24
ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 160 ቅዳሜ መጋቢት 17 2003 አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 160 ቅዳሜ መጋቢት 17 2003 በሊቢያ

awramba 160

Embed Size (px)

Citation preview

Page 1: awramba 160

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 160 ቅዳሜ መጋቢት 17 2003

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 160 ቅዳሜ መጋቢት 17 2003

በሊቢያ

Page 2: awramba 160

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 160 ቅዳሜ መጋቢት 17 2003

45% . . . !

ር ዕ ሰ አ ንቀፅ

T’@Í=”Ó ›?Ç=}` Ç©ƒ ŸuÅ

ª“ ›²ÒÏõì<U TV

(›É^h ¾” ¡/Ÿ kuK? 03/04 ¾u?.l 1540)

U/ª“ ›²ÒЋ Ó³¨< KÑW¨<wgƒ �Â

Ÿõ}— ›²ÒÏ ›u?M ¯KT¾G<

›²ÒϨc”cÑÉ Ñ/Ÿ=Ç”

Ÿõ}— ]þ`}a‹

›?MÁe Ñw\c<^õ›?M Ó`T

¯UÅ™‹ ›uu „L

cKV” VÑeƒ°Óeƒ ¨”ÉS<

iÁß“ Te�¨mÁ }hK cÃñ}hK ¨ÇÏ

¢Uú¨<}` îG<õ SpÅe õeN

Ó^ò¡e ›?Ç=}` ’w¿ Seõ”

(0911 18 09 33)E-Mail:[email protected]

¾´Óσ ¡õK< eM¡eM¡:- ®911 62 92 78 ®911 62 92 82 0911 15 62 48

þ.X.l [email protected]://www.awramba.com

›d�T>¨<ብሉ ኤርዝ ጀነራል ቢዝነስ

ኃላ/የተ/የግል/ማህበር

ማን ምን አ ለ

2

45 በመቶ የሚለውን አሃዝ ሲመለከቱ የተለመደው በተጨባጭ የማይታይ የኢኮኖሚ ዕድገት አዲስ መግለጫ ሊመስልዎት ይችላል፡፡ አይደለም፡፡ የተለመደው የዋጋ ጭማሪ እንጂ፡፡ ይህ አሃዝ ዕድገትን ሳይሆን ስረ ብዙ የቁልቁለት ጉዞ መባቻን ያመለክታል፡፡ ጭማሪው ቀድሞውኑ እጅግ ፈታኝ በሆኑ ጫናዎች ተከበው ባሉት ጋዜጦች የሕትመት ዋጋ ላይ መሆኑ ደግሞ የበለጠ አስደንጋጭ ያደርገዋል፡፡

የ45% አሃዛዊ መግለጫው ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት በጋዜጦች ላይ የጨመረውን የጋዜጣ ሕትመት ዋጋ አስመልክቶ ለደንበኞቹ በላከው ደብዳቤ ላይ ያስቀመጠው መግለጫ ነው፡፡ በተለይ እጅግ በፈታኝ ሁኔታ ላይ ለነበረው የግል ፕሬስ የመንቀሳቀሻ ዓለም ራሱን እንዲገድል በማስገደድ ግብአተ መሬቱን የማስፈፀሚያ ደወል ሆኖ አግኝተነዋል፡፡ ኃሳብን መግደል፣ ዴሞክራሲን መግደል አይገባም - አይቻልም!

ለዋጋ ጭማሪው የጉምሩክ ቀረጥን ጨምሮ አንዳንድ ሰበቦች ተዘርዝረዋል፡፡ ዓለም አንድ መንደር በሆነችበት የዘመን ምዕራፍ ላይ በመሆናችን፣ የተለያዩ የመረጃ መረቦችን መፈተሻችን አልቀርም፡፡ ስንፈትሽ ደግሞ በዚህ ደረጃ የዋጋ ጫና መከመር የሚያስፈልግበትን ተጨባጭ ሁኔታ ልናገኝ አልቻልንም፡፡ ዘርፉም ቢሆን ልዩ ድጋፍ የሚያስፈልገው እንጂ ሥልታዊ ጫናዎችን ፈጥሮ በራሱ ጊዜ ህልውናውን እንዲያጠፋ የሚደረግበት አይደለም፡፡ ሊሆንም አይገባም!

የኢፌዴሪ ሕገመንግስት ዴሞክራሲያዊ መብቶችን አስመልክቶ ድንጋጌውን ባሰፈረባቸው የአንቀጽ 29 ሃሳቦችም ሆነ የመገናኛ ብዙኃንና የመረጃ ነጻነት አዋጁ ለዚህ ዓይነቱ ሥልታዊ ጥቃት በር አይከፍቱም፡፡ መብቶች በሕግ ደረጃ በመደንገጋቸው ብቻ ተጠቃሚው ተጎናጽፏቸዋል ማለት አይደለም፡፡ ከተለያየ አቅጣጫ ድንጋጌዎቹን የሚያጠናክር አሰራር መኖር አለበት፡፡ መገለጫው ተግባር

እና ተግባር ብቻ ነው፡፡የብርሃንና ሰላም ማተሚያ

ድርጅት መግለጫ ፍፁም ድንገተኛ ብቻ አይደለም፡፡ ከጀርባው ፍፁም ረቂቅ በሆነ ሥልት ሀሳብን በነፃ በመግለፅ መብት ላይ የተመዘዘ ሰይፍ አለ ብለን እንድናምን የሚያስገድደን ነው፡፡ ለዚህም ነው ሰይፉ ወደ ሰገባው ካልገባ የሚያጠፋው የነገይቱን ሀገራችንን ተስፋና የዴሞክራሲ ሥርዓት ምሶሶውን ነው ስንል በአፅንኦት የምናሳስበው፡፡ ሌላም ማንሳት የምንፈልገው ነጥብ አለ፡፡

ምንም እንኳ በሀገራችን የሕትመት ዘርፍ ያለው ተጨባጭ እውነታ እጅግ አሳሳቢ ቢሆንም፣ በመንግስት በኩል ይህን ሕጸጽ ለመቅረፍ ከመጣር ይልቅ ከድጡ ወደማጡ ዓይነት አካሄድ ይስተዋልበታል፡፡ ጥናታዊ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት፣ ዕለታዊ የጋዜጦች ስርጭት አንድ ጋዜጣ ለ1400 ያህል ሰዎች ነው፡፡ ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ሰይፍ ተመዞበታል፣ በአስቸኳይ ወደሰገባው

ይመለስ!!እንዲህም ሆኖ ግን አካሄዱ

ለብዙ ሚሊዮኖች ምንም የሚሆንበት አቅጣጫ መሆኑን ለማስተዋል የተለየ ግንዛቤ አይጠይቅም፡፡ በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ሕዝብ ካሉበት ዘርፈ ብዙ ችግሮች አንፃር እስካሁን በነበረው የጋዜጦች ዋጋ እየከፈለ የሚያነበው አቅሙ ፈቅዶ እንዳልሆነ እናውቃለን፤ ይታወቃል፡፡ 45 በመቶ ጭማሪ ማለት ደግሞ እስካሁን በሚገዛበት ዋጋ ላይ ግማሽ ያህል መጨመር ማለት ነው፡፡

አዎን! ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ሰይፍ ተመዞበታል፡፡ በአስቸኳይ ወደሰገባው ይመለስ፤ ይህ ካልሆነ መዘዙ በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ጭል ጭል በማለት ላይ ያለችን መብራት ለማጥፋት መጣደፍ መሆኑ እንዲታወቅ እናሳስባለን፡፡

ለማይገሰሱ ዴሞክራሲያዊ መብቶች በጋራ እንቁም!

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!

45% . . . !

‹‹ትልቁ የጋዜጦችን ወጪ የሚሸፍነው የማስታወቂያ ገቢ ነው ... የማስታወቂያ ገቢ ያላቸው ጋዜጦች በአሁኑ ጭማሪ አይጎዱም፡፡››

አቶ ሽመልስ ከማል/የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስቴር ም/ኃላፊ/

ብርሀንና ሰላም በቅርቡ በጋዜጦች ላይ ያደረገው የዋጋ ጭማሪን በተመለከተ ሰንደቅ ጋዜጣ ላቀረበላቸው ጥያቄ የሰጡት ምላሽ፡፡

የካቲት 2000 ዓ.ም ተመሠረተ

አውራምባ ታይምስ፡- በብሉ ኤርዝ ጀነራል ቢዝነስ ኃላ/የተ/የግል/ማህበር ስር የሚታተም፤ በፖለቲካዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር፤ በንግድ ሚኒስቴር በቁጥር 020/2/6572/2001 የተመዘገበ ሳምንታዊ ጋዜጣ ነው፡፡

አድራሻ አራዳ ክ/ከተማ ቀበሌ 09

የቤት ቁጥር 191

ከአራት ኪሎ ወደ ፒያሳ በሚወስደው መንገድ ፣ ከራስ መኮንን ድልድይ አለፍ ብሎ ወደ ሀገር ፍቅር ቲያትር መገንጠያ አስፋልት ላይ በሚገኘው ባህረ ነጋሽ ሕንፃ ግቢ ውስጥ፡፡

አታሚ፡-

ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ክ/ከተማ፡- አራዳቀበሌ፡- 17የቤት ቁጥር፡- 984

ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ሰይፍ ተመዞበታልበአስቸኳይ ወደሰገባው ይመለስ!

‹‹ወደብ ባይኖርም መርከቦች አሉን፡››

ጠ/ሚ/ር መለስ ዜናዊ

የኢትዮጵያ ንግድ መርከብ ድርጅት ያስመረቃቸውን ባሕረኞች በጽ/ቤታቸው ተቀብለው ባነጋገሩበት

ወቅት ከሰነዘሩት አስተያየት የተወሰደ፡፡

‹‹ሁሉም የሚለው እንደዛ ነዋ! ሙባረክም እኮ ‹‹(እዚህ ይደገማል

ብላችሁ አታስቡ) ይህ ቱኒዚያ አይደለም›› ብሎ ነበር፡፡ ጋዳፊም

በተራው፣ ‹‹ይህ ካይሮ አይደለም፤ አትልፉ›› ብሏል፡፡ ... የአምባገነኖች

አንዱ ችግር ይሄ ነው፡፡››

አቶ ስዬ አብርሃ/የአንድነት ለፍትህና ዴሞክራሲ ም/

ሊቀመንበር/

የኢህአዴግ ባለሥልጣናት ከፍተኛ የኢኮኖሚ እድገት እያስመዘገበች

ባላቸው ኢትዮጵያ ውስጥ፣ የሰሜን አፍሪካ አይነት ሕዝባዊ ተቃውሞ

አይከሰትም ማለታቸውን አስመልክቶ ካፒታል ጋዜጣ ላቀረበላቸው ጥያቄ

የሰጡት ምላሽ፡፡

Page 3: awramba 160

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 160 ቅዳሜ መጋቢት 17 2003

አደህይቶ እና አደንቁሮ የመግዛት ሙከራ እስከመቼ?

ኮሜንተሪሥልጣን ላይ ያለው አካል ለዴሞክራሲ ያለው ታማኝነት ጥያቄ ውስጥ መግባቱ ባይቀርም የራሱ የግሉ ፕሬስም አስተዋጽኦ ሊዘነጋ አይገባም፡፡ ፕሬሱ በየጊዜው ከውጭ የሚደረስበትን ችግር ለመወጣት የተለያዩ እርምጃዎችን ሲወስድ መቆየቱ ይታወሳል፡፡ ለምሳሌ በቅድመ ምርጫ 97፣ በተለይ 1980ዎቹ መጨረሻ እና 1990ዎቹ መጀመሪያ ታፔላ ‹ጋዜጠኞችን› በማዘጋጀት የእስር ቤት እና የፍርድ ቤት ፍዳዎችን እንዲወጡላቸው ማድረግ ነበር፡፡ ምርጫውን ተከትሎ ከተፈጠረው ሁኔታ ጋር በተያያዘም ብዙዎች ሀገር ለቀዋል፡፡ ከዚያም በኋላ ከሀገር መሰደድን የመረጡ አሉ፡፡ አስደናቂው ነገር ግን የግሉ ብቻ ሳይሆን በዚህ ወቅት ከመንግስቱም የተሰደዱ መኖራቸው ነው፡፡ ስደትን ያልመረጡት ደግሞ በርዕሰ አንቀጽ የፍራቻ ቅሬታ መግለጽ፣ ዋጋ በመጨመር፣ መንግስት ጉያ በመሸጎጥ፣ ወይም ከደረቅ ጥላቻና ጽንፍ በመውጣት ለሚደርስባቸው ተፅዕኖ ምላሽ ሲሰጡ ታይተዋል፡፡ ሌሎችም ከመንግስት ስሜት ጋር የሚለዋወጡ ሞቅ ቅዝቅዝ፣ ግንፍል እርግት ያሉ ርዕሰ አንቀጾችን የግጭት ማስወገጃ ዘዴ አድርገው ተጠቅመውበታል፡፡ ሌሎች ደግሞ አግቦን፣ ተረታ-ተረትንና ስላቅን በመጠቀም ቁጣን ሳይቀሰቅሱ መልዕክት ለማስተላለፍ ይጥራሉ፡፡ የባሰባቸው ደግሞ ድምፃቸውን አጥፍተው ከገበያ ይወጣሉ፡፡ አንዱም እርምጃ ግን ዘርፉን ጠቃሚ ሆኖ አልተገኘም፤ እንደውም እየጎዳው እንጂ፡፡ ለምሳሌ የነፃው ፕሬስ ማሳያ የሚባሉት ሁሉ የሚሰሩበትን መንፈስ የሚገዛው ‹‹ዕድሜን እንደምንም ማቆየት›› የሚል መርህ እየመሰለ/እየሆነ መጥቷል፡፡ ስለዚህ በአመዛኙ ከአቅም በታች እየሰሩ ነው ለማለት ይቻላል፡፡ ይህም መንግስት እየለካ በሚሰጠው ብቻ እየሰሩ በማስታወቂያም በሽያጭም ከሚገኘው ትርፍ ማስተማመንን ግብ ላደረጉትም ሽፋን ሆኗል፡፡ የስደቱ አማራጭም ክስተቱን እንደ ፋሲካ ለቆጠሩት መልካም አጋጣሚ ሆኖላቻዋል፡፡

ማ ስ ታ ወ ቂ ያ

3

እናስመስል ካልተባለ አዲሱ መንግስት የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም የነፃውን ሚዲያ ሰላማዊ ዕድገት ከማስተጓጎል ቦዝኖ አያውቅም፡፡ ለምሳሌ ሁልጊዜ በየፍርድ ቤቱ የሚቀርቡ ጋዜጠኞች እንዳይጠፉ ማድረግ እንደ ስልት ይጠቀመው የነበረ ማዋከቢያ ዘዴው ነበር፡፡ ከ1997 በኋላ ደግሞ ነፃ/የግሉ ፕሬስ ከመቼውም ጊዜ በላይ አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል፡፡ ከወዲሁ ፍቃድ በመከልከልና የተሰጣቸውም ቢሆኑ እውነት እንኳን ቢሆን መዘገብም ሆነ መተንተን እንዳይችሉ ከሽብርተኝነት ጋር አያይዞ የሚያስቀጣ ሕግ በማውጣት አፈናውን አርቅቆታል፡፡ በስመ ነፃ ጋዜጣ አርካሽ እንቅስቃሴዎች፣ ማስታወቂያ መከልከል/ለተመረጡ ብቻ መስጠት፣ በመንግስት ሚዲያዎች ከሽብርተኛ ጋር አያይዞ በማቅረብ በማስራራት ማስነጠል፣ መደብደብ፣ አልፎ ተርፎ ‹አንተን ማሰር ሰልችቶናል ስለዚህ... › ማለት ተጀምሯል፡፡ ሁኔታው መንግስት ወሰኑን እያጣ መሄዱንና ጋዜጠኞቹ ሽብር ውስጥ እንደተዘፈቁ ያመላክታል፡፡ የነፃው ፕሬስ አቅም ማጣት እየተባባሰ ለመምጣቱ የራሱ አስተዋጽኦ እስከምን ድረስ ነው ለሚለው ጥያቄ አንዱ መልስ ጫናዎችን ለማስወገድ ወይም ለመቋቋም ከወሰዳቸው እርምጃዎች ውስጥ ይገኛል፡፡

ነፃው ፕሬስ ችግሮችን ለመቋቋም የሞከረበት መንገድበነፃው ፕሬስ ላይ በየጊዜው የሚፈጠርበትና እየተባባሰ ስለሚሄድበት ችግር ሲዘከር

ጋዜጣ ማንበብ ባህል የሆነባቸው እንደ አሜሪካ ያሉ ሀገራት ውስጥ ጋዜጣን ‹‹ደህና ሁኚ›› የሚያስብሉ ምክንያቶች እየበረከቱ ነው፡፡ ከእነዚህ ምክንያቶች ዋንኛው የድረ-ገጾች መስፋፋት ነው፡፡ ስለዚህ ጋዜጦች የሠራተኞቻቸውን ቁጥር፣ የጋዜጣውን ቁጥርና መጠን በመቀነስ ላይ ናቸው፡፡ አንዳንድ ጋዜጦች በየቤቱ የማድረስ አገልግሎትም እያቋረጡ ለገበያ የሚቀርቡት በየጋዜጣ መሸጫ መቆሚያዎች ብቻ ሆኗል፡፡ በቅርቡ የተከሰተው የኢኮኖሚ ቀውስም ሁኔታውን አባብሶታል፡፡ ይህ ሁኔታ የጋዜጣ ዘመን እያበቃለት ይሆን? አሰኝቷል፡፡ አንዳንዶች ቢሆንም እንኳን ይኼን ያህል እንባ የሚያስረጭ አይደለም ይላሉ፡፡ መከራከሪያቸው ደግሞ እድሜ ለቴክኖሎጂ ዘገባዎችን እንዲያውም በበለጠ ፍጥነት ማግኘት እየተቻለ መሆኑ ነው፡፡ ይህ እንግዲህ በየቀኑ በመቶዎች የሚቆጠሩ ዕለታዊ ጋዜጦች እየወጡ ለብዙ አስርት ዓመታት፣ ቀላል የማይባሉትም ለመቶ ዓመታት ሲነበቡባቸው በኖሩ ሀገራት መሆኑን ልብ ይሏል፡፡ በኒህ ሀገራት ዛሬም አንድ የሚዲያ ተቋም ብቻ 40 እና 50 ዕለታዊ ጋዜጦችን እያስተዳደረ የሀገሪቱ አጠቃላይ ቅጂዎች ህትመት በሚሊዮን የሚቆጠሩበት ነው፡፡ በዚያ ላይ በርካታ ቻናሎች፣ እጅግ ፈጣንና የማይቋረጥ የድረ-ገጽ አገልግሎት፣ እጅግ ብዙ ታብሎይድ፣ በርካታ ሲቪል ማኅበራትና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚያዘጋጇቸው ኁልቆ መሳፍርት የውይይት መድረኮችና በየዕለቱ ለገበያ የሚቀርቡ ደረጃቸውን

የጠበቁ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች የሚፃፉ መፅሐፍት የሚወጡባቸው ሀገራት መሆኑን አንዘንጋ፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ የጋዜጣ ዘመን እያበቃ ይሆንን?

ወደራሳችን ስንመጣ ግን እንኳን ድረ-ገጹና በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ቅጂዎች ይቅርና ከአንድ እጅ ጣት ብዙም የማይበልጡት ሳምንታዊ ነፃ ጋዜጦችም ድሎት እየሆኑብን ነው፡፡ ሥርዓቱና የሀገሪቱ የሚዲያ ሕግ፣ የህብረተሰቡ ግንዛቤና የሙያተኛው ደረጃ ከሕዝቡ ድህነት ጋር ተደማምሮ የሀገሪቱን ሁኔታ በአፍሪካ ሀገራት ሥነ-ልክ እንኳን እጅግ ዝቅ ያለ ነው፡፡ ዘርፉ በችግሮች ተተብትቦም ቢሆን፣ በጥራቱ አለም የለምም ለማለት የሚያወላዳበት

ደረጃ ላይ ደርሶ እየተንገታገተ እስከአሁን ቆይቷል፡፡ የተደረገውም በብዙ ውጣ ውረድ እንደሆነ ግልፅ ነው፡፡ የክሱ መዓት፣ የዛቻውና ሰብቁ (አዲስ ዘመን ላይ የሚወጡ ጽሑፎችን ልብ ይሏል) ሁኔታ ብዙ ያሳያል፡፡ በእርግጥም የሰብዓዊ መብት ጥበቃም ሆነ ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች ድርጅት ሀገሪቱን የሚያውቋት በጥሩ ገድሏ አይደለም፡፡ ሽልማቱ ያበሳጫቸው ወገኖች በተቃራኒው ቢጮሁም ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ በጨረስነው የፈረንጆቹ ዓመት በድርጅቱ የተሸለመው በእንዲህ ዓይነት ሁኔታው ውስጥ መስራቱን ለማመስገን ነው፡፡ ከፋም ለማም የመንግሥት ለውጡን ተከትሎ በተፈጠረው የነፃ ፕሬስ እንቅስቃሴ ለብዙዎች ተስፋን ፈንጥቆ ነበር፡፡ በዚህም የሚያስመሰግነው እርምጃ መውሰዱን ዛሬም አይካድም፡፡ ይሁን እንጂ ወደ ገፅ 15 ዞሯል

በብርሃኑ ደቦጭ

ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ሰይፍ ተመዞበታልበአስቸኳይ ወደሰገባው ይመለስ!

Page 4: awramba 160

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 160 ቅዳሜ መጋቢት 17 2003

የትኩረት ማስቀየሻ ስልት? ወይስ የዳግም ጦርነት ነጋሪት?

ፊ ቸ ር4

ከ12 ዓመት በፊት...ዋሽንግተን ውስጥ ነው፡፡ የኤርትራ መንግስት በእናት አገራቸው ላይ የፈጸመው ወረራ ያስቆጣቸው በርካታ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮ-አሜሪካውያን ለጊዜው የፖለቲካ ልዩነቶቻቸውን ወደጎን በማድረግ የአምባሳደሩን ጥሪ አክብረው ዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ኤምባሲ የመሰብሰቢያ አዳራሽ አጨናንቀውታል፡፡ የተለያየ ይዘት ያላቸው ጥያቄዎች ከዚህም ከዚያም ይሰነዘራሉ፡፡ አምባሳደሩና ባልደረቦቻቸው ይመልሳሉ፡፡ ሁኔታው ግን እንደአጀማመሩ አልቀጠለም፡፡በድንገት አንድ በ40ዎቹ ማገባደጃ ላይ የምትገኝ ኢትዮጵያዊት ቅድመ ሁኔታ በሚመስል መንገድ ያልተጠበቀ ጥያቄ አቀረበች፡፡ ‹‹አቶ መለስ ያመጡብን ጣጣ ነው...›› ስትል ጀመረች፡፡ ‹‹... በመጀመርያ እሳቸው ከስልጣን ይውረዱ ከዚያ ሁላችንም ባለን አቅም ተረባርበን ጦርነቱን በድል እንወጣዋለን፡፡›› ይህ የቅድመ ሁኔታነት ስሜት የሚነበብበት የጥያቄ አቀራረብ ባልደረቦቻቸውን በግርታ ቢመታቸውም አምባሳደሩ ግን በተለመደው የተረጋጋና ማመቻመች በተንጸባረቀበት አመላለሳቸው የተፈጠረውን ውጥረት ረገብ አደረጉት፡፡ ከኤርትራ ጋር በተያያዘ ጠንከር ያሉ ጥያቄዎች መቅረባቸው ግን በዚያው አላቆመም፡፡

ከ12 ዓመት በኋላ... አዲስ አበባ ውስጥ ነው፡፡ በባሕሪያቸውም፣ ባሳለፉት የዲፕሎማትነት ተሞክሯቸውም ነገሮችን በተቻለ መጠን አመቻምቸው በማስተናገድ ይታወቃሉ የሚባልላቸው አምባሳደሩ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ዴኤታ እዚህ ነጥብ ላይ ሲደርሱ የዲፕሎማትነት ካባቸውን በመጠኑ ገፈፍ አድርገው ጠንከር ያለውን አቋም በቁርጠኝነት ይፋ አደረጉት፡፡ “አቋማችን ...” አሉ አምባሳደሩ ሚ/ር ዴኤታ “...በዚህ ሁኔታ ይህ ሊቀጥል አይገባውም የሚል ነው፡፡” ከዚህ በኋላ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት የስብሰባ አዳራሽ የታደሙት ጋዜጠኞች ተከታታይ ጥያቄዎቻቸውን ማዝጎድጎድ ጀመሩ፡፡ ‹‹ጠ/ሚ/ሩ ሲናገሩ በኤርትራ የመንግስት ለውጥ እንዲኖር ይፈለጋል ብለዋል፡፡ እንደውጪ ጉዳይ ሚ/ር መ/ቤት ኃላፊነትዎ ሊያረጋግጡልን ይችላል?››‹‹የኤርትራን መንግስት ማስወገድ ከፍተኛ ትኩረት የተሰጠው ይመስላል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ካለው ስር የሰደደ ድህነት በላይ የኤርትራ ጉዳይ ይብስብናል?››‹‹በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ወቅት ይህን ማድረግ የሚቻልበት ሰፊ እድል ነበር፡፡ አሁን ምን አዲስ ነገር ተገኘ?››‹የዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ በኤርትራ ላይ አቋም ካልያዘ በኢትዮጵያ በኩል የሚወስደው እርምጃ እስከምን የቀጥላል?››...እና የመሳሰሉት፡፡ ለእነዚህ ጥያቄዎችና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚ/ር ዴኤታ የሆኑት አምባሳደር ብርሃነ ገ/ክርስቶስ መንግስታቸው በኤርትራ መንግስት ላይ አድርጌዋለሁ ያለበትን የአቋምና የስትራቴጂ ለውጥ መንስኤ ሲገልጹ ከዚህ ቀደም ከሚታይበት የማመስ ተግባር በተለየ መንገድ የ24 ሰዓት ስላደረገው መሆኑን ለማብራራት ሞከሩ፡፡ አዲሱ ክስተት በዋሽንግተኑ ኤምባሲ

ለተገኙት ታዳሚዎች በተሰጡት ምላሾች የተገኘው አንጻራዊ ፋታን ሊሰጥ የሚችል አይመስልም፡፡ ምክንያቱም አሁን እየቀረበ ያለው ምክንያት ግን ብዙዎችን አላሳመነም፡፡

በሰሜን አሜሪካ - ሚኒሶታ የሚኖሩት የፖለቲካል ሳይንስ ተመራማሪና ተንታኝ ጃዋር ሲራጅ መሐመድ የቀረበው ምክንያት አጥጋቢ አይደለም ከሚሉት ወገኖች አንዱ ናቸው፡፡ ለዚህም አቶ ኢሳያስ የኢትዮጵያን ደህነነት እና መረጋጋት መፈታተን የጀመሩት ከበፊት ጀምሮ ከመሆኑ በተጨማሪ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ግን ይህን ዓላማቸውን የሚያሳኩበት ዕድል እየተመናመነ መሆኑን ይጠቅሳሉ፡፡ “እንደሚታወቀው አቶ ኢሳያስ አቶ መለስን የሚፈታተነው የኢትዮጵያን ተቃዋሚዎች በመጠቀም ነው። ይህ የኤርትራ እና የኢትዮጵያ አማጺያን ግንኙነት ደግሞ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሻከረ በመሄድ በአሁኑ ወቅት አብዛኞቹ ቡድኖች በግልጽ ባይናገሩም ከኤርትራ ጋር ሆኖ ኢትዮጵያ ውስጥ የመንግስት ለውጥ ማምጣት እንደማይቻል ድምዳሜ ላይ ደርሰዋል።” ካሉ በኋላ ለዚህም ሶስት መሰረታዊ ምክንያቶችን ያስቀምጣሉ፡፡

የኤርትራ መንግስት •መቼም በቂ እርዳታ ለአንድም ቡድን ሰጥቶ አያውቅም። እንዲያውም ተቃዋሚዎቹ በሙሉ ኃይላቸው እንዳይታገሉ በማገድ፣ አልፎ አልፎ የሽብር ጥቃት እንዲያደርሱ ያስገድዳቸዋል። በተጨማሪም፣ የቡድኖቹ መሪዎች ወደ ሀገር ውስጥ ገብተው እንዲዋጉ

አይፈቅድም። ብዙዎቹ በቁም እስር እንዳሉ ነው የሚነገረው። የእነዚህ ቡድኖች መሪዎች በኤርትራ ካምፖች ውስጥ ይሰቃያሉ።

የኤርትራ መንግስት •በኢትዮጵያ ተቃዋሚ ቡድኖች የውስጥ ፖለቲካ ውስጥ ጣልቃ በመግባት የፈለገውን ሽሮ ለመሾም የሚያደርገው ጫና ብዙዎቹን አስኮርፏል። ኢሳያስ እንደ ሎሌ ሊጠቀምባቸው እንጂ የትግል አጋር ሊሆናቸው እንደማይችል ሁሉም እየተረዱ መሆኑን እያየን ነው።

በአሁኑ ወቅት •በአረብ ሀገራት ዜጎች ያለጠመንጃ እና የውጪ እርዳታ በሰላማዊ ትግል አምባገነኖችን በመገርሠስ ነጻነታቸውን መጎናጸፍ መቻላቸው፣ በኢትዮጵያ ለውጥ ለማምጣት የኤርትራን አስፈላጊነት አሳንሶታል። ከዚህ በፊት የኤርትራን ድጋፍ አስፈላጊነት አበክረው ሲናገሩ የነበሩ ዛሬ አመለካከታቸውን ቀይረው እየተመለከትን ነው።

‹ወይ ፖሊሲውን

ወይ ራሱን›

የሰሜን አፍሪካ አገራት ሕዝባዊ አመፅ በዴሞክራሲያዊ ምርጫ ለዚያውም ወደ

መቶ በመቶ በተጠጋ ‹የሕዝብ› ድምፅ ስልጣን ተቆናጠናል ያሉትን ሳይቀር አሽቀንጥሮ እየጣለ ባለበት ቅጽበት ጠ/ሚ/ር መለስ ዜናዊ “አሰና” በተባለው የኤርትራ መንግስት ተቃዋሚ ራዲዮ ጣቢያ ላይ የሰጡት ቃለ ምልልስ የተጠበቀ ዓይነት እንዳልነበር ብዙዎች ይስማሙበታል፡፡ ጠ/ሚ/ሩ ረዥም ጊዜ በወሰደ በዚህ ቃለ ምልልሳቸው የኢሳያስ አስተዳደርን አስመልክቶ ሁኔታውን በሁለት በመክፈል የሰጡት ማብራርያ የተለያየ አንድምታ ፈጥሯል፡፡የመጀመሪያው ተቃዋሚዎች ‹‹የአቶ መለስ ተማፅኖ›› ሲሉ የተቹትና ጠ/ሚ/ሩ ‹‹የኢትዮጵያ መሪ በመሆኔ ጉዳዩ አይመለከተኝም›› ካሉ በኋላ ‹‹እንደኤርትራ ሕዝብ ወዳጅነቴ›› በሚል የሰጧቸው ግላዊ አስተያየቶች የኤርትራውያኑ ነፃ አውጭ ፋኖ ያስመሰላቸው መሆኑ ነው፡፡ በአጠቃላይ ለሕዝቡ፣ ለአዲሱ ትውልድ እና በስልጣን ላይ ያለው መንግስት የወደፊቷን ኤርትራ ተስፋ የሚያጨልም መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ከዚሁ ለኤርትራ ሕዝብ ከተገለጸ ግላዊ አስተያያት አንዱ ‹‹ሁሉም ሕዝብ ሰላም ይገባዋል፤ በተለይ ግን የኤርትራ ሕዝብ ሰላም ይገባዋል፡፡...›› የሚል ሲሆን ይህን ያሉበትን መንገድ መንገድ አስመልክቶ አስተያየታቸውን ለአውራምባ ታይምስ የሰጡት የወቅቱ የመድረክ ሊቀ መንበር የሆኑት አቶ ገብሩ አስራት ‹‹የቃለ ምልልሱ ማጠንጠኛ የሕግም የሞራልም መሰረት በሌለው መንገድ የብዙዎች ሕይወት መስዋዕት የሆነበትን የድንበር ግጭት መሬት በመለዋወጥ እንፍታው የሚልና ጠ/ሚ/ሩ ለኤርትራ የጠበቀ ወዳጅ መሆናቸውን አጽንኦት የሰጡበት ተማጽኖ ብቻ ነው፡፡›› ሲሉ ተችተውታል፡፡ እንደ አቶ ገብሩ ሁሉ ሌሎች ወገኖች የሚያቀርቡትን መሰል አስተያየት ቀደም ሲል በኤርትራ ነፃነት በነበራቸው ድርሻ ይቀርቡባቸው ከነበሩት ተቃውሞዎች ጋር በተያያዘ የራዲዮ ጣቢያው ላነሳላቸው ጥያቄ ጉዳዩን ከሕዝቦች ነጻነትን የማክበር ገለልተኛ አስተሳሰብ ጋር አያይዘው መልሰውታል፡፡ ቀጥሎ የቀረበላቸው ጥያቄ ግን በኤርትራ ጉዳይ ላይ የዳር ተመልካች ሊሆኑ እንደማይችሉ ያመላከተና አዲሱን የመነጋገርያ አጀንዳ የከፈተ መሆኑ አልቀረም፡፡ ጥያቄው ‹‹ኤርትራ ላይ አዲስ ስትራቴጂ ነድፋችኋል?›› የሚል ነበር፡፡ የአቶ መለስ የመንደርደርያ ኃሳቦች ከተገባደዱ በኋላ ‹ወይ ፖሊሲው ወይ ስርዓቱ› እንዲቀየር ቀደም ሲል ይደረጉ ከነበሩ ጫናዎች በተጨማሪ በወታደራዊ መስክ ሳይቀር እንደሚገልጹት ይፋ

በውብሸት ታዬ

አዲሱ አቋም!

የኢትዮጵያ መንግስት በቅርቡ በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን አማካይነት በኤርትራ ላይ የአቋምና የስትራቴጂ ለውጥ በማድረግ በአስመራ ያለውን ስርዓት

ለማስወገድ መወሰኑን ይፋ አድርጓል፡፡ የዚህ በዲፕሎማሲው ዓለም በማይጠበቅ አገላለጽ ይፋ የተደረገ አቋም አንድምታዎች ምንድናቸው? ቀጣዩ ፊቸር

የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችን፣ የፖለቲካ ተንታኞችን፣ የወታደራዊ ሳይንስ ባለሙያዎችንና የተለያዩ ወገኖችን ትንታኔ አካቶ የቀረበ ነው፡፡ በውብሸት ታዬ

ሚዛናዊነት የለም፡፡ ከሚታወቀው እውነታ

ተነስቶ ካሉብን ችግሮች እንዴት እንላቀቃለን? በጎ

ጅምሮቻችንን እንዴት እናጎለብታለን? ወዘተ ከማለት

ይልቅ ከፈለጋችሁ ተቀበሉ፤ አለዚያ መንገዱን

ጨርቅ ያድርግላችሁ ዓይነት ነገር ነው ያለው፡፡...”

Page 5: awramba 160

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 160 ቅዳሜ መጋቢት 17 2003 ፊ ቸ ር 5አደረጉ፡፡

የስትራቴጂ ለውጥ ተደርጓል?ጠ/ሚ/ሩ መደበኛ የመግለጫ አሰጣጥ ፕሮቶኮልን ባልጠበቀ ሁኔታ ያን ያህልም ዕውቅና ባልነበረው የራዲዮ ጣቢያ ሙሉ ምስሉና ዓላማው ተገማች ያልሆነ በተባለለት አዲስ አቋም እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙርያ ቃለ ምልልስ ባደረጉ ማግስት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤትና በየደረጃው ያሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት ገደምዳሜ መግለጫዎች ግርምትን አጭረዋል፡፡ ሁኔታው ትኩረታቸውን የሳበው የፖለቲካ ተንታኞች ደግሞ ቀደም ሲል የነበረው የውጭ ጉዳይና የአገራዊ ደህንነት ፖሊሲ ስትራቴጂ መፈተሽ እንዳለበት ያሳስባሉ፡፡ በእርግጥ ቀደም ሲል በሰነድ ጭምር ሰፍሮ ሲሰራበት በነበረው የአቋምና የስትራቴጂ ፖሊሲ ለውጥ ተደርጓል ወይ? ሲሉም ይጠይቃሉ፡፡ ይህ በውጭ ጉዳይ ላይ የሚያጠነጥን የፖሊሲና ስትራቴጂ ማብራሪያ ኤርትራን አስመልክቶ የሚኖረው አቋም መለስተኛ ከፍተኛ ግቦችን ታሳቢ ያደረገና አገራዊ ጥቅማችንን በሰከነ መንፈስ በመመርመር ላይ የተመሰረተ መሆን እንዳለበት ይገልፃል፡፡ መለስተኛው ግጭትን ማስወገድ ሲሆን የኤርትራ በጎም ሆነ አሉታዊ ተፅዕኖ እጅግ መለስተኛ በመሆኑ በዚህ የተነሳ ከዋናው ዓላማችን የምንዘናጋበት ምንም ምክንያት ሊኖር አይችልም ይላል፡፡ በሁለት መልኩ ግጭቶችን ማስወገድ እንደሚቻልም ጥቆማ ይሰጣል፡፡ የመጀመሪያው የአደጋ ተግላጭነትን በመቀነስ በሻዕቢያ በኩል ሌላ ዙር ግጭት ቢቀሰቀስ ተጎጂው ማን እንደሆነ ማሳየት ሲሆን ሁለተኛው በስልጣን ላይ ያለው ቡድን ወይም ፖሊሲውን መቀየር አልያም ከስልጣን መወገድ መሆኑን ያሰምርበታል፡፡ የመጀመርያውን በእጃችን ላይ ያለ ሁለተኛውን ከቁጥጥራችን ውጪ የሆነ ይለዋል፡፡ አሁን ተደረገ በተባለው ለውጥ ይህ ከቁጥጥራችን ውጭ የነበረ መንገድ በእጃችን የገባበት ሁኔታ ግን አልተገለጸም፡፡ ይህም በመሰረተ ጉዳዩ ተጨባጭነት ላይ ጥያቄ እንዲነሳ መንገድ ከፍቷል፡፡ የመድረኩ ሊቀ መንበር የሆኑት አቶ ገብሩ ጉዳዩን በስነ አመክንዮ ከመዘኑ በኋላ ወደዚህ አቋም የሚመራ መሰረት እንደሚያጡበት ይናገራሉ፡፡ በተለይ በዚህ ወቅት ሻዕቢያ ከራሱ የውስጥ ችግር አልፎ ለሌሎች የስትራቴጂ ለውጥ ምክንያት እስከመሆን የሚያደርስ ነባራዊ አቅም የለውም፡፡ ጃዋር ሲራጅ በአቶ ገብሩ አስተያየት ይስማማሉ፡፡ እንደፖለቲካ ተንታኙ ዕምነት ኢትዮጵያ ከኤርትራ በኩል ያላት ስጋት በከፍተኛ ሁኔታ እየቀነሰ በመሆኑ ኤርትራ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ደህንነት፣ ጸጥታና ሰላም ከድሮ የበለጠ አስጊ ሆናለች ለማለት የሚያስችል ምንም ምክንያት የለም። መንግስት በአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ሰሞን ተሞከረ የተባለው የሽብር ጥቃት እንደ ምሳሌ ያቀርባል። ኤርትራ ከጦርነቱ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ አምባሳደሯን ወደ አዲስ አበባ ልካ፣ ጎን ለጎን የሽብር ጥቃት በአፍሪካ ህብረት ላይ ማድረስ ትሞክራለች ብሎ ማሰብ አስቸጋሪ ነው። አምባሳደሯን የምትልከው ሀገሪቷ ከዓለም ማሕበረሰብ መነጠሏ እየጎዳት ስለሆነ ያፍሪካን ህብረት ለማባበል በመሆኑ ይህ ህብረት በስብሰባ ላይ እያለ አዲስ አበባን ማጥቃት የባሰ ይጎዳታል እንጂ የሚረዳት አይሆንም ሲል በመንግስት ባለስልጣናት እየተሰጠ ያለውን ሰበብ ያጣጥሉታል፡፡

ታዲያ የሰሞኑ የኢትዮጵያ መንግስት ፉከራ ለምንድነው የሚል ጥያቄ ሲነሳ ገዢው ቡድን ከውስጥ ይነሳብኛል ብሎ የሚፈራውን ህዝባዊ አመፅ ለማክሸፍ ብሎም ለማፈን የሚያደርገው ቅድመ ዝግጅት ነው የሚል ምላሽ ይሰጣል፡፡ ጃዋር ሁኔታውን ባለፉት ወራት ህዝባዊ አመፅ የተነሳባቸው ገዢዎች፣ ለገጠማቸው ቀውስ የውጪ ጠላትን ሲያሳብቡ ከታዩበት ክስተት ጋር ያያይዙታል፡፡ “የቱኑዚያው ቤን አሊ አልቃኢዳን ከሰሱ። የግብጹ ሙባረክ አንዴ አክራሪ ጽንፈኞችን ሲከስ ከርሞ አልሳካ ሲለው፣ ሸሪኩ የሆነቸውን የእስራኤል ስለላ ድርጅት ሞሳድ ማመካኘት ጀመረ። የየመኑ አሊ አብደላ ሳሌህም እንደዚሁ አልቃኢዳ እያለ ሲጮህ ቆየና ምዕራባውያን ደጋፊዎቹ አላምን ሲሉት እንግዲያውስ እራሳችሁ እስራኤል እና አሜሪካ ናችሁ ወጣቶቹን ያነሳሳችሁብኝ አለ። በተመሳሳይ ሁኔታ የሊቢያው ጋዳፊም አንዴ አልቃኢዳን ሌላ ጊዜ ኢምፔሪያሊስቶችን ሲረግም እናያለን። ለየት ባለ መልኩ፣ ባህሬን የኢራን ጣልቃ ገብነት ነው ስትል፣ በኢራን ለተነሳው አማጽ ደግሞ አህመዲነጃድ አሜሪካን ሲከስ ከርሟል።” ይለካሉ፡፡

የተአማኒነት ችግርየመንግስት ሹማምንት ለሕዝብ ይፋ በሚያደርጓቸው የአፈፃፀም ሪፖርቶችም ሆነ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በሚሰጧቸው መግለጫዎች የተአማኒነት ጥያቄዎች ይነሳሉ፡፡ ተዓማኒነትን ጥያቄ ላይ ከሚጥሉት ጉዳዮች አንዱ እክሎች ሲያጋጥሙ መፍትሔ ተብለው የሚወሰዱ እርምጃዎች ያልተጠኑና ችግሩን የሚያባብሱ ሆነው መገኘታቸው እንደሆነ

ይነገራል፡፡ እንደሁኔታዎቹ የስሱነት መጠን የሚያስከፍሉት ዋጋም ይለያያል፡፡ የቀድሞው የመከላከያ ሚኒስትር የነበሩት አቶ ስዬ አብርሃ ባለፈው ሳምንት ለአንድ ጋዜጣ በሰጡት ቃለ ምልልስ ላይ የገለፁትም ይህንኑ ነበር፡፡መንግስት በሰሜን አፍሪካ የተከሰተው የሕዝብ አመፅ ምንም እንዳላሳሰበው ከገለጸ በኋላ በምክንያትነት ያስቀመጠውም በእነዚያ አገራት ያለው የዴሞክራሲያዊና ሰብአዊ ቀውስ እዚህ የማይታይ መሆኑን ነው፡፡ አቶ ስዬ ‹‹በእነዚህ ሰዎች ላይ ካለኝ እውቀት አንፃር የሰሜን አፍሪካው ሕዝባዊ አመፅ እጅጉን ያስጨንቃቸዋል፡፡...›› ካሉ በኋላ ችግሩን ለመፍታት ግን አስከፊ የተባለ አቅጣጫ እንደሚወስዱ ጠቁመዋል፡፡ የሕግ ባለሙያና የኢትዮጵያውያን ብሔራዊ አንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ዘሪሁን ገ/እግዚአብሔር “ጥያቄው የትም፣ መቼም እና በማንም ቢነሳ የሞራልና የሕግ ፅንስ ሃሳብ ሕዝቡን ትክክለኛ ስለሚያደርጉት ገዥ ስርዓቶች ያመጧቸው መመሪያዎችና ሕጎች ሚዛን መዋዠቁ አይቀርም” ካሉ በኋላ በተለይ ከእውነታ የራቁ መሸንገያዎች ትክክለኛ መረጃ የማግኘት መብት ባላቸው ዜጎች ላይ ሲፈጸሙ መኖራቸው አንድ ሕዝብ በአገሩ ሁለንተናዊ ጉዳዮች ላይ የባለቤትነት ስሜት እንዳይኖረው በማድረግ የልዕልና ኃይሉን እንደሚያሳጣው ይናገራሉ፡፡ አቶ ዘሪሁን የሕዝብን መሰረታዊ ጥያቄዎች ለመመለስ ከመሞከር ይልቅ እንደሌሉ ለማስመሰል የሚደረገው ሙከራ ተአማኒነትን ከማሳጣት አልፎ በሌሎች አገሮች እንደታየው ሁሉ ባልታሰበ ወቅት በመፈንዳት ከፍተኛ ቀውስ ሊያስከትል እንደሚችል ያስጠነቅቃሉ፡፡ የተአማኒነት አደጋዎች መምጫቸው ያለመታወቁም ሌላው ፈተና እንደሆነ ይገለጻል፡፡ ከ1983ቱ የስርዓት ለውጥ በኋላ ብቻ እንኳ ላለፉት 20 ያህል ዓመታት በተቃውሞው ጎራ ጉልህ አስተዋጽኦ የነበራቸው ፖለቲካ ፓርቲዎች በአገር አቀፉ ምርጫ ወቅት ምንም ድምፅ አጡ ቢባል ድክመት አልነበረባቸውም የሚል መከራከርያ ባያስነሳም በ”አሸናፊው” ወገን ላይ የተአማኒነት ጥያቄ ማስነሳቱ አልቀረም፡፡ በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ከፍተኛ ኢኮኖሚስት ሆነው ያገለገሉት ዶ/ር ታደሰ ብሩ በአንድ ጥናታዊ ጽሁፋቸው የኢሕአዴግ መንግስት በአገር አቀፍ ምርጫ ወቅት ‘የሚያገኘው’ የተቃዋሚዎችን ሚና መና የሚያስመስል ውጤት የሕጋዊነት ጥያቄ እያመጣበት እንደሚቸገር የጠቆሙት የ99.6 በመቶው ውጤት ከመከሰቱ ከአምስት ዓመታት በፊት ነበር፡፡ ዶ/ር ታደሰ በዚሁ ጥናታዊ ሥራቸው ያነሱት ሌላው ነጥብ የኤርትራ ጉዳይ ሉዓላዊት ከተባለች በኋላ እንኳ ከኢትዮጵያ ልሂቃን አእምሮ መውረድ ያልቻለ መሆኑ ነው፡፡ ጀርመን ውስጥ ያለውን የመላው አፍሪካውያን ኮሙኒቲ ለረዥም ጊዜ በፕሬዝዳንትነት የመሩት አቶ አድማሱ ኃይሉ/አሁን የኢአዴድ ፓርቲ ሊቀ መንበር ናቸው/ በበኩላቸው የተአማኒነት ችግሩ እየጎላ የመጣው ገዥው ፓርቲ በረዥም ጊዜ ይሰጣቸው በነበሩ አጠራጣሪ፣ የተጋነኑና ከእውነታ የራቁ መግለጫዎች ድምር ውጤት ነው ይላሉ፡፡ ከጥቂት ሳምንታት በፊት ጀርመን ውስጥ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን ጋር ባደረጉት ውይይት በስፋት ይንጸባረቅ የነበረውም ይኸው እንደነበር ያስታውሳሉ፡፡“ተአማኒነቱን አደጋ ውስጥ ከሚከቱት ነገሮች አንዳንዶቹ በተዛባ ስሌት የሚይዛቸው አስተሳሰቦች ናቸው፡፡ ለምሳሌ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎቻችን በረሃብ አለንጋ እየተገረፉ ባሉበት ሁኔታ ልዩ እገዛ እንደተደረገላቸው አነጋገራቸው የሚያሳብቅባቸውን ጥቂት ‘ልማታዊ ባለኃብቶች’ በቴሌቭዥን በማቅረብ ስለተትረፈረፈ የኢኮኖሚ ትሩፋት ይሰብካል፡፡ ሚዛናዊነት የለም፡፡ ከሚታወቀው እውነታ ተነስቶ ካሉብን ችግሮች እንዴት እንላቀቃለን? በጎ ጅምሮቻችንን እንዴት እናጎለብታለን? ወዘተ ከማለት ይልቅ ከፈለጋችሁ ተቀበሉ፤ አለዚያ መንገዱን ጨርቅ ያድርግላችሁ ዓይነት ነገር ነው ያለው፡፡...” ይህ በየጥቃቅኑ ጉዳይ ሳይቀር ማንንም የማያሳምን አቀራረብ ፈታኝና ወሳኝ በሆኑ አጋጣሚዎች የሕዝቡን ድጋፍ እንደሚያሳጣ ይናገራሉ፡፡ ግንቦት 5/1990 እና ሚያዚያ 5/1994

በመንግስት በኩል ኤርትራን አስመልክቶ የተቀየረው የስትራቴጂና የአቋም ለውጥ የአቶ ኢሳያስ አስተዳደር ወይ ፖሊሲውን እንዲቀይር ያለዚያም ከስልጣኑ እንዲወገድ እስከመንቀሳቀስ የሚዘልቅ መሆኑ ሲገለፅ የትኩረት አቅጣጫ የማስቀየር ተራ ስልት ነው ከሚለው ነቀፋ በተጨማሪ ወደኃይል እርምጃ የሚገባበት አጋጣሚ ቢፈጠር በኢትዮጵያ ሕዝብ በኩል ያልሻረ ቁስል እንዳለ ይገልፃል፡፡ ማንነታቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ አንድ የቀድሞው የኢትዮጵያ ጦር ሰራዊት ጄኔራል መኮንን በሁለቱ አገራት መካከል ዳግም ግጭት ይቀሰቀስ እንደሆን ላቀረብንላቸው ጥያቄ የ1990ውን የ”ድንበር” ግጭት ተሞክሮ በማስታወስ ሊደረግ አይችልም ብሎ መደምደም

እንደማይቻል ይገልጻሉ፡፡ “በአገራችን ላይ ሊያስከትል ስለሚችለው ሁለንተናዊ ምስቅልቅል ለጊዜው እንተወውና “ጦርነትን መፍጠር እንችላለን” ይሉ የነበሩ የጦር አዛዦች የነበሩት መንግስት በጎረቤት የአፍሪካ አገራት ፈፅሞ ባልተጠበቀ ወቅት የተቀሰቀሱ የሕዝብ አመፆች ምን እያስከተሉ እንዳሉ እያየ የሁኔታዎችን አካሄድ አስልቶ እርምጃዎችን ሊወስድ አይችልም ማለት አጠራጣሪ ነው” ይላሉ፡፡ በሌላ በኩል ሻዕቢያ ለአገራችን ስጋት ነው እስከተባለ መፍትሔው ውስጣዊ ብቃትን ማደራጀት እንጂ ስርዓቱን ማስወገድ አይደለም” ካሉ በኋላ “ኢትዮጵያ የየራሳቸው አጀንዳ ባላቸው፣ ለደህንነቷ ተጨባጭ ስጋት በሆኑና በኢኮኖሚ አቅማቸውም ጠንካራ መሰረት ባላቸው አገራት የተከበበች መሆኗ ይታወቃል፡፡ መንግስትን እስከመቀየር መንቀሳቀስ የሚለው በሌላ አገር ... ለነገሩ ኤርትራን አገር ያደረጋትም ኢሕአዴግ ነው... ጣልቃ መግባት መሆኑን ብንተወው እንኳ ስንቱን እያስወገዱ መቀጠል ይቻላል? የዚህ ዓይነቶቹ የእናስወግዳለን መግለጫዎችስ በሂደት ሊያስከትሉብን የሚችሉት ዲፕሎማሲያዊ መዘዝስ ተስተውሏል ወይ? ...” ሲሉ አከታትለው ይጠይቃሉ፡፡ ጃዋር ከዚህ ኃሳብ ጋር በሚመሳሰል መንገድ ጦርነት ሊነሳ አይችልም በሚለው ግምት ላይ ያለውን ጥርጣሬ ይገልጻል፡፡ “አቶ መለስም ይህንን ዘዴ በደንብ ያውቁታል፣ ሲጠቀሙበትም ኖረዋል። አሁንም የሕዝባዊ አመፅን በመፍራት ነው የጦርነት ከበሮ መደለቅ የጀመሩት። የተፈራው አመፅ ከተነሳ እና የስልጣን ወንበራቸውን ካወዛወዘው እንደዛቱት በኤርትራ ላይ ጦርነት እንዳይከፍቱ ያሰጋል። አመጽ ካልተነሳ ግን እንደተለመደው የአንድ ሰሞን ወሬ ሆኖ ያልፋል።...” ሲል፡፡

ቀደም ሲል የተጠቀሱት ከፍተኛ መኮንን ያሰመሩበት ሌላው ነጥብ የተጠቀሰውን ዓይነት የስትራቴጂ ለውጥ አድርጎ ሕዝባዊ ጠቀሜታ ያለው ፋይዳ ላይ ለመድረስ መሪዎች በመሰል አጋጣሚ ትተው ያለፉት የተአማኒነት ተሞክሮ ትልቁን ስፍራ የሚይዝ መሆኑ ነው፡፡ በዚህ በኩል የ10ሺዎችን መስዋዕትነትን ባስከፈለ ጦርነት ማግስት የድንበር ኮሚሽኑ የሰጠውን ውሳኔ አስመልክቶ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ስዩም መስፍን አማካይነት የተሰጠው ፈፅሞ ከእውነታው የራቀ መግለጫና መግለጫውን በማመን በአደባባይ የተካሄደው የደስታ መግለጫ እውነታ ሲገለጥ በሕዝቡ ላይ ያደረሰው የመናቅ ስሜት ከሌሎች አገራት ጋር በሚከሰት መሰል አጋጣሚ ላይ አሉታዊ ጥላውን ማሳረፉ አይቀርም በማለት ጥርጣሬያቸውን ይገልፃሉ፡፡ ዓለም አቀፍ የሕግ ባለሙያ የሆኑት ዶ/ር ያዕቆብ ኃ/ማርያም በበኩላቸው የሁለቱ አገራት የ1990 ዓ.ም የግጭት መንስኤ፣ ሁለቱን አገራት ይገዛቸው የነበረው የአልጀርስ ስምምነት የክርክሩ ሂደትና የመረጃ አቀራረብ፣ የድንበር ኮሚሽኑ የመጨረሻ ውሳኔና ውሳኔው ኃላፊነት በጎደለው መንገድ ለሕዝብ ይፋ የተደረገው ሃሰተኛ መረጃ ያለውን አሉታዊ አንድምታ ይገልፃሉ፡፡ የዚያን ዓይነቱ ዓለም ያወቀው ከእውነት የራቀ መግለጫ ተሰጥቶ እስካሁን ይቅርታ ያለመጠየቁ ደግሞ በእጅጉ አሳፋሪ መሆኑን ይናገራሉ፡፡ በኢፌዴሪ የሚኒስትሮች ም/ቤት ተወስኖ ግንቦት 5 ቀን 1990 ዓ.ም የተሰጠው መግለጫ ምንም እንኳ ቀደም ሲል በነበረው ቀን “የኤርትራ መንግስትና አገሪቱን በመምራት ላይ ያለው ሕዝባዊ ግንባር” የኢትዮጵያን ድንበር ዘልቆ መግባት ሉአላዊነቷን ቢዳፈርም ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ለቅቆ ወደነበረበት እንዲመለስ ይጠይቃል፡፡ መግለጫው አደገኛ መዘዝ ሊያስከትል የሚችለውን የእብሪት ወረራ የፈፀመውን አካል ማስጠንቀቂያ የሰጠበት መንገድም አሁን ለብዙዎች ግልፅ ባልሆነ አደጋ ላይ ከሚሰጠው የጠነከረ አቋም

ጋር ሲነፃፀር በእጅጉ የተለሳለሰ እንደነበር ይነገራል፡፡ ይህ በአራት አጫጭር አንቀፆች የተቋጨው የሚኒስትሮች ም/ቤት መግለጫ ብዙ ቦታዎች ላይ “የኤርትራ መንግስት፣ሕዝባዊ ግንባር” የሚሉትን ሐረጎች መደጋገሙ ይጠቀሳል፡፡ ከዚያ ይልቅ በወቅቱ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ሊቀ-መንበር የነበሩት ኮምፓውሬ ለአቶ ኢሳያስ ፅፈውት የነበረው የማሳሰቢያ ደብዳቤ ጠንካራ አቋም የተንፀባረቀበት በሚል ተጠቃሽ ሰነድ ለመሆን በቅቷል፡፡ ከአራት ዓመታት በኋላ ማለትም ሚያዚያ 5 ቀን 1994 ዓ.ም ዘሄግ ላይ የተሰየመው የድንበር ኮሚሽን ያስተላለፈውን ውሳኔ አስመልክቶ የሚኒስትሮች ም/ቤት በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አማካይነት የሰጠው መግለጫ ግን በጦርነቱ ዋዜማ ላይ የነበረውን “የኤርትራ መንግስት እና ሕዝባዊ ግንባር” የሚሉ ቃላት “የሻዕቢያ መንግስት” በሚል ተክቶታል፡፡ “ሁለተኛውና ዋንኛው ነጥብ ግን....” ይላሉ የፖለቲካ ተንታኞች “የመግለጫው ማብራሪያ በቁጥር ሁለት ላይ ያሰፈረው “በምዕራቡ አካባቢ አገራችን ካቀረበችው ጥያቄ በመነሳት ሻዕቢያ ይገባኛል ብሎ ወረራ የጀመረበትን የባድመ አካባቢ የኢትዮትያ እንደሆነ አረጋግጧል” ካለ በኋላ “በተጨማሪም በባድመ አካባቢ ኢትዮጵያ ስታስተዳድረው የነበረው ቦታ ሁሉ የኢትዮጵያ እንዲሆን ወስኗል” ይላል፡፡ እውነታው ግን ውሎ አድሮ እንደታየው መሆኑ መንግስት ከኤርትራ ጋር በተያያዘ የሚያነሳቸው ጉዳዮች የቱንም ያህል የአሳሳቢነት ይዘት ቢኖራቸው ከጥርጣሬ የማያማልጡ መሆናቸው እንደሆነ ይገለፃል፡፡

“መንግስት ቅየራውን ለእኛ ተውት”የኤርትራ ተቃዋሚዎች ሕብረት

አምባሳደር ብርሃነ ገ/ክርስቶስ መንግስታቸው የስትራቴጂና የአቋም ለውጥ ስላደረገበት ምክንያት ሲገልፁ “በኤርትራ በኩል ኢትዮጵያን ለመበተን፣ ልማቷን ለማደናቀፍ ያልተሞከረ ነገር የለም፡፡ የቴረሪስት ኃይልን በማሰልጠን እንቅስቃሴ ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ ...” ካሉ በኋላ በአሁኑ ወቅት ግን ይህ ተግባሩ የ24 ሰዓት ሥራው በመሆኑ ስርዓቱ ሊቀጥል አይገባም ሲሉ ደመደሙ፡፡ መደበኛ ተግባሩን የኤርትራን መንግስት ከስልጣን ማስወገድ ያደረገው የኤርትራ ተቃዋሚዎች ሕብረት ግን የመንግስት ቅየራውን ነገር ለእኛ ተውት ሲል ተደምጧል፡፡ የተቃዋሚዎች ሕብረቱ ለአንድ ሳምንት ያህል አዲስ አበባ ውስጥ ባደረገው ሰፊ ጉዳዮችን የሚተነትን ጉባኤ ካነሳቸው ነጥቦች አንዱ ይኸው የኢህአዴግ መንግስት “የኤርትራን መንግስት እስከመቀየር” የሚለው አቋሙ እንደነበረ መረጃዎች አመልክተዋል፡፡ ጉባኤተኞቹ በውጭ ኃይሎች ስርዓቱን ለመቀየር የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን እንደጣልቃ ገብነት እንደሚመለከቷቸው ግልጽ አድርገዋል፡፡ የተቃዋሚዎቹ መግለጫ ባልተለመደ መንገድ በአደባባይ የሌላ አገር መንግስት ስለመቀየር መወሰኑን ለሚገልፀው የኢትዮጵያ መንግስት የመጀመርያው ቀይ መብራት ተደርጎ ተወስዷል፡፡ ጃዋር በኤርትራ የኢሳያስን መንግስት በኢትዮጵያ ጦር ገርሥሶ የተረጋጋ መንግስት መፍጠር አስቸጋሪ መሆኑን ይገልጻል፡፡ ከመጀመሪያው የኤርትራ ሕዝብ ምንም ያህል ኢሳያስን ቢጠላም፤ ለረጅም ዘመናት እንደ ጠላት ሲያያት የኖረችው ኢትዮጵያ ሀገራቸውን ስትወር ደስተኛ ይሆናሉ ብሎ መገመት የዋህነት ከመሆኑም በላይ ሌላ መዘዝም እንደሚያስከትል ያሰምርበታል፡፡ ይኸውም የኢትዮጵያ ጦር ኤርትራን መውረር የኤርትራ ብሔረተኝነት እንዲያገርሽ ማድረጉ ሲሆን ይህ ደግሞ ኢሳያስ ከተወገደ በኋላ እራሱ፤ ስልጣን የሚይዘው ቡድን እንደ የኢትዮጵያ ሎሌ ስለሚታይ፣ ተቀባይነት የሚያሳጣው መሆኑ ነው፡፡

በሌላ በኩል የዚህ ዓይነቶቹን አቋሞች አዲሱ የኢትዮጵያ መንግስት መገለጫ አድርገውም የሚገምቱ ፖለቲከኞች ሁኔታውን ቀየም ሲል በግብፅ መንግስት ላይ ይሰጡ ከነበሩ መግለጫዎች ጋር ያነፃፅሯቸዋል፡፡ “እንደተለመደው ጠ/ሚ/ር መለስ በዓለም አቀፍ ሚዲያ ላይ ቀርበው በአባይ ጉዳይ ግብፅ ኢትዮጵያን በጦርነት ልታሸንፋት አትችልም አሉ፡፡ ብዙዎች በጦርነት ዋዜማ ላይ እንዳለን አድርገው መወያየት ጀመሩ፡፡ እንደተለመደው ሌሎች ባለስልጣኖቻቸው የወረደላቸውን አቅጣጫ ተከትለው የጉንደቱን ታሪካዊ ድል መዘከር ጀመሩ፡፡ ጥቂት ቆይቶ እንደተገመተው ጉዳዩ ተንኖ ቀረ፡፡ ሁለቱም ግን በጦርነት ዙሪያ የሚያጠነጥን ቅኝት ነበራቸው፡፡ ....”

በእርግጥ ወደ ጦርነት ቢገባስ? የስትራቴጂና አቋም ለውጡ በእርግጥ ወደ ጦርነት ቢያመራስ? የሚለውን ኃሳብ ጉዳዩን በቅርበት ለሚከታተሉ ወገኖች ስጋት ማጫሩ አልቀረም፡፡ “አያምጣው እና አቶ መለስ የሚሉትን የስትራቴጂ ለውጥ ወደ ተግባር ለውጠው ኢሳያስን በኃይል ለማውረድ ወንድሞቻችንን ወደ አስመራ ከላኩ፣ መዘዙ ከፍተኛ ነው የሚሆነው።” የሚለው ጃዋር ምንም እንኳ ላለፉት አስር ዓመታት ድርቅ ባለ ፖለቲካው የሀገሪቷን ኢኮኖሚ ስላደቀቀ እና ሕዝቡን መተንፈሻ ስላሳጠው ኢሳያስን ማሸነፉ ቀላል ሊሆን ቢችልም የዚያ አይነት ጦርነት በኢትዮጵያም ሆነ በኤርትራም የውስጥ ቀውስ ሊያስከትል እንደሚችል ያሳስባል፡፡

በጦሩ ላይ የሚያስከትለውን አሉታዊ ጫና ሲገልጽም “ኢሳያስን በኢትዮጵያ ጦር ከስልጣን ማስወገድ ማለት የኤርትራን መከላከያ ኃይል መደምሰስ ማለት ነው። ይህ ደግሞ አዲሱ መንግስት ሰላም እና ጸጥታን ለማስከበር የሚያስችለው አቅም እንዲያጣ ያደርገዋል። በእንደዚያ አይነት ሁኔታ ውስጥ አሁን በቡድኖች መካከል ያለው ፍጥጫ ወደ እርስ በርስ ጦርነት ሊለውጥ ይችላል። አማራጩ የኢትዮጵያ ጦር ረዘም ላለ ጊዜ እዚያ እንዲቆይ ማድረግ ነው። ይህ ደግሞ ከላይ የጠቀስነው የኤርትራ ብሔረተኝነት በባሰ ሁኔታ ያነሳሳል።” ይላል፡፡

ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ልትወጣው ካልቻለችው ከፍተኛ የኢኮኖሚ ቀውስ አንጻር ወደ ጦርነት ሲገባ ኢኮኖሚው የበሰ መዳሸቁ እንደማይቀር የኢኮኖሚ ጠበብቶች ይገልጻሉ፡፡ ኢትዮጵያ ባለፈው ጦርነት ላይ 350 እስከ 500 ሚሊዮን ዶላር እንዳወጣች ይገመታል። የዓለም ባንክ ማስረጃ እንደሚያሳየው ከጦርነቱ በፊት ( 1996 እ.ኤ.አ) በ 12.6% እያደገ የነበረው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ጦርነት በመነሳቱ ወደ -3.5% (ኔጋቲቭ) አሽቆለቆለ። አሁንም የሚወራው ጦርነት ከተነሳ የዚያን አይነቱን ኪሳራ ማስነሳቱ አይቀሬ ያደርገዋል፡፡

በሌላ በኩል ከአስር ዓመት በፊት በአቶ ኢሳያስ እብሪት እና ድፍረት የተንገበገበው እና ምናልባትም አሰብን እናስመልሳለን በሚል ጭምር የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ የኢኮኖሚ እና የሰው ህይወት ኪሳራውን ውጦ ከአቶ መለስ ጋር ቆሞ ነበር። ዛሬም እንደዚያ ይሆናል ማለት አስቸጋሪ ነው የሚሉት ጃዋር በኑሮ ውድነት እየተጠበሰ፣ በአምባገናነዊ ስርዓት ስር የሚኖር ህዝብ ሌላ የጦርነት ጫወታ ይደግፋል ብዬ አላምንም ሲሉ ይገልጻሉ፡፡

አተርፍ ባይ አጉዳይ ላለመሆን...

የአምባገነናዊ ስርዓት መሪዎች የውስጥ ችግር ሲነሳባቸው ከውጪ ጠላት ጋር በመዋጋት የሕዝቡን ቀልብ ከውስጥ ወደ ውጭ እንዲያዘነብል ሲሞክሩ ይታያሉ፡፡ አንዳንዶቹ ይሳካላቸዋል። ሌላ ጊዜ ደግሞ መፍትሔ ብለው የዘየዱት ስልት እነሱኑ መልሶ ሲበላቸው ይስተዋላል፡፡ አርጀንቲናን ሲገዛ የነበረው ወታደራዊ መንግስት፣ የተጋፈጠውን ህዝባዊ አመጽ እና የኢኮኖሚያዊ ቀውስ ለመቋቋም በማሰብ ፎክላንድ (Falklands) ተብላ በምትጠራው ደሴት ላይ የይገባኛል ጥያቄ በማንሳት በ1982 ከእንግሊዝ ጋር ወደ ጦርነት ገባ። መጀመሪያ ላይ የሀገሪቱ ሕዝብ ቀድሞ በልቡ አዝሎት ከነበረው ቁጭት የተነሳ ቢደግፈውም፣ በማርጋሬት ታቸር የምትመራው እንግሊዝ ጦርነቱን ስታሸንፍ አርጀንቲናውያን መንግስታቸውን አፋጠጡት። ይህም የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ ቀውሱ ተባብሶ፣ አምባገነናዊውን ስርዓት ፈረካከሰው፡፡ ጃዋር መሐመድ የዚህ ዓይነቱ የተዛባ ስሌት የሚያስከትለውን ውድቀት በማስታወስ ማንኛውም መንግስት የሚከተለውን የጭንቅ መገላገያ መስመር በጥንቃቄ መፈተሽ እንዳለበት ሲመክር “የውስጥ ቀውስን ለመሸፋፈን ወደጦርነት ለመግባት የሚያስቡ መንግስታት ጥንቃቄ ቢያደርጉ የተሻለ ነው። ስልጣንን ለማጠንከር ሲሞከር ያለችውን በፍጥነት እንዳታፈተልክ መጠንቀቅ ይበጃልና!” በሚል ማስጠንቀቂያ ጭምር ነው፡፡ ...

ጉባኤተኞቹ በውጭ ኃይሎች ስርዓቱን ለመቀየር የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን እንደጣልቃ ገብነት

እንደሚመለከቷቸው ግልጽ አድርገዋል፡፡ የተቃዋሚዎቹ መግለጫ ባልተለመደ መንገድ በአደባባይ የሌላ አገር መንግስት ስለመቀየር

መወሰኑን ለሚገልፀው የኢትዮጵያ መንግስት የመጀመርያው ቀይ መብራት ተደርጎ ተወስዷል፡፡

Page 6: awramba 160

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 160 ቅዳሜ መጋቢት 17 20036

[ባለፈው ሳምንት ስለ ጆን ስትዋርት ሚል የጀመርነው ፅሁፍ ከልጅነት ህይወቱ እና ከግለ-ታሪኩ ባሻገር በ1861 ያሳተመው “Utilitarianism” ሥራ ላይ ብቻ ያተኮረ ነበር፡፡ ዛሬ ደግሞ ከነፃነት እና ከውክልና የመንግስት ዓይነት ጋር የሚያያዙትን ሥራዎቹን እንደሚከተለው ቀጥለንባቸዋል፡፡]የተሰኘው ሥራው ከሊበራል ግለኝነት (Liberal Individualism) ዘመን አይሽሬ ገለፃዎች እንደ አንዱ ሆኖ ሁል-አቀፍ ተቀባይነትን ያገኘ ነው፡፡ በጆን ስትዋርት ሚል የህይወት ዘመን ውስጥ ከየትኛውም የፅሁፍ ሥራዎቹ ይልቅ ገኖ የወጣ ነበር፡፡ ሚል ለነፃነት (Liberty) የነረበው አረዳድ በኋላ “Negative liberty” ወይም ከእንቅፋት የፀዳ፣ ገደብ የሌለበት፣ ጣልቃ የማይገባበት ነፃነት እንደሚባለው ዓይነት ነው፡፡ እንደርሱ ሀሳብ ስሙን ሊወክል የሚችለው ነፃነት የራሳችንን መልካም ነገር በራሳችን መንገድ የመፈለግ ወይም የመከተል ነፃነት ነው፤ ይህም የሌሎችን ተመሳሳዩን የማድረግ ጥረት ሳንገድብ ወይም ሳናደናቅፍ ነው፡፡ ማንም ቢሆን - ግለሰብም ሆነ መንግስት - በሌሎች ላይ የሚደርስ ጉዳትን ለመከላከል ካልሆነ በቀር በማንኛውም ምክንያት ማንኛውንም ሰው እንዳይናገር፣ ሀሳቡን በህትመት እንዳይገልፅ ወይም በድርጊት እንዳይተገብር የመገደብ መብት የለውም፤ እናም ሚል “ጉዳት” ወይም “harm” ሲል ተጨባጭ፣ መለካት የሚችል ጉዳት ማለቱ ነው፡፡ እዚህ ላይ ሚል የተረዳው የማይመስለው ችግር ይህ “ጉዳት” የተሰኘው መርህ ከትግበራው ይልቅ ሲናገሩት እጅግ ቀላል መሆኑን ነው፡፡ አንድን ሰው እራሱን ከመጉዳት እናቅበው ዘንድ መብቱ የለንም፡፡ ሙሉ ለሙሉ እራስን የሚመለከቱ ድርጊቶች ከማህበራዊ ድርጊቶች በተለየ የድርጊቶቹ ባለቤት ከሆነው ግለሰብ በቀር ለማንኛውም ሰው ግድ አይሰጡም (በድጋሚ ይህ ልዩነት ተግባራዊ ሊያደርገው በሞከረው በማንኛውም ሰው ዘንድ የመሆኑን ችግር ሚል ያወቀው አይመስልም)፡፡ በሁሉም ሰው ከተደገፈው አስተያየት አንድ ሰው ብቻ የተለየ ሀሳብ ቢኖረው እንኳን እርሱን ዝም ለማስባል ይህ ምክንያት ላይሆን ይችላል፡፡ ሁሉም ሀሳቦች በነፃነት ውይይት እንዲደግባቸው እስካልተፈቀደ ድረስ እውነት ምንድነው፣ ሀሰት ምንድነው የሚለውን ማንም ሊያውቅ አይቻለውም፡፡ ውይይትን የማይፈቅድ ቅድመ-ምርመራ አድራጊ (Censor) ማንም የሌለውን ስህተት ያለመስራት ችሎታ ይጠይቃል፡፡ እጅግ የምንጠነቀቅላቸው እምነቶች እንኳን እውቅና ለማግኘት አደባባይ ወጥተው ፉክክር እንዲገጥሙ እስካልተፈቀደለቸው ድረስ ህይወት አልባ ጭፍን እምነቶች ይሆናሉ፡፡ እውነት ከሆኑ ፉክክርን የሚፈሩበት ምንም ነገር የለም፤ ስህተት ከሆኑ ስህተት መሆናቸውን ማወቃችን እራሱ የተሻለ ነው፡፡ ሰፋ ባለ መልኩ፣ ሚል “የኑሮ ቤተ-ሙከራዎች” በማለት የሚጠራውን እሳቤ ይደግፋል፡፡ የጉዳት መርህ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ሁሉም የማህበረሰብ አባላት የትኛውንም ያህል ያልተለመደ ቢሆን በፈለጉት በማንኛውም መንገድ ያለ ጣልቃ-ገብ በመኖር የየራሳቸውን ማንነት እስከጫፍ ድረስ እንዲያጎለብቱ ሊፈቀድላቸው ይገባል፡፡ እዚህ ላይም በድጋሚ ሚል የጠቃሚያዊነት አቀንቃኝ (ዩቲሊታሪያን) ነኝ ብሎ ከሚያስበው ያነሰ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ጠቃሚነትን (utility) በተመለከተ መከራከሪያ ነጥብ እያዳበረ እንደሆነ ያምናል፤ ነገር ግን የተሻሻለ

የጠቃሚነት ዓይነት ነው፡፡ እንዲህም ይላል፡- ‹‹ጠቃሚነትን በሁሉም የሞራል ጥያቄዎች እንደመጨረሻው ጥሪ እመለከተዋለሁ፤ ነገር ግን ደረጃ በደረጃ እያደገ እንደሚሄድ ፍጡር በሰው ዘላቂ ፍላጎቶች ላይ መሠረት በማድረግ ሰፊ አግባብ ያለው ጠቃሚነት ሊሆን ይገባዋል፡፡›› -(On Liberty, Introduction)ሚል በፃፈው ላይ በዋናነት የሚንፀባረቀው እርካታ ወይም ደስተኝነት ሳይሆን እንደ እውነት፣ አእምሮአዊ መገለጥ፣ ግላዊ ጥንካሬ እና እንደ ግለሰባዊ ግለ-ምሉዕነት (self-realisation) ያሉ ነገሮችን መፈለግ ወይም መከተል ነው፡፡ ከዚህ

በተቃራኒው፣ አላዋቂነት የሰፈነበትና መቻቻል የሌለው ሕዝባዊ ምልከታ አናሳዎችን እና ግለሰቦችን በቁጥሮች ክብደት ሊጠራርጋቸው የመቻሉን እድል ይጠላል፤ ያ ትልቅ ብቃት ወደታች ሰምጦ ሊቀር ይችላል፡፡ ‹‹የግለሰባዊነት በነፃነት መዳበር የመልካም ሁኔታ ቀዳሚው መሠረት መሆኑ ከግንዛቤ ገብቶ ቢሆን፤ እንዲሁም ሥልጣኔ፣ ሥርዓት፣ ትምህርት፣ ባህል በሚሉት ቃላት ከተሰየሙት ሁሉ ጋር የተጣመረ ንጥረ ነገር ብቻ ሳይሆን በራሱ የእነዚህ ነገሮች ሁሉ ወሳኝ ክፍል እና ሁኔታ መሆኑ ከግንዛቤ ገብቶ ቢሆን፣ ነፃነት ከደረጃው ዝቅ ስለማለቱ ምንም ዓይነት ስጋት ላይኖር ይችል ነበር - (On Liberty, ch3) ምናልባትም ላይኖር ይችላል፤ ነገር ግን ይህ ከ”ዘመን አይሽሮ” ጠቃሚያዊነት (ዩቲሊታሪያኒዝም) እጅግ የተለየ ነው፡፡ የሚል አብላጫውን ያለማመን ሁኔታ “Considerations on Representative Government” በተሰኘ ሥራውም የሚተይ ነው፡፡ ቢያንስ ለራሱ ጉዳዮች ኃላፊነትን ለመውሰድ የሚያስችለውን ያህል ለሰለጠነ እና ለተቀናጀ ሕዝብ የውክልና መንግስት (representatives government) ከሁሉም የተሻለ የመንግስት ዓይነት እንደሆነ ይቀበላል፡፡ “የውክልና” መንግስት ሲል አስፈፃሚው አካል የሚመረጠውና ተጠሪነቱ (ከ)የተወካዮች ምክር ቤት የሆነበትና ይህ ምክር ቤትም በተራው የሚመረጠውና ተጠሪነቱ (በ)ለሕዝቡ የሆነበት ፓርላመንታሪ ወይም የፓርላማ ሥርዓት የሚያራምድ መንግስት ማለቱ

ነው፡፡ ከጥቂት ተጠቃሾች - ያልተማሩ፣ ወንጀለኛ እና እራሳቸውን መርዳት ከተሳናቸው - በስተቀር ሁሉም አዋቂ ሰው፣ ወንድም ሆነ ሴት ቢያንስ አንድ ድምፅ ሊኖረው እንደሚገባ ሚል ያምናል፡፡ ሴቶችን ድምፅ እንዳይሰጡ መከልከል የተወሰኑ ወንዶችን ቀይ ፀጉ ስላላቸው ብቻ እንዳይመርጡ ከመከልከል እኩል ምክንያታዊነት የጎደለው ነው፡፡ (ሚል ከእንጀራ ልጁ ከሄለን ቴይለር ጋር በመሆን በ1869 የፃፈው “The Subjection of Women” ሴቶችን ስለሚያሳትፍ ምርጫ የተደረገ ቀደምት ጥሪ ነው፡፡ የውክልና መንግስት በመደበኛው ዜጋ ዘንድ ጠንካራ ሀሳቦችን፣ ኃላፊነትን

እና ተሳትፎን በማበረታታቱ ምክንያት የተሻለ እንደሆነ ያስባል፡፡ በሌላ በኩል ፍፁም ሥልጣንን የጨበጠ (Despotic) መንግስት ተገዥዎቹን ፍላጎት አልባና ጭምት ያደርጋቸዋል፡፡ የውክልና መንግስት በራሳቸው የሚተማመኑ፣ ንቁ እና ጠንካራ አስተሳሰብ ያላቸው ግለሰቦችን፣ እንዲሁም እንዲህ ያለ ሕዝብ አንድ ለመሆን የተጣመረበትና ሥርዓት፣ መሻሻል እና መረጋጋት የሚለመልምበት ማህበረሰብን ይፈጥራል፡፡ ሆኖም የውክልና መንግስት ጉድለቶች እና አደጋዎችም አሉት፡፡ ሚል ከሁሉም በላይ ስጋት ያደረበት የአብላጫው አምባገነንነት ነው፡፡ መንግስት በቁጥር አብላጫነት ላይ ብቻ የሚመረኮዝ ከሆነ ተራነት እና አላዋቂነት በጉልብትና እና በአብርሆት (enlightenment) ላይ አይቀሬ የበላይነት ይጎናፀፋሉ፡፡ በተጨማሪም መንግስት አብላጫውን የሚያስደስቱ ፖሊሲዎችን መምረጡ አይቀሬ ነው፤ እነዚያ ፖሊሲዎች በመሠረታዊ ገፅታቸው ጠቃሚም ይሁኑ ጎጂ፡፡ ስለዚህም የፖለቲካ ሥልጣን ውክልና ከፖለቲካ ትምህርት ጋር እጅ ለእጅ ተያይዞ መጓዝ እንዳለበት ሚል አፅንኦት ይሰጣል፡፡ አባላቱ ኃላፊነት ተሰምቷቸው ድምፅ ለመስጠት እጅግ አላዋቂ ሆነው ሙሉ ለሙሉ ነፃ የሆነ የመራጭ ስብስብ ይኖራል ማለት ምክንያታዊነትን ያጣ ነው፡፡ ከፖለቲካ ትምህርቱ ስኬት ጋር በተያያዘ አንድ ሰው ከአንድ በላይ ድምፅ የሚሰጥበት (plural voting) ሥርዓት መዘርጋት እንዳለበትና ግለሰቦች ከአንድ በላይ ድምፅ ለመስጠት ብቁ መሆናቸውን

ለማሳየት የሚገመገሙበት የፈተና መዋቅር እንደሚያስፈልግ ያምናል፡፡ እንዲሁም የአናሳዎች ውጤታማ ውክልና ይረጋገጥ ዘንድ ተመራጮች የሚያገኙት መቀመጫ ከተሰጣቸው ድምፅ ጋር በተመጣጠነ መልኩ የሚሆንበትን (proportional representation) እሳቤ በማቀንቀን የመጀመሪያው ባይሆንም ከቀደምቶቹ መካከል ነው፡፡ እርሱ የሚደግፈው ውስብስብ (ዘርፈ ብዙ) ሥርዓት ቶማስ ሔር ከተባለ የለንደን ጠበቃ የተወረሰና በ1859 “A Treatise on the Election of Reprentatives, Parliamentary and Municipal” በተሰኘ መፅሐፉ የገለፀው ነበር፡፡

በግለ-ታሪኩ ከተገለፀው ከልጅነት ህይወቱ በኋላ ጎልማሳው ሚል እውቀታዊ በሆነ መልኩ መንቀሳቀስ ስለመቻሉ የህሊና ሥራዎቹ እማኝ ናቸው፡፡ እርሱም እንደሚያረጋግጠው፣ ስሜትን በሚሰባብር መንገድ የተማረው ሚል፣ ውስብስብ ባህሪው እጅግ ጥልቅ፣ ወስጣዊና ሁልጊዜ ወጥ በማይሆኑ ጠንካራ ስሜቶች የተሞላ ነው፡፡ የጠቃሚያዊነት (ዩቲሊታሪያኒዝም) እሳቤን በፍፁም ሊተወው አልተቻለውም፤ ይሁንና “እርካታ” ማለት እርሱ (ሚል) ያፀደቃቸው እንቅስቃሴዎች ናቸው በሚለው መልኩ ላለመለወጥ አልተቻለውም፡፡ ያልተገደበ ነፃነትን ያወድሳል፣ ነገር ግን ያልተገደበ ነፃነት ከሥርዓት የለሽነት እና ከብጥብጥ ይልቅ እርሱ ዋጋ የሚሰጣቸውን ውጤቶች ያስከትሉ እንደሚሆኑ ጥርጣሬ አለው፡፡ የውክልና መንግስትን እና ከሞራል አንፃር በመደበኛ ዜጎች ላይ አለው የሚለውን የማበረታታት አስተዋፅዖ ያደንቃል፣ ነገር ግን የምሁራን እና የሞራላዊ ልሂቃን ተፅዕኖን ቀጣይነት በሚያረጋግጥ መልኩ ነገሮች እንዲዋቀሩ ይፈልጋል፡፡ የሚል ድባባዊ አፃፃፍ የሀሳብ መጣረስን እና ጥበትን የሚደብቅ ሲሆን፣ እርሱም በህይወት ዘመኑ ሁሉ ስፋት ባለው አስተምህሮት ተኮር እና ዝርዝር ትምህርት የተጎዳ ነበር፤ ነገር ግን ጆን ስትዋርት ሚል ለፖለቲካ እሳቤ ያበረከቱት አስተዋፅዖ ከምንም በላይ በክርክሮች እና ሥራዎቻቸው ባንፀባረቁት ውጤት ላይ ከሚመረኮዝ - ጆን ራውልስ እና ሮበርት ኖዚክ አባል ከነበሩበት - አያሌ የፀሐፍት ስብስብ ውስጥ አንዱ ነበር፡፡

የአብላጫው አምባገነንነት የውክልና መንግስት አዳጋ

ጆን ስትዋርት ሚል /1806-73/

ማ ስ ታ ወ ቂ ያ

የጫጩት ማስፈልፈያ ማሽኖችን

ኢንኩቤተሮችን

የፖለቲካ ፈ ላ ስፎች

መጠናቸው ከትንሽ እስከ ትላልቅ •ማለትም ባለ 50፣100፣200፣300፣400፣500... •ወዘተ እንቁላል በመያዝ ጫጩቶችን ማስፈልፈል የሚችሉ የክልል ደንበኞች ሙሉ ክፍያ •በአድራሻችን ከላኩ ወይም በአካል ከከፈሉ በሚኖሩበት ከተማ ሆነው ማሽኑን የሚረከቡበትን ሁኔታ እናመቻቻለን፡፡ በብዛት ለሚያዙ የዋጋ ቅናሽ አለን•

ሻያ ኤሌክትሮ መካኒካል ቴክኖሎጂ ኃ/የተ/የግ/ማህበር

በተመጣጣኝ ዋጋ በነጠላና በብዛት እናቀርባለን ይጠይቁን መጠናቸው ከትንሽ እስከ ትላልቅ ማለትም

ስልክ 0911 69 31 02/0913 54 87 21/

እንደርሱ ሀሳብ ስሙን ሊወክል

የሚችለው ነፃነት የራሳችንን

መልካም ነገር በራሳችን

መንገድ የመፈለግ ወይም

የመከተል ነፃነት ነው፤ ይህም

የሌሎችን ተመሳሳዩን የማድረግ

ጥረት ሳንገድብ ወይም

ሳናደናቅፍ ነው፡፡ ማንም ቢሆን

- ግለሰብም ሆነ መንግስት

- በሌሎች ላይ የሚደርስ

ጉዳትን ለመከላከል ካልሆነ

በቀር በማንኛውም ምክንያት

ማንኛውንም ሰው እንዳይናገር፣

ሀሳቡን በህትመት እንዳይገልፅ

ወይም በድርጊት እንዳይተገብር

የመገደብ መብት የለውም

Page 7: awramba 160

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 160 ቅዳሜ መጋቢት 17 2003

ትውልዱን አንርገም

7

አመሻሹ ላይ ደስ የሚልና ቀዝቀዝ ያለ አየር ይነፍሳል፡፡ ወበቁ፣ ንዳድና ቃጠሎው አልፏል፡፡ ጩኸትና ግርግሩ ረግቧል፤ የእለት ውጥረቱ ሰክኗል፡፡ ጨረቃዋ ፏ ብላለች፡፡ ከቀኑ ይልቅ አመሻሹ ያምራል፡፡ እንደ ዘፋኙ፣ ‹‹ምሽቱ ደመቀ፣ ምሽቱ›› ያሰኛል፡፡ ብዙ ሰዎች ለተፈጥሮ ግዜ አንሰጥም፡፡ ስለመዝናናት ያለን ግንዛቤም እጅግ ውስን ነው፡፡ ሳይከፍሉ መዝናናት ያለም አይመስለን፡፡

በተለምዶ 22 (ማዞሪያ) ከሚባለው ሰፈር ቁልቁል ወደ ቦሌ መድሃኒዓለም በእግሬ እጓዛለሁ፡፡ ለወትሮው በዚህ መንገድ የማቀናው በታክሲ ነበር፡፡ እነሆ ዛሬ ነሸጥ ቢያደርገኝ፣ የምሽቱን ጣፋጭ አየር እየማግሁና ከራሴ ጋር እያወጋሁ አስደሳች ጉዞዬን ተያይዣለሁ፡፡ ከዓመታት በፊት እዚሁ ቦሌ ት/ቤት ስማር ከምኖርበት አካባቢ ወደ ት/ቤቱ የምመላለሰው በእግር ጉዞ ነበር፡፡ ያኔ እምብዛም አይርቀኝም፡፡ ዛሬ ግን ሁለት ታክሲዎች ይዤ እመጣለሁ፡፡ ቀድሞ አንዳፍታ በእግሬ ፉት እለው የነበረውን መንገድ ዛሬ ንክች አላደርገውም፡፡ ‹‹ቴክኖሎጂ ያቀራርባል›› ይባላል፡፡ ነገር ግን፣ የትራንስፖርት አገልግሎቱ ሲሟላ ይህ ቦታ ጭራሽ ራቀኝ፡፡ ታክሲ ሲመጣ ቅርብ የነበሩት ቦታዎች ሁሉ ቀስ በቀስ ይርቁኝ ጀመር፡፡ ስለሆነም ‹‹ቴክኖሎጂ አቀራርቧል›› ሲሉ፣ ‹‹የለም፣ ቴክኖሎጂ አራርቋል›› እላለሁ፡፡ በእግሬ 10 ደቂቃ ይወስድብኝ የነበረውን መንገድ ዛሬ ከ10 ደቂቃ በላይ በትራንስፖርት ጥበቃ አሳልፋለሁ፡፡ ቅርብ የነበረው ቦታ ጭራሽ መራቁን አስመልክቼ ሀሳቤን በግጥም ቋጥሬው ነበር፡፡ ሰዎች ‹‹ሉላዊነት›› ሲሉ እኔ ‹‹ልላዊነት›› ብዬ፡፡

ፊት ቅርብ ነበር ከቦሌ መርካቶ፣ አሁን ግን ሎንችናው፣

ታክሲው ባሱ ሞልቶ፣ ተራርቆ ቀረ ቦሌና መርካቶ፡፡

አንድ የሰማሁት ታሪክ ነበር፡፡ የሃገራችን እውቅ አትሌት ነው አሉ፡፡

በእግሩ ሲጓዝ ያዩት አንድ ሰው ማንነቱን ይለዩና የመኪናቸውን መስኮት ዝቅ አድርገው፣ ‹‹አንተ ሰው፣ ወዴት ነህ? ና ግባና በመኪና ልሸኝህ›› ቢሉት፣ ‹‹የለም፤ ስለምቸኩል በእግሬ እሄዳለሁ፤ እርስዎ ቀስ ብለው ይሂዱ›› አላቸው አሉ፡፡ እንግዲህ በዚህ አትሌት እይታ የትራንስፖርት አገልግሎቱ ያዘገያል፤ ቅርብ የነበረውን ቦታ ያርቃል ማለት ነው፡፡ ብዙዎቻችን ቀድሞ በእግራችን የምንዘልቀውን መንገድ ዛሬ ያለሚኒባስና ኮንትራት ታክሲ አንሞክረውም፡፡ የአምስት ደቂቃው መንገድ ገና በሀሳብ ያዳክመናል፡፡ ልባችንም አይነሳ፣ እግራችንም አይንቀሳቀስ፡፡ እውን ቴክኖሎጂ አቀራርቦናል?

መቼም የእግር መንገድ የሚጠቅመው ከራስ ጋር ለመወያየት፣ አካባቢን ለመታዘበ ነውና በዚህ ጉዞዬ ላይ አንድ ማስታወቂያ አየሁ፡፡ ይህን አስገራሚ ማስታወቂያ ብሄራዊ ቴአትር አካባቢና ሜክሲኮም አይቼው ነበር፡፡ አንዳንዶቻችሁም ሳታዩት አልቀራችሁም፡፡ ማስታወቂያው የሰይጣን እምነት መጽሐፍ ነው፡፡ እንዲህ ይላል፡- ‹‹ከዘመኑ የዓለም እውነታ ጋራ የሚያጓጉዘው በጥቁር ጥበብ ዘዴና በባለጥንታዊ የአስማት ቁልፍ ድግምት የሚጠቃለለው የሰይጣን ሃይማኖት ባለ 263 ገፅ ጽሑፍ በአማርኛ ተተርጉሟል፡፡›› ማስታወቂያው ይህን ይልና የአዘጋጁንና የተርጓሚውን ስም ጠቅሶ፣ ‹‹አስማት ለማሰራት የምትፈልጉ በዚህ ቁጥር ይደውሉልን›› ሲል ሰይጣናዊ እምነት በመጽሐፍና በሲዲ የቀረበልን መሆኑን ‹‹ያበስራል››፡፡

እዚህ ላይ ነው የአብዬ መንግስቱ ለማ ግጥም የሚታሰበኝ፡፡ ነፍሳቸውን ይማርና ጋሽ መንግስቱ ለማ ከዛሬ 50 ዓመታት በፊት በፃፉት ግጥም ‹‹መርፌ ትሰራለህ?›› ሲሉ ጠይቀው ነበር፡፡ ዛሬም ለእኛ ኢትዮጵያውያን የሚያስፈልገን ሙያ መርፌ መስራት ነው ወይስ አስማትና ድግምት? ከፈረንጁ ዓለም መቅዳት ያለብን ጥንቆላና አምልኮ ወይስ የአካፋና ዶማን ጥበብ? አፄ ቴዎድሮስ ነጮቹን፣ ‹‹ሕዝቤን አስተምሩልኝ፤

አሰልጥኑልኝ፤ እውቀታችሁን አካፍሉኝ፤ የእጅ ሙያተኞች ላኩልኝ›› እያሉ ሲወተውቱና ሲማጠኑ ፈረንጆቹ የፈሰሰ ውሃ የማያቀኑ የሃይማኖት ሰባኪዎችን እየላኩ ያማርሯቸው ነበር፡፡ ዛሬ ደግሞ የልጅ ልጆቻቸው እውቀትና ቴክኖሎጂውን ትተን አስማትና አፍዝ አደንግዙን እየቃረምን ነው፡፡

ስንት ሺህ ዘመናት የማረሻ ቴክኖሎጂን መቀየር ያልቻልን፣ ከዝናብ ግብርና መላቀቅ የተሳነን፣ በምፅዋትና እርጥባን የምንኖር ዜጎች በጥብቅ የሚያስፈልገን ከድህነት፣ ከበሽታና ከጉስቁልና የሚያላቅቀን ጥበብ እንጂ ጥንቆላና አስማት ነውን? መቼም ግሎባላይዜሽን የማያሳየን ጉድ የለም፡፡ እንደ ጥንብ-አንሳ (አሞራ) ውዳቂውን እየለቀሙ የሚያመጡብን ‹‹ወገኖቻችን›› መብዛታቸው በእጅጉ የሚያሳዝን ነው፡፡ በአውሮፓ እግር ኳስ ደንዝዘናል፡፡ በጫትና በመጠጥ ሱስ ደንዝዘናል፡፡ ከዚህ ድንዛዜ የሚያነቃን እንጂ ተጨማሪ መደንዘዝ ውስጥ የሚጥለንን መች ፈለግን? የሚያስፈልገን ባለራዕይ ሕዝብና ባለራዕይ መንግስት ነበር፡፡ የሰይጣን እምነት ለሃገራችን ችግር ‹‹በቡሃ ላይ ቆረቆር›› ነው፡፡

ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም ‹‹የክህደት ቁልቁለት›› በተባለ መጽሐፋቸው፣ ለአያሌ ዘመናት ባለህበት እርገጥ ወይም የእንፉቅቅ የሆነ ኑሯቸውን ታዝበው ሲጽፉ ይህን ብለው ነበር፡-

‹‹በ1860 አፄ ቴዎድሮስን ሊወጋ የመጣው በናፒየር የሚመራው የእንግሊዝ ጦር በመጓጓዣ ዘዴው ከቴዎድሮስ ጦር የተሻለ አልነበረም፤ በእንስሳት እየተጠቀመ ነው መቅደላ የደረሰው፡፡ በ1888 በአፄ ምኒልክ ዘመን የኢጣልያ ጦር ኤርትራን በቁጥጥሩ ስር አድርጎ ትግራይን አቋርጦ አምባለጌ ሲደርስ መጓጓዥው ያው አጋሰስና አህያ ነበር፤ የአፄ ምኒልክም ጦር ከአምባለጌ እስከ አድዋ ያለውን የኢጣልያ ጦር ያሸነፈው ከመሀል ሀገር በአጋሰስና በአህያ ያለውን ጭኖ ነበር፤ ከአርባ

ዓመታት በኋላ በ1928 የኢጣልያ ጦር በመሬት በጦር መኪናና በታንክ፣ በሰማይ በአውሮጵላን መርዙን እየዘራ ሲመጣ፣ የአፄ ኃ/ሥላሴ ጦር ወደማይጨው የዘመተው ያው እንደተለመደው አህያ እየነዳ ነበር፡፡ በ1860 አፄ ቴዎድሮስን ሊወጋ ወደመቅደላ ከመጣው የእንሊዝ ጦር ጀምሮ እስከ ማይጨው ጦር (ማለት ከ1860 እስከ 1928) አራት ትውልዶች ያህል በቅለዋል፤ በዚያው ግዜ ውስጥ የኢጣልያና የእንግሊዝ ትውልደች ምን ያህል መጥቀው እንደሄዱ መዘርዘር አስፈላጊ አይሆንም፡፡ የሚደንቀው ደግሞ የወያኔ ልጆች በ1982 አዲስ አበባ ሲገቡ አህያ እየነዱ ነበር አሉ! እንግዲህ ይህንን ተጨባጭና ጉልህ እውነት የምንቀበለው እንዴት ነው? ልንክደው አንችልም፡፡ የአዕምሮና የመንፈስ ችግር አለብን፡፡ በአዕምሮና በመንፈስ ኃይሉ የማይጠቀም ሕዝብ አህያ ከመንዳት ሊወጣ አይችልም፡፡››

(የክህደት ቁልቁለት፤ መስፍን ወልደ ማርያም፤ 2003፤ ገፅ 14)

በእርግጥም ፕ/ሩ በጥብቅ የሚያስፈልገን አህያ ከመንዳት የሚያወጣን እውቀት እንጂ የሰይጣን እምነትና አፍዝ አደንግዝ አይደለም፡፡ እጦታችን የጥንቆላ እጦት መች ሆኖ? ከቶም የሃይማኖት ችግር የለብንም፡፡ የትም የምንቃርመውን አግበስብሰን አምጥተን ሕዝባችን ላይ መድፋት ያለብን አይመስለኝም፡፡ ይህች ሀገር ቅራቅንቦውን ሁሉ ለቃቅመን የምናጠራቅምባት ቅርጫት መች ሆነች? የወገናችን ጥያቄ አፍዝ አደንግዝን አስማት ትሰራለህ ሳይሆን ‹‹መርፌ ትሰራለህ?›› የሚል ነው፡፡ ሃይማኖት አልቸገረንም፡፡ እስልምናው አለን፤ ክርስትናው አለን፤ በሀኢውም እንዲሁ፡፡ ከራሳችን አልፈን ለሌላው ዓለም የምናካፍለው እምነት ሞልቶናል፡፡ ‹‹የሰይጣን እምነትና የጨለማ አሰራርን፣ ድግምትና አፍዝ

እንደ አቮካዶ ሾጠጥ ብሎ እንደ ማንጎ የተሟለለው ጭንቅላቱ፣ እንዲሁም የካሮት ቅርፅ የተላበሰው አገጩና እንደ ጥቅል ጎመን እጥፍ ያለው ጆሮው ወዳጄን የፈጣሪ ሥራ ሳይሆን አትክልት ተራ ተጠፍጥፎ የተሰራ አስመስሎታል፡፡

ይህ ወዳጄ በንግግሩ መሀል እንደ እንቁራሪት የሚንቋረር ድምፅ እንዳይፈጠርበት በመስጋት አስቀድሞ ጉሮሮውን አፀዳውና አፉን አሞጠሞጠ፡፡ ደመና እንደኪንታሮት በተንጠለጠለበት ጨፍጋጋ ቀን ምን ዓይነት ብራ ወሬ ይነገረኝ ይሆን ብዬ ጆሮዬን ቀሰርኩለት፡፡

‹‹...ኢትዮጵያ ስሟ በዓለም ላይ በበጎ አይነሳም... በአንድ መፅሐፍ ላይ ስሟ ለረሀብ ምሳሌ ይሆን ዘንድ ተጠቅሷል...›› ማለት ጀመረ፤ ይሉኝታ ቢሱ ወዳጄ፡፡ ይህ ዓይነቱ ወሬ ተደጋግሞ ከመወራቱ የተነሳ እንደሰነበተ ወጥ ዕጅ ዕጅ ብሎኛል፤ አፍንጫዬም የሚሰነፍጥ ሽታውን መቋቋም አቅቶት ቀዳዳዎቹ ለመደፈን ተቃርበው ነበር፡፡

አፍንጫዬን በሶፍት ደፍኜ ልሰማው ብሞክረም የማይቻል ሆነብኝ፡፡ ወዳጄ በህይወት ያለውን ትውልድ ምንም እንዳልሰራ ወቀሰው፡፡ አፈር የበላውን ትውልድ የክብር መጎናጸፊያ አልብሶ ይኼን ትውልድ አራቆተው፡፡ መተቸት አላረካ ሲለው ዘለፈው፡፡

“አንተ አፈር የበላው ትውልድ አባል ነህ?”

“አይደለሁም” አለኝ፡፡ “የዚህ ትውልድ አባል ከሆንክ

ምን ሰራህ ታዲያ?” ብለውም የረባ ምላሽ ሊሰጠኝ ስላልቻለ መሸነፉ ገባኝና መነታረኬን አቆምኩም፡፡

ሀገሪቱ በሌላው ዓለም ጥሩ ስም እንደሌላት ያወቅነው ዛሬ አይደለም እኮ፡፡ በጣም ቆይቷል፡፡ በድርቅ፣ በሰብዓዊ መብት አያዝ፣ ነፃውን ፕሬስ፣... ባጠቃላይ በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ አደጋ ስሟ በሚገባ በመጥፎ ተራግቦላታል፡፡ በዘመናት ሲነገር የሰነበተውን ወሬ ዛሬ እንደአዲስ ነገር ማውራት በስንት “መከራ” የበሉትን ምግብ በከንቱ ማትነን ነው የሚሆነው፡፡

ብዙዎች ለሀገሪቱ ዕድገት አስተዋፅኦ ማድረግ እንዳለባቸው በመዘንጋት ወሬ በማመላለስ ብቻ ዘመናቸውን ይፈጃሉ፡፡ ሌሎቹም ከተጠያቂነት የሚያመልጡ ይመስላቸዋል

መሰለኝ “መፅሐፈ ባልቴት” ይመስል ዝም ብለው ይተረተራሉ፡፡

ሲጀመር ይኼን ትውልድ መውቀስ (መገሰፅ) ያለበት የረባ ሥራ ያልሰራ ግለሰብ አልያም ተቋም (የሚዲያም ሆነ ሌላ ዓይነት) አይደለም፡፡ ተጎልቶ ከሚውል ማኅበረሰብ ውጪ ለውጥ ያመጣ ሃያሲ ቢገስፅም ያምርበታል፡፡

አለበለዚያ ሁሉም አንደበት አለኝ እያለ፣ እንዲሁም መድረኩንና ድምፅ ማጉያውን የማግኘት ዕድሉ ስለሰመረለት ብቻ ትውልድን መርገም የለበትም፡፡ በዚያ ላይ እርግማን ያቆረቁዛል እንጂ ሲየሳድግ ታይቶም ተሰምቶም አይታወቅም፡፡

በርግጥ ይኼ ትውልድ ታሪክ የለውም? አልሰለጠነም? ለማኝና ረሃብተኛ የሆነው በማን ውድቀት ይሆን? ታሪክ ማለት ሐውልት ቀርጾ ማቆም ብቻ ነው እንዴ? መሰልጠን ወይም ሥልጣኔ የሚባለው ከአንድ ድንጋይ ቤተ-መቅደስ መፈልፈል ብቻ ነው?

ለማንኛውም ሰው ሁሉ የአስተዳደጉ ውጤት ነው፡፡ የአንድ ልጅ አስተዳደግ እንደ ግራዋ እንጨት የተጣመመ ከሆነ ሀገር የምትባለዋ ራሱ እድገቷ እንደ ግራዋ ቅርንጫፍ ውልግድ ውልግድ ያለ ይሆናል፡፡ የተወላገደ ህብረተሰብ ፈጣሪዎቹ እኛው፤ ተራጋሚዎቹም እኛው፡፡ ቀጣዩን ፅሁፍ በማንበብ ከእርግማን እንውጣ!

ልመናን የሚያበርታቱትና ሕፃናት በልመና ተኮትኩተው እንዲያድጉ ዕድሉን የሚመቻቹት የገዛ ወላጆቻቸውና አሳዳጊዎቻቸው ናቸው፡፡ አንድ ኢትዮጵያዊ ሕፃን ገና በሕፃንነቱ፣ ምናልትም ከወፌ-ቆመች አልፎ በ36 ወራቶች ሲከበብ እናትና አባቱ ልመናን ያለማምዱታል፡፡ በግልፅ ለመናገር ልጃቸውን “ለማኝ” ያደርጉታል፡፡

ይህ አስተዳደግ በተለምዶ “ድሆች” የሚባሉትን የህብረተሰብ ክፍሎች ብቻ የሚመለከት አይደለም፡፡ ሀብታም የሚባሉትም ቢሆኑ ለልመና መስፋፋት “ተጠያቂ” ናቸው፡፡ ድሆቹ ልጆቻቸውን ወደ ጎረቤት በመላክ ክብሪት ለምነው እንዲያመጡ ያደርጓቸዋል፡፡ ሀብታሞቹ እንደ ድሆቹ ልጆቻቸውን ክብሪት ባያስለምኑም፣ እናታቸው “አባታችሁ ሶደሬ እንዲወስዳችሁ ለምኑት” በማለት ተተኪው ትውልድ የሚባለው ልመናን ከአባቱ ጋር ይለማመደዋል፡፡

“እስኪ ሂድና ከእገሌ የእሳት ፍም ለምነህ አምጣ!” ለምነህ የሚለው ቃል መርዘኛ በመሆኑ የታዳጊዎቹን የራስ ቅል ይመርዛል፡፡ የተመረዘ ትውልድ ማርከሻ እስካላገኘ ድረስ እየሞተ ይሄዳል እንጂ ነፍስ አይዘራም፡፡ የአሳዳጊዎችም ሆነ የወላጆች የልጅ አስተዳደግ ካልተለወጠ ወደፊትም ለማኝ ሆነን እንደምንቀጥል እርግጠኛ ነን፡፡

በልመና ኮትኩታችሁ ያሳደጋችሁትን ትውልድ መልሳችሁ ስትወቅሱት ከሞራል አንፃር ቀላችሁ ትገኛላችሁ፡፡ አንድም ሰው ታሪክ ሰራ፣ ሚሊዮን ሕዝብም ታሪክ ሰራ የሚጠራው የሀገሪቱ ስም ነው፡፡ አንድም ሰው ለመነ፣ እልፍም ሰው ለመነ ሀገሪቱ “ለማኝ ነሽ” ከሚል ተምዘግዛጊ ቃል የምታመልጥበት ምክንያት አይኖርም፡፡

ችግሩ የአንድ ሰው ጦስ ትርፉ ለሀገር ጭምር መሆኑ ነው፡፡ አንድ ኢትዮጵያዊ በኢትዮጵያ ምድር እየለመነ ቢታይ “እገሌ የሚባል እንቶ ፈንቶ ሰው ለመነ” ተብሎ አይደለም ዜና የሚሰራው፡፡ ቢሆንማ ጥሩ ነበር፡፡ ግን በዚያ ሰው ምክንያት “ኢትዮጵያ የምትባለው ታሪካዊ ሀገር፣ ያን ሁሉ ቅርሶች የፈጠረች ሀገር ትላንት በዓለም ላይ ተፅዕኖ ማሳረፍ የቻለች ሀገር ዛሬም እየለመነች ነው” ነው የሚባለው፡፡

አንዲት ሀገር በአንድ ግለሰብ ትወሰናለች፡፡ ያ ግለሰብ ሀገሪቱን ጥላሸትም ሆነ ሽቶ ለመቀባት በቂ ኃይል አለው፡፡ በመሆኑም አንድ ሥራ ሲሰራ ሰው በመምረጥ፣ ያኛውን ህብረተሰብ ከዚህኛው ማኀበረሰብ በማበላለጥ አይደለም፡፡ ከታችኛው ተርታ ሰው እስከመጨረሻው የሀገሪቱ አስተዳዳሪ ድረስ የተወረወረው ቀስት ግቡን መምታት አለበት፡፡

እባካችሁ አታስቁን! ትላንት ማታ ሲጋራ ለመለኮስ ፈልጎ ልጁን ለላይተር “ልመና” ያሰማራ ጋዜጠኛ፣ ዛሬ ጠዋት በሬዲዮና በቴሌቪዥን እንዲሁም በጋዜጦች “ትውልዱ ልመና ውስጥ ተዘፍቋል፤ ታሪክ መስራት አልቻለም” ብሎ ቢጨቀጭቀኝ እግሬን ሰቅዬ ነው የምስቅበት፡፡ በዚያ ላይ ራሱን አየሰደበ መሆኑን ሊያውቀው ይገባልና እባካችሁ አለቦታው አታስቁን! “እናቴ” ሞታ እያለቀስኩ ጋዜጠኛው እንዲህ ያለውን የተቃረነ ዘገባ ቢያስተላልፍ፣ ለቅሶዬን

አቋርጬ እንደምስቅበት ካሁን ሊያውቀው ይገባልና እባካችሁ ሀዘናችንን ረግጠን በሳቅ እንድንንፎለፎል አታድርጉን!

ሌላው ይኼ ትውልድ አብዝቶ የሚረገምበት “ዐብይ” ጉዳይ አለ፡፡ በዚያን ዘመን የነበረው (አፈር የበላው) ትውልድ አብዛኛውን ሥልጣኔውን ያሳየው በድንጋዮች ላይ በመመርኮዝ ነው፡፡ በሌላ ቋንቋ፣ ያ ትውልድ ድንጎይ ወዳጅና ለድንጋይ ትልቅ አክብሮት የነበረው ማኅበረሰብ ነበር፡፡ አክሱም፣ ላሊበላ፣ የጀጎል ግንብ፣ የጎንደር ቤተ-መንግስትና ሌሎችም የታሪክ ቅርሶች ግድግዳቸውና ማገራቸው ድንጋይ ነው፡፡

በወቅቱ የነበረው ትውልድ ማንነቱን መግለፅ የፈለገው በድንጋይ ሊሆን ይችላል፡፡ ይኼ የግል መብቱ ነው፤ የግል ስሜቱም ጭምር፡፡ ስሜቱም ስለሆነ ድንጋይ በማንከባለልና ድንጋይ በማስዋብ፣ ድንጋይ ፀሐይ ለመሞቅ ከመቀመጫነት ባለፈ ታሪክ ሊሆን እንደሚችል አሳይቶን አልፏል - ያ ትውልድ! ግን ደግሞ የዛሬው ትውልድ ታሪክ መስራት ያለበት የግድ በድንጋይ ብቻ ነው ተብሎ መታመን የለበትም፡፡ የዚህ ትውልድ ፍላጎቱና ስሜቱ ሌላ ነገር ሊሆን ይችላል፡፡

በዚያ ላይ ደግሞ የትውልዱን ስሜትና ፍላጎት ጠብቆ ተገቢውን ሂስ መስጠት፣ ከተማረውም ካልተማረውም የሰው ዘር የሚጠበቅ ነገር ነው፡፡ አንድ ሰው ከምንም በላይ የሌላውን ስሜት መረዳት አለበት፡፡ የሌላውን ስሜት መረዳት የማይችል የትኛውንም ትምህርት በማዕረግ ያጠናቀቀ ሰው ቢሆን እንኳን ሌላ ሰው መሄስ አይችልም፡፡ እምቢ ብሎ ቢሄስ እንኳን የተማረበትን ዩኒቨርስቲ ያስገምታል፡፡ ማዕረጉንም ለጥርጣሬ ይዳርገዋል፡፡

አንዲት ሴት ካሮት መብላት ካልወደደች አልወደደችም ነው፤ አለቀ፡፡ በ”ግድ” ሴቲቱን ለመመገብ የሚደረግ ሩጫ ጠብ ያጭራል፡፡ ይኼም ትውልድ ድንጋይ ካልፈለገ አልፈለገም ነው፤ አለቀ፡፡ በዚህ ምድር ላይ የመኖር ስሜቱ የሌላቸውና በየእንጨቱ በገመድ ተንጠልጥለው ያገኘናቸውን ሰዎቻችንን በአባዲና መኪና ወደምኒሊክ ሆስፒታል ልከናቸው የለም እንዴ? ... ምክንያቱም የስሜት ጉዳይ

በሰሎሞን ሞገስ

[email protected]

‹‹መርፌ ትሰራለህ?››

ወደ ገፅ 23 ዞሯል

ወደ ገፅ 23 ዞሯል

ኮሜንተሪ

በታዲዎስ ጌታሁን

Page 8: awramba 160

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 160 ቅዳሜ መጋቢት 17 2003የ አቤቶ ወግ8

ባለፈው ሳምንት በዚህ አምድ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትራችንን አንስተናቸው ነበር፡፡ ዛሬም ደገምናቸው፡፡ መጀመሪያ አካባቢ ስቅታ ያስቸግርብኛል ብዬ በመስጋት ላላነሳቸው አስቤ ነበር፡፡ ኋላ ላይ ሳስበው ግን እንደውም

‹‹አንድ ያጣላል!›› እንዲል የሀገሬ ሰው መደጋገሜ ፍቅራችንን የሞቀ ያደርገዋል የሚለው ሀሳቤ አሸነፈኝ እና ድጋሚ እርሳቸውን ማንሳቴ ክፋት የለውም ስል ዛሬም ተመለስኩባቸው፡፡ርዕሴ ‹‹ግልፅ ያልሆነ ደብዳቤ ለክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር›› ይላል፡፡ ለምን…? መልዕክቱ ግልፅ ያለሆነ በመሆኑ ነውን…? በፍፁም አይደለም፡፡ እንኪያስ አንዳንዶች ‹‹ግልፅ ደብዳቤ…›› እያሉ የሚሰዱላቸው ደብዳቤዎች እርሳቸው የማይወዷቸውን፤ እርሳቸውም ብቻ ሳይሆኑ እኔን ጨምሮ ወዳጆቻቸው የማንወዳቸውን ጥያቄዎች እና ሀሳቦች ያዘሉ ሆነው ስላገኘኋቸው፤ ይህ ደብዳቤም ከነዛ እንደ አንዱ እንዳይታይብኝ በመስጋት ነው፡፡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር እንግዲህ የምጽፍልዎ ደብዳቤ ከሆነ አይቀር ሰላምታን ላስቀድማ…! እንዴት አሉልኝ! ቤተሰብ በሙሉ ሰላም ነው… ሰላምዎ ይብዛ አንበሳዬ…!ቤተሰብ ብዬ ከጀመርኩ አይቀር … ለመሆኑ የቤትዎ ነገር እንዴት እየሄደልዎ ነው? መቼም ‹‹ቤተሰሪ ደም የለውም›› ይሉት ብሂል በርስዎ እንደማይደርስ እገምታለሁ፡፡ ደግሞም እንዳይደርስብዎ እፀልያለሁ ‹‹ደም ከማጣት ይሰውርዎ!›› ባለፈው ሳምንት ውስጥ አንድ ጋዜጣ በአራት ኪሎ ቤተመንግስት ውስጥ ሰማኒያ ሚሊዮን ብር የሚፈጅ መኖሪያ ቤት ለርስዎ እና ለመላው ቤተሰብዎ እየተገነባ እንደሆነ ይፋ አድርጓል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ አንዳንዶች ‹‹ከግንባታው ይልቅ በጀቱን መጥራት ይከብዳል›› እያሉ ብሩ ስለመብዛቱ አስተያየት እየሰጡ ነው፡፡ ይኸው አሁን ከተማው ሁሉ ሌላ ወሬ ያጣ ይመስል የሚያወራው እሱኑ ሆኗል፡፡ ቤቱ በአራት ኪሎ ቤተመንግሰት ውስጥ ከመገንባቱ አንፃር፣ ሰማኒያ ሚሊዮን ብር ከፍጀቱ አንፃር ከወዘተ አንፃር… ጉዳዩ የሚመለከተውም የማይመለከተውም እንዳሻው እየቧለተ ነው፡፡ አንዳንዶችማ ‹‹አይመለከታችሁም!›› ብለን ስንገስፃቸው … ሰማኒያ ሚሊዮን ብር የፈጀ ቤት ሲገነባማ ሰማኒያ ሚሊዮኑም ህዝብ ይመለከተዋል፡፡ በማለት እየመለሱልን ይገኛሉ እንደነዚህ ሰዎች አባባል ለዚህ ቤት ግንባታ እያንዳንዱ የኢትዮጵያ ህዝብ ህፃን አዋቂ ሳይለይ አንድ አንድ ብር አዋጥቷል እያሉ የማይሆን ስሌት እያሰሉ ይገኛሉ፡፡ እኔ በበኩሌ ግን ኪሴን ፈትሼ ካስቀመጥኩት ብር ምንም ስላልጎደለኝ ከኔ አልወሰዱም ብዬ ተቆርቋሪነቴን አሳይቻለሁ፡፡ ሌሎችም በበኩላቸው ‹‹ጠቅላይ ሚኒስትራችን በሚቀጥለው ምርጫ አልወዳደርም ብለዋል፡፡ ታድያ ለማን ይድላው ብለው ነው ቤት የሚገነቡት?›› ሲሉ እየጠየቁ ነው፡፡ መቼም የዛሬ ሰው ቧልት አያልቅበትም አይደል? ከኒህ ቧልት ከማያልቅባቸው መካከል የሆኑት ሌሎች ደግሞ ‹‹እንግዲህማ ይሄን ሁሉ ወጪ አውጥተው ገንብተው ቢያንስ ቤቱ ሞቅ ሞቅ እስኪል ድረስ ሌላ አምስት አመት እርሳቸው ወይም ለርሳቸው የቅርብ የሆነ ሰው የጠቅላይ ሚኒስትርነቱን ቦታ ይዞ እንዲኖርበት ጥረት ያደርጋሉ እንጂ አይለቁም ማለት ነው፡፡›› እያሉ እየገመቱ ነው፡፡ የቅርብ ሰው ሲሉ የጠቀሱት ማንን ለማለት ፈልገው እንደሆነ የቱንም ያኽል ለማውጣጣት ብሞክር ሳይሆንልኝ ቀርቷል፡፡ የሆነስ ሆነና ቤቱን የማስገንባቱን ኃላፊነት ከስንት ስራ ጋር

ግልፅ ያልሆነ ደብዳቤ ለክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር!

ደርበው ባለቤትዎ እየሰሩ መሆኑን በሰማሁ ጊዜ ደስታ ፍንቅል አድርጎኝ እንዲህ ነው እንጂ ጎበዝ… ‹‹ባልና ሚስት ከአንድ በህር ይቀዳል›› ስል መተረቴን አልደብቅዎትም፡፡ የቤቱን ጉዳይ ስቋጭ የማይፈርስ የማይታደስ ፅኑ ቤት እንዲሆንልዎ እመኛለሁ፡፡እኔ የምልዎ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ሻቢያ ሆዬ ‹‹አዲስ አበባን አፈራርሼ ባግዳድ አደርጋታለሁ›› የሚል ነጠላ ዜማ ሰሞኑን እያንጎራጎረ መሆኑን ነግረውን ነበር፡፡ እርግጥ ነው የማልደብቅዎ ነገር አንዳንድ ወገኖች ይህንን በሰሙ ጊዜ የሻቢያው ሰውዬ (ስማቸውን ቄስ ይጥራውና!) በአፍሪካ

ህብረት ስብሰባም አልመጡ፣ በሚዲያም ብቅ አላሉ እንደሚባለው ለራሳቸው (ከዚህ ከጋዳፊ ነው ቀጣፊ ከተባለ ሰውዬ ቀውስ በኋላ) በጠና ታመው ሀኪም ቤት ለሀኪም ቤት እየተመላለሱ ናቸው… ታድያ ከጠቅላይ ሚኒስትራችን ጋር የት ተገናኝተው ነው አዲሳባን ባግዳድ ባላደርጋት… ብለው የዛቱባቸው? በሚል ጥያቄ ተነስተው ብዙ ብዙ ክፉ ነገሮችን ሲናገሩ ሰምቻለሁ፡፡ ብቻ በዚህ ደብዳቤ እንዲህ እንዲህ አሉ ብዬ ብል ወሬ ማመላለስ ይሆንብኛል ብዬ ለዛሬ ትቼዋለሁ፡፡ ይልቅስ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር ሻቢያ የፈለገውን ያህል አዲሳባን ባግዳድ ለማድረግ ዕቅድ ቢኖረው የፈለገውን ያህል እኛን ብቻ ሳይሆን ቀጠናውን ለማተራመስ አጀንዳ ቢይዝ የአዲስ አበባን ህዝብ ግን ለተቃውሞ የማደራጀት አቅም እንደሌለው ላረጋግጥልዎ እወዳለሁ፡፡ እንኳንስ የአዲስ አበባን ህዝብ ለተቃውሞ ሊያደራጅ ይቅርና የራሱን ሀገር ሰዎች በጥቃቅንና አነስተኛ እንኳ ማደራጀት የማይችል መሆኑ በእውነት ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ እኔ ታማኝዎም ከአንዳንድ የአዲሳባ ነዋሪዎች ለመሰለል እንደሞከርኩት ህዝቡ ለሻቢያ ክፉ ጥላቻ አለው፡፡ እንደውም አንዳንዶች የኛን ሰዎች ራሱ የሚጠሉት ድሮ ያኔ በበረሀ ለነበረው ትግል ‹‹ከሻቢያ ጋር አብራችኋል›› በሚል ቂም መሆኑን ጠቁመውኛል፡፡ እናም የአዲሳባ ህዝብ ሻቢያ እንኳንስ በኢሳያስ እና ያቺ ማናት ‹‹ሄለን መለሰ›› በተሰኘች ተወዳጅ ዘፋኛቸው ራሱ አዘፍኖ ‹‹አዲሳባን ለማተራመስ›› ነጠላ ዜማ ቢለቅ የሚሰማው የለምና አይስጉ፡፡ውድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዛሬ ይህንን ደብዳቤ ለእርስዎ ለመፃፍ ሳስብ ብዙ አውጥቼ አውርጄ ተጨንቄ እና ተጠብቤ ነው፡፡ እስከ አሁን ያነሳነው እንደው ለመንደርደሪያ ያኽል ነውንጂ ዋናው ጉዳይ ከስር አለ፡፡ ከስር ስለሚነሳው ዋናው ጉዳይስ ቢሆን እርሳቸውን ከማደክም ለሌሎች ብናገር አይቀልም ነበር? ብዬም ተጨንቄ ነበር ነገር ግን የነገሩ ቁልፍ እርስዎ ብቻ መስለው ታዩኝ፡፡ ክቡር ሆይ ምንም ነገር አይጠራጠሩኝ እኔ የመልካም ገፅታ አምባሳደር ነኝ፡፡ እንኳንስ ሌላ ቀርቶ በሀገሪቱ ታላላቅ አለማቀፍ ስብሰባዎች ሲኖሩ እንኳ እንግዶች ሀገሪቷን ‹‹የአመዳሞች ሀገር›› እንዳይሏት አደባባይ ስወጣ ፊቴን በቫዝሊን አውዝቼ የምጠብቅ፣ ቫዝሊን ካጣሁ ደግሞ ጎስቋላ ገፄን እንግዶች እንዳያዩት እስኪሄዱልኝ ድረስ ጥቅልል ብዬ ቤቴ የምውል ሰው ነኝ፡፡ የኔ መልካም ገፅታ አምባሳደርነት በዚህም አያበቃም ለበርካቶችም ይህንኑ ስሰብክ ቢመለከቱኝ በየአውቶቡስ ፌርማታው ‹‹ኢየሱስ ጌታ ነው!›› ከሚለው መንፈሳዊም ሆነ በየቤተስኪያኑ ደጃፍ ‹‹ወዮላችሁ!›› ከሚለው ባህታዊ ብበልጥ እንጂ አላንስም፡፡ ሆኖም ግን አሁን ስብከቴን የሚገዳደሩ ሁኔታዎች እየተከሰቱ ይገኛሉ፡፡ ባለፈው ሰሞን የኑሮ ውድነት ለበርካታ ትችቶች ሲያስዳርገን ‹‹ምናለ በሉ አሁን እርሳቸው አንድ መላ ባያበጁለት›› እያልኩ ስወራረድ ቆይቻለሁ፡፡ አላሳፈሩኝም፡፡ እግዜር አያሳፍርዎ! በአንድ ስብሰባ የዋጋ ተመን አውጥተው ውርርዱን እንዳሸንፍ አድርገውኛል፡፡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር እርስዎ ‹‹ይሁን›› ብለው ያልሆነ ነገር የለም፡፡ እርስዎ ይሁን ካሉ ነጋዴው ባያዋጣውም ይሸጣል፡፡ አስፈጻሚውም ባይዋጥለትም ያስፈጽማል፡፡ እርስዎ ‹‹ይሁን›› ካሉ መሬት መንቀጥቀጥ ይቆማል! የባህር መናወጥም ይፀናል! ለዚህም ነው ዛሬ እርስዎ ‹‹ይሁን›› ይሉ ዘንድ ይህንን ደብዳቤ መፃፌ… ክቡር ሆይ ባለፈው ገበያው በዋጋ ውድነት ህዝቡን ከጃፓን ሱናሜ እኩል ሲያናውጠው ተርጋጋግቶ

የነበረው እርስዎ ‹‹ይርጋ›› ስላሉ ነበር፡፡ ይኽው ዛሬ እርስዎ ትንሽ ስራ በዛብዎ መሰል ‹‹ይሁን›› ብለው ካረጋጉት በኋላ ገሚሱ ዋጋው ተመልሶ ተሰቅሏል፡፡ ገሚሱ ከገበያ ጠፍቷል፡፡ ገሚሱ… ብቻ የተረጋጋው መልሶ መናወጥ ጀምሯል፡፡ እግዜር ያሳይዎ የእግዜር ውሃ እንኳ ሳይቀር ከ200 ፐርሰንት በላይ ጭማሪ አደርጓል፡፡ ልብ ያድርጉልኝ ቢራ እና ለስላሳ ዋጋ ይቀንስ ብለው በቃልዎ እንዳላፀኑ ዛሬ ውሃ ይህንን ያኽል ጭማሪ አሳየ ሲባል እርስዎ ባይሰሙ ነውንጂ ሰምተው ቢሆንማ እንዲህ አይደረግም ነበር፡፡ እባክዎ ክቡርነትዎ ዛሬ ነገ ሳይሉ ስኳር፣ ዘይት፣

ውሃ ሳይለዩ… የሁሉም ዋጋ ‹‹ይርጋ›› ይበሉ እና እኛም ሀገሪቷ የጥጋብ ሀገር ነች ብለን አፋችንን ሞልተን እንናገር፡፡ እባክዎ… ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዋናው ለርስዎ ይህንን ደብዳቤ ያስፃፈኝ ጉዳይ ይኽውልዎጋዜጣ እና ሌሎች የህትመት ዋጋዎች እኮ የትየሌሌ ጭማሪ አደረጉ!! መቼም ለንባብ እዚች ኢትዮጵያ ውስጥ ከርስዎ የቀረበ ማንም ያለ አይመስለኝም፡፡ በአንድ ወቅት ራሱ ፌስ ቡክ በተባለው የማህበራዊ ድህረ ገፅ ላይ አንድ ወዳጃችን በአንድ ገጠር ሄዶ ፎቶ ያነሳውን ቤተ መፀሀፍት አሳይቶን ነበር፡፡ የቤተ መፀሀፍቱ ስም ምን እንደሚል ያውቃሉ? ‹‹እንደ መለስ ዜናዊ … መፀሀፍት መደብር›› አዩ ክቡር ሚኒስትር እያንዳንዱ ዜጋ እርስዎን ከመፀሀፍት ጋር እንዴት እንደሚያቆራኝዎት… ምነው እንኳ ራስዎም ባለፈው ጊዜ ‹‹ያሉኝ ንብረቶች መፀሀፍቶችና ጥቂት ሱፎች ናቸው›› አላሉም እንዴ? ታድያ ለንባብ ከርስዎ የቀረበ ማን አለ? እውነቱን ለመናገር የዛሬ ጊዜ ጋዜጠኞች ሀሳባቸውን በጋዜጣ ለመግለፅ የማይችሉበት ደረጃ ላይ ሊደርሱ መሆኑን ቢሰሙ ምን ይሉ ይሆን? መፃፍ ሱስ የሆነባቸው አንዳንድ ጋዜጠኞችማ ከንግዲህ ሀሳባችንን በህዝብ መፀዳጃ ቤቶች እንገልፅ እንደሁ እንጂ ጋዜጣ የማሳተም ነገር በዚህ ዋጋ የማይታሰብ ነው እያሉ እያማረሩ ይገኛሉ፡፡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ንባብ ዜጎችን ከመገንባት አንፃር ያለውን ጠቀሜታ ለርስዎ ለማስረዳት ብሞክር ‹‹ለቀባሪው አረዱት›› ይሆንብኛል፡፡ ደግሞም የመንገድ እና የህንፃ ግንባታ ብቻውን የትም የማያደርስ ዕድገት እንደሆነም ይሰወርዎታል ብዬ አላምንም፡፡ የእርስዎ አይነት ጎበዛ ጎበዞችንም መገንባት አለብን፡፡ የእርስዎ አይነት ጎበዝ ደግሞ የሚገነባው በአሸዋ እና በስሚንቶ ሳይሆን በንባብ ነው፡፡ አሁን እየመጣ ባለው ሁኔታ ግን ከሰዎች ገፅ ላይ የስነልቦና ንባብ ከማድረግ የዘለለ ከጋዜጦች እና መፀሀፎች ገፅ ላይ ዕውቀት ለማንበብ አቅም ያለው ሰው ያለ አይመስለኝም፡፡ ክቡር ሚኒስትር ላለፉት በርካታ አመታት የፕሬስ ነፃነት ተረጋግጧል ስንል በምድረ በረሀ ሳይቀር ሰብከናል፡፡ ሀሳብን የመግለፅ ነፃነት ተንሰራፍቷል ስንል በየጓዳ ጎድጓዳው አስተምረናል፡፡ አሁን ግን ሀሳብን የመግለጽ ነገር አደጋ ላይ ወድቋል፡፡ የሚገርሞት ነገር ሀሳብን በመግለጽ ነፃነት ላይ አንዳች የውስጥ አርበኛ የገባ ነው የሚመስለው፡፡ ይሄውልዎ ድሮ ድሮ ጋዜጣ እንኳ ቢወደድ ቡና እተፈላ ጎረቤት ከጎረቤት ተጠራርቶ መረጃ ይለዋወጥ ነበር፡፡ ዛሬ ግን ቡናውም ለአንድ ኪሎ ከመቶ ሰላሳ እስከ መቶ ሃምሳ ብር እየተሸጠ ነው፡፡ ታድያ በየት በኩል ሀሳብ ይገለፃል፡፡ ሀሳብ ገባን እኮ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር፡፡ ግድየሎትም ክቡር ሆይ በሌሎች ሸቀጣ ሸቀጦች ላይ ዋጋ ጨመረ ሲባል በስግብግብ ነጋዴዎች ስናመካኝ ቆይተናል፡፡ አሁን ግን በንባብ ዋጋ ላይ የተጨመረው ጭማሪ ልናሳብብ ልናመካኝ የምንችልበት አይደለም መንግስት የጨመረው ነውና! በእውኑ በአንባቢው ጠቅላይ ሚኒስትር የምትመራ ሀገር የንባብ ዋጋ ይህን ያህል ጨመረ ቢባል ምን ይባላል? በምንስ ይመካኛል? ስለዚህ እባክዎ ጠቅለይ ሚኒስትር በህትመት ዋጋ ላይ የዋጋ ቅናሽ ‹‹ይሁን›› ይበሉ እርሶ ይሁን ሲሉ የማይሆን ነገር የለምና!!በመጨረሻምከማቱሳላ የረዘመ የጠቅላይ ሚኒስትርነት ዘመንን ያድልልኝ (ያንስ ይሆን?) ወዳጄ አማን ያሰንብተን!

[email protected]

ክቡር ሆይ በሌሎች ሸቀጣ ሸቀጦች ላይ ዋጋ ጨመረ ሲባል በስግብግብ ነጋዴዎች ስናመካኝ ቆይተናል፡፡ አሁን ግን በንባብ ዋጋ

ላይ የተጨመረው ጭማሪ ልናሳብብ ልናመካኝ የምንችልበት አይደለም መንግስት የጨመረው ነውና! በእውኑ በአንባቢው ጠቅላይ

ሚኒስትር የምትመራ ሀገር የንባብ ዋጋ ይህን ያህል ጨመረ ቢባል ምን ይባላል? በምንስ ይመካኛል?

ስለዚህ እባክዎ ጠቅለይ ሚኒስትር በህትመት ዋጋ ላይ የዋጋ ቅናሽ ‹‹ይሁን›› ይበሉ እርሶ ይሁን ሲሉ የማይሆን ነገር የለምና!!

Page 9: awramba 160

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 160 ቅዳሜ መጋቢት 17 2003

ማ ስ ታ ወ ቂ ያ

9ኮሜንተሪ

95 በመቶው ህይወትዎ የሚመራውና የስኬታማነት አድማስዎ የሚወሰነው በሳብኮንሼስ ማይንድዎ መሆኑን ያውቃሉ? ብዙዎች መድረስ የሚፈልጉበት ደረጃ መድረስ እየፈለጉና እየተመኙ፣ እቅድ እያወጡና አላስፈላጊ ባህሪን ለመተው እየወሰኑ የማይሆንላቸው የሳብኮንሼስ ማይንዳቸውን ሀያል ጥበብ ባለማወቃቸውና 95 በመቶው ፍላጐታቸውና እቅዳቸው በዚሁ አዕምሯቸው የሚቀለበስ በመሆኑ ነው፡፡ዘማይንድ - 4 የተባለውና ሰሞኑን ታትሞ ለንባብ የበቃው የዶ/ር አቡሽ አያሌው መፅሐፍ በሳብከንሼስ ማይንድ ምንነትና አጠቃቀም ዙሪያ ሰፋ ያለ ሙያዊ ትንታኔ የያዘ ሲሆን በሰሚናሩ ወቅት የሚመረቅ ይሆናል፡፡ በዕለቱ፡-

1. 97 በመቶው ህዝብ በትክክል እንደማይጠቀምበት በሚነገርለት የሳብኮንሼስ ማይንድ ምንነትና አጠቃቀም ዙሪያ በደራሲውና ሞቲቬሽናል ስፒከሩ ዶ/ር አቡሽ አያሌው ትምህርት ይሰጣል!!2. በዘርፉ ከፍተኛ ልምድና እውቀቱ ባላቸው ሞቲቬሽናል ስፒከር የሆኑት ህንዳዊው አሳይ ዱራይ በሰብኮንሼስ ማይንድ ዙሪያ ጥናታዊ ፅሁፋቸውን ያቀርባሉ!!3. በሳብኮንሼስ ማይንድ አጠቃቀምና አስተሳሰብ ህይወታቸው የተለወጡ ሰዎች የህይወት ተሞክሯቸውን ያካፍላሉ!!4. በሳብኮንሼስ ማይንድ ዙሪያ በቪዲዮ የታገዘ ትምህርት ይሰጣል5. ስለ ሳብኮንሼስ ማይንድ ከታዳሚዎች በሚነሱ የተለያዩ ጥያቄዎች ዙሪያ ውይይት ይደረጋል፡፡

6. በሳብኮንሼስ ማይንድ ዙሪያ የተቀናበሩ አዝናኝ የኪነ-ጥበብ ዝግጅቶች ይቀርባሉ

ነፃ ሰሚናር በሳብኮንሼስ ማይንድ ምንነትና አጠቅቀም ዙሪያዘማይንድ 4 መፅሐፍ በገበያ ላይ ውሏል፤ ይመረቃል!!

ቦታ፡- ሀገር ፍቅር ቲያትር አዳራሽ ሚያዚያ 2/2003 (እሁድ ከጧቱ 2፡00-6፡00)

የመግቢያ ዋጋ፡- ካሁን ቀደም ካነበቧቸው የዶ/ር አቡሽ አያሌው መፅሐፍት አንዱን ይዘው ከመጡ በነፃ ይካፈላሉ፤ ወይም በዕለቱ ሰሚናሩ በሚሰጥበት

ቦታ አንድ መፅሐፍ ብቻ ገዝተው ሰሚናሩን በነፃ መካፈል ይችላሉ፡፡

ተጨማሪ ምርቃት፡- አንድ መፅሐፍ ይዞ የመጣ ሌሎች 3 ሰዎችን በነፃ እንዲካፈሉ መጋበዝ ይችላል!!

ድሮ በልጅነቴ ወደ ቄስ ትምህርት ቤት ካልገባሁ ብዬ የረበሽኩት ረብሻ ታወሰኝ፡፡ ወላጆቼ ጥያቄዬን ተቀብለው ት ም ህ ር ት አስጀመሩኝ፡፡ አዲስ

የነበረውን የቄስ ትምህርት ቤት አካባቢ ስለምደው እንደመጀመሪያው አልወደድኩትም፡፡ ወደ ቄስ ትምህርት ቤቱ ሂድ ሲሉኝ የፈረዱብኝ ይመስለኝ ጀመር፡፡ ለብቻዬ ሰፈር መዋሌን ደግሞ ወላጆቼ አልወደዱትም ነበር፡፡

ወደ ቄስ ትምህርት ቤቱ መሄድ የጠላሁት አካባቢውን ስለለመድኩት ብቻ አልነበረም፡፡ የኔታ (መምህራችን) ኃይለኛ ነበሩ፡፡ የሚያረፍድ ተማሪ አይወዱም፡፡ ለትምህርታችንም ትኩረት እንድንሰጥ ይገፋፉን ነበር፡፡ ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ይከታተሉን ነበር ማለት ይቻላል፡፡ በመንደራችን ሲያልፉ እንኳ ቃኘት ያደረጉ ነበር፡፡ አስታውሳለሁ ስናጠፋ ካዩን ትምህርት ቤትም ቢሆን ትንሽ ተግሳጽ እና አለንጋ ይጠብቀን ነበር፡፡ ብቻ ከሶስት ቀን እረፍት በኋላ ተመልሼ ትምህርት ጀመርኩ፡፡ እየቆየሁ የኔታን ወደድኩዋቸው፡፡ ትምህርቱንም እንደዛው፡፡ ዛሬ ላይ ሆኜ ደግሞ የየኔታ ኃይለኝነት ለምን እንደነበር ገብቶኛል፤ ውዴታቸው እስከምን እንደነበርም ተገልጾልኛል፡፡ የኔታ ምርጥ መምህር፡፡ የኔታ ምርጥ አባት፡፡

ትምህርት ቤት እንደ ስሙ ሁሉ ትምህርት መቅሰሚያ ነው፡፡ ገና በልጅነትም ቢሆን እንኳ ከአዳዲስ Õደኛ የምንተዋወቅበት፣ ከቤት ወጥተን የምንውልበት ቦታ፡፡ ይህ ቦታ (ትምህርት ቤት) የአንድን ሀገር መጻኢ ዕድል በመወሰን ረገድ ወሳኝ ድርሻ ያላቸው ዜጎች የሚፈልቁበት ነው፡፡ የማይሞተው የሰው ልጅ ማደጊያ ስፍራ - ትምህርት ቤት፡፡

የዘርፉ ምሁራንም እንደሚስማሙት፣ ትምህርት ለልማት (ለኢኮኖሚያዊ ለውጥ እና ለማህበራዊ ለውጥ) ወሳኝ ነው፡፡ እናም ትምህርት ለልማትና ለዕድገት መሠረታዊ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ትኩረት ተሰጥቶት ሊሰራበት የሚገባ መሆኑ አያጠያይቅም፡፡ ብቁና መልካም፣ ብሎም ተወዳዳሪ ዜጋ በማፍራት ረገድ ትምህርት ቤቶችና መምህራን የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳሉ፡፡

ተማሪዎችም በአብዛኛው አካባቢያቸውን ከመምሰላቸውም በተጨማሪ የእውነት አባት ብለው የሚያስቡዋቸውን መምህራኖቻቸውን ይከተላሉ፡፡ መምህራንም ሙያው የሚጠይቀውን ሥነ-ምግባር በተከተለ ሁኔታ ሊቃኙና እንቅስቃሴያቸው ሁሉ በዚህ መስመር እንዲሆን የሥነ-ምግባርም የሞራልም ግዴታ አንዳለባቸው ይታመናል፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሚስተዋለው ግን፣ መምህራን ወዴት እያመሩ ነው; ትምህርትስ እየገጠመው ያለው አደጋ ምን ያህል አሳሳቢ ነው; ሀገራችንስ ወዴት እያመራች ነው; ብለን እንድንጠይቅ ያስገድደናል፡፡ ሁሉም መምህራን ባይሆኑም የተወሰኑት የሚያደርጉት ነገር በተከበረው ሙያ ላይ ጥላ ማጥላቱ የማይቀር ነውና ሊታሰብበት ግድ ይላል፡፡

በተለይም አንዳንድ በመንግስት ትምህርት ቤቶች የሚያስተምሩ መምህራን ግብራቸው የሚያሳፍር ከመሆኑም በላይ በሙያው ላይ ያለንን እምነትና ከበሬታ እያወረደው ነው፡፡ ድሮ ድሮ መምህራን ከሚለብሱት ልብስ ንጽህናና ዓይነት ጀምሮ ሲጨነቁ ይስተዋል ነበር፡፡ ከትምህርት ቤት ውጭም ቢሆን እያንዳንዱ እንቅስቃሴያቸው ጥንቃቄ የተሞላበት እንደነበር የምናስታውሰው እውነት ነው፡፡ አሁን ግን የሚስተዋለው የተለየ ነው፡፡ ምንም እንኳን #ፋሽን$ መከተል ተገቢ አይደለም ብዬ ባላስብም አንዳንድ መምህራን ግን ለየትኛው ቦታ ምን ዓይነት ልብስ መልበስ እንዳለባቸው’ በትምህርት ቤትም ምን ዓይነት

ባህሪይ ማሳየት እንደሚጠበቅባቸው የረሱት ይመስላል፡፡

መምህራን በእያንዳንዱ እንቅስቃሴያቸው ውስጥ ተማሪዎቻቸውን ከግምት ሊያስቡ ግድ ነው፡፡ ነፃነታቸውን እየተጋፋሁ አይደለም፡፡ ጋውን ለብሶ ማስተማር የማይወድ መምህር ዩኒፎርም ልበሱ ብሎ ተማሪዎቹን የማዘዝ የሞራል ብቃት አይኖረውም፡፡ (ጋውን የመልበስን ሥነ-ሥርዓት ልብ ይLEል፡፡) በተማሪዎቻቸው ፊት ቀርበው ዕውቀታቸውን ሲያካፍሉም ያልተገቡ ተግባራትን እና የቃላት ምልልሶችን ማድረግ ክብራቸውን ያወርደዋል፡፡ አንዳንዶቹ መምህራን የእረፍት ጊዜያቸውን የሚያሳልፉባቸው ቦታዎች ሁኔታው ወዴት እያመራ ነው ብለን እንድንጠይቅ ያስገድደናል፡፡

ከላይ እንደጠቀስኩት ድሮ ለየኔታ የነበረን ክብር አሁንም ድረስ የዘለቀ ነው፡፡ እርሳቸውን ብቻ አይደለም በተለያዩ የትምህርት ደረጃዎች ያስተማሩኝ መምህራኖቼን አሁንም ድረስ አከብራቸዋለሁ፡፡ ወቅታዊ ግጭቶችም ቢሆኑ በመምህራኑ ላይ የነበረኝንና ያለኝን ክብር አልቀነሰውም፡፡ መምህራኑም ለመከበር ሳይሆን ለሙያው ያሳዩት የነበረውን ቁርጠኝነት ሳስብ ያስቀናኛል፡፡ መንፈሳዊ ቅናት፡፡

የኔታ ይወዱን ነበር፡፡ ጎበዝ ተማሪዎች እንድንሆን ያበረታቱን ነበር፡፡ ስናጠፋ ይቀጡን ነበር የቅጣቱ ደረጃና ዓይነት ቢለያይም ለኛ ጥሩ ከማሰብ የመሆኑ ነገር አያከራክርም፡፡ መምህር አባት ነው፡፡ መምህራን ተማሪዎቻቸውን ያለአንዳች መመዘኛ በእኩል መንፈስ መውደድ አለባቸው፡፡ መምከርና መገሰጽም የዕለት ተዕለት ሥራቸው ሊሆን ይገባል፡፡ ተማሪዎች ያጠፋሉ፡፡ ከጥፋታቸው መመለስ ደግሞ የመምህራንም ኃላፊነት ነው፡፡ በዚህ ረገድ ብርቱ ሥራ መሰራት አለበት፡፡ በአንፃሩ ተማሪዎችም መምህራኖቻቸውን ማክበር አለባቸው፡፡ ታላላቆቻችንን ማክበር ባህላዊም ሃይማኖታዊም መርህ ነው፡፡

በአለቆቻቸው እንዲወደዱ ብቻ የትምህርቱን ሥራ እርግፍ አድርገው ትተው በፖለቲካ ሥራ ሲጠመዱ የሚታዩ መምህራን ቁጥር ቀላል አይደለም፡፡ ማንኛውም ሰው በፈለገው የፖለቲካ ድርጅት አባል መሆንና መሳተፍ መብቱ መሆኑን ሕጉ በግልጽ ያስቀምጣል፡፡ የፖለቲካ እንቅስቃሴው ዋናውንና ግልጋሎት ለመስጠት ኃላፊነትና ግዴታ የገባበትን ሥራ ግን ማዛነፍ የለበትም፡፡ እንዲህ ዓይነቱ እንቅስቃሴ ሰሞኑን ረገብ

ቢልም በሌሎችም የመንግስት መ/ቤቶችም አንዳንድ የድርጅት አባሎች ነን ባዮች ይዘምሩት የነበረው #ጉሮ ወሸባ$ አሰልቺ ብቻ ሳይሆን አስጨናቂም ነበር፡፡ መምህራኑ ላይ ሲሆን ደግሞ በፖለቲካ ሥራው ውጤታማ ለመባል የሚተጉትን ያህል ለተማሪዎቻቸው ዕውቀታቸውን ለማካፈል አለመጣራቸው በእርግጥም ሊያሳስበን ይገባል፡፡ መምህራን የሚመዘኑት በፖለቲካ አመለካከታቸው ሳይሆን በመምህርነት በሚሰጡት ግልጋሎት ነው መሆን ያለበት፡፡

በዚህ መካከል በፖለቲካ ተሳትፎዋቸው ለመወደድና ስማቸውን ለማግዘፍ ሲሉ እርስ በእርስ የሚያደርጉት ሽኩቻ በራሱ መምህራኑ ትምህርት ፍለጋ ለሚመጡት ተማሪዎች ጊዜ እንዳይኖራቸው ማድረጉ ሀቅ ነው፡፡ በፖለቲካው መስክ የሚያገኙትን ሥልጣን ወይም ሌላ #ጥቅም$ ማጣት ስለማይፈልጉ ሙሉ ትኩረታቸውን በፖለቲካው ሥራ ላይ ማዋላቸው አይጠረጠርም፡፡ ትምህርቱ ጉድ የሚፈላበትም ይኼኔ ነው፡፡

በትምህርት ቤቶች አካባቢ በርከት ያሉ ቪዲዮ ማሳያ’ ፕሌይ ስቴሽን ማጫወቻ’ ጫት መቃሚያዎችና ሌሎች የ#ንግድ$ ቤቶች በስፋት ተከፍተው በስራ ላል መሆናቸውን እናያለን፡፡ እንዲህ ባሉ ቤቶችም መምህራኑ ደንበኛ ሆነው ከተማሪዎቻቸው ጋር ከላይ በጠቀስኳቸውና ሌሎች መሠል ቤቶች ደንበኞች መሆናቸው ይነገራል፡፡ ከተማሪዎቻቸው ጋር #አታካብድ$ #አታካብጂ$ የሚባባሉ መምህራን መበራከታቸውም ይደመጣል፡፡

መምህራኑም ተማሪዎቹም የሀገር ሀብቶች ናቸው፤ የዚህች ሀገር ዜጎች፡፡ ዜጎች ደግሞ እንዲህ ባለው ነገር ሲዘፈቁ ሀገር ወዴት እያመራች ነው ልንል እንገደዳለን፡፡ ነገስ የዚህች ሀገር ተስፋ ምንድ ነው;

ሥራቸውን በጊዜው የማያከናውኑ መምህራን ከባድ ቅጣት ሊጣልባቸው ይገባል፡፡ በመንግስት ት/ቤቶች አሁን እየሆነ ያለው ግን አካሄዱን ድጋሚ እንዲጤን ያስገድዳል፡፡ መምህራኑ በጊዜው ሥራ ላይ ባይገኙ እንኳ ያለፈውን ክፍለ ጊዜ ለማካካስ (በብዙ የመንግስት ት/ቤቶች ማካካሻ ክፍለ ጊዜዎች የተለመዱ ናቸው) ከርዕሰ መምህራኑ ወይንም እነርሱ ከሚወክሉት ሰው ፎርም ወስዶ መሙላትና ክፍለ ጊዜውን #መሸፈን$ የተለመደ አሰራር መሆኑ ይስተዋላል፡፡ ያላስተማሩትን ትምህርት ጊዜ ወስዶ ማካካስ ባልከፋ ነበር፤

ተማሪዎቹ ብዙውን የትምህርቱን ክፍል በማካካሻ እንዲጨርሱ ማድረጉ ነው ችግሩ፡፡ መምህራኑም በጊዜው አለማስተማራቸው ብዙም አለማሳሰቡ ነው ከባዱ ነገር፡፡ #ፎርሙ ካለ ምን ችግር አለ;$

ትምህርት ለልማት መሠረታዊ ነገር ነው፡፡ በትምህርት ነው የሀገር ስም መለወጥ የሚቻለው፡፡ ትምህርት ሲስፋፋ ነው ሀገር በእውቀት #የመጥለቅለቅ$ አጋጣሚውን የምታገኘው፡፡ ግን ምን ዓይነት ትምህርት; በምንስ ዓይነት መምህር; የመምህራኑን አቅምና ችሎታቸውን ማጎልበት ተገቢ ነው፡፡ ወደ መስመር መመለስም የሁላችንም ድርሻ ነው፡፡

ሙያው ክቡር ነው፡፡ መምህርነት እንደሙያ የራሱ የሥነ-ምግባር አካሄዶች (code of conducts) አሉት፡፡ ይህ መርህ ደግሞ በትክክል ሲተገበር ሙያው ይከበራል፡፡ መምህራኑ ያላከበሩትን ሙያቸውን ማንም እንዲያከብርላቸው ሊጠብቁ አይገባም፡፡ የትምህርት ማስረጃውስ #ከነሙሉ ክብሩና ጥቅሙ ጋር$ አይደል የሚለው; ዛሬ ያልገራነውን ባህሪይ ነገ ማነጽ አይቻለንም፡፡ የከፋ አደጋ ሳያጋጥመን ከወዲሁ ልናጤነው ግድ ነው፡፡

የዚህችን ሀገር መጻኢ ዕድል የሚወስኑ ተወዳዳሪና ብቁ ዜጎችን ለማፍራት ብቁ መምህራንም ያስፈልጉናል፡፡ ከሁሉ ነገር በፊትም የተማሪዎችን ማንነት ለማረቅ መምህራኑ ላይ ብርቱ ሥራ መስራት ያስፈልገናል፡፡ እዚህ ጋ አንድ እውነት ለማከል ወደድኩ፣ ትምህርት ቤቶችም ወላጆችን የሕንፃ ማሰሪያ ገንዘብ ለመጠየቅ ብቻ ሳይሆን ስለመማር ማስተማሩ ሂደት ለማወያየት ቢጋብዙዋቸው መልካም ነው፡፡ ጥራት ብለን የምንፎክርበት ነገርም መምህራንን ከማረቅ ይጀምራል፡፡ ለግጦሽ የተሰማሩ ከብቶች በእረኛቸው እንደሚዳኙት& እንደ እረኛቸው አያያዝ ፀባያቸው እንደሚገራ ሁሉ፡፡ ተማሪዎችም በመምህራኖቻቸው መንገድ ይÕዛሉ፡፡ ጥሩ መምህር ጥሩ ተማሪ፣ ጥሩ ዜጋ የመፍጠር አጋጣሚው ሰፊ ነው፡፡ ይችላልም፡፡

ኢትዮጵያችን ሆይ መልካም ዜጎች የሚኖሩብሽ ሁኚልን፡፡ የራዕይሽ ስኬት በኛ በልጆችሽ ይወሰናል፡፡ እንድንረከብሽ የሚያስችል ዕውቀትና አቅም ለመፍጠር ያስችለን፡፡ ለዘላለም የመኖርሽን ምኞት ከልባችን ያድርገው፡፡ ከቃል በዘለለ በተግባር የምንኖርልሽ ያድርገን፡፡

የኔታን የሚያስናፍቁት #ሰሞንኛ$ መምህራን

በአብርሃም ተስፋዬ

Page 10: awramba 160

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 160 ቅዳሜ መጋቢት 17 2003እ ን ግ ዳ10

እንግዲህ ጋዜጠኛ እንደመሆንህ ቃለምልልሱን ሙያዊ በሆኑ ጥያቄዎች ዙሪያ ብንጀምር፤ እንደሚታወቀው ከ1983ቱ የመንግስት ለውጥ በኋላ ኢትዮጵያ ውስጥ ነፃ ፕሬስ ሲፈቀድ የመጀመሪያዋን የግል ጋዜጣ ለንባብ ያቀረብኸው አንተ ነህ 18 ዓመት ወደ ኋላ ልመልስህና ያኔ የነበረው ድባብ እንዴት ታስታውስዋለህ?

አዎ እንግዲህ የመጀመሪያዋ የግል ፕሬስ ጋዜጣ ያቋቋምኩት እኔ ነኝ፡፡ እሷም “ኢትኦጲስ” ነች፡፡ በዛን ጊዜ በእኛ ውስጥ የነበረው ስሜት ይህ ሕዝብ ለብዙ ሺህ አመታት የታፈነ ህዝብ እንደመሆኑ፤ ከዘመናት በኋላ የመተንፈሻ ቀዳዳ ሲከፈት በርትተን እስከ መጨረሻው መቀጠል አለብን የሚል ፅኑ እምነት ነበረን፡፡ ይህንንም ያኔ በስልጣን ላይ የነበሩት የኢህአዴግ አመራሮች ይረዳሉ በሚል ተስፋ ነው፡፡ ነገር ግን እነሱ እኛ እንዳሰብነው ሊረዱን አልቻሉም፡፡ ከዚች ጋዜጣ ሁለተኛ እትም አንስቶ ነው ኢትዮጵያ ውስጥ በነፃ ፕሬስ ላይ የክስ መዓት ማዝነብ የተጀመረው:: ያኔ ለቃቅመው ማዕከላዊ እስር ቤት ከተቱን፡፡ ከዚያን ጊዜ አንስቶ በርካታ ፈተናዎችን እየተጋፈጥን ቀጠልን፡፡ በነገራችን ላይ ይህ ታሪክ የሚመሳሰለው ከተማሪዎች ንቅናቄ ጋር ነው፡፡ እንዴት ያልከኝ እንደሆነ በአፍሪካ የተማሪ ንቅናቄ እውን የሆነባት የመጨረሻዋ አገር ኢትዮጰያ ናት፡፡ እንደሚታወቀው በሌሎች የአፍሪካ አገሮች የተማሪ ንቅናቄዎች የተጀመሩት ቀደም ብሎ ቢሆንም ኢትዮጵያዊያን ተማሪዎች ግን በጣም አርፍደው ነው ወደ ንቅናቄው የገቡትና ንቅናቄውንም እውን ያደረጉት፡፡ ሆኖም አርፍዶም ቢነሳ ደማቁን ታሪክ በመፃፍ ረገድ ውጤታማ ነበር፡፡ የኢትዮጵያ ፕሬስም ታሪክ እንደዛው ነው፡፡ ምንም እንኳን ከሌሎቹ ዘግይቶ መጨረሻ ላይ የጀመረ ቢሆንም በአፍሪካ ውስጥ ደማቁ የነፃ ፕሬስ ተጋድሎ ታሪክ ያለው ኢትዮጵያ ውስጥ ነው፡፡

ከ1997 ዓ.ም በኋላ የተከሰተው ሁኔታስ እንዴት ታስታውሰዋለህ?

የ1997 ሁኔታ የተለየ ነው፡፡ ፕሬሱ በብዙ ፈተናዎች ሲያልፍ የዚህ ሁሉ ጫፍ ምርጫ 97 ላይ ሲቋጭ ትመለከታለህ፡፡ ምርጫውን ተከትሎ በ1998 መጀመሪያ ኢትዮጵያ ውስጥ የነበሩ የነፃ ፕሬስ ውጤቶች ሙሉ ለሙሉ የተዘጉበት አሳዛኝ ታሪክ እናገኛለን፡፡ ይህ እርምጃ በአፍሪካም ሆነ በአለም ደረጃ ተወዳዳሪ የለውም ብንል ማጋነን አይሆንም፡፡ ከ1998 ጀምሮ እስከ 2000 ዓ.ም ድረስ እንግዲህ ምንም ነገር ያልነበረበት የጨለማ ጊዜ ልትለው ትችላለህ፡፡ ከ2000 ዓ.ም ጀምሮ የ”አዲስ ነገር” እና የ”አውራምባ ታይምስ” ጋዜጦች መምጣት ፕሬሱ በፊት ወደነበረበት የነፃነት ደረጃ እንዲመለስ ማድረግ ባይቻል እንኳን በብዙ ችግሮች ውስጥ አንባቢ መረጃ እንዲያገኝ በማድረግ ረገድ እንዲሁም ክፍተቱን በመሙላት ብዙ ጥረቶች ተደርገዋል፡፡

ሰሞኑን በማተሚያ ቤት የተደረገው የዋጋ ጭማሪስ አሉታዊ ተፅእኖው ምንድነው ትላለህ?

ከተለያዩ ዘገባዎች ለመረዳት አንደቻልኩት ይህ ጭማሪ የፕሬሱ አሳዛኝ ዕጣ ፈንታ መገለጫ ነው፡፡ አንድ ጋዜጣ ከሰባት ብር በላይ ለአንባቢ ካልቀረበ በስተቀር መቀጠል የማይቻልበት ደረጃ ላይ እንደተደረሰ ያሳያል፡፡ መጠነኛዋን የብርሃን ጭላንጭል ጠፍታ እስከናካቴው ወደ ድቅድቅ ጨለማ ተመልሰን እንዳንገባ ያሰጋል፡፡ እውነት ለመናገር ከዚህ የዋጋ ጭማሪ ጋር በተያያዘ አንድ ያልተመለሰልኝ ጥያቄ አለ፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ከማተሚያ ቤቱ ኃላፊዎች ማብራሪያ ካልተሰጠ በስተቀር ለመቀበልም ይቸግራል፡፡ የማተሚያ ቤት ወረቀት ወደ አገር ውስጥ የሚገባበት የአገባብ ሂደት በቅርብ ስለማውቀው ነው መቀበል የቸገረኝ፡፡ የብርን የምንዛሬ ተመን ማነስ (Devaluation) ከሆነ ለጭማሪው ምክንያት ወረቀቱ ካለበት አገር ታዞ፣በመርከብ ተጓጉዞ፣ ከወደብ ኢትዮጵያ ድርስ ገብቶ ማተሚያ ቤት ለመድረስ ብዙ ወራቶች ይፈጃል፡፡ አሁን በመሃል ያለው ጊዜ ያየን እንደሆነ ግን ጥቂት ሳምንታት

በአሁኑ ዘመን አንድ የአገር መሪ 20 ዓመት ስልጣን ላይ መቆየት የለበትም

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ

አንጋፋው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በኢትዮጵያ የነጻ ፕሬስ ታሪክ ውስጥ የጎላ ሚና አለው፡፡

የመጀመሪያዋ የነጻ ፕሬስ ውጤት ከሆነችው ‹‹ኢትኦጲስ›› አንስቶ ለመጨረሻ ጊዜ እስከሰራባቸው

ምኒልክ፣ አስኳልና ሳተናው ጋዜጦች ድረስ በኢህአዴግ መንግስት ላይ የሰላ ትችት በመሰንዘር

ይታወቃል፡፡ በዚህም የኢትዮጵያን እስር ቤቶች በተደጋጋሚ ጎብኝቷል፡፡ የ1997ቱን ምርጫ

ተከትሎ በተፈጠረው ቀውስ ከባለቤቱ (አለም አቀፍ ተሸላሚ ሰርካለም ፋሲል) ጋር ለእስር ተዳርጓል፡

፡ ከቃሊቲ መልስ የህትመት ፍቃድ ቢከለከልም በውጭ በሚገኙ ድረገጾች አማካኝነት በየሳምንቱ

ሀሳቡን ይገልጻል፡፡ ሰሞኑን የሰሜን አፍሪካው ህዝባዊ አመጽ ከኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ ጋር

እያመሳሰለ ለንባብ ያበቃቸው ጽሁፎቹ በኢትዮጵያ መንግስት ዘንድ አልተወደዱለትም፡፡ የፌደራል

ፖሊስ ከፍተኛ ኃላፊ ‹‹አንተን ማሰር ሰልችቶናል፤ ከድርጊትህ የማትታቀብ ከሆነ መንግስት እርምጃ

ይወስድብሀል›› ሲሉ ማስጠንቀቂያ እንደሰጡት በሚዲያዎች ይፋ ካደረገ ወዲህ በአገር ውስም

በውጪም መነጋገሪያ ሆኗል፡፡ እሱ ግን ‹‹ማስጠንቀቂያውን የሰጡኝ ኃላፊ የተግባር እንጂ የቃላት

ሰው አይደሉም፤ ከልባቸው ነው የነገሩኝ ማስጠንቀቂያውንም ከምር ወስጄዋለሁ፡፡ መጻፌን ግን

አላቆምም፡፡ የሚወሰድብኝ እርምጃም ካለ ለዴሞክራሲ የሚከፈል መስዋዕትነት ነው የሚሆነው››

ይላል፡፡ ባልደረባችን ዳዊት ከበደ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ አነጋግሮታል፡፡

Page 11: awramba 160

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 160 ቅዳሜ መጋቢት 17 2003 11እ ን ግ ዳ

ብቻ ናቸው በመሀከል ያሉት፡፡ በአዲሱ የምንዛሬ ዋጋ ከሩሲያ ወይም ከህንድ ታዞ በምን አይነት ፍጥነት አዲስ አበባ ሊገባ እንደቻለ ለማመን ተቸግሬአለሁ፡፡ ስለዚህ በዚህ ፍጥነት ለዚያውም የፕሬሱን ህልውና በሚፈታተን መልኩ ጭማሪ ማድረጉ ምናልባት በሰሜን አፍሪካ ያለውን ሕዝባዊ እንቅስቃሴ በመፍራት ሆን ተብሎ የጋዜጦች ቁጥርና የስርጭት መጠን ለመቀነስ እንደተፈለገ ያሳያል፡፡ ደግሞም ካለው ስጋት አኳያ ዋናው ምክንያት ይህ ይመስለኛል፡፡

በኢትዮጵያ የነጻ ፕሬስ ታሪክ ውስጥ የአሁኑ አይነት ጭማሪ ታይቶ አይታወቅም፡፡ በዚህ አስቸጋሪ የኑሮ ውድነት ላይ እንደገና በአንባቢ ላይ ጭማሪ ማድረግ ከባድ እንደሚሆን ጥርጥር የለውም፤ እንደው ምን መደረግ አለበት ትላለህ? አንድ አስገራሚ የራሴ ተሞክሮ ልንገርህ፡፡ የመጀመሪያዋ ነፃ ጋዜጣ “ኢትኦጲስ” ዋጋዋ 0.60 ሳንቲም ነበር፡፡ በማተሚያ ቤቶች ላይ ጭማሪ ተደረገና ወደ አንድ ብር ከፍ ማድረግ ግድ ሆነ፡፡ በዛ ወቅት “ህዝቡ እንዴት በአንድ ብር ገዝቶ ያነባል” ብለን በጣም መደንገጣችንን አስታውሳለሁ፡፡ በወቅቱ በመፅሔትና ጋዜጣ ስራ ላይ ከተሰማሩ ሌሎች ጋዜጠኞች ጋር ተመካክረን “መንግስት በወረቀት ላይ የጣለው ታክስ ሊያነሳ ይገባል” የሚል አቋም ላይም ደረስን፡፡ ምክንያቱም ይህ አይነቱ አሰራር በሌሎችም አገሮች ላይ የተለመደ ነው፡፡ ለህብረተሰቡ በጣም መሰረታዊ በሆኑ ሴክተሮች ላይ መንግስት ተመሣሣይ እርምጃ ይወስዳል፡፡ ይህንን ታሳቢ አድርገን በወቅቱ ጥያቄያችንን ለመንግስት አቀረብን፡፡ በወቅቱ የነበረው ጥያቄ በጋዜጦች ላይ ብቻ ሳይሆን ደብተር፣ መፅሐፍና ሌሎች ወሳኝ ነገሮችንም ጭምር የሚመለከት ነበር፡፡ መንግስት ግን ጥያቄአችንን ሲሰማ ሳቀብን፡፡ እኛ ግን ተስፋ አልቆረጥንም በ1998 ዓ.ም ፕሬሱ መቃብር ውስጥ እስከባበት ጊዜ ድረስ አጀንዳውን እንደ አጀንዳ ይዘን ገፍተንበታል፡፡ ወደ ጥያቄህ ስመለስ አሁንም ቢሆን የጋዜጣ አሳታሚዎች ተደራጅታችሁ ጉዳዩን ለመንግስት ሃላፊዎች ማቅረብ አለባችሁ፡፡ ምክንያቱም ስለ ወረቀት ስናወራ የምናወራው ስለ ጋዜጣ ብቻ አይደለም ስለ መፅሐፍ፣ ስለ ደብተርና ስለ ሌሎች መሰረታዊ ነገሮች ነው፡፡ አንድ ሰው በዳቦ ብቻ አይኖርም፡፡ የመንፈስ ምግብ እውቀት ነው፡፡ ስለዚህ በመንግስት በኩል አንድ እርምጃ መወሰድ ያለበት ይመስለኛል፡፡

ከዚሁ ጋር አያይዤ አንድ ጥያቄ ላንሳ፡፡ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ም/ኃላፊ የሆኑት አቶ ሽመልስ ከማል ዛሬ ለወጣው ሰንደቅ ጋዜጣ (ቃለምልልሱ የተደረገው ባለፈው ረቡዕ ነው) በሰጡት አስተያየት “ጭማሪው ማስታወቂያ ያላቸው ጋዜጦችን አይጎዳም” ብለዋል፡፡ ይህ አስተያየት ከፕሬስ ነጻነት አንጻር እንዴት ትገመግመዋለህ? አስተያያታቸው “ፕሬሱ ቢጠፋ አንቆጭም” የሚል መልዕክት ያዘለ ይመስላል፡፡ እኔም አስተያየታቸውን አይቼ አዝኛለሁ፡፡ ለአገር የሚያስብ መንግስት ነፃ ፕሬስ ሲጠፋ ሊቆጨው ይገባል፡፡ እሳቸው ግን በርካታ ፕሬሶች ቢጠፉ አንቆጭም፤ የራሳችን የሆኑ ትንሽ ጋዜጦችን ይዘን ወደፊት መራመድ እንችላለን የሚል መልዕክት ለማስተላለፍ እንደፈለጉ ነው የገባኝ፡፡ እሳቸው ባሉት መስፈርት የምንሄድ ከሆነ ለ80 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ህዝብ አንድ የአማርኛ ጋዜጣና ሁለት የእንግሊዝኛ ጋዜጦች ብቻ ናቸው የሚቀሩት፡፡ ይህ ለ80 ሚሊዮን ሕዝብ ይበቃል ብለው በቅንነት ከልባቸው መከራከር ይችላሉ? አይመስለኝም፡፡ በቅንነት ነገሮችን ከመረመርን በአልጄሪያ ከ100 እና ከ150 በላይ ጋዜጦች አሉ፡፡ ኡጋንዳ ውስጥ ከ20 በላይ የግል ሬዲዮኖች አሉ፡፡ ይህ በመሆኑ አልጄሪያም ኡጋንዳም አልተጎዱም፡፡ ቱኒዚያን ያመሰው የሕዝብ ማዕበል አልጄሪያን ዘሎ ነው የሄደው፡፡ ከሊቢያና ከግብፅ ጋር ሲነፃፀር ሕዝቡ በተወሰነ መልኩም ቢሆን መፈናፈኛ ስላገኘ ነው፡፡ በአጠቃላይ ካለው ነባራዊ ሁኔታ አንፃር አስተያየታቸውን ስገመግመው አቶ ሽመልስ ተሳስተዋል ባይ ነኝ፡፡ ስለ ሰሜን አፍሪካ አንዳንድ ነጥቦች ካነሳህ አይቀር በእነዚህ አገሮች ላይ ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ ጥቂት ነገሮች ላንሳልህና እስኪ እንደ ጋዜጠኛ ከቱኒዚያ ጀምሮ ያለውን ሁኔታ እንዴት ተከታተልከው?

የቱኒዝያው ማንም ያልጠበቀው ዱብዕዳ ነው ማለት ይቻላል፡፡ የሰሜን አፍሪካ አገሮች በተለይ ደግሞ ቱኒዚያ በፈረንጆቹ አጠራር Stable (የተረጋጋች) አገር ነበረች ማለት ይቻላል፡፡ ከአፍሪካና ከአረቡ አለም አገራት አኳያ ስታነጻጽራቸው ከአውሮፓ ጋርም ቅርበት ስላላቸው የሰሜን አፍሪካ አገራት Progressive (የሚያድጉ/ተራማጅ) ናቸው፡፡ ለምሳሌ ቱኒዚያን ስትመለከታት ከአረብነት ይልቅ ወደ ፈረንሳዊነት (በጂኦግራፊ ብቻ ሳይሆን በአስተሳሰብም በዝንባሌም) የምትጠጋ አገር ነች፡፡ እናም እነዚህ የሰሜን አፍሪካ አገሮች በጣም የሚሞካሹና እንደሞዴልም የሚወሰዱ ነበሩ፡፡ ሕዝቡም Secular ነው፡፡ በሰሜን አፍሪካ ውስጥ ሃይማኖት እና ፖለቲካ ስር የሰደደ ነው፡፡ ግልፅ የሆነ የወሰን ምልክት (Demarcation) ያለበት አካባቢ ስለነበረ ማንም አልጠበቀም፡፡ በቱኒዚያ ከተነሳ በኋላ ወደ ሌሎች አገሮች ይዛመታል ብሎ ማንም የጠረጠረ አልነበረም፡፡ እኔም ራሴ በኢንተርኔት ላይ ሁኔታውን በስፋት ስከታተልና በጊዜው የሚሰጡትን ትንታኔዎች ስመረምር ያው ከቱኒዚያ ያልፋል የሚል ግምት አልነበረኝም፡፡ ቢሆንም ቤን ዓሊ ሲወርድ ተቃውሞው በቤን አሊ የሰልጣን መልቀቅ ይደመደማል ብሎ ማንም አልጠበቀም፡፡ …ተዓምር የተፈጠረው መቼ ነው ካልከኝ፡፡ ፕሬዚዳንት ቤን አሊ በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ ተኩስ እንዲከፈት ለኢታማዦር ሹሙ ትዕዛዝ

መቀመጫዎች አገሪቱ ውስጥ ላለው የታመመ፣ የተጓለደለ የፖለቲካ ስርዓት መገለጫ ነው፡፡ ስለዚህ በቀላሉ ሕዝቡ አይቶ ሊረዳው የሚችለው ነገር ነው፡፡

በእነዚህ የሰሜን አፍሪካ አገራት ያለው የሰራዊቱ አደረጃጀትስ ከኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ ጋር እንዴት ታነጻጽረዋለህ?

በቱኒዚያም በግብፅም ለውጥ ሊመጣ የቻለው ሰራዊቱ በሕዝብ ላይ አልተኩስም በማለቱ ነው፡፡ ግብጽን ያየህ እንደሆነ ሙባረክ ከሞላ ጎደል ለ30 ዓመት የመሩት መንግስት በተግባር ወታደራዊ መንግስት ነው፡፡ የሲቪል መንግስትነቱ በስም ብቻ ነበር፡፡ ምክንያቱም አብዛኞቹ ሚኒስትሮቻቸውን የተመለከትን እንደሆነ በ30ዓመት ሂደት ውስጥ ወታደሮች ነበሩ፡፡ የወታደሩ ጥቅማጥቅምና ሁኔታ በዚህ ብቻ አይደለም የሚገለፀው፡፡ ግብጽ ውስጥ ሁለት አይነት መንግስት ነው ያለው እስኪባል ድረስ የግብፅ ሰራዊት በግብፅ ውስጥ የነበረው ሚና በመንግስት ውስጥ የሚገኝ መንግስት /State with state/ ነበር፡፡ በግብፅ ኢኮኖሚ ውስጥ አንዱ ትልቁ ነጋዴ የጦር ሰራዊት ነው፡፡ ትላልቅ የንግድ ተቋማት የሚያንቀሳቅሰው የጦር ሀይሉ ነው፡፡ ደግሞም ኩባንያዎቹ እጅግ በጣም አትራፊዎች ናቸው፡፡ ሙባረክ አንድም ቀን እነዚህን አትራፊ የንግድ ተቋማት ልመርምር /ኦዲት ላስደርግ/ ብለው አያውቁም፡፡ እነዚህን ከፍተኛ ጄኔራሎች አንድም ለ30 ዓመት በስልጣን ላይ ያቆያቸው ይህንን ችለው መኖራቸው ነው፡፡ በግብፅ ውስጥ ስለ መንግስት ለውጥ ከተነሳ የግብፅ ሰራዊት በተለይም ከፍተኛ ጀኔራሎች ከሙባረክ በላይ ምንም የተሻለ ነገር ሊያስቡ አይችሉም፡፡ ከሙባረክ የተሻለ ሊያደርግላቸው የሚችል ምንም ነገር የለም፡፡ ማግኘት የሚችሉትን ነገር በሙሉ ሙባረክ ሰጥቷቸዋል፡፡ በመጨረሻው ሰዓት ላይ ግን ሰራዊቱ ከሙባረክና ከአገሩ አንዱን እንዲመርጥ ሲገደድ አገሩንና የአገሩን ሕልውና መርጧል ማንም ከዛ በፊት የነበረ ተንታኝ እንደዚህ አይነት ምርጫና አቋም ለመውሰድ ህሊና ያለው የግብፅ ጄኔራል አለ ብሎ ለመናገር አልደፈረም፡፡ ወደ ተቃዋሚዎች ብትሄድ፣ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ብትሄድ፣ ከግብፅ ጋር የጠበቀ ግንኙነት የነበራቸው ከግብፆች ጋር የቆሙ አሜሪካኖች ጋር ብትሄድ እንደዚህ አይነት ሃሳብ የሚሰጥህ ተንታኝ ጨርሶ አታገኝም ነበር፡፡ በመጨረሻ ሰዓት ላይ ግን ከጥቅማቸው ይልቅ ህሊናቸውን አስቀድመዋል፡፡ ከራሳቸው ጥቅም ይልቅ አገራቸውን አስቀድመዋል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ሰራዊት፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት ከፍተኛ መኮንንኖች፣ የጦር አዛዦችና ጄኔራሎች በኢህአዴግና በአገራቸው መካከል መምረጥ የሚገደዱ ከሆነ እኔ አገራቸው እንደሚያስቀድሙ ትንሽም ብትሆን ጥርጣሬ የለኝም፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ በርካታ ትንታኔዎችን በየሳምንቱ ውጭ በሚገኙ የተለያዩ ድረ-ገፆች ትሰጣለህ፡፡ በሰሜን አፍሪካ የተፈጠረው አይነት ክስተት በኢትዮጵያ ሊከሰት የሚችልባቸውን አጋጣሚዎች ብዙ ጊዜ ዘርዝረሀል፡፡ በእነዚህ ጽሁፎችህም ምክንያት በፖሊስ ኮሚሽን እንደተጠራህና ማስጠንቀቂያም እንደተሰጠህ በተለያዩ ሚዲያዎች ገልጸሀል፡፡ በተለይ አንድ የተቋሙ ከፍተኛ ኃላፊ ‹‹አንተን ማሰር ሰልችቶናል ከድርጊትህ የማትታቀብ ከሆነ እርምጃ ይወሰድብሀል›› እንዳሉህም ተናግረሀል፡፡ ‹‹የህግ ስርዓትን በተከተለ መልኩ ክስ ቀርቦብህ በፍርድ ቤት ትቀጣለህ›› ለማለት ነው ወይስ ምን አይነት እርምጃ ነው? የሚል ጥያቄ የሰነዘሩ አንባቢዎች ገጥመውኛልና ብታብራራው?

እንግዲህ እሳቸው በግልፅ ነው ያስቀመጡልኝ “በሕግ አይደለም የምንጠይቅህ” ብለውኛል፡፡ አሁን በቀጥታ ነው የምገልፃቸው፡፡ “በሕግ አይደለም፣ አንተን ማሰር ሰልችቶናል ነው ያሉኝ” ከዚህም ባሻገር ‹‹በምርጫ 97ን ወቅት እንደሆነው የደሃ ልጅ አይሞትም በዚህ አገር ላይ የምትመኘው አይነት የግብፅና የቱኒዚያ አይነት ረብሻ ቢነሳ የድሃ ልጅ አይሞትም፡፡ አንተ ላይ ነው እርምጃ የምንወስደው፡፡ እንድታውቀው ይሄ የመንግሰት ውሳኔ ነው፡፡ አያደርጉትም ብለህ እንደምትጠራጠር ይገባኛል ግን እኔ የምመክርህ የመንግስት ውሳኔ መሆኑን እንድትረዳ ነው›› ብለው ነው የነገሩኝ፡፡ እንዲያውም መጨረሻ ላይ ውይይታችንን የዘጋነው እጃቸውን እያወዛወዙ ተጠንቀቅ! ተጠንቀቅ! በማለት ነው፡፡ እና አንተ በጠየቅከኝ አይነት መልኩ አይደለም፡፡ ይሄ ማስጠንቀቂያውን አኔ ከምር ነው የምወስደው፡፡ ከዚህ በፊትም እንዳልኩት ማስጠንቀቂያውን የሰጡኝ ኃላፊ የቃላት ሰው አይደሉም፡፡ የፊታቸው ገፅታ፣ ሁኔታቸው፣ የቃላት ሰው እንዳልሆኑና ለዛቻ ያህል ብቻ የሚናገሩ ሰው እንዳልሆኑ፣ ሲናገሩኝም ደግሞ በደንብ ያስታውቃል፡፡ ሰውየው የድርጊት ሰው ናቸው፡፡ ብዙ ዓመታትን በታጋይነት እንዳሳለፉ የሚያስታውቁ ናቸው፡፡ ይሄ እንግዲህ ማስጠንቀቂያ ደርሶኛል፡፡ እንደ ማስጠንቀቂያ አድርጌ ከምር ወስጄዋለሁ፡፡ ሁልጊዜም ያሳስበኛል፡፡ ሆኖም ግን እኔ መክፈል ካለብኝ የሚከፈለውን ዋጋ መክፈል አለብኝ ብዬ ወስኛለሁ፡፡ እስክንድር እንግዲህ የቤተሰብ ኃላፊ ነህ፡፡ የአንድ ልጅ አባትም ነህ፡፡ ልጃችሁም የተወለደው ሁለታችሁም (አንተም ባለቤትህም) እስር ቤት

በአሁኑ ዘመን አንድ የአገር መሪ 20 ዓመት ስልጣን ላይ መቆየት የለበትም

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ

ወደ ገፅ 23 ዞሯል

ሲሰጥ ነው፡፡ እዚህ ላይ ነው የሰሜን አፍሪካ ታሪክ የተለወጠው ምናልባትም ደግሞ የአንባገነኖችን ፍፃሜ እውን ከሆነ የምንመለሰው እዚህች ቦታ ላይ ነው…፡፡ ኢታማዦር ሹሙ አልተኩስም አለ፡፡ (ምናልባት እግዚአብሔር ጣልቃ ገብቶ መሆን አለበት) ቤን አሊም ዓለምም እኩል ደነገጠ በ48 ሰዓታት ውስጥ የቱኒዚያ፣ የሰሜን አፍሪካ ምናልባትም የአለም ታሪክ ተለወጠ ማለት ነው፡፡ በነገራች ላይ በሰሜን አፍሪካ የተፈጠረውን ክስተት የምናመሳስለው ወደኋላ ተመልሰን ከበርሊን ግንብ መፍረስ ጋር ነው፡፡ ያን ጊዜ እንደዚሁ የዲሞክራሲ አብዮት በምስራቅ አውሮፓ በቀድሞ ሶቪየት ህብረት ውስጥ እንደዛው ሳይታሰብ እንደቀልድ ለመከሰት በቅቷል፡፡ የአውሮፓንም ታሪክ አንዴ ለውጦ አልፏል፡፡ እውነት ለመናገር የአውሮፓን ታሪክ ብቻ ሳይሆን ከዛ በኋላ የላቲን አሜሪካም ሆነ የእስያ በርካታ አገሮች ዲሞክራሲያዊ የሆኑት ከዛ በኋላ ነው፡፡ በአፍሪካ ውስጥም ጥቂት አገሮች ዴሞክራሲያዊ የሆኑት በዛ ሰበብና ውጤት ነው፡፡ አሁን ወደ ሰሜን አፍሪካ በምንመጣበት ጊዜ የአረቡንም ዓለም በእርግጥ እየለወጠው ነው፡፡ ይኼ ምንም አያጠራጥርም፡፡

ከቱኒዝያ በኋላ በሌሎችም በርካታ አገሮች ተቃውሞው እንዲቀጣጠል ያደረገው የቱኒዝያ ወኔ ብቻ ነው የሚሉ ተንታኞች የመኖራቸውን ያህል የአመታት ቅድመ ዝግጅት ውጤት ነው በማለት (ለምሳሌ በግብጽ ከስምንት አመት በፊት መጀመሩን ያወሳሉ) ወደ ሌሎች አገሮች መዛመቱን በተመለከተ ምን ትላለህ? ግብፅ ላይ ተመሳሳይ አብዮት መከሰቱ የቱኒዚያው ለግብፅ ምሳሌው ነው፡፡ የግብፅ ደግሞ ለመላው አረብ ምሳሌ ሆኗል፡፡ አረቦች አይነተኛ ምሳሌና አይነተኛ ሞዴል አድርገው የሚመለከቷት ግብፅን ነው፡፡ ስለዚህ የአረቡ አለም ተለውጧል፡፡ ስለዚህ አሁን ጥያቄው የዲሞክራሲ አብዮት ወደ ጥቁር አፍሪካ ይዛመታል ወይ ነው፡፡ አሁን በዓለም ብቸኛዋ የአምባገነንነት ምሽግ አፍሪካ ነች፡፡ በአህጉር ደረጃ ማለቴ ነው፡፡ (ይህንን ያልኩበት ምክንያት በዚህች አህጉር ዲሞክሪሲያዊ ያልሆኑት አገሮች ዲሞክራሲያዊ ከሆኑት አገሮች በቁጥር ብልጫ ስላላቸው ነው) ስለዚህ የሁሉም ሰው፣ የሁሉም ተንታኞችና መንግስታት ጥያቄ ወደ ጥቁር አፍሪካ ይሸጋገራል ወይ? የሚል ነው፡፡ ወደ ጥቁር አፍሪካ የሚሸጋገር ከሆነ ደግሞ የሚጀምረው በኢትዮጵያ እንደሆነ በአገር ውስጥም በውጪም ያሉ የተለያዩ ተንታኞች ይስማሙበታል፡፡

አመጹ ወደ ጥቁር አፍሪካዊያን የሚሸጋገር ከሆነ የሚጀምረው ኢትዮጵያ ላይ ነው ብለው ተንታኞቹ ግምታቸውን ሲሰጡ ምን አይነት ነጥቦችን በማስቀመጥ ነው?ለዚህ አንዱ ምክንያት ከቅርብ ጊዜ ታሪካችን ጋር የተቆራኘ ስለሆነ ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ በጥቁር አፍሪካ ውስጥ ኢትዮጵያ በህዝብ ቁጥር ሁለተኛና ትልቅ ከሚባሉት አገሮች መካከል አንዷ መሆኗ ነው፡፡ ግብፅ በአረቡ አለም ውስጥ ያላትን ቦታ፣ ኢትዮጵያ ደግሞ በጥቁር አፍሪካ በተለይ ደግሞ ከስነ-ልቦና አኳያ (የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ መሆኗ በቅኝ ግዛት ያልተገዛች ብቸኛ ጥቁር አፍሪካዊ አገር ስለሆነች) ለውጡ ወደ ኢትዮጵያ የሚመጣ ከሆነ፤ ከግብፅ ወደ ሌሎቹ የአረብ አገሮች እንደተስፋፋው ሁሉ ከኢትዮጵያም ወደ ጥቁር አፍሪካ አገራት ይስፋፋል፡፡ በዘርፉ የተሰማሩ አጥኚዎችና ምሁሮች የሚሉት የሄንኑ ነው፡፡ እኔም በእነሱ ትንታኔ እስማማለሁ፡፡

እንግዲህ ‹ወደ ኢትዮጵያ የሚዛመት ከሆነ› በሚለው ነጥብ ስንነጋገር ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ነባራዊ ሁኔታም መመልከት ተገቢ ይሆናልና ሁኔታውን ከኢትዮጵያ ጋር ስናቆራኘው ኢትዮጵያ ውስጥ ለመከሰት ያለው ዕድል ከአገራቱ ነባራዊ እውነታ አንጻር በንጽጽር ብታስቀምጥልን? ስምንት ነባራዊ ሁኔታዎች አሉ፡፡ ሰፋ ባለ መልኩ ማሕበራዊና ኢኮኖሚያዊ የሆኑ ነባራዊ ሁኔታዎች እንዲሁም ፖለቲካዊ ነባራዊ ሁኔታዎች ብለን በሁለት ልንከፍላቸው እንችላለን፡፡ በሰሜን አፍሪካ የህዝብን ተቃውሞ ለማቀጣጠል ዋነኛ ምክንያት የሆነው የዋጋ ግሽበትና የስራ አጥነት ችግር ነው፡፡ እነዚህን ሁለት ግብዓቶች በኢትዮጵያ ውስጥ ስትመለከት ከሰሜን አፍሪካ በተባባሰ ሁኔታ ነው ያለው፡፡ ለዚህ አንድ በጣም ቀላል ማስረጃ ልስጥህ ኢትዮጵያኖች ወደ ግብፅ የሚሄዱት ለስራ ፍለጋ እስከ 20ሺህ ብር እየተጠየቁና እየከፈሉ ነው፡፡ ይሄ የሚያሳየው በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የስራ አጥነት ከግብጽ እጅግ የባሰ መሆኑ ነው፡፡ ወደ ሊቢያ ለመሄድ እስከ 50ሺህ ብር ያህል የሚከፈል ይመስለኛል፡፡ እርግጥ ወደ ሊቢያ ብዙ ጊዜ የሚኬደው ወደ አውሮፓ ለመሻገር ነው፡፡ ግን ባለው መረጃ ብዙዎቹ ሊቢያ ውስጥ ይቀራሉ፡፡ ስለዚህ እነዚህ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ግብዓቶች የምንላቸው ኢትዮጵያ ውስጥ በባሰ ሁኔታ ነው ያሉት፡፡ ይህንን ግምት ውስጥ በማስገባት ነው ኢትዮጵያ ውስጥ ይዛመታል የሚል ግምት እየተሰጠ ያለው፡፡ ሌሎቹ ስድስት ግብዓቶች ደግሞ ፖለቲካዊ ናቸው፡፡ ከሙስና ስንጀምር ምንም እንኳን ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ሙስና በአፍሪካ ደረጃ ስንመለከተው ዝቅተኛ ሊባል የሚችል ቢሆንም በኢትዮጵያ ደረጃ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ ነው የመጣው፡፡ አንዱ ሕዝቡን የሚያበሽቀው ሙስናው ከታች ካለው ይልቅ እላይ ባሉት ባለስልጣኖች አካባቢ የተባባሰ ነው፡፡ በጣም ተባብሷል፡፡ እንዲያውም በግብፅ የሰሜን አፍሪካን የተመለከትክ እንደሆነ ሙስናው ዕላይ ካሉትም እታች ባሉት በጣም የተባባሰ ነው ብለህ መከራከር ትችላለህ፡፡ እኛ አገር ግን ተገላቢጦሽ ነው፡፡ በሕዝቡ ውስጥ

የሚፈጠረው ስሜት የከረረ ነው የሚሆነው፡፡ እላይ ባለ አካባቢ ሙስናወ አለ፡፡ ዱላው ግን የሚያርፈው “ሙስናን እየተዋጋን ነው” እየተባለ ታች ባሉት ላይ ነው፡፡ ዋናው ሙስናውን የሚፈፅሙት ከሞላ ጐደል የሚነካቸው እንደሌለ ነው በአብዛኛው ሕዝብ ውስጥ ያለው ግንዛቤ፡፡ አንዱ ይሄ ነው፡፡ ሁለተኛው አንድ ፓርቲ በስልጣን ላይ ለረዥም ጊዜ የመቆየቱ ሁኔታ ስንመለከት፡፡ በግብፅም ሆነ በቱኒዚያ ስልጣን የያዙ ፓርቲዎች ከ20 ዓመት በላይ ነው በስልጣን ላይ የቆዩት፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ገዢ ፓርቲም ከጥቂት ወራት በኋላ 20 ዓመት ይደፍናል፡፡ በእነዚህ ሕዝባዊ ተቃውሞ በተፈጠረባቸው የሰሜን አፍሪካ አገሮች ፓርቲዎቹ ስልጣን ላይ መቆየት ብቻ ሳይሆን የመሪዎቹ ስልጣን ላይ የመቆየቱ ነገር አንዱ ትልቅ የሕዝብ ብሶት የፈጠረ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥም በተመሳሳይ መንገድ ነው ኢህአዴግ ስልጣን ላይ የቆየው፡፡

እዚህ ላይ ላቋርጥህና አንድ ጥያቄ ላንሳ ከዛ አያይዘህ ትመልስልኛለህ፡፡ የኢህአዴግ አመራሮች በተደጋጋሚ የሚጠቅሷቸው አገሮች አሉ (ጃፓንና ስዊድንን የመሳሰሉ) በእነዚህም አገሮች አንድ ፓርቲ ለረጅም ጊዜ ስልጣን ላይ ይቆያል በሚል ከዚሁ ጋር አያዘህ እንድትመልስልን ስለፈለኩ ነው

አንድ ፓርቲ ለረዥም ጊዜ ስልጣን ላይ የሚቆይባቸው ምዕራባዊያን አገሮች አሉ፡፡ ራሳቸው ጠ/ሚኒስትሩም በተደጋጋሚ በምሳሌነት የሚያነሱት ጃፓንና ስዊድንን ነው፡፡ የስዊድንና የጃፓንን ነባራዊ ሁኔታ ስትመለከት ገዢ ፓርቲዎቹ ስልጣን ላይ ለረዥም ጊዜ ይቆዩ እንጂ ጠቅላይ ሚኒስትሮቻቸው ከአምስት ዓመት በላይ ስልጣን ላይ አይቆዩም 10 ዓመት ስልጣን ላይ የቆየ የስዊድሽ ጠ/ሚኒስቴር እኔ በግሌ ሰምቼ አላውቅም፡፡ ትንሽ ሪሰርች ለማድረግ ሞክሬያለሁ፡፡ በጃፓን ታሪክ አምስት ዓመት ስልጣን ላይ የቆየ ጠ/ሚኒስትር አንድ ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ ምንም እንኳን በአንድ ፓርቲ የቆየባቸው ዲሞክራሲያዊ አገሮች ቢሆንም ውስጡ ለውጥ አለ፡፡ እንግዲህ ቅድም ወደ ጀመርኩት ሀሳቤ ስመለስ በሦስተኛ ደረጃ ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ነው፡፡ ቱኒዚያም ግብፅም ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት የተገደበባቸው አገሮች ናቸው፡፡ ኢትዮጵያም ከዚህ አንጻር ካየነው ትብሳለች እንጂ አትሻልም፡፡ በተለይ ከግብፅ ጋር ስናነፃፅራት በጣም ወደኀDላ ነች፡፡ ግብፅ ውስጥ ጋዜጦች የተሻለ ነፃነት አላቸው፡፡ ኤሌክሮኒክስ ሚዲያዎች የተሻለ ነፃነት አላቸው፡፡ በእኛ አገር የሚታየው አረብሳትም ቢሆን አብዛኞቹ ፕሮግራሞቹ ከግብፅ የሚተላለፉ ናቸው፡፡ ስለዚህ በዚህም ደረጃ የኢትዮጵያን ነባራዊ ሁኔታ ስንመለከተው ከሰሜን አፍሪካ አገራት በባሰ ሆኖ ነው የምናገኘው፡፡ አራተኛው የመደራጀት ነፃነንትን የሚመለከት ነው፡፡ ይኼን ስንል የሲቪክ ተቋማት እንቅስቃሴ ኢትዮጵያ ውስጥ ገደብ ተጥሎበታል፡፡ ይሄ ቀጥታ የተኮረጀው ከሩሲያ (የፑቲን አስተዳደር) ነው፡፡ አምስተኛው ምክንያት በተፅዕኖ ምክንያት የተቃዋሚዎች መቀጨጭ ነው፡፡ እንግዲህ በእርግጥ ተቃዋሚዎች በቱኒዚያም በግብፅም ከኛ አገር የተሻሉ አይደሉም፡፡ እርስ በእርስ የሚናከሱ ናቸው፡፡ የውስጥ ድክመት ያለባቸው ናቸው፡፡ ወደ ሕዝብ መግባት ያልቻሉ ናቸው፡፡ ይኼ ድክመታቸው እንደተጠበቀ ሆኖ ግን ለመቀጨጫቸው ለመዳከማቸውና የሞት አፋፍ ላይ ለመድረሳቸው ዋነኛው ምክንያት የመንግስት ጭቆና ነው፡፡ የመንግስት ተፅዕኖ ነው፡፡ በኢትዮጵያም ውስጥ ያለው ሁኔታ የዚህ ፎቶ ኮፒ ነው፡፡ የኛ ተቃዋሚዎች የውስጥ ድክመት የለባቸውም ብሎ የሚመሰክርላቸው የለም፡፡ ይኼ እንደተጠበቀ ሆኖ ግን በመንግስት በኩል ከፍተኛ ተፅዕኖ እንዳለባቸውና ያለባቸውን ችግር እንዳባባሰባቸው፤ ይሄንን ደግሞ ሕዝብን ቅር እንደሚያሰኘው የታወቀ ነው፡፡ ስድስተኛው በጣም መሠረታዊው የምንለው ከፖለቲካና ነባራዊ ሁኔታዎች አንፃር የፍትሐዊ የምርጫ ስርዓት ጉዳይ ነው፡፡ አሁን በተመሳሳይ ደረጃ ሳይሆን በተባባሰ ሁኔታ ነው ያለው፡፡ እነዚህ ስድስት ነባራዊ ሁኔታዎች ተጠቃልለው መገለጫቸው ፓርላማ ውስጥ ካሉት 547 መቀመጫዎች አንዱ ብቻ በተቃዋሚዎች እጅ መሆኑ ነው፡፡ ግብፅም ውስጥ ሙባረክ የሚመሩት ገዥው ፓርቲ ወደ 90 በመቶ ያህል መቀመጫ ነበራቸው፡፡ ቤን አሊ የሚመሩት ፓርቲም 92 በመቶ የፓርላማ መቀመጫ ተቆጣጥሮ ነበር፡፡ ፓርላማ ውስጥ ያለው የተጋነነ የገዥው ፓርቲ

Page 12: awramba 160

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 160 ቅዳሜ መጋቢት 17 2003

ማ ስ ታ ወ ቂ ያ

12

“እውነቱን ለመናገር በስሜም ሆነ በፎቶግራፌ ቴምብር ስለመዘጋጀቱ ፈጽሞ አላውቅም፣ አንድ ግለሰብ ቢያንስ ጉዳዩን ለእኔ ሳያሳውቅ በእኔ ስም ቴምብር የማተም ስልጣን እንዳለው

አድርጎ ማሰቡ እጅግ ያስገርማል፡፡ በእርግጥ ይህ ተፈጽሞ ከሆነ የሚጣራ ጉዳይ ይሆናል፡፡ እኔ የግለሰቦችን ተክለስብእና በማጉላት ጉዳይ ጨርሶ አላምንም፡፡ የእኔንም ሆነ የሌሎችን ተክለስብእና በማጉላት ተግባር ላይ ተጠምጄም አላውቅም፡፡ ዛሬ፣ በድሮ ዘመን ይደረግ እንደነበረው አይነት የመለስን

በርካታ ፎቶግራፎች በተለያዩ የኢትዮጵያ ቦታዎችም ሆነ በመንግስት መስሪያቤቶች ተሰቅሎ የምትመለከቱ አይመስለኝም፡፡ እኔ በፍልስፍናዬ እንዲህ አይነቱ የግለሰቦችን ስብዕና የማጉላት

አስተሳሰብ በጽኑ እቃወመዋለሁ፡፡ ትርጉም አልባነቱ ግለሰቦችን ለሚያመልኩ ሰዎች ብቻ ሳይሆን መመለካቸው ተገቢ እንደሆነ

አድርገው ለሚቀበሉ ግለሰቦችም ጭምር ነው፡፡ ለሁለቱም ወገኖች ከሰብአዊነት የወጣ አስተሳሰብ ነው፡፡

ይህ ፖስተር የሚገኘው በስቴድዮም ቤተዛታ ሆስፒታል አጠገብ ሲሆን የፌደራል ወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትር ከዲኬቲ ኢትዮጵያና ከኢትዮጵያ ወጣቶች ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር ያሰራው ነው

ኤልሻዳይ በተሰኘ ግብረሰናይ ድርጅት ተዘጋጅቶ በመስቀል አደባባይ ኤግዚብሽን ማዕከል በር ላይ ተሰቅሎ የሚገኝ

በልደታ አልሳም ህንጻ አካባቢ ለምርጫ ቅስቀሳ ሲባል ተሰቅሎ የሚገኝ

በደቡብ ክልል፣ሐዋሳ ከተማ ለግንቦት 2002ቱ የምርጫ ቅስቀሳ የተሰቀለ ቢል ቦርድ

p Ç T@ S ´ “ —አቶ መለስ በአደባባይ ስለተሰቀሉ ፖስተሮቻቸው ምን አሉ?

ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊየዛሬ ሁለት ሳምንት በጽ/ቤታቸው ለውጭ ጋዜጠኞች መግለጫ

በሰጡበት ወቅት ከተናገሩት የተወሰደ

Page 13: awramba 160

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 160 ቅዳሜ መጋቢት 17 2003

p Ç T@ S ´ “ —

አ ፍታ113

ነው?ብዙ ነገር አግኝቻለሁ፡፡ ራሴን፣ የምፈልጋቸውን ነገሮችና ከምንም በላይ ለረዥም ጊዜ አጥብቄ ስፈልገውና ስፀልይበት የነበረውን ምንም ነገር ላይ መሠረት ያላደረገውን ፍቅርን (Unconditional Love) ፈልጌ አግኝቻለሁ ብዬ አስባለሁ፡፡ ብዙ ነገር ደግሞ ገና ይቀረኛል፡፡ ይቀጥላል፡፡የኒያና የውበት ሥራ ሥልጠና ማዕከል ምን እየሰራ ይገኛል?ማዕከሉ ከመጀመርያው በውበት ሥራ ሥልጠና ፍቃድ አውጥቶ የተንቀሳቀሰ፣ ብዙ ሥራ የሰራ፣ ያንቀሳቀሰና አሁንም እየሰራ የሚገኝ ት/ቤት ነው፡፡ አሁን ይበልጥ ያተኮርነው ለመማር ካላቸው ፍላጎት ባሻገር፣ ሕይወታቸውን ሊቀይሩ የሚችሉ፣ ነገር ግን የገንዘብ አቅምን ያጡ ልጆች በዚህ ሙያ እንዲያድጉ በማድረግ ላይ ነው፡፡ ልጅሽ የኦቲዝም ችግር ነበረበት፡፡ እንዴት ነው? የጆይ ኦቲስቲክ ማዕከል ተጠናክሯል?ጆጆ [ልጇ] በጣም ደህና ነው፡፡ ትልቅ ለውጥ አለው፡፡ እሱና እኔ ደስተኞች ነን፡፡ በብዙ የሰዎች ፀሎት ይመስለኛል ከፍተኛ ለውጥ አምጥቶ ዛሬ አድጎ 19 ዓመት ሞልቶታል፡፡ እኔም ጋሼ እያልኩት ሲሆን፣ እኩያ ጓደኞቹን እየፈለገ ነው፡፡ ሌሎችም በማዕከሉ ያሉ ልጆች ለውጥ አላቸው፡፡ ማዕከሉም እያደገና ጥሩ ነገር እየሰራ በመሆኑ በብዙ ልጆች ላይ ለውጥ እያመጣን ነው፡፡ እኛም ይበልጥ እያወቅን አዳዲስ ነገር እየፈጠርንላቸው እንገኛለን፡፡ በጆይ ማዕከል ጥሩ ነገር እየሰራንና

ዘሚ ለዘሚ ራሷን እንዴት ትገልፃለች?ዘሚ ዘሚ ነች፡፡ ለምክንያት የተፈጠረች ሰው ነችም ብዬ አስባለሁ፡፡ ሁሉም ሰው የተፈጠረበት የራሱ ምክንያት አለው፡፡ ምክንያቴ ደግሞ ወደ እዚህ ዓለም መምጣትና ወደ ዓለም የመጣሁት ለሌሎች ወገኖች፣ ለሀገርና ለዓለም የምችለውን ነገር አስተዋፅኦ ለማድረግ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ ራስን፣ ውበትን፣ እውነትን፣ ሕይወትን ፍለጋ ወዘተ እየተባለ ... ‹‹ፍለጋው አያልቅም›› እስከሚባል ድረስ ተዘፍኗል፡፡ ሕይወት ሁሌም በፍለጋ የተሞላች መሆን አለባት?እ ... ሕይወት ስለሆነ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡ ምክንያቱም ሕይወት እንቆቅልሽ በመሆኗ ዛሬን እንጂ ነገን አናውቅም፡፡ ዛሬን ያወቅነው ደግሞ ዛሬን በመኖራችን ነው፡፡ ሁሉም ነገር እየሆነ ያለው በአጋጣሚ ነው፡፡ ሁልጊዜ ቆም ብለን እናስባለን፡፡ እንፈልጋለን፡፡ ፍለጋ ሁሌም አለ ብዬ አምናለሁ፡፡ ራስህን ማነኝ? ምን ስሰራ ከረምኩ? ወዴት ነው የምሄደው? በማለት ትጠይቃለህ፡፡ ይኼ ሁሉ ፍለጋ ነው፡፡ ሁሉም ፍለጋዎች ምርምሮች ናቸው፡፡ ምርምርህ አያልቅም፡፡ የሰው ልጅ ሁሌ መፈለግ አለበት፡፡ የሚጥመውም ሁሌ ፍለጋ ውስጥ ሲኮን ነው፡፡ የሚያገኛቸው ነገሮች አሉ፡፡ ብዙ ያገኘናቸውና የጨበጥናቸው፣ እንዲሁም የሚቀሩ አሉ፡፡ ፍለጋ ከቆመ ደግሞ የሕይወት ጣዕሙ ይጠፋል ብዬ አስባለሁ፡፡ ፍለጋ እስከሞት የማያቆም ከሆነ፣ ዘሚ ከፍለጋዋ ምን አገኘች? ምን እየፈለገች

ብዙ ብዙ ልጆችን እያሰተማርን ነው፡፡ እነርሱም እየበዙ ነው፡፡ ማዕከሉ በጣም ትንሽ ቢሆንም፣ የወላጆች ተሳትፎና ስለችግሩ ያለው የግንዛቤ ደረጃ እያደገ ነው፡፡ በዚህ በጣም ደስተኞች ነን፡፡በአንድ የቴሌቪዥን ቶክ ሾው ላይ የቁንጅና ውድድር ማድረግ ተገቢ አለመሆኑን በግልፅ ስትናገሪ አድምጫለሁ፡፡ ምክንያትሽ ምን ነበር?በትክክልና በእርግጠኝነት ውድድሩ አያስፈልግም፡፡ እንኳን የውበትን የምንም ነገር ውድድርን አልወድም፡፡ አልደግፍምም፡፡ ከራስ ጋር መወዳደር በቂ ነው፡፡ ሁሉም ሰው በጎ ነገር ስላለው በችሎታው መኖር ይኖርበታል፡፡ ዓለማችንን ያበላሸናት በውድድር ይመስለኛል፡፡ ዓለም ቆንጆ የምትሆነው ሁላችንም እኩል መራመድ ስንችል ነው፡፡ አንዱን ለማስበለጥና አንዱም ለመብለጥ በሚሮጥበት ጊዜ ብዙ ሰዎችን ኋላ ጥሎ መሄድ አለ፡፡ ብዙ ሰው ወደኋላ መቅረቱ ደግሞ ይጎዳናል፡፡ ሁላችንም ውቦችና ቆንጆዎች ነን፡፡ ከዛ በላይ መሄድ አንችልም፡፡ ውበትን ለውድድር የምታቀርበው አይደለም፡፡ አይቀርብም፡፡ ውበትን ልናሳየውና ልናደንቀው እንችላለን፡፡ ነገር ግን ባልፈጠርነው ሥራ ነው የምናወዳድረው፡፡ ያ የፈጣሪ ሥራ ሲሆን የፈጣሪን ሥራ ደግሞ ማወዳዳር አንችልም ብዬ አምናለሁ፡፡ ለቁንጅና ውድድር ምን ያህል ነው የምናወጣው ብለህ ስታይ ከበስተጀርባው ብዙ ደስ የማይሉና አስቀያሚ ነገሮች አሉ፡

ወደ ገፅ 16 ዞሯል

‹‹እያዳንዳችን ውስጥ ዘረኝነት አለእከሌ እከሌ ሳይባል ነፃ ሆነን ከመረመርነው እናገኘዋለን››

ወ/ሮ ዘሚ የኑስ

የኒያና የውበት ሥራ ሥልጠና እና የጆይ ኦቲስቲክ

ልጆች ማዕከል መስራች፣ ባለቤትና አስተማሪ፣

እንዲሁም የሁለት ልጆች እናት ነች፡፡ ‹‹ማንም

እንዲሰጠኝ ሳልፈልግና ሳልጠብቅ እኔና እኔ

ስናወራ የዶክተሬት ማዕረግ ለራሴ እንድሰጥ

ራሴ ፈቀደችልኝ - የዛሬ 15 ዓመት፡፡

በቀጣይም፣ በመጪው ጥቅምት 6/2004

በሚውለው የልደት ቀኔ ላይ ለራሴ

የፕሮፌሰርነት ማዕረግን እሰጣለሁ፡

፡ ከሕይወትና ከአካባቢዬ ራሴን

አስተምራለሁ፡፡›› ካለችንና ስለወቅታዊ

የአረብ ሀገራት ሁኔታና ስለኢትዮጵያ

ፖለቲካ በነፃነት፣ በግልፅ ከምታወራው፣

ውበትን መስራት እንጂ ማወዳደርን

ከምትነቅፈው ወ/ሮ ዘሚ የኑስ ጋር አንዳፍታ

ቆይታ ያደረገው ኤልያስ ገብሩ፣ አንዳፍታን እንዲህ

አሰናድቶልናል፡፡

ዳ ሰ ሳ

ሪያድ አብዱልወኪል [email protected]

በየዓመቱ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ አዘጋጅነት የሚሰናዳው የመጻሕፍት ዐውደ-ርዕይና የሽያጭ መርሀ-ግብር ባሳለፍነው ሳምንት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዋና ግቢ ውሰጥ ተካሂዶ ነበር፡፡በዚህ ከመጋቢት 05 እስከ መጋቢት 11 ቀን 2003 ለሰባት ቀናት ሲካሄድ በቆየው ዐውደ-ርዕይና የሽያጭ ሳምንት ላይ የዩኒቨርሲቲ ፕሬሱን ጨምሮ በርካታ መጻሕፍት አሳታሚና አከፋፋዮች ተሳታፊዎች ነበሩ፡፡ከዩኒቨርሲቲው ቤተ-መጻሕፍት ስብስቦች ውስጥ ለዕይታ የበቁ ቀደምት የመመረቂያ ጽሑፎች፣ የጥናት ወረቀቶች እና የምርምር ሥራዎች ለዐውደ-ርዕዩ ልዩ ድባብ የፈጠሩና ዝግጅቱንም ድምቀት አላብሰው ያለፉ ነበሩ፡፡ ከእነዚህ በአስራ ሁለት ረጃጅም ጠረጴዛዎችና በስድስት የመስታወት ማሳያዎች ውስጥ በወግ በወጉ ከተደረደሩ መጻሕትፍ መካከል፣ ከሃያ አምስት ዓመት በፊት ለሕትመት የበቃውና በመጠን ዳጎስ ያለው ‹‹አጭር የኢትዮጵያ ሥነ-ጽሑፍ ታሪክ›› የተሰኘው የአምሳሉ አክሊሉ መጽሐፍ አንዱ ሲሆን መጽሐፉን በብሬይል ጽሕፈት ተዘጋጅቶ መመልከቴ ገረሜታን ሳያጭርብኝ አላለፈም - የአድናቆታዊ ገረሜታን፡፡ በዚህ ረገድ ዩኒቨርሲቲ ፕሬሱ መጻሕፍት በተለያዩ መንገደች ለአካል ጉዳተኞች ተደራሽ ሊሆኑ የሚችሉበትን ዘዴዎች እንዲተልም እየጠቆምኩ፣ ጥሩ ፋና የሆነችንን ‹‹አንድ ክንፍ›› መድብል ደራሲን ሳላደንቅ አላልፍም፡፡ከላይ የጠቀስኩላችሁ የጥናትና ምርምር ሥራዎች እንዲሁም የዲግሪ ሟሟያ ጽሑፎች፣ ‹‹Don’t Touch›› (‹‹አይንኳቸው››) የሚል ጽሑፍ የተለጠፈባቸው፣ የሚታዩ ነገር ግን የማይነኩ፣ የመጻሕፍት ወዳጆችን ልብም መያዝ የቻሉ ስብስቦች ነበሩ፡፡ በ1963 በለማ ወልደማርያም የተዘጋጀውን ‹‹የብላቴን ጌታ ህሩይ ወልደስላሴ የሕይወት ታሪክ›› እና የፈቃደ አዘዘን ‹‹የኢትዮጵያ ብሔረሰቦች ሥነ-ቃል ጥናት፣ ቅኝትና ሙግት›› ጨምሮ ከተለያዩ የማሕበራዊ ሳይንስ ትምህርት ክፍሎች የቀረቡ ጽሑፎች ለዕይታ ቀርበው ነበር፡፡በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የተዘጋጁ የመመረቂያ ስራዎችም ነበሩ፡፡ በአሸናፊ ሙሉጌታ በጽሕፈትና በካሴት (በድምጽ)፣ ‹‹በጅጅጋ አካባቢ የሚኖሩ የሶማሌ ብሔረሰብ ባሕላዊ አኗኗርና ሙዚቃቸው›› በሚል ርዕስ የተዘጋጀው ጥናታዊ ጽሑፍ በዚህ ዘርፍ ሳይጠቀስ መታለፍ የሌለበት ሆኖ አግኝቼዋለሁ፡፡እነማን ነበሩ?ዘንድሮ ሲካሄድ ለአምስተኛ ግዜ በሆነው የመጻሕፍት ዐውደ-ርዕይና ሽያጭ ሳምንት ላይ የዩኒቨርሲቲ ፕሬሱን፣ የዩኒቨርሲቲውን መጻሕፍት ማዕከል፣ የቋንቋዎች ጥናት ተቋምና የቋንቋዎችና ባሕሎች አካዳሚን ሳይጨምር፣ ከሰላሳ የማያንሱ የመጻሕፍት አሳታሚዎች፣ አከፋፋዮችና ነጋዴዎች ታድመዋል፡፡ የትምህርት ጥናትና ምርምር ተቋም በትምህርቱ አካባቢ ላይ ያተኮሩ በርካታ ጆርናሎችን ይዞ ቀርቦ የነበረ ሲሆን፣ በምስራቅና ደቡባዊ አፍሪካ ላይ የማሕበራዊ ትምህርት ጥናት የሚያደርገው ድርጅት (‹‹Organization for Social Science Research in Eastern and Southern Africa - OSSREA››) በክፍለ-አህጉራቱ ላይ የቀረቡትን የጥናት ውጤቶች እጅግ ዝቅተኛ በሆነ ዋጋ ይሸጥ እንደነበር ተመልክቻለሁ፡፡ቅድስተ ማርያም ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ፣ በመርሀ-ግብሩ ላይ የሳተፈ ብቸኛው የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ነበር፡፡ የዩኒቨርሲቲ ኮሌጁ የመጻሕፍት መደብር የጥናትና በሕግ ትምህርት ክፍሉ በዓመት ሁለት ግዜ የሚታተመውን ‹‹Mizan Law & Review›› መጽሔቶቹን ይዞ ተገኝቷል፡፡በቀድሞው አየር ኃይል ግለ-ታሪክ ላይ ያተኮረውና በጋዜጠኛና ደራሲ ዘነበ ወላ የአርትኦት ንድፊያ የተከወነው ‹‹አስተኳሹ›› የተሰኘው መጽሐፍ፣ በራሱ በመጽሐፉ ደራሲ አማኑኤል ሀዲስ ሲሸጥ እንደነበር አስተውያለሁ፡፡ ወጣት አንድነት ኃይሉም የመጀመርያው የሆነውን ‹‹የአንድ አገር ሕዝቦች›› የተሰኘ መጽሐፉን ይዞ ተገኝቶ ነበር፡፡ቅናሽ እና እውነተኛ ቅናሽከአምናው ጋር ሲነፃፀር አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስም ሆነ ሌሎች የዐውደ-ርዕዩ እና የሽያጭ ሳምንቱ ተሳታፊዎች ሕብረተሰቡ መጻሕፍቱን እንዲገዛ የሚጎተጉት ቅናሽ አድርገው ነበር ለማለት አልደፍርም፡፡በተለይ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ በርካ

የምልከታና የሽያጭ ሳምንቱ ድባቦች

ታ መጻሕፍቱ ላይ ከአስር ብር የገፋ ቅናሽ አላደረገም ማለት ይቻላል፡፡ የባህሩ ዘውዴ ምርጥ ሥራ እነደሆነ የሚነገረው “Society, State & History” በዘጠና (90.00) ብር ሲሸጥ፣ ‹‹ኢትዮጵያውያን በአሜሪካ ማሕበራዊና ሥነ-ልቦናዊ ትንተና›› በስልሳ አምስት ብር (65.00) ብር፣ እንዲሁም በቅርቡ ለንባብ የበቃውና በአዶልፍ ፓርላስክ ተፅፎ በተጫነ ጀምበሬ ወደ አማርኛ የተመለሰው ‹‹የሃበሻ ጀብድ›› በአርባ ብር ተሸጠዋል፡፡ በተለይ የመጨረሻው መጽሐፍ ፈላጊው በርክቶ ነበር፡፡ አምና ከአስር ብር ባነሰ ዋጋ ሲሸጡ የነበሩ፣ ‹‹Kassa & Kassa›› የመሳሰሉ መጻሕፍት ዘንድሮ ለአይን እንኳን አጥቻቸዋለሁ፡፡በኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ባሕሎች አካዳሚ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ጥናትና ምርምር ማዕከል በተለያዩ የሀገራችን ብሔረሰብ ቋንቋዎች የሚነገሩ ተረቶችንና ምሳሌያዊ አነጋገሮችን ከነአማርኛ ትርጉማቸው ያቀረበባቸውን መጻሕፍት በርካቶች ተሻምተው ገዝተውታል - በእውነተኛ ቅናሽ፡፡የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መጻሕፍት ማዕከል ያቀረባቸውን መጻሕፍት ያለምንም ቅናሽ የጀርባ ሽፋናቸው ላይ ባለው ዋጋ ሲሸጥ የነበረ ሲሆን የኢትዮጵያ ደራሲያን ማሕበርም መጻሕፍቱን በሽፋን ዋጋቸው ሲሸጥ ገጥሞኛል፡፡ ደራሲያን ማህበሩ ቅናሽ ያላደረገበትን ምክንያት ጠይቄ፣ ‹‹ማሕበሩ መጀመርያ ዋጋውን የሚተምነው ሕብረተሰቡን ታሳቢ በማድረግ ስለሆነ፣ የመጻሕፍቱ ሽፋን ላይ የሚታተመው መሸጫ ዋጋ ዝቅ የተደረገ ነው›› የሚል ቀና ምላሽ አግኝቻለሁ፡፡ድርጅታቸው ምን እንደሚባል ስጠይቅ፣ ‹‹ለምን ፈለግክ?›› ብለው መልሰው ከጠየቁኝ በኋላ፣ ‹‹ማሕሌት አሳታሚ›› እንደሚባል የነገሩኝ የአሳታሚው የሽያጭ መኮንኖች በትህትናቸውና በ50% (በመቶ ሃምሳ) ቅናሻቸው ምክንያት በበርካታ አንባቢያን መጻሕፍት መደርደሪያዎች ላይ በርካታ መጻሕፍት እንዲኖሩ አድርገዋል፡፡የማህበራዊ ጥናት መድረክ በአፍሪካም (‹‹OS-SREA››) እንዲሁ የ50% (ሃምሳ በመቶ) ቅናሽ በማድረግ በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ እና ጤና ነክ ዘርፎች ላይ የጥናት ውጤት የሆኑ መጻሕፍትን ቅንነትን በተሞላ ቅናሽ ይዞ ቀርቦ ነበር፡፡‹‹ልዩ›› ኹነቶችለሁለት አስርት ዓመታት እስልምናን ይዘታቸው ያደጉ መጻሕፍትን ያሳተመውና እያሳተመ የሚገኘው ነጃሺ አሳታሚ እስልምና ተኮር የሆኑ መጻሕፍትን፣ ስብከቶችን እና ሃይማኖታዊ ዝማሬዎችን ይዞ ቀርቦ የነበረ ሲሆን፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃና መምሪያ ስር የሚገኘው ማህበረ-ቅዱሳንም ኦርቶዶክሳዊ ይዘት ያላቸውን በርካታ መጻሕፍት፣ የስብከትና የመዝሙር ካሴትና ሲዲዎችን ለታዳምያኑ እንካችሁ ብሏል፡፡ እንዲሁም፣ በኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ-ክርስቲያናት ሕብረት ስር የታቀፉት የራዕይና የበዕምነት መጻሕፍት መደብሮች በወንጌላውያን ከተጻፉና ከተተረጎሙ መንፈሳዊ መጻሕፍት በተጨማሪ፣ በስኬትና ብልፅግና ዙርያ የሚያጠነጥኑ መጻሕፍትን ይዘው መገኘት ችለው ነበር፡፡በሽያጭና ምልከታ ሳምንቱ ላይም፣ የሕፃናት መጻሕፍት ገዢ አላጡም፡፡ በኩር ኮሚኒኬሽን ‹‹አና›› በሚል ስያሜ የሳተማትን የሕፃናት መጽሔት በስድስት (6.00) ብር ሲሸጥ፣ የ‹‹ራዕይ›› አንባቢያን ማህበር በበኩሉ የአባላቱን ቁጥር በማበራከት ሥራ ላይ ሲተጋ ተስተውሏል፡፡ብዙ ... ተባዙ!የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ ስለሚያዘጋጃቸው የመጻሕፍት ሽያጭና ዐውደ-ርዕይ መርሀ-ግብሮች ማስታወቂያ አለማስነገሩ በርካታ የመጻሕፍት አፍቃርያን ስለክስተቱ ‹‹መችና የት›› እንዳያውቁ እንዳደረጋቸው እሙን ነው፡፡ ይህን ጽሑፍ እያነበቡ እንኳ ባለማወቃቸው ስላመለጣቸው በረከት መቆጨታቸው አይቀርም፡፡ መጻሕፍት የሕዝብን ንቃተ-ህሊና ከፍ ከማድረግና ግንዛቤን ከመፍጠር ባለፈ ለአንዲት ሀገር ዋነኛ የዕድገት ምንጭ የሆኑ ሕዝቦቿን ዕውቀትንና ክህሎትን፣ ብሎም ፅናትን የሚያስታጥቁ መሳሪያዎች ናቸው ብል በፍፁም እያጋነንኩ አይደለም፡፡ የሀገሪቱ ዕድገትም ሆነ ውድቀት ሕዝቦቿ ከንባብ በተለይም ከመጻሕፍት ንባብ ጋር ካላቸው ቅርርብና እውቂያ አንፃር የሚወሰን ነው፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስም ሆነ በሌሎች ተቋማት በኩል የሚደረጉ መሰል ተግባራት እንዲበዙልን ምኞቴም ፀሎቴም ነው፡፡

ሰላም ለእናንተ ይሁን!

Page 14: awramba 160

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 160 ቅዳሜ መጋቢት 17 200314

ሕብር ስኳር አክሲዮን ማህበር Hiber Sugar Share Company

ሕብር ስኳር አ.ማ ከ5,280 በላይ የሚሆኑ አባላቱን በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽ/ቤት ማስፈረም ጀምሯል፡፡ ቀዳሚዎቹ ፈራሚዎች የቦርድ አባላትና 32ቱ ዋና መስራቾች ሆነዋል፡፡

ስለሆነም እስከ ጥር 25/2003 ዓ.ም አክሲዮን የገዛችሁ የተከበራችሁ የሕብር ስኳር አ.ማ ቀሪ መሥራች አባላትና ባለአክሲዮኖች በሚከተለው ሠንጠረዥ መሠረት በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ቢሮ ቀርባችሁ እስከ መጋቢት 30 ቀን

2003 ቀን ድረስ እንድትፈርሙ የአክብሮት ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

ስማችሁ የሚጀምርበት ፊደልና ተራ ቁ. የመፈረሚያ ቦታ(A)የ አ ዝርያ(ከተራ ቁ. 1-913)

ዋናው መስሪያ ቤትሜክሲኮ አደባባይ አጠገብ ጨለለቅ አልሣም ታወር 2ኛ እና 3ኛ ፎቅ

(B, C, D, E)በ፣ ቸ፣ ጨ፣ ደ፣ ኢ፣ ኤ፣ እ ዝርያ(ከተራ ቁ. 914-1789)

ቅርንጫፍ 4 ጽ/ቤትአምስት ኪሎ አ.አ.ዩ ቴክኖሎጂ ፋኩልቲ ፊት ለፊት

(F, G, H, I, J, K) ፈ፣ ገ፣ ሀ፣ ሐ፣ኀ፣ ኸ፣ ጀ፣ከ፣ቀ ዝርያ(ከተራ ቁ. 1790-2731)

ቅርንጫፍ 1 ጽ/ቤትደብረ ዘይት መንገድ ተሻለ ገራዥ አጎና ሲኒማ ቤት አጠገብ ባለኬር ሕንፃ 1ኛ ፎቅ

(L, M, N, O, P, Q, R) ለ፣ መ፣ ነ፣ ኦ፣ ጰ፣ ረ ዝርያ(ከተራ ቁ. 2732-3613)

ቅርንጫፍ 3 ጽ/ቤት መገናኛ መንገድ ትራንስፖርት ሕንፃ ጀርባ ራሒም ሕንፃ 1ኛ ፎቅ

(S, T) ሰ፣ ሠ፣ ሸ፣ ተ፣ ጠ፣ ፀ፣ ጸ ዝርያ(ከተራ ቁ. 3614-4656)

ቅርንጫፍ 5 ጽ/ቤትሰሜን ማዘጋጃ ሸገር መናፈሻ አካባቢ ብርሃን ሕንፃ 1ኛ ፎቅ

(U, V, W, Y, Z)ኡ፣ ቪ፣ ወ፣ የ፣ ዘ፣ ዝርያ (ከተራ ቁ. 4657-5280)

ቅርንጫፍ 2 ጽ/ቤትመርካቶ ክፈለ ሀገር አውቶቢስ ተራን አለፍ ብሎ ሸዋ ፀጋ ሕንፃ 2ኛ ፎቅ

ወደ ሰነዶች ምዝገባና ጽ/ቤት ለፊርማ በምትመጡበት ጊዜ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ወይም መንጃ ፍቃድ ወይንም ፓስፖርት 1. አክሲዮን የገዛችሁበትን የምዝገባ ቅጽ2. ገንዘብ የከፈላችሁበትን የባንክ ደረሰኝ3. ሕጋዊ ውክልና ማስረጃ4. ለሕፃናት የገዛችሁ (የልደት ሰርተፍኬት)5. በጋራ የገዙ ባለትዳሮች የጋብቻ ሰርተፍኬት (አንዳቸው እንዲፈርሙ)6. በማህበር የገዛችሁ (የተወከላችሁበትን ቃለ-ጉባዔ፣ መተዳደሪያና መመስረቻ ጽሁፎች ወይም የምዝገባ ሰርተፍኬት)

ይዛችሁ እንድትቀርቡ እያሳሰብን ሰነድ ላይ ፊርማችሁን ያላኖራችሁ አባላት የሕብር ስኳርን የአክሲዮን ባለቤትነት ሰርተፍኬት ማግኘት የማትችሉ መሆናችሁን ከወዲሁ እናስታውቃለን፡፡

ለስራ ቅልጥፍና ሲባል የምዝገባ ተራ ቁጥራችሁን በስልክም ሆነ ዋናው መ/ቤት በመምጣት ለማወቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ የሕብር ስኳር አክሲዮን ሽያጭ ማጠናቀቂያ ጊዜ የካቲት 30/2003 ዓ.ም ስለሆነ በቀሩት ቀናት ብቻ መስራች አባላት አክሲዮናችሁን እንድታሳድጉና ሌሎች ፍላጎት ያላችሁ ሁሉ አክሲዮን በመግዛት የመጨረሻው ዕድል ተጠቃሚ እንድትሆኑ ጥሪ እናቀርባለን፡፡

የአንድ አክስዮን ዋጋ • = 1000ዝቅተኛው የአክሲዮን መጠን 1ዐ አክሲዮኖች • = 10,000የአገልግሎት ክፍያ 7• %

አክስዮን መግዛት የምትፈልጉ ሁሉ በኢትዮጵያ ፖስታ ድርጅት መላው ቅርንጫፎች እና በዋናው መስሪያ ቤት እንዲሁም በሽያጭ ወኪሎች አማካይነት መጠቀም የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

አድራሻ፡- ሕብር ስኳር አ.ማ ሜክሲኮ ከዲ’አፍሪክ ሆቴል ፊት ለፊት ታደሰ ተፈራ ሕንፃ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ. 105ስልክ ቢሮ 0118501357/58 E-mail - [email protected] web - www.hibirsugarethiopia.com

ስማችሁ የሚጀምርበት ፊደልና ተራ ቁ. የመፈረሚያ ቦታ(A)የ አ ዝርያ(ከተራ ቁ. 1-913)

ዋናው መስሪያ ቤትሜክሲኮ አደባባይ አጠገብ ጨለለቅ አልሣም ታወር 2ኛ እና 3ኛ ፎቅ

(B, C, D, E)በ፣ ቸ፣ ጨ፣ ደ፣ ኢ፣ ኤ፣ እ ዝርያ(ከተራ ቁ. 914-1789)

ቅርንጫፍ 4 ጽ/ቤትአምስት ኪሎ አ.አ.ዩ ቴክኖሎጂ ፋኩልቲ ፊት ለፊት

(F, G, H, I, J, K) ፈ፣ ገ፣ ሀ፣ ሐ፣ኀ፣ ኸ፣ ጀ፣ከ፣ቀ ዝርያ(ከተራ ቁ. 1790-2731)

ቅርንጫፍ 1 ጽ/ቤትደብረ ዘይት መንገድ ተሻለ ገራዥ አጎና ሲኒማ ቤት አጠገብ ባለኬር ሕንፃ 1ኛ ፎቅ

(L, M, N, O, P, Q, R) ለ፣ መ፣ ነ፣ ኦ፣ ጰ፣ ረ ዝርያ(ከተራ ቁ. 2732-3613)

ቅርንጫፍ 3 ጽ/ቤት መገናኛ መንገድ ትራንስፖርት ሕንፃ ጀርባ ራሒም ሕንፃ 1ኛ ፎቅ

(S, T) ሰ፣ ሠ፣ ሸ፣ ተ፣ ጠ፣ ፀ፣ ጸ ዝርያ(ከተራ ቁ. 3614-4656)

ቅርንጫፍ 5 ጽ/ቤትሰሜን ማዘጋጃ ሸገር መናፈሻ አካባቢ ብርሃን ሕንፃ 1ኛ ፎቅ

(U, V, W, Y, Z)ኡ፣ ቪ፣ ወ፣ የ፣ ዘ፣ ዝርያ (ከተራ ቁ. 4657-5280)

ቅርንጫፍ 2 ጽ/ቤትመርካቶ ክፈለ ሀገር አውቶቢስ ተራን አለፍ ብሎ ሸዋ ፀጋ ሕንፃ 2ኛ ፎቅ

Page 15: awramba 160

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 160 ቅዳሜ መጋቢት 17 2003 15

ፕሬሱ ምን ያድርግ? በአጠቃላይ በነፃው ፕሬስ ድንጉጣዊ እርምጃ ፕሬሱን የበለጠ ለአምባገነኖች ከማጋለጥ በቀር የፈየደለት የለም፡፡ እስከ አሁን የነፃው ፕሬስ አባላት የሄዱበት ሁኔታ ለአምባገነኑ የተመቻቹ፣ እንደውም ከጊዜ ወደጊዜ ለእነርሱ ያለው ንቀት እንዲያድግ አድርገውታል፡፡ በዚህ ከባቢ እየሰሩ ካሉት አንዳንድ የነፃው ፕሬስ ውጤቶች ረዥም ጊዜ በገበያ ላይ መቆየትን ብቻ በራሱ የስኬት ምልክት አድርገው መውሰዳቸው ሊያነጋግር የሚገባ ይመስለኛል፡፡ ጋዜጦች በተቻለ አቅም ትርፋቸውን ለማስጠበቅና ቀጣይነታቸውን ብቻ ለማረጋገጥ የሚሞክሩ በመሆኑ አንባቢዎቻቸውን እያጡ ተቀባይነታቸው እያነሰ ላለመሄዱ መከራከር የሚችሉበት መሞገቻ ያላቸው አይመስልም፡፡ ጋዜጠኛ የሚለውን ስም ይዘው ሀገሪቱ ባለችበት በአሁን ሰዓት የሚያስከፍለውን መስዋዕትነት ግን ለመክፈል ዝግጁ አለመሆናቸው እንኳን ለሌላው አብርኆት ሊያስገኙ ለራሳቸውም ያነሳቸው ናቸው እንዳያስብል ያሰጋል፡፡ ስለዚህ ፕሬሱ ከመድበስበስ ቀጥተኛነትን፣ ከዕድሜ ጥራትን፣ ከራስ ማዕቀፍ ወደ ሕዝባዊነት የመምጣት ስልትን መከተል ያሻዋል፡፡ ያን ጊዜ ጥሬና ገለባውን ከብስሉና ፍሬው መለየት ይቻላል፡፡

ሕዝብ ምን ያድርግ? ይህ በእንዲህ እያለ ባለፉት ሦስትና አራት ዓመታት ብቻ ከእጥፍ በላይ የጨመረው የጋዜጦች ዋጋ ሰሞኑን ይጨመራል በተባለው እስከ ሃምሳ በመቶ የሚደርስ የህትመት ጭማሪ ምክንያት ችግሩ ክፉኛ ሳይባባስ አይቀርም፡፡ ይህን የአታሚ ድርጅት/መንግሥት ዋጋ ጭማሪ ተከትሎ ጋዜጦች ብሶታቸውን በዘገባም፣ በርዕሰ አንቀጽ መልክም እያነሱ ነው፡፡ ድርጅቱም አሳታሚዎችን ለማነጋገር እንደሞከረ ተሰምቷል፡፡ እንደምክንያት ያቀረበውም የወረቀት ዋጋ በዶላርና በወደብ ዋጋ ጭማሪ ምክንያት ማሻቀቡን ነው፡፡ በዚህ አጋጣሚ ጋዜጦች የሕትመትና

የሽያጭ ዋጋቸውን እየተናዘዙልን ነው፡፡ የሚቀርቡት መረጃዎች የጋዜጣዎቹ ድርጅቶች ምን ያህል ጋዜጦችን ለአንባቢው ለማድረስ እየደጎሙት እንደሆነ የሚያመለክቱ ናቸው፡፡ ጋዜጦቹ ኢትዮጵያ ውስጥ ባለው ነባራዊ ሁኔታ ምጣኔ ሀብታቸው ውሱን በመሆኑ በጉዳቱ አንዳንዶች ከገበያ የመውጣት ዕድላቸው ከፍተኛ ሊሆን ይችላል፡፡ ለሙያው ያላቸው ቁርጠኝነት ግምት ውስጥ እየገባ በመሄዱ ምክንያት በተፈጠረ የተሳሳተ ግንዛቤ ሁኔታውን የጋዜጠኞቹ ብቻ አድርጎ የመመልከት ሁኔታ እንዳይፈጠር ያሰጋል፡፡ የነፃው ፕሬስ ጉዳይ ግን የራሱ ጉዳይ ብቻ ተብሎ የሚተው ሊሆን አይገባም፡፡ ምክንያቱም ከሰው ልጆች መሠረታዊ መብቶች አንዱ የሆነውን የመናገርና የመፃፍ መብት እንደፈለጉ እንዲፈነጩበት ለመንግስትና ለጋዜጠኞች አሳልፎ መስጠት ስለሚሆን ነው፡፡ ችግሩ ኢትዮጵያውያን ይኼን ለመቆጣጠር ጥረት የማናደርግ፣ ግዴታችንም እንደሆነ የማንረዳ መሆኑ ነው፡፡ በቅርብ ያነጋገርኩት አንድ ጋዜጠኛ ‹‹ይህቺ ሀገር በአሁን ሰዓት ለሕዝቦቿ ብለህ ስትሰራ ከሕዝቧ የምትነጠልባት ሆናለች›› ሲል አምርሮ የወቀሰው አለምክንያት እንዳልሆነ እንረዳለን፡፡ እንደዚህ ሰው አገላለጽ በዘመዱ ሠርግ ላይ እንኳን ይገኝ አይገኝ ድምጽ እስከመሰጠት እንደደረሰበት ያስታውሳል፡፡ ለእንደዚህ ዓይነት ጩኸቶች ጆሯችንን መስጠት ተገቢ ነው፡፡ ዴሞክራሲ እንዲያብብ በተለምዶ ‹የዴሞክራሲ መፅሐፍ ቅዱስ› የሚሉትን ጋዜጣን መታደግ አስፈላጊ ነው፡፡ ይህንን ለማድረግ ሕዝቡ በተለያየ ምክንያት ጋዜጦች ሲዳከሙ ስለ መረጃ ስርጭትና ዝውውር ነፃነት ሲባል እነርሱን ለመደገፍ የሚቆሙ በጎ አድራጎት ድርጅቶች ሀገሪቱ ካለችበት ተጨባጭ ሁኔታ አንፃር ማቋቋም ይችል ይሆንን? መንግስትስ በሆነ መልኩ፣ ለምሳሌ የፈረንሳይ መንግስት እንዳደረገው ዕድሜያቸው 18 ዓመት ለሆናቸው ወጣቶች በየቀኑ በምርጫቸው የፈለጉት ጋዜጣ እንዲደርሳቸው ለማድረግ ለጋዜጣ ኩባንያዎች ሊከፍል ባይሻ እንኳ ወረቀት ላይ የተጣለውን ‹ግብር› ሊያነሳ ይችል ይሆን? አሊያም እንደ ሕንድ ጋዜጦችን

ለመደጎም ቅድምናን ይወስድ ይሆን? የሀገሪቱን ተጨባጭ ሁኔታ ለሚገነዘብ ግን መንግስት አንዱንም ለማድረግ ፍላጎት እንደሚኖረው ደፍሮ መናገር አይቻልም፡፡ ይልቅስ መንግስት የመረጃ ምንጮችን፣ ስርጭትንና ትንተናን በሚቻለው አቅም ሁሉ በስሩ ለማድረግ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ለመቆጣጠር እየታተረ ነው፡፡ ሥልጣን ላይ ያለው አካል የሚያወራውና የሚሰራው አልገጥም፣ አልስተካከልና አልመጣጠን እያለውና በፕሮፓጋንዳ ወሳኝነት የሚያምን በመሆኑ ጭምር በየጊዜው የሚሰበስባቸው ጋዜጠኞችና ኃላፊዎች/ጎቤላውያን የሚያወሩት ‹ዝክረ ነገር› በአንጋፋው ጋዜጠኛ ማዕረጉ በዛብህ አነጋገር ውሸት መሆኑን እያወቁት እውነት ነው ብለው የሚያምኑ መስለው ለመታየት ይበልጥ የሚጥሩ ሆነው ተገኝተዋል፡፡ የራሱን ሕዝብ በሀሰት በማሳሳት የሚጠላው መንግስትና የምትጎዳው ሀገር ይጭነቃት እንጂ፣ እነርሱማ ‹‹ፕሮፐጋንዳ፡ ዘ ፎርሜሽን ኦፍ ሜንስ አቲቱድ›› በተሰኘ መፅሐፍ (ገጽ 196-197) እንደተገለጸው፣ በራሳቸው ምንም የሚያምኑት ነገር ስለሌላቸው ዘመን ሲቀየር ቆዳቸውን ገልብጠው ለሌላ አስተሳሰብ ለማሸርገድ የሚሳናቸው አይደሉም፡፡ ስለዚህም ሀገሪቱና ሕዝቦቿ ከመቼውም ጊዜ በላይ ወይ ለመንግሥት ቅጥ ያጣ ‹ዓይናችሁን ጨፍኑ ላሞኛችሁ› ዓይነት ፕሮፓጋንዳ እንዲጋለጡ፣ አሊያም ከሀገር ውስጥ መረጃን ከማግኘት በሳተላይት እና በድረ-ገጽ መረብ የሚንሸራሸሩ መረጃዎች ላይ መመስረትን እንዲመርጡ አድርጓቸዋል፡፡ ከዚህም የከፋው ደግሞ ሁሉንም እርግፍ አድርጎ፣ ራሱን ንቆ ለዕለት ጉርሱ ብቻ የሚታትርው ባተሌና ብኩን ሆኖለታል፡፡ ስለዚህ ወቅት እየጠበቀ የሚጨምረው ዋጋ ከመንግስት አቅም በላይ የሆነ አስገዳጅ ሁኔታ ገጥሞ ነው ቢባል እንኳን ጮቤ የሚያስረግጠው እንጂ እንዲለወጥ የሚሻው አይሆንም፡፡ ይህም ሀሳብ ያጠረውን ሕዝብ እንደፈለገው ለማበጃጀት ያስችለዋል፡፡ ይህም የመረጃ የበላይነትን ሰጥቶት ያሻውን ሚስኢንፎርም እና ዲስኢንፎርም እያደረገ ለመኖር ያስችለዋል፡፡ ባጠቃላይ ድንቁርና ይንሰራፋል፡፡ በእርግጥም በሀገሪቱ የሚታዩ ጥቃቅን ክስተቶች ሲገጣጠሙ የሚገኘው ምስል የሚያሳየው ይህንን ግብ ለማሳካት የሚደረገው ሩጫ ነው፡፡ የሲቪል

ማኅበረሰባትን የገንዘብ ምንጭ ለማድረቅ የወጣው 90/10 በመቶ ሕግ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ገቢያቸውን አስመልክቶ የወጣው ሕግ፣ በአንዳንድ የግል ተቋማት ላይ የሚወርደው ውክቢያ፣ ባልታወጀ ሕግ ሥርዓቱን የሚተቹ ዜጎችን በየሚሰሩበት መሥሪያ ቤት እና ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጭምር ባሉ ካድሬዎችና ባለሥልጣናት ግፊት ከሥራ ማባረራቸው ሥርዓቱ ዜጎችን ሲሆን አደህይቶ/ኅሊና አሳጥቶ መንፈሰ ልዕልናቸውን አላሽቆ ለመግዛት ወይም ድምፃቸው ሳይሰማ እንዲሞቱ እንደፈለገ ተደርግ ያስወስዳል፡፡ በጋዜጠኞች ላይ የሚጣለው የገንዘብ ቅጣትና የጋዜጣ ፈቃድ ቅድመ-ሁኔታና የዝግጅቱ ዋጋ ከፍተኛነት ሥራውን የማይሞከር ለማድረግና ከተሞከረም አስጨናቂ ከባቢ ፈጥሮለት ብዙዎች እንዲሸሹት ለማድረግ ያለመ ላለመሆኑ በእርግጠኝነት መሞገት አይቻልም፡፡ ይኼን ስንመለከት ደግሞ አደህይቶ ብቻ ሳይሆን አደንቁሮ ለመግዛት ማለሙን ከሚያሳዩ ብዙ ምልክቶች አንዱ ብቻ እንደሆነ አድርገን ልንወስደው እንችላለን፡፡በዚህም አለ በዚያ፣ የሆነው ሁሉ ከሆነ እኛ ምን እናድርግ? ቅድሚያ ሀሳብን በነፃ ለመግለጽ የማያወላዳ ማኅበረሰብን እና ሥርዓትን መፍጠር የዕለት ተዕለት ትጋት መሆን አለበት፡፡ ይኼ ደግሞ ጥቂት እንኳን ቁጭት ሲኖረን ነው፡፡ ከቅርብ ጎረቤት ሀገር ሳይቀር በዝቅተኛ ዋጋ የሚሸጠው ጋዜጣ ዋና ገቢው ከማስታወቂያ በመሆኑ ነው፡፡ ሰሞኑን ጋዜጦች እየደጎሙ መሆኑን ቢገልጹልንም የጋዜጦቹ ዋጋ አሁንም ከፍተኛ በመሆኑ መግዛት አቅቶ በኪራይ (ተገቢ ባይሆንም) ለማንበብ ተገደናል፡፡ ስለዚህ የበኩላችንን ሚና መጫወት ካለብን ሁኔታው የግድ እንድንገዛ የሚጠቁም ነው፡፡ በተቻለም አቅም ሀሳባችንን እየገለጽንባቸው አስተዋጽኦ ልናደርግላቸው ይገባል፡፡ አንድ ጋዜጣ በጥሩ የምጣኔ ሀብት ላይ የተመሠረተ ነው የሚሰኘው እስከ 60 በመቶው ለማስታወቂያ ማዋል ሲቻለው ነው፡፡ ይህም ከብዙ ጥቅሞቹ አንዱ ጋዜጣውን በዝቅተኛ ዋጋ ለአንባቢያን ለማዳረስ ስለሚያስችል ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ደረጃቸውን የጠበቁ ዓምደኞችንም ሆነ አርታኢ ለመቅጠርና ጥራት ያለው ሥራ ለመስራት ያስችለዋል፡፡ በሀገሪቱ ያሉ ጋዜጦች ከሁለቱ በስተቀር ይኼን ለማድረግ የአለመቻላቸው ምስጢር

በቅጡ መታየት ይኖርበታል፡፡ በግልጽ የሚታየው ምክንያት በሀገሪቱ የተንሰራፋው ዕመቃ ነው፡፡ የትኛውም ድርጅት ለግሉ (ለነፃው) ፕሬስ፣ በተለይም ጠንከር ያለ ሂስ በመንግስት ላይ ለሚያስተናግዱ ጋዜጦች ማስታወቂያውን መስጠት አይፈልግም፡፡ ስለዚህ ማስታወቂያ የሚሰጠው በስርጭት መጠንና በሌሎች የግብይት ሕግ/ፅንሰ ሀሳብ ላይ ተመስርቶ ሳይሆን መንግስትን የማይጋፉትን መርጦ ይመስላል፡፡ በዚህ ረገድ ከፍተኛ የገበያ ጥናት ባለሙያ ያሏቸውና ስመጥር ድርጅቶች የሆኑት ሳይቀሩ የዚህ እወደድ ባይነት ሰለባ ሆነዋል፡፡ አተቱም ገተቱም ተሰብስቦ የታተመበትን ባለ191 ገጽ አንድ ‹መጽሐፍ› 40 የሚደርሱ ሀገሪቷ ያሏት ድርጅቶች ሁሉ ስፖንሰር ለማድረግ መንጋጋታቸው ጥሩ ማሳያ ይሆናል፡፡ አሁን አሁንማ በአንድ ወገን ታሪክ እንፅፋለን ብለው የሚነሱ ወገኖችን ስፖንሰር ለማድረግ ደጅ በመጥናት አሽቋላጮች መፅሐፍትን በ1ኛና ሁለተኛ ደረጃ ስፖንሰር ምልክቶች በመሙላት ወደ መጽሔትነት ደረጃ እያወረዱት ነው፡፡ በአጠቃላይ በሀሳብ የበላይነትና አሳማኝነት ላይ ሳይሆን በመጠቃቀምና በመሟሰን ላይ መሠረቱን ያደረገ እንዲህ ዓይነቱ ሥርዓት ስር ከመስደዱም በላይ በሀገሪቱ ያሉ ድርጅቶችም በሀቀኝነት መስራት እየተሳናቸው መምጣቱን ያመለክታል፡፡ የኢትዮጵያ ድርጅቶች ትዝብት ላይ እንዳይወድቁ ስማቸውን የሚመጥን ሀቀኝነት በማሳየት ሀሳብን በፅሑፍ የመግለፅ ነፃነትን መደገፍ እንዳለባቸው መጠቆም ያሻል፡፡ እንደ ደራሲያን፣ ጋዜጠኞች፣ የመምህራንና የትምህርት ተቋማት፣ የአታሚዎችና አሳታሚዎች ማኅበራት ለየማኅበራቸው አባላትና የሀገሪቱ ዜጎች ዕውቀትን በመሻትና በመፍጠር ሁሉም እኩል ዕድል እንዲኖረው ጥያቄ ለማቅረብ በጊዜያቸው አንድ ጊዜ እንኳን ወኔውን እንዲያገኙ ማንቃት ያስፈልጋል፡፡ ለጋዜጣና ለመፅሐፍ ህትመት የሚውሉ ወረቀቶች ላይ የተጣለ ግብር እንዲነሳ፣ በየጊዜው ያለምክንያትም በምክንያትም ህትመት ላይ የሚደረገው ጭማሪ ሥርዓት እንዲይዝ በየዝግጅቱ ክራቫትን እያሳመሩ ለሚዲያ ሽፋን የሚራወጡት የማኅበራት መሪዎች ኃላፊነታቸውን እንዲወጡና አደህይቶም ሆነ አደንቁሮ መግዛት አዳጋች እንዲሆን እየተመኘሁ መልዕክቴን እቋጫለሁ፡፡

አደህይቶ እና...

ዓለም አቀፍ

በጆአፍም ጋስካር

በሰሜን አፍሪካ ሕዝባዊ ተቃውሞዎች፣ ሰልፈኞች አደባባይ ይዘው ከወጧቸው መፈክሮች መካከል፣ (‹‹Yesterday we were all Tunisians. Today we are Egyptians. Tomorrow we will all be Free››) የሚለው ንግርታዊነትን የተላበሰ ነበር፡፡ (የመፈክሩ የአማርኛ ተለዋጭ፣ ‹‹ትላንት - ነበርን ሁላችንም ቱኒዚያውያን፤ ዛሬን - ሆነናል ግብፃውያን፤ ነገን - እንሆናለን ሁላችንም ነፃ›› የሚል አይነት መንፈስ አለው)፡፡ እናም፣ ይህን እና ሌሎች ንግርታዊ የሕዝባዊ አብዮቶች መፈክሮች እንዲሁ በእጅ ከፍ ተደርገው የተያዙና ቃላት የታተሙባቸው ብቻ አልነበሩም፤ ሆነውም አልቀሩም፡፡ በተግባር ደረጃ፣ ‹‹ዱዋሊዝም›› አጅ-እግር ያለው በአፍሪካ ብቻ ይመስላል - እጅግ ከመጉላቱ የተነሳ፡፡ የዛሬን አያድርገውና ሊቢያ በአንድ ‹‹ሕጋዊ›› መንግስት ነኝ በሚል እንጃ የሁለት ‹‹መንግስታት ሀገር› ከመሆኗ በፊት፣ ሀገሪቱን በብቸኝነት ‹‹ሲፈነጩባት›› የቆዩት ሙአመር ጋዳፊ ነበሩ፡፡ ይህችን ሜዲትራኒያን ባሕር በሰሜን፣ ግብፅ በምስራቅ፣ ሱዳን ደቡብ-ምስራቅ፣ ቻድና ናይጀር (ወይም ኒጀር) በደቡብ፣ አልጄሪያና ቱኒዚያ በምዕራብ የሚያዋስኗትን በርሃማና በርሃ የሆነቸውን ሀገር ‹‹ታላቋ ሶሻሊስት ሕዝባዊት ሊቢያ አረብ ጃማህሪያ›› ሲሉ ነው የሚጠሯት - ጋዳፊ፡፡ ‹‹ታላቋ›› የሚሏት ሊቢያ የብቻቸው እንዳልሆነች አስረግጦ ያሳወቃቸው አማፂ ኃይል፣ በዓለም ኃያላን ሀገራትና መንግስታት ድጋፍ እየተጠናከረ መምጣቱ የአገዛዛቸው መጨረሻ ጫፍ ላይ እንደሚገኙ ፍንጭ ሰጥቷል፡፡ ኮሎኔል ጋዳፊ በአሁኑ ወቅት ትሪፖሊንና አብዛኛውን ምዕራባዊ ሊቢያን ለግዜው ተቆጣጥረው የሚገኙ ሲሆን፣ በሙስጠፋ አብዱል ጃሊል የሚመራው የ‹‹ሪፑብሊክ ሊቢያ ብሔራዊ የሽግግር ሸንጎ››፣ መቀመጫውን ቤንጋዚ (ምስራቅ ሊቢያ) ያደረገ፣ አብዛኛውን ምስራቃዊ ሊቢያን ይዞ የሚገኝ፣ ሕዝባዊ አመፅ የወለደው የጋዳፊ ሊቢያን የተጋፈጠ ኃይል ነው፡፡ ጋዳፊም ለአማፂው ቡድን በዋዛ እጅ የሚሰጡ አይነት አልሆኑም፡፡ ሥልጣናቸውን ለማስጠበቅ ሲሉ የሚወስዷቸው የኃይል እርምጃዎች፣ በተለይ የአማፂው ቡድን ጠንካራ መቀመጫ በሆነችው ምስራቅ ሊቢያ - ቤንጋዚ - ላይ የወሰዷቸው፣ ከአማፂዎቹ ተርፎ በርካታ ንፁህ ሊቢያውያንን መጉዳቱ የዓለምን ማህበረሰብ ያሳሰበው ጉዳይ ሆኖ የቆየ ነበር፡፡ ይህም ስጋት እየተባባሰ መሄዱ ነበር የአረብ ሊግ፣ ተ.መ.ድ፣እና ሌሎች በርካታ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅቶች በአገዛዛቸው ላይ አስቸኳይ እርምጃ እንዶወሰድና የሀገሪቱ ሲቪሎች ጥበቃ ይደረግላቸው የሚሉ

ጥሪዎቻቸውን እንዲያጠናክሩ ያደረጋቸው፡፡ በመጨረሻም ተሳክቶላቸው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ም/ቤት በጋዳፊ አገዛዝ ላይ አስፈላጊና አግባብ ነው ያለውን ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

ውሳኔው . . .

የተ.መ.ድን ቻርተር በተከተለ መንገድ፣ በሊቢያ ያለውን ሁኔታ ለመቅረፍና ሁኔታው ለዓለም ሰላምና ደህንነት ስጋት በመሆኑ፣ የፀጥታው ም/ቤት በሊቢያ ላይ የተለያዩ እርምጃዎችን የሚፈቅድ ውሳኔውን ያስተላለፈው በየካቲት 28/2003 ላይ ነበር፡፡ አስቸኳይ የተኩስ አቁም እንዲደረግ፤ ሙሉ በሙሉ የጥቃት እርምጃ እንዲቆም፤ ሁሉም በሲቪሎች ላይ የሚሰነዘሩ ጥቃቶችና ኢ-ፍትሃዊ አያያዞች እንዲገቱ የሚያሳስበው የም/ር ቤቱ ተቀዳሚ የውሳኔው አካል ነው፡፡ ለሊቢያውያን አግባብነት ላለው ጥያቄ ምላሽ ለማግኘት የሚያስችሉ ጥረቶች አስፈላጊ መሆናቸውን በማስመር እና ወደሰላማዊና ዘቂ የፖለቲካ ማሻሻያዎች የሚመራ ውይይት ለማመቻቸት የተ.መ.ድ ዋና ፀሃፊ ልዩ ምልዕክነኞቻቸውን ወደ ሊቢያ ለመላክ የወሰኑት ውሳኔ፣ እንዲሁም የአፍሪካ ህብረት የሰላምና ፀጥታ ካውንስል ‹‹አድ-ሆክ›› ከፍተኛ ባለሥልጣናት ኮሚቴ ለተመሳሳይ ዓላማ ልዩ መልዕክተኞቻቸውን ለመላክ የወሰኑት ውሳኔ የችግሩን አሳሳቢነት የሚያጎላው መሆኑን በመዘርዘር፣ የሊቢያ ባለሥልጣናት ዓለም አቀፍ ሕጎችን እንዲያከብሩ ጥያቄ ያቀርባል - ውሳኔ 1973፡፡ በዚህ ጥያቄ ሳያበቃም ሰብዓዊ መብቶች፣ የስደተኞች ሕግና ሲቪሎችን ለመጠበቅ (እና መሰረታዊ ፍላጎታቸውን ለማሟላት) ሁሉንም አስፈላጊ እርምጃዎች እንዲወስዱና ሰብዓዊ ድጋፋ በፍጥነት የሚተላለፍበትን የተቀላጠፈና ከእንቅፋት የፀዳ መንገድ እንዲያሰፍኑ የሊቢያ ባለሥልጣናትን አበክሮ በማስገንዘብ፣ አባል ሀገራት ሊወስዷቸው የሚችሏቸውን ወታደራዊ እርምጃዎች በዝርዝር አስፍሯል፡፡

ሲቪሎችንና በሀገሪቱ ለጥቃት በተጋለጡ ሲቪሎች በብዛት የሚኖሩባቸውን አካባቢዎች - ቤንጋዚን ጨምሮ - ለመጠበቅ ‹‹ሁሉንም አስፈላጊ እርምጃዎች›› እንዲወስዱ ሥልጣን የሚሰጠው ይህ ውሳኔ፣ አስቀድሞ በወጣው በውሳኔ (ቁጥር) 1970 (2011)፣ በአንቀጽ 9 የተካተተውን ግን እንደማይመለከት ያስቀምጣል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ፣ በየትኛውም የሊቢያ ግዛት ውስጥ ማንኛውንም አይነት የውጭ ኃይል ወረራን በግልፅ ከልክሏል፡፡

ጉዳዩ የሚመለከታቸው አባል ሀገራትም በተሰጣቸው ሥልጣን መሰረት የሚወስዱትን እርምጃ ወዲያው ለድርጅቱ ዋና ፀሃፊ እንዲያሳውቁ ‹‹ይጠይቃል›› የሚለው የውሳኔው አካል ሲሆን፣ በክልሉ ዓለም አቀፍ ሰላምና ደህንነት መጠበቅን በተመለከቱ ጉዳዮች የአረብ ሀገራት ሊግ ወሳኝ ድርሻ እንዳለው በማተት፣ የሊጉ አባል ሀገራት ከሌሎች አባል ሀገራት ጋር ለተጠቀሱት ግቦች ትብብራቸውን እንዲያደርጉ አሁንም በመጠየቅ ወደ ዋናው የውሳኔው እርምጃ ያመራል፡፡

ሲቪሎችን ለመጠበቅ እርዳታ ለማድረግ ሲባል፣ በሀገሪቱ የአየር ክልል ሁሉም በረራዎች የታገዱበት ይህ የውሳኔው ክፍል፣ ብቸኛ ዓለማቸውን በሰብዓዊ ድጋፍ ላይ ያደጉ (ከላይ በተጠቀሰው መሰረት ሥልጣን ተሰጥቶአቸው ለሚከናወኑ በረራዎች) በረራዎችን ግን ሚመለከት አይደለም፡፡ በዚህ ውሳኔ (1973) የታየው ሌላው ጉዳይ በውሳኔ 1970 (2011) የታየውን ይመለከታል፤ ያም የጉዞ (መንቀሳቀስ) ገደብ ነው፡፡ ይህም እገዳ ተፈፃሚ ከሚሆንባቸው ሰዎች መካከል ቁረን ሳህሊ ቁረን አል-ቃዳፊ (በቻድ የሊቢያ አምባሳደር እና ለሥርዓቱ ቅጥር ነፍሰ-ገዳዮችን በመመልመልና በማደራጀት ቀጥተኛ ተሳትፎ ያደረጉ) እና ከሎኔል አሚድ ሁሴይን አል-ኩኒ (የደቡብ ሊቢያ ገዥ እና ገዳይ ቅጥረኞችን በመመልመል ቀጥተኛ ተሳትፎ ያላቸው) ይጠቀሳሉ፡፡

ንብረታቸው እንዳይንቀሳቀስ እግድ የተጣለባቸው ደግሞ፣ አቡ ዛይድ ኡማር ዶርዳ (የውጭ ደህንነት ድርጅት ዳይሬክተር)፤ ሜጀር ጄኔራል አቡባክር ዩኒስ (መከላከያ ሚኒስትር)፤ ማቱቅ ሞሀመድ (ሴክሬታሪ ኦፍ ዩቲሊቱስ) እና ሌሎች ተካትተውበታል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ፣ ሙሉ በሙሉ የሙአመር ጋዳፊ ቤተሰቦች

ብቻ በብቸኝነት ያዟቸው ድርጅቶች ለሥርዓቱ የገንዘብ ምንጭነት ሊውሉ ይችላል በሚል ሁሉም ላይ ማለት ይቻላል እግድ ተጥሏል፡፡

የሊቢያን አገዛዝ ከሚወስዳቸው አስከፊ እርምጃዎች ያቅባል ተብሎ ከተወሰደው የምክር ቤቱ ውሳኔ በተጓዳኝ፣ ሌላው በርካታ ሀገራትን እያነጋገረ ያለው ከበረራ ነፃ ቀጠናውን ተፈፃሚ ለማድረግ እየተወሰደ ካለው ወታደራዊ እርምጃ ጋር የኃያላን ሀገራትንና ወታደራዊ ቡድኖችን የሚመለከተው ጭብጥ ነው፡፡

ፔንታጎን ባለፈው ሀሙስ እንዳስታወቀው አሜሪካ በጋዳፊ ኃይሎች ላይ የታወጀውን ዘመቻ መሪነቷን ለሰሜን አትላንቲክ ቃልኪዳን አገሮች (ኔቶ) እስከዛሬና ነገ ድረስ ልታሸጋግር እንደምትችል ነው የተጠቆመው፡፡ ያን ብታደርግም ቅሉ፣ ቀጣይነቱ አስፈላጊ ሆኖ እስከተገኘ ድረስ የአውሮፕላን ጥቃት መሰንዘሯን ልትገፋበት የመቻሏ እድል እንዳለ ተጠቁሟል፡፡ የኦባማ አስተዳደር የሊቢያው ዘመቻ ወደ ‹‹ኔቶ›› በአፋጣኝ እንዲሸጋገርለት በእጅጉን የፈለገው ሆኗል፡፡ ይህም ምናልባት አሜሪካ በአረቡ ዓለም ካላት የጣልቃ ገብነት ተሞክሮ ጋር ሊያያዝ እንደሚችል ተገምቷል፡፡ የኔቶ አዛዥ - ‹‹ኖርዝ አትላነቲክ ካውንስል›› - ይህንኑ የአሜሪካ ፍላጎት በሚመለከተውን ጉዳይ፣ ማለትም የጥምረቱን ኃይሎች መሪነት እንዲረከብ፣ የመጨረሻ ስምምነት ለማድረግ በብራሰልስ ለቀናት ተሰይሞ ነበር፡፡ ካውንስሉ ለአንድ ሳምንት ያህል ተሰብስቦ ቢመካከርም ውሳኔ ላይ ለመድረስ ቀላል አልሆነለትም፡፡ ካጋጠሙት አለመግባባቶች መካከል አጠቃላዩን ፖለቲካዊ ቁጥጥር እና ተልዕኮው ሊሚኖረው ይገባል የሚሉት ዋነኞቹ ያላግባቡ ነጥቦች ናቸው፡፡

አሜሪካ ፍላጎቷ ከተሳካ በቀጣይ የሚኖራት ድርሻ ‹‹ድጋፍና እርዳታ የማድረግ አስተዋጽኦ›› እንደሚሆን የኋይት ኃውስ ፕሬስ ሴክሬታሪ ጄይ ካርኔይ የገለፁት ባለፈው ሃሙስ ነው፡፡ ይህም ድጋፍና እርዳታ የአሜሪካንን የስለላ ተቋማትንና ወታደራዊ ብቃቶቿን፣ የኤሌክትሮኒክ ሽበባን (ሮኬቶችንና ሚሳየሎችን ለማደን)፣ የጥምረቱን አውሮፕላኖች ነዳጅ መሙላት፣ ሊቢያን በአየርና በሳተላይት መከታተል ያካትታል፡፡ የኦባማ አስተዳደር ዘመቻው እንዲጀመር ከሁሉም ቀድመው ግፊት ያደረጉ የጥምረቱ አባል ሀገራት አማራጭ መፍትሄ ይዘው እንዲመጡ እየወተወታቸው ይገኛል፡፡ ይህም ይሳካ ዘንድ ሴክሬታሪ ክሊንተን ከእንግሊዝ፣ ፈረንሳይና ቱርክ አቻዎቻቸው ጋር መክረዋል፡፡ ሌላው ከዚሁ በሊቢያ ላይ እየተወሰደ ካለው እርምጃ ጋር በተያያዘ የሩሲያ ፖለቲከኞች አለመግባባት ትኩረት የሳበ ሆኗል፡፡ እንደዘገባዎች ከሆነ ፕሬዝዳንት ሜድቬዴቭ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ፑቲን የፀጥታው ም/ቤት በወሰነው ውሳኔ የተለያያ አቋም ነው ያንፀባረቁት፡፡ ይህንኑ ተከትሎ ፕሬዝዳንት ኦባማ ለሩሲያው አቻቸው ስልክ በመደወል፣ በሊቢያ ላይ ለተወሰደው እርምጃ ወሳኝ የነበረውን የሀገራቸውን ድምፅን በድምፅ የመሻር መብት ተጠቅመው ሩሲያን የውሳኔው አካል በማድረጋቸው አድናቆታቸውን ገልፀውላቸዋል፡፡ የአፍሪካውያኑ የተቃውሞ ንዝረት ከሰሜን አፍሪካ (በስተምዕራብ አቅጣጫ) ተነስቶ የአህጉሪቱን ሰሜን-ሰሜን-ምስራቅ ጫፍ አቅጣጫ ይዞ፣ በርሃ እያቆራረጠ ባሕር ተሻግሮ መካከለኛው ምስራቅ ለመዝለቅ ብዙም ግዜ አልወሰደበትም፡፡ የንዝረቱ መጠን መንቀጥቀጥ ሆኖ ከተለወጠባቸው መንግስታት መካከል የመን፣ ባህሬን፣ ሶርያ … ተጠቃሾች ናቸው፡፡ ይህም ንዝረት ምንም እንኳን ባህር የተሻገረ ቢሆንም፣ የኋላ ኋላ ወደ ተቀሩት የአፍሪካ አህጉር አቅጣጫዎች ተመልሶ ሊመጣ የሚችል ነው - የአብዛኞቹ የአፍሪካ ሀገራት ዴሞክራሲያዊም ሆኑ ሌሎች ጥያቄዎች ከሰሜን አፍሪካና ከመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት እምብዛም አይለይምና፡፡ በዓአቀፍ ሕግ ለአንዲት ሀገር መንግስት እውቅና ለመስጠት የራሱ ሥነ-ሥርዓት አለው፡፡ ይህ አካሄድ በፈረንሳይና በፖርቹጋል በውል ይጠበቅ አይጠበቅ በእርግጠኝነት እስከአሁን ባይታወቅም፣ ሸንጎው በእነዚሁ ሁለት ሀገራት የሊቢያውያን ብቸኛው ‹‹ሕጋዊ ወኪል›› ተብሎ እውቅና ተሰጥቶታል፡፡

የተ.መ.ድ ውሳኔ ተፈፃሚነትና የኃያላኑ ‹‹አለመግባባት››

Page 16: awramba 160

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 160 ቅዳሜ መጋቢት 17 2003

ሴት

16

፡ ዕርቃነ ስጋ እስከማውጣት ይደርሳል፡፡ ያንን ደግሞ በትክክል መፍረድም አንችልም፡፡ አንቺም በዳኝነት ሥራው ተሳትፎ ስለነበረሽ ከምትይው ነገር ጋር አይጋጭም?ቁንጅና፣ ፋሽን ሾውና ሞዴሊንግን ማሳየት እወደዋለሁ፡፡ እደግፈዋለሁ፡፡ ውበትንም እኩል እሰራለሁ፡፡ አደንቃለሁ፡፡ አወራለሁ፡፡ ይኼ ማሳየት እንጂ ማወዳደር አይደለም፡፡ ውድደር አቅርበህ ‹‹እከሌ አከሊትን ትበልጣለች፡፡ ሁሉም ውድቅ ናቸው፤ አንደኛዋ ይህች ነች›› ነው የሚባለው፡፡ የማንም ልጅና ውበት ውድቅ አይደለም፡፡ ሁሉም ውበት አንደኛ ይወጣል ባይ ነኝ፡፡ እኔ ውበትን እሰራለሁ እንጂ አላወዳድርም፡፡ ስለውበት በጣም ስለማደንቅ አወራለሁ፡፡ ነገር ግን ዳኛ ሆኜ ብዙ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሰርቻለሁ፡፡ ይኼ ስህተት መሆኑን አስተምሮኛል፡፡ ውስጡ ስትገባ ሁሉንም ታውቃለህ፡፡ አለበለዚያ ማውራት አትችልም፡፡ እስከአሁን ድረስ በሰራንባቸውም ባልሰራንባቸውም ፍርደ-ገምድል ነን፡፡ ትክክለኛ ፍርድ ፈርደን አናውቅም፡፡ ‹‹የሚሰራው ሥራና ቁንጅናን ማወዳዳር ቆሻሻ ሥራ ነው›› ብዬ አፌን ሞልቼ መናገር እችላለሁ፡፡ተወዳዳሪ የነበሩ ብዙ ልጆች ሲያድጉ መወዳደራቸው ስህተት መሆኑን ይስማማሉ፡፡ ይህንን ብዙዎች ይነግሩኛል፡፡ የሚያወዳድሩትን ተዉ እያልን ነው፡፡ ፈረንጅ ስላደረገውና ዓለም ስለተሳሳተ ማድረግ የለብንም፡፡ በውድድሮች ላይ ሰዎች ቢወዛገቡ አይገርመኝም፡፡ ከዚህ በፊት አይቻለሁ፡፡ በዚህ ከቀጠለ ገና ብዙ ውዝግብ ይኖራል፡፡ ካወቁት ማንም ወላጅ ልጁ፣ ወንድም እህቱ እዛ ውስጥ እንድትገባ የሚፈልግ አይመስለኝም፡፡ እንዳልኩት ከበስተጀርባ ብዙ አስቀያሚ ነገሮችን አይተናል፡፡ ፊት ለፊት የምናየው ነገር ውሸት ነው፡፡ እውነቱ ይኼ ነው፡፡ ሰዎች ሳያወዳድሩን የተሻልን ሆነንና በራስ ተማምነን መቆም እንችለለን፡፡ ደግሞስ ማነው አወዳዳሪው? ማንስ ነው አዘጋጅ? ማነው ተጠቃሚው? ... ቶሎ መንቃት አለብን፡፡ ውስጣችንን ፈትሸን መልካም ነገሮች ብቻ ከውስጣችን ሊወጡና ውጫዊ ማንነታችንንም ልንቀበለው ይገባል፡፡ከውበት ወጣ እንበልና፤ ስለአረብ ሀገራት ሕዝባዊ ተቃውሞዎች እናውራ፤ ሊቢያ በአሁን ወቅት አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ትገኛለች፡፡ መጨረሻው ምን የሚሆን ይመስልሻል?ፖለቲካ ውስጥ እያስገባኸኝ ነው፡፡ [ረዥም ሳቅ] አዎ ... የሊቢያ መጨረሻ ደስ የሚል አይመስለኝም፡፡ ፈጣሪ ይጠብቃቸው፡፡ ጥሩ ነገር ይምጣላቸው፡፡ ሁልግዜ የማየው፣ ከፍተኛ የእርስ በእርስ ፉክክሮች የምንላቸው ነገሮች ዓለማችንን እያበላሹ ነው፡፡ ዓለማችን ቆንጆ መሆን ትችላለች፡፡ ሁላችንም በቂ ነገር ኖሮን ተደስተን መኖር የምንችልባት ናት፡፡ ግን ስግብግቦችና ኃያላን ሀገራትም ስላሉ ነገሮች ሁሉ እየተበላሹ ይገኛሉ፡፡ እነአሜሪካን ምን እየሰሩ ነው? ለምንድን ነው እንደዚህ እንድንሆን የሚያደርጉት? ምንድን ነው ያለው እንቆቅልሽ? ማየት እንችላለን፡፡ ጋዳፊስ ቢሆኑ ለምን ሕዝባቸው በዚህ ዓይነት ነገር ያዙት? የምንፈትሻቸው ነገሮች አሉ፡፡ ለእኔ እነዚህ ነገሮች ስግብግብነት ናቸው፤ ሌላ ትርጉም የለውም፡፡ ይኼ ደግሞ እንደዚህ አይነት ነገር ያመጣል፡፡ ይኼ ባይኖር ኖሮ ያ ሁሉ ገንዘብ እያላቸው አይደለም ለአምስት ሚሊዮን ዜጎቻቸው ለሌላም ይተርፉ ነበር፡፡ አሜሪካውያን ደግሞ የራሳቸው አጀንዳና የሚፈልጉት ነገር አለ፡፡ በዚህ ግዜ ክፍተት አገኙ፡፡ ክፍተቱንም ሕዝቡና መንግስት ሰጣቸው፡፡ ... የኢራቅን ሁኔታ አይተናል፡፡ እስከአሁን ደም እየፈሰሰ ነው፡፡ መጨረሻው ጥሩ ካልሆነ፣ ጋዳፊ መውረድ አለባቸው እያልሽኝ ነው?ጋዳፊ የግድ መውረድ አለባቸው፡፡ ይኼን ያህል ግዜ ለአንድ መሪ ጥሩ ነው ብዬ አላስብም፡፡ ጥፋት ያለበት አወራረዱ ላይ ነው፡፡ ሲወርዱ ሕዝቡ ብዙ ነገር አሳልፎ እዚህ ላይ ትዕግስት መውሰድ አለበት፡፡ የራስህን ጉድ ለሌላ ማውጣት የለብህም፡፡ እኛ ደግሞ ከዚህ ምን እንማራለን ብለን ማየት ይኖርብናል፡፡ እኛ ራሳችን መጠንቀቅ አለብን፡፡ ሁላችንም አንድ ሕዝብና ወገን ነን፡፡ ከአሁኑ እንደ አንድ ቤተሰብ ሆኖ ሕዝብ፣ መንግስትና ተቃዋሚ ፓርቲዎች ተሰባስበን ‹‹ለሀገራችን ምን ይበጀናል?›› ማለት አለብን፡፡ ከዚህ ነገር የመንማረው፣ ለልጄ፣ ለልጆቻችኝ የምናስቀምጥላቸው

ምንድን ነው? እንደዚህ መሆኑ ማነው የሚጠቀምበት? ብለን እኛም ከአሁኑ ማሰብና መነጋገር አለብን፡፡ አሉታዊ ነገሮቻችንን ማስወጣት አለብን፡፡ በዚህ ላይ ብዙ ሴቶች ቢሰሩበት ጥሩ ነው፡፡ እናቶች ጎበዞች ናቸው፡፡ ወንዶቻችንም ጎበዞች ናችሁ ግን ሴቶች ይህንን የማየት ችሎታና ‹‹እንዴት አድርጌ አስታርቃለሁ፣ አስባስባለሁ?› የሚል ክህሎት በተፈጥሮ አላቸው ብዬ አስባለሁ፡፡ እንደዛ ቢደረግ፣ ‹‹No!›› ቢባል ... መቃወም ነውር የለውም፡፡ የማንፈልገውን ነገር መናገር አለብን ብዬ አስባለሁ፡፡ ግን ስሜታዊ ሆነን መጯጯህ የለብንም፡፡ የምንጎዳው እኛው ነን፡፡ በሊቢያ የሞቱትን ሕፃናትና የጠፋውን ንብረት ማነው የሚተካው? አሜሪካውያን ምንም እየሆኑ አይደለም፤ ሀገራቸው በሰላም ተቀምጠዋል፡፡ የሊቢያ ሕዝብ እየተጨፋጨፈና እሳት እየተንቦለቦለ ነው፡፡ እኛ ሀገረ ያ እንዳይሆን፣ ለእነርሱም ጥሩ እንዲመጣ እንመኛለን፡፡ ቃዳፊ ጥሩም የሚያስጠላም ነገር ነበራቸው፡፡ እኔም ራሴ በሴቶች ዙሪያ በቅርበት ያየኋቸው የሚዘገንኑ ነገሮች ነበሩ፡፡ እኛም ሀገር ሲመጡ ምን ሲሰሩ እንደነበር እናያቸዋለን፡፡ ያ ከአንድ መሪ የሚጠበቅ አይደለም፤ ያሳፍራል፡፡ ይሄ ሲገርመኝ ነበር፡፡ ሀገራቸውም ሄጄ በሕዝቦቻቸው ላይ የነበረውን ጫና ተመልክቻለሁ፡፡ ... እኛም ጠንቀቅ ማለት አለብን፡፡ [እየሳቀች] .....[ዘሚ ተከታዩን ጥያቄ እየመለሰች በነበረበት ወቅት ቃለ ምልልስ በምናደርግበት መኪናዋ በጎን መመልከቻ መስታወት በኩል አንዲት አዳጊ የአዕምሮ ሕመም ችግር የነበረባትን ልጅ ተመለከተች፡፡ ይቅርታም ወዲያው ጠይቃኝ ከመኪናዋ ወረደች፡፡ ልጅቷንም በፍቅር ስማ በማነጋገር፣ ከልጅቷ እናት ጋርም ስለችግሯ ሃሳብ በመካፈል ስልክ ተቀያይራ ነበር]‹‹በሀገራችን እንደዚህ አይነት ነገር ሊከሰት ይችላል›› ለሚሉ አስተያየትስ?[በጣም ዘና በማለትና ለመናገር በጣም ነፃ በመሆን] ... እውነቱን ልንገርህ፡፡ እኔ እንደሚመስኝ፣ ይኼን ነገር እኛ አልፈነዋል፡፡ የሕይወትና የዓለማችን ሕግጋት አሉ ብዬ አምናለሁ፡፡ እኛ ያሳለፍነው ነገር ቀላለ አይደለም፡፡ ከዘውዱ ዘመን ጀምሮ በተማሪዎች ንቅናቄ፣ በደርግና እስከ 97 ምርጫ ድረስ ይኼን እኛ አልፈነዋል፡፡ ጦርነት፣ አስቀያሚ ነገር፣ ውረድ አትውረድ፣ በኃ/ስለሴ ግዜ ሕዝቡና ተማሪው አደባባይ ወጥቶ ሰላማዊ ሰልፍ ያደርግ በነበረበት ግዜ መታሰር፣ መገደል ... ይኼንኑ ነው፡፡ እኛ ያን ሁሉ ስቃይ ያለፍነውና ከአሁን በኋላ ወደእዛ የምንመለስ አይመስለኝም - በተለይ ብልጥ ከሆንን! ሕግጋቱም ይመልሰናል ብዬ አላስብም፤ አይመልሰንም፡፡ ልማት ላይ ያለን ይመስለኛል፡፡ በተለይ ሁላችንም አንድ ሆነን ከገሰገስን የኛ ግዜ ነው፡፡ በዚህ ስጋቴ ትንሽ ሲሆን ትንሿም ሰውና ሞኞች ስለሆንን ነው፡፡ ሰዎች እዚህ ጋር እንጂ አርቀን አናይም፡፡ ‹‹ለምን ይሄ ሁሉ ነገር?›› ብለን ማሰብ አለብን፡፡ በዛ ማነው ተጠቃሚው? ለምንድን ነው ልጄና የደሃው ልጅ የሚገደለው? ማነውስ የሚገደለው? ዞሮ ዞሮ በዚህ ችግር ውስጥ የሚገባው፣ እሳት የሚጎርሰው ማነው? ወጣቱ ወይስ ደሃው? በሊቢያ እያየን ያለነው ይኼን ነው፡፡ ሌላውማ ልጁን ሰብስቧል፡፡ ... ብልጥ እንሁን፡፡ በሉሲ፣ በጦርነትና በብዙ ነገር ቀዳሚ ነን፡፡ አሁንም በጥሩ ነገር ቀዳሚ መሆን እንችላለን፡፡ በሀገራችን ነባራዊ ሁኔታ መንግስትና ተቃዋሚዎች አብረው አይሰሩም እኮ፡፡የሚያሳዝነው እሱ ነው፡፡ እሱን ነው አሁን እኔ የምቃወመው፡፡ ሁለቱም ማንን ነው መምራት የፈለጉት? እኛን፣ ሕዝቡን አይደለም?! እኛ ደግሞ ድምፃችንን ማሰማት አለብን፡፡ ‹‹ልትመሩን ከፈለጋችሁ አንድ ላይ ስሩ›› ብለን ማሳመን አለብን፡፡ እኔን ሊመሩ አይደለ ይሄ ሁሉ ሩጫ? የኔ ድምፅ መሰማት አለበት፡፡ የቱ፣ ምንድን ነው የሚበጀን መባል አለበት፡፡ እነርሱ በተጣሉ ቁጥር እኛ፣ ሕዝብና ሀገር ነው የሚጎዳው፡፡ ስለዚህ ይተራረሙ፤ ተቃውሞ ካለ ይስማሙ፡፡ ‹‹ይሄ ይሻላል›› እያልን እንደሀገራችን ወግ ቢሆኑ ምን አለበት፡፡ የእኛ ችግር የውጭውን መምሰል ስንፈልግ ነው፡፡ የውጭውን ትተን ‹‹እኛ የምናደርገውና የምንፈልገው ምንድን ነው?›› ማለት ይገባናል፡፡ ትልቁ ስህተት ራሳችንን አለመሆናችን ነው፡፡ ችግሮችን መፍታት የምንፈልገው በእነአሜሪካ መንገድ፣

መሆን የምንፈልገው እንደነአሜሪካ፡፡ ይኼን ማድረግ አንችልም፣ አይሆንም፡፡ እኔ ሌላ ሰው ልሁን ብል አልችልም፡፡ ራስህን መሆን የቻልክ ዕለት ግን ሁሉም ነገር ይስተካከልልሃል፡፡ ስለዚህ አሁንም አልዘገየም፡፡ ብዙ ችግር አሳልፈናል፡፡ ልጆቻችን በየመንገዱ ወድቀዋል፡፡ ሕፃናትቶች ያሉት በየጉድጓዱ ነው፡፡ ከሀገር ውጣና ተመልከት! የት ነው ያለነው? የእኛ ሴቶችና ወንዶች የትነው ያሉት? ያለነው ስቃይ ላይ ነው፡፡ ይኼንን እያየን ‹‹ጉዳዩ የእኔ ነው ብለን በአንድ ላይ ሁላችንም መምጣት አለብን፡፡ አንዳንዴ እኮ በጎ ነገር እንዲመጣ እናት ለልጇ ስትል እንደምታደርገው ራስን ዝቅ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ሀገር ማለትም እንደዛ ነው፡፡‹‹እነ አሜሪካና ቻይና ምን አደረጉ?›› ማለትን ማቆም አለብን፡፡ ልምድ እየተባለ በመንግስትም ሆነ በሕዝብ በኩል የሚመጣውን ነገር አልወደውም፡፡ ሌሎች ሀገራት ‹‹ምን እያደረጉ ነው?›› የሚለውን በፖለቲካውም ገልብጠን እናስቀምጠዋለን፡፡ ያንን ትተን፣ ምን ይሻላል ብለን የራሳችንን የጀመርን ዕለት ያኔ ሰው እንሆናለን፡፡ ለዚህ ግልፅ ውይይት፣ ምን እናድርግና መልካም ልብ ያስፈልጋል፡፡ እያዳንዳችን ውስጥ ዘረኝነት አለ፡፡ እከሌ እከሌ ሳይባል ነፃ ሆነን ይኼንን ከመረመርነው እናገኘዋለን፡፡ ዘረኝነት በዘር በሌላም ነገር አለብን፡፡ ሁሌ አንዱ ከአንዱ የበላይ ነው፡፡ ይኼ ዘረኝነት መቆም አለበት፡፡ የለየን ቋንቋ ነው፡፡ ትግሬ፣ አማራ፣ ኦሮሞ፣ ጉራጌ ... ይባላል፡፡ ሰው ሰው ነው፡፡ በተለይ ይሄ ቀርቶ ወደ አንድነት መምጣት አለብን፡፡ በአፍሪካ መሪዎች ላይ የሚታየው አምባገነንነትና ለረዥም ዓመታት ሥልጣንን የሙጥኝ የማለቱ የመጨረሻ መፍትሄ?ይኼንን በሁለት ነገር ማየት እንችላለን፡፡ አንድ መሪ ለአንድ ሀገር ሰላም የሚያመጣና ጥሩ መሪ ሆኖ ረዥም ግዜ ከቆየ፣ ሌላው አደረገው ብለን ለምን እኛ እንከላከላለን፡፡ .. እንደገና ደግሞ ነገሮች የሚሰለቹም ከሆነ ታውቃለህ፣ በቃኝም ልትል ትችላለህ፡፡ መሰልቸትም ስላለ ለውጥ ትፈልጋለህ፡፡ ያኔ ደግሞ ለምን አይሆንም፣ እንደው ለለውጥም ቢሆን ትላለህ፡፡ የሚሆነው ይኼን ማስታረቅ ነው፡፡ ተጠንቅቀን ነገሮችን ካደረግናቸው ለእኛ የሚበጀንን ቤተሰብ ሆነን በመመካከር፣ ዘር ሃይማኖት ሳንል የሚሻለንን መወሰን አለብን፡፡ አሜሪካ የተደረገው ነገር ለእኔ አይሰራልኝም፡፡ መራራ ሽንፈት ላንቺ ምንድን ነው?አላውቅም፤ እኔ የምሰተው ምላሽ እናንተ የምትፈልጉ አባባል ላይሆን ይችላል፡፡ ግን ለእኔ መራራ ሽንፈት እየቻልኩ አለመስራት፣ እውቀት ኖሮኝ እውቀቴን አለመጠቀሜ ነው፡፡ ሞክረህ የማይሳካ ነገር ለእኔ ሽንፈት አይደለም፡፡ ቢያንስ ሞክረሃል፡፡ ለምሳሌ ሥልጣን ቢኖረኝ በኋላ ላዝንበት የምችለው ነገር በሥልጣኔ ላይ ሆኜ አለመጠቀሜ (በገንዘብ አይደለም)፣ በሥልጣን ተጠቅሜ በጎ ነገር አለመስራቴና ለውጥ አለማምጣቴ፣ መምራት እየቻልኩና በሀገር ላይ ለውጥ ማምጣት ስችል አለመምራቴና አለመቻሌ፣ ሥልጣን ላይ ሆኜ ብዙ ሕዝብ መርዳት ስችል አለመርዳቴና ማስተላለፍ የሚገባኝን እየቻልኩ ያንን ማድረግ ባለመቻሌ ተሸንፌያለሁ፡፡ ይኼ የመጨረሻ ሽንፈቴ ነው እላለሁ፡፡ በመጨረሻ፤ የበርማዋ የነፃነት ታጋይና በቅርቡ ከቁም እስረኝነት የተፈታችው ማነች?አላውቃትም! ስለበርማ አላውቅም፡፡ [ሳቅ] አንድ ነገር እዚህ ላይ ልንገርህ፤ አሁንም ብዙ ነገራችን ከውጪ ሀገራት ጋር የተያያዘ ነው፡፡ እኔ ስለእርሷና ስለበርማ የማጠናበት አንጎል የለኝም፡፡ አንጎሌ እዚሁ በብዙ ነገር በተያዙ ልጆች ላይ ነው ያለው፡፡ በኦቲዝም ለረዥም ዓመት ጥፋት ሳያጠፉ የታሳሩትን ልጆች ጠይቀኝ፡፡ በድህነትና በመኃይምነት ስለታሰሩት ወገኖቼ ላውራልህ፡፡ [እየሳቀች] ይቅርታ ካልመለስኩልህ፡፡ ተንጠልጥለናል፤ ከታች ያለውን እናፅዳው፡፡ [ዘሚ ስለእሷ ለማወቅ አንጎልሽን ባትሰጪም ሳን ሱቺ ነች]

ጉራማይሌውሙዚቃዊ ቋንቋ

በቋንቋ ይገለፃሉ የሚባሉ ነገሮች አሉ፡፡ አንዱ ፍቅር ነው፡፡ ፍቅር በተለያየ ቋንቋ ይገለፃል፡፡ በአይንም ይገባል ይላሉ፡፡ ያ እንዴት ይሆን? ተሞክሮ ያለን እናውቀዋለን፡፡ ለዚያ ይሆን የሙዚቃዋ ንግስት አስቴር አወቀ ‹‹ፉርሽ ፉርሽ አለ ደከመ ጉልበቴ፣ ፍቅር ገባ ባይኔ ከዳኝ ሰውነቴ›› ማለቷ? ከዚህ ቀደም በዚሁ ዓምድ ላይ ወንዶች ፍቅራቸውን ለሴቶች እንዴት አድርገው በሙዚቃ እንደሚገልፁላቸው ለማየት ሞክረናል፡፡ የእሷስ? እሷ ለእሱ ያላትን ፍቅር፣ ጥርጣሬ፣ አክብሮት ... እንዴት ትገልፀዋለች? በተቃራኒው ያሉት ከሚገልጹት ፍፁም የተለየ እንደሆነ ተገንዝበን ይሆን? የተወሰኑ ምሳሌያዊ መገለጫዎችን እንመልከት፡፡ስለእንስት አቀንቃኞች ስንነጋገር፤ ለአንዳንዶቹ የመኖር ሊሆን ይችላል ወይም ሌላ ... ተስፋ ‹‹ዓይን›› ነው ‹‹አይኑ፣ ተስፋዬ ነው አይኑ›› ስትል ፍቅርዓዲስ የምታቀነቅነውን ያህል፣ ለድምፃዊት አስቴር ደግሞ ‹‹ከከንፈሩ ሲሸሽ ሲገለጥ ጥርሱ›› ስትል የእሱ መሆን ያስመኛትን የሰውነት ክፍል ‹‹ጥርሱ›› መሆኑን ነግራናለች፤ ‹‹አንድም ተፈወስኩኝ አንድም ተሸሸኩኝ፣ በእጁ በመዳፉ ስንቱን ተሻገርኩኝ›› ስትል መዳፉ ለእሷ ከመዳፍም በላይ መሆኑን ከፀደኒያ አንደበት ሰምተናል፡፡ ‹‹ ... ባማረው ባትህ እስቲ ተለመነኝ?›› ‹‹አቦ ሸማኔ›› በተሰኘው ዜማዋ እጅጋየሁ ሺባባው ተማጽናለች፡፡ በእያንዳንዱ ወንድ ውስጥ የተወሰነም ቢሆን የሴትነት ባህሪ እንዳለ ሳናስተውል አልቀረንም፡፡ ለዛም ይመስለኛል ወንድ ደራሲያን ለወንድ እና ለሴት ዘፋኞች ገጥመው የሚያበረክቱት ግጥም ልዩነት ያለው የሚሆነው፡፡ ለሴቶች ገጥመው ሲሰጡ ሙሉ ለሙሉ የሴትነት መንፈስን ተላብሰው እና መንፈሳዊ ስሜቱን ተጋርተው ይመስለኛል፡፡ በፍቅር ግንኙነት ወቅት በራስ በመተማመን የማያምን አለ ቢሉኝ አያሳምነኝም፡፡ የሙዚቃ ዓለም ውስጥ እንዳለን ሆነን እናስብና በዚህ ‹‹በራስ መተማመኑ በኩል›› ማን የበለጠውን ቦታ ይይዛል ብለን እንጠይቅ፡- በዚህ ላይ እርማት እሻለሁ “ባልተከለከለ በሚበላ ፍሬ አገኝሃለው ተው በኋላበእጅ አዙር አይደለም፤ መጥቼፊት ለፊት ነው የማገኝህ ኮርቼ...” ስትል አበባ ደሳለኝ የእሱ ኩራት ምንም እንደሆነ እና እሱን የማግኘት በራስ መተማመኗ እስከምን ድረስ እንደሆነ አስጠንቅቃዋለች፡፡ ምን አልባትም ይህ ዘፈኗ “ ‹ቆይ እኔ አይደለሁም ባላምበረክካት እንደኮራችብኝ ልክ ባላስገባት›ያልኩት ውሸቴን ነው አሁን አላመርምራሴን እያታለልኩ ከእንግዲስ አልኖርም” ላለው አቀንቃኝ ማስተማሪያ ይሆን? ይህ ብቻም አይደል፤ በፍቅር ውስጥ ፀብ መኖሩ እንዳለ ሆኖ እንደየሁኔታው ይቅር መባባልም የሚበረታታ ነገር ነው፡፡ በይቅርታ አድራጊነት በኩል ማን ቀዳሚውን የይቅርታ ሰጪነት ቦታ ይይዛል፡- “አስቀይመኸኝ ውስጤን ብትጎዳውእየዋሸኸኝ ሆዴን ቢከፋው ማለፍ ይሻላል ይቅር ብያለሁ” በማለት ለይቅርታ እንደማትሰስት እና የይቅርታ ግዜ እንደማይረፍድ ድምፃዊት ፀደኒያ ብታሳውቅም “አልረፈደብሽም አልዘገየሽም ወይለወደደ ጊዜው ፋታ ይሰጣል ወይ?በማለት ለይቅርታ ቀነ ገደብ በማስቀመጥ ‹እንደረፈደ› እና ‹እንዳትሞክረው› በሚመስል መልኩ ድምፃዊ ሙሉቀን ለይቅርታ ማን ቀና እንዳልሆነ አሳይቶናል፡፡ መለያየትን ‹ክፉ› ከሚል ቃል ውጭ ትርጓሜ ያጣለት ይመስላል - አርቲስት ጥላሁን ገሰሰ፡፡ በእርግጥም ልክ ነው፡፡ ክፉ ማለት ንፉግ ማለት አይደል? እንዲያ ነው፡፡ የምንወደው ሰው ሲለየን/ስትለየን የምናገኘውን ደስታ በመለያየት ምክንያት እየተነፈግን ነው፡፡ መለያየትን ፉርሽ የሚያደርገው ቃል ‹ጽናት› ነው፡፡ አቀንቃኙ ገረመው ግን በዚህ በመራራቅ ጉዳይ መፈተኑን እና አስጨናቂ ምርጫ ውስጥ መግባቱን “ቁርጡን ንገሪኝ ባክሽ አደራ እኔም የራሴን ህይወቴን ልምራአልታይ አለኝ ሴት ካንቺ ሌላለራሴ አልሆንኩም እኔ አጣሁ መላ” ሲል የተሰላቸ በመሰለ መንገድ ገልጾላታል፡፡ ምን አልባትም፣ “ትዝታን ከልብህ ይዝራ ይሰማ ድምፄ አልፎ ጋራ ይድረስ ከአገር ቤት ሩቅ ሃገር ያውጋልህ ናፍቆቴን ያብስር አልወላወልኩም ከልቤ እጠብቅሃለሁ ርሃቤ ...” ስትል “ሃሎ አዲስ አበባ” በሚለው ዘፈኗ የምናውቃት ድምፃዊት፣ ትዝታ ጽናት እንደሆናት ለሚገልፀው አባባሏ የሚያሳፍር መልስ አይሆንባት ይሆን?የሴቶቹ አዘፋፈን ወደ ሩህሩህነት፣ ወደ ልምምጥ ያደላል የሚል ትችት ብጤ ይሰነዘርበታል፡፡ የተወሰነ እስማማለሁ፡፡ በሴቶች ውስጥ ከወንዶች በበለጠ ሩህሩህነት አለ ብል ራስ ወዳድነት አይሆንብኝም፡፡ አንዳንዴ (ቢያንስ በአንድ ካሴት ውስጥ ከአንድ በላይ) “ያለእርሱ ምንም እንደማይቋቋሙ” አድርገው ያስቡና መኖራቸው እዛ ጋር ያቆመ እንዲመስለን ያደርጉናል፡፡ “ባትለየኝ እኔን ምን አለ ... የልቤን አቅም ስታውቀውትዝታን መቋቋም አቅቶኝ ስትርቀኝ መንፈሴት ጨነቀው” ስትል ፍቅርዓዲስ ‹ተመለስ› በተሰኘው ዜማዋ ድክመቷን አስደምጣናለች፡፡ ሔለን በርኼ “እስቲ ልሂድ ደግሞ እንግዲህ ምን ቀረኝ ፍቅሬ አልቋል አለኝ” ‹ምን ቀረኝ› የሚለው አባባል ‹እሱ ብቻ ነው ያለኝ› የሚለውን አባባል እንደሚያጠናክር ልብ ይሏል፡፡ ዘሪቱ ከበደ “ስተወኝ ተውኩ ራሴን ጣልኩ እኔን ከፋው ውስጤን ሐዘን በላኝ በቁሜ ሳሳሁ ተለየኝ አቅሜ” ይህን ዜማ ስንሰማ እውነት ነው ብለን ብናስብ ይህቺ አቀንቃኝ ከዚህ ቀን ያለፈ እድሜ ያላትም አይመስለንም ነበር፡፡ በመለያየት ወቅት ጥንካሬዋ፣ ቁንጅናዋ፣ ውበቷ፣ ሃይለኝነቷ ... ያለእሱ ባዶ እንደሆነ አድርጋ ታቀነቅናለች፡፡ እሱ በእሷ ውሎ ውስጥ ከሌለ “ምንም” የለም ብላ ስለምታስብም እሱን ለማሳመን ማቀንቀኗን ከድክመቷ ትጀምራለች፡፡ የእሱስ? ሁሉም ባይባልም ከእሷ በእጅጉ የተለየ ነው ያሰኛል፡፡ “ተለያዩ ሲባል ኧረ ሰዉ ምን ይለናል?እሺ የኛስ ይሁን የሰማን ሰው ምን ይለናል ....‹ግዴለም› አትሂጂ አብሮ መኖር ይሻለናል”ሲል እሱን የቆረቆረው እሷን ከማጣቱ ይልቅ የሰው ትዝብት መሆኑን ገልጾላታል፡፡ ለዚህም ‹ግዴለም› የምትለዋ አባባል ጥሩ ማሳያ ናት ብዬ አምናለሁ፡ “እንግዲህ የሩቅ ሰው ተጓዥ አልጠብቅምቢጤዬን መፈለግ ሳይሻል አይቀርም” ሲልም አርቲስት መሐሙድ ለነገሩ መፍትሄ ከመፈለግ ይልቅ ወደአፋጣኝ እርምጃ እንደገባ አሳይቶናል፡፡ ያኔ እንዳልነው ነው፡፡ ፍቅር ይቅር ባይ ነው፣ ታጋሽ ነው ... ፍቅር ሁሉንም ነገር ነው፡፡ ያን የምንገልፅበት መንገድ ደግሞ አንዱ ሙዚቃ ነውና መልዕክት የምናስተላልፍበት መንገድ በተቀባዩ ስነልቦናም ሆነ ልቦና ውስጥ “ቁጭ” የሚል ነገር በመሆኑ ልንጠነቀቅለት ይገባል፡፡ በዚህ ዙርያ በሙዚቃዎቻችን ስለተገለጹት አውስተን የምንጨርስ አይመስለኝም፡፡ እና አንድ ቀን መመለሳችን አይቀርም ማለት ነው!

‹‹እያዳንዳችን ውስጥ...

Page 17: awramba 160

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 160 ቅዳሜ መጋቢት 17 2003 ል ዩ ቅ ኝ ት 17

ትርምስ፣ መደማመጥ አለመቻል፣ ማስነጠስ፣ ማሳል በተናጠልም ሆነ በአንድነት ማክሰኞ፣ ሐሙስና ቅዳሜ የሚውለውን የገበያ ስፍራ ይገልፀዋል፡፡ በሚደምቅበት “ቅዳሜ” ቀን መጠሪያውን አድርጓል፤ ከቡታጅራ 18 ኪሎ ሜትር ርቀት በምትገኘው እንሴኖ ከተማ ላይ የሚገኘው ቅዳሜ ገበያ፡፡

የእህል፣ የጥራጥሬ፣ የቅባትና የቅመማ ቅመም አይነቶች፣ ለእለት ተዕለት ለቤት ውስጥ መጠቀሚያነት የሚሆኑ የምግብ አይነቶች እንዲሁም ልባሽ ጨርቅን ጨምሮ ሌሎች ቁሳቁሶች በዚህ ገበያ ላይ ቢኖሩም በዋናነት የማረቆ በርበሬ ማዕከልነቱ ይታወቃል፡፡ አራት ማዕዘን ቅርፅ በያዘ ሰፊ ሜዳ ጠርዝ ላይ ያለው አቧራው የሚጨሰው የማረቆ በርበሬ መሸጫ- የቦታው ብራንድ ነው፡፡

በአንድ ርምጃ ርቀት የበርበሬ ዛላ “ቁልል” በቦታው ይታያል፡፡ ሁሉም ሻጮች ሴቶች መሆናቸውን የቃኘሁ ሲሆን እያንዳንዳቸው አንድና ከአንድ በላይ የበርበሬ አይነት ይዘው ገዢን ለመሳብ ይጥራሉ፡፡ አንገታቸው ላይ ሁሉም ማለት ይቻላል በጨሌ የተሰራ ጌጥ አድርገዋል፡፡ ገበያው ላይ የተለያዩ ጎሳዎች ለግዢም ሆነ ለሽያጭ ይንሸራሸራሉ፡፡ ብዙዎቹን (ገዢንም ሆነ ሻጭን) ፍሎራይድ የበዛበት ውሃ ከመጠጣት ሳቢያ ጥርሳቸው መወየቡ ያመሳስላቸዋል፡፡

እዚያው ገዛች እዚያው ሸጠችሰኔ ማለቂያና ሐምሌ ላይ ቃሪያ

ይደርሳል፡፡ እየቆየ ሲሄድ (ሲያረጅ) መልኩ ይቀላል በዚህ ጊዜ (በመስከረም ወር) ስሙ በርበሬ የሆነው ተክል ለለቀማ ብቁ ይሆናል፡፡ ይህም ቅዳሜ ገበያ በሰው ነጭ የሚሞላበት ጊዜ ለመቃረቡ ምልክት ነው፡፡

ገበያው ከጠዋቱ ሦስት ሰዓት እስከ ምሽቱ አንድ ሰዓት ይውላል፡፡ ሻጮች ከሜዳው ላይ ውልፍት አይሉምና ምሳን “አስበውት” ይውላሉ፡፡ ግፋ ቢል ሸንኮራ መጥጠው ኃይል ቢገነቡ ነው፡፡ ከራስ ማሰሪያቸው በላይ ፀሐይ መከላከያ “ኬሻ” ኮፍያ ጣል ማድረግ ልማዳቸው ነው፡፡

በምትግለው ቅዳሜ ሻጮች ከቡታጅራ ወደ ዝዋይ የሚወስደው መንገድ አጋማሽ ድረስ ገብተው ከመኪና “እየተጋፉ” ሳይቀር ገዢን ይጣራሉ፡፡ ዛሬ ገበያ የደራላቸው ቦታ ላይ ነገ ሌላ ሰው በርበሬ ሊያነጥፍበት ይችላል፡፡ “ይህቺ ትላንት የሸጥኩባት ‹‹አኪሬ›› የቆመባት የመሸጫ ስፍራ ነች” ብለው በቦታ አይጣሉም፡፡ “የጎላ የእርስ በርስ ግጭቶች የለብንም” የሚሉት አንጋፋዋ ወ/ሮ ፋንታዬ ኬኖሮ ከገዢ ጋር ግን በገንዘብ እና ከበርበሬ ጥራት ጋር በሚፈጠር አለመተማመን የፖሊስ እርዳታ የሚያስፈልገው ግጭት ድረስ እንደሚደርሱ ተናግረዋል፡፡

“የሴት ገንዘብ ሆኖ እንጂ ጥሩ ጥቅም አግኝቼበታለሁ” በማለት ዘጠኝ ዓመት የሰሩበት የበርበሬ ንግድ አዋጪ መሆኑን የሚጠቅሱት ወይዘሮዋ ቀዳዳዎችን ሲደፍኑ ገንዘቡ አልበረክት አላቸው እንጂ ስራው እንደሚደጉማቸው ይናገራሉ፡፡

500 ብር ይዘው በመውጣት ከገበሬ ገዝተው፣ ለተጠቃሚ ሸጠው ይገባሉ፡፡ ካልተሸጠላቸው ለቀጣዩ የገበያ ቀን ቀጠሮ ይይዙለታል፡፡ ገበያ ቀዝቅዞም ሆነ በርካታ ሻጮች ከመኖራቸው ሳቢያ ገዢ ምርጫው ካላደረጋቸው ሞጆ ወስደው ለሚቸረችሩ በዱቤ ሰጥተው ቤታቸው ይገባሉ፡፡ ይህ የሌሎች በርበሬ ሻጮችም የዘወትር ተግባር ነው፡፡

ለብዙሐኑ የበርበሬ ንግድ በዋነኛነት ከሚያከናውኑት የግብርና ሰራ ተጨማሪ የገቢ ምንጫቸው ነው፡፡ ወ/ሮ ፋንታዬ “የበለጠ ከግብርና እንጠቀማለን” ሲሉ እውነታውን ያጠናክሩታል፡፡ በተለይ ከየካቲት አንስቶ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ ምርት እያነሰ የማረቆ በርበሬ ገበያ ይቀዘቅዛል፡፡ እነ ወ/ሮ ፋንታዬ እና እሙነሽም የበለጠ ትኩረታቸውን ወደ ግብርናው ያደርጋሉ፡፡ ይህም ቢሆን

ግን ቢያንስ በሳምንት አንዴ ቅዳሜ - አቧራማው ቅዳሜ ገበያ ላይ በርበሬን ከመቸርቸር ውጪ የሚያደርጋቸው አይደለም፡፡ ገዢ ግን በዚህ ወቅት ጥሩ በርበሬ ይገኛል ብሎ ስለማያስብ እምዛም አይጎበኛቸውም፡፡

እሙነሽ መልቲሮ እንሴኖ-ቅዳሜ ገበያ ላይ ከ10 ዓመት በላይ በበርበሬ ንግድ አሳልፋለች፡፡ ሐሙስና ቅዳሜ ገበያ ስትወጣ የተቀሩትን ቀናት በግብርና ታሳልፋለች፡፡

“ቆንጆ ነው” ብላ በፈገግታ የምትናገርለት የበርበሬ ንግድ ለማጦፍ አንድ ሺህ ብር ይዛ በመውጣት የምትቀበለው ከገበሬዎች ሲሆን ቅዳሜ ገበያ ድረስ ይዘው ስለሚመጡ ገዝታ “ለበላተኛ” ትሸጣለች፡፡ “ከ10-15 ኪሎ ያህል ከገበሬ ላይ እገዛና ለተጠቃሚ እሸጣለሁ፡፡ ንግዱ ከግብርና ስራ ጋር ተደማምሮ ከባለቤቴ ጋር ተረዳድተን ቤት እንድሰራ አድርጎናል” ስትል የንግዱን ትሩፋት ታሳያለች፡፡

እንደ እሙነሽ ገለፃ ከአንድ ኪሎ በርበሬ ላይ በአማካይ ሁለት ብር ከሃምሳ ሳንቲም ታተርፋለች፡፡ “18 ብር ገዝቼ 20 ብር እሸጣለሁ፡፡ የምገዛበት ብር ቢጨምርም ከሁለት እስከ ሦስት ብር አትርፌ እሸጠዋለሁ” ባይ ነች፡፡

እንሴኖ- ቅዳሜ ገበያ ላይ ከ17 ኪሎ ግራም ጋር እኩሌታ ያለው “ፈረሱላ” ስሙ እንጂ ተግባራዊ እውቂያው አናሳ ነው፡፡ ፈረሱላ/ ግማሽ ፈረሱላ በርበሬን ዋጋ የሚጠይቅና የሚናገር ገዢ እና ሻጭ አታገኙም፡፡ የሚደራደሩት በኪሎ ግራም ነው፡፡ በአሁን ጊዜ በቦታው የበርበሬ መሸጫ ዋጋ ከ21-24 ብር ሲሆን እንደ የአይነቱ ይለያያል፡፡ ልኬቱ በእጅ በሚንጠለጠል ሚዛንና በነሲብ ይካሄዳል፤ ሻጮቹ አፈስ አፈስ ያደረጉና “በዚህ ያህል ዋጋ ይውሰዱት” ብለው በግምት ዋጋ ይተምኑሎታል፡፡

ጥሩ በርበሬን በማየት ብቻ እንደሚያውቁት የገለፁልኝ አንድ ገዢ ሻጮች በርበሬን ውሃ እየነከሩ ኪሎ እንዲያነሳ በማድረግ ያለ አግባብ ተጠቃሚ ለመሆን እንደሚጥሩ ገልፀዋል፡፡ ሻጮችም ይህንን አይክዱም፡፡ ለዚህ “ዘዴ” መሰል ክዋኔ የሚዳረጉት የበርበሬ ሽያጭ ላይ የሚገኘው ገንዘብ አጥጋቢ አለመሆን ነው ይላሉ፡፡

ረገጣመስከረም በርበሬ የሚደርስበት ወቅት

ነው፡፡ ጥቅምት ደግሞ ምርቱ የሚሞላበት ጊዜ በመሆኑ የበርበሬ ንግድ ይጦፋል፡፡ በዚህ ጊዜ ሙህዲን የከሲ እና ጓደኞቹ “ረገጣ” ያደራላቸዋል፡፡ “ረገጣ” በርበሬን በማዳበሪያ “ለማጨቅ” የሚጠቀሙበት የመጠቅጠቅ ‹‹ስትራቴጂ›› ነው፤ አዳጊዎች (ወጣቶች) ማዳበሪያው ላይ ሻማቸውን አውልቀው “ፊጥ” ይሉና በርበሬውን እየረገጡ የመያዝ አቅሙ ከፍተኛ

እንዲሆን ያደርጋሉ፡፡ ለዚህም ሲባል ለማውለቅ ቀላል የሆኑ (ነጠላ ጫማዎች) መጫማትን ያዘወትራሉ፡፡

እንደ ሙህዳን ገለፃ ለረገጣ የሚያስከፍሉት ብር እንደ ወቅቱና እንደማዳበሪያው መጠን ይለያያል፡፡ እንደ አላባ በርበሬ ሁሉ ተወዳጅ የሆነው የማረቆ በርበሬ በሚደርስበት ወቅት ተፈላጊ ናቸውና ደረታቸውን ነፋ ያደርጋሉ፤ እግሮቻቸው በቀላል ብር በርበሬዎቹን አይደፈጥጡም፡፡ ከትንሹ እስከ ትልቁ ማዳበሪያ ድረስ ከሦስት እስከ 15 ብር ድረስ ያስከፍላሉ፡፡

እስማዔል አህመድ በተለይ በርበሬ የደረሰበት ወቅት ከሆነ ማክሰኞ እና ሐሙስ ሰበቦችን እየደረደረ ከት/ቤት በመቅረት ረገጣ ላይ ይውላል፡፡ “ለምን ከት/ቤት ቀረህ ሲሉኝ አሞኝ ነው እላለሁ፡፡ ረገጣ እንደምሰራ የሚያውቁ አንዳንድ አስተማሪዎች ግን ለምን እንደምቀር ያውቃሉ፡፡ ያው ገንዘብ ከለመድክ ...” በማለት ከትምህርት ይልቅ ልቡ ወደ ረገጣ እንደሸፈተ ይናገራል፡፡

እንሴኖ ከተማ መስቃን ወረዳ፣ ቀበሌ 01 የሚገኘው የማረቆ በርበሬ መሸጫ ስፍራ ላይ የሚገኙ “ረጋጮች” በተደራቢነት በርበሬ ማሻሻጥ (ድለላ) ይሰራሉ፡፡

የማይታሰበው “ይማርዎ”ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት መጠናቀቅ

በኋላ ለጦርነቱ የዋሉ ኬሚካል ጋዞች የፕላኔታችንን አብዛኛውን ክፍል በክለዋል፡፡ በዚህ ወቅት ከጣሊያኗ ሴንተሊና ደሴት በስተቀር ስፓኒሽ ፍሉ የሚባል ወረርሽኝ ይዛመታል፡፡ በአገራችንም በሽታው በህዳር ወር ስለገባ “የህዳር ወረርሽኝ” ተባለ፡፡ ጦርነቱ ከበላው በላይ ህዝብ የገደለው ይህ እስከሞት የሚያደርስ በሽታ የጀመረው ሰው ያስነጥሰዋል፡፡ በዚህም ሳቢያ የወቅቱ የሮማ ሊቃነ ጳጳስ “የሚያስነጥሰው ሰው ስታዩ ይማርህ በሉ” ብለው ትዕዛዝ አስተላለፉ፡፡ ዓለም ላይም ተለመደ፤ “ያኑርዎ” እስከሚል ምላሹ ድረስ ማለት ነው፡፡ ቅዳሜ ገበያ ላይ ግን ከዚህ የተለየ ነው፡፡

እሙነሽ መልቲሮ “ተጠቃሚ ነኝ” ማለቷን በድንገት ረስታ ስራው አሉታዊ ጎኑ ማመዘኑ ታወሳት፡፡ “ስራው ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ያመዝናል፡፡ በርበሬው ውሃ የነካው ከሆነ ብርድ ሳንባችንን

ሊነካን ይችላል፡፡ ይህም የህክምና ወጪ ስለሚያስወጣን ነው ለዚህም ነው ጉዳቱ ያመዝናል ማለቴ” ስትል አስረዳችኝ፡፡ ብርቱዋን ሴት በቀን ምን ያህል ጊዜ እንደምታስነጥስ ብትጠይቋት ፊቷን የሞላው ፈገግታ “ሳቅ” ወልዶ እየተንከተከተች “መዓት ጊዜ ያስነጥሰኛል፡፡ ተቆጥሮ አያልቅም” ስትል የማስጠነሱ ድግግሞሽ በቁጥር ብዛት መገመት አዳጋች መሆኑን ትጠቁማለች፡፡

በኪሎ እየተሰፈረ እንደሚሸጠው በርበሬ የልኬት መጠን ቢኖረው ገበያው ላይ በማስነጠስ የሚወጣው የፈሳሽ መጠን ብዙ ሊትር በወጣው ነበር፡፡ ደጋግመው የሚያስሉ አሉ፡፡ እዚህም እዚያምጋ ደጋግሞ “እንትሹ...” በሽ ነው፡፡ መደራደር ጀምረው ሳይጨርሱ ምናልባትም ደጋግመው ያስነጥስዎታል፤ ሻጭም እንደዚያው ነው፡፡ ገበያው መሀከል በሰው ተከበው አስነጥስዎት “ይማርዎ” የሚሎት በማጣትዎ ግራ ከገባዎት ለቦታው አዲስ ሰው ነዎት ማለት ነው፡፡ ገበያው ላይ “እንትሹ...” ማለት ብርቅ አይደለም፡፡

እርስ በርስም “ይማርዎ” አይባባሉም፡፡ “እንዴት?” ብትሏቸው “ስንቱን ስንት ጊዜ ይማርህ ብለን እንችላለን?” ሲሉ ጥያቄዎን በጥያቄ ይመልሱሎታል፡፡

የቅኝት ፀሐፊዎም እያሳለና እያስነጠሰ ድምፃቸውን የተቀበላቸው ሰዎች ሲያስነጥሱ “ይማርዎ” ቢላቸውም በተራው ሲያስነጥስ ግን “ይማርህ” ብሎት “ያኑርህ” ብሎ የመልስ ምት የቸረው አላገኘም፡፡

የገበያው የመድረክ ተሳታፊዎች አፍንጫን ከሚሰረስረው የበርበሬ ሽታ ጋር ከመለማመድ ብዛት ማስነጠስ አልተዋቸውም፡፡ ተደጋጋሚ ማስነጠስ የራስ ምታት እንደሚያስከትል የሚገልፁት የአንገት በላይ ስፔሻሊስት የሆኑት ነጋ ኪሮስ (ዶ/ር) ደጋግመው የሚያስነጥሱ ሰዎች ከአፍንጫቸው ፈሳሽ እየተንቆረቆረ ስለሚወጣ ስራን ለመከወን ከማዳገቱም በላይ ተጨማሪ መዘዝ እንዳለው ይጠቀማሉ፡፡ “ብዙ ፈሳሽ ከፈሰሰ በኋላ አፍንጫቸው የመታፈን ባህሪ ስለሚያመጣ መተንፈስ ያስቸግራቸዋል” ይላሉ፡፡

በርበሬን ጨምሮ ዘወትር በሚያስነጥሱ፣ በሚያስሉ፣ በሚሰነፍጡ፣ በሚሰረስሩ ነገሮች የተከበቡ ሰዎች በሂደት ሽታውን ይላመዱታል፡፡ ይህ ግን የጎላ የጤና ችግር አንዳልሆነ ነጋ ኪሮስ ይጠቁማሉ፡፡ “ቅመማ ቅመም እና በርበሬ የሚሸጡ ሰዎች አካባቢያዊ ሽታ ምንም አይላቸውም፡፡ ነገር ግን ‹‹አለርጂ›› ያለበት ሰው እዚያ አካባቢ ሊሰራ አይችልም፡፡ ምክንያቱም ህመሙ ይነሳበታል፡፡ ፈሳሽ ከአፍንጫው እንደ ውሃ ይንቆረቆራል እንዲሁም ስለሚበላው (ስለሚያሳክከው) ህይወቱ የመከራ ይሆናል” ሲሉ አለርጂ ላለባቸው ሰዎች ስራው አስቸጋሪ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የማረቆ በርበሬ በሚከፋፈልበትና በሚቸረቸርበት በዚህ ማዕከል በበርበሬ ሽታ ሳቢያ ‹‹አለርጂ›› ተፈጥሮባቸው ስራቸውን ያቆሙና የግድ “የሚታገሉ” አሉ፡፡ ጀንበር ስትጠልቅ ገበያው እየተቀዘቀዘ ቢሄድ፣ በርበሬው ሲወጣ፣ ሲገባ ሁሉ ተደጋጋሚው ማስነጠስ ትኩረት ሰራቂ መሆኑን ያጤነ ቦታው ቅዳሜ ገበያ ከመባል ባለፈ ከማስነጠስ ጋር የተያያዘ ስም ቢለጠፍበት ብሎ ሀሳብ ሊያዋጣ ይችላል፡፡

በርበሬ በሚደርስበት እና ገበያው በሚደራበት የመስከረም እና ጥቅምት ወር የሚያስለውና የሚያስነጥሰውም ቁጥር የሚያይልበት ነው፡፡ የቀዘቀዘው መድረክ ለመድመቅም ወራቶቹን እየተጠባበቀ ነው፡፡ ያኔ “ኤር በርበሬኦ” (በማረቆኛ ጥሩ በርበሬ ማለት ነው) በብዛት ይገኛልና ለገዥ፣ ሻጭና ረጋጭ ምርጡ ጊዜ ነው፡፡ በዚህ ጊዜ ስፍራውን ከጎበኙ ምርጡ በርበሬ የሚደርስበት ወቅት ነው ብለው በማሰብ “ስገዛ ይመረቅልኛል” ብለው ካሰቡ ተሳስተዋል፡፡ ከኪሎ ግራሙ በላይ “ፍንክች” የለም፡፡ ነገር ግን ያለ ፍላጎትዎ የሚመረቅሎት አንድ ነገር ብቻ ነው፤ አቧራ፡፡

የማረቆ በርበሬ በጣዕሙ፣ ባለማቃጠሉ፣ የሴትን ልጅ ሙያ በማጉላቱ በኩል ምርጥ መሆኑ ይነገርለታል፡፡ የበርበሬውን የገበያ እምብርት ቃኝቶ የተመለሰው አቤል

ዓለማየሁ ‹‹ያኑርህ›› እያሉት የሚያነቡትን ተከታዩን ፅሁፍ አሰናድቷል፡፡

‹‹ይማርዎ›› የማይባሉበት ስፍራ

Page 18: awramba 160

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 160 ቅዳሜ መጋቢት 17 2003ፓ ር ላ ማ18

በሱራፍኤል ግርማ

ማክሰኞ መጋቢት 13 ቀን 2003 ዓ.ም የ1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን፣ 16ኛ መደበኛ ስብሰባውን ያከናወነው የኢ.ፌ.ዴ.ሪ 4ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአጀንዳነት የያዘው የትራንስፖርት ሚኒስቴርን የ2003 በጀት ዓመት የ8 ወር ዕቅድ አፈፃፀም ማድመጥ ነበር፡፡

የትራንስፖርት ሚኒስትሩ አቶ ድሪባ ኩማ የመሥርያ ቤታቸውን የ8 ወር ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ባቀረቡበት ጉባዔ ላይ የተመዘገበው የቀሪ አባላት ብዛት ከወትሮው ጫን ያለ ነበር - 224፡፡

ሪፖርቱ ካካተታቸው ጉዳዮች ውስጥ የብዙዎቹን እንደራሴዎች ትኩረት የሳበውና በርካታ ጥያቄዎችን ያስከተለው የመንገድ ትራንስፖርት አገልግሎትን የሚመለከተው ከፍል ነበር፡፡

የመንገድ ትራንስፖርት አልግሎት “ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ቀልጣፋ፣ ብቁ፣ ኢኮኖሚያዊና ስርጭቱም የተመጣጠነ” ሆኖ በሀገሪቱ እንዲስፋፋ በበጀት ዓመቱ የትኩረት አቅጣጫዎች ተቀምጠው እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን የሚገልፀው ሰነድ የታቀዱ እና የተከናወኑ ተግባራትን አስፍሯል፡፡

ከታቀዱ ተግባራት መካከል የመንገድ ትራንስፖርት አገልግሎትን ማስፋፋት እና የመንገድ ትራፊክ ደህንነትን ማረጋገጥ ዋና ዋናዎቹ መሆናቸውን የገለፁት አቶ ድሪባ ኩማ፣ የመንገድ ትራንስፖርት አገልግሎትን ለማስፋፋት የፍላጎትና አቅርቦት ዳሰሳ መከናወኑን ለም/ቤቱ ነግረዋል፡፡ “ዳሰሳውን በማከናወን ከፍተኛ የመጫን አቅም ያላቸውን የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብሶች ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡበትን አሊያም በሀገር ውስጥ የሚገጣጠሙበትን መንገድ የሚጠቁም ጥናት በመከናወን ላይ ይገኛል” ያሉት ሚኒስትሩ ሌሎች ነጥቦችንም አንስተዋል፡፡

አቶ ድሪባ በንባብ ባቀረቡት ሪፖርት መሠረት በስምንት ወራት ውስጥ በትራንስፖርት አገልግሎት መስክ መልካም ክንውኖች ተፈፅመዋል፡፡ የህብረተሰቡን የጉዞ ፍላጎት በተወሰነ ደረጃ ለማሟላት ሰባት አዳዲስ መስመሮች ተከፍተው በጠቅላላ የመስመሮች ብዛት ወደ 116 እንዲያድግ ሆኗል፡፡ የልጆች ትራንስፖርት ክፍያ እና በተሳፋሪ የሚያዙ ዕቃዎች ክፍያን በተመለከተ መመሪያ ጸድቆ ተግባራዊ የተደረገ ሲሆን አፈፃፀሙም በተዘረጋው የክትትልና

ቁጥጥር ሥርዓት መሠረት እየተከናወነ ይገኛል፡፡

ምንም እንኳን ሚኒስትሩ ስለልጆች የትራንስፖርት ክፍያ እና የዕቃ ክፍያ ሲገልፁ በእርግጠኝት ቢሆንም በተጨባጭ ያለው እውነታ ግን ከዚህ የተለየ ነው፡፡ በአዲስ አበባም ሆነ በሌሎች ከተሞች በሚገኙ አውቶብስ ተራዎች ውስጥ ሕፃናት ከአዋቂ እኩል ሙሉ ሂሳብ ሲከፍሉ እና ተሳፋሪዎች ለያዙት ዕቃ ተገቢ ያልሆነ ክፍያ እንዲፈፅሙ ሲጠየቁ በየዕለቱ መታዘብ የዕለት ተለት ክስተት ከመሆኑ ባሻገር “ታዲያ ‹የተዘረጋው የክትትልና ቁጥጥር ሥርዓት› የታለ?” የሚል ጥያቄን ያጭራል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ከጊዜ ወደ ጊዜ መጨመሩንና የሕዝብ ብዛቷ ማሻቀቡን ተከትሎ የተባባሰውን የትራንስፖርት

ችግር ለመቅረፍ መሥሪያ ቤታቸው “እየተጋ” መሆኑን ያስታወሱት አቶ ድሪባ፣ በከተማዋ የብዙሃን ትራንስፖርት አገልግሎት እየሰጠ ያለውን አንበሳ አውቶብስ የማገዝ ሥራ መከናወኑን ገልፀዋል፡፡

ይኼኔ ነበር ከም/ቤቱ የትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በአዲስ አበባና በሌሎች ከተሞች ስለሚስተዋለው የትራንስፖርት ችግር “በአዲስ አበባ ከተማ ታክሲዎች ያለአግባብ አቆራርጦ መጫን፣ ከታሪፍ ውጭ የመጫንና መኪኖች እያሉ ህብረተሰቡ ትሪንስፖርት አጥቶ መንገላታት፣ እንዲሁም የገጠር አማራጭ የትራንስፖርት አገልግሎት ተገቢው ተኩረትና ክብደት ተሰጥቶት በታቀደው መሠረት ለምን አይፈፀምም?” የሚል ጥያቄ የቀረበው፡፡

ሚኒስትሩም፣ በአዲስ አበባ ያለውን ችግር በታክሲ የቀጠና ስምሪት እንደሚወገድ ለጥያቄ አቅራቢዎቹ ገልጸው ነበር፤ በትክክል መቼ እንደሚጀመር ባያሳውቁም፡፡

ሌላው በሪፖርቱ ውስጥ የተካተተው፣ የአየር ትራንስፖርት ለዓለም አቀፍ ውድድር የተጋለጠ እንደመሆኑ መጠን በኢንዱስትሪው ያለውን የዓለም አቀፍ ሁኔታ እያጤኑ የውድድር ብቃቱን በየጊዜው እያጎለበቱ መሄድን እንደሚጠይቅ የሚያስገነዝበው ሰነድ በስምንት ወራት ውስጥ የዘርፉን የሰው ኃይል ብቃት የማሻሻልና አዳዲስ ብቁ ባለሙያዎችን የመፍጠር ሥራዎች መከናወናቸውን ይጠቅሳል፡፡

ነገር ግን በኢትዮጵያ አየር መንገድ ደስተኛ ባለመሆናቸው የተነሳ ወደሌሎች ተፎካካሪ አየር መንገዶች እየፈለሱ ስለሚገኙ ባለሙያዎችና ፍልሰቱን ለመግታት ምን እንደተሰራ በሪፖርቱ ካለመካተቱ ባሻገር በአየር መንገዱ የተላለፉ ውሳኔዎችን አስመልክቶ

የቀረበ ሪፖርት አልነበረም፡፡በሌላ በኩል የኢትዮጵያ አየር

መንገድ ባለፉት ስምንት ወራት ውስጥ 872 ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ለማግኘት ታቅዶ 1.2 ቢሊዮን ብር ለማግኘት መቻሉን የሚያሳየው ሰነድ ‹‹ከዕቅዱ በላይ 140 በመቶ ክንውን›› መመዝገቡን ያስረዳል፡፡

የኢፌዴሪ የትራንስፖርት ሚኒስቴር ለም/ቤቱ ካቀረበው ሪፖርት ውስጥ “ትንሽ” ግራ የሚያጎባው የአብዛኛዎቹ ክንውኖች የዕቅድ አፈፃፀም ሆኖ ተስተውሏል፡፡

ለአብነት ያኽልም፣ - የባህር ዳር ኤርፖርት

ቀዝቃዛ መጋዘን ግንባታ የዕቅድ አፈፃፀም 52.3% ፤

- የመቀሌ ኤርፖርት ቀዝቃዛ መጋዘን ግንባታ የዕቅድ አፈፃፀም 56.6%፤

- የጅጅጋ ኤርፖርት የአውሮፕላን ማረፊያ ሜዳ ግንባታ ዕቅድ አፈፃፀም 74.9%፤

- የሰመራ ኤርፖርት የአውሮፕላን ማረፊያ ሜዳ ግንባታ የዕቅድ አፈፃፀም 74.3%፤

- ለሀገር ውስጥ በረራ ለማቅረብ ከታቀደው የመቀመጫ በኪሎ ሜትር ጥምረታ ውስጥ የተፈፀመው 76.6% ነው፡፡

- የደረቅ ወደቦችን አስተዳደር ብቃት ለማሳደግ የሚያግዙ ሥራዎችም የዕቅዱ 60% መከናወኑን የስምንት ወራቱ ሪፖርት ያሳያል፡፡

የበጀት ዓመቱን ሁለት ሶስተኛ ጊዜ በሚዳስሰው ሪፖርት የተጠቀሱት የዕቅድ አፈፃፀሞች ግን ተመልካችን “አስፈፃሚው አካል ዕቅዱን ሲነድፍ ከአቅሙ በላይ አድርጎ ነው ወይስ እየሰራ ያለው ከአቅሙ በታች ነው?” ሲል እንዲጠይቅ መገፋፋታቸው አልቀረም፡፡

ለአውራምባ ታይምስ አንባቢያንበጋዜጣ የህትመት ዋጋ ላይ ማተሚያ ቤት ባደረገው አስደንጋጭ የዋጋ ጭማሪ ምክንያት ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ በጋዜጣችን መሸጫ ዋጋ ላይ መጠነኛ የዋጋ ማስተካከያ

ለማድረግ እንደምንገደድ እንገልጻለን አሳታሚው

8 ወራት8 ወራትየትራንስፖርት ሚኒስቴር

የአዲስ አበባ ከተማ

ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ

ከጊዜ ወደ ጊዜ

መጨመሩንና የሕዝብ

ብዛቷ ማሻቀቡን ተከትሎ

የተባባሰውን የትራንስፖርት

ችግር ለመቅረፍ መሥሪያ

ቤታቸው “እየተጋ” መሆኑን

ያስታወሱት አቶ ድሪባ፣

በከተማዋ የብዙሃን

ትራንስፖርት አገልግሎት

እየሰጠ ያለውን አንበሳ

አውቶብስ የማገዝ ሥራ

መከናወኑን ገልፀዋል፡፡

Page 19: awramba 160

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 160 ቅዳሜ መጋቢት 17 2003 ዜ ና ዎ ች 19

የሦስተኛ ወገን መድኅን ሽፋን ሊጀመር ነው

በሱራፍኤል ግርማ

ባሳለፍነው ማክሰኞ የትራንስፖርት ሚኒስትር የሆኑት አቶ ድሪባ ኩማ የመ/ቤታቸውን የስምንት ወር ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት የተሽከርካሪ አደጋ የሦስተኛ ወገን መድኅን ሽፋን በቅርቡ እንደሚጀመር ገለፁ፡፡ የመድረክ አባል ከሆኑት አቶ ግርማ ሰይፉ “የሦስተኛ ወገን መድኅን አዋጅ ከፀደቀ ቆይቷል ለምንድነው ተግባራዊ የማይሆነው?” የሚል ጥያቄ የቀረበላቸው አቶ ድሪባ፣ ከተሽከርካሪ ባለንብረቶች እና ኢንሹራንስ ኩባንያዎች ጋር ውይይት ተካሂዶ አዋጁን የሚያስፈፅም ደንብ መዘጋጀቱንና ደንቡ በሚኒስትሮች ም/ቤት ከፀደቀ በኋላ ወደ ተግባር እደሚገባ ተናግረዋል፡፡ በአገሪቱ ውስጥ እየደረሰ ያለውን የተሽከርካሪ አደጋ ለመቀነስ እና አደጋ የሚደርስባቸው ወገኖች በማንኛውም ጊዜ በማንኛውም የህክምና መስጫ ቦታ በአስቸኳይ የህክምና አገልግሎት የሚያገኙበትን ሁኔታዎች ለማመቻቸት የተሽከርካሪ ባለንብረቶች የተሽከርካሪ አደጋ የሦስተኛ ወገን መድኅን ሽፋን እንዲኖራቸው ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ሚኒስትሩ አስረድተዋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የአገር ውስጥና የውጭ አገር የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት ፍላጐትን ለማሟላት በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የአዳዲስ ኤርፖርቶች ግንባታ፣ የነባር ኤርፖርቶች ማስፋፊያ እና የማጠናከር ሥራዎች በመካሄድ ላይ እንደሚገኙ ሚኒስትሩ ባቀረቡት ሪፖርት ላይ ተጠቅሷል፡፡ በሪፖርቱ ላይ እንደተመለከተውም የኰምቦልቻ ኤርፖርት የአውሮፕላን ማረፊያ ሜዳ ግንባታ፣ የጅማ፣ የጅጅጋ፣ የሠመራ እና የአሶሳ ኤርፖርቶች የመንገደኞች ማስተናገጃ ሕንፃዎች ግንባታ እየተከናወኑ ይገኛል፡፡ በ2003 በጀት ዓመት ለመንገድ ጥገና፣ ለመልሶ ግንባታ ሥራዎች እንዲሁም ለትራፊክ ደህንነት ሥራዎች ማስፈጸሚያ በጠቅላላው 1.34 ቢሊዮን ብር ለፌዴራል እና ለክልል መንገድ ኤጀንሲዎች ተመድቦ እንቅስቃሴ መደረጉ ተገልጻDል፡፡ በምክር ቤቱ ቀርበው “በቀጣይ ዓመታት ውስጥ 2516 ኪ.ሜ የባቡር መሠረተ ልማት ለመገንባት ታቅዷል” ላሉት ሚኒስትር ድሪባ ስለ ኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር ቀጣይ ዕጣፈንታ ጥያቄ ቀርቦላቸው ነበር፡፡ አቶ ድሪባም ድርጅቱ በአሁኑ ሰዓት ያሉት ቴክኖሎጂዎች ከ100 ዓመት በላይ ያስቆጠሩ መሆናቸውንና ሥራው የተቋረጠ መሆኑን በማስታወስ ሠራተኞቹ በብረት ኰርፖሬሽን ውስጥ ገብተው እየሰሩ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ አቶ ድሪባ አክለውም፣ አዲሱን የባቡር መሠረተ ልማት ለመዘርጋትና አገልግሎት ለመስጠት የምህንድስና ትምህርት በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ 5 ሺህ፣ እንዲሁም በቴክኒክና ሙያ የሰለጠኑ 25 ሺህ ባለሙያዎች እንደሚያስፈልጉ ተናግረዋል፡፡ አቶ ድሪባ ኩማ እንዳሉትም ባለሙያዎችን በአገር ውስጥ ለማሰልጠን ከተጀመረው እንቅስቃሴ ባሻገር በውጪ አገር ከሚገኙ ልምድ ካላቸው የትምህርት ተቋማት ጋር በተደረገው ቴክኒካል ትብብር አማካኝነት 17 ባለሙያዎች ወደ ውጪ ሄደው የድህረ-ምረቃ ሥልጠና እንዲጀምሩ ተደርጓል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የ40 ሚሊዮን ዶላር ብድር አገኘ

በሱራፍኤል ግርማ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አምስት ቦይንግ 777-200LR የመንገደኛ አውሮፕላኖችን መግዣ የሚሆን 40 ሚሊዮን ዶላር ከአፈሪካ ልማት ባንክ በብድር አገኘ፡፡ አየር መንገዱ ከ2010-2018 (እ.አ.አ) ድረስ ሊያከናውን ካቀዳቸው የኢንቨስትመንት ሥራዎች ውስጥ አንዱ ለሆነው የአውሮፕላኖች ግዢ ማከናወኛ የሚሆነውን ብድር ባንኩ ያፀደቀለት ያሳለፈነው ረቡዕ በቱኒዚያ ርዕሰ መዲና ቱኒዝ ውስጥ ነው፡፡ ዘመናዊዎቹ ቦይንግ 777 አውሮፕላኖች አየር መንገዱ እየተገለገለባቸው ያሉትን አውሮፕላኖች የሚተኩ ሲሆን ከአፍሪካ ወደተቀረው የዓለም ክፍል የሚደረጉ የረዥም ርቀት በረራዎችን ይሸፍናሉ፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ2010-2018 (እ.አ.አ) ሊያከናውን ያቀዳቸው ፕሮጀክቶች ከ400 በላይ ለሚሆኑ ሰዎች የአጭር ጊዜ የሥራ ዕድል የሚፈጥር ሲሆን ከ800 ለሚበልጡ ደግሞ ለመካከለኛ ጊዜ የሥራ ዕድል ይፈጥራል፡፡ አየር መንገዱ ከዚህ ቀደም እ.አ.አ በ2009 ዓ.ም እንዲሰሩለት ያዘዛቸውን አምስት ቦይንግ 777 አውሮፕላኖች ሕዳር 8 ቀን 2003 ዓ.ም መረከቡ ይታወሳል፡፡ በአምስት ቦይንግ 777-200LR አውሮፕላኖች ባለቤትነት ከአፍሪካ አህጉር ሀገራት ቀዳሚ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ከ300 በላይ ሰዎችን ማሳፈር የሚችሉትን አውሮፕላኖች ወደ ዋሽንግተን እና ወደ ቤይጂንግ ለሚያደርጋቸው የረዥም ርቀት በረራዎች እየተጠቀመባቸው ይገኛል፡፡

የእንግሊዝ የንግድ ኩባንያዎች በአዲስ አበባ ንግድ ም/ቤት ውይይት ያደርጋሉ

በኤልያስ ገብሩ

ከ12 የእንግሊዝ ታላላቅ የንግድ ኩባንያዎች የተውጣጡና በለንደን የንግድ ኢንዱስትሪ ም/ቤት ኃላፊ በሆኑት በሚስተር ሱፕ ሀሽ ታክራር የሚመራ የእንግሊዝ የንግድ ልዑካን ቡድን ሰኞ በአዲስ አበባ ንግድ ም/ቤት ውይይት ያደርጋል፡፡ በተጠቀሰው ዕለት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ በኢትዮጵያና በእንግሊዝ አገራት፣ ብሎም በአገሪቱ ባሉ ኩባንያዎች መካከል የንግድ ኢንቨስትመንት እንቅስቃሴን ለማዳበር የሚደረግ ውይይት በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበር አዳራሽ እንደሚደረግ የም/ቤቱ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዲፓርትመንት ክፍል ባለሙያ የሆኑት ወ/ሮ ሄለን ተካ ለአውራምባ ታይምስ ገልፀዋል፡፡

በሱራፍኤል ግርማ

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በተደጋጋሚ ለሚከሰተው የኢንተርኔት እና የሞባይል አገልግሎት መቋረጥ ምክንያቱ በመሬት ውስጥ የተቀበረው የፋይበር ኦፕቲክስ ኬብል በተደጋጋሚ በመቆረጡ መሆኑን የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር አቶ ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል ገለፁ፡፡

መጋቢት 15 ቀን 2003 ዓ.ም ፓርላማ ቀርበው ከም/ቤቱ አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡት ሚኒስትሩ፣ “ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ የፋይበር ኦፕቲክስ ኬብል መቆራረጥ በጣም አስደንጋጭ ነው፤ ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ በሰው ሆን ተብሎ የሚፈፀም፣ በመንገድና ሕንፃ ግንባታዎች እንዲሁም በኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጥም ችግሩ እየተፈጠረ ነው” ብለዋል፡፡

ለም/ቤት አባላት ምላሽ በሰጡበት ወቅት የሞባይል አገልግሎት ከመስፋፋቱ ጋር በተያየዘ የሞባይል ሂሳብ አሞላል ላይም ለውጥ እንደሚመጣ ጠቁመዋል፡

፡ ሚኒስትሩ እንዳሉት ከሆነ አሁን እየተሰራበት ከሚገኘው ካርድ በተጨማሪ በኤሌክትሮኒክስ መንገድ ሂሳብ መሞላት ይጀመራል፤ ለዚህ የሚያገለግሉ ማሽኖችም ተገዝተው አገር ውስጥ ገብተው በሙከራ ላይ ይገኛሉ፡፡

ለአቶ ደብረጽዮን ከቀረቡላቸው ጥያቄዎች መካከል በአዲሱ የቴሌ አወቃቀር የተነሳ የሚደመጡትን ቅሬታዎች የሚመለከት ይገኝበታል፡፡ “ኢትዮ-ቴሌኮም ባካሄደው የሪፎርም ሂደት ምደባ ያላገኙ ዜጎች ዕጣ ፈንታ ምን ይሆናል?” ለሚለው ጥያቄ ምላሽ መስጠት የጀመሩትም ምደባው የተካሄደው በዕቅድ መሆኑን በመግለፅ ነበር፡፡ “ከቀረቡት 1196 ቅሬታዎች ውስጥ 155 ብቻ ተገቢ ናቸው” ያሉት ሚኒስትሩ፣ አብዛኛው ቅሬታ ደረጃ 4 እና ደረጃ 5ን እንደሚመለከት ካስታወሱ በኋላ እስካሁን ድረስ ከደረጃ 4 ቅሬታ አቅራቢዎች ውስጥ 75 ሰው ብቻ እንዳልተስተናገደና የእነሱ ጉዳይ ሲያልቅ የ5ኛ ደረጃ ቅሬታን ማየት እንደሚጀመር ተናግረዋል፡፡

ለኢንተርኔት መቋረጥ ምክንያት የፋይበር ኦፕቲክስ መቆራረጥ መሆኑ ተገለፀ

8 ወራት8 ወራት

በሱራፍኤል ግርማ

ለረዥም ጊዜ ለመንግስት ሠራተኞች ብቻ ሲሰጥ የነበረውን የጡረታ ሽፋን የግል ደርጅቶች ሠራተኞች እንዲያገኙ ለማድረግ ራሱን የቻለ የግል ድርጅቶች ሠራተኞች ጡረታ ዐቅድ እና የጡረታ ፈንድ እንዲቋቋም መንግስት ያሳለፈውን ውሳኔ የሚያስተገብር ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ፡፡

መጋቢት 15 ቀን 2003 ዓ.ም 17ኛ መደኛ ስብሰባውን ባከናወነው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ረቂቁ ቀርቦ ውይይት በተደረገበት ወቅት በም/ቤቱ በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የመንግስት ረዳት ተጠሪ የሆኑት አቶ መለስ ጥላሁን ስለአዋጁ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

“ከግሉ ክፍለ ኢኮኖሚ የተሰማሩት ዜጎች የማህበራዊ ዋስትና ሽፋን እንዲኖራቸው ማድረግ በሕገመንግስቱ የተገለፀውን የዜጎች ማህበራዊ ዋስትና የማግኘት መብት ማረጋገጥ፣ ድህነትን ለመቀነስና

በምድባው ወቅት አድሎ የፈፀሙ ኃላፊዎች መቀጣታቸውን የገለፁት አቶ ደብረጽዮን፣ በአዲሱ ቴሌኮም መዋቅር ውስጥ መካተት ያልቻሉት የቀድሞ ሠራተኞች ፍላጎታቸው የአገልግሎት ካሳ ተቀብለው መሰናበት በመሆኑ ካሳ የመክፈል ሥራው የቀረቡት ቅሬታዎች ታይተው ካለቁ እና ወደ ኩባንያው የሚገባው የሰው ኃይል አደረጃጀት ከተጠናቀቀ በኋላ እንደሚከናወን ተናግረዋል፡፡

በተያያዘ ዜና መጋቢት 15 ቀን 2003 ዓ.ም 17ኛ መደበኛ ስብሰባውን ያከናወነው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ዕጩ ዳኞችን፣ የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ዕጩ ም/ፕሬዝዳንትና የፌዴራል የከፍተኛና የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤቶች ዕጩ ዳኞችን ሹመት አፅድቋል፡፡

ነገር ግን በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዘናዊ አቅራቢነት ሹመታቸው ከፀደቀላቸው ዳኞች መካከል ለፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ዕጩ ም/ፕሬዝዳንት ሆነው የቀረቡት የአቶ ሀብቴ ፍቻላ ቦንቻ ሹመት በአቶ ግርማ ሰይፉ ተተችቷል፡፡

ዕጩ ም/ፕሬዝዳንቱ ከዚህ ቀደም ኢህአዴግን ወክለው የፓርላማ አባል የነበሩ መሆናቸውን ያስታወሱት አቶ ግርማ፣ “ግለሰቡ ከዚህ ቀደም የፖለቲካ ተመራጭ የነበሩ እንደመሆናቸው መጠን የፖለቲካ ወገንተኝነታቸውን ይተዋሉ ብለን አናስብም” የሚል አስተያየት ሰንዝረዋል፡፡

በኤልያስ ገብሩ

የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሚኒስትር የሆኑት ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የ2011 “Jimmy and Rosalynn Carter Humanitarian Award” የተሰኘ ሽልማትን ከትናንት በስትያ በአሜሪካን አርሊንግተን ቨርጂኒያ ተቀበሉ፡፡

ሽልማቱን የሰጠው ጂሚ ኤንድ ሮዛሊን ካርተር ፋውንዴሽን የተባለው ለትርፍ ያልተቋቋም ድጋፍ አድራጊ ተቋም ሲሆን ዶ/ር ቴድሮስ በዓለም አቀፍ ደረጃ በፍጥነት እያደገ በመጣው የጤናው ዘርፋ ላይ የላቀ አመራር በማሳየታቸውና ኢትዮጵያ በዋና ዋና ዓለም አቀፍ ፎረሞች ላይ ንቁ ተሳታፊ እንድትሆን ባደረጉት ጥረት መሆኑን በዕለቱ የተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ያስረዳል፡፡

የካርተር ፋውንዴሽን ፕሬዝዳንትና ዋና ሥራ አስፈፃሚ የሆኑት ዶ/ር ጆን ሃርድማን በሽልማት ሥነ-ሥርዓቱ ወቅት ዶ/ር ቴድሮስ በዓለም አቀፍ ፈንድ ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ፣ ቲቢ እና ወባ ለመዋጋት እ.ኤ.አ ከሐምሌ 2009 ጀምሮ የፈንዱ የቦርድ ሊቀመንበር በመሆንና እንዲሁም ከግንቦት 2009 ጀመሮ በአፍሪካ ሕብረት የጤና ሚኒስትሮች ኮንፈረንስ ላይ ኢትዮጵያ በሊቀመንበርነት እንድትወከል በማድረግ ባላቸው ኃላፊነት የላቀ የአመራር አቅም በማሳየታቸው አክብሮት እንደሚገባቸው ተናግረዋል፡፡

ዶ/ር ጆን አስተያየታቸውን በመቀጠል ‹‹ዶ/ር ቴድሮስ በኢትዮጵያ ጠንካራ ብሔራዊ የጤና ሥርዓት እንዲገነባ ያላሰለሰ ጥረት በማድረግና በአገሪቷ ያለውን የጤና አገልግሎቶች

አወቃቀርና አቅምን ለማሻሻልና በእናቶች እንክብካቤ ዙሪያ የተለየ ትኩረት በመስጠት የላቀ የአመራርነት ብቃት አሳይተዋል›› ሲሉ ገልፀዋል፡፡

በተጨማሪም የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ አደገኛ የስርጭት መጠን የነበራቸውን እንደ ወባና ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ያሉ ተላላፊ በሽታዎች የስርጭት አድማሳቸውና ጎጂነታቸው እንዲቀንስና እንዲገታ ጥረት ማድረጋቸውን ዶ/ር ጆን ማብራራታቸው ተዘግቧል፡፡ በዚህም መሠረት እ.አ.አ በ2002 በኢትዮጵያ የነበረው የኤች.አይ.ቪ ኤድስ የስርጭት መጠን ከ6.4 በመቶ በ2010 ወደ 2.1 በመቶ እንዲቀንስ የዶ/ር ቴድሮስ ሚና ስላለበት ይኼ በስኬትነት ተገልጾላቸዋል፡፡ ዶ/ር ቴድሮስ በተለያዩ ወቅቶች የተለያዩ ዓለም አቀፍ ሽልማት መቀበላቸው ይታወቃል፡፡

የሠራተኛውን በሥራ ውጤታማነት ለማሳደግ ከሚቀየሱ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች መካከል አንዱ ይሆናል” ያሉት ረዳት ተጠሪው፣ የግል ሠራተኞችም የጡረታ ሽፋን እንዲያገኙ ማድረግ የኢንዱስትሪ ሰላምና መረጋጋትን እንደሚያመጣ ገልፀዋል፡፡

አዋጁን ማውጣት አስፈላጊ የሆነበትን ምክንያት የአገሪቱን ሕዝቦች ደረጃ በደረጃ የማሕበራዊ ዋስትና ተጠቃሚ ማድረግ በኢፌዴሪ ሕገመንግስት ላይ በመደንገጉ፣ ከአገሪቱ ማሕበራዊ ፖሊሲ ጋር የሚጣጣም የግል ድርጅት ሠራተኞች የጡረታ ዕቅድ እንዲኖር በማስፈለጉ፣ የማሕበራዊ ዋስትና ጥቅሞች አሰጣጥን አስመልክቶ በየጊዜው የተደረጉ ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል ሁኔታዎችን ለማመቻቸት፣ በግል ድርጅቶች ውስጥ ተቀጥረው የሚያገለግሉ በርካታ ሠራተኞችና ተተኪዎቻቸውን የማህበራዊ ዋስትና መብት ለማረጋገጥ እና ለአስተዳደር ፋይናንስ ሥራ

አመራር እንዲያመች የግል ድርጅት ሠራተኞች ፈንድ ለብቻው እንዲደራጅ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ መሆኑን አቶ መለስ አስረድተዋል፡፡

አዋጁ ከመጽናቱ አስቀድሞ ሠራተኛ በቋሚነት ቀጥረው የሚያሰሩ ነገር ግን የጡረታ ዕቅድም ሆነ የፕሮቪደንት ፈንድ ሽፋን የሌላቸው የግል ድርጅቶች በመኖራቸው ምክንያት የጡረታ መዋጮ ያልተከፈለበትን አገልግሎት ለጡረታ አበል አወሳሰን መያዝ ስለማይቻል አዋጁ ከመፅናቱ በፊት በሥራ ላይ የነበሩ ሠራተኞች አዋጁ ከሚፀናበትና መዋጮ መክፈል ከሚጀምሩበት ጊዜ አንስቶ ያለው አገልግሎታቸው ብቻ እንደሚታሰብ በረቂቁ ላይ ሰፍሯል፡፡

ረቂቁ ሲፀድቅ የጡረታ ፈንድ የሚቋቋም ሲሆን፣ በዚህም መሠረት ለጡረታ ፈንድ በሠራተኛው ደመወዝ ላይ ተመስርቶ የሚደረገው መዋጮ በግል ድርጅቱ 11 በመቶ እና በግል ድርጅት ሠራተኛው 7 በመቶ ይሆናል፡፡

ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ዓለም አቀፍ ሽልማት አገኙ

የግል ድርጅት ሠራተኞች ጡረታ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ

የኢህአዴግ እና የፓርላማ አባል •የነበሩት የከፍተኛ ፍ/ቤት ም/

ፕሬዝዳንት ሆነው ተሾሙ

Page 20: awramba 160

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 160 ቅዳሜ መጋቢት 17 2003ጤ ና20

በመጀመሪያ አለርጂን እንዴት ይገልፁታል?ከአንገት በላይ አለርጂ ተብሎ ተለይቶ ሳይሆን አለርጂ በአጠቃላይ የአንድ በሽታ ችግር ነው፡፡ አንዱ አለርጂ ከአንገት በላይ አካባቢ በአፍንጫ ላይ የሚከሰት ሲሆን በሳንባና በቆዳ አካባቢም በተለያየ መልኩ ሊከሰት ይችላል፡፡ አለርጂ ሲባል ሰፊ ነው፡፡ የአፍንጫ አለርጂስ?በመጀመሪያ አፍንጫ ምን እንደሆነ መመልከቱ ይጠቅማል፡፡ ብዙ ሰው አፍንጫችን ለመልክ የቆመ አድርጎ ያስበዋል፡፡ አፍንጫ ትልቅ ስራ አለው፡፡ የማሽተትና የመተንፈስ ሥራ የእሱ ነው፡፡ በተጨማሪም ብዙ ሰው የማያውቀው ነገር፣ አፍንጫችን ከውጭ የሚመጣውን አየር አምቆ፣ አፅድቶና አርጥቦ ወደ ሳንባ ያቀርባል፡፡ ሳንባችን ሁልጊዜ የሚያገኘው የተመቻቸ አየር ነው፡፡ እንዲሁም እንዳንኮላተፍ ድምፃችንን አስተካክሎ ለማውጣት ይረዳል፡፡ ሆኖም በእነዚህ የአፍንጫ ስራዎች ላይ መስተጓጎል የሚያደርሱ በሽታዎች ብዙ ናቸው፡፡ ከእነዚህም ውስጥ አንዱ አለርጂ ሲሆን ሰውነታችን የማይፈልገው ባዕድ ነገር ሲኖር አፍንጫችን ውስጥ ያሉ የውስጥ አካላት ይቆጣሉ፡፡ እነሱ በሚቆጡበት ጊዜ አፍንጫችን ውስጥ ያሉ የውስጥ ስጋዎች ይነፋሉ፡፡ አለርጂ ሰው የማይፈልገው ሲመጣበትና ሲያጋጥመው፣ ወይም ከዛ ጋር ንክኪ ሲኖር የሚያጋጥም በሽታ ነው፡፡ ያም ከምንበላው፣ ከምንጠጣው፣ ከምናሸተውና ከንክኪም ሊሆን ይችላል፡፡የዚህ መነሻው ምንድን ነው?ይኼን በሁለት ነገር እንለየዋለን፡፡ ወቅታዊ፣ ጊዜና ወቅትን ጠብቆ የሚመጣ (Seasonal) እና ዓመቱን ሙሉ ሳያቋርጥ የሚመጣው (perennial) አለርጂ ይባላሉ፡፡ የመጀመሪያዎቹ በተለይ ክረምት አከባቢና ክረምት ሊወጣ ሲል ከሳር፣ ከአበባ ብናኝና ከቅጠላ ቅጠል ጋር ወራትን ጠብቀው ሊመጡ የሚችሉ ናቸው፡፡ የአበባ ብናኝ በእንግሊዘኛው አጠራር ‘pollen’ ይባላል፡፡ የሳር አለርጂ ብዙ ጊዜ ሳር በሚበቅልባቸው አካባቢዎች ያጋጥማል፡፡ ወቅቱ ሲያልፍ አለርጂው አይኖራቸውም፡፡ በዚያች በተወሰነች ጊዜ ግንኙነት ስለሚኖራቸው ችግሩ ይከሰትባቸዋል፡፡ ሁለተኛው የአለርጂ ዓይነት ደግሞ ዓመቱን ሙሉ ከሚገኙ ነገሮች ለምሳሌ አቧራ፣ ለአይን የማይታዩ እንደ ‘mite’ ዓይነት ሕዋሳት፣ ከዱቄት፣ ከፈንገስ፣ ከተለያዩ እቤት ውስጥ ካሉ የዕርጥበትና የሚሸትቱ ነገሮች ይመጣል፡፡ ከምንም በላይ የምንጠጣው፣ የምንበላው፣ የምንጠቀመው ነገር ለዚህ መነሻ ሊሆን ይችላል፡፡ ጊዜው ግን አይታወቅም፡፡ ለአለርጂ በተፈጥሯቸው ስስ የሆኑና ያልሆኑ ሰዎች አሉ?ለአለርጂ ስስ (sensitive) ሆኖ የተፈጠረ፣ ያልተፈጠረ የሚባል ነገር የለም፡፡ አለርጂ በዘር የሚተላለፍ ነው፡፡ ለምሳሌ አለርጂ እናትና አባት ካላቸው ብዙ ጊዜ ልጆች ላይ ይከሰታል እንጂ ስስ ተብሎ የሚገለፅ

አይደለም፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ ‹ሳይነስ›ን እንዴት እንረዳው?ብዙ ሰው አፍንጫውን ሲያመው ‹ሳይነስ› ብሎ ነው የሚገልፀው፡፡ ይኼ ተለምዶ ሲሆን ሕብረተሰቡ ማወቅ የሚገባው ‹ሳይነስ› ማለት ቦታው ነው፡፡ አፍንጫችን አካባቢ ከጎን ጎን፣ ከፊት፣ ከኋላ የሚቀመጡ ክፍትና ባዶ የሆኑ አራትና አምስት ቦታዎች አሉ፡፡ እነዚህ ‹ሳይነስ› ይባላሉ፡፡ የእነዚህ ክፍት ቦታዎች በሽታም የ‹ሳይነስ በሽታ› ይባላል፡፡ ይኼ አለርጂ በአደጋ፣ ዕጢም ሊወጣበት በሌላም ነገር ሊከሰት ይችላል፡፡ በተለይ ግን አለርጂን የሚጠቃው አለርጂክ ፌናይተስ ወይም አለርጂ የአፍንጫ በሽታ ሲሆን ምልክቱ ከሌሎቹ የተለየ ነው፡፡ በምን መንገድ?ማስነጠስ፣ ከአፍንጫ ውሃ መሰል ፈሳሽ መንቆርቆር፣ አፍንጫን መብላትና መቆጥቆጥ፣ ዓይን፣ ላንቃንና ጆሮን መብላት፣ ትንፋሽ መከልከልና ማፈን... የመሳሰሉት ምልክቶቹ ናቸው፡፡ ይኼ ችግር ያለባቸው በአጠቃላይ ፊታቸውን ጥሩ ስሜት አይሰማቸውም፡፡ ፈሳሹ ደግሞ ምንም ከለር የለውም፡፡ ቢጫ ወይም አረንጓዴ አይደለም፡፡ ብዙ በሃረብ ይፈጃል፡፡ እንዲሁም አፍንጫችን የመተንፈሻ አካል ዋናው ስለሆነ በችግሩ ምክንያት የአፍንጫ ውስጥ ስጋ ስለሚቆጣ ይነፋልና አየር አያስገባም፡፡ በዚህ የታመሙ ሰዎችን ትንፋሽ ይከለክላቸውና በአፋቸው ይተነፍሳሉ፡፡ ያኔም አፋቸውና ጉሮሮዋቸው ይደርቃል፡፡ ስለዚህ በዚህ በአለርጂ ምክንያት ጥሩ ሕይወት አይኖራቸውም ማለት ነው፡፡ ቀንም ለሊትም ስለሚያሰቃያቸው ራስ ምታት ይመጣባቸዋል፡፡ ‹ሳይነስ›ና የአፍንጫ አለርጂ ይገናኛሉ?አዎን፡፡ ከላይ እንደገለፅኩልህ ነው፡፡ አለርጂ አጠቃላይ ነው፡፡ ማንኛውም ነገር አፍንጫን ሳይነካው ወደ ሳምባ አይገባም፡፡ ብዙ ጊዜ አፍንጫ አካባቢ የ‹አለርጂ ሳይነስ› ያላቸው ሰዎች አሉ፡፡ ከዛም አልፎ ወደ ሳንባ ወርዶ ሳንባቸውን የሚነካ፣ የሚያፍን፣ የሚያስልና የሚያጠቃ አለ፡፡ ትንፋሻቸውን ይከለክላቸዋል፡፡ ስለዚህ ‹ሳይነስ›ና የአፍንጫ አለርጂ ግንኙነት አላቸው፣ የተዛመዱም ናቸው፡፡ አንዳንዴ

ሁለቱም አሉ፡፡ አንዳንዱ አፍንጫው አካባቢ ብቻ የሚቀር አለ፡፡ ሁለቱም በአንድ ጥላ አለርጂ ተብለው ይገለፃሉ፡፡ ከወቅታዊ አለርጂ ጋር በተያያዘ በአገራችን መስከረምና ጥቅምት ወራት አከባቢ፣ አበባ በሚያብበበት ጊዜ የአበባው ሽታ የሚያስከትለው ምንድን ነው? ከአበቦች የወንዴ ዘር ፍሬ የሚበንነው ብናኝ በንፋስ በንኖ አፍንጫ ውስጥ ይገባል፡፡ ለብናኙ አለርጂ ያለባቸው ሰዎች ብቻ ይጎዳሉ፡፡ ሌላውን ሰው ምንም አይለውም፡፡ አንዳንዴ ሰዎች ለቅዝቃዜ ሲጋለጡ፣ ቀዝቃዛ መጠጦችን በተለይም አልኮል ሲጠጡ ያስነጥሳቸዋል፡፡ ይኼ ለአለርጂ ምክንያት ይሆናል? ጥሩ ጥያቄ ነው፡፡ ብዙ ጊዜ ሰዎች ቅዝቃዜና ቀዝቃዛ አየር ብለው ከችግሩ ጋር ያያይዙታል፡፡ ብዙ ጊዜ መፅሀፍ

በኤልያስ ገብሩ

የአፍንጫ አለርጂየዶ/ር ነጋ ከፍተኛ

የአንገት በላይ ክሊኒክ

ባለቤትና ከአንገት በላይ

ስፔሻሊስት የሆኑት ዶ/ር

ነጋ ኪሮስ በአፍንጫ

አለርጂ የጤና ችግር

ዙሪያ ከአውራምባ

ታይምስ የጤና አምድ

ፀሃፊ ጋር ተከታዩን

ሙያዊ ቃለ ምልልስ

አድርገዋል፡፡

ያስጠቁናል፡፡ በተለይ ይኼ አይነት ችግር የሚኖረው በትልልቅ ከተሞች አካባቢ ሲሆን ኑሮውም የተፋፈገ ስለሆነ ነው፡፡ በገጠር አካባቢ እንደዚህ አይነት በሽታዎች ብዙም አትመለከታቸውም፡፡ ብዙ ሰው አዲስ አበባ ከተማ ሲመጣ ነው አመመኝ የሚለው፡፡ ያ የአካባቢና የአኗኗር ሁኔታ ነው፡፡ ይኼ ትልቅ አስተዋፅኦ አለው፡፡ ስለ ምርመራዎቹስ ምን ይላሉ? ምርመራው በሦስት ይከፈላል፡፡ አጠቃላይ የሕክምና ሂደት እነዚህን ደረጃዎች ይይዛል፡፡ መጀመሪያ የበሽተኛውን ታሪክ መጠየቅ አለብህ፡፡ ይኼ ወሳኝ ነው፡፡ በዚህ 80 በመቶ የበሽተኛውን ችግር ማወቅ ይቻላል፡፡ ወደሌላ ወጪና ዝርዝር ነገር ከመግባት በፊት ጊዜ ሰጥቶ በሽተኛውን እንዴት እንደሚያመው ብትጠይቀው ስለበሽታው መረዳት ይቻላል፡፡ ሁለተኛ በእጅ በመዳሰስ፣ በአይን በማየትና በመመርመር የሚገኝ ነው፡፡ ሦስተኛው ደረጃ ዘመኑ ባፈራቸው መሳሪያዎች ተደግፈህ ልታውቅበት የምትችልበትን ታውቃለህ፡፡ አፍንጫ ትንሽ ቀዳዳዎች አሉት፡፡ እዛ ገብተህ እንደልብ ለማየት እንድትችል ረቂቅ መሳሪያዎች አሉ፡፡ ኢንዶስኮፒ፣ ኤክስሬይ፣ አልትራሳውንድ፣ ኤም.አር.አይ፣ የአፍንጫ ሲቲ ስካን ይጠቀሳሉ፡፡ በዚህ መሠረት ማወቅ ይቻላል፡፡ እነዚህ ዋናዎቹ የመመርመሪያ ዘዴዎች ናቸው፡፡ ሕክምናዎቹ፣ መድኃኒቶቹ... ? ሁለት ዓይነት ሕክምና አለው፡፡ አንደኛ በመድኃኒት በሽተኛው የሚታከምበት ሁኔታ አለ፡፡ ሁለተኛው ደግሞ በቀዶ ጥገና ነው፡፡ የተለያዩ መድሃኒቶች ቢኖሩም ብዙ ጊዜ አለርጂን እስከመጨረሻው የሚያጠፋ መድኃኒት የለም፡፡ መድኃኒቶቹ ብዙ ጊዜ የመትከላከልባቸው ናቸው፡፡ እነሱን በመጠቀም ችግር በሚኖርበት ጊዜ እንዲወገዱ ማድረግ ይቻላል፡፡ በሁለተኛ ደረጃ በዋናነት ደግሞ በተደጋጋሚ አለርጂ በሚመጣበት ጊዜ አፍንጫ ውስጥ የሚወጡ ትርፍ ስጋዎች አሉ፡፡ ይኼንን በቀዶ ጥገና በማውጣት ነው ልትገላግላቸው የምትችለው፡፡ ሦስተኛው ሕክምና እኛ አገር የለም፡፡ በውጭ አገር ግን ይጠቀሙበታል፡፡ ግለሰቡን ለየትኛው አለርጂ እንደሆነ የቆዳ ምርመራ (Skin test) ይደረግለታል፡፡ በዚህ ምርመራ ላይ የተለያዩ የአበባ፣ የአቧራ፣ የእንስሳትና የተለያዩ ነገሮችን ይወጋሉ፡፡ ከዛ ግለሰቡ ለየትኛው ነገር አለርጂ እንደሆነ ይለያል፡፡ ለምሳሌ ለአባባ የወንዴ ዘር ብናኝ አለርጂ የሆነ ሰው ለሁለትና ሦስት ዓመታት በምርመራው መሠረት አለርጂ የሆነበትን ነገር በጥንቃቄ በትንሽ በትንሹ እየወሰደ ሰውነቱ እንዲለምድ ይደረጋል፡፡ ይኼ ይኼን ያህል አጥጋቢ ውጤት ባይኖረውም ብዙ ጊዜ ይጠቀሙበታል፡፡ መድሃኒቶቹ ደግሞ አንቲ ሂስታሚን ይባላሉ፡፡ ብዙ ጊዜ እንጠቀምበታለን፡፡ ሰውነታችን ያ ባዕድ የሆነ ነገር ወደ አፍንጫ ወይም ወደ መተንፈሻ አካል በሚጣበት ጊዜ ሰውነታችን ሲቆጣና ሲታመም ሂስታሚን የሚባል ኬሚካል ይረጫል፡፡ ያ ሂስታሚን የሚባለ ለዚህ ለአፍንጫችን ውሃ መንቆርቆር፣ በአፍንጫ ውስጥ ስጋ በማሳበጥ መታፈንን የሚያግዝ ኬሚካል ነው፡፡ አንቲ ሂስታሚን ሂስታሚን እንዳይመነጭ የሚረዳ መድኃኒት ነው፡፡ በዚህ የተለያዩ መድኃኒቶች አሉ፡፡ ሁለተኛው ስቲሮይድ የሚባሉ ሆርሞኖች ለሕመምተኛው ይሰጣሉ፡፡ በመጨረሻም ለአንባቢያን ማስተላለፍ የምፈልገው፣ ሰዎች ለምን ነገሮች አለርጂ እንደሆኑ ለይተው ማወቅና ራሳቸውን በቅድሚያ መመርመር ይገባቸዋል፡፡ ከላይ በገለፅኩት መሠረት ለችግሩ ከሚያጋልጡ ነገሮች በተቻለ አቅም ራሳቸውን መጠበቅ ይኖርባቸዋል፡፡ እንዲሁም በየቤቶቻችንና በየሆቴሎች የሚነጠፉት ምንጣፎች አቧራን፣ በዓይን የማይታዩ ረቂቅ ተዋሲያንና ቆሻሻዎችን የሚይዙ በመሆኑ ትልቅ የንፅህና ጥንቃቄ እንደሚያስፈልጋቸው ለመግለፅ እወዳለሁ፡፡

ላይ እንደሚገለፀውም አለርጂ መነሻው ቅዝቃዜ አይደለም፡፡ መነሻው ከሚበሉ፣ ከሚጠጡና ከሚሸተቱ.. ነገሮች ጋር ነው እንጂ በሌላ አይደለም፡፡ በበረዷሟና እጅግ በሚበርደው ሳይቤሪያ የሚኖሩ ሰዎች አሉ፡፡ እዛ የሚኖሩ ሰዎች በ‹ሳይንስ› የተጠቁ ሰዎች አይደሉም፡፡ የበለጠ ቅዝቃዜ ሲሰማ ሰውነት የመቋቋም ኃይል ያጣና የበለጠ ችግሩን ያባብሰዋል እንጂ በቀጥታ ብርድ ለአለርጂ መነሻ አይደለም፡፡ አለርጂው ከአፍንጫ ሕዋስ ወይም ሕብረ ሕዋስ ጋር ነው ግንኙነት ያለው? አይደለም፡፡ ያ ባዕድ ነገር አፍንጫ ውስጥ ካለው ስጋ ጋር ይገናኝና ባዕድ መሆኑን ሰውነታችን ይገነዘበውና ምላሽ ይሰጣል፡፡ በዛን ጊዜ ለመከላከል ሲባል ሰውነታችን ወደ ደም የሚያፈሳቸው ፈሳሾች አሉ፡፡ ይኼ የአፍንጫ ውስጥ ስጋዎች እንዲነፉና እንዲቆረቆሩ ያደርጋል፡፡ በአንዳንድ ሰዎች አፍንጫ ላይ ሽፍታና ውሃ የመቋጠር ነገር ይታይባቸዋል፡፡ ለምን? ከላይ እንደገለፅኩት አለርጂዎች የተለያዩ ናቸው፡፡ በቆዳና በአይን ብቻ የሚከሰት አለ፡፡ ዓይንን ይበላል፣ ይቀላልና ይደፈርሳል፡፡ እንዲሁም ሌላ ነገር ሳያማቸው ቆዳቸውን የሚያሳክካቸው አሉ፡፡ እንደ ችፌ የሆነ እግር፣ እጅና ፊታቸው ላይ ይከሰታል፡፡ ይኼ ራሱን የቻለ የቆዳ ችግር ነው፡፡ ከአፍንጫ አለርጂ ጋር የተያያዘ አይደለም፡፡ የሲጋራ ጭስ፣ ሺሻና ጫት ችግሩን አይፈጥሩም? አንዱ የአለርጂ መነሻ የሲጋራ ጭስና ብናኝ ነው፡፡ ያ በሚሸታቸው ጊዜ፣ በተለይ ከጭሱ ይልቅ ትርኳሹ በጣም በንኖ በአፍንጫ ሲሸተት በጣም ችግር ያመጣል፡፡ የመጨረሻ የአለርጂ ጠላት እሱ ነው፡፡ ሲጋራን ከማጨስ መቆጠቡ አጠያያቂነት የለውም፡፡ በሁለተኛ ደረጃ ሲጋራ ጉሮሮ አካባቢ የሚያመጣው ጠንቅ አለ፡፡ የጉሮሮ ካንሠር መነሻ ነው ተብሎ ከሚጠሩት አንዱ ሲጋራ ነው፡፡ የተጠቀሱት ሁሉ ለችግሩ ያጋልጣሉ፡፡ የበሽታው ቁጥር እየጨመረ እንጂ እየቀነሰ አይመጣም፡፡ ባዕድ ልማዶች በቀነሱ ቁጥር በሽታውንም ይቀንሳሉ፡፡ ይኼ አያጠያይቅም፡፡ ሰዎች ጫት ሲቅሙና ሺሻ ሲያጨሱ በብዛት ተፋፍገው ነው፡፡ በጠባብ ቦታና ክፍል ውስጥ 10 እና 15 ሰው ተኩኖ የሚተነፈሰው አየር የተበከለ ነው፡፡ የአከባቢና የራስ ንፅህናን ያለመጠበቅ ነገር ስላለ ለአለርጂና ለትንፋሽ በሽታዎች ይጋለጣሉ፡፡ሀገራችን የተለያዩ መልክአ ምድሮችና ስነ-ምሕዳሮች ባለቤች ነች፡፡ የተለያዩ የዛፍና የዕፅዋት ዝርያዎች ይበቅሉባታል፡፡ ከሌሎች አገሮች አንፃር የእነዚህ ተፈጥሯዊ ሽታና ብናኝ ለአፍንጫ አለርጂ ምን አይነት አስተዋፅኦ ያደርጋል? እኔ እንዳየሁት፣ ከውጪ አገራት አንፃር ስታነፃፅረው የውጭዎቹ አካባቢ የበለጠ ይጎዳሉ፡፡ ምክንያቱም የአካባቢ ብክለት በኢንዱስትሪ፣ በመኪና ጭስና በተለያዩ ኬሚካሎች አለ፡፡ በዚህ ሕፃናትና አዋቂዎች በብዛት ይጎዳሉ፡፡ ይኼ በእኛም አገር አለ፡፡ ግን ከውጪው ጋር የምታነፃፅረው አይደለም፡፡ አገራችን በተፈጥሮ የተመቸ፣ ደጋ፣ ወይን አደጋና ቆላ ተብሎ የተከፈለ ነው፡፡ ሰው ደጋ ካልተመቸው ወይና ደጋ ሄዶ ይቀመጣል፡- እያቀያየረ፡፡ አዲስ አበባ ውስጥ ራሱ የተለያዩ የአየር ፀባይ አቀማመጦች አሉ፡፡ ቄራ አከባቢ የማይመቸው ሰው ንፋስ ስልክ ሄዶ ሊሻለው ይችላል፡፡ የአገሪቷ አቀማመጥ በሽታውን ለመከላከል የሚደግፍ እንጂ መጥፎ አይደለም፡፡ ብክለቱም ከውጭው ጋር ሲነፃፀር ያን ያህል ነው፡፡ ከሙያ ልምድዎ አንፃር በአብዛኛው በአገራችን ለችግሩ የሚያጋልጡት?እንደሚታወቀው የአኗኗራቸው ሁኔታ ከኑሯችን ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ብዙ ጊዜ ለአለርጂ የአከባቢና የራስህ ንፅህና ትልቅ ተፅዕኖ አላቸው፡፡ አካባቢያችን የተበከለና ኑሯችንም ያን ያህል ንፅህናውን የጠበቀ አይደለም፡፡ እነዚህ ለ‹ሳይነስ› በሽታ

ሁለት ዓይነት ሕክምና

አለው፡፡ አንደኛ

በመድኃኒት በሽተኛው

የሚታከምበት ሁኔታ

አለ፡፡ ሁለተኛው ደግሞ

በቀዶ ጥገና ነው፡

፡ የተለያዩ መድሃኒቶች

ቢኖሩም ብዙ ጊዜ

አለርጂን እስከመጨረሻው

የሚያጠፋ መድኃኒት

የለም፡፡ መድኃኒቶቹ ብዙ

ጊዜ የመትከላከልባቸው

ናቸው፡፡

Page 21: awramba 160

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 160 ቅዳሜ መጋቢት 17 2003 ተ ጠ የ ቅ 21

የዞናዊ ስምሪቱን እንዴት አያችሁት? የቀጠና ስምሪቱን በጥሩነቱ

አምነንበትና ወደን ፈቅደን የአዲስ አበባ መንገድ ትራንስፖርት ቢሮ ባደራጀን መሠረት ለመጀመር በዝግጅት ላይ ነን፡፡ ከቢሮው የቀረቡልንን የሥራ ማንዋሎች ገምግመን እንደሚበጀን ተረድተናል፡፡

የዞን ስምሪቱን ለመጀመር አንቅስቃሴ ማድረግ ከጀመራችሁ ምን ያህል ጊዜ ሆናችሁ?

ከነሐሴ 2001 ዓ.ም ጀምሮ እንቅስቃሴዎችን ጀምረናል፡፡ በመሐል ግን ቢያንስ ለአንድ ዓመት ያክል ተስተጓጉለን ነበር፡፡ ለዚህም ምክንያቱ የአዲስ አበባ መንገድ ትራንስፖርት ቢሮ ሊያከናውናቸው የሚገቡ ነገሮች ባለመሟላታቸው ነው፡፡

የትራንስፖርት ችግርን ለመፍታት ባለንብረቶች በማሕበር መደራጀታችሁ የግድ አስፈላጊ ነው?

በመጀመሪያ ደረጃ አንድ ማህበር ሲቋቋም ከሥራው ጋር ተያያዥ የሆኑ ችግሮችን ለማስወገድ ነው፡፡ በተናጥል የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች በጋራ ቢሆኑ ይበልጥ ውጤት ያስገኛሉ፡፡ ስለዚህ በማህበር ከመደራጀት ውጪ ይህን የሥራ ዘርፍ ከወደቀበት ማንሳት አይቻልም፡፡

ማንኛውም ባለንብረት አባል የመሆን ግዴታስ አለበት?

አዎ፡፡ ምክንያቱም አባል ካልሆነ ሊንቀሳቀስም አይችልም፡፡ ማንኛውም ታክሲ በስምሪት በሚሰራበት ወቅት የታፔላ መለያ ሊኖረው ይገባል፡፡ ይህንን ደግሞ በበላይነት የሚቆጣጠሩት ማህበራት ናቸው፡፡ ስለዚህ ማህበራቱ ታፔላ እና የስምሪት መስመር ሊሰጡ የሚችሉት ለአባላት ብቻ ነው ታፔላ የሌለው መኪና ደግሞ መስራት አይችልም ስለዚህ በሥራው ለመቀጠል የማሕበር አባል መሆን ግዴታ ነው፡፡

እስካሁን ያለው አሰራር በአንፃራዊነት ከዞናዊ ስምሪት የተሻለ አትራፊ እንደመሆኑ መጠን የዞን ስምሪት ተግባራዊ ሲሆን ለሥርዓቱ ተገዢ ለመሆን ምን ያክል ዝግጁ ናቸሁ?

በመጀመሪያ ደረጃ “አያተርፍም” የሚባለው ነገር ላይ አንስማማም፡፡ ምክንያቱም መስመሮቹ ተጠንተዋል፡፡ አንድ መኪና በተመደበበት ዞን ውስጥ በሚገኝ አንድ መስመር ላይ እንዲሰራ የሚደረገው ቢበዛ አንድ ወር ነው፡፡ ስለዚህ ዞኑ ውስጥ ያሉትን መስመሮች በፍርርቅ ስለሚያገኛቸው የሚጎዳ አይኖርም፡፡ በነገራችን ላይ ከስምሪቱ ትልቅ ተጠቃሚ የሚሆነው ባለንብረት ነው፡፡ ቢያንስ መኪናው የት እንዳለ ማወቅ ይችላል፡፡ ለሥርዓቱ ተገዢ መሆንን በተመለከተ ደንቡን አክብሮ የማይሰራ ማንኛውም ባለንብረት በመንግስት ይቀጣል፡፡

ድልድሉ በሚካሄድበት ጊዜ ለማሕበራት ሥራ አስፈፃሚዎች ቅርበት ያላቸው ባለንብረቶች አትራፊ የሆኑ መስመሮችን እንዲያገኙ መደረጋቸው እየተገለፀ ነው፤ በዚህ ላይ ምን አስተያየት አላችሁ?

ይኼ እንግዲህ ተራ አሉባልታ ነው፡፡ ድልድል ከመካሄዱ በፊት በሚዲያ ተጠርተዋል፡፡ በወቅቱ የመጡት በአግባቡ ተስተናግደዋል፡፡ በከተማዋ ውስጥ ያለው መስመር ውስን ነው በሰዓቱ የመጡት ትርፋማ መስመር ላይ ተመድበዋል፡፡ ግን ያ ያመለጣቸው መስመር እንዳመለጣቸው ይቀራል ማለት አይደለም፤ በፍርርቅ ይደርሳቸዋል፡፡

የዞን ስምሪቱ ለመዘግየቱም በምክንያትነት እየተቀመጠ ያለው ማህበራቱ የቤት ሥራቸውን በጊዜ ሰርተው አለማጠናቀቃቸው መሆኑ ነው. . .

እኛ ሥራችንን በአግባቡ ጨርሰናል፡፡ ዝግጁ ነን፡፡ አሁን ሁሉም ነገር መልክ ይዟል፡፡ ባለንብረቶች ታፔላና የጎን ቁጥር ወስደዋል፡፡ የአዲስ አበባ መንገድ ትራንስፖርት ቢሮ ይህንን ፈር ለማስያዝ የሚሰራቸው ሥራዎች አሉ፡፡ እንደመንግስት አካል የሚሰራቸውን ሥራዎች አላጠናቀቀም፡፡ ሥራውን አጠናቆ እኛን “ቀጥሉ” ቢለን ምንም የሚያግደን ነገር የለም፡፡ ስለዚህ ማህበራት በራሳቸው ያዘገዩት ነገር አይደለም፡፡

እናንተ ዘግጁ ከሆናችሁ የዞን ስምሪቱ መቼ ይጀምራል?

በትክክል መቼ እንደሚጀመር የምናውቀው ነገር የለም፡፡

እስከዛ ድረስ ቢያንስ የየማሕበራት አባላቱ ተገልጋዩን በአግባቡ እንዲያስተናግዱ ማድረግ አትችሉም?

ያንን ማድረግ አንችልም፡፡ ግን ችግሩን እስከዛ ድረስ “ጋብ” ለማድረግ ማን ምን መስራት እንዳለበት በትክክል ይታወቃል፡፡ እኛ ትክክለኛ የመንግስት ግብር ከፋዮች ነን ስለዚህ እኛም ሆንን ሌላው የሕብረተሰብ ክፍል በሚከፍለው ግብር የተቋቋመው ፖሊስ ሥነ-ሥርዓት የማስከበር ኃላፊነት አለበት፡፡ ከዚህ በተጨማሪ “ፀጥታ እንዲያስከብሩ” ብሎ ያሰማራቸው ደንብ አስከባሪዎች ሥራቸውን በአግባቡ መስራት ነበረባቸው ግን ከእነሱ የሚጠበቀውን ሲሰሩ አይስተዋልም፤ ከዛም አልፈው እኛ ላይ ትልቅ በደል እያደረሱብን ነው፡፡

... ገባኝ ተራ አስከባሪዎቹ በደል እያደረሱ ያሉት እናንተ እንደምትሉት

የታክሲ ማህበራትና የዞን ስምሪት አወቃቀር

ከሆነ እናንተ ላይ ነው፡፡ የእኔ ጥያቄ የነበረው ግን ሕዝቡን ያማረረውን ቆራርጦ መጫን ለማስቆም ማሕበራት ኃላፊነት እንደሚሰማው አካል ምን ሰርተዋል ወይም እየሰሩ ነው? የሚል ነው፡፡

እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ሕገ-ወጥ ሥራዎችን እናወግዛለን፡፡ እንደ ባለንብረትም በንብረታችን ላይ ሕገ-ወጥ ሥራ እንዲሰራ አንፈልግም፡፡

እኮ በንብረታችሁ የሚፈጸመውን ሕገ-ወጥ ድርጊት ማስቆም አትችሉም?

ይኼ እንዳይሆን አንድ ችግር አለ፡፡ እሱም የታሪፍ ጉዳይ ነው፡፡ ትናንት የነበረውን ሁናቴ በማገናዘብ ነው ታሪፍ የተሰላው፡፡ እሱ ደግሞ አያዋጣም፡፡ ይኼን መነሻ በማድረግ ነው ሾፌሮች ለባለንብረት የሚያስገቡትንና የራሳቸውን የዕለት ገቢ ለመሸፈን የሚቆራርጡት፡፡ ስለዚህ መንግስት ወቅቱን ያገናዘበ ታሪፍ አውጥቶ ችግሩን ማቃለል ይችል ነበር፡፡

ህብረተሰቡ አሁን ባለው የታክሲ ዋጋ እየተማረረ ባለበት ሰዓት ታሪፍ ትንሽ

የአዲስ አበባ ከተማ የታከሲ አገልግሎት በዞናዊ ስምሪት እንዲዋቀር መደረጉን አስመልክቶና በሥራው ላይ ስለሚስተዋሉ ችግሮች በመገናኛ ዞን የዜብራ ታክሲ ባለንብረቶች ማህበር ም/ሰብሳቢ ከሆኑት አቶ ዘሪሁን ደሳለኝ፣ የብሌን ታክሲ ባለንብረቶች ማህበር ሂሳብ ሹም ከሆኑት አቶ ዳንኤል ዘውዴ፣ የፀሐይ ታክሲ ባለንብረቶች

ማህበር ሰብሳቢ ከሆኑት አቶ አበባው ካሳ፣ እንዲሁም ከአዲስ ህይወት ባለንብረቶች ማህበር ደግሞ አቶ ገብሩ አርጋውን ሱራፍኤል ግርማ በጋራ አነጋግሯቸዋል፡፡

ነው እያላችሁ ነው? ተገቢ ነውስ? አዎ፡፡ የታሪክ ክለሳ

እንዲደረግ እየጠየቅን ነው፡፡ አሁን ያለው ታሪፍ በቂ አይደለም፡፡ ሊያሰራን አይችልም፡፡ “ተገቢ ነው ወይ?” ብለህ ለጠየከው ከአቅማችን በላይ ስለሆነ ነው፡፡ ለምሳሌ 7 ኪ.ሜ 2 ብር ከ25 ሳንቲም ይከፈልበታል ግን የቤንዚን ዋጋ ከ18 ብር በላይ ነው፡፡ አስበው እንግዲህ የጎማ ዋጋ 1200 ብር ነው፤ ዘይትም ጨምሯል፡፡ ለጥገና የሚወጣ ወጪ አለ ስለዚህ የወቅቱን ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ ታሪፍ ሊከለስ ይገባል፡፡

እሺ ... ወደ ባለንብረቶች ቅሬታ እንመለስ፡፡ ምንም እንኳን የማህበር አባላት ቢሆኑም ከማህበራት ግን የሚያገኙት ጥቅም /ዕገዛ አለመኖሩን የሚገልፁ አሉ...

ይህንን የሚሉት ሰዎች የእኛን ቢሮዎች የማያውቁት ናቸው፡፡ ወደ ቢሮዎቻችን ለሚመጡት አባላት ሁሉ በቅርበት እንዲከታተሉን እንነግራቸዋለን፡

የማህበራት ገንዘብ ተመዝብሯል የሚባለውስ?

ይኼም ሐሰት ነው፡፡ ጥያቄውን ይዘው ለመጡ ባለንብረቶች የባንክ ቡካችንን አሳይተናቸው ተማምነናል፡፡ ይኼ ሁሉ ውዥንብር የመጣው ስለ እንቅስቃሴያችን ቀርቦ የጠየቅን ባለመኖሩ ነው፡፡ ግን እኛ ለአባላቶቻችን ዘይት በቅናሽ እያቀረብን ነው፣ ሌሎች እገዛዎችንም እያደረግን ነው፡፡

አዲስ ታክሲ የገዙ ባለንብረቶች የማሕበር አባል ሲሆኑ በቂ የግንዛቤ ማስጨበጫ እንዳልተሰጣቸውና የማይመለከታቸውን ውዝፍ ሂሳብ እንዲከፍሉ የተደረገውስ በምን አግባብ ነው?

ይኼ እንደየ ማሕበሩ ያለያያል፡፡ ውዝፍ የሚያስከፍሉ አሉ፤ የማያስከፍሉም አሉ፡፡ እንዲከፍሉ የተደረገበትም ምክንያት - ነባር አባላት ባዋጡት ገንዘብ አዲስ ገቢዎች ተጠቃሚ መሆናቸው ካልቀረ ለሚያገኙት አልግሎት የሚሆን ክፍያ እንደፈፀሙ ስለሚቆጠር ነው፡፡

አቶ ዳንኤል ዘውዴ አቶ አበባው ካሳ አቶ ዘሪሁን ደሳለኝ አቶ ገብሩ አርጋው

እኛ ትክክለኛ የመንግስት ግብር ከፋዮች

ነን ስለዚህ እኛም ሆንን ሌላው የሕብረተሰብ ክፍል

በሚከፍለው ግብር የተቋቋመው ፖሊስ ሥነ-ሥርዓት

የማስከበር ኃላፊነት አለበት፡፡ ከዚህ በተጨማሪ “ፀጥታ

እንዲያስከብሩ” ብሎ ያሰማራቸው ደንብ አስከባሪዎች

ሥራቸውን በአግባቡ መስራት ነበረባቸው ግን ከእነሱ

የሚጠበቀውን ሲሰሩ አይስተዋልም፤ ከዛም አልፈው

እኛ ላይ ትልቅ በደል እያደረሱብን ነው፡፡

Page 22: awramba 160

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 160 ቅዳሜ መጋቢት 17 2003

‹‹በኢትዮጵያ እግር ኳስ ውስጥ ተስፋ ሰጪ ነገር አለ››

ስ ፖ ር ት22

ወደ ኢትዮጵያ ከመጡ ስምንት ወር ሆኖታል፡፡ በዚህ ጊዜ ውስጥ በዋናነት አከናውኜዋለሁ የሚሉት ምንድን ነው?በዝግመታዊ ሂደት የተለያዩ ስኬቶችን እንዳገኘሁ ይሰማኛል ተጨዋቾች ላይ መሻሻሎችን አይቻለሁ፡፡ ቡድኑን ብትገመግመው በስምንት ወር ውስጥ ለውጦችን አስመዝግቧል፡፡ በፊፋ በሚወጣው ወርሀዊ የአገራት የእግር ኳስ ደረጃ ኢትዮጵያ 20 የሚሆኑ ደረጃዎችን ማሻሻል መቻሏ ጥሩ ነገር ነው፡፡ ማዳካስካርን በሜዳዋ ማሸነፋችን ታንዛኒያ በምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ ሻምፒዮና ላይ አራት ውስጥ መግባታችን መልካም ቢሆንም ከዚህ የበለጠ መሻሻል እና ትልልቅ ድሎችን ማስመዝገብ አለብን፡፡ በጥቅሉ ክብር ልንሰጣቸው የሚገቡ መሻሻሎች አሉ፡፡

አንዳንዶች ናይጄሪያን ለመግጠም የያዙት የተጨዋቾች ስብስብ በታንዛኒያው የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ ዋንጫ ከተካፈለው የተሻለ ነው ብለው ያምናሉ፡፡ ሌሎች ደግሞ በሃሳቡ አይስማሙም፡፡ የእርስዎ አስተያየት ምንድን ነው? አዎ! መጠነኛ ለውጦች አሉ፡፡ የተጨዋቾች ስብስቡ የተሻለ ነው፡፡ አዳዲስ የተመረጡት ልጆች ቡድኑን ያጠናክሩታል፡፡ ቡድኑ ላይ በአጠቃላይ መሻሻሎች አሉ፡፡ ተጨዋቾቹ የልምምድ ጊዜውንና መጠኑን ይወዱታል፡፡ አዳዲሶቹ ልጆችም እዚህ ስሜት ውስጥ ገብተዋል፡፡ በቴክኒክም ሆነ በአካል ብቃት ደረጃ ተሰጥኦዋቸውን እያዳበሩ እንደመጡ በሁለት ስምንት ጊዜ ውስጥ መረዳት ችያለሁ፡፡

ይህ ከሆነ ታዲያ ከነገው የአቡጃ የናይጄሪያና የኢትዮጵያ ጨዋታ የተሻለ ነገር እንጠብቅ?ናይጄሪያ ትልቅ ቡድን መሆኑን ማንም ያውቃል፡፡ ተጨዋቾቹ የተጠሩት ሊጫወቱባቸው ከሚያልሟቸው የዓለማችን ትልልቅ ቡድኖች ነው፡፡ ጆን ኦቢ ሜኬልን ከቼልሲ [ባለፈው ሳምንት ለቼልሲ 90 ደቂቃ አልተሰለፈም] ነንማዲ አዲማዲን ከኤሲ ሚላን ጠርታለች፡፡ መልበሻ ክፍሏ በታላላቅ ተጨዋቾች በመሞላቱ የተጋነነ ግምት እንድንሰጣት አያደርግም፡፡ ስብስቡን ማወቃችን ምን አይነት አጨዋወት ይዘን መግባት እንዳለብን እንድናውቅ ይረዳናል፡፡

በጨዋታው ሊመዘገብ ይችላል ብለው የሚያስቡትን ውጤት ሊገምቱ ይችላሉ?ቁማርተኛ አይደለሁም፡፡ መገመት ቁማር መጫወት ስለሆነ አላደርገውም፡፡ አገርን የሚያኮራ ውጤት ለማምጣት እንደምንጓዝ ግን እምነቴ ነው፡፡

ስለ ናይጄሪያ ብ/ቡድን ምን አይነት መረጃዎችን አገኙ? ከሴራሊዮን ጋር ካደረጉት ጨዋታ በኋላ አሁን ሚኬልን ወደ ቡድኑ ቀላቅለውታል፡፡ ጆሴፍ ዮቦ፣ ኦቢፋሚን ማርቲንስ፣ ኦያዝ ኦዲሚውንጌን የመሳሰሉ ተጨዋችን እንደምንፋለም እናውቃለን፡፡ በሳምንቱ አጋማሽ በመጐዳቱ የሚያጡት ብቸኛ ተጨዋች ምርጡ ግብ ጠባቂው (ቪንሰንት ኢንዬማ) ነው፡፡ የእሱ አለመኖር ምናልባት ሊጐዳቸው ይችላል፡፡ ስለ እነርሱ ብዙ ስለሚወራ እና ቅርበትም ስላለኝ መረጃዎች አሉኝ፡፡

የዘር ሀረግዎ ከናይጄሪያ ይመዘዛል፡፡ እናት አገርዎን በተቃራኒነት ለመፋለም መዘጋጀትዎም የበርካታ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሐንን ትኩረት ስቧል፡፡ ይህ ምን አይነት ስሜት ፈጠረብዎት? በአንድ ጐኑ ኩራት ይሰማኛል፡፡ ቤተሰብዎቼ ከአገሪቷ ከመውጣታቸው በፊት ብዙ መስዋዕትነትን የከፈሉባት አገር ነች፡፡ እናት ምድርህ ላይ ተመልሰህ በተቃራኒነት መጫወት በራሱ ኩራት እንዲሰማህ ያደርጋል፡፡ ቤተሰቦቼም የኢትዮጰያ ደጋፊ እንደሚሆኑ ነግረውኛል፡፡ ሁሌም ከጐኔ ናቸው፡፡

በአገራቸው ኢትዮጵያን ሊደግፉ? አዎ! ግን ለዚህ ጨዋታ ብቻ ነው፡፡ በናይጄሪያ አክስቶች፣ አጎቶች እና የአክስትና የአጎት ልጆች አሉኝ፡፡ ሁሉም ጨዋታውን ቢመለከቱ ደስ ይለኛል፡፡

ምን አይነት አጨዋወት ለመተግበር አስበዋል? ወደ እዚህ (ኢትዮጵያ) በመጣሁ ጊዜ ስመለከት ተጨዋቾች የሚያደርጉት የኳስ ቅብብል አስደስቶኛል፡፡ በመቀባበል ላይ ያተኮረ እግር ኳስ (Passing Football) እና ቦታ ጠብቆ የሚደረግ አጨዋወት እመርጣለሁ፡፡ ሁሉም የመከላከል፣ የማደራጀትና የማጥቃት ሚና ላይ ተሳታፊ እና ጠንካራ ሆነው ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ እፈልጋለሁ፡፡ በታክቲክ ዲሲፕሊንድ ሆነን 4-5-1 ልንተገብር እንችላለን፡፡ ይህ ጐልፍ ወይም ቴኒስ አይደለም፤ የቡድን ስፖርት ነው፡፡ ሁሉም ኃላፊነቱን ከተወጣና ማድረግ ያለበትን ካደረገ ይዘን የገባነውን አጨዋወት ልንተገብር እንችላለን፡፡ በጋራ እንከላከላለን፤ ስናጠቃው እንደዚያው ነው፡፡

የቡድንዎ ተፅዕኖ ፈጣሪ ተጨዋች ማነው? ሦስት እና አራት ተጨዋቾችን ልጠራልህ እችላለሁ፡፡ ፍቅሩ ተፈራ [በደቡብ አፍሪካ ለሱፐር ስፖርት ዩናይትድ ይጫወታል] የወቅቱ በጣም ትልቅ ተጨዋች ነው፡፡ ከአገር ውጪ መጫወቱ ትልቅ ልምድ እንዲያካብት አድርጐታል፡፡ ይህን ልምዱንም ያጋራል፡፡ አምበሉ ሳምሶን ሙልጌታ ልምድ ያለው መሪ ነው፡፡ ቡድኑን በመምራት በኩል ትልቅ እገዛ ያበረክታል፡፡ አጥቂው ዑመድ ራሱ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሆኗል፡፡ ከስድስት ወር በፊት የነበረው እና ያሁኑ ዑመድ ኡኩሪ ብዙ ልዩነት አላቸው፡፡ በጣም ተሻሽሏል፡፡ ጠንካራ ጭንቅላት አለው፡፡ ኳስ ሲቀበል እና ተቆጣጥሮ በፍጥነት ያሰበውን ሲያደርግ... ብቻ በሁሉ ረገድ እድገት አሳይቷል፡፡ ትልቅ ተጨዋች ሆኗል፡፡

በብ/ቡድኑ ውስጥ ጥሩ እና መጥፎ የሚሉት ያጋጠምዎት ነገር ምንድን ነው? ስለ መጥፎ ነገር አላስብም ስራዬን በጣም እወደዋለሁ፡፡ አጋጣሚውን አግኝቼ ተሰጥኦ ያላቸውን ልጆች ማሰልጠን በመቻሌ እና ወደ ቡድን ስርዓት ውስጥ ማስገባት በመቻሌ ደስ ይለኛል፡፡ ጠቃሚ ስራ ስለመስራቱ እና የያዝኳቸው እቅዶች ስለመተግበሬ የሚረጋገጠው በሂደት ነው፡፡ በታክቲክ ስራ በኩል መስራት አለብን፡፡ ለዚያ የሚጠቅሙ ነገሮችን በመስራት ለውጥ የሚኖረው በፍጥነት አይደለም፡፡ በናይጄሪያ፣ በጋናና ደ/አፍሪካ በርካታ የእግር ኳስ አካዳሚዎች አሉ፡፡ በሁሉም ስፍራዎች በርካታ ሳር የለበሱ የመጫወቻ ሜዳዎች ታገኛለህ፡፡ በአዲስ አበባ ግን ይህ የለም፡፡ ልጆች በመንገድ ላይ ሲጫወቱ ታያለህ፡፡ ይህ በጣም ትልቅ ችግር ነው፡፡ ግን ነገሮች ተስፋ ሊያስቆርጡህ አይገባም፡፡ 11 ተጨዋቾች ይዘህ ሜዳ ከገባህ የምትችለውን መስራት አለብህ፡፡

ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር ያሎት ግንኙነትስ እንዴት ነው? ጥሩ የሆነ ሙያዊ ግንኙነት አለን፡፡ እንከባበራለን፡፡መደበኛ የሆነ የማያስማማ ጉዳይ ሊኖር ይችላል፡፡ ይህ ደግሞ በስራ ቦታ የሚያጋጥም ነው፡፡ አንተ ጋዜጠኛ ነህ በስራ ቦታ የማትስማማባቸው ነጥቦች ይኖራሉ፡፡ ይህ ግን ሙያዊ ግንኙነቶችህን ሊረብሽብህ አይገባም፡፡ ከማንም ጋር ጥሩ ግንኙነት እንዲኖረኝ እፈልጋለሁ፡፡ በእንግሊዝም አሰልጣኝ በተጨዋች ምርጫ፣ በገንዘብ ነክ ነገሮች እና በሌሎች ሁኔታዎች ከክለብና ከፌዴሬሽን ኃላፊዎች ጋር አለመስማማት ይኖራል፡፡ አሰልጣኙ የሚፈልገውን ነገር ክለቡ ወይም ፌዴሬሽኑ የማይቀበሉበት ሁኔታ ይኖራል፡፡ ይህ ሊያስጨንቅህ ይችላል ግን ሊያስፈራህ አይገባም፡፡ ባያስማማህም ለውሳኔዎች ክብር መስጠት አለብህ፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ያጣውን ስኬት

እቆማለሁ፡፡ ሁሌም የተሻለ ቦታ ለመድረስ የምጥር ሰው ነኝ፡፡ ለምሳሌ ወደ በታንዛኒያ የሄደነው ምንም ዝግጅት ሳናደርግ ነው፡፡ ከ12 አገሮች ጋር ተፎካካሪ ሆነናል፡፡ ለፍፃሜ ያላለፍነውም እድለኛ ስላልሆንን ነው፡፡

ተጨዋቾችዎ በጣም ተግባቢና ሳቂታ ሰው መሆንዎን ይናገራሉ፡፡ እኔም በልምምድ ጊዜ ተመሳሳይ ነገር አይቼቦታለሁ...የመጀመሪያው ነገር ሙያዊ ክብር መስጠት ነው፡፡ አብረን ስንሆን እንቀልዳለን፣ እንሳሳቃለን፡፡ ይህም ሙያዊ ግንኙነታችን እንዲጠናከር ያደርገዋል፡፡ ተጨዋች ተስፋ ሲቆርጥ ጥሩውን ነገር እየነገርክ ማበረታታት አለብህ፡፡ አዕምሮው ከተለወጥከው የምትለውን ለማድረግ አይቸገርም፡፡ በራሳቸው በጣም እንዲተማመኑ እነግራቸዋለሁ፡፡ ከአሰልጣኞችም ጋር ጥሩ ግንኙነት አለኝ፡፡ የሚሰሩትን ስራ ማበረታታት ወዳለሁ፡፡ ኧ... ተጨዋቾቼን ሁሉ ብትጠይቅ ስለ እኔ የሚነግሩህ ነገር ተመሳሳይ ነው፡፡ ወደ ልምምድ ሲመጡ ሳይነግሩኝ በፊት ፊታቸውን አይቼ ስሜታቸውን እረዳለሁ፡፡ የተጨነቁበትን ነገር እንዲነግሩኝ አደርጋለሁ፡፡ በሙያቸው ደስተኛ እንዲሆኑ ሁሌም እነግራቸዋለሁ፡፡ ሰላማዊ ግንኙነት መፍጠርን እወዳለሁ፡፡

ቅድም በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ [ያነጋገርኳቸው ማክሰኞ አመሻሹን ከሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በኋላ ነው] ረዳት አሰልጣኝዎ አጥናፉ አለሙን ጥሩ አጋዥዎ መሆናቸውን በመግለፅ አወድሰዋቸዋል፡፡ ከሳምንት በፊት ከአፍሮ ኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያ ጋር በነበርዎ ቆይታ ላይ ግን ረዳቴ አስተርጓሚ ብቻ ነው ብለው ነበር፡፡ ሁለቱ አይጣረስም? ማለት የፈለግኩት እንደዚያ አልነበረም፡፡ እንደዚያ የተረዱኝ ግን አሉ፡፡ ‹‹የምፈልገውን በአግባቡ በመተርጐም ሃሳቤ እንዲደርስልኝ በማድረጉ በኩል በልምምድ ላይም ሆነ ከዚህ ውጪ ባለ ጊዜ ይረዳኛል- ጥሩ አስተርጓሚ ነው›› ማለቴ ነበር፡፡ በዚህ አጋጣሚ አስተያየቴ አድናቆታዊ እንደሆነ ሰዎች እንዲረዱልኝ እፈልጋለሁ፡፡

ግን እውነት ጥሩ ረዳት አሰልጣኝ አለዎት? አዎ! በጣም ጥሩ ነው፡፡

በተደጋጋሚ ጊዜ ወደ ሀዋሳ ይሄዳሉ ምክንያትዎ ምንድን ነው?ያን ያህል ብዙ ጊዜ አልተጓዝኩም፡፡ የተወሰኑ ጉዞዎችን ግን አድርጌያለሁ፡፡ የመጣሁት በክረምት ወራት በመሆኑ ለልምምድ አዳማና ሀዋሳ መሄድ ነበረብን፡፡ አዲስ አበባ እንደ ብዙዎቹ ዋና ከተሞች በውጥረት የተሞላች ነች፡፡ ለንደንም በጣም ቢዚ ነች፡፡ ሀዋሳን በጣም እወዳታለሁ፡፡ እዚያ ስሆን ዘና እላለሁ፡፡ ሁሉ ነገር ንፁህ ነው፡፡ የእረፍት ጊዜ ለማሳለፍ ተመራጭ ቦታ ነው፡፡

በመጨረሻ ለመጀመሪያ ጊዜ ከለንደን ወደ አዲስ አበባ በመጣሁበት ወቅት የተመለከትኩት የስታዲየም ጨዋታን ሳይሆን የመንገድ ላይ እግር ኳስን ነው፡፡ ሲጫወቱ ያየኋቸው አዳጊዎች በቴክኒኩ በኩል ያላቸው ችሎታ ማራኪ መሆኑ አስገርሞኝ ነበር፡፡ አዎ... ጥንካሬ የላቸውም ነገር ግን በቴክኒኩ በኩል የበለፀጉ ናቸው፡፡ በመንገድ ላይ የሚጫወቱትን ተጨዋቾች ተሰጥኦ ሳይ ‹‹ለመስራት ምቹ ነው›› አልኩ፡፡ ለምሳሌ ስፔናዊያንን ተመልከት ሰውነታዊ ጥንካሬ የላቸውም ግን በጣም ቴክኒሺያን ናቸው፡፡ ያን ነገር እዚህም አይቻለሁ፡፡

እውን ኢትዮጵያዊያን ተጨዋቾች ቴክኒሺያን ናቸው? በጣም ቴክኒሺያን ናቸው፡፡ [ይህንን ሰሞኑን በዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን ላይም እየተናገሩ ነው] በታንዛኒያ ብዙ ሰዎች ያደነቁትም ይህንኑ ነው፡፡ ልባቸውን የኢትዮጵያዊያን ማራኪ የኳስ ቅብብል አስሸፍቶት ነበር፡፡ በቴክኒኩ ረገድ ጥሩ ቢሆኑም ግን... ኧ... ሌሎች ነገሮች ላይ ማለትም በአካል ብቃት በኩል ለመዳበር ጊዜ ቢጠይቅም መሰራት አለበት፡፡ ናይጄሪያን ልንሆን አንችልም፡፡ መስራት ያለብን ራሳችንን ሆነን ነው፡፡ በጥቅሉ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ውስጥ ተስፋ ሰጪ ነገር አለ፡፡

ማስገኘት የሚችል የአሰልጣኝነት ልምድ እንደሌለዎት የሚናገሩ አሉ...[አቋርጠውኝ ቆጣ ብለው] ስንት ዓመት ነው ያሰለጠንኩት?

አስር ዓመት የሚጠጋ ጊዜ እንዳሰለጠኑ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ግን የሰሩት በክለብ ደረጃ ብቻ ነው፡፡ [የግርምት ፈገግታ] በእንግሊዝ በትልቅ ደረጃ ማሰልጠን የሚችል ፈቃድ ካላቸው አሰልጣኞች አንዱ ነኝ፡፡

እሱን አውቃለሁ፡፡በርግጥ ለስልጠና ልምድ ትልቅ ጥቅም አለው፡፡ ልምድ ከሌለህ ግን ውጤታማ አትሆንም ማለት አይደለም፡፡ የባርሴሎናውን ጋዲዮላ ተመልከተው ያለው የማሰልጠን ልምድ አራት ዓመት ነው፡፡ ግን ውጤታማ ስራ ሰርቷል፡፡ በብቃት ማሰልጠን የሚያስችል አዕምሯዊ ብቃት ይኑርህ እንጂ ልምድን በሂደትና ከምታገኛቸው ሰዎች ጥሩ ግንኙነት ካለህ ታገኘዋለህ፡፡ ከአስተያየቱ በተቃራኒነት

ኢፊ ኦኑራ [የኢትዮጵያ ብ/ቡድን ዋና አሰልጣኝ]

በፊፋ ወርሃዊ የእግር ኳስ ሰንጠረዥ 124ኛ ደረጃ ላይ የምትገኘው ኢትዮጵያ፤ 39ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠችውን ናይጄሪያ ለመግጠም ነገ ማምሻውን በአቡጃ ብሔራዊ ስታዲየም ቀጠሮ ይዛለች፡፡ የቡድኗ አባላትንም ማክሰኞ ማምሻውን “መልካም ውጤት” ብላ ራት ጋብዛና አበረታትታ ወደ ልካለች፡፡ የዘር ሐረጋቸው ከናይጄሪያ የሚመዘዘው ስኮትላንዳዊው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ኢፌም (ኢፊ) ኦኑራ እናት ምድራቸው ባላት የእግር ኳስ ስም እንደማይጨነቁና ቤተሰባቸውም ለእሳቸው ሲሉ ኢትዮጵያ እንድታሸንፍ እንደሚፈልጉ ገልፀዋል፡፡ አቤል ዓለማየሁ 13 ሺህ ዶላር ወርሃዊ

ክፍያ ኪሳቸው ከሚያስገቡት የ43 ዓመቱ ጎልማሳ አሰልጣኝ ጋር ወደ ንስሮቹ ዘንድ ከመብረራቸው በፊት ቆይታ አድርጓል፡፡

ጥቂት መረጃዎች በቁጥር፡- 124፡- የኢትዮጵያ ወቅታዊ የእግር ኳስ ደረጃ

39፡• - የናይጄሪያ ወቅታዊ የእግር ኳስ ደረጃ

18፡• - የኢትዮጵያ ብ/ቡድን ወደ አቡጃ ይዟቸው የሄደው የተጨዋቾች ብዛት

3• ፡- ከጊኒ፣ ማዳጋስካርና ናይጄሪያ ጋር በምድብ ሁለት የተደለደለው የኢትዮጵያ ብ/ቡድን በሦስት ነጥብ በናይጄሪያ በግብ ክፍያ ተበልጦ ሦስተኛ ነው፡፡ ሦስተኛ ጨዋታውንም ነገ ያደርጋል፡፡

2፡• - ቡድኑ ከማቅናቱ አንድ ቀን በፊት የተቀነሱ የመጨረሻ ተጨዋቾች ሲሆኑ እነሱም የሀዋሳ ከነማው ዘነበ ከበደ እና የመከላከያው ጫላ ድሪባ ናቸው፡፡

1፡• - ለዋልያዎቹ ከአገር ውጪ የሚጫወት ብቸኛው ተጨዋች የሱፐር ሰፖርቱ ፍቅሩ ተፈራ ነው፡፡

Page 23: awramba 160

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 160 ቅዳሜ መጋቢት 17 2003 23

አደንግዝን ይዤላችሁ መጣሁ›› ብሎ በየአደባባዩና በየመደብሩ መቸርቸር ያልበላንን እንደማከክ ነው፡፡ አልያም ድምፃዊው፣

‹‹ይገርማል ... ይገርማል

ተርቦ እሳት ይሞቃል

ተጠምቶ ልብስ ይደርባል ... ››እንዳለው መሆኑ ነው፡፡ ተምረናል፣ አውቀናል፣ በቅተናል የሚሉ ሰዎች እኛን የሚያንፀንን፣ ኑሯችንን እንዴት ማሻሻል እንደሚገባን የሚያሳየንን እውቀትና ጥበብ ያሳዩን - ያስተምሩን፡፡ የሚያስፈልገን እውቀትና ብልፅግና ጤናችን የሚጠበቅበት፣ አዕምሯችን የሚያድግበት፣ ኑሯችን የሚሻሻልበት ዘዴ ነው፡፡

ከጥቂት ወራት በፊት የአንድ ጠንቅ-ዋይ አስገራሚ የወንጀል ታሪክ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን (ኢሬቴድ) ቀርቦ ነበር፡፡ በብዙ መቶ የሚቆጠሩ ወገኖቻችን በዚህ አባይ ጠንቅ-ዋይ መጭበርበርና ኑሯቸውም መናጋቱ ተገልጿል፡፡ ከዚያ ታሪክ የምንገነዘባቸው ሁለት ነገሮች አሉ፡፡ የመጀመርያው፣ ኢትዮጵያውያን ለዚህ አይነቱ ከንቱ ዕምነትና አምልኮ ምን ያህል የተጋለጥንና የመጣው ንፋስ ሁሉ በቀላሉ የሚወስደን የዋሆች መሆናችንን ነው፡፡ ሁለተኛውና በደንብ ያላስተዋልነው ምንድን ነው ብዙዎቻችን ያልደከምንበትን፣ ያልወጣን ያልወረድንበትን ኃብትና ጥሪት በአጭርና በአቋራጭ መንገድ ለማግኘት ምን ያህል ጥልቅ ፍላጎትና ጉጉት ያለን መሆናችንን ነው፡፡ ያ ሁሉ አማኝ ጤናውንና ንብረቱን ያጣው ያልሰራበትን ታምራዊ ኃብት አገኛለሁ በሚል ነበር፡፡ ‹‹አተርፍ ባይ አጉዳይ›› ሆነ እንጂ፡፡ ባለውቃቢው ለሕዝብ ከቀረበ በኋላም ጥቂት የማይባል ሕብረተሰብ ‹‹ጀግና ነው! ሰራላቸው፡፡ አንበሳ ነው! ሸወዳቸው›› በሚል ውስጣዊ አድናቆት ሲሰጠው እንጂ ሰውዬውን ሲጸየፍና ሲያወግዝ እምብዛም አላየሁም፡፡ ይሄ ደግሞ ይበልጥ አሳዛኝ ነው፡

፡ ዛሬም ከዚህ አይነቱ አምልኮ የሚያላቅቀን እንጂ እዚሁ አዘቅት ውስጥ መልሶ የሚዘፍቀንን ወጥመድ አንሻም፡፡ በእምነት ነፃነት ስም በግሎባላይዜሽን (‹‹ገድሎ በላ›› ይሉታል) ስም መልካሙን ባህላችንን የሚሸረሽር፣ ማንነታችንን የሚያጠፋ፣ እድገታችንን የሚያቀጭጭ ቀንበር ሊጫንብን አይገባም፡፡

በያዝነው የመጋቢት ወር የወጣው አዲስ ጉዳይ መጽሔት (ቅፅ 5፣ ቁጥር 85) በንፋስ ስልክ ላፍቶ፣ በአቃቂና ቂርቆስ ክፍለ ከተሞች ሕዝብን ሲያጭበረብሩ የነበሩ 5 ጠንቅ-ዋዮች መኖሪያቸው ከጥንቆላ ጎጇቸው ተነስቶ ወደ ወህኒ ቤት እንዲዛወር መደረጉን ዘግቧል፡፡ ‹‹ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ እናድናለን፤ መንፈሳዊ ኃይል አለን፤ በሽታ እንፈውሳለን፤›› ሲሉ ራሳቸውን በመለኮትና በሀኪም ሙያ የዶሉ ነበሩ ሲል የገለፃቸው መጽሔቱ፣ ጉዳያቸውን የተከታተለው ፍ/ቤት ከ15 እስከ 25 ዓመት እስር እንደፈረደባቸው ገልፆ ነበር፡፡ ችግራችን የመርፌ ሰኪዎች ሳይሆን የመርፌ ሰሪዎች ነው፡፡ ሀገራችን የምትሻው አንደርቢ የሚያወርድላት ጥንቆላ ሳይሆን ዝናብ የሚያወርድላት እውቀት ነው፡፡ የሚያስፈልገን አፍዝ አደንግዝ ሳይሆን የሚያነቃን፣ ከአፍዝ አደንግዝ የሚያላቅቀን የአዕምሮ እውቀት ነው፡፡ አጥብቀን የምንሻው አህያ ከመንዳት የሚያወጣንን ጥበብ ነው (አህያ መንዳት ነውር ነው ለማለት ሳይሆን ወደተሻለ የቴክኖሎጂ ሥልጣኔ የሚያሸጋግረን ለማለት ነው)፡፡

በዚሁ ጉዳይ ላይ አንድ ያነበብኩትን ታሪክ ጠቅሼ ሀሳቤን ልቋጭ፡፡ አዳሙ ተፈራ የተባሉ ጸሐፊ፣ ‹‹የኢትዮጵያውያን ማንነት በባዕዳን ቅኝት›› በተባለው መጽሐፋቸው የቀደሙ ወገኖቻችን በአጉል አምልኮና ጥንቆላ መከራቸውን ያዩ እንደነበር ጽፈዋል፡፡ አቶ አዳሙ በዚህ ላይ ያቀረቡት መረጃ ራስል ስለሀገራችን

የጠቀሰውን ነው፡፡ ታሪኩ እንዲህ ይላል፡-

‹‹ሌላው ፒርስ (እንግሊዛዊ ሀገር ጎብኚ) የተገነዘበውና የደረሰበት አንዱ ጉዳይ የደብተራው ነገር ነበር፡፡ ይህ ደብተራ በመላ ሀገሪቱ የተዘዋወረ ትልቅና ታዋቂ ደብተራ ነበር፡፡ ያልተማሩትንና ድሆችን እያታለለና እያሞኘ የኖረ ሰው ነው፡፡ ‹የታመሙ እፈውሳለሁ፤ በሰይጣን የተለከፈን አካባቢ አነፃለሁ፤ ክፉ መንፈስን አስለቅቃለሁ› የሚል ነበር፡፡

ይህ ደብተራ ሁልግዜ ሥራውን የሚጀምረው ጸሃይ ሲደራ ነው፡፡ ምንም እሳት በአካባቢው እንዳይኖር ያዝና ወደ በር ስር ጠጋ ብሎ ይመጣል፡፡ ፀሎት በሚጀመርበት ሰዓት ሰዎች ከእርሱ ፈንጠር ብለው እንዲቆሙ ይነግራቸዋል፡፡ ይህንን የሰዎቹን ከአጠገቡ መራቅ አጋጣሚ በመጠቀም የጠርሙስ ስባሪ በመያዝ የደረቀ ፋንድያ በጠርሙስ አማካይነት በጸሃይ ጨረር እንዲቀጣጠል ያደርጋል፡፡ ከዚያም እጣን ላይ ሲወረውረው ቡልቅ ያለ ጪስ ያወጣል፡፡ ከዚያም ወደ ሰማይ ያንጋጥጥና እነዚያን በዙሪያው የተኮለኮሉትን ሰዎች ወደ አጠገቡ እንዲቀርቡ እየጠራ በአርምሞ ፀሎቱን እግዚአብሔር እንዲሰማውና የማይታየውንም ሆነ የሚታየውን ጠላቱን ሁሉ ለማጥፋት ሲል እሳት ከላይ እንደላከ ይነግራቸዋል፡፡

ይህን የተጭበረበረ ዘዴ ለመረዳት ያልተሳነው ፒርስ ደብተራው የተጠቀመውን ዘዴ ለአከባቢው ባለሥልጣን ራሱ ሞክሮ አሳይቶታል፡፡ ይሁን እንጂ ይህን የተማረ ደብተራ ማጋለጥና ታሪኩንም ማውጣት ትልቅ ብልግና ነው ተብሎ ይታመናል፡፡››

እንግዲህ አያቶቻችን ‹‹አዋቂ ነን›› የሚሉ ሰዎችን ያልጠየቁትን ጥያቄ እኛ የልጅ ልጆቻቸው መጠየቅ መቻል አለብን፡፡ እንደ አብዬ መንግስቱ፣ ‹‹መርፌ ትሰራለህ?›› እያልን፡፡

‹‹መርፌ ትሰራለህ...

ስለሆነ ብቻ!ባለፈው ዘመን ኖረው

ያለፉት ሰዎች የሥልጣኔያቸው መሠረት ጭቃ ቢሆን ኖሮ፣ በዚህ ዘመን ላይ ኗሪ የሆነው ሕዝብ የጭቃ ታሪክ ስለሌለህ አልሰለጠንክም ይባል ነበር ማለት ነው? ድንጋይ አንከባሎና ጠርቦ መሰልጠን እንደሚቻል ሁሉ ድንጋይ በጠላት ላይ ወርውሮ ታሪክ መስራትም ይቻላል፡፡ ለመሆኑ ታሪክ የሚባለው ሐውልት ቀርጾ ማቆም ብቻ ነው እንዴ?

ሕዝቦች በወረርሽኝ አልቀው ስጋዎች ሁሉ ቢሞቱ እንኳን፣ መንፈስ ግን ከማይረሳቸው የታሪክ ሰዎች መካከል አንዱን ላንሳ - ያውም ከሚረገመውና በህይወት ካለው ትውልድ!

በአንድ ወቅት ኃይሌ ከፖልቴርጋት ጋር ያደረገውን “ታሪካዊ” የሩጫ ትንቅንቅ ብዙ ኢትዮጵያዊያን ተመልክተውታል፡፡ በዚያ የምጥ ቀን በመሰለው ደቂቃ ቆሞ ሲያጨበጭብ የነበረው ኢትዮጵያዊ ሁሉ እንጀራ በልቶ የጠገበ አልነበረም፡፡ ቁርስና ምሳውን መብላት ያልቻለው ኢትዮጵያዊ ጭምር ሆዱ በረሀብ እየነደደ ሩጨውን በስሜት ተነክሮ ሲያይ እንደነበር ታሪክ ምን ማለት እንደሆነ የሚያውቁ ሰዎች ያስታውሱታል፡፡

ያ ሥልጣኔ የተከተለ ታሪካዊ ሩጫ ረሃብ የማስረሳት ኃይል ነበረው፡፡ ምናልባትም እኮ ኃይሌ ሩጫውን ትቶ ድንጋይ ማንከባለል ቢጀምር የማንንም ቀልብ መስረቅ አይቻልም ነበር፡፡ ሰዎች ባልተመሩበት ሜዳ ላይ የሚሰማሩ ከሆነ ምርትም ሆነ ምርጥ ውጤት መሰብሰብ አይችሉም፡፡ ሮጦ በማምለጥም፣

ቆሞ በመጋፈጥም ታሪክ መስራት ይቻላል፡፡ ታሪክ ሲባል ግድ ከድንጋይና ከዓለት ጋር “ብቻ” መጣመር የለበትም፡፡

የቀደሙት አባቶቻችሁ ያቆሙትን ሐውልት ሮማውያኖቹ የወሰዱት ሀገራቸው ታሪክ ስለሌላት አልነበረም፡፡ ለጥቁር ሕዝብ ይኼን የመሰለ ብርቅዬ የድንጋይ ሥራ አይገባውም፤ የጥቁሮች ታሪክ ጥቁርነታቸው ብቻ ነው ብለው አስበውም ይሆናል ሐውልቱን ነቅለው የወሰዱት፡፡

ያ ትውልድ የሚማርክ ታሪክ ስለፈጠረ ተወሰደበት፡፡ ይኼም ትውልድ እየተወሰደበት ነው እኮ! ኃይሌ ስንት ጊዜ ነው ወደ ሮም የተወሰደው? ሮሞች ዛሬም በታሪካችን እንደሚማረኩ ግልፅ ማስረጃ እኮ ነው፡፡ ይህ ዘመን የዲፕሎማሲያዊ በመሆኑ የዚህ ትውልድ ተንቀሳቃሽ ታሪኮች እንደ ሐውልቱ በግድ አይደለም ወደ ሮም የሚወሰዱት፡፡ ሐውልቱ በጠብ መንጃ ወደ ሮም ሲገባ፣ ዛሬ ደግሞ የታሪክ ሰዎቻችን ከአውሮፕላን ሲወርዱ ቀይ ምንጣፍ ተነጥፎላቸው ነው ወደ ሮም የሚገቡት፡፡

ይህን ትውልድ “ሙሉ ለሙሉ” እንድታመሰግኑት ግፊት የሚያደረግባችሁ መድፍ ወይም ላውንቸር ከኋላችሁ ሊገተር አይገባም፡፡ በርግጥም ይህ ትውልድ ጎልተው የሚታዩ ጥፋቶችን እያጠፋም ሊሆን ይችላል፡፡ ግን ደግሞ በሙሉ መንፈሳችሁና ልባችሁ አትዝለፉት! የሰራውን በጎ ሥራ ስታውጁለት ደስ ብሎት ለመልካም ሥራ ይነሳሳል! “ኢትዮጵያዊነትና ታሪክ ሰሪነት ይደበዝዛል እንጂ ሙሉ ለሙሉ አይለቅም!”

}SdeK¨< Ÿ}c\ ð×” ¾h¨` ¨<H TVmÁ U`„‹ ÃÖ”kl ƒ¡¡K—¨<” ¾w^²=M

¾h¨` ¨<H TVmÁ ÃÖkS<

Brazmart International General Trading Plc. Address!- •Urail Alem Brehan Plaza 1st Floor #106 1. ›<^›?M u?} ¡`e+Á” ›”vu= ¯KU w`H” ýL³ 1— öp u=a lØ` 1062. Ku< ›Åvvà òƒ Kòƒ dS<›?M I”íuT”—¨<U ¾vD”vD“ ¾h¨` u?ƒ n ‹ SgÝ“ ”Ç=G<U u¾I”í SX]Á SÅwa‹ ÁÑ–< M::

c=Ѳ< ƒ¡¡K— ¾w^²=M U`ƒ SJ’<” Á[ÒÓÖ<! Tel. 251-11 552 -6011 /12 Fax 251-11-5526012

ትውልዱን...ልዩነት እንደተጠበቀ ሆኖ) ጥሩና ብሩህ አዕምሮም አላቸው፡፡ አገርን ለመምራት አያንሱም፡፡ ነገር ግን 20 ዓመት በጣም በዝቶባቸዋል፡፡ የዓለማችን ጂኒየስ አልበርት አንስታይን ራሱ ዛሬ በህይወት ቢኖር አንድን አገር ለ20 አመት በብቃት መምራት አይችልም፡፡ ዘመኑ ራሱ ውስብስብ ሆኗል፡፡ በዚህ ውስብስብ በሆነ ዘመን፣ ውስብስብ የሆነ ችግር ላለባት አገር 20 ዓመት ውስጥ ዳይናሚዝምና ኢነርጂን ጠብቆ መምራት አይቻልም፡፡ ከአንድ ሰው ብቃት ከሰውነት ብቃታችን ባሻገር አንድ ሰው ሊወጣው አይችልም፡፡ ስለዚህ አቶ መለስ የዛሬ 20 ዓመት የነበራቸው ዳይናሚዝም ዛሬ ስለሌላቸው፣ የዛሬ 20 ዓመት የነበራቸው የስራ ልኬትና ፍላጐት ስለሌላቸው ከዚህ አኳያ ሲታይ ስልጣን መልቀቅ አለባቸው ብዬ አምናለሁ፡፡ ግን አሁንም መሰረታዊ ምክንያቱ ይሄ አይደለም፡፡

ታዲያ መሰረታዊ ምክንያቱ ምንድነው

መሰረታዊው ምክንያት ምን መሰለህ፤ እኔ አቶ መለስ ዴሞክራት አይደሉም ብዬ ስለማምንና ኢትዮጵያ ውስጥ ዲሞክራሲያዊ ሽግግር እንዲኖር ደግሞ እሳቸው ከፖለቲካው ዓለም መልቀቃቸው አስፈላጊ ነው ብዬ ስለምገነዘብ ነው፡፡ እኔ ኢህአዴግ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ሊሆን ይችላል ብዬ አምናለሁ፡፡ ያ ግን ሊሆን የሚችለው ኢ-ዴሞክራሲያዊ የሆኑ አመራሮቹ ከወረዱለት ብቻ ነው፡፡ እኔ በግሌ ሁሉም የኢህአዴግ አምስት ሚሊዮን አባላት የዴሞክራሲ

ጠላት ናቸው ብዬ አላምንም፡፡ ከኢህአዴግ ውስጥ ጥቂት ሰዎች ናቸው በዴሞክራሲ የማያምኑት፡፡ ኢትዮጵያ ለዴሞክራሲ ገና ነች ብለው ከልባቸው አምነው ወደ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንዳትገባ ዕንቅፋት ሆነው የተቀመጡ የኢህአዴግ አመራሮች አሉ ብዬ አምናለሁ፡፡ የእነዛ ሰዎች ተምሳሌትና አውራ ደግሞ አቶ መለስ ናቸው ብዬ አምናለሁ፡፡ ስለዚህ ለዲሞክራሲያዊ ስርዓት ሽግግር የእሳቸው ከፓርቲና ከመንግስት ስልጣን መልቀቅ በጣም አስፈላጊ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ ከስልጣን እንዲነሱ በደብዳቤዬ የጠየኩት ለዚህ ነው፡፡ የአቶ መለስ መሰናበት ኢህአዴግን ዴሞክራሲያዊ የፖለቲካ ድርጅት ያደርገዋል የሚለው አመለካከትህ ብዙ ሰው የሚጋራው ይመስለሀል?

ቱኒዚያ ውስጥ ገዥው ፓርቲ እኮ ዛሬ በነፃነት እየተንቀሳቀሰ ነው፡፡ ማንም አልመጣበትም፡፡ የቤን አሊ መሄድ ብቻ ነው ለዴሞክራሲያዊ ሽግግር ምክንያት የሆነው፡፡ በግብፅም ኤም.ዲ.ፒ በሚቀጥለው ምርጫ ለመወዳደር እየተዘጋጀ ነው፡፡ ደግሞም ማንም አይከለክለውም፡፡ እንዲያውም ብዙ መቀመጫዎች ያሸንፋል እየተባለ ነው፡፡ ምርጫውን አያሸንፍ እንጂ መቀመጫውን እንደሚያሸንፍ እኔም አልጠራጠርም፡፡ ነገር ግን ኤም.ዲ.ፒ እንደ አንድ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ በፖለቲካ ስርዓቱ ውስጥ ለመሳተፍ የሙባረክን ከስልጣን መውረድ እንደ ቅድመ ሁኔታ አስፈልጓል፡፡ በተመሳሳይ መንገድ ግን ኢህአዴግ

ውስጥ እያላችሁ ነው፡፡ እንደ ልጅ አባት እንደ ቤተሰብ ኃላፊ ከዚህ ማስጠንቀቂያ በኋላ አሁንም መጻፍህን ቀጥለሀልና ውሳኔው ከባድ አይደለም ትላለህ?

ውሳኔው ብቻዬን ሆኜ የወሰንኩት አይደለም፡፡ ባለቤቴ አለች፡፡ ከባለቤቴ ጋር የወለድነውና የምናሳድገው ልጅ አለ፡፡ ግን የግድ መሆን ካለበት ምን ይደረግ እንግዲህ መከፈል ያለበት መስዋዕትነት መክፈል ነው፡፡ ምንም ይሁን ምን ከባድ መስዋዕትነት ቢያስከፍልም መጻፌን ቀጥያለሁ፡፡ ልጄን በጣም ነው የምወደው ባየሁት ቁጥር በጣም ነው የምንሰፈሰፈው፡፡ ባለቤቴንም በጣም አከብራታለሁ፡፡ እወድዳታለሁ፡፡ ስለዚህ ያው ቀላል አይደለም፡፡ በአንድ በኩል በዜግነት ያለብኝን ኃላፊነት እወጣለሁ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ከቤተሰቤ ጋር የወሰንኩት ነው፡፡ ባለቤቴም ታምንበታለች የእሷ ጠንካራ ድጋፍ አለኝ፡፡ ስለዚህ በፅሁፎቼ እንደቀጠልኩ ነው፡፡

አዎ ከዛ በኋላም ቀጥለሃል፡፡ እንዲያውም በቅርቡ አንድ አነጋጋሪ ደብዳቤ ለጠ/ሚ/ር መለስ ጽፈሀል፡፡ ደብዳቤህ አቶ መለስ ስልጣን እንዲለቁ የሚጠይቅ ነው፡፡ አዎንታዊ ምላሽ አገኛለሁ ብለህ ነው ያንን ደብዳቤ የጻፍከው፤ምክንያትህስ ምንድነው? ስልጣን እንዲለቅቁ በደብዳቤ የጠየኩበት ምክንያት አንደኛ በአሁኑ ዘመን አንድ የአገር መሪ 20 ዓመት በስልጣን ላይ መቆየት የለበትም፡፡ አቶ መለስ ትልቅ ስም አላቸው፡፡ ይሄንን አልከራከርም፡፡ (በመካከላችን ያለው የፖለቲካ

አንደ አንድ ዴሞክራሲያዊ፣ የፖለቱካ ድርጅት በሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ አረማመድ፤ የቀጣዩን ትውልድ የፖለቲካ ስርዓት አካል ለመሆን አቶ መለስን ሊያሰንብት ይገባል ብዬ ከልቤ አምናለሁ፡፡ አቶ መለስና ሌሎች አመራሮች ‹‹በዴሞክራሲ የማያምኑ›› ብለሀቸዋል እዚህ ድምዳሜ ላይ ለመድረስ መሰረታዊ ምክንያት አለህ? አቶ መለስ በፍልስፍናና አበይዲዮሎጂ ደረጃ ሊብራል ዲሞክራሲ ለኢትዮጵያ አይጠቅማትም ብለው ያምናሉ፡፡ ተሳስተዋል፡፡ መሰረታዊው መነሻ እሱ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በዓለም ላይ ያለው ብቸኛው መንገድ ሊበራል ዴሞክራሲ ነው፡፡ ዛሬ ለሰው ልጅ የሚጠቅመው ብቸኛው መንገድ እሱ ነው፡፡ ይሄንን ነው እንግዲህ አቶ መለስ የማይቀበሉት፡፡ ይሄንን ስለማይቀበሉ ነው ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ በደንብ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ዕውን ሊሆን ያልቻለው፡፡ ይሄንን በግላቸው ሊያምኑ ይችላሉ፡፡ አትመኑ ማንም አይላቸውም፡፡ ማለትም አይቻልም፡፡ ብዙዎቻችን (ብዙሃኑ ኢትዮጵያዊያን) ግን በዚህች አገር የሚበጀው ስርዓት ሊበራል ዴሞክራሲ ነው ብለን እናምናለን፡፡ ነፃና ፍትሃዊ የሆነ የምርጫ ስርዓትን ዕውን ማድረግ የሚቻለውም በዚህ መንገድ ነው፡፡ አቶ መለስ ብቻ አይደሉም በነገራችን ላይ እንደዚያ የሚያስቡት፡፡ ሌሎችም አሉ በኢህአዴግም ውስጥ ከኢህአዴግም ውጪ፡፡ ቁጥራቸው ግን በጣም አናሣ ነው፡፡ ብዙሃኑ ሊበራል ዴሞክራሲን እንደሚፈልግ ጥርጥር የለውም፡፡

በአሁኑ ዘመን አንድ የአገር መሪ...

Page 24: awramba 160

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 160 ቅዳሜ መጋቢት 17 200324 ማስታወቂያ