24
ቃና ሐምሌ 30- ነሐሴ 13 ቀን 2003 (August 6-19, 2011) ዩጋንዳ 1,500 ሺልንግ / ኬንያ 60 ሺልንግ / ደቡብ ሱዳን 3 ፓውንድ አንደኛ ዓመት ቁጥር 004 በደቡብ ሱዳን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከንግድ ባንክ ብድር እንዲያገኙ ሊደረግ ነው ፍቅርተ የሸቀጣ ሸቀጥ መደብር qየባህል ልብሶችና ማንኛውም የባልትና ውጤቶች በጅምላና በችርቻሮ መሸጫ qባህላዊ ምድላው መግብን፤ ክዳውንትን ብጅምላን ብንጽልን መሸጢ ድኳን 1- ካሳንጋ፣ ካባላጋላ ፖሊስ ጣቢያ ከፍ ብሎ 2 ናኩላቢ፣ ቡኬሳ ጋፕኮ ነዳጅ ማደያ ፊት ለፊት በእዚህ ዕትም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለኡጋንዳ ተጓዦች የታሪፍ ማሻሻያ አደረገ ኢትዮጵያ እና ኡጋንዳ ቪዛ እና ተደራራቢ ቀረጥ ሊያስቀሩ ነው በፖለቲካው ረገድ በምስራቅ አፍሪካ ዋ ነኛ ሚና እየተጫወቱ የሚገኙት ኢትዮ ጵያ እና ኡጋንዳ ተደራራቢ ግብር እና ቪዛ ለማስቀረት መንገድ የሚጠርግ ስ ምምነት ተፈራራሙ፡፡ ሁለቱ ሀገራት የተፈራረሙት ስምምነ ት “የጋራ የስትራቴጂክ አጋርነት” በሚ ል የሚጠራ ሲሆን ይህም እንደ ኢንቨ ስትመንት፣ መከላከያ እና ጸጥታ፣ ጤና፣ ትምህርት፣ እርሻ፣ ውሃ እና ኢነርጂ ዘር ፎች ወደፊት ለሚደረጉ ስምምነቶች መ ሰረት የሚጥል ነው፡፡ በስምምነቱ ላይ ፊርማቸውን ያኖሩት የ ኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ እና የኡጋንዳ አቻቸው ሳም ኩቴሳ ነበሩ፡፡ ሁለቱ ባለስልጣናት በተስፋለም ወልደየስ ሐበሻዊ ቃና ወደ ገጽ 2 ዞሯል በምግብ ዋጋ ላይ የሚታየው የዋጋ ግ ሽበት አሁንም እየጨመረ እንደሚገኝ የ ኢትዮጵያ ስታትስቲክስ ባስልጣን የሚ ያወጣው ወርሃዊ ሪፖርት አመለከተ፡፡ በሰኔ ወር የተመዘገበው የ45.3 በመቶ የዋጋ ግሽበት በሐምሌ ወር 47.7 በመ ቶ መድረሱን ሪፖርቱ ያሳያል፡፡ አጠቃ ላይ የዋጋ ግሽበቱም በሰኔ ወር ከነበረበ ት 38.1 በመቶ ወደ 39.2 በመቶ ከፍ ብ ሏል፡፡ የአንድ ሀገር ኢኮኖሚ ጤናማ አ ንዲሆን ከተፈለገ አጠቃላይ የዋጋ ግሽ በቱ ከሁለት ዲጂት በታች እንዲሆን ይ ጠበቃል፡፡ “በምግብ ነክ ዝርዝር ውስጥ ከሚካተ ቱት መካከል በሐምሌ ወር ጭማሪ የታ የው በእህል፣ የቅባት እህሎች፣ ቡና፣ ቃ ሪያ እና በሌሎችም የምግብ ዓይነቶች ነ ው” ሲል ሪፖርቱ ያትታል፡፡ “ምግብ ነ ክ ያልሆኑ አብዛኞቹ ዝርዝሮችም የመ ጨመር አዝማሚያ አሳይተዋል” ይላል፡ ፡ ጭማሪ ካሳዩት ውስጥ የአልባሳት፣ የ በኢትዮጵያ የምግብ የዋጋ ግሽበት መጨመሩን ቀጥሏል በ ኒው ቢዝነስ ኢትዮጵያ ሪፖርተር ወደ ገጽ 2 ዞሯል የኦሮሞ ኮሚዩኒቲ በኡጋንዳ ህልም አልባው ኤርትራዊ ወጣት አዳም ረታ ይናገራል ዳር እና ዛንዚባር በፍቃዱ ጅሬኛ ለማ ይባላሉ። የተ ወለዱት በኢትዮጵያ ኦሮሚያ ክል ል ውስጥ ነው። በኡጋንዳ የኦሮሞ ማህብረሰብ ሊቀመንበር ናቸው። የኦሮሞ ማህብረሰብ በሚያደርጋ ቸው እንቅስቃሴዎች ዙሪያ ከ“ሐበ ሻዊ ቃና” ጋር ቆይታ አድርገዋል። l l l ሰሎሞን ከኤርትራውያን ስደተኛ ቤተሰቦቹ ሱዳን ውስጥ ነው የተወ ለደው። ወላጆቹን ግን አያውቃቸ ውም። አባቱ እርሱ ከመወለዱ በ ፊት ነበር የሞተው። እናቱ ደግሞ እርሱን ስትገላገል በወሊድ ምክንያ ት አርፋለች። እርሱን ያሳደጉት ለነ ፍሳቸው ያደሩ እማሆይ ስላስ የሚ ባሉ እናት ናቸው። l l l በክረምት ከሰፈሬ እስከ ወመዘክ ር ድረስ በእግር ሄጄ መፅሐፍ የማ ነብበት ጊዜ ነበር፡፡ ዝናቡ ይደብ ራል፣ የሰፈርህ ሜዳ ጭቃ ነው ኳ ስ አታለፋም፣ ተሰላችተሃል፡፡ አን ብበህ ወደ ቤትህ ስትመለስ፣ አእ ምሮህ ውስጥ የሚንሳፈፈው ልብ ወለድና ፋንታሲ ብቻ አይደለም፡ ፡ በካፊያ መበስበስህን ማማረር፣ ማታ ተኝተህ ‘እዛ ድረስ ምን አስ ለፋኝ?’ እያልክ ራስህንም መቀናቀ ንህ ነው፡፡ ልብስህ ቆሽሿል፣ ያለካ ልሲ ያደረግከው ሸራ ጫማ ረጥ ቦ፣ እግሮችህ ጨቅይተው እውስ ጡ ይንሸራተታሉ፡፡ ከዚህ ነው የ ወጣኸው፡፡ l l l ልክ እንደአዲስ አበባ ሁሉ ዳሬሰላ ምም ወደ ጎን እየተለጠጠች የመጣ ች ይመስላል። ረዘም ያሉ ህንጻዎ ችን ግን የምታገኙት በከተማይቱ መሃል ብቻ ነው። እነርሱም ቢሆ ኑ እንደአዲስ አበቤዎቹ እንኳ አይ ረዝሙም። የከተማይቱ መሃል እን ደ ዳርቻዎቹ ሰፊ ቦታ ያካለለ አይ ደለም። ዛንዚባር ማለት የባህር ዳርቻ እና መዝናናት ብቻ እንዳልሆነ ተረዳ ሁ። ከአየር ማረፊያው ወደ ከተማ በምጓዝበት ጊዜም የተመለከትኩት ይህንኑ የሚያረጋግጥ ነበር። በደቡብ ሱዳን ቅርንጫፍ ከፍቶ የሚ ሰራው መንግስታዊው የኢትዮጵያ ንግ ድ ባንክ በሀገሪቱ ለሚኖሩ ኢትዮጵያው ያን የብድር አገልግሎት መስጠት ሊጀ ምር ነው፡፡ የብድር አልግሎቱን ለመጀመር የታሰ በው ኢትዮጵያውያን በደቡብ ሱዳን ተ ወዳዳሪ አንዲሆኑ በማሰብ እንደሆነ የ ኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም መስፍን በተለይ ለሐበሻ ዊ ቃና ገልጸዋል፡፡ “ደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ ባንክ አለ ን ግድ ባንክ፡፡ ኢትዮጵያውያን ሀገራቸው ውስጥ ትንሽ ኮላተራል ካለቻቸው አገራ ቸው ያለውን ኮላተራል ይዞ እዚያ ብድ ር እንዲሰጥ እናመቻቻለን፡፡ ይህንን ብ ድር ተጠቅመው መወዳደር አለባቸው” ይላሉ፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በደቡብ ሱዳን ቅርንጫፉን በይፋ የከፈተው እ.ኤ.አ በ መስከረም 2009 ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት ገንዘብ የማስቀመጥ፣ የደመወዝ ክፍያ፣ ለአገር ውስጥና ለዓለም አቀፍ ድርጅቶ ች የዋስትና ሰነድ የመስጠት እንደዚሁ ም የዶክመንተሪ ክሬዲት እና ኮሌክሽን አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡ የ70 ዓመት አንጋፋ ድርጅት የሆነው የ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በመላው ኢትዮ ጵያ 401 ቅርንጫፎች ያሉት ሲሆን በደ ቡብ ሱዳን ያለው ከሀገር ውጭ ያለ ብ ቸኛው ቅርንጫፍ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ን ግድ ባንክ በደቡብ ሱዳን ያለውን የባን ክ ቁጥሮች አነሳነት በመመልከት ቅርን ጫፍ ከከፈቱ ሶስት የውጭ ሀገር ባንኮ ች አንዱ ነው፡፡ ተቀማጭነታቸውን ደ ቡብ ሱዳን ያደረጉ ኢትዮጵያውያን እ ና ኤርትራውያን የባንኩ ተጠቃሚዎች ናቸው፡፡ እ.ኤ.አ ከ2005 ጀምሮ በከፊል ራሷን ስታስተዳደር የቆየችው ደቡብ ሱዳን በ ሐምሌ ወር ሀገር መሆኗን ተከትሎ ኢት ዮጵያውያንን ጨምሮ በርካታ የውጭ ሀገር ባለበብቶች መዋዕለ ንዋያቸውን በሀገሪቱ ለማፍሰስ ጥናቶች እያከሄዱ ይገኛሉ፡፡ ይህንን የኢትዮጵያውያንን ባለሀብቶች ፍላጎት ከግምት ውስጥ መ ንግስት ምን እያደረገ እንደሚገኝ የተጠ የቁት አቶ ኃይለማርያም ሀገራቸው ከደ ቡብ ሱዳን ጋር ስምምነት ለመፈራረም በሂደት ላይ እንደሆነች ተናግረዋል፡፡ “አጠቃላይ የሆነ ስምምነት እያረቀቅ ወደ ገጽ 2 ዞሯል በተስፋለም ወልደየስ ሐበሻዊ ቃና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከኢንተቤ ወ ደ አዲስ አበባ ለሚበሩ ተጓዦች የዋጋ ማሻሻያ አደረገ፡፡ አየር መንገዱ ከአርብ እና እሁድ በስ ተቀር በቀን ሁለቴ ከኢንተቤ ወደ አዲ ስ አበባ የሚበር ሲሆን የዋጋ ማሻሻያው ን ያደረገው በለሊት ለሚያደርገው በረ ራ ነው፡፡ የአየር መንገዱ የለሊት በረራ ከለሊቱ 10 ሰዓት ተነስቶ ከንጋቱ 12 ሰዓ ት ገደማ አዲስ አበባ የሚደርስ ነው፡፡ አየር መንገዱ ከቀኑ 11 ሰዓት ተኩል ተ ነስቶ ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከሩብ ገደማ አዲስ አበባ የሚገባ የበረራ ጊዜም አለ ው፡፡ ለዚህ በረራ ደንበኞች እንዲከፍሉ የሚጠየቀው ገንዘብ 517 ዶላር ነው፡፡ የ ለሊት በረራ ዋጋውም ተመሳሳይ የነበረ ሲሆን አሁን ግን በ50 ዶላር እንዲቀንስ መደረጉን ኢትዮጵያ አየር መንገድ የኡ ጋንዳ ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ እርምጃቸ ው ረጋሳ ለሐበሻዊ ቃና ተናግረዋል፡፡ “በለሊቱ በረራ የሚሄዱትን ተጓዦ ች ቁጥር ለማሳደግ ሲባል የዋጋ ማሻሻ ያ አድርገናል” ይላሉ ወይዘሮ እርምጃ ቸው፡፡ የለሊቱ በረራ ከአንድ ዓመት በፊት የ ተጀመረው ወደ ምዕራብ፣ መካከለኛ ው እና ደቡብ አፍሪካ ለሚጓዙ ደንበኞ ች ታስቦ እንደሆነም ያስረዳሉ፡፡ወደ እ ነዚህ የአፍሪካ ሀገራት የሚጓዙ ደንበኞ ች ከዚህ ቀደም ለሊቱን በአዲስ አበባ ያ ሳልፉ እንደነበር የተናገሩት ስራ አስኪያ ጇ ይህም ለተጓዦች የማይመች ከመሆ ኑ በተጨማሪ አየር መንገዱን ለተጨማ ሪ ወጪ ይዳርገው ነበር፡፡ በኡጋንዳ የሐበሻዊ ቃና ዘጋቢ ገጽ 12

Habeshawi kana 004

Embed Size (px)

DESCRIPTION

 

Citation preview

Page 1: Habeshawi kana 004

ሐምሌ 30-ነሐሴ 13 ቀን 2003 (August 6-19, 2011) ሐበሻዊ ቃና 1

ቃናሐበሻዊሐምሌ 30-ነሐሴ 13 ቀን 2003 (August 6-19, 2011) ዩጋንዳ 1,500 ሺልንግ / ኬንያ 60 ሺልንግ / ደቡብ ሱዳን 3 ፓውንድአንደኛ ዓመት ቁጥር 004

በደቡብ ሱዳን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከንግድ ባንክ ብድር እንዲያገኙ ሊደረግ ነው

ስልክ-0712360631, 0701726165

ፍቅርተ የሸቀጣ ሸቀጥ መደብር

qየባህል ልብሶችና ማንኛውም የባልትና ውጤቶች በጅምላና በችርቻሮ መሸጫ

qባህላዊ ምድላው መግብን፤ ክዳውንትን ብጅምላን ብንጽልን መሸጢ ድኳን

ቁ 1- ካሳንጋ፣ ካባላጋላ ፖሊስ ጣቢያ ከፍ ብሎቁ 2 ናኩላቢ፣ ቡኬሳ ጋፕኮ ነዳጅ ማደያ ፊት ለፊት

በእዚህ ዕትም

ዘጠና ቀናት በጆበርግ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለኡጋንዳ ተጓዦች የታሪፍ ማሻሻያ አደረገ

ኢትዮጵያ እና ኡጋንዳ ቪዛ እና ተደራራቢ ቀረጥ ሊያስቀሩ ነው

በፖለቲካው ረገድ በምስራቅ አፍሪካ ዋነኛ ሚና እየተጫወቱ የሚገኙት ኢትዮጵያ እና ኡጋንዳ ተደራራቢ ግብር እና ቪዛ ለማስቀረት መንገድ የሚጠርግ ስምምነት ተፈራራሙ፡፡ ሁለቱ ሀገራት የተፈራረሙት ስምምነት “የጋራ የስትራቴጂክ አጋርነት” በሚል የሚጠራ ሲሆን ይህም እንደ ኢንቨስትመንት፣ መከላከያ እና ጸጥታ፣ ጤና፣ ትምህርት፣ እርሻ፣ ውሃ እና ኢነርጂ ዘርፎች ወደፊት ለሚደረጉ ስምምነቶች መሰረት የሚጥል ነው፡፡ በስምምነቱ ላይ ፊርማቸውን ያኖሩት የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ እና የኡጋንዳ አቻቸው ሳም ኩቴሳ ነበሩ፡፡ ሁለቱ ባለስልጣናት

በተስፋለም ወልደየስ

ሐበሻዊ ቃና

ወደ ገጽ 2 ዞሯል

በምግብ ዋጋ ላይ የሚታየው የዋጋ ግሽበት አሁንም እየጨመረ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ ባስልጣን የሚያወጣው ወርሃዊ ሪፖርት አመለከተ፡፡ በሰኔ ወር የተመዘገበው የ45.3 በመቶ

የዋጋ ግሽበት በሐምሌ ወር 47.7 በመቶ መድረሱን ሪፖርቱ ያሳያል፡፡ አጠቃላይ የዋጋ ግሽበቱም በሰኔ ወር ከነበረበት 38.1 በመቶ ወደ 39.2 በመቶ ከፍ ብሏል፡፡ የአንድ ሀገር ኢኮኖሚ ጤናማ አንዲሆን ከተፈለገ አጠቃላይ የዋጋ ግሽበቱ ከሁለት ዲጂት በታች እንዲሆን ይጠበቃል፡፡ “በምግብ ነክ ዝርዝር ውስጥ ከሚካተ

ቱት መካከል በሐምሌ ወር ጭማሪ የታየው በእህል፣ የቅባት እህሎች፣ ቡና፣ ቃሪያ እና በሌሎችም የምግብ ዓይነቶች ነው” ሲል ሪፖርቱ ያትታል፡፡ “ምግብ ነክ ያልሆኑ አብዛኞቹ ዝርዝሮችም የመጨመር አዝማሚያ አሳይተዋል” ይላል፡፡ ጭማሪ ካሳዩት ውስጥ የአልባሳት፣ የ

በኢትዮጵያ የምግብ የዋጋ ግሽበት

መጨመሩን ቀጥሏልበ ኒው ቢዝነስ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

ወደ ገጽ 2 ዞሯል

የኦሮሞ ኮሚዩኒቲ በኡጋንዳ

ህልም አልባው ኤርትራዊ ወጣት

አዳም ረታ ይናገራል

ዳር እና ዛንዚባር

በፍቃዱ ጅሬኛ ለማ ይባላሉ። የተወለዱት በኢትዮጵያ ኦሮሚያ ክልል ውስጥ ነው። በኡጋንዳ የኦሮሞ ማህብረሰብ ሊቀመንበር ናቸው። የኦሮሞ ማህብረሰብ በሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ዙሪያ ከ“ሐበሻዊ ቃና” ጋር ቆይታ አድርገዋል።

l l l

ሰሎሞን ከኤርትራውያን ስደተኛ ቤተሰቦቹ ሱዳን ውስጥ ነው የተወለደው። ወላጆቹን ግን አያውቃቸውም። አባቱ እርሱ ከመወለዱ በፊት ነበር የሞተው። እናቱ ደግሞ እርሱን ስትገላገል በወሊድ ምክንያት አርፋለች። እርሱን ያሳደጉት ለነፍሳቸው ያደሩ እማሆይ ስላስ የሚባሉ እናት ናቸው።

l l l

በክረምት ከሰፈሬ እስከ ወመዘክር ድረስ በእግር ሄጄ መፅሐፍ የማነብበት ጊዜ ነበር፡፡ ዝናቡ ይደብራል፣ የሰፈርህ ሜዳ ጭቃ ነው ኳስ አታለፋም፣ ተሰላችተሃል፡፡ አንብበህ ወደ ቤትህ ስትመለስ፣ አእምሮህ ውስጥ የሚንሳፈፈው ልብወለድና ፋንታሲ ብቻ አይደለም፡፡ በካፊያ መበስበስህን ማማረር፣ ማታ ተኝተህ ‘እዛ ድረስ ምን አስለፋኝ?’ እያልክ ራስህንም መቀናቀንህ ነው፡፡ ልብስህ ቆሽሿል፣ ያለካልሲ ያደረግከው ሸራ ጫማ ረጥቦ፣ እግሮችህ ጨቅይተው እውስጡ ይንሸራተታሉ፡፡ ከዚህ ነው የወጣኸው፡፡

l l l

ልክ እንደአዲስ አበባ ሁሉ ዳሬሰላምም ወደ ጎን እየተለጠጠች የመጣች ይመስላል። ረዘም ያሉ ህንጻዎችን ግን የምታገኙት በከተማይቱ መሃል ብቻ ነው። እነርሱም ቢሆኑ እንደአዲስ አበቤዎቹ እንኳ አይረዝሙም። የከተማይቱ መሃል እንደ ዳርቻዎቹ ሰፊ ቦታ ያካለለ አይደለም።ዛንዚባር ማለት የባህር ዳርቻ እና መዝናናት ብቻ እንዳልሆነ ተረዳሁ። ከአየር ማረፊያው ወደ ከተማ በምጓዝበት ጊዜም የተመለከትኩት ይህንኑ የሚያረጋግጥ ነበር።

በደቡብ ሱዳን ቅርንጫፍ ከፍቶ የሚሰራው መንግስታዊው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሀገሪቱ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የብድር አገልግሎት መስጠት ሊጀምር ነው፡፡ የብድር አልግሎቱን ለመጀመር የታሰ

በው ኢትዮጵያውያን በደቡብ ሱዳን ተወዳዳሪ አንዲሆኑ በማሰብ እንደሆነ የ

ኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም መስፍን በተለይ ለሐበሻዊ ቃና ገልጸዋል፡፡ “ደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ ባንክ አለ ን

ግድ ባንክ፡፡ ኢትዮጵያውያን ሀገራቸው ውስጥ ትንሽ ኮላተራል ካለቻቸው አገራቸው ያለውን ኮላተራል ይዞ እዚያ ብድር እንዲሰጥ እናመቻቻለን፡፡ ይህንን ብድር ተጠቅመው መወዳደር አለባቸው” ይላሉ፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በደቡብ ሱዳን

ቅርንጫፉን በይፋ የከፈተው እ.ኤ.አ በመስከረም 2009 ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት ገንዘብ የማስቀመጥ፣ የደመወዝ ክፍያ፣ ለአገር ውስጥና ለዓለም አቀፍ ድርጅቶች የዋስትና ሰነድ የመስጠት እንደዚሁም የዶክመንተሪ ክሬዲት እና ኮሌክሽን አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡ የ70 ዓመት አንጋፋ ድርጅት የሆነው የ

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በመላው ኢትዮጵያ 401 ቅርንጫፎች ያሉት ሲሆን በደቡብ ሱዳን ያለው ከሀገር ውጭ ያለ ብ

ቸኛው ቅርንጫፍ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በደቡብ ሱዳን ያለውን የባንክ ቁጥሮች አነሳነት በመመልከት ቅርንጫፍ ከከፈቱ ሶስት የውጭ ሀገር ባንኮች አንዱ ነው፡፡ ተቀማጭነታቸውን ደቡብ ሱዳን ያደረጉ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን የባንኩ ተጠቃሚዎች ናቸው፡፡ እ.ኤ.አ ከ2005 ጀምሮ በከፊል ራሷን

ስታስተዳደር የቆየችው ደቡብ ሱዳን በሐምሌ ወር ሀገር መሆኗን ተከትሎ ኢት

ዮጵያውያንን ጨምሮ በርካታ የውጭ ሀገር ባለበብቶች መዋዕለ ንዋያቸውን በሀገሪቱ ለማፍሰስ ጥናቶች እያከሄዱ ይገኛሉ፡፡ ይህንን የኢትዮጵያውያንን ባለሀብቶች ፍላጎት ከግምት ውስጥ መንግስት ምን እያደረገ እንደሚገኝ የተጠየቁት አቶ ኃይለማርያም ሀገራቸው ከደቡብ ሱዳን ጋር ስምምነት ለመፈራረም በሂደት ላይ እንደሆነች ተናግረዋል፡፡ “አጠቃላይ የሆነ ስምምነት እያረቀቅ

ወደ ገጽ 2 ዞሯል

በተስፋለም ወልደየስ

ሐበሻዊ ቃና

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከኢንተቤ ወደ አዲስ አበባ ለሚበሩ ተጓዦች የዋጋ ማሻሻያ አደረገ፡፡አየር መንገዱ ከአርብ እና እሁድ በስ

ተቀር በቀን ሁለቴ ከኢንተቤ ወደ አዲስ አበባ የሚበር ሲሆን የዋጋ ማሻሻያውን ያደረገው በለሊት ለሚያደርገው በረ

ራ ነው፡፡ የአየር መንገዱ የለሊት በረራ ከለሊቱ 10 ሰዓት ተነስቶ ከንጋቱ 12 ሰዓት ገደማ አዲስ አበባ የሚደርስ ነው፡፡ አየር መንገዱ ከቀኑ 11 ሰዓት ተኩል ተ

ነስቶ ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከሩብ ገደማ አዲስ አበባ የሚገባ የበረራ ጊዜም አለው፡፡ ለዚህ በረራ ደንበኞች እንዲከፍሉ የሚጠየቀው ገንዘብ 517 ዶላር ነው፡፡ የለሊት በረራ ዋጋውም ተመሳሳይ የነበረ

ሲሆን አሁን ግን በ50 ዶላር እንዲቀንስ መደረጉን ኢትዮጵያ አየር መንገድ የኡጋንዳ ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ እርምጃቸው ረጋሳ ለሐበሻዊ ቃና ተናግረዋል፡፡“በለሊቱ በረራ የሚሄዱትን ተጓዦ

ች ቁጥር ለማሳደግ ሲባል የዋጋ ማሻሻያ አድርገናል” ይላሉ ወይዘሮ እርምጃቸው፡፡ የለሊቱ በረራ ከአንድ ዓመት በፊት የ

ተጀመረው ወደ ምዕራብ፣ መካከለኛው እና ደቡብ አፍሪካ ለሚጓዙ ደንበኞች ታስቦ እንደሆነም ያስረዳሉ፡፡ወደ እነዚህ የአፍሪካ ሀገራት የሚጓዙ ደንበኞች ከዚህ ቀደም ለሊቱን በአዲስ አበባ ያሳልፉ እንደነበር የተናገሩት ስራ አስኪያጇ ይህም ለተጓዦች የማይመች ከመሆኑ በተጨማሪ አየር መንገዱን ለተጨማሪ ወጪ ይዳርገው ነበር፡፡

በኡጋንዳ የሐበሻዊ ቃና ዘጋቢ

ገጽ 12

Page 2: Habeshawi kana 004

ሐምሌ 30-ነሐሴ 13 ቀን 2003 (August 6-19, 2011)ሐበሻዊ ቃና2

ን ነው” ይላሉ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ፡፡ “አጠቃላይ ነገር ስለምንሰራ እዚያ ውስጥ ዜጎች ከዜጎች ልውውጥ ይኖራል፡፡ ሁለትዮሽ ነው፡፡ እነርሱም እኛ ጋር መስራት እንዲችሉ፤ የእኛዎቹ ደግሞ የሀገሩን ህግ ጠብቀው የቻሉትን እንዲሰሩ ለማድረግ ጥረት ይደረ

ጋል” ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያ ለደቡብ ሱዳን ነጻነት ካበረከተ

ችው አስተዋጽኦ በመነሳት የተለየ የሆነ መበረታቻ ለዜጎች እንደማይኖርም ገልጸዋል፡፡ “እኛ ኢትዮጵያውያን ሳይወዳደሩ የተለየ ነገር እንዲያገኙ አንፈልግም፡፡ ኪራይ ሰብሳቢነት ነው የሚሆነው፡፡ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ነው የምንፈልገው፡፡ የላቀ ስራ ለመስራት ምን ይጎድላቸዋል ብለን እሱን መደገፍ ነው የምንመርጠው፡፡ ሳይወዳደሩ ከሌላ

ው የተለየ ትርፍ አገኛለሁ ማለት አገርን ይጎዳል፡፡ ስለዚህ ራሳችን የማናደርገውን ሌላው ጋር አድርጉ ብለን አንሄድም” ሲሉ አብራርተዋል፡፡መንግስት ለባለሀብቶች ከሚሰጠው ድጋ

ፍ ባሻገር ብዙዎች እንደሚሰጉት ደቡብ ሱዳን በቅርቡ ከተለየችው ሰሜን ሱዳን ጋር ግጭት ውስጥ ብትገባ ለዜጎቹ ተገቢውን ድጋፍ እንደሚያደረግም ይናገራሉ፡፡ “የኢትዮጵያ መንግስት መጀመሪያ ደቡብ

ሱዳን ሰላም እንዲሆን ይሰራል፡፡ ደቡብ ሱዳን ሰላም አይሆንም የሚል ግምገማ የለንም፡፡ ግምገማችን ይሄ ቢሆንም ድንገት የሚፈጠር ነገር ካለ የመን እና ሊቢያ ላይ እንዳደረግነው ሁሉ እንዳደረግነው ሁሉ እናደርጋለን” ብለዋል፡፡ በየመን እና ሊቢያ በተቀሰቀሱት ግጭቶች ምክንያት የተወሰኑ ኢትዮጵያውያን በዓለም የስደተኞች ድርጅት (አይ ኦ ኤም) ድጋፍ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡

ዜና

ቃናሐበሻዊበሐበሻ ኮሚዩኒኬሽን ሊትድ በየ15 ቀኑ

የሚታተም ጋዜጣ

ዋና አዘጋጅ- ተስፋለም ወልደየስ

የዝግጅት ክፍሉ አድራሻ

ዩጋንዳ ካምፓላ

ጋባ ሮድ-ካንሳንጋ

ዲዲስ ወርልድ አጠገብ ባለው የናይል ቢራ

ማከፋፈያ ህንጻ አንደኛ ፎቅ ቁጥር 6

ስልክ +256-778-693669

ኢሜይል [email protected]

ፖ.ሳ.ቁ - 28268ካምፓላ-ኡጋንዳ

ሐምሌ 15 ቀን በካምፓላው ሙኞንኞ ሪዞርት ማዕከል በተደረገው በዚህ የፊርማ ስነስርዓት ላይ የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን ለማቋቋም የቀረበውን ሰነድ በፊርማቸው አጽድቀዋል፡፡ “በሁለቱም ሀገራት ተደራራቢ ግብር ለማስቀረት የሁለቱ ሀገራት የገንዘብ ሚኒስትሮች መስማማት አለባቸው” ይላሉ አቶ ኃይለማርያም፡፡ “ይህ ጠቅላላ ስምምነት ተደራራቢ ግብር ለማስቀረት ወደሚደረግ ድርድር ይመራቸዋል፡፡”

ተደራራቢ ግብር ማለት በተመሳሳይ የገቢ፣ የንብረት እና የገንዘብ ዝውውሮች ላይ በሁለት እና ከዚያ በላይ ሀገሮች የሚጣሉ ታክሶችን የሚገልጽ ነው፡፡ “ይህ ስምምነት እንደሚፈረም ተስፋ አደርጋለሁ” ሲሉ እምነታቸውን የሚናገሩት አቶ ኃይለማርያም “ነገር ግን በጠቅላላ ስምምነቱ መሰረት ድርድር መደረግ ይኖርበታል” ይላሉ፡፡ “የጋራ የስትራቴጂክ አጋርነት” ስምምነቱ ሁለቱ አገራት ከተደራራቢ ግብር ባ

ከመክፈቷ በፊት ነበር፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ እና የኡጋንዳው ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ስምምነቱን እ.ኤ.አ በህዳር 1993 ፈርመዋል፡፡ ከሁለት ዓመት በኋላ ደግሞ ኢትዮጵያ ቆንስላ ጽህፈት ቤቷን በኡጋንዳ ከፍታለች፡፡ እ.ኤ.አ በ1995 የቆንስላው ጽህፈት ቤት ወደ ኤምባሲ ደረጃ ከፍ ቢልምና የመጀመሪያው አምባሳደር ቢሾምም በሁለቱ ሀገራት መካከል የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን ለማቋቋም የተፈረመው ስምምነት እስከአሁንም ድረስ ተግባራዊ ሳይደረግ ቆይቷል፡፡ ኢትዮጵያ ከረጅም ዓ

ረሃብ ስንት ቀን ይሰጣል?

ኢትዮጵያ እና... ከገጽ 1 የዞረ

ባለፉት 60 ዓመታት በምስራቅ አፍሪካ ከታዩት የከፋ ነው የተባለለት ድርቅ ባስከተለው ረሃብ ወደ 10 ሚሊዮን የሚጠጋ ህዝብ ተጠቂ ሆኗል፡፡ ይፋዊ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ከዚህ ቁጥር ውስጥ ሩብ ያህል የሚሆኑት ኢትዮጵያውያን ናቸው፡፡ በኢትዮጵያ ችግሩ የገረፋቸው በምስራቅ፣ በደቡብ ምስራቅ እና በደቡብ ኢትዮጵያ የሚገኙ አካባቢዎች ናቸው፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ረሀብ ክፉኛ ያጠቃው በምስራቅ ኢትዮጵያ የሚገኘው የሶማሌ ክልል ነው፡፡ በደቡብ ምስራቅ ኢትዮጵያ ኦሮሚያ ክልል ውስጥ የሚገኘው የቦረና አካባቢም እንዲሁ ጉዳቱ በግልጽ የሚታይበት ነው፡፡ ደቡብ ኢትዮጵያ አካባቢው እንደወትሮው ለምለም ቢሆንም ፈረንጆቹ “ግሪን ሀንገር” በሚሉት ረሀብ የሚሰቃዩ በርካታ ሰዎች ያሉበት ነው፡፡ አካባቢዎቹን የጎበኙ ጋዜጠኞች በሄ

ዱባቸው ቦታዎች ሁሉ በረሃቡ ምክንያት ሰዎች እየሞቱ እንደሆነ መረዳታቸውን ለሐበሻዊ ቃና ከአዲስ አበባ ገልጸዋል፡፡ “ረሃብ አለ፡፡ በመንደሮች ውስጥ በርካታ ሰዎች እየሞቱ ነው፡፡ በተለይ ህጻናት፡፡ ነገር ግን የሞቱ ሰዎች የሚመዘገቡበት የመረጃ ስርዓት ስለሌለ ምን ያህል እንደሆኑ ማወቅ ያስቸግራል” ሲል አንድ ስሙ እንዲጠቀስ ያልፈለገ ጋዜጠኛ ተናግሯል፡፡ “በሶማሌ ክልል ባሉ ካምፖች ውስጥ ግን የሚሞቱት ስለሚመዘገቡ ቁጥሩ ይታወቃል፡፡ ከሁለት ሳምንት በፊት በነበረ መረጃ መሰረት በካምፖች ውስጥ ከአንድ ሺህ ሰው 10 ሰው

ይሞታል፡፡ ቁጥሩ 13 ከደረሰ በይፋ ጠኔ (ፋሚን) ደረጃ ደርሷል ይባላል” ሲል ጋዜጠኛው ያብራራል፡፡ በሶማሌ ክልል ውስጥ ባሉ ካምፖች

ውስጥ ያሉ ሰዎች ምንም እንኳ ከሶማሊያ የመጡ ስደተኞች ናቸው ቢባልም ጋዜጠኞች እንደሚሉት ከሆነ ግን ብዙ ኢትዮጵያውያን ሶማሌዎችም እንደስደተኛ ተመዝግበው እርዳታ እየተቀበሉ ነው፡፡ “ኢትዮጵያውያኑ ካምፕ ለመግባት ከሶማሊያ ነው የመጣነው ይላሉ” ይላል ጋዜጠኛው፡፡ በሶማሌ ክልል ማንነት መለየት አዳጋች እንደሆነው ሁሉ በደቡብ በኩል ደግሞ በትክክል የተራበው

ን ሰው ቁጥር ማወቅ አስቸጋሪ ነው፡፡ በረድኤት ድርጅቶች እና በመንግስት መካከል የሚታየው ከፍተኛ የቁጥር ልዩነት አሁንም እንዳወዛገበ ነው፡፡ ከሆሳዕና ከተማ አቅራቢያ ያለችውን

ታዛ ከተማ የጎበኘ ሌላ ጋዜጠኛ በአካባቢው ላይ የዳሰሳ ጥናት ባደረገው ወርልድ ቪዥን እና በመንግስት የወረዳ ኃላፊዎች ዘንድ የቁጥር መፋለሶችን አስተውሏል፡፡ “ወርልድ ቪዥን 37 ሺህ ነው ሲል መንግስት ደግሞ 10 ሺህ ነው ይላል” ሲል ትዝብቱን ለሐበሻዊ ቃና አካፍሏል፡፡

ወደ ደቡብ ምስራቅ ኢትዮጵያ የተጓዘ ሌላ ጋዜጠኛ በበኩሉ በየመንገዱ ከብቶች ሞተው መመልከቱን ተናግሯል፡፡ ጋዜጠኛው የተመለከታቸው የቦረና እና ጉጂ ዞኖች ነዋሪዎች አርብቶ አደሮች ሲሆኑ ህይወታቸው የተቆራኘው ከከብቶቻቸው ህልውና ጋር ነው፡፡ የከብቶችን ወተት ያጡ እና በረሃቡ የተጎዱ በርካታ ህጻናት በእነዚህ አካባቢ መሞታቸውን ጋዜጠኛው ያስረዳል፡፡ የረሃቡ ሁኔታ በኦሞ ሸለቆ ያሉ ኢት

ዮጵያውንን ከጎረቤት ሀገር ዜጎች ጋር እንዲጋጩ እና ደም እንዲቃቡ አድርጓቸዋል፡፡ የኢትዮጵውያን ሜርሊ (ኝያንጋቶም) ጎሳ አባላት ዓርብ ሐምሌ 29 ድንበር ተሻግረው ባደረሱት ጥቃት 20 ኬንያውያንን መግደላቸውን የሀገሪቱ ብዙሃን መገናኛዎች ዘግበዋል፡፡ ኢትዮጵያውያኑ ወደ 200 የሚጠጋ ከብቶች መዝረፋቸውም ተነግሯል፡፡ ድንበርተኞቹ ኢትዮጵያውያን እ

ና ኬንያውያን አርብቶ አደሮች ሲሆኑ ከብቶቻቸው ከዘራፊ ለመከላከል ጦር መሳሪያ ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ ናቸው፡፡ በእነዚህ አካባቢዎች የከብት ዘረፋ የተለመደ ቢሆንም አካባቢውን ክፉኛ የጎዳው ድርቅ ግን ግጭቱን አባብሶታል፡፡ በርካቶች በድርቁ ምክንያት የሚበላ ለማግኘት ወደ አሳ ማጥመድ ፊታቸውን እንዲያዞሩ አስገድዷቸዋል፡፡ የቱርካና (ሮዶልፍ) ሀይቅን ለመጠቀም የሚደረገው ሽሚያ ደገም የግጭቶች መነሻ እየሆኑ ነው፡፡

በኡጋንዳ የሐበሻዊ ቃና ዘጋቢ

ቤት ኪራይ፣ የኮንስትራክሽን ግብዓቶች እና ነዳጅ ይገኙበታል፡፡ ሆኖም የምግብ ዋጋ ዝርዝሮችን በሚያሳየው የሪፖርቱ ክፍል የተ

መዘገበው ጭማሪ በሰኔ ወር ከተመዘገበው ረገብ ያለ መሆኑን ያሳያል፡፡ በመላው ሀገሪቱ የሚታየው አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ባለፈው ዓመት ጋር በሐምሌ ወር ከነበረው ጋር ሲነጻጸር 19.8 በመቶ መጨመሩን ሪፖርቱ ያመለክታል፡፡ ምግብ ነክ ባልሆኑ ዓይነቶች ላይ የሚታየው የዋጋ ግሽበት ካለፈው ዓመት ሐምሌ ወር ጋር ሲነጻጸር በ22.6 በመቶ ጭማሪ ያሳያል፡፡

በደቡብ ሱዳን....

ሻገር በኢሚግሬሽን እና ቪዛ ጉዳይ ላይ “ፕሪንሲፕል ኦፍ ሪሲፕሮሲቲ” እንዲጠቀሙ የሚያስችላቸው ነው፡፡“ፕሪንሲፕል ኦፍ ሪሲፕሮሲቲ” ተግባራዊ የሚደረገው ሁለት አገራት የጉዞ ገደቦች እና ቪዛ ለማግኘት መሟላት የሚገባቸውን ጉዳዮች ለማላላት ውሳኔ ላይ ሲደርሱ ነው፡፡ ይህ መርህ ሁለቱ አገራት በወንጀል የሚፈልጓቸውን ሰዎች አንዱ ለአንዱ አሳልፎ እንዲሰጥ የሚያደርግ ነው፡፡ መርሁ ስራ ላይ እንዲውል ግን በሁለቱ አገራት የኢሚግሬሽን ባለስልጣናት አማካኝነት ስምምነት ተዘጋጅቶ መፈረም ይገባዋል፡፡

“በዚህ ስምምነት መሰረት ወደፊት በሁለቱ ሀገራት ይፈረማል ተብሎ በሚጠበቀው የጋራ መግባቢያ ሰነድ በሚፈረም ጊዜ ዝርዝር ድርድሩ ይካሄዳል፡፡ በሁለቱ ሀገራት ፓርላማዎችም በስተኋላ ላይ መጽደቅ ይገባዋል” ሲሉ አቶ ኃይለማርያም ተናግረዋል፡፡ “በሁለቱ ፓርላማዎች ከመጽደቁ በፊት ግን ተፈጻሚነት አይኖረውም፡፡” ኢትዮጵያ እና ኡጋንዳ የዲፕሎማቲክ ግንኙነታቸውን የጀመሩት እ.ኤ.አ በ1970 ዓ.ም ነው፡፡ ሁለቱ አገራት የግንኙነትና ትብብር ስምምነት የተፈራረሙት ኢትዮጵያ የቆንስላ ጽህፈት ቤቷን በኡጋንዳ

መታት በኋላ አዲስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መሾሟን ተከትሎ ግን ሀገሪቱ ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ላላት ግንኙነት ትኩረት መስጠት ጀምራለች፡፡ ይህ ትኩረት በተለይም በምስራቅ አፍሪካ በይነ መንግስታት ድርጅት (ኢጋድ) ጥላ ስር ላሉ የምስራቅ አፍሪካ ላይ ያይላል፡፡ ሀገሪቱ ቀድሞ በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር የነበሩትን አቶ ኃይለኪሮስ ገሰሰን በሱዳን፣ የቀድሞው የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የነበሩትን ደግፌ ቡላን በኡጋንዳ መመደቧ በምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ እየጨመረ የመጣውን ፍላጎቷን ያሳያል፡፡

ከገጽ 1 የዞረ

በኢትዮጵያ የምግብ... ከገጽ 1 የዞረ

ፎቶ (ጎን እና ከላይ) ከሆሳዕና ከተማ አቅራቢያ ባለችው ታዛ ከተማ በሺህዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች የምግብ ዕርዳታ ያስፈልጋቸዋል፡፡

በምግብ ከተጠቁት የከተማዋ እና አካባቢያዋ ነዋሪዎች መካከል አብዛኞቹ እናቶች እና

ህጻናት ናቸው(ግራ ታች) በቦረና ድርቅ በርካታ ከብቶችን

ገድሏል፡፡

Page 3: Habeshawi kana 004

ሐምሌ 30-ነሐሴ 13 ቀን 2003 (August 6-19, 2011) ሐበሻዊ ቃና 3

ዜና

ሐበሻዊ ቃና በፌስ ቡክ habeshawi kana ብላችሁ ፈልጉን

“ላይክ” () የሚለውን ምልክት ተጫኑ

ወቅታዊ ዘገባዎች፣ “ሊንኮች”ን እና

ፎቶዎች ያገኛሉ

ባለፉ የጋዜጣው እትሞች ላይ የወጡ

ጽሁፎችን ያገኛሉ

ማስታወቂያ

q የሴትና የወንድ አልባሳትን

q ሻርፖችን

q የጠረጴዛና የአልጋ ልብሶችን

q የተለያዩ የባልትና ውጤቶችን

ሁሉንም በተመጣጣኝ ዋጋ ያገኛሉ

ሜሪ መጥቶ ምን ጠፍቶ!

አድራሻችን- ካምፓላ ካሳንጋ

ሰንሻይን ሆቴል ፊት ለፊት

ስልክ 0702003484

የሐበሻ ምርቶችን ከፈለጉ ይጎብኙን

ስለ ኑሮ ውድነትትልቁ ጥያቄ የዋጋ ግሽበት ነው፡፡ በእ

ርግጥ የከተማው ኖሮ የተናጋበት ዋናው ምክንያት እንደምታውቁት የዋጋ ንረቱ መጀመሪያ የሚያጠቃው የመንግስት ሰራተኛውን እና አነስተኛ ገቢ ያለውን የህብረተሰብ ክፍል ነው፡፡ የመግዛት አቅሙን በከፍተኛ ሁኔታ ስለሚያሽመደምድ ማለት ነው፡፡ በእኛ ሀገር ያለውን የዋጋ ግሽበት ሁኔታው ምንድነው? የሚለውን ማጥናት ያስፈልጋል፡፡ አንዱ የዋጋ ግሽበት ዋናው ምንጭ የሆነው የነዳጅ ዋጋ ነው፡፡ በመካከለኛው ምስራቅ በተፈጠረው ችግር ምክንያት የነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ ደረጃ ጨምሯል፡፡ እኛ ደግሞ ነዳጅ አምራች አይደለንም፡፡ ስለዚህ የዋጋ ንረት ቢመጣ ስለዚህ ከውጭ የሚመጣ ነው፡፡ ሁለተኛው የዓለም የምግብ ዋጋ ከፍ ብ

ሏል፡፡ የዓለም የምግብ ዋጋ ወይም ደግሞ የግብርና ምርቶች ቡናን ጨምሮ ከ

ፍ ብሏል፡፡ ቡና ዓለም ላይ የሚሸጥበት ዋጋ “ጉድ” ነው፡፡ ስለዚህ ቡና ዓለም ላይ የሚሸጥበት ዋጋ ነው ሀገር ውስጥም ሊሆን የሚችለው፡፡ ከዓለም ዋጋው ጋር ተመሳሳይ ነው ማድረግ እንጂ የምንችለው እኛ የምንቆጣጠረው አይደለም፡፡ የዓለም የቡና ዋጋ ከፍ ካለ እኛ ሀገርም በግድ ነው ከፍ የሚለው ማስቆም አንችልም፡፡ ስለዚህ የቡና ዋጋ በኪሎ ወደ መቶ ብር ገደማ ደርሷል፡፡ ይሄ የዓለም ዋጋ ነው፡፡ ምንም ማድረግ አንችልም፡፡ ስለዚህ ቡና ገዝቶ ለመጠጣት የሚፈልግ ሰው በዓለም ዋጋ ገዝቶ ነው የሚጠጣው ማለት ነው፡፡ እራሱ የሚያመርት ካልሆነ በስተቀር፡፡ ለዚህ መንግስት ምን አደረገ ነው? መንግስት የዓለም ዋጋን መቆጣጠር አይችልም፡፡ ሁሉንም ነገር ከፍብሏል፡፡ ድሮ በአን

ድ ብር የምንገዛው ሳሙና አሁን 30 ብር ሆኗል፡፡ ሳሙናን መደጎም ከጀመርን ሌላውንም መደጎም ከጀመርን ማቆሚያ

የለውም፡፡በምንም መንገድ ጤፍ የዛሬ አምስት አ

መት 200 ብር የነበረበት ቦታ ጋር ሊወርድ አይችልም፡፡ በምንም ተዓምር፡፡ ሊሆን የሚችለው አንድ ዋጋ ላይ ከደረሰ በኋላ ተረጋግቶ ሳይጨምር እንዲቆይ ማድረግ ነው፡፡ እርግጥ ነው በዚህ ሂደት ውስጥ ህብረ

ተሰቡ በተለይ አነስተኛ ገቢ ያለው የህብረተሰብ ክፍል፣ የመንግስት እና ተቀጣሪ ሰራተኛው ክፉኛ ተጎድቷል፡፡ ይህንንም መንግስት ይቀበለዋል፡፡

ስደተኞችን በተመለከተሀገራችን ውስጥ የስራ ፈጠራ ይህ ለስ

ደተኛ፣ ይሄ ለዳያስፖራ፣ ይሄ ለሴት፣ ይሄ ለወንድ እያለን መከፋፈል አንችልም፡፡ ሀገራችን ውስጥ በአጠቃላይ ስራ ሊፈጥሩ የሚችሉትን መያዝ ያለብን፡፡ አሁን ዳያስፖራውን አነሳስታችኋል (እንባላለን)፡፡ አገር ውስጥ ያለው ሰው ደግሞ ተቀይ

ሟል፡፡ ለምንድነው የተቀየመው? “ጅቡቲ ሄደን መምጣት አለብን ማለት ነው?” እያለ ነው፡፡ “እኛም ጅቡቲ ሄደን ቆይተን ከመጣን መሬት በነጻ ትሰጡናላችሁ” ፣ ሌላም ሌላም ይላል ፡፡ “እኔ ፕሮፌሰር ሆኜ እዚህ እየፈጋሁ አገር ጥሎ ለሄደ ሰው እያደላችሁ ነው” እያለ አንገታችንን ነው የያዘው፡፡ “የምታዳሉ ከሆነ ሀገሬን ጥዬ መሄድ አለብኝ ማለት ነው” ይላል፡፡ እኛ ላሜቦራዎች እነዚያ ዳያስፖራዎች ብለው ነው የሰየሙት፡፡ ስለዚህ ማቆም ነበረብን፡፡ ከዚህ በኋላ ዳያስፓራውም ሀገር ውስ

ጥ ያለውም በውድድር መሆን አለበት፡፡ የነጻ ገበያ የሚፈቅደውን ውድድር ተወዳድሮ ያሸነፈ ይወሰድ፡፡ እኛ ግን ለውድድር የሚያስፈልገውን ሪሶርስ ማቅረብ አለብን፡፡ ከዚያ ውጭ ለስደተኛ ስራ ፈጠራ ብለን ብንመጣ እዚያ ያለው ስራ አጥ መዓት ነው፡፡ ሀገሩ ብቻ ቁጭ ስላለ የተሰደደውን እየለቀምን ስራ እየሰጠን እ

ኔ ደግሞ እዚህ ቁጭ ያልኩት ስራ ሳላገኝ የሚል ጥያቄ ይነሳል፡፡ በርካታ ወጣቶች እኮ አሉ ስራ የማያገኙ፡፡ ስላልተሰደዱ አይታዩም፡፡ ግን የስደተኞች መብት እና ጥቅም ባሉ

በት ሀገር እንዲጠበቅ አቅደን እየሰራን ነው፡፡ ለምሳሌ መካከለኛው ምስራቅ አካባቢ እነሱ ባሉበት አካባቢ ቆንስላ ከፍተን ጥቅሞቻቸውን እና መብቶቻቸውን ለማስከበር እየሄድን ነው ያለነው፡፡ የየሀገሩ መንግስታት ግን መፍቀድ አለባቸው፡፡ ይሄ ዲፕሎማሲ ነው፡፡ አሸንፈን ነው መብታቸውን የምናስከብረው፡፡ ሳዑዲ አረቢያ ላይ ያሉ የእኛ ዜጎች ባ

ሪያዎች ናቸው፡፡ ዘመናዊ ባሪያዎች ናቸው፡፡ ፓስፖርታቸው ይይዛል፡፡ ከዚያ በኋላ በስሙ ስም ነው ኢንቬስት ቢያደርጉ፣ ገንዘብ ቢያስቀምጡ፣ እንደፈለገ ነው የሚያደርጋቸው፡፡ ዛሬ ከፈለገ ንግዳቸውን ዘግቶ ይመልሳል፡፡ ይሄ የመንግስታቸው ፖሊሲ ነው፡፡ በቅርቡ ሳዑዲ አረቢያ ነበርኩ፡፡ ለንጉሱም ጭምር ይሄን አቀረቡ፡፡ “እባክዎን ይሄ ነገር ዜጎቻችንን እየጎዳ ነው፡፡ እርሶ አሳቢ ነዎት፣ የበላይ ጠባቂም ነዎት፡፡ ስለዚህ እባክዎትን ለዜጎቻችን ትንሽ ይከፍትላቸው” አልኳቸው፡፡ ከዚያ 30 ሺህ እሺ አሉ፡፡ “ከዚህ በፊት የመጣውን ትመልሳለህ፡፡ አዲስ የሚመጣው ግን ህጋዊ በሆነ መንገድ 30 ሺህ ይምጣ” አሉ፡፡ ይሄም አንድ መሻሻል ነው፡፡ ከዚህ በኋላ በህጋዊ መንገድ 30 ሺህ እንልካለን በሀገሩ ተመዝግበው የሚኖሩ እንልካለን፡፡ እዚያ ያሉትን መልሰንም ቢሆን እንደምንልክ እናያለን ብለን መልሱን ይዘን መጣን፡፡ በየሀገሩ ያለው በጣም አግባብ ያልሆነ

ፖሊሲ ነው፡፡ ያ ፖሊሲ ደግሞ የየመንግስታቱ ስለሆነ ምንም ማድረግ አንችልም፡፡ ዲፕሎማሲ መስራት ካልሆነ በስተ

ቀር፡፡ ስለዚህ ተዘንግቶ ሳይሆን ችግሩ ይሄ ነው፡፡ ሁለተኛው በሀገር ቤት ውስጥ መስራት ነው፡፡ ሁላችሁም እንደምታውቁት እነዚህ ሰዎች የቤት ሰራተኛ ለመሆን ነው የሚሄዱት፡፡ አዲስ አበባ ላይ የቤት ሰራተኛ የለም፡፡ አዲስ አበባ ላይ የቤት ሰራተኛ ዋጋ 700 ወይም 800 ብር ደርሷል፡፡ ሰው የቤት ሰራተኛ ፈልጎ አያገኝም፡፡ ነገር ግን አረብ አገር ሄዶ እየተሰቃየ መስራት ይፈልጋል፡፡ ይሄ የአመለካከት በሽታ ነው፡፡ አገሩ ተመሳሳይ ስራ አለ፡፡ በእርግጥ እኔ ያልገባኝ ነገር ሊኖር ይችላል፡፡ እኛ እንደ ህብረተሰብ የቤት ሰራተኞችን በጣም የምንጨቁን ከሆነ ማየት አለብን፡፡ ካልሆነ የቤት ሰራተኝነት ኢትዮጵያ ውስጥ በታጣበት ሁኔታ ይሄ ሁሉ ሴት ለምንድነው ለመሰቃየት የሚጎርፈው ፡፡ አነጋግረናቸው ነበር፡፡ ከቤት ወጥተው አያውቁም፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ግን ብዙ ቤት ውስጥ ማታ ትምህርት እየተማሩ ነው የቤት ስራ የሚሰሩት፡፡ ይህን ነጻነት ትተው ለምንድነው እዚያ መታሰር የፈለጉት? ይሄ የአመለካከት በሽታ ቢሆን ነው እንጂ ምን ማለት ነው፡፡ ከከምባታ እና ሀዲያ አካባቢ ወደ ደቡ

ብ አፍሪካ የሆነ ዕድል አለ እያለ የሚጎርፍ አለ፡፡ ከሞት ተርፈህ የምታገኘው ዕድል አለ ብሎ ይህን ሁሉ ስቃይ እየበላ እዚያ ድረስ የሚያስኬደው ምን ዕድል ቢኖር ነው፡፡ በየቀኑ ነው ሬሳ የምንረከበው፡፡ እዚያ ያለው ኤምባሲያችን ሬሳ እየጫነ ይለፋል፡፡ ይህ ለምን ይሆናል? በእርግጥ አንዳንድ የተሳካለቸው አሉ፡፡ ሁሉም መጥፎ ነው ማለት አይደለም፡፡ ግን እሱም በጣም ከባድ ነው፡፡ በበቂ መጠን የስራ ዕድል ተፈጥሯል ወ

ይ? ገና ነው፡፡ ስራ አጥ አሁንም አለ፡፡ በበቂ ዕድል ገና አልተፈጠረም፡፡ የስራ አጡ ቁጥር በጣም ብዙ ነው፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በካምፓላ

የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ለስራ ጉዳይ ወደ ኡጋንዳ በመጡበት

ወቅት ኡጋንዳ ከሚኖሩ እና በኤምባሲ በኩል ግብዣ ከተደረገላቸው ኢትዮጵያውያን ጋር አጠር ያለ ውይይት አካሄደው ነበር፡፡ መሃል

ካምፓላ በሚገኘው ሴሬና ሆቴል ሐምሌ 15 ቀን በተደረገው ውይይት ላይ ከተገኙ ኢትዮጵያውያን መካከል ሁለት ሰዎች ለሚኒስትሩ ጥያቄ

የማቅረብ ዕድል አግኝተው ነበር፡፡ ሚኒስትሩ ከሰጡት ምላሽ ረዥም ምላሽ የቀነጨብነውን እንደሚከተለው አቅርበነዋል፡፡

n ኢትዮጵያ ውስጥ ቡና ገዝቶ ለመጠጣት የሚፈልግ ሰው በዓለም ዋጋ ገዝቶ ነው የሚጠጣውn ድሮ በአንድ ብር የምንገዛው ሳሙና አሁን 30 ብር ሆኗልn በምንም መንገድ ጤፍ የዛሬ አምስት አመት 200 ብር የነበረበት ቦታ ጋር ሊወርድ አይችልም

n አዲስ አበባ ላይ ሰው የቤት ሰራተኛ ፈልጎ አያገኝምn ሰው ጅቡቲ ሄደን መምጣት አለብን ማለት ነው ወይ እያለ ነውn ሳዑዲ አረቢያ ላይ ያሉ የእኛ ዜጎች ዘመናዊ ባሪያዎች ናቸውn በደቡብ አፍሪካ በየቀኑ ነው ሬሳ የምንረከበው

Page 4: Habeshawi kana 004

ሐምሌ 30-ነሐሴ 13 ቀን 2003 (August 6-19, 2011)ሐበሻዊ ቃና4

q ጥቆማ…q ጸሁፍ

በሐበሻዊ ቃና ፖስታ አድራሻ

ፖ.ሳ.ቁ 28268 ካምፓላ-ኡጋንዳ በኩል

ያድርሱን፡፡

ሁዳዴ እንደተፈሰከ ነው። አንድ ወዳጄ መጣና “ሰርግ ጋብዤሃለሁ” አለኝ። የግብዣው ድንገተኝነት አስገርሞኝ በለከፋ ልመል

ስለት አሰብሁና “እንዴ? ዘንድሮስ እንዲያው የከንፈር ወዳጅ መያዝህን እንኳ ሳታበስር ነው እንዴ ሰርግ የምትጋብዘን” አልኩት። ከት ብሎ ሳቀና ፣ “አረ እባክህ የእኔ አይደለም። እኔ ራሴ መናጢ ስደተኛ…አረ ያንድ ወዳጄ ነው…ከአሜሪካ ነው የመጡት እዚህ ተጋብተው ሊመለሱ” አለኝ። የእርሱን ሚና ሳይነግረኝ በደፈናው ብቻ “ቅዳሜ ተጋብዘሃል። ሌላ ፕሮግራም እንዳትይዝ፣ እንደው አደራ። ፕሪሚየር ሊግ የለ ባርሴሎና…እባክህ እንዳትቀር፣ የጥሪ ወረቀቱን ነገ አመጣልሃለሁ” አለኝና ሃሳብ ውስጥ ጣለኝ። ቅዳሜ ደግሞ ባርሴሎና ማንችስተር ዩናይትድን “የሚያሽከረከርበት” ቀን ስለነበር ሃሳብ ገባኝ። “ምነው ባልጠፋ ቀን…” ብዬ ገና ሳልጨርስ “አይ እንግዲህ…ብቻ እንዳትቀር አደራህን” አለኝና ጉዳዩ ለውይይትም ክፍት እንዳልሆነ ፈርጠም አድርጎ ነገሮኝ ካጠገቤ እብስ አለ። ሰርጉ ታዋቂ በሆነው የ “ኢትዮጵያ ቪሌጅ ሬስቶ

ራንት” ነበር የተዘጋጀው። “የኢትዮጵያ ቪሌጅ (ገጠር) ሬስቶራንት” የሚለው ስም ሁሌ ግራ እንዳገባኝ ነው። በየትኛው የኢትዮጵያ ገጠር ነው ሬስቶራንት ያለው እያልኩ ራሴን እጠይቃለሁ። የገጠር ሰው ተከፍሎ ገንዘብ የሚበላበት ቤት ከተማ መኖሩን ያውቃል እንጂ በገጠር ውስጥ ሬስቶራንት የለም። ለማንኛውም ካምፓላ ውስጥ በቀላል አጠራሩ “ቪሌጅ” የሚባለውን ምግብ ቤት ከአንጀቴ እወደዋለሁ። የምግብ ቤቱ ባለቤት ማሜ ጥራ ግራ ሬስቶራንቱን ካምፓላ ውስጥ አሉ ከሚባሉ ቤቶች አንዱ በማድረጓ ሁሌም በልቤ “ጎበዝ” እንዳልኳት ነው። ቪሌጅ በራሱ በጣም ደስ ይላል። የውሰጥ አሰራ

ሩ ለዓይን ሳቢ ነው። በዚያ ላይ እግር ኳስ እና ዘፈን የሚታይበት ትልቅ ስክሪን አለ። ፕሪሚየር ሊግንማ እዚያ ካልተመለከትኩ እግር ኳስ ያየሁም አይመስለኝ። እግር ኳስ ላይ በጣም የሚያሰጋኝ ነገር የመብራት መቋረጥ ነው። እግር ኳስ እያየሁ መብራት ከጠፋ ጠቅላላ ስሜቴ አብሮ ቁምጥ ይላል። ለዚህ ለዚህ ቪሌጅ አስተማማኝ ነው። እናም ሰርጉ በምወደው ቪሌጅ መሆኑ ደስ አለኝ። የባርሴሎናን ጨዋታና ያንን ሰርግ ማስታረቅ የ

ዚያን ሰሞን ከፍተኛው ፈተናዬ ሆኖ ከረመ። “ምነው እሁድ ቢያደርጉት” እያልኩ ሳማርር አንድ ሃሳብ መጣልኝ። ጥሪው ከምሽቱ 12 ተኩል እንድትገኙ የሚል ስለሆነ በሰዓቱ ተገኝቼ እስከ ሁለት ሰ

ዓት ተኩል ግንባሬን አስመትቼ ከዚያ “ላጥ ብዬ” ጨዋታውን ማየትና ሲያልቅ መመለስ። በርግጥም ጥሩ ሃሳብ ነበር። በሰዓቱ ተገኘሁ። ስገባ “ምነው ለማኝ ሳያራ” የተባለ ይመስል ከአስተናጋጆቹ በቀር አንድም ተጋባዥ አልመጣም። “ገና አሁን ‘ክራይሲስ’ መጣ” አልኩና በሆዴ እንዳመጣጤ ተመልሼ ውልቅ አልኩ። ወደ ሌላ ቡና ቤት ሄጄ ተሰይምኩ። የቻምፒየንስ ሊግ የመጨረሻ ጨዋታ 3 ሰዓት የሚጀመር ቢሆንም ዲ.ኤስ.ቲ.ቪ ገና በግዜ ጀምሮ ስለጨዋታው ማስተዋወቅ ጀምሮ ነበር። ይህንን እየተመለከትኩ አመሸሁ። አንድ ሰዓት ተኩል ግድም ሲሆን “አሁንስ እንኳን ተጋባዦቹ ሙሽሮቹም ይመጣሉ” ብዬ ወደ ቪሌጅ የሚያስኬደውን የካባላጋላ ዳገት ተያያዝኩት። እንዳሰብኩትም ግቢው ግጥም ብሎ መቀመጫ

እንኳ አልነበረም። በስተኋላ ላይ አንድ ጠረጴዛ ከበው ከተቀመጡ ሰዎች ዘንድ አንድ ያልተያዘች ወንበር አየሁና ወደዚያው ሄድኩ። “ሰው አለው?” ብዬ ጠይቅኩ። “አረ ይቀመጡ” ተብዬ ቁጭ አልኩ። የሙሽሮቹ ሰገነት በ“አብዷል ግላሱ” ተንቆጥቁጦ በእርግጥም ዙፋን መስሏል። አሁን መሽሮቹን መጠበቅ ያዝን። ጠረጴዛው ላይ የተደረደሩት መጠጦች ሙሽሮቹ እስኪመጡ ላይነኩ “ተኮንነው” ግን ተሸልመው ተቀምጠዋል። ሙሽሮቹን በናፍቆት ስንጠብቅ ጊዜው ገፋ። አብረውኝ የተቀመጡ በዕድሜ የገፉ ሰው እንደቀልድም፣ እንደቁጭትም አድርገው “ምነው አንዳንድ እንኳ ቢፈቅዱልን?” አሉ የተኮለኮሉትን ቢራዎች እያዩ። ዓይናችን ስር በረድፍ የቆሙትን ቢራዎች ዓይን ዓይናቸውን እናያለን። ባንድ ወገን የካምፓላ ሙቀት የፈጠረው ጥማት በሌላው ደግሞ የቢራው አምሮቱ ይዞ እየወዘወዘን የተከፈተልንን የአማርኛ ዘፈን እንኳ በቅጡ ማድመጥ አልቻልንም። ሰዓቴ ሁለት ሰዓት ተኩል መሆኑን ያሳያል። በእ

ቅዴ መሰረት ግንባሬን አሳይቼ እሰወራለሁ ያልኩበት ነበር። ሆኖም ልክ በዚያው ሰዓት ሁለት ነጫጭ መኪኖች ሙሽሮቹንና ሚዜዎችን ይዘው ከግቢው ሲገቡ ቪሌጅ ያኔ በአሸባሪዎች ፍንዳታ የተናጋቸውን ያህል በሆታ ተነቃነቀች። “ክቡራን እድምተኞች ሙሽሮችን ለመቀበል እንነሳ፤ በጭብጨባ” ብሎ አስተናጋጁ አወጀና ሁላችንም ተነስተን ማጨብጨብ ጀመርን። እኔ ዓይኔ ያለው እነዚያ የሚደፍራቸው የጠፉ የመሰሉ ቢራዎች ላይ ነው። ዓይኔን ከቢራው ልንቀልህም ብለው “በፖሊስ እንጂ” የሚል ይመስል ይበልጥኑ ትክ ብሎ ቀረ። “ሙሽራዬ” የሚለው ዘፈን እስከመጨረሻው የድምጽ ገደብ ድረስ ተለቀቀና ካባላጋላ ብቻ ሳይሆን ሙየንጋና ካንሳንጋም የታመሰ መሰለ። ሙሽሮቹ ጽዋቸውን አንስተው ሲጎነጩ ያ ሁሉ

ታዳሚ “አሁን ተፈቅዶልሃል” የተባለ ይመስል ቢራውንና ለስላሳውን እያስከፈተ “ምነው’ቴ” በመሰለ “ቁጭት” ያንን በድርቅ የተንቃቃ ጉሮሮውን

ያርስ ጀመር። ቢራዎች መከፈት ሲጀምሩ የአስተናጋጅ መንጋ ይራወጥ ገባ። ጸጥ ብሎ የነበረው ቤት በቅጽበት ተለውጦ ግርግሩ ሌላ ሆነ። ወዲያው ዘፈን እየተከታተለ ተለቀቀ እና ሞቅ ሞቅ አለ። አስተናጋጆቹ ይራወጣሉ። “እኔ ቢራ አልጠጣም ለስላሳ” ለሚሉት ፍላጎታቸውን ለማርካት ጥድፊያ ሆነ። አንድ ሁለት ቢራ እንደተጎነጨን “ራት አንሱ” ተባለ። የጸምና የፍስክ ለየብቻው ተደርድሯል። ምግብ በየዓይነቱ ጠረጴዛ ሞልቶ ተትረፍርፏል። ራት ተበልቶ እንዳለቀ፣ ሳህን ማንሳቱ ራሱን የቻ

ለ ግርግር ሆነ። ከዚያ በኋላማ የአማርኛ ዘፈን በየዓይነቱ እየተዘፈነ ገሚሱ በቴፕ፣ ገሚሱ በዲቪዲ ሆኖ “ይኼማ ያለ ዳንኪራ እንዴት ይሆናል?” የተባለ ይመስል ታዳሚው ሁሉ እየተነሳ እስክስታውን ያስነካው ገባ። አንድ ጠረጴዛ የተዳበልኳቸው ወይዛዝርት ቢራውን፣ እስክስታውንም አልነኩትም። ብቻ! ለስላሳውና የግል ወሬዎቻቸውን ይኮመኮማሉ። “እንዴት አይነሽጣቸውም?” እያልኩ እገረምና መልሼ ደግሞ “ምናልባት ሃይማኖታቸው አይፈቅድላቸው ይሆናል” እላለሁ። ከእኔ ጋር ወሬም አላወሩ። አረ! ዞር ብለውም አላዩኝም። ከፊታችን ባለው ጠረጴዛ ዙሪያ ያሉት ኤርትራውያን (አምቼዎቹ) ደግሞ አንድ ዘፈን እንዲያመልጣቸው የሚፈልጉ አይመስሉም። እየተነሱ እስክስታውን ያቀልጡታል። ኤርትራውያን በአማርኛ ዘፈን ሲጨፍሩ ማየቱ ደስ ብሎኝ እነርሱን ስመለከት ከመካከላቸው አንዷን ሌላ ቦታ እንዳየኋት ትዝ አለኝ። ከቆንጅናዋ ባሻገር የታወሰኝ እረፍት የለሽ ልጇ ነበር። ያየሁትን ሁሉ ካልነካሁ የሚለውን የአራት ወይ

ም የአምስት ልጇን ዛሬም እገባበት እየገባች ጎትታ ታመጣዋለች። ደቂቃ ሳይቆይ መልሶ ይጠፋል። ልጇን መጠበቁን እና እስክስታውን አብራ ማስኬዷ አስገረመኝ። ለልጇ ያላትን ትዕግስት ደግሞ አደነቅሁ። ዛሬም እንደበቀደሙ ከገባበት ስታመጣው አቅፋ እያጫወተቸውና እየተሳሳቁ ነበር። ይኼኔ እኔ በልጅነቴ ቢሆን ኖሮ በደርግ “የዲሲፕሊን መቀስ ፊት” የነበረችው እናቴ መጀመሪያ የምታደርገው ለመግረፊያ የሚሆን ሳማ ፍለጋ መሄድ እንደነበር አስታውሼ የልጁን እና የእኔን አስተዳደግ ማነጻጸር ጀመርኩ። በልጆች አያያዝ ላይ በትውልዶች መካከል ያለውን ልዩነት እያሰብኩ ስቆዝም ድንገት ልጇ ከየት መጣ ሳይባል ከእኔ ጋር ሆነ። እንደፈረደባት ልጇ ሰው እንዳያስቸግር ብላ ልትወስደው ወደ እኔ መጣች። ለካ እኔ ብኣ አይደለም ያስታውስኳት። እርሷም አውቃኝ ኖሮ ፈገግ አለች። “እንዴት ነሽ?” አልኳት። በጣም ቀልጠፍ ባለ አማርኛ “እግዚያብሔር ይመስገን” ስትለኝ ነው አምቼ መሆኗን ያወቅሁት።የአማርኛው ዘፈን አሁንም ይደለቃል። ዲጄው

“የአማርኛ ብቻ” የሚል ቀጭን ትዕዛዝ የተሰጠው

ይመስል የሌላ ብሔር ዘፈን አያጫውትም። በድርጊቱ ተገርሜም፣ አፍሬም ነበር። በዲጄው የዘፈን አመራረጥ ምክንያት ይመስላል ተነስተው የሚጨፍሩትም ሰዎች አንድ ዓይነት ነበሩ። ወደ መጨረሻ ገደማ ግን ማን እንደነገረው ባላውቅም የትግርኛ፣ የኦሮምኛ፣ ጉራጊኛ እና ወላይትኛ ዘፈኖችን አጫወተና ሰርጉ እንደገና እንደአዲስ ተደበላለቀ። ይበልጥ ሞቅ አለ። ራቅ ብሎ ከሚስቱ ጋር ምሽቱን ሲቆዝም የነበረ አንድ የማውቀው ሰው ኦሮምኛ ሲዘፈን ደስ ብሎት ከሚስቱ ጋር ተነስተው ጨፈሩ። ትግርኛውም ሲመጣ ትግርኛ ተነጋሪ መቀመጫው ላይ አልነበረም። “ያምቡሌ” የሚለው ዘፈን በዲጄ ሲለቀቅ ደግሞ ቪሌጅ የተገለጠ መሰለ፡፡ ከዚያ በኋላ ያ ሰርግ እጅግ አስደሳች ሆነ፡፡ ቴዎድሮስ ካሳሁን የተለያዩ ብሔሮችን፣ ኤርትራንም ጭምር በስም እየጠራ “የ…ልጅ የለውም አባይ” ሲል ያልተደሰተ አልነበረም፡፡ ከሁሉ የሚገርመው ግን በዚያ ሁሉ የደስታ ሆታ

መካከል አንደኛው አስተናጋጅ አንደኛውን ካልገደልኩ ብሎ መነሳቱ ነበር፡፡ ረብሻው እኛ የተቀመጥንበት አካባቢ ስለነበር ሳያሳዝነን አልቀረም፡፡ ካልገደልኩ ብሎ ያዙኝ ልቀቁኝ ባለ ቁጥር አንዴ የቪሌጅ ባለቤት ማሜ በሌላ ጊዜ ደግሞ ሌሎች በየተራ እየመጡ ቢለምኑት ሰውየው ባሰበት፡፡ ሌላኛው ደግሞ ሳይናገር ሳይጋገር፣ መልስም ሳይሰጥ ስራውን ብቻ ይሰራል፡፡ ይህንን እንደፍርሃት የወሰደው ጠበኛ ያዙኝ፣ ልቀቁኝ ማለቱን አላቆም አለ፡፡ አሁን ያ ትዕግስተኛው ትዕግስቱ አልቆ ኖሮ እመር ብሎ ተነሳ፡፡ ጠበኛው በዚህ ጊዜ ድንፋታው ሁለት መልክ ያዘ፡፡ ገላጋይ ሲኖር መደንፋት፣ ገላጋይ ሳይኖር ረጋ ማለት፡፡ በደነፋ ቁጥር “እባክህ” ያላለው አልነበረም። አጅሬ እባክህ በተባለ ቁጥር እየባሰበት ያንን ቆንጆ ሰርግ ሊያበላሸው ሆነ። “አለጠብ የምናውቀው ነገር ይጥፋ? ምነው ዛሬ

እንኳ ቢታገስ?” አለች እኔ ካለሁበት ጠረጴዛ ዙሪያ ከተቀመጡት አንደኛዋ። “ኤጭ…ኤዲያ!” አለች ደገመችና። ይኼ ሁሉ ሰው “ሃይ” ብሎት፣ በርካታ ሰው አዝኖበት፣ ይረጋጋል ይተዋል ሲባል ድንገት ደግሞ “ግንፍል አለብኝ” ዓይነት ተነስቶ “ና ውጣ!” ይለው ጀመር። ‘አይ እንግዲህ አሁንስ አበዛው። ይህንን ኩታራ በጥፊ የሚለው ከጠፋ የቀረው ምርጫ ያው ባላንጣው አንፈራፍሮ እንዲለቀው ማድረግ ነው” አልኩና፣ ‘በል የእኔ ወንድም….መደባደብ አይደል የምትፈልገው? አንግዲያው ይኼ ሰርግ ነው። ሰው ሊደሰት ነው የመጣው። ከሰውየው ጋር ወደ ውጭ ውጡ። ውጭ ያለው መንገድ የሰጠ ነው። እዚያ ይለይላችሁ’ ልለው እንደወሰንኩ አንድ ሰው ጠጋ ብሎ በጆሮው የሆነ ነገር ሹክ አለው። ተናጋሪው ምን እንዳለው ባይታወቅም ለጠብ ይጋበዝ የነበረው በቅጽበት አደብ ገዝቶ ቁጭ አለ። እኛም ትኩረታችንን ወደ ጭፈራው መለስን።

የካባላጋላው የሐበሻ ሰርግበይስሐቅ ክፍሌ

የሐበሻ ኑሮ

ካምፓላ ኡጋንዳ

ምስጋና

ጆኒ ሉሉ የተባልኩ ኢትዮጵያዊ ነኝ፡፡ በጁላይ 11 ካምፓላ ላይ በተከሰተው ድንገተኛ የቦምብ አደጋ ጉዳተኛ የሆንኩ ነኝ፡፡ የዚህ ጋዜጣ ያለፈው ዕትም ላይ የእኔ ታሪክ ታትሞ ወጥቷል፡፡ ከአዘጋጁ ጋር ለመገናኘት ጊዜ ስላልነበር በአደጋው ጊዜ የረዱኝን ሰዎች የማመስገን ዕድል አላገኘሁም፡፡ አሁን ዕድሉ ተሰጥቶኛልና ምስጋናዬን አቀርባለሁ፡፡ ለመላው የካምፓላ ነዋሪ ምስጋና የማ

ቀርበው ሁሉንም ጉዳተኞች ወክዬ ነው፡፡ ሐበሻ በሙሉ ሁሉንም ጉዳተኞች በገንዘብ በመደገፍ፣ ሆስፒታል ድረስ ተገኝተው በማጽናናት እና ያለመሰልቸት ሲንከባከቡ ስላየሁ በሁሉም ስም ለማመስገን ነው፡፡ ክስተቱ ምንም እንኳ የሚያስደነግጥ ቢሆንም ወገናችን እንደዚህ ለሰው አዛኝ እና ሩህሩህ መሆኑን ማየቴ በጣም በወገኔ እንድኮራ አድርጎኛል፡፡ አንዳንዶች ልክ የስጋ ዘመድ የታመመባቸው እስኪመስል ድረስ ውለው አድረው ተንከባክበውናል፡፡ በእኔ በኩል በእውነቱ ሰዎችን ለማመ

ስገን ቃላት አይኖረኝም፡፡ በሆስፒታል ሆኜ፣ ከሆስፒታል ከወጣሁም በኋላ በብዙ ነገር ሲረዱኝ የነበሩ ሰዎች በርካታ ናቸው፡፡ መቼም ብዙ ስለሆኑ ስም ለመዘርዘር ይከብዳል፡፡ ግን ያደረጉልኝን እግዚያብሔር እና እነሱ ያውቃሉ፡፡ ለእነዚህ ሰዎች ማለት የምችለው በእውነቱ ብድርን የሚከፍል እግዚያብሔር ነውና እርሱ ጤናችሁን፣ ቤተሰባችሁን፣ ስራችሁን፣ ሰላማችሁን ፍቅራችሁን አብዝቶ አብዝቶ ይባርክ፡፡ ህይወታችሁ ሰላምና ደስታ የተሞላው እንዲሆን ልባዊ ምኞቴን እገልጻለሁ፡፡ በመጨረሻ ግን በግሌ ማመስገን የም

ፈለገው እንድ ሰው አለኝ፡፡ በአደጋው ሆስፒታል ገብቼ አራት ቀን ሙሉ ሁለት ዶክተሮች እየተፈራረቁ ቢያዩኝም ችግሬን ሊያውቁት አልቻሉም ነበር፡፡ በስተኋላ ላይ ከሌላ ዶክተር እንደሰማሁት አራተኛውን ቀን ያለ ህክምና አልፌ ቢሆን ኖሮ ሟች እንደነበርኩ ነው፡፡ ከዚህ የተረፍኩት እግዚያብሔር በላከልኝ ትልቅ ሰው ነው፡፡ አቶ ግዛው ይባላል፡፡ የኢትዮጵያ ቪሌጅ ባለቤት የሆነችው የማሜ የልጆች አባት ነው፡፡ እውነት ለመናገር ይህንን ሰው ባለኝ ቀሪ የህይወት ዘመኔ በሙሉ ልረሳው አልችልም፡፡ ምክንያቱም ዶክተሮች እየተሰቃየሁ እያዩ ደህና ነህ ውጣ ባሉኝ ጊዜ እርሱ ግን በፍጹም አይወጣም ብሎ ህይወቴን ያተረፈውን ህክምና እንዳገኝ አስደርጎኛል፡፡ አቶ ግዛው በዚያን ጊዜ በቀላሉ የማይ

ገኘውን የካምፓላ ኢንተርናሽናል ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተርን ካለበት ፈልጎ አምጥቶ፣ ችግሬን አስረዳልኝ፡፡ የጉዳዩን አሳሳቢነት የተመለከተው ዶክተር ሞሰስ የተባለው ሚዲካል ዳይሬክተር አራት ሰዓት ከ30 ደቂቃ የፈጀ ቀዶ ህክምና አድርጎልኝ በድጋሚ ለመኖር በቅቻለሁ፡፡ ለዶክተር ሞሰስ በዚህ አጋጣሚ የከበረ ምስጋናዬን አቀርባለሁ፡፡ ለአቶ ግዛው ደግሞ አንተን፣ ቤተሰብህን እና ልጆችህን እግዚያብሔር ይባርክ፡፡ ረጅም እድሜ እመኝልሃለሁ፡፡ እንዲሁም አቶ ማስረሻ በራሱ አነሳሽነት በውጭ ሀገር ከሚገኙ ወገኖች ጋር ተገናኝቶ ገንዘብ አሰባስቦ እንድንረዳ እድርጎናልና እርሱንም ከልቤ አመሰግናለሁ፡፡ ቤተሰቤን፣ ባለቤቴን እና ጓደኞቼንም ከልብ አመሰግናለሁ፡፡

በጆኒ ሉሉ ካምፓላ ኡጋንዳ

ማስታወቂያ

q አስተያየት

ደብዳቤዎች

Page 5: Habeshawi kana 004

ሐምሌ 30-ነሐሴ 13 ቀን 2003 (August 6-19, 2011) ሐበሻዊ ቃና 5

ሐበሻ በምስራቅ አፍሪካ

የአሮሞ ኮሚዩኒቲ መቼ ነው የተቋቋመው? ለምንስ ማቋቋም አስፈለገ? የተመሰረበት ዓላማው ምንድነው?የኦሮሞ ኮሚዩኒቲ በኡጋንዳ የተቋቋመው

እ.ኤ.አ በ2004 ነው። ከዚያ በፊት ሙከራዎች ነበሩ። በ2004 (እ.ኤ.አ) ተደራጅቶ፣ መተዳደሪያ ደንቡን አጽድቆ፣ በመንግስት ፍቃድ አግኝቶ ስራውን የጀመረበት ነው። የኦሮሞ ኮሚዩኒቲ በኡጋንዳ ማቋቋም ያስፈለገበ

ት ምክንያት ብዙ የኦሮሞ ስደተኞች እዚህ ተበታትነው በሚገኙበት ሰዓት መታመም መቸገር፣ መረጃ ማጣት አለ። ስደተኞች የተለያዩ ችግሮች ይገጥማቸው ነበር። እነዚህን ችግሮች መነሻ በማድረግ የታመመውን ለማስታመም፣ የሞተውን ለመቅበር በማሰብ ይሄ የኦሮሞ ስደተኞች ማህበር [እ.ኤ.አ] በ2004 ተቋቋመ። የኦሮሞ ስደተኞች ኮሚዩኒቲ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ግዛት ወሰንን አይከተልም። የተከተለው የኦሮሞ ማህብረሰብን ማሰባሰብ ነው። ይህ ያስፈለገበት ምክንያት ምንድነው? አንድ ዓይነት ባህል እና ቋንቋ ያለን ሰዎች ስለሆንን፣ ደስ የሚለን እና የሚከፋን ነገር የምንጋራ በመሆኑ፣ በአገራችንም ውስጥም አንድ ዓይነት በደል የምንበደል ሰዎች ስለሆንን በየጊዜው ተገናኝተን በደላችንንም፣ ችግራችንንም ለመረዳዳት ነው። አልፎም በዚህ በስደት አገር መውለድ፣ ቤተሰብ ማፍራት አለ። ለቤተሰቦቻችን ቋንቋችንን፣ ባህላችንን አስተላልፈን ለመስጠት ነው። በጋራ ችግራችን ላይ በጋራ ለመቆም ነው። ለዚህ ነው የተቋቋመው። አሁን ያለው እንቅስቃሴ ምን ይመስላል? የራሱ ጽህፈት ቤት እና የቦርድ አባላት አሉት? አባሉትስ ምን ያህል ናቸው? አወቃቀሩ እና አሰራሩስ አንዴት ነው? መጀመሪያ ስንገናኝ የኦሮሞ ኮሚዩኒቲ አባላት ወ

ደ 150 እንሆን ነበር። በመዋቅራችን የጠቅላላ ጉባኤ አባላት አሉ። በስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ውስጥ ሰባት ሰዎች፣ በሽማግሌዎች ኮሚቴ ውስጥ ሶስት ሰዎች፣ በኦዲቲንግ ኢንስፔክሽን [ቁጥጥር] ኮሚቴ ደግሞ ሶስት ሰዎች፣ እና የተለያዩ ባህላዊ እና ትምህርታዊ እንቅስቃሴዎች የሚያካሂዱ ኮሚቴዎች በስሩ ጠቅልሎ ነው። የቦርድ አባላትን አልወክልንም። ያለን መዋቅር ይሄ ሆኖ በየጊዜው የአባላቱ ቁጥር ይቀንሳል፣ ይጨምራል። አንዳንድ ጊዜ የስደተኛ መጠን ወደ ውጭ በመሄድና በተለያየ ምክንያት ይቀንሳል። በእነዚህ አመታት ውስጥ በየጊዜው በስብሰባዎች ላይ በአማካይ ከ70 ያላነሱ አባላት ይገኛሉ። በየጊዜው ስብሰባ ይደረጋል ማለት ነው? የተለያዩ ዝግጅቶች ታዘጋጃላችሁ?ይሄ ህዝብ ጥሩ ባህል እያለው ጥሩ ባህሉን እያ

ጣ ነው። ኦሮሞ ኮሚዩኒቲ ይሄንን ባህል ከትውልድ ወደ ትውልድ ለማስተላለፍ፣ በየጊዜው በባህሉ ውስጥ ያሉትን በዓላት ያከብራል። ለምሳሌ እሬቻ በየዓመቱ ያከብራል። እሬቻ በዓል ማለት ለኦሮሞ በየዓመቱ ለእግዚያብሔር ምስጋና የሚሰጥበት “ታንከስ ጊቪንግ” ነው። እኔ ወደ ኡጋንዳ ከመጣሁ ሶስት ዓመት ነው። ሶስቱን አመት አክብረናል። በፊትም ቢሆን እንዲሁ ሲከበር ነው። እሬቻ በዓል በባህሉ ውሃ ዳርቻ ያለበት ቦታ ተሂዶ ነው የሚከበረው። ቦታውም እርጥብ እና ለምለም መሆን አለበት። ለተምሳሌትነትም ቄ

ጤማ ሁሉ ይያዛል። እግዚያብሔርን በፈጠረው ነገር እናመሰግናዋለን የሚል ሀሳብ እንዳለው ነው የማውቀው። ይህንን የሚያሟላ ቦታ ካምፓላ ላይ አግኝታችኋል? ከካምፓላ ዳርቻ ላይ ሉቢሪ የሚባል ሐይቅ አ

ለ። መንግስት እናስፈቅዳለን። ሐይቁ አካባቢ እናከብራለን። በኦሮሞ ባህል ለእግዚያብሔር ምስጋና የሚቀርበው በሶስት ቦታ ነው። አንድ-እርጥበት ባለበት፣ ሁለት-ከመሬት ከፍ ባለ ቦታ እንደ ተራራ፣ ሶስት-ጥላ ባለበት ነው። እሬቻ ደግሞ የምናከብረው በአገራችን ክረምት አልቆ መስከረም ሲመጣ በ17 መስቀል ሲሆን በሳምንቱ በ24 ነው። እሬቻ የሚከበረው ያ ክረምት፣ ያ ጭቃ፣ ያ ጨለማ ማለፉን ለማመስገን ነው። በዓሉ የሚከበረው ወደ ብርሃን ስትወጣ ነው። በክረምት የእርሻ ጊዜ ምርት ለማግኘት ዘርተህ ቡቃያው በደንብ ሲወጣ ማለት ነው። እሬቻ ሲከበር ቡቃዮች አድገው ያፏጫሉ። የጤፍ ዘለላ አይተህ እንደሆነ በዚያን ጊዜ በንፋስ ያፏጫል። ሳሮችም በንፋስ ያፏጫሉ። የአበባ ወቅት ነው። ያን ጊዜ ለእግዚያብሔር ምስጋና ለማቅረብ ነው የምናከብረው። ውሃ ዳር የምናከብረው እርጥብ አካባቢ ስለሆነ እና እግዚያብሔር የፈጠረው ስለሆነ ነው። በእዚያ ቦታ እግዚያብሔርን ነው የምንለምነው። የኢትዮጵያ ማህብረሰብ እያለ የኦሮሞ ማህብረሰብ ለብቻው ወጥቶ የራሱን ማህበር ለምን ማቋቋም አስፈለገው? የኢትዮጵያ ማህብረሰብ አብዛኛው አባላትም በተለያዩ ምክንያት ከሀገራቸው የወጡ ስደተኞች ነው። ሁለቱም ማህበረሰቦች ይዘው የተነሱትም አላማ ተመሳሳይ ነው።

እኛ በኢትዮጵያ ማህብረሰብ ውስጥ ገብተን አልወጣንም። መጀመሪያውኑ ድሮም ይኖር ይሆናል። እኛ ግን እዚህ የኦሮሞ ኮሚዩኒቲ ነው ያቋቋምነው። የኦሮሞ ኮሚዩኒቲ ማቋቋም ያስፈለገበት ምክንያት ሰዎች ችግራቸውንም ሆነ ደስታቸውን ሲገልጹ የሚመሳሰላቸውን ፈልገው ነው። ስለምንመሳሰል፣ አንድ ዓይነት ሰዎች ስለሆንን፣ ለዚያ ስንል ተፈላለገን በማህበር ተቋቋምን። በኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ ህዝቦች አሉ። ኢትዮጵያ ውስጥ የተለያየ ዓይነት ዘፈን፣ ለቅሶ እና ቋንቋ አለ። ኢትዮጵያ ውስጥ የተለያየ ህዝብ አለ ማለት ነው። እነዚህ ህዝቦች በየራሳቸው ሁኔታ ይፈላለጋሉ። የኢትዮጵያ የፖለቲካ ድንበርን ያልተከተልነው የተለያየን ሰዎች ስለሆንን ነው። በኢትዮጵያ የፖለቲካ ድንበር አንድ ላይ መቆም በሚያስፈልገን ጊዜ ከኢትዮጵያም ኮሚዩኒቲ ጋር ሆነ ከሌሎች ጋር አብረን እንቆማለን። እኛ ብቻችንን መቆም አንፈልግም። የኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ የፖለቲካ ድንበርን ነው የ

ተከተለው። የሰዎችን የመተዋወቅ እና የመፈላለግ ሂደት አልተከተለም። አንድ መታወቅ ያለበት ግን እኛ የኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ ተቃራኒ አይደለንም። ከኢትዮጵያ የመጣን ኦሮሞዎች ነን። አብዛኛው የኦሮሞ ህዝብ ኢትዮጵያ ውስጥ ነው ያለው። ግን እዚህ እንደኦሮሞ በቅርበት፣ በጋራ ለመረዳዳት እና የሚደርስብንን በጋራ ለመወጣት የተደራጀን ነን። የኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ ድጋፍ በሚፈልጉበት ጊዜ እኛም፣ እነሱም አብረን የምንሰራበት አጋጣሚዎች አሉ። አሁን ለምሳሌ በኢትዮጵያውያን ላይ የመልሶ መስፈር (ሪሴትልመንት) ጫና አለ። ይህንን በማናገኝበት ጊዜ አብረን በጋራ ቆመን ለምን አንጠይቅም ብለን እንጠይቃለን። ሌላው ግን የእኛ ህዝብ ብዙ ስለሆነ አመት በዓ

ል እናከብራለን። እሬቻ ስናከብር ኦሮሞዎች ናቸ

ው ገብቷቸው የሚያከብሩት። የእኛን የባህል ዝግጅት (ካልቸራል ሾው) ስናካሂድ የእኛን ባህል ነው የምናሳየው። የኢትዮጵያን ህዝብ በጠቅላላ የሚያስደስቱ ወይም የሚያሳትፉ ላይሆኑ ይችላሉ። ስለዚህ በራሳችን ተደራጀን ማለት ነው እንጂ ከኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ የመውጣት፣ የመገንጠል፣ ያለመፈለግ አይደለም። የኦሮሞ ኮሚዩኒቲ ከሌላው ኮሚዩኒቲ በተለየ የሚደርስበት ችግር ወይም ጫና አለ ነው የምትሉት? እኛ ከሀገራችን ስንወጣ እንደኦሮሞ ተጠቅተን ነ

ው። ኦሮሞ መሆን በራሱ ወንጀል አለው። የምንኖርበት አካባቢ ያስጠቃናል። በ1991 የፌደራል ክልሎች አዋጅ ቁጥር ሰባት ሲታዋጅ ኦሮሚያ የራሷን ክልል አግኝታለች። በዚህ ክልሏ ውስጥ ያሉ ሀብቶችን ያለህዝቡ ፍቃድ ገዢው መንግስት መጠቀም ይፈልጋል። ይህ ሀብት ለተወሰኑ ጥቂት ሰዎች መጠቀሚያ ሆኗል። እንደ ወርቃችን እና ጠቅላላ መሬታችን ማለት ነው። የኢትዮጵያ መንግስት በአጠቃላይ ሳይሆን አንድ ብሔር እንደፈለገ የሚበዘብዘው ነው። ይሄንንም የሚመለከቱ የኦሮሞ ምሁራን እና ህዝቡ ጥያቄ እንዳያነሱ ይፈልጋል። ይህንን ጥያቄ የማንሳት አቅም አላቸው የሚባሉትን ያጠቃል፣ ያስራል፣ ያሰቃያል። ጥቃቱ በእኛ ላይ ይብሳል ማለት ነው። ብዙ መሞት፣ ብዙ መታሰር አለ። በኦፊሴል በማይታወቁ እስር ቤቶች ውስጥ እንሰቃያለን። ይህንን በመረጃ የምናቀርበው ነው። ከዚህ ስቃይ ለመሸሽ ነው እዚህ የመጣነው። ይ

ህ በመንግስት የሚደረግብን ልዩ ትኩረት ያሰባስበናል። አንድ ዓይነት ቋንቋ እና ባህል ስላለን ያ ያሰባስበናል። ኦሮሞዎች ፍቅራችን እና ጥላቻችን አንድ ዓይነት ስለሆነ እንሰባሰባለን። ይህ ማለት ሌ

በፍቃዱ ጅሬኛ ለማ ይባላሉ። የተወለዱት በኢትዮጵያ ኦሮሚያ ክልል ውስጥ ነው። በ1978 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የመጀመሪያ

ዲግሪያቸውን በውጭ ቋንቋዎች እና ስነ ስሁፍ አግኝተዋል። በመንግስት እርሻዎች ልማት ሚኒስቴር በህዝብ ግንኙነት ክፍል የህትመት

ውጤቶች አርታኢ ሆነው ሰርተዋል። በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የግብርና ቢሮ ውስጥ የህዝብ ግንኙነት እና ስልጠና መምሪያ ተጠባበቂ

ኃላፊም ነበሩ። “በመንግስት አድሏዊ አሰራር” ከዚህ ስራ መሰናበታቸውን የሚናገሩት አቶ በፍቃዱ አዳማ (ናዝሬት) በሚገኘው ሪፍት

ቫሊ ኮሌጅ ውስጥ ሌክቸረር ሆነው ማገልገል ጀምረው ነበር። ሆኖም ደረሰብኝ በሚሉት እስራት ምክንያት በመስከረም 1999 ዓ.ም

አገር ለቀው ለመውጣት መገደዳቸውን ያስረዳሉ።

ወደ ኡጋንዳ ከመጡ በኋላ ከተባበሩት መንግስታት የስደተኞች መርጃ ድርጅት (ዩ.ኤን.ኤች.ሲ.አር) ጋር በትብብር በሚሰራው ኢንተር ኤይድ ውስጥ

በኢትዮጵያ ቋንቋዎች አስተርጓሚነት ተቀጥረው እየሰሩ ይገኛሉ። ከዚህም ባሻገር በኡጋንዳ የኦሮሞ ማህብረሰብ ሊቀመንበር ናቸው። የኦሮሞ ማህብረሰብ

በሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ዙሪያ ከ“ሐበሻዊ ቃና” ጋር ቆይታ አድርገዋል።

የኦሮሞ ኮሚዩኒቲ በኡጋንዳ

ላውን የኢትዮጵያ ህዝብ እንጠላለን ማለት አይደለም። የኢትዮጵያ ህዝብ አብሮ መቆም ካለበት አብረን እንቆማለን። እንደኦሮሞ ደግም እንበደላለን። ይህንን ለመቋቋም ደግሞ አንድነት እና መደራጀት ያስፈልገናል። ነገር ግን እኛ እዚህ ስደተኞች ነን። የፖለቲካ ስራ አንሰራም። ኮሚዩኒቲው ሲቋቋም የወሰን ግዛትን መሰረት አያደርግም ብለዋል። የኦሮሞ ህዝብ በምስራቅ አፍሪካ ውስጥ በተለያየ ቦታ ይገኛል። በኬንያ ድንበር አካባቢ ያለውን እንደምሳሌ ብንወስድ እንኳ የቦረና ህዝብ ድንበር ተሻግሮ በሁለቱም አገራት ይገኛል። አንድ ዓይነት ቋንቋ እና ባህል ካላቸው ከእነዚህ ኦሮሞዎች ጋር ያላችሁ ግንኙነት ምን ይመስላል?ከወሎ እና ቦረና ተሰደው የመጡ ኦሮሞዎች አ

ሉ። የማህበራችን አባል ናቸው። በኢትዮጵያ ውስጥ ኦሮሚያ ተብሎ ከተከለለው ውጭ ያሉትንም እንረዳቸዋለን። ጥገኝነት ለማግኘት በሚያደርጉት እንቅስቃሴ እንረዳችዋለን። “ፕሮሰስ” ሲያደርጉም እንደዚያው። እነርሱ ሁሉ የእኛ ማህብረሰብ አባል ናቸው። የኦሮሞ ኮሚዩኒቲ በናይሮቢ፣ በሚኒሶታ፣ በአ

ውሮፓ እና በአውስትራልያ አለ። ከእነዚህ ኮሚዩኒቲዎች ጋር እርስ በእርስ እንተጋገዛለን። ባለፈው ዓመት በኡጋንዳ ውስጥ የቦምብ ፍንዳታ ደርሶ ነበር። በዚህ ፍንዳታ አራት የኦሮሞ ኮሚዩኒቲ አባላት ከሶማሌዎች ጋር ባላቸው የፊት መመሳሰል በጥርጣሬ ታስረው ነበር። በዚህ ጊዜ በመገናኛ ብዙሃን እና በኢንተርኔት አማካኝነት የታሰሩትን ለማስፈታት ጥረት ስናደርግ አብረውን ጥረት አድርገዋል። ከእነዚህ ማህበራት ጋር አብረን እንሰራለን ማለት ነው። የኢኮኖሚ ችግር ሲገጥመን ይረዱናል። የወደፊት እቅዳችሁ ምንድነው? በየጊዜው ለሚመጡ ስደተኞች አንድ ቋሚ ነገር ለማቋቋም ያሰባችሁትስ ነገር አለ?በዚህ ማህበር ሕግ መሰረት አመራር በየሁለት ዓ

መቱ ይለወጣል። በመጪው ነሐሴም አዲስ አመራር ይለውጣል። እኔ ሁለት ዓመት ስለሞላኝ ጨርሻለሁ ማለት ነው። አሁን ባለው ዕቅዳችን መሰረት ቀጣዩ ቢሮ መክፈት ነው። ለጊዜው “ቡኬሳን” [ምግብ ቤት] እየተጠቀምን ነው። አዲስ የሚመጡ ስደተኞች መረጃ እንዲያገኙ፣ የት መሄድ እንደሚችሉ ኮሚቴዎች ማደራጀት ነው። እነዚህ ኮሚቴዎች ስደተኞችን እንዲረዱ ማድረግ ነው። እዚህ ስራ አጥ የሆኑ የኦሮሞ ስደተኞች ስራ የሚያገኙበት መንገድ ለማመቻቸት አንድ “ፕሮጀክት ፕሮፖዛል” እየተሰራ ነው። ለወደፊት ደግሞ እኛ በስደት ዕድሜ ልካችንን እ

ንድንኖር አንፈልግም። አገራችንን እንወዳለን። የአገራችን የአስተዳደር ሁኔታ ሲሻሻል፣ ሰው በእኩልነት ሰርቶ መኖር የሚችልበት ደረጃ ሲደርስ ወደ ሀገራችን እንመለሳለን። ያ ሁኔታ ካልተቻለ የዓለም የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች በኢትዮጵያ ውስጥ እየደረሰ ላለው የኦሮሞ በደል ልዩ ትኩረት እንዲሰጡ እንፈልጋለን። በብዛት ሰው ይወጣል። በኬንያ ብቻ አይደለም። ኦሮሞ በጅቡቲ፣ በሶማሌ፣ በጎንደር ይወጣል። ድንበራችን ብዙ ነው። ለእነዚህ ዓለም ትኩረት እንዲሰጣቸው እንፈልጋለን። መልሶ እንዲያሰፍራቸው እና እንዲያቋቁማቸው ወይም ደግሞ በአገር ውስጥ ያለውን በደል እና ስቃይ አለም እንዲያተኩርበት እንፈልጋለን።

በዓለም አቀፍ ደረጃ በየዓመቱ ጁን 20 ታስቦ የሚውለው የዓለም የስደተኞች ቀን በኡጋንዳ ኦልድ ካምፓላ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ሲከበር የኦሮሞ ኮሚዩኒቲ አባላት የአሮምኛ ዘፈን እና ጭፈራ አቅርበው ነበር

ፎቶ

- ተስፋ

ለም ወ

ልደየ

Page 6: Habeshawi kana 004

ሐምሌ 30-ነሐሴ 13 ቀን 2003 (August 6-19, 2011)ሐበሻዊ ቃና6

የስደት ዓለም

በዚህ በአሜሪካ አሁን በጋ (Summer) ነው። ብዙ ሠራተኞች እረፍት ለመውጣት ጥሩ አጋጣሚ አድርገው የሚጠቀሙበት ጊዜ ይህ የበጋው ወራት ነው። ትምህርት ቤትም ተዘግቷል። ልጆቹ በሙሉ በየመንገዱ፣ በየመዝናኛው ይተረማመሳሉ። በተለይ ወደ ማታ ላይ ሕጻናቱን አምጥቶ የሚያፈሳቸው ማን እንደሆነ እንጃ።ትምህርት ቤት ሲዘጋ ወላጅ ሁሉ ሕጻናቱን የ

ሚያስቀምጥበት ሥፍራ መፈለግ አለበት። ትምህርት ቤት የሚፈለገው ልጆቹ ሔደው ዕውቀት እንዲቀስሙ ብቻ ሳይሆን መዋያም እንዲያገኙ ነው። ልጆችህን ትምህርት ቤት ካልላህክ የት ታደርጋቸዋለህ? ጎረቤት ትቻቸው ልሒድ ወይም ሠራተኛ ልቅጠርላቸው አይባል ነገር። ሠራተኛ እንኳን አሜሪካ ኢትዮጵያም እየጠፋ ነው። ዕድሜ ለትምህርት ቤት፤ እዚያ አስቀምጦ ወደ ሥራ።እንዲህ ዓይነቱ የአሜሪካው የበጋ ወራት ሲመ

ጣ ደግሞ ልጆቹን ማስቀመጫ ቦታ፣ የሚሠሩት ሥራ መስጠት ያስፈልጋል። አለበለዚያ ትምህርት ቤት ይዟቸው የነበሩት ልጆች ተለቀው የማይሆን ነገር ውስጥ ሊገቡ ይቻላሉ። ይህንን ለመታደግ “ልጆቻችሁን እንያዝላችሁ፣ እናስጠናላችሁ፣ ስፖርት እናሰልጥንላችሁ” ወዘተ ወዘተ የሚሉ የተለያዩ ማስታወቂያዎችን ማየት የተለመደ ነው። እናም ልጆቻችንን በአንዱ ቦታ በጋውን እንዲያሳልፉ በማስመዝገብ፣ ካለችን ቆጥበን በመክፈል ልጆቹ ትምህርትም መዝናኛም ባለበት ሁኔታ እረፍታቸውን እንዲያሳልፉ እናደርጋለን። ይህ ዓይነቱ አጋጣሚ መቸም እኔ ራሴ ልጅ በነ

በርኩበት ጊዜ፣ ትምህርት ቤት ሲዘጋ እንዴት አሳልፍ እንደነበር እንዳስታውስኝ ያደርገኛል። ያኔ ትምህርት ቤት መዝጊያ ሰኔ 30 ነበር። “ሰኔ 30፤ የተማሪ አበሳ” ይባልም ነበር። የሚያልፈው እና የሚወድቀው የሚለይበት፤ ካርዳችንን ተቀብለን ግማሹ በደስታ፣ ግማሹ በልቅሶ ወደቤቱ የሚሔድበት የልጅነታችን አጓጊ ቀንም ነበር።ተማሪዎች ሲጣሉ እና ቂም ሲያያዙ “ቆይ፣ ሰኔ

30 ያገናኘን” መባባል የተለመደ ነበር። በክረምቱ ምክንያት ትምህርት ቤት ስለሚዘጋ የተጣሉትን ደቁሶ፣ ዓመቱ ሙሉ አንጀት ሲያቃጥል የነበረውን ሁሉ ዋጋውን ሰጥቶ እስከ መስከረም ነገሩ ስለሚረሳ ከአስተማሪ ቅጣት ለማምለጥ ስለሚያስችል ነበር - ሐሳቡ። አንዳንድ ጊዜ አስተማሪውም “ሊቀምስ” ይችላል። ተማሪ ጥጋበኛ አይደል?ትምህርት ቤት ከተዘጋ በኋላ ተማሪው ከጭቃ

ው እና ከዝናቡ ጋር ጭቃ እና ዝናብ ሆኖ ወደሚያሳልፍበት የሁለት ወራት ጊዜ ይገባል። ከገጠር አካባቢ የመጣው ተማሪ ወደ እርሻው፣ ወደ ጉልጓሎው፣ ወደ ጥጃ ጥበቃው ይመለሳል። የከተማውም ልጅ ቢሆን፣ ከጥቂቱ በስተቀር፣ ቤተሰቦቹን በአቅሙ ወደ መርዳት የመሔድ ግዴታ አለበ

ት። እንደማስታውሰው ክረምት በመጣ ቁጥር ጭቃ መስለን እና ጭቃ ሆነን የአቅማችንን “ለወላጆቻችን ለመታዘዝ” እንሞክር ነበር። ክረምት ለጨዋታ እና ለመዝናናት አይመች

ም። ኳስ ለመጫወት ሜዳው በሙሉ በውሃ ይሸፈናል። እንኳን የመንደራችን ሜዳዎች አዲስ አበባ ስቴዲየም ራሱ ውሃ ይቋጥራል። የቤት ውስጥ መጫወቻ ሥፍራ፣ ኳስ ሜዳ የሌለባት ብቸኛ አገር መቸም ኢትዮጵያችን ሳትሆን አትቀርም። እንኳን በየመንደሩ ያለን ሕጻናት ብሔራዊ ቡድኑም በክረምት የሚጫወትበት ሜዳ የሌለበት አገር ነው።በክረምቱ ትልቁ መዝናኛችን፣ ከቤተሰባችን

ም ቁጣ ለመዳን፣ ኩሽኔታችንን እየነዳን የማገዶ እንጨት ሰበራ ወደ ጫካ እንወጣለን። ብዙ ጊዜ ዝናሙ የሚዘንበው ወደ ከሰዓት በኋላ ነው። ለምን በዚያ ፕሮግራም እንደሚመጣ እግዜር ይወቀው። ቁልፉ በእርሱ እጅ ነው። ብቻ ጳጉሜን ላይ ካልሆነ ዝናቡ በጠዋቱ አያስቸግረንም። ቁርሳችንን በልተን ወደ ጫካ የተተኮስን የማታው ዝናብ ሳይጠምደን እንመለሳለን። አንዴ ከያዘ የማይለቀው አህያ የማይሸከመው ዝናብ ከመጣ የልጅ ጀርባችን ያጎብጠዋል፤ በረዶው መላጣ ራሳችንን እየቀጠቀጠ መግቢያ ያሳጣናል። ቆረቆራችንን ያፈርጠዋል።ቢሆንም ቤት ስንደርስ የወላጆቻችን ፈገግ

ታ እና ምርቃት ያንን ሁሉ ነገር ያስረሳናል። ትኩስ ትኩሱ ይቀርብልናል። ከትኩስ ሽሮ እስከ ትኩስ አሹቅ (ዲዘርት መሆኑ ነው) በደስታ ይቀርብልናል። ያንን በራበው ሆዳችን ላክ ላክ እያደረግን እንቅልፍ ሰዓታችንን እንጠብቃለን። ቴሌቪዥን የለ፣ ፊልም የለ፣ እንዳሁኑ ልጆች “ጌም የለ” ….። ሐምሌን እንዲህ ጨርሰን ነሐሴ ሲመጣ ከ

እንጨት ለቀማውም ከሌላውም ሥራ የሚገላለግለን የፍልሰታ ጾም ነው። ፍልሰታ የልጆች ጾም ስለሚባል አንገታችን ላይ ሚጢጢ ያንገት ልብስ እየጠመጠሙ ወደ ቤተ ክርስቲያን ይልኩናል። እውነቱን ለመናገር ከጽድቁ ይልቅ ትዝ የሚለን ከቅዳሴ በኋላ የምንበላው ንፍሮ እና ቆርበን ስንመጣ እቤት የሚጠብቀን እንክብካቤ ነው። የቆረብን ቀንማ ምን ብናጠፋ ማን ንክች ሊያደርገን? ባይሆን ባይሆን በዕዳ ለሌላ ቀን ያስተላልፉታል። በሚቀጥለው ጊዜ በጥፋት ስንገኝ የቆረብን ዕለት ያናደድናቸውን ደምረው ቂማቸውን ይወጡብናል። እዚህ የፈረንጁ አገር፣ ልጆቹ ትምህርት ቤ

ታቸው ሲዘጋ ምን እንደሚሆኑ እና ምን እንደሚያደርጉ ማሰብ የወላጅ ትልቁ ጭንቀት ነው። አንዱ ቦታ አስቀድሞ ተመዝግቦ እና ከፍሎ መዘጋጀት የወላጅ ግዴታው ነው። ገና በሙዓለ ሕጻናት ዕድሜ ካሉት እስከ ወጠጤ

ጎረምሳዎቹ (Teenagers) ድረስ የሚውሉበት ሥፍራ አላቸው። ያንን የሚያዘጋጁት ደግሞ የግል ተቋማትም፣ የመንግሥት ተቋማትም ጭምር ናቸው። መንግሥት ለወጣቱና ለሕጻኑ ካላሰበ ምኑን መንግሥት ሆነው?በምኖርበት አካባቢ ልጆችን በዚህ የዕረፍት

ወቅት ከሚያስተናግዱት መካከል የአካባቢው መስተዳደሮች (ቀበሌ እንበላቸው?) አንደኛዎቹ ናቸው። በመጠነኛ ክፍያ ለሕጻናቱ እና ለወጣቶቹ መርሐ ግብሮች ያሰናዳሉ። የተለያዩ ስፖርቶች፣ ጉብኝቶች፣ ዋናዎች፣ እንደየዕድሜያቸው ከእኩዮቻቸው ጋር ትውውቆች እና ጨዋታዎች ያዘጋጁላቸዋል። ለአንድ ልጅ በቀን ከ50 ዶላር ያላነሰ ያስከፍላሉ። የግሎቹ የሚያስከፍሉት ከዚህ በጣም ይወደዳል። ይህ የቀበሌዎቹ ሰርቪስ ገሚሱም በተለያየ መልኩ ሳይደጎም የሚቀር አልመሰለኝም። አለበለዚያ እንዲህ ርካሽ ሊሆን አይችልም ነበር።

ትምህርት ቤት ሲዘጋ…

ኤፍሬም እሸቴ

በአሜሪካ ዕለት ከዕለት፤ ሳምንት ከሳምንት አንድ ዓይነት ነገር እ

ያሰቡ እና እየሰሩ ለመኖር አልተፈጠርኩም ብየ ሳምን የቆየሁ ቢሆንም አሜሪካ ግን ሳልወድ በግዴ በተመሳሳይ ሳምንታዊ ፕሮግራም እና ልማድ እንድኖር አስገድዶኛል፡፡ ይህንን የኑሮ ዘይቤ ለምጀው ተፈጥሮዬ ላደርገው ትንሽ ሲቀረኝ፤ ሰሞኑን ልጄ ከእንቅልፌ ቀሰቀሰኝ፡፡ የነገሩ መነሻ መጪው የሰመር ዕረፍት ነበር፡፡“Abuka! When will your summer break

starts?” I asked my son.“You are Dady!, you’r suppose to know it.”

he replied. He is trying to remind me about my own Ignorance. Then he continues “Any way, summer break will begin after a couple of weeks. But it offcially starts on June 21st”“It is good to know” I replied. The I added “I

think we need to have a paln for the summer break”This time my son switched in to his angry

mode. “ Dadyeeee! I am tried of this planning thing. Summer break means a break from EV-ERY THING. I don’t want to plan any thing”My son’s frustration reminded me my self

imposed ‘planning obssession’.ሁሉም ኢትዬጵያዊ ይህንን ግብ የሚፈጽምበት መን

ገድ የተለያየ ነው፡፡ የእኔም እንዲሁ፡፡ ከሰኞ እስከ አርብ ልጆች ትምህርት ቤት ስለሚውሉ፤ የቤት ሥራ ከማሰራት ውጪ ብዙ ሥራ አይጠበቅብኝም፡፡ ቅደሜ እና እሁድ ግን ከባድ ቀኔ ነው፡፡ የተለመደው የሰንበ ት ቃሌ አንድ ነው፡፡‹‹ልጆች! የዛሬ ዕቅዳችሁን ጽፋችሁ አምጡ!›› እላለ

ሁ፡፡እንደተለመደው ‹‹በቃላችንን ብንነግርህስ?›› ይላሉ፡

፡ ግን እንደማይሆን ስለሚያውቁ ባላቸው አቅም ሞጫጭረውያመጣሉ፡፡ በዕቅዳቸው ወስጥ ምን ማካተት እንዳለባ

ቸው ስለለመዱ፤ የሚጽፉት አያጡም፡፡-መኝታ ማንጠፍ፤ ክፍላቸውን ማጽዳት-ቴሌቪዥን ማየት-ማንበብ-ስዕል መሳል-ብስክሌት መንዳት-ላይብረሪ/ፓርክ መሄድ-ሂሳብ መማር-ሀ ሁ ሂ መማር (በእነርሱ አገላለጽ)-ፕሮጀክት የሚሉት ነገር መስራት-መጫወት- የመሳሰሉ ነገሮችን ይደረድራሉ፡፡ዋናው ዓላማዬ ‹‹ደበረኝ›› እና ‹‹ምን ልሥራ›› ማለትን

እንዳይለምዱ ነው እንጂ ቀኑን ሙሉ ሲጫወቱ የሚውሉበትም ጊዜ አለ፡፡ በሌላ አንጻርም ይህን ማድረጌ ለራሴም በግሌ የምሰራውን የምሰራበት ነጻ ጊዜ እንዲኖረኝ ለማድረግም ጭምር እንጂ፡፡ለልጆች ቅዱስ የሰመር ፕሮግራም የሚሆነው ኢትዬ

ጵያ ሄደው ቢከርሙ ነበር፡፡ ሁሉም ወላጅ በግሉ የሚመኘው፤ ቀን ጠብቆም የሚያደርገው ይሄንኑ ነው፡፡ እንደ እኔ ላሉ የዲቃላ ባሕል ልጆች ግን አንድ የተቀናጀ መላ የሚያስብ ሰው ወይም ቡድን ቢኖር ግን ቅዱስ ነገር ነበር፡፡ ልክ እንደ ‹‹ሀገርህን እወቅ›› ፕሮግራም ወይም ‹‹የአሜረካ ፒስ ኮር›› ዓይነት ድርጅት ቢኖረን ተመኘሁ፡፡

ዳድመው እዚያው ቴሌቪዥኑ ላይ እንዳያፈጡ ወላጅ የቻለውን ያህል ይሞክራል። አሜሪካ ላለ ልጅ መቸም ጠላቱ ቴሌቪዥን እና ይኼ ስኳር የሚበዛበት ጣፋጭ ምግብ ነው። የዚህን የቴሌቪዥንን ነገር፣ በየጣራቸው ላ

ይ ዲሽ የሰቀሉ የአገር ቤት ወላጆችም ሊያስቡበት ይገባል። ዲሽ መግጠማቸውን እንጂ ልጆቻቸው ምን እንደሚያዩ ሳያዉቅ የልጆቻቸው መጥፊያ እንዳይሆንባቸው ብርቱ ጥንቃቄ ይፈልጋል። ቴሌቪዥን ሕጻናቱን ያደንዛል። ያደነዝዛል። ከማንበብ ይልቅ ፊልም እና “ጌም” ብቻ የሚወዱ ስልቹዎች ያደርጋቸዋል። ብዙ ሰዓት ቁጭ ስለሚሉም ሰውነታቸው አላስፈላጊ በሆነ ውፍረት ይወጠራል። ገና በልጅነታቸው የበሽታ ዓይነት ይሸከማሉ። ድሮ ድሮ ወፍራም ልጅ ስናይ “የሀብታም ል

ጆች” እያልን ስንቀናባቸው ኖረን አሁን ቀጭን መሆን ዋጋ ያለው አገር መጣንና በተራችን ልጆቻችን እንዳይወፍሩ እንጨነቃለን። በየጊዜው የነርሱን ኪሎ መለካቱ፣ ወፈሩ አልወፈሩ እያሉ ማሰቡ የአሜሪካ ወላጅ አንዱ ግዴታ ነው። ድሮ አገር ቤት “ምነው ልጄ ወፍራም በሆነልኝ” ሲባል ሰምተን አሁን ደግሞ (አሜሪካ) “ኧረ ልጄ ወፈረብኝ/ እየወፈረብኝ ነው/ ሊወፍርብኝ ነው” የሚል ጭንቀት መስማት ግርምት ይፈጥራል።በሁሉም በሁሉም፣ በአሜሪካ ትምህርት ቤ

ት ሲዘጋ፣ ከውፍረታቸው እስከ መዋያ ቦታቸው፣ ከትምህርታቸው እስከ መዝናኛቸው ወላጅ የቤት ሥራ የሚበዛበት ጊዜ ይሆናል። እናም አንዳንዴ “ምናለበት የሀገሬ ልጆች እንዲህ ዓይነቱን የልጆች መዋያ በየመንደሩ ባገኙ” የሚል ቁጭት ውስጤን ይበላኛል። ሜዳው ሁሉ ዛኒጋባ እየተቀየሰበት፣ ልጆቹን አንድም ለሥራ ፈትነት፣ አንድም ለጫት ቃሚነት፣ አሁን እንደምሰማው ደግሞ “ለሺሻ ሱሰኝነት” አሳልፈን እየሰጠናቸው ነው። ቢያንስ ቢያንስ እነዚህ አሁን የሚገነቡትን

“ኮንዶሚኒየም” ሕንጻዎች እና አዳዲስ መንደሮች እንኳን በሕግ ደረጃ ለሕጻናት መጫወቻ የሚሆን ቦታ እና አረንጓዴ ሥፍራ እንዲኖራቸው በማስገደድ ልጆቻችን እንደ ማንኛውም ልጅ የሚቦርቁበት፣ የሚጫወቱበት፣ ወደ አስፓልት ከመውጣት ይልቅ ከመንገድ የሚርቁበትን ሁኔታ ማመቻቸት ይገባል። ተደርጎ ከሆነም ደግሞ እሰየው ደስ ያሰኛል። እንቅፋት የእግራችንን ጥፍር እየነቀለውም ቢሆን፣ የወዳደቁ ነገሮች እየወጉንም ቢሆን ኳስ ያንከባለልንበት “እንትና ሰፈር ሜዳ፣ ቀበሌ ምንትስ ሜዳ” ናፈቀኝ። ለአሁኖቹም ሕጻናት ተመኘሁላቸው።

ከወደድኩላቸው ዝግጅት አንዱ ሕጻናቱን እና ወጣቶቹን ይዘው ወደ ሙዚየም ጉዞ ማድረጋቸው ነው። እንደየዕድሜያቸው የሚመጥናቸውን ያሳዩዋቸዋል። ስለ አገራቸው እንዲያውቁ ያስተምሯቸዋል። በዚያ ዕድሜ “ሙዚየም መሔድን” እንዲለምዱም በልቡናቸው ይቀርጹባቸዋል። እዚያ ባለው ቤተ መጻሕፍትም እንዲያነቡ ያበረታቷቸዋል። መሸት ሲል ወላጅ ሁሉ ልጁን ከያስቀመጠበ

ት ይሰበስባል። ወራቱ በጋ ስለሆነ ፀሐይ ቶሎ አትጠልቅም። ይህንን ጽሑፍ እየጻፍኩ ባለሁበት ሰዓት (ከምሽቱ 2 ሰዓት ላይ) ውጪው ወከክ ብሎ ይታየኛል። ፀሐይ ወደ ቤቷ ተጠቃላ ለመግባት ትንሽ ይቀራታል። ስለዚህ ልጆቹን ወደ ውጪ ይዞ መውጣት ለሚችል ወላጅ ጊዜው ይመቻል። ሳይመሽ ወደቤት ከገቡ ተሽቀ

ድሮ ድሮ ወፍራም ልጅ ስናይ “የሀብታም ልጆች”

እያልን ስንቀናባቸው ኖረን አሁን ቀጭን

መሆን ዋጋ ያለው አገር መጣንና በተራችን

ልጆቻችን እንዳይወፍሩ እንጨነቃለን።

ማስታወቂያ

በዚህ ጋዜጣ ማስታወቂያ ለማውጣት ከፈለጉ

በ+256-778-693669ይደውሉልን

በናኦድ ቤተሥላሴ (ሜሪ ላንድ፣ አሜሪካ)

ይህ ጽሁፍ የተወሰደው ከናኦድ ጡመራ ናኦድ ላይቭ ብሎግ ስፖት ዶት ኮም ነው

A break from every thing

ይህ ጹሁፍ ከኤፍሬም እሸቴ ጡመራ አደባባይ ብሎግ ስፖት ዶት ኮም የተወሰደ ነው

Page 7: Habeshawi kana 004

ሐምሌ 30-ነሐሴ 13 ቀን 2003 (August 6-19, 2011) ሐበሻዊ ቃና 7

የስደት ዓለም

በሊቢያ እና ግብጽ ድንበር የምትገኛዋ ሳሉም በረሃማ ነች። በዚያ ምህረት አልባ በረሃ ላይ አንድ ትንሽዬ እና ደካማ ፍጡር ራሱን ከአሸዋ እና ንፋስ ለመከላከል እየሞከ

ረ ይንከላወሳል። ትግሉ ግን ከተፈጥሮ ጋር ብቻ አልነበረም። ውስጡን ከሚያብሰከስከው ስጋት እና የደህንነት ማጣት ስሜት ጋርም ነው። ይህ ፍጡር ሰሎሞን ይባላል። የራሴ የሚለው ምንም ነገር የሌለው፣ ብቸኛ፣ የ17 ዓመት ወጣት ኤርትራዊ ስደተኛ ነው። ከዕድሜው በላይ ቁም ነገረኛ የሆነው ሰሎሞን

ህይወቴ የተገረመ ነው ብሎ ያምናል። “ከውልደቴ ጀምሮ ጨምሮ አስቸጋሪ ህይወት ነው ያሳለፍኩት። የህጻንነት ጊዜ የሚባል አልነበረኝም። ትምህርት ቤትም አልገባሁም” ይላል ስለ ህይወቱ ሲያስረዳ። ሰሎሞን ከኤርትራውያን ስደተኛ ቤተሰቦቹ ሱዳን ውስጥ ነው የተወለደው። ወላጆቹን ግን አያውቃቸውም። አባቱ እርሱ ከመወለዱ በፊት ነበር የሞተው። እናቱ ደግሞ እርሱን ስትገላገል በወሊድ ምክንያት አርፋለች። እርሱን ያሳደጉት ለነፍሳቸው ያደሩ እማሆይ ስላስ የሚባሉ እናት ናቸው። ነፍስ ሲያውቅ ጀምሮ ኑሮን ለማሸነፍ ውሃ መሸ

ጥ የጀመረው ሰሎሞን በ12 ዓመቱ ሌላ ትልቅ መከራ ወደቀበት። እንደእናት ያሳደጉት እማሆይ ስላስ ሞቱ። ብቻውን ቀረ። “አሁንም ድረስ በጣም ትናፍቀኛለች። ያለችን አንድ ቤተሰብ እርሷ ነበረች” ይላል በሀዘን ስሜት ተውጦ። ከእማሆይ ስላስ ሞት በኋላ አንድ ሱዳናዊ ሊያ

ሳድገው ይስማማል። ሆኖም የሚከተለውን የክርስትና ሃይማኖት በእስልምና እንዲለውጥ ያስገድደዋል። “ገና ከስላስ ሞት ሳላገግም ግፊት ያሳደርብኝ ጀመር። ይሄኔ ጥዬ ወጣሁ” ይላል ለምን ከአዲሱ አሳዳጊ እንደሸሸ ሲተርክ። ሽሽቱ ከነበረበት አነስተኛ ከተማ ከፍ ወዳለችው አል ፋው አደረ

ሰው። በእዚያ ለስድስት ወር ያህል ቆየ። ቀን ቀን ያደገበትን ውሃ መሸጥ ሲያከናውን ይውልና ማታ ላይ ጎኑን ለማሳረፍ ወደ አውቶብስ ማቆሚያዎች ጎራ ይላል። እንዲህ እንዲህ እያለ ወደ ሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም የሚወስደው ገንዘብ አጠራቀመ። ካርቱም ለአንድ የህግ አገልግሎት በሚሰጥ ድርጅት የጽዳት ስራ አገኘ። ሰሎሞን ጎሮሮውን መድፈን ባያቅተውም የተሻ

ለ ኖሮ ፍለጋ በአንድ ሆቴል ውስጥ ካገኛቸው ኤርትራውያን ጋር ወደ ሊቢያ ለመሻገር ተስማማ። እ.ኤ.አ በ2009 ሊቢያ ሲደርስ ዕድሜው ገና 15 ነበር። “ሌላ ቦታ ያለውን ስለማላውቅ ሊቢያ የተሻለ ህይወት ያለ መስሎኝ ነበር። ዕቅዱ ግን ከትሪፖሊ ባህር አቋርጦ ወደ አውሮፓ መሄድ ነበር። ነገር ግን እንዲያ ለማድረግ ዋጋው የሚቀመስ አልነበረም።” አብረውት ሊቢያ ዋና ከተማ ትሪፖሊ የገቡ ተ

ሳክቶላቸው ጣሊያን ገቡ። ደጋፊ እና አጋዥ የሌለው እርሱ ግን ብቻውን ቀረ። ትሪፖሊ ያለው የወታደር ብዛት ያሰጋው ሰሎሞን ቤንጋዚ ወደተሰኘችው ከተማ ሄደ። እዚያም በካፌ ውስጥ ስራ አገኘ። አብዛኛውን ጊዜ ስራ ላይ የሚያሳልፈው ሰሎሞን ከተማይቱን ለመመልከት ወጣ የሚለው ከስንት አንዴ ነበር። ከእነዚህ አጋጣሚዎች በአንዱ ግን ለእስራት በቃ። ምክንያቱ ደግሞ በአንገቱ ላይ ያንጠለጠለው መስቀል ነበር። በእስላማዊቷ ሊቢያ መስቀል አድርጎ በመገኘቱ ብቻ ወደ እስር ቤት ተወረወረ። “ለማየት ያህል በአነስተኛ ቀዳዳ ብርሃን በሚገ

ባበት ትንሽዬ ጨለማ የእስር ክፍል ውስጥ አስቀመጡኝ” ይላል የታሰረበትን ክፍል ሲያስታውስ። “ወደ እስር ክፍል ስገባ ዓይኔ እንዳላይ ተሸብቦ ስለነበር የት እንደታሰርኩ አንኳ አላወቅኩም ነበር። ከእስራኤል እንደመጣሁ ደጋግመው ይናገሩ ነበር። በኤሌክትሪክ ንዝረት ያሰቃዩኝ ነበር። በጣም ፈርቼ ነበር” ሲል እየተንቀጠቀጠ የነበረበትን ሁኔታ ይተርካል።

እስካሁንም እልባት ያላገኘው የሊቢያ አብዮት በየካቲት ሲፈነዳ ሰሎሞን ከሌሎች እስረኞች ጋር ተለቀቀ። ተለቅቆም ግን ሰላም አላገኘም። ሙአመር ጋዳፊ መልካቸው ጠቆር ያሉ ቅጥረኞችን አሰልፏል በሚል ከሰሃራ በታች ካሉ ሀገሮች የመጡ ስደተኞች ላይ ጥቃት መፈጸም ተጀመረ። የጋዳፊ ተቃዋሚዎች ዋነኛ ቦታ በሆነችው ቤንጋዚ ስደተኞች የጥቃቱ ዋና ኢላማ ሆኑ። ለህይወቱ የሰጋው ሰሎሞን የሊቢያ ቀይ ጨረቃን ሙጥኝ አለ። የዓለም የስደተኞች ድርጅት (አይ.ኦ.ኤም) በመጋቢት ወር ስደተኞችን ከሊቢያ ሲያስወጣ ሰሎሞንም አንዱ ሆነ። በሺህዎች የሚቆጠሩ ስደተኞችን ተከትሎ በሰሜን ምስራቅ ግብጽ ወደምትገኘው ሳሉም ተጓጓዘ። በሳሉም በያዝነው ሐምሌ ወር መጀመሪያ ላይ የ

ቀሩ የሊቢያን ጦርነት የሸሹ በመቶዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች ነበሩ። ምንም እንኳ በእርሱ ዕድሜ ያሉ ሌሎች ኤርትራውያን ስደተኞች በሳሉም መጠሊያ ጣቢያ ውስጥ ቢኖሩም ሰሎሞን ግን አሁንም ብቻውን ነው። ከተባበሩት መንግስታት የስደተኞች መርጃ ድርጅት ባገኘው ፕላስቲክ አነስተኛ ድንኳን ቀልሶ በእርሷ

የዓለም ትኩረት በምስራቅ አፍሪካ ስለተከሰተው ድርቅ እና ስለሚያስከትለው ተጽእኖ በሆነበት በአሁን ወቅት ሌላ ቀውስ በአንድ የኢትዮጵያ ጥግ ድምጽ አጥፍቶ ሊፈነዳ እየተንተከተከ ይገኛል። ቀውሱ ደግሞ ወደ ኢትዮጵያ ከሚጎርፉ ኤርትራውያን ጋር የተያያዘ ነው። ማለቂያው የማይታወቅ የወታደራዊ አገልግሎት

እና የሰብዓዊ መብት ጥሰትን ሽሽት ነው ያሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኤርትራውያን በየወሩ ወደ ኢትዮጵያ ይመጣሉ። በሰሜን ኢትዮጵያ የሚገኙ የስደተኛ መጠለያ ጣቢያዎችን በቅርቡ የጎበኙት የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች መርጃ ድርጅት (ዩ.ኤን.ኤች.ሲ.አር) ረዳት ኮሚሽነር ኤሪካ ፌለር የተመለከቱትን “የወጣት ፊቶች ባህር” ሲሉ በድንጋጤ ገልጸውታል።ከሶማሊ እና ሱዳን በርካታ ስደተኞች በተጨማ

ሪ ኢትዮጵያ 48 ሺህ የሚጠጉ ኤርትራውያን መጠጊያ ሆናለች። ከእነዚህ አብዛኞቹ ኤርትራውያን ስደተኞች ወጣት፣ የተማሩ እና ገና ያላገቡ ወጣት ወንዶች ናቸው። የስደተኞቹ ቁጥር በየወሩ ማሻቀቡን ቀጥሏል። በየወሩ ከ800 እስከ አንድ ሺህ የሚጠጉ ኤርትራውያን ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ። ከ

እነዚህ መካከል ቁጥራቸው ቀላል የማይባል አለጠባቂ ድንበር የሚሻገሩ ህጻናት ይገኙበታል። እስከ ስድስት ዓመት ያላቸው ህጻናት ሁሉ ተሰድደው ይመጣሉ። እነዚህ ለጋ ህጻናት እንክብካቤ የሚያገኙት በመጡበት ቡድን ውስጥ ባሉ በዕድሜ ከፍ ባሉ ሌሎች ህጻናት ነው።

እኛን በአግባቡ እንድታስናግደን አልጠብቅም።” ለተሻለ መጻኢ ህይወት ገንዘብ ማጠራቀም ለ

ሚመኘው ሰሎሞን ሕይወት አስቸጋሪ ነበረች። “ዕቅዶች አሉኝ። ገንዘብ አጠራቅሜ ጥሩ ትምህርት ለመማር ከዚያም የተሻለ ህይወት መኖር እፈልጋለሁ። ይህንን ዕድል እስካሁንም አላገኘሁም” ይላል። ሰሎሞን ወደፊት ጥሩ ዕድሎች እንደሚያጋጥሙት ያምናል። “በህይወት ውስጥ ምንም ነገር እንደነበረ አይቆይም። ነገሮች ባልተጠበቀ ሁኔታ በበጎ መልኩ ሊለወጡ ይችላሉ” ሲል ይተነብያል።የሰሎሞን ትንበያ በስተመጨረሻ እውን ሆኗል።

የስዊዲን መንግስት ከሳሉም ስደተኛ ጣቢያ ለመልሶ ማስፈር ለመውሰድ ከተስማማባቸው 145 ስደተኞች መካከል አንዱ ሰሎሞን ሆኗል። ሰሎሞን ይህን ዕድል ቢያገኝም ነገ የሚያመጣለትን ደፍሮ ማሰብ አልሆነለትም። “በስተመጨረሻ ወደተሻለ ቦታ ለመሄድ ይህንን ዕድል ለማግኘት በመቻሌ ደስተኛ ነኝ። ነገር ግን እዚያ እስከድርስ ድረስ አላምንም። ህይወቴ እንደድሮው ሊቀጥል ይችል ይሆናል” ሲል ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ ያስረዳል።

ህልም አልባው ኤርትራዊ ወጣት

በናያና ቦሴሳሉም-ግብጽ

የማያቋርጠው የስደተኞች ጎርፍ በአሁኑ ወቅት ካለው የስደተኞች አገልግሎት መስጫ አቅም በላይ ሆኗል። የችግሩን መጠን የተመለከቱት ፌለር ዩ.ኤን.ኤች.ሲ.አር የረጅም ዓመት የስራ ቆይታቸው ይህን የመሰለ ነገር አለማየታቸውን ተናግረዋል። ረዳት ኮሚሽነሯ እና አብረዋቸው የመጡ የል

ውስጥ ይኖራል። ሰሎሞን እንዲህ ገለልተኛ እንዲሆን ያደረገው ያለፈበት መራራ ህይወት ነው። አሁንም ቢሆን የደረሰበትን ማሰቃየት ትውስ እያለው ይረበሻል። በዚህ ምክንያትም ከሰዎች ጋር ተቀራርቦ መነጋገርም ሆነ ጓደኛ ማፍራት አልቻለም። ሰዎችን ለማመንም ይቸገራል። “ጥሩ የህጻንነት ጊዜ አልነበረኝም። ዕድሉን ሳገኝ

ጓደኛ አፈራ ይሆናል” ይላል እርግጠኛነት በማይነብበት ድምጽ። “ነገር ግን ምን የምናገረው ይኖራል? ከችግሮቼ በቀር የማጋራው ምንም ነገር የለኝም። ስለሳለፍኩት ህይወት ልነግራቸው እችል ይሆናል ነገር ግን ስለወላጆቼ እና ስላስ በፍጽም ትንፍሽ አልልም። ስለእርሱ ሳስብ አሁንም ድረስ ህመም ይሰማኛል። ገና አልተፈወስኩም”በሰው መሃል እንዲህ በብቸኝነት የሚሰቃየው ሰ

ሎሞን ከስደተኛ ጣቢያው ጥሩ ነገር የሚለው ነገር የግብጽ ባለስልጣናትን ብቻ ነው። “በሳሉም ያሉትን ወታደሮች ላደንቃቸው እወዳለሁ። ያልተገባ ጸባይ ብናሳያቸውም እንኳ ጫፋችንን አይነኩንም” ይላል። ከዕድሜው በላይ ብልህነት በሚታየበት አነጋጋርም እንዲህ ይላል። “ግብጽ በአስቸጋሪ ሁኔታ ላይ ነች። ያለመንግስት ያለች ሀገር

ዑካን ቡድን አባላት በሰሜን ኢትዮጵያ ሽሬ አካባቢ የሚገኘውን የምዝገባ ጣቢያ ተዘዋውረው ጎብኝተዋል። እንደባጉና ተብሎ በሚጠራው ቦታ ወዳለው የምዝገባ ቦታ በቅርቡ የመጡ ስደተኞችንም አነጋግረዋል። አዲ ሀሩሽ እና ማይ ማኒ የተባሉትን የስደተኛ ጣቢያዎችንም ተመልክተዋል። በሁለቱ ጣቢያዎች የሚገኙ ስደተኞች ችግራቸ

ውን ዓለም ያውቅላቸው ዘንድ ረዳት ኮሚሽነሯ እንዲረዷቸው ተማጽነዋል። “የወጣትነታችንን ሩብ ማብቂያው በማይታወቅ ወታደራዊ አገልግሎት በአገር ቤት አሳልፈን። ሌላኛውን ሩብ ደግሞ በስደተኛ ጣቢያ ውስጥ ፈጀን። ዩ.ኤን.ኤች.ሲ.አር ልጆቻችንን እንደወላጆቻቸው ዕድሜያቸውን በስደተኛ ጣቢያዎች ውስጥ እንዲፈጁ መፈቀድ አለበትን?” ስትል የሴቶች ተወካይ የሆነች አንዲት ስደተኛ ፌለርን ጠይቃለች። ፌለር በበኩላቸው የስደተኞች ካሰቡት ጊዜ በላ

ይ ለረጅም ጊዜ መቆየታቸው እንደሚሰማቸው ገልጸውላቸዋል። ኤርትራውያን ስደተኞች ወደ ኢትዮጵያ መምጣት የጀመሩት እ.ኤ.አ ከ2000 ጀምሮ ነው። በመጀመሪያ የደረሱት በስደተኛ ጣቢያ ያሳለፉት ጊዜ ሲሰላ አንድ አስርት ተሻግሯል። “እነዚህ ተስፋ ያላቸው ወጣቶች ቢሆኑም ተስፋ

ግን እየታያቸው አይደለም” ይላሉ ፌለር። “የዓለም አቀፍ ማህበረሰቡ እነዚህን ወጣቶች መንከባከብ ላይ ከማተኮር ይልቅ ያለውን ችግር በደንብ ተመልክቶ በወደፊት ሕይወታቸው ላይ ጥሪቱን ማፍሰስ ይገባዋል።” በአሁኑ ወቅት ወደአገር ቤት በፍቃደኝነት መመ

ለስ ከምርጫ ውስጥ የሚገባ ባለመሆኑ ዩ.ኤን.ኤ

በረጅሙ እና የማይገፋ በሚመስለው ቀን ሰሎሞን በበረሃማዋ ሳሉም ከመንገድ ጠርዝ ተቀምጦ ይተክዛል

በክሱት ገ/እግዜያብሔር ሽሬ-ኢትዮጵያ

ች.ሲ.አር ለኤርትራውያን ስደተኞች እየተከተለ ያለው ብቸኛ ቋሚ መፍትሔ መልሶ ሰፈራ ብቻ ነው። ፌለር ለስደተኞች እንዳብራሩት ከሆነ በተለያዩ አገራት የሚሰጠው የመልሶ ማስፈር ዕድል ውሱን ነው። ዩ.ኤን.ኤች.ሲ.አር እነዚህን የመልሶ ማስፈር ዕድሎች ለመጨመር ይሰራል። “ሕይወት በስደተኛ መጠለያ ጣቢያ ከባድ ነው”

ይላል ከሁለት ወራት በፊት ወደዚህ ቦታ የመጣው የስምንት ዓመት አዳጊ። እዚህ ረጅም ጊዜ ለመቆየት “እምብዛም የሚያጓጓ” ነገር እንደሌለም ያክላል። በስደተኛ ጣቢያዎች ውስጥ ባለው አስቸጋሪ ኑሮ እንደዚሁም ራስን ለመቻል እና የከፍተኛ ትምህርት ለመቀጠል ያለው ዕድል ውሱን መሆን በሺህዎች የሚቆጠሩ ኤርትራውያንን እንደገና ወደ ሶስተኛ አገራት እንዲሰደዱ እያደረጋቸው ነው። ብዙዎች ሱዳን እና ግብጽን ወደ አውሮፓ እና መካከለኛው ምስራቅ መሸጋገሪያ አድርገው ይጠቀማሉ። ወደእነዚህ ሀገራት በህገወጥ አጓጓዦች የሚደረገው ጉዞ ግን በአብዛኛው አደገኛ ነው። ይህንን ዳግም ስደት ለማቆም አንድ እርምጃ መ

ወሰድ እንዳለበት የሚያሳስቡት ፌለር ለዓለም አቀፉ ህብረተሰብ ጥሪ ያቀርባሉ። “የዓለም አቀፉ ህብረተሰብ ኢትዮጵያን እና እንደ ዩ.ኤን.ኤች.ሲ.አር ያሉ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ለእነዚህ ሰዎች ሁነኛ አማራጭ እንዲያቀርቡ እርዳታ ሊሰጧቸው ይገባል። ይህ የሚሆን ከሆነ እነሱም ራሳቸውን ለህገ ወጥ አዟዟሪዎች አሳልፈው በመስጠት ራሳቸውን አደጋ ላይ አይጥሉም።”

እንደ ገበቴ ውሃ...

ሁለቱም ጽሁፎች የተወሰዱት ከዩ.ኤን.ኤች.ሲ.አር ኦፌሲሊያዊ ድረ ገጽ ነው

ረዳት ኮሚሽነር ኤሪካ ፌለር እና የዩ.ኤን.ኤች.ሲ.አር የኢትዮጵያ ተወካይ ሞሰስ ኦኬሎ በሰሜን ኢትዮጵያ ያሉ ስደተኛ ጣቢያዎችን በጎበኙበት ወቅት ጠባቂ ከሌላቸው ኤርትራውያን አዳጊዎች ህጻናት ጋር ተገናኝተዋል

ፎቶ

- ክሱ

ት ገ

/እግዚ

ያብሔ

ፎቶ

- ናያና

ቦሴ

Page 8: Habeshawi kana 004

ሐምሌ 30-ነሐሴ 13 ቀን 2003 (August 6-19, 2011)ሐበሻዊ ቃና8

የስደት ዓለም

መጀመርያ ወደ ሱዳን ኤምባሲ ሄዳችሁ ሱዳን የመግቢያ ቪዛ ታወጣላችሁ፡፡ ከዚያ በጎንደር በመተማ በኩል ወደ ሱዳን ትገሠግሣላችሁ፡፡ ‘የሱዳን ሕዝብ ጥሩ ነው፣ለስደተኞች ይራራል‘ ይላሉ ጣልያን የገቡት ብዙዎቹ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች፡፡ እዚያ የታወቁ ሁለት አሸጋጋሪዎች አሉ፡፡ በአካል አታገኟቸውም፡፡ ስልካቸውን ከሀገር ሳትወጡ ይዛችሁ መሄድ አለባችሁ፡፡ አለበለዚያም ጣልያን የገባ ሰው ሊነግራችሁ ይገባል፡፡አንዳች ሰዋራ ሥፍራ ተደብቃችሁ በስልክ ታገ

ኟቸውና የጉዞ ዋጋ እና ቀን ትነጋገራላችሁ፡፡ እነርሱም ገንዘቡን ይዛችሁ የምትመጡበትን ቦታ እና ቀን ይነግሯችኋል፡፡ በተባላችሁት ሌሊት እቦታው ስትደርሱ እንደ እናንተ በቀጠሮ የመጡ ሌሎች ስደተኞችን ጨምረው በጭነት መኪና ወደ ሊቢያ ድንበር ትወሰዳላችሁ፡፡ ጉዞው ሌሊት ሌሊት፣ ያውም አብዛኛው በእግር፣ ጥቂቱ ደግሞ በመኪና ስለሆነ ከሃያ ቀን እስከ አንድ ወር ይፈጃል፡፡ሊቢያ ድንበር ስትደርሱ የሱዳን አሸጋጋሪዎች ለ

ሊቢያ አሸጋጋሪዎች ያስረክቧችኋል፡፡ ዋጋ ተነጋግራችሁ አሁንም ጉዞ ትጀምራላችሁ፡፡ ግማሹን በእግር ግማሹን በፒክ አፕ መኪና፡፡ ደረቅ ዳቦ እና ውኃ ይሰጣችኋል፡፡ መንገድ ላይ የሚሞቱ ልጆች ይኖራሉ፡፡ አሸዋውን ማስ ማስ አድርጎ በመቅበር ጉዞ መቀጠል ነው፡፡«በእግር ወይንም በመኪና ስትጓዝ በእንጨት የ

መስቀል ምልክት የተሠራበት ነገር ካየህ እዚያ ቦታ አንድ አበሻ ስደተኛ ተቀብሯል ማለት ነው፡፡» ብሎኛል ጣልያን ያገኘሁት ልጅ፡፡ «ሰው ከታመመ እንደ በሽታው ነው፡፡ መጠነኛ ከሆነ በድጋፍ ይሄዳል፡፡ ከባድ ከሆነ ግን ቁርጥ ወገን ያስፈልገዋል፡፡ ከቡድኑ ከተቆረጥክ ችግር ስለሚያጋጠምህ አንዳንዱ ትቶህ ይሄዳል፡፡ ብዙ ጊዜ ግን የቂርቆስ ልጆች ይተዛዘናሉ፡፡ እንዲያውምከቂርቆስ ልጅ ጋራ አብረው ቢሰደዱ ቢያገኝም ያበላል ቢያጣም ያዝናል ሆዱተብሎ ተዘፍኖላቸዋል፡፡» አለኝ ሮም ያገኘሁት

የአዲስ አበባው የቂርቆስ ልጅ፡፡ አዲስ አበባ ስለ ቂርቆስ ሠፈር ልጆች አያሌ አስገራሚ እና አስቂኝ ነገሮች እሰማ ነበር፡፡ እዚህ ጣልያን ደግሞ አገር ጉድ የሚያሰኝ ገድላቸውን መስማት ጀምሬያለሁ፡፡ሊቢያ ስትገቡ የተቀበሏችሁ አሸጋጋሪዎች ከትሪ

ፖሊ አጠገብ የገጠር መንደር ውስጥ በተሠራ አዳራሽ አስገብተዋችሁ ይጠፋሉ፡፡ ከዚያ ሌሎች አሸጋጋሪዎች ደግሞ ይመጡና «ትሪፖሊ ሩቅ ስለሆነ እንድንወስዳችሁ መቶ መቶ ዶላር ክፈሉ» ይሏችኋል፡፡ ታድያ የቂርቆስ ልጆች ምን አደረጉ መሰላችሁ፡፡ የተወሰኑት ልጆች ሌሊት ተደብቀው ይወጡና እግራቸው ወዳመራቸው ሲጓዙ ለካስ ትሪፖሊ ቅርብ ነው፡፡ ተመልሰው ይመጡና ሌሎችን ልጆች ነጻ ያወጧቸዋል፡፡ ከእነርሱ በኋላ ለሚመጡት ስደተኞች ደግሞ ግድግዳው ላይ በአማርኛ እንዲህ ብለው ይጽፋሉ «እንዳት ሸወዱ፣ ትሪፖሊ ቅርብ ነው፡፡ ብር ስጡን ቢሏችሁ አትስጡ፡፡ በዚህ እና በዚያ አድርጋችሁ ጥፉ» ይሄ ማስታወቂያ አያሌ ስደተኞችን ታድጓቸዋል፡፡ አይ የቂርቆስ ልጆች፡፡ ነፍስ ናቸውኮ፡፡

በዳንኤል ክብረት

ማስታወቂያ

መመረሽ፣መፈረሽ፣ፎቶዎች- ዩ.ኤን.ኤች.ሲ.አር

አፍሪካውያን ስደተኞች እንዲህ በተጨናነቀ ሁኔታ፣ በአነስተኛ ጀልባ ታጉረው፣ ሜድትራንያን ባህርን አቋርጠው፣ ጣሊያን ለመግባት ይሞክራሉ

Page 9: Habeshawi kana 004

ሐምሌ 30-ነሐሴ 13 ቀን 2003 (August 6-19, 2011) ሐበሻዊ ቃና 9

የስደት ዓለምትሪፖሊ ገብታችሁ የመርከብ ወረፋ መጠበቅ ነ

ው፡፡ ክፉ ፖሊሶች ካገኟችሁ በመኪና ጭነው እንደ ገና ወደ ሱዳን ድነበር ወስደው ያሥሯችኋል፡፡ እዚያ እሥር ቤቱ በጣም አሰቃቂ ነው፡፡ እዚያም ቢሆን የቂርቆስ ልጆች ካሉ መከራው ይቀልላል፡፡ ከእሥር ቤቱ ለመውጣት የገንዘብ ጉቦ ያስፈልጋል፡፡ ያንን ደግሞ ለማግኘት ወይ አስቸጋሪ ሥራ መሥራት ያለበለዚያም ደውሎ ከዘመድ ማስመጣት ያስፈልጋል፡፡ እዚያ እሥር ቤት ብዙ ልጆችን ያስፈታ አንድ የ

ቂርቆስ ልጅ ነበር፡፡ ሥራ ይወዳል፡፡ ሲጋራ፣ ብስኩት እና ሳሙና እየሸጠ ይኖር ነበር፡፡ በዚያ እሥር ቤት ብዙ ጊዜ የቆየው ሌሎችን ሲያስ ፈታ ገንዘቡ እያለቀበት ነው ይባላል፡፡ ሌሎች ደግሞ በሌላ ነገር ይተርቡታል፡፡ ከእሥር ቤቱ ሊወጣ በር ላይ ሲደርስ «አንድ ሲጋራ አለህ» የሚል ገዥ ሲመጣ ለርሱ ሊሸጥ እየተመለሰ ነው፡፡ እንዲያውም አንድ ጊዜ በአጥር ዘለሎ ሊያመጥ ሁሉም ነገር ተስተካክሎለት ነበር፡፡ ሊዘልል አንድ እግሩን እንዳሣ «አንድ ሲጋራ አለህ» የሚለውን ሲሰማ ተመልሶ መጣ ይባላል፡፡በቤንጋዚ ወደብ አሻጋሪዎች እና ተሻጋሪዎች አ

ይገናኙም፡፡ ሃያ እና ሰላሣ ሰው እስኪሞላ የሚመዘግቡ ሰዎች አሉ፡፡ የቡድኑ አባላት ሲሟሉ ገንዘብ ይከፍሉና ወደሚሻገሩበት ወደብ ይወሰዳሉ፡፡ የመሻገሪያዋ ጀልባ ብዙ ጊዜ ከቆርቆሮ እና ከእንጨት የምትሠራ ናት፡፡ ለአንዱ ስደተኛ አሻጋሪዎቹ የመርከቧን አነዳድ ያሳዩታል፡፡ ትምህርቱ ቢበዛ ከአንድ ቀን በላይ አይሰጥም፡፡ለዚያ መከረኛ «ካፒቴን» የጀልባዋን ኮምፓስ አ

ሥረው ካርታውን ያስረክቡታል፡፡ ምግብ እና መጠጥ ይጫናል፡፡ እንደ ጀልባዋ ስፋት ከሃያ እስከ ሠላሳ ስደተኛ ይሳፈራል፡፡ በሌሊት የጣልያንን መብራት በሩቁ እያዩ ጉዞ ይጀመራል፡፡ አሻጋሪዎቹ ጀልባዋ ስትነሣ ይመለሳሉ፡፡ ከዚህ በኋላ ዕዳው የስደተኞቹ ነው፡፡ጉዞው እስከ አስራ ሰባት ሰዓት ይፈጃል፡፡ የአን

ዱ እግር ከሌላው ጀርባ ጋር ተሰናስሎ ተኮራምቶ መጓዝ ብቻ ነው፡፡ ሙቀቱ እና ተስፋ መቁረጡ አ

ንዳንዶችን ራሳቸውን ወደ ባሕሩ እንዲጥሉ ያደርጋቸዋል፡፡ በተለይም መርከቡ መንገድ ከሳተ፡፡ የሚያስጎበኘኝን የቂርቆስ ልጅ «ለምንድን ነው

ጣልያን ውስጥ የቂርቆስ ሠፈር ልጆች የሚበዙት፡፡ እንዲያውም ሮም ውስጥ የቂርቆስ ልጆች ብቻ ያሉበት አንድ ሕንፃ አሳይተውኛል፤» አልኩና ጠየቅኩት፡፡ «ምናልባት የሱዳን ኤምባሲ ሠፈራችን ውስጥ ስለሆነ ይሆናል በሱዳን በኩል እያቋረጥን የመጣነው» አለና ቀለደብኝ፡፡ «ቆይ ግን ለመንገዱ ብዙ ዶላር ያስፈልጋል ሲባል ነበር የምሰማው፤ እንዴት ነው ጉዳዩ» አልኩት፡፡ «ቂርቆስ የድኻ ሠፈር ነው ብለው ስማችንን ያጠፉትኮ የቦሌ ልጆች ናቸው፤ እነርሱ አውሮፕላን ሲያዩ ስለሚውሉ የገዙ እየመሰላቸው ነው፤ እንዲያውምኮ መንግሥት ሀብታም ገበሬዎችን ብቻ ሳይሆን እኛንም መሸለም ነበረበት፤ የመረጃ እጥረት ነው» አለኝ፡፡«እንዴት?» አልኩት፡፡ «እስኪ ተመልከት እኛ የ

ቂርቆስ ልጆች የመንግሥትን እጅ ሳንጠብቅ፤ አነስተኛ ፣ጥቃቅን ሳንል፤ ራሳችንን በራሳችን ረድተን እዚህ መድረሳችን አያሸልመንም» አለና ሳቀ፡፡ «ሀብታም ገበሬዎች ራሳቸውን ቻሉ እንጂ የሕዝብ ቁጥር አልቀነሱም፤ እኛ ግን ራሳችን ንም ቻልን፣ከሀገር በመውጣታችን ደግሞ የሕዝብ ቁጥር ቀነስን፡፡ ከዚህ በላይ ምን የሚያሸልም ነገር አለ፡፡ አየህ እኛ እንደ ቦሌ ልጆች ጆግራፊን በቲቪ ሳይሆን በተግባር ነው የምንማረው»«ደግሞምኮ የአባቶቻችንን ደም የመለስን እኛ ነ

ን» አለኝ እየሳቀ፡፡ «እንዴት?»«ጣልያን ባሕር አቋርጦ ሀገራችንን ወረረ፡፡ እኛ

ደግሞ የአባቶቻችንን ደም ለመበቀል ባሕር አቋርጠን ሀገሩን ወረርነዋ፤ አንተ ቂርቆስኮ የጀግና ሠፈር ነው» አለና ሳቀ፡፡«እውነት ግን ለምንድን ነው የቂርቆስ ልጆች እ

ዚህ የበዛችሁት?» «ምን መሰለህ ይህንን በረሃ ለማቋረጥ ከሁለት እስከ ሦስት ወር ይፈጃል፡፡ የገንዘብ፣ የምግብ፣ የውኃ ችግር አለ፡፡ ካልተዛዘንክ በቀር ይህንን በረሃ ልታልፈው አትችልም፡፡ እኛ ደግሞ ከልጅነታችን ተዛዝነን መኖር ለም

ደናል፡፡ ስለዚህ እየተደጋገፈክ መጓዝ ነው፡፡ ያው እንግዲህ ባሕር ኃይልም አየር ኃይልም እየመጣ ይቀጥላል»«የቀድሞ ወታደሮችም ይመጣሉ ማለት ነው»

«አይ እነርሱ አይደሉም፡፡ በአውሮፕላን ጣልያን የገባው ስደተኛ አየር ኃይል ይባላል፡፡ በባሕር የገባው ደግሞ ባሕር ኃይል ይባላል፡፡ ታድያ አየር ኃይሉ ባሕር ኃይሉን ይንቀዋል፡፡»«ለምን?» «ያው መከፋፈል ለምዶብን ነዋ፤ አታ

ይም መንገድ ላይ እንኳን ጉስቁል ያለ አበሻ ካዩ ሰላም አይሉንም፡፡ ጣልያኖች እንደሆኑ አየር ኃይልም ሆንክ ባሕር ኃይል ሚኒስትር አያደርጉህም፤ ሁሉም ያው ሲኞራ ቤት ነው የሚሠራው፡፡«ሲኞራ ቤት ደግሞ ምንድን ነው?» «ሰው ቤት

ተቀጥሮ መሥራት ማለት ነው፡፡ እዚህ ብዙው አበሻ እንደዚያ ነው የሚሠራው፡፡ ያውም ለሴቶች እንጂ ለወንዶች ሥራ አይገኝም፡፡ ድድ ስታሰጣ መዋል ነው፡፡»«ግን ምን ላይ እየኖርክ ድድ ታሰጣለህ» አልኩ

ት፡፡ «እዚህ አበሻ ከድንኳን ሰባሪነት ወደ ሕንፃ ሰባሪነት ተሸጋግሯል» «እንዴት እንዴት ሆኖ» «ያንን ሁሉ በረሃ አቋርጠህ፤ ባሕር ሰንጥቀህ ጣልያን ስትገባ ምንም ነገር አታገኝም፡፡ ከምግብ በቀር ቤት እንኳን የሚሰጥህ የለም፡፡ ለተወሰነ ጊዜ መጠለያ ውስጥ ያስገቡህና በኋላ ሠርተህ ብላ ብለው ያሰናብቱሃል፡፡ ያን ጊዜ ችግር ውስጥ ትወድቃለህ፡፡ አበሻ ታድያ ይሰባሰብና በልዩ ልዩ ምክንያት የተዘጋ ሕንፃ ያስሳል፡፡ የተወሰነ ጊዜ ሁኔታውን ታይና ሃያ ሠላሳ ሆነህ በሩን ሰብረህ ትገባለህ፡፡ ከዚያ ክፍሎቹን መከፋፈል ነው፡፡»«ባለቤቶቹስ» «ባለቤቶቹ ኡኡ ይላሉ፡፡ ፖሊስ

ይመጣል፤ ግርግር ይፈጠራል፡፡ የሰው ልጅ ሜዳ ላይ ወድቆ እንዴት ሕንፃ ተዘግቶ ይኖራል ብለህ ትከራከራለህ፡፡ መቼም የሰው መብት በመጠኑም ቢሆን የሚከበርበት ሀገር ነውና የሰው መብት ተከራካሪድር ጅቶችም አብረውህ ይጮኻሉ፡፡ በመጨረሻ ታሸንፍና ትኖርበታለህ፡፡»«መብራት እመደንበሽ

ማስታወቂያ

በባህር ተሻግረው ጣሊያን የሚገቡ ስደተኞች በፖሊሶች ከተያዙ ላምፔዱሳ በሚገኘው እስር ቤት ይታሰራሉ

ወደ ገጽ 21 ዞሯል

ጣሊያን ላምፔዱሳ የሚገኘው የእስረኞች ማረፊያ ይህን ይመስላል

Page 10: Habeshawi kana 004

ሐምሌ 30-ነሐሴ 13 ቀን 2003 (August 6-19, 2011)ሐበሻዊ ቃና10

ጥበብ

የግጥም ጥግ

ግርማ ተስፋውu u u

ይወዘውዘኛል ያላጋኛል ምነው ከወዲያ ከወዲህማረፊያ እንደጠፋው እንደ በረሃ ርግብጨለማ እንደዋጠው ክንፉ እንደረገፈልክ እንደ ሌሊት ወፍ ያርደኛል ምነው?ሳልወድ እየሞትኩኝበናፍቆት ላልቅ ነው።ባልተፈጠርኹብሽምነው ባለወቅኹሽባይጠራ ስሜባልታወቅ ባንቺ - የሚያስብለኝ በዝቶአንቅሬ እንዳልተፋሽ-አውጥቼ እንዳልጥለሽየሚያረገኝ ማነው ከፍቅርሽ ቡትቶ?የማላውቀው ፍቅርሽ - ጥሱን ጥቡሳሱንአሸክሞኝ ኖሮ- ለምን አልተውኩሽም?ለምን አትበቂኝም- ለምን አትፈቺኝም?እትብቴን በልተሻልመንታ ወንድሜንም ነጥለሽ ወስደሻልየ‘ንግዴ ልጅ እና እትብቴን ገብሬ ነጻ ካልለቀቅሽኝ ባንቺው ፍቅር አዚም ሁሌም ካታለልሽኝየኔም ፍቅር ይግባሽ እባክሽን ፍቺኝ።

ፍቺኝ

ለጋው የጭረት ዛፍ ፤ በስለት ተፍቆጅማቱ ተፈትሎ ፤ እርስበርስ ተጣብቆባንገትሽ ላይ ታስሮ ፤ በእግርሺ ላይ ተጠልቆከእበት ካዛባው ጋር ፤ አብሮሽ ተጨማልቆ...መሄድሽን ለማቆም ፤ ተጣብቆሽ ቢውልምገመድ አሰረ እንጅ ፤ ታሰረ አይባልም።

በይርጋ ገላው

ገመድ ለላሚቱ

ማስረሻ ማሞ

በዘመን ተገፍቶ እምቧለሌ ብሎቀንበር ተቆራኝቶ ከ’ርፍ ተዋውሎከመሬት ጋር ታስሮ፤ በማቲ ተከቦበልጅ ተቀይዶ፤በትላንት ተሰልቦለዘመናት ሲያዘግም ሲኳትን የመጣውቢያርስ ቢኮተኩት ከጥግ የማይደርሰው ፤ የሀገሬ ገበሬ የበሮቹ ጌታ የአድባሩ አለኝታ የቤቱ መከታከመስኩ መዋሉ ፤ ከመስኩ ማደሩከብቱን መከተሉ ጥጃውን ማሰሩበተስኪያን መሳሙ ጥዋውን ማድረሱበሰርክ በሰዓታት መቆም መጎንበሱምንድን ነው ውጤቱ? በአይናችን ያየነው የዚህ ትሩፋቱ?

ምን ይኾን አንድምታው?

u u u

የማይጣላ ህሊና ያለው!እንዴት የታደለ ነው?ህሊናውን የገደለ ሰው!ማን ሊቀረው? ማን ሊያቅተው?የጉልበቱ መሣሪያ ነውጊዜ ጉልበቱን እስቲሰብረው፡፡

የታደለ...

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም

u u u

በ1950ዎቹ እና በ1960ዎቹ ተዝፈነው እስካሁንም ተወዳጅ የሆኑ ዘፈኖችን የቀድሞ ለዛውን ሳይለቅ መልሶ በመጫወት የሚታወቀው “የአዲስ አኩስቲክ ፕሮጀክት” ባንድ ስራዎቹን በአልበም አቀና

ብሮ ሊያወጣ ነው። ለባንዱ የመጀመሪያ የሆነው እና “ትውስታ” የሚል ስያሜ የተሰጠው ይህ አልበም ነሐሴ 3 ቀን 2003 ዓ.ም ገበያ ላይ ይውላል ተብሎ ይጠበቃል። አልበሙ የጥላሁን ገሰሰን “ኡኡታ አያስከፋም”፣ አሊቢራ እና መሐሙድ አህመድ የተጫወቱትን “ሃማሌሌ” እና የምኒልክ ወሰናቸውን “ትዝታ አያረጅም” እና አንድ የሶማሊኛ ዘፍን ጨምሮ አስር ጥኡመ ዜማዎች የተካተቱበት ነው፡፡አዲስ አኩስቲክ ባንድ ኤሌክትሪክ የማይጠቀሙ አኩስቲክ የ

ሙዚቃ መሳሪያዎችን በሚጫወቱ ሙዚቀኞች የተዋቀረ ነው፡፡ የባንዱ መሪ ታዋቂው ጊታር ተጫዋች ግሩም መዝሙር ነው፡፡ ግሩም የሸዋንዳኝ ኃይሉን ሙሉ አልበም ያቀነበረም ነው፡፡ በባንዱ ውስጥ አኩስቲክ ጊታር እና አኮርዲዮን ለባንዱ ይጫወታል፡፡ ታዋቂው ጊታሪስት ተጫዋች ሄኖክ ተመስገን በቤዝ፣ አንጋፋው ድምጻዊ ተጫዋች አየለ ማሞ መለያቸው በሆነው ማንዶሊን፣ በህይወት የሌለው የሀገር ፍቅሩ ድምጻዊ ፍሬ

አዲስ አኩስቲክ ባንድ አልበም ሊያወጣ ነው

ው ኃይሉ ልጅ ዳዊት በክላርኔት፣ ወጣቶቹ ናትናኤል ተሰማ እና ምሳሌ ለገሰ በድራም፣ ከበሮ እና ፐርከሽን ባንዱን ህይወት የሚዘሩበት ናቸው፡፡

ከዝነኛው አቀንቃኝ ማርክ አንቶኒ ጋር ለሰባት አመታት የነበራትን ትዳር በማፍረሷ እና በአሜሪካን አይዶል ዳኝነቷ ምክንያት የብዙሃን መገናኛን ቀል

ብ ስባ የከረመችው ድምጻዊት እና አክተረስ ጄኔፈር ሎፔዝ ሰሞኑን ደግሞ ከኢትዮጵያ ጋር ስሟ ተደጋግሞ ይነሳ ይዟል፡፡ ጄነፈርን ከኢትዮጵያ ጋር ያገናኛት የፊልም ስራ ነው፡፡ “ዘ ባክ አፕ ፕላን” የተሰኘውን ሮማንቲክ ኮሜዲ ፊልም ከሰራች በኋላ ከስክሪን ርቃ የነበረችው ጄነፈር አሁን “ሁዋት ቱ ኤክስፔክት ሀዌን ዩ አር ኤክስፒክቲንግ” የተሰኘ ፊልም እየሰራች ነው፡፡ የፊልሙ ርዕስ የተወሰደው በመላው ዓለም 16 ሚሊዮን ኮፒ ያህል በመቸብቸብ የምርጥ መጽሀፍት ዝርዝር ውስጥ ካለው እና እርጉዝ ሴቶች ምን ማድረግ እንዳለባቸው ምክር ከሚሰጠው መጽሐፍ ነው፡፡ የፊልሙ ታሪክም ከእርጉዝ ሴቶች ጋር ይይዛል፡፡ ፊልሙ ወላጅ ለመሆን በመዘጋጀት ላይ ስላሉ አራ

ት ጥንዶች የሚተርክ ነው፡፡ ጄነፈር ከባሏ ልጅ ማግኘት ባለመቻሏ ጉዲፈቻ ፍለጋ ዓይኗን ወደ ኢትዮጵያ የምትጥል እንስት ሆና በፊልሙ ላይ ትጫወታለች፡፡ የፊልሙ አዘጋጆች ጄነፈር ከኢትዮጵያ በጉዲፈቻ የምትወስድበትን ትዕይንት ለመቅረጽ ወደ ኢ

ጄነፌር ሎፔዝ ከኢትዮጵያ ጋር የተያያዘ ፊልም እየሰራች ነው

ትዮጵያ ለመሄድ አልመረጡም፡፡ ይልቅስ እዚያው አሜሪካ አትላንታ ውስጥ ኢትዮጵያን የሚመስል ቦታ ገንብተው ቀረጻውን አካሂደዋል፡፡ ለዚህ ትዕይንት ሲባልም የፊልሙ ሰሪዎች በርካታ ኢትዮጵያውያንን በአጃቢ ተዋናይነት ለመቅጠር ማስታወቂያ አውጥተው ነበር፡፡ በማስታወቂያው መሰረት በፊልሙ ላይ መሳተፍ ከቻሉ ሰዎች ውስጥ አትላንታ የሚገኘው የአድማስ ሬድዬ አዘጋጅ ቴዎድሮስ አንዱ ነበር፡፡ ቴዎድሮስ አዲስ አበባ በሸገር ኤፍ ኤም ለሚተላለፈው

“ታዲያስ አዲስ” የሬድዬ ፕሮግራም እንደተናገረው ቀረጻው ባለፈው አርብ ሐምሌ 29 ቀን የተካሄደ ሲሆን ከቀኑ ስምንት ሰዓት እስከ ለሊቱ ስምንት ሰዓት ቆይቷል፡፡ በፊልሙ ላይ በእውኑ ዓለም አትላንታ ላይ ፓስተር የሆኑ አባት የኦርቶዶክስ ቄስ ሚና ተሰጥቷቸው መስራታቸውንም ተናግሯል፡፡ ቀረጻው የተካሄደበት ቦታ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ የገጠር አውሮፕላን ለማስመሰል እንደተሞከረ አስረድቷል፡፡ በዚህ ፊልም ላይ ከጄነፌር ሎፔዝ በተጨማሪ ካሜሮን

ዳያዝ እና ክሪስ ሮክ ይተውኑበታል፡፡ ፊልሙ እ.ኤ.አ በ2012 የእናቶች ቀን በሚከበርበት ሳምንት በግንቦት ወር ለዕይታ ይበቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

“ዴርቶጋዳ” የተሰኘውን አነጋጋሪ መጽሐፍ ለንባብ ያበቃው ይስምዐከ ወርቁ በዚህ ሳምንት መጀመሪያ “ተልሚድ” የተሰኘ መጽሀፉን ለገበያ አውሏል፡፡ “ተልሚድ” ከመጀመሪያ መጽሀፉ “ዴርቶጋዳ”ም ሆነ ቀጥሎ ካሳተመው ተመሳሳይ ጭብጥ ይዞ ካሳተመው “ራማቶሓራ” የቀጠለ አለመሆኑን ይስምዐከ በመግቢያው ላይ ጽፏል፡፡ የሁለቱ ተከታይ የሆነ መጽሐፍ በመጻፍ ላይ እንደሆነም ገልጿል፡፡ “በእርግጥ ይብሰል በማለት እጅ ሳበዛበት ከእኔ ጋር ቆየ እንጂ ‘ተልሚድ’ ከሁለቱ ተከታታይ ልቦለዶቼ ቀዳሚ ነበር” ሲል አብራርቷል፡፡ ሁለቱ ተከታታይ መጽሐፍት በሺህዎች የሚቆጠሩ ኮፒዎች

እንደተሸጡ ቢነገርም የመጽሐፉ ጭብጥ ግን በሃያስያን ዘንድ በከፍተኛ ሁኔታ ተተችቷል፡፡ መጽሐፍቶቹ የያዙት “የልጅ ሀሳብ” ነውሲሉ ያጣጡለትም አሉ፡፡ ይህ ትችት የሸነቆጠው የሚመስለው ይስማዕከ ድፍረት የታከለበትን እና ትህትና የለሽ አስተያየቱን አንዲህ ሲል በመግቢያው ላይ አስፍሯል፡፡ “ (ተልሚድ) እንክት ብሎ በስሏል ማለቴ አይደለም፡፡ ሆኖም ይህችን በትህትና ብልም በዚህች ቀዳዳ ልግባ የሚልን አላስገባም፡፡ እንዲህ ባለች የትህትና ቀዳዳ የሚገቡ፣ ቢችሉ መልሰን እንፍጠርህ የሚሉ ደፋሮች አይታጡም፡፡ ያገኘኝ ሁሉ እንደ እርጥብ ጭቃ ጠፍጥፎ በራሱ አምሳል እንዲሰራኝ የምፈቅድ አይደለሁም” ብሏል፡፡ “ተልሚድ” ቀድሞ የደርግ ወታደር፣ በስተኋላ ላይ ደግሞ ደ

ራሲ የሆነን ሰው ዋና ገጸ ባህሪው ያደረገ መጽሐፍ ነው፡፡ መጽሐፉ ገበያ ላይ በዋለ ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ወደ 20 ሺህ ገደማ ኮፒዎች መሸጡን የአዲስ አበባ ምንጮች ለሐበሻዊ ቃና ተናግረዋል፡፡ መጽሐፉ የገበያ ዋጋው 40 ብር ነው፡፡

የ “ዴርቶጋዳ” ደራሲ ሶስተኛ ልቦለድ

መጽሐፉን ለንባብ አበቃ

ኤርትራዊው ሳሚ ብርሃኔ እና ዝነኛው ኡጋንዳዊ ዘፋኝ ካሚሊዮን ዳግም በነጠላ ዜማ ተጣመሩ፡፡ ሳሚ እና ካሚሊዮን ባለፈው ሳምንት በጋራ የለቀቁት ነጠላ ዜማ “ቢዩቲ” ይሰኛል፡፡ ሁለቱ ድምጻውያን ከዚህ ቀደም እንደሰሩት እና ተወዳጅ እንደሆነው “ክበብዋ” ሁሉ እንግሊዘኛ እና ትግርኛ በማፈራረቅ ነው የሚያቀርቡት፡፡ ሃይቅ ዳርቻ ቀረጻው የተከናወነውን ይህንን ሙዚቃ ዳይሬክት ያደረገው ዲዳክ የሚባል ባለሙያ ሲሆን የካሚዮሊን ድርጅት የሆነው “ሊዮን አይላንድ” ከዝግጅቱ ጀርባ አለ፡፡ ሳሚ በዚህ ሙዚቃ ቪዲዮው ኤርትራዊ እንስቶችን አሳትፏል፡፡ በሳምንት ሁለት ጊዜ የሚወጣው የኡጋንዳው “ዘ ኦብዘርቨር” ጋዜጣ የሙዚቃ ቪዲዮውን “እንደ ርዕሱ ሁሉ ቆንጆ የሆነ ሲል አሞካሽቶታል፡፡

ሳሚ እና ካሚሊዮን እንደገና

ለበርካታ ዓመታት ኑሮውን በለንደን አድርጎ ቆይቶ የነበረው አሁን በሕይወት የሌለው የአንጋፋው ድምጻዊ ተፈራ ካሳ ልጅ ግርማ አዲስ አልበሙን ባለፈው ሳምንት ለአድማጮች አቀረበ፡፡ “እኔ አይደለሁማ” የሚል ስያሜ የተሰጠው ይኸው አልበም በቮይስ ሙዚቃ ቤት አማካኝነት ነው ለገበያ የዋለው፡፡ ግርማ በዚህ አልበሙ “ስራ ፈቶ ሲያሽ” የሚለውን የአባቱን ዜማ መልሶ ተጫውቶታል፡፡ ይህ ዘፈን የቀድሞ ለዛውን በጠበቀ መልኩ እንዲቀርብ በማለትም አባቱን በወቅቱ አጅቦት የነበረውን መሐሙድ አህመድን አሁንም በድጋሚ እንዲያጅበው አድርጓል፡፡ በሞት የተለዩትን እንደእነ ጥላሁን ገሰሰ ያሉትን አጃቢዎች ደግሞ በጎሳዬ ተስፋዬ እና ማዲንጎ አፈወርቅ ተክቷቸዋል፡፡ የዘፈኑ አቀናባሪ አበጋዙ ክብረወርቅ ደግሞ ኖታውን መልሶ በመጻፍ እንዲሰራ አድርጓል፡፡ በዚህ ዘፈን ላይ ሳክስፎን ተጫዋቹ ያሬድ ተፈራ እና ጊታሪስቱ ፋሲል ውሂብ ተሳትፈዋል፡፡ ለ“እኔ አይደለሁማ” አልበም በዕውቀቱ ስዩምን ጨምሮ አሉ የተባሉ ገጣሚያን ስራዎቻቸውን እንዳዋጡ የ“ታዲያስ አዲስ” የሬድዬ ፕሮገራም አዘጋጅ ተወልደ በየነ ተናግሯል፡፡

ግርማ ተፈራ ካሳ በአዲስ አልበም መጣ

Page 11: Habeshawi kana 004

ሐምሌ 30-ነሐሴ 13 ቀን 2003 (August 6-19, 2011) ሐበሻዊ ቃና 11

ጥበብጥበብ

አዳም ረታ ይናገራልስድስት መጽሐፍትን ጽፏል፡፡ “ማህሌት”፣“ግራጫ ቃጭሎች” ፣ “አለንጋና ምስር” ፣ “እቴ ሜቴ ሎሚ ሽታ” እና “ይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድ” ይሰኛሉ፡፡ የተለያዩ ደራሲዎችን ስራዎች

በያዘው “አባ ደፋር እና ሌሎች አጫጭር ልቦለዶች” ውስጥም የእርሱ ስራዎቹ ተካትተዋል፡፡ አዳም ረታ ይባላል፡፡ የ52 ዓመቱ አዳም ከአገሩ ከወጣ በኋላ ለረጅም አመታት በሆላንድ እና

ካናዳ ኖሯል፡፡ አዲስ አበባ እያለ እና ወደ ውጭ አገር ከሄደ በኋላ የጻፋቸው ታሪኮች በየዓመቱ ልዩነት ታትመው ለንባብ እየበቁ ይገኛሉ፡፡ የራሱ የሆነ የአጻጻፍ እና የአተራረክ ስልት የሚጠቀመው

አዳም በቅርቡ ወደ አገር ቤት ተመልሷል፡፡ ወደ አዲሳባ መምጣቱን አስመልክቶም የስነ ጽሁፍ ባለሙያዎች በስራዎቹ ላይ ጥናታዊ ጽሁፍ ያቀረቡበት ውይይት ተካሂዷል፡፡ በዚህ አጋጣሚ አዳምን

በጽሁፎቹ እና በፎቶ ብቻ የሚያውቁት አድናቂዎቹ ከእርሱ ጋር የመገናኘት ዕድል አግኝተዋል፡፡ የሰሞኑ መወያያ ሆኖ የከረመው አዳም ከዛሬ ሁለት ዓመት በፊት ከ“አዲስ ነገር” ጋዜጣ በቀረቡለት

ጥያቄዎች ላይ ተንተርሶ ረዘም ያለ ጽሁፍ ከሚኖርበት ካናዳ ልኮ ነበር፡፡ አዳም በብዕሩ ስለራሱ የተናገረውን ለዚህ ጋዜጣ በሚስማማ መልኩ አሳጥረን አቅርበነዋል፡፡

ጅማሬአምስተኛ ከፍል እያለሁ በትምህርት ቀን መጨ

ረሻ አርብ አርብ ከሰአት በኋላ ተማሪዎች ሪፖርት እናቀርባለን፡፡ ደንቡ ከጋዜጣ ያነበብነውን ወይም ከሬድዮ የሰማነውን በራሳችን አማርኛ አሳጥረን ፅፈን ክፍል ውስጥ ቆመን ማንበብ ነው፡፡ ሁልጊዜ የምናቀርብባቸው ዝርዝር አርዕስቶች ታዲያ የጃንሆይ ጉብኝት፣ የአዲስአባ አንደኛ ዲቪዚዮን እግር ኳስ ጨዋታ ውጤትና የመካከለኛው ምስራቅ ግጭት ነበሩ፡፡ በእነዚህ አርዕስት ሚሊዮን ሪፖርቶች ነው የፃፍኩት ማለት እችላለሁ፡፡ ባይሆንም እንደዛ ተሰማኝ፡፡ በዚህ ሰበብ ሰለቸኝ፡፡ እግር ኳስ እወዳለሁ ግን ስፅፈው ሰለቸኝ፡፡ ሰለቸኝ ስልህ ቀላል አይደለም፡፡ አሁን ድረስ የእዚያ ደለል አልፎ አልፎ ይሰማኛል፡፡ የተለመደው አርብ መጣና ሬድዮ አዳምጬ ወይም ጋዜጣ አንብቤ ሪፖርት ማቅረብ ነበረብኝ፡፡ ያው ስለተሰላቸሁ አልፅፍም ብዬ ለራሴ ወሰንኩ፡፡ ከቤቴ ወደ ትምህርት ቤት ስሄድ (በዚህ ውሳኔዬ መንስኤ ስለማደርስብኝ የቅጣት ስታይል እያሰብኩ) አንድ አስቂኝ ነገር መንገድ ላይ ታዘብኩ፡፡ የሆኑ ዶሮ ነጋዴዎች አንድ ድልድይ አጠገብ ቆመው እያለ አውሎ ነፋስ (ጠሮ) ተነስቶ ሲያተራምሳቸውና ዶሮዎች ከቅርጫቶቻቸው አየበረሩ ሲወጡባቸው፣ እነሱን ለመያዝ ሲወድቁና ሲነሱ አየሁ፡፡ ያን የመሳሰለ፣ ከዛ ጋር የተያያዘ ጉዳይ፡፡ መሃል መንገድ ትምህርት ቤት ሳልደርስ ‘ለምን ይሄን መንገድ ላይ ያየሁትን ሪፖርት አላደርግም?’ አልኩ፡፡ ምክንያቱ፣ ገጠመኙ ጨዋታ አለው፡፡ አስፈግጎኛል ወዘተ...፡፡ መንገድ ዳር ቁጭ ብዬ የማስታውሰውን ሁሉ ሉኬ ላይ ሞልቼ ክፍሌ ገባሁ፡፡ ተራዬ ደርሶ አንብብ ስባል በትምክህት ከጋዜጣ ላይ ያገኘሁት ነው አልኩና ቆሜ የፃፍኩትን አንቸለቸልኩ፡፡ ክፍሉ ትንሽ ተዝናና፡፡ አስተማሪዬ ግን ጨርሼ ስቀመጥ ‘ጢሜን’ አበረሩኝ፡፡«ይሄን ከጋዜጣ ላይ ያነበብከው?» አሉኝ፡፡«አዎ»«እንዲህ አይነት ወሬ ጋዜጣ ላይ አይወጣም፡፡

ራስህ ያደረግከው ነው» አሉኝ፡፡ያልተገነዘብኩት ነው፡፡ ቀሽምነቴ ነው፡፡ መዋሸ

ት አልችልም፡፡«አዎ» አልኩ፡፡ ከዛ ወደ ክፍሉ ዞር አሉና «አዳሙ ደራሲ ይሆናል» አሉ፡፡ ደራሲ እራሱ

በትክክል ምን እንደሆነ አላውቅም፡፡ አስተማሪዬ ለምን ከጋዜጣ እንዳልገለበጥኩ አልጠየቁኝም፡፡ በትክክል ምን ለማለት እንደፈለጉአልገባኝም ነበር ያኔ፡፡

ስልቹው አዳም እዚህ ላይ ቀላል ብትሆንም ሳከብራት የኖርኩት

ን ትዕዛዝ ጥሼ ስፅፍ ከውስጤ የተሰማኝ ነገር ቢኖር ነው፡፡ ያ የተሰማኝ ነገር ስልቹነት ሳይሆን አልቀረም፡፡ የእኔ አንዱ የበላይ ጠባቂ ማን መሰለህ? የመሰላቸት ስሜት፡፡ እንዳንድ ሃያሲያን ስልቹነት የፈጠራ ስራ እንድትሰራ ይተነኩሳል ይላሉ፡፡ Boredom provokes.ምናልባት ይሄ መሰላቸት የመጣው የምኖርበት

ሕብረተሰብ ሁለንተና በሕግ የተሳሰረ፣ በአመክንዮ የተታመ፣ መነሻውንና መድረሻውን ቀድሞ የደነገገ፣ ባለው አቅም በደንብ የተደራጀ ስለሆነ ይሆናል፡፡ በረባም ባልረባም ጉዳይ ከመስመር አውቀህም ይሁን ሳታውቀው ብትወጣ የሚሰጥህ ምላሽ አድማ ይመስላል፡፡ አንደኛው ‘ሰው ምን ይላል?’ ነው፡፡ ይሄ ምድርን ይቆጣጠራል፡፡ ሁለተኛው ‘እግዜር ይይልህ’ ነው፡፡ ከመሃል አንተ ነህ፡፡ በዚህ አጣብቂኝ መሃል ምን ታደርጋለህ? የተቃርኖዎች ሕግ ማማሩ ያው የሚያሽህ ሕብረተሰብ በፈጠረው ቃልና ሰዋሰው ቢያንስ አእምሮሀን ነፃ ታወጣለህ፡፡ ያው ሕብረተሰብ ካሳደጋቸው

ቃላት ወስደህ እነሱን ጠፍጥፈህ ኮሳሳ የሆነች የራስህን መጠለያ ታበጃለህ፡፡ ዙሪያህን ከሚነፍሰው የማይመች ዶፍ ተጋርደህ የትም ባይደርስም ነፃነትህን ታውጃለህ፡፡ ደራሲ ገና ብዕሩን ሲያነሳ ወደደም ጠላም ገባው

ም አልገባውም በዚያን ጊዜ ‘ጎታች’ ነው ብሎ ለተሰማው፣ መሆኑን እንኳን ባላወቀው ነገር/እሴት ላይ ተቀናቃኝ ነው (subversive)፡፡ መሰላቸት ወደ ተቀናቃኝነት፣ ተቀናቃኝነት ወ

ደ መድረስ ወሰደኝ? የምክንያት ግኑኝነት ይኑራቸው እንጃ፡፡ ይሄ በልጅነቴ የበቀለው ነገር ሳድግ አበበብኝ? እንጃ፡፡ በተጨማሪም ገና በልጅነቴ አንዳንድ ነገሮች መፃፍ ስለጀመርኩ ያኔ መፃፍ ጥሩ ነው ብሎ የነገረኝ ሰው ይኑር አይኑር ወይም ደስ ብሎኝ እንደዛ ለመፃፍ በራሴው ልነሳሳ አላውቀውም፡፡ እላይ ካነሳሁልህ አይነት መሰል ሳያባሩ ከኖሩ ገጠመኞች የተጠፈጠፈም ላይሆን ይችላል፡፡ ይሄን የሚፃረሩ ሌሎች ገጠመኞች ቢኖሩም ረስቸአቼው ይሆናል፡፡

የመጽሐፍት ዓለምሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ስገባ መፃፍ እፈ

ልጋለሁ ግን ምን ማድረግ እንደሚገባኝ ደቃቃ ዕውቀት የለኝም፡፡ ጥያቄው እዚህ ላይም ይመጣል፡፡ ለምን ለመፃፍ እርሳስ ይዤ ቁጭ አልኩ? ምን ነገረኝ? ምናልባት ሃሳቤን እንዳልገልፅ የሚያስረኝ አካባቢ ነበርኩ (ለምሳሌ ማሽሟጠጥ) እንጃ፡፡ ማንም ደራሲ በል ተቀመጥና እንዲህ አድርገህ ፃፍ አላለኝም፡፡ታዲያ ለመፃፍ ስቀመጥ በትክከል ምን ማድረግ

እንደሚገባኝ አላውቅም፡፡ ድርሰት መጀመሪያ ማዕከልና መጨረሻ አለው ይላሉ፡፡ መለስተኛ ሁለተኛ፣ ሁለተኛ ደረጃም ትማራለህ፡፡ ይሄ ራሱ አይገባኝም ነበር፡፡ አንድ ነገር መቼ ነው እንዴት ነው ማዕከል የሚሆነው? እላለሁ፡፡ እንዴት ነው የምትፅፈው? ለምንና መቼ ትጨርሰዋለህ? እንዴት ትጀምረዋለህ? የምትጀመረው በምን ነው? መፃፊያ ጉዳይ የት ታገኛለህ? ልፈታው የማልችል ቋጠሮ ነበር፡፡ እነዚህ ሁለንተናዊ ጥያቄዎች ቢሆኑም መልስ የሚሰጥህ የለም፡፡ መልስም የሚገኝለ

ት አይመስልም፡፡ ዕደሜዬ 13 እያለ (አልረሳውም) አንድ ቀን የታ

ደሰ ሊበን ‘ጅብ ነች’ የተባለው አጭር ታሪክ ክፍል ውስጥ በአስተማሪያችን ተነበበ፡፡ በታሪኩ አጨራረስ ልረሳው የማልችል መደነቅ ተሰማኝ፡፡ እንዲህ ነው የሚፃፈው አልኩ፡፡ በትንሹ የነቃኁት ያኔ ይመስለኛል፡፡ ቆይቶም ታደሰ ሊበን ይዞኝ አልሄደም፡፡ ምክንያቱም ልጅ ነህና ትረሳለህ፡፡ ዛሬ ምን-ምን ታሪኮች ከእሱ እንዳነበብኩ ትዝ የሚሉኝ ሁለት ብቻ ናቸው፡፡ ከዛ የቀረኝ አምልኮ የአንዱ መፅሐፍ አርዕስት ብቻ ነው (ሌላው መንገድ)፡፡ እንደዛ የሚያምር አርዕስት በአማርኛ ስነፅሑፍ እስከዛሬ አላጋጠመኝም፡፡ በሁለት ቃላት ቀውስና እርጋታ (chaos and order) ተጠቅልለው ተቀምጠዋል፡፡ ይሄን አርዕስት ሲሰሙ አይኖቼ ዕንባ ቢያቀሩ አይግረምህ፡፡ በዛን ጊዜ ያላነበብኳቸው የአማርኛ ልብወለድ

መፃሕፍት አልነበሩም ማለት እደፍራለሁ፡፡ ቢረቡም ባይረቡም፡፡ ቢደነቁም ባይደነቁም፡፡ አነባለሁ እንጂ የስነፅሑፍ አለም ይኑር አይኑር አላውቅም፡፡ በታሪኩ እደሰታለሁ ወይም እደበራለሁ እንጃ? ለምን? እንዴት? የመሳሰለ ትንተናም አላደርግም፡፡ ምክንያቱም አልችልም፡፡ ትንተናም አላነበብኩም፡፡ አልተማርኩም፡፡ “ራሴላስ”ን ትምህርት ቤት እንዳነበብን ትዝ ይለኛል፡፡ በዝርዝር ግን አላስታውስም፡፡ ባስታውስ ደረቅ ፍልስፍና መሆኑ ነው፡፡ ከዛ በኋላም አላነበብኩትም፡፡ ያንጊዜ አካባቢ በእንግሊዘኛ የግሪክና የሮማን

ሚቶሎጂ፣ የተለያዩ አገር ተረቶች (ጀርመን፣ እንግሊዝ፣ ጃፓን፣ ቻይና ወዘተ.....) አነባለሁ፡፡ የትምህርት ቤታችን ቤተመፃሕፍት ከሲታ ቢሆንም እነዚህ አይጠፉም፡፡ በካሪኩለም ከተደነገጉልን ከ“ራሴላስ”፣ ከ“አርአያ”፣ ከ“እንደወጣች ቀረች” ከከበደ ሚካኤል የ“ሮሚዮና ጁሊየት” ትርጉም የበለጠ እነዚህ ተረቶች ይመስጡኝ ነበር፡፡ በዚህ ዘመን ውስጥ የመጀመሪያ የእንግሊዘኛ ልብወለዴን አነበብኩ፡፡ ‘ዘ ዊዛርድ ኦፍ ኦዝ‘ የሚባል፡፡ ይሄም ረዥም ተረት በለው፡፡ ፋንታሲው ልቤን ሰውሮት ነበር፡፡ ተረትና ሚቶሎጂ ስለምወ

ድ (ያን ጊዜ ብዙ ልዩነታቸው አይገባኝም) እንደ እነሱ ለማድረግ አስራ አምስት አመት ሳይሞላኝ ብዙ ተረቶች ፅፌ ጠፍተውብኛል፡፡ ለዚህ ስራዬ በተለይ የሶስት ወር የክረምት እረፍት ሙሉ ነፃነት ይሰጠኝ ነበር፡፡ በትምሀርት ጊዜ ስፅፍ ከያዘኝ አባቴ አይፈቅድም፡፡ ብዙ ዕውቀት በንባብና በማዳመጥ ከሌሎች ት

ሰበስባለህ፡፡ በሬድዮ ድርሰትና ተረት ሲነበብ ትያትር ሲሰራ ትሰማለህ፡፡ የሉተራን ብስራተ ወንጌል ሬድዮ ጣቢያ ነበረ በዚህ የማልረሳው፡፡ በተጨማሪም በዛን ጊዜ ብዙ ባይባሉም የትርጉም መፃሕፍት ነበሩ፡ ‘እንደ ሰው በምድር እንደአሳ በባሕር’፣ ‘ሳይላኩ የቀሩ ደብዳቤዎች’ (አርዕስቱን ልክ ነኝ?) ‘ታራስ ቡልባ’ የመሳሰሉ፤ ሁለት ሶስቴ የምታነባቸው እንደ ‘ዛዲግ ወይም ዕድል’ (ቮልቴየር) ‘ሞንተክሪሰቶ ካውንት’ የመሳሰሉ፡፡ ባጠቃላይ ይሄን ይመስላል፡፡ ያልተቀናበረ ያጋጠመኝን መፅሐፍ ብዙ ጊዜ በ

መዋስ የማነብበት ወቅት ነው፡፡ ከፈጣን ፍስሃ በላይ አትሄድም፡፡ ይሄ ደሞ በተራራቀ ጊዜ ስለሚሆን ማንበብህንም ባትረሳውም ምን እንዳነበብክ ግን ልትረሳው ትችላለህ፡፡ ያገኘሁትን በማነብበት በራሴ ልብወለድ የማፍቀር ልፋት ውስጥ ሰርጎ ገብቶ ስርአት የሚያስዝልኝ መሰረተ ልማቱ አልነበረም፡፡ ቢኖርም እንዳለ አላውቅም፡፡ (ደስታ ተክለወልድ የሚባሉ ታላቅ ሊቅ እንዳሉ ያወቅሁት በ1970 ዎቹ መሃል ከአስራ አምስት አመታት በኋላ ነው) የሚያሳዝን ነገር አለው፡፡ በግል የማውቀው ደራሲም ይሁን በማንበብ እንዲህ አድርግ ብሎ የመከረኝ ሰው አልነበረም፡፡ እንደዛሬ ተሰባብሰቦ መነጋገሪያ ቦታና ጊዜ ነበር? ቢኖርም አላውቅም፡፡

የመንፈስ አባቶችየማነበው መፅሐፍ ካጣሁ ብዙ ጊዜ በክረምት

ዘነበወርቅ ከብስራተወንጌል ሬድዮ ጣቢያ ጀምሮ(ሰፈሬ እዛ ነበር) እስከ ብሄራዊ ወመዘክር ድረስ በእግር ሄጄ መፅሐፍ የማነብበት ጊዜ ነበር፡፡ ዝናቡ ይደብራል፣ የሰፈርህ ሜዳ ጭቃ ነው ኳስ አታለፋም፣ ተሰላችተሃል፡፡ አንብበህ ወደ ቤትህ

ስትመለስ፣ አእምሮህ ውስጥ የሚንሳፈፈው ልብወለድና ፋንታሲ ብቻ አይደለም፡፡ በካፊያ መበስበስህን ማማረር፣ ማታ ተኝተህ ‘እዛ ድረስ ምን አስለፋኝ?’ እያልክ ራስህንም መቀናቀንህ ነው፡፡ ልብስህ ቆሽሿል፣ ያለካልሲ ያደረግከው ሸራ ጫማ ረጥቦ፣ እግሮችህ ጨቅይተው እውስጡ ይንሸራተታሉ፡፡ እግርህን ታጥበህ መተኛት አለብህ፡፡ እና በርዶሃል፡፡ እንደበረደህ አትናገርም ምክንያቱም ‘ጥጋበኛ’ ትባላለህ፡፡ ከዚህ ነው የወጣኸው፡፡ በፀጥታ ወደ ራስህ ገብተህ ፔርሱስ አንድሮሜዳን እንዴት ደራጎኑን ገሎ ከሰንሰለቷ ነፃ እንዳወጣት ታስባለህ (በኋላ ከርሞ ከርሞ ይሄ የግሪክ አምላክ ቅዱስ ጊዩርጊስ እንደሆነ አንድሮሜዳም ብሩታዊት እንደሆነች ተረዳሁ)፡፡ ዝናብ፣ ለምሳ ስለጠፋህና ልብስህ ስለቆሸሸ በወላጆችህ መተረብ፣ እና የመንፈስ አባቴ ይሄ ነው፡፡ እግረመንገድህን ልብ ሳትል በማንበብ ሂደት የ

ምትማራቸው አስፈላጊ ነገሮች ይኖራሉ፡፡ ለምሳሌ አንዳንድ መፃሕፍትን ለማንበብ የቃላት ሃብት ግድ ይላል፡፡ ከፍቅር እስከመቃብር (ፍእመ) የተማርኩት አንዱ ትልቁ ነገር ቃላት ነው፡፡ ቃላቱ ይከብደኝ ነበር፡፡ እና ስራዬ እሱን ሳነብ ቃላት እየለቀምኩ ለብቻ እያወጣሁ አባቴን መጠየቅና ማጥናት ነበር (አባቴ የዲማ ሰው ነው)፡፡ ‘ዋሽንት’ ለማለት ‘አንዲር’ ይላል ፍእመ (ያኔ ‘ለምን አንዲር ይላሉ? ዋሽንት አይሉም?’ እል ነበር ‘ለምን ቀላል አያደርጉትም?’ ግን ይሄ ከቀላልና ከከባድነት ጋር አይያያዝም)፡፡ ከዚህ በኋላ ወጣ ብለህ ማዘጋጃና ብይ ትጫወታለህ፡፡ በአይንህ ቂጥ ሚንስከርት ያደረገች የጋሼ ማንትስ ልጅ ስታልፍ ታያለህ፡፡ እትዬ ወርቄ አስነጥሶአቸው ሲምሉ ትሰማለሀ፣ ፍስሃና አብዱራህማን ከቤት ጀርባ ተደብቀው ሲጋራ ይለምዳሉ፣ እነዚህ የትዕምርት ግጭቶች ናቸው ራሴን የሰጡኝ፡፡ አእምሮህ በልቦለድ ገፀባህርያት ተመስጦ እያለህ የምትቀሰቀሰው ግርማ የተባለ ልጅ ኳስ ሲደርብህ ነው፡፡ ይሄ ብውዝ ነው የመንፈስ አባትህ፡፡ ዩንቨርሲተ ስገባ በትርፍ ጊዜዬ አነባለሁ፡፡ የተገ

ኘውን እሞክራለሁ፡፡ ግን ይሄ ደራሲ ደስ ብሎኛል ብዬ የፃፋችውን ሁሉ ላነብ አልነሳም፡፡ ምክንያቱም የዩንቨርሲቲው ኬኔዲ ላይብረሪ መፃሕፍት መደርደሪያ አለም የተሰበሰበበት ነው፡፡ አዳልተህ አትችልም፡፡ በዚያ ዘመን ዛሬም ደጋግሜ ባነባቸው ቅር የማይሉኝ ጥሩ ደርሰቶች አንብቤአለሁ፡፡ የብርሃኑ ዘሪሁን “የቴዎድሮስ ዕንባ”፣ የበአሉ “ከአድማስ ባሻገር”ና “የሕሊና ደወል”(ሃዲስ) ልብወለዶች፣ “እሳት ወይ አበባ” ፣ የዳኛቸው “እምቧ በሉ ሰዎች”ና “አደፍርስ”፣ “ልጅነት”፣ የፀጋዬ “እሳት ወይ አበባ”ና “የከርሞ ሰው” የመሰሉ ድራማዎች የሰይፉ መታፈሪያ “አፈር ያነሳ ስጋ”፣ የደበበ ግጥሞች ወዘተ፡፡ የማነበው ግን የፈጠራ ስራዎችን ብቻ ነው፡፡

የአብዮት ጊዜአብዮት ሲመጣ(እንዲመጣ ሲደረግ) ልብወለ

ድ መፃሕፍት ቢረባም ባይረባም በፓምፍሌት ተተኩ፡፡ መጀመሪያ ሰሞን ደስ የሚል ነገር ነበረው፡፡ ምክንያቱም አዲስ ነው፡፡ (እዚህ ዘመን ላይ ቦታ ስለማይበቃን ልዝለለው እንጂ በሰፊው የምለው ኑዛዜያዊ ግለሂስ ነበር) ብዙ ሳልቆይ ሲጀመር መሰላቸቴን ያጠፋው የመሰለኝ ለአብዮት/ለትግል ማሟያ የተፈጠረው ስነፅሁፍ ወደ አሰልቺ ነገር ተለወጠ፡፡ ከላይ ያነሳሁልህን ‘ሰው ምን ይላል’ ና ‘እግዜር ምን ይላል’ ን ፖለቲከኞች ከሕዝብ ነጥቀው ‘ድርጅቴ ምን ይለኛል?’ በሚለው ተኩት፡፡ እግዚአብሄር ከስልጣን ወረደ፡፡ ባህላዊው የተባለው ሕብረተሰብ ኋላቀር ነው ተባለ፡፡ እግዚ

ወደ ገጽ 13 ዞሯል

አዳም ከረጅም ዓመታት የውጭ ሀገር ቆይታ በኋላ ወደ ሀገሩ ከተመለሰ በኋላ ያገኙት አድናቂዎቹ ፊርማውን በመጽሀፍቶቹ ላይ እንዲያሰፍርላቸው ተሻምተዋል

ፎቶ

- ኢዮ

ብ ም

ህረተ

አብ

Page 12: Habeshawi kana 004

ሐምሌ 30-ነሐሴ 13 ቀን 2003 (August 6-19, 2011)ሐበሻዊ ቃና12

ጥበብ

ዘጠና ቀናት በጆበርግኡጋንዳ ካምፓላ ቺቲንታሌ ተብሎ በሚጠራው ቦታ የ

ሚገኘው እና “ቨርጅን አይላንድ” የሚል ስያሜ የተሰጠው መዝናኛ ቦታ ዘወትር እሁድ ምሽት በሰዎች ይሞላል። “እንቅልፍ በማይተኛባቸው” አርብ እና ቅዳሜ ስራ የሚበዛበት “ቨርጅን አይላንድ” ላለፉት ሶስት ወራት በሰንበት ምድርም አያርፍም። ምክንያቱ ደግሞ ደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ ከሚገኝ አንድ ትልቅ ግቢ ሃያ አራት ሰዓት ሙሉ በቀጥታ የሚተላለፈው የ“ቢግ ብራዘር” የቴሌቭዥን ፕሮግራም ነው። በጎጆ ቤት መልክ የተሰራው ይህ መዝናኛ ቦታ በሁለ

ት ተቃራኒ ጥጎች ላይ ካንጠለጠለው ፍላት ስክሪን ቴሌቪዥኖች ባሻገር አንዱን ግድግዳ አቡጀዲ አልብሶ ፕሮግራሙን በፕሮጀክተር አማካኝነት በትልቁ ያስተላልፋል። “ቨርጅን አይላንድ” ሌሎች መዝናኛ ቦታዎች እንደሚያደርጉት የቴሌቪዥን ምስሉን እያሳየ ድምጹን አይነፍግም። ለዚህም ይመስላል የፕሮግራሙ “ቁርጥ ቀን” በሆነው እሁድ ዕለት በርካቶች ወደ እዚህ መዝናኛ ቦታ መሄድ የሚመርጡት። እሁድ በመላው አፍሪካ ያሉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የፕሮግራሙ ተከታታዮች በሚሰጡት ድምጽ ከተወዳዳሪዎች መካከል የሚባረረው የሚታወቅበት ነው። የመጨረሻው የ“ቁርጥ ቀን” በ“ቨርጅን አይላንድ” ልዩ ነ

በር። ከ14 ሀገራት የመጡ 26 ወጣቶችን በአንድ ግቢ በማሰባሰብ ከዛሬ ሶስት ወራት በፊት የተጀመረው ይህ ፕሮግራም በየሳምንቱ እሁድ ከተወዳዳሪዎች መካከል በድምጽ የተፈረደባቸውን እያባረረ ለመጨረሻው ዕለት የደረሰው ሐምሌ 24 ቀን 2003 ዓ.ም ነበር። ለመጨረሻው ዙር ካለፉ ሰባት ተወዳዳሪዎች መካከል የኡጋንዳ ተወካይ መገኘት ጉዳዩ የብዙዎችን ትኩረት እንዲስብ አድርጓል። ዕለታዊ የሀገሪቱ ጋዜጦች እና ኤሌክትሮኒክስ ብዙሃን መገናኛዎች ስለተወካያቸው “ሻሮን ኦ” ሳምንቱን ሙሉ ጽሁፎች ሲያስነበቡ፣ የሀገሬውም ሰው ድምጽ እንዲሰጣት ሲቀሰቅሱ ከርመዋል። ተከታታይ ዘገባዎቹ የፈጠሩት ትኩሳት በርካቶች ለጉዳ

ዩ ትኩረት እንዲሰጥ አደረገ። “ኦብሴሽን” የተሰኘው ዝነኛ የሙዚቃ ቡድን አባል የሆነችው ተወካያቸውን መጨረሻ ለማየትም በየመዝናኛ ቦታዎች ተሰበሰቡ። በ“ቨርጅን አይላንድ” የፕሮግራሙን ማጠናቀቂያ ለመመልከት የመጣው ተመልካች ከመብዛቱ የተነሳ መቀመጫ ሁሉ ጠፍቶ ነበር። በቦታው የነበረው ድባብ ካምፓላ በዓለም እግር ኳስ ዋንጫ የመጨረሻ ቀን ያሳለፈችበትን ጊዜ ያስታውሳል። ይህ ግን ለኡጋንዳውያን አንድን ዓለም አቀፍ አሊያም አህጉር አቀፍ ውድድር ከመመልከት የዘለለ ነበር። የትም አትደርስም ብለው የገመቷት የሀገራቸው ልጅ ከመጨረሻዎቹ ሰባት ተወዳዳሪዎች መካከል መገኘቷ ለሀገራቸው ክብር እና ኩራት እንዲጨነቁ አድርጓቸዋል።

ሃኒም እንደ ዳኒ?እንደ ኡጋንዳዊቷ ሻሮን ሁሉ ኢትዮጵያዊቷ ሃኒም ሳት

ጠበቅ ነበር ለመጨረሻ ዙር የደረሰችው። የሀገሯ ልጅ ዳኒ በውድድሩ አጋማሽ ላይ መሰናበቱ የእርሷም እጣ እንደእርሱ ይሆናል ተብሎ ተገምቶ ነበር። በኡጋንዳ ዕለታዊ ጋዜጣ “ዴይሊ ሞኒተር” ላይ ስለ የ“ቢግ ብራዘር” ተከታታይ ዘገባዎችን የሚያወጣው ሮበርት ካሉምባ ሃኒ ለመጨረሻው ውድድር ሳትደርስ እንደምትባረር ተንብዮ ነበር፡፡ እንደ ብዙዎቹ ኢትዮጵያውያን ሴቶች ሃኒም ቆንጆ ነች ብሎ የሚያምነው ካሉምባ ጠንካራ ጎኗ በውይይ

ቶች ላይ በደንብ መሳተፍ መቻሏ እንደሆነ ይናገራል፡፡ ከዚያ ባሻገር ግን እንደ ዳኒ ሁሉ በአፍሪካውያን ተመልካቾች የሚፈለገውን “እብደት” እና “ወሲብ ቀመስ” ትዕይንቶችን አለማሳየቷ እንደሚጎዳት ገምቶ ነበር፡፡ ኢትዮጵያውያን ምንም እንኳ እንግሊዘኛ ቢናገሩም ቋ

ንቋው የአፍ መፍቻቸው ባለመሆኑ እንደሌሎቹ እንደልብ ሀሳባቸውን ለመግለጽ የሚከብዳቸው ናቸው ብሎ ያምናል፡፡ ይህንንም ዳኒ ሆነ ሃኒ ላይ ማስተዋሉን ይናገራል፡፡ በእነዚህም ምክንያቶች ኢትዮጵያውያን ወደራሳቸው መሰብሰብ ወይም ቁጥብ መሆን እንደሚያዘወትሩ ያስረዳል፡፡ ይህ በተመልካች የማይወደድ በመሆኑ ዳኒ ለመባረር መብቃቱን ሃኒም ተከታይ እንደምትሆን እርግጠኛ ነበር፡፡ ስለ “ቢግ ብራዘር” የሚዘግቡ የተለያዩ ድረገጾችም ይህንኑ ሀሳብ ይጋራሉ፡፡ የካሉምባም ሆነ የድረ ገጾቹ ግምት ግን አልሰራም፡፡ በፕሮግራሙ አሰራር መሰረት ተወዳዳሪዎቹ እርስ በእ

ርስ በሚሰጣጡት ድምጽ ከውድድሩ እንዲባረሩ የሚፈልጉትን ይጠቁማሉ፡፡ ለመባረር በዕጩነት የሚቀርቡ ተወዳዳሪዎች ሳምነቱን ሙሉ በተመልካች ድምጽ እንዲሰጥባቸው ይደረጋል፡፡ ዘወትር እሁድም የሚባረረው ይለያል፡፡ ሃኒ በተደጋጋሚ ለመባረር እጩ ሆና ቀርባለች፡፡ ሆኖም በአብዛኛው ከኢትዮጵያውያን ተመልካቾች በምታገኘው ድምጽ ስትተርፍ ቆይታለች፡፡ ለመጨረሻው ሳምንት ውድድር ለማለፍ በተደረገው ትንቅንቅም የሆነው ይሄ ነው፡፡ ሃኒ ከተወዳዳሪዎቹ መካከል የሚባረረውን መጠቆም አልፈልግም ብላ እራሷን ለዕጩነት ብታቀርብም የሀገሯ ዜጎች ድምጽ ሰጥተው ለመጨረሻው ዙር አሳልፋዋታል፡፡

የመጨረሻው መጨረሻ ለመጨረሻ ዙር ያለፉት ሃኒን ጨምሮ ሰባት ተወዳዳሪ

ዎች ነበሩ፡፡ ካረን አን ቪና የተሰኙት ሁለት ናይጄሪያውያን እንስቶች፣ አልቃሻው እና አወዛጋቢው ደቡብ አፍሪካዊ ሉክሌይ፣ ጎረቤቱ ዜምባቢያዊ ዌንዳል፣ ያያትን ሁሉ የሚወድ የሚመስለው የማላዊ ዜጋ ሎምዌ እና ምንም አታውቅም ተብላ በሀገሯ ሰዎች ሳይቀር የምትሸነቆጠው ሻሮን ኦ ከሃኒ ጋር ለመጨረሻ ውድድር ያለፉ ናቸው፡፡ እነዚህ ተወዳዳሪዎች ለመጨረሻው ዙር በመድረሳቸው ብቻ 10 ሺህ ዶላር ይሰጣቸዋል፡፡ ሳምንቱን ሙሉ ከተመልካች በተሰበሰበ ድምጽ ከፍተኛውን ቁጥር ያገኙት ሁለት ተወዳዳሪዎች ደግሞ 200 ሺህ ዶላር ወደ ኪሳቸው በማስገባት የአሸናፊነት አክሊል ይደፋሉ፡፡ከውድድሩ ማጠቃለያ አስቀድሞ በተሰበሰበ የህዝብ ድ

ምጽ መሰረት ሃኒ ዝቅተኛውን ድምጽ በማግኘት መጨረሻ ሆና ነበር፡፡ የመጀመሪያዎቹን ሁለት ደረጃዎች የተቆጣጠሩት ደግሞ ከተወዳዳሪዎቹ መካከል ብዙ ድራማ መሳይ ትዕይንቶችን ሲያሳዩ የከረሙት ናይጄሪያዊቷ ካረን እና ደቡብ አፍሪካዊው ሉክሌይ ነበሩ፡፡ ውጤቱ ሐምሌ 24 ይፋ ሲደረግ ግን ያልተጠበቀ ነገር ተከሰተ፡፡ ሃኒ እንደተገመተው መጨረሻ መሆኗ ቀርቶ ናይጄሪያ

ዊቷን ቪናን በልጣ ስድስተኛ ሆነች፡፡ ያሸንፋል ተብሎ የተገመተው ሉክሌይ ደግሞ ደረጃውን የግል አውሮፕላን አብራሪ በሆነው ዜምባቤያዊው ዌንደል ተነጠቀ፡፡ ደቡብ አፍሪካውያን ያዩትን ማመን አልቻሉም፡፡ ውድድሩ በሀገራቸው የሚካሄድ ለስለነበር በ“ቢግ ብራዘር” ስቱዲዮ የተገኙት በርከት ብለው ነበር፡፡ በሉክሌይ መሸነፍ ቁጣቸውን የገለጹት ታዲያ መድረኩ ላይ በመውጣት

ጭምር ነበር፡፡ ግርግሩ የበረደው ፖሊስ በስፍራው ደርሶ ካስታገሳቸው በኋላ ነበር፡፡

አወዛጋቢው ውጤት ውጤቱን ያጣጣሉት ግን ደቡብ አፍሪካውያን ብቻ

አልነበሩም፡፡ ሌሎች አፍሪካውያንም የሉክሌይ መሸነፍ አልተዋጠላቸውም፡፡ ከእነዚህ መካከል አንዱ የሆነው ታዋቂው የኡጋንዳ ስታንድ አፕ ኮሜድያን ዳንኤል ኦማራ ነበር፡፡ በናይጄያዊቷ ካረን ማሸነፍ የሚስማማው ኦማራ ሉክሌይ ሶስተኛ መውጣት አልነበረበትም ባይ ነው፡፡ “ በካረን መሸነፍ ላይ ችግር የለበኝም፡፡ እርሷ ለውድድሩ የሚሆን ሰብዕና እና አመለካከት አላት፡፡ ነገር ግን ከእርሷ ጋር ማሸነፍ የነበረበት ሉክሌይ ነው” ለሐበሻዊ ቃና ተናግሯል፡፡ “አስቀድሞ የሚገመት ነገርን አልወድም፡፡ ነገር ግን አንዳንዴ ነገሮች ግልጽ የሚሆኑበት ጊዜ አለ” ሲል የደቡብ አፍሪካዊው ለአሸናፊነት ያደርጋቸው የነበሩ ትዕይንቶች በግልጽ የሚታዩ እንደነበር ያብራራል፡፡ ሃኒ ልክ እንደ ስሟ “ጣፋጭ” ነበረች የሚለ

ው ኦማራ በቆይታዋ መደሰቱን ይገልጻል፡፡ ኢትዮጵያዊቷ ስድተኛ መውጣቷን ሲመለከት የሀገሩ ልጅ ሻሮንም ብዙ እንደማትራመድ መገመቱን ይናገራል፡፡ “እንደ ሃኒ አይነት ሴት እንዲህ አይነት ደረጃ ከሰጡ ሻሮንም ብዙ እንደማትቆይ ገምቼ ነበር” ይላል፡፡ ግምቱ ትክክል ነበር፡፡ ኡጋንዳዊቷ ሻሮን ከሃኒ ከፍ ብላ በአምሰተኛነት ውድድሩን ጨርሳለች፡፡ “ሃኒ ጥሩ ሰብዕና ያላት፡፡ ነገር ግን በ

ቢግ ብራዘር አፍሪካውያን ድምጽ የሚሰጡት ጥሩ ላልሆኑ ሰዎች ነው፡፡ የናይጄሪያ ወይም የሌላ አፍሪካ ሀገር ፊልሞችን ብትመለከት ብዙ ጩኸት፣ ለቅሶ፣ ውዝግቦች እና ጥሎች የተሞላ ሆኖ ታገኘዋለህ፡፡ ለዚህ ይመስለኛል ካረን ልታሸነፍ የቻለችው” ሲል የናይጄሪያዊቷን አሸናፊ ሞገደኛ ባህሪ ዕርጋታ ከነበራት ሃኒ ጋር ያነጻጽራል፡፡ ከውድድሩ ማጠናቀቂያ በኋላ ሃኒን በ

ደቡብ አፍሪካ ያገኘቻት ኡጋንዳዊት ጋዜጠኛ ኒጄል ናስርም በኢትዮጵያዊቷ መደመሟን ለሐበሻዊ ቃና ገልጻለች፡፡ የውድድሩን ማጠናቀቂያ ለመዘገብ ደቡብ አፍሪካ ተገኝታ የነበረችው የ ኡጋንዳው ዕለታዊ ጋዜጣ “ኒው ቪዥን” ዘጋቢ ናይጅል በቲቪ ታያት በነበረችው እና በአካል ባገኘቻት ሃኒ መካከል ልዩነት ማየቷን ትናገራለች፡፡ “በአካል ስታገኛት እንድትግባባት የሚገፋፋህ የሚስብ ነገር አላት፡፡ በቲቪ ከምትጣው ይልቅ በአካል ይበልጡኑ ተግባቢ ናት” ትላለች፡፡ ሃኒ የምትናገራቸው ቁም ነገሮች ከህግ ተማሪነቷ ጋር ተዳምሮ ከሌሎች ለየት እንደሚያደርጋት ናይጅል ታስረዳለች፡፡ “ ሌሎች ተወዳዳሪዎች ስለሀገራቸው ከሚያውቁት በላይ ሃኒ ስለ ሀገሯ ጠንቃቃ ታውቃለች” ስትል የኢትዮጵያዊቷን ጉብዝና ትመሰክራለች፡፡

Page 13: Habeshawi kana 004

ሐምሌ 30-ነሐሴ 13 ቀን 2003 (August 6-19, 2011) ሐበሻዊ ቃና 13

ማስታወቂያ

አብሄር ቢሞትም የነበረው ቢናቅም ቦታውን የነዚህን ሁለት ስራ መስራት እንችላለን የሚሉ ድርጅቶች ወሰዱት፡፡በልጅነቴ ያስደስተኝ የነበረው ግን ልብ ያላልኩ

ት ያለማንም ቁጥጥር ማሰብ መፈለጌ ከፈተናው አላመለጠም፡፡ እንደውም ፈተናው በፒር ፕሬዠር (peer presure)ታጠቀ፡፡ በተለያየ አቅጣጫ የአብዮቱ ግራኞች (ተቃዋሚ የሚባለውም ሁሉም) ደራስያንና ድርሰትን አጥፍተው ነው ለተሰሚነት የሰሩት፡፡ ማለት ከ “ኢማጂኔቲቭ ሊትሬቸር” ወደ ፕሮፓጋንዳ ተሄደ፡፡ ቀደምት ደራሲያን በተለያየ ስየማ እየተቀነበቡ (ፍሬምድ አየሆኑ) ዝም እንዲሉ ሆነ፡፡ የዚያን ጊዜ ድርሰቶች/ግጥሞች በአብዛኛው ፕሮፓጋንዳ ነበሩ፡፡ ፕሮፓጋንዳ ታዲያ ብዙ ጊዜ ስለአለቀ እውነት ደጋግሞ የሚያወራ ነው፡፡ ፖርኖግራፊክ ነው፡፡ በተቃራኒው የፈጠራ ደራሲና የፈጠራ ድርሰት ቢዋጣም ባይዋጣም በምናባቸው አማራጭ ማሕበራዊ አሴት ያሳያሉ፡፡ የፀጋዬ ገብረመድህን ግጥሞች ከፀጋዬ ደብተራ

ው ግጥሞች የበለጠ ደስ ይሉኛል ካልክ ባንዳ ነህ፡፡ በተገላቢጦሽ ካልክ አናርኪስት ነህ፡፡ የፈለከውን የወደድከውን ለመውደድ በየትም አቅጣጫ መናገር የማትችልበት ጊዜ ነበር፡፡ ይሄን የተረዳሁት ረቂቅ ፈላስፋ ስለነበርኩና ሁሉ ነገር ስለገባኝ አልነበረም፡፡ ተደጋግሞ ስሰማውና በቀጥታና በተዘዋዋሪ ስከለከል ሰለቸኝ፡፡ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ መከልከል ይሰለቻል፡፡ ልክ ተደጋግሞ እንደተጠጣ አጃ ወይም ጠዋትና ማታ እንደተበላ ካሮት ወይም የፈለግከውን፡፡ ምናልባት የገጠመኝ የተለየ ነገር ይሆናል፡፡ የሩስያ ልብወለድ ካነበብክ፣ የደባሪ ሩስኪ(ሶሻል ኢምፔሪያሊዝም) ታነባለህ፣ የአሜሪካን ደራሲ ካነበብክ በኢምፔሪያሊዝም ልትለከፍ ነው፡፡ ወይም ጆሊ ጃክ ነህ፡፡ ዋናው ማንበብህ አሳስቧቸው ሳይሆን የዛን ዘመን ትውልድ ለማጥፋት ሆነ ብለው ታጥቀው የተነሱ ሰዎች ያሉ ይመስላል፡፡ ማን ገባው? ምናልባት

የገባቸው? እንደ አቤ ጉበኛ እንደ ሃዲስ አለማየሁ ያሉ ደራስያን ነበሩ፡፡ ‘አድሃሪ’ በተባለ ቃል ተቀንብበው እንዲሰወሩ ሆነ፡፡ የገባው ጥቂት ነው፡፡ አዲስ የነበሩት ‘የትግል’ ቃላቶች አውዳቸው ቀ

ስበቀስ መለወጥ ብቻ ሳይሆን በራሳቸውም ክሊሼ ሆኑ፡፡ ቦታው በሸርና በሴራ ምናብ ተወሰደ፡፡ ግጥም በጣም አፈቅር ነበር፡፡ ቀላል ፍቅር አልነበረም፡፡ ግጥም ካየሁ የፖለቲካ ካምፕ አልለይም ነበር፡፡ ያኔ እንደዚህ አይነት ነገር ማድረግ ፍርድቤት ሳትሄድ ያስቀጣሃል፡፡ ትክክል ሆነም አልሆነም በራስ መረጃ ያለመነቃነቅ የባርነት መሰረት መሆኑን በጭላንጭልም ቢሆን የምትረዳው ያኔ ነው፡፡

እንቅፋቱ መአትበነዚህ ሁሉ ሳልፍ ተከትሎኝ የመጣ ደራሲ አል

ነበረም፡፡ ምናልባት በዛን ጊዜ የነበርኩበትን ሁኔታ የሚያብራራ ልብወለድ የፃፈ ቢኖር ኖሮ ልከተለው ምክንያት ሊያሳድገኝም መንደርደሪያ ይኖረው ነበር፡፡ ግን የትኛውም ልብወለድ በስሜት ህዋሳቶቼና በሕልሞቼ ከለቀምኳቸው እኩል አልነበሩም፡፡ ሁልጊዜ በቃል ልናገረው የማልችል ነገር አለ፡፡ ደራሲዎቹ ሁሉ ቢዘሉም ባይዘሉም የሆነ ነገር የሚዘሉ ይመስለኛል፡፡ በሆነ መልክ የእኔ አይደሉም፡፡ ምናልባትም የልጅነት ልምዴ ጥቅጥቅ (intense) ወይም ‘ልዩ’ ስለነበረ ይሆናል፡፡ ስራ ስገባ እንደ ጠበቅሁት አልነበረም፡፡ በሙያ

ዬ አንድ ነገር ለመስራት እለፋለሁ፡፡ ግን እንቅፋቱ መአት ነው፡፡ አፍጥጬ እያማሁ መቀመጥ አልወድም፡፡ በስፋት ማንበብ የጀመርኩት በዚህ ጊዜ ነው፡፡ ታዲያ አንደንዴ በማንበብ ላይ እያለሁ የልጅነቴን የተረት ድርሰቶቼን እያሰብኩ ለምን እንደዛ ጊዜ አልዕፍም እላለሁ፡፡ ግን ጊዜዬን የኑሮ እንቅፋትና ቸልተኛ የሚያደርግ መዝናናት ይሻማኛል፡፡ ማምለጥ ነበረብኝ፡፡ ሁልጊዜ ‘ምናለበት ብፅፍ?’ እያልክ መኖር አትችልም፡፡መፃፍ ከጀመርኩ በኋላ ስራ ላይ ባጋጠመኝ ቀ

ናሽ ልምድ ድርሰቶቼ ይታተማሉ ብዬ አስቤ አላ

ውቅም፡፡ ምክንያቱም ያለሁበት የኑሮ መስመር ውስጥ የእንቅፋት ኪነት የሚሰሩ ይሄንንም እንደልዩ ሃብት(ውርስ) የሚቀባበሉ ስለነበሩ ነው፡፡ ይሄ የደርግ ወይም የኢሰፓ ስርአት ነው ብዬ አላሳብብም፡፡ ማንም የተዘፈቀበትና ማንም ከማንም የሚጋሩት መጣኝ ባህል ነው፡፡ የሚሰድበውን ካልሰደብክለት፣ የሚያማውን ካላማህለት ታላቅ እውነት እንደተበላሸበት ሁሉ ቅር የሚለው ብዙ ነው፡፡ ምቀኝነትና እንቅፋትነት በፖለቲካ አጀንዳ ስር ተጋርደው ሕብረተሰቡ ውስጥ የገቡበት ዘመን ነው፡፡ አንዳንዱ ምቀኝነቱን ትግል ነው ቢል፣ ይሄንንም አሸሼ እያለ የሚያጅበው መአት ዘማሪ ዕንጥል አይጠፋም፡፡ በጂኦግራፊ ሙያዬ ያኔውኑ ብቀጥል ኖሮ ምናልባት ብፅፍም ወደ ደራሲነት አላጋድልም ነበር፡፡ ብቻ ምን ይታወቃል፡፡ ስለዚህ ለመተንፈስ ወደ ሌላ ተፈጥሮዬ ወደሚያዳላበት ወይም ወደ ልጅነቴ ፣ ወደ አደግሁበት ወደነካካሁት ማንም ወደማይነዘንዘኝ ወረቀትና ብዕር ዞር አልኩ፡፡

ጠረጴዛ ላይ የተኛ ነጭ ልሙጥ ወረቀትና እላዩ ላይ ተቀርፆ የተጋደመ እርሳስ እጅግ ማራኪ ምስል አላቸው ለእኔ፡፡ ከልጅነቴ ጀምሬ ስራ እስክይዝ ድረስ እየሰራሁ

ም እያለሁ የተገነዘብኩት ነገር ቢኖር የተለወጠ ቢመስልም የብዙ ነገሮች ውስጠት እንዳልተለወጠ ነበር፡፡ መአት ሰው በተከታታይ ሕይወቱ ያልፍና ግን እንቅፋትነት እነበረችበት ኩርሲ ላይ ጥርሷን እየፋቀች ተቀምጣለች፡፡አንደ ምሳሌ አድርጌ አንድ በደራሲዎች የተዘለ

ለ ሴማ ባነሳ እወዳለሁ፡፡ በሃይለስላሴ አስተዳደር የወጣቶች አንዱ ባህርይ እርስ በርስ የመተማመን ነበር፡፡ የሃይለስላሴ/ ፊውዳል ስርአት ለዛን ጊዜ ታዳጊ ትውልድ የሰጡት ትልቅ ስጦታ የመተማመን ካፒታል ነበር፡፡ ይሄ ስጦታ ከስድሳ ስድስት በኋላ በመጡ ፖለቲካና ፖለቲከኞች በተለያዩ የድርጅቶች ምሕፃር ስር እየተሸነሸነ ጠፋ፡፡ ይሄን የጠፋ ካፒታል ወደ ነበረበት ለመመለስ በተለያየ መልክ የተቀናበሩ የኑዛዜ ልብወለዶች ትል

ቅ ማዕከል ሆነው ማገልገል ይችሉ ነበር፡፡ ግን አልሆነም፡፡ እንዲህ የሆነበት ምክንያት እንደሚመስለኝ የፈጠራ ችሎታ ያላቸው ሰዎች ስላሌሉ ሳይሆን ሆን ተብሎ እንዲጠፉ/እንዲገለሉ ስለተደረገ ነው፡፡ ራሱን ከታሪክ አውጥቶና እንዳልነበረበት ሁሉ ተነጥሎ ስህተተኛነትና ሐጢያተኛነትን ወደሌላ የሚያሸጋገር የናስ (escapegoat) ባህል ሌላ ሊያደርግ አይችልም፡፡ ይሄ ፓቶሎጂ ዛሬም ድረስ አለ፡፡ ስለ እኔ ጥሩ ካልጣፍክ በነገር እጥፍሃለሁ የሚል ድርጅት እንደ አፈር ነው፡፡ ከተናዛናዥ ሃያሲ ከመሰሉ ግለሰቦች ጀርባ በአጎዛ ተጋርዶ ያሌለ የሚመስል ሁልጊዜ ምላሱን እንደ እርሳስ እየቀረፀ የተቀመጠ ድርጅት አለ፡፡ ልበልህ በዛን ሰሞን የዚህ አይነት ድርሰቶች ቢያ

ጋጥመኝ ያ ደራሲ ደፋር ጭብጥ አንስቷልና ላመልከው ወይም እሱን ለመምሰል እጥር ነበር፡፡ በዚያ ዘመን እስከዛሬ ባነባቸው ቅር የማይሉኝ ጥሩ ደርሰቶች አንብቤአለሁ፡፡ ግን ጥቂት ናቸውና ያልቃሉ፡፡ ሃያሲ አይደለህም፡፡ ስታነባቸውም አትኖርም፡፡ ብዙዎቹ የሚያጋጥሙኝ የማይመስጡ ናቸው፡፡ የምልህ ዛሬ ሳነብ ልጅ ሆኜ ያነበብኩት ከመሰለኝ አርፌ ጠላ አልጠጣም? እድሜህ አስር ሳይሞላ የሰማኸውን የሳቅህበትን የአለቃ ገብረሃናን ቀልድ እያዳነቀ የሚንከተከት በእድሜ የአንተ እኩያ የሆነ የሰላሳ አመት ሰው ሲያጋጥምህ ያኔ ሆስፒታል ውሰዱኝ ትላለህ፡፡ከስራ ውጭ ባለኝ ጊዜ የእንግሊዘኛ ትሪለር

(thriller) ማንበብ ጀመርኩ፡፡ ቀስ በቀስ ሳይንስ ፊክሽን፡፡ ብዙ ባይሆንም ‘ስነፅሁፍ’ ማንበብ ጀመርኩ፡፡ በተፅዕኖ ደረጃ (ማለት ቢያንስ በጉዳይ) ሊኖርብኝ ይገባ የነበረው ሳይንስ ፊክሽን ነበር፡፡ ግን አይደለም፡፡ ምናልባት የወደድኩት እንዳሻ ከ ‘ማነብ ነፃነት’ ጋር ስላገናኘኝ ይሆናል፡፡ ይሄ ደሞ ከልጅነቴ ጀምሮ ተረቶች ስለምወድ የእነሱም ተፅዕኖ ይሆናል፡፡ ዛሬ እንኳን ሲኒማ በተለይ በሲ.ጂ.አይ ከተሰራ (ለእኔ ገነት ነገር ነው) ተሻምቼ የማየው ሳይንስ ፊክሽን ነው፡፡ ግን ይሄ ሁሉ ከማየው፣ መሬት ላይ እግሬ ስር ካለ ዕውነታ

አዳም ረታ ይናገራል...

ወደ ገጽ 21 ዞሯል

ከገጽ 13 የዞረ

ፎቶ

- ሪፖ

ርተር

ጋዜጣ

አዳም ከሸገር ኤፍ ኤም ጋር በቅርቡ ባደረገው ቆይታ 3 ሺህ ገጽ የሚፈጅ መጽሀፍ ጽፎ እንደጨረሰ ተናግሯል

Page 14: Habeshawi kana 004

ሐምሌ 30-ነሐሴ 13 ቀን 2003 (August 6-19, 2011)ሐበሻዊ ቃና14

የመጀመሪያ ልጃችንን ለመውለድ ሽር ጉድ ትላለች። ዝሆን አክላለች። ግራና ቀኝ ጎንጮቿ የበሰለ ሾላ መስለዋል። እንደማ

ለች ነበረች። ትንሽ ዓለም ሰርታ እኔ፣ እሷና ልጇ ብቻ እንድንኖርባት። በዘሮቿ ምን እንደምትባል ስለምታውቅ እንደሆነ የገባኝ በኋላ ነው። አረብ የተጫወተባት እንዴት ቀና ብላ ሰውን ታያለች ይሆን? ከመቅደስ ሁኔታ የተረዳሁት የአረብ ስም እንዲነሳ አለመፈለጓ ነው። ከአረብ ጠመንጃና ፈንጂ እየተቀበሉ ወገናቸውን ሲገሉ ከነበሩት የበለጠ ማን ሸርሙጣ አለ? ያውም ነፍስ የሚያጠፋ ሽርሙጥና። መንጌ ዕውነቱን ነበረ እንዴ? ‘የአረብ አገር እግዜር የሌለበት ቦታ ነው’ ትላለች። ‘እግዜርን አያውቁም’ ትላለች። እንድጠላት ጠብቀው ይሆን? የወለደችልኝን እንድጠራጠር?ሆስፒታል በጀርባዋ ተኝታ ማደንዘ

ዣ አሸንፋ የወለደችውን ወንድ ልጅ ነርሷ ክንዷ ላይ ስታሳቅፋት ፊቷ በዕንባ ታጠበ። ነርሷ እንደ እህቷ እያባበለቻት፤ በዚህች የመተዛዘን ትዕይንት የዳች (ሆላንድ) ሴቶችን ሁሉ ወደድኩ። ሚስቴ በአገሯ አሉባልተኞች ተላግጦባት እንደተኛች፣ በአረብ ወንዶች ሲገሰስና ሲደፈር ከነበረ የነጠፈ ከመሰላት ማሕጸንዋ፣ ከተመሰቃቀለ ዘመን በኋላ፣ ወርቅ የመሰለ ወንድ ልጅ ተፈልቅቆ ሲወጣ፣ አብራት ያለቀሰችው፣ እንግዳ በሆነ መልክ የምጠረጥራትና ችላ የምላት የፈረንጅ ነርስ ነበረች። መቅደስን ሳይሆን አቅፌ ለማባባል የፈለግሁት ‘አነከ’ የምትባለዋን ያቺን የዳች ነርስ ነበር። ያን ዕንባ የጠረጉ የሚያምር ቀለም የተነከሩ ጥፍሮቿን አልረሳም። ግራና ቀኝ ወደ ላይና ወደታች የቆመ ቢጫ ጸጉር ያላትን ልጅ-እግር ሴት አልረሳትም።ትግላችን ከራሴና ከወገኔ ጋር ነበር።

ወገኔ ከተባለ። መቅደስ ለምን አለቀሰች?በደከመ ድምጽ “መንገዱ” አለች

ኝ። ይሄንንም መልስ አልረሳም። ጉዞው። ምጡ አልነበረም። መንገዱ። ወዙን ካጣ ከደረቀ ነፍሰጡር አፏ

ይኼ ቃል ወጣ። የተነፈሰ ሆዷን ሳምኩላት። ልጁን አቅፌ አልጋዋ ዙሪያ መነጽሬ ዘሎ እስኪወድቅ ደነስኩ። እርግማናችንን አብረን እንድንሰርዝ ላሳያትም ነበር። አነከ ነርሷን ለእኔም ለመቅደስም ዘመዳችን ሆነች። ለልጃችን ለቶማስ እናት ሁኚው አልናት። ትንሽ ቤታችን ወስደን እጇን ይዤ በተሰባበረ እንግሊዘኛና ዳች እጆቿ የተባረኩ እንደሆኑ ነገርኳት። የሰንጋ ተራ ትዕቢቴን ደንሀግ ሆስፒታል አንዲት ሴት ፈረንጅ እግር ስር ጣልኩ። ልጁ መጀመሪያ የሰማው ድምጽ ‘የአንቺና የእናቱ ዕንባ ሲወድቅ ነው አልኳት። በአስራ አምስት ቀኑ የቶማስ እትብት ደርቆ ሲወድቅ ለቅሜ ያዝኩት። አስገርዤም ልፎውን ‘ፎርምሊንዲሃይድ’ በተሞላ ትንሽ ብልቃጥ አስቀመጥኩት። ጊዜ አልፎ ይሔ ልጅ ሲቆም የደንሀ

ግን አየር እየጠባ ከጎሮሮ የሚወጣ ቋንቋ ይናገራል። የተሻለ ይማራል፣ ይበላልም። የሆላንድን ሳቅና ለቅሶ ይኖራል። እና እዚህ ይረጋል። የሆላንድን ጦርነቶች ሊዋጋ ይወጣል። ሕይወት በፍጹም ልምድ ትዋጥና የአባቱንና የእናቱን አገር ይረሳል። ይፈረድበታል? እኛን ያጋጠመችን ዓይነት ነርስ ያጋጥመዋል፤ ይህችን ትንሽ አገርም በቀለሙ ይሞላታል። ‘የኢትዮጵያ ዋና ከተማ ማነው?’ ተብሎ ሲጠየቅ በጉብልነቱ ‘ክሎትዛክ’** ቢል ይፈረድበታል?

ልፎበአዳም ረታ

*

ትረካ

(ክፍል ሶስት)

በመቅደስ እየተተቸሁ የልጄን ልፎና እትብት መኝታ ቤቴ ሳጥን ውስጥ አስቀምጩአለሁ። አልፎ አልፎ እሷ በሌለችበት ከተደበቁበት አውጥቼ የስጋ ቁራጮቹ መልካቸው እንዴት እንደተለወጠ አጠናለሁ። የስጋ ቁራጮቹ የሚያስተምሩኝ ነገር ቢኖር እንግዳ በሆነ መልክ ተስፋ እንድቆርጥ ነው።ከዕለታት አንድ ቀን የመቅደስ እናት በ

ጠና እንደታመሙ የሚነግር ደብዳቤ ደረሰን። በጋራ የደረሰን ወሬ ይኼ ነው። በግል ስልክ በቅሎ ቤት እናቴ ጋር ስደውል የተነገረኝ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ነው። ‘በቃ እንደተኙ ቀሩ?’ ‘ግራ የሚያጋባ ዘመን ነው፣ ጋደም ብሎ መሞት? በትንታ መሞት ድሮ ሰምቼ አላውቅም፣ እንዲህ ያለ ለነጋሪ ያስቸገረ ነገር፣ ወጣቱማ ረገፈ ረገፈ ልጄ፤ እሳቸውማ ከታመሙ ከረሙ እኮ፣ ከረሙ። ውስጣቸውን የሚበላ ነገር ነበር። አይናገሩ አይጋገሩ። እሳቸው ነፍሳቸውን ይማር እንጂ ያው መቼም።እናንተስ? ልጁስ? ማን ነበር ስሙ ልጄ፣ ያ ጓደኛህ ማሞ ልጅ ወለደ እኮ! በዚህ ሲሄድ በዚህ ይመጣል። መጣጣፍ አቆማችሁ? አሁን እሷ መሞቷን እንዳትነግራት። ብቻ ከቻላችሁ ይዘሃት ና። ካልቻላችሁ ያው በአገሩ ደንብ ፈረንጅ አገር አርዳት?’እንደሞቱ ባልነግራትም መሞታቸውን

ጠርጥራ ‘ለማንኛውም ልያት’ ብላ ተነሳች። አነከን ከተዋወቅናት ጀምሮ መቅደስ የምትሄድበት የዳች ሪፎርም ቤተክርስቲያን የትኬት ወጪዋን ቻሏት። አፍ አውጥታ አትንገረኝ እንጂ ‘ታመሙ’ ብዬ ከነገርኳት ጀምሮ ልጇን እያጠባች ባዶ አየር ውስጥ ዕንባ ባቀረሩ አይኖቿ ታፈጥ ነበር። ‘ልጁን ይጎዳዋል’ እንኳን ብላትም እህል የመብላት ወስፋቷ ተቆረጠ። ድብን ባለ ሌሊት ተነስታ ‘ልጁን አለቀሰብኝ ላጥባው’ ብላ በማመሃኘት ማድ ቤት ገብታ ስታለቅስ ሁለት ሶስቴ አግኝቼአታለሁ። ያፈላሁትን ቡና ሳትጠጣው (‘ቡናና ፍቅር በትኩሱ ነው’ ብላ እንዳልተረተች) ያልተቀመሰለት የቀዘቀዘ ቡና ከፊቷ አነሳለሁ። ‘እማማ ቶማስን ሳታየው’ በሚል የእሮ

ሮ ሽፋን፣ የግል ለቅሶዋን ታለቅሳለች። ይኼ ቁጭቷ የወጣላት መቃብራቸው

ን ሳታይ ነው። የመቃብር ሲሚንቶው ላይ ወደቀች። ነጠላዋን ግራና ቀኝ ዘረጋች። በዚያ ጸጥታ ሰው ባልነበረበት ባሜኬላና በሌሎች ሙታን መሃል እርሟን አወጣች። ፊቷን በጥፍሮቿ ቀደደች። ጸጉሯን በጭብጥ ከአናቷ ላይ ነጨች። ከራሷ ቁጣ ላድናት ስይዛት ትግሌን እየጣሰች። ወደ እናቷ መቃብር እየቀረበች እየተጠጋች እንዲህ እንዲህ እያለች ልቤን ሰበረችው። ‘እኔ ነኝ የገደልኩሽ!’‘እማማ እኔ ነኝ ሐጢያተኛዋ!’‘ተቃጥዬ ያቃጠልኩሽ!’ ‘እኔ የማልረባ ልጅሽ ነኝ ማሪኝ እማ

ማ!”‘ይቅር በይኝ እማማ አሳልፍልሻለሁ መ

ስሎኝ ነው፤ ባላውቅ ነው!’‘እማማዬ ብዙ አላውቅም እማምዬ!’‘ልደፋልሽ በአንቺ ቦታ!’‘ባጠባሽኝ የበደልኩሽ፣ ባጠባሽኝ የራ

ቅሁሽ!’“በጥጋቤ እኔ ነኝ የገደልኩሽ!’‘እኔም አልተመቸኝም እኰ!’ለእኔም ያለቀሰች መሰለኝ። ገና አንድ

እግራችን ከአገር ሲወጣ የእናቶቻችን የልብ ምት አፍታ ይወርዳል፣ አዲስ በሽታ ይበረታባቸዋል፣ ሊነኩን እጃቸውን ሲዘረጉ ሲያጡን፣ ጣቶቻቸው በቆፈን ይረግፋሉ። ፊቴን በአንድ እጄ ጋርጄ ልቤን በለቅሶ

ቀደድኩ……..ምናለ እነ እንትና ከእሷ ቢማሩ…….እንትና……….ያ……..

* * *

አንድ ቀን ሆስፒታል ሆስፒታል በሽተኛ ሆኖ ተኝቶ ሚስቴን ‘የአረብ ሸርሙጣ’ ብሎ ያማት ስልክ ደወለ። ከርሞ ከርሞ። “ታዲያስ ጠፋህ ምነው?”አፉ ውስጥ ‘ተሳስቼያለሁ’ የሚል ቃ

ል የሚወጣበት አይነት ሰው አይደለም። ኩፍ ያለ ነው ድምጹ። የሆነ ውስጡ ነፋስ ያረገዘ። ‘ደርግን እቃወም ነበር’ በተባለ ቋንቋ የተለጠጠ…..ባረጀ በሬ የሚንገታገት……“አልጠፋሁም”“በሽተኛ አንዴ ብቻ ነው የሚጠየቀ

ው?”“ልጅ መጣ፣ አልተመቸኝም”“ለመሆኑ ባለቤትህ ደህና ናት?”“ደህና ናት”“ላያት እፈልግ ነበር። በባሕላችን አራ

ስ መጠየቅ ይገባታል። በተለይ በስደት ላይ ዘመድ የለ፣ ምን የለ……እኛው ዘመድ ካልሆንን….”“እሱስ አዎ”“የሚቀጥለው ሳምንት አመጣለሁ”“ያኔ አንኖርም”“እንዴት?”“ኢትየጵያ እንሄዳለን”“ለምን ደህና?”“የመቅደስ እናት ታመዋል”“ለማንኛውም ከሰው መውራት ጥሩ

ነው……….ነገ ብቅ እላለሁ”ምን ማለት ነው ማውራት ጥሩ ነው

ማለት?እምቢ አላልኩትም። ማለት ይገባኝ ነ

በር። ግን የአዲስ አባ ማህበራዊነቷና ሰውን አለመደበር ገና ከደም ስሬ ተቀርፎ ተንጠፍጥፎ አልወጣም።መቅደስ በሸቀች። “ማንም ሃበሻ ደጄ እንዳይደርስ”“ሊጠይቅሽ ነው፣ ለሌላ ነገር አይደ

ለም”“አሁን አንድ ነገር ውሰድልኝ ሊልህ ነ

ው። ራሱ አይልክም? የሰለለበትን ገንዘብ ምን ያደርገዋል? አታምነኝም እንጂ አገር ቤት እንደምንሄድ ሰምቶ ነው ‘ልምጣ’ የሚለው”“ምን? ማን ይነግረዋል? ለማን ነግረ

ሻል?” “ለማንም። ግን ያውቃሉ እንጃ። እና

ቴ ምን እንደታመመች በዝርዝር ያውቃል ይሄኔ” አለች በብስጭት“ከሰው ካልሰማው ታዲያ? ቢሰማ

ስ። ከፈለግን ‘ዕቃህን አንወስድም’ ማለት እንችላለን”“ይቀፈኛል”“አንቺ ዝም ብለሽ ነው”“ለምን ሙጭጭ ይላል?”“አዲስ አባ እየናፈቀችው ይሆናል”“አውትኬሪንግ አዳክሞት ነገር ነገር

እያለው ፖሊተከኛ የሆነ ነው”አልሰማኋትም።በበነጋታው ሲመጣ በፖስታ የታሸ

ገ ነገር ለአባቱ እንድሰጥለት ጠየቀኝ። መቅደስን ሳያያት አኩርፋ መኝታ ቤት እንቅልፍ እንደያዛት ሁሉ ተኝታ ቀረች። ትንሽ አወራርቶ ቡና ጠጥቶ ሊሄድ ሲል፤ ክፉን በክፉ መቃወም ባልፈ

ልግም “ምንድነው ውስጡ ?” አልኩት።“ስኮች ቴፕ አለህ?” አለኝ ያልጠየቅ

ሁትን።“አዎ”ክርታሱን ክፈተና አሳየኝ። “ባታየው አትወስደውም ነበር?” አ

ለኝ “አልወስድም። ድራግ ቢሆንስ? እ?”“በዚህ እንኳን አንጠረጠርም”ሁለት ትልልቅ ካፖርቶች ናቸው። ሆ

ን ብዬ አተኩሬ አየሁት። ለመጀመሪያ ጊዜ ያወቅሁት መሰለኝ። የአዲስ አባን ትዝታ ከዚህ ሰው ማግኘት እንደማልችል ገባኝ። በመልሴ የተከፋ አይመሰልም፡ ቢገባውም ያልገባው ዓይነት ተዋናይ ሆነ። * * *አዲስ አባ አስራ አምስት ቀን ያህል ቆ

ይተን ለመመለስ ሁለት ቀኖች ሲቀረን ፖስታዬን እና ክርታሴን አንጠልጥዬ እንትና በሰጠኝ አድራሻ ታክሲ ይዤ ሄድኩ። ስድስት ኪሎ አፍንጮ በር አካባቢ ነበር። በር ሳንኳኳ የከፈቱልኝ ጥምጥም ያደረጉ፣ ጺማቸውን የተላጩ ሽበት ጣል ጣል ያደረገበት ገጽ ያላቸው መልከ መልካም ጠይም ሽማግሌ ነበሩ። መምጣቴን ቀደም ብዬ ስልክ ደውዬ ነግሬያቸው ስለነበር፣ በስሜ ጠርተው በትህትና እንድገባ ጋበዙኝ። ቤት ውስጥ እርሳቸውና ፊታቸው ብቻ እስኪቀር የተከናነቡ ሌላ ሴት ነበሩ። ገና እንደተቀመጥኩ ራት በልቼ (ማታ ላይ ነበር የደረስኩት) እንድሄድ ሲጠይቁኝ፣ በስነስርዓት ተከላክዬ ፖስታውንና ዕቃቸውን በእጃቸው ሰጠኋቸው። ስለልጃቸው ጤንነት ከጠየቁኝ በኋላ

የሚያበረታታቸውን መልስ ሰጥቼ ከተቀመጥኩበት ስነሳ፣ አንድ የሚያጫውቱኝ ነገር ስላለ በጥሞና እንድሰማቸው አግባቡኝ እና ተመልሼ በመቻቸት ተመልሼ ተቀመጥኩ። “እግዚያብሔር አንድ ነው፣ አየህ። ስ

ሙን ሰዎች ይለያዩታል እንጂ አላህ ብትል እግዚያብሔር ብትል አንድ ነው። ቅደመ አያቴ እስላም ነበሩ። ልጃቸው ክርስቲያን አገባና ከዚያ በኋላ ክርስትናው ቤታችን ገባ። የድሮ ሰዎች ናቸው። ለምን? በለኝ። አላህ በለው እግዜር በለው ያው ነው። ልጄ ሆላንድ የቤተክርስቲያን አመራር ይሰራል ሲባል ሰምቼያለሁ፣ እሱም አንዴ ሰላም ሊል ደውሎ አጫውቶኛል። ልክ ነው? (‘አረ የማይገባበት ቦታ የለም’) አንድ ነገር ልንገርህ እኔ ወደ ቅድመ አያቶቼ ሃይማኖት ተመልሻለሁ። ግድግዳ ላይ በመስታወት ውስጥ ሆ

ኖ የተሰቀለው ዳንቴል የመሰለ የአረብኛ ነገር የተጻፈበት ነገር አሳዩኝ። “ አረብኛውን ባለውቀውም አላህ ከ

ሰዎች ጋር በሚገባቸው ቋንቋ ይናገራል። ነብዩም እንዲህ ነው የሚያስተምሩት፤ ስማቸውን ይባርክና። ግን ልጄን እንዲከፋው አልፈልግም ‘አባቱም እናቱም ሰለሙ’ ተብሎ ቢሰማ ያዝናል፣ ይበሳጫል (አረ ካሽ ካገኘ ግድ የለውም)። ግን እዚያም ስገዱ ነው፣ እዚህም ስገዱ ነው። ‘አለማየሁ’ የተባለ ስሜ ‘አብዱላሂ’ አሰኝቼዋለሁ። የሰፈር ሰው ገና ‘አለማየሁ’ ነው የሚልኝ። ክፋት የለውም። እንዲህ ያደረግነው ለጥቅም አይደለም። ለእሱ ነው። ለእመነቱ ነው። ታዲያ ከልጄ ጋር ተገናኝታችሁ ድንገት ወሬ ቢነሳ መነሳቱ መቼም አይቀር፣ እንደሰለምኩ አትንገረው። ይሄን ቃል ግባልኝ። ያለዛሬ አይቼህ አላውቅም። መቼም ታምነህ የተላክ ሰው ስለሆንክ፣ ብትግባቡ ነው መቼም (‘ከቴም ተግባባን’) ቢሰማ ችግር ይኖረዋል? እንጃ እንግዲህ ባትነግረው፣ ባታወራው ይመረጣል። እንዳይሳትህ ብዬ ነው። ሴትየዋ/ ባለቤታቸው ከእኛ ራቅ ብ

ለው በጋቢያቸው ተሸፋፍነው ታስረ

ው የተቀመጡ መስለዋል። ቃል አውጥተው አይነገሩኝ አንጂ ከአስተያየታቸው፣ ከአንገት አደፋፋቸው እየተለማመጡኝ እንደሆነ ይገባኛል። የሰውዬው ከአፌ ቃል እንደማይወጣኝ በተፈጥሮዬ (ምናልባት ስወለድ ጀምሮ ወይም ከእናቴ ሆድ ጀምሮ ለሃይማኖት ግድ እንደሌለኝ፤ እንደውም እሳቸው ያሉት የእግዜር መመሳሰል ትልቁ እውነት እንደሆነ አንስቼ) ሳይሆን አይቀርም ምስጢር ቀርቃሪ በመሆኔ ትንፍሽ እንደማልል፣ አንዲት ቃል ከአፌ ጠብ እንደማትል ቃሌን ሰጠሁዋቸው። ክርስቶስን ጠርተው መረቁኝ። ከተቀመጡበት ተነስተው ትከሻዬ ላ

ይ ሳሙኝ። ሲሰናበቱኝ እና ሲሸኙኝ ሽማግሌ

ው አይኖች ውስጥ ሊሸፍኑት ያልቻሉት ወፍራም እፍረት ነበር። ለመቅደስ ይሄን ሁሉ አልነገርኳት

ም። * * *ግን ነገ ልሄድ ዛሬ፣ አንድ የቀረኝን ነ

ገር ማድረግ ነበረብኝ። ከሰዓት በኋላ ላይ ሻንጣዬን በርብሬ የልጄን “ልፎ” እና እትብት ያለባቸውን ብልቃጦች ይዤ ወደ ጓሮ ወጣሁ። መቅደስ ቆማ ታየኛለች። ቶማስ ደረቷ ላይ ያለቅሳል፣ አዲስ አባ ከገባሁ ጀምሮ ያለቅሳል። አዲስ አባን አልወደደውም ወይም አየሩ ቀጥኖበታል። ከቤቱ ጀርባ ረግረግ የመሰለች ቦታ አለች። ረባዳ በመሆኗ ውሃ ስለምትሰበስብ ይሆናል። መሬቱን በገሶ ቆፈርኩና ቆዳዎቹን በህብረት የአጥቅ ርዝመት ያለው ጉድጓድ ውስጥ ከጠርሙሳቸው አውጥቼ ቀበርኳቸው። ጥላ ስር ያስቀመጥኩትን፣ ለዚህ ጉዳይ ያመጣሁትን የቀርከሃ ፍል ወስጄ እዚያ ተከልኩትና በባልዲ ውሃ እያመላለስኩ አጠጣሁት። በድንገት መቅደስን ዞሬ አየኋት ግንባሯን በሀሳብ ከስክሳለች። ‘ምነው ሳቅሽ ጠፋ?’ ብዬ ልጠይቃት ፈለግሁ። ልጁ ከደረቷ ወርዶ መሬት ለመሬት ሊንቧች ይንፈራገጣል። በጠዋት አይሮፕላን ላይ ወጥተን ሳ

ይ፣ አዲስ አባ ወደታች የተተመተመች አረንዛ ቦታ እንደምትመስል አየሁ። መሬት ላይ ቆሜ አረንጓዴ የሚመስሉኝ ዛፎች እንኳን ከዚያ ርቀት አመዳም ናቸው። በሀሳቤ በስሜት ከረሳሁት፣ ስጋ ከቀበርኩበት መሬት ረግረጉን የጠባ በእፍኝ የሚያዝ ወፍራም መለሎ ቀርከሃ ሲበቅል ታየኝ። እምቢልታ የሆነ ዕለት እንደተረቱ ዋሽንት ግጥም የሚያንቸረችር። ‘እዛም የለሁእዚህም የለሁ ባሌለሁበት ያሌለሁበትን እየተመ

ኘሁ’ * * *

ደክንሀግ ስገባ ስለሰለሙት የእንትና እናት እና አባት አላወራሁም። ማውራት የአራዳ ልጅ ደንብ አይደለም። አዲስ አባ ባቡር ጣቢያ ጠይቁ። ያ ብቻም አይደል። ክፉን በክፉ አትቃወሙ ይላል ቁልቁሉ መጽሀፍት ሁሉ።

(ተፈጸመ)

* ልፎ ማለት ወንዶች ሲገረዙ ከብልታቸው ተቆርጦ የሚቀበረው (የሚጣለው) ቁራጭ ነው።

** ‘** ‘ክሎትዛክ’ (Klootzak) ማለት በዳች ቋንቋ ቆለጥ የሚቀመጥበት የቆዳ ኮሮጆ ነው

ይህ አጭር ልቦለድ የተወሰደው አዳም ረታ በቅርቡ ካሳተመው አምሰተኛ መጽሀፉ “ያመጣል

መንገድ፣ ይወስዳል መንገድ” ነው

እግዚያብሔር አንድ ነው፣ አየህ። ስሙን ሰዎች ይለያዩታል እንጂ አላህ ብትል

እግዚያብሔር ብትል አንድ ነው። ቅደመ

አያቴ እስላም ነበሩ። ልጃቸው ክርስቲያን አገባና ከዚያ በኋላ

ክርስትናው ቤታችን ገባ።

Page 15: Habeshawi kana 004

ሐምሌ 30-ነሐሴ 13 ቀን 2003 (August 6-19, 2011) ሐበሻዊ ቃና 15

መጽሐፍ

በቅርብ ለንባብ የበቁ መጽሐፍት

የ“ነጋሶ መንገድ” የተሰኘው እና በሐምሌ ወር ለንባብ የበቃው መጽሐፍ የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት የሆኑትን የዶክተር ነጋሶ ጊዳዳን ህይወት የሚያስቃኝ ነው፡፡ የመጽሀፉ ደራሲ ዳንኤል ተፈራ በመግቢያው ላይ እንደጻፈው የዶክተር ነጋሶን ታሪክ ለማዘጋጀት ከእርሳቸው ጋር ሶስት ወር የፈጀ ቃለ መጠይቅ አድርጓል፡፡ “የ“ነጋሶ መንገድ” በተሰኘው በዚህ መጽሀፍ ውስጥ ነጋሶ የተጓዙበትን ረዥምና አባጣ ጎባጣ የበዛበት የህይወት መንገድ እናገኛለን” ይላል በመጽሀፉ ጀርባ የተጻፈ ማስተዋወቂያ፡፡ ከባለቤቱ አንደበት የተቀዳ ነው የተባለለት ይህ መጽሀፍ የነጋሶን ከልጅነት እስከ ዕውቀት ያለ የህይወት ታሪክ በስድስት ምዕራፎች ከፋፍሎ አቅርቧል፡፡ የመጀመሪያው ምዕራፍ የ“አባታቸው

ልጅ” የሚል ርዕስ ያለው ሲሆን ስለነጋሶ የልጅነት ጊዜ፣ የታወቁ የፕሮቴስታንት ቄስ ስለነበሩት የነጋሶ አባት እና ቤተሰቦቻቸው የሚተርክ ነው፡፡ “ላለመስማማት መስማማት” የሚል ርዕስ የተሰጠው ሁለተኛ ምዕራፍ ነጋሶ ጀርመን ሀገር በነበሩበት ጊዜ እንዴት ኢህአዲግን አንደተቀላቀሉ የሚያወሳ ነው፡፡ “ስልጣን እና ፖለቲካ” በሚለው ሶስተኛ ምዕራፍ ነጋሶ ከተለያዩ የመንግስት የኃላፊነት ደረጃዎች አንስቶ እስከ ፕሬዝዳንትነት የሰሩባቸውን ጊዜያት ይዳስሳል፡፡ አሁንም ቢሆን ከጀርባው በርካታ ምስጢሮች እንደተሸፈኑ ተቀምጠዋል በሚባልለት የህወኣት ክፍፍል እና ተሃድሶ ዙሪያ የሚያጠነጥነው አራተኛ ምዕራፍ ያልተሰሙ አንዳንድ ነገሮችን በውስጡ ይዟል፡፡ በክፍፍሉ ወቅት ከህወኣት እንዲወጡ ስ

በኢትዮጵያ ዘመናዊ ታሪክ ውስጥ ጉልሕ ሥፍራ ያላቸው ዐፄ ምኒሊክ የተጻጻፏቸውን ደብዳቤዎች ጳውሎስ ኞኞ ከሃያ አምስት ዓመታት በፊት አዘጋጅቶ ነበር፡፡ ከ1978 ዓም በፊት፡፡ በዚሁ ዓመት መጽሐፉ ይታተም ዘንድ ለመነጋገር ጳውሎስ ለኩራዝ አሳታሚ ሰጠው፡፡ በኋላ ሲጠይቅ «የበላይ አካል ወሰደው» ተባለ፡፡ የበላዩ አካል ማነው? ብሎ ቢጠይቅ ግን መልስ ሰጭ አላገኘም፡፡ይኼ 2245 የዐፄ ምኒሊክ ደብዳቤዎችን የያዘው

መጽሐፍ ከሃያ አምስት ዓመታት በኋላ በአስቴር አሳታሚ ድርጅት አሳታሚነት ሰሞኑን ታትሟል፡፡ በዘመኑ የነበረውን የውስጥ ግንኙነት፣ የመኳንን

ት እና የመሳፍንት ሁኔታ፣ የመንግሥትን አሠራር፣ የመሪዎችን አስተሳሰብ፣ የሕዝቡን እና የኑሮውን ሁኔታ እና ሌሎችንም በደብዳቤዎቹ ውስጥ ይገኛሉ፡፡ጳውሎስ ኞኞ የኢትዮጵያን ነገር በኢትዮጵያኛ ከ

ጻፉልን ጥቂት ኢትዮጵያውያን አንዱ ነው፡፡ ብዙዎቹ ምሁራን ለጆርናሎች እና ለወርክሾፖች እንጂ ለሕዝብ የሚሆን ትሩፋት የላቸውም፡፡ ጳውሎስ ኞኞ ግን እኛ የምናነባቸውን ብዙ ሥራዎች አትርፎልናል፡፡ የጳውሎስ ሥራዎችን ከልጅነታችን ጀምሮ አንብበናቸዋል፡፡ አስደናቂ ታሪኮችን ብዙዎቻችን ታች ክፍሎች ሆነን ነው ያነበብናቸው፡፡ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ከተካተቱት ደብዳቤዎች

መካከል እጅግ ወሳኙ ደብዳቤ ራሱ ጳውሎስ ኞኞ ለጓድ ተስፋዬ ወልደ ሥላሴ (ነፍሳቸውን ይማርና) የጻፈው ደብዳቤ ነው፡፡ በወቅቱ የኢሠፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ የፖለቲካ ቢሮ ተለዋጭ አባል፣ የሀገር እና ሕዝብ ደኅንነት ጥበቃ ሚኒስትር ለነበሩት ተስፋዬ ወልደ ሥላሴ ጳውሎስ የምሬት ደብዳቤ ጽፏል፡፡በዚህ ደብዳቤው ጳውሎስ ለሀገሬ ልሥራ ባለ የ

ሚደርስበትን እና የደረሰበትን መከራ ዘርዝሮታል፡፡ በየዘመናቱ ያሉ ደራስያን ያጋጠማቸውን እና የሚያጋጥማቸውን መከራ ነው በደብዳቤው ውስጥ የምናየው፡፡ ጳውሎስ መጽሐፎቹ ይወሰዱበታል፣ “ማን ወሰዳቸው?” ሲል የበላይ አካል ይባላል፡፡ ይህ የበላይ አካል ግን አይታወቅም፡፡ የሰበሰብካቸውን ማስረጃዎች በአስቸኳይ አስረክብ ይባላል፡፡ “ማን አለ?” ሲል የበላይ አካል ይባላል፡፡በዚህ ምክንያት ካሁን አሁን ያለኝን ሁሉ ማስረ

ጃ ይህ ማነነቱ ያልታወቀ የበላይ አካል ይወስድብኝ ይሆን? በሚል ሰቀቀን ውስጥ መግባቱን ይገልጣል፡፡ “የኢትዮጵያን ሕዝብ እና መንግሥት አልበደልኩምና ከሀገር እንድወጣ ይፈቀድልኝ” ብሎ አመለከተ፡፡ በዚህ ማመልከቻው ለመሣፈርያ የሚሆን ገንዘ

ብ ለመለመን እንዲፈቀድለት፣ ከሀገር እንዲወጣ እንዲፈቀድለት፣ ከሀገር ሲወጣም ዶክመንቶቹን ይዞ እንዲሄድ እንዲፈቀድለት ለምኗል፡፡የጳውሎስ ደብዳቤ መልስ ሳያገኝ የደርግ ዘመ

ን አለፈ፣ ደብዳቤው የተሰጣቸው ተስፋዬ ወልደ ሥላሴ ታሠሩ፤ በኋላም ራሱ ጳውሎስ ኞኞ አረፈ፡፡ ከሃያ አምስት ዓመታት በኋላ ግን መጽሐፉ እጃችን ገባ፡፡ ምስጋና ለቤተሰቦቹ እና ለአሳታሚዎቹ፡፡እኔ ግን ሁለት ነገሮች ነገር ቅር አሉኝ፡፡ ምነው

ለመጽሐፉ የደከመው፣ ደክሞም ያዘጋጀው፣ አዘጋጅቶም ሲታተም ሳያይ ያለፈው የጳውሎስ ኞኞ ታሪክ ሲሆን በመግቢያ፣ ካልሆነም በጀርባ ሽፋኑ ሳይጠቀስ ቀረ፡፡ ሥራው ያለ ሠሪው ምንድንነው?ቢያንስ በቀጣይ ይታተማል የተባለው መጽሐ

ፍ ሲታተም ስለ ጳውሎስ ኞኞ አጭር ታሪክ መካተት አለበት፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ዐፄ ምኒሊክ ደብዳቤ የጻፉ

በትን ቋንቋ አሁን ባለው አስተሳሰብ ለማረም መሞከር ስሕተት ይመስለኛል፡፡ አንደኛ በዘመኑ ስላለው አስተሳሰብ ማወቅ የሚቻለው በቃላቱ ነው፡፡ አስተሳሰበ በዋናነት የሚገለጠው በቋንቋ ነውና፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ስለ ዐፄ ምኒሊክ ስንጽፍ በራሳችን ቋንቋ እንጻፍ እንጂ እንዴት ዐፄ ምኒሊክን በእኛ ዘመን ቋንቋ እናስጽፋቸዋለን? የአሳታሚዎቹ ችግር ይገባኛል፡፡ ግን ችግሩን ካ

ልተጋፈጥነው ለሁለት ሺ ዘመናት የተከማቸውን የኢትዮጵያ ዶክመንት አርመን እንዴት እንዘልቀዋለን? እኛ የሞቱ አባቶቻችንን ቋንቋ መረዳት አለብን እንጂ እንዴት የሞቱ ሰዎች የኛን ቋንቋ ተረዱ እንዴት ይባላሉ? በዚህ ሃሳብ ምክንያት ብዙዎቹ ደብዳቤዎች ም

ኒሊክ ሳያውቁ «መታረማቸውን» ጳውሎስ ኞኞ ካሰባሰባቸው መካከልም ሁለቱ ደብዳቤዎች መቅረታቸው የችግሩን ሥር መስደድ ያሳያል ፡፡

ለተደረጉ አባላት ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የተናገሩትን እና ነጋሶ የመለሱት አንዱ ነው፡፡ “መለስ ስለ መቀሌ ውሳኔ ‘ጃኬታቸው

ን አስወልቀን ራቁታቸውን አባረርናቸው’ እያለ ሲናገር እጄን አነሳሁና ‘ይቅርታ! አሁንስ መንግስቱን መሰልከኝ’ አልኩት፡፡ ቤቱ በድንጋጤ ተናወጸ፡፡ በተለይ ከጎኔ ተቀምጣ የነበረችው ገነት ዘውዴ ‘እንዴት ከመንግስቱ ጋር ታወዳድረዋለህ’ በማለት ስቅስቅ ብላ አለቀሰች” ይላሉ ነጋሶ በመጽሀፉ፡፡ እንዲህ የተሰማቸውን ይናገሩ የነበሩት ነጋሶ በስተመጨረሻ ኢህአዴግ በቃኝ አሉ፡፡ ይህን ውሳኔያቸውን እና ከዚያ በኋላ ያለውን ህይወታቸውን ዋጋ የተከፈለበት የነጻነት መንገድ በሚል ምዕራፍ ይተነተናል፡፡ ነጋሶ ከፕሬዝዳንት ስልጣናቸው በግል ፍቃዳቸው ከለቀቁ በኋላ በተወለዱበት ደምቢ ዶሎ ለፓርላማ ተወዳድረዋል፡፡ በምርጫ 97 ብቸኛው የግል ተመራጭ ሆነውም ፓርላማ ገብተዋል፡፡ ከአምስት ዓመት በኋላ ደግሞ በፖለቲካ ፓርቲ ስር መታገል እንደሚሻል አምነው የአንድነት ለፍትህ እና ለዲሞክራሲ ፓርቲን ተቀላቅለዋል፡፡ ስደስተኛው እና የመጽሐፉ የመጨረሻ

ምዕራፍ አባሪ ሰነዶችን የያዘ ነው፡፡ ዶክተር ነጋሶ በየጊዜው የተጻጻፏቸው ደብዳቤዎች ከአባሪ ሰነዶቹ መካከል ይገኙበታል፡፡ መጽሐፉ እንደ አባሪ ሰነዱ ሁሉ 41 ፎቶዎችንም በውስጡ አካትቷል፡፡ ፎቶዎቹ ከነጋሶ የልጅነት ጊዜ፣ እስከ የጀርመን የስደት ህይወት፣ ከቤተመንግስት ቆይታቸው እስከ ቤተሰብ ህይወታቸው ያለውን ሁኔታ የሚያስቃኙ ናቸው፡፡

ደራሲ፡- ዳንኤል ተፈራ ጀ.

አታሚ፡- ንግድ ማተሚያ ድርጅት

ዋጋ፡- 50 ብር

ገጽ፡- 384

አዘጋጅ፡- ጳውሎስ ኞኞ

አታሚ፡- ርኈቦት አታሚዎች

ዋጋ፡- 120 ብር

ገጽ፡- 622

ደራሲ፡- አበበ ቶላ

ዋጋ፡- 26 ብር፣ 15 ዶላር፣ 15 ዩሮ

ገጽ፡- 152

“ከዚህ በኋላ በሻዕቢያና በህወሃት መካከል ችግር ተፈጥሮ ወደ ጦርነት የምንገባ ከሆነ የእኛን ህዝብ

ሂዱና ተዋጉ ብዬ አልቀሰቅስም! ”አዲሱ ለገሰ (የቀድሞ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር)

ይህ

ጹሁ

ፍ ከ

ዳንኤ

ል ክ

ብረት

ጡመ

ራ (ዳ

ንኤል

ክብ

ረት ዶ

ት ኮ

ም )

የተወ

ሰደ ነው

ብዙዎች የሚያውቁት አቤ ቶኪቻው በሚለው የብዕር ስሙ ነው፡፡ እውነተኛ የመዝገብ ስሙ አበበ ቶላ ነው፡፡ በአዲስ አበባ ውስጥ ባለ አንድ የግል ኮሌጅ ውስጥ የሚሰራው አበበ በ“አውራምባ ታይምስ” ጋዜጣ ላይ በየሳምንቱ ያወጣቸው በነበሩ ስላቅ አዘል ጽሁፎቹ ይታወቃል፡፡ አበበ በህዝቡ ውስጥ ያለውን ስሜት በጽሁፎቹ ለማንጸባረቅ ይጥራል፡፡ ሰሞነኛ ጉዳዮችን እያነሳ ይተቻል፣ ይቧልታል፣ ይሳለቃል ባስ ሲልም ያሽሟጥጣል፡፡ በዚህ መጽሐፍ ላይ ከተካተቱት 27 ጽሁፎች ውስጥ እብዛኞቹ በ“አውራምባ ታይምስ” ጋዜጣ ላይ ወጥተው የነበሩ ናቸው፡፡ ለንባብ በቅትው የሚያውቁት ቀሪዎቹ ጽሁፎች ደግሞ አበበ በየወቅቱ የሚሰማውን ለመግለጽ እየጻፈ ያስቀምጣቸው የነበሩ ናቸው፡፡ “ጽሁፎቹ ኢትዮጵያ ውስጥ ባለው የፖለቲካ እና ማህበራዊ ሁኔታ ላይ የሚያተኩሩ ናቸው” ሲል አበበ ከአዲስ አበባ በስልክ ለሐሻዊ ቃና ተናግሯል፡፡ “ስላቆች ከአቤ ቶኪቻው” የተሰኘው መጽሐፍ መጀመሪያ የ

ታተመው በአሜሪካ ሲሆን ሀገር ቤት ከታተመው አምሳያው በሶስት ጽሁፎች የላቀ ነው፡፡ አበበ ከአገር ቤት አስቀድሞ መጽሀፉን በውጭ ያሳተመው እርሱ የሚጽፋቸውን ዓይነት ተቺ ጽሁፎች የያዘ መጽሐፍ ለማሳተም የሚደፍር አታሚ በመጥፋቱ እንደሆነ ይገልጻል፡፡ ይህንን የአታሚ ችግር “የአቤ ቶኪቻው ሽሙጦች” በሰተኘው የመጀመሪያው መጽሐፉ ጊዜ መቅመሱንም ይናገራል፡፡ “ ‘የአቤ ቶኪቻው ሽሙጦች’ን ማተሚያ ቤቶች አልቀበልም ብለውኝ ነበር” ሲል ለሐበሻዊ ቃና ያስረዳል፡፡ የአሁኑን መጽሀፍ አሜሪካ አስቀድሞ ካሳተመ በኋላ በኢትዮጵያም ለመድገም ተመሳሳይ ችግር ገጥሞት እንደነበር ይናገራል፡፡ ሆኖም በስተመጨረሻ “ስም የለሽ” ማተሚያ ቤት ለማሳተም መብቃቱን ይገልጻል፡፡ አበበ በ“አቤ ቶኪቻው” ሰም የሚያቀርባቸውን ጽሁፎች እን

ደቀድሞው በ“አውራምባ ታይምስ” ሳይሆን በ “ፍትህ” ጋዜጣ ላይ ማቅረብ ቀጥሏል፡፡ ጹሁፎቹን መከታተል የሚፈልጉ በፍትህ ኦፊሴሊያዊ ድረ ገጽ www.feteh.com ያገኟቸዋል፡፡

ከመጽ

ሐፉ

የተ

ወሰደ

ከመጽሐፉ የተወሰደ

የነዳጅ ዋጋ ጭማሪው ጋሽዬ እንዳሉት… (ሁልጊዜ እንደባዳ በማዕረግ ስማቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ እያልኩ እንዳላርቃቸው ሰግቼ ነው ጋሼ ማለቴ!) እናም ጋሽዬ እንዳሉት የሚያመጣው ለውጥ ኢምንት በሆነ ኖሮ እርሳቸውም፣ እኔም፣ ድርጅታቸውም፣ ድርጅቴም፣ መንግስታቸውም፣ መንግስቴም ምነኛ ደስ ባለንና ብርጭቆ ባጋጨን ነበር፡፡ ነገሩ ግን የተገላቢጦሽ ሆነና ብርጭቆ ለማጋጨት አልታደልንም! በምትኩ በነዳጅ ጭማሪው ሳብያ ብዙ ነገር ጨምረውባቸው ከተከፉ ሰዎች ጋር እየተጋጨን እንገኛለን… ( “ለአባይ ያሰብኩትን ነዳጅ ወሰደብኝ” በሚል ርዕስ ከቀረበው የተወሰደ)

Page 16: Habeshawi kana 004

ሐምሌ 30-ነሐሴ 13 ቀን 2003 (August 6-19, 2011)ሐበሻዊ ቃና16

የጉዞ ማስታወሻ

ወደ ታንዛንያ መዲና ዳሬ ሰላም ከመጣሁ ሰባት ወር አለፈኝ። ወደዚህ

ስመጣ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰማኝን ግን አሁንም አስታውሰዋለሁ። በዕለቱ የነበረው የሙቀት መጠን በዲግሪ ሴልሺየስ ሲለካ 37 ደርሶ ነበር። ከወበቁ የተነሳ ልክ ከአውሮፕላን ስወጣ ለቅጽበትም ቢሆን ኦክሲጅን የተቋረጠ ነበር የመሰለኝ። በውሃ ውስጥ ለመተፈንስ እንደመሞከር በሉት። ራሴን ከሁኔታው ጋር እስካላምድ ጥቂት ጊዜ ወስዶብኝ ነበር። ሰውነቴ ከሙቀቱ ጋር ሲላመድ አ

ይኖቼ ዙሪያ ገባውን ማስተዋል ጀመሩ። ለአስር ወራት ቤቴ የሚሆነውን ሀገር እቃኝ ገባሁ። አፍቃሪዎቿ ዳር እያሉ የሚያቆላምጧት ዳሬ ሰላም ውብ ናት። የባህር ዳርቻዋቿ ትንፋሽ አስቆራጭ ናቸው። በፖስት ካርድ ላይ ብቻ ስታዩት የከረማችሁት ቦታ እንደመገኘት ነው። በዚያ ዝናብ እንኳ ጠብ የማይል በሚመስልበት ሞቃታማ አየር ከተማይቱ እንዴት በአረንጓዴ እንደተሸፈነች መመልከት ያስገርማል። ከከተማይቱ እምብርት በቀር ዛፎች የትም ይገኛሉ። ልክ እንደአዲስ አበባ ሁሉ ዳሬሰላ

ምም ወደ ጎን እየተለጠጠች የመጣች ይመስላል። ረዘም ያሉ ህንጻዎችን ግን የምታገኙት በከተማይቱ መሃል ብቻ ነው። እነርሱም ቢሆኑ እንደአዲስ አበቤዎቹ እንኳ አይረዝሙም። የከተማይቱ መሃል እንደ ዳርቻዎቹ ሰፊ ቦታ ያካለለ አይደለም። ዳርቻዎቹ ሰፋፊና በየጊዜው እንደመንግስት እርሻ ወደ ጎን የሚሰፉ ናቸው። በርካታ ታንዛንያውያን የስራ ገበታቸው መሃል ከተማ ቢሆንም የሚኖሩት በከተማ ዳርቻዎች ነው። በተጨናነቀው እና ጫጫታ በበዛበት የከተማይቱ እምብርት መኖር የመረጡ ታንዛንያውያን ጥቂት ናቸው። አብዛኞቹ የመሃል ከተማ ነዋሪዎች ህንዶች እና አረቦች ናቸው። ስለ ህንዶች ካነሳሁ ዘንድ ዳሬ ሰላ

ም ከመጣሁ በኋላ የተደነቅሁበትን ነገር ላጫውታችሁ። በመላው ታንዛንያ ሂዱ ህንዶችን የትም ታገኛላችሁ። አብዛኛው ንግድ የተያዘው በእነርሱ ነው። በህንድ ውቅያኖስ ዳርቻ የተገነቡትን አብዛኞቹን የዳር ሪዞርት በባለቤትነት የሚያስተዳድሩት እነርሱ ናቸው። የጌጣጌጥ ሱቆች እና ቡቲኮችንም የተቆጣጠሩት ህንዶች ናቸው። ምስራቅ አፍሪካን ለመጀመሪያ ጊዜ የሚጎበኝ ኢትዮጵያዊ በዚህ መደመሙ አይቀርም። አብዛኞቹ የእኛ አገር የንግድ ስራዎች ባለቤትነት በራሳች የተያዘ ነው። እዚህ አገር እንደሚታየው ህንዶች የዕለት ተዕለት ህይወታችን አካል ሊሆኑ ቀርቶ ከአስተማሪነት በዘለለ በትልቅ ባለሀብት ደረጃም መመልከት የጀመርነው ከቅርብ አመታት ወዲህ ነው።

እንደሰማሁት ከሆነ ህንዶቹ በታንዛንያ ለዘመናት ከመቆየታቸው የተነሳ ኑሯቸውን ሙሉ ለሙሉ በሀገሪቱ መስርተው መኖር ከጀመሩ ቆይተዋል። ብዙዎቹ ልጆቻቸውን የወለዱት በታንዛንያ ነው። በታንዛንያ ተወልደው ካደጉት ህንዶች ውስጥ አብዛኞቹ እናት ሀገር ህንድን ተመልክተው አያውቁም። የታንዛንያ ዜግነት ስላላቸው ከሀገሬው ተወላጆች እኩል መብት አላቸው። በንግድ ስራዎች ላይ ባላቸው ብቃት የተነሳም ከታንዛንያውያን የተሻለ የተደላደለ ኑሮ ለመኖር ችለዋል።ህንዶች ታንዛንያን ቤታቸው አድርገ

ው መኖር የመረጡት ኑሮ በዚህ አገር ርካሽ በመሆኑ እና የገቢ ግብር ስለማይከፍሉ እንደሆነ የአገሬው ሰዎች አጫውተውኛል። ህንዶቹ ጥሩ ይከፈላቸዋል፤ በርካታ ገንዘብም ይቆጥባሉ፤ ስለዚህም አሪፍ ኑሮ ይኖራሉ። ይህቺ አገር በአገራቸው የማይገኙትን አይነት ኑሮ እና መንደላቀቅ ብትሰጣቸውም አብዛኞቹ ህንዳውያን ግን ከአገሬው ሰው ጋር አይቀላቀሉም። በሌላው አገር አንደሚያደርጉት ሁሉ የሚጋቡት ከመሰሎቻቸው ጋር ነው። በአጋጣሚ ያገኘሁት አንድ ህንዳዊ ያጫወተኝ ለዚህ ሁነኛ ምሳሌ ይሆናል። እርሱ እንደገረኝ ከሆነ በህንድ የሚኖሩት ቤተሰቦቹ የሚያገባትን መርጠውለታል። በዚያን ጊዜ ከዚህ ቀደም አይቷት እንኳ የማያውቀውን ህንዳዊት ለመግባት ወደ ህንድ ለመጓዝ እየተዘጋጀ ነበር። ጋብቻውን በህንድ ከፈጸመ በኋላ ደግሞ ባለቤቱን ወደ ታንዛንያ ይዞ ይመለሳል። ከዚያ ልጆች ይወለዳሉ፣ የታንዛንያዊ ዜግነተም ያገኛሉ፣ የህንዶች የበላይነትም በተተኪዎቹ እንደተጠበቀ ይቆያል። ከህንዶች ቀጥሎ አገሩን የወረሩት ቻይ

ናውያን ናቸው። እነርሱም እንደጎረቤቶቻቸው የሚቆጣጠሯቸው ንግዶች እና ድርጅቶች አሏቸው። ታንዛንያውያን ከዚህ በኋላ ነው የሚመጡት። በክብር ደረጃ ካየነው ታንዛንያውያን በገዛ አገራቸው ሶስተኛ ደረጃ ላይ የሚቀመጡ ናቸው። ኬንያውያን እንኳ በብዙ ድርጅቶች ውስጥ ከእነርሱ የተሻለ ቦታዎች ይዘዋል። እንዲህ አይነት ሁኔታዎችን ተመልክታችሁ ታንዛንያውያን የት ቦታ ላይ እንዳሉ መገመት ትችላላችሁ። ለዚህ ደግሞ ታንዛንያውያን ራሳቸው የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ አለ። ስለታንዛንያውያን ሲነገር እንደምሰማ

ው እና ራሴም እንደታዘብኩት ህዝቡ በተፈጥሮ በጣም ዘገምተኛ ነው። ምንም ነገር ይስሩ ምንም ፈጠን የማለት ሁኔታ አይታይባቸውም። ዋና ዋና የንግድ ዘርፎች እና ቁልፍ የሆኑ የድርጅት ቦታዎች በውጭ ዜጎች ሲያዙ የበይ ተመልካች የሆኑበት አንዱ ምክንያት ይህ ይመስለኛል። ቀላል ምሳሌ ላቅርብ። ታንዛንያ ላይ ወደ አንድ ምግብ ቤት ጎራ አላችሁ እንበል። ምግብ ታዛላችሁ። ትዕዛዛችሁን የተቀበለው አስተናጋጅ ከምግብ ጋር የሚመለሰው ምግብ ማዘዛችሁን ከረሳችሁ በኋላ ሊሆን ይችላል። አንዲት ቀላል ነገር ለማድረግ “ዘመናት” ይ

ወስድባቸዋል። ስለምግብ ቤት ካነሳሁ አይቀር ታንዛ

ንያውያን ስለሚያዘወትሯቸው ምግቦች ጥቂት ልበላችሁ። እኛ እንጀራ ሳንበላ አንድ ቀን ለማሳለፍ እንደሚከብደን ሁሉ ታንዛንያውያንም ኡጋሊ እና ሩዝን ሳይቀምሱ ማደር አይሆንላቸውም። ኡጋሊን ለማታውቁ የእኛኑ ገንፎ ማለት ነው። ገንፎው የሚሰራው ከበቆሎ ዱቄት ሲሆን ለመባያነት መረቅ (ሶስ) ይጠቀማሉ። ማባያው ግን እንደ እኛ በበርበሬ ወይም በሚያቃጥል ቅመማ ቅመም የሚሰራ ሳይሆን ከስጋ ወይም ከተቀቀለ ባቄላ የሚሰራ ነው። በገጠሪቱ ኢትዮጵያ እንደሚዘወተረው ታንዛንያውያን ገንፏቸውን የሚበሉት በእጃቸው ነው። ዶሮ ሌላው ተዘውታሪ ምግብ ነው።

ዶሮ በኢትዮጵያ የሚያገኘውን “ክብር እና ፍቅር” እዚህ ቢሳል እንኳ ጠብ አይልልትም። በኢትዮጵያ አመት በዓል በደረሰ ቁጥር ዶሮ ለመብላት የነበረንን ጉጉት ሳስበው እና እዚህ ዶሮ ወደ ዕለት ምግብ የወረደበትን ሁኔታ ሳጤን ግርም ይለኛል። እኛ አገር ዶሮ የምንበላው ግፋ ቢል በዓመት ሶስቴ ወይም አራቴ ነው። እዚህ ግን ዋጋው ርካሽ በመሆኑ ከዕለት ገበታ ዝርዝር አይጠፋም። አንድ መረሳት የሌለበት ሐቅ ግን አለ። የእዚህ አገር ዶሮ በመጠን ከእኛም በጣም ያንሳል። ስብ እንዳይከማቹ በሚል ይመስላል ዶሮዎቹ እምብዛም እንዲያድጉ አይፈልጉም። ገና አደግ ሲሉ ቢላ አንገታቸው ላይ ያርፋል። የለጋ መሆናቸው ነገር ዶሮ በአገር ቤ

ት የሚያገኘው የነበረውን ሌላ “እንክብካቤም” አሳጥቶታል። እኛ አገር ዶሮ ታርዶም ቢሆን ተገቢው የ“እጥበት እንክብካቤ” ያገኛል። እዚህ እንደዚያ አይደለም። አስተጣጠባቸው እንዲያው ለኮፍ ለኮፍ ነው። በዚህ ምክንያት ዶሮዎቹ ተጠብሰውም ቢሆን ለመብላት አልደፍርም። አስተጣጠቡን ሳስብ የመብላት ፍላጎቴ ይቆለፋል። ሌሎች ምግቦቻቸውን ለመብላት ያለኝ ፍላጎትም ተመሳሳይ ነው። ደግሞ ብቻዬን አይደለሁም። በርካታ ኢትዮጵያውያን ከምግቦቻቸው ጋር ለመላመድ ሲቸገሩ አስተውያለሁ። ኢትዮጵያውያኑ እኔ በአብዛኛው እንደማደርገው ወይ የራሳቸውን ምግብ ያበስላሉ አሊያም የአገሬው ምግብ ምርጫቸው ውሱን ነው። ከታንዛንያውያን ጋር የምግብ አስተጣ

ጠብ ላይ የተለያየ አቋም ቢኖረንም የእጅ አስተጣጠብ ባህላችን ግን ተመሳሳይ ነው። አንድ ሰው ከመብላቱ በፊት እና በኋላ የጣት ውሃ ይቀርብለታል። ምግብ ካዘዙ በኋላ ለመታጠብ ብድግ ማለት በአገሬው ምግብ ቤቶች ዘንድ አያስፈልግም። በሞቃታማው አገር የሞቀ ውሃ በማስተጠቢያ ተደርጎ ወዲያውኑ ይመጣሎታል። እንደ ዶሮ ምግባቸው ሁሉ ሌላው ል

ለምደው ያልቻልኩት ነገር የታንዛንያ የታክሲ ትራንስፖርት ጉዳይ ነው። በነገራችን ላይ ከኢትዮጵያ ጋር ሲነጻጸር በታንዛንያ መኪና በጣም ርካሽ ነው። ኢትዮጵያ በጣም ውድ የሚባለው ቪት

ዝ የተሰኘው መኪና እዚህ በሁለት ሺህ ዶላር አሊያም ከዚያ ባነሰ ማግኘት ይቻላል። መኪና እንዲኖራቸው እየተመኙ አቅም ላጠራቸው ኢትዮጵያውያን ታንዛንያ ህልማቸውን አንዲኖሩ ታደርጋለች። ታንዛንያውያን ይህንን የመኪና ዋጋ

መርከስ በአግባቡ ተጠቅመውበታል። በርካታ ታንዛንያውያን በቤተሰብ ደረጃ ቢያንስ አንድ መኪና አላቸው። ለዚህም ነው የታንዛንያ መንገዶች በተለይ በስራ መግቢያ እና መውጫ ሰዓት በሚያስመርር ሁኔታ የሚጨናነቁት። አገሪቱ ከጎረቤቶቿ ኬንያ እና ኡጋንዳ በተሻለ ሰፋፊ መንገዶች ቢኖሯትም ከአንድ ቦታ ወደ አንድ ቦታ መንቀሳቀስ ረጅም ጊዜ ይወስዳል። በተለምዶ ከሰባት እስከ 10 ደቂቃ መውሰድ የሚገባው መንገድ አንድ ሰዓት እና አንድ ሰዓት ተኩል ቢወስድ አይገረማችሁ። ይህ ታዲያ በስራ ሰዓት ነው። በስራ መግቢያ እና መውጫ ሰዓትማ እንደአገሬው ሰዎች በታክሲው ውስጥ ቁጭ ብሎ እንቅልፍ መተኛት ሳይሻል አይቀርም። ቢያንስ የእንቅልፍ ሰዓት እዚህ አካክሶ ቤት ሲገባ ሌላ ነገር መስራት ያስችላል። መኪና የሌላቸው የዳሬ ሰላም ነዋሪዎ

ች ሶስት የመጓጓዣ መንገዶችን ይጠቀማሉ። የመጀመሪያው እና ርካሽ በመሆኑ በብዙዎች ዘንድ የሚመረጡት “ዳላ ዳላ”ዎች ናቸው። “ዳላ ዳላ” በሚለው ስያሜ የሚጠቀሙት በእኛ ሀገር ሚኒ ባስ ብለን የምንጠራቸው እና ኮስተር እና ሃይገር ባስ የመሳሰሉት ጭምር ናቸው። “ዳላ ዳላ”ዎች ለአንድ ጉዞ የሚጠይቁት ከ200 እስከ 350 የታንዛንያ ሽልንግ ነው።በወቅቱ ምንዛሬ መሰረት አንድ የኢትዮጵያ ብር ከ100 የታንዛንያ ሽልንግ ጋር ይመጣጠናል። እንደ “ዳላ ዳላ”ዎች በ“አስገራሚው”

የታንዛንያ ትራፊክ ሕግ የተጠቀመ የለም። የትራፊክ ሕጉ እንደፈለጉ እንዲጭኑ ፈቅዶላቸዋልና ነው አስገራሚ ማለቴ። ለ“ዳላ ዳላ”ዎች ትርፍ ሰው ወይም ከአቅም በላይ የሚባል ነገር የለም። በአንድ ሚኒባስ ውስጥ ከ25 እስከ 30 ሰው ታጭቆ አስቡት። በዚያ የታንዛንያ ሙቀት ሰው በሰው ላይ ተደራርቦ ትንፋሽ ያሳጥራችኋል። በዚያ ላይ የፈለጉበት ቦታ ላይ ሲደርሱ ወራጅ ብሎ ዱብ ማለት የለም። “ዳላ ዳላ”ዎች ልክ እንደ አዲስ አበባ አውቶብሶች ሁሉ ማቆሚያ በእነሱ አጠራር “ስቴጅ” አላቸው። ማቆሚያዎቹ በየአጭር ርቀቱ መገኘታቸው በ

ዳር እና ዛንዚባርበስመኝሽ ይቆዬ

በተለይ ለሐበሻዊ ቃና

Page 17: Habeshawi kana 004

ሐምሌ 30-ነሐሴ 13 ቀን 2003 (August 6-19, 2011) ሐበሻዊ ቃና 17

የጉዞ ማስታወሻአሊያም በባህር። በአውሮፕላን ከሰላሳ ደቂቃ ያነሰ ጊዜ የሚወስደው ጉዞ በባህር ሲሆን እንደሚጠቀሙበት ዓይነት የጀልባ ዓይነት ከሁለት ሰዓት እስከ ሶስት ይፈጃል። ምረጭ ብባል በባህር መጓዝን እመርጣለሁ። “ፌሪ” ተብለው በሚታወቁ የጀልባ ዓይነቶች የሚደረግ ጉዞ ምን እንደሚመስል ማወቅ ፈልጌ ነበር። ነገር ግን ጋባዦቼ አስቀድመው የአውሮፕላን ትኬት ልከው ነበርና የባህር ጉዞ ሲያምረኝ ቀረ። ከዋናው የታንዛንያ ክፍል በ25 ማይል

ርቀት ላይ በምትገኘው ደሴት ላይ ባለው አነስተኛ እና የተጨናነቀ አየር ማረፊያ ስደርስ ዛንዚባር ማለት የባህር ዳርቻ እና መዝናናት ብቻ እንዳልሆነ ተረዳሁ። ከአየር ማረፊያው ወደ ከተማ በምጓዝበት ጊዜም የተመለከትኩት ይህንኑ የሚያረጋግጥ ነበር። የማርፈበት ሆቴል የሚገኘው በከተማይቱ መሃል ነው። ከዛንዚባር ወደብ አቅራቢያ ስለሚገኝ አካባቢው ሁሌም እንደተዋከበ ነው። ከዳሬ ሰላም ከመነሳቴ በፊት አስበው የነበረው በባህር ዳርቻ ባለ ሪዞርት እንደሚያሳርፉን እና ለማየት የጓጓሁትን እንደልብ ለመኮምኮም ነበር። መዝናናቱ ሲቀር ስለዛንዚባር ከዚህ ቀደም ያልሰማኋቸውን ነገሮች ለማሰስ ተነሳሁ። ብዙ ርቀት መጓዝ አላስፈለገኝም። ያረ

ፍኩበት ሆቴል በራሱ ለካ የሚነገርለት ታሪክ አለው። ግራንድ ፓላስ ይባላል። በዛንዚባር ውስጥ ካሉት ህንጻዎች አሳንሰር (ሊፍት) የተገጠመለት ብቸኛው ህንጻ እንደሆነ ነገሩኝ። ይህንን ስሰማ “ስቶን ታውን” ተብሎ የሚጠራውን የከተማ ክፍል ለማየት ይበልጥ ጓጓሁ። “ስቶን ታውን” የከተማይቱ ጥንታዊ ክፍል ነው። ላለፉት 200 ዓመታት እምብዛም ሳይለወጥ እንደነበረ የቆየ ነው። በጠባቦቹ የስቶን ታውን መንገዶች ስጓዝ ግን ይህንን ቦታ ከዚህ ቀደም ያየሁት ዓይነት ስሜት ተሰማኝ። የመንገዶቹ አቀያየስ፣ የቤቶቹ አሰራር፣ የሰዎቹ አለባበስ ሁሉም ማለት ይቻላል ለእኔ እንግዳ አልነበሩም። ስቶን ታውንን ከዚህ ቀደም ተመልክቼው አላውቅም። በህልሜ እንኳ እንዲህ ዓይነት አካባቢ መጓዜን አላስታውስም። “እና ለምንድነው ያየሁት ያየሁት የመሰለኝ?”ድንገት አንድ ነገር ብልጭ አለለኝ። እ

ንዴ!....። አካባቢውን የሚመስል ቦታ የት እንደተመለከትኩ አስታወስኩ።....አዎ! በእርግጥም ስቶን ታውን የሚመስለው ጀጎልን ነው። የሐረሩን ጀጎል። ስቶን ታውን የጀጎል ትልቁ ግልባጭ ነው ብዬ ብናገር ስህተተኛ የምባል አይመስለኝም። ድንቅ አለኝ። የአገሬን ቦታ ባህር ተሻግሬ ስመለከተው እንዴት ድንቅ አይለኝ። በስቶን ታውን ጠባብ መንገዶች መጓ

ዜን ቀጥያለሁ። አንዳንዶቹን መንገዶች ብሎ ከመጥራት መተላለፊያ ማለት ይቀላል። እንደ እኔ ለመጀመሪያ ጊዜ ይራመድባቸው የያዘ ደግሞ መደናገሩ አይቀርም። ከአንዱ ቅያስ ወደ ሌላኛው እያለ ሲባዝን ሰዓታት መፍጀቱ አይቀርም። ደግነቱ መተላለፊያዎቹ በራሳቸው

እና ዳር እና ዳር የተገጠገጡት ቤቶች የሚያፈዙ አይነቶች ናቸው። አብዛኞቹ ቤቶች የተገነቡት ከመቶ አመት በፊት ቢሆንም ምንም ሳይነካኩ እንደነበሩ አሉ። ብዙዎቹ በተለያየ ዲዛይን በእጅ የተቀረጹ የእንጨት በሮች ያላቸው ናቸው። እነዚህ ውብ የኪነ ህንጻ ውጤቶች ሳይሆኑ አይቀርም ስቶን ታውንን እንደ ጀጎል ሁሉ በተባበሩት መንግስታት የባህልና የሳይንስ ድርጅት (ዩኔስኮ) አማካኝነት በዓለም ቅርስ መዝገብ ላይ እንድትሰፈር ያደረጋት። ከተማይቱ ትንሽ እንደመሆኗ መጠ

ን እና መንገዶቿም መተላለፊያ የሚባሉ ዓይነት በመሆናቸው አብዛኛው የአገሪቱ ነዋሪ የህዝብ መጓጓዣ አይጠቀምም። ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ለመሄድ የእግር ጉዞ ወይም ብስክሌት መጠቀምን ይመርጣሉ። ራቅ ብለው በመንደሮች ውስጥ የሚኖሩ ወደ ከተማ ለመምጣት “ዳላ ዳላ” ይጠቀማሉ። “ስፔሻል ሃይር” እዚህም አለ። ከአንዱ ሱቅ ወደ ሌላ መሄድ የሰነፈ እነዚህን ኮንትራት ታክሲዎችን ይጠቀማል። ገና በቅጡ ተደላድሎ በታክሲ ውስጥ ሳይቀመጥ ግን የሚፈልገው ቦታ ይደርስና ይገላገላል። ስቶን ታውን አንድ የዛንዚባር ምልክ

ት እንደሆነው ሁሉ ህዝቦቿም የደሴቲቱ መለያ ተደርገው ይወሰዳሉ። ዛንዚባሪያውያን ዋናውን የታንዛንያ ክፍል እና ደሴቶችን ያቀፈችው እና በኦፊሴል “ሪፐብሊክ ኦፍ ታንዛንያ” በመባል የምትታወቀው አገር አካል ቢሆኑም ራሳቸውን በራሳቸው የሚያስተዳድሩ ናቸው። የራሳቸው ፕሬዝዳንት፣ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት እና ምክትል ፕሬዝዳንት አላቸው። በህዝብ በቀጥታ የሚመረጡ 150 አባላት ያሉት ፓርላማም የአስተዳደሩ አካል ነው። “ዛንዚባሪ” ተብለው የሚጠሩት የደሴ

ቲቱ ተወላጆች 800 ሺህ ይጠጋሉ። ዘጠና በመቶ የሚሆኑት ዛንዚባሪያውያን የእስልምና እምነት ተከታዮች ሲሆኑ ቀሪዎቹ የክርስትና እና ሂንዱይዝም ሃይማኖትን ይከተላሉ። በዛንዚባር የእስልምና ተከታዮች እንደመብዛታቸው አረብኛ ቋንቋ የሚዘወትር የሚመስለው አይጠፋም። ዛንዚባሪያውያን ግን ከታንዛንያውያን በተሻለ በተሻለ ጥርት ያለውን ስዋህሊ የሚያቀላጥፉ ናቸው። በመላው ዓለም ታንዛንያውያን ትክክለኛ የስዋህሊ ቋንቋ ተናጋሪዎች ተደርገው መወሰዳቸው ሲታሰብ የዛንዚባሪያውያንን የቋንቋ ደረጃ ከፍ ያደርገዋል።ታንዛንያውያን በእንቅስቃሴዎቻቸው

ሁሉ ዘገምተኞች እንደሆኑ አጫውቼያችዋለሁ። ዛንዚባሪያውያን ይብሳሉ። አረ! አንዳንዶች ለንጽጸር ሁሉ አይቀርቡም። እንደ መሃል ሀገር ነዋሪዎች ሁሉ ዛንዚባሪያውያን ንግድ ላይ የሉበትም። እዚህ በህንዶች ምትክ አረቦች አብዛኛውን ነገር ተቆጣጥረውታል። ዛንዚባሪያውያን ንግድ ብቻ ሳይሆን ሌላውንም ስራ በቅጡ አይሰሩም። የዛንዚባሪያውያን የስራ ባህል አስመልከቶ አንድ ጓደኛዬ ያጫወተኝን ላካፍላችሁ። እንደአርሱ አባባል ከሆነ ዛንዚባሪያውያን በቀ

ኑ ውስጥ የሚሰሩበት ሰዓት ቢደመር ሁለት ሰዓት ብቻ ይሆናል። ወደ ቢሮ ከጠዋቱ ሶስት ሰዓት እ

ስከ አራት ባለው ጊዜ ይገባሉ። ለሻይ እረፍት እና ለምሳ ይወጣሉ። በወጡበት የሚከወኑት ዕለታዊ ስራ ደግሞ አለባቸው። ለሚስቶቻቸው አስቤዛ መሸመት። ከሌላ ሰው መረጋገጥ አልቻልኩም እንጂ የዛንዚባር ሴቶች ገበያ መውጣት አይፈቅድላቸውም አሉ። ባሎቻቸው በምትኩ ሸመታውን ያደርጉላቸዋል። የዛንዚባር ወንዶች በሃይማኖታቸው ምክንያት ሁለት እና ሶስት ሚስት ማግባት ስለሚፈቀድላቸው ያለባቸውን የ“ስራ ጫና” እና የሚያጠፉትን ሰዓት መገመት ትችላላችሁ። ከዕለታዊ የገበያ ስራቸው ሲመለሱ ደግሞ የማይስተጓጉለው የጸሎት ስነስርዓት አለ። ቀኑ እንዴት እንደሄደ እንኳ ሳይውቁት ወደ ቤት መሄጃቸው ይደርሳል። ህይወት እንዲህ እያለች ትቀጥላለች።ዛንዚባሪያውያን ሰላማዊ ናቸው።

እንደ ህዝቦቿ ሁሉ የአገሪቱ የጸጥታ ደህንነት አስተማማኝ ነው። ከአገሪቱ ይበልጥ የወደደደኩትም ይህንን እንደፈለጉ በማንኛውን ሰዓት፣ ቀንም ሆነ ማታ፣ ወደየትኛውም ቦታ ቢሄዱ ምንም ችግር የማይጋጥም መሆኑ ነው። በመንገዶች ላይ ፖሊስ እንኳ አልተመለከትኩም። ወደ ዛንዚባር ያመጣኝ ነገር የሙዚቃ ድግስ ነው ብያችሁም አልነበር። ታዲያ ይህ የሙዚቃ ፌስቲቫል የሚካሄደው በምሽት ነው። በአብዛኛው እስከ እኩለ ለሊት ገደማ ድረስ ይቆያል። በዚህ ዝግጅት የሚታደሙ ከመላው ዓለም የመጡ ሙዚቀኞች እና ተመልካቾች ያለምንም ችግር፣ ያለምንም ጥበቃ ሲወጡ እና ሲገቡ ተመልክቼያለሁ። የእጅ ቦርሳው የወደቀበት ሰው ከ

ሰዓት ቦታ ወደ ነበረበት ቦታ ተመልሶ ፈልጎ የሚያገኝበት አገር ነው። የማያውቁትን እንግዳ ሰው ከመንገድ ጠርተው የሚገዙትን ነገር ነግረው ገንዘብ አስጨብጠው ይላኩት። አይጨንቁ። ከአዘዙት ነገር ጋር ተመልሶ ይመጣል። ሌላ ምሳሌ። “ስፔሻል ሃየር” ተኮናተሩ እንበል። ሙሉ ክፍያውን ለመስጠት ገንዘብ አልበቃዎትም ወይም አልያዙም። ይህንኑ ለሹፌሩ አስረድተው ነገ ተመልሶ እንዲመጣ ይንገሩት። አምኖዎት ይሄዳል።እንዚህ የዛንዚባር እውነታዎች በ

ደሴቲቱ ልንመለከተው ከምንቋምጠው ውጭ ብዙ የሚታይ ነገር እንዳለ አስረጂ ይመስሉኛል። ዛንዚባር ታሪክ እና ባህል የሞላባት አገር ናት። ይህንን የዛንዚባር ገጽታ ከማይጠገበው የባህር ዳርቻ ቆይታ ጋር ማግኘት እድለኝነት ነው። እኔ እድለኛ ነበርኩ። በህይወት ሳሉ መታየት ከሚገባቸው ድንቅ ቦታዎች አንዱን ተመልክቻለሁና።

ጀ እንጂ የእርሶ መውረጃ በመሃል ሲሆን አንዱ ማቆሚያ ደርሰው ወደ ሚፈልጉበት ቦታ መመለስ ግድ ነው። “ዳላ ዳላ”ዎችን መጠቀም እንግዲህ ይህንን ሁሉ ችለው ነው። ተረቱስ “ልጅ ሲወዱ ከነ***” አይደል። “ዳላ ዳላ” አያሻኝም ያለ እንደ ርቀቱ

ሁኔታ ከ1500 እስከ 5000 ሺህ የታንዛንያ ሽልንግ ከፍሎ በ“ባጃጅ” መሄድ መብቱ የተጠበቀ ነው። ባጃጆች በበርካታ የኢትዮጵያ ከተሞች የሚገኙ በመሆናቸው ብዙዎች ታውቋችዋላችሁ ብዬ እገምታለሁ። ችግሩ ባጃጆች ወደ ከተማ መሃል መግባት አይፈቀድላቸውም። ልክ እንደ አዲስ አበባ በዳርቻዎች ላይ ብቻ ነው የምታገኟቸው። ክፍት በመሆናቸው ሙቀት ባለባቸው እንደ ድሬዳዋ ባሉ የሀገራችን ክፍሎች ተወዳጅ እንደሆኑት ሁሉ ዳሬ ሰላም ላይም ለአየር ጸባዩ ተመራጭ መጓጓዣ ናቸው። ከባጃጅ ለጥቆ ያለው ሶስተኛው አማራ

ጭ መጓጓዣ እነርሱ “ስፔሻል ሃየር” እኛ “ኮንትራት ታክሲ” ብለን የምንጠራው ነው። ይህ የመጓጓዣ ዓይነት ከሁሉም የሚወደድ በመሆኑ ለአገሬው እንግዳ በሆኑ፣ ጥሩ ገቢ ባለቸው ወይም የምሽት ጉዳያቸውን ከውነው በሚመለሱ ሰዎች ዘንድ ተመራጮች ናቸው። እነዚህን የመጓጓዣ አይነቶች እየተጠቀምኩ ዳርን ከላይ ታች አዳረስኩ። ከከተማይቱ የአኗኗር ዘይቤ ጋር ለመላመድ አንድ ወር እንኳ አልወሰደብኝም። ሌሎች የአገሪቱን ክፍሎች ለመመልከት ግን ወራት መጠበቅ ነበረብኝ። በአገሪቱ ውስጥ ካሉ ቦታዎች ታሪካዊ

እንደሆነችው የዛንዚባር ደሴት ልቤን ያማለለው የለም። ስለ ዛንዚባር ብዙ ሰምቻለሁ። ስለሚያማምሩ የባህር ዳርቻዎቿ፣ ስለ ድንቅ የተፈጥሮ ስጦታዎቿ፣ ስለ አይጠገቤ ዙሪያ ገባዋ፣ ስለ ታሪካዊ ህንጻዎቿ እና ዋና ከተማዋ…ብዙ ብዙ ነገር። ወደዛንዚባር ለመጀመሪያ ጊዜ የሄድኩት እንደ ቱሪስት ለጉብኝት አልነበረም። በጋዜጠኝነት ሙያዬ በደሴቷ ላይ በየዓመቱ በደማቅ ሁኔታ የሚደገሰውን የሙዚቃ ዝግጅት እንደዘግብ ተጋብዤ እንጂ። የሙዚቃ ዘግጅቱ በዓለም ዙሪያ ስሙ የገነነ ቢሆንም በእርሱ ላይ ከመገኘት በላይ ያጓጓኝ በተንጣለለ ነጭ አሸዋ ላይ ሆኖ ህንድ ውቅያኖስ ዳር ላይ ሆኖ ለጥ ያለውን ሰላማዊ ውሃ መመልከት ነበር። ይህን በአእምሮዬ የታተመ ምስል በእውን ለመመልከት ጓጉቼያለሁ። ወደ ዛንዚባር ለመጓዝ ያሉት በአየር አ

ማራጮች ሁለት ናቸው። ወይ በአየር

ዳር እና ዛንዚባርፎቶዎች- ተስፋለም ወልደየስ

Page 18: Habeshawi kana 004

ሐምሌ 30-ነሐሴ 13 ቀን 2003 (August 6-19, 2011)ሐበሻዊ ቃና18

የከተማ ቧልት

በጀርባዬ ተኝቻለሁ፡፡ በተንቀሳቃሽ አልጋ ላይ ተጋድሜ ወደ ቀዶ ጥገና ክፍል እየተነዳሁ ነው፡፡ ብዛት ያላቸው ሐኪሞች ያሉበት፣ አጥንት የሚሰብር ብርድ ያለበት ክፍል ገባሁ፡፡ አፋቸውን በጨርቅ ያሰሩ ሐኪሞች ከበቡኝ፡፡ “በሽተኛን ክፉ ነገር ላለመናገር ይሆን አፋቸውን የሸፈኑት?” ብዬ ጠርጥሬ ሳልጨርስ አንዱ ዋዘኛ መሳይ ሐኪም ወደ እኔ ቁልቁል አንገቱን ሰብሮ “እሺ አንበሳው!” አለኝ፡፡ እንዳልፈራ ሲያግባባኝ መሆኑ ነው፡፡ በሆዴ ታዝቤ ዝም አልኩ፡፡ ይኸው ሐኪም ቃሉን ደገመው፤ “አንበሳው!” አሁን አላስቻለኝም፤ “ዶክተር እንዲህ

ከተያዙ በኋላ አንበሳነት ምን ዋጋ አለው!?” አልኩት፡፡ ሳቀ፡፡ “‹በእናንተ እጅ ወድቄ ምን አንበሳነት አለ› አለኝ እኮ!” በማለት አሻሽሎ በመናገር ባልንጀሮቹን አሳቃቸው፡፡ ወዲያው ለእኔም ማደንዘዣ ተሰጠኝ፡፡ አንበሳነትም፣ ሰውነትም ቀረና ገላዬን ለስለት አሳልፌ ሰጠሁ፤ ለቀዶ ሕክምና፡፡ ከዚህ በኋላ ነገሮች ሁሉ የሆኑት በማይጻፍለት፣ በማይነገርለት ዓለም ውስጥ እያለሁ ነው፡፡ እነሆ ነጋዴዎቻችን ሰሞኑን ከፍተኛ ማ

ጉረምረም ውስጥ ይገኛሉ፡፡ ሞገሳቸው፣ አንበሳነታቸው ጠፍቶ “የተጠየቅነው የዓመት ግብር ገቢያችንን ያማከለ አይደለም” እያሉ እንደቀውስ ብቻቸውን እያወሩ ነው፡፡ ዳቦ ሻጩ፣ ባለጠጅ ቤቱ፣ ፀጉር አስተካካዩ፣ ባለ ብስኩት ቤቱ ሁሉ ሳይቀር በተጠየቀው ግብር ኀዘን ገብቶት ንግዱን ለመተው እያሰላሰለ ነው፡፡ ከግብር ያለአግባብ መጨመር ጋር ተያ

ይዞ ክፍለ ከተማዎች ግብር ከሚከፍሉት በላይ የንግድ ፈቃዳቸውን በሚመልሱ ሰዎች እየተጨናነቁ ነው፡፡ ጉዳችን ፈላ! ምን ልንበላ? ምን ልንጠጣ? ፀጉራችንን ማን ሊያስተካክለን? ቁርስ እና ምሳችንን በብስኩት እና በሻይ ለመሸወድ ሲያምረን ከየት ልናገኝ ነው? ይሄ ሁሉ ስራ በየቀበሌው በተደራጁት የሸማቾች ኅብረት ሥራ ማኅበራት ሊሠራ ታስቦ ይሆ

ን? እንጃ! ነጋዴው እንኳን እንዲህ በግብር ተወጥሮ ሳይወጠርም በዋጋ ንረት እኛን ወጥሮናልና ከዚህ ግብር ክፍያ በኋላ ወዮልን! ጎበዝ፤ ኧረ ጸልዩልን! ወይዘሮ ንፍሮ በንግድ ሥራ ሰባት ልጆ

ቻቸውን የሚያስተዳድሩ እናት ናቸው፡፡ ንግዳቸው ደጃፋቸው ላይ የሚካሄድ ቢሆንም “ንግድ ፈቃድ አውጪ፤ ‘ቲን ነምበር’ ውሰጂ” የሚል ወዳጅ መሳይ ምቀኛ መካሪ ገጥሟቸው እንደ ትልቅ ነጋዴ ሁሉን ነገር አወጡ፡፡ ዛሬ ታዲያ በግብር ጥያቄ ምክንያት መጀመሪያ ደም ፍላት፣ ቀጥሎ ደም ብዛት ይዟቸው ለአልጋ ተዳርገዋል፡፡ ሲያሳዝኑ!“አንድ ቀን ጉልቴ ላይ ከሰል ማንደጃ

ዬን እያያዝኩ ሳለ ማስታወሻ ደብተራቸውን የያዙ የቀበሌ ሰዎች ወደ እኔ መጡ፡፡ “ምን እየሸጥሽ ነው?” አሉኝ፡፡ “ቅቅል እና ጥብስ” አልኩ፡፡ እነሱም ጽፈው ሄዱ፡፡ አገር አማን ነው ብዬ ግብር ልከፍል ስሄድ ሁለት ሺህ ብር ተባልኩ፡፡ እኔ እኮ የምሸጠው ጥብስ እና ቅቅል የበቆሎ እሸት ነው፡፡” ወይዘሮ ንፍሮ ሲናገሩ እንባቸው ዐይናቸው ላይ ኳስ ሠራ፡፡ በጣም አሳዘኑኝ፡፡“የተጠየቅኩት ብር ሁለት ሺህ ብር ነ

ው፡፡ እኔ ሁለት ሺህ የሚባለውን ቁጥር የማውቀው በዓመተ ምሕረት ላይ ብቻ ነው፡፡ አሁን ያለንበት ዓ.ም. ስንት ነው? አዬ ጉዴ! ኧረ እሱም ጠፍቶኛል፡፡ በምን ምክንያት ሁለት ሺህ ብር እንደጠየቁኝ አልገባኝም” ይላሉ ወይዘሮ ንፍሮ በኀዘን እየደጋገሙ፡፡ ከዚህ ወዲያ ያለውን የወይዘሮ ንፍሮን ንግግር ገጣጥሞ ለመረዳት ይቸግራል፡፡ ለማንኛውም እንዲህ ዓይነት መዓት ውስጥ ለገባችሁ ነጋዴዎች ሁሉ እግዚሃር ይሁናችሁ! ወደ ሕመሜ ልመልሳችሁ፡፡ አንድ ወ

ዳጄ ሊጠይቀኝ ወደ ቤቴ መጣ፡፡ ይዞ የመጣው እንደሌሎች በሽተኛ ጠያቂዎች ሙዝ ወይም ብርቱካን ወይም ጭማቂ /ኡኡይ አጓጉል ነገር እየጻፍኩ ራሴን አስጎመዠሁት!/ ሳይሆን ምክር ነበር፡፡ “ለ

ፈሰሰህ ደም ሥጋ ነገር ብታገኝበት ጥሩ ነው፡፡ እንደ ቅቅል ነገር፤ ቀይ ወጥም ቢሆን፤ መረቅ ወይም ሾርባ፣ በርገር፣ ስጋ ፍርፍር፣ ዶሮ ብታገኝ ቁስልህ ቶሎ ይደርቃል፡፡ በተለይ አልጫ ጥብስ ፍርፍር ነገር ወይም ጎመን በሥጋ ዓይነት ለስላሳ ነገር… ” አለኝ፡፡ሳቄ መጣ፡፡ በጣም ሳቄ መጣ፡፡ በሽታ

በሰባበረው ድምፅ እዝን ብዬ፣ “ሌላው ያቅሙን ምናምን ይዞ ይመጣል አንተ “ሜኑ” ይዘህ መጣህ?” አልኩት፡፡ ወዳጄ እፍር አለ፡፡ በእሱ እፍረት እኔም አፈርኩ፡፡ በዘንድሮ የኑሮ ውድነት ይሄን ሁሉ ከየት ያመጣል? አልኩ፡፡ ቢሆንም ለእኔ ማዘን ነበረበት፡፡ የምግብ ዝርዝር ይዞ መጥቶ ለምን ያስጎመዠኛል? …ኧረ ኑሮ ሊያጠፋን ነው ጎበዝ! ኧረ ሊያጠፋን ነው! የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገት ቀጥሏ

ል፤ በዋጋ ንረቱ መጨነቃችንም ቀጥሏል፤ ግብሩም ቀጥሏል፤ የሚሊየነር ልማታዊ ባለሐብቶች ብዛት ቀጥሏል፤ የሚሊዮኖች መራብም ቀጥሏል፤ የተማረ የሰው ኃይል ከየዩኒቨርስቲው መውጣት ቀጥሏል፤ ሥራ አጥነቱም ቀጥሏል፤ የመብራት አልፎ አልፎ መጥፋትም ቀጥሏል፤ መብራት ወደ ጁቡቲም ተቀጥሏል፤ ሁሉ ነገር “እንደገና” ቀጥሏል፡፡እግዚሃር የተመሰገነ ይሁንና የዘገባ ም

ህዳሩ ከበፊቱ ሰፋ ብሎ ቀጥሏል፡፡ ጥጋብ እና ረሃብ ጎን ለጎን በመንግሥት ሚዲያዎች የሚዘገቡበት ጊዜ ላይ ደርሰናል፡፡ “በማንትስ ክልል በዚህ በያዝነው ክረምት አጥጋቢ የእህል ምርት እንደሚገኝ የክልሉ መንግሥት አስታወቀ” የመጀመሪያው ዜና ቢሆን፣ “በማንትስ ክልል በተከሰተው ድርቅ ለተጎዱ ወገኖቻችን የእርዳታ እህል ሊከፋፈል ታስቧል ወይም እንዴት መከፋፈል እንዳለበት ሰፊ ጥናት እየተደረገ ነው ወይም እየተከፋፈለ ነው” የሚለው ዜና ሁለተኛው ይሆናል፡፡ ታዲያ የዘገባ ምህዳሩ አልሰፋም ትላላችሁ!?

ባንድ ሻሸመኔ አካባቢ በምትገኝ ኩየራ የተባለች ትንሽ ከተማ ውስጥ ብቻውን የሚኖር ሰው ነበር፡፡ የድንች እርሻውን ለመቆፈር ቢፈልግም ከማርጀቱ የተነሳ አቅም ስላጣ በእስር ቤት ለሚገኘው አንድ ልጁ ደብዳቤ ፃፈለት፡፡“ውድ ልጄ ገብሬ፤በዚህ ዓመት ድንች የምተከል መስሎ

ስላልተሰማኝ ሐዘን ተሰምቶኛል፡፡ በእርጅና የተነሳ አቅሜ ስለደከመ እርሻውን ለመቆፈር አልቻልኩም፡፡ አንተ እዚህ ብትኖር ኖሮ ትቆፍርልኝ ስለነበር አልጨነቅም ነበር፡፡አፍቃሪ አባትህ፤ከኩየራ”ከ3 ቀናት በኋላ አባትየው ዝዋይ እሥ

ር ቤት ውስጥ ከተቀፈደደው ልጁ የተላከ ደብዳቤ ደረሰው፡፡

ከጥብስ እና ቅቅል እስከ የዘገባ ምህዳር

የፌስ ቡክ ስላቅ

የፌስ ቡክ ስላቅ

ለቀበሌ 18 ጽ/ቤት አስተዳደር፤

አዲስ አበባ

እኔ የዚህ ቀበሌ ነዋሪ የሆንኩ ወይዘሮ መላ ጥላዬ ስሆን የማመለ

ክተውም ከዚህ እንደሚከተለው ነው፡፡ እነሆ ፍሬ ነገሩም በትናት

ናው ዕለት ጎረቤቴ የሆነችው ወይዘሮ ትጓደድ መንግሥቱ፣ “ነይ ቡ

ና ጠጪ!” ብላ ቤቷ ጠራችኝ፡፡ እኔም ከጉርብትናዬና ካለን የቆየ

ወዳጅነታችን በመነሳት እሺ ብዬ ሄድኩኝ፡፡ ቡና ስንጠጣ ያለ ስኳ

ር እንደማልጠጣ እያወቀች ባዶውን ቡና ሰጠችኝ፡፡ “ምነው አንቺ

ዬ?” ስላት፣ “ስኳር ከየት ይመጣል ብለሽ ነው? እንደ ዳቦ በሰል

ፍ እየገዛሁ ላምጣልሽ ወይ!?” አለችኝ፡፡ እኔም ተናድጄ፣ ደስ አ

ይበላት ብዬ፣ ባዶውን ቡና ያለስኳር ልቤን እያቃጠለኝ ጠጣሁት፡፡

ከዚያ ቡናውን ጠጥቼ በጓሮ በኩል ልወጣ ስል፣ በአንድ ማዳበሪ

ያ ሆኖ የታሰረ እህል አገኘሁ፡፡ ቀስ ብዬም ስነካው ጤፍ መሆኑን አ

ረጋገጥኩ፡፡ ማዳበሪያውን ፈልፍዬም ሳየው ምን የመሰለ ጥቁር

ጤፍ ሆኖ አገኘሁት፡፡ ጽህፈትቤቱ በሕገ ወጥ መንገድ እህል የሚያ

ከማቹ ሰዎችን ጠቁሙ በማለት ባስታወቀው መሠረት ይኸው መ

ጠቆሜን እያሳወቅሁ እህሉም ሃያ ኪሎ ጤፍ እንደሚደርስ ባለቤ

ቷን ወይዘሮ ትጓደድን በብልሃት ጠይቄ ለማወቅ መቻሌን በትህት

ና እገልጻለሁ፡፡

ከዚህ ጋርም ተያይዞ አንድ ኪሎ ቡና መቶ ብር እየተሸጠ በሚ

ገኝበት በዚህ ወቅትም ወይዘሮ ትጓደድ ከየት አግኝታ እንዳፈላች

ማጣራት እንዲካሄድ በድጋሚ እጠይቃለሁ፡፡

የወ/ሮ መላ ማመልከቻ

“ውድ አባዬስለ እግዚሃር ስትል ያንን መሬት እንዳ

ትቆፍረው! አደራ! የገደልኳቸውን 3 ሰዎች በሙሉ የቀበርኩት እዚያ ነው!ልጅህ ገብሬ”በማግስቱ ጠዋት 2 ሰዓት ላይ የክልሉ

ና የፌዴራል የፀጥታ ሰዎችና ፖሊሶች በአካባቢው ደርሰው ጠቅላላ መሬቱን ቆፍረውና አገላብጠው አስከሬን ፈለጉ፡፡ ነገር ግን ምንም ሬሳ ሊያገኙ ስላልቻሉ ሽማግሌውን አባት ይቅርታ ጠይቀው ሄዱ፡፡ በዚያኑ ቀን ሽማግሌው አንድ ደብዳቤ ደረሰው፡፡“ውድ አባዬአሁን ባለሁበት ሁኔታ ላደርግልህ የም

ችለው ይህን ብቻ ነው፡፡ አሁን የፈለግኸውን መዝራት ትችላለህ፡፡ልጅህ ገብሬ፡፡”

“ምስኪን ፑር” ሲል ራሱን የሚጠራ ፀሀፊ “ጓደኛዬ የነገረኝ ወሬ ነው” ብሎ በፌስ ቡክ ከጻፈው የተወሰደ

የገብሬ ቁምነገር

በእግዜር /ከአራት ኪሎ/

እነሆ ተከፈተ፤ ምኑ? አፋችን፤ ለምን? ለመሳቅ፡፡ በአፍሪካ የመጀመሪያው የሳቅ ት/ቤት በኢትዮጵያ ተከፈተ፡፡ በአዲስ አበባ ዋና ዋና መንገዶች ሰሞኑን ከሚታዩ ማስታወቂያዎች አንዱ ይሄ ነው፤ “በአፍሪካ የመጀመሪያው የሳቅ ት/ቤት ተከፈተ” የሚል፡፡ ማስታወቂያው ላይ ጥርሶቹ የሚታዩ ጎልማሳ አንድ ፈረንጅ አቅፎ “ሲስቅ” ይታያል፡፡ /የሳቁ ምንጭ እርሷው ትሆን?/ በሁለተኛው የማስታወቂያ ገጽ ደግሞ ኑሮ እና ዕድሜ ያደቀቃቸው የሚመስሉ ባልቴት እንዲሁ አፋቸውን እንደነገሩ ከፍተው ይታያሉ፡፡ ጥርሳቸው ስላለቀ እየሳቁ መሆኑን ማወቅ ይቸግራል፡፡ ያም ሆነ ይህ ኢትዮጵያ ከአፍሪካ የመጀመሪያዋ የሳቅ ት/ቤት ባለቤት ሆናለች፡፡ እልልልልልል….!“ሳቅ” የሚለውን ቃል ከሳቴ ብርሃን

የአማርኛ መዝገበ ቃላት ውስጥ ፈለግኩት፤ አጣሁት፡፡ ጉድ እኮ ነው፤ ባለ አንድ ሺ ሦስት መቶ ዘጠና ስምንቱ ገጽ መዝገበ ቃላት “ሳቅ” የሚለውን ቃል አለማካተቱ አስገራሚ ነው፡፡ “ቃሉ አማርኛ አይደለም ማለት ነው?” ራሴን ጠየቅኩ፡፡ ደግሜ “ሳቀ” ወይም “ሣቀ” በሚለው በግስ ቅርፁ ፈለግኩት፤ አሁንም አላገኘሁትም፡፡ እንግዲህ “ሳቅ” ኢትዮጵያዊ አይደለም ማለት ነው፡፡ ለማንኛውም በአፍሪካ የመጀመሪያ

ው የሳቅ ት/ቤት ተከፍትዎልዎታል፡፡ የሚፈልጉት በየትኛው ደረጃ ነው? በዲግሪ? በዲፕሎማ? ወይስ እንዳቅምዎ በሰርተፍኬት? …ከእንግዲህ ወዲያ በሆነው ባልሆነው መሳቅ፣ በሳቅ የትምህርት ዘርፍ የተመረቀ ምሁር መገለጫ እንጂ የጤና መራቅ ምልክት ተደርጎ አይወሰድም፡፡ በዋጋ ንረት መጨነቃችን ቀጥሏል፤

ግብሩም ቀጥሏል፤ የሚሊዮኖች መራብም ቀጥሏል፤ ሁሉ ነገር “እንደገና” ቀጥሏል፡፡ በአፍሪካ የመጀመሪያው የሳቅ ት/ቤትም ተከፍቷል፡፡ “የሳቅ ንጉሥ” ተብሎ የሚታወቀ

ው ወንድማችን በዓለም ድንቃድንቅ መዝገብ ላይ ስሙ መስፈሩ ይታወሳል፡፡ እኔ መቼም ጠርጣሪ ነኝና፣ “የዚህ ወንድማችን ስም በዓለም ድንቃድንቅ መዝገብ ላይ የሰፈረው ረዥም ሳቅ በመሳቁ ሳይሆን ኢትዮጵያዊ ሆኖ መሳቅ በመቻሉ ይሆን እንዴ?” እላለሁ፡፡ “ሳር እስቃለሁ እንደ ማሽላ፣ነገር በሆዴ እየተብላላ!”

ሳቅ ኢትዮጵያዊ አይደለም

Page 19: Habeshawi kana 004

ሐምሌ 30-ነሐሴ 13 ቀን 2003 (August 6-19, 2011) ሐበሻዊ ቃና 19

የአገር ቤት ጨዋታ

‹‹ሰላም ባስ›› ወደ መቀሌ በየዕለቱ በረራ ካላቸው አገር አቋራጭ አውቶቡሶች መካከል ግንባር ቀደሙ ነው፡፡ መነሻውን ከመስቀል አደባባይ አድርጎ የደሴን፣ የሐይቅን እና የወልዲያን ከተሞች አቋርጦ በአላማጣ እና በማይጨው ጋራዎች ሰንጥቅ መቀሌ ለመግባት ሁለት ቀናት ይወስድበታል፡፡ ይህን አድካሚ ጉዞ ቀላል ለማድረግ ‹‹ሰላም ባስ›› ተንቀሳቃሽ ፍሪጅ፣ የሙቀት መቆጣጠሪያ እና የጥንቃቄ ቀበቶ ለተሳፋሪዎቹ አዘጋጅቷል፡፡ ከዚህም ባሻገር በውስጡ ሁለት የማይታክቱ የቴሌቪዥን ስክሪኖች ተገጥመውለታል፡፡ ቴሌቪዥኖቹ ከተጨቆኑ ቀልዶች አንስተው ለጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ውዳሴ እስከተዜሙ የትግርኛ ዜማዎች ድረስ ተሳፋሪዎቻቸውን ያስኮመኩማሉ፡፡ በዚህ የ780 ኪሎ ሜትር የመቀሌ ጉዞ ተጓዡ ከቴሌቪዥኖቹ በብዛት እንዲኮመኩም የሚጋበዘው ግን የኤርትራ ሙዚቃዎችን ነው፡፡በአመዛኙ በኤርትራ ሙዚቃዎች የሚ

ታጀበው የሁለት ቀናት ጉዞ ሲጠናቀቅም ቢኾን ዉቧ መቀሌ የራሷን ዜማዎች አሰናድታ አትጠብቅም፤ ይባስ ብላ እሷም በኤርትራ ቅኝት ያለዕረፍት ትደንሳለች፡፡ይህ ኹኔታ አሥመራ ተወልዶ ላደገው

ጸጋዬ ገብረ ትንሣኤ የፈጠረበት ስሜት ከአግራሞትም በላይ ነው፡፡ ለ23 ዓመታት በኤርትራ ሲኖር ራሱን ከሙዚቃ ነጥሎ አያውቅም፡፡ ከሁለቱ ጎረቤት አገራት የከረረ ጦርነት በኃላ ግን ኢትዮጵያዊ የትግርኛ ሙዚቃዎችን በአሥመራ ሊሰማቸው አልታደለም ነበር፡፡ በኤርትራ የኢትዮጵያ ሙዚቃዎችን በይፋ መስማት ክልክል መኾኑን የሚናገረው ጸጋዬ ከ

ሦስት ዓመታት በኃላ በቀይ መስቀል እርዳታ ለእናቱ አገሩ ሲበቃ ተመሳሳይ ኹኔታ እንደሚያጋጥመው እርግጠኛ ነበር፡፡ ኾኖም መቀሌ ከተማ ሲደርስ ያጋጠመው የተገላቢጦሹ ነው፡፡ጸጋዬ ‹‹ አርነት እና ሰማዕታት›› በሚባ

ሉት የአሥመራ ጎዳናዎች ዘወትር የሚንቆረቆሩት የኤርትራ ዜማዎች ‹‹ የጠላት አገር›› ተብላ በምትፈረጀው መቀሌ አሁንም አሁንም በየሄደበት ሁሉ ሲደመጡ ያለበትን እስኪጠራጠር ድረስ ተገርሟል፡፡ ጸጋየ ግርምቱን ‹‹ዘይሕሰብ ነገር!›› በማለት ነው የሚገልፀው፡፡‹‹ የማይታሰብ ነገር!›› ከኢትዮጵያ ታላላቅ ከተሞች ተርታ የ

ምትመደበው መቀሌ በ2001 ዓ.ም ይፋ በሆነው የሕዝብ ቆጠራ መሠረት 215 ሺህ ነዋሪዎችን ታቅፋለች፡፡ በዛ ካሉ መዝናኛ ሥፍራዎቿ በሁሉም አቅጣጫ የሚሰሙት በከበሮ የደመቁ ሙዚቃዎች ከተማዋን ያለ ዕረፍት ያስደንሷታል፣ይንጧታል፡፡ ምንም እንኳ የብዙዎቹ ቅኝትና ምንጭ ከኤርትራ ቢኾንም፡፡በከተማዋ ዘመናዊ የምሽት ክበቦች ው

ስጥ አንዱ በኾነው ‹‹ክለብ አቢሲኒያ›› ሙዚቃ የሚያጫውተው ‹‹ዲጄ›› አማኑኤል በከተማዋ ስም ካላቸው የሙዚቃ አጫዋቾች አንዱ ነው፡፡ ዐማኑኤል በልዩ ልዩ ዝግጅቶች እና በየምሽቱ ከሚያጫውታቸው ሙዚቃዎች በአማካይ 90 ከመቶ የሚኾኑት የኤርትራ ሙዚቃዎች እንደኾኑ ይናገራል፡፡ በስተኋላ ላይ ግን ይህ ኹኔታ የተወሰነ መሻሻል እያሳየ እንደ ኾነ ያስባል፡፡ ‹‹ በአንድ ምሽት እስከ አምስት የሚደርሱ የእኛን አገር የትግርኛ ሙዚቃዎች ለመቀላቀል እሞክራለኹ›› ይላል አማኑኤል፡፡

ዲጄ ዐማኑኤል በከተማዋ ያለው የኤርትራ የሙዚቃ የበላይነት በሙዚቃ ብቻ የተወሰነ አለመሆኑን ይገልጻል፡፡ እርሱ በንብረትንት የሚያስተዳድረው የቪሲዲ ማከራያ እና ማከፋፈያ ማዕከል ብዙዎቹ ደንበኞች የሚፈልጉት ከትግርኛ ሥራዎች ይልቅ የኤርትራ ድራማዎችን እና ፊልሞችን ነው፡፡በመቀሌ ከተማ ያሉት የሙዚቃ ቤቶች

ከዐማኑኤል ሐሳብ ጋር የሚጣጣም ሥራ የሚሰሩ መኾናቸውን የሚመሰክር የራሳቸው የዕለት ዕለት ትዕይንት ይስተዋልባቸዋል፡፡ ብዙ መደብሮች ‹‹አዲስ የኤርትራ ድራማዎች አስገብተናል›› የሚሉ ማስታወቂያዎችን ከደጆቻቸው ያስደምጣሉ፤ የውስጠኛው ገጽታቸውም ይህንኑ እውነታ በሚያዉጁ ማስታወቂያዎች የተሞላ ነው፡፡የከተማዋ ሰፋፊ ካፊቴሪያዎች እና ድራ

ፍት ቤቶችም በየሳምንቱ የዕረፍት ቀናት ደንበኞቻቸውን የሚያስኮመኩሙት ከኤርትራ የሚሠራጨውን ‹‹ሞይዛክ›› የተሰኘውን የሙሉቀን የቴሌቪዥን ፕሮግራም ነው፡፡ በእነዚህ ቀናት የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ሥርጭቶቹን የሚያስተናግድ ካፌ ማግኘት አዳጋች ነው፡፡ከዓመታት በፊት በኤርትራ ቴሌቪዥን

ዘወትር ዐርብ እና እሁድ ይተላለፍ የነበረው ተከታታይ ድራማ የከተማዋን ነዋሪ ቀልብ ገዝቶ ነበር፡፡ ይህ ‹‹ዝባን ሕጊ›› (በህግ አምላክ እንደማለት ነው) የተሰኘው ተከታታይ ድራማ ይቀርብ በነበረበት ወቅት ብዙዎቹ የከተማዋ መዝናኛ ቤቶች በተመልካች ይጨናነቃሉ፡፡ አንዳንዶቹም ድራማው በሚታይበት ወቅት ለሚሰጡት ማንኛውም አገልግሎት ተጨማሪ ክፍያን ይጠይቁ ነበር፡፡ ‹‹ዝባን ሕ

በመሐመድ ሰልማን

ጊ›› የከተማችን ፕሪምየር ሊግ ኾኖ ቆይቶ ነበር›› ይላል በወቅቱ የነበረውን ኹኔታ የሚያስታውሰው የከተማዋ ነዋሪ አታኽልቲ ገብረ ሕይወት፡፡የመቀሌ የቪሲዲ ማከራያ መደብሮች

ም ቢኾን ከአገር ውስጥ የትግርኛ ሙዚቃዎች እና ሌሎች የጥበብ ሥራዎች ይልቅ በኤርትራ ፊልሞች እና የሙዚቃ ክሊፖች የተሞሉ ናቸው፡፡ ከኤርትራ ቴሌቪዥን እየተቀዱ በሲዲ ተዘጋጅተው በመላው ትግራይ በሺዎች የሚሰራጩት እነዚህ ልዩ ልዩ የጥበብ ሥራዎች መቀሌን እምብርታቸው ያደረጓት ይመስላሉ፡፡ ዐማኑኤል ‹‹ የኤርትራ ‹MP3›ዎች እና የዘፈን ክሊፖች ከአዲስ አበባ ጭምር እየተዘጋጁ ወደ መቀሌ ይላካሉ›› ይላል በመደብሩ የ‹‹ላየንስ›› እና የ‹‹ኢቫንጋዲ›› ሪከርድስ ዓርማን የያዙ ብዛት ያላቸው ሲዲዎችን እያመለከተ፡፡ እንደ አማኑኤል ገለጻ ትልልቅ አሳታሚዎች ጭምር በዚህ ዘርፍ መሠማራታቸው የኤርትራ ሙዚቃዎች በክልሉ ያላቸውን የገበያ ስፋት እና ተቀባይነት የሚያሳይ ነው፡፡የመቀሌ ነዋሪ የኾነው አታኽልቲ የኤ

ርትራ ሙዚቃ ለትግራይ ሕዝብ ባለው የቋንቋ ቅርበት ምክንያት ተቀባይነት እንዳገኘ ይገምታል፡፡ ‹‹ሙዚቃ ድንበር የለውም›› የሚለው አታኽልቲ ተመሳሳይ ቋንቋ በሚናገሩ ሕዝቦች መካከል ይህን ያህል መወራረስ መከሠቱ አስገራሚ እንዳልኾነ ያምናል፡፡ ከሙዚቃ እና ድራማዎች ባሻገር የኤርትራውያን የኾኑ ቃላትም ሰርገው እንደገቡ አታኽልቲ እንደማስረጃ ያቀርባል፡፡ እንደ ምሳሌም በመቀሌ እና አካባቢዋ የሚዘወትሩ ቃላትን ይጠቅሳል፡፡ “‹‹አይደል?›› ለማለት ‹‹ሙሽ?››፣ ‹‹እሺ›› ለማለት ደግሞ ‹‹ሃራ

ይ››…ወዘተ የእኛ ትግርኛ ያልኾኑ ነገር ግን አሁን በስፋት የተለመዱ ውርስ ቃላት ናቸው፡፡”የኤርትራ ኮከብ ድምፃዊ የነበረው አብ

ርሃም አፈወርቂ ድንገተኛ ሞት ሲሰማ በመቀሌ ትልቅ መነጋገርያ እንደ ነበር የሚያስታውሰው አታኽልቲ ይህም የሕዝቦቹን ትስስር አጉልቶ የሚያሳይ እንደ ኾነ ይሞግታል፡፡23 ዓመታትን በአሥመራ ቆይታ ያደረ

ገው ጸጋዬ ገብረ ትንሣኤ የግጥም እና የዜማ ደራሲ ነው፡፡ ሥራዎቹን ስማቸው ጎልተው ለሚወሱ የኤርትራ ድምፃውያን አበርክቷል፡፡ እንደ እርሱ አመለካከት የትግርኛ ዘፈኖች ከኤርትራ ሙዚቃዎች የማይተናንስ አቅም አላቸው፡፡ ‹‹ችግሩ በስፋት ለመደመጥ ቦታ አለማግኘታቸው ነው›› ባይ ነው፡፡ጸጋዬ በኤርትራ ቆይታው የአብረሃም ገ

ብረ መድኀንን ‹‹ምግበይ›› የተሰኘውን አልበም ከእንግሊዝ አስመጥቶ አሥመራ ውስጥ ለማሰራጨት ቀዳሚ እንደነበር ይናገራል፡፡ ያን ጊዜ የሙዚቃውን ከፍተኛ ጥራት እና ተቀባይነት ተከትሎ ሰዎች ድምፃዊው ‹‹ኤርትራዊ ልጃችን ነው›› በማለት እስከ መከራከር ደርሰው እንደነበር ይተርካል፡፡ የትርሃስ ታረቀኝን ‹‹ ኮበለይ›› የተሰኘ

ውን ተደማጭ ሙዚቃ የስቱዲዮ ቀረጻ እና የድምጽ ተዋሕዶ (ሚክሲንግ) ሥራ የሠራው የትግርኛ ሙዚቃ አቀናባሪው ፍቅረ ተሾመ በበኩሉ በትግራይ የሚታየው የኤርትራውያን የሙዚቃ የበላይነት ብዙ አይቀጥልም፡፡ ፍቅረ ‹‹ተስፋ የሚጣልባቸው ዕምቅ አቅም ያላቸው ዘ

ወደ ገጽ 21 ዞሯል

“‹‹አይደል?›› ለማለት ‹‹ሙሽ?››፣ ‹‹እሺ›› ለማለት ደግሞ

‹‹ሃራይ››…ወዘተ የእኛ ትግርኛ ያልኾኑ ነገር ግን አሁን በስፋት የተለመዱ ውርስ

ቃላት ናቸው

ቢኾንም መቀሌ የሚንጧት እና ያለ ዕረፍት የሚያስደንሷት በከበሮ የደመቁ ሙዚቃዎች ናቸው፡፡ የብዙዎቹ ቅኝትና ምንጭ ግን ኤርትራ ነው፡፡

ፎቶ

- ኢ

ትዮ

ጵያን

ሪቪ

Page 20: Habeshawi kana 004

ሐምሌ 30-ነሐሴ 13 ቀን 2003 (August 6-19, 2011)ሐበሻዊ ቃና20

በምን እንዝናና?

ሙዚቃ

ዩጋንዳ

የት ሄደን እንዝናና?

መቼ፦ ከሰኞ እስከ እሁድ የት፦ ሲኒፕሌክስ - ጋርደን ሲቲ- ከኡቹሚ ሞል በላይ ሶስተኛ ፎቅሰዓት፦ ከቀኑ አምስት፣ ስምንት፣ አስር ሰዓት እንደዚሁም ከምሽቱ አንድ ሰዓት ተኩል፣ ሶስት ሰዓት ተኩል የመግቢያ ዋጋ፦ 16ሺህ ሽልንግ ( ዘወትር ማክሰኞ ስምንት ሺህ)

ሲኒፕሌክስ በዚህ እና በቀጣዩ ሳምንት ከሚያሳያቸው ፊልሞች መካከል Winnie the Pooh የካርቱን ፊልም እና Super 8 የሳይንስ ፊክሽን ይገኙበታል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የ X-Men ተከታታይ ፊልም የሆነው X-Men፡ First Class እና Hanna ለዕይታ ቀርበዋል፡፡

ኬንያ

ሞውሪስ ኬይራ የ“ወርልድ ሙዚቃ” ስልትን ከሚጫወቱ ጥቂት ኡጋንዳውያን አንዱ ነው፡፡ እንደ አማርኛው “ባለ ጋሪው” መልዕክት ባለው “ቦዳ ቦዳ” ዘፈኑ ይበልጥ ይታወቃል፡፡ በቅርቡ “ራዲዮ ፍራንስ ኢንተርናሽናል” (አር.ኤፍ.አይ) ከተሰኘው ዕውቅ የፈረንሳይ ሬድዬ ጣቢያ ሽልማት የተበረከተለት ሞውሪስ በተለያዩ ሀገራት ዝግጅቶቹን ሲያቀርብ ቆይቷል፡፡ ከድምጻዊነቱ ሌላ ጥሩ ጊታር ተጫዋች የሆነው ሞውሪስ የመድረክ ዝግጅቶቹን የሚያቀርበው በጊታሩ ታጅቦ ነው፡፡

መቼ፦ ነሐሴ 27 ቀን 2003 ዓ.ምየት፦ ካምፓላ ሴሬና ሆቴል ሰዓት፦ ከምሽቱ አንድ ሰዓት የመግቢያ ዋጋ፦ 50 ሺህ ሽልንግ

በሲኒማ ቤትፊልም

የአሲአን ፊልም ፌስቲቫልፊልም መቼ፦ ነሐሴ 10 እና 11 ቀን 2003 ዓ.ም የት፦ አሊያንስ ፍራንሴዝሰዓት፦ ከምሽቱ አስራ እንደ ሰዓት ተኩል እና አንድ ሰዓት ተኩል መግቢያ፦ በነጻ

ሱዶኩከ 1 እስከ 9 ያሉ ቁጥሮችን በባዶ ቦታዎች ውስጥ ያስገቡ፡፡ ይህ ማለት እያንዳንዱ መደዳ እና

እያንዳንዱ 3 x 3 የሆነ ሳጥን ከ 1 እስከ 9 ያሉ ቁጥሮችን ይይዛል፡፡አንድን ቁጥር በባዶ ቦታዎች

ላይ ሁለት ጊዜ ደግሞ ማስገባት አይቻልም፡፡

መልካም ጨዋታ

የወርልድ ሙዚቃ ኮንሰርት

ማስታወቂያ

የስራ ማስታወቂያ

ተፈላጊ ችሎታ:-

l በየሀገራቱ በየጊዜው የሚደረጉ ክንውኖችን ተከታትሎ መዘገብ የሚችል (የምትችል)l መረጃዎችን መሰብሰብ እና ማጠናቀር የሚችል (የምትችል) l ጥሩ የመጻፍ ችሎታ ያለው (ያላት)l የኮምፒዩተር እና ኢንተርኔት ዕውቀት ያለው(ያላት)

ተፈላጊ የትምህርት ደረጃ እና የስራ ልምድ:-

ከታወቀ ዮኒቨርስቲ/ኮሌጅ በጋዜጠኝነት፣ ማስ ኮሚዩኔኬሽን፣ ቋንቋ እና ስነ ጽሁፍ ወይም ተያያዥ የትምህርት ዘርፎች ተመርቆ ቢያንስ አንድ ዓመት የስራ ልምድ ያለው (ያላት)

አስራ ሁለተኛ ክፍል ጨርሶ(ሳ) በዘጋቢነት ቢያንስ ሶስት ዓመት የስራ ልምድ ያለው (ያላት)

ደመወዝ:- በስምምነት

አመልካቾች ካሪኩለም ቪቴ (ሲቪ)፣ የትምህርት እና የስራ ማስረጃዎችን ኮፒ እንደዚሁም ቢያንስ ሁለት የጸሁፍ ናሙናዎችን በድርጅቱ የፖስታ ወይም ኢሜይል አድራሻ አያይዘው እስከ መስከረም 5 ቀን 2004 ዓ.ም ድረስ መላክ ይገባቸዋል፡፡

አድራሻ Habesha Communications Ltd

P.O.Box 28268 Kampala, Uganda

[email protected]

ሐበሻ ኮሚዩኒኬሽንስ ሊሚትድ በየ15 ቀኑ ለሚያሳትመው “ሐበሻዊ ቃና” ጋዜጣ ዘጋቢዎችን ለመቅጠር ይፈልጋል፡፡ “ሐበሻዊ ቃና” በኡጋንዳ፣ በኬንያ እና ደቡብ ሱዳን ላይ የሚያተኩር ጋዜጣ ሲሆን በሶስቱ ሀገራት ላሉ አማርኛ አንባቢዎች የሚቀርብ ነው፡፡ ድርጅቱ በእነዚህ ሶስት ሀገራት ዘጋቢዎችን ቀጥሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

የደቡብ እስያ ሀገራት (አሲያን) ቀንን ምክንያት በማድረግ ነሐሴ 10 እና 11 ቀን 2003 ዓ.ም የታይላንድ፣ ማሌዥያ እና ፊሊፒንስ ፊልሞች በአሊያንስ ፍራንሴዝ አዳራሽ ውስጥ ለዕይታ ይበቃሉ፡፡ በ0727 600622 ወይም በ0727 340045 ደውለው ስለፊልሞቹ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

ከፊሊፒንስ - ነሐሴ 11ከታይላንድ - ነሐሴ 11

ከማሌዥያ - ነሐሴ 10ከታይላንድ- ነሐሴ 10

Page 21: Habeshawi kana 004

ሐምሌ 30-ነሐሴ 13 ቀን 2003 (August 6-19, 2011) ሐበሻዊ ቃና 21

ሔርናንዴዝ:- ወደባዕድ ሀገር ሄዶ መጫወት ምንጊዜም ካባድ ነው:: ነገር ግን የአባቴ እና እህቴ አብረውኝ ሊኖሩ መምጣት ትልቅ እገዛ አደርጎልኛል:: ነገሮችን በጣም ወደቀላል ለውጦልኛል:: በእርግጥ እኔ ከሜክሲኮ የሚናፍቀኝ ነገር ምግብ እና ባህል ሳይሆን ቤተሰቤ ነው፣ ማታ ማታ ተሰብስበን አንድ ላይ የምናወራው:: ጥያቄ:- እንግሊዘኛ ቋንቋ መናገርህ የረዳህ አይመስልህም?ሔርናንዴዝ:- እንደመጣሁ ጥሩ እናገ

ር ነበር:: ከዚያም ቀስ በቀስ የተሻለ መርዳት እና መናገር ጀመርኩ እወነቱን ለመናገር እንግሊዝኛ ማወቄ በደንብ ጠቅሞኛል:: በመልበሻ ክፍል ከቡድን አጋሮቼ ጋራ በቀላሉ እና በፍጥነት እንድግባባ ረድቶኛል::ጥያቄ:- እስኪ ወሬያችንን ቀየር እናድርግ:: ለክለብ እና ብሔራዊ ቡድን 14 ቁጥር ማሊያ እንዴት ልትለብስ ቻልክ?ሔርናንዴዝ:- የእድል ጉዳይ ነው (ሳ

ቅ):: መጀመርያ ለቺቫስ ስጫወት 45 ቁጥር ተሰጠኝ፣ ከዚያ 25:: ቀጥሎ አንድ ተጨዋች ክለቡን ሲለቅ 14 ቁጥር መልበስ ጀመርኩ:: እንደ አጋጣሚ ሆኖ ዓለም ዋንጫ ላይ ሚጉዌል ሳባህ በመጎዳቱ 14 ቁጥር እንድለብስ ተደረግሁ:: ወደ

መናዊ ትግርኛ ሙዚቃ መጫወት የሚችሉ ወጣቶች ብቅ እያሉ ነው›› ይላል፡፡ ኾኖም በኅብረተሰቡ ውስጥ የሠረጸው የኤርትራ ሙዚቃን አልቆ የማየት አባዜ ፍቅረን ያንገበግበዋል፡፡ ሰው አሪፍ የትግርኛ ሙዚቃ ሠርተን እንኳ የሚያደንቅልን ‹‹ቁጭ የኤርትራ ዘፈን ነው የሚመስለው’ኮ በማለት ነው››፡፡ ይላል በቁጭት፡፡ለዓመታት በዲጄነት የሰራው ዲጄ ዐማ

ኑኤል በዚህ ይስማማል፤ ‹‹ አገር ውስጥ ጥሩ ጥሩ የትግርኛ ዘፈኖች ተሠርተው የኤርትራ ባለመኾናቸው ብቻ ተውጠው ይቀራሉ፡፡››ዲጄ ዐማኑኤል በሚያዘጋጃቸው የ‹‹ዴ

ይ ፓርቲዎች››ም ኾነ በምሽት ክበቦች ታዳሚዎቹ የኤርትራ ሙዚቃን እንዲጋብዛቸው አስጨንቀው እንደሚጠይቁት ይናገራል፡፡‹‹ሰውን የምታዝናናው በሚወደው ሙዚቃ ነው፤ በግድ የእኛን ስማ ብለኽ አትግተውም›› ይላል የኤርትራ ሙዚቃዎች በነዋሪዎቹ ዘንድ ያላቸውን ተቀባይነት ሲያብራራ፡፡ዲጄ ዐማኑኤል የኤርትራ ሙዚቃዎች

በከተማዋ እንዲህ ሥር መስደድ እንደ ዐቢይ ምክንያት የሚያነሣው የኢትዮጵያ የትግርኛ ዘፋኞች አዲስ እና ያልተለመደ ሥራን ይዘው ለመቅረብ አለመድፈራቸውን ነው፡፡ ‹‹የእኛዎቹ ሥራዎች በባህል የተደረቱ እና የትግል ዜማዎች የሚበዙባቸው ናቸው፡፡››የ‹‹ሱዳን ትሪቡን›› ድረ ገጽ በ2001

ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ከጦርነት መልስ ለመጀመርያ ጊዜ የኤርትራ ሙዚቃዎችን ማሳየት መጀመሩን ትልቅ ዜና አድርጎ ዘግቦት ነበር፡፡ መቀሌን አላያትም ማለት ነው፡፡ በእርግጥም መቀሌ በኤርትራ ሙዚቃ ደንሳ የምትደክም አትመስልም፡፡ ሙዚቃ ጦርነት አይገባውም አንዴ?

ይህ ፅሁፍ በጥር 2 ቀን 2001 በወጣው የአዲስ ነገር ጋዜጣ ሶሻል አምድ ላይ ታትሞ እንደነበረ ይታወሳል፡፡ የውጭ ሚዲያ ዘጋቢዎች ማህበር ከአሜሪካና ፈረንሳይ ኤምባሲዎች ጋር እ.ኤ.አ በ2009 በመተባበር ባዘጋጀው የሚዲያ ፅሁፍ

ውድድርም በጋዜጣ ዘርፍ ተሸላሚ ሆኗል፡፡

ና ውኃ አይቆርጡባችሁም» ?«ብዙ ጊዜ መብራቱን እንጂ ውኃውን መቁረጥ ያስቸግራቸዋል፡፡ የሮም ሕንፃዎች የድሮ ሕንፃዎች ናቸው፡፡ የውኃ መሥመሩ በቀላሉ አይገኝም፡፡ መብራቱን ግን ቢቆርጡትም እንቀጥለዋለን፡፡ አንድ ልጅ እንዲያውም በዚያ ምክንያት ሥራ አግኝቷል፡፡»«መብራት በመቀጠል?» «አዎ፤ የቤቱን

መብራት ሲቆርጡት በመንገድ ከሚያልፈው መብራት ሌሊት ቀጠለው፡፡ ፖሊሶቹ ሲመጡ ይበራል፡፡ ሄደው ከዋናው ማጥፊያ ቢያለያዩትም ይበራል፡፡ አይተው ስለማያውቁ ግራ ገባቸው፡፡ በኋላ ከመንገዱ መብራት መቀጠሉን ሲያዩ እንዴት ሊቀጠል እንደቻለ ማመን አልቻሉም፡፡ እና ትተውት ሄዱ፡፡ ይሄው ፏ ብሎልሃል፡፡ ልጁም ታድያ ኤሌክትሪክ ሠራተኛ ሆኖ ቀረ»«ሴቶች ሲኞራ ቤት ይሠራሉ አልከኝ፤

ወንዶችስ ምን ይሠራሉ?» «ወንድ ከሆንክ አልፎ አልፎ ነው ሥራ የምታገኘው፡፡ ችግር አለ፡፡ አንዱ አበሻ ሲርበው ሴት ነኝ ብሎ ሲኞራ ቤት ተቀጥሮ ነበር አሉ፡፡» «እውነትክን ነው ወይስ ቀልድ ነው» «እኔ ሲያወሩ ነው የሰማሁት፡፡» «እሺ ከዚያስ» «ልጁ ጢም የለውም፤ መልኩ የሴት ድምጽ ነው፡፡ እንዲያው ልጆች በሌላ ነገር ይጠረ ጥሩታል» «ምን ብለ» «ነገርዬው የለውም ይሉታል» «እሺ»

«እና ጉልበታም ነው፤ ሥራዋን ፉት፣ ጭጭ ነበር አሉ የሚያደርጋት፡፡ አንድ ቀን የሽንት ቤቱን በር ሳይዘጋው ረስቶት፣ ቆሞ ሽንቱን ሲሸና ሲኞራው በሩን ሲከፍት ፌንት ወጣ አሉ፡፡ ነፍሷ ደሞዟን ሳትቀበል ከቤት ወጥታ ጠፋች፡፡ በኋላ ግን እንደዚያ ያደረገው ሥራ ስላጣ መሆኑን ሲኞራው ሲሰማ አድንቆ ካምፓኒው ውስጥ ቀጠረው አሉ»«ተው እባክህ፤ ይሄን የመሰለ ፊልም አ

ይቻለሁ፤ ሲኮምኩ ይሆናል» «ኩምክና አይደለም፤ የሆነ ነው ብለውኛል» «እሺ ይህንን ሁሉ ባሕር አቋርጦ የመ

ጣ ሰው መጨረሻው ምንድን ነው?»«ወይ ትመርሻለህ፣ ወይ ትፈርሻለህ፣ ወ

ይ ትደነብሻለህ» «ምንድን ነው መመረሽ፣ ምንድን ነው መደንበሽ፣ ምንድን ነው መፈረሽ»«ጣልያን ለመኖር የሚመጣ የለም፣ ስለ

ዚህ ትንሽ ገንዘብ ነገር ቆጣጥረህ ወደ እንግሊዝ ትሻገራለህ፤ ይኼ መመረሽ ይባላል፡፡ ያለበለዚያ ደግሞ እዚሁ የመኖርያ ፈቃድ አወጥተህ የተሻለ ሥራ ካገኘህ ትኖራለህ፤ ይኼ ደግሞ መፈረሽ ይባላል፡፡ ሁለቱም ካልሆነልህ ደግሞ ትጀዝብና ደንብሸህ ትኖራለህ፡፡

ሚላኖ፣ ጣልያን

ይህ ጹሁፍ ከዳንኤል ክብረት ጡመራ (ዳንኤል ክብረት ዶት ኮም ) የተወሰደ ነው። ጽሁፉ

በ2002 ዓ.ም ለንባብ የበቃ ነው።

መመረሽ፣መፈረሽ...

ከገጽ 8 የዞረ

ቺካሪቶ...ከገጽ 23 የዞረ

ማንችስተር ስመጣ ደግሞ ይኼው ቁጥር ክፍት ሆኖ ጠበቀኝ:: በሚደንቅ ሁኔታ አባቴ ከሜክሲኮው ፑኤብላ ጋራ ሻምፕዮን ሲሆን 14 ቁጥር ለብሶ ነበር:: እና የታሰበበት ጉዳይ ባይሆንም ጥሩ አጋጣሚ ነው::ጥያቄ:- እግር ኳስ እንዴት ጀመርክ፣ ፍቅሩስ ከየት መጣ?ሔርናንዴዝ:- ሁሉም የቤተሰቤ አባል

እንደሚነግረኝ ከሆነ ከሕፃንነቴ ጀምሮ ኳስ መጫወት እወድ ነበር:: በየሳምንቱ ግጥሚያዎች ለማየት ስታዲየም እገባ ነበር:: የተጨዋቾችን ስም እና የማሊያ ቁጥር እይዛለሁ:: ሕይወቴ በሙሉ በእግር ኳስ ዙርያ ያጠነጠነ ነበር፣ ስለጨዋታው ከማውራት አልፎ እስከመጫወት ድረስ:: ፕሮፌሽናል ተጨዋች እንደምሆ

ን አውቅ ነበር:: ከዚያ በተጨማሪ አባቴ ሲጫወት እመለከት ነበር፡፡ አያቴ ደግሞ በእነርሱ ጊዜ ስለነበረው ጨዋታ ይተርክልኛል:: እንደዚህ አድገህ ደግሞ ኳስ ተጨዋች አለመሆን ይከብዳል::ጥያቄ:- ልጅ ሆነህ ያንተ ተምሳሌት ወይም ጀግናህ ማን ነበር?ሔርናንዴዝ:- ሁሉንም ተጨዋቾች እ

መለከታለሁ፣ አንድ የሆነ የሚያስደስት ነገር ሲያደርጉ ካየሁ እቤት እመጣና ያንን ለማድረግ እሞክራለሁ:: የእኔ ጀግኖች ሁልጊዜም አባቴ እና አያቴ ሲሆኑ ወደፊትም ሆነው ይቀጥላሉ:: ከእነርሱ ባሻገር እርሱን ለመምሰል የምጥረው የብራዚሉ ሮናልዶን ነው:: ሮናልዶ ታላቅ ተጨዋች እንደሆነ አስባለሁ፣ በርግጥ ለዐ

ይን ከሚስቡ ቡድኖች ውስጥ ብራዚሎች ተጠቃሽ ናቸው:: በተለይ በፈረንሳይ 1998 ዓለም ዋንጫ ላይ የነበረው ቡድናቸው ብዙ አድናቂ አግኝቷል፣ ምስጋና ለአጨዋወታቸው ይግባና::ጥያቄ:- በመጨረሻ፣ ዘንድሮ ሜክሲኮ ከ17 ዓመት እድሜ በታች ያዘጋጀችውን ዓለም ዋንጫ መውሰዷን እንዴት አየኸው?ሔርናንዴዝ:- ከዚህ በፊት እንደተናገር

ኩት ለእነዚህ ታዳጊዎች የሚመጥን የአድናቆት ቃል ያጥረኛል:: ፔሩ ባዘጋጀችው የ2005 ተመሳሳይ ውድድር ላይ ብካፈልም እነዚህ ልጆች የተቀዳጁትን ድል አላገኝሁም:: የሜክሲኮን ስም በየቦታው ከፍ ስላደረጉ ኩራት ተሰምቶኛል::

በኤርትራ ሙዚቃ...ከገጽ 19 የዞረ

በሊቢያ ያለውን አለመረጋጋት የሸሹ 500 የሚጠጉ ስደተኞች ማዕበል ታግለው በዚህ ዓይነት ሁኔታ ነው ባለፈው ግንቦት ጣልያን የገቡት

ፎቶ

- ዴ

ይሊ

ኒው

ለኛ እርምጃ ነው፡፡ በዚህ ውሳኔ ደቡብ አፍሪካዎች እጅግ ቅር ተሰኝተዋል፡፡ በፉትቦልና በኢኮኖሚ የተራመድን ነን በሚል ከኢትዮጵያ አዎንታዊ ምላሽ ጠብቀው ነበር፤ ሳይሆን ቀረ አንጂ፡፡ በዚህም የተነሳ በመጀመሪያው ጨዋታ በሉሲዎች ላይ ማጉላላቶች እንዳይፈጠሩ ከወዲህ ወገብን ጠበቅ ማድረግ ይበጃል፡፡ ባያና ባያና ወይም ልጃገረዶቹ በሚል

ቅፅል መጠሪያቸው የሚታወቁት የደቡብ አፍሪካ የሴቶች ኦሊምፒክ ቡድን አባላት የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ሶዌቶ ላይ ከኢትዮጵያ አቻቸው ጋር ካከናወኑ በኋላ በጎረቤት ሀገር ሞዛምቢክ በሚካሄደው የመላው አፍሪካ ጨዋታዎች ይሳተፋሉ፡፡ ማፑቶ ላይ በሚካሄደው ውድድር ባያናዎች ሶስት ጨዋታዎች ይጠብቋቸዋል፡፡ አጋጣሚው ለልጃገረዶቹ ጥሩ የዝግጅት ዕድል ይፈጥርላቸዋል፡፡ በአንፃሩ ሉሲዎች አንድም የአቋም መፈተሻ ጨዋታ ሳያደርጉ ወደ ደቡብ አፍሪካ የመውረዳቸው ዕድል እየሰፋ መጥቷል፡፡ በቡድኑ ዝግጅት ዙሪያ ዋና አሰልጣኝ አብርሃም ሲናገር የልጆቹን መነሳሳት እና ለሥራ ያላቸውን ፍላጎት አድንቆ ስልጠናውን ለመፈተሸ ግን የአቋም መፈተሻ ጨዋታ አለማግኘቱ እንደሚያስጨንቀው አልሸሸገም፡፡ “የቀረን የሃያ ቀናት ዕ

ድሜ ብቻ ነው” ሲል የታሪካዊው ጉዞ መጀመሪያ አፍንጫቸው ጋር እንደደረሰ ሁለት ስሜት ውስጥ ሰጥሞ ያስረዳል፡፡ አንደኛው ስሜት የተጫዋቾቹን ለውጤት መጓጓት የሚወክል ሲሆን ሌላኛው በአቋም መፈተሻ ጨዋታ እጦት መራባቸውን ያሳያል፡፡ በፉትቦል በተራመዱ ሀገሮች ለብርታት እና ፍጥነት በሚል በተግባር ላይ የሚውለው የውሃ ውስጥ ልምምድ በአሰልጣኙ አማካይነት ለሉሲዎች እየተሰጣቸው ይገኛል፡፡ “1 ሜትር በሚጠልቅ የመዋኛ ገንዳ ውስጥ እየተንቀሳቀሱ ፍጥነታቸውን እና ብርታታቸውን እንዲያሻሽሉ ያግዛቸዋል” ሲል አብርሃም ያስረዳል፡፡ አክሎም ይህን ልምድ ጋናን ሊገጥሙ ወደ አክራ ባቀኑበት ወቅት ከማርሴይ ዴሳዪ እንዳገኘውና በቂ የስልጠና ማኑዋል እንደተቀበለው ተናግሯል፡፡ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ የደረሱት ሉሲዎች

በትጋት ልምምዳቸው ቢያካሂዱም በአስተዳደራዊው መስመር ያለው ክፍትት

ግን ያስደነግጣል፡፡ ይህን ቡድን ከወርሃ ታህሣሥ ጀምሮ በማጣሪያው ላይ ለማሳተፍ ፌዴሬሽኑ 2.8 ሚሊዮን ብር ማውጣቱ ታውቋል፡፡ እስካሁን በድጋፍ መልክ የተገኘው የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ በአዘኔታ የሰጣቸው 500 ሺህ ብር ብቻ ነው፡፡ ኦሊምፒክ ኮሚቴው በፋይናንስ የመደገፍ ግዴታ የሚኖርበት ቡድኑ ለለንደን ኦሊምፒክ ማለፉን ካረጋገጠ በኋላ ነው፡፡ እስከዛው ግን ኃላፊነቶች ሁሉ ፌዴሬሽኑ ላይ ናቸው፡፡ የእግር ኳሱ አስተዳዳሪዎች ደግሞ በዚህ ጉዳይ ትልቅ ድክመት ይታይባቸዋል፡፡ አብዛኞቹ ተጫዋቾች ከአዲስ አበባ ውጪ ከሚገኙ የክልል ከተሞች የመጡ ሲሆን ኑሮዋቸውን የሚገፉት በኪራይ ቤት ውስጥ ነው፡፡ ፌዴሬሽኑ በየወሩ በነፍስ ወከፍ 300 ብር ይከፍላቸዋል፡፡ ለአንድ የብሔራዊ ቡድን ተወካይ ያውም በአሁኑ ጊዜ በወር ከ30 የአሜሪካ ዶላር በታች መክፈል እጅግ የሚያሳዝን ነው፡፡ ሌላኛው የሉሲዎች ችግር ትጥቅ ነው፡፡ አሁንም ድረስ ልምምድ የሚሠሩት በወንዶቹ ማልያ ነው፡፡ እንደውም ማልያው እየሰፋቸው በመርፌ እያጠበቡት እስከ መለማመድ ደርሰዋል፡፡ በዚያ ላይ የማልያው መጠን (ሳይዝ) ትልቅ በመሆኑ ይከብዳቸዋል፡፡ ይህ ፌዴሬሽኑን ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ የስፖርቱን አመራሮች ክፉኛ ያስወቅሳቸዋል፡፡

ይህ ጹሁፍ ከጋዜጠኛ ኤርሚያስ አማረ “ፌስ ቡክ” ገጽ የተወሰደ ነው

የድንቅነሽ...ከገጽ 8 የዞረ

ሉሲዎች አሁንም ድረስ

ልምምድ የሚሠሩት በወንዶቹ

ማልያ ነው፡፡ እንደውም

ማልያው እየሰፋቸው በመርፌ

እያጠበቡት እስከ መለማመድ

ደርሰዋል

ጋር አይገናኝም፡፡ ወደ ሌላ ጋላክሲ መብረርና በሎንቺና ስንዴ ለመግዛት ተፍኪ መውረድ የተለያዩ ናቸው፡፡ በራሴ ማህበራዊና መልካምድራዊ ማጣቀሻ የሚያጫውተኝ ነው የፈለኩት፡፡ ሌላኛው የመንፈስ አባቴ ይሄ ሊሆን ይ

ችላል፡፡ ዛሬ በምፅፍበት ጊዜ ያኔ በልጅነቴ ምን ምን እንዳሰላቸኝ አውቃለሁ፡፡ የምጓዝበት መንገድ ሁሉ በኩርባ የተሞላ ነው፡፡ ማንኛውንም ያነበብኩት ደራሲ ባለፈበት እንዳላልፍ ስጠመዘዝ ነው የምውለው፡፡ ይሳካ አይሳካ ኪዳነምህረትና ቅን ዚቀኛ ያውቃሉ፡፡ በሆነ አያኖ አንዳንድ ያሰላቹኝም ይሁኑ ያላሰላቹኝ የቀድሞ ደራሲያን የምጓዝበትን ካርታ ሰርተውልኛል፡፡ የደረሰብኝ ተፅዕኖ ይሄ ነው፡፡ ‘የበላይ ጠባቂ ደራሲ’ ሲባል ደሞ ከዛ

ብዙ የማይርቅ ጥያቄም አለ፡፡ ‘የእሱ ተፅዕኖ አለብህ?’ የሚል፡፡‘አከሌ ተፅዕኖ አለበት’ ሲባል አሳሳቢ

ው ወይም አከራካሪው ተፅዕኖ መኖሩ አለመኖሩ ሳይሆን በዚህ አባባል ጠቅላላ የግለሰቡ ወይም የተጠያቂው ደራሲ ልፋት የሚዘነጋበት ጊዜ ሰለአለ ነው፡፡ ለመሆኑ አንድ ደራሲ ራሱን መሆን አቁሞ ሌላ ደራሲ የሚመስለው መቼ ነው? የ

ሚለውን ጥያቄ መመለስ አዳጋች ነው፡፡ ከባድ ጥናት ወይ አፍረተቢስ አሉባልታ ሊመልሰው ግን ይችላል፡፡ ምርጫው እንደግለሰቡ ነው፡፡ ዋናው ነጥብ ግን የደራሲውን የመምረጥ ፈቃድ (freewill) መተናኮስ ወይም መዘንጋት ይሆናል፡፡ የምንወለድበት የምንማርበት ሕብረተሰብ በተለያየ መንገድ የተያያዘና መረጃ የሚለዋወጥ አካል ስለሆነ የት ጋ ነው የአንዱ ደራሲ ዘይቤና አሰራር በሌላ ደራሲ ተጠልፎ የሚወሰደው ብለን ብንጠይቅ ከመልሱ ይልቅ ግምቶች ውስጥ አንገባለን፡፡መገንዘብ የሚገባን የመፃፍ አቃቂር ከ

“እመ ኅበ አልቦ” አለመፈጠሩ ነው፡፡ ስንወለድ ቋንቋ ዘዬና ፊደል ያለበት ህብረተሰብ ውስጥ ነው የምንመጣው፡፡ ተረት የማውቀው ተረት አንብቤ ወይም ሰምቼ ነው፡፡ የተረት ጉርሻ በጉንጬ ይዤ አልተወለድኩም፡፡ ወይም እትብቴ ላይ ቋጥሬ አልወጣሁም፡፡ በተለያየ ደረጃና መልክ ደራሲው ራሱንና ውጩን ነው፡፡በልማዴ አንድ ሮማንቲክ ደራሲን ወይ

ም የሆነ ናቹራሊስት ደራሲ ወይም ሌላ አይነት ባነብና ብወደው ተጠርጌ አልወሰድም፡፡ ሁልጊዜ ወደ ራሴ እመለሳለሁ፡፡ የምሰፍረው እራሴው ኢጎ(ego) ውስ

ጥ ነው፡፡ ምናልባት ‘ነፃ’ ደራሲ ለመሆን የሆነ ኢጎ ይጠይቃል፡፡ በሌሎች ታላቅነት የማይበረግግ፡፡ ከሌሎችም ስማቸው ከተጠራ ተወዳጅ ስህተቶችና ስኬቶች ጋር አብሮ የማይሄድ፣ ቢረባም ባይረባም የራሱን እድሞ ሰርቶ የሚጠለል፡፡ በሕይወቴ ብዙ ሰዎች በህብረት ሲሳሳቱ አይቼአለሁ፡፡ ሰዎችን ተከትዬ ተሳስቼአለሁ፡፡ ቆይቶ የምረዳው እውነት ግን ይቺ በራሴ የስሜት ህዋሳቶች የተገነዘብኳት ናት፡፡ ያቺ ጠይቄ የተሰማችኝና ያሰብኩባት ናት፡፡ አልፎ አልፎ በተቀራረበ ሰሞን የምፅፋቸው ድርሰቶች የሚቀባበሉዋቸው ቃላት ወይም ድምፆች ይኖራሉ፤ አንዳንድ ጊዜም ኩነት ይሆናል፡፡ ከራሴ ወደ ራሴ የሚመጣውን ቅብብል እንኳን አልወደውም፡፡ ከራሴም ጋር ሳላቋርጥ ‘መባጠስ’ አለበኝ፡፡ እና ብዙ ጊዜ አርትኦት ስሰራ አላማዬ ይሄን ዳና የመሰረዝ ነው፡፡ የሚገርው ራስህን ለመሆን ከባድ ጉዳይ አይደለም፡፡ ምክንያቱም እዚህ ነህ፡፡ ‘ስታይል ሰውዬው ነው’ ይላሉ ፈረንጆች፡፡በንባብ ካሳለፍኩት ልምድ ልርቅ የም

ጥርበት አንዱ መንገድ ክሌሼ (ንትብ ቋንቋ) ባለመጠቀም ነው፡፡ ግን ከመጠቀም ስትገሸሽ ቀድሞህ የነበረውን የአፃፃፍ ስርአት ማለት ‘አባቶችህ’ የዘሩትን ሳር ከምትግጥበት መስክ በሆነ መልክ ራቅህ ማለት ነው፡፡ በሌላ አባባል ዘዬዎ

ችህን ለመቀበል የሚጠበቅብሀን ታሪካዊ ሃላፊነትን (እንዲህ የሚከራከሩ ሊኖሩ ይችላሉ) መዘንጋትና ለተግባቦት ረዥም ጊዜ የተቀመጠውን የልዋጭና የንጽጽር መረብ መፈታተን ነው፡፡ ሩሲያዊው ፎርማሊስት ቪክቶር ሽኮሎቭስኪ ዲፋሚሊያራዜሽን (defamiliarization) ይለዋል፡፡ በአማርኛ ‘እንግዳ ማድረግ’ ልበለው? አንድ አባባል ሲለመድ ወይም ሲሰለችህ የምትወደውን ነገር ሁሉ ሊያበላሽብህ ይችላል፡፡ ኪነጥበብ አንዱ ግቡ በመሰላቸት የጠፋብህን ነገር፣ ልምድ የመሳሰለ መልሶ ሕይወት መስጠት ነው፡፡ እንደ ሽኮሎቭስኪ እምነት የኪነጥበብ ዋናው ግቡ ይሄ ነው፡፡ አንዳንዶቹ ፎርግራውንዲንግ (foregrounding) ይሉታል፡፡ እኔ እዚ ነገር ላይ ብቻ አተኩራለሁ ማለቴም አይደለም፡፡ ሃሳቡን ነው፡፡ሕግ የሚባል እንዳለ ሳላውቅ፣ ቢኖሩ

ም ሳይገቡኝ ነው መፃፍ የጀመርኩት፡፡ ያኔ የዘሪሁን አስፋው “የልብወለድ አላባውያን”ና የብርሃኑ የግጥም ግንዛቤ መስጫ መጽሐፍት አልነበሩም፡፡ አንዳንድ ቢኖሩም ግዕዝኛቸው እንደ ግድግዳ ስለሚሆን ብዙ አያስቀርቡኝም፡፡ ለዚያን ጊዜው መፃፍ ለጀመረው እኔ ሕጎች የተባሉት ልክ እንደ አየር ሕይወቱ ውስጥ በነፃ የታደሉ ነበሩ(ዛሬም ጭምር)፡፡ እስከ አሁንም ድረስ የማላውቃቸው ብዙ ሕጎች አሉ፡፡ ስላላወቅኋቸውም አላፍርም፡፡

ምክንያቱም የተሰራበት ወይም የሚሰራበት ቢሆንም በራሴ ልፋት ላገኛቸው እንደምችል ስለማምን ነው፡፡ እንዳንዴም ከሰራሁባቸው በኋላ የማውቃቸው ሕጎች አሉ፡፡ ድርሰቴን ፅፌው ካለቀ በኋላ የምለካው ውስጤ በሚሰማኝ ስሜት ነው፡፡ ያንን ሴንሴቢሊቲ ማንም ቀዳሚ ደራሲ ወይም ሃያሲ ሊያስተምርህ ወይም ሊተካው አይችልም፡፡ የማውቀው ያንን ነው፡፡ እነ እከሌ ያደርጉታል ብዬ ህልዮ ተበድሬ በዛ መልክ ልፃፍ አልልም፡፡ለምሳሌ ሎሬት ፀጋዬ ‘የፀጋዬ ቤት’ን የ

ፈጠረው ከስሜቱ ይመስለኛል፡፡ ከበደ ሚካኤል ‘ከበደ ቤት’ ን ሲገጥሙ ከስሜታቸው የመጣ ይመስለኛል (ባልሳሳት እሳቸውም ስም አልሰጡትም ነበር መሰለኝ)፡፡ እስኪ ‘ከበደ ቤት’ የሚባል ልፍጠር ብለው አንድ ጠዋት አልተነሱም፡፡ የልብህን ምት ከተከተልክ የምትደርስበት የራስህ ቦታ አለ፡፡ ሰፈሬ ከበቀለ ዋርካ ላይ ዘልዬ ብወርድ እግሮቼ የሚያርፉት ማርስ ወይም ጁፒተር አይደለም፡፡ዛሬ አንዳንዶቹን ወደርየለሽ ናቸው ብ

ዬ አነባቸው የነበሩትን ልብወለዶች ካጋጠሙኝ ተመልሼ አነባለሁ፡፡ የሆነ ውለታ አለብኝ ማለት ነው፡፡ ውለታቸውን የምከፍልበት መንገድ ግን እንደእነሱ አስመስዬ በመስራት አይደለም፡፡ ሳደርግ ራሴን ሰርዤ አይደለም፡፡ በራሴው መንገድ ነው፡፡

ከገጽ 19 የዞረአዳም ረታ...

ማንኛውንም ያነበብኩት ደራሲ ባለፈበት እንዳላልፍ ስጠመዘዝ ነው የምውለው፡፡ ይሳካ አይሳካ ኪዳነምህረትና ቅን ዚቀኛ ያውቃሉ፡፡ “

Page 22: Habeshawi kana 004

ሐምሌ 30-ነሐሴ 13 ቀን 2003 (August 6-19, 2011)ሐበሻዊ ቃና22

ስፖርት

24 ተጫዋቾች እና 3 አሰልጣኞች ከአንድ ወጌሻ ጋር ከአዲስ አበባ 42 ኪሎ ሜትር ርቀት በምትገኘው ደብረዘይት ከተማ መሽገዋል፡፡ ጉዞዋቸውን የጀመሩት በወርሃ ታህሣሥ ሲሆን መድረሻቸው ደግሞ ለንደን ናት፡፡ እነ ዴቪድ ቤካም አምባሳደር ሆነው የቀሰቀሱላት ለንደን በፓሪስ ላይ የበላይነቱን ተቀዳጅታ 30ኛውን የበጋ ኦሊምፒክ ከጁላይ 27 እስከ ኦገስት 12 ቀን 2012 ድረስ ለመደገስ ጎምበስ ቀና በማለት ላይ ትገኛለች፡፡ የእኛም እህቶች በውድድሩ ሀገራቸው

ን ሊወክሉ 180 ደቂቃዎች ብቻ ቀርቷቸዋል፡፡ አፍሪካ በለንደኑ ኦሊምፒክ በሴቶች እግር ኳስ የሁለት ኮታዎች ባለቤት ናት፡፡ በአንደኛው መስመር ኢትዮጵያ እና ደቡብ አፍሪካ ሲፋጣጡ፤ በሁለተኛው መስመር ኢኳቶሪያል ጊኒ ናይጄሪያን ትፋለማታለች፡፡ ሉሲ ወይም ድንቅነሽ በሚል ቅፅል የሚታወቁት የሴቶች ኦሊምፒክ ቡድን አባላት ከሐምሌ 1 ጀምሮ ልምምዳቸውን ቢሾፍቱ መኮንኖች ክበብ ተቀምጠው እያካሄዱ ናቸው፡፡ የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ አብርሃም ተ/ኃይማኖት ሲሆን አብረውት ሁለት ረዳቶች ይገኛሉ፡፡

ሉሲዎች የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ኦገስት 27 (ቅዳሜ) ጆሃንስበርግ ላይ ያከናውናሉ፡፡ የሚጫወቱት ደግሞ የታዋቂው የደቡብ አፍሪካ ክለብ ኦርላንዶ ፓይሬትስ ሜዳ በሆነው ኦርላንዶ ስቴዲየም ላይ ነው፡፡ ስቴዲየሙ 40 ሺህ ተመልካቾችን ያስተናግዳል፡፡ በእርግጥ ጨዋ

ታው የሚካሄድበት ትክክለኛው ቦታ በዘመነ አፓርታድ ጥቁሮች ከጆሃንስበርግ ተገፍተው እንዲኖሩ በተፈረደባቸው የትግል ከተማዋ ሶዌቶ ውስጥ ነው፡፡ ሶዌት ከእንግሊዝኛው South Western Townships የተወሰደ ሲሆን ከመሐል ጆሃንስበርግ በደቡብ ምዕራብ አቅጣጫ

የሚገኝ የጥቁሮች መናኸሪያ ነው፡፡ በሶዌቶ 1.5 ሚሊዮን ጥቁር ደቡብ አፍሪካዊያን ይኖራሉ፡፡ በቅርቡ ይፋ በሆነ አንድ መረጃ አርባ ከመቶ የሚሆነው የጆሃንስበርግ ነዋሪ በሶዌቶ ከትሟል፡፡ የመልሱ ጨዋታ ሴፕቴምበር 11 ወይ

ም በእኛ የእንቁጣጣሽ ዕለት ይካሄዳል፡

፡ እህቶቻችን በአዲስ ዓመት ዋዜማ ታሪካዊ ድል ያጎናፅፉናል የሚል ተስፋ በብዙዎች ልቦና ውስጥ ተሰንቋል፡፡ የሉሲዎች ተጋጣሚ የሆነው ደቡብ አፍሪካ በመላው አፍሪካ ጨዋታዎች ላይ የሚካፈል ሲሆን ኢትዮጵያን ከመግጠሙ በፊት ተከታታይ ጨዋታዎችን ለማድረግ ይገደዳል፡፡ በዚህም የተነሳ አዲስ አበባ ላይ የሚካሄደው ጨዋታ የቀን ለውጥ እንዲደረግበት ፊፋን ጠይቆ ነበር፡፡ ፊፋ በተጠየቀው መሠረት ኢትዮጵያ ፈቃደኛ መሆኗን እንድታሳውቅ ወደ አዲስ አበባ ደብዳቤ ላከ፡፡ አንዳንድ ማንገራገሮች ከታዩ በኋላ የፌዴሬሽኑ ኃላፊዎች ከመስከረም 1 ፍንክች አንልም የሚል ምላሽ ሰጡ፡፡ ደቡብ አፍሪካ ጥቅሙን ለማስጠበቅ ሲል በፊፋ በኩል የላከው ልመና ተቀባይነት ሳያገኝ ሲቀር እንደገና በካፍ መስመር ማግባባት ጀመረ፡፡ በዚህ በኩል የመጡት ደግሞ የካፍ ዋና ፀሐፊው ሙስጣፋ ፋህሚ ናቸው፡፡ ግብፃዊው የካፍ የበላይ በተደጋጋሚ አቶ ሣህሉን በስልክ ለማግባባት ቢሞክሩም ሳይሰምርላቸው ቀርቷል፡፡ አሁን ጨዋታው በተያዘለት ቀን እንዲ

ካሄድ ፊፋ አዟል፡፡ በኋላ ለውጥ ተደርጎ ውጤት ቢጠፋ እንኳን ሁሉም ነገር በፕሮግራም ለውጡ ላይ ይደፈደፋል፡፡ ስለዚህ በመጀመሪያው መፅናታቸው ትክክ

የድንቅነሽ ፈተና፤ ማልያ እያጠበበች ትለማመዳለች

በስፖርት ቤተሰቡ ዘንድ የሰሞኑ መነጋገሪያ ሆኖ የከረመ ዜና ቡና ኤርትራዊ በረኛ ሊያስፈ

ርም ነው የሚለው ጉዳይ ነው፡፡ ቡና ዘንድሮ በበረኛ በኩል ብዙ ችግር ገጥሞት ነበር፡፡ ሶስት በረኞችን ያህል ቀያይሯል፡፡ ቋሚ ተሰላፊነቱን የያዘው ካሜሮናዊው ሙስጠፋ ነበር፡፡ እሱም ወደሀገሩ ሔዶ ሳይመለስ ቀረ፡፡ የሁለተኛው ዙር የዝውውር መስኮት ሲከፈት ነበር የአሁንን በረኛ ያገኙት፡፡ በቀጣዩ አመት የበረኛ ችግርን ለመቅረፍ በኢንተርናሽናል ውድድር ማለትም በካፍና በሴካፋ ለሚ

የኢትዮጵያ ግማሽ ሊግ በቀጣይ የውድድር ዘመን በ14 ክለቦች መካከል ይካሄዳል፡፡ ግማሽ ሊግ ያልኩት ከአዲስ አበባ በስተሰሜን ያለው ግዛት ተቆርጦ ስለሚቀር ነው፡፡ ዋና ከተማዋ በ6 ክለቦች ስትወከል በሕዝብ ብዛት ቀዳሚ የሆነው ኦሮሚያ 3 ወኪሎች አሉት፡፡ ደቡብም 3 አሉት፡፡ አዲስ አዳጊው አርባምንጭ ከነማ ከሁለት ዓመት በፊት ስሙን የቀየረው አርባምንጭ ዳሸን ቢራ ነው፡፡ ይህ ቡድን የዝነኛው አርባምንጭ ጨርቃ ጨርቅ ሕጋዊ ሳይሆን መንፈሳዊ ወራሽ ነው፡፡የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን ከሚበ

ጠብጡት ነገሮች ጉዞው አንዱ አይደለም? በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ረጅሙ ርቀት (891 ኪሜ) ወደ አዲግራት ነበር፤ እስከ መቀሌ በአውሮፕላን ከዚያም በየብስ የሚደረስበት፡፡ ትራንስ በመውረዱና ከታች ቡድን ባለመምጣቱ ቢያንስ ለአንድ ዓመት ሽቅብ መብረር ቀርቷል፡፡ በአንፃሩ ደግሞ አርባምንጭ ተተክቷል፡፡ ለአዲስ አበባ ክለቦች ቅርቡ ሜዳ ሰበታ ነበር፤ 25 ኪሎ ሜትር ብቻ ይርቃቸው ነበር፡፡ ለከርሞ የሰቤን ቦታ ደዘ ወስዶበታል፤ ይቅርታ ቢሾፍቱ፡፡ አዲግራት ደግሞ በሐረር ተተክቷል፡፡በ2004 በአውሮፕላን የሚኬድባቸ

ው የሊግ ጨዋታዎች ድሬዳዋ፤ አርባምንጭ እና ሐረር ናቸው፡፡ የሐረሩ ቀጥታ ሳይሆን ድሬዳዋ በአየር ከተገባ በኋላ በመኪና የሚደረስ ነው፡፡ እስቲ በመሬት ላይ ከመዲናዋ ያላቸውን ርቀት እንመልከት፡-* ከአዲስ አበባ ደብረዘይት:- 41 ኪሜ* ከአዲስ አበባ አዳማ:- 98 ኪሜ* ከአዲስ አበባ አሰላ:- 175 ኪሜ* ከአዲስ አበባ አዋሳ:- 273 ኪሜ* ከአዲስ አበባ ይርጋለም:- 318 ኪሜ* ከአዲስ አበባ አርባምጭ:- 491 ኪሜ* ከአዲስ አበባ ድሬዳዋ:- 494 ኪሜ* ከአዲስ አበባ ሐረር:- 513 ኪሜ

ቅዱስ ጊዮርጊስ ከአስር ዓመታት በላይ የፔፕሲን ማስታወቂያ በማልያው ደረት ላይ ለጥፎ በመጫወት ላይ ይገኛል፡፡ በቀጣዩ ዓመት ፔፕሲ ቦታውን ለሳዑዲ ስታር እንደሚለቅ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ ሳዑዲ ስታር የሼህ መሐመድ አልአሙዲን ኩባንያ ሲሆን ሙሉ መጠሪያው Saudi Star Agricultural Development Plc ይሰኛል፡፡ ኩባንያው በጋምቤላ ክልል ሩዝ ለማምረት 10 ሺህ ሄክታር በሊዝ ሲረከብ ለእግር ኳስ ክለቡ ሞቅ ያለ ክፍያ ይሰጣል፡፡ ፔፕሲ መተዋወቅ ሲጀምር ሞሓ በዓመት 300 ሺህ ብር ከፍሏል፡፡ ሳዑዲ ስታር ለሩዝ ስንት ይከፍል ይሆን?

በኤርሚያስ አማረ

ቤልጅየም

ወደ ገጽ 21 ዞሯል

የ2012 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያን ሳንጨርስ የ2014 የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ከች ብሎብናል፡፡ የአፍሪካ ዞን የ2014 የዓለም ዋንጫ የቅድመ-ማጣሪያ ድልድል ሪዮዴጄኔሮ ላይ ይፋ ሆኗል፡፡ የአፍሪካ ዞን ማጣሪያ 3 ዙሮች ይኖሩታል፡፡ በመጀመሪያው ዙር ወደ ምድብ ፉክክሩ ለመግባት በ24 ቡድኖች መካከል የደርሶ መልስ ግጥሚያ ይደረጋል፡፡ 12ቱ አሸናፊዎች 28ቱን ይቀላቀሉና በ10 ምድብ አራት-አራት ቡድኖች ተደልድለው የሁለተኛ ዙር ጨዋታቸውን ያካሂዳሉ፡፡ በሶስተኛው ዙር አስሩ የየምድቡ አሸናፊዎች በደርሶ መልስ እንዲጫወቱ ተደርጎ አምስቱ አሸናፊዎች ወደ ብራዚል ያቀናሉ፡፡ በምድብ ድልድሉ መሰረት ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሶማሊያ ደርሷታል፡፡ የመጀመሪያው ጨዋታ ህዳር 1 በሶማሊያ ሜዳ ይሆናል፤ መልሱ ደግሞ በአዲስ አበባ ህዳር 5 ይካሄዳል፡፡ ዋልያዎች ለ2012 የጋቦንና ኢኳቶሪ

ያል ጊኒ የአፍሪካ ዋንጫ በምድብ 2 የማጣሪያ ጨዋታቸውን እያካሄዱ ሲሆን የፊታችን ሴፕቴምበር 4 ኮናክሪ ላይ ጊኒን ይገጥማሉ፡፡ በምድቡ የመጨረሻ ጨዋታ ኦክቶበር 9 በአዲስ አበባ ማዳጋስካርን ያስተናግዳሉ፡፡ ምድቡን ጊኒ በ10 ነጥብ ስትመራ ናይጄሪያ በ7 ትከተላለች፡፡ ኢትዮጵያ 4 ይዛ ሶስተኛ ናት፡፡ 1 ነጥብ ያላት ማዳጋስካር ከታች ተቀምጣለች፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ቀጣይ ፈተና

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ

ማስታወሻ፡- የአንዳንድ ከተሞች ርቀት ከመንገድ ግንባታዎች በኋላ በተለምዶ ከሚታወቀው ርቀት መጠነኛ ለውጥ አምጥቷል፡፡

ይህ ጹሁፍ ከጋዜጠኛ ኤርሚያስ አማረ “ፌስ ቡክ” ገጽ የተወሰደ ነው

የኢትዮጵያ ቡና እግር ኳስ ቡድን የ2003 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድርን ማሸነፍ ተከትሎ ለክለቡ ጸሀይ የወጣለት ይመስላል፡፡ የክለቡ ደጋፊዎች ባደረጉት የገንዘብ ማሰባሰቢያ ሶስት ሚሊዮን ብር ያዋጡለት ሲሆን ሀበሻ ቢራ የተሰኘው ድርጅት ደግሞ አንድ ሚሊዮን ብር ክፍሎ ክለቡን ስፖንሰር እንደሚያደርግ ተሰምቷል፡፡ ናይኪ የሰኘው ትጥቅ አምራች ድርጅትም የቡና ገበያ ስፖንሰር ለመሆን መስማማቱ ተዘግቧል፡፡ የቡና ደጋፊዎች በማህበራቸው አማካ

ኝነት የገቢ ማሰባሰቢያ ያዘጋጁት ሐምሌ 16 ቀን 2003 ዓ.ም አዲስ አበባ በሚገኘው ኢንተርኮንቲኔታል ሆቴል ውስጥ ነበር፡፡ ለገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅቱ 200 ያህል ሰው ጥሪ ቢደረግለትም የተገኘው 80 ሰው ብቻ ነበር፡፡ ጥሪ ተደርጎላቸው ከቀሩት መካከል አንዳንዶቹ ባለመገኘታቸ ይቅርታ ጠይቀው ድጋፍ እንደሚሰጡ አሳውቀዋል፡፡ በፕሮግራሙ ከፍተኛውን ገንዘብ ያዋ

ጡት የክለቡ የቦርድ ፕሬዘዳንት አቶ ኤ

ሃድራው የደራለት ቡና

ሊያስ ኡመር ሲሆኑ 300 ሺህ ብር ለግሰዋል፡፡ የኢንተር ኮንቲኔታል ሆቴል ባለቤት አቶ ስማቸው ደግሞ 170ሺ ብር ሰጥተዋል፡፡ ቡናን ስፖንሰር በማድረግ የሚታወቀው ወርቤክ ድርጅት ባለቤት አቶ ወርቅሽት100ሺ ብር አበርክተዋል፡፡ በገቢ ማሰባሰቢያው ላይ ሌሎች 50 ሺህ እና 40 ሺህ ብር የሰጡ ሲሆን በግል በአማካኝ የተዋጣው 10 እና 15 ሺህ ብር ነበር፡፡ቡና የገቢ ማሰባሰቢያ ስኬት ዜና ሳይ

ቀዘቅዝ ነበር ሀበሻ ቢራ ክለቡን በ2004 ዓ.ም ስፖንሰር ለማድረግ መጠየቁ የተሰ

ማው፡፡ ሀበሻ ቢራ ለክለቡ ለአንድ ዓመት አንድ ሚሊዮን ብር ለመሰጠት መስማማቱ ነው የሚነገረው፡፡ ሀበሻ ቢራ በምስረታና በግንባታ ላይ ሲሆን ቡናን ይዞ ወደገበያ ሊገባ እንዳሰበ አይጠረጠርም፡፡ በ1995ዓ.ም ዳሸን ቢራ የቡና ስፖንሰር ነበር፡፡ በ2000ዓ.ም ሜታ ቢራ የቡና ስፖንሰር ሆኖ በጋራ ሰርተዋል፡፡ አሁን ደግሞ ሀበሻ ቢራ ሲመጣ ቡና በቢራ ትሪክ ሰራ ማለት ነው፡፡ የመጠጥ ድርጅቶች ቡና በርካታ ደጋፊ

ስላለው ምርታቸውን ለማስተዋወቅ ተመራጭ ያደርጉታል፡፡ የቡና የመጀመሪ

ያው ስፖንሰር ራሱ ቡና ነበር፡፡ ድርጅቱ ለክለቡ ካምፕ ሰርቶ ቡና በሚል ማሊያው ላይ አጽፎ ገባ፡፡ ከዚያ በኋላ ደግሞ በ1990 ዓ.ም ከድርጅቱ ውጭ አልቲሜት ሞተርስ የተባለ የላንድሮቨር እና ቢ.ኤም.ደብሊው አስመጪ ድርጅት ለሁለት ዓመት ያሀል ስፖንሰር አደረገው፡፡ እስካሁን ከፍተኛ ገንዘብ በመክፈል ክለቡን ስፖንሰር ያደረጉ አራት ድርጅቶች ናቸው፡፡ ቡና ለተወሰነ ጊዜም ቢሆን “ወርቤክ”

የተሰኘውን የቡና ላኪ ድርጅት ማስታወቂያ በማልያው ለጥፎ ታይቷል፡፡ የ“ወር

ቤክ” ባለቤት አቶ ወርቅሸት በራሳቸው ወጪ ቡና ለብሶ የሚጫወተውን ማልያ በውጭ ሀገር አሰርተው በማስመጣት የሚታወቁ ናቸው፡፡ ክለቡ ከዚህ በኋላ ግን ለማልያ መጨነቅ ያለበት አይመስልም፡፡ ምክንያቱም ዓለም አቀፉ ትጥቅ አምራች ድርጅት ናይኪ የኢትዮጵያ ቡናን ስፖንሰር ለማድረግ ከክለቡ ጋር በቅርቡ ስምምነት ላይ በመድረሱ ነው፡፡ ስምምነቱን በመሐል ሆኖ የሚያስፈፅመው የአትሌት ዘነበች ቶላ ባለቤት አቶ ወንድወሰን ነው፡፡ ዘነበች ዜግነቷን ቀይራ እና ማርያም ዩሱፍ ጀማል ተሰኝታ ለባህሬን እየሮጠች የምትገኝ ውጤታማ አትሌት ናት፡፡ በኢትዮጵያ ቡና እና የናይኪ ስምም

ነት መሰረት ትጥቅ አምራች ድርጅቱ ለ2004 የቡናን ማልያ ራሱ ባዘጋጀው ዲዛይን ሠርቶ ያቀርባል፡፡ ይህ ሰምምነት ማልያ፣ ቁምጣ፣ ገምባሌ፣ ካሶተኒ እና የመጫውቻ ጫማንም ያጠቃልላል፡፡ ናይኪ ቢጫ ቀለም ያለውን የቡድኑን ማልያ እጅጌ ጉርድ፣ እጅጌ ሙሉ እና በባለኮሌታ ዓይነቶች ለመስራት ተስማምቷል፡፡ በተመሳሳይ በቡናማው ቀለምም ሶሰት ዓይነት ማልያዎች ይቀርባሉ፡፡ እያንዳንዱ ተጫዋች ስሙና ቁጥሩ የተፃፉበት በድምሩ ስድስት ማልያዎች ከናይኪ በሻንጣ ይላክለታል ማለት ነው፡፡

ቡና የኤርትራን በረኛ ሊያስፈርም ነው?ያደርጉት ተሳትፎ ለቡድኑ የሚመጥን በረኛ እየፈለጉ ነው፡፡ ይህን ቦታ ለመሸፈን የቀይ ባህሩን በረኛ ዳንኤል ጎይቶምን ወደ ቡድናቸው ሊያመጡ ነው እየተባለ እየተነገረ ነው፡፡ ዳኤልን ሌላ የኢትዮጵያ ክለብ እየፈለገው ነው ቢባልም ወሬው በስፋት ያለው ቡና ላይ ነው፡፡ ሶስት የሚያህሉ የቀይባህር ተጨዋቾችም ከኢትዮጵያ ክለቦች ጋር ግንኙነት እንደፈጠሩ ነው የሚወራው፡፡ የዛሬ ወር ግድም 13 የቀይ ባህር ተጨዋቾች ታንዛኒያ ላይ መጥፋታቸው ይታወቃል፡፡ ተጨዋቾቹ ወደ ጁባ ሳይሄዱ እንዳልቀሩ ጭም

ጭምታ አለ፡፡ አንድ ተጨዋች አለምአቀፍ ዝውው

ር ሲያደርግ የአገሩ ፌዴሬሽን መልቀቂያ መስጠት አለበት፡፡ የኮበለሉት የኤርትራ ተጨዋቾች ፌደሬሽናቸው መልቀቂያ አይሰጣቸውም፡፡ ዳንኤል አራት ጊዜ ለጎትያ ካፕ ስዊድን ሄዷል፡፡ ከኮበለለት ውስጥም አራት ተጨዋቾች የስዊድን ጥምር ዜግነት እንዳላቸው ይነገራል፡፡ ጥምር ዜግነት ያላቸው ተጨዋቾች መልቀቂያ ከአንደኛው ሀገር እንኳን ቢከለከሉ በፊፋ ህግ መሰረት ከሌላኛው አገር ሊያገኙ ይችሉ ይሆናል፡፡

ከጊዮርጊስ መንደርቅዱስ ጊዮርጊስ ሁለት አዳዲስ ል

ጆች አስፈርሟል፤ ሽመልስ በቀለን ከአዋሳ እንዲሁም የአማካይ ተከላካዩ ተስፋዬ አለባቸውን ከሰበታ ከነማ፡፡ ለአማካይ አጥቂው ሽመልስ 350 ሺህ የፊርማ ሰጥተውታል፡፡ ከውጪ ተጫዋቾች ደግሞ ሱላ ማቶቩ (ዩጋንዳ)፣ ፕሪንስ ጎድዊን (ጋና) እና አንቶኒ ቦንጎሌ (ዩጋንዳ) ተሰናብተው በረኛው ሮበርት ኦዳንካራ እና ተከላካዩ አይዛክ ኢሲንዴ (ሁለቱም ከዩጋንዳ) ብቻ ከክለቡ ጋር እንዲቀጥሉ ተደርጓል፡፡

ከላይ ያሉት ዘገባዎች የተጠናቀሩት ገነነ መኩሪያ ቀድሞ ያዘጋጀው በነበረው ጋዜጣው ስም ከከፈተው ሊብሮ ዶት ኮም ከተሰኘው ድረ ገጽ እና ከኤርሚያስ አማረ ፌስ ቡክ ገጽ ነው

Page 23: Habeshawi kana 004

ሐምሌ 30-ነሐሴ 13 ቀን 2003 (August 6-19, 2011) ሐበሻዊ ቃና 23

ስፖርት

ሀገር “የሌለው” ሜሲ

ጥያቄ:- የሜክሲኮ ውጤታማነት ምስጢር ምንድነው?ሔርናንዴዝ:- የቡድኑ ጠንካራ ሰራተኝነት እና

ትኩረት መስጠት የማሸነፍ ተነሳሽነት ውስጥ እንድንጓዝ ረድቶናል:: የጎል እድሎችን በአግባቡ ተጠቅመናል:: እንደዛ መሆኑ ሰዎች ቀላል አድርገው እንዳያስቡ ውድድሩ ሳይጀመር ምንም ግዴታ ወይም ጫና የለብንም ብለን በማሰብ እያንዳንዱን ጨዋታ ለማሸነፍ እና እያንዳንዱን ውድድር በስኬት ለመጨረስ ተጫውተናል:: ነገር ግን ድል የሚገኘው በጠንካራ ስራ ብቻ ነው:: ጥያቄ:- ቢሆንም ከማሸነፍ ውጪ ያለ ውጤት ለሜክሲኮዊያን እንደውድቀት ነው::ሔርናንዴዝ:- በዚህ እይታ አልስማማም:: በር

ግጥ አሸነፍንም ተሸነፍንም የሚከተለውን እናውቃለን:: ለዚያም ነው ማሸነፍን ግባችን አድርገን ወደ ውድድሩ የገባነው:: እንዳስብነውም ተሳክቶለናል:: ዋናው ቁምነገር ውጤታማ መሆናችን ሲሆን ደጋፊያችን የሚጨፍርበት ስጦታ በማበርከ

ታችን በጣም ተደስቻለሁ:: በውድድሩ ፈታኝ ሁኔታዎችን ማለፋችን ድሉን የበለጠ ጣፋጭ አድርጎልናል:: ከብሔራዊ ቡድኑ ጋራ ያገኘሁት የመጀመርያ ዋንጫ በመሆኑ እጅግ አርክቶኛል::ጥያቄ:- ይህ ቡድን የሜክሲኮ የምንጊዜም ምርጡ እንደሆነ ታስባለህ?ሔርናንዴዝ:- የምጠላው ነገር ቢኖር ማነፃፀር ነ

ው:: እንደተጫዋች አሰልጣኝ የሚልህን መተግበር ነው፣ በብሔራዊ ቡድን ደግሞ የበለጠ:: በቡድ

ኑ የተደረገልኝ አቀባበል እና እርዳታ በጣም አስደስቶኛል:: ለኤልትራይ ከለር [የሜክሲኮ ብሔራዊ ቡድን ቅጥል ስም ነው] በእያንዳንዱ ሰከንድ የማደርጋት እንቅስቃሴ ታላቅ ስሜት ይሰጠኛል:: ላለፈ ነገር አልኖርም፡፡ የሚያበረታታኝ የዛሬ እና የወደፊቱ ሕይወት ነው::ጥያቄ:- ስለ ብሔራዊ ቡድንህ በዚሁ እናብቃና ስለክለብህ እንነጋገርሔርናንዴዝ:- በማንችስተር አስገራሚ እንክብ

ካቤ ተደርጎልኛል፣ ለተሰጠኝ አመኔታ እኔም ምላሹን መክፈል እሻለሁ:: የመጀመርያ ዓመቴ የተሳካ ነበር:: ዘንድሮም የበለጠ አስተዋፅኦ ማበርከት አለብኝ:: ከዚህ ቡድን ጋራ ወደፊት ብዙ ጥሩ ጊዜ እንደሚኖረኝ አስባለሁ፣ በቀጣዩም ውድድር በማገኘው እድል በጣም ደስተኛ ነኝ::ጥያቄ:- ከዚህ ቀደም ሜክሲካዊ ተጨዋቾች በሌላ ሀገር ሲጫወቱ ለመልመድ ሲቸገሩ ይታይ ነበር:: ያንተ ምስጢር ምንድነው?

በፍፁም ሜዳ ውስጥ መኖር አልነበረበትም:: በሁለቱ የመጀመርያ የምድብ ጨዋታዎች ከ

ቅድሚያ ተሰላፊዎች ውስጥ መካተቱ በጣም ይገርማል:: ከቡድን ስብስብ አንዱ መሆኑ ልክ አይደለም:: የፍፁም ቅጣት ምት ለመምታት በዚያ ቦታ መገኘት አይገባውም:: ምክንያቱም የሚከተለው ውጤት ይታወቃላ:: የዑራጋዩ በረኛ ሙስሌራ ደመ ነፍሱ ወደጠቆመው አቅጣጫ ተወረወረ:: የዓለም ትልቅ ቡድኖች ካላቸው በላይ ምርጥ ስብስብ አለን ብለው ደረታቸውን የነፉ የሰማያዊ እና ነጭ ለባሾቹ ደጋፊዎች ኩራት በስከንዶች ውስጥ ተነነ:: በደጋፊዎች እና ሚዲያ ጩኸት ለሀገራዊ ግዴታ የተጠራው ካርሎስ ቴቬዝ ተመረጠ ተሰለፈ፣ አንገቱን ደፋ፣ ሀገሩን አሳፈረ:: አርጀንቲናውያን በጥፈራቸው ውስጥ መሸሸግ ተመኙ::የውድቀቱ ዋነኛ ተጠያቂ እርሱ ነ

ው፣ የማንችስተር ሲቲዎች ፊትውራሪ ካርሎስ ቴቬዝ! ደጋፊው “ኡኡ!” አለ፣ አሰልጣኙ ሰርጂዮ ባቲስታ መረጠላቸው:: ያ “የሕዝቡ ሰው” ሕዝቡን ቀበረ:: የቴቬዝ ኃጢያት በዛ ሊባል ይችላል:: አዎ በዝቷል:: በኮፓ አሜሪካ ብቻ ሳይሆን በ2010 ዓለም ዋንጫ ማጣርያ ሁለቴ በቀይ ካርድ ሲወጣ፣ አንድ ጊዜ ሪጎሬ ስቶ የሀገሩን የደቡብ አፍሪካ ጉዞ ምጥ ውስጥ የከተተው እርሱ ነበር::ነገር ግን የሚዲያው እና የሕዝቡ የ

ሰላ ትችት ቴቬዝ “ጀግናቸውን” በጨረፍታም አልነካም:: ከእርሱ ይልቅ ዒላማቸው ሁሉ ያነጣጠረው የዓለም ቁጥር አንዱ ሊዮኔል ሜሲ ላይ ነበር፡፡ ከባርሳ ጋራ በትንሹ ሶስት የሻምፕዮንስ ሊግ እና አራት የላሊጋ ዋንጫ ማግኘቱ እና በተከታታይ የዓለም ኮከብ መሆኑ ከሀገሩ ደጋፊዎች ብዙ እንዲጠበቅበት አድርጎታል፣ ኃላፊነቱን አብዝቶታል:: በ1993 የኮፓ አሜሪካ ዋንጫን ካገኘች ወዲህ በብሔራዊ ቡድን ደረጃ አንድም ክብር ያላየችው የኳስ ሀገር አርጀንቲና በርካታ ኮከቦችን ብታፈራም ከድል ድርቅ የሚያድናት ልታገኝ አልቻለችም::አርዬል ኦርቴጋ፣ ጋብርኤል ባቲስቱ

ታ፣ ሁዋን ቬሮን፣ ማርሴሎ ጋያርዶ፣ ሄርናን ክሬስፖ፣ ፓብሎ አይማር፣

ዋወት ለሜሲ አይመቸው ወይም ሜሲ ለአርጀንቲና ያለው ዋጋ ዝቅ ያለ ነው” የሚሉ የዋለሉ ስሜታዊ ትንታኔዎች ቢሰጡም ያለው ሪከርድ ግን ደካማ እንደሆነ ያሳብቁበታል:: በአራቱ ግዙፍ መድረኮች ያስቆጠራ

ቸው ጎሎች ሶስት መሆናቸው መስማት ለማመን ያዳግታል:: በባርሳ አድራጊ እና ፈጣሪ የሆነው ጥበበኛው ሊዮ ሀገሩ አርጀንቲና ኮፓ አሜሪካን አዘጋጅታ ከደካማዋ ቬኑዝዌላ በታች መጨረሷ ጣቶች ሁሉ በእርሱ ላይ እንዲቀሰሩ አድርጓል:: በሜዳ ላይ የተቃውሞ ጩኸቶች የተሰሙበትም በዚህ ምክንያት ነው:: በሁኔታው የተበሳጩት የአርጀንቲና ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ሁሊዮ ግሮንዶና “ይሄ ልጅ ከእንግዲህ ለሀገሩ አልጫወትም የሚል ውሳኔ ላይ ሊደርስ ይችላል” በማለት ሲያስፈራሩ፣ ማራዶና በበኩሉ “ሜሲ ብቻውን ተዓምር እንዲፈጥር የሚፈልጉ ሰዎች ደደብ መሆን አልባቸው:: እኔንም በእርሱ እድሜ ሚዲያው እና የማይረቡ ሰዎች ይተቹኝ ነበር:: ከዓለም ዋንጫ ድል በኋላ ግን የገቡበት ጠፋ” ሲል ለሜሲ ተከላክሏል::በሶስት የተለያዩ አሰልጣኞች ታክቲክ

ውስጥ ጎልቶ መታየት የተሳነው የ24 ዓመቱ ሜሲ ከፊቱ ከባድ ፈተናዎች ይጠብቁታል:: አዲስ ከተሾሙት አሰልጣኝ አሌሃንድሮ ሳቤላ ጋራ በመሆን አርጀንቲናን የ2014 ዓለም ዋንጫ ተካፋይ ማድረግ የመጀመሪያ ግዴታው ይሆናል:: በደቡብ አሜሪካ አገሮች መካከል የሚደገረው የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ረጅም ጊዜ በመውሰዱ የተነሳ “ማራቶን” ተብሎ ነው የሚጠራው፡፡ አሰልቺ እና አድካሚው ማጣሪያ እና ለዝግጅት በቂ ጊዜ አለመኖሩ ጋር ተዳምሮ ተጨዋቾቻቸው በአውሮፓ ለከተሙ እንደ አርጀንቲና ላሉ ሀገሮች ያልተጠበቀ አደጋ የሚደቅን ነው:: ይህን ቀዳሚ መሰናክል በብቃት ማለፍ ለሜሲ ከሀገሩ ሕዝብ ጋራ የመታረቂያ መድረክ ሊሆን ይገባል:: ይህን የሚያሳካ ከሆነ ብራዚል በምታዘጋጀው የዓለም ዋንጫ ላይ አንድ የቀረችውን ሕያው ሆኖ የመቅረት እድል በእግር ኳሷ ምድር መጠቀም የእርሱ ፋንታ ይሆናል:: ወርቃማውን ውብ ዋንጫ ከፍ አድርጎ መሳም! እስከዚያ ድረስ ግን የአርጀንቲና ጉዳይ እንደ ሕልም እያባነነው ይኖራል::

ሁዋን ሮማን ሪኬልሜ፣ ሀቪዬር ሳቪዮላ፣ አንድሬስ ዲ አሌሳንድሮ እና ሀቪዬር ዜኔቲን የመሳሰሉ እንቁዎችን ብታፈራም የልቧን የሚያደርሱላት ሊሆኑ አልቻሉም:: የዓለም ወጣቶች ዋንጫ ላይ የሚያንፀባርቁት ጥበበኞቿ የዋናውን ቡድን ማልያ ሲለብሱ ከስመው የውድድር አሟሟቂ እና የግምት ዋንጫ ብቻ ተሸልሞ መመለስ የተለመደ ነው:: በእርግጥ አርጀንቲና በእነ ቴቬዝ እና ሜሲ ሁለት የኦሎምፒክ ክብር ተቀዳጅታለች:: ያ ድል ግን ለታንጎዎች

ማስተዛዘኛ እንጂ የሚፎከርበት አይደለም:: ንጉሳቸው ዲዬጎ አርማንዶ ማራዶና ያሳያችውን ጀብዱ እንደምፅአት ቀን ምንጊዜም በጉጉት ይጠባብቃሉ:: “ አምላካቸው” ማራዶና ለቦካ ጁኒየርስ እና ለናፖሊ የሰራውን ተዓምር በአልቢቼሌስቴ ቀለም ደግሞ ስለፃፈው የሀገሪቷ ዘለዓለማዊ ጣዖት አደርገውት ይኖራሉ:: ዓለም ዋንጫ ወደቤታቸው ከመጣ 25

ዓመታት ቢያልፉም ልክ እንደዛሬ ክስተት በፍቅር ይተርኩታል:: ማራዶና አሰል

ጣኝ እንዲሆን ጎትጉተው የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን በማጣሪያ ግጥሚያ በትንሿ ቦሊቪያ 6-0 መራር ሽንፈት ሲቀምስ እና በዓለም ዋንጫ ላይ ደግሞ በጀርመን 4-0 አሸማቃቂ ውጤት ሲያስመዘግብ ተመልክተዋል፡፡ ሆኖም ማራዶና አሁንም ቢሆንም በሕዝቡ እንከን የለሽ ሆኖ ይመለካል:: ሜክሲኮ ዓለም ዋንጫ ላይ የጫነውን ዘውድ ማንም እንዲነካበት አይፈልጉም:: ዲዬጎ ለእነርሱ ከእግር ኳስም በላይ ነው:: ይህ ልባቸው ነው ለሜሲ ለመራ

ራት ያልፈቀደው:: የሜሲ የባርሴሎና ገድል በሀገሩ ፊት

ምንም ነው:: የእርሱ የዓለም ኮከብነት ለአርጀንቲና ምን ይረባታል?! በእግር ኳሱ ዓለም የአድናቆት ቃላት ቢጠፋለትም በሁለት ዓለም ዋንጫዎች እና ኮፓ አሜሪካ ውድድር ላይ የተሰለፈው ሜሲ ለሀገሩ ከተራ ተጨዋች በታች አስተዋፅዖ ማሳየቱ ከታላላቅ ተጭዋቾች ተርታ የመጠራቱን ነገር ጥያቄ ውስጥ አስገብቶታል:: ችግሩን ለመጠቆም፣ “የአርጀንቲና አጨ

ቺካሪቶ: የማንችስተርን ውለታ መክፈል አለብኝበዓለም እግር ኳስ ውስጥ በአንድ የውድድር ዓመት ውስጥ ወዲያውኑ አስገራሚ ተፅዕኖ የፈጠሩ ተጨዋቾች በጣም

ጥቂት ናቸው:: አንዱ ምሳሌ ደግሞ ሀቪዬር “ቺካሪቶ” ሔርናንዴዝ ነው:: የሚደንቅ ችሎታ ከሞያ አክባሪነት እና ጎል አነፍናፊነት ጋራ አጣምሮ መያዙ በአምና ውድድር ከታዩ ክስተቶች ዋነኛው ያደርገዋል:: ሀገሩ ሜክሲኮን ለጎልድ ካፕ ዋንጫ

ድል ካበቃ በኋላ ስላገኘው ስኬት እና ቀጣይ እቅዶቹ ይናገራል::

ወደ ገጽ 21 ዞሯል

“ለመምሰል የምጥረው የብራዚሉ ሮናልዶን ነው:: ሮናልዶ ታላቅ ተጨዋች

እንደሆነ አስባለሁ

Page 24: Habeshawi kana 004

ሐምሌ 30-ነሐሴ 13 ቀን 2003 (August 6-19, 2011)ሐበሻዊ ቃና24

VAMBECO ENTERPRISES LTD

Vambeco is noted for excellence of its work, innovation and experience in tackling both complex and simple projects efficiently. Since we started working in Uganda we have established ourselves as one of the leading credible contractors in the region. We are very pleased to have made such

a positive impact in the building and water engineering sector. We work in a manner that protects and promotes the health and well being of the individual and the environment.

As challenging as it is operating in a highly competitive construction sector in a developing country like Uganda, where very many foreign companies from China are competing for any available job, Vambeco Enterprises Ltd, located on Kanjokya Street, in Kamwokya has firmly stood the test of time. This success can be attributed to the high quality of work and commitment.

Vambeco Enterprises Ltd was formed in August 1999, as a result of merging Bagatansi Builders Uganda Limited and Viera Sarl Rwanda. Bagatansi Builders Uganda Limited was in the building sector in Uganda for 144 years while Viera Sarl was in Rwanda engaged in the construction of water projects and emergency relief construction projects since 1994.Kampala is their headquarters for thee Great lake region with branch offices in Nairobi, Kenya and Kigali, Rwanda.

With over 20years of experience in Water Engineering, Vambeco endeavors to provide the following activities around the great lake region.

q Supply and Installation of Pre-Paid Water Meters,q Construction of Water and Sanitation Projects,q Building Projects such ass Schools, Hospitals, Churches, Mosques,q Design and Construction of Utilities in Refugee/ IDP camps,q Construction of Water Reservoirs of all sizes,q HHDPE Pipe Laying,q Steel Tower and Water Tank Installation, q River Intake Works, q Slow sand filtration , water intake treatment Works & q Construction of reinforced concrete reservoirs

For more information, contact us on: Mobile: +256 772748351, 07772 716220, Plot 43, Kanjokya Street, Kamwokya. Fax: +256 414 530136 P.O.Box 166220, Kampala Uganda.

Email: [email protected], Telephone: +256 414 543510, Website: wwww.vambeco.com