚያጥበረብሩ ሕንፃዎች እየገረመምን መገረማችን አልቀረም፡፡ አንዳንዴ ባለሕንፃዎቹን ሰዎች ስናስብ ‹‹ምን ቢያደርጉ ነው እንዲህ የሞላላቸው?›› እያልን በሆዳችን እናማቸዋለን፡፡ ከንጋት እስከ ውድቀት ለመታተሩማ ከእኛ ማን በልጦ፡፡

ሆኖም ያን ያህል ተላሎች አይደለንም፡፡ መቆርቆዛችንን የሚፈልጉ ሰዎች እንደሚኖሩ እንጠረጥራለን፡

፡ አንዳንድ መሰሪዎች ዘወትር ስለምሳና እራት ብቻ እያሰብን ሌላ ነገር በልቦናችን ጭራሹኑ ሽው ባይል አይጠሉም፡፡ እንዲያውም እኛ ተቆራምደን የተጋደምንበት መደብ በጎረበጠን ቁጥር እነሱ ተንሰራፍተው የተቀመጡበት ወንበደር ላይ ሲደላደሉ ታዝበናል፡፡ ረሀብ ያመነመነው ገላችንን፣ ችግር ያራከሰው ማንነታችንን ተመልክተው ወደ እንስሳነት እንደወረድን ስለገመቱ ቁራሽ ዳቦ እያሳዩ ‹‹በቃላችን እደሩ›› ብለውናል፡፡ ግብዣቸውን ‹‹ይቅርብን›› ማለታችን ቢያስከፋቸውም፣ አይናችን ከዳቦው ላይ ተነስቶ ሌላ ነገር እንዳያማትር የቻሉትን ያደርጋሉ፡፡

እና ሙግቱ ከራሳችን ጋር ነው፡፡ በጠኔ ተደቁሰንም ሆን ከምሳና እራት የላቀ ነገር ማሰብ እንችላለን ወይ? የለበስነው እራፊ ጨርቅ ላያችን ላይ ተበጣጥሶም ቢሆን ከሸማና ሀር አርቀን ማለም እንችላለን ወይ? ከነፎከታችን፣ ከነውጋታችን የአታላዮች መጠቀሚያ፣ የሆዳሞች ሎሌ መሆንን እንጠየፋለን ወይ? አሞሌ ጨው እየቀመሱ ወደ መታጎሪያው በረት ከሚወስዱት ኮርማ እንሻላለን ወይ?

መሻል አለብን፡፡ ሰው አይደለንም እንዴ? እንደሰው ክቡር የሚያሰኙንን የረቀቁ እሳቤዎች ሁሉ የሚያውቅ፣ የሚጠይቅ፣ የሚያብላላና የማያስደፍር ስብዕናን መላበስ መቻል አለብን፡፡ ፊት ለፊታችን ከተደቀነው፣ ከቅርቡ አሻግረን ማየት መቻል አለብን፡፡ ከሆንነው ሁሉ በላይ መሆናችንን ማወቅ አለብን - መድህናችን የሚገኘው በዚህ ፈታኝ እውቀት ውስጥ ነውና!

በቃልኪዳን ይበልጣል

እያልጎመጎምን የምናስታምመው ሕመምአንዳንድ መሰሪዎች

ዘወትር ስለምሳና እራት ብቻ

እያሰብን ሌላ ነገር በልቦናችን

ጭራሹኑ ሽው ባይል አይጠሉም፡

፡ እንዲያውም እኛ ተቆራምደን

የተጋደምንበት መደብ በጎረበጠን

ቁጥር እነሱ ተንሰራፍተው

የተቀመጡበት ወንበደር ላይ

ሲደላደሉ ታዝበናል፡፡ ረሀብ

ያመነመነው ገላችንን፣ ችግር

ያራከሰው ማንነታችንን ተመልክተው

ወደ እንስሳነት እንደወረድን

ስለገመቱ ቁራሽ ዳቦ እያሳዩ

‹‹በቃላችን እደሩ›› ብለውናል፡፡

Page 10: አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 166 ቅዳሜ ሚያዚያ 29 2003 ኢሕአዴግ … · ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ አውራምባ ታይምስ 4ኛ

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 166 ቅዳሜ ሚያዚያ 29 200310

p Ç T@ S ´ “ —

(ክፍል አንድ)

... የጎዳና ሕይወት አንገሽግሾኛል፡፡ እዛው ገዳናዬ ላይ ሆኜ የኤፍ.ኤም ራዲዮ ጣቢያ እንግዳ ሆነው የቀረቡ የአእምሮ ሐኪም፣ የሱስ ተጠቂዎች ሕክምና እንደሚያገኙ፣ ሕክምናውም በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል እንደሚሰጥ ሲያስረዱ ሰምቼ ትኩረቴን ሳቡትና የጎረቤቴን ራዲዮ ተቸክዬ አዳመጥኳቸው፡፡

እሳቸው አስረድተው እንደጨረሱ አንድ ሀሳብ ብልጭ አለልኝ፤ ‹‹እኔ ምንም ቤተሰብና ረዳት ባይኖረኝም ይህን ሕክምና የማግኘት፣ በኢትዮጵያዊነቴ የመታከም መብት የለኝም?›› የሚል፡፡

ጊዜ ሳላባክን ተነሳሁና ለብርታት የምትሆነኝን ሁለት መለኪያ አረቄዬን ተጎነጨሁ፡፡ በፍጥነት ቀበሌ ደረስኩ፤ ያውቁኛል፡፡ ሁኔታዬም ያስደነግጣል መሰል ... ብቻ ፋይል ማገላበጥ ሳያስፈልገው (እድሜ ለቢ.ፒ.አር) ካዛንችስ አካባቢ ለሚገኘው ‹‹ቦርቸሌ›› በሚባል ለሚታወቀው ጤና ጣቢያ የነፃ ሕክምና ፈቃድ ተሰጠኝ፡፡

‹‹ቦርቸሌ›› ጣጣ ሳያበዙ አስተናገዱኝ፡፡ ዶክተሩ ጋር አቀረቡኝ፡፡ ከዶክተሩ ጋር በአጭር ንግግር ነው የተግባባነው፡፡

‹‹የጳውሎስ አልጋ አይገኝም፤ አማኑኤል ተመሳሳይ ሕክምና ይሰጣል፤ እዛ ልጻፍልሽ›› ሲለኝ አላንገራገርኩም፡፡ ወረቀቴን ይዤ ዕለቱን በደስታ እየሰከርኩ፣ እየጦዝኩ ... የሆንኩትን ሆኜ አድሬ በማግስቱ በጠዋት ተነስቼ ለድፍረት የምታግዘኝን አረቄዬን ተጎንጭቼ የታክሲም ሆነ የትራንስፖርት ስለሌለኝ በእግሬ ከሸራተን አካባቢ አማኑኤል ሆስፒታል ደረስኩ፡፡

በስንት ጦርነት ወረፋ ደርሶኝ የነፃ ሕክምና ካርዴን ተቀበሉኝ፡፡ ዶክተር ጋር ለመቅረብ ግን አስር ብር ተጠየቅኩ፡፡ ከየት ላምጣ ... አምርሬ አለቀስኩ፡፡ አንዱ ከኋላዬ የነበረ አስር ብሩን አስያዘልኝና ለማመስገን’ንኳ ፋታ ሳይሰጠኝ ከፊቴ ተሰወረ፡፡ አንዲት ደርባባ ሴትዮ ደሞ፣ ‹‹አይዞሽ የኔ ልጅ፤ እግዚአብሔር ምህረቱን ይላክልሽ ... ላንዳንድ ነገር

ይሁንሽ›› ብለው አስር ብር ሰጡኝ፡፡አማኑኤል ሆስፒታል

ለመድረስ በዱቤ አስቀድቼ የያዝኳትን አረቄ እየተጎነጨሁ፤ ሲደክመኝ የሲጋራ ቁሩዬን እያጨስኩና እያረፍኩ፤ ዳግም በጎዳና ኑሮ መሰንበቴ ተደማምሮ ያለኝ ጠረን ቢገፋተርም፣ ነርሷ ተቋቁማ ምን እንደምፈልግ ሳስረዳት በጥሞና አዳመጠችኝ፤ ተረዳችኝ፡፡ ዶክተሩ ጋር በፍጥነት አቀረበችኝ፡፡

ከዶክተሩ ጋር ዘለግ ያለ ጊዜ የወሰደ ቆይታ ደረግን፡፡ የሱስ ሕክምና በአማኑኤል ሆስፒታልም እንደሚሰጥ አስረዳኝ፡፡ አልጋ አንደሚሰጠኝ ተስፋ ሰጠኝ፡፡ በማግስቱ በጠዋት እንድመጣ ተነግሮኝ ተሸኘሁ፡፡ በዕለቱ በተስፋ ተሞልቼ፣ ለምኜና ቀፋፍዬ አረቄዬን በኮዳ አስቀድቼ ጎዳናዬ ላይ እንደ ልማዴ አደርኩ፡፡

. . .በጠዋት አማኑኤል ልሄድ ስነሳ

ጓደኛዬን መንገድ አገኘሁትና እንዲሸኘኝ፣ የት እንደምሄድ በግልጽ ነገርኩት፡፡ ቁርስ ጋብዞ፣ ኮዳዬ ላይ ትንሽ አንጠባጥቦልኝ፣ ለእጄም አስጨብጦኝ ሸኘኝ፡፡

አማኑኤል ስደርስ ወረፋው አይጣል ያስብላል፡፡ ወረፋ ይዤ እዛው ሆስፒታሉ ፊት ለፊት ካለ አረቄ ቤት ጎራ አልኩ፡፡ አሁን ትንሽ ሞቅ ብሎኛል፡፡ ዶክተሩ ጋር ስቀርብ እንደልብ ፈታ ብዬ አወራለሁ እያልኩ ሳሰላስል ስሜ ተጠርቶ ገባሁ፡፡

ዶክተሩ በራሴ ፈቃድ ከሱስ ለመላቀቅ በመምጣቴ እያመሰገነ ተቀበለኝ፡፡ ጊዜ ወስዶ አነጋገረኝ፡፡ ‹‹ለጊዜው አልጋ እስኪገኝ መድኃኒት አዝልሻለሁ፤ ባለሽበት ትወስጃለሽ›› ሲለኝ ሰማይ እንደተደፋበት

በላዕከ ተ/ማርያም

41) ሜዳውን ጨርሶ እንደቆለቆለ ዓባይ ጋማ አውጥቶ አንበሳ መሰለወረደ እያገሳ በጎርናና ድምፅ ትንፋሹ እስኪመስል የደመራ ጢስ

42) አዘንኩለት ለዓባይ ተናደድኩለት አፍ እጁን አውጥቶ ሲለምን ምፅዋት 43) ይቅረብ ከዳኛ ፊት ይከሰስ ዓባይ ሀብታችንን ሲዘርፍ ኖሮ የለም ወይ 44) የእንጨት ቤት አልሰራ ግድግዳ

አይመርገው ዓባይ ለምንድነው ጭቃ እሚያቦካው 45) መቆንጠሩን ትተን ዓባይን በጭልፋ ለልማት እንዲውል እንዛቀው ባካፋ 46) ተው ተመለስ ዓባይ ተው ተመለስ ጣና ዝና ያለተግባር አይበጅህምና

47) ወሬ እያቀበለ ዓባይም እንደሰው ከጎረቤቶቼ ሊያቆራርጠኝ ነው 48) እግዜር ኢትዮጵያን ሲፈጥር አየና ግብፅን ልፈጠር አለ ዓባይ ተነሳና 49) ዓባይ ምን ሥራ አለው የሚያስጠራ ስም ውሃ መቅዳት እንጂ ለግብፅ ለሱዳን 50) አዋሽ ሥራ ሰርቶ በገንዘብ ሱከብር አይቀናም ወደ ዓባይ ደህይቶ ሲቀር

51) ያንበሳ ምሳሌ ዓባይ ጎምላላው አሥር ውሻ ቢጮህ ቢሮጥ ከኋላው አይቆም አይመለስ መሄድ ብቻ ነው

52) የዓባይ አሽከርነት አይጠቅምም ደቅርብን

መብራት ካላበራ ውሃ ካልቀዳልን 53) ማን አደፈረሰው ዓባይን ረግጦ አፈር አፈር ይላል ጣዕሙ ተለውጦ

54) ዓባይ መሽቶበታል ማደሪያ እንስጠው የያዘውን ንብረት ሰው እንዳይቀማው 55) ጎበዝ በኢትዮጵያ መች ጠፋና ጀግና “ጥራኝ ዱሩ” የሚል ዓባይ አለ ገና

56) ከወፍ ከአራዊቱ እግዜር ከሰራው ለማዳ አልሆን ያለው ዓባይ ብቻ ነው

57) ዓባይ ይሰደዳል ሳይል አንጃ ግራንጃ ገንዘብ ካላገኘ መመለሱን እንጃ 58) ካሉን ሀሉ ወንዞች ከምናውቃቸው ትልቅ ባገራችን ዓባይ ብቻ ነው

59) ጓደኞቹ ከብረው በወርቅ በብር ዕድለቢሱ ዓባይ ይዝቃል አፈር

60) እንደ ዓባይ ማን አለ የጦር መኮንን በእልህ የሚያስፎክር ግብፅና አበሻን

ዓባይን በጭልፋ(ክፍል ፫)

‹‹Info››ዋን ለኛ ብላችሁ ጃም የምታረጉልን ቤርሙዳ አካባቢ ‹‹vacation›› ብትወስዱስ?

በአካል እጅጉ [email protected]

Hi! ሰላም ነው!? እኔ የምለው፣ ያ ማታ 2 ሰዓት ላይ ዜና የሚያነበው ሰውዬ ሁሌ ቦንድ ቦንድ የሚለው እኔ ቤት ያለው ቲቪ ላይ ብቻ ነው ወይስ እናንተም ጋም ያው ነው? . . . አይ እውነት ሁሌ ማታ ማታ እሱን እየሰማን ቦንድ ሲታተመና ሲገዛ ከማየት ውጪ ስለ ቺኮቻችን ሁላ ‘ኮ ህልም አልመጣልን አለ! ... የምር ግን ስለ አባይ ግድብ ... እንዴት እንደሚገደብ ምናምን ካላወሩ ዛሬን መዋል ሳይቻላቸው የሚቀር ከሆነ፣ ለምን ለ‘ኛም ለነሱም ሲባል እዛ አባይ መሀሉ ላይ ‹‹ጊዜያዊ የማስተላለፊያ ጣቢያ›› አያዘጋጁም? ... የእውነት እንዲያውም ይሄን ሰሞን አሪፍ ዝናብ እየዘነበልን አይደል ... እና በቃ ደህና ደራሽ መቶ ለግድቡ ቢጠራርግልን እንዴት ሰላም ነበረው? ... (እየው ደግሞ ለግድቡ ነው ያልኩት) ...የምር ግን አንተ ወይም አንቺ የሆነ የሚገርም ደብተራ ፈልጋችሁ ‹‹ኢቴቪ ላይ ከአባይ ግድብ፣ ከትራንስፎርሜሽን እቅድ፣ ከህዳሴ ... ›› ምናምን ውጪ እንዳይወራ ብላችሁ ያስደገማችሁ ካላችሁ፣ በ‘ናታችሁ በሁሉም ብላችሁ ድግሙን አስፈቱልን፡፡እናማ በቃ፣ አሁን ሁሌ ስትሰሙ ‹‹ህዳሴውን እናበስራለን!›› ... ‹‹የትራንስፎርሜሽን እቅዱን እናሳካለን!›› ... ‹‹ግድቡን እንገድባለን!›› ... ‹‹ኢትዮጵያን ከመካከለኛ ገቢ ሀገራት ተርታ እናሰልፋለን!›› . . . ምናምን እየተባለ አይደል? እና በቃ እናደርጋለን ማለት ሳያስቡት ለምዶባቸው የእውነት ማድረጉን እንደ ትርፍ ነገር ወይም እንደ የልጅ ልጆቻችን ሥራ እንዳይቆጥሩት ... የምር ያ ሰውዬ ‘ኮ ልቡን ለከተፈችው ልጅ ቆይ ዛሬ እጠይቃታለሁ ... ቆይ ነገ እጠይቃታለሁ ሲል ነው መንገድ ላይ አግኝተው ሌላ ሰው ማግባቷን የነገሩት ...በserious ግን፤ እስከ ዛሬ ህዳሴ ስንል ማለት ነው፣ ስንት ሳንለውጥ የረሳነው ነገር አለ መሰላችሁ ... የእውነት እስቲ አሁን እዛ መቶ ብር ላይ ያለው ሰውዬ ዘንድሮም በቁምጣ እርሻ ማረስ ነበረበት? የምር አሀ ስለህዳሴው እየተረክን ቁምጣ ለብሶ የሚያርስ ሰውዬን ገንዘብ ላይ ማስቀመጥ ምን ይባላል? ... እና እንደ suggestion ማለት ነው፣ መቶ ብራችን ላይ ያ በቲቪ የሚተዋወቀውን ትራክተር ዱቅ አድርገን፣ ሰውዬውና ባለትራክተሩ፣ ‹‹እኔ ልንዳው፤ ተው እኔ ልንዳው›› አይነት ልማታዊ ፉክክር ውስጥ ሲገቡ አንስተን ብራችን ላይ ዱቅ ማድረግ፡፡ እየው! ከዛ በኋላ መቶ ብራችንን ባየን ቁጥር ‹‹ልማታዊ ተነሳሽነት›› እስከ ጫፍ ይወረን ነበር፡፡አይ ግን አሁን አንዳንዴ ዝም ብዬ ሳስበው፣ ‹‹ኧረ ሀበሻ!›› ሊያስብሉ የሚችሉ ችሎታዎቻችንን አድቀን እየተጠቀምንባቸው አይደለም፡፡ የእውነት እስቲ አስቡት፤ አሁን ይሄን ሰሞን ማለት ነው በእያንዳንዱ መሥሪያ ቤት ያለ እያንዳንዱ ሰው የአንድ ወር ደሞዙን ለግድቡ እንዲለግስ ‹‹almost›› ምትሀታዊ በሆነ ሁኔታ እያስማማን አይደል!? እና በቃ እንዲህ አይነት ማጂካል የማስማማት ችሎታ ካለን፣ ለምንድን ነው እነጋዳፊ ይሄን ያህል ሲባሉ ዝም ብለን ያየናቸው? የምር የምር ደስ አይልም ... የእውነት እዩ፣ ዕዛ ኖቤል ነው ምንድን ነው የሚሉት ዝግጅት ላይ ‹‹እንደ ሀገር›› ሊያሸልመን የሚያስችለውን ችሎታ በኢትዮጵያችን ውስጥ ብቻ ደብቆ ማቆየት በኋላ ‹‹ቲች! የሌለ ነው የቆጨኝ!›› ብሎ ለልጆቻችን መናዘዝን ያመጣል ... እናም በዚህ ዙሪያ የሚመለከታችሁ ሰዎች የሆነ ነገር አድርጉና የሆነ ነገር በሉን፡፡ግን ግን ስለ‹‹ኧረ ሀበሻ!›› ነገሮች ካነሳን አይቀር እንዲህ ስኳር፣ ዘይት ምናምን የሆነ ምሸግ ውስጥ የምትደብቁ ነጋዴዎች፣ እኛን ሳታማክሩ ልትወሩ ያሰባችሁት ሀገር ማንን ነው!? አይ የምር እኛ ጤነኛ ‹‹traders›› አሉን፣ አለን ብለን በምናስብበት ጊዜ፣ እንዲህ ለእቃ ፊልም የሚወጣው አይነት ትግል ሲፈጠር፣ አይደለም ሀገር ፕላኔታችንን ሰተን ራሱ የማንመልሰው እንቆቅልሽ ነገር ነው ...የእውነት ሳላሾፍ፤ ግን እዚህ አብሯችሁ የተፈጠረ ሕዝብ እያለ ገና ለገና ‹‹ነገ ይጨምራል፤ ስለዚህ ዛሬ እኔ ... ›› አይነት የዜሮነት ሙድ የምር የምር ከልብ ይደብራል፡፡ እስቲ አሁን ዝም ብላችሁ ስታስቡት፣ ያ ቀንዳሙ ሰይጣን ስለምታደርጉት ነገር ቢሰማ፣ ‹‹ቲች! ብለው ብለው በለጡኝ!?›› አይነት ከባድ ትካዜ ውስጥ ባትከቱት ነው? ... እናማ ማለት ነው ነገሮች እንዲሀ ሲከብዱ ‹‹መላው እኮ እዛ ጋር ነው›› የሚል ጥሩ አዋቂ ጥፍት ሲልብን በቃ ያ ቲቪ ላይ የሚነግሩን የትራንስፎርሜሽን እቅድ እስኪሳካ እኔ ነኝ ያለ ‹‹ሀይበርኔሽን›› የሚያስተምረን መለኛ ሰው ብናገኝ ይፀድቅብን ነበር! የምር አሁን እስቲ እናንተ የዋጋ ውድነቱን ይቆጣጠረዋል ብላችሁ ‹‹near›› አንስታይን አይነት ቀመር አድርጋችሁ ስለ‹‹price limi››ቱ የነገራችሁን ሰዎች፣ አሁን እቃዎቹ አይደለም ሱቅ ሼልፍ ላይ ቀርቶ ድሮ በተነሱት ፎቶ እንኳን አልገኝ ሲሏችሁ ‹‹አቦ መች ነው የምንነቃው?›› የሚያስብል ቅዥት አልሆነባችሁም? አይ የምር ግን የምር ማለት ነው፣ አሁን ሌላ ምንም ሰው ሳይመጣብን እንዲህ እርስ በእርስ ስንሸዋወድ አንድ መሆኑን ትተን የሆነ ሶስት አይነት ሕዝብ የፈጠርን አይመስልም?እና ብቻ በዚህም በዛም ስንት ለምን እንደተደረጉ/እንደሆኑ ግራ የሚያጋቡ ነገሮች በዝተዋል፡፡ ኧረ ደግሞ ረስቸው፤ እናንተ ለበዓል ‘ለት ዶሮ እንሰራለን አንሰራም ብላችሁ ድራማ ያቀረባችሁ ሰዎች ... እንዴት ነው እስካሁን በፍቃደኝነት ‹‹ጤነኛ ነን ወይ›› ብላችሁ አንዱ ጤና ጣቢያ ራሳችሁን ቼክ አላስደረጋችሁም? ... እንዴ! የእውነት ተዉ እንጂ! ተው እንጁ! ... አለመስራት አኮ ሀጢያት ነው አልተባለም ... ዝም ብሎ መቀመጥን ‘ኮ ሕግ አልከለከለም፡፡ እንዲህ ‹‹እሱም ከሰራማ እኔም ... ›› አይነት ሙድ የምር ያቀያይማል፡፡መሰራት የሌለበትን ነገር መስራት፤ መሰራት ያለበት ነገር ደግሞ አለመስራት በቃ ግርም ግርም የሚል አንቆቅልሽ ነው፡፡ እንደው ካነሳሁት አይቀር፤ መብራት ‹‹ኃይሎቻችን››? ይሄን ሰሞን ቤት ስንገባ ጠብቃችሁ መብራቱን የምታጠፉት ሳይጠፋ ውሎ ቢያድር ቅር የሚለን እየመሰላችሁ ነው? አይ የምር ስንት ሲቃ የሚያሲዝ ‹‹event›› እያለ መብራት መጣ ብቻ ሲባል ሰምተን ሲቃ እንዲተናነቀን ስታደርጉ፣ አለ አ እኛስ አውቀናችኋል፣ እነዛን ኤክስፖርት እናደርግላችኋለን ያልናቸውን ሰዎች ግን ‹‹ወይኔ ጉዳችን›› እያስባላችሁ ባታስደነግጡን ነው?እና ማለት ነው አሁን ይሄ የአባይን ነገር ወንዙን ራሱ ገና በዚህ ዓመት ‹‹discover›› ያደረግነው እስኪመስል ድረስ ‹‹fever›› እየለቀቁብን አይደል? እና በቃ ይገነባል ብለው የነገሩን ዕለትን ለምን ብሔራዊ በዓል ብለነው ሁለተኛ እንቁጣጣሽ አናደርገውም? የምር ምናልባት ምንአልባት አንዱ መቶ ምነው ቢለን ‹‹ሲለይልንስ›› ብለን ብንመልስ ነው፡፡ቆይ ቆይማ! ... ይሄ መቼ ለት የፕሬስ ‹‹ነፃነት›› - ነፃነት የሚለው ቃል በታይፕ ስህተት ነው የገባው ብላችሁ ራሳችሁን የሞገታችሁ ሳልዋሽ ማለት ነው ስህተቱ ከኔ ነው - እና የፕሬስ ‹‹ነፃነትን›› (እየው እንዳትስቁ እሺ) ለማክበር የተሰበሰቡ ጊዜ ቀድመው የደረሱ ታዳሚዋች ቀን ሁላ አሳስተው የገቡ እስኪመስላቸው ድረስ ነገሩን ታችና ላይ ብጥብጥ ያደረጋችሁት ሰዎች ምነው? ‹‹ልማታዊ የፕሬስ ነፃነትን በማስፈን ከአፍሪካ የቀዳሚነት ደረጃን ለመያዝ እንተጋለን ብላችሁን አልነበር እንዴ? እና ያላችሁን ረስታችሁት ነው ወይስ የዛኔ እንደዛ ያላችሁን የዛን ቀን ‹‹የወሰዳችሁት ነገር›› የሌለ አደፋፍሯችሁ ነው? አይ ግን የምር የስብሰባው ቀን እንደዛ ብታደርጉ አይደለም ታዳሚው ወንበሮቹ ራሳቸው ነፍስ ቢኖራቸው ተነስተው ባይነኩት ነው? እና ማለት ነው ትንታ እንኳን ሳያስቸግራቸው የፕሬስ ነፃነት እስከ ጫፍ ተከብሯል የሚሉን ሰዎች፣ የፕሬስ ነፃነትን እንደ ‹‹ፋሲካ›› የአንድ ቀን ሙድ አድርገው እንዳይሆን ... የምር የሰው ነገር እኮ አይታወቅም፡፡ብቻ በዚህም በዚያም የፕሬስ ነፃነትን ለትራንስፎርሜሽን እቅዳችን መሳካት ሳታውቁ በስህተት እያወቃችሁ በድፍረት እንደግብአት ሳታስቡ የቀራችሁ ቀማሪዎቻችን ለምን በዚህ ሳምንት እቅዱን ሪቫይዝ አድርጋችሁ ነፃነቷን ‹‹front page›› ላይ አትከቷትም፡፡አይ ግን ሳላሾፍ፤ እናንተ ሬዲዮኗን፣ ኢንርኔቷን፣ ‹‹info››ዋን ለኛ ብላችሁ ጃም የምታረጉልን ‹‹የልማት ጀግኖች››፣ ለጀግንነታችሁ መልስ እንዲሆን ለአመስትና አስር ዓመት ቤርሙዳ አካባቢ ‹‹vacation›› ብትወስዱስ? የምር የምር እኛም እናንተም እንረፍ እንጂ!

ከአዲስ አበባ ጓዳዎች አንዱ:-

አማኑኤል ሆስፒታልአስቴር ጩጬ ትባላለች፡፡ የሁለት ልጆች እናት ናት፡፡ ነፍስ ካወቀች እስከ አሁኑ ደቂቃ ያለውን የግል ሕይወቷን ዳጎስ ባለ መጽሐፍ ለመተረክ ቆርጣ ተነስታለች፡፡ እስከ አሁን ከአስር ደብተር በላይ ጽፋለች፡፡

ከአራቱ ደብተሮች የተቀነጨበው እንዲህ ይነበባል፡፡

በስንዱ አበበ

ከዶክተሩ ጋር ዘለግ ያለ ጊዜ የወሰደ ቆይታ ደረግን፡፡ የሱስ ሕክምና በአማኑኤል ሆስፒታልም እንደሚሰጥ አስረዳኝ፡፡ አልጋ አንደሚሰጠኝ ተስፋ ሰጠኝ፡፡ በማግስቱ

በጠዋት እንድመጣ ተነግሮኝ ተሸኘሁ፡፡

ወደ ገፅ 23 ዞሯል

Page 11: አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 166 ቅዳሜ ሚያዚያ 29 2003 ኢሕአዴግ … · ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ አውራምባ ታይምስ 4ኛ

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 166 ቅዳሜ ሚያዚያ 29 2003

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

11

p Ç T@ S ´ “ —

አ ፍታ1የዜማና ግጥም ደራሲ፡፡] በቲያትርም እንደ ወጋየሁ ንጋቱ፣ እትዬ አስናቁ፣ ወ/ሮ አስካለ አምነሸዋን ለሙያቸው ፍፁም የሆኑና ታማኝ ሰዎች ናቸው፡፡ ብሔራዊ ቴአትር የበሰለ ሥራ ስለሚሰጥህ ለዚያ ዝግጁ መሆን አለብህ፡፡ ብዙዎቹ ባለሙያዎችም የምታከብራቸው ናቸው፡፡ ስላደኩበት፣ ስላረጀሁበት ሳይሆን በተነፃፃሪነት ሳየው ልዩ ስለሆነ ነው፡፡ ከወጣቶች ሁሉን ነገር አሟልቶ የሰጣት የምለው አዜብ ወርቁን ነው፡፡ [ማክሰኞ በብሔራዊ ቴያትር የሚታያው ‹‹የሚስት ያለህ›› ቲያትር ተርጓሚና አዘጋጅ ናት፡፡] ብቃት ያላት፣ ቆራጥና ድርጊቷ ከልቧ የሚመነጭ ነው፡፡ እንከን የማይወጣላት አመለ ሸጋም ነች፡፡ ከራሷ ሰውን የምታስቀድም እና የምትረዳ ነች፡፡ በሙያዋ ያገዟት ሰዎች እነማን ናቸው? በሙያዬ ውስጥ በፍቅር ተቀብለው እንድሰራ ያደረጉኝ እትዬ አስናቀች (አስናቀች ወርቁ)፣ መራዐዊ ስጦት እና አብዛኛውን ጊዜ በሰራሁበት በዘመናዊ ኦርኬስትራ ውስጥ የሚገኙ ሙዚቀኞች ሁሉ እጅግ የማልረሳቸው ያገዙኝ ውድ ጓደኞቼ ናቸው፡፡ ያ አንጋፋ ስብስብ አሁን የት ደረሰ? እኔ እንደ ምንም ብዬ በወር አንድ ጊዜ በብሔራዊ ቴአትር እንድንገናኝ አድርጌያለሁ፡፡ ቁጥራችን ወደ ሰላሳ ይጠጋል፡፡ [በወር አንዴ ሲሰባሰቡ ከጥበብ ሰዎች በተጨማሪ በወቅቱ የቴአትር ቤቱ ባልደረባ የነበሩ የቢሮ፣ የፅዳት እና የጥበቃ ባለሙያዎችም ይገኙበታል፡፡]

አስናቀችን ትጠይቂያታለሽ? በምን ሁኔታ ላይ ትገኛለች?ሰሞኑን እኔም ትንሽ ችግር ላይ ስለነበርኩ [ልጇ ታሞባት ነበር፣ አሁን ግን በጥሩ ሁኔታ ላይ ይገኛል] ጊዜ ስላጣሁ አልሄድኩም፡፡ አልፎ አልፎ ግን ጠይቃታለሁ፡፡ ሁሉን አሟልቶ የሰጣት፣ በጣም የፍቅር እና የሙያ ሴት ናት፡፡ በመጨረሻ አልጋ ላይ መቅረቷ በጣም ያሳዝናል፡፡ [በነገራችን ላይ ከአስናቀች ወርቁ ጋር ቆይታ ለማድረግ ሁኔታዋን በቅርብ የሚከታተሉት እና በህይወት ታሪኳ ዙሪያ ‹‹አስናቀች ወርቁ›› የሚል መፅሐፍ ከፃፉት (ተንቀሳቃሹ ቤተ-መፅሐፍት) ጋሽ ጌታቸው ደባልቄ ጋር ለመሄድ ቀጠሮ ይዘን በወቅቱ አመም ስላደረጋቸው ቀጠሯችን ለሳምንታት ተራዝሞ እስካሁን አልተሳካም፡፡ የሚገርመው ደግሞ ባለፈው

ቅጥር መቼና በምን?ብሔራዊ ቴያትር በ1958 ዓ.ም በተቀጠርኩበት የድምፃዊነት ሙያ በርካታ ሥራዎችን ሰርቻለሁ፡፡ በይበልጥ ከጌጡ አየለ ጋር በምንሰራቸው የኮሜዲ ዘፈኖች ከተመልካች ከፍተኛ ፍቅር እና አድናቆት አግኝተንበታል፡፡ ‹‹ህልሜን ፍታልኝ›› ይህ ከጌጡ አየለ ጋር የተጫወትኩት የኮሜዲ ዜማ እያዝናና ቁም ነገር የሚሰጥ ነው፡፡ በርካታ ሰውም በፍቅር ይወደው ነበር፡፡ ከጌጡ ጋር ከአስር በላይ የሚሆኑ የብሔራዊ ቴያትር አዳራሽን ሕዝብ የሚያነቃንቁ ዜማዎችን ሰርተናል፡፡ ‹‹የፌዝ ዶክተር›› የፌዝ ዶክተር ለመጀመሪያ ጊዜ የሰራሁት ቲያትር ነው፡፡ የወከልኩት የዱካ ሴት ገፀ-ባህሪይን ነበር፡፡ ጥላ፣ አምታታው በከተማ፣ የባላገር ፍቅር፣ ፍቅር የተራበ፣ ስምንቱ ሴቶች - ሌሎች የተወንኩባቸው ቲያትሮች ናቸው፡፡ ‹‹አምታታው በከተማ››ይህን ሙዚቃዊ ቲያትር ስሰራ መጀመሪያ ላይ ‹‹ቤትም እኮ ነበር›› የሚል፣ በተለይ የትዳር ዓለም ያሉ ሴቶች ውስጥ ያለ ዘፈን እጫወታለሁ፡፡ ወክዬ የተጫወትኳት የገጠር ሴት ገፀ-ባህሪይ ደግሞ አለች፡፡ ሁለቱንም የወከልኩት እኔ እንደሆንኩ ብዙዎች አያውቁም ነበር፡፡ ሲነገራቸውም በጣም ይጠራጠሩ ነበር፡፡ አርቲስት ሁሉንም መስሎ እና አስመስሎ መጫወት አለበት፡፡ ከፊልም በቅርቡ የተመረቁትን ዱካ እና ያ ልጅን ጨምሮ ማራ፣ የህሊና ዳኛ እና በበርካታ ፊልሞችን ላይ ሰርቻለሁ፡፡ ገና ያልወጡም አሉ፡፡

አገርን ማወቅ ሰው ውጪ አገርን ለማየት እንደሚጓጓው እኔ አገሬን ለማወቅ በጣም እፈልግ ነበር፡፡ በሥራዬ ሳቢያም በየክፍለ አገራቱ ተዟዙሬ በርካታ ትዝታዎችን ያስቀረሁባቸው ደስ የሚል ጊዜ አሳልፌያለሁ፡፡ አድናቆቷን ለማን?ለሙያው እስከ ህይወት መስዋዕትነት ሊከፍል ይችላል የምለው መርዐዊ ስጦትን ነው፡፡ [የክላርኔት ተጨዋች፣

አርብ ጋሽ ‹‹ጌቾ›› ብሔራዊ ቴአትር ውስጥ ወድቀው የስብራት አደጋ ደርሶባቸው ሆስፒታል ተኝተዋል፡፡ አውራምባ ታይምስ ለሁለቱ ዘመን አይሽሬ የጥበብ ሰዎች ሙሉ ጤንነትን ብቻ ሳይሆን ሌሎችን ለመርዳት የተንቀሳቀሱ እግሮችና እጆች ልቦናቸው ለሁለቱ ሰዎችም ክፍት እንዲሆን ይመኛል፡፡] አንጋፋ የጥበብ ሰዎችን ማንነት የሚያጎላ፣ የሚዘክር የጥበብ ውጤት ወይም ማኅበር እና መድረክ በአገራችን የለም ማለት ይቻላል፡፡ ችግሩ የቱጋ ነው ብለሽ ታስቢያለሽ?ሙያው ለሕዝብ ይጠቅማል እንጂ ሙያተኛው አልተጠቀመም፡፡ በድሮ ዘመን አርቲስቱ የሚታየው እንደ ‹‹ዝቅተኛ›› ነገር ነበር፡፡ ነገር ግን ይንቁት የነበሩ ሰዎች ሁሉ በሙያው ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡ ከድሮ ጀምሮ እንደ ሌሎች የሙያ ዘርፎች ሁሉ የኪነ-ጥበብ ሙያም የሚከበር ቢሆን ኖሮ መሰረት ይዞ መጥቶ ዛሬ ጥሩ ደረጃ ላይ ይደርስ ነበር፡፡ ማኅበር ሁሌም ይቋቋማል ግን ውጤታማ አይደለም፡፡ በርግጥ አሁን ፍንጮች ይታያሉ፡፡ ለሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ምን መልዕክት አለሽ?በግል የሚደረግ እንቅስቃሴ ተተረማምሶ ከመቅረት ውጭ ምንም ስለማይፈይድ ይህ ጉዳይ በመንግስት ደረጃ ታስቦ እንደሌላው ሙያ ሊከበርና ቦታ ሊሰጠው ይገባዋል፡፡ አሁን ቴክኖሎጂው ስለተራቀቀ እና የሰውም የግንዛቤ ደረጃ ከፍ ስላለ መሰረት አኑሮ መሄድ ይቻላል፡፡ እስካሁን ላለነው ግን ሙያችን እንደሁ ባክኖ ነው የቀረው፡፡ ‹‹በህይወቴ ሰራሁ›› የምትይው ትልቁ ቁም ነገር?በጣም የጎላ ባይሆንም ውስጤ ግን በጥሩ የሚያስታውሰው ነገር አለ፡፡ ድሮ ብሔራዊ ‹ቴአትር ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ቴአትር› ተብሎ በሚጠራበት ወቅት ሠራተኛው ጡረታ እና ህክምና አልነበረውም፡፡ ባለስልጣኑ በፈለገ ጊዜ ሊያባርህ እና በጥበቃ ከበር እንዳታስገባው ካለ ልትቀር ትችላለህ፡፡ ከለውጡ (ከ1966 በኋላ) የመንግስት ቋሚ ሠራተኛ እንድንሆን፣ የጡረታ እና የህክምና መብት እንዲከበርልን የሚል

ወደ ገፅ 23 ዞሯል

“የአድማ መሪ ነሽ ተብዬ ለአራት ወር ታስሬያለሁ”

ፍቅርተ ደሳለኝ [አርቲስት]

66 ዓመት ደፍኗታል፡፡ በ1992 ዓ.ም ጡረታ እስከወጣችበት

ጊዜ ድረስ እንደ ቤቷ በምታየው ብሔራዊ ቴያትር ለ34 ዓመታት

አገልግላለች፡፡ ከጌጡ አየለ ጋር በመሆን ታቀርባቸው የነበሩ

የኮሜዲ ይዘት ያላቸው ዘፈኖቿ በሕዝብ ውስጥ እንድትገባ

አድርጓታል፡፡ የመስራት አቅም አሁንም አብሯት እንዳለ በቅርቡ

በተመረቁ ፊልሞች ላይ እያስመሰከረች ነው፡፡ አቤል ዓለማየሁ

“ሙያው ለሕዝብ ይጠቅማል እንጂ ሙያተኛው አልተጠቀመም”

ከምትለው አንጋፋዋ ፍቅርተ ደሳለኝ ጋር አንዳፍታ አውርቷል፡፡

አርቲስት ጌታቸው ደባልቄ ከባድ ጉዳት ደረሰባቸው

አቤል ዓለማየሁ

ጉዳታቸው ለህክምና 105 ሺህ ብር አስከፍሏል •

የጥበብ ቤተሰቡ ከአጠገባቸው እንዲሆን ተጠይቋል •

በኢትዮጵያ ኪነ-ጥበብ ዙሪያ ባላቸው የጠለቀ ዕውቀት እና በሚሰጡት ትንታኔ ‹‹ተንቀሳቃሹ ቤተ-መፃህፍት›› እየተባሉ የሚወደሱት አንጋፋው ጌታቸው ደባልቄ (አርቲስት) ባለፈው ሳምንት ብሔራዊ ቴያትር ውስጥ ወድቀው ከባድ የስብራት አደጋ አጋጠማቸው፡፡ ስብራቱን በሰው ሰራሽ አጥንት ለመቀየር 105 ሺህ ብር ወጪ ተደርጓል፡፡

ጡረታ ቢወጡም አዘውትረው ከማይጠፉበት ብሔራዊ ቴአትር ባለፈው ሳምንት አርብ በቴአትር ክፍል ውስጥ በመውደቃቸው የዳሌ አጥንታቸው መሰበሩን አርቲስቱ ለአውራምባ ታይምስ ገልፀዋል፡፡ በተለያዩ የህክምና ባለሙያዎች ከታዩ

በኋላ በአገር ውስጥ ህክምና ሊረዱ እንደማይችሉ ቢነገራቸውም ሰዎች ጠቁመዋቸው ወደ ኪዩር ሆስፒታል አቅንተው በቀዶ ጥገና ተፈጥሯዊ አጥንታቸው ወጥቶ ብረት ነክ የዳሌ አጥንት ቅየራ (Hip Replacement) እንደተደረገላቸው በቅርብ የሚከታተላቸው ሳሙዔል ታዬ (ነርስ) ነግሮናል፡፡ ልጃቸው መዓዛ ጌታቸው ለቅየራው ብቻ 105 ሺህ ብር እንደከፈሉ ገልፃ ‹‹ገንዘቡን ያገኘነው ከዚህም ከዚያም ተሯሩጠን በብድር ነው›› ብላለች፡፡ ያነጋገርናቸው የቅርብ ወዳጆቻቸው የቀዶ ጥገና የህክምናውን ክፍያ ብድር ለማቃለልም ሆነ በቀጣይነት ህክምናቸውን ለመከታተል ይረዳቸው ዘንድ በአገር ውስጥም ሆነ በውጪ የሚገኘው የጥበብ ቤተሰብ ከጎናቸው ተሰልፎ የገንዘብ አቅማቸውን እንዲያጠናከር ጥሪ አቅርበዋል፡፡

አርቲስቱ በቅርቡ አሜሪካ ከሚገኙ የጥበብ ቤተሰብዎች ዘንድ የግብዣ ወረቀት ተልኮላቸው ኤምባሲ ገብተው ቃለ-ምልልስ በማድረግ ግንቦት 10 የቪዛ ቀጠሮ የነበራቸው ሲሆን ከተሳካም በቀጣዩ ወር መጨረሻ ወደ ቦታው ያቀኑ የነበረ ቢሆንም በደረሰባቸው ጉዳት ሳቢያ ጉዟቸው ጥያቄ ምልክት ውስጥ ገብቷል፡፡ ‹‹እሱን ጊዜው ሲደርስ እናወራዋለን›› በማለት ወደ አሜሪካ ስለማቅናታቸው እርግጠኛ እንዳልሆኑ ጌታቸው ደባልቄ ለአውራምባ ታይምስ ገልፀዋል፡፡

ሚያዚያ 20/1928 ዓ.ም. ደብረ ፅዮን ገደም የተወለዱት ‹‹ጋሽ ጌቾ›› በ1994 ዓ.ም. በአዲስ

አበባ ማዘጋጃ ቤት ቴአትርና ሙዚቃ ማስፋፊያ ክፍል የተቀጠሩ ሲሆን ከዚያም ወደ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ቴአትር (በአሁን አጠራሩ ብሔራዊ ቴአትር) ተዛውረው ለረዥም ዓመታት በተዋናይነት፣ በቲያትር ደራሲነት፣ አዘጋጅት እንዲሁም ለበርካታ ዓመታት የቴአትር ክፍል ኃላፊ፣ የህዝብ ግንኙነት፣ የፕሮግራምና ፕሮዳክሽን ተጠባባቂ ኃላፊ ሆነው አገልግለዋል፡፡ አሁንም ተወዳጅነታቸው ያልቀነሰው የግርማ ነጋሽ ‹‹የኔ ሀሳብ››፣ ‹‹ምነው ተለየሽኝ›› የሚሉትን የዘፈን ግጥሞች ደርሰዋል፡፡ ለሌሎች ድምጻዊያንም ግጥሞች አበርክተዋል፡፡ ከኢትዮጵያ ሥነ-ጥበባትና መገናኛ ብዙሀን ሽልማት ድርጅት በ1994 ዓ.ም. በቴአትር ዘርፍ የህይወት ዘመን ተሸላሚ መሆናቸው ይታወሳል፡፡

እንቅስቃሴ ማድረግ እንዳለባቸው ስለተነገራቸው መጠነኛ በሆነ መልኩ ‹‹ብድግ ቁጭ›› ማለት የጀመሩት ጋሽ ጌቾ በትላንትናው ዕለት ሆዳቸውን ታመው ህክምና እንደተደረገላቸው ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡ በሆስፒታሉ የሚቆዩት ለአንድ ሳምንት እንደሆነ አስቀድሞ ስለተነገራቸው ምናልባትም ከነገ በስቲያ ይወጣሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ /አውራምባ ታይምስ ለተንቀሳቃሹ ቤተ-መፃህፍት ሙሉ ጤንነትን ከልብ ትመኛለች፡፡/

ውነትን እራኩት እውነት ሲያጣጥር እያየሁት ታንገቱ ገመድ ገብቶበት የፊጥኝ ታስሮ ሲያቃትት

ውስጤ በነገር ገልምቶ ሰውነቴ እየታማከንፈር ነክሼ እንዳልሰማ

አይኖሩ እኖር ብዬ እሰነብትአለባብሼ በሽፍንፍን ተመሳስዬ አለፍኩት

(ሐምሌ 2000) - እሰይ ፍልስምናእንዳልካቸው ይመር

ያገኘሁት እውነት መስሎኝ ...

ሸሸሁኝ ቢጋፉ ተውኳቸው ቢከፉ ጣልኳቸው ቢከብዱ እንዲህ ተለያይተን

የማይተዉ እነሡቡና ‘ሚጠጡበት

ሥሜን እያነሡ፤ የነገሩ ፍቺ የገባኝ ምስጢሩ

በመጥላታቸው ውስጥ ያ...መውደድ መኖሩ፡፡

ስብጥር ዘቢብ መልኪ 2002

Page 12: አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 166 ቅዳሜ ሚያዚያ 29 2003 ኢሕአዴግ … · ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ አውራምባ ታይምስ 4ኛ

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 166 ቅዳሜ ሚያዚያ 29 200312

Page 13: አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 166 ቅዳሜ ሚያዚያ 29 2003 ኢሕአዴግ … · ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ አውራምባ ታይምስ 4ኛ

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 166 ቅዳሜ ሚያዚያ 29 2003

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

13

እ ን ግ ዳ

Page 14: አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 166 ቅዳሜ ሚያዚያ 29 2003 ኢሕአዴግ … · ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ አውራምባ ታይምስ 4ኛ

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 166 ቅዳሜ ሚያዚያ 29 200314 ተጠየቅ

ባለፈው ሳምንት በ‹‹ተጠየቅ›› አምዳችን ‹‹የዳያስፖራ ቤቶች ግንባታ ዕግድና ያልተቋጨው ውዝግብ›› በሚል ርዕስ በጣሊያን ሮም በሚገኙ 60 ኢትዮጵያውያን ተቋቁሞ ስለነበረው አዲስ ሮም የመኖሪያ ቤት ኃላፊነቱ የተወሰነ የሕብረት ሥራ ማሕበር አመሰራረት፣ አባላት ስላሰባሰቡት ገንዘብና በቀድሞ ሥራ አመራር ኮሚቴ በዕምነት ማጉደል የተነሳ የማሕበሩን ገንዘብ ያለአግባብ ለግል ጥቅም ማዋላቸውን የተመለከቱ ጉዳዮችን፣ የዚህንም ክስና የፍርድ ውሳኔ፣ እንዲሁም ከማሕበሩ ቤት ግንባታ መቆም ጋር ተያይዞ የተነሱ ቅሬታዎችን በመያዝ የሚመለከተውን የመንግስት አካል በማነጋገር ፅሁፉን ለአንባቢያን ማቅረባችን ይታወቃል፡፡

ባለፈው ሳምንት ሀሙስ ዕለት የቦሌ ክፍለ ከተማ የሕብረት ሥራ ማህበራት ማደራጃና ልማት የሥራ ሂደት አስተባባሪ የሆኑት አቶ ጎይቶኦም ግርማይን አውራምባ ታይምስ ከሰዓት በኋላ ስለጉዳዩ ጠይቃ ምላሽ በማግኘት ከቢሯቸው ስንወጣ በር ላይ ማሕበሩን በተመለከተ ሌላ ቅሬታ ካላቸው የማሕበሩ አባላት መካከል አቶ ዳዊት መስፍንና አቶ ሙሉጌታ በልሁ የዚህን ፅሁፍ አቅራቢ አነጋግረውት ነበር፡፡

በወቅቱ ግለሰቦቹ የሚያቀርቧቸውን ቅሬታ በማድመጥና ሕጋዊ መረጃዎችን በመመልከት የሚመለከተውን አካል አነጋግሮ ቀደም ሲል ከተዘጋጀው ፅሁፍ ጋር ለማካተት የጊዜ ጥበት መኖሩን በመግለፅ ቅሬታቸው በዚህኛው ሳምንት ሊስተናገድ እንደሚችል አውራምባ ታይምስ ለአቶ ዳዊትና ለአቶ ሙሉጌታ አስረድታ ስምምነት ላይ ደረሱ፡፡

‹‹አዝነናል››ፅሁፉ በጋዜጣው ከተስተናገደም በኋላ በርካታ

የስልክ ጥሪዎች ከአገር ውስጥና ከጣሊያን ሮም ድረስ በተደጋጋሚ ተደውለው ለአውራምባ ታይምስ ጋዜጣ ትልቅ አክብሮትና አመኔታ እንዳላቸው፣ ነገር ግን በወጣው ዘገባ ማዘናቸውን ገልፀውልናል፡፡ ለሚደውሉት ግለሰቦችም አውራምባ ታይምስ ገለልተኛ የሚዲያ ተቋም መሆኗን በማስታወስ ስለነበረው ሁኔታ ካስረዳናቸው በኋላ የሚያነሱትን ቅሬታ በማድመጥና በእጃቸው ላይ የሚገኙትን ሕጋዊ መረጃዎች በመመልከት ቅሬታቸውን እንዲህ አቅርበነዋል፡፡

አቶ ዳዊት መስፍን የማሕበሩ አባል ሲሆኑ ከጣሊያን ሮም አዲስ አበባ ከመጡ ሁለት ወራት ሆኗቸዋል፡፡ የመጡበትም ምክንያት ለእረፍት እና ማሕበሩ ከተመሠረተ ጀምሮ የተለያዩ ችግሮች ስለነበሩበት እንደማሕበርተኛ ችግሮችን ለማስተካከልና ማሕበርተኛው ከመንግስት በተሰጠው የመኖሪያ ቤት ቦታ ላይ ግንባታው የሚያከናውንበትን ሁኔታ ለማመቻቸት እንደሆነ ይናገራሉ፡፡

የቀድሞ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ባባከናቸው ገንዘቦች እንደማይደሰቱ፣ ገንዘቡ እንዲመለስ ደግሞ ቢቻል በሰላም በሽማግሌዎች፣ ካልሆነ ደግሞ ‹‹ገንዘብ ያለአግባብ ለግል ጥቅም አውለዋል›› የተባሉት ግለሰቦች በሕግ ተጠይቀው እንዲመልሱ ከማሕበርተኛው ጋር በመሆን በሚደረገው ጥረት ላይ መገኘታቸውን የማሕበሩ አባል ተናግረዋል፡፡ ‹‹...በግለሰቦቹ ላይ ቀርቦ ለነበረው ክስ የማሕበሩ ሊቀመንበር የሆኑት አቶ በቀለ ከበደ ባደረጉት የመጀመሪያ እንቅስቃሴ ላይ ምንም አይነት ተቃውሞ የለኝም›› የሚሉት አቶ ዳዊት ሊቀመንበሩም በወቅቱ ጥሩ ሥራ መሥራታቸውን አልሸሸጉም፡፡

በሥራ አመራር ኮሚቴ ያለመወከል ጥያቄኖቬምበር 14/2010 እ.ኤ.አ 30 የማሕበሩ አባላት

ፊርማቸውን በማኖር ከጣሊያን ሮም ለአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር የቦሌ ክ/ከተማ የሕብረት ሥራ ማሕበር ማደራጃ፣ ‹‹በአሁኑ ጊዜ በሥራ ላይ ያለው የአዲስ ሮማ የሕብረት ስራ ማሕበር የስራ አመራር ኮሚቴ የማይወክላቸው መሆኑን በመጥቀስ ደብዳቤ ፅፈው ነበር፡፡

በደብዳቤው መሠረትም በአሁን ወቅት የማሕበሩን የሥራ ኃላፊነት የተረከበው የሥራ አመራር በተለይም የማሕበሩ ሊቀመንበር በየጊዜው የሚወስዳቸው እርምጃዎች ሁሉ መንግስት በሰጣቸው እና የአፈር ግብርና ሊዝ በስማቸው በተከፈለበት መሬት ላይ አቅማቸው በሚፈቅደው መሠረት ባገኙት ዕድል ራሳቸውን ጠቅመው ለአገር ጥቅም የሚውል ቅርስ ለመጣል ያላቸውን ዕድል ለመጠቀም እንዳይችሉ እንቅፋት እንደሆነባቸው ተገልፃEል፡፡ ተያይዞም በሥራ ላይ ያለው የአመራር ኮሚቴ፣ በተለይ የሊቀመንበሩ አሠራር ማሕበርተኛውን ሙሉ በሙሉ ያላሳተፈ መሆኑን በተደጋጋሚ ለማስረዳት መሞከራቸውን፣ ማሕበሩ ከጊዜ ወደ ጊዜ ማለቂያ ወደሌለው ውዝግብ እየሄዳ እንዳለ፣ አብዛኛው የማሕበር አባልም ሀሳቡን ባልሰጠበትና ባልተስማማበት ውሳኔ ተጎጂ እየሆነ እንደሚገኝ በመጠቆም የሥራ አመራሩ የማሕበሩን አባላት ሃሳብ ሳይጠይቅና ሳያገኝ ከፈፀማቸው ተግባራት መካከል ‹‹ዋና ዋና ናቸው›› የተባሉት ዘጠኝ ጉዳዮች ተጠቅሰዋል፡፡

‹‹ሕንፃ ተቋራጩን አናምንበትም››

ከላይ በተገለፀው ደብዳቤ ላይ የማሕበሩ አባላት በሙሉ ያልተስማሙበትን ባለአራት ፎቅ ሕንፃ የአባላቱን አቅምና የመስራት ጉልበት ያላገናዘበውን ውሳኔ በሙሉ የተቀበሉት በማስመሰል የማይታወቁ ዶክመንቶችን በማቅረብ የግንባታ ፈቃድ እንዲወጣ መደረጉ ተጠቅሷል፡፡ ይህንን በተመለከተ ከአባላቱ ውስጥ 2/3ኛው አባል እስካልተስማማበት ድረስ ተፈፃሚነት ሊኖረው እንደማይችል፣ እንደዚህ አይነት ውሳኔዎች በማሕበሩ መተዳዳሪያ ደንብ አንቀጽ 12.1.7 የተዘረዘረውን መሠረተ ሃሳብ የሚቃረን በመሆኑና ጉዳዩንም የማሕበሩ ሥራ አመራር እንዲያስተካክል በተደጋጋሚ ተጠይቆ ለማስተካከል ፍቃደኛ ሆኖ አለመገኘቱም በደብዳቤው ውስጥ ተዘርዝሯል፡፡

በሌላ በኩል ሕንፃ ተቋራጭ ድርጅቱን በተመለከተ አቶ ዳዊት ሌላ ቅሬታ አላቸው፡፡ ‹‹ዩኒቲ ኢንጂነሪንግ ፒ.ኤል.ሲ የቤቶቹን ግንባታ ለማከናወን በጨረታ ማሸነፉን በአቶ በቀለ በኩል ተነግሮን ነበር›› የሚሉት የማሕበሩ አባል የሕንፃ ተቋራጩ ስለያዘው ፍቃድ፣ ከማሕበሩ ጋር ስለተደረጉ ውሎች፣ ‘Bills of Quantity’፣ የሥራ ደረጃና ብቃት፣ አንድ የሕንፃ ተቋራጭ ሊያሟላ የሚገባቸውን ነገሮች፣ ወዘተ.. አለማየታቸውንና አለማወቃቸውን ያስረዳሉ፡፡ እንዲሁም በኖቬምበር 14/2010 እ.ኤ.አ ለቦሌ ክ/ከተማ የሕብረት ሥራ ማሕበር ማደራጃ በተፃፈው ደብዳቤ ላይም 30 ቅሬታ አቅራቢ አባላቶች ሕንፃ ተቋራጩን ተቃውመውታል፡፡

እነኚህ 30 የማሕበሩ አባላቶች ‹‹በሀገራችን የተደነገገው የሕንፃ ግንባታ ጨረታ አወጣጥ ሕግ በሚያዘው መሠረት አስፈላጊ የሆነው የጨረታ ማስታወቂያ ሳይወጣና ትክክለኛው ውድድር ሳይደረግ ጠቅላላ ጉባኤውም ሳያውቅ እና ሳይስማማበት ሥራውን ለአንድ ሕንፃ ተቋራጭ አሳልፎ በመስጠት፣ እንዲሁም በአዲስ ሮማ ማሕበር ባንክ ቁጥር 01280/340973 ከተቀመጠው ገንዘብ ላይ 2,700,000 ወጭ አድርገዋል›› ሲሉ አዲሱን የሥራ አመራርን ይወቅሳሉ፡፡

ሆኖም ሜይ 4, 2010 እ.ኤ.አ በማሕበሩ ሊቀመንበር አቶ በቀለ ከበደ ለዩኒቲ ኢንጂነሪንግ ፒ.ኤል.ሲ በተፃፈው ደብዳቤ ላይ ለ’Sub structure’ ኮንትራት ሥራ ዋጋ ክፍያ 13.473.483 ብር ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ በማሕበሩ ተቀባይነት እንዳገኝ ያሳያል፡፡ የውል ስምምነቱም በማሕበሩ በኩል አቶ በቀለ አየለ እና በሕንፃ ተቋራጩ አቶ ወንድወሰን ተስፋዬ መካከል የተደረገ ሲሆን በምስክርነት ወ/ሮ ገነት ከበደ፣ አቶ ነጋሽ መኮንን እና ወ/ሮ ሰብለ ደስታው ስምና ፊርማቸውን አኑረዋል፡፡

ክስና ፍርድሚያዚያ 4/ 2002 እነአቶ ሀሰን ሁሴን (ዘጠኝ)

ሰዎች በአዲስ ሮማ የመኖሪያ ቤት የሕብረት ሥራ ማሕበርና በአቶ በቀለ ከበደ ላይ በፌዴራል መጀመሪያ ፍርድ ቤት የእግድ ጥያቄን የሚመለከት ክስ አቅርበው ነበር፡፡ ግንቦት 2/2002 በፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ መሠረት ከሳሾች ‹‹የተከሳሽ ማሕበር ሒሳብ ይታገድልኝ›› ሲሉ መጠየቃቸውንና ተከሳሽም በጠበቆቻቸው አማካኝነት ‹‹እግድ ሊሰጥ አይገባም›› በማለት አስተያየት መስጠቱንና ፍርድ ቤት ጉዳዩን መመርመሩን ጠቅሷል፡፡ ከሳሾች የጠየቁት ዳኝነት ‹‹ለማሕበሩ ያዋጣነው መዋጮ በሙሉ ይጠፋል ብለን ስለምንገምት በሕገ ደንብ መሠረት የሽምግልና ዳኝነት ጉባኤ ይሾምልን›› የሚል በመሆኑ ፍ/ቤቱም ጉዳዩ ታይቶ ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ ከሳሾች በማሕበሩ ያዋጡትን መዋጮ በተመለከተ ብቻ መታገድ ያለበት መሆኑን ስላመነ በኮንስትራክሽንና ቢዝነስ ባንክ ውስጥ የ1ኛ ተከሳሽ ሂሳብ ካለው ከሳሾች የሆኑት የዘጠኝ ሰዎች መዋጮ ብቻ አግዶ እንዲይዝ አዟል፡፡

እንዲሁም ከሳሾች ካወጡት ገንዘብ በተጨማሪ ‹‹የማሕበሩ ሒሳብ በሙሉ ይታገድልን›› ያሉትን በተመለከተ አለመታገዱ እንዴት የእነሱን መብት ሊጎዳ እንደሚችል ያልገለፁ በመሆኑ እንዲሁም ሙሉ በሙሉ የማሕበሩን ገንዘብ ማገድ ማሕበሩ ሥራ እንዳይሰራ ማድረግ ስለሆነ በዚህ ረገድ የቀረበውን ፍ/ቤት አለመቀበሉንና ለክስ መስማት የተያዘው ቀጠሮ አለመቀየሩን ግንቦት 2/2002 ዓ.ም በዳኛ አደይ ንጉሴ የተሰጠው ትዕዛዝ ያሳያል፡፡

ሚያዚያ 20/2002 ዓ.ም አቶ ሙሉጌታ በልሁን ጨምሮ ሌሎች ሦስት የቀድሞ የማሕበሩ አመራሮች ለጉዳያቸው ዕልባት ‹‹የሽምግልና ጉባዔ እንዲሰየም›› ክስ በማሻሻል ለፍርድ ቤት ሲያመለክቱ ተከሳሾች ደግሞ ግንቦት 6 /2002 ለቀረበባቸው ክስ በፅሁፍ ምላሽ የተለያዩ ነገሮችን በመግለፅ ፍ/ቤቱ ሒሳብ አጣሪ እንዲሾም፣ ክሱን ውድቅ እንዲያደርግና ወጪ ኪሳራቸውን ከሳሾች እንዲተኩ በመጠየቅ የሰነድ ማስረጃ አቅርበዋል፡፡ ፍርድ ቤቱም ጉዳዩን መርምሮ ፍርድና ትዕዛዝ የሰጠ ሲሆን በግራ ቀኙ በእያንዳንዳቸው በኩል አንድ የሽማግሌ ዳኛ እንዲመርጡና እነዚሁ ሁለት ሽማግሌዎች አንድ ሰብሳቢ ሽማግሌ በስምምነት እንዲመርጡ አዝዟል፡፡ እንዲሁም ከሳሾች ወይም ተከሳሾች የየራሳቸውን አንድ አንድ የሽምግልና ዳኞች ትዕዛዝ ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር በአንድ ወር ጊዜ ካልመረጡ አንደኛው ወገን ለችሎቱ በሚያቀርበው ጥያቄ መሠረት በፍ/ቤቱ ሬጀስትራር በኩል የሚመረጥ መሆኑን ተዘርዝሯል፡፡

ሕዳር 14/2003 ዓ/ም ለፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት በአመልካች በእነ አቶ ሙሉጌታ በልሁ በኩል አቶ በቀለ መኮንን፣ በተጠሪ ማሕበሩ በኩል ደግሞ አቶ ታምሩ ወንድማገኘሁ እንደተመረጡ ማስረጃዎች ያስረዳሉ፡፡ ነገር ግን፣ በሁለቱ ወገኖች በኩል ተመሳሳይነት ባለው የክስ ሁኔታ ግንቦት 24/2003 ዓ.ም በጠቅላይ ፍርድ ቤት የይግባኝ ቀጠሮ እንዳለ ለማወቅ ተችሏል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ደብዳቤየኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒትቴር ለክፍለ

ከተማው የሕ/ሥራ ማሕበራት ማደራጃና ልማት ዋና የሥራ ሂደት ሚያዝያ 17/2003 ደብዳቤ በመፃፍ ሮም የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ማሕበሩ ያካሄዳቸውን ስብሰባዎችና ውሳኔዎች የያዘ ሰነድ ኮፒ ተልኮለት ለአፈፃፀም እንዲረዳ መጋቢት 10/2003 በቁጥር T-31/24/03 በተፃፈ ደብዳቤ አያይዘው መላካቸውን ይገልፃል፡፡ በማያያዝም፣ ‹ከኤምባሲያችን የደረሰንና የተላከላችሁ ሠነድ መጥፋቱ በመገለፁ ኮፒው ሮም ከሚገኘው ኤምባሲያችን ተጠይቆ የመጣ እንጂ በአሁን ወቅት የተላለፈ የማሕበሩ ውሳኔ አለመሆኑን እየገለፅን በእናንተም በኩል ይኼው ግንዛቤ እንዲወሰድበት እንጠይቃለን፡፡›› በማለት የመ/ቤቱ የቆንስላ ክትትልና ድጋፍ ዳይሬክተር አቶ መላኩ በዳዳ የፈረሙበት ደብዳቤ ያስረዳል፡፡

ሚያዚያ 20/2003 የቦሌ ክ/ከተማ አስተዳደር ንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት የሕ/ሥራ ማሕበራት ማደራጃና ልማት ዋና የሥራ ሂደት ለአዲስ ሮማ የጋራ ሕንፃ የመኖሪያ ቤት ሕ/ሥራ ማሕበር ደብዳቤ ፅፎ ነበር፡፡

በአባላቱ መካከል በየጊዜው የማሕበሩን ግንባታ አስመልክቶ ከፍተኛ በሆነ አለመግባባት ምክንያት 30 የሚሆኑ የማሕበሩ አባላት ለማሕበሩ በተፈቀደው ከG+1 ጀምሮ ለመገንባት ከተሰጠ ፈቃደ ምትክ ወደ G+4 ለማሻሻል የማሕበሩ ሥራ አመራር የሚወስዳቸው እርምጃዎች ጠቅላላ የማሕበሩ አባላት በጠቅላላ ጉባኤ ያላስተላለፈው፣ አብዛኛው የማሕበሩ አባልም ሃሳቡን ያልሰጠበትና ያልተስማማበት ውሳኔ፣ እንዲሁም የሕብረት ሥራ ማሕበርን መርህ ያላካተተ ጨረታ በማካሄድ ለኮንትራክተር ስራውን እንዲጀምር መሰጠቱን ማመልከታቸውን ደብዳቤው ጠቅሷል፡፡

እንዲሁም አባላት በሙሉ ስምምነት ላይ መድረስ ባለመቻላቸው እና በጠቅላላ ጉባኤ ባልተወሰነ የግንባታ ፈቃድ ወደ G+4 መሻሻሉና አዲስ የግንባታ ፈቃድ መሰጠቱ የጠቅላላ አባላት ውሳኔ እና ፍላጎት ባለመሆኑ ከማሕበራት አዋጅ እና ደንብ ውጪ ሆኖ መገኘቱን ደብዳቤው ይገልፃል፡፡ በመጨረሻም በአንድ አካባቢ የተለየ የሕንፃ ከፍታ መኖር አካባቢውን ስለሚረብሽ የማሕበር አባላት በተስማሙበት እና ‹‹በአንድ ወጥ ማሕበራት መስተናገድ አለባቸው›› የሚል ደብዳቤ

ከሕብረት ሥራ ማህበራት ማደራጃና ልማት ዋና የሥራ ሂደት አስተባባሪ የደረሰው በመሆኑ ማሕበሩ ይህንን ተገንዝቦ በመጀመሪያ ማሕበሩ ሲቋቋም በተሰጠው ውል መሠረት መገንባትና በተፈቀደለት

ከፍታ ግንባታውን እንዲቀጥል በአቶ ጎይቶኦም ግርማይ የተፃፈው ደብዳቤ ያመላክታል፡፡

የመፍትሄ ሃሳቦችአቶ ዳዊት በማሕበሩ ውስጥ ያሉትን ችግሮች

ለመፍታት መፍትሄ ያሏቸውን ሃሳቦች ለአውራምባ ታይምስ ገልፀው ነበር፡፡ የሁሉም ዓላማ ቤት መስራት በመሆኑ ያለስምምነትና ፍቅር ቤት መስራት እንደማይቻል በማስገንዘብም ‹‹አቶ በቀለና የቁጥጥር ኮሚቴው ከዚህኛው ወገን ጋር በጋራ ተገናኝተው ቅን በሆነ መንገድ ያለ ጥላቻ ቤታችንን እንዴት አድርገን እንስራው በሚለው ላይ መወያየት ይገባናል›› ብለዋል፡፡

አያይዘውም፣ የማሕበሩ ገንዘብ ግልፅ በሆነ ሁኔታ ለሁሉም አባላት ሪፖርት መቅረብ እንደሚኖርበት፣ ከማሕበሩ ‹‹ተሰረዙ››ና ወደ ማሕበሩ ‹‹ገቡ›› የሚባሉት ሰዎች ስም ዝርዝር ግልፅ መደረግ እንደሚገባው፣ አቶ በቀለ ሊቀመንበር በመሆናቸው ብቻ እንደፈለጉ መሆን እንደማይችሉና ሕንፃ ተቋራጩን ለመወሰን ሁሉም መስማማት እንደሚኖርበት በመፍትሄነት ተናግረዋል ፡- አቶ ዳዊት፡፡

አቶ ሙሉጌታም በበኩላቸው ብዙሃን አባላት የለፉበት ነገር ከንቱ መቅረት እንደሌለበት ጠቅሰው፣ ‹‹ለመወያት መስማማት አልቻልንም፣ ሁላችንም እንደ ምርጫችን ቤት መስራት እንድንችል የግድ መስማማት ይኖርብናል›› ሲሉ ሃሳባቸውን ገልፀዋል፡፡

የአዲስ ሮማ የቤት ግንባታ መጨረሻ ምን ይሆን?

አቶ ዳዊት በማሕበሩ ውስጥ ያሉትን ችግሮች ለመፍታት መፍትሄ ያሏቸውን ሃሳቦች

ለአውራምባ ታይምስ ገልፀው ነበር፡፡ የሁሉም ዓላማ ቤት መስራት በመሆኑ ያለስምምነትና

ፍቅር ቤት መስራት እንደማይቻል በማስገንዘብም ‹‹አቶ በቀለና የቁጥጥር ኮሚቴው ከዚህኛው

ወገን ጋር በጋራ ተገናኝተው ቅን በሆነ መንገድ ያለ ጥላቻ ቤታችንን እንዴት አድርገን

እንስራው በሚለው ላይ መወያየት ይገባናል›› ብለዋል::

በኤልያስ ገብሩ

Page 15: አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 166 ቅዳሜ ሚያዚያ 29 2003 ኢሕአዴግ … · ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ አውራምባ ታይምስ 4ኛ

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 166 ቅዳሜ ሚያዚያ 29 2003

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

15ማ ስ ታ ወ ቂ ያ

Page 16: አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 166 ቅዳሜ ሚያዚያ 29 2003 ኢሕአዴግ … · ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ አውራምባ ታይምስ 4ኛ

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 166 ቅዳሜ ሚያዚያ 29 200316

ከቀድሞ ድርጅትዎ ሕወሓት የለቀቁት የ1993ቱ መሰንጠቅ ከመከሰቱ በፊት እንደነበር ይነገራል፡፡ ምክንያትዎ ምንድነው?

እንግዲህ ይዘኸው የተነሳኸው፣ አሳካዋለሁ ብለህ የታገልክበት ዓላማ አቀጣጫውን ሲስት የምታደርገው ነው፡፡ በመሰረቱ፣ ከምስረታው ጀምሮ ድርጅቱን እስከለቀኩበት 1985 ዓ.ም ድረስ በቅን ልቦና አብሬው ቆይቻለሁ፡፡ በእነዚህ ሁሉ ጊዜያት ለተፈፀሙ ስህተቶችና የሚያስጠይቁ ድርጊቶች ደግሞ ኃላፊነቱን ለመውሰድ ዝግጁ ነኝ፡፡ ‹አረና› የተመሰረተው ከሶስት ዓመታት በፊት እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ከዚያ በፊት የተቃውሞውን ጎራ ለመቀላቀል ያደረጉት ጥረት ነበር?

የተጠናከረ ትግል ለማድረግ ድርጅት ወሳኝ ነገር ነው፡፡ በሌላ በኩል ተቃውሞህን የምትገልፅበትና የምትታገልበት መንገድ ብዙ ነው፡፡ ‹አረና›ን ከመመስረታችን በፊት በ1997 ዓ.ም በግሌ ለሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ተወዳድሬ ነበር፡፡ ውጤቱ እንኳን አይደለም ያኔ አሁን እንኳን ምን እየተደረገ እንዳለ የማያውቅ ኢትዮጵያዊ ያለ አይመስለኝም፡፡ ከዚያ በኋላ የታገልንለት ዓላማ መክኖ ከሚቀር ብለን ‹አረና ትግራይ›ን መሰረትን፡፡ ሕወሓት በትግሉ ወቅት በስፋት ይንቀሳቀስባቸው የነበሩ አከባቢዎች በተለይ በትግራይ ሕዝብ ላይ የሚፈፀሙት ማለቂያ የለሽ አፈናዎች እየባሰባቸው መጥተዋል፡፡የተወሰኑትን ቢገልፁልኝ?

አንዱን የአፈና ሥልት ልጥቀስልህ፡፡ ለምሳሌ በገጠር አካባቢ አምስት አምስት አባዎራዎች በአንድ ላይ እንዲደራጁ ይደረግና ከአምስቱ ቤተሰብ አንደኛው ሊቀ-መንበር፣ ሁለተኛው ም/ሊቀ-መንበር ይደረጋል፡፡ ይኸው ሁኔታ ወደ ቤተሰብ ይገባና አባት ሊቀ-መንበር፣ እናት ም/ሊቀ-መንበር ሆነው ልጆቻቸውን በፖለቲካዊ አካሄድ እንዲመሩ ይገደዳሉ፡፡ በከተማም፤ በቀበሌ፣ በቀጠና፣ በም/ቤት አደራጅተው እያንዳንዷ የማኅበረሰቡ እንቀስቃሴ ሪፖርት ትደረጋለች፡፡ ወደ ት/ቤት ስትሄድ የሕወሓት አባል ያልሆነ መምህር ዕድገት እንዳያገኝ ይደረጋል፡፡ ተማሪዎችም እንዲሁ አባል እንዲሆኑ፣ ያለዚያ ግን ዝቅተኛ ውጤት እንዲያገኙ፣ ከዩኒቨርሲቲ ሲወጡም ሥራ እንዳያገኙ ይደረጋሉ፡፡ተማሪዎች ሰንደቅ ዓላማ ሲወጣ የሚዘምሩት የሕወሓትን የበረሃ መዝሙር ነው የሚል ነገር ሰምቼ ነበር፡፡ ትክክል ነው?

በእርግጥ ከሞላ ጎደል የኢትዮጵያ ሕዝብ መዝሙር የሚዘመርባቸው ቦታዎች አሉ፡፡ በአብዛኛው ግን የሕወሓት መዝሙር ነው፡፡የመዝሙሩ ማጠንጠኛ ምንድነው?

ዘይንድይቦ ጎቦዘይንሰገሮ ሩባፍፁም ወይከ የለን መስመር’ዩ ኃይልና ሕዝቢ’ዩ ኃይልና ... ማለትም፡- የማንወጣው ተራራ፣ የማንሻገረው ወንዝ የለም፤ ፍፁም ከቶ የለም፤ መርህ ነው ኃይላችን፤ ሕዝብ ነው ኃይላችን እንደማለት ነው፡፡ ሰሞኑን እየተደረገ ያለውን ያየን እንደሆነ በመቀሌ አካባቢ ለተከታታይ ቀናት ሕገ-ወጥ ናቸው የተባሉ ቤቶችን በማፍረስ ሕዝቡን እየበተኑት ነው፡፡ እነዚህ ነዋሪዎች ከቀበሌውም ሆነ ሌሎች የመስተዳድር አባላት ይሁንታ አግኝተው ነው ቤቶቹን የገነቧቸው፡፡ ሕገ-ወጥ ናቸው ከተባለም ማኅበረሰባዊ መፈናቀል እንዳይከሰት ጥንቃቄ ተወስዶ እንጂ በዚህ መንገድ አይደለም፡፡ ሁኔታውን በመቃወም አቤቱታ ለማቅረብ በወጡ ዜጎች ላይ አስለቃሽ ጭስና ደሚ ጥይት ተተኩሶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ ሁኔታው አስከፊ ሆኗል፡፡ ነጋዴውና ሰራተኛው በስጋትና በጭንቀት እየተርበደበደ ይገኛል፡፡አረና ትግራይን ከሕወሓት የተገነጠሉ አመራሮች ስብሰብ አድርጎ የመመልከት ሁኔታ አለ፡፡ እንዴት ይመለከቱታል? ከቀድሞ ማንነታችሁ ጋር በተያያዘ በምስረታው ወቅት ያጋጠሟችሁ ችግሮችስ ነበሩ?

ከሕወሓት አመራር የተገነጠሉ ለሚለው፣ የሕወሓት አመራር የነበሩት ሶስት ብቻ ናቸው፡፡ በተረፈ ፓርቲው እንደተመሰረተ ‹አረናን እንዴት እንከላከለው?› በሚል 14 ገፅ ጽሑፍ ተሰራጭቶ ነበር፡፡ እነማን ናቸው? ከእነማን ጋር ይገናኛሉ? የት ይውላሉ? በሚል እስካሁንም በስለላ ክትትል ስር ነን፡፡የ2002 ዓ.ም አጠቃላይ ምርጫ ከመካሄዱ በፊት በፓርቲያችሁ ላይ ‹‹እነአሞራውን ከኢሰፓ ጋር ሆነው ያስገደሉ ናቸው›› የሚል ቅስቀሳ ተደርጎባችሁ ነበር ይባላል፡፡ የዚህ ቅስቀሳ መንሳኤ ምንድነው?

የሚገርምህ አሞራን ያሰለጠንኩት እኔ ነኝ፡፡ በምርጫ ቅስቀሳው ወቅትማ ያልተባለ፣ ያልተደረገ የለም፡፡ እንዲያውም በረሃ እያለን ወደ ጦርነት ስንሄድ እንዘፍነው የነበረውን ‹ውፈር› የተባለ ዘፈን በከተማ አደባባዮች ላይ በስክሪን እያቀረቡ ምርጫውን ጦርነት አስመስለውት ነበር፡፡ ደግሞ ይኼ ‹ኢሰፓ› የሚለው ፍርጃን የሚጠቀሙበት መንገድ አስገራሚ ነው፡፡ በመሰረቱ እኮ በሽግግር መንግስቱ ወቅት የኢሰፓ አባላት የነበሩ ለሁለት ዓመታት ያህል ከፖለቲካዊ መብቶቻቸው እንዲታገዱ ተወስኖ ጊዜው ካለፈ በኋላ በ1987 ዓ.ም ተነስቷል፡፡ ስለዚህ አሁን የዜግነት መብቶቻቸውን ተጠቅመው በሚያምኑበት የፖለቲካ መስመር ተሳትፎ ማድረግ እንደሚችሉ መረሳት የለበትም፡፡ቀደም ሲል ለሕወሓት ሠራዊት ወታደራዊ ሥልጠና ይሰጡ እንደነበር ገልጸውልኛል፡፡ እርስዎ ክህሎቱን ከየት ቀሰሙት?

በንጉሡ ጊዜ የጦር ሠራዊት አባል ነበርኩ፡፡ በ1961 ዓ.ም በ2ኛ ክ/ጦር ሰሜን እዝ 31ኛ ኮማንዶ ሻለቃ ውስጥ ተመድቤ፣ በእስራኤሎች የስፔሻል ኮማንዶ ሥልጠና ተከታትያለሁ፡፡ በኋላም የጤና ረዳትነት ሥልጠና በማግኘት ከተዋጊ ልዩ ኃይሉ ጋር ሰርቻለሁ፡፡በቅርቡ በመንግስት በኩል ከተሰጡ መግለጫዎች አንዱ፣ ‹‹የኤርትራን መንግስት እስከማስወገድ የሚዘልቅ የአቋም ለውጥ አድርገናል›› የሚል ነው፡፡ በእርግጥ ብዙዎች የአንዳንድ ኢሕአዴግ አመራሮችን የቀደሙ አቋሞች በመዘርዘር፣ ‹‹ኢሕአዴግ በኤርትራ መሪዎች ላይ የሚጨክንበት አንጀት የለውም›› ሲሉ ይተቹታል፡፡ እንዴት ይገመግሙታል?

በመሰረቱ መግለጫው እርስ በርሱ የተጣረሰ ነው፡፡ በአንድ በኩል እናስወግዳለን ይላሉ፡፡ በሌላ በኩል የኤርትራን መንግስት የማስወገድ ጉዳይ የኤርትራውያን የውስጥ ጉዳይ ነው ይላሉ፡፡ ዋናው ነገር ግን ይህ ኤርትራን የማስወገድ ነገር እስከየት ድረስ ይሄዳል? የሚለው ነው፡፡ ያለአግባብ ያጣናቸውን መብቶቻችንን ያስከብርልናል ወይ? ሉዓላዊነታችንን ያስከብርልናል ወይ? የባሕር በር ባለቤትነታችንን ያረጋግጥልናል ወይ? የሚሉት መመለስ አለባቸው፡፡ ከሆነ እንደግፈዋለን፡፡ ያለዚያ ግን ዓላማ የለሽ ይሆናል፡፡ በኤርትራ ጉዳይ ላይ በአጠቃላይ ኢሕአዴግ፣ በተለይ ግን የቀድሞ ድርጅትዎ ሕወሓት አንዳንድ አመራሮች ‹‹ከኤርትራውያን በላይ ለኤርትራ ሽንጣቸውን ገትረው ጥብቅና ይቆማሉ›› የሚለው ነቀፋስ?...

‹‹የኤርትራን መንግስት ማስወገድ የባሕር በራችንን የማያስመልስ ከሆነ ዓላማ የለሽነት ነው››

አቶ አስገደ ገ/ሥላሴ(የአረና ትግራይ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል)

በ1967 ዓ.ም ወደ በረሐ በመግባት ሕወሓትን ከመሰረቱት 11 ታጋዮች አንዱ ሲሆኑ፣ ለሠራዊቱ ወታደራዊ ሥልጠና በመስጠትም ይታወቃሉ፡፡ ከ17 ዓመታት ፈታኝ ትግል በኋላ፣ ለሥልጣን የበቃው ድርጅታቸው ግን ከተነሳለት ዓላማ በተቃራኒው በዜጎች ላይ የሚፈጽማቸው ሁለንተናዊ በደሎች አስከፊ ደረጃ ላይ ደርሰዋል በሚል አቋም፣ ‹‹እስከ 1985 ዓ.ም ድረስ በፍጹም ቅንነት ያገለገልኩትን ድርጅት ለቅቄ ወጥቻለሁ›› ሲሉ ይገልፃሉ፡፡ ‹‹ኢሕአዴግ በታሪኩ ዴሞክራሲያዊ ሆኖ አያውቅም፤ የተለየ ሀሳብ የሚያቀርቡ ወገኖችንም ጠላት አድርጎ ስለሚያያቸው፣ ባለው አቅም ሁሉ ከመታገል ወደ ኋላ አይልም›› ከሚሉት የአረና ትግራይ ለፍትሕና ሉዓላዊነት ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል አቶ አስገደ ገ/ሥላሴ ጋር ቀጣዩን ቆይታ ያደረገው ባልደረባችን ውብሸት ታዬ፣ አዛውንቱ ፖለቲከኛ በቀድሞ ድርጅታቸው የሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች አያያዝ ላይ ያለው አካሄድ በእጅጉ እያሳሰባቸው እንዳለ ለመታዘብ ችሏል፡፡

ወደ ገፅ 21 ዞሯል

Page 17: አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 166 ቅዳሜ ሚያዚያ 29 2003 ኢሕአዴግ … · ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ አውራምባ ታይምስ 4ኛ

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 166 ቅዳሜ ሚያዚያ 29 2003

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

ል ዩ ቅ ኝ ት 17

አብዛኛው የታሪክ ክፍሏ በጦርነት የተሞላው ኢትዮጵያ፤ ዳር ድንበሯን የደፈሩ፣ ነፃነቷን ለመግፈፍ የሞከሩ ጠላቶቿን የሀፍረት ማቅ አከናንባ ወደየመጡበት ሸኝታለች፡፡ ከእነዚያ ጀግኖች ልጆቿ መሐል ደግሞ አብዲሳ አጋ አንዱ ነው፡፡

በ1911 ዓ.ም ይህቺን ዓለም የተቀላቀለው አብዲሳ አጋ ከፊደል ጋር ትውውቅ የጀመረው የትውልድ ቀየው በሆነችው፣ በወለጋ ጠቅላይ ግዛት ውስጥ በምትገኘው የነጆ ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ነበር፡፡

የጨቅላነት ጊዜውን በነጆ እና በነቀምት በቡረቃ ያሳለፈው ትንሹ አብዲሳ ብዙም ከፍ ሳይል የሕይወቱን አቅጣጫ የሚቀይር ነገር ተከሰተ፡፡ ከታላቅ ወንድማቸው ጋር በርስት ጉዳይ አለመግባባት ውስጥ የነበሩት የአብዲሳ አባት ታላቅ ወንድማቸውን በጦር ወግተው በመግደላቸው የሞት ፍርድ ተፈፃሚ ሆነባቸው፡፡ በደረሰበት ድርብ ሀዘን ልቡ የተሰበረው ታዳጊም፣ ‹‹ቀጣዩ የህይወቴ መስመር ምንድን ነው ሊሆን የሚችለው?›› የሚል ሀሳብ ገባው፡፡ ሀገሩን በወታደርነት ለማገልገል የነበረው ፅኑ ፍላጎትም ‹በገነት የጦር ት/ቤት ተመዝገብ› ሲል ገፋፋው፡፡ ይሁን እንጂ በወቅቱ አብዲሳ ገና የ14 ዓመት ልጅ ስለነበር በ‹‹ቦይ እስካውት›› ክፍል ውስጥ እንዲደለደል ሆነ፡፡

የመጀመሪያ ግዳይ በተመደበበት ክፍል ውስጥም ሆኖ

የእንግሊዘኛ ቋንቋ፣ የእግረኛ ሰልፍ እና የከባድ መሣሪያ ተኩስ ትምህርት ቀስሟል፡፡ የገነት የጦር ት/ቤት ቆይታውን ሲያጠናቅቅ የ50 አለቃነት ማዕረግ ያገኘው ወጣቱ አብዲሳ፣ የጀግንነት ተጋድሎውን ‹‹አሀዱ›› ያለው በ1928 ዓ.ም ሲሆን፣ የመጀሪያ ግዳዩም የፋሺስት ኢጣሊያ ወታደር ነው፡፡ በወቅቱ ፋሺስት ኢጣሊያ ኢትዮጵያን ስትወር በወለጋ በኩል የገባውን ጠላት ለመውጋት በኮሎኔል በላይ መሪነት የገነት ጦር ከደጃዝማች ሀብተ ማርያም ጦር ጋር ለመቀላቀል ሲሄድ አንዱ ዘማች የነበረው አብዲሳ፣ ወደ ምዕራብ ኢትዮጵያ ጉዞ በሚያደርጉበት ጊዜም ከፋሺስት ጋር በተደረጉ የተለያዩ ውጊያዎች ጀብዱዎችን ፈጽሟል፡፡

በመንገዳቸው ያገኙትን ወራሪ እየደመሰሱና አይሮፕላኖቹንም እያጋዩ ነቀምት የደረሱት የገነት ጦር አባላት፣ ጊምቢንና ጮሊን አቋርጠው ጌራ ላይ ከልዑል ራስ እምሩ ጦር ጋር ተቀላቀሉ፡፡ ሆኖም የጎጀብ ወንዝ ድልድይ በመፍረሱ ጉዞውን ለጊዜው እንዲገታ የተደረገው ሠራዊት በድንገት የፋሺስት ኢጣሊያ ጦር ከአየርና ከምድር ጥቃት ይፈፅምበት ጀመር፡፡ በድንገተኛው ውጊያ ራስ እምሩና ኮሎኔል በላይ ሲማረኩ፣ የመቁሰል አደጋ የደረሰበት አብዲሳ በጣሊያን ወታደሮች ወደ ቦንጋ ተወሰደ፡፡

ከሶስት ወር ሕክምና በኋላም ከሌሎች ጓዶቹ ጋር ወደ ጅማ ወህኒ ቤት ‹‹የተዘዋወረ›› ሲሆን በጅማና አዲስ አበባ ወህኒ ቤቶች ለሶስት ወር ተኩል ታስሮ በቁም እስረኛነት ቢለቀቅም ከእስር ቤት ጋር እስከ ወዲያኛው አልነበረም የተቆራረጠው፡፡

በሰው ሀገር እስርየካቲት 12 ቀን 1928 ዓ.ም በብርሃኑ

ደቦጭና ሞገስ አስገዶም የቦምብ ጥቃት የተቃጣበት ግራዚያኒ በአዲስ አበባ ነዋሪዎች ላይ ጭፍጨፋ እንዲፈፀም ትዕዛዝ አስተላለፈ፡፡ በመጀመሪያ ተጠርጣሪነት ወደ ምርመራ ክፍል ከተወሰዱት መካከል አንዱ የነበረው ወጣቱ አርበኛ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ተቀምጦ ለወራሪው ኃይል ፋታ እንደማይሰጥ ስለታመነ ‹‹ሞቃዲሾ ተወስዶ ይታሰር›› የሚል ውሳኔ ተላለፈበት፡፡

ሞቃዲሾ ደናኔ ወህኒ ቤት ውስጥ ከፍተኛ በደልና ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት ሲፈጸምበት ከቆየ በኋላ ደግሞ ሌላ ተስፋ አስቆራጭ ውሳኔ ተላለፈበት - በምድረ ጣሊያን እንዲታሰር፡፡

ጣሊያን እንደደረሰም መጀመሪያ እንዲገባ የተደረገው አኛኖ ከተባለ እስር ቤት ነው፡፡ ከዚያም የኢትዮጵያ፣ የዩጎዝላቪያ፣ የእንግሊዝና የፈረንሳይ እስረኞች ወደሚገኙበት ቦጀሪያሌ እስር ቤት ገባ፡፡ እዚህ እስር ቤት እንዳለ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት በመፈንዳቱ እስር ቤቱን በሚጠብቁ ጣሊያናዊያን ዘንድ ‹ድንገት በጦርነቱ መሐል እነዚህ ሁሉ እስረኞች አምልጠው ከጠላቶቻችን ጋር ቢደባለቁስ?› የሚል ፍርሀት አረበበ፡፡ ፈርተውም ቁጭ አላሉም፤ እስረኞቹን በሙሉ በሰንሰለት እያቆራኙ በባቡር ጭነው ቪላ አስባዳ ከሚባል በታ ወደሚገኘው ካምቦ ኢንቴርናቴ ማጎሪያ አጋዟቸው፡፡

አብዲሳ አጋም ከአገሩ በብዙ ሺህ ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ በመገኘቱና በእስር ቤቶች ውስጥ በሚደርስበት ስቃይ የተነሳ የመንፈስ ድካም እንዳይደርስበት አብረውት ከታሰሩ ኢትዮጵያውያንና የሌላ አገር ዜጎች ጋር ከእስር ስለሚያመልጥበት ሁኔታ አብዝቶ መምከሩን አዘወተረ፡፡ ነገር ግን ይህ ድርጊቱ አልተወደደለትም፤ ስለዚህ በአንዲት ጠባብ ክፍል ውስጥ ብቻውን እንዲታሰር ተደርጎ እያንዳንዷን እንቅስቃሴዎቹን የሚከታተሉ ጠባቂዎች ተመደቡበት፡፡

ታሪከኛዋ ብርድ ልብስተፈፃሚ የሆነበት የቅጣት ዓይነት

እጅጉን ፈታኝ ቢሆንበት ወደነበረበት ቦታ የሚመለስበትን ዘዴ ማውጠንጠኑን ተያያዘው፡፡ በዚህም መሠረት ጠባቂዎቹ ወደ ውጪ ሊያወጡት ሲመጡ ‹‹አሞኛል›› በሚል ሰበብ ተጠቅልሎ መተኛትን የመጀመሪያው እርምጃው አደረገ፡፡ ይህ ብልሀቱ ውጤት ሳያስገኝለት ሲቀር ደግሞ አዕምሮውን መቆጣጠር እንደተሳነው ሰው በመሆን ‹‹ዕብደቱን›› አወጀ፡፡ በዕብደት ድርጊቱ የተበሳጩት የፋሺስት ወታደሮች አውቆ ማበዱን እንዲተው ከፍተኛ ድበደባ ቢፈፅሙበትም ‹‹ወይ ፍንክች!›› ሆነ አቋሙ፡፡

በብዙ ድብደባና በሐኪም ምርመራ ዕብድ መሆንና አለመሆኑን ማረጋገጥ ቢሳናቸው መልሰው ከነበረበት ክፍል ቀላቀሉት፡፡ ከጓደኞቹ ጋር በተቀላቀለ ማግስት ግን ሌላ ተስፋ አስቆራጭ ነገር ተከሰተ፡፡ በጠዋት ወደታሰረበት ክፍል የመጡት አራት ወታደሮች ክስ እንደተመሰረበተት በመንገር ወደ ሊቼ የአውራጃ ፍርድ ቤት ወሰዱት፡፡

ከችሎት የተሰየሙት ‹‹ዳኞችም›› የተከሰሰበትን ጉዳይ ሳይነግሩትም፣ ሌሎች ጥያቄዎችን ሳይጠይቁትም የቀረበላቸውን ሰነድ ብቻ ተመልክተው የሶስት ወር ቀጠሮ በመስጠት እስከዚያው ድረስ የነበረበት እንዲቆይ ትዕዛዝ አስተላለፉ፡፡ ይኼኔ ነው አንግዲህ የቀጠሮዋ ቀን ከመድረሷ በፊት የእስር ቤት ጓዶቹን አስተባብሮ ማምለጥ እንዳለበት የወሰነው፡፡ ‹‹ፍላጎት ካለ መንገድ አለ›› እንዲሉም በወቅቱ በመላው አውሮፓ የተቀጣጠለው የሁለተኛው የዓለም ጦርነት ለአብዲሳ አጋ እና ለወዳጆቹ ማምለጥ ምቹ ሁኔታ ፈጠረላቸው፡፡

ጦርነቱ በተፋፋመበትና በእንግሊዝና በአሜሪካ እንዲሁም በሩሲያ የሚመራው ኃይል በጀርመንና በጣሊያን ላይ መልሶ ማጥቃቱን ባጠናከረበት ወቅት በአንደኛው ምሽት የእንግሊዝ ተዋጊ አውሮፕላን እስር ቤቱን በቦምብና በመትረየስ አረሰው፡፡

የእስር ቤቱ ጠባቂዎች በጥቃቱ ተደናግጠው ‹‹እግሬ አውጪኝ›› ማለታቸውን ያስተዋሉት እስረኞችም ቀድሞ በተመካከሩት መሠረት ዕቅዳቸውን ተግባራዊ ማድረግ ጀመሩ፡፡ የዕቅዱ አቀነባባሪ የሆነው አብዲሳ ታስሮ የነበረው ከምድር ርቀት ባለው ፎቅ ላይ በመሆኑ ከነበረበት ክፍል ወደታች ለመውረድ አንድ ዘዴ ማፍለቅ ግድ ሆነበት - የብርድ ልብሱን ተልትሎ እንደገመድ መጠቀም፡፡

ሜጀር አንቶኒዮከዚያ ከሌሎች ያመለጡ እስረኞች

ጋር በመሆን በጣሊያን ተራራዎችና ሸንተረሮች ላይ በትውልድ አገሩ የጀመረውን የአርበኝነት ተጋድሎ ቀጠለ፡፡ ከጊዜ ወደ ጊዜም ቀደም ባሉት ዓመታት በጣሊያን ጦር ተማርከው የነበሩ የተለያዩ አገራት ወታደሮች፣ እስረኞችና ስደተኞች ተቀላቅለዋቸው ቁጥራቸው ከፍ እያለና የአሜሪካና የእንግሊዝ ጦር የሚያደርጉላቸው ድጋፍ እየጨመረ በመምጣቱ የአርበኞቹን ጦር በአራት ክፍል ማደራጀት አስፈላጊ ሆኖ ተገኘ፤ ሜጀር አንቶኒዮ (አብዲሳ አጋ) የአራተኛው ክፍል መሪ ሆነ፡፡

የአርበኞቹ መጠናከር፣ ይባስ ብሎም ‹ከእኛ በቀር ማንም ሊኖርበት አይገባም› በሚሏት አውሮፓ ላይ በጥቁር አፍሪካዊ የሚመራ ጦር ድል እየተቀዳጀበት መምጣቱ ያበሳጨው የፋሺስትና የናዚ ጣምራ ጦር በአርበኞቹ ላይ የሚሰነዝረውን ጥቃት አጠናክሮ ተያያዘው፤ የአርበኞቹ ሠራዊት ባደረገው መከላከልና መልሶ ማጥቃት ሙከራው ሳይሳካ ቀረ እንጂ፡፡

ሜጀር አንቶኒዮ በጣሊያን ምድር ላይ ለበርካታ ጊዜያት ከናዚና ከፋሺስት ግዙፍ ጦሮች ጋር ውጊያ ቢያደርግም ከማሸነፍ በቀር ሽንፈትን ቀምሶ አያውቅም፡፡ ድንገት የሚፈፀሙበትን ጥቃቶች ሳይቀር በብቃት ሲመክት ለቆየው ወጣቱ አርበኛ ሞንታሬ አሌ በተባለው ስፍራ ላይ ያደረገው ውጊያ ጉልሁን ስፍራ ይይዝለታል፡፡

በተጠቀሰው ቦታ ላይ ባልታሰበ ሁኔታ ከበባ የፈፀመው የጀርመን ናዚ ጦር ሁለት ቀን ሙሉ አርበኞቹ የመሸጉበትን አካባቢ በከባድ መሣሪያ ሲደበድብ ቢቆይም በብዙ ጭንቀትና ጥበት ያንን ውርጅቢኝ ለማምለጥ ቻሉ፡፡ ከዚያማ ምን ይጠየቃል ... ነገሩ የተገላቢጦሽ ሆነና አረፈው፡፡ ለጀርመኑ ጦር ሌላ አጋዥ ኃይል እንዳይመጣለት መንገዶችንና ድልድዮችን በዳይናማይት በማፈራረስ መሰናክል ከመፍጠሩም ሌላ በተባበሩት ኃይላት እየተሳደደ የመጣው የጀርመን ጦር ወደ ምስራቅ አውሮፓ በሚሸሽ ጊዜ በአብዲሳ አጋ ሠራዊት ይታጨድ ጀመር፡፡

አብዲሳ አጋን፣ ዩጎዝላቪያዊው ካፒቴን ጁሊዮታቺክ፣ ሜጀር ማርዮን እና ሌተና ኮሎኔል ፋይልን (አራቱም የአርበኞች ሠራዊት መሪዎች ናቸው) ለማረከ አሊያም አንገታቸውን ቆርጦ ላስረከበ የወርቅ ኒሻንና መቶ ሺህ ሊሬ እንደሚሸልም የዱቼ ሙሶሎኒ መንግስት ማሳወቁ፣ ጥቁር አፍሪካዊው ለጣሊያን መንግስት የቱን ያህል መቀመጫ ያሳጣ እንደነበር ማሳያ ነው፡፡ ቃል በተገባው የሽልማት ዓይነትና ብዛት የጎመዥው ማርሻል ባሎምባሪኒ የተባለ የጦር መሪ ጀሌዎቹን አስከትሎ ‹‹ግዳዩ›› ካለበት ድረስ ዘለቀ፡፡ ሆኖም ማርሻሉ አብዲሳን ለምሳ ሲያስበው እራሱ የአርበኞቹ ቁርስ ሆኖ ቀረበ፡፡ የመጣበትንም ምክንያት ከተናዘዘ በኋላ ተገደለ፡፡

እቺ ባንዲራ...ሁለተኛው የዓለም ጦርነት አሸናፊውና

ተሸናፊው እየለየ ሲመጣ የጣሊያን መዲና የሆነችው ሮም በተባበሩት

ኃይላት እጅ ወደቀች፡፡ የተባበሩት ኃይላት ጦር ዋና አዝማች የነበሩት ፊልድ ማርሻል ባንካውንትም ‹‹የጠላት ጦር ሸሽቶ እንዳያመልጥ ድልድዮችንና የባቡር ሐዲዶችን በማፈራረስ አሰናክሉ›› የሚል መልዕክት ለአርበኞቹ ያስተላለፉ ሲሆን አርበኞቹም ግዳጃቸውን በሚገባ ተወጥተዋል፡፡

ጣሊያን ሙሉ በሙሉ ከፋሺስትና ከናዚ ጦር ነፃ በወጣች ጊዜ ጀግናው አብዲሳ አጋ በስሩ ሆነው ሲዋጉ የነበሩ አርበኞችን አስከትሎ ወደ ሮም አቀና፡፡ እጅግ አስደማሚ በሆነው የድል አድራጊ ጉዞውም፣ ለእስር በሄደባት ጣሊያን የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ እያውለበለበ ነበር ወደ ዋና ከተማዋ የዘለቀው፡፡ የተባበሩት ኃይላት ዋና አዝማች ፊልድ ማርሻል ባንካውንት ከደስታ ብዛት የእጃቸውን የወርቅ ሰዓትና የጀብድ ኒሻኖች ከሸለሙት በኋላ በአውደ ውጊያ ላይ የማረካቸውን እጅግ በርካታ ከባድና ቀላል መሣሪያዎች እንዲሁም ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች ቆጥሮ በማስረከብ ወደ ቀጣይ ግዳጁ ተሰማራ፡፡

ከርክክቡ በኋላ የእንግሊዝን የወታደር ልብስ ለብሶ ከነተከታዮቹ ወደ ጀርመን በመዝመት ወታደራዊ ግዳጁን በብቃት ሲወጣ ቆይቷል፡፡ ምንም እንኳን አብዲሳ አጋ ከፍተኛ የጀግንነት ሥራ ሲፈፅም ቢቆይም ዘወትር ወደምትናፍቀው ሀገሩ ለመመለስ በቀላሉ የሚቻል አልሆነለትም፡፡ ለዚህም ምክንያቱ በጀግንነቱ የተደነቁት እንግሊዞች ዜግነቱን ቀይሮ እነሱን እንዲያገለግል መፈለጋቸው ነበር - ባይሳካላቸውም፡፡ የሆነው ሆኖ ከብዙ እንግልት በኋላ ጀግናው አብዲሳ አጋ የኢትዮጵያን አየር ለመተንፈስ በቃ፡፡ ከዛስ?

...ሞኝ ነሽ ተላላ፤ የሞተልሽ ቀርቶ...

የልጅነትና የወጣትነት ዘመኑን በአገር ውስጥም ሆነ ግዞተኛ በነበረበት ባዕድ አገር ለኢትዮጵያ ነፃነት ዘብ ቆሞ ሲዋጋ ያሳለፈው አብዲሳ አጋ ወደ አገር ቤት ከተመለሰ በኋላ በተለያዩ የጦር ክፍሎች ውስጥ ሲያገለግል ቢቆይም የልፋቱን እንዳላገኘ ለ30 ዓመታት በትዳር አብረውት የዘለቁት ወ/ሮ ቀለሟ ፈለቀ ይናገራሉ፡፡

ከግማሽ ክ/ዘመን በላይ ባስቆጠረው መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ ቁጭ ብለን የባለቤታቸውን ታሪክ የተረኩልን ወ/ሮ ቀለሟ፣ ምንም እንኳን የስመጥሩ ጀግና ባለቤት ቢሆኑም ድሮም ሆነ ዘንድሮ በኑሮ በኩል ችግር እንዳለባቸው

ከማስረዳት ወደኋላ አይሉም፡፡ ከ1952 ዓ.ም በፊት ካዛንቺስ የነበረውን ቤታቸውን አከራይተው በአነስተኛ ዋጋ አቧሬ አካባቢ በመከራየት ኑሯቸውን ለማሸነፍ መሞከራቸውን የሚያስታውሱት የዕድሜ ባለፀጋዋ፣ ‹‹በ1970 ዓ.ም ሲሞት የጀግና አሸኛኘት ከመደረጉ ውጪ አብዲሳ ለአገሩ በሰራውና በዋለው ውለታ መጠን ምንም አልተደረገለትም›› ይሉናል፡፡

እዚህ ጋር በአንድ ወቅት አፄ ኃይለሥላሴ ስጦታ እንዳበረከቱለት በማስታወስ ለወ/ሮ ቀለሟ ጥያቄ ሰነዘርን፡፡ እሳቸውም በምፀት ፈገግታ ታጅበው ንጉሱ አብዲሳን ያስታወሱት ከዓመታት በኋላ መሆኑንና ‹‹ስጦታውም›› ያገለገለች ኦፔል መኪና ከስድስት መቶ ብር ጋር መሆኑን ነገሩን፡፡ ‹‹በወቅቱ ጃንሆይ እንደሚፈልጉት ሲነገረን በጣም ነበር የፈራነው፡፡ ምክንያቱም ሁሌ ይበሳጭ ስለነበር አንድ ነገር ተናግሮ ሊቀጡት የተጠራ መስሎን ... ‹ሽልማቱን› ይዞ ሲመጣ እንኳን በዚህ አለፈልህ ነው ያልነው›› ሲሉ ያካፈሉን ትውስታም በአገሩም ሆነ በባዕድ ምድር ጠላትን ያስጨንቅ የነበረው አርበኛ ምን ያክል የአመድ አፋሽነት ስሜት አንጀቱን ያላውሰው እንደነበር የሚጠቁም ነው፡፡

የአብዲሳ አጋ ባለቤት ከአብዲሳ ትዝታዎች መካከል አንድ የሚገርም፣ ከመግረም አልፎ የሚያስተዛዝብና ‹‹ለምን?›› የሚያሰኝ ትዝታ አካፈሉን፡፡ በጣሊያን እስር ቤት ካፈራቸው ወዳጆቹ መካከል አንዱ የሆነው ዩጎዝላቪያዊው ማርሻል ቲቶ የአገሩ መሪ ሆኖ ለጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ በመጣ ጊዜ ለንጉሱ ያቀረበው የመጀመሪያ ጥያቄ “ጀግናው ወዳጄ አብዲሳን ማግኘት እፈልጋለሁ” የሚል ነበር፡፡ ነገር ግን አፄ ኃይለ ሥላሴ እዚሁ ይኖር የነበረውን አብዲሳ አምባሳደር አድርገው ወደ ውጪ ሀገር እንደላኩት ለማርሻሉ ገለፁለት፡፡

በመጨሻዎቹ የዕድሜ ዘመኑ የሌተና ኮሎኔልነት ማዕረግ ያገኘው የሀገር ባለውለታ፣ ዕድሜ ልኩን ለከፈለው ከባድ መስዋዕትነት ‹‹ማካካሻ›› ይሆን ዘንድ የሁለት መቶ ብር የጡረታ አበል ለቤተሰቦቹ ይሰጣል፡፡ በሞት ከተለየ በኋላ ያለው የቤተሰቡ ሁኔታ ምን ያክል አስቸጋሪ መሆኑን ለመረዳት ብዙም አያዳግትም፤ ‹‹እሱ እኮ ለአገሩ እንጂ ለቤተሰቡ አንድም ቀን አስቦ አያውቅም›› ከሚሉት የዘጠኝ ልጆቹ እናት ጋር ጥቂት ደቂቃዎችን ቆይታ ማድረግ በቂ ነው፡፡

ሰሞኑን ደግሞ የአብዲሳ አጋን ቤተሰብ የሚያሳስብ ጉዳይ ተከስቷል፡፡ ቦሌ ወሎ ሰፈር የሚገኘው እና ከ1952 ዓ.ም ጀምሮ ከባለቤታቸው ጋር ሲኖሩበት የቆየው ቤት በመልሶ ማልማት ምክንያት ሊፈርስ መሆኑ ነው ወ/ሮ ቀለሟን ያሳሰባቸው፡፡ የቤቱን በልማት ምክንያት መፍረስ እንደማይቃወሙ የሚያስገነዝቡት ወ/ሮ ግን ‹‹አብዲሳ ካለው ታሪክ አንፃር መኖሪያ ቤቱን አፍርሶ ታሪኩን ከማዳፈን፣ የሚመለከተው የመንግስት አካልም ሆነ ሌሎች ተቆርቋሪዎች የእሱንም ሆነ የሌሎች አርበኞችን ተጋድሎ የሚዘክር ነገር እዚሁ ቢያቋቋሙ ለመጪው ትውልድም አስተማሪ ይሆናል›› ሲሉ የመፍትሔ ሀሳብ ያቀርባሉ፡፡

ጉዳያቸውንም ለቂርቆስ ክ/ከተማ አስተዳደር የሥራ ኃላፊዎች ‹‹እንዴት ይሻላል?›› በሚል አቅርበው ‹‹የአብዲሳ አጋን ታሪክ እናውቃለን፤ ግን ምን እናድርግ ከላይ የወረደልን አቅጣጫ የለም›› የሚል ምላሽ አግኝተዋል፡፡

አብዲሳ አጋ አባል የሆነበት የጀግኖች ማሕበርም የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ለሆኑት አቶ ኩማ ደመቅሳ ለአብዲሳ አጋ ቤተሰብ እገዛ እንዲደረግ እና ታሪኩን የሚዘክር ነገር እንዲከወን በመስከረም 28 ቀን 2003 ዓ.ም በጻፈው ደብደቤ ጠይቆ ነበር - እስካሁን ምላሽ ባያገኝም፡፡

ከዚህ በተጨማሪ፣ ቀደም ባሉት ዓመታት በአንደኛ ደረጃ የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ መፅሐፍ ላይ የነበረው የአብዲሳ አጋ ታሪክ አሁን በተዘረጋው ክልላዊ የትምህርት ሥርዓት ውስጥም ይገኝ እንደሆን፣ ካልተገኘም ምክንያቱን ለማጣራት ሙከራ አድርገን ነበር፡፡ ነገር ግን በትምህርት ሚኒስቴር የገጠመንን ሁኔታ በአግባቡ አጣርተን ወደፊት ለማቅረብ ብናስብም፣ በወቅቱ ያገኘናቸው የሥራ ኃላፊዎች ጥያቄያችንን ባግባቡ ሊያስተናግዱ ባለመፍቀዳቸው ሙከራችን አለመሳካቱን ልንገልፅ እንወዳለን፡፡

[በአብዲሳ አጋ ተራኪነት፣ በመርስዔ ኃዘን አበበ

አዘጋጅነት የታተመውን “በኢጣሊያ በረኻዎች” የተሰኘ

መፅሐፍ በመሠረታዊ ማጣቀሻነት መጠቀማችንን

ስንገልፅ በአክብሮት ነው፡፡]

አብዲሳ አጋ እና የማይዘነጋ ውለታውሚያዚያ 27 ቀን በሚከበረው የአርበኞች የድል ቀን ዋዜማ በኢጣሊያ ወረራ ወቅት አኩሪ ገድል ወደፈጸመው እና የአገር ባለውለታ ወደሆነው አብዲሳ አጋ መኖሪያ ቤት ያመራው ሱራፍኤል ግርማ ከባለቤቱ ወ/ሮ ቀለሟ

ፈለቀ ጋር ቆይታ አድርጓል፡፡ ታሪክ በማጣቀስም የአርበኛውን አስደናቂ ሕይወት በተከታዩ ፅሁፍ ያወሳል፡፡ አውራምባ ታይምስ እንኳን የአርበኞቹን የድል ቀን ደግመን ደጋግመን ለማክበር አበቃን ይላል፡፡

በጣሊያን እስር ቤት ካፈራቸው

ወዳጆቹ መካከል አንዱ የሆነው

ዩጎዝላቪያዊው ማርሻል ቲቶ

የአገሩ መሪ ሆኖ ለጉብኝት ወደ

ኢትዮጵያ በመጣ ጊዜ ለንጉሱ

ያቀረበው የመጀመሪያ ጥያቄ

“ጀግናው ወዳጄ አብዲሳን ማግኘት

እፈልጋለሁ” የሚል ነበር፡፡

Page 18: አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 166 ቅዳሜ ሚያዚያ 29 2003 ኢሕአዴግ … · ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ አውራምባ ታይምስ 4ኛ

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 166 ቅዳሜ ሚያዚያ 29 200318

ሴት

አንዳንድ ነገሮች አግባብ ባልሆነ ይሰየማሉ፣ ይታወቃሉ፣ ወይም ይፈረጃሉ፡፡ ይህ አግባብነት በሌለው ሁኔታ የሚደረግ ስያሜ የራሱ ጫና አለው፡፡ ይህ ነገር በተወሰነ ሁኔታ እውነታም አለው ልንል የሚያስደፍረን ነጥብ አለው፡፡ ለዛሬ ከእነዚህ እውነት ከሚመስሉ ነገር ግን ስናስተውላቸው ከዚያ ይልቅ ሌላ አቅጣጫን የያዙ (ኃሳቢነትን የተሞሉ) ብንላቸው ‹‹የሚሻል›› ያልነውን እናንሳ ፡፡ ከዚህ በሁለት አቅጣጫ የተጠፈረ ጉዳይ አንዱ

ለተደጋጋሚ ማሳሰቢያዎች ‹ጭቅጭቅ› በሚል የሚሰጠው ስያሜ ነው፡፡ አለመግባባት የሚለውን ቃል ብንጠቀም ይሻላል፡፡

ተደጋጋሚ ያለመግባባት ወይም ጭቅጭቅ ከወንዶች ይልቅ ሴቶች ላይ (በቤተሰብ፣ በትዳርም ሆነ በፍቅር ግንኙነት ወቅት) ያመዝናል የሚል መከራከርያ ይቀርባል፡፡ ጭቅጭቅን ማን ይወዳል? አሁን የምናነሳው ግን ሌላኛውን ‹‹ጭቅጭቅ›› ነው፡፡ ‹‹ወንዶችም እኮ እንደሴት ባይሆንም ይጨቃጨቃሉ›› ብለው ሊያግባቡ የሚሞክሩም አይጠፉም፡፡ እነሱ ከተጨቃጨቁ እንዲያውም እንደጭቅጭቅ ሳይሆን ኃላፊነትን እንደመወጣት ሲቆጥሩት ይስተዋላል፡፡ ለእኛ ብቻ ያሰቡ እንዲመስለን እስከማድረግ ተድበስብሶ የሚያልፍበት ሁኔታ ብዙ ነው፡፡

ሴቶችን ብቻ ተጨቃጫዎቂ ናቸው ብለን እንድናስብ የሚያደርጉ ሚሊዮን ነገሮች ይደረደሩ ይሆናል፡፡ አንድ ፈገግ ከሚያሰኝ እውነታ ብጀምር፤ የኢትዮ-ቴሌኮም’ዋ ሴት ‹‹ያሎት ቀሪ ሒሳብ...›› የምትለዋን ማሳሰቢያ እንደ ‹‹ጭቅጭቅ›› የምንቆጥር ቀላል አይደለንም፡፡ እርግጥ የ904ቷ ሴት ነገር አሰልቺ ነገር መሆኑ አይካድም፡፡ የማስታወስ ግዴታዋን እየተወጣች እንደሆነ ልብ ይባል፡፡ ከዛ ይልቅ ግን አንድ ጥያቄ እናንሳ ይህ እንደአሰልቺ የምናየው ነገር በሴት ድምፅ እንዲሆን ለምን ተመረጠ? በአጋጣሚ? እንድንል ያደርገናል፡፡

አንዳንዶች፣ (በሞባይል ስልካቸው በቂ ሂሣብ የሌላቸው) ወደሚፈልጉበት ቦታ ሲደውሉ ይህቺው ሴት ኦፕሬተር ማሳሰቧን በተማፅኖአዊ ንግግር ትጀምራለች፡፡ ‹‹ያሎት ቀሪ ሒሳብ .... እባክዎን...›› በማለት፡፡ ይሄኔ ታዲያ እርስዎ ‹‹ኤጭ... ይቺ ነዝናዛ ሴትዮ፣ የቤቴ ጭቅጭቅ ሳያንሰኝ በገዛ ስልኬም ...›› ማለትዎ አዲስ አይሆንም፡፡

ከዚህ ወጣ ስልንስ? መቃረን ሲበዛ ወደጭቅጭቅ ይለወጣል፡፡ በሁለት ተመሳሳይ ጾታ (ጓደኞች) መካከል በሚኖር ያለመግባባት የሚፈጠር ጭቅጭቅ የተቃረነውን ሃሳብ አንድ እንዲሆን ከመፈለግ ቢሆንም መጨረሻው ላያምርም ይችላል፡፡ ለምን? ቢሉ፤ በዚህኛው የጓደኝነት ጭቅጭቅ ውስጥ ራስ ወዳድነትና ‹ይሄ ለእኔ› የማለት ነገር ሊያመዝን ይችላልና ነው፡፡

በትዳር ውስጥ የሚያጋጥም ጭቅጭቅስ? የዚህ አይነቱ አጋጣሚ እየተደጋገመ ከሄደ መስመሩን ስቶ ያልተፈለገ ምስቅልቅል ሊፈጥር ይችላል፡፡ ‹‹ጨቅጫቃ ሚስት ነው ያለችኝ›› ብለህ አታውቅ ይሆን? ነገር ግን ያ አለመግባባት ከምን እንደመጣ የምናውቅ ምን ያህሎቻችን ነን? በትዳር ላይ የሚከሰት አለመግባባት ከላይ እንደጠቀስነው ከራስ ወዳድነት የመነጨ አይደለም፡፡

አንተ ከጓደኞችህ ጋር ስትዝናና የምታወጣው ብር ቅንጣት ታክል ላያምህ ይችላል፡፡ (የሚገርመው ደግሞ የምትዝናናው ቤትህ ሙሉ ሳይሆን ይሆናል) ነገር ግን ወደቤትህ ስትገባ ከባለቤትህ የሚቀርብልህ የ‹‹ይሄ ጎድሏል›› ጥያቄን ልክ እንደጭቅጭቅ ማየትህ አግባብነት ይኖረው ይሆን? ወይም የገባህላትን ቃል አልፈፀምክ ይሆናል፡፡ (የገባኸው ቃል እንደአስፈላጊነቱ በትዳራችሁ ላይ የተመሰረተም ሊሆንም ይችላል) ያ ካልተፈፀመ ክርክሩ ይበዛና ጭቅጭቅ ይሆናል ማለት ነው፡፡ የእርሷ ተጨቃጫቂነት ለእሷ ብላ ወይም ላንተ ብላም ላይሆን ይችላል - ነገር ግን ለትዳራችሁ፡፡

በእሷ ጭቅጭቅ ውስጥ ራስ ወዳድነት የማይታይበት ሁኔታ ያመዝናል፡፡ አምሽተህ ስትገባ ምነው አመሸህ የምትልህ፣ ያለአግባብ ወጪ ስታወጣ አይሆንም የምትልህ፣ ... (አንተ እንደ ጭቅጭቅ የምትቆጥረው) ይሄ ሁሉ ነገር ለእሷም ላንተም እንዲሁም ለትዳራችሁ ብላ አይመስልህም? አንተ እንዲያ በማድረግህ ለእሷ ጎልቶ የሚታያት የትዳራችሁ መጎዳት ነውና ትረበሻለች፡፡ እናም በጽሞና የመነጋገር ነገር እዚህ ጋር ሊያበቃ ይችላል፡፡ በእርጋታ ልታስረዳህ ያልቻለችውን ነገር በኃይለ ቃል ወይም ያንን ነገር ደጋግማ በማንሳት ልታሳምንት ትሞክራለች፡፡ ያ ጭቅጭቅ ሊመስልህ ይችላል፡፡ እኔ ግን አሳቢነት ነው በሚለው እስማማለሁ፡፡

የጭቅጭቃችሁ መነሻ ኃሳብ በራሱ ራሱን የቻለ ልዩነት እንዳለው አስተውል፡፡ ያንተ ጭቅጭቅ የሚጀምረው ለምን ይሄን ለበስሽ? ለምን አመሸሽ (ሴት ሆነሽ በሚል ድምጸት)? ለምን ስልክሽ ተዘጋ? ለምን ጓደኞቼ ሲመጡ ስቀሽ አልተቀበልሽም… ማለቴ እንዲያም ለምን ሳቅሽ አለ ለካ? ለምን ምግብ አልሰራሽም?... ወዘተ ሊሆን ይችላል፡፡ ይሄ ምንን እንደሚያሳይ ልብ በሉ፡፡

ለምን እንዲህ ትጠጣለህ? ለምን ከቤት ውጪ ያለአግባብ ታጠፋለህ? ለምን ታመሻለህ (ከአንተ የጥያቄ ትርጓሜ በተለየ መልኩ)... - ይሄ የሴቷ ‹ጭቅጭቅ› ሊሆን ይችላል፡፡ እንግዲህ ጭቅጭቅ መስሎ የሚታየን ነገር አንዱ ለአንዱ መተሳሰብ ነው ካልን ማንኛችን እንሆን ለራሳችን ብቻ አስበን እየተጨቃጨቅን ያለነው?

ላንተ - እንዝናና፣ እናምሽ፣ እንጠጣ፣ አንተ ያልከው ይሁን፣ እሺ...እሺ...እሺ ብላ ሁሉንም እንደአንተ ምቾት እና አስፈላጊነት የምትጠብቅልህ ከሆነ ብቻ ጤናማ ግንኙነት ማለት ይህ ነው ብለህ ልታስብ ትችላለህ፡፡ ያ አይሆንም፡፡ ሁለት ነገሮች በኃይል ሲፋጩ ብርሃን ሊፈጠር ይችላል ብዬ አስባለሁ፡፡ ደግሞ ዓለም ሚዛኗን ጠብቃ የምትጓዘው በፍጭቶች መካከል ነው፡፡

ዓለም ሚዛኗን ጠብቃ የምትጓዘው በፍጭቶች መካከል ነው

በመቅደስ ፍስሐ [email protected]

በኤልያስ ገብሩ

የዘንድሮ የዓለም የፕሬስ ቀን ‹‹የ21ኛው ክፍለ ዘመን ሚዲያ አዲስ አማራጮችና ጋሬጣዎች›› በሚል መርህ ቃል ባሳለፍነው ማክሰኞ ዕለት በሂልተን ሆቴል በተከበረበት ወቅት

በፕሮግራሙ አካሄድ ላይ የተፈጠረ ውዝግብ በጣም አሳዛኝና አሳፋሪ እንደነበር የተለያዩ ባለ ድርሻ አካላት ገልጸዋል፡፡

በወቅቱ የእለቱን ምርሀ ግብር እና የመድረክ ተሳታፊዎች የሚያሳይ ሁለት አይነት ገላጭ ወረቀቶች ተዘጋጅተው ስለነበር የበዓሉ ስነ ሥርዓት ከመጀመሩ በፊት በሆቴሉ በአንድ ስፍራ ላይ ሁለት ዙር የተጓዘ የሽምግልና ሂደትን በማስተናገድ ፕሮግራሙ እንዳይካሄድ አዳራሹ ይዘጋ እስከመባል የተደረሰበት ሁኔታ እንደነበር በወቅቱ በግርግሩ መሀከል የነበሩ ሰዎች ለአውራምባ ታይምስ ተናግረዋል፡፡

የዓለም የፕሬስ ቀንን ለማሰብ የሆርን ኦፍ አፍሪካ ፕሬስ ኢንስትቲዩት፣ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮ ጽ/ቤት፣ የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ጋዜጠኞች ማሕበርና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ‹‹ጋዜጠኞች

ሕብረት›› በተባበሩት መ ን ግ ስ ታ ት የ ት ም ህ ር ት ፣ የሳይንስና የባሕል ድርጅት (ዩኔስኮ) ድጋፍ በጋራ አዘጋጅተው ነበር፤ በሒልተን ሆቴል፡፡ በእለቱም የተለያዩ ባለ ድርሻ አካላት በስፍራው ከጥዋቱ 2፡30 ሰዓት ጀምሮ በመገኘት ስማቸውን እ ያ ስ መ ዘ ገ ቡ ና መግቢያ በር ላይ በነበሩ ፕሮግራም አ ስ ተ ባ ባ ሪ ዎ ች አማካኝነት ጠረጴዛ ላይ የተቀመጡትን የስድስት ድርጅቶች አርማ ያለበትን ፕሮግራም ሲሰጡ ተ ስ ተ ው ለ ዋ ል ፡፡ ፕሮግራሙም ከተዘጋጀለት የጊዜ መርሃ ግብር ከአንድ ሰዓት በላይ መዘግየቱ በግልፅ የታየ ሲሆን በታዳሚዎች ላይ ግራ የመጋባት ስሜትን ታይቷል፡፡

ከ ዚ ያ ም በኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ጋዜጠኞች ማሕበር ፕሬዝዳንት አቶ አርጋው አሽኔ የ‹‹እንኳን ደህና መጣችሁ›› መልዕክት የ ተ ጀ መ ረ ው ፕሮግራም በተመድ ዋና ፀሀፊ ባን ኪሙን፣ የዩኔስኮ ዳይሬክተር ጄኔራል ኤሪና ቦኮቫ፣ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ዦን ፒንግ እና የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሚኒስትር አቶ በረከት ስምኦን በ ተ ወ ካ ዮ ቻ ቸ ው አ ማ ካ ኝ ነ ት መ ል ዕ ክ ቶ ቻ ቸ ው በየተራ ተነበበ፡፡

የመረጃ ተደራሽነት የእውቀት ሽግግርን ለማጎልበት እንደሚረዳ ባን ኪሙን በመልዕክታቸው የገለፁ ሲሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ በተለይም የምርመራ ጋዜጠኞች ኢላማ ተደርገው የተለያዩ ጥቃቶችና አደገኛ ሁኔታዎች እንደሚገጥማቸው በመጥቀስ ሁሉም ለፕሬስ ነፃነት ሊነሳና ንቁ ሊሆን እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

የዩኔስኮ ዳይሬክተር ጀኔራል መልዕክት ባለፉት 20 ዓመታት ውስጥ የሚዲያ ማህዳሩ ጥሩ ለውጥ እንዳለው፣ ነገር ግን በየሳምንቱ በዓለም ዙሪያ ግጭቶችና የተለያዩ ስቃዮች በመኖራቸው እነዚህን ተከታትለው የሚዘግቡትን ጋዜጠኞች ክብርና ጀብድ ሊዘነጋ እንደማይገባ

አስገንዝበዋል፡፡ ‹‹በአፍሪካ ብዙ አገሮች ሀሳብን በነፃነት

የመግለፅ ችግሮች በመኖራቸው፣ የተበረዙና የተዛቡ መረጃዎች ለሕዝብ ስለሚሰራጩ በዘርፉ ብዙ ሊሰራበት ይገባል፡፡›› የሚለው የዣን ፒንግ መልዕክት በአፍሪካ የፕሬስ ነፃነት ወደ ፊት መጓዝ ስለሚኖርበት የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ይኼንን ተረድቶ ጠንክሮ እንደሚሰራ ጠቅሶ በአሁን ወቅት በቂ መረጃ ያለው ዜጋ ስለሚያስፈልግ መንግስታት፣ የሚዲያ ተቋማት፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ የተባበሩት መንግስታትና ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ እጅ ለእጅ ሆነው በመስራት ነፃ ሀሳቦችን ሊያንሸራሽሩ እንደሚገባ መልዕክቱ ጨምሮ አስረድቷል፡፡

የአቶ በረከት ስምኦንን መልዕክት ያደረሱት የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ ሽመልስ ከማልም ከደርግ መንግስት ውድቀት በኋላ መንግስት ወዲያውኑ ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ ነፃነት በኢትዮጵያ ተግባራዊ እንዲሆንና ቅድመ ምርመራም መቅረቱን ከገለፁ በኋላ ባለፈው ስርዓት የጋዜጠኞች ማሰልጠኛ ተቋም ባለመኖሩ ሳቢያ የእውቀት ውስንነት መኖሩን በመጥቀስ በወቅቱ የነበሩ ብዙ ጋዜጠኞች ከደርግ ጋር ቁርኝት እንደ ነበራቸው ተናግረዋል፡፡

በ1997 ዓ.ም. በነበረው አገራዊ ምርጫ የግል ጋዜጦች ሕብረተሰቡን ግራ በማጋባት ችግር ውስጥ ከትተውት እንደነበር ያስታወሱት አቶ ሽመልስ ከዚያ በኋላ በፕሬስ ዙሪያ የተለያዩ ሕጎች መውጣታቸውን በመስረዳት ‹‹ግልፅነትና ተጠያቂነት ያለው መልካም አስተዳዳርን ያለ ፕሬስ ነፃነት ማስፈን አይቻልም›› ብለዋል፡፡ መንግስት መገናኛ ብዙሐን አስፈላጊ ያሉትን መረጃዎች እንዲያገኙ የሚያስችሉ ምቹ የሆኑ ጉዳዮችንና ስርዓት መዘርጋቱን አስረድተዋል፡፡

ከተወካዮች ንግግር በኋላ በመጀመሪያው መርሀ ግብር መሠረት የዛሚ ኤፍ ኤም 90.7 ሬዲዮ ጣቢያ ዋና ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሚሚ ስብሃቱ ‹‹ሚዲያ ለሕዝብ ጥቅም›› በሚል ርዕስ ሀሳብ እንዲያንሸራሽሩ የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ማሕበር ፕሬዚዳንት አቶ መሠረት አታላይ በአወያይነት መመደባቸውን ቢያሳይም የተካሄደው ግን ተሸሽሎ በመጣው በሁለተኛው ፕሮግራም መሰረት ሲሆን አቶ መሠረትና የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ዳይሬክተር አቶ ደስታ ተስፋው ከሚሚ ስብሀቱ ጋር በመሆን ‹‹ሚዲያ በሕዝብ ጥቅም፣ በአገር ግንባታና ዘላቂ ልማት›› ላይ ያለውን ፋይዳ በአቶ ብሩክ ከበደ አወያይነት ማካሄድ ሲጀምሩ አቶ ደስታ እና መሰረት እንዳልተዘጋጁበት ገልፀው ለተወሰኑ ደቂቃዎች ሀሳባቸውን ሰነዘሩ፡፡ መሰረት አታላይ ‹‹የመጣሁት ለሚሚ አወያይ ለመሆን እንጂ ሀሳብ ልሰነዝር አልነበረም›› ካለ በኋላ የፕሮግራሙን በድንገት መቀየር ‹‹የሚዲያውን ቀልጣፋነት ያሳያል›› በማለት ቀልዷል፡፡ የመድረኩ አወያይ ደግሞ በመጀመሪያው ፕሮግራም ስማቸው ያልተጠቀሰው የፋና ብሮድካስቱ አቶ ብሩክ ከበደ መሆናቸው አነጋጋሪ ነበር፡፡ በመድረኩ የነበሩት ሦስቱ የዘርፉ ‹‹ባለሙያዎች›› ባቀረቡት ንግግር ላይ ‹‹ቤቱ ውይይት አድርጎ ወደ ቀጣይ ፅሁፎች እንሂድ›› በሚሉና ‹‹የሃሳብ ተመሳሳይነት ሊኖር ስለሚችል ሌሎች አቅራቢዎች በመድረክ ሃሳባቸውን ከሰነዘሩ በኋላ ቤቱ ይወያይበት›› በሚሉ መሀከል የሃሳብ ልዩነቶች ተፈጠሩ፡፡ ‹‹የሃሳብ ተመሳሳይነት ሊኖር ስለሚችል ሌሎች አቅራቢዎች በመድረክ ሃሳባቸውን ከሰነዘሩ በኋላ ቤቱ ይወያይበት›› ባዮች ቁጥራቸው በርካታ መሆኑን በጭብጨባ ቢገልፁም አወያዩ አቶ ብሩክ ከበድ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ ሽመልስ ከማልን ሀሳብ ተንተርሰው ‹‹ቤቱ ጥያቄ አቅርቦ እና ውይይት አድርጎ ወደ ተከታዩ ፕሮግራም እንሂድ›› በማለት ሀሳባቸውን ሞሉ፡፡ ከዚያ በኋላ ነገሮች መልካቸውን እየቀየሩ መጡ፡፡ በቀጣይነት አቶ አማረ አረጋዊ (ሪፖርተር) የኢትጵያን የሁለት አስርት ዓመታት የሚዲያ ሥነ-ምህዳር ሁኔታ የሚያሳየውን ትንታኔ ይመራሉ የተባሉት ወ/ሮ ኤምራኬብ አሰፋ (ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ) ቢሆኑም ‹‹የሙሉቀን የመድረኩ መሪ እኔ ነኝ፡፡ ወረቀቱም ይህንን ያሳያል›› በማለት ሁለተኛውን የታደለ ፕሮግራም ተንተርሰው ‹‹ከመድረክ አሎርድም›› ያሉት አቶ ብሩክ ሀሳብ ያልተዋጠላቸው እና ከመድረክ ጀርባ ምን እየተሰራ እንደነበር የገባቸው አቶ አማረ

ፕሬሱን በአሳፋሪ ሁኔታ ያገለለው የፕሬስ ነፃነት ቀን - በሒልተን

‹‹ከመርህ አኳያ የፕሬስ

ነፃነትን የሚያፍኑ አካላትና

ግለሰቦች ቀኑ በሚከበርበት ቦታ

ላይ መቀመጥ አይገባቸውም፡

፡ በእኛ አገር ከመጣህ የፕሬስ

ነፃነትን የሚያፍነው መንግስት

ነው፡፡ በዕለቱም ከመንግስት

ቁልፍ ሰዎች ተገኝተዋል፡፡ ሆኖም

አብዛኛው ጋዜጠኛ በመንግስት

መገኘት ቅር እስካልተሰኘ

ድረስ ችግር አልነበረውም፡

፡ ነገር ግን የዕለቱን አጀንዳ

መንግስት በሚፈልገው መንገድ

ተቆጣጥሮታል››

Page 19: አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 166 ቅዳሜ ሚያዚያ 29 2003 ኢሕአዴግ … · ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ አውራምባ ታይምስ 4ኛ

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 166 ቅዳሜ ሚያዚያ 29 2003

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

ዜ ና ዎ ች 19

ማዕቀፍ እንደሚደግፉ ገልፀዋል፡፡ የቅኝ ግዛቱን ዘመን ውሎችም ሲያብጠለጥሉ ታይቷል፡፡ በመጨረሻም ኢትዮጵያ ስድስቱ ሀገራት የፈረሙበትን የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት ወደ ፓርላማ ወስዳ ከማፅደቋ በፊት ጊዜ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል፡፡

እነዚህ አዲስ አቀራረቦችም በአንዳንድ ወገኖች ዘንድ ጥርጣሬን መፍጠራቸው አልቀረም፡፡ ብዙዎች ከሚያነሷቸው ጥርጣሬዎች፣ ግብፃውያን ለዘመናት ሲያራምዱት የኖሩትን ግብፅ ‹‹የተለየ ታሪካዊ መብት አላት››ን አስተሳሰብ ልዑካኑ ሙሉ ለሙሉ የነቀፉ መሆናቸው፤ የግብፅን አብዮት የመሩና ዕውቅ ግለሰቦች ቢሆኑም፣ እንደ መንግስት አቋም ተደርጎ ሊታይ የማይችል መሆኑ፣ እንዲሁም የኢትዮጵያ ግድብ ግንባታ ሀገራቸውን እንደማይጎዳ ለማስጠናት ጊዜ የጠየቁበት አቀራረብ ለጥርጣሬዎቹ መንገድ እንደከፈተ እየተገለፀ ይገኛል፡፡

የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ቃል አቀባይ የሆኑት አምባሳደር ዲና ሙፍቲ

ግን ጥርጣሬዎቹን እንደማይቀበሏቸው ለአውራምባ ታይምስ ገልፀዋል፡፡ ‹‹ምንም እንኳን ልዑካኑ የግብፅ መንግስትን ባይወክሉም፣ ያላቸው ፖለቲካዊ አቅም ቀላል አይደለም›› ያሉት አምባሳደር ዲና፣ ከልዑካኑ ውስጥ ሶስቱ በቀጣዩ የግብፅ ፖለቲካ ውስጥ በከፍተኛ ቦታ ላይ የሚገኙ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡ ይህ ደግሞ ግለሰቦቹ ግብፅ በምትመሰርተው መንግስት ውስጥ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚኖራቸውን ተፅዕኖ እንደሚያመለክት አስገንዝበዋል፡፡

በሌላ በኩል ኢትዮጵያ የትብብር ማዕቀፉን ወደ ፓርላማ ወስዳ እንዳታስፀድቅ ጊዜ መጠየቃቸው በግድብ ግንባታው ላይ የሚያመጣው ለውጥ አለመኖሩን፣ ‹‹እስካሁን የትብብር ማዕቀፉን ከፈረሙት ስድስት ሀገራት አንዳቸውም ወደፓርላማ ወስደው አላስፀደቁም፡፡ ክረምት ላይ ደግሞ ፓርላማዎች ይዘጋሉ፡፡ ስለዚህ ግብጻውያኑ መንግስት እስከሚመሰርቱበት መስከረም ድረስ ጊዜ ብንሰጣቸው ብዙ ለውጥ አያመጣም፡፡›› ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ቲታስ ኢንተርናሽናል ሆቴል

ዛሬ ይመረቃልበአዳማ ከተማ የተገነባው ቲታስ

ኢንተርናሽናል ሆቴል፣ ዛሬ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተመርቆ ይከፈታል፡፡ ይኸው ባለ 4 ኮከብ ሆቴል 125 የአልጋ ክፍሎች፣ 250 ተስተናጋጆችን በአንዴ ሊያስተናግድ የሚችል ትልቅ ሬስቶራንት፣ መዝናኛ ክለብ፣ 1500 ተሰብሳቢዎችን የሚይዝ ሁለገብ ሲኒማና የመሰብሰቢያ አዳራሽ እንዲሁም ባንክና መድኃኒት ቤትን ጨምሮ ልዩ ልዩ የአገልግሎት ክፍሎች እንዳሉት የገለፁት የሆቴሉ ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ ሆቴሉ 84 ሚሊዮን ብር የጨረሰና በሙሉ አቅሙ ሥራ ሲጀምር ለ131 ዜጐች ሥራ እንደሚያስገኝ ገልፀዋል፡፡

በኤልያስ ገብሩ

መንግስት በቅርቡ ‹‹ታላቁ የሚሊኒየም ግድብ›› በማለት ይዞት የተነሳው አጀንዳ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሲመኘውና ሲጠብቀው የነበረው የረዥም ጊዜ ሕልም ቢሆንም፣ በአምስት ዓመቱ ዕቅድ ላይ ሳይካተት በድንገት መቅረቡ በተግባራዊነቱ ላይ ትልቅ ጥርጣሬ እንዲኖር ማድረጉን የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ገለፀ፡፡

ፓርቲው ባለፈው ማክሰኞ ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ኢትዮጵያ በተፈጥሮ የታደለች ሀገር መሆኗን ጠቅሶ፣ በመልካም አስተዳዳር እጦትና ብሔራዊ ጥቅምን ለማስከበር ከሚደረግ ጥረት ማነስ የተነሳ፣ ከዛሬ 50 ዓመት በፊት ጀምሮ የተጠናው የአባይ ወንዝ ግድብ ለጎረቤት ሀገራት ትልቅ የኢኮኖሚ

አውታር ሆኖ ሲያገለግል ለባለቤቶቹ ግን ከዜማ እንጉርጉሮ የዘለለ ያተረፈው ፋይዳ እንዳልነበረ አስታውቋል፡፡

የአባይን ግድብ ለማጠናቀቅ ያስፈልጋል የተባለው የገንዘብ መጠንና የመንግስት ቅድመ ዝግጅት አለመኖር፣ እንዲሁም በአምስት ዓመቱ የዕድገትና የለውጥ ዕቅድ ላይ አለመያዙ በአንድ ሀገር የልማት ስኬት ላይ ጥያቄ እንደሚያስነሳ ፓርቲው ጠቅሷል፡፡

እንዲሁም ዜጎች ለግድቡ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲያደረጉ የተላለፈው ጥሪና አሁን በየመስሪያ ቤቱ በማናጅመንት ኮሚቴ እየተወሰነ የሚተላለፈው መግለጫ፣ በየመስሪያ ቤቱ ባለው ሰራተኛ ላይ የውስጥ ፍላጎት ስለመሆኑና በአፈፃፀም ላይ የሚኖረውን ግልፅኝነትና ተጠያቂነት ለጥርጣሬ በር

እንደሚከፍት መግለጫው ያስረዳል፡፡ ‹‹የግብፅ የዲፕሎማሲ

ቡድንም በሀገራችን ያለውን የህዳሴ ግድብ አስመለክቶ ከመንግስት ባለሥልጣናት ጋር ያደረገው ንግግር የሁለቱንም ሀገራት ፍትሐዊ የህዝብ ጥቅም እንደሚያስከብር መግለፅ በተፈጥሮ ሀብታችን ላይ የመጠቀም መብታችንን ሳንጠቀምበት የቆየነው በራሳችን መንግስት ድክመት መሆኑን አመላካች ማስረጃ ነው›› ሲል የገለፀው መኢአድ፣ ግድቡ ለኃይል ማመንጫ ብቻ ሳይሆን፣ በምግብ ራሳችንን ለመቻል የሚያግዝ የመስኖ አገልግሎት ጥቅም እንዲሰጥ በዕቅድ ውስጥ ተካትቶ መስራት እንደሚገባውና የሙስና ጉዳይ ሊታሰብበትም እንደሚገባ መግለጫው አሳስቧል፡፡

‹‹የአባይ ግድብ ለእውነተኛ ብሔራዊ ጥቅም እንጂ ለፖለቲካ ፕሮፓጋንዳ መሆን የለበትም››

መኢአድ

በሱራፍኤል ግርማ

የአውሮፓ ሕብረት መሠረት የተጣለበት ግንቦት ዘጠኝ ወይም የአውሮፓ ቀንን አስመልክቶ ሕብረቱ አዲስ አበባ በሚገኘው ጽ/ቤቱ ትላንት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነበር አምባሳደር ዣቪየር ማርሻል የሕብረቱ ተወካዮች ከአቶ መለስ ዜናዊ ጋር ባደረጉት ውይይት በፕሬስ ነፃነት ላይም መነጋገራቸውን የገለፁት፡፡

ከአውራምባ ታይምስ፣ ‹‹ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በተለያዩ ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ስትነጋገሩ በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ ስላለው የፕሬስ ሁኔታ አንስታችኋል ወይ? ምን ምላሽስ

አገኛችሁ?›› የሚል ጥያቄ የቀረበላቸው አምባሳደር፣ በደፈናው ‹‹ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር የተወያየነው እንዳጋጣሚ በዓለም አቀፍ ደረጃ የፕሬስ ነፃነት የተከበረበት ዕለት እንደመሆኑ መጠን በጉዳዩ ላይ ተነጋግረንበታል›› የሚል መልስ ሰጥተዋል፡፡

መግለጫው በተሰጠ ጊዜ የአውሮፓ ሕብረት የውጭ ጉዳዮች ከፍተኛ ተጠሪ እና የአውሮፓ ኮሚሽን ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑት ካትሪን አሽተን የላኩት መልዕክት በወኪላቸው በኩል ቀርቧል፡፡ ሉዓላዊነትን ከማጠናከሩና የኢኮኖሚ ብልፅግና እንዲመጣ ከማስቻሉ በላይ፣ በ27ቱ አባል ሀገራት ውስጥ የሚገኙ

ከ500 ሚሊዮን በላይ አውሮፓዊያን ዴሞክራሲያዊ እና ሰብዓዊ መብቶቻቸው እንዲከበር ማስቻሉን በመልዕክታቸው ገልፀዋል፡፡

በአሁኑ ሰዓት ሕብረቱ ያሉትን የዲፕሎማሲ፣ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና የወታደራዊ ችግር አፈታት ልምዶች በመጠቀም በሰሜን አፍሪካ ያለውን ቀውስ ለማረጋጋት እየጣረ መሆኑን የሚያበራራው የከፍተኛ ተጠሪዋ መልዕክት፣ ‹‹የአውሮፓ ሕብረት ወጥ የሆነ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ እንዲኖረው በማድረግ እየተወሳሰቡ የመጡትን ዓለም አቀፍ ችግሮች ለመቀረፍ ጥረት እናደርጋን›› ብለዋል፡፡

በሱራፍኤል ግርማ

በኢትዮጵያ የተለያዩ ክልሎች ግዙፍ የኢንዱስትሪ ዞኖች እየተስፋፉ መሆኑን የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መኮንን ማንያዘዋል ገለጹ፡፡ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት ባለፈው ማክሰኞ ለሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የመስሪያ ቤታቸውን የዘጠኝ ወር ሪፖርት ባቀረቡ ጊዜ ሲሆን፣ የኢንዱስትሪ ዞኖቹ የሚቋቋሙባቸው ቦታዎች ዱከም፣ ለገጣፎ እና ኮምቦልቻ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

250 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ባስመዘገበ የቻይና ባለሀብት ኢስተርን የኢንዱስትሪ ዞን በሚል ስያሜ ዱከም ላይ የሚቋቋመው የኢንዱስትሪ ዞን በ200 ሄክታር መሬት ላይ የሚያርፍ ሲሆን፣ 80 ፋብሪካዎችን እንደሚያካትትና ለ37 ሺህ ሰዎች የሥራ ዕድል እንደሚፈጥር

ሪፖርቱ ያመለክታል፡፡ከአዲስ አበባ ወጣ ብላ

በምትገኘው ለገጣፎ ላይ አክጉን ኮንስትራክሽንና ማሺነሪስ በተባለ የቱርክ ኩባንያ የሚቋቋመው ‹‹ኢትዮ-ቱርክ የኢንዱስትሪ ዞን›› በርካታ ፋብሪካዎችን የሚይዝ መሆኑን፣ በ1460 ሄክታር መሬት ላይ እንደሚያርፍና በ2.8 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር እንደሚቋቋም አቶ መኮንን ገልፀዋል፡፡

በአቶ መኮንን ገለፃ መሠረት፣ በኢንዱስትሪ ዞን ልማት በጥናት የተለየው ሌላኛው ፕሮጀክት የኮምቦልቻ የጨርቃጨርቅ ክላስተር መንደር ነው፡፡ በ300 ሚሊዮን ዶላር ካፒታል እንደሚቋቋም ያስረዱት የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ፣ ፕሮጀክቱ ከ120 በላይ ኢንተርፕራይዞችን እንደሚያቅፍና የክላስተር መንደሩን

ሊያለሙ የሚችሉ ኩባንያዎችን ከሕንድ፣ ከቻይና እና ከሌሎች ሀገራት ለማግኘት ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ፣ የመንግስት ልማት ድርጅቶችን የሥራ አፈፃፀም በተመለከተም በሪፖርቱ ውስጥ ተካቷል፡፡ የድርጅቶቹን ትርፍ በሀገር ውስጥ ሽያጭ 31 ቢሊዮን ብር ለማድረስ ታቅዶ 28 ቢሊዮን ብር ማስመዝገብ መቻሉን፣ ከ18 የልማት ድርጅቶች የ51 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የኤክስፖርት ሽያጭ መከናወኑንና ድርጅቶቹ ከታክስ በፊት 1.6 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማስመዝገባቸውን አቶ መኮንን ያቀረቡት ሪፖርት ያመለክታል፡፡

ፕራይቬታይዜሽንን በተመለከተ ደግሞ 20 የመንግስት ድርጅቶች ለጨረታ መቅረባቸውን፣ 12 ድርጅቶች ደግሞ በቀጥታ ሽያጭ ወደግል ንብረትነት መዘዋወራቸው ተገልጿል፡፡

‹‹በፕሬስ ነፃነት ላይ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ተነጋግረናል››

ዣቪየር ማርሻል/የአውሮፓ ሕብረት የኢትዮጵያ ተጠሪ/

20 የመንግስት ድርጅቶች በጨረታ ፣ 12 ድርጅቶች ደግሞ በቀጥታ ሽያጭ ወደግል ይዞታ ተዘዋወሩ

‹‹ግብፃውያኑ መንግስት ...

አረጋዊ አዲስ ተሻሽሎ የመጣ (ሁለተኛ ፕሮግራም) መኖሩን ወደ ላይ ከፍ አድርገው በማሳየት አቶ ብሩክ ወርደው መጀመሪያ በወጣው ፕሮግራሙ መሰረት ዝግጅቱ የማይቀጥል ከሆነ ‹‹ፅሁፌን አላቀርብም፤ ስለ ፕሬስ ነፃነት እጨነቃለሁ፡፡ በፕሬስ ነፃነት ቀን ሳንሱር ልደረግ አይገባም›› በማለት አዳራሹን ለቀው ሲወጡ ነገሩ የተገለጠላቸው በርካታ ጋዜጠኞች እና ተሳታፊዎች አዳራሹን ለቀው ወጥተዋል፡፡ አቶ ሽመልስ ግን ለጀርመን ሬዲዮ ጣቢያ ‹‹ስብሰባውን ረግጦ የወጣው አቶ አማረ አረጋዊ ብቻ ነው›› ብለዋል፡፡

ትርምሱ ለምን ተፈጠረ?በዕለቱ በሒልተን ሆቴል ታድመው

ፕሮግራሙን ሲከታተሉ የነበሩትን የመድረክ ፓርቲ አባል አቶ ገብረ ገ/ማርያም ‹‹በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚከበር ትልቅ በዓል ላይ የውጪ አገር እንግዶች፣ የመንግስት ባለስልጣናትና የአገሪቷ ነፃ ፕሬስ አባላት ባሉበት እንደዚህ አይነት ነገር መደረጉ ያሳዝናል›› በማለት ስለተፈጠረው ጉዳይ ለአውራምባ ታይምስ ምላሻቸውን ሰጥተዋል፡፡ ‹‹በመጀመሪያ የተሰጠው ፕሮግራም ትክክል ነው እላለሁ›› የሚሉት የመድረኩ አባል የስድስት ተቋማት አርማ ያለበት የመጀመሪያው ፕሮግራም መቀየሩ በአገር ደረጃ የሚያሳስብ መሆኑን ይናገራሉ፡፡

አያይዘውም አሁን ባለንበት የቴክኖሎጂ ዘመን አንድ ሰዓት ያህል ፕሮግራም አዘግይቶ መጀመሩ ተገቢ አለመሆኑን ጠቅሰው ሌላ የተዘጋጀ ሁለተኛ ፕሮግራም ካለ ለታዳሚዎች መጀመሪያ መሰጠት እንደ ነበረበት አቶ ገብሩ ገልፀዋል፡፡

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋም በዕለቱ የተደረገው ነገር በጣም አሳፋሪ መሆኑን ጠቅሰው በመጀመሪያ የተያዘ የስብሰባ አጀንዳ እያለ ከመጋረጃ በስተጀርባ ተጠራርተው ያንን ለመለወጥ የተደረገውን ነገር ‹‹ኢ-ዴሞክራሲያዊ›› ይሉታል፡፡ ‹‹ስብሰባውን ረግጠው የወጡት ሰዎች በጣም ተገቢ ነገር አድርገዋል›› በማለትም ለአውራምባ ታይምስ ምላሻቸውን ሰጥተዋል፡፡

‹‹የፕሬስ ቀን እንዴት ቢከበር መልካም ነበር?›› ለሚለው ጥያቄያችን ጋዜጠኛ እስክንድር ሲመልሱ ‹‹ከመርህ አኳያ የፕሬስ ነፃነትን የሚያፍኑ አካላትና ግለሰቦች ቀኑ በሚከበርበት ቦታ ላይ መቀመጥ አይገባቸውም፡፡ በእኛ አገር ከመጣህ የፕሬስ ነፃነትን የሚያፍነው መንግስት ነው፡፡ በዕለቱም ከመንግስት ቁልፍ ሰዎች ተገኝተዋል፡፡ ሆኖም አብዛኛው ጋዜጠኛ በመንግስት መገኘት ቅር እስካልተሰኘ ድረስ ችግር አልነበረውም፡፡ ነገር ግን የዕለቱን አጀንዳ መንግስት በሚፈልገው መንገድ ተቆጣጥሮታል›› ሲል ተናግሯል፡፡ አቶ ሽመልስ ለጀርመን ድምፅ ‹‹ባለ ድርሻ አካል ስለሆንን ተገኝተናል›› በማለት መገኘታቸው አግባብ እንደ ነበር ጠቁመዋል፡፡

በዕለቱ የተፈለገው ነገር አቶ አማረን ተንኩሶ የ20 ዓመቱን የኢትዮጵያ የፕሬስ ሂደትን ማሳየት እንዳልተፈለገ አድርገው የተረዱት አቶ ገብሩ በአገር ደረጃም ሆነ እንደ አንድ ዜጋ በጣም ማፈራቸውን ገልፀዋል፡፡ ‹‹እለቱንም ለማክበር ጥሪ ያደረገልን ሆርን ኦፍ አፍሪካ ፕሬስ ኢንስቲትዩት ነው፡፡ የጠራኝ ድርጅት ባለቤት (አቶ አማረ አረጋዊ) ስብሰባውን ጥሎ ከወጣ ለምንድን ነው የምቀመጠው?›› ሲሉ ራሳቸውን በመጠየቅ በአዳራሹ ከቀሪዎቹ ጋር መቀመጥን እንዳልመረጡ ተናግረዋል፡፡

የዓለም የፕሬስ ቀን በሚከበርበት ዕለት እንደዚህ አይነት ችግር በመፈጠሩ በቀጣይ ጊዜያቶች ምን አይነት ድባብ ይፈጥራል ብለናቸው ‹‹ከማሳሰብ በላይ ማቅ ያስለብሳል›› ያሉት አቶ ገብሩ በ1997 ዓ.ም. የነበሩ ጋዜጦች ቁጥር ምን ያህል አሽቆልቁሎ በአሁን ጊዜ በጣት የሚቆጠሩ ብቻ እንደሚገኙ ስም እየጠቀሱ በመግለፅ ‹‹የፕሬስ ነፃነት ችግር ላይ ነው›› ብለዋል፡፡

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በበኩላቸው የ20 ዓመት የኢትዮጵያን የፕሬስ ሂደት በመገምገም የኢትዮጵያ ፕሬስ ከውልደቱ አንስቶ በትግል ውስጥ መሆኑን፣ ከ1997-98 ዓ.ም. ድረስ የግል ፕሬስ ሙሉ በሙሉ ተዘግቶ እንደነበር፣ ከ2000 ዓ.ም. በኋላ እንደ አዲስ ነገር እና አውራምባ ታይምስ ያሉ ጋዜጦች በጨለማ ውስጥ ለነበረው ነፃ ፕሬስ ብርሃን ትንሽ ፈንጥቀው እንደነበር ይናገራሉ፡፡ አያይዘውም ‹‹እነዚህን ለማዳከም ብዙ አይነት ተፅዕኖዎች ነበሩ፡፡ አሁንም የዋጋ ጭማሪ አንዱ አካል ነው፡፡፡ የፕሬስ የዕድገት ሂደት ተገድቧል፡፡ እኔን በምሳሌነት መጥቀስ ይቻላል፡፡ ፍቃድ አውጥቼ ለመስራት ተከልክያለሁ፡፡ ይኼ ለፕሬስ ነፃነት አፈና ጉልህ ማስረጃ ነው፡፡ በአጠቃላይ ሲታይ የነፃው ፕሬስ ሁኔታ በሞትና በሽረት መካከል ነው›› ሲሉ ፕሬሱ እንቅፋት እንደተጋረጠበት አሳይተዋል፡፡

በቀጣይም የአገራችን የፕሬስ ሁኔታ ምን ይመስላል? ለሚለው ጥያቄ ጋዜጠኛ እስክንድር ምላሽ አላቸው፡፡ ‹‹በአጠቃላይ በዓለም ላይ ያለ ሕዝብ፣ በመካከለኛው ምስራቅ፣ በአረብ አገራትና በኤሽያ ነፃነት እየሰፋና ዴሞክራሲያዊ የሆኑ

አገሮች ቁጥር እየጨመረ ቢሆኑም ኢትዮጵያ በተቃራኒው ጎራ ትገኛለች›› ያሉት ጋዜጠኛው ‹‹ይህ ስለማያስኬድ ዓለም በሚሄድበት አቅጣጫ መቀላቀሏ አይቀርም›› ሲሉ ሀሳባቸውን ሰጥተዋል፡፡

‹‹በዕለቱ በአቶ ሽመልስ ከማል አማካኝነት የተነበበውን የአቶ በረከት ስምኦን መልዕክት በጥሞና ላዳመጠ ኢትዮጵያ የፕሬስ ነፃነት ሞልቶ የተትረፈረፈባት ቢል ላያስገርም ይችላል፡፡ አሳዛኙ ነገር እነዚህ ሁለት ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት መንግስትን ይተቻሉ ለሚባሉ ሚዲያዎች ቃለምልልስ ለመስጠት እንኳን ፍቃደኛ አይደሉም፡፡›› የሚሉት የአውራምባ ታይምስ ማኔጂንግ ኤዲተር አቶ ዳዊት ከበደ በኢትዮጵያ ስላለው የሚዲያ ቢዝነስ ሀሳባቸውን ለመሰንዘርና ለማወያየት በመጀመሪያው ፕሮግራም ላይ ተመድበው ስማቸው ተካትቶ የነበረ ቢሆንም ኮሙኒኬሽን ፅ/ቤት እንደበተነው በተነገረው ሁለተኛው ወረቀት (ፕሮግራም) ላይ ስማቸው ተሰርዞ በዝግጅቱ ውጪ እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡ ‹‹በዕለቱ መድረኩ ቢሰጠኝ ኖሮ ሁሉም ሙያተኛ ባለበት ከእነዚህ ኃላፊዎች ጋር ባሉ ችግሮች ዙሪያ ፊት ለፊት የመወያየት ዕድል ይኖረን ነበር፡፡›› በማለትም ይህንን በትዕግስት ለመቀበል ከመንግስት አካላት ዘንድ ፍቃደኝነት አለመኖሩ እንዳሳዘናቸው ይናገራሉ፡፡ ‹‹ዓለም አቀፍ የፕሬስ ቀን በየዓመቱ በሚከበርበት ጊዜ በዚያ ሙያ ውስጥ ያሉ ሙያተኞች ሙያቸውን እንዴት እንደሚያሳድጉ፣ የሚደርስባቸውን ጥቃት እንዴት መከላከል እንዳለባቸውና በአጠቃላይ ሙያተኞች በጋራ የሚመክሩበት ቀን መሆኑን›› አቶ ዳዊት ገልፀው በፕሬስ ነፃነት ቀን ይህ በመታፈኑ በእጅጉ ማዘናቸውን ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ አካባቢ ጋዜጠኞች ማሕበር ፕሬዝዳንት የሆኑት አቶ አርጋው አሽኔን ‹‹በመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ተዘጋጅቶ የወጣው ፕሮግራም ዝርዝር ሁላችንም የተቀበልነው ነው›› በማለት ለሰንደቅ ጋዜጣ የገለፁት ትክክል መሆን/ አለመሆኑን ለማወቅ ጥያቄ አቀረብንላቸው፡፡ ‹‹አዎን›› በማለት ምላሽ ከሰጡን በኋላ በመጀመሪያ የነበረው ፕሮግራም ሰኞ ማታ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ተነጋግረው ሊቀየር እንደቻለ ያስረዳሉ፡፡

‹‹ፕሮግራሙ ከመጀመሩ በፊት ሁለተኛው ፕሮግራም ለምን ለታዳሚው አልተበተነም ነበር?›› ብለን ለጠየቅናቸው ጥያቄ የመጀመሪያውን ፕሮግራም ሆርን ኦፍ አፍሪካ ፕሬስ ኢንስቲትዩት ቀድሞ መበተኑን ጠቅሰው እየተለሳለሱም ቢሆን በአጠቃላይ በፕሮግራሙ ዙሪያ ችግሮች መኖራቸውን ባይሸሽጉም ስለ ችግሮቹ ዝርዝር ማብራሪያ ለመስጠት በቀጣይ ጥያቄዎቻችንን ላይ ቁጥብነት ታይቶባቸዋል፡፡

እውነታውና የአቶ

በረከት መልዕክትየጋዜጠኛ መታሰር፣ አለመታሰር

ከፕሬስ ነፃነት ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት እንደሌለው የሚናገሩት ጋዜጠኛ እስክንድር ‹‹በሰሜን ኮሪያ፣ በሳውዲ አረቢያ፣ በየመን... የታሰረ ጋዜጠኛ የለም፡፡ ነገር ግን የፕሬስ ነፃነት እና ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ ሁኔታ አለ ተብሎ አይታሰብም›› በማለት አቶ ሽመልስ ከማል ባነበቡት መልዕክት ላይ ‹‹አንድም የታሰረ ጋዜጠኛ የለም›› ሲሉ የተናገሩትን ተችተዋል፡፡

ጋዜጠኛ እስክንድር የተለያዩ ገለልተኛ ዓለም አቀፍ ተቋማት በኤርትራ ውስጥ ሀሳብን የመግለፅ ነፃነት የለም ሲሉ የሚያወጡትን ሪፖርት እነ አቶ ሽመልስ ‹‹ትክክል ነው›› ብለው እንደሚመሰክሩት ‹‹ይህ ችግር በኢትዮጵያ ቢኖርም ባለስልጣናቱ ግን ለምን እንደማይቀበሉ አይገባኝም?›› ሲሉ ይጠይቃሉ፡፡

የፕሬስ ነፃነት አለመኖሩን መሸፋፈንና መድረክ ላይ ተቀምጦ የፕሬስ ነፃነት አለ ማለት አይቻልም›› የሚሉት ጋዜጠኛ እስክንድር ዴሞክራሲን ለማስፈን ኢህአዴግ በመጀመሪያ የሕዝብን ሃሳብ የመግለፅ ነፃነት እና የመደራጀት መብቶችን ማረጋገጥ እንደሚኖርበት አስገንዝበዋል፡፡

የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሚኒስትር ዴኤታ የሆኑት አቶ ሽመልስ ከማል ጋር ስለተፈጠረው ጉዳይ ለመጠየቅ በተደጋጋሚ ወደ ተንቀሳቃሽ ስልካቸው ደውለንላቸው የመጀመሪያ ጥያቄያችንን ካደመጡን በኋላ ከ30 ደቂቃ በኋላ ደግመን እንድንደውል በገለፁልን መሠረት የስልክ ጥሪ ብናደርግም ሥራ ላይ መሆናቸውን ገልፀው ሌሎች የሚመለከታቸውን አካሎች ማነጋገራችንን ከጠየቁን በኋላ ‹‹እኔው ራሴ ሥራ እንደ ጨረስኩ እደውላለሁ›› ቢሉም ሳይደውሉ ቀርተዋል፡፡ እንዲሁም የፕሮግራሙ አንዱ አዘጋጅ የሆነው የሆርን ኦፍ አፍሪካ ፕሬስ ኢንስቲትዩት ኃላፊ እና የሪፖርተር ጋዜጣ ዋና ሥራ አስኪያጅ ለሆኑት አቶ አማረ አረጋዊ ተደጋጋሚ የስልክ ጥሪ ብናደርግም ተንቀሳቃሽ ስልካቸው ስለማይነሳ ሀሳባቸውን ማካተት አልቻልንም፡፡

Page 20: አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 166 ቅዳሜ ሚያዚያ 29 2003 ኢሕአዴግ … · ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ አውራምባ ታይምስ 4ኛ

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 166 ቅዳሜ ሚያዚያ 29 2003ጤ ና20

በኤልያስ ገብሩ

በኢ ት ዮ ጵ ያ ከ ስ ም ን ት ሰዎች መካከል ሶስቱ ስር በሰደደ ድህነት ውስጥ ይገኛሉ፡፡ በአገሪቷ ያለው የጤና አ ገ ል ግ ሎ ት

አቅርቦት እጅግ ውስን ነው፡፡ ባልተመጣጠነ የአመጋገብ ሥርዓት ምክንያት በጣም አስደንጋጭ ለሆነ የጤና እክል መጋለጥ፣ ዕድሜን ሊያሳጥሩ በሚችሉ በሽታዎች መጠቃት ከሕክምና አገልግሎት ውሱንነት ጋር በቅርብ የተቆራኙ ናቸው፡፡

የጨቅላና ሕፃናት ሞት መጠን አሁን ድረስ በኢትዮጵያ ከፍተኛ ነው፡፡ ለሞት ምክንያት ሊሆኑ የሚችሉት እንደ ወባ፣ ሳምባ ምች እና ተቅማጥ ያሉ በሽታዎችን በቀላሉ መከላከል እንደሚቻል በኢትዮጵያ የሚገኘው ‘Save The Children’ የተባለው ዓለም አቀፍ የረድዔት ድርጅት መረጃ ያስረዳል፡፡ ይህም የህፃናትን ሞት መጠን መቅጨት ባይቻል እንኳን ስኬታማ መከላከል ማድረግ እንደሚቻል ያሳያል፡፡

ስንት ሞት?መረጃዎች እንደሚያሳዩት

በአገራችን ከአስር ነፍሰ-ጡር ሴቶች ሶስቱ ብቻ ተገቢውን የቅድመ-ወሊድ ሕክምናና ክትትል በጤና ድርጅቶች ያገኛሉ፡፡ ከአስር ነፍሰ-ጡር ሴቶች አንድ ብቻ በጤና ባለሙያ እገዛ ትወልዳለች፡፡ በየዓመቱ ከ17 ሺህ በላይ እናቶችና ከ100 ሺህ በላይ ጨቅላ ህፃናት ከእርግዝናና ከወሊድ ጋር

በተያያዙ ለሞት ይዳረጋሉ፡፡ በዓለም ውስጥ 8.1 ሚሊዮን

ሕፃናት አምስተኛ የልደት ቀናቸውን ሳያከብሩ ይህችን ዓለም በሞት ይሰናበታሉ፡፡ የሚያሳዝነው ግን የአብዛኛቹ ሞት ምክንያት በቀላሉ ሊመከቱ የሚችሉ በሽታዎች መሆናቸው ነው፡፡

በኢትዮጵያም ከ10 ህፃናት መካከል አንዱ አምስት ዓመት ሳይሞላው የሚሞት ሲሆን፣ ከላይ እንደተገለፀው በሽታዎቹን በቀላሉና በአነስተኛ ወጪ መከላከል እንደሚቻል ባሳለፍነው ሳምንት በሐዋሳ ከተማ ‹‹ሁሉም›› በሚል መርህ ቃል በወሊድ ምክንያት ሕይወታቸውን ስለሚያጡ እናቶችና ሕፃናት ‹‹Save the Children››፣ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር፣ ዩ.ኤስ.ኤ.አይ.ዲ.፣ ከፍተኛ ባለሥልጣን እና ሌሎች የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በተደረገው የውይይት መድረክ ላይ የቀረቡት መረጃዎች ያስረዳሉ፡፡

መንግስትመንግስትም የእናቶችን ሞት

ለመቀነስ ከፖሊሲ አውጪዎች ጀምሮ እስከ ታችኛው የሕብረተሰብ ክፍል ድረስ በተዘረጋ መዋቅር እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝና የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራምም በመላው አገሪቷ እንዲተገበር በማድረግ ከ34 ሺህ በላይ የጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞችን አሰልጥኖ በሁሉም የአገሪቱ ቀበሌዎች መመደቡንና ሰራተኞቹም ኅብረተሰቡን እያገለገሉ እንደሚገኙ ይናገራል፡፡

ምንም እንኳን መንግስት የጤና ተቋማትን የማስፋፋት ሥራን እያካሄደ እንደሚገኝ ቢገለፅም፣

በጤና ተቋማትና በባለሙያ እገዛ የሚወለዱ እናቶች ቁጥር እጅግ አናሳ ነው፡፡ ይህም በመሆኑ፣ በቀላል የህክምና ዕርዳታና አገልግሎት ከእርግዝና እና ወሊድ ጋር የተያያዙ ችግሮችን ማስወገድ ቢቻልም፣ በሺዎች የሚቆጠሩ እናቶች እና ጨቅላ ህፃናት በየዓመቱ መሞታቸው አልቀረም፡፡

ችግሮችና መፍትሄዎችበኢትዮጵያ የእናቶች ሞትን

ከሚያስከትሉት ዋና ዋና ምክንያቶች መካከል ከወሊድ በኋላ ከፍተኛ የደም መፍሰስ፣ የተራዘመ ምጥ፣ ኢንፌክሽኖች፣ ሕገ-ወጥና አደገኛ ውርጃ እና በእርግዝና ወቅት የሚከሰት ክፉኛ የደም ግፊት መጨመር ተጠቃሾች ናቸው፡፡

እነዚህንም ችግሮች ለመቅረፍ በእርግዝና ወቅት የቅድመ ወሊድ ክትትልን በጤና ተቋማት አማካኝነት በሰለጠነ ባለሙያ ማከናወን፣ እንዲሁም ከወሊድ በኋላ ተገቢውን የሕክምና ክትትል ማድረግ ተጠቃሽ ዕልባቶች ናቸው፡፡

አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ሩቅ በሆኑ አካባቢዎች የሆስፒታልና የሌሎች የጤና አገልግሎቶች ውስኑነት ባለበት ሁኔታ የሚኖር ነው፡፡ መንግስት በገጠር መሰረታዊ የጤና አጠባበቅና

አሳሳቢው የሕፃናት ሞትመንግስት በገጠር መሰረታዊ የጤና አጠባበቅና ጥንቃቄ እንዲኖር 33 ሺህ ያህል የጤና

ኤክስቴንሽን ሰራተኞችን ቢያሰማራም፣ ለ33 ሺህ ሰዎች የተመደበው አንድ የሕክምና ዶክተር

ብቻ ሲሆን ከወሊድ ጋር የተያያዙ ተገቢውን የጤና እንክብካቤ ለማድረግ ሙሉ በሙሉ

የሰለጠኑ የሕክምና ባለሙያዎችና ተቋማት በጣም አነስተኛ ናቸው፡፡

የኃዘን መግለጫ

በታላቁ የአፋር ሀይማኖታዊ አባት መሪ በተከበሩ ሱልጣን አሊሚራህ ሀንፈሬ ከዚህ ዓለም በሞት መለየት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለፅን ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እንዲሁም ለመላው የኢትዮጵያ

ህዝብ መጽናናትን እንመኛለን፡፡ የአፋር ውኃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት

ጥንቃቄ እንዲኖር 33 ሺህ ያህል የጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞችን ቢያሰማራም፣ ለ33 ሺህ ሰዎች የተመደበው አንድ የሕክምና ዶክተር ብቻ ሲሆን ከወሊድ ጋር የተያያዙ ተገቢውን የጤና እንክብካቤ ለማድረግ ሙሉ በሙሉ የሰለጠኑ የሕክምና ባለሙያዎችና ተቋማት በጣም አነስተኛ ናቸው፡፡ ማኅሕበረሰቡ ምን አይነት የጤና አጠባበቅ አገልግሎቶችን መጠቀም እንዳለበት ለመረዳት የእውቀት ውስኑነት መኖሩ በማስረጃነት የሚቀርብ ሲሆን፣ ለዚህም ችግር መንግስትን በመደገፍ ዕውቀት ያላቸው የጤና ዘርፍ ባለሙያዎችን በመጨመር በየዓመቱ 1500 ያህል ነርስና አዋላጆችን በቂ ትምህርት ሰጥቶ ለማሰልጠን ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባ በመፍትሄነት ተጠቅሷል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞ ከፍተኛ ደረጃ ያለው የጤና አገልግሎት በቤት፣ በጤና ማዕከላትና በሆስፒታል ደረጃ የሰው ልጆች ወሳኝ ኩነቶች የሆኑትን የውልደትና ሞት ምዝገባዎችን በተመለከተ ሕግ እንዲወጣና የወጣውም ሕግ ተግባራዊ መሆኑን ማረጋገጥ ተገቢ መሆኑን መረጃዎች ያስረዳሉ፡፡

ያለዕድሜ ጋብቻና የመረጃ ዕጦት

በአገራችን በአንዳንድ ቦታዎች

የሚደረጉ ያለ ዕድሜ ጋብቻዎች ያለዕድሜ የሚከሰት እርግዝና እንዲመጣና ህፃናት አምስት ዓመት ሳይሞላቸው ሕይወታቸውን እንዲያጡ የሚሆኑበትን አጋጣሚ ከፍ ያደርጋለረ፡፡ የትምህርት ውስኑነትም እናቶች ለልጆቻቸው ማድረግ የሚገባቸውን እንክብካቤ እንዳያደርጉ የበኩሉን ሚና ይጫወታል፡፡ ሌላው አስቸጋሪው ጉዳይ ወዲያውኑ የተወለዱ ህፃናትን ጡት ማጥባት ለህፃናቱ ጎጂ እንደሆነ ተደርጎ የሚወሰደው ዕምነት ነው፡፡ ህፃናት ተፈጥሯዊ ገንቢ ንጥረ ነገር ያዘለውን የእናት ጡት ወተትን ወዲያው እንደተወለዱ ካልወሰዱ በሽታ የመከላከል አቅማቸውን የሚያጎለብቱበትን አንቲቦዲ፣ ቫይታሚን ኤ እና ኬ፣ እንዲሁም ሎሎች ወሳኝ ንጥረ ነገሮችን እንዳያገኙ ያደርጋቸዋል፡፡

ልጃገረዶችን በጉዳዮ ዙሪያ በማስተማር ያለእድሜ የመውለድ ችግርን መቀነስ፣ ለኅብረተሰቡ ያለእድሜ ጋብቻና እርግዝና አደገኛ መሆኑን መስተማር፣ በተለያዩ ማኅበረሰብ አቀፍ ተግባራት ላይ ለህፃናት የእናት ጡት ወተትን ማጥባትና ሌሎች የጤና አጠባበቅ ተግባራትን እንዲያደርጉ ተገቢውን መረጃ መስጠት ከላይ ለተነሱት ችግሮች መፍትሄ ናቸው፡፡

የመጣ መርሐ-ግብር? እጃችን ላይ ያለው የፕሮግራም ዝርዝር ጋሽ አማረ ጽሑፉን ሲያቀርብ፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህርትና የፕሬዝዳንቱ ቢሮ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ወ/ሮ ኤምራኬብ አሰፋ እንደሚያወያዩ የሚጠቁም ነው፡፡ ታዲያ አቶ ብሩክ የሚለን ምንድነው? እኛም ግራ ተጋባን፤ እዚህ ደረጃ የሚደርስ ነገር አልጠበቅንማ!

አንድ አንድ ማይክ ተይዞ የቀጠለው ንትርክ ብዙ አልቆየም፡፡ ጋሽ አማረ ‹‹This is sabotage›› በማለት ሻጥር እየተሰራ መሆኑን ከገለፀ በኋላ፣ በፕሬስ ነፃነት ቀን በፕሬስ ነፃነት ላይ በሳንሱር ጫና እየተደረገ በመሆኑ፣ ጽሑፉን እንደማያቀርብ በመናገር ይቅርታ ጠይቆ ከስብሰባው ወጣ፡፡ ቀጥሎም አብዛኛው ታዳሚ እያጉረመረመ ወጣ፡፡

ሁሉም ሰው ነገሩ ሁሉ ቁልጭ ብሎ የገባው የጋሽ አማረን መውጣት ተከትሎ እንደ አዲስ የተበተነውን ሌላ መርሐ-ግብር ሲመለከት ነበር፡፡ እኩለ ቀን ላይ የታደለው ይህ መርሐ-ግብር፣ እንደ ጠዋቱ የፕሮግራሙ አዘጋጆችና ስፖንሰሮች ሎጎ ወይም አርማ የለበትም፡፡ ይህ ብቻ አይደለም፤ የአንዳንድ ተሳታፊዎች የአባት ስም ተረስቶ በእጅ ጽሑፍ የተጨመረበት ነበር፡፡ እነዚህ ነገሮች አዲሱን መርሐ-ግብር እዚያው ሒልተን አካባቢ ኢንተርኔት ካፌዎች ውስጥ የተሰራ ያስመስሉታል፡፡ ከነዚህ ባሻገር ከቀደመው መርሐ-ግብር ጋር ምን ያለያየዋል?

- ጋሽ አማረ በዩኔስኮ መሪ ቃል ላይ ሊያቀርብ የተዘጋጀበትን ርዕሰ ጉዳይ አስቀርቶ በኢትዮጵያ የሁለት አሥርት ዓመታት የሚዲያ ሥነ-ምህዳር ዙሪያ ብቻ ጽሑፍ እንዲያቀርብ ያዛል፤

- ከጋሽ አማረ ጽሔፍ በኋላ ያወያያሉ የተባሉት ወ/ሮ ኤምራኬብ በአዲሱ መርሐ-ግብር ከነጭራሹ ተሰርዘዋል፤

ፕሬስ እና ነፃነቱን ...- በወ/ሮ ኤምራኤብ

ምትክ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጋዜጠኝነትና ኮሙኒኬሽን ትምህርት ዲን የሆኑት ዶ/ር ገብረመድህን ሰምዖን ተተክተዋል፡፡

- የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ሽመልስ ከማል ለጋሽ አማረ በተሰጣቸው ርዕስ ላይ የሚሉት እንደሚኖር በዚህ በአዲሱ መርሐ-ግብር ተጠቅሷል፤

- ሌላም ለውጥ አለ፡፡ በጠዋቱ መርሐ-ግብር በሚዲያ ቢዝነስ ዙሪያ የታምራት ገብረጊዮርጊስን ጽሑፍ ተከትሎ የአወያይነት ሚና የነበረው የአውራምባ ተይምስ ማኔጂንግ ኤዲተር ዳዊት ከበደ በአዲሱ መርሐ-ግበር እንዲሰረዝ ተደርጓል፡፡

- በዳዊት ምትክ ደግሞ ከፕሮግራሙ አዘጋጆች አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጋዜጠኞች ኅብረት ሊቀ-መንበር፣ አቶ አንተነህ አብርሃም ስሙ ሰፍሯል፡፡

እዚህ ላይ አንድ ያስገረመኝን ነገር ልንገራችሁ፡፡ በአዲሱ መርሐ-ግብር የዳዊት ቦታ የተሰጠው አንተነህ አብርሃም፣ ጋሽ አማረ ‹‹የፕሮግራሙ አካሄድ ልክ አይደለም፤ ሳንሱር መደረግ የለብንም›› እያለ መድረኩ ላይ በሚናገር ሰዓት፣ እኔ ‹‹አዲሱ›› እያልኩኝ የምጠራውን ፕሮግራም በእጁ ይዞ ‹‹ሁላችንም የተስማማንበት መርሐ-ግብር ነው፣ “ሴንሰርሺፕ” የሚባል ነገር የለም›› በማለት ለታዳሚያን ይናገር ነበር፡፡ ‹ይኼ ምን ያስገርማል?› እንደምትሉኝ አልጠራጠርም፡፡ እኔንም ያስገረመኝ ይኼ አይደለም፡፡

እኔ እና ዳዊት እንዲህ ያለው ውዥንብር ጭራሽ በፕሬስ ነፃነት ቀን የተፈፀመ መሆኑ አስደንቆን ቢሮ ተመልሰናል፡፡ ብዙ ሳይቆይ የዳዊት ስልክ ጮኸ፤ ደዋዩም አንተነህ አብርሃም ነበር፡፡ የሚከተለውን ለዳዊት ይለዋል፡

- ‹‹ዳዊት የት ሄድክ፣ እየጠበቅንህ እኮ ነው፣ ፕረዘንቴሽን እኮ አለብህ ... ፡፡›› አሁን ይኼን ምን ትሉታላችሁ? መድረክ ላይ ቆሞ ዳዊት የተሰረዘበትን መርሐ-ግብር ‹‹የተስማማንበት ፕሮግራም ነው›› ሲል ያደመጥነው ሰው እንደገና ‹‹ና እና አቅርብ›› ማለቱ ምን እያለ ነው? አዲሱን መርሐ-ግብር እርሱም እራሱ አያውቀውም? ወይስ ሌላ ሶስተኛ መርሐ-ግብር አለ? ለነገሩ በማግስቱ ከወጡት ጋዜጦች አንዱ ምላሹን ግልፅ ያደረገው ይመስለኛል፡፡ (የረቡዕ ጋዜጦች የዚህን ቀን ክስተት ምን ያህል በተራራቀ መንገድ እንደዘገቡት የታዘበ ካለ የሀገራችንን የፕሬስ ነፃነት ሁኔታ በትክክል ይረዳዋል፤ የታዘብነውን ታዝበናል፡፡) ሰንደቅ ጋዜጣ? ሁለቱንም መርሐ-ግብሮች ከነነፍሳቸው አቅርቧቸው ነበር፤ እናም እኔ ‹‹አዲሱ›› ካልኩት መርሐ-ግብር ግርጌ ‹‹በኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት የቀረበ›› የሚል ማስታወሻ አስፍሮበታል፡፡ አቶ አንተነህ የዳዊትን መሰረዝ ካላወቀ፣ የራሱን መጨመር አላወቀም ማለት ነው፡፡ ጋሽ አማረ ደግሞ ሻጥር መሰራቱን ነገረን፡፡ የፕሮግራሙ አዘጋጆች አስተናባሪዎች ብቻ ሁኑ ተባሉ፡፡ ታዲያ የዓለም የፕሬስ ነፃነት ቀን ተከብሮ አለፈ ሊባል ነው?

አቶ ሽመልስ ከማል በተለያዩ መድረኮች በተደጋጋሚ የሚናገሩት ነገር አለ፡- ‹‹አንድም የታሰረ ጋዜጠኛ የለም፤ በሀገራችን የፕሬስ ነፃነት ተከብሯል፡፡›› ጋዜጠኛ ስለመታሰሩ የመከራከር ዓላማ የለኝም፡፡ ነገር ግን አውቀውትም ሆነ ሳያውቁት ከአካላዊ እስራት በላይ በሆነ የፍርሃት እስራት የተቆፈደዱት የሀገራችን ጋዜጠኞች ቁጥር ቀላል አይደለም፡፡ ይህ ፍርሃት በመንግስታዊ ተቋማት ኃላፊዎች፣ መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶችና በቢዝነስ ኮሚኒቲው አባላት ጭምር የተንሰራፋ መሆኑ ደግሞ የምንገኝበትን ሁኔታ አስደንጋጭ ያደርገዋል፡፡ አንድ ሁለት

Page 21: አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 166 ቅዳሜ ሚያዚያ 29 2003 ኢሕአዴግ … · ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ አውራምባ ታይምስ 4ኛ

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 166 ቅዳሜ ሚያዚያ 29 2003

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

21

አሳሳቢው የሕፃናት ሞት

ምሳሌዎችን ወይም ገጠመኞችን ልጥቀስ፡፡

በአንድ ወቅት በየዓመቱ የሚከበረውን የሴቶች ቀን አስመልክቶ ለሚጠናቀር ጽሑፍ በአንድ መንግስታዊ ባልሆነ ድርጅት ውስጥ ኃላፊና የሕግ ባለሙያ የሆኑ ሴትን አነጋግረን ነበር፡፡ በሴቶች መብት ላይ ተመርኩዘን ጥቂት ጥያቄዎችን አቅርበንላቸው የነበረ ሲሆን፣ በወቅቱ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ በእስር ላይ ይገኙ ስለነበር ተቋማቸው በዚህ ጉዳይ ላይ ምን ዓይነት እንቅስቃሴ እንዳደረገና እንዲያብራሩልንም ጠየቅናቸው፡፡ እርሳቸውም በአግባቡ መልሰውልን ተሰነባበትን፡፡ ከአንድ ቀን በኋላ ግን ‹‹ጋዜጣው ከመውጣቱ በፊት የተሰራውን ጽሑፍ ካላሳያችሁኝ›› በማለት የሙጥኝ ያዙን፡፡ የሕግ ባለሙያ እንደመሆናቸው መጠን ይህንን እንኳን እርሳቸው መንግስትም ማድረግ እንደማይችል ሊገነዘቡ እንደሚገባ ገለፅንላቸው፡፡፡ እኚህ ሴት ቢሮ ድረስ መጥተው እምባ አልቅሰዋል፡፡ ይህ ከምንም የመጣ አይደለም፤ ከፍርሀት ነው፡፡ ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገመንግስት መስፈሩን አጥተውት አይደለም፤ ሊጥሰው የተዘጋጀ ቢኖርስ ብለው እንጂ፡፡

አሁን በቅርቡ ከሳምንታት በፊት ደግሞ የአንድ ጋዜጣ መታገድን አስመልክቶ በጋዜጣችን ‹‹ተጠየቅ›› አምድ ስር ለምናዘጋጀው ጽሑፍ ምላሽ ይሰጡን ዘንድ ያነጋገርናቸው አንድ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን ኃላፊ በዕለቱ ጥያቄያችንን አክብረው በአግባቡ ምላሻቸውን ሰጥተውን ነበር፡፡ ይሁንና ግን ከቀናት በኋላ ከጽሑፉ አዘጋጅ ጋር ያደረጉትን ተጨማሪ የስልክ ውይይት ተከትሎ ጽሑፉ ከመውጣቱ በፊት ሊያዩት ይችሉ እንደሆን ጠይቀውት ኤዲቶሪያል ፖሊሲያችን እንደማይፈቅድ አስረድቷቸዋል፡፡ እኚህ ኃላፊ ቅድመ-ምርመራ ላድርግ እያሉ እያስገደዱን አልነበረም፤ ሆኖም ሌላው ቢቀር ነገ ከበላይ ኃላፊ ሊመጣባቸው የሚችለውን ይሰጋሉና ቀድመው መመርመር

ፈለጉ፡፡ ለዚህ ሁሉ ተጠያቂው

የፕሬስ ሕጉ አይደለም፤ ቀስ በቀስ በእያንዳንዱ የኅብረተሰብ ክፍል እየተሹለከለከ የተንሰራፋው ፍርሃት እንጂ፡፡

ከዚህ ባሻገር ፍርሃቱን ከግራና ከቀኝ እያጀቡት ያሉት ኢኮኖሚያዊና አስተዳደራዊ ጫናዎች ልብ ሊባሉ ይገባል፡፡ የጋዜጣ ህትመት ዋጋ በከፍተኛ መጠን መጨመሩን ተከትሎ የሀገሪቱ የጋዜጣ ድርጅቶች አቤቱታቸውን ሲያሰሙና በአንባቢ ላይ የጋዜጣ ሽያጭ ዋጋ መጨመር ፕሬሱ ላይ ተፅዕኖ ይኖረዋል ሲሉ፤ አቶ ሽመልስ አሁንም ለሰንደቅ ጋዜጣ በሰጡት ምላሽ የትም ሀገር የጋዜጣ ትርፍ ሰርኩሌሽን ሳይሆን ማስታወቂያ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡ የማስታወቂያ ድርቅ የመታቸው ጋዜጦችስ? መንግስት የግሉን ፕሬስ በጠላትነት መመልከቱ የተለመደ ነውና ከመንግስት ጋር መጣላት የማይፈልገው ነጋዴ እንዴት ብሎ ድርጅቱንና ምርቱን በነዚህ ጋዜጦች ያስተዋውቅ?

አንድ የህትመት ውጤት፣ በተለይም የማስታወቂያ ገቢው የማያስተማምነው ጋዜጣ በሚወጣበት ቀን አርፍዶ ወጣ ማለት ወይም ሌሎች ጋዜጦች ቀደሙት ማለት የጋዜጣ ሽያጭ መጠኑም ስጋት ውስጥ ገባ ማለት ነው፡፡ ይህ ባለበት ሁኔታ እንደምንም የያዘውን ማስታወቂያ ይዞ ወደ ብቸኛው ማተሚያ ቤት በመክነፍ በጊዜ የገባ ጋዜጣ፣ የማሽን መበላሸቱን ጉዳይ ለጊዜው ትተን፣ መታተም ከጀመረ በኋላ አዲስ ዘመንና ሄራልድ የመሳሰሉ የመንግስት ጋዜጦች ከመጡበት መቋረጡ ግድ ነው፡፡ ይህን ያውቁ ኖሯል? የመንግስት ጋዜጣ በየትኛውም ሰዓት ይምጣ ምን ጊዜም ቅድሚያ ይሰጠዋል፤ የግል ጋዜጣ ከዚያ በኋላ ቀስ ብሎ ይታተማል፡፡ የመንግስትን ፕሮፓጋንዳ የያዙት እንጂ ከመንግስት የተለየ ሀሳብ የሚያንፀባርቁት ቢያረፍዱም ግድ የለም፤ አርፍደው ቢከስሩም እንደዚያው፡፡

ለ መ ጠ ቃ ቀ ስ የሞከርኳቸው ችግሮች ጥቂቶች እና

ጥቅሎች ናቸው - ቢያንስ እነዚህ እያሉ የፕሬስ ነፃነት ሰፍኗል ማለት እንደማይቻል ለማሳየት ያህል፡፡ እነዚህ እና መሰል ሁኔታዎች ይነሱና ውይይት ይደረግባቸው ዘንድ ነበር የዓለም የፕሬስ ነፃነት ቀን የመከበሩ ዓላማ፡፡ እነዚሁ ነባራዊ ችግሮች እንዳይነሱ ነበር የሒልተኑ ውዥንብር የተፈጠረው፡፡ መንግስት የግሉን ፕሬስ እንደጦር በመፍራትም ሆነ እንደ የድንበር ጠላት በመጥላት፤ ቢችል ቢያገልለው ባይችል ደግሞ በሆነ መንገድ የራሱ ሊያደርገው እንደሚጥረው ሁሉ፣ የግሉም ፕሬስ ፍፁም ላይሆን ይችላል፡፡ ሆኖም በአንድ የሕግ ጥላ ስር ሆኖ ሳለ የግሉን ፕሬስ በጠላትነት መፈረጅ በራስ አለመተማመንን ከማንፀባረቁ ባሻገር፣ በተመሳሳይ ዓይን መታየትን ያስከትላል፡፡ መንግስት የግሉን ፕሬስ አባላት የሀገሪቱ ዜጎች፣ የኢትዮጵያ ተቆርቋሪዎች እንደሆኑ አምኖ እስካልተቀበለ ድረስ፣ ቀጣይ የዓለም የፕሬስ ነፃነት ቀናትም ቢሆኑ ዳግመኛ የሚወቀስባቸው እና የሚወገዝባቸው መሆናቸው አይቀሬ ነው፡፡ ፕሬስ እና ነፃነቱን ካብ ለካብ ማስተያየቱ ማቁለጭለጭ እንጂ ማስፈን አይሆንምና፡፡

ስለሀገራችን የፕሬስ ነፃነት ሁኔታ ቢያንስ በፕሬሱና በመንግስት መካከል ምንም የሚደበቅ ነገር የለም፤ ሁለቱም ወገን ያለውን ሀቅ ያውቁታል፡፡ ልክ ነው፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የእስር ወሬ ቀንሷል፤ ዛቻና ማስፈራራቱ ግን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ እንዳለ ነው፡፡ የኢራኑ አሕመድ በተቀረው ሕይወቱ በሚወደው የጋዜጠኝነት ሙያ እንዳይሰራ ታግዷል፤ የጋዜጣ ፈቃድ የተከለከሉ ጋዜጠኞች በሀገራችን የሉም? አሕመድ ዘይዳባዲ የዩኔስኮን ሽልማት እንዲያገኝ ውሳኔውን ካስተላለፉት የ12 ሰዎች ቡድን አባላት ውስጥ ከ97 ምርጫ በኋላ ለእስር የተዳረገችውና የቀድሞ ምኒልክ ጋዜጣ አዘጋጅና አሳታሚ ሰርካለም ፋሲል አንዷ መሆኗን በማስታወስ እዚህ ላይ አበቃሁ፡፡

ዓመት ዓመት የድርሰን!

ይኼ በጣም ትልቅ ነጥብ ነው፡፡ ይህ ‹‹ሽንጥ ገትሮ ጥብቅና መቆም›› በትግሉ ወቅትም ነበር፡፡ ያን ጊዜ የአሰብ ጉዳይ ሲነሳ እንኳ ልዩነታችን የሁለት ሀገር ዜጎች የሆንን ያህል እስከመወዛገብ ያደረሰን ነበር፡፡ በምንም አግባብ አሰብ የኤርትራ እንዳልሆነች ይታወቃል፡፡ እነዚያ የሕወሓት አመራሮች ግን ይህን ሀሳብ የምናነሳውን ‹‹ትምክህተኞች ናቸው›› የሚል ቅስቀሳ ያካሂዱብን ነበር፡፡ ለነገሩ በቅስቀሳ ያቆመ ብቻ አልነበረም፡፡ ለምሳሌ ስብሃት ነጋ ‹‹በኤርትራ ነፃነት ላይ የሚቃወም ሳለ ከምንጠላው ሻዕቢያ ጎን ተሰልፈ እንዋጋዋለን›› ብሎ ነበር፡፡ ምን ማለት ነው? እስከዚህ ድረስ ወሰን የተሻገረ ተቆርቋሪነት ምንድነው? የሚል ጥያቄ ይፈጥራል፡፡ ...

...በቅርቡ ደግሞ ጠ/ሚ/ሩ ‹‹አሰና›› ለተባለው የኤርትራ መግስት ተቃዋሚ ራዲዮ በሰጡት ቃለ-ምልልስ፣ የድንበር ኮሚሽኑ ‹‹አንድም ቀን የኢትዮጵያ ሆነው የማያውቁ መሬቶችን ሰጥቶናል›› ሲሉ በታሪክ ሰነድ ላይ የሚመዘገብ ምስክርነት ሰጥተዋል፡፡ ይህ አባባል የተገለጸበትን ሥልት የሚገባው ይገባዋል፡፡ ሌላም ልጨምርልህ፡፡ ከኤርትራ ተሰደው በኢትዮጵያ የስደተኞች ካምፕ ያሉ 12ኛ ክፍልን ያጠናቀቁ የኤርትራ ተወላጆች ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡበት ነጥብ ከእኛዎቹ በጣም ዝቅ ባለ እንዲሆን ተደርጓል፡፡ ቅድሚያ የሚሰጠው ለዜጎች ነው ወይስ ለሌላ? ...በነገራችን ላይ፣ በትግሉ ወቅትም በርካታ የሕወሓት ሠራዊት አባላት ሻዕቢያን እንዲያግዙ ይላኩ ነበር ይባላል፡፡ እንዲያውም አንዱን ኦፕሬሽን አቶ አርከበ ዕቁባይ እንደመሩት አንድ ጽሑፍ ላይ አንብቤያለሁ፡፡ መጠኑን ያስታውሱታል?

65 ሺህ ያህል የሕወሓት ሠራዊት ሻዕቢያን ለማዳን ተሰልፏል

... ማለትም በተለያዩ ጊዜያት፡፡ ሁለት ሺህም፣ ሶስት ሺህም፣ ስድስት ሺህም እየተላከ ማለት ነው፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይም በወቅቱ ተቃውሞ ይቀርብ ነበር፡፡የአባይ ወንዝ ለኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫነት የመገደብ እንቅስቃሴ ተጀምሯል፡፡ የፓርቲያችሁ አቋም ምንድን ነው?

በፓርቲያችን ፕሮግራም ላይ በተፋሰሱ ዙርያ ያለንን አቋም በግልፅ አስቀምጠነዋል፡፡ አባይ ብቻ ሳይሆን ሌሎች ወንዞቻችን አጠቃቀም በስፋት ተዳሷል፡፡ ዝናብ ጠብቀን መኖር አንችልም፡፡ ስለዚህ አባይን የመገደቡ ሀሳብ ጥሩነት ምንም አያጠያይቅም፡፡ ብዙ ችግሮች መኖራቸውን መቀበል ግን ያስፈልጋል፡፡ የተጠላለፉ ችግሮች አሉበት፡፡ ሕዝቡን በጉዳዩ ላይ ሀሳቡን በነፃነት እንዲገልፅ መፍቀድ ግድ ይላል፡፡ ምሁራን በጉዳዩ ላይ መግባት አለባቸው፡፡ የተለያዩ አስተሳሰቦች መንሸራሸር አለባቸው፡፡ግን እርስዎም ቀደም ሲል እንደጠቀሱት፣ ገዢው ፓርቲ ቀርጾ ከሚያራምደው አስተሳሰብ የተለየ ሀሃሳብ ያላቸውን አይቀበልም የሚል ወቀሳ ይቀርብበታል፡፡

ኢሕአዴግ አንድም ቀን ዴሞክራት ሆኖ አያውቅም የምለውም ለዚህ ነው፡፡ የኢትዮጵያን ሕዝብ በሶስት መደብ ከፍሎታል፡፡ በኢሕአዴግ እምነት ‹‹ወዳጅ፣ ጠላት እና መሀል ሰፋሪ›› የሚባሉ መደቦች አሉ፡፡ ወዳጅ የሚባሉት ራሱ ጠፍጥፎ የሰራቸው፣ በራሱ ሳንባ የሚተነፍሱና ያለውን ሁሉ አሜን ብለው ተቀብለው የሚያስተጋቡለት ናቸው፡፡ የተለየ ሀሳብ የሚያቀርቡት ደግሞ ጠላት ይባላሉ፡፡ አንድን የሕዝብ ክፍል ጠላት ብለህ ከፈረጅከው ደግሞ የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ ምን እንደምታደርገው ይታወቃል፡

፡ ገለልተኛ አስተሳሰብ ያላቸውን ደግሞ መሀል ሰፋሪ ይላቸዋል፡፡ እነዚህ እንደሁኔታው እየታየ ብትር ሊሰነዘርባቸው የሚችሉ ናቸው፡፡ በ1969 ዓ.ም በሕወሓት ውስጥ ተከስቶ የነበረው ‹ሕንፊሽፊሽ› (ቀውስ) የተቋጨውም በዚሁ የተለየ ሀሳብን ያለማስተናገድ እምቢተኝነት ነበር፡፡ ...

... ዋና ዋናዎቹ ጥያቄዎቻችን የፖለቲካ ጥያቄዎች ነበሩ፡፡ በወቅቱ የኤርትራ ጉዳይ፣ ከኢትዮጵያ ድርጅቶች ጋር ተስማምተን ልንሰራ የምንችልባቸው አማራጮች፣ አመራሩ በሕገ-ደንቡ መሰረት መመረጥ አለበት የሚለው ጥያቄ (ቤተሰባዊነትና ወረዳዊነት ሰፍኖ ስለነበር)፣ የሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች መከበር ጉዳይና የመሳሰሉት ነበሩ፡፡ ያ ጥያቄ በመቅረቡ ግን ብዙዎች ታሰሩ፤ ተባረሩ፤ ሌሎች ደግሞ ትግሉን አቋርጠው ወጡ፡፡ ከነበረው ኃይል ከሶስት እጥፍ በላይ ተቀነሰ፡፡ እና ኢሕአዴግ ዛሬም ራሱን ከመፈተሽ ይልቅ እንደቀድሞው ቀጥሏል፡፡ ውይይት ያስፈልጋል፡፡ ከሕዝቡ እና ከምሁራኑ ጋር በአባይ ብቻ ሳይሆን በአሰብ ጉዳይም መወያየት አለበት፡፡ የአሰብን ወደብ በሕጋዊ መንገድ ማግኘት እየቻልን አጥተናል፡፡ በአገር አንድነት ጉዳይ ለራሳችን የሚበጀንን ትተን ከኤርትራና ከኤርትራውያን ጥቅም አንጻር የምናሰላው ለምንድነው? ይህ ሚዛኑን የሳተ ተቆርቋሪነት ማቆም አለበት፡፡ እንዴ ... መንግስቱ ኃ/ማርምን በአምባገነንነቱና በገዳይነቱ እናውቀዋለን፤ መቼም ግን በኢትዮጵያ አንድነት አይታማም፡፡እስኪ አሁንም ወደትግራይ ልመልስዎ፡፡ ከፖቲካዊ አንቅስቃሴዎች ውጭ በመሰረተ-ልማት ግንባታ በኩል ያለው ሁኔታ ምን ይመስላል?

በጣም አሳዛኝ ነው፡፡ ሕክምና ያለው ለስም ብቻ ነው፡፡ ብዙዎቹ ከተሞች ውሃ የላቸውም፡፡ ሽሬን ብታይ ላለፉት 20 ያህል ዓመታት በውሃ እጦት ቀውስ ውስጥ ነበረች፡፡ በመንገድ በኩል እንዲሁ በጣም አስከፊ ነው፡፡ ... እንዲያውም እኮ ባለፈው ዓመት የትግራይ ክልል ምርጫን ለመዘገብ መጥተህ በነበረበት ወቅት ስለታዘብከው የፃፍከውን ጽሑፍ ጋዜጣችሁ ላይ አንብቤዋለሁ፡፡ የሚባለውንና በተጨባጭ ያለውን እውነታ የሚገልፅ ጽሑፍ ነበር፡፡ ... እንግዲህ በዚህ ሁኔታ ነው ስለልማት ብዙ የሚባለው፡፡የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የሆኑት አቶ አባይ ወልዱ ከክልሉ ሕዝብ 64 በመቶ ያህሉ ከችግር የተላቀቀ ስለመሆኑ መግለፃቸውን በሚዲያ ተከታትዬ ነበር፡፡

እ...ህ (በረዥሙ፣ በቁጭት ከተነፈሱ በኋላ) 64 በመቶ የሚሉት ቀርቶ፣ ምነው 20 በመቶ እንኳ በተላቀቀና ደስ ባለን፡፡የኢፈርት ድርጅቶች አስተዋጽኦስ ምን ይመስላል? እነመሰቦ፣ መስፍን ኢንጂነሪንግ፣ ሱር ኮንስትራክሽን፣ ሜጋ፣ ጉና፣ አድዋ ጨርቃ ጨርቅ፣ ወዘተ በቢሊዮን የሚቆጠር ካፒታል

እንዳላቸው ይታወቃል፡፡ እንዲያውም ለክልሉ ልማት እጃቸውን በሰፊው ይዘረጋሉ ነው የሚባለው፡፡ ይስማሙበታል?

እውነቱን ልንገርህ? እስካሁን ለማኅበራዊ ልማት ያደረጉት አስተዋጽኦ ከ30 ሚሊዮን ብር አይበልጥም፡፡ እያንዳንዳቸው ግን ከ400 እስከ 800 ሚሊዮን ብር በዓመት ያተርፋሉ፡፡ መሰቦ አንድ ት/ቤት በ17 ሚሊዮን ብር አሰርቷል፡፡ ለአንድ የአካል ጉዳተኞች ተቋም 11 ሚሊዮን ብር ወጥቷል፡፡ መቀሌ ከተማ ውስጥ ለተሰሩት ኃውልቶች ደግሞ እንዲሁ የተወሰነ ወጥቷል፡፡ በተረፈ ግን ገንዘቡ የት ነው የሚሄደው የሚለው አጠያያቂ ነው፡፡ ሕዝቡ መነገጃ ከመሆን አላለፈም፡፡ ለጊዜው የአቀጣጠር መስፈርቱንና የተጠቃሚነታቸውን መጠን እንተወውና፣ በእርግጥ በየድርጅቶቹ ውስጥ ሰራተኞች ተቀጥረው የሚሰሩበት የሥራ ዕድል መኖሩ መልካም ነገር ነው፡፡ እውነታው መገለጥ አለበት፡፡ እንግዲህ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሕይወቱን እየገፋ ያለው በእንደዚህ መሰሉ አስከፊ መከራ ውስጥ ነው፡፡

‹‹የኤርትራን መንግስት...

ውይይት ያስፈልጋል፡፡ ከሕዝቡ እና ከምሁራኑ ጋር በአባይ ብቻ ሳይሆን በአሰብ

ጉዳይም መወያየት አለበት፡፡ የአሰብን ወደብ በሕጋዊ መንገድ ማግኘት እየቻልን

አጥተናል፡፡ በአገር አንድነት ጉዳይ ለራሳችን የሚበጀንን ትተን ከኤርትራና

ከኤርትራውያን ጥቅም አንጻር የምናሰላው ለምንድነው? ይህ ሚዛኑን የሳተ

ተቆርቋሪነት ማቆም አለበት፡፡ እንዴ ... መንግስቱ ኃ/ማርምን በአምባገነንነቱና

በገዳይነቱ እናውቀዋለን፤ መቼም ግን በኢትዮጵያ አንድነት አይታማም፡

Page 22: አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 166 ቅዳሜ ሚያዚያ 29 2003 ኢሕአዴግ … · ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ አውራምባ ታይምስ 4ኛ

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 166 ቅዳሜ ሚያዚያ 29 2003ስ ፖ ር ት22በአቤል ዓለማየሁ

ህይወት በየመን ምን ይመስላል? ወደዚያ ከተጓዝክ ምን ያህል ጊዜ ሆነህ?በየመን አራተኛ ዓመቴን ጀምሬያለሁ፡፡ እንደምታስታውሰው እዚያ እንደሄድኩ የአል ሂላል ቡድን አሰልጣኝ ነበርኩ፡፡ በዚያ ለአንድ ዓመት ያህል ከሰራሁበት ወቅት የሊጉ ሁለተኛ ሆነን በማጠናቀቃችን የእሲያ ሻምፒዮና ላይ ጥሩ ተወዳዳሪ ለመሆን ችለናል፡፡ የኦሎምፒክ ቡድኑን ለማሰልጠን ማስታወቂያ ሲወጣ ተወዳድሬ ስላለፍኩ ላለፉት ሦስት ዓመታት ማለት ይቻላል የኦሎምፒክ ብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ሆኜ እየሰራሁ ነው፡፡በእነዚህ ጊዜያት በውጤትም ሆነ በልማት ስራዎች ላይ ያስመዘገብካቸው ነገሮች ምንድን ናቸው?አብዛኛው ጊዜዬን ያተኮርኩት በልማት ስራዎች ላይ ነው፡፡ እዚህ አገር ውስጥ እያለሁ በህፃናት፣ አዳጊና ወጣቶች ላይ ስሰራ ያካበትኩት ልምድን ተጠቅሜ ማንዋል በማዘጋጀት በመላ አገሪቱ ለሚገኙ አሰልጣኞች በመስጠት ትልቅ ስራ ለመስራት ሞክረናል፡፡ በዚህ ስራ የተደሰቱት የፌዴሬሽኑ ኃላፊዎች ስራውን እንድሰራላቸው በየክልሉ ላሉ የፕሪምየር እና ብሔራዊ ሊግ አሰልጣኞች የማሻሻያ ኮርስዎችን እንድሰጥላቸው አድርገዋል፡፡ እኔንም የተለያዩ ኮርሶችን እንድወስድ ጃፓን [ሁለት ጊዜ]፣ ጆርዳንና ኩዌት ልከውኛል፡፡ ያለኝን የልምድ እና እውቀት መደርጀት የተመለከቱት የየመን እግር ኳስ ፌዴሬሽን ኃላፊዎች የፌዴሬሽኑ የቴክኒክ ዳይሬክተር ስላደረጉኝ ከኦሎምፒክ ቡድኑ አሰልጣኝነት ጋር ጎን ለጎን ኀላፊነቱን እወጣለሁ፡፡ በካፍ ያለህ ደረጃ የቱጋ ነው?የመን ሆኜ ካፍ ስለመደበኝ ከአብርሃም ተ/ሃይማኖት ጋር ቁጥራቸው አርባ ለሚሆኑ አሰልጣኞች ኢትዮጵያ ውስጥ ኮርስ ለመስጠት ችያለሁ፡፡ ያለኝ የካፍ ሲ ላይሰንስ ሲሆን አፕግሬድ ግን አድርጌዋለሁ፤ እያደረኩትም ነው፡፡ኢትዮጵያዊያን ኳስ አንከባላዮች ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ወደ የመን እያቀኑ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በአሁኑ ሰዓት ምን ያህል ተጨዋቾች እና አሰልጣኞች እዚያ አሉ?በተደጋጋሚ በተለያዩ ሚዲያዎች ላይ እንደገለፅኩት ኢትዮጵያዊያን ተጨዋቾች በየመን የሊጉ ውበቶች ናቸው፡፡ ያላቸው ክህሎት ሊጉን እያጣፈጠው ነው፡፡ በአሰልጣኝ ስዩም ከበደ የሚመራው የቲላ ቡድን በስድስት ነጥብ ልዩነት የሊጉ መሪ ሲሆኑ የቡድኑ አጥቂ ታፈሰ ተስፋዬ በከፍተኛ ጎል አግቢነት ይመራል፡፡ አማካይ ክፍሉን በጥሩ ሁኔታ የሚመራው ለሚ ኢታና ነው፡፡ እነዚህ ተጨዋቾች አገር ውስጥ መጥተው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን መደገፍ ይችላሉ፡፡ [ያነጋገርኩት አሰልጣኝ ኦኑራ ከመሰናበታቸው ስድስት ቀን በፊት ነው] የአል ስከር ተጨዋች የሆነው ዮርዳኖስ አባይ የረዥም ጊዜ የሊጉ ልምድ አለው፡፡ የክለቡ ጎል አግቢ ነው፡፡ ተስፋሁን የሚባል ኒያላ ከፕሮጀክት ጀምሮ ያሳደግነው ልጅ አለ የዋዳአ ሰንአ ተጨዋች ነው፡፡ ብርሃኑ ቃሲም [የቀድሞ የአዳማ ከነማ እና የኢትዮጵያ ቡና አጥቂ] ከዚህ የሄደው ከእኔ ጋር ሲሆን እስካሁን ድረስ የአል ሂላል ተጨዋች ነው፡፡ እሱም እንዲሁ ግብ በማግባቱ በኩል ጥሩ ነው፡፡ ያሬድ አበጀ አሁን ከተፈጠረው የፀጥታ ጉዳይ ጋር በተያያዘ አደጋ ቢደርስበት ኃላፊነት የሚወስድ አካል በመጥፋቱ ከሁለት ሳምንት በፊት ወደ አገር ቤት ተመልሷል፡፡ [ያነጋገርኩት በያዝነው ወር የመጀመሪያ ቀናት ነው፡፡] በአሰልጣኝነት በኩል ወርቅ ደርገባ፣ መርሻ ሚደቅሳ፣ ገ/መድኃን ኃይሌ፣ እኔና ስዩም ተሳትፈናል፡፡ ወርቁ፣ መርሻና ገ/መድኃን ወደ አገር ቤት ቢመለሱም እዚያ በነበሩ ጊዜ ጥሩ ነገር አሳይተዋል፡፡ ሌላው የመን ውስጥ ትልቅ ስምና ተወዳጅነት ያተረፈው አንዋር ያሲን በፊት ለተጫወተበት እና አሁን ሁለተኛ ዲቪዚዮን የሚወዳዳረው ሄርሞክ ክለብ አሰልጣኝ ነው፡፡ ወደ አንደኛ ዲቪዚዮን ለመመለስ ጫፍ ላይ ደርሷል፡፡ በክለቡ በጣም የሚከበርና የሚወደድ ተጨዋች ነው፡፡ ጥሩ ስራም እየሰራ ነው፡፡በየመን ያሉ ኢትዮጵያውያን ተጨዋቾች ወቅታዊ ብቃት ጥሩ ከሆነ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር ግንኙነት ተፈጥሮ ወደ እዚህ ሊመጡ ያልቻሉበት ምክንያት ምንድን ነው? በእኔ በኩል የመን ብቻ ሳይሆን አውሮፓ ውስጥ የማያቸውን ኢትዮጵያዊያን ተጨዋቾች ወደ አገራቸው መጥተው ለብሔራዊ ቡድን የሚጠቅሙበትን ሁኔታ እንዲፈጠር የሚደረገውን ለመፈፀም ዝግጁ ነኝ፡፡ ክፍተቱ

ያለው ወቅታዊ ሁኔታውን አስመልክቶ የመረጃ ልውውጥ አለመኖር ነው፡፡ አውሮፓ ውስጥ የሚጫወቱ ኢትዮጵያውያን ተጨዋቾች አግኝተሀል? ስዊድን ውስጥ አሉ፡፡ የሱፍ አለ፡፡ [ለሆላንድ ወጣት ቡድን ተጫውቷል፡፡ በ1993 ኢትዮጵያ በተሳተፈችበት የአርጀንቲናው የወጣቶች ዓለም ዋንጫ ላይ ኢትዮጵያን በተቃራኒ ከመግጠሙ

በላይ ጎል አስቆጥሯል] የአጥቂ ክፍላችን የሳሳ ስለሆነ ሳልሀዲንም መምጣት ነበረበት ብዬ አስባለሁ፡፡ ለሚቀጥሉት ጨዋታዎች በተለይ የመን ውስጥ ያሉትን በማስተባበሩ በኩል እኔ አለሁ፡፡ የአውሮፓ ውስጥ ያሉትንም በሂደት የምንሄድበት ይሆናል፡፡ የአገር ጉዳይ ስለሆነ የመስራቱ ግዴታ አለብኝ፡፡በቅርቡ በየመን የተፈጠረው ህዝባዊ አመፅ ቆይታችሁን ከባድ አያደርገውም? እኔ እስካለሁ ድረስ በየመን ያሉ ኢትዮጵያዊያን ህይወት የተረጋጋ ነው ማለት ይቻላል፡፡ እዚያ ያለው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከኢትዮጵያ ማህበረሰብ ጋር በመተባበር የዜጎቻችንን ህይወት በመጠበቅ ረገድ ሰፊ ስራ እየሰራ ነው፡፡ በየጊዜው ራሳቸውን እንዴት መጠበቅ እንዳለባቸው ትምህርቶች ይሰጣሉ፡፡ ወደ አገር ቤት ለሚመለሱም ከኢትዮጵያ መንግስት ጋራ በመተባበር በሰላማዊ ሁኔታ እየተመለሱ ናቸው፡፡ የኢትዮጵያ እና የየመን ግንኙነት ጥንታዊ በመሆኑ አንድ ቤተሰብ ናቸው፡፡የኢትዮ-የመን የወዳጅት ጨዋታን የማዘጋጀት ሀሳብ ከየመን እግር ኳስ ፌዴሬሽን መንጭቶ አንተም መልዕክቱን ይዘህ ወደ ኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን መጥተህ እንደነበር አስታውሳለሁ፡፡ ሀሳቡ ‹‹ሀሳብ ምን ደረሰ? ሁለቱ ብ/ቡድኖችን በየአመቱ የደርሶ መልስ ጨዋታ እንዲያደርጉ አሊያም በየዓመቱ በተራ በተራ እዚህ ወይም እዚያ የወዳጅነት ጨዋታ ማዘጋጀት ላይ መሰረት ያደረገ ሀሳብ ነበር፡፡ በውድድር ካለንደር አለመጣጣም ምክንያት [የየመን ሊግ እረፍት ሲሆን እዚህ ውድድር፤ እዚህ እረፍት ሲኮን እዚያ ውደድር እየሆነ ማለቱ ነው] እስካሁን አይደረግ እንጂ አሁንም የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት ሼህ አህመድ አሌህሲ ዓመታዊ ጨዋታው እንዲዘጋጅ ፍላጎታቸው ነው፡፡ እግር ኳስ ከኢኮኖሚ ደረጃ (የገንዘብ አቅም) ጋር የሚገናኝ ነው ይባላል፡፡ የየመን ኢኮኖሚያዊ አቅሟ የዳበረ የሚባል ባይሆንም መሻሻል ያሳየ ነው ይባላል፡፡ እግር ኳስዋ ግን በዓለም ደረጃ እድገት አላሳየም ለምን ይመስልሀል? እንዳልከው እግር ኳስ ከአቅም (ኢኮኖሚ) ጋር የሚያያዝ ነው፡፡ የየመን ኢኮኖሚ ከፍ እያለ የመጣው ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ነው፤ እግር ኳሱም እንደዚያው፡፡ በዓለም አቀፍ እግር ኳስ ተሳትፏቸው ታዳጊ እና ወጣት ላይ መስራት የጀመሩት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ቢሆንም ለውጥ አለ፡፡ አዳጊ ቡድኑ ፊንላንድ ላይ የዓለም ዋንጫ ተሳታፊ ነበር፡፡ አዳጊውም ሆነ ወጣት ቡድኑ በኤሺያ ሻምፒዮና ላይ ይሳተፋሉ፡፡ ባለፈው ዓመት ቻይና ላይ ወጣት ቡድኑ ተከፍሏል፡፡ ታዳጊ እና ወጣት ላይ ጥሩ እየሰሩ ስለሆነ እነዚያ ልጆች ሲደርሱላቸው ወደ ፊት ዋናው ብሔራዊ ቡድንን መጥቀም ይችላሉ ብዬ አስባለሁ፡፡ እኔ ራሱ በኦሎምፒክ ቡድኑ ውስጥ ከያዝኳቸው ተጨዋቾች ውስጥ 80 በመቶ የሚሆኑት ከስር ያደጉ ናቸው፡፡ ከዋናው ብ/ቡድን ያሉኝ ሁለት ተጨዋቾች ብቻ ናቸው፡፡ ምክንያቱም ብዙዎች አቅማቸውን እና ዕድሜያቸውን የጨረሱ ስለሆነ ነው፡፡ የመኖች ከአገራቸው ወጥቶ የሚጫወት ተጨዋች አላቸው?ኦማንና አቡዳቢ ውስጥ የሚጫወቱ ሁለት ተጨዋቾች አሏቸው፡፡

የየመን እግር ኳስ ከኢትዮጵያ በጣም የወረደ ነው ሲባል ይሰማል፡፡ ለዚህ እንደ ማረጋገጫ የሚሰጠውም ወደዚያ የሚጓዙት የጨዋታ ዘመናቸውን የጨረሱ ተጨዋቾች መሆናቸው ነው፡፡ የመጫወቻ ዕድሜያቸው ላይ ሆነው የሄዱትም ቢሆን ወደ ብ/ቡድን እና ወደ አገራችን ክለቦች ሲመለሱ አቋማቸው ወርዶ መታየቱ ነው፡፡ ማንም ተጨዋች የመን ቢጓዝ ይሳካለታል የሚሉም አሉ፡፡የየመን ሊግ ደካማ የሚባል አይደለም፤ ጠንካራ ነው፡፡ ከእኛ አገር ጋር ስናነፃፅረው ብዙም ልዩነት የለውም፡፡ ከሊጉ የወጡ ተጨዋቾች በታዳጊ እና በወጣቶች አህጉራዊ ውድድር ላይ እንድትካፈል አድርገዋታል፡፡ ብሔራዊ ቡድን ላይ እንደ ኢትዮጵያ ተመሳሳይ ችግር አለ፡፡ የሊጉ ደካማ መሆን ሁለቱም ብ/ቡድኖች ላይ ይንፀባረቃል፡፡ በልማት ስራዎች ላይ ግን የመን የተሻለ ስራ እየሰራች ነው፡፡ በተለይ የሙያተኞችን ብቃት ለማሻሻል ይጥራሉ፡፡ በወራት ልዩነት ኮርስ እንዲያገኙ ይደረጋል፡፡ የእስያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አባል አገር ብትሆንም ግንኙነቷን በማስፋት ከአፍሪካ፣ ከአውሮፓ ባለሙያዎችን እየጠራች ታሰራለች፡፡ የራሷን ሙያተኞችም ብቃት ታሻሽላለች፡፡ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ላይ የተሰጠው ትኩረት ሰፊ ነው፡፡ በፕሪምየር ሊጉ ላይ ያሉ ክለቦች ሁሉ ወደ ፕሮፌሽናሊዝም እየሄዱ ነው፡፡ ከአምስት ሺህ እስከ አስራ አምስት ሺህ የመያዝ አቅም ያለው ስታዲየም እንዲኖራቸው በእስያ አንደ አንድ መስፈርት ስለሚቀመጥ ያንን ሁሉም የፕሪምየር ሊጉ ክለቦች እየሰሩ ነው፡፡ የእነ ስዩም፣ የእነ ዮርዳኖስ ክለብ የራሳችሁ ስታዲየም አላቸው፡፡ የስምንት ቡድኖች ስታዲየም ደግሞ እያጠናቀቀ ነው፡፡ ‹‹ወደ የመን የሚሄዱት የጨረሱ ተጨዋቾች ናቸው›› ያልኩህን አልመለስክልኝም፡፡ እ…ይሄን ብዙ አልስማማበትም፡፡ ቀደም ባለው ጊዜያት ከዓለም ዙሪያ ወደ ኳታር፣ ዱባይ፣ ኩዌት፣ ጆርዳን፣ ኦማን፣ የመን የሚሄዱት የጨዋታ ዘመናቸውን ያገባደዱ ተጨዋቾች ናቸው፡፡ ጨርሰው እንኳን ቢሆን ለሊጉ የሚሰጡት ጥቅም ስለሚኖር ይፈለጋሉ፡፡ በየመንም ያው ተመሳሳይ ነው፡፡ የገንዘብ አቅምም አብሮ የሚሄድ ነው፡፡ ለምሳሌ ሙልጌታ ምህረትን [የደደቢት አምበል ነው] ለመውሰድ የጠየቁ ክለቦች ነበሩ፡፡ ነገር ግን ለተጨዋቹና ለደደቢት የሚከፈለው የዝውውር ክፍያ እጅግ በጣም ብዙ ነው፡፡ ለታፈሰ ለዝውውር ብቻ ከ300 ሺህ ብር በላይ ወጥቷል፡፡ ስለዚህ ብዙ ክለቦች ይህንን ያህል ከፍለው የማዘዋወር አቅም ስለማይኖራቸው የሚሄዱ የአገልግሎት ጊዜያቸውን ጨርሰው ግን አሁንም መጥቀም ወደሚችሉት ይሆናል፡፡ እነዚህም ቢሆኑ 20 በመቶ እንኳን አይሞሉም፡፡ ብርሃኑ፣ ዮርዳኖስ፣ ታፈሰ፣ ለሚ ወጣት ሆነው ሄደው እየሰሩ የሚገኙ ናቸው፡፡ [ረዥም ጊዜ ተጫውተው ከሄዱት ውስጥ አንዋር ያሲን፣ ጌታቸው ካሳ (ቡቡ)፣ አሸናፊ ግርማ፣ ባዩ ሙሉ፣ ያሬድ አበጀ፣ ሰለሞን ግርማ (ልምጭ) ይጠቀሳሉ፡፡]ቅድም ስለ የመን ሊግ ስትነግረኝ ‹‹ጠንካራ ነው ከኢትዮጵያ ብዙም ልዩነት የለውም›› ብለኸኛል፡፡ የኢትዮጵያ ሊግ ‹‹ጠንካራ›› ነው? [ሳቅ] እንደዚያ ማለቴ አይደለም፡፡ [እንደውም አሁን

ያለው ፉክክር ይሻላል] ጠንካራ ሊግ ስለሌላቸው ዋና ብሔራዊ ቡድናቸው በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለውን ውጤት ወደ ታች ጎትቶታል ማለቴ ነው፡፡ የመን ውስጥ ጫት እየቃሙ መጫወት አስገራሚ ነገር አይደለም ይባላል፡፡ ይህ ኢትዮጵያውያኑንም እንደሚጨምር ሰምቻለሁ፡፡ እንዲህ ሲባል ሰምቻለሁ፡፡ እስከማውቀው ድረስ የመን ያሉ ኢትዮጵያውያን ተጨዋቾች ለሊጉ አርዓያ የሚሆኑ ናቸው፡፡ ጫት መቃም በሰውነት አቋማቸውና በብቃታቸው ላይ የሚያሳድረውን ተፅዕኖ ስለሚያውቁ ከዚህ የፀዱ ናቸው፡፡ ለዚህም የናይጄሪያ፣ ካሜሮን፣ ግብፅ፣ ሱዳን፣ ኢራን ተጨዋቾች ያላሳኩትን በሊጉ ኮከብ ተጨዋች እና ኮከብ ጎል አግቢ መሆን ችለዋል፡፡ የወከሉት የኢትዮጵያን ስም ነውና እኛም የቅርብ ክትትል እና የምክር ስራዎች እናከናውናለን፡፡ የየመን ተጨዋቾች ልክ ነው ሁሉም ባይሆኑ ጫት ይቅማሉ፡፡ ይህንን በተለይ በብሔራዊ ቡድን ሲመረጡ በማስተማር እየለወጥነው ነው፡፡ የመቆጣጠሪያ ዘዴዎችንም እየዘረጋን ነው፡፡ [ከአዘጋጁ፡- አንድ ከየመን የመጣ ተጨዋች በአንድ ወቅት ይህን ጥያቄ አንስቼበት ‹‹እዚያ በግልፅ ስለሚደረግ ነው የጎላው እንጂ እዚህ አገርም እየቃሙ የሚጫወቱ ተጨዋቾች አሉ›› ብሎኛል፡፡ በእርግጥ የዚህ ጽሁፍ አዘጋጅም መረጃው አለው፡፡]በርካታ ኳስ አንከባላይ ኢትዮጵያውያን በፀጥታ ችግር እየተቋረጠ በሚጀመረው በየመን ሊግ ለመሳተፍ ባላቸው ፍላጎት ሳቢያ [ከሚገኘው ጥቅም አንፃር] በጥብቅ እየፈለጉህ ነበር፡፡ ትክክል ነኝ? በርካታ ተጨዋቾች ወደ የመን መጥተው ለመስራት ይፈልጋሉ፤ አሰልጣኞችም ጭምር፡፡ አቅም በፈቀደ መጠን ሳደርገው እንደነበረው የአገሬ ተጨዋቾችና አሰልጣኞች (የሙያ ጓደኞቼን) ለመርዳት አሁንም ዝግጁ ነኝ፡፡ አሁን ያለው የፀጥታ ሁኔታ ብዙም አስተማማኝ ስላልሆነ ሊጉ እንኳን እየተቋረጠ - ይጀመራል፡፡ ቪዛም ብዙ እየተሰጠ ስላልሆነ ሁሉም ክለቦች ከኢትዮጰያ ብቻ ሳይሆን በጎረቤት አገሮች እንኳን ተጨዋቾች እያስመጡ አይደለም፡፡ በዚህ ምክንያት በዚህ የውድድር ዓመት ብዙ ልረዳቸው ባልችልም እንዳልከው ብዙ ተጨዋቾች በጥብቅ እየፈለጉኝ ነበር፡፡ [ብዙ ተጨዋቾች ወደ የመን የተመለሰው አብርሃም ፈቃደኛ ከሆነ የመን ሄደው መጫወት እንደሚችሉ ስለሚያስቡ ደጋግመው ይደውሉለት ነበር፡፡ ተጨባጭ ሁኔታውን ቢነግራቸውም ሊረዱት እንዳልቻሉ ነግሮኛል፡፡ በዚህም ሳቢያ በተለይ ያልመዘገበው እና የማያውቀው ቁጥር ተንቀሳቃሽ ስልኩ ላይ ሲደወልበት እየተሳቀቀ ከማንሳት ይቆጠብ ነበር፡፡ አዳጊ፣ ወጣት እና ዋናው የኢትዮጵያ ብ/ቡድን ከየመን አቻው ጋር የወዳጅነት ጨዋታ ማድረግ ስለሚፈልጉ ይህን ለማሳካት እንደሚጥር ገልጿል፡፡ የመን የሴቶች ብ/ቡድን ባይኖራትም ጋናን አሸንፈው ወደ ግማሽ ፍጻሜው ለተቀላቀሉት የሴቶች የኦሎምፒክ ብ/ቡድን ከጆርዳን ጋር የወዳጅነት ጨዋታ እንዲያደርጉ ሁኔታዎችን ለማመቻቸት እንደሚጥር ገልጾልኛል፡፡]

አብርሃም መብራቱ [የየመን እግር ኳስ ፌዴሬሽን ቴክኒካል ዳይሬክተርና የኦሎምፒክ ብሔራዊ ቡድኑ ዋና አሰልጣኝ]

በሰሜን አፍሪካ የተነሳው ህዝባዊ አመፅ ከጎበኟቸው አገራት አንዷ የመን ነች፡፡ በዚያ ኳስ ለማንከባለል የሄዱ በርካታ ኢትዮጵያውያን ይገኛሉ፡፡ በርካቶችም ወደዚያው ማቅናት ይፈልጋሉ፡፡ የየመን እግር ኳስ ፌዴሬሽን ቴክኒካል ዳይሬክተርና የየመን ኦሎምፒክ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ የሆነው አመለ ሸጋው አብርሃም መብራቱ ለእረፍት አዲስ

አበባ በመጣበት ወቅት የአውራምባ ታይምስ የስፖርት ገፅ አዘጋጅ ላነሳቸው የመንን ማዕከል ላደረጉ እግር ኳሳዊ ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥቷል፡፡

ባለፈው እሁድ መነሻና መድረሻውን በሃዋሳ ኃይሌ ሪዞርት አድርጎ የተደረገው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በደማቅ ሁኔታ እንደተካሄደ በቦታው በመገኘት ለመታዘብ ችለናል፡፡ ‹‹ሁሉም›› በሚል መሪ ቃል በወሊድ ምክንያት የሚያጋጥምን የእናቶች እና ህፃናት ሞት ለመቀነስ ሀሳቦች የተንሸራሸሩበት ይህ መድረክ ህፃናት የተካፈሉበት የሁለት ኪሎ ሜትር፣

‹‹ኢትዮጵያዊያን ተጨዋቾች የየመን ሊግ ውበቶች ናቸው››

በርካቶች የተሳተፉበት የሰባት ኪሎ ሜትር እና የ21 ኪሎ ሜትር የክለብ አትሌቶች ውድድርን አካሂዷል፡፡ በርካታ ህዝብም እየተዝናና ተከታትሎታል፡፡

አዘጋጆቹ ‹‹ከ40 በላይ ዓለም አቀፍ ተሳታፊዎች ይገኛሉ›› ብለው የነበረ ሲሆን ከዚያም የላቀ በርካታ የውጪ አገር ዜጎች እንደነበሩ ተመልክተናል፡፡ ይህም የደቡቧን መዲና ለማስተዋወቅ ያለውን ሚና ከፍተኛነትን ያሳያል፡፡ የሀዋሳው ዝግጅት ታላቁ ሩጫ እስካሁን ያካሄዳቸውን ውድድሮች ቁጥር 64 አድርሶታል፡፡

‹‹ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ጠንካራ መሆናቸውን ስለ ማውቅ በማሸነፌ ተደንቄአለሁ›› በማለት የገለፀልን ኬንያዊው ኪሙታይ ኪፕሊሞ 63 ደቂቃ ከ10 ሰከንድ በመግባት አምና የአገሩ ልጅ ዊልሰን ቺቤት እንዳደረገው ሁሉ የግማሽ ማራቶን ሩጫ አሸናፊ ሆኗል፤ በሦስት ሰከንድ ሪከርድ በማሻሻል ጭምር፡፡ በጎዳና ላይ የሃዋሳ ህዝብ በጥሩ

ሁኔታ እንዳበረታታው የገለፀው ኩሙታይ ኪፕሊሞ ከኢትዮጵያዊው የምንግዜም የዓለም የረዥም ርቀቶች ንጉስ ኃይሌ ገ/ሥላሴ ጋር በእንግሊዝ እና በአሜሪካ ሁለት ጊዜ ጎን ለጎን መሮጥ በመቻሉ ‹‹ደስተኛ ነኝ›› ብሏል፡፡

ከኬኒያ ዋና ከተማ ናይሮቢ 50 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘው ኢልዶሬት ከተማ ወጣ ብሎ የሚኖረው እና የኬኒያ ብ/ቡድን አባል የሆነው አትሌቱ ባለፈው ሳምንት አርብ አዲስ አበባ ከገባ ጀምሮ በቆይታው በሁሉ ረገድ ደስተኝነት እንደተሰማው ገልጿል፡፡ ዲሹ ዲዳ እና ሰቦቃ ዲባባ ሁለተኛና ሦስተኛ ሆነዋል፡፡

በሴቶች አርሲ-በቆጂ የተወለደችው ሲሳይ ሜኤሶ 1፡16.41 በመግባት አሸናፊ ለመሆን ችላለች፡፡ በማራቶን እና በግማሽ ማራቶን ዓለም አቀፍ ውድድሮች ላይ የምትሳተፈው የኦሜድላዋ አትሌት ከብዙ ጥረት በኋላ ወደ ውጤት የመጣች አትሌት ነች፡፡ የዛሬ ወር ገደማ በግሪክ በማራቶን

64- አዲስ ሪከርድ- ተስፈኛ ሴት

አሸናፊ ነበረች፡፡ በሀዋሳው ውድድር ላይ ጠንካራ ፉክክር እንደገጠማትና ሙቀቱ አስቸግሯት እንደነበር አልሸሸገችም፡፡ በማራቶን 2፡35፣ ውስጥ የሮጠችው ተስፈኛዋ አትሌት በኦሎምፒክ እና በዓለም ዋንጫ አገሯን ወክላ የመሳተፍ ትልቅ ራዕይ እንዳላት ገልፃለች፡፡ ድንቅነሽ መካሳ እና እህቴ ብዙነህ ሁለተኛ እና ሦስተኛ ሆነዋል፡፡

አብርሃም መብራቱ የመን ያሉ ኢትዮጵያዊያን ተጨዋቾች የአገራቸውን

ብ/ቡድን የሚጠቅሙበትን ሁኔታ እንዲፈጠር እጥራለሁ ይላል፡፡

ኪሙታይ ኪፕሊሞ፡- ‹‹በማሸነፌ ተደንቄአለሁ››

ሲሳይ ሜኤሶ፡- ‹‹በኦሎምፒክ

እና ዓለም ዋንጫ

አገሬን መወከል

አልማለሁ››

Page 23: አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 166 ቅዳሜ ሚያዚያ 29 2003 ኢሕአዴግ … · ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ አውራምባ ታይምስ 4ኛ

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 166 ቅዳሜ ሚያዚያ 29 2003

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

23

}SdeK¨< Ÿ}c\ ð×” ¾h¨` ¨<H TVmÁ U`„‹ ÃÖ”kl ƒ¡¡K—¨<” ¾w^²=M

¾h¨` ¨<H TVmÁ ÃÖkS<

Brazmart International General Trading Plc. Address!- •Urail Alem Brehan Plaza 1st Floor #106 1. ›<^›?M u?} ¡`e+Á” ›”vu= ¯KU w`H” ýL³ 1— öp u=a lØ` 1062. Ku< ›Åvvà òƒ Kòƒ dS<›?M I”íuT”—¨<U ¾vD”vD“ ¾h¨` u?ƒ n ‹ SgÝ“ ”Ç=G<U u¾I”í SX]Á SÅwa‹ ÁÑ–< M::

c=Ѳ< ƒ¡¡K— ¾w^²=M U`ƒ SJ’<” Á[ÒÓÖ<! Tel. 251-11 552 -6011 /12 Fax 251-11-5526012

ከምሬት ብዛት ሊያስቀን የሚደርስ እውነታ እናያለን፡፡ አዲስ አበባ ውስጥ ተመሳሳይ የትምህርት ደረጃ ኖሯቸው በግልና በመንግስት ትምህርት ቤቶች የሚያስተምሩ ሁለት መምህራንን ብናነጻጽር፣ ይህንን እውነታ ማየት እንችላለን፡፡ ለነገሩ የግል መስሪያ ቤቶች ጉዳይ አሁንም ስግብግብ ነጋዴዎችን የሚመለከት ቢሆንም፣ ተቀጥረው የሚሰሩት ግን እንደዜጋም፣ እንደነጋዴም፣ እንደሰራተኛም ሊታሰብላቸው ይገባል፡፡

ከጠዋት ሁለት ሰዓት እስከ አስራ አንድ ሰዓት ድረስ እየሰሩ ወርሃዊ ደሞዛቸው አራትና ስምንት መቶ ብር የሆኑ የሰርተፊኬትና የዲፕሎማ መምህራን ብዙ ናቸው፡፡ ከእንግዲህ በየዘርፉ በየሙያው ዓይነት ተመልከቱ፡፡ በሀገራችን አገባባዊ ትርጉም ተምረው ስራ ላይ ተሰማርተዋል የተባሉ በርካታ ሰራተኞች በዚህ የደሞዝ ማዕቀፍ ውስጥ ናቸው፡፡

ታዲያ ነዳጅ በጨመረ ቁጥር እየተሳቀቁ፣ አርባ ስምንት ብር የገዟትን አንድ ሊትር ዘይት ድረሽ ድረሽ ብለው፣ አንድ ሊትር ነጭ ጋዝ አስራ አራት ብር ገዝተው፣ አንድ ደረቅ እንጀራ ሁለት ብር ከሃምሳ ገዝተው ኑሮን የሚኖሩ እነዚህ ዜጎች ናቸው፡፡ ለመሆኑ ማን ልብ እያላቸው፣ ማን እያሰባቸው ይሆን;

ሶስት፡- መንገስትም ቢሆን ያደርጋል ተብሎ ይጠበቅ ከነበረው የደሞዝ ጭማሪ በታች እንደ ጨመረ ብዙዎች ይስማማሉ፡፡ በሰላሳና አርባ ፐርሰንት ብቻ የሚወሰን ጭማሪ ያደርጋል ብሎ ላለመገመት ታላቁ መነሻ መንግስት ቀድሞ ይሰጣቸው የነበሩ የሚያጓጉ መግለጫዎች ነበሩ፡፡

የሆነው ሆኖ፣ ሀገራችን ይህን በመሰለ የወል እውነታ ውስጥ እንዳለች እየታወቀ፣ የኑሮ ውድነት ከእለት እለት ሲባባስ፣ አሁንም መፍሄ እየተባሉ የሚወሰዱ እርምጃወች ችግር ሲያባብሱ እንጅ ሲያሻሽሉ እያየን አይደለም፡፡

የተነሳሁበት የዋጋ ተመንና የሸቀጥ መጥፋት ለዚህ ታላቁ ማሳያ ነው፡፡ መንግስት በበቂ ጥናትና ሥነ-ዘዴ ላይ ሳይመረኮዝ በስሜት በመነሳት ብቻ (ይመስላል) የዋጋ ተመን አወጣ፡፡ አንዳንዶቹ ተመኖች ሳምንት ሳይሞላቸው እንደገና እንደታዩ የሚታወስ ነው፡፡

ቀጥሎም ሆዳም ነጋዴዎች ምን ሊያደርጉ ይችላሉ ተብሎ የተደረገ ቅድመ-

ዝግጅ ስላልነበረ፣ የለም የሚባል ነገር ሲበዛ ስር-ነቀል ያልሆኑ የተውተፈተፉ እርምጃዎች መወሰድ ጀመሩ፡፡ አንደኛው ክፍለ ከተማ ሱቆችን አሸግሁ ሲል፣ ሌላኛው ክፍለ ከተማ ውስጥ አንድ ሊትር ዘይት በአርባ ስምንት ብር ይቸረቸራል፡፡

ነገሩ ሊበቃን የሚገባው ከሃምሳ ፐርሰንት በላይ የሆነውን የንግድ እንቅስቃሴ ሰላሳ የማይሞሉ ግለሰቦች እንደ ተቆጣጠሩት በሰማን ጊዜ ነበር፡፡ ኢትዮጵያን ያክል ሀገር፣ ሰማኒያ ሚሊዮንን ያክል ሕዝብ የሚያዳርስን የንግድ እንቅስቃሴ ሰላሳ በማይሞሉ ሰዎች እጅ ነበር፡፡ እነሆ ያለከልካይ፣ ያለ ሃይ ባይ ስንበዘበዝ ኖርን፡፡

በነገራችን ላይ፣ መንግስት በቂ ጥናት አካሂዶ ወደ እርምጃ ገብቶ ቢሆን ኖሮ፣ ይህ መልካም ጎን በሆነ ነበር፡፡ ሰላሳ የማይሞሉ ሰዎችን ተቆጣጥሮ ገበያውን ማስተካከል ሲቻል፣ ለመቆጣጠር የሚያስቸግሩ እልፍ የችርቻሮ ሱቆች ላይ ቀዳሚው የዋጋ ተመን ወደቀ፡፡ በኅብረት ሥራ ሱቆችና መንግስት መቸርቸሪያና ማከፋፈያ ብሎ ባስቀመጣቸው ሱቆች በር ላይ ከጠዋቱ አንድ ሰዓት ላይ ረዥም ሰልፍ ማየት የተለመደ ሆኗል፡፡ ለዚያውም መታወቂያ እየተጠየቀ ለመግዛት፡፡

እኔ የምለው፣ አንድ ኢትዮጵያዊ በገዛ ሀገሩ ላይ እንዴት በነጻነት መገበያየት ይቸገራል; መታወቂያ ካልያዝክ ዞር በል የሚባለውስ ስለምንድን ነው; የቦሌ ነዋሪ ቂርቆስ ሄዶ መግዛት ካልቻለ፣ የጉለሌ ነዋሪ መርካቶ ገብቶ መግዛት ካልቻለ፣ እንደምን ያለ የገበያ ሥርዓት እየገነባን ነው;

መንግስት በተለያየ መግለጫ ላይ በቂ የሸቀጥ ክምችት እንዳለ ይናገራል፡፡ በተለይ የዘይትና የስኳር፡፡ ስለዚህ መታወቂያ እየጠየቁ (እያጉላሉ) የመገበያየቱ ጥቅም ምንድን ነው; በዚህ ሂደትስ እስከመቼ ድረስ ነው መጓዝ የምንችለው; ለነገሩ እኮ መንግስት በተመናቸው ሸቀጦች ብቻ ሳይሆን፣ በሌሎችም ነገሮች ላይ የዋጋ ንረት እየተባባሰ እንጅ እየቀነሰ አልመጣም፡፡ ይህ ደግሞ ከትንሹ ጫማ ማስጠረግ ጀምሮ እስከ መጨረሻው ትልቅ ነገር ከእጥፍ በላይ ያልጨመረ ነገር የለም፡፡

እውነት ነጋዴዎች ከተገቢው በላይ እየጠየቁ፣ ያለአግባብ እየከበሩ ከሆነ፣ አስፈላጊው ጥናት እየተካሄደ

እርምጃ ይወሰድ፡፡ ነገር ግን ሆይ ሆይታችን የአንድ ሰሞን እየሆነ ተቸገርን፡፡ በዚህ ዓመት የመጡት ሰሞነኛ ጉዳዮች ሚዲያው መንግስት ሕዝቡ የሚያስባቸው የሚያወራቸው ነገሮች በርካታ ናቸው፡፡ ይህም የዋጋ ማረጋጋትና የዋጋ ተመን የአንድ ሰሞን ወሬ ከመሆን አላለፈም፡፡ እንዴት ቢሉ፣ አሁን ሚዲያውም መንግስትም መናገር የሚፈልጉትና የሚችሉት ስለአባይ ግድብ ብቻ ነው፡፡

የዋጋ ተመን ሲያወጣ የነበርና እስከ መጨረሻው ተከታትዬ ሸማቹን ከበደል እታደጋለሁ ሲል የነበረ የመንግስት አካል ዛሬ ከወዴት ጠፋ፡፡ መቸም መንግስት የአባይን ጉዳይ የሚያስተባብር አንድ አካል ሳይሰይም አይቀርም፡፡ ይህኛው አካል የተሰየመበትን ስራ ይስራ፡፡ የዋጋ ተመንን አስከብራለሁ ያለም ያስከብር፡፡

ለነገሩ በዚች ሀገር በዚህ ጊዜ የተሰጠውን ኃላፊነት ቀን ከሌሊት የማይዘነጋ ቢኖር የተቃዋሚ ፓርቲዎችን ትንፋሽ እየተከታተለ አስፈላጊውን ሁሉ እንዲያደርግ የተሰየመ አካል ብቻ ነው፡፡ ሀገር ውስጥ ያሉም ይሁኑ ውጭ ሀገር ያሉ ተቃዋሚ ግለሰቦችና ፓርቲዎች የሰሩት ብቻ ሳይሆን የተናገሩት፣ አንዲያም ሲል ያሰቡት ይደረስበትና ወዲያውኑ አስፈላጊ ነው ያሉትን እርምጃ ይወስዱባቸዋል፡፡ የመልስ ምቱ መግለጫ ከመስጠት እስከ በምክር ቤት ማስፈራራትና መኮነን ይደርሳል፡፡

ዋጋ ማረጋጋትን በኃላፊነት የወሰደ ወይም የተቀበለ አካል ግን አንድ ሰሞን ፋታ የሚነሳ ዜናና መግለጫ ሰጠ፡፡ ድሃውን ከቀማኛ ነጋዴ ጋር አጋፍጦ ዝም አለ፡፡ እንግዲህ ድሆች ምን ይዋጠን; እንዲሁ ሳስበው ተቃዋሚ ፓርቲን እንጅ ተቃዋሚ ነጋዴን የሚቆጣጠር፣ የሚገዛ ያለ አይመስለኝም፡፡

እንደመውጫልተወው ልተወው ኑሮዬን

ልተወውከንቱ መጨነቄ ሲቀር ለሚቀረው

ዐይኔም ይፍሰስ ይጥፋ ከቶ ይቅርብኝ

መጥፎ ማዬት እንጅ ምን አተረፈልኝ

ጆሮየም ይደፈን ይቅር ልደንቁርለምንም አይረባኝ መጥፎ ከማዳመጥ ከክፋት በቀር

(ዮናስ አድማሱ 1956)

ጥያቄ አቅርበን ነበር፡፡ ሰላማዊ ሰልፍ እስከ መውጣት ደርሳችሁበታል የሚባለው ነው?አዎ! ያኔ ‹‹የአድማ መሪ ነሽ›› ተብዬ ለአራት ወር ወህኒ ቤት (ከርቸሌ) ታስሬያለሁ፡፡ በወቅቱ አቶ ፀጋዬ ገ/መድኅን (ሎሬት) በኪነ-ጥበበ ሙያው ያስፈልገናል ብለን አስመጣነው፡፡ በሠራተኛው መሀል ግን መከፋፈል ተከሰተ፡፡ ለፈለገው ሰው ደሞዝ ይጨምራል፣ ደስ ያላለውን ይተወዋል፣ የፈለገውን በዘበኛ የማባረር ነገር ነበር፡፡ ሰልፍ ወጥተን በጥይት የሞተብን ሰው ነበር፡፡ በዚያን ሰዓት እኔ በድፍረት እሳተፍ ነበር፡፡ ‹‹የአድማ መሪ›› በሚል ታድኜ ከሰልፉ ከአንድ ሳምንት በኋላ ከቤቴ ስያዝ የነበረኝን ደስታ አትጠይቀኝ፡፡ [ሳቅ ብላ በደስታ ስሜት ውስጥ ሆና] ወቅቱ 1969 ዓ.ም መጨረሻ አካባቢ ይመስለኛል፡፡ እነ ጌታቸው ደባልቄ፣ ወጋየሁ ንጋቱ ሁሉ ታስረው ነበር፤ አራተኛ ክፍለ ጦር፡፡ እኔን ግን በአጃቢ ይዘው ወስደው ወህኒ ቤት አሰሩኝ፡፡ የንጉሳዊ ቤተሰብ ሴት እስረኞች የነበሩበት ወቅት ነበር፡፡ በኋላ ግን ‹‹መታሰራችሁ በስህተት ነው፣ ጥያቄያችሁ አልገባንም ነበር›› ተብለን ይቅርታ ተጠይቀን ተፈታን፡

፡ የአራት ወር ደሞዛችንን ግን አልሰጡንም፡፡ ‹‹ይኼ አንዴ ገቢ ሆኗል፤ ወደፊት እንክሳችኋለን›› አሉን፡፡ በሂደት ጥያቄያችን መልስ አገኘ፤ ቋሚ ሠራተኛ ሆንን፤ ጡረታ ተከበረልን፤ የግማሽ ክፍያ የህክምና አገልግሎትም አገኘን፡፡ በዚህ ሥራዬም በጣም እደሰታለሁ፡፡ በማጣትሽ የሚቆጭሽ ነገር? እግዚአብሔር ይመስገን ምንም የሚቆጨኝ ነገር የለም፡፡ የሰው ልጅ ከተፈጠረ ራሱን መተካት ያለ ነገር ነው፡፡ ራሴን ተክቻለሁ፡፡ በተረፈ ቲያትር እና ፊልም ህይወቴ እስካለ ድረስ ካስት ካደረጉኝ እሰራለሁ፡፡ በሙያሽ በገንዘብ ተጠቃሚ ሆነሻል? በገንዘብ አልተጠቀምኩም፡፡ ይህ ታዲያ ቁጭት አይፈጥርብሽም? ምንም አይደለም፡፡ አምላክ በፈቀደ ነው የሚሆነው፡፡ ገንዘብ ይጠቅማል ግን ካልሆነ ምንም ማለት አይደለም፡፡ ለእለት መብላቴን፣ መጠጣቴንና ጤና መሆኔን እንጂ ገንዘብ መጣ - ቀረ ብዬ አልጨነቅም፡፡ እንደ ሌሎች አርቲስቶች መኪና የለኝም፡፡ G+2 ቤት ባልሰራም የራሴ በቂ ቤት አለኝ፡፡ ልዝናና ባልልም ተቸግሬ አላውቅም፡፡ ባለኝ

ነገር እግዚአብሔርን አመስግኜ እኖራለሁ፡፡ እስከ ዛሬ ስንት ባሎች አግብተሻል? ኡውው... እንደዚህ ዓይነት ጥያቄ አይጠየቅም፡፡ እንዴ! አበዛኸው፡፡ [ሳቅ በሳቅ] የመጀመሪያ ባለቤቴን አገባሁ፤ አንድ ልጅ ወለድን ሰባት ዓመት ከቆየን በኋላ አልተስማማንም ተለያየን፡፡ ከዚያ በኋላ አሁን ካለው ባለቤቴ ጋር ረዥም ጊዜ ቆይተናል፤ ሁለት ወልደናልም፡፡

ዛሬ የሚከበር በዓል አለ፡፡ [ያነጋገርኳት ከትላንት በስቲያ፣ ሚያዚያ 27 ቀን ነው] ለምን የሚከበር ይመስልሻል? ሚያዚያ 27 የሚከበረው ለምን ነበር ‘ባክህ? እንዴ! ምን ሆኜ ነው ግን? [ግራ ተጋብታ ቀኝ እጇን አፏ ላይ አደረገች] የአድዋ ድል ነው? የአድዋ ድል መታሰቢያማ የሚከበረው የካቲት 23 ነው፡፡ አ...የካቲት 23 ነው፡፡ ወይኔ ጉዴ! እኔ እንጃ ጠፋብኝ፡፡ አየህ አረጀሁ፣ ረሳሁት፡፡ [ፋሽስት ኢጣልያ ከ1928-1933 ለአምስት ዓመት ኢትዮጵያን የመቆጣጠር ሙከራው በኋላ ዳግም ድል የተመታበት የአርበኞች የድል በዓል መታሰቢያ ነው፡፡ ዘንድሮ ለ70ኛ ጊዜ ተከብሯል፡፡]

“የአድማ መሪ ነሽ...

ተቃዋሚ ፓርቲን እንጅ ...

ሰው ክው አልኩ፡፡ጎዳና ነው የምኖረው፡፡

ብርዱን ካለ አረቄ አልቋቋመውም፡፡ እንዴት ጎዳና ላይ ሆኜ መድኃኒትና አረቄ አብሬ እወስዳለሁ ብዬ አነባባሁበት፡፡ ከዶክተሩ ቢሮ በግድ ተጎትቼ እያነባሁ፣ የታዘዘልኝን መድኃኒት አስታቅፈው ከግቢው አስወጥተው ሸኙኝ፡፡

ሐኪሙ፤ የተፃፈልኝ የሪፈራል ተመላላሽ ሕክምና እንጂ ለአልጋ እንዳልሆነ፤ ሌላ ወረቀት ከቀበሌ እንዳመጣና ለዛውም ሳልጠጣ ከመጣሁ አንደሆነ የሚያናግረኝ ያስጠነቀቀኝን እያሰብኩ ዞረብኝ፡፡ እንደምንም እግሬን እየጎተትኩ የጎዳና ጥጌ ጋር ደረስኩ፡፡

በባዶ ሆዴ የሰጡኝን ቫይታሚን በጭላጭ አረቄዬ ተጉመጥምጬ፣ ተሸፋፍኜ ተኛሁ፡፡ እግሬ አልንቀሳቀስ ሲለኝ አስታውሳለሁ፡፡ እግሬ ከአእምሮዬ መልዕክት መቀበል ያቆመ መሰለኝ፡፡

በውድቅት ሌሊት ጠዋት የሸኘኝ ጓደኛዬ፣ ‹‹ጩ! ጩ! ቀጮ ... ›› ሲቀሰቅሰኝ በሰመመን ውሃ እንዲያቀብለኝ ለመንኩት፡፡ ምግብ ገዝቶ አበላኝ፡፡ ሚሪንዳ አጠጣኝ፡፡ (የድሮ ማንነቴን እያሰበ እንባው ሲንቆረዘዝ አያለሁ፡፡ ብዙ የመናገር አቅሙ ከየት ይምጣ!)

‹‹ጠዋት እኔ እቀሰቅስሻለሁ - ለጥ በይ›› ብሎ አጽናንቶኝ ትቶኝ ሄደ፡፡ አራት ቫይታሚንና አራት የእንቅልፍ ኪኒን ዋጥኩና ተሸፋፍኜ ለጥ አልኩ፡፡

. . .ጠዋት ስነቃ በእልህ

ነቃሁ፡፡ ቀጥታ ቀበሌ ሄጄ፣ ዶክተሩ የጠየቀኝን ወረቀት አስፃፍኩ፡፡ ወረቀቱን ይዤ ጓደኛዬ ቤት ሄድኩና አማኑኤል ልተኛ እንደሆነ ነግሬያት ገላዬን ታጥቤ፣ የምቀይረው ልብስ ሰጥታኝ ቀይሬ፣ ፀጉሬን ጎንጉኜ ቆንጆ ልጅ

ሆኜ አመስግኘ ስሰናበታት የታክሲ ወረደችልኝ፡፡

ምሽቱን በጀንትል ሙድ አረቄዬን ልጠጣ አሰብኩ፡፡ በውስጤ፣ ‹‹ለዛሬ ልጠጣህ’ንጂ ከነገ በኋላ መገላገያህን አገኛለሁ›› እያልኩ ልቤ የደስታ ከበሮ እየደለቀ አመሸሁ፡፡ በጣም ሳልሰክር ወጥቼ እህቴ ቤት ሄድኩ፡፡ ልክ እንደ እንግዳ ዘው ብዬ ቤቷ ገብቼ አደርኩና በጠዋት ወደ አማኑኤል አመራሁ፡፡ ጥርሴን ሳይቀር ቦርሼ ፏ ብያለሁ፡፡

ዶክተሩ ሲያየኝ ተገረመም፤ ተደሰተም፡፡

በሆስፒታሉ አልጋ ተሰጥቶኝ እንድተኛ ቀንደኛ ተባባሪ ሆነኝና ሁሉን ሂደት ጨርሼ የሚፈርም ዋስ ያስፈልጋል ተባልኩ፡፡

ምንም ዘመድ - ማንም አንደሌለኝ ስናገር ሰሚ አጣሁ፡፡ እዬዬዬን አቀለጥኩት፡፡ ጭራሽ በግቢው ያሉት ሰዎች እንኳን ሊያዝኑልኝ ፈሩኝ፡፡ ሆስፒታሉ ፊት ለፊት ካለው አረቄ ቤት ገብቼ ለግቼ - ለግቼ ወደ ሆስፒታሉ ተመልሼ ስድብና እርግማኔን አቀልጠው ያዝኩ፡፡

ሰው በሀገሩ፣ በዜግነቱ ብቻን’ኳ ሕክምና አያገኝም? ዘመድ፣ አዝማድ፣ ወገን፣ ገንዘብ የሌለው መሞት አለበት? እያልኩ ሳብድ፣ የሆስፒታሉ የመዝገብ ቤት ሠራተኛ ቢሮው ይዞኝ ገባና አዋርቶኝ የእንጀራ እናቴን ስልክ አስታውሼ ሰጠሁት፡፡

የእንጀራ እናቴም አልተገኘችም፡፡

አምርሬ ሳለቅስ ራሱ ዋስ ሆነኝ፡፡ ሁሉንም ጉዳይ ራሱ ገደለልኝ፡፡ ነርሷ ሳሙናና ፒጃማ ሰጥታ ወደ ሻወር ክፍሉ ስታስገባን አይቶ በጣም አመስግኜው ተለያየን፡፡

ከሻወር ስወጣ ለብሼ የመጣሁትን ልብስ ለነርሷ አስረክቤ፤ በተሰጠኝ አልጋ ላይ

ጥቅልል ብዬ ተኛሁ፡፡ ከአማኑኤል ጓደኞቼ ጋር እንዲህ ተገናኘሁ፡፡

. . .ከእንቅልፌ ስነቃ

አይኔም፣ አእምሮዬም ተከፍቷል፡፡ ያለሁበትን ሆስፒታል አሰላሰልኩ፡፡ ተነስቼ በክፍሉ ውስጥ ያሉትን ሕመምተኞች ተዋወኳቸው፡፡ እነሱ ክፍል ከመግባቴ በፊት ምን ስሆን፣ እንዴት ሲያደርገኝ እንደነበር ነገሩኝ፡፡ የነገሩኝን የራሴን ሁኔታ እንደ ቀልድ አሳስቄ አለፍነው፡፡

አልጋዬ ላይ ቁጭ ብዬ በክፍሌ ያሉት የአእምሮ በሽተኞች እሚሆኑትና እሚያደርጉትን እንደፊልም እያየሁ፣ ራሴን ከየአንዳንዳቸው ጋር እያነጻጸርኩ በሀሳብ ስናውዝ ዋልኩ፡፡

ወደ አስር ሰዓት ግድም ግቢውን ልጎበኘው ብዬ ከሴቶች ዋርድ ወጣሁ፡፡ በዓይን የማውቃቸው ሁለት ወመኔዎች ‹‹ድምቅ›› ብለዋል፡፡ አመጣጤንና አገባቤን ተወራራንና በዛው መጦዝ እንደምፈልግ ጠቆምኳቸው፡፡ መላ መኖሩን ነገሩኝ፡፡ የዛሬን ብቻ ቅበሩኝ ብዬ ለመንኩዋቸው፡፡

‹‹ፍራንክ አለሽ?›› አለኝ አንዱ፡፡

ሁለት ብር አቀበልኩት፡፡

‹‹እኛ ተጠቁረናል፡፡ ከ’ኛ ጋር እንዳትታይ፡፡ ጠብቂን፤ ምልክት ስንሰጥሽ ትከተይናለሽ›› አሉኝ፡፡

አንዱ ሮጦ ዋርድ (መኝታ ክፍሉ) ደርሶ መጣ እና ጠቅሰውኝ ወደ ክበብ አመሩ፡፡ ተከተልኳቸው፡፡

በጥንቃቄ እንድጠቀም አስጠነቀቁኝ፡፡ ፍራንክ ካለኝም ሊያቀብሉኝ ተስማማን፡፡ወዲያው ከነሱ ዞር ብዬ ሀሺሼን ነፋሁ፡፡ ደስ አለኝ፡፡ መነጽሬም ተቀየረ፡፡ የአማኑኤል ኑሮዬም ሀ ብሎ ተጀመረ፡፡

(ይቀጥላል)

አማኑኤል . . .

Page 24: አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 166 ቅዳሜ ሚያዚያ 29 2003 ኢሕአዴግ … · ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ አውራምባ ታይምስ 4ኛ

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 166 ቅዳሜ ሚያዚያ 29 200324 ማ ስ ታ ወ ቂ ያብርሃ

ንና ሰ

ላም ማ

ተሚያ ድ

ርጅት