4
uôÅ^M Ö?“ Øun T>’>e‚` ¾›=ƒÄåÁ ¾Qw[}cw Ö?“ ›=”e+ƒ¿ƒ www.ephi.gov.et ²?“ ኢሕጤኢ ነሐሴ 2008 pê 1 lØ` 10 የበጀት ዓመቱ የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ተካሄደ የ2008 በጀት ዓመት የእቅድ ክን ውን አፈጻጸም የኢንስቲትዩቱ የበላ ይ ሃላፊዎችና የዳይሬክቶሬት ሃላ ፊዎች በተገኙበት ሐምሌ 29 እስከ 30/2008 ዓ.ም በኢንስቲትዩቱ አዳ ራሽ ግምገማና ውይይት ተካሄደ፡፡ የስብሰባው ዋና አላማ የ2009 በጀ ት ዓመት ዕቅድ በተገቢው መንገድ ለማከናወን፣ያለፈውን በጀት ዓመት አፈጻጸም በመገምገም ያሉ ጠንካራ ጎኖችና ክፍተቶችን በመለየት የቀጣ ዩን በጀት ዓመት ዕቅድ በማጽደቅ ወደ ሰራተኛው በማውረድ በትክክል ስራዎችን ለመፈጸም ታስቦ የተዘጋ ጀ የውይይት ስብሰባ ነው፡፡ የ2008 በጀት ዓመት የእቅድ አፈጻ ጸም ሪፖርት በዕቅድ፣ክትትልና ግ ምገማ ዳይሬክቶሬት የቀረበ ሲሆን በበጀት ዓመቱ የታቀደውንና የተከና . . .ወደ ገጽ 4 ዞሯል በኢሕጤኢ የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ቢሮ በየወሩ የሚዘጋጅ ወነውን በማነጻጸር በቁጥርና በመቶ ኛ ከመገለጹም በላይ የእያንዳንዱን ዳይሬክቶሬት ካስቀመጠው ግብ አን ጻር የደረሰበትን የአፈጻጸም ደረጃ ተ ዘርዝሮ በጽሁፍ ቀርቧል፡፡ በተጨማሪም በቀረበው ዓመታዊ የ ኢንስቲትዩቱ የእቅድ ክንውን ላይ ተቋሙ የደረሰበት የአፈጻጸም ደረጃ 60 በመቶ መሆኑንና የመልካም አ ስተዳደር ችግሮችን ከመፍታት አን ጻር ደግሞ ከፐብሊክ ሰርቪስ በተዘ ጋጀው ቼክ ሊስት መሰረት 66.5 በ የኢንስቲትዩቱ የህዝብ ክንፍ ስብሰባ ለ3ኛ ጊዜ ተካሄደ የኢንስቲትዩቱ የህዝብ ክንፍ ስብሰ ባ የኢንስቲትዩቱ የበላይ ሃላፊዎች ና ከኢንስቲትዩቱ ጋር በጋራ የሚሰ ሩ ተቋማት ተወካዮች በተገኑበት ነ ሃሴ 3/2008 ዓ.ም ለ3ኛ ጊዜ በኢን ስቲትዩቱ አዳራሽ ተካሄደ፡፡ ዶክተር አመሃ ከበደ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር በስብሰባው መክፈ ቻ ስነ-ስረዓት ላይ እንደተናገሩት የ ስብሰባው ዋና ዓላማ እስካሁን በጋ ራ የሰራናቸውንና ኢንስቲትዩቱ እየ ሰራ ያለውን ዋና ዋና ስራዎች በመ ገምገምና በመወያየት በ2009 በጀት ዓመት ከኢንስቲትዩቱ የህዝብ ክንፍ ከሆኑ ተቋማት ጋር በተሻለ መንገ ድ በመስራት የህብረተሰቡን ጤና ለ ማሻሻል መሆኑን ገልጸዋል፡፡ አቶ አረጋ ዘሩ የዕቅድ፣ ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ሃላፊ የኢንስ ቲትዩቱን የ2008 በጀት ዓመት ዋ ና ዋና የእቅድ አፈጻጸም በጽሁፍ ያ ቀረቡ ሲሆን የተሰሩ ስራዎችን፣በመ ሰራት ላይ ያሉ እና ታቅደው ያልተ ከናወኑ ስራዎች ምን ደረጃ ላይ እ ንደሚገኙ በጽሁፍ ዘርዝረው አቅር በዋል፡፡ ዶክተር አመሃ ከበደ የኢንስቲትዩ ቱ ዋና ዳይሬክተር በቀረበው ሪፖር ት ላይ መሰረት በማድረግ ውይይቱ ን የመሩ ሲሆን ከተሳታፊዎች በር ከት ያሉ የተለያዩ ጥያቄዎችና አስ ተያየቶች ላይ ሰፋ ያለ ውይይት ተ ካሄዷል፡፡ ከተወያዮቹም በእቅዱ ላይ መጨመ ር አለባቸው ያሏቸውን በዝርዝር በ ማቅረብ የገለጹ ሲሆን ኢንስቲትዩቱ ም የበለጠ መሻሻልና መስተካከል ያ ለበትን በማስተካከል በቀጣይ የበለ ጠ ትኩረት አድርጎ እንደሚሰራ በዋ ና ዳይሬክተሩ በኩል ተገልጿል፡፡ በመጨረሻም የህዝብ ክንፍ የጋራ ኮ ሚቴ በማቋቋም በቀጣይ የህዝብ ክ ንፍ ስብሰባ ሳይቆራረጥ እንዲካሄድ በተለይም ከህብረተሰቡ ጋር ግንኙነ ት ያላቸውን ጉዳዮች ላይ ትኩረት ተደርጎ መሰራት እንዳለበት የጋራ ስ ምምነት ላይ ተደርሶ የእለቱ ውይይ ት እና ግምገማ ተጠናቋል፡፡

uôÅ^M Ö?“ Øun T>’>e‚` ¾›=ƒÄåÁ ¾Qw[}cw Ö?“ … · 2016-09-22 · ነሐሴ 2008 pê 1 lØ` 10 Ñê 2 የድንገተኛ በሽታ መሰረታዊ የቅኝት

Embed Size (px)

Citation preview

uôÅ^M Ö?“ Øun T>’>e‚`¾›=ƒÄåÁ ¾Qw[}cw Ö?“ ›=”e+ƒ¿ƒ

www.ephi.gov.et

²?“ ኢሕጤኢ ነሐሴ 2008 pê 1 lØ` 10

የበጀት ዓመቱ የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ተካሄደየ2008 በጀት ዓመት የእቅድ ክንውን አፈጻጸም የኢንስቲትዩቱ የበላይ ሃላፊዎችና የዳይሬክቶሬት ሃላፊዎች በተገኙበት ሐምሌ 29 እስከ 30/2008 ዓ.ም በኢንስቲትዩቱ አዳራሽ ግምገማና ውይይት ተካሄደ፡፡የስብሰባው ዋና አላማ የ2009 በጀት ዓመት ዕቅድ በተገቢው መንገድ ለማከናወን፣ያለፈውን በጀት ዓመት አፈጻጸም በመገምገም ያሉ ጠንካራ ጎኖችና ክፍተቶችን በመለየት የቀጣዩን በጀት ዓመት ዕቅድ በማጽደቅ ወደ ሰራተኛው በማውረድ በትክክል ስራዎችን ለመፈጸም ታስቦ የተዘጋጀ የውይይት ስብሰባ ነው፡፡የ2008 በጀት ዓመት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በዕቅድ፣ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት የቀረበ ሲሆን በበጀት ዓመቱ የታቀደውንና የተከና

. . .ወደ ገጽ 4 ዞሯል

በኢሕጤኢ የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ቢሮ በየወሩ የሚዘጋጅ

ወነውን በማነጻጸር በቁጥርና በመቶኛ ከመገለጹም በላይ የእያንዳንዱን ዳይሬክቶሬት ካስቀመጠው ግብ አንጻር የደረሰበትን የአፈጻጸም ደረጃ ተዘርዝሮ በጽሁፍ ቀርቧል፡፡በተጨማሪም በቀረበው ዓመታዊ የ

ኢንስቲትዩቱ የእቅድ ክንውን ላይ ተቋሙ የደረሰበት የአፈጻጸም ደረጃ 60 በመቶ መሆኑንና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ከመፍታት አንጻር ደግሞ ከፐብሊክ ሰርቪስ በተዘጋጀው ቼክ ሊስት መሰረት 66.5 በ

የኢንስቲትዩቱ የህዝብ ክንፍ ስብሰባ ለ3ኛ ጊዜ ተካሄደ

የኢንስቲትዩቱ የህዝብ ክንፍ ስብሰባ የኢንስቲትዩቱ የበላይ ሃላፊዎችና ከኢንስቲትዩቱ ጋር በጋራ የሚሰሩ ተቋማት ተወካዮች በተገኑበት ነሃሴ 3/2008 ዓ.ም ለ3ኛ ጊዜ በኢንስቲትዩቱ አዳራሽ ተካሄደ፡፡ዶክተር አመሃ ከበደ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር በስብሰባው መክፈቻ ስነ-ስረዓት ላይ እንደተናገሩት የስብሰባው ዋና ዓላማ እስካሁን በጋራ የሰራናቸውንና ኢንስቲትዩቱ እየሰራ ያለውን ዋና ዋና ስራዎች በመ

ገምገምና በመወያየት በ2009 በጀት ዓመት ከኢንስቲትዩቱ የህዝብ ክንፍ ከሆኑ ተቋማት ጋር በተሻለ መንገድ በመስራት የህብረተሰቡን ጤና ለማሻሻል መሆኑን ገልጸዋል፡፡አቶ አረጋ ዘሩ የዕቅድ፣ ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ሃላፊ የኢንስቲትዩቱን የ2008 በጀት ዓመት ዋና ዋና የእቅድ አፈጻጸም በጽሁፍ ያቀረቡ ሲሆን የተሰሩ ስራዎችን፣በመሰራት ላይ ያሉ እና ታቅደው ያልተከናወኑ ስራዎች ምን ደረጃ ላይ እ

ንደሚገኙ በጽሁፍ ዘርዝረው አቅርበዋል፡፡ዶክተር አመሃ ከበደ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር በቀረበው ሪፖርት ላይ መሰረት በማድረግ ውይይቱን የመሩ ሲሆን ከተሳታፊዎች በርከት ያሉ የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ላይ ሰፋ ያለ ውይይት ተካሄዷል፡፡ከተወያዮቹም በእቅዱ ላይ መጨመር አለባቸው ያሏቸውን በዝርዝር በማቅረብ የገለጹ ሲሆን ኢንስቲትዩቱም የበለጠ መሻሻልና መስተካከል ያለበትን በማስተካከል በቀጣይ የበለጠ ትኩረት አድርጎ እንደሚሰራ በዋና ዳይሬክተሩ በኩል ተገልጿል፡፡በመጨረሻም የህዝብ ክንፍ የጋራ ኮሚቴ በማቋቋም በቀጣይ የህዝብ ክንፍ ስብሰባ ሳይቆራረጥ እንዲካሄድ በተለይም ከህብረተሰቡ ጋር ግንኙነት ያላቸውን ጉዳዮች ላይ ትኩረት ተደርጎ መሰራት እንዳለበት የጋራ ስምምነት ላይ ተደርሶ የእለቱ ውይይት እና ግምገማ ተጠናቋል፡፡

ነሐሴ 2008 pê 1 lØ` 10 Ñê 2

www.ephi.gov.et

የድንገተኛ በሽታ መሰረታዊ የቅኝት ዘዴ ስልጠና ለባለሞያዎች ተሰጠ

የኢንስቲትዩቱ የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች ቁጥጥር ማዕከል ድንገት የሚከሰቱ የበሽታ ወረርሽኝን ለመቆጣጠርና ለመከላከል የሚያስችል የድንገተኛ በሽታ መሰረታዊ የቅኝት ዘዴ ስልጠና በህብረተሰብ ጤና አደጋዎች ቁጥጥር ላይ ለሚስሩ ከክልል፣ከዞን ፣ከወረዳዎችና ከሆስፒታሎች ለተመረጡ ባለሞያዎች በቤንሻንጉል ጉምዝ እና በጋምቤላ ክልሎች ከነሃሴ 23 እስከ 27/2008 ዓ.ም ስልጠና ሰጠ፡፡የስልጠናው ዋና ዓላማ የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች ቁጥጥር ላይ የሚሰሩ ባለሞያዎችን መሰረታዊ የህብረ

ተሰብ ጤና አደጋ ቁጥጥር ላይ ያላቸውን እውቀት በስልጠና ከፍ በማድረግ በቀጣይ ሶስት ዓመታት ተለይተው በተቀመጡት 21 የቅኝት በሽታዎች በክልሎቹ በወረርሽኝ መልክ ከመከሰታቸው አስቀድሞ በመተንበይ እና ቅድመ ዝግጅት በማድረግ እንዲሁም በመለየት ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚቻልበትን መንገድ ለመፍጠር ያስችል ዘንድ የተዘጋጀ ስልጠና ነው፡፡በስልጠናው ወቅት መረዳት እንደተቻለው ስልጣኞች ከስልጠናው በኋላ የበሽታዎችን ቅኝት በማድረግ በመተንተን እና በማደራጀት ለሚ

መለከተው ክፍል በማቅረብ አፋጣኝ ምላሽ በመስጠት የመረጃ አቢዮት እንዲሳካ ከፍተኛ ስራ ይሰራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ስልጠናውን የሰጡት የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች ቁጥጥር ማዕከል ባለሞያዎች፣ከክልል ጤና ቢሮዎች እና ከአለም ጤና ድርጅት ተወክለው በመጡ ባለሞያዎች ሲሆን ስልጠናው በገለጻና በማብራሪያ የማስተማር ዘዴዎች ከመሰጠቱም በላይ ስልጣኞች ሰፊ ጊዜ ወስደው ውይይት በማድረግ የተረዱትን ሃሳብ በመግለጽና ያልገባቸውን ደግሞ በመጠየቅ ብሎም ከአሰልጣኞች በቂ ማብራሪያና መልስ በመስጠት ስልጠናው

የ3ኛው ዙር የወባ በሽታ ጠቋሚ የዳሰሳ ጥናት ውጤት ይፋ ሆነ

የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የባክቴርያል፣ ፓራሳይቲክ እና ዞኖቲክ በሽታዎች ምርምር ዳይሬክቶሬት በሀገር አቀፍ ደረጃ ወባን ለማጥፋት የተደረገውን የ3ኛውን ዙር የወባ በሽታ ጠቋሚ የዳሰሳ ጥናት ውጤት የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ተወካዮች እና የተለያዩ የመንግስትና የግል ሚዲያዎች በተገኙበት በአዲስ አበባ ኢሊሊ ሆቴል ጳጉሜ 4/2008 ይፋ አደረገ፡፡የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በሀገር አቀፍ ደረጃ ወባን ላማጥፋት እ.ኤ.አ ከ2010 እስከ 2015 የወጣውን መርሀ ግብር አፈጻጸም ለመገምገም ከመስከረም እስከ ታህሳስ 2015 ባሉት ጊዜያት የዳሰሳ ጥናት አካሂዷል፡፡ይህም ጥናት የተካሄደው በጤና ጥ

በቃ ሚኒስቴር፣ በክልል ጤና ቢሮዎች፣ በኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና ሌሎች አጋር ድርጅቶች ጋር በጋራ በመሆን ሲሆን እንደጥናቱ ግኝትም ሁሉም የሚመለከታቸው ተቋማት በሽታውን ለመቆጣጠርና ለመከላከል የሚጠበቅ

ባቸውን ተወጥተዋል፡፡ ጥናቱ በዘጠኝ ክልሎች እና በአንድ የከተማ አስተዳደር/ድሬዳዋ/ በሚገኙ 14000 አባዎራዎች ያካተተ ሲሆን 55000 ነዋሪዎች ተሳትፈውበ

. . .ወደ ገጽ 4 ዞሯል

ተካሂዷል፡፡በመጨረሻም ሰልጣኞች ስለስልጠናው የተሰማቸውን እና በቀጣይ ከሚመለከተው አካል ለጤናው ዘ . . .ወደ ገጽ 4 ዞሯል

ነሐሴ 2008 pê 1 lØ` 10 Ñê 3

በጊኒዎርም በሽታ ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጠ

www.ephi.gov.et

በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳይ ላይ ስብሰባ ተካሄደ ዶክተር ከበደ ወርቁ የጤና ጥበቃ ሚንስተር ዲኤታ እና ዶክተር አመሃ ከበደ የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር በተገኙበት የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አጠቃላይ ሰራተኞች በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳይ ላይ ነሃሴ 12/2008 ዓ.ም በኢንስቲትዩቱ ግቢ ውስጥ በሚገኘው የትምህርት ክፍል አዳራሽ ስብሰባ አካሄዱ፡፡የስብሰባውም ዋና አላማ በወቅታዊ ሃገራዊ ሁኔታዎች ላይ ውይይት በማድረግ በሃገሪቱ ውስጥ በአንዳንድ ቦታዎች ላይ እየተፈጠሩ ያሉ ችግሮችን ግንዛቤ በመፍጠር ችግሮቹ በሰላም የሚፈቱበትን መንገድ አቅጣ

ጫ ለማስቀመጥ ታስቦ የተዘጋጀ የውይይት ስብሰባ ነው፡፡

ዶክተር ከበደ ወርቁ ወደ ሃገራዊ ወ

የጊኒዎርም በሽታ የሚጠፋበት ፕሮግራም እና ያለበትን ወቅታዊ ሁኔታ ለተለያዩ የመገኛኛ ብዙሃን በኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር እና በካርተር ሴንተር ኢትዮጵያ ካንትሪ ዳይሬክተር ነሐሴ 26/2008 ዓ.ም በጤና ጥበቃ ሚኒስተር አዳራሽ ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጠ፡፡የጋዜጣዊ መግለጫው ዋና አላማ የጊኒዎርም በሽታን የማጥፋት ዘመቻ ከተጀመረ ጀምሮ ሁለት ጊዜ ተመሳሳይ ጋዜጣዊ መግለጫ የተሰጠ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በሀገራችን የበሽታው ወቅታዊ ሁኔታ ያለበትን ተጨባጭ እውነታ በህብረተሰቡ ዘንድ ግንዛቤ ለማስጨበጥ የተዘጋጀ ነው፡፡ዶክተር ዳዲ ጅማ የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ይህንን በዓለም ላይ በመጥፋት ላይ ያለ በሽታ ነገር

ግን በጥቂት የዓለም ሃገሮች ኢትዮጵያን ጨምሮ የሚገኝ በመሆኑ ከሀገራችን ለማጥፋት እንቅስቃሴ ከተጀመረ ረጅም ጊዜ ቢሆንም እስከ አሁን ድረስ ከሃገራችን አልጠፋም፤ካሉ በኋላ በአሁኑ ሰዓት በጋምቤላ ክልል በአኝዋክ ዞን በጎግ ወረዳ በሽታው የተገኘባቸው ሁለት ግለሰቦች ከመገኘታቸው ውጪ በሌሎች አካባቢዎች በሽታው በመጥፋት ላይ ይገኛል፡፡ስለዚህ ይህ የ3ኛ ጊዜ የሚሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የጊኒ ዎርም በሽታን ከሐገራችን ጨርሶ ለማጥፋት ለ3 ተከታታይ ዓመታት ክትትል በማድረግ ዜሮ ሪፖርት ካስመዘገብን ብቻ ስለሆነ ነጻነን የምንለው ለዚህ ስኬት ደግሞ የሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ወሳኝ እና አስፈላጊ ሚና ይጫወታል በተለይም የመገናኛ ብዙሃን ከፍተኛውን ሚና ይጫወታሉ ሲሉ አስገንዝበዋል፡፡ዶክተር ዘሪሁን ታደሰ የካርተር ሴ

ንተር ኢትዮጵያ ካንትሪ ዳይሬክተር በበኩላቸው መንግስትና የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የጊኒዎርም በሽታን ለማጥፋት ባላቸው ከፍተኛ ቁርጠኝነት በሽውን ለማጥፋት በየጊዜው የሚደረጉ ጥረቶችን ለህብረተሰቡ በይፋ ጋዜጣዊ መግለጫ መሰጠታቸው አንዱ ማሳያ ነው፤ካሉ በኋላ በሐገራችን አፋጣኝ ትኩረት ከሚሹ በሽታዎች ጊኒዎርም አንዱ በመሆኑ በሁሉም የሃገሪቱ ክልሎች የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች እና የመገናኛ ብዙሃን አስተዋጽኦ እጅግ ከፍተኛ ነው፡፡ ስለሆነም የመገናኛ ብዙሃን በየምትወክሏቸው የመገናኛ ዘዴዎች ተጠቅማችሁ በሽታውን ለማጥፋት በመላ ሀገሪቱ እየተደረገ ያለውን ዘመቻ ከግብ ለማድረስ ስለ በሽታው መንስኤ፣ስለሚተላለፍባቸው መንገዶች እንዲሁም የበሽታው ምልክት የታየበትን ሰው ለሚመለከተው የጤና ተቋማት ህብረተሰቡ ሪፖርት እንዲያደርግ፣ይህንንም በማድረጉ 2000 ብር እንደሚሸለም ተከታታይነት ባለው መንገድ በህብረተሰቡ ዘንድ መረጃውን የማስረጽ ስራ ከእናንተ ከመገናኛ ብዙሃን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ከተለያዩ መገናኛ ብዙሃን የመጡ ባለሞያዎች የተለያዩ ጥያቄዎች ተነስተው በሁለቱ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጪዎች ተገቢው ምላሽ ተሰጥቷል፡፡

. . .ወደ ገጽ 4 ዞሯል

ነሐሴ 2008 pê 1 lØ` 10 Ñê 4

www.ephi.gov.et

. . .ኢንስቲትዩቱ የእቅድ ክንውን ላይ ተቋሙ የደረሰበት የአፈጻጸም ደረጃ 60 በመቶ መሆኑንና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን. . .

ከገጽ 2 የዞረ

. . . . የ3ኛው ዙር የወባ በሽታ

ከገጽ 1 የዞረ . . . .የበጀት ዓመቱ ዕቅድ

ከገጽ 3 የዞረ . . . .በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ

ቅታዊ ሁኔታ ውይይት ከመግባታቸው አስቀድሞ በመግቢያ መልክ ስለሃገሪቱ መልካም እስተዳደር ፣ስለሙስና እንዲሁም በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ስለተከሰቱት የአማራና የኦሮሚያ ግጭቶች ሁኔታ በጽሁፍ አቅርበዋል፡፡በቀረበው የመግቢያ ጽሁፍ ላይ ተሰብሳቢዎች ውይይት እንዲያደርጉበት መድረኩን ክፍት በማድረግ ወደ ታዳሚው ሃሳቡን በመዘርጋት ውይይቱን ከዶክተር አመሃ ከበደ ጋር በጋራ መርተዋል፡፡ተሰብሳቢዎችም በነጻነት በወቅታዊ የሃገሪቱ ጉዳይ ላይ የሚሰማቸውን አሰተያየትና ጥያቄዎችን ያቀረቡ ሲሆን መንግስት በህብረተሰቡ በኩል የሚነሱትን የተለያዩ ችግሮች በማወያየት ለመፍታት ለምን ጥረት

አላደረገም? አሁን ለማወያየት ያለው ጥረት እጅግ አልዘገየም ወይ?ህገመንግስቱ በሚፈቅደው መሰረት ህዝቡ በሚወጣው ሰላማዊ ሰልፍ ባለቤት የሌለው ሰልፍ እየተባለ ከመንግስት በሚዲያ ሲገለጽ ይሰማል፡፡ ነገር ግን የግድ የፖለቲካ ፓርቲ ሰልፉን መጥራት አለበት ወይ? እራሱ ህዝቡ የሰላማዊ ሰልፉ ባለቤት መሆን አይችልም ወይ? በልማት ምክያት ከተለያዩ ቦታዎች የሚነሱ የህብረተሰብ ክፍሎች ዘላቂ መፍትሄ ሳይሰጣቸው ለምን ይነሳሉ? በዚህ ምክንያት በርካታ ህብረተሰብ ለችግር እየተጋለጠ እና እየተንከራተተ ነው፡፡ በሃገራችን ፍትሃዊ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት አለ ወይ?እነዚህንና የመሳሰሉትን ጥያቄዎችና አስተያየቶች ከተሰብሳቢዎች የተነሱ ሲሆን ሚኒስትሩ እና የኢንስቲትዩቱ

ዋና ዳይሬክተር በነበረው የውይይት መድረክ ላይ ሊመልሱ የሚችሉትን ከመለሱ በኋላ በሃገሪቱ የበላይ ሃላፊዎች መመለስ ያለባቸውን ጥያቄዎች ለሚመለከተው አካል እንደሚያቀርቡ ገልጸዋል፡፡በመጨረሻም ሚኒስትሩ በማጠቃለያቸው ላይ እንደገለጹት ሁሉም ነገር አግባብ ባለው መንገድ የህብረተሰቡን ጥያቄ ለመመለስ መንግስት እየሰራ ነው፡፡ ነገር ግን በአመጽና በሁከት የሚመጣ ለውጥ ስለሌለ ለሃገሪቷም ትልቅ የኢኮኖሚ ውድመት ስለሚፈጥር ሁሉም በሰላም መፈታት አለበት፡፡ በቀጣይ መንግስት ችግሮቹን በቅደም ተከተል የሚመለሱበትን መንገዶች እያመቻቸ ነው፡፡ ስለዚህ ሰላም ከምንም በላይ ነውና ለሰላም እንታገል በማለት የእለቱን ስብሰባ ደምድመዋል፡፡

ታል፡፡በአጠቃላይም ጥናቱ በኢትዮጵያ የወባ በሽታ ስርጭት እንደቀነሰና የበሽታው መከላከያ መሳሪያዎች አጠቃቀም መሻሻሉን አመላክቷል፡፡ ከነዚህም ውስጥ፡-

ከፍታው ከ2000 ሜትር በሆኑ ቦታዎች ከሚኖሩ ሰዎች በ2011 እ.ኤ.አ በተካሄደው ተመሳሳሳይ ጥናት ከ1000 ውስጥ በ13ቱ ላይ የነበረው የበሽታው ክስተት አሁን ወደ 5 ዝቅ ብሏል፣

ወባ በሚተላለፍባቸው አካባቢዎች ከሚኖሩ አባዎራዎች ሁለት ሶስተኛዎቹ ቢያንስ አንድ የወባ መከላከያ አጎበር በቤታቸው ይገኛል፣ ቢያንስ አንድ የመኝታ አጎበር ከሚገኝባቸው አባዎራዎች ውስጥ ሰባ በመቶ ህጻናትና ሰባ አራት በመቶ ነፍሰ ጡር እናቶች አጎበር ይጠቀማሉ በ2011 እ.ኤ.አ ከጥናቱ ሁለት ሳምንት በፊት ሃያ በመቶ የሚሆኑት ህጻናት ላይ ከፍተኛ ትኩሳት ሪፖርት የተደረገ ሲሆን አሁን ግን አስራ ስድስት በመቶ ብቻ ነው፣ ከፍተኛ ትኩሳት ሪፖርት ከተደረገባቸው ህጻናት መካከል ሰላሳ ስ

ምንት በመቶዎቹ ብቻ በ24 ሰዓት ውስጥ ህክምና አግኝተዋል፡፡

ይህ ጥናት በብሔራዊ የወባ መቆጣጠርና እና ማጥፋት መርሃ ግብር /2011 እስከ 2015 እ.ኤ.አ/ የተገኙ ውጤቶችን እና የነበሩ ድክመቶችን በተጨማሪም ያመላክታል፡፡ የጥናቱ ውጤቶች በቀጣይ ማለትም ከ2014 እስከ 2020 የወባ በሽታን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠር ብሎም ለማጥፋት የሚደረገውን ጥረት አጠናክሮ ለመቀጠል ለጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጠቃሚ ግብዓቶችን እንደሚሰጥ ይጠበቃል፡፡

ከገጽ 2 የዞረ

. . የድንገተኛ በሽታ መሰረታዊ

ርፍ ሊደረግ የሚገባውን ትኩረትና ድጋፍ አስተያየት ከመስጠታቸውም

በላይ በሰለጠኑት ስልጠና መሰረት አስፈላጊ የሆኑትን መረጃዎች ሁሉ በመከታተል ለሚመለከተው አካል እንደሚያደርሱ ከገለጹ በኋላ ስልጠናው ተጠናቋል፡፡

ይኸው ስልጠና በቀጣይ በሌሎች ክልሎች ለሚገኙ የጤና ቢሮ ባለሙያዎች በተመሳሳይ ሁኔታ የሚሰጥ ይሆናል፡፡

መቶ መድረሱን ተገልጿል፡፡በቀረበው የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ለሁለት ቀናት ግምገማና ውይይት የተደረገ ሲሆን ያለፈውን በጀት አመት ክፍተቶችንና ጠንካራ ጎኖችን በመለየት በክፍተቶቹ ላይ በቀጣይ ትኩረት በመስጠት እንዲሰሩ

አቅጣጫ ተሰጥቷል፡፡በበጀት ዓመቱ ስራዎች እንዳይሰሩ ትግዳሮት ፈጥረው የነበሩትን ጉዳዮች በተቋሙ ሃላፊዎችም ሆነ ሰራተኛው በኩል ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት በቀጣዩ በጀት ዓመት እንዳይደገሙ መደረግ እንዳለበት አቅጣጫ በማስቀመጥ የግምገማውና የውይይቱ ስብሰባ ተጠናቋል፡፡