16
Zethiopia, Ethiopian American Community News NO.86 Sep 2014 202 518 0245 P.o.box 2049, Fairfax, VA 22031 www.zethiopia com 202 518 0245 P.o.box 2049, Fairfax, VA 22031 www.zethiopia com [email protected] ዘኢ ዮጵያ መልካም አዲስ ዓመት ይሁንልን! We feature traditional Ethiopian foods Yes we CATER! ኬተር እናደርጋለን 213.992.4334 Call To Listen Call To Listen Calls use mobile minutes. Free with unlimited plans Ethiopian Satellite Television ሰባ ደረጃ የሚል አዲስ ነጠላ ዜማ ያወጣው ቴዲ አፍሮ የሙዚቃ ትርኢቶቹን ሰሞኑን በአሜሪካ ተዘዋውሮ በማሳየት ላይ ይገኛል። በመድረክ የነገሥታቱን የዳግማዊ ምኒልክን የእቴጌ ጣይቱንና የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን ፎቶግራፎችና ፣ ታሪካዊ ሁነቶችን የፎቶግራፍ ፊልም እያስነሳ የመድረኩን ጀርባ አልብሷቸው ታይቷል። በተለየ አቀራረቡና በተለመደው ሙዚቃው አድናቂዎቹን ሲያስዘልል ከርሟል። ከዚህ በፊት በገጠሙት አንዳንድ ችግሮች ሳቢያ ለእነዚህኞቹ በሚገባ የተዘጋጀበት ይመስላል። ቀደም ሲል አንድ አምስት ቦታዎች የሠረዛቸው ዝግጅቶች የነበሩት ሲሆን በዚህኛው እንደገና ተጠናክሮ ሊሄድባቸው መነሳቱም ተሰምቷል። ለተጨማሪ አስተያየት ገጽ 15 ይመልከቱ። የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ አንጋፋ ታጋይ፣ የቀድሞ የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንትና የድርጅቱ ሥራ አስፈጻሚ የነበሩት አቶ ገብሩ አስራት ድርጅታቸውን በተለያዩ የሥራ ኃላፊነት አገልግለዋል። ህወሓት ለሁለት ከተከፈለና ድርጅታቸውን ለቀው ከወጡ በኋላም የዓረና ትግራይ ለዴሞክራሲና ሉዓላዊነት መስራችና ሊቀመንበር እንዲሁም የአንድነት ግንባር ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ሠርተዋል። የ63 ዓመቱ አቶ ገብሩ ያለፉበትን የትግል ህይወት መስመርና ድርጅት እንዲሁም የኢትዮጵያ ፖለቲካ ታሪክ ወቅታዊ ሁኔታ የገመገመ አንድ ተነባቢ መጽሐፍ ይዘው መጥተዋል። ዘኢትዮጵያ ቃኝቶታል ገጽ 2 ላይ አለ! "ይህንን ትምህርት ሳየው የኛ አባቶች ፍልስፍና በጣም ረቆ ይታየኛል። ይበልጥ ከእግዚአብሔር ጋር የተገናኘ ሆኖ ምጡቅ ነው።" መምህር ዶ/ር ዘበነ ለማ ባለፈው የዘኢትዮጵያ ጋዜጣ እትማችን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ምእመናን ዘንድ በሚሰጡት መንፈሳዊ የትምህርት አገልግሎት ታዋቂ የሆኑት መምህር ዘበነ ለማ ከሐዋርድ ዩኒቨርስቲ በልዩ ማዕረግ በዶክትሬት መመረቅን አስመልክቶ መዘገባችንና በትምህርት፣በአገልግሎትና በህይወት ታሪካቸው ዙሪያ ያደረግነውን ቃለ መጠይቅ ይዘን እንደምንቀርብ ገልጸን ነበር። ለሚሰጡት መንፈሳዊ የወንጌበገጽ 9 ይገኛል Dr. Catherine Hamlin, co-founder of Hamlin Fistula Ethiopia turned 90 years young earlier this year. She has been nominated for the 2014 Nobel Peace Prize by Dr. Tedros Adhanom, foreign minister of Ethiopia for her lifetime of devotion and service to the women of Ethiopia inflicted with obstetric fistula, a devastating child birth injury. ባለፈው ቅዳሜ ስምፔምበር 6/2014 በጀርመን ፍራንክፈት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን አርቲስት ዓለም ፀሐይ ወዳጆን በመሸለም አከበሯት። የኢትዮጵያ ናሽናል አርት ካውንስል (The Ethiopian National Arts Council - ENAC) በመባል የሚታወቀውና በጀመርን የሚገኘው ድርጅት በሚያደርገው ዓመታዊ ዝግጅቱ አርቲስት ዓለም ፀሐይ ወዳጆን የዓመቱ ተሸላሚ አድርጓል። ፎቶ ግራፉ ላይ ከዓለም ፀሐይ ጋር የሚታዩት የልዑል አስራተ ካሳ ልጅ ልዑል ዶ/ር አስፋው ወሰን አስራተ፣ ናቸው። ዘገባውን በገጽ 3 ይመልከቱ ቴዎድሮስ ጸጋዬ የአዲስ አበባ ከተማ የሬዲዮ ፕሮግራሞች አፍቃሪ በሳምንት ሁለት ጊዜ በድምሩ ለ 5 ሰዓታት ያህል ከቴዎድሮስ ጸጋዬ ጋር አብሮት ይቆያል። ርዕስና ጉዳይ የማያልቅበት ጋዜጠኛና ገጣሚ ቴዎድሮስ ጸጋዬ በሁለገብ ዝግጅቱ የታወቀ ነው። ገጽ 6 Ten years ago in 2004, a small IT company was formed by two ambitious Ethiopian-American entrepreneurs amid a lot of uncertainties and challenges. Today Bilen Corp is a growing information and technology firm which boasts clients such as State and Federal governments, IMF, world bank and large non-profit organizations. In an exclusive interview with Zethiopia, on June 19, 2014 during their company’s 10-year anniversary celebration, the two founders discussed their challenges, achievements, vision and philosophy. Page 11 Ephrem and Mike በቅዳሜ ስፕቴምበር 13 ልዩ ዝግጁቱ የዋሽንግተን ዲሲ ሚየር ግሬይንና የቀድሞ የኢትዮጵያውያን ወዳጅ ካውንስል ማን ጂም ግራምን ጨምሮ በርካታ እንግዶች ተካፋይ ናቸው። አርቲስት ይሁኔ በላይና የተለያዩ የባህላዊ ሙዚቃ ቡድን አባላትም ተካተውበታል። በሚቀጥለው እትም ዘገባውን ይዘን እንቀርባለን። እስከዚያው የኮሙዪኒቲያችንና የዘኢትዮጵያ ጋዜጣ የረጅም ጊዜ አጋር ለሆኑት ለኢትዮጵያ የሎው ፔጅ ቤተሰቦች ለቱቱ ለይሁኔ ለሰላምና ፍቅር እንኳን ለ20ኛው ዓመት አደረሳችሁ እንላለን። መልካም አዲስ ዓመት ዘኢትዮጵያ! ሉዓላዊነትና ዴሞክራሲ በኢትዮጵያ Page 11 photo Joni Kabana አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ

መልካም አዲስ ዓመት ይሁንልን! · ዘኢትዮጵያ ጋዜጣ Zethiopia Ethiopian American Community News NO.86 Sept 2014 202 518 0245 P.o.box 2049, Fairfax, VA

  • Upload
    others

  • View
    13

  • Download
    0

Embed Size (px)

Citation preview

Page 1: መልካም አዲስ ዓመት ይሁንልን! · ዘኢትዮጵያ ጋዜጣ Zethiopia Ethiopian American Community News NO.86 Sept 2014 202 518 0245 P.o.box 2049, Fairfax, VA

Zethiopia, Ethiopian American Community News NO.86 Sep 2014 202 518 0245 P.o.box 2049, Fairfax, VA 22031 www.zethiopia com

202 518 0245 P.o.box 2049,

Fairfax, VA 22031 www.zethiopia com

[email protected]

ዘኢትዮጵያ

መልካም አዲስ ዓመት ይሁንልን!

We feature traditional Ethiopian foods

Yes we CATER!

ኬተር እናደርጋለን

213.992.4334Call To ListenCall To Listen

Calls use mobile minutes.Free with unlimited plans

Ethiopian Satellite Television

ሰባ ደረጃ የሚል አዲስ ነጠላ ዜማ ያወጣው ቴዲ አፍሮ የሙዚቃ ትርኢቶቹን ሰሞኑን በአሜሪካ ተዘዋውሮ በማሳየት ላይ ይገኛል። በመድረክ የነገሥታቱን የዳግማዊ ምኒልክን የእቴጌ ጣይቱንና የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን ፎቶግራፎችና ፣ ታሪካዊ ሁነቶችን የፎቶግራፍ ፊልም እያስነሳ የመድረኩን ጀርባ አልብሷቸው ታይቷል። በተለየ አቀራረቡና በተለመደው ሙዚቃው አድናቂዎቹን ሲያስዘልል ከርሟል። ከዚህ በፊት በገጠሙት አንዳንድ ችግሮች ሳቢያ ለእነዚህኞቹ በሚገባ የተዘጋጀበት ይመስላል። ቀደም ሲል አንድ አምስት ቦታዎች የሠረዛቸው ዝግጅቶች የነበሩት ሲሆን በዚህኛው እንደገና ተጠናክሮ ሊሄድባቸው መነሳቱም ተሰምቷል። ለተጨማሪ አስተያየት ገጽ 15 ይመልከቱ።

የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ አንጋፋ ታጋይ፣ የቀድሞ የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንትና የድርጅቱ ሥራ አስፈጻሚ የነበሩት አቶ ገብሩ አስራት ድርጅታቸውን በተለያዩ የሥራ ኃላፊነት አገልግለዋል። ህወሓት ለሁለት ከተከፈለና ድርጅታቸውን ለቀው ከወጡ በኋላም የዓረና ትግራይ ለዴሞክራሲና ሉዓላዊነት መስራችና ሊቀመንበር እንዲሁም የአንድነት ግንባር ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ሠርተዋል። የ63 ዓመቱ አቶ ገብሩ ያለፉበትን የትግል ህይወት መስመርና ድርጅት እንዲሁም የኢትዮጵያ ፖለቲካ ታሪክ ወቅታዊ ሁኔታ የገመገመ አንድ ተነባቢ መጽሐፍ ይዘው መጥተዋል። ዘኢትዮጵያ ቃኝቶታል ገጽ 2 ላይ አለ!

"ይህንን ትምህርት ሳየው የኛ አባቶች ፍልስፍና በጣም ረቆ ይታየኛል። ይበልጥ ከእግዚአብሔር ጋር የተገናኘ ሆኖ ምጡቅ ነው።"

መምህር ዶ/ር ዘበነ ለማ

ባለፈው የዘኢትዮጵያ ጋዜጣ እትማችን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ምእመናን ዘንድ

በሚሰጡት መንፈሳዊ የትምህርት አገልግሎት ታዋቂ የሆኑት መምህር

ዘበነ ለማ

ከሐዋርድ ዩኒቨርስቲ በልዩ ማዕረግ በዶክትሬት መመረቅን አስመልክቶ

መዘገባችንና

በትምህርት፣በአገልግሎትና በህይወት ታሪካቸው ዙሪያ ያደረግነውን ቃለ

መጠይቅ ይዘን እንደምንቀርብ ገልጸን ነበር። ለሚሰጡት መንፈሳዊ

የወንጌበገጽ 9 ይገኛል

Dr. Catherine Hamlin, co-founder of Hamlin Fistula Ethiopia turned 90 years young earlier this year. She has been nominated for the 2014 Nobel Peace Prize by Dr. Tedros Adhanom, foreign minister of Ethiopia for her lifetime of devotion and service to the women of Ethiopia inflicted with obstetric fistula, a devastating child birth injury.

ባለፈው ቅዳሜ ስምፔምበር 6/2014 በጀርመን ፍራንክፈት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን አርቲስት ዓለም ፀሐይ ወዳጆን በመሸለም አከበሯት። የኢትዮጵያ ናሽናል አርት ካውንስል (The Ethiopian National Arts Council - ENAC) በመባል የሚታወቀውና በጀመርን የሚገኘው ድርጅት በሚያደርገው ዓመታዊ ዝግጅቱ አርቲስት ዓለም ፀሐይ ወዳጆን የዓመቱ ተሸላሚ አድርጓል። ፎቶ ግራፉ ላይ ከዓለም ፀሐይ ጋር የሚታዩት የልዑል አስራተ ካሳ ልጅ ልዑል ዶ/ር አስፋው ወሰን አስራተ፣ ናቸው። ዘገባውን በገጽ 3 ይመልከቱ

ቴዎድሮስ ጸጋዬየአዲስ አበባ ከተማ የሬዲዮ ፕሮግራሞች አፍቃሪ በሳምንት ሁለት ጊዜ በድምሩ ለ 5 ሰዓታት ያህል ከቴዎድሮስ ጸጋዬ ጋር አብሮት ይቆያል። ርዕስና ጉዳይ የማያልቅበት ጋዜጠኛና ገጣሚ ቴዎድሮስ ጸጋዬ በሁለገብ ዝግጅቱ የታወቀ

ነው። ገጽ 6

Ten years ago in 2004, a small IT company was formed by two ambitious Ethiopian-American entrepreneurs amid a lot of uncertainties and

challenges. Today Bilen Corp is a growing information and technology firm which boasts clients such as State and Federal governments, IMF, world bank

and large non-profit organizations. In an exclusive interview with Zethiopia, on June 19, 2014 during their company’s 10-year anniversary celebration,

the two founders discussed their challenges, achievements, vision and philosophy. Page 11

Ephrem and Mike

በቅዳሜ ስፕቴምበር 13 ልዩ ዝግጁቱ የዋሽንግተን ዲሲ ሚየር ግሬይንና የቀድሞ የኢትዮጵያውያን ወዳጅ ካውንስል ማን ጂም ግራምን ጨምሮ በርካታ እንግዶች ተካፋይ ናቸው። አርቲስት ይሁኔ በላይና የተለያዩ የባህላዊ ሙዚቃ ቡድን አባላትም ተካተውበታል። በሚቀጥለው እትም ዘገባውን ይዘን እንቀርባለን። እስከዚያው የኮሙዪኒቲያችንና የዘኢትዮጵያ ጋዜጣ የረጅም ጊዜ አጋር ለሆኑት ለኢትዮጵያ የሎው ፔጅ ቤተሰቦች ለቱቱ ለይሁኔ ለሰላምና ፍቅር እንኳን ለ20ኛው ዓመት አደረሳችሁ እንላለን። መልካም አዲስ ዓመት ዘኢትዮጵያ!

ሉዓላዊነትና ዴሞክራሲ በኢትዮጵያ

Page 11

photo Joni Kabana

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ

Page 2: መልካም አዲስ ዓመት ይሁንልን! · ዘኢትዮጵያ ጋዜጣ Zethiopia Ethiopian American Community News NO.86 Sept 2014 202 518 0245 P.o.box 2049, Fairfax, VA

ዘኢትዮጵያ ጋዜጣ Zethiopia Ethiopian American Community News NO.86 Sept 2014 202 518 0245 P.o.box 2049, Fairfax, VA 22031 www.zethiopia com 2

የፖለቲካ ፓርቲ ተጀመረ!

እንደ አቶ ገብሩ መጽሐፍ - ከ1930ዎቹ ቀደም ብሎ በኤርትራና በደቡብ ምስራቅ ኢትዮጵያ ትጥቅ አንግበው ከሥርዓት ጋር መፋለም የጀመሩ ግንባሮች ነበር። እነዚህ ከማዕከሉ ርቀው ይንቀሳቀሱ የነበሩ ቢሆንም ወደኋላው ላይ በአዲስ አበባ ጭምር እየተጧጧፉ ለመጡት አገር አቀፍና ብሔር ተኮር ድርጅቶች እንዲሁም የተማሪ ቤት የፖለቲካ እንቅስቃሴዎች ምክንያት ሆነዋል። በመሆኑም ከኤርትራና ከሶማልያ ድርጅቶች ቀጥሎ በ1960 በጀርመን ሃምቡርግ ከተማ በእነ ኃይሌ ፊዳ የተመሠረተው “የመላው ኢትዮጵያ ሶሻሊስት ንቅናቄ” /መኢሶን/ አንጋፋው ፓርቲ ነው። ይሁን እንጂ አቶ ገብሩ ይህን ያገኙት ተስፋዬ መኮንን በ1985 ይድረስ ለባለ ታሪኩ በሚል ርዕስ ካሳተሙት መጽሐፍ ገጽ 119 ላይ መሆኑን ጠቅሰው “አንዳንዶች መኢሶን በ1960 መመስረቱን እንደሚጠራጠሩ” ገልጸዋል። ለታሪክ በተውት መጽሐፋቸው የዘገቡት ግን “መረጃው ትክክል ነው ብለን ከተቀበልነው” (ገጽ35) በሚል ጥርጣሬ ነው። የ66 አብዮቱ ከመፈንዳቱ 10 ዓመት በፊት መሆኑ ነው።

በ1964 በጀርመን በርሊን በእነ አቶ ብረሃነ መስቀል ረዳ፣ ኢያሱ ዓለማየሁ ዘርኡ ክሸን ተስፋይ ደበሳይ የተቋቋመው የኢትዮጵያ ሕዝቦች አርነት ድርጅት / ኢሕአድ/ ኋላም አገር ቤት ከነበሩት እንደ አብዮት የመሳሰሉ ቅድመ ፓርቲ ድርጅቶች ጋር አብሮ ሲሰራ ቆይቶ መዋሃዱንና የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ/ ኢሕአፓ ተብሎ መሰየሙን ተመሳሳይ ምንጭ ጠቅሰው ጽፈዋል። ከእነዚህ የህብረ ብሔር ከሆኑት የመኢሶንና የኢሕአፓ ፓርቲዎች ቀጥሎ ምናልባትም ቀደም ብለው ሌሎች የብሔር ድርጅቶች እየተቋቋሙ መምጣታቸውን ጽፈዋል። ቀደም ሲል በሜጫና ቱለማ የመረዳጃ እድር እንቅስቃሴ ሲያደርግ የቆየው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር /ኦነግ/ በ1966 በይፋ መቋቋሙን ዘግበዋል።

ከእነዚህ ሁሉ የቀደመውና እንደ ሌሎቹ በኤርትራ ተጠልሎ ይንቀሳቀስ የነበረው የብሔር ድርጅት በ1962 በትግራይ ተወላጆች የተቋቋመውና በመምህር ዮሐንስ ተክለ ኃይማኖት “ማህበር ፖለቲካ” ተብሎ የሚጠራው ነው። የትጥቅ ትግል በማንሳት ከኤርትራ ድርጅቶች ቀጥሎ በሰሜን ኢትዮያ የተቋቋመው ግምባር ገድሊ ሓርነት ትግራይ /ግገሓት/ የትግራይ ትግሪኝ ወይም ኤር-ትግራይ በሚል ኤርትራና ትግራይን አቀናጅቶ አንድ አገር ለመፍጠር የተነሳ መሆኑ በመጽሐፉ ተጽፏል። ለማንኛውም እነዚህኞቹን ጀብሃ ኢሕአደንን ደግሞ ሻዕቢያ እየደገፉት ለትጥቅ ትግል ዝጅግት ሲያደርጉ እስከ 1967 በኤርትራ ቆይተዋል። የትጥቅ ትግል ለማድረግ በኤርትራ እየተደገፉ ከተቋቋሙ የትግራይ ብሔር ድርጅቶች መካከል

ሌላኛው መጀመሪያ ማህበረ ገስገስቲ ብሔረ ትግራይ ቀጥሎም ተጋድሎ ሓርነት ህዝቢ ትግራይ /ተሓህት/ እያደርም ህወሓት ሆኖ የወጣው ድርጅት መሆኑን ከገብሩ መጽሐፍ መረዳት ይቻላል። የትግራይ ተማሪዎች ገና ዩኒቨስቲ መግባት ሳይደርሱ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እያሉ ይቀሰቀሱ እንደነበር ገብሩ የራሳቸውን ታሪክ እያመሳከሩ እንዲህ ጽፈዋል፟-

“ገና ዘጠነኛ ክፍል እያለሁ አንዳንድ ከቀዳማዊ ኃለሥላሴ ዩኒቨርስቲ የመጡ ስለአገሪቱ ፖለቲካ ችግሮች እያነሱ ይቀሰቅሱ ነበር..በ1960ዎቹ መጀመሪያ የክልሉ ተወላጆች የሆኑ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ክረምት ለዕረፍት እየመጡ ፖለቲካዊ ቅስቀሳዎችን ያካሂዱ ነበር።” (ገጽ 40) “የትግራይ ተወላጅ የሆኑት የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ለእረፍት ሲመጡ የክረምት አካዴሚያዊ ትምህርት እንሰጣለን በሚል ሽፋን የፖለቲካ ትምህርት መስጠት ጀምረው ነበር። እነዚህ አስተማሪዎች የሚሰጡን ትምህርት አብዛኛውን ጊዜ የቀዳማይ ወያኔ እንቅስቃሴን በተመለከተ ሰፊ ማብራሪያ ይሰጡን ነበር” (ገጽ 41” ብለዋል። የትግራይ ብሔርተኞች የተለያየ ስያሜና የፖለቲካ አስተሳሰብ ቢኖራቸውም ዞሮ መግቢያ መደምደሚያቸው ያቺው ትግራይነታቸው መሆኑን ለማስተዋል የአቶ ገብሩ መጽሐፍ ጥሩ የማመሳከሪያ ሰነድ ነው። ከትግራይም ደግሞ እንዲሁ ወደ ጎጥ እየወረዱ ይሄዳሉ። እነሆ የገብሩ ቃል!

“በትግራይ የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች ተሓትን ጨምሮ እጅግ ወግ አጥባቂ ባህል የተጠናወታቸው ነበሩ። የድርጅቶቹ አመራሮቹም ቢሆኑ ከዚህ የጸዱ አልነበሩም። እንዲያውም አንዳንዶቹ ሥር የሰደደ ኋላ ቀርነትና ጎጠኝነት የተጠናወታቸው ነበሩ።(ገጽ 82)

ከፍ ሲል ያየነውና አቶ ገብሩ በመጽሀፋቸው በአንጋፋነታቸው ከጠቀሷቸው ህብረ ብሄር የፖለቲካ ድርጅቶች መኢሶን አንዱ ነበር። የዚሁ ድርጅት አመራር የነበሩት ዶ/ር ነገደ ጎበዜ ሰሞኑን “ይድረስ ከየካቲት ለግንቦት” ብለው በወቅቱ ይዋደቁ የነበሩት የኢትዮጵያ ተማሪዎች ዓላማና አደረጃጀት ምን እንደነበር ባወሱበት በዚህ መጽሐፋቸው እንዲህ ብለዋል “ በዛሬው ግርግርና የብሄር /ብሄረሰብ ድርጅቶች ማየል የተነሳ ብዙ ሰው ልብ የማይለው ቁም ነገርና እኛ መኢሶኖች የቀሰምነው ትምህርት አለ፡፡ መሬት ለአራሹ ብለን ያኔ ስንዋደቅ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝቦች ደህንነት በአንድ ላይ ታግለን ነው፡፡ የደርግ መንግስት የመኢሶን መሪዎች በማለት በአንድ ቀን አምስት ታጋዮችንን ማለትም፤ ሀይሌ ፊዳን፤ ዶክተር ንግስት አዳነን፤ ቆንጂት ከበደን፤ ደስታ ታደሰንና ሃይሉ ገርባባን ወስዶ ሲረሽን እነዚህ መሪዎቻችን ከኦሮሞ፤ ከትግራይ፤ ከአማራና ከጉራጌ ብሄሮች የተውጣጡ ዜጎች ነበሩ፡፡ ለዚህ ወይም ለዚያ ብሄር ሳንል በአንድ መንፈስ በአንድ አላማ በወንድማማችነት መንፈስ ታግለናል፡፡”

እነ አቶ ገብሩ የሞቱለት ድርጅት በራሳቸው መጽሐፍ ገጽ 43 ላይ እንደምናስተውለው ገና ከማለዳው በትግራዮቹ ታጋዮች ዘንድ “የታላቋ የኢትዮጵያ አስተሳሰብ አራማጅ” ተብለው መወጀንልና መፈራረጅ የነበረ መሆኑን ነው። የካቲት 11 ቀን 1967 ደደቢት ላይ ትጥቅ ትግል የጀመረው ተሓህት ጠመንጃ ማጮህ የጀመረው ወዴት እንደሚሄድ ምን እንደሚፈልግ አጥርቶ ሳያውቅ፣ በገብሩ አነጋገር “በሰነድ የሰፈረ የፖለቲካ ፕግራም” ሳይኖረው

ነው። “ተሓህት ውስጥ እስከ 1968 ዓም ድረስ የዚህ ዓይነቱ ክፍተት ስለነበር አባላቱ የተሓህትን ዓላማ በመሰላቸው መንገድ ይገልጹት ነበር። አንዳንዶቹ የተሓህት ዓላማ የትግራይን ሕዝብ ነጻ ማውጣት ነው ሲሉ” ሌሎች ደግሞ የመደብ ትግል በማካሂያድ ጭቁኖችን ነጻ ለማውጥት ነው ይሉ ነበር። የብሔር ጥያቄና የመደብ ትልግ የተዘባረቁበትና አቅጣጫም ያጡበት ሁኔታ ነበር።”45

እዚህ ላይ ይህን የአቶ ገብሩን አባባል ለመፈተሽ ያህል፣ የመደብ ትግልና ጭቆናን

ለመቃወም ማልደው የተነሱ እንደ ኢሕአፓና መኢሶን የመሳሰሉት ሌሎች ድርጅቶች ቀድመው በተቋቋሙበት፣ በመላው ኢትዮጵያ ተማሪዎች ለለውጥ በተነሳሱበት ሁኔታ፣ የትግራይ ልጆች ለብቻቸው ተነጥለው በረሃ መግባታቸው፣ የመደብ ትግል ሳይሆን የብሔር ፖለቲካን ማራመዳቸውን ያመለክታል። ሁለቱን ማጣመር የሚቻል እንኳ ቢሆን ሁለቱንም ያጣመረ ፕሮግራም መቅረጽ አያቅታቸውም ነበር። ግን ጨወታው ወዲህ ይመስላል።

ለማንኛውም ገብሩ ራሳቸው ድርጅቱ ከተቋቋመ አንድ ዓመት በኋላ የካቲት 1968 በአመራሩ ተረቆ የጸደቀውን ማኒፊስቶ ወይም መርሐ ግብር ሲጠቅሱት እንዲህ ብለዋል “ ...የአብዮታዊው ትግል ዓላማ ከባላባታዊው ሥርዓትና ከኤምፔሪያሊዝም ነጻ የሆነ የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ ማቋቋም ይሆናል” (ገጽ 51) እዚህ ጋር ምንም እንኳ ይህ ትግራይን ለመገንጠል ያቀደ ማኒፌስቶ በአባላቱ ዘንድ ውዝግብ ፈጥሮ ከ6 ወራት በኋላ ቢለወጥም ይህን በአረቀቁት የአመራር አባላት ውስጥ የተቋጠረውን

ችግር መገንዘብና መታዘብ ይቻላል። ይህን እንኳን ሌላው ሰው ገብሩ ራሳቸው በገጽ 98 እንደሚከተለው ታዝበውታል።

“በዚሁ አንደኛ ድርጅታዊ ጉባኤ ድርጅቱን ይመራ የነበረው ማዕከላዊ ኮሚቴ ባሰራጨው የፖለቲካ ፕሮግራም ያካተተውን የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የማቋቋም ዓላማ አንስቶ አልተቸም።...ማን በፕሮግራሙ እንደካተተው የመለየትና ኃላፊነት የመውሰድ ድፍረቱም አልነበራቸውም....

ሁሉም እኔ አልነበርኩበትም የሚል መግለጫ ሲሰጡ ይደመጣሉ።”

ረቂቅ ፕሮግራሙን እንዲያዘጋጁ ድርጅቱ በወቅቱ መድቧቸው የነበሩት ሁለት ሰዎች ግን መለስ ዜናዊና አባይ ፀሐዬ መሆናቸውን ገብሩ ጽፈዋል። ይህን የማስተዋል ጥቅሙ፣ ነገር መደበቅ፣ መቅጠ ሽምጥጥ አድርጎ በግልም ሆነ በቡድን መካድ ገና ከማለዳው አብሯቸው ተወልዶ ያደገ ልማድ መሆኑን ነው። እንጂማ በፕሮግራም የተጻፈን ነገር ማን እንደጻፈው ማን እንዳዘጋጀው ሳያታወቅ ቀርቶ አይደለም። ከዚህ መጽሐፍና ከሌሎችም መረጃዎች በመነሳት ሕወሓት ማለት አመራሩ ዐይኑን በጨው አጥቦ የሚቀጥፍበት፣ አባላቱም ያዩትን እንዳላዩ ሆነው ማለፉን የተካኑበት ብሔርተኝነት ብቻ አቆራኝቷቸው ተቻችለው የሚኖሩበት ድርጅት ነው ማለትም የሚቻልበት ሁኔታ ይታያል።

ትግራይ ባንዲራ ነበራት እንዴ?

አቶ ገብሩ ብዙ የተዋደቁለትን ድርጅት አመራሩንና ጓደኞቻቸውን ሲተቹ አንዳንዱን ማፍረጥ እንደፈሩት ቁስል ቀስ ብለው የሚነካኩት መሆኑ ቢያስታውቅም አንዳንዱን ግን ያለምህረት ይሉታል። ለምሳሌ ይህንን በመጽሐፋቸው ገጽ 100 ላይ የታዘቡትን የድርጅታቸውን ጉድና ትዝብት እንመልከት፣ “መጀመሪያ ባንዲራው

ታሪክ የሚታወቀው ሲጻፍ ወይ ሲነገር ነው። መታመን አለመታመኑም የሚያከራክረው ተጽፎ ወይም በሌላ ቅርጹ ተመዝግቦ ሲገኝ ብቻ ነው። የታሪክ ታሪክነቱ ስነ ጽሑፉነቱ ሳይሆን ሁነቱ ክስተቱ በሆነ የጊዜ ገደብ ውስጥ መደረግ መፈጸሙ ነው። ካልሆነ ግን ልብወለድ ድርሰት መሆኑ አይቀርም። ሆነም ቀረ ግን ተፈጽሟል እንዲህ ሆኗል እንዲያ ነበር እያሉ ከነማረጋገጫው የሚነግሩን ታሪክ ዘጋቢዎች አሉ። ለተአማኒነቱ ሲባል ከስሜታዊ ወገንተኝነቱ እንዲጸዳ ታሪክ በታሪክ ሠሪዎች ባይጻፍም፣ እነሱ የሚተዉት ማስታወሻ ግን ለታሪክ ፀሐፊዎች ግሩም ስጦታ መሆኑ የታመነ ነው። አቶ ገብሩ አስራት በዚህ ረገድ ለታሪክ ፀሐፊዎች አንድ ማስታወሻ ትተዋል። መጽሐፉ ሰፕቴምበር 1/2014 በዋሽግንተን ዲሲ በተደረገ አንድ ሥነ ሥርዓት ተመርቋል። ዶ/ር ካሳ አያሌው በመሩት በዚህ የመጽሀፍ ምርቃት ፕሮግራም ላይ ተገኝተው መጽሐፉን የቃኙት አቶ ፈቃደ ሸዋቀናም መጽሐፉ ለሌሎች ፀሐፊዎች፣ ተመራማሪዎች፣ ፓለቲከኞችና አንባቢዎች እርሾ ሊሆን የሚችል ፈር ቀዳጅና አከራካሪ መጽሐፍ ሆኖ አግኝቸዋለሁ” ብለዋል።

እንደተባለውም ማከራከሩ አይቀርምና ታሪክ ፀሐፊዎች ወደፊት ፍሬውን ከገለባ ለይተው እውነቱን ከሐሰት አበራይተው ይህን ያለንበትን ዘመን ይገልጹታል። የታሪክ ማስታወሻ መተው እየተበራከተ ባለበት በዚህ ዘመን ዘመኑን አሳምሮና ወክሎ የሚገልጸው ታሪክ የትኛው እንደሆነ ማወቁ ይቸግረን ይሆናል።

ቢሆንም ነገሮች በፍጥነት መደበላለቅ በያዙበት በዚህ ዘመን የተደበላለቀ ስሜት የሚፈጥረው የአቶ ገብሩ መጽሐፍ ለታሪክ የሚተወው ማስታወሻ ምን ሊሆን እንደሚችል መቃኘቱ አይከፋም። ዘመኑን ያልተረጋጋ፣ የአፈና፣ የስደት፣ የመከፋፈል፣ የመከራ፣ የእስርና የጭቆና በማድረግ ግንባር ቀደም ተዋናይ ከሆኑት ሰዎች መካከል እግዜር አንዳንዱን እየመዘዘ ቶሎ ሳይዘነጉት፣ እያደረጉ ያሉትን ነገር ቆም ብለው አስተውለው እንዲጽፉት ሲያደርግ ደስ ያሰኛል። አቶ ገብሩም በመጽሀፋቸው ደጋግመው የሚጠቀሙባት “ አሁን ቆም ብዬ ሳዬው፣ አሁን መለስ ብዬ ሳየው፣ አሁን ሳጤነው” የምትል አገላለጽ አለች። ይክፋም ይልማም ቆም ብለው የሚቆጩበት ነገር አለ ማለት ነው። ለምሳሌ በመጽሀፋቸው ገጽ 249 ላይ “አሁን ሳጤነው በአብዮታዊ ዴሞክራሲ እምነታችን ምክንያት የመረጃ ፍሰትን ገድበን የአገራችንን የአስተሳሰብ እድገት በመጎተታችንና በማጫጨታችን እጸጸታለሁ።” ብለዋል።

ይህን ያጫጩትን የአስተሳሰብ እድገት ለማምጣት ከህሊናቸው ጋር ተማምለው ፋይዳ ያለው መጽሀፍ ለማዘጋጀት መነሳታቸውን በመግቢያቸው ጽፈዋል። “ ስለሆነም ለኀሊናዬ ትክክል የመሰለኝን ሁሉ ለማስፈር ሞክሬም፣ ሰማዕታቱ የተሰውለትን ዓላማ ለማክበር ሞክሬያለሁ” (ገጽ4) በማለት ከደጋፊዎቻቸውና ተቃዋሚዎቻቸው የሚመጣባቸውን ነቀፌታ የገመቱ መስለዋል። ሚዛናዊ ነኝና ልብ አድርጉልኝ ነው ነገሩ። ቢሆንም ነቀፌታውና ውርጅብኙን ያቆሙት ዘንድ ግን አይችሉም። የሚችሉትና ችለው ያሳዩት ነገር ለታሪክ የሚሆን ማስታወሻ መተው ነው። እሱን ትተውልናል! ጥያቄው

የተውልን ነገር ምንድነው? የሚለው ነው። በዚህ ዘገባ “ሉዓላዊነትና ዴሞክራሲ በኢትዮጵያ” ከሚለው ባለ 516 ገጽ መጽሐፋቸው የተውልንን ማስታወሻ ከመጠነኛ አስተያየት ጋር መቃኘት ሞክረናል።

መቸም የዘንድሮ መጽሐፍ ከድንጋይ ዳቦ ዘመን ካልጀመረ፣ ታሪክ ካላስተማረ አይሆንለትም። መጀመሪያ ረጀሙና ገናናው ታሪካችንን አንስተን እንጸልይበት ካለለ ወደ ፍሬ ነገሩ መምጣት ያስቀስፋል። ስለዚህ አንዴ ሺ ዘመን አንዴ መቶ ዓመት እየሆነ እንደ ስቶክ ማርኬት ገበያ የሚወጣ የሚወርደውን ዘመን እንለፈውና ወደ አቶ ገብሩ ዘመን ቀረብ ብሎ ያለውን የመጽሐፋቸውን ገጽ ገለጥ ገለጥ እናድርገው።

መጽሐፉ በስድስት ም ዕራፎች በበርካታ ን ዑስ ም ዕራፎች የተከፋፈለ በቁመቱም ዘለግ ያለ ባለ 516 ገጽ ነው። አክሱምን የድርጅታቸውን የትጥቅ ትግል ዘመን ህወሓት ለሥልጣን የበቃበትንና ከኤርትራ ጋር በመንግሥት አብሮ የኖረበትን እንዲሁም ጦርነቱንን ከጦርነቱ በኋላ ያለውን ሁኔታ ሁሉ በዝርዝር ይዳ ስ ሳል። ሰለኢትዮጵያ የዴሞክራሲና ሰብ አዊ መብቶች አያያዝ ስለምርጫን የፖለቲካ ምህዳር መስፋት መጥበብ ያነሳል። መፍትሔ ሀሳቦች ናቸው የሚላቸውንም ሰንዝሯል። እጅግ የተደከመበት መጽሐፍ መሆኑ ያስታውቃል። ከመጽሐፉ ፍሬ ነገሮች ጥቂቶቹን ለመጋራት ያህል የሚከተለው ቅኝት ተደርጋል።

ከመጽሐፉ የተወሰዱ• ህወሃት በ17ቱ የትግል ዓመታቱ 54ሺ ሰዎች መሞታቸውንና ከነዚህ 90 ከመቶ የሚሆኑት የገጠር ወጣቶች ናቸው። በገጽ 165 ።

• “የህወሓት/ኢህአዴግ መሪዎች በሚሊዮኖች የሚገመት ገንዘብ እያፈሰሱ ህዝቡ ትግላቸውን እንደገድለ ሰማዕታት እንዲቀበለው አድርገው በሥልጣን ለመቆየትና ከሞቱም በኋላ ዘለዓላማዊ ክብርና ዝና ለማግኘት መሞክሩን ተያዘውታል። ይህን የህዝብና የሰማዕታት የተጋድሎ ታሪክ ጠቅልለው ለአንድ ሰው ለማሸከም ይሞክራሉ። ሰውየው ከሰውነት አልፎ እንዲመለክ ለማድረግ ይሞክራሉ። ይህን ሁሉ የሚያደርጉትም በአሁኑና በወደፊቱ ተግባሮቻቸው ከመኖር ይልቅ ባለፈው ታሪክ መኖሩ ለሥልጣናቸው ህልውና ጠቃሚ ሆኖ ስላገኙት ነው።(ገጽ 4)

• እጅግ የሚያናድደኝ ይህ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የሚተላለፈው የዘመነ ምኒልክ የጎፌሬዎች ቀረቶና ሸለላ ነው።- ስብሀት ነጋ ገጽ 303

• የደርግ ሠራዊት አባላት በግለሰብ ደረጃ እውቀታቸውንና ክህሎታቸውን በጥቅም ላይ የሚያውሉበትና አዲስ በተደራጀው ሠራዊት ውስጥ በአባልነት የሚቀጥሉበት ሁኔታ ቢመቻች ኖሮ ከፖለቲካው አንጻር ይፈለግ የነበረውን የብሔር ብሄረሰብ ስብጥር ከማሟላትም ሌላ የረጅም ጊዜ ልምዳቸውንና እውቀታቸውን አገራዊ ሠራዊት ለመገንባት ባዋሉት ነበር።222

• አሁን ሳጤነው በአብዮታዊ ዴሞክራሲ እምነታችን ምክንያት የመረጃ ፍሰትን ገድበን የአገራችንን የአስተሳሰብ እድገት በመጎተታችንና በማጫጨታችን እጸጸታለሁ። ገጽ 249

• .. ኢህ አዴግ ተቃዋሚዎችን ለመድፈቅና ለማጥፋት ከሚጠቀምባቸው ስልቶች የአመራር አባላቱንና ከፍተኛ ኃላፊዎችን መቆጣጠር። በጥቅም መግዛትና መደለለል ነው። በክፍያ መዝገብ ስማቸው የሠፈረ አሁን ድረስ ተቃዋሚዎች ነን እያሉ የሚንቀሳቀሱ የማውቃቸው አሉ። የነዚህ ሰዎች ተቀጣሪነት ያወቅኹት በኢሕአዴግ አመራር አባልነቴ ሳይሆን ቅርበት ከነበረኝ የደሐኀንነት አባላት ነውና አሁንም የነዚህን የማውቃቸውን ሰዎች ስም ላለመጥቀስ መርጫለሁ። 251

• ኢሕአዴግ አማራው ክልል ውስጥ ሲንቀሳቀስ ጠባቦች መጥተው ሊውጡህ ስለሆነ ከ እነርሱ የሚያድንህ ከኢህ አዴግ ጎን ተሰለፍ ብሎ ይቀሰቅሳል። በኦሮሚያ በትግራይና በሌሎች ክልሎች ደግሞ ትምክህተኞች ዳግም አንሰራርተው ሊውጡህ ነው ኢሕ አዴግን ካልተቀበልክና ካልደገፍክ መቀመቅ ትገባለህ እያለ በማስፈራራት ይቀሰቅሳል። ገጽ 199

• የሓየሎም ሞት ገዳዩ ኤርትራዊ መሆኑን እያወሱ ከኤርትራ ከነበረው አለመግባባት ጋር ያያዙታል። ይህ ፍጹም ሊሆን አይችልም ብሎ ለማለትም ያዳግታል። 265

• (ስለተባረሩ ኤርትራውያን) ጉቦ እየተሰጣቸው መባረር ያለባቸውን እያስቀሩና መባረር የሌለባቸውን ያባርሩ እንደነበር የሚባረሩት ንብረታቸውን ሲሸጡ ተደራጅተው ንብረቱን በርካሽ ይገዙ እንደነበር ኋላ ላይ ተጋልጧል።...እኛን ፀረ- ኤርትራውያንና ፀረ- ዴሞክራሲያዊ ናቸው እያሉ ሲከሱን የነበሩ ቱባ ባለሥልጣኖች ሳይቀሩ ኤርትራውያን ሲባረሩ ቪላዎቻቸውንና የንግድ ድርጅቶቻቸውን ገዝተው እንደነበር ተራው ዜጋ ሳይቀር ያውቀዋል። ሆኖም የህወሃት/ኢህአዴግ አመራር በአንዱ ወይም በሌላው ከኤርትራውያን ጋር በተያያዘ ወንጀል ተዘፍቀው ስለነበር “በመስተዋት በተሠራ ቤት የሚኖር ሰው በድንጋይ አይጫወትም” እንዲሉ ምንም ማድረግ አልቻሉም። 281

ሉዓላዊነትና ዴሞክራሲ በኢትዮጵያ

የአቶ ገብሩ አስራት መጽሐፍ ቅኝት

ወደ ገጽ 4

ስፕቴምበር 1 2014 በዋሽንግተን ዲሲ በተደረገው የአቶ ገብሩ አስራት መጽሐፍ ምርቃት ሥነሥር ዓት ላይ አቶ ገብሩ አስራት፣ ዶ/ር ካሣ አያሌውና አቶ ፈቃደ ሸዋቀና

Page 3: መልካም አዲስ ዓመት ይሁንልን! · ዘኢትዮጵያ ጋዜጣ Zethiopia Ethiopian American Community News NO.86 Sept 2014 202 518 0245 P.o.box 2049, Fairfax, VA

ዘኢትዮጵያ ጋዜጣ Zethiopia Ethiopian American Community News NO.86 Sept 2014 202 518 0245 P.o.box 2049, Fairfax, VA 22031 www.zethiopia com 3

“በየመድረኩ የሚታየውን የህዝቡን ቁጭትና ተነሳሽነት ከአንድ ዓመት በፊት ቢሆን ኖሮ

በዚህ መልኩ አናገኘውም ነበር” አቶ ነዓምን ዘለቀ

በቅርቡ፣ በየመን መንግሥት የፀጥታ ኃይሎች፣ ለኢትዮጵያ መንግሥት ተላልፈው የተሰጡት፣ የግንቦት 7ቱ ዋና ጸሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ፣ በመላው ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን እያንቀሳቀሱ መሆናቸውን፣ ድርጅታቸው ግንቦት 7 አስታወቀ። የድርጅቱ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ነዓምን ዘለቀ ለዘኢትዮጵያ ጋዜጣ እንደገለጹት “በአሜሪካ አውሮፓ ካናዳ፣ አውስትራሊያ፣ ደቡብ አፍሪካንና ደቡብ ኮሪያን ጨምሮ በ27 የተለያዩ የዓለም ከተሞች የተሳኩ ስብሰባዎች የተደረጉ” ሲሆን “ድርጅቱ በርካታ አዳዲስ አባላትን አፍርቷል። የፋይናስና የሞራል ድጋፍም አግኝቷል።”

“እኔ በተካፈልኩባቸው የአትላንታና የላስ ቬጋስ ስብሰባዎች ላይ ከጨረታ ብቻ በድምሩ ከ20ሺ ዶላር በላይ ሲገኝ ፣ሊቀመንበሩ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ በተገኙበት የዋሽንግተን ዲሲው ስብሰባው ላይ፣ ሌሎቹን ገቢዎች

ሳይጨምር፣ ከጨረታ ሽያጭ ብቻ እንዲሁ ከ20ሺ ዶላር በላይ ድጋፍ” መገኘቱን ገልጸዋል። “በየመድረኩ የሚታየውን የህዝቡን ቁጭትና ተነሳሽነት ከአንድ ዓመት በፊት ቢሆን ኖሮ አናገኘውም ነበር” በማለት የአንዳርጋቸው እስር የቀሰቀሰው ህዝብ “ምን እናድርግ?” የሚሉ ጥያቄዎችን እያቀረበ መሆኑን ገልጸዋል።

እንደ አቶ ነዓምን ገለጻ በሁሉም ከተሞች በተደረጉ ህዝባዊ ስብሰባዎች ከመቸውም ጊዜ የበለጠ ህዝብ፣ ቁጭቱን ለመግለጽ የተገኘ ሲሆን በየቦታው የተሰማሩት የግንቦት 7 አመራር አባላትም ህዝባዊ ውይይቶቹን መርተዋል። ስለ ወቅታዊው የፖለቲካ ሁኔታና ትግሉ የደረሰበትን ደረጃ በማስረዳት እንዲሁም ወደፊት መደረግ ስላለባቸው የትግል እንቅስቃሴዎች ማብራሪያዎች እንደተሰጡ ገልጸዋል። ድርጅታቸው ግንቦት ሰባት “ሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት በማናቸውም የተባበረ ኃይል መወገድ አለበት” ብሎ እንደሚያምን የገለጹት አቶ ነዓምን፣ ለዚህ ሲባል “ ተመሳሳይ የትግል መስመር ላይ ከሚገኙት የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር ውህደት፣ ከዚያም ጥምረት እንዲሁም አገር አቀፋዊ ኃይል መፍጠር ስለሚቻልበት ሁኔታ ምክክሮች እየተደረጉ ስለመሆናቸው ለህዝቡ መገለጹንና ህዝቡም ለዚህ ድጋፉን እንዲሰጥ ድርጅታቸው ግንቦት ሰባት መጠየቁን ሥራ አስፈጻሚው አስረድተዋል።

የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌን እገታንም አስመልክቶ በዲፕሎማሲውም መስክ በተለይ የእንግሊዝ መንግሥት ጉዳዩን ልዩ ትኩረት እንዲሰጠው የግንቦት ሰባት ከፍተኛ አመራር አባላት ጉዳዩ ከሚመለከታቸው የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተወካዮች ጋር መነጋገሩን አቶ ነዓምን ተናግረዋል። በዋነኝነት ግን ህዝቡ በቅርቡ ለንደን ላይ ካደረገው ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ በተጨማሪ በተለያዩ አገሮች በሚገኙ የእንግሊዝ ኤምባሲዎች ላይ ተቃውሞን በማስማት ላይ ይገኛል። ግንቦት 7 “በሳምንት አንድ ሰዓት ለአንዳርጋቸው!” በሚል ባወጣው መርሃ ግብር መሠረት ህዝቡ በዚያች አንድ ሰዓት ውስጥ በፋክስ፣ በኢሜል፣ በስልክና በመሳሰሉ መንገዶች በየአቅራቢው የሚገኙትን የእንግሊዝ ኤምባሲዎች እንዲጎተጉት ተደርጓል። ስለሆነም ጉዳዩ ትኩረት እያገኘ መጥቷል። “ጉዳዩ እስከጠቅላይ ሚኒስትሩ ደርሶ የሚታወቅ እንደሆነም እናውቃለን” ያሉት አቶ ነዓምን በዚህ የተነሳ “በፊት ዞር ብለው ሊያዩን እንኳ ፈቃደኛ ያልነበሩ የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ባለሥልጣናት አሁን አሁን ግን በአካል እያገኙን ለመነጋገር ፈቃደኛ” በመሆናቸው አንዳንድ ውይይቶችን ለማድረግ ተችሏል። በህዝቡ በኩል ያለው የተቃውሞ ግፊት ግን አሁንም ተጠናክሮ መቀጠል ይኖበታል ብለዋል። (ዘኢትዮጵያ)

አንዳርጋቸው እያንቀሳቀሱ ነው!

የዘኢትዮጵያ ስንኞች (ደረጀ ደስታ)

እስኪ ደግሞ እንግጠም!

የአንዳርጋቸው ሰሌን

ላንድ ሰው ተነጥፋ

ሯሷና አቅፋ ተኛች

ሌላ ተጠይፋ!

የአንዳርጋቸው ሰሌን

ሰው የተገፈፈችው

ተዘርግታ ብትቀር

ራሷን አቀፈችው!

አቋም!

ከሰው ከራሴ ጋር ተስማምቼ እንድቆም

ከየቱ እኔነቴ ከነማን ጋር ልቁም?

ነፋስ ወዴት ይንፈስ ወዴት ልከተለው

ቋሚስ የቆመበት መሠረቱ የት ነው?

ባቋማቸው የጸኑ እንዴት ተባርከዋል

የነፋስ መንገዱን ምስጢሩን አውቀዋል።

እንዲህ ነው እንጂ አቋም

እንዲህ ነው እንጂ ፍርድ፤

አልገባኝም ብሎ ከንቱ ከማበድ።

አቋም የጀግኖች ነው- የሚደነቁቱ

አስብ ባይ ወላዋይ ሆነው ከቀሩቱ።

አቋም ለፈሪዎች እንዴት ሆኖ ይሆናል

ጀግናማ ጠቢብ ነው ፈጥኖ ይወስናል!

ስህተቱ ኋላ ነው- ጀግንነቱ ይቅደም

ለጸጸት ጊዜ አለው- የሚወድመው ይውደም !

የዋንጫ

ተጫወቺ አገሬ - ሰው ይሁንልሽ ኳስሽ

እርገጪው ጠልዢው ዋንጫው እንዲደርስሽ!

ቃል ነበረኝ

እኔ ብቻ ብለው

ባይለው ሌላ ሰው

እኔ ብቻ ብወድ

ፍቅርን ብቀድሰው

አቤት በገለጽኩት

በራሴ ብቻ ቃል

እንኳንስ ለፍቅሬ

ለዓለም ይበቃል!

ወደ ውስጥ ሸሸሁ - ተሰደድኩ ወደኔ

ተይዞ እንዳይዘኝ - የገዛ ወገኔ

አውቃለሁኝ እንጂ እንዴት ነው ማላውቀው

ባላውቅ ሶቅራጥስ ነኝ ባውቅስ ደሬ አይደለሁ!

ትንሽ የሚገዛት- አንዲት ትልቅ አገር

አውቃ ይሆናልና- አልሙትላት ይቅር

ብጀግን መግደል ነው - ብፈራም መሞት

መፍትሄው ምን ይሆን - አጣሁ መድኃኒት፤

ሳይገድሉ መጀገን - ሳይፈሩ መሞት

ይሄው ነው መዳኛው- የምነትና ዕውቀት!

እኔ አሸብር!

አገር ሰጥቻቸው - ሕይወት ትቼላቸው

እየፈራሁ ብሸሽ - ምነው አሸበርኳቸው!

እንኳን ሰው ይቅርና አገርም ተይዟል

መያዝ እንደሌባ ለኢትዮጵያም ደርሷል

የአሮጌ ዓመት ልጆች

ዘመን የለበሱ

በቀየሩት ቁጥር

መስሏቸው የታደሱ

እንኳን አደረሰን

መልካም አዲስ ዓመት

ይላሉ ሲመኙ

ቀን የቀየሩ ለት

እንግዳ ነኝ

ያድንቁሽ ጨረቃ

ይሙቅሽ ፀሐይ

ይግጠሙልሽ ዓለም

ይሰገዱሽ ሰማይ

እኔ ምን ቤት ነኝ

ምን ጥልቅ አርጎኝ

ባልገባኝ ውበት

በሌለኝ እውቀት

ባልተሰጠኝ መብት

ስቀኝ የምገኝ!

እኔ ምን ቤት ነኝ

ማን ከሰው ቆጥሮኝ!

እኔ ምን ቤት ነኝ

ምን አገር ኖሮኝ

ስቀኝ የምገኝ!

እሱም መች ሆነለኝ

ቅኔ መቀኘቱ

ሲናገሩ አስሬ

ዝምታን መፍታቱ

ምናባቷንስና

ደግሞኮ ፍቅር ናት!

ረሀቧ ይጣፍጣል

ጥሟ ጥም ይቆርጣል

ባልበላም ባልጠጣም

ካገር ማን ይበልጣል! ሆድ ካገር ይሰፋል

የተባለ ቀን ነው

ሆድ ካገር ሰፍቶ

እኛ የጠበብነው

ለማንኛውም...!

እኔ ሆዴ ሰፍቶ

እሱ ጠበበና

አገሬን ተውኩለት

ይስፋለት አልኩና

የጠባብ ሰው ነገር

አሁንም ጠበበው

ከስደት አገሬም

ሊያስወጣኝ አማረው!

ቃየል አንተ አቤል እኔ

ሔዋን አንቺ አዳም እኔ

ጽድቅና ኩነኔ

ሆነና ነገሩ

መደማመጥ ጠፋ

በየቤት አገሩ!

*ይህ ሰሌን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ይተኙብት

ነበር የተባለው ነው።

ሕልሜ ሆይ!

በውኔም በሕልሜም

ከሆንሽብኝ አንቺ

በውኔ አግብቼሽ

በሕልሜ እንድትፈቺ

አንቺ ልጅ ሕልሜ ሆይ

ሕልም እንደፈቺው ነው

ያገቡሽ ይፍቱልኝ

ሕልሙማ የኔነው

ባለፈው ቅዳሜ ስምፔምበር 6/2014 በጀርመን ፍራንክፈት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን አርቲስት ዓለም ፀሐይ ወዳጆን

በመሸለም አከበሯት። የኢትዮጵያ ናሽናል አርት ካውንስል (The Ethiopian National Arts Council - ENAC) በመባል የሚታወቀውና በጀመርን የሚገኘው ድርጅት በሚያደርገው ዓመታዊ ዝግጅቱ አርቲስት ዓለም ፀሐይ ወዳጆን የዓመቱ ተሸላሚ አድርጓል።

የድርጅቱ መስራችና ሥራ

አስኪያጅ አቶ ተፈሪ ፈቃደ ለዘኢትዮያ ጋዜጣ እንደገለጹት ካውንስሉ የኢትዮጵያን እውቅ የኪነጥበብ ባለሙያዎች

በተለይም በኢትዮጵያ የሚገኙትን አንጋፋ አርቲስቶችን ለመንከባከብና ድጋፍ ለመሰጠት ጭምር የተቋቋመ ነው። ካውንስሉ በየዓመቱ ከጳጉሜ 1-5 ድረስ አርቲስቶች እንዲከበሩና በመጨረሻው ቀን ጳጉሜ አምስት ደግሞ በልዩ ዝግጅት እንዲታሰቡ ያደርጋል። የዓመቱንም ተሸላሚ አርቲስቶች ይመርጣል። ለምሳሌ

ባለፈው ዓመት ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህንን ሸልሟል፡፡

በዘንድሮው ዝግጅቱም አርቲስት

ዓለም ፀሐይ ወዳጆን በመሸለም በህይወት ታሪክና በጥበባዊ ሥራዎቿ ዙሪያ የተቀናበሩ ዝግጅቶችን አቅርቧል። በተለያዩ በተለይም በኢትዮጵያ የሚገኙ እንደ መርዓዊ ስጦት፣ ጌታቸው ደባልቄ፣ ተስፋዬ ገሠሠ፣ ደበበ እሸቱ፣ ጌትነት እነየው፣ የመሳሰሉ አርቲስቶች ስለ አርቲስት ዓለም ፀሐይ የሰጡትን ምስክርነትና

ዓለም ፀሐይ ወዳጆ ተሸለመች!

አድናቆት በአዳራሹ ለነበሩ እንግዶች አቅርቧል። በአካል ተግኘተው የየራሳቸውን አድናቆት የገለጹላት ግለሰቦችም ነበሩ።

አቶ ተፈሪ እንደገለጹት ከካውንስሉ በተጨማሪ፣ ሌሎች ሁለት ድርጅቶች የየራሳቸውን ሽልማቶች አበርክተውላታል። ስቱትጋርት የሚገኘው የኢትዮ ብሪጅ ኢትዮጵያውያን ማህበርና ኑረምበርግ የሚገኘው “እንደ ዜጋ የኢትዮጵያውያን መረዳጃ ማህበር” አድናቆትና ክብራቸውን በሽልማት አጅበዋል።

እውቁ ገጣሚ በእውቀቱ ስዩምና አርቲስት ሐረገወይን አሰፋም ከኢትዮጵያ ተጋብዘው በክብር እንግድነት ተገኝተዋል። የስነጥበብ ሥራዎቻቸውን ማቅረባቸውና

ለዚህም አድናቆ የተቸራቸው መሆኑን አቶ ተፈሪ ገልጸዋል።

በጀርመን ነዋሪ፣ የአፍሪካና የመካከለኛው ምስራቅ ጉዳዮች አማካሪና፣ የካውንስሉ የበላይ ጠባቂ የሆኑት የልዑል አስራተ ካሳ ልጅ ልዑል ዶ/ር አስፋው ወሰን አስራተ፣ ለአርቲስቷ የተዘጋጀውን ሽልማት ማበርከታቸውም ተገልጿል። ከኢትዮጵያ ደራሲ አያልነህ ሙላት እንዲሁም ታዋቂው የሙዚቃ አቀንባሪና ተጫወች ዳዊት ይፍሩን ጨምሮ ሌሎችንም በአባልነት የያዘው ካውንስሉ እድሜና ኑሮ ያደከማቸውን፣ አንጋፋ የኢትዮጵያ አርቲስቶች መርጃ የሚሆን ገቢ የማፈላለግ ሥራም እንደሚሠራ ገልጸዋል። የዚህ አካል በሆነው

ዝግጅትም ላይ የተለያዩ የፋሽን ትርኢቶችና የኪነጥበብ ሥራዎች ቀርበዋል። የጣይቱ የባህል ማዕከል መስራችና ሥራ አስኪያጅ ዓለም ፀሐይ ወዳጆን ለማክበር ከቀረቡት ዝግጅቶች አንዱ የጣይቱ ድራማ እንደነበርም አቶ ተፈሪ አስረድተዋል። ላለፉት 14 ዓመታት በዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው የጥበብ ማዕከል፣ በየወሩ የመጨረሻው ዓርብ፣ በሚሰናዳው የግጥም ምሽት፣ በርካታ የጥበብ ሰዎች ታሪክና ሥራዎቻቸው እንደሚከበሩ ይታወቃል። አርቲስት ዓለምፀሐይ ለተመሳሳይ ዝግጅት ወደሌሎቹ የአውሮፓ አገራት ማቅናቷ ታውቋል። (ዘኢትዮጵያ)

ፍትህ ሚኒስቴር በ6 የግል ሚዲያ ተቋማትና ባለቤቶቻቸው ላይ ክስ መመስረቱን ተከትሎ 16 የሚደርሱ አሳታሚዎችና ጋዜጠኞች አገር ለቀው የወጡ ሲሆን መንግስት በበኩሉ፤ አንድም የተሰደደ ጋዜጠኛ እንደሌለ አስታወቀ፡፡

የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሽመልስ ከማል በተለይ ለአዲስ አድማስ በሰጡት ቃለ ምልልስ፤ በሙያው ምክንያት በደረሰበት

ጫና አንድም የተሰደደ ጋዜጠኛ የለም ብለዋል፡፡

“በአገሪቱ የፕሬስ ስራ ከተጀመረ አንስቶ አንድም የተሰደደ ጋዜጠኛ የለም” ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው፤ አሁን ተሰደናል የሚሉ ግለሰቦች ሙያውን የኢኮኖሚ ጥገኝነት መጠየቂያ እያደረጉት ነው እንጂ መንግስት በጋዜጠኞች ላይ ምንም ዓይነት ክስ አላቀረበም ብለዋ -፡ ክሱ በአሣታሚዎችና ባለቤቶች ላይ የቀረበ መሆኑን በመጠቆም፡፡

ተሰደዱ የተባሉት ጋዜጠኞች የጋዜጠኝነት ስነ ምግባር ያላቸው አይደሉም ያሉት አቶ ሸመልስ፤ “ያልተከሰሰ ሰው ምን አገኘኝ ብሎ ነው የሚሰደደው?” ሲሉ ጠይቀዋል፡፡ ለኢኮኖሚ ጥገኝነት ሲል ከአገር የወጣ ሁሉ ተሰደደ ሊባል እንደማይችልም አስረድተዋል፡፡ (ምንጭ አዲስ አድማስ)

መንግስት አንድም የተሰደደ ጋዜጠኛ የለም አለ

2

Page 4: መልካም አዲስ ዓመት ይሁንልን! · ዘኢትዮጵያ ጋዜጣ Zethiopia Ethiopian American Community News NO.86 Sept 2014 202 518 0245 P.o.box 2049, Fairfax, VA

ዘኢትዮጵያ ጋዜጣ Zethiopia Ethiopian American Community News NO.86 Sept 2014 202 518 0245 P.o.box 2049, Fairfax, VA 22031 www.zethiopia com 4ከመቀየሩ በፊት የህወሓት ባንዲራ ጥቁርና ቀይ ነበር። “ቀይ መስዋአትነት ቢጫ ተስፋ ኮከብ ዓለም አቀፋዊነት በመጀመሪያ ባንዲራው ለምን ጥቁር ቀለም ተካተተ የሚል ጥያቄ ሲቀርብም በደፈናው የድሮው ትግራይ ባንዲራ ያን ይመስል ስለነበር ነው። የሚል መልስ ይሰጥ ነበር። ሆኖም ተሓህት/ህወሓት ይል ከነበረው ውጭ በታሪክ ትግራይ የራሷ ባንዲራ ነበራት የሚል ማረጋገጫ አላገኘሁም።” ብለዋል። መቸም አቶ ገብሩ ያላገኙትን አንባቢዎችስ ብንሆን ከየት እናመጣዋለን!

ሉዓላዊነት በሶማልያም በኩል ነበር!

አቶ ገብሩ ትሑት መሆናቸው ንግግራቸውንም ትችታቸውንም በወጉ ማድረጋቸው ያስመሰግናቸዋል። አንዳንዴ አፍታተው ወይም ጠበቅ አድርገው ሀሰቱን ሀሰት እውነቱን እውነት ቢሉ ከዚያም ርቀው ምነው አንዳንድ ነገሮች ማለት በቻሉ ያሰኛል ። ብዙ ማስረጃ እየደረደሩ የሞገቱትን ሐቅ እንኳ ደፍረው እንዲህ ነው ብለው አይቋጩትም። እያደር ህብረ ብሄራዊና ለሉዓላዊነቱ የሚቆረቆር ድርጅት እየመሰለ መምጣቱን መግለጽ የሚፈለገው ድርጅታቸው በሶማልያ ወረራ ጊዜ እንደሌሎቹ ወረራውን ማውገዝ ብቻ ሳይሆን ከደርግ መንግሥት ጋር ተሰልፎ ለእናት አገሩ ለመዋጋት ሀሳብ የነበረው መሆኑ እንዲመዘገብለትና የክህደት ታሪኩ እንዲፋቅለት ሲጥር መኖሩ ይታወቃል። ይህን በጨርፍታ አንስተው የተቹት አቶ ገብሩ የአቶ ስብሐት ነጋን አንዲት አብነት አንስተው እንደሚከለተው ጽፈዋል፦

“የድርጅቱ ሊቀመንበር ስብሐት ነጋ ሶማልያ በኢትዮጵያ ላይ ጥቃት ስትሰነዝር ከደርግ ጋር በመሆን ጥቃቱን ለመመከት ሓሳብ አድርገን ነበር ቢልም በድርጅቱ ታቅፎ የነበረው አባል ሁሉ ይህን ዓይነት ጥሪ እንደተደረገ ፍጹም አያስታውስም። አባባሉም በሰነድ ሊደገፍ የሚችል አይደለም። ያ ቢሆን ኖሮ የተቃወሙትንና የመስፋፋት ፖሊሲውን ያደናቅፋሉ ያላቸውን የኦሮሞ ተወላጆች ያሰረውና የገደለው ዚያድ ባሬ ተሓህት/ህወሓት በሞቃዲሾ ተወካይ ኖሮት እንዲንቀሳቀስ ባልፈቀደ ነበር። የሶማልያ የይለፍ ፓስፖርት ለተሓህት/ህወሃት ባለሥልጣናት አባላት ባልሰጠ ነበር። ለተሓህት/ህወሃትን በጦር መሣሪያ ባላስታጠቀ ነበር። 93

እንዲያውም ገብሩ ይህኑ የሚያጠናክር መረጃ በሌላኛው ገጽ 117 ላይ ሰጥተዋል። “ የህወሃት ፖለቲ ቢሮው እኔና አው አውሎም ወደ ኤርትራ ሳህል ሄደን ..የሶማልያ መንግሥት የሰጠንንና በሻዕቢያ በኩል ተጓጉዞ እንዲደርሰን የተስማማንበትን ከ3ሺ በላይ ክላሺንኮቭና ሲሞኖቭ ጠመንጃዎች ከነመሰል ጥይቶቻቸው የመረከብ...ተልእኮም ሰጥቶን ነበር” እያሉ ጽፈዋል። ስለዚህ ድርጅታቸው የአገር ሉዓላዊነት ሊያሳስበው ቀርቶ ከወራሪው ኃይል ጋር ተስማምቶ መሣሪያ እስከመታጠቅ መድረሱን አጋልጠዋል። ይሁን እንጂ ሉዓላዊነትን በኤርትራ ብቻ ሳይሆን በሶማልያም በኩል አያይዘው ቢያነሱትና ቢያሰፉት መልካም ነበር። ለወረራውም ቢሆንኮ ኤርትራ እናት አገሯን ከእናት አገሯም ትግራይን ነው የወረረችው ሶማሌን ግን ጎረቤቷን ነው የወረረችው ብለው የሚያስቡ ሰዎች አሉ። ወይንም አለን።

ኤርትራን እናስተኛት!?

ከገብሩ መጽሀፍ የሉዓላዊነት ፍሬነገሮች ሁለቱን ዋና ዋና ነገሮች አውጥተን ብንመለከት አንደኛው ቁጭታቸው ሌላኛው ስጋታቸው ነው። ስለተቆጩበት እንዲህ ይላሉ-፤ “ከሁሉም በላይ የሚከነክነው በወቅቱ ኢትዮጵያ በዓሰብ ላይ የነበራትን የባለቤትነት መብት ያመለምንም ድርድር ለሻዕቢያ አሳልፋ መስጠቷና በታሪክ ትልቅ ጥቁር ነጥብ መጣሉ ነው። ከ30 ዓመት በላይ የህዝቦችን ደም ያፋሳሰሰው ጦርነት በሰላም መፈታቱ ተገቢ ቢሆንም የኢትዮጵያ ጥቅሞች ሳይከበሩ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በአንድ ኮንፈረንስ ለኤርትራ ነጻነት ሕጋዊ እውቅና መስጠቱ ግን ከፍተኛ ስህተት ነበር። የኮንፈረንሱ ተሳታፊዎች ከዚህ ስህተት ተጠያቂነት ሊያመልጡ ባይችሉም ዋናው ተጠያቂ ግን ውሳኔውን የቀየሰውና ተቀብይነት እንዲያገኝ ቁልፍ ሚና የተጫወተው የህወሓት/ኢሕአዴግ አመራር ነው። (ገጽ 184)

ስጋታቸው ደግሞ የኤርትራ መንግሥት መቸም አይተኛልንም የሚል ነው። “ ..እንደኔ አመለካከት በኢሳያስ የሚመራው የሻዕቢያ መንግሥት ኢትዮጵያን ለመውረር ያነሳሳውን በአካባቢው የኢኮኖሚ፣ የወታደራዊና የዲፕሎማስያዊ የበላይነት የመጎናጸፍ ፍላጎት እስካሁና አልጠፋም።..ኢትዮጵያን በማዳከምና በመበታተን በአካባቢው የበላይ የሚሆንበትን ስትራቴጂ ቀይሶ በመንቀሳቀስ ከትግራይ ጀምሮ እስከ ኦጋዴን ትግል እያካሄድን ነው ብለው ለሚያምኑ....መጠጊያ ሆኖ ሥልጠናና

ትጥቅ በመስጠት ኢትዮጵያን ለማተራመስ እየሠራ ነው፡፡

(ገጽ 427)

እነዚህን የአቶ ገብሩ ሁለት ቁጭትና ስጋት ፈጣሪ ነገሮችን ብንመለከት። አንደኛ የፈሰሰ የቀይ ባህር ውሃ አይታፈስም። ጥፋተኞችን ለፍርድ ማቅረብም ቢሆን አገርና ዘመን ላይ አይፈረድም። በታሪክ ተጠያቂ የሚባለውም ነገር ታሪክ ማንን ጠይቆ እንዳፋጠጠ ስላማናውቅ ብዙ አንራቀቅበትም። እንኳን ሊያፋጥጣቸው ይኸው ታሪክ ሰሪዎቹ በቁማቸው መጽሀፍ እየጻፉ በቁማችን ያስነበቡናል። ኤርትራ ትወረናለች አትተኛልንም ማለቱም ጥሩ ስጋት ነው። ታዲያ እንድትተኛልን ምን ማድረግ ይበጃል? ኤርትራ ኢትዮጵያን መጥላት ትታ ራሷን ብቻ ብትወድ ኖሮ ይኼኔ የት በደረሰች ብሎ መምከር ይቻል ይሆናል። ግን ትግሬ ለአማራው፣ አማራው ለትግሬ፣ ኦሮሞው ለአማራ፣ አማራው ለኦሮሞው፣ እስካልተኙ ድረስ እኛም ለኤርትራ ኤርትራም ለኛ ትተኛለች ብሎ መጠበቅ አይሆንልንም። መቸም በዚሁ ገመድ ሲጠላለፉና ሲገዳደሉ የኖሩት ምሁራኑ ፖለቲከኞቻችን ይህን አፍታተው የሚያውቁት ጉዳይ ሊሆን ይችላል። ይልቁንስ መበላላት የትም ካልቀረ ኤርትራውያን ተመልሰው መጥተው እዚሁ ከኛው ጋር እየተበላሉ ቢኖሩ ይሻላቸዋል ብሎ ከመቀለድ ጋር ቁጭት የሚፈውሰውን ስጋት የሚያስቀረውን ዘለቄታዊ መፍትሔ ማሰቡና ስለሱ መጻፉ ይበጃል።

የአቶ ገብሩ መጽሀፍ ጉልበቱ አንባቢን እስከዚህ ድረስ በሀሳብ መንዳቱ ነው። የሚያሳስበው ትልቁ ነገር የኤርትራ ጉዳይ የውስጥ ጉዳይ ሆኖ ይዝለቅ ወይስ እዚያው እየተገፋ ከባህር ይጥለቅ የሚለው ጥያቄ ነው። ቀኝ እጁ ኢትዮጵያዊ ግራ እጁ ኤርትራዊ እየሆነበት ግራ የተጋባ ትውልድ፣ አንዴ እንጣበቅ አንዴ እንላቀቅ፣ ከሚል ማለቂያ አልባ ፍልሚያ የሚገላገልበት መካሪ መጽሀፍ ማስፈለጉን የገብሩ መጽሐፍ ሹክ ይላል። ካለበለዚያ መሬት ወንበር የሆነ ይመስል እስኪ እሱን የተቀመጥክበትን መሬት አቀበልኝ አይባልም። ስለዚህ ይህን ችግር አሰብ፣ ወደብ፣ ባድመ፣ ሉዓላዊነት፣ የሚል ጥያቄ ብቻውን አይፈታውም። ከወንድማማቾች ጋር ዘላቂ ሰላም የሚመጣው፣ መሬት በመተሳሰብ ሳይሆን፣ እርስ በርስ በመተሳሰብ ነው። እሱን ደግሞ ስላቃተን ነው ወንድም ወንድሙን ወግቶ ድል ሊነሳ በረሃ የሚወርደው። በእነ አቶ ገብሩ መጽሐፍ የሚታየውም ይኸው ነው። ማንኛቸው ኢትዮጵያዊ ማንኛቸው ኤርትራዊ መሆናቸውን መለየት እስኪያቅታቸው ድረስ እንደቆቅ ሲጠባበቁና ሲተናነቁ ኖረው መጨረሻቸውና መጨረሻችን እንዲህ ሆኖ ቀርቷል። አቶ ገብሩ እንደሚነግሩን በድርጅታቸው ህወሃት የትግል ዘመን የሞቱት የትግራይ ልጆች ብዛት ወደ 54ሺ ይጠጋል። ይሄ ቁጥር ባንድ ሰሞኑ የባድመ ጦርነት ብቻ ካለቁት 70 እና 80ሺ ሰዎች ቁጥር ጋር ሲተያይ በራሱ የሚናገረው ነገር ይኖረዋል። የሚሰማው ከተገኘ!

ለማንኛውም አቶ ገበሩ የድንበር ማካለልንና የአልጀርስ ስምምነትን አለመቀበልንና ኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነቷን የምታረጋግጥበትን መንገድ የመሻት አስፈላጊነትን በመፍትሔነት ከዘረዘሯቸው ሀሳቦች ውስጥ ይካተታሉ። ይህ ሁሉ የሁለቱ አገሮች ግንኙነት በዚሁ ይቀራል ኤርትራም እንደወጣች ትቀራለች፣ ወይም እንደ አንዳንዶቹም የታባቷንስና በዚያው መቅረት አለባት ከሚል ስጋትና ፍላጎት የመነጨ ይመስላል። ያም ሆኖ ግን ገብሩ ምንም እንኳ ትልቁ ተስፋ ሰጪ ነገር አድርገው ባያጎሉትም በገጽ 478 ላይ በመፍትሄነት ከዘረዘሯቸውና በመጨረሻውና በ4ኛ ደረጃ ባሰፈሩት ላይ፣ “ሁለቱ አገሮች የላቀ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ትስስር ለማድረግ ከተስማሙ፣ ህዝቡን በስፋት ያሳተፈና የቆየውን ባላንጣነት የሚያስወግድ ግንኙነት እንዲመሠርቱ ህዝቦቻቸው በነጻ የሚገናኙበት ሁኔታ መመቻቸት አለበት” ብለዋል። የህዝብ ለህዝቡ ግኑኝነት መሻሻል (ኖርማይላዜሽን) በሰከነ መርሃ ግብር ተደግፎ ወደላቀ ትስስር ለማምራት በር ከፋች መሆን እንዳለበት አሳስበዋል። በአቶ መለስ ወገኖችና በእነ አቶ ገብሩ ወገኖች በኩል የነበረው አንዱ ፈተና ይሄን የህዝብ ለህዝብ ሚዛን የመጠበቅ ችግር መሆኑንም ከጠቅላላው የአቶ ገብሩ መጽሀፍ ይዘት መረዳት ይቻላል። ሻዕቢያና ወያኔ ተብለው ትግራይ ትግሪኝ ሆነው አብረው ለአንድ ዓላማ ለሞቱት ሰዎች ቀላል ያልሆነው ኖርማላይዜሽን ለሌላው ሊከብድ መቻሉንም ከመመርመር ጋር፣ ይህን ሀሳብ ከመደገፍ የተሻለ ሌላ አማራጭ ያለ አይመስልም። በመጽሐፍ የተዘረዘሩት ሌሉቹ የአቶ ገበሩ አማራጮችም ከዚህኛው ጋር ባይሻሙ ይሻላቸው ነበር።

ወያኔን አትናገሩ ህወሓትን ግን እንደፈለጋችሁ!

ማለት የፈለጉትን አይበሉት ወይም ካሉት በላይ አይግለጹት እንጂ አቶ ገብሩ አስራት በተዋቃሚው ጎራ የሚታመሙበት አባባል ያላቸው ይመስላል። የምርጫ 97ን ወቅት እያሰቡ እንዲህ ጽፈዋል “የወቅቱ ተቃዋሚዎች የትግራይን ህዝብና ህወሓትን ያለመየት ችግር የሚጀምረው ከህወሓት ስያሜያቸው ነበር። ምንም

እንኳን ህወሃት “ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ተብሎ ቢጠራም ተቃዋሚዎች ህወሃትን የሚጠሩት ወያኔ ብለው ነበር። ወያኔና ህወሃት አንድ አይደሉም። ወያኔ በትግራይ ህዝብ ሥነ-ልቦና ከፍተኛ ቦታ ያለው የአልገዛምና የእምቢተኝነት መገለጫ ነው። ህወሓትም ይህን ስያሜ የመረጠው

የህዝቡን የቆየ ሥነ-ልቦና ለማጋራት ነው።” ወረድ ብለውም “ኢህአዴግ ራሱ በፈጠረውና አንዳንድ ተቃዋሚዎችም ባስተጋቡት የፍርሃት ድባብ ምክንያት ብዙ የትግራይ ተወላጆች በገዛ አገራቸው በስጋት እንዲኖሩና አማራጭ አጥተው የኢህአዴግን ከለላ እንዲሹ አድርጓቸዋል። ለህወሓት/ኢህአዴግ አንዱ የሥልጣን መሠረት የሆነውም የእነዚህ በስጋት የተዋጡ ዜጎች ሥነ-ልቦና ነው።” (ገጽ 436)

አቶ ገብሩ ይህን ይበሉ እንጂ በድርጅታቸውም በኩል ያለውንም የተጠያቂነት ችግርና ድርሻ አልዘነጉትም። ምክንያቱም ቀደም ሲል በመጽሐፋቸው በገጽ 140 ላይ የሚከተለውን ጽፈዋል “ የጠባብነት ጥያቄ ከተነሳ መጠየቅ የነበረበት ከጅምሩ ብሔራዊ (ትግራዊነት?) ስሜትን ከአገራዊ አንድነትና ስሜት በላይ በማስጮኽ ይቀሰቀስ የነበረው አመራሩ ነበር። ድርጅቱ (ህወሃት) ከሌሎች አገር አቀፍና ብሔር ተኮር ድርጅቶችጋ ያደረገው ትስስር ደካማ ነበር። እንዲያውም ከመሸ በኋላ ከኢሕዴን ጋር ከፈጠረው ግንባር ውጪ፣ ለአስራ ሶስት ዓመታት ያህል በብሄር ተደራጅቶ በተናጠል የተጓዘበት ሁኔታ ነበር። የላብ አደሩ ፓርቲ ሲመሰረት እንኳን ብሔር ተኮር መልክ ይዞ (ትግራይ ብቻ ሆኖ?) እንዲደራጅ ተደርጓል፡፤ እነዚህ በአመራሩ የተቀየሱ ዓላማዎች አደረጃጀቶችና የትግል ስልቶች በታጋዩ ሥነ-ልቦናና አስተሳሰብ ላይ ተጽእኖ ነበራቸው። የታጋዩ አስተሳሰብ ቅድሚያ ተሰጥቶት የተገነባበት አቅጣጫ በብሔራዊ ወይም ክልላዊ ማንነቱ እንጂ በኢትዮጵያዊ ማንነቱ ዙሪያ አልነበረም። በአጠቃላይ የተከተልነው የትግል ስልት ዋና

ማጠንጠኛም ብሄራዊ እንጂ አገራዊ ወይም መደባዊ አልነበረም”

በወዲያና ወዲህኞቻችን ምህረት አልባ ነቀፋ አጣብቂኝ ውስጥ ያሉት ገብሩ ይህን ሲሉ በፍጹም ቅንነት የተናገሩት መሆኑን ያለጥርጥር መገመት ይቻላል። አቶ ገብሩ በዚህ መጽሐፋቸው ያወቁትን ሁሉ ተናግረዋል ማለቱ ጨርሶ የማይታሰብ ቢሆንም ሆን ብለው ያጣመሙት ነገር አለ ብሎ ለማሰብም ይቸግራል። የሚያግባባ ነገር ላይጽፉ ይችላሉ የጻፉት ግን ያመኑበትን ነው ብሎ ማሰቡን መጽሐፋቸው አይከለክልም።

ሉዓላዊነት እና ባለማህተቡ ኢህአፓ

ምንም እንኳ የድርሻቸውን ያህል ስህተትና ተጠያቂነትን የሚጋሩ ቢሆንም፣ ምንም እንኳ አብረዋቸው በእምነት ተሳፍረው እንድ ዓለም ሰፍተው እንደመንደር ጠበው፣ በክህደት የተንጠባጠቡ ቢኖሩባቸውም፣ ምንም እንኳ የእድሜና የርዕዮተ ዓለም ለጋነት እናም የዋህነት ለቅጽበት አሳስቶ የፈጃቸው ቢመስልም፣ በእናት አገር ኢትዮጵያ ፍቅር ግን ስተው ያልተገኙት የኢህአፓ ልጆች ታሪክ እያደር ይፈካል። እንደ ስልባቦት ከላያቸው የሚገፈፈው ስህተታቸው ሲነሳ እንደ ወተት የነጣው የልጅነት ልባቸው ወከክ ብሎ ይታያል። ያን ጊዜ ገድላቸው እንኳን በወዳጆቻቸው የኛ ልጆች አይደላችሁም ብለው በፈጇቸው ጠላቶቻቸው አንደበት ጭምር ይመሰከርላቸዋል። ኢህአፓዎች ሥርዓትን

እንጂ አገራቸውን አለመክሰሳቸው ለሌሎች ሁሉ እንጂ ለራሳቸው ወገን ብቻ ያልሞቱ የማንነት ስግብግቦች አለመሆናቸውን እነሆ ታሪክ ይናገርላቸዋል። በገዛ ግዛቱ እንደ ውጭ ጠላት እያሳደደ በወጋቸው፣ በቀድሞው የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ድርጅት፣ ፖሊት ቢሮ አባልና አንጋፋ ታጋይ አቶ ገበሩ አስራት ብዕር ሳይቀር እንደሚከተለው ተመስክሮላቸዋል!

“ኢህአፓ በአብዛኛው የመኻል አገር ከተሞች በምሁራንና በወጣቶች ከፍተኛ ድጋፍ የነበረው ፓርቲ ቢሆንም በብሔር ድርጅቶች ዘንድ ተቀባይነት አልነበረውም። በተለይ ተሓትና ኦነግ የብሔር ብሔረሰብ አቋሞቹን በተመለከት በጥርጣሬ ይመለከቱት ነበር። .....ኢህአፓ በመርህ በደረጃ የብሔር ብሔረሰቦችን መብት እስከመገንጠል ተቀብሎ ከብሔሮች ትግል ይልቅ ለመደባዊ ትግል ቅድሚያ መስጠት ይኖርበታል በማለቱና በኤርትራ ጥያቄ ቁርጥ ያለ አቋም ባለመውሰዱ በአንዳንድ ብሔር ተኮር ድርጅቶች በተለይ ደግሞ በተሓትና በሻዕቢያ የታላቋ ኢትዮጵያ (ግሬተር ኢትዮጵያ) አቀንቃኝ ወይም የንኡስ ከበርቴ ትምክህተኛ ፓርቲ የሚል ስም አሰጥቶታል። (አረጋዊ በርሔም በመጽሐፋቸው ገጽ 119 ያሉትን መጥቀሳቸውን ጠቅሰዋል)ገጽ 53። “ኢህአፓ በፕሮግራሙ ውስጥ የኤርትራ ጥያቄ በሰለማዊ መንገድ መፈታት እንዳለበት ከመግለጹም በላይ በዲሞክራሲያ በሚያወጣቸው መግለጫዎች ከሰላማዊ ድርድር ውጭ ሌላ መፍትሔ ማፈላለግ እልቂት እንጂ ሌላ ውጤት እንደማይኖረው በተደጋጋሚ ይገልጽ ነበር። ይህ የኢህአፓ አቋም የኤርትራን ድርጅቶች የሚያረካ

አልነበረም። የኤርትራ ድርጅቶች ኢሕአፓ በሁለት ጉዳዩች ላይ ጠንከር ያለ አቋም እንዲኖረው ይፈልጉ ነበር። አንደኛው አቋም የኤርትራ ጥያቄ የቅኝ ግዛት መሆኑንና ቅኝ ገዢዋም ኢትዮጵያ እንደሆነች መቀበል ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ጥያቄው በኤርትራ ነጻነት መፈታት እንዳለበት መቀበል ነበር። እነዚህ ሁለት አቋሞች ከኢህአፓ ሊገኙ ባለመቻላቸው የኤርትራ ድርጅቶች በኢሕአፓ ላይ ከፍተኛ ጥርጣሬና ጥላቻ ነበራቸው። የኢህአፓ አቋም ባይዋጥላቸውም ኢህአፓ ደርግን ከማዳከም አንጻር ሊኖረው ከሚችለው አስተዋጽ ኦንጻር ድጋፋቸውን ይሰጡት ነበር። (ገጽ 54)

ሻእቢያዎቹ ይሰጡ ነበር የተባለውም ድጋፍ ወዲያ ተቋርጦ እንዲያውም ህወሃት ኢሕአፓን ወግቶ ሲያጠፋው እንደ ገብሩ አገላለጽ “ ሻዕቢያ አስተያየት ባለመስጠት የዝምታ ድጋፉን ሰጥትቶታል። ኢሕአፓ የኤርትራ ጥያቄ የቅኝ ግዛት ነው አፈታቱም በነጻነት መሆን አለበት፣ ብሎ ቁርጥ ያለ አቋም ባለመውሰዱ እሳት ሲጎርስ በአንጻሩ የሚፈልገውን አቋም ለወሰደው ህወሓት በመሪዎቹ በእነ ሮመዳን መሐመድ ኑርና በኢሳያስ አፈወርቂ አማካይነት ከፍተኛ ምስጋና ችረውታል። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ከኢሕአፓ ይልቅ ከህወሓት ጋር የተሻለ ግንኙነት ነበራቸው። (ገጽ 105)

የኢህአፓ የወቅቱ ተቀናቃኝና የፖለቲካ ባላንጣ እንደነበረ የሚነገረው መኢሶን አመራር የነበሩት ዶ/ር ነገደ ጎበዜም በበኩላቸው በአዲሱ መጽሐፋቸው “ኢህአፓን ጨምሮ የየካቲት ሃይሎች እንደ ንጉሱ ዘመን አንዱን ወገን ብቻ እያወገዙ ከመቀጠል ይልቅ የሁለቱም ተጠያቂነት ብቻ ሳይሆን የኤርትራ ግንባሮች በጠባብ አጀንዳ ተሰማርተው ከኤርትራም ከኢትዮጵያም

ህዝቦች የጋራ ጠላቶች ጎን መሰለፋቸውን” ወደ ማውገዝ ተሸጋግረዋል ሲሉ የወቅቱን ሁኔታ ጽፈዋል። ኢትዮጵያውያን ሁልጊዜም መንግስታቸውንና ሥርዓቱን ለመቃወም ሲሉ የውጭ መንግሥታትን እርዳታ ይሹ ይሆናል። በ ኢትዮጵያዊነታቸው ግን አይደራደሩም። ሉዓላዊነት ማለት እሱ ማለት ከሆነ በጣልያንም በሶማሌም በሻዕቢያም ዘመን ኢትዮጵያውያን ሲያከብሩትና ሲሞቱለት የኖሩት ጉዳይ ነው።

አሳሩ ገና ነው! መቸም እኛ ከገብሩ አናውቅም

የህወሃት ሰዎችም ደጋፊዎችም በኤርትራ ጥያቄና ወዳጅነት ላይ ሌላውን ሲከሱም ሆነ ሲወቅሱ ሲደመጥ መኖራቸው ይታወቃል። እሱስ ይቅር መቸም ፖለቲካቸው እንደሱ ነው። ወቀሳቸው ግን ኤርትራውያንን በፀረ ኤርትራዊነት እስከመክሰስ ከሄደ ምን ይባላል? ሉዓላዊነትና ዴሞክራሲ በኢትዮጵያ የሚለው የአቶ ገብሩ አስራት መጽሐፍ ከገጽ 125 እስከ 126 ያስፈረውን አንዲት አንቀጽ ቀንጭበን እንመልከት!

በ1970ዎቹ መጀመሪያ ላይ የኤርትራ ድርጅቶች ከደርግ ጋር ሊደራደሩ ነው የሚል ጭምጭምታ በተሰማበት ወቅት ህወሃቶች እጅግ ተናደን ነበር። በአንድ በኩል ሻዕቢያ ተስፋ ቆርጦ ትግሉን አቋርጦ እጁን ለደርግ ሊሰጥ ነው የሚል ስጋት ነበር፣

የታጋዩ አስተሳሰብ ቅድሚያ ተሰጥቶት የተገነባበት

አቅጣጫ በብሔራዊ ወይም ክልላዊ ማንነቱ እንጂ

በኢትዮጵያዊ ማንነቱ ዙሪያ አልነበረም። በአጠቃላይ

የተከተልነው የትግል ስልት ዋና ማጠንጠኛም ብሄራዊ

እንጂ አገራዊ ወይም መደባዊ አልነበረም”

በ1970ዎቹ መጀመሪያ ላይ የኤርትራ ድርጅቶች ከደርግ ጋር ሊደራደሩ ነው የሚል ጭምጭምታ በተሰማበት ወቅት ህወሃቶች እጅግ ተናደን ነበር። በአንድ በኩል ሻዕቢያ ተስፋ ቆርጦ ትግሉን አቋርጦ እጁን ለደርግ ሊሰጥ ነው የሚል

ስጋት ነበር፣ በሌላ በኩል ደግሞ ሻዕቢያ በኤርትራ ነጻነት ጉዳይ ላይ ከደርግ ጋር ሊደራደር ነው የሚል ስጋት ነበር።

ሁለተኛው ስጋት አግባብ አልነበረም፡፡

ወደ ገጽ 5

የአቶ ገብሩ አስራት..... ከገጽ 2

Page 5: መልካም አዲስ ዓመት ይሁንልን! · ዘኢትዮጵያ ጋዜጣ Zethiopia Ethiopian American Community News NO.86 Sept 2014 202 518 0245 P.o.box 2049, Fairfax, VA

5

ርዕሰ አንቀጽ

የዓመት ደንበኛችን ይሁኑ ስለ ድጋፍዎ እናመሰግናለን

በወታደራዊው ደርግም፣ በኢህአፓም፣ በመኢሶንም፣ በትንላንትናው ቅንጅትም፣ ምናልባትም የንጉሠ ነገሥቱንም ዘመን ጨምሮ አሁን ደግሞ የወያኔ ሃርነት ትግራይ ሰዎች፣ በመጸሐፍ መልክ የሚተውትን የታሪክ ማስታወሻን ለተመለከተ ሰው ሁሉም ዘንድ የሚያስተውለው አንድ የጋራ ነገር ያለ ይመስላል። አብዛኞቹ በየመስመራቸው ትክክል ነን ባይ መሆናቸው እንደተጠበቀና የሚፈቅድም ሆኖ ፣ ነገር ግን ለቅንነት ህልምና ድካማቸው ሲሉ በከፈሉት መስዋዕትነት እየተመሰጡ ያስገኙትን ውጤት ሳይሆን የወጡትን ውጣ ውረድና የከፈሉትን ዋጋ በመተረክ ተጠምደው ይታያሉ። የተሳካ ህልማቸውን ሳይሆን የጨነገፈ ውጥናቸውን በማብራራትና የመዋቀሻ ምክንያታቸውን ሲደረድሩ ኖረው ያልፋሉ። ከተለያየ ዓለም ለናሙና ወደ ኢትዮጵያ ተልከው አንዳቸው ርዕዮተ ዓላማቸውን አንዳቸው ብሔርተኝነታቸውን ከፊላቸው ሐይማኖትና እምነታቸውን ሌሎችም ከእነዚህና ከሌሎች አንድ ሁለቱን እያጣመሩ የሞቱላቸው ዓላማዎች በርካታ ናቸው። ለዓላማ መሞት የሚጣፍጠውን ያህል ለዓላማም ሲባል መግደል ጣፋጭና እንደየአግባቡም ጀግነንት እየሆነ መታየቱም አልቀረም። ከሌላ ዓላም የመጡ የመሰሉት እነዚሁ ሰዎች ከሌላው ዓለም ያልመጡ ጠላት ወንድሞቻቸውን እየገደሉ በጨዋ ቋንቋ እየተፋለሙ ወገናቸውን ነጻ ለማውጣት ወገናቸውን ሲገድሉ መኖራቸውን ጽፈዋል። ትግል እየኮመጠጠ ድል እየጣፈጠ ጣፋጭ የልጅነት ህይወት ትዝታ ሁሉ ቀርቶ አብዮት፣ ቀይ ሽብር፣ ነጭ ሽብር፣ በረሃና ታጋይነት እንደ ትዝታ ሙዚቃ ወደኋላ እየተደመጠ የቂም ቅብብሎሽ ውርስ ተጧጡፏል።

ድጅርተኝነት ጎሰኝነት ሀይማኖተኝነት ክፍለሐገርተኝነት አውራጃና ወራዳዊነት....የቡድናዊ ማንነት መገለጫዎች ቢሆኑም እስከማገዳደል ከሄዱ ግን ሰውኝነት ሳይሆኑ ጅብኝነት ቀበሮኝነት እየሆኑ መሄዳቸው አይቀርም። ቡድናዊ ማንነቶች ለግለሰቦች ጥቅም ሲባሉ የሚፈጠሩ እንጂ ግለሰቦች ለቡድኖች አልተሰሩም። ግለሰቦች ምርጫ አላቸው። ልክ የፖለቲካ ድርጅት መለዋወጥ እንደሚችሉት ሁሉ እነዚህንም መቀያየር ይችላሉ። መቀየር እንኳ የማይችሉ ቢሆኑ ከተጽኗቸው ውጪ መሆን ይችላሉ። አማራ ኦሮሞ ትግሬ ናችሁ እየተባሉ እንኳ ይህን የማህበር አስተሳሰብ ላያቸው ላይ መጫን የማይፈልጉ፣ ምንም ነገር ሳይደገፉ ብቻቸውን መኖር የሚችሉ ሰዎች ብዙ ናቸው። በማንነታቸው እንኳ ተለይተው ለጥቃት የተጋለጡ እንኳ ቢሆን ነገርን አለቅጥ አያዳንቁም። ልክ እንደ ሌላው ወንጀል ሁሉ እንዲህ ያለ ነገር ሁለተኛ እንዳይከሰት ተከስቶም ቢገኝ በህግና ሥርዓት መፍትሔ እንዲያገኝ ይታገላሉ። በራሳቸው ላይ ሲደርስ ብቻ ሳይሆን በሌሎችም ላይ እንዳይደርስ መሰረታዊ የሆኑ መብቶች ለሁሉም ሰዎች እንዲጠበቁ ይታገላሉ እንጂ የራሴ ነው ያሉትን ብቻ እየለዩ አይጮኹም። በአሜሪካ ጥቁሮቹን እየለዩ የሚገድሉ ነጮች መኖራቸው ጥቁሮችንም መርጠው ፕሬዚዳንት ያደረጉ ነጮች መኖራቸውን አይጋርደውም። በጥቁሮች ላይ የሚደርሰው በደል የሚያንገፈግፋቸው ፕሬዚዳንት ኦባማ ለነጮችም ጭምር የገቡትን ቃል ኪዳናቸውን አያስለውጣቸውም። እንኳን እሳቸው ሌሎቹም ነጮቹም ጥቁሮቹም በረሃ እንገባለን ዱር እንወርዳለን አይሉም። የመሰልጠንና መጽሐፍ የመግለጥ ጥቅሙ ይህም ጭምር ነው። እንጂ ማርክሲዝምና ሌኒንዝምንም ወይም ሊብራልም ሆነ አብዮታዊ ዴሞክራሲን እየኮሙከሙ ስለግሎባላይዜሽን እየተደመሙ በቡድናዊና ድርጅተኝነትን ተለክፈው አገር ማመስ አይደለም።

ድርጅታችን ቅዱስ ነው ብሔረሰባችን የጠራ ነው በማንነታችን እንኮራለን ማለት እውቀት አይደለም። ይልቁንም ማንነት ውልደት ሳይሆን እውቀትም ጭምር ነው። ተሸናንፎ ሳይሆን ተደጋግፎ የመኖር ፍልስፍና ጥቅሙ የሚታየው የዚህ እውቀት ባለቤት ሲሆኑ ጭምር ነው። ታላላቅ አገሮች የተሰሩት በመሸናነፍ ሳይሆን በመደጋገፍ ነው። ማስገበር እንኳ ቢኖር ቀጥሎ ማክበርና መከባበር ይቀጥላል። እንጂ ቂም እየተሽከረከረ የገዛ የተገዛውን - የተገዛው የገዛውን ሲያፈራርቁ አንዱን ሲነቅሉ አንዱን ሲተክሉ አይኖሩም። አያቶቻችን ይገዙ ነበርና እኛም በተራችን እንግዛ ማለትም አያቶቻችን ተገዝተው ነበርና እኛም በተራችን ነጻ ወጥተን ልንገዛ ይገባናል ማለትም ያው የገዢነት ፍላጎት ነው።

በማንነታችን እንኮራለን ማለትም ደግሞ ሁልጊዜ ልክ ላይሆን ይችላል። ለነገሩ መኩራትን ምን አመጣው? ማን ላይስ ነው የሚኮራው? ደግሞም እዚያም ቤት ኩራት አለና ጨዋታው አያዋጣም። ኩራቱ የአመድ በዱቄት ሳቅ፣ የደሃ ብሽሽቅ ከሆነ ደግሞ ይበልጥ ኪሳራ ነው። በማንነት መኩራት የግድ አስፈላጊ ነገር ከሆነ መኩራት ያለበት ሰው ከኩራት ነጻ የሆነ ሰው ነው። በሰው የማይኮራ ሰውም የማይኮራበት ሰው ነጻ ሰው ነው። ኩራት ከዚህ ነጻነት ይመነጫል። አንሳለሁም እበልጣለሁም ያላለ ሰው ችግር የሌለበት ሰው ያገኘውን ሰው ሁሉ ያከብራል። ያገኘውን ሰው ሁሉ ያከበረ ሰው ደግሞ በሁሉም ይከበራል። የሚንቀው የሚለክፈው ሰው እንኳ ቢገጥመው ይህ ሰው ትንሽ እውቀት ይጎድለዋል ብሎ ታዝቦት እልፍ ብሎ ይሄዳል እንጂ ስለማንነቱ ሲሟገት አይገኝም። ምክንያቱም ማንነት በውስጣዊ ልበሙሉነት እንጂ በውጫዊ ሙግት አይረጋገጥም። ሰዎች ስለ በላይነታቸው የድንቁርና ጉራ መሽቶ እስኪነጋ ይደስኩራሉ፣ ስለበታችነት ስሜታቸውም ሲሉ ወይም እኩልነታቸውን ለማረጋገጥ ታጋይ ይሆናሉ፣ በረሃም ይወርዳሉ። ተመልሰው ሲመጡ ያው በረሃ ያወጣቸውን ነገር እዚያው ተቀምጦ ያገኙታል። እንዲያውም ባይብስ! ሰዎች ሥልጣን ያገኘን እንደሁ እንከበራለን ብለው ያስባሉ። ሆዳቸውን ይሞሉ ይሆናል እንጂ አይከበሩም። ያው እነመንግሥቱ እነመለስ ዜናዊ ተፈሩ እንጂ አልተከበሩበትም። የገዛ ወዳጆቻቸውና ጓዶቻቸው ሳይቀሩ በታሪክ ፊት አጋድመው ይሳለቁባቸዋል እንጂ አላከበሯቸውም። በእርግጥ የታደሉት አንዳንድ ነገሥታት የማይወደዱ ይሆናሉ እንጂ ከንቀቱ ሠፈርስ የሉበትም። በዚህም ዘመን ጠቅላይ ሚኒስትር ጥራ ቢሉት ራሱ መጣ እንደሚባሉት እንደ አቶ ኃይለማርያም ዓይነቶቹም አሉ። ሥልጣን ክብርና ሞገስን የማያስገኝ ላለመሆኑ ምሳሌ ናቸው። እንዲያውም አንዳንድ ጊዜ እንዲህስ ከሆነ ይቅርብኝ አንተ እዚያው ጠቅላይ ሚኒስትር ሁንበት እየተባለ የሚቀለድበት ዘመን መምጣቱን ኃይለማርያም ሳያስገነዝቡን አይቀርም። ለመለስ ያልሆነ ለኃ/ማርያም እንዴት ይሆናል? ሥልጣን ይዘው ሥልጣን ያጡ መሆናቸው ባለሥልጣን መባል በስም መጠራት ብቻውን ማንነትን የማይሰጥም የማይገልጥም ሳይሆንባቸው አልቀረም። ትግሬነት ብቻውን ጀኔራል ያደረገው ሀብት አዝንቦበት ያበለጸገው ሰው እንዳለ ሁሉ፣ ከለማኝነትም ያላወጣው በየሄደበት የማንም አፍ መክፈቻና የፖለቲካ መለማመጃ መወቀሻ መጠቃቀሻ ያደረገውም እድለ ቢስ ትግሬ አለ። ታዲያ በስመ ትግሬነት ሁሉም ስለትግሬነታቸው ብቻ ቺርስ ቢባባሉ ሌሎችም በዚህ ቀንተው እኛም በተራችን ቺርስ ለመባባል ነጻ አውጪ እናቋቁም ቢሉ ምን ሊባል ይችላል? አማራውን አሸንፈን መጣን ያሉ ሰዎች፣ አማራውን እንደ ጎጆ ቤት ሳር ቢመዙት ቢመዙት አላልቅ ብሏቸው ተቸግረዋል። ሌሎችም ነገ ትግሬውንም ሆነ ኦሮሞውን እንዲሁ እናድርግ ቢሉት ይህ መሆኑ አይቀርም። ስብከት አጃጅሏቸው ታሪክ ጥራዝ አስነጥቋቸው፣ ጫካ የገቡትም እንደነሱ የሆነውን የአማራ ገበሬ ያዩ ቀን ግራ ተጋብተዋል። ከብዙ እልቂት በኋላ ችግሩ የማንነት ሳይሆን የኑሮ ደረጃ መደብ ሆኖባቸው፣ ገዢ መደብና ተገዢ መደብ እያሉ ሲራቀቁ፣ እሱንም እውቀት አድርገውት መጽሐፍ ሲለቀልቁ ይታዘቧል እንጂ ምን ይሏል!

አገር ባህልና ልማድን መገልበጥ የመጽሐፍን ገጽ እንደ መገልበጥ የቀለለ እየመሰላቸው ከዚህም ከዚያም በቃረሙት ቲዮሪ መርቅነው ጎራ ለይተው ሲያዋክቡን የኖሩትም ሰማዕታት እልፍ ናቸው። ላመነቡት የጎሳም ሆነ የፖለቲካ ፍልስፍና ወድቀዋልና ስለጽናታቸው አጨብጭብናል። እነሱንም አጥተናቸው ባዶአችንን በመቅረታችንም አዝነናል። የተራረፉትም አንድ መሆንም ማድረግም አቅቷቸው እየበጣጠሱን ነው። ሞተናልናል አትናገሩን፣ ቆሰለናልና አትነካኩን ባዮችም እየሆኑ በህይወት ያለው አምባገነን ሳያንሰን የሰማዕታት አምባገነኖች እየሆኑ የሚያውኩንም ሞልተዋል። በጣም የሚገርመው ግን ጎሳም ሆነ ከፖለቲካ ድርጅታቸው የቆረቡ፣ ሞታቸውን እንጂ የሞቱለትን ዓላማ ፍሬ ማየትም ሆነ ማሳየት ያቃታቸው፣ በየአቅጣጫቸው ቢሞቱ ጥቅሙ ምንድነው? ኃይ ዌይ መንገድ ስተው ከማይሆን ኤግዚት ገብተው ሲነዱ ሲነዱ ሲነዱ ኖረው ሲያበቁ የተሳሳተ ኤግዚት ብወስድም በነዳሁት መንገድ ርዝመትና በአነዳዴ ጽናት ልደነቅ ይገባኛል ሲሉ ዝምብለው ይገረማሉ እንጂ ምን ይላሉ። ችግሩ መንገድ የጠፋባቸው እኛን ጭነው ከሆነ ነው። እንግዲህ የነጻነት ተዋጊ ተሽከርካሪዎች እልፍ ናቸውና ሁላችንም በየተጫንበት ሆነን መቀጠል ወይስ መድረሻችንን መጠየቅ ይኖርብናል? ይህን መጠየቅ ጠቃሚ ሳይሆን አይቀርም። ስለዚህ እንደ የተሳፈርንበት መኪና የብሔር መኪና የያዙትም የሐይማኖቱን የሚያሽከርክሩትም ፖለቲካውን የሚነዱትንም የሰላምም የትጥቅም የምርጫም የእርግጫም የሚሉትንም ሁሉ ወዴት እየነዱን እንደሆነ በድፍረት ልንጠይቃቸው ይገባናል። ጓደኞቻቸው ከሚጽፉልን መጽሐፍትና ከቅርብ ጊዜ ታሪኮቻቸው እንዲሁም ከማያቋርጥ ዲስኩራቸው መረዳት እንደምንችለው ችግሩ መሠረታዊ አቅጣጫን ያለማወቅና በተገኘው ጎዳና ሁሉ ጭልጥ ብሎ የመሄድ ነው። ስለዚህ በድፍረት እንጠይቃቸው። ሊቆጡን ወይም በለመዱትና በሚወዱት ፍረጃና ስም ማጥፋት ሊያስፈራሩን ይችላሉ። ከደረሰብን በላይ ምን እንሆናለን? ዝምብለን አጭር ጥያቄ እንጠይቃቸው- ወዴት እየነዳችሁን ነው? መነዳት ብንተውና ራሳችንን ችለን መንገዳችንን አጥንተን መሄድ ብንችልማ አንድ ነገር ነበር። ግን አልቻልንም። ሁሌም መንገዱን አጥርቶ የማያውቅ ሰው አጨበርብሮ የሚነዳን ለዚህ ነው። ለማንኛውም ወዴት እየሄድን ነው፣ ወይ እንወቅ ወይ እንጠይቅ! (ዘኢትዮጵያ)

በሌላ በኩል ደግሞ ሻዕቢያ በኤርትራ ነጻነት ጉዳይ ላይ ከደርግ ጋር ሊደራደር ነው የሚል ስጋት ነበር። ሁለተኛው ስጋት አግባብ አልነበረም፡፡ ...ከባለቤቱ ያወቀ ቡዳ ነው እንዲሉ ባለቤቶቹ ችግራችንን በአንድነት ማዕቀፍ እንፈታለን ሲሉ፣ እኛ የለም ይህን መሆን የለበትም ብንል፣ የድርጅቶቹን ነጻነት ከመጻረራችን ባሻገር፣ የኢትዮጵያን ጥቅም እየጎዳን እንደነበር አልተገነዘብነውም ነበር። ከዚህ በመነሳት ሻዕቢያ ከደርግ ጋር ሊደራደር ነው የሚለውን ወሬ ስንሰማ ሻዕቢያን በተምበርካኪነት ፈርጀን መክሰስ ጀመርን። የኤርትራ ነጻነት እርግፍ አድርጎ ትቶ ከደርግ ጋር ሊታረቅ እንደሚችል ገመትን። የደርግና የሻዕቢያ ጌቶችም ሶቭዬቶች ስለሆኑ ሊያስታርቋቸው ይችላሉ የሚል ግምት ስለነበረንም ስለ ኤርትራ የምንጽፋቸው ጽሑፎችና የምናወጣቸው መግለጫዎች ሁሉ የኤርትራ ህዝብ ከነጻነት ባሻገር ሌላ መፍትሔው እንዳይቀበል የሚሰብኩ ነበሩ። እንዲያውም አንዳንድ የምናወጣቸው ጽሑፎች ከኢትዮጵያ ሳይሆን ከኤርትራ ድርጅት የመነጩ ይመስሉ ነበር። ህወሓት ኤርትራን በተመለከት ካቀረባቸው ጽሑፎች አንዱ “ብረት ህዝቢ ኤርትራ ቁልቁል አፉ አይድፋእን!” “የኤርትራ ጠመንጃ አፈሙዝ ቁልቁል አይዘቀዘቅም!” በሚል ርዕስ የተጻፈው ነበር። ይህ በመለስ ዜናዊ የተጻፈው ጽሑፍ ምሁሩና አርቆ አሳቢው ኤርትራዊው ተስፋ ጽዮን መድኃኔ ለጻፈው የተሰጠ ምላሽ ነበር፡፡...ባለቤቶቹ ጉዳዩ ሳያሳስባቸው ህወሃት ተቆርቋሪ ሆኖ መቅረቡ ያስገርማል። ኤርትራዊ ስለ አንድነትን ሲጽፍ አንድነትም ለሁለቱም ህዝቦች የሚጠቅም ሆኖ ሳለ፤ መገንጠልን ደግፈን ያን ያህል ርቀን መሄድ ባልንበረብን ጉዳዩም ይበልጥ ለኤርትራውያን መተው ነበረብን። 126

አቶ ገብሩ በመጽሀፋቸው ከቀድሞ የትግል ጓዶቻቸው ያለ ይቅርታ የሚወቅሷቸውና አውራ ተጠያቂ የሚያደርጓቸው ሟቹን አቶ መለስ ዜናዊና አቶ ስብሐት ነጋን ነው። በተለይ እጅጉን በተማረሩበትና የመጽሐፋቸውም ርዕስና ማጠንጠኛ ያደረጉት የኤርትራ ጥያቄና የሉዓላዊነት ጉዳይ ዋነኛ ተጠያቂዎቹ እነዚህ ሁለት ሰዎች ናቸው። አቶ ሥዩም መስፍን፣ ብረሃነ ገ/ክርስቶስ ኤታማዦር

ሹሙ ሳሞራ የኑስ፣ ሟቹ የቀድሞ ደህንነት ሹሙ አቶ ክንፈ ገመድህንና የአሁኑ ደህንነት ሹም አቶ ጌታቸው አሰፋ እንዲሁም የአቶ መለስ አማካሪ የነበሩ አቶ ሙልጌታ ዓለምሰገድን በተለያዩ ጊዜያት ኤርትራን አስመልክቶ በወሰዷቸው አቋሞቻቸውና ባሳዩት ተባባሪነት ታሪክ እንዲወቅሳቸው ያጠቆሯቸው ይመስላል። የስብሀትና የአቶ መለስ ግን የተለየ ነው።

ሻዕቢያዎቹ ከህወሓቶች ሁሉ አጥብቀው የሚወዷቸውና የሚያምኗቸው አቶ ስብሐት ነጋን መሆኑን ገብሩ ጽፈዋል። እንዲያውም ባንድ ወቅት ኢሳያስ ሞቅ ብሏቸው “ ስብሐት ነጋ ስልጣኑን ሳይለቅ አጥብቆ ቢሄድ ኖሮ የሻዕቢያና በሕወሃት መካከል አለመግባባት እንደማይፈጠር “መናገራቸውን በገጽ 223 ጽፈዋል። ስብሐት “ ከድርጅቱ የጸጥታ ክፍል /ሐለዋ ወያነ/ ጋር በመሆን ቀውስ ፈጣሪዎች በተባሉት ላይ የምርመራና የማጣራት ሥራ ሲያካሂድና አብዛኛውን ጊዜ የቅጣት ውሳኔ ሲሰጥ የነበረ የአመራር አባል ነበር።101” ያሉት ገብሩ ስብሐት በዚያ ልምዳቸው የተነሳ የራሳቸውን ሥልጣን ሲክቡና ሰዎቻቸውን ቦታ ቦታ ሲያዙ መኖራቸውን ይገልጻሉ። የኤርትራን ጉዳይን በሚመለከትም ስብሐት በገዛ ፍቃዳቸው መሬት አሳልፎ ይሰጡ እንደነበር እንዲህ ሲሉ ጽፈዋል። “በ1990 ዓም ግጭቶች የተኪያዱባቸውን አንዳንድ የምዕራብ ትግራይ አካባቢዎች ስብሐት ነጋ በሊቀመንበርነት ሥልጣኑ ከህዝቡ ፍላጎት ውጭ ከ1974 እስከ 1976 ባለው ጊዜ ለሻዕቢያ የሸለማቸው ነበሩ። ስብሓት መንደሮቹን ለሻዕቢያ አሳልፎ ሲሰጥ ከህወሃት የህዝብ አደረጃጀት አባላት ከፍተኛ ተቃውሞ ቢገጥመውም ማዕከላዊ ኮሚቴው ግን ለጉዳዩ እምብዛም ትኩረት አልሰጠውም ነበር።” 109

አይ መለስ ዜናዊአቶ ገብሩ በጣም የሚወቅሷቸውን አቶ መለስ ዜናዊን ደግሞ እንዲህ ገልጸዋቸዋል

“መለስ በወታደራዊና በሕዝብ አደረጃጀት እንቅስቃሴዎች ይህ ነው የሚባል ሚና ባይጫወትም ታጋዮችን በመቀስቀስና በመስበክ ጽሑፎችን ቶሎ በማንበብና በመጻፍ ረገድ ከፍተኛ ችሎታ ነበረው። ዐልፎ ዐልፎም ድንጋይ ዳቦ ነው ብሎ እስከማሳመን ይደርስ ነበር። አብዛኛው ገበሬና ዝቅተኛ የትምህርት ደረጃ የነበረው የድርጅቱ አባል በመለስ የስብከት ችሎታ እጅግ ይገረም ነበር። ይህ በአብዛኛው የድርጅቱ አባላት ተሰሚነት እንዲያገኝ ረድቶታትል፡፤ በ1969 ዓም ከጦርነት አፈግፍጓል ተብሎ በደረሰበት ብርቱ ሂስ ሞራሉ ዝቅ ብሎ የነበረውም መለስ ከሁለተኛው ድርጅታዊ ጉባኤ

በኋላ ሲያንሰራራና የሐሳብ መሪነት ለመጨበጥ ሙከራ ሲያደርግ ታይቷል።113

ሌሎች አቶ መለስን እንዴት እንደሚያይዋቸው ሲጽፉም

“አረጋዊ በርሄና ግደይ ዘርአ ፅዮን መለስን ጽናት እንደሌለው ከመጠን በላይ ተናጋሪና ተግባር ላይ እንደማይገኝ ታጋይ ያዩት ነበር114” ብለዋል። ይሁን እንጂ አቶ መለስ

ዜናዊ ገና ከጧቱ በሥራ አጋጣሚ ከተቀራረቧቸው “እነ ተወልደ ወ/ማርያምን ስዬ አብርሃን፣ ክንፈ ገ/መድህን ሳሞራ የኑስ ጋር የጠበቀ ዝምድና መስረታቸውንና ወደ ሥልጣን መፈናጠጣቸውን ጽፈዋል።

በመለስ ተወጥረው በተያዙበት የኢትዮ-ኤርትራ አንድ ስብሰባ ላይ የቀድሞ አቋማቸውን ሽምጥጥ አድርገው ሲክዱ አቶ ስዬ ንዴታቸውን መቆጣጠር ያቅታቸዋል ። በቃለ ጉባኤ የተያዘ ነገር እንዴት ይክዳሉ? መለስ ይቺን አጥተዋት አይደለም። ገብሩ እንዲህ ጽፈውታል-

ስዬ “መለስ የቀድሞ ሐሳቡን ለውጦ ሌላ ሐሳብ እያቀረበ እያጭበረበረ ነው፣ ይህ አኪያሄዱ ትክክል አይደለም፣ የአቋም መንሸራተቱን ለማረጋገጥ በቃለ ጉባኤው የሰፈረው ይታይልኝ ብሎ አለ። ....ቃለ ጉባኤው ቢታይ በአግባቡ ያልተመዘገበ ሆኖ ተገኘ። ምክንያቱም ቃለ ጉባኤ ያዡ በረከት ስለነበር አልመዘገበውም።” (ገጽ 340) መለስ ምናቸው ሞኝ ነው። እነ በረከትን ቃለ ጉባኤ እያስያዙ ካልሆነ እነዚህን ሰዎች የት ይችሏቸዋል። መቸም ተንኮለኛ ናቸው ። ተቃናቃኛቸው ስዬን በልማት ስም ከመከላከያ ሚኒስትርነት አንስተው የኤፍረት ስራ አስኪያጅ ሲያደርጓቸው ማዕከላዊ ኮሚቴ ብዙም ያላስታውለው ጉዳይ ነበር ይላል የገብሩ መጽሐፍ። ለነገሩ ስመ ገናና የመሰሉት ስዬም ከዚህ ተነስተህ እዚያ ሂድ ከዚያ ወደዚህ ና ሲባሉ ዝምብለው የሚሽከርከሩ ኖረዋል እንዴ ያስብላል።

መለስ ግምገማና ስብሰባ የሚወዱትን ጓደኞቻቸውን በስብሰባ እያጠመዱ እሳቸው በጎን ሥራቸውን ይሠሩ ነበር። ይህም ሌላው ጮሌነታቸው ነበር “ የሥራ አስፈጻሚውንና ማዕከላዊ ኮሚቴውን በማያባራ ውይይት ጠምዶ ዋነኛ የሥልጣን ማስጠበቂያ መሣሪያዎች የሆኑትን የጸጥታና የመከላከያ ኃይሎችን እያባባለ ድጋፋቸውን ለማሰባሰብ እየተቀንሳቀሰ እንደነበር መገንዘቡም ከባድ አልነበረም። (ገጽ 340)

መለስ ጮሌ ብቻ ሳይሆኑ ለሥልጣናቸው ሲሉ የማይፈነቅሉት ድንጋይ የማይክዱት ነገር የለም። ሌላው ቀርቶ ለሥልጣን ያበቃቸውን የትግራይ ህዝብና ጓደኞቻቸውን እንኳ አሳልፈው ከመስጠት አልተመለሱም። አጣብቂኝ ውስጥ ገብተው ከሥልጣናቸው ሊባረሩ በደረሱበት አንድ ወቅት ድርጅታቸውን ህወሃትን ትተው የአማራው ወኪሎች ነን የሚሉ ብአዴኖችን ተቀላቅለው እንዴት ከጎናቸው እንዳሰለፏቸውና ህወሓቶችን ክስ እንደመሰረቱባቸው ይታያል። ነገሩ ሲወራ የቆየ ቢሆንም ገብሩም በዚህ መጽሐፋቸው አረጋግጠውታል። አዲሱ ለገሠ እነዚህ ሰዎች (እኛን) ጠባቦችና የበሰበሱ ናቸው- ብሎ ተናግሮ ነበር። 391 ....በተለይ አዲሱ አፈንጋጮች የበሰበሱና ጠባቦች ነበሩ እያለ የትግራይ ህዝብ በተለየ ሁኔታ ተጠቃሚ ሆኗል የሚለውን የመለስን የፕሮፖጋንዳ ጨዋታ ከመጠን በላይ ያራግበው ነበር። (ገጽ 392) ። በአቶ መለስ እርዳታ ከጀኔራሎችም እነ ባጫ ደበሌ ሳይቀሩ የትግራይ ገበሬዎች የበለጠ ተጠቃሚ ሆነዋል ሁሉ ነገር ትግራይ ትግራይ ብቻ መሆን የለበትም ብለው እስከመናገር መድረሳቸውና ሥርዓቱን በጠባብ ብሔርተኝነት መክሰሳቸው ታይቷል።

አቶ መለስ የፓርቲ አባሎቻቸው ድጋፍና ድምጽ በጎደላቸው ወቅትም ባለቤታቸውና ማሰማራታቸውን ገብሩ ጽፈዋል። “አዜብ ለመለስ ድጋፍ ለመሰብሰብ በቤተ መንግሥት ቅልጥ ያለ ግብዣ እያዘጋጀች ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትን ታምበሸብሽ ነበር” ገጽ 351 ብለዋል።

ከአቶ ገብሩ አጻጻፍ የዘወትር አቶ መለስ አቋማቸውን በፍጥነት በመገለባበጥ የሚታወቁ የልባቸውን ካደረጉ በኋላ ፈጥነው ይቅርታ ተሳስቻለሁ ብለው አ ም ታ ተ ው እ ን ደ ሚ ያ ል ፉ

ዘኢትዮጵያ ጋዜጣ በሰሜን አሜሪካ በተለይም ዋሽንግተን ሜሪላንድና ቨርጂኒያ ነዋሪ ለሆኑ ኢትዮጵያውያን ከጁላይ 2002 ጀምሮ የሚታተም፣ ተባባሪ አዘጋጅ ተስፋዬ የማነ ተሰማ

202 518 0245 P.o.box 2049,

Fairfax, VA 22031 www.zethiopia com

[email protected] Newspaper Editor - Dereje Desta አዘጋጅ ደረጀ ደስታ

ገብሩ አስራት... ከገጽ 4 የዞረ

ወደ ገጽ 6

202-518-0245

ዘኢትዮጵያ ጋዜጣ Zethiopia Ethiopian American Community News NO.86 Sept 2014 202 518 0245 P.o.box 2049, Fairfax, VA 22031 www.zethiopia com

ስዬ “መለስ የቀድሞ ሐሳቡን ለውጦ ሌላ ሐሳብ እያቀረበ እያጭበረበረ ነው፣ ይህ አኪያሄዱ ትክክል አይደለም፣

የአቋም መንሸራተቱን ለማረጋገጥ በቃለ ጉባኤው የሰፈረው ይታይልኝ ብሎ አለ። ....ቃለ ጉባኤው ቢታይ በአግባቡ ያልተመዘገበ ሆኖ ተገኘ። ምክንያቱም ቃለ ጉባኤ ያዡ በረከት ስለነበር አልመዘገበውም።” (ገጽ 340) መለስ ምናቸው ሞኝ ነው። እነ በረከትን ቃለ

ጉባኤ እያስያዙ ካልሆነ እነዚህን ሰዎች የት ይችሏቸዋል። መቸም ተንኮለኛ ናቸው ። ተቀናቃኛቸው ስዬን በልማት ስም ከመከላከያ ሚኒስትርነት አንስተው የኤፈርት ስራ አስኪያጅ ሲያደርጓቸው፣ ማዕከላዊ ኮሚቴው ብዙም

Page 6: መልካም አዲስ ዓመት ይሁንልን! · ዘኢትዮጵያ ጋዜጣ Zethiopia Ethiopian American Community News NO.86 Sept 2014 202 518 0245 P.o.box 2049, Fairfax, VA

ዘኢትዮጵያ ጋዜጣ Zethiopia Ethiopian American Community News NO.86 Sept 2014 202 518 0245 P.o.box 2049, Fairfax, VA 22031 www.zethiopia com 6Yes I want to subscribe Zethiopia Newspaper

Name------------------------------------------------

Address-----------------------------------------------

City................................................................................

State...................Zipcode............................................

Phone,...........................................................................

Email.................................................................................

Starting date...................................................................

For only $40.00

Ze Ethiopia Corp.P.o.box 2049,

Fairfax, VA 22031 www.zethiopia com

[email protected]

Zethiopia Newspaper

ዘኢትዮጵያ ጋዜጣ ቤትዎ እንዲላክልዎ ከፈለጉ ከዚህ ቅጽ ጋር የዓመት ደምበኝነት ሞልተው 40 ዶላር ይላኩልን

የአዲስ አበባ ከተማ የሬዲዮ ፕሮግራሞች አፍቃሪ በሳምንት ሁለት ጊዜ በድምሩ ለ 5 ሰዓታት ያህል ከቴዎድሮስ ጸጋዬ ጋር አብሮት ይቆያል። ርዕስና ጉዳይ የማያልቅበት ጋዜጠኛና ገጣሚ ቴዎድሮስ ጸጋዬ በሁለገብ ዝግጅቱ የታወቀ ነው። ባለፉት 6 ዓመታት በሸገር ኤፍ ኤም 102 ነጥብ 1 እንዲሁም በኤፍ ኤም አዲስ 97 ላይ ሲደመጥ ቆይቷል። የሸገሩ “ልኬት” እና የኤፍ ኤም አዲስ 97ቱ “ርዕዮት” ፕሮግራሞቹ በበርካታ አድማጮቹ ተወዳጅ ነበሩ። ቴዎድሮስ ቅኔ ቋጣሪ ስንኝ ደርዳሪ ነው። “ነፍስ ጡር ስንኞች” በሚል አንድ የግጥሞች መድብል አሳትሟል። ቴዎድሮስ ለእውቅ ድምጻውያን ግጥም እየደረሰ ይሰጣል። አሁን በቅርቡ እንኳ ወጥተው በመደነቅ ላይ የሚገኙት የሚካኤል በላይነህ የዜማ ግጥሞች አምስት ያህሉ የሱ ናቸው። አንቺ የሌለሽ ጊዜ፣ ትንታ፣ ትመጪ እንደሁ፣ ስንዋደድ፣ቅኔ ውበት የተባሉት ይገኙበታል። ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በህግ ትምህርት ተመርቆ ቢወጣም ሬዲዮ ላይ ወጣ እንጂ ወደ ጥብቅና ዳኝነቱ አልሄደም። ከሁለት ዓመቱ ጀምሮ ዐይነ ስውር የሆነው ቴዎድሮስ ባለትዳርና የ8 ወር ሴት ልጅ አለችው። ባለፈው ወር የጣይቱ ባህል ማዕከል ወርሃዊ የግጥም ምሽት በልዩ እንግድነት ተጋብዟል። የዘኢትዮጵያው ተባባሪ ተስፋዬ ተሰማ የሚከተለውን ቃለ መጠይቅ አድርጎለታል።ዘኢትዮጵያ - አንተ ራስህን እንዴት ነው የምታየው ጋዜጠኛ ነህ ወይስ የህግ ባለሙያ?

ቴዎድሮስ- አንድ ሰው የግድ አንድ መጠሪያ ይኑረው ስለማይባል እኔ ጋዜጠኛም ነኝ የህግ ባለሙያም ነኝ ራሴን እንደዚያ ማየት ይቀለኛል።

ዘኢትዮጵያ - ወደ የትኛው ሙያ ታዘነብላለህ?

ቴዎድሮስ- ብዙ የሠራሁበት ጋዜጠኛነቱና ስነ ስጹሁፍ

ስለሆነ ወደ ጋዜጠኝነቱ የማደላ ይመስለኛል።

ዘኢትዮጵያ - በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በህግ ትምህርት መመረቅህን አውቃለሁ። ለምን ወደ ጋዜጠኝነቱ ጭልጥ ብለህ ሄድክ?

ቴዎድሮስ - በየትኛውም አገር አንድ የህግ ባለሙያ በተለያዩ የህግ ዘርፎች ሊሰማራ ይችላል። እንደ አጋጣሚ ሆኖ እኔ ኢትዮጵያ ውስጥ ልሰማራባቸው የምፈልጋቸው የህግ ዘርፎች እንደሚፈለገው ስላይደሉ እኔም ራሴን እዚያ ውስጥ ማግኘት አልቻልኩም።

ዘኢትዮጵያ - አንተ በየትኛው የህግ ዘርፍ ነበር ለመሰማራት የፈለግከው?

ቴዎድሮስ - እኔ በተማርኩበት ሙያ አገሬን ማለገልገል የምፈልገው በዳኝነት ዘርፍ ነበር። በኢትዮጵያ ውስጥ አሁን ባለው መንግስት ጤናማ የፍትህ ሥርዓት ስለሌለ የዳኝነት ሥርዓት ባልተረጋገጠበት፣ የህግ የበላይነት ባልተከበረበት፣ የፍትህ ሥርዓቱ አካል ሆኖ ማገልገል ያፈና ሥርዓቱ እንዲጠበቅ አንድ ተጨማሪ ኃይል ሆኖ ማገልገል ሆኖ ስለታየኝ በህግ ዘርፉ ልሰማራ አልቻልኩም።

ዘኢትዮጵያ - የህግ የበላይነት አልተከበረም ስትል ምን ማለትህ ነው?

ቴዎድሮስ - በኔ ግምት የዚህን ጉዳይ ያህል በምሳሌ ለማስረዳት የቀለለ ነገር ያለ አይመስለኝም። ጋዜኞች ሀሳባቸውን በነጻነት በመጻፋቸውን በመናገራቸው ዜጎች ከመንግሥት የተለየ የፖለቲካ አቋም ስላላቸው ብቻ፣ በአሸባሪነት የሚታሰሩበት አገር፣ ፍርድ ቤት ነጻ ያለውን ሰው መልሶ ለማሰር የማያሳፍረው መንግሥት መኖሩን በማየት ብቻ የዳኝነት ሥርዓቱ ነጻና ራሱን ችሎ የቆመ አለመሆኑን መገንዘብ ትችላለህ።

ዘኢትዮጵያ - እንደ ሕግ ባለሙያነትህ የኢትዮጵያን የህግ ሥርዓት ስታየው የፍትህ መበዛባት አለበት የሚያሰኝህንና ለዚህም የምትጠቅሰው ጥቂት ማስረጃዎች ካሉህ እስኪ ንግረኝ

ቴዎድሮስ - የመናገር ነጻነትን ተጥቅመው መንግሥትን በመቃዋማቸው እነ እስክንድር ነጋ፣ ርዕዮት ዓለሙ፣ ውብሸት ታዬ፣ ሌሎችንም ጋዜጠኞች በአሸባሪነት ወንጀል፣ የህግ አንቀጽ ተጥቆስባቸው ተከሰው፣ ፍርድ ቤቱም ይህንን ክስ ተቀብሎ ፈርዶባቸው በእስር ቤት እየማቀቁ ይገኛሉ። በህገ መንግሥቱ ላይ በተደነገገው

የመድበለ ፓርቲው ሥርዓት መሠረት፣ የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅት አቋቁመው፣ መንግሥት ላይ የሰላ ትችት በማቅረባቸው፣ እነሱም እንዲሁ በአሸባሪነት ተከሰው በፍርድ ቤት ተፈርዶባቸው በእስር የሚሰቃዩ እንደነ አንዱ ዓለም አራጌ ኦልባና ሌሊሣ፣ በቀለ ገርባንና ሌሎችንም መጥቀስ ይቻላል።

ዘኢትዮጵያ - በኢትዮጵያ ውስጥ ለተከሰተው የፍትሀ መዛባት መንግሥት (ፖለቲከኞቹ) ብቻ ሳይሆኑ ዳኞቹና ዐቃቤ ህጎቹስ ተጠያቂነት ያለባቸው ይስመስልሃል?

ቴዎድሮስ - የፍትህ መዛባት የብዙ ድምሮች ውጤት ነው። ከዘርፎቹ አንዱን እንኳ ወስደን፣ የዳኝነት ነጻነቱን ብናይ፣ ተቋማዊ ነጻነትና ግለሰባዊ ነጻነትን ያካትታል። ለምሳሌ ሕገመንግሥቱ ዳኞች ሥራቸውን በነጻነት እንዲያከናውኑ በግልጽ የሚናገር ቢሆንም ይህ ነጻነት በተግባር ካልተተረጎመ ግን ዋጋ የለውም።

ዘኢትዮጵያ - በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት ዳኞችና ዐቃቢህጎችስ የራሳቸውን ነጻነት ለማስከበር ይሄ ነው የሚባል እንቅስቃሴ አድርገዋል?

ቴዎድሮስ - የመንግስትን ተጽእኖ አንቀበልም ብለው በግልጽ የተቃወሙና ለፍትህ የቆሙ ጥቂቶችን አውቃለሁ። ለምሳሌ ቅንጅቶችን አልከሰም ብሎ መንግሥትን በመቃወም ራሱን ከሥርዓቱ የለየው አቶ ዓለማየሁ ዘመድኩንን ፣ በ97 ምርጫው የተፈጠረውን ሁኔታ እንዲያጣራ የተቋቋመው ኮሚሽን ሰብሰባ የነበሩትን እነ አቶ ፍሬ ሕይወት ሳሙኤልን፣ እነ ወ/ት ብርትኳን ሚደቅሳን መጥቀስን እንችላለን። የእነኚህን ዓይነት የነጻነት ቀናኢ የሆኑ ግለሰቦች ቁጥር በፍትህ ሥርዓት ውስጥ ማበራከት ከተቻለ ከግለሰቦቹ (ዐቃቤ ህጎቹና ዳኞቹ ማለት ነው) የነጻነት ትግል የተቋሙን ነጻነት መውለድ ይቻላል ብዬ አስባለሁ።

ዘኢትዮጵያ - አሁን ለጊዜው የፍርድ ቤቱን ነገር እንተውውና እና አሁን አንተ የፍትሕ ሥርዓቱ ስለተበላሸ ነው ማለት ነው ወደ ጋዜጠኝነቱ የመጣኸው?

ቴዎድሮ- (ሳቅ) ለነገሩስ ሚዲያውስ ቢሆን መች ጤና አለው ብለህ ነው። ወደ ጋዜጠኛነቱ እንዳደላ ያደረጉኝ ሁለት ምክንያቶች ናቸው። አንደኛ ቅድም እንደነገርኩህ ጋዜጠኝነቱ ውስጤ ያለ ነገር ስለሆነ። ሁለተኛ የሕግና የፍትህ ሥርዓቱን ለመቀየር ከሚፈጀው ጊዜ ጉልበትና አቅም ይልቅ መገናኛ ብዙሃንን ተጠቅሞ በህብረተሰቡ ውስጥ በጎ

ተጽእኖ ማሳደሩ ቀሎ ስላገኘሁት ስለሆነ ይሆናል።ዘኢትዮጵያ - በኢትዮጵያ ውስጥ ከ6 ዓመታት በላይ የሬዲዮ ፕሮግራሞችን በግልህ ትሰራ እንደነበር አውቃለሁ፣ በእነዚያ ሬዲዮ ፕሮግራሞች ምን ዓይነት ውጤት ነበር ማየት የፈለግከው?

ቴዎድሮስ - ምን ያህል ተሳክቶልኝ እንድነበር ባላውቅም እኔ እጥር የነበረው በህብተረሰቡ ውስጥ የሀገር ፍቅርን እጅግ ከፍ ማድረግና ኢትዮጵያዊነትን የበለጠ ማቀጣጠል፣ ዜጎችን መልካም ስነምግባርና የኃላፊነት ስሜት እንዲሰማቸው ማድረግ፣ በአጠቃላይ እውነትን ከውሸት የሚለይ ስለ አገሩ በቅጡ የሚያውቅ፣ የሚያነብና የሚጠይቅ ትውልድ መፍጠር ነበር።

ዘኢትዮጵያ - በፕሮግራሞችህ የፖለቲካ ጉዳዮችን በቀጥታ ታነሳ ነበር እንዴ?

ቴዎድርስ - እንግዲህ የዚህ ጥያቄ መልስ ፖለቲካ ምንድነው ለሚለው ጥያቄ በምንሰጠው ብያኔ ላይ ይመሰረታል። እንደኔ እምነት ቀጥተኛና ወቅታዊ ፖለቲካዊ ጉዳዩችን ማንሳቱ እጅግ ጠቃሚና አስፈላጊ መሆኑ

ቴዎድሮስ ጸጋዬ

የተለያዩ አጋጣሚዎችን እየጠቀሱ ጽፈዋል። ከሁሉም የእግር እሳት ሆኖ የሚያቃጥላቸው ኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ዋስትና ሊሰጥ በሚችል መልኩ ሊጠናቀቅ ይችል ነበር ያሉት የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ባልፈለጉት መንገድ ድንገት መጨናገፉ ነው። እንደገብሩ ገለጻ ለዚህ ዋነኛ ተጠያቂው አቶ መለስ ናቸው እንዲህ ጽፈዋል፦

መለሰ በዚህ ዓይነት የተወሳሰበና ተንኮል የተሞላበት አግባብ ብቻውን ያደረገውን የጦርነቱን ሂደት የማስቆም ውሳኔ ተገቢ እንዳልነበረና ይህን ለመወሰንና ለማወጅ የሚያስችል ሥልጣን እንዳልነበረው ኋላ ላይ ሂስ ሲቀርብለት “አዎን ስህተት ፈጽሜያለሁ ሆኖም ከጦር ግንባር ሳገኘው የነበረው መረጃ ጦርነቱን ለማስቀጠል ያስችላል የሚል ስላልነበረ ከዚህ ተነስቼ ጦርነቱን በ24 ሰዓት ውስጥ እንዲቆም አውጃለሁ። የሥራ ባልደረቦቼን ማማከር ነበረብኝ ይህን ባለማድረጌ ተሳስቻለሁ።” አብዛኛዎቹ የማዕከላዊ ኮሚቴ ወታደራዊ እዝ አባላትና የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት አዋጁን የሰማነው እንደተራው ዜጋ በመገናኛ ብዙኃን ስለነበር አዋጁ የተጣደፈው ምናልባት በግንባር የነበሩት አዛዦች ግምገማቸውን አስተላልፈው መቀጠል እንደማይችሉ ስለገለጹ ሊሆን ይችላል የሚል ግምት ነበረን። ነገር ግን የግንባር አዛዦቹ ግምገማ ለማዕከላዊ እዙና ለሥራ አስፈጻሚው አባላት የደረሰው መለስ ጦርነቱ እንዳበቃ ካወጀ ከቀናት በኋላ ነበር። ይህ በመሆኑ የግንባር አዛዦቹ ግምገማ እርሱ ከሚፈለገው ውጭ እንደማይሆን አስቀድሞ በደጋፊዎቹ ተነግሮታል የሚል ግምት አለኝ። ሳሞራና ተከታዮቹ ከነዚህ ህወሓት ውስጥ ቴክኒካል አሬንጅመቱን ተቀብለን እንፈርም ከሚሉ ወገኖች ጋር ጥብቅ ግንኙነት ነበራቸው። 314-315

በተቃዋሚዎች ምሽግ ላይ እልል በል!- አብ ዱፋዖም አልል!

በአጠቃላይ የመንግሥት ሥልጣን ከመቆጣጠራችን በፊት ስንጠቀምባቸው የነበሩትን ጠላትና ወዳጅ የሚለዩ ፅንሰ ሐሳቦች መንግሥት ካቋቋምን በኋላም አላስወገድናቸውም ነበር። 186

አብ ዱፋዖም አልል- በምሽጋቸው ላይ እልል በል!

በ002 ምርጫ ወቅት ኢህአዴግ ያልተገበረው የአፈና ስልትና ያላካሄደው ወከባ አልነበረም። ወቅቱ ነጻና ፍትሀዊ ምርጫ የተካሄደበት ሳሆን በተቃዋሚዎች ላይ ግልጽ ጦርነት የታወጀበት እንበር። ለነገሩ በዚህ የምርጫ ዋዜማ ህወሓት/ኢህ አዴግ አብአብ ዱፋዖም አልል- በምሽጋቸው ላይ እልል በል! የሚለውን የትጥቅ ትግል የድል ዘፈን በተደጋጋሚ ያስዘፍን ነበር። ይህ የዋዛ ቢመስልም መልዕክቱን በጥልቀት ለተመለከተው በተቃዋሚዎች ላይ እንደ ደርግ ጦርነት መታወጁ ግልጽ ነበር።463

ትግራይና ኤርትራ - አንቺው ታመጪው አንቺው ታሮጪው

አቶ ገብሩ ስለ ህወሓትና ሻዕቢያ ግንኙነት አንድነትና ልዩነት ሲናገሩ የሚከተለውን ብለዋል ” እውነቱን ለመናገር ግን ግኙነታችን ሞቅ ሲል ልክ እንደ አንድ ድርጅት በጋራ የምንሠራበት ግንኙነቱ ሲቀዘቅዝ ደግሞ በዓይነ ቁራኛ የምንተያይበት ሁኔታ ነበር እንጂ ግንኙነታችን ስትራቴጂያዊ አይደለም የሚለው አቋማችን ግንኙነትቻን ላይ ስለሚኖረ ተጽ እኖ በግልጽ ተዘርዝሮ አልተቀመጠም ነበር። ስለዚህ ከሻ ዕቢያ ጋር አሉን ያልናቸው የፖለቲካ ልዩነቶቻም የይዘት ሳይሆን የስም ብቻ እንደነበሩ እነዚህ ያደረግናቸው የፖለቲካ ለውጦች ያሳያሉ...በመሆኑም ሁለቱም ድርጅቶች በተጨባጭ ከቃላት ያለፈ የር ዕዮት ዓለምም የስትራቴጂም ልዩነት አልነበራቸውም ማለት ይቻላል። (ገጽ 236)

ስለዚህ በሁለቱ መካከል የዓላማም ሆነ የስትራቴጂም ልዩነት ከሌለ ወደ ግጭት የወሰዳቸው ወይም ህመማቸው ታዲያ ምንድነው የሚል ጥያቄ ያጭራል።

አቶ ገብሩንና መሰሎቻቸውን ሁሌም የሚያበግናቸው ነገር ከበረሃ ጀምሮ የሻዕቢያ ባለሥልጣናት ለህወሓት ባለሥልጣናት የሚያሳዩት ንቀትና የሚፈጽሙት የትዕቢት ድርጊት ነው። እንደገብሩ መጽሐፍ ያኔ ሁለቱ ሻዕቢያና ህወሓት ወዳጅ መንግሥታት በነበሩ ጊዜ ኢሳያስ ምንም የፕሮቶኮል አግባብ ሳይጠብቁ መኪናቸውን አስነስተው መቀሌ ይገቡ ነበር። ከካርቱም አልበሽርን ከአዲስ አበባ አቶ መለስን ይዘው መቀሌ ላይ ስብሰባ ይቀምጡ ነበር። ሌላው ቢቀር ፕሮቶኮል አለመጠበቁን ያማርሩ የነበሩት የወቅቱ ፕሬዚዳንት

ዶ/ር ነጋሶም ስለ ጉዳዩ ቅሬታቸውን መግለጻቸውን እንዲህ ሲሉ ጽፈዋል”

“የወቅቱ የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ነጋሶ በሽርና ኢሳያስ አፈወርቂ ያለ እርሱ እውቅና በበርካታ አጋጣሚዎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጡና ....365 ሲያሰኘን እንደ መንግሥት ሲያሰኘን እንደታጋይ ሆነን የፈለግነውን እንግዳ ወደ ኢትዮጵያ ስናስገባና ስናስወጣስ ነጋሶ ከፕሮቶኮልና ከአሠራር አንጻር ላነሳው ጥያቄ ክብደት ልንሰጠው በተገባ ነበር። በሽርና ኢሳያስ አዲስ አበባ ሳይደርሱ በቀጥታ ወደ መቀሌ መጥተው በወቅቱ ርዕሰ ብሔር ካልነበረው ከመለስጋ ሶስቱን አገሮች በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ብዙ ጊዜ ይነጋገሩ ነበር። 365

ይህ የሚሆነው እንግዲህ አቶ ገብሩ ፕሬዚዳንት ሆነው በሚያስተዳድሯት የትግራይ ክልል ዋና ከተማ መቀሌ ውስጥ ነው። ይህም ሳይበቃ ለኤርትራ አዋሳኝ በሆነቸው የትግራይ ክልልና ድንበር ውስጥ በሚፈጸሙ አንዳንድ ቅሬታዎች የተቆጡት አቶ ኢሳያስ በአስመራ የኢትዮጵያ አምባሳደር ለነበሩት አቶ አውአሎም ዛሬ ሄጄ ገብሩን

ሰድቤ እመጣለሁ ብለው እየነዱ እንደሚመጡ ገብሩ ጽፈዋል።

ዋነኛው ችግርና ለግጭት ያበቃቸው ምክንያት ግን የኢኮኖሚ ግኙነት መሆኑን አቶ ገብሩ በመጽሐፋቸው ለማሳየት ሞክረዋል። ይህም ቢሆን ኤርትራን አምራች ኢትዮጵያን ሸማች ከማድረግ ኤርትራን መሪ ኢትዮጵያን ተከታይ የማድረግ አዝማሚያ መታየቱ ዋነኛው ሰበብ ይመስላል። መጽሐፉ “ ሻዕቢያዎች ኢትዮጵያን ለመቆጣጠር ስለነበራችው ህልምና ነጻነታቸውን ባወጁ ሁለተኛው ወር ላይ ሐምሌ 1983 ከፍተኛ የኢኮኖሚ ኮንፈረንስ ማዘጋጀታቸውን፣ በኮንፈረንሱም የኢትዮጵያን አየር መንገድ እንደገና አዋቅሮ ከኤርትራውያን ጋር የጋራ አክስዮን ኩባንያ እንዲፈጠር፣ ትግራይ ውስጥ የሚሠራውን የመንገድ ፕሮጀክት ሁሉ ኤርትራውያን እንዲገነቡት፣ ቀይ ባህር የንግድ ድርጅት በሚል አንድ የንግድ ኩባንያ እንዲቋቋም ማንኛውም ኤርትራዊ 500 ብር አውጥቶ አክስዮን እንዲገዛ የመሳሰሉት ውጥኖች መኖራቸው በመጽሀፉ

አቶ ገብሩ... ከገጽ 5

በሻዕቢያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ከፍተኛ የፀረ- ትግራይ ቅስቀሳ ይደረግ ነበር።“በአንድ ወቅት ከትግራይ ወደ ኤርትራ የሚገባውን ማንኛውንም ሸቀጥ በመከልከል ጉሮሮአችንን ለማነቅ እየተንቀሳቀሱ ነው ነው የሚል

የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ ይደመጥ ነበር። ይህን የሰሙ ኢትዮጵያውያን ኤርትራውያንና የተወሰኑ የሻዕቢያ አባላትት እጅግ ተደናግጠው ምን እየተደረገ እንው? ይህ የፕሮፖጋንዳ ዘመቻስ ወዴት እያመራ ነው?”

የሚል ስጋት አድሮባቸው ነበር። ኢሳያስ የመጨረሻውን ስብሰባ ከኛ ጋር ሲያደርግም “የዚህ ዓይነት ዘመቻ እየተኪያሄደ ያለው

ለምንድነው? ብለን ስንጠይቀው ለጥያቄያችን ያህን ያህል ክብደት ሳይሰጠው “የምታነሱት ነገር በሚዲያ ሲተላለፍ ባልሰማም ሰዎች

ሲንጫጩ ሰምቼ እስቲ በቴሌቪዥን የተላለፈውን አሳዩኝ ብዬ ምጽዋ ላይ ተመልክቼው ነበር። የተላለፈው መልዕክት ትንሽ የተጋነነ ቢሆንም

መሠረታዊ ስህተት ግን አላየሁበት። አሁንም ትግራይ ጉሮሮአችንን ለማነቅ እየተንቀሳቀች ነው። ብሎ አረፈው። 256

ወደ ገጽ 12

ወደ ገጽ 10

Page 7: መልካም አዲስ ዓመት ይሁንልን! · ዘኢትዮጵያ ጋዜጣ Zethiopia Ethiopian American Community News NO.86 Sept 2014 202 518 0245 P.o.box 2049, Fairfax, VA
Page 8: መልካም አዲስ ዓመት ይሁንልን! · ዘኢትዮጵያ ጋዜጣ Zethiopia Ethiopian American Community News NO.86 Sept 2014 202 518 0245 P.o.box 2049, Fairfax, VA

ዘኢትዮጵያ ጋዜጣ Zethiopia Ethiopian American Community News NO.86 Sept 2014 202 518 0245 P.o.box 2049, Fairfax, VA 22031 www.zethiopia com8

ገበታ ምግብ ቤት በንጽህና በምግብ ጥራትና መስተንግዶ ተወዳዳሪ ያልተገኘለት ልዩ የኢትዮጵያውያን ምግብ ቤት

በሜሪላንድ ሲልቭር ስፕሪንግ ከወዳጅ ዘመድ ጋር ይምጡ ጥሩ መስተንግዶ ይጠብቅዎታል

ኬተሪንግ ወይም ቱጎ ማዘዝ ከፈለጉ ይደውሉ 301-588-0000አድራሻችን 8123 Georgia Ave. Silver Spring MD, 20910

202 518 0245

Page 9: መልካም አዲስ ዓመት ይሁንልን! · ዘኢትዮጵያ ጋዜጣ Zethiopia Ethiopian American Community News NO.86 Sept 2014 202 518 0245 P.o.box 2049, Fairfax, VA

ዘኢትዮጵያ ጋዜጣ Zethiopia Ethiopian American Community News NO.86 Sept 2014 202 518 0245 P.o.box 2049, Fairfax, VA 22031 www.zethiopia com 9

መምህር ዶ/ር ዘበነ ለማመምህር ዘበነ በመስጠት ላይ ስለሚገኙትና ሊሰጡት ስላሰቡት አገልግሎት ተጠይቀው ከፊሉን እንዲህ ብለው ዘረዘሩ-

ዓርብ ዓርብ በደብረ ገነት መድኃኒዓለም የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ይሰጣል። እሁድ ከቅዳሴ በኋላ ሁልጊዜ ሰፊ ትምህርት ይኖራል። ቅዳሜ ከሰዓት በኋላ በኒው ዎርድል ሬዲዮ ላይ ከ4-5 ሰዓት ያለው የሬዲዮ ዝግጅታችን አለ። ሰኞ ሰኞ ጉባኤ ከሳቴ ብርሐን፣ በ4646 ሴሚናሪ ላይ ያለው፣ በጣም ብዙ ህዝብ በየሳምንቱ እየመጣ የሚማርበት ነው። የሚሰጠውም ትምህርት በሥጋ እንዴት መኖር ይቻላል ከዚያም በላይ ሰማያዊ መንግሥትን እንዴት መውረስ ይቻላል ለብዙዎች ተስፋ የሆነው እግዚአብሔር ስለሆነ ያ እግዚ አብሔር እንዴት ነው ተስፋ የሆነው የሚለው እሱ ይሰጣል። ከዚያ ውጭ ግን ሜሪላንድ ያሉ ሰዎች፣ ዲሲ ያሉ ሰዎች፣ ጧት እሁድ የተለያዩ ቤተከርስቲያናት ነው የሚሄዱት። የሰኞ ጉባኤ የሚርቃቸው ሊኖሩ ይችላሉ። ስለዚህ በተወሰነ ጊዜ ዲሲ ጉባኤ ተደርጎ አንድ ቦታ ላይ ሁሉንም ሰው እየጠራን ጉባኤ ለማድረግና ለማስተማር እንደሱ ዓይነት እቅዶች አሉኝ። በፊት ሜሪላንድ ረቡዕ ረቡዕ አስተምር የነበረው ከትምህርቴ ጋር አልሄድ ብሎ ነበር እሱ ተቋርጧል። አሁን ግን በተወሰነ ጊዜ የማስተማር ሀሳብ አለኝ። አብረውኝ ብዙ መምህራን አሉ እዚህም ደግሞ ከነሱም ጋር እየሆነን ከእውነተኛ መምህራን ጋር ሆነን እውነተኛ ትምህርት ለመስጠት እንተጋለን።

ዘኢትዮጵያ- ካህን ስለሆኑ በቅስናቸው የቅዳሴ አገልግሎት አለባቸው። በዚያ ላይ የደብሩ አስተዳዳሪ ናቸው። አሁን ደግሞ መጽሐፍትን በማዘጋጀት ሥራ ላይ ተጠምደዋል። የማስተማር አገልግሎቱ አልተቋረጠም። ወደ ተለያዩ ጉባኤዎቹ መጓዛቸው እንደተጠበቀ ነው። በዚህ ዓመት እንኳ አውሮፓ ቢያንስ 6 ጊዜያ ያህል ለመጓዝ እቅድ አላቸው። በዚሁ ዓመት በየስቴቱ ለመሄድና በወር አንዴ ወጣ እያሉ አንድ 10 የሚሆኑት ቦታዎች ተዘዋውረው ለማገልገልም እየተዘጋጁ ነው። የሚቀጥለው ጥያቄ ቀረበላቸው፤-

እንግዲህ መምህር- ትምህርቱም አለ፣ መጽሐፍ መጻፉም አለ፣ ያው ቤተሰብም ያለ ይመስለኛል። ለመሆኑ ጊዜው እንዴት ነው የሚበቃው? ከየትስ ነው የሚመጣው? ወይስ ጌታ እንደ ወይንጠጁ ጊዜውንም ይባርከዋል ?

መምህር ዘበነ - (ሳቅ) እሱን በተመለከተ ብዙ ጊዜ አንድ አባባል አለኝ እዚህ አገር ብዙ ነገር አይተህ ከሆነ ሁሉም ነገር የተባረከ ይመስልሃል። ምግቡም ውሃውም የሚጠጣው በትልልቅ እቃ ነው። ከሁሉም ግን ሰዓትና ጊዜው አልተባረከም። እንዴት እልም እልም እንደሚል ይታያል። እና እንደው እግዜአብሔርን ስለማመስግነው በእቅድ ስለማደርገው ጊዜዎች ይኖራሉ። እና አንዳንድ ሰው በጣም ይገርመዋል። እና እንዴት ነው እንዲህ እያገለገልክ እንደገና ተምረህ ይላሉ። በተለይ በምርቃቱ ቀን የሆነውን የተመለከቱ አንዳንድ የቤተከርስቲያኒቱ ትልልቅ ሰዎች አሉ፣ እና ሲቀልዱ እንዴ ምንድነው መምህር ላንተ ሰዓቱን ያበዛዋል እንዴ 12ቱን ሰዓት 24፣ ሃያ አራቱን ቱን 48 ያደርግልሃል እንዴ ይላሉ። ምክንያቱም ማህበረሰባችን ሰፊ ነው፣ ለቅሶ አለ፣ የታመመ ሰው አለ፣ ክርስትና አለ በርግጥ አንዳንድ ጊዜ ያልደረስኩላቸው ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ ያን ማድረግ ባለመቻሌ በቃ በውስጤ ይሰማኛል። ይህም ሆኖ ግን አሁንም እግዚአብሔር ባመቻቸልኝ መጠን እሱን ማድረግና ለሚፈልጉኝ መድረስ እፈልጋለሁ። ግን እግዜአብሔር ይመስገን አሁንም ኢትዮጵያ ብዙ ቤተክርስቲያናት እናሰራለን። ብዙ ቦታ ላይ በጣም በጣም ጥሩ ጥሩ ነገሮች እናደርጋለን። ችግረኞች እንረዳለን ይህ ሁሉ አለ። እና እግዚአብሔር በሁሉም ነገር ላይ እጁን ሲልክ ነገሮች ይከናወናሉ። እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ሁሉንም እግዚአብሄር ያሳካዋል።

"ይህንን ትምህርት ሳየው የኛ አባቶች ፍልስፍና በጣም ረቆ ይታየኛል። ይበልጥ ከእግዚአብሔር ጋር የተገናኘ

ሆኖ ምጡቅ ነው።"

ባለፈው ዘኢትዮጵያ ጋዜጣ እትማችን በበርካታ የኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አማኞች ዘንድ የሚታወቁት መምህር ዶ/ር ዘበነ ለማ፣ ሜይ 2014 ዓም፣ ትምህርታቸውን ከተከታተሉበት ከሐዋርድ ዩኒቨርስቲ፣ በሊደርሽፕ (ሥነ አመራር) ፣ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን ከፍ ካለው ማዕረግ ጋር መቀበላቸውን መዘገባችንና ያደረግንላቸውን ቃለመጠይቅ ይዘን እንደንምቀርብ መግለጻችን ይታወሳል። መምህሩ በሐዋርድ ዩኒቨርስቲ ቆይታቸው በሁሉም ኮርሶችና ሴሚናሮች የላቁ ውጤቶችን ማስመዘገባቸውን፣ ለፒ. ኤች.ዲ ያቀረቡት ጥናታዊ የምርምር ጽሑፍም (PHD dissertation) ከሌሎቹ ተማሪዎች ልቆ መገኘቱ በዩኒቨርስቲው የምርቃት ሥነ ሥርዓት ላይ ተገልጾላቸዋል። ይህ ትምህርትና ተጨማሪ እውቃተቸው በወደፊቱ የመንፈሳዊ አገልግሎታቸውና እቅዶቻቸው ላይ ስለሚኖረው ጠቀሜታና እስካሁንም ያስገኙላቸውን ጥቅሞች አስመልክቶ በህይወት ታሪካቸውም ዙሪያ ጭምር ያደረግነውን ትምህርታዊ ቃለ መጠይቅ የመጀመሪያ ክፍል ይዘን ቀርበናል።

ዘኢትዮጵያ- ጤና ይስጥልኝ መምህር

መምህር ዘበነ- ጤና ይስጥልኝ ደረጀ ዘኢትዮጵያ

ዘኢትዮጵያ- ሠርፀ ድንግል ነው?

መምህር- ምን?... የክርስትና ስም ነው?

ዘኢትዮጵያ- አዎ!

መምህር ዘበነ- አንተ ቄስ አይደለህ የክርስትና ስም ምን ያደርግልሃል? (ሳቅ)... ሠርፀ መድኀን ነው። ሠረፀ ወጣ ማለት ነው መድኀን ማለት መድሃኒት ማለት ነው።

ዘኢትጵያ- ለምንድነው የክርስትና ስም ያስፈለገው? በቤተርክስቲያን ይሰጠናል፣ የምንጠራው ግን በየስማችን ነው።

መምህር ዘበነ - ሁለት ልደት አለው ሰው። የዮሐንስ ወንጌል 3 ላይ ጌታ ለኒቆዲሞስ እንደሚነግረው የሥጋ ልደት አለ፣ የመንፈስ ልደት አለ። የሥጋ ልደት ከእናት ከአባት ነው። አንድ ሰው ሰው የሚሆነው ከአባት ወገን ዘር ይከፈላል፣ ከእናት ወገን ደግሞ ደም ይወሰዳል። በአርባ መልክ ተስዕሎ መልክ ይቀረጽለታል። የዚያን ጊዜ ከእናት ከአባቱ 9 ወር ከአምስት ቀን ሲሞላ ይወለዳል። ሲወለድ ስም ይሰጡታል። የራሳቸው ስም መጠሪያ የተጽዕዎ ስም የሚባለው ይሰጠዋል። ኋላ ደግሞ ወይ በአርባ ወይ በሰማንያ ቀኑ ቤተመቅደስ ሄዶ ከመንፈስ ቅዱስ ይወለዳል። ከማኀፀነ ዮርዳኖስ፣ ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ ይባላል። ልክ ዮርዳኖስን እንደ እናት ማህፀን፣ መንፈስ ቅዱስን ደግሞ እንደ አባት ዘር ወስዶ ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ (አብራክ ማለት ጉልበት ማለት ነው) ይወለዳል። ያኔ ደግሞ ስም ይሰጠዋል። መነሻው ጥንትም በብሉይ ዘመን ጌታ ስም እየለወጠ እግዚአብሔር ስም እየለወጠ የሚጠራቸው ሰዎች ነበሩ። ለምሳሌ አብራም ነበር የአብርሐም ስም ። አብራም ማለት አባት እንደ ማለት ነው። አብርሐም ማለት ግን አበ ብዙሃን ማለት ነው። ያዕቆብ የሚለው ስም እስራኤል ወደሚለው ስም ተቀይሯል። ያዕቆብ የሚለው አቃፄ ሰኮና- ሰኮና እግር የሚይዝ- ሲወለድ የኢሳውን እግር ይዞ ነው የወጣው። በኋላ ግን እግዚአብሔር ስሙን ቀይሮ እስራኤል ይለዋል። ወደ አዲስ ኪዳን ስንመጣ ስማቸውን ይቀይራል ለምሳሌ ኬፋ የነበረው ስምዖንን ጴጥሮስ ብሎ ይጠራዋል። እና የተመለደ ነው። የእግዚአብሒር ክብር በኛ ላይ እንዲያድር ሲባል ክርስትና ስም በዚያ ምክንያት በቤተክርስቲያን ይሰጣል።

ዘኢትዮጵያ- አሁን መምህር ነው የምትባለው፣ ትምህርት ቤት ከመግባትህም በፊት መምህር ነበርክ።

መምህር ዘበነ- አዎ አስተምር ነበረ። በልጅነት ጀምሮ ነው። በህፃንነት ጀምሮ ነው ቤተከርስቲያን ያደግኩት። ግን ንባብ እየተማርኩ የቤተከርስቲያንን ሥርዓቷን ሁሉንም ቅዳሴውንም ዜማውንም እየተማርን አድገን፣ ጎን ለጎን ደግሞ ዘመናዊውን ትምህርት እየተማርን በኋላ ደግሞ በአዲስ አበባ መንፈሳዊ ኮሌጅ (Theology Collage) ሲከፈት፣ እዚያ ደግሞ ለአምስት ዓመት ተከታትዬ ስንወጣ “ሑሩ ወ መሐ” “ሄዱ አስተምሩ” በሚል መምህር የሚል ቅጽል ተሰጥቶን ለሁላችንም አንድ ነገር ገንዘብ ስናደርግ የሚሰጠን ስም ነውና መምህር ተብዬ ነው የምጠራው አሁንም እንደዚያ ተብዬ እጠራለሁ።

ዘኢትዮጵያ- መምህር ከመባላችሁም በፊት ትምህርት ቤት እያላችሁ ግን

ዘኢትዮጵያ ጋዜጣ202-518-0245

ደቀመዝሙር ነበር የምትባሉት የነበረው?

መምህር ዘበነ- አዎ እዚያ ውስጥ ሆነን ደቀመዝሙር ነበር የምንባል የነበረው።

ዘኢትዮጵያ- ግን የሕይወት ታሪክህ እንደሚያስረዳው እየተማርክም ታስተምር ነበር።

መምህር- አስተምር ነበረ። በፊትም ከመግባቴ በፊት አስተምር ነበር።

ዘኢትዮጵያ- እና ያኔ ስታስተምር ምን ትባል ነበር?

መምህር- ዲያቆና ነው። በዲያቆን ነው። ዲያቆን ተብዬ ነበር የምጠራው። ከልጅነት ጀምሮ በክህነት ነው። ድቁና ክህነት ነው። ክህነት ድቁና ቅስና ጵጵስና ነው። ሶስቱን ነው።

ዘኢትዮጵያ- በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተከርስቲያን መምህር ለመባል እንዴት ነው አሰያየሙ? ማንስ ነው መምህር የሚለው፣ የእናንተ በትምህርት ቤት ገብታችሁ ስለሆነ ነው።

መምህር ዘበነ- ራስ በራስ አይሰየምም። በአብነት ትምህርት ቤት ዜማ አቋቋም ቅኔ ብሉይ አዲስ አለ፣ የሊቃውንት አለ፣ መጽሐፈ መነኮሳት አለ፣ በእነዚያ ተምሮ በማስተማር ላይ ያለው መምህር ነው አስመክስሮ፣ እንደዚሁ ደግሞ በቤተክርስቲያን በማስተማር የሚሰጠው በዚያው በቤተክርስቲያኒቱ ነው። በእንደዚሁ ደግሞ ሁለቱንም አጣምረው የሚይዙም አሉ- የአብነት ትምህርቱን፣ የዘመናዊ ትምህርቱን፣ የቲዮሎጂካል የምንለውን ይሄ የሥነ መለኮት አስተሳሰብውንና ፍልስፍናውንም የሚይዙት፣ ሲወጡ መምህራን ናቸውና ቤተከርስቲያኒቱ ራሷ መምህር ትላቸዋለች። እንጂ በራስህ ዝምብለህ ለራስህ አትሰጥም። መቶ አለቃ ብሎ ራሱን የሚሰይም የለም። ካልተሰጠው በስተቀረ።

ዘኢትዮጵያ- አሁን ከትምህርት ቤት ከወጣህ በኋላ ተመልሰህ ትምህርት ቤት ገብተህ በመንፈሳዊም በዓለማዊውም ትምህርት በኩል እየገፋህ ነው። ያው መምህር ነው የምትባለው አሁንም?

መምህር ዘበነ- አሁንም መምህር ነኝ፣ በክህነቴ ደግሞ ቀሲስ ነኝ።

ዘኢትዮጵያ- ይሄ መምህርነት እስከመጨረሻው ይቀጥላል ማለት ነው ?

መምህር ዘበነ- አዎ እስከመጨረሻው ይቀጥላል

እንደሱ ነው የሚባለው።

ዘኢትዮጵያ- አሁን የፒ ኤች ዲ (የዶክትሬቱ) ተጨምሮ ባለፈውም ጋዜጣውም ላይ እንዳልነው መምህር ዶ/ር ዘበነ ለማ እያልን ነበር። እግንዲህ እየረዘመ ሊመጣ ነው።

መምህር ዘበነ- መምህር ዘበነ የሚለውን እወደዋለሁ እኔ...

ዘኢትዮጵያ- አዎ እኛ ደግሞ ዶ/ር መምህር የሚለውን ልንወደው እንችላለን ላጻጻፍ...ልማዱም ስለሆነ ይሆናል እንደዚያ ብሎ መጥራት። ወደ ትምህርቱ እንምጣና በምንድነው የተመረቅከው የማስተርሱንም ጨምረህ ንግረን፤

መምህር- እንግዲህ አዲስ አበባ ላይ እንዳለ ቲዮሎጂ በሚል የሥነ መለኮት ትምህርት እንማራለን። ከዚያ ቀጥዬ የተማርኩት በማስተርሱ ላይ ስለ ዓለም ሐይማኖቶች ፍልስፍናና አስተሳሰብ (world religions and philosophy) ማለት ነው። የፍልስና ትምህርት ነው ማለት ይቻላል። በማስተርሱ እሱን ነው። አሁን ደግሞ በፒ ኤች ዲው ላይ በዚህ በሊደርሺፕ ላይ አጠቃላይ የሥነ አስተዳደርን ነገር በተመለከተ ለማንኛውም ድርጅት ለመንፈሳዊውም ሆነ ለዓለማዊም ይሆናል፣ አጠቃላይ እሱን በተመለከተ በእሱ ጉዳይና በዚህ ደግሞ በቢሊካል አርኪዮሎጂ (Biblical archaeology) በያዘ እነዚህ ነገሮች ላይ ነው እንግዲህ ጥናቱ። ስለዚህ ማስተርሱ የዓለም ሐይማኖትና ፍልስፍና ሲሆን በዶክትሬት ጥናቱ ደግሞ በሊደርሺፕ ላይ ያተኮረ ነው።

ዘኢትዮጵያ- እስቲ እነዚህ ነገሮች እንያቸው። ምን ማለት ናቸው? እያንዳንዳቸውን በአጫጭር እንኳ ብናያቸው

መምህር ዘበነ- እንግዲህ ወርድል ሪሊጅን አንዱን እምነት ብቻ የሚመለከት ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ የዓለም ሐይማኖት ምንድነው? ምንድነው መነሻው? አንድ ሰው ለማመን ራሱ ምንድነው መነሻው? ለምንድነው የምናምነው? ማንን ነው የምናምነው? የሚለው አንድ ትልቅ ነገር ነው። እና የዓለም ሐይማኖቶች የዓለም እምነቶች፣ ጥናት ስንለው ቅድመ ልደሰት ክርስቶስ የነበሩ እምነቶች አሉ። እግዚ አብሔር በርግጥ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተከርስቲያን እሳቤ መሠረት ሶስት ናቸው ሕግጋቱ ደረጃቸው። አንደኛው ሕገ ልቦና የሚባለው ነው፤ ሁለተኛው ሕገ ኦሪት የሚባለው ነው፤ ሶስተኛው ሕገ ወንጌል የሚባለው ነው። ከሌላው ዓለም ይኸኛው ለየት ያለ ነው። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ

ቤተክርስቲያንና አስተሳሰብ ትንሽ ለየትና ረቀቅ ያለ ነው። ሕገ ልቦናው ላይ አንዳንድ ፈላስፎች ቀድመው የሚያስቡት ህሳቤ አለ። በጥንት ግሪክ። እና የኛ ትንሽ ለየት ያለ አለ። በዚህ ሲቀመጥ በዓለም እምነቶች ስናይ እንዳልኩህ ቅድመ ልደተ ኢየሱስ የነበሩ እምነቶች አሉ፤ ሂንዱይዝም እምነት አለ። መስራቹ ብዙም አይታወቅም ማን እንደመሠረተው። ግን ቅድመ ልደተ ክርስቶስ 6ኛው ላይ ነው። ከሂንዱ የወጣው ቡድሐ የመሠረተው እምነት አለ። የቡዲዝም እምነት ነው። ከዚያ ውጭ የኮንፊሺየስ አስታሰብ በቻይና እንደምነት ነው። ዞራስተር (zoroaster) በፕርሺያ የመሠረተው አስተሳሰብ አለ። ስለ ዞራስተር

ኒቼ (Niche) ዞራስተር ተናገር በሚል የራሱን ሀሳብ እንደ ዞራስተራ አስተሳሰብ አድርጎ የጻፈው አለ። ዞራስተር ቅድመ ልደተ ክርስቶስ የነበረ ነው። ኒቼ ደግሞ የቅርብ ሰው እና ዞራስተር ራሱ የመሠረተው አስተሳሰብ አለ። እምነት ነው። የእምነት መሪ ነው።

ከዚያ አልፈን ሽንቶይዝም የሚባል እምነት አለ፣ ጃይኒዚም የሚባል እምነት አለ። እንዳለ ዝምብሎ ደግሞ በጥንት የሚታመነው ይሄ የጥንቱ -ፕሪሚቲቭ የሚባሉ ደግሞ አሉ። ዝምብሎ በተለያየ ነገር የሚያመልክ ሰው ይኖራል። እና ያን እምነት ነውና እነዚህ እምነቶች ምንድነው መነሻቸው? አስተሳሰባቸው? እነማንናቸው የመሠረቷቸው? የሚለው ከፍልስፍናው ጋራ አንድ ላይ ነው በማስተስርስ ደረጃ ስንማረው በሱ ደረጃ ነው። ከክርስቶስ ልደት በኋላ ለምሳሌ ብዙ ዓይነት እምነቶች አሉ። ለምሳሌ ቅድም ያልኩህን ሶስቱን ሕግጋት በኢትዮጵያ ውስጥ የተቀመጡትን እንዳለ ወደ ጎን ትቻቸው በኛ ያለውን ከዚያ በኋላ በተለያየ ጊዜ የሚነሱ እምነቶች አሉ።

በጣም በሚገርመው ሁኔታ እስካሁን እምነቶች ይጀመራሉ። ለሰይጣን ራሱ እምነት አለው። ወደ 1960ዎቹ አካባቢ የነበረ Anton Szandor Lavey የሚባል ታዋቂ ጸሐፊና የሙዚቃ ሰው ለሰይጣን መጽሐፍ ቅዱስ ጽፎለታል። ዘ ሳታኒክ ባይብል (The Satanic Bible) በሚል የራሱ ተከታዮች አሉት ቁጥራቸው ይታወቃል። እና ምንድነው ሰውን ሊያምን እንዲያስነሳው የሚያደርገው ለሚለው ጥያቄ አንዳንድ የሚነሳ አስተሳሰብ አለ። አንዳንድ የኒዩሮ ሳይንስ (Neuroscience) ተመራማሪዎች ይህን ይመራመራሉ። ለምሳሌ በጣም አንድ ጥሩ መጽሐፍ አለ፤ ዶ/ር አንድሩ ኑበርግ የሚባል ሰው የጻፈው ። ወደ ገጽ 10

Page 10: መልካም አዲስ ዓመት ይሁንልን! · ዘኢትዮጵያ ጋዜጣ Zethiopia Ethiopian American Community News NO.86 Sept 2014 202 518 0245 P.o.box 2049, Fairfax, VA

ዘኢትዮጵያ ጋዜጣ Zethiopia Ethiopian American Community News NO.86 Sept 2014 202 518 0245 P.o.box 2049, Fairfax, VA 22031 www.zethiopia com 10

በአቶ ከባዱ በላቸው

የዘኢትዮጵያ ጋዜጣንየዓመት ደንበኝነት ይግዙ 202-518-0245

ክሎዚንግ ወይም ሴትልመንት(ካለፈው የቀጠለ)

የቤት ባለቤትነት

አቶ ከባዱ በላቸው ባላቸው መደበኛ ሥራቸው ሶስተኛው የሞርጌጅ ተቋሚ በሆነው ፋኒሜ (Fannie Mae) ሲሆን በተደራቢነትም ከዚሁ ጋር በተተያያዘ የቤት ግዢ እና ሽያጭ ኤጄንት እንዲሁም የሪል ስቴት የኢንቨስትመትን ባለሙያ ናቸው። በዚህ የስራ መስክ ከ10 ዓመት በላይ ልምድ አላቸው። አቶ ከባዱ አሜሪካ ከምትሰጣቸው እድሎች አንዱ እና ዋነኛው የቤት ባለቤትነት ነው ብለው ያምናሉ። ኢትዮጵያዊው ማህበረሰብ ይህንን መጠቀም እና የራሱን ወይም የቤተሰቡን የገንዘብ/የሀብት አቋም ማጠናከርም ይችላል ብለው ያምናሉ። ሪል እስቴት እንደማንኛውም የንግድ ዘርፍ ተጠንቅቀው እና ተግተው ከሰሩበት ጥሩ የኢንቨስትመት ዘርፍም ሆነ ተጨማሪ የገቢ ምንጭ ሊሆን ይችላል ይሉናል። ካላቸው ልምድ ተነስተው ይህን የአሜሪካን ድሪም እንዴት ማሳካት እንደሚቻል በዚህ አምድ ተከታታይ ምክር ይለግሱናል።

American Dream

ክሎዚንግ ወይም ሴትልመንት ተብሎ የሚጠራው የቤት ግዢና ሽያጭ የሚከናወንበት የመጨረሻው ሂደት ሲሆን የንብረት ባለቤትነት (ታይትል) ከሻጭ ወደ ገዢ የሚዛወርበት እና ግዢው በብድር (ሎን) የሚካሄድ ከሆነ ገዢው የቤቱን ታይትል ለብድሩ ማሰተማመኛነት (ሞርጌጅ ወይም ዲድ ኦፍ ትረስት ) የሚሰጥበት ክንውን ነው።

ሴትልመንት የሚከናወንበት ቀን እና ሰዓት ቀደም ሲል ሻጭ እና ገዢ በድርድራቸው ወቅት የተስማሙበት ቀን ይሆናል። ካቅም በላይ የሆኑ ወይም አስገዳጅ ሁኔታዎች ካጋጠሙ ይህንን ቀን በስምምነት ማዘዋወር ይቻላል። ይህን የሽያጭ እና ገዢ ስምምነት ወይም የንብረት ዝውውር የሚያስፈጽመው ድርጅት (ሴትልመንት ወይም ክሎዚንግ ካምፓኒ) ለዚህ የመጨረሻ ውል መካሄድ የሚያስፈልጉትን ቅድመ ሁኔታዎች አጠናቆ መፈረም እና መመዝገብ (ሪከርድ መደረግ) የሚገባቸውን ቅፆች (ሴትልመንት ዶክመንቶች) አዘጋጅቶ በሁለቱም ወገኖች እንዲፈረሙ በእለቱ ያቀርባል። በተጨማሪም ገዢው ግዢውን ለማካሄድ ከአበዳሪ ባንክ ገንዘቡን የሚበደርበትን የህግ ሰነድ (ሞርትጌጅ ዶኩመንት) ከአበዳሪው ባንክ በሚያገኘው መሠረት ለተበዳሪው ፊርማ በዚሁ ጊዜ ያቀርባል።

አበዳሪው ባንክ በክሎዚንግ ቀን ቀደም ብሎ የሚወሰዱትን የብድር ዓይነት (ተርምስ)፣ መጠን (አማውንት) የክፍያውን ዝርዝር (ፔይመንት ብሬክዳውን) እናን ሌሎችንም የውሉ ባህርዮች (ሎን ተርምስ) የሚያስረዳ ቅጽ (ትሩዝ ኢን ሌንዲንግ የሚባለውን ቅጽ) ሊልክልዎ ይገባል። እንዲሁም ሻጭ እና ገዢ የሚከፍሏቸውን የተለያዩ የሴትልመንት ክፍያዎች (ክሎዚንግ ፊስ) በዝርዝር የሚያሳይ የቅድሚያ ግምት ሰነድ (ጉድ ፌዝ ኢስትሜት) አስቀድሞ ሊልክላቸው ይገባል። ይህ ከሆነ ሻጭም ሆነ ገዢም ጥያቄ ወይም መስተካከል ያለበት ነገር ካጋጣማቸው ከክሎዚንግ ቀኑ በፊት ተነጋግረው ከጨረሱ በኋላ በዕለቱለት አዲስ (ሰርፕራይዝ) እንዳይሆንባቸው እና የክሎዚን ሥርዓቱ ፈጠን ብሎ እንዲካሄድ ይረዳል።

የቤት ሽያጭ እና ግዢ በሚካሄድበት ጊዜ የሚከፈሉ በጣም በርካታ የተለያዩ ክፍያዎች (ፊስ ኤንድ ቻርጅስ) አሉ። ከእነዚህ በጥቂቱ የባለቤትነት ማረጋገጫ ምርመራ ክፍያ (ታይትል ሰርች ፊ) ፣ የባለቤትነት ኢንሹራንስ (ታይትል ኢንሹራንስ) ክፍያ ፣ የመመዝገቢያ (ሪከርዲንግ ፊ)፣ የባለቤትነት ዝውውር ቀረጥ (ታክስ) ክፍያ፣ የአሻሻጭ ድርጅቶች ክፍያ (ብሮከርስ ኮሚሽን)፣ የቤት ግምት ክፍያ (አፕሬዘርስ ፊ) የቤት ምርመራ (ኢንስፔክሽን) ክፍያ፣ የቤት መተማመኛ (ሆም ዋራንቲ) ክፍያ እና ሌሎችም በርካታ ክፍያዎች በሁለቱም ወገን ሊኖሩ ይችላሉ። እነዚህን ክፍያዎች መጠናቸውን እና ማን እንደሚከፍላቸው በዝርዝር የሚያስረዳው ቅጽ በመንግስት የተደነገገው ሀድ ዋን የሚባለው ነው። በዚህ ቅጽ መሠረት ሁሉም ወጭዎች ተደምረው በሽያጭም በገዢም ወገን ያለባቸውን ጠቅላላ ወጪ (ቶታል ክሎዚንግ ኮስት) ያሳያል። በዚህ መሠረት የሚከፍሉት ገንዘብ ካለ በዕለቱ በተረጋገጠ የክፍያ ዓይነት (ባንክ ሰርትፋይድ ቸክ ወይም መኒ ኦርደር) ይዞ መቅረብ ያስፈልጋል።

በክሎዚንግ ቀን መመልከት እና መፈረም የሚኖርብዎ ቅፆች በጣም በርካታ ስለሚሆኑ እንዲሁም ብዙዎች ውስብስብ ያሉ ሊሆን ስለሚችሉ በተቻለ መጠን አስቀድሞ ተረድቶ መቅረብ በዕለቱ ብዙ እንዳይደናገሩ ይረዳዎታል። ያምሆኖ ግን እያንዳንዱን ቅፅ በሚገባ ተረድተው እና ተስማምተው እንዲፈርሙ የክሎዚንግ ኤጀንት ወይም አተርኒው እንዲሁም ቤት ግዢውን የሚረዳዎት ኤጀንትዎ ሊያስረዱዎት ህጋዊ ግዴታ አለባቸው።

በሴትልመንቱ ቀን ከሚከናወኡ ጉዳዮች ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው፤

ሽያጩን ህጋዊ የሚያደርጉ የተለያዩ ቅጾች በገዢም በሽያጭም ወገን ይፈረማሉ።ገዢውንና የገዢው አበዳሪ ባንክ ግዢውን ለመፈጸም የሚያስፈልገውን ገንዘብ በተረጋገጠ ቼክ ወይም በባንክ ዝውውር (ዋየር ትራንስፈር )ያስረክባሉ።

ሻጭ የቤቱን የባለቤትነት ይዞታ (ታይትል/ዲድ) ፈርሞ ባለቤትነቱን ለገዢ ያስተላልፋል።

ሻጭ የቤቱን ቁልፍ ለገዢ ያስረክባል።

ሻጭ ያለበት ቀሪ ብድር ክፍያ (ፔይ ኦፍ አማውንት) እና ጠቅላላ የሽያጭ ክፍያ (ቶታል ክሎዚንግ ኮስት) ከመሸጪያ ዋጋው ተቀንሰው የሚቀረው የገንዘብ መጠን (ባላንስ) ካለ በተረጋገጠ ቸክ ወይም በባንክ ዝውውር በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ውስጥ ይደርሰዋል።

የሴትልመንት ኩባንያው በውሎ መሠረት ለተለያዩ አካላት መክፈል የሚገባቸውን ክፍያዎች (ዲስፐርስመንት) ተከታትሎ ያከናውናል።የቤቱ የባለቤትነት ዝውውር በሚመለከተው ካውንቲ ወይም ሲቲ የህዝብ መዝገብ ቤት እንዲመዘገብ ይደረጋል።

የቤቱን ሽያጭ እና ግዢ ውል የሚያስረዱትን እና የብድሩን ስምምነት የያዙትን ሰነዶች በአግባቡ ከተፈረሙ በኋላ ሙሉ ቅጾቹ ለሽያጭ እና ገዢ ይሰጣሉ።

ይሄ ሁሉ አካሄድ ያለመስተጓጎል ከተፈፀመ ከዚህ ቀን ጀምሮ ቤቱ የእርስዎ (ገዢ) ነው ማለት ነው። የአሜሪካ ምኞት/ህልም (አሜሪካን ድሪም) ከሚባሉት አንዱን እና ዋናውን በማሳካትዎ እንኳን ደስ ያልዎት!

በፊት ለምን እናምናለን የሚል አርቲክል ነበረ፣ በኋላ ላይ ግን በእግዚአብሔር ማመን ጭንቅላትህን ይቀይረዋል የሚል...ሳይንቲስቶች ናቸው እነሱ ተመራምረው የሚያስቀምጡት ነገር አለና... ያንን ነው የምናየው።

ፍልስፍናው ሰዎች ለምን ሊያምኑ ይችላሉ? ምንድነው የሚያምኑትስ የሚለውን ነገር የሚያይ ነው። በፍልስፍናው ረገድ በጣም በርካታ ነገሮች ይኖራሉ። የሐይማኖታዊ ፍልስፍና አለ። ከሐይማኖት ውጭ ያለ ፍልስፍና አለ። ታላላቆቹን የግሪክ ፈላስፎች ለምሳሌ ሶስቱን ሶቅራጥስ ፕሌቶና አርስቶትልን ብናይ እነሱ የተፈላሱፉባቸው ነገሮች አሉ። እነሱ ራሳቸውን ችለው ነው። በሀይማኖቱ ውስጥ ደግሞ አለ። በዚያ ውስጥ ደግሞ ይህንን ትምህርት ሳየው የኛ አባቶች ፍልስፍና ደግሞ በጣም ረቆ ይታየኛል። ይበልጥ ከእግዚአብሔር ጋር የተገናኘ ሆኖ ምጡቅ ነው። በጣም የመጠቀ አስተሳሰብ አለ እና ዛሬ ሳይንሱም ያልደረሰበትን በዚህ በተለይ በሐይማኖት ትምህርት ውስጥ ሳይንስና እምነትን ደግሞ ጎን ለጎን ታያቸዋለህ። አንዳንዱ እንደተቃራኒ ሀሳብ ያያቸዋል። አንዳንዱ ይገናኛሉ ብሎ ያስባል። እኔ ይገናኛሉ ብዬ የማስብባቸው ነገሮች አሉ ይጣላሉ ብዬ የማስብባቸው ነገሮች አሉ። አንዳንድ በዚህ ላይ የጻፍኳቸውም ወረቀቶች ነበሩ በዚህ በትምህርት ቤት ውስጥ። እና ያ ዓይነት

አስተሳሰብ አለ። በአጠቃላይ ይህን የሚመመለከት ነው።

በመጨረሻም አሁን ወደ ተመረቅኩበት ትምህርታዊ ጥናቴ (Doctoral study) ስመጣ ሊደርሺፕ ላይ የተለያየ ዓይነት የሊደርሺፕ ነገር አለ። ሊደርሽፕ ስንል ቃሉ ራሱ የሚለው ምንድነው የሚለው ወሳኝ ነው። አመራር ህግ አለው፣ ሥርዓት አለው፣ የራሱ የሆነ ሳይንስ የራሱ የሆነ ፍልስፍና አለው። ምንድነው ሊደርሽፕ? ሊደርሽፕ ላይ ከቤተሰብ ጀምሮ እያንዳንዱ ሰው መሪ ሊሆን ይችላል። እስከ ትልቅ ድርጅቶችም አገርም እስከመምራት ያለው ያ የመምራት ደረጃ ነው። እና መጽሐፍ ቅዱስም ላይ እንደዚሁ መሪዎችን እናያለን። በተለያየ ነገር በተለይ በዚህ አሜሪካን አገር ሁሉም ዓይነት ፍልፍስና ውስጥ እግዚአብሔር የትኛውም ቦታ ይገባል። አንዳንድ አገሮች ላይ እግዚአብሔር የሚል ነገር ቀድሞ እንዳይጠራ የሚል ነገር አለ። እዚህ ግን ሁሉም ነገር ውስጥ ይገባል። እና ይታያል እና የተለያዩ ዓይነት የአመራር ነገሮች ስላሉ እነዚያን የሚመለከቱ ትምህርቶች ናቸው። መሪዎች ምን መሆን አለባቸው? ምንድነው መለያቸው? ጥሩ መሪዎች አሉ መጥፎ መሪዎች አሉ። ምንድነው የነሱ መገለጫ የሚለውን ነገር ሁሉ የምናይበት ትምህርት ነው በአብዛኛው።

እንደተጠበቀ ሆኖ ስለ አገር ፍቅር ስለ ታሪክ ስለ ባህል ስለ ብሄራዊ ማንነት፣ ስለ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ስለ ሕግ የበላይነት በማውራት የትውልድን አመለካከት ማቃናት እጅግ ጠቃሚ መሠረታዊ የፖለቲካ ሥራ ነው ብዬ እላለሁ።

ዘኢትዮጵያ - በአሁኑ ወቅት በብሄራዊ ማንነት (በኢትዮጵያዊነት) ዙሪያ የትውልዱን አመለካከት እንዴት ብታየው ነው፣ የምታቃናው የተዘናፈ ነገር አለ ማለት ነው?

ቴዎድሮስ - እንግዲህ አሁን በሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት፣ በጫካ እያለ 17 ዓመት፣ በሥልጣን ላይ ደግሞ ለ23 ዓመታት ሲቆይ እንደ አገር በኢትዮጵያዊነት ዙሪያ ከሚያስተሳስሩንን ጉዳዮች ይልቅ፣ በሚያለያዩን የጎሳና የሀይማኖት ጉዳዮች ላይ አትኩሮ በመስራት ላይ ነው። መቸም ለአርባ ዓመታት ያለማቋረጥ በዚህ የፀረ ኢትዮጵያዊነት ፕሮፖጋንዳ ጫና ሥር ያለፈ ትውልድ፣ በኢትዮጵያዊነት ዙሪያ ላይ ያለው አመለካከት አልተዛነፈም ልትለኝ አትችልም። ለዚህ ነው በኢትዮጵያዊነት፣ በአንድነት፣ በብሔራዊ ማንነት በጋራ እሴት ዙሪያ ላይ እሠራ ነበር ያልኩህ።

ዘኢትዮጵያ - አሁን በሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት አንተ በምትለው መጠን፣ ኢትዮጵያዊነትንና ብሔራዊ ማንነትን ለማዳካም እየሠራ ነው ትላለህ?

ቴዎድሮስ - እንዴ! እንዴ! የራሱን የኢህአዴግን የፖለቲካ አደረጃጀትና የመንግሥት አስተዳደር ዘዬውን ተመልከት። ገና ከመነሻው ፖለቲካው በዘር ላይ የተመሠረተ ነው። ፓርቲዎቹ ከኢትዮጵያ ወይም ከህብረ ብሄራዊነት ይልቅ በጎሳ የተደራጁ ናቸው። የአከላለል ሥርዓቱ ራሱ ችግር አለው። ሌላ ስንት ኢትዮጵያዊያንን የሚያስተሳሰርና አንድ የሚያደርግ መንገድ እያለ፣ በዘር ላይ ብቻ የተመሰረተ ነው። አገሪቱ በአሁን ወቅት የጋራ የመግባቢያ ቋንቋ እንዳይኖራትም ተደርጓል። በዚህም ምክንያት የዜጎች በአገሪቱ ተዘዋውሮ የመኖርና የመሥራት መብት በቁሙ ሞቷል። ከዚህ በላይ ብሄራዊ ማንነትን ማዳከም ምንድነው?

ዘኢትዮጵያ - ኢህአዴጎች የሚሉት አገሪቱ በኢኮኖሚ ስታድግ የኢኮኖሚ ትስስሩ አንድነትን ያመጣዋል ብለው ያስባሉ አንተ ምን ትላለህ?

ቴዎድሮስ - ይኸውልህ ተስፋዬ ብሄራዊ ማንነት ወይም ኢትዮጵያዊነት

ህንጻ በመገንባት አይመጣም። አገር የምትሰራው በሰው ልብ ውስጥ ነው። አገርን በሰው ልብ ውስጥ የሚሠሩት ደግሞ ስለ መሪያዎቻችን የምንሰማው ገድል፣ ስለ ኢትዮጵያ የተከፈለው መስ ዋእትነትና ዋጋ፣ ባህሎቻችንን የጋራ እሴቶቻችን ህዝቡ ለዘመናት በፍቅርና በመዋሃድ እንዴት እንደኖረ የሚያወሳውን ታሪክ በማስተማር ነው። አሁን በሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት ግን ከእነዚህ ሁሉ ነገሮች በተቃራኒው የቆመ ነው፡፡ ኢህአዴጎች እንደሚሉት ኢኮኖሚው አላደገም እንጂ፣ አድጎ ቢሆን እንኳ የዜጎችን ኪስ በመሙላት ወደ ዜጎች መድረስ አይቻልም።

ዘኢትዮጵያ - ከብሔራዊ ማንነትና ከኢትዮጵያዊነት በተቃራኒ ስለ መቆማቸው በምን ታስረዳለህ?

ቴዎድሮስ - በጣም ጥሩ። አንደኛ የፖለቲካ ፍልስፍናቸው እሳካሁን እየሰሩበት ያለውና ውጤቱ የትኛውም ብሄር የትኛውን ብሄር እንዲጠላ እንዲፈራና እንዲጠረጠር የሚያደርግ ነው። ሁለተኛ ለኢትዮጵያ ብዙ የሠሩ ዋጋ የከፈሉ ታላላቅ አስተሳሳሪ መሪዎቻችንን የሰሩት ጥሩ ሥራ ከማንሳት ይልቅ በአሉታ መክሰስና በማዋረድ ኢህአዴጎች ብቻ አዲስ ታሪክ አዲስ ነገር የፈጠሩ መስለው ራሳቸውን ያቀርባሉ። የአገር ፍቅር ቁንጮ መገለጫ የሆነው ባንዲራ እንኳ በየክልሉ በመሸንሸኑ የባንዲራውን አንድ የማድረግ ኃይል ለመቀነስ ሞክረዋል። በጣም በርካታ ምሳሌዎችን መጥቀስ እችል ነበር። ዝምብሎ በከንቱ ጊዜ ማጥፋት ስለመሰለኝ ነው። የሚያሳዝነኝ ነገር ግን ከዚህ ሁሉ ዓመታት የስህተት ጉዞ ከመመለስ ይልቅ አገሪቷ ምንም ትሁን ምንም እኛ ብቻ በሥልጣን እንቆይ ማለታቸው ነው።

ዘኢትዮጵያ - ኢህአዴጎች ዓላማችን ብለው የተነሱበት ነገር አለ። እሱም በኢትዮጵያ ውስጥ ለዓመታት የኖረ የብሔር ጭቆና ነበር፣ እኛም ለዚህ ችግር መፍትሔ ሰጥተናል ብለው ያምናሉ። ይህንንም እንደ ስኬት ይቆጥሩታል። እዚህ ላይ ያንተ አስተያየት ምንድነው?

ቴዎድሮስ - መጀመሪያ በኢትዮጵያ ውስጥ ጨቋኝም ተጨቋኝም ብሔር አለ ብዬ አላምንም። የኢትዮጵያ የመደብ ጭቆና እንጂ የብሄር ጭቆና መሠረታዊ ችግር ነበር ብዬም አላምንም። በዚያም ላይ የብሄር ጭቆና አለ ብለው ያወሩ የነበሩ ሰዎች (ባለፈው ዘመን የነበሩ ግራ ዘመም ፖለቲከኞች) የኢትዮጵያን ህዝብ አስተሳሰብ በውል አጥንተው የደረሱበት

ድምዳሜም አልነበረም። እንደኔ እንደኔ የብሔር ፖለቲካ በማንሳት ወደ ሥልጣን ጉዞ ታጋዮችን ለማፍራት ሥልጣን ከያዙ በኋላ ደግሞ ህዝብን ለመከፋፈል የተጠቀሙበት መንገድ ነው።

ዘኢትዮጵያ - ይህን ያህል በሥልጣን ላይ ካለው መንግሥት ፍላጎትና እምነት በተቃራኒ ቆመህ ምንም ችግር አልደረሰብህም ነበር?

ቴዎድሮስ - በርካታ ችግሮችና ተጽእኖዎች ነበሩ። የምስራቸውን ፕሮግራሞች ሳንሱር በማድረግ፣ በመቁረጥና በመቀጠል የፕግራሜን ይዘት የማዳከም ሥራ ይሠሩ ነበር። እነሱ ከፕሮግራሙ የቆረጡትን ነገር በላይቭ ከተናገርኩ ቀጥተኛ ማስፈራሪያና ማስጠንቀቂያም ይሰጠኝ ነበር። ሌላ ሌላ ብዙ ብዙ ችግሮችም አጋጥመውኛል። ከዚህ ሁሉ መከራ በኋላ ሬዲዮ ፕርግራሜን ዘጉት፣ ለራሴም ህይወት የሚያሰጋኝ ደረጃ ስደርስ አገር ለቅቄ ተሰደድኩ።

ዘኢትዮጵያ - የጣይቱ የጥበብና የባህል ማዕከል ባለፈው የኦገስት 2014 ወርሃዊ የግጥም ምሽቱ፣ አንተን እንግዳው አድርጎ ልዩ ዝግጅት አድርጎልህ ነበር ምን ተሰማህ?

ቴዎድሮስ- እዚህ አሜሪካን አገር በኢትዮጵያውያን እንዲህ ዓይነት የአገርህን ባህል ታሪክ የሚያቆይ ሥነጥበብና ኪነጥበብን የሚያበረታታ ዝግጅት መኖሩ በጣም አስደንቆኛል። ይህንንም ዝጅግት ለ14 ዓመታት ደከመኝና ሰለቸኝ ሳትል የምትካሄደውን ተወዳጇን አርቲስት ዓለም ፀሐይ ወዳጆን እጅግ ሳላደንቅና ሳላመሰግን አላልፍም። በነገራችን ላይ በዚያ ዝግጅት በመገገኘት ሰዎች ብዙ ነገር ይማራሉ። ይዝናናሉ፣ አገሬን እወዳለሁ የሚል ሁሉም ኢትዮጵያዊ ይህንን ዓላማ ሊደግፍ ይገባዋል።

ዘኢትዮጵያ - አንተ በግልህ ላንተ የተለየ ዝግጅት መደረጉ ምን ስሜት ፈጠረብህ? መቸም ይህ ዝግጅት የተደረገለህ በህግ ባለሙያነትህ ወይም በጋዜጠኝነትህ ሳይሆን በገጣሚነትህ መሰለኝ?

ቴዎድሮስ - በእነዚህ የጥበብ አፍቃሪ ወገኖቼ መካከል መገኘት በራሱ ትልቅ ክብር ነው። እኔን ለማበረታት ልዩ ዝግጅት መደረጉ ለመገልጽ የማልችለው ደስታ በውስጤ ፈጥሯል። በእርግጥ ጣይቱ የባህል ማዕከል ለኔ ብቻ ሳይሆን ከኔም በፊት፣ ለኢትዮጵያ የሥነ ጥበብ ዘርፍ አስተዋጽኦ ላደረጉና ለማድረግ ለሚሞክሩ ሁሉ ማበረታት ልማዳቸው እ ን ደ ሆ ነ

DR. L. LEWIS WALL, PRESIDENT OF HAMLIN FISTULA USA, AND MR. MARTIN ANDREWS, CEO OF

HAMLIN FISTULA ETHIOPIA, KINDLY REQUEST YOUR PRESENCE AT A CELEBRATION IN HONOR OF

DR. CATHERINE HAMLINFOR HER 90TH BIRTHDAY & 2014 NOBEL PEACE PRIZE NOMINATION

BY HIS EXCELLENCY DR. TEDROS ADHANOM, FOREIGN MINISTER OF ETHIOPIA

SATURDAY, SEPTEMBER 27, 2014

11:00 AM to 2:00 PM

THE RITZ-CARLTON WASHINGTON, D.C.

1150 22ND STREET NW, WASHINGTON, D.C. 20037

$100 CONTRIBUTION PER GUEST

To RSVP visit http://hamlinfistulausa.org/. Space is limited.

Our program will consist of a special message from Dr. Catherine delivered by her granddaughters Sarah and Catherine Hamlin. Mamitu Gashe and several other notable guests will be gathered to support

Dr. Hamlin’s call to eradicate childbirth injuries. We look forward to having you join us in celebrating Dr. Hamlin’s

lifetime devotion to our global mothers. For questions, please contact 202-695-8233 or [email protected]

GRACIOUSLY SPONSORED BY JOHNSON & JOHNSON AND ETHIOPIAN AIRLINES

Dedicated to the treatment, care and prevention of obstetric fistula

For our latest news and to make a donation, please

visit our website at

www.hamlinfistulausa.org

መምህር ዶ/ር ዘበነ... ከገጽ 9

ቴዎድሮስ ጸጋዬ ከገጽ 6

ወደ ገጽ 14

Page 11: መልካም አዲስ ዓመት ይሁንልን! · ዘኢትዮጵያ ጋዜጣ Zethiopia Ethiopian American Community News NO.86 Sept 2014 202 518 0245 P.o.box 2049, Fairfax, VA

ዘኢትዮጵያ ጋዜጣ Zethiopia Ethiopian American Community News NO.86 Sept 2014 202 518 0245 P.o.box 2049, Fairfax, VA 22031 www.zethiopia com 11

People

Blen Corp

Zethiopia - Hello Mike, What’s going on tonight?

Mike: Our Company, Blen Corp, has been around for ten years, so we are celebrating a milestone. But we are also looking forward to the future.

Zethiopia - What is the reason of your celebration?

Mike: It’s the moment in time that we need to pause and reflect up on. Beyond that, it’s a night to network and see good friends. That is really the whole reason we’re doing this.

Zethiopia - You’ve been around for 10 years, what is your greatest accomplishment?

Mike: The last ten years were about the fundamentals - getting the fundamentals of the business right. That is being financially sustainable, building the right team, being able to make sure that you are disciplined about project delivery, getting new contracts and getting the system right. These were our first steps. In the future, we think the down payment we’ve made over the past ten years has the potential for a huge dividend down the line. Our biggest accomplishment is that we

built a solid team that is going to help us move forward. That is the key for any kind of company: to build a solid team.

Zethiopia: So your major accomplishment is to get the business right? And what is your business?

Mike: We do software development and visual communications. We are two-tiered company. We focus on a couple of things. We focus on building a specific technology service to Government or Non-Profit businesses. Based on the project, we try to cater services towards the business, so we are very specific about the kind of project we’re doing. We narrow the number of things we do to two things. It used to be many things to many people. We don’t do that anymore. So we are more focused and project-delivery oriented. And in the long run, that is what’s going to pay for the day. So being an expert in one field is a much better accomplishment for a business.

Zethiopia: Who are you targeting?

Mike: In the biggest sense, the sector that we are targeting is the federal Government. It is the biggest client we have. There are state governments as well. There are large non-profit organizations like the World Bank and IMF- clients we already have. We worked on projects for large Fortune 500 companies and GEICO. It’s a wide range of clients.

Zethiopia: How do you describe your company in terms of staff?

Mike: We don’t get excited when the times are good and we don’t get too low when things are bad. When we actually do our business you don’t see much reaction one way or the other. So when the times are good we don’t react too much and when times are bad we don’t react too much either. As a business we’ve obviously grown. We use to be two-people Company. Now we have 12 people working full time. We have grown enough to helps us propel different things. Ultimately, I think for a service company, especially the IT field, is becoming more and more difficult. So we wanted to become a product company. That is our calling and that’s ultimately what is going to work for us. To that end,

we are building a product right now. The service side of the business is effectively subsidizing the product line that we are building. So we think there is a potential down the line if we get the system right. There is a huge potential for some of the products we are building. We have a patent-pending product right now in the pipe line that we are raising money with venture capital. That is the way we see the future. We build products and we solve big problems. To that end, there are couple of things I will focus on. There are four things that we think is the time for: One is Education, the second is Energy, then Security and Transportation. These are the pillars of any society that we think, if we build the right product the time is actually now. Like Google is the global search engine, we hope to have something like that for education or energy and transportation.

Zethiopia: Are all of your employees Ethiopians?

Mike: Fifty percent of the employees are Ethiopians and the rest are diverse.

Zethiopia: Are they all full time employees?

Mike: Yes. The interesting thing is that there are challenges that nobody tells you about as the business grows, such as how to manage relationships. You have to maintain the timesheets, make sure that everyone is paid on time and all invoices are taken care of. All of these responsibilities are handled between Ephrem and me. As the employees grow, it will become its own entity. But we are not worried about what needs to happen. It’s going to become its own entity as the employees grow. I am not worried about the number of people or employees we have. In all honesty we want to grow for the right reason and with the right people. One of our biggest achievements is building a strong team and we don’t want to disrupt it. Otherwise it’s not worth it. I don’t want to dread it. I want to work with people I like.

Zethiopia: How do you compete with big companies as far as Technology is concerned?

Mike: The biggest competition is

Ten years ago in 2004, a small IT company was formed by two ambitious Ethiopian-American entrepreneurs amid a lot of uncertainties and challenges. Today Bilen Corp is a growing information and technology firm which boasts clients such as State and Federal governments, IMF, world bank and large non-profit organizations. In an exclusive interview with Zethiopia, on June 19, 2014 during their company’s 10-year anniversary celebration, the two founders discussed their challenges, achievements, vision and philosophy. Excerpts are as follow:

Ephrem – Founder of Blen Corp.

Zethiopia: What are you celebrating tonight and why?

Ephrem: We are celebrating ten years of making Blen. A business founded about 14 years ago by Ethiopian-Americans and has survived many things including the economy. We are very proud to celebrate our tenth year in 2014. It’s a big thing for us. You hardly see business making it this long. It is an idea we started about 14 years ago it is like giving birth and it’s growing now.

Zethiopia: Where were you ten years ago?

Ephrem: Ten years ago we started with the Ethiopian community. We didn’t see anything to venture out and start a business in our community especially in our field. That’s what makes it very special. We started with the community and now we are the Ethiopian community and represent Ethiopian community. Looking at 10 years back and looking at where we are now is completely amazing.

Zethiopia: What are you trying to accomplish?

Ephrem: We are trying to accomplish the American Dream. It can happen to someone that is not born in America. We were born abroad and came here because things are not good in Ethiopia. We are not quite there yet but we are in the right path. American dream can be accomplished by anyone. I’m just an average guy, if I can make it anyone can.

Zethiopia: How did Blen Start?

Ephrem: I started Blen as soon as I graduated from college. I graduated from University of Maryland as a graphic designer and Art Studio Major in 2002. It was very difficult to find a job. I had to survive, so I asked myself, why not starts a visual communication company in our community? Things were different back then. It was learning and a teaching experience. My very first print project was with Alemtsehay Wodajo, she was organizing something for Tsegaye Gebremedhen’s event. At the time I didn’t even know what Print Design and Web Design was. It was a learning experience. I’m always grateful for Ethiopian Community business back then. A lot of businesses in the community were starting such as Taytu Entertainment, Ethio Sound, Noam Records and other businesses as well. We did a lot of visual covers for CDs and other print job for the community. We use to be called Blen Graphics. And that’s when the company ignited.

Zethiopia: How did you meet Mike?

Ephrem: We met at the Ethiopian Students Association. He went to Tacoma Park College. I approached him because I heard he used one of my art works and I wanted to know why he used without my permission. Mike happens to be a genius. I’m just an artistic person. Mike does all the implementation.

turn to P13

Mike Endale Ephrem Girma

We are a small, creative team of developers that love technology.

turn to P13

Page 12: መልካም አዲስ ዓመት ይሁንልን! · ዘኢትዮጵያ ጋዜጣ Zethiopia Ethiopian American Community News NO.86 Sept 2014 202 518 0245 P.o.box 2049, Fairfax, VA

ዘኢትዮጵያ ጋዜጣ Zethiopia Ethiopian American Community News NO.86 Sept 2014 202 518 0245 P.o.box 2049, Fairfax, VA 22031 www.zethiopia com 12

Ethiopia Stepping Up Efforts To Show Dam's Benefits To Downstream CountriesThe Ethiopian government will consolidate diplomatic efforts to create awareness among downstream countries -- Sudan and Egypt -- that the Grand Ethiopian Renaissance Dam (GERD) it is constructing will benefit all downstream countries.

The dam is on a stretch of the Blue Nile that runs through Ethiopia.

Ministry of Foreign Affairs spokesman ambassador Dina Mufti told the Ethiopian news Agency (ENA) on Monday April 6/2014, that efforts to make clear that the dam would ensure the benefits of downstream countries would be further strengthened.

He urged the Egyptian government to refrain from the confused stand it had been reflecting and respect the voice of the Ethiopian people.

"The Egyptian government is expected to stop threatening Ethiopia of breaching international principles and realise the benefits the dam provides to the Egyptian people," he said.

Mufti vowed the construction of the dam -- which would be the largest hydro-electric power plant in Africa when completed with capacity to generate 6,000 megawatts of power -- would not be suspended as Ethiopia has full rights to utilise the river's potential.

ዘኢትዮጵያ ጋዜጣ 202 518 0245 P.o.box 2049, Fairfax, VA 22031 www.zethiopia com

ታሪክና ሥነፅሁፍዓለማየሁ ገ/ሕይወት

ባለፈው ወር የዘኢትዮጵያ እትም ቃል በገባነው መሠረት እነሆ ሃገራችንን ከጎበኙ ሰዎች የጉዞ ማስታወሻዎች በጥቂቱ ልናካፍላችሁ ወደድን።

የጉዞ ማስታወሻ ወይም Travel Writing ከኢልብወለድ ዘርፍ የሚመደብ ሲሆን ፀሃፊዎቹ በሚዘዋወሩበት ሃገር ወይም ክፍለ ግዛት የሚያጋጥሟቸውንና ስሜታቸውን የሚነኳቸውን ሁኔታዎች የሚዘግቡበት ነው። ፀሃፊዎቹ የሚጓዙበት ምክንያት ምንም ይሁን ምን፣ በእግረመንገድም እንኳ ቢሆን የሚያነሷቸው ገጠመኞች፣ ታሪኮችና ትዝታዎች በሰው ልጅነታችን ብቻ ሊነኩን ሊማርኩን ይችላሉ። የአንድ ጉዞ ዓላማ ለደስታ፣ ለመዝናናት፣ አዳዲስ አካባቢዎችን ለማወቅና ለማጥናት፣ ለትምህርት፣ ለህክምና፣ ለዘመድ ጥየቃና ለመሳሰሉት ሊሆን ይችላል። የመንግስታቸውን ወይም የድርጅታቸውን ተልዕኮ ይዘው የሚጓዙም ይኖራሉ። ከዚህ ለየት የሚሉት መንፈሳቸው በተጎዳ ጊዜ ከገቡበት ሃዘንና ጭንቀት ለመውጣት ሲሉ አካባቢያቸውን ለቀው የሚሄዱት ናቸው።

እንደ አውሮፓ አቆጣጠር በ1766 “የፈረንሳይና የጣሊያን ጉዞ” የተሰኘ መፅሐፍ ያሳተመው ቶባያስ ስሞሌት ለዚህ ቅርብ ምሳሌ ነው። በደብዳቤ መልክ የፃፈውን ይህን ሥራውን ከመጀመሩ በፊት ከባለቤቱ ጋር ሃገረ እንግሊዝን የለቀቁት በደረሰባቸው ከባድ ሃዘን ምክንያት ነበር። በ1763 የአሥራ አምስት ዓመት ዕድሜ የነበራትን ኤልሳቤጥ የተባለች አንድዬ ልጃቸውን ሞት ይነጥቃቸዋል። በዚህም የተነሳ በቤታቸውም ሆነ በሃገራቸው ከሁለት ወር በላይ መቀመጥ አልቻሉም። ወደ እንግሊዝ ሃገር የተመለሱት በፈረንሳይና በጣሊያን ልዩ ልዩ ከተሞች ለሁለት ዓመታት ያህል ያደረጉትን ጉብኝት ካጠናቀቁ በኋላ ነው። መፅሃፉም የዚሁ ጉዟቸው ማስታወሻ ሆነ። ስሞሌት በማስታወሻው በፈረንሳይ ዋና ከተማ ፓሪስ ሆኖ ከፃፈው በጥቂቱ እንጠቅሳለን።

“ክቡር ሆይ፣ ከቦሎኝ ተነስተን ስላደረግነው ጉዞ ብዙም የምነግርዎት የለኝም። አየሩ ማለፊያ ነበር። መንገዱም ቢሆን ለክፉ አይሰጥም። በሞንትሬልና በአሚየንስ ደህና ማረፊያ አግኝተናል። በቆምንባቸው ሌሎች ቦታዎች ግን የሚበቃንን ያህል አቧራ ጠጥተናል። ስንቱን አፍንጫ የሚወጋ ቆሻሻም ሳንወድ በግድ ታጥነናል። መቼም ስለ አቤቪልና አሚየንስ ከተሞች ለመተረክ አልቃጣም፤ እንዲሁ በእግረ መንገድ ቃኘናቸው እንጂ ብዙ አልቆየንባቸውምና።” እያለ ይቀጥላል።

ከአንድ መቶ ዓመታት በፊት ወደ ሃገራችን ከመጡ የውጭ ሃገር ሰዎች አንዱ የሆነው ዊንስታንለይ “የአቢሲንያ ጉዞ” በሚል ርዕስ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1881 ባሳተመው መፅሃፉ የዘመኑን የሃገራችን ገፅታ እሱ በተመለከተበት መነፅር ያሳየናል። ብዙም ያልታወቀች ስለሚላት ሃገርና ስለ ህዝቧ በዘገበበት በዚሁ መፅሃፉ የተደሰተባቸውን፣ የተገረመባቸውን፣ ያዘነባቸውንና የደነገጠባቸውን ሁነቶች እንመለከታለን። አንዳንድ ጊዜ በተለይ የዚህ ዘመን ትውልዶች የማናውቃቸውን ነገሮች በዝርዝር ይገልፅልናል። ለምሳሌ ያህል ስለ ራስ አሉላ ቁመናና ገፅታ፣ ስለተደረገለት መስተንግዶና ስለተበረከተለት ስጦታ የፃፈውንና በግርድፉ ወደ አማርኛ የመለስነውን ቀጥለን እንመልከት።

“መቼም የራስ አሉላን ቁመና ስመለከት

በጣም ነበር የተገረምሁት:: እንደ እውነቱ ከሆነ እስከዛሬ ካየኋቸው ኢትዮጵያውያን መካከል በመልከ መልካምነታቸውም ሆነ በመላ ፍጥረታቸው እሳቸውን የሚተካከል አልገጠመኝም:: ቁመታቸው መካከለኛ ነው:: እድሜያቸው ወደ ሰላሳ አምስቱ ይመስላል:: የፊታቸው ቅርጥ ሞለል ያለ ነው:: መልካቸው የቀይ ዳማ ሲሆን ጎላ ጎላ ያሉ ጥቋቁር አይኖች አሏቸው:: ሰልከክ ያለ የሚባል አፍንጫቸውና ልከኛ ሆነው የተሠሩት አፍና ጉንጮቻቸው ግርማ ሞገስ ሰጥቷቸዋል:: የጢማቸው በቅጡ አለመያዝ ብዙም አላጓደለባቸውም:: ጠጉራቸው ቢጎፍርም በወጉ የተያዘ መሆኑ ያስታውቃል። አለባበሳቸው ማለፊያ ነው “ እያለ ይቀጥልና የወርቅ ሃብል አንገታቸው ላይ ማሰራቸውን፣ ከቆዳ በተሠራ ቀይ ሰገባ ውስጥ የተከተተ ጎራዴ መታጠቃቸውን ይዘረዝራል:: ወረድ ብሎ ደግሞ፣

“ተተካክለው የተፈጠሩና በጥንቃቄ የተያዙ የሚመስሉ እግሮቻቸው አልተሸፈኑም:: ኋላ ውዬ አድሬ እንደተረዳሁት ሰውየው የኮሩና የደሩ፤ ብዙም በእግር መሄድ የማይፈቅዱ ኖረዋል። እግሮቻቸውን ለክፉ ቀን እንዲያገለግሏቸው የቆጠቧቸው ይመስላሉ። መቼም የአበሾችን ዕድሜ እንዲህ በቀላሉ ማወቅ ያስቸግራል። ራስ አሉላ ከአርባ ዓመት በላይ ናቸው ስባል ማመን አልቻልኩም። ፍፁም አይመስሉም። በራስ አርኣያም ነገር እንዲሁ ተሞኝቻለሁ። ቁመናቸውንና መላ ሁኔታቸውን ስመለከት ከስድሳ ዓመት በላይ ይሆናቸዋል ብዬ እንዴት ልገምት እችላለሁ?! “ ቀጠል አድርጎም፣

“ራስ አሉላ ገና ምልክት ሲሰጧቸው አሽከሮቻቸው ፈጥነው ፈረሳቸውን አቀረቡላቸው። በሃገሩ ወግና ባህል መሠረት ያጌጠ ነው። በዚያ ላይ ማለፊያ ኮረቻ ተጭኗል። ያማረና አለፍ አለፍ ብሎ በብር የተለበጠ ቀሚስ ለብሷል። ፈረሳቸው ላይ ከመውጣታቸውም በፊት ሰላምታቸውንና የንጉሡን በጎ ምኞት ገለፁልኝ። ረዥምና አድካሚ ጉዞ ማድረጌን ጠቁመው አረፍ እንድል ከመከሩኝና በማግሥቱ ጠዋት እንድንገናኝ ቀጠሮ ከሰጡኝ በኋላ ተራራውን ቁልቁል ወርደው ወደ መኖሪያ ቤታቸው አመሩ...” ይለናል። የተስተናገዱበትን የራስ አሉላ ቤት አስመልክቶ ሲፅፍ ደግሞ እንዲህ ይላል።

“ቅጥር ግቢው ከሶስት ሜትር በላይ በሚሆን ቀርቅሃ ታጥሯል። ራስ አሉላ እኛን በተቀበሉበትና ባስተናገዱበት ቤት ዙሪያ ሶስት ወይም አራት ተመሳሳይ ጎጆ ቤቶች ይታያሉ። ቤቱ ፍፁም ንፁህ ነው። መቀመጫዎች ፈንጠር ብለው ተቀምጠዋል። ከቱርክና ከእንግሊዝ ሃገር የመጡ ስጋጃዎችም ተነጥፈውበታል። የቀረበልን ጠጅም እጅግ ግሩም ነበር። እንደው በጠቅላላው ከራስ አሉላ ጋር በቆየሁባቸው ጊዜያት በዙሪያቸው ያሉ ነገሮች በሙሉ ጥራት ያላቸው መሆናቸውን ተገንዝቤያለሁ። ጠጅ የጠጣንባቸው ከቀንድ የተሠሩ ዋንጫዎች እንኳ በብር የተለበጡ ናቸው።”

“... ለአንድ እኩል ሰዓት ያህል ስለመንገዱ ሁኔታ፣ ስለሱዳን ቆይታዬና ስለኢትዮጵያና ሱዳን የአየር ጠባይ በንፅፅር እያወጋን ከቆየን በኋላ “ለመሆኑ ክርስቲያን ነህ?” የሚል ቀጥተኛ ጥያቄ አቀረቡልኝ። ብዙም ሳይቆይ አንዱ አገልጋይ ገብቶ ማረፊያ ድንኳናችን የተሰናዳ መሆኑን ሲናገር እጅ ነስቼ ወጣሁ። ከተዘጋጀልን ድንኳን እንደደረስኩ

ሃያ ያህል ጠባቂዎችንና አንድ የነሱን አለቃ አገኘሁ። ባገር ውስጥ እስካለሁ ድረስም ከእኔ እንደማይለዩ ተነገረኝ። ወደ ውስጥ ስገባ መቀመጫና ምንጣፍም ከቤተመንግስት ተልኮልኝ ኖሯል። ... አብዛኞቹ ምንጣፎች የእንግሊዝ ስሪቶች መሆናቸው በንድፋቸው ይታወቃል። እቃዎቼን በቅጡ አሰናድቼ ገና ሳልጨርስ ከቤተመንግስት የተላኩልኝን ስጦታዎች ዝርዝር የያዘ የንጉሡ መልዕክተኛ መጣና ውጪ በታላቅ ሥነሥርዓት እንድረከብ አሳሰበኝ። በጅሮንድ እንግዳና ረዳቶቻቸው እዉጪ ቆመው ይጠባበቁ ኖሯል። ... የተላከልኝ ስጦታም አራት ሰንጋ፣ ስምንት በግ፣ ስድስት ጠርሙስ ጠጅ፣ ስድስት ቅርጫት ሙሉ አምባሻ፣ ሁለት ጠርሙስ ቅቤ፣ በርበሬ፣ ማር፣ አሥራ ሁለት ዶሮና ወተትም ያካተተ ነበር። ዝርዝሩ ዘለግ ባለ ድምፅ ሲነበብ እቃዎቹ በቅደም ተከተል ወደፊት ይቀርባሉ:: የርክክቡ ሥነሥርዓትም ግንባራቸው መሬቱን እስኪነካ በሚጎነበሱት ሁለት ተወካዮቼ አማካይነት ደመቅ ባለ ሁኔታ ይከናወን ነበር።” ሲል ዘግቧል።

የዛሬውን በዚሁ ከማጠናቀቃችን በፊት ከሃገራችን ደራሲያን መካከል የብላታ ወ/ጊዮርጊስ ወ/ዮሃንስ ምናባዊ ሥራ የሆነው “አግዐዚ፣ ወደ ውጭ አገር ሔጄ ነበር” የተባለ መፅሐፍ ስለ ጉዞና ጥቅሙ የሚለውን እናካፍላችሁ። በ1938 ዓ.ም. በተከታታይ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ፣ በ1961 ዓ.ም. ደግሞ በመፅሐፍ መልክ የታተመው ይህ ታሪክ ቀመስ ልብ ወለድ ለትምህርት ወደ ባህር ማዶ የሚሄድ ወጣትን እይታ የሚወክል ነው። አግዐዚ በሄደበት አገር ከሚያጋጥሙት ነገሮች ባሻገር ስለሃገሩ የሚሰማውን በጎም ሆነ ክፉ እያንሰላሰለ ይተክዛል። ወ/ጊዮርጊስ በሚጣፍጥና ሃሳባቸውን ወለል አድርጎ በሚያሳይ ቋንቋ ከፃፉት ለአብነት ያህል የተወሰኑ አንቀፆችን ቀጥለን እናቀርባለን።

“ሰማዩን በአኤሮፕላን ሲንሸረሸሩበትና ነፋስን እየሰነጠቁ በስንጣቂው ውስጥ ሲተላለፉ ታላቅ እውቀት ይገኛል:: የብሱን በባቡር ሲሽከረከሩት፣ መሬቶችን ሁሉ እያቋረጡ ሲሄዱ ከፍ ያለ ጥበብ ይወረሳል:: ባህሩን በመርከብ ሲንሳፈፉትና የማዕበላትን ወሬሳ አነሳስ እየተከላከሉ ሲታለፍ የሚታየው ትንግርትና የሚገጥምህ አድናቆት ምን ተብሎ ይነገራል::”

“ያላየኸውን ባወራልህ የማትበላው የፆም ምግብ ይሆንብህ ይሆን? ማየቴ ማየት እንዲሆንልህ እንዴት ብየ ልንገርህ? እንዴትስ አድርጌ ላስረዳህ? የነፋሱ አነፋፈስና አንቀሳቀስ ደስታዎች በሰውነትህ እንዲንቀሳቀሱ ያደርጋቸዋል። የማዕበሉ አዘላለል ረድፍ ረድፍ እያበጀ ሲገነፍልና ፈረሰኛውን ፈረሰኛ እየተከታተለው ባህሩን እየለቀቀ በተፈጥሮ ሳይሆን በገዛ ሃይሉ ባበቀለው ክንፍ አግድም ሲንቻረር “የእግዚአብሔር መንፈስ በውሃዎች ላይ ይሰፍ ነበር” የተባለው ቃለ ኦሪት ሲተረጎም ታየዋለህ። ማዕበሉ እንደ ሰገኖ አንገቱን አስግጎ በኋላ እግሩ ቀጥ ብሎ ቁሞ እንደገና በፊት እግሩ ደፋ ሲል በስግደት ላይ የሚገኝ ባሕታዊን ይመስላል። ይህንም ይተወውና ሲያጋፍትና በዳልጋው ልዩ ልዩ ጅምናስቲክ ሲሠራ በተፈጥሮው ፈጣሪውን የሚያመሰግን ተግባር ይፈፀምበታል። ... ፀሃዩና የባህሩ ፅርየት ሲፈካከር አይነ ወርቅ የሆኑ ብልጭልጭታዎችና የዕንቁ ጠቃጠቆ የመሳሰሉ ወራውርቶች እንደ ቢራቢሮ ሲፈናጠዙና እንደ ጅራታም ኮከብ ሲወረወሩ የአይኖችህ ነፀብራቆች አብረው ይወነጨፋሉ።”

ቸር ይግጠመን!

-የጉዞ ማስታወሻ

ለጉብኝት፣ ዘመድ መጠየቅ፣ ለመታከም ለማስታመም፣ በሠርግና ምርቃት ለመገኘት፣ ብሎም ለአጭር ጊዜ ስብሰባም ሆነ፣ የንግድ ጉዳይ ለመፈጸም ከአሜሪካን ኢምባሲ የሚጠየቀው የቪዛ ዓይነት የጉብኝት ቪዛ፣ ወይም ቢ ዋን ቢ ቱ ይባላል።

የቪዛ ማመልካቻው ፎርም፣ (DS 160) እንደ ድሮው በወረቀት የሚሞላ ሳይሆን በኤምባሲው ድህረገጽ ላይ ነው የሚሞላው። ፎርሙን ገና መሙላት ሲጀምሩ በኤ ኤ (AA) የሚጀምር የመለያ ቁጥር ይሰጥዎታል። ፎርሙን የሚሞሉት የአመልካቹን ወይም የአመልካቿን፣ ኢንፎርሜሽን የሚያውቁ ከሆነ ነው። ፎርሙን መሙላት ጀምረው፣ በቂ ኢንፎርሜሽን ከሌለዎ ተመልሰው በሌላ ጊዜ ሊሞሉ ይችላሉ። ፎርሙን ሞልተው ከጨረሱ በኋላ የቪዛ ቀረጥ (Visa fee) በአቢሲኒያ ባንክ ቅርንጫፍ መክፈል ይገባዎታል። ክፍያውን ከከከፈሉ በኋላ በኢምባሲው ድህረ ገጽ ወይንም የቨርጂኒያ ቁጥር ደውለው ለኢንተርቪው ቀጠሮ ይይዛሉ። ከኢምባሲው የሚያገኙት ቀጠሮ ከ15 ቀን በላይ ስለሚሆን፣ የሚሄዱበት ጉዳይ ከመድረሱ አስቀድመው ፎርሙን መሙላትና ቀጠሮ መያዝ ይኖርብዎታል። የአሜሪካን ኤምባሲም ሆነ የጉብኘት ቪዛን በተመለከተ የወጡ ደንቦች ለአመልካቹ ቪዛ ለመስጠት በአጠቃላይ ሶስት መመዘኛዎች አሏቸው።

1ኛ ይህ ግለሰብ ከአሜሪካ ቆይታው በኋላ ወደ አገሩ ይመለሳል ወይ? ከአገሩ ጋርስ ያለው ቁርኝት ምን ያህል የጠበቀ ነው የሚል ነው። ይህን ለመመርመር የኤምባሲው የቪዛ ሰጪዎች (ቆንስላዎቹ) አመልካቹ ቤት፣ ቤተሰብ፣ ንብረት ሥራ ወይምን ንግድ እንዳለውና ጉዳዩን ሲጨርስ ወደ አገሩ እንደሚመለስ ማሳየት አለበት። ስለዚህ የቤት ካርታ፣ የመኪና ባለቤትነት መታወቂያ ወይም ንግድ እንዳለው አልያም ሥራ እንዳለው( ከመ/ቤቱ) ማስረጃ ማሳየት ይኖርበታል።

2ኛ ቆንስላዎቹ የሚያዩት ሁለተኛውን ነገር ጎብኝው አሜሪካን አገር በሚቆይበት ጊዜ የመንግሥት እርጥባን (public assistance) ተጠቃሚ ይሆናል ወይንስ አይሆንም የሚለውን ነው፣ ለዚህ ደግሞ ጋባዡ (ለዘመድ ጥየቃ ለሠርግ ለምረቃ የሚመጡ ከሆነ) የድጋፍ ፎርም (I-134) እና የጋባዡን ገቢ፣ ያሉትን ንብረቶች የሚያሳዩ መረጃዎች ለኢምባሲው ማሳየት ይኖርብዎታል። እነዚህም የታክስ ወረቀት፣ የባንክ ደብተር፣ ከጋባዡ አሰሪ ደብዳቤ ብሎም ቤት ካለው የቤት ካርታ ማሳየት ይገባዎታል። እነዚህ መረጃዎች ጎብኝው አሜሪካ በሚቆይበት ጊዜ የሚያበላው፣ የሚያጠጣውና የገንዘብ ድጋፍ የሚያደርግለት ግለሰብ ስለሚኖር የአሜሪካ መንግሥትን እርዳታ ሊጠይቅ አይችልም የሚለውን ስጋት ሊያሳምን ይችላል።

3ኛ ቪዛ ጠይቂው የሚሄድበት ምክንያት እውነተኛ ነውን የሚለው ነው። ለምሳሌ የታመመ ሰው ለማስታመም፣ ወይም የምትወልድ ለማረስ ከሆነ፣ ከሐኪም የድጋፍ ደብዳቤ፤ ለምረቃ ከሆነ ከትምህርት ቤት ደብዳቤ፤ ለስብሰባ ከሆነ ከጋባዡ ደብዳቤ፣ ለሠርግ ከሆነ ደግሞ የሠርግ ወረቀትና ሆቴል የተያዘበት ማስረጃ ያስፈልጋል።

እነዚህ ማስረጃዎች ቢኖሩም አመልካቹ ቃለ መጠይቅ በሚደረግለት ጊዜ ስለራሱም ሆነ ስለጋባዡ አጥጋቢ መልስ ካልሰጠ ቪዛ ላያገኝ ይችላል። ስለዚህ ለኢንተርቪው መዘጋጀት ያስፈልጋል። ምን ዓይነት ጥያቄዎች ይኖራሉ? ምን መመለስ አለብኝ? የሚለውንና ስለሚሄድበት ጉዳይም ሆነ ስለጋባዡ በቂ ኢንፎርሜሽንና ግንዛቤ ሊኖረው ይገባል። ለምሳሌ ሠርግ ከሆነ ማን ነው የሚያገባው? የትና መቼ? ምረቃም ከሆነ እንደዚያው ማን ነው የሚመረቀው ከየት ዩኒቨርስቲ (ት/ቤት) እንደሆነ ማወቅ ያስፈልጋል።

ለጉብኝት ቪዛ ጠበቃ መያዝ አያስፈልግም። ጊዜያዊ የጉብኝት ቪዛ ለማግኘት ብሎ እውነት ያልሆነ ኢንፎርሜሽን በፎርሙ ላይም ሆነ በቃለመጠይቅ ጊዜ መስጠት ብዙ ጉዳት አለው። ሌላ ጊዜ ቪዛ እንዳያገኙም ሆነ አሜሪካም እንዳይገቡ ሊያሳግድዎ ይችላል። አመልካቹ ቪዛ ከተከለከ ይግባኝ ማለት አይችልም። ግን እንደ አዲስ ሌላ ጊዜ ማመልከት ይችላል። ወይም ጋባዡ የሱ ተወካይ የሆነውን የኮንግረስ አባል ወይም ሴናተር እርዳታ ጠይቆ ጉዳዩ እንደገና እንዲታይ ሊጠይቅ ይችላል። አመልካቹ እድሉን አግኝቶ ከመጣ ወይም ከመጣች፣ ለ6ወር የሚሆን ጊዜያዊ ፍቃድ ሊሰጠው ይችላል።

ዶ/ር ፍጹም አቻምለህ ዓለሙ ከሃገንጋሪ ቡዳፔስት በህግ የመጀመሪያ ዲግሪውን ያገኘው እ.ኤ.አ. በ1988 ነበር። ከኢትዮጵያ ለትምህርት ከሄደበት ሃንጋሪ ትምህርቱን እንደደረስ ለተደማሪ ትምህርት በቡዳፔስት ከሚሰራበት የሰብዓዊ መብት ድርጅት ስኮላርሺፕ አግኝቶ ወደ አሜሪካ መጥቷል። እንደገና ወደ አውሮፓ ቡዳፔስት በመመለስ በሃንጋሪ ታዋቂ ለሆነ አንድ ሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ጠበቃና የፕሮጀክት ማኔጀር ሆኖ ሠርቷል። ከ1996 ጀምሮ ወደ አሜሪካ በምመጣት በተለያዩ ቦታዎች ሲሠራ ከቆየ በኋላ ከዲሴምበር 2003 ጀምሮ የራሱን የፍጹም አቻምየለህ የጥብቅና ድርጅት አቋቁሞ እየሠራ ነው።

ዶ/ር ፍፁም አቻምየለህ

አንዳንድ ነገሮች ስለሕግ

ጥቂት ነገሮች ስለጉብኝት ቪዛ

ተመልክቷል፡፡ አስመራና መቀሌ ላይ ብዙ ምክክሮች ቢደረጉም ጨርሶ ሊስማሙ የሚችሉበት ሁኔታ ግን አልነበረም።ከዚያም አልፎ ወደ በጥቃቅን ጉዳዮች ሁሉ ወደ መጨቃጨቅና የንግድ ልውውጥና የገንዘብ ዝውውርን እስከ መገደብ ተደረሰ። ሁኔታው ከባለሥልጣናቱ እጅ ወጥቶ ወደ ህዝብና ሚዲያ ጆሮ መድረስ ጀመረ። ኤርትራን የሚከሱት አቶ ገብሩ አንዱን ምናልባትም የግንኙነት መበጠሻ የሆነውን የመጨረሻ አጋጣሚ እንደሚከተለው ገልጸውታል፦

በሻዕቢያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ከፍተኛ የፀረ- ትግራይ ቅስቀሳ ይደረግ ነበር።“በአንድ ወቅት ከትግራይ ወደ ኤርትራ የሚገባውን ማንኛውንም ሸቀጥ በመከልከል ጉሮሮአችንን ለማነቅ እየተንቀሳቀሱ ነው ነው የሚል የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ ይደመጥ ነበር። ይህን የሰሙ ኢትዮጵያውያን ኤርትራውያንና የተወሰኑ የሻ ዕቢያ አባላትት እጅግ ተደናግጠው ምን እየተደረገ እንው? ይህ የፕሮፖጋንዳ ዘመቻስ ወዴት እያመራ ነው?” የሚል ስጋት አድሮባቸው ነበር። ኢሳያስ የመጨረሻውን ስብሰባ ከኛ ጋር ሲያደርግም “የዚህ ዓይነት ዘመቻ እየተኪያሄደ ያለው ለምንድነው? ብለን ስንጠይቀው ለጥያቄያችን ያህን ያህል ክብደት ሳይሰጠው “የምታነሱት ነገር በሚዲያ ሲተላለፍ ባልሰማም ሰዎች ሲንጫጩ ሰምቼ እስቲ በቴሌቪዥን የተላለፈውን አሳዩኝ ብዬ ምጽዋ ላይ ተመልክቼው ነበር። የተላለፈው መልዕክት ትንሽ የተጋነነ ቢሆንም መሠረታዊ ስህተት ግን አላየሁበት። አሁንም ትግራይ ጉሮሮአችንን ለማነቅ እየተንቀሳቀች ነው። ብሎ አረፈው። 256

ይህን ካለ በኋላም ኢትዮጵያ ኤርትራ ያቀረበቻቸውን የኢኮኖሚና ማህበራዊ ጥያቄዎች ብትመልስ እንድሚሻላት ደጋግሞ አሳሰበን። በኛ በኩል ደግሞ እየቀረበ ያለው ጥያቄ አግባብነት እንደሌለው ደጋግመን መለስንለት። “መልሳችሁ ይህ ከሆነ ከ እንግዲህ በሁለት አገሮች መካከል ግንኙነት ልሊኖር አይችልም አለ። እንዲያውም ድንበራችንን የሚያካልል ኮሚቴ(በአስቸኳይ) ይቋቋም የሚላ አሳብ አቀረበ። 256

ወደ አዲስ አበባ ከተመለስን በኋላ አስመራ ላይ የሆነውም ሁሉ ለመግለጽ አስችኳይ የህወሓት ሥራ አስፈጻሚ ስብሰባ እንዲጠራልን መለስን ጠየቅነው። ሻዕቢያ ወረራ ያካሂዳል ብለን እናምናለን አናምን ተብሎ በተሰጠ የፖሊት ቢሮው ድምጽ መለስ ዜናዊ ስዩም መስፍን ስዬ አብርሃ ስብሐት ነጋ ክንፈ ገ/መድህን ሲሆኑ ወረራ ያካሂዳል ብለን እናምናለን ያሉት ዓባይ ተወልደ ወልደ ማርያም፣ ዓለምሰገድ ገ/አምላክ ዓባይ ፀሐዬ እና ገብሩ አስራት ነበሩ። (ገጽ 258) በፀረ ሻዕቢያ አቋማቸው ይታወቃሉ የተባሉት አቶ ስዬ አብርሃ እስከዚያ ድረስ ታውረው ነበር ማለት ይሆን? እስከ ህወሓት አምስተኛው ጉባኤ ድረስ አልነቁም ነበር።

ከዚያ በኋላ የአቶ ገብሩ መጽሀፍ እንደሚያትተው አይቀሬው ጦርነት ተካሄደ። በጦርነቱ ዙሪያ በተያዘው አቅዋምና እሱን ተከትሎ በተነሳ ክፍፍል አቶ መለስ ተቀናቃኞቻቸውን በሙሉ እንዴት አድርገው ከፓርቲው እንዳባረሩ መጽሀፉ ይተረካል። መለስ የኢህአዴግ ጽ/ቤት እንዲታሸግና እንዲፈተሽ ማድረጋቸውን ለዚህም ደህነቱ አቶ ክንፈ ታዘው መፈጸማቸውን ያትታል። ከዚያ በኋላማ በቃ ከአቶ መለስ በስተቀር ሌላው የአመራር አባል ከራስ ጠጉሩ እስከ እግር ጥፍሩ እየተፈተሸ ወደ ስብሰባ አዳራሾች መግባት ጀመረ ብለዋል ከአፈንጋጮች አንዱ የተባሉት አቶ ገብሩ አስራት፡

፡ አቶ መለስ በብቸኝነት ወጡ!

እሱ በህይወት ኖሮ ይህን መጽሀፍ ባሳተምኩ ኖሮ ደስ ይለኝ ነበር ያሉት አቶ ገብሩ ይህን መጽሐፍ ለማሳተፍ ያሰብኩት ከመለስ ዜናዊ እልፈት በፊት ቢሆንም በተለያዩ ምክንያቶች አልተሳካልኝም ብለዋል። እሱ በሕይወት ኖሮ መልስ ቢሰጥበት

ደስ ባለኝ” በማለት ይህ ባለመሆኑ ቅሬታ እንደሚሰማቸው ገልጸዋል። አቶ መለስን በህይወት ያሉትንም ሰዎች የሚተቹት በቂም በቀል ሳይሆን ሥርዓቱን ለመተችት እንደሆነም ጽፈዋል። መልካም ንባብ! (ዘኢትዮጵያ)

አቶ ገብሩ... ከገጽ6

Page 13: መልካም አዲስ ዓመት ይሁንልን! · ዘኢትዮጵያ ጋዜጣ Zethiopia Ethiopian American Community News NO.86 Sept 2014 202 518 0245 P.o.box 2049, Fairfax, VA

13ዘኢትዮጵያ ጋዜጣ Zethiopia Ethiopian American Community News NO.86 Sept 2014 202 518 0245 P.o.box 2049, Fairfax, VA 22031 www.zethiopia com

The senior staff of Hamlin Fistula Ethiopia are joining with Hamlin Fistula USA to host a fundraising event on Saturday September 27th from 11am to 2 pm at the Ritz-Carlton, Washington DC (see invitation in this publication)

Mamitu Gashe, ex fistula patient turned world-renowned fistula surgeon and grand daughters Sarah and Catherine Hamlin will join with many other VIP guests for what promises to be a very informative and joyous celebration of a living legend. The event will feature an eight-minute excerpt pre-release of a 2014 feature film “Go On” about the life of Drs. Reginald and Catherine Hamlin and Hamlin Fistula Ethiopia.

The Ethiopian American community has been instrumental in its support of Hamlin over the years. A very successful campaign in 2007 / 2008 resulted in the construction of a satellite Hamlin hospital in Harer in eastern Ethiopia. Dr. Hamlin and her staff have cured over 40,000 women since the founding of the Hospital in 1974.

I approached Mike to be my partner shortly after I started Blen Graphics. I realized that he was intelligent early on. I offered him 49% of the business and that’s when everything started to happen and he just took off with it. He is one of the smartest guy I know and he is extremely talented. If it wasn’t for Mike, I don’t think I would be here today. I would have given up or do something else.

Zethiopia: It was just the two of you. How many people do you have working for you at this time?

Ephrem: We have eleven employees all together, seven of whom are full time. It’s so hard for me to see that it is not only me that survive off of Blen but I have six other people that survive off of Blen who work and live a normal life. It is a blessing. I give a lot of credit to the team we built. We all met in the Ethiopian community area. It’s a great team. It’s not mine only but Blen is everybody’s now. We make sure that we all have a sense of ownership. We make sure they come to work for themselves. If you ask anybody that works for Blen, they will tell you that they work for themselves. You can see what kind of work we do with this beautiful group. We have big clients all the way to the Whitehouse. We built petitionwhitehouse.gov. It’s all about the team.

One of the things we started in the process of making Blen is The Blen Art Show. This is to celebrate and encourage the works of an Ethiopian contemporary

artists. Most of them are so talented but they go unnoticed in our community. We want to expose these young talents. I wish we can do these events more often.

Zethiopia: Mike tells me that you are the soul of the company. What is your contribution to Blen Corp now?

Ephrem: One thing I noticed about myself is that I’m good with people and I am energetic. I can bring people together and have something happen. As far as artistic contributions, I am the creative director. Any design and visual work has to go through me that came from the artistic and visual experience that I have. Even now when we have products, I don’t let anything go. I am the visual designer. Even if we hire another designer, I will make sure that things communicate well. I think that’s what I’m good at. I am a visual person. I am an artist and visual communicator. I play huge role in this area.

Zethiopia: What is your vision for the Future?

Ephrem : For me, Blen is not about making money. It’s about having an idea that can take us somewhere, that can show what we can do. I am surrounded with great developers and with people with amazing ideas. We can be the next Facebook or Google with the potential we have. So, Blen is not about making money but making an Idea that works.

- “It is a two-and-a-half-year-old infant but is doing well, don’t discredit it” Debretsion

Currently, the House of Peoples’ Representatives (HPR) is busy listening to and discussing the performance of the various government institutions.

Listening to performance reports before the completion of every fiscal year is one of the tasks of Parliament. However, the trend that is being observed in the House is an unprecedented one. The Ethiopian Peoples’ Revolutionary Democratic Front-dominated Parliament dominated assembly of lawmakers has begun challenging and criticizing government reports and anything they deem inappropriate unlike previous times.

This was witnessed on Thursday when the minister of Communication and Information Technology, Debretsion Gebremichael

(Ph.D.) was presenting the 10-month work performance to which most of the reports focused on the success he said was achieved in the Telecom service. But the MPs were critical of the report.

While highlighting the work performance of Ethio Telecom, which is responsible to the Ministry of Communication and Information Technology, Debretsion reported that the number of mobile subscriber in the current month of the fiscal year had reached 22.4 million while the plan was to make it at least 23.86 million by the end of the year.

Similarly, his report showed that the number of landline telephone users had reached 825,000 whereas the plan was to be 872,000. Meanwhile, the telecom company has managed to take home some 4.379 million birr which surpassed its target of 4.056 million birr. Moreover, it was able to achieve and deliver the global linkage capacity to 8.686 Gb/s while the plan was to meet its capacity level to 9.675Gb/s at the end of the fiscal year.

The minister’s report indicates the telecom service had already been set to maximize its service for the remaining two years of the GTP period. Accordingly, the plan is raise the number of mobile subscribers, landline telephone users and internet service users and Global Linkage Capacity to 40 million, 3.69 million and 20 Gb/s respectively.

The minister told the MPs over 17.7 billion birr has been earned in the past ten months from telecommunication and postal services which is 92 percent of the plan for the year

However, the minister’s reported did not escape strong comments and challenging

criticism from MPs, specially with regard to “poor quality of telecom services” and frequent interruption of mobile networks.

Of course, Debretshion, on his part, did not deny the criticism but tried to defend Ethio telecom with a heightened emotion.

An MP questioned him saying that the telecom company is providing poor quality service and said that there was “an almost no mobile service”, adding that the public was “severely complaining about the poor service.”

But Debretsion continued defending the sole telecom provider saying, “It is doing well despite its under-reestablishment and redevelopment process as a newly-born company”.

“It [Ethio Telecom] is like a newly-born infant. It is only a two-and-a-half-year-old infant. It is undergoing reconstruction. But it strives to do its best. We could not halt the service just because it’s reconstructing,” Debretsion, whose tone sounded agitated, told lawmakers.

Meanwhile, the MPs still kept posing even stronger questions which showed that they were not convinced by the minister’s defense.

This continued after House Speaker, Abadula Gemeda, resumed the second round of question and answer session.

“Hon. Minster, we appreciated your report. I have noticed that you are emotionally defending the telecom service provider. However, if you go to the different woredas or even bigger towns, you can see frequent network interruption. There is even no service in some areas,” one of the MPs said. The question in turn made Debretsion smile and Speaker Abadula and the rest of MPs

joined him with laughter.

“Sorry if you find me pretty emotional. But that might be my nature but I am not annoyed. It is rather my pleasure to see our parliament like this sort of interaction and more debate,” was Debretsion’s which in turn made the MPs smile.

A few years ago the management of Ethio telecom had been outsourced to France telecom before it was retained back six months ago. The very reason of outsourcing the company to the French company was to reform it and upgraded its management to an advanced level believed to be more competitive in the global arena.

But observers question that the outsourcing of the company bore less result than the intended goal it was expected to achieve. In fact, the company is still run by the same CEO from France Telecom.” By restructuring the former ETC (Ethiopian Telecommunications Corporation) and re-establishing it as a new company and outsourcing the management to France Telecom, the initial plan was to elevate it to a more advanced level.

“Since the management has been overtaken by the French company, which is a key part of the reformation, it has done the necessary transitional work and was able to build the capacity of local managers that can take over the management responsibility from them. Hence the management positions have been handed over back to Ethiopians, except for the CEO’s position,” he said.

(The Reporter)

MPs lambast Debretsion over Ethio-Telecom’s “poor service”

Hamlin Fistula ....continued from page 1Blen... Ephrem from page 11

actually dealing with us. We are small enough not to be the big guys. The big companies don’t care about us. But the interesting thing is, we make this durable and solid relationship with our partners that the bigger clients consider us as partners because we deliver and we want to continue to deliver to our clients to keep the relationship solid. In my view I could be wrong, but the next five years to ten years, especially in America, will be one of the more important times in the history of this nation. The reason is simple. For instance, the education system that student has to go to school for nine months was designed by some congressman in the 1900. That does not work anymore. So you hear people saying that the education system is broken. But who is going to fix the problem. It’s us. The people who are in the right time and the right place and we feel like we are there. If we get the focus on what we believe in and be disciplined and stick with our core principle, we are the once who will set up the next five years or seven years. The next nine years will be the most innovating things not only Blen Corp but companies in general.

Zethiopia: You are competing with big companies. How do you manage that?

Mike: If we get disciplined and we get the mechanics right and believe in our core principle

I think we will be the one to set the next seven or eight years. We just don’t want to be around for ten years. We want to see the bigger horizon – the next nine years is going to be the most amazing time for us. We’re going to see the most innovating things not only from Blen Corp but other companies in general as well. We’ll see amazing things such as self-driving cars and other great things and we are in the middle of it. We are going to do everything to be part of it in the meaningful way. We want to contribute in a positive way to technology.

Zethiopia: Do you mind naming some of you clients?

Mike: We work with a lot of clients. Geico for instance – insurance, World Bank, EPA, Energy Star, are among our clients. We also work with AIR, which is the largest educational organization. We work with department of Education. We have a long list. We cannot talk about some of the companies for obvious reasons. It is really interesting that a company founded by two Ethiopian- American guys is doing some of the most amazing things that we cannot talk about with these big companies. We’ve been very fortunate and lucky. Most importantly the relationship we built with our clients will save the day. That‘s where the future is for us.

Zethiopia: What is the most challenging thing for you?

Mike: The biggest challenge is running the business. I wake up in the morning and I have to do a number of things. I look at yesterday’s expenses, make sure our employees are paid on time and make sure we have money in the bank. For that to happen you have to invoice our clients. If they don’t pay on time then you have to figure out a way to put money in the bank so employees are paid. So the challenge for small business is that you are responsible for everything. From picking up the trash, fixing the toilet, invoicing your clients to guaranteeing new business. You have to make sure your project is done on time and make your clients happy – so all these things are challenges. There were times we have been burned. There were times that I didn’t want to get out of my bed. But If I have to do it over again, I would not change a thing.

Zethiopia: How do you describe yourself? Do you consider yourself as a businessman?

Mike: It’s very hard to talk about yourself but personally, I consider

myself as a problem solver. That’s the description I want. But most importantly, I want people to think of me as enabler and facilitator to do great things.

Zethiopia: What is your vision?

Mike: I don’t want to lose the fulfillment I get from Blen. I want to be happy with the things I do. I want to make sure that the things we do are meaningful and worthwhile. If you ask anyone from Blen Corp, they ‘ll tell you the same thing. We all want to make sure that what we do is meaningful.

Zethiopia: What can you tell me abour Ephrem?

Mike: Ephrem is the heart and soul of Blen. He is Brilliant. Blen belongs to Ephrem because he created it. We’ve been partners for the last 14 years and he has been a fantastic partner. He is a wonderful president. He is mature and knows how to handle difficult times. He gave me 49% of the company when we met and when I was in High school he recruited me so I feel indebted to him.

Blen...Mike from page 11

Page 14: መልካም አዲስ ዓመት ይሁንልን! · ዘኢትዮጵያ ጋዜጣ Zethiopia Ethiopian American Community News NO.86 Sept 2014 202 518 0245 P.o.box 2049, Fairfax, VA

ዘኢትዮጵያ ጋዜጣ Zethiopia Ethiopian American Community News NO.86 Sept 2014 202 518 0245 P.o.box 2049, Fairfax, VA 22031 www.zethiopia com 14

እትዬ ብርቄ (ከአርአያ ጌ. ተክለአቢብ)

አጭር ልቦለድ

ቤተሰብ

ሐምራዊት ተስፋ

ክፍል ሶስት

Yes I want to subscribe Zethiopia Newspaper

Name------------------------------------------------

Address-----------------------------------------------

City................................................................................

State...................Zipcode............................................

Phone,...........................................................................

Email.................................................................................

Starting date...................................................................

For only $40.00

Ze Ethiopia Corp.P.o.box 2049,

Fairfax, VA 22031 www.zethiopia com

[email protected]

Zethiopia Newspaper

ዘኢትዮጵያ ጋዜጣ ቤትዎ እንዲላክልዎ ከፈለጉ ከዚህ ቅጽ ጋር የዓመት ደምበኝነት ሞልተው 40 ዶላር ይላኩልን

እትዬ ብርቄ ተከሰዉ ፍርድ ቤት ቀረቡ። ከዚያም ክሱ ተነቦላቸዉ ክሱን ይቃወሙ እንደሆነ ተጠየቁ።

“በጣም እቃወማለሁ” አሉ ድምፃቸዉን ከፍ አድርገዉ።”

መሃል ዳኛዉ እንዳቀረቀሩ ከመነፅራቸዉ ዉጭ አጮልቀዉ እያዩዋቸዉ “ክሱን ለምን እንደምትቃወሚ አስረጂ” አሏቸዉ።

“ነፍሷን ይማረዉና ለልጅቷ የሰጠኋትን መድሃኒት ያዘዘልኝ የጤና ጣቢያዉ ዶክተር ነዉ። ተክልዬ ባይደርሱልኝ ኖሮ እኔንም ገድሎኝ ነበር። ስለዚህ ዶክተሩ ወንጀለኛ ስለሆነ ተጠርቶ ይጠየቅ። እኔ ግን ወደቤቴ ልሂድበት።”

“የተጠየቅሺዉ የክሱን አቀራረብ በተመለከተ ነዉ” አሉ ዳኛዉ ቆጣ ብለዉ።

“እኔም የምለዉ እሱን ነዉ። የእኔ ስም ወጥቶ የዶክተሩ ስም ይተካ።”

ዳኞቹ ድምፃቸዉን ዝቅ አድርገዉ ተነጋገሩ። ከዚያም የመሃል ዳኛዉ ድምፃቸዉን እንደመጠራረግ ብለዉ መናገር ጀመሩ።

“ጥፋተኛ ነሽ? አይደለሽም?” አሏቸዉ።

ብልጭ አለባቸዉ።

“አይ እንግዲህ የምናገረዉ አማርኛ አልገባ ካላችሁ አስተርሚ ይምጣ። ጉድ’ኮ ነዉ ... የዶክተሩን ጥፋትና የኔን ንፅህና ዘርዝሬ እየተናገርኩ እንዴት ጥፋተኛ ነሽ ወይ ብላችሁ ትጠይቁኛላችሁ?” አሉና ፊታቸዉን ወደ አቃቤ ህጉ አዙረዉ “ ይህ ሁሉ ያንተ ስራ ነዉ ። እኔን ለማጉላላት ብለህ ሞነጫጭረህ ያቀረብከዉ ክስ መሆኑን እዚህ ያለ ሰዉ በሙሉ ያዉቃል” አሉት ሁልጊዜም ሲናደዱ እንደሚያደርጉት ግራ አይናቸዉን ጨፈን አድርገዉ።

“ስርአት ባለዉ መልኩ የተጠየቅሺዉን ብቻ መልሺ። ይህ ፍርድ ቤት ነዉ። አቃቤ ህጉን የመናገር መብት የለሽም” አሉ የመሃል ዳኛዉ መነፅራቸዉን በእጃቸዉ ከፍ ዝቅ እያደረጉ።

ከዚያም የቀበሌና የእድር ስብሰባ ላይ እንደሚያደርጉት የቀኝ እጃቸዉን ሲያወጡ“የምትናገሪዉ ነገር ካለሽ መናገር ትችያለሽ” አሏቸዉ።

“ለመሆኑ እናንተ ዳኞች የዚህን ሰዉየ ማንነት ታዉቃላችሁ?” አሉ በሌባ ጣታቸዉ ወደ አቃቤ ህጉ እየጠቆሙ።

“ብርቄ ለመጨረሻ ጊዜ ፍርድ ቤቱ ሊያስጠነቅቅሽ ይገደዳል። የፍርድ ቤቱን ክብር ልትጠብቂ ይገባል። አለበለዚያ ግን ፍርድ ቤቱ ተገቢዉን እርምጃ ይወስድብሻል” አሉ ዳኛዉ ተቆጥተዉ።

ንዴታቸዉን መቆጣጠር ስላልቻሉ “ለመሆኑ እኔም እንደዜጋ የመናገር መብት የለኝም?” አሉ የመሃል ዳኛዉን አፍጥጠዉ እያዩዋቸዉ።

“ምንድን ነዉ የምትናገሪዉ? ቀደም ሲል እንደተነገረሽ ስርአት ባለዉ መልኩ የመናገር መብትሽ የተጠበቀ ነዉ” አሉ የቀኝ ዳኛዉ ከአቀረቀሩበት መዝገብ ቀና ብለዉ። ለመጀመሪያ ጊዜ ጣልቃ ገብተዉ መናገራቸዉ ነበር።

“ይመናሹ የተባለችዉ መተተኛ ሰላቢ ሴት ቀንደኛ ጠላቴ ነች ...” ብለዉ የጀመሩትን አረፍተ ነገር ሳይጨርሱ የመሃል ዳኛዉ ጣልቃ ገብተዉ “አሁን ይሄ ከክሱጋ ምን ግንኙነት አለዉና ነዉ የሌላ ሰዉ ስም የምትጠቅሺዉ?” አሉዋቸዉ ተናደዉ።

“ጌታዉ ያስጨርሱኛ! ሴትየዋ ልትቀበለኝ ስታደባ ቆይታ በአቃቤ ህጉ በኩል አገኘችኝ” አሉ በቁጨት ከንፈራቸዉን እየነከሱ።

ዳኞቹ የተከሳሽን ጤንነት በመጠራጠር ትኩር ብለዉ አዩዋቸዉ። ከዚያም የመሃል ዳኛዉና የቀኝ ዳኛው በሹክሹክታ መንጋገር ጀመሩ።

“ብርቄ” አሉ የመሃል ዳኛዉ ድምፃቸዉን ከፍ አድርገዉ።

“አቤት” አሉ ፈጥነዉ።

“እስካሁን ድረስ የምትናገሪዉን አግባብነት ፍርድ

ቤቱ አላመነበትም” ሲሉዋቸዉ ቱግ አሉ።

የፍርድ ቤቱንም ፈቃድ ሳይጠይቁ መናገር ጀመሩ። “ይመናሹ ያገባችዉ ወደል ሰዉየ ከትዳር ዉጭ የሚወለድ አንድ ልጅ አለዉ። የእድራችንን ገንዘብ አጭበርብሮ ቢበላም ጥሩ ...” ብለዉ የጀመሩትን አረፍተ ነገር ሳይጨርሱ የመሃል ዳኛዉ በመዶሻዉ ጠረንጴዛዉን መቱት። ከዚያም ወደ ስነስርአት አስከባሪዉ እየተመለከቱ “ፖሊስ የታለ?” አሉት።

ፖሊሱ እንደገባም “ተከሳሽ የጤና ችግር አለብሽ ... ማለቴ የአእምሮ ...?”

“ወዴት ... ወዴት!? ጭንቅላቷን ታማ ፀበል ለፀበል የምትንከራተተዉ ይመናሹ መሆኗን አገር ያዉቃል። የነፃ ህክምና እያፃፈች ብዙ ጊዜ ጤና ጣቢያና አማኑኤል ሆስፒታል ታክማለች ...”

“ቆይ እስኪ ... እንዴት ነዉ ነገሩ?” አሉ የመሃል ዳኛዉ እንደመሳቅም እየቃጣቸዉ። ከዚያም “ማን ነበረች ያልሻት?” አሉዋቸዉ።

“ይመናሹ ትባላለች። የገመቹ እንጀራ እናት ነች።”

“ምንድን ነዉ ከክሱጋ በተያያዘ ልትነግሪን የፈለግሺዉ?” አሉዋቸዉ የመጨረሻ እድል ለመስጠት ብለዉ።

“ገመቹ ያገባዉ የአቶ ማትያስን ልጅ ነዉ። አቶ ማትያስ የቀበሌ ሊቀመንበር በነበረበት ጊዜ የሰራዉን ታዉቃላችሁ። ጉቦ ተቀብሎ የቀበሌዉን አዳራሽ በርካሽ ዋጋ ኮንትራት በመስጠቱ ጠቁሜበት ተከሶ ነበር። ፍርድ ቤትም ቀርቤ መስክሬበታለሁ። ከዚያም ተፈርዶበት ታስሮ ከተፈታ ገና ሶስት ወሩ ነዉ።”

“እሽ ... ገመቹስ ከክሱጋ የሚያገናኘዉ ነገር ምንድን ነዉ?” አሉ ግራ የተጋቡት የቀኝ ዳኛ።

“አቃቤ ህጉ ያገባዉ የአቶ ማትያስን ታናሽ ወንድም ልጅ ነዉ። ያቺ መናጢ ...”

የጀመሩትን አረፍተ ነገር ሳይጨርሱ የመሃል ዳኛዉ አቋረጧቸዉ።

“ፍሬ ያለዉ ነገር ይሆናል በሚል እስካሁን ድረስ

ሰማንሽ። ከዚህ በኋላ ግን ይበቃል። የፍርድ ቤቱን ጊዜ አለአግባብ ነዉ ያባከንሺዉ” በማለት ቀጠሮ ሰጥተዉ አሰናበቷቸዉ።

እትዬ ብርቄ በመጀመሪያ የፍርድ ቤት ዉሎዋቸዉ በኋላ መደንዘዝ ጀምረዉ ነበር። የምር መሆኑ የገባቸዉም የአቃቤ ህግ ማስረጃ ተሰምቶ እንዲከላከሉ ብይን ሲሰጥ ነዉ። ዶክተሩን ጨምሮ በርካታ ምስክሮችን ቢቆጥሩም ጥፋተኛ ናቸዉ ተብለዉ የአምስት አመት እስር ተፈረደባቸዉ። ይግባኝ ቢይጠይቁም ፀናባቸዉ።

የቃልቲ ማረሚያ ቤትን ቀስ በቀስ መላመድ ሲጀምሩ ግን ነገሮችን ማስተዋል ጀመሩ። እናም ተገቢ አይደለም በሚሏቸዉ ጉዳዮች ላይ ቅሬታ ማሰማቱን ተያያዙት። በዚህም ምክንያት በአጭር ጊዜ ዉስጥ በእስረኛዉ ዘንድ መታወቅ ጀመሩ።

እንዳጋጣሚ በታሰሩ በወሩ የእስረኞችን ሁኔታ የሚከታተል የአለም አቀፍ ቀይ መስቀል ተወካዮች መጥተዉ ነበር። እስረኞች ቅሬታ የሚያሰሙላቸዉ ተወካዮች ሲመረጡ እትዬ ብርቄም ከምድባቸዉ ተመረጡ። በስብሰባዉ እለትም ምን ያህል አመታት ቢታሰሩ ነዉ እስከሚባል ድረስ በርካታ ቅሬታዎችንና አስተዳደራዊ በደሎችን ዘርዝረዉ አስረዱ። እስረኞችም በየመሃሉ ንግግራቸዉን በጭብጨባ አዳነቁላቸዉ። የዚያን ቀን በደስታ ተንበሽብሸዉ ዋሉ። እንደዉም ከእስርም የሚፈቱ መስሏቸዉ ነበር።

ሊጠይቋቸዉ ለሚመጡት ሰዎችም “በቅርቡ የኢትዮጵያ እስረኞች ዋና ፀሃፊ በሚል ማእረግ በቲቪ የምቀርብበት ጊዜ ሩቅ አይደለም። እንደዉም ለስራ ጉዳይ መፈታቴ የማይቀር ነዉ” እያሉ ይናገሩ ነበር።

ሆኖም ግን ብዙም ሳይቆዩ ከሌሎች እስረኞችጋ ወደ ዝዋይ ማረሚያ ቤት ተላኩ። ከዚያ በኋላ ድምፃቸዉ እየጠፋ ሄዶ ከነጭራሹ ስማቸዉንም የሚያነሳ ሰዉ አልነበረም።

በአለማችን ያሉ የነበሩ የተለያዩ አስተማሪዎች የሚደጋግሟት አንዲት ምክር

አለች። ይህች ምክርም በእግዚያብሄር ቃል ተደጋግማ ተጽፋለች። ምክሯም እንዲህ ትላለች፤ “ከሰው አፍ የምትወጣ ቃል በሰው ህይወት ላይ ትልቅ ተጽእኖ አላት”። እውነቱም ያ ነው! ከሰው አፍ የሚወጣው ቃል ወይ የበረከት ምንጭ ይሆናል ወይ የእርግማን፤ የምንናገረውን ቃል አፍሰን እንበላለን።” በተደጋጋሚ፣ የጨለመ ንግግርን የምንናገር ከሆነ፣ ውስጣችን የቆዘመ የተመረረ ተስፋን ያጣን ሰዎች ወደ መሆን አቅጣጫ በፍጥነት እየገሰገስን እንሄዳለን ማለት ነው።

ይህ እንዴት ይሆናል? ቃላታችን ደስታና ሰላማችንን ለመወሰን ያለው ሀይል ምንድነው? የምንናገረው ቃል እንዲሁ ተኖ አይጠፋም። ደጋግመን ስንናገረው እውነታችን ሆኖ በአይምሮዋችን እራሱን አንግሶ ይቀመጣል። ለምሳሌ ደጋግመን የምሬት ቃላት ስንናገር የምሬት አስተሳሰብና አመለካከት በአይምሮዋችን ውስጥ ነግሶ ይቀመጣል። በአይምሮ የነገሰ ሀሳብ ደግሞ የህይወት መነጽራችን ይሆናል።በሌላ አነጋገር ውጩን የምንመለከትበት መነጽር

ይሆናል። አረንጓዴ አድርጎ የሚያሳይ መነጽር ያደረገ ሰውና ሰማያዊ አድርጎ የሚያሳይ መነጽር ያደረገ ሰው ምንስ አንድ አይነት ስእል ቢቀርብላቸው የሚያዩት መነጽራቸው የሚያሳያቸውን ከለር ነው። ሰው ውጩን የሚያይበትን እይታ የሚወስነው በውስጡ የነገሰው ሀሳብ ነው። በውስጣችን የምሬት ንዴት ሀሳብ ካለ በውጩ ምንስ ያማረ ነገር ይኑር ለእኛ ግን ሁሉን ተርጉሞ የሚያሳየን በውስጣችን የነገሰው ምሬትና ንዴት ነው። በአይምሮዋችን የተስፋ መቁረጥ ስሜት እግሩን አስፋፍቶ ከተቀመጠ፣ እውነታችን ሆኖ መነጽራችን ሆኖ ህይወትን ሁሉ የሚያሳየን ያ በኛ ውስጥ ያለው የተስፋ መቁረጥ ስሜት ነው። የጨለሙ ቃላቶችን ስንደጋግም የጨለሙ ሀሳቦች በኛ ነግሰው እንዲመሩን መንገድ እንከፍታለን።

ቃላታችን ሰላማችንን ብቻ ሳይሆን በህይወት የምንራመድበትን እርቀትም ይወስናል። አድቃቂ ቃላት ስንናገር ደቀን እንድንቀር በራሳችን ላይ ከወዲሁ እንተነብያለን። እኔ አያልፍልኝም እኔ ደካማ ነኝ፣ ህይወቴ መራራ የመረረች ነን ብለን ስናወራ፣ የተሻለ ያበበ ያማረ ነገር ከኛ ህይወት ጋር እንደማይዛመድ እራሳችንን እንመስጠዋለን፤ ወዳበበ አቅጣጫ ሳንራመድ እንቀራለን፤ በያንዳንዱ ምርጫችን ደካማ እድለ ቢስ አድርጎ የሚያስቀረንን ምርጫ እናደርጋለን። በሌላ በኩል

አዳሽ ቃላት ስንናገር አይምሮዋችንም እየታደሰ ይመጣል። የተስፋ፣ የሰላም ቃላት ስንናገር እኛም በተስፋና በሰላም እየተሞላን እንመጣለን። በአይምሮዋችን ያለው የበራ ሀሳብም ወደበራ አቅጣጫ ሰተት አድርጎ ይወስደናል። እስቲ በአለማችን በተለያየ አቅጣጫ ትላላቅ ቦታ የደረሱ ሰዎች የተናገሩትን የጻፉትን ነገር እናንብብ፤ በደረሱበት ቦታ ላይ ቃላታቸው ምን ያህል ሀይል እንዳለው አይምሮዋቸውን ለማደስ ምን ያህል እንዳበረከተ ደጋግመው ይናገራሉ። የተስፋ ቃል ከአፋቸው እንደማይጠፋም ይመሰክራሉ።

እውነቱ ያ ነው። ጨለማና ብርሀን አብረው አይቀመጡም። የጨለመ ንግግር እየተናገርን ወደ ተስፋ መንደር ልንደርስ አንችልም።በጨለመ ሀሳብ ተውጠን የተስፋ መንደርን ልንጎበኛት አንችልም። “ በራሴ፣ በቤተሰቤ፣ በህዝቤ ላይ እየተነበይኩ ያለሁት ምን አይነት ቃል ነው?” ብለን ራሳችንን እንመርምር። ልጆቻንን በተመለከተ ቃላታችን እንዴት ሊያድሳቸው ወይ ሊያጎሳቁላቸው እንደሚችል በሚቀጥለው እንመለከታለን፤ እስከዛው ለሁላችን መልካም ቆይታ።

ቃላት

ሰምቻለሁ። በኔ ዝግጅት ብዙ ሰዎች ተገኝተው የደመቀ ፕሮግራሙ መደረጉም አስደስቷኛል።

ዘኢትዮጵያ - በሙዚቃም ዙሪያም ጥሩ እውቀት እንዳለህ፣ ለብዙ ድምጻውያንም ግጥም እንደምትደርስ ይታወቃል። በተጨማሪም “ነስፍ ጡር ስንኞች” የተሰኘ የግጥም መድብል አሳትመሃል። እስኪ ስለ ሳላተምከው የግጥም መድብ ንገረን?

ቴዎድሮስ - መጽሐፉ 76 ግጥሞችን የያዘ ነው። በግጥሞቹም ውስጥ እምነቴን ስሜቴንንና አመለካከቴን ገልጨበታለሁ ብዬ አስባለሁ።

ዘኢትዮጵያ - አሁን እዚህ አገር ምን ልትሰራ አቅደሃል በጋዜጠኝነት ለመሥራት ሀሳብ አለህ ?

ቴዎድሮስ - ጋዜጠኝነቱን ከልቤ የምወደው ሙያ ነው። መቸም ቢሆን አልተወውም። በተለይም አሜሪካን አገር የተሻለ ነጻነት ስላለ በኢትዮጵያዊነትና በዴሞክራሲ በፍትህ ዙሪያ ብዙ ለመሥራት ፍላጎት አለኝ። በኢትዮጵያዊነትና በብሄራዊ ስሜትና ማንነት በዴሞክራሲና በፍትህ ዙሪያ ነጻ ሚዲያ በማቋቋም ከኔ ጋር ለመስራት የሚፈልጉ ወገኖች ስላሉ ከነሱ አብሮ ለመስራት በዝግጅት ላይ ነኝ።

ዘኢትዮጵያ - ነጻ ሚዲያ በአንተ እይታ ምንድነው?

ቴዎድሮስ - ነጻ ሚዲያ በአጭር ኢንተርቪው ተወርቶ የሚያልቅ ጉዳይ አይደለም። በትንሹ ግን ሚዛናዊ የሆነ፣ በተሻለ መጠን እውነትን ለማቅረብ የሚጥር፣ ከስሜታዊነታ ከአሉባልታና ከስም መጠፋፋት ነጻ የሆነ፣ በኃላፊነትና በጨዋነት ለህብረተሰቡ አዎንታዊ አስተዋጽ ኦ የሚያደርግ ማለት ይመስለኛል።

ዘኢትዮጵያ - ጋዜጠኛ ሆነህ ስትሰራ በነበረት ወቅት በድፍረትና በጥልቀት የምትጽፋቸው ጽሁፎችና በምታቀርባቸው የኢንተርቪው ጥያቄዎች ብዙ አድማጮችህ ደስተኛ ቢሆኑም አንዳንድ ሰዎች ግን ቴዲ ኢንተርቪው ሲያደርግ በጥያቄ ያፋጥጣል ይሉሃል ስለዚህ ነገር ምን ትላለህ?

ቴዎድሮስ - እኔ ኢንተርቪው የማደርገው ጥሩ ነገሮች እንዲበረታቱ የማናውቀውን እንድናውቅ የተሳሳተ ነገር እንዲታረም በተሻለ መጠን በኢንተርቪው እውነቱ ጠርቶ እንዲወጣ እፈልጋለሁ። እና ሁሉ ጊዜ ሰዎችን አላፋጥጥም። ሰውን ሁሉ ማፋጠጥም ተገቢ ነው ብዬ አላምንም። ሲናገሩ ዝም ብዬ የምሰማቸው ሰዎች አሉ። ኢንተርቪው እንደምናወራበት ርዕስና እንደ ተጠያቂው ማንነት የሚወሰን ነው።

ቴዎድሮስ.... ከገጽ 10

Page 15: መልካም አዲስ ዓመት ይሁንልን! · ዘኢትዮጵያ ጋዜጣ Zethiopia Ethiopian American Community News NO.86 Sept 2014 202 518 0245 P.o.box 2049, Fairfax, VA
Page 16: መልካም አዲስ ዓመት ይሁንልን! · ዘኢትዮጵያ ጋዜጣ Zethiopia Ethiopian American Community News NO.86 Sept 2014 202 518 0245 P.o.box 2049, Fairfax, VA

16ዘኢትዮጵያ ጋዜጣ Zethiopia Ethiopian American Community News NO.86 Sept 2014 202 518 0245 P.o.box 2049, Fairfax, VA 22031 www.zethiopia com

703.931.2700

202-518-0245

የዘኢትዮጵያ ጋዜጣ ደንበኛ ነዎት የደንበኝነት ቅጽ ሞልተው ጋዜጣው ካልደረስዎት

ይደውሉልን ክፍያ ሳይፈጸሙ ጋዜጣው እየደረስዎት ከሆነ ግን ስህተቱ የኛ ነው፣ መቸም እርስዎም ምን ይደረጋል ማድረግ

ያለብዎትን እርስዎ ያውቃሉ 202 518 0245

www.metrolabdc.com

KASSAHUN TEFERAOffice 202-234-1234Cell 202 413-1092Fax 202 234 1339 Metro Lab, LLC 3422

George Avenue NW Washington, D.C. 20010

Business Hours:8am-5pm Monday - Friday

8am-1pm Saturday

Laboratory Testing Services

Call To Listen

712.432.6885Calls use mobile minutes. Free with unlimited plans.