48
ገጽ 1 | እሑድ | ኅዳር 17 ቀን 2004 የእሑድ እትም ኅዳር 17 ቀን 2004 ትኩስና ተጨማሪ መረጃዎችን በድረ ገጻችን ያገኛሉ www.ethiopianreporter.com ቅፅ 17 ቁጥር 11/ 1208 ጳጉሜን 6 ቀን 1987 ተመሠረተ ዋጋው ብር 7.00 FREE PRESS FREE SPEECH FREE SPRIT | ነፃ ፕሬስ ነፃ ሐሳብ ነፃ መንፈስ 2 ክፍል - 1 - 48 ገጽ ክፍል - 2 - 24 ገጽ ክፍል - 3 - 36 ገጽ 108 ገጽ ሪፖርተር በዚህ ዕትም ‹‹ሕዝብን መምራት በብልኃት›› - ይኑር! ‹‹ጭር ሲል አልወድም›› - ይቁም! ወደ ክፍል 1 ገጽ 43 ዞሯል ወደ ክፍል 1 ገጽ 43 ዞሯል አዲስ አበባ ውስጥ በተካሄደው የኢጋድ የመሪዎች ጉባዔ ላይ የተገኙት የሶማሊያ የሽግግር መንግሥት ፕሬዚዳንት ሼክ አህመድ ሸሪፍና የሚመሩት ልዑክ ኢትዮጵያ ሶማሊያ ውስጥ አልሸባብን ለመፋለም ለሚደረገው እንቅስቃሴ ድጋፏን እንድትሰጥ ተስማምተዋል:: በጉባዔው ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ፣ የኬንያ ፕሬዚዳንት ሞአይ ኪባኪና የጂቡቲ ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌህ ተገኝተዋል:: ዝርዝሩን በክፍል 1 ገጽ 43 ይመልከቱ ወደ ሶማሊያ ሊዘምት ነው የኢትዮጵያ ሠራዊት በብሔራዊ ባንክ የአገር ውስጥ ወርቅ ግብይት እስካሁን ገዥ አልቀረበም በዳዊት ታዬ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለአገር ውስጥ የወርቅ ጌጣጌጥ አምራች ዕደ ጥበባትና ወርቅ ቤቶች የሚሆን ጥሬ ወርቅ ሽያጭ መጀመሩን ካስታወቀ ሁለት ሳምንታት ያለፉት ቢሆንም፣ እስካሁን አንድም ገዥ አለመቅረቡ ታወቀ:: የሪፖርተር ምንጮች እንደገለጹት፣ ባንኩ ለአገር ውስጥ ወርቅ አቅራቢዎች ጥሬ ወርቅ መሸጥ መጀመሩን የሚገልጸው ማስታወቂያ ይፋ ከሆነበት ጊዜ ወዲህ፣ ለሽያጭ አዘጋጅቶት የነበረው ወርቅ ሳይሸጥ ቀርቷል:: ወርቅ ለመግዛት ፈቃድ የወሰዱ ዕደ ጥበባትና ወርቅ ቤቶች በመመርያው መሠረት ግዥውን ለመፈጸም ያልቻሉበትን ምክንያት በተመለከተ ፈቃዱን ከሚሰጠው ማዕድን ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ እንደሚለው ደግሞ፣ ከብሔራዊ ባንክ ግዥ እንዲፈጽሙ ፈቃድ የተሰጣቸው 14 የሚሆኑ ዕደ ጥበባት ለግዥው ዝግጁ ባለመሆናቸው ነው:: ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የመጨረሻው የመብት አስከባሪ ተቋም አይደለሁም አለ በታምሩ ጽጌ የሰብዓዊ መብቶችን ጥሰት ለማስቆም ወይም ለመከላከል፣ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመኮ) የመጀመርያውና የመጨረሻው ተቋም አለመሆኑን ኮሚሽነሩ ሕዳር 14 ቀን 2004 ዓ.ም. አስታወቁ:: ኮሚሽነሩ አምባሳደር ጥሩነህ ዜና ይኼን ያስታወቁት፣ ‹‹የኢትዮጵያ ብሔራዊ የሰብዓዊ መብቶች የድርጊት መርሐ ግብር ዝግጅት›› በሚል ነገና ከነገ ወዲያ በሸራተን አዲስ ስለሚካሄደው አገር አቀፍ ስብሰባ፣ ከፍትሕ ሚኒስቴር ጋር በመሆን በጋራ በሰጡት መግለጫ ላይ ነው:: ኮሚሽነሩ እንደገለጹት፣ ከኮሚሽኑ በላይ የሆኑ ወይም ኮሚሽኑ ሊያዛቸው የማይቻለው ሁለት ተቋማት አሉ፤ እነሱም ፍርድ ቤትና ፓርላማ ናቸው:: በፍርድ ቤት የተያዘን ጉዳይ መመልከት የሚቻለው ጉዳዩ በሕጉ አግባብ መያዙን፣ መቅረቡንና በትክክለኛው መንገድ እየሄደ መሆኑን ብቻ ነው:: ሁለቱ ተቋማት በያዙት ጉዳይ ላይ ገብቶ ለማዘዝ አቅምም መብቱም የለውም:: ከሁለቱ ተቋማት ወይም በማንኛውም ተቋም ውስጥ በመግባት ይኼ ትክክል አይደለም፣ መስተካከል አለበት በማለት የማዘዝና የማስፈጸም ሥልጣን የለውም ብለዋል:: አምባሳደር ጥሩነህ ስለ ኮሚሽኑ ከላይ የሰጡትን ማብራሪያ የተናገሩት በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው የታሰሩ ሰዎችን የሰብዓዊ መብት አያያዝ በሚመለከት ምንም የሠራው ሥራ እንደሌለና የሚያስተላልፈው ፎቶ በሪፖርተር/ናሆም ተስፋዬ

Reporter Issue 1208

Embed Size (px)

Citation preview

ገጽ 1 | እሑድ | ኅዳር 17 ቀን 2004

የእሑድ እትም

ኅዳር 17 ቀን 2004 ትኩስና ተጨማሪ መረጃዎችን በድረ ገጻችን ያገኛሉ www.ethiopianreporter.com

ቅፅ 17 ቁጥር 11/ 1208 ጳጉሜን 6 ቀን 1987 ተመሠረተ ዋጋው ብር 7.00

FREE PRESS FREE SPEECH FREE SPRIT | ነፃ ፕሬስ ነፃ ሐሳብ ነፃ መንፈስ

2

ክፍል - 1 - 48 ገጽ ክፍል - 2 - 24 ገጽ ክፍል - 3 - 36 ገጽ

108 ገጽ

ሪፖርተር

በዚህ ዕትም

‹‹ሕዝብን መምራት በብልኃት›› - ይኑር! ‹‹ጭር ሲል አልወድም›› - ይቁም!

ወደ ክፍል 1 ገጽ 43 ዞሯል

ወደ ክፍል 1 ገጽ 43 ዞሯል

አዲስ አበባ ውስጥ በተካሄደው የኢጋድ የመሪዎች ጉባዔ ላይ የተገኙት የሶማሊያ የሽግግር መንግሥት ፕሬዚዳንት ሼክ አህመድ ሸሪፍና የሚመሩት ልዑክ ኢትዮጵያ ሶማሊያ ውስጥ አልሸባብን ለመፋለም ለሚደረገው እንቅስቃሴ ድጋፏን እንድትሰጥ ተስማምተዋል:: በጉባዔው ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ፣ የኬንያ ፕሬዚዳንት ሞአይ ኪባኪና የጂቡቲ ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌህ ተገኝተዋል::

ዝርዝሩን በክፍል 1 ገጽ 43 ይመልከቱ

ወደ ሶማሊያ ሊዘምት ነውየኢትዮጵያ ሠራዊት በብሔራዊ ባንክ

የአገር ውስጥ ወርቅ ግብይት እስካሁን ገዥ አልቀረበምበዳዊት ታዬ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለአገር ውስጥ የወርቅ ጌጣጌጥ አምራች ዕደ ጥበባትና ወርቅ ቤቶች የሚሆን ጥሬ ወርቅ ሽያጭ መጀመሩን ካስታወቀ ሁለት ሳምንታት ያለፉት ቢሆንም፣ እስካሁን አንድም ገዥ አለመቅረቡ ታወቀ::

የሪፖርተር ምንጮች እንደገለጹት፣ ባንኩ ለአገር ውስጥ ወርቅ አቅራቢዎች ጥሬ ወርቅ መሸጥ መጀመሩን የሚገልጸው ማስታወቂያ ይፋ ከሆነበት ጊዜ ወዲህ፣ ለሽያጭ አዘጋጅቶት የነበረው ወርቅ ሳይሸጥ ቀርቷል::

ወርቅ ለመግዛት ፈቃድ የወሰዱ ዕደ ጥበባትና ወርቅ ቤቶች በመመርያው መሠረት ግዥውን ለመፈጸም ያልቻሉበትን ምክንያት በተመለከተ ፈቃዱን ከሚሰጠው ማዕድን ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ እንደሚለው ደግሞ፣ ከብሔራዊ ባንክ ግዥ እንዲፈጽሙ ፈቃድ የተሰጣቸው 14 የሚሆኑ ዕደ ጥበባት ለግዥው ዝግጁ ባለመሆናቸው ነው::

ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የመጨረሻው የመብት አስከባሪ ተቋም አይደለሁም አለ በታምሩ ጽጌ

የሰብዓዊ መብቶችን ጥሰት ለማስቆም ወይም ለመከላከል፣ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመኮ) የመጀመርያውና የመጨረሻው ተቋም አለመሆኑን ኮሚሽነሩ ሕዳር 14 ቀን 2004 ዓ.ም. አስታወቁ::

ኮሚሽነሩ አምባሳደር ጥሩነህ ዜና ይኼን ያስታወቁት፣ ‹‹የኢትዮጵያ ብሔራዊ የሰብዓዊ መብቶች የድርጊት መርሐ ግብር ዝግጅት›› በሚል ነገና ከነገ ወዲያ በሸራተን አዲስ ስለሚካሄደው አገር አቀፍ ስብሰባ፣ ከፍትሕ ሚኒስቴር ጋር በመሆን በጋራ በሰጡት መግለጫ ላይ ነው::

ኮሚሽነሩ እንደገለጹት፣ ከኮሚሽኑ በላይ የሆኑ ወይም ኮሚሽኑ ሊያዛቸው የማይቻለው ሁለት ተቋማት አሉ፤ እነሱም ፍርድ ቤትና ፓርላማ ናቸው:: በፍርድ ቤት የተያዘን ጉዳይ መመልከት የሚቻለው ጉዳዩ በሕጉ አግባብ መያዙን፣ መቅረቡንና በትክክለኛው መንገድ እየሄደ መሆኑን ብቻ ነው:: ሁለቱ ተቋማት በያዙት ጉዳይ ላይ ገብቶ ለማዘዝ አቅምም መብቱም የለውም:: ከሁለቱ ተቋማት ወይም በማንኛውም ተቋም ውስጥ በመግባት ይኼ ትክክል አይደለም፣ መስተካከል አለበት በማለት የማዘዝና የማስፈጸም ሥልጣን የለውም ብለዋል::

አምባሳደር ጥሩነህ ስለ ኮሚሽኑ ከላይ የሰጡትን ማብራሪያ የተናገሩት በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው የታሰሩ ሰዎችን የሰብዓዊ መብት አያያዝ በሚመለከት ምንም የሠራው ሥራ እንደሌለና የሚያስተላልፈው

ፎቶ በ

ሪፖርተ

ር/ናሆ

ም ተ

ስፋዬ

ገጽ 2 | እሑድ |ኅዳር 17 ቀን 2004

አድራሻ፡- ቦሌ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 03 የቤት ቁጥር 2347 ፖስታ 7023 አ.አ ኢትዮጵያ

ማስታወቂያ ሽያጭና ስርጭት 0910 885206/ 011 6 61 61 79/ 85

[email protected] E-mail: [email protected]

Website: www.ethiopianreporter.com

ዋና ሥራ አስኪያጅ፡ አማረ አረጋዊዋና አዘጋጅ፡ መላኩ ደምሴአራዳ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 13/14 የቤት ቁ. 481ምክትል ዋና አዘጋጅ፡ ዘካሪያስ ስንታየሁከፍተኛ አዘጋጅ፡ ዳዊት ታዬ አዘጋጆች፡ ሔኖክ ያሬድ ጌታቸው ንጋቱ

ምሕረት ሞገስኃይሌ ሙሉ

ረዳት አዘጋጆች፡ ታደሰ ገ/ማርያም ምሕረት አስቻለው ታምሩ ጽጌ የማነ ናግሽ

ዋና ግራፊክ ዲዛይነር፡ ይበቃል ጌታሁንከፍተኛ ግራፊክ ዲዛይነር፡ ቴዎድሮስ ክብካብግራፊክ ዲዛይነሮች፡ ፀሐይ ታደሰ ፋሲካ ባልቻ እንዳለ ሰሎሞን ስሜነህ ሲሳይ ቢኒያም ግርማ ነፃነት ያዕቆብ ቤዛዬ ቴዎድሮስዋና ፎቶ ግራፈር፡ ናሆም ተስፋዬፎቶ ግራፈሮች ታምራት ጌታቸው መስፍን ሰሎሞን

ካርቱኒስት፡ ኤልያስ አረዳ

በሚዲያና ኮምዩኒኬሽንስ ሴንተር (ኤም.ሲ.ሲ) ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር

እየታተመ የሚወጣ ጋዜጣ

እሑድ ኅዳር 17 ቀን 2004

በጳጉሜን 6 1987 ተጀመረ በሳምንት ሁለት ጊዜ የሚታተም አድራሻ ስልክ 0910-885206/ 011-661 61 79/85/87 ፋክስ: 011-661 61 89

ከፍተኛ ሪፖርተሮች፡ ደረጀ ጠገናው ብርሃኑ ፈቃደሪፖርተሮች፡ ብርቱካን ፈንታ ምዕራፍ ብርሃኔማርኬቲንግ ማናጀር፡ እንዳልካቸው ይማምሴልስ፡ ቤዛዊት ፀጋዬ' Hና Ó`T' w\¡ S<K<Ñ@�' IK=ና ከuደማስታወቂያ ፕሩፍሪደር፡መሳይ ሰይፉ፤ ብሩክ ቸርነት፤ ኤፍሬም ገ/መስቀልኮምፒውተር ጽሑፍ፡ ብርቱካን አባተ፣ ሄለን ይታየው፣ አፀደ ካሳዬ፣ ፍሬሕይወት ተሰማሕትመት ክትትል፡ ተስፋዬ መንገሻ፣ የየሱስወርቅ ማሞ፣ ገዛኸኝ ማንደፍሮዌብ ሳይት፡ ቤዛዊት ተስፋዬ፣ ቢኒያም ሐይሉ

ርእሰ አንቀጽ‹‹ሕዝብን መምራት በብልኃት›› - ይኑር!

‹‹ጭር ሲል አልወድም›› - ይቁም!ከማብራራት ይልቅ ማደናገር፣ ከማረጋጋት ይልቅ ማስጨነቅ፣ ከማቅረብ ይልቅ ማራቅ፣

ከምስጋና ይልቅ ወቀሳ፣ ከመስጠት ይልቅ መውሰድ፣ ከፍቅር ይልቅ መቃቃር፣ ከመደገፍ ይልቅ ማጣደፍ ሲበዛና ሲዘወተር መፈክሩ ‹‹ጭር ሲል አልወድም›› ነው ወይ? ያሰኛል::

በኅብረተሰባችን ውስጥ መልስ ያላገኙ በርካታ ጥያቄዎች እየተንሸራሸሩ ናቸው:: በቅንነትና በኃላፊነት ስሜት መልስ ለመስጠት የተዘጋጀ ኃላፊና ተቋም ቢያገኙ፣ ጥያቄዎቹና ቅሬታዎቹ በቀላሉ የሚመለሱና የሚረጋጉ ናቸው:: ይህ ስላልሆነ ግን አላስፈላጊ መጠራጠርና መደናገር እያስከተሉ፣ መንግሥት በቅንነትና ለአገር የሚጠቅም ነገር ቢያውጅም፣ ‹‹ጎሽ›› ከማለት ይልቅ ‹‹ለምን?›› የሚል ስሜት እንዲፈጠር እያደረጉ ናቸው::

ከባንክ ተበድሬ ይህንና ያንን እሠራለሁ ብሎ ያቀደ ዜጋ፣ በአሁኑ ጊዜ ባንኮች ለማበደር ዝግጁ ናቸውን? አታበድሩ የሚል መመርያ ወጥቷልን? እያለ መጠራጠርና መፍራት ጀምሯል:: ገንዘብ ማስገባትና ማስወጣት እያሰጋው ነው:: መበደርም፣ ማስቀመጥም፣ ማውጣትም አይቻልም ተብሎ ሳይሆን፣ አዋጅ ወጣ መመርያ ተላከ ሲባል የሚያስረዳውና ሀቁን የሚነግረው ስለሚያጣ ነው:: ባንክን በተመለከተ አዕምሮው ውስጥ እየተቀረፀ ያለው በየቀኑ መመርያ እየወጣና እየተቀየረ መሆኑን ነው::

ይህን መሬት ወስጄ ይህን እገነባለሁ ብሎ የተዘጋጀም የሊዝ አዋጅ መውጣቱን ሲሰማ ፍርኃት፣ ፍርኃት እያለው ነው:: አትገንባ የሚል ሕግ ወጥቶ አይደለም:: የሊዝ አዋጁም አይቻልም ስላለ አይደለም:: በትክክል የሚያብራራና የሚያስረዳ ስለጠፋ የመሬት ኢንቨስትመንትና የግንባታ ሥራ ጥርጣሬ ውስጥ ገብቷል::

ዳያስፖራው ኢትዮጵያዊ አገሩ ውስጥ ገብቶ አንዳንድ ነገር ለመሥራት ወስኖ ለመምጣት ሲዘጋጅ፣ የሆነውንና ያልሆነውን ወሬ እየሰማ ሀቁን ማወቅ ተስኖት ዕቅዱን ለመቀጠል ፈራ ተባ ሲልና ጥያቄ ሲያበዛ እየተስተዋለ ነው::

ፈቃድ ማውጣትና መሥራት የሚፈልገው፣ ፈቃድ ማሳደስ ያሰበው፣ ፈቃድ ለመቀየር የሚጠይቀው ዜጋም እንደ ድሮው ቀልጣፋና አበረታች መሆኑን ሲያጣው እንዴት ነው ነገሩ? እያለ ለመሥራትም ፈራ ተባ እያለ ነው:: እውነትም ለመሥራት አስቸጋሪ ሆኖ ሳይሆን፣ እውነትም መንግሥት ከልክሎ ሳይሆን፣ እውነትም መንግሥት ሥርዓት ለማሳያዝ ያቀደው ለዘለቄታው ሳይሆንና አገርን የሚጎዳ ሳይሆን፣ መመርያውን በግልጽ ተረድቶ በግልጽ የሚያስረዳ ተቋምና ኃላፊ እየጠፋ ስለመጣ ነው:: ተጠቃሚው ኅብረተሰብ አልቀላጠፍ ሲለው ጥላቻውን በአዋጁና በመመርያው ላይ እያደረገ ነው::

ሁለት መሥሪያ ቤቶች፣ ሁለት ወረዳዎች፣ ሁለት ክፍላተ ከተሞች፣ ሁለት የአንድ ዓይነት መሥሪያ ቤት ኃላፊዎች አንድ ዓይነት ነገር ሲናገሩና ሲሠሩ አይሰሙም:: በአንድ አዋጅ፣ በአንድ ደንብና በአንድ መመርያ ላይ ያላቸው አመለካከት፣ አፈጻጸምና አስተያየት የተለያየ ነው::

ይህ ሁኔታም ኅብረተሰቡን እየረበሸው ነው:: አንዱ ለሕንፃ ስለሚፈለግ ዛሬ አፍርሱ ይላል:: ሌላኛው ይፈርሳል ግን እስከዚያው ድረስ ቆዩ ይላል:: ሌላው ሥራ ላይ ለማዋል ገና ስለሆነ አትጨነቁ ይላል:: ሌላው አሁን ካልፈረሰ ከሰዓት በኋላ መጥተን እናፈርሰዋለን ይላል:: ሌላው ባለሰባት ፎቅ ሕንፃ መሠራት አለበት ይላል:: ሌላው ግድ የለም በአራት ፎቅ ይቻላል ይላል:: ሌላው ለመንገድ ይፈለጋል ይላል:: ሌላው አትጨነቁ ለመንገድ አይፈለግም ይላል:: መተራመስ ነው:: ‹‹ጭር ሲል አልወድም›› ነው::

ሌላው በሕገወጥ መንገድ የያዘው መሬት አለ:: ሌላው ለዓመታት አጥሮ ያስቀመጠው መሬት አለ:: እንዲህ ዓይነቱ ሳይነካ፣ ሳይወቀስና ሳይነጠቅ ሌላው በአግባቡ የወሰደና ግንባታ ያካሄደ ሲነጠቅ ይታያል:: መተራመስ ነው:: ሞላጫው ይከብራል:: ሀቀኛው ይቀጣል ይሰቃያል:: ፍትሕ ማግኘትም መርህ መሆኑ ቀርቶ ገጠመኝ ሆኗል:: መተራመስ ነው:: ‹‹ጭር ሲል አልወድም›› ማለት ይኼ ነው::

መንግሥትም እንደ መንግሥት ገዢው ፓርቲም እንደ ገዢ ፓርቲነቱ የአመራርና የአባላት ሥልጠና እያካሄደ ነው፤ ግምገማ እየተደረገ ነው ሲባል ኅብረተሰቡ በአዎንታ ይቀበለዋል፤ ለውጥ ይኖራል ብሎም ተስፋ ያደርጋል:: ሁለት አንድ ዓይነት ኃላፊዎች ሲያጠፉ አንዱ ተቀጥቶ ሌላው ባለበት ሲቀጥል ወይም የተሻለ ኃላፊነት ሲሰጠው ደግሞ ኅብረተሰቡ ግራ ይጋባል:: ግምገማ ተካሄደ ተብሎ ይነገራል:: አንዳንዱ ራሱ ተገምጋሚ መሆን ሲገባው ገምጋሚና ወቃሽ ሆኖ የበላይነት ሲይዝ ይታያል:: ራስህን በራስህ ገምግም ብሎ መተውና ብቁና ነፃ አካል አስመጥቶ እንዲገመገም ማድረግ ውጤቱ የተለያየ ነው:: ይህም መጠራጠርንና እምነት ማጣትን እያስከተለ ነው:: ‹‹እንዴት ነው ነገሩ?›› የሚል ስሜት እየተስፋፋ ነው፤ እየተጮኸም ነው:: ግምገማውና ሥልጠናው እውነት ለውጥ ለማምጣት ነው? ወይስ ‹‹ጭር ሲል አልወድም›› ነው? የሚል ጥያቄም እያስከተለ ነው::

እያልን ያለነው መንግሥት ለምን ግብር ክፈሉ አለ አይደለም:: ግብር መከፈል አለበት ብቻ ሳይሆን መንግሥት የግብር ሥርዓት እንዲኖርና እንዲጠናከር ማድረግ አለበት:: መንግሥት ለምን የመሬት ሕግ አወጣ እያልንም አይደለም:: የመሬት ሥርዓትም መኖር አለበት:: የንግድ ፈቃድ ለምን አውጡ አድሱ ተባለ እያልንም አይደለም:: የፈቃድ አወጣጥ፣ እድሳትና አመላለስ ሥርዓትም መኖር አለበት:: ለሁሉም ሥርዓት ይኑር፣ ጠንካራ ሥርዓትም ይፈጠር:: ሥርዓት የሚያስከብሩ ሥርዓት ያላቸው ተቋማትና ኃላፊዎችም ይኑሩ:: እዚህ ላይ ችግር የለብንም:: ችግሩ ግን ሥርዓት ለማስያዝ እየተባለ እየተደረገ ያለው ሥርዓት የሚያሳጣ እየሆነ ነው::

በሥርዓቱ ከመሥራት ይልቅ አዋጅና መመርያ ይበዛል:: ማስረዳትና ማብራራት ስለሌለ ሕዝብ ይፈራል፤ ይደናበራል:: አንዱ ሳይረጋጋ ሌላው ይከተላል:: በዚህ ላይም መረን የለቀቀ ሙስና አለ:: ይህ ሁሉ ተደማምሮ አካሄዱ ሁሉ እምነትና መረጋጋት ከመፍጠር ይልቅ ፍርኃትና መረባበሽን እያስከተለ ነው::

እንዲህ ዓይነቱን ሁኔታ ለመፍታት መንግሥት ቁጭ ብሎ ያስብ፤ ሕዝቡን ያዳምጥ፤ የፈራና የተረበሸ ሁሉ ኪራይ ሰብሳቢ ነው ብሎ ራሱን አያጽናና:: የሕዝብን ችግር ማዳመጥ የአመራር የጥበብ መጀመሪያ ነው::

መፈክሩ ይቀየር፤ መፈክሩ ‹‹ሕዝብን መምራት በብልኃት›› የሚል ይሁን! ‹‹ጭር ሲል አልወድም›› የሚለው መፈክር ይቁም!

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 3 | እሑድ | ኅዳር 17 ቀን 2004 ክፍል-1

በብርቱካን ፈንታ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሥሩ የሚገኘውንና ብቸኛ የሆነውን የሥነ ፆታ (Gender) የትምህርት ክፍል ሦስት ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ለስድስተኛ ጊዜ ዋናውን ግቢ ለቅቆ እንዲወጣ በማድረጉ በትምህርት ክፍሉ፣ በሠራተኞችና በተማሪዎች ዘንድ ተቃውሞ ገጠመው::

የትምህርት ክፍሉ ሠራተኞች ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የሥነ ፆታ የትምህርት ክፍል ከተመሠረተ አሥር ዓመት ያህል የሆነው ሲሆን፣ ከሦስት ዓመት ወዲህ ግን ዩኒቨርሲቲው ግልጽ ባልሆነ ምክንያት አንዴ ከግቢው በማስወጣት፣ ሲያሻው ደግሞ ወደ ግቢው

በመመለስ ሠራተኞችንና ተማሪዎችን ለእንግልት ዳርጓል::

የትምህርት ክፍሉ ገና ያልተጠናከረና ድጋፍ የሚያሻው ሆኖ ሳለ አሁን ደግሞ አዲስ ተማሪዎች ከተመዘገቡ በኋላ ወደ አቃቂ ካምፓስ ይሂዱ መባሉ ጥያቄ እንደፈጠረባቸው የሚገሩት ሠራተኞቹ፣ አቤቱታቸውን በተደጋጋሚ ለዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ቢያቀርቡም መፍትሔ እንዳላገኙ ተናግረዋል::

የትምህርት ክፍሉ ከዋናው ግቢ ርቆ ከሄደ የህልውናው ጉዳይ እንደሚያሰጋቸው የሚናገሩት ሠራተኞቹ፣ ለዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ይህንን ቢያሳውቁም ዩኒቨርሲቲው ግን ዕቃዎቹን በሙሉ ጭኖ አቃቂ ወስዶታል::

ከዚህ ቀደም ቦሌ ፍሬንድሽፕ ሕንፃ ጀርባ ባለ ስፍራ እንዲገባ ተገድዶ በነበረበት ወቅት፣ ላይብራሪዎች ሳይቀሩ ባዶዋቸውን ይውሉ እንደነበር ሠራተኞቹ ገልጸው፣ ወደ ዋናው ግቢ በድጋሚ እንዲመለስ ሲታዘዝ ደግሞ ላይብራሪው እየሞላ ብዙ ጊዜ ቦታ ይጠፋል:: ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ ዋናው ግቢ ምርምር ለሚሠሩ፣ በሥነ ፆታ ዙርያ ትምህርት ለሚወስዱና ለትምህርት ክፍሉ አመቺ እንደሆነ ይናገራሉ:: የትምህርት ክፍሉ አቃቂ ከገባ ግን አገልግሎቱን ፈላጊዎች ሙሉ በሙሉ እንደሚያጣ በእርግጠኝነት ይናገራሉ::

ከዋናው ግቢ ውጪ ባሉ ቦታዎች እንዲሄዱ ሲታዘዙ መሄዳቸውንና አንዳንድ ጊዜም ዓመት ሳይሞላቸው

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሥርዓተ ፆታ ዲፓርትመንት ተቃውሞ ተነሳበት

ወደ ክፍል 1 ገጽ 43 ዞሯል

ወደ ክፍል 1 ገጽ 43 ዞሯል

ከኔትወርክ ፍተሻ ጋር በተያያዘ

ቻይናዊው የዜድቲኢ ባለሙያ የኢትዮ ቴሌኮም ኢንጂነሩን በስለት ወጋውበኃያል ዓለማየሁ

ዜድቲኢ የተባለው የቻይና የቴሌኮም ኩባንያ ከአዲስ አበባ በስተደቡብ 600 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው በነገሌ ቦረና አካባቢ የተዘረጋው የቴሌኮም ኔትወርክ ጥራቱ ተቀባይነት እንደሌለው በመግለጽ የተሠራውን ሥራ ውድቅ ያደረገው የኢትዮ ቴሌኮም ኢንጂነር፣ ኔትወርኩን በዘረጋው የዜድቲኢ ቻይናዊ ባለሙያ በስለት ተወግቶ ጉዳት እንደደረሰበት፣ ለፕሮጀክቱ ቅርበት ያላቸውና ድርጊቱን ያዩ የዓይን እማኞች ለሪፖርተር ገለጹ::

ድርጊቱ የተፈጸመው ባለፈው ሳምንት ዓርብ መሆኑን የገለጹት ምንጮች፣ የኢትዮ ቴሌኮም ኢንጂነር ለቻይናው ባለሙያ ክፍያ የሚያሰጠውን የተቀባይነት ሠርተፍኬት በመንፈጉ ምክንያት መሆኑን አረጋግጠዋል::

‹‹የተዘረጋው ኔትወርክ ተቀባይነት እንደሌለውና የተቀባይነት ሠርተፍኬት ሊሰጠው እንደማይገባ ኢትዮጵያዊው ኢንጂነር ካብራራ በኋላ፣ በእሱና በቻይናው ባለሙያ መካከል ለረጅም ሰዓታት ውዝግብ ተፈጥሮ ነበር፤›› ሲሉ የገለጹት ምንጮች፣ ከውዝግቡ በኋላ የቻይናው ባለሙያ ኢንጂነሩን ደረቱ አካባቢ በስለታማ መሣርያ እንደወጋው አብራርተዋል::

ኢንጂነሩ በስለቱ ከተወጋ በኋላ በአካባቢው በነበሩ ሠራተኞች አማካይነት በፍጥነት ሐዋሳ ከተማ ወደሚገኝ ሆስፒታል መወሰዱንና ለሦስት ቀናት ሕክምና ከተከታተለ በኋላ ባለፈው ማክሰኞ ከሆስፒታል መውጣቱን አስታውቀዋል::

የኢንፎርሜሽንና የኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ዶክተሩ ደብረ ፅዮን ገብረ ሚካኤል በአገር አቀፍ ደረጃ በ1.5 ቢሊዮን ዶላር በዜድቲኢ የሚዘረጋው ኔትወርክ የደረጃ ጥራቱ እንደሚፈተሽና ጥራቱ የተጠበቀ ካልሆነም ውድቅ እንደሚደረግ፣ በሚዘረጋው ኔትወርክ ጥራት ላይ ምንም ዓይነት ድርድር እንደማይደረግ ቀደም ሲል ለሪፖርተር መግለጻቸውን

በቴዎድሮስ ክብካብ

የእንግሊዝ መንግሥት ለኢትዮጵያ በተያዘው ዓመት 219 ሚሊዮን ፓውንድ ለመርዳት ዕቅድ እንዳለው አስታወቀ:: ባለፈው ዓርብ ምሽት በእንግሊዝ ኤምባሲ በኢንተርናሽናል ኢንስፓይሬሽን ፕሮጀክት የመግባቢያ ሰነድ ላይ ሲፈረም፣ በኢትዮጵያ የእንግሊዝ ኤምባሲ ምክትል ኃላፊ ሚስተር ክረስ አለን ዕርዳታው ለተለያዩ ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ እንደሚሰጥ አረጋግጠዋል::

የእንግሊዝ የዕርዳታ ድርጅት (UK-AID) ጋር በስፖርት፣ በድህነት ቅነሳና በጤና ዘርፍ የመግባቢያ ሰነዱ ከትምህርት ሚኒስቴር፣ ከሕፃናት፣ ሴቶችና ወጣቶች ሚኒስቴር ጋር ተፈርሟል:: በሥነ ሥርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴና የዩኒሴፍ ተወካዮች ተገኝተዋል::

ሚስተር አለን በተለይ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በተያዘው ዓመት በኢትዮጵያ ለሚከናወኑ ሥራዎች ከሚለገሰው ከዚህ ገንዘብ ውስጥ 2.5 ሚሊዮን ፓውንድ ለስፖርት፣ ለድህነት ቅነሳና ለጤና የሚውልም ይገኝበታል:: ይህ የሙከራ ፕሮጀክት በአራት ክልሎች ውስጥ ተግባራዊ እንደሚደረግም ይጠበቃል:: ክልሎቹም ኦሮሚያ፣ አማራ፣ አዲስ አበባና ቤንሻንጉል ጉሙዝ ናቸው::

የመግባቢያ ስምምነቱን በተመለከተ ለሴቶች፣ ሕፃናትና ወጣቶች ሚኒስቴር ዴኤታው ለአቶ አልማው መንግሥት ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፣ ‹‹ይህን ሥራ አስቀድመን መሥራት የጀመርን ሲሆን፣ ነገር ግን ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ

እንግሊዝ ለኢትዮጵያ 219 ሚሊዮን ፓውንድ ልትለግስ ነውየሚጀመርበትን ቀን ስንጠባበቅ ነው እስካሁን የቆየነው:: ይህ ፕሮጀክት ራሱን የቻለ የተዋቀረ ኮሚቴ አለው፤ የኮሚቴው አባላት ከትምህርት ሚኒስቴር፣ ከሴቶች፣ ሕፃናትና ወጣቶች ሚኒስቴር፣ ከስፖርት ኮሚሽን፣ ከኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴና ከፓራ ኦሊምፒክ የተውጣጡ ናቸው፤›› ብለዋል::

አቶ አልማው አክለውም ስፖርትን መሠረት ያደረገ የትምህርትና የጤና ሥራ ለመሥራት የታቀደበት ምክንያት፣ ስፖርት በጣም ለውጥ ያመጣሉ ተብለው ከታሰቡ እንቅስቃሴዎች መካከል ተጠቃሽ በመሆኑ ነው:: ‹‹ስፖርትን የመረጥንበት ምክንያት ደግሞ በትምህርት ቤት ያሉትንና ከትምህርት ቤት ውጪ ያሉትን ልጆች ለማጠንከር ስለሚረዳን ነው፤›› ብለዋል::

ይህንን ሥራ በአስፈጻሚነት የሚከታተሉት ብሪቲሽ ካውንስልና ዩኒሴፍ መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን፣ ሚስተር አለን፣ ‹‹እኛ ይህን ዳጐስ ያለ ገንዘብ የመደብነው በመላው አገሪቱ ለሚካሄዱ የስፖርት፣ የድህነት ቅነሳና የጤና ሥራ ለመሥራት ስለሚያስችለን ነው:: ያለጊዜያቸው ለሚቀጩ ሕፃናትና በወሊድ ምክንያት ለሚሞቱ እናቶችም ድጋፍ ይሰጣል ብለን እናምናለን፤›› ሲሉ አስረድተዋል::

የእንግሊዝ የዕርዳታ ድርጅት ኢትዮጵያን ጨምሮ በአፍሪካ የተለያዩ አራት አገሮች ውስጥ በተመሳሳይ ሁኔታ ዕርዳታ እያደረገ እንደሚገኝ ታውቋል:: ከሞዛምቢክ፣ ከናይጄሪያና ከኡጋንዳ በተሻለ ለኢትዮጵያ የሚሰጠው ድጋፍ በከፍተኛ ደረጃ ብልጫ እንዳለው ተገልጿል:: እንግሊዝ ለኢትዮጵያ ዕርዳታ ከሚያደርጉ አገሮች መካከል በዋናነት ትጠቀሳለች::

ሚስተር ክረስ አለን

ፎቶ በ

ሪፖርተ

ር/ናሆ

ም ተ

ስፋዬ

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 4 | እሑድ |ኅዳር 17 ቀን 2004ክፍል-1

በብርቱካን ፈንታ

የምሥራቅ ድል አንደኛ ደረጃ የሕዝብ ትምህርት ቤት መንግሥት ከሕግ ውጭ ጣልቃ በመግባት አመራሮችን እየሾመ ነው በሚል ከአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ጋር በመወዛገብ ላይ ነው:: የቦሌ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽሕፈት ቤት በበኩሉ ትምህርት ቤቱ አመራሮችን በሕጉ መሠረት እኛ እንሾማለን ካለ መንግሥት ድጋፉን ያቋርጣል አለ::

የትምህርት ቤቱ የትምህርት አመራር ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ደጉ ተበጀ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የትምህርት ቤቱ ደንብ ርዕሰ መምህርና ምክትል ርዕሰ መምህር በትምህርት ቤቱ አመራር ኮሚቴ እንዲመረጡ ቢደነገግም፣ መንግሥት ግን የራሱን ሰዎች በማምጣት ይሾማቸዋል፣ ለሌላ ሥራ ሲፈልጋቸውም ያለምንም ርክክብና ግንዛቤ ያነሳቸዋል::

‹‹ከዚህ ቀደም መንግሥት ጣልቃ በመግባት ርዕሰ መምህርና ሁለት ምክትል ርዕሰ መምህራንን ይሾማል:: ለክፍለ ከተማ ሥራ ወይም ለሌላ ጉዳይ ሲፈልጋቸው ደግሞ ምትክ ሳያዘጋጅ ያነሳቸዋል:: ባለፈው ዓመት ለክፍለ ከተማ ሥራ ስለፈለጋቸው ከቦታቸው በማንም ሳይተኩ አንስቷቸዋል:: በዚህም ምክንያት ከጥር 2003 ዓ.ም እስከ መስከረም 2004 ዓ.ም ድረስ ትምህርት ቤቱ ያለ ርዕሰ መምህርና ምክትል ርዕሰ መምህር ሲመራ ቆይቷል፤›› በማለት አቶ ደጉ አስረድተዋል::

ልምድና ብቃት ያላቸው መምህራን በትምህርት

ቤቱ ውስጥ ቢኖሩም እንዲወዳደሩ እንኳን መንግሥት ዕድሉን እንደማይሰጥ የሚናገሩት አቶ ደጉ፣ መንግሥት ከሕግ ውጭ መሾምና መሻሩ የትምህርት ቤቱን ህልውና ስጋት ውስጥ ከቶታል::

የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች የሥራ ሒደት ኃላፊ አቶ ደምር ዘውዱ በበኩላቸው፣ ትምህርት ቤቱ መምህራንንም ሆነ ርዕሰ መምህራንን ለመቅጠር አቅም የሌለው በመሆኑ መንግሥት እየቀጠረ ያስማራለታል::

‹‹ከተማው ውስጥ ያሉ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች አቅም ኖሯቸው ራሳቸውን ማስተዳደር ባለመቻላቸው መምህራን በየጊዜው ይለቃሉ:: መንግሥትም ለትምህርት ቤቱ ህልውና ሲል መምህራን በመቅጠርና ሌሎች ግብዓቶችን በማሟላት ድጋፍ ይሰጣል:: የርዕሰ መምህራንንም ደመወዝ መክፈል ስለማይችሉ መንግሥት ራሱ እየቀጠረ ደመወዝ ይከፍላቸዋል፤›› ሲሉ አቶ ደምር አብራርተዋል::

ሌሎች የሕዝብ ትምህርት ቤቶች ‹‹መንግሥት ለምን አመራሮችን ይቀጥርልናል?›› የሚል ጥያቄ አንስተው እንደማያውቁ ያብራሩት ኃላፊው፣ የምሥራቅ ድል ትምህርት ቤት ይህንን ጥያቄ ማንሳቱ ምናልባትም በሙስና ምክንያት ያገኟቸው የነበሩ አንዳንድ ጥቅማ ጥቅሞችን በማጣታቸው ሊሆን እንደሚችል ተናግረዋል::

ሕጉ አያዝም በሚል ትምህርት ቤቱ ዝም ከተባለ እንደሚፈርስ የሚናገሩት አቶ ደምር፣ መንግሥት

የሕዝብ ትምህርት ቤቶችን ወደ ራሱ ለማዛወር እየሠራ በመሆኑ እስከዚያው ድረስ ብቸኛው መፍትሔ ይህ ብቻ ነው ብለዋል::

እስከ 2002 ዓ.ም ድረስ የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር የነበሩት የወረዳ ሹመት በማግኘታቸው ለስምንት ወራት ያህል ትምህርት ቤቱ ያለ ርዕሰ መምህር ቆይቷል:: በዚህ መካከል በነበረው ክፍተት የትምህርት ቤቱ አመራር ኮሚቴ ርዕሰ መምህርና ምክትል ርዕሰ መምህር መድቧል:: ነገር ግን ርዕሰ መምህሩ የተሻለ ሥራ አግኝቶ በመልቀቁ ምክንያት መንግሥት በድጋሚ ርዕሰ መምህር በመሾሙና ምክትሎቹም ሁለት መሆን ስላለባቸው አንድ ተጨማሪ ርዕሰ መምህር መሾሙን አቶ ደምር ገልጸዋል::

የቦሌ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽሕፈት ቤት የመምህራንና የትምህርት አመራር ልማት ውስጥ የሚሠሩ አንድ ባለሙያ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ መንግሥት ቦታው ላይ የራሱን ሰው መሾሙ ፖለቲካዊ አንድምታ አለው:: ቦታው ላይ መሆን ያለበት ፖለቲከኛ በመሆኑ መንግሥት የራሱን ሰው አስቀምጧል:: ትምህርት ቤቱ የራሱን ሰው መሾም እፈልጋለሁ ካለም መንግሥት ለቀጠራቸው 25 መምህራንና የሚመረጡትን አመራሮች ደመወዝ መክፈል ያቋርጣል:: ለትምህርት ቤቱ የሚደረገው ማንኛውንም ዓይነት ድጋፍ ያቋርጣል::

የመንግሥት ጣልቃ ገብነት ትምህርት ቤቱንና የትምህርት ቢሮውን አወዛገበ

ወደ ክፍል 1 ገጽ 43 ዞሯል

በታምሩ ጽጌ

ኢትዮጵያን ለማተራመስ የአመፅ አማራጭ ባስቀመጠው የግንቦት 7 አሻባሪ ድርጅት ውስጥ በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን፣ የሽብርተኝነት ድርጊቶችን ለመፈጸም በማሴር፣ በማቀድ፣ በማነሳሳት፣ በማዘጋጀት፣ በመሳተፍ፣ አባል በመሆን፣ አገር በመክዳት፣ በመሰለልና ድጋፍ በመስጠት ወንጀል ተሳትፈዋል በሚል ተጠርጥረው ክስ ከተመሠረተባቸው 24 ተከሳሾች መካከል፣ ስምንቱ ከግንቦት 7 ተከሳሾች ጋር በጅምላ መከሰሳቸውን በመቃወም ክሱ ተለይቶ እንዲቀርብላቸው፣ ክሱን በመመርመር ላይ ለሚገኘው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሦስተኛ ወንጀል ችሎት ህዳር 13 ቀን 2004 ዓ.ም. አመለከቱ::

በጠበቆቻቸው አማካይነት፣ ‹‹ክሳችን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአሸባሪ ድርጅትነት ከፈረጀው ከግንቦት 7 ጋር ተቀላቅሎ ሊታይ አይገባም፤›› በማለት የተቃውሞ ክስ ያቀረቡት አንዱዓለም አራጌ፣ ናትናኤል መኮንን፣ ዮሐንስ ተረፈ፣ የሽዋስ ይሁን ዓለም፣ ክንፈ ሚካኤል ደበበ፣ ምትኩ ዳምጤ፣ እስክንድር ነጋና አንዱዓለም አያሌው ናቸው::

የተጠርጣሪዎቹ ክስ እንዲለይ ስለተፈለገበት ምክንያት ያስረዱት ጠበቆቻቸው፣ አንደኛ በክሱ ላይ በተጠቀሰባቸው የወንጀል ሕግና በፀረ ሽብርተኝነትን አዋጅ አንቀጽ መሠረት ድርጊቱ እውነት መሆኑ ከተረጋገጠባቸው ከዕድሜ ልክ እስከ ሞት ሊያስቀጣቸው የሚችል መሆኑን ነው::

በመሆኑም የሕግ ደረጃዎችን ባልጠበቀ መልኩ በቀረበ ክስ እንዳይቀጡ ክሱ ተለይቶ መታየት

ያስፈለገበትንም ምክንያት ጠበቆቹ ለፍርድ ቤቱ አስረድተዋል:: አቶ አንዱዓለም አራጌ በሕግ አግባብ በተቋቋመና ፈቃድ ተሰጥቶት የሚንቀሳቀስ ሕጋዊ ፓርቲ (አንድነት) ቃል አቀባይ መሆኑን፣ አቶ ናትናኤል መኮንንም የዚሁ ፓርቲ አባል መሆኑን፣ አቶ እስክንድር ነጋም ጋዜጠኛና የፖለቲካ ተንታኝ በመሆኑ፣ በአገር ውስጥ በሌለና በአገሪቱ ፓርላማ በአሸባሪነት በተፈረጀው የግንቦት 7 ድርጅት አባል ስላልሆኑ፣ ተቀላቅለው መከሰሳቸው ሊጎዳቸው እንደሚችል በዝርዝር አስረድተዋል::

ሌላው ጠበቆቹ ያነሱት ተቃውሞ በተጠርጣሪዎቹ ላይ የቀረበው ክስ በሚያስረዳው ዝርዝር ውስጥ፣ የወንጀሉ ድርጊት ቦታና ጊዜ ባለመጠቀሱ፣ የወንጀል ሕጉ በሚያዘው መሠረት መገለጽና መዘርዘር እንደሚገባው አስረድተው፣ ክሱን ተከላከሉ ቢባል የተጠርጣሪዎችን የመከላከል መብት ሊያጣብብ ስለሚችል፣ ተስተካክሎና ተገልጾ በዝርዝር እንዲቀርብላቸው ትዕዛዝ እንዲሰጥላቸው ነው::

በሕገ መንግሥቱ የተፈቀዱ መብቶች በክሱ ውስጥ እንደ ወንጀል ሆነው የቀረቡት፣ ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ መብትና የመሳሰሉት መቅረትና መስተካከል እንዳለባቸው፣ በሽብርተንነት አዋጁ የተጠቀሱት አንቀጾች ተጨፍልቀው አንድ ተከሳሽ በሁለት አንቀጾች የተጠየቀበት ሁኔታ ስላለ፣ ተከላከሉ ቢባል ስለሚያስቸግር ሊስተካከል እንደሚገባ በመጠቆም ጠበቆቹ ተቃውሞአቸውን ለፍርድ ቤቱ አቅርበዋል::

በተጠርጣሪዎቹ ላይ ክሱን ያቀረበው የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ በክሱ ላይ ላቀረበው ተቃውሞ በሰጠው ምላሽ፣ የተለያዩ የወንጀል ተሳትፎ ያላቸው

ተጠርጣሪዎች ተጠቃለው በአንድ ላይ ክስ ሊቀርብባቸው እንሚቻል፣ ወንጀሉ የተፈጸመበትን ጊዜና ቦታ አልተጠቀሰም ለሚል ለቀረበው ተቃውሞም ሕጉ ‹‹በተቻለ መጠን›› ስለሚል፣ ከ2001 ዓ.ም. እስከ 2003 ዓ.ም. በሚል መጠቀሱን፣ ክሱ በሕጉ አግባብ በዝርዝር የቀረበ መሆኑን፣ ተከሳሾቹ ድርጊቱን ፈጽመዋል ሳይሆን፣ አሲረዋል፣ አቅደዋል፣ ወዘተ የሚል መሆኑንና ሌሎችንም ተቃውሞዎች ውድቅ እንዲያደርግለት ጠይቋል:: ሙያቸውንና በሕግ አግባብ የተቋቋመን የፖለቲካ ፓርቲ ከለላ በማድረግ ሲንቀሳቀሱ ተገኝተዋል በሚል በመጠርጠራቸው ክሱ ተለያይቶ መቅረብ እንደሌለበትም በማስረዳት፣ ተቃውሞው ውድቅ እንዲደረግ ዓቃቤ ሕግ አመልክቷል::

ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙን ክርክር አድምጦና ከሕጉ ጋር አገናዝቦ በሰጠው ብይን፣ ዓቃቤ ሕግ በአንደኛ ክሱ የወንጀል ድርጊቱ የተፈጸመበትን ጊዜና ቦታ እንዲገልጽ፣ በአራተኛው ክስ ላይ የሚታየው የአርትኦት ችግር እንዲታረምና ተስተካክሎ እንዲቀርብ ትዕዛዝ ሰጥቶ፣ የተጠርጣሪ ጠበቆች ያቀረቧቸውን ሌሎች የተቃውሞ ሐሳቦችን ሳይቀበላቸው ቀርቷል::

ዓቃቤ ሕግ በሁሉም ተከሳሾች ላይ በሚል በአንደኛ ክሱ አካቷቸው የነበሩት የቀድሞ አዲስ ነገር ማኔጂንግ ዳይሬክተር መስፍን ነጋሽንና ማኔጂንግ ኤዲተር አብይ ተክለ ማርያምን እንደማያካትት በመግለጽ እንዲታረም አድርጓል::

ፍርድ ቤቱ ዓቃቤ ሕግ አስተካክሎ የሚያቀርበውን ክስ ለመስማትና የተጠርጣሪዎቹን የእምነት ክህደት ቃል ለመቀበል ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቶ ችሎቱ ተጠናቋል::

ስምንት የሽብር ወንጀል ተጠርጣሪዎች ከግንቦት 7 ተከሳሾች እንዲለዩ ተጠየቀ

ክሱ በከፊል እንዲሻሻል ትዕዛዝ ተሰጠ

የከሰረው ድርጅት ንብረቶች ተሽጠው ለሕብረትና ለአቢሲኒያ ባንኮች እንዲከፈል ተወሰነበለምለም ፀጋይ

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሰባተኛ ፍትሐ ብሔር ችሎት በስማቸው ደምሴ ኢንቨስትመንት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ስም የተመዘገቡ የቆርቆሮ ማምረቻ ማሽኖችና ስድስት ተሽከርካሪዎች፣ በሐራጅ ተሸጠው በቅድሚያ ለሕብረት ባንክ ቀጥሎም ደግሞ ለአቢሲኒያ ባንክ እንዲከፈሉ ህዳር 7 ቀን 2004 ዓ.ም. ትዕዛዝ አስተላለፈ::

ፍርድ ቤቱ ትዕዛዙን ሊያስተላለፍ የቻለው ሕብረት ባንክ በኢቢሲኒያ ባንክና በማኀበሩ መካከል በተደረገው የአፈጻጸም ክርክር፣ ንብረቶቹን ለማኅበሩ በሰጠው ከ14 ሚሊዮን ብር በላይ የብድር ውል በመያዣነት ስለያዛቸው፣ ከአቢሲኒያ ባንክ በፊት በቅድሚያ እንዲከፍለው ጥቅምት 7 ቀን 2004 ዓ.ም. ያቀረበውን አቤቱታ በመቀበል ነው::

አቢሲኒያ ባንክም ሕብረት ባንክ ላቀረበው የቅድሚያ መብት አቤቱታ ጥቅምት 24 ቀን 2004 ዓ.ም. ባቀረበው አስተያየት፣ ንብረቶቹ ተሸጠው ለሕብረት ባንክ ቢከፈል እንደማይቃወም ከገለጸ በኋላ ቀሪው ገንዘብ እንዲከፍለው ፍርድ ቤቱን ጠይቋል::

ይህ የፍርድ አፈጻጸም መሠረት ያደረገው አቢሲኒያ ባንክ መክሰሩ በፍርድ ቤት በታወጀው ማኅበር ላይ ታህሳስ 9 ቀን 2002 ዓ.ም. የ17.9 ሚሊዮን ብር ክስ አቅርቦ፣ ሚያዚያ 21 ቀን 2003 ዓ.ም. ማኅበሩ እንዲከፍል የታዘዘበትን ውሳኔ ነው::

አቢሲኒያ ባንክ በማኅበሩ ላይ ያቀረበው ክስ እንደሚያስረዳው፣ ማኅበሩ ከባንኩ ጋር በተለያዩ ጊዜያት በፈጸመው የብድር ውል 72 ሚሊዮን ብር ተበድሮ ግዴታውን ሊወጣ ባለመቻሉ፣ በመያዣ የተያዙ ንብረቶችን በመሸጥና በማከራየት 55 ሚሊዮን ብር ሊያስመልስ ችሏል::

ማኅበሩ በጊዜያዊ ኦቨርድራፍት ብድር ውል የወሰደውን 11.7 ሚሊዮን ብር መያዣ ስላልነበረው ማስመለስ አለመቻሉን አቢሲኒያ ባንክ ያቀረበው ክስ ያስረዳል:: ከዚህም በተጨማሪ አቢሲኒያ ባንክ በማኅበሩ ስም የሚገኝ ሕንፃ በ6.1 ሚሊዮን ብር ካሸጠ በኋላ ሕብረት ባንክ የቅድሚያ መብት አለው ተብሎ በፍርድ ቤት በመወሰኑ፣ በማኅበሩ ላይ በድምሩ የ17.9 ሚሊዮን ብር ክስ ሊያቀርብ እንደቻለ አቢሲኒያ ባንክ በክሱ ላይ ጨምሮ ገልጿል::

ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል

ባንክ 44.4 ሚሊዮን ብር

የተጣራ ትርፍ አገኘበብርቱካን ፈንታ

የኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ አክሲዮን ማኅበር እ.ኤ.አ. በ2010/2011 በጀት ዓመት 44.4 ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን፣ ትናንት በጠራው የባለአክሲዮኖች ሁለተኛ ዓመታዊ መደበኛና አንደኛ ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ አስታወቀ::

ባንኩ በዚሁ በጀት ዓመት ያገኘው ጠቅላላ ትርፍ ከታክስ በፊት 56.7 ሚሊዮን ብር ነው:: ከተጣራው 44.4 ሚሊዮን ብር ውስጥ 34 ሚሊዮን ብሩ ለባለአክሲዮኖች እንደሚከፈል ተገልጿል::

የባንኩ ጠቅላላ ሀብት 1.9 ቢሊዮን ብር ሲደርስ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ75 በመቶ ብልጫ አሳይቷል:: የባንኩ ጠቅላላ ተቀማጭ ገንዘብ 1.5 ቢሊዮን ብር መሆኑን፣ ይህንንም ገንዘብ ያስቀመጡ ደንበኞች ቁጥርም 50 ሺሕ መድረሱ ታውቋል:: በተጠቀሰው የበጀት ዓመት ውስጥ ባንኩ ለ1,284 ተበዳሪዎች በአጠቃላይ 654 ሚሊዮን ብር ብድር መስጠቱ ተገልጿል::

ባንኩ ቀጣይ የአምስት ዓመት ዕቅዱን አስመልክቶ ባቀረበው ሪፖርት ተቀማጭ ገንዘቡን ወደ 7.6 ቢሊዮን ብር ለማሳደግ አቅዷል:: የተከፈለ ካፒታሉንም 700 ሚሊዮን ብር ያደርሳል ተብሏል::

ባንኩ የሚያደበድረው ገንዘብ እጥረት ዋነኛ ችግር እንደነበር በሪፖርቱ ላይ ተገልጿል:: ባለአክሲዮኖችም የባንኩን ችግር ለመቅረፍ ያላቸውን አክሲዮን በእጥፍ እንዲያሳድጉ ከራሳቸው ከባለአክሲዮኖች ጥሪ ቀርቧል::

በገዛ ፈቃዳቸው ሥራቸውን በለቀቁ ሁለት የቦርድ አባላት ምትክ ጉባዔው አዲስ ምትክ የቦርድ አባለት ምርጫ አካሂዷል:: ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ አክሲዮን ማኅበር ከተቋቋመ ሁለት ዓመት ከስምንት ወራት የሞላው ሲሆን፣ 7,400 ባለአክሲዮኖችና በአጠቃላይ 36 ቅርንጫፎች አሉት::

በዳዊት ታዬ

የጥራት ደረጃ ማረጋገጫ ሳይሰጣቸው ለገበያ መቅረብ እንደማይችሉ አስገዳጅ ደረጃ የወጣባቸው የታሸጉ ውኃዎች፣ የአርማታ ብረቶችና የኤሌክትሪክ ዕቃዎች አምራችና አቅራቢዎች ውስጥ አንዳቸውም አስገዳጅ ሕጉን ተግባራዊ አለማድረጋቸው ተገለጸ::

አስገዳጅ ሕጉን ተከትሎ የጥራት ማረጋገጫውን ከሚሰጠው የተስማሚነት ምዘና ኤጀንሲ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ የተጠቀሱት አምራቾች ምርቶቹን ለገበያ ከማቅረባቸው በፊት፣ የጥራት ማረጋገጫ መውሰድ እንደሚኖርባቸው ይፋ መመርያ የተላለፈው መስከረም 23 ቀን 2003 ዓ.ም.

ቢሆንም፣ እስካሁን ምርቶቻቸውን አላስፈተሹም:: እንደ መረጃው ከሆነ የተስማሚነት ምዘና

ኤጀንሲ አስገዳጅ ሕጉ ይመለከታቸዋል ለተባሉ ድርጅቶች መረጃ ያስተላለፈ ሲሆን፣ እስካሁን ምርቶቻቸውን ለገበያ ከማቅረባቸው በፊት ማረጋገጫውን ሊወስዱ አልቻሉም::

በተለይ የኤሌክትሪክ ዕቃዎችና የአርማታ ብረት አምራቾችና አስመጪዎች ምንም ዓይነት የጥራት ማረጋገጫ ሠርተፍኬት ሳይዙ ምርቶችን በመሸጥ ላይ ናቸው ተብሏል::

አንዳንድ የውኃ አምራቾች ግን የታሸጉ ውኃዎችን እንዲያመርቱና በጤንነት ላይ ችግር እንደማያስከትል ከመድኃኒት አስተዳደርና ቁጥጥር ባለሥልጣን ሠርተፊኬት አግኘተናል በማለት፣ አስገዳጅ ሕጉን ተግባራዊ አለማድረጋቸውንም

መረጃዎች ያስረዳሉ::አምራቾቹ የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና

ኤጀንሲ ባስቀመጠው ደረጃ መሠረት የምርቶቹ አጠቃላይ ይዘት የተቀመጠውን ደረጃ ማሟላት አለሟሟላቱን ለማረጋገጥ የሚያስችለውን ምዘና ባለማድረጋቸው፣ በቀጣይ ዕርምጃ ለመውሰድ የሚያስችል ዝግጅት እየተደረገ ነው ተብሏል::

ዕርምጃው እንደዲወሰድም ጉዳዩ ለሚመለከተው የንግድ ሚኒስቴር መረጃ የቀረበለት መሆኑም ታውቋል:: በአሁኑ ወቅት ከ20 በላይ የሚሆኑ የታሸጉ ውኃዎች አምራቾች እንዳሉ ይታወቃል:: የአርማታ ብረትና የኤሌክትሪክ ዕቃዎች አምራችና አስመጪዎች ቁጥር ከ500 በላይ እንደሚሆኑ ይገመታል::

አስገዳጅ ደረጃ የወጣላቸውን ምርቶችን ማስገደድ አልተቻለም

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 5 | እሑድ | ኅዳር 17 ቀን 2004 ክፍል-1

በኃያል ዓለማየሁ

ሜፖ በተባለው የሚድሮክ ኢትዮጵያ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት እየተገነባ የሚገኘው የአፍሪካ ኅብረት ሆቴል ፕሮጀክት፣ ለአራት ወራት ያህል ግንባታው በመቋረጡ ፕሮጀክቱን በእጅጉ ሊያጓትተው እንደሚችል የውስጥ ምንጮች ለሪፖርተር ገለጹ፡፡

የሆቴሉ ፕሮጀክት ከአፍሪካ ዋና ኅብረት መሥሪያ ቤት ፕሮጀክት ጋር ከሁለት ዓመት

በፊት እኩል የተጀመረ ቢሆንም፣ በቻይና ኮንተራክተሮች የተያዘው ባለ ረጅም ፎቅና ሰፊ ዘመናዊ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ግንባታ ተጠናቋል፡፡ በሆቴሉ ፕሮጀክት ግን የተወሰነው ፎቅ ከወጣ በኋላ ግንባታው በድጋሚ መስተጓጎሉን ምንጮች ጠቁመዋል፡፡

ቀደም ሲል ሚድሮክ ኮንስትራክሽን የአፍሪካ ኅብረት ሆቴልን ጨምሮ ሌሎች ፕሮጀክቶችን በማጓተቱ ፕሮጀክቶቹ ወደ ሜፖ የተላለፉ

ወደ ክፍል 1 ገጽ 43 ዞሯል

ፍርድ ቤት በወ/ሮ ሻዲያ መዝገብ ላይ ሥልጣን የለኝም አለበለምለም ፀጋይ

የፍትሕ ሚኒስቴር በወ/ሮ ሻዲያ ናዲምና በሼክ መሐመድ ሁሴን አል አሙዲ ላይ አቅርቦት በነበረው ብይን እንዲሰጥ የአፈጻጸም ማመልከቻ የቀረበለት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሰባተኛ ፍትሐ ብሔር ችሎት፣ ህዳር 8 ቀን 2004 ዓ.ም. በሰጠው ትዕዛዝ የወ/ሮ ሻዲያን ጉዳይ ለማየት ሥልጣን እንደሌለው ገለጸ::

ፍርድ ቤቱ የሰጠው ትዕዛዝ እንደሚያስረዳው፣ ሚኒስቴሩ እንዲከፈለው የጠየቀው በወ/ሮ ሻዲያ ስም የሚገኘው 2.5 ሚሊዮን ዶላር በጂቡቲ በሚገኝ ባንክ ውስጥ የተቀመጠ በመሆኑ ፍርድ ቤቱ የማዘዝ ሥልጣን የለውም::

የወ/ሮ ሻዲያ ጠበቃ አቶ ሰለሞን ተሾመ ኅዳር 8 ቀን 2003 ዓ.ም. ጽፈው ለፍርድ ቤቱ ባቀረቡት አስተያየት፣ በጂቡቲ የሚገኘው ገንዘብ ለሚኒስቴሩ ወጪ ሆኖ ቢከፈለው እንደማይቃወሙ ቢገልጹም፣ ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን መፈጸም የሚቻለው ጂቡቲ ባለ ፍርድ ቤት መሆኑን ለሚኒስቴሩ ገልጾ ጥያቄውን ውድቅ አድርጐታል::

ፍርድ ቤቱ ይህን ትዕዛዝ ቢሰጥም በሼክ አል አሙዲ ላይ ቀርቦ የነበረውን የ905,158.16 ዶላር የአፈጻጸም ጥያቄ በመቀበል፣ ሚኒስቴሩን በሼክ አል አሙዲ ስም የሚገኝ ንብረት ዝርዝር ወይም የባንክ ሒሣብ ቁጥር እንዲገልጽ አዞታል:: ፍርድ ቤቱ ይህን ያዘዘው የሼክ አል አሙዲ ጠበቃ አቶ መከተ ዳኘው አፈጻጸሙ መሠረት የተደረገበትን ውሳኔ በመቃወም በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት ይግባኝ በማለታቸው አፈጻጸሙ እንዲቆም ቢጠይቁም፣ ሰበር ችሎት አፈጻጸሙን ባለማገዱ ጥያቄው ተቀባይነት እንደሌለው ከገለጸ በኋላ ነው::

ፍርድ ቤቱ በ905,158.16 ዶላሩ ላይ ቀርቦ የነበረውን የወለድ ጥያቄ የሼክ አል አሙዲ ጠበቃ አቶ መከተ ዳኘው ኅዳር 8 ቀን 2004 ዓ.ም. ያቀረቡትን

የአፍሪካ ኅብረት ሆቴል ፕሮጀክት በድጋሚ ተስተጓጎለ

ወደ ክፍል 1 ገጽ 43 ዞሯልፎቶ በ

ሪፖርተ

ር/ናሆ

ም ተ

ስፋዬ

ግንባታው የተጠናቀቀው የአፍሪካ ኅብረት ሕንፃና ግንባታው እንደገና የተስተጓጎለው የአፍሪካ ኅብረት ሆቴል

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 6 | እሑድ |ኅዳር 17 ቀን 2004ክፍል-1

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 7 | እሑድ | ኅዳር 17 ቀን 2004 ክፍል-1

ፖ ለ ቲ ካ

በየማነ ናግሽ

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ መንግሥት በቅርቡ ይፋ ያደረገውን የከተማ መሬት በሊዝ ስለ መያዝ አዋጅ፣ የዜጎችን ሕገ መንግሥታዊ የመሬት ባለቤትነት የሚፃረርና መሬትን ሙሉ ለሙሉ በመንግሥት ቁጥጥር ሥር እንዲሆን የሚያደርግ ነው በማለት ተቃውሞውን ገለጸ:: የፌዴራል ሥርዓቱን በመፃረር ክልሎቹን ባለማማከር፣ በሁሉም ከተሞች ላይ ተግባራዊ የሚያደረግ በመሆኑም አግባብ ያልሆነ አዋጅ በማለት ኮንኖታል::

መድረክ ህዳር 13 ቀን 2004 ዓ.ም. ለመገናኛ ብዙኃን ባሰራጨው መግለጫ፣ አዲሱ የከተማ ቦታ በሊዝ የመያዝ በሚመለከት የወጣው አዋጅ ‹‹መሬት የሕዝብና የመንግሥት ነው›› የሚለው ሕገ መንግሥታዊ የዜጎች መብት በመጣስ የመሬት ይዞታን ሙሉ ለሙሉ ወደ መንግሥት የሚያዛውር መሆኑን ጠቅሶ፣ ዕርምጃውን በሕገወጥነት አውግዟል:: አዋጁ ቀደም ሲል የወጡ የፕሬስን፣ የሲቪክ ማኅበራትን፣ የፖለቲካ ፓርቲ ምዝገባንና ፀረ ሽብርን ከሚመለከቱ አወዛጋቢ አዋጆች እኩል አንድምታ ያለው መሆኑን በመረዳት፣ ሕጉም ሆነ አፈጻጸሙ የዜጎችን መሠረታዊ የመሬት ባለቤትነትን በመንጠቅ፣ ለኢሕአዴግ ካድሬዎች ሙስናና ዘረፋ አመቺ ሁኔታ የሚፈጥር ነው ብሎታል:: ‹‹አንድ የከተማ ቦታና ቤት ባለንብረት የሆነ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ቤቱን ለመሸጥ ከገዢው ፓርቲ የሚደራደረው በቤቱ ጣርያና ግድግዳ ላይ ብቻ እንደሚሆን የተደነገገበት ነው፤›› በማለት ሕጉ መሬት ላይ መሠረት የሌለው ቤት ያለ ማስመስሉን ጠቁሟል:: ‹‹ሰው መሬት ላይ ያፈራው ነገር የራሱ ነው›› የሚል በሕገ መንግሥቱ መስፈሩ የጠቆሙት የመድረክ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል አቶ ገብሩ አስራት፣ ይኼ አዋጅ ግን መሬትንና በመሬት ላይ የተፈራውን ነገር ለያይቶ ለማስቀመጥ እየሞከረ መሆኑን ለሪፖርተር ገልጸዋል::

የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅዱን ለማስፈጸም የዜጎችን ሀብትን የማፍራትና የማስተላለፍ መብቶች በሚፃረር ሁኔታ የተወጠነና በድህነትና በኑሮ ውድነት አረንቋ ውስጥ እየማቀቀ ካለው ሕዝብ በቢሊዮኖች የሚገመት ገንዘብ ለመሰብሰብ ያለመ መሆኑንም አቶ ገብሩ አስረድተዋል:: ከዚህ በተጨማሪም ዕርምጃው የዜጎች ሀብት ነጠቃ ከመሆኑም ባሻገር፤ ይህንን በሚመለከት የግል ተበዳዮች አቤቱታቸውን ወደ አስፈጻሚ የመንግሥት መሥርያ ቤት እንዲያቀርቡ ማስገደዱ፣ የዳኝነት አካላትን ሕገ መንግሥታዊ መብት የነጠቀ መሆኑን ፓርቲው ያስረዳል::

ከአዲሱ አዋጅ ጋር በተያያዘ የሚነሳ ቅሬታ መቅረብ

ያለበት ለአስፈጻሚ የመንግሥት መሥሪያ ቤት እንዲሆን የተደነገገ ሲሆን፣ መድረክ ሕገወጥ አካሄድ መሆኑን ያስረዳል:: እንደ ፓርቲው እምነት፣ ይኼ ዕርምጃ በፍትሐዊነት የመዳኘት ሥልጣን ከፍርድ ቤቶች ተነጥቆ ለከተማ ቦታና ለሊዝ ባሥልጣናት መስጠት ነው:: ‹‹ይህንን በማድረግም የኢሕአዴግ መንግሥት እስከዛሬ ይዞት የሚኖረውን ኪራይ ሰብሳቢነት ሕጋዊ ሽፋን ሰጥቶት ተጨማሪ ሕይወት መቀጠሉን ያሳያል፤›› ይላል የፓርቲው መግለጫ::

‹‹የፍትሕ አካላትን አቅም ማጎልበትና ነፃነታቸውን ማክበር ሲገባ ከዲሞክራሲያዊ አግባብ ውጪ ሥልጣን ይዘው ለሚቆዩ የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች የተበዳይን አቤቱታ አሳልፎ መስጠት አጥብቆ የሚቃወም መሆኑን የሚገልጸው መድረክ፣ የዳኞች አሿሿምና ስንብት ሒደት የራሱ መሠረታዊ ችግር ያለበት መሆኑን ደጋግሞ መግለጹ የሚታወስ ነው:: ይኼው ሳያንስ አዲሱ የሊዝ አዋጅ ደግሞ የፍርድ ቤቶችን ሥልጣን መንጠቅ የዜጎችን የፍትሕ መሻትና እምነት ከመሠረቱ የሚሸረሽር ነው፤›› ይላል::

መድረክ እንደሚለው፣ አዋጁ የከተማ ነዋሪ ዜጎችን

ሕገ መንግሥታዊ መብታቸውን ገፍፎ የመንግሥት ጭሰኛ የሚያደርግ ነው:: የመድረክ አመራር አባል አቶ ገብሩ አስራት በሰጡኑ ማብራሪያ፣ በ1994 ዓ.ም. የወጣው የሊዝ አዋጅን ጨምሮ ኢሕአዴግ ላለፉት 20 ዓመታት ሲከተለው የቆየው አካሄድ የዜጎችን መብት የሚፃረርና ለካድሬዎች ሙስናና ኪራይ ሰብሳቢነት የተመቸ መሆኑን የገለጹ ሲሆን፣ አሁን ደግሞ በባሰ መልኩ ሕገ መንግሥቱ ለዜጎች ያረጋገጠላቸው የንብረት ባለቤትነት መብትን በመናድ፣ ሙሉ ለሙሉ ለመንግሥት አሳልፎ የሚሰጥ መሆኑን ያስረዳሉ::

መድረክ በመሬት ባለቤትነት ላይ ያለውን ግልጽ ያልሆነ አቋም ተጠይቀው በሰጡት ምላሽ፣ መሬትን ለመሸጥና ለመለወጥ የሕዝብ ውሳኔ ያስፈልገዋል በሚል ድርጅታዊ አቋም ያልተያዘበት ቢሆንም፣ የመሬት ባለቤትነት ሙሉ ለሙሉ የሕዝብ መሆን እንዳለበት የፓርቲው እምነት መሆኑን

ተናግረዋል:: ይኼ አዋጅ ግን መሬት የሕዝብና የመንግሥት ነው የሚለው ሕገ መንግሥታዊ ድንጋጌ በመጣስ፣ የከተማ የመሬት ይዞታ በስልታዊ መንገድ የመንግሥት እንዲሆን ማድረጉን ይናገራሉ::

መድረክ የዚሁ አዋጅ ሌላ እንከን ያለው የከተማ ቦታ ባለቤትነት ዝውውር ጉዳይ በመደበኛ ፍትሐ ብሔር ሥነ ሥርዓት ሕግ መሠረት አለመመራቱና በሕጉም መሠረት መዳኘት አለመቻሉን ነው:: ይኼ ደግሞ አዋጁ ‹‹የአገር መሪው ወይም የእሱና የእርሱ ቡድን አባላት ድንጋጌ ከማድረግ ያለፈ ትርጉም አይኖረውም፤›› ብሎታል::

በተጨማሪም መድረክ የአዋጁ እንከኖች ብሎ ነቅሶ ካወጣቸው ሕገ መንግሥተዊ መጣረሶች መካከል፣ ሕጉ የፌዴራል መንግሥት አባላት የሆኑት ክልሎችን ሳያማክር በአገሪቱ መላ ከተሞች ተግባራዊ የሚደረግ መሆኑን ነው:: መድረክ እንደሚለው፣ በፌዴራል ሥርዓቱ ሕገ መንግሥታዊ ድንጋጌ መሠረት ክልሎች በግዛታቸው ላይ የራሳቸውን ሕግ የማውጣት መብት ያላቸው ቢሆንም፣ ይኼ አዋጅ ይህንን ድንጋጌ መፃረሩ፣ የክልሎች የራስ ገዝ አስተዳደር መርህን

የሚፃረር የኢሕአዴግን የእጅ አዙር አገዛዝ የሚያረጋግጥ ነው:: የመንግሥት ባለሥልጣናት በመንግሥት ሚዲያ በሰጡዋቸውት ማብራሪያዎች መሠረት፣ ነባር ይዞታዎች ወደ ሊዝ ሥርዓት የሚቀየሩበት ዝርዝር ጥናት በሚቀጥሉት አራት ዓመታት የሚደረግ መሆኑ ደግሞ፣ በሕዝብ መብት ላይ ያለ በቂ ቅድመ ጥናት ዕርምጃ እየተወሰደ መሆኑን መድረክ አንጸባርቋል::

አቶ ገብሩ የግሌ ነው በማለት በሰጡት አስተያየት፣ ኢሕአዴግ የመሬት አውታሮችን በሙሉ በመንግሥት ቁጥጥር ሥር ለማድረግ እየሞከረ ሲሆን፣ አዋጁ የመሬት ባለቤትነት ሕገ መንግሥታዊ መርህን አደጋ ላይ የጣለ ከመሆኑም ባሸገር፣ የገጠርንም መሬት በተመሳሳይ በመንግሥት ቁጥጥር ሥር ለማድረግ ያለመ ፖለቲካዊ አንድምታ እንዳለው አብራርተዋል::

በተመሳሳይ መድረክ የመንግሥት ቤቶች ኪራይን አስመልክቶ መንግሥት የወሰደውን ዕርምጃም ከፉኛ ተችቷል:: በገጠር ያለውን የኑሮ ጫናን መቋቋም አቅቶት ወደ ከተማ እየፈለሰ ያለው የገጠር ሕዝብ ቁጥር ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሶ፣ በከተሞች የተፈጠረውን የቤት እጥረት ግምት ውስጥ ያስገባል:: እንዲሁም በየከተማው ጉራንጉር ትናንሽ ክፍሎችን እየተከራዩ ጥቃቅን የንግድ እንቅስቃሴዎችን የሚያካሂዱ ዜጎች ቁጥርም ከፍተኛ እንደነበር ይገልጻል:: ባለፉት 20 ዓመታት መንግሥት እነዚህን ሰዎች በያሉበት አድራሻ የንግድ ፈቃድ እየሰጣቸውና ባለጉዳዩን በኢፍትሐዊ ተመን እያስለቀሰም ጭምር ግብር እየሰበሰበ መቆየቱን ያስረዳል:: መድረክ ይኼ አሠራር ለሙሰኛ የመንግሥት ባለሥልጣናትና ካድሬዎች መበልፀጊያ አመቺ እንዲሆን ‹‹ሕገወጥ የተከራይ አከራዮች›› በማለት ያወጣው መመርያም አግባብነት እንደሌለው ነው የሚያትተው:: የሕግ ጥሰቱ ለሁለት አሠርት ዓመታት የቆየ ቢሆንም፣ አሁን የተከሰተ በማስመሰል የዜጎችን ኑሮ ለማተራመስ መነሳሳቱን መድረክ ኢሕአዴግን ይኮንናል::

የመድረክ ሰዎች እንደሚሉት ቀድሞውንም ቢሆን በመንግሥት ይዞታ ሥር ያሉት የንግድ ቤቶች ወደግል ይዞታ መዛወር ነበረባቸው:: ሕገወጥ የተከራይ አከራይ ክስተትም ገና ከጅምሩ በመልካም አስተዳደር ዕርምጃ መታረም የነበረበት እንደሆነ ያምናል:: ‹‹ያለመታደል ሆነና የኢሕአዴግ ሥርዓት ለሕገወጥነት በሮቹን ሁሉ ክፍት አድርጎ በአገርና ሕዝብ ጥቅሞች ላይ ከፍተኛ ጉዳቶች ደርሰው ካበቁ በኋላ፣ ሕጋዊ ዕርምጃዎችን ስለመውሰድ አደንቋሪ ፕሮፓጋንዳዎችን የሚያሳይበት ነው፤›› በማለት ተችቷል::

በተጨማሪም ዜጎች የመጠለያ ችግራቸውን ለመቅረፍ መፍጨርጨር ሲያሳዩ ዝም ብሎ ቆይቶ ግንባታዎቹ ከተጠናቀቁ በኋላ ‹‹የጨረቃ ቤት›› በማለት የሕዝብ ንብረት ያለአንዳች ካሣ ሲወስድና ሲያፈርስም መመልከቱን መድረክ ይገልጻል:: በመሆኑም ፓርቲው እንደሚለው፣ እነዚህ ሕገወጥ ግንባታዎችም ሆኑ ሕገወጥ የማፍረስ እንቅስቃሴዎች በመንግሥት ካድሬዎች የኪራይ ሰብሳቢነትና ሙሰኝነት ባህሪ የተፈጸሙ በመሆናቸው፣ በገለልተኛ አካላትና ባለሙያዎች መጣራት እንዲደረግባቸው ይጠይቃል:: ስለዚህም ችግሮቹ በሙሉ በመልካም አስተዳደር እጦት የተፈጸሙ በመሆናቸው ነፃ የኅብረተሰብ ውይይት እንዲደረግባቸው አሳስቧል::

መድረክ የገጠር ነዋሪ አርሶ አደር የይዞታ ባለቤት መሆን እንዳለበትና የከተማ ነዋሪውም የመኖርያ ቤት የሠራበት መሬት ባለቤትነት እንዲረጋገጥ እታገላለሁ ያለ ሲሆን፣ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ መብቱን የሚጋፉ አዋጆችንና ድርጊቶችን ለመቃወም በሚደረገው እንቅስቃሴ ተሳታፊ እንዲሆን ጥሪ አድርጓል::

‹‹የከተማ ሊዝ አዋጅ ለኢሕአዴግ ካድሬዎች ሙስና አመቺ ሁኔታ የሚፈጥር ነው›› መድረክ

ዕርምጃው የዜጎች ሀብት ነጠቃ ከመሆኑም ባሻገር፤ ይህንን በሚመለከት የግል ተበዳዮች አቤቱታቸውን ወደ አስፈጻሚ የመንግሥት መሥርያ

ቤት እንዲያቀርቡ ማስገደዱ፣ የዳኝነት አካላትን ሕገ መንግሥታዊ መብት የነጠቀ መሆኑን ፓርቲው ያስረዳል::

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 8 | እሑድ |ኅዳር 17 ቀን 2004ክፍል-1

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 9 | እሑድ | ኅዳር 17 ቀን 2004 ክፍል-1

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 10 | እሑድ |ኅዳር 17 ቀን 2004ክፍል-1

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 11 | እሑድ | ኅዳር 17 ቀን 2004 ክፍል-1

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 12 | እሑድ |ኅዳር 17 ቀን 2004ክፍል-1

በናታን ዳዊት

የአቅም ጉዳይ ሆነና በአገር ደረጃ አምርተን ወደ ውጭ ከምንልከው ምርት ይበልጥ ከውጭ ገዝተን የምናስገባቸው ምርቶች በመጠን ሆነ በዋጋ በእጅግ ይበልጣሉ::

የአገራችንን የወጪና የገቢ ምርት ሚዛን የሚመለከቱ መረጃዎች የሚነግሩን ይህንኑ ነው::

በጥቅሉ በግልም ሆነ በጋራ የምንጠቀምባቸው ማንኛውም ዓይነት ምርት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ከውጭ ከሚመጡ ምርቶች ጋር የተሳሰሩ መሆኑን እንረዳለን::

ትንሽ ከምንላት መርፌ ጀምሮ ትልልቅ ማሽነሪዎች ድረስ ያሉ ዕቃዎች በሙሉ የሚመጡት ከውጭ ነው:: ይህም በውጭ ምርቶች ጥገኞች መሆናችንን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል:: ከውጭ እያመጣን ከምንጠቀምባቸው ዕቃዎች እዚህ በቀላሉ ሊመረቱ የሚችሉ ቢኖሩ እንኳን በስም የውጭ ዕቃ ተሽቀዳድሞ የመግዛቱ አባዜ አለቀቀንም::

እዚህ ሊመረቱ የሚችሉ ምርቶችን በማሳደግ በአገር ውስጥ ምርቶችን ለምን አንጠቀምም? የሚለው ጉዳይ ይቆየንና፣ በገፍ እያስገባን ስላለው የውጭ ምርቶች እንነጋገር::

በዓይነትም በመጠንም እየጨመረ የመጣው የውጭ ምርት ከዚህም በኋላ ቢሆን እየጨመረ

ቅድሚያ ለጥራትስለመምጣቱ አይጠረጠርም:: በተለይ ከአገሪቱ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ጋር ተሳስሮ ሊያስፈልጉ የሚችሉ ምርቶች የግድ ከውጭ መግባት አለባቸውና በገቢና በወጪ ገቢያችን መካከል ለዓመታት የዘለቀውን ሰፊ ልዩነት ለማጥበብ ብዙ መድከም፣ ብዙ መሥራትና ረዘም ያለ ዓመታት መጠበቅም ግድ ይለናል::

ከውጭ የምናመጣው ምርት በዋጋ ደረጃ ከፍ እያለ በመምጣቱም ወጪያችንም በዚያው ልክ እየጨመረ በመሄዱ፣ ለትንሹም ለትልቁም የውጪ ምርት በቢሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር እያፈሰስን እንገኛለን:: የውጭ ምንዛሪው በምንም ዓይነት መንገድ ቢመጣም፣ ይህ ሁሉ ዕቃ ግን ጥራቱን የጠበቀና ምርቱ ለሚሰጠው አገልግሎት የሚመጥን ዋጋ እየከፈልንበት ነው ማለት አይቻልም::

በርካታ ወደ አገር ውስጥ የሚገቡ ምርቶች የጥራት ደረጃቸው እጅግ ደካማ ነው:: ዛሬ ተገዝተው ቀናት እንኳን ሳይቆዩ የሚበላሹ ምርቶች ገበያውን ተቆጣጥረውታል:: በስመ ቅናሽ ዋጋ የሚቸበቸው የውጭ ምርቶች የአገልግሎት ዘመናቸው

እንዲያጥር ተደርጎ እየተመረቱ መሆኑም ትልቅ ችግር እየሆነ መጥቷል:: በርካታ ምርቶች ቢያንስ ያገለግላሉ ተብሎ ከሚቀመጥላቸው የጊዜ ገደብ ላይ ሳይደርሱ ሲበላሹ ማየት የተለመደ ነው:: አንድ መገልገያ ዕቃ ሊያሟላ የሚገባውን ግብዓት ሳያካትት እንዲመረትና ወደ አገር ውስጥ እንዲገባ የሚደረጉ አሠራር ከተለመደ ሰነባብቷል::

ምርጥ ነው ተብሎ በአማረ ቀለማት ተጋጊጦ የገጠምነው የበር እጀታ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ እጃችን ላይ ቅንጥስ ሲል፤ ለዓመታት እጠቀምበታለሁ ብለው የተገዙት የተለያዩ የኤሌክትሪክ ማከፋፈያዎች በሳምንቱ ቀልጦ የማግኘቱ ጉዳይ ብዙዎቻችንን ያጋጠመ ጉዳይ ስለመሆኑ አይጠረጠርም::

ትላልቅ በምንላቸው ዕቃዎች ላይም ተመሳሳይ ክስተት ያጋጥመናል:: ይህ ሁሉ እንግዲህ በመከራ በሰበሰብነው የውጭ ምንዛሪ ተገዝተው የሚገቡ ዕቃዎች ናቸው:: የጥራት ደረጃቸው የዘቀጠ ምርቶች ዛሬ ገዝተናቸው የሚፈለገውን ያህል አገልግሎት ሳይሰጡና ሲበላሹ የግድ መተካት ስላለብንም ችግር ደጋግሞ ይገጥመናል:: መደጋገሙ ደግሞ ጥራታቸውን ያልጠበቁ ምርቶች በግል ከሚያስከትሉብን ወጪ ባሻገር በአገር ደረጃ የሚያስከትሉት ጥፋት እጅጉን የገዘፈ መሆኑን ያሳየናል::

በመሆኑም ከውጭ የምናስገባቸው ምርቶች የጥራት ደረጃ የምዘና ጉዳይ በብርቱ ሊታሰብበት ይገባል:: በዚህ ሥራ ኃላፊነት የተሰጠውም አካል ቢሆን አስገዳጅ ፍተሻ የሚያደርግባቸውን አንዳንድ ምርቶች በቅጡ እየፈተሸና ዕርምጃ እንዲወሰድባቸው እያደረገ ያለመሆኑ፣ የጥራት ጉዳይ አሳሳቢነቱ እየጨመረ እንደመጣ ያመላክተናል:: በምናስገባቸው የምርት መጠን ልክ ጎን ለጎን ጥራቱ ስለመጠበቁ ማረጋገጫ ሊሰጥ የሚችለው አካል የሚታይ ዕርምጃ ይወሰድ::

በውድነህ ዘነበ

በኢትዮጵያ የግብርና አብዮት ለማካሄድ ከሚያስፈልጉ በርካታ ግብዓቶች መካከል ምርጥ ዘር አንዱና ዋነኛው ነው:: የዚህ የምርጥ ዘር ግብዓት በሚገባው መልኩ አለመሟላት ለበርካታ አርሶ አደሮች ራስ

ምታት ሆኗል:: ምርጥ ዘርን በገንዘብ እጥረት እንዲሁም በአቅርቦት ችግር ምክንያት ማግኘት ካልቻሉ አርሶ አደሮች መካከል አቶ ጉርሜሳ አዳሙና አቶ ጴጥሮስ ማትዮስ ተጠቃሾች ናቸው::

አቶ ጉርሜሳ በምዕራብ ኦሮሚያ ዞን ደንቢ ዲማ ቀበሌ ነዋሪ ናቸው:: አርሶ አደር ጉርሜሳ ከባለቤታቸውና ከሦስት ልጆቻቸው ጋር በዚህ ቀበሌ ውስጥ በሚገኝ አንድ ሔክታር መሬት ኑሯቸውን ይገፋሉ:: የ46 ዓመቱ ጎልማሳ ከሦስት ዓመት በፊት ነው ትዳር መሥርተው አባወራ የሆኑት:: ይሁንና ግን በቂ ገንዘብ ስለሌላቸው ለእርሻ ሥራ የሚሆን በሬ የላቸውም:: በገንዘብ እጥረት ምክንያት ምርጥ ዘርም ሆነ ማዳበርያ በተገቢው መንገድ ማግኘት አልቻሉም::

የሚያርሱበት በሬ ባለመኖሩ ከሦስት ዓመት በፊት ወደ አካባቢው የመጣውን ራውንድአፕ የተሰኘ ኬሚካል መሬት ለማረስ እንደሚጠቀሙ አቶ ጉርሜሳ ለሪፖርተር ገልጸዋል:: ራውንድአፕ የተሰኘው ኬሚካል የአሜሪካ ኩባንያ በሆነው ግዙፉ የእርሻ ኬሚካሎች አምራች በሆነው ሞንሳቶ ይመረታል:: የዚህ ኬሚካል በኢትዮጵያ ብቸኛ ወኪል የሆነው መኩቡ ኢንተርፕራይዝ ሲሆን፣ ኩባንያው ለዓመታት ባደረገው ከፍተኛ ጥረት በግብርና ሚኒስቴር ተቀባይነት አግኝቶ በኤክስቴንሽን ፕሮግራም እንዲታቀፍ ተደርጓል::

ራውንድአፕ መሬት ለእርሻ በሚፈለግበት ወቅት በውኃ ተበጥብጦ ይረጫል:: ርጭቱ እንደተካሄደ በመሬቱ ላይ ያለ አረንጓዴ ዕፅዋት ሁሉ ወደ ብስባሽነት ብሎም መሬቱ እንደታረሰ ሁሉ ያኮፎኩፋል:: ርጭት በተካሄደበት መሬት ላይ የሚዘራው እህል ወፎች እንዳይበሉት የተወሰነ ይጫጫርና ይዘራል:: ይህ አሠራር በአካባቢው ተቆርቋሪዎች ሙሉ በሙሉ ዕውቅና ባይቸረውም፣ የግብርና ባለሙያዎች ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ይገልጻሉ::

ይሁንና አርሶ አደር ጉርሜሳ ግማሽ ሔክታር መሬት ላይ ለዘሩት ጤፍ የሚበቃ ራውንድአፕ መግዛት ባለመቻሉ መሬቱ በደንብ እንዳለማ ይገልጻል:: በተቀረው ግማሽ ሔክታር መሬት ላይም በወቅቱ ምርጥ ዘር ባለማግኘታቸው የከረመ በቆሎ ለመዝራት ተገደዋል:: ሪፖርተር በስፍራው ተገኝቶ እንዳረጋገጠው፣ ከኢትዮጵያ ምርጥ ዘር ድርጅት ዘር የገዙ ገበሬዎችና አርሶ አደር ጉርሜሳ የዘሩት በቆሎ በአንድ ዓይነት ደረጃ ላይ አይገኝም:: የሌሎች ገበሬዎች የበቆሎ ማሳ ትላልቅ አገዳና ከሁለትና ከሦስት በላይ የበቆሎ እሸት ይዘው ሲቆሙ፣ የአቶ ጉርሜሳ ማሳ የጫጨና የቀነጨረ በቆሎ ከሁለት ያነሰ ትናንሽ የበቆሎ እሸት ከመያዝ አልዳነም::

‹‹ገንዘብ ስለሌለኝ ባለፈው ዓመት ከዘራሁት በቆሎ የተወሰነውን ለዘር ይዤ ነው የዘራሁት:: አገዳው ቀጫጫ በመሆኑ፣ ወቅቱን ያልጠበቀው የጥቅምት ዝናብ ጉድቶታል፤›› ሲሉ አቶ ጉርሜሳ የጠፋ ማሳቸውን በሐዘን እየተመለከቱ

የአርሶ አደሮች የምርጥ ዘር እጦትና የመንግሥት የዘር አብዮት

ለሪፖርተር ገልጸዋል::በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን የሚገኘው ባኮ ወረዳ

የበቆሎ አገር ነው:: በወረዳው ከበቆሎ በተጨማሪ ጤፍ፣ ማሽላ፣ ስንዴና በርበሬ በስፋት ይመረታል:: የወረዳው ግብርና ጽሕፈት ቤት ተጠባባባቂ ኃላፊ አቶ ሞቱማ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ከሌሎች ጊዜያቶች በተሻለ በ2003 ዓ.ም. የምርት ዘመን ዋነኛ የግብርና ግብዓቶች የሆኑት ምርጥ ዘርና ማዳበርያ በወቅቱ ነው ወደ አካባቢው የመጡት:: ይህንንም ምርት ያቀረቡት የኢትዮጵያ ምርጥ ዘር ድርጅትና የኦሮሚያ ምርጥ ዘር ድርጅት ናቸው:: ምንም ዓይነት እጥረት አለመኖሩንም ይገልጻሉ::

ተጠባባቂ ኃላፊው ጨምረው እንደገለጹት፣ ከካቻምናም የከረመ ዘር በመኖሩ ለገበሬው በወቅቱና በበቂ ደረጃ ምርጥ ዘር ደርሷል:: ይሁንና አቶ ጉርሜሳን የመሳሰሉ በርካታ አርሶ አደሮች በገንዘብ እጥረት ምርጥ ዘሩን ማግኘት አልቻሉም:: ባለማግኝታቸውም በተደጋጋሚ በመታረሱ ምክንያት

የተዳከመው የእርሻ መሬት አስፈላጊውን ግብዓት ባለማግኘቱ በሔክታር የሚሰጠው ምርት ቀንሷል::

አርሶ አደሮች ምርጥ ዘርና ሌሎች የግብርና ግብዓቶችን በአግባቡ ካልተጠቀሙ የማሳቸው ምርት ከመቀነሱ በተጨማሪ በሚፈጠረው ወቅታዊ ያልሆነ የአየር ለውጥ ለግሽበት ይዳረጋል:: ‹‹በአንድ ሔክታር መሬት ላይ በቆሎና ጤፍ ለማምረት ራውንድአፕ ኬሚካልን በብድር ነው የምገዛው:: ዘንድሮ ብድር ስላልተሰጠኝ በጥሬ ገንዘብ ገዝቼ ነው የዘራሁት፤›› የሚሉት አቶ ጉርሜሳ፣ የተዘራው ጤፍ ባልተጠበቀው ዝናብ ምክንያት ረግፏል:: ‹‹ዝናብ ከመዝነቡም በላይ ጤፍ ሲነሳ ሊበቅል ይገባው የነበረው ሳር ጤፉን ውጦታል:: በቆሎውም አቅም አጥቶ ተሰባብሮ መሬት በልቶታል፤›› ሲሉ አቶ ጉርሜሳ አክለው ሐዘን በተሞላበት ስሜት ይገልጻሉ::

‹‹ምናልባት የጤፍና የበቆሎ ምርጥ ዘሮችን ብጠቀም ካልተጠበቀው ዝናብ ከሚያደርሰው ጥፋት የተረፈ ምርት

ላገኝ እችል ነበር፤›› ሲሉ አቶ ጉርሜሳ ይገልጻሉ:: አርሶ አደር ጴጥሮስ ግን በገንዘብ እጥረት ሳይሆን የሚፈልጉትን መጠን ምርጥ ዘር ባለማግኘታቸው የሚፈልጉትን እህል መዝራት አልቻሉም:: አቶ ጴጥሮስ በደቡቡ ክልል በዳውሮ ዞን ኢስራ ወረዳ ነዋሪ ናቸው:: አርሶ አደር ጴጥሮስ ከሁለት ሚስቶቻቸው ስምንት ልጆች ያፈሩ ጠንካራ አርሶ አደር ሲሆኑ፣ ከአንድ ሔክታር ከፍ በሚል የእርሻ መሬታቸው የግብርና ሥራዎችን በማካሄድ ይተዳደራሉ::

አቶ ጴጥሮስ በሲሶ መሬታቸው እንሰት ያለሙ ሲሆን፣ ሲሶውን ለከብቶች ግጦሽ እንዲሆን ባዶውን ትተውታል:: የተቀረው መሬት ላይ ጤፍ ለመዝራት ቦታውን ቢያዘጋጁም፣ ምርጥ ዘር ባለማግኘታቸው ሳያለሙ የምርት ዘመኑን አሳልፈዋል:: አቶ ጴጥሮስ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የጤፍ ዘር ከገበያ ገዝተው ቢዘሩ የተሻለ ምርት እንደማያገኙ ስለሚያውቁ ጤፍ ከመዝራት ተቆጥበዋል:: መሬቱ ጦም እንዳያድር በሚል ባቄላ እንደዘሩም ገልጸዋል::

በኢትዮጵያ ሁሉም አርሶ አደሮች ምርጥ ዘሮችን ይጠቀሙ ቢባል ሰባት ሚሊዮን ኩንታል እንደሚያስፈልግ የግብርና ሚኒስቴር መረጃዎች ይጠቁማሉ:: ይሁንና ከተመሠረተ 30 ዓመታትን ያስቆጠረው የኢትዮጵያ ምርጥ ዘር ድርጅት ለአርሶ አደሮች በማቅረብ ላይ የሚገኘው ግን የዚህን ቁጥር አሥር በመቶ ያህል ነው::

በ1970ዎቹ ላይ የተመሠረተው የኢትዮጵያ ምርጥ ዘር ድርጅት በ2003 ዓ.ም. የምርት ዘመን 20,560 ሔክታር መሬት በዘር ሸፍኗል:: ከዚህ መሬት ውስጥ የድርጅቱ ይዞታ የሆነው ስድስት ሺሕ ሔክታር ነው:: የተቀረው አርሶ አደሮችና ባለሀብቶች በኮንትራት የሚያለሙት ነው::

አርሶ አደሮች 5,369 ሔክታር መሬት አልምተው ምርቱን ለድርጅቱ ይሸጣሉ:: የባለሀብቶች የኮንትራት እርሻ 5,774 ሔክታር ስፋት አለው:: የተቀረው መሬት ደግሞ ለሠርቶ ማሳያ የሚውል ነው:: በአጠቃላይ 20,560 ሔክታር መሬት በምርት ዘመኑ በዘር የተሸፈነ ሲሆን፣ ከተሸፈነው መሬት 442,372 ኩንታል ምርት ይገኛል ተብሎ ታቅዷል::

ይህ ምርት በራሱ በአገር ደረጃ የሚፈለገውን ሰባት ሚሊዮን ኩንታል ለማሟላት አነስተኛ ቢሆንም፣ ድርጅቱ ሁሉንም መጠንም ቢሆን ለአርሶ አደሮች አያቀርብም:: የኢትዮጵያ ምርጥ ዘር ድርጅት የዘር ማምረትና ማዘጋጀት ወሳኝ የሥራ ሒደት አስተባባሪ አቶ ፈለቀ ገዛኸኝ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ከእርሻ ምርምር ጣቢያዎች በምርምር የሚገኘው የመጀመርያው ግኝት ቅድመ መሥራች ዘር በማሳ እንዲበዛ ይደረጋል:: የተባዛው መሥራች ዘር በድጋሚ ተዘርቶ የተመሰከረለት ዘር ይሆናል:: ለአርሶ አደሩ የሚከፋፈለውም ይህው የተመሰከረለት ዘር ነው::

የኢትዮጵያ ምርጥ ዘር ድርጅት የተመሰከረለት የሚባለውን ለአርሶ አደሮች የሚያካፍለውን ዘር የሚያለማው በሦስት ሺሕ ሔክታር መሬት ላይ ብቻ ነው:: በዚህ መሠረትም በአጠቃላይ በምርት ዘመኑ ይመረታል ተብሎ ከሚገመተው 442,372 ኩንታል ምርት ውስጥ ለአርሶ አደሮች ይከፋፈላል ተብሎ የሚጠበቀው 354,981 ኩንታል ምርጥ ዘር ብቻ ነው::

በምርጥ ዘመኑም ያልተጠበቀ ዝናብ በጥቅምት ወር በመከሰቱ የተወሰነ የምርት መቀነስና የቀለም ለውጥ (ጥራት) ችግር ሊኖር እንደሚችል አቶ ፈለቀ ገልጸዋል:: የኢትዮጵያ ምርጥ ዘር ድርጅት እርሻዎች የሚገኙት በጎንዴ ጦያ፣ አርዳይታ፣ ሻሎ፣ ጊቤ፣ ቻግኒና ቁንጽላ አካባቢዎች ነው:: ከነዚህ ማሳዎች ውስጥ የጊቤንና የቻግኒ እርሻ መሬቶችን ያገኘው በቅርቡ ነው:: ድርጅቱ ባሉት በነዚህ ስድስት እርሻ ጣቢያዎች

አርሶ አደር አቶ ጉርሜሳ አዳሙ

ፎቶ

በሪ

ፖር

ተር

/ ታ

ምራ

ት ጌ

ታቸ

ወደ ክፍል-1 ገጽ 13 ዞሯል

ከክፍል-1 ገጽ 12 የዞረ

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 13 | እሑድ | ኅዳር 17 ቀን 2004 ክፍል-1

በብርሃኑ ፈቃደ

ላለፉት አምስት ቀናት እዚህ አዲስ አበባ ቆይታ ያደረጉ የኔዘርላድስ ኩባንያዎች ልዑካን በኢትዮጵያ ለገበያ የሚውሉ የግብርና ምርት ዘሮችን ለማምረት የሚያስችላቸውን እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ቆይተዋል::

ባለፈው ረቡዕ ከኢትዮጵያ ዘር አቅራቢዎችና አስመጪዎች ጋር አብረው ስለሚሠሩበት መንገድ ተነጋግረው ነበር::

የኢትዮጵያ ዘር አምራቾች ማኅበር ፕሬዚዳንት ከአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ጋር ባዘጋጀው የንግድ ግንኙነት ውይይት ላይ ደቾቹ ይስማማናል ከሚሉት ኢትዮጵያዊ ኩባንያ ጋር ለመጣመርና አብሮ ለመሥራት ውይይት አድርገዋል::

ዘጠኙን የኔዘርላድስ ኩባንያዎች ወክሎ የመጣው የፕላንተም ማኅበር ዳይሬክተር ዶክተር ሎቫርስ ኔይልስ ለሪፖርተር ሲናገሩ፣ ልዑካኑ ለገበያ ለሚውሉ ሰብሎች፣ አትክልትና ፍራፍሬዎች ዘር ማምረት እንደሚችሉ ከግብርና ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ወንድይራድ ማንደፍሮ ጋር ባካሄዱት ውይይት እንደተገለጸላቸው አስታውቀዋል::

ልዑካኑ የኢትዮጵያ አየር ንብረትና ፀባይ ለዘር ምርት ተስማሚ ሆኖ እንዳገኙት ተናግረዋል:: በቻይናና በሌሎች አገሮች የሚያከናውኑትን የዘር ምርት ወደ ኢትዮጵያ የሚያዛውሩበት ዕድል ካለም ያንን ለማድረግ እንደሚሞክሩ ዶክተር ኔይልስ ገልጸዋል::

የኢትዮጵያ ዘር አምራቾች ማኅበር ፕሬዚዳንት አቶ መላኩ አድማሱ ለሪፖርተር እንዳስታወቁት፣ ከዚህ በፊት ገበሬ ዘር ከመንግሥት ድርጅቶች ብቻ ያገኝ የነበረ ቢሆንም፣ ለግል ድርጅቶችም ዘር የማምረት ዕድል በመሰጠቱ ለገበሬው አቅራቢ የሚሆኑበትን መንገድ ለማበርከት ማኅበሩን መሥርተዋል::

የኔዘርላድስ ባለሀብቶች ከኢትዮጵያውያኑ ጋር

ኔዘርላንዳውያን ዘር ለማምረት የሚጣመራቸው ኩባንያ እየፈለጉ ነው

ቢጣመሩ የቴክኖሎጂና በዕውቀት ያካበቱትን ልምድ መጋራት እንደሚያስችል አቶ መላኩ ተናግረዋል::

በሔክታር እስከ 300 ኩንታል ምርት ሊያስገኝ የሚችል የዘር ቴክኖሎጂ እንዳላቸው ይገልጻሉ:: በተለይ በድንች ምርት ረገድ ሩስያ ሳትቀር የደቾቹ ቴክኖሎጂ ውጤት በሆነው ዘር እየተጠቀሙ የድንች ምርታቸው ከፍተኛ እንደሆነላቸው ዶክተር ኔይልስ ይናገራሉ::

አቶ መላኩም ይህንኑ ተናግረው፣ ምርቱ እዚህ ቢጀመር ለገበሬው ከሚያስገኘው ጠቀሜታ በተጨማሪ ለሥራ ዕድል ማስገኘቱና የውጭ ምንዛሪ ማዳኑ ተጨማሪ ጥቅም እንደሆነም አብራርተዋል::

ሆኖም ለአንድ የድንች ዘር እስከ 7,000 ዩሮ ሊጠይቅ እንደሚችል ኩባንያዎቹ ራሳቸውን ለኢትዮጵያውያኑ ሲያስተዋውቁ በነበረበት ወቅት ለመረዳት ተችሏል:: ይህንኑ በተመለከተ ያነጋገርናቸው ዶክተር ኔይልስ፣ ይህ የአውሮፓውያን ገበሬዎች የመግዛት አቅም ነው ብለዋል:: በዚህ ፕሪምየም ዋጋ እዚህ ይሸጣል ማለት እንዳልሆነና ነገር ግን እንዲህ ባለው ዋጋ ገዝቶ ማምረት የሚፈልግ ኩባንያ ሊኖር እንደሚችልም አስታውቀዋል::

‹‹በነባር ዝርያዎች የትም ልንደርስ አልቻልንም:: የሚፈለገውን ምርት ሊሰጡን አልቻሉም:: ለምሳሌ በቆሎን ብንወስድ፣ በሔክታር ከ18 ኩንታል በታች ነው የሚሰጠው፤›› ያሉት አቶ መላኩ፣ ያለ ዘረ መል

ምህንድስና አንድን ዝርያ ከሌላው በማዳቀል እስከ 50 ኩንታል የበቆሎ ምርት በሔክታር ማግኘት እንደተቻለ ይናገራሉ:: ይህን ሁሉ ምርት ለማግኘት ግን ወቅት ጠብቆ መዝራት፣ ማዳበሪያ መጠቀም፣ ጸረ ተባይና የአረም ለቀማውን ሁሉ ከዘር ጋር አብረው የሚቀርቡ ሥራዎች እንደሆኑም ተናግረዋል::

በኢትዮጵያ እስከ 90 በመቶ የሚደርሰው የዘር አቅርቦት ገበሬው እርስ በርሱ በሚያደርጋቸው ልውውጦችና በባህላዊ መንገድ በሚካሄዱ የዘር ግብይቶች ገበሬው የሚያገኛቸው ናቸው:: መንግሥት ገበሬው በዚህ መልኩ ለሚያካሂዳቸው የዘር ልውውጦች ሙሉ የባለቤትነት መብቱን እንደሚያረጋግጥ እንደተገለጸላቸውና ትኩረታቸውንም በገበያ ተኮር ሰብሎች፣ አትክልቶችና ፍራፍሬዎች ላይ እንደሚያደርጉ ደቾቹን የወከሉት ዶክተር ኔይልስ ገልጸዋል::

እነዚህ የኔዘርላንድስ ኩባንያዎች በአብዛኛው ዘር አምርተው ለውጭ ኩባንያዎችና የግብርና ውጤቶችን ለሚያመርቱ የሚሸጡ ናቸው:: ተሳክቶላቸው እዚህ ቢያመርቱ እንኳ አብዛኛው የዘር ምርት ለውጭ ገበያ እንደሚቀርብ የሚጠበቅ ነው::

ፕላንተም 400 የኔዘርላንድስ ኩባንያዎችን በአባልነት ያቀፈ ማኅበር ነው:: በርካቶቹ ዕፅዋትን በማዳቀል፣ በቲሹ ካልቸር፣ በዘር ንግድ ሥራ የተሰማሩ ናቸው:: በዓመት ከ2.2 ቢሊዮን ዮሮ ያላነሰ ገንዘብ የሚያንቀሳቅሱት የፕላንተም አባላት በብዛት ወደ ፈረንሳይና አሜሪካ ምርቶቻቸውን ይልካሉ::

በሌላ በኩል በቅርቡ የተቋቋመው የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲ፣ በአምስት ዓመት ውስጥ የሚያደርጋቸውን እንቅስቃሴዎች የሚያመላክት ሰነድ እያዘጋጀ እንደሚገኝ አስታውቋል:: በራዕ ሰነዱም የኢትዮጵያን ብዙሃ ሕይወት በማስጠበቅ፣ የዘር ምርት ሥርዓት እንደሚዘረጋ ለማወቅ ተችሏል::

የበቆሎ፣ የጤፍ፣ የማሽላ፣ የዳጉሳ፣ የስንዴ፣ የገብስ፣ የሩዝ፣ የቦሎቄ፣ የአኩሪ አተር፣ የባቄላ፣ የምስር፣ የሽምብራ፣ የተልባ፣ የጐመንዘር፣ የሰሊጥ፣ የለውዝ በተጨማሪም የከብቶች መኖና የጥጥ ምርጥ ዘሮችን ከእርሻ ምርምር ጣቢያዎች እየተረከበ ያባዛል::

ይሁንና የአቅም ውስንነት ቢኖራቸውም በቅርብ ሦስት ክልሎች አማራ፣ ኦሮሚያና ደቡብ ክልሎች ምርጥ ዘር ድርጅቶችን አቋቁመው እየተንቀሳቀሱ ነው:: ለእነዚህም የክልል ምርጥ ዘር ድርጅቶች የቴክኒክና የተለያዩ ድጋፎችን በመስጠት ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ምርጥ ዘር ድርጅት ነው::

የግብርና ባለሙያዎች እንደሚገልጹት፣ በኢትዮጵያ ምርጥ ዘሮችን የማቅረብ ሥራ በችግሮች የተሞላ ነው:: ምክንያቱንም ባለሙያዎቹ ሲገልጹ፣ የግብርና ምርምር ጣቢያዎች የአንድ ዘር ቅድመ ዘርን ተመራምሮ ለማውጣት ረዥም ጊዜ ይፈጅባቸዋል:: ከዚህ በተጨማሪም ኢትዮጵያ ሰፊና የተለያዩ የአግሮ ኢኮሎጂ ቀጠናዎች ያሏት እንደመሆኑ፣ በአንዱ አካባቢ ምርጥ የተባለ ዘር በሌላ አካባቢ ምንም ጥቅም የሌለው ዘር ሊሆን ይችላል:: በዚህ ላይ የግብርና ምርምር ተቋማትም ሆኑ የምርጥ ዘር ድርጅቶች የአቅም ውስንነት ያለባቸው በመሆኑ አስፈላጊውን ዘር በበቂና በሥርዓቱ ለአርሶ አደሩ በማቅረብ በኩል ችግር አለባቸው::

የግብርና ምርትን ከእጥፍ በላይ የማሳደግ ዕቅድ ያወጣው የኢትዮጵያ መንግሥት፣ የዘር ነገር እንደ አርሶ አደር ጉርሜሳና አርሶ አደር ጴጥሮስ ሁሉ ራስ ምታት ሆኖበታል:: መንግሥት በ2003 ዓ.ም. ያፀደቀው የዕድገትንና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ እንደሚገልጸው፣ 200 ሚሊዮን ቶን የነበረውን የአርሶ አደሩን ምርት በ2007 ዓ.ም. 400 ሚሊዮን የማድረስ ዕቅድ አውጥቷል:: ይህንን ምርት ለማምረት ሰባት ሚሊዮን ኩንታል ምርጥ ዘር የሚያስፈልግ ቢሆንም፣ ይህንን ዘር በአገር አቀፍ ደረጃ ያቀርባሉ ተብሎ ኃላፊነት የተጣለባቸው ተቋማት የአቅም ውስንነት አለባቸው::

ለምሳሌ በ2004 ዓ.ም. የምርት ዘመን ከኢትዮጵያ ምርጥ ዘር ድርጅት 800 ሺሕ ኩንታል ምርጥ ዘር ቢጠበቅም፣ የድርጅቱ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በማሳ ላይ ያለው ግምታዊ የምርት መጠን ከከረመው ምርት ጋር ተዳምሮ በግማሽ የቀነሰ 400 ሺሕ ኩንታል ምርት ነው ያለው::

የዘርፉ ባለሙያዎች እንደሚጠቁሙት፣ በምርጥ ዘር በኩል አንዳች ለውጥ ማምጣት ካስፈለገ ባለሀብቶች በሰፊው ወደ ዘር ማምረት መግባት አለባቸው:: አርሶ አደሮችም የምርጥ ዘር ጥቅምን በሚገባ ተገንዝበው ፍጆታቸውን በራሳቸው እንዲያመርቱ መሆን አለበት:: የምርምር ተቋማትም በብዛት አዳዲስ ዝርያዎችን እንዲያወጡ ያወጡትንም ቅድመ መሥራች ዘር የሚያባዙ ተቋማት በስፋት ሊፈጠሩ ይገባል:: ባለሙያዎቹ ይህ ሁሉ ሲሆን የአገሪቱን አግሮ ኢኮሎጂያዊ ቀጠናዎች ከግምት ያስገባ ሥራ ሊሠራ ይገባል ይላሉ::

የኢትዮጵያን የግብርና ኤክስቴንሽን ለዓመታት ሲደግፍ የቆየው ሳሳካዋ ግሎባል በእነዚህ ጉዳዮች ጠቀሜታ ያምናል:: የሳሳካዋ ግሎባል የምርጥ ዘር ባለሙያ አቶ ቴዎድሮስ ጣሰው እንደገለጹት፣ አግሮ ኢኮሎጂ ቀጠናዎችን ባገናዘበ መልኩ ምርጥ ዘር ሊመረትና ገበሬዎችም የራሳቸውን ዘር እንዲያመርቱ ዕድሎች መከፈት አለባቸው:: የእሳቸው መሥርያ ቤት ከግብርና ሚኒስቴር ጋር እየሠራ መሆኑን አቶ ቴዎድሮስ ገልጸው፣ መሥርያ ቤታቸው ምርጥ ዘር እየገዛ በገበሬ ማሳ ላይ

የሠርቶ ማሳያ ተግባራትን በማከናወን ላይ መሆኑን ገልጸዋል::ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ ወገኖች እንደሚገልጹት

ግን፣ መንግሥት በምርጥ ዘር ብዜት በኩል የግል ኩባንያዎችን ተሳትፎ በጥንቃቄና በስጋት ይመለከተዋል:: ምክንያታቸውን ሲገልጹ፣ የግል ኩባንያዎች አትራፊ እንደመሆናቸው ትርፍ በሚያስገኙ ምርቶች ላይ ያተኩራሉ:: በተጨማሪም እነዚህ የግል ኩባንያዎች የምርጥ ዘር የዋጋ ንረት ሊፈጥሩ ይችላሉ:: በእርግጥም የኢትዮጵያ ምርጥ ዘር ድርጅት አንድ ኩንታል ድቃይ ምርጥ ዘር በቆሎ በ1,329 ብር ይሸጣል:: ድቃይ ያልሆኑትን ደግሞ በኩንታል 713 ብር ይሸጣል:: የአገር ውስጥ የግል ባለሀብቶች ግን አንድ ኩንታሉን ድቃይ ምርጥ ዘር በቆሎ ከ1,500 ብር በላይ ሲሸጡ፣ ፓዮኔር የተሰኘው የውጭ አገር የዘር ኩባንያ ከ2,000 ብር በላይ ይሸጣል:: ፓዮኔር ዘሩን የሚያስመጣው ከውጭ አገር እንደሆነ መረጃዎች ይጠቁማሉ::

ባለሙያዎቹ የእነዚህ ኩባንያዎች መኖር ጠቀሜታ ቢኖረውም፣ በምርጥ ዘር ዋጋ ላይ ተፅዕኖ ሊፈጥር እንደሚችል ያስተዋለው መንግሥት ዘርፉን ብዙም ክፋት እንዳላደረገው እምነታቸውን ይገልጻሉ::

አቶ ፈለቀ ግን አማራጭ የለም ይላሉ:: ምክንያታቸውም በምርጥ ዘር ድርጅቶች ብቻ የኢትዮጵያ የምርጥ ዘር ፍላጎት አይሟላም:: በመሆኑም የግል ኩባንያዎች በሰፊው እንዲገቡ ቢደረግ በዋጋ በኩል ውድድር ስለሚኖር ያን ያህል ስጋት እንደማይሆን ያብራራሉ:: በግብርና ዘርፍ አንዳች አብዮት ለማምጣት የሚንቀሳቀሰው መንግሥት የምርጥ ዘር ችግር ምላሽ ሊያገኝ እንደሚገባው ድምዳሜ ላይ መድረሱን የሚያመላክቱ ዕርምጃዎችን መውሰድ ጀምሯል::

ከእነዚህ በርካታ ዕርምጃዎች መካከል በዋናነት ሁለት ውሳኔዎች ጎልተው ይወጣሉ:: የመጀመርያው በአገሪቱ የሚገኙት የግብርና ምርምር ተቋማት አንድ ምርጥ ዘር ለማግኘት ረጅም ጊዜ የሚወስድባቸው በመሆኑ ከውጭ አገር ምርጥ ዘር በማስገባት ተጨማሪ አጫጭር ሙከራዎችን በማድረግ ብቻ ለአባዢ ድርጅቶች እንዲያቀርብ የሚል ነው::

እንደምርምር ተቋማቱ ሁሉ የኢትዮጵያ ምርጥ ዘር ድርጅትም ባካሄደው የመሠረታዊ የሥራ ሒደት ለውጥ ከውጭ አገር ዘር በማስገባት እያባዙ እንዲያቀርቡ አቅጣጫ መያዙን አቶ ፈለቀ ገልጸዋል::

ሌላኛውና ዋነኛው የሚኒስቴሮች ምክር ቤት ባለፈው ዓመት መጨረሻ ያቋቋመው የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲ የተሰጠው ኃላፊነት ነው:: አዲሱ ኤጀንሲ የአገሪቱ የግብርና ዘርፍ አብዮት ማምጣት የሚያስችሉ ተግባራትን እንዲያከናውን ኃላፊነት ተጥሎበታል::

ኤጀንሲውም ሥራ ከመጀመሩ በፊት የአገሪቱ ግብርና ዘርፍ ዋነኛ ችግሮች የትኞቹ እንደሆኑና በምን መልኩ ችግሮቹ እንደሚቀረፉ ጥናት አስጠንቷል:: ለጥናቱም በሚል ሚሊንዳና ጌት ፋውንዴሽን ፋይናንስ አድርጓል:: ኤጀንሲው የግብርና ዘርፍ ዋነኛ ችግር ካላቸው ስምንት ጉዳዮች መካከል ምርጥ ዘር አንዱ ሆኖ ተቀምጧል::

በአቶ ካሊድ ቦምባ የሚመራው ይህ የግብርና ትራንስፎርሜሽን የዘርፉን ችግር ለመፍታት አዋጅ ከማርቀቅ ጀምሮ የተለያዩ ዕርምጃዎችን ይወስዳል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማትም በገንዘብና በቴክኒክ ድጋፍ ያደርጉለታል ተብሎ ይጠበቃል::

ምናልባትም የአቶ ካሊድ ኤጀንሲ ከተሳካለት የአርሶ አደር ጉርሜሳና የአርሶ አደር ጴጥሮስ ሐዘን በደስታ ይቀየር ይሆናል:: በዚህም ዘርፉ ለውጥ ካመጣ የሁለቱ አርሶ አደሮች ብቻ ሳይሆን የ85 በመቶ የአገሪቱ ሕዝብ እፎይታ ያገኛል:: 80 በመቶ የሚሆነው የአገሪቱ የውጭ ንግድ ገቢ የሚገኘው ከዚሁ የግብርና ዘርፍ እንደመሆኑ የምሥራች ይሆናል::

የአርሶ አደሮች...ከክፍል-1 ገጽ 12 የዞረ

ዶክተር ሎቫርስ ኔይልስ አቶ መላኩ አድማሱ

Advertisement for Tender

The Ethiopian Orthodox Tewahedo Church Development and Inter Church Aid

Commission (EOTC-DICAC) is a multipurpose registered Ethiopian Residence Charity

NGO organized before 40 years as a development wing of the church undertaking different

sustainable development and emergency activities in different regions of the country.

One of the activities that EOTC-DICAC involved is clergy training which is designed to

capacitate the parish church servants both in spiritual and developmental activities. Based

on this, DICAC now intends to construct clergy Training Center at East Shoa Diocese

of Sodere Felege Selam Medihanialem Monastery. So that EOTC-DICAC invites

contractors of category BC/GC 6 and above who fulfill all the requirements.

Firms to engage in this tender should have enough relevant experiences, good

relationship with previous clients, have clearance from the concerned body to

participate in tender, have renewed license, VAT, TIN and registration certificate

from MoWUDC.

Documents can be purchased for a non refundable fee of Birr 150 /One

Hundred Fifty/ from the commissioner’s casher at Arat Kilo, in front of Tourist

Hotel from the 3rd date of this advertisement for the next three consecutive days.

Original & copies of the quotation & all relevant credentials with a Bid Bond of

20,000 in the form of certified cheque (CPO) should be submitted in the address

specified below.

Bidders should sign in all pages of the original bid document, stamp on it and

wax sealed for both original & copy and then an outer envelope.

The date for submission of bids shall be at the 9th day from the advertisement up

to 12:00 local time and opened on the same date at 2:00 at the commission’s hall

in the presence of bidders or representative who choose to attend.

DICAC has the right to reject the bid fully or partially.

Telephone: 011 155 35 66

011 157 16 32

ፎቶ በ

ሪፖርተ

ር/መስፍ

ን ሰሎ

ሞን

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 14 | እሑድ |ኅዳር 17 ቀን 2004ክፍል-1

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 15 | እሑድ | ኅዳር 17 ቀን 2004 ክፍል-1

በኃይሌ ሙሉ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ኩማ ደመቅሳ ባለፈው ሳምንት ለተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡት አጭር መግለጫ በከተማዋ የተከሰተው የኑሮ ውድነት ለአስተዳደሩ ከባድ ፈተና እንደሆነበት ገልጸዋል:: ለአንድ ዓመት ያህል በኅብረተሰቡ ዘንድ መነጋገሪያ የሆነው የግሽበት ጉዳይ በርግጥም መፍትሔ ያጣ ይመስላል:: መንግሥት የኑሮ ውድነቱን ለመቅረፍ ይረዳኛል በማለት ባለፈው ዓመት የወሰደው የዋጋ ተመን ዕርምጃም ኅብረተሰቡን ከድጡ ወደ ማጡ ጨመረው እንጂ የተሻለ ነገር አላመጣለትም:: በአገሪቱ የተከሰተው ግሽበት ትክክለኛ ምንጩ ተለይቶ ባለመታወቁም እስካሁን ድረስ መፍትሔ ሊገኝለት አልቻለም::

ኢትዮጵያ ውስጥ ግሽበት መታየት የጀመረው እ.ኤ.አ. ከ2003/2004 ግድም ነበር:: መንግሥት በወቅቱ ለግሽበቱ መከሰት ዋነኛ ምክንያቶች ናቸው ብሎ የጠቀሳቸው ነገሮች የኢኮኖሚ ዕድገት፣ የሕዝቡ ገቢ መጠን መጨመርና የሕዝብ ቁጥር መጨመር ነበሩ:: የኢኮኖሚ ዕድገቱን ተከትሎ የገቢ መጠኑ የጨመረው ሕዝብ የተለያዩ ምርቶችን መግዛት መጀመሩ ችግሩን እንዳስከተለ ኢሕአዴግ ይገልጽ ነበር:: ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊም በተለያየ ጊዜ በፓርላማ ቀርበው በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ ሲሰጡ ይህንን ይገልጹ ነበር:: ስኳርና ሲሚንቶን በምሳሌነት ሲጠቅሱ የነበሩት አቶ መለስ፣ ቡና በጨው ይጠጣ የነበረው አርሶ አደር የኢኮኖሚ ዕድገት ማስመዝገቡን ተከትሎ ስኳር መጠቀም መጀመሩን ይህም በገበያ ላይ እጥረት መፍጠሩን፣ በተመሳሳይ ሁኔታም በአገሪቱ የሚካሄደው ግንባታ የሲሚንቶ እጥረት መፍጠሩን ይገልጹ ነበር::

እ.ኤ.አ. በ2007/2008 ላይ በዓለም ላይ የተከሰተውን የኢኮኖሚ ቀውስ ተከትሎ የነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ ደረጃ ሲጨምር ከዚህ ጋር ተያያዥነት ያለው የምግብ ዋጋ ጨመረ:: መንግሥትም ለነዳጅ ይሰጥ የነበረውን ድጐማ አቁሞ ስንዴን ከውጭ በማስመጣት በድጐማ ለኅብረተሰቡ ማከፋፈል ጀመረ:: የአቅርቦትና ፍላጐት አለመጣጣም አገሪቱ ውስጥ አለ በሚባልበት ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ የምግብ ዋጋ መጨመሩ ለመንግሥት ዱብ ዕዳ ነበር:: በዚህም ምክንያት እ.ኤ.አ. መስከረም በ2010 የዋጋ ግሽበቱ ሁለት አሃዝ (10.6 በመቶ) ገባ:: ከዚህ በኋላ ነው እንግዲህ መንግሥት በገበያ ሥርዓቱ ላይ ጣልቃ መግባት የጀመረው::

መንግሥት የውጭ ንግድን ያበረታታል፤ ከውጭ የሚገቡ አላስፈላጊ ምርቶችን ያስቆማል በሚል እምነት የብርን የመግዛት አቅም በ20 በመቶ ቀነሰ:: የኢኮኖሚ ተንታኞች እንደሚሉት፣ ይህ ጣልቃ ገብነት ጊዜውን ያልጠበቀና በቂ ጥናት ያልተካሄደበት በመሆኑ ግሽበቱን አባብሶታል:: አገሪቱ የተለያዩ ምርቶችን ከውጭ ማስገባቷን በመቀጠሏ የዋጋ ንረቱ ተባብሶ ቀጠለ:: እ.ኤ.አ. መስከረም በ2010 የጀመረው የዋጋ ግሽበት በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ 40.1 በመቶ ደረሰ:: በሁኔታው ግራ የተገባው መንግሥት ግሽበቱ የተከሰተው ከውጭ በሚመጣ ምርት ሳይሆን ጥቂት ግለሰቦች የገበያ ሥርዓቱን በመቆጣጠራቸው ምክንያት መሆኑን በመግለጽ በ17 ምርቶች ላይ የዋጋ ተመን ጣለ:: በቂ ጥናት ሳይካሄድበት የተተገበረ ነው ተብሎ በብዙዎቹ ትችት የቀረበበት ይህ የዋጋ ተመን ዕርምጃም ከአምስት ወር በኋላ ተነሳ::

የዋጋ ተመን ዕርምጃው የገበያውን ሥርዓት እንዳይሆን አድርጐ አተራምሶት ነው ያለፈው:: የዋጋ ተመን የተጣለባቸው አብዛኛዎቹ ምርቶች የዋጋ ተመኑ ከመጣሉ በፊት ከነበራቸው ዋጋ በእጥፍ ጨምረዋል::

የዛሬ ዓመት የተከሰተው የዋጋ ንረት አሁንም ሊስተካከል አልቻለም:: አብዛኛው የኅብረተሰብ ክፍልም በኑሮ ውድነቱ እየተጐዳ ይገኛል:: የዋጋ ተመኑ ሲጣል ለውጥ ይኖራል የሚል ግምት የነበረው ኅብረተሰብ የዋጋ ተመኑ መነሳቱን ተከትሎ የተለያዩ ሸቀጦች ዋጋ በከፍተኛ ደረጃ መጨመሩን ሲመለከት፣ ‹‹ትሻልን ሰድጄ ትብስን አመጣሁ›› ማለቱ አልቀረም::

ሪፖርተር ያነጋገራቸው የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች መንግሥት የዋጋ ተመን ዕርምጃ

መውሰዱ ኑሮ ውድነቱን እንዳባባሰውና የሸቀጦችን ዋጋም እንዳይመለስ አድርጐ ወደ ላይ የሰቀለው መሆኑን ይናገራሉ::

የኢኮኖሚ ባለሙያ የሆኑት አቶ ሚካኤል መላኩ እንደሚሉት፣ በፖሊሲ ደረጃ በአንድ አገር ውስጥ የኑሮ ውድነት ሲከሰት የዋጋ ተመን መጣሉ ምንም ችግር የለውም:: ዕርምጃው ሲወሰድ ግን የኑሮ ውድነት እንዲከሰት አድርገዋል ተብለው የሚታሰቡ ምርቶችን ለይቶ ማወቅ ያስፈልጋል::

እንደሜክሲኮና ብራዚል የመሳሰሉ አገሮች በቁጥር 150 በሚደርሱ ሸቀጦች ላይ የዋጋ ተመን እንደሚጥሉና የተጣለውም የዋጋ ተመን ገበያውን አረጋግቶ እንደሚቀጥል የሚገልጹት አቶ ሚካኤል፣ የኢትዮጵያ መንግሥት የወሰደው የዋጋ ተመን ዕርምጃ ውጤት ሳያስገኝ እንዲነሳ የተደረገው ከመነሻው ጥናትን መሠረት ያደረገ ባለመሆኑና የአፈጻጸም ችግር በመኖሩ ነው የሚል እምነት እንዳላቸው ያስረዳሉ::

እርሳቸው እንደሚሉት፣ ጥቂት ግለሰቦች የተወሰኑ መሠረታዊ ምርቶችን በመቆጣጠር የፈለጉትን ዋጋ በኅብረተሰቡ ላይ እየጫኑ ነው በሚል እምነት መንግሥት በእነዚህ ምርቶች ላይ የዋጋ ተመን መጣሉ አንዱ አነጋጋሪ ጉዳይ ሲሆን፣ ከዚህ ጋር ተያይዞም ‹‹ጥቂት ግለሰቦች በእርግጥ እነኝህን ምርቶች መቆጣጠራቸውን የሚያሳይ ጥናት ተካሂዷል ወይ?›› የሚል ጥያቄ መነሳት እንዳለበት ይገልጻሉ::

መንግሥት በጥቂት ግለሰቦች ተፅዕኖ ሥር ወድቀዋል በሚል የዋጋ ተመን ከጣለባቸው ምርቶች መካከል ቢራ፣ ሥጋ፣ ዘይትና ስኳር እንደሚገኙበት ይታወሳል::

‹‹የዋጋ ንረት የታየባቸው ምርቶች በጥቂት ግለሰቦች ቁጥጥር ሥር ውለዋል የሚለው የመንግሥት መነሻ ምን ያህል ትክክል ነው? የምርቶቹ ዋጋ የተወደደበት ምክንያትስ ተለይቶ ተጠንቷል ወይ?›› ሲሉ የሚጠይቁት አቶ ሚካኤል፣ ምርቶቹ በጥቂት ግለሰቦች ተፅዕኖ ሥር ወድቀዋል ቢባል እንኳን የተጠቀሱት ምርቶች በኑሮ ውድነት ኢንዴክስ ላይ ምን ያህል ወሳኝነት አላቸው? ድርሻቸውስ ምን ያህል ነው? የሚሉት ጥያቄዎች በአግባቡ ተጠንተው ምላሽ አግኝተዋል የሚል እምነት እንደሌላቸው ያስረዳሉ:: ‹‹ቢራ በኑሮ ውድነት ላይ ምን ያህል ተፅዕኖ ነበረው? ከነበረውስ ምን ያህል ነው ድርሻው?›› ሲሉ ይጠይቃሉ::

የዋጋ ተመኑ ዕርምጃ ያልተሳካበት ዋነኛ ምክንያት ነው ተብሎ በአቶ ሚካኤል የተጠቀሰው ምርቶቹ የተሠራጩበት አካሄድ ነው:: እርሳቸው እንደሚሉት፣ የተወሰኑ መሠረታዊ የፍጆታ ምርቶችን ከውጭ ማስመጣት ጀምሮ የነበረው መንግሥት ችርቻሮ ውስጥ መግባት አልነበረበትም:: መንግሥት ራሱ የምርቶቹ አቅራቢና ቸርቻሪ ከሚሆን ይልቅ ጥናት አካሄዶ ሥርጭቱ በሌሎች አካላት የሚከናወንበትን መንገድ ማመቻቸት ይገባው እንደነበርም ይገልጻሉ::

መንግሥት የዋጋ ተመን ዕርምጃውን ሲወስድ የንግድ ማኅበረሰቡ አባላት ውሳኔው ተግባራዊ ከመሆኑ በፊት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት መካሄድ እንደነበረበት ገልጸው ነበር:: ውሳኔው ጥናትን መሠረት አድርጐ የተተገበረ መሆኑን በመግለጽ ውይይት ማካሄዱ አስፈላጊ አለመሆኑን አስታውቆ የነበረው መንግሥት ግን ውሎ ሳያድር ነበር ዘይትን ጨምሮ በአንዳንድ ምርቶች ላይ የዋጋ ማስተካከያ ያደረገው::

የዋጋ ተመኑ ዕርምጃ ከመወሰዱ በፊት በቂ

ጥናት ሊከናወን እንደሚገባ፣ ከሚመለከታቸው አካላት ጋርም በመወያየት ጠቃሚ ግብረ መልስ የሚገኝበትን ሁኔታ ማመቻቸት ይቻል እንደገበር የሚናገሩት አቶ ሚካኤል፣ በአፈጻጸም ሒደት ላይ ችግር የተከሰተው በአስፈጻሚ አካላት አቅም ማነስ ምክንያት ነው የሚል እምነት እንዳላቸው ይናገራሉ::

መንግሥት በተወሰኑ ምርቶች ላይ የጣለውን የዋጋ ተመን ካነሳ በኋላ አብዛኛዎቹ ምርቶች የዋጋ ተመኑ ከመጣሉ በፊት ከነበራቸው ዋጋ በላይ ጨምረዋል:: ሰላሳ ብር ይሸጥ የነበረው ዘይት ሰባ ብር ገብቷል:: አምስት ብር ይሸጥ የነበረው ሳሙናም 11 ብር እየተሸጠ ነው:: ስልሳና ሰባ ብር ይሸጥ የነበረው አንድ ኪሎ ስጋም 120 ብር ገብቷል::

የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች የዋጋ ተመን ዕርምጃ መወሰዱን ተከትሎ በወቅቱ በሰጡት መግለጫ ጥናትን መሠረት ባላደረገ መልኩ የተጣለው የዋጋ ተመን ከጥቅሙ ጉዳቱ እንደሚያመዝን መናገራቸው ይታወሳል:: በምርቶቹ ላይ የአቅርቦት እጥረት ፈጥሮ የጥቁር ገበያ ይስፋፋል ሲሉም ተደምጠዋል:: ተቃዋሚዎች እንዳሉትም፣ መንግሥት ዕርምጃውን በወሰደ በማግስቱ የምርት እጥረት ተከስቷል:: የወሰደው ዕርምጃ ውጤት እንዳላስገኘለት የተገነዘበው መንግሥትም ከአምስት ወር በኋላ የዋጋ ተመኑን ለማንሳት ተገድዷል:: መንግሥት የወሰደው የዋጋ ተመን ዕርምጃ የኑሮ ውድነትን ችግር መቅረፍ እንዳልቻለ ሁሉም የሚስማማበት ጉዳይ ቢሆንም፣ የአብዛኛዎቹ መሠረታዊ የፍጆታ ምርቶች ዋጋ ተመኑ ከመጣሉ በፊት ከነበረው ዋጋ በላይ መጨመሩ የዋጋ ተመኑ ያስከተለው ችግር ነው ወይስ አይደለም በሚለው ጉዳይ ላይ ግን ባለሙያዎች የተለያየ አስተያየት አላቸው::

እንደ አቶ ሚካኤል ገለጻ፣ የዋጋ ተመኑ ከፍተኛ የዋጋ ንረት አስከትሏል ብሎ ለመናገር ጥናት ማካሄድ ያስፈልጋል:: የዋጋ ተመኑ ዕርምጃ ከተወሰደ በኋላ ሰው ሠራሽ የዋጋ ንረት መከሰቱን የሚናገሩት አቶ ሚካኤል፣ ችግሩን ለመቅረፍ ከተፈለገ በተሳሳተ መንገድ በሰዎች ጭንቅላት ላይ የቀረውን ግሽበት ማጥፋት ግድ የሚል መሆኑን ይናገራሉ::

‹‹በሰዎች ጭንቅላት ላይ የተቀረፀውን ግሽበት አለ የሚለውን አመለካከት በምን መልኩ ማጥፋት ይችላል?›› ለሚለው ጥያቄ ማብራሪያ ሲሰጡም፣ ከጥቂት ዓመታት በፊት በአገሪቱ የተፈጠረውን የስንዴ እጥረት በምሳሌነት ይጠቅሳሉ::

ከጥቂት ዓመታት በፊት በአገሪቱ ውስጥ የስንዴ እጥረት መከሰቱን ተከትሎ መንግሥት ከውጭ ስንዴ ማስገባቱን፣ የመጣው ስንዴ ለሕዝብ ከተሸጠ በኋላም የስንዴው ዋጋ አለመቀነሱን ያስታወሱት አቶ ሚካኤል፣ በከፍተኛ ደረጃ ንሮ የነበረው የስንዴ ዋጋ መቀነስ የጀመረው ‹‹በአገሪቱ የሚታየው የስንዴ ዋጋ በዓለም አቀፍ ደረጃ ካለው ዋጋ ጋር እስከሚስተካከል ድረስ በብዛት ስንዴ ወደ አገር ውስጥ አስገባለሁ፤›› ብሎ መንግሥት ካሳወቀና የገባውን ቃልም ከተገበረ በኋላ መሆኑን ይገልጻሉ:: እርሳቸው እንደሚሉት፣ በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ የተከሰተውን ሰው ሠራሽ የዋጋ ንረት ለማስተካከል ከተፈለገም በተመሳሳይ ሁኔታ ዕርምጃ በመውሰድ ግሽበት አለ የሚለውን የሕዝቡን የተሳሳተ ግምት ማጥፋት ግድ ይላል::

የኢዴፓ ሊቀመንበር አቶ ሙሼ ሰሙም በአቶ ሚካኤል ሐሳብ ይስማማሉ:: መንግሥት በበቂ ጥናት ላይ ሳይመሠረት የዋጋ ተመን መጣሉ በምርቶች ላይ ሰው ሠራሽ እጥረት ይፈጥራል::

አቶ ሙሼ እንደሚሉት፣ በቂ ጥናት ሳያደርግ የዋጋ ተመን በሚወሰንበት ጊዜ ገበያ ላይ ያለው ዋጋ መንግሥት ካወጣው ዋጋ ጋር ስለማይመጣጠን ነጋዴው ኅብረተሰብ ሸቀጡን ከስሮ መሸጥ ስለማይፈልግ ደብቆ ያስቀምጣል:: መንግሥት ዝቅተኛ ዋጋ በሚያወጣበት ጊዜም ወደ ፊት እጥረት ሊያጋጥም ይችላል በሚል መላምት ሸማቹ በዝቅተኛ ዋጋ የተገኘውን ምርት በሙሉ ጠራርጐ በመግዛት የምርት እጥረት እንዲፈጠርና የግብይት ሥርዓቱ እንዲዛባ የሚያደርግ መሆኑን ያስረዳሉ::

‹‹መንግሥት ዋጋ ሲተምን በምርቶች ላይ የጣለው ዋጋ የውሸት ዋጋ ነበር:: በቂ ጥናት ያልተካሄደበት በመሆኑ በተደጋጋሚ ክለሳ ተደርጐበታል:: ይህም ሰዎች የምርቶቹ ዋጋ ወደ ፊት ሊወደድ ይችላል የሚል ትንበያ (Speculation) እንዲኖራቸው አድርጓል፤›› በማለት በምርቶች ላይ የተፈጠረው ግሽበት ሰው ሠራሽ መሆኑን ይገልጻሉ::

አቶ ሙሼ እንደሚሉት፣ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ የግብይት ሥርዓታቸው ኋላቀር በሆኑ አገሮች የዋጋ ተመን መጣል የዋጋ ንረትን ለመቀነስ አያስችልም:: እንደ ብራዚል በመሳሰሉት አገሮች ያሉት ተቋሞች የተሟሉ በመሆናቸውና የተረጋጋ ኢኮኖሚና ዘመናዊ የመረጃ ልውውጥም ስላላቸው የዋጋ ተመን ቢጣል ውጤት ሊያስገኝ እንደሚችል የጠቆሙት አቶ ሙሼ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ግን የዋጋ ተመን ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ እንደሚያመዝን ያስረዳሉ::

‹‹ዘመናዊ የንግድ ሥርዓት በሌለበት፣ በገበያው ሥርዓት ሁለት ሦስት ደላሎች በሚሳተፉበት እንዲሁም በቂ መረጃ በሌለበት ሁኔታ የዋጋ ተመን ዕርምጃ መውሰድ የኑሮ ውድነትን ችግር አይቀርፍም፤›› ይላሉ::

አቶ ሙሼ እንደሚሉት፣ በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ ለተከሰተው የዋጋ ንረት አንዱ ምክንያት የዋጋ ተመን ዕርምጃ ሲሆን፣ የብር የመግዛት አቅም መቀነስም ችግሩን በማባባስ የራሱን ተፅዕኖ ፈጥሯል::

ከውጭ በሚመጡ ምርቶች ላይ የሚታየው ግሽበት ከጠቅላላው የአገሪቱ ገቢና ከኢኮኖሚ ዕድገት ጋር የሚገናኙ በመሆኑ በቀላሉ ማስቆም እንደሚያስቸግር የሚገልጹት የኢዴፓው ሊቀመንበር፣ የዋጋ ተመኑን ተከትሎ የተፈጠረውን ግሽበት ግን የሰዎችን የተሳሳተ መላምት በማጥፋትና መተማመንን በመገንባት ማስተካከል እንደሚቻል ያስረዳሉ::

‹‹የዘይት ዋጋ ይጨምራል ብሎ ዘይት የደበቀ ሰው ዘይት በሰፊው ሲቀርብ ሲያይ ዋጋ ይጨምራል ብሎ ማሰቡን ያቆማል:: ሸማቹም በማንኛውም ጊዜ ዘይት አገኛለሁ ብሎ ስለሚተማመን ከፍጆታው በላይ መግዛት ያቆማል፤›› በማለት ሰው ሠራሽ ግሽበት በሒደት የሚስተካከልበትን የመፍትሔ ሐሳብ ይሰነዝራሉ::

የቀድሞ የፓርላማ አባልና የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ አመራር አባል አቶ ተመስገን ዘውዴ በበኩላቸው፣ መንግሥት የፖለቲካ ጥቅም ለማግኘት ሲል ባለፈው ዓመት የወሰደው የዋጋ ተመን ዕርምጃ በጥናት የተደገፈ ባለመሆኑ የኑሮ ውድነቱን እንዳባባሰው ይገልጻሉ::

‹‹ውሳኔው በጥናት ያልተደገፈ በመሆኑ ውጤት ሳያስገኝ በጥቂት ወራት ውስጥ እንዲነሳ ተደርጓል:: ዕርምጃው ባለሙያዎች ሳይመክሩበት በትዕዛዝ የተፈጸመ ነው፤›› ያሉት አቶ ተመስገን፣ መንግሥት በመሠረታዊ የፍጆታ ምርቶች ላይ የጣለው የዋጋ ተመን ችግሩን በዘላቂነት ሊፈታ አለመቻሉን አውቆ ተመኑን ሲያነሳ ኅብረተሰቡ በመንግሥት ላይ እምነት በማጣቱና እጥረቱ እንደሚቀጥል በመረዳቱ ሰው ሠራሽ የዋጋ ንረት መከሰቱን ይገልጻሉ::

ሪፖርተር ያነጋገራቸው ሁሉም አስተያየት ሰጪዎች እንደሚሉት፣ ጥናትን መሠረት ያላደረገውን የመንግሥት ጣልቃ ገብነት ተከትሎ በአገሪቱ ውስጥ ሰው ሠራሽ የምርት እጥረት የተከሰተ ሲሆን፣ ይህንን እጥረት ለመቅረፍም በሒደት የሕዝቡን መተማመን መገንባት ያስፈልጋል:: መንግሥት በገበያ ሥርዓቱ ላይ ጣልቃ ሲገባም በቂ ጥናት ማካሄድ እንደሚኖርበትም እነኝሁ ተንታኞች ያስገነዝባሉ::

ያለ ጥናት የተተገበረው የጣልቃ ገብነት መዘዝ

የዛሬ ዓመት የተከሰተው የዋጋ ንረት አሁንም ሊስተካከል አልቻለም:: አብዛኛው የኅብረተሰብ ክፍልም በኑሮ ውድነቱ እየተጐዳ ይገኛል:: የዋጋ ተመኑ ሲጣል ለውጥ ይኖራል የሚል ግምት የነበረው ኅብረተሰብ የዋጋ ተመኑ መነሳቱን ተከትሎ

የተለያዩ ሸቀጦች ዋጋ በከፍተኛ ደረጃ መጨመሩን ሲመለከት፣ ‹‹ትሻልን ሰድጄ ትብስን አመጣሁ›› ማለቱ አልቀረም::

‹‹ውሳኔው በጥናት ያልተደገፈ በመሆኑ ውጤት ሳያስገኝ በጥቂት ወራት ውስጥ እንዲነሳ

ተደርጓል:: ዕርምጃው ባለሙያዎች ሳይመክሩበት በትዕዛዝ የተፈጸመ ነው፤››

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 16 | እሑድ |ኅዳር 17 ቀን 2004ክፍል-1

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 17 | እሑድ | ኅዳር 17 ቀን 2004 ክፍል-1

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 18 | እሑድ |ኅዳር 17 ቀን 2004ክፍል-1

Introduction PATH is an international, nonprofit organization that provides appropriate health technologies and vital strategies that change the way people think and act. PATH’s focus areas include health technologies; maternal and child health; reproductive health; vaccines and immunization; and emerging and epidemic diseases.

The Help Ethiopia Address the Low TB Performance (HEAL TB) Project is funded by United States Agency for International Development (USAID) and led by Management Sciences for Health (MSH) in Collaboration with PATH and other partners. The project intervenes in four technical areas: (1) Strengthening and Expansion of DOTS (Improved CDR and TSR); (2) Response to Emergence of MDR-TB; (3) TB/HIV Collaboration, and (4) Health Systems Strengthening. PATH is seeking the following consultants for the TB Knowledge, Attitudes and Practices (KAP) Survey that is going to be conducted in Amhara and Oromia regions in Ethiopia.

1. Study Coordinator: TB Knowledge, Attitudes and Practices (KAP) Survey

Dates of Consultancy: Up to 90 days from 15 December 2011 to 15 March 2012

Supervisor: Community TB Advisor

Consultant’s Tasks

• Coordinate the planning and implementation of the survey in collaboration with designated Ethiopia and U.S.-based PATH staff members.

• Recruit and manage field researchers with quantitative research expertise to execute the survey.

• Work with PATH staff to facilitate in-country IRB approval & develop and co-facilitate training of the research team

• Oversee the field pre-testing and revision of the survey questionnaire/instruments during the training week.

• Facilitate, supervise and lead entry into communities during the field work, including recruitment of survey respondents, in conjunction with the research team.

• Oversee data collection including coordinating the research team and completion of full and accurate data entry.

• Participate in data analysis and report-writing as needed.

Qualifications• An advanced degree (MA) in the social sciences or research-related field is a

minimum requirement. A postgraduate degree or progress towards a postgraduate degree is desirable.

• Experience as a survey team leader/coordinator

• Experience in quantitative and qualitative research procedures is imperative and experience in planning and coordinating public health and/or TB research projects in Ethiopia is highly desirable.

• Good command over local language (Amharic and Oromia) and English.

2. Research Interviewers: TB Knowledge, Attitudes and Practices (KAP) Survey

Dates of Consultancy: Up to 45 days from 01 January 2012 – 28 February 2012

Supervisor: Study Coordinator

Consultant’s Tasks

• Participate in five-day training on KAP assessment methodology; pilot and revise KAP assessment questionnaires

• Participate in translation of interview guides

• Conduct assessment interviews with respondents in accordance with the assessment sampling plan

• Record daily field notes from field work; provide all completed questionnaires to the Study Coordinator

• Additional duties assigned from time to time

Qualifications

• An advanced degree (MA) in the social sciences or research-related field is a minimum requirement.

• Experience in quantitative and qualitative research procedures is imperative

• Experience with public health and TB in particular is desirable.

• Good command over local language (Amharic and Oromia) and English.

APPLICATION GUIDELINES Interested applicants should submit cover letter and resume to PATH on or before Friday December 9, 2011 12:30pm addressed to: PATH Ethiopia Country Program, Rear side of Getu Commercial Center, 1st Floor, P.O.Box 493 Code 1110, Telephone: 0115-504255/504316, Addis Ababa, Ethiopia.

INVITATION FOR CONSULTANCY SERVICES

TB Knowledge, Attitudes and Practices (KAP) Survey: Study Coordinator and Study Interviewers

በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተቀናጀ የመሬት መረጃ አያያዝ ሥርዓት ዝርጋታ ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት የሚከተለውን ሥልጠና በሥልጠና ማዕከላቸው በብቃት የሚያሰለጥኑ ተቋማትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡የሥልጠናው ዓይነት

TOR 1- BASIC SPATIAL INFORMATION TECHNOLOGY TRAINING TYPES/ LOTS/

LOT-A PRACTICAL BASICS OF GIS AND REMOTE SENSING TECHNIQUE WHICH INCLUDES TRAINING OF:

1. PARTICAL BASIC APPLICATION OF GEOGRAPHIC INFORMATION SYSTEM (ARC GIS DESKTOPE)

2. PRACTICAL BASIC APPLICATION OF REMOTE SENSING (ERDAS IMAGINE)

LOT-B AERIAL PHOTOGRAPHY AND DIGITAL PHOTOGRAMNERY.LOT-C CADASTERAL LAND SURVEYING AND INSTRUMENTSLOT-D ARCHICADTOR 2- BASIC INFORMATION TECHNOLOGY TRAINING TYPES/LOTS/LOT-A SPSS DATA ORGANIZATION, MANAGEMENT ANALYSISLOT-B DATABASE MANAGEMENT SYSTEMLOT-C NETWORK INSTALLATION CONFIGURATIONLOT-D ADVANCE NETWORKING/CCNA

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ ይጋበዛሉ፡፡

1. በጨረታው መወዳደር የሚችሉ ተጫራቾች ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡና የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው የሥልጠና ወይም የኮንስልታንሰ ፍቃድ ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ 2. ተጫራቾች ለዚሁ ጨረታ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ፕሮጀክት ጽ/ቤቱ በሚገኝበት የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከያና መቆጣጠሪያ ኤጀንሲ ህንፃ 4ኛ ፎቅ ፋይናንስና የሰው ኃይል አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 6 በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በቀን 15/03/04 በወጣው መሠረት እስከ ቀን 28/03/04 ባሉት 1ዐ የሥራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 5ዐ(ሃምሣ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡

3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚወዳደሩበትን ጠቅላላ ዋጋ 2% (ሁለት በመቶ) በሲፒኦ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ማስያዝ አለባቸው፡፡ ተጫራቾች በጨረታ ማስከበሪያነት የሚያስይዙት ስፒኦ የቴክኒክ ሰነዳቸው ባለበት ኤንቨሎፕ ውስጥ በማካተት ማሸግ ይኖርባቸዋል፡፡

4. ተጫራቾች የመጫረቻ ፋይናንሻልና ቴክኒካል ሰነዳቸውን አንድ ኦሪጅናልና አንድ ኮፒ የእያንዳንዳቸው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ከ15/03/04 ጀምሮ ባሉት 1ዐ የሥራ ቀናት የውስጥ ጨረታው ማብቂያ በ28/03/04 ቀን ድረስ ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ 11፡3ዐ ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው፡፡

5. ጨረታው በቀን 29/03/04 ከጠዋቱ 4፡ዐዐ ሰዓት ላይ ፋይናንስና የሰው ኃይል ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 6 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡

6. ተጫራቾች የሥልጠናው አይነቶችን በከፈልም ሆነ በሙሉ መወዳደር ይችላሉ፡፡

7. ፕሮጀክት ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

8. ተጫራቾች የሥልጠናው ዓይነቶችን/training lots / በከፊልም ሆነ በሙሉ መወዳደር ይችላሉ፡፡

9. ተጫራቾች ለዚሁ ሥልጠና በተዘጋጀው ዝክረ - ተግባር / ToR/ በተዘረዘረው መግለጫ መሠረት የቴክኒ(ልና ፋይናንሽያል ፕሮፖዛል ማዘጋጀት ይኖርባቸዋል፡፡

አድራሻ፡- ከጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን ፊት ለፊት እሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከያና መቆጣጠሪያ ኤጀንሲ ህንፃ 4ኛ ፎቅ ፋይናንስና የሰው ኃይል አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 6

ስልክ 011-1552659 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተቀናጀ የመሬት መረጃ

ሥርዓት ዝርጋታ ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 19 | እሑድ | ኅዳር 17 ቀን 2004 ክፍል-1

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 20 | እሑድ |ኅዳር 17 ቀን 2004ክፍል-1

ተ.ወ.ማ. የድለላ ሥራ (ኮሚሽን ኤጀንት)TWM BROKERAGE (COMMISSION AGENCY)

የሚሸጡ ቤቶች1. ቦሌ ሆምስ ቦታው 500 ካሬ G+1 አዲስ ፎቅ ቤት ያለው 2. አሮጌው አውሮፕላን ማረፊያ ቀበሌ 12 ቦታው 600 ካሬ G+1 ቤት ያለው 3. ቃሊቲ ለፋብሪካ የሚሆን ቦታው 10,000 ካሬ 1,200 ካሬ መጋዘንና G+1 ቢሮ ያለው4. ሮፓክ ሪል እስቴት ግቢ ውስጥ ቦታው 1,000 ካሬ አዲስ ቆንጆ ቪላ ቤት ያለው 5. ቦሌ ሸገር ሕንፃ ጀርባ ቀበሌ 19 ቦታው 700 ካሬ G+1 ፎቅ ቤት ያለው 6. ቦሌ ኦሎምፒያ አካባቢ 2 ቦታዎች 620 ካሬና 1,081 ካሬ የድሮ ቪላና G+1 ፎቅ ቤት ያለው 7. መስቀል ፍላወር መንገድ ዳር 500 ካሬ ለፎቅ የሚሆን ቦታ 8. ቦሌ ቀበሌ 20 ጃፓን ኤምባሲ አካባቢ 3 ቪላ ቤቶች 500 ካሬና 700 ካሬ ስፋት ያላቸው 9. መካኒሳ ቦታው 1,000 ካሬ G+2 አዲስ ቤት ያለው 10. ሲ ኤም ሲ መንገድ ዳር ለፎቅ የሚሆን ለ7 ፎቅ መሠረት የወጣለት ቦታው 700 ካሬ 11. ሲ ኤም ሲ መንገድ ዳር ለፎቅ የሚሆን ቦታው 680 ካሬ ቪላ ቤት ያለው

• የሚሸጡ ሆቴሎች፤ እንግዳ ማረፊያ (ገስት ሃውስ) አሉን • የሚከራይም ሆነ የሚሸጥ ቤት ካሎት ይደውሉልን፡፡

ስልክ 0911 21 12 67/22 08 22Email – [email protected]

[email protected]

ህዳር 15 ቀን 2004 ዓ.ም

ማስታወቂያበሐረሪ ሕዝብ ክልላዊ መንግስት የሸንኮር አካባቢ ቀበሌ መስተዳደር ፖሊስ ጽ/ቤት በቁጥር 0158/80/80/200 በቀን 22/2/2004 በፃፈው ደብዳቤ ወ/ሮ አበራሽ ንጉሴ በሸንኮር ወረዳ 09 ካምፕ ውስጥ ነዋሪ የሆነች በቀን 10/2/2004 ዓ.ም በጽ/ቤቱ በመቅረብ ማንነቷን በውል የማያውቋት ግለሰብ የ3 ቀን ልጅ ይዛ ከቤትዋ መጥታ መዳኒት ገዝቼ እስክመለስ ሕፃኗን ጠብቂልኝ ብላቸው መጥፋቷን ገልጸዋል፡፡ ፖሊስ ሕፃኗን ወደ አቤኔዘር ሕፃናት ማሳደጊያ አስገብቷታል፡፡ ስለዚህ የሕፃኗን ወላጆች ነን ወይም ወላጆቿን እናውቃለን የሚል ካለ ከታች በተገለፀው አድራሻ በአካል በመቅረብ እንድታሳውቁን በትህትና እንጠይቃለን፡፡

አድራሻ፡- አቤኔዘር ሕፃናት ማሳደጊያ ማህበር ሐረር ቢራ

ፈረንሳይ ካምፕ ፊት ለፊት

ሐረር ስልክ 025 866 91 01

አዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ላፍቶ የቤት/ቁ 828 ወረዳ 4

ስልክ 011 371 69 87

ህዳር 15 ቀን 2004 ዓ.ም

ማስታወቂያበሀዋሳ ከተማ አስተዳደር በታቦር ክፍለ ከተማ በሆገኔ ዋጮ ቀበሌ ነዋሪ

ከነበሩት ከወ/ሮ አልማዝ ደርጋሳ እና ከአቶ ብርሃኑ ለታሞ የተወለዱ ሕፃን

መስከረም ብርሃኑ እና ሕፃን ታሪኳ ብርሃኑ ሁለቱንም ወላጆቻቸውን በሞት

ስላጡ በከፍተኛ ችግር ውስጥ ያሉ መሆኑን በመጥቀስ ሀዋሳ ከተማ አስተዳደር

ሴቶች ሕፃናትና ወጣቶች መምሪያ ሕንፃናቱን በሻሎም ችልድረንስ ሆፕ አሶሴሽን

ውስጥ አማራጭ የማሳደጊያ አገልግሎት የማያገኙበት ሁኔታ እንዲመቻችላቸው

በመግለጽ ሕፃናቱን በቁጥር ሴ/ህ/ወ/ጉ/አ-500/6 በ28/7/2003 በተፃፈ ደብዳቤ

ለማሳደጊያው አስረክቧል፡፡ እነዚህን ሕፃናት በተመለከተ በተከፈተው የፍ/ቤት

መዝገብ ቁጥር 08931 ላይ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በ11/3/2004

ዓ.ም በሰጠው ትዕዛዝ የሕፃናቱን ቀሪ ቤተሰቦች ብሎ ተፈልገው ከታህሳስ 3

ቀን 2004 ዓ.ም በፊት እንዲቀርቡ አዟል፡፡ ስለሆነም የሕፃናቱን ቀሪ ቤተሰቦች

ነን የሚል ወገን ካለ ከ3/4/2004 ዓ.ም በፊት በአካባቢው በሚገኘው የፖሊስ

ጣቢያ እንዲቀርቡ በሻሎም ችልድረንስ ሆፕ አሶሴሽን ቢሮ እንዲቀርቡ ወይም

በ3/4/2004 ዓ.ም በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ቦሌ ምድብ 1ኛ ፍ/ብሔር

ችሎት እንዲቀርቡ፡፡ ከታች በተገለፀው አድራሻ በአካል በአቅረብ እንዲያሳውቁን

በትህትና እንጠይቃለን፡፡

አድራሻ፡- ሻሎም የሕፃናት ማሳደጊያ ልዩ ስሙ ሀይቅ ዳር ክፍለ

ከተማ ቀበሌ ጉዱመሌ

ሀዋሳ ስልክ ቁጥር 0462211033

ወይም ሀዋሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ

ኮርፖሬሽኑ ምንም ዓይነት የፋይናንስ እጥረት

አልገጠመውምየኢፌዲሪ ስኳር ኮርፖሬሽን መንግሥት የነደፈውን

የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ መሠረት በማድረግ በአምስት ዓመታት ውስጥ አሥር አዳዲስ የሥኳር ፋብሪካዎችን ለመገንባት አቅዶ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ በነባር የስኳር ፋብሪካዎች ላይም ከፍተኛ የማስፋፊያ ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል:: ዓላማውም አሁን በሒደት ላይ የሚገኙ የማስፋፊያና አዳዲስ የስኳር ልማት ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅ በአምስቱ ዓመት ዕቅድ መገባደጃ ላይ የአገራችን ስኳር የማምረት አቅም አሁን ከሚገኝበት በአምስት እጥፍ እንዲያድግ ማድረግ ነው::

የስኳር ልማት ዘርፉ በአምስት ዓመቱ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ከፍተኛ ትኩረት የተሰጠው በመሆኑም ለቀጣይ ተከታታይ ዓመታትም ሆነ ለያዝነው በጀት ዓመት በቂ የሥራ ማስፈጸሚያ በጀት ተመድቦለት ሥራው በከፍተኛ ርብርቦሽ በመከናወን ላይ ይገኛል:: በያዝነው በጀት ዓመት እንኳን በአጠቃላይ ለነባርና አዳዲስ ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ የተመደበው በጀት 18.3 ቢሊዮን ብር ሲሆን፣ የኦፕሬሽን በጀቱን ሲጨምር በጠቅላላው ወደ 20.3 ቢሊዮን ብር ነው::

እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ እሁድ ህዳር 10 ቀን 2004 ዓ.ም. በወጣው ሪፖርተር ላይ ‹‹ስኳር ኮርፖሬሽን የፋይናንስ እጥረት ገጥሞኛል አለ›› በሚል ርዕስ ፈፅሞ በየትኛውም መድረክ ላይ ያልተገለጸና ዓርብ ህዳር 8 ቀን 2004 ዓ.ም. በተወካዮች ምክር ቤት ከንግድና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮማቴ ጋር በተካሄደው ውይት ላይም ፈፅሞ ያልተጠቀሰ፣ የተዛባና በየትኛውም ሪፖርት ላይ ያልቀረበ ዘገባ ታትሞ ወጥቷል::

ዘገባው አያይዞም በመጠናቀቅ ላይ የሚገኙት የማስፋፊያ ፕሮጀክቶች ከተጠበቀው በላይ ወጪ ማስከተላቸው በአዳዲስ ፕሮጀክቶች ላይ ጫና እንዳሳደረና ከባንክ የሚገኘው ገንዘብ የራሱ ጣራ ያለው መሆኑም የገንዘብ እጥረቱን በብድር ለመሸፈን እንዳይቻል ተፅዕኖ መፍጠሩን ኮርፖሬሽኑ እንደገለጸ አድርጎ አቅርቧል::

በመሠረቱ ኮርፖሬሽኑ የሚያካሂዳቸውን ነባርም ሆነ አዳዲስ ፕሮጀክቶች ለማከናወን ያጋጠመው ምንም ዓይነት የፋይናንስ እጥረት የለም:: የማስፋፊያ ፕሮጀክቶቹ በተያዘላቸው ጊዜ አለመጠናቀቅ ከፕሮጀክቶቹ ሊገኝ ይችል የነበረውን ተጨማሪ ገቢ ለጊዜው እንዳይገኝ አድርጓል የሚል

እንደ አስተያየት ከመቅረቡ ውጪ ከእነዚህ ፕሮጀክቶች ገቢ ባለመገኘቱ ምክንያት አዳዲስ ፕሮጀክቶች እንዳይከናወኑ ያደረገበት ሁኔታ የለም:: ምክንያቱም ለሁሉም ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ በቂ በጀት ተመድቦ እየተሠራ ነውና:: ኮርፖሬሽኑ ከባንክ የሚያስፈልገውን ብድር ሁሉ አግኝቷል፣ የብድር ጣሪያ ገድቦታል የተባለውም ሐሰት ነው::

ስለዚህ ጋዜጣው በቀረበው ሪፖርተር ላይ ግልፅ ያልሆነ ጉዳይ ቢኖር ኮርፖሬሽኑን ጠይቆ በመረዳት ትክክለኛ መረጀ ማስተላለፍ ሲገባው፣ ከእውነት የራቀና በኮርፖሬሽኑ ያልተገለጸና የተዛባ ዘገባ ማቅረቡ ፈፅሞ ተገቢ አለመሆኑን ማስገንዘብ እንወዳለን::

በመሠረቱ አንድ ኃላፊነት የሚሰማው ፕሬስ ሊከተለው የሚገባው ሙያዊ ስነምግባር ለእውነት መቆምና እውነትንና እውነትን ብቻ ለሕዝብ ማድረስ ነው:: ጋዜጠኛው በትክክለኛ እውቀት ላይ የተመሠረተ፣ ተጨባጭነት ያለውና በትክክለኛ ማስረጃ የተደገፈ ዘገባ ቅንነት በተሞላበት መንፈስ ለሕዝብ የማቅረብ ሙያዊ ግዴታ አለበት:: በተሰማራበት የጋዜጠኝነት ሙያ አማካኝነት ያገኘነውን አጋጣሚ ለግል ፍላጎቱ የሚያውል ጋዜጠኛና የሜዲያ ተቋም እያደር በሕዝብ ዘንድ ያለውን ታማኝነት እያጣ ይሄዳል:: የሚፈለገውን መረጃ ጠይቆ ማግኘት እየተቻለ ጨረፍታ ይዞ አንድ ጉዳይ ከተገለጸበት አውድ ውጪ ማቅረብ ተገቢ አይደለም:: ማንኛውም የሚያቀርበው ዘገባ ከየአቅጣጫው ጉዳዩ የሚመለከታቸውን አካለት ሐሳብና ማብራሪያ ያካተተ እንዲሆን ይጠበቃል፣ ይገባልም:: ከዚህ አኳያ ሲታይ ጋዜጣው የተከተለው የዘገባ አቀራረብ ተገቢውን የሚዲያ ሥነ ምግባር የተከተለ ነው ማለት አይቻልም:: በጉዳዩ ላይ ግልፅ ያልሆነ ነገር ካለ ኮርፖሬሽኑን ጠይቆ ማብራሪያ ሊያገኝ ይችል ነበር:: ነገር ግን ጋዜጣው ይህን አላደረገም:: ስለዚህ ኮርፖሬሽኑን አስመልክቶ ጋዜጣው ያቀረበው ዘገባ ፍፁም ሐሰትና ከእውነት የራቀ መሆኑን አንባቢያን እንዲረዱት እንፈልጋለን:: ከዚህም አልፎ የተለያየ አሉባልታ በመንዛት መርሃ ግብሩ አይሳካም የሚል መልዕክት ለማስተላለፍ በተለያየ ፀረ ልማት ስልት እየተደረገ ያለው ዘመቻ አገርንና ወገንን ከመጉዳት አልፎ የሚፈይደው ነገር እንደሌለ ግልፅ ሊሆን ይገባል::

ስኳር ኮርፖሬሽን

ከአዘጋጁ እሁድ ኅዳር 10 ቀን 2004 ዓ.ም. ታትሞ በወጣው ሪፖርተር ጋዜጣ ላይ “ስኳር ኮርፖሬሽን የፋይናንስ እጥረት ገጥሞኛል አለ” በሚል የወጣው ዘገባ ስህተት መሆኑን ከላይ እንደተጠቀሰው ኮርፖሬሽኑ ለሪፖርተር በላከው ደብዳቤ አስታውቋል::

ነገር ግን ኮርፖሬሽኑ የ2003 ዓ.ም. ጥቅል የአፈጻጸም ግምገማና የ2004 ዓ.ም ዕቅድና በጀት በሚል ርዕስ በገጽ 4 እና 5 ላይ

ባቀረበው ሪፖርት፣ የገንዘብ እጥረት የገጠመው መሆኑን በግልጽ አስቀምጧል:: የገንዘብ እጥረት መኖሩን የሚገልጸውን ይህንኑ ሪፖርት፣ እንደሚከተለው ቀንጭበን አቅርበነዋል::

አዳዲስ ፕሮጀክቶችን በተመለከተ

የአዳዲስ ፕሮጀክቶችን ጥናትና ዲዛይን እንዲሁም የኮንስትራክሽን ሥራ በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ለማከናወን የሚችሉ የመፈጸም አቅም ያላቸው ተቋማት አለመኖር፣

አቅም እየገነቡ ለመሥራት ቢሞክርም የአምስት ዓመቱን መጠነ ሰፊ የስኳር ልማት

ዕቅድ በወጣው ፕሮግራም መሠረት ለማካሔድ ከኮርፖሬሽኑ የስኳር ሽያጭ የሚገኘው የስኳር ኢንዱስትሪ ልማት ፈንድ አነስተኛ መሆንና በዚያው ልክ ለአዲስ ልማት የሚያስፈልገው ገንዘብ ከፍተኛ በመሆኑ የሚከሰት የፋይናንስ እጥረት መኖር፣

በመጠናቀቅ ላይ የሚገኙት የማስፋፊያ ፕሮጀክቶች ከተጠበቀው በላይ ወጪ ማስከተላቸው እንዳለ ሆኖ በመጠናቀቂያ ዓመታቸው የሚፈልጉት ፋይናንስ አዳዲስ ፕሮጀክቶች ፋይናንስ ላይ ጫና ማሳደሩ፣

ልማቱን ለመደገፍ ከባንክ የሚገኘው ገንዘብ የራሱ ጣራ ያለውና የፕሮጀክቶቹም የፊዚካል ዕቅድ በዚሁ መሠረት መቃኘቱ አስገዳጅ መሆኑ::

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 21 | እሑድ | ኅዳር 17 ቀን 2004 ክፍል-1

ደ ላ ላ ው

እንደ ልማዴ ጠዋት ተነሳሁና የማንጠግቦሽ ወርቅ እጅ የፈረፈረውን ልሰለቅጥ ቸኮልኩ:: ፓ! ያ ጥዑም ፍርፍር ታየኝ:: ይኼኔ ለፍርፍር ስቋምጥ ብታይ “አይ ሐበሻ ያው መሆን አይቀር! እንጀራን በእንጀራ ይበላል” ብሎ የሚያሽሟጥጠኝ አይጠፋም እኮ። እዬዬም ሲደላ አሉ። እንጀራንም በእንጀራ አዳብለው የሚበሉ እኮ የታደሉ ናቸው:: ‹‹እሱ የከፈተውን ጉሮሮ ሳይዘጋው አያድርም›› የምትለዋ ተረት እንደ ዳቦ በግራም አሳባ ወጪ ያልጨመረችባቸው ናቸው። በዚህ ጊዜም ቢሆን ታዲያ ምንም ህሊናቸውን ሳይቀፈው አላግባብ መበልፀግን እንደ ጥሩ ሥራ ፈጣሪነት፣ ሥልጡንነትና ልማታዊነት የሚቆጥሩም ቁጥራቸው አልቀንስ ብሏል።

ማንጠግቦሽን ያገናኙኝን ሰዎች፣ ሰዓታትና ደግ ደግ

ዓመታት በእኔና በባዶ ሆዴ ስም አመሰገንኩ:: ይኼኔ እኮ ምስጋና ኪስ አይገባም ብለውኝ ይሆናል:: አሁን እኔ ኪስ ውስጥ ምን ይገኛል በእናታችሁ? ባለውለታና ዘመድ አልኖርህ ብሎኝ ነው እንጂ ቤቴ ተጣጥፌ የተቀመጥኩት:: መቼም ይህችን የመመሰጋገንና የመፈላለግ ነገር ካነሳን ላይቀር ትንሽ እንበል።

አሁን አሁን ወዳጅ ዘመድ ቤት ሄዶ መጠያየቅ ያን ያህል እየሆነ ነው። ስለዚህ ነገር አንስተን ከባሻዬ ልጅ ጋር ስንጫወት ምን አለኝ መሰላችሁ? ‹‹በአሁን ዘመን ልጠይቀው ብለህ ወዳጅህ ወይ ዘመድህ ዘንድ ብትሄድ ተጣልተህ ልትመጣ ትችላለህ፤›› አለኝ። ግርም እያለኝ ‹‹እንደ አውሬ ክትት እያለ ሰው እርስ በርሱ ሽሽት በያዘበት ጊዜ ወዳጄን ብጠይቀው ለምን ብሎ ነው የሚቀየመኝ?›› ብዬ ጠየቅኩት። ‹‹አይ አንበርብር የእኛ ሕዝብ እኮ ብቻውን መብላት አይችልም። ሆኖም በዚህ የኑሮ ዙር በከረረበት ቀውጢ ጊዜ እንኳን የሚያካፍለው ራሱንም መመገብ አቅቶታል። በምግብ ራሳችንን ሳንችል ዘለን እንጣጥ እንጣጥ ማለት ምን የሚሉት ነው? ላያዋጣን ነገር ራሳችንን መቻልን ችላ ብለነው ይኼው እዛው ተጎልተው፤›› አለኝ። ትንሽ ቆየና ‹‹ተወው የእኛ ነገር እንቁራሪት በሬን አክላለሁ ብላ ተሰንጥቃ ሞተች ዓይነት ነው። መጀመሪያ በምግብ ራሳችንን ነፃ ሳናወጣ በከንቱ እንቆለላለን። ለማንኛውም የምትጠይቀው ዘመድህ ወይም ወዳጅህ ለምን እንደሚቀየምህ ታውቃለህ?›› አለኝ:: ለምን አልኩት:: ‹‹በአንድ ጉዳይ ላይ መወያየት ስትጀምር በሐሳብ መለያየት ትጀምራለህ:: ይኼኔ ጉድለቴን አወቀው ብሎ ይጠምድሃል። ስለዚህ አርፈህ መቀመጥን የመሰለ ነገር የለም፤›› ብሎኝ ነበር። እውነት ነው! እኛ የሐበሻ ልጆች ‹‹ገመና›› የሚል ድራማ እንጂ የራሳችንን ጉድለት የሚያሳየንንና የሚጠቁመንን ገመና ገላጭ አንፈልግም። ‹‹ተከድኖ ይብሰል›› እያልን ውስጥ ለውስጥ እንንተከተካለን:: ቅድሚያ ለሐሜት እየሰጠን

እንበላላለን::ቆይ እኔ ምለው ይኼ “ሙሰኛ” እና ‹‹ኪራይ ሰብሳቢ››

የሚባለው ተለጣፊ ስም እንደ መኪና ቦሎ በግዴታ ሰው ላይ መለጠፍ ጀመረ እንዴ? እንዴት መሰላችሁ እንዲህ ማለቴ፣ አንድ ለማኝ መጣና ኮስተር ብሎ ‹‹ትሰጠኛለህ ወይስ አትሰጠኝም?›› ብሎ አፋጠጠኝ። በውስጤ ደግሞ እንዴት ያለ አለማመን መጣ? ልመናም አብዮት ሊያስነሳ ይሆን? እያልኩ ‹‹ምን?›› ስል ጠየቅኩት። ‹‹ደግሞ ምን ትለኛለህ እንዴ? የበላኸውን ነዋ አንት ኪራይ ሰብሳቢ ሞላጫ ሌባ›› እያለ በአደባባይ ዘልፎኝ ሲያበቃ ፎክሮብኝ ሄደ። ይኼኔ ነበር በዚህ አጋጣሚ ስንቶች ንፁኅን እንደሚንገላቱና እንደሚኮነኑ የገባኝ።

አዬ! ባልበላ አንጀቴ ከምቃጠል ባይሆን ትንሽ ልቀማምስ ብዬ ከአልጋዬ ወረድኩና ማንጠግቦሽን ብፈልጋት እሷ እቴ የለችም! ሁሉንም ትታው እንደወትሮው የምትቀማምሳት ብላ ምንም ሳታስቀምጥልኝ እልም ብላለች:: ይህች ሴትዮ ልታሳብደኝ ነው እንዴ? ቁርሴን ሳትሠራ የት ነው የሚያሮጣት እያልኩ ሳስብ ለሴቶች የተጠራ ስብሰባ ላይ ለመታደም ቀበሌ በራለች:: ለመጀመሪያ ጊዜ የሴቶች የመብትና የእኩልነት ጥያቄ ልቤ ውስጥ ደወለ:: ለካ እንደዚህ ነው ነገሩ? የሴቶች የመብት እንቅስቃሴ እያደገ መሄዱ የገባኝ ማንጠግቦሽ ቁርሴን መሥራቷን ስታቆም ነው:: መጨቆኗን አልወደውም:: ከማናችሁም በላይ ለመብቷና ለእኩልነቷ የምቆረቆረው እኔ ውድ ባለቤቷ ነኝ:: ባለሙያነቷንም አደንቀዋለሁ እፈልገዋለሁ:: ጭራሽ ኑሮ እንዲህ ከብዶ ሳለ ያለችዋም ጣፍጣ ካልተበላች ከዚህ ይበልጥ ምን መኖርን የሚያስጠላ አለ ትላላችሁ? ጭራሽ ብሎ ብሎ ሚስቶቻችንም ተወደዱና አረፉት ማለት ነው? ኑሮስ እሺ በነዳጅ ዋጋ መጨመር፣ በምንዛሪ ዋጋ መናር ነው ይባል:: ሴቶቻችን እንዲህ ከቤታቸውና ከፍቅራቸው የሚያርቃቸው የመብት ዋጋ መኖር ነው ሊባል ነው? ሃሃሃ ሳይወዱ አይስቁ አለ ያገሬ ሰው::

ጓዳ ገብቼ ማንጎዳጎዱን ሳስበው የማልችልበትን መሞከሩ ከንቱ ነው አልኩ። ካፖርቴን ደርቤ ከቤት ወጣሁ። ሙያን ከእናቴ ቀጥሎ እንደ ማንጠግቦሽ ካለች ባለሙያ ሚስት መማር አንደነበረብኝ ሳስብ ቆጨኝ:: መች ይኼ ይመጣል አልን? አስቀድመን የጊዜያችንን ክስተት ማወቅ ብንችል ዓለማችን እንዲህ በፈርጀ ብዙ ቀውሶች ትናወጥ ነበር? እንዲያው ግን ዝም ብዬ ሳስበው ነገን የማየት ልዩ ችሎታ ያላቸው ናቸው የኪራይ ሰብሳቢነት ማጥ ውስጥ የሚዘፈቁት እላለሁ::

ነገን የማየትና የማቀድ ልምድ ክህሎት የሚገኘው ከሕዝብ ጉሮሮ እየነጠቁ ከሆነስ ይቅር:: ‹‹የሰው ገንዘብ በልቶ እንቅልፍም አይተኙ›› ነውና ተረቱ::

ከቤቴ ልክ እንደወጣሁ ማንጠግቦሽ የፆታ አቻዎቿን ሰብስባ ምናምኑን እየሰበሰበች ታቃጥላለች:: እንዲያ ተሰባስበው ሳያቸው የታህሪር አደባባይ ሠልፍ ውስጥ የገባሁ መሰለኝ:: የሠልፉ መሪ ደግሞ ማንጠግቦሽ ትሆን ብዬ ሳስብ ብርክ ያዘኝ:: ዘልዬ ሄጄ ‹‹ምን መሆንሽ ነው?›› ስል ጠየቅኳት:: ‹‹ውይ ተነሳህ እንዴ አንበርብርዬ በል መጣሁ ጠብቀኝ ዛሬ እኮ ህዳር ሚካኤል ስለሆነ ቆሻሻ ላቃጥል ወጥቼ ነው እንጂ አልረሳሁህም፤›› አለችኝ ተረጋግታ:: አስተውዬ ሌሎችን ሳያቸው በሰላም ተረጋግተው ቆሻሻ እያቃጠሉ መሆኑን አጤንኩ:: ዞረብኝ። ስላልበላሁ ይሆን ክፉ ክፉውን የማስበው? ስለማንበላ ይሆን ክፉ ክፉ እያሰብን በነገር የምንዘነጣጠለው ያስብላል:: በሐሜትና በምቀኝነት በተፈተለ ቢሮክራሲ ተተብትበን ስንታይ እውነትም ያሰኛል::

ወዲያው ሳይታወቅብኝ “ነው እንዴ? እኔኮ ምን ሆናብኝ ነው? በሰላም ይሆን ያጣኋት? እያልኩ አሰብኩ እኮ፤” ብዬ አብሬያት ትንሽ ቆምኩ:: ይኼኔ

እኮ ሁሉም እኔን እያዩ ለሚስቱ የሚቆረቆር ውድ ባል ነው እያሉ ይሆናል:: ‹‹ልማታዊ አፍቃሪ›› ሳይሉኝ ይቀራሉ ብላችሁ ነው? እንዲህ እያሰብኩ ሳለሁ ባሻዬ ክልፍ ክልፍ ሲሉ በፍጥነት መጡ። “ወይኔ እንቅልፍ ሠራልኝ:: ደህና አደራችሁ?” ብለው ተቀላቀሉን:: “ምን ነው ባሻዬ ቀጠሮ አለዎት እንዴ ዛሬ?” አልኳቸው:: ያለወትሯቸው በዚህ ጠዋት ምን ይሠራሉ እያልኩ በውስጤ። “ታዲያሳ! ዛሬ እኮ ህዳር ሚካኤል ነው:: ያኔ የበሽታ ወረርሽኙን ይጠራርግልናል ብለን ቆሻሻ ሰበሰብን አቃጠልን:: እንዳሰብነው ሆነና ድራሹን አጠፋልን:: አሁን ታዲያ ይኼን ሸረኛ፣ ሙሰኛ፣ ምቀኛ፣ ሐሜተኛ፣ ውዥንብር ፈጣሪን፣ የኑሮ ውድነትንና ያሉብንን ችግሮች እንዲጠራርግልን በማሰብ እዚህ ቀጠሮ ይዘን ነበር፤›› አሉና ሁሉንም ሠፈርተኛ እያዩ በዓይናቸው ሰላምታ ሰጡ:: “ታዲያ ባሻዬ ለእንዲህ ያለ መልካም ሐሳብ ምን ነው አልጠሩኝ?” አልኳቸው:: “እግርህ ከተማውን ሙሉ ሲዞር፣ ጭንቅላትህ በነገር ሲወጠር፣ ኪስህ በወጪ ሲቦን እየዋለ ደግሞ ከእንቅልፍ ብትጎል በሰማይ ቤት አንጠየቅም? ነውር ነው። ለእንዲህ ያለው ተግባር እኛ እንበቃለን፤” አሉና እሳቱን ሊያነዱ አጎንብሰው ይቆሰቁሱት ገቡ። ካልቆሰቆሱት አይነድም ነዋ የሚባለው። ቆሻሻን ማቃጠል ግን የበለጠ አየር መበከል መሆኑን ልነግራቸው ይገባኛል::

ቆሻሻ እያቃጠልን ሠፈርን በአስከፊ ጭስ ከምናውደው አካባቢያኝን እያፀዳን ቆሻሻውን ለሌላ ተግባር መገልገል እንደምንችል ሰበኩኝ:: ቆሻሻ ማቃጠል አየሩን በመበከል ለበሽታ የሚዳርግ ሽታ ማምጣት ስለሆነ ይህ ባህል መቀየር እንዳለበት በሚገባ ተናገርኩ:: መልዕክቴ ገባቸው መሰል ሁሉም አንገታቸውን ነቀነቁልኝ:: ባሻዬ ግን፤ ‹‹ቆሻሻ ሲቃጠል መጥፎ መንፈስም እንደሚቃጠል መርሳት የለብንም፤›› አሉ:: እኔ ደግሞ ‹‹የለም መጥፎ መንፈስን ከቆሻሻው ጋር ወደ መጣያው ቦታ መወርወር እንችላለን፤›› በማለት ሞገትኩ:: ባሻዬ ነገሬ ባይጥማቸውም ለጊዜው ዝም አሉ:: በሐሳብ ብንለያይም የብዙኅን ድምፅ እንደሚገዛን ማወቅም ትልቅ ፀጋ ነው:: መደማመጥ የጠፋ ዕለት ነው መፍራት ያለብን:: ፍርኃት የሚባለው ጠላታችን እንዳይነግስ እስቲ እንደማመጥ::

ችግሮቻችንና ሸክሞቻችን እነባሻዬ እንዳሰቡት እንደ ጭስ በነው የሚጠፉ ቢሆኑማ በየቀኑ ከተማውን እናጥነው አልነበር? አይ ልማድ? ነገሩ ጨንቋቸው እንጂ ጭሱ አየር ከመበከል ባለፈ የአንዳንድ ሰዎችን የተበከለ አስተሳሰብ ያሽራል ብለው አምነው አይደለም። አዎ! ‹‹የጨነቀው እርጉዝ ያገባል›› ሲባል አልሰማችሁም? ኑሮ ከበደን ብለን መፍትሔ ፍለጋ እንጮኻለን:: መፍትሔ እንካችሁ ከማለት በየጋዜጣውና በየቴሌቪዥኑ ኑሮ እየከበደ መምጣቱን እንደ ገደል ማሚቶ መልሰው ይተርኩልናል። ለቀባሪው ማርዳቱን ትተው መፍትሔውን ቢፈልጉ? ብልሹ አሠራሮች ተወግደው በመፍትሔ አዘል አዲስ አሠራር የሚታጠኑበት እንዲሆንልን ተመኘሁ። ህዳር ሲታጠን እያልን በተበከለ በጭስ ከምንታፈን ብልሹ አሠራሮችን እንጠናቸው:: መልካም ሰንበት!

ብልሹ አሠራሮች ይታጠኑ

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 22 | እሑድ |ኅዳር 17 ቀን 2004ክፍል-1

ሪፖርተር፡- ለመንገድ ግንባታ በጀታችሁን የምትሸፍኑት እንዴት ነው? ከአስተዳደሩ ከሚመደብላችሁ በጀት ሌላ አማራጭ የፋይናንስ ምንጭስ አላችሁ?

ኢንጂነር ፍቃዱ፡- የመንገድ ግንባታ ከፍተኛ በጀት የሚጠይቅ ሥራ ነው:: ስለዚህ ከመጀመሪያው ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄደ ያለው የመንገድ ግንባታ አስተዳደሩ በሚያገኘው በጀት ላይ የተመሠረተ ነው:: ስለዚህ በራሱ በሚያገኘው በጀት ላይ ተመሥርቶ እየሠራ ነው ቢባልም፣ ከሚታመነው በላይ ተሠርቷል:: የከተማውን ልማት ስትመለከት ብዙዎቹ ነዳጅ አግኝተን የምንሠራቸው የሚመስሉ ናቸው:: ምክንያቱም በአንድ ዓመት ውስጥ ከ60 እስከ 70 ፕሮጀክቶች ናቸው የሚካሄዱት:: እነዚህን ፕሮጀክቶች ማካሄድ በጣም ከባድ ሆኖ ስለሚታይ ነው እንጂ፣ አሁን ከተማችን ያላት የመሠረት ልማት ኔትወርክ 3 ሺሕ 512 ኪሎ ሜትር ነው:: የዚህን ሽፋን ከለማው አካባቢ ጋር ሲተያይ 12.9 በመቶ ነው:: ይህንን ደረጃ በተለይ ከሰሐራ በታች ካሉ አገሮች ጋር ስታስተያየው ልዩነት አለ:: የእነሱ ከ20 እስከ 25 በመቶ ነው:: ከዚህ አንፃር ገና ብዙ መሥራት እንዳለብን ነው የሚያሳየው:: ስለዚህ የመንገድ ግንባታ ሥራው ከፍላጐቱ አኳያ በቀጣይ አስተዳደሩ በሚመድብለት በጀት ብቻ ለመቀጠል እንደማይችል ባለፉት ሁለትና ሦስት ዓመታት ታይቷል:: በእኔ እምነት የአዲስ አበባ የመንገድ ግንባታ ሒደት የፌዴራል መንግሥትም ኃላፊነት ሊሆን ይገባል:: ምክንያቱም የውጭ ዕርዳታዎች የሚስተናገዱት በፌዴራል መንግሥት አማካይነት ስለሆነ፣ የፌዴራል መንግሥት ሌሎች ዓለም አቀፍ አበዳሪዎችና ዕርዳታ ሰጪዎች ፍላጐት ኖሯቸው አዲስ አበባ ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ ማድረግ ይችላል:: እንዲህ ቢደረግ አሁን ካረጋገጥነው የመሥራት አቅም በላይ ገንዘብ ብናገኝ ብዙ መሥራት እንችላለን::

ሪፖርተር፡- አስተዳደሩ በራሱ መንገድ ከውጭ ብድርና ዕርዳታ የሚያገኝበት አሠራር የለውም?

ኢንጂነር ፍቃዱ፡- እኛ በራሳችን አልፎ አልፎ የምንሄድባቸው አሉ:: ለምሳሌ በራሳችን መንገድ የውጭ መንግሥታት በብድር እንዲያግዙን ያደረግንበት ሁኔታ አለ:: ለምሳሌ ለቀለበት መንገዱ ወደ 200 ሚሊዮን ብር ከቻይና መንግሥት ተገኝቶ ተሠርቷል:: ከዚያ በኋላም የኢትዮ-ቻይና ወዳጅነት መንገድም በዚህ መልክ ነው የሠራነው:: የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች አደባባይ (የጐተራ ማሳለጫ) የተሠራው በዕርዳታ ነው:: ከዳያስፖራ አደባባይ በቀበና አድርጐ ምኒሊክና አራት ኪሎ የሚወስደው መንገድ የከተማው አስተዳደር ራሱ ሄዶበት በዕርዳታና በብድር የተሠራ ነው:: ይህ በጣም ጥቂቱ ነው:: ስለዚህ በቀጣይ እንዲህ ባለው ዕርዳታና

ብድር የምንታገዝበት ሁኔታ ካልተፈጠረ፣ በተለይ አሁን በመንገድ ግንባታ ላይ እየታየ ባለው ከፍተኛ ዋጋ አስተዳደሩ በሚመድበው በጀት ብቻ የተፈለገው ያህል መሥራት አይቻልም:: ስለዚህ እንደተባለው የውጭ ድጋፍ ቢኖር ይመረጣል::

ሪፖርተር፡- መሥሪያ ቤታችሁ ባለፉት ሁለትና ሦስት ዓመታት የጠየቀውን ያህል በጀት ከአስተዳደሩ ማግኘት ካለመቻሉም በላይ፣ በተለይ ባለፈው ዓመት ከቀዳሚው በጀት ዓመት ያነሰ በጀት ተመድቦለታል:: በጀታችሁ ለምን ተቀነሰ?

ኢንጂነር ፍቃዱ፡- በከተማው ውስጥ እንደሚታወቀው ሁሉም ነገሮች አንደኛ ደረጃ ጥያቄ ናቸው:: አንድም የወረደ ጥያቄ የለም:: ሁሉም ቅድሚያ የሚሰጣቸው ናቸው:: መንገድ፣ ውኃ፣ የኮንዶሚኒየም ቤት ግንባታ፣ ትምህርትና ጤና ላይ የሚሠራ ሥራ ቅድሚያ የሚሰጠው ነው:: ከዚህ አኳያ አስተዳደሩ ከሚያገኘው ገንዘብ ላይ ለእነዚህ ሁሉ ማዳረስ ይጠበቅበታል:: ስለዚህ በሌሎች ዘርፎች ላይ የሚያወጣቸው ወጪዎች እየጨመረ ሲመጡ ከመንገድ ላይ የማሸጋሸግ ሁኔታ ነው የተደረገው::

ሪፖርተር፡- ከመንገድ ግንባታ ጋር ተያይዞ በተደጋጋሚ ትችት ከሚቀርብባቸው ጉዳዮች መካከል መንገዶች ያለጥራት መገንባታቸው፣ የፍሳሽ መስመር ሳይኖራቸው መሠራታቸውና የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ:: እንዲህ ዓይነት ችግሮች ግንባታዎች ከመደረጋቸው በፊት የዲዛይን ሥራ ላይ ቀድሞውኑ የታሰበበት አይመስልም ይባላል::

ኢንጂነር ፍቃዱ፡- አሁን በከተማው ውስጥ የፍሳሽ መስመር ችግር የሚታይባቸው ነባሮቹ መንገዶች ናቸው:: ችግሩ ደግሞ ሊቃለል የሚችለው በእነዚህ ነባር መንገዶች የማሻሻል ሥራ በመሥራት ነው:: እነዚህ መንገዶች በሚሠሩበት ጊዜ የነበረው የፍሳሽ መጠንና አሁን ዓመታት ካስቆጠሩ በኋላ ወደ መንገዶቹ የሚገባው የፈሳሽ መጠን በጣም ተለያይቷል:: የተቀበሩት የውኃ ማስተንፈሻ ቱቦዎች ይህንን አገልግሎት እየሰጡ አይደለም:: መቀበል ካልቻሉ ደግሞ ያለው ወይም የሚመጣው ችግር መንገዶቹ ላይ ውኃ በብዛት ተተፍቶ አስፓልቱን ማበላሸት ነው:: ከዚህ አንፃር በነባሮቹ መንገዶች ላይ የጥገናና የመጥረግ ሥራ ከማከናወን ያለፈ መሠረታዊ ለውጥ የሚያመጣ ሥራ መሥራት አይቻልም::

ሪፖርተር፡- መሠረታዊ የሆነ ለውጥ ለማምጣት ለምንድነው የማይቻለው?

ኢንጂነር ፍቃዱ፡- እነዚህ መንገዶች እንደገና መሠራት ስላለባቸው ነው:: እንደገና መሥራት አለባቸው:: ሙሉ በሙሉ ለመሥራት መንገዱ እንደገና መሠራት አለበት:: አንድ መንገድ የተወሰነ ዓመት

ካገለገለ በኋላ ማሻሻልና አቅሙን ማሳደግ የግድ ነው:: ስታሻሽለው እነዚህን የፍሳሽ መስመሮች ሁሉ መቀየር ይጠይቃል:: አሁን ያላቸው ስፋት 60 ሴንቲ ሜትር ከሆነ በቀጣይ ከአንድ ሜትር በላይ ነው የሚፈልጉት:: የቦሌ መንገድ ችግር ይህ ነው:: የቦሌን መንገድ ዝም ብሎ ለተመለከተው በክረምት ወራት በተለይ ካራማራ አካባቢ ያለው ድልድይ ድረስ ውኃ ሞልቶ የሚታይበት ምክንያት፣ ከላይ ጀምሮ ያሉት የፍሳሽ መስመሮቹ ስትራክቸሮች ሞልተው የሚተፉ እንጂ ፍሳሹን ይዘው የሚቀጥሉበት አቅም የላቸውም:: እነሱ ራሳቸው የያዙትን ውኃ ወደ አስፓልቱ ነው የሚተፉት:: ይህም የሆነው ጠባብ ስለሆኑ ነው:: ከአስፓልቱ የሚመጣውን ተጨማሪ ውኃ ሊያስተናግዱ አልቻሉም:: ስለዚህ በዚህ አካባቢ በቀጣይ የሠራነው ዲዛይኑን የመቀየር ሥራ ሲሆን፣ በዚህም የፍሳሽ መስመሩን መጠን እንዲሰፋ አድርገናል::

ሪፖርተር፡- ነባሮቹን መንገዶች እንተዋቸውና በቅርብ በተሠራው የቀለበት መንገድ ላይ በተለያዩ ቦታዎች ላይ በክረምት ወቅት ብዙ ውኃ ይተኛባቸዋል:: የፍሳሽ መስመሩም ችግር አለበት:: ይህ ለምን ሆነ?

ኢንጂነር ፍቃዱ፡- በቀለበት መንገድ ላይ በሁሉም ቦታ ችግር አለ ማለት አይቻልም:: የተወሰኑ ቦታዎች አሉ:: በተለይ ትልቅ ችግር ያለባቸው የቀለበት መንገድ ክፍሎች ድልድይና ረባዳ የሆኑ አካባቢዎች ናቸው:: ለምሳሌ ከቦሌ ተነስተን ወደ ዮሴፍ ብንሄድ መጀመሪያ ላይ የምናገኘው ቦታ አንዱ ነው:: ቡልቡላ ድልድይ ከዮሴፍ አቅጣጫ ከሚካኤል አካባቢ የሚመጣው ፍሳሽ ወደ ድልድዩ ነው የሚሄደው:: ድልድዩ ላይ በብዛት ስለሚጠራቀም ወደ ወደ ፍሳሽ ማስወገጃው ለመግባት የተበሱት ቦታዎች ይህንን ፍሳሽ የማስተናገድ አቅማቸው በጣም አነስተኛ ነው:: ነገር ግን መበሳት ያለባቸውን ያህል በስተናቸዋል:: ከዚያ በላይ መብሳት ስትራክቸሩን ማበላሸት ነው:: ስለዚህ የተበሱት አገልግሎት እየሰጡ ነው:: ዝናብ በኃይል በሚወርድበት ጊዜ ግን የግድ ውኃ ይተኛበታል::

ሪፖርተር፡- ይህንን ችግር ለመቅረፍ ሌላ መፍትሔ እንዴት አይኖርም? ይህንን ያህል ዓመት ያለመፍትሔ መቆየት አልነበረበትም የሚሉ ባለሙያዎች አሉ::

ኢንጂነር ፍቃዱ፡- እነዚህን ነገሮች ለማስተካከል ሌሎች ዕርምጃዎች መወሰድ አለባቸው:: ጥናትም እያጠናን ነው:: ጥናቱም ውኃው ከሚካኤልም ሆነ ከዮሴፍ አቅጣጫ ዳገቱን ጨርሶ ወደ ረባዳው በሚመጣበት ጊዜ ይህንን ፍሳሽ የሚቀለብሱና ውኃውን ተቀብለው ወደ ጐን የሚያፈሱ መስመሮች መሠራት እንዳለባቸው ያመለክታል:: እንዲህ ዓይነቱን ሥራ ለመሥራት እያጠናን ነው:: ገንዘቡ ከተገኘ

ይተገበራል:: ብዙዎቹ የፍሳሽ ችግሮችም በዚህ መንገድ ነው ሊስተካከሉ የሚችሉት:: ያለበለዚያ ድልድይ አፍርሶ እንደገና ለመገንባት ምን ያህል ውድ እንደሆነ ይታወቃል:: ሌላው መጀመሪያውኑ የማከፋፈል ሥራ መሠራት ነበረበት:: የፍሳሽ መስመሩ በቀጥታ ወደ ወንዞቹ ከሚያልፍ ወይም ወደ ድልድዮቹ ከሚሄድ በሌላ አቅጣጫ የሚወርድበት ነገር ቢሠራ ሊደርስ የሚችለው የውኃ ክምችት ሊቀንስ ይችል ነበር::

ሪፖርተር፡- ይህ መጀመሪያ ለምን አልታሰበም?

ኢንጂነር ፍቃዱ፡- ይህ አልታሰበም:: ያልታሰበ ነገር ስለሆነ ነው:: ዲዛይኑ ላይም የለም::

ሪፖርተር፡- ከዚህ በኋላ በሚሠሩ መንገዶች ላይ ተመሳሳይ የሆነ ችግር እንዳይከሰት ምን ማረጋገጫ አለ?

ኢንጂነር ፍቃዱ፡- እንደተመለከትነው ከቀለበት መንገዱ ጋር የሚገናኙት መንገዶች ሁሉ ውስጥ ለውስጥ የሚመጡ ስለሆኑና ተሽከርካሪዎች ከእነዚህ መንገዶች ጭቃ ይዘው የሚወጡ በመሆኑ፣ አሁን የጠቀስኳቸውን የውኃ መቀበያ ሲሊንደሮችን ይሞላቸዋል:: እነዚህ ከተከደኑ ውኃው ወደ መንገዱ የሚደርስበት ምክንያት የለም:: አሁን አንዳንዱ ቦታ ላይ እየነቀልን እናስተካክላለን:: ከዚህ በመማር እንደዚህ ዓይነት በማኑዋል የሚሠሩ ፍሳሽ ተቀባዮች በእኛ ከተማ ሁኔታ ሊሠሩ እንዳልቻለ ነው:: ከዚያ በኋላ በሚሠሩ በቀጥታ ወደዚያ እንዲገባ የተደረገበት አሠራር እየተከተልን ነው:: በተመሳሳይ በፍሳሽ ማስወገጃዎች ላይ እንደዚህ ዓይነት ችግር እንዳይፈጠር ድልድዮቹ መዳረሻ አካባቢ አሁን ያልኩህን ዓይነት ፍሳሹን መስበሪያ መስመሮች ይሠራሉ:: በአጠቃላይ ግን ቀለበት መንገድ ላይ ያለውን ሙሉ ችግር ለማቃለል የሚቻለው፣ መንገዱ አሥረኛ ዓመት እየሞላው ስለሆነና ወደ እድሳት የምንሄድ ስለሆነ በዚህ ወቅት ችግሩን ለመፍታት ታስቧል::

ሪፖርተር፡- በከተማው ውስጥ ለሚገነቡ መንገዶች ተብሎ የተለያዩ ግንባታዎች ይፈርሳሉ:: በመንገዱ ግንባታ ሰበብ ግንባታዎቻቸው የሚፈርሱባቸው ባለይዞታዎች ለሚፈርስብን ንብረት የሚሰጠን ካሣ እጅግ አነስተኛ ነው ይላሉ:: ለካሣ የሚሰጠው ገንዘብ የፈረሰውን ንብረት የሚመጥን አይደለም ይላሉ:: ይህ የብዙዎች አስተያየት ነውና እንዲህ ዓይነቶቹን አቤቱታዎች እንዴት ነው የምታስተናግዱት?

ኢንጂነር ፍቃዱ፡- የከተማዋ የመንገድ የካሣ ክፍያ በርካታ ነው:: ሁሉም መንገዶች በለማ አካባቢ የሚሠሩ በመሆኑ የማትከፍለው ዓይነት የካሣ ክፍያ የለም:: አስተዳደሩ ለሚነሳ የውኃ መስመር፣ ለሚነሳ ስዌሬጅ፣ ለሚነሳ የኤሌክትሪክና የስልክ መስመር ካሣ ይከፍላል:: ከዚህ በተጨማሪ ለቤቶች፣ ለአጥሮች

‹‹የውጭ መንግሥታት አብረውን የሚሠሩበት ሁኔታ ከተመቻቸ በርካታ አዳዲስ መንገዶች ይኖሩናል››ኢንጂነር ፍቃዱ ኃይሌ፣ የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅ

ኢንጂነር ፍቃዱ ኃይሌ በአዲሰ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ፋክልቲ የሲቪል ኢንጅነሪንግ ዲግሪያቸውን ካገኙ በኋላ ወደ ሥራው ዓለም የተቀላቀሉት በኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን መሥርያ ቤት ውስጥ ነበር::

በኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ውስጥ ከፕሮጀክት ማኔጀርነት ጀምሮ በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ ሠርተዋል:: ዋና መሐንዲስና የመንገድ ዘርፍ ልማት ፕሮግራም አስተባባሪ በመሆን አገልግለዋል:: ከዚያም በ1995 ዓ.ም. የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆነው ተመድበው እስካሁን በዚሁ ኃላፊነት እየሠሩ ይገኛሉ:: መሥርያ ቤቱን በኃላፊነት ከተረከቡ በኋላ የአዲስ አበባ መንገድ ግንባታ ምን ደረጃ ላይ እንዳለ፣ በተለይም የመንገድ በጀት አጠቃቀም፣ የግንባታዎች መዘግየት፣ ለመንገድ ግንባታ ለሚነሱ ቤቶች ካሣ አከፋፈል፣ በቅርቡ ይጀመራል ተብሎ ስለሚጠበቀው የቦሌ መንገድ ግንባታ፣ በመንገድ ዳርቻ ላይ ባሉ ትላልቅ የቢዝነስ ማዕከሎች ላይ ሊያሳድር የሚችለውን ተፅዕኖና በመንገድ ግንባታ ዘርፍ ከኅብረተሰቡ የሚሰነዘሩ ተደጋጋሚ ጥያቄዎችን መሠረት በማድረግ ዳዊት ታዬ አነጋግሯቸዋል::

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 23 | እሑድ | ኅዳር 17 ቀን 2004 ክፍል-1

ወደ ክፍል-1 ገጽ 30 ዞሯል

በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ለሚነሱት እንዲሁ ካሣ ይከፍላል:: ሙሉ ለሙሉ ለሚነሱት ቦታ የመስጠት ግዴታ አለበት:: ከዚያም የፈረሰባቸውን ንብረት ግምት ወስደው ለፈረሰው ቤት ይመጥናል የሚለውን ገንዘብ ይሰጣል:: ለውኃ፣ ለስልክና ለኤሌክትሪክ መስመሮች የካሣ ግምታቸውን ራሳቸው ነው የሚያወጡት:: እነዚህ አካላት ራሳቸው ግምት እንዲያወጡ የሚደረጉት የመንግሥት አካላት ስለሆኑ ነው:: ለሌሎች የካሣ ክፍያ ተከፋዮች ደግሞ ግምቱን የሚሠሩት የየክፍላተ ከተሞች የመሬት አስተዳደር ባለሥልጣናት ናቸው:: የመሬት አስተዳደሩ የሚሠራበት ተመን አለ:: ይህንን ተከትሎ ልኬት አድርጐ በዚያ መሠረት ክፍያ ይፈጸማል::

ዋናው ጉዳይ እነዚህ ነገሮች እየታዩ መሻሻል የሚደረግባቸው መሆን አለባቸው የሚል ነው የእኛ እምነት:: አንድ ጊዜ ያስቀመጥከውን ይዘህ የዕቃዎች ዋጋ እየጨመረ ባለበት ጊዜ ያንን ይዘህ እጠቀማለሁ ማለት አይቻልም:: ስለዚህ ካልተሳሳትኩ ከሦስትና ከአራት ጊዜ በላይ የአዲስ አበባ አስተዳደር ካቢኔ ከወቅቱ ዋጋ ጋር እንዲጣጣም እያደረገ የካሣ ክፍያዎች እንዲፈጸሙ አድርጓል:: የተነሽዎችን ጥያቄ ከወቅቱ የገበያ ዋጋ ጋር የማጣጣሙ ሥራ ይሠራል:: ይህም ሆኖ ግን አሁን እንደጠቀስከው ብዙዎቹ ቤት የሚፈርስባቸው ሰዎች መጀመሪያ የሠሩትን ዓይነት ቤት መልሰን የምንሠራበት ዋጋ አልተሰጠንም የሚል ቅሬታ አላቸው::

ሪፖርተር፡- እንዲህ ዓይነት ቅሬታ ሲመጣ እንዴት ታስተናግዳላችሁ? አስተዳደሩ የመጨረሻውን የካሣ ክፍያ ማስተካከያ መቼ ነው ያደረገው?

ኢንጂነር ፍቃዱ፡- አሁን በጠቀስኩት አኳኋን አስተዳደሩ እየተመለከተ ያስተናግዳል:: የካሣ ክፍያ ማስተካከያውን በ2003 ዓ.ም. አድርጓል:: በተወሰነ መቶኛ ማካካሻ ይደረግላቸው ተብሎ እንዲስተካከልላቸው ተደርጓል:: ይህ የመሥሪያ ቤታችን ሥራ ሳይሆን የአስተዳደሩ የተለያዩ አካላት ሥራ ነው:: የእኛ ግዴታ ግን እነዚህ የሚመለከታቸው አካላት የሚያመጡትን የካሣ ክፍያ ባስያዝነው በጀት አማካይነት መክፈል ነው::

ሪፖርተር፡- ከመንገድ ግንባታ ጋር በተያያዘ ሁሌም የሚታየው ትልቅ ችግር አንድ መንገድ በተያዘለት የጊዜ ገደብ ያለመጠናቀቁ ጉዳይ ነው:: በተለይ የአገር ውስጥ ኮንትራክተሮች ላይ ይህ ጐልቶ ይታያል:: ለምሳሌ በሁለት ዓመት ያልቃል የተባለ መንገድ ከሦስትና ከአራት ዓመታት በላይ ለምን ይዘገያል?

ኢንጂነር ፍቃዱ፡- አሁን በአጠቃላይ አዲስ አበባ ውስጥ በተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብ ያለቁ ፕሮጀክቶች ብዙ አይደሉም:: ብዙዎቹ ፕሮጀክቶች በኮንትራት ከተገባላቸው ጊዜ በኋላ ቆይተው ነው የሚያልቁት:: ለዚህ ዋነኛው ምክንያት የወሰን ማስከበር ችግር ነው::

በወቅቱ ቤቶችን አንስቶና የሚመለከታቸውን የመሠረተ ልማት አቅራቢ መሥርያ ቤቶች እንዲያነሱ በማድረግ ኮንትራክተሩ ሥራ እንዲቀጥል የማድረጉ ነገር በጣም ጊዜ እየወሰደ ነው:: ይህም ሆኖ ግን ባለፉት ሁለት ዓመታት መሻሻል እየታየ ነው:: እንደሚታወቀው ብዙዎቹ ፕሮጀክቶቻችን ከ1998 እስከ 2000 ዓ.ም. የተጀመሩ ናቸው:: እነዚህ ፕሮጀክቶች ከመጀመሪያውኑ ሲገባባቸው የወሰን ማስከበር ሥራ ተጠናቅቆ ባለመሆኑ ኮንትክተሩ እነሱን እያዳመጠ ነው የሚሠራው:: ይህ በመሆኑ ጊዜ እየፈጀ ነው::

ሪፖርተር፡- ሁሌም የወሰን ማስከበር ጉዳይን በምክንያትነት ማቅረብ ይቻላል? ለወሰን ማስከበሩስ መፍትሔ እንዴት ይጠፋል?

ኢንጂነር ፍቃዱ፡- ይህንን ችግር ለመቅረፍ አንድ አቅጣጫ ተቀምጧል:: ይህም በወሰን ማስከበር ምክንያት የሚዘገዩትን ፕሮጀክቶቻችንን በጊዜ እንዲጠናቀቁ ለማድረግ እንዲቻል፣ በቀጣይ የምንገባባቸው ፕሮጀክቶች ከዚህ ከወሰን ማስከበር ችግር የፀዱ እንዲሆኑ ነው በስትራቴጂ ደረጃ የተቀመጠው:: ስለዚህ የመንገድ ሥራዎችን ለኮንትራክተር ከማቅረባችን በፊት በየክፍለ ከተማው በዲዛይኑ መሠረት እንዲፈርሱ ተደርጐ ሰዎቹም ካሣቸው ተከፍሏቸው ሌሎችም ተቋማት የሚያዛውሩትን ከጨረሱ በኋላ ጨረታ እናወጣለን ብለን አቅደናል:: ይህ ሲደረግ ኮንትራክተሩ ወደ ሥራ ይገባል፤ በአንድ ጊዜ ኃይሉን ተጠቅሞ በአጭር ጊዜ ይሠራል የሚል አቅጣጫ ተቀምጧል:: ሌላው ችግር የዲዛይን ነው:: ዲዛይኖች በየጊዜው ዕጣ ፈንታቸው መከለስ ነበር:: ይህም ለመንገድ ግንባታ በወቅቱ አለመጠናቀቅ ምክንያት ሆኗል::

ሪፖርተር፡- ለምንድነው በተደጋጋሚ ዲዛይኖች የሚከለሱት?

ኢንጂነር ፍቃዱ፡- የሚፈለገውን ደረጃ ባለማሟላታቸውና ካለው ሁኔታ ጋር ባለመገናዘባቸው እንደገና እንዲስተካክሉ እየተደረገ ይህንን በማስተካከል ሒደት ላይ ጊዜ የፈጁበት ሁኔታ አለ:: ይህም ለመንገዶቹ መዘግየት እንደምክንያት የሚታይ ነው:: ሌላው የኮንትራክተሮቹ አቅም ነው:: የኮንትራክተሮቹ አቅም በብዙ ሁኔታ የሚገለጽ ነው:: የማኔጅመንት፣ የፋይናንስና የባለሙያ ችግሮች አሉባቸው:: እነዚህ ችግሮች ተደምረው የወሰን ማስከበር ችግሩ መከላከያ ባይሆንላቸው ኖሮ ብዙዎቹ ኮንትራክተሮቻችን ሊቀጥሉ የሚችሉበት ሁኔታ የለም:: ከዚህ አንፃር በእኛ (አስተዳደሩ) አካላት በኩል ከመንገድ ላይ መነሳት ያለባቸው ነገሮች በሙሉ ወቅቱን ጠብቀው በጊዜ ስለማይነሱ፣ ደካማ አፈጻጸም ያላቸው ኮንትራክተሮች በዚያ እያሳበቡ ከቅጣት የሚድኑበት ሁኔታ ነው የታየው:: ስለዚህ በዋናነት ለፕሮጀክቱ መዘግየት የሚጠቀሰውን

ችግር አቃለን መግባት ከቻልን ኮንትራክተሮቹ ተጠያቂ የሚሆኑበትና ለቅጣት የሚዳረጉበት ሁኔታ ይኖራል::

ሪፖርተር፡- ባለሥልጣኑ መንገዶችን በተያዘለት የጊዜ ገደብ ባለመጠናቀቅ ከፍተኛ የሆነ ወጪ እያወጣ ነው:: ይህ ትልቅ ጉዳት አይደለም?

ኢንጂነር ፍቃዱ፡- ፕሮጀክቶች እየዘገዩ ሲሄዱ ጉዳቱ የሁሉም ነው:: መንግሥትም ይጐዳል:: ምክንያቱም መደረግ የሌለባቸው ነገር ግን በመዘግየቱ ምክንያት የወጡትን ዋጋዎች የማካካስ ሥራ ይሠራል:: ይህ ወጪ ሌላ ፕሮጀክት ሊሠራበት የሚችል ነበር:: ሁለተኛ ከኮንትራክተሮቹ አንፃርም ሲታይ ኮንትራክሮቹ አቅማቸው ይደክማል:: የሚደክምበትም ምክንያቱም እኛ ለኮንትራክተሮች የምንሰጣቸው ማካካሻ ሁሉንም ዓይነት ወጪዎቻቸውን የሚሸፍን ባለመሆኑ ነው:: ማካካሻ የሚከፈላቸው ለሲሚንቶ፣ ለነዳጅ፣ ለብረትና ለአስፓልት የዋጋ ንረት ነው:: የሠራተኛ ደመወዝ በየጊዜው ነው የሚያድገው:: የመለዋወጫ

ዕቃዎችም እንዲሁ ይጨምራሉ:: ሌሎች ጭማሪዎች ቢኖሩባቸውም እኛ ማካካሻ ስለማንሰጥባቸው ኮንትራክተሮችን ለኪሣራ የሚዳርጋቸው ነው:: በአጠቃላይ የመንገድ ግንባታ ተጀምሮ በወቅቱ ካልተጠናቀቀ ችግር በመንግሥት፣ በኮንትራክተሩና በኅብረተሰቡም ላይ ጫና አለው::

ሪፖርተር፡- የእናንተም በወቅቱ ገንዘብ ያለመክፈል ችግር ለመንገድ መዘግየት ምክንያት እንደሆነ ይነገራል::

ኢንጂነር ፍቃዱ፡- ይኼ አልፎ አልፎ የሚደርስ ነው:: ዋና ችግር አድርጌ የምወስደው አይደለም:: ከታክስ የተሰበሰበ ገንዘብ ነውና የምንጠቀመው አልፎ አልፎ ከፋይናንስ ቢሮ የመዘግየት ነገር አለ:: ይህ መዘግየት ግን ኮንትራክተርን ተስፋ የሚያስቆርጥ አይደለም::

ሪፖርተር፡- የቦሌ መንገድ በቅርቡ ይገነባል ተብሏል:: ይህ ግንባታ ተደራራቢነት ስላለው በቦሌ መንገድ ባሉ የንግድ ተቋማት ላይ ተፅዕኖ ሊያሳድር አይችልም?

ኢንጂነር ፍቃዱ፡- የቦሌን መንገድ በተመለከተ የትራፊክ ማኔጅመንት ፕላኑ ተሠርቷል:: ይህም በአምስት ክፍል ተከፋፍሎ ነው የተሠራው:: የአሠራር ቅደም ተከተልም ተቀምጦለታል:: ለምሳሌ የአሠራር ቅደም ተከተሉን ስንወስድ በመጀመርያ ይጀመራል ተብሎ የተወሰደው ከፍላሚንጐ ኦሎምፒያ ድረስ ያለው መንገድ ነው:: ሌላው በዕቅድ የያዝነው በቀኝ በኩል ያሉት መንገዶች መጀመርያ ተሠርተው ይጠናቀቁና የግራው እንዲቀጥል ነው:: በአንድ ጊዜ ሁሉም መንገዶች አይዘጉም:: ይህ ባለመሆኑ በንግድ ማዕከላት ላይ የፈሩትን ያህል ጉዳት ሊደርስ አይችልም:: መንገዱ ትልቅ በመሆኑ ግንባታው ብዙ ትራፊክ ሊቀንስ ይችላል:: ግን ይህን ያህል ትልቅ ጉዳት የሚያደርስ አይደለም:: አቋርጠው ለሚሄዱ አማራጭ መንገድ ተይዟል:: በዚህ መልክ ስለሚስተናገድ በግንባታ ወቅትም ሆነ ከግንባታ በኋላ በንግድ ማዕከላት ላይ ተፅዕኖ የሚያደርግ ነገር የለም::

ሪፖርተር፡- ግንባታው ከተጠናቀቀ በኋላ ሕንፃዎች ይከለላሉ፤ መግቢያ መውጪያቸውም ሊዘጋ ይችላልና ለዚህ መፍትሔው ምንድነው?

ኢንጂነር ፍቃዱ፡- ለምሳሌ በቀላሉ የደንበል ሲቲ ሴንተርን ብንወስድ ሁለት መስመር ያለው የላይኛው መንገድ ከኦሮሚያ ጽሕፈት ቤት ጀምሮ በፊት ለፊቱ ነው የሚያልፈው:: ዋና መንገዱ ከሥር ነው የሚሆነው:: ስለዚህ የሲቲ ሴንተሩ ተጠቃሚዎች በላይኛው ተጠቅመው ነው የሚወጡትና ግብይታቸውን የሚፈጽሙት:: ይህ እስከ መጨረሻ ድረስ ያለ ነው:: ከኦሮሚያ ጽሕፈት ቤት እስከ ሸዋ ዳቦ፣ ከዚያ በኋላ ደግሞ አገልግሎት ይሰጣል:: ከዚያ ወሎ ሠፈር ኢንተር ሴንተር ጋ ከመድረሱ በፊት ወደ መሬት ይገባና ካራማራ

የቦሌን መንገድ በተመለከተ የትራፊክ ማኔጅመንት ፕላኑ ተሠርቷል:: ይህም በአምስት ክፍል ተከፋፍሎ ነው የተሠራው:: የአሠራር ቅደም ተከተልም ተቀምጦለታል:: ለምሳሌ የአሠራር ቅደም ተከተሉን ስንወስድ በመጀመርያ ይጀመራል ተብሎ የተወሰደው ከፍላሚንጐ ኦሎምፒያ ድረስ ያለው መንገድ ነው:: ሌላው በዕቅድ የያዝነው በቀኝ በኩል ያሉት መንገዶች መጀመርያ ተሠርተው ይጠናቀቁና የግራው እንዲቀጥል ነው:: በአንድ ጊዜ ሁሉም መንገዶች አይዘጉም:: ይህ ባለመሆኑ በንግድ ማዕከላት ላይ የፈሩትን ያህል ጉዳት ሊደርስ አይችልም::

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 24 | እሑድ |ኅዳር 17 ቀን 2004ክፍል-1

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 25 | እሑድ | ኅዳር 17 ቀን 2004 ክፍል-1

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 26 | እሑድ |ኅዳር 17 ቀን 2004ክፍል-1

የስብሰባ ጥሪየአንበሳ ኢንሹራንስ ኩባንያ የባለአክስዮኖች 4ኛ ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ህዳር 30 ቀን 2004 ዓ.ም. በአዲስ አበባ አክሱም ሆቴል ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ ስለሚካሄድ በተጠቀሰው ቀን፣ ሰዓትና፣ ቦታ በስብሰባው ላይ እንዲገኙልን የኩባንያው የዲሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን በአክብሮት ያስተላልፋል::

1. አራተኛ የመደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳ፣ 1.1 አጀንዳ ማፅደቅ፣ 1.2 ከኩባንያው ምስረታ በኋላ የተደረጉ

የባለአክሲዮኖችና የአክሲዮን መጠን ዝውውሮችን ማፅደቅ፣

1.3 የ2010/11 ዓ.ም የዲሬክተሮች ቦርድ ዓመታዊ ሪፖርት ማድመጥ፣

1.4 የ2010/11 ዓ.ም የውጪ ኦዲተሮች ዓመታዊ ሪፖርት ማድመጥ፣

1.5 በቀረቡት ሁለት ሪፖርቶች ላይ ተወያይቶ ማፅደቅ፣

1.6 የዲሬክተሮች ቦርድን ወርሃዊ አበልና ክፍያ መወሰን፣

1.7 ለመጪው ዘመን የውጭ ኦዲተሮችን መምረጥና የክፍያ መጠን መወሰን፣

1.8 የጎደሉ የዲሬክተሮች ቦርድ አባላትን በተመለከተ ተወያይቶ መወሰን፣

1.9 የጉባዔውን ቃለ ጉባዔ ማጽደቅ፣

2. ማሳሰቢያበስብሰባው ላይ መገኘት የማይችሉ ባለአክሲዮኖች በንግድ ሕጉ አንቀጽ 402 መሠረት ጉባዔው ከመካሄዱ እጅግ ቢዘገይ ከሦስት ቀን በፊት ኮሜት ሕንፃ አንደኛ ፎቅ በሚገኘው በኩባንያው ጽ/ቤት በመቅረብ ለዚሁ ዓላማ የተዘጋጀውን የውክልና ፎርም ሞልተው በመፈረም ወይም ውል ለማዋዋል ሥልጣን በተሰጠው አካል የተረጋገጠና በጉባዔው ለመካፈል የሚያስችል የውክልና ሥልጣን የተሰጣቸው ወኪል በጉባዔው ዕለት ውክልና የተሰጠበትን ኦሪጅናልና አንድ ፎቶ ኮፒ ይዘው በመቅረብ ጉባዔውን መሳተፍ ይችላሉ::

የአንበሳ ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ.) የዲሬክተሮች ቦርድ

የጨረታ ማስታወቂያ

አዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ. በአዋጅ ቁጥር 97/90 መሠረት በዋስትና የያዛቸውን

• Astro (pwore) • Astro (pwore) • Double axel /የደረቅ ጭነት ተሳቢ/• Double axel /የደረቅ ጭነት ተሳቢ/

ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋለ፡፡ በዚህም መሠረት የሚከተለውን መግለጫ አውጥቷል፡፡1. የመኪናዎቹን ሁኔታ ማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች በቅድሚያ

ሠነዱን በመግዛት መገናኛ አካባቢ በሚገኘው ፈለቀ የነዳጅ ማደያ ውስጥ በመቅረብ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከ3 እስከ 6 እና ከ7 እስከ 10 ሰዓት ማየት ይቻላል፡፡

2. ስለጨረታው አካሄድና የተሽከርካሪን ዝርዝር ሁኔታ የሚገልጸውን ሠነድ ከአዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ. ዋናው መ/ቤት አዋሽ ታውርስ 11ኛ ፎቅ በመምጣት የማይመለስ ብር 30 /ሰላሳ ብር/ እየከፈሉ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ከወጣበት ቀን ጀምሮ መውሰድ ይቻላል፡፡

3. ተጫራቾች የሚጫረቱበት መኪና የመነሻውን ዋጋ 20% /ሃያ በመቶ/ በጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ በባንክ ክፍያ ማዘዣ /ሲ.ፒ.ኦ/ አሠርተው ጨረታው በሚካሄድበት ዕለት ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

4. ጨረታው የሚካሄደው ህዳር 6 ቀን 2004 ዓ.ም. ከጠዋቱ 3፡30-5፡30 ባለዕዳዎች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው፤ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ. ዋናው መ/ቤት አዋሽ ታወርስ የመሰብሰቢያ አዳራሽ 12ኛ ፎቅ ውስጥ ይካሄዳል፡፡ (ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ውስጥ ካልተጠናቀቀ ጨረታው ሊራዘም ይችላል፡፡)

5. በጨረታው አሸናፊ የሆነ ተጫራች ያሸነፈበትን ዋጋ በ15 ቀን ውስጥ ለባንኩ ገቢ ማድረግ ይኖርበታል፡፡

6. ከላይ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ገቢ የማያደርግ ተጫራች ጨረታው ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ አይመለስለትም፡፡

7. በንብረቶቹ ማስተላለፍ ሂደት ለመንግስት የሚከፈል ማንኛውንም ክፍያ ወይም ግብር ተጨማሪ እሴት ታክሱን ጨምሮ ገዢው ይከፍላል፡፡

8. መኪናውን በጨረታ ከገዙ በኋላ ከመኪናው ውስጣዊም ሆነ ውጫዊ የአካል ሁኔታ በተለይም ከሰሌዳ፣ ሞተር እና ሻንሲ ቁጥሮች ጋር በተያያዘ የሚቀርበውን ማንኛውንም ጥያቄ ባንኩ የማያስተናግድ መሆኑን ከወዲሁ ያስታውቃል፡፡

9. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-557-01-35 በመደወል ወይም አዋሽ ታወርስ 11ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የባንኩ ብድር አስገቢና ፎርክሎዥር ዋና ክፍል በአካል በመቅረብ መጠየቅ ይቻላል፡፡

10. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ.

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 27 | እሑድ | ኅዳር 17 ቀን 2004 ክፍል-1

ተ ሟ ገ ት

ወደ ክፍል-1 ገጽ 45 ዞሯል

በደሣለኝ መንግሥቴ፣ ዓቃቤ ሕግ/የሊዝ አዋጅ አርቃቂ ቡድን ሰብሳቢ

ፖርተር ባለፈው የጻፍኩትን ጽሑፍ በአግባቡ በማውጣቱ በቅድሚያ አመሰግናለሁ:: ከሌሎች የግል ጋዜጦች በተለየ ሁኔታ በሊዝ አዋጁ ዙሪያ

የአንድ ወገን ሐሳብን ብቻ ሳይሆን፣ የሁሉንም የተለያዩ አካላት እንዲሁም የመንግሥትን አቋም ጭምር በማስተናገዱ ከፍተኛ የሆነ አክብሮት አለኝ::

ከዚህ ቀጥሎ በተለያዩ ጉዳዮችና ህዳር 3 ቀን 2004 ዓ.ም. ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ መምህር ዳንኤል ስለ አዋጁ ሕገ መንግሥታዊነት በሰነዘሩት ትችት ዙሪያ አስተያት እሰጣለሁ::

ነባር ይዞታን ወደ ሊዝ ማስገባት በተመለከተ የተለያዩና ትክክል ያልሆኑ ዘገባዎች ይወጣሉ:: ለመሆኑ ይዞታን ወደ ሊዝ ማስገባትን በተመለከተ አዲሱ አዋጅ አዲስ ሐሳብ ይዟል? ይህን ጉዳይ ለማወቅ አዋጅ ቁጥር 272/1994 አንቀጽ 3 የተፈጻሚነት ወሰን ንዑስ አንቀጽ 2 በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) የተመለከተው ቢኖርም እስካሁን ድረስ ወደ ሊዝ ባልገባ፡-

ሀ) ማንኛውም የከተማ ቦታ ይዞታ ላይ አዋጅ ተፈጻሚ የሚሆነው ክልል ወይም የከተማ አስተዳድር በሚወስነው ጊዜና ቦታ ይሆናል ይላል::

ስለዚህ ይህን የቀድሞውን አዋጅ ነባር ይዞታ ወደ ሊዝ እንዲገባ የደነገገ ነበር:: ነገር ግን ክልሎችም ሆነ የከተማ አስተዳደሮች በሕግ የተጣለባቸውን ግዴታ ወይም ሥልጣን በአግባቡ ባለመወጣታቸው አንቀጽ 3 ተግባራዊ ሳይሆን ቆይቷል:: ነገር ግን ጉዳዩን ካለማወቅ ወይም በስህተት ወይም ሆን ብሎ ሕዝቡን በወሬ በማተራመስ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ቀውስ በከተሞቻችን ላይ ለመፍጠር ሊሆን ይችላል፣ የተለያዩ ጸሐፊዎችም ሆኑ ጋዜጦች በዚህ ዙሪያ ብዙ ውዥንብር በመጻፍ ሕዝብንና መንግሥትን ለማቃቃር ተፍ ተፍ በማለት ላይ ናቸው:: ባለማወቅ ወይም ጥቅማቸው የተነካባቸው ሰዎች የሚያናፍሱትን ወሬና በተለያዩ ጋዜጦች ላይ በዕውቀት ላይ ሳይመሠረቱ የሚጻፉ ጽሑፎችን በማንበብ ለተሳሳቱ ይህን ጽሑፍ አንብበው እውነታውን ሲያውቁት ለመንግሥታችን ያላቸው ክብር የበለጠ ይጨምራል::

ነገር ግን ጥቅማቸው የተነካባቸውና በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ሕዝብ ከመንግሥት ጋር ያለውን ቁርኝት በከፍተኛ ሁኔታ ጠንክሮ፣ መንግሥት ለነደፈው የአምስት ዓመቱ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ መሳካት ሕዝቡ የሚያደርገውን ከፍተኛ ድጋፍ ለመቀልበስ የሚደረገው ሕዝብን የማደናገር ወሬ ማለትም ሕገ መንግሥታዊነት የሌለው አዋጅ ነው፤ መንግሥት ከመሬት ገንዘብ በማግኘት ጡንቻውን ለማፈርጠም ነው፤ መንግሥት ነባር ይዞታን ሊቀማ ነው፤ ወዘተ የመሳሰሉትን አሉባልታዎችና ሕዝቡን በወሬ የማተራመስ ዘመቻ ምንም ዓይነት ፋይዳ የለውም::

መንግሥት ነባር ይዞታዎችን ወደ ሊዝ በማስገባት ገንዘብ ማጋበስ ወይም ባለይዞታዎችን ለማፈናቀል ቢሆን ዓላማው አዲስ ሕግ ማውጣት ወይም ማሻሻል አያስፈልገውም ነበር:: ምክንያቱም ከ10 ዓመት በፊት የወጣው አዋጅ ቁጥር 272/1994 አንቀጽ 3 ንዑስ አንቀጽ 2(ሀ) ይፈቅድለታል:: የመሬት ማኔጅመንት ፖሊሲው እንዲሁም ረቂቁን አዋጅ በምናዘጋጅበትም ጊዜ የመንግሥት አቋም ነባር ይዞታዎች ለመንጠቅ አይደለም:: ነባር ይዞታ ወደ ሊዝ የሚገባው ተጠንቶ ሕዝብ በጥናቱ ላይ ተወያይቶበት የሕዝቡን የኑሮ ደረጃ በአገናዘበ መልኩ መግባባት ተደርሶበት መሆን ስላለበት ነው፣ ወደፊት በሚደረገው ጥናት መሠረት ነባር ይዞታ ወደ ሊዝ ይገባል ተብሎ የተቀመጠው:: ስለዚህ ሁሉም አካል ሊያውቀው የሚገባው ይህንን ሀቅ ነው:: በዚህ ሥራ በቆየሁባቸው ጊዜያት ከክቡር አቶ መኩሪያ ኃይሌ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ጋር በተደጋጋሚ በመሬት ማኔጅመንት ፖሊሲው እንዲሁም በአዋጁ ረቂቅ ላይ ዘወትር እንወያይ ነበር:: የመንግሥትንም አቋም በአግባቡ ያስቀምጣሉ:: የአርቃቂ ቡድኑ ከሕግ አንፃር ያለውን አቋም በመግለጽ ያለውን አሳማኝ ምክንያት ማቅረብ እንደሚችልና ለመከራከርም መድረኩ ነፃ ነበር:: በዚህም መሠረት ተከራክረን ያሳመንናቸውና ያስቀየርናቸው ነጥቦች አሉ:: እሳቸውም በማሳመን ያስቀየሩን ብዙ ሐሣቦች አሉ:: ከምንም በላይ ግን ሕገ መንግሥታዊነቱና የሕዝብ ጥቅም ላይ ምንም ዓይነት ድርድር የለም::

በተደጋጋሚ የሚያነሱት ሐሣብ ለብዙኅኑ ሕዝብ የሚጠቅም መሆን እንዳለበት፣ በአሁኑ ወቅት ሕዝብ ከመንግሥት ጎን በመቆም ለዕቅዱ መሳካት እያደረገ ላለው ከፍተኛ ድጋፍና ድህነትን የማጥፋት ትግል አክብሮት

አዲሱ የሊዝ አዋጅ የሕዝብን ጥቅም ከማስከበር በቀር ሕገ መንግሥቱን አይፃረርም

ልንሰጥና በቅንነት ልናገለግለው እንደሚገባ ነው:: በዚህ አጋጣሚ መናገር የምፈልገው ነገር ቢኖር መጽሐፍ ቅዱስ ‘’ክብር ለሚገባው ክብር ስጡ ይላል’’:: ለክቡር አቶ መኩሪያ ኃይሌ ከፍተኛ የሆነ ክብር አለኝ:: ምክንያቱም ከፍተኛ አገራዊ ራዕይና ለሚመሩት ሥራ ከፍተኛ የሆነ ዕውቀትና ክህሎት ያላቸው፣ ሠርተው የሚያሠሩ ከምንም በላይ ግን ባለሙያ የሰጣቸውን ሥራ መስመር በመስመር የሚያነቡና ከባለሙያ ጋር በጓደኝነት መንፈስ የሚወያዩ ናቸው::

ይህ የሊዝ አዋጅ የወጣበት ምክንያት ከላይ በአብራራኋቸው ምክንያቶችና የተሳሳቱ ጸሐፊዎች እንደሚጽፉት አይደለም:: ከተሞች ልማትን ከማረጋገጥ አኳያ ያላቸው ዋነኛ ሀብት መሬት ነው:: ይህ የከተሞች መሬት የላቀ ልማታዊ አስተዋጽኦ ባለው አኳኋን ጥቅም ላይ ከዋለ ትልቅ የልማት አቅም መሆን የመቻሉን ያህል፣ በአግባቡ ጥቅም ላይ የሚውልበት ሥርዓት ካልተመቻቸ ለኪራይ ሰብሳቢነት የተመቸ ይሆናል:: እንደሚታወቀው

እንዲጣጣም ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ ነው:: ሰኔ 2003 ዓ.ም. በተካሄደው ኮንፈረንስ የማጠቃለያ

ውይይት ላይ ለተነሱ ጥያቄዎች ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የተናገሩትን ማንሳት እፈልጋለሁ:: ‹‹መሬት ፍትሐዊ በሆነ መንገድ ለኅብረተሰቡ እየተሰጠ አይደለም፤ ጥቂቶች ናቸው ያለአግባብ እየበለፀጉበት ያሉት:: ስለዚህ መሬት መቸብቸብ አይቻልም፤ ከአሁን በኋላ ተቆልፎበታል:: በአሁኑ ወቅት ሕዝባችን ለልማት ከጎናችን ቆሟል:: ቢያንስ በትንሹ 80 በመቶ ሕዝባችን ከጎናችን

ነው:: ስለዚህ ኅብረተሰቡን በአግባቡ ፍትሐዊ በሆነ መንገድ ልናገለግለው ይገባል፤›› በማለት ነበር ሚኒስትሮች፣ የክልል ፕሬዚዳንቶችና የአገሪቱ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ውይይት ላይ ትዕዛዝ ያስተላለፉት:: ስለዚህ አዋጁ የወጣበት ዓላማ ድብቅ አጀንዳቸውን ለማሳካት በተለያዩ ጋዜጦች ላይ ለሕዝብ ተቆርቋሪ በመምሰል ጩኽት እንደሚያሰሙት አሳሳች መሲሆች አለመሆኑን እየገለጽኩ፣ አዋጁ የተሻሻለበትን ዓላማም ግልጽ ሊሆንልን ይገባል::

ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ መምህር ዳንኤል ስለ አዋጁ ሕገ መንግሥታዊነት በሰነዘሩት ትችት ዙሪያ የምለው አለኝ::

የሊዝ የመሬት ሥሪት የለውም ስለ ከተማ መሬት የሚያነሳው የለም በማለት የአዋጁ ሕገ መንግሥታዊነትን ጥያቄ ውስጥ አስገብተዋል:: ከጸሐፊው ጋር በዚህ ነጥብ በፍፁም በፍፁም አልስማማም:: መምህር እባክዎን የሕገ መንግሥቱን አንቀጽ 40 ንዑስ አንቀጽ 3-7 እና 89(5) ያንብቡ::

ለዚህም እንደማስረጃ ያቀረቡት ሕገ መንግሥቱ ስለ ከተማ መሬት የሚያነሳው የለም በማለት ሲሆን፣ ነገር ግን መጀመሪያ ስለ ከተማ መሬት ሕገ መንግሥቱ ላይ የለም ብለው ያነሱትን ነጥብ ዝቅ ብለው የጠቀሱትን አንቀጽ 40 ንዑስ አንቀጽ 3 ቀድመው ቢያዩት መልስ ሊሰጠዎት ይችላል:: እሱም ‘’የገጠርም ሆነ የከተማ መሬትና የተፈጥሮ ሀብት ባለቤትነት መብት የመንግሥትና የሕዝብ ብቻ ነው፤’’

ይላል:: ስለዚህ ሕገ መንግሥቱ ስለ ከተማ መሬት አያወራም ላሉት ይህንን አንቀጽ ማየቱ መልስ ሊሆን ይችላል:: ለነገሩ እርስዎም ቢሆኑ ጽሑፍዎ ላይ ከመጀመሪያ ትችትዎ ዝቅ ብለው ይህን አንቀጽ ጠቅሰዋል:: ምናልባት የማስተዋል ችግር ካልሆነ የዕውቀት ማነስ አይመስለኝም::

ሌላው የተቹት ነጥብ የከተማ መሬት ለምን በሊዝ በክፍያ ይተላለፋል የሚል አንድምታ ያለው ነው:: የሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 40(4) እና (5) የኢትዮጵያ አርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች መሬት በነፃ የማግኘትና ከመሬታቸው ያለመነቀል መብታቸው የተከበረ ነው:: አፈጻጸሙን በተመለከተ ዝርዝር ሕግ እንደሚወጣ በግልጽ አስቀምጧል:: ምንም እንኳ የከተማ ቦታ የመንግሥትና የሕዝብ መሆኑን በአንቀጽ 40(3) ቢገልጽም የገጠር መሬት ለአርሶ አደሩና ለአርብቶ አደሩ በነፃ እንደሚሰጥ ሲገልጽ የከተማ ነዋሪ የከተማ ቦታ በነፃ ይሰጠዋል አላለም:: በነፃ የሚሰጣቸውን በግልጽ ዘርዝሮ አስቀምጧል:: ስለዚህ የከተማ ቦታ በነፃ እንደማይሰጥ ግልጽ

ላው የተቹት ነጥብ የከተማ መሬት ለምን በሊዝ በክፍያ ይተላለፋል የሚል

አንድምታ ያለው ነው:: የሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 40(4) እና (5) የኢትዮጵያ አርሶ አደሮችና

አርብቶ አደሮች መሬት በነፃ የማግኘትና ከመሬታቸው ያለመነቀል መብታቸው

የተከበረ ነው:: አፈጻጸሙን በተመለከተ ዝርዝር ሕግ እንደሚወጣ በግልጽ አስቀምጧል:: ምንም እንኳ የከተማ ቦታ የመንግሥትና የሕዝብ

መሆኑን በአንቀጽ 40(3) ቢገልጽም የገጠር መሬት ለአርሶ አደሩና ለአርብቶ አደሩ በነፃ እንደሚሰጥ ሲገልጽ የከተማ

ነዋሪ የከተማ ቦታ በነፃ ይሰጠዋል አላለም:: በነፃ የሚሰጣቸውን በግልጽ ዘርዝሮ አስቀምጧል:: ስለዚህ የከተማ ቦታ በነፃ እንደማይሰጥ ግልጽ ነው:: በተጨማሪም ሊያግባባን የሚችለው

ትልቁና ዋናው ምክንያት ለከተማ መሬትና ለገጠሩ መሬት መንግሥት ሊያሟላላቸው

የሚገባው መሠረተ ልማቶችን ስናይ፣ የሰማይና የመሬት ያህል ልዩነታቸውና የበጀት ፍላጎታቸው የሰፋ ነው::

ከዚህ ቀደም በነበሩት ጊዜያት የከተማ መሬት ባለቤት እንደሌለውና የማያልቅ ሀብት እንደሆነ ተቆጥሮ በግድ የለሽነት ሲባክንና ለኪራይ ሰብሳቢነት ዋነኛ ምንጭ ሆኖ ቆይቷል::

ስለዚህ በመሬት ላይ ያለውን የኪራይ ሰብሳቢነት ፖለቲካዊ ኢኮኖሚ በመናድ በምትኩ የልማታዊነት ፖለቲካዊ ኢኮኖሚን መሠረት ያደረገና ከአጠቃላይ የአገሪቱ የልማትና የመልካም አስተዳደር አቅጣጫዎች አንፃር ግልፅና ተጠያቂነት የሰፈነበት የአሠራርና የሕግ ማዕቀፍ አዘጋጅቶ ተግባራዊ ማድረግ ያስፈልጋል:: የከተማ ቦታን በሊዝ የማስተዳደር ሒደት በትክክለኛ መረጃ ላይ የተመሠረተ፣ ግልጽ፣ ቀልጣፋ፣ ውጤታማና ተገማች እንዲሆን እንዲሁም ያለ አግባብ በመሬት ላይ ተጨማሪ ነገር ወይም ወጪ ሳያወጡ ለመክበር የሚሯሯጡ ብልጣ ብልጦችና ኪራይ ሰብሳቢ ቢሮክራቶችን ለመዋጋት፣ ከአገራችን የማኅበራዊና የኢኮኖሚያዊ ዕድገት ደረጃ ጋር

ነው:: በተጨማሪም ሊያግባባን የሚችለው ትልቁና ዋናው ምክንያት ለከተማ መሬትና ለገጠሩ መሬት መንግሥት ሊያሟላላቸው የሚገባው መሠረተ ልማቶችን ስናይ፣ የሰማይና የመሬት ያህል ልዩነታቸውና የበጀት ፍላጎታቸው የሰፋ ነው::

ስለዚህ መንግሥት በከተማ ለሚያስገነባው መሠረተ ልማት በጀት ያስፈልገዋል:: ይህንን በጀት ደግሞ ከሌላ ገቢ አምጥቶ መሸፈን የማይቻል መሆኑ የሚያግባባን ይመስለኛል:: መሬት የከተማ ሁለገብ የሀብት ምንጭና የልማት ፋይናንስ አመንጪ መሆኑ በፖሊሲዎቻችን በግልጽ የተቀመጠ አቅጣጫ ነው:: ሆኖም ግን ከተሞች የመሬት ሀብታቸውን በአግባቡ በማልማትና በማስተዳደር ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ልማትን ለማስፋፋትና የልማት ግቦችን ለማሳካት የሚያስፈልገውን የፋይናንስ ሪሶርስ በቀጣይነት በማመንጨት ረገድ ከፍተኛ ፈተናና ችግር ውስጥ ይገኛሉ:: በአሁኑ ወቅት የከተሞች የመሠረተ

ልማት ፍላጎት እጅግ ሲበዛ ከፍተኛ ከመሆኑ አንፃር የሚጠይቀውም በጀት እንዲሁ ከፍተኛ ነው:: ስለዚህ ከተሞቻችን ከመሬታቸው ገቢያቸውን በአግባቡ በመሰብሰብ መሠረተ ልማት ገንብተው ሕዝቡን ተጠቃሚ ማድረግ አለባቸው:: ለዚህም ነው በሊዝ አዋጅ 90 በመቶ የሚሆነው የሊዝ ገቢ ለሌላ ጉዳይ እንዳይውል፣ ይህ ተደርጎ ቢገኝ ግን ይህንን ተግባር የፈጸመው አካል እንደሚቀጣ በግልጽ ያስቀመጠው::

ሌላው ሕገ መንግሥታዊ ነው ብለው የተቹት ነጥብ በአንቀጽ 40(3) የገጠርም ሆነ የከተማ መሬትና የተፈጥሮ ሀብት ባለቤትነት መብት የመንግሥትና የሕዝብ ብቻ ነው:: መሬት የማይሸጥ የማይለወጥ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና የሕዝብ የጋራ ንብረት ነው የሚለውን ሐሳብ በመግለጽ፣ መንግሥት ይህንን በሚቃረን መልኩ የጋራ የሆነውን መሬት ብቻውን በመያዝ እየሸጠ ነው:: እስካሁን እንደምናውቀው ደግሞ ሕዝቡ መንግሥት እንደኛ ሆኖ መሬት ለራሱ (Own) ያድርግልን አላለም በማለት፣ ሕገ መንግሥቱ ተጥሷል ብለዋል:: አንቀጽ 40(3) ብቻ አይተን የምንተች ከሆነ ልክ እንደርስዎ ተሳስተን ሕዝብንም እናሳስታለን:: ስለዚህ አንቀጽ 40ን ሁሉንም ንዑስ አንቀጾች በደንብ ማንበብና ሌሎች ከዚህ አንቀጽ ጋር ግንኙነት ያላቸው ሐሳቦች መኖራቸውንና አለመኖራቸውን እናረጋግጥ:: ከዚያ በኋላ ነው እርግጠኛ ሆነን መንግሥት ሕገ መንግሥቱን ጥሷል ብለን በድፍረት መናገር ያለብን::

የእርስዎ ትልቁና ታሪካዊው ስህተት እዚህ ላይ ነው:: ለጠቅላላ ዕውቀትዎ የሕገ መንግሥቱን አንቀጽ 40(6) እና አንቀጽ 89 ማሳየቱ ከስህተትዎ እንዲማሩ ይረዳዎታል:: ከስህተትዎ እንደሚማሩም እርግጠኛ ነኝ:: ምክንያቱም በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ አስተማሪ መሆንዎን ስለገለጹ ምሁር ከስህተቱ ይማራል የሚል አቋም ስላለኝ ነው:: ከስህተቱ የማይማር ምሁር ካለ ምሁር መሆኑን መጠራጠር ነው:: አንቀጽ 40(6) ‘’የመሬት ባለቤትነት የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ መንግሥት ለግል ባለሀብቶች በሕግ በሚወሰን ክፍያ በመሬት የመጠቀም መብታቸውን ያስከብርላቸዋል:: ዝርዝሩ በሕግ ይወሰናል›› ይላል:: እንግዲህ ከዚህ አንቀጽ የምንረዳው ነገር ቢኖር የጋራ ባለቤትነታቸው እንደተጠበቀ ሆኖ ነገር ግን መንግሥት በሕግ በሚወሰን ክፍያ መሠረት ለግል ባለሀብቶች መሬት እንደሚያከራይ ያስቀምጣል::

በተጨማሪም በአንቀጽ 89(5) መንግሥት መሬትንና የተፈጥሮ ሀብትን በሕዝብ ስም በይዞታው ሥር በማድረግ ለሕዝቡ የጋራ ጥቅምና ዕድገት እንዲውል የማድረግ ኃላፊነት አለበት ይላል:: ስለዚህ ሕገ መንግሥቱ በግልጽ ከላይ በተዘረዘሩት አንቀጾች ለመንግሥት በሕግ መሠረት የማስተዳደር ኃላፊነትና ግዴታ ጥሏል:: በዚህም መሠረት መንግሥት ሕገ መንግሥቱ በጣለበት ግዴታ ወይም በሰጠው ሥልጣን መሠረት የተለያዩ ሕጎችን እንደ ሊዝ አዋጅ፣ ደንብና መመሪያ እንዲሁም የኢንቨስትመንት አዋጅና ሌሎችንም ሕጎችን በማውጣት መሬትን ለሕዝቡ የጋራ ጥቅምና ዕድገት እያዋለ ነው:: ስለዚህ የተከበሩ መምህር ሕዝቡ መንግሥት እንደኛ ሆኖ መሬት ለራሱ (Own) ያድርግልን አላልንም በማለት ሕገ መንግሥቱ ተጥሷል ብለዋል:: አሁንስ ምን ይላሉ? እውነት እውነት እልዎታለሁ:: አዋጁ በምንም ዓይነት መስፈርትና በየትኛውም አንቀጽ ሕገ መንግሥቱን የሚቃወም ሐሳብ የለውም::

በሚቀጥለው ክፍል ሁለት ደግሞ እንደ ሥጋት በአነሷቸው ነጥቦች ላይ አስተያየቶች ለመስጠትና በአዋጁ ላይ ማብራሪያዎች ለመስጠት እሞክራለሁ::

ቸር ይግጠመን

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 28 | እሑድ |ኅዳር 17 ቀን 2004ክፍል-1

የአገር ውስጥ ዜና የዓለም ዜናተስፍሽ እና ገብርሽ

የሳምንቱ ገጠመኝ

የሰብዓዊ መብቶች የድርጊት መርሐ ግብር ዝግጅት ተጀመረ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የሰብዓዊ መብቶች የድርጊት መርሐ ግብር ዝግጅት መጀመሩን ፍትሕ ሚኒስቴርን ጠቅሶ አዲስ ዘመን ዘግቧል:: በአምስት ዓመቱ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ መሠረት በሚቀጥሉት ዓመታት በዲሞክራሲ፣ በመልካም አስተዳደርና በሰብዓዊ መብቶች ዘርፍ የተካተቱ ዕቅዶችን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል የብሔራዊ የድርጊት መርሐ ግብር ዝግጅት ተጀምሯል:: ዕቅዱ በአገሪቱ ሁሉን አቀፍ በሆነ መልኩ ለሰብዓዊ መብቶች አጠቃላይ ትኩረት ሰጥቶ ሲዘጋጅ የመጀመርያ መሆኑ ተጠቁሟል:: የድርጊት መርሐ ግብሩ ዝግጅት በፍትሕ ሚኒስቴር ሰብሳቢነት፣ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ምክትል ሰብሳቢነትና በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ጸሐፊነት እንደሚከናወን ተመልክቷል:: የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር፣ የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር እንዲሁም የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤትን በአባልነት በማካተት ከፍተኛ አመራር የሚሰጥበት የብሔራዊ አመራር ኮሚቴ መዋቀሩን ዘገባው ጨምሮ አስታውቋል::

ከሚኒስቴሩ የሥራ ሒደት ሳይሆን ውጤት እንደሚጠበቅ ተገለጸ

የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ያለፈው ዓመት ችግሮቹ ያሉበትን ደረጃ በዕቅዱ አካቶ የሥራ ሒደት ሳይሆን ግብና ውጤት ማሳየት እንደሚጠበቅበት የሕዝብ ተወካዮች ምር ቤት የባህል፣ ቱሪዝምና መገናኛ ብዙኅን ቋሚ ኮሚቴ ማሳሰቡን አዲስ ዘመን ዘግቧል:: በ2003 ዓ.ም. የኪራይ ሰብሳቢነት፣ የፀረ ዲሞክራሲ አመለካከቶችና ተግባሮች፣ የቡድንተኝነትና የጥቅም ትስስር (ኔትወርክ) እና የመሳሰሉት ችግሮች በ2004 ዓ.ም. ዕቅድ ውስጥ ያሉበት ደረጃ አለመካተቱን እንደ ድክመት ያነሳው ቋሚ ኮሚቴው፣ በአዲሱ አመራር የሥራ ሒደቶችን ሳይሆን ውጤታቸውን እንደሚጠብቅ በአጽንኦት ገልጿል:: በቀጣዮቹ መድረኮች ላይም ስለሒደት ሳይሆን ስለውጤት ገለጻና ማብራሪያ እንዲሰጥ ተገልጾለታል:: እንዲሁም በሚኒስቴሩና በሚመራቸው ተጠሪ ተቋማት እየተፈጠረ ያለው የቡድን መንፈስ ለውጥ ማምጣቱን ማረጋገጥ አለበት መባሉን ዘገባው አመልክቷል::

በ300 ሚሊዮን ብር የተገነባው የወይን ጠጅ ፋብሪካ ማምረት

ጀመረ

በባቱ ከተማ ከ300 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የተገነባው የወይን ጠጅ መጥመቂያ ፋብሪካ ማምረት መጀመሩን ኢዜአ ዘገበ:: ካስትል ወይን ጠጅ ፋብሪካ 18 ዘመናዊ የወይን ጠጅ መጥመቂያ ማሽኖችና ጋኖች አሉት:: በባቱ ከተማ ዙሪያ በ120 ሔክታር መሬት ላይ ለምቶ ለፋብሪካው ግብዓት ከዋለው የወይን ፍሬ በቅርቡ ከግማሽ ሚሊዮን ጠርሙስ በላይ የወይን መጠጥ የመጥመቅ አቅም ይኖረዋል ተብሏል:: በመሆኑም ፋብሪካው ከአንድ ዓመት በኋላ በሙሉ አቅሙ የሚያመርተውን ከአንድ ሚሊዮን ጠርሙስ በላይ የወይን ጠጅ ለአውሮፓ፣ ለአሜሪካ፣ ለምሥራቅና ለደቡብ አፍሪካ አገሮች ገበያ እንደሚያቀርብም ተገልጿል:: ፋብሪካው በየዓመቱ አቅሙን በማጠናከር አገሪቱ ከዘርፉ የምታገኘውን የውጭ ምንዛሪ በእጥፍ በማሳደግና የገጽታ ግንባታ ሥራዎችን ለማከናወን አቅዶ እየሠራ መሆኑ ተገልጿል::

በሴቶች ላይ የሚደርስ ጥቃት እንዲቆም ኮሚሽኑ አሳሰበ

በሴቶች ላይ የሚደርሱ ማናቸውም ዓይነት ጥቃቶችን ለማስቆም ሁሉም ባለድርሻ አካላት ኃላፊነታቸውንና የዜግነት ግዴታቸውን እንዲወጡና ዕርምጃ እንዲወስዱ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን አሳሰበ:: የሴቶች የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች የሚፈጸሙት በማኅበረሰቡ ውስጥ፣ በቤት ውስጥ፣ በትምህርት ቤቶችና በሥራ ቦታዎች መሆናቸውን ኮሚሽኑ በላከው መግለጫ አስታውቋል:: እነዚህን ጥቃቶች ለማስቆም በዋናነት የመከላከል ሥራው ቅድሚያ ሊሰጠው እንደሚገባው ኮሚሽኑ አስታውቋል:: የመከላከያ ሥራውና ስልቱ ሁሉንም የኅብረተሰብ ክፍሎችና ባለድርሻ አካላት ያካተተ ሆኖ፣ በተለይ በታዳጊ ሕፃናትና ወጣቱ ትውልድ ላይ ልዩ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባ አሳስቧል:: የሚፈለገው ለውጥ ኅብረተሰቡ ሰብዓዊ መብትን ባህል እንዲያደርግ ሲሆን፣ ለዚህም በዋነኛነት የነገው አገር ተረካቢ የሆኑት በየደረጃው ያሉ ሕፃናትና ወጣቶች ማዕከል ያደረገ ቢሆን ውጤታማ እንደሚሆን ገልጿል:: በመሆኑም ጥቃት የሚጸየፍ ትውልድ ለመፍጠር፣ ሰብዓዊ መብቶችን ለማክበርና ለማስከበር ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ ኮሚሽኑ አሳስቧል::

አንድ ቀን ቤቴ አልጋ ላይ ጋደም ባልኩበት ጓደኛዬ ስልክ ይደውልልኝና ‹‹ጊዜ ካለህ የልጆች የትምህርት መጻሕፍት አጋዛኝ›› ይለኛል:: መሄጃ አጥቼ ደብሮኝ ነበርና መንቀሳቀሻ በማግኘቴ የጓደኛዬን ጥያቄ በደስታ ተቀብልኩት:: እናም ብሔራዊ ቴአትር አካባቢ ልንገናኝ ተቀጣጠርን::

ጊዜ ሳላጠፋ ወጣሁና ከጦር ኃይሎች ወደ ብሔራዊ ቴአትር የሚያደርሰኝን ታክሲ ተሳፈርኩ:: የተሳፈርኩበት ታክሲ ስላልሞላ ረዳቱ ይጣራል፤ ‹‹ፍርድ ቤት፣ ልደታ፣ ሜክሲኮ፣ ብሔራዊ፣ ካዛንችስ፤›› ይልና ተሳፋሪዎች ሊገቡ ሲሉ ‹‹ሜክሲኮ ሳይሻገር›› በሚለው ማስጠንቀቂያው ይመልሳቸዋል:: ተሳፋሪዎቹም ‹‹ለምን?›› ብለው ሳይጠይቁ የሚመለሰው ይመለሳል፤ የሚገባም ካለ ሊሄድ ካሰበበት ሳይሆን ረዳቱ የመደበለት ቦታ ላይ ይወርዳል:: በልቤ ‹‹መብቱንና ግዴታውን አውቆ ራሱን የማያስከብር›› አልኩ::

ይህ በዚህ ታክሲ ብቻ ሳይሆን በበርካታ ጉዳዮች ላይም የሚገጥም ነው:: ለዚህ አንዱ ምክንያት መንግሥት የትራንስፖርት ታሪፍ ሲያወጣ፣ ሲያሻሽልና ተግባራዊ ሲያደርግ በበቂ ሁኔታ ኅብረተሰቡ እንዲያውቀው አለማድረጉ ነው:: መሄጃ ቦታዎቹ ከነታሪፋቸው ሕዝቡ በሚያየው ቦታ መኪና ውስጥ መለጠፍ አለበት:: በተጨማሪም በመገናኛ ብዙኃን መረጃዎቹ መተላለፍ አለባቸው:: ይህ አስቸጋሪ ከሆነ ደግሞ በበራሪ ወረቀቶች በየጊዜው ማሰራጨት ይቻላል::

እግረ መንገዴን የታዘብኩትን ስገልጽ ዋናውን እንዳልተወው ወደ መነሻ ሐሳቤ ልሂድ:: የተቀጣጠርንበት ደርሼ ወዳጄን ስላገኘሁት ተያይዘን ብሔራዊ ቴአትር ጀርባ ወዳሉት መጻሕፍት መሸጫ ሱቆች አመራን:: አንድ ሁለት መጻሕፍት መሸጫ ቤቶችን ከጎበኘን በኋላ የምንፈልጋቸውን የ7ኛ፣ የ5ኛ እና የ2ኛ ክፍል ተማሪዎች የመማሪያ መጻሕፍት መምረጥ ጀመርን:: የመረጥናቸውን የመጻሕፍቱን ዋጋ ስንጠይቅ ግን ደነገጥን:: እንደየመጠናቸውና ይዘታቸው 35፣ 40፣ 45 እና 50 ብር ተብሎ ነበር የተነገረን::

ፈጠን አልኩና 50 ብር የተጠየቅንበትን አንዱን የ7ኛ ክፍል መጽሐፍ ዋጋ ከጀርባው ላይ ስመለከት 11 ብር ከ65 ሳንቲም ይላል:: ዓይኖቼን ባለማመን ደግሜ ስመለከተው ዋጋው ያው ነው:: ከወዳጄ ጋር ተያየንና መጻሕፍት ሻጩ ተሳስቶ ይሆን ብለን ከመጻሕፍቱ ጀርባ ያለውን ዋጋ እየጠቆምነው ጠየቅነው:: ጥያቄችን ቢገባውም ብዙም አልተገረመም:: እንዲያውም ይግረማችሁ ብሎ ነው መሰል ‹‹መጻሕፍቱ ሰሞኑን ከ80 እስከ 120 ብር ድረስ ሲሸጡ ነበር፤›› አለን::

የመረጥናቸውን መጻሕፍት ትተን አሮጌዎቹ ወደሚሸጡበት አካባቢ ሄድን:: እዚያም የጠበቀን ያው ነበር:: የ2ኛ ክፍል መማሪያ መጻሕፍት ቢያንስ አምስት ብር ቢበዛ ደግሞ ሰባት ብር ብቻ ትርፍ ይጠየቅባቸዋል ብለን ብናስብም የተጠየቅነው ግን 60 ብር ነበር:: ድርጊቱ እያበሳጨን በስንት ክርክር የተለያዩ ዓይነት መጻሕፍትን ከ25 እስከ 45 ብር ገዝተን ወደመጣንበት ተመለስን::

አገራችን ከተያያዘቻቸው ልማቶች አንዱ የትምህርት ሽፋንን ማስፋት ነው:: ይህን ዳር ለማድረስ ደግሞ የመማሪያ መጻሕፍት ሕትመትና ሥርጭት ከፍላጎት ጋር መጣጣም አለባቸው:: በተለይ በአንደኛ ደረጃ ሳይክል ያሉ ትምህርት ቤቶች የመጻሕፍት ሥርጭት ብቃታቸው ሳይጠና የማስተማሩ ፈቃድ መሰጠቱና ወላጅ በራሱ እንዲገዛ መደረጉ ተገቢ አይመስለኝም:: ይህ ሳይሆን እንዲያስተምሩ ከተፈቀደላቸው ደግሞ መንግሥት መጻሕፍቱን በበቂ መጠን ማቅረብ አለበት:: ይህ ካልተደረገ ግን ወላጅ የአንዳንድ ስግብግብ ነጋዴዎች ሲሳይ ነው የሚሆነው፤ እየሆነም ነው::

ሁኔታው በዚህ ከቀጠለ ደግሞ ብቃት ያለው ዜጋን ለማፍራት የሚደረገው ተግባር ይደናቀፋል:: ምክንያቱም በመጻሕፍት ግዢና በትምህርት ቤት ወርኃዊ ክፍያ መብዛት ናላው የዞረና የተማረረ ወላጅ፣ የማስተማሩን ነገር ወደ ጎን ብሎ የልጆችን ሆድ መሙላት መቻል በራሱ በቂ ነው ወደሚል አንድምታ እንዲያመራ ያስገድደዋልና::

(ወንድወሰን አለምነህ፣ ከጦር ኃይሎች)

ግብፃውያን አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ከተሰየሙ በኋላ

ለተቃውሞ ወጡግብፃውያን አዲስ የተመረጡትን የአገሪቱን

ጠቅላይ ሚኒስትር በመቃወም በድጋሚ በታህሪር አደባባይ ለተቃውሞ መውጣታቸውን ዓለም አቀፍ የዜና አውታሮች ዘግበዋል:: አልጄዚራ እንደዘገበው የቀድሞውን ፕሬዚዳንት ሆስኒ ሙባረክን ከሥልጣን ለማውረድ በዚህ አደባባይ ተደርጐ የነበረው የተቃውሞ ሠልፍ አሁንም በስፋት ቀጥሏል:: ከሙባረክ መውረድ በኋላ በወታደራዊ ኃይል ስትመራ የቆየችው ግብፅ አሁንም ከትርምስ መውጣት አለመቻሏ ብዙዎችን አሳስቧል:: አዲስ የተመረጡት ካማል አል ጋንዘሪ በሆስኒ ሙባረክ አገዛዝ ወቅት እ.ኤ.አ ከ1996 እስከ 1999 ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው አገልግለዋል:: በሙባረክ ላይ የሕዝብ አመፅ ሲነሳ ግን ራሳቸውን ከሙባረክ በማራቅ የአማፅያንን ጐራ ተቀላቅለዋል:: ሕዝቡም አዲሱን ጠቅላይ ሚኒስትር ‹‹አንፈልጋቸውም›› የሚል መፈክር በማሰማት ባለፈው ዓርብ ታህሪር አደባባዩን አጥለቅልቆታል::

ኢራን 12 የሲአይኤ ወኪሎችን አሰርኩ አለች

ኢራን በድብቅ ለአሜሪካው የስለላ ድርጅት (ሲአይኤ) ሲሰልሉ አግኝቻቸዋለሁ ያለቻቸውን 12 ግለሰቦችን በቁጥጥር ሥር ማዋሏን ዘ ጋርዲያን ዘግቧል:: የአገሪቱን ባለሥልጣናት ጠቅሶ ዘገባው እንዳመለከተው፣ ግለሰቦቹ የኢራንን የፀጥታና የጦር ኃይል የደኅንነት ሚስጥሮችን ሲያሰባስቡ ነበር:: በጣም በጥብቅ ጥበቃና ጥንቃቄ ሥር የሚገኘውን የኑክሌር ፕሮግራሟን ሚስጢር ሲሰበስቡ መያዛቸውንም ገልጻለች:: ኢራን በቁጥጥር ሥር ስላዋለቻቸው ግለሰቦች ዜግነት ምንም ያላለች ሲሆን፣ የሲአይኤ ባለሥልጣናትም እስከ ዓርብ ምሽት ድረስ በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥበዋል:: ካለፈው ወር ጀምሮ በኑክሌር ግንባታ ዙሪያ ዋሽንግተንና ቴህራን ሲወዛገቡ ቆይተዋል:: አሜሪካ ኢራን የኑክሌር ቦምብ እየሠራች ነው በማለት በአገሪቱ ላይ ማዕቀብ በመጣል ስትቃወም ቆይታለች::

በየመን አዲስ ግጭት ተቀሰቀሰየየመኑ ፕሬዚዳንት አሊ አብደላ ሳላህ

በአገሪቱ አልቆም ያለውን የሕዝብ አመፅ ለማርገብ ከረጅም ጊዜ ውትወታ በኋላ ሥልጣናቸውን ለምክትላቸው ለማስረከብ የስምምነቱን ፊርማ መፈረማቸውን ተከትሎ፣ በአገሪቱ አዲስ ግጭት መነሳቱን አልጄዚራ ዘግቧል:: ግጭቱ የተፈጠረው በፕሬዚዳንት አብደላህ ሳላህ የወንድም ልጅ በሚመራው የጦር ኃይልና መንግሥትን ከድተው ተቃዋሚዎችን በተቀላቀሉት ጄነራሎች በሚመራው ጦር መካከል ነው:: ግጭቱ በሁለቱ የጦር መሣርያ በታጠቁ ቡድኖች መካከል ይሁን እንጂ የሞት ፅዋን እየቀመሱ ያሉት ሰላማዊ ዜጎች መሆናቸውን ዘገባው አመልክቷል:: የመናውያን ፕሬዚዳንቱ ሥልጣናቸውን ለምክትላቸው ማስረከባቸውን በመቃወም በዋና ከተማዋ ሰነዓና በታይዝ ከተማ ውስጥ ለተቃውሞ ወጥተዋል:: ፕሬዚዳንቱም በ30 ቀናት ውስጥ ሥልጣናቸውን እንዲያስረክቡ ጠይቀዋል::

ሶሪያ የዓረብ ሊግን ቀነ ገደብ ተላለፈች

ሶሪያ ለስምንት ወራት የቆየውን ደም አፋሳሽ የሕዝብ አመፅ ተከትሎ ሊጣልበት የተወሰነውን የኢኮኖሚ ማዕቀብ ከመወሰኑ በፊት፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ የዓረብ ሊግ ታዛቢዎችን እንድታስገባ ተሰጥቷት የነበረውን ቀነ ገደብ ተላለፈች:: ኦሶሼትድ ፕሬስ እንደዘገበው፣ የዓረብ ሊግ ሶሪያ ታዛቢዎችን በ24 ሰዓት ውስጥ እንድታስገባ ደንግጐ ነበር:: ነገር ግን ቀነ ገደቡ እስከአለፈበት ዓርብ ከሰዓት በኋላ ድረስ ከደማስቆ የወጣ ምንም ዓይነት መግለጫ አልተገኘም:: በዚሁ ሳቢያ የዓረብ ሊግ አባላት በአገሪቱ ላይ ስለሚጣለው ማዕቀብ ለመነጋገር እንደሚሰባሰቡ ተገልጿል:: ፕሬዚዳንት በሽር አልአሳድን ከሥልጣን ለማውረድ በአገሪቱ በተነሳው የሕዝብ አመፅ ከመንግሥት በሚሰነዘር የኃይል ጥቃት እስካሁን ከ3500 በላይ ሰዎች መገደላቸው ተረጋግጧል:: ፕሬዚዳንት አሳድ በዜጎቻቸው ላይ እየወሰዱት ያለውን የኃይል ዕርምጃ እንዲያቆሙ ከዓለም መንግሥታት ጫና ሲፈጠርባቸው መቆየቱን ዘገባው አስታውሷል::

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 29 | እሑድ | ኅዳር 17 ቀን 2004 ክፍል-1

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 30 | እሑድ |ኅዳር 17 ቀን 2004ክፍል-1

Invitation to Bid for Car Rental Service Agreement

1. Marie Stopes International Ethiopia (MSIE) a partner of Marie Stopes International, is a not- for profit organisation established to ensure the provision of quality and sustainable Family planning/ Reproductive health services to safeguard the reproductive right of women, men and young people in the country.

2. MSIE invites sealed bids from eligible bidders for the provision of car rental services including light and heavy duty vehicles for a contract period of one year.

3. Interested bidders may obtain the bidding documents during office hours’ starting from the first day this notice is announced to the public against payment of non-refundable administrative charge of Birr 100.00 (one hundred birr) from the following address:

Marie Stopes International EthiopiaWolo Sefer, Ethio- China Road

In front of Tebabaer Berta BuildingKirkos Sub City, Kebele 02

House No. 174Addis AbabaP.O. Box 5775

Tel: 011-5509307, 0115509250 or 0115509463

4. Wax sealed and stamped bids must be delivered to the above office on or before 15th December 2011 at 10:00 am. Late bids shall be rejected.

5. Bidders are required to attach renewed license, business profile and recommendation

letter of organizations so far served. 6. MSI Ethiopia reserves the right to reject any or all bids and not obliged to accept least

prices. MSIE

‹‹የውጭ መንግሥታት...ላይ ይወጣል:: ስለዚህ ፍሬንድሽፕ አካባቢ ብዙም የሚቀየር ነገር የለውም:: ዞሮ ዞሮ ከዚህ በኋላ ዋናው መንገድ ላይ ፓርኪንግ አይኖርም:: ማዞሪያ ቦታዎች እንደ ልብ አይኖሩም:: አሁን በየቦታው የምናያቸው የተሽከርካሪ ማዞሪያዎች አይኖሩም::

ሪፖርተር፡- በቦሌ መንገድም ሆነ በአብዛኛው በከተማው የሕንፃ አገነባቦችን ስናይ የፓርኪንግ ቦታን ታሳቢ የሚያደርጉ አይደሉም:: ይህንን ያህል መንገድ ተሠርቶ ፓርኪንግ ከሌለ በቦሌ መንገድ ላይ ያሉ ትላልቅ የቢዝነስ ተቋማት ላይ ተፅዕኖ አይፈጥርም? የሕንፃዎቹ ተጠቃሚዎች ተሽከርካሪዎቻቸውን የት ሊያቆሙ ይችላሉ?

ኢንጂነር ፍቃዱ፡- በዚህ መስመር ላይ ፓርኪንግ የለም:: መኪና መንገድ ላይ ማቆም አይፈቀድም:: ሕንፃዎቹ በሚገነቡበት ጊዜ በፓርኪንግ እንዲጠቀሙባቸው የተሰጣቸውን ከሥር ያሉ ቦታዎች ለተለያዩ ጉዳዮች እያዋሉ ያሉ አሉ:: አሁን ግድ ሲሆን ለተለያየ ጥቅም ያዋሉትን ቦታ ወደ መኪና ማቆሚያነት መቀየር ይኖርባቸዋል:: ከዚህ ጐን ለጐን እያሰብን ያለነው ዋናው መንገድ በሚሠራባቸው ቦታዎች ላይ የመኪና ማቆሚያ ሼልፍ ሕንፃዎች እንዲኖሩ እያሰብን ነው:: ክፍት ቦታዎች ለዚህ እንዲውሉ ይደረጋል::

ሪፖርተር፡- የአስኮ መንገድ ግንባታ እጅግ በመጓተቱ የተነሳ የአካባቢው ነዋሪዎች እየተመረሩ ነው:: እስካሁን ያልተጠናቀቀበት ምክንያት ምንድነው?

ኢንጂነር ፍቃዱ፡- ለአስኮ መንገድ መዘግየት ዋነኛው ምክንያት የወሰን ማስከበር ችግር ነው:: የወሰን ማስከበሩ ችግር ባልተቃለለበት ሁኔታ ነው የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን ሥራውን ለመጀመር የገባው:: ወደ ሥራው እንደገባ ግን በ2001 ዓ.ም. ምንም መነቃነቅ አልቻለም:: ወዲያው ክረምቱ ገባ:: በክረምቱ ምክንያት ተነካክቶ የነበረው ነገር ጨቀየ:: በዚህም በኅብረተሰቡ ላይ ችግር ደረሰ:: ከዚያ በመጠናከር የወሰን ማስከበሩን ሥራ ወደ መሥራት ነው የተኬደው:: በዚህ ደረጃ አስተዳደሩ እንዲሁም በከንቲባው ጭምር በተወሰደ ዕርምጃ የተሻለ ነገር ተፈጠረ:: በመጀመሪያ በዕቅድ ደረጃ ፕሮጀክቱ የወሰን ማስከበር ችግር ስለነበረው ባለሥልጣኑ በራሱ ኃይል ነው ለመሥራት ያሰበው:: ምክንያቱም የወሰን ማስከበር ችግር ያለበት ቦታ ኮንትራክተር ካስገባን ለተጨማሪ ካሣ ክፍያ ነው የሚዳርገን:: አሁን በከተማው ዘገዩ የሚባሉት በርካታ መንገዶች ለመዘግየታቸው ቀደም ብዬ ከገለጽኳቸው ምክንያቶች ውጪ፣ ወሰን ባለማስከበር የሚዘገየው ግንባታ ያስከተለባቸውን ወጪ ኮንትራክተሮቹ ይጠይቃሉ:: ትከፍላለህ::

ስለዚህ ብዙ ዕዳ ውስጥ እንዳንገባ ብለን ነው

ከዊንጌት አስኮ ሳንሱሲ ድረስ ያለውን ይህንን መንገድ በራስ ኃይል ለመገንባት የፈለግነው:: ከዚያ በኋላ ግን በወሰን ማስከበሩ ላይ የተሻለ ሥራ ተሠርቷል ብለን ስላመንን፣ በ2003 ዓ.ም. ሥራውን በመክፈል 2.5 ኪሎ ሜትሩን መንገድ ከዊንጌት አስኮ ጫማ ፋብሪካ ድረስ ያለውን ጨረታ አውጥተን ለኮንትራክተር ሰጥተናል:: ከአስኮ ጫማ ፋብሪካ እስከ ሳንሱሲ ያለው 200 ሜትር አስፓልት የማልበስ ሥራ ካልሆነ በስተቀር በአሁኑ ወቅት አልቋል ማለት ይቻላል:: በአጠቃላይ በዚህ ዓመት ያልቃል ብለን እንጠብቃለን:: እዚህ አካባቢ በቫርኔሮ የሚሠራ ሌላ መንገድ አለ:: ከአስኮ አዲስ ሠፈር እስከ ትራፊክ ሠፈር ድረስ ያለው የ2.5 ኪሎ ሜትር መንገድ ሥራ እየተጠናቀቀ ነው:: በሦስተኛ ደረጃ ከፊሊጶስ በጊዮርጊስ አድርጐ አስኮ አዲሱ ሠፈር የሚመጣ መንገድ፣ ከአስኮ አዲሱ ሠፈር እስከ ጊዮርጊስ መቃረቢያ ድረስ ያለውን መንገድ ባለሥልጣኑ በ1998 ዓ.ም. የጨረሰው ነው:: ግን ከዚያ መጥተን በጊዮርጊስ አድርገን ወደ ፊሊጶስ መግቢያ ድልድይ ሊኖረው የሚገባ በመሆኑ፣ የድልድዩን ሥራ ዲዛይን ለኮንሰልታንት ተሰጥቶ ዲዛይኑ አልቆ አሁን ጨረታ ላይ ነው ያለው:: ሥራውም ዘንድሮ ይጀመራል::

ሪፖርተር፡- በዚህ አካባቢ ያለው የመንገድ ሥራ ያዝ ለቀቅ እያለ እንዲያውም ዓመታት እያስቆጠረ መሄዱ ከታሰበው በላይ ወጪ እንዳስወጣችሁ ይታመናል::

ኢንጂነር ፍቃዱ፡- መንገዱ በአብዛኛው በራስ ኃይል የተሠራ በመሆኑ በዚህ ረገድ እንደ ኮንትራክተር ኪሣራችንን አናይም:: ለኮንትራክተር ተሰጥቶ ይህንን ያህል መዘግየት ቢኖር ኖሮ ከኮንትራቱ ዋጋ ያልተናነሰ ለተጨማሪ ክፍያ ይዳርገን ነበር::

ሪፖርተር፡- በርካታዎቹ የአዲስ አበባ መንገዶች የጥገና ያለህ የሚሉ ይመስላሉ:: በክረምት ጥገና ማድረግ ባይቻልም ክረምቱ ከወጣ በኋላ በበቂ ሁኔታ ያለመጠገናቸው ምክንያቱ ምንድነው? የጥገና በጀታችሁስ ምን ይመስላል?

ኢንጂነር ፍቃዱ፡- በበኩላችን ጥገና ላይ ፈጣን ነን:: የክረምቱ ወራት እንዳለቀ ወዲያው በየቦታው ለትራፊክ ችግር ይፈጥር የነበረውን ነገር የመፍታት ሥራ በጥሩ ሁኔታ ነው የምንሄደው:: ነገር ግን ለጥገና እየተሰጠን ያለው በጀት ግን በጣም አነስተኛ ስለሆነ የመቀባት ዓይነት ሥራ ነው የምንሠራው:: ምክንያቱም በክረምት መንገዱ ይፈርስና መልሰህ ትጠግናለህ:: ይህ የሚመነጨው ከበጀት እጥረት ነው:: በጀቱ ቢኖር ኖሮ ዘንድሮ የምትጠግነው ጥገና ቢያንስ ሁለት ሦስት ዓመት የሚያቆይ ይሆን ነበር:: እንዲህ ያሉ ጥገናዎችን በዋና ዋና መስመሮች ላይ እናደርጋለን:: ዋና ዋና መስመሮችን አጥንተን እንጀምራለን:: ለምሳሌ

100 ሚሊዮን ብር ለጥገና ጠይቀህ 40 ሚሊዮን ብር ቢሰጥህ ጦር ኃይሎች አካባቢ ያለውን መንገድ ጠግኜ ሌላውን መንገድ አልጠግንም የምትልበት ስትራቴጂ አይኖርም:: በ40 ሚሊዮን ብሯ በተቻለ መጠን ለሁሉም የሚዳረስበትን አሠራር ነው የምትከተለው:: ሁሉንም ለማዳረስ የምታደርገው ጥገና ከጥራትና ከአገልግሎት አኳያም ብዙ ጊዜ የሚሠራ አይደለም:: ስለዚህ ዋነኛ ምክንያቱ የበጀት እጥረቱ ነው:: የበጀት እጥረቱ ባይኖርብህ ብዙ ትሠራለህ:: በዚህ ምክንያት ጥገና የምናካሂደው ስትራቴጂካዊ በሆነ መንገድ ነው:: ነገ አፍርሰን እንደ አዲስ የምንሠራቸው መንገዶች ላይ ብዙ ጥገና አናደርግም:: ይህ ጥፋት ስለሚሆን ነው::

ሪፖርተር፡- በመንገድ ግንባታም ሆነ በጥገና ሥራ በተደጋጋሚ የሚጠቀሰውን ይህንን የበጀት ችግር እንዴት ማቃለል አስባችኋል? እስከመቼስ እንዲህ እየተባለ ይቀጥላል?

ኢንጂነር ፍቃዱ፡- ይኼ ትልቅ ችግር ነው:: በአገራችን የሚሠሩ መንገዶች የጥገና በጀታቸው ይሸፈናል የሚባለው በመንገድ ፈንድ ጽሕፈት ቤት ነው:: የመንገድ ፈንድ ጽሕፈት ቤት ግን ሁሉም የመንገድ ኤጀንሲዎች የሚጠይቁትን ያህል መመለስ የሚችልበት ደረጃ ላይ አይደለም:: ተቸግሯል:: እኛም ችግሩ ስለሚገባን ሁልጊዜ እንናገራለን፤ የሚሰጠን መልስ ግን ከዚህ በላይ ልናግዛችሁ አንችልም የሚል ነው:: ይህ እንዳለ ሆኖ የአዲስ አበባ አስተዳደር በተለይ በዚህ ዓመት ጥገና ላይ ልዩ ትኩረት ነው የሰጠው:: ካቢኔውም ሆነ ከንቲባውም ነባሮቹን መንገዶች በደንብ መያዝ ስላለብን ሌላ ዓመታት ላይ ከምታደርጉት ጥገና በተሻለ ሥሩ ብለዋል:: ከመንገድ ፈንድ የሚፈለገው ገንዘብ ካልተገኘ ሌሎችንም መንገዶች ዘግተን ቢሆን በራሳችን በጀት እንሠራለን የሚል አቋም ነው ያለው:: በዚህ መነሻነት በበጀት ዓመቱ 23 ኪሎ ሜትር መንገድ በተጠናከረ መንገድ እንጠግናለን:: የሚጠገኑትንም መንገዶች መርጠናል:: የተጀመረም አለ:: ብዙ ጊዜ እንደምናደርገው ከመስከረም እስከ ህዳር ባለው ጊዜ ጉድጓድ የማጥፋት ሥራ ነው የምንሠራው:: በዚህ ደረጃ ሳየው ጥቂት የሚባል ካልሆነ በስተቀር በአብዛኛው ሠርተናል:: የተጠናከረውን ጥገና ደግሞ እንቀጥላለን::

ሪፖርተር፡- በከተማዋ ውስጥ ያለውን የትራፊክ መጨናነቅ ለመቀነስ ይገነባሉ የተባሉ ተላላፊ መንገዶች አሉ:: ከዚህ ውስጥ በቄራ አካባቢ ይገነባል የተባለው መንገድ አንዱ ነው:: እንዲህ ያሉ ሥራዎች አሁን ምን ደረጃ ላይ ናቸው?

ኢንጂነር ፍቃዱ፡- የአዲስ አበባ ከተማ ችግር የኔትወርክ ርዝመት አይደለም:: ትራንስፖርቱ ችግር የሚገጥመው መኪናው ማቋረጫ ላይ ሲደርስ ነው:: ማቋረጫዎች ላይ ያለውን ችግር ለመቅረፍ መጀመሪያ ዲዛይኖች እየተሠሩ ነው ያሉት:: ባለፈው ከጦር ኃይሎች ኮካ ኮላ መገንጠያ ጀምሮ እስከ መገናኛ ያለው መንገድ ዲዛይን ተሰጥቷል:: ይኼ ከባቡሩ መስመር ጋር አብሮ ተጣጥሞ የሚሠራ ሆኖ ኡራኤል ላይ፣

መገናኛ ላይ፣ ሜክሲኮ ላይ ያሉትን ችግሮች እንዴት አድርገን ነው የምንፈታቸው በሚል የዲዛይን ሥራዎች እየተሠሩ ነው:: እንደተጠቀሰውም ከፑሽኪን አደባባይ እስከ ጐተራ ባለው መንገድ የመሀል መንገዱ ዕድሜውም ያረጀ በመሆኑ በአዲስ ዲዛይን እየተሠራ ነው:: በተለይ ቄራና ጐፋ ላይ ችግሮችን ለመፍታት የተለያዩ ዲዛይኖች እየተሠሩ ነው:: ጐፋ ማዞሪያ ላይ ቀደም ሲል የቀረበ ዲዛይን ነበር:: ይህ ዲዛይን ከሚፈጀው መሬት አኳያ የማሻሻል ሥራ እየተሠራ ነው:: ዞሮ ዞሮ ቀጥታ የሚሄደውን በሥር፣ አቋራጩን ደግሞ በድልድይ የማሻገር ሥራ ይሠራል:: በሌሎች ቦታዎችም ተመሳሳይ ጥናቶች እየተካሄዱ ነው:: አቅም በፈቀደ መጠን በዚህ ዓመት ጭምር የሚጀመሩ ናቸው:: የወሰን ማስከበሩ ሥራ ከተጠናቀቀ በኋላ የሚቀድመውን አይተን እንሠራለን:: ከዚህ አንፃር ብዙ የሕዝብ ጥያቄ ያለበት የፈረንሣይ መንገድ ነው:: ይህ የፈረንሣይ መንገድ ከስድስት ኪሎ አንበሳ ግቢ ጀምሮ በጃንሜዳ አድርገን አሁን ያለውን ድልድይ አስቀርተን ዲዛይን እየሠራን ነው::

ሪፖርተር፡- ወደ ፈረንሣይ የሚወስደው መንገድ ላይ ያለውን ድልድይ ማስቀረት ለምን አስፈለገ?

ኢንጂነር ፍቃዱ፡- ድልድዩ ወደታች የገባና ብዙ አደጋ ያደረሰ በመሆኑ ነው:: እሱን ድልድይ አስቀርተን ወደ ግራ በመሸሽ ወደ ፈረንሣይ ኤምባሲ አጥር ተጠግቶ በመካከል አቋርጦ የሚመጣ የመንገድ ዲዛይን ተሠርቷል:: ሰሞኑን ምልክት ተደርጐ ማፍረስ ይጀመራል:: ከዚህም ሌላ ከፈረንሣይ አቦ ጀምሮ እስከ ጉራራ (ፊልም ማዕከል) ድረስ በ25 ሜትር ሠፍቶ ይሠራል::

ሪፖርተር፡- ዘንድሮ የአዳዲስ መንገዶች ግንባታ ዕቅድ የለም ለምን?

ኢንጂነር ፍቃደ፡- በዋነኛነት የተያዘው ዕቅድ ቀደም ብለው የተጀመሩትን መንገዶች የማጠናቀቅ ሥራ ነው:: በሌላ በኩል ደግሞ የወሰን ማስከበር ሥራቸው አስቀድሞ የተጠናቀቀላቸው መንገዶች አሉ:: እንዲህ ዓይነቱ ችግር ከተቀረፈ በበጀት ዓመቱ የምንፈራረማቸው አዳዲስ መንገዶች በብዛት አሉ::

ሪፖርተር፡- በቅርቡ ገጠማችሁ የተባለው የበጀት እጥረት በቀጣዩ ዓመትም ይቀጥላል?

ኢንጂነር ፍቃደ፡- አስተዳደሩ እየሠራ ያለው ለአንድ ዓመት አይደለም:: ለሦስትና ለአራት ዓመት በጀት እየያዘ ነው ያለው:: በዚህ ዘርፍ በቀጣይ የሚሠሩትን ሥራዎች ከወዲሁ እያዘጋጀን በመሆኑ ለምንሠራቸው ሥራዎች ተጨማሪ በጀቶች እየጠየቅን ነው ያለው:: ከዚህ አንፃር የአዲስ አበባ አስተዳደር አቅም ካለውና የውጭ መንግሥታት አብረውን የሚሠሩበት ሁኔታ ከተመቻቸ በርካታ አዳዲስ መንገዶች ይኖሩናል ነው የምንለው::

ከክፍል-1 ገጽ 23 የዞረ

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 31 | እሑድ | ኅዳር 17 ቀን 2004 ክፍል-1

እ ኔ እ ም ለ ው

በመስፍን ተፈሪ ፀጋው

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር!

የዚህ ጽሑፍ አቅራቢ መስፍን ተፈሪ ፀጋው እባላለሁ:: በአዲስ አበባ ከተማ በጉለሌ ክፍለ ከተማ በተለምዶ አጠራር አዲሱ ገበያ በሚባለው አካባቢ ነዋሪ ስሆን፣ አሁን በጡረታ ላይ የምገኝ የ78

ዓመት አዛውንት ነኝ::ይህንን ደብዳቤ ለመጻፍ ምክንያት የሆነኝ ሰሞኑን በዜና

ማሰራጫዎች መነጋገሪያ ሆኖ የሰነበተው የከተማን ቦታ በሊዝ ስለመያዝ የወጣው አዋጅ ነው::

በንጉሡ ዘመን የሠራኋቸው ሦስት ደጃፍ ቤቶች ነበሩኝ:: ደርግ ሁለቱን ቤቶች ወርሶኝ የምኖርበትን ቤት ተወልኝ:: ይህንን አንድ ይዞታዬን አሻሽዬ ለመጠቀም ወይም ለሌላ ወገን አስተላልፌ በማገኘው ገቢ አነስተኛ ቤት ከከተማ ዳርቻ ላይ ገዝቼ፣ በተረፈው ልጆቼን ለማቋቋምና ኑሮዬን ለማሸነፍ አቅጄ የይዞታ ማረጋገጫ ለማግኘት ካመለከትኩ ከብዙ ውጣ ውረድ በኋላ ካርታዬን ከተረከብኩ አንድ ዓመት ይሆነኛል:: ይህንንም ካርታ በማግኘቴ መንግሥትን እያመሰገንኩ ሳለሁ ነባር ባለይዞታዎች ይዞታቸውን ለሌላ ሲያስተላልፉ፣ ይዞታው ወደ ሊዝ እንደማገባና የሊዝ ክፍያ እንደሚከፈልበት ተደጋጋሚ መገለጫ ሲሰጥ በመስማቴ፣ ኑሮዬን ለማሸነፍ እንደ አማራጭ የወጠንኩት ተስፋ በዚህ አዋጅ ምክንያት ደበዘዘ::

አዋጁ ደርሷቸው ካነበቡት ግለሰቦች እንደተረዳሁትና በዜና ማሰራጫዎች በተሰጡት መግለጫዎች መሠረት፣ ነባር ባለይዞታዎች ይዞታቸውን ለሌላ ወገን ሲያስተላልፉ የሊዝ ክፍያ እንደሚከፍሉና ይዞታውም ወደ ሊዝ ሥሪት እንደሚገባ በይፋ ተነግሯል:: አዋጁ እንዴት ወደኋላ ሄዶ ይሠራል? ይዞታችንን ለረዥም ዓመታት በዕድርና በቀበሌ አስተባባሪነት ውኃ፣ መብራት፣ ስልክና መንገድ እየሠራን እንደአቅማችን ወጭ በማውጣት ላለማነው ይዞታ ሊዝ መክፈል አለባችሁ ማለት ተገቢ ነውን?

ያለንበትን አካባቢ ለኑሮ አመቺ ለማድረግ ትውልዳችን

ጭምር የደከመበትን ድካም ከንቱ አድርጎ፣ የእኛ ነው የምንለውን በብዙ ድካምና ጥረት ያፈራነውን ሀብትና ንብረት ገበያው በሰጠን ዋጋ በፈለግነው ሁኔተ ለመሸጥ ባለመቻላችን ሕገ መንግሥታዊ መብታችንን አይነካም? ዜጎች ቋሚ ንብረት አፍርተው ወደ ትውልድ እንዲተላለፍ ለማድረግ የሚኖረንን መብትስ አይገድብም? በንብረታችን ላይ ያለንን ዋስትናስ አያሳጣንም?

አዋጁ መሬት በአንድ ዓይነት የይዞታ ሥሪት እንዲያዝ የማድረግ ዓላማ ካለው፣ ይዞታዎች ወደ ሊዝ ሥርዓት እንድገቡ ሲደረግ ይዞታው ሊዝ ሆኖ እንዲመዘገብ፣ ካርታው የሊዝ ዘመኑ ተጠቅሶ ያለክፍያ የሊዝ ውል ማዋዋል እየተቻለ፣ የሊዝ ክፍያ እንዲከፈል መደረጉ ግልጽ ካለመሆኑም በላይ ቅሬታ አሳድሯል:: በአካባቢያችን በአብዛኛው ባለይዞታ እንደአቅሙ አነስተኛ ቤትና ሰርቪስ ቤት ሠርቶ እየኖረ ስለሚገኝ፣ ይዞታው ወደ ሊዝ ሲዞር 50 በመቶ ካልገነባ የመሸጥና የመለወጥ መብት ሊነፍግ እንደሚችል ከወዲሁ ለመተንበይ ይቻላል::

በመሆኑም በአብዛኛው የከተማ ባለይዞታ በዚህ ሁኔታ ላይ ስላለ ከፍተኛ ስጋት አድሮበታል:: ይህንን አዋጅ ለማስፈጸምም እስርና ቅጣት በስፋት ተቀምጧል ይባላል:: የቅጣት ድንጋጌው ከሌሎች አዋጆች የተለየ በመሆኑ ማስፈራሪያነቱ ይበዛል:: ሌሎች አዋጆች ሲወጡ አዋጁን የጣሰ ሰው አግባብ ባለው የአገሪቷ ሕግ ይቀጣል በሚል ደንግገው ያልፋሉ:: ይህ ድንጋጌ ከማስፈራሪያነት አልፎ ተግባራዊ በሚሆንበት ጊዜ አጨቃጫቂ ሁኔታዎች ሊያስከትል ይችላል::

የሕዝብን ዕድገትና ልማት ለማምጣት እየተሠራ ሕዝብን የሚጎዳ አዋጅ ለምን ይወጣል? ሥርነቀል የሆኑ አዋጆች ከመውጣታቸው በፊት ሕዝቡ ሊመክርበት አይገባምን? ክቡርነትዎ እነዚህን አዋጆችና ሊወጡ የታሰቡ ደንቦችን ያውቋቸዋልን?

በከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ሲነገር እንደሰማነው በመንግሥት የሚወጡ አዋጆችና ዕቅዶች የሚወጡት አብዛኛውን ሕዝብ ተጠቃሚ ለማድረግና የአገር ዕድገትን ለማምጣት እንደሆነ ይነገራል:: በዚህ ሐሳብ የመንግሥት ደጋፊ የሆንን አረጋውያን በሙሉ

የምንስማማበት ነው:: ነገር ግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሕዝብን ተጠቃሚ ለማድረግ በሚል ሽፋን የሚወጡ ሕጎች ይዘታቸው የተለየ ሆኖ ይታያል:: ይህም አዋጅ ብዙኅኑን ተጠቃሚ የማያደርግና ጎጂ ተፅዕኖ ያለው ነው:: ይህ ከሆነ ዕድገትና ልማት ምንድን ነው? ደርግ የተወልንን የራሳችን የሆነውን ቤትና ንብረት አከራይተን ኑሯችንን ለማሸነፍ የምናደርገው ጥረት ‹‹ጥቂት ኪራይ ሰብሳቢዎች›› አሰኝቶናል::

የግል ንብረታችንን እያከራየን የምንኖር አረጋዊያን ጥቂት ሳንሆን ብዙ ነን:: የኪራይ ሰብሳቢነት ትርጉምስ ይኼ ነው ወይ? የመንግሥት ዓላማ ፍትሐዊ አሠራርን በማምጣት መልካም አስተዳደር እንዲሰፍን፣ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የተሻለ የኑሮ ደረጃ ላይ እንዲደርስና ዲሞክራሲ የሰፈነባት የበለፀገች አገርን ለመገንባት መሆኑ በሁላችንም ዘንድ የሚታወቅ ነው:: ሆኖም የበታች ሹማምንቶችና አንዳንድ ባለሥልጣናት ሆነ ብለው ከዚህ ዓላማ ውጪ አዋጆችንና መመርያዎችን በማውጣት ሕዝብን እያደናገሩ፣ በመንግሥትና በሕዝብ መካከል መቃቃር እንዲፈጠር ለማድረግ እየሞከሩ መሆኑን በግሌ ለመገንዘብ ችያለሁ::

የሚወጡት አዋጆች፣ ደንቦችና መመርያዎች በልማት ተሳታፊ ሊሆኑ የሚችሉና ለአገር ዕድገት የጎላ አስተዋጽኦ የሚኖራቸውን ጥቂት ባለሀብቶች የሚያሸማቅቅና የሚያስበረግግ፣ ሌሎች ዜጎችም የግል ንብረት እንዳይኖራቸውና ሀብት የማፍራት መብትና ነፃነት እንዳያገኙ የሚሞክሩ ሆነው ይታያሉ:: ይህንንም አስመልክቶ ሰሞኑን አንዳንድ ባለሥልጣናት በመሬት ጉዳይ በሚሰጡት መግለጫ ሕዝቡ እየተደናገረ ቅሬታ እየተሰማው ይገኛል:: ጉዳዩ በሚመለከታቸው የመንግሥት ባለሥልጣናት የተሰጠውም መግለጫ በቂና ግልጽ አልነበረም:: መግለጫው አዋጁን ከማብራራት ይልቅ የማረጋጋት ሥራ ላይ ያመዘነ ነበር:: የአዋጁን ዋነኛ ይዘት አስመልክቶ የተሰጠው ማብራሪያ በሕግ ባለሙያዎች ያን ያህል ተቀባይነት እንዳላገኘም በይፋ እየተነገረ ይገኛል::

በሌላ በኩል አዋጆችና መግለጫዎችን በዜና ማሰራጫዎች ለመስጠት የሚቀርቡ ባለሥልጣናት የተረጋጋ መግለጫ አይሰጡም፤ ቁጣ ይቀድማቸዋል:: እንዲያውም በሹማምንቶቹ ሲሰጡ የሰነበቱት መግለጫዎች ሕዝቡን

የሚያስቆጡ፣ የአዲስ አበባ ከተማ እንዳይረጋጋና በሥልጣን ላይ ያለው ፓርቲ ወደፊት በምርጫው አሸናፊ እንዳይሆን የታለሙ እንቅስቃሴዎች ይመስላሉ::

በተለይ በአዲስ አበባ ብዙ ችግሮት ይታያሉ:: ከዋናው መሥርያ ቤት እስከ ክፍለ ከተማ በአግባቡ አቤቱታን ተቀብሎ የሚወስን የለም:: ሠራተኛው በቂ ክህሎት የለውም:: የቡድን ሥራ ይበዛል፤ መብትን መጠየቅ ሙስና ሆኗል:: የአመለካከት ችግር አለ፤ ሙስና ከመቼውም ጊዜ በላይ ተንሰራፍቷል፤ የሚፈርም የለም፤ ፍርኃት ነግሷል፤ በየጊዜው የሚወጡ መመርያዎች ችግሩን የሚያባብሱ እንጂ የሚያሻሽሉ አይደሉም:: ተገልጋዩ ተማሯል፣ ተሸማቋል፣ መፍትሔና ትኩረት ይሻል::

የመሬት ጉዳይ በተረጋጋ መንፈስ ተጠንቶ ቋሚ የሆነ መፍትሔ ለምን አይፈለግለትም? በመሬት ዙርያ ጥናት ሲደረግ የፖለቲካ ሹመኞች ብቻ ሳይሆኑ የሕግ አማካሪዎችና ሌሎች ባለሙያዎች ተቀላቅለው ለምን አይሠሩም? ሹመኞች የአቅም ማጣትና የሙያ ክህሎት እንደሚጎድላቸው እየታወቀ ለምን ዝም ይባላል? እነዚህ ጥያቄዎች በተገቢ ሁኔታ ታይተው አግባብ ያለው ምላሽ ካላገኙ፣ ሕዝቡ በመንግሥት ላይ ያለው እምነት እየተሸረሸረ ችግር ሊያስከትል ይችላል::

በመሆኑም ይህ አዋጅ እንዳለ ሥራ ላይ የሚውል ከሆነ በዕድሜ የገፋን አረጋውያንና ሌሎች የኅብረተሰብ አካላት ጉዳት ሊያስከትልብን ከመቻሉም በላይ፣ ከፍ ያለ ፖለቲካዊ ችግር ሊያስከትል ስለሚችል አዋጁ እንዲሻሻል ማድግ አስፈላጊ ነው:: የአዋጁ ማሻሻያ ጥናት ላይም የሕግ አማካሪዎችና ሌሎች ባለሙያዎች ሊሳተፉ የሚችሉበትና ሕዝቡም ሐሳቡን የሚገልጽበት ሁኔታዎች ሊመቻቹ ይገባል::

ከዚህ በተጨማሪ በመሬት ነክ ጉዳዮች ሆን ብለው ወይም በአቅም ማነስ አደናጋሪ መግለጫዎችን በመስጠት በመንግሥትና በሕዝብ መካከል ክፍተት እንዲፈጠር በሚያደርጉና የራሳቸውን ጥቅም የሚያሳድዱ ባለሥልጣናት መኖራቸው ስለሚታማ፣ በቂ ጥናት ተደርጎ የማስተካከያ ዕርምጃ ሊወሰድ ይገባል በማለት ክቡርነትዎ በአንክሮ እንዲያዩት ለማሳሰብ ይህንን ግልጽ ደብዳቤ ጽፌያለሁ::

ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የተላከው የአዛውንቱ አቤቱታ

በሙናዬ አለባቸው

ጎበዝ እንዴት ነው ነገሩ? እንደማመጥ የሚባለው እንገለማመጥ ተብሎ ተተርጉሟል እንዴ? ነው ወይስ አንዱ ሲናገር ሌላው በጥሞና መስማት ትቶ በነገር ቁም ስቅል ማሳየት ተጀምሯል? ድሮ ነው አሉ:: ሰውየው በማለዳ ተነስቶ በየጎዳናው ላይ ያገኛቸውን ሁሉ ‹‹እንደምን አደራችሁ›› እያለ ሰላምታ ሲያቀርብ ሁሉም እየገላመጡት ያልፋሉ:: ግራ ቢገባው ለወዳጁ የደረሰበትን በማስተዛዘን ይነግረዋል:: ወዳጅ ተብየው የሰውየውን ብሶት ከሰማ በኋላ፣ ‹‹ቀበጡ አንተ ነህ ከማታውቀው ጋር ሰላምታ ለመለዋወጥ የከጀልከው፤›› ይለዋል:: ሰውየው የወዳጁ አስተያየት አበሳጭቶት ስለነበር፣ ‹‹ይብላኝላችሁ ለእናንተ እንጂ ዝም ማለትም ይቻል ነበር፤›› አለው አሉ::

ዝም ማለት ሲቻል ዝም የማይባልበት ጉዳይ ቢገጥመኝ ነው ይህንን ሐሳብ ወደእናንተ ለመወርወር ያሰብኩት:: እናንተም ምናለበት አርፈህ ብትቀመጥ ካላላችሁኝ እነሆ:: በቅርቡ በመሥርያ ቤታችን ውስጥ ተከታታይ ስብሰባዎችን እያደረግን ነው:: ዋናው ምክንያት ደግሞ ዘንድሮ ያቀድነው ዕቅድ በትክክል እየተተገበረ እንደሆነ ለመቃኘትና ችግሮች ካሉ ደግሞ የዕርምት ዕርምጃ ለመውሰድ ነው:: ይህ የተቀደሰ ዓላማ ፈሩን ስቶ በነገር አርጩሜ እንካ ቅመስ ስንባባል ከረምን:: የውይይታችን መነሻና መድረሻው ሥራው መሆኑ ቀርቶ ግለሰቦች ባቀረቡት ሐሳብ ምክንያት ብቻ የጥቃት ዒላማ መሆን ጀመሩ::

የበጀት ዓመቱን የሦስት ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ምዘና አድርገን በተፈጠሩ ችግሮች ላይ ሙያዊ ውይይቶችንና ክርክሮችን ስንጀምር ድንገት ሳይታሰብ ‹‹ኪራይ ሰብሳቢነት›› የሚለው የዘመናችን ክሊሼ ድንገት መድረኩን ተቆጣጠረው:: መሥርያ ቤታችን በተፈጥሮው ከገንዘብም ሆነ ከንብረት ጋር ግንኙነት የሌለው፣ ነገር ግን በሴክተር ዘርፎች ውስጥ የሚከናወኑ አፈጻጸሞችን ነው የሚቆጣጠረው:: መሥርያ ቤቱ ውስጥ ደግሞ የተለያዩ የሙያ ባለቤቶች ከነልምዳቸው አሉ:: በዕቅድ አፈጻጸም ላይ ያጋጠሙ ችግሮች ተነቅሰው ሲወጡና የችግሮቹ ምንጮች ሲነገሩ ‹‹ኪራይ ሰብሳቢ›› የሚለው ድንፋታ ከየት እንደመጣ ሊገባን አልቻለም::

ዕቅዱ በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳና የውጤት መለኪያ መሠረት ሊካሄድ ያልቻለው በአስፈጻሚው መሥርያ ቤት ውስጥ ከሥራ ይልቅ ስብሰባ በመብዛቱ ነው፤ የዕቅድ አተገባበር መለኪያዎችና መቆጣጠርያዎች አልታዩም፤ ከሥር ከሥር ይታዩ የነበሩ ችግሮች ክትትል ይደረግባቸው

ሲባል ችላ ተብለዋል፤ ከሚሠራው ይልቅ ለማይሠራው አግባብ ያልሆነ ጥቅም እየተሰጠ ተስፋ አስቆራጭ ድርጊቶች ተባብሰዋል፤ የቁጥጥር ሥርዓቱ በባለሙያ አልተመራም፤ ወዘተ የሚሉ መሠረታዊ ጉዳዮች ሲነሱ በዓይን ጥቅሻ የሚግባቡ የጥቅም ተሳስሮ ያላቸው ግለሰቦች ‹‹ኪራይ ሰብሳቢነትን›› ለዓላማቸው ማሳኪያ የማያስፈልግ ቦታ ላይ መዘዙት:: ይኼ እንግዲህ በኔትወርክ የተሳሰሩና ለግላዊ ጥቅም ያቆበቆቡ ግለሰቦች አገራዊ ጥቅምን አጣጥለው ሌሎችን ለመምታት እንዴት እንደሚገለገሉበት ያሳያል::

እንዲህ ዓይነቱ ከንቱ ነገር ያልጣማት አንዲት ባለሙያ፣ ‹‹ሙያና ፖለቲካን ነጣጥለን ብናየው ጥሩ ይሆናል:: ሁለቱን ነገሮች አንድ ላይ ለማስኬድ መሞከር ከያዝነው አጀንዳ ጋር ይጣረሳል:: እየተነጋገርን ያለነው የሙያንና የልምድን ተሞክሮ ያዋሀደ ውጤት እንዴት መገኘት ይኖርበታል የሚለውንና ለውድቀት የሚዳርገው ደግሞ ምንድን ነው? በሚለው ላይ ስለሆነ አግባብነት የሌላቸው ነገሮች እዚህ ባይቀርቡ ይሻላል፤›› በማለት ሐሳብ አቀረበች:: ይህ አስተያየት ያልተዋጠላቸው ግለሰቦች እጆቻቸውን ወደላይ ቀሰሩ:: በተለይ አንደኛው፣ ‹‹እንዲህ ዓይነቱ በማር የተለወሰ መርዝ ለዕድገታችን ነቀርሳ ነው፤›› ሲል ብዙዎቻችን ደነገጥን:: ሰውየው ቀጠለ:: ‹‹ሙያና ፖለቲካን ነጣጥለን እንይ ማለት የኪራይ ሰብሳቢዎች አጀንዳ እንጂ ልማታዊነት አይደለም፤›› እያለ ሲንጨረጨር በበኩሌ የምገባበት ጠፋኝ:: እንዴ ግለሰቡ ጠቡ ከባለሙያዋ ጋር ነው ወይስ ከተሰጠው አስተያየት ጋር? የፈለገ ቢሆንስ በሙያ ጉዳይ ላይ እናተኩር ማለት ይኼንን ያህል የሚያሳብድ ከሆነ ሌላ ነገር ቢመጣ ምን ሊኮን ነው? እጅግ በጣም ያሳስባል::

ሌላኛው እጁን አወጣ ተፈቀደለት:: በነገራችን ላይ በሙያዊ ተልዕኮ ላይ ያለን ሰዎች ነገር ዓለሙን ትተን የሚባለውን በድንጋጤ ማዳመጥ ጀመርን:: ሰውየው እንዲህ በማለት ጀመረ:: ‹‹እስካሁን የሰማናቸው አሉባልታዎች በየድራፍት ቤቱና በየካፌው የምንሰማቸው የኪራይ ሰብሳቢዎች እሮሮ ናቸው:: ስብሰባ በዛ፤ ፍትሐዊ ያልሆነ ምዘና ይካሄዳል፤ ለባለሙያዎች ዕድል አይሰጥም፤ የማይሠራ ይጠቀማል፣ ወዘተ የሚባሉት በሙሉ በአገር ወዳድነት ስም የተሸፈኑ የኪራይ ሰብሳቢነት አጀንዳዎች ናቸው፤›› ሲል፣ እኔ ደግሞ በልቤ መቼ ይሆን ይህ ሁሉ ድንፋታ የሚያበቃው ማለት ጀመርኩ:: ውስጤ ከመታፈኑ የተነሳ ጨነቀኝ:: ‹‹ኪራይ ሰብሳቢነትን›› የሚያወግዙት ግለሰቦች ተራ በተራ እየተነሱ እስኪበቃቸው አጥረገረጉን:: ከአንድ ሰዓት በላይ ሙያዊ ውይይት ቆሞ የደርግ ዘመን እስኪመስል ድረስ መፈክር በሚመስሉ አስተያየቶች ተደበደብን:: ይብላኝ ለአገሬ ያሰኛል::

ሰዎቹ እስኪበቃቸው ከተናገሩ በኋላ ሌላ አስተያየት ተጠየቀ:: ያችው ባለሙያ ጓደኛችን እጇን እንደገና አወጣች ተፈቀደላት:: እኔና መሰሎቼማ ሁሉንም ነገር ትተን ማዳመጣችንን ቀጥለናል:: ባለሙያዋ እንዲህ አለች:: ‹‹እጅግ በጣም ሲበዛ አዝናለሁ:: እኔ እዚህ መሥርያ ቤት ውስጥ ተቀጥሬ በመሥራቴ ምክንያትና በሰጠሁት አስተያየት ሳቢያ እንዲህ ዓይነቱ ዘለፋ መቅረብ አልነበረበትም:: እየተነጋገርን የነበረው የታቀደው ዕቅድ በሚገባ ተግባራዊ ያልሆነው በምን ምክንያት ነው ሲባል፣ የታዘብናቸውን ችግሮች በሙያዊ መንገድ ነበር ያቀረብነው:: አሁን ግን ሙያችንን የሚያኮስስና ከሥራችን ጋር የማይገናኝ ስያሜ እየተለጠፈብን ነው:: ሕግ ካለ እሱን በሕግ እንጨርሳለን:: በዕቅዳችን ላይ የምናደርገው ውይይት እንዲህ ፈሩን ስቶ በመፈክር ጋጋታ የሚቀጥል ከሆነ ሥራ ለማቆም እገደዳለሁ፤›› ስትል መደናገጥ ተፈጠረ:: እንዲያ ለያዥ ለገናዥ ያስቸገሩት ሳይቀሩ ተወራጩ:: ምክንያቱ ደግሞ ግልጽ ነው:: ይህች ባለሙያ በአንድ ዓለም አቀፍ ድርጅት አማካይነት ተቀጥራ ለረጅም ዓመታት ከአውሮፓ በትምህርትና በልምድ ያካበተችውን ዕውቀት ለመስጠት የመጣች ናት:: የእሷ መሄድ ምናልባት በበላይ አካል ሊያስጠይቅ ይችላል::

ውይይቱን የሚመራው ሰው፣ ‹‹ሁላችንም የምንነጋገረው በጋራ ጉዳይ ላይ ነው:: ማንም ሰው ደግሞ የፈለገውን አስተያየት የመስጠት ሕገ መንግሥታዊ መብት አለው:: ኪራይ ሰብሳቢነት እንደምታውቁት የልማት ፀር ነው:: ኪራይ ሰብሳቢነት በተጠራ ቁጥር ለምን መበርገግ እንደሚፈለግ አይገባኝም:: አሁንም ይህ ታሳቢ መደረግ አለበት፤›› በማለት አስተያየቱን አጠናቆ መድረኩን እንደገና ክፍት አደረገው:: አንድ ታዋቂ ባለሙያ እጃቸውን አውጥተው ዕድል ካገኙ በኋላ፣ ‹‹እየተነጋገርን ያለነው በዕቅዱ ተግባራዊነትና በአፈጻጸም ወቅት ስላጋጠሙ ችግሮች ነው:: ስለኪራይ ሰብሳቢነት ከተነሳ ደግሞ፣ የዕቅድ አፈጻጸሙን ያስተጓጎሉትና አንገመገምም ብለው የሚያድበሰብሱት ናቸው ኪራይ ሰብሳቢዎች? ወይስ ሙያዊ የመፍትሔ መንገድ የሚጠቁሙት ናቸው? ይህ ምላሽ ካላገኘ ይኼ ስብሰባ ዋጋ አይኖረውም፤›› ብለው ቤቱን በአንድ እግሩ አቆሙት:: በበርካታ መሥርያ ቤቶች የሚደርሱት ጉድለቶች በአፈጻጸም ችግሮች ምክንያት ነው የሚባለውም በእንዲህ ዓይነቱ አሳዛኝ ተግባር ምክንያት መሆኑን ገለጹ:: ‹‹የገዛ ኃጢያታቸውን መደባበቅ የሚፈልጉ የተቧደኑ ሰዎች እኛን ባለሙያዎችን በእንዲህ ዓይነት መንገድ እያዋረዱን ችግር ሲፈጥሩ ልንታገስ አይገባም፤›› በማለት በቁጣ አስተያየታቸውን አጠቃለሉ::

ከፀጥታው ብዛት ስፒል ብትወድቅ እንኳን ይሰማ

ነበር:: ሰብሳቢው እንደተለመደው ወደ ባልደረቦቹ አየ:: ፀጥታ ሰፍኗል:: በዚህ መሃል ያችው ባለሙያ ለሦስተኛ ጊዜ እጇን አወጣች:: ‹‹በእኔ አስተያየት የመሥርያ ቤቱ ችግሮች ነገሮችን ሁሉ ‘ኪራይ ሰብሳቢ’ በሚለው ሐረግ ውስጥ ለመሸጎጥ የምትፈልጉ ናችሁ:: ድክመታችሁን የምትሸፍኑት ይህንን ሐረግ በየቦታው በመሸጎር ሌሎችን በማሸማቀቅ ነው:: የዕቅዱ ስኬታማ አለመሆን ዋነኛ ምክንያቶች ሆናችሁ መፍትሔ ይፈለግ ሲባል መፈክር መፍትሔ የሚሆን ይመስል ግራ ታጋቡናላችሁ:: አሁንም ይህንን አባዜያችሁን ትታችሁ በሙያዊ መንገድ መፍትሔ የማንፈልግ ከሆነ ለሚመለከተው የበላይ አካል ሪፖርት እጽፍና ምላሹን እጠብቃለሁ:: የበላይ አካሉም እንደናንተ ‘ኪራይ ሰብሳቢ’ በሚል ካለፈው ፍርዱን ለህሊናዬ ትቼ ውሳኔዬን እንደነገርኳችሁ አደርጋለሁ፤›› አለች::

በሰብሳቢያችን አማካይነት የአሥር ደቂቃ እረፍት ታወጀልን:: ለጊዜውም ቢሆን ተነፈስን:: ባለሙያዎች በዚያች አሥር ደቂቃ ውስጥ ሰብሰብ ብለን ተነጋገርን:: የባልደረባችንን አቋም አፀናን:: እረፍት አልቆ ስንመለስ የሰብሳቢያችንም ሆነ የሌሎቹ መንፈስ ተለውጦ ጠበቀን:: ሰብሳቢያችን፣ ‹‹በሚቀጥለው ሳምንት በስፋት በዕቅዱና ቀደም ሲል በተነሳው የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከት ላይ እንነጋገራለን:: ለጊዜው ይኼንን ስብሰባ እዚህ ላይ ዘግቼዋለሁ፤›› በማለት አረዳን:: እንደማመጥና እንነጋገር ሲባል ግልምጫና ቁጣ የሚቀድም ከሆነ እንዴት ስለ ጋራ ጉዳዮቻችን መነጋገር ይቻላል? ሙያን ለሙያተኛ፣ ፖለቲካን ለፖለቲከኛ እንተው ሲባል እንዴት ተደርጎ ከተባለ የመማር ትርጉሙ ምን ሊሆን ነው?

በእንዲህ ዓይነት መንፈስ ውስጥ ሆነን ለአገር የማይጠቅሙ አቋሞችን ማራመድ ምን ይጠቅማል? እርግጠኛ ነኝ የሚቀጥለው ሳምንት ስብሰባ ሙያን ማዕከል የሚያደርግ ሳይሆን የግለሰቦችን ገመና በመሸፋፈን ሌሎችን የመወንጀያ መድረክ ነው የሚሆነው:: በበኩሌ ‹‹ኪራይ ሰብሳቢነት›› የሚለው እሳቤ ባያሳስበኝም፣ ያለቦታው ማንም እየተነሳ እንደ ገደል ማሚቶ ሲያስተጋባው ግን አዝናለሁ:: እርስ በርስ ተቧድነው የግል ጥቅማቸውን እያሳደዱ ለአገር ተጨማሪ እሴት የማያመጡ ሰዎች ሲቀልዱበት ያሳዝናል:: በሙያዊ ጉዳይ ላይ የተለያየ አመለካከት በመያዝ ለተሻለ ነገር ማሰብ ይቀድማል? ወይስ በጠባብ ቡድናዊ ፍላጎት ውስጥ ተውጦ አገራዊውን ራዕይ መርሳት ይሻላል? ዝም ከማለት ይልቅ እንወያይበት በማለት ነው ይህንን የሰነዘርኩት::

ሙያዊ ጉዳዮቻችን ለምን የፖለቲካ ሰለባ ይሆናሉ?

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 32 | እሑድ |ኅዳር 17 ቀን 2004ክፍል-1

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 33 | እሑድ | ኅዳር 17 ቀን 2004 ክፍል-1

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 34 | እሑድ |ኅዳር 17 ቀን 2004ክፍል-1

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 35 | እሑድ | ኅዳር 17 ቀን 2004 ክፍል-1

ብሔራዊ የዳኝነት ሥልጣንና

የተከራካሪዎች ፈቃድበጌታሁን ወርቁ

ኢትዮጵያውያን በዕለት ተዕለት የማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ መስተጋብራት የተለያዩ የውል ወይም ከውል ውጪ ግንኙነቶች እርስ በርሳቸው ይመሠርታሉ:: በእንዲህ ዓይነት ግንኙነቶች የሚነሱ ክርክሮች ስለሚታዩበት ቦታና ተፈጻሚ ስለሚሆነው ሕግ ግልጽ ሕግጋት አሉ:: የፍርድ ቤቶችን ሥልጣን የሚወስኑ አዋጆችና መሠረታዊ መብቶችን የሚወስኑ ሕግጋት ክርክሮቹን የሚመሩ ደንቦችን ስለሚደነግጉ ተፈጻሚነታቸው ጥያቄ ውስጥ አይገባም:: ኢትዮጵያዊ ወይም በኢትዮጵያ ሕግ የተቋቋመ ድርጅት ከሌላ አገር ሰው (የተፈጥሮ ሰው ወይም ድርጀት) ጋር ከሚያደርገው የማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት የሚመነጩ ክርክሮች ስለሚታዩበትና ዳኝነት ስለሚሰጥበት ሁኔታ ግን የተወሰኑ ክፍተቶች ይታያሉ::

ለዚህ ጽሑፍ መነሻ የሆነኝ የኢትዮጵያ የመንግሥትና የግል ድርጅቶች የፋይናንስ ተቋማትን ጨምሮ በሚፈጽሟቸው ውሎች ውስጥ ስለሚካተቱ የዳኝነት ሥልጣንን የተመለከቱ ደንቦች ነው:: እነዚህ ደንቦች ኢትዮጵያ ውስጥ በተመዘገበውና ውጭ ባለው ድርጅት መካከል ከውል አፈጻጸም ጋር አለመግባባት ቢነሳ ጉዳዩ የሚታየው ውጭ ባሉ ፍርድ ቤቶች እንዲሆን፤ ተፈጻሚ የሚሆነው ሕግ ደግሞ እንዲሁ የውጭ አገር ሕግ እንዲሆን የሚስማሙበት ሁኔታ አለ:: ለአብነት ያህል የባንኮችን ተሞክሮ ብንወስድ የብሔራዊ የክፍያ ሥርዓት አዋጅ በደነገገው መልኩ የሚጠቀሙበትን የኤሌክትሮኒክ የክፍያ ሥርዓት በተሻለ ቴክኖሎጂ ለመቀየር የሶፍትዌር፣ የሃርድዌር፣ የጥገናና የምክር ወዘተ. የግዥና የአገልግሎት ውሎች ከውጭ ድርጅቶች ጋር ይዋዋላሉ:: በሁለቱ መካከል የሚደረጉ አብዛኞቹ ውሎች የዳኝነት ሥልጣን ከኢትዮጵያ ውጪ ያሉ ፍርድ ቤቶች እንዲኖሩዋቸው በማለት መስማማት ልምዱ ሆኗል:: ከውል መፈጸም ጀምሮ ያለው ዋናው ሥራ ኢትዮጵያ ውስጥ እየተከናወነ፣ አንዳንዴ ድርጅቶቹም ቅርንጫፍ ወይም ወኪል እያላቸው የውጭ ድርጅቶቹ በኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶችና ሕግጋት ለመዳኘት ፈቃደኛ አይሆኑም:: የዚህ ዋነኛ ምንጩ የውጭ ድርጅቶች የመደራደር አቅም እጅጉን ከኢትዮጵያኑ ስለሚበልጥ ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያ ውስጥ የተመዘገቡት ድርጅቶችም ጉዳዩን የምር ስለማይከራከሩበት ይመስላል:: ታዲያ በዚህ ጽሑፍ ስለ ብሔራዊ የዳኝነት ሥልጣን (Judicial jurisdiction) ፅንሰ ሐሳብና መርሆዎች የተወሰነ በማብራራት ተዋዋይ ወገኖች በውላቸው ላይ የኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች ሥልጣን እንዳይኖራቸው የሚስማሙትን የውል ቃል ቅቡልነት (Validity) ለመፈተሽ ሙከራ ይደረጋል::

ብሔራዊ የዳኝነት ሥልጣን ምንድን ነው?

ብሔራዊ የዳኝነት ሥልጣን ማለት በአንድ አገር ያሉ ፍርድ ቤቶች ተከራካሪዎች ላይ ወይም ንብረቶቻቸው ላይ አስገዳጅ ውሳኔ ለመስጠት ያላቸው ሥልጣን ነው:: ለምሳሌ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ፍርድ ቤቶች የቀረበላቸውን ጉዳይ ተቀብሎ ለመወሰን ሥልጣን ስለመኖር አለመኖራቸው ማጣራት ብሔራዊ የዳኝነት ሥልጣንን መወሰን ነው:: አንድ አገር ውስጥ ያሉ ፍርድ ቤቶች የዳኝነት ሥልጣን ካላቸው የሚሰጡት ውሳኔ በሌላ አገር ዕውቅና የሚሰጠውና የሚፈጸም ይሆናል:: በአንድ አገር የብሔራዊ የዳኝነት ሥልጣን ኖሮ በፍርድ ቤት ውሳኔ ከተሰጠ በሌላ አገር ያሉ ፍርድ ቤቶች የጉዳዩን

ዝርዝር ይዘት (The merits of the case) ሳይመለከቱ ውሳኔውን እንዳለ ያስፈጽማሉ:: ለምሳሌ ኢትዮጰያ ውስጥ የሚኖር የውጭ ዜጋ ላይ የብሔራዊ ዳኝነት ሥልጣን ኖሮት የኢትዮጵያ ፍርድ ቤት ውሳኔ ቢሰጥ፣ ዜጋ የሆነበት አገር ባለው ንብረት ላይ ፍርዱ ተፈጻሚ ይሆናል::

ብሔራዊ የዳኝነት ሥልጣን ሰዎችን የሚመለከት (Judicial jurisdiction in personam) ወይም ንብረቱን የተመለከተ (Judicial jurisdiction in rem) ሊሆን ይችላል:: የሁለቱ ልዩነት የሚቀርበው የክስ ዓይነትና የሚጠየቀው ዳኝነት ላይ ነው:: ሰዎችን የሚመለከት

ሥልጣን በአብዛኛው የተለመደ ሲሆን፣ ክሱ የሚቀርበው በተፈጥሮ ወይም በሕግ ሰውነት ያለው አካል ላይ ነው:: የሚጠየቀው ዳኝነትም ተከሳሹ ሊፈጽመው ስለሚገባው ግዴታ ነው:: አንድ ሰው የተወሰነ ገንዘብ እንዲከፍል፣ የሆነ ድርጊት እንዲፈጽም ወይም ከመፈጸም እንዲታቀብ የሚቀርቡ ክሶች በዚህ ሥር የሚወድቁ ሲሆን፣ በዚህ ጽሑፍም ምልከታ የሚደረግባቸው ናቸው:: ንብረትን የተመለከተ ሥልጣን (An action in rem) ተከሳሽ ተብሎ የሚጠራው የተፈጥሮ ወይም የሕግ ሰው ቢሆንም፣ የሚጠየቀው ዳኝነት ንብረትን በተመለከተ ይሆናል:: የአንድ ተንቀሳቃሽ ንብረት ስመ ንብረት እንዲዞር የሚቀርብ ክስ ከዚህ ወገን የሚመደብ ነው:: በዚህ ጽሑፍ ሰዎችን የሚመለከቱ የብሔራዊ የዳኝነት ሥልጣን መርሆዎችን በመዳሰስ ተከራካሪ ወገኖች በፈቃዳቸው የፍርድ ቤትን ሥልጣን የሚያስወግዱበትን ወሰን ብቻ እንቃኛለን::

የብሔራዊ የዳኝነት ሥልጣን የሚወስኑ መርሆች

በአንዲት አገር ውስጥ ያሉ ፍርድ ቤቶች ሰዎችን በተመለከተ የብሔራዊ ዳኝነት ሥልጣን የሚኖራቸው በሦስት መልኩ ነው:: እነዚህ በኢትዮጵያ የፍትሐ ብሔር ሥነ ሥርዓት ሕግ ላይ ማብራሪያ የጻፉት ፕሮፌሰር አለን ሴድለር የተነተኗቸውና ለዘመናት የኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች ተሞክሮ ላይ ተፅዕኖ ያደረጉ ናቸው:: የመጀመሪያው ተከሳሹ የአገሪቱ ዜጋ ከሆነ ወይም መደበኛ ቦታውን በአገሪቱ ካደረገ (Domiciliary)፤ ሁለተኛው የክርክሩ መነሻ ድርጊት በዚያች አገር የተፈጸመ በሆነ ጊዜና ሦስተኛው ተከሳሹ በአገሪቱ ፍርድ ቤት ለመዳኘት ፈቃድ ከሰጠ ነው:: ከእነዚህ ምክንያቶች አንዱ ካለ የአንዲት አገር ፍርድ ቤቶች ክርክሮቹን ተቀብለው የሚከራከር ብሔራዊ የዳኝነት ሥልጣን ይኖራቸዋል::

የመጀመሪያው ምክንያት ዜግነት ወይም መደበኛ ቦታ ነው:: በዚህ መርህ መሠረት ለምሳሌ ጉዳዩ ኢትዮጵያ ውስጥ የተፈጸመ ባይሆን እንኳን ተከሳሹ ኢትዮጵያዊ ወይም መደበኛ ቦታው ኢትዮጵያ ከሆነ የኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች የብሔራዊ ዳኝነት ሥልጣን ይኖራቸዋል:: ተከሳሹ ኢትዮጵያዊ ካልሆነ ወይም መደበኛ ቦታው ኢትዮጵያ ካልሆነ ከሳሹ ኢትዮጵያዊ ቢሆን እንኳ ሌሎች ምክንያቶች እንደተጠበቁ ሆኖ የኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች ክርክሩን ሊቀበሉ አይችሉም:: ኢትዮጵያዊ ዜጋ የሚባለው በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 6 መሠረት ወላጆቹ/ቿ አንደኛቸው ኢትዮጵያዊ/ት ከሆነ/ች ወይም በሕግ የኢትዮጵያ ዜግነት ካገኘ(ች) ነው:: የአንድ ሰው መደበኛ ቦታ (Domicile) ኢትዮጵያ ናት የሚባለው ደግሞ በፍትሐ ብሔር ሕጉ አንቀጽ 183 መሠረት የተቀመጠውን ትርጓሜ ካሟላ ነው:: በዚህ ድንጋጌ መሠረት የአንድ ሰው መደበኛ ቦታ ማለት ይህ ሰው በነዋሪነት ዓይነት (Permanently) እዚያው ቦታ በመኖር አሳብ የጉዳዮቹና የጥቅሞቹ ዋና ስፍራ ያደረገው ቦታ ነው:: በተግባር በነዋሪነት የመኖር ሐሳብን ማረጋገጥ አስቸጋሪ በመሆኑ በጊዜ ሒደት በተለመደ የመኖሪያ ቦታ (Habitual residence) መርህ ተለውጧል:: በሕግ ሰውነት የተሰጣቸው ተቋማትም በተቋቋሙበት አገር ዜግነታቸው ይወሰናል::

በዜግነት ወይም በመደበኛ ቦታ የብሔራዊ የዳኝነት ሥልጣን የመወሰን አመክንዮ በአገርና በዜጋ መካከል ያለው ቁርኝት ነው:: አገር (መንግሥት) ለዜጋው በሚሰጠው ብሔራዊ ጥቅም መልስ በአገሪቱ ፍርድ ቤቶች ለመዳኘት ፈቃድ ሊሰጥ ይገባዋል የሚል መነሻ አለ:: ሰውዬው ከአገሩ ወጥቶ ቢኖር እንኳን ባለመኖሩ

ዜግነቱ እንደማይቋረጥ መብትና ጥቅሞቹም እንደሚጠበቁ ሁሉ ለአገሪቱ ፍርድ ቤቶችም ሥልጣን ዕውቅና ሊሰጥ ይገባል:: ሆኖም በፍትሃዊነት አስተምህሮ (Fairness theory) የዜጋው የአካል ቅርበት ከዜግነቱ በተሻለ ግምት ውስጥ እንዲገባ ተደርጓል:: ሁለተኛው ምክንያት ድርጊቱ የተፈጸመበት ቦታ ሲሆን ነው:: አንድ ውል በሚፈረምበትና በሚፈጸምበት አገር ያለ ፍርድ ቤት በውሉ ምክንያት የሚነሱ ክርክሮች ለማስተናገድ ሥልጣን አለው:: አንዳንዴም ውሉ አንድ አገር የተመሠረተ ቢሆን እንኳ የሚፈጸመው ሌላ አገር ከሆነ ሁለተኛው አገር ሥልጣን ሊኖረው

ይችላል:: ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩ ሁለት ነጋዴዎች ኬንያ ላይ የሽያጭ ውል ፈርመው ንብረቱ የሚረከብበት ቦታ ኢትዮጵያ ከሆነ የኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች ብሔራዊ የዳኝነት ሥልጣን ይኖራቸዋል:: ከውል ውጭ የሆኑ ኃላፊነቶችም በተመሳሳይ መርህ ይገዛሉ:: ለምሳሌ አንድ ኬንያዊ ከኬንያ ወደ ኢትዮጵያ መኪና ሲነዳ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚሽከረከር መኪና ቢገጭ፣ ከግጭቱ ጋር የተያያዙ የኃላፊነትና የካሳ ጉዳዮች በኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች የሚታዩ ይሆናል::

ሦስተኛው በተከራካሪዎች ፈቃድ የሚመሠረት

ብሔራዊ የዳኝነት ሥልጣን ነው:: አንድ ሰው ኢትዮጵያዊ ዜጋም ባይሆን፤ ድርጊቱም ኢትዮጵያ ውስጥ ባይፈጸም በኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች ለመዳኘት ፈቃድ ከሰጠ ፍርድ ቤቶቹ ብሔራዊ የዳኝነት ሥልጣን ይኖራቸዋል:: ፈቃድ በግልጽ (Express) ወይም በዝምታ (Implied) ሊሰጥ ይችላል:: ተዋዋዮቹ በውላቸው ላይ ክርክራችን በኢትዮጵያ ፍርድ ቤት ይታያል በሚል ከተስማሙ ግልጽ ፈቃድ መስጠታቸው ሲሆን፣ በኢትዮጵያ ፍርድ ቤት ክስ ቀርቦበት የመከላከያ መልሱን ያቀረበ የውጭ ዜጋ ደግሞ በፍርድ ቤቱ ለመዳኘት በዝምታ ፈቃድ መስጠቱን መገንዘብ አያስቸግርም:: ይሁን እንጂ ተከሳሹ የቀረበው የፍርድ ቤቱን ሥልጣን ለመቃወም ብቻ ከሆነ ለፍርድ ቤቱ ሥልጣን ፈቃድ ሰጠ አያሰኘውም:: ከሳሹም ኢትዮጵያ ፍርድ ቤት ክስ ካቀረበ የፍርድ ቤቱን የዳኝነት ሥልጣን መቀበሉን ስለሚያመለክት ከተከሳሹ የሚቀርቡ የማቻቻል (Set off) ወይም የተከሳሽ ከሳሽነት (Counter claim) ጥያቄዎችም ላይ ፍርድ ቤቱ ሥልጣን ይኖረዋል:: በጊዜ ሒደት የዳበሩ ተጨማሪ አስተምህሮዎች ቢኖሩም ሙያዊ ስያሜ (Legal jargon) ስለሚበዛ እንዳይወሳሰብም ይኸው ይበቃል::

የአገራችን ሕግ ምን ይላል?

ቀደም ባሉት ክፍሎች የተገለጹ ጽንሰ ሐሳቦች ከሥነ ሕግ (Jurisprudence) በመነሳት የቀረቡ ሲሆን፣ መርሆዎቹ በኢትዮጵያ ሕግ ስለመካተት አለመካተታቸው ማየቱ ተገቢ ነው:: ብሔራዊ የዳኝነት ሥልጣንን በተመለከተ የተለያዩ መርሆዎች በተለያዩ ሕግጋት ተሰበጣጥረው የሚገኙ ሲሆን፣ ፍርድ ቤቶችም በተለያየ መልኩ ያስተናግዱታል:: የፌዴራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ የግለሰብ ዓለም አቀፍ ሕግን የሚመለከቱ ጉዳዮች የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የመጀመሪያ ደረጃ የፍትሐ ብሔር የዳኝነት ሥልጣን እንደሆነ ቢደነግግም፣ የብሔራዊ የዳኝነት ሥልጣንን በምልዓት የሚገዛ ሕግ የለም:: የንግድ ሕግ (አንቀጽ 647)፣ የባህር ሕግ (አንቀጽ 208,237) እና የፍትሐ ብሔር ሥነ ሥርዓት ሕግ (አንቀጽ 8,20) ከብሔራዊ የዳኝነት ሥልጣን ጋር የሚያያዙ ድንጋጌዎችን ቢያስቀምጡም ምሉዕ አይደሉም:: ብሔራዊ የዳኝነት ሥልጣን የግለሰብ ዓለም ዓቀፍ ሕግ (Private International law) ጥያቄ ሲሆን፣ ኢትዮጵያ ደግሞ ይህ ሕግ የላትም:: በረቂቅ መልክ የተዘጋጀ አዋጅ ቢኖርም፣ የሕግ ውጤት ስለሌለው የአገራችንን የብሔራዊ ዳኝነት ሥልጣን ለመተንተን አይጠቅመንም::

ኢትዮጵያ ብሔራዊ የዳኝነት ሥልጣንን የሚገዛ ሕግ የላትም ማለት ግን የውጭ ነገር (Foreign element) ያለው ጉዳይ በፍርድ ቤቶች አይስተናገድም ማለት አይደለም:: አንዳንድ የሕግ ባለሙያዎች በፍርድ ቤቶች ተሞክሮ ዙሪያ ጥናት በማድረግ የፍርድ ቤቶቹን አቋም ገልጸዋል:: እንደ ባለሙያዎቹ አገላለጽ፣ የኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች ሦስት ዓይነት ተሞክሮ አላቸው:: የተወሰኑት ብሔራዊ የዳኝነት ሥልጣንን በዝምታ በማለፍ ጉዳዩን መርምረው ውሳኔ ይሰጣሉ:: ሌሎቹ ደግሞ ወደ ፍትሐ ብሔር ሥነ ሥርዓት ሕግ በመሄድ ብሔራዊ የዳኝነት ሥልጣንን ይወስናሉ:: ቀሪዎቹ ደግሞ ከላይ በተመለከተው ክፍል የገለጹትን አጠቃላይ የሥነ ሕግ መርሆዎች ተፈጻሚ ያደርጋሉ:: የሥነ ሥርዓት ሕጉ ለብሔራዊ ዳኝነት ሥልጣን ያለውን ተፈጻሚነት በተመለከተ የተወሰኑ ክፍተቶች ይታያሉ:: መጀመሪያ በሥነ ሥርዓት ሕጉ ስለ ግዛት ክልል የዳኝነት ሥልጣን (Local jurisdiction) የተደነገጉት ድንጋጌዎች ዓላማ በዜጎች መካከል ለሚደረጉ ሙግቶች ነው:: ሲቀጥል የሥነ ሥርዓት ሕጉ በጊዜው የነበሩትን መብትና ግዴታ የሚወስኑ ሕግጋትን (Substantive laws) ለማስፈጸም እንጂ የግለሰብ ዓለም ዓቀፍ ሕግን ታሳቢ ያደረገ አይደለም:: ከዚያ ውጭ ግን በአብዛኛው ፍርድ ቤቶች የሚከተሉት የሥነ ሥርዓት ሕግ መርሆዎች ከላይ የተመለከትናቸውን በፕሮፌሰር አለን ሴድለር አቋም የተገለጹትን ነው:: ይህ ደግሞ በጊዜ ሒደት የዳበሩትን የፍትሃዊነት አስተምህሮ (The fairness theory) እና የአነስተኛ ግንኙነት አስተምህሮ (Minimum contact theory) መሠረት ያላደረገ ስለመሆኑ ትችት ይደርስበታል:: ለዓብነት ያህል ብሔራዊ ዳኝነት በዜግነት ብቻ ላይ መወሰን ተቀባይነቱ እንደቀነሰ ይነገራል:: ምክንያቱም ዜግነት የፖለቲካ ትስስርን የሚያመለክት ነው:: ዜግነቱ ኢትዮጵያዊ የሆነ ቤተሰብና ንብረት ግን ሌላ አገር መሥርቶ የሚኖርን ሰው ኢትዮጵያ ፍርድ ቤት ተሟገት ማለት ፍትሐዊ እንደማይሆን አንዳንድ ባለሙያዎች ይገልጻሉ::

ተዋዋይ ወገኖች የብሔራዊ ዳኘነት ሥልጣንን በስምምነት ማስቀረት ይችላሉን?

ኢትዮጵያ ውስጥ ነዋሪ የሆኑ የተፈጥሮና የሕግ ሰዎች ከውጭ ተቋማት ጋር የተለያዩ ዓይነት ውሎች ይዋዋላሉ:: በፋይናንስ ተቋማት የተለመዱትን ለመጥቀስ የገንዘብ ዝውውር ስምምነት፣ (Money transfer agreement) የሶፍትዌር ግዥና ጥገና ውል፣ (Software and maintenance agreement)

የማማከር (Consultancy) አገልግሎት፣ የዓለም ዓቀፍ ባንኪንግ አገልግሎት (ኤል.ሲ፣ዓለም ዓቀፍ የገንዘብ ዝውውር) ወዘተ. ይጠቀሳሉ:: እነዚህ ውሎች በአብዛኛው የሚዘጋጁት በውጪ ድርጅቶች እንደመሆኑ መጠን የአገር ውስጥ ድርጅቶች የመደራደር አቅማቸው አነስተኛ ነው:: በእነዚህ ስምምነቶች አብዛኛውን ጊዜ አከራካሪ የሚሆነው በስምምነቱ ላይ የሚነሱ ክርክሮች የሚታዩባቸው የዳኝነት ቦታዎችና ተፈጻሚ ስለሚሆነው ሕግ የሚወስኑት ድንጋጌዎች ናቸው:: የውጭ ድርጅቶቹ ከስምምነቶቹ መሠረት የሚነሱ ክርክሮች በራሳቸው አገር ሕግ ራሳቸው አገር እንዲታይ የውል ቃል ይቀርፃሉ፤ በድርድር ለመለወጥም ፈቃደኛ አይሆኑም:: እነዚህ የአገር ውስጥ ተቋማት በስምምነቶቹ ክርክር ቢነሳ በውጭ አገር የሚያወጡት የትራንስፖርት፣ የመጠለያ (Accommodation) የዳኝነት ክፍያና ለጠበቃ አገልግሎት የሚከፍሉት ገንዘብ ብዙ እንደሚሆን አከራካሪ አይሆንም:: ኢትዮጵያ ውስጥ ክስ ለማቅረብ የተስማሙበት የውል ቃል እንደሚያስራቸው በማመን አይሞክሩትም:: ለመሆኑ እነዚህ ስምምነቶች በማንኛውም ጊዜ ቅቡል (Valid) ናቸው ወይ? የሚለውን ነጥብ ለማየት እንሞክር::

በዚህ ረገድ ፕሮፌሰር አለን ሴድለር በኢትዮጵያ ሥነ ሥርዓት ሕግ ላይ በጻፉት ትንተና የአንድን ፍርድ ቤት የመዳኘት ሥልጣን በማስወገድ የሚደረጉ ስምምነቶች እንደ ጉዳዩ ዓይነት እንደሚወሰን በቀደምት የኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች የቀረቡ ጉዳዮችን መሠረት በማድረግ ይገልጻሉ:: በአንድ የጭነት ደረሰኝ (Bill of lading) ስምምነት የተጠየቀ የካሳ ጉዳይ ተዋዋዮቹ የኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች ሥልጣን እንደሌላቸው በመግለጽ በግሪክ ፍርድ ቤት ለመዳኘት በመስማማታቸው ድንጋጌው በፍርድ ቤቱ ተቀባይነትን አግኝቷል:: እንደ ፕሮፌሰር አለን ሴድለር የስምምነቶቹ ተፈጻሚነት (ተቀባይነት) የሚወሰነው ጉዳዩ ከኢትዮጵያ መንግሥት (ሕዝብ) ፖሊሲ (Ethiopia’s public policy) ጋር ባለው ቁርኝት መጠን ነው:: ጉዳዩ ከኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች ውጭ መታየቱ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም የሚነካ ከሆነ ሌላ አገር ለመዳኘት የተስማሙበት የውል ቃል ተፈጻሚነት እንደማይኖረው ይገልጻሉ:: ከላይ የቀረበውም የጭነት ደረሰኝ የካሳ ጉዳይ ከሕዝብ ጥቅም (ከብሔራዊ ጥቅም) ጋር ያለው ቁርኝት አናሳ ስለመሆኑ ግንዛቤ መውሰድ አዳጋች አይደለም:: በሌላ በኩል ግን የኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶችን ሥልጣን በውል ማስወገድ ብሔራዊ (ሕዝባዊ) ጥቅም በሚንፀባረቅባቸው ጉዳዮች ከሆነ ተቀባይነት የለውም:: ፕሮፌሰር አለን ሴድለር ይህን አቋም በምሳሌ ያብራራሉ:: ኢትዮጵያውያን ወላጆች ልጃቸው እንግሊዝ አገር እንዲማር ላኩት እንበል:: ወላጆቹ እንግሊዝ ካለ ዘመዳቸው ጋር ባደረጉት ስምምነት ልጃቸውን እንዲንከባከብላቸውና ትምህርቱን እንዲቆጣጠርላቸው በመስማማት በተወሰነ ገንዘብ የሥራ ዋጋ ክፍያ ተስማሙ እንበል:: በተጨማሪ ስምምነታቸው ክርክር ከተነሳ የእንግሊዝ ፍርድ ቤቶች ሥልጣን እንዳላቸውም ተስማሙ:: ወላጆቹ ዘመዳቸው ግዴታውን በአግባቡ እየተወጣ አይደለም በሚል ምክንያት ክፍያውን ለዘመዳቸው መፈጸም ቢያቆሙና እርሱም በኢትዮጵያ ፍርድ ቤት ክስ ቢያቀርብ እንግሊዝ እንዲታይ የተስማሙት የውል ቃል መከራከሪያ ሊሆን እንደማይገባ ሴድለር ይገልጻሉ:: ምክንያቱም ኢትዮጵያዊ የሆነ ሕፃን ትምህርቱን በተመለከተ ኢትዮጵያ ጠንከር ያለ ጥቅም ስላላት እንደሆነ አክለው ይገልጻሉ::

ከዚህ ትንትና በመነሳት የተወሰኑ ነጥቦችን ማንሳት እንችላለን:: የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶችን ሥልጣን የሚያስወግዱ ስምምነቶች ግላዊ ጥቅም (Private interest) ብቻ ካላቸው ተቀባይነት ይኖራቸዋል:: ሌላው ጉዳዩ የሕዝብ (የብሔራዊ) ጥቅምን የተመለከተ ከሆነ ደግሞ የውል ስምምነቱም ቢኖር በኢትዮጵያ ፍርድ ቤት ክስ ለመመሥረት የሚቻል መሆኑን ነው:: ከፋይናንስ ተቋማት ጋር በተያያዘ በተነሳው ጉዳይ ስንመለከተው የሶፍትዌር ወይም የገንዘብ ዝውውር ስምምነቶች ብሔራዊ (ሕዝባዊ) ጥቅም የሚንፀባረቅባቸው ስለመሆኑ አከራካሪ አይሆንም:: እነዚህ ጉዳዮች የኢትዮጵያን የፋይናንስ ተቋማት የገንዘብ ዝውውር ላይ ተፅዕኖ የሚያሳድሩ ከመሆናቸው ከላይ የአገሪቱን የኢኮኖሚና ኢንቨስትመንት ሁኔታን የሚወስኑ ናቸው:: ስለዚህ እነዚህ ውሎች ሲመሠረቱ በተቻለ መጠን ተፈጻሚ የሚሆነው ሕግና የክርክር ቦታ ኢትዮጵያ እንዲሆን መስማማት ተገቢ ነው:: የድርድር አቅም ማነስ ይህን የማያስችል ከሆነ ደግሞ ስምምነቱም ተፈርሞ በኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች መብትን ለመጠየቅ ሙከራ ቢደረግ አግባብ ይሆናል:: አንዳንድ ጊዜ ውል በተፈጸመ ጊዜ ስለ ክርክር ቦታና ሕግ የተባለ ነገርም ከሌለ ከፍ ባለ የሕዝብ ጥቅም (Public policy) አመክንዮ ክርክሩ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲደረግ ጥረት ቢደረግ መልካም ይሆናል:: የኢኮኖሚ አቅም ድርድርን ሚዛናዊ እንዳይሆን ባደረገበት በዚህ ዘመን ደግሞ ከኢትዮጵያ ሕግና የፍርድ ቤት ሥርዓት ጋር ተቀራራቢ በሆነ አገር እንዲዳኝ መደራደር ከመጥፎዎቹ ምርጫ ቀዳሚው ሊሆን ይገባል::

ከአዘጋጁ፡- ጸሐፊውን በ[email protected] ማግኘት ትችላላችሁ::

ብሔራዊ የዳኝነት ሥልጣን ማለት በአንድ አገር ያሉ ፍርድ ቤቶች ተከራካሪዎች ላይ ወይም ንብረቶቻቸው

ላይ አስገዳጅ ውሳኔ ለመስጠት ያላቸው ሥልጣን ነው:: ለምሳሌ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ፍርድ ቤቶች የቀረበላቸውን ጉዳይ ተቀብሎ ለመወሰን ሥልጣን

ስለመኖር አለመኖራቸው ማጣራት ብሔራዊ የዳኝነት ሥልጣንን መወሰን ነው::

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 36 | እሑድ |ኅዳር 17 ቀን 2004ክፍል-1

Invitation to Consultancy BIDThe Ethipian Catholic Secretariat/ECS Health and HIV/AIDS Unit would like to invite eligible consultants who can offer training on ‘’Good Governance and Leadership for Ethiopian Catholic Church (ECC) Health Institutions Management Team and Board Members.’’

Detailed terms of reference can be obtained from the Ethiopian Catholic Secretariat/ECS, Health and HIC/AIDS unit Room No. 22, Near Catholic Cathedral School, Piazza, Addis Ababa .

Interested Consultants can collect this TOR within five working days from the date of this notice.

Ethiopian Catholic Secretariat/ECS deserves the right to reject any or all bids.

The Ethiopian Catholic Secretariat/ECS Tel.251 011 155 03 00 ext.245

የድርጅት አርማ (Logo) ዲዛይን እና

የንግድ ተሸከርካሪዎች ዲኮር ሥራ

ጨረታ ማስታወቂያልዩ ልዩ የእርሻና ኢንዱስትሪ ምርቶችን ከውጭ አገርና ከአገር ውስጥ አምራቾች በመረከብ በቀጥታ ለተጠቃሚው ሕብረተሰብ ለሚያቀርቡ ልዩ ልዩ የንግድ ድርጅቶች፣የህብረት ሥራ ማህበራትና አገልግሎት ሰጭዎች በጅምላ ለማከፋፈል፣በ600 ሚሊዮን ብር የተፈቀደ ካፒታል ተቋቁሞ አክሲዮኖችን ለሕዝብ በመሸጥ ላይ ያለው ሐሴት የጅምላ ንግድ ሥራ አ.ማ ከ2004 በጀት ዓመት ጀምሮ ወደ ኦፕሬሽን ሥራው በመግባት የግዥ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ በዚሁ መሠረት፡-

1. ማህበሩ እስካሁን ሲጠቀምበት የነበረውን አርማ (Logo) ፤ የማህበሩን ዓላማና ተግባር ይበልጥ ገላጭ በሆነ መልኩ ማሻሻል ወይም በአዲስ መልክ ማሠራት፣

2. አዲስ የገዛቸውን የንግድ ዕቃ ማመላለሸ መኪናዎች አክሲዮን ማህበሩ በሚያከፋፍላቸው ልዩ ልዩ ሸቀጦች ፎቶግራፍና ሞዴሎች ዲኮር ማስደረግ ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው ድርጅቶች/ባለሙያዎች የአክሲዮን ማህበሩን ዝርዝር መግለጫ (ፕሮፋይል) የማይመለስ ብር 50 ከፍለው በመግዛት ለሥራው ብቁ የሚያደርጋቸው ቴክኒካል ፕሮፓዛል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ5 የሥራ ቀናት ጊዜ ውስጥ እንዲያቀርቡ ይጋብዛል፡፡ በቴክኒካል ፕሮፖዛሉ ብቁ ሆነው የሚመረጡ ተጫራቾች ብቻ የሚሠሩበትን ዋጋ እንዲያቀርቡ ይደረጋል፡፡ ለተጨማሪ መረጃ ስ.ቁ 011-4-440-31-03

ሐሴት የጅምላ ንግድ ሥራ አ.ማለማህበረሰቡ የታመነ ገበያ!

Labour Contract የህንጻ ሥራ ጨረታለደረጃ 5 የህንጻ ተቋራጭ በሙሉ

ድርጅታችን ግዮን ኢንዱስትሪያልና ኮሜርሻል በንግድ፣በአገልግሎት ሰጪ እና በኢንዱስትሪያል የሥራ መስክ ተሰማርቶ አጥጋቢ ውጤት በማስመዝገብ ላይ የሚገኝ ድርጅት ነው፡፡

ድርጅታችን በዊንጌት ቀለበት መንገድ አጠገብ በ5000 ሜ.ካ ቦታ ላይ ለቅይጥ አገልግሎት የሚውል የህንጻ በ3 /phase/ በ1000 ሜ.ካ. ቦታ ላይ የሚያርፍ ህንጻ ሲሆን በLabour Contract ለመሥራት የምትፈልጉ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላችሁ ደረጃ 5 የህንጻ ተቋራጭ እና ከዚያም በላይ በሙሉ እንድትወዳደሩ ተጋብዛችኋል፡፡

የጨረታውን ሠነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 ቀናት ውስጥ በብር 50.00(ሃምሳ) በመክፈል በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍል ከተማ ዊንጌት ቀለበት መንገድ አደባባዩን ዝቅ ብሎ በስተቀኝ በኩል በሚገኘው ዋናው መ/ቤት አስተዳደርና ሕግ መምሪያ በመቅረብ መወሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ስ.ቁ 011-279-33 60ሞባይል 0910-143089ፖ.ሣ.ቁጥር 22669

አዲስ አበባ

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 37 | እሑድ | ኅዳር 17 ቀን 2004 ክፍል-1

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 38 | እሑድ |ኅዳር 17 ቀን 2004ክፍል-1

ማስታወቂያ

ይህን አምድ አእምሮ ጤና ክብካቤ ማህበር - ኢትዮጵያ ከፊንላንድ ሪፑብሊክ ኤምባሲ ጋር በመተባበር ያቀርብላችኋል::

ለአስተያየቶቻችሁ፣ስልክ 011-6627155/6189750ፖ.ሣ.ቁ. 27667 ኮድ 1000E-mail: [email protected]

Web Site: www.mhsethio.org

በፀረ-ድብርት መድሀኒቶች ዙሪያ ሰፋ ያለ ማብራሪያ እንድንሰጥ በርካታ ጥያቄዎች የቀረቡ በመሆኑ በዚህ ጽሁፍ ስለነዚህ መድሀኒቶች ሰፋ ያለ ማብራሪያ እናቀርባለን::

የፀረ-ድብርት መድሀኒቶች አጭር ታሪክየፀረ- ድብርት መድሀኒቶች (antidepressants) ጥቅም ላይ መዋል የጀመሩት እኤአ በ1950 ዎቹ አጋማሽ ጀምሮ ነው:: እነዚህ የመጀመሪያ ትውልድ መድሀኒቶች ኢትዮጵያን ጨምሮ በመላው አለም በሚገኙ በማደግ ላይ ባሉ አገራት ጥቅም ላይ የሚውሉ ሲሆን በበለጸጉት አገራት ግን ባለፉት አሰርት አመታት በተደረጉ ምርምሮች የተገኙ መድሀኒቶች የቀደሙትን መድሀኒቶች ሙሉ ለሙሉ ተክተዋቸዋል ለማለት ይቻላል:: ከእነዚህ ከቀደሙት መድሀኒቶች ውስጥ የመጀመሪያው ኢሚፕራሚን ተብሎ የሚጠራው ሲሆን በተከታታይ የሱ ዝርያ የሆኑ እንደ አሚትሪፕቲሊን ፣ ክሎሚፕራሚን ኖርትሪፕቲሊን የመሳሰሉት በልዩ ልዩ የፋርማሴዩቲካል ላብራቶሪዎች ሊቀመሙ ችለዋል:: በቅርብ ጊዜ የተሰሩት መድሀኒቶች ፍሎክሲቲን፣ ሰርትራሊን፣ ሲታሎፕራም፣ ፈሉቮክሳሚን የመሳሰሉት ዋጋቸው ውድ በመሆኑ ለድሀው የህብረተሰብ ክፍል በቀላሉ መጠቀም የሚቻሉ አይደሉም:: በርግጥ በሀገራችን ከነዚህ አዲስ መድሀኒቶች አቅርቦታቸው አስተማማኝ ባይሆንም ፍሎክሲቲንና ሰርትራሊን የተባሉት ጥቅም ላይ ውለዋል::

የእነዚህ መድሀኒቶች ተግባር ምንድን ነው?የመድሀኒቶቹ ተግባር ከመግለጽ በፊት የድብርት ምልክቶች መንስኤዎችን መመልከት ጠቃሚ ነው:: በበርካታ ጥናቶች እንደተመለከተው የዲፕሬሽን ህመም ምልክቶች መንስኤ በአንጎል ውስጥ መልእክት አስተላላፊ የሆኑ ንጥረ ነገሮች (neurotransmitters) በበቂ መጠን ያለመኖር ነው:: ከነዚህ መልእክት አስተላላፊ ንጥረ ነገሮች በተለይ ሴሮቶኒን (serotonine) ና ኖርኤፒኔፍሪን (norepinephrine) የተባሉት ዋነኞቹ ናቸው:: የፀረ-ዲፕሬሽን መድሀኒቶች ዋነኛ ተግባርም በነዚህ ንጥረ ነገሮች ዙሪያ ነው:: መድሀኒቶቹ የሴሮቶኒንና ኖርኤፒኔፍሪን ተግባር እንዲቀላጠፍ እንዲሁም የቆይታና የአገልግሎት ጊዜያቸው እንዲጨምር በማድረግ በአንጎል የነርቭ ህዋሳት (neurons) መካከል ያለው የመልእክት ልውውጥ የተሻለ እንዲሆን ያደርጋሉ:: የመድሀኒቶቹ ተግባር ጠቅለል ባለ መልኩ ከላይ የተገለጸውን ሲሆን የተሟላ

ውጤት ለማግኘት እስከ ስድስት ሳምንትና ከዚያ በላይ ሊወስድ ይችላል:: አዲሶቹ መድሀኒቶች ከቀደምት መድሀኒቶች የሚለዩት በዋናነት በሚፈጥሩት የማይፈለግ የጎንዮሽ ውጤት (side effects) ሲሆን በውጤታማነት ደረጃ መሰረታዊ ልዩነት በመካከላቸው የለም:: ለልዩነቱ መንስኤ የሆነው ምክንያት እነዚህ አዳዲስ መድሀኒቶች የተሻለ የተመረጠ ኢላማ ያላቸው በመሆኑ ነው:: ይህም ማለት ከዲፕሬሽን ጋር ተያያዥነት የሌላቸውን የመልእክት አስተላላፊ ንጥረ ነገሮች ተግባር የማይነኩ በመሆናቸው የሚያስከትሉት የጎንዮሽ ውጤት አነስተኛ ነው:: የቀደሙት መድሀኒቶች ግን ከላይ ከተጠቀሱት ለዲፕሬሽን ምልክቶች መንስኤ ከሚሆኑት መልእክት አስተላላፊ ንጥረ ነገሮች በተጨማሪ የሌሎችንም ተግባር የሚያውኩ በመሆናቸው በርከት ያሉ የማይፈለጉ የጎንዮሽ ውጤቶች ያስከትላሉ:: እነዚህ የማይፈለጉ የጎንዮሽ ውጤቶች ምን ምንድን ናቸው?ከላይ እንደተጠቀሰው በተለይ ቀደም ብለው የተሰሩት ፀረ-ዲፕሬሽን መድሀኒቶች በርከት ያሉ የማይፈለጉ የጎንዮሽ ውጤቶች ያሏቸው ሲሆን አብዛኞቹ በቀላሉ ለመቋቋም የማያስቸግሩና በጊዜ ሂደት እየጠፉ የሚሄዱ ናቸው:: ከነዚህ የማይፈለጉ የጎንዮሽ ውጤቶች የተወሰኑትን ለመጥቀስ ያህል እንቅልፍ እንቅልፍ ማለትና መፍዘዝ፣ ከመቀመጫ ሲነሱ ብዥ ማለትና ማዞር፣ የአይን እይታ ብዥ ማለት፣ የምራቅ መቀነስና የአፍ መድረቅ፣ የሆድ ድርቀትና የሽንት መያዝ የመሳሰሉት ይገኙበታል:: በርካታ ሰዎች እነዚህን ስሜቶች በቀላሉ ሊቋቋሟቸው የሚችሏቸው ናቸው:: ጥቂቶች በነዚህ ስሜቶች ምክንያት መድሀኒቶቹን ሲያቋርጡ ይታያሉ:: ምንም እንኳን እነዚህ ስሜቶች ደስ የማይሉና የሚረብሹ ቢሆኑም ሀኪም ሳያማክሩ በራስ አነሳሽነት መድሀኒቶቹን ማቋረጥ ተገቢ አይደለም:: ሀኪም ማማከርና ተገቢውን ምክር ማግኘት እንዲሁም ችግሩ መቋቋም ከሚችሉት በላይ ከሆነ ሌላ ተለዋጭ መድሀኒት እንዲታዘዝ ማደረግ ይቻላል:: አዳዲሶቹ መድሀኒቶች ዋጋቸው ውድ በመሆኑ ብዙሀኑ ተጠቃሚ ሊያገኛቸው አይችልም እንጅ በጎንዮሽ ውጤት ደረጃ ቀለል ያሉ ናቸው:: ለምሳሌ፦ ፍሎክሲቲን የተባለው ፀረ-ዲፕሬሽን መድሀኒት መጀመሪያ አካባቢ እንቅልፍን የመረበሽና በተወሰነ ደረጃ ጭንቀትን የማባባስ ፀባይ የሚታይበት ቢሆንም እነዚህ ምልክቶች የሚቆዩት ለአጭር ጊዜ ብቻ ነው::

መድሀኒቱን ጠዋት ጠዋት መውሰድ በእንቅልፍ ላይ የሚፈጥረውን ተፅእኖ ይቀንሰዋል:: የፀረ-ዲፕሬሽን መድሀኒቶች ውጤታማነታቸው ምን ያህል ነው?ለዲፕሬሽን ህክምና የሚውሉት መድሀኒቶች ጥቅም ላይ መዋል ከጀመሩ ከአምሳ አመታት በላይ የተቆተሩ ሲሆን በነዚህ አመታት የሰውን ልጅ ስቃይ በማቃለል መድሀኒቶቹ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርገዋል:: በእርግጥ የነዚህ መድሀኒቶች ዋነኛ ተግባር በሽታውን ሙሉ ለሙሉ ነቅሎ ማስወገድ ሳይሆን ለህመሙ ምልክቶች መንስኤ የሆኑትን በአንጎል ውስጥ የሚከሰቱ ኬሚካላዊ መዛባቶችን በማስተካከል ታማሚው የጤንነት ስሜት እንዲሰማው ማድረግ ነው:: እነዚህ መድሀኒቶች በተገቢው መጠን ከተወሰዱ እስከ ሰባ ከመቶ የሚሆኑት ታካሚዎች በስድስት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ ጤንነታቸው ሊስተካከል ይችላል:: መድሀኒቶቹንም በተከታታይ ቢያንስ ለ ስድስት ወራት ሳያቋርጡ መውሰድ ግድ ይላል:: ከዚህ ጊዜ በፊት መድሀኒቶቹ ከተቋረጡ ህመሙ ተመልሶ ቶሎ ሊያገረሽ ይችላል:: የዲፕሬሽን ህመም የማገርሸት ጸባይ ያለው በመሆኑ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ አስፈላጊ ነው:: የህመሙ ማገርሸት ምልክቶች በዋናነት የድብርት ስሜት፣ መጨነቅና እንቅልፍ ማጣት ሲሆኑ እነዚህ ምልክቶች መታየት እንደጀመሩ ፈጥኖ ሀኪም ማማከር ያስፈልጋል:: እዚህ ላይ ማስታወስ የሚያስፈልገው አንድ የዲፕሬሽን ህመምተኛ የሆነ ሰው ራሱን ከሚያስጨንቁና ውጥረት ከሚፈጥሩ ሁኔታዎች በተቻለ መጠን ራሱን መጠበቅ እንዳለበት ነው:: በቂ እንቅልፍ ማግኘት፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ፣ ራስን ጤናማ በሆኑ መንገዶች ማዝናናትና ከልዩ ልዩ ሱሶች ራስን መጠበቅ ዲፕሬሽን እንዳያገረሽ ከሚረዱ መንገዶች ጥቂቶቹ ናቸው:: ዲፕሬሽን ባገረሸ ቁጥር ወደ ሙሉ ጤናማ ደረጃ የመመለስ እድል እየቀሰ እንደሚመጣና መድሀኒትም ለረጅም ጊዜ መውሰድ እንደሚያስገድድ መረዳት ያስፈልጋል:: እነዚህ መድሀኒቶች ሱስ አስያዥ ናቸውን? ይሄንን ጥያቄ ለማንሳት ያስገደደን ዋናው ምክንያት በርካታ ሰዎች እነዚህ መድሀኒቶች ሱስ አስያዥ እንደሆኑ ሲናገሩ ስለሚደመጥ ነው:: ሱስ ማለት በአንድ ኬሚካል ስነ-ልቦናዊ ወይም አካላዊ ጥገኝነት ስር መውደቅ ማለት ነው:: ይህም ማለት በሱስ የተጠቃ ሰው ያንን ኬሚካል ካላገኘ ልዩ ልዩ ጤናማ ያልሆኑ ስሜቶች ይሰሙታል ማለት ነው:: በዚህም ምክንያት እነዚህን ስሜቶች ለማስታገስ ሲል ያንን

ኬሚካል መጠቀሙን ይቀጥላል:: በእርግጥ በስነ-አዕምሮ ህክምና አንድ ሰው ሱሰኛ ነው ለማለት ከዚህ የሚከተሉት መስፈርቶች መሟላት ይኖርባቸዋል፦ • የሱስ ተጠቂው ግለሰብ የሚወስደው የኬሚካል

መጠን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣት፤ ማለትም የሚፈልገውን ውጤት (ስካር፣ እርካታ…) ለማግኘት በቀላሉ ያለመቻል::

• ኬሚካሉን በማይጠቀምበት ወቅት ልዩ ልዩ አካላዊና ስነ ልቦናዊ ችግሮች መከሰት፣

• የሚወስዱትን መጠን መቆጣጠር ያለመቻል፣ • በርከት ያለ ያልተሳካ የማቆም ሙከራ፣ • ጊዜን ማባከን፤ በሱስ የተጠቁ ሰዎች አብዛኛውን

ጊዜያቸውን የሚያጠፉት ለሱሳቸው ማርኪያ የሚሆነውን ነገር በመፈለግ፣ በመጠቀምና፣ ከስካራቸው ለመላቀቅ ነው::

• ራስን ማግለል፤ የሱስ ሕመምተኛ ሰዎች አስፈላጊ ከሆኑ ማኅበራዊ ተሰትፎዎች የተገለሉ ናቸው:: ለቤተሰባቸውም በቂ ጊዜ አይሰጡም:: መዝናኛቸውም ያው ሱሳቸውን በማርካት ነው::

• በጤናቸው ላይ የሚያደርሰውን መቃወስ እያወቁም ቢሆን ማቆም አይችሉም::

ከእነዚህ ከላይ ከተጠቀሱት ባህሪያት 3 ወይም ከዚያ በላይ የሚያሳይ ሰው የሱስ ተጠቂ ነው ብሎ መናገር ይችላል:: ከላይ በተጠቀሱት መስፈርቶች ሲለካ ፀረ-ዲፕሬሽን መድሀኒቶች መጠነኛ የሆነ የመላመድ ፀባይ የሚያሳዩ ቢሆንም በሱስ ደረጃ የሚፈረጅ አይደለም:: መድሀኒቶቹን ያለሀኪም ምክር በድንገት ማቋረጥ ለተወሰኑ ቀናት የሚቆይ የእንቅልፍ መረበሽ፣ የውጥረት ስሜትና ድብርት ሊያስከትል ይችላል:: እነዚህን ስሜቶች ነው ሰዎች እንደ ሱስ የሚቆጥሯቸው:: ከሀኪም ጋር በመመካከር ቀስ በቀስ መጠኑን እየቀነሱ ማቋረጥ ከላይ የተጠቀሱት ስሜቶች እንዳይከሰቱ ያደርጋል:: ስለዚህ እነዚህ መድሀኒቶች ሱስ አስያዥ ናቸው በሚል የተሳሳተ ግምት መድሀኒቶቹን ከመውሰድ መቆጠብ ወይም ሌሎች እንዳይወስዱ ማድረግ የራስንም ሆነ የሌላውን ስቃይ ማራዘም ነው:: እዚህ ላይ ደግመን ማስታወስ የሚገባን ዲፕሬሽን ካልታከሙት አደገኛ ውጤት ሊያስከትል የሚችል አደገኛ በሽታ መሆኑን ነው::

የፀረ-ድብርት መድሀኒቶች ምንነትና ተግባርዶ/ር ሰለሞን ተፈራ

(የአዕምሮ ህክምና ኮንሰልታንት ስፔሻሊስትና በአአዩ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ረ/ፕሮፌሰር) ([email protected])

የሂሣብ ምርመራ አገልግሎት ጨረታየባቱ ኮንስትራክሽን አ/ማ የ2003 በጀት ዓመት ሂሳብ በውጪ ኦዲተር ማስመርመር ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተገለጹትን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

1. ሕጋዊና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን የሀገር ውስጥ ገቢ ንግድና ቫት፤ሌሎችንም የንግድ ታክሶችን የከፈሉና ማስረጃ የሚያቀርቡ፤

2. የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሠርተፍኬት/ምስክር ወረቀት/ ማቅረብ የሚችሉ፤

3. ከሦስት ድርጅቶች ሂሳብ መመርመራቸውን የሚገልጽ ማስረጃ የሚያቀርቡ፤

4. ተጫራቾች ታክስን ጨምሮ የሚያስከፍሉትን የአገልግሎት ዋጋ፤ረቂቅ የሂሣብ ሰነድ ከደረሰበት ጊዜ ጀምሮ የሂሳብ ምርመራውን አጠናቀው የሚያስረክቡበትን ጊዜ በመግለጽ የጨረታ ሰነዶቻቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 /አሥር/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት ማቅረብ ይችላሉ፡፡

ባቱ ኮንስትራክሽን አክሲዮን ማኅበር

ለበለጠ መረጃ፡ በስልክ ቁጥር 011 3 21 50 20 011 3 21 02 48 ይደውሉ

ናይል ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ1. ጉዳት/አደጋ ደርሶባቸው ለደንበኞቹ ተገቢውን ካሣ ከፍሎ በውክልና የተረከባቸውን ከዕዳ እና

ዕገዳ ነፃ የሆኑ ልዩ ልዩ ተሽከርካሪዎች፣ የተለያዩ የተሽከርካሪ አካሎች፣ እና2. ያለገለገሉ የኩባንያው ተሽከርካሪዎች

ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል:: የተሽከርካሪ የስም ማዘዋወሪያ፣ የጉምሩክ ቀረጥ፣ ግብርና ሌሎች ወጪዎች ቢኖሩ በአሸናፊው የሚሸፈኑ ይሆናሉ::

ንብረቶች የሚገኙበት የኩባንያው ሪከቨሪ አድራሻ፣

ቃሊቲ ሪከቨሪ ፡ አዲስ አበባ አቃቂ-ቃሊቲ ክ/ከተማ፣ ቀበሌ 11፣ ከኮሜት ትራንስፖርት አ.ማ. በስተ ምሥራቅ ቀለበት መንገድ ኤኤምቢ ኮንስትራክሽን አጠገብ

ኮሜት ሪከቨሪ ፡ ሳሪስ አቦ አካባቢ ቀለበት መንገድ አጠገብ እንዲሁም ፡ አንድ ቻይና ሞተር ሳይክል (3-023ጎን)እና 86 ከረጢት ሲሚንቶ

ጎንደር ቅርንጫፍ ይገኛል

ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ንብረቶቹ በሚገኙበት አድራሻ በሥራ ሰዓት ሄዶ በማየት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድና የጨረታ ማቅረቢያ ቅፅ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) ከፍሎ መውሰድ ይችላል:: የጨረታ መነሻ ዋጋ 15% ቫት ያላካተተ መሆኑን እየገለጽን ማንኛውም ተጫራች የሚጫረትበትን የእያንዳንዱን ምድብ እቃ ዋጋ 15% ቫት ጨምሮ በጨረታ ማቅረቢያ ቅፅ ላይ በመሙላት ለእያንዳንዱ ምድብ ዕቃ የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የጨረታ መነሻ ዋጋውን 10% (አሥር ከመቶ) በኩባንያው ስም ከተዘጋጀ በባንክ ከተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) ወይም የኢንሹራንስ ቦንድ ጋር በኤንቨሎፕ በማሸግ እስከ ሕዳር 22 ቀን 2004 ዓ.ም. እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ የኩባንያው ዋና መ/ቤት በሚገኝበት ጐተራ ምድር ቤት ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላል:: ጨረታው ሕዳር 23 ቀን 2004 ዓ.ም. ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጐተራ በኩባንያው ዋና መ/ቤት የስብሰባ አዳራሽ ከጠዋቱ በ2፡30 ሰዓት ይከፈታል:: ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ ለተሸናፊዎች ሙሉ በሙሉ የሚመለስ ሲሆን ለአሸናፊዎች ግን ከሚገዙበት ዋጋ ጋር ይታሰባል::ተጫራቾች ለተጫረቱበት ንብረት አሸናፊነታቸው ከተገለፀበት ዕለት ጀምሮ በአሥር ቀናት ውስጥ ክፍያውን አጠናቀው ንብረቱን ባያነሱ ያስያዙት ገንዘብ በመቀጫ መልክ ለኩባንያው ገቢ ሆኖ አሸናፊነታቸው ይሰረዛል:: ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ለተጨማሪ ማብራሪያበስልክ ቁጥር፡- 011-442-14-99/011-442-60-00/091-143-02-92/ በመደወል መጠየቅ ይቻላል::

ናይል ኢንሹራንክ ኩባንያ አ.ማ.

ጨረታ ማስታወቂያ (ቁጥር 47/2004)

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 39 | እሑድ | ኅዳር 17 ቀን 2004 ክፍል-1

ዓ ለ ም አ ቀ ፍ

በግዛቸው አበበ

‹‹አደል አል-ጁበር ደግሞ ማን ነው?›› የሚሉ አንባብያን እንደሚበዙ የታወቀ ነው። ይህ ሰው ባለፈው ወር የሁሉም የዓለማችን ሚዲያዎች ግንባር ቀደም ዜናዎችን ያነበነቡለት ሰው ነው። ሁሉም ሚዲያዎች ለማለት በሚያስደፍር መልኩ የዚህን ሰው ሹመት (ሥልጣን) ብቻ እየጠቀሱ ነበር ዜናውን የሚያጎርፉት:: ልክ ስለ አንድ መንፈሳዊ ነገር ወይም ገና ስም ላልወጣለት አሻንጉሊት የሚናገሩ በሚያስመስል አወራረድ ነበር ገጠመኙ የሚተረክለት። የዚህ ሰው ማንነቱ ሳይሆን እሱን በማስታከክ ሊከተል ይገባል የተባለው ነገር በአሜሪካና በአውሮፓ ቤተ መንግሥቶችና ፓርላማዎች ውስጥ ያሉ ባለሥልጣናትን አነጋግሯል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትም አንድ ሁለት ነገር ሲል ተሰምቷል። አሁን እንኳ የእሱን ዜና ይዘው የወጡ ድረ ገጾችን በማየት ስሙን መፈለግ ምን ያህል ከባድ ሥራ እንደሚሆን ለማየት ይቻላል። አል-ጁበር ድንገት ስሙ ማንነቱም ጭምር ከነአካቴው ተዘንግቶ ወይም ወደ ጎን ተትቶ ወይም ከቁብ ሳይቆጠር ዓለም ዓቀፍ ሚዲያዎችን ያጣበበ ‹‹መንፈስ›› ሆነ።

አደል አል-ጁበር ኢራን ልታስገድለው ነበር የተባለለት በአሜሪካ የሳዑዲ ዓረቢያ አምባሳደር ነው። አል-ጁበር ጦርነት ለመቆስቆስ ለሚያመች አጀንዳ ተዋኝ እየተደረገ ይሆን? ዜናው በሰፊው ሲሠራ አል-ጁበርን መግደል ያስፈለገው ለምን እንደሆነ፣ የአልጁበር መሞት በአገሩ ወይም በአሜሪካ ላይ ሊያስከትለው ስለነበረው ጉድለት፣ ገዳዮቹ ምን ጥቅም ለማግኘት እንዳሰቡ ምንም የተባለ ነገር የለም። እንዲያው ዝም ብሎ ስሜትን ለማስደሰት ወይም የመግደል ሱስን ለማርካት ቢባል እንኳን ታዲያ ሰዎችን ወይም ዲፕሎማቶችን በቀላሉ መግደል የሚቻለው አሜሪካ ውስጥ ነው ብሎ የሚያምን ይኖራልን ያስብላልና አሳማኝነቱ የወረደ ነው። በእርግጥ አሜሪካ ለጦርነት ሲባል የፈጠራ ስጋት ወይም ተጨባጭ አደጋ ሠርታ ወይ አሠርታ የአዞ እንባ እያነባች ‘አደጋ አድራሹን ለመበቀል’ በሚል ጦርነት የማካሄድ ልማድ ያላት አገር ናት። በቅርቡ ‹‹TOP SECRET›› የሚለው ርዕስ ተነስቶለት ለአሜሪካ ሕዝብ ይፋ የተደረገው ‹‹ዘመቻ ኖርዝውድስ›› (Operation Northwoods) ለዚህ የአሜሪካ ባህሪ አንዱ አብነት ነው። የኢራቁ የአውዳሚ ጦር መሣሪያ ባለቤትነት ውንጀላም ሌላው። ኦባማ፣ አደል አል-ጁበርና ሐሰን አል-ካታኒን ላለፉት ስድስት ወራት ተመሳሳይ ገጠመኝ ደርሶባቸው የነበሩ ሰዎች ናቸው። የድንገቱ ሚዛን ግን በአል-ጁበር ላይ ገንኖ ታይቷል።

ከሸፈ የተባለው ሙከራ በኢራን የታቀደ ነበር ተብሎ በኢራን ላይ የጦርነት ዛቻ፣ የዕገዳና የውግዘት መዓት እንዲዥጎደጎድ ምክንያት ሆኗል። የአሜሪካና የአውሮፓ መሪዎችና ከፍተኛ የጦር ወይም የደኅንነት ባለሥልጣናት አል-ጁበርን ዘንግተው ‘ሰይጣናችን’ የሚሏትን ኢራንን አብጠልጥለዋል። በዚህ ወቅት ጦርነት ሳይሆን ማዕቀብን እመርጣለሁ ካለችው ከጀርመን በስተቀር ኃያላን የሚባሉት አገሮች ሁሉ ‹‹ሁሉም አማራጭ በጠረጴዛ ላይ ነው›› ሲሉን ከርመዋል። ከጠረጴዛው ሥር ምን እንዳለ ግን ማወቃቸውን እንጃ። ዓለማችን ይህን መሰል ዛቻ ላለፉት 35 ዓመታት ማለትም የአሜሪካና የአውሮፓ ሸሪክ የነበረው የኢራኑ ንጉሣዊ አገዛዝ ከተገረሰሰበት ጊዜ ጀምሮ አስተናግዳለች። የኢኮኖሚ ማዕቀብ በማድረግ የአሜሪካን የሚወዳደር የለም:: አሜሪካን ተከትለው ደግሞ አውሮፓዊ ሸሪኮቿ

ማዕቀብ ይጥላሉ። አሁን ደግሞ አስገራሚው የኢኮኖሚ ችግር

የማዕቀቦች እመቤት የሆነችውን አሜሪካንም እያሰቃየ ነው። ይህ እንግዲህ ከጠረጴዛው ላይና ከሥሩ ያለው ለየቅል መሆኑን ያመላክታል። በእርግጥ እመቤት አሜሪካ ማዕቀብ ስትጥል የአውሮፓ፣ የካናዳና የሌሎች ሸሪክ አገሮች መንግሥታት መቶ በመቶ ያስፈጽሙት እንጂ፣ የዚህ ዓይነት አጋጣሚዎችን የተለየ የቢዝነስ በረከት ምንጭ አድርገው የሚጠቀሙባቸው የአሜሪካ ካምፓኒዎች ብዙ መሆናቸውን መዘንጋት አይገባም። ቀን የጦር መሣሪያ ማዕቀብ ተጣለ ሲባል ማታ ማዕቀብ የተጣለበት አገር ቤተ መንግሥት በስልክ ጥሪ ይጥለቀለቃል ይባላል:: ለዚህም ሳይሆን አይቀርም የጦር መሣሪያ ማዕቀብ ተጣለ እየተባለ ማንም የጦር መሣሪያ አጥቶ የማያወቀው።

ሐሰን አል-ካታኒ በፓኪስታን የሳዑዲ ዓረቢያ ዲፕሎማት የነበረ ሰው ነው። ባሳለፍነው ግንቦት ወር ውስጥ ከነበሩት ሰኞዎች በአንዷ በፓኪስታኗ ካራቺ ውስጥ ከመኖሪያ ቤቱ ወደ ሥራ ቦታው ይጓዝበት በነበረበት መኪና ላይ ጥቃት በከፈቱ ሁለት ታጣቂዎች ተገድሏል። አጥቂዎቹ በሞተር ሳይክል ላይ ሆነው በባለ ዘጠኝ ሚሊ ሜትር ሽጉጥ ተኩሰው ከገደሉት በኋላ መሰወራቸውን የአካባቢው ፖሊስ አዛዥ ተናግረዋል። ያ ወር ቢን ላደን በአሜሪካ ኃይሎች ተገደለ የተባለበት [‘የተባለበት’ ያልኩበት ምክንያት የቢን ላደንን መገደል የሚገልጽ ሦስተኛ ዜና ስለሆነብኝና ሌላ አራተኛም አምስተኛም ዜና ሊመጣ ይችላል በማለት ብቻ ነው። ለዚህም ታላላቅ አሜሪካዊ ሚዲያዎችን መጥቀስ ይቻላል] ጊዜ ነበርና የፖሊስ አዛዡ ሁለቱ ጉዳዮች ግንኙነት ይኖራቸው ይሆናል የሚል ጥርጣሬ ይዘው ምርመራ መጀመራቸውንም አሳውቀዋል። ዲፕሎማቱ ይጓዝባት የነበረችው ቶዮታ-ኮሮና መኪና ወንፊት ሆናለች ያለው የፓኪስታን ፖሊስ ‹‹አሸባሪዎቹን›› በማሳደድ ላይ መሆኑን ገልጿል። ነገሩን ቀለል አድርገው ያዩት የሳዑዲ ባለሥልጣናት ግድያውን ‹‹ወንጀል›› ብለው በመጥራት ለምርመራው ከፓኪስታን ፖሊስ ጋር አብረው እንደሚሠሩ ነው ለሮይተርስ የገለጹት። አልቃይዳ ከተጨማሪ ዛቻ ጋር የጥቃቱን ኃላፊነት እንደሚወስድ ለኤኤፍፒ አሳውቋል። የሳዑዲ ባለሥልጣናትና ሚዲያዎች ነገሩን ወዲያውኑ ችላ ብለውታል። ለማንኛውም ይህ ዲፕሎማት ሞቷል አልቃይዳም እጄ አለበት ብሏል፤ ሞቅ ያለ የወሬ ዘር ግን አልነበረም። የፓኪስታንና የሳዑዲ ዓረቢያ ሚዲያዎች ነካክተውታል፣ የፈረንሳዩን የዜና ወኪል ኤኤፍፒን በመጥቀስ አልጄዚራ መጠነኛ ዘገባ ሠርቶበታል።

የዚህ ሰው ሞት በምን ያህል ሚዲያዎች እንደተዘገበና ምን ያህል የዓለማችን ሕዝብ ዜናው እንደደረሰው መገመት ይከብዳል:: የዚህ ጽሑፍ አንባቢያን ለየራሳቸው ምስክር ይሆናሉ። ማንም ሰው ገና ሳይጀመር ከሸፈ በተባለ የግድያ ሙከራ ውስጥ ‹‹በመንፈሱ›› መነጋገሪያ የሆነውን የአል-ጁበርን ያህል አነጋጋሪ ሆኖ አለመገኘቱን ይረዳል። ለመረዳት የሚከብደው ለምን ለሚለው ጥያቄ መልስ ፍለጋ ማሰላሰሉ ሊሆን ይችላል።

ኦባማም በዚህ ዓይነት መስመር ውስጥ አልፈዋል። የትኛው ኦባማ? ከተባለ ያው የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ኦባማ ናቸው። እዚህ ላይ በአሜሪካ ፎክስ ኒውስ የቀረበውን ‹‹ኦባማን መግደል›› የተሰኘውን ቀልድ ወይም ለቀልድ ይሁን ለምር በጉግል ላይ ኦባማን ለገደለ መቶ ሺሕ ዶላር እሸልማለሁ ብሎ ቃል ስለ ገባውና

ኤፍቢአይን ሥራ ስላበዛበት ሰው እየተነጋገርን አለመሆኑ ልብ ሊባል ይገባል። በትክክል ኦባማን ለመግደል መሣርያ አንስተው የተገኙ ሰዎችና ስላደረጉት የግድያ ሙከራዎች ነውና የምናወራው። እነዚህ ሙከራዎች ምን ያህል ተነገረላቸው? ምን ያህል ሕዝብስ ነው የሰማው? በማለትና ፍርዱን ለአንባብያን ለመተውም ነው የታሰበው።

ከግድያ ሙከራዎቹ አንዱ በቅርቡ የተከናወነ ነው። ‹‹ሁለት ጥይቶች ዋይት ሐውስን መቱ›› ሲሉ ሲቢኤስና አሶሼትድ ፕሬስ የዋይት ሐውስ ባለሥልጣናትን ጠቅሰው ዘግበዋል። ዘገባዎቹ አንድ የኦባማ የግል ጠባቂና (Budy Guard) የደኅንነት ሠራተኛ የጥይት ጭረቶቹ እንዳገኛቸው ገልጸዋል። ከጥይቶቹ አንዱ በዋናው ቤተ መንግሥታዊ መኖሪያ ትይዩ የሆነ (living quarters of the executive mansion) መስኮት ሰባብሮ ከውስጠኛው ጥይት ተከላካይ መስታወት ላይ ነጥሮ ተመልሷል ተብሏል። ከዚያ መስኮት ትይዩ ያሉ ክፍሎች የአሜሪካ ቀዳማዊ ቤተሰብ መኖሪያዎች ናቸው:: በዚያች የተኩስ ዕለት ኦባማና ባቤታቸው ሚሸል ጉዞ ላይ እንደነበሩ (ለዘጠኝ ቀናት ሃዋይ፣ ካሊፎርኒያ፣ ሳንዲያጎና ኤዥያ የተካተቱበት) ቢገልጹም ዋይት ሐውስ ውስጥ አብረው የሚኖሩት ሁለት ልጆቻቸው ከነሴት አያታቸው በዚያች ምሽት የት እንደነበሩ የተገለጸ ነገር የለም።

የ21 ዓመት ዕድሜ ያለው ኦስካር ራሜሮ ኦርቴጋ ኸርንናንዴዝ ሁለቱን ጥይቶች የተኮሰው እሱ ነው ተብሎ በቁጥጥር ሥር ውሎ ፒተርስበርግ በሚገኝ ፍርድ ቤት ቀርቧል። ተጠርጣሪውን የሚያውቁት ሰዎች ኦርቴጋ ለኦባማ ከፍተኛ ጥላቻ እንዳለውና ኦባማን ‹‹ፀረ ክርስቶስ››፣ ‹‹ሰይጣን›› ብሎ እንደሚጠራቸው ይናገራሉ:: እነዚሁ ሰዎች ኦርቴጋ ያሻውን የሚናገር ግልጽ ሰው ነው ቢሉም አንዳንድ የአሜሪካ ሚዲያዎች የአዕምሮ ችግር ሊኖርበት ይችላል ሲሉ ዘግበዋል። ኦርቴጋ ያካሄደውን የመግደል ሙከራ ‹‹ከአምላክ የተሰጠኝ ተልዕኮ ነው›› ብሎ መናገሩን ለአዕምሮው መዛባት ምልክት አድርገው ወስደውታል ወይም ወስደውለታል። የወንጀል ምርመራ ባለሥልጣናት ኦርቴጋ ንክ መሆኑንና አለመሆኑን ለመረጋገጥ ምርመራችውን እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል። ከፊል አውቶማቲክ መሣሪያ ይዞ የዘመተው ኦርቴጋ አጋር እንደሌለው ወይም ቅጥረኛ እንዳልሆነ ማረጋገጥን በሚመለከት ብዙ የተባለ ነገር የለም። ለነገሩማ ፕሬዚዳንት ኬኔዲ ስለተገደሉበት ምክንያትና ስለ ገዳያቸውም አልፎ አልፎ ቢሆን የሚነገረው የረባ ግብ የሌለው፣ ከአንዱ ገዳይ ነው ተብሎ ከተከሰሰው (እሱም በፖሊስ ቁጥጥር ሥር እያለ ተገድሏል) ሰው በስተቀር ማንም ተጠያቂ ያልተደረገበት ተራ ወንጀል ዓይነት ተደርጎ ነው እስካሁን የዘለቀው።

ኦርቴጋ ሙከራውን ባደረገበት ቦታ የነበሩ የዓይን ምስክሮች ‹‹ከተኩሱ በኋላ አንዲት ሴዳን በከፍተኛ ፍጥነት ከቦታው ስትሸሽ አይተናል፤›› ሲሉ ፖሊስ ደግሞ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ በኦርቴጋ ስም የተመዘገበች ‹‹ሆንዳ›› መኪና አሳቻ ቦታ ላይ ቆማ ማግኘታቸውን ተናገረዋል። ሆንዳዋ ውስጥ ለማነጣጠር የሚረዳ መነፅር፣ ወደ ዋይት ሐውስ ከተተኮሱት ጥይቶች ጋር የሚመሳሰሉ ያልተተኮሱ ጥይቶች፣ የተተኮሱ ጥይቶች ቀለሆችና እነሱን መተኮስ የሚችል ጠመንጃ ማግኘታቸውን ጨምረው ገልጸዋል። መጀመሪያ ላይ ሁለት ጥይቶች ዋይት ሐውስን መቱ ተብሎ የነበረ ቢሆንም፣ ከ15 ቀናት በኋላ ኤፍቢአይ ዋይት ሐውስ የተመታው በበርካታ ጥይቶች መሆኑን ይፋ አድርጓል።

ኦርቴጋ ከዚህ በፊት በሦስት የአሜሪካ ግዛቶች ለእስር ተዳርጎ የነበረ ሰው ነው። ኦርቴጋ ‹‹በእብደት›› ተነሳስቶ ፕሬዚዳንቱ ከሥራ መልስ (ማታ) ሊገኙ የሚችሉበትን ትክክለኛ ሕንፃና ክፍል አጥንቶ ትክክለኛውን መስኮት በጥይት መታ፤ ይህም በግሉ የተነሳሳበት ጉዳይ ነውና ችላ ተባለ፣ ብዙ ሊወራለት አልተገባም ብለን እንለፈውና ወደ ሁለተኛው የመግደል ሙከራ እንለፍ።

ይኸኛው ሙከራ የተደረገው በወርሐ ሐምሌ ሲሆን ሞካሪው የኡዝቤክ ተወላጅ በሆነው ኡሉግቤክ ኮዲሮቭ ነው። ኮዶሮቭ እ.ኤ.አ. ከሐምሌ 9 እስከ 13 ቀን 2011 ኦባማን ለመግደል አራት ተከታታይ ሙከራዎችን በማድረግ፣ የእጅ ቦምብና ጠመንጃ ይዞ በመገኘት በሚል የቀረቡበት ክሶች በአላባማ ግዛት በርሚንግሃም ውስጥ ፌደራላዊ የዳኞች ቡድን (Federal Grand Jury) ባለበት ተሰምቷል። ኮዲሮቭ ኤም 15 ጠመንጃ ወንጀለኛ መስሎ ከሚሠራ የደኅንነት ሰው (Undercover Agent) መግዛቱም ተረጋግጧል። ኮዲሮቭ ለያንዳንዱ የመግደል ሙከራ እስከ አምስት ዓመት (ለአራቱ ሙከራዎች ሃያ ዓመት ማለት ነው)፣ በእጁ ለተገኘ ለእያንዳንዱ የጦር መሣሪያ አሥር ዓመት (ለእጅ ቦምቡ አሥር፣ ለጠመንጃው ሌላ አሥር ዓመት ማለት ነው) በጠቅላላቅ የ40 ዓመት እስራትን የሚያከናንብ ፍርድ ይጠብቀዋል። ኮዲሮቭ እ.ኤ.አ. በ2009 ወደ አሜሪካ በተማሪዎች ቪዛ የገባ ቢሆንም፣ ትምህርት ላይ ባለመገኘቱ እ.ኤ.አ. ከሚያዝያ 2010 ጀምሮ ቪዛው ተሰርዞበት ሕገወጥ ሆኖ አሜሪካ ውስጥ በመኖር ላይ ያለ ሰው ነው።

ሰውዬው አክራሪ ነው የሚል ጭምጭምታ የተሰማ ቢሆንም ከየትኛው ድርጅት ጋር ግንኙነት እንደነበረው የተባለ ነገር የለም:: ይህን የማጣራት ክትትልም አልተደረገም። ዜናው ብቅ ባለበት ጊዜ አሜሪካ ውስጥ ያሉ የሪፐብሊካን ፓርቲ ደጋፊዎች ያሰማሩት ቅጥረኛ እነደሆነ ተነግሮ ነበር:: እየዋለ እያደረ ግን እሱም እንደ ኦርቴጋ በግሉ ለመግደል የተነሳሳ መሆኑን ብቻ የሚያሳዩ ዜናዎች ነው የተሰሙት። ያም ሆነ ይህ ይህም የአገሪቱን መሪ ሊገድል ከነሙሉ ትጠቁ የተገኘ ሰው ዓለምን የሚያጯጩህ አልሆነም። በድረ ገጽ ላይ እስካሁን የሚነበቡ ዜናዎች ልዩ ጥንቃቄ የታከለባቸው ይመስላሉ። ከአንዱ ድረ ገጽ ወደ ሌላው የሚሸጋገር ሰው ያንኑ የመጀመሪያውን በድጋሚ እያነበበ እስኪመስለው ተመሳሳይ የቃላት፣ የአገላለጽና የዓረፍተ ነገር አወራረድ ነው የሚያየው።

የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ኦባማና የሳዑዲው ዲፕሎማት አል-ጁበር በተመሳሳይ ፈተናዎች ውስጥ አለፉ፤ ዓለማችን ለአል ጁበር ተጯጯኸ፤ ይህ መጯጯህ እዚህ የደረሰው ከወደ አሜሪካ በታየው ግርግርና በተቀሰቀሰው ትኩሳት ተገፋፍቶ ነው። በጣም የሚገርመው የፕሬዚዳንት ኦባማ አል-ጁበርን ለመግደል ተጠነሰሰ ከተባለው ሴራ ጋር በተገናኘ ለተፈጠረው ትኩሳት ዋና አንቀሳቃሽ ነበሩ:: ነገር ግን ሚስተር ኦባማም ሆኑ የፔንታጎንና የዋይት ሐውስ ጓዶቻቸው ኦባማ የአሜሪካ አንደኛ ወኪል መሆንና የኦባማ መጠቃት የአሜሪካ መጠቃት ሆኖ ሊታያቸው አለመቻሉ አስገራሚ ነው። እርግጥ ነው ከአደል አል-ጁበርም ሆነ ከኦባማ ለአሜሪካ ማንም ላይበልጥ ይችላል፤ ነገር ግን ለአሜሪካ ጦርነት ከሁሉም ነገር ይበልጣል።

በሰላም ያቆየን።ከአዘጋጁ፡- ጸሐፊውን በኢሜይል አድራሻ

[email protected] ማግኘት ይቻላል::

ከኦባማና ከአል-ጁበር ለአሜሪካ ማን ይበልጣል?ፕሬዚዳንት ኦባማ አደል አል-ጁበር

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 40 | እሑድ |ኅዳር 17 ቀን 2004ክፍል-1

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 41 | እሑድ | ኅዳር 17 ቀን 2004 ክፍል-1

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 42 | እሑድ |ኅዳር 17 ቀን 2004ክፍል-1

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 010/2004

ሕብረት ባንክ አ.ማ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎችን ባሉበት ሁኔታ በዝግ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ eKV}a‡ ´`´` G<’@ Ÿ²=I u ‹ ”ÅT>Ÿ}K¨< k`vDM::

ተ.ቁ የሠሌዳ ቁጥር የሞተር ጉልበት የሻንሺ ቁጥር ¾V}` lØ`የጨረታው መነሻ ዋጋ

(በብር)1 3-0684 አ.አ. 124cc 41050008 04000022 6,706.682 3-1082 አ.አ. 173.6cc LZS1CLL0745160165 ZS162FMK241300018 5,871.923 3-1081 አ.አ. 173.6cc LZSJCLL0045160198 ZS162FKM2413000001 9,901.124 3-0313 አ.አ. 173.6cc LZSJCLC0845160143 ZS16FMK241300016 6,973.925 3-1084 አ.አ. 173.6cc LZSJCLL0345160129 ZS162FMK24130045 8,104.926 3-1088 አ.አ. 173.6cc LZSJCLL0345160180 ZS162FMK241300003 8,449.207 3-0323 አ.አ. 173.6cc LZSJCLL0545160133 ZS162FMK241300066 5,780.928 3-0324 አ.አ. 173.6cc LZSJCLL0545160133 ZS162FMK241300015 6,462.92

u²=G< SW[ƒ፡-

1. ንብረቶቹን ለማየት ለሚፈልጉ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ጠዋት ከ 2፡ዐዐ - 6፡ዐዐ ፣ ከሰዓት በኋላ ከ 7፡ዐዐ - 1ዐ፡ዐዐ ድረስ በባንኩ ዋና መ/ቤት ደብረዘይት መንገድ ግሎባል ሆቴል ዝቅ ብሎ ሚክዎር ፕላዛ ህንፃ ግቢ ውስጥ በመገኘት ማየት ይቻላል፡፡

2. ተጫራቾች ለተጫረቱት ንብረቶች የጨረታ መነሻ ዋጋ ¼ኛ ወይም 25% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ /ሲ.ፒ.ኦ/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

3. አሸናፊ የሚሆነው ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በ15 ቀናት /አሥራ አምስት ቀናት/ ጊዜ ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ይኖርበታል፤ ባይከፍል ግን ጨረታው ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ አይመለስለትም\ ሆኖም ጨረታውን ላላሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ አሸናፊው ከተለየ በኋላ ይመለስላቸዋል፡፡

4. }Ý^Œ‹ K›”É ¨ÃU Ÿ›”É uLà KJ’< V}` dáKA‹ SÝ[ƒ ËLK<:: 5. ተጫራቾች በሌላ ተጫ^ች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡

6. ተጫራቾች V}` dáKA‡” የሚገዙበት ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎኘ uTÉ[Ó በባንኩ ዋና መ/ቤት ንብረት አስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት ዋና ክፍል፤ ሚክዎር ኘላዛ ሕንፃ ምድር ቤት ÃI Teታ¨mÁ Ÿ¨×uƒ k” ËUa እeŸ ታIde 3 k” 2004 ¯.U Ÿk’< 10:00 c¯ƒ ድረስ በሥራ ሰዓት ማቅረብ ይችላሉ፡፡

7. ሞተር ሳይክሎቹን በገዥው ስም ለማዛወር ባንኩ ለሚመለከተው መንግሥታዊ አካል ማረጋገጫ ይጽፋል፡፡

8. ተጨማሪ እሴት ታክስ እና ሌሎች ገዢ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ታክf‹“ ግብሮችን ገዢው/አሸናፊው ይከፍላል፡፡

9. ጨረታው የሚከፈተው ታIde 4 k” 2004 ዓ.ም ከጠዋቱ በ3፡30 ሰዓት በዋናው መሥሪያ ቤት ውስጥ ይሆናል፡፡

10. ለበለጠ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0114-65 52 22 የውስጥ መስመር 212 ወይም 261 ወይም 0114-67 32 08 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡ 11. ባንኩ ”w[„ች” ለመሸጥ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በጨረታው አይገደድም፡፡

ሕብረት ባንክ አክሲዮን ማኀበር

የሽያጭ ጨረታ ቁጥር 17/ተረፈ ምርት/2004

የኢትዮጵያ ቆርኪና ጣሳ ማምረቻ ኢንዱስትሪ አ.ማ. የተለያዩ የጥሬ ዕቃ ማጊያዎች፤ ተረፈ ምርቶች፤ ለድርጅቱ አገልግሎት የማይሰጡ ብረታ ብረቶች፤ ንቃይ ቆርቆሮዎች እና ወራጅ እንጨቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት፤

1. ስለአሻሻጡ የተዘጋጀውን እና የንበረቱን ዝርዝር ሁኔታ የያዘውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 20 /ሃያ ብር/ በመክፈል ከፋብሪካው የሽያጭ ክፍል መውሰድ ይችላል፡፡

2. ተጫራቾች የጨረታው ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ለእያንዳንዱ እቃ ብር 5,000 /አምስት ሺህ ብር/፤ ለቁርጥራጭ ላሜራዎች እና አገልግሎት ለሰጠ የመዳብ ሽቦ ለእያንዳንዱ ብር 10,000 /አስር ቪህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ (CPO) ወይም በፋብሪካው ሂሳብ ክፍል በጥሬ ገንዘብ የተከፈለበትን የሚያረጋግጥ የገንዘብ መቀበያ ደረሰኝ የጨረታው ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

3. ተጫራቾች የተጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ ላይ በመሙላት በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ አድርገው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ታህሣሥ 16 ቀን 2004 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4 ሰዓት ድረስ በፋብሪካው ውስጥ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡

4. ጨረታው ታህሣሥ 16 ቀን 2004 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡30 በፋብሪካው ቅጥር ግቢ ውስጥ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ቦታ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

5. የጨረታው አሸናፊ እንደታወቀ ለተሸናፊዎች ያስያዙት ገንዘብ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡ አሸናፊውም ያሸነፈበት ዕቃ አነሳስና የገንዘብ አከፋፈል በጨረታ ሰነዱ በዝርዝር በተገለፀው መሠረት ይሆናል፡፡

6. ፋብሪካው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ

የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ የኢትዮጵያ ቆርኪና ጣሳ ማምረቻ ኢንዱስትሪ አ.ማ.

ስልክ ቁጥር 011-439-0244፣ 011-439-4095ፋክስ ቁጥር 011-439-0216

አዲስ አበባ

OPEN TENDEREast Africa Bottling share company (EABSC), invites sealed bids from eligible bidders for the supply of 1200 pcs of shirts (Gents and Ladies), 1200pcs of trousers/skirt, 1800pcs of different colour overalls, 600pcs of different color Ladies apron, 200pcs of different colour Grown, 250pcs of Beep trousers, 1200pcs of Blouse, 1800 pairs of shoes (different size), 1200pcs of Jacket and 1800pcs of cape.

All Bids Must be accompanied by a Bid security in the form of CPO for 5% of the total amount of your offered price. The CPO should be prepared in the name of EAST AFRICA BOTTLING S.C All quotation should be accompanied with sample which shall be submitted to the address below on or before Nov 30,2011.

Bidders who submitted document without CPO and sample will automatically be rejected.

After official award, the winner should deliver the respective uniforms within one months at East Africa Bottling Share Company store. The Company has the right to cancel the award and will not refund the bid security should the winner fails to deliver the uniform on the agreed date.

East Africa Bottling Share Company has the right to reject the tender partially or fully.

EAST AFRICA BOTTLING SHARE COMPANYJIMMA ROAD-ADDIS ABABA

Tel: +251-0112755476 OR +251-0112776450

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 43 | እሑድ | ኅዳር 17 ቀን 2004 ክፍል-1

በብሔራዊ ባንክ... ከክፍል-1 ገጽ 1 የዞረ

በየማነ ናግሽ

ባሳለፍነው ሳምንት ወታደሮችዋን ሶማሊያ ውስጥ አስገብታለች የሚሉ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ዘገባዎችን ስታስተባብል የቆየችው ኢትዮጵያ፣ ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ሶማሊያ ወታደራዊ ዘመቻ ለማድረግ ኦፊሴላዊ ጥያቄ እንደቀረበላትና መስማማቷን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለሪፖርተር አረጋገጠ::

ባለፈው ዓርብ በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የተመራው የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በየነ መንግሥታት ድርጅት (ኢጋድ) የመሪዎች ስብሰባ በሸራተን አዲስ ሲካሄድ፣ ሶማሊያ ውስጥ በአልሸባብ ላይ እየተከናወነ ባለው ወታደራዊ ዘመቻ ኢትዮጵያ እንድትሳተፍና ጽንፈኛውን ቡድን ለመጨረሻ ጊዜ ለመደምሰስ በሚደረገው ዘመቻ ይፋዊ ጥያቄ

ቀርቦላታል:: የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር

ዲና ሙፍቲ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ኢትዮጵያ ለአካባቢው ሰላም ሲባል በኢጋድ የቀረበላትን ጥያቄ ስትቀበል የቆየች ሲሆን፣ አሁንም የቀረበላትን ጥያቄ ተቀብላ አስፈላጊውን ድጋፍ ታደርጋለች::

የኢትዮጵያ ወታደሮች በአካባቢው ከተሰማራው የአፍሪካ ኅብረት ሰላም አስከባሪ ኃይልና በቅርቡ ሶማሊያ ከገባው የኬንያ ጦር ኃይል ጋር ተቀላቅለው አንድ የተጣመረ ኃይል እንዲፈጠርም ተወስኗል:: የኢትዮጵያ ወታደሮች ወደ ሶማሊያ መግባታቸውን ሲያስተባብል የነበረው መንግሥት፣ ኢጋድ ከወሰነ ግን ሊዘምት እንደሚችል መግለጹ ይታወሳል:: ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ በመሩት የኢጋድ የመሪዎች ስብሰባ ላይ ነበር ኢትዮጵያ በአልሸባብ ላይ ለሚካሄደው ዘመቻ

ድጋፍ እንድትሰጥ በይፋ ጥያቄው የቀረበላት:: አምባሳደር ዲና ለሪፖርተር እንዳረጋገጡት፣

ኢትዮጵያ የሶማሊያን የሽግግር መንግሥት፣ የአፍሪካ ኅብረትን የሶማሊያ የሰላም አስከባሪ ኃይልና ኬንያን የምትረዳው በወታደራዊ፣ በፖለቲካዊ፣ በዲፕሎማሲያዊና በተለያዩ መንገዶች ነው:: የኢትዮጵያ ድጋፍ ሁሉን አቀፍ መሆኑን አመልክተው፣ የኢጋድ መሪዎች አልሸባብን ለመምታት በሚደረገው ጦርነት የኢትዮጵያ እገዛ እጅግ በጣም አስፈላጊ መሆኑን አምነውበታል ብለዋል::

ኢትዮጵያ በደቡብ ሱዳንና በሱዳን መካከል በምትገኘው አወዛጋቢዋ የአቢዬ ግዛት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ሥር ያሰማራቻቸው የሰላም አስከባሪ ወታደሮቿ በድርጅቱ ከፍተኛ አድናቆት ያገኙ መሆኑን በማስታወስ፣ በአካባቢው ለሰላምና ለደኅንነት

የምታደርገው አስተዋጽኦ በሶማሊያም እንዲቀጥል ነው ኢጋድ ጥሪውን ያቀረበው::

የአፍሪካ ኅብረትና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በሶማሊያ የሚሰማራውን የተጣመረ ወታደራዊ ኃይል ለማንቀሳቀስ እየተነጋገሩበት መሆኑን፣ በአፍሪካ ኅብረት የሰላምና ደኅንነት ኮሚሽነር አምባሳደር ራምታኔ ላማምራ ለሪፖርተር ገልጸዋል::

ከሁለት ዓመታት በፊት የሶማሊያ እስላማዊ ፍርድ ቤቶች ኅብረትን በመቃወም በሶማሊያ የሽግግር መንግሥት ጥሪ ወደ አካባቢው የዘመተው የኢትዮጵያ ወታደራዊ ኃይል፣ ቡድኑን በታትኖ ከሦስት ዓመት ቆይታ በኋላ መመለሱ የሚታወስ ነው:: ኢትዮጵያ በአሸባሪነት ከፈረጀቻቸው አምስት የአገር ውስጥና የውጭ ድርጅቶች መካከል፣ ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት እንዳለው የሚነገርለት አልሸባብ አንዱ ነው::

የኢትዮጵያ ሠራዊት ወደ ሶማሊያ ሊዘምት ነው

የመንግሥት ጣልቃ...ከክፍል-1 ገጽ 4 የዞረ

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ... ከክፍል-1 ገጽ 3 የዞረ

‹‹መመርያው በቅርብ ላይወጣ ይችላል›› ከሚል ግምትና አብዛኛዎቹ ማሟላት ያለባቸውን መሣሪያዎች ማሟላት ባለመቻላቸው የተፈጠረ ክፍተት እንጂ፣ ዝግጅቱን እንዳጠናቀቁ ግዥውን የሚጀምሩ መሆኑን ይኼው የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል::

በአሁኑ ጊዜ ተፈላጊውን መሣሪያ ያሟሉና በሚያመርቱት ወርቅ ላይ ሊኖሩ የሚገባቸውን ማህተሞችና ሎጎዎች አስቀርፀው የጨረሱ የባለቤትነት ማረጋገጫ ማውጣት የሚኖርባቸውም በመሆኑ፣ በወርቅ ግዥው ላይ መዘግየት መፈጠሩን

የሚያመለክተው የሚኒስትሩ መረጃ፣ ከዕደ ጥበባቱ ያለቀላቸው የወርቅ ጌጣጌጦችን ገዝተው የሚሸጡ ወርቅ ቤቶችም የወርቅ ንግድ ማረጋገጫ ሠርተፍኬት በመውሰድ ላይ ናቸው ተብሏል::

የወርቅ ንግድ ማረጋገጫ ሳይኖር በወርቅ ንግድ ላይ መሰማራት ስለማይቻል፣ በአዋጁ መሠረት እስካሁን በአዲስ አበባ ለወርቅ ንግድ ማረጋገጫ ሠርተፍኬት የተሰጣቸው 150 ያህል ወርቅ ቤቶች ናቸው:: ከአዲስ አበባ ውጭ ባሉ ከተሞች የሚገኙ ነጋዴዎች ለወርቅ ንግዱ ማረጋገጫ እንዲወስዱ እየተደረገ ነው::

እስካሁንም ከትግራይ ክልል 71 ወርቅ ቤቶች የወርቅ ንግድ ማረጋገጫ ሠርተፍኬት ተቀብለዋል:: በአዋሳና በጅማ ከተሞችም የፈቃድ አሰጣጡ ይቀጥላል ተብሏል:: ይህ የማረጋገጫ ፈቃድ ሳይያዝ ወርቅ መነገድ

የማይቻል በመሆኑ፣ በወርቅ ንግድ ላይ የተሰማሩ ሁሉ መረጃው እንዲኖራቸው መደረጉ ተገልጿል:: በዚህ መሠረት ፈቃዱን ሳያገኙ ግዥም ሆነ ሽያጭ ማከናወን በወንጀል እንደሚያስጠይቅ ያስረዳል::

የከበሩ ማዕድናትን የሚመለከተውን አዋጅ ተከትሎ የወጣውን ይህንን መመርያ ብሔራዊ ባንክ፣ ማዕድን ሚኒስቴርና ጂኦሎጂካል ሰርቬይ በጋራ የሚያስፈጽሙት እንደሆነ ይታወቃል::

መግለጫ እነሱን የማይወክል መሆኑን በየፍርድ ቤቱ እያስታውቁ መሆኑን አስመልክቶ ለተነሳላቸው ጥያቄ ነው::

‹‹ተጠርጣሪዎቹ በተያዙበትና በታሰሩበት ቦታ በተደጋጋሚ ሄደን ጎብኝነተናል:: መብታቸው በትክክል መጠበቁንና በአግባቡ መያዛቸውን ነግረውናል:: የተያዙበትን ጉዳይ በራሳቸው አንደበት አስረድተውናል፤›› በማለትም ኮሚሽነሩ ቢናገሩም፣ በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሦስተኛ ወንጀል ችሎት ጥቅምት 30 ቀን 2004 ዓ.ም. ክስ ከተመሠረበታቸው 24 ተጠርጣሪዎች መካከል፣ የአንድነት ለፍትሕና ለዴሞክራሲ ፓርቲ አባል አቶ ናትናኤል መኮንን፣ በማዕከላዊ እስር ቤት እያለ የደረሰበትን የሰብዓዊ መብት ረገጣን በማስታወቅ፣ ኮሚሽኑ ተጠርጣሪዎችን በሚመለከት በመገናኛ ብዙኃን ያሰራጨው መረጃ የተሳሳተ፣ ከእውነት የራቀና በተለይ እሱን የማይወክል መሆኑን መግለጹን መዘገባችን ይታወሳል::

የሰብዓዊ መብቶች ድንጋጌ የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት አካል እንዲሆን መደረጉንና የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥትም በዓለም ላይ ምርጥ ከሚባሉት ሕገ መንግሥቶች አንዱ መሆኑን የገለጹት ደግሞ የፍትሕ ሚኒትስሩ አቶ ብርሃን ኃይሉ ሲሆኑ፣ መንግሥት ሕገ መንግሥቱን ማፅደቅ ብቻ ሳይሆን ተግባራዊ ለማድረግ ብዙ መሥራቱን አስረድተዋል::

የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት አያያዝን በሚመለከት በተለያዩ ዓለም አቀፍና የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን በተዛባ መንገድ ሪፖርቶች ሲያቀርቡ እንደሚታዩ የገለጹት ሚኒስትሩ፣ ብዙዎቹ ተዓማኒነት የሌላቸው፣ የኢትዮጵያን ሁኔታ በተጨባጭ የማያመላክቱ መሆናቸውን ተናግረዋል:: በተጨባጭ ማስረጃ የሚቀርብባቸው የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ካሉ፣ መንግሥት ለማስተካከል ወደኋላ እንደማይል፣ በቀጣይ ነገሮችን ለማስተካከል ቁርጠኝነት ወስዶ እየተንቀሳቀሰ መሆኑንና የድርጊት መርሐ ግብሩንም የቀረጸው ለዚሁ መሆኑን አብራርተዋል::

‹‹መንግሥት በኢትዮጵያ ውስጥ ምንም ዓይነት የሰብዓዊ መብት ረገጣ የለም ብሎ ያምናል?›› በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ፣ ‹‹በሕገ መንግሥቱ የተቀመጡ አንቀጾች በጣም ሰፊ ናቸው:: ተግባራዊ ለማድረግ ሰፊ የማስፈጸም አቅም ይጠይቃል:: በማንኛውም አገር ሕገ መንግሥት የሚሰጣቸውን መብቶች ተግባራዊ ለማድረግ ረጅም ጊዜ ያስፈልጋል:: ቀድሞ የሕዝቡን አስተሳሰብ መለወጥ ያስፈልጋል:: አለበለዚያ አይቻልም:: በደርግ አገዛዝ ውስጥ ያለፈን ኅብረተሰብ በውስጡ ያለውን ጠባሳ በቀላሉ መቀየር ግድ ይላል:: አመራሩ ራሱ ለውጥ ማምጣት አለበት:: የዳበረ የዴሞክራሲ ሥርዓትና መልካም አስተዳደር የዳበረባት አገር ሆናለች ማለት ሳይሆን፣ ገና ተግባራዊ ለማድረግ የሚጣርባት ነች፤›› በማለት አቶ ብርሃን መልስ ሰጥተዋል::

በሕገ መንግሥቱ ውስጥ የተቀመጡ መብቶችን ሁሉ በአጭር ዓመት ተግባራዊ ይሆናሉ ብሎ መጠበቅ እንደማይቻል የተናገሩት ሚኒስትሩ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የሰብዓዊ መብቶች ድርጊት መርሐ ግብር ዝግጅትና የዕድገትና ትራንስፎርሜን ዕቅድ ዝግጅቶች አፈጻጸምን የበለጠ የጠራ ለማድረግ ዕድል እንደሚፈጥር አስረድተዋል::

ዓለም አቀፍ ተቋማት የሚያወጡት ሪፖርቶች በኢትዮጵያ ውስጥ በትክክል እየሆነ ካለው ነገር ተነስተው የሚዘጋጁ አለመሆናቸውንና መንግሥትም በወቅቱ ምላሽ የሰጠባቸው መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሩ፣ በሕገ መንግሥቱ ላይ የተቀመጡት ሰብዓዊ መብቶችን የሚመለከቱ አንቀጾች መሠረታዊ አቅጣጫዎች መሆናቸውን፣ አፈጻጸማቸውም በዝርዝርና በዕቅድ የሚሆን መሆኑን አስረድተዋል:: የሠለጠነው ዓለምም ተፈጻሚ የሚያደርገው የኅብረተሰቡን ዕድገት እያየ እንጂ፣ በአንድ ጊዜ ፈጽሜለሁ አይልም በማለት አብራርተው፣ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ረገጣ እንዳለ ስለሚያወጡዋቸው ሪፖርቶች በሚመለከት ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል:: አንዳንድ ጉድለቶች እንደሚኖሩ አምነው ለማስተካከል ጥረት እንደሚደረግም ጠቁመዋል::

‹‹ዓለም አቀፍ ሪፖርት ሲባል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሚያወጣው ሪፖርት ወይስ በየጋዜጣው የሚወጣው ሪፖርት?›› የሚል ጥያቄ በማንሳት ማብራሪያ የሰጡት አምባሳደር ጥሩነህ ደግሞ፣ ‹‹ዓለም አቀፍ ሲባል ክብደት አለው:: አንድ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት የሚያወጣው ሪፖርት ለማንም ተዓማኒ አይደለም:: እሱ የፈለገውን ሪፖርት ይፋ ማድረግ ይችላል:: ነገር ግን ከሕዝብ አስተያየት ጋር ሊመደብ ይችላል፤›› ብለዋል::

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሪፖርት ከሆነና ኢትዮጵያም ሪፖርት አድርጋ አገሮች እንደተወያዩበትና በአገር ውስጥም ውይይት መደረጉን፣ መገምገሟን፣ ብዙ አስተያየቶች መምጣታቸውንና በተወሰኑትም ተጠያቂ እንደሆነች የገለጹት አምባሳደር ጥሩነህ፣ ሌሎች አገሮች የበለጸጉት ሳይቀሩ የተለያዩ ችግሮች እንደተነሳባቸው ሁሉ፣ በኢትዮጵያም ያሉ በጎ ሥራዎችና ችግሮች መነሳታቸውን እንጂ፣ እሳቸው በዓለም አቀፍ ድርጅቶች ውስጥ በሚሠሩበት ጊዜም ቢሆን በተለይና አስጊ በሆነ መንገድ ስሟ ሲጠራ ሰምተው እንደማያውቁ አስረድተዋል::

በአገር ውስጥ ሆነው ስለ ሰብዓዊ መብቶች ከሚሟገቱ ድርጅቶች ጋር ለምን ተባብረው እንደማይሠሩ ለተጠየቁት ከሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ሰመጉ) ጋር በጋራ ለመሥራት እየተነጋገሩ መሆኑን አስታውቀው፣ ከሌሎች ድርጅቶችም ጋር እየሠሩ መሆናቸውን ጠቁመዋል::

ሰብዓዊ መብት... ከክፍል-1 ገጽ 1 የዞረ

መዘገባችን ይታወሳል:: የተዘረጋው የቴሌኮም ኔትወርክ አሁን

በአገልግሎት ላይ ካለው ኔትወርክ ጋር ከመዋሀዱ በፊት፣ በሦስተኛ ወገን ጥብቅ ፍተሻ እንደሚደረግበት ሚኒስትሩ አስረግጠው ተናግረዋል::

በተፈጠረው ያልተጠበቀ ክስተት የተገረሙ የኢትዮ ቴሌኮምና የዜድቲኢ ከፍተኛ አመራሮች

ችግሩን በሰላም ለመፍታት እየተንቀሳቀሱ መሆናቸውን ምንጮች ጠቁመዋል:: ችግሩን ለመፍታትም የዜድቲኢ ምክትል ኃላፊ አዲስ አበባ መግባታቸውም ታውቋል::

ስማቸውን ለመግለጽ ያልፈለጉ አንድ የሕግ ባለሙያ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በቻይናው ባለሙያ የተፈጸመው ድርጊት በመግደል ሙከራ

ሊያስከስስ ይችላል::ከኢትዮ ቴሌኮም ኢንጂነሮች በተጨማሪ

ገለልተኛ የሆነ ሌላ ኩባንያ በ1.5 ቢሊዮን ዶላር እየተዘረጋ የሚገኘውን ኔትወርክ ጥራት በመፈተሽ ላይ ነው:: የሚደርስበትን ውጤት በሁለት ወራት ውስጥ ያሳውቃል ተብሎ ይጠበቃል::

የተፈጠረውን ችግር አስመልክቶ ከኢትዮ ቴሌኮም መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም::

ከኔትወርክ ፍተሻ... ከክፍል-1 ገጽ 3 የዞረ

ልቀቁና ቦታ ቀይሩ እንደሚባሉ የሚናገሩት እነዚሁ ሠራተኞች፣ ለዚህ ሁሉ እንግልት የሚሰጣቸው ምላሽ ‹‹የቤት ኪራይ ተወዶብናል፤ ክፍሎቹን ለሌላ የትምህርት ክፍል እንፈልጋቸዋለን፤›› የሚሉና ግልጽ ያልሆኑ ምክንያቶች እንደሆነ ይጠቁማሉ::

ዩኒቨርሲቲው በሚያደርስባቸው እንግልት ተስፋ የቆረጡና የሰለቻቸው ሠራተኞች አንዳንዶቹ ቀድሞ ይሠሩባቸው ወደነበሩት የትምህርት ክፍሎች ሲመለሱ፣ የትምህርት ክፍሉ ኃላፊ የነበሩትን ጨምሮ ሌሎች ደግሞ የመልቀቂያ ደብዳቤ በማስገባት ላይ ናቸው::

ያነጋገርናቸው የትምህርት ክፍሉ የዘንድሮ

ተመራቂ ተማሪዎች በተፈጠረው ሁኔታ ችግር ውስጥ መግባታቸውን ገልጸው፣ ለዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ፔቲሽን ቢያስገቡም ምላሽ ማግኘት አልቻሉም:: የትምህርት ክፍሉ የመማር ማስተማር ሒደት በማቆሙ ማን ዘንድ መሄድ እንዳለባቸው ግራ መጋባታቸውን ተናግረዋል::

ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ የዩኒቨርሲቲው ኃላፊ በበኩላቸው፣ ወደ አቃቂ ካምፓስ እንዲሄድ የታዘዘው የሥነ ፆታ የትምህርት ክፍል ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ አምስት የትምህርት ክፍሎች ናቸው:: የተመረጡበትም ምክንያት የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞችን ብቻ የያዙ የትምህርት

ክፍሎች ዩኒቨርሲቲው በገጠመው የቦታ ጥበት ሳቢያ ወደ አቃቂ እንዲሄዱ በመወሰኑ ነው::

የሥነ ፆታ የትምህርት ክፍል ሠራተኞች የሥራ መልቀቂያ ደብዳቤ ማስገባት የዩኒቨርሲቲውን አመራሮችን ማሳሰቡን ገልጸው፣ ከሠራተኞቹ ጋር በአስቸኳይ ውይይት በማድረግ ችግሩን ለመቅረፍ መታሰቡን አስረድተዋል::

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሥር የሚገኘው የሥነ ፆታ የትምህርት ክፍል በኢትዮጵያ ብቸኛው በድኅረ ምረቃ ፕሮግራም የሚያስተምር የትምህርት ክፍል ነው:: በአሁኑ ወቅት በጠቅላላው 34 ያህል ተማሪዎች እንዳሉት ለማወቅ ተችሏል::

በቅርቡ የትምህርት ቤቱ የአመራር ኮሚቴ የሾማቸውን ርዕሰ መምህር መንግሥት ቦታው ላይ እሳቸው መቀመጥ እንደማይችሉ ነግሮ በማሳመን በስምምነት እንዲለቁ ማድረጉን የሚናገሩት ምንጮች፣ በትምህርት ቤቱ ውስጥ ትርምስ እንዳይፈጠር በሚል ኮሚቴው የሾማቸውን ሁለተኛውን ምክትል ርዕሰ መምህር አለማንሳቱን ተናግረዋል::

ችግሩ ከሕግ ጋር የተገናኘ ሳይሆን የትምህርት ቤቱ አቅም ጉዳይ መሆኑን የሚናገሩት ምንጮች፣ መንግሥት እገዛውን ሙሉ በሙሉ ካቆመ የትምህርት ቤቱ ህልውና አደጋ ውስጥ ይወድቃል:: ብቸኛው አማራጭም መንግሥት በሚሾማቸው አመራሮች መቀጠል ብቻ መሆኑን ጨምረው ገልጸዋል::

አቶ ደምርም ሆኑ የክፍለ ከተማው ባለሙያ ትምህርት ቤቱ ኮሚቴው በመረጣቸው ርዕሰ መምህራን የሚመራ ከሆነ መንግሥት ድጋፉን እንደሚያቋርጥ ይግለጹ እንጂ፣ በ1993 ዓ.ም የወጣው የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር የሕዝብ ትምህርት ቤቶች አዋጅ ይህንን አካሄድ ይፃረራል:: አዋጁ እንደሚለው ርዕሰ መምህርና ምክትል ርዕሰ መምህራን በትምህርት ቤቱ ኮሚቴ ይመረጣሉ:: ትምህርት ቢሮው ደግሞ ለትምህርት መሣሪያዎችን፣ ለመምህራን፣ ለሕግ፣ ለኦዲትና ለሌሎች ቴክኒክ ነክ አገልግሎቶች ድጋፍ ይሰጣል::

መቃወሚያ በመቀበል ውድቅ አድርጐታል:: የቀረበው መቃወሚያ እንደሚገልጸው፣

አፈጻጸሙ መሠረት የተደረገበት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሐምሌ 27 ቀን 2003 ዓ.ም. የሰጠው ውሳኔ በገንዘቡ ላይ ወለድ ይከፈል ብሎ አልወሰነም::

ሚኒስቴሩ ጥቅምት 8 ቀን 2004 ዓ.ም. በተጻፈ የአፈጻጸም ማመልከቻ፣ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሐምሌ 27 ቀን 2003 ዓ.ም. የሰጠው ውሳኔ እንዲፈጸምለት ይኼንን ፍርድ ቤት መጠየቁን መዘገባችን ይታወሳል::

ወ/ሮ ሻዲያ የቀድሞው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ታምራት ላይኔ በተከሰሱበት በሥልጣን አለአግባብ መጠቀምና በሙስና ወንጀል በግብረ አበርነት ጥፋተኛ መባላቸው ይታወሳል:: ከዚሁ ወንጀል ጋር በተያያዘ ወ/ሮ ሻዲያና ግብረ አበሮቻቸው ከሼክ አል አሙዲ ላይ 16 ሚሊዮን ዶላር አጭበርብረው በመውሰድ እያንዳንዳቸው ድርሻቸውን በውጭ ባንኮች በማስቀመጣቸው መቀጣታቸውም ይታወሳል::

ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሐምሌ 27 ቀን 2003 ዓ.ም. የሰጠው ውሳኔ እንደሚያስረዳው፣ በወ/ሮ ሻዲያ ስም በባንክ ኢዶ ስዊዝ ሜሪ ራዥ ጂቡቲ በሚገኙ ሁለት የባንክ ሒሳቦች እንዲሁም ባለዕዳዋ በራሚስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ስም በዚሁ ባንክ የሚያንቀሳቅሱት ገንዘብ ለሚኒስቴሩ ወጪ ተደርጐ እንዲከፈል ብሎ አዟል::

ውሳኔው ጨምሮ እንደሚያስረዳው፣ ሼክ አል አሙዲ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከዚህ በፊት የወሰነላቸው ዘጠኝ ሚሊዮን ዶላር ለማስፈጸም በስዊዝ ፍርድ ቤት የአፈጻጸም ማመልከቻ አስገብተው 6.5 ሚሊዮን ብር እንዲወስዱ ቢፈቀድላቸውም፣ እሳቸው ግን ስዊዝ ባንክ ከሚገኘው የወ/ሮ ሻዲያ ሒሳብ ላይ ከ9.9 ሚሊዮን ብር በላይ ወስደዋል::

በዚህም ምክንያት የወሰዱትን ትርፍ 905,158.16 ዶላር ለሚኒስቴሩ መሥርያ ቤት እንዲመልሱ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ሊያዝ ችሏል::

ፍርድ ቤት በወ/ሮ .... ከክፍል-1 ገጽ 5 የዞረ

መሆናቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ ሜፖ የሆቴሉን ፕሮጀክት ከተረከበ አንድ ዓመት ቢያልፈውም፣ ከተወሰኑ ፎቆች በላይ ማውጣት እንዳልቻለ የገለጹት ምንጮች፣ ከዚህ በተጨማሪ ባለፉት አራት ወራት ‹‹በሲሚንቶ እጥረት›› በሚል ምክንያት ግንባታው መቋረጡን አስረድተዋል፡፡

በግንባታው ላይ አስተያየታቸውን የሰጡት ውስጥ አዋቂ ምንጮች ሜፖ ከመንግሥት በተሰጠው ልዩ ፈቃድ ሲሚንቶ በርካሽ ከውጭ ማስገባት የሚችል ቢሆንም፣ ባለው የሥራ አመራር ችግር የሲሚንቶ እጥረት በመፈጠሩ ግንባታው መስተጓጎሉን አብራርተዋል፡፡

ከሆቴሉ ፕሮጀክት ጎን ለጎን በ123.7 ሚሊዮን ዶላር የተገነባው የአፍሪካ ኅብረት ዋና ጽሕፈት ቤት የመጀመሪያ ደረጃ የስትራክቸር የጥራት ፍተሻ እንዳለፈ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ጽሕፈት ቤቱም በመጪው የፈረንጆቹ አዲስ ዓመት እንደሚመረቅ ይጠበቃል፡፡

የተገነባው የአፍሪካ ኅብረት ሕንፃ ባለ 20 ፎቅ ዋና ቢሮ፣ ከ2,500 ሰዎች በላይ የሚይዝ ዘመናዊ የመሰብሰቢያ አዳራሽና 32 የተለያዩ መለስተኛ መሰብሰቢያ አዳራሾች ሲኖሩት፣ ርዝማኔውም 99.9 ሜትር ነው፡፡ የጽሕፈት ቤቱ ሕንፃ በ112 ሺሕ ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ ነው፡፡

የአፍሪካ ኅብረት... ከክፍል-1 ገጽ 5 የዞረ

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 44 | እሑድ |ኅዳር 17 ቀን 2004ክፍል-1

DAPT-Assessments and Participatory Trainings (DAPT) E-mail: [email protected]

Development Action Promoters Team [DAPT] is well qualified pool of professionals owning leading Assessments and Participatory Trainings consultancy firm since Aug 2007. DAPT is dedicated to work in partnership, providing proven technical expertise and services for various national and international NGOs, privet and Governmental organizations. To contribute efforts on the fight against HIV/AIDS and bring change about social development, the firm is complimenting the works of various key actors in Ethiopia, promoting consultation platforms and strengthening a comprehensive Responses Management System (ARMS).

Taking the opportunity to host Satellite Symposia at ICASA 2011, we are inviting all esteemed partners to share national experiences, promote achievements and foster collaborative learning’s on the fight against the epidemic. The symposia sessions are prepared with highly attractive and generous packages including vivid demonstrations of commitments, showcase interesting findings, review of institutions work with exhibitors contest and award statements of best practices.

(Please see sessions at the web of www.ICASA2011addis.org or you may request to apply or any information, writing to [email protected], calling to +251921880966/+251912742566/+251911228115

1 Sharing National Experiences and Exchange of Technicalities (NEXT) on multifaceted responses to HIV/AIDS

4 Dec 2011 (9:00 – 11:30)

2 Review of organizations/institutions works with their programs on HIV/AIDS/STDs

4 Dec 2011 (11:30 – 12:00)

3 Review Discussion on the partnership modality, process, procedures and principles of collaborative issues that have been helping achieve impact mitigation based on UNGASS criteria

6 Dec 2011 (7:00-8:30)

4 Awarding “Statements of Best Practices 7 Dec 2011 (7:00-8:30)

DAPT: Development Actions Promoters Team 4U

Opportunity to attend/Participate Satellite Symposia at The 16th International Conference on AIDS and

Sexually Transmitted Infections in Africa (ICASA 2011), Dec 4 – 8, 2011,Addis Ababa, Ethiopia

የጨረታ ማስታወቂያ

መሰቦ የህንፃ መሳርያዎች ማምረቻ ኃላ.የተ.የግል ማህበር

ሮማናት ፎሌክሲብል ፓኬጂንግ ዩኒት ከዚህ በታች የተገለፁት

የፕላስቲክ ጥሬ ዕቃዎች እና ተረፈ ምርቶችን፤

150,000 ኪ.ግ Granulated ስክራፕ7000 ኪ.ግ ፐርጅድ ስክራፕ5,000 ኪ.ግ UV 20% Master Batch

25 ኪ.ግ Filming grade

1,000 ኪ.ግ Green maser batch

1,000 ኪ.ግ Red master batch

1,000 ኪ.ግ Yellow master batch

2,575 ኪ.ግ Red brown master batch

በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ስለሚፈልግ የሚከተሉትን

መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን ይጋብዛል፡፡ ስለሆነም ተጫራቾች፡-

1. ህጋዊ የንግድ ፍቃድ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ

መሆናቸውን ማረጋገጫ ማቅረብ አለባቸው፣2. ተጫራቾች ለሚሰጡት ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ

ቼክ (CPO) በድርጅቱ ስም ማስያዝ አለባቸው፣

3. የታክስ ከፋይነት ቁጥር (TIN) ማረጋገጫ ማቅረብ

አለባቸው፣

4. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 50.00

በመክፈል አዲስ አበባ ላንቻ ዘፍኮ ህንፃ 4ኛ ፎቅ በሚገኘው

የመሰቦ ህንፃ መሳሪያዎች ማምረቻ ኃላ.የተ.የግል ማህበር

ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ወይም መቀሌ መሰቦ ስሚንቶ ፋብሪካ

ፊት ለፊት ከሚገኘው የሮማናት ፍሌክሲብል ፓኬጅንግ

ዩኒት ዋና ቢሮ በመቅረብ ማመልከት ይቻላል፡፡ 5. የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱን ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ

በ10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ገንዘቡን ሙሉ በሙሉ

ከፍሎ ንብረቱን የማንሳት ግዴታ አለበት፡፡ 6. ጨረታው ከወጣበት 17/04/2004 ዓ.ም. ጀምሮ ለ7

ተከታታይ የስራ ቀናት ይቆያል በ8ኛው የስራ ቀን

27/04/2004 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም

ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመቀሌ ፋብሪካው ቅጥር

ግቢ ውስጥ ይከፈታል፡፡ 7. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ

በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃስ.ቁ. 034-559-13-28/29 መቀሌወይምስ.ቁ. 0114663292 አዲስ አበባደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 45 | እሑድ | ኅዳር 17 ቀን 2004 ክፍል-1

የአፋልጉኝ ማስታወቂያበቀን 27/4/2003 ዓ.ም በስም ፈለቀች የምትባል ግለሰብ ዉብነሽ አዳሚቱሉ የሚል ስም የወጣላትን ህጻን በኦሮሚያ ክልል አዳሚቱሉ ከተማ 01 ቀበሌ ጨፌ ጅላ መዉጫ አከባቢ ወ/ሮ ቡርቱካን አኖሬ ቤት ዉስጥ በእንግድነት አድራ ጥላ ስለጠፋች ማንኛዉም የህጻኗ እናት የምትገኝበትን አድራሻ የሚያውቅ ወይንም የህጻኗ ወላጅ ነኝ የሚል ግለሰብ በዚህ ስልክ ቁጥር ለቢሮአችን እንዲያስታውቅ እንጠይቃለን፡፡

ኪንግደም ቪዥን ኢንተርናሽናልአዳማ ፕሮጀክት

ስልክ ቁጥር 0221114188 0221114187

የጨረታ ማስታወቂያ

1. ሰሜን ገበያ አጠቃላይ ነጋዴዎች አክሲዮን ማኅበር በዲስ አበባ ለሚያስገነባው ባለ አራት

ፎቅ ቅይት የገበያ ማዕከል የአማካሪነት አገልግሎት በግንባታ ቁጥጥርና ኮንትራት አስተዳደር ሥራ

በማወዳደር ለማሠራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ደረጃ 3 እና በላይ

የሆኑ አማካሪዎች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛሉ፡፡

2. ተጫራቾች ለጨረታ ሲወዳደሩ የሚከተሉትን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

• በቫት ምዝገባ የምስክር ወረቀት

• ለበጀት ዓመቱ የታደሠ የንግድ ፈቃድ

• ግብር ከፋይ መሆኑን የሚገልፅ መለያ (Tin Numbere)

• አግባብ ያለው የሥራ ፈቃድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ከከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን

ሚኒስቴር እንዲሁም ሌሎች ጨረታውን መወዳደር የሚያስችሉ ማስረጃዎችን ፎቶ

ኮፒ ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

3. ተጫራቾች የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 10ኛ ቀን ድረስ ዘወትር

በሥራ ሰዓት ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ደየማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል

አዲሱ ገበያ ከኖክ በስተጀርባ ከሚገኘው የአ/ማ/ሩ ጽ/ቤት በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡

4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድን እንደሚከተለው ማቅረብ አለባቸው፡፡

4.1. የሚወዳደሩበትን የቴክኒካል ፖሮፖዛል እና ፋይናንሻል ፕሮፖዛል ዋናውን እና

ኮፒውን በተናጠል በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ አለባቸው፣

4.2. የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ሴኪውራቲ ለብቻው በታሸገ ኤንቨሎፕ ታሽጎ ቢድ

ሲኩውሪቲ (Bid Security) ተብሎ በግልፅ መፃፍ አለበት፣

4.3. የጨረታ ማስከበሪያው ብር ጨረታውን የሚሞሉበትን ጠቅላላ ዋጋ 1% አንድ

በመቶ ቢድ ቦንድ ወይም ሲፒኦ በሰሜን ገበያ አጠቃላይ ነጋዴዎች አ/ማ ስም

ማስያዝ ይኖርበታል፣

5. ተጫራቾች የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ባሉት 10 የሥራ ቀናት ውስጥ

በአ/ማ/ሩ ጽ/ቤት እስከ 10ኛው ቀን 6፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ 10ኛ ቀን የሥራ

ቀን ሆኖ ባይገኝ የጨረታ ማስገቢያው ቀን በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ይሆናል፡፡

ጨረታውም በ10ኛው ቀን በ6፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት

በዕለቱ በ8፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡

6. አንድ ተጫራች በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

7. አሠሪው መ/ቤት የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፈል የመሠረዝ

መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር 011 127 18 48/0911 41 11 19

የሰሜን ገበያ አጠቃላይ ነጋዴዎች አክሲዮን ማህበር

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 46 | እሑድ |ኅዳር 17 ቀን 2004ክፍል-1

ስፖርት

የኢትዮጵያ ቡድን ነገ ከሱዳን ጋር ይጫወታል

በረኛ ሌላው የእግር ኳስ ችግር እየሆነ ነውበደረጀ ጠገናው

በታንዛኒየ አስተናጋጅነት የሚከናወነው የምሥራቅና መካከለኛው አፍሪካ (ሴካፋ) አገሮች የእግር ኳስ ሻምፒዮና ከተጀመረ ሦስተኛ ቀኑን አስቆጥሯል:: በሻምፒዮናው የሚሳተፈው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ትናንት ወደ ሥፍራው አምርቷል:: ነገ ከሱዳን አቻው ጋር ከቀኑ ስምንት ሰዓት ጀምሮ ይጫወታል::

ናምቢያና ማላዊ ተጋባዥ የሆኑበት የሴካፋ እግር ኳስ ሻምፒዮና በምድብ አንድ ታንዛኒያ፣ ሩዋንዳ፣ ናምቢያና ጅቡቲ ሲገኙ፤ በምድብ ሁለት ደግሞ ኡጋንዳ፣ ብሩንዲ፣ ዛንዚባርና ሶማሊያ፤ እንዲሁም በምድብ ሦስት ሱዳን፣ ማላዊ፣ ኬንያና ኢትዮጵያ ተደልድለዋል:: የዞኑ እግር ኳስ ምንም እንኳ ደካማ ቢሆንም የኢትዮጵያ ምድብ ‹‹የሞት ምድብ›› ተብሎ እየተነገረለት ይገኛል::

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ከአፍሪካ ዋንጫ ከራቀ ሦስት አሥርት አስቆጥሯል:: በችግሩ ዙርያም ብዙ ተብሏል:: የአንድ ሙያተኛን ውጤት መመዘን ይቻል ዘንድ ጊዜ ሊሰጠው እንደሚገባ ቢታመንም፤ ለአጭር ጊዜም ቢሆን በውጭ አሠልጣኝ ተሞክሮ የተገኘ ውጤት የለም:: ከዚህ አንጻር በአሁኑ ወቅት በታንዛኒያ ዳሬሰላም የሚገኘው የኢትዮጵያ ቡድን ከምድቡ ‹‹ያልፋል፣ አያልፍም›› በሚል የስፖርት ቤተሰቡን ለሁለት የከፈለበት ሁኔታ ፈጥሯል::

በአዲስ አበባ ስታዲዮም ከ1960 ዓ.ም. ጀምሮ እግር ኳስን እንደተከታተሉ የሚናገሩት አቶ ደበበ እንግዳወርቅ እንዲህ ይላሉ፣ ‹‹በመናገር ለውጥ የሚገኝ ቢሆን ኖሮ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ዙርያ የተናገርነው ከበቂ በላይ ነው:: እንዳለመታደል ሆኖ ግን ከመጠላለፍ ባለፈ ምንም ሥራ መሥራት ባለመቻላችን ዛሬም እግር ኳስ ቀረ እያልን እግር ኳሱን እየገደልነው ነው፤›› ብሎ ከዚህ ውጭ ምንም ነገር ማለት እንደማይፈልግ ተናግሯል::

በአሠልጣኝ ሰውነት ቢሻው ዋና አሠልጣኝነት ወደ ታንዛኒያ ያመራው የኢትዮጵያ ቡድን በዋናነት የበረኛ ችግር እንዳለበትም የሚናገሩ አሉ:: እንደእነዚህ የእግር ኳስ ቤተሰቦች በአሁኑ ወቅት ከሁሉም በላይ የእግር ኳሱን ሌላው ችግር ሆኖ እየተጠቀሰ የሚገኘው የበረኞች

ጉዳይ ነው:: ለዚህም ወደ ታንዛኒያ ካመራው የአገሪቱ ብሔራዊ ቡድን በዋና በረኛነት የተጓዘው በደደቢት እግር ኳስ ክለብ ሦስተኛ በረኛ ሆኖ በማገልገል ላይ የሚገኘውን ተጫዋች ነው ይላሉ::

ይህንኑ በተመለከተ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የፌዴሬሽን ሰው እንደተናገሩት ከሆነ፣ ‹‹ፌዴሬሽኑም

ሆነ ክለቦች ከወዲሁ ካላሰቡበት ትልቅ ችግር እየሆነ ያለው የብሔራዊ ቡድን በረኛ ጉዳይ ነው:: በአሁኑ ወቅት በፕሪምየር ሊጉ ከስድስት ያላነሱ አፍሪካውያን በረኞች የክለቦቻችን ዋና በረኞች ናቸው፤›› ብለው፣ መጥቀስ ካስፈለገም የመብራት ኃይሉ ካሜሮናዊ ኢማኑኤል ሴቮ፣ የኢትዮጵያ ቡናው ኬንያዊ ዘካሪያስ ኤሊያንጐ፣

የቅዱስ ጊዮርጊሱ ኡጋንዳዊ ሮበርት ኦዳንካሪ፣ የደደቢቱ ደቡብ አፍሪካዊ ጃኮቭ ሞቴት መክሃሲና ሐረር ቢራም እንደዚሁ በውጭ በረኛ እየተጫወቱ መሆናቸውን ተናግረዋል::

ከዚህ አንጻር በቀጣይ የብሔራዊ ቡድን በረኛ ለማግኘት እንደሚያስቸግር፣ ያሉትም ቢሆን የመመረጥ ዕድሉን የሚያገኙት በጨዋታ ላይ ባልታዩበት ስለሚሆን የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ከወዲሁ ሊያስቡበት እንደሚገባም እኚሁ የፌዴሬሽን ሰው ይናገራሉ:: አቶ ደበበ በበኩላቸው፣ ‹‹ፕሮፌሽናሊዝም›› ያመጣው ነገር በመሆኑ ምን ማድረግ ይቻላል ሲሉ የጉዳዩን አሳሳቢነት ‹‹በእንቅርት ላይ . . .›› እንደሚባለው ዓይነት እግር ኳሱ በችግር ውስጥ እንዳለ ያስረዳሉ::

በአገሪቱ እንደ እግር ኳሱ ሁሉ በበረኛ ላይ የተሠራ ሥራ እንደሌለ አመላካች ስለመሆኑም የሚናገሩ አሉ:: እንደነዚህ ወገኖች ቀደም ሲል ጊላ ሚካኤል ተስፋማርያም (ቀይ ባሕር)፣ ጌታቸው አበበ (ዱላ) (ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ ወንድሙ ተክሉ (ካንጋሮ) መቻል፣ አፈወርቅ ጠናጋሻው (ወደፊት)፣ ለማ ክብረት (እርምጃችን)፣ ተካበ ዘውዴ (ድሬዳዋ ጨርቃ ጨርቅ)፣ ደሳለኝ ገብረጊዮርጊስ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ አሊ ረዲ (ኢትዮጵያ ቡና) በሌሎች በአገሪቱ ብሔራዊ ቡድን ታሪክ ያላቸው በረኞች እንዳልነበሩ ሁሉ በአሁኑ ወቅት የበረኛ ችግር እዚህ ደረጃ ላይ መገኘት እንደሚያሳዝናቸው ይናገራሉ::

ቅዱስ ጊዮርጊስ የአትሌቲክስ ክለቡን አፍርሻለሁ አለ

በደረጀ ጠገናው

የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማኅበር ከእግር ኳስ ቀጥሎ ሲያስተዳድረው የቆየውን የአትሌቲክስ ክለቡን ከዚህ ወር ጀምሮ ያፈረሰ መሆኑን አስታወቀ:: አትሌቶቹ በበኩላቸው የስፖርት ክለብ ውሳኔ ተገቢና ወቅታዊ ባለመሆኑ ጉዳዩን በሕግ አግባብ ለመጠየቅ እየተነጋገሩ መሆኑን ገልጸዋል::

በአገሪቱ የመጀመርያው ሕዝባዊ ክለብ እንደሆነ የሚነገርለት አንጋፋው የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማኅበር ከእግር ኳሱ ቀጥሎ በአገሪቱ የአትሌቲክስ ስፖርት ላይ ድርሻውን ለመወጣት ከ1996 ዓ.ም. ጀምሮ የአትሌቲክስ ክለብ አቋቁሞ ሲንቀሳቀስ መቆየቱ ይታወቃል::

ይሁን እንጂ በያዝነው ወር የክለቡ አትሌቶች የስፖርት ክለቡ ለውድድር ዓመቱ ከያዘው በጀት ውጭ አትሌቶች ያቀረቡት የደመወዝ ጭማሪ ክለቡ ካለው አቅም ጋር ሊጣጣም ባለመቻሉ የአትሌቲክስ ክለቡን ለማፍረስ መገደዱን የስፖርት ክለቡ የማርኬቲንግና ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዘካሪያስ ጌታቸው ለሪፖርተር ገልጸዋል::

የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማኅበር የአትሌቲክስ ክለቡን ካቋቋመበት ከ1996 ዓ.ም. ጀምሮ በስፖርት ክለቡ መቆየቱን የሚናገረውና በአንድ ሺሕ 500 ሜትር ለለንደን ኦሊምፒክ ሚኒማ አሟልቶ በዝግጅት ላይ የሚገኘው አትሌት መኰንን ገብረ መድኅንና ሌሎቹም አትሌቶች በበኩላቸው ክለቡ ከተቋቋመ

ጀምሮ ሲከፈላቸው የቆየው ወርኃዊ ክፍያ ከ500 እስከ 700 ብር በመሆኑ ከጊዜው የኑሮ ውድነት አንጻር መጠነኛ የደመወዝ ጭማሪ በጠየቁ ማግስት ክለቡ እንዲፈርስ መደረጉን ሰማን ይላሉ::

አትሌቶቹ ያቀረቡትን የደመወዝ ጭማሪ ለማሟላት ክለቡ አቅም የለኝም እያለ ነው ለሚለው አትሌት መኰንን፣ ‹‹አቅም የለኝም ማለትና ክለብ ማፍረስ የተለያዩ ነገሮች ናቸው:: በስፖርት ክለቡ ተይዘን በቆየንባቸው ዓመታት ውስጥ ሲከፈለን የቆየው ከ500 እስከ 700 ብር ድረስ ነው:: ብዙዎቻችን አትሌቶች ከክፍለ ሀገር የመጣን እንደመሆናችን መጠን ደግሞ ገንዘቡ ወጪያችንን እንኳ መሸፈን አልቻለም:: ከዚህ ችግር ተነስተን ነው የደመወዝ ጭማሪ እንዲደረግልን የጠየቅነው:: ከዚህ አንጻር የክለቡ ምክንያት እውነት የአቅም ችግር ከሆነ መነጋገርና ውሳኔ ላይ መድረስ ሲቻል ፈርሷል ማለት ምን ማለት ነው?›› ሲል ይጠይቃል::

ቀጣይ ውሳኔያቸውን በተመለከተ አትሌቶቹ የውድድር ዓመቱ የተጀመረ በመሆኑና በዚህ ወቅትም የትም መሔድ ስለማይችሉ ቢያንስ የበጀትና የውድድር ዓመቱ እስኪጠናቀቅ ድረስ ሊበተኑ እንደማይገባ ከስፖርት ክለቡ ጋር እንደተነጋገሩ፣ ሆኖም ግን የተሰጣቸው መልስ የክለቡ መፍረስ እውን ስለመሆኑ በመሆኑ ጉዳዩን በሕግ አግባብ ለመጠየቅ ከሕግ አዋቂ ጋር በመነጋገር ላይ መሆናቸውን ተናግሯል::

በሌላ በኩል የስፖርት ክለቡ ኅዳር 16 ቀን 2004 ዓ.ም. ሊያደርግ የነበረውን ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባዔ ወደ ኅዳር 23 ቀን 2004 ዓ.ም. የተላለፈ መሆኑም ታውቋል::

‹‹ውሳኔው ወቅታዊ አይደለም›› አትሌቶች

የኢትዮጵያ ቡና ዘካሪያስ ኤሊያንጐ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን

የቅዱስ ጊዮርጊስ ሮበርት ኦዳንካሪ

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ

የ2004 ዓ.ም. አንደኛው ዙር የመጀመርያው ሳምንት የውድድር ፕሮግራም

መብራት ኃይል - ሲዳማ ቡና በ18/03/2004፣በ10 ሰዓት በአዲስ አበባ ስታዲዮም

ኢትዮጵያ ባንክ - አዳማ ከነማ በ18/03/2004 በ12 ሰዓት በአዲስ አበባ ስታዲዮም

ድሬዳዋ ከነማ - ሙገር ሲሚንቶ በ17/03/2004 በ10 ሰዓት ድሬዳዋ

ኢትዮጵያ ቡና - ሐረር ቢራ በ17/03/2004 በ10 ሰዓት በአዲስ አበባ ስታዲዮም

ሐዋሳ ከነማ - አየር ኃይል በ17/03/2004 በ9 ሰዓት ሐዋሳ ላይ ሲጫወቱ

የቅዱስ ጊዮርጊስና የደደቢት እግር ኳስ ክለቦች ለብሔራዊ ቡድኑ ከአራት በላይ ተጫዋቾችን ያስመረጡ በመሆኑ በፌዴሬሽኑ መተዳደርያ ደንብ መሠረት የሚያርፉ ስለመሆኑ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የላከው የውድድር መርሐ ግብር ያስረዳል::

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 47 | እሑድ | ኅዳር 17 ቀን 2004 ክፍል-1

ስፖርት

Vegetable Advertisement

•Sweet Green Pepper and Hot Green Pepper is available with a good price, 12 birr per 1 kg.

•We can give delivery service from Debrezeit to Addis Ababa with a minimum quantity of 50 kg.

•For more information you can contact us:

Tel. 0911 86 49 890921 77 41 92

መነሻና መድረሻውን መስቀል አደባባይ በማድረግ ለ11ኛ ጊዜ ዛሬ በሚካሔደው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከ300 በላይ ከአውሮፓና ከተለያዩ አገሮች የመጡ የውጭ አገር ዜጐች እንደሚሳተፉ ሲታወቅ፣ ከአገር ውስጥ ከ36 ሺሕ በላይ ተሳታፊ እንደሚታደም ዝግጅት ክፍሉ አስታውቋል::

ዛሬ በሚከናወነው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የአገር ውስጥና በተለይም ከኬንያውያን ታዋቂ አትሌቶች መካከል ኒኮላስ ኪፕኬምየን እና ፔተር ለሙያን የመሳሰሉት ሲጠቀሱ ከአገር ውስጥ ያለፈው ዓመት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አሸናፊዎች አዝመራው በቀለና ሱሌ ኡታራን ጨምሮ ሌሎችም በርካታ ታዋቂ አትሌቶች ይሳተፋሉ ተብሏል::

ብዙ ኅብረተሰብን በማሳተፍ ከአፍሪካ በግንባር ቀደምትነት በሚጠቀሰው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ከገቡት የእንግሊዝ፣ የኖርዌይ፣ የአሜሪካ፣ የጃፓን፣ የስዊድንና የኔዘርላንድስ ዜጐች በዋናነት እንደሚጠቀሱ የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ አቶ ኤርምያስ አየለ ለሪፖርተር ገልጸዋል::

እንደዋና ሥራ አስኪያጁ ገለጻ፣ ከታዋቂ ኬንያውያን አትሌቶች

በተጨማሪም ወደ 20 የሚጠጉ ኬንያውያን ተማሪዎች በመድረኩ ይሳተፋሉ:: ‹‹ለልጆች እንሩጥ›› (Running for a Child) በሚል መሪ ቃል በዚህ ሳምንት እስከ አንድ ሚሊዮን የሚጠጋ ብርና በቀጣይም የተለያዩ ቻሪቲዎችን በማዘጋጀት እስከ አምስት ሚሊዮን ብር ገንዘብ ለማሰባሰብ ዕቅድ መያዙንም የዝግጅት ክፍሉ ጋዜጣዊ መግለጫ ይፋ አድርጓል::

በዘንድሮው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የሚሳተፉ ታዋቂ አትሌቶች ‹‹ኦልትራ›› የተሰኘ ዘመናዊ የርቀት መቆጣጠርያ መሣሪያ እንደሚጠቀሙም መግለጫው አክሏል::

በሌላ በኩል በዘንድሮው የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ተሳታፊ ለመሆን የሚያስችለው ትኬት ከጊዜ ገደቡ ቀደም ብሎ የተጠናቀቀ መሆኑን ተከትሎ በልዩ ትዕዛዝ ቲሸርት ታትሞ በገበያ ላይ እንደዋለ የሚናገሩ አሉ:: ይህንኑ በማስመልከት ዋና ሥራ አስኪያጁ ‹‹ብዙ ነገር እየተባለ ስለመሆኑ እንሰማለን:: ነገር ግን በተጨባጭ የደረስንበትና የተጨበጠ መረጃ አልደረሰንም፤›› ብለዋል:: ለአሸናፊ አትሌቶች እስከ 140 ሺሕ ብር እንደተዘጋጀም ተነግሯል::

የፌዴሬሽኑ ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ መልቀቂያ

ማስገባቱ ተሰማ

‹‹የማውቀው የሰብሳቢውን ብቻ ነው››አቶ አሸናፊ እጅጉ የፌዴሬሽኑ ጽ/ቤት ኃላፊ

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሥራ አስፈጻሚ አቅራቢነት በጠቅላላ ጉባዔ ፀድቆ ኃላፊነቱን ሲወጣ የቆየው የፌዴሬሽኑ ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ አባላት አንዳንዶቹ በራሳቸው ፈቃድ ለፌዴሬሽኑ የሥራ መልቀቂያ ደብዳቤ ማስገባታቸው ተሰማ:: ፌዴሬሽኑ በበኩሉ የደረሰኝ የመልቀቂያ ደብዳቤ የሰብሳቢው ብቻ መሆኑን ይገልጻል::

ቀድሞ የእግር ኳስ ዳኛ በነበሩትና በአሁኑ ወቅት በግል ሥራ ላይ ተሰማርተው በተደራቢነት በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ በመሆን በፌዴሬሽኑ ጠቅላላ ጉባዔ ኃላፊነት ተሰጥቷቸው የቆዩት አቶ ሰሎሞን ዓለምሰገድና ባልደረቦቻቸው በሚመሩት ተቋም ባለባቸው የሥራ ጫና የፌዴሬሽኑን ኃላፊነት ለመተው ባገባደድነው ሳምንት መጀመርያ የሥራ መልቀቂያ ማስገባታቸው ምንጮች ለሪፖርተር ገልጸዋል::

ጉዳዩን በማስመልከት በስልክ ያነጋገርናቸው አቶ ሰሎሞን ዓለምሰገድም መልቀቂያውን ለፌዴሬሽኑ አስገብተው መልስ እየጠበቁ መሆኑን አረጋግጠዋል:: በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አሸናፊ እጅጉ በበኩላቸው ‹‹የኮሚቴው ሰብሳቢ የሥራ መልቀቂያ ማስገባታቸው እውነት ነው የተቀሩትን በሚመለከት ግን መረጃው የለኝም፤›› ብለዋል::

ሰብሳቢው ያቀረቡት ምክንያት አለ ወይ? ለሚለው አቶ አሸናፊ፣ ‹‹ተደራራቢ የሥራ ጫና አለብኝ ብለው እንደሆነ፣ ነገር ግን ፌዴሬሽኑ ገና መልስ እንዳልሰጠ ተናግረዋል:: አቶ ሰሎሞንም ለመልቀቂያቸው በምክንያትነት ያቀረቡት የሥራ ጫና እንደሆነ አረጋግጠዋል::

ይህንኑ ለአንዳንድ ክለቦች ጥያቄ አቅርበን ማናቸውም ስለጉዳዩ የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ተናግረዋል:: ነገር ግን እየተባለ ያለው ነገር እውነት ከሆነ ኃላፊነታቸውን በለቀቁት ምትክ በእጩነት የሚቀርቡ ሰዎችን አስመልክቶ የክለቦች አስተያየትና ጥቆማ ቢታከለበት እንደሚሻል ክለቦቹ ይናገራሉ:: ምክንያቱም የሚሉት እነዚሁ ክለቦች፣ ሁሉ ነገር በፌዴሬሽኑ ይሁንታ ብቻ የሚጠናቀቅ ከሆነና ኃላፊነቱን የሚረከበው አካልም የሚመለከተው የሕግ ጉዳይም ስለሚሆን ብዙውን ነገር አስቸጋሪ ያደርገዋል ከሚል እሳቤ እንደሆነ ተናግረዋል::

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዛሬ ይካሔዳልከተለያዩ አገሮች ከ300 በላይ ተሳታፊዎች ይሮጣሉ

መግለጫው በተሰጠበት ወቅት

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 48 | እሑድ |ኅዳር 17 ቀን 2004ክፍል-1

ዲዛይንና ዝግጅት በሚዲያ ኮምዩኒኬሽን ሴንተር አሳታሚ የሚዲያና ኮምዩኒኬሽን ሴንተር አታሚ፡ ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ክ/ከተማ፡ አራዳ ቀበሌ፡ 17 የቤት ቁጥር፡ 984

+24+36 (108)