16
ገጽ 4 በውስጥ ገጾች ገጽ 11 ሰኞ ብዕራችን ለኢትዮጵያ ህዳሴ ይተጋል! ከ 27 ዓመታት ... ወደ ገጽ 4 ዞሯል 80ኛ ዓመት ቁጥር 144 ጥር 24 ቀን 2013 ዓ.ም ዋጋ 10.00 ማህሌት አብዱል አዲስ አበባ ፦ በ27 ዓመታት የልማት ዘፈንና ፉከራ በኋላ የትግራይ ህዝብ በችግር ላይ ወድቆ መገኘቱ አሳፋሪ እንደሆነ የኢሳት ሥራ አስኪያጅ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ አመለከቱ ። ለተፈጠረው ችግር ተጠያቂው ክልል ሲመራ የነበረው የህውሓት ቡድን መሆኑን አስታወቁ። አቶ አንዳርጋቸው በወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታዎች ዙሪያ በተለይ ከአዲስ ዘመን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ ከ27 ዓመታት ዘፈንና ፉከራ በኋላ የትግራይ ህዝብ በምግብ እህል እንኳን ራሱን ባልቻለበት ሁኔታ የምግብ እርዳታ ተቀባይ ሆኖ ማየት እጅግ አሳፋሪ ነው። ክስተቱ ቡድኑ 27 ዓመታት በሙሉ በበላይነት ኢትዮጵያን በገዛበትና ባስተዳደረበት ወቅት ማንኛውንም ነገር ያደረገው ለራሱ ጥቅም እንደሆነ የትግራይ ህዝብ ከተጨባጭ የዛሬ ህይወቱ እንዲያስተውል እድል እንደሰጠው አስታውቀዋል። ቡድኑ በመላው አገሪቱ የዘረፈውን ሀብት በጣም ጥቂት ለሆኑ የራሱ የቅርብ ሰዎች ብቻ መጠቀሚያ አድርጎት እንደነበር አሁን ያለው ሁኔታ በገሃድ አሳይቷል ያሉት አቶ አንዳርጋቸው ፣ ሲፈጽሙት የነበረው ወንጀልም ከትግራይ ህዝብ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንዳልነበረው ማየት እንዳስቻለ ገልጸዋል ። የትግራይ ህዝብ እንደ 27 ዓመቱ የልማት ዘፈንና ፋከራ ቀርቶ ሌሎች የሀገሪቱ ህዝቦች ያገኙትን የፖለቲካ ነፃነት የተነፈገ ነው ። ህዝቡ ይህንን ጠንቅቆ ያውቀዋል ያሉት አቶ አንዳርጋቸው ይህም ቡድን የሚመራበት " ከ 27 ዓመታት የልማት ዘፈንና ፉከራ በኋላ የትግራይ ህዝብ በችግር ላይ ወድቆ መገኘቱ አሳፋሪ ነው" - አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ የኢሳት ሥራ አስኪያጅ አጥፍቶ ጠፊው ትህነግ/ህወሓት/ (1967 -2013 ዓ.ም) “አገራዊ እሴት፣ አገራዊ ጀግና እና አገራዊ ታሪክ ሳይኖር አገር ወዳድ ትውልድ ሊኖር አይችልም” - ዶክተር አልማው ክፍሌ የታሪክና የህግ መምህር ፎቶ -በገባቦ ገብሬ "የህወሓት ፖሊሲዎች የኢትዮጵያን ፖለቲካ እና ኢኮኖሚ ምስቅልቅል ውስጥ የከተቱ ነበሩ" - ጊታ ፓሲ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ገጽ 12

ሰኞ ከ 27 ዓመታት የልማት ዘፈንና ፉከራ በኋላ ... · 2021. 2. 1. · ገጽ 4 በውስጥ ገጾች ገጽ 11 ሰኞ ብዕራችን ለኢትዮጵያ

  • Upload
    others

  • View
    7

  • Download
    0

Embed Size (px)

Citation preview

Page 1: ሰኞ ከ 27 ዓመታት የልማት ዘፈንና ፉከራ በኋላ ... · 2021. 2. 1. · ገጽ 4 በውስጥ ገጾች ገጽ 11 ሰኞ ብዕራችን ለኢትዮጵያ

ገጽ 4

በውስጥ

ገጾች

ገጽ 11

ሰኞ ብዕራችን ለኢትዮጵያ ህዳሴ ይተጋል!

“ ከ 27 ዓመታት ... ወደ ገጽ 4 ዞሯል

80ኛ ዓመት ቁጥር 144 ጥር 24 ቀን 2013 ዓ.ም ዋጋ 10.00

ማህሌት አብዱል

አዲስ አበባ ፦ በ27 ዓመታት የልማት ዘፈንና ፉከራ በኋላ የትግራይ ህዝብ በችግር ላይ ወድቆ መገኘቱ አሳፋሪ እንደሆነ የኢሳት ሥራ አስኪያጅ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ አመለከቱ ። ለተፈጠረው ችግር ተጠያቂው ክልል ሲመራ የነበረው የህውሓት ቡድን መሆኑን አስታወቁ።

አቶ አንዳርጋቸው በወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታዎች ዙሪያ በተለይ ከአዲስ ዘመን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ ከ27 ዓመታት ዘፈንና ፉከራ በኋላ የትግራይ ህዝብ በምግብ እህል እንኳን ራሱን ባልቻለበት ሁኔታ የምግብ እርዳታ ተቀባይ ሆኖ ማየት እጅግ አሳፋሪ ነው።

ክስተቱ ቡድኑ 27 ዓመታት በሙሉ በበላይነት ኢትዮጵያን በገዛበትና ባስተዳደረበት ወቅት ማንኛውንም ነገር ያደረገው ለራሱ ጥቅም እንደሆነ የትግራይ ህዝብ ከተጨባጭ የዛሬ ህይወቱ እንዲያስተውል እድል እንደሰጠው አስታውቀዋል።

ቡድኑ በመላው አገሪቱ የዘረፈውን ሀብት በጣም ጥቂት ለሆኑ የራሱ የቅርብ ሰዎች ብቻ መጠቀሚያ አድርጎት እንደነበር አሁን ያለው ሁኔታ በገሃድ አሳይቷል ያሉት አቶ አንዳርጋቸው ፣ ሲፈጽሙት የነበረው ወንጀልም ከትግራይ ህዝብ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንዳልነበረው ማየት እንዳስቻለ ገልጸዋል ።

የትግራይ ህዝብ እንደ 27 ዓመቱ የልማት ዘፈንና ፋከራ ቀርቶ ሌሎች የሀገሪቱ ህዝቦች ያገኙትን የፖለቲካ ነፃነት የተነፈገ ነው ። ህዝቡ ይህንን ጠንቅቆ ያውቀዋል ያሉት አቶ አንዳርጋቸው ፣ ይህም ቡድን የሚመራበት

" ከ 27 ዓመታት የልማት ዘፈንና ፉከራ በኋላ የትግራይ ህዝብ በችግር ላይ ወድቆ

መገኘቱ አሳፋሪ ነው"- አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ የኢሳት ሥራ አስኪያጅ

አጥፍቶ ጠፊው ትህነግ/ህወሓት/

(1967 -2013 ዓ.ም)

“አገራዊ እሴት፣ አገራዊ ጀግና እና አገራዊ ታሪክ ሳይኖር አገር ወዳድ

ትውልድ ሊኖር አይችልም”- ዶክተር አልማው ክፍሌየታሪክና የህግ መምህር

ፎቶ

-በገባ

ቦ ገብ

"የህወሓት ፖሊሲዎች የኢትዮጵያን ፖለቲካ እና

ኢኮኖሚ ምስቅልቅል ውስጥ የከተቱ ነበሩ"

- ጊታ ፓሲ

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደርገጽ 12

Page 2: ሰኞ ከ 27 ዓመታት የልማት ዘፈንና ፉከራ በኋላ ... · 2021. 2. 1. · ገጽ 4 በውስጥ ገጾች ገጽ 11 ሰኞ ብዕራችን ለኢትዮጵያ

አዲስ ዘመን ሰኞ ጥር 24 ቀን 2013 ዓ.ም

ዜና

ገጽ 2

ማህሌት አብዱል

አዲስ አበባ፡- በቀጣዮቹ ስድስት ወራት ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ በኦሮሚያ ክልል 350 ሚሊዮን ብር ለማሰባሰብ መታቀዱን በኦሮሚያ ክልል የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት አስታወቀ። ባለፉት አስር ዓመታት ለግድቡ ግንባታ ከክልሉ 1 ቢሊዮን 900 ሚሊዮን ብር መሰብሰቡን ገለጸ።

በኦሮሚያ ክልል የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ ቆንጂት በቀለ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንዳስታወቁት፤ በመላው የክልሉ አካባቢዎች ሰፊ የንቅናቄ ስራ በመስራትና ህዝቡን በማስተባበር በመጪዎቹ ስድስት ወራት ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ 350 ሚሊዮን ብር ለማሰባሰብ ታቅዷል። በተለይም ህዝቡ በቦንድ ግዢ በስፋት እንዲሳተፍ በማድረግ የቁጠባ ባህሉን ለማሳደግ ይሰራል።

ባለፉት አስር ዓመታት በክልሉ ለግድቡ ግንባታ 1

ቢሊዮን 900 ሚሊዮን መሰብሰቡን ያስታወሱት ሃላፊዋ፤ የግድቡ ግንባታ በተባለው ጊዜ ያለመጠናቀቁ፣ በታሰበው ልክ በጥራት ያለመከናወኑና የአመራር በቃት ችግር መታየቱ ህዝቡ በግንባታው ላይ ጥርጣሬ አሳድሮበት እንደቆየ አስረድተዋል።

ሆኖም የለውጡ ሃይል ወደ ስልጣን ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ በህዝብ የሚነሱ ቅሬታዎችን ሆነ ያሉበትን ተጨባጭ ችግሮች እንዲፈቱ አቅጣጫ በማስቀመጡና ጠንካራ ስራዎች በመሰራታቸው በአጭር ጊዜ ውስጥ የመጀመሪያው ዙር የግድቡ ውሃ ሙሌት ማከናወን መቻሉን ገልጸዋል። ይህም ተዳክሞ የነበረው የህዝብ ተሳትፎ ዳግም እንዲያንሰራራ ማድረጉን አመልክተዋል።

በአሁኑ ወቅትም የኢትዮጵያን እድገት በማይሹ የውጭ ሃይሎች እየተደረገ ያለው ጫና በክልሉ ህዝብ ዘንድ ከፍተኛ ቁጭት በመፍጠሩ ህዝቡ አቅሙ የፈቀደውን ሁሉ ለማድረግ ቁርጠኝነቱን ማሳየቱን

አመልክተው ፣ የክልሉ መንግስት ይህንን የህዝብ መነሳሳት እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም የግድቡ ግንባታ ከዳር እንዲደርስ በሁሉም አካባቢዎች ሰፊ የማነቃቂያ መድረኮች ለማዘጋጀት ማቀዱን ጠቁመዋል።

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ምክትል ፕሬዚዳንት ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ በበኩላቸው፤ ‹‹ፕሮጀክቶችን በፍጥነትና በጥራት በመጨረስ ለወዳጆቻችንም ሆነ ለጠላቶቻችን ትልቅ መልዕክት ማስተላለፍ ይገባናል። እንደ ህዳሴ ግድብ ያሉ ትልልቅ ፕሮጀክቶችን በመጨረስ በተለይም ለጠላቶቻችን ያለንበትን ሁኔታ ማሳየት አለብን›› ብለዋል።

በተለያዩ የልማት ስራዎች የህብረተሰቡን ተሳትፎ በጣም ጠንካራ እንደነበር ያስታወሱት ምክትል ፕሬዚዳንቷ፤ ይህም የክልሉ መንግስት ማንኛውንም ፕሮጀክት ለመስራት የህዝቡ አጋርነት እንደማይለየው በማመን መሆኑን ተናግረዋል። ይሁንና የህዝቡ ተሳትፎ ቀጣይነት እንዲኖረው የአመራሩ የአመራር

ብቃትና በቁርጠኝነት ማስተባበር የሚጠይቅ መሆኑን አስገንዝበዋል።

‹‹ከኦሮሚያ ክልል ስፋትና ከህዝቡ ቁጥር አንፃር እስካሁን የተሰበሰበው ገንዘብ በቂ የሚባል አልነበረም›› ያሉት ወይዘሮ ጫልቱ፤ ለዚህም ፕሮጀክቱን ሲያስተባብር የነበረው የመንግስት አካል በህዝብ ዘንድ ታዓማኒነት ማጣት ትልቅ ድርሻ እንዳለው አስረድተዋል። ከዚህም ባሻገር በክልሉም ሆነ በአገር ደረጃ የነበረው አለመረጋጋት ቀላል የማይባል አሉታዊ ሚና እንደነበረው አመልክተዋል።

የክልሉ የግድቡ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤቱ በኮምዩኒኬሽን ስር እንዲሆን መደረጉ እንደተጨማሪ ስራ እንጂ ዋና ስራ እንዳልሆነ ተደርጎ መታየቱ ሌላኛው ክፍተት እንደነበር ያመለከቱት ወይዘሮ ጫልቱ፤ ‹‹ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የክልሉ ብቻ ሳይሆን የአገርም ዋና ስራ በመሆኑ በሁሉም ደረጃ ያለ አመራር ለግንባታው መጠናቀቅ ሃላፊነቱን በሚገባ ሊወጣ ይገባል›› ብለዋል።

እፀገነት አክሊሉ

አዲስ አበባ፦ አሁን ባለው ሁኔታ በተለያዩ ክልልች አልፎ አልፎ የታየው የአምበጣ መንጋ ከብዛቱ አንጻር ያደረሰው ጉዳት መጠነኛ መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የዕጽዋት ጥበቃ ዳይሬክተር አቶ በላይነህ ንጉሴ በተለይ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደገለጹት፣ ዳግም የተከሰተው የአምበጣ መንጋ በየትኛውም ክልል ላይ በሰብል ላይ ያደረሰው ጉዳት ከመንጋው ብዛት አንጻር አነስተኛ ነው።

እንደ አገር ስናየው ዳግም የተከሰተው የአንበጣ መንጋ በምሥራቁ ክፍል መቀነስ አሳይቷል ፤ አፋርና አማራ ክልል ላይ ከአምስት ቀን በፊት ጀምሮ ታይቶ ነበር በተደረገው ከፍተኛ የመከላከል ጥረት ግን ከአማራ ክልል ወደ ትግራይ ከዚያም ወደ ኤርትራ አመርቷል ያሉት አቶ በላይነህ ፣

በዚህ ቆይታውም በሰብል ላይ የተጋነነ ጉዳት አድርሷል ማለት አይቻልም ብለዋል።

አምበጣው በምሥራቁ የአገሪቱ ክፍልም እየተስተዋለ ከመሆኑ ጋር በተያያዘ የተጠናከረ የርጭት ሥራ እየተሠራ ነው ያሉት አቶ በላይነህ፣ ነገር ግን ቀደም ብሎ ከተከሰተው የአምበጣ መንጋ ጋር ሲነጻጸር መጠኑ የቀነሰ ነው። በሶማሌ ክልል ፊቅ ዞንም ተመሳሳይ ክስተቶች ታይተው የቁጥጥር ሥራ ሲሠራ ስለነበር አሁን ላይ መጠናቸው ቀንሶ በየሦስት ወይም አራት ቀኑ አንዳንድ ቢታዩም እሱንም የማጥፋት ሥራው በተጠናከረ ሁኔታ እየተሠራ መሆኑን አብራርተዋል።

እንደ አቶ በላይነህ ገለጻ አሁን ላይ የአምበጣ መንጋው ጠንከር ባለ ሁኔታ የሚታየው በኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን ነው ፤ በዚያም ሰፋ ያለ ርጭት እየተካሄደ በመሆኑ ከቁጥጥር ውጪ አይደለም። በተመሳሳይ በደቡብ ክልልም እየገባ ያለበት ሁኔታ ስለታየ የመከላከሉ ሥራ በተጠናከረ መንገድ እየተሠራ መሆኑን አመልክተዋል።

የተሰበሰቡ ሰብሎች ላይ ጉዳት አድርሷል እየተባለ ነውና ጉዳቱ እንዴት ይገለጻል ? ተብለው ለተጠየቁት ሲመልሱም “ አሁን ያለን የመከላከል አቅም የተሻለ በመሆኑ አምበጣው እንደአመጣጡ ሰብል አብቃይ ቦታዎች ላይ ከመድረሱ በፊት ቆላው ላይ እየተመታ ስለሆነ አማራ ክልልም ሆነ ኦሮሚያ ባሌ ዞን ላይ በሰብል ላይ ያደረሰው ጉዳት ያን ያህል አይደለም” ብለዋል።

የአምበጣ መንጋ ጉዳት አድርሶ የነበረው ቀደም ባለው ጊዜ ምንም ሳንዘጋጅ በመጣበት ወቅት ነው ፣ አሁን ላይ የመከላከል አቅማችን ስለዳበረ ችግሩን በአስተማማኝ ሁኔታ መቋቋም እንደተቻለም ገልጸዋል።

አምበጣ ባለፈው ጊዜ እንደ አገር ብዙ ዋጋ አስከፍሎናል ያሉት አቶ በላይነህ፣ ይህ ሁኔታ ዳግም እንዳይከሰት ልምድ የቀሰሙ ባለሙያዎችን በማዘጋጀት የርጭት ሥራውን በአውሮፕላንና በመኪና በማድረግ ጥሩ ሥራ እየተሠራ ውጤትም እየተገኘበት መሆኑን ጠቁመዋል።

በዚህ ሥራ ላይ ደግሞ የዓለም ባንክን ጨምሮ ሌሎች

ለጋሽ አካላት እያደረጉ ያሉት ድጋፍ መልካም መሆኑን የገለጹት አቶ በላይነህ ፣ አሁን ላይ የአምበጣ መንጋ ለአገራችን ስጋት መሆኑ ቀርቶ እንደ አመጣጡ በብቃት ለመመለስ በሚያስችል ቁመና ላይ ነን ብለዋል።

የአምበጣ መንጋ በመጣ ቁጥር የለጋሽ አካላትን እጅ ማየት ደጅ መጥናት የለብንም ያሉት አቶ በላይነህ፣ ከዚያ ይልቅ መቀመጫውን ኢትዮጵያ ውስጥ ያደረገው “የምሥራቅ አፍሪካ በረሃ አምበጣ መከላከያ ድርጅት” አቅምን የበለጠ ማሳደግ እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል። ለዚህም አባል አገራት ገንዘብ እያሰባሰቡ መሆኑን ገልጸዋል።

በሌላ በኩልም ህብረተሰቡ የአምበጣ መንጋ መጣም አልመጣም ከመጣም ጉዳቱ ሰፊ እንዳይሆን የመኸር እርሻውን በቶሎ መሰብሰብ ፣ በተቻለ መጠንም ማሳውን ነቅቶ መጠበቅ፣ አምበጣ ሲያይም የራሱን መከላከል እያደረገ ለሚመለከታቸው አካላት ጥቆማ መስጠት እንዳለበት አሳስበዋል።

ለታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ከኦሮሚያ ክልል 350 ሚሊዮን ብር ለመሰብሰብ መታቀዱ ተገለጸ

በተለያዩ ክልሎች የታየው የአምበጣ መንጋ ከብዛቱ አንጻር ያደረሰው ጉዳት መጠነኛ መሆኑ ተገለጸ

Page 3: ሰኞ ከ 27 ዓመታት የልማት ዘፈንና ፉከራ በኋላ ... · 2021. 2. 1. · ገጽ 4 በውስጥ ገጾች ገጽ 11 ሰኞ ብዕራችን ለኢትዮጵያ

ገጽ 3

ዜና

አዲስ ዘመን ሰኞ ጥር 24 ቀን 2013 ዓ.ም

እፀገነት አክሊሉ

አዲስ አበባ፦ የህግ ማስከበር ዘመቻውን ተከትሎ የተከሰተውን የሰብዓዊ ዕርዳታ ፍላጎት ለማሟላትና ህዝቡም በጥቂት ጊዜያት ውስጥ የመጀመሪያ ዙር ዕርዳታን ለማድረስ በሙሉ አቅም እየተሠራ መሆኑን ብሔራዊ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።

የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር አቶ ዳመና ዳሮታ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዳስታወቁት ፣ በትግራይ ክልል የተከሰተውን የህግ ማስከበር ዘመቻ መጠናቀቅ ተከትሎ በህዝቡ ላይ የተፈጠረውን የሰብዓዊ ድጋፍ ፍላጎት ለማሟላት ኮሚሽኑ በከፍተኛ ቁርጠኝነት እየተንቀሳቀሰ ነው።

እንደ አቶ ዳመና ገለጻ፣ ምንም እንኳን የጁንታው ቡድን የአካባቢውን መሰረተ ልማት ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ አውድሞ የሄደ ቢሆንም በተገኘውና መሬት ላይ ያለውን አማራጮች በሙሉ በመጠቀም በአጭር ቀናት ውስጥ ሁሉም ህዝብ የመጀመሪያ ዙር ዕርዳታ እንዲያገኝ እየሠራን ነው።

መቀሌን ጨምሮ በመላው ትግራይ የመብራት፣ የባንክ ፣ የስልክ በጠቅላላው መሰረታዊ የሚባሉ ፍላጎቶች ተቋርጠው የቆዩ በመሆኑ ገንዘብ ያለው እንዲሁም የመንግሥት ሠራተኛው ገንዘቡን አውጥቶ ሸምቶ ለመብላት የሚችልበት ሁኔታ አልነበረም ያሉት አቶ ዳመና ፣ይህ ደግሞ የተረጂው ቁጥር ከፍ እንዲል አድርጎታል ብለዋል። ይህም ሆኖ በተለይም የመጀመሪያ ዙር ዕርዳታው በፍጥነት እንዲደርስ ኮሚሽኑ የተቻለውን ሁሉ እያደረገ ውጤቶችንም እያየ መሆኑን ገልጸዋል።

ቀደም ሲል ዕርዳታን በተለያየ መልኩ ለማዳረስ ቢሞከረም የጸጥታ ሁኔታ አስተማማኝ አለመሆን በትራንስፖርት ጉዞው ላይ እንቅፋት ሆኖ እንደነበር የተናገሩት አቶ ዳመና ፣አሁን ላይ መከላከያና ሌሎች የጸጥታ አካላት ሙሉ ኃላፊነቱን ወስደው በመንቀሳቀሳቸው ዕርዳታ እየተጓጓዘ ነው፤ አስጊ ናቸው ተብለው የተለዩ አካባቢዎች ላይም መኪኖች በእጀባ እንዲሄዱ በማድረግ ዕርዳታውን የማዳረሱ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉን አብራርተዋል።

ሞገስ ተስፋ

አዲስ አበባ፡- እንሰት ኢትዮጵያ ያልተጠቀመችበት ትልቅ ሀብት መሆኑን በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የባዮቴክኖሎጂ መምህር እና ተመራማሪ ዶክተር አዲሱ ፍቃዱ ገለጹ።

ዶክተር አዲሱ በተለይም ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፣ እንሰት 20 ሚሊዮን የሚሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ በቀን ሦስት ጊዜ መመገብ የሚያስችል እንደ ሀገር ያልተጠቀምንበት ሲሳይ ፤ እስካሁን በጣም ያጣነው ትልቅ ሀብት ነው።

ህዝቡ በባህላዊ መንገድ ለራሱ ምግብ አዘጋጅቶ ከመጠቀም ውጪ ለገበያ በማቅረብ ገቢ ማግኘት ባለመቻሉ እንደሀገር ትልቅ የሀብት ብክነት አለ ያሉት ተመራማሪው ፣ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ እያንዳንዱ ከመቶ በላይ እንሰት ቢኖረውም ለምግብ የሚያውለው ግን ከአምስት አይበልጥም ብለዋል። ነገር ግን ቀሪውን በዘመናዊ መንገድ አምርቶ ለገበያ የሚቀርብበት መንገድ ቢኖር ከሀገር አልፎ ለአፍሪካ ብሎም ለዓለም ገበያ መቅረብ የሚችል እምቅ ሀብት እንደሆነ ገልጸዋል።

እስካሁን ድረስ ከእንሰት ማግኘት የሚገባን ጥቅም ሩቡንም ማግኘት አልተቻለም ያሉት ተመራማሪው፣ በባህላዊ መንገድ የሚፋቅበት ዘዴ እና የሚጓጓዝበት መንገድ ኋላቀር በመሆኑ ከአንድ እንሰት ከ24 እስከ 25

በመቶ የሚሆነው ይበላሻል ብለዋል።ዩኒቨርሲቲው በተለይም ከፍተኛ የሆነ የእንሰት

ክምችት በሚገኝባቸው የሲዳማ፣ ደቡብ እና አንዳንድ የኦሮሚያ አካባቢዎች በመዘዋወር ባካሔደው ጥናት እንሰት በባህላዊ መንገድ በሚዘጋጅበት ወቅት ከፍተኛ በሆነ ደረጃ እንደሚባክን ማረጋገጥ እንደተቻለ አስታውቀዋል።

እንደ ዶከተር ፍቃዱ ገለፃ ፣ እንሰትን በትክክል እና በአግባቡ ጥቅም ላይ እንዲውል ቢደረግ ከፍተኛ ገቢ የሚያስገኝ ቢሆንም በትክክል ጥቅም ላይ እንዲውል ለማድረግ ትኩረት አልተሰጠውም።

ዩኒቨርሲቲው እንሰት ላይ ከ5 ዓመት በላይ ጥናት እና ምርምር በማድረግ በብዙ መልኩ በማዘጋጀት ለምግብ አገልግሎት መዋል የሚችል መሆኑን በጥናት ግኝታቸው ያረጋገጡ መሆኑን ጠቁመዋል። ድርቅ መቋቋም አቅሙም ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል።

እንሰት ትኩረት ቢሰጠው ከጤፍ እኩል የሚሆንበት አጋጣሚ እንዳለ የገለጹት ተመራማሪው፣ የምግብ ዋስትናን እንደሀገር ለማረጋገጥ ወሳኝ ምርት ነው ብለዋል። ጉዳዩ በሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ትኩረት የተነፈገው በመሆኑ አርሶ አደሩ እንሰቱን እየነቀለ ወደ ጫት ማሳውን እያዞረ እንደሆነ አመልክተዋል።

ይህን ስጋት ለመቀነስ ዩኒቨርሲቲው እንሰት

"ለህዝባችን በጥቂት ጊዜያት ውስጥ የመጀመሪያ ዙር ዕርዳታን ለማድረስ በሙሉ አቅማችን እየተንቀሳቀስን ነው "

አቶ ዳመና ዳሮታ ብሔራዊ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር

በቅርቡ ደግሞ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ሥራ አስፈጻሚ ሰብሳቢ የሆኑበት ቡድን በመመስረትና በክልል ከሚንቀሳቀሱ ዓለም አቀፍ ለጋሽ ድርጅቶች ጋር በመሆን እንዲሁም የክልል ቢሮ ኃላፊዎችን ጨምሮ ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት የተካተቱበት ሌላ የሰብዓዊ ድጋፍ ማስተባበሪያ ማዕከል ተመስርቷል ብለዋል። በዚህም እቅድ ወጥቶ ዕርዳታው በምን ሁኔታ ለዜጎች መድረስ አለበት የሚለው በየቀኑ እየተገመገመ ችግሮች ሲኖሩም በፍጥነት መፍትሔዎች እየተቀመጡ መሆኑን አመልክተዋል።

እያንዳንዱ ተቋማት ከአስቸኳይ ጊዜ ዕርዳታ ምላሽ አኳያ ምን ሊሠሩ ይገባል የሚለውን በመለየት የሥራ ድርሻቸውን በመስጠት ድጋፎቹ ወደዞኖቹ ለማውረድ የድጋፍ ስርዓት ተዘርግቷል ፣ ከዚህ አንጻር አሁን ላይ ጥሩ ሂደት አለ ብሎ ማለት ይቻላል ብለዋል።

ቀደም ሲል በአካባቢው የነበረው መንግሥታዊ

አደረጃጀት በመፍረሱ ህጋዊ የሆነ ሰነድ መጥፋት ባለሙያ ማጣት እንዲሁም ድጋፉ በተወሰነ ቦታ ላይ ብቻ መወሰኑ ችግር ሆኖ መቆየቱን አስታውሰው፣ አሁን ላይ ግን መላ ትግራይ አስቸኳይ የሰብዓዊ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው በመሆኑ ይህንን ታሳቢ ያደረገ ሥራ እየተሠራ መሆኑን ጠቁመዋል።

እንደ አቶ ዳመና ገለጻ ፣ ኮሚሽኑ አሁን ላይ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች አስቸኳይ የሰብዓዊ ድጋፍ የሚሆንም ከዚህ ቀደም በክልሉ ተከማችቶ በመጠባበቂያነት የተያዘ ከመቶ ሺ ኩንታል በላይ የምግብ እህል የነበረው በመሆኑ እሱን የማከፋፈል እንዲሁም ከማዕከልም በርካታ ሰብዓዊ ቁሳቁሶችን የማጓጓዝ ሥራ እየሠራ መሆኑን አብራርተዋል።

ከዚህ በተጨማሪም በብሔራዊ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን በኩል ከጅቡቲ በቀጥታ እየገባ ያለው ከ2 መቶ ሺ ኩንታል በላይ የምግብ እህል መኖሩን

ጠቁመው ፣ መቶ ሺ ኩንታል የሚገመት እህል ደግሞ በልማታዊ ሴፍቲኔት በኩል እየገባ ይገኛል ፤ ይህንን በማቀናጀት በጣም በፈጠነ ሁኔታ ለህዝቡ እንዲዳረስ በርካታ ትራንስፖርት አቅራቢዎችን በማዘጋጀት እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል።

አሁን በክልሉ ሰብዓዊ ድጋፎችን ከኮሚሽኑና ከማዕከሉ ጋር በትብብር የሚሠራው የክርስቲያን በጎ አድራጎት ድርጅት ነው ያሉት አቶ ዳመና፣ ከለጋሽ ድርጅቱ ጋርም ሰፊ የሥራ ትስስርን በመፍጠር የመቀሌ ከተማን ጨምሮ የተወሰኑ ቦታዎች ላይ ድጋፍ ማድረግ ተችሏል። በዚህም እስከ አሁን በመቀሌና ዙሪያዋ መቶ ሺ ኩንታል የሚገመት የምግብ እህል በመሰራጨት ላይ ነው ብለዋል።

ዕርዳታውን ተደራሽና ፈጣን ለማድረግ በመቀሌ ላይ ከፌዴራልም ከክልሉ የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም ከህብረተሰቡ የተውጣጡ አካላት ያሉባቸው የተለያዩ አደረጃጀቶች መፈጠራቸውን ጠቁመው ፣ እነዚህም በሳምንት ሁለት ጊዜና ከዚያ በላይ ዕርዳታ እየተሰጠባቸው ባሉና ባልደረሰባቸውም ቦታዎች በመንቀሳቀስ ቅኝትና ግምገማ እያደረጉ መፍትሔ እያበጁ እንደሄዱ አስታውቀዋል።

በቀጣይ ባንኮችም በስፋት ሥራ ሲጀምሩ፣ የመሰረተ ልማቶችም ወደቀድሞ ሁኔታቸው ሲመለሱ፣ የመንግሥት ሠራተኞች ሥራቸውን ሲጀምሩ፣ የሸቀጦች እጥረት ሲፈታ በጠቅላላው ክልሉ ወደቀድሞ ሁኔታው ሲመለስ በትክክል ዕርዳታ የሚያስፈልጋቸው ምን ያህል ዜጎች አሉን የሚለውን ለመለየት ይቻላል ያሉት አቶ ዳመና ፣ አሁን ላይ ግን በመላው ትግራይ የመጀመሪያ ዙር ዕርዳታ የማዳረሱ ሥራ በሰፊው እንደሚሠራ አብራርተዋል።

ይህ ወገኖቻችን ላይ የደረሰውን ችግር በመንግሥት እንዲሁም በክልሉ ከዚህ ቀደምም በብቃት ሰብዓዊ ዕርዳታ ሥራን ሲያከናውን ከነበረው የክርስቲያን በጎ አድራጎት ድርጅት ጋር በመቀናጀት እየሠራን ነው፤ ነገር ግን ከችግሩ ግዝፈትና ስፋት አንጻር በጎ ፍቃደኞች በተለይም ሌሎች ምርት የሰበሰቡ ክልሎች በኮሚሽኑ እንዲሁም በጊዜያዊ አስተዳደሩና በሌሎች ህጋዊ በሆኑ አካላት በኩል በጥሬ ገንዘብ አልያም በዓይነት ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

እንሰት ኢትዮጵያ ያልተጠቀመችበት ትልቅ ሃብት መሆኑ ተገለጸ

ሳይባክን እየተዘጋጀ ለምግብነት የሚውልበትን መንገድ የማብላያ ማሰሮ እና እርሾ በማዘጋጀት ምርታማ መሆን እንደሚቻል ለማህበረሰቡ የግንዛቤ ስራ እየተከናወነ

መሆኑን ጠቁመው ፣ የምርምር ውጤቱ ህዝቡ ጋር እንዲደርስ የባለድርሻ አካላትን ጥረት እንደሚጠይቅ ገልጸዋል።

Page 4: ሰኞ ከ 27 ዓመታት የልማት ዘፈንና ፉከራ በኋላ ... · 2021. 2. 1. · ገጽ 4 በውስጥ ገጾች ገጽ 11 ሰኞ ብዕራችን ለኢትዮጵያ

አዲስ ዘመን ሰኞ ጥር 24 ቀን 2013 ዓ.ም

ዜና

ገጽ 4

ከ1ኛው ገጽ የዞረ

መንገድ እጅግ ኋላቀር እንደነበር የሚያሳይ ነው ብለዋል ። ከህግ ማስከበር ዘመቻ በፊት ከአንድ ሚሊዮን በላይ

የሚሆን የክልሉ ህዝብ በሴፊቲኔት ሲረዳ ነበር ያሉት አቶ አንዳርጋቸው ፣ ከዚህ በተጨማሪም በቀጥተኛ እርዳታ የሚኖረው ህዝብ ቁጥርም ቀላል እንዳልነበር አስታውቀዋል። በዋነኛነት ያጋጠመው የምግብ እህል እጥረት ከህግ ማስከበር ዘመቻው ጋር የተያያዘ እንዳልሆነ ህዝቡ ሊረዳው እንደሚገባ አመልክተው ፤ " መንግስት ተደራርበው ለህዝቡ የከበዱትን ችግሮች ግምት ውስጥ አስገብቶ በተቻለው መጠን እና ፍጥነት ህዝቡ የረሃብ አደጋ ላይ እንዳይወድቅ ማድረግ። ህዝቡ በመድሃኒት እጥረት ችግር እንዳያጋጥመው አስፈላጊውን ነገር በፍጥነት ማቅረብ ይጠበቅበታል። ከዚህም መንግስት የተቻለውን ያህል እያደረገ ነው" ብለዋል ።

አሁንም በተበጣጠሰ መልኩ በየጎሮኖውና በየጥሻው የተደበቁ የጁንታው ርዝራዞች የመንግስት ጥረት በተሟላ መንገድ እንዳይከናወን እያደረጉ ናቸው። ምግብና መድሃኒት የጫነውን ተሽርካሪ ሞት አፋፍ ላይ ለደረሰ ለገዛ ወገናቸው እንዳይደርስ ለማድረግ የሽብር ወሬ እየነዙ እንደሆነ አመልክተዋል ።

በእንዲህ አይነት ሁኔታ አስቀድመንም ያለፍን በመሆኑ መንግስት ይህን ሁኔታ እልህ አስጨራሽ እንደሚሆን አውቆ እራስን ማዘጋጀት ይኖርበታል ያሉት አቶ አንዳርጋቸው ፣ መንግስት መስራት ያለበትን ነገር ከመስራት ውጪ ምንም ሌላ አማራጭ እንደሌለው አስታውቀዋል።

ከ15 ያልበለጡ ዲያስፖራዎች ባገኙት የመገናኛ ብዙሃን ተጠቅመው የሚነዙት ፕሮፓጋንዳ በየትኛውም ድርጅትና ህዝብ አይን ቦታ የሚሰጠው እንዳልሆነ

ጠቁመው ፣ ከነሱ በመነሳት ዲያስፖራው በሙሉ እንዲህ አይነት አሳፋሪ ተግባር ይፈጽማል ለማለት አልደፍርም ብለዋል ። እነዚህ ሰዎች ተደማጭነት አላቸውም ብለው እንደማያምኑ ገልጸዋል ።

በዚህ ሰዓት ላይ እነሱ የሚፈልጉት ነገር ግልጽ ነው። እነሱ የሚፈልጉት ለትግራይ ህዝብ የመድሃኒትና የምግብ እርዳታ በአስቸኳይ ደርሶ ከችግር እንዲታደጉ ሳይሆን በሚሊኖች የሚቆጠሩ የትግራይ ዜጎቻችን የሚያልቁበት ሁኔታ እንዲፈጠር እንደሆነ ጠቁመዋል።

ችግሩ ሲፈጠር የኢትዮጵያ መንግስት ህዝባችንን አስጨረሰ የሚል የፖለቲካ ፕሮፖጋንዳ ለመንዛት ነው። ይህ አካሄዳቸው የተለመደና በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ያለ፣ የኢትዮጵያ ሊሂቃን የትግል አቅጣጫ እንደሆነም አስታውቀዋል ።

"የዚህ አይነት አመለካከት በእኛ አገር ስር የሰደደ ነው። የሰው ልጅ በሰውነቱ የሁሉም ነገር ግብ ሳይሆን የፖለቲካ ሊሂቃኑ የፖለቲካ ግብ ማዳረሻ መሳሪያ ተደርጎ የኖረ ነው። የሰው ህይወትን ያህል ነገር ለፖለቲከኛው ወደ ግቡ መድረሻ ቁማር ሆኖ ነው የቆየው። እናም በዚህ መልኩ የተቃኘ የፖለቲካ ባህል ነው ያለን። የሰው ልጅ ህይወት ክቡርነት የማይታወቅበት ሁኔታ ነው ያለው" ብለዋል ።

እነዚህ ኃይሎች በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ለፍላጎትና ግባቸው ሲባል እንዲያልቁ ለማድረግ እየሰሩ ነው ። ይህንን ታሳቢ የሚያደርጉና የሚያበረታቱ ስራዎችን መስራታቸው ብዙም አይገርመምም ። በውጭ ብቻ ሳይሆን በአገር ውስጥም በእንዲህ አይነት አመለካከት የተቃኙ በርካታ የፖለቲካ ሊሂቃን መኖራቸውንም አስታውቀዋል።

" ከ 27 ዓመታት...

በጋዜጣው ሪፖርተር

አዲስ አበባ ፦ ህወሓት ሲጠቀምባቸው የነበሩ ፖሊሲዎች የኢትዮጵያን ፖለቲካ እና ኢኮኖሚ ምስቅልቅ ውስጥ የከተቱ እንደነበሩ በኢትዮጵያ አዲስ የተሾሙት የአሜሪካ አምባሳደር ጊታ ፓሲ አስታወቁ ።

አምባሳደሯ በአሜሪካ ከሚገኝ ከአንድ የመገናኛ ብዙሀን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዳስታወቁት ፣ ህወሓት ሲጠቀምባቸው የነበሩ ፖሊሲዎች የኢትዮጵያን ፖለቲካ እና ኢኮኖሚ ምስቅልቅል ውስጥ የከተቱ ነበሩ። ሀገሪቱን ለሥራ እጥነት ፣ ለዋጋ ግሽበት እና አካታች ላልሆነ የዕድገት መጠን የዳረጉ ናቸው ። በኢትዮጵያ ያለው የመሬት ፖሊሲ አርሶ አደሩን የመሬት ባለቤትነት የነፈገ እንደሆነ አስታውቀዋል ።

ጦርነቱ በህወሓት ጁንታ ቀስቃሽነት የተጀመረ እንደሆነ አመልክተው ፣የህወሓት ቡድን ከሁለት አሥርት ዓመታት ተኩል በላይ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ እና ፖለቲካ በብቸኝነት ተቆጣጥሮ እንደነበር አስታውቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የፖለቲካ ምኅዳሩን ለማስፋት እና ኢኮኖሚውን ክፍት ለማድረግ ቃል መግባታቸውን የገለጹት አምባሳደር ጊታ፣ "እንደዚህ ዓይነቱን የተመቻቸ ሁኔታ መፍጠር የአማካይ ኢትዮጵያውያንን አኗኗር ለማሻሻል የሚረዳ ነው ብለዋል፤

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የወጠኗቸውን

"የህወሓት ፖሊሲዎች የኢትዮጵያን ፖለቲካ እና ኢኮኖሚ ምስቅልቅል

ውስጥ የከተቱ ነበሩ" - ጊታ ፓሲ

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር

ዴሞክራሲ እውን ለማድረግ የጀመሩትን ሪፎርም አሜሪካ እንደምትደግፍም አስታውቀዋል

አሜሪካ በህዳሴው ግድብ ዙሪያ በሚደረጉ ውይይቶች ላይ የታዛቢነት ሚናዋን መጫወት እንደምትቀጥል እና ኢትዮጵያ እና ግብፅ ፍሬ የሚያፈራ ውይይት ማድረጋቸውን እንዲቀጥሉ እንደምታበረታታ ገልጸዋል።

እንደዚህ ዓይነቱ ግዙፍ የኃይል እምቅ አቅም ላይ ከስምምነት መድረስ ለሁሉም ሀገራት የአሸናፊነት አካሄድ መሆኑን ጠቁመዋል ።

"እኛ ከሌሎች ሰላም ወዳድ ሀገራት ጋር በመሆን ኢትዮጵያ እና ግብፅ ጉዳዩን በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ መግፋታችንን እንቀጥላለን" ብለዋል

ጌትነት ተስፋማርያም

አዋሽ ሰባት:- ሁለት ቢሊዮን ብር ወጪ የሚደረግባቸው የባቡር ማገናኛ ፕሮጀክቶች መጀመራቸውን የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን አስታውቋል።

የኢትዮ- ጂቡቲ ባቡር መስመርን ከአዋሽ ሀገር አቀፍ ነዳጅ ማከማቻ ዴፖ ጋር የሚያገኝ የአምስት ኪሎ ሜትር ባቡር መስመር እና የኢትዮ- ጂቡቲ ባቡር መስመርን ከአዋሽ- ኮምቦልቻ - ወልዲያ የባቡር መስመር ጋር የሚያገናኝ የአንድ ነጥብ አምስት ኪሎ ሜትር ባቡር ፕሮጀክት በትናንትናው እለት ተጀምሯል።

በወቅቱ የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ስንታየሁ ወልደሚካኤል እንደገለጹት፤ የማገናኛ ባቡር መስመር ፕሮጀክቶቹ ለሀገራዊ ልማት ያላቸው ፋይዳ ጉልህ ነው።

ኢትዮጵያ ወደብ አልባ ሆና ነዳጅን በከፍተኛ መጠን የምታስገባ ሀገር መሆኗን ያስታወሱት ዶክተር ስንታየሁ፤ የኢትዮ- ጂቡቲ ባቡር መስመርን ከአዋሸ ሀገር አቀፍ ነዳጅ ማከማቻ ዴፖ ጋር የሚያገኘው የአምስት ኪሎ ሜትር ባቡር መስመር ግንባታ ሲጠናቀቅ ነዳጅ ወደከተሞች በፍጥነት ለማዳረስ ትልቅ አቅም እንደሚፈጠር ገልጸዋል።

የመንግሥት ኃላፊዎች ፣ ኮርፖሬሽኑ እና የነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ለፕሮጀክቶቹ መጀመር ትኩረት በመስጠት ውይይት እና ድርድር ሲያደርጉ መቆየታቸውን ጠቁመው፤ ግንባታው በመጨረሻ እውን በመሆኑ ለሀገር የሚበጅ ውጤት እንደሚያመጣ እምነታቸው መሆኑን አስታውቀዋል።

የኢትዮ- ጂቡቲ የባቡር መስመርን በግንባታ ላይ ከሚገኘው የአዋሽ-ኮምቦልቻ -ወልዲያ ባቡር መስመር ጋር ለማገናኘት የተያዘው ፕሮጀክት የባቡር መስመሮቹን የበለጠ ውጤታማ ለማድረግ እና አቅማቸውን ለመጨመር የሚያስችል እርምጃ መሆኑን ገልጸዋል። ፕሮጀክቶቹም በጥንቃቄ የሚመሩና እንደዚህ ቀደሙ የባቡር ፕሮጀክቶች የሚጓተቱ ሳይሆን በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ እንዲጠናቀቁ እንደሚደረግ አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ታደሰ ኃይለ ማርያም በበኩላቸው፣ ኢትዮጵያ በዓመት ሶስት ቢሊዮን ዶላር ወጪ

የሚደረግበትን ነዳጅ ከውጭ ሀገራት ታስገባለች። ይህም ከሀገሪቷ አጠቃላይ የወጪ ንግድ ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ መጠን ያለው ነው ብለዋል።

ለሀገር ልማት ከፍተኛ ግልጋሎት የሚሰጠውን ነዳጅ በፍጥነት እና ሳይባክን ለመጠቀም የዴፖ ማገናኛ የባቡር መስመር ግንባታው ወሳኝነቱ የጎላ እንደሆነ አመልክተዋል።

ከጂቡቲ ነዳጅ ተሸክመው የሚጓጓዙ ቦቴ ተሽከርካሪዎች መንገድ ላይ በተለያየ ምክንያት ሶስት እና አራት ቀን እንደሚቆዩ የተናገሩት አቶ ታደሰ፤ የማገናኛ ባቡር ግንባታው ሲጠናቀቅ ግን የጊዜ ቆይታቸውን ወደሰዓታት እንደሚቀንሰው ገልጸዋል።

ዓለም በአሁኑ ወቅት የቧንቧ መስመሮችን ለነጃጅ ማስተላለፊያነት በአማራጭነት እየተጠቀመ መሆኑን ተናግረው፤ በሁለተኛነት የባቡር መስመርን ተመራጭ እንደሆነ ጠቁመዋል ።

በኢትዮጵያ ግን ተሽከርካሪዎችን ለነዳጅ ማመላለሻነት ጥቅም ላይ እየዋሉ በመሆኑ በከተሞች ለሚታየው የነዳጅ እጥረት እና ወረፋ ምክንያት ከመሆኑ በላይ ለብክነትም እየዳረገ መሆኑን ገልጸዋል። በቀጣይ ነጃጅ ከጅቡቲ ወደ አዋሽ ዴፖ እና ሌሎችም ማከማቻዎች በማጓጓዝ ችግሮቹን ለመቀነስ ጥረት እንደሚደረግ አመልክተዋል።

የትራንስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ አወል ወግሪስ እንደገለጹት፤ የባቡር ማገናኛ ፕሮጀክቶቹ ኢትዮጵያ እያከናወነች ለሚገኘው የልማት ሥራዎች መፋጠን ትልቅ ድርሻ አላቸው። በመሆኑም ግንባታዎቹ በጊዜያቸው እንዲጠናቀቁ የአካባቢው ማህበረሰብ ጨምሮ ባለድርሻ አካላት በሙሉ የተቀናጀ ትብብር ሊያደርጉ ይገባል።

ለፕሮጀክቶቹ መሳካት እንደአፋር ክልል ተወላጅነትም የበኩላቸውን ሰፊ ጥረት እንደሚያደርጉ የገለጹት አቶ አወል፤ በፕሮጀክቶቹ ግንባታ በተያዘለት ጊዜ ብቻ ሳይሆን በተያዘለት በጀት እንዲጠናቀቅ ችግሮችን እየቀረፉ መስራት እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።

ከባቡር ማገናኛ ፕሮጀክቶቹ በተጨማሪ የነዳጅ ማራገፊያ መሰረተ ልማቶች እንደሚገነቡ በእለቱ ተገልጿል። ለአጠቃላይ ለፕሮጀክቶቹ ማስፈጸሚያ ሁለት ቢሊዮን ብር መመደቡ ከኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል ።

በሁለት ቢሊዮን ብር ወጪ የሚገነቡት የባቡር ማገናኛ ፐሮጀክቶች ተጀመሩ

Page 5: ሰኞ ከ 27 ዓመታት የልማት ዘፈንና ፉከራ በኋላ ... · 2021. 2. 1. · ገጽ 4 በውስጥ ገጾች ገጽ 11 ሰኞ ብዕራችን ለኢትዮጵያ

Website - www.press.et Email - [email protected] Facebook - Ethiopian Press Agency

ርዕሰ አንቀፅ

ግንቦት 30 ቀን 1933 ዓ.ም ተቋቋመ

አዲስ ዘመን

የዝግጅት ክፍል ፋክስ - 251-011-1-56-98-62

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ

ስልክ ቁጥር - 011-126-42-22

ዋና አዘጋጅአንተነህ ኃ/ብርሃን ወ/መድህን

አድራሻ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከ

ወረዳ 06

የቤት ቁጥር 319

ኢሜይል - [email protected]

ስልክ ቁጥር - 011-1-26-42-40

አዲስ ዘመን ሰኞ ጥር 24 ቀን 2013 ዓ.ም ገጽ 5

የገበያ ልማትና ፕሮሞሽን ዘርፍ

ኢሜይል - [email protected]

ስልክ - 011-156-98-73

ፋክስ - 011-126-58-12

የማስታወቂያ መቀበያ ክፍል

ስልክ - 011-156-98-65

ፋክስ፡-011-157-44-40

የማስታወቂያ ሽያጭ ማስተባበሪያ

ስልክ - 011-1-26-43-39

ማከፋፈያ

ስልክ - 011-157-02-70

የገንዘብ ኖት ለውጡ ፋይዳይህ አምድ በተለያዩ ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ዜጎች ነፃ ሀሳባቸውን የሚሰጡበት ነው። በዓምዱ ላይ የሚወጡ ጽሁፎች የዝግጅት ክፍሉን አቋም አያመለክቱም።

ነፃ ሃሳብ

ብስለት

ሀገር ማለት ሰው ነው። ሰው ነው ሀገር ማለት። የሚል አበባል በጆሮዬ እየሰማሁ መኖር ከጀመርኩ ዓመታት ተቆጥረዋል። ሀገር ሰው ከሆነ ያለሰው ሀገር ካልኖረ ኢትዮጵያ የማን ሀገር ናት? የማናት እማማ ኢትዮጵያ? ሰው ማለት ሀገር ከሆነ ሰው ለሀገሩ ሠርቶ ለእናቱ ታዞ ሀገርን ቤቱ አድርጎ መኖር ነው የሀገር ሰውነት ልኩ ከተባለ የዚህች ሀገር ልጅ መሆን ሀገርን ሀገር የሚያሰኛት ሰው ውስጧ እንዳይኖር ለምን ተፈረደባት? ለምን ይሆን የልጆቿ አንዳንድ ጡብ ተገንብቶ ውቡን የኢትዮጵያ አልፍኝ መሠራት ያቃተው እያልኩ አስባለሁ።

ለምን ይሆን ሰው ማለት ሀገር ሰው ደግሞ ፍጥረቱ ከእናት በሆነባት ምድር የእናት እንባ እንዳይደርቅ ችግርን በችግር ላይ መከፋትን በመከፋት ላይ ደራርበን ደራረተን ውድ የሆነውን የሰው ልጅ ደስታ የምናጠፋ፤ የኛ የሆነውን የሥራ ድርሻ ወደ ላይ በመግፋት መሰረቱ ይናጋ ዘንድ የማድረጋችንስ ምስጢር ምንድነው። የሰው መሆን ውሉ ማሰሪያው የፍቅር ገመድ መቋጠሪያው በአረንጋዴ ቀይ ብጫ ቀለማት ህብር የተገመደበት ሆኖ ሳለ ቀዩን ከቢጫው ቢጫውን ከአረንጓዴው በመለያየት የእያንዳንዷ ችግር መነሻ ምክንያት መሆናችን ሳያንስ ጣታችንን በሌሎች ላይ መቀሰር የሚመለከተው አካል ልብ ይበል ማለት ያበዛንበት ምክንያትስ ለምን ይሆን ነው ጥያቄዬ?

ሀገር የልጆቿ ቤት፣ ልጆቿ ደግሞ የእርሷ ውበት ከሆኑ ኃላፊነትን በመሸሽ ወይም ለመወጣት ባለመፈለግ ሰበብ ይህን የሚመለከተው አካል ይመልስ የሚሉት ቢህል ከየት ይሆን የመጣው። የሀገር ሰው መሆንን ልኬት ወደ ጎን ትቶ መንግሥት የሾመው ሚኒስትር እንኳን ይህ የመንግሥት ሥራ ነው እያለ ኃላፊነቱን በይደር ሲያቆየው መመልከት ህመም በሆነባት ሀገር መንግሥት ማነው? ንገሩኝ እስኪ ማነው መንግሥት? ኃላፊነት ተሰጥቶት የህዝብ እንደራሴ እንደልቤ እንደሃሳቤ ብሎ ወደፊት ያስቀመጠው ሰው ይህ የመንግሥት ሥራ ነው ካለ፤

ሀገር ማለት...ይመራናል ብለን እላይ ያስቀመጥነው ሌላ መሪ ከሻተ ማነው ሀገር ማለት ሰው መሆኑን የሚያጠይቀን።

ከማህበረሰቡ እንጀምር። ከግቢው ጠራርጎ ያወጣወን ቆሻሻ ከአጥር ጊቢው ወጪ አዝረክረኮ የሚመለከተው አካል መጥቶ ያንን ለሱም ይሁን ለልጆቹ ጤና ጠንቅ የሆነ ቆሻሻ እንዲያነሳለት ይጠብቃል። በሰፈር ውስጥ ቤት ለማሠራት ያሰበ ሰው የአካባቢው ነዋሪ የሚገለገልበት መንገድ የግንባታ ቁሳቁስ ማስቀመጫ አድርጎት፣ መተላለፊያ ጠፍቶ ህብረተሰቡ ከመቸገሩም በላይ መንገዱ ጉዳት ሲደርስበት የሚመለከተው አካል መጥቶ እንዲጠግንለት ይጠብቃል። ለአሰሱም ለገሰሱም የራሳችንን ኃላፊነት ሳንወጣ ሥራዎችን በአጠቃላይ ለሚመለከተው አካል አሳልፈን ከሰጠን ሀገር የሰው ናት ሀገር የህዝቦች ናት ለማለት የሚያስችል ድፍረትን ከየት ይሆን የምናገኘው።

እንቀጥል ከታች በቅርበት ህብረተሰቡን ለማገልገል የተመሰረቱ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ማለትም ወረዳዎች ውስጥ አገልግሎት በተገቢው መንገድ የማገኘቱ ነገር ጭንቅ ሆኖ ይታያል። ምን ይሻላል የሚል መፍትሔ ስጠይቅ እስኪ ለሚመለከተው አካል እናመልክት ይሆናል መልሱ፤ ለሥራው ይመጥናል ቦታው ላይ ተቀምጦ ዜጎችን ያገለግላል ተብሎ ዜጎች ከሚከፍሉት ግብር ደሞዙን እየተቀበለ እንዴት ነው እሱ የተቀመጠበት ወንበር ከልኩ በላይ ሆኖ ለሱ ሥራ ለሚመለከተው አካል ስሞታ የሚኬደው? የህግ አገልግሎት ለማግኘት እንደው ፍርድ ቤት ከመሄድ ይልቅ ጥቃቴን ውጬው ዝም ልበል በሚሉ ዜጎች የተሞላች ሀገር፣ ሰው ደግሞ ለሰው መድሃኒቱ ነው በተባለላት ሃገር፣ ሰው ለሰው ተሳስሮ በሰውኛ መስተጋብር ተደጋግፎ ታላቋን ኢትዮጵያ በሚያነሳባት፤ በዚህች ቅድስት ምድር ሁሉም ኃለፊነቱን እየገፋ የመንግሥት ጫንቃ ላይ መጣሉ ከታች የተጀመረው ብልሹ አሠራር መሆኑ እሙን ነው። ሆድ የባሰው ህብረተሰብ ብሶትና ዕንባ ብቻ ሆኖ ቀለቡ ምን ሀገር አለ ሲል ሀገር ማለት ሰው በሆነባት እናት ሃገር፤ ምን ሰው አላት፤ ኦና ቤት ነው እየኖርን ያለነው የሚሉት ብሂል በጣም ተንሰራፍቶ ሰው አልባ ምድር ሊያሰኛት የተዘጋጀበት ወቅት ላይ

መድረሳችን ለምን ይሆን እያልኩ አስባለሁ። የመንግሥት ሠራተኛ ተብሎ ህዝብን

ለማገልገል የተቀመጠ በተለያየ የሙያ ዘርፍ ሀገር ከፍላበት ያስተማረችው ማህበረሰብ ወንበሩ ይሁን ሌላ በትእቢት ተወጥሮ ኃለፊነትን ለመወጣት ትውውቅን የሚያስቀድም አገልግሎት ለመስጠት በገዛ ሀገሩ በገዛ ወገኑ ቤት አንዱ ልጅ አንዱ የእንጀራ ልጅ የሚሆንበት አካሄድ የት ያደርሰን የሆን እያልኩ አስባለሁ። የወደቀውን ለማንሳት እጅ እንደመዘርጋት በተኛበት ረጋገጦ ከታች እየሠራ የመጣውን የችግር ቁልል እንኳን ሳያፈርስ ከላይ ሲደርሱ ወደታች ማየትን መጠየፍ ምን ይሉታል? የረገጡት የችግር ቁልል ከድቷቸው መሬት ላለመፈጥፈጣቸው ምን ዋስትና ኖራቸው ነው ጆሮ ዳባ ልበስን ዓይነት ብሂል የተለማመዱት።

የሀገር መሰርት የሚጣለው ሰው በመሆን ውስጥ ሆነ የሰውንት መስፈርት ከላያችን ተገፎ እንስሳዊ ከእንስሳ ያነሰ የወረደ ስነ ምግባር ውስጥ ገብተን ሀገር የሌላ ሰው እስኪመስለን ግራ በመጋባት ባለመከባበር ስሜት ውቧን ሀገራችንን በፍቅር ገመድ እስረን ማገሩን ለማቆም አለመታደላችን ለምን ይሆን? ለምን ይሆን የኛ የሆነውን የቤት ሥራ ሳንሠራ የሌሎችን ኃላፊነት በመጠበቅ ብቻ አንድ ዕርምጃ ሳንራመድ ተራራውን መሻገር የሚያምረን፤ ሀገራችን ጨለማ ውስጥ ገብታ እንኳን ድቅድቁ ሳያስፈራን ያለችውን ጭላንጭል ቦግ ብላ እንዳትነድ አለማድረግ ለምን አልተቻለንም።

እኛ አባቶቻችን ያቆዩልንን፤ የደም ዋጋ የተከፈለላትን ሀገራችንን ይዘን እንዳናስቀጥል ያደረገን የክፋት ገደል ደፍነን፤ የተከፈለላትን የደም ዋጋ እንድታወራርድ አድርገን በመጠፋፋት ያጨቀየናትን ሀገራችንን፤ ከታች ጀምሮ የሚጠበቅብንን የቤት ሥራ ባለመሥራታችን ውሉ የጠፋበት ትብትብ ውስጥ ከተትናት፤ ለሚመለከተው አካል የተውናትን ሀገራችንን በጋራ በአንድነት በመደማመጥና በመከባበር ስሜት በመሥራት ለልጆቻችን ሰውና ሀገር አንድ ሆነው የተጣጣሙባትን የአንድነት ሀገር እናስረክባቸው። እንደሚያምርብን ያኑረን እላለሁ።

ከሰሜን ደቡብ፤ ከምዕራብ ምስራቅ፤ በልዩነት ውስጥ በደመቀ አንድነት በሚኖሩ ህዝቦች የደመቀች፣ ለዘመናት ሉዓላዊነቷን አስከብራ የኖረች፣ የታላላቅ ታሪኮችና ገድሎች አውድ፣ የጥቁር ህዝቦች የነጻነት ተምሳሌት፣ የበርካታ ብርቅና ደንቅ ሰው ሰራሽ ተፈጥሯዊ ቅርሶች መገኛ፣ ዓባይን ጨምሮ የታላላቅ ወንዞች ምንጭ፤ የኦሎምፒኩ መድረክ ፈርጥ፣ የጀግኖች እናት፣ የሰው ልጆች መገኛ ወዘተ ወዘተ በሚሉ ቃላት የኢትዮጵያን ታላቅነት ለመግለጽ ቢሞከርም ይህንን እውነታ ለመግለጽ ብዕር እንኳን አቅም ያጣል።

ኢትዮጵያ ታላቅ አገር ናት ሲባል እንዲሁ ለሞራል ብቻ የሚባል ነገር አይደለም። ይህንን ታላቅነቷን እንድትጎናጸፍ በየዘመናቱ ዋጋ የከፈሉና የሚከፍሉ እልፍ ልጆች ስላሏት እንጂ! የኢትዮጵያ ታላቅነት ያልገባቸው ትናንሾች ከራሳቸው የፖለቲካ ትርፍ ጋር አስልተው ይህ ካልሆነ ወይም ይህ ካልተደረገ ኢትዮጵያ ትፈርሳለች ብለው ቢያሟርቱም ሟርቱ እነሱን ጠርጎ ከመሄድ ውጪ ኢትዮጵያ እንደብረት ጠንክራ ዛሬም አለች።

ሉዓላዊነቷ በተከበረ አገር ላይ መኖር የቻልነው ጠላት ጠፍቶና ተንኳሽ ሳይኖር ቀርቶ አይደለም። ከራሳቸው ህይወት ይልቅ አገርንና ህዝብን የሚያስቀድሙና ለዚህ ደግሞ ክቡር ህይወታቸውን ጭምር የሰጡ እልፍና እልፍ የቁርጥ ቀን ልጆች ኢትዮጵያ ስለወለደች እንጂ! በሺዎች ዓመታት የኢትዮጵያ ታሪክ አገራችን የደረሰባትን ወረራ ለመቀልበስ ካካሄደችው ፍትሃዊ ጦርነት ውጪ አንድም ጊዜ የሰውን ድንበር ተጋፍታ አታወቅም። ይልቁኑ ጎረቤት ሱዳንና ሶማሊያን ጨምሮ በርዋንዳ ብሩንዲ ለወንድምና እህት አፍሪካውያን በሰላም መኖር ትልቅ ላቅ ያለ ዋጋ ከፍላለች።

ይህንን ጉዳይ አስመልክቶ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዓብይ አህመድ ከሰሞኑ ባስተላለፉት መልዕክት “ኢትዮጵያ ታላቅ ሀገር ናት። ሐሳባችን፣ ሥራችንና ንግግራችን ሁሉ ታላቅነቷን የሚመጥን መሆን ቢችል መልካም ነው። ካልሆነ በኢትዮጵያ ሚዛን ተመዝነን እንቀላለን። ኢትዮጵያ መዝና ታላቅነቱን የመሰከረችለትን ማንም አያቀልለውም። ኢትዮጵያ ያቀለለችውንም ደግሞ ማንም አያከብደውም። ታሪካችን

አዎን ኢትዮጵያ ታላቅ አገር ናት!ይሄንን ይመሰክራል፤ ዛሬም እየመሰከረ ነው።

ኢትዮጵያ ታላቅ ናት ስንል ከዜጎቿም፣ ከመሪዎቿም፤ ታላቅ ገድል ፈጽመናል ከሚሉ ሰዎች ሁሉ በላይ ታላቅ ናት ማለታችን ነው። በየትኛውም ዘርፍ ያሉ ልሂቃን፣ የትኛውንም የተቀደሰ አጀንዳ አንግበው የተመሠረቱ ድርጅቶች፣ ሐሳብና ርዕዮተ ዓለሞች ሁሉም ከኢትዮጵያ በታች ናቸው። ኢትዮጵያ ለሺዎች ዘመናት ሠርተውና ተጋድለው ያለፉ መሪዎችና ዜጎች ድምር ውጤት ናት።

ኢትዮጵያ - ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ፣ ከሰሜን እስከ ደቡብ ሰፍተውና መልተው የሚኖሩ፣ የሚሠሩና የሚጋደሉ ልዩ ልዩ ሕዝቦች ውጤት ናት። ታሪክ ያልመዘገባቸው፣ የታሪክ ድርሳናት የማያውቋቸው እልፍ አእላፍ ታሪክ ሠሪዎች በደምና በአጥንት፣ በላብና በወዝ በጽኑዕ መሠረት ላይ የገነቧት ሀገርም ናት። ግለሰቦች ለኢትዮጵያ የማይናቅ አስተዋጽዖ ያደርጋሉ፤ የኢትዮጵያ ህልውና ግን በግለሰቦች አይወሰንም። ግለሰቦች ለክብሯ ሲሉ ደማቸውን ሊያፈስሱ፣ አጥንታቸውን ሊከሰክሱ፣ መስዋዕት ሆነው ሊያስቀጥሏት ይወስኑ ይሆናል፤ ነገር ግን “እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል” እንዳለችው የቤት እንስሳ፣ ለግለሰቦች ሲባል ሀገር እንድትሞት ወይም እንድትኖር ለድርድር አትቀርብም።”

አባባሉ ትልቅ እውነታነት አለው። የሁሉም ጀግንነትም ሆነ አኩሪ ሥራ ከኢትዮጵያ ጋር በምንም ሚዛን አብሮ ሊመዘንና ሊስተካከል ወይም፣ ደግሞ፣ ልቆ ሊገኝ አይችልም። የሁሉ ኢትዮጵያዊ አኩሪ ገድልና ጀግንነት በኢትዮጵያ የታሪክ ማህደር ውስጥ ተመዝግቦ ይቀመጣል እንጂ ከኢትዮጵያ ጋር በፍጹም አይወዳደርም። ምክንያቱም ኢትዮጵያ ለኢትዮጵያውያን በዚህ ዓለም ካሉ ነገሮች ሁሉ ልቃ የምትገኝ ውድ ነገር ናትና።

ይሁንና የኢትዮጵያ ታላቅነት እውን ሆኖ የሚቀጥለው ደግሞ መላ ዜጎቿ ለዚህ ስምና ደረጃ በሚመጥን መልኩ ሲንቀሳቀሱና ለታላቅነቷ ሲታትሩ ብቻ እንደሆነ ደግሞ ሊዘነጋ አይገባም። ይህ እውን የሚሆነው ለእውነት በመቆም፣ አሉባልታን በመጠየፍ፣ ለሥራ በመትጋትና ለሉዓላዊነቷ ሳያወላውሉ በመቆም ብቻ ነው!

Page 6: ሰኞ ከ 27 ዓመታት የልማት ዘፈንና ፉከራ በኋላ ... · 2021. 2. 1. · ገጽ 4 በውስጥ ገጾች ገጽ 11 ሰኞ ብዕራችን ለኢትዮጵያ

አዲስ ዘመን ሰኞ ጥር 24 ቀን 2013 ዓ.ምገጽ 6

ማረፊያ

ዓለም አቀፍ

‹‹ሞንታርቦ››ው

89 በመቶ ስኬታማ የሆነው የኖቫቫክስ ክትባትዋለልኝ አየለ

በሀገረ እንግሊዝ እየተመረተ ያለው የኖቫቫክስ ክትባት 89 በመቶ ስኬታማ መሆኑን ባለፈው ቅዳሜ አልጀዚራ ዘግቧል። ክትባቱ የክሊኒካል ቤተ ሙከራ ሂደቱን አልፏል። ከሁለት እስከ ሦስት ባሉት ወራት ውስጥ ፈቃፍ አግኝቶ ሙሉ የክትባት መድኃኒት ይሆናል ተብሎም ይጠበቃል ። በምርምሩ የተሳተፉት የህክምና ባለሙያዎች እንዳሉት ክትባቱ የኮሮና ቫይረስን የመተላለፍ ሂደት የሚቀንስ ነው።

የኖቫቫክስ ክትባት ከፊል ሙከራዎች የተካሄዱት አዲስ የኮሮና ቫይረስ ዝርያ እያስጨነቃት ባለችው ደቡብ አፍሪካ ነው። 60 በመቶ ስኬታማ መሆኑ የተረጋገጠውም እዚያው ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ነው።

የኖቫቫክስ ካምፓኒ በስድስት አካባቢዎች የመዲሃኒት ፋብሪካዎች እንደሚኖሩት ተናግሯል። የት የት እንደሚሆኑ ግን ለጊዜው አልተገለጸም። መድኃኒቱን ለማምረት ከሰባት አገራት የተውጣጡ ስምንት የዕፅዋት አይነቶችን ለመቀመሚያነት ተጠቅሟል። በዓመት ሁለት ቢሊዮን ዶዝ ክትባት እንደሚያመርትም ተገልጿል።

ወደፊት የሚሻሻልና የሚቀየር ነገር መኖሩንም አመልክቷል። ለክትባቱም በዩናይትድ ኪንግደም ዕድሜያቸው ከ18 እስከ 84 የሚሆኑ 15 ሺህ ያህል ሰዎች ተመዝግበዋል።

ኖቫቫክስ አሁን ላይ ከአሜሪካ የምግብና

የመድኃኒት አስተዳደር እና ከሌሎች አካላት ጋር ውይይት እያደረገ ሲሆን ፣ ክትባት ከዚህ በፊት በተለያዩ አገሮች ተመርተው ውጤታማ ከሆኑ መድኃኒቶች ጋር ተቀራራቢ ነው ተብሏል።

አሁንም በተለያዩ የዓለም አገራት የኮሮና ቫይረስ ክትባት ሙከራ እየተደረገ ነው። በአንዳንድ አገሮችም ክትባቱ እየተሰጠ ነው። ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ሙሉ ክትባት ሲሰጥ

አልታየም እንጂ አገራት ክትባት አገኘን ማለት የጀመሩት ገና ኮሮና እንደገባ ጀምሮ ነው። ወዲህ ደግሞ አዳዲስ የኮሮና ቫይረስ ዝርያ ተገኘ እየተባለ ሌላ ጭንቀት ውስጥ እየተገባ ነው።

ዘካርያስ ዶቢ

መሥሪያ ቤቴ በአዲስ አበባ ከተማ አንድ ዋና መንገድ ላይ ነው። ሁለተኛ ፎቅ ላይ በስራ ተጠምጃለሁ። ከዋና ጎዳናው ከወትሮው ወጣ ያለ ድምጽ ሰማሁ፤የማስታወቂያ ወይም የጥሪ ድምጽ ነው። በዚያውም ልፍታታ ብዬ ለስራዬ ውል አብጅቼለት በመስኮት ቁልቁል መመልከት ጀመርኩ።

ለወትሮው እንዲህ ያሉ ማስታወቂያዎች በተሽከርካሪ ላይ ትላልቅ ድምጽ ማጉያዎች ተጭነው የሚከናወኑ ናቸውና ተሽከርካሪ መፈለግ ጀመርኩ። ይህን መልዕክት ለማስተላለፍ በሚል የተዘጋጀ አንድም መኪና ማግኘት አልቻልኩም። አሁንም ፍለጋዬን በርቀት ጭምር ወደ ግራም ወደ ቀኝም እያደርግሁ ቀጠልኩ።

በመሀል ያ ድምጽ ተመልሶ መጣ። ድምጹ የሚወጣበትን አካባቢ ለየሁ። አንድ ሰው ድምጽ ማጉያ ይዞ አንዴ ወደኋላ ሌላ ጊዜ ወደፊት ወደጎን እያለ እየተናገረ ነው። ስፒከር ግን አጠገቡ የለም፤ ይህ ድምጽ ያለ ግዙፍ ስፒከር እንዴት እንዲህ ሊሰማ ቻለ ብዬ አሁንም አካባቢውን መቃኘት ውስጥ ገባሁ። ወዲያው አንድ ለየት ያለ ሰው ተመለከትኩ። ያ ሰው በጭንቅላቱ ላይ ትልቅ ስፒከር/ሞንታርቦ/ ተሸክሞ ዋየርለስ መነጋገሪያ የያዘውን ሰው ይከተለዋል።

ይህን ጉድ ተመልከቱ ብዬ አጠገቤ የሚገኙትን ባልደረቦቼ አስነስቼ አሳየኋቸው። ሰዎቹ ማስታወቂያውን መኪና ተከራይተው ማስነገር ለብዙ ወጪ ሊዳርጋቸው እንደሚችል አስበው ሊሆን ይችላል ይህን ያደረጉት። ምናልባትም ይህን አይነቱ መልዕክት የማስተላለፊያ መንገድ ተመራጭና ተደማጭ ያደርገናል ብለውም ይሆናል።

ጎበዝ ለእኛ ለአድማጮቹ ማዘን ከቀረ ቆይቷል። የድምጽ ብክለት እየተባለ ብዙ ቢወራም፣የመጣ ለውጥ ግን የለም። የእነዚህ ሰዎች መልዕክት ማስተላለፊያ መንገድ

ደግሞ ወጣ ያለ ነው። ድምጽ ማጉያውን የተሸከመው ሰው ጆሮ የሰው ጆሮ አይደለም እንዴ?

በዚህ ላይ ሌሎች ጎጂ ነገሮች በሰውየው ላይ ሊደርሱ አይችሉም ወይ? የሰውዬውን ሁኔታ ስመለከተው ለእዚህ ሥራ በኪራይ የተገኘም አይደለም፤በቀጥታ ማስታወቂያውን ከሚሰሩት አንዱ ነው፤ቁመናው ያስታውቃል። በኪራይ የተገኘ ሰውስ ቢሆን ለምን በዚህ አይነት ሁኔታ ውስጥ እንዲሰራ ይደረጋል። ይህ በጣም የሚያሳስብ ጉዳይ ነው። ለጆሮው እንኳ አለመታሰቡ ምን ይባላል?

ሞንተርቦ መንፈሳዊው፣ አለማዊው ጥሪ ይተላለፍበታል፤የንግዱ ማስታወቂያ በዓይነት ዓይነት ይነገርበታል፤ሰው ታመመብን ለውጪ ሀገር ህክምና እርዱን ባሉ ድጋፍ ይሰበሰብበታል፤ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ጥሪ ይቀርብበታል። አሁን አሁንማ ባንኮችም ድንኳናቸውን ተክለው ቆጥቡ ይሉበታል። ደም ለግሱ ይባልበታል፤ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ግዙን ይሉበታል። እነዚህ ከብዙ በጥቂቱ አገልግሎቶቹ ናቸው።

ጥሪው ወይም ማስታወቂያ በግልጽ መኪኖች /በፒክ አፕ፣በአይሱዙ /፣ በሚኒባሶች፣ ወዘተ. በየጎዳናው፣ በየአደባባዩ፣በየገበያው ስፍራ ፣ወዘተ ይተላለፋል። ትላልቅ መድረኮች ሳይቀሩ ይካሄዱበታል። የማስታወቂያና መልዕክት ማስተላለፊያ መሳሪያ በመሆን በስፋት እያገለገለ ባለው ሞንታርቦ።

በእርግጥ መልዕክት ለማስተላለፊያ ፣ለማስታወቂያ .ወዘተ አንጀት አርስ ነው። አልሰማም ያለውን ጭምር አንዲሰማ ማድረግ ይቻላል። በሞንታርቦ ጥሪ እየተላለፈ ነው፣ትምህርትና ሰበካ እየተካሄደ ነው ከተባለ ጥሪው ከፍ ያለ ነው። ሞንታርቦ በራሱ ብቻ ብዙ ወጪን ስለሚጠይቅ። አሁን አሁን ራሱን የቻለ የማስታወቂያ ስራ በመሆን ብዙዎችን እንጀራ በቅጡ እያበላም ይመስለኛል። መልካም ነው።

መልዕክት ወይም ጥሪ በደረቁ ማስተላለፍ

የተፈለገውን ያህል ውጤታማ ሊያደርግ አይችልምና ማስታወቂያንና ትምህርትን እያጀቡ በዚህ አይነቱ መንገድ ማስተላለፍ ውጤታማ አያደርግም ተብሎ አይታሰብም።

በሀገራችን ማስታወቂያ ማስነገሪያና መልዕክት ማስተላለፊያ መንገዶች እንደ የዘመኑ ይለያያሉ። ጥሩምባ በማሰማት መልዕክቴን ስሙኝ ሲባል ተኖሯል። ይህ ብዙ ዘመናትን ቢያስቆጥርም ህያው ነው። በአብዛኛው እድሮች ለቀብር ጥሪ ይጠቀሙበታል፤ለስብሰባ እና ለተለያዩ የሥራ ዘመቻዎች ጥሪ ሲደረጉበትም ይስተዋላል።

መልዕክት ማስተላለፊያው ወይም ጥሪ ማድረጊያው መንገድ እየተሻሻለ መጥቶ የድምጽ ማጉያዎች /ሜጋ ፎኖች / ጥቅም ላይ ውለዋል። እነዚህ በባትሪ ድንጋይ የሚሰሩ ሜጋ ፎኖች ማስታወቂያ ለመንገርም ሆነ ጥሪ ለማስተላለፍ ሲያገለግሉ ቆይተዋል፤አሁንም እያገለገሉ ይገኛሉ። በተለይ እየተዘዋወሩ መልእክት ለማስተላለፍ በእጅጉ ጠቅመዋል።

ቴፕ ሪከርደሮች በፈጠሩት ምቹ ሁኔታ ድምጽን በካሴት በመቅረጽ መልዕክት እንዲተላለፍ ሲደረግም ቆይቷል። የቴፕ ሪከርደሮቹ የድምጽ ማጉያ ለእዚህ አይነቱ ስራ ምቹ በመሆኑ ማስታወቂያን በተለያዩ ሙዚቃዎች እያጀቡ ለማቅረብ ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል።

አሁን ደግሞ ግዙፍ ድምጽ ማጉያዎች ይህን ሥራ ተረክበውታል። ድምጽ ማጉያዎችን ህዝብ በብዛት በሚተላለፍባቸው ቦታዎች፣በስብሰባ አደራሾች፣ጎዳናዎች ወዘተ. ላይ በማስቀመጥ መልዕክት የማስተላለፍ ማስታወቂያ የማስነገር ስራዎች ተለምደዋል። በተሽከርካሪዎች ላይ ግዙፍ ድምጽ ማጉያዎችን/ሞንታርቦ / በመጫን አካባቢዎችን ድብልቅልቅ በማውጣት ያም ያም የሚተላለፈውን መልዕክት በግድ ጭምር እንዲሰማ ማድረግ ውስጥ ተገብቷል።

ድምጽ ማጉያዎቹ ሰዎች እንዲደማመጡ ምንም አይነት እድል አይሰጡም፤ሰዎች ሳይወዱ በግድ ውይይታቸውን ጭውውታቸውን ያቋርጣሉ። በምትኩ ድምጽ ማጉያዎቹ የጎረሱትን መልዕክት ወይም

ማስታወቂያ በየሰው ጆሮ ይሰዳሉ። ሳይወዱ በግድ እንዲሰሙ ያደርጋሉ።

ሰዎች በመኪና ላይ ሆነው በተዘጋጀላቸው ድምጽ ማጉያ በመጠቀም ጥሪ ያስተላልፋሉ፤አለዚያም የተቀረጸ መልዕክት በድምጽ ማጉያው በመጠቀም ያስተላልፋሉ። መኪናዎቹ ጀነሬተር ይጫንባቸዋል፤ ትላልቅ ስፒከሮች ይደረጉላቸዋል። ይህም የዘመኑ የተለመደ የማስታወቂያ ማስነገሪያና መልዕክት ማስተላለፊያ መንገድ ሆኗል።

ድምጽ ማጉያዎቹ እንደ አቅም እንዳቅም ተደርገውም ተሰርተዋል። የበረሮ መድኃኒት ሻጭ ነኝ የሚለው የሆነ ጥግ ላይ ሆኖ መድኃኒቱን ግዙኝ ይልባቸዋል። በአንድ ወቅት አንድ የበረሮ መዳህኒት ሻጭ መልዕክቱን ሲያስተላልፍ ከዚህ መኪና ላይ መድኃኒቱን ያገኛሉ ሲል ሰምቼ ዞር ስል ግዙኝ ባዩ ሰውዬና ድምጽ ማጉያው ብቻ ነበሩ በስፍራው ያሉት፤መኪና የለም። መልዕክቱ የተዘጋጀው በመኪና ለሚደረግ ሽያጭ ብቻ ነው።

በመኪና ወይም በተለያየ መንገድ ሰዎችን በሚረብሽ መልኩ በትላልቅ ድምጽ ማጉያዎች በየመንገዱ ማስታወቂያዎች መልቀቅ እንዲሁም መልዕክት ማስተላለፍ በድምጽ ብክለት የሚያስጠይቅ ቢሆንም፣እነ እከሌ ተጠየቁ ሲባል ግን አይሰማም። ይህ ቢሆን ኖሮ እንዲህ ቅጥ ባጣ መልኩ ባልተስፋፉ ነበር። ማስታወቂያዎቹ በህዝብ ፣በተለያዩ መስሪያ ቤቶች ትምህርት ቤቶች ላይ ሊያስከትሉ የሚችሉት ረብሻ ማንም እንደሚረዳው ቢታወቅም እነሱን የደረሰባቸው ግን የለም።

ይሄ ችግር ሄዶ ሄዶ የደረሰበትን ደረጃ እያየን ነው። ግዙፍ ድምጽ ማጉያ ሰው እያሸከሙ ማስታወቂያ እስከ ማስነገር መልዕክት እስከማስተላለፍ የደረሰው ተግባር በሰዎች ጤና ላይ ሊያደርስ የሚችለው አደጋ ለምን ሊታይ አልቻለም። ዛሬ ሰውን ሞንታርቦ አሸክመው ማስታወቂያ ያስነገሩ ሰዎች፣ነገ ለሞንታርቦው ሀይል የሚለግሰውን ጀነሬተር አሸከመው አያስከትሉም ተብሎ አይታሰብና ጉዳዩ ይታሰብበት እላለሁ!!

Page 7: ሰኞ ከ 27 ዓመታት የልማት ዘፈንና ፉከራ በኋላ ... · 2021. 2. 1. · ገጽ 4 በውስጥ ገጾች ገጽ 11 ሰኞ ብዕራችን ለኢትዮጵያ

አዲስ ዘመን ሰኞ ጥር 24 ቀን 2013 ዓ.ም ገጽ 7

ገበያና ግብይት

ኢኮኖሚ

የምድር በረከትኢትዮጵያ ወርቅ፣ፕላቲኒየም፣ኒኬልና ታንታለምን

የመሰሉ የማዕድን ሃብት እንዳላት በታሪክ የሚታወቅ ቢሆንም የማዕድን ዘርፉ ግን ገና ብዙ እንዳልተሰራበትና ለሀገር ኢኮኖሚያዊ እድገት የሚጠበቅበትን አስተዋፅኦ እያበረከተ እንዳልሆነ ከኢትዮጵያ ማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር በተለያዩ ግዚያት የወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ።

እ.ኤ.አ በ2014 ሃገሪቱ ከማዕድን የወጪ ንግድ 541 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ያገኘች ቢሆንም እ.ኤ.አ ከ2015 አስከ 2019 ባለው ግዜ ውስጥ ከማዕድን የወጪ ንግድ የሚሰበሰበው ገቢና ለዓመታዊ የተጠራ ሀገራዊ ምርት የሚያበረክተው አስተዋፅኦ እየቀነሰ ስለምጣቱ ይኸው መረጃ ይጠቁማል።

እ.ኤ.አ በ2013/14 የዘርፉ ዓመታዊ እድገት 3 ነጥብ 2 ከመቶ ነበር። እ.ኤ.አ በ2014/15 ግን ወደ 25 ነጥብ 6 በመቶ ከፍ ማለት ችሏል። ይሁን እንጂ በዚሁ አልቀጠለም። ይልቁንም አሽቆለቆለ እንጂ። እ.ኤ.አ በ2015/16 ወደ 3 ነጥብ 3 በመቶ መውረዱ በመረጃው ተመላክቷል።

እ.ኤ.አ በ2016/17 29 ነጥብ 8 ከመቶ፣እ.ኤ.አ በ2017/18 ደግሞ 20 ነጥብ 8 በመቶ እንደነበር የጠቀሰው መረጃው እ.ኤ.አ በ2018 የማዕድን ዘርፉ ለዓመታዊ የተጠራ ሀገራዊ ምርት ያለው አስተዋፅኦ እ.ኤ.አ በ2013 ከነበረው 9 ነጥብ 1 ከመቶ ወደ 1 ከመቶ ማሽቆልቆሉን አመልክቷል። በ2011/12 ከማዓድን ዘርፉ ከ600 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ ለማግኘት ታቅዶ የተገኘው 618 ሚሊዮን ዶላር መሆኑን መረጃው ጠቅሷል።

ሃጋራዊ ለውጡን ተከትሎ የማዕድን ዘርፉ ለሃገሪቷ ኢኮኖሚ የሚያበረክተውን አስተዋፅኦ ከፍ ለማድረግና የውጪ ምንዛሬ ግኝትን ለማሳደግ ጥረቶች በመደረግ ላይ ናቸው። በዚህም መነሻነት በዘንድሮው በጀት ዓመት የመጀመሪያው ስድስት ወር ከማዕድን ወጪ ንግድ

አስናቀ ፀጋዬ

በተለይ ደግሞ ከወርቅ ማዕድን ከፍተኛ ገቢ መገኘቱን ነዳጅና ማዕድን ሚንስቴር አስታውቋል።

የነዳጅና ማዕድን ሚንስቴር ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክ ተር ወይዘሮ ፍሬሕይወት ፍቃዱ እንደሚገልፁት ከማዕድን ወጪ ንግድ ውስጥ በዋናነት የሚጠቀሰው ወርቅ ቢሆንም እምነበረድ፣ የከበሩ ማዕድናትና ሌሎች የኮንስትራክሽን ማዕድናት በወጪ ንግድ ውስጥ የተካተቱ የገቢ ማስገኛ ምንጮች ናቸው። በዚሁ መሰረትም በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ስድስት ወር ውስጥ ከአጠቃላይ የማዕድን የወጪ ንግድ 339 ነጥብ 5 የአሜሪካን ዶላር ገቢ ተገኝቷል።

ለውጭ ገበያ ከቀረቡት ማዕድናት ወርቅ 335 ነጥብ 54 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በማስገኘት ከፍተኛውን ድርሻ ይዟል። ኤመራልድ፣ ሳፋየርና ኦፓል ከተሰኙ

የከበሩ ማዕድናት የወጪ ንግድ ደግሞ 3 ነጥብ 9 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ተገኝቷል። ለኮንስትራክሽን(ግንባታ) ግብዓት የሚውሉ ማዕድናት በአብዛኛው ለሀገር ውስጥ ገበያ የቀረቡ በመሆናቸው በወጪ ንግዱ ከተገኘው አጠቃላይ ገቢ ጋር የሚጠቃለል እንዳልሆነ ወይዘሮ ፍሬህይወት ተናግረዋል።

እንደ ዳይሬክተሯ ገለፃ የወርቅ ማዕድንን የብሔራዊ ባንክ ገዝቶ ለዓለም ገበያ የሚያቀርብ ሲሆን፣ ሌሎቹ የከበሩ ማዕድናት ግን በአብዛኛው የላኪነት ፍቃድ በተሰጣቸው ድርጅቶች አማካኝነት ወደ አውሮፓ፣እስያና አሜሪካ ሃገራት ይላካሉ። ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ጊዜ ጋር የወጪ ንግዱ ሲነፃፀር የአሁኑ የስድስት ወር አፈፃፀም በጣም ከፍተኛ ሆኖ ተገኝቷል። ኦሮሚያ፣ ጋምቤላ፣ ቤንሻንጉል ደቡብ ብሄሮች፣ብሄረሰቦችና

‹‹በውጪ ሀገር የደከምኩበትን ጉልበት ግማሹን ያህል በሀገሬ ላይ ብሰራ ምንያክል ውጤታማ መሆን እንደምችል ስለተረዳሁ ነው ወደ ሀገር ቤት የመጣሁት። እዚህም ከመጣሁ በኋላ ምን ብሰራ የት ቦታ ብሰራ ያዋጣኛል የሚል መጠነኛ ጥናት አደረኩ ። ብዙ የሥራ ቦታዎችንም ተመልክቻለሁ። ሆኖም ግን በአንዳንድ አካባቢዎች ተመሳሳይ የሆኑ ስራዎች ናቸው የሚበዙትና የሚሰሩት ። ለምሳሌ አንድ ሰው የጀበና ቡና ለመነገድ ሥራ ከጀመረ ሌላውም በቅርብ ቦታ ላይ ተመሳሳይ ሥራ ይጀምራል። አንድ አይነት ሥራ በአንድ አካባቢ ላይ ሲኖር ተጠቃሚዎች አማራጭ ስለሚያገኙ ጥሩ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን በአንድ አካባቢ ላይ ተመሳሳይ ሥራ ከበዛ ደግሞ በስራው ላይ ለተሰማራው አካል የገበያ እጥረት ይፈጠራል።ስለዚህ ይሄንን ግምት ውስጥ ባስገባ መልኩ ነው ለንግድ የሚሆን አካባቢና የምነግደውን ስራ መወሰን የቻልኩት›› ትላለች ወይዘሪት ጸሀይ ታሪኩ።

ወጣት ፀሀይ ለረጅም ዓመታት የስራ ቦታዋን ያደረገችው ግብጽ ሀገር ነበር። እዛ በነበረችበት ወቅት ቀን ቀን በቤት ሠራተኛነት እየዋለች ማታ ደግሞ ከሌሎች አራት ጓደኞቿ ጋር ሆነው በተከራዩት ቤት ኑሮን ይገፋሉ ። በዚህ ሁኔታ ስምንት ዓመታትን አሳልፋለች። የ12ኛ ክፍል ትምህርቷን አጠናቅቃ ወደ ግብጽ ከመሄዷ በፊት ግን የነበራት ዓላማ በከፍተኛ የትምህርት ተቋሟት መግባትና መማር ነው። ሆኖም ግን በወቅቱ በ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ያገኘችው ውጤት ለዚህ ብቁ ስላላደረጋት ምርጫዋን ወደ ውጪ ሀገር መሄድና ሰርቶ ገንዘብ ማግኘትን አድርጋለች ። በዚሁ መሰረት ግብጽ ሀገር ሰው ቤት ሰርታ ያገኘችውን ገንዘብ ቋጥራ ወደ ሀገሯ ተመለሰች።

ወጣቷ ታዲያ ቀድሞውንም ቢሆን ራስን መቻል፣ ሰርቶ መለወጥ ወይም ተምሮ ትልቅ ደረጃ መድረስ

በጋዜጣው ሪፖርተር የሚል ውስጣዊ ፍላጎትና ምኞት አላትና ለፍታና ሰርታ ባገኘችው ገንዘብ መገናኛ አካባቢ የህጻናት ልብስ መሸጫ ሱቅ ከፈተች።

የንግድ ስራ ጠንካራ መሆንን ይጠይቃል። ስልቹ ሰው፣ ደከመኝ የሚል፣ ጊዜውን ከስራው ውጪ የሚያባክን ነጋዴ መሆን አይችልም። ንግድ ሙሉ ጊዜን ይጠይቃል። ጠንካራ ሰራተኛ የሆነ ሰው ደግሞ ውጤታማ ይሆናል፤ በአጭር ጊዜም ያድጋል ትላለች ። ነገር ግን ብዙ ሰዎች ንግድ መነገድ ይፈራሉ ምክንያቱም መጀመሪያ አካባቢ ደንበኛ እስኪኖር እና ሰዎችም ቤቱን እስኪያውቁና እስኪለምዱት ድረስ ኪሳራ አለው።ወጪ እንጂ ገቢ አይታሰብም። ስለዚህ እከሌ ከስሮ ነው ከንግድ የወጣው ሲሉ ይሰማል።

አንድ ሰው አንድ ንግድ ቤት ሲከፍት የመጀመሪያውን ዓመት የስራ መለማመጃና የኪሳራ እንደሚሆን አውቆና አምኖ መሆን አለበት ። እሷም ይሄንን ሥራ ስትጀምር በዚሁ ሂሳብ ነው። ገበያ ሳይኖርም የቤት ኪራይ መክፈል የግድ ነው። ሌሎች ሌሎች መንግሥታዊ ወጪዎችም ይቀጥላሉ። ‹‹መገናኛ አካባቢ ያሉ ቤቶች ኪራይ ውድ ናቸው። ስለዚህ ቢያንስ ለአንድ ዓመት የቤት ኪራይ ያለ ሥራ ልከፍል እንደምችል አምኜ ለዚህም የሚሆነኝን ጠቀም ያለ ገንዘብ አዘጋጅቼ ነው ሥራ የጀመርኩት ። በእኔ ሥራ ዛሬ እሁድ ነው፤ በዓል ነው፤ መሸ ብሎ መዝጋት አይቻልም። ምክንያቱም ብዙ ገበያተኛ የሚመጣው ከስራ ሰዓት ውጪ አመሻሽ ላይ ነው። በእረፍት ቀን ቅዳሜና እሁድ ነው የልጆች ልብስ ለመግዛት፣ ለልደትና አራስ ለመጠየቂያ ልብስ ለመግዛት ሸማቾች የሚመጡት።ስለዚህ ሁልጊዜ ሱቄ ክፍት መሆን አለበት። ››ትላለች ያለ እረፍት እየሰራች መሆኗን ስትገለጽ።

ወጣት ጸሀይ እንደምትለው፤ የሱቅ ሥራ ብዙውን ጊዜ ከባድ የሚሆነው ለብቻው ለሚሰራ ሰው ነው። አሁን ባለሁበት ሁኔታ ሠራተኛ ለመቅጠር አቅም

የለኝም። ስለዚህ እቃ ማቅረቡንም ሱቅ መክፈትና መሸጡንም ማታ ማምሸቱንም ሁሉ ችዬ እሰራለሁ። አጋዥ ሰው ቢኖር በጣም ጥሩ ነው። አንድ ሰው ዕቃ ለማምጣት ገበያ ሲሄድ ሌላው ሰው ደግሞ ሱቅ ሳይዘጋ ሽያጩን ያከናውናል። በዚህ መልኩ ውጤታማ መሆን ይቻላል። አንድ ሰው ብቻውን ሁሉንም ሥራ ራሱ ብቻ የሚሰራ ሲሆን ግን ትንሽ ይከብዳል። ቢሆንም ግን በሰው አገር ከመልፋት በሀገር ላይ እንደመስራት የሚያስደስት ነገር የለም ።

ብዙ ወጣቶች ከሀገራቸው የሚወጡት በውጪ ሀገር የተሻለ ገንዘብ ለማግኘት በማሰብ ነው። ነገር ግን በሀገር ውስጥ ወጣቱ የብድር አገልግሎት የስራ መነሻ ገንዘብ ማግኘት ከቻለ በሀገር ውስጥ እንደመስራት የሚያስደስት ነገር የለም በማለት ነው ጠንክሮ በሀገሩ ተሯሩጦ የሚሰራ ሰው ውጤታማ እንደሚሆን ወጣት ፀሀይ የተናገረችው ።

የመገናኛ አካባቢ ሳምንቱን ሙሉ አመሻሹ ላይ ከፍተኛ በሆነ መልኩ የጎዳና ላይ ንግድ ደርቶ ይታያል። ከአዋቂ እስከ ህጻን ፣ የሴት እና የወንድ አልባሳት፣ የህፃናት መጫወቻ ሳይቀር በየአይነቱ ሽያጩ የሚደራበት ነው። አላፊ አግዳሚውም በአጋጣሚ ያየውን ያጋጠመውን ሁሉ እየሸመተ ያልፋል። ይሄ በህጋዊ ነጋዴዎች ላይ ትልቅ ጫናን የሚያስከትል መሆኑን ወጣት ፀሀይ ትናገራለች።

የጎዳና ላይ ንግድ በሱቅ ውስጥ ከሚሸጡ ልብሶች በጥራትም በዋጋም ያንሳል።ሆኖም ግን ሰዎች የዋጋውን መቀነስ ብቻ አይተው ይገዛሉ። በሌላ መልኩ ደግሞ በሱቅ ላይ የሚገኙ ልብሶችም ቢሆኑ ጎዳና ላይ ሲሸጡ ዋጋቸው ዝቅተኛ ነው።የዚህ ዋናው ምክንያት የጎዳና ነጋዴዎች የቤት ኪራይ የለባቸውም። ከመንግሥት ግብርም ሆነ ሌሎች ወጪዎችን አይጠየቁም ።በዚህ ምክንያት ከህጋዊ ነጋዴው ባነሰ ዋጋ ይሸጣሉ። ይሄ ደግሞ ፍትሀዊ ውድድር እንዳይኖር ከማድረጉም ሌላ

ህጋዊው ነጋዴ ገበያ በማጣት እንዲከስር ያደርገዋል። ስለዚህ ሁሉም ሰው ተወዳድሮና ሰርቶ የልፋቱን ተጠቃሚ እንዲሆን ህጋዊ መስመሩን መከተል አለበት ስትል መልዕክቷን አስተላልፋለች።

ህዝቦች፣ትግራይ ክልሎች የወርቅ ማዕድን ወደ ብሔራዊ ባንክ በመላክ በዋናነት ይጠቀሳሉ።

የከበሩ ማዕድናትን በተለይ ኦፓል ለውጪ ገበያ በማቅረብ ደግሞ የአማራ ክልል ሰፊ ድርሻ ይዟል። ሳፋየርና ኤመራልድ ማዕድናትን ለውጪ ገበያ በማቅረብ ደግሞ ኦሮሚያ ክልል ተጠቃሽ ነው። የባለፈው ዓመት የአንድ ዓመት የወጪ ንግድ አፈፃፀም 207 ነጥብ 8 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር አካባቢ ነበር። ሆኖም በዘንድሮው በጀት ዓመት በስድስት ወር ብቻ የተሻለ አፈፃፀም ማስመዝገብ ተችሏል። በስደስት ወር ብቻ የ 140 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ልዩነት እንዳለውም አመልክተዋል።

ከማዕድን የወጪ ንግድ የተገኘው ገቢ ከአምናው ጋር ሲነፃፀር የዘንድሮው ከፍ ሊል የቻለውም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ የወርቅ ዋጋን በማሻሻሉ አንዱ ምክንያት ሲሆን፣ሌላው የዓለም አቀፍ የወርቅ ዋጋ መጨመር ለወጪ ንግድ ገቢው ከፍተኛነት አስተዋፅኦ አድርጓል። የኮንትሮባንድ ንግድ እንዲቀንስ የተሰሩ ስራዎችም ለገቢው ማደግ የራሳቸውን ሚና ተጫውተዋል። በዚህ በኩል የተሰራው ሥራ በሰዎች እጅ ያሉ ወርቆች በተለይ በድምበር አካባቢዎች በአብዛኛው ወደ ብሔራዊ ባንክ እንዲገቡ ለማድረግ አግዟል።

ዋና ዳይሬክተሯ እንደሚሉት ሚኒስቴር መሥሪያቤቱ ከወርቅና ከሌሎች የማዕድን ሃብቶች ወጪ ንግድ አሁን ከተገኘው በላይ ገቢ ለማግኘት የዕቅድ ክለሳ በማድረግ ወደተግባራዊ እንቅስቃሴ ገብቷል። በተለይ ደግሞ ከወርቅ ውጪ ባሉ ሌሎች የከበሩና ከፊል የከበሩ ማዕድናት የወጪ ንግድ የተሻለ ገቢ እንዲያስገኙ ጥረት እየተደረገ ሲሆን፣ለዚህም የማዕድን እምራቾችንና ገዢዎችን የሚያገናኙ የገበያ ማዕከላት በመገንባት ላይ ናቸው። ሚንስቴር መስሪያ ቤቱ በቀጣይ ከክልሎች ጋር ያለውን ግንኙነት ይበልጥ በማጠናከር፣የክትትልና ድጋፍ ስራዎችንም በማከናወን በዘርፉ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ከመቼውም ጊዜ እየተንቀሳቀሰ ነው። የተዘጉ የወርቅ ኩባንያዎችን ለመክፈትም በሂደት ላይ ይገኛል። እነዚህ ሁሉ እርምጃዎች ከወርቅ ማዕድን የወጪ ንግድ የሚገኘውን ገቢ ለማሻሻል የበለጠ ያግዘዋል።

ያንሰራራው የማዕድን ወጪ ንግድ

ንግድ - አክሳሪም ፤ አትራፊም

ፍትሀዊ የሆነ የንግድ ውድድር እንዲኖርና ሁሉም የልፋቱን ያህል ተጠቃሚ እንዲሆን ህገወጥ የጎዳና ላይ ንግድ

መቆም አለበት፤

በስድስት ወራት ከወርቅ የወጪ ንግድ ከ335 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ ገቢ ተገኝቷል፤

Page 8: ሰኞ ከ 27 ዓመታት የልማት ዘፈንና ፉከራ በኋላ ... · 2021. 2. 1. · ገጽ 4 በውስጥ ገጾች ገጽ 11 ሰኞ ብዕራችን ለኢትዮጵያ

ዳንኤል ዘነበ

በየትኛውም የዓለማችን ክፍል በባህላዊም ሆነ በዘመናዊ መንገድ የሚሰጡ ትምህርቶችን ውጤትና የተማሪዎች የዕውቀት ጥግ ለመለካት ምዘና ማካሄድ የተለመደ ጉዳይ ነው። በተለይ በዘመናዊ የትምህርት ስርዓት ውስጥ የትምህርት ምዘና ከመማር ማስተማሩ ሂደት ጎን ለጎን በእኩል ዓይን ይታያል። የተለያዩ ሀገራት በፈተና/ምዘና ስርዓት ሂደታቸው ላይ የተለያዩ የልኬት ደረጃና የምዘና ዘዴ የሚጠቀሙ ሲሆን፤ ኮምፒዩተርን መሰረት ያደረገ የፈተና እና የምዘና ስርአትን በስፋት አገልግሎት ላይ እየዋለ ይገኛል።

በአብዛኛው የዓለማችን ክፍል የሚጠቀምበት ወረቀትና እርሳስን መሠረት ያደረገውን የፈተና ስርዓት ነበር። የኢንፎርሜሽንና ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ለዘመናዊው የማህበረሰብ ግንባታ ዋነኛው አማራጭ ሆኖ መጥቷል። ይሄንኑ ተከትሎ በትምህርት ዘርፍ ተራማጅ ውጤት ለማምጣት አጋዥነቱ ጎልቶ የሚጠቀሰው የኢንፎርሜሽንና ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ አንዱ ክፍል ወደ ሆነው ኮምፒዩተርን መሰረት ወዳደረገው የፈተና እና የምዘና ስርአት ተሸጋግሯል። ኮምፒዩተርን መሠረት ያደረገ የፈተናና የምዘና ሥርዓት ከአራት አስርት ዓመታት በላይ በተለያዩ መልኮች ጥቅም ላይ ሲውል ቆይቷል።

የሀገራት ተሞክሮ በዓለም አቀፍ ደረጃ በስፋት ተቀባይነት ከማግኘት

ባሻገር በስፋት እያገለገለ በሚገኘው ኮምፒዩተርን መሰረት ባደረገ የፈተና ስርዓት በርካታ ሀገራት ውጤታማ ሆነዋል። ከሀገራችን ነባራዊ ሁኔታ አንፃር ቀረብ ሊሉ የሚችሉትን እንደ ናይጄሪያ፣ ግብጽ፣ ኢንዶኔዥያ ያሉ ሀገራት ኮምፒዩተር ላይ የተመሠረተ ፈተና በመጠቀም ተማሪዎቻቸውን በመመዘን እጅግ የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ የቻሉ በመሆን ረገድ ይጠቀሳሉ። እነዚህ ሀገራት ኮምፒዩተር ላይ የተመሠረተ የፈተና ስርዓትን ለመገንባት ያለፉበትን ተሞክሮ ሀገሮቹ ከኢትዮጵያ ጋር ተመሳሳይ ወይም ተቀራራቢ የህዝብ ብዛት፣ የመሠረተ ልማት ግንባታ እና የምጣኔ ሀብት ደረጃ ያላቸው

አዲስ ዘመን ሰኞ ጥር 24 ቀን 2013 ዓ.ምገጽ 8

ማህደረ ጤና

ማህበራዊ

አስኳላሪፎርም የሚሻው የፈተና ስርዓት

የአጥንት መሳሳት ችግርና ህክምናው

ናቸው። በተጨማሪም እንደ ጆርጂያ፣ ፊንላንድ፣ ሆላንድ እና ፈረንሳይ የመሳሰሉ የበለፀጉ ሀገራት ተሞክሮ፤ ኮምፒዩተር ላይ የተመሠረተ ፈተና ስርዓትን መዘርጋት መቻል ያለውን ፋይዳ ያመላክታል።

የሀገራችንን የፈተና ስርዓት የማዘመን ሂደት በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የተማሪዎች ምዘና ስርዓት

ባህላዊ ነው። በሀገራችን ተግባራዊ እየተደረገ የሚገኘው ባህላዊ የፈተና ስርዓት እጅግ በጣም ውስብስብ፣ አድካሚና ከፍተኛ ወጪ የሚያሳጣ፤ ለስርቆት፣ ኩረጃና ለሌሎች ዘርፈ ብዙ ችግሮች የሚዳርግ እንደሆነ በተደጋጋሚ ይጠቀሳል። በሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ በተመሳሳይ ችግሮቹ እንዳሉ በማመን መፍትሄ ፍለጋ ሲዳክር ይስተዋላል። ኤጀንሲው ከፈተና ስርዓቱ ጋር ተያይዞ ለሚስተዋሉ ችግሮች መፍትሄ ለማበጀት ባለፉት ዓመታት ጥናቶች ሲያካሂድ ነበር። ከባህላዊ የፈተና /ምዘና ስርዓት በመውጣት ወደ ዘመናዊ ስርዓት መሸጋገርን የመፍትሄ ቁልፍ እንደሆነ በማመን እንቅስቃሴ ከጀመረ ውሎም አድሯል።

ሪፎርም የሚሻው ባህላዊ የፈተና ስርዓቱን ከላይ የተጠቀሱትን ሀገራት ተሞክሮ መሠረት በማድረግ ኮምፒዩተርን መሠረት ወደ አደረገ የፈተና ስርዐት መሸጋገር የተሻለ መፍትሔ ሆኖ ብቅ ብሏል። በኮምፒዩተር ላይ የተመሠረተ የፈተና ስርዓት መዘርጋቱ ችግሮቹን ሙሉ ለሙሉ መቅረፍ ባይቻልም በከፍተኛ ሁኔታ ማቃለል እንደሚያስችል በማመን በቅርቡ ተግባራዊ ለማድርግ ቅድመ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ለማወቅ ተችሏል። በሀገራችን ተግባራዊ የሚደረገው ኮምፒዩተርን መሰረት ያደረገው የፈተና ስርዓት በነባሩ የአመዘጋገብ ስርዓት ሲፈጠሩ የነበሩና የተፈታኝ ተማሪዎችን የወደፊት እድል የሚያበላሹ በርካታ ችግሮችን መቅረፍ ያስችላል፡፡ ከዚህ አኳያ በወረቀትና በእርሳስ ከሚሰጠው የፈተና ስርዓት ያሉትን ጥቅሞች መመልከቱ ያስፈልጋል።

የፈተና ደህንነትን ማስጠበቅ በኮምፒዩተር ላይ የተመሰረተ ፈተና የመጀመሪያው

ከፈተና ደህንነትን ከማስጠበቅ አኳያ ያለው ጠቀሜታ ይጠቀሳል። በወረቀት እርሳስ ምዘና አሰጣጥ እያንዳንዱ

የፈተና ወረቀት፣ የማስተላለፊያ ሂደት ውስጥ ፈተናው ለአደጋ ሊጋለጥ ወይም ሊሰረቅ የሚችልበት ሁኔታ አለ። በፈተና ስርዓቱ ክፍተት የሚፈጥሩ ችግሮችን ኮምፒዩተርን መሰረት ባደረገ የፈተና /የምዘና ስርዓት ወቅት መፍትሄ ያገኛሉ። መልካ ምድራዊ ሁኔታ አልያም የተፈታኙ መሠረት ምንም ይሁን ምን ሁሉንም የደህንነት አደጋዎች ይቀንሳል። በርካታ የታተሙ የፈተና ወረቀቶች ላይ ሊደርሱ የሚችሉትን መጠነ ሰፊ የስርቆትና የመጥፋት አደጋዎች በመቀነስ ከደህንነት ጋር ተያይዞ ሲፈጠሩ የነበሩ ችግሮችን ይቀርፋል። በተማሪዎች መካከል መኮራረጅ እንዳይኖር በማድረግ ብሎም ሌሎች አድካሚ የስራ ሂደቶችን ማቃለል ያስችላል።

ከተለዋዋጭነት አኳያሌላው የተለዋዋጭነት አኳያ ሲሆን፤ ኮምፒዩተር

ላይ የተመሰረተ ፈተና በምዘና አስተዳደር መስኮች በኩል ተለዋዋጭ ፈተናዎችን ያቀርባል። የአቅርቦት ሞዴሎቹ የተሟሉ ሆነው የሚገኙት በወረቀት እርሳስ ፈተና/ምዘና እንጠቀም ከነበረው አስተዳደር መስኮቶች ጀምረው በተከታታይ እንደ አስፈላጊነቱ ለአንድ የተወሰነ ፕሮግራም የተመረጠው አስተዳደራዊ አካሄድ የተፈታኞችን ተደራሽነት፣ ደህንነት፣ የቅንብር መንገዶች፣ የህትመት ድግግሞሽ እና ስታንዳርድ ማውጣትን ጨምሮ የተለያዩ ውሳኔዎችን ያካትታል። በወረቀት ላይ ከተመሰረተው ጋር ሲነጻጸር የተፈታኙን ተደራሽነት ማሻሻል የሚችለው ከፍላጎት እና አቅርቦት ጋር ሲነጻጸር የደህንነት ተጽእኖ ቀለል ማድረግ የሚችለውን ውስን የአስተዳደር መስኮቶችን የጊዜ ሰሌዳ ማስያዝ ይቻላል።

የፈተና ውጤትን በፍጥነት ይፋ ማድረግ ኮምፒዩተር ላይ የተመሠረተ ፈተና የውጤት ሪፖርቶች

በፍጥነት እና ትክክለኛነትን ይጨምራል። የምዘና ሰጪው ተቋምም የመፈተኑ ሂደት እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ የፈተናውን ውጤቶች ለተፈታኞቹ የማቅረብ አማራጭ አላቸው። ይሁን እንጂ ፈተናው መጠናቀቁን ብቻ ለማረጋገጥ ውጤቶቹ እስከሚቀጥሉ ቀናት ሊቆዩ ወይም ሊዘገዩ ይችላሉ። አስቸኳይ ውጤት ሪፖርት ለማድረግ ብዙውን

ጊዜ በኮምፒዩተር ላይ የተመሠረተ ፈተና ይጠበቃል፤ ከይዘት እና መቁረጫ ነጥብ ጋር በተያያዘ ሁሉም ፎርሞች ሚዛናዊ እንዲሆኑ ይጠይቃል። ወዲያውኑ ፈተናዎችን ማረም በጥያቄ ባንክ መጠን፣ በጥያቄ ምርጫ፣ ፎርሞች ማደራጀት እና ስታንዳርድ ማውጣት ላይ ተጽእኖ አለው።

ወጥነትበወረቀት እና እርሳስ የምዘና ዘዴ አካባቢ ውስጥ ያለው

አለመመጣጠን የምዘና ውጤቶች የፈታኞችን እውነተኛ ችሎታ የሚያንፀባርቁ አይደሉም ማለት ይቻላል። ለምሳሌ በትልቅ የመፈተኛ ክፍል ውስጥ ፈተና በሚወሰድበት ወቅት ሊኖሩ የሚችሉ መረበሽን ማየት ይቻላል። ስለሆነም ቁጥጥር ከሚደረግባቸው አካባቢዎች ውስጥ ኮምፒዩተር ላይ የተመሠረተ ፈተና የምዘና ማዕከላት መኖራቸው ይበልጥ አስተማማኝ ውጤቶችን በሚያስገኘው የፈተና አካባቢ ውስጥ ወጥነትን በጉልህ ያረጋግጣል።

በዳታ የበለፀገ የምዘና ውጤት ትክክለኛ የመለኪያ አስፈላጊነት በሁሉም የሙከራ

መርሃ ግብር ማዕከል ላይ እንደሚገኝ ይታመናል። የወረቀትና እና እርሳስ ምዘና ለቀላል ትንታኔ አስፈላጊ የሆኑትን መሠረታዊ መረጃዎችን ብቻ ይሰጣል። ከእነዚህ መሠረታዊ ነገሮች ባሻገር በቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተ የምዘና አሰጣጥ የመጀመሪያ እና የመጨረሻ ሰዓትን የእረፍት ጊዜን እያንዳንዱ የጥያቄ ክፍል የሚወስደውን የጊዜ መጠንን እና የዳሰሳ ጥናት ምላሾችን ጨምሮ በርካታ መረጃዎችን ያቀርባል። እንደ ነጻ አወቃቀር ጽሁፍ እና መጣጥፎች ያሉ የተገነቡ ምላሾች በእጅ ከተጻፉ ምላሾች ጋር ተያያዥነት ያላቸው መረጃዎች ሳይኖሯቸው በኤሌክትሮኒክስ በቀላሉ ሊመዘገቡ፣ ሊሰበሰቡ ይችላሉ። ሊጠፉ እና ብዙ ጊዜ ሊቀየሩ ከሚችሉ ከወረቀት እና እርሳስ ምላሾች በተቃራኒ በኮምፒዩተር ላይ የተመሰረቱ ምዘናዎች ሁሉንም ምላሾች የቁልፍ ጭረት (key stoke) በመባል በሚታወቅ ሂደት ይመዘገባሉ። ይህ እጅግ በጣም የበለጸገ የአቀራረብ ዘዴ ነው። ተፈታኙን እና የምዘና ባህሪያትን ለመገምገም እንዲሁም ለደህንነት ምርመራዎች የመረጃ ምንጭ መኖር አስፈላጊ ነው።

አስመረት ብስራት

የአጥንት መሳሳትን በተመለከተ መረጃ ይሰጡን ዘነድ ያነጋገርናቸው የጭንቅላት፣ የህብረሰረሰርና የነርቭ ቀዶ ህክምና እስፔሻሊሰት ዶክተር ዘነበ ገድሌ ስለህመሙ ያነገሩንን እነሆ በማህደረ ጤና ገፃችን ልናካፈላችሁ ወደድን። ዶክተር ዘነበ ስለዚህ በሽታ እንዲህ ብለው ይጀምራል፡፡ የአጥንት መሳሳት ሲባል አጥንት ውስጡ ያለውን የተሰራበትን ንጥረ ነገር እያጣ መሄዱ በዚህ ስያሜ እንዲጠራ አድርጎታል።

ከፕሮቲንና ከተለያዩ ተፈጥሯዊ ከሆኑ ንጥረ ነገሮች እየጠፋ መሄድ ነው የአጥንት መሳሳት ችግርን የሚያስከትለው። ይህ ችግር በተፈጥሮ የሚመጣ ወይም በሂደት የሚመጣ ሊሆን ይችላል። የሰው ልጅ አጥንት በተፈጥሮው ማደግ የሚያቆምበት ጊዜ አለው። ይህ ሲባል ከ25 እስከ 35 ዓመት ድረስ አጥንት የጥንካሬ ደረጃውን ይዞ ይጨርሳል ማለት ነው። ከተወሰነ ደረጃ በኋላ በተለይም ሴቶች ላይ የሆርሞን ለውጦች ስለሚኖሩ አጥንት ውስጥ ያለውን ይዘት እንዲቀንስ ያደርጋል።

አጥንት በተፈጥሮው ከምግብ የተሰራ ስለሆነ ለዚህ አጥንት መገንባት የሚያስፈልገውን ንጥረ ነገር ሳያገኝ መቆየቱ በሚፈለገው ደረጃ ጥንካሬ እንዳይኖረው አድርጎ ለዚህ ችግር ተጋላጭ እንዲሆን ያደርገዋል ማለት ነው። ምግብ ሲባል እንደ ካልሲየም የመሳሰሉትን ንጥረ ነገሮች በውስጡ የያዘ፣ እንደ ወተት፣ ቅባትና አሳ የመሳሰሉትን በምግብ ውስጥ ሲያካትት ማለት ነው። ሶስተኛው ደግሞ ከፀሀይ ብርሃን የምናገኘው ንጥረ ነገር ቆዳችን ላይ ካለው ንጥረ ነገር ጋር ተዳምሮ የሚፈጠረው ቫይታሚን ዲ እንዲያገኝ ያደርገዋል። ይህ በልጆች የእድገት ጊዜ ላይ የሚከሰት አይነት ነው።

ሌሎቹ ደግሞ ከምንወስዳቸው መድሃኒቶች ጋር የተያያዙ ናቸው። የአጥንትን የውስጥ ይዘትን የሚቀንሱ መድሀኒቶች አሉ። አጥንት እንዲሳሳና እንዲሰበር ያደርገዋል።

የአጥንት መሳሳት እንዳለብን በምን ልናውቅ እንችላለን?

በሀገራችን የህክምና ደረጃ በአብዛኛው ህመም

ካጋጠመን በኋላ ወደ ህክምና ተቋማት ስለምንሄድ ችግሩን ቀድሞ መገንዘብ ትንሽ ይከብዳል። ነገር ግን እድሜው እየገፋ የሄደ ሰው፤ ከ45 ዓመት በላይ የሆነች ሴት አስቀድማ ይሄንን ማወቅና ወደ ህክምና ተቋም በመሄድ በምርመራ ወቅት የአጥንት ጥንካሬ መጠንን በመመርመር ያሉ ችግሮችን ተረድቶ ጥንቃቄዎች እንዲኖሩ በቅድመ ምርመራ ሊታወቅ ይችላል።

በሽታው ገና ሲጀማምር ብዙ ምልክት አያሳይም፤ ነገር ግን አንዴ አጥንት ከሳሳ ወዲህ የሚከተሉት ምልክቶች ይታያሉ፤ የጀርባ ህመም፣ ከጊዜ በኋላ ቁመት መቀነስ፣ መጉበጥ፣ በቀላሉ የሚሰበር አጥንት ሀኪም ጋር መቼም መሄድ የግድ ይሆናል። በቤተሰብ ተመሳሳይ በሽታ ካለ የተለያዩ መድሃኒቶችን (Corticosteroid) የሚወስዱ ከሆነ የወር አበባ ማየት ቶሎ ካቆመ እንደ መነሻ በማሰብ ጥንቃቄ ማደረግ ይገባል።

ተጋላጭነትለአጥንት መሳሳት ሊያጋልጡ የሚችሉ እንደ እድሜ፣

ዘር፣ የአኗኗር ዘዬ፣ የጤና ሁኔታ እና መድሃኒቶችን የመውሰድ ሁኔታዎች ይኖራሉ፡፡ ሊቀየሩ የማይችሉ የአጥንት መሳሳትን የሚያመጡ አንዳንድ ሁኔታዎች ሊቀየሩ አይችሉም። በፆታም ሴቶች ከወንዶች የበለጠ ተጋላጭ ናቸው፡፡ እድሜ በጨመረ ቁጥር በአጥንት መሳሳት የመጠቃት እድል ይጨምራል፡፡ በቤተሰብ ተመሳሳይ በሽታ ካለ የሰውነት አቋም በቁመት አጠር ያሉ ሰዎች ከጊዜ ጋር የአጥንት ክብደት ሲቀንስ የበለጠ ይጎዳሉ፡፡

የአጥንት መሳሳት በአብዛኛው በካሺየም የበለፀጉ የምግብ አይነቶችን በማያዘወትሩ ሰዎች ላይ ይበረታል፤ የአመጋገብ ችግር ያለባቸው፣ የጨጓራ ወይም የአንጀት ቀዶ ጥገና ካደረጉ፣ አንዳንድ መድሃኒቶችን ለረጅም ጊዜ መውሰድ ለምሳሌ የሚጥል በሽታ መድሃኒት፣ የጨጓራ መድሃኒት፣ የካንሰር መድሃኒቶችን የሚወስዱ ተገላጭነታቸው ይጨምራል።

የአንጀት በሽታ፣ የአንጀት ቁስለት፣ የኩላሊት ወይም የጉበት በሽታ፣ ካንሰር፣ የመገጣጠሚያ በሽታ፣ የአኗኗር

ሁኔታ፣ ብዙ ሳያንቀሳቅሱ መዋል፣ የአልኮል መጠጥን አብዝቶ መጠቀምና ሲጋራ ማጨስ ለአጥንት መሳሳት የበለጠ ተጋላጭ ናቸው። በተጨማሪም እድሜያቸው ከ65 ዓመት በላይ የሆኑ ሴቶች፣ ከ70 ዓመት በላይ የሆኑ ወንዶች፣ 45 ዓመት ሳይሞላቸው ያረጡ ሴቶች፣ ከዚህ በፊት የአጥንት ስብራት በተደጋጋሚ ያጋጠማቸው ሰዎችና ስትሮይድ የሚባሉ የመድሃኒት አይነቶችን የሚጠቀሙ ሰዎች ይበልጥ ተጋላጭ ናቸው።

ከአጥንት መሳሳት ጋር ተያይዞ ምን ሊመጣ ይችላል?

የአጥንት ስብራት (በተለይ አከርካሪ ወይም ወገብ) ዋነኛው እና ከባዱ ችግር ነው፡፡ የወገብ ስብራት ብዙውን ጊዜ በመውደቅ ምክንያት ይመጣል፡፡ ነገር ግን የአከርካሪ ስብራት ሳይወደቅም ሊመጣ ይችላል፡፡

በተለምዶ የአጥንት መሳሳት የምንለው አጥንታችን ጥንካሬውን አጥቶ ሲሳሳና በዚህም ምክንያት የአጥንት መድከም ሲኖር እንደመሆኑ በአብዛኛው ጊዜ ህመሙ ቢኖርም እንኳን ምንም ምልክት ስለማያሳይ እንዲሁም አንድ ሰው አጥንቱ ቢሳሳ እንኳን አጥንቱ መሳሳቱን ሊያውቅ ስለማይችል “ዝምተኛ ህመም” እንደሆነ ይታሰባል።

የዚህ በሽታ ተጠቂዎች አጥንታቸው በቀላሉ

የመሰበር አጋጣሚው ከፍተኛ ሲሆን ስብራት ካጋጠማቸው በኋላም ወደ ቀድሞ የተለመደ የእለት ተዕለት ተግባራቸው ለመመለስ ጊዜ ይፈጅባቸዋል፡፡ በአጥንት መሳሳት ምክንያት የሚፈጠር የአጥንት ስብራት በአብዛኛው የሚፈጠረው በዳሌ አካባቢ፤ በአከርካሪ አጥንት ላይ እንዲሁም የሰዓት ማሰሪያ አንጓ ላይ ነው፡፡

ምርመራና ህክምናሰዎች የዚህ ህመም ተጠቂ መሆናቸውን

ለማወቅ DEXA(Dual Energy X-Ray Ab-sorp Hometry) የሚባል መሳሪያን በመጠቀም የአጥንት እፍጋትን መለካት ይቻላል ማለት

ነው፡፡ ይህን ልኬት በመጠቀምም በዳሌ አጥንት፤ አከርካሪ አጥንት እንዲሁም የሰዓት ማሰሪያ አንጓ አካባቢ ያለ የአጥንት እፍጋትን መለካት ይቻላል፡፡ ስለዚህ ይህ ምርመራ የአጥንት ስብራት ሳይከሰት በፊት አጥንት መሳሳት መኖሩን የምናይበት ነው፡፡

የአጥንት መሳሳት ችግር ተጠቂ የሆኑ ሰዎች የህክምና አማራጮችን ስንመለከት መድሃኒት መውሰድ እንዲሁም ጤነኛ የኑሮ ዘይቤን መከተል፤ በቂ የካልሲየም፤ የቫይታሚን ዲ እንዲሁም የሰውነት እንቅስቃሴ ማድረግ ያስፈልጋቸዋል። በአጥንት መሳሳት ምክንያት የአጥንት ስብራት ሲያጋጥም አፋጣኝ የህክምና እርዳታ ማግኘት የግድ ነው። የተመጣጠነ ምግብ መመገብ እንዲሁም በቂ ካልሲየም እና ቫይታሚን ዲ ማግኘት፣ በየእለቱ መደበኛ የሰውነት እንቅስቃሴ ማድረግ፣ ሲጋራ አለማጨስ እና አልኮል መጠጥ የመውሰድ ልምድን መቀነስና የአጥንት እፍጋት ምርመራን ያካተተ መደበኛ የጤና ምርመራ ማድረግ የሚሉት ይጠቀሳሉ።

ለሁሉም የጤና ችግሮች መከሰት የአኗናር ዘያችን ምክንያት መሆኑን የሚጠቅሱት ዶክተር ዘነበ ጤናችን በእጃችን በመሆኑ ሰው ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግ ጤናማ ሆኖ መኖር ይጠበቅበታልና የራሳችንን ጤና ራሳችን እንጠብቅ የሚለውን የእለቱ መልዕክታቸውን በማስተላለፍ ተሰናበትን።

ለአጥንት መጠንከር የሚረዱ ምግቦች

Page 9: ሰኞ ከ 27 ዓመታት የልማት ዘፈንና ፉከራ በኋላ ... · 2021. 2. 1. · ገጽ 4 በውስጥ ገጾች ገጽ 11 ሰኞ ብዕራችን ለኢትዮጵያ

9አዲስ ዘመን ሰኞ ጥር 24 ቀን 2013 ዓ.ም ማስታወቂያ

Page 10: ሰኞ ከ 27 ዓመታት የልማት ዘፈንና ፉከራ በኋላ ... · 2021. 2. 1. · ገጽ 4 በውስጥ ገጾች ገጽ 11 ሰኞ ብዕራችን ለኢትዮጵያ

አዲስ ዘመን ሰኞ ጥር 24 ቀን 2013 ዓ.ምገጽ 10ማህበራዊ

ትዝብት

አንተነህ ቸሬ

የሃሳብ ነፃነት ማለት የሕዝብን ደህንነት አደጋ ላይ መጣል ማለት አይደለም!

ሰሞኑን ስለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የጤንነትና የደህንነት ሁኔታ የተሰራጨው ሐሰተኛ መረጃ ብዙዎችን ስጋት ላይ የጣለና በርካታ ‹‹ትንታኔዎችን›› እና ‹‹ግምቶችን›› የጋበዘ ሆኖ ታዝበናል። ከዚህ ቀደምም የሐሰት መረጃዎችን ሲያሰራጩ በነበሩና ጥፋታቸውን እንዳይደግሙ ተግሳፅ ባልተሰጣቸውና ሕጋዊ እርምጃ ባልተወሰደባቸው ‹‹የሹም ዶሮዎች›› አማካኝነት የተሰራጨው መረጃ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ደጋፊዎች ብቻም ሳይሆን ‹‹ደጋፊያቸው አይደለንም›› የሚሉ ወገኖችንም ጭምር ያስጨነቀና ያነጋገረ ጉዳይ ነበር።

በእርግጥ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ካላቸው የኃላፊነት ደረጃ አንፃር ስለእርሳቸው የተወራው ጎልቶ ወጣ እንጂ ስለመረጃና ደህንነት አገልግሎት መስሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተርም አደገኛ የሐሰት መረጃ ሲሰራጭ ነበር። ስለሁለቱም ሹማምንት የተወራው መረጃ በሀገር ቤትም በውጭም ያሉ በርካታ ሚሊዮን ኢትዮጵያውያንንና የኢትዮጵያን ወዳጆች አስጨንቋል።

‹‹መንግሥት አጃቢዎቼን ሊያነሳብኝ ነው … በሌሊት ተከበብኩ›› … የብሔር ስም እየጠሩ ‹‹ … ሀጫሉን የገደለው ያ ብሔር ነው፤እርምጃ ውሰዱበት …›› በሚሉ ኃላፊነት የጎደላቸው ቀስቃሽ መረጃዎች ምክንያት በአንድ ጀንበር በመቶዎች የሚቆጠሩ ንጹሃን በአሰቃቂ ሁኔታ ሲገደሉ፤ ሺዎች ደግሞ ሲዘረፉና ሲፈናቀሉ የተመለከተ ሁሉ ስለጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ስለመረጃና ደህንነት መስሪያ ቤቱ አለቃ ጤንነት/ደህንት የሚሰራጭ አሉታዊ መረጃ ቢያስጨንቀው አያስገርምም።

‹‹የመረጃው ጌቶች›› እነማን ናቸው? ምክንያታቸውስ?

እነዚህ አደገኛ የሐሰት መረጃዎችን የሚያሰራጩ ግለሰቦች ሲያሻቸው የዩኒቨርሲቲ መምህር፣ ሲፈልጉ ዳያስፖራ፣ ሌላ ጊዜ አክቲቪስት ነን የሚሉና በመንግሥት የአስተዳደር መዋቅር ውስጥ ተቀምጠው ያሉ ‹‹የሹም ዶሮዎች›› ናቸው። በእነዚህ ግለሰቦችና ቡድኖች ግንዛቤ መሰረት መረጃን ከእነርሱ በስተቀር የሚያውቅ ሌላ ግለሰብ የለም፤ የምስጢራዊ መረጃዎች ባለቤቶች፣ የመረጃዎቹ ተንታኞችና የመረጃዎቹን ውጤት ወሳኞች እነርሱ ናቸው። ከደህንነት ሰዎች ጋር ግንኙነት እንዳላቸውም ያስወራሉ።

‹‹እነዚህ ‹የሹም ዶሮዎች› እንዲህ ዓይነት መረጃዎችን የሚያሰራጩበት ዓላማና ምክንያት ምንድን ነው›› ብሎ መጠየቅ የጉዳዩን ውል ለመያዝ የሚደረገውን ጉዞ አመቺ ያደርገዋል። መቼም እንዲህ ዓይነት አደገኛ መረጃዎችን የሚያሰራጩ ሰዎች የድርጊታቸው መነሻ/ዓላማ ቀላል ነው ብሎ አለመገመትና ማሰብ ሞኝ አያስብልም።

ከምክንያቶቻቸው መካከል፣ በእነርሱ ጥላ ተከልለው የራሳቸውን ድብቅ የፖለቲካ አጀንዳ ማስፈፀም የሚፈልጉ አካላትን (ምናልባትም በመንግሥት የአስተዳደር መዋቅር ውስጥ ያሉ) እያስፈፀሙ ነው የሚለው ግምት አንዱ ሊሆን ይችላል። ለዚህ ተግባራቸው የሚበረከቱላቸው ቁሳዊና ሌሎች ጥቅሞችና ማታለያዎች ደግሞ በዚሁ የይሆናል መላምት ስር የሚጠቃለሉ ገፊ ምክንያቶች ተደርገው ሊጠቀሱ ይችላሉ።

ግለሰቦቹ ራሳቸው የሚያራምዱትን አቋም ማስፈፀም ደግሞ ሌላው ምክንያት ነው ተብሎ ይገመታል። ይህኛው ምክንያት አደገኛ የሐሰት መረጃዎችን የሚያሰራጩት ግለሰቦች የሌሎች ተልዕኮ አስፈፃሚዎች ከመሆን ተሻግረው የራሳቸውን ዓላማና አቋም የሚያሳዩበትና የሚተገብሩበት መንገድ ነው። ከላይ ከተጠቀሱት ሁለት ግምቶች በተጨማሪ ሌሎች ምክንያቶችም ሊኖሩ ይችላሉ።

በእርግጥ ምክንያቶቻቸው ሁሉንም ሰው ላያስማሙ ይችላሉ። አንድ የማይካድ ሃቅ ግን አለ። ይኸውም ከሌሎች በተቀበሉትም ይሁን በራሳቸው ፍላጎት፣ እነዚህ አካላት አደገኛ የሐሰት መረጃዎችን ሲያሰራጩ የሕዝብን ደህንነት አደጋ ላይ መጣላቸው ነው። ከቤት በሰላም ወጥቶ ተመልሶ መግባትን እንደቅንጦት የሚያይ ሕዝብ ስለጠቅላይ ሚኒስትሩ ደህንነት መጥፎ ወሬ ሲሰማ ጭንቀቱና መረበሹ የዋዛ አይሆንም።

‹‹ጌታዋን የተማመነች በግ …›› ነገሩን አስገራሚም አስቂኝም የሚያደርገው የሐሰት

መረጃዎችን የሚያሰራጩ ግለሰቦችና ቡድኖች በግልፅ እየታወቁ ሳለ የንጹሃንን ሕይወት አደጋ ላይ ሊጥል የሚችሉ መረጃዎችን ሲያሰራጩ እንኳንስ ሕጋዊ እርምጃ ሊወሰድባቸው ይቅርና ኮስተር ባለ ዓይን የሚያያቸው አንድም የመንግሥት አካል አለመኖሩ ነው። መረጃ

አሰራጭዎቹን አደብ የሚያስገዛቸው አካል አለመኖሩን ስንታዘብ ‹‹ … እንዲህ ዓይነቱን መረጃ እንዲናገሩ/እንዲጽፉ ተልዕኮ የሚሰጣቸው የመንግሥት አካል አለ እንዴ?›› ወደሚል ግምታዊ ጥያቄ ለማምራት እንደገደዳለን።

ከሁሉም ቅድሚያ የዜጎችን መሰረታዊ ደህንነት ሊጠብቅ የሚገባው መንግሥት፣ የዜጎችን መሰረታዊ ደህንነት አደጋ ላይ ሊጥሉ የሚችሉ አደገኛ መረጃዎችን የሚያሰራጩ አካላትን ዓይቶ እንዳላየ ማለፉ ለብዙ ግምቶችና ይሆናሎች ቢጋብዝ የሚያስገርም አይሆንም።

የመንግሥትን ዝምታ የታዘቡ ሁሉ ግራ ተጋብተው ‹‹ … እነዚህ ሰዎች’ማ የተማመኑትን ተማምነው ነው እንጂ እንዲህ ዓይነት አደገኛ የሐሰት መረጃ አያሰራጩም ነበር። ወንጀል ቢሰሩም መከታ የሚሆንላቸው ባለስልጣን አለ ማለት ነው …›› እያሉ ይገምታሉ፤ተጨማሪ ውዥንብር እንዲፈጠርም ያደርጋሉ። በአጠቃላይ በአንድ በኩል የመረጃዎቹን ሐሰተኛነትና አደገኛነት፤በሌላ በኩል የመንግሥትን ዝምታ የተገነዘበ ሰው ሁሉ ‹‹ጌታዋን የተማመነች በግ ላቷን ደጅ ታሳድራለች›› ቢል አይፈረድበትም።

ችግሩን የበለጠ ውስብስብ የሚደርገው እነዚህን አደገኛ የሐሰት መረጃዎች የሚያሰራጩ ግለሰቦች በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ተከታዮችና ደጋፊዎች ያሏቸውና እንደታማኝ የመረጃ ምንጭም የሚቆጠሩ መሆናቸው ነው። በተደጋጋሚ የሐሰት መረጃዎችን ሲያሰራጩ ተከታዮቻቸውና ደጋፊዎቻቸው እነርሱን ከመምከርና ከመተቸት ይልቅ ይባስ ብለው የማበረታታቸውና እንደጀግና የመቁጠራቸው አሳዛኝ እውነት ሲደመርበት ደግሞ ጉዳዩ ከውስብስብነት የተሻገረ ትርጉም እንዲኖረውና ከዚህ ቀደም የታዩት አሰቃቂ ክስተቶች እንዲደገሙ የሚያደርግ ይሆናል።

ለመሆኑ መንግሥት ምን አለ?ከላይ እንደተገለፀው እነዚህ አካላት አገርንና ሕዝብን

አደጋ ላይ የሚጥሉ አደገኛ የሐሰት መረጃዎችን ሲያሰራጩ ምንም ዓይነት ሕጋዊ እርምጃ አልጎበኛቸውም። በድርጊታቸው የመፀፀትና እውነተኛ ይቅርታ የመጠየቅ ፍላጎትም አላሳዩም። እንዲያውም አንዳንዶቹ ‹‹የመረጃ ጌቶች›› እገሌ የተባለው ሰው ነው ያሳሳተኝ … ፎቶውን ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ እለጥፈዋለሁ …›› በማለት የፌዝ ምላሽ ሰጥተዋል።

‹‹የአገሪቱ እንቅስቃሴዎች ሁሉ በዕይታው ስር እንደሆኑ›› የሚገመተው የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት (National Information and Se-curity Service - NISS) መሥሪያ ቤት ‹‹ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብታቸውን ያላግባብ ተጠቅመው አገልግሎቱን በተመለከተ ሃሰተኛ መረጃዎችን በማህበራዊ ትስስር ገጾቻቸው በማሰራጨት ህብረተሰቡን ለማደናገር ሲሞክሩ የነበሩ አንዳንድ የማህበራዊ ሚድያ አንቂዎች›› ከህገወጥ ድርጊታቸው ሊታቀቡ እንደሚገባ ከማሳሰብ ባለፈ ሌላ ያለው ነገር የለም። ድንቄም ‹‹የማኅበራዊ ሚዲያ አንቂዎች››¡

በመገናኛ ብዙኃን የተላለፈው የአገልገሎት መሥሪያ ቤቱ አጭር መግለጫ ‹‹ … ከዚህ በኋላ የሀሰት መረጃዎችንና አሉባልታዎችን በማህበራዊ ትስስር ገጾች በማሰራጨት የሀገርን ብሄራዊ ጥቅምና ህልውና ለመጉዳት እንዲሁም የህዝብን ሰላምና ደህንነት ስጋት ላይ ለመጣል የሚንቀሳቀሱ አካላት ላይ ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ማስረጃዎችን በማጠናቀር በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ እንደሚያደርግ ያስታውቃል። ብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት በሀገር ላይ የሚቃጡ የፀጥታና የደህንነት ስጋቶችን በማስቀረት ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን ከማንኛውም ጊዜ በላይ ከሁሉም የጸጥታና የደህንነት ተቋማት ጋር ተቀናጅቶ እየሰራ ይገኛል … ›› ይላል።

ገዥው ብልፅግና ፓርቲ በበኩሉ፤ ህብረተሰቡ ማንኛውንም ጉዳይ አስመልክቶ በማህበራዊ ሚዲያ የሚለቀቁ መረጃዎችን ትክክለኛነት በጥንቃቄ ማጣራት ይኖርበታል›› የሚል ምክር አዘል መልዕክት አስተላልፏል። ፓርቲው በመግለጫው ‹‹ … በአሁኑ ወቅት በመላው ዓለምም ሆነ በአገራችን በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚሰራጩ ሃሰተኛ ወሬዎች እየተበራከቱ ይገኛሉ። ማንኛውም ዜጋ በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩ

መረጃዎችን ከመቀበሉ በፊት ከተረጋገጠና ከትክክለኛ ምንጭ የተገኙ መሆናቸውን በጥንቃቄ ማጣራት አለበት። ከሰሞኑ የፓርቲያችን ፕሬዚዳንትና የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር የሆኑትን ክቡር ዶክተር አብይ አህመድን ጤንነትና ደህንነት አስመልክቶ በማህበራዊ ሚዲያ የተናፈሰው ወሬ ፍጹም መሠረተ ቢስና ሆን ተብሎ ህብረተሰቡን ለማደናገር ኃላፊነት በማይሰማቸው አካላት የተሰራጨ ነውረኛ የሀሰት መረጃ ነው። ህዝባችን ለወደፊቱም ከተመሳሳይ ሀሰተኛ ወሬዎች መጠንቀቅ ይኖርበታል። ህብረተሰቡን የማደናገርና ውዥንብር የመፍጠር ዓላማ ይዘው ሃሰተኛ ወሬዎችን እየፈበረኩ የሚያሰራጩ የጥፋት አካላትን በጥብቅ ተከታትሎ የህግ ተጠያቂ ማድረግ የመንግሥት ኃላፊነት ይሆናል›› በማለት አደገኛውን መረጃ ያሰራጩት አካላት በሕግ ተጠያቂ እንደሚሆኑ ፍንጭ መሳይ ነገር ሰጥቷል። ‹‹ተገቢው እርምጃ ተወስዶ ሕግ ይከበራል?›› የሚለውን ወደፊት የምናየው ይሆናል።

የሃሳብ ነፃነትና የሕዝብ ደህንነት የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት መሥሪያ

ቤት በጉዳዩ ላይ ባወጣው መግለጫ ‹‹ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብታቸውን ያላግባብ ተጠቅመው …›› የምትል ሐረግ ትገኛለች። በእርግጥ ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ከመሰረታዊ የሠው ልጅ መብቶችና ነፃነቶች መካከል አንዱ እንደሆነ የሚካድ አይደለም። ሃሳብን በነፃነት መግለፅ ማለት ግን በሐሰት መረጃ የሕዝብን ደህንነት አደጋ ላይ መጣል ማለት አይደለም! ሃሳብን በነፃነት መግለፅም ቢሆን ገደብ የለውም ማለት አይደለም። በዚህ መሠረታዊ መብትም ላይ ገደብ የሚጣልበት ጊዜ አለ።

ከዚህ ጋር ተያይዞ መዘንጋት የሌለበት ጉዳይ በሃሳብ ነፃነት ስም የሕዝብን ደህንነት አደጋ ላይ መጣል ተገቢ እንዳልሆነ ሁሉ የሕዝብን ደህንነት በመጠበቅ ስምም ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብትን አደጋ ላይ መጣል ተገቢ እንዳልሆነ ነው። ሁለቱን ማምታታት የሕዝብን ደህንነት መጠበቅ ያለመቻል ድክመትንና ድብቅ የፖለቲካ ዓላማ የማስፈፀም ሴራን ከመሸፈንና አምባገነንነትን ሕጋዊ ከማድረግ ፍላጎቶች የሚመነጭ አደገኛ አካሄድ ነው። ሃሳብን በነፃነት የመግለፅም ሆነ የሕዝብን ደህንነት የመጠበቅ ስራዎች የሚተገበሩባቸው የየራሳቸው የሆኑ በቂ ወሰኖች አሏቸው። እንዲያው አንዳንድ ጊዜ ከበድ ያሉ ችግሮች ተፈጥረው ገደብ የሚጣልበት ጊዜ ሊኖር ይችላል አልን እንጂ በዚህ መብት ላይ ገደብ መጣል ሳያስፈልግም የሕዝብን ደህንነት ማስጠበቅ ይቻላል።

እንደመፍትሄመንግሥት የሕዝብን ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥሉ

እጅግ አደገኛ የሐሰት መረጃዎች ሲሰራጩ ዝምታን መምረጡ የሚያስገርምና ተስፋ የሚያስቀርጥ ቢሆንም ሕዝቡም የራሱ ኃላፊነት አለበት። የመረጃዎቹን ምንጮች ታማኝነት መገምገም፣ ምንጮቹ ከዚህ ቀደም ስለነበራቸው ልምድ/ታሪክ ማጣራት፣ የመረጃዎቹ ዓላማዎች ምን ሊሆኑ እንደሚችሉ ማሰላሰል፣ የታወቀ የመንግሥት አካል ማረጋገጫ እስከሚሰጥ ድረስ መረጃዎቹን ለሌሎች አለማጋራት እንዲሁም አደገኛ የሐሰት መረጃዎችን በሚያሰራጩ አካላት ላይ መንግሥት ተገቢውን ሕጋዊ እርምጃ እንዲወስድ ግፊት ማድረግ ከሕዝቡ የሚጠበቁ ኃላፊነቶች ናቸው። እነዚህ የመፍትሄ እርምጃዎች ሐሰተኛ መረጃዎቹ ሊፈጥሩ የሚችሏቸውን አደጋዎች ሙሉ በሙሉ ማስቀረት ባይችሉ እንኳ አደጋዎቹን ለመቀነስ ግን ያስችላሉ።

በእርግጥ ‹‹የሹም ዶሮዎቹ›› የሐሰት መረጃዎችን ሲያሰራጩ ከመምከርና ከመተቸት ይልቅ ይባስ ብለው እነርሱን የሚያበረታቷቸውና እንደጀግና የሚቆጥሯቸው ተከታዮቻቸውና ደጋፊዎቻቸው ግን የሐሰት መረጃዎችን ለማጣራት የሚያስችል ብቃትና ዝግጅት አላቸው ተብሎ አይታሰብም።

እስኪ በዚች ጥያቄ ልሰናበት … አደገኛ የሐሰት መረጃዎችን ያሰራጩት አካላት ድርጊታቸው አደገኛ መሆኑ እየታወቀም ምንም አልተባሉም፤ታዲያ የሰሞኑ አደገኛ የሐሰት መረጃዎቻቸው ከዚህ ቀደም እንደታዩት አሰቃቂ ግድያዎች፣ የአካል ጉዳቶች፣ የንብረት ውድመቶችና ሌሎች ችግሮች አስከትለው ቢሆን ኖሮ ተጠያቂዎቹ እነማን ይሆኑ ነበር?!

በእርግጥ ‹‹የሹም ዶሮዎቹ›› የሐሰት

መረጃዎችን ሲያሰራጩ ከመምከርና ከመተቸት ይልቅ ይባስ ብለው እነርሱን የሚያበረታቷቸውና እንደጀግና የሚቆጥሯቸው ተከታዮቻቸውና ደጋፊዎቻቸው ግን የሐሰት መረጃዎችን ለማጣራት የሚያስችል ብቃትና ዝግጅት አላቸው ተብሎ አይታሰብም

Page 11: ሰኞ ከ 27 ዓመታት የልማት ዘፈንና ፉከራ በኋላ ... · 2021. 2. 1. · ገጽ 4 በውስጥ ገጾች ገጽ 11 ሰኞ ብዕራችን ለኢትዮጵያ

አዲስ ዘመን ሰኞ ጥር 24 ቀን 2013 ዓ.ም ገጽ 11

ነፃ ሃሳብ

አጥፍቶ ጠፊው ትህነግ/ህወሓት/ (1967 -2013 ዓ.ም)

ቁምላቸው አበበ በአማራ ባህል፣ ቱሪዝምና ማስታወቂያ ቢሮ፤ በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት፤ በደቡብ መገናኛ ብዙኀን፤ በጋዜጠኝነትና በታሪክ ባለሙያነት ያገለገሉ ሲሆን፤ የደቡብ ኤፍ ኤምን ከባልደረቦቻቸው ጋር በመሆንም አቋቁመዋል። በፌዴራል ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅትና በአለ በጅምላ በኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተርነት አገልግለዋል። ከአአዩ በቋንቋና ታሪክ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን የሰሩ ሲሆን፤ በዚሁ ዩኒቨርሲቲ በጋዜጠኝነትና ኮሙዩኒኬሽን ሁለተኛ ዲግሪያቸውን በማጠናቀቅ ላይ እያሉ ባጋጠማቸው ድንገተኛ ህመም ተስተጓጉሏል። ጥልቅ ሀሳብ ያዘሉ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩሩ ፁሑፎችን በማህበራዊ ሚዲያና በተለያዩ ጋዜጦች በማውጣት ይታወቃሉ።

በቁምላቸው አበበ ይማም (ሞሼ ዳያን) [email protected]

ኮምኒዝም እንደተንኮታኮተ

በ20 ዓመታት ውስጥ በቼክ፣ ስሎቫክና ሀንጋሪ 37 የፖለቲካ ፓርቲዎች

በየሀገራቱ አሸንፈው ፓርላማ ገብተው ነበር።

በ2012 እኤአ ግን በምርጫ 5በመቶ ድምጽ ባለማግኘታቸው ብዙዎች

ተሰርዘዋል

( ክፍል ሁለት )የትህነግ /ህወሓት የውድቀት ቁልቁለት አሀዱ ብሎ

የጀመረው የብሔር ጥያቄን ከመደብ ጭቆና አጃምሎ በውልውል ደደቢት የካቲት 11 ቀን 1967 ዓ.ም በ11 አንጋቾች በርሀ የወረደ ጊዜ ነው። በዓመቱ በ1968 ዓ.ም በማኒፌስቶው የአማራን ሕዝብና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን የትግራይ ሕዝብ ጠላት አርጎ ሲፈርጅ መሻገሪያም መመለሻም ድልድዩን አፈረሰ። ውሎ ሳያድር ከብሔርተኛ ድርጅትነት ወደ ማርክሲስት ሌኒኒስት ሊግነት ግራ ኋላ ሲዞር በተፈጠረ የርዕዮት ዓለም ልዩነትና አለመግባባት ሶስት የድርጅቱ መስራቾች እነ ግደይ ዘራፂዮን ፣ አስፋሃ ሀጎስ እና አረጋዊ በርሄ ቀኝ ኋላ ዞሩ። እነ መለስም የአክራሪ ብሔርተኝነት ሸሚዛቸው ላይ የአለማቀፍ ሕብረተሰባዊነትን ሽርጥን አንገታቸው ላይ አደረጉ። ወለፈንዲዎችን አብዮታዊ ዴሞክራሲ እና ዲሞክራሲያዊ ማዕከልነትን እንደ ኩታ ከላይ ጣል አደረጉ። የማይታረቁ ፅንሰ ሀሳቦችን ማለትም አብዮት ብሎ ዴሞክራሲ፣ ዴሞክራሲ ብሎ አብዮት፤ ዴሞክራሲ ብሎ ማዕከላዊነት፣ ማዕከላዊ ብሎ ዴሞክራሲያዊነት፤ በማዛነቅ ማደናገሩን ተያያዘው። አብዮትና ዴሞክራሲ፣ ማዕከላዊና ዴሞክራሲ፤ አብረው አይኖሩም ። አይሄዱም። እንደ እንግሊዙ የግሎሪየሰ እና የፈረንሳይ አብዮቶች ዴሞክራሲን ሊያዋልድ ይችላል እንጅ ከዴሞክራሲ ጋር በአብሮነት አይዘልቁም። ለዚህ ነው በአለማችን ከተካሄዱት ህልቁ መሳፍርት ከሌላቸው አብዮቶች ዴሞክራሲን ያዋለዱት በጣት የሚቆጠሩ ብቻ የሆኑት። በማዕከላዊነት የዕዝ ጠገግ መመሪያን ከላይ ወደ ታች እያወረዱም። ለዚህ ነው አብዮታዊ ዴሞክራሲ እና ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት ያልተባረኩ አስመሳይ ጋብቻዎች ናቸው የምለው ።

ትግራይን በመዳፉ ሲያስገባ የትግራይን ሪፐብሊክ ጭምብል አወለቀና በህልሙም በእውኑም እመራታለሁ ብሎ ያላሰባትንና አምርሮ የሚጠላትን ሀገር ስለመግዛት መተወን ጀመረ ። እንዲህ በማምታታት ፣ በፈጠራ ትርክትና ቁጭት ያሰባሰባቸው ጭፍራዎቹ ትግራይ ነጻ ከወጣች ከዚህ በኋላ አንዋጋም ሲሉት ደግሞ የሀውዜን ዘግናኝ ጭፍጨፋ አቀነባብሮ በገበያ ቀን በርካታ ንጹሐን እንዲገደሉ በማድረግ ፤ አንዋጋም ያሉትን ታጋዮች ትግራይ ነጻ ብትወጣም ደርግ ካልወደቀና መላ ኢትዮጵያ ነጻ ካልወጣ ነገ እንደሀውዜን እንጨፈጨፋለን ብሎ በማስፈራራትና በማታለል ብዙዎቹን መልሶ ከጎኑ ማሰለፍ ቻለ። አዲስ አበባን ሲቆጣጠር ደግሞ የአልባንያን ሶሻሊዝም አሽቀንጥሮ ጥሎ ነጭ ካፒታሊስት ነኝ ብሎ አረፈው። ከ70ሺህ በላይ ታጋዮች የተሰውለትን አላማ ጠልፎ የስልጣኑ ማደላደያና የጥቂቶች መክበሪያ አደረገው። ዴሞክራሲ፣ ፍትሕ፣ እኩልነትና ነጻነት በለየለት ፈላጭ ቆራጭነት፣ ጭቆናና ግፍ ተተካ። ደርግን ጥሎ ዳግማዊ ደርግ ሆነ ። ፖለቲካው አሳታፊ ከመሆን ይልቅ አስመሳይና አግላይ ሆነ። የፖለቲካ ምህዳሩ እንደተከረቸመ ቀረ። ኢኮኖሚውም ፍትሐዊና አካታች ከመሆን ይልቅ ብዙኃኑን የበይ ተመልካች አደረገው። ሙስና ገነገነ። ዘረፋ ሙያ ሆነ ። ትህነግ ላለፉት 46 ዓመታት ለስልጣን ሲል ያልሆነውና ያልሄደበት መንገድ የለም። በክህደት፣ በሴራ፣ በደባ በቅጥፈት፣ በጥላቻ፣ በዘረፋ፣ በጭካኔ፣ በጉግማንጉግ ፣ ወዘተረፈ ተወልዶ አድጎና ጎልምሶ ሞቷል። ፖለቲካዊ ሞቱን ከምስረታው እኩል ጀምሯል የምለው ለዚህ ነው። ከስብሀት ጋር የማልስማማውም በዚህ የተነሳ ነው። "እኛ የሞትነው ስማችን (ህወሓት/ኢህአዴግ) ወደ ብልፅግና የተቀየረለት ነው ። አሁን ቀብራችንን ነው እያስፈጸማችሁ ያላችሁት፤ "ቢልም ፤ ለእኔ ግን ከፍ ብሎ ለመግለጽ እንደሞከርሁት ትህነግ መሞት የጀመረው በግልብና ድቡሽት ትንተናው ላይ ክህደትንና ሴራን ለንጥቆ ከተመሠረተባት ከየካቲት 11

ቀን 1967 ዓ.ም ዕለት ጀምሮ ነው።በክፍል አንድ መጣጥፌ ፖለቲካዊ ትንተናው

በአመክንዮና በተጠየቅ ሳይሆን በስሜትና በግዓብታዊነት የተቃኘ መሆኑ ፤ ለችግሮች ሀገረኛ መፍትሔ አለመሻት እና የተረክና የታሪክ ምርኮኛ መሆን ለትህነግም ሆነ በ60ዎቹ እንደ እንጉዳይ ፈልተው ለነበሩ የፖለቲካ ድርጅቶች ውድቀት በምክንያት መጠቀሳቸው እንዳለ ሆኖ።

ኮምኒዝም እንደተንኮታኮተ በ20 ዓመታት ውስጥ በቼክ ፣ ስሎቫክና ሀንጋሪ 37 የፖለቲካ ፓርቲዎች በየሀገራቱ አሸንፈው ፓርላማ ገብተው ነበር። በ2012 እኤአ ግን በምርጫ 5በመቶ ድምጽ ባለማግኘታቸው ብዙዎች ተሰርዘዋል። ፓርቲዎች ለመራጮች የገቡትን ቃል ኪዳን ሳይፈጸሙ ሲቀር፤ ፕሮግራሞቻቸውና ፖሊሲዎቻቸው ሲከሽፉ መራጩ ፊት ስለሚነሳቸው ይሰረዛሉ። ይህ ቀናው ከፖለቲካ የመሸኛው መንገድ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል። በሀገራችን ይህ ነው የሚባል የርዕዮት ዓለም ወይም የፕሮግራም ልዩነት ሳይኖራቸው እንደ አሸን የፈሉ ፓርቲዎችን ለማንገዋለል ከድህረ ምርጫ በኋላ ይህን መስፈርት ስራ ላይ ማዋል። እንደ አማራጭ ስልት ሊያገለግል ይችላል። አሁን ለመወዳደር ከተለዩት 52 የፖለቲካ ፓርቲዎች ውስጥ ከ5በመቶ በታች ድምጽ ያገኘውን ማሰናበት እንደ ማለት ነው ።

ትህነግ/ህወሓትም ሆነ ሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዎችን ለውድቀት ከሚዳረጉ ፈተናዎች አምስቱ ግንባር ቀደም ናቸው። እነሱም ፦1ኛ. ጥርት ያለ የፖለቲካ ፕሮግራም አለመቅረጽ፤ 2ኛ. በሕገ ወጥ ተግባር ወይም ወንጀል ተሰማርቶ መገኘት፤ 3ኛ.የመወዳደሪያ ስትራቴጂ መክሸፍ፤ 4ኛ. በፓርቲዎች ውስጥ የሚፈጠሩ መከፋፈሎች የሚፈቱበት አግባብ ፤ 5ኛ. የፓርቲው የአደረጃጀትና አወቃቀር ጥንካሬ ናቸው። እያንዳንዳቸውን በወፍ በረር ስንመለከታቸው፤

1ኛ. ጥርት ያለ የፖለቲካ ፕሮግራም አለመቅረጽ፤ ትህነግን ለውድቀት ከዳረጉት ዐበይት ምክንያቶች ቀዳሚው በአመክንዮና በተጠየቅ የተተነተነ ወጥ የፖለቲካ ፕሮግራም መቅረፅ አለመቻሉ ነው። ይህ አልበቃ ብሎት ፕሮግራሙን በፈጠራ ትርክትና ጥላቻ መለሰኑ ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ እንዲሰነጣጠቅ ፤ መስራች አባላቱ በጥርጣሬ እንዲተያዩና አንጃ መጎንቆል ጀመረ። መስራቹ አረጋዊ በርሔ በአርፋጁ ስብሀት ሲተካ፤ ገሰሰ አየለ/ስሁል/ በመሰሪው ስብሀት ሴራ ተገደለ። የብሔር ጥያቄን ከመደብ ትግል ጋር እያፈራረቀና እያጃመለ የጠራ ፕሮግራም ሳይቀርጽ እስከ 1971 ዓ.ም በአፈተት ከዘለቀ በኋላ የትግራይ ማርክሲስት ሌኒኒስት ሊግ /ትማሌሊ/ ይዞ ብቅ አለ። ከአክራሪ ብሔርተኝነት ወደ ኮሚኒስትነት ተቀየረ ። የሚገርመው ከምስራቅ አውሮፓዊ አልባኒያ የቀላወጠው ፕሮግራም ማህበራዊ መሰረቱ ላቭ አደሩ ሲሆን በጊዜው አይደለም ላቭ አደር ጠግቦ የሚያድር አርሶ አደር እንኳ ብርቅ ነበር። የአልባኒያም ሆነ የትግራይና የኢትዮጵያ ሕዝብ የልቦና ውቅር ደግሞ በቅድም ሆነ በስፌት ሊገናኝ አይችልም ነበር። ሌላው ለትግራይ ሪፐብሊክ ምስረታ እታገላለሁ ብሎ ጀምሮ በርሀ ከወረደ በኋለ ድንገት እንደ እስስት ተቀይሮ ራሱን የብሔር ብሔረሰቦች ቃፊር አደረገ ። ወደ አራት ኪሎ ሲቃረብ ደግሞ አብዮታዊ ዴሞክራሲንና ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነትን አስቀድሞ ነጭ ካፒታሊስት ሆኛለሁ አለ። ውሎ ሳያድር ደግሞ ልማታዊ መንግስት ነኝ አለ። ይህ ሁሉ መቅበዝበዝ የጠራ ፕሮግራም እንዳልነበረውና ግቡም ስልጣን፣ ዘረፋና በቀል እንደነበር የሚያሳይ ነው። የመክሰሚያና የመለወጫ መንገድ ወይም የመውጫ ስትራቴጂ ስላልነበረው መጨረሻው ራስን በራስ ማጥፋት ሆኗል።

2ኛ. በሕገ ወጥ ተግባር ወይም ወንጀል ተሰማርቶ መገኘት፤ ትህነግ ውልደቱም እድገቱም ጉልምስናውም

ሆነ ሞቱ በዘረፋ፣ በግድያ፣ በሴራ፣ በደባ፣ በቅጥፈት፣ በውልስትና፣ በክህደት፣ በስልጣን ጥመኝነት፣ በራስ ወዳድነት፣ ወዘተረፈ ያለፈ ነው። ባንክና ሀገር ዘርፏል፤ በትግል ጓዶቹም ሆነ እንደሱ በርሀ በወረዱ ድርጅቶች ላይ ክህደት ፈጽሟል፤ ከ20 ዓመታት በላይ በሀሩርና በቁር በቀበሮ ጉድጓድ ሆኖ ሲጠብቀው፤ በደስታውም በሀዘኑም ከትግራይ ሕዝብ ጎን የነበረውን፤ አለኝታው፣ መከታውና አጋዡ የነበረውን፤ ከትግራይ ሕዝብ ጋር የተጋባውንና የተዋለደውን የሰሜን ዕዝ ክዷል። በሰራዊቱ ላይ ለመስማት የሚሰቀጥጡ፣ ለማየት የሚዘገንኑ ግፎችን ፈጽሟል። የዕዙን የጦር መሳሪያ ዘርፏል። አውድሟል። ሀገርን ከአንድም ከሁለት ሶስት ጊዜ በላይ ከድቷል። የኢፌዴሪን ሕገ መንግስት በተደጋጋሚ ጥሷል። የሀገሪቱን የምርጫ ሕጉን ጥሶ ምርጫ አካሂዷል። እጁን በደም ታጥቧል፤ የትግራይ ሕዝብ በርሀብ እንደ ቅጠል እየረገፈ የነፍስ አድን እህል ሽጦ የጦር መሳሪያ የገዛ አረመኔ ነው። ትህነግ ከጸሐይ በታች ያልጣሰው ሕግ፤ ያልፈጸመው ወንጀል የለም። በሀገሪቱ የወንጀልም ሆነ የፍትሐብሔር ሕጎች መጠየቁ እንዳለ ሆኖ፤ ትህነግ በአመጽ ተግባር ተሰማርቶ መገኘቱና ኢሕገ መንግስታዊ ምርጫ በማካሄዱ ሕጋዊ ሰውነት ተሰርዟል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ባለፈው ሳምንት እንዳስታወቀው፤ ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ /ሕወሓት/ "የአመፅ ተግባር ላይ ተሰማርቷል ወይ?"የሚለውን ሁኔታ ለማጣራት በፓርቲው የተሰጡ መግለጫዎችንና በይፋ የሚታወቁ ጥሬ ሀቆችን በማቅረብ፣ ፓርቲው ኃይልን መሠረት ያደረገ የአመፅ ተግባር ላይ መሳተፉን አረጋግጧል፡፡

በተጨማሪም ፓርቲው መልስ የመስጠት ዕድል እንዲኖረው በማሰብ በፓርቲውና በቦርዱ መካከል አገናኝ በመሆን ይሠሩ የነበሩትን የፓርቲውን የአዲስ አበባ ቢሮ የቀድሞ ተወካይ ለማነጋገርጥረት ያደረገ ሲሆን፣ ተወካዩም ፓርቲውን መወከል እንደማይችሉ ገልጸዋል። በመሆኑም በአዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀጽ 98/1/4/ መሠረት፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የፓርቲውን ሕጋዊ ሰውነት ሰርዟል።

የአየለ ጫሚሶው ቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ የመሥራች አባላት ዝርዝር የቦርዱም ሆነ የፖሊስ ኮሚሽኑ የማጣራት ሥራ የሚያሳየው ፓርቲው እያወቀ ወይም ማወቅ እየተገባው በቃለ-መሀላ በተረጋገጠ ሰነድ ያቀረበው የመሥራች አባላት ስም ዝርዝር የተጭበረበረ መሆኑን ምርጫ ቦርድ ገልጾ ስለዚህ በአዋጅ 1162/2011 አንቀጽ 98/1ሠ/ መሠረት የቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ እንዲሰረዝ ተወስኗል፡፡ በሌላ በኩል በትግራይ ክልል ሲንቀሳቀሱ የነበሩ፤ " ዓሲምባ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /አዴፓ/"፤ ትግራይ /ባይቶና/"፤ ሳልሳይ ወያኔ ትግራይ ሳወት/"በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በምዝገባ ሒደት ላይ እያሉ፤ በትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ውስጥ በተካሄደ ሕገወጥ ምርጫ ስለመሳተፋቸውና የፓርቲዎቹ አመራሮች በአመፅ ተግባር መሳተፋቸው ለቦርዱ መረጃ በመድረሱ፤ስለ እንቅስቃሴያቸው ማብራሪያ እንዲያቀርቡ ትዕዛዝ መስጠቱን የሪፖርተር ዘገባ ያስረዳል። ደጋግሜ ለመግለጽ እንደሞከርሁት የትህነግ/ህወሓት ጉዳይ ሰፊና ጥልቅ ጥናት የሚጠይቅ ከመሆኑ ባሻገር በራሱ ዳጎስ ዳጎስ ያሉ በርካታ መጽሐፍት የሚወጣው ስለሆነ በዚህ አምድ ሁሉንም ማስተናገድ ስለማይቻል ቀጣዩን ሶስተኛውንና ምን አልባትም የመጨረሻ የሚሆነው ሶስተኛ ክፍል እንደ ፈጣሪ ፈቃድ ይዤ እመለሳለሁ።

ሀገራችን ኢትዮጵያ በጀግኖችና ሀቀኛ ልጆቿ ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!

አሜን ።

Page 12: ሰኞ ከ 27 ዓመታት የልማት ዘፈንና ፉከራ በኋላ ... · 2021. 2. 1. · ገጽ 4 በውስጥ ገጾች ገጽ 11 ሰኞ ብዕራችን ለኢትዮጵያ

ፎቶ

- በገ

ባቦ ገ

ብሬ

አዲስ ዘመን ሰኞ ጥር 24 ቀን 2013 ዓ.ም ገጽ 12

ወቅታዊ ጉዳይ“አገራዊ እሴት፣ አገራዊ ጀግና እና አገራዊ ታሪክ ሳይኖር አገር ወዳድ ትውልድ ሊኖር አይችልም”

- ዶክተር አልማው ክፍሌ የታሪክና የህግ መምህር

ለአገራችን ወቅታዊ ችግሮች መንስኤዎቹ የተሳሳቱ ትርክቶች፣ የታሪክ ንግርታችንና የህግ

አፈጻጸም ሁኔታዎች እንደሆኑ ብዙዎች ይስማማሉ። የህገመንግሥት ጉዳይም እንዲሁ ችግር

መሆኑ ይጠቀሳል። በእነዚህ ጉዳይ ላይ ለዓመታት ሲሠሩ የቆዩና በሙያው ልምድ ያላቸውን

በኮተቤ መልቲፖሊታል ዩኒቨርሲቲ የህግና ታሪክ መምህሩ ዶክተር አልማው ክፍሌን ስለጉዳዩና

መፍትሔው እንዲያወጉን ጋብዘናቸዋል። ከእርሳቸው ጋር ያደረግነውን ቆይታም እንደሚከተለው

አቅርበነዋልና ተከታተሉን።

ጽጌረዳ ጫንያለው

አዲስ ዘመን፡- ህግና ታሪክ እንዴት ይሰናሰላሉ?ዶክተር አልማው፡- ታሪክ ማለት ሰው ባለፉት ዓመታት

ከነበረው አካባቢ ማለትም የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና ማህበራዊ የህግ መስተጋብሩ እንዴት ተከወነ የሚለውን የምናይበት ነው። ነገር ግን ሁሉንም መጻፍ አይቻልምና በተጻፈ መልኩ ለማስቀመጥ የተቻለው እንደህግና ፖለቲካ ዓይነቶቹን በመሆኑ በየፈርጃቸው ጽፈንና አስቀምጠን ተተኪው እንዲረዳው ተደርጓል። ስለሆነም ህግም እንዲሁ አንዱ የታሪክ አካል ሆኖ በመቀመጡና ለትውልድ በመተላለፉ ከታሪክ ጋር ይሰናሰላል ማለት እንችላለን።

ታሪክ ትናንት ነው። ትናንት ምን አለ፣ ምን ጉዳት ነበር፣ ለዛሬ ቢመጣ ምን ይጠቅማል የሚለውን ማያም ነው። ታሪክ የትናንቱን ማወቂያ፣ የነገ ማቀጃና የዛሬ መኖሪያም ነው። ምክንያቱም ትናንትን ያላወቀ ዛሬ ሊኖር አይችልም። ትናንት እውቀት ነው፣ ትናንት ማንነት ነው፣ ትናንት መረጃ ነው፤ ትናንት ትምህርት ቤት ነው። በመሆኑም ትናንትን በሚይዘው ታሪክ ውስጥ ህግ ይታያል፤ ይተገበራል፤ ለትውልድም ይሻገራል። በዚህም ነው ህግና ታሪክ የተቆራኙ ናቸው የሚባለው። ነገር ግን አሁን ነገሮች ተቀይረው ኢኮኖሚውን፣ ማህበራዊውን፣ ህጉን ትቶ ፖለቲካ ብቻ ሆነና ብዙ ነገሮች ተረሱ። ታሪክ ለብቻው ህግም ለብቻው መጓዝ ጀመሩና ምንነታቸውን ረሱ። በዚህም በፖለቲካው ብቻ መመራት ተጀመረ። እንደ አገር በስርዓትና በምርምር እንዲሁም በእውቀት የተጻፈ ታሪክን ይዞ መቀጠል ቀረ። ከ1960ዎቹ ጀምሮ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲና የኢትዮጵያ ምርምር ጥናት የተጻፉ ታሪኮች አይደለም ኢትዮጵያን ሌሎችን ከፍ የሚያደርጉ ነበሩ። ሆኖም ቦታውን ፖለቲካ ስለያዘው አልተቻለም። እንደውም የመባያ መንስኤ አደረጓቸው።

በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ታሪኮችን በሦስት መልኩ ከፍሎ ማየት የሚቻል ሲሆን፤ የመጀመሪያው ተጓዦቹ ሚሲዮኖች የጻፉት ነው። ባህሉን፣ ቋንቋውን እንዲሁም ህዝቡን ሳያውቁ ያዩትንና የፈለጉትን ይጽፉ ነበር። ሁለተኛው ገድል ጸሐፊዎች ሲሆኑ፤ የነገስታትን ጨምሮ ሌሎች በቅርብ የሚያውቋቸውን ሰዎች የሚጽፉት ናቸው። ዋና ግባቸውም ስልጣንን ማረጋገጥ እንጂ ህዝቡና መንግሥት በመረዳት ሳይንስ ማቀራረብ አይደለም። ለዚህ ማሳያው በማይረዱት መንገድ ታሪክን መጻፋቸው ነው። ለምሳሌ ህዝብ ለታላላቅ ሰዎችና ለሚፈሯቸው ሰዎች ‹‹አባ›› የሚለው ስያሜ ይሰጣሉ ብለው የመነኩሴውን አባ ፣ አባገዳን ጠቅሰው አባ ጨንገሬን ይጨምራሉ። ይህ ደግሞ ካለማወቅ የመጣ እንደሆነ እንረዳለን። ነገርግን በዚህ ሥራቸው ህብረተሰቡን አደናብረውታል።

ሦስተኛው የአጻጻፍ ዓይነት የልምድ ጸሐፍት የጻፉት ሲሆን፤ በታሪክ አጻጻፍ እውቀት ያተቃኙ፣ የሚያመጣውን ችግር የማያውቁ፣ ለህዝቡ ምን ይጠቅመዋልና ምን ያስተምረዋልን በአግባቡ የማይረዱት ናቸው። በዚህም የታሪኩ መረጃ በሚፈለገው መልኩ እንዳይደርስ ሆኗል። የተበላሹ ትርክቶችም የተቀመጡት በዚህ የተነሳ ነው። ያልገባውን ህዝብ ለማተራመስ መሰረት የሆኑትም ለዚህ ነው። ጽሑፎቻቸው ፖለቲካ አዘል ሲሆን፤ መሰረት የሌለው ትውልድን ለመፍጠር አስችሏል።

በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ታሪክ ከፖለቲካው ውጪ ያላየ፣ ሰሜን ተኮር የሆነና ሌሎችን ያልዳሰሰ በመሆኑ ዛሬ ድረስ የሁሉ ነገር መሰረት ቢሆንም እንዳንታይ አድርጎናል። ሞልቶ የፈሰሰው ስለ ገዢዎችና አገዛዛቸው ብቻ መሆኑም ሌላ ተወቃሽነቱን ያመጣ ነው። መንግሥት ሲያጽፈው ክፍያና ስልጣን የሚፈልጉ ጸሐፍት ደግሞ የመንግሥት አቀንቃኝ እንጂ ሌላ ሊሆኑ አይችሉም። በዚህም ፖለቲካው ከሚገባው በላይ ፈርጥሞ ምህዳሩን ሞልቶት ኢትዮጵያና ህዝቦቿ በታሪካቸው እንዳይታወቁ አድርጓቸዋል። ይህ ሆነ

ማለት ደግሞ ህግን ጨምሮ ሌሎችን አንኳር አገር የሚገነቡ የታሪክ አካላት እንዳይታዩና እንዳይፈጸሙ ሆነዋል። በዚህም እኔ አልተጻፍኩም የሚለው አካል ብቅ ብሎ ዱላ እንዲያነሳና ለዚያ መክፈል ያለበት ብሔር አለ ብሎ እንዲያስብም ሆኗል።

አለ የሚባለው ከ1960 ጀምሮ የነበረውም ታሪክ በእንግሊዝኛ የተጻፈ፣ ለህዝቡ ተደራሽ ያልሆነ በመሆኑ ህዝቡ የሚያውቀውና እየኖረበት ያለው ፖለቲከኞች፣ አክቲቪስቶች የጻፉትን እንዲሆንም መሰረት ጥሏል። ይህ ደግሞ ታሪክን በአግባቡ የሚረዳ አካል እንዳይኖር አድርጎታል። በኃይለሥላሴ ታሪኩ ሞአ አንበሳ እምዘነገደ ይሁዳ ንጉሰ ነገሥት ዘኢትዮጵያ የሚል መልክ እንዲይዝ ተደርጎ የተጻፈ ነው፣ በደርግ ደግሞ የሶሻሊዝም ከየት ወዴትን የሚያቀነቅን መልዕክት የያዘ ነበር። በኢህአዴግ ደግሞ ታሪክ ሙሉ ደብዛው ጠፋና ብሔር ብሔረሰቦች ከየት ወዴት የሚል ፖለቲካ አዘል መልዕክትን የሚያ ስተላልፍ ነው። በዚህም ታሪክ ሥራውን ሳይሠራ እስከዛሬ እንዲዘልቅ ሆኗል።

በተለይ በ27 ዓመታት ውስጥ የታሪክ ትምህርት ቤቶች ሳይቀሩ ደብዛቸው ጠፍቷል። መምህራንም ከሥራቸው ተፈናቅለዋል። የታሪክ መጸሐፍትም ሆኑ ጽሑፎች ከገበያ እንዲወጡ፣ በትምህርት መልክ እንዳይሰጡና ማጣቀሻ ጭምር እንዳይሆኑም ታግደዋል። ስለሆነም ትውልድ ትናንቱን በሚገባ እንዳይረዳና ነገን አቅዶ እንዳይንቀሳቀስ ተፈርዶበታል። ስለ አገሩም ማሰብ እንዳይችል በሩ ተዘግቷል። ስለዚህ የጋራ ምንም የሌለው ዜጋ ሆኖ ህግ የማያከብር ፣ ታሪክ የማያውቅና ጥላቻና መበጣበጥ ምግባሩ ተደርጎ ለብሶታል።

አዲስ ዘመን፡- የታሪክ ምሁራን እርስ በእርሳቸው ባለመስማማታቸው ትውልዱ ታሪኩን እንዳያውቅና ለተተኪ እንዳያስተላልፍ ሆኗል ይባላል። ምክንያቱ ምን ይሆን?

ዶክተር አልማው፡- አንድን ነገር ለመረዳት ያደግ ንበት ማህበረሰብ፣ ቤተሰብ፣ አኗኗራችን፣ ኢኮኖሚው፣ ሃይማኖቱ፣ የትምህርት ደረጃችን፣ የምንከተለው ፖለቲካ እንዲሁም የተማርነው ትምህርት ወሳኝነት አለው። በዚህም የታሪክ ምሁሩም ስምምነቱ በዚህ ሁኔታ ላይ ይመሰረታል። በእርግጥ በቋሚው ነገር መስማማት አለ። ልዩነቱ ማብራሪያ አሰጣጡ ላይ ነው። ለዚህ ደግሞ መሰረታዊ ነገር ጣልቃ ገብነቶች ናቸው። ፖለቲካው፣ ኢኮኖሚያዊ ጫናው፣ ልዩ ፍላጎቱ ፣ የውጭ ስፖንሰሩ ወዘተ ታሪክ በስምምነት እንዳይነገር ያደርጋል። ከሁሉም በላይ ከውጭ አገራት የሚደረጉ ታሪክ የማጥፋት ዘመቻዎች ትልቅ ችግር ፈጣሪ ናቸው። መጥፎ ታሪክ የሚጽፉ አካላትን ስፖንሰር እስከማድረግ ይደርሳል።

እንደ አገር የፈረንጅ ወዳጅ የለንም። ምክንያቱም የሴራ ፖለቲካ አለበት። ከአደዋ በኋላ ኢትዮጵያ የሠራችው ገድል ዘመን ተሻጋሪ ከመሆኑም በላይ ፈረንጆችን ያሸማቀቀ ነው። አይሸነፉምንም ቢሆን አጥፍቷል። ይህ ደግሞ ለፈረንጆቹ ከባድ ሽንፈትና የፈለጉትን እንዳያገኙ ያደረገ ነው። እንደፈሯትም እንዲኖሩ ያስቻለ ነው። በመሆኑም አሁንም ድረስ የእርሷን ማደግና መበልጸግ ስለማይፈልጉ ጸረ-ኢትዮጵያ የሆኑ አካላትን ሁሉ ይደግፋሉ። በቋሚነት እንዳትረጋጋም ይጥራሉ። ከእነዚህ መካከል ደግሞ የታሪክ ምሁራን የተጣመመ አስተሳሰብ ትልቁ የፍላጎታቸው ማሳኪያ ሲሆን፤ ጽሑፎቻቸውን ኢትዮጵያን በሚያባላ መልኩ እንዲያደርጉ ይከፍሏቸዋል። የትምህርት እድልም እየሰጡ በሚፈልጉት መልኩ ያሰለጥኑና የፈለጉትን መልዕክት እንዲያስተላልፉ ያደርጓቸዋል። ይህ ደግሞ አለመስማማትን በሚገባ ያመጣል።

ትውልዱም የአገሩን ሳይሆን የውጪውን የሚናፍቀ ውና የሚመርጠውም በተማረው ታሪክ የእውቀት ሚዛን የውጪዎችን አድርጎ ስለሚወስድ ነው። ስለዚህ ምንም

ትክክል ነገር ቢነገረው የማያምነው ለዚህ ነው። በተለይ በታሪክ እነ ኦነግና ህውሓት ብዙ ፖለቲካዊ ጨዋታ ስለተጫወቱ ብሔራዊ ጀግኖችን ይዞ የሚጀግን ዜጋ እንዲጠፋ ሆኗል። ብሔራዊ ጀግና ጠለሸና የለም ማለት አገር ወደቀ፣ ማንነት ተጥላላ፣ አገር የሠራችው ድልና ገድል ጠፋ ማለት ነው። ስለዚህም ይህ እየሆነ ይገኛልም። ለዚህ ነው ዛሬ የጋራ ራዕይ ይዞ በመስማማት አገርን ለማሳደግ የሚጥር የጠፋውም።

ታሪክ ሲበላሽ ብሔራዊ እሴቶችም አብረው ይበላሻሉ። ለምሳሌ ባንዲራ፣ ገንዘብና በዓላት የተለየ መልክ የኖራቸውም ከዚህ አኳያ መሆኑ ግልጽ ነው። ሁሉም በየሰፈሩ ባንዲራን ፈጥሯል፤ የሚሟገተውም ለብሔሩና ለሰፈሩ ልጅ ነው። ከዚያ ውጪ አይወክለኝም፣ አይመለከተኝም ባይነት ሰፍኗል። ስለዚህም እንደተባለው በታሪኩ ማብራሪያ የታሪኩ ምሁር መለያየትና አገርን ለማውደም የተሠሩ ሥራዎች ይህንን ሁሉ አስከትለዋል። አሁንም ቢሆን መሰረታቸው ከእንደገና እንዲመለስ ካልተሠራ በቀላሉ አይፈታም። ምክንያቱም የጋራ በዓላት በትውልዱ ዘንድ የጭቆና እንደሆኑ ይታሰባሉ። ለአብነት ዓደዋ የዓለም መሆኑ ቀርቶ የአማራ ተደርጎ ተወስዷል። እናም አሁን ጀምሮ ኢትዮጵያን የሚያጠለሽ ምሁር እየወሰዱ ሁለተኛና ሦስተኛ ድግሪ እየሰጡ የማስተማራቸው ምስጢር ማክሰም ይገባል። የተሳሳቱ ትርክቶችን የሚዘሩ አካላትን ተጠያቂ ማድረግ መጀመር ያስፈልጋል። ታሪክ አገርን እንደሀገር የሚያስቀጥል ሳይሆን የግለሰብን ጥቅም የሚያስከብሩ ሆኗልና ይህንን ከመሰረቱ ማድረቅ ላይ ሁሉም መረባረብ አለበት። ብሔር ያለአገር ይጓዝ ይመስል የብሔር ልዕልናን እያስከበሩ ብሄር ተኮር አገርንም የሚፈጥሩ አካላትን ሀይ ማለት ቅድሚያ መሰጠት ይገባል።

የእስከዛሬዋ አገር በመላዕክት የተገዛች አልነበረችም። ገዢዎች በጠመንጃ ገዝተዋት ያውቃሉ። ስለ ፍትህ ፣ ስለ ዴሞክራሲ የማያውቁ ገዢዎችም ሲገዟት ኖረዋል። ስለዚህም ህዝብ ተጨቁኖ ፈተናን አሳልፏል። ነገር ግን የተግባሩ ባለቤት ገዢዎች እንጂ ህዝቦች አልነበሩም። ዛሬ እንደሚባለው አማራው፣ ትግሬው፣ ኦሮሞውና ሌላው ህዝብ አንዱ አንዱን አልጨቆነም። በባለስልጣናቶቹ የስልጣን ጥም የሆነ ነው እንጂ። ገዢው መደብ ግዛቱን ለማስፋፋትና አልገዛም ያሉትን ለማስገዛት የተሳሳቱ ትርክቶችን ትተን ተግባሩን ፈጽሞታል። በግለሰቦቹ ጥፋት አንድ ብሔር ላይ ይህንን በደል ያለ አግባብ መጫን ተገቢነት የለውም። አንድን

ብሔር ለብቻው የተሰበረ አድርጎ መውሰድም አይገባም። ሁሉም ህዝብ የጉዳት ሰለባ የሆነበት ጊዜ ነበረው። እናም በእያንዳንዱ እንቅስቃሴያችን ይህንን ማየት ይገባናል።

አገሪቱ ውስጥ ጥግ የያዘ ድህነት አለ። ፍትሐዊነት የለም። ብልሹ አስተዳደሮች በሰፊው ይታያሉ። የፖለቲካ ባህላችን የሰለጠነ አይደለም። ልዩነትን በቀናነት ማስተናገድ ያመናል። በዚያ ላይ ሥራ አጡ ብዙ ነው። ተደራሽ የሆነ ፖለቲካዊ ኢኮኖሚ ፣ ዴሞክራሲያዊ የሆነ ፖለቲካ፣ የሃሳብ የበላይነትም የለም። በተለይም በብሔር ላይ ተመርኩዞ የሚመሰረት የፖለቲካ ፓርቲ አግላይና አንገዋላይ ነው። እናም እንደ ህዝብ ተመርጦ መፈናቀል፣ ተመርጦ መግደል፣ ተመርጦ መቀማት አለ። እናም ይህንን ለማስወገድ አንድነት ብቻ ነው መፍትሔው። የቀደመና መልካሙ ታሪካችን ብቻም ነው የሚያሻግረው። ስለሆነም ትውልዱ ታሪኩን በሚገባ እንዲረዳ ከተፈለገ ይህንን ማድረግ ግድ ይላል።

ፍራቻው ፣ ገበያው ላይ ያለው ፖለቲካ፣ የፖለቲካው አደረጃጀት፣ የህጉ አደረጃጀት፣ ከ1972 ዓ.ም ጀምሮ የታሪክ ምሁራን ማህበር እንዳይቋቋም መታገዱ፣ ነፃ ተቋም ያለመኖሩና መሰል ችግሮች በታሪክ ምሁራን መካከል መቀራረብ እንዳይኖርና አገር በታሪክ እንዳትሠራ ያደረገ ሌላው ምክንያት ነው። ሆኖም አሁን በመጣው መንግሥት መነጋገር ተጀምሯል። ማህበሩ ከተፈቀደ ደግሞ ይበልጥ የምርምር፣ የስርጸትና መሰል ክፍሎች ስለሚኖሩት ገበያ ላይ ከሚወጡትና ለህትመት ከሚቀርቡት መጽሐፍት ጀምሮ ተገምግመው ለህዝብ እንዲደርሱ ይደረጋል። ህዝብም መርጦ አንባቢና ታሪኩን አዋቂ ይሆናል።

የሚነበቡ ታሪካዊ መጽሐፍትን የሚፈልጉ በርካታ በመሆናቸው ግራ መጋባትን ያስቀርላቸዋል። የተሳሳቱ ትርክቶችም ቦታ አይኖራቸውም። በተለይም ለሁሉ ነገር መነሻው ትምህርት በመሆኑ የታሪክ ትምህርቶች በአግባቡ የሚሰጡበትን ሁኔታ ያመቻቻል። አገራዊ ራዕይ፣ አገራዊ አጀንዳና ህዝባዊ ብልጽግናን የማይፈልጉ ወረበሎች ተሰብስበው የመሰረቱትን ታሪክም ከምድረገጽ ማጥፋት ያስችላል። አንደኛ ደረጃ ብሔር ነን በአገር ደረጃ በፍጹም መታሰብ እንዳይኖርም ዕድል ይሰጣል። ምክንያቱም ያልተጋባና ያልተዋለደ የለምና ሁሉም ታሪኩን መርምሮ እንዲረዳ ይሆናልና።

አዲስ ዘመን፡- ታሪክ ለአገር ግንባታ ምን አስተዋፅኦ አለው፤ ከህግ አንጻር የሚታይበት ሁኔታ አለ? በተለይ በፌዴራልና በክልል ህገመንግሥት?

Page 13: ሰኞ ከ 27 ዓመታት የልማት ዘፈንና ፉከራ በኋላ ... · 2021. 2. 1. · ገጽ 4 በውስጥ ገጾች ገጽ 11 ሰኞ ብዕራችን ለኢትዮጵያ

ገጽ 13አዲስ ዘመን ሰኞ ጥር 24 ቀን 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ ጉዳይዶክተር አልማው፡- የኢትዮጵያ ታሪክ በፖለቲካው

የተበላ ነው። ምክንያቱም ከፖለቲካ ውጪ 100 በመቶ የሚታይ አንድም ነገር የለም። ኢኮኖሚው እንኳን በሁለተኛ ደረጃ ነው የሚታየው። እንደ ታሪክ ዓይነቶቹ ደግሞ ሙሉ ለሙሉ ጠፍተዋል። ነገር ግን ታሪክ አገር ሲገነባ ሥራውን ሠርቶ እውነቱን ለህዝብ በማሳየት ነው። ማን መጥፎ ማን ጥሩ ሠራ በሚገባ ያሳያል። እያስተማረ ከችግሮች ትምህርትን ሰጥቶ ነገን የተሻለ እንዲያደርጉ የሚጠቁምም ነው። ታሪክ ዛሬ መኖሪያ አይደለም። ትናንት ምን ነበር ያለው የሚለውን ያሳያል እንጂ። እናም ሰው በፖለቲካ፣ በህግ፣ በኢኮኖሚ፣ በሳይንስ፣ በቴክኖሎጂ ወዘተ እንዴት ኖረ የሚለውን በእውቀት ያስጨብጣል። ለቀጣይ ህይወቱም የተሻለውን ያመቻቻል። ነገር ግን የታሪክ ምሁሩና ፖለቲከኛው ቦታ ተቀያይሮ ትክክለኛው ታሪክ እንዳይደርስ ሆኗል። በዚህም ዳቦ ሳይሰጡት ነገ እንሰጥሀለን እያሉ በማስጎምዡት አብሮነቱን ቀምተው ታሪኩን ከህጉ ነጥለው አሳዩትና ህግ አክባሪ፣ ታሪክ ሠሪ ትውልድ እንዳይፈጠር ሆነ። ትናንቱን ያላወቀ ዛሬን አይጠይቅም። ዛሬን ያልኖረም ነገን አያውቅም። በዚህም ህግ ያለማክበር መብትና ልምድ ተደረገ። የሚረቀቁ ህጎችም ቢሆኑ መሰረታዊ መብቶችን የሚያስከብሩ እንዳይሆኑ ሆኑ። በዚህም ታሪክ ከህግ አንጻር ገደብ የለሽ ነበር ብሎ ማንሳት ይቻላል። አገር ላይ በነፃነት መኖር ታሪክ ተቆርጦ በመጣሉ ነው።

በታሪክ ሁሉም ብሔር በአብሮነት ይኖር ነበር። አሁን በተፈጠረ ህግ ግን በአንድ ክልል ውስጥ ከብሔሩ ውጪ ተጠቃሚ፣ ባለሀብት፣ የመኖር መብት ያለው አካል የለም። ፈላጭ ቆራጩ የክልሉ ተዋላጅ ብቻ ነው። በዚህም በታሪክ የነበረው በአብሮ መሥራት፣ በአብሮ ማደግና አገርን ማስቀጠል ቦታቸውን ለቀቁ። በተለይ አመራሩ የአገር ቢሆንም ከሰፈር እንዳይዘል ተደረገ። በመሆኑም ከፌዴራል እስከ ክልል ያለው ህገመንግሥት አግላይ አንገዋላይና ሰፈርን የማስከበር ሥራ የሚሠራም ሆነ። ለዚህ ደግሞ መሰረቱ ህውሓት ሲሆን፤ 27 ዓመት ሙሉ ሠርቶበት አንድ ትውልድ ስላፈራበት ነው።

አዲስ ዘመን፡- 27 ዓመታትን ስልጣን ላይ የቆየው ህወሓት በፖለቲካው ላይ የፈጠረው መዘበራረቅ አሁን ላለንበት ቀውስ አድርሶናል። ከዚህ አኳያ ያለውን ሁኔታ እንዴት ያዩታል?

ዶክተር አልማው፡- ህወሓት መራሹ መንግሥት ከጫካ ጀምሮ ሁለት የተጻረረ ሃሳብ ይዞ የመጣ ነው። አብዮታዊ ዴሞክራሲን ያቀነቅናል። ነገር ግን የራሱን ጥቅም ያስከብራል። በተለይ ኢትዮጵያን ማፍረስ ዋነኛ ግቡ ነበር። አዲስ ፖለቲካና አዲስ አገር መመስረት መሰረታዊ ጉዳዩ ነው። አገራዊ እሴት፣ አገራዊ ጀግና እና አገራዊ ታሪክ ሳይኖር አገር ወዳድ ትውልድ ሊኖር አይችልም። ስለዚህም ከ27 ዓመት በላይ በተሠራው ሥራ ብሔር እንጂ አገር የሚለው እንዳይታሰብ ሆኗል። ብጥብጥና ጥላቻም የዚሁ ውላጅ ናቸው።

በፊት ላይ ዴሞክሪያሲያዊና ህዝብን የሚጠቅም ባይሆንም አገር የሚለው ስብዕና ግን አልጠፋም። ለዚህም ማሳያው ጠላት ሲመጣ ልዩነታቸውን ለነገ ትተው አገርን አሻግረዋል። ህወሓት መራሹ መንግሥት ሲመጣ ግን አንዱ ብሔር ከሌላው ብሔር ጋር የት ቦታና እንዴት ሊጣላ ይችላል የሚለውን እያቀደና በተግባር እየተረጎመ 27 ዓመት ሙሉ የሠራ በመሆኑ አገር መውደድ ብቻ ሳይሆን አገርን መጥራት እንዳይቻልም ነው የሆነው። አገሬ የሚል አካል ከተገኘ ሁሉ ነገር ያከትምለታል።

ካለፉት ሁለት ዓመታት ጀምሮ የተሻሉ ነገሮች ቢመጡም አሁንም የተተከለው ተክል በብዙ መንገድ እየሠራ አይደለም። ለአብነት የክልሎች፣ የዞኖችና የወረዳዎች አወቃቀር የህውሓትን ሥራ በተወ መልኩ አይደለም። በዚህም ማዕከላዊ መንግሥቱ ያልተጠናከረና ክልሎች የፈረጠሙ እንዲሆኑ አድርጓል። ስለዚህም ምርጫ ማካሄድን፣ የፈለጋቸውን መግደልን እንድናይ ሆነናል። ህወሓት ባለስልጣኑን ሳይቀር በምርጫ የተቀመጠ መንግሥት ስለሌለ ነገ ይህ ቢወድቅ በሚል መንፈስ ሁለት አምላኪ አድርጎታል። በዚህም የክልልና የፌዴራል አሠራሮች ተለያይተው ህዝቡ እንዳይረጋጋ መንገድ ጠርጓል። ከዚያ ውጪ አዲሱ መንግሥት ከህወሓት የተረከባቸው ባለስልጣናት ስላሉም ጥቅማቸውን ከህዝብ ስለሚያስበልጡ ሸምጋይና ሲያደርጉት የቖዩትን መተው ስለማይፈልጉ አለመረጋጋቱ እንዲቀጥል ሆኗል።

በሌላም በኩል መንግሥት በህወሓት ጥፋት ብዙ ችግሮች ተጋርጠውበታል። ከእነዚህ መካከል ግንኙነቱ አሁንም ድረስ ከጽንፈኛው ጋር የሆነ ብዙ አመራር መኖሩ፤ አገር በብዙ እዳ ውስጥ መሆኗ፤ ታችኛው ክፍል ላይ ያለው አመራር በአብዛኛው የተጨመላለቀና በአሠራር እንኳን በብዙ መልኩ ያልጸዳ መሆኑ፤ በገንዘብ ሁሉን ነገር ማድረግ እንደሚቻል የሚያምን መሆኑ፣ የህዝብ ጠባቂ ተብሎ የተሰየመውም አካል ለመኖር ሲል ያለ አግባብ ሰውን እየገደለ መቀጠሉ፤ ነፃ ተቋማት አለመፈጠራቸው በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው።

ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ያሉ አመራሮች፣ መምህራንና ተማሪዎችም ቢሆኑ የጁንታው ምልምሎችን ያካተተ መሆኑ

መረጋጋት እንዳይመጣ አድርጓል። ስለዚህም ይህንን እስኪያጸዳ ድረስ በአመራር ዘንድም ሆነ በዜጋው ላይ ትልቅ ፈተና ጥሏል ማለት ይቻላል።

የህወሓት ጁንታ ህግን ሳይቀር የዘወረ ነው። እንዴት ከተባለ በዋናነት በአምስት መንገድ አበላሽቶታል። አንደኛው ሰዎች ሙስና ውስጥ እንዲዘፈቁ በማድረግ ሲሆን፤ ነፍስህ በእጃችን ነች በማለት የፈለጉትን ማስደረጋቸው ነው። ሁለተኛው ደግሞ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን በመጠቀም በብሔር መለያያና ችግር መፍጠሪያ ማዕከል አድርጎ መሥራቱ ነው። ለዚህ ደግሞ የማይመረቁ የደህንነት ሰዎችን ሳይቀር ይጠቀም ነበር። ሦስተኛው ስፖርትን ከፖለቲካ ጋር ማስተሳሰሩ ሲሆን፤ አጀንዳ ተሰጥቷቸው ህዝብን እንዲበርዙና ከህግ ውጪ እንዲሆኑ ያደረገበት ነው።

አራተኛው ኢኮኖሚውን ማናወጥ ሲሆን፤ ህዝብ የሚፈልገውን ከገበያ በማጥፋት ሲንጫጫ ይቆይና እኔ እያለሁ በማለት ከመጋዘን አውጥቶ ያቀርብና እርሱን ብቻ እያመኑ እንዲቀጥሉ ያደረገበት ነው። የብሔር ተኮር ግጭቶችን በተለያየ መንገድ በመፍጠር መሥራቱ ሌላው ህግ ማስጣሻ ነበር። በግጦሽና በውሃ ምክንያት ውጊያ እንዲያደርጉ አንዱን ወገን በመደገፍ አስጨርሶ የእንትና ብሔር በእንትና ተጠቃ እያለ ሽማግሌ እየሆነ ስልጣኑን ከህግ ውጪ ማራዘሙ ነው። ሚዲያውን ወጥሮ በመያዝ እነርሱ ከሚፈልጉት ውጪ እንዳይዘገብ ማድረጉ፤ የክልል ህገመንግሥት እንዲኖር መፈቀዱና ዜጎች በፈለጉበት ቦታ እንዳይኖሩ መገደቡም ህጉን ሳይቀር እንደዘወረው የሚያሳይ ነው። ብሔርና ሃይማኖት እንደ ኢትዮጵያ ደምና አጥንት መሆኑን ስለሚያውቅ ሥራውን ከህግ ጋር አያይዞ ሴራውን ደግሞ ከህግ ውጪ እየፈጸመ መቆየቱ ችግሮች በቀላሉ መፍትሔ እንዳያገኙ ያደረገበት ነው።

አዲስ ዘመን፡- የኢትዮጵያ ህግ እንዴት ይታያል፤ በህግ የመመራቱ ሁኔታስ እንዴት ይገመገማል ?

ዶክተር አልማው፡- መጀመሪያ መስማማት የሚያስፈልገው በምድር ላይ ሙሉ ፍትህ እንደሌለ ነው። ምክንያቱም ህግ ለጉልበተኛ፣ ለገንዘበኛ፣ ለሹመኛ፣ ለመልከኛ ያደላል። እነዚህ አካላት ፍርድቤት ሳይሄዱ ፍርዳቸውን ያስጨርሳሉ። ክፍተት ተጠቅመውም ልክ እንዳልሆነ ያሳምናሉ። ስለዚህም ፍትህ በኢትዮጵያ ደረጃ ብቻ ሳይሆን በዓለምም ክርክርን ማሸነፍ ነውና ከባድ ነው። ስለ እውነት ሳይሆን ስለክርክር ማሸነፍ ብቻ የሚያቀነቅን ነው። ከዚያ ውጪ ሲታይ ግን በአገር ደረጃ ምን ዓይነት ህግ የማስከበር ሥራ አለ የሚለውን መመልከት ይቻላል።

እንደ ኢትዮጵያ ህግ ከፍትህ ተቋሙ ጀምሮ ችግር ያለበት ነው። ምክንያቱም ገለልተኛነት ይጎለዋል። ህጉ በሹመኞች የሚመራ ነው። ዳኛው ፍርዱን ሲሰጥ ሁለት ዓይነት አቅጣጫን ተከትሎ ነው። የመጀመሪያው በማስታወሻ የሚሠራው ሲሆን፤ የፖለቲካ ውሳኔ በሚል የሚከናወነው ነው። የእንትና ሚኒስቴርና ክፍለከተማ ይጽፍና ሞት የተፈረደበትን ሰው ልቀቁ ይባልበታል። ነፃ የሆነው ደግሞ ይታሰር ይባላል። ስለዚህም የማስታወሻ ማስፈጸሚያ ህግ የሚከወንበት ነው። ሌላውና ሁለተኛው ጥቂት ሀቀኞችን ትተን ስንት ትከፍላለህ ተብሎ የሚፈረድ ፍርድም ያለበት ነው። ስለዚህም እንደ አገር ያለው የህግና ህግ መከበር በተለይ በፍትህ ስርዓቱ ላይ የሹመኛና በጥቅመኛ የሚሠራው አካል ውሳኔ ፍርድ ነው። በዳኝነት ሥራ ላይ በተሳተፍኩባቸው ጊዜያት ደግሞ ይህንን አረጋግጫለሁ።

በአገር ውስጥ በህግ የመመራቱ ጉዳይ አገራዊ ራዕይና ህዝባዊ አገልግሎትን ያነገበ አይደለም። ገና ብዙ የሚጠራ ነገርን ይፈልጋል። ገለልተኛ የፖለቲካ ድርጅት፣ ገለልተኛ ተቋምም እስካልተመሰረተለት የባለስልጣናት አገልጋይ መሆኑ አይቀርም። እስከ አሁን ድረስም ህዝብንና እውነትን የሚያገለግል ተቋም አልተመሰረተም። አሁን ያሉት ጅማሮዎች እንዳሉ ሆነው።

በህግ መመራትን ለማምጣት አገር የሚያሻግር ህገመንግሥት ያስፈልጋል። ለዚህ ደግሞ ያለአግባብ የገቡ ህጎች አሁን በተጀመረበት ሁኔታ እየተስተካከሉ መሄድ ይገባቸዋል። ከግለሰብ የጀመረ ሥራንም ይጠይቃል። መብቱ የተነካ ሰው ሁሉ መጮህ አለበት። በጋራ ጉዳይ ላይ መደራደርም አይገባም። አድርባይነትን ማስወገድ፣ ሌሎች ክልሎች ላይ የሚኖሩ ዜጎች ሲመጡ እንደ ወራሪ አድርጎ የሚያየው የክልሎች አግላይ የሆነ ህገመንግሥትና የአወቃቀር ስርዓት በህግ መስተካከል ይኖርበታል። ህብረ ብሔራዊነትን በህገመንግሥቱ ማሳየት ይገባል።

አዲስ ዘመን፡- በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች የሚፈጸሙ የህግ ጥሰቶች ንጹሐንን እየማገዱ ይገኛሉ። እንዲህ ዓይነት ጉዳዮችን ፈር ለማስያዝ ምን መደረግ አለበት?

ዶክተር አልማው፡- አሁን ያለው ችግር ለዘመናት የተሠሩ ሥራዎች ውጤት ነው። ዘመናችን ያለፈው በቂም፣ በበቀል፣ በጥላቻና በቁርሾ ነው። አንድም አገርን ሊያሻግር የሚችል ፣ አብሮነትን ሊያጠናክር የሚችል ነገር አልተሠራም። ስለዚህም ያበበውና የጎለመሰው ዘር እንጂ አገር አይደለም። ይህ ደግሞ በቀላሉ የሚጠፋ አይሆንም። አሁንም ብዙዎችን በግፍ ያጣነው ለዚህ ነው። ነገር ግን በተወሰደው የህግ ማስከበር ሥራ ጁንታው ተይዞ ለኢትዮጵያ ህዝብ አንድ ድል ተገኝቷል። ሁሌ ነዳጅ የሚያርከፈክፍና ክብሪት የሚጭር እጅን ማሰር ተችሏል። በዚህም ማሰቢያ ጊዜ ተገኝቷል ብዬ አምናለሁ። ምክንያቱም እሳቱ ይለኮሳል ሳይሆን የተለኮሰው እንዴት ይጠፋል ላይ ለመሥራት ያግዛል።

አሁን ያለው አመራር ብዙ ድክመቶች ቢኖሩትም አገር ወደማለት የመጣ ስለሆነም መፍትሔዎች መምጣታቸው አይቀርም ብዬ አስባለሁ። ስለዚህ ይህንን ይዞ የተሻለውን ለማምጣት የእያንዳንዱ ዜጋ ጉዳይ መሆን አለበት። እሳት ለኳሹ ህወሓት ብቻ ስላልሆነም እየለዩ ወደ ህግ ማቅረብ ላይም የህዝቡ ተሳትፎ መላቅ ይኖርበታል። በተለይ ከህወሓት ጋር ክርስትና የተነሳሱ፣ ጡት የተጠባቡ እንዲሁም ፍቅር እስከመቃብርን የተፈራረሙ አሉና እነርሱን አሳልፎ ከመስጠት አንጻር ያላሰለሰ ጥረት ያስፈልጋል።

በህወሓት መመታት ድንኳን ቤታቸው ጥለው ኀዘን ውስጥ የተቀመጡ በርካቶች ናቸው። ስለሆነም ጊዜ ይጠብቃሉና ለአገር ደህንነት ሲባል እነርሱን ማሳፈር ይገባል። ለዚህ ደግሞ መንግሥት እያደረገ ያለው ነገር የሚያስመሰግነው ነው። መቼም ቢሆን በአገር ተስፋ አይቆረጥምና ማንም ምንም ያድርግ ለአገር ታማኝ መሆን ከሁሉም ይጠበቃል። ስለዚህም ያለችውን ተስፋ አሟጦ መጠቀምና ወደፊት መራመድ ያስፈልጋል። ጉዳዩ አገርን የማዳን እንጂ የፓርቲና የብሔር ጉዳይ እንዳልሆነ ማሰብም ይገባል። ወቅታዊ ሁኔታው ደግሞ ብሔርና ፖለቲካን ብቻ ያነገበ በመሆኑ ከእርሱ መራቅና ስለሰው ልጅ ማሰብ ከምንም በላይ ስንቃችን ይሁን። አሁን ያለው መንግሥት በግብጽ፣ አውሮፓ ህብረትና መሰል አካላት ስለተወጠረ ህዝብ ሊያግዘው ያስፈልጋል።

አዲስ ዘመን፡- የህግ ማስከበሩን ሁኔታ እንዴት

ይገመግሙታል?ዶክተር አልማው፡- ህወሓት የትግራይን ህዝብ በልቶ

የጨረሰ ነው። በተለይም ኢትዮጵያ የሚልን ህዝብ በብዙ ነገር ገሎታል። ውስጡ እንደ ካንሰር ሆኖ ሲገለው ለትግራይ ህዝብ እስከአሁን አልደረስንለትም የሚል እምነት አለኝ። ስልጣን ከያዙ በኋላ ደግሞ ከቅምጦቻቸው እስከ ቤተሰባቸው የደረሰ ድርጅትና ሀብት ሲያከማቹ ቆዩ እንጂ ድሃዋ የትግራይ እናት እጅ ላይ የገባ ነገር አልነበረም። ሁሉም ሲረዳ የነበረው መከላከያ ሠራዊቱ ከኮቾሮው ላይ በቀነሳት ገንዘብ ነው። ትምህርትቤት፣ ጤና ጣቢያና ሌሎች የአገልግሎት ተቋማትም ቢሆኑ የተሠሩት በእርሱ ገንዘብና ጉልበት ነው። ግን እኔን አልፎ ለምን በሚል ቅናት ደጉን የአገር መከታ ተኩሶበታል። ስለዚህም የማይወዳጁትን ህወሓትን ልክ ማስገባቱ ትክክል ነው። ወደፊትም ይህ ነገሩ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት። የትግራይ ህዝብም ቢሆን ትውልዱን፣ ዘመኑን፣ ንብረቱንና ማንነቱን የቀማውን የህወሓት ጁንታ መቼም መታገስ የለበትም። ከህግ ማስከበሩ ጎን መቆም አለበት።

አዲስ ዘመን፡- በኢትዮጵያ የፍትህ መዘግየቶች ይታያሉ። ይህ ደግሞ ለወንጀል መባባስ መሰረት ጥሏል ይባላል። ይህንን እንዴት ያዩታል?

ዶክተር አልማው፡- እውነት ነው። ብዙ ጊዜ የሚተቸውም በዚህ ነው። እንደውም የዘገየ ፍርድ እንዳልተፈረደ ይቆጠራል ይባላል። ቆይቶ የሚወሰድ ዕርምጃ ብዙ ነገር ያሳጣል። ከምንም በላይ ደግሞ ቂም ይፈጥራል። የራስን ፍትህ ወደመውሰድ እንዲያመራም የሚያደርግ ነው። መንግሥት በደህንነቱ አማካኝነት ማን ምን እንዳደረገ ያውቃል። ሆኖም ዕርምጃው ዘግይቶ ይወሰዳል። በእርግጥ ይህ የሆነበት በቂ ምክንያት ይኖር ይሆናል። ባለፈው በፓርላማ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት ዓይነት ችግር። ከዚያ በተጨማሪ የጸዳ አመራር አለመኖርም እንዲሁ። ስለሆነም ከበጣም መጥፎ መጥፎ እንዲወሰድ ሆኖ የፍትህ መዘግየቶች ተፈጥረው ችግሮች እየተባባሱ እንዲሄዱ አድርጓል።

አዲስ ዘመን፡- በቀጣይ የህግ የበላይነትን ለማስፈንና አገር አሁን ካለችበት ችግር እንድትወጣ ምን ይደረግ?

ዶክተር አልማው፡- ህዝብ እንደ ህዝብ አገሩን ማስቀጠል አለበት። አገር ሲቀጥል ዴሞክራሲ ይኖራል፣ ማደግ ይቻላል። ወንጀለኛ ሁሌም ወንጀለኛ ነውና ሊታገሰው አይገባም። ቤተሰቡም ቢሆን አሳልፎ መስጠትን መለማመድ አለበት። የሞራል ዝቅጠት የሌለበትና በውስጡ ስነምግባሩ ያበበ ትውል.ድ መፍጠር ላይም ሊሠራ ይገባል። ወጣቱ ደግሞ ዘመኑን ማስበላት የለበትም። በፊሽካ የሚሰለፍ ሰው ፈጥሬያለሁ ሊባል አይገባውም። በእውቀትና በማስተዋል መመራት ይጠበቅበታል። አገሩ ከፈረሰ ስደተኛ፣ ዘመንና ራዕይ የሌለው እንደሚሆን ማሰብ ይኖርበታል። ፖለቲከኛው በበኩሉ አገር ስትኖር መምራት እንደሚችል ማመን አለበት። በውድድርና በሃሳብ ልዕልና የሚያምን፤ ለአሸናፊ ሃሳብ የሚገዛና ዴሞክራሲያዊ ውድድር የሚያደርግ እንዲሁም አቃፊ ፖለቲካ የሚያራምድ መሆንን ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባል።

በመንግሥት በኩል መሠራት ያለበት ያለ ሥራ የተኮለኮሉ ተቋማትንና አመራሮችን ማስወገድ፤ አገዛዝን የሚያገለግሉ ሠራተኞችን መለየት፤ ዘመን ተሻጋሪና በእውቀት የሚመራ ፖሊሲ፣ ሠራዊት መፍጠር ነው። የፋይናንስ ስርዓቱንም በሚገባ መመርመር ይገባዋል። በሰንሰለት የተያዙ ውሾች መሳይ ተቋማትን ማፍረስና በራሳቸው ውሳኔ ሰጪ እንዲሆኑ ማድረግም አለበት። ለአገር፣ ለህዝብና ለትውልድም ባለውለታ የሚሆንበትን አሠራር መዘርጋት ዋነኛ ተግባሩ ሊሆን ያስፈልጋል።

የፖለቲካው አካሂድ፣ ዴሞክራሲያዊ ማህበረሰብ መፍጠርም ይገባል። ይህ ማለት ውሸትን የሚጸየፍና ስለእውነት ራሱን ጭምር አሳልፎ የሚሰጥ ህብረተሰብ መፍጠር ያስፈልጋል። በደልን የማይቋቋም ማለትም በራሱ ላይ ብቻ ሳይሆን በሌሎች ላይ የሚሆነውን የሚቃወም ዜጋ ማፍራትም ተገቢ ነው። ዴሞክራሲያዊ መሪ መፈጠር፣ በምርጫ መጥቶ ህዝቡ ያስቀመጠውና ህዝቡ የሚፈልገውን መሪ ማስቀመጥም ይገባል።

እንደ ዝንጀሮ አባት ተከታዮችን እያሳደደ የሚያጠፋ ሳይሆን ተተኪ መሪዎችን በዴሞክራሲያዊ ስርዓትና በእውቀት ቃኝቶና አሳድጎ ማፍራትም አለበት። ቋንቋ፣ ብሔር፣ ሃይማኖት የማይወስነው ፖለቲካ መፍጠር፣ ፖለቲካ ውድድር ሀብት፣ ሃሳብ ፣ ሙግትና በእውቀት ማሸነፍ ያለበት መሆኑን ማሳየትም ይኖርበታል። በተለይም ፖለቲካው እንደ ኳስ ወደ መሀል ገብቶ የሚችል የሚጫወትበት ማድረግ ላይ በስፋት መሥራት አለበት። ይህ ነገር ሲፈጠር ደግሞ መረጋጋት ይመጣል። ሳንጃው ወደ ልማት ይቀየራል። የጦር መሳሪያ ላይ የሚወጣው ገንዘብም አገር ይገነባል። የሚሞተውም ሰው ሀብት ይሆናልና እነዚህን መሥራት ከምንም በላይ አስፈላጊ ነው።

አዲስ ዘመን፡- ስለሰጡን ማብራሪያ እናመሰ ግናለን።

ዶክተር አልማው፡- እኔም አመሰግናለሁ።

Page 14: ሰኞ ከ 27 ዓመታት የልማት ዘፈንና ፉከራ በኋላ ... · 2021. 2. 1. · ገጽ 4 በውስጥ ገጾች ገጽ 11 ሰኞ ብዕራችን ለኢትዮጵያ

ውብሸት ሰንደቁ

በዚህ ዘመን ያለ ብረት ግብዓትነት የሚሠሩ ግንባታዎችም ሆነ ሌሎች ሥራዎች ኢምንት ናቸው ቢባል ማጋነን አይሆንም። ብረት በግብዓትነት በማያገለግልበት ቦታ እንኳን የሥራው መከወኛ መሣሪያ ሆኖ መገኘቱ ግድ ሆኗል። ታዲያ ይህ እንደ ግብዓትም እንደመሣሪያም የሚያገለግል ቁስ ጥራቱን ያልጠበቀ ሆኖ ሲገኝ የሚያደርሰው ድንገቴም ይሁን የዘገዬ አደጋ ከፍተኛ ስለሚሆን በዘርፉ የተሠማሩ ኢንዱስትሪዎች ላይ በከፍተኛ ትኩረትና ክትትል ማድረግ የግድ ነው፡፡

የሀገሪቱን የብረት ምርት ፍላጎት ከማሟላት አለፍ ብሎም ወደ ውጪ ገበያዎች በመላክ ምንዛሬ ለማግኘት ሲባል የሀገር ውስጥና የውጪ ባለሀብቶች በብረት ማልማት ዘርፍ ላይ በተለያዩ ቦታዎች ተሰማርተው ይገኛሉ። እነዚህ ብረት አምራቾች ጥራቱን ያልጠበቀ ምርት ከአመረቱ ወደ ውጪ ቢልኩ የውጭ የገበያ ንግድን እጀ ሰባራ የሚያደርጉ፤ በሀገር ውስጥ ቢሸጡ ደግሞ ሕዝብን ለአደጋ የሚያጋልጡ ይሆናሉና ነው ቁጥጥርና ክትትል ማድረጉ አሥፈላጊ ሆኖ የሚገኘው። ሆኖም በኢንዱስትሪዎች ሥራው የሚከወነው ሳይንሳዊ መንገድን ተከትሎ ነውና ጥራቱን ለማስጠበቅ የሚደረገው ክትትልና ቁጥጥርም በሳይንስ የታገዘ ሊሆን ይገባል። ከሁሉም ቀዳሚው ደግሞ የትኞቹ የብረት ምርቶች አስገዳጅ የጥራት ደረጃን እንዲያሟሉ መገደድ አለባቸው የሚለውን የመለየት ተግባር ነው።

ይህንና መሰል ተግባራትን እንዲያከናውን የተቋቋመው መንግሥታዊ ተቋም የብረታ ብረት ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ይሰኛል። ይህ የብረት ኢንዱስትሪ ምርት ዘርፍ ለአገር ኢኮኖሚ ዕድገት ከሚኖረው አስተዋፅዖ አንፃር በቅርበት ድጋፍ የሚሰጥ ጠንካራ ተቋም በማሥፈለጉ የብረታ ብረት ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 182/2002 ተቋቁሟል። የብረታ ብረት እና ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ዘርፉንም በቀዳሚነት እንዲመራ

አዲስ ዘመን ሰኞ ጥር 24 ቀን 2013 ዓ.ም ገጽ 14

ኢንዱስትሪኢኮኖሚ

ከኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበርበየሳምንቱ ሰኞና ዓርብ የሚቀርብ

የመምህራን፣ ርዕሳነ መምህራን እና ሱፐርቫይዘሮች ሙያዊ ፍቃድ አሰጣጥ እና እድሳት

የብረት ምርት ጥራት ደረጃዎችን በአስገዳጅነት

ይጠበቃል። የብረታ ብረት እና ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ከማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች የሚመደብ ሲሆን በዓለም አቀፍ የኢንዱስትሪዎች ደረጃ መሰረት ብረታ ብረት እና ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ በመባል በሁለት ይከፈላል፡፡

በመሰረታዊ ብረታ ብረት ኢንዱስትሪ የሚመደቡት ከብረት ማጣራት ጀምሮ የተለያዩ መጠን ያላቸውን የመጀመሪያ ደረጃ ምርቶችንና እነዚህን ምርቶች በግብዓትነት በመጠቀም ዝርግና ጥቅል ልሙጥ ብረቶችን፣ የተለያዩ ቅርፅ ያላቸው ድፍንና ክፍት ረጃጅም የብረት ምርቶችን፣ ሽቦዎችን፣ የሽቦ ገመዶችን፣ ቆርቆሮዎችንና ምስማሮችን የማቅለጥ፣ የማሞቅና የመዳመጥ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የሚመረቱ ናቸው።

በኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪነት የሚመደቡት ደግሞ የብረታ ብረት ኢንዱስትሪ ውጤትን በግብዓትነት በመጠቀም የተለያዩ ቅርፅ ማውጫ ቴክኖሎጂዎችን ማለትም በማቅለጥ ቅርፅ ማውጣት፣ በማነፅ፣ በብየዳ፣ በመቀጥቀጥ መሣሪያዎችንና የተለያዩ መገልገያ ዕቃዎችን የሚያመርቱ ናቸው፡፡

ይህን መሰረት በማድረግ በአሁኑ ጊዜ በብረታ ብረት ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ፊታውራሪነት አስገዳጅ

እና አስገዳጅ ያልሆኑ ደረጃ የሚያስፈልጋቸው ምርቶች ደረጃ እንዲወጣላቸው እየተሰራ ነው። በዘርፉ አስገዳጅ እና አስገዳጅ ያልሆኑ የምርት ደረጃ የሚያስፈልጋቸው ምርቶች እየለየ ደረጃ እንዲወጣላቸው እየሠራ መሆኑን ከብረታ ብረት ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

በዚህም ደረጃ ከሚያሥፈልጋቸው የብረት ምርት ዓይነቶች መካከል የቤት ክዳን ቆርቆሮ በአስገዳጅ የምርት ጥራት ደረጃ ሲፀድቅ የመኪና ፍሬን ሸራ አመራረት ደግሞ አስገዳጅ ባልሆነ የምርት የጥራት ደረጃ ፀድቋል። በቀጣይ 12 የምርት ዓይነቶችን አስገዳጅ ባልሆነ የምርት ጥራት ደረጃ ለማፅደቅ የጥራት ደረጃ ምክረ ሃሳብ ተዘጋጅቶ ለኢትዮጵያ ደረጃዎች ኤጀንሲ ተልኮ ክትትል እየተደረገ መሆኑ በመረጃው ተመላክቷል።

አስገዳጅ ካልሆኑ የጥራት ደረጃ ፕሮፖዛል ተዘጋጅቶ ደረጃ ለማሰጠት ክትትል ከሚደረግባቸው የምርት ዓይነቶች መካከል ቁርጥራጭ ብረቶች፣ የትራንስፎርመር አመራረት፣ የቀለጠ ብረት በጨረር የጥራት ደረጃን ማረጋገጥ ይገኙበታል።

የተለያዩ የማሽን ክፍሎችን ለማምረት የሚያስፈልግ

የቀለጠ ብረት አጠቃቀም፣ ጠፍጣፋ እና ብይድ የሌላቸውን ክብ ብረት መሰራት ያለበት ሁኔታ፣ የማይዝግ ብረት ለማምረት መከተል የሚገቡ የአሠራር ሥርዓቶች፣ ከጠፍጣፋ ብረት ምርት እንዴት መመረት እንዳለበት የሚሉትንም ደረጃቸውን ለማፅደቅ በእንቅስቃሴ ውስጥ ካሉ ምርቶች መካከል ይጠቀሳሉ።

ለግንባታ የሚውሉ የብረት ዓይነቶችን ከፍተኛ እና ዝቅተኛ የልኬት መጠን የሚታወቅበት፣ በሙቀት የሚሠሩ የአንግል ብረቶች፣ ለውኃ እና ለጋዝ ማስተላለፊያ የሚያገለግሉ የቧንቧ ብረቶች መገጣጠሚያ፣ መቀያየሪያና ማገናኛ ምርቶች እንዲሁም ለነዳጅ ማስተላለፊያ የሚውሉ የብረት ዓይነቶች ሂደት ምን መሆን አለበት የሚሉትና ውስጣቸው ክፍት የሆኑ ከፍተኛ የጥራት ደረጃ ያላቸው የብረት ዓይነቶች ላይም በአስገዳጅ የጥራት ደረጃ ከሚፀድቁ መካከል ተካተዋል።

አስገዳጅ እና አስገዳጅ ያልሆኑ የምርት ደረጃዎችን ማውጣት አምራቾችና ተጠቃሚዎች ተገቢውን አገልግሎት እንዲያገኙና የሸማቾችንም መብት ለማስጠበቅ ጠቀሜታ አለው። ይህም የምርት ጥራትን ለማስጠበቅ፣ ወደ አገር ውስጥ የሚገቡ ምርቶችን ለመቆጣጠር፣ አምራች ኢንዱስትሪዎች ተረፈ ምርቶችን በመቀነስ ትርፋማነታቸው እንዲጨምር እና በምርምር ዘርፍ እንደ መነሻ ሃሳብ በመሆን ያገለግላል። ከዚህ በተጓዳኝም ገቢና ወጪ ምርቶች ደረጃቸውን የጠበቁ ሆነው ለተጠቃሚው ተደራሽ እንዲሆኑ ያስችላል።

ይህም ለአገሪቱ የኢኮኖሚ ዕድገት ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው እና የቴክኖሎጂ ሽግግርን በማፋጠን የአገሪቱ ምርቶች በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ አስተዋጽኦ እንዳለውም የኢንስቲትዩቱ መረጃዎች አመላክተዋል፡፡

በአጠቃላይ ደረጃዎች በተለይም አስገዳጅ ደረጃዎች የምርቶች ጥራት ማስጠበቂያ መንገዶች ናቸው። የምርቶችን ዓይነት ለይቶ እና የጥራት ደረጃ አውጥቶ ኢንዱስትሪዎች በዚያ መሰረት አምርተው ለገበያ እንዲያቀርቡ ማድረግ የገበያ ተወዳዳሪነት ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የሀገር ክብር ማስጠበቂያ ጉዳይም ነው።

ለግንባታ የሚውሉ የብረት ዓይነቶች፣ በሙቀት የሚሠሩ የአንግል ብረቶች፣ ለውኃ እና ለጋዝ ማስተላለፊያ የሚያገለግሉ የቧንቧ ብረቶች መገጣጠሚያ እና ሌሎችም በአስገዳጅ የጥራት ደረጃ ከሚፀድቁት መካከል ተካተዋል፤

በትምህርት ሥርዓታችን የሚፈለገውን የትምህርት ጥራት ለማምጣት በየደረጃው ያሉ መምህራንና የትምህርት ተቋማት አመራር ወሳኝ ሚና አላቸው። የመምህርነት ሙያ ቀደም ሲል በሠለጠኑበት እውቀት ብቻ በመጠቀም የሚሠራበት ሳይሆን በየጊዜው የራስን አቅም መገንባትን የሚጠይቅ መሆኑ ግልጽ ነው። በሥራ ያሉትን የማብቃት ሥራ መስራትና አዲስ ወደ ሙያው የሚገቡትንም በሙያ ማስተዋወቂያ ፕሮግራም ውስጥ እንዲያልፉ በማድረግ የማስተማር ብቃታቸውን በቀጣይነት ማረጋገጥ ያስፈልጋል። በመሆኑም የመምህራንና የትምህርት ተቋማት አመራር የሚጠበቀውን ውጤታማነት ለማረጋገጥ ራሳቸውን የማብቃት ሙያዊ ግዴታ አለባቸው። ይህን ሙያዊ ግዴታቸውን ለመወጣት እንዲያስችላቸው ለመምህራንና ለትምህርት ተቋማት አመራር መንግሥት አስፈላጊውን ተከታታይ የሙያ ማሻሻያና የትምህርት ደረጃ ማሻሻያ ሥርዓት ዘርግቶ በመተግበር ላይ ይገኛል። ስለሆነም በየወቅቱና በየደረጃው በትምህርት ሙያ ላይ ለሚሰማሩ ጀማሪዎች በሙያው መቀጠልና ብቃታቸውን ማሳደግ እንዲችሉ የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና ዕድሳት ሥርዓት ተዘርግቷል።

ይህ የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና እድሳት ሥራ ጠቀሜታውም ለጀማሪዎች እንደ ባለሙያ መቀበያና ብቃት ማረጋገጫ (Acceptance to the profession) የሚያገለግል ሲሆን፣በሥራው ውስጥ ላሉት ደግሞ ያሉባቸውን ክፍተቶች በመለየትና ተገቢውን ሙያዊ ሥልጠናዎች በማመቻቸት ለተሻለ ውጤት እንዲሰሩ ማድረግ ነው። በአጠቃላይ የመምህራንና ትምህርት ተቋማት የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና እድሳት ስርዓት ማለት ሙያው የሚጠይቀውን ስነምግባር ፤እውቀት፤ክህሎትና የተግባራት ክንውን ባካተተ ሁኔታ ተገቢውን ሙያዊ ብቃት ስታንዳርዶችን/professional Competence Standards/የሚያሳይ ስርዓት ነው። ይህ ስርዓት በፍላጎታቸው ወደ ሙያው የሚገቡ ዜጎች ከመጀመሪያ አንስቶ ተከታታይነት ባለው

አግባብ የተቀመጠውን የሙያ ብቃት ደረጃ ማሟላታቸውን በማረጋገጥ ወደ ሙያው እንዲገቡና በሙያው እንዲቀጥሉ ማስቻል ነው። በመሰረቱ የመምህራንና የትምህርት ተቋማት አመራር ሙያዊ እንቅስቃሴ ዋና ግብ የተማሪዎችን ውጤት ማሻሻል ነው።

የሙያ ፈቃድ ሥርዓት ሁለት ዋና ዋና መሠረታዊ ቁልፍ ሐሳቦችን ይይዛል። አንደኛው የሙያ ፈቃድ መስጠት ሲሆን ፤ሁለተኛው ደግሞ የሙያ ፈቃድ ማደስ ነው ። የሙያ ፈቃድ መስጠት ማለት ሙያው የሚጠይቀው ሥነ ምግባር፣ እውቀት፣ ክህሎትና የተግባራት ክንውንን ባካተተ ሁኔታ ተገቢውን ሙያዊ ብቃት ስታንዳርዶች (Professional Competence Stanadards) በማስቀመጥ የት/ቤት አመራሮችና መምህራንን ወደ ሙያው እንዲገቡ ማድረግ ነው፡፡

የሙያ ፈቃድ ማደስ ማለት የአመራሩና የመምህሩ በተለያዩ ቅደም ተከተል ባላቸው ደረጃዎች የቆይታ ጊዜ በመጠበቅ ተከታታይነት ባለው ሁኔታ የሙያ ብቃት ደረጃ ማሟላታቸውን ማረጋገጥ ለደረጃው ብቁ ከሆኑ በሙያው እንዲቀጥሉ ለማስቻል በእጃቸው የሚገኘውን የሙያ ፈቃድ የማደስ ሥርዓት ነው።

የመምህራንና የትምህርት ተቋማት አመራር የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና እድሳት ዓላማና አስፈላጊነት መሠረታዊ ነገር በት/ቤቶች የሚሰጠውን ትምህርት ጥራት ለማስጠበቅ እየተደረገ ያለውን ጥረት ለመደገፍ የመምህራንና የትምህርት ተቋማት አመራር የሙያ ብቃት በማስጠበቅ የመምህርነትንና የት/ተቋማት የአመራርነት ሙያዊ ክብርን አሁን ካለበት ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሳደግ የመምህርነትንና የት/ተቋማት አመራር ሙያዊ ስራን በየጊዜው ተከታታይነት ባለው ሁኔታ ራሳቸውን ለማብቃት በሚጥሩ ትጉኃን ሙያተኞች ለመሸፈን የሀገራችንን የሙያ ፈቃድ ሥርዓት በመዘርጋትና በመተግበር የመምህራን፣ርዕሰ መምህራንና ሱፐርቫይዘሮችን ሙያዊ ብቃት ለመመዘን፤ ለሚመለከታቸው ሁሉ ግብረመልስ ለመስጠትና መምህራን፣ርዕሰ መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች

የሚሰለጥኑበትን ተቋምና የሥልጠና ሥርዓት ለመወሰን ያስችላል።

የተፈጻሚነት ወሰን ይህ የሙያ ፈቃድና እድሳት ሥርዓት በመንግሥት፣

በሕዝብ፣ በግልና በሃይማኖት ተቋማት ፈቃድ ተሰጥቷቸው በሚተዳደሩ የአፀደ ህፃናት፣ የመጀመሪያ፣ የሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤቶችና በመምህራን ትምህርት ኮሌጆች ውስጥ የሚያስተምሩ መምህራን እንደዚሁም ከአፀደ ህፃናት እስከ መሰናዶ ትምህርት ተቋማት በሚሠሩ አመራሮች ላይ ተፈጻሚነት ይኖረዋል።

የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና እድሳት መርሆዎች (principles)

መምህራንና የትምህርት ተቋማት አመራር በየደረጃው የተቀመጡትን የሙያ ብቃት ደረጃዎች ሲያሟሉ የሙያ ፈቃድ ይሰጣቸዋል/ይታደስላቸዋል። የሙያ ፈቃድና ዕድሳት የቆይታ ጊዜያትን ጠብቆ ተከታታይነት ባላቸው ደረጃዎች የሚከናወን ሲሆን፤ ደረጃዎችን በመዝለል የሚፈጸም አይሆንም። የሙያ ፈቃድና ዕድሳት ከመምህራንና ከትምህርት ተቋማት አመራር የደረጃ እድገት መሰላል ጋር የተሳሰረ ነው።የሙያ ፈቃድና እድሳት የሚያገለግለው ፈቃድ ለተሰጠበት የትምህርት እርከን ብቻ ይሆናል። የሙያ ፈቃድ ያልያዙ ወይም ያላቸውን የሙያ ፈቃድ ያላሳደሱ መምህራንና የትምህርት ተቋማት አመራር በሙያው መቀጠል አይችሉም። የሙያ ፈቃድና ዕድሳት ግልጽና ተጨባጭ መረጃዎችን መሠረት ባደረገ ፍትሐዊ የምዘና ሂደት ይከናወናል።

የሙያ ፈቃድ ዓይነቶችበሙያ ፈቃድ አሰጣጥ ሥርዓት ውስጥ አራት የፈቃድ

ዓይነቶች ይኖራሉ። እነርሱም ጊዜያዊ የሙያ ፈቃድ (Provisional License) ፣ የመጀመሪያ የሙያ ፈቃድ (Initial Professional License)፣ ሙሉ የሙያ ፈቃድ (Full Professional License) እና ቋሚ የሙያ ፈቃድ (Permanent Professional License) ናቸው።

ሀ) ጊዜያዊ የሙያ ፈቃድ አሰጣጥ፦ ጊዜያዊ ፈቃድ በመምህርነት ወይም በርዕሰ መምህርነትና በሱፐርቫይዘርነት ሙያዊ ሥልጠና ሳይወስዱ በማስተማር ወይም በአመራር ሥራ እንዲያገለግሉ ከአፀደ ሕፃናት እስከ መሰናዶ ትምህርት ቤቶች ለተመደቡ መምህራን፣ርዕሰ መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች ለሁለት ዓመታት ብቻ እንዲያገለግል በጊዜያዊነት የሚሰጥ ፈቃድ ሆኖ ፈቃዱ አይታደስም።

ለ) የመጀመሪያ ሙያ ፈቃድ አሰጣጥ፦ የመጀመሪያ የሙያ ፈቃድ ለሁለት ዓመታት ብቻ የሚያገለግል ሆኖ በጊዜያዊ የመምህርነት ወይም የርዕሰ መምህርነት ወይም የሱፐርቫይዘርነት ፈቃድ ሲያገለግሉ ለቆዩና ከመምህራን ትምህርት ተቋማት በመምህርነት ወይም በትምህርት ተቋማት አመራርነት ሰልጥነው በሙያው ለመቀጠል ለአመለከቱ ሙያተኞች የሚሰጥ የሙያ ፈቃድ ዓይነት ነው። የመጀመሪያ የሙያ ፈቃድ አይታደስም እንደጊዜያዊ ፈቃድ ሁሉ አይታደስም ።

ሐ) ሙሉ የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና እድሳት አፈጻጸም ፦ ሙሉ የሙያ ፈቃድ የመጀመሪያ ሙያ ፈቃድ በመያዝ ሲሠሩ ቆይተው በተገቢው መንገድ ያጠናቀቁ መምህራን፣ርዕሰ መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች የሙያ ፈቃዱን ለማግኘት ሲያመለክቱና በደረጃው የሚሰጥ የሙያ ፈቃድ ሲሆን፤ ለመምህራን በየሦስት ዓመት ለሦስት ጊዜያት፤ ለአመራሮች ደግሞ በየሦስት ዓመት ለሁለት ጊዜያት የሚታደስ ይሆናል።

መ) ቋሚ የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና እድሳት አፈጻጸም፦ ቋሚ የሙያ ፈቃድ ማለት ሙሉ የሙያ ፈቃድ ይዘው በዚህ ደረጃ የሚደረጉትን የሙያ ፈቃድ እድሳት አጠናቀው ቋሚ የሙያ ፈቃድ ለማግኘት ለአመለከቱ መምህራን፣ርዕሰ መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች ለደረጃው የሚሰጥ ሲሆን፤ ለመምህራን በመጀመሪያ በሦስት ዓመት ቀጥሎ በአምስት ዓመታት ለሁለት ተከታታይ ጊዜያት የሚታደስ ይሆናል። ለርዕሰ መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች ግን ቋሚ የሙያ ፈቃድ አይታደስም።

Page 15: ሰኞ ከ 27 ዓመታት የልማት ዘፈንና ፉከራ በኋላ ... · 2021. 2. 1. · ገጽ 4 በውስጥ ገጾች ገጽ 11 ሰኞ ብዕራችን ለኢትዮጵያ

አዲስ ዘመን ሰኞ ጥር 24 ቀን 2013 ዓ.ም ገጽ 15

ፋሽን

አዲስ ዘመን ድሮ

መዝናኛ

አብርሃም ተወልደ

ኃይለማርያም ወንድሙ

የእንግሊዝ የፋሽን ካውንስል የሽልማት አሰጣጡን ቀየረበዚህ ዓመት የእንግሊዝ የፋሽን ካውንስል ከዚህ

ቀደም ግለሰቦችን እና ተቋማትን በተለያየ ዘርፍ እያጨ እንደሚሸልመው ሳይሆን በተለየ የሽልማት ስርዓት ማምጣቱን ኢንዲፔንደንት የተባለ የወሬ ምንጭ አስነብቧል።

ከ800 የዓለም የፋሽን ኢንዱስትሪ ቁልፍ አባላት መካከል በጥንቃቄ ከተመረመሩ በኋላ 20 ግለሰቦች እና ብራንዶች ካከል በተለይ ለማህበረሰብ እና ለአካባቢ ደህንነት ለአበረከቱት አስተዋጽዎ እውቅና ተስጥቷል።

ከእነዚህ አውቅና እና ሽልማት ከአገኙት አሸናፊዎች መካከል የብሪትሽ ቮግ አዘጋጅ ኤድዋርድ ኤንኒንፉል ቻኔል እና የበርበሪው ሪካርዶ ቲስ ይገኙበታል። ሽልማቱን የተጎናጸፉት እነዚህ ግለሰቦች እየተስፋፋ ለመጣው የፋሽን ኢንዱስትሪ እና እየተጎዳ ላለው አካባቢ ጥበቃ፤ ጉዳት ለመቀነስ ኢንዱስትሪውን ለማዘመን በአደረጉት ጥረት ነው።

ሌላኛው የኢንዱስትሪው ኮከብ ከሆኑት መካከል ስቴላ ማካርቲን ናት። የስቴላ ማርቲን ተሸላሚ መሆን ለማንም የማያስገርም እና አሻሚ የማይሆነው ነው። የሚለው የወሬ ምንጩ በተለይ ለኢንዱስትሪው ዘላቂነት እና መጽናት ላደረገችው አስተዋጽኦ እንደሚገባትም አስነብቧል።

ማካርትኒ ለረጅም ዓመታት ለአካባቢ ጥበቃ ተስማሚ የሆኑ የፋሽንንም የተከተሉ የፈጠራ ሥራዎች ስትሠራ የኖረች ዝነኛ ዲዛይነር ናት። ዲዛይነሯ አገልግለው በተጣሉ ቁሳቁሶች መልሶ መጠቀም የተለያዩ የፋሽን ውጤቶችን ከፈጠራ ጋር በማቅረብ የአካቢውን ብክለት ለመከላከል የራሷን ጥረት ስታደርግ ነበር።

የፈጠራ ባለሙያዋ የራሷን ድርጅት ኤል ቪ ኤም ኤች ለተባለ ድርጅት ከሸጠች በኋላ ለዚሁ ድርጅት ሥራ አስኪያጅ አማካሪ በመሆን እያገለገለች ሲሆን፤ በሥራዋም ድርጅቱ እንዴት የአካባቢን ብክለት መከላከል እንደሚችል እና ለህብረተሰቡ የሚያደርገው አስተዋጽኦ እንዴት ማድረግ እንደሚገባው ነው።

የብርቲሽ የፋሽን ካውስል በበኩሉ “ስቴላ ማካርቲን ለፋሽን ኢንዱስትሪ ዘለቄታማነት እና ወደ ኢንዱስትሪው

ለሚገቡ አሻራዋን ያኖረች ናት፤ ከእዚህም በተጨማሪ ባለሙያዋ በጨርቅ ላይ በሚሠሩ የፈጠራ ሥራዎች በተለያዩ ሂዶች በመደገፍ በዘመን መካከል የማይናድ እና የማይረሳ ውለታ ነው” ብሏል።

ድርጅቱ አክሎ “ስቴላ የፋሽኑን ዋና ንድፍ “ዲ ኤን ኤ” በመቅረጽ በአጠቃላይ የፈጠራ ችሎታ እና ዘላቂ የኢንዱስተሪ ደረጃን ከፍ አድርጓል። ዘላቂ ልምዶች ያለምንም እንከን ወደ ቅንጦት እና የፈጠራ ሥራዎች ሊዋሃዱ እንደሚችሉም ያሳየች ባለሙያ ናት” ብሏል።

ሌላኛው በብሪታኒያ የፋሽን ካውንስል ተሸላሚ እና በብሪታኒያ የእጅ ቦርሳ ዲዛይነሩ አንያ ሂንድ ማርች ነው። ይህ ንድፍ አውጪ ግለሰብ “የግሪን ፒስ” አምሳደር በመባል የሚታወቅ ሲሆን እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2007 “እኔ የፕላስቲክ ሻንጣ አይደለሁም” በሚለው አባባሉም ይታወቃል። ለአካባቢ ጥበቃ የተለየ አመላካከት እንዳለውም ይነገርለታል።

አንያ ሂንድ ማርች ለትልቁ ለንደን የፋሽን ሳምንት ከመዘጋት ይልቅ ሱቁን ለሦስት ቀን በመዘጋት ያገለገሉ የፕላስቲክ መጠጫዎችን መሰብሰቢያ አድርጎታል። ይህም እንዴት አንድ ጊዜ የምንጠቀምባቸው ቁሶች አካባቢን እንደሚጎዳ ለማሳየት በሚል አስቦ እንደሆነ ምንጩ አስነብቧል።

ይህም ዲዛይነሩ ሱቁን ለመሙላት 90 ሺህ የፕላስቲክ ጠርሙሶቹን ተጠቅሟል ይህም በየ 8 ነጥብ 5 ደቂቃው እጅግ ብዙ የፕላስቲክ ጠርሙሶች እንደሚጣሉ ለማሳየት የሞከረበት ሥራም ነበር።

በየሳምንቱ አርብ ሂንድ ማርች ከሚያገኘው ሽያጭ ትርፍ ለራሱ እና ለሌሎች ጉዳዮች ከመጠቀም ይልቅ የሚያገኘውን በሙሉ ለአካባቢ በጎ አድራጎት ቮይስ ፎር ኔቼር መስጠትን መርጧል።

ሂንድ ማርክ በወረርሽኙ ወቅት ለህክምና ባለሙያዎች የሚታጠብ እና እንደገና ሊለበሱ የሚችሉ

ጋዎኖቹን በማዘጋጀት ላደረገው ጥረት ሽልማት ተጥቶታል።

ሌላኛው በካውንስሉ ሽልማት ካገኙት በላሙያዎች መካከል ዲዛይነር ክሪስቶፈር ራቤርን ነው። ይህ ዲዛይነር የተራረፉ እና የተጣሉ ጨርቆችን በመጠቀም እንደገና ጥቅም ላይ በማዋል የወንዶች ልብሶችን እና “ሪያቡረን” የተባለ ታዋቂ የንግድ ምልክት ለመፍጠር ችሏል።

በክርስቶፈር ፈጠራ “ሪበርን” የንግድ ምልክት እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2009 ጥሩ እና ውበት ያላቸውን ለክረምት የሚሆኑ አልባሳት እንዲሁም ሙሉ ልብስ ጃኬቶች እና ኒሎን ፓራሹት ለማምረት እና ለማስተዋወቅ ችሏል። ከዚህም በተጨማሪ የወታደር ልብሶችንም ለማዘጋጀት ችሏል።

ካውንስሉ ስለ ዲዛይነር ክርስቶፈር ሲናገር “ክርስቶፈር ማለት ለሚሠራበት ንግድ ምልክት የሚተጋ እና የድርጅቱንም ስም ለመገንባት የሚጥር ኢንዱስትሪውም ዘላቂ እንዲሆን ደግፏል” ብሏል።

የእንግሊዝ የፋሽን ካውንስል አክሎ እንዳለው ክሪስቶፈር “የፋሽኑ ዲዛይነሮች የቅጦት ጽንሰ ሃሳቦችን በመተው ወደ በዓላዊ ፋሽን ደንበኛ እንዲሳብ የተረፉ ጨርቆችን እንደገና ጥቅም ላይ በማዋል “ራበርን” የተባለውን የንግድ ምልክት ከፍ ብሎ እንዲታይ እንዲሁም ለቀጣይ ትውልድ ለአካባቢ ጥበቃ ለሚረዱ ዲዛይነሮች “መነሻ” ነው”

ቴሪሳ የተባለች በአሥራዎቹ ዕድሜ ላይ የምትገኝ ወጣት እንዲህ ብላለች፦ “አንዳንድ ጊዜ፣ አንድን ፋሽን የምወደው ማስታወቂያ ላይ በተደጋጋሚ ስላየሁት ነው። አንድን አለባበስ ብዙ ጊዜ በመመልከትህ ያንን ፋሽን ለመከተል ልትፈተን ትችላለህ።” ማስታወቂያ ተጽዕኖ የሚያደርግባቸው ሴቶች ልጆች ብቻ አይደሉም። ዚ ኤቭሪቲንግ ጋይድ ቱ ሬይዚንግ አዶለሰንት ቦይስ የተባለው መጽሐፍ እንዲህ ይላል፦

“ወንዶች ልጆችም በፋሽን በቀላሉ ሊማረኩ ይችላሉ። የንግዱ ዓለም ገና ከልጅነታቸው ጀምሮ በእነሱ ላይ ተጽዕኖ ለማድረግ ይጥራል።” ነገር ግን ከሚታየው ማስታወቂያ በመውጣት ለአካባቢም ለግልም የሚጠቅሙ ምርቶች ላይ ማተኩር ተገቢ ነው።

መለዮውን አነሳለሁ ብሎ ወድቆ ሞተአዲስ አበባ (ኢ.ዜ.አ)፡- በሐይቆችና ቡታጅራ

አውራጃ ግዛት ውስጥ መጋቢት ፲፪ አንድ የወህኒ ቤት ዘበኛ በመኪና በሚጓዝበት ጊዜ የወደቀበትን መለዮውን አነሳለሁ በማለት ከመኪና ወድቆ ሕይወቱን አጥቷል። አደጋው የደረሰው የአሥር አለቃ ከበደ ማሞ የተባለ ሾፌር ቁጥር ፫፻፲፪ አዲስ አበባ በሆነ መኪና ከሐይቆችና ቡታጅራ አውራጃ ግዛት ወህኒ ቤት ፤ እስረኞችን ለሥራ ይዞ ወደ አዳሚ ቱሉ አግጣጫ ሲጓዝ ነው። በዚህ ጉዞ መኪናው ፩፻፷፩ ኪሎ ሜትር ርቆ ከሚገኝ ሥፍራ ላይ ሲደርስ እስረኞቹን አጅቦ ይሔድ የነበረው ወታደር በላቸው አላምነህ የተባለ የወህኒ ቤቱ ባልደረባ ከመኪናው ላይ መለዮው ወድቆበት ከመሬት ለማንሳት ርሱ ከመኪናው ወድቆ ወዲያውኑ ሕይወቱ ማለፉንና የዚህ ሰው አስከሬን ለምርመራ ወደ ዳግማዊ ምኒሊክ ሆስፒታል መላኩን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ፖሊስ ማስታወቂያ ክፍል አስታወቀ።

(መጋቢት 17 ቀን 1960 የወጣው አዲስ

ዘመን)ዓመፀኛው ዝንጀሮ ተገደለአዲስ አበባ (ኢ.ዜ.አ)፡- ሁለት ቀን ሙሉ በመንደር

ውስጥ እየተዘዋወረ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጉዳት ያደረሰው ዝንጀሮ ተገደለ።

በልደታ ወረዳ መካኒሳ ቀበሌ ውስጥ ከመጣበት ያልታወቀ አንድ ገመር ዝንጀሮ መጋቢት ፲፱ቀን ፯ ሰዎች ነክሶ ከማቁሰሉም በላይ በመንደሩ የሚገኙትን ውሾች ሁሉ እንዲባረሩ አድርጓል።

በዚሁ ዝንጀሮ ከተነከሱት ፯ ሰዎች መካከል ፬ቱ በብርቱ ስለቆሰሉ ለሕክምና ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውን ከአሜሪ ሉተራን ሚሲዮን ቄስ ዓለም ታደሰ በላይ ገልጠዋል። በአውሬው ጉዳት እንዳይደርስባቸው ይከላከሉ ከነበሩት ሠፈረተኞች መካከል የስንካሳ ጋራዥ ሠራተኞች ትናንት በ፲፩ ሰዐት ገደማ ላይ በሦስት ጥይት ከመቱት በኋላ፤ ዝንጀሮው የሞተ መሆኑን ከሠፈረተኛው ለመረዳት ተችሏል።

ዝንጀሮው ጤነኛ ወይም በውሻ በሽታ የተለከፈ አለመሆኑን የመካኒሳ ቀበሌ ምክትል ፖሊስ ጣቢያ ሊያረጋግጥ አልቻለም።

በሠፈረተኛው ሰው ላይ ጉዳት ያደረሰው ዝንጀሮ እሬሳ አሁንም ከመካኒሳ በታች ከሚገኘው ወንዝ ዳር ተጥሎ ይገኛል።

(መጋቢት 21 ቀን 1960 የወጣው አዲስ ዘመን)

፪ ሄሊኮፕተሮች አደጋ ደረሰባቸውአዲስ አበባ (ኢ.ዜ.አ)፡- ሁለት ሄሊኮፕተሮች ትናንት

በደረሰባቸው አደጋ ምክንያት ወድቀው፤ አንደኛው ፈጽሞ ተቃጥሎ ከጥቅም ውጪ ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ መጠነኛ ጉዳት ደርሶበታል። በሁለቱም ሄሌኮፕተሮች ውስጥ በነበሩት ሰዎች ላይ አንዳችም ጉዳት አልደረሰም።

ሁሄ ፪ የሚባለው የካርታ አነሳስ ድርጅት ሄሌኮፕተር ከአዲስ አበባ በስተሰሜን እንጦጦ አጠገብ በሚገኘው በራስ ካሳ ሠፈር በሥራ ጉዳይ ሲበር በደረሰበት ብልሽት ወድቆ ሲቃጠል ከውስጡ የነበሩት ሁለት አሜሪካኖች ወጥተው እሳቱን ለመከላከል ያደረጉት ሙከራ ሳይሳካላቸው በመቅረቱ ሄሌኮፕተሩ ተቃጥሎ ከጥቅም ውጪ ሆኗል።

የመጀመሪያው ሄሌኮፕተር አደጋ በስምንት ሰዐት ገደማ እንደተሰማ የኢትዮጵያ ጦር ሠራዊት ሄሌኮፕተር አስፈላጊውን ርዳታ ለማድረግ ልኮ አደጋው በደረሰበት ሥፍራ ለመውረድ ሲያንዣብብ ከዛፍ ጋር ስለተጋጨ ወድቋል።

የመጀመሪያው ሄሌኮፕተር ዓይነት በሆነው በጦር ሠራዊት ሄሌኮፕተር ውስጥ ተሳፍረው በነበሩት ፯

ሰዎች ላይም አንድም ዓይነት ጉዳት አልደረሰባቸውም። አደጋው የደረሰበት ምክንያት በመመርመር ላይ መሆኑ ታውቋል።

(መጋቢት 25 ቀን 1960 የወጣው አዲስ ዘመን)

፮ ሰዎች በእሳት ቃጠሎ ሞቱፍቼ (ኢ.ዜ.አ)፡- በእንሳሮ ወረዳ ግዛት ውስጥ "ጥቁር

ዱር" በተባው ቀበሌ አቶ ተሰማ እርግጤ የተባሉ ሰው ጎረቤት በሌለበት ሥፍራ አዲስ በሠሩት ቤት ውስጥ ከ፭ ቤተሰቦቻቸው ጋር በእሳት አደጋ ተቃጥለው መሞታቸውን የእንሳሮ ወረዳ ግዛት ጽሕፈት ቤት ማስታወቁን የአውራጃው ግዛት ዋና ጸሐፊ አቶ ጥላን ደጀን ገለጡ።

ይህ አሰቃቂ አደጋ ሊደርስ የቻለው በምን ዓይነት ሁኔታ እንደሆነ ለማወቅ ባይቻልም ፤ባለቤቱ አቶ ተሰማ እርገጤ አዲስ የሠሩት ቤት ሳይመረግ ዙሪያውን በገለባ የተሸፈነ እንደነበር ዋና ጸሐፊው አረጋግጠዋል።

ይኸው ቤት ባልታወቀ ምክንያት ሌሊት በእሳት ተያይዞ ሲቃጠል ሰዎቹ የሚወጡበት ቦታ ስላጡ ፤ራሳቸው አቶ ተሰማ እርገጤና ባለቤታቸው እመት ብዙነሽ በየነ ከ፬ ልጆቻቸው ጋር ተቃጥለው ሞተዋል። በዚሁ የእሳት ቃጠሎ የሞቱት አቶ ተሰማ እርገጤና የወይዘሮ ብዙነሽ በየነ ልጆች ላቀች ተሰማ በለጠ ተሰማ ፀሐይ ተሰማና እምዬ ተሰማ የተባሉ ናቸው።

ከዚህም በቀር በዚሁ በእሳት ቃጠሎ አራት ፍየሎች ተቃጥለው የሞቱ መሆናቸው ታውቋል።

(መጋቢት 28 ቀን 1960 የወጣው አዲስ ዘመን)

በዛሬው የአዲስ ዘመን ድሮ አምዳችን አዲስ ዘመን ላይ ከወጡ ፅሑፎች መካከል በሀገር ውስጥ በሰዎች ላይ የደረሱ የተለያዩ አደጋዎች ላይ የተፃፉት ላይ አተኩረናል። በ1960 ዓ.ም ከታተሙት አዲስ ዘመን ጋዜጦች ካገኘናቸው መረጃዎች ውስጥ በአዲስ አበባ እንጦጦ አካባቢ ሄሌኮፕተር ተከስክሶ ሲቃጠል 6 ሰዎች ምንም ሳይሆኑ መትረፋቸውን ይገልፃል። በወቅቱ የተከሰከሰውን ሄሌኮፕተር ለማየትና አደጋ የደረሰባቸውን ለማዳን ሌላ ሄሌኮፕተርም ከዛፍ ጋር ተጋጭቶ ተከሰከሰ ይለናል የወቅቱ ዜና። በሌላ ዜናውም በመካኒሳ አካባቢ ዝንጀሮ በመንደር ውስጥ እየተዘዋወረ ሰዎች ማቁሰሉንና ውሾችን ማባረሩን ይገልጻል። ሌሎችም አደጋ ተኮር ዜናዎች አክለን በዚህ እንድታነቡት ጋብዘናል።

Page 16: ሰኞ ከ 27 ዓመታት የልማት ዘፈንና ፉከራ በኋላ ... · 2021. 2. 1. · ገጽ 4 በውስጥ ገጾች ገጽ 11 ሰኞ ብዕራችን ለኢትዮጵያ

22 ሰኞ ጥር 24 ቀን 2013 ዓ.ም

በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ

ስፖርትአዲስ ዘመን

ብርሃን ፈይሳ

በኢትዮጵያ ብቸኛው ኢንተርናሽናል ውድድር የሆነው የጃንሜዳ ኢንተርናሽናል አገር አቋራጭ ውድድር ትናንት ለ38ኛ ጊዜ ተካሂዷል። ክልሎችን፣ ከተማ አስተዳደሮችን፣ ክለቦችንና የአትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከላትን እንዲሁም የጎረቤት አገራት አትሌቶችን የሚያሳትፈው ይህ ዓመታዊ ውድድር በመደበኛነት በጃንሜዳ የሚካሄድ ቢሆንም ቦታው ለውድድሩ አመቺ ባለመሆኑ ምክንያት በሱሉልታ ልዩ ስሙ ቆዳ ፋብሪካ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ተካሂዷል።

ውድድሩ በተለያዩ ዘርፎችና ርቀቶች የተካሄደ ሲሆን ፤ በወጣት ሴቶች 6 ኪሎ ሜትር ለምለም ንብረት ከአማራ ክልል፣ አንችንአሉ ደሴ ከሲዳማ ቡና እንዲሁም መዲና ኢሳ ከአማራ ክልል ከአንድ እስከ ሶስት ያለውን ደረጃ በመያዝ ውድድራቸውን አጠናቀዋል። በ10 ኪሎ ሜትር አዋቂ ሴቶች ዘውዲቱ አደራው ከአማራ ብድርና ቁጠባ፣ ትዕግስት ጌትነት ከአዊ ልማት ማህበር እና ገበያነሽ አያሌው ከመከላከያ የወርቅ ብርና ነሐስ ሜዳሊያ ተሸላሚዎች ሆነዋል።

በ8ኪሎ ሜትር ወጣት ወንዶች በረከት ዘለቀ እና ገበየሁ በላይ ከአማራ ብድርና ቁጠባ አንደኛ እና ሁለተኛ ሲሆኑ፤ ጭምዴሳ ደበሌ ከኦሮሚያ ክልል ሶስተኛ በመውጣት አሸናፊዎች ሆነዋል። በ10 ኪሎ ሜትር ወንዶች ንብረት መላክ ከአማራ ክልል፣ ለጥቂት የተቀደመውና ውድድሩን ሲመራ የቆየው ዳንኤል ሲሞል ከኬንያ እንዲሁም ገመቹ ዲዳ ከኦሮሚያ ክልል

የጃንሜዳ ኢንተርናሽናል አገር አቋራጭ ውድድር ተካሄደ

ተከታትለው በመግባት የሜዳሊያ ባለቤት ሆነዋል። በቡድን ውጤትም በወጣት ወንዶችና ሴቶች አማራ

ክልል፣ በአዋቂ ሴቶች አማራ ክልል፣ በአዋቂ ወንዶች መከላከያ እንዲሁም በድብልቅ ሪሌ ፌዴራል ማረሚያ ቤት የዋንጫ ባለቤት ሆነዋል። በአጠቃላይ ውጤትም

አማራ ክልል የበላይነቱን ይዟል። ድብልቅ ሪሌ ውድድር ፌዴራል ማረሚያ ቤቶች፣ የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት እንዲሁም ኦሮሚያ ክልል ቀዳሚዎች ሆነዋል።

ሽልማቱን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ፣ የአዲስ አበባ

አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ቢንያም ምሩጽ ይፍጠር እንዲሁም የፌዴሬሽኑ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ቢልልኝ መቆያ አበርክተዋል። በዚህ ውድድር ላይ አሸናፊ የሆኑት አትሌቶች እአአ ከማርች 6-7/2021 በቶጎ ሎሚ በሚካሄደው የአፍሪካ አገር አቋራጭ ውድድር አገራቸውን ወክለው የሚሳተፉም ይሆናል።

አሸናፊ የሆኑ አትሌቶች ከሜዳሊያ ባሻገር የገንዘብ ተሸላሚዎችም ሆነዋል። በዚህም መሰረት በአዋቂዎች የውድድር መድረክ በሁለቱም ጾታ ከአንድ እስከ ስድስት ያለውን ደረጃ ለያዙ አትሌቶች ከ40ሺ እስከ 6ሺ ብር ተበርክቶላቸዋል። በሁለቱም ጾታ የወጣት ምድብ ከአንደኛ እስከ ስድስተኛ ለወጡት ከብር 25ሺ እስከ 4ሺ ተሸላሚዎች ሆነዋል። በድብልቅ ሪሌ በቡድን ከአንደኛ እስከ ስድስተኛ ደረጃ ለሆኑት ከ18ሺ እስከ 6ሺ ብር

እንዲሁም በሁሉም ምድብ በቡድን ከአንድ እስከ ሶስት ያሉትን ደረጃዎች ለያዙ አትሌቶች ከዋንጫ ባሻገር ፌዴሬሽኑ ከ15ሺ እስከ 7ሺ ብር አበርክቶላቸዋል። በዚህም የቬትራን ተወዳዳሪዎችን ጨምሮ ፌዴሬሽኑ የ558 ሺ ብር ሽልማት ማውጣቱም ታውቋል።

ይህ ቦታ ለማስታወቂያ ክፍት ነው!