12
November, 2016 የኢትዮዽያ ኤምባሲ ስቶክሆልም ወርሀዊ ቡለቲን

November, 2016 - Ethiopian Embassy in the Nordic …ethemb.se/wp-content/uploads/2017/08/November-2016...አዲሱ የኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር 3. የኮንሱለር

Embed Size (px)

Citation preview

Page 1: November, 2016 - Ethiopian Embassy in the Nordic …ethemb.se/wp-content/uploads/2017/08/November-2016...አዲሱ የኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር 3. የኮንሱለር

November, 2016

የኢትዮዽያ ኤምባሲ

ስቶክሆልም

ወርሀዊ ቡለቲን

Page 2: November, 2016 - Ethiopian Embassy in the Nordic …ethemb.se/wp-content/uploads/2017/08/November-2016...አዲሱ የኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር 3. የኮንሱለር

Embassy of Ethiopia. Stockholm , Birger Jarisgatan 39, P.o.Box 10148 SE-100 55 Stockholm, Tel. +46812048500

E-mail: [email protected]

3

ማ ው ጫ ገ ጽ

መቅድም

1

4

7

7

1. የፖለቲካ አምድ ………………………………………

የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ዓመታዊ የፖሊሲ

ንግግር

2. የኢኮኖሚ አምድ ………………………

አዲሱ የኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር

3. የኮንሱለር አምድ …………………………

የሚሲዮኑ አገልግሎት አሰጣጥ

Page 3: November, 2016 - Ethiopian Embassy in the Nordic …ethemb.se/wp-content/uploads/2017/08/November-2016...አዲሱ የኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር 3. የኮንሱለር

Embassy of Ethiopia. Stockholm , Birger Jarisgatan 39, P.o.Box 10148 SE-100 55 Stockholm, Tel. +46812048500

E-mail: [email protected]

4

መ ቅ ድ ም

ኤምባሲያችን በአገራችን የሚከናወኑ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮችን በተመለከተ በኤምባሲው

ድህረ ገጽ እንዲሁም በማህበራዊ ሚዲያ (Facebook እና twitter) ለኢትዮዽያውያንና ትውልደ ኢትዮዽያውያን

እንዲደርስ ለማድረግ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ በአሁኑ ወቅት ይህንኑ የመረጃ አቅርቦታችንን ለማሳደግ እና

ኮሚኒቲያችንንም የበለጠ ለመድረስ የመጀመሪያውን የአማርኛ ወርሀዊ ቡለቲን አዘጋጅቷል፡፡ ይኸው የመጀመሪያ

ወርሀዊ ቡለቲን በአገራችን ወቅታዊ የፓለቲካ ሁኔታ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ እንቅስቃሴ እንዲሁም የአገልግሎት

አሰጣጣችን ላይ ያተኮረ መረጃዎችን ያካተተ ነው፡፡

በዚህ የህዳር ወር እትም በፖለቲካ አምድ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ መስከረም 30 ቀን 2009

ዓ.ም. ለሕዝብ ተወካዮችና ለፌዴሬሽን ምክር ቤቶች አምስተኛ ዘመን ሁለተኛ ዓመት የሥራ ዘመን የጋራ ጉባኤ ላይ

ያቀረቡትን የፖሊሲ ንግግር ቅኝትና በአገራችን በቅርቡ ለተከሰተው ሁኔታ መንስኤዎች እና በቀጣይነት ሊወሰዱ

የሚገባቸውን የሪፎርም እርምጃዎችን ለመዳሰስ ተሞክሯል፡፡ በኢኮኖሚ አምድም በቅርቡ በጠቅላይ ሚኒስትር

ኃይለማርያም ደሳለኝ እና በጅቡቲ ፕሬዚዳንት የተመረቀው አዲሱ የኢትዮ-ጅቡቲ የምድር ባቡር ለኢኮኖሚ ግንባታ

አዲስ ምእራፍ ከፋች የሚሉ ጽሁፎች ቀርበዋል፡፡ በተጨማሪም በኮንሱላር አምድ የሚሲዮኑ አገልግሎት አሰጣጥ

ከየት ወዴት በሚል ዳሰሳ የተደረገ ሲሆን፣ በቅርቡ በአገልግሎት አሰጣጣችን ላይ የተደረጉ ማሻሻያዎችን ለማሳየት

ተሞክሯል፡፡

ውድ አንባቢያን ለቀጣይ ዝግጅት ግብአት ይሆነን ዘንድ በመጽሄቱ ይዘትና ዝግጅት ላይ ያላችሁን ጥያቄም ሆነ

አስተያየት በኢሜይል አድራሻችን [email protected] እንድትልኩልን በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡ በማህበራዊ

ሚዲያችንም በfacebook: Embassy of Ethiopia, Sweden እና በtwitter account: Ethiopia in Sweden

@ETHinSweden እንዲሁም በድህረ-ገፃችን www.ethemb.se መከታተል የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

Page 4: November, 2016 - Ethiopian Embassy in the Nordic …ethemb.se/wp-content/uploads/2017/08/November-2016...አዲሱ የኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር 3. የኮንሱለር

1

Embassy of Ethiopia. Stockholm , Birger Jarisgatan 39, P.o.Box 10148 SE-100 55 Stockholm, Tel. +46812048500

E-mail: [email protected]

1

የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት አመታዊ የፖሊሲ ንግግር

ቅኝት

በኢፌዲሪ ህገመነግስት አንቀጽ 71 በተደነገገው መሰረት

ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ የህዝብ ተወካዮች እና

የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች አምስተኛው ዘመን ሁለተኛ

አመት የስራ ዘመን የጋራ ጉባኤ መስከረም 30 ቀን 2009

ዓ.ም ከፍተዋል᎓᎓

ክቡር የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት በምክር ቤቶቹ ጣምራ

ስብሰባ ባደረጉት የፖሊሲ ንግግር ኢትዮጵያን

ለማተራመስ የሚደረገውን ሙከራ መንግስትና ህዝብ

እንደሚፋለሙት፣ የወጣቶች፣ የሲቪል ሰርቪሱንና ዝቅተኛ

ገቢ ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚነት

ለማሳደግ መንግስት ተጨማሪ እርምጃዎችን

እንደሚወስድ፣ የፌዴራል መንግስቱ በአዲስ መልክ

እንደሚዋቀር እና የህዝብ ምክር ቤቶች የተለያዩ ድምጾች

የሚሰማባቸውና የሚፎካከሩባቸው መድረኮች እንዲሆኑ

ለማድረግ የምርጫ ህጉ እንደሚሻሻል አመልክተዋል᎓᎓

ላለፉት 25 አመታት አስተማማኝ ሠላም ተጎናጽፋ

በቆየችው አገራችን ባለፈው አመት በተለያዩ አካባቢዎች

ሁከትና ግጭት መቀስቀሱን፣ በሁከቱ የወጣቶችና የፀጥታ

አስከባሪዎች ህይወት ማለፉንና ቀላል የማይባል ንብረትም

መውደሙን፣እንዲሁም የዜጎች የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ

መስተጓጎሉንና ሰርተው ኑሮአቸውን ለማሸነፍ

የሚንቀሳቀሱ ዜጎች ለብዙ ፈተናዎች መዳረጋቸውን

ፕሬዚዳንቱ አብራርተዋል᎓᎓ በአንዳንድ የሀገሪቱ ክልሎች

ህገመንግስታዊ ስርአቱን በሀይል ለመናድ ሲካሄዱ የቆዩ

አፍራሽ እንቅስቃሴዎች እንደነበሩም ፕሬዚዳንቱ

ጠቁመዋል᎓᎓ በህዝቡ ዘንድ በተለይ በወጣቶች በኩል

የተነሱ ፍትሀዊ ጥያቄዎችን ተገን በማድረግ አፍራሽ

ሀይሎች ቅሬታን ወደ ሁከትና ጥፋት ለመቀየር

መረባረባቸውን፣ሀገሪቱ በዕድገት ጎዳና መገስገስ

በጀመረችበት በዚህ ወቅት የኒዮሊበራል አጀንዳቸውን

ሊጭኑብን የተዘጋጁ ሀይሎች ወደ ትርምስ እንድንገባ

አቅደው አገራችንን ለማተራመስ በስፋት እየተንቀሳቀሱ

መሆኑን አስታውቀዋል᎓᎓በተለይ ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ

ግድብ ግንባታ በመላ የአገራችን ህዝቦች ተሳትፎና በአገራዊ

አቅማችን በመተማመን መገንባት መጀመራችን

ያስቆጣቸው አገሮች ጽንፈኛ የዳያስፖራ ሀይሎች

ከቀሰቀሱት ነውጥ ጋር በመመጋገብ አገራችንን

ለማተራመስ በቀጥታ እየተረባረቡ እንደሚገኙ

አመልክተዋል᎓᎓ኦነግና ግንቦት ሰባት ከኤርትራ መንግስትና

Page 5: November, 2016 - Ethiopian Embassy in the Nordic …ethemb.se/wp-content/uploads/2017/08/November-2016...አዲሱ የኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር 3. የኮንሱለር

2

Embassy of Ethiopia. Stockholm , Birger Jarisgatan 39, P.o.Box 10148 SE-100 55 Stockholm, Tel. +46812048500

E-mail: [email protected]

2

ከግብጽ ተቋማት ጋር እጅና ጓንት በመሆን ባቀናበሩት

የጥፋት እንቅስቃሴ በርካታ አገራዊና የውጭ ባለሀብቶች

ኢንቨስትመንቶች ላይ ውድመት መፈጸማቸውን

አረጋግጠዋል᎓᎓ ድርጊቱ ከወጣቶች ፍትሀዊ ጥያቄዎች ጋር

አንዳችም ዝምድና የለውም ያሉት ፕሬዚዳንቱ መንግስት

ይህን የመሰለ ፀረ ሰላምና አፍራሽ እንቅስቃሴ ለመመከትና

ወንጀለኞችንም በህግ ተጠያቂ ለማድረግ እንደሚሰራ

አስታውቀዋል᎓᎓ ፕሬዚዳንቱ 100 ሚሊዮን ከሚገመተው

የአገሪቱ ህዝብ ግማሽ የሚሆነው ወጣት በመሆኑ

በህብረተሰባችን ውስጥ የሚካሄዱ ማንኛውም የልማት

ስራዎች የግድ ወጣት ተኮር ባህሪ ሊኖራቸው እንደሚገባ

ገልጸው መንግስት ከመቼውም ጊዜ በተለየ ለወጣቶች

የሀብትና የስራ ዕድል ፈጠራ ልዩ ትኩረት በመስጠት

በሁሉም የአገሪቱ ወረዳዎች የሚገኙ ወጣቶችን ተጠቃሚ

የሚያደርግ የወጣቶች ተንቀሳቃሽ ፈንድ በ10 ቢሊዮን ብር

በጀት እንደሚቋቋም አመልክተዋል᎓᎓ ከሶስተኛው አገራዊ

ምርጫ በኋላ መንግስት የወጣቶች የልማት ተጠቃሚነት

ፓኬጅ ቀርጾ በርካታ ስራዎችን ያከናወነና ወጣቶችን

ተጠቃሚ ያደረገ ቢሆንም አሁንም በገጠርና በከተማ

ለሚኖሩ ወጣቶች ህይወት መሻሻል አገልግሎት

የሚያገኝባቸው ተቋማት ከማስፋፋት ባለፈ የስራ ዕድል

ሊፈጠርለት ይገባል ብለዋል᎓᎓ ፈንዱ የወጣቶችን

ተጠቃሚነት በሚያረጋግጥ መልኩ ተግባራዊ እንዲሆን

የስራ ፈጠራ የሚያተኩርባቸው መስኮች ተለይተውና

ከወጣቶች ጋር ተመክሮባቸው ወደ ትግበራ እንደሚገባ

ጠቅሰው መንግስት በፈንዱ አጠቃቀምና በፕሮጀክት

ትግበራ ላይ ከወረዳ አመራሮችና ከወጣቶች ጋር

በመመካከር የአቅም ግንባታ ድጋፍ በመስጠት

የሚያስፈጽም መሆኑን አስታውቀዋል᎓᎓ ፕሬዚደንቱ

አያይዘውም የሲቪል ሰርቪሱን ጨምሮ ዝቅተኛ ገቢ

ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚነት ማሳደግ

የሚያስችሉ ተጨማሪ እርምጃዎች መንግስት

እንደሚወስድ፣ለዚህም የአገሪቱ ሲቪል ሰርቪስ ከኢኮኖሚ

ዕድገቱ ጋር ተመጋጋቢ በሆነ ደረጃ ተጠቃሚ እየሆነ

እንዲሄድ በየወቅቱ የዋጋ ግሽበትን ታሳቢ ያደረገ የደመወዝ

ማስተካከያ እንደሚደረግ አስታውቀዋል᎓᎓

ሌላው በፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ንግግር

ትኩረት የተሰጠው የፌዴራል መንግስቱን በአዲስ መልክና

ቅኝት ለማዋቀር ተግባራዊ እርምጃ እንደሚወሰድ፣

የመንግስትን ስልጣን ያላግባብ የመጠቀም ዝንባሌን

ለመግታት ብቃትና ቅንነት ያላቸውን በሀላፊነት ላይ

በማስቀመጥ የመንግስት የስራ አፈጻጸም በውጤት ብቻ

የሚመራ እንዲሆን የሚያስችል ስርአት እንደሚዘረጋ

አስታውቀዋል᎓᎓

ፕሬዚዳንቱ መንግስት በነደፈው መሰረታዊ የለውጥ

አቅጣጫ በተለይም ላለፉት 15 አመታት ፈጣን ዕድገት

መመዝገቡን ጠቅሰው በሁሉም መስክ የተጀመሩ መልካም

ስራዎች በማጠናከር አገሪቷን ከድህነት ለማውጣት

Page 6: November, 2016 - Ethiopian Embassy in the Nordic …ethemb.se/wp-content/uploads/2017/08/November-2016...አዲሱ የኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር 3. የኮንሱለር

3

Embassy of Ethiopia. Stockholm , Birger Jarisgatan 39, P.o.Box 10148 SE-100 55 Stockholm, Tel. +46812048500

E-mail: [email protected]

3

የሚደረገውን ጥረት ለማስቀጠል፣ የተመዘገቡ ድሎችን

በማስጠበቅ መልካም ጅምሮችን ዳር በማድረስ የህዝቡን

ተጠቃሚነት በስፋት ማሳካት እንደሚገባ አመልክተዋል᎓᎓

አያይዘውም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከዕድገት ጋር ተያይዘው

በመጡ ችግሮች እንዲሁም በየደረጃው የሚገኙ

የመንግስት አመራር አካላት በቅንነትና በታማኝነት ህዝብን

ከማገልገል ጉድለቶች የመነጩ መሆናቸውን ገልጸዋል᎓᎓

የመልካም አስተዳደር ችግሮችም ሆነ የህዝቡን

ተጠቃሚነት በተገቢው ደረጃ ያለማረጋገጥ ድክመት

ከእዚህ የሚመነጩ መሆናቸውን አስምረውበታል᎓᎓ ከዚህ

በመነሳት የመንግስትን ስልጣን ያለአግባብ የመጠቀም

ዝንባሌን የሚገታና በውጤት አልባነት ስልጣን ላይ

ተቀምጦ መቆየት የማይቻል መሆኑን የሚያረጋግጥ አዲስ

የመንግስት ምክር ቤት እንደሚደራጅ ተናግረዋል᎓᎓

መንግስት የተከሰቱ ችግሮችን በአስተማማኝ መልኩ

በመፍታት በሁሉም መስክ ሚዛኑን የጠበቀ ህገ

መንግስታዊ ስርአት የተከተለ ትግል መጠናከር

እንደሚገባው የሚያምን መሆኑንና ለዚህም ከቀጣዩ

ምርጫ በፊት የህዝብ ምክር ቤቶች የተለያዩ ድምጾች

የሚሰሙባቸውና የሚፎካከሩባቸው መድረኮች እንዲሆኑ

ለማድረግ በገዥው ፓርቲና በተቃዋሚ ፓርቲዎች መካከል

በሚደረግ ድርድር የምርጫ ህጉ እንደሚሻሻል

አስታውቀዋል᎓᎓አገሪቱ የምትመራበት የምርጫ ህግ በብዙ

ሀገራት የሚሰራበት ቢሆንም ከአገሪቷ ተጨባጭ ሁኔታ

በመነሳት የሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ድምጽ ሊሰማ

የሚችልበትን አሰራር መፍጠር አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱን

አብራርተዋል᎓᎓

በዴሞክራሲያዊ መንገድ በተካሄደ ምርጫ የህዝብ ድምጽ

ያስገኘው ውጤት መሆኑ ባያጠያይቅም በአገሪቷ ወሳኝ

የስልጣን አካል በሆነው ምክር ቤት የማይወከሉ ድምጾች

እንዲኖሩ በማድረጉ ከገዥው ፓርቲ በተለዩ ፓርቲዎች

የሚወከል ጥቅምና ፍላጎት ያላቸው ማህበረሰቦችን

የሚወክሉ ፓርቲዎች በምክር ቤቶች የመሳተፍ ዕድል

ሳያገኙ ቀርተዋል ብለዋል᎓᎓ በመሆኑም ዲሞክራሲያዊ

መንገዶችን በማስፋትና በህግ ማዕቀፍ በተደገፈ አኳሀን

የአብላጫ ድምጽ እና የተመጣጣኝ ውክልና ስርአቶችን

ያጣመረ እንዲሆን የሚያስችል የምርጫ ህግ ማሻሻያ

የሚደረግ መሆኑን አመልክተዋል᎓᎓

የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ ለሀገራችን የህልውና ጉዳይ

በመሆኑ ከህዝብ ለቀረቡ ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት፣

የህዝቡን ቀጥተኛ የፖለቲካ ተሳትፎ በማጎልበት የመድብለ

ፓርቲ ስርአትን ማጠናከር፣መልካም አስተዳደርን ማስፈን

እና የተጀመረውን የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግር

ማስቀጠል የአስፈጻሚው አካል የትኩረት አቅጣጫ መሆኑ

ተመልክቷል᎓᎓ የፕሬዚዳንቱን ንግግር ተከትሎም

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ

በአዲስ መልክ ያደራጁትን ካቢኔ ለህዝብ ተወካዮች ምክር

ቤት አቅርበው ማስጸደቃቸው ይታወቃል᎓᎓

Page 7: November, 2016 - Ethiopian Embassy in the Nordic …ethemb.se/wp-content/uploads/2017/08/November-2016...አዲሱ የኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር 3. የኮንሱለር

4

Embassy of Ethiopia. Stockholm , Birger Jarisgatan 39, P.o.Box 10148 SE-100 55 Stockholm, Tel. +46812048500

E-mail: [email protected]

4

አዲሱ የኢትዮ-ጂቡቲ ምድር ባቡር ለኢኮኖሚ

ግንባታ አዲስ ምዕራፍ ከፋች

አገራችን ኢትዮጵያ ካለፉት አስራ አምስት ዓመታት ወዲህ

ባለሁለት አሀዝ የኢኮኖሚ ዕድገት እያስመዘገበች

ትገኛለች። አገራችን ያስመዘገበችው ይህ ፈጣን እድገት

ለበርካታ የአገራችን ዜጐች የስራ እድል በመፍጠር

የዜጐቻችን የእለት ተእለት ህይወት ከመለወጡም ባሻገር

በአገራችን ኢኮኖሚያዊ ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች ላይ

አወንታዊ ተጽእኖ አሳድሯል፡፡ ከዚህም ባሻጋር አገሪቱ ወደ

ውጪ የምትልካቸው ምርቶች (export goods) እና ወደ

አገር ውስጥ የምታስገባቸው ምርቶች (importe goods)

በከፍተኛ ደረጃ እንዲጨምር አድርጓል። ሆኖም የወጪ

ምርቶቹን ወደ ወደብ ለማጓጓዝም ሆነ ገቢ ምርቶችን ወደ

አገር ውስጥ ለማስገባት ከትራንስፖርት እና ሎጅስቲክ ጋር

ተያይዞ የተፈጠረው ፈታኝ ሁኔታ በቀላሉ የሚታይ

አይደለም። በተለይ ገቢ ምርቶች በወቅቱ ከወደብ ላይ

ስለማይነሱ የኮንቴይነሮች የማቆያ ክፍያ (storage fee)

መጨመር፣ እንዲሁም ምርቶቹን ወደ አገር ውስጥ

ለማጓጓዝ ረዥም ጊዜ የሚፈጅ በመሆኑ የምርቶቹ ዋጋ

በከፍተኛ መጠን እንዲጨምር ከማድረጉም ባሻገር

በኢኮኖሚው ላይ የሚያሳድረው አሉታዊ ተፅዕኖ ቀላል

አይሆንም። መንግስትም እነዚህን ችግሮች ለመቅረፍ እና

የምርት ግብአቶችንና ምርቶችን በአነስተኛ ዋጋ እና በአጭር

ጊዜ በብዛት ለማጓጓዝ እንዲቻል የመጓጓዣ አቅርቦቱን

ዘመናዊና ፈጣን ለማድረግ የባቡር መስመር ግንባታው

የሀገራችንን የልማት አጀንዳ ቀዳሚ ትኩረት እንዲሆን

ተደርጓል፡፡

እ.ኤ.አ ኦክቶበር 5 ቀን 2016 በክቡር ጠ/ሚኒስትራችን አቶ

ኃይለማርያም ደሳለኝ ተመርቆ ስራውን በይፋ የጀመረው

አዲሱ የኢትዮ ጂቡቲ የምድር ባቡር ፕሮጀክት መስመር

ጉልህ ድርሻ ይይዛል፡፡

አዲሱ የባቡር መንገድ ከመቶ ዓመት በላይ አገልግሎት

ሲሰጥ ከነበረው የኢትዮ ጂቡቲ ምድር ባቡር (Chemin

de fer Ethiopie/ CDE) መስመር ትይዩ የተዘረጋ ነው።

ነባሩ የኢትዮ ጂቡቲ ምድር ባቡር በአፄ ምኒሊክ እና

በስዊዙ አማካሪያቸው Alfred Ilg ሀሳብ የተጠነሰሰ ሲሆን

ከጂቡቲ እስከ ድሬዳዋ ድረስ ያለው መስመር እ.ኤ.አ

ከ1897 እስከ 1901 ተገንብቷል። በወቅቱ የጂቡቲ ቀኝ ገዢ

ከነበረችው ፈረንሳይ ጋር በ1908 በተደረገው ስምምነት

ለፕሮጀክቱ የሚያስፈልገው ፋይናንስ በመገኘቱ ከድሬዳዋ

- አዲስ አባባ ድረስ የመስመር ዝርጋታ ሥራው እ.ኤ.አ

Page 8: November, 2016 - Ethiopian Embassy in the Nordic …ethemb.se/wp-content/uploads/2017/08/November-2016...አዲሱ የኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር 3. የኮንሱለር

5

Embassy of Ethiopia. Stockholm , Birger Jarisgatan 39, P.o.Box 10148 SE-100 55 Stockholm, Tel. +46812048500

E-mail: [email protected]

5

በ1917 ተጠናቋል። ነባሩ የኢትዮ ጂቡቲ ምድር ባቡር

ለአንድ ክፍለ ዘመን ያህል ለሁለቱ አገራት የትራንስፖርት

አገልግሎት በመስጠት ለኢኮኖሚ ዕድገት አስተዋጽኦ

ከማበርከቱ በላይ የባቡር መስመሩን ተከትሎ ያሉ ከተሞች

የንግድ እንቅስቃሴ እንዲያድግ እንዳደረገ ይታመናል።

ሆኖም የባቡር መስመሩ ከአንድ ክፍለ ዘመን በላይ

በማገልገሉ፣ ለጥገና የሚውሉ ወጪዎች ከስራ ማስኬጃ

ወጪው/operation cost መብለጥ እንዲሁም ዘመናዊ

ከሆኑ የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡሶችና የጭነት ማመላለሻ

ተሽከርካሪዎች ጋር በተወዳዳሪነት ለመስራት ባለመቻሉ

ምክንያት በኢትዮጵያና በጂቡቲ መንግስታት ውሳኔ

አገልግሎቱ እ.ኤ.አ በ2008 ዓ.ም እንዲቆም ተደርጓል።

በአሁኑ ወቅት ዘመኑ የደረሰበትን ፈጣንና ዘመናዊ የባቡር

ትራንስፖርት ለመገንባት ይቻል ዘንድ በኢትዮጵያ እና

በጂቡቲ መንግስታት በተደረሰ መግባባት እንዲሁም

ከቻይና EXIM ባንክ በተገኘ የ3 ቢሊዮን ዶላር ብድር አዲስ

የኢትዮ ጂቡቲ የምድር ባቡር (electrified standard

gauge railway) ለመገንባት እ.ኤ.አ በ2011 ስምምነት ላይ

ተደርሷል።

የአገራችንን የተለያዩ ከተሞችን ለማገናኘት እና ከተሞቹንም

ከተለያዩ የወደብ በሮች ጋር ለማስተሳሰር በአንደኛው

የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ እና በሁለተኛው

የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የባቡር መሰረተ ልማት

ዝርጋታ ቅድሚያ የተሰጠው የልማት ፕሮግራም ነው።

በሁለተኛው የአድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን

እየተገነቡ ያሉ የምድር ባቡር ፕሮጀክት ሲጠናቀቁ አገራችን

ወደ ውጭ የምትልካቸው እና ወደ አገር ውስጥ

የምታስገባቸው ምርቶች ዙሪያ ሲያጋጥም የነበረውን

ከትራንስፖርት ጋር የተያያዘ ችግር በመቅረፍ ለኢኮኖሚው

ዕድገት ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ይጠበቃል።

የኢትዮ ጂቡቲ የባቡር መስመር 758 ኪ.ሜ ርዝመት ያለው

ሲሆን ከዚህ ውስጥ በኢትዮ ጂቡቲ ድንበር ላይ

ከምትገኘው ደወሌ እስከ ጂቡቲ 100 ኪ.ሜ ይሸፍናል።

ከአዲስ አበባ እስከ ጂቡቲ በተዘረጋው መስመር ላይ 16

የባቡር ጣቢያዎች ያሉ ሲሆን የፕሮጀክቱ የሙከራ ስራ

ከተጠናቀቀ ስድስት ወራት በኃላ ምድር ባቡሩ በሙሉ

አቅሙ ስራ ሲጀምር ፍጥነታቸው 120 ኪ.ሜ በሰዓት የሆኑ

በኤሌክትሪክ ኃይል የሚሰሩ ባቡሮች አገልግሎት መስጠት

ይጀምራሉ። ይህም ቀደም ሲል ከ7 እስከ 10 ቀናት ይፈጅ

የነበረውን ጉዞ በ12 ሰዓታት ያሳጥረዋል። ፕሮጀክቱ 3.4

ቢሊዮን ዶላር የወጣበት ሲሆን ግንባታው China

Railway Group እና China Civil Engineering and

Construction በተባሉ ሁለት የቻይና ኩባንያዎች የካቲት

2004 ዓ.ም ተጀምሮ መስከረም 25 ቀን 2009 ዓ.ም

ለምረቃ በቅቷል።

Page 9: November, 2016 - Ethiopian Embassy in the Nordic …ethemb.se/wp-content/uploads/2017/08/November-2016...አዲሱ የኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር 3. የኮንሱለር

6

Embassy of Ethiopia. Stockholm , Birger Jarisgatan 39, P.o.Box 10148 SE-100 55 Stockholm, Tel. +46812048500

E-mail: [email protected]

6

የምረቃ ስነስርዓቱ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም

ደሳለኝ፣ የጂቡቲ ፕሬዚዳንት እስማኤል ኡመር ጌሌ፣

በአገራችን ጉብኝት ሲያደርጉ የነበሩት የቶጎ ፕሬዚዳንት

ፋውራ ናሲንጌና ሌሎች የመንግስት ባለስልጣናት

ተገኝተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ኃ/ማርያም ደሳለኝ

በምርቃት ስነስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር የባቡር

መስመሩ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሪክ ኃይል የሚሰራ

በመሆኑ አገሪቷ አረንጓዴ ኢኮኖሚን ለመገንባት

የምታደርገውን ጥረት የሚደግፍ መሆኑን፣ ፕሮጀክቱ

አገሪቷ የተያያዘችውን የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ እድገት

ለማፋጠን የሚኖረው አገራዊ ፋይዳ ጉልህ መሆኑንና

የባቡር መስመሩን ተከትለው የሚገነቡት የኢንዱስትሪ

ፓርኮች ለበርካታ ዜጎች የስራ ዕድል የሚፈጠሩ

መሆናቸውን እና ፕሮጀክቱ በኢትዮ ጂቡቲ መካከል

ያለውን ታሪካዊ ግንኙነት ከማበልፀግ ባለፈ የአገራቱን

የኢኮኖሚ ትስስር ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር መሆኑን

ጠቅሰዋል። በማያያዝም የባቡር መስመር ግንባታ ከፍተኛ

ፋይናንስና ቴክኖሎጂ የሚጠይቅ፣ ከብሄራዊ የልማት

ስትራቴጂ ጋር ተሳስሮ የሚፈፀምና የአመራሩን የማስፈፀም

ብቃት የሚጠይቅ መሆኑን ገልፀዋል።

የጂቡቲው ፕሬዚዳንት እስማኤል ኡማር ጌሌ በበኩላቸው

የባቡር መስመር ግንባታው የሁለቱን አገራት ህዝቦች

ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መስተጋብር የበለጠ እንዲጠናከር

ያደርጋል ብለዋል። ፕሮጀክቱ የአፍሪካ ህብረት በአጀንዳ

2063 አህጉሪቷን በመሰረተ ልማት ለማስተሳሰር በያዘው

የምዕራብና ምስራቅ አፍሪካ የባቡር ኔትዎርክ ዕቅድ ውስጥ

አንዱ መሆኑን ጠቁመው ፕሮጀክቱ የሁለቱም አገራት

ህዝቦች የጋራ ንብረት በመሆኑ ሁሉም ሊጠብቀው

እንደሚገባ ገልጸዋል።

የአዲሱ ምድር ባቡር ቴክኒካዊ ሥራዎች በቻይናውያን

ተቆጣጣሪዎች፣ ቴክኒሻኖችና የጣቢያ አስተባባሪዎች

የሚመራ ሲሆን በአምስት አመታት ጊዜ ውስጥ

በኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች የሚተኩ ይሆናል። በሂደት

ቻይናውያንን የሚተኩ ኢትዮጵያውያን ስልጠና እየወሰዱ

ሲሆን ይህም በዘርፉ ለሚደረገው የቴክኖሎጂ ሽግግር

ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ይጠበቃል። ከየብስ

ትራንስፖርት ጋር ሲነጻጸር የባቡር ትራንስፖርት አነስተኛ

ዋጋ የሚያስከፍል በመሆኑ ፍሰትን በመጨመር ለኢኮኖሚ

ዕድገት አይነተኛ ሚና ይኖረዋል።

አዲሱ የኢትዮ-ጂቡቲ ምድር ባቡር በአገራችን ገቢና ወጪ

ምርቶች በወደብ ላይ የሚቆዩበትን ጊዜ በማሳጠር ለወደብ

Page 10: November, 2016 - Ethiopian Embassy in the Nordic …ethemb.se/wp-content/uploads/2017/08/November-2016...አዲሱ የኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር 3. የኮንሱለር

7

Embassy of Ethiopia. Stockholm , Birger Jarisgatan 39, P.o.Box 10148 SE-100 55 Stockholm, Tel. +46812048500

E-mail: [email protected]

7

አገልግሎት ክፍያ ይወጣ የነበረውን ወጪ በመቀነስ

ከፍተኛ የሆነ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ይኖረዋል። ፕሮጀክቱ

የ6 ወራት የሙከራ ጊዜ ተጠናቆ ተሳፋሪዎችና ጭነት

የማጓጓዝ አገልግሎቱን ሙሉ በሙሉ ሲጀምር የባቡር

መስመሩን ተከትለው የሰፈሩ ከተሞች ኢኮኖሚ እንዲነቃቃ

ከማድረጉም በላይ ለንግድና ኢንቨስትመንት የበለጠ አመቺ

ያደርጋቸዋል። ፕሮጀክቱ ከሚኖረው ኢኮኖሚያዊ

ጠቀሜታ ባሻገር ከታዳሽ ሀይል የሚመነጭ የኤሌክትሪክ

ሃይል የሚጠቀም በመሆኑ ለአካባቢ ተስማሚ

(environmental friendly) ያደርገዋል። ይህም አገራችን

ለነደፈችው ለአካባቢ የማይበገር እረጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ

ስትራቴጂን ለመተግበር አይነተኛ ሚና ይኖረዋል።

የስቶክሆልም የኢትዮዽያ ኤምባሲ

አገልግሎት አሰጣጥ ሂደት ከየት ወዴት!

በስዊድን ስቶክሆልም የሚገኘው የኢትዮዽያ ኤምባሲ

ከተከፈተበት ጊዜ ጀምሮ በስዊድንና በሌሎች

የኖርዲክ አገሮች ለሚኖሩ ኢትዮዽያውያን፣ ትውልደ

ኢትዮዽያውያንና የውጭ አገር ዜጐች የተለያዩ

የቆንስላ አገልግሎቶችን ማለትም የቪዛ፣ የፓስፖርት ፣

የትውልድ ኢትዮዽያዊ መታወቂያ ካርድ፣ የሰነድ

ማረጋገጥ፣ የውክልና እና ሌሎች የተለያዩ

አገልግሎቶች እየሰጠ የቆየ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ኤምባሲው የሚሰጠውን አገልግሎት ለተገልጋዮች

ፈጣንና ምቹ ለማድረግ በየጊዜው ከተገልጋዮች

የሚቀርቡ ቅሬታዎችን እና በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ

የሚያጋጥሙትን ክፍተቶች በመፈተሽ የተለያዩ

የማስተካከያ እርምጃዎችን ሲወስድ ቆይቷል፡፡

ከተወሰዱት እርምጃዎች መካከል ቀደም ሲል ለግማሽ

ቀን ብቻ ሲሰጥ የነበረውን የቆንስላ አገልግሎት

በርካታ ተገልጋዮች ካላቸው ውስን ጊዜ አንፃር

በተፈለገው ጊዜ ተገቢውን አገልግሎት ማግኘት

እንዲችሉ ሳምንቱን ሙሉ (ከአርብ በስተቀር) ሙሉ

ቀን እስከ 15:30/3:30 pm ድረስ አገልግሎት

እንዲሰጥ አድርጓል፡፡ እንዲሁም ከዚህ ቀደም በስልክ

የአገልግሎት መረጃ ማግኘት የሚቻለው ለ2 ሁለት

ሰአታት ብቻ የነበረ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ተገልጋዮች

ባመቻቸው ሰዓት ስልክ በመደወል የፈለጉትን መረጃ

ማግኘት እንዲችሉ ተደርጓል፡፡ የፓስፖርት እና

የትውልድ ኢትዮዽያዊ መታወቂያ ካርድ ለማውጣት

የሚወስደው ጊዜ ረጅም ከመሆኑ ጋር ተያይዞ

Page 11: November, 2016 - Ethiopian Embassy in the Nordic …ethemb.se/wp-content/uploads/2017/08/November-2016...አዲሱ የኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር 3. የኮንሱለር

8

Embassy of Ethiopia. Stockholm , Birger Jarisgatan 39, P.o.Box 10148 SE-100 55 Stockholm, Tel. +46812048500

E-mail: [email protected]

8

በተገልጋዮች ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታን ፈጥሮ እንደነበር

የሚታወቅ ነው፡፡ ሆኖም በአሁኑ ወቅት ምንም

እንኳን የመዘግየት ችግሩ ሙሉ በሙሉ ተቀርፏል

ባይባልም በሁለት ሳምንት አንድ ጊዜ ለሚመለከተው

መ/ቤት ሲላክ የነበረውን አሰራር በማሻሻል በየሳምንቱ

በልዩ ፓውች /DHL/ ለሚመለከተው አካል በመላክ

ከዚህ ቀደም ከነበረው ባጠረ ጊዜ ማስተናገድ

ተችሏል፡፡

በተጨማሪም ኤምባሲው ስለሚሰጣቸው

አገልግሎቶች ግልጽ የሆነ መረጃ ለተገልጋዮች ተደራሽ

ከማድረግ አንፃር ሲታይ የኤምባሲው ድረ ገጽ ላይ

በየጊዜው በመጫን በቀላሉ መረጃዎችን እንዲያገኙ

መደረጉ በተለይም በኤምባሲው የሚሰጡ ልዩ ልዩ

የአገልግሎት አይነቶች፣ አገልግሎቶች የሚሰጡበት

ስታንዳርድ እና አገልግሎቱን ለማግኘት መሟላት

ያለበት ቅድመ ሁኔታ ያካተተ የዜጎች/አገልግሎት

ቻርተር በማዘጋጀትና ተገልጋዮች እንዲያውቁት

በማድረግ ቀልጣፋና ፍትሀዊ አገልግሎት እየተሰጠ

ይገኛል፡፡ ተገልጋዮችም ወደ ኤምባሲው

በሚመጡበት ጊዜ በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ በነፃነት

ያላቸውን ሀሳብ ወይም ቅሬታ እንዲያቀርቡ

የአስተያየት መስጫ ሳጥን የተዘጋጀ ሲሆን፣

ከተገልጋዮች የተሰጡ አስተያየቶች የአገልግሎት

አሰጣጡን ለማሻሻልና የበለጠ ቀልጣፋ ለማድረግ

የበኩሉን አስተዋጽኦ አበርክቷል ማለት ይቻላል፡፡

ኤምባሲያችንም በቅርቡ በዘረጋው አዲስ አሰራር

እ.ኤ.አ. ከኦከቶበር 2016 ጀምሮ የቪዛ አገልግሎት

ጥያቄ ሙሉ በሙሉ በፖስታ እንዲስተናገድ ተደርጓል፡

፡ አዲሱ የቪዛ አገልግሎት አሰጣጥ ሥራ ላይ ከመዋሉ

በፊት ለሁለት ወራት የማስተዋወቅ ሥራ በመስራት

ተገልጋዮች በቂ ግንዛቤ እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡ አዲሱ

አሰራር በአካል በመምጣት ይባክን የነበረውን ጊዜ እና

አላስፈላጊ ወጪን ያስቀረ በመሆኑ ተገልጋዮች ባሉበት

ሁነው እየተስተናገዱ ይገኛሉ፡፡

በመጨረሻም ኤምባሲው የተገልጋዮች እርካታ ከጊዜ

ወደ ጊዜ እየጨመረ እንዲመጣ በአገልግሎት አሰጣጥ

ላይ የሚያጋጥሙ ማነቆዎችን በየጊዜው በመለየት እና

በመፈተሽ ማነቆዎቹ እንዲፈቱ ከሚመለከታቸው

የመንግስት አካላት ጋር በጋራ በመሆን የጀመረውን

ስራ አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡ ኤምባሲው

አገልግሎት አሰጣጡን በሚመለከት ከተገልጋዮች

የሚቀርቡ አስተያየቶችን ተቀብሎ ለማስተናገድ

ምንጊዜም ዝግጁ መሆኑን እየገለጽን፣ በኢሜል

አድራሻችን [email protected] ወይም በስልክ

ቁጥራችን +46812048500 አስተያየታችሁን

ልትሰጡን የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡

Page 12: November, 2016 - Ethiopian Embassy in the Nordic …ethemb.se/wp-content/uploads/2017/08/November-2016...አዲሱ የኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር 3. የኮንሱለር

9

Embassy of Ethiopia. Stockholm , Birger Jarisgatan 39, P.o.Box 10148 SE-100 55 Stockholm, Tel. +46812048500

E-mail: [email protected]

9