8
ቃልህ ተገኝቶአል እኔም በልቼዋለሁ አቤቱ፥ የሠራዊት አምላክ ሆይ፥ በስምህ ተጠርቻለሁና ቃልህ ሐሤትና የልብ ደስታ ሆነኝ። ኤር. Ŧ Ɖ፥Ŧ Ɗ 1 ቁጥር - ግንቦት ፪ሺህ ዓመተ ምሕረት MAY 2011 [email protected] የእግዚአብሔርን ቃል ቀላቅለው እንደሚሸቃቅጡት እንደ ብዙዎቹ አይደለንምና፤ በቅንነት ግን ከእግዚአብሔር እንደ ተላክን በእግዚአብሔር ፊት በክርስቶስ ሆነን እንናገራለን። 2ቆሮ. 214 ሐዋርያው ጳውሎስ ይህን ቃል የተናገረው ለቆሮንቶስ ምእመናን በሁለተኛው መልእክቱ ነው። የቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን ደማቅና ብዙ ኅብር ያላት ዝንጉርጉር ቤተ ክርስቲያን ናት። ከመጀመሪያው መልእክት ስንመለከት አብዛኞቹ ምእመናን እንደ ሥጋ ምኞት የሚመላለሱ የማያድጉ ወይም ከሕጻን ምግብ ማለፍ የተሳናቸው ሥጋውያን ክርስቲያኖች ናቸው። 1ቆሮ. 2 እና 3 ውስጥ ሦስት ዓይነት ሰዎች እናያለን፤ እነዚህም ፍጥረታዊ፥ መንፈሳዊ እና ሥጋዊ ናቸው። 1 የቆሮንቶስ ምእመናን ከርሞ ጥጃ ሆነው ለመቅረት የተዳረጉት ከሥጋዊነት የተነሣ ሲሆን የማያድግ ክርስቲያን ደግሞ በቀላሉ የሚታለልና የሚሸነገል፥ በቀላሉም የሚወናበድና ስቶ ለማሳት የማይመለስ ነው። ይህ ጥቅስ የተጻፈበትን ዐውድ ስናጤን ጳውሎስ ወደ ቆሮንቶስ ሊመጣ ማሰብንና መምጣቱ በኀዘን እንዳይሆን እነርሱ እንደተረዱት ሳይሆን ስለ እውነተኛ ማንነቱና አገልግሎቱ ይነግራቸዋል። እያገለገለ እንደሚዞርና በጉዞው ሁሉ እርሱም ሆነ ክርስቲያኖች ሁሉ የክርስቶስ ሽታና መዓዛ መሆናቸውን አውስቶ የእውቀቱን ሽታ በእነርሱ የሚገልጥ እግዚአብሔርን አመስግኖ ክርስቲያኖች ለሚሞቱት የሞት ሕይወትን ለሚያቅፉት የሕይወት ሽታ መሆናቸውን አስረዳቸው። ከዚህ አያይዞ ነው ስለ ሸቃጮችና ስለ መሸቃቀጥ የተናገረው። ይህ ቃል የተጠቀሰው ከሽታ ወይም ከሽቱ ጋር መሆኑን አንዘንጋ። ሽታን የሚሰጥ ሽቱ በዚያን ዘመን ውድ ነገር ሆኖ ግን በቀላሉ የሚቀላቀል፥ የሚቀጥንና ለገበያ የሚውል ሸቀጥ ነው። መሸቃቀጥ የተባለው ቃል καπηλεύοντες (ካፔሎዎንቴስ) መሠረቱ καπηλεύω ካፔሉዎ የሚል 1 ስለነዚህ ሦስት ዓይነት ሰዎችና በተለይም ስለ መንፈሳዊው ሰው ይበልጥ ለመረዳት በሉዊስ ስፔሪ ሼፈር የተጻፈውንና መንፈሳዊው ሰው ተሰኝቶ ወደ አማርኛ የተረጎምኩትን መጽሐፍ መመልከት ይረዳል። መጽሐፉን ማግኘት የማይችሉ ከኢንተርኔት http://good-amharic-books.com/onebook.php?bookID=39 መመልከት ወይም ወደ ኮምፒዩተር መጫን ይቻላል። ሲሆን ትርጉሙ ለትርፍ ሲባል እያሳነሱ እየቀነሱ መሸጥ፥ መቸርቸር ማለት ነው። በጳውሎስ ዘመን ዕቃን ቀላቅለው እንደሚሸቃቅጡት ሰዎች የመሰለ ሥራ በቃሉ እና በአገልግሎት ላይ እያደረጉ የሚሠሩ ሰዎች ነበሩ። እንዲያውም፥ እንደ ብዙዎቹስለሚል ብዙ ነበሩ። ያኔ ብዙ ከነበሩ ዛሬ በብዙ ተባዝተው ቢገኙ ማስገረም የለበትም። ሸቃጮች በራጅ (X-Ray) ሲታዩ ምን ይመስላሉ? ሸቃጮች ምን ያደርጋሉ? ሸቃጮች ለትርፍ ብለው ትክክለኛውን ትክክለኛ ካልሆነው ጋር ቀይጠው፥ አቅጥነው፥ አብዝተው ለገበያ የሚያቀርቡ አጭበርባሪዎች ናቸው። ይህ ከሁለት አቅጣጫ ይታያል። ለብዙዎቹ ጉዳት ለአንዱ ግን ጥቅም ነው። ጥቅሙ የሻጩ፥ የሸቃጩ ነው። የረከሰ ዋጋ ያለውን ወይም ምንም ዋጋ የሌለውን ነገር በከበረውና በውዱ ላይ ጨምሮ በከበረው ዋጋ ይሸጠዋል። ጉዳቱ ደግሞ የሸማቾቹ ነው። የረከሰውን፥ የቀጠነውን፥ የተበረዘውን፥ የተቀላቀለውን በውዱ ዋጋ ይገዛሉ። እጦት አለበት፤ አንድ ሊትር ወተት በመጠጣት ፈንታ 2/3ወይ 3/4ብቻ ከተጠጣ እጦት አለበት፤ የጎደለው ይኖራል ማለት ነው። ሸቃጮች በሁለት መንገድ ሊሸቃቅጡ ይችላሉ። አንዱ መጨመር ነው። ሌላው መቀነስ ነው። ጨማሪ ሸቃጮች ለአቅራቢውና ሻጩ ጥቅሙ ከገንዘብና መሰል ጥቅሞች ጋር መቆራኘቱ ነው። ለሸማቹ ግን የጉዳቱ ዓይነት ብዙ መጠኑም ሰፊ ነው። አንዳንዱ ጉዳት እምብዛም ጉዳት አይደለም። በሸቃጮች ከሚደረጉት ለምሳሌ፥ ቅቤ ውስጥ ማርገሪን ወይም የቀለጠ ሞራ ቢከለስ፥ በማር ውስጥ የቀለጠ ስኳር፥ የላም ወተት ውስጥ የዱቄት ወተት ወይም ወተት ያልሆነ የእህል ጭማቂ፥ የስንዴ ዱቄት ውስጥ የላመ የበቆሎ ዱቄት ቢጨምሩ ለሻጩ ትርፍ ያስገኛል፤ ገዥውን ግን በመጠኑ በገንዘብ በኩል ይጎዳዋል እንጂ ብዙም አይጎዳውም:: በወተት ውስጥ ውኃ ቢጨመር ይቀጥናልና ምንነቱ ተቀነሰ፤ ጉዳቱ ግን ብዙም አይደለም። ነገር ግን ከስግብግብነት የተነሣ ማቅጠንና መበረዝ ብቻ ሳይሆን የሚጎዱ ነገሮችንም ሸቃጮች ሊጨምሩ ይችላሉ። በርበሬ ውስጥ የቀይ ሸክላ ዱቄት ጨምሮ ሲሸጥ ተይዞ የታሰረ ሰው ዜና አንብቤአለሁ። ጤፍ ውስጥ አሸዋ፥ የስንዴ ዱቄት ውስጥ የኖራ ድንጋይ ዱቄት የጨመሩ አሉ። አንድ ጓደኛዬ በገጠር ሲኖር በልጅነቱ ኪኒን እንዲገዙ ተልከው ጠመኔ በምላጭ አስተካክለው ቀርጸው ኪኒን አስመስለው አምጥተው ይሰጡ ነበር። እንዲህ ያለው ነገር ጉዳቱ የገንዘብ ብቻ መሆኑ ይቀራል። ይህ ሲሆን አካልም እየተጎዳ ነውና ይህ አደጋ መፈጸሙ ሲታወቅ እርምጃ መወሰድ አለበት እንጂ ከቶም በዝምታ መታለፍ የለበትም። ይህ ቁሳዊ መሸቃቀጥንና አካላዊ ጉዳትን የተመለከተ ነው። እንደ ቁሳዊው መሸቃቀጥ ሁሉ መንፈሳዊ መሸቃቀጥም አለ። የዚህ መንፈሳዊ መሸቃቀጥ ጉዳት ደግሞ አካልን ብቻ ሳይሆን አካልን ጨምሮ፥ አእምሮን፥ ነፍስን፥ መንፈስንም ነው የሚጎዳው። ለመሸጥ ብለው የሚያጋንኑና የሚያሳስቱ፥ ከመጠን ያለፈ አጋንነው የሚያስተዋውቁ ነጋዴዎች ወይም ለመመረጥ ብለው የማያደርጉትን የሚቀባጥሩ ፖለቲከኞች ወይም ራሳቸውን ከተገቢው በላይ የሚያስተዋውቁ ሰዎች በምዕራቡ ዓለም hucksters ይባላሉ። የግል

(X-Ray) - deqemezmur – Be a disciple, Make Disciples ...deqemezmur.com/.../uploads/2015/04/Ezra-Literature-Mag-Issue-010.pdf · ገድል ሲነበብ ስለማያምኑ ሰዎች

  • Upload
    lykien

  • View
    257

  • Download
    0

Embed Size (px)

Citation preview

Page 1: (X-Ray) - deqemezmur – Be a disciple, Make Disciples ...deqemezmur.com/.../uploads/2015/04/Ezra-Literature-Mag-Issue-010.pdf · ገድል ሲነበብ ስለማያምኑ ሰዎች

ቃልህ ተገኝቶአል እኔም በልቼዋለሁ አቤቱ፥ የሠራዊት አምላክ ሆይ፥ በስምህ ተጠርቻለሁና ቃልህ ሐሤትና የልብ ደስታ ሆነኝ። ኤር. ፥ 1

ቁጥር ፲ - ግንቦት ፪ሺህ ፫ ዓመተ ምሕረት MAY 2011 [email protected]

የእግዚአብሔርን ቃል ቀላቅለው እንደሚሸቃቅጡት እንደ ብዙዎቹ አይደለንምና፤ በቅንነት ግን

ከእግዚአብሔር እንደ ተላክን በእግዚአብሔር ፊት በክርስቶስ ሆነን እንናገራለን። 2ቆሮ. 2፥14

ሐዋርያው ጳውሎስ ይህን ቃል የተናገረው ለቆሮንቶስ ምእመናን በሁለተኛው መልእክቱ ነው። የቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን ደማቅና ብዙ ኅብር ያላት ዝንጉርጉር ቤተ ክርስቲያን ናት። ከመጀመሪያው መልእክት ስንመለከት አብዛኞቹ ምእመናን እንደ ሥጋ ምኞት የሚመላለሱ የማያድጉ ወይም ከሕጻን

ምግብ ማለፍ የተሳናቸው ሥጋውያን ክርስቲያኖች ናቸው። በ1ቆሮ. 2 እና 3 ውስጥ ሦስት ዓይነት ሰዎች እናያለን፤ እነዚህም ፍጥረታዊ፥ መንፈሳዊ እና ሥጋዊ ናቸው። 1 የቆሮንቶስ ምእመናን ከርሞ ጥጃ ሆነው ለመቅረት የተዳረጉት ከሥጋዊነት የተነሣ ሲሆን የማያድግ ክርስቲያን ደግሞ በቀላሉ የሚታለልና የሚሸነገል፥ በቀላሉም የሚወናበድና ስቶ ለማሳት የማይመለስ ነው።

ይህ ጥቅስ የተጻፈበትን ዐውድ ስናጤን ጳውሎስ ወደ ቆሮንቶስ ሊመጣ ማሰብንና መምጣቱ በኀዘን እንዳይሆን እነርሱ እንደተረዱት ሳይሆን ስለ እውነተኛ ማንነቱና አገልግሎቱ ይነግራቸዋል። እያገለገለ እንደሚዞርና በጉዞው ሁሉ እርሱም ሆነ ክርስቲያኖች ሁሉ የክርስቶስ ሽታና መዓዛ መሆናቸውን አውስቶ የእውቀቱን ሽታ በእነርሱ የሚገልጥ እግዚአብሔርን አመስግኖ ክርስቲያኖች ለሚሞቱት የሞት ሕይወትን ለሚያቅፉት የሕይወት ሽታ መሆናቸውን አስረዳቸው። ከዚህ አያይዞ ነው ስለ ሸቃጮችና ስለ መሸቃቀጥ የተናገረው።

ይህ ቃል የተጠቀሰው ከሽታ ወይም ከሽቱ ጋር መሆኑን አንዘንጋ። ሽታን የሚሰጥ ሽቱ በዚያን ዘመን ውድ ነገር ሆኖ ግን በቀላሉ የሚቀላቀል፥ የሚቀጥንና ለገበያ የሚውል ሸቀጥ ነው። መሸቃቀጥ የተባለው ቃል καπηλεύοντες (ካፔሎዎንቴስ) መሠረቱ καπηλεύω ካፔሉዎ የሚል

1 ስለነዚህ ሦስት ዓይነት ሰዎችና በተለይም ስለ መንፈሳዊው ሰው ይበልጥ ለመረዳት በሉዊስ ስፔሪ ሼፈር የተጻፈውንና መንፈሳዊው ሰው ተሰኝቶ ወደ አማርኛ የተረጎምኩትን መጽሐፍ መመልከት ይረዳል። መጽሐፉን ማግኘት የማይችሉ ከኢንተርኔት ከ http://good-amharic-books.com/onebook.php?bookID=39 መመልከት ወይም ወደ ኮምፒዩተር መጫን ይቻላል።

ሲሆን ትርጉሙ ለትርፍ ሲባል እያሳነሱ እየቀነሱ መሸጥ፥ መቸርቸር ማለት ነው። በጳውሎስ ዘመን ዕቃን ቀላቅለው እንደሚሸቃቅጡት ሰዎች የመሰለ ሥራ በቃሉ እና በአገልግሎት ላይ እያደረጉ የሚሠሩ ሰዎች ነበሩ። እንዲያውም፥ “እንደ ብዙዎቹ” ስለሚል ብዙ ነበሩ። ያኔ ብዙ ከነበሩ ዛሬ በብዙ ተባዝተው ቢገኙ ማስገረም የለበትም።

ሸቃጮች በራጅ (X-Ray) ሲታዩ ምን ይመስላሉ?

ሸቃጮች ምን ያደርጋሉ? ሸቃጮች ለትርፍ ብለው ትክክለኛውን ትክክለኛ ካልሆነው ጋር ቀይጠው፥ አቅጥነው፥ አብዝተው ለገበያ የሚያቀርቡ አጭበርባሪዎች ናቸው። ይህ ከሁለት አቅጣጫ ይታያል። ለብዙዎቹ ጉዳት ለአንዱ ግን ጥቅም ነው። ጥቅሙ የሻጩ፥ የሸቃጩ ነው። የረከሰ ዋጋ ያለውን ወይም ምንም ዋጋ የሌለውን ነገር በከበረውና በውዱ ላይ ጨምሮ በከበረው ዋጋ ይሸጠዋል። ጉዳቱ ደግሞ የሸማቾቹ ነው። የረከሰውን፥ የቀጠነውን፥ የተበረዘውን፥ የተቀላቀለውን በውዱ ዋጋ ይገዛሉ። እጦት አለበት፤ አንድ ሊትር ወተት በመጠጣት ፈንታ 2/3ኛ ወይ 3/4ኛ ብቻ ከተጠጣ እጦት አለበት፤ የጎደለው ይኖራል ማለት ነው። ሸቃጮች በሁለት መንገድ ሊሸቃቅጡ ይችላሉ። አንዱ መጨመር ነው። ሌላው መቀነስ ነው።

ጨማሪ ሸቃጮች ለአቅራቢውና ሻጩ ጥቅሙ ከገንዘብና መሰል

ጥቅሞች ጋር መቆራኘቱ ነው። ለሸማቹ ግን የጉዳቱ ዓይነት ብዙ መጠኑም ሰፊ ነው። አንዳንዱ ጉዳት እምብዛም ጉዳት አይደለም። በሸቃጮች ከሚደረጉት ለምሳሌ፥ ቅቤ ውስጥ ማርገሪን ወይም የቀለጠ ሞራ ቢከለስ፥ በማር ውስጥ የቀለጠ ስኳር፥ የላም ወተት ውስጥ የዱቄት ወተት ወይም ወተት ያልሆነ የእህል

ጭማቂ፥ የስንዴ ዱቄት ውስጥ የላመ የበቆሎ ዱቄት ቢጨምሩ ለሻጩ ትርፍ ያስገኛል፤ ገዥውን ግን በመጠኑ በገንዘብ በኩል ይጎዳዋል እንጂ ብዙም አይጎዳውም:: በወተት ውስጥ ውኃ ቢጨመር ይቀጥናልና ምንነቱ ተቀነሰ፤ ጉዳቱ ግን ብዙም አይደለም።

ነገር ግን ከስግብግብነት የተነሣ ማቅጠንና መበረዝ ብቻ ሳይሆን የሚጎዱ ነገሮችንም ሸቃጮች ሊጨምሩ ይችላሉ። በርበሬ ውስጥ የቀይ ሸክላ ዱቄት ጨምሮ ሲሸጥ ተይዞ የታሰረ ሰው ዜና አንብቤአለሁ። ጤፍ ውስጥ አሸዋ፥ የስንዴ ዱቄት ውስጥ የኖራ ድንጋይ ዱቄት የጨመሩ አሉ። አንድ ጓደኛዬ በገጠር ሲኖር በልጅነቱ ኪኒን እንዲገዙ ተልከው ጠመኔ በምላጭ አስተካክለው ቀርጸው ኪኒን አስመስለው አምጥተው ይሰጡ ነበር። እንዲህ ያለው ነገር ጉዳቱ የገንዘብ ብቻ መሆኑ ይቀራል። ይህ ሲሆን አካልም እየተጎዳ ነውና ይህ አደጋ መፈጸሙ ሲታወቅ እርምጃ መወሰድ አለበት እንጂ ከቶም በዝምታ መታለፍ የለበትም።

ይህ ቁሳዊ መሸቃቀጥንና አካላዊ ጉዳትን የተመለከተ ነው። እንደ ቁሳዊው መሸቃቀጥ ሁሉ መንፈሳዊ መሸቃቀጥም አለ። የዚህ መንፈሳዊ መሸቃቀጥ ጉዳት ደግሞ አካልን ብቻ ሳይሆን አካልን ጨምሮ፥ አእምሮን፥ ነፍስን፥ መንፈስንም ነው የሚጎዳው።

ለመሸጥ ብለው የሚያጋንኑና የሚያሳስቱ፥ ከመጠን ያለፈ አጋንነው የሚያስተዋውቁ ነጋዴዎች ወይም ለመመረጥ ብለው የማያደርጉትን የሚቀባጥሩ ፖለቲከኞች ወይም ራሳቸውን ከተገቢው በላይ የሚያስተዋውቁ ሰዎች በምዕራቡ ዓለም hucksters ይባላሉ። የግል

Page 2: (X-Ray) - deqemezmur – Be a disciple, Make Disciples ...deqemezmur.com/.../uploads/2015/04/Ezra-Literature-Mag-Issue-010.pdf · ገድል ሲነበብ ስለማያምኑ ሰዎች

ቃልህ ተገኝቶአል እኔም በልቼዋለሁ አቤቱ፥ የሠራዊት አምላክ ሆይ፥ በስምህ ተጠርቻለሁና ቃልህ ሐሤትና የልብ ደስታ ሆነኝ። ኤር. ፥ 2

ቁጥር ፲ - ግንቦት ፪ሺህ ፫ ዓመተ ምሕረት MAY 2011 [email protected]

ሕይወትና ምስክርነታቸውን የማናውቃቸውን ሰዎች ስለቀባጠሩ ብቻ መርጠናቸው እናውቃለን። ይህ ቃል በማስታወቂያ ኢንዱስትሪ ተግተው የሚሠሩትን አጋናኞች የሚወክል ቃልም ነው። አንድ የእንግሊዝኛ ትርጉም (NET) 2ቆሮ. 2፥14ን በዚህ ቃል ነው የተረጎመው። የንግድ ማስታወቂያ የሚሠሩ ሰዎች ለማሳመን ብለው እንደሚያጋንኑ ጥርጥር የለበትም። ስለዚህ ሰለባቸው እንሆንና የማንፈልገውን ነገር ለማንጠቀምበት ዓላማ በማንችለው ገንዘብ እንገዛለን። ከገዛን በኋላ ነው ለጥቂት ጊዜ ቀውሰን እንደነበርን የሚገባን። ለምን ገዛነው? ብዙውን ጊዜ በማስታወቂያቸው ተሸንግለንና ተማርከን ነው የምንገዛው።

በመንፈሳዊው ረገድም የማያስፈልገንን ነገር የሚሸጡልንና ያንንም ደባልቀው የሚያቀርቡልን ብዙዎች አሉ። ወደ ቆሮንቶስ ምእመናን የመጡት እንዲህ ያሉ ሸቃጮች ነበሩ። እነዚህ ሸቃጮች በቀላሉ አማኝ ወደሆኑ ሰዎች በማሳሳቻ ስልቶቻቸው ይመጣሉ። የሚፈጥሩትና የሚጨምሩት እውነተኛውን የሚያረክስ ነገር ነው። በ1 ሊትር ውኃ ግማሽ መለኪያ ወተት ጨምረን ውኃ ነው ወይም አምቦ ውኃ ነው ብንል የሚያምነን የለም። የውኃው መልክ ተቀይሮ አጓት መስሏሏ! ግን አንድ ሊትር ወተት ውስጥ አንድ መለኪያ ውኃ ብንጨምር የሚያውቁት የወተቱን ጣእም የሚለዩት ብቻ ናቸው። የሚያውቁት ይለዩታል። ለማወቅ ደግሞ ዋናው መንገድ አንድ ነው። የቀጠነውን ወተት ለማወቅ ዋናው መንገድ ያልተበረዘውን ወተት ጣእም አስቀድሞ ማወቅ ነው።

ወደ ስሕተትና ወደተበረዙት ትምህርቶች ስንመጣም የተሸቃቀጠውን፥ የተበረዘውንና የቀጠነውን ከምንጩና ከዋናው ለይቶ የማወቁ ብቸኛ መንገድ ዋናውን ጠንቅቆ ማወቅ ነው። ዋናው ያልተበረዘው፥ ጤነኛውም ያልተመረዘው ነው። የቅቤ ውስጥ ሞራ መበረዝ ነው፤ የዱቄት ውስጥ ኖራ ግን መመረዝ ነው። ይህኛው የኋላኛው ሸቃጭ ለራሱ ጥቅም ማግኘቱ ብቻ ሳይሆን ሌላውንም መጉዳቱ በዝምታ መታለፍ የለበትም። ዝም ከተባለ አደጋ ብቻ ሳይሆን የአደጋው ሰለባዎች ሌሎችን በመመረዝ አደጋውን ከአደጋ ወደ መቅሰፍት ያሸጋግሩታል።

የገላትያ አብያተ ክርስቲያናት የተሸነገሉበት ዋና ስሕተት ደኅንነታቸው ደኅንነት እንዲሆን በተቀበሉት ጸጋ ላይ ሌላ መጨመር እንዳለባቸው የሚነግሩአቸው ሸንጋዮች ገብተው ጸጋን በሥራ ከለሱባቸው። ፈጥነው ወደ ሌላ ወንጌል ዘወር አሉ። በመንፈስ ጀምረው በሥጋ ሊጨርሱ ሮጡ። በክርስቶስ ነጻነትን አግኝተው በባርነት ቀንበር ሥር ወደቁ። በእምነት ድነው ሕግን ጠብቀው ሊጸድቁ ጣሩ። በመስቀሉ ላይ ከተፈጸመው ከአዲሱ ኪዳን ጥላ ስር ወጥተው ማንም ጠብቆ ሊድንበት ባልቻለው በአሮጌው ኪዳን ታዛ ስር መሆንን መረጡ። እንዴት? ለምን? በራዦች ገብተው በረዙአቸው።

ዛሬም ወይ ወደ ብሉይ ኪዳን ሕግ አስከባሪነት ወይም ወደራሳቸው ሕግ ጥበቃ ሰዎችን የሚስቡና የሚጠፍሩ ሸቃጮች አሉ። ዋናውን የወንጌሉን ጣእም አጣጥመን ካላወቅን የቀጠነውና የተበረዘው ኪሳራ ብቻ ሳይሆን ከዚያም ላለፈ ጉዳት ሊዳርገን ይችላል። በአንዳንድ ሃይማኖቶች የሚጨመሩ ነገሮች እንዴት ተቀባይ እንደሚያገኙ ሳስብ ምክንያቱ የዋናውን ወንጌል ጣዕም አለማወቃቸው መሆኑን እረዳለሁ። ሰሞኑን በአገራችን ኦርቶዶክስ አማንያን የምትደነቀውን የክርስቶስ ሠምራን ገድል አነበብሁ። ያለጥርጥር ይህ የሰይጣን ትውከት የሆነ መጽሐፍ ነው። አላዋቂ ሃይማኖተኞች ግን እንደ ገድል ያዩታል፤ ጠቅላላው መጽሐፍ ይህንን የሚመስል ነውና ከገድሉ የአንዱን ወር የጥቅምትን ብቻ ዝርዝሩ የተቀነሰለትን በአጭሩ እነሆ፤

መልአኩ ሚካኤል ክርስቶሥ ሰምራን ወደ ጣና በሕር ወስዶአት እዚያ ውስጥ ሰውነቷ ተበጣጥሶ እንደ መረብ ሆኖ ዓሣዎች በውስጧ እስኪያልፉ ድረስ 12 ዓመት ቆማ ጸለየች። እዚያ ሳለች ጌታ መጣና በ4 ወር አንድ አንድ ቀን የሚዘንብ የዝናብ ነጠብጣብ ያህል ነፍሳት መርታ ወደ መንግሥተ ሰማያት ትገባ ዘንድ ቃል ተገባላት፤ ስትሞትም መላእክት ብቻ ሳይሆኑ እናቱ ማርያምም እንደምትቀበላት ተነገራት። በሌላ ጊዜ ክርስቶስና ማርያም መጥተው ማርያም አቅፋት፥ ጡቷን አጥብታት፥ ጌታ ከጎኑ በፈሰሰው ደሙ ግንባሯ ላይ ቅዱስ ሥሉስ ብሎ ጽፎባት ወደ ሰማይ አረገ። በሌላ ጊዜ ራሱን ለሰይጣን የሰጠውን ማዕቀበ እዝጊ የተባለ ሰውን ጌታ ዘንድ ቀርባ ይቅርታ ለምና ምሕረት አስገኘችለት። የሕጻን ቂርቆስ ምላስ ተሰጣት፤ ቂርቆስም በሞተው ልጇ ፈንታ

ልጅ ሆኖ ተሰጣት። ስትጸልይ ቀድሞ ረዳዒ በሆናት በሚካኤል ላይ ገብርኤልና ሩፋኤል ተጨምረውላት ማርያም እናት ክርስቶስ አባት ሆኑላት። መጥምቁ ዮሐንስና እስጢፋኖስ አቆረቡአት፤ የጌታን ጣት እንደ ጡጦ ጠብታ ጠገበች። አንድ ቀን ሦስት ሰዎች የጌታን ሥጋ ወደም ወስደው እህል ሳይበሉ ከሰው ስላወሩ በሕይወታቸው ወደ ሲዖል ወረዱ፤ እነዚህ እንዲማሩላት ማልዳ ተማሩላትና ከሲዖል ወጡ። የኢየሱስ፥ የማርያምና የመላዕክት ስዕል ያለበት መስቀል ይዛ ሳለ ከመስቀሉ ውስጥ እራሴን አትንኪው የሚል የክርስቶስን ቃል ሰማች፤ ያም ጌታ በመስቀሉ አብሯት መሆኑን እንድታውቅ ነው። በሌላ ጊዜ ሚካኤል ወደ ሰማይ አሳረጋትና ጌታ በየቀኑ ከሲዖል 3ሺህ ሰዎችን እንድታወጣ ሥልጣን ሰጣት። [በነቅዱስ ያሬድ ዘመን ኖረች ይባላልና በግምት በ550 ዓ. ም. ተወለደች ብንል እስካሁን 1.6 ቢሊየን ነፍሳት ከሲኦል ነጥቃለች፤ እዚህ ያላመነ ሰው እዚያ ሄዶ ወረፋ መጠበቅ ይችላል ማለት ነው!] ገድል ሲነበብ ስለማያምኑ ሰዎች ጠይቃ ከልብ የሚያምኑ ሁሉ እንደሚገቡ ተነገራትና ከዕርገቷ ስትመለስ ሚካኤል ወደ ሥጋዋ ወስዶ ሳትፈልግ በግድ አስገባት። ወደ ሮሐ ሄዳ 120 ቀን ጾማ የላሊበላን መቃብር ስትሳለም ላሊበላ አነጋገራትና ስሟን በወርቅ ቀለም ጻፈው። አንድ ቀን ሽንኩርት በልታ የማርያምን ስዕል ስትሳለም ስዕሉ የበላሽው ሽንኩርት ሸቶኛልና ወደኋላ ተመለሺ አለቻት፤ ደንግጣ ስትወድቅም ስዕሊቱ በእጅዋ አነሣቻት። ለአንድ ዲያቆን ሽንኩርት በልቶ ቤተ ክርስቲያን እንዳይገባ ነገረችው፤ ያ ሰው ግን ስለርሷ ሐሜት አወራ ስለዚህም ቅጣት መልአክ ቆዳውን ገፈፈውና ቁርበቱ በተገፈፈ ሰውነቱ እስከ ዕለተ ሞቱ ድረስ የክርስቶስ ሠምራን ገድል ሲያወራ ኖረ።2

ይህ በዚያን ዘመን ወይም በዘመናችን የተፈጠረ ልብ ወለድ እንኳ ከሆነ አዝናኝ ሳይሆን አሳች ልብ ወለድ ነው። ሰዎች ይህን መሳዩን ነገር ሊቀበሉ ለምን ቻሉ? ስንል ወይ ወንጌሉን ከቶም አለማወቅ፥ ያለዚያም አውቆ ሸቃጭ መሆን ነው። እንግዲህ ለዚህ መሰሉ ስሕተት መፍትሔው ምንድርነው ቢባል ዋናውን ማወቅ ነው። የዋናውን ጣእም ያወቀ የተበረዘውን ወዲያው ይለየዋል። ሐሰተኛውን የማወቂያ ዋናው ስልት እውነቱንና እውነተኛውን ማወቅ ነው።

ቀናሽ ሸቃጮች በንግድ ዓለም የሚነግዱ ቀያጮችና ሸቃጮች

በመጨመር ብቻ ሳይሆን በመቀነስም ጥቅም ያገኛሉ። ለምሳሌ፥ ከኮካ ኮላ ውስጥ ስኳሩን ስኳርና ኮካውን ኮካ የሚያደርገውን ወይም ከቡና ውስጥ ቡናውን ቡና የሚያደርገውን

ካፊን (caffeine) የተባለውን አንቂ ንጥረ ነገር ያወጡና ዳየት ኮክ (Diet Coke) ወይም

ዲካፊኔይትድ ካፊ (Decaffeinated Coffee) ወይም ከወተቱ ስባቱን ያወጡና (Fat-free ወይም

Skim Milk) ብለው ለሸማች ያቀርባሉ። ቡናውም ቡና አይደለም፤ ወተቱም አጓት ነው፤ ኮካውም ኮካነት የለውም። ግን ገበያ አለው።

ልክ እንደ እነዚህ ደግሞ ዋናውን ነገር ቀንሰው ከእውነት የጎደለ ጎዶሎ ትምህርት የሚያቀርቡ አስተማሪዎች አሉ። እነዚህ ሸቃጮች ናቸው። ለምሳሌ፥ ወንጌልን ወንጌል የሚያደርገው ነገር ከውስጡ ከወጣ ወንጌሉ እንደምን ወንጌል መሆን ይችላል? ወንጌል ማለት ከግሪክ ቋንቋ የመነጨ ቃል ሆኖ የምሥራች ማለት ነው። አንድ ወሬ የምሥራች ለመሰኘት መልካም ዜና መያዝ አለበት። የወንጌሉ መልካም ዜና ሰው ኃጢአተኛ በመሆኑ በኃጢአቱ ምክንያት ሞት የተገባው ሆኖ ሳለ የኃጢአቱ ዋጋ በመስቀል ላይ ሥጋ ለብሶ ሰው በሆነው አምላክ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ፈጽሞ የተከፈለ መሆኑ ነው። ኃጢአተኛ ሰው ይህን አምኖ ከኃጢአት ሕግና ከሞት ኩነኔ መዳን ይችላል። ይህንን ትልቅ እውነት ከወንጌሉ ውስጥ መዝዘን ካወጣነው ወንጌሉ ወንጌል መሆኑ ይቀራል።

የኢየሱስ ሥጋ መልበስና በመስቀል መሞት ከወንጌሉ ከወጣ ወንጌሉ የጀርባ አጥንት እንደሌለው ሆኖ ይወድቃል። ለምን? የምሥራቹ የተገለጠው በዚህም ነው። ኢየሱስ ሥጋ የለበሰው ለምክንያት ነው፤ ለዓላማ ነው። ኃጢአት የሚሰረይበት ደም ያስፈልጋል። ደም ደግሞ

2 ገድለ ክርስቶስ ሠምራ ትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት፥ አዲስ አበባ፥ ዓ/ም፥ ገጽ 42-60።

Page 3: (X-Ray) - deqemezmur – Be a disciple, Make Disciples ...deqemezmur.com/.../uploads/2015/04/Ezra-Literature-Mag-Issue-010.pdf · ገድል ሲነበብ ስለማያምኑ ሰዎች

ቃልህ ተገኝቶአል እኔም በልቼዋለሁ አቤቱ፥ የሠራዊት አምላክ ሆይ፥ በስምህ ተጠርቻለሁና ቃልህ ሐሤትና የልብ ደስታ ሆነኝ። ኤር. ፥ 3

ቁጥር ፲ - ግንቦት ፪ሺህ ፫ ዓመተ ምሕረት MAY 2011 [email protected]

ከወንዝ አይቀዳም። ሙሴ አንድ ጊዜ ለቅጣት የዓባይን ወንዝ ወደ ደም ለውጦ ነበር፤ ግን የኃጢአት ስርየት የሚገኝበት ጌታ ውሃን ወደ ወይን እንደለወጠ ውኃን ወደ ደም በመቀየር አይመጣም። ኃጢአትን የሚያስተሰርየው ደግሞ ደም ብቻ ሳይሆን ሕይወት ያለበት ደም ነው። የዓለምን ኃጢአት የሚያስተሰርየው የነፍስ ዋጋ የተከፈለበት የእግዚአብሔር በግ ደም ደግሞ ሕይወት ያለው ብቻ ሳይሆን ኃጢአት የሌለበት ደም ነው። ጌታ ሥጋ የለበሰው ሥጋ ለመልበስ ብቻ ሳይሆን በሥጋው ኃጢአታችንን ለመሸከምና በደሙ ኃጢአታችንን ለማስተስረይ ነው። መስዋዕትነቱ ደግሞ በሚታይና በተገለጠ ሁኔታ የተፈጸመ ነው። የተገደለው ታንቆ ወይ ታፍኖ አልነበረም። ወይም በብሉይ ሕግ ወንጀለኞች እንደሚገደሉ ተወግሮ ሳይሆን በብሉይ ኪዳን መሥዋእት እንደሚደረግ ከፍ ብሎና ደሙ ፈስሶ ነው። ይህንን እውነት ከወንጌል መንቀስ ወንጌልን ማኮላሸት ነው።

የጌታን ትንሣኤና አምላክነት ከወንጌሉ መምዘዝም የወንጌልን ወንጌልነት መግደል ነው። የጌታ አምላክነት ከጊዜ በኋላ የሆነ ሳይሆን አምላክነቱ ከዘላለም ነው። ሰው ሲሆን አምላክነቱ አልተቀነሰም። ቃል ሥጋ ሆነ ማለት ከአምላክነት ተቀነሰ ማለት ሳይሆን አምላክነቱ ሳይቀነስ ሥጋ ሆነ ማለት ነው። ያ በቤተ ልሔም ግርግም የነበረው ሕጻን፥ ያ በእናቱ ጉያ የነበረ ጨቅላ ከፍጥረት በፊት ቃልን ሲናገር ዓለማት ካለመኖር ወደ መኖር የመጡበት የዘላለም አምላክ ነው።

ትንሣኤውም የኛ የራሳችን ትንሣኤ በኩራት ብቻ ሳይሆን የዚያ በመስቀል ላይ የሆነው መሥዋእት በቂና ተቀባይነትን የተቀዳጀ መሥዋእት የመሆኑ ምስክርም ነው። የማንነቱ መግለጫና የመጨረሻው የሁሉ አሸናፊ፥ ሞት የተሸነፈበት ፊሽካ የተነፋበት ማረጋገጫ ነው። እነዚህ ነገሮች ከወንጌሉ ከተቀነሱ ወንጌሉ ከውስጡ ማሩ የወጣበት ቀፎ ብቻ ሊሆን ነው።

እነዚህ ከላይ ያየናቸው ሁለት ዋና ዋና ነጥቦች፥ እውነቱን ማጉደልና ውሸትን መጨመር ሸቃጮችና ቀያጮች

የሚያደርጓቸው ትልልቅ የማሳሳቻ ስልቶች ናቸው። እኛስ እንዴት ነን ታዲያ? የምናስተምርና የምንሰብክ እንዴት ነው የምናገለግለው? የምንሰማና የምናደምጥስ

እንዴት ነው የምንሰማና የምናደምጠው? እንደሚሸቃቅጡት አንዳንዶች እንዳንሆንና

የሚሸቃቅጡትንም ለይተን እንድናውቅ ጌታ ይርዳን። አሜን።

እግዚአብሔር ከአርያም ይባርካችሁ። * * * * * ዘላለም መንግሥቱ © 2011 (፪ሺህ፫) ዕዝራ ስነ ጽሑፍ አገልግሎት

አያትና ልጂት

አንዲት ትንሽ ልጅ ከአያትዋ ጋር እየተንሸራሸሩ ቆይተው ወደ ቤት ገቡና ተቀምጠው ያወራሉ። ልጂቱ የአያትዋን የግንባሩን፥ የጉንጮቹን መጨማደድ ትክ ብላ አየችና፥ “አያቴ፥ አንተን የፈጠረህ እግዚአብሔር ነው?” አለችው።

አያትም፥ “አዎን፥ የኔ ቆንጆ፤ ከብዙ ብዙ ዓመታት በፊት ነው የፈጠረኝ” አላት።

ልጂቱም መልሳ፥ “እኔንስ የፈጠረኝ እግዚአብሔር ነው?” አለች።

አያትም፥ “አዎን፤ አንቺንም ከ6 ዓመታት በፊት የሠራሽ እርሱ ነው” አላት።

ልጂቱም የሁለታቸውንም ፊት ደባብሳ ተገረመችና፥ “እግዚአብሔር ከፊት ይልቅ እያሻሻለ መሥራት ጀምሯል! አይገርምም?” አለች።

ሁለት ተኩላዎች

አንድ አባትና ልጅ ሲያወጉ አባትየው በሰዎች ውስጥ ስለሚደረገው ጦርነት ይነግረው ጀመር። “ሰማህ ልጄ? በሰው ውስጥ፥ በእያንዳንዳችን ውስጥ ሁለት ተኩላዎች አሉ፤ ሁሌ ይዋጋሉ፤ ሁሌ ጦርነት ነው። በኔም ውስጥ፥ ባንተም ውስጥ፥ በሁሉም ሰው ውስጥ” አለው። ልጁም፥ በደንብ ይሰማ ጀመር።

“እና አንዱ ክፉ ተኩላ ነው። ንዴት፥ ቅንዓት፥ ስስት፥ ኩራት፥ ውሸት፥ ጥላቻ፥ ትዕቢት፥ ምቀኝነት ነው። ሌላኛው ደግሞ ፍቅር፥ ሰላም፥ ደስታ፥ ታጋሽነት፥ ቸርነት፥ ታማኝነት፥ የዋኅነት፥ እንዲህ ያለው ነው” አለው።

ልጁም ለጥቂት ካሰበ በኋላ፥ “የትኛው ተኩላ ነው ኃይለኛው?” ብሎ ጠየቀው።

አባትየውም፥ “በደንብ የምትመግበው ተኩላ ነው ኃይለኛው” አለው።

ዝንጀሮ አያት

ያኔ በደርግ ጊዜ አንድ አባቷ ማርክሲስት እናቷ ክርስቲያን የሆነች ልጅ እናቷን፥ “እማዬ፥ ሰው እንዴት ነው የተፈጠረው?” አለቻት።

“ሰው የተፈጠረውማ በመጀመሪያ እግዚአብሔር አዳምንና ሔዋንን ፈጠረና ከዚያ እነርሱ ልጆች ወልደው ክዚያ ልጆቻቸው ልጆች ወልደው እንዲያ ያለ የሰው ዘር ምድርን ሞላ” ብላ ነገረቻት።

በሌላ ጊዜ ደግሞ ተመሳሳይ ጥያቄ አባቷን ጠየቀች። አባቷም፥ “ከሰዎች በፊት ዝንጀሮዎች ነበሩ፤ ሰው የመጣው ከዝንጀሮ ነው” አላት። አሁን ግራ ተጋባች።

ወዲያውኑ እናቷጋ ሄዳ፥ “ማሚ፥ አንቺ ሰውን እግዚአብሔር ፈጠረው አልሽኝ። አባዬ ደግሞ ሰው ከዝንጀሮ መጣ ይላል። ሁለቱም እንዴት ትክክል ሊሆን ይችላል?” ብላ ጠየቀቻት። ወዲያውም አባትየው ምን እንደምትመልስላት ሊሰማና ሊቀልድባት መጣ።

እናቲቱ በባሏ ከሃዲነት በጣም ትናደድ ነበርና፥ “ሚሚዬ ሁለታችንም ልክ ነን። እኔ የነገርኩሽ የኔ ወላጆች የመጡበትን መስመር ነው። አባትሽ የነገረሽ ደግሞ የሱ ወላጆች የመጡበትን መንገድ ነው።” ብላ መለሰችላት።

Page 4: (X-Ray) - deqemezmur – Be a disciple, Make Disciples ...deqemezmur.com/.../uploads/2015/04/Ezra-Literature-Mag-Issue-010.pdf · ገድል ሲነበብ ስለማያምኑ ሰዎች

ቃልህ ተገኝቶአል እኔም በልቼዋለሁ አቤቱ፥ የሠራዊት አምላክ ሆይ፥ በስምህ ተጠርቻለሁና ቃልህ ሐሤትና የልብ ደስታ ሆነኝ። ኤር. ፥ 4

ቁጥር ፲ - ግንቦት ፪ሺህ ፫ ዓመተ ምሕረት MAY 2011 [email protected]

ለእግዚአብሔርም ክብርና ምስጋና ከኢየሱስ ክርስቶስ የሚገኝ የጽድቅ ፍሬ ሞልቶባችሁ፥ ለክርስቶስ ቀን ተዘጋጅታችሁ ቅኖችና አለ ነውር እንድትሆኑ የሚሻለውን ነገር ፈትናችሁ ትወዱ ዘንድ፥ ፍቅራችሁ በእውቀትና በማስተዋል ሁሉ ከፊት ይልቅ እያደገ እንዲበዛ ይህን እጸልያለሁ።

ፊል. 1፥9-11

ባለፈው ሐዋርያው ጳውሎስ ራሱ የፊልጵስዩስን ምእመናን እንዴት እንደወደዳቸው መናገሩን ተመልክተናል። የወደዳቸው በክርስቶስ ፍቅር ነበር። ፍቅር የሚለው ቃል አንጀት የሚለው ቃል መሆኑ ውስጣዊና ከርኅራኄ ጋር የተቆራኘ እንደሆነም ተመልክተን ነበር። አሁን ደግሞ በፊል. 1፥9-11 የራሳቸው ፍቅር እንዲያድግና እንዴትና ለምን ማደግ እንደሚገባው ያስተምራቸዋል።

ፍቅር የሚያድግ ነገር ነው። ፍቅር የሚበዛ ነገር ነው። ፍቅር ስሜት ቢኖርበትም ፍቅር ስሜት ብቻ አይደለም። የበሰለ ፍቅር እንዲያውም ልብ ሲመታ ብቻ ሳይሆን ልብ መምታቱ ሳያቆም አእምሮ ሲያስብም ነው። ፍቅር ሲያድግ በእውቀትና በማስተዋልም ሲያድግ ውብ ነው።

አንድ ጊዜ ቴክሳስ ውስጥ አንድ ሰው በገጠር መንገድ መኪናውን እየነዳ ሲሄድ ከግጦሽ ሜዳው ወደ መንገድ የወጣ አንድ ጥጃ ገጨና ገደለ። እዚያው ቆሞ ሳለ የጥጃው ባለቤት ደረሰና መነጋገር ጀመሩ። የገጨው ሰው የጥጃውን ዋጋ ሊከፍል ተስማምቶ ዋጋውን ጠየቀ። ገበሬውም፥ “አሁን ወደ $200 ነው። ግን 4 ዓመት ቢቆይ ኖሮ $990 ይሆን ነበር” አለው። ሰውየውም ቼኩን አውጥቶ ሁለት ቼኮች ላይ ጻፈና፥ “ምረጥና አንዱን ውሰድ፤ ይህ $200 ተጽፎበታል፤ አሁኑኑ ወደ ባንክ ሄደህ መውሰድ ትችላለህ። ይህኛው ደግሞ እንደግምትህ $990 ተጽፎበታል፤ ቀኑን እንደምታየው ከዛሬ 4 ዓመት በኋላ እንድትወስደው ነው የጻፍኩበት” አለው። ጥጃው ጥጃ ነው፤ የዛሬ 4 ዓመት ወይፈን ሆኖ ብዙ ዋጋ ያወጣል፤ ግን ብዙ ዋጋ ደግሞ አስከፍሎ ነው ብዙ የሚያወጣው።

የሚያድግ ነገር ዋጋ ያስከፍላል። ፍቅር የሚያድግ ነገር ነው። ፍቅር ስለሚያድግ እና ሲያድግ ዋጋ ያስከፍላል። አንድ የታወቀ መጽሐፍ ቅዱስ ኮሌጅ ሥራ መሪ በአንድ ንግግሩ ላይ ሁለት ልጆች እንዳሉትና ከሁለቱ አንዱ ብዙ ወጪ እንደሚያስወጣው አንዱ ግን ምንም ወጪ እንደማያስወጣው ተናግሮ ምንም የማያስወጣው ሞቶ ወደ ጌታ የተሰበሰበው ልጁ ሲሆን ብዙ ወጪ የሚያስወጣው አብሮት ያለው በሕይወት ያለ የሚያድግ ልጁ መሆኑን አብራራ። ሕይወትና እድገት ዋጋ ያስከፍላል።

አንዳንድ ዐረፍተ ነገሮችን፥ በተለይም በጳውሎስ መልእክት ውስጥ የሚገኙ ዐረፍተ ነገሮችን በትክክል ለመረዳት እንዳሉ በቀጥታ ከማንበብ ይልቅ ከኋላ ወደ ፊት ወይም ከቀኝ ወደ ግራ (እንደ ዕብራይስጥ) ማንበብ ይረዳል። ጳውሎስ ዕብራዊ ቢሆንም የጻፈው በግሪክ ቋንቋ ነው። በጻፈበት በግሪክ ቋንቋም ይህን አካሄድ አንዳንዴ መከተል የሚያስፈልግባቸው ቦታዎች ብዙ ናቸው።

እነዚህን ሦስት ጥቅሶች ከላይ እንዳልኩት በኋላ ማርሽ እየነዳን ከጥያቄ ጋር ብንጽፋቸው ይህን ይመስላሉ፤

ምን አደርጋለሁ? እጸልያለሁ።

ስለምን? ፍቅራችሁ በእውቀትና በማስተዋል ሁሉ ከፊት ይልቅ እያደገ እንዲበዛ።

ለምን? የሚሻለውን ነገር ፈትናችሁ ትወዱ ዘንድ።

እኮ ለምን? ለክርስቶስ ቀን ተዘጋጅታችሁ ቅኖችና አለ ነውር እንድትሆኑ።

እንዴት? ከኢየሱስ ክርስቶስ የሚገኝ የጽድቅ ፍሬ ሞልቶባችሁ እንድትገኙ።

ዓላማው? ለእግዚአብሔርም ክብርና ምስጋና እንድትሆኑ።

ጳውሎስ የጸሎት ሰው ነው። አንዳንድ ጊዜ፥ ምናልባትም ብዙ ጊዜ፥ ጸሎቶቻችን ከእጅ ወደ አፍ ብቻ ናቸው። ቢያልፉም ከዚያ ብዙም አይርቁም። ለአካላዊ፥ ቁሳዊ፥ እና መሰል ምድራዊ በረከቶች መጸለይን ማለፍ ማደግና መባረክ ነው። ጳውሎስ ለፊልጵስዩስ ምእመናን ሲለምን ብናስተውለው የሚያንገዳግድ ትልቅ ጸሎት ነው የጸለየላቸው።

ጳውሎስ በሕይወቱ የጸሎት ሰው ነው። በብዙ መልእክቶቹ ይህንን እውነት እናያለን። ከሕይወቱም ይህንን እንረዳለን። የጳውሎስ ሕይወትና አገልግሎት የተሳካ፥ ውጤታማ፥ ፍሬያማ ሕይወትና አገልግሎት ነበር። ፍሬያማ ሕይወትና አገልግሎት በጸሎት ካልታጀበ አይገኝም። ፍሬያማ ሕይወትና አገልግሎት ማለት ከፈተና የጸዳ ኑሮ ማለት አይደለም። ጳውሎስ ራሱ የስደት ምልክትም ነው። እየተሰደደ ኖሮ አንገቱ ተቀልቶ የተገደለ የወንጌል ሰው ነው። ራሱ በ2ጢሞ. 3፥12 በእውነትም በክርስቶስ ኢየሱስ እግዚአብሔርን እየመሰሉ ሊኖሩ የሚወዱ ሁሉ ይሰደዳሉ ብሎአል። እግዚአብሔርን ይመስለዋል ማለት ነው። ግን ይህ ሁሉ (መምሰሉም፥ መሰደዱም) በጸሎት ባይታሽ ኖሮ አይቻልም ነበር። በራሱ ጸሎት ብቻ አይደለም። ሐዋርያው ጳውሎስ የጸሎትን ምንነት አጥብቆ የሚያውቅ ነውና ራሱ መጸለይ ብቻ ሳይሆን ቅዱሳንም እንዲጸልዩለት ያሳስብ ነበር፤ ሮሜ 15፥31-32፤ ቆላ. 4፥3-4፤ 1ተሰ. 5፥25፤ 2ተሰ. 3፥1-2፤ ዕብ. 13፥18።

እንዲህ ጳውሎስ ራሱ የጸሎት ሰው መሆኑን ካየን የሚጸልይላቸውን ነገሮች እንይ። ቀደም ሲልም (በቁ. 3-5) እንደሚጸልይላቸው ነግሮአቸዋል፤ ያውም በደስታ። እዚህ ግን የሚጸልይላቸውን ነገር ልማዳዊ ጸሎት ሳይሆን የተሰላ፥ የተስተዋለ ጸሎት ነው። ፍቅራቸው እንዲያድግ ጸለየ። ስለአዳጊ ፍቅር የጸለየላቸው ቃል አስደናቂ ነው። ቃሉ በቀጥታ ሲታይና በጥሬው ሲተረጎም ይህን ይመስላል፤ ἵνα ὑµῶν ἡ ἀγάπη περισσεύῃ ἔτι μᾶλλον καὶ µᾶλλον ይሆን ዘንድ የእናንተ ፍቅር የሚበዛ ጨምሮ ደግሞ ጨምሮ።

እያደገ እንዲበዛ የሚለው አገላለጥም አጥጋቢ ነው። የጳውሎስ ጸሎት ተግባራዊ ጸሎት መሆኑን የምናስተውለው የሚደረጉ ተግባራዊ ነገሮችን በመዘርዘሩ ነው። እንድ. . . እንድ. . . የሚለው ዝርዝር ይህን የያዘ ነው። አምስት ጊዜ ተዘርዝሮአል። እንዲበዛ፥ ትወዱ ዘንድ (እንድትወዱ)፥ እንድትሆኑ፥ እንድትገኙ፥ እንድትሆኑ። ይህ ተግባር ነው።

ይህ ፍቅር እንደ ሰው ፍቅር የጠበበ ሳይሆን እንደ መለኮት ፍቅር የበዛና የሚበዛ እንዲሆን ነው ጸሎቱ። ጳውሎስ ለሮሜ ሰዎች ሲጽፍ ከእርስ በርስ ፍቅር በቀር ምንም ዕዳ እንዳይኖር ጽፎአል፤ ሮሜ 13፥8። የፍቅር ዕዳ ግን ሊኖርብን ይችላል፤ ምክንያቱም ይህ ከፍለን የማጨርሰው ዕዳ ነው። ፍቅር ከሆነ ጌታ እጅ የተቀበልነው ፍቅር ከምንሰጠው ሁሌም ያነሰ ነውና ከፍለን አንጨርስም፤ ስለዚህ ባለዕዳዎች ሆነን ኖረን፥ ምናልባት ጀምረን ብቻ ወይም ጥቂት ከፍለን እንሰናበታለን።

Page 5: (X-Ray) - deqemezmur – Be a disciple, Make Disciples ...deqemezmur.com/.../uploads/2015/04/Ezra-Literature-Mag-Issue-010.pdf · ገድል ሲነበብ ስለማያምኑ ሰዎች

ቃልህ ተገኝቶአል እኔም በልቼዋለሁ አቤቱ፥ የሠራዊት አምላክ ሆይ፥ በስምህ ተጠርቻለሁና ቃልህ ሐሤትና የልብ ደስታ ሆነኝ። ኤር. ፥ 5

ቁጥር ፲ - ግንቦት ፪ሺህ ፫ ዓመተ ምሕረት MAY 2011 [email protected]

ፍቅር እንደ እሳት ነው፤ ካልተቆሰቆሰ ይከስማል። ፍቅርን ተቀብለን ካስቀመጥነው ይቀመጣል። ለምንም የማይረባ ሆኖ ይቀመጣል። አንድ ሕመምተኛ እንዳደረገው ነው። በሽተኛው ሐኪሙን ካየው ከወር በኋላ ሄዶ፥ “ዶክተር፥ ባለፈው ወር መጥቼ ከተመለስኩ ወዲህ ይኸው ምንም አልተሻለኝም” አለው።

“እንዴ! እንዴት? መድኃኒቱ ላይ የተጻፈውን አወሳሰዱን ልብ ብለህ አላነበብክም እንዴ?” አለው።

“እሱንማ አንብቤአለሁ ግን ከካርቶኑ ውስጥ ብልቃጡን አውጥቼ ሳነበው አጥብቃችሁ ገጥማችሁ ዝጉት ይላል። ታዲያ ሐኪሙ ዝጉት ያለውን እኔ እንዴት እከፍታለሁ ብዬ አልከፈትኩትም” አለና አረፈው። መድኃኒቱን ገዝቶአል፤ ግን አልወሰደውም። ከብልቃጡ ካልወጣ፥ ለፈውስ ካልሆነ ጥቅም እንደሌለው ሁሉ ተግባር ከሌለ፥ አድጎ ካልተረፈ ፍቅርም እንዲህ ነው። ጳውሎስ ፍቅራቸው እያደገ እንዲበዛ መጸለዩ ድንቅ ጸሎት ነው።

ለምን እያደገ እንዲበዛ ጸለየ? የሚሻለውን ፈትነው ይወዱ ዘንድ። ፍቅር ሳሩን ቅጠሉን አይወድድም። ፍቅር ዕውር ነው የሚባለው አባባል አባባል እንጂ እውነት አይደለም። ፈረንሳዮች ሲተርቱ ፍቅር አንድ ዓይኑ ዕውር ነው፤ የሚያየው ዓይኑም ደካማ ነው፤ በደንብ አያይም ይላሉ። አይደለም። ፍቅር ብሩህ ዓይኖች አሉት። የማይወደደውን የሚወድደው ሳያይ ቀርቶ ሳይሆን በእርግጥ አትኩሮ አይቶ ነው።

ጳውሎስ ፍቅር እንዲበዛ መጸለዩ የተሻለውን ፈትኖ ከመውደድ ጋር አያይዞ ነው። ስለዚህ ፍቅር ስሜት ቢገለጥበትም ስሜት ብቻ አለመሆኑን እናያለን። ትክክለኛ ፍቅር ፈትኖ መውደድ ነው። ምክንያቱም የማንፈትን ከሆነ የማይወደደውን ሁሉ ልንወድ እንችላለን። ከጥሩና ከመጥፎ መምረጥ ቀላል ነው። ነገር ግን ከጥሩና ከበጣም ጥሩ ቀላል አይደለም። ከበጣም ጥሩና ከእጅግ በጣም ጥሩ መካከል ማማረጥ ደግሞ ከባድ ነው። በክርስትና ጉዞአችን ዓይን አዋጅ የሚሆኑብን ብዙ ነገሮች ሊያጋጥሙን ይችላሉ። ፈትነን መውደድና መምረጥ ካልቻልን የራሱ የምርጫችን ሰለባዎች እንሆናለን።

የፍቅራቸው ፈትኖ የተሻለውን በመውደድ ማደግ የተቆራኘበት ቀጣዩ አሳብ ለክርስቶስ ቀን ተዘጋጅተው የመገኘታቸው አስፈላጊነት ነው። የክርስቶስ ቀን ክርስቶስ ዳግም የሚመጣበት ጊዜ ነው። ክርስቶስ በሚመጣበት ጊዜ በሕይወት ቢኖሩ እንዲያ እንዲኖሩ፥ ክርስቶስ በዘመናቸው ካልመጣ ደግሞ እርሱን በመጠበቅ እስከ ሕይወታቸው ፍጻሜ ዝግጁ ሆኖ መኖርን መናገሩ ነው። ክርስትና የዝግጁነትና እርሱን በመጠባበቅ የምንኖረው ኑሮ ነው።

ክርስቶስ ዛሬ እኩለ ሌሊት ላይ እንደሚመጣ ወይም እኛ ዛሬ እኩል ሌሊት ላይ እንደምንሞት የምናውቅ ቢሆን የምድር የመጨረሻ ሰዓቶቻችንን እንደት እናሳልፍ ይሆን? አንዴ ይህን ጥያቄ ለቤተ ክርስቲያናችን አንድ ቡድን አቅርቤ የተሰጡኝ መልሶች ንስሐ እንደሚገቡ፥ የተጣሉአቸውን ሰዎች እንደሚታረቁ፥ ያስቀየሙአቸውን ሰዎች ይቅርታ እንደሚጠይቁ፥ ያካበቱትን ንብረት ለድኆችና ለችግረኞች እንደሚሰጡ ወዘተ ነበር የነገሩኝ። አዲስ ክርስቲያን ሳለሁ ካነበብኳቸው መጻሕፍት በአንዱ ውስጥ ጆን ዌስሊ የተባለው የስነ መለኮት ሊቅና ሰባኪ ይህን ጥያቄ ተጠይቆ የመለሰው መልስ ትዝ ይለኛል። ዘመኑ ረዝሞ ቃል በቃል አላስታውሰውም ግን የመለሰው መልስ ይህን የሚመስል ነው፤ ዛሬ ሌሊት እንደምሞት ባውቅ አሁን ከሰዓት በኋላ የማጠናውን ጥናቴን እቀጥልና ከእገሌ (ስሙን አላስታውስም) ቤት ሄጄ ቤተ ሰቡን እጎበኛለሁ፤ ከዚያ ከቤተ ሰቤ ጋር ራት በልቼ አመሻለሁ፤ የቤተ ሰብ አምልኮ ካደረግን በኋላ ይህን ያህል በምድር ስለኖርኩ አመስግኜ በሰላም እተኛለሁ፤ ከዚያ ስነቃ ራሴን መንግሥተ ሰማያት ውስጥ አገኛለሁ። ይህ ነበር መልሱ። ምንም የተለየ ነገር እንደሚያደርግ ሳይሆን በዚያ ቀን ሊያደርግ ያቀደውን ብቻ ነበር እንደሚያደርግ የተናገረው። ዝግጁ ሕይወት እንዲህ ነው። ግርግር የለም፤ አዲስ ነገር ማድረግ የለም። መጽዳትና ንስሐ መግባት የለም፤ ባይደረግ ቅር የሚያሰኝ ነገር የለም። ተዘጋጅቶ የሚኖር ሰው እንደሚኖረው ሁሉ ለመሞትም የተሰናዳ ነው። ለክርስቶስ ቀን ተዘጋጅቶ መኖር ይህ ነው።

የጌታን ቀን ደግሞ ቅኖችና አለነውር ሆኖ ነው የሚጠበቀው። አለነውር ἀπρόσκοποι (አፕሮስኮፖይ) የሚለው ቃል ἀπρόσκοπος ከሚለው ቃል የወጣ ይህ ደግሞ በተራው πρόσκοπος (ፕሮስኮፖስ) ከሚል ሆኖ ἀ አፍራሽ፥ ግሡ προσκοπή ደግሞ ነቀፋ ወይም የሚያስነቅፍ ነገር ነው። ነቀፋ አልባ፥ ነውር የለሽ ስለመሆን መናገሩ ነው። መጽሐፍ ቅዱስን የሚያውቁ ሰዎች ነውር የሚለውን ቃል በብዛት የምናገኘው ኦሪት ዘሌዋውያንና ዘኁልቁ ውስጥ መሆኑን ያውቃሉ። ቃሉ በተለይ ለመሥዋእት የሚቀርብ እንሰሳ መሆን ያለበትን ሁኔታ ያመለክታል። የፊልጵስዩስ ምእመናን ይህ ተጸለየላቸው። ለጌታ እንደሚቀርብ መስዋዕት ነውር የሌላቸው ይሆኑ ዘንድ። ድንቅ ጸሎት። እኛም በሰውነታችን፥ በአኗኗራችን፥ በአገልግሎታችን ሁሉ ይህን እንድንመስል ይፈለጋል። ስለእኛ እንዲህ የሚጸልዩልን ካሉን የተባረክን ነን። እኛስ የምንጸልይላቸው አሉ? ጳውሎስ ይህን ከነውር የጸዳ ኑሮ በ2፥14-15ም ይጠቅሰዋል። በተጨማሪ ኤፌ. 1፥4፤ ቆላ. 1፥21-22፤ 2ጴጥ. 3፥14 እና ይሁ. 24 ተመልከቱ።

ቅንነት የሚለው ቃል ግሩም ቃል ነው። ይህ ቃል ካልተተረጎመ መቅኒውን አናገኘውም። የአማርኛው ቃልማ ጨርሶውኑ አሳቡን አያሳይም። ቅኖች (ቅንነት) የተሰኘው εἰλικρινεῖς (ሄሊክሪኔይስ) ማለት በፀሐይ የተመረመረ፥ የተፈተነ ማለት ነው። ይህ ቃል በተጻፈበት ዘመን ሸክላ የሚሠሩና የሚሸጡ ሰዎች ሸክላው ስንጥቅ ቢኖረው ሰም ይቀቡታል። እና የዋሆቹ ገዥዎች የሸክላውን ጤንነት ሲፈትኑ ውኃ ጨምረው አለማፍሰሱን አረጋግጠው ይገዛሉ። እቤታቸው ወስደው ውኃ ጨምረው እምድጃ ሲጥዱት ግን ሰሙ ቀልጦ ውኃው እሳቱ ውስጥ ይቸለሳል። ብልሆቹ ሸማቾች ግን ሸክላውን በውኃ ሳይሆን በፀሐይ ይፈትኑታል። የሸክላ ዕቃውን ወደ ፀሐይ አቅጣጫ ብድግ አድርገው ያዩታል። የሰም ምርጊት ከኖረበት ስንጥቁ ይታያል። በፀሐይ መፈተን እንዲህ ነው። ጳውሎስ የፊልጵስዩስን ክርስቲያኖች ይህን ነው የሚላቸው፤ በውኃ ሳይሆን በፀሐይ የተፈተናችሁ ሁኑ፤ ቀዝቃዛ ውኃ የማታፈስሱ ብቻ ሳትሆኑ የፈላውንም ውኃ የምትይዙ ስንጥቅና ሽንቁር የሌለባችሁ ሁኑ ይላቸዋል። በእሳት ፈትኖት ፈተናውን የሚያልፍ ሕይወት ምንኛ የተባረከ ሕይወት ነው!

ከኢየሱስ ክርስቶስ የሚገኝ የጽድቅ ፍሬ ሞልቶባችሁ እንድትገኙ ብሎም ጸለየላቸው። የጽድቅ ፍሬ እኛ የምንሠራው መልካም ሥራ አይደለም። የምናፈራው እንጂ የምንሠራው አይደለም። ፍሬ ብቻ ሳይሆን ምን ዓይነት ፍሬና የማን ፍሬ መሆኑም ነው የተጻፈው። ፍሬው የጽድቅ ፍሬ ሲሆን የፍሬው ምንጭም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

ሐዋርያው ጳውሎስ በሮሜ 5፥1 እና 9 በእምነት፥ ማለትም በክርስቶስ በማመን ስለመጽደቅ ይናገራል። ደግሞም ከዚህ ጽድቅ በፊት በሥጋ ሳለን በሕግ የሚሆን የኃጢአት መሻት በብልቶቻችን ለሞት የሚሆን ፍሬ ሊያፈራ ይሠራ እንደነበርና አሁን ግን በክርስቶስ በኩል ለሕግ ሥራ ስለተገደልን ለእግዚአብሔር የሚሆን ፍሬ እንድናፈራ ዘርዝሮ ጻፈ፤ ሮሜ 6፥21-22 እና 7፥4-5። በገላ. 5፥22 ደግሞ ስለ መንፈስ ፍሬ ይናገራል። እነዚህ ጳውሎስ በሮሜና በገላትያ እዚህም በፊል. 2፥9 የሚጠቅሳቸው ፍሬዎች በኛ ውስጥ የሚታዩ ነገር ግን እርሱ እግዚአብሔር የሚያፈራቸው ፍሬዎች ናቸው። ዮሐ. 15፥1-16 ጌታ ስለ ግንድ፥ ቅርንጫፍና ፍሬ ያስተማረው ምሳሌ ነው። ገበሬው አብ፥ ግንዱ እርሱ፥ ልናፈራና ፍሬያችን ሊኖር የተነገረን ቅርንጫፎቹ እኛ ነን። ቅርንጫፍ በራሱ ማፍራት አለመቻሉ ትምክህቱን ያስወግደዋል።

ጳውሎስ ለፊልጵስዩስ ምእመናን የሚጸልየው ይህ ፍሬ እንዲኖር አይደለም። እንዲሞላባቸው ነው። በዚህ ፍሬ የተንዠረገጉ ቅርንጫፎች እንዲሆኑ ነው። ጌታም በዮሐ. 15፥ 5 እና 8 ፍሬ እንድናፈራ ብቻ ሳይሆን ብዙ ፍሬ እንድናፈራ ነው የተናገረው። ብዙ ፍሬ አብን ያስከብረዋል። የጽድቅ ፍሬ በክርስቶስ አምነን ከጸደቅን በኋላ የምናሳየው ተግባራዊና አብ የሚከብርበት ኑሮአችንና አመላለሳችን ነው። ጳውሎስም እዚህ የጻፈው የፊልጵስዩስ አማኞች ለእግዚአብሔር ክብርና ምስጋና እንዲሆኑ ነው። እንዴት ድንቅ ጸሎት ነው!

Page 6: (X-Ray) - deqemezmur – Be a disciple, Make Disciples ...deqemezmur.com/.../uploads/2015/04/Ezra-Literature-Mag-Issue-010.pdf · ገድል ሲነበብ ስለማያምኑ ሰዎች

ቃልህ ተገኝቶአል እኔም በልቼዋለሁ አቤቱ፥ የሠራዊት አምላክ ሆይ፥ በስምህ ተጠርቻለሁና ቃልህ ሐሤትና የልብ ደስታ ሆነኝ። ኤር. ፥ 6

ቁጥር ፲ - ግንቦት ፪ሺህ ፫ ዓመተ ምሕረት MAY 2011 [email protected]

የክርስቲያን ጥሪና የኑሮው ዓላማ የእግዚአብሔር ክብር ነው። ምንም ነገር ብናደርግና ስናደርግ መጠየቅ ያለብን ፈታሽ ጥያቄ፥ “ይህ እግዚአብሔርን ያስከብረዋልን?” የሚል መሆን አለበት። ከምንም ውሳኔ በፊት ይህን ጥያቄ መጠየቅ እግዚአብሔር የሚከብርበትን አሳብ እንድናስብ፥ እርሱ የሚከብርበትን ውሳኔ እንድንወስን፥ እርምጃ እንድንራመድና ኑሮ እንድንኖር እጅግ ይረዳናል። እግዚአብሔር በሕይወታችን፥ ማለት፥ በአመላለሳችንና በአገልግሎታችን ቢከብርና ስሙም ቢመሰገን በመልካም መጫወት ብቻ ሳይሆን ግብም ማስቆጠር ነው። ጳውሎስ እንደጸለየላቸው የፊልጵስዩስ አማኞች፥ እኛም ለእግዚአብሔርም ክብርና ምስጋና ከኢየሱስ ክርስቶስ የሚገኝ የጽድቅ ፍሬ ሞልቶብን፥ ለክርስቶስ ቀን ተዘጋጅተን ቅኖችና አለ ነውር እንድንሆን የሚሻለውን ነገር ፈትነን እንወድ ዘንድ፥ ፍቅራችን በእውቀትና በማስተዋል ሁሉ ከፊት ይልቅ እያደገ እንዲበዛ ጌታ ራሱ ይርዳን። አሜን።

እግዚአብሔር ከአርያም ይባርካችሁ።

* * * * * ዘላለም መንግሥቱ © 2011 (፪ሺህ፫) ዕዝራ ስነ ጽሑፍ አገልግሎት

እግሬ አውጪኝ አንድ ባላገር አንድ ምሽት ወደ ከተማ ከመግባቱ ሁለት ወሮበሎች አቁመው ያለውን ገንዘብ እንዲያወጣና እንዲሰጥ አዘዙት። ሰውየውም ዱላውን አንስቶ እየቃጣ መደባደብና ትግል ጀመረ። እነዚያ ሁለቱም አንዱ ጨብጦ ሲይዘው ሌላው ኪሱን ፈትሾ ያለውን ቦርሳ አወጣና ሲያይ ሁለት ብር ብቻ ነው ያለበት። በካልቾ መታውና፥ “ይኼ ሁሉ ግብግብ ትግል ለሁለት ብር ነው? በል ጫማህን አውልቅና ጥለህ ሂድ” ሲለው ባላገሩ ጫማውን አውጥቶ ከስር የደበቃትን ብር ጨብጦ ፊቱን መልሶ እየሮጠ፥ “ምነው ልያ ብቻ፤ እመጫሚያዬ ውስጥ የሸጎርኩትን 200 ብር እንዳትዘርፉኝ እንጂ!” አለና እግር አውጪኝ ሽሽቱን ቀጠለ።

በዝግታ

አንድ ሰነፍ ተማሪ በየጊዜው እያረፈደ ባረፈደ ቁጥር ደግሞ ሰበብ እየፈጠረ ይመጣል። አንዳንዴ አውቶቢስ አመለጠኝ፥ ሌላ ጊዜ እናቴ ቁርሴን በጊዜ አልሰራችልኝም ነበር፥ ሌላ ጊዜ ትንሹ ወንድሜ መጽሐፎቼን ደብቆብኝ፥ እያለ እየቀባጠረ ያሳብባል።

አንድ ቀን አርፍዶ መጣ፤ ግን ሰበቡ ሁሉ አለቀበትና አስተማሪው፥ “ዛሬስ ምን አስረፈደኝ ልትል ነው?” አለው። ቢያስብ የሚመጣለት ጠፋ። ግን እመንገድ ላይ ያየው ለአሽከርካሪዎች ማሳሰቢያ የትራፊክ ምልክት ትዝ አለውና፥ “እዚያ ታች ያለው እመንገድ ላይ ያለው የትራፊክ ምልክት” አለው።

“የትራፊክ ምልክቱ? እሺ፥ መሾፈር ጀመርክ? እርሱ ደግሞ ምን አድርጎ አዘገየህ?” አለው።

“ከፊታችሁ ትምህርት ቤት አለና ቀስ በሉ ስለሚል ቀስ አልኩ” አለው።

እንግዲህ እነዚህን የሚያህሉ ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን፥ እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ ቶሎም የሚከበንን ኃጢአት አስወግደን፥

የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ፤

እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና።

ዕብ. 12፥1-2

ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለ ማርያም በአንድ ንግግራቸው፥ጉዞአችን ረጅም፥ ትግላችን መራራ፥ ግባችንም እሩቅ ነው ብለው ነበር። ረጅም ከሆነ፥ መራራ ከሆነ፥ እሩቅ ከሆነ ሐሞት የሚያፈስ ነገር ነው። የሚያበረታታ ነገር ከሌለ፥ ቀድሞ ደርሶ አይዞህ የሚል ከሌለ ያታክታል። ለነገሩ የኮሎኔሉ ትግል መራራ ሆኖ ግቡም ሳይደረስ ጉዞውም በ17 ዓመት ተቀጨ። 70 ዓመት የሮጡትም የሕልም እንጀራ ሆኖባቸው ከሩጫው መስመር ወጡ።

መጽሐፍ ቅዱስ በአዲስ ኪዳን የክርስትናን ሕይወትና ጉዞ በተለያዩ ጉልበትን፥ ስሜትን፥ መንፈስን በሚነኩ ሦስት የእስፖርት ቃላት ይገልጠዋል። እኒህም መታገል፥ መጋደል፥ እና ሩጫ ናቸው። ሐዋርያው ጳውሎስ በዘመኑ የተለመዱትን እነዚህን ሦስት እስፖርቶች ጠቅሶ እንዴት መታገል፥ እንዴት መጋደል፥ እንዴት መሮጥ፥ እንዴት ሰውነታችንን መግዛትና ማስገዛት እንዳለብን አስተምሮአል። ይህን ብቻ ሳይሆን በነዚህ መስኮች የሚለፉ በመጨረሻ የሚያገኙትን ሽልማትም አብሮ ተናግሮአል።

መታገል፥ መጋደል፥ ሩጫ ሦስት ዋና ዋና ክፍሎች አሉት። ለማስታወስ እንዲረዳን እነዚህን ሦስት ነጥቦች በአንድ ቃል አስሬ ብሩሽ ብዬዋለሁ። ብ፥ ብቃት፤ ሩ፥ ሩጫ፤ ሽ፥ ሽልማት። ብሩሽ። እነዚህን ሦስት ቃላት ከማየታችን በፊት ግን ሦስቱን እስፖርቶች በትንሹ እንመልከት።

መታገል 2ጢሞ. 2፥5 ደግሞም በጨዋታ የሚታገል ማንም ቢሆን፥ እንደሚገባ አድርጎ ባይታገል፥ የድሉን አክሊል አያገኝም።

በጳውሎስ ዘመን መታገል የተለመደና የተወደደ ጨዋታ ነው። ጳውሎስ የተጠቀመበት ቃል አትሌኦ ከሚል ግስ የወጣ ነው። አትሌቲክስ የሚለው ቃል የተሠራበት ማለት ነው። ታዲያ መታገል ብቻ ሳይሆን እንደሚገባ አድርጎ መታገል ይፈለጋል። እንደሚገባ የሚለው ቃል እንደማይገባ አድርጎ መታገልም እንዳለ ያሳያል። በሁሉም እስፖርት ውስጥ አሻጥር አለ። ሣይታዩ በሾኬ መጥለፍ፥ በክርን መግፋት አለ። የማይታይ ወይም የሚታይ መማታትም አለ። ከቅጣት ምት እስከ ከሜዳ መባረር ሊኖር ይችላል። ታዋቂው የእግር ኳስ ተጫዋች ዚነዲን ዚዳን ትዝ ይለናል? እስፖርት ደንብና ሕግ አለው። ደንብና ሥርዓት ከሌለውማ እስፖርት መሆኑ ቀርቶ ፍጅት ነው። በቡጢ ጨዋታ በቡጢ

Page 7: (X-Ray) - deqemezmur – Be a disciple, Make Disciples ...deqemezmur.com/.../uploads/2015/04/Ezra-Literature-Mag-Issue-010.pdf · ገድል ሲነበብ ስለማያምኑ ሰዎች

ቃልህ ተገኝቶአል እኔም በልቼዋለሁ አቤቱ፥ የሠራዊት አምላክ ሆይ፥ በስምህ ተጠርቻለሁና ቃልህ ሐሤትና የልብ ደስታ ሆነኝ። ኤር. ፥ 7

ቁጥር ፲ - ግንቦት ፪ሺህ ፫ ዓመተ ምሕረት MAY 2011 [email protected]

የሚማታ መምታት የሌለበት ቦታ አለ። ሯጭ በተለይ አጭርና መካከለኛ ርቀት ከሆነ የሚሮጥበትን መስመር ተከትሎ መሮጥ አለበት። የተገባ አጨዋወት አለ። ያልተገባም አለ። ደግሞም በጨዋታ የሚታገል ማንም ቢሆን፥ እንደሚገባ አድርጎ ባይታገል፥ የድሉን አክሊል አያገኝም።

1ቆሮ. 9፥25 የሚታገልም ሁሉ በነገር ሁሉ ሰውነቱን ይገዛል፤ እነዚያም የሚጠፋውን አክሊል ሊያገኙ ነው፥ እኛ ግን የማይጠፋውን።

ሌላው ታጋይ የሚያደርገው ሰውነቱን መግዛት ነው። ይህ በሥርዓት ወይም በደንብ አካልን መግራት ነው። መግራትን ለፈረስ፥ ለወይፈን፥ አንዳንዴም ለሰው፥ በተለይም ለአንደበት እንጠቀምበታለን። ሥርዓት መያዝ ማለት ነው። ልክ መሆን፥ ልቅ አለመሆን፥ አለመፋነን ነው። የሚታገል ሰውነቱን ይቆነጥጣል፥ ይቆጣጠራል። ክርስቲያንም እንደዚሁ መሆን አለበት ነው የሚለን ጳውሎስ። ክርስቲያንም ታጋይ ነው፤ ታዲያ ትግሉ እንደሚገባ፥ በሥርዓት፥ ሰውነትን በመግዛት፥ በመግራት መሆን አለበት። ምኞታችን፥ አንደበታችን፥ አእምሮአችን፥ አሳባችን የተገራ ነው?

መጋደል ሁለተኛው ጳውሎስ የተጠቀመበት የእስፖርት ቃል መጋደል ነው። በሮማውያን ዘንድ እውነተኛ መጋደል ያለበት እስፖርት አለ። እነዚህ እስፖርተኞች መታገልና መደባደብ ብቻ ሳይሆን እውነተኛ መጋደልም ይጋደላሉ። በተለይ በሮም ግላዲዬተርስ የሚባሉት ሲጋደሉ ማየት የሚዘወተር እስፖርት ነው። በዚህ ስፖርት ደም ካልፈሰሰ፥ ሞት ካልኖረ አይፈጸምም። ይህ በነጥብ ብዛትና በጎል ቁጥር ማሸነፍ የሚወሰንበት አይደለም። እኛ ከሰይጣን ጋር ያለንን የሞት ሽረት ትግል ያሳያል። ኤፌ. 6፥12 መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ። ስለዚህ ምን አድርጉ አለ ጳውሎስ? 14-18 ስለዚህ በክፉው ቀን ለመቃወም፥ ሁሉንም ፈጽማችሁ ለመቆም እንድትችሉ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ አንሡ። እንግዲህ ወገባችሁን በእውነት ታጥቃችሁ፥ የጽድቅንም ጥሩር ለብሳችሁ፥ በሰላም ወንጌልም በመዘጋጀት እግሮቻችሁ ተጫምተው ቁሙ፤ በሁሉም ላይ ጨምራችሁ የሚንበለበሉትን የክፉውን ፍላጻዎች ሁሉ ልታጠፉ የምትችሉበትን የእምነትን ጋሻ አንሡ፤ የመዳንንም ራስ ቁር የመንፈስንም ሰይፍ ያዙ እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ነው። በጸሎትና በልመናም ሁሉ ዘወትር በመንፈስ ጸልዩ፤ በዚህም አሳብ ስለ ቅዱሳን ሁሉ እየለመናችሁ በመጽናት ሁሉ ትጉ።

ጳውሎስ ይህን መልእክት ሲጽፍ እነዚህን ተጋዳዮች እያሰበ ይሆን? ወይስ መደበኛ የሮም ወታደሮችን ትጥቅ እያሰበ ይሆን? እኛም ታጋዮች ብቻ ሳንሆን ተጋዳዮችም ነን። ታዲያ መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለም። መንፈሳዊ መጋደል ነው። ተጋድሎው ከመንፈሳዊ ኃይላትና ሠራዊት ጋር ነው። ስፍራው ሰማያዊ ቦታውም የሰው አእምሮና ልብም ነው። ውጊያውም እስክንሞት የማያበቃ ነው። ደስ የሚለው የድል ተስፋና ቃል አለን። ደግሞም ድል ያደረገው ጌታ ከኛ ጋር ነው።

ሩጫ ሦስተኛው የጳውሎስ ቃል ሩጫ ነው። ሩጫ ጠንካራ እስፖርት ነው። ለኢትዮጵያውያን ከረሃብ ቀጥሎ የምንታወቅበት መታወቂያችን ሩጫ ነው። ስመጥር ሯጮች አሉን። ሐዋርያው ጳውሎስ የክርስትናን ጉዞ

ከትግልና ከሩጫ ጋር ማመሳሰሉ ትክክለኛ ምስል ነው። ሩጫ ይጀመራል፤ ትግልና ተጋድሎ አለበት፤ ማለቁ ደግሞ አይቀርም። ትልቁ ልዩነት የክርስትናን ጉዞ ከእሽቅድምድሙና ከትግሉ የተለየ የሚያደርገው በእሽቅድምድሙና በትግሉ ሁለቱ ታግለው አንዱ፥ ወይም በሩጫ ሜዳ ብዙዎች ሮጠው ከ1ኛ እስከ 3ኛ የሚወጡት ብቻ ናቸው የሚያሸንፉት። በክርስትና ጉዞ ግን ግቡ መጨረሱ ነው።

ቀጥሎ ቀደም ሲል ብሩሽ ብለን ሰይመን አንጠልጥለን የተውናቸውን ሦስት ቃላት በተለይ ከሩጫ ጋር አያይዘን እንመልከት።

1. ብ-ብቃት። ለሩጫም ሆነ ለሌላው ሁሉ ስፖርት የመጀመሪያው ተፈላጊ መለኪያ ብቁ ሆኖ መገኘት ነው። አስቀድሞ በአካል ብቁ መሆን ተገቢ ነው። ለምሳሌ፥ እግር የሌለው ሰው ለሩጫ ብቁ አይደለም። ቀጥሎም ለመሮጥ ራስን በማዘጋጀት ብቁ መሆን ወይም በሌላ ቃል በልምምድ ራስን ብቁ ማድረግ ነው። እግር የሌለው ሰው ለመሮጥ ብቁ እንዳልሆነ ሁሉ እግር ያለው ሁሉ ደግሞ ሯጭ ሊሆን አይችልም።

በመንፈሳዊ ረገድም ብቃት የመጀመሪያው አስፈላጊ ነገር ነው። የአምናው Winter Olympics እኔ በምኖርበት አገር ነው የተደረገው። ደቡብ አፍሪቃ የተደረገው የዓለም እግር ኳሳ ዋንጫ ትዝታም ገና ትኩስ ነው። በነዚህና በሌሎቹም በማናቸውም ውድድሮች ማንም ተወዳዳሪ ዘው ብሎ ሜዳ ገብቶ መወዳደር አይችልም። የሚገቡት ግለሰቦችም ቡድኖችም አስቀድሞ የታወቁ ናቸው። ለመሮጥ በመጀመሪያ ወደ ሜዳ የሚገቡ ሆኖ መገኘት ግድ ነው። የገቡ ለመሆን መመዝገብ ግድ ነው። በመንፈሳዊው ሩጫም ብቁ መሆን፥ መመዝገብ ይፈለጋል። በቤተ ክርስቲያን ሳይሆን በሰማዩ መዝገብ። ይህ ነው ብቃት።

2. ሩ-ሩጫ። ሁለተኛው ክፍል ዋናው ነገር ነው። ብቁ ሆነው ከተገኙ በኋላ መሮጥ ይቻላል። ሩጫው ደግሞ ጀምረው ከሜዳ የሚወጡበት ሳይሆን ታግሠው የሚያጠናቅቁት ነው።

እራሱ ትግሉ፥ መጋደሉ፥ ሩጫው የራሱ ወግና ሥርዓት፥ ሕግና ደንብ ያለው ነገር ነው። እንዲያው በመላ ወይም እንደወደዱ የሚሮጡት አይደለም። ይለቅ እንጂ ብቻ ልሩጠው ብለው የሚሮጡትም አይደለም። መጨረስ ትልቅ ግብ ቢሆንም ብቻውን በቂ አይደለም። በሩጫው ወይም በትግሉ ውስጥ ሥርዓት አለ፤ ደንብ አለ። ግብ አለ፤ ዓላማ አለ።

1ቆሮ. 9፥24-27 በእሽቅድምድም ስፍራ የሚሮጡት፥ ሁሉ እንዲሮጡ ነገር ግን አንዱ ብቻ ዋጋውን እንዲቀበል አታውቁምን? እንዲሁም ታገኙ ዘንድ ሩጡ። የሚታገልም ሁሉ በነገር ሁሉ ሰውነቱን ይገዛል፤ እነዚያም የሚጠፋውን አክሊል ሊያገኙ ነው፥ እኛ ግን የማይጠፋውን። ስለዚህ እኔ ያለ አሳብ እንደሚሮጥ ሁሉ እንዲሁ አልሮጥም፥ ነፋስን እንደሚጎስም ሁሉ እንዲሁ አልጋደልም፤ ነገር ግን ለሌሎች ከሰበክሁ በኋላ ራሴ የተጣልሁ እንዳልሆን ሥጋዬን እየጎሰምሁ አስገዛዋለሁ።

የሚሮጥ ያለ አሳብ አይሮጥም። አሳብ ሲል ዒላማ፥ ግብ ማለት ነው። አስቦ አልሞ ነው የሚሮጠው ሯጭ። የሚታገል ወይም የቡጢ ተማችም ነፋስ እንደሚጎስም በባዶ ቦታ እየሰነዘረ ወይም ነጥብ የማያስገኝ ቦታ እየቃጣና እየመታ ሰውነቱን በከንቱ አያደክምም።

ሩጫም እንዲሁ ሥርዓት አለው። በፈለጉት መንገድ መፋነን የለም። በመንገዱ፥ በመስመሩ ነው የሚርሮጠው። ሩጫ ትእግሥት ይጠይቃል። በተለይም የረጅም ርቀት ሩጫ ጠንካራ ትእግሥት ይጠይቃል። የሚፈትኑ፥ ከመንገድ የሚያስወጡ፥ በጅምር የሚያስቀሩ፥ ከመቀጠል ወደኋላ የሚገቱና የሚጎትቱ ነገሮች አሉ። የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ፤ ሩጫ ትእግሥት ይጠይቃል።

ሩጫ ተስፋም አለበት። የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ፤ ከፊት ተስፋ

Page 8: (X-Ray) - deqemezmur – Be a disciple, Make Disciples ...deqemezmur.com/.../uploads/2015/04/Ezra-Literature-Mag-Issue-010.pdf · ገድል ሲነበብ ስለማያምኑ ሰዎች

ቃልህ ተገኝቶአል እኔም በልቼዋለሁ አቤቱ፥ የሠራዊት አምላክ ሆይ፥ በስምህ ተጠርቻለሁና ቃልህ ሐሤትና የልብ ደስታ ሆነኝ። ኤር. ፥ 8

ቁጥር ፲ - ግንቦት ፪ሺህ ፫ ዓመተ ምሕረት MAY 2011 [email protected]

ከኖረ አሁን ያለው ሁኔታ ተራራ ይሁን ሜዳ፥ ደልዳላ ይሁን ጎርበጥባጣ መሮጥ ይቻላል። ይቻላል!

ጳውሎስ ሥርዓቱን በተመለከተ ሌላም የእስፖርተኛ ቃል ተጠቅሞአል። “የተጣልሁ እንዳልሆን” የሚለው ቃል በስፖርት ቋንቋ “ፋውል” የሚባለውን ሠርቶ ከሜዳ መባረር ወይም ያስቆጠሩትን ግብና ነጥብ ማጣት ነው። በእግር ኳስ “ኦፍ ሳይት” ገብቶ ግብ ቢገባ ግቡ ይሰረዛል። ሰዎች ጎል ገባ ብለው ቢጨፍሩም ዳኛው ስሕተቱን ካወቀ ይሰርዘዋል። ያኔ የተመልካቹ ሙቀትና ጫጫታ ወደ መቀዝቀዝና ዝምታ ይቀየራል። አንዳንዶቹ በጣም ይበሳጫሉ። አንዳንድ ተጫዋቾች ሆን ብለው ያጠፋሉ ከዚያ ከጨዋታው ሜዳ ይወጣሉ። እግር ኳስ የምንወድ ቢጫ ካርድና ቀይ ካርድ ምን እንደሆነና ምን እንደሚያደርግ እናውቃለን።

በክርስትና ጉዞና አገልግሎት ውስጥ ተለፍቶ ዋጋ የሌለው፥ እርባና የሌለው፥ የማያስመሰግን፥ እንዲያውም የሚያስነቅፍ ነገር የሚኖርበት ጊዜ አለ። እንዲያ ሲሆን የሚያሳዝን ነው። በስሙ ትንቢት ተናግሮ፥ አጋንንት አውጥቶ፥ ብዙ ተአምራት አድርጎ፥ የዚያን ጊዜም፥ ከቶ አላወቅኋችሁም፤ እናንተ ዓመፀኞች፥ ከእኔ ራቁ ብዬ እመሰክርባቸዋለሁ። (ማቴ. 7፥23) ከተባሉ ቀድሞውኑ ትክክል ያልሆነ ትግልና ሩጫ ነበረ ማለት ነው። ጎሉ እየገባ ነው ግን አይቆጠርም። ከዚህ ከንቱና የማያስመሰግን ልፋት እግዚአብሔር ይጠብቀን።

3. ሽ-ሽልማት። ከሩጫው ፍጻሜ በኋላ ሽልማት አለ። ይህ የሚታገሉለት የሚጋደሉለት የሚሮጡለት የግቡ ውጤት ነው፤ የሩጫው አጎልባች ተስፋ ነው። የጌታ ተከታዮች ረጅም ይሁን አጭር መንፈሳዊ ጉዞአችንን ሳንታክት እንድንጨርስ የሚያስችለን የማያልቅና የማይቋረጥ የኃይል ተስፋ ተሰጥቶናል።

ኢሳ. 40፥31 እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ ይሮጣሉ፥ አይታክቱም ይሄዳሉ፥ አይደክሙም።

አንዳንዶች ለሽልማት አይደለም የሚሮጡት ለመጨረስ ብቻ ብለው ነው። ለዚህ ዕድሜያቸውም አይገታቸውም። በ1976 ዲሚትሪዮን ዮርዳኒዲስ የተባለ የ98 ዓመት ሽማግሌ ማራቶንን በ7 ሰዓት ከ33 ደቂቃ ጨረሰ። በ2002 ጄኒ ዉድ-አለን የተባለች የ90 ዓመት ሴት ለንደን ውስጥ በ11 ሰዓት ከ34 ደቂቃ ጨረሰች። እነዚህ ለ1ኛነት አይደለም ሩጫቸው። ሩጫን ስለመጨረስ በዕዝራ #8 ላይ ስለ አንድ ጃፓናዊ ማራቶን አጨራረስ ጽፌ ነበር። ይህ ሺዞ ካናኩሪ የተባለ ጃፓናዊ ማራቶንን የጨረሰው በሁለት ሰዓት ወይም በሁለት ቀን ወይም በሁለት ወር ሳይሆን በ54 ዓመት ከ8 ወር ነበር። ዋና ነገሩ መጨረሱ ነበር።

ሐዋ. 20፥24 ነገር ግን ሩጫዬንና ከጌታ ከኢየሱስ የተቀበልሁትን አገልግሎት እርሱም የእግዚአብሔርን ጸጋ ወንጌልን መመስከር እፈጽም ዘንድ ነፍሴን በእኔ ዘንድ እንደማትከብር እንደ ከንቱ ነገር እቆጥራለሁ።

በሩጫችን ውስጥ የሚረብሹንና ሩጫችንን እንዳንፈጽም ወይም ከንቱ የሚያደርጉብን ነገሮች ሊገጥሙን ይችላሉ። አንድ አሜሪካዊ ከሳን ፍራንሲስኮ እስከ ኒው ዮርክ በእግሩ ተጉዞ ነበር። ከአሜሪካ ምዕራብ እስከ ምሥራቅ ማለት ነው። ጉዞውን አጠናቅቆ እግሩ አትላንቲክ ውስጥ ሲጠልቅ በብዙ ጭብጨባና ሁካታ ደማቅ አቀባበል ተደረገለት። ከዚያም ጋዜጠኞች የተለያዩ ጥያቄዎች አቀረቡለት። ከጥያቄዎቹ አንዱ፥ “በዚህ ጉዞህ በጣም ያስቸገረህ ነገር ምን ነበር? አራዊት? ዝናብ? የፀሐይ ሐሩር? ወይስ ምን?” የሚል ነበር። ሰውየው የሰጠው መልስ፥ “እነዚህ ሁሉ ነገሮች አላስቸገሩኝም፤ በጣም ያስቸገረኝ ነገር እጫማዬ ውስጥ የሚገቡት አሸዋዎች ነበሩ” አለ። በጣም ጥቃቅን፥ ግን በጣም አስቸጋሪ ነገሮች ናቸው።

በአንድ ጓደኛችን ሠርግ ላይ ሚዜ ከሆኑቱ አንዱ ወንድም ለሠርጉ ገዝቶ ባደረገው ጫማ ሲሰቃይ ውሎ፥ በቀኑ መጨረሻ መራመድ እስኪሳነው ደርሶ ነበር። እንዴት ተሳስቶ ከእግሩ ቁጥር ያነሰ ጫማ እንደገዛ እያሰበ

ሲበሳጭ ዋለ። ሁሉ ነገር ከተጠናቀቀ በኋላ ወደ ማረፊያው ገብቶ መጀመሪያ ያደረገው ነገር እግሩን ከጫማው ውስጥ ማውጣትና ተቆልፈው የዋሉ የእግር ጣቶቹን ማፍታታት ነበር። ሲያወጣው እግሩ በስሎአል። ምን ዓይነት የጫማ አሠራር መሆኑን ለማየት ጫማው ውስጥ እጁን ሲያስገባ ቆዳው እንዳይጨማደድ በውስጡ የተወተፈውን ወረቀት አገኘ! ለካስ ጣቱን ሲያሾቅለት የዋለው የተወተፈው ጋዜጣ ነበር!

ሩጫን በትእግሥት እንደሚገባ ሮጦ መጨረስ ምንኛ ደስ የሚያሰኝ መታደል ነው! ጳውሎስ አሯሯጡንና አጨራረሱን እንንዲህ ሲል ይገልጣል፤

2ጢሞ. 4፥7-8 መልካሙን ገድል ተጋድዬአለሁ፥ ሩጫውን ጨርሼአለሁ፥ ሃይማኖትን ጠብቄአለሁ፤ ወደ ፊት የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል፥ ይህንም ጻድቅ ፈራጅ የሆነው ጌታ ያን ቀን ለእኔ ያስረክባል፥ ደግሞም መገለጡን ለሚወዱት ሁሉ እንጂ ለእኔ ብቻ አይደለም።

ሩጫን መጨረስ በራሱ ትልቅ እርካታን የሚሰጥ ደስታን የሚፈጥር ክንዋኔ ቢሆንም ሽልማት መኖሩ ደግሞ ሌላ ግፊት ነው። የአገራችንን ታዋቂ ሯጮች የሕዝባቸው ደማቅ አቀባበልና ከዚያ የሚከተለው ድግስና ሽልማት የሚያስደስታቸው ይመስለኛል።

እሮም በባዶ እግሩ፥ ቶኪዮ በጫማ ድል ነሺው አበበ በሁለቱም ከተማ

እየተባለ ሲዜም ሳይደሰት ይቀራል? ከንጉሡ ፊት ቀርቦ ሲሸለም ያን ድካም ሁሉ እንደ ከንቱ ሳይቆጥረው ይቀራል?

እኛም በሩጫ ላይ ያለን ክርስቲያኖች ነን። ከፊታችን ቀድመው ሩጫቸውን ጨርሰው እንደ ጳውሎስ ሩጫውን ጨርሻለሁ የሚሉን ቅዱሳን አሉን። የእነርሱ ትጋትና ሩጫቸውን መጨረስ ሊያደፋፍረንና ሊያበረታታን ይገባል።

ይልቁንም እያየነው እንድንሮጥ የተነገረን አንድ አለ፤ እርሱም የእምነታችን ራስና ፈጻሚ የሆነው ኢየሱስ ነው። የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን

ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ፤ እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና።

እኛንም የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶ ይጠብቀናል። ይህን የጽድቅ አክሊል ከጻድቁ ፈራጅ እጅ እንቀበላለን። ያ ቀን ምንኛ የእጅግ ታላቅ ደስታ ቀን ይሆን!

እስከዚያ ግን ክርስትናችን እንዴት ነው? ብቁዎች ሆነን ተገኝተናል? በእርሱ ታውቀናል? ወደ ሜዳው ገብተናል? ትግላችን፥ መጋደላችን፥ ሩጫችን እንዴት ነው? እንደሚገባ የምንታገል ነን? ሰውነታችንን የምንገዛ፥ በአሳብ የምንሮጥ፥ ነፋስን የማንጎስም ነን? የሚያስቸግሩን ጥቃቅን አሸዋዎች ወይም ጫማችን ውስጥ የተወተፉ ለመሮጥ ይቅርና ለመራመድ እንኳ የሚያስቸግሩን ውታፎች፥ የሚከብቡን ኃጢአቶች አሉ? እነዚህን ሁሉ ጥሰን የምናልፍና የምንገሰግስ ሯጮች እንድንሆን ጌታ ራሱ ይርዳን። አሜን።

እግዚአብሔር ከአርያም ይባርካችሁ።

* * * * * ዘላለም መንግሥቱ © 2011 (፪ሺህ፫) ዕዝራ ስነ ጽሑፍ አገልግሎት